ውሉደ ብርሃን ሚድያ @weludebirhan Channel on Telegram

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

@weludebirhan


የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ውሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚገልፁ መረጃዎችን እንዲሁም ማስታወቂያዎችን የምንለቅ ስለሆነ እንድትከታተሉን እንጠይቃለን።

👋👋👋👋👋👋👋👋👋👋
መልእክት ካሎት በዚህ ሊንክ ይላኩልን
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
@saint_kirkos

ውሉደ ብርሃን ሚድያ (Amharic)

ውሉደ ብርሃን ሚድያ የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ውሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚገልፁ መረጃዎችን እንዲሁም ማስታወቂያዎችን የምንለቅ ስለሆነ እንድትከታተሉን እንጠይቃለን. ይህ አዝናኝ ቫይረስ የአስተማሪ መረጃና መልክቶቻችንን ከሚተክሉት ጊዜም በቀጣይ ማያቋርጥና መጠናቀቅ የሚችሉ አስተማሪነት ያሉትን ያልሆኑ ለማንበብ አሰብን. ምንም ልብስ እና ስለጥንቃቄ ወደ እዚህ ቦታ መልእክቱን ትክክለኛውን ይቀላቁ።

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

28 Dec, 05:21


➡️ሊሰጡ ያሰቡትን  በነዚ ቀናቶች በሰንበት ት/ቤቱ አዲስ በሚሰራው ህንፃ ጋር ይዘው መተው ለክፍሉ አገልጋዮች ይስጡ።

✤ ማግሰኞ ምሽት ከ12 እስከ 1:30
✤ ቅዳሜ ምሽት ከ12 እስከ 1:30
✤ እሁድ ጠዋት ከ3 እስከ 5:00
✤ሰኞ የበዓል ዋዜማ ሙሉ ቀን

👉በ0938017220 /0913035001 ይደውሉ


    መልካም በዓል የ120 ቤተሰብ


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

28 Dec, 02:59


የዕለቱ ስንቅ

👉ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ👈


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

27 Dec, 09:26


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

27 Dec, 05:00


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

27 Dec, 02:59


የዕለቱ ስንቅ

👉ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ👈


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

26 Dec, 10:45


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

26 Dec, 02:59


የዕለቱ ስንቅ

👉ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ👈


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

25 Dec, 16:58


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን ከእስራኤል መሳፍንት አንዱ ጌዴዎን አረፈ

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

25 Dec, 16:58


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን ከእስራኤል መሳፍንት አንዱ ጌዴዎን አረፈ::

ይህም ከነገደ ምናሴ የሆነ የአባቱ ስም ዮአስ ይባላል ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ተገለጠለትና ለእስራኤል ምስፍና ሾመው። የጣዖታቱንም መሠዊያ እንዲያፈርስ ዛፎችንም እንዲቆርጥ አዘዘው መሠዊያም ለእግዚአብሔር ሠርቶ በዚያ በሰበረው ዕንጨት እንዲሠዋ አዘዘው ሁሉንም እንዳዘዘው አደረገ።

እግዚአብሔር የላከው መልአክም ተመለከተው እስራኤልን ከምድያም እጅ ታድናቸዋለህና ከሠራዊትህ ጋር ሒድ እነሆ ላክሁህ አለው።
ጌዴዎንም አድናቸዋለሁ እንዳልክ እስራኤልን በእጄ ታድናቸው እንደሆነ እነሆ እኔ በአደባባይ የተባዘተ ፀምርን እዘረጋለሁ ጠል በምድር ላይ ሳይወርድ በፀምሩ ላይ ብቻ ቢወርድ አድናቸዋለሁ እንዳልክ እስራኤልን በእጄ እንድታድናቸው ያን ጊዜ አውቃለሁ አለ እንዳለውም ሆነ።

ጌዴዎንም በማግሥቱ ማልዶ ሒዶ ያንን ጠመቀው ከዚያ ፀምር አንድ መንቀል ሙሉ ውኃ ወጣ። ጌዴዎን እግዚአብሔርን በቊጣህ አትቆጣኝ ዳግመኛ አንድ ጊዜ ልናገር በፀምር ላይ ብቻ ሳይወርድ ጠል በምድር ሁሉ ላይ ይውረድ አለው። እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት እንዳለው አደረገ። ፀምሩ ብቻ ደረቅ ሁኖ ጠል በምድር ሁሉ ላይ ወረደ።

