ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ስለ ድንግል ማርያም...!
"አንቺ የተከበርሽ የተደነቅሽ ድንግል ሆይ ከየትኛውም ታላቅነት በላይ ታላቅ ነሽ፤ እንዳንቺ ያለ ታላቅነት ያለው ርሱ ማን ነው? አንቺ የእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ድንግል ሆይ ከፍጥረታት መኻከል ከማን ጋር ላወዳድርሽ? ከኹሉም በላይ ታላቅ ነሽ፤ የዐዲስ ኪዳን ታቦት ወርቅን ሳይኾን ንጽሕናን የተጐናጸፍሽ! እውነተኛው መና በውስጧ ያኖረችው መሶበ ወርቅ የተቀመጠባት ታቦት ነሽ ይኸውም ሥጋን የተዋሐደው መለኮት ነው፤ ከለመለመችው ምድርና ከፍሬዋ ጋር ላነጻጽርሽን? ግን አንቺ ኹሉንም ትልቂያቸዋለች ምክንያቱም “ምድር የእግሬ መረገጫ ናት” ተብሎ ተጽፏልና (ኢሳ 66፡1)
O noble Virgin, truly you are greater than any other greatness. For who is your equal in greatness, O dwelling place of God the Word? To whom among all creatures shall I compare you, O Virgin? You are greater than them all. O Covenant, clothed with purity instead of gold! You are the Ark in which is found the golden vessel containing the true manna, that is, the flesh in which divinity resides. Should I compare you to the fertile earth and its fruits? You surpass them, for it is written: “The earth is my footstool” (Is 66:1).
ነገር ግን አንቺ ፍጹም የኾነውን የባሕርይ አምላክ እግር፣ ራስ እና መላ አካል ይዘሻልና፤ ሰማይ ታላቅ የኾነ ቢኾንም ግን ያንቺ አቻ አይኾንም “ሰማይ ዙፋኔ ነው” ተብሎ ተጽፏልና (ኢሳ 66፡1)፤ አንቺ ደግሞ የአምላክ ማደሪያ ነሽ፤ መላእክት እና የመላእክት አለቆች ታላቅ ናቸው ብልም አንቺ ከኹሉም ታላቅነት በላይ ነሽ፤ ይኸውም መላእክት እና ሊቃነ መላእክት ባንቺ ማሕፀን ላደረው ለርሱ በረአድ የሚያገለግሉ በመኾናቸው በፊቱ መናገር የማይችሉትን አንቺ በነጻነት ታናግሪዋለሽ፡፡ ኪሩቤልን ታላቅ ናቸው ብንልም አንቺ ከነርሱ ታላቅነት በላይ ነሽ፤ ኪሩቤል የእግዚአብሔርን ዙፋን ይሸከማሉ (መዝ 80፡1፤ 99፡1)፤ አንቺ ግን እግዚአብሔርን በእጅሽ ያዝሽው፤ ሱራፌልንም ታላቅ ናቸው ብልም አንቺ ከነርሱ ታላቅነት በላይ ታላቅ ነሽ፤ ሱራፌል በክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ (ኢሳ 6፡2)፤ ፍጹም የኾነውን ጌትነቱን ማየት አይችሉም አንቺ ግን ፊቱን እያየሽ እና እየዳሰስሽ ጡትን በከበረ አፉ ውስጥ አጥብተሻልና ከነርሱ ትልቂያለሽ፡፡
But you carry within you the feet, the head, and the entire body of the perfect God. If I say that heaven is exalted, yet it does not equal you, for it is written: “Heaven is my throne” (ibid.), while you are God’s place of repose. If I say that the angels and archangels are great—but you are greater than them all, for the angels and archangels serve with trembling the One who dwells in your womb, and they dare not speak in his presence, while you speak to him freely. If we say that the cherubim are great, you are greater than they, for the cherubim carry the throne of God (cf. Ps 80:1; 99:1), while you hold God in your hands. If we say that the seraphim are great, you are greater than them all, for the seraphim cover their faces with their wings (cf. Is 6:2), unable to look upon the perfect glory, while you not only gaze upon his face but caress it and offer your breasts to his holy mouth….
ሔዋን የሙታን እናት ናት “ኹሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲኹ ኹሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይኾናሉና” (1ቆሮ 15፡22) እንደተባለ፤ ሔዋን ከዛፍ ፍሬ ወስዳ ባሏ ከርሷ ጋር እንዲበላ አድርጋለች፤ በዚኽ ምክንያት እግዚአብሔር “ከዚኽ በበላችኊ ጊዜ ትሞታላችኊ” ካላቸው ዛፍ በሉ (ዘፍ 2፡17)፤ ሔዋን ፍሬውን ወስዳ የተወሰነውን በልታ የተወሰነውን ለባሏ ሰጠችው፤ ርሱም በላው ሞተም፡፡ አንቺ ብልኅ ድንግል ሆይ በአንቺ ግን የእግዚአብሔር ልጅ የኾነው የሕይወት ዛፍ ዐደረ፤ በእውነትም አካሉን ሰጥቶናል እኛም ከርሱ በልተናል፤ ሕይወት ለኹሉም እንዲኽ ተሰጠ፤ ባንቺ በተወደደው ልጅሽ በእግዚአብሔርነቱ ምሕረት ኹሉም ወደ ምሕረት መጣ፤ በዚኽም ምክንያት ነው መንፈስሽ በአምላክሽ በመድኀኒትሽ ሐሤት ያደረገው"
As for Eve, she is the mother of the dead, “for as in Adam all die, even so in Christ shall all be made alive” (1 Cor 15:22). Eve took from the tree and made her husband eat of it along with her. And so they ate of that tree of which God had told them: “The day you eat of it, you shall die” (Gen 2:17). Eve took from it, ate some of it, and gave some to her husband with her. He ate of it, and he died. In you, instead, O wise Virgin, dwells the Son of God: he, that is, who is the tree of life. Truly he has given us his body, and we have eaten of it. That is how life came to all, and all have come to life by the mercy of God, your beloved Son. That is why your spirit is full of joy in God your Savior!
St. Athanasius, Fourth Century Homily of the Papyrus of Turin, ed. T. Lefort, in Le Muséon 71 (1958): 216-217 .
………………………………………………
https://t.me/orthodoxawitewahdo
ቻናሉን ተቀላቅለው ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ወንጌል ይማሩ...!
ይቆየን