🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸 @hamdquante Channel on Telegram

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

@hamdquante


ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።

እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante

አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸 (Amharic)

አሁን የመልካም ቋንጤ እና ሐዲስ መሰረት የመከታተል ስለ እስልምና እና አማራጭ መፍትሔ ቻናል ነን። በተጨማሪ አሁን የመልካም ይዞታዎችን የምንመካከርበት እና የምንማማርበት ያለው ማንኛውንም ይደምስስ እና በአንዲት ማድረግ አሁን ይገናኘዋል። እንምሰልን በቻናሉስ ከሚገኘው በጣም በ @hamdquante_bot ውስጥ መጠቀም ይገባል።

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

07 Dec, 18:33


📞እህታችን አፋልጉልን!!

   "እህታችን ካሚላ ሰመሩ ዛሬ ረፋድ አካባቢ ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም፤ የደረሰችበት የገጠማት ማወቅ አልቻልንም። ከቤት ከወጣችበት ሰዓት ጀምሮ ፍለጋው የተጀመረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የት እንዳለች ማወቅ አልተቻለም። በዚህም ሁሉም ቤተሰብ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል። ስለሆነም ለአላህ ብላችሁ ተባበሩን!!"
ይላሉ ቤተሰቦቿ


ስሟ:   ካሚላ ሰመሩ ስትሆን
     አጠር ብላ ጠየም ያለች ናት።


ከቤት ስትወጣ የለበሰችው:  ሰማያዊ ሺቲ እና ጥቁር ጃኬት ነበር፤ ጃኬቱ ባለ ኮፍያ ሲሆን ኮፍያው ጋ ጥጥ ነገር አለው።

ትኖርበት የነበረው ሰፈር: አዲስ አበባ "ፉሪ" ነበር



👌እህታችን ቲንሽ የአእምሮ ህመም ያለባት መሆኗ የበለጠ ጉዳዩ አስጨናቂ ስላደረገው: የተጠቀሰው ዐይነት ምልክት ያያችሁ ሁሉ ሰብዓዊ ትብብራችሁ እንድታደርጉላቸው ቤተሰቦቿ በአላህ ስም ይጠይቃሉ!!

📞የወንድሟ ስልክ
       +251922961904  ዐብዱል ፈታሕ





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

07 Dec, 17:34



ሱቁ በራፍጋ የተሰለፈው ህዝብ ሳይ እኮ ሻማ ያለቀ መስሎኝ ነበር;

ለካስ…………
ሻማው አለ: ግን ደረሰኙ በምን ይቁረጠው??




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

07 Dec, 17:04


🇪🇹
የአባይ ልጅ የውሀ  ጥማቱን ሳይቆርጠው
የህዳሴውን ልጅ ጨለማውን ዋጠው??




🕯ባለ ሱቅ ሻማ አቀብለኝ

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

07 Dec, 16:41



     ከብዙ ሙስሊም ሴቶች የሚገርመኝ ባህሪ………

  ጅምር ላይ አንገት ደፊ እና ሼመኛ ዐይነት ነገር ይሆኑና;
  ልክ ለፊታቸው ቢጫ ዱቄት፣ ለከንፈራቸው ቀይ ቀለም መግዛት የሚችሉበት ደሞዝ ማግኘት ሲጀምሩ:
  አኽላቃቸው እና ማንነታቸው ጥለው ከቁጥጥር ውጭ የሚሆኑት ነገር ነው።



ውበትሽ እርጋታሽ ላይ ነው ያለው እቴዋ!!

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

07 Dec, 16:04



   አዩብ አስ-ሲኽቲያኒ እንዲህ አለ

  አንድ ሰው ሁለት ባህሪያት እስኪኖረው ድረስ ክቡር አይሆንም…...
1ኛ, ከሰዎች እጅ መብቃቃት
      እና

2ኛ, ከእነሱ የሚደርስበት ሙሲባ በይቅር ባይነት ማለፍ።




👌በምንም ነገር ላይ ጥገኛ አትሁን!!

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

07 Dec, 15:44



አንድ ወንድ ፂሙን በመላጨቱ ብቻ 4 ዐይነት ወንጀሎች ይሰበስባል፦

🔥የረሱልﷺ ትዕዛዝ ይቃረናል፤
🔥በከሃዲያኖች ይመሳሰላል፤
🔥በሴቶች ይመሳሰላል፤
🔥ሸይጣንን ይታዘዛል!!




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

07 Dec, 14:11



    እስልምና የሁሉም ነብያቶች ጥሪ!!

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና ሩኅሩኅ በሆነው:
  የምድር የሰማይ ብቸኛ ፈጣሪ የሆነው አላህ የደነገገው፤ ነብያቶች ወደ ህዝቦቻቸው ያስተላለፉት፤ ፍትሕ እና ሰላም የሚረጋገጥበት፤ የተቀበለው ሲድን የተቃወመው የሚከስርበት ሰማያዊ የሆነ ሐይማኖት እስልምና ብቻ ነው!!

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፦
📖{إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ}
{አላህ ዘንድ (የተደነገገ) ሐይማኖት ኢስላም ብቻ ነው።}

     [አል_ኢምራን¹⁹]


🟤የነብዩ ዒሳﷺ እና የሐዋርያዎቹ ሐይማኖት……
📖{فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ}
{ዒሳ ከነርሱ ክህደትን በተመለከተ ጊዜ "ወደ አላህ ረዳቴ ማን ነው" አለ። ሐዋርያት "እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህ አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ ሙስሊሞች መሆናችንን መስክር" አሉ።}

   [አል_ዒምራን:⁵²]


🟤የፊርዐውን ደጋሚዎች አምነው የተደፉለት ሐይማኖት……
📖{وَمَا تَنقِمُ مِنَّآ إِلَّآ أَنْ ءَامَنَّا بِـَٔايَٰتِ رَبِّنَا لَمَّا جَآءَتْنَا ۚ رَبَّنَآ أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًۭا وَتَوَفَّنَا مُسْلِمِينَ}
{የጌታችን ተኣምራቶች በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በቀር ከእኛ አትጠላም፡፡ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ፡፡ ሙስሊሞች ሆነን ግደለን፡፡}

    [አል_አዕራፍ:¹²⁶]


🟤ነብዩ ሱለይማንﷺ ንግስቷን የተጣራበት ሐይማኖት……
📖{أَلَّا تَعْلُوا۟ عَلَىَّ وَأْتُونِى مُسْلِمِينَ}
{በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ሙስሊሞችም ሆናችሁ ወደኔ ኑ።}

  [አል_ነምል: ³¹]


🟤የነብዩ ኢብራሂምﷺ ሐይማኖት……
📖{مَا كَانَ إِبْرَٰهِيمُ يَهُودِيًّۭا وَلَا نَصْرَانِيًّۭا وَلَٰكِن كَانَ حَنِيفًۭا مُّسْلِمًۭا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ}
{ኢብራሂም የሁዳም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን ወደ ቀጥተኛው ሐይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡}

    [አል_ዒምራን:⁶⁷]


🟤የነብዩ ኑኅﷺ ሐይማኖት……
📖{وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُسْلِمِينَ}
{ከሙስሊሞች እሆን ዘንዳ ታዝዣለሁ።}

     [ዩኑስ:⁷²]


🟤የነብዩ ሙሳﷺ ሐይማኖት……
📖{وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰقَوْمِ إِن كُنتُمْ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوٓا۟ إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ}
{ሙሳም አለ፡ "ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ: ሙስሊሞች የሆናችሁ እንደ ሆነ: በአላህ ላይ ተመኩ፡፡"}

     [ዩኑስ:⁸⁴]


🟤የሌሎችም ነብያቶች ሐይማኖት……
📖{شَرَعَ لَكُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِۦ نُوحًۭا وَٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِۦٓ إِبْرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰٓ ۖ أَنْ أَقِيمُوا۟ ٱلدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا۟ فِيهِ ۚ كَبُرَ عَلَى ٱلْمُشْرِكِينَ مَا تَدْعُوهُمْ إِلَيْهِ ۚ ٱللَّهُ يَجْتَبِىٓ إِلَيْهِ مَن يَشَآءُ وَيَهْدِىٓ إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ}
{ለእናንተ ከሐይማኖት ያንን በእርሱ ኑኅን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፤ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን: ሐይማኖትን በትክክል አቁሙ፤ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ (እምነት) ይመርጣል፤ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል፡፡}

    [አል_ሹራ: ¹³]


🟤የሁሉም ነብያቶች ሐይማኖት……
📖{قُلْ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَآ أُنزِلَ عَلَىٰٓ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطِ وَمَآ أُوتِىَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍۢ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ}
{"በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም (በቁርኣን)፣ በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ በነገዶችም ላይ በተወረደው፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው (አመንን)፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች (ሙስሊሞች) ነን" በል፡፡}

      [አል_ዒምራን:⁸⁴]



እስልምና፦
   የዓለማት ብቸኛ ፈጣሪ እና አስተናባሪ ከሆነው አላህ ዘንድ: ወደ ባሮቹ የተላለፈው ብቸኛው ሐይማኖት እሱ በመሆኑ;
   ከእስልምና ሌላ ሐይማኖት መንገድ አድርጎ ለያዘ ሰው ምንም ዐይነት ተቀባይነት አይኖረውም።
📖{وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًۭا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْءَاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ}
{ከኢስላም ሌላ ሐይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይነት የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው።}

     [አል_ዒምራን:⁸⁵]


👌ከነብዩ ኑኅﷺ ጀምሮ፣ ከእሱ በፊት ኣደም እና ልጆቹ፣ እንዲሁም አጠቃላይ ስማቸው የተነገረንም ይሁኑ ያልተነገሩን ነብያቶች በአጠቃላይ የተላኩበት እና ጌታቸውን ሲያመልኩበት የነበረው ብቸኛው እና እውነተኛው ሐይማኖት እስልምና ብቻ ነው!!

   ከነብዩ ሙሐመድﷺ በፊት የተላኩ ነብያቶች የተለያየ የሆነ መፅሐፍ እና ድንጋጌ ቢሰጣቸውም በመሰረታዊነት የተላኩት ግን ሁሉንም በእስልምና ላይ ነው።
ለምሳሌ………
   አሰጋገዳቸው፣ የጾማቸው ስርዓት፣ እና የመሳሰሉ የአምልኮ ተግባሮች የአንዱ ነብይ ስርዓት ከሌላው ሊለይ ይችላል፤ ይሁን እንጂ በሁሉም ነብያት ስርዓት የሚሰገደውም ይሁን የሚጾመው ብቸኛ ለሆነው ለልዕለ ሀያሉ አላህ ነው!!


እንደ ቀን ጨረቃ፦
   ግልፅ እና ብርኃናማ ለሆነው እስልምና ለወፈቀን አላህ ምስጋና እያደረስን: ከዚህ መንገድ በተቃራኒ ላሉት ሁሉ አላህ በዕዝነቱ እንዲመራቸው የዘወትር ምኞት እና ጥሪያችን ነው!!





🖊አቡ ሙSሊM ሐምዱ ቋንጤ
        ከፉርቃን ሰማይ ስር!!

https://t.me/islmina_min_ale
👆
👇
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

07 Dec, 05:57



ልታገኘው የምትፈልገው ወርቅ የሚገኘው
ልትገባበት ከምትፈራው ዋሻ ውስጥ ነው!!




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

05 Dec, 15:00


👇
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

05 Dec, 08:39


🎧
    አል_አዕራፍ መሃከለኛው ከፍታ!!


     ከማንበብ ይልቅ ማድመጥ ለሚቀናችሁ

    አንባቢው 🤝ጀዛከላሁ ኸይረን!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

05 Dec, 05:07



የመንገዱ መጥበብ የቁልፎቹ መብዛት ያለው መሰናክል
ውስብስቡን ዐይቼ ተስፋ እቆርጥና አብቅቶልኛል ስል፤

የጀሊሉ ፈረጅ በጥበብ ተሞልቶ ዕዝነት ታክሎበት
ባላሰብኩት መልኩ ሕይወቴ ሰምሮልኝ አየዋለሁ ድንገት።


አላሁመ ለከ አምሮ የገዘፈ ምስጋናና ሽኩር
ፀጋህ አመስግኜ ፈተናህ ማልፍበት አጎናፅፈኝ ሰብር!!

🔓ثم فرجت



https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

04 Dec, 17:58


🤲 يَا رَبِّ لَكَ الْحَمْدُ……
كَمَا يَنْبَغِي لِجَلَالِ وَجْهِكَ , وعظيم سُلْطَانِكَ!!




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

04 Dec, 04:31


♻️
  የማይታይ ብርኃን  የማይሰማ ጩኸት
የማይገለፅ ስሜት  የማይኖር ነፃነት፤

የማይፈታ ቅኔ  ትርጉም አልባ ተረት
የዱንያ እንቆቅልሽ  ይህ ነው የኔ ሕይወት!!

እኔም አልገባኝም!!


https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

03 Dec, 18:03



   አንዲት ሴት ተገላልጣ በመውጣቷ ብቻ ከምትሰበስባቸው ወንጀሎች ውስጥ……
🔥የመገላለጧ ወንጀል፣
🔥ወደ እሷ የሚመለከቱት ወንጀል፣
🔥ልባቸውን ያበላሸችባቸው ወንጀል፣
🔥በዚህ አርኣያ የሚያደርጓት ወንጀል፣
🔥በእሷ ሰበብ ሀራምን የሚያፈላልጉት ወንጀል፣
🔥ልጆቻቸው ያበላሸችባቸው ወላጆች እርግማን፣

🔥እና የመሳሰሉት



📞እህት ኣለም………
ማንነትሽ ተከብሮ: ዋጋሽ ጨምሮ ተፈላጊነት ማግኘት የምትችይው;
ሐያሽን ተላብሰሽ ጌታሽን ስትታዘዢ ነው።


🔥ሐያሽ ከተወገደ………
አንቺ ማለት ለገበያ የቀረበ ርካሽ ቁስ ነሽ!!






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

01 Dec, 16:02



አንድም ሰው አእምሮው ላይ ጉድለት ቢኖርበት እንጂ;
ከአኼራ ዱንያ ሊያስቀድም አይችልም!!

/ኢማሙ ሲዕዲ/




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

01 Dec, 15:51


🤲
     አላሁመ………

ሁሉም "ይጠቅመኛል" ወደ ሚለው ሲጠጋ;
አንተን  መርጠን ወደ አንተ ሸሽተናል !!

                🤲اللهم يسر لنا🤲





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

01 Dec, 13:27



አንድ ሰው ከዐይንህ እንዲርቅ ከፈለክ:

ብር አበድረው;
አሊያም
ብድር ጠይቀው ይላሉ።


اللهم أغننا من فضلك العظيم!!

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

01 Dec, 10:10



ድብቅ ወንጀሎች…………

ከአላህ መልእክተኛ እንዲህ ተላልፏል፦
«لَأَعْلَمَنَّ أَقْوَامًا مِنْ أُمَّتِي يَأْتُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ بِحَسَنَاتٍ أَمْثَالِ جِبَالِ تِهَامَةَ بِيضًا فَيَجْعَلُهَا اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ هَبَاءً مَنْثُورًا»
«ከህዝቦቼ ውስጥ (እንዲህ እንደ ሚሆኑ) የማውቃቸው ሰዎች አሉ; የቂያማ ቀን "ቲሀባ" እንደ ተባለው ተራራ የገዘፈ መልካም ስራ ይዘው ይመጣሉ፤ አላህ የተበተነ አቧራ ያደርግባቸዋል።»


ከባልደረቦቻቸው አንዱ:
«يَا رَسُولَ اللَّهِ صِفْهُمْ لَنَا جَلِّهِمْ لَنَا أَنْ لَا نَكُونَ مِنْهُمْ وَنَحْنُ لَا نَعْلَمُ »
«የአላህ መልእክተኛ ሆይ እኛም ሳናውቅ ከእነርሱ እንዳንሆን ምን ዐይነት እንደ ሆኑ ግለፁልን አብራሩልን»
አላቸው።

«أَمَا إِنَّهُمْ إِخْوَانُكُمْ وَمِنْ جِلْدَتِكُمْ وَيَأْخُذُونَ مِنْ اللَّيْلِ كَمَا تَأْخُذُونَ وَلَكِنَّهُمْ أَقْوَامٌ إِذَا خَلَوْا بِمَحَارِمِ اللَّهِ انْتَهَكُوهَا»
«እነርሱ ማለት፦ ወንድሞቻችሁ ናቸው፤ ከእናንተው ቆዳ ናቸው (የተለዩ አይደሉም)። ለሊት እንደ ምትሰግዱት እነርሱም ይሰግዳሉ። ነገር ግን
እነርሱ (ከሰው) ሲነጠሉ አላህ ዕርም ያደረጋቸው ነገሮችን ይዳፈራሉ።»

ብለው መለሱላቸው።


ለዚህም ዑለማዎች አንድ ሰው……
ለመንሸራተቱ
ጀሀነም ለመውረዱ
የቂያማ ቀን ለመክሰሩ

ምክንያት ይሆኑታል ብለው ከሚጠቅሷቸው ትላልቅ ነጥቦች አንዱ ይህ ከሰዎች ሲነጠል የሚፈፅመው ወንጀል ነው። ይላሉ




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

30 Nov, 15:06


🔥
     ድብቅ ወንጀሎች………

   ለብቻህ ስትነጠል የምትሰራቸው ዒባዳዎች ለፅናት ሰበብ እንደ ሚሆኑህ ሁሉ;
    ለብቻህ ስትነጠል የምትሰራቸው ወንጀሎች ለመንሸራተት ምክንያት ይሆኑሃል!!