ጌዴዎንንም የእግዚአብሔር መንፈስ ረድኤት አጸናው ነጋሪትንም መታ አብያዜርም በኋላው ሁኖ ደነፋ። ወደ ነገደ ምናሴም ሁሉ መልክተኞችን ላከ እርሱም ከኋላው ሁኖ ደነፋ ወደ ነገደ አሴር ወደ ነገደ ዛብሎን ወደነገደ ንፍታሌምም መልእክተኞችን ላከ ወጥተውም ተቀበሏቸው።

ጌዴዎንም ከርሱ ጋር ያሉ ወገኖቹም ሁሉ ሔዱ አሮኤድ በሚባል አገርም ሰፈሩ የምድያምና የአማሌቅ ሠራዊትም በእንበሬም ቆላ መሠዊያ ቀኝ ሰፈሩ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እጃችን አዳነችን ብለው እንዲይመኩብኝ የምድያምን ሰዎች በእጃቸው መጣል እንደማልችል ካንተ ጋር ያሉ ሕዝብ ብዙ ናቸው አለው።

እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው ከእናንተ የሚፈራ የሚደነግጥ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይመለስ ብለህ ለሕዝቡ ንገራቸው። ሕዝቡም ከገለዓድ ተመለሱ ከሕዝቡም ሁለት እልፍ ከሁለት ሽህ ተመልሰው እልፍ ሰዎች ቀሩ እግዚአብሔር ጌዴዎንን ገና ብዙ ሕዝብ አሉ ወደ ውኃ አውርደህ በዚያ ፈትናቸው እኔ ይሒዱ የምልህ ሰዎች እነሳቸው ካንተ ጋር ይሒዱ አለው ሕዝቡንም ወደ ውኃ አወረዳቸው ።

እግዚአብሔር ጌዴዎንን ውሻ በምላሱ ጠለፍ ጠለፍ አድርጎ እንዲጠጣ ከውኃው ጠለፍ ጠለፍ አድርጎ የሚጠጣውን ሁሉ ለብቻው አቁመው ውኃን ይጠጣ ዘንድ በጉልበቱ የተንበረከከውንም ሁሉ ለብቻው አቁመው አለው ።

በምላሳቸው ጠለፍ ጠለፍ አድርገው የጠጡ ሰዎች ቊጥራቸው ሦስት መቶ ሆነ የቀሩት ሕዝብ ግን ውኃን ይጠጡ ዘንድ በጉልበታቸው ተንበረከኩ ። እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንደዚህ በእጃቸው ውኃን በጠጡት በእነዚህ ሦስት መቶ ሰዎች አድናችኋለሁ የምድያምን ሰዎች በእጅህ እጥላቸዎለሁ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ቤታቸው ይመለሱ አለው ።

በዚያችም ሌሊት እሊያ ሦስት መቶ ሰዎች መለከትን ነፉ ይህ የእግዚአብሔር ኃይልና የጌዴዎን ጦር ነው ብለው ጮኹ ።

የምድያምም ሰዎች የመለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔር በልባቸው ፍርሀትን አሳድሮባቸው ደንግጠው ሸሹ እግዚአብሔርም ያንዱን ሰይፍ ወዳንዱ ወደ ጓደኛው መለሰ በሠራዊቶቻቸው ሁሉ እርስበርስ መተላለቅ ሆነ መኳንንቶቻቸውን ኄሬብንና ዜብን ነገሥቶቻቸው ዛብሄልንና ስልማናንም ገደሏቸው ከምድያምም ሠራዊት ፈረሰኞችና ጦረኞችን አንድ መቶ ሁለት ሽህ ገደሉ ።

ከዚህም በኋላ የምድያም ሰዎች በእስራኤል ፊት ተዋረዱ ዳግመኛም ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም በጌዴዎንም ዘመን ምድር አርባ ዘመን አረፈች ።

ከዚህም በኋላ በሰላም በፍቅር አረፈ ለእግዚአብሔም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን ።


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

25 Dec, 02:59


የዕለቱ ስንቅ

👉ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ👈


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

24 Dec, 13:53


ታህሳስ ፲፭/፳፻፲፯
= = = =
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጰያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ ለአባ ክፍለ ዮሐንስ ዘወልደ ማርያም ቤተ መጻሕፍት የተለያየ ይዘት ያላቸውን ፲፯ (አስራ ሰባት ) መጻሕፍትን ዛሬ በስጦታ አበርክቶልናል።
🙏 ከሃያ ቀን በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጰያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ ዳይሬክተር ዶ/ር ዮሐንስ አድገህ ሰንበት ትምህርት ቤታችንን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

