ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን) @fionteabewzeorthodox Channel on Telegram

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

@fionteabewzeorthodox


በዚኽ ቻናል ጽሑፍ የሃይማኖታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን) (Amharic)

ይህ ቻናል ጽሑፍ ከኦሮዱን ኦርቶዶክስ ትክክለኛ አገልግሎት እንዲሆን ይቀርባል። በዚህ ቻናል ጽሑፍ የሃይማኖታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ በመሆኑ እና የሚለያየውን መረጃዎችን ይወቁ። እንደ ርሑስ የተቀረው የቻናላ ሥራ ነው ፡፡ የአገልግሎት እንቅስቃሴ በግምት ሌላ ምርጫ ይሰጠዋል ፡፡ ይሁንም በዚህ ቻናል ጽሑፍ ለአገልግሎት የአስተያየት ዓሳ ውስጥ የተወሰነው ተግባር አጠናቅቋል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

19 Feb, 02:08


"ወደ እምነትና ሕይወት የማያደርስ የቲዎሎጂ እውቀት የአጋንንት ድግምት ያኽል ነው"

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 20:14


https://youtu.be/q9FKmWHWbHQ?si=PcB0w2xeke3z_vCN

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 17:54


መሻገር 

Transcend አማርኛ አቻው መሻገር ከምናየው ከምናውቀው በላይ ያለ እውነታ ማለት ነው። የምናውቀው የምናየው በስሜት ሕዋሳቶቻችን የምንደርስባቸው ነገሮች በእውቀት የምናውቃቸው ታሪኮች እውነታው እሱ ብቻ አይደለም። መሻገር (transcend) ማድረግ አለበት።

ምሳሌ:-
አብርሃም የኹሉ አባት (አበ ብዙኀን)  ተብሏል። “ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፤ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።” ዘፍ.17:5

አብርሃም የዓለምን ሕዝብ ግን አላስገኘም። ከጥፋት ውኃ በኋላ የሰው ዘር መነሻው ኖኅ ነው። አብርሃም  አሥራ ኹለቱ ልጆች ከእርሱ አብራክ ከወጣው ያዕቆብ መገኘት ነው። አብርሃም ምልክት ነው። የእምነት ምልክት። አብርሃም በእንዴት ያለ እምነት ልጁን ጨክኖ ሊሠዋ ስለት እነሣ። ፈጽሞ ይስሃቅ በእርሱ ልብ ተሠውቷል። አብርሃም ምን ቢያምን በእርጅና ልጁን ሊያርድ ቆረጠ? ከዚያ በፊት አልተደረገ ፣ መጽሐፍ ላይ አላነበበ፣ እግዚአብሔር በድምጽ ብቻ ያናገረው ሰው ነው። እና እንዴት ቢያምን ነው ልጁን የሚሠዋው።

እሺ እሱ አምኖ አደረገ እንበል። እኛ አብርሃም ምሳሌ እያየን፣ ወንጌል ተሰብከን፣ ስንት መጽሐፍ እንብበን ቄስ ዲያቆን ሰበካ ጉባኤ ምናምን አገልግለን ዛሬ “ልጅህን እረድልኝ” የሚል ድምጽ ብንሰማ እንታዘዛለን። ልጃችሁን ስታርዱ አስቡት። ይኽ ታሪክ ነው መሻገር transcend የሚባለው።


አብርሃም እግዚአብሔር አብን ወካይ ነው። አንድያ ልጁን እስከ ሞት የሰጠው እግዚአብሔር አብ ብቻ ነው። ያውም ለመስቀል ሞት። ያውም ለውርደት ሞት። "በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።" ዮሐ.3:16

አብርሃም አንድያ ልጁን ሰጠ። አብርሃም ሌሎች ልጆች አሉት ግን ታሪኩ ማንጸሪያ ነው። የመጀመሪያ ልጁ ነው። አብ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የባሕርይ ልጁን ወልድን ሰጠን። ፍቅር መስጠት ብቻ ነው። ሰጥቶ መቀበል ዲፕሎማሲ ነው። መውደድ ብቻ ነው ሲወዱ መልሶ መውደድ ብድር ነው። ከአብርሃም ወደ አብ ማደግ። 


ማማተብ

ማማተብ ትርጉሙ መባረክ ፣ ማመልከት፣ ምልክት ማድረግ ማለት ነው። ማማተብ የአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ፊትን ማመልከት መባረክ ነው። ይኽ የምናየውና የምናደርገው ነው። ይኽ ትርጉም መሻገር transcend ሲያደርግ ሙሴ በበትሩ ባሕር እንደ ተሻገረ ዓለም ለመሻገር መስቀሉን እንደ ድልድይ እያነጠፍን ነው፣ እየተመረኮዝን ነው።
ማማተብ በአጋንንት የተሞላውን ዓለም በሰይጣን ፊት መለከት እየነፋን ነው። ሞትና ትንሣኤውን እየተከልን ነው።

መስቀል መሳለም

መስቀል ሲሳለም ግንባርና ከንፈር መስቀሉን ማስነካት ነው። ይኽ የክርስቶስን ቁስል መሳም ነው። ደሙን ማሽተት ነው። አፍንጫ በሽቱ ጠረን ደስ እንደሚሰኝ በክርስቶስ ደም ነፍስን ማሽተት ነው። ካልኾነ ሺኽ ግዜ ስትስም ብትውል ለውጡን አታይም ትርጉምም አይሰጥም። ለብዙ ሰው መስቀል መሳለም ለሰላምታ ነው። መስቀል መሳለም ሰላምታ መስጠት አይደለም። ቄሱን አባን ሰላም ልበል ይላል። አይደለም።

ቤተ ክርስቲያን መሳም (መሳለም)

ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት። እናቱ ድንግል ማርያም እንደ ሳመችው ሰሎሜ አቅፋ እንደ ሳመችው የክርስቶስን አካል መሳም ነው። ከንፈርህን ይቀድሳል። 

ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባት

ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባት ወደ ሕንጻ መግባት አይምሰልህ። ወደ ገነት መግባት ማለት ነው። ገነት ውስጥ ስትኾን ጥሞናህን አስብ። ቤተክርስቲያን ውስጥ ስታወራ ስትስቅ ገነት ውስጥ ኾነህ እየሳቅህ መኾኑ ነው። እኛ ደግሞ እንጣላበታለን እንጠላላበታለን። ምክንያቱም ሕንጻ ውስጥ ነና።

እንዲኽ እያለ ነው መንፈሳዊ ሕይወት የሚሻገረው። ካልኾነ ደረቅ ሕይወትን እየኖርክ እግዚአብሔርን በጥቅስ እየሸመደድን እንኖራለን። እግዚአብሔር ቢሮ ውስጥ ያስቀመጥነው ያክል ስሜት እያዳበን እንኖራለን።

ቅዳሴ፣ ቡራኬ፣ ቁርባን፣ ትምህርት፣ ጸሎት
...... እያለ መቀጠል ነው። መሻገር transcend ማድረግ ግድ ነው።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 16:54


ውስጣችን ያለውን የጥምቀት ከውር ማየት!! ከውር የብርና ወርቅ ማቅለጫ ነው።
"ማቅለጫ ለብር፥ ከውር ለወርቅ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይፈትናል።" ምሳ.17:3

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 16:22


እየተጨነቅን ፈለግንኽ

"ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።" ሉቃ.2:48

ጌታ አሥራ ኹለት ዓመት ኾኖታል። ሰው ያውቃል መንገድ ያውቃል መጠየቅ መናገር ይችላል። እመቤታችንና ዬሴፍ ግን ጌታን በማጣታቸው ተጨንቀው እየፈለጉት ተመለሱ። እንዲኽ የማለቷ ዋና ምክንያቷ አይሁድ ልጄን ይገድሉብኛል የሚል ስጋት ስለነበራት ነው። ምክንያቱም ከዚኽ በፊት አስቀድሞ ጌታችን ገና የኹለት ዓመት ሕፃን ሳለ ሄሮድስ ሊገድለው ሽቶ ሲያሳድደው ነበርና ነው።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 16:13


ሞክሯቸው

ማማተብ ?
ቅዳሴ ?
ቡራኬ ?
መስቀል ፣ ቤተ ክርስቲያን መሳለም ?
ቤተ ክርስቲያን?
ቤተክርስቲያን መግባት ምን ማለት ነው?


ምንድነው ውሳጣዊ ትርጉማቸው? ከነዚኽ የቀረበና የቀለሉ ቃላት የሉንም። የየእለት ተግባራችን ናቸው። የምጠይቃቸው ሰዎች መልሰው እንኳ አያውቁም። ስለሚዘምሩት መዝሙር ትርጉም አያውቁም። ይኼ እንዴት አይቆጨንም።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 16:00


ትብብር ስለመጠየቅ !!

ኹሌም በማልፈልገውና በማይጠቅመኝ አካባቢ መቆየት ምርጫዬ አይደለም። ካልጠቀመኝ ከጎዳኝ ባልንጀርነትን እንኳ አላቀርብም። በሩቅ ነው የምሸሸው። ፌስቡክ ስላላስደሰተኝ ዘግቼዋለኹ።

በማይጠቅማችሁ፣ በማትማሩበት ይልቁንም በሚያነጫንጫችሁ የቴሌግራም ግሩፕ ውስጥ መቆየት አያስፈልግም።

እኔ ሰው ላስደስት፣ አዲስ መረጃ ልንገር ብዬ አልጽፍም። ዋና ጉዳዬ ለሰው መንፈሳዊ ሕይወት ቅርብ የኾኑ መሠረታዊ ትምህርት ላይ ማተኮር ነው። የግድ ልናውቃቸው የሚገቡ የየእለት ሕይወት ኑሮ ላይ ማተኮርና ፍንጭ መስጠት ነው። ተጨማሪ ስህተትን ለማረም ምልከታን ማሳየት ነው። ከዚያ ውጭ ጉዳይ የለኝም። ለእኔ ቤተ ክርስቲያን እና ሀገር አንድ ናቸው። አንዱ ለአንዱ ነፍስና ሥጋ ናቸው። እንዲመርና እንዲጠቅም አድርጌ እጽፋለኹ። ቅዱሳን ብፁዓን ማለት አልችልበትም።

ቅዱስ ኤፍሬም በትርጓሜው ይኽንን አይነት መልእክት እንዳለው አንቤያለሁ።
የሚቆላምጥ ንግግርም ትምህርትም አልወድም። ማስመሰል የምጸየፈው ነገር ነው። ሳቄ ሳይመጣ አልስቅም፣ የመድረክ ድምቀት የሰው አንቱታ አይስበኝም። እኔ ጥቂቷን ቅርቧን ነገር እንዲያውቁ ማገዝ ነው።