   ታላቁ የሙስሊሞች መሪ የነበረው ዑመር ቢን ዐብዱል ዐዚዝ እንዲህ ይል ነበር፦
  "ከሰዎች ጋ ሲሆን ሸይጣን የሚራገም; ከሰዎች ሲሰወር ሸይጣን የሚታዘዝ አትሁን!!"






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

30 Nov, 06:36



እጅግ በጣም አስፈሪ የሆነ ማስጠንቀቂያ ነው!!

"لا تجعل الله أهون الناظرين إليك"
አላህ ወዳንተ ከሚመለከቱት ሁሉ የቀለለው አታርገው!!



ምን ማለት እንደሆነ ገብቶሃል??………
   አላህ የማይወደው፣ ሰዎች የሚጠየፉት፣ ባህል የሚቃረን፣ ማንነት የሚያረክስ የሆነ ወንጀል:
መስራት እንደሌለብህ ውስጥ እያወቀም በስሜት እና በሸይጣን ተሸንፈህ ልትሰራ ትችላለህ; ይህንን የምታፍርበት እና የምትሳቀቅበት ወንጀል በምትሰራው ጊዜ ቤተሰቦችህ፣ ጓደኞችህ፣ ጎረቤቶችህ፣ የምታውቃቸውም ይሁን የማያውቁህ ሰዎች እንዳያዩህ ትጠነቀቃለህ ትደበቃለህ:
  ግን ልዕለ ሀያሉ: የሩቅ ነገርም ይሁን ድብቅ ሚስጥር የማይደበቅበት የሆነው አላህ እንደ ሚመለከትህ ውስጥህ እያወቀም ምን ዴንታ አይኖርህም።
በዚህ ጊዜ…………
  አላህ ወዳንተ ከሚመለከቱት ሁሉ የቀለለው አድርገኸዋል ይባላል።

ስትፈፅመው ሰዎች ቢያዩህ የምትሳቀቅበት ወንጀል;
  አላህ እያየህ ስትሰራው ምንም የማይመስልህ ልብህ ምንኛ ቢደርቅ ነው ከቶ???





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

29 Nov, 11:03



     ይህንን አስተውለው ኖሯል!!??………


📖{أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ}
{ወደ ግመል እንዴት እንደተፈጠረች አይመለከቱምን?}

  [አል_ጋሺያ:¹⁷]


ግመል ከሌሎች እንስሳቶች በተለየ መልኩ፦
ስጋዋ ይበላል፣
ወተቷ ይጠጣል፣
ሽንቷ ይፈውሳል፣
ለጭነት ያገለግላል፣
ለመጓጓዣነት ይውላል፣
ጥም እና ረሀብ ይታገሳል፣
ከበድ ያለ ጭነት ይሸከማል፣
ረዘም ያለ መንገድ ያቋርጣል፣




ከግመል ሌላ እነዚህን ሁሉ አገልግሎት ያሟላ እንስሳ ማግኘት የማይታሰብ ነው።



👇👇👇
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

29 Nov, 10:26



    ኸድር ዐለይኺ ሰላም…………
በአላህ ትዕዛዝ ህፃን ልጅ ገደለ፤ በገደለው ጊዜ ወላጆቹ ሲወልዱት ተደስተው በነበረው ልክ ልባቸው አዘነ:


ህፃኑ ባይገደል እና ቢያድግ ኖሮ………
  ወላጆቹ አኼራቸውም ዱንያቸውም የሚያሳጣቸው አመፀኛ ሊሆን ነበር።

ሁል ጊዜ…………
   የአላህ ውሳኔ በጥበብ እና በፍትሕ የተሞላ ነው!!


    ሁሌም አላህ የሚወስነው ለአንተ የተሻለው ነውና ውሳኔውን ውደድ!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

28 Nov, 17:56



ትዳር ከእብደት ለመጠበቅ ምክንያት እንደሆነው ሁሉ;
ላጤነትም ለእብደት ምክንያት ይሆናል።




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

28 Nov, 07:45



በጣም ሰቃቅለህ እንዲያዋርዱህ አትፍቀድላቸው;
በጣም አሳንሰህም አትበድላቸው፤

እነርሱ እነሱ እንዲሆኑልህ ልካቸውን ስጣቸው!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

27 Nov, 16:23



    እስልምና ብቻ………
ዓለምን አንድ ያደረገ እምነት‼️

  በዘር፣ በቋንቋ፣ በመልክም ይሁን በተክለ ቁመና የማይገናኙ፤ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ የሆኑ ሙስሊሞች የሆነ ቦታ ላይ ተገናኝተው;
💫ኢስላማዊ ሰላምታ ተለዋውጠው፤
💫ሰላታቸው አንድ ላይ ሰግደው፤
💫አንድ ላይ ጌታቸውን ለምነውና አውስተው፤
💫ከፊላቸው ለከፊላቸው ዱዐ ተደራርገው፤
💫በኢስላማዊ ሰላምታ ተሰነባብተው፤
💫በሁሉም ነገራቸው ተግባብተው ይለያያሉ‼️



♻️በተቃራኒው የሌላ እምነት ተከታዮች ግን;
💫የአንድ ሀገር ዜጋ ሆነው፣
💫በአንድ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ሆነው፤
👉ቋንቋቸው አማርኛና ኦሮምኛ ስለ ሆነ ብቻ ተስማምተው መቀደስ (ማስቀደስ) አቅቷቸው ሲጣሉ ለማየት ችለናል።

   ታድያ ሐበሻ እና ፈረንጅ ሆነው ከተገናኙ እንዴት ተግባብተው እንዴት ሊፀልዩ ነው⁉️


🟤በሁሉም የዓለም ክፍል ያሉ ሙስሊሞች በዓመት ውስጥ ሁለት በዓላት አሏቸው። እነዚህ በዓሎች በመላው ዓለም
💫በተመሳሳይ ቀን እና
💫በተመሳሳይ ስርዓት

ተከብረው ይውላሉ።
በሆነ ሀገር እየተከበረ በሌላ ሀገር የሚተው (የማይታወቅ) ኢስላማዊ በዓል (ስርዓት) የለም።
ምክንያቱም፦
እስልምና ማለት ለአጠቃላይ ለሰውና ለአጋንንት ወደ ጌታቸው እንዲዳረሱበት የተዘረጋላቸው መንገድ (እምነት) እንጂ የሆነ ሀገር ህዝቦች ወይም የሆነ ብሄር ህዝቦች ባህል መገለጫ አይደለም።


♻️በተቃራኒው የሌላ እምነት ተከታዮች ግን;
💫አንድ ሀገር ላይ የሚከበረው በዓል ሌላ ሀገር ላይ አይታወቅም።
ወይም
💫አንድ ሀገር ላይ የሚከበረው ሌላ ጊዜ; በሌላ ሀገር የሚከበረው ደግሞ በሌላ ጊዜ ይሆናል።
ለምሳሌ፦
ኢትዮጵያ ውስጥ ዓመት ሲቀያየር “ዘመነ ዮሃንስ፣ ዘመነ ሉቃስ” የሚባሉት በሌላው ዓለም የማይታወቁ ናቸው። እንዲሁም;
የፈረንጆች የገና በዓል እና የኢትዮጵያ የገና በዓል በተለያዩ ቀናቶች ነው የሚከበረው።


🟤በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች በአምላክነት ደረጃ የሚገዙት የሁሉም ፈጣሪ የሆነው አንድ አላህ ብቻ ነው። ከእሱ ውጪ ማንንም አምላክ አድርገው አይገዙም። ከአላህ ውጪ ያለን ማንኛውም አካል መለመን፣ መጣራት፣ ስለት መግባትም ይሁን ሌላ አምልኮ መስጠት በየትኛውም የዓለም ክፍል ቢፈፀም ከእስልምና ያስወጣል። ሙስሊሞች ዘንድ በሆነ ሀገር እየተመለከ በሌላ ሀገር የማይመለክ (የማይታወቅ) አምላክ ወይም መልኣክ የለም። ይህንን የሚፈፅም ካለ እንደ ተባባልነው ከእስልምና የወጣ ይሆናል።


♻️በተቃራኒው የሌላ እምነት ተከታዮች ግን;
የሚያመልኳቸው አማልክቶች ከመብዛታቸው እንደየ ሀገሩ ይለያያል። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚመለኩት በአጠቃላይ በሌሎች ሀገሮች አይገኙም። ወይ የራሳቸው ጨምረው ወይም ቀንሰው ያመልካሉ።
  ምን ይሄ ብቻ! ኢትዮጵያ ውስጥ ራሱ እንደየ ክልሉ ይለያያል። ለምሳሌ ትግራይ ውስጥ “አቡነ አረጋዊ” ብለው ያመልካሉ ሌሎች ክልሎች ላይ ግን ይህንን አለ ማምለክ ብቻም ሳይሆን ሲቃወሙትም ይታያሉ።

  እውን ያሉበት እምነት ወደ ፈጣሪ የሚያደርስ ከሆነ አንድ ፈጣሪ በሁሉም ዓለም ይመለካል እንጂ በክልል ተከፋፍሎ የሚመለክበት እምነት እንዴት ሊኖር ይችላል⁉️⁉️



🖊አቡ ሙስሊም ከፉርቃን ሰማይ ስር!!

  https://t.me/islmina_min_ale

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

27 Nov, 11:35



   ዱዐቶች ቸላ ያሉት እና ሙስሊሞች የተዘፈቁበት አደጋ
ልቅ የሆነ የሙስሊም ሴቶች የገበያ ውሎ

  በአሁን ሰዓት በየሚዲያው ከሚተላለፉ የሽያጭ ማስታወቂያዎች የበለጠ ሙስሊም ሴቶች በየመደብሩ አሰማርቶ የገበያ መሳቢያ ማድረግ የተለመደ ተግባር ሆኗል።

  ገበያ መውጣታቸው ብቻ የከፋ ጉዳይ ሆኖ ሳለ የሚወጡበት አወጣጥ ሲታይ ነገሩ እጅግ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱ ያሳያል።

  ያካበድኩ ሊመስላችሁ ይችላል; ግና… እውነታው ይህ ነው።
  ከቡቲክ እስከ ኤሌክትሮኒክስ መሸጫ: ከፋርማሲ እስከ ጌጣጌጥ መሸጫ ብትዘዋወሩ……
  ማንነት በሚቀይሩ ቀለማት ተቀባብተው አሳሳች በሆኑ አልባሳት የተፈተኑ ሙስሊም ሴቶች በየሱቁ በአስተናጋጅነት ተደርድረዋል። ይህ እጅግ በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳምም ጉዳይ ነው።

በእርግጥም………
   የኑሮ ሁኔታ ግድ ሆኖባቸው እና የቤተሰብ ሀላፍትና ተሸክመው በተለይ ደግሞ ከተለያዩ ክፍለ ሀገራት መጥተው ስራ ላይ የተሰማሩ ምስኪን እህቶቻችን እንዳሉ እሙን ነው።

  አነርሱ እንኳ አላህ የተሻለ መብቃቂያ ይስጣቸውና ባህሪያቸውም ይሁን አለባበሳቸው ለፊትና እንዳልተዘጋጁ ይመሰክራል።

  እነዝያ በቀለም ደምቀውና በሜካፕ ተሽሞንሙነው: ፈገግታቸውና ፊታቸው አይቶ ገዢ ለመሳብ የተዘጋጁ እህቶች አላህን ፈርተው ከመጥፋትም ከማጥፋትም ሊጠነቀቁ ይገባቸዋል።

  ከእነርሱ ጀርባ ያላችሁ አባቶችና ባሎችም; የሙስሊም ሴቶች ይበልጥ ንፅህናቸው ስለ ሚከጀል የአጥፊዎች ዐይን ዘወትር እንደ ሚከታተላቸው አውቃችሁ ሀላፍትናችሁ ልትወጡ ይገባችኋል።


    🖊አቡ ሙስሊም ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

27 Nov, 11:09


👇👇

ይህንን ተጭነው ጎራ ይበሉ!!

👆👆

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

27 Nov, 06:38


✍️
  በአሁኑ ሰዓት ሰላማዊ ሆኖ ለመኖር አስራ አንድ መፍትሔዎች አሉ።

   አስሮቹ; ከሰዎች መገለል ሲሆኑ
አስራ አንደኛው;  👉ዝምታ ነው!!


  https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

26 Nov, 16:28


👌
ሚፈፀመው እልቂት   ሚታየው ግድያ
ሁሉንም ተጠቅሷል   በረሱል ትንቢያ።

መንስኤው ተነግሯል  እንዲሁም መፍትሄው
ሽንፈቱንም ድሉም  ይጠብቃል ጊዜው።


ሽንፈቱ በወንጀል   ድሉ በተውበት
ተጣምሮ ይመጣል  ዕወቅ ይህን እውነት።


በወንጀልህ መዘዝ  የመጣው ሙሲባ
ካለቀስክ ይነሳል  የተውበት እንባ።

🖊H.K




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

25 Nov, 17:35


🤲ጌታዬ ሆይ የአንተ ነኝ
             ወደ ራሴ አታስጠጋኝ!!



https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

24 Nov, 18:01



   መች ነው ምታገባው⁉️

"እኔ ብሞት ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ነው ሌላ ሚስት የምታገባው?" ብላ ስትጠይቀው
"የቀብርሽ አፈር ሲደርቅ" አላት።

"ቃል ትገባልኛለህ?" አለችው
"አዎን!" አላት።


  ከጊዜ በኋላ ሚስት ትሞታለች። ባልም ሌላ ሚስት ማግባት ይፈልግና ሁሌም ጠዋት ጠዋት እየሄደ ቀብሯን ይጎበኛል።
  የመቃብሯ አፈር ሁሌም እርጥብ ሁኖ ያገኘዋል። ባልም "ይህማ ሙእጂዛ ነው!" ብሎ እየተገረመ ይመላለሳል።

  ከዕለታት አንድ ቀን አጋጣሚ በሌሊት ወደ መቃብሯ ሲሄድ ወንድሟን ቀብሯ አካባቢ ያገኘዋል።

"እዚህ ምን እየሰራህ ነው?" ሲለው
"የእህቴ ኑዛዜ እየፈፀምኩኝ ነው" አለው።

"ምንድን ነው የተናዘዘችልህ?" ሲለው
"በየቀኑ ወደ ቀብሯ እየመጣሁ በውሃ እንዳርሰው አደራ! ብላኝ ነበር"
{إِنَّ كَيْدَكُنَّ عَظِيمٌ}




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

24 Nov, 10:55



    ሁለት ዐይነት ሪዝቆች አሉህ; ጊዜያዊ እና ዘውታሪ ይባላሉ።


⚫️ጊዜያዊ ሪዝቅ ከሚባሉት ውስጥ፦
  ጤንነት, ዝርያ, ሀብት ንብረት, ትዳር, ስራ, ሀላፍትና እና የመሳሰሉ ዱንያዊ መጠቃቀሚያ ነገርች ይካተታሉ።
  እነዚህ አላህ በዱንያ ሕይወት ቆይታህ ትጠቃቀምባቸው ዘንድ አግርቶ ያመቻቸልህ ሪዝቆች ሲሆኑ: አላህ በፈለገው ጊዜ እነሱን በማንሳት ወይም አንተን በመውሰድ ከተጠቀሱ ሪዝቆችህ ጋ ያለያይሃል። ስለሆነም "ጊዜያዊ ሪዝቅ" ተብለው ይሰየማሉ።

⚫️ዘውታሪ ሪዝቅ ከሚባሉት ውስጥ፦
  ከለይል የምትሰግደው ሰላት ካለህ, ዱሃ ላይ የምትሰግደው, ከቁርኣን የምትቀራው, ከአዝካር የምታዘወትረው, ለወላጆችህ የምታደርገው እንክብካቤ, አጠቃላይ መልካም ስነ_ምግባርህ እና የመሳሰሉት ይካተታሉ።
  አላህ የዚህ ዐይነቱ ሪዝቅ ከወፈቀህ አጀልህ ሲደርስ ዱንያን ተሰናብተህ ብትወጣ እንኳ ነገ አላህ ፊት ነጃ ከሚወጡት እንድትሆን ሰበብ የሚሆኑህ ሁሌም ከአንተ ጋ የሚቆዩ ዘውታሪ የሆኑ ሪዝቆች ናቸው።


ይህንን ከተገነዘብክ…………
  በጊዜያዊው ተታለህ ዘውታሪውን እንዳታስመልጥ!!






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

23 Nov, 04:56



ውሻ =>ፍራቻህን;
ሰዎች =>ፍላጎትህን እንዲያውቁ አትፍቀድላቸው።

ይህንን ካወቁ ሁሉቱም ይበሉሃል!!

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

22 Nov, 18:51



ይህንን ትልቅ አንቀፅ ልብ ብለነው እናውቅ ይሆን?………
📖{وَفِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ}
{በገንዘቦቻቸውም ላይ: ለለማኞችና ከልመና ለተቆጠቡ (ደሀዎች) መብት አለ።}


መጥተው ለሚለምኑህ ደሀዎችም ይሁን ከልመና ተቆጥበው አንገታቸው ሰብረው ለተቀመጡ ምስኪኖች ከንብረትህ ላይ አንስተህ ሰደቃ ስታደርግላቸው ከአንተ ንብረት ወይም ከአንተ መብት ለእነሱ ቀንሰህ እንደሰጠህ የምታስብ ከሆነ በጣም ተሳስተሃል።

ባይሆንስ;
አላህ አንተጋ አስቀምጦት የነበረው አደራ ነው በአግባቡ ያደረስከው። ለዚህም ሲባል ትመነዳለህ።
አላህ ከሰጠህ ላይ ለደሀዎች የማትሰጥ ስግብግብ እና ስስታም ከሆንክ ደግሞ የተቀመጠብህን አደራ በአግባቡ ማድረስ አልቻልክም።
በዚህም ምክንያት ትጠየቃለህ: ትቀጣለህ!!