( ዩኒቨርሲቲው በ፳፻፲፮ የተለያዩ መጻሕፍትን አበርክቶልን ነበር )

✍️ ውድ አባላትና ኦርቶዶክሳውያን በተለያየ የስራ መስክና የስልጣን እርከን እንዲሁም የዕውቀት ደረጃ የምትገኙ እናት ሰንበት ትምህርት ቤታችሁን አለንልሽ እንድትሏት ሌሎችም መጥተው እንዲጎበኙ ምክንያት እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
✍️ ይህንን እድል ያመቻቸውን ወንድማችን አዲስ ታከለን  ለማመስገን እንወዳለን።

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

24 Dec, 12:11


👉ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ👈


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

24 Dec, 08:01


እናስተዋውቃችሁ
       👉 የመጽሐፋ ርዕስ ፦ ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት
       👉 አዘጋጅ ፦ መ/ር አንዷለም ዳግማዊ
       👉 የታተመበት ወቅት ፦፲፱፺፰ (1998) ዓ.ም
       👉 የገጽ ብዛት ፦  ፬፻፫ (403)
       👉 የታተመበት ማተሚያ ቤት ፦ አይገልጽም
       👉 የመጽሐፍ ዋጋ ፦ ፳፭ (25)

መጽሐፉ በአምስት ምዕራፎች የተከፈለ ነው።

ምዕራፍ ፩
       የነገረ ማርያም አስተምህር የት መጣና እድገት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ምዕራፍ ፪
       ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላት /ሱታፌድርሻ/
ምዕራፍ ፫
        የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት በነገረ ድኅነት ውስጥ ያለው መሰረታዊ ሚና
ምዕራፍ ፬
        የወላዲተ አምላክ ዘላለማዊ ድንግልና ከሚስጢረ ድኅነት ጋር ያለው ጥልቅ ግንኙነት
ምዕራፍ ፭
        ክብረ ቅድስት ደንግል ማርያም ከነገረ ድኅነት ጋር ያለው ምስጢራዊ ትስስር

      በአጠቃላይ በእነዚህ አምስት ምዕራፎች ስለ እመቤታችን አመጣጥ በቅዱሳት መጻሕፍት በብዙ ኅብርና አምሳል መመሰሏን ስለድንግልናዋ ስለ ክብሯ ስለሕይወት ታሪኳ ከነገረ ድኅነት ጋር አጣምሮ የሚያብራራ መጽሐፍ ነው።

👉👉👉ከ ዲ/ን ጥላዬ አያሌው

👉 ዘወትር ከሰኞ -እሁድ ከቀኑ 7:00-ምሽት 2:00 ወደ አባ ክፍለዩሐንስ ቤተ መጽሐፍት በመምጣት የብርሃን መንገድ የሚሆኑ መጻሕፍትን ያንብቡ።

👉ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ👈


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

24 Dec, 02:59


የዕለቱ ስንቅ

👉ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ👈


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ


Youtube | Facebook | Telegram | Tiktok

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

24 Nov, 18:17


ዛሬ የሰንበት ጉባኤ ሕዳር ፲፭/፳፻፲፯ ዓ.ም. እንደዎትሮ ተከናውኖ ውሏል።

የሰንበት ትምህርት ቤታችን ወርሃዊ የጸሎት መርሐ ግብር በርከት ያሉ አባላት በተገኙበት በካህናት ማዕጠንት ታጅቦ ተከናውኗል። በዕለቱም የወንድማችን አንዱአለም አድባሩን (ወልደ ጊዮርጊስ ) ነፍስ ፈጣሪ በቀኙ እንዲያሳርፋት በጸሎት ታስቧል።



ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 የዩቲዩብ ገፅ
https://www.youtube.com/@weludebirhan9612
👉 የፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/saintkirkosweludebirhan/
👉 የቴሌግራም ገፅ
https://t.me/weludebirhan
👉 የቲክቶክ ገፅ
https://www.tiktok.com/@weludebirhan?_t=8fSm647llUD&_r=1