በመኾኑም ብዙ ለሚያነጫንጫችሁ ምቾት ለማይሰጣችሁ ይኽ ገጽ ለእናንተ አይደለምና እንድትለቁ አሳስባለሁ። በገዛ ስልካችሁ ለምን ትናደዳላችሁ። ወደሚመጥናችሁ ደስ ወደሚላችሁ ወደምትማሩበት ተቀላቀሉ። ልመናዬ ነው።


ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 15:45


ከየካቲት 11 የትግራይ ሕዝብ ምን አገኘ?
ሌ/ጄነራል ዮሐንስ

ሁለት ትልልቅ ሀገር ያጠፋ ጦርነት
ከሌላው ሕዝብ የመነጠል ስሜት
ጠላት ኾኖ መታየት
ሚሊየን የሚቆጠሩ ልጆቹን ማጣት!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 15:21


አንብቡት

ቢያንስ ርእሱን ብቻ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 14:52


እውቀት 

ሁሉም የነገረ መለኮት ትምህርት (ቲዎሎጂ) የአደባባይ ትምህርት አይደለም። ኹሉም አይነት ትምህርት ለኹሉም ሰው የሚኾን አይደለም። ለሕጻን ኹሉም ምግብ በአንዴ አይሰጠውም። ወተት፣ ፍትፍት፣ ሥጋ፣ አጥንት እያለ ይሄዳል። ቤተክርስቲያን ውስጥ 20 ዓመት ስለኖሩ አዋቂ አይኮንም፣ ገዳማት ስለተዞረ በየመድረኩ ስለታየን እውቀት አይመጣም። 

እውቀት ገንዘብ የሚኮንባቸው መንገዶች ትምህርት እና ንባብ፣ አስተውሎት ወይም አሰላስሎት (ቅጥነተ ኅሊና ናቸው። እነዚኽም ቢኾኑ የሚደርስባቸው ጥቂት ነው። ድርስ እውቀት የሚባል ነገር የለም። 

ቁጭ ብሎ መማር የተማርነው ከጌታ ነው። ክርስቶስ ያመልክታችሁ እግዚአ ኩሉ ኢየሱስ ፊደል ተምሯል አሌፍ ቤት ጋሜል .. እያለ አጥንቷል። ቀለም እየበጠበጠ ስእል መሳል ተምሯል። (ተአምረ ኢየሱስ)

ምከራብ ተገኝቶ የመጽሐፍ ጥቅል ሲነበብ ሰምቶ መምህራኑን ጠይቋል። ቁጭ ብሎ ተምሯል። ምን እያለን መስሎሃል? “ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት” ሉቃ.46

የኢየሱስን አስተዳደግ ተመልከት “ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።” ሉቃ.2:52

ይኽንን አይቶ የማይደነቅ እንዴት ያለ አዕምሮ ነው። ማዕምረ ኅቡአት በጥበብ ፣ በቁመት፣ በሞገሥ ማደግ። ይኽ በከንቱ ተጻፈን? 
ለማወቅ መማርን በቀስታ ማደግን፣ ጥበብን መሻትን በተግባር አሳያን። ጥበብ ጎሎት፣ እውቀትን ሽቶ ጥበብና እውቀትን ከፍጡራን ፈልጎ አልተማረም። ባለመማር ባለ ማወቅ ጥበብ በማጣት ሰው ተገድቶ ነበር። ያዳናን በአርአያ ጭምር ነው። በሱታፌ እንዴት መዳናችንን እንደምንጓዝበት አሳየን። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 14:29


የሙከራ ጥያቄ

ጥንተ አብሶ (የቀደመ በደል) ምን ማለት ነው? የትኛው ነው የአዳም በደል የሚባለው?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 12:59


"አንተ የምታስተካክለውን ነገር እግዚአብሔር አስተካክልልኝ ብለኽ አታልቅስ፣ አትጠብቅ። ራስኽ አስተካክል"

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 02:45


የጥንተ አብሶ ጉዳይ ጥያቄ ኾኖ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ መነሣት የጀመሩት የስዊድን ሚሽነሪዎች ናቸው። ፕ/ር መስፍንና ዶ/ር አክሊል የጻፉትን መጽሐፍ እንዲኹም ቃለ ምልልሳቸውን ስሙ።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 01:03


እግዚኦ

በነገረ ክርስቶስ ላይ የተሰነዘረ ምንፍቅና 

አርዮስና አውጣኪ በአንድነት የታዩበት የምንፍቅና ትምህርት በ"ሐዋርያ መልሶች" እነርሱም በዚኽ መልኩ አልመነፈቁም!!

1.  ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው ወራት አብን አምልኳል።

2. “ለኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋሕዶ በኋላ አብ አምላኩ ነው” 

 3. "ቃል የተዋሐደው ሥጋ ስላልተለወጠ አሁንም ያንሳል፣ አምላኬም ያለው በሥጋው ነው፤ ሥጋው ያንሣልና።" 


3. "ለሥግው ቃል አንድ ፈቃድ እንዳለው ነገር ግን የሥጋ ፈቃድ ለመለኮት ፈቃድ ለዘላለም ሲገዛ ይኖራል" 


4. "ቃል የተዋሐደው የጎሠቆለ ሰውነትን ነው"

በጥቅሉ ትምህርቱ ፍጡር ማለት ይኽ ነው 


መማር ማንን ገደለ ካልተማረ ካላነበበ ምነው ዝም ማለትን ማን ከለከለው። ነገረ መለኮት ትምህርት ዘሎ የሚገባበት አይደለም። ቃላት አጠቃቀም በጣም ከባድ ናቸው። እንደ ወረደ ትርጉም አይሰጠውም። 
ይኽንን ነው ትውልድ እያስተማረ ወጣቱም እየተማረ ያለው የቲክቶክ ሊቃውንት።  እየሰሙት ተማርን ለሚሉት ሰዎች ጆሮ አዘንኩ።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 00:17


ክህነት!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Feb, 00:02


ዐድዋ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

17 Feb, 23:26


ሚያ ሞተሊ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

17 Feb, 19:56


ቅዳሴ ስቀድስ ሳስቀድስ ኖሬያለሁ. ምክንያቱም ቅዳሴ በድምጫ ቢሆንም ተምሬ የለ ሰዓታት እቆምን የለ። አውቃለሁ ብዬ ነበር። ቅዳሴን ሳነብ። የመጀመሪያዋ ቃል “ይኽች ቀን ምን የምታስፈራ ናት መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ የወረደባት” ሲል ይህች ሰዓት ሲል ትርጉሙን አነበብኩት። ለካስ ቅዳሴ የሚቀደሰው በሰው ጊዜ ወይም ሂያጅ ሰዓት ውስጥ አይደለም በዘለዓለም ሰዓት ውስጥ ነው። ዘለዓለም ደግሞ ሰዓት ወይም ጊዜ የሚባል ነገር የለም። ቅዳሴ ከጊዜ ውጭ ያወጣል። ከቤተ ክርስቲያን አስቀድሰን ስንወጣ ነው ወደ ምድር ወደ ሂያጅ ሰዓት የምንመለሰው departure and arrival እንደ ማለት መሆኑን አነበብኩ ማለት ነው። የእስከ ዛሬ ቅዳሴ አውቃለሁ እቀድሳለሁ ያልኩት ለካ አላውቅም ነበር። ለካስ ደንቁሬ ነው የኖርኩት። 

ቅዳሴ ጥሩ ድምጽ ማንንም እንደ ሚማርክ አውቃለሁ ጥሩ ቅዳሴ የተረጋጋና በጥሩ ድምፅ ሲቀደስ በጣም ደስ ይላል። ለካስ ቅዳሴ እሱ አይደለም። እዚያ ቃል ውስጥ ያለው የካህኑ ልምጃ፣ ነፍስን ማንጻቱ፣ አምስቱ ሕዋሳት በአንድ ላይ ሲጋደሉ፣ ኃጢአት በጆሮ ገብቶ በልብ በሚያርፈው ቃል በሰውየው ተሰጥዖ እየተናደ እየፈረሰ ሲወጣ፣ ኃጢአት አቅም ሲያጣ ከሰውየው የቅድሴ ሱታፌ ነፍሱ ስትነቃቃ፣ “ተአምሁ በበይናቲክሙ” እያለ ጎንበስ ጎንበስ ብሎ ሰላምታ ሲሰጣጥ ከውስጥ ለመግባት የሞከረው ሰይጣን እየተራገፈ ሲወጣ፣ ሰይጣን በተራው ፍላጻውን እየላከ የቄሱን ኃጢአት ይነግርሃል፣ ያንተን በደል ይነግርሃል ጣተን ይቀስርብሃል። 

አንዳንዴ የምታየውን የእመቤታችንን ስዕል ሁሉ ያሰድብሃል በጣም ያበሳጭሃል፣ ሕሊናህን ወደ ቤት ይወስደዋል፣ ቅዳሴ መካከል ቆመህ በሕሊናህ ከሰው ያደባድብሃል። ካህኑ በየመካከሉ እየወጣ በመስቀል ይባርካል “አርህቅ እግዚኦ እምኔየ ወእምነ ኩሉ ሕዝብከ” ጊንጡ እባቡ ከይሲውን ያባርራል። ሰይጣን ሳያቋርጥ ጾሩን ያፈሰዋል አንዴ ካህኑጋ አንዴ እንትጋ ይመጣል ። ቅዳሴው ተገባዶ ሥጋ ወደሙ ይሰጣል። አንተ ቆመህ ትቀራለህ። የተዋሐደህ ክርስቶስ የለም። የአንተ አካል የእርሱ አካል አልሆነም። ቆመህ ተመለስክ። ሰይጣን በጣም ይደሰታል። ጎሽ ጉድ ሆኜ ነበር ይላል።  ይህንን ሳነብ እስከ ዛሬ ደወል ተደውሎ ገብቼ ሳስቀድስ ቅዳሴ የማውቅ የመሰለኝን ደንቁሬ ኖሯል እልና እቀጥላለሁ። 

እናም መጨረሻ አንድ ነገር ተመኘሁ ሌላው ሌላው ቢቀር ሦስት ነገሮች እንዲገቡኝ ሁሌ እመኛለሁ እንዲገባኝ ማንበብ እቀጣለሁ። ሌላውን ተስፋ ቆርጩ ሳይሆን በቃ አቅሜም አይደለም አልችልም የምሰማውን የሰማሁትን በእምነት እቀበላለሁ። ቢያንስ ግን ሦስቱን ለማወቅ እጓጓለሁ ቤተ ክርስቲያን ፣ ጥምቀት፣ መስቀልን በተመለከት። ሌላውን እስክሞት እንደማላውቅ አውቃለሁ። 

ከአንድ ዓመት በፊት ጽፌ ዛሬ የለጠፍኩት የግል ምልከታዬ ነው!!