👌ማስተንተን የልብ ብርኃን ይቸራል!!




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

22 Nov, 12:39



እናቱን የሚያከብረው ወንድ:

እሱ ራሱ ነው………
ለእህቶቹ የሚራራው
እና
ሚስቱን የሚንከባከበው!!




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

22 Nov, 10:50



    ኡሙ ሰለማ አላህ ስራዋን ይውደድላት: እንዲህ በማለት ትነግረናለች፦

«كان أحب الثياب إلى رسول الله ﷺ القميص»
«የአላህ መልእክተኛ ﷺ  በጣም የሚወዱት ልብስ ቀሚስ ነበር።»


👌ጁሙዐ ቀን ብቻ ሳይሆን ሁሌም!!
   ቀሚስ የጁሙዐ ልብስ ወይም የሰላት ልብስ ሳይሆን; የሙስሊሞች ልብስ ነው!!




ቀሚስ

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

20 Nov, 06:16



    መሃከለኛው ከፍታ……… "አል_አዕራፍ"

ስለ አዕራፍ ምን አሳወቀህ??!!
    በጥልቅ ምኞት እና በአስጨናቂ ስጋት መሃል ሰፋሪዎች መንፈሳቸው የሚወጠርበት መሃከለኛው ከፍታ ቦታ ነው።

"አዕራፍ" ይባላል፦
   በጀነት እና በጀሃነም መሃል የሚገኝ ከፍታ ቦታ ነው። እዚህ ቦታ ላይ የሚሆን ሰው በቦታው ከፍታ ምክንያት የጀነት ሰዎች ያሉበት ፀጋም ይሁን የጀሀነም ሰዎች ያሉበት ስቃይ ያላንዳች መቸጋገር አንገቱን በማዟዟር ብቻ መመልከት ይችላል።

በመሆኑም………
   ወደ ጀነት ሰዎች በተመለከተ ጊዜ ልቡ ጥልቅ በሆነ ምኞት ሲዋልል: ወደ ጀሀነም ሰዎች በሚመለከት ጊዜ ሁለመናው አስጨናቂ በሆነ ስጋት ይናወጣል።


አዕራፍ ላይ የሚቀመጡ ሰዎች እነማን ናቸው??………
   ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የዲን ምሁራኖች እና የቁርኣን ተንታኞች ብዙ ዐይነት ነጥቦች የጠቀሱ ቢሆንም: ግልፅ ከሆነው የቁርኣን አንቀፅ እና ከሰሓባዎች ገለፃ ጋ የሚገጥመው;
  እነዚህ ሰዎች ዱንያ ላይ የሰሩት መልካም ስራ እና የተዳፈሩት ወንጀል እኩኩል ሆኖ: ወደ ጀነትም ይሁን ወደ ጀሀነም መግባት ያልቻሉ ሰዎች ናቸው።
   ጀነት እንዳይገቡ የሰበሰቡት ወንጀላቸው ሲያግዳቸው፤ ወደ ጀሀነም እንዳይወረወሩ ያስቀደሙት መልካም ስራቸው ይከላከልላቸዋል።



   የቁርኣን ተርጓሚ እና ከሊቅ ሰሓባዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ስለ አዕራፍ ሰዎች ሲናገር፦
  "መልካም ስራው እና መጥፎ ስራው እኩኩል የሆነበት ሰው ከአዕራፍ ሰዎች ጋ ይሆናል። መሃል ላይ ይቆሙና የጀነት ሰዎች ሁኔታ እና የጀሀነም ሰዎች ሁኔታ ይመለከታሉ። ወደ ጀነት ሰዎች በተመለከቱ ጊዜ "የአላህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን" ብለው ይጣሯቸዋል፤ ፊታቸው ወደ ጀሀነም ሰዎች ባዞሩ ጊዜ ደግሞ "ጌታችን ሆይ ከበደለኛ ሰዎች ጋ አታድርገን" ብለው ይፀልያሉ።

  የመልካም ስራ ባለቤቶች ከፊት_ለፊታቸው እና ከበስተ_ኃላቸው የሚያበራላቸው ብርኃን ይሰጣቸዋል። በዚህ ቀን ለሁሉም ሰው የየራሱ ብርኃን ይሰጠዋል። ልክ ወደ ሲራጥ እንደ ደረሱ አላህ ከሙናፊቆች ላይ ብርኃናቸው ያጠፋባቸዋል:  የጀነት ሰዎች ለሙናፊቆች የገጠማቸውን በተመለከቱ ጊዜ "ጌታችን ሆይ ብርኃናችን አዝልቅልን" ብለው ይለምናሉ።

  የአዕራፍ ሰዎች ግን ብርኃናቸው አይወሰድባቸውም: ባይሆን እጃቸው ላይ ያለውን ብርኃን እንዲዘልቅላቸው ከጅለው ይቆያሉ፤ በመጨረሻም የጀነት ሰዎች ጀነትን ገብተው ከጨረሱ በኋላ እነዚህ የአዕራፍ ሰዎችም አላህ ጀነት ያስገባቸዋል።"


  አላህ በተከበረው ቃሉ የእነዚህ ሰዎች ሁኔታ በማላቅ በቦታው ስም የተሰየመ አንድ ትልቅ የቁርኣን ምዕራፍ ካወረደ በኋላ: የጀነት ሰዎች ፀጋ እና የጀሀነም ሰዎች መከራ በከፊሉ ይጠቅስና: በሁለቱ መሃል ስለ ሚደረገው የጀሀነም ሰዎች የሚያስቆጭ ቃለ ምልልስ ይነግረንና ስለነዚህ ሰዎች ጠቅለል ባለ መልኩ እንደ ሚከተለው ያወሳልናል፦

  📖{وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُونَ}
  {በመካከላቸውም  ግርዶሽ አለ፡ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቋቸው ሰዎች አሉ፡፡ የጀነትንም ሰዎች ሰላም ለእናንተ ይሁን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም (የአዕራፍ ሰዎች) የሚከጅሉ ሲሆኑ ገና አልገቧትም፡፡} [⁴⁶]
  {وَإِذَا صُرِفَتْ أَبْصَٰرُهُمْ تِلْقَآءَ أَصْحَٰبِ ٱلنَّارِ قَالُوا۟ رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا مَعَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ}
  {ዐይኖቻቸው ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜ; "ጌታችን ሆይ! ከበደለኞች ጋር አታድርገን" ይላሉ፡፡} [⁴⁷]
  {وَنَادَىٰٓ أَصْحَٰبُ ٱلْأَعْرَافِ رِجَالًۭا يَعْرِفُونَهُم بِسِيمَىٰهُمْ قَالُوا۟ مَآ أَغْنَىٰ عَنكُمْ جَمْعُكُمْ وَمَا كُنتُمْ تَسْتَكْبِرُونَ}
  {የአዕራፍ ሰዎችም በምልክታቸው የሚያውቋቸውን  ሰዎች ይጣራሉ፡፡ "ስብስባችሁና በብዛታችሁ የምትኮሩ መሆናችሁ ከእናንተ ምንም አልጠቀማችሁ" ይሏቸዋል፡፡}  [⁴⁸]
  {أَهَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَقْسَمْتُمْ لَا يَنَالُهُمُ ٱللَّهُ بِرَحْمَةٍ ۚ ٱدْخُلُوا۟ ٱلْجَنَّةَ لَا خَوْفٌ عَلَيْكُمْ وَلَآ أَنتُمْ تَحْزَنُونَ}
{እነዚያ አላህ በችሮታው አያገኛቸውም ብላችሁ የማላችሁት (ደካሞች) እነዚህ ናቸውን? "ጀነትን ግቡ ፍርሃት የለባችሁም እናንተም አታዝኑም" (ተባሉ ይሏቸዋል)፡፡} [49]



  የጀነት ሰዎች ጀነት, የእሳት ሰዎች ጀሀነም ከገቡ በኋላ መሃላቸው ላይ ግርዶሽ ይደረጋል። የግርዶሹ በጀሀነም በኩል ያለው ስቃይ ሲሆን በጀነት በኩል ያለው ፀጋ እና ደስታ ነው። ከዚህ ግርዶሽ ከፍታ ቦታው ላይ "አዕራፍ" ተብሎ በተሰየመው ቦታ ላይ ነው እነዚህ አጅራቸው እና ወንጀላቸው እኩል የሆነባቸው ሰዎች የሚቀመጡት። ወደ ጀሀነም ሲያየዩ ፈርተው በአላህ እየተጠበቁ፤ ወደ ጀነት በሚዞሩ ጊዜ ደግሞ ከጅለው አላህን ሲማፀኑ ይቆዩና በመጨረሻም በአላህ ቱሩፋት ማረፊያቸው ጀነት ትሆናለች።


ከዚህ ዳሰሳ ሁለት ዋና ዋና ትምህርቶች እናገኛለን:
1ኛው,
ከወንጀል መራቅ ካልተቻለም መቀነስ!!
   እነዚህ ሰዎች የሰበሰቡት ወንጀል ካስቀደሙት መልካም ስራ ጋ እኩል በሆነ ጊዜ ጀሀነም ከመግባት ተርፈው ቢያንስ መሃል ላይ ለመስፈር በቁ። እንደው ከሰሩት ወንጀል ላይ ሌላ ተጨማሪ አንዲት ወንጀል ብቻ ጨምረው የሰሩ ቢሆን ኖሮ የወንጀል ሚዛናቸው ከብዶ ወደ እሳት ከመወርወር የሚያስጥላቸው አልነበረም።
ስለሆነም…………
      ይህንን የተገነዘበ ሁሉ በተቻለው ልክ ከወንጀል ሊርቅ ግድ ይለዋል።

2ኛው, መልካም ስራን ማብዛት እና አሳንሶ አለማየት!!
   አዕራፍ ላይ መሃል ሰፍረው የሚቆዩ ሰዎች ወደ ጀነት ለመግባት የሚቀራቸው አንዲት መልካም ስራ ብቻ ነበረች። ከኢስቲግፋር፣ ከሰደቃ፣ ከሰላት፣ ከቁርኣን፣ ከዱዓ፣፣፣፣ አንዲት ብቻ ተጨማሪ መልካም ስራ የሰሩ (የጨመሩ) ቢሆን ኖሮ ወደ ጀነት ገብተው ደስታቸውን ሀሴት ሊያደርጉ እንጂ ጀነትን ከቅርብ ርቀት እያዯት መግባት ተስኗቸው አይቁለጨለጩም ነበር።
ስለሆነም……………
   አላህ በየትኛው ስራህ ሚዛንህ ደፍቶልህ ጀነት እንደሚለግስህ አታውቅምና ባገኘኸው አጋጣሚ: በቻልከው ልክ መልካም ስራ ለመስራት ለማብዛት ታገል እንጂ በፍፁም "እቺ ምን አላት?" ብለህ እንዳታሳልፍ።



🖊አቡ ሙSሊM ሐምዱ ቋንጤ
       ከፋርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

19 Nov, 07:31



🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

17 Nov, 14:30


የዋለ ለማደሩ, ያደረ ለመዋሉ ምንም ዋስትና በሌለው በስጋት እና በጭንቀት በተሞላው የዱንያ ሕይወት;
  አንጀት በሚበላ ልብህን በሚሰብር ሀዘን "አሉኝ" የምትላቸው ወገኖችህ መነጠቅህ ዱንያን የበለጠ ከባድ ያደርጋታል።



  በድንገተኛ አደጋ ባጣሃቸው ስትደነግጥ, በህመም ተሰቃይተው የሄዱት: የበለጠ ስቃያቸው ስታስታውስ ትታመማለህ፤
  ጌታህ ግን በሁሉም ላይ የራሱ የሆነ ጥበብ አለው!!

  እናም ወንድሜ;
የሁሉም እጣ ፋንታ የሆነውና ሁሉም ወረፋው ጠብቆ የሚሄድበት ሞት ሁሉም ቤት መግባቱ፣ የሁሉም ልብ ማስደንገጡ አይቀሬ ነው።

    ከድንጋጤው ተረጋግተህ ህመምህ ሊያስታግስልህ የሚችል ነገር ቢኖር;
  ያጣኸው ወገንህ በእስልምና ላይ ሆኖ ከሞተ ብቻ ነው!!


አዎን!!
አላህ ለአንድ ባሪያው የሚሰጠው ትልቁ ክብር؛
  በእስልምና ላይ እንዲሞት ሲወፍቀው ነው።




🤲አላህ በእስልምና አኑሮ: በእስልምና ይግደለን!!

https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

17 Nov, 14:26


100%


https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

17 Nov, 10:34



ብር ያለው ምንም ነገር ማድረግ ይችላል
ብሎ የሚያምን ሰው;
ብር ለማግኘት ሲል ምንም ነገር ሊያደርግ ይችላል።







https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

16 Nov, 07:29


🌑
    ሞት አብዝቶ መፍራት………
ሕይወትን በትክክል ካለመኖር የሚመነጭ ስሜት ነው!!






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

15 Nov, 17:57



ስለ ትዳር ክፋት የሚያወሩ ወንዶች ሁሉ
ሚስቶቻቸው በየዓመቱ እርጉዞች ናቸው
አሉ



ተዉ ግን ይጋቡበት!!

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

15 Nov, 17:46



   ቸርነት እና ጀግንነት ወንድማማቾች ናቸው;
  ገንዘቡን መስጠት ያልቻለ ነፍሱን መሰዋት አይችልም!!
        /ኢማሙ ዘኸቢ/




👍

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

15 Nov, 17:42



የሸሪዐ ዕውቀት በተማረ ሰው ላይ፦
እርጋታ፣ ብስለት እና የአላህ ፍራቻ መላበስ ግዴታ ይሆንበታል!!

ኢማሙ ማሊክ
📚جامع بيان العلم وفضله (٧١٠/١)




👍በትክክል!!

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

15 Nov, 11:19


🌅
ብርኃን የሚያመነጭ የሆነው አካል;
የቃጠሎውን ህመም መሸከም መቻል አለበት!!






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

14 Nov, 18:35



     ቀና በል ቀን አለ!!

መንገድ ሁሉ እንቅፋት  በሆነበት ዐለም
መነሳት ነው እንጂ   መውደቅ ብርቅ አይደለም።

ሰው ብታጣ ዛሬ   አትዘን ወንድሜ
አግኝቶ ማጣትን   ያስተምራል እድሜ።

ሲኖርህ የኖረ   ስታጣ ብታጣው
አለኝ ያልከው ወዳጅ   ከፊት ባታገኘው።


የዛሬው ውድቀትህ መማሪያህ ነውና
ባጣኸው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና።

መሙላት ቢቸግርህ  ቀን እየጎደለ
አታቀርቅር ተነስ   ቀና በል ቀን አለ!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

14 Nov, 06:42



መሞትን አትፍራ
እያሉ የሞቱት ብዙኃን ናቸው!!






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

14 Nov, 06:38



ኖረህ ከምትረሳ………
ጠፍተህ መናፈቅህ በስንት ጣእሙ!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

14 Nov, 06:27



    እንዲጎዳኝህ የምትፈልገው ተጎዳኝ!!

  ከማንም ጋ ሁን: ከማንም ጋ ኑር: በጠባቡ ቀብርህ የሚጎዳኝህ ብቸኛው ነገር፦
     ዛሬ ያሳመርከው መልካም ስራህ
ወይም
     ዛሬ ያተረማመስከው ወንጀልህ ነው።


  ቀብር ውስጥ ይመጣና  "أنا عملك الصالح" ወይም "أنا عملك الخبيث"  ይለዋል።


  ነገ በጨለማው ጉድጓድ ባማረ መልክ ማራኪ መዓዛ ይዞ ጭርታህን እንዲያስወግድልህ; መልካም ስራህን ብቻ ተጎዳኝ!!



🤝 https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

13 Nov, 10:32


አንዳንድ ሰዎች ደግሞ እንደ ፎቶ ናቸው!!
ባቀረብካቸው ልክ ጥራታቸው ይወርድብሃል።



https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

13 Nov, 08:32


👇

ይህንን ተጭናችሁ ግቡ!!

👆

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

13 Nov, 03:26



    በ2ቱ ምኞቶች መሃል የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት;


🌑የዱንያ አምላኪዎች ምኞት…………
📖{…يَا لَيْتَ لَنَا مِثْلَ مَا أُوتِيَ قَارُونُ…}
{…ወይ ምኞታችን: ለቃሩን የተሰጠው ዐይነት ለእኛም በኖረን…}

   [አል_ቀሰስ:⁷⁹]


🌴የዳሩሰላም ናፋቂዎች ምኞት………
📖{ …تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ}
{…ሙስሊም ሆኜ ግደለኝ: በደጋጎችም አስጠጋኝ።}

  [ዩሱፍ:¹⁰¹]



ጎራህን ምረጥ!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

12 Nov, 17:17



አሕመቅ መጎዳኘትም መጣላትም ሙሲባ ነው።

ቀብር የሚቆፍር የቀን ሰራተኛ ነበር። እሱም ዕለቱ ይደርስና ይሞታል። አንዱ አሕመቅ ነው አሉ የእሱ መሞት ሲነገረው:

"እሰይ እንኳን ሞተ:
ለወንድሙ ጉድጓድ የቆፈረ ሰው ራሱ ይገባበታል ማለት እንዲህ ነው።"
አለ ይባላል




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

12 Nov, 04:15



ለአላህ ብዬ እወድሃለው ስትል፦
አንተና ወንድምህ መሃል የምታደርጉት ቃል_ኪዳን ነው።

🤝የሁለታችሁም እጅ ይጣመርና ተያይዛችሁ ጀነት ለመግባት የምትገቡት ቃል_ኪዳን ነው። አንደኛችሁ እሳት ላይ እየወደቀ ሌላኛው ዐይቶ አያልፈውም።
ከፍርዱ ቀን በኋላ ደረጃችሁ ተበላልጦ ልትለያዩ ትችላላችሁ እንጂ; ወደ ጀነት በምታደርጉት ጉዞ በፍፁም እንዳትለያዩ!!