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

24 Nov, 05:04


🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼

ጾመ ነቢያት፤
.
      “ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል።” ማቴ፡፲፥፵፩።
            ይኸንን ኃይለ ቃል በወንጌል የተናገረው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ነው።በመሆኑም ሃይማኖት ያለው ሰው ሁሉ ጌታ የተናገረውን ይህን የሕይወት ቃል አምኖ ይቀበላል።ምክንያቱም ቃሉን ሰምቶ ተግባራዊ ማድረግ ቤት የተባለ ሰውነትን በጽኑዕ ዓለት (በማናቸውም መከራ በማይናወጥ ሃይማኖት) ላይ መመሥረት ነውና።ማቴ፡፯፥፳፭።ሰማይም ምድርም ያልፋሉ ቃሉ ግን አያልፍም።ማቴ፡፭፥፲፰።
          ቅዱሳን ነቢያትን ከሁሉ አስቀድሞ የተቀበላቸው እግዚአብሔር ነው።ከማኅፀን ጀምሮ የመረጣቸውና ሀብተ ትንቢትን ያሳደረባቸው እርሱ ነው።ኤር፡፩፥፭።የልጁን  (በተዋህዶ የከበረ የኢየሱስ ክርስቶስን) መልክ እንዲመስሉ የወሰነላቸው (ያዘጋጃቸው)፥ ያጸደቃቸውና ያከበራቸው እርሱ እግዚአብሔር ነው።ሮሜ፡፰፥፴፭።እነርሱም በጾምና በጸሎት ተወስነው በብዙ መሥዋዕትነት አገልግለውታል።ዕብ፡፲፩፥፴፯።በዚህም በምድር በረከትን፥በሰማይ ደግሞ የዘለዓለምን ሕይወት አግኝተውበታል።ራእ፡፮፥፲፩።
.
          ቅዱሳን ነቢያትን የምንቀበለው እንዴት ነው? ሃይማኖት ላለው ሰው ይህ ጥያቄ አይከብደውም።ምክንያቱም እነርሱን መቀበል ማለት፦ሃይማኖታቸውን፥ምግባራቸውን፥ትሩ ፋታቸውን፥መጻሕፍቶቻቸውን፥ቃል ኪዳናቸውን፥አማላጅነታቸውን፥ጾም እና ጸሎታቸውን ጭምር አምኖ መቀበል መሆኑን ያውቃል።ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው (በተዋህዶ ሰው በሆነበት ዘመን) ጾማቸውን ሲጾም፥ጸሎታቸውንም ሲጸልይ እናገኘዋለን።ነቢያቱ፦ ሙሴ፥ ኤልያስ፥ሕዝቅኤልና ዕዝራ ፵፣፵ ዕለት የጾሙትን ጾም፦ሳይጨምር ሳይቀንስ ፵ መዓልት እና ፵ ሌሊት ጾሟል።ምክንያቱም የተቀበላቸው እስከ ጾማቸው ነውና።ዘጸ፡፳፬፥፲፰፣፩ኛ፡ነገ፡፲፱፥፬፣ሕዝ፡፴፯፥፩፣ዕዝ፡ሱቱ፡፲፫፥፳፫፣ማቴ፡፬፥፩።ጸሎታቸውን ሲጸልይ ደግሞ፦ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ፦”አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ፤”ብሏል።መዝ፡፳፩፥፩፣ማር፡፲፭፥፴፬።
.
             ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦እከብር አይል ክቡር፥እጸድቅ አይል ጻድቅ ሲሆን የጾመውና የጸለየው፦እርሱን አብነት አድርገን ጾመ ነቢያትን እንድንጾም እና ጸሎተ ነቢያትን እንድንጸልይ ነው።ይኸውም እኛ በነፍስም በሥጋም እንጠቀም ዘንድ ነው።ለዚህም ነው፦”ነቢይን በነቢይ ስም የተቀበለ (በስማቸው የተማጸነ፥በአማላጅነታ ቸው የታመነ፥ቃል ኪዳናቸውን ተስፋ ያደረገ፥ጾማቸውን የጾመና ጸሎታቸውን የጸለየ) የነቢዩን ዋጋ ይወስዳል፤”ያለው።የእነርሱ ዋጋ ከላይ እንደ ተናገርነው ከምንም በላይ የሆነው የዘለዓለም ሕይወት ነው።” ... ደስ ይበላችሁ፥ሐሴትንም አድርጉ፥ዋጋችሁ በሰማያት ብዙ ነውና፥ ከእናንተ አስቀድሞ የነበሩ ነቢያትንም እንዲሁ አሳድደዋቸው ነበርና፤”ይላል።ማቴ፡፭፥፲፪።
.
          እንግዲህ ቅዱሳን ነቢያትን መቀበል ጾማቸውን ጭምር መቀበል መሆኑን አምነን፥ እነርሱ ያገኙትን በረከት ለማግኘት፥ከገቡበት ውሳጤ መንጦላዕትም ለመግባት ጾመ ነቢያትን እንጹም።ይህ ከጌታ በዓለ ልደት አስቀድሞ፦ከመንፈቀ ኅዳር (ከኅዳር ፲፭ ቀን) ጀምሮ የሚጾመው ጾም ከሰባቱ አጽዋማት እንዱ ነው።ቅዱሳን ነቢያት “ይወርዳል ይወ ለዳል፤” እያሉ በተስፋ እንደጾሙት እኛም ከበዓለ ልደት አስቀድመን እንጾመዋለን።የጾሙን በረከት ያሳድርብን።
“መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያደርሰንም (አያቀርበንም)፥ብንበላም አይረባንም፥ ባንበላም አይጎዳንም።” ፩ኛ፡ቆሮ፡፰፥፰።
.
ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