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

16 Feb, 02:04


እግር ማጠብና ትኅትና 

እግር ማጠብ ትኅትና ነው? እጅ  ማስታጠብስ ቢኾን? ጌታ ትኅትና ያሳየው በእግር ማጠብ ነው። እርሱ ጌታ መምህር ሲኾን እግር አጠበ። ሐዋርያትም እንዲኹ አድርጉ አላቸው። በወቅቱ ሰው የሚሄደው ያለ ጫማ ነው። በጣም ይቆሽሻል። የግድ ምሽት ሲኾን መታጠብ አለበት። እግር ያገኘውን ሲረግጥ ስለሚውል ሌላ ሰው ሊነካው አይፈልግም። ስለዚኽ ሰውየው የራሱን እግር ያጥባል። ድንጋይ የመታው ይደማል፣ እሾኽ የወጋው ይቆስላል፣ በሽታም ይይዛል። ባክቴሪያም አለው። ያንን በእጅ መንካት ደግሞ ይጸየፉ ነበር። 

ጌታ ትኅትና ያለው እግር ማጠቡን አይደለም። ለሌላው ሰው የሚደረግን ጥቅም ነው። ሳይወደው እግሩን ቢያጥበው ትኅትና አይደለም። ሌላው ሊያደርገው የማይወደውን የዝቅታ ነገርን ማድረግ የሰውየውን ቁሻሻ ማራገፍን መምረጥ ነው። 

እግር ለማጠብ ከሚታጠበው ሰው እግር ሥር ማጎንበስን መንበርከክን ይጠይቃል። ይኽም የሚያመለክተው ከፍታ ያልነው በዝቅታ ውስጥ ክብር ያለው በውርደት ውስጥ ነው ማለት ነው። ትኅትናን በእግር ማጠብ ገለጣት። እኛ እግር ብናጥብ እንደ ሶፍት የለሰለሰ፣ ያልቆሸሸ እግር ነው። ዋና ምልክቱ ግን መታዘዝ ነው። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

16 Feb, 00:14


በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ዋላ ቀበሌ በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች መሰደዳቸውና መኖርያ ቤታቸው መቃጠሉ ተገለጸ !

በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ዋላ ቀበሌ ቦሬ ከተማ በሚገኙ ከሺህ በላይ በሆኑ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ባነጣጠረ ጥቃት መኖርያ ቤቶቻቸው እንዲሁም የንግድ ሱቆቻቸውን ጨምሮ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ተናግረዋል፡፡ የጥቃቱ መነሻ ምን እንደሆነ እስከ አሁን በትክክል አልታወቀም፡፡

ጥቃቱ በትናንትናው ዕለት የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ  በተተኮሰ ጥይት የተጀመረ ሲሆን በቀበሌው የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ ስጋት ላይ ናቸው ተብሏል።

ጉዳዩን ለማረጋጋት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እና የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በሥፍራው ቢገኙም ጥቃቱ እስከ አሁን እንዳልቆመና ወደ ሌላ ቀበሌ እየተዛወረ ነው ተብሏል።

የአካባቢው ነዋሪዎችም ጥቃቱን ሸሽተው ወደ አጎራባች የደቡብ ክልሎች  እየሄዱ  እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

15 Feb, 21:47


ድርጊትን ሐሳብ ይቀድመዋል ሐሳብ ከየት ይመጣል?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

15 Feb, 20:46


አፍ ከመክፈት ቀድሞ አዕምሮ መክፈት!! "ግም ለግም አብሮ ሲተኛ የኔ ሽታ የኔ ሽታ ይባባላል"

መጋቤ ሐዲስ ደጉ ዓለም ካሳ

ቀድሞስ መች ጥያቄውን በአግባብ ይረዱትና ነው እሰጥ አገባ የጀመሩት? እንኳን መልሱን ጥያቄውን እንኳ በአግባብ አይረዱትም።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

15 Feb, 19:22


https://www.youtube.com/live/Miyf_x3U89A?si=nlZYZpLSOAH888IJ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

15 Feb, 18:31


https://www.youtube.com/live/3PgQeJyX8hw?si=myi_9M9Kn7bc6Qcw

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

15 Feb, 17:08


ለማድረግ ማሰብ!!


ለአንድ ዓመት ቅዳሜን እረፍት አልነበረኝም የቤተ ክርስቲያን የተጋድሎ ሂደት ጉዳይ የውይይት ቀን ነበር። ሰሞኑን ጥቂት ቅዳሜዎች እረፍት አገኛለሁ። በመኾኑም ማድረግ ያለብኝን በማሰብ ነው ያጋራኹት። 

ይኹን እንጂ ሌሎችም ቀዳሚ የምላቸውና አርዕስት አሉ። ለጥቂት ሰዎች ብቻ የሚሰጡ ናቸው። 

፩. የመጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እናጠናለን ስልጠና መስጠት።
 
፪. ቅዱስ ቁርባን መቀበል እፈልጋለሁ ግን መወሰን አቃተኝ ፣ እቆርብ ነበር ግን አቆምኩ ለሚሉ ሰዎች። 

፫. በሕይወቴ ያሳለፍኩት ጠባሳ በጎዳኝ ሰው ቂም ይዣለሁ፣ ይቅር ማለት አልቻልኩም። ምን ማለት ነው? እንዴት ይፈታል? 

፬. ገንዘብ ለምን እከፍላለኹ? በነጻ የተቀበልከውን በነጻ ስጥ ይላልና! የክፍያ ጥቅሙና ውጤቱ!! የሚሉ አጀንዳዎች ናቸው ያሉኝ። 

፭. መናዘዝ እፈራለኹ፣ የምደብቀን ነገር አለኝ ሳስበው ያስደነግጠኛል፣ በጣም ምሥጢር ነው። እንዴት ልናዘዘው የሚጎተጉተኝን እንዴት ላስቁመው?

መመሪያዎች 

፩. ሁሉም በክፍያ ብቻ ይሰጣሉ
፪. ቀላል ስላልኾኑ ለውሳኔ መዘጋጀት 

ብዛት

ቁጥር ፩ ስልጠና 10  ሰው ብቻ (፫ ወይም ፬ ቀን ብቻ)

ቁጥር ፪ ስልጠና ጥቅል ትምህርት በጋራ ፣ግላዊ ምክንያት  ትምህርት፣  ውሳኔ እስከ ተግባር በግል ብቻ። ፬ ሰው ብቻ።

ቁጥር ፫ ትምህርት ፣ ክትትል ውሳኔ በግል። ፬ ሰው ብቻ

ቁጥር ፬ በጋራ ፲ ሰው ብቻ

ቁጥር ፭ በግል ፬ ሰው ብቻ

ክፍያ በአንድ ቀን በውጭ ሀገር ያሉ በቀን $25  ኢትዮጵያ ብር 250።

በጣም ከበዛ ፬ ሳምንት ብቻ ይወስዳል። ከአራቱ አንዱን አጀንዳ ብቻ ነው ላስተምር የምችለው። 

በአካል ኾኖ  በቤተ ክርስቲያን፣ በማኅበር ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ለሚያዘጋጁ በነጻ!! 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

15 Feb, 15:36


ዘመናዊ ትምህርት

ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት ስንልክ በጸሎት የማይጀመርበት ትምህርት ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወደሌለበት ፣ እግዚአብሔር ወደማይጠራበት፣ ስለ እግዚአብሔር ወደማይሰማበት፣ እግዚአብሔርን ወደማያምን የትምህርት ሥርዓት እየላክናቸው ስለኾነ ጸሎት ምክር ክትትል የሚያስፈልገው ቤተክርስቲያን በጥብቅ ማስተማር ያለን ለዚኽ ነው። በራሱ ሥርዓት እግዚአብሔር አልባ እንዳያደርጋቸው።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

14 Feb, 21:48


"በሰው ፊት ያለኽን ቦታ ከተቀበልክ ራስኽን ስታታልል ትኖራለኽ"

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

14 Feb, 19:11


https://youtu.be/00owRWEStl4?si=AHZ-aYXbcSCLnRhJ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

14 Feb, 19:11


ዘቅዝቆ ለመሸከን አጥብቆ ማሰር 

“አጥብቆ ማሰር ዘቅዝቆ መሸከም ያስችላል።” ጠብቆ መማር ምንፍቅና ሲመጣ ይመክታል። ከማኅበራዊ ሚዲያ ቀነጫጭቦ መምህር መምሰል አልያ ወደ መድረክ ፍጻሜው የሜዳ ላይ መናፍቅ መኾን ነው። 

ውኃ ዋና እንዴት እንደ ለመድን አስታውሳለኹ። የኩሬው ዳር ላይ መንቦጫረቅ መዝለል ነው። ከጉልበት ያላለፉ ውኃ ላይ መንቦጫረቅ፣ ዳር ላይ ሳርና ድንጋይ ይዞ እግር ማወራጨት። አንድ እግርን የውኃውን ወለል እየነኩ በአንድ እግር እየመቱ መዋኘት። ሲቀጥል በወገብ ላይ ቅል አልያ አንሳፋፊ ፕላስቱክ አስሮ ወገብን ማለማመድ፣ ዋና በሚችሉ ታላላቆች እገዛ ቀስ እያሉ ወደ መሐል ጠጋ ማለት። በሌሎች ቅርብ ክትትል መዋኘት እየኝ ተከታተለኝ እያልን መልመድ። ከዚያ ራስህን ስትችል ሰውነትህ ሲቀልህ እንደ ፈለክ ትዋኛለኸ። ዘለኽ አትገባም። 

ትምህርት እንዲኹ ነው። ትምህርቱም አስተማሪውም እንዲኹ ናቸው። እየታሳስትን፣ ከሚበልጡን እየሰማን በመጠናችን እያደግን፣ ከዚያም መደበኛ የትምህርት ገበታ ላይ መሰለፍ፣ ከዚያም በማንበብ ማበልጸግ ነው። ኹሌም ማንበብ መመርመር ነው። እንዲኽም ኾኖ ብዙ አይጠራቀምም። ከዚያ ነው ለሌላው ለመትረፍ ለማስተማር መሞከር። ዘሎ ማኅበራዊ ሚዲያው ውስጥ መግባት በገዛ እጅ ዋናውን ሳይልውቁ ባሕር መጥለቅ ነው። 

አንደ ጴንጤ ጥቅስ እያነሱ ለመተንተን ለመዝለል አይኾንም። ንባብ ትርጉም ምስጢር እያሉ ማራቀቅ ይጠይቃል። ሌላው የጥቅል ትምህርት አለ ይኽ ማለት የትምህርቱ ሙሉ ትርጉምና ቅርጽ ነው። ለምሳሌ ድኅነት ምንድነው? ሰው ምንድነው? ፍጥረቱ ዓላማው፣ መጨረሻው…. 