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

11 Nov, 17:26


🚫
     ማንበብ ክልክል ነው¡¡

    አንድ ባለስልጣን አማኑኤል ሆስፒታልን እየጎበኙ አንድ በሽተኛ ያጋጥማቸውና ጠጋ ብለው
  "ወደዚህ እንዴት ልትመጣ ቻልክ ማለቴ የህመምህ መንስኤ ምንድነው?' ብለው ይጠይቁታል ።

በሽተኛውም መለሰ...
'"ይሄ ሁሉ መዓት የወረደብኝ አንዲት መናጢ ሴት ሳገባነው።
ይሀውሎት አንዲት አግብታ የፈታችና ቆንጆ ሴት ልጅ ያለቻት ወይዘሮ አገባለው።
እናም ይህቺ ቆንጆ ልጅ የእንጀራ ልጄ ሆነች ማለት ነው።
ከዛ አባቴ አንድ ቀን ሊጎበኘን ይመጣል።  በዚህች ቆንጆ ልጅ ፍቅር ይከንፍና በግድ ያገባታል።
ስለዚህ የእንጀራ ልጄ የእንጀራ እናቴ ሆነች ማለት ነው።  ባለቤቴም ለኔ አንድ ወንድ ልጅ ትወልድልኛለች።

  በመሆኑም የኔ ልጅ ለእንጀራ እናቴ ወንድም ስለሆነ ለአባቴ ደግሞ ዋርሳ ሆነ ማለት ነው ምክንያቱም አባቴ የእንጀራ ልጄን አግብቷልና።
እና እንደነገርኩህ የእንጀራ ልጄ አባቴን ስታገባ እሷ በመጀመሪያ የእንጀራ እናቴ ሆነች በኋላ ላይ ደግሞ ወንዱ ልጄ ለእንጀራ እናቴ ወንድም ስለሆነ እርሱ ደግሞ በተዘዋዋሪ አጎቴ ሆኖ እርፍ!
ሚስቴ ደግሞ የእንጀራ እናቴ እናት ስለሆነች የእንጀራ አያቴ ሆና እርፍ!
የእንጀራ እናቴ የእንጀራ ልጄ መሆኗን አትርሳ። እንዲሁም የራሴ የገዛ ሚስቴም የእንጀራ ልጅ ልጅ መሆኔንም አትዘንጋ። ይሄ ሁሉ ሲሆን እኔን የገረመኝ የእንጀራ አያቴን ስላገባሁ ለሚስቴ የእንጀራ የልጅ ልጇ እና ባሏ ብቻ ሳልሆን የራሴም አያት መሆኔ ነው።

ወደዚህ ወደ አማኑኤል ሆስፒታል አብጄ የመጣሁበት ምክንያቴም ይሄው ነው!!"
🤝ደህና ዋሉ!!



https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

11 Nov, 09:52


📖
    ከቁርኣን ተኣምራት
  አንዲት ቃል በአንድ ምዕራፍ ውስጥ አምስት ቦታ ላይ ተጠቅሳለች። ይቺ አንዲት ቃል አገባቧን ምክንያት በማድረግ አምስቱም ቦታ ላይ የተለያዩ የሆኑ ትርጉሞች ይዛለች።

📖ሱረት አል_ነምል ከፍታችሁ ብትቀሩ {ننظر} የምትለዋ ቃል በአምስት አንቀፆች ላይ ተጠቅሳ ታገኟታላችሁ: አምስቱም ቦታ ላይ የተለያየ ትርጉም አላት።
አብረን እንመልከት፦

1ኛው,
📖{سَنَنظُرُ أَصَدَقْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ الْكَاذِبِينَ}
{እውነት ብለሃል ወይስ ከውሸታሞች ሆነሃል እናያለን።}
[:²⁷]
እዚህ ቦታ ላይ سننظر ማለት እናረጋግጣለን ማለት ነው።

2ኛ,
{اذْهَب بِّكِتَابِي هَٰذَا فَأَلْقِهْ إِلَيْهِمْ ثُمَّ تَوَلَّ عَنْهُمْ فَانظُرْ مَاذَا يَرْجِعُونَ}
{ይህንን ደብዳቤዬ ይዘህ ሂድ: እነርሱም ላይ ጣለው: ከዚያም ዘወር በልና ምን እንደሚሉ ተመልከት።}
[²⁸]
እዚህ ቦታ فانظر ማለት ስማ አድምጥ ማለት ነው።

3ኛ,
{قَالُوا نَحْنُ أُولُو قُوَّةٍ وَأُولُو بَأْسٍ شَدِيدٍ وَالْأَمْرُ إِلَيْكِ فَانظُرِي مَاذَا تَأْمُرِينَ}
{እኛ የሀይል ባለቤት: የጠንካራ ሰራዊት ባለቤትም ነን፤ ትዕዛዙ ወደ አንቺ ነው: ምን እንደምታዢ አስተውይ።}
[³³]
እዚህጋ فانظري አስተውይ አስቢ ነው።


4ኛ,
{وَإِنِّي مُرْسِلَةٌ إِلَيْهِم بِهَدِيَّةٍ فَنَاظِرَةٌ بِمَ يَرْجِعُ الْمُرْسَلُونَ}
{እኔም ወደ እነሱ ስጦታ የምልክ እና መልእክተኛውም በምን እንደሚመለስ የምጠባበቅ ነኝ።}
[³⁵]
እዚህጋ فناظرة የተፈለገበት መጠባበቅ ነው።


5ኛ,
{قَالَ نَكِّرُوا لَهَا عَرْشَهَا "نَنظُرْ "أَتَهْتَدِي أَمْ تَكُونُ مِنَ الَّذِينَ لَا يَهْتَدُونَ}
{ዙፋንዋን አሳስቱባት: ታውቀው እንደሆነ ወይም ከእነዝያ ከማያውቁት ትሆን እንደሆነ እናያለን አላቸው።}
[⁴¹]
እዚህ ጋ ننظر የተፈለገበት እናውቃለን ማለት ነው።


ማስተንተን የልብ ብርኃን ይቸራል!!



🖊አቡ ሙSሊM ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

10 Nov, 18:33


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

👉⭕️በታላቁና በተወዳጁ ወንድማችን
አቡ የሕያ ኢልያስ አወል
በህመም ምክንያት በመስጅደ አል-ኑር  እና በመድረሳ ተቋርጦ የነበረው ደርስ በ الله  ፍቃድ ዛሬ ሰኞ ይጀመራል ።



https://t.me/Abu_Yehya_ilyas_Awel

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

10 Nov, 15:55


✍️
  ዒማማ ላይ ማበስ የተረሳው ሱና!!

   ከመረሳቱ አልፎ ዒማማቸው ላይ የሚያብሱ ሰዎች ስታይ ልትገረም ሁላ ትችላለህ። ዳሩ ግን ዘንግተኸው እንጂ ውዱ ነብይህﷺ ውዱእ በሚያደርጉ ጊዜ ዒማማቸው ላይ ማበሳቸው ከተለያዩ ሶሓባዎች ተላልፎልናል።

💫ኢማሙ ቡኻሪ ሰኺኽ ውስጥ በዘገቡት ጃዕፈር ቢን ዓምር ከአባቱ እንዲህ በማለት ያስተላልፋል፦
«رأيت نبي ﷺ يمسح على عمامته وخفيه»
«ነብዩﷺ ዒማማቸው እና ኹፋቸው ላይ ሲያብሱ አይቻለሁኝ።»


💫ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሌላ ሓዲስ ሙጊራ ቢን ሹዕባ እንዲህ ይላል፦
«توضأ رسول الله ﷺ فمسح بناصيته وعلى العمامة وعلى الخفين.»
«የአላህ መልእክተኛﷺ ውዱእ አደረጉ, (ከፊት ባለው ፀጉራቸው) በዒማማቸው እና በኹፋቸው ላይ አበሱ።»

=>አል_ናሲያ (بناصيته) ማለት፦ ግንባር ላይ ፀጉር መብቀል የሚጀምርበት ቦታ ነው።
=>አል_ኹፈይን (الخفين) ማለት፦ እግር እስከ ቁርጭምጭሚት የሚሸፍን የካልሲም ይሁን የጫማ ዓይነት ነው።

  ሁለቱ የሙስሊሞች መመለሻ በሆኑ ሰኺኽ [ቡኻሪ እና ሙስሊም] ላይ የተዘገቡ ነብዩﷺ ውዱእ በሚያደርጉ ጊዜ ዒማማቸው ላይ ያብሱ እንደ ነበር የሚጠቅሱ ሓዲሶች ናቸው።

💫ኢማም ኢብኑ ኻጀር አል_ዓስቀለኒ ፈትሕ ላይ በጠቀሰው ኢብኑ ሙንዚር እንዲህ ይላል፦ "ይህ ነገር በእርግጥም ከአቡ በክር እና ከዑመር ተረጋግጧል። የአለህ መልእክተኛﷺ ደግሞ «ሰዎች አቡ በክር እና ዑመርን ቢታዘዙ ቀጥተኛው መንገድ ይመራሉ።» ብለዋል።"
  ዒማማ ላይ ማበስ ነብዩﷺ ብቻ ሳይሆኑ በላጭ የተባሉ ባልደረቦቻቸው ይሰሩት እንደ ነበር የሚያጠናክር ንግግር ነው።

ሁኔታው……
  1ኛ, ዒማማው ላይ ሁለቱ እጆቹ ልክ ጭንቅላቱ ላይ እንደ ሚያብሰው ከፊት ጀምሮ ወደ ኋላ ይወስድና ወደ ጀመረበት ይመልሳቸዋል።

2ኛ, ከፊት ያለው ፀጉሩ በጣቶቹ አስገብቶ ያስነካና እጆቹ አሁንም ወስዶ ይመልሳል።

  መስፈርቱ……
1ኛ, ጭንቅላት ላይ የተጠቀለለ (የተጠመጠመ) መሆን አለበት።
ሳይጠመጠም ዝም ብሎ ጣል የተደረገ ከሆነ ዐረቦች ዘንድ "ዒማማ" የሚል ስያሜ አይሰጠውም።
2ኛ, የተጠመጠመው ዒማማ ከኋላ ቲንሽዬም ቢሆን ጭራ ሊኖረው ይገባል።
  ጭራ ሳይኖረው የተጠቀለለ ከሆነ ወይም በአንድ በኩል ተጠቅልሎ አንደኛው የተንጠለጠለ ከሆነ የሙስሊሞች ሳይሆን "አህሉ_ዚማ" (ከለላ የተሰጣቸው ያልሰለሙ) ሰዎች መገለጫ እንደ ነበር ስለ ሚያወሱ ዑለማዎች ያወግዙታል።


   ከዚህ በተጨማሪ እንደ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ
"እንደ ካልሲ ውዱእ ላይ ተኹኖ መለበሱ እና ለካልሲ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ልክ መሆኑን" ሸርጥ ያደርጋሉ።
   ዒማማ በተመለከተ ግን ይህንን የሚገድብ ግልፅ መረጃ የለውም። አላሁ አዕለም!!

እናም ወዳጄ፦
  ይህ ከነብዩﷺ እና ከባልደረቦቻቸው መገኘቱ የተረጋገጠ ሱና ነውና ልትረሳው ጭራሽ ቸላ ልትለው አይገባም።




🖊አቡ ሙስሊም ፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

10 Nov, 14:16



የውዱእ አደራረግ በተመለከተ…………

አንድ ሰው በአራት ዐይነት መልኩ ውዱእ ማድረግ ይችላል።
1ኛው, አንድ አንድ ጊዜ ማድረግ ይችላል፤
2ኛ, ሁለት ሁለት ጊዜ ማድረግ ይችላል፤
3ኛ, ሦሥት ሦሥት ጊዜ ማድረግ ይችላል፤
4ኛ, የተወሰኑ ክፍሎቹ ሦሥት ሦሥት, ሌሎቹ ሁለት ሁለት, ሌሎቹ ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ በማድረግ አፈራርቆ ማድረግ ይችላል።



ኢማሙ ቡኻሪ እና ሙስሊም ቀጣዩን ሐዲስ ያስተላልፉልናል፦
አንድ ሰው ለዐብዱላህ ኢብኑ ዘይድ "የአላህ መልእክተኛﷺ እንዴት ውዱእ ያደርጉ እንደነበር ልታሳየኝ ትችላለህን?" ብሎ ጠየቀው።" ዐብዱላህ ኢብኑ ዘይድም "አዎን!" አለውና……
«فدعا بماء فأفرغ على يديه فغسل مرتين ثم مضمض واستنشق ثلاثاً ثم غسل وجهه ثلاثاً ثم غسل يديه مرتين إلى المرفقين ثم مسح رأسه فأقبل بهما وأدبر بدأ بمقدم رأسه حتى ذهب بهما إلى قفاه ثم ردهما إلى المكان الذي بدأ به منه ثم غسل رجليه»
«ውሃ አስመጣና እጁ ላይ አፍስሶ ሁለት ጊዜ አጠባቸው፤ ከዝያም ሦሥት ጊዜ ተጎመጠመጠ: በአፍንጫውም ውሃ አስገብቶ አስወጣ፤ ከዝያም እጆቹ እስከ ክርኖቹ ሁለት ጊዜ አጠበ፤ ከዝያም ጭንቅላቱን አበሰ: ከፀጉር መብቀያው ጀምሮ ወደ ማጅራቱ ወሰደና መልሶ ወደ ጀመረበት መለሰው፤ ከዝያም እግሮቹን አጠበ።»


ይህ ሐዲስ አንድ ሰው እያፈራረቀ ውዱእ ማድረግ እንደሚችል የሚያስረዳ ግልፅ መረጃ ነው።

NB: በተጠቀሱት መልኩ በአራቱም ዐይነት ውዱእ ማድረግ የሚቻል የሚያብቃቃ ከመሆኑም ጋ የተሻለው ወይም በላጭ የሚሆነው ግን ሦሥት ሦሥት ጊዜ ማድረጉ ነው!!
NB: በየትኛውም ዐይነት አደራረግ ጊዜ ፀጉር የሚታበሰው አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑ ይታወቅ!!






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

10 Nov, 11:28



ባለቤቷን መቼም የማይከስርባት ጉዞ………

📖{وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَى رَبِّي سَيَهْدِينِ}
{እኔ ወደ ጌታዬ ኺያጅ ነኝ: በእርግጥም ይመራኛል አላቸው።}

[አል_ሳፋት: ⁹⁹]



🤝ተጨማሪ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ!!

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

10 Nov, 09:03



     እማ……………
     
የቁንጅናሽ ውበት………
በፀሀይ በኮከብ መጠን አይለካም
ስላንቺ ለመግለፅ ፊደል አይሰካም 
               እናቴ

ጨረቃ ነሽ ብዬ ክብርሽን አልነካም።

      ልዩ ሴት ነሽ አንቺ………
ከፀሀይ የደመቅሽ ካደይ የምትፈኪ
በምንም ዐይነት ልክ ሚዛን አትለኪ
 
      እማ………
ልቤ ነሽ የደስታ ሙዳይ

የህይወት የነፍሴ ጉዳይ

         እማ………
የማልፈታሽ ሥውር ቅኔ
ምሳሳልሽ ልክ እንደ ዐይኔ።

        እማ………
የዘመን ውል መቋጠሪያ
የእናትነት ቃል መቁጠሪያ።

           እማ………
የምትደምቂ እንደ ፀሀይ
የማልደርስሽ እንደ ሰማይ።

          እማ………
ለመሸ ቀን ውብ ጨረቃ
የማትዋሽ የውርሥ ዕቃ!!

          እማ………
የተሥፋ ዐለም የነፍስ ሀሴት
የፍቅር መልክ የእውነት ሴት።

         የኔ እናት………   
ደባብሳና አብሳ አቅፋ የምትሥም
ዘላለም ሰርክ አዲስ ፍቅሯ የማይከስም!!
        (የተወሰደ)




ተጨማሪ ለማንበብ👇👇👇👇
      👉       ይህንን ይጫኑ

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

09 Nov, 05:59



     አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፦

📖{لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا}
{አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም…}


ነገሩ እንዲህ ከሆነ…………
   አላህ ቁርኣንን እንድናስተነትን ሲያዘን: በማንችለው ነገር አላስገደደንም ማለት ነው።


ለዚህም ነው ያገራው፦
📖{وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ}
{በእርግጥም ቁርኣን ለመገንዘብ አገራነው: የሚገሰፅ አለን?}

   [አል_ቀመር:¹⁷]




ማስተንተን የልብ ብርኃን ይቸራል!!