22 Nov, 06:41


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 የዩቲዩብ ገፅ
https://www.youtube.com/@weludebirhan9612
👉 የፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/saintkirkosweludebirhan/
👉 የቴሌግራም ገፅ
https://t.me/weludebirhan
👉 የቲክቶክ ገፅ
https://www.tiktok.com/@weludebirhan?_t=8fSm647llUD&_r=1

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

21 Nov, 03:54


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 የዩቲዩብ ገፅ
https://www.youtube.com/@weludebirhan9612
👉 የፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/saintkirkosweludebirhan/
👉 የቴሌግራም ገፅ
https://t.me/weludebirhan
👉 የቲክቶክ ገፅ
https://www.tiktok.com/@weludebirhan?_t=8fSm647llUD&_r=1

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

19 Nov, 06:31


👉ማስታወሻ:-ትኬቱን በምግባረ ሰናያት ክፍል አገልጋዮች እጅ እና በሰንበት ት/ቤቱ
መዝሙር ቤት ያገኛሉ።

➡️ለበለጠ መረጃ የሚመለከተውን አካል ያናግሩ
           በ0978102785 /094 425 3623

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

18 Nov, 09:21


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።
የውሉደ ብርሃን ሰ/ት ቤት አባ ክፍለ ዮሐንስ ቤተ መጽሐፍ ክፍልን አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሻገር በማሰብ በቀን ፰/፫/፳፻፲፯.ዓ.ም በቁጥር 9 ለሚሆኑ የክፍሉ አገልጋዮች መሰረታዊ የቤተ መጽሐፍ አገልግሎት (ላይብረሪ ሳይንስ) ስልጠና የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት ቤት አገልጋይ በሆነው  ዲ/ን ኤልያስ ተሰጠ።

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

17 Nov, 15:19


ዛሬ የሰንበት ጉባኤ ሕዳር ፰/፳፻፲፯ ዓ.ም. እንደዎትሮ ተከናውኖ ውሏል።

ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 የዩቲዩብ ገፅ
https://www.youtube.com/@weludebirhan9612
👉 የፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/saintkirkosweludebirhan/
👉 የቴሌግራም ገፅ
https://t.me/weludebirhan
👉 የቲክቶክ ገፅ
https://www.tiktok.com/@weludebirhan?_t=8fSm647llUD&_r=1

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

15 Nov, 19:42


ዓርብ ህዳር 06 ቀን 2016 ዓ.ም
ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንስ የማያይ ማን ነው
መዝ 89፣48
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ፣ምህረትና ቸርነት፣ ፍቅርና አንድነት በዓለማችን፣ በሀገራችን፣ በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን
የወንድማችን አንዱዓለም አድባሩ
አጭር የሕይወት ታሪክ (ዜና መዋዕል)
ወንድማችን አንዱዓለም አድባሩ (ወልደጊዮርጊስ) የተወለደው በአዲስ አበባ ከተማ በ1960 ዓ.ም. ሲሆን ዕድሜ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተምሯል፡፡

ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ተከታታይ ትምህርት (ኮርስ ) ከተማረ በኋላ በተለያዩ ክፍሎች በአገልጋይነት ተመድቦ እና በመዘምራንነትም ሲያገለግል የነበረ ወንድማችን ነበር፡፡

ወንድማችን ወልደጊዮርጊስ (አንዱዓለም አድባሩ) በነበረበት የአካል ጉዳት ሳያማርር አቅሙ በቻለ ኑሮን ለማሸነፍ ራሱን ለማስተዳደር ጥረት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ከተወሰኑ ወራት ወዲህ በአደረበት ህመም በጸበል እና በህክምና ሲረዳ ቆይቷል፡፡
በሥጋ ቅርብ የሆኑ ቤተሰቦች በአቅራቢያው ስላልነበሩ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ከእርሱ ጋር በመነጋገር ከነበረበት ህመም አንጻር የተሻለ ሕክምና እና እንክብካቤ ወደሚያገኝበት መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል ከመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲገባ በማድረግ ሲረዳ ቆይቶ ትናንት ሐሙስ ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን ሆነና ከዚህ ሥጋዊ ድካም ተጠራ፡፡
ሰው ሥጋዊ ፍጥረት በመሆኑ፡ ሕማምና ድካም የማይለየው ስለሆነም፡ በዚህ የወንድማችን እረፍት ሞት ሰውን እንደጥላው የሚከተለው መሆኑንም ተረድተናል፡፡
ቢሆንም የወንድማችን ስንብት ሥጋዊ እና ጊዜያዊ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ይህንንም ያልነው ያለበቂ ምክንያት አይደለም፡፡ በቂ ሕያውና ዘለዓለማዊ ምክንያት እና ምስክር ስላለን ነው፡ይኸውም፦
1ኛ፦ ሥጋዊ ያልንበት ምክንያት፡ ምንም እንኳን ከወንድማችን ወልደጊዮርጊስ ጋር ለጊዜው በሥጋ የተለያየን ቢሆንም፡ በእውነትና በመንፈስ ፡ እንዲሁም በነፍስ ግን፡ ዘለዓለማዊ አንድነትና ተዋሕዶ ያለን በመሆኑ ነው፡፡
2ኛ፦ ጊዜያዊ ያልነው ደግሞ፡ ይህንኑ ሥጋዊውን መለየት ብቻ ሲያመለክት፤ እርሱም ቢሆን በጣም አጭርና ጊዜያዊ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡
ወንድማችን አንዱዓለም አድባሩ ከታመመ ጊዜ ጀምሮ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ምግባረ ሠናያት ክፍል እና አንዳንድ አባላት በማስታመም እና በተለያየ መልክ በማገዝ ፣እንዲሁም ህመሙ የቅርብ አስታማሚ የሚፈልግ በመሆኑ የተሻለ ህክምና እንዲያገኝ ወደ መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እንዲገባ በተለያየ መልኩ ለተረዳችሁ፣ዜና ዕረፍቱ ከተሰማ ጀምሮ መረጃው ለሚመለከታቸው ሁሉ እንዲደርስ በማድረግ እንዲሁም አስከሬኑን ከዚያ በመኪና ለማምጣት እንዲሁም የአስከሬን ሳጥን ለማዘጋጀት ለአንዳንድ ወጪዎች በገንዘብ ለረዳችሁ በዝማሬ ለተሳተፋችሁ መዘምራን በቀብሩ ላይ ለተገኛችሁ ሁሉ አምላከ ቅዱሳን ዋጋችሁን ይክፈላችሁ፡፡
በተለይም የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ወንድማችንን ላለፉት ስምንት ወራት በማስታመም ላደረገው ከፍ ያለ ዕገዛ እኛም ባለ ዕዳ ነንና ማዕከሉን ከማመስገን ጋር አቅማችን በፈቀደ መጠን እንድንረዳው ልናስታውስ እንወዳለን፡፡
የወንድማችን ወልደጊዮርጊስ (አንዱዓለም አድባሩ) ቀብር ዛሬ ህዳር 06 ቀን 2016 ዓ.ም በቅዱስ ዮሴፍ መካነ መቃብር ያገለገለበት የመካ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስያን ውሉደ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት መዘምራን እና አብሮ አደግ ጓደኞቹ በተገኙበት ተፈጸመ፡፡
አምላከ ቅዱሳን ነፍሱን በገነት ያሳርፍልን፡፡