ነገረ ሥላሴን ከነገረ ክርስቶስ ማያያዝ ነገረ ሥላሴን የሳተ ሰው ነገረ ሥጋዌን ይስታል። ነገረ ሥጋዌን የሳተ ወይም ያልተረዳ ነገረ ማርያምንብይስታል። 

አበው ከመጠምጠም መማር ይቅደም ይላሉ። የት ተማርክ ሲሉት የሚጠቅስው አብነት የሌለው የእለት ፉጨት የሰማትን ያክል ከተናገረ በኋላ ምላስ ይሰበሰባል። ትክክል ይሁን አይሁን ሚዛን እንኳ የለውም። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

14 Feb, 19:04


ትምህርት ከየት

ስለ ቤተ ክርስቲያን ወይም ሃይማኖታዊ እውቀት ከየት ታገኛላችሁ።  ቀደም ብዬ የጠየኩት ጥያቄ ነበር። ጥቂት ለመጠቆም ያክል ነው። 

በሃይማኖት መጽናት መንፈሳዊ ሰው ለመኾን የእግዚአብሔር ቃል መሠረቱ ነው። ያለ እግዚአብሔር ቃል መንፈሳዊ ሕይወት ያለ ዝናም ልምላሜን እንደ መጠበቅ ያክል ነው። “የምታደርገውን ነገር ኹሉ የእግዚአብሔር ቃልን ድጋፍ ፈልግ” የሚለን ዮሐንስ ዘሰዋስው ነው። 

እውቀት ድንቁርናን (አለማወቅ) ለመቀነስ ነው። አለማወቅ የኃጢአት መግቢያ ቀዳዳም ነውና። እውነተኛ ትምህርት የሚያስፈልገው የስህተት ትምህርት በሁሉ ኑሯችን ስለገባ ነው። 
ይኹን እንጂ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እያገኘን ያለነው ከየት ነው? ለሚለው ጉዳይ መታሰብ አለበት። 

ጉባኤያት 

ጉባኤያት ሲባል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ በጉባኤ የምንማርበት ማለት ነው። በመደበኛው ጉባኤ ቤት የአብነት ትምህርት የሚሰጥበት የቤተ ክርስቲያን የትምህርት ምንጭ ነው። 

ይኹን እንጂ ለምእመናን ግን የቤተ ክርስቲያን መድረኮች የሰንበት ትምህርት ቤት ጉባኤያት ለሃይማኖት ትምህርት መሠረት ናቸው። በደረጃ ያሳድጋሉ። ይጠይቃሉ መልስ ይሰጣል። በዚኽም ኮርስ ስልጠና፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቴች…. እውቀት ሰጭ ናቸው። 

ለማስተማር ለሚዘጋጅም ሰው ከታች መጀመር ጠቃሚ ናቸው። ማስተማር የሚጀመረው ከታች ነው። ጥቂት የተማሯትን ለቅርብ ላሉት ማስተማር ነው። 

በቤተ ክርስቲያን የሚደረጉ የመድረክ ጉባኤያት ሌላው ጠቃሚ ናቸው። ተከታታይ ትምህርት፣ ስብከት፣ ልዩ ጉባኤያት ናቸው። 

በቤተክርስቲያን ትምህርት እውቀት የሚገኘው በመሳተፍ ነው። መምህር ከተማሩው ምእመኑ ከመምህሩ ከካህኑ የሚኖረው የመማማር ኂደት ነው። የሱታፌ ትምህርት ነው። 

ሌላው መጽሐፍት ንባብ ነው። ንባብ በጣም ጠቃሚ ነው። ለሚማረውም የሚያስተምረውም። መጽሐፍት የብዙ እውቀትን በአንድ ሰብስበው ይገኛሉ፣ ተጠቃሽ ናቸው። አንድ ርእስ በሰፊው የተነትናሉ። በመኾኑን በአንድ ርእስ ላይ ሰፊ እውቀት ያስጨብጣሉ። 

በአሁኑ ጊዜ አብዛኛው ሰው የእውቀት ምንጭ ወይም የትምህርት መድረክ ያደረገው ማኅበራዊ ሚዲያ ነው። በተለይ ለብዙ ጥያቄዎች ወይም መሠረታዊ ትምህርት ለሌለው ሰው አደገኛ ነው። ስለ ሃይማኖቱ ትምህርት እውቀት የሌለው የተነገረው ኹሉ ትክክል የሚመስለው አልያ የሚያስተምረው ሰው የቤተ ክርስቲያን ሰው ስለተባለ ሊሰማ ይችላል። ይሁን እንጂ ትምህርቱ የቤተክርስቲያን ላይኾን ይችላል። 

በማኅበራዊ ሚዲያ የሚኖረው ትምህርት ንፁሕ ብቻ አይደለም። እንክርዳዱ ብዙ ነው። በጣም ብዙ ቆሻሻ ወደ አእምሮ ይከታል። የሰይጣን አሠራርም ይኽው ነው። ማጣሪያ የለንም። በቀላሉ ለጥቃት እንጋለጣለን። 

የእውቀት የመሠረታዊ ትምህርት ሚዲያውን ያደረገ ሰው ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱን ማወቅ አለበት። መረጃ ሊገኝ ይችላል። ጥቅል እውቀት ሊሰጥ ግን አይችልም። ተከታታይነት ቀጣይነት የለውም። በተለይ ሱታፌ የለውም። በትምህርት ውስጥ አንሳተፍም። 

ስለኾነም በአጥቢያችን በቅርባችን የጉባኤ ትምህርት ፣ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ፣ የምንማርባቸው መምህራን፣ የምናነባቸው መጽሐፍት ያስፈልጉናል። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

14 Feb, 15:01


https://youtu.be/00owRWEStl4?si=AHZ-aYXbcSCLnRhJ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

14 Feb, 14:11


የነቢዩ ዮናስ ምልክት

ጌታችን፡- “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል። አለ። ጌታችን እንዲህ ማለቱ በመቃብር ሦስት ሌሊትና ሦስት መዓልት ስለማደሩ ተጨንቆ አይደለም። እርሱ ከሕመማቸው ፈውሶ ከሞት እንደሚያስነሣቸው ሲነግራቸው ነው እንጂ። ማቴ.12:39

እነዚኽ ወገኖች ጌታችን በፊታቸው የፈጸማቸውንና ሊክዷቸው የማይቻላቸውን ከቃላት በላይ የሆኑትን ተአምራት ከማየት የታወሩ ናቸውና ጌታችንን ፡-“መምህር ሆይ! ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን” ብለው ጠየቁት፡፡ ስለ እርሱ የመሰከሩትን ነገሥታትንና ነቢያትን ወደ ጎን በመተው ፊቱን ወደ ነነዌ መለሰ፡፡

እነዚህ ወገኖች ከዮናስ ምንም ዓይነት ምልክትን ያላስተዋሉ፤ ብዙ ተአምራትን ያዩ በስተመጨረሻ የተአምራቱ ባለቤት የሆነውን ጌታችንን ክደው በእርሱ ላይ የፈረዱ ናቸው። ዮናስ የነነዌን ጥፋት አውጆ ነበር። በእነርሱም ላይ ፍርሃትን ፈጠረባቸው ድንጋጤም ዘራባቸው። እነርሱም በተሰበረ መንፈስ ሆነው ንስሐ በመግባት የንስሐን ፍሬ አፈሩ። አሕዛብ ይህን መረጡ ኢግዙራን ወደ እግዚአብሔር ቀረቡ፡፡ ኢአማንያን ሕይወትን አገኙ፤ ኃጢአተኞች አበደላቸው ተመለሱ፣ ግዙራን ግን ግራ መጋባት ውስጥ ወደቁ:: ስለዚህ እነዚህ አሕዛብ ባላመኑት አይሁድ ላይ ይፈርዱባቸዋል። ዮና.3:1

እንዲህም ስለሆነ ጌታችን ለአይሁድ "ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጣችሁም" ብሎ መለሰላቸው:: የዮናስ ስብከት የነነዌ ሰዎችን በሁለት መንገድ ጠቅሟቸዋል። አንደኛው በዮናስ የተነገረውን ቃል አንቀበልም ቢሉ ኖሮ ከነሕይወታቸው ወደ ሲኦል ይወርዱ ነበር። ነገር ግን በንስሐ ከኃጢአታቸው ተመልሰዋልና እንደ ዮናስ ከሞት ተነሥተዋል (ድነዋል)፡፡ እንዲህም ስለሆነ መጽሐፍ ስለ ጌታችን፡ "እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል” አለን። ሉቃ.2:34

እነዚህ ወገኖችም በእርሱ ሞት በሕይወት ሊኖሩ ወይም በሞቱ እነርሱም አብረው ለመሞት የተጠሩ ናቸው። "የነነዌ ሰዎች" በማለቱ ጌታችን ትውልዱ እንደ ነነዌ ተገደውም ቢሆን ማመናቸው እንደማይቀር ሲያመላክተን ነው፡፡

እነዚህ ወገኖች እግዚአብሔር ለሳሙኤል ከሰማይ መብረቅና ነጎድጓድ በማሰማት ምልክትን እንደሰጠው አስታውሰው እርሱንም “ከሰማይ ምልክትን እንዲያሳያቸው ጠይቀውት ነበር። ስለዚህ ጌታችን ከላይ ከሰማይ ምልክትን ሲጠብቁ ከታች ከጥልቁ በማምጣት ስለ ነነዌ ጥፋት የታወጀውን አዋጅ ነገራቸው፡፡

ምክንያቱም ከሰማይ የሆነውን ቢነግራቸው አላመኑምና እንደ ዮናስ ከጥልቁ በማምጣት ምልክትን እንደሚያሳያቸው ነገራቸው። ዮናስ ከዓሣ አንባሪ ሆድ ውስጥ ከወጣ በኋላ ምሥራችን ሳይሆን የነገራቸው የከተማዋን መጥፋት ነበር፡፡ ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያት የሆነው እንዲሁ ነው፡፡

ጌታችን “ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል” አላቸው:: በዚህም ቃሉ እርሱን መግደል እንደማይችሉ ይበልጥ እንዲገነዘቡ አደረጋቸው። የእርሱ ሞት አስቀድሞ በዮናስ ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት በምሳሌ ተገልጦ ነበርና፡፡