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

09 Nov, 03:46



    ጌታቸው ላይ መልካም ግምት ያላቸው ባሮች;
 
በፍፁም ከዱዐ🤲 አይቋረጡም!!


https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

08 Nov, 19:24



   መንገዱን ጠበባት፣ አጋዥም የላት፣
ወደ ፊት መሄድ አይጠቅማት; መመለስም አይበጃት፤

ብትቆይ ትሞታለች; ብትዘል ትወድቃለች፤


  አንዳንዴ ሕይወት እንዲህ ትሆንብሃለች።
አጋዥ ይርቅሃል፤ መወሰን ይከብድሃል፤ መፈፀም ያስፈራሃል፤ መቆየቱ ያሳስብሃል።


ሆኖም ግን; አንድ ነገር ላይ እርግጠኛ ሁን፦
  የጭንቀት መዳኛና የችግር መፍትሔ ያለው ወደ ☝️አላህ በመመለስ ብቻ ነው!!
    📖{رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ}





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

07 Nov, 19:19


🇵🇸
   ሀዘንሽ ይከብዳል  እንባሽ ያቃጥላል;
አብሽሪ ፈለስጢን……
  የቀበርሽው ልጅሽ  ድል ሆኖ ይበቅላል!!



https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

06 Nov, 18:26



ምክር ለልጆች………………

ብልህ ከሆንክ ወላጆችህ በሕይወት ሳሉ መንከባከብ ባትችል ቢያንስ…ቢያንስ አታሰቃያቸው።


ለምን እንደሆነ ታውቃለህ??……………
አንተ አዛ እያደረግሃቸው ባለህበት ሁኔታ የሞቱ እንደሆነ; ወላሂ ነው የምልህ ፀፀቱ ቁጭቱ አትችለውም!!


አራዳ ከሆንክ;
ወላጆችህን ታዘዝ!!

https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

06 Nov, 15:52



    ምክር ለወላጆች……………

   ምንም ነገር ቢቀርብህ እንኳ  ልጅህን በተውሒድ, በሱና እና በአኽላቅ አሳድገው።


ለምን እንደሆነ ታውቃለህ??…………
   ሞተህ ቀብረውህ, አልቅሰው ወይም ተላቅሰው ከሄዱ በኋላ ሁላቸውም ሲረሱህ እጁን ዘርግቶ…………
🤲اللهم اغفر لأبي🤲
🤲اللهم اغفر لأمي🤲


እያለ የአኼራው ሕይወትህ ሊያሳምርልህ የሚችለው በዚህ መልኩ ያሳደከው ልጅህ ነው!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

06 Nov, 11:00



    መሞት መለያየት አይደለም!!

  በእርግጥም አኼራ ላይ እንገናኛለን፤ ከባዱ መለያየት ማለት;
  ከፊላችን ጀነት ገብቶ: ሌላኛችን እሳት ሲገባ ነው።


   🤲አላህ ሁላችንም በጀነት ይሰብስበን🤲



https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

06 Nov, 08:17


🛌 አስቸኳይ የሰላተል ጀናዛ ጥሪ

[ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّآ إِلَيْهِ رٰجِعُونَ] ["إِنَّ لِلَّـهِ مَا أَخَذَ، وَلَهُ مَا أَعْطَى، وَكُلُّ شَيءٍ عِنْدَهُ بِأَجَلٍ مُسَمَّىً"]

💥 ዛሬ የወንድማችን
አቡ ኒዕመተላህ ዐብዱልፈታሕ እህት ወደ አኼራ ሄዳለች አላህ የጀነት ያድርጋት!!

🕌 በአላህ ፍቃድ ዝሁር ላይ አለም ባንክ ኢማሙ አሕመድ (ሜዳ) መስጂድ ይሰገድባትና

🛣️ እዛው አለም ባንክ መቅበራ ትቀበራለች

📮በመሆኑም መገኘት የምትችሉ በአጠቃላይ ተገኝታችሁ እንድትሰግዱና  እንድትሸኙ ጥሪ ተላልፎላችኋል‼️

  📌 ሰላተል ጀናዛ ዝሁር አለም ባንክ ኢማሙ አሕመድ (ሜዳ) መስጂድ።

  📌 ቀብር ከሰላተል ጀናዛ በኋላ እዛው አለም ባንክ ባለው መቅበራ ይሆናል።

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

05 Nov, 12:25



እንዲህ ትላለች…………
በወንዶች በሆነ ነገራቸው የምቀና ብሆን ኖሮ; ወደ መስጂድ በሚያደርጉት ጉዞ እቀናባቸው ነበር።

የሕይወት ውጣ ውረድ ሲወጥራቸው; በፈለጉት ሰዓት ወደ መስጂድ ሸሽተው መንፈሳቸው ያድሳሉ!!







https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

05 Nov, 06:56



ውሻህ አንተ ላይ መጮህ ከጀመረ………
ሌላ የሚመግበው ሰው መኖሩን እርግጠኛ ሁን!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

05 Nov, 05:18



    ሰው ከንቱ;…………

ሲታይ ከማያምር  ፈሳሽ ይፈጠራል
  በሆዱ ሰገራ  ተሸክሞ ይዞራል
ነገም ይሞትና  ጀናዛው ይገማል


እንዴት በዚህ መሃል………
ውበት አለኝ ብሎ  በመልኩ ይኮራል??






አቡ ሙSሊM
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

04 Nov, 19:14



     ቸኩለህ አትፍረድ!!

አንዳንዴ የተዛነፉ የሚመስሉ ነገሮች ተረጋግተህ ስታያቸው የተቃኑ ሆነው ታገኛቸዋለህ።
   በሁሉም ላይ ለመወሰን ሁሉንም በእርጋታ ማየቱ የግድ ነው።


  ሁሉም መስመሮች ለየብቻ አተኩረህ እያቸው አንድም የተጣመመ የለባቸውም።




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

04 Nov, 19:13



     ሞት ደህንነት አያቆየውም፤
   በሽታም አያፈጥነውም‼️


ለዚህም ነው;
  "በሽታው ፀንቶበታል በቅርብ ሊሞት ነው" የተባለው ታማሚ እየኖረ ዶክተሩ ቀድሞ የሚሞተው።

            

https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

04 Nov, 09:57



    ንስሩ እባብ አዝሎ ከፍታ ላይ እየበረረ ነው;

ንስሩ:   "ብጥለው ይነድፈኛል" ይላል።
እባቡ:   "ብነድፈው ይጥለኛል" ይላል።
ተመልካቾች:  "እንዴት የሚዋደዱ ጓደኛሞች ናቸው?" ይላሉ።

የብዙኃኖች ጥምረት እንዲህ ያለ ነው!!



https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

04 Nov, 06:42



    የቁርኣን መጀመሪያዎች……………

ቁርኣን ውስጥ መጀመሪያ የተጠቀሰው ተግባር;
«☝️አላህን በብቸኝነት ማምለክ» ነው።

ሱረቱል ፋቲሃ 5ኛው አንቀፅ ላይ እንዲህ ተቀምጧል፦
📖{إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ}
{አንተን ብቻ እንገዛለን: ከአንተም ብቻ እገዛን እንጠይቃለን።}



ቁርኣን ውስጥ መጀመሪያ የተላለፈው ጥሪ;
«☝️አላህን በብቸኝነት ወደ ማምለክ» ነው።

ሱረቱል በቀራህ አንቀፅ ቁጥር 21 ላይ
📖{يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ}
{እናንተ ሰዎች ሆይ! ያ እናንተንም እነዝያ ከእናንተ በፊት የነበሩትንም የፈጠረው ጌታችሁ ተገዙት። (ቅጣቱን) ትጠነቀቁ ዘንዳ ይከጀልላችኋል።}



ቁርኣን ውስጥ መጀመሪያ የተጠቀሰው ትዕዛዝ;
«አላህን በብቸኝነት ስለ ማምለክ» ነው።

ከላይ በተጠቀሰው የ"ጥሪ" አንቀፅ ላይ ጥሪው ከተላለፈ በኋላ የተቀመጠው ትዕዛዝ።
ሱረቱል በቀራህ አንቀፅ ቁጥር 21 ላይ
📖{ ……اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ}
{……ያ እናንተንም እነዝያ ከእናንተ በፊት የነበሩትንም የፈጠረው ጌታችሁ ተገዙት። (ቅጣቱን) ትጠነቀቁ ዘንዳ ይከጀልላችኋል።}



  ቁርኣን ውስጥ መጀመሪያ የተጠቀሰው ክልከላ;
«ለአላህ ቢጤ ማድረግ» ነው።

ከመጀመሪያው የትዕዛዝ አንቀፅ ቀጥሎ በሚመጣው አንቀፅ ላይ የመጀመሪያው ክልከላ እናገኛለን።
ሱረቱል በቀራህ አንቀፅ ቁጥር 22
📖{فَلَا تَجْعَلُوا لِلَّهِ أَندَادًا}
{ለአላህ ቢጤ አታድርጉለት።}




♻️የመፈጠራችን ሚስጥር የሆነው «አላህን በብቸኝነት የማምለክ» አላማ በተቀደሰው የአላህ ንግግር ውስጥ እንዲህ ቅድሚያ ይዞ እናገኘዋለን።






🖊አቡ ሙSሊM ሐምዱ ቋንጤ
          ከፉርቃን ሰማይ ስር!!

👇  👇  👇  👇  👇  👇  👇
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

03 Nov, 19:28



የሆነ ሰው……………

"አንዴ ብቻህን ላናግርህ ፈልጌህ ነበር"
ብሎህ ያውቃል? ምን ዐይነት ስሜት ነው የሚሰማህ??

ፍራቻ፣ ድንጋጤ፣ ስጋት፣ ዐስር ዐይነት ሀሳቦች አእምሮህ ውስጥ ይርመሰመሳሉ ኣ?

ለምን ፈለገኝ?፣ ምን ሊጠይቀኝ ነው?፣ ስለ ምን ሊያወራኝ ነው?፣፣፣ የመሳሰሉ ሀሳቦች ይመላለሱብሃል።

በአጠቃላይ…………
ለአፍታም ቢሆን መንፈስህ ይረበሻል!!



እንግዲያውስ አላህ የቀጠረንን አስታውስ፦
📖{وَكُلُّهُمْ آتِيهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَرْدًا}
{የቂያማ ቀን ሁላቸውም ለየብቻ ሆነው ይመጣሉ።}


ጓደኛ የለ፣ ቤተሰብ የለ፣ ወዳጅ ዘመድ የለ፣ ከኻሊቀ ሰማዋቲ ወልአርድ ጋ ብቻህን ቆመህ ት ጠ የ ቃ ለ ህ ።
አስበነው ተዘጋጅተናል ወይ???







https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

03 Nov, 16:41



  በደረቀው መሬት  ከሞተ በኋላ
ከዝናቡ ጠጥቶ  እንደ ሚበቅል ሁላ

ችግር መከራውን  እጦቱን ተሻግረህ
  የትግስትህ ፍሬ  በስሎ ታየዋለህ!!
ታገስ ብቻ!!




🖊አቡ ሙስሊም!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

03 Nov, 06:52



ወደ ከፍታችን እንዴት እንመለስ???

የሁሉም ሙስሊሞች ምኞት «ወደ ነበረን ከፍታችን መመለስ»

የሁሉም ሙስሊሞች ቁጭት «የነበረን ከፍታችን ማጣታችን» 
ሲሆን………
የሁሉም ሙስሊሞች ችግር ደግሞ «ወደ ነበረን ከፍታችን እንዴት እንመለስ?» ብለን አለ መጠየቃችን ነው።

አላህ በቁርኣን ውስጥ መልእክተኛውﷺን አርዓያ አድርገን እንድንከተል ያዘናል። በዚህም መሰረት መልእክተኛው እና ባልደረቦቻቸውን የነበሩበት የጭቆናና የበደል ቀንበር ሰብረው ሀያልና የበላይ በመሆን ከፍታቸውን ያረጋገጡበት መንገድ ማጤንና መከተል የግድ ይለናል።

ከአላህ እገዛና ውሳኔ በኋላ ከፍታቸውን ለመቆጣጠር የወጡበት ትልቁ መሰላላቸው ቁርኣን እና ሐዲስ መማርና ማስተማር ነበር። በየትኛውም ዘመንና ቦታ ላይ የሚኖሩ ሙስሊሞች ይህንን መሰረት እስካላሳመሩ ድረስ መቼም ከበታችነትና ከውርደት ሊላቀቁ አይችሉም።
ጥቂት ምሳሌዎችን አብረን እንመልከት


🌑ምሳሌ1, የአላህ መልእክተኛ የዳዕዋቸው ጅምር ላይ ብዛታቸው ጥቂት አቅማቸው ደካማ ሆነው በእሳቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ከፍተኛ በደልና ስቃይ ሲደርስባቸው ነበሩ። የአላህ መልእክተኛ በተከበረው ካዕባ ዙሪያ ለአላህ ለመስገድ ሱጁድ በወረዱበት አረመኔ ጠላቶቻቸው የግመል ፈርስ የመሰለ ቆሻሻ ነገር ጀርባቸው ላይ ጭነውባቸዋል። ሴቶች፣ ባሪያዎች እና ህፃናቶች እንዲወግሯቸው አድርገዋቸዋል።
  ይህንን ሁሉ ስቃይ የደረሰባቸው ረሱል ግን ያለ ምንም ተስፋ መቁረጥና መዳከም ባደረጉት የማስተማር ሂደት ሀገሩንም ህዝቡንም ለእስልምና የተንበረከከ ሆኖ አይደለም ረሱልን ሊያሰቃይ ይቅርና ስማቸውን እንኳ በክፉ ያነሳ (የተሳደበ) የመገደል እርምጃ ይወሰድበት ተጀመረ። ታድያ ይህንን የመሰለ የእስልምና የበላይነት ሊረጋገጥ የቻለው ህዝቡን ቁርአንና ሐዲስ በማስተማር ነበር።።


🌑ምሳሌ 2, ከትላልቅ የረሱል ባልደረባዎች ውስጥ አንዱ የሐበሻዎች ፈርጥ የነበረው «ቢላል» ነበር። እንደ ሚታወቀው ጅምር ዳዕዋ ላይ ከፍተኛ ስቃይ ካስተናገዱ ሰሓባዎች አንዱም ቢላል ነው። ሲያሰቃዩትም በጠራራ ፀሀይ በጋለ አሸዋ ላይ ከጀርባው ድንጋይ በማስቀመጥ ያሰቃዩት ነበር። ባደረጉት ትዕግስት፣ በነበራቸው ፅናትና ዒልም ምክንያት ግን ያ ጀርባው ላይ ድንጋይ ተደርጎ ሲሰቃይ የነበረው ቢላል በተከበረው ካዕባ ላይ በመውጣት ድምፁን ከፍ አድርጎ አዛን ለማድረግ በቃ። ይህንንም ታሪክ የተቀየረው በምንም ሳይሆን በመማር ማስተማር ነበር።


🌑ምሳሌ3, ቀደም ብለው ወደ እስልምና ገብተው የነበሩ ሙስሊሞች ከሚደርስባቸው ስቃይ አንዱ ሀገራቸውና ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸው ነበር። ምክንያቱም ሙስሊሞች ሆነው እስልምናቸውን እያንፀባረቁ መቀጠል ስለ ማይችሉ ያላቸው አማራጭ መሰደድ ብቻና ብቻ ነበር። ሆኖም ግን ሀገራቸው ለቀው ቢሰደዱም በየሄዱበትና ባረፉበት ቦታ ሁሉ ባደረጉት የመማር ማስተማር ስራ እስልምና ተስፋፍቶና አይሎ መጀመሪያ ሙስሊሞች ሲባረሩበት የነበረው ሀገር በመጨረሻም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ለሙስሊሞች ግብር እየከፈሉ እንዲኖሩ ተደረጉ። ታድያ ይህንን ዐይነት ስር ነቀል ለውጥ ከየት መጣ? ከተባለ ትልቁ ምክንያት የነበረው ቁርኣንና ሐዲስ በማስተማር ነበር።

ዛሬም
የእስልምና ህግጋት ተግባራዊ እንዲደረጉ፣ ነብያችንና እስልምናችን እንዳይነኩብን የምንፈልግ ከሆነ፤
በየ መንግስታቶችና ገዢዎች ከሚደርሱብን በደሎች ተላቀን እንደ ቢላል ከፍ ብለን የአላህን ቃል ማስተላለፍ የምንፈልግ ከሆነ፤
በየ ሀገሩ ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰው በደልና ጭቆና አብቅቶ የበላይነታቸው እንዲያረጋግጡ የምንፈልግ ከሆነ

ሰላማዊ ሰልፍ በውጣት፣ እንደ ምንም ተሽሎክሉኮ ፓርላማ በመግባት ወይም ቦታ ለመያዝ በሚል ወንዶችና ሴቶች እያተራመሱ የፈላስፎች አስተሳሰብ በመጋት ሳይሆን
ሁላችንም ወደ ራሳችን ተመልሰን የዲናችን መሰረት የሆነው ቁርኣንና ሐዲስ መማርና መተግበር ይኖርብናል። በዚህ ነው ትክክለኛው የበላይነት መጎናፀፍ የምንችለው።።



🖊አቡ ዒርፋን ሐምዱ ቋንጤ
ከፉርቃን ሰማይ ስር

👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

02 Nov, 17:32


👌
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

02 Nov, 07:24



     ምንሞች……………

  ሁለት ሰዎች ተጨቃጭቀው ወደ ዳኛ ይሄዳሉ። ዳኛው ሁለቱንም ለማድመጥ ቅድሚያ ለከሳሽ "ተናገር" አለው።

"ክቡር ዳኛ! ይህ ሰው የሚከብድ ዕቃ ተሸክሞ መንገድ እየሄደ ነበር። በመሄድ ላይ ሳለ የተሸከመው ዕቃ ይወድቅበታል: አጠገቡ ያለ ሰው ሲፈልግ እኔን አገኘኝና አሸክመኝ አለኝ። ካሸከምኩት ምን እንደሚከፍለኝ ስጠይቀው;
   ምንም ነገር አለኝ።

  በዚህም ተስማምተን አሸከምኩት። ካሸከምኩት በኋላ ግን ምንም ነገሩ አልሰጥም አለኝ።"
አለ።

ዳኛው: "ይህ ነው ጉዳያችሁ?" ሲል
ሁለቱም: "አዎን" አሉት።

ዳኛው ለከሳሹ "ና ወደኔ" አለውና ከፊት ለፊት ጠረፔዛ ላይ የተቀመጠው መፅሀፍ እንዲያነሳ ነገረው። ከሳሹም አነሳ።

"ከመፅሀፉ ስር ምን አገኘህ?" ሲለው
"ምንም ነገር" አለው።
"በቃ ምንም ነገሩ ውሰድና ተስማሙ" አለው።



ምንም ነገር አያውቁም
ምንም ምክንያት የላቸውም
ዝም ብለው ይዘጉናል ያኮርፉናል!!