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

14 Nov, 12:32


ዜና እረፍት

«ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንስ የማያይ ማን ነው?» መዝ.89:48

የሰንበት ት/ቤታችን አባል አንዱዓለም አድባሩ ባደረበት ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ወንድማችን በሰንበት ት/ቤታችን መዝሙር ክፍል እና በተለያዩ ክፍሎች ሲያገለግል ቆይቷል።

የወንድማችን አስክሬን ነገ ዓርብ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ከረፋዱ 5:00 በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ከደረሰ በኋላ ቀብሩ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6:00 የሚፈፀም መሆኑን እንገልፃለን።

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

04 Nov, 14:59


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 ዩቲዩብ
👉 ፌስቡክ
👉 ቴሌግራም
👉 ቲክቶክ

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

03 Nov, 18:31


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 ዩቲዩብ
👉 ፌስቡክ
👉 ቴሌግራም
👉 ቲክቶክ

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

03 Nov, 11:07


፳፫/፪/፳፻፲፯ ዓ.ም. በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የማህሌተ ጽጌ አምስተኛ ሳምንት ከፎቶ ማህደር

ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 ዩቲዩብ
👉 ፌስቡክ
👉 ቴሌግራም
👉 ቲክቶክ

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

28 Oct, 15:32


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 የዩቲዩብ ገፅ
https://www.youtube.com/@weludebirhan9612
👉 የፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/saintkirkosweludebirhan/
👉 የቴሌግራም ገፅ
https://t.me/weludebirhan
👉 የቲክቶክ ገፅ
https://www.tiktok.com/@weludebirhan?_t=8fSm647llUD&_r=1

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

27 Oct, 18:01


https://youtu.be/aV_4Gf9usPg?si=lQn4W9umwIWJi0sy

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

27 Oct, 16:13


የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ውሉደ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

የአባ ክፍለ ዮሐንስ ዘወልደ ማርያም መታሰቢያ ቤተ-መጽሐፍ የመጽሐፍ የአባላት ዕቁብ

* የአባላት የመጽሐፍት ንባብ ለማሳደግ እና ቤተ-መጽሐፉን በበለጠ ለማደራጀት ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ የአባላት እቁብ ሲሆን በዚ መሰረት በ ፳፻፲፯ (2017) ዓ.ም. ለመሳተፍ የምትፈልጉ ነባር የእቁብ አባላት እና አዳዲስ አባላት ከጥቅምት ፲ (10) - ጥቅምት ፲፯ (17) እንድትመዘገቡ እያልን እቁቡ ሦስት መደቦች ሲኖሩት

1ኛ ባለ 1020 ብር 20 ብር ለቤተ መጽሐፉ
2ኛ ባለ 520 ብር 20 ብር ለቤተ መጽሐፉ
3ኛ ባለ 320 ብር 20 ብር ለቤተ መጽሐፉ

* እቁቡ ከ ጥቅምት እስከ ነሐሴ ለ11 ወራት የሚቆይ ሲሆን አንደኛው ዕጣ ለቤተ መጽሐፉ የመጽሐፍ ማደራጃ የሚወጣ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- እቁቡን ጀምሮ በቂ ባልሆነ ምክንያት ለተከታታይ ሶስት ወራት ያልጣለ እጣ ውስጥ የማይገባ ሲሆን እንዲሁም ለአምስት ተክታታይ ወራት ያልጣለ አባል እንዳቋረጠ ተቆጥሮ የጣለው ብር ተመላሽ የማይደረግ እና ለቤተ መሐፍቱ ገቢ የሚሆን መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ለመመዝገብ፡- 0919834565
እንዳለ ሴሳ

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

27 Oct, 04:15


፲፮/፪/፳፻፲፯ ዓ.ም. በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የማህሌተ ጽጌ አራተኛ ሳምንት ከፎቶ ማህደር

ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 ዩቲዩብ
👉 ፌስቡክ
👉 ቴሌግራም
👉 ቲክቶክ

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

24 Oct, 18:58


👉የሚያስፈልጉ ነገሮች👇
1,ወራጅ እንጨት ብዛት 6×300=1800
2,ቃሚ እንጨት ብዛት 5×250=1250
3,ቃሚ እንጨት ማገር 2 እስር ×600=1200
4,ቆርቆሮ ብዛት 20×700=14000
5, የእንጨት ሚስማር  1 ከግማሽ=420
6,የቆርቆሮ ሚስማር  1 ከግማሽ=330
7.የኤሌክትሪክ ገመድ 2.5 10×50=500
8.አንፓል ትልቁ 2×250=500
9.ማብሪያ ማጥፊያ 1×50=50
👉አጠቃላይ ወጪ  (ሃያሺ ሀምሳ ብር) 20.050