አቤል በተገደለበት ጊዜ ምንም ምድር አፍ ባይኖራት "አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ” ተብሎ ተጽፎ የለምን? የጌታችንም ስለ እርሱ ሥጋ ወደ መቃብር መውረድን በተናገረ ጊዜ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል" ብሎአልና ምድር ልብ አላትን? በዚህ ቃሉ "ዮናስ ምንም በዓሣ አንባሪ ሆድ ውስጥ ቢሆን እንዳልሞተና እንዳልበሰበሰ እንዲሁ ጌታችንም "ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም” እንዲል በምድር ልብ ውስጥ ቢሆንም ሕያው (በመለኮት) በመሆኑ መበስበስን አላየም። መዝ.15:10

 ዮናስ ከዓሣ አንባሪ ሆድ ውስጥ ወጥቶ የነነዌ ሕዝብ ንስሐ እንዲገባና በሕይወት እንዲኖር እንደሰበከ እንዲሁ ጌታችንም ደቀ መዛሙርቱን ወደ አሕዛብ ሁሉ በመላኩ አሕዛብ ከኃጢአታቸው ፈጽመው ተመልሰው በሕይወት እንዲኖሩ እንዲሰብኩ ላካቸው። ስለዚህ ሦስቱ ቀናት የሚታሰቡት የሞተበትና የተነሣበትን በአንድነት ተቆጥረው ነው::

ጌታችን “ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች” አለ፡፡ ንግሥተ ዓዜብ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ እርሷ ወደ ሰሎሞን እንደሄደች ቤተ ክርስቲያንም ወደ ጌታችን ቀርባለች። ንግሥተ ዓዜብ በዚህ ትውልድ ላይ እንደምትፈርድ እንዲሁ ቤተ ክርስቲያንም በትውልዱ ላይ ትፈርዳለች።

ንግሥተ ዓዜብ የሚያልፈውን ጥበብ ከሟች ንጉሥ ሰሎሞን ዘንድ አግኝታ ከሄደች እንዴት ቤተ ክርስቲያን ሕያው ከሆነው ንጉሥ ዘንድ የማያልፈውን ጥበብ ለመስማት አትሄድ! ስለዚህ “ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን" ተብሎ ተጻፈልን፡፡
@ኅብረ ወንጌል 


ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

13 Feb, 17:23


ሦስት ቀን የከረምንበት ሱባኤ ወጉባኤ ኢትዮጵያ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

13 Feb, 17:20


https://youtu.be/00owRWEStl4?si=EpRtH7k5bPJZxvo9

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

13 Feb, 16:21


ጥምቀት 

ጥምቀት ከጌታ ሞትና ትንሣኤ ጋር የምንተባበርባት ሞተን ተቀብረን ሞትን አሸንፈን የምነሣባት በር ከፋች ናት ብለናል። የብሉይ ኪዳኑ ምሳሌ አንዱ ነቢዩ ዮናስ ነው። 
“እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።” ዮና.2:1 
ዮናስ ወደ ባሕር ተጣለ ታላቅ አሳ ዋጠው። ወደ ባሕር መጣሉ የጥምቀት አምሳያዋ ነበር። በአሳ መዋጡ መቃብሩ ነው። ጌታ ሞትና ትንሣኤውን በዮናስ መመሰሉን ይነግረናል። 

“ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።” ማቴ.12:40

ከሰማይ ምልክትን የጠየቁ ፈሪሳውያን ከምድሩ ምልክት ጠቀሰላቸው። የዮናስ ወደ ባሕር መጣሉ አሳ ሆድ ውስጥ ሳይሞት መቆየቱ፣ የጥምቀት የሞትና ትንሣኤ አምሳል መኾኑን አስረዳ። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

11 Feb, 14:25


 ትንቢተ ዮናስ በነገረ መለኮት ትንታኔ


                    ምዕራፍ ሁለት


የትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ ሁለት የሚያስረዳ የዮናስን ጸሎትና ኑዛዜ ነው። 

“እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ” የሦስት ቀን ጉዳይ ለጌታችን ሞትና ትንሣኤ ምሳሌ ሆኖ መቆየቱን ጌታ ጠቅሶታል። 


ዮናስን መርከበኞቹ ሊያድኑት ብዙ እንደጣሩ ጲላጦስ ጌታ ሊያተርፈው እንደሞከረ የሚያሳይ ነው። ዮናስ ከዚህ የሦስት ቀን መከራ ተርፎ እንደገና ወደ አገልግሎት ይመለሳል። ይኽ የጌታን ትንሣኤ ያሳያል። ከጌታ ወገኖች ሳይቀር ብዙዎች ጌታን ከሞት ይነሣል ብለው አላመኑም ነበር። ጌታ ግን እንደተናገረው በሦስተኛው ቀን ተነሣ። ሰዎች ዮናስ ሶስት ቀን በአሳ ሆድ መቆየቱን ላያምኑ ይችላሉ። እንደውም ታሪኩ ለሕጻናት የሚነገር አፈ ታሪክ ይመስላል። ነገር ግን እውነት ነው። አሳው ግዙፍ  በመሆኑ ለዮናስ በቂ ክፍል ነበረው። የቆየው በእግዚአብሔር ተአምር ነው። 


በነዚኽ ቀናት ዮናስ እየጾመ እየጸለየ በራሱ ሕይወት ዙሪያ ሰፊ ትንታኔ እየሰጠ ቆየ። ብዙውን ጊዜ በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ጥቂት ሰዎች በሕይወታቸው ወሳኝ በሆኑ ውሳኔዎች ከመወሰዳቸው በፊት በገለልተኛ ቦታ በመሆን የራሳቸውን ሕይወት ይተነትናሉ፣ ሱባኤ ይገባሉ። የእግዚአብሔር ፈቃድ በሕይወታቸው ምን እንደሆነ መርምረው ለማወቅ ይጥራሉ። ዮናስ በነዚኽ ቀናት ይበልጥ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ዶግማ ተማረ ተረዳ። ለአገልግሎት የጠራው ማን እንደሆነ ተረዳ። የአገልግሎቱን ጥሪ ሳያውቅ የሚያስተምረው ስለማን እንደሆነ የማያውቅ አገልጋይ "ሽቱ ተቀብቶ ወደ ንብ ቀፎ እንደሚሄድ" ጅል ሰው ነው። 


ዮናስ በእስራኤል ከተማ ሳለ አልጸለየም፣ ወደ አገልግሎት ሲላክም አልጸለየም፣ ለመሸሽ መርከብ ውስጥም ቢሆን መጸለይ አልፈለገም። ከዚያ ይልቅ ታችኛው የመርከቧ ክፍል ተኝቶ ነበር። ይኽ ሁሉ ዮናስ ጥፋቱ ነበር። አሁን ግን የሚጸልይበት ጊዜ ደረሰ “ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦” እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ በተለያየ ምክንያት ወደ ጸሎት ይገፋናል። መጸለይ ባቆምንበት ጊዜ ግዴታ የሆነ አስገዳጅ ጸሎት ውስጥ ይከተናል። ከጸሎት ውጭ ምንም ማድረግ በማንችልበት መንገድ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶ እግዚአብሔርን እንድናስታውስ ያደርጋል።


በለአም የእግዚአብሔርን መልአክ ያየው ከነ አህያው አጣብቂኝ ውስጥ ከቶት መሆኑን አስብ። እግርህን ሰብሮ ሆስፒታል ውስጥ ተኝትህ እንድትጸልይ ሊያድርግ ይችላል። ሥራ ሥራ እያልክ ቢዚ ስትሆንን ለጸሎት ሰዓትና ጊዜ ስታጣ አጣብቂኝ ውስጥ ይከትህና በል ለጸሎትም ጊዜ ይኑርህ ያንተ ልፋት ብቻ የትም አያደርስህም ይላል። 


ዮናስ በዚኽ ጊዜ አሳ ሆድ ውስጥ መጸለይ ጀመረ። አሁን የእግዚአብሔር ሰው ወደሚያደርገው ተግባሩ ተመለሰ። ያለ ጸሎት አገልጋይነት ያለ ጸሎት የእግዚአብሔር ልጅነት የለም። በጸሎት የእግዚአብሑር ልጅ መሆንህን ትገልጻለህ። ወላጁን የዘነጋ ልጅ ከንቱ ነው። ዮናስ ጸሎት ሲጀምር በሕይወቱ ለውጥ ማየት ይጀምራል። 


ጸሎቱን በእግዚአብሔር መንፈስ መጸለይ  ጀመረ። ሲጀምር ደግሞ በተስፋ ነበር “በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ” ጸሎትህን በማማረር አትጀመር ተስፋ ይታይህ። ሁሉም ሰው የዮናስን የጸሎት መመሪያ ሊከተል ይገባዋል። ሲኦል ማለት ጥልቅ ጉድጓድ ማለት ነው። ሲኦል ቦታ አይምሰልህ ሁኔታ (state) ነው። ይኽንን ትምህርት ለብቻው እመለስበታለሁ። ሲኦል ብዙውን ጊዜ መቃብር ለሚለው አቻ ሆኖ የገባ ቃል ነው። አስፈሪ ሁኔታ ማለፉ ያለበትን ዓለም እንዲገነዘብ ያስቻለው ከመሆኑም በላይ ኑዛዜውን እንዲያቀር አደረገው። 


ስንጸልይ እግዚአብሔር እየሰማን መሆኑን ማወቅና ማመን ከሁሉም ነገር ይቀድማል። እየቀደሰ እየዘመረ “እግዚአብሔር ግን ይሰማኝ ይሆን” ብሎ የጠየቀ አማኝ እየጸለየ አይደለም። በጸሎታችን እርግጠኝነት ሊሰማን ይገባል። ምክንያቱም እግዚአብሒር የምህረት አምላክ ነውና። መስማት ብቻ ሳይሆን አዳምጦ መልስ ይሰጠናል። ንሰሐችንን ይቀበላል።


ዮናስ ጸሎቱን ሲጀምር ምንም ያየው ነገር የተለወጠ ነገር የለም። ግን እንደሚቀየር አመነ። እግዚአብሔር እየሰማው መሆኑን አመነ እርግጠኛ ነበር። አሁን እምነቱን ቀይሯል። 

በባሕር ጥልቅ ውስጥ መሆኑ ምን ያክል አስፈሪ መሆኑን እንገንዘብ። ጨለማ ክፍል ውስጥ ነው። ጥቅጥቅ ያለ ዋሻ። ሦስት ቀን በአሳ ሆድ ውስጥ ምን ተሰምቶት እንደሆነ አናውቅም። እንዴት አሳለፈው? የመከራ ቀኖች እንዲህ በቀላ አይገፉምና ያውም ቀን ይሁን ማታ በማያውቅበት ሁኔታ ላይ። "ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ" ይላል። 