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

01 Nov, 18:00



    አንበሳ የመሆን ህልም ያላት ድመት;
የአይጥ ፍላጎትዋን በመተው መጀመር አለበት!!



ሁላችንም በውስጣችን አንበሳ አለን: የሚነቃነቅ ኃይል አለ። በመጀመሪያ ግን ለትንንሽ፣ ምቹ፣ ሊተነበይ የሚችል የምግብ ፍላጎታችንን ለማጣት ፈቃደኞች መሆን አለብን።
  ያኔ ብቻ ነው የራሳችንን አቅም ግርማ በእውነት መቀበል የምንጀምረው።





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

01 Nov, 16:51



    “ዝሙተኛዋ”………
ተብላ እስከምትታወቅበት ድረስ አፀያፊ ስራ ላይ የኖረች ሴት;
   ለውሻ ባጠጣችው ውሀ የምትድን ከሆነ,


አንድ ሙስሊም………
   ከመንገድ ላይ “ሙስሊሞች ዐዛ ያደርጋል” ብሎ ያሰበው;
  እንቅፋት በማስወገዱ ጀነት የሚወርስ ከሆነ,


አንድ ሰው………
   ብዙም ቦታ ሳይሰጣት በተናገራት ንግግር;
        የአላህ ውዴታ የሚጎናፀፍ ከሆነ,


መቶ ሰው የገደለ ነፍስ ገዳይ………
   ወደ አላህ ተውበት አድርጎ ባለበት ቅፅበት ሙቶ;
    የጀነት መላኢካዎ የሚያነሱት ከሆነ,

እንዴት ብለህ ከኸይር ስራ ትሳነፋለህ????

እነዚህ………
   ከላይ የተጠቀሱ ሰዎች በእርግጥም እንዳንተው ሙስሊሞች ነበሩ። እንዳንተው ከሰላትም ይሁን ከፆም የየራሳቸው ድርሻ ነበራቸው። ለመዳናቸው ጀነት ለመውረሳቸው ለየት ባለ መልኩ ሰበብ የሆናቸው ግን የተጠቀሰው የቅፅበት ስራቸው ነው።


ተውሒድህን ጠብቅ!!
   በማስከተል የትኛውንም ኸይር ስራ መስራት እየቻልክ "እቺ ምን አላት" ብለህ እንዳታስመልጥ። ከስራዎችህ አላህ በየትኛው ሰበብ እንደሚያድንህ አታውቅም።

ደግሞም ዕወቅ………
  መዳን የሚገኘው በብዛት በተሰራው ሳይሆን:
          በኢኽላስ በተሰራው ነው!!





🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
     👇  👇  👇  👇  👇  👇  👇
     https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

01 Nov, 12:58



    የልብ መፅናት!!
የልብ መፅናት በሁለት ነገሮች ይገኛል፦

1ኛው, ለአላህ ያለህ ውዴታ ለሁሉም ነገር ካለህ ውዴታ በላጭ ሆኖ ሲገኝ!!
  የአላህ ውዴታ የሚያስገኝ ነገር: የሌላ ነገር ውዴታ ከሚያስገኝ ነገር ጋ ሲገጣጠሙ; የአላህ ውዴታ የሚገኝበት የሆነው ይቀደማል።
  ይህ ነገር ብዙኃኖች የሚሞግቱት ግን ደግሞ ጥቂቶች ብቻ የሚተገብሩት ነጥብ ነው።
   ሰዎች በሙከራ ጊዜ ወይ ይከብራሉ: አሊያም ይዋረዳሉ!!


2ኛው, የአላህ ትዕዛዛት እና ክልከላውን ማላቅ!!
     የአላህ ትዕዛዛት እና ክልከላ ማተለቅ አንዲት ቀልብ ፀንታ እንድትቆም ትልቅ የሆነ ሰበብ ነው። ምክንያቱም; ትዕዛዝ እና ክልከላ ማተለቅ አዛዡ ወይም ከልካዩ ከማተለቅ የሚመጣ ከበሬታ ነው።






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

01 Nov, 05:03



    አቡ ኹረይራ ባስተላለፈው…………

ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦
«من توضأ فأحسن الوضوء ثم أتى الجمعة، فاستمع وأنصت، غفر له ما بينه وبين الجمعة وزيادة ثلاثة أيام، ومن مس الحصى، فقد لغا»
«አሳምሮ ውዱእ አድርጎ ወደ ጁሙዐ የመጣ, ከዝያም ኹጥባ ፀጥ ብሎ ያዳመጠ የሆነ ሰው; በዚህኛው እና በሌላኛው ጁሙዐ መሃል እና ሦሥት ቀናቶች ተጨምረው ያለው ወንጀሉ ይማርለታል። (በኹጥባ ሰዓት) ጠጠር እንኳ የነካ በእርግጥም ተጫውቷል።»



በሓዲሱ ከምናገኛቸው ትምህርቶች………
💫ኹጥባ ሲደረግ በእርጋታ ፀጥ ብሎ ማዳመጥ ግዴታ እንደሆነ:
       እና
💫በኹጥባ ሰዓት የትኛውም ዐይነት ተጨማሪ እንቅስቃሴም ይሁን ንግግር ማድረግ የኹጥባው ምንዳ እንደ ሚያሳጣ እንገነዘባለን።





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

31 Oct, 17:24


☝️አላህ………
   የማይመለስ የማይቀየር የሆነ ውሳኔ ወስኗል:


   ከአላህ ሌላ የወደደ የሆነ ሰው; አላህ በዝያኑ ነገር ይቀጣዋል።

   ከአላህ ሌላ የፈራ የሆነ ሰው; አላህ በራሱ ላይ ይሰልጠዋል።
 
   ከአላህ ሌላ ባለ ነገር ላይ የተጠመደ ሰው; ውጤቱ ፀፀት እና ቁጭት ያደርግበታል።

  በአላህ ላይ ከአላህ ሌላ ያስቀደመ ሰው; በፍፁም በረካ አያደርግለትም።

   አላህን አስቆጥቶ ሌላን ያስደሰተ የሆነ ሰው; አላህ ያንኑ አካል በራሱ ላይ ያስቆጣበታል።
       /ኢማም ኢብኑል ቀይም/






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

31 Oct, 16:52



ያልፋል………………
እያልን ብዙ አሳልፈናል። አሁንም ሀሳብ አልቀየርንም:
ያልፋል…………………




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

30 Oct, 18:02



ንግግሩ የለሰለሰ;
ለመወደድ ያስገድዳል!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

30 Oct, 14:10



ምስኪኑ ውዱእ ለማድረግ ወደ ወንዝ ይገባል። ከላይ የደረባቸው ልብሶቹ እንዳይበሰብሱ በሚል ከወንዙ ዳር አስቀምጧቸው ነበር የገባው።


አንዱ ቀዥቃዣ ከሩቅ ሆኖ ሲከታተለው ነበርና ልክ አይታየውም ብሎ ሲገምት ቀስ ብሎ ይመጣና ልብሱ ላይ የአህያ ፊት ይስልበትና ቀስስስ ብሎ ሳያየው ይሄዳል።

ሰውየው ውዱኡን ጨርሶ ሲመለስ ልብሱ ላይ የአህያ ፊት በትልቁ ተስሎ አገኘው።

ድንግጥ አለና…………
"ልብሴ ላይ ፊቱ የጠረገው ማን ነው??"



የታሪኩ ተናጋሪ………
"በጣም ከመሳቄ የተነሳ አፌ ላይ የነበረው ውሃ በጆሮዬ ወጣ" ይላል።





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

30 Oct, 08:54



የተበታተነው ኡመት አል_ኢስላም;
በ "ላ ኢላሃ ኢለላህ" ገመድ አስተሳስሮ አንድ ለማድረግ መጣር ቢያቅትህ:



ከብዙ የኹራፋት፣ የስሜት፣ እና የብልሽት መንገዶች ርቆ በቀደምቶች መንገድ ላይ የተሰባሰበውን የሰለፍዮች ዳዕዋ በዘር እና በብሄር አግማምተህ ክፍተት ለመፍጠር የምትጥረው የፊትና ክብሪት ሆይ!!

☝️አላህ
ወገብህ እምሽክ
ሕይወትህ ምስቅልቅል ያድርገው!!







https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

29 Oct, 10:38



    እንዴት አይቆጣ ቅጣቱ አይምጣ??

🌑ወደ ተውሒድ መጣራት እንደ አሳፋሩ ነውር እየታየ:
   ወደ ክህደት መጣራት ግን ነፃነት እና መብት እንደሆነ ሁሉም ያስባል¡¡

🌑በሰላት ወቅት እና በደርስ ጊዜያት መስጂዶች ተራቁተው:
   የጨዋታ ማዕከላት እና የመዝናኛ ክበባት በሙስሊም ወጣቶች ይጨናነቃሉ¡¡

🌑አንድ መስጂድ ለማቆም ወይም መድረሳ ለመገንባት ዓመታት እየተደከመ እንኳ አጋዥ ጠፍቶ:
   ለብልሽት ስቴድየም እና ለአሉባልታ ተቋማት ግን ሁሉም ተፎካክሮ ሚሊየኖች ይለግሳል¡¡

🌑ፂም አስረዝሞ ኣማኢም መጠምጠም እና ኒቃብ ለብሶ ክብርን መሸፈን እንደ ኋላ ቀርነት እየታሰበ:
  በፍሪዝ መፈንዳት እና ተገላልጦ መውጣት እንደ ስልጣኔ ይታያል¡¡



🌑ሙስሊሞች………
    የሴቶቻቸው መገላለጥ፣
    በመሃላቸው ያለው መመቃኘት፣
    ዲናቸው ቸላ ብለው ለዱንያ ማጎብደድ፣
    ገበያ ቦታ ላይ የሚያደርጉት የሸሪዐ ጥሰት፣
    ሀብታሞች የንብረታቸው ዘካ አለ መስጠት፣
    የረሱልﷺ ትዕዛዛት ቸላ ብለው መርሳታቸው፣
    ከአላህ ጠላቶች ጋ ያላቸው ልቅ የሆነ ወዳጅነት፣
እና
  መሰል የሆኑ ብልሽቶች በአጠቃላይ;


🌑ምድር ላይ…………
   ለኑሮ ውድነት
  ለተፈጥሮ አደጋ መከሰት
  ብልሹ የሆነ አስተዳደር እንዲሰፍን
እና
   አጠቃላይ ለምድር ስርዓ ብልሽት ምክንያት የሚሆኑ ወንጀሎች ናቸው።



መንስኤው እኛው ነን: መፍትሔውም እኛውጋ ነው!!
     ………ተውባ………ተውባ………ተውባ…………




🖊አቡ ዒርፋን ሐምዱ ቋንጤ
      ከፉርቃን ሰማይ ስር!!

https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

29 Oct, 07:22



ጫማህ ከጠበበህ…………
የዱንያ መስፋቷ ትርጉም አይሰጥህም!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

29 Oct, 06:14



መሆኑን አላህ ከፈለገው;
"እንዴት?" ብለህ አትጠይቅ!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

28 Oct, 16:28



ተውበት ከመፈለግ……
ወንጀልን መተው ይቀላል!!
/ይሉ ነበር ደጋጎች
/


https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

28 Oct, 08:34



  ትናንትን መርሳት አላህን ከማስቆጣት ሲሆን: ተቃራኒውም በተቃራኒው!!


   የአላህ መልእክተኛﷺ ከያዕቁብ ዝርያ የነበሩ ሦሥት ሰዎች አላህ በዚህ ነገር እንደ ፈተናቸው እና ፈተናውን የተቀበሉበት ሁኔታ የተረኩልንን ታላቁ ሰሀብይ አቡ ሁረይራ እንደሚከተለው አስተላልፎልናል፦


   «ከበኑ ኢስራኢል ራሰ_በራ, ለምጣም እና ዕውር የሆኑ ሦሥት ሰዎች ነበሩ። አላህ ሊፈትናቸው ፈለገና ወደ እነሱ መላኢካ በሰው መስሎ ላከባቸው።


🌑ወደ ለምጣሙ መጣ፦
  "ከሁሉም ነገር አንተ ዘንድ የበለጠ አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው?" አለው
"ቆንጆ የሆነ መልክ፣ ቆንጆ የሆነ ቆዳ እና ይህንን ሰዎች የሚያነውሩብኝ የሆነው ለምጥ እንዲወገድልኝ" አለው። መላኢካውም አበሰው: ለምጡን ተወገደለትና ቆንጆ የሆነ መልክና ቆዳ ተሰጠው። አስከትሎ
"ከሀብትስ ምን ዐይነት ንብረት ነው የምትፈልገው?" ሲል ጠየቀው
"ግመል ወይም ከብት" አለው።
ብዙ የሆኑ ግመሎች ተሰጠውና "አላህ ይባርክልህ" ብሎት ሄደ።


🌑ወደ ራሰ_በራው መጣ፦
  "ከሁሉም ነገር አንተ ዘንድ የበለጠ አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው?" አለው
"ቆንጆ የሆነ ፀጉር እንዲኖረኝ እና ይህ ሰዎች እያነወሩብኝ ያለው ነገር እንዲወገድልኝ" አለው።
መላኢካውም አበሰው: ራሰ በራነቱ ተወገደለትና የሚያምር የሆነ ፀጉር ተሰጠው።
"ከሀብትስ ምን ዐይነት ንብረት ነው የምትፈልገው?" ሲል ጠየቀው
"ግመሎች ወይም ከብቶች" አለው
ብዙ የሆኑ ከብቶች ተሰጠውና "አላህ ይባርክልህ" ብሎት ሄደ።


🌑ወደ ዕውሩ መጣ፦
  "ከሁሉም ነገር አንተ ዘንድ የበለጠ አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው?"
አለው
"አላህ ዐይኔን መልሶልኝ እንደ ሰዎች መመልከት ነው የምፈልገው" አለው።
መላኢካውም ዐይኑን አበሰለትና ዕይታው ተመለሰለት።
"ከሀብትስ ምን ዐይነት ንብረት ነው የምትፈልገው?" ሲል ጠየቀው
"በጎች ወይም ፍየሎች" አለው ከበግ ወይም ከፍየል ተሰጠው።



  ለሁሉም የተሰጧቸውን ወልደው ተባዙላቸው። ለዛኛው ሸለቆ የሚሞሉ ግመሎች፣ ለሌላኛው ሸለቆ የሚሞሉ ከብቶች እና ለዚህኛው ሸለቆ የሚሞሉ በጎች ሆኑላቸው።


ከጊዜያት በኋላ ይህንኑ መላኢካ በሰው ተመስሎ ተመልሶ መጣ።

🌑ለምጣም ወደነበረው ጋ መጣና፦
  "ምስኪን ሰው ነኝ፣ ጉዞ ወጣሁኝና ወደ ሀገሬ ሳልመለስ ስንቄ ተቋረጠብኝ፣ በአላህ እገዛ ከዝያም በኋላ በአንተ እገዛ እንጂ ወደ ሀገሬ መመለስ አልችልም፣ እንደው ያማረ መልክ… ያማረ ቆዳ… ሰፊ ሀብት በሰጠህ አላህ ይሁንብህ: ወደ ሀገሬ ሚያደርሰኝ አንድ ግመል ስጠኝ"
አለው።
  "እነዚህ የምታያቸው ግመሎች የብዙ ቤተሰብ መብቶች ናቸው" አለው።
"እኔ እኮ የማውቅህ ይመስለኛል፣ ከዚህ በፊት ሰዎች የሚሳለቁብህ ለምጣም እና ደሀ አልነበርክም እንዴ?" አለው።
"ኣ…ኣ…ይ ይህ እኮ ከአባት ከአያቶቼ የወረስኩት ሀብት ነው" አለው።
"እንግዲያውስ እየዋሸኸኝ ከሆነ አላህ ወደ ነበርክበት ይመልስህ" ብሎት ትቶት ሄደ።


🌑ራስ_በራ ወደነበረው ጋ መጣና፦
  ለለምጣሙ የጠየቀው ዐይነት ጥያቄ ጠየቀው: ለእሱም ለምጣሙ የመለሰለት ዐይነት ምላሽ መለሰለት።
"እንግዲያውስ እየዋሸኸኝ ከሆነ አላህ ወደ ነበርክበት ይመልስህ" ብሎት ትቶት ሄደ።


🌑ዕውር ወደነበረው ጋ መጣና፦
  "ምስኪን ሰው ነኝ፣ ጉዞ ወጣሁኝና ወደ ሀገሬ ሳልመለስ ስንቄ ተቋረጠብኝ፣ በአላህ እገዛ ከዝያም በኋላ በአንተ እገዛ እንጂ ወደ ሀገሬ መመለስ አልችልም፣ ዐይንህን በመለሰልህ እና ሰፊ ሀብት በሰጠህ አላህ ይሁንብህ: ወደ ሀገሬ የምደርስበት በግ  ስጠኝ" አለው።
"እኔማ ዕውር ሰው ነበርኩኝ፤ አላህ ዐይኔን መልሶ ውለታ ውሎልኛል። ከምታያቸው በጎች የፈለከውን ያህል ውሰድና የፈለከውን ያህል ተውልኝ። በአላህ እምላለሁ ምንም ያህሉ ብትወስድብኝ አልወቅስህም።" አለው።

የዛኔ…………
  "ንብረትህን ያዝ! አላህ በረካ ያድርግልህ!!
ባይሆን ተፈትናችኋል: አላህ ከአንተ ወደደልህ፤ በባልደረቦችህ ግን ተቆጥቷል!!"
አለው።"


ሁላችንም……………
   ደስ የማይል ትናንት አሳልፈናል። በህመም፣ በእጦት፣ በጭንቅ፣፣፣፣ በተለያዩ መቸጋገሮች አልፈን:
ዛሬ ላይ…………
    በዐፊያ እና በመብቃቃት አላህ የተሻለ ሐያት እና ማንነት ወፍቆናል።

የትናንቱ ማንነታችን አስታውሰን;
   በዛሬው ፀጋ አላህን አመስግነን ሐቁን እንጠብቃለን?? ወይስ???