           ባሉበት ሆነው አማራጩን
          በመጠቀሞ ድጋፍ ያድርጉ👇

👉7000062151108 በንብ ባንክ
ደጀኔ መራ እና ተመስገን አለሙ  እና አየለ ሞላ

እግዚአብሔር ይስጥልን እናመሰግናለን
        
           የምግባረ ሰናያት ክፍል!

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

24 Oct, 08:37


ዜና እረፍት
.
በሰንበት ትምህርት ቤታችን የ7 ዙር ተማሪ የነበረው እና ለረዥም ዓመት በመዝሙር ክፍል እና በተለያዩ ክፍላት ላይ ያገለገለው መንፈሳዊ ወንድማችን አለማየሁ ጉልላት በአደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ሥርዓተ-ቀብሩ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ቀን 14/02/2017 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይፈፀማል፡፡

አምላከ ቅዱስ ቂርቆስ ነብሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን፡፡ ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናት ያድልልን፡፡
.
የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ውሉደ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

23 Oct, 13:46


ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 የዩቲዩብ ገፅ
https://www.youtube.com/@weludebirhan9612
👉 የፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/saintkirkosweludebirhan/
👉 የቴሌግራም ገፅ
https://t.me/weludebirhan
👉 የቲክቶክ ገፅ
https://www.tiktok.com/@weludebirhan?_t=8fSm647llUD&_r=1

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

23 Oct, 09:08


የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ውሉደ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

የአባ ክፍለ ዮሐንስ ዘወልደ ማርያም መታሰቢያ ቤተ-መጽሐፍ የመጽሐፍ የአባላት ዕቁብ

* የአባላት የመጽሐፍት ንባብ ለማሳደግ እና ቤተ-መጽሐፉን በበለጠ ለማደራጀት ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ የአባላት እቁብ ሲሆን በዚ መሰረት በ ፳፻፲፯ (2017) ዓ.ም. ለመሳተፍ የምትፈልጉ ነባር የእቁብ አባላት እና አዳዲስ አባላት ከጥቅምት ፲ (10) - ጥቅምት ፲፯ (17) እንድትመዘገቡ እያልን እቁቡ ሦስት መደቦች ሲኖሩት

1ኛ ባለ 1020 ብር 20 ብር ለቤተ መጽሐፉ
2ኛ ባለ 520 ብር 20 ብር ለቤተ መጽሐፉ
3ኛ ባለ 320 ብር 20 ብር ለቤተ መጽሐፉ

* እቁቡ ከ ጥቅምት እስከ ነሐሴ ለ11 ወራት የሚቆይ ሲሆን አንደኛው ዕጣ ለቤተ መጽሐፉ የመጽሐፍ ማደራጃ የሚወጣ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- እቁቡን ጀምሮ በቂ ባልሆነ ምክንያት ለተከታታይ ሶስት ወራት ያልጣለ እጣ ውስጥ የማይገባ ሲሆን እንዲሁም ለአምስት ተክታታይ ወራት ያልጣለ አባል እንዳቋረጠ ተቆጥሮ የጣለው ብር ተመላሽ የማይደረግ እና ለቤተ መሐፍቱ ገቢ የሚሆን መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ለመመዝገብ፡- 0919834565
እንዳለ ሴሳ

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

20 Oct, 11:23


https://youtu.be/3TJjaUUIk60?si=NIV3AWGzCSsGYj-E

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

20 Oct, 04:03


፱/፪/፳፻፲፯ ዓ.ም. በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የማህሌተ ጽጌ ሦስተኛ ሳምንት ከፎቶ ማህደር።

ለቤተሰብ ለወዳጅ ያጋሩ።


ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

👉 የዩቲዩብ ገፅ
https://www.youtube.com/@weludebirhan9612
👉 የፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/saintkirkosweludebirhan/
👉 የቴሌግራም ገፅ
https://t.me/weludebirhan
👉 የቲክቶክ ገፅ
https://www.tiktok.com/@weludebirhan?_t=8fSm647llUD&_r=1

3,142

subscribers

9,304

photos

59

videos