አንድ ሰው ጥፋት ሲሰራ የሚሰማው ጥልቅ ውስጥ እንደገባ ሰው ይሰማዋል። በጣም ጨለማ ክፍል ለማንም ቢሆን ይስፈራል። ይኽ ሁኔታ በራሱ ወደ ጸሎት ይመራል። ዮናስ በዚኽ ማዕበል ማለፍ የድንገት የተፈጠረ ነገር አይደለም። የእግዚአብሔር እጅ ነበር። ማስተማሪያው መንገድ ነው። እግዚአብሒር ዮናስን ሊያድን የወሰድበት መንገድ መሆኑ ገብቶታል። 


በአሳ ሆድ ውስጥ ሆኖ ማዕበሉ ይሰማው ነበር “ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ” ማዕበል በባሕርዩ ሰላም ይነሳል። ዮናስ አርፎ መተኛት አይችልም ማረፍ አይታሰብም ነበር። በዚኽ ሁኔታ መቆየት ቀላል አይደለም። ዮናስ የጥልቁን ኑሮ ቀመሰው ተሰቃየ። “እኔም፦ ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ” እግዚአብሔር በእርሱ እንዳዘነ ተረዳ። እኔም አልታዘዝኩም አውቃለሁ። ነገር ግን አሁንም ትወደኛለህ አለ። በትኅትና ሆኖ ጸለየ። ይቅር በለኝ እንደገና መቅደስህን እንዳይ አድርገኝ ወደቀደመ ማንነቴ አገልግሎቴ መልሰኝ ሲለው ነው። በዚኽ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እየተናዘዘ ነው።


ዮናስ አሳ ሆድ ውስጥ ቢሆንም በውኃ ከመጥለቅለቅ አላመለጠም “ውኆችም እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠምጥሞ ነበር” ሲል ይገልጸዋል። አስገራሚ ነው። አሳ ሆድ ውስጥ ሆኖ በጨለማ ውስጥ በውኃ በስብሶ ነበር። ቅዝቃዜ በራሱ አጥንቱን ተሰማቶታል። ሰውነቱን ረብሾታል። አሳው ጢሻ ለጢሻ የወሰደው ይመስል ሳሩ፣ ሐረጉ ሁሉ አንገቱን ጠምጥሞ መተንፈስ ከለከለው። እንዴት ምቾቱ እንዳሳጣው ተመልከት። 


አሳው ወደ ባሕሩ የመጨራሻው ክፍል ገብቶ ስለነበር “ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ” አለ። ከአሳ ሆድ ውስጥ ሆኖ አሳው ተራራ ግርጌ እንደሚመዘግዘግ ታወቀው። ከባሕር በታች ያሉ ተራሮችን በምናቡ አየ። 


ዮናስ ማንም ሰው ወደ እርሱ ሊመጣ እንደ ማይችል አውቋል። በምድር ላይ ዮናስ ያለበትን ስሜት የሚረዳ የለም ብሎ አስቧል። እርሱ የገባበት ቦታ የገባ የለም አለ። እዚኽ መጥቶ ሊያድነኝ የሚችል የለም። ከእግዚአብሔር ውጭ ማንም ሊደርስ በማይችል ቦታ ወሰደው። አንዳንዴ የሚገጥሙን መከራዎች ብር፣ ሀብት፣ ዝና፣ ዘመድ፣ ሥልጣን፣ ጎሳህ የማይደርሱበት ቦታ አለ።  አንተ የራስህ በምትለው እገዛዋለሁ እንደፈለኩ አደርገዋለው በምትለው ግዛት ውስጥ ብቻህን ወስዶ ልክህን ያሳይሃል። ትንሿን ነርቭህን ተጭኖ የሚረዳህ ስታጣ ያኔ ትጸልያለህ። ጣትህ ላይ ትንሽ ቁስል ወጥታ ሙያህ ሊፈውሳት አቅቶት እንቅልፍ ትነሳሀለች። ስንቶችን ስታንበረክክበት የነበረ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

11 Feb, 14:25


ገንዘብ አንተ ጋር ሲደርስ አንተን ማዳን አልችልም ይልሃል። ያኔ ሊደርስልህ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ታውቃለህ። ከጸሎት ውጭ ምንም ማድረግ የማትችልበት ቀን አለ። ያ የእግዚአብሔር እቅድ ነው። 


ዮናስ እኔ አሁን ከሁሉም ዓለም ሩቅ ነኝ፤ ያለሁበትን ቦታ እንኳ የሚያወቅ የለም ከዚኽ ጥልቅ አድነኝ አለ። ይኽ ስሜት በምቹ አልጋ ላይ ሆነን እንኳ ሊሰማን ይችላል። አልጋውን አሳ ያደርገዋል። ሌሊቱን የረዘመ ይመስልሃል። ወደ ጥልቁ ሲገባ መቀበሩን አውቋል። ከጉድጓዱ አውጣኝ አለ። “አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ” ዮናስ ትንሣኤ ሙታንን አሳሰበን። 


“ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች” በጥልቁ ሳለ በጣም ተክዟል። ደክሟል፣ ተሰላችቷል። እኔ ተስፋ ቆርጫለሁ ጥቅም የለሽ ነኝ ይሁን እንጂ የኔን ደካማነት አላይም አንተ እንደ እኔ አይደለህም። ማሰብ የምፈልገው ያንተን መሐሪነት ደግነት ነው የሚወደውን አምላክ አሰበ። ከምንም በላይ ድካሜን የምታውቅ አነተ ነህ አለ። 


“ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች” በጥልቁ ውስጥ ሆኖ ጸሎቱን በቤተ መቅደስ እንደሚጸልየው ሆኖ ታሰበው። አንድ ቀን ዳግም ወደ ቤተ መቅደስ ሄዶ እንደሚጸልይ አመነ። ዛሬ ያልሔድክበትን መቅደስ እንዲህ ትናፍቀዋለህ። ይኽ የዮናስ የባሕር ውስጥ ተሞክሮ ነው። ዮናስ የራሱን ልብ በመከተሉ ተጎዳ፣ ተሳሳተ። እግዚአብሔር የሚወደው እስራኤላውያንን የርሱን ሕዝቦች ብቻ ይመስለው ነበር። አሁን ግን ሁሉንም እንደሚወድ ተረድቷል። ሰይጣን ምንም ጥሩ ነገር ቢነግርህ፣ ተአምር ቢያሳይህ አትመነው ሊያጠምድህ ነው። "ቤትህን እሳት ቢያቃጥልብህ ከሰይጣን ውኃ አትዋስ" ያልኩህን አስታውስ። “ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል ” ዝም ብለህ ኢየሱስ ክርስቶስን ተከለል። እውነት እሱ ብቻ ነው። ትጉህ እረኛ እርሱ ነው። 


ዮናስ በስተ መጨረሻ ሙሉ ተስፋ አሳደረ። ወደ ቤተ መቅደስ እንደሚመለስ መስዋዕትም እንደሚሰዋ አሰበ። ተስፋው ብርዱን ውርጩን አስረሳው። ከመከራው ይልቅ ተስፋው በለጠበት። ምንም ውስጥ ብትሆን ዓይንህን ጨፍነህ ተስፋን እያት። ሰላም ከሌላ ቦታ አትፈልግ አስተሳሰብህ ውስጥ ናት። እግዚአብሒር ከልብህ በላይ ላንተ ቅርብ ነው። በትኅትና ሆኖ ጸልየ “እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” ኃጢአቱን ተናዘዘ አሁን ጥሪውን ሊፈጽም ተዘጋጅቷል። ምድሪቱን ዳግም እንደሚያይ እያሰበ ነው። ከሕዝቡም ዳግም ሊገናኝ መሆኑ ታየው። ደግሜ ከአንተ ፊት አልጠፋም የትም ቢልከው እንድሚሄድ ተልእኮውን እንደሚፈጽም ወሰነ። "የተሳልኩትን ሁሉ እፈጽማለሁ" ብሎ ማረጋገጫ ሰጠ።  መዳኑን እየጠበቀ ነው ወደ ወደብ መድረሱ ታወቀው “ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” እግዚአብሔር ተአምር እንዲያደር ጠበቀ። ሞቶ ነበር ዳግም ሊኖር ናፈቀ። ልሙት እንጂ አልጸልይም ያለው ዮናስ ጸሎት ሕይወቱ እንደቀየረው ተረዳ። ጸሎት ይቀይራል። የሞትና የትንሣኤን ምስጢር አስረዳን። ጥምቀትን አሳየን።  ከጸሎቱ ከተስፋው ከእግዚአብሒር ምህረት የተነሳ ማንም እንዳይጠፋ አይፈልግም። ሁሉም እንዲድኑ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን አወቀ። 


በምስቅልቅል ጊዜ እንጸልይ፣ ስንጸልይ እንናዘዛለን። እንመን፣ ከልብ እንጸልይ በሌላው አናላክክ ስንጸልይ ሁሉም ይለወጣል፣ ተአምር ይደረጋል፣ የተለየ ሕይወት ይሰጣል። ዮናስ ባይጸልይ ኖሮ አሁን የምናነበውን ትንቢተ ዮናስ አናገኘውም ነበር። በጸሎት አዲስ ቀን እናያለን “እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፥ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው” ይላል። አሳው በባሕርይው ከዋጠ አይተፋም ቀረጣጥፎ ያስቀር ነበር። ከነቢዩ ይልቅ አሳው የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመረዳት ምላሽ ሰጠ። ዮናስን አጓጉዞ በወደብ ደረቁ ሥፍራ ተፋው። 


መ/ር ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

10 Feb, 18:39


ቀደምት እናቶቻችን ዳዊት ደጋሚ ነበሩ። እግዚአብሔር ይባርክሽ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

10 Feb, 17:33


የሚገርም ልብ ነው። እጣ የሚጥሉት ጸጥ ባለ ማዕበል ሳይሆን መርከቢቱ ልትሰበር ቀርባ በማዕበል ውስጥ ነው። እጣው እውነቱን መሰከረ። ሁሉም ተፈጥሮ የእውነት ምስክርነት ሰጡ። ዮናስ ግን አልሰማም አለ። እጣው ምክንያቱ አንተ ነህ ንሰሐ መግባት አለብህ ይለው ነበር። ዮናስ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ ቆጠረ። ምስቅልቅል እየተፈጠረ እያዩ ምንም እንዳልተፈጠረ ማሰብ ከተጠያቂነት አይስመልጥም። ሁሉንም መልእክት አቃለለ ናቀ።