🖊አቡ ዒርፋን ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

27 Oct, 16:12



    ረሱልﷺን………………

   አብረዋቸው በነበሩ ጊዜ: "ሙሐመድ አል_ኣሚን" (ታማኙ ሙሐመድ"
ብለው የሰየሟቸው ሰዎች ራሳቸው ናቸው;

  በተቃረኗቸው ጊዜ "አል_መጅኑን አል_ሷሂር" (እብዱ ደጋሚ) ብለው የሰየሟቸው።



ስትቃረናቸው ሁሌም ይጃጃሉብሃል!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

27 Oct, 14:52



   ዐረቦች ነብዩﷺ ተልከው እስልምና ከመቀበላቸው በፊት ዓለም ላይ እረኛ የሌላቸው መንጋዎች ነበሩ፤
  ረሱልﷺ ተልከውላቸው በእስልምና መኖር ሲጀምሩ ሙሉ ዓለም ቀጥ አድርገው ይዘው የገዙ መሪዎች ሆኑ።



  ጊዜ ጊዜን እየተካ ሲሄድ ዕልቅና ያገኙበት የስኬትና የሰላም መንገድ የነበረው እስልምናቸው ቸላ ሲሉ እና የነብያቸውﷺ ትዕዛዞች በጣሱ ጊዜ ይኸው ክብር እና ዝናቸው ጠፍቶ ሌላው ዓለም እነርሱን ይመራ ጀመረ።

  እስልምና በመያዛችን አይደለም ወደ ኋላ የቀረነው;
  እስልምና ላይ ባለ መስራታችን እንጂ!!





እስልምና የጥበብ ሁሉ መክፈቻ;
ወደ ሁሉም ስኬት መዳረሻ ነው!!

https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

27 Oct, 03:18



የሌሎች ማንነት ለማጠልሸት የምትጠቀምበት ሀይል;
የራስህ ማንነት ለማነፅ ብትጠቀምበት ኖሮ…………
ምንኛ በተስተካከልክ ነበር!!





⛅️ሰናይ ውሎ!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

26 Oct, 19:15



ሁለት ዐይነት ወንድሞች አሉኝ…………

እናቴ የወለደችልኝ,
እና
ክስተቶች የወለዱልኝ!!

ولو شئت لسميت




ለሁለቱም እ ሰ ዋ ለ ሁ!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

26 Oct, 06:40



ውድቀት ያታልላል
ስኬት ደግሞ በቅድሚያ ዋጋ ያስከፍላል
ከድል በፊት ያለው ውጣ ውረድ ያስጨንቃል።



👇join እያደረጋችሁ እንነጋገር👇👇
https://t.me/+jmMRlELT7vYyYTVk

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

25 Oct, 18:41



ወንድነት በራሱ ሌላ ፈተና ነው…………

ከፍቶህ ስታለቅስ ቢያዩህ
"ወንድ አይደለህ እንዴ እንዴት ታለቅሳለህ?"
ይሉሃል።





ከቻልክ ☝️ለሰማዩ 🤲አልቅስ
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

25 Oct, 17:35



    ይታዩኛል  ብዙ ልብሶች
ከውስጣቸው  የሉም ሰዎች።





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

25 Oct, 11:22



    ዛሬ የከተማ አስተዳደሩ ይመጣሉ:
"ስለሆነም፦ ግብር ላይ ከልክ በላይ የተጠየቃችሁ፣ የይዞታ ማረጋገጫ የተከለከላችሁ፣ የመስሪያ ቦታ ማስፋፊያ የምትፈልጉ፣ የብድር አገልግሎት ማግኘት የምትፈልጉ፣ የትኛውም ዐይነት ጥያቄ ወይም ቅሬታ ያለባችሁ የከተማችን ነዋሪዎች አስተዳደሩ በሚመጡበት ሰዓት ተገኝታችሁ ጥያቄያችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ!!"

     የሚል ዜና ቢለቀቅ የከተማው ነዋሪዎች በምን ዐይነት መልኩ ተዘጋጅተው ጥያቄያቸውን የሚያቀርቡ ይመስላችኋል???

ልብ ማለት ያለባችሁ…………
ይህ አስተዳደር ጥያቄያቸው ተቀብሎ ቢያስተናግድ እንኳ
1ኛ, የተሟላ የሆነ መልስ አይሰጣቸውም
2ኛ, በተወሰነ መልኩ ቢሰጣቸው እንኳ ከእነሱ የሚፈልገው ነገር አለ
3ኛ, ጥያቄያቸው ተቀብሎ ከእነሱ ምንም ባይቀበል እንኳ መመፃደቁ አይቀሬ ነው።



ላስታውሳችሁ የፈለኩት…………
ስለ አስተዳደር ምናምን ሳይሆን የአላህ መልእክተኛﷺ «አላህ ጥያቄያችሁ የሚቀበልበት ሰዓት ነው።» ብለው ከቀጠሩን ወቅቶች ሁለቱ ብቻ ለማስታወስ ነው።


ውዱ ነብይﷺ ስለ ዕለተ ጁሙዐ ቱሩፋት በተናገሩበት ሓዲስ ላይ እንዲህ ይላሉ፦
 «فيه ساعة، لا يوافقها عبدٌ مسلمٌ، وهو قائم يصلي، يسأل الله تعالى شيئًا، إلا أعطاه إياه»
  «በጁሙዐ ቀን አንዲት ሰዓት አለች, አንድም ሙስሊም የሆነ ባሪያ የሚሰግድ ሆኖ አላህን ምንም ነገር አይጠይቅም:  ያንን ነገር ቢሰጠው እንጂ።»


 
  ከላይ የተጠቀሰው የጁሙዐ ዕለትን ብቻ የተመለከተ ሲሆን በእያንዳንዱ ቀን የሚዘዋወር የሆነ ቀጠሮም አለልን። ነብዩﷺ ስለ አላህ በነገሩን፦
 «ينزل ربنا تبارك وتعالى إلى السماء الدنيا كل ليلة حين يبقي ثلث الليل الآخر؛ فيقول: من يدعوني فأستجيب له؟ من يسألني فأعطيه؟ من يستغفرني فأغفر له؟»
«በሁሉም ሌሊት ላይ ከሌሊቱ የመጨረሻው 1/3ኛ ሲቀር የተባረከ እና የላቀው ጌታችን ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል: "ማን ነው የሚጠራኝ አቤት የምለው? ምን ነው የሚጠይቀኝ የምሰጠው? ማን ነው ማረኝ የሚለኝ የምምረው?" ይላል።»




  ከላይ በተጠቀሰው ምሳሌ የከተማዋ ነዋሪዎች ለከተማው አስተዳደር እንደዛ የሚጓጉ ከሆኑ:

እኛ ሙስሊሞች……………
   ሰጥቶ ማያልቅበት፣ የሙሉ ፀጋ እና ቱሩፋት ባለቤት የሆነው ልዕለ ሀያሉ አላህ ጠይቀነው ሊሰጠን የሚጠብቀን ከሆነ የበለጠ ጓጉተን ልንዘጋጅ አይገባንም ወይ??



መጠየቅ አቅቶን እንጂ
በፍፁም ሊሰጠን ሰስቶ አይደለም!!






🖊አቡ ዒርፋን ሐምዱ ቋንጤ!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

24 Oct, 19:11



   አብሽሩ ወንድሞቼ ደረሰላችሁ እንጂ አልደረሰባቹም!!



📖{قُل لَّن يُصِيبَنَا إِلَّا مَا كَتَبَ اللَّهُ لَنَا…}
{አላህ ለእኛ የፃፈልን እንጂ አይነካንም በል…}



{ለእኛ} እንጂ "በእኛ ላይ" አላለም።
ምክንያቱም፦
   ለሙእሚን የሚገጥመው የትኛውም ዐይነት ክስተት ለእሱ ነው እንጂ በእሱ ላይ አይደለም።

ኸይር ከሆነ፦
   ለእሱ የፈጠነ ምንዳ ይሆንለታል፤
ሙሲባ ከሆነም፦
  ለአኼራ የሚከማች ምንዳ ይሆንለታል።



የእዝነቱ ነብይ ሙሐመድﷺ የተናገሩትን አስታውስ፦
«عَجَباً لأمْرِ الْمُؤْمِنِ إِنَّ أَمْرَهُ كُلَّهُ لَهُ خَيْرٌ، وَلَيْسَ ذَلِكَ لأِحَدٍ إِلاَّ للْمُؤْمِن: إِنْ أَصَابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ فَكَانَ خَيْراً لَهُ، وَإِنْ أَصَابَتْهُ ضَرَّاءُ صَبَرَ فَكَانَ خيْراً لَهُ»
«የኣማኝ ነገር በጣም ያስገርማል: ነገሩ በአጠቃላይ ለእሱ ኸይር ነው። ይህ ደግሞ ለኣማኝ እንጂ ለማንም አይሆንም።
  መልካም ነገር ካጋጠመው, አላህን ያመሰግናል: ለእሱ ኸይር ይሆንለታል፤
  ጉዳት ካጋጠመው, ትዕግስት ያደርጋል ለእሱ ኸይር ይሆንለታል።»






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

24 Oct, 16:49



    ብዙኃህን ሙስሊሞች……………

   እስልምና ማስተማር እና ማስተላለፍ የዑለማዎች እና የዱዓቶች ብቻ ስራ ይመስላቸዋል። በእርግጥም ስለ እስልምና በማወቅም ይሁን በማሳወቅ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት እነዚሁ የእስልምና ዱዓቶች ናቸው። እናም ይህ ምስኪኑ ሙስሊም ራሱን ከዑለማዎች ወይም ከዱዓቶች ጋ ሲያነፃፅር በመሃላቸው በጣም ሰፊ የሆነ ልዩነት ይታየዋል: የዛኔ "እኔማ ወደ እስልምና የማደርገው ጥሪ የለም" ብሎ ራሱን ወደ ኋላ ያሸሻል።
ይህ ፍፁም ስህተት ነው!!

እያንዳንዱ ሙስሊም…………
   ባለበት ቦታ ላይ ሆኖ በሚችለው ልክ ወደ እስልምና የመጣራት ግዴታ አለበት። የአንተ ንግግር ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያደርግ የሚችለው ባለህ የኢኽላስ ልክ ብቻ ነው። የቁርኣን የሓዲስ አንቀፆች መዘርዘር ባትችል እንኳ የምታውቀውን ብቻ አስተላልፈህ ሂድ።

አላህ አወድሶ ያወሳው ሰውዬ አስታውስ፦
 📖{وَجَاءَ مِنْ أَقْصَى الْمَدِينَةِ رَجُلٌ يَسْعَى قَالَ يَا قَوْمِ اتَّبِعُوا الْمُرْسَلِينَ}
{ከከተማይቱ ሩቅ ቦታ አንድ ሰው እየሮጠ መጣ: "ህዝቦቼ ሆይ መልእክተኞቹን ተከተሉ" አለ።}

  [ያሲን:²⁰]


ዓሊም ወይም ጥበበኛ አልተባለም………
  {ሰው} ነው የተባለው። የተለየ ሰው ባይሆንም የሰራው  ስራ ግን ትልቅ ስለነበር ታላቁ አላህ በታላቁ ቁርኣን አውስቶት እስከ ዱንያ ፍፃሜ እየተነበበ ይወሳል።

ራስህን የማይጠቅም የማይረባ ሰው አድርገህ አትሳል;
  ታገል ☝️አላህ ያግዝሃል!!


ይህ እስልምና የሁላችን አደራ ነው;
በጋራ እንጠብቀው!!








https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

24 Oct, 07:14


☝️
    አላሁመ…………

   አንተ እንዳለኸኝ በማስታውስ ጊዜ;
ምንም ነገር እንዳላጣሁኝ ዐይነት  ይሰማኛል!!




🤲አደራህ…… እንዳተወኝ🤲
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

24 Oct, 05:31



    ይህማ እንዴት ሊሆን ይችላል?? እንዴትስ ይሳካል???
አትበል!!



ዘከሪያ እና መርየም ይህንን ጥያቄ በጠየቁ ጊዜ አላህ የመለሰላቸውን ተመልከት፦
📖{…هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٌ…}
{…እሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው…}





ከባድ ቢመስልህም ለአላህ ቀላል ነው!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

23 Oct, 15:43



ልጅህ እያየ ለእኔ ቢጤ የምትሰጠው አንድ ብር;
ስለ ሰደቃ ከምታደርጋቸው ዐስር ሙሓደራዎች የበለጠ ተፅእኖ ይኖረዋል!!







https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

22 Oct, 17:04



     ትዝብት እና ምልከታ!!

    ስንቱ ለዘመናት ጤናው እና ወጣትነቱን ሰውቶ፣ ምን አልባትም ሕይወቱን ዋስትና ሰጥቶ የደከመበት፤ ያከማቸው ሀብቱ: አስፈሪ እና አስደንጋጭ በሆነው የእሳት አደጋ ሲወድምበት;
  ማትረፍ እና መከላከል ባይችሉ እንኳ አዝነው መቀመጥ ተስኗቸው

  "እሰይ! ደስ የሚል አጋጣሚ ነው" ብለው ዝርፊያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ስናስብ ምን አልባትም "አይገርምም የሌባ ባህሪ ነው" ብለን ልናልፈው እንችል ይሆናል።

ግን…………
   ከሰውነት ሚዛን ወርደው፣በክፋት እና በጭካኔ ሰይጣንን የሚፎካከሩ የሰው አረመኔዎች ማለት፦
  በመርካቶው የእሳት አደጋ ጊዜ የተሰረቀ ዕቃ መሆኑን እያወቁ ከእነዚህ አፀያፊ ሌቦች ዕቃውን የሚገዙ ነውረኛ ነጋዴዎች ናቸው!!


ከዚሁ በተጨማሪ…………
  በእነደዚህ ዐይነት የድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ ከሚደረጉ የስርቆት ዘዴዎች አንዱ;
  ፌክ እና የውሸት አካውንቶች በማዘጋጀት "ተጎጂዎችን እንርዳ" በሚል ውሸት በተጎጂዎች ስም ከየዋሁ ማህበረሰብ የሚሰበሰበው ዐይነት ዘዴ ነው። እናም ማህበረሰቡ ይህንን በመገንዘብ ለእያንዳንዱ የድጋፍ እንቅስቃሴው ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊኖረው ይገባል።


እግረ መንገድ ማንሳት የምፈልገው ሀሳብ……
  በተለይም ታዋቂ የሆኑ ሙስሊም አክቲቪስቶች እና የሚዲያ ሰዎች ይመለከታል።


እሱም፦
  ህዝቡን ተጎጂዎች እንዲረዳ በሚደረገው እንቅስቃሴ ፍትሀዊነት እና ግልፀኝነት የግድ መረጋገጥ አለባቸው። ስለሆነም: ለእርዳታ ጥሪ ሲደረግ የአንድ ተጎጂ ወይም የሁለት ተጎጂዎች አካውንት ለጥፎ በንጥል እንዲረዱ ከማድረግ; ሁሉንም ተጎጂዎች እንደደረሰባቸው ጉዳት መጠን ድጋፍ ያገኙ ዘንድ ለሁሉም የሚሆን የጋራ አካውንት ተከፍቶ በጋራ እንዲረዱ ቢመቻች ሁሉም በልበ ሰፊነት እንዲንቀሳቀስ ያግዘዋል የሚል ሀሳብ አለኝ።





ከወደዳችሁት share ይደረግ!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

22 Oct, 08:28



ጀነት ከላይ እየተጌጠች,
ጀሀነም ከታች እየተቀጣጠለች


በሁለቱ መሃል ሆኖ ተኝቶ የሚያድረው እንዴት ያለ አስገራሚ ሰው ነው??
/ይላል ከሰለፎች አንዱ/



https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

22 Oct, 08:10



ከሰዎች አላህን አብዝቶ የሚታዘዝ ሰው ማለት፦
አላህን ማመፅ አብዝቶ የሚጠላው ነው!!
/አቡ በክር አስ_ሲዲቅ/








https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

21 Oct, 19:49



    የዱንያ ምሳሌ……………

📖{…فَجَعَلْنَاهَا حَصِيدًا كَأَن لَّمْ تَغْنَ بِالْأَمْسِ…}
{…ትናንት እንዳልነበረች የታጨደች አደረግናት…}



☝️ላ ኢላሃ ኢለላህ!!
እቺ ናት ዱንያ
   ስንት ዓመት ተደክሞ, ስንት ትግል ታግሎ, ስንት መከራ እና ስቃይ ተጋፍጦ የተሰበሰቡ ሚለየኖች ይኸው በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ ሁሉም ትናንት እንዳልነበረ ዐይነት ወደ አመድነት ተቀይሯል።

"ዱንያ ከሀዲ ናት" የሚባለው ለዚህ ነው። የለፋላት የደከመላት የማታውቅ ውለታ ቢስ ከሀዲ!!