ሰዎቹ የሚችሉትን ሁሉ የድርሻቸውን ተወጡ። ስለ ራስህ ንገረን አሉት ጠይቁት። ዮናስ ምንም ሳይሸሽግ ሁሉንም ነገር ስለራሱ ነገራቸው። ዮናስ የዋኅ ሰው ነው ያሰኘው ይኽ ነው። ዮናስ እየሸሸ ቢሆንም ስለ እግዚአብሔር ግን መሰከረ። ስለ ራሱም አልሸሸገም፤ የማመልከውም ሰማይና ምድርን የፈጠረውን እግዚአብሔርን ነው አለ። እርሱንም እንደ ሚያገለግል ተናገረ። ተሸሽጌያለሁ ብሎ አልዋሸም። እግዚአብሔርን ሰበከላቸው። “እርሱም፦ እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ አላቸው”

ኃጢአት ሰርቻለሁ ነገር ግን እግዚአብሔር ባዘዘኝ ሀሳብ አልተስማማሁም አለ። አሁን ነገሮችን ደግሞ ማሰብ ጀመረ። ወደ ልቡ ተመለሰ። እሱ የሁሉም ነገር ምክንያት ነበር። ተስፋ መቁረጥ ተሰምቶታል፤ ተሰላችቷል ነገሮች ሁሉ አስጠልተውታል። እንዲኽ በመሰልቸት የሚያገልግል ብዙ ነው። ያለ እግዚአብሒር መንፈስ ውስጡ ተረብሾ እንዲሁ የሚቆም አለ የቀዘቀዘ አገልግሎት ከባድ ነው። በርዶህ መደሰት አትችልማ። ያለ እግዚአብሔር መንፈስ በቀሚስ ፋሽን መደሰት አይቻልማ። የሚብለጨለጭ አገልጋይ ውስጡ ባዶ መሆኑን ለመደበቅ ሲሞክር ነው። ውጭው አምሮ ውስጡ ሲደርቅ አይጣል ነው ወዳጄ። የደረቀ ነገር መሰበሩ አይቀርም መጀመሪያ ውስጥህ ይሙቅ። ፈረጂያ ቀሚስ ብቻ ሕይወት አይሆንም፣ ቆብ ብቻውን አገልግሎት አይሆንም ዝና ብቻውን ሰው አይለውጥም። ሳንቲም መልቀል ከበሽታ አያስጥልም። 

ዮናስ ተነስቶ ከመጸለይ ይልቅ ሞቱን የመረጠ አሳዛኝ ነቢይ ነው። ከምጸልይ ሞት ይሻለኛል አለ። “እርሱም፦ ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው” የራሱን ታሪክ ነገራቸው ተናዘዘ፤ ጥሪውን መናቁንም አመነ። እነርሱም የምትነግረን ነገር ከምታምነው ጋር አንድ አይደለም አሉት። እንዴት ሰማይና ምድሩን የፈጠረው አመልካለው እያልክ ለምን ትተኛለህ? ለምን አትጸልይም አሉት። እግዚአብሔርን እያመለከ ይኽንን ማድረጉ ተደነቁ። እያገለገለ ለጸሎት የሰነፈ ሰው መጨረሻው ውድቀት ነው።  

ዮናስ የነገራቸውን አመኑ፤ ነቢይነቱን ተቀበሉ፤ አልጠሉትም። በእሱ ጥፋት ላይ ሳይሆን ዮናስ በሚድንበት ነገር ላይ አተኮሩ። አንተ ምክንያት ሆነህ በአንተ ምክንያት መስጠም የለብምን አንተም መዳን አለብህ አሉ። አንተ ደግሞ እግዚአብሒርን የምታውቅ ከሆነ ምን እንደምናደርግ ምራን አሉት “ባሕሩንም ሞገዱ አጥብቆ ያናውጠው ነበርና፦ ባሕሩ ከእኛ ዘንድ ጸጥ እንዲል ምን እናድርግብህ? አሉት።

እርሱም፦ ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው” ዮናስ በደለኛ እኔ ነኝ ብሎ በራሱ ፈረደ። በራሱ የፈረደ ሰው ተጨማሪ ክስ የለበትም። ወቃሽም የለበትም። ራስህን ለመከላከል ስትል ነው ሁሉም በማስረጃ የሚሞግትህ። ያኔ መግቢያ ታጣለህ። በራስ እንደ መፍረድ ጥሩ ነገር የለም። የዮናስ የዋኅነቱ በራሱ መፍረዱ ነው። እውነቱን ተናገረ ጥፋቱ እኔጋ ነው አለ። እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ ሁሉም ነገር መፍትሔ ያገኛል አለ። አቤት የዋኅነት። ጳጳሱ፣ ቄሱ፣ መሪው፣ ሚኒስቴሩ፣ ፖለቲከኛው በእኔ ጥፋት ነው ሀገር የሚታመሰው በኔ ምክንያት ነው ሰው የሚሞተው ብሎ ቢፈርድና ቢጸጸት ሀገር ይድን ነበር። ሁሉም እኔ የለሁበትም ባይ ነው። "በአንዳንድ አካላት" እያሳበበ ይኖራል።

መርከበኞቹ ጥሩ ልብ ነበራቸው። ዮናስን ለማትረፍ ብዙ ደከሙ። ለዮናስ ጸለዩለት “ሰዎቹ ግን ወደ ምድሩ ሊመለሱ አጥብቀው ቀዘፉ፤ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግ አብዝቶ ይናወጥባቸው ነበርና አልቻሉም። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው፦ አቤቱ፥ እንደ ወደድህ አድርገሃልና እንለምንሃለን፤ አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳታደርግ እንለምንሃለን አሉ” በእርሱ ነፍስ እንዳይጠየቁ ጸለዩ። እንዴት ያለ ጥንቃቄ ነው?። እግዚአብሔር በነቢዩ ደም እንዳይጠይቃቸው ተጠነቀቁ። 

ዛሬ የሰው ነፍስ ለማጥፋት ጥንቃቄ የለም። የሰው መዳን ግድ የማይሰጣቸው አገልጋዮች ሕዝቡን የሚፈልጉት ለደሞዛቸው ብቻ የሆኑ አገልጋዮች ያሳዝናሉ። ለምታገለግላቸው ሰዎች ትጸልያለህ? ስለ በደሉህ ሰዎች ትጸልያለህ። ባንተ ምክንያት ስላዘኑ ሰዎች ትጸልያለህ? ሁሉ ይቅርና ጸልይልን ላሉህ ሰዎች ትጸልያለህ? ወይስ መኝታ ብቻ ነው።

ዮናስ ወደ ባሕር ሲጥሉት ችግሩ ቀለለ። የችግሩ ምክንያት ተገኘ አስወገዱት። አንዳንዴ እንዲኽ ይሆናል። ችግሩ አገልጋዩ ከሆነ በንጽሕና ተጠንቅቆ ማስወጣት ተገቢ ነው። አገልጋይ ነውና እንደ ፈለገኝ ልፈንጭ አይባልም። ተጠንቅቀህ በጸሎት ዞር አድርገው። በትህትና አሰናብተው። “ዮናስንም ወስደው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጡ ጸጥ አለ።” አበቃ።

በነሱ ዓይን ዮናስ ሞቷል። በባሕር ቀብረውታል። ለእሱ ሕይወት ሲባል ዮናስ ወደ ባሕር ልብ ገባ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚኽ ነው ዮናስን በምሳሌ የጠቀሰው። “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም” ማቴ.16:4 አለው።

 ዮናስ በባሕር ልብ ውስጥ በአሳ ተዋጠ። የጌታ ወደ መቃብር መግባት ምሳሌ ሆነ። የዮናስ ወደ ባሕር መጣል የመርከበኞቹ መዳን ሆነ። የጌታ መሰቀልና መሞት ለአዳም ዘር ሁሉ መዳን ሆነ። ባሕሩ ጥምቀትን ይወክላል። በመጠመቃችን የጌታን ሞትና ትንሣኤ እንሳተፋለን እንመስለዋለን። “በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ” ቆላ.2:12

አይሁድ ጌታን ሰቅለው ሲቀብሩት በቃ አለቀ ደቀቀ ተገላገልን ብለውት ነበር። በአይሁድ ልብ ጌታ ሞቶ ይቀራል ብለው ነበር። ነገር ግን ከመቃብር በኋላ ሕይወት አለ። ዮናስ አልሞተም በባሕር ውስጥ ተቀብሮ ነበር። ከሶስት ቀን በኋላ ሌላ ታሪክ ይጀምራል።

መርከበኞቹ ዮናስን ከጣሉት በኋላ ማዕበሉ ጸጥ አለ። በሆነው ነገር እግዚአብሔር አከበሩ። ዮናስ ሳያስበው በሕይወታቸው ላይ ተጽዕኖ አሳደረ። ትክክለኛውን እግዚአብሔርን አወቁት። እነርሱ የሚያመልኩት ነፋስና ባሕርን ነበር። አሁን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አቀረቡ። “ሰዎችም እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ፥ ለእግዚአብሔርም መሥዋዕትን አቀረቡ፥ ስእለትንም ተሳሉ” ምዕ.1:16

                      መ/ር ንዋይ ካሳሁን

 

 

 

 

 

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

10 Feb, 17:33


 

ትንቢተ  ዮናስ በነገረ መለኮታዊ ትንታኔ

ምዕራፍ አንድ

 

ቅዱስ ዮናስ የብሉይ ኪዳን ነቢይ ሲሆን ቁጥሩ ከደቂቀ ነቢያት መካከል ነው። የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ማወቅ ሐዲስ ኪዳንን ለመረዳት መሠረት ነው። በብሉይ ነቢያቱን የላከ  በሐዲስ ኪዳን ሐዋርያቱን የላከ እግዚአብሔር አንድ ነው። ነቢያትን ትንቢት ለመጻፍ ያንሳሳ መንፈስ ቅዱስ ነው ሐዋርያቱንም ወንጌልን መልእክታትን እንዲጽፉ ያነሳሳው ያው መንፈስ ቅዱስ ነው “በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል” ኤፌ.2:20

ዮናስ ማለት በእብራይስ ቋንቋን ርግብ ማለት ሲሆን የኖረው ከ786 – 746 ዓመተ ዓለም አካባቢ እንደሆነ የመጽሐፉ ይዘት ያስረዳል። ዮናስ በንጉሡ በዳግማዊ ኢዮርብአም ዘመን የነበረ ነቢይ ሲሆን  በገሊላ ከምትገኘው ጋትሔፌር የሆነው የአማቴ ልጅ መሆኑን መጽሐፉ በመግቢያው ነግሮናል።

ዮናስ ትንቢት የተናገረው ከጌታ መወለድ በፊት በ8ኛው ምእተ ዓለም በፊት ሲሆን የነቢያት ዋና ተግባር ሕዝቡ በአንድ አምላክ እንዲያምኑ፣ ንሰሐ እንዲገቡ፣ ስለሚመጣው መሲህ እንዲረዱ መናገር ነው። ሰው እንዴት ንሰሐ እንደሚገባ መሲህ እንዴት ይመጣል? የሚል ትምህርት ነው። የዮናስ ትንቢት ዓላማ ነነዌን ወደ ንሰሐ መመልስ ነው። የእግዚአብሔር ርኅራኄና ፍቅር እንክብካቤ ግልጽ ሆኗል። 