ወንድሞቻችን አብሽሩ………
🤲አላህ በተሻለ ምትክ ይቀይርላችሁ!!
🤲በደረሰባችሁ ሙሲባም ይመንዳችሁ!!






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

21 Oct, 18:53



    ቁጣህን አንሳና እዝነትህ ላክልን
በዳይ አጥፊዎች ነን ዐይተህ እለፍልን!!




🤲ረሕማከ ረበና🤲
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

21 Oct, 17:01



አትዘን!!

ምክንያቱም፦
ትናንትና ብዙ አዝነህ ዐይተኸዋል: ግን በማዘንህ የተቀየረ ነገር አለ??

ንግድህ ከስሮ አዝነሃል: ከዝያ ተርፎልሃል?
አላማህ ተከሽፎ አዝነሃል: ከዝያ ተሳክቷል?
ያሰብከው ተበላሽቶ አዝነሃል: ከዝያ ተመልሷል?


ሀዘን…………
የትናንቱ ኪሳራህ ላይመልስ
የነገው ስኬትህ ላያመጣልህ
የዛሬው ደስታህን የሚሰርቅ ብቻ ነው።






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

21 Oct, 07:58



📖{وَآتَاكُم مِّن كُلِّ مَا سَأَلْتُمُوهُ…}
{የለመናችሁትን ሁሉ ሰጥቷችኋል…}

[ኢብራሂም:³⁴]


ከለመናችሁት "ከፊሉን" ሳይሆን {ሁሉንም}
አዎን…………
አላህ የለመንከውን ሁሉ ይሰጥሃል!!


ወይ ቀጥታ የፈለከው ይሰጥሃል፣
ወይም በእሱ አምሳያ ሙሲባ ይመልስልሃል፣
ወይም ለአኼራ ድልብ አድርጎ ያስቀምጥልሃል።
ከአንተ የሚጠበቀው መለመን ብቻ ነው!!



https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

20 Oct, 16:56



  ወንጀሌን ሳስበው  ብዛቱ ያስፈራል
የአላህ እዝነት ግን  ከሁሉም ይሰፋል!!

   ያድነኛል ብዬ  ምለው ስራ የለኝ
እዝነትህ ብቻ ነው  ተስፋ የሚሰጠኝ!!






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

20 Oct, 08:35



    ላጤነት ስቃይ እንደሆነ የምታውቀው፦
ሚስቶች ከጀነት ፀጋ ውስጥ ተጠቅሰው ስታይ ነው!!

   ትዳር ፀጋ እንደሆነ የምታውቀው፦
ጀነት ውስጥ ላጤ እንደሌለ ስትረዳ ነው!!



📖{قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَلِكُمْ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ}
{ከዚህ ሁሉ የሚሻል ልንገራችሁን? በላቸው: (እሱም) ለእነዝያ አላህን ለፈሩት ጌታቸው ዘንድ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ ጀነቶች፣ ንጹህ የሆኑ ሚስቶችም፣ ከአላህ የሆነ ውዴታም (በጀነቷ) ውስጥ ዘውታሪ ሲሆኑ አላቸው፤ አላህም በባሮቹ ተመልካች ነው።}

     [አል_ዒምራን:¹⁵]


📖{…وَلَهُمْ فِيهَا أَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَهُمْ فِيهَا خَالِدُونَ}
{…ለእነሱም እሷ (ጀነት) ውስጥ ንጹህ የሆኑ ሚስቶች አሉላቸው፤ እነሱም እሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።}

  [አል_በቀራ:²⁵]






🤝ጋብቻ ይለምልም……ላጤነት ይመንምን!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

20 Oct, 03:09


✍️
      ሁሉም በስራው ነው‼️

📖{كُلُّ امْرِئٍ بِمَا كَسَبَ رَهِينٌ}
{ሁሉም ሰው በሰራው ተያዢ ነው።}



💫ፊርዓውን በጀሀነም አዝቅጥ ሲቀጣጠል;
ሚስቱ ግን ከፍ ባለው ጀነት ትጠቃቀማለች።

💫ነብየላህ ኑህﷺ ከፍ ባለው ጀነት ሲጠቃቀሙ;
ልጃቸውና ሚስታቸው በጀሃነም ይቀጣጠላሉ።

💫ነብዩላህ ሉጥﷺ ከፍ ባለው ጀነት ሲደሰቱ;
ሚስታቸው ጀሀነም ትወርዳለች።

💫ነብዩላህ ኢብራሂምﷺ ከፍ ያለው ጀነት ሲወርሱ;
አባታቸው ወደ ጀሀነም እሳት ይወረወራል።

💫ነብዩ ሙሐመድﷺ በጀነት ሲነግሱ;
አባታቸው ጀሀነም ይገባል።

💫ዓልይ ወደ ጀነት ሲጓዝ;
አባቱ አቡ ጧሊብ ወደ እሳት ይነዳል።


ምክንያቱም፦         👇👇👇
{كُلُّ امْرِئٍ بِمَا كَسَبَ رَهِينٌ}
{ሁሉም ሰው በሰራው ተያዢ ነው።}



"ዘሬ መሰረቴ ከእንትን ነው” ብለህ አትታለል
    ማንነት የሚለካው በስራ ነው!!


👇  👇  👇  👇  👇  👇  👇
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

19 Oct, 16:36



የወጠንኩት ባይሳካ
ሊጡን ገና ባይቦካ

እንዳሰብኩት ባልጋግረው
ግን አይቀርም ለእኔ ያለው።


የዛኔ ግን ሁሏም አልፋ
ስኬት ለኔ ተንሰራፋ
ለሰው ልጅ ነው ዋናው ተስፋ!!



  🌌መልካም_ምሽት

https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

19 Oct, 10:38



አንድ ሰው በሚሞት ጊዜ…………

በታሪክ ተሰምቶ የማይታወቅ የሆነ ሁለት ኪሳራዎች በንብረቱ ላይ ይከስራል። አለ

"ምንና ምን ናቸው ኪሳራዎቹ?"
ተብሎ ሲጠየቅ

"ሲሞት ንብረቱን በአጠቃላይ ይወሰድበታል;
ከዝያም
ስለ እያንዳንዱ ንብረቱ ይጠየቃል።"
አለ
/የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ/






https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

19 Oct, 07:57



    ጊዜው…………

  ከምን ጊዜውም በበለጠ ሙስሊሞች በአንድነት ገመድ ተሳስረው ሊያብሩበት እና ሊጠናከሩበት አስፈላጊ የሆነ ጊዜ ነው።

ስለሆነም………
  ሙስሊሞች መሃል መለያየት እና መከፋፈል አምጥተው ለመነቋቆር ምክንያት ከሚሆኑ ነገሮች ሁሉ ርቆ:
  ሕብረት እና አንድነት እንዲመጣ ሊያግዙ በሚችሉ ነገሮች ላይ ብቻ ማተኮር የበለጠ አስፈላጊ ነው!!





https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

18 Oct, 16:12



   የዩሱፍ ወንድሞች ከአባታቸው ጋ ጥቅም እንደ ሚያገኙበት ባሰቡ ጊዜ ለዩሱፍ፦
    "ወንድማችን" አሉት።

ልክ ጥቅሙ አብቅቷል ብለው ባሰቡ ጊዜ
   "ልጅህ" ማለት ጀመሩ።

በዚች ዱንያ ላይ ብዙኃኖች ካየን አነጋገራቸው ከጥቅማቸው ጋ አብሮ ይቀያየራል!!


💫የምንወደው ሰው ሲታመም;
        "ፈተና ነው" ብለን;
የምንጠላው ሰው ሲታመም ደግሞ
      "ቅጣት ነው" እንላለን።


💫በምንወደው ሰው ላይ ሙሲባ ሲደርስ
   "መልካም ስለ ነበረ ነው" ብለን
በምንጠላው ሲደርስ ደግሞ
"ሰዎችን ይበድል ስለ ነበር ነው" እንላለን።


ወዳጄ……
የአላህን ውሳኔ በስሜትህ ልክ ለክተህ ከማከፋፈል ተጠንቀቅ።
  የአላህ ግርዶሽ ከልሎልን እንጂ ሁላችንም አንገት የሚሰብር ወንጀል ተሸክመን የምንዞር ነውረኞች ነን!!



🤲አላህ የተሻለ ለሆነው ይግጠመን🤲
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

18 Oct, 03:13



      ምድር………

“የሚፈፀሙብኝ ወንጀሎች፣ የሚደረጉብኝ አመፆች ከብደውኛል፤ አቅሜ አልቻለም።”
ብላ የምትንቀጠቀጥ ነው የሚመስለው።

  ጎርፍ
    ድርቅ
     አውሎ ነፋስ
       የመሬት መንቀጥቀጥ
                  የፀሀይ ግርዶሽ

ሁሉም ከአመፃችን እንመለስ ዘንዳ ማስፈራሪያ ናቸው።
ማን ነው የሚነቃው??




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

17 Oct, 17:50



    ዱንያ ላይ ሆነህማ አታስበው…………

ኢማሙ አሕመድ አላህ ይዘንላቸው ተጠየቁ፦

  "መች ነው የምታርፈው?" ሲባሉ
"ጀነት ውስጥ የመጀመሪያ ተረከዜን ሳሳርፍ" አሉ።


ዱንያማ………
   ከጫፍ እስከ ጠረፍ በድካም እና በእንግልት የተሞላች ናት።




https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

17 Oct, 08:32



"ትክክለኛው የፈጣሪ እምነት እስልምና ነው, እኔ ግን አልችለውም………"


  እድሜዋ ከወጣትነት የተሻገረ ቢሆንም እሷ ግን "እምቢ አላረጅም" እያለችው እንደሆነ ንግግሯ እና ውጫዊ ገፅታዋ ያሳብቁባታል፤ አለባበስዋ ሸይጣን ለፊትና የሚፈልገውን ፕሮቶኮል ያሟላ ዐይነት ነው። እንደ ማንኛውም ደምበኛ አገልግሎት ፈልጋ መጥታ የምትፈልገው ዕቃ በመምረጥ ላይ ሳለች በመሃል……

"አክራሪ ሙስሊም ነህ ኣ?" አለችኝ
"እንዴት?" ብዬ ጥያቄዋ በጥያቄ መለስኩላት።
"ሴት አትጨብጥም ምናምን ኣ?" ብላ ሁለተኛ ጥያቄ አስከተለች።

ንግግር ላለ ማርዘም ብዬ "ያው………" ስል
"ባክህ እኔም ድሮ እንዳንተ ነበርኩ" አለችኝ።


አሁን ጨዋታው አጓጓኝና በፍጥነት እና በመገረም "እንዴት!?" ብዬ ጠየኳት።
ሳቅ አለችና "ድሮ በልጅነቴ ሙስሊም ሆኜ ነበር" አለችኝ።
አሁንም በድጋሚ "እንዴት?" አልኳት

  "ሰፈር አብረን የምንማር ሙስሊም ጓደኛ ነበረችኝ። በቃ በጣም እንዋደድ፤ ብዙ ጊዜም አብረን እናሳልፍ ነበር። እናም እሷ የምታደርገው ነገር እየማረከኝ እኔም ሙስሊም ሆንኩኝ።" አለችኝ

"እሺ ከዝያስ?" ብዬ አሁንም በጉጉት መጠየቄ ቀጠልኩኝ
"ከዝያማ እኔም እሷም ሁለታችንም ኒቃብ ለበስን፣ ወንድ አንጨብጥም አልን፣ ከቤተሰብ ከሁሉም ተጣላሁኝ። ሁላቸውም ይቅርብሽ ሲሉኝ እምቢ ብዬ መኖር ጀመርኩኝ። እንደውም ኡስታዝ… …… ጋ ነበር የምንቀራው" ብላ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚታወቁ ኡስታዞች የአንዱ ስም ጠራችልኝ።

አሁንም ሳቀችና "አሁን ራሱ ቁርኣን መቅራት እችላለሁ ልቅራልህ?" አለችኝ።
"ኣኣኣይ መጀመሪያ ታሪክሽ ጨርሽልኝ" አልኳት።

"በቃ ሌላ ምንም ታሪክ የለም: የተወሰነ ጊዜ ከቆየሁኝ በኋላ በጣም ከበደኝ" አለች
"ምኑ??" ስላት
"በቃ እስልምና ውስጥ "እንዲህ አድርጉ፣ እንዲህ አታድርጉ" የሚባሉ ነገሮች ጠንካራ ሰው ከሆነ እንጂ አይችላቸውም። በቃ ሴት ከሆንክ ከወንድ አታወራም፣ በቀን አምስት ጊዜ ይሰገዳል፣ የማይፈቀዱ ነገሮች ከሰራህ አላህ ይቆጣል እኔ ደሞ ዘና ብዬ መኖር ነው የፈለኩት። አሁን ሙስሊም ብሆን እኮ ሱሪ ለብሼ አልወጣም ነበር" ብላኝ አሁንም ትስቃለች።


እኔ ግን የሆነ በቃ አሳዘነችኝም ደበረችኝም………
"ኣኣይ እንዳልሽው ለሰው ልጅ የሚከብድ የሆነ ትዕዛዝ የለበትም፤ ግን ደግሞ በዘላለማዊው ሀገር ደስተኛ ሆነሽ ለመኖር በዚች ሀገር ላይ የአላህ ትዕዛዝ ማክበር አለብሽ ነው።" አልኳት

"አውቃለሁ ትክክለኛው የፈጣሪ እምነት እስልምና ነው!! እኔ ግን ትዕዛዞቹ ከብደውኛል" አለችኝ

"እና እንዲው መቀጠል ነው የምትፈልጊው?" አልኳት
"ለወደፊት ፈጣሪ ያውቃል አሁን ግን ዘና ማለት ነው ምፈልገው" አለችኝና………

"አሁንማ ብታይ አንድ ወንድሜ ሙስሊም ሆኖ: በቃ እንዳንተው አክራሪ ሆኗል፤ ሴት አይጨብጥም፣ ሴት አያወራም: እንደውም አምጥቼው አስተዋውቅሃለው።" አለችኝ


  ቦታው የስራ ቦታ እንደመሆኑ ሌላም ደምበኛ እየመጣ ምናምን; እኔም የሆነ የአስተሳሰቧ ድክመት ስለ ደበረችኝ ከዚህ በላይ ማስረዘም አልፈለኩም። መመለሷ ላይቀር ተለያየን።

ከቅናቻ በኋላ ከመጥመም
ከብርሃን በኋላ ከሚመጣ ፅልመት

     🤲አላህ ይጠብቀን
🤲
[ከፈረሳው በፊት የተከሰተ የግል ገጠመኜ ነው]




🖊አቡ ሙSሊM ሐምዱ ቋንጤ!!
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

17 Oct, 08:17


👇

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

17 Oct, 03:12



  በዚህ ዘመን በደዕዋው ዘርፍ ላይ ያለው ምቀኝነትና ክፋት በዱንያ ጉዳዮች ላይ ከሚታየው በሽታ በጣም የራቀና የባሰ ነው።
  አላማችን ዳዕዋውን ማስፋት ከሆነ ለምን እንበላላለን ይሄ ብንደብቀው እንኳ የማይደበቅ አሳፋሪ ግን በገሃድ የሚታይ ነውር ነው።

   በግል ጉዳይ በሆነ ወንድሙ ላይ ያቄመው ሁላ በደዕዋ ሽፋን  እየጮኸ ህዝብ ማደናገር በጣም የተለመደ ሆኗል። ወንድሜ በዚህ ዘመን ያለው እንቅፋት ብዛት በርብርብ ለመጋፈጥ እንኳ የሚፈትን ነው። ትብብሩ ቢቀር አንዱ ሌላውን ከደዕዋ መስክ ለማውጣት አለፍ ሲልም ለማጥፋት መነሳት ግን ለደዕዋው እዳ መሆን፣ ተያይዞ መክሰም ነው የሚያስከትለው። ከፍትጊያው መጨረሻ ደግሞ የሚያተርፈው ሌላ ነው።

ስለዚህ………
    ከወንድምህ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘህ ክፍተቶችን እየተራረምክ ተደጋግፈህ ለመጓዝ ሞክር። ይሄ ካልሆነልህ ከነ ድክመቱ እያስታመሙ የሆነን ቀዳዳ እንዲሸፍን መተው የተሻለ ሊያተርፍ ይችላል።

ልትሰብረው ወይም ከደዕዋው ዘርፍ አሽቀንጥረህ ልታስወጣው ከመነሳትህ፣
ልቡ ባንተ እንዲያዝን ከማድረግህ በፊት
    ደግመህ ደጋግመህ አስብበት።

 

https://t.me/mesjidalteqwawenabo
👆
👇
https://t.me/hamdquante

🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

16 Oct, 16:01


📖{وَعَسَى أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَعَسَى أَن تُحِبُّوا شَيْئًا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ}
{…የሆነን ነገር ለእናንተ የተሻለ ሆኖ ሳለ ልትጠሉት ትችላላችሁ: የሆነን ነገር ለእናንተ ክፋት ሆኖ ሳለ ልትወዱት ትችላላችሁ፤ አላህ ያውቃል: እናንተ ግን አታውቁም።}

  [አል_በቀራ:²¹⁶]


ይህንን የአላህ ማስታወሻ የተገነዘበ ሰው፦
💫መልካም ነገር ሲገጥመው በደስታ ፈንጥዞ ድንበር አያልፍም።
ምክንያቱም፦
  ከጀርባው ምን እንዳለ አያውቅም!!

💫መጥፎ ነገር ሲገጥመውም ተክዞ በሀዘን ድንበር አያልፍም።
ምክንያቱም፦
  ከጀርባው ምን እንዳለ አያውቅም!!






https://t.me/hamdquante

11,775

subscribers

2,171

photos

187

videos