ዮናስ በብዙ መልኩ የተለየ ነቢይ ነው። አይሁዳዊ ነው። የተላከው ግን ወደ አሕዛብ አሦራውያን ሲሆን በጣም በጠላትንነት የሚተያዩ ሕዝቦች ነበሩ። አሦራውያን እስራኤላውያንን  ገዝተዋቸው ነበር። ነነዌ የታላቋ የአሦራውያን ዋና ከተማ ነበረች። በወቅቱ በጣም ጠንካራ ሕዝቦች ነበሩ። እግዚአብሔር ሕዝቡ ንሰሐ የሚገባ ልብ እንዳላቸው ስለሚያውቅ ስለሆነም የራሱን ሰው ነቢዩ ዮናስን ላከው። ዮናስ ግን አሦራውያንን ስለሚጠላቸው አይሁድ ወዳልሆኑት መሄድ እንቢ አለ። “የእግዚአብሔርም ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፦ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ ክፉታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ “ አለው።

ዮናስ ተልእኮውን ሲሰማ ግራ ተጋባ ተበሳጨ። እግዚአብሔር የሚፈልገውን ተልእኮ ነው የሚሰጠን እንጂ እኛ በፈለግነው አገልግሎት ብቻ እንዳንሰማራ ትምህርት ነው። በደመቀበት ጭብጨባ ባለበት ብቻ ሳይሆን እርሱ ባሰማራንም መሄድን ያስረዳናል። እግዚአብሔር ከለመድነው ከምንፈልገው ውጪም ተልእኮ አለው። እግዚአብሔር ወደራሱ ሊመልሳቸው ፈለገ። ጳውሎስ አይሁድን ብቻ ሊያስተምር ነበር፤ ይደክም የነበረው እግዚአብሔር ግን ወደ አሕዛብ እንዲሔድ ነገረው። ጳውሎስ በመጀመሪያ ብዙም ባይደሰትም በኋላ ግን ወደ አሕዛብ በመሄድ መክሊቱን መቶ እጥፍ አድርጎ በአገልግሎቱ የተሳካለት የአሕዛብ ሐዋርያ ሆኗል።

ዮናስ ለነነዌ ስበክ ተባለ። የሰዶም ገሞራ ሰዎች እንደ ነነዌ ሰዎች እድል ተሰጥቷቸው ነበር። ነገር ግን አልጠቀሙበትም ነነዌ ሰዎች ግን የንሰሐ ብርሃን እንደ መጣላቸው ያወቁ ሰዎች ናቸው። አገልግሎት ማለት በራሳችን ሃይማኖት ውስጥ ብቻ ላሉት አይደለም። አይመስሉንም ይጠሉናል ለምንላቸው ሁሉ መሆን አለበት። የኔን ስላልተከተልክ ብሎ ጥላቻ፣ ንቀት፣ ስድብ ይኽ የእግዚአብሔር ሰው መሆን መለኪያ አይደለም። ለነሱ የእግዚአብሔር ፍቅር ማሳየት ተገቢ ነው።  እግዚአብሔር በማያምኑትም ዘንድ ይድኑ አላማ አለው።

ዮናስ አሦራውያን ሕዝቦችን አይወዳቸውም ነበር። በመሆኑም አገልግሎቱን እንቢ አለ። የሕዝቡን መዳን እንቢ አለ። ተልእኮውን መቀበል አልፈለገም። ይልቁንም ከአገልግሎቱ መሸሽን መረጠ። ሰውን የምትጠላ ከሆነ ክርስቲያን መሆን አልጀመርክም። የእግዚአብሔርንም ሀሳብ አትከተልም ማለት ነው። ፍቅር የእግዚአብሔር ባሕርይ ነው። የአገልግሎት መሠረቱ ያንተ ፍላጎት ሳይሆን ፍቅር ነው።

“ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይኰበልል ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፥ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ። እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፥ በባሕርም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች” ቁ.3

የሰዎቹን  ንሰሐ መግባት አልወደደም፤ በመሆኑም ወደ ተርሴስ መሄድን መረጠ። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ስትወጣ ወደ አደጋ ትቀርባለህ፤ አደጋው ደግሞ ላንተ ብቻ ሳይሆን በዙሪያህ ላሉ ሰዎች ሁሉ ይተርፋል። በዚኽ መልክ በእኛ ዙርያ ያሉ ብዙ ነፍሳትን እንጎዳለን አደጋ እንጋርጥባቸዋለን። እንዲህ ያለ ጉዳይ ብዙ ሰውን ይረብሻል።

“መርከበኞቹም ፈሩ፥ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱም እንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር።”

በመርከብ ውስጥ ያሉት ሁሉ መጸለይ ጀመሩ። ከችግሩ ሊያመልጡ ብዙ ሞከሩ። ጸሎት ትልቅ መፍትሄ መሆኑን የተረዱ ሰዎች ናቸው። መርከቢቱን ከሸክሟ ሊያቀሉ እቃቸውን ወደ ባሕር ጣሉ። ዮናስ ግን ምንም ማድረግ አልፈለገም፤ ወደ መርከቢቱ ታችኛው ክፍል ገብቶ ተኛ። ምክንያቱ ደግሞ ከእግዚአብሔር “ስላመለጠ” ነው። እግዚአብሔርን አኩርፏል፤ ተደበቀ። ግዴለሽ ስትሆን እንዲኽ ነው።  

ዮናስ ለዚኽ ሁሉ ምክንያት እርሱ እንደሆነ እያወቀ ንሰሐ መግባት አልፈለገም፤ ይልቁንም መሸሽን መረጠ። መጸለይ እንኳ አልፈለገም። ተኝቶ ያንኮራፋ ነበር። ምንም እንዳልተፈጠረ ሆነ። አንዳንዴ ቤተ ክርስቲያንን ራሳችን እንደ በጠበጥን እያወቅን እና ስለተጠቀምን ብቻ ስለ ብዙዎች መጥፋት መጎዳት ምንም የማይመስለን አለን። ዮናስን እንመስለዋለን። ምእመናን ቁም ስቅል ሲያዩ እኛ ሰራሁላቸው የምንል። ሌላው ወንድሙ ተጨንቆ የታባቱ የሚል ግብዝ ብዙ ነው። ይቅርታ ማለትን ተጸይፎ ፍርድ ቤት የሚያንከራትት  አገልጋይም አለ።

ትልቅ ጥፋት ሰርተን ምንም እንዳልተፈጠረ ማሰብ እንሞክራለን። ትርምስ ሲፈጠር ምክንያቱ እኔ ነኝ ማለት አንፈልግም። ቤተሰብ ሲበጠበጥ ባል በሚስቱ ሚስት በባል ትደፈድፍና ራሷን ንጹሕ ታደርጋለች እንጂ እኔ ነኝ ምክንያቱ አትልም። እሱም እንዲሁ።

“የመርከቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን እንደ ሆነ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ አለው” ቁ.6

ለነቢዩ ድምጽ ከአሕዛቡ የመርከብ አለቃ መጣ። አንተ አስተማሪ ነኝ ብለህ ነገር ግን አልሰማ ካልክ እግዚአብሔር የመሳሪያ ችግር የለበትም።  “ተነስተህ አምላህን ጥራ አለው”  ጸልይ ብሎ አዘዘው። ይህንን ማስተማር የነበረበት ዮናስ ቢሆንም አልሰማ ስላለ አስተማሪ ተላከበት። ከጸለየ ንሰሕ ትገባለህ የእግዚአብሔር ፈቃድ የቱ ነው ብለህ በግልጽ ታያለህ።

የእግዚአብሔር መልእክት ከሁሉም አቅጣጫ ወደ ዮናስ መጣ። በብዙ ነገር ይቀሰቅሰው ነበር። ከማዕበሉ ከነፋሱ ከመርከብ አለቃው መልእክት መጣበት። መጨረሻ ደግሞ እጣ እንጣል አሉ። “እርስ በእርሳቸውም፦ ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እናውቅ ዘንድ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ”   

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Feb, 20:34


የቤት ለቤት አገልግሎት እንሰጣለን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Feb, 20:31


ይቀደሳል ይቀደሳል

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Feb, 19:31


እኛና ነነዌ



ወቅቱ በቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ በቀናት አነስተኛ የሆነችው ጾም፤ ጾመ ነነዌን የምንጾምበት ወቅት ነው፡፡ ቀኑ እንጂ ተግባሩና ትምህርቱ ግን ሰፊ ነው። ነነዌን ብዙ ጊዜ ከምንሰማውና ካስተማርነው በላይ ትልቅ ምስጢራዊና ታሪካዊ ከተማ ናት፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያና ነነዌን የምናነጻጽርበት ብዙ ገጽታ አለን፡፡


ነነዌ የአሦራውን ጥንታዊ ከተማ ስትሆን በላዕላይ መስጴጦምያ በአሁኑ አጠራር በሰሜናዊ ኢራቅ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ ከተማዋን ሶርያ ቱርክ ኢራን ያዋስኗታል፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 1800 ዓ.ዓ በኩሽ ልጅ ናምሩድ የተቆረቆረች ከተማ እንደሆነች መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ዘፍ. 10፤11 


በወቅቱ በአሦራውያን ግዛት ትልቋ የዓለም ከተማ ስትሆን በወቅቱ ታላቅ የሃይማኖት መዲና እንዲሁም የአሦራውያን አማልክት (ኬሽታር) ማማለኪ ስፍራ ተገንብቶባትም ነበር፡፡ ከተማዋ በተደጋጋሚ መሬት መንቀጥቀጥ አደጋ   ሲገጥማት የማምለኪያ ስፍራው ቢወድምም ከተማዋ እንደ ገና በ2260 ዓ.ዓ  አካዲን በተባለው ንጉሥ በድጋሚ ታንጻለች፡፡


ነነዌ በመጀመሪያ ስሟ የተጠቀሰው በዘፍጥረት 10፡11 ላይ ሲሆን የአሦር ግዛት ዋና ከተማ ነበረች፡፡ በንጉሡ ሕዝቅያስ ዘመን የይሁዳ ነቢይ የነበረው ኢሳይያስ የኖረባት፤ ሰናክሬም በ705 - 681 ዓ.ዓ የገዛት፤ በኋላም በሁለት ልጆቹ አድራማሌቅና ሶርሶር በተባሉ ልጆቹ የተገደለባት ከተማ ናት፡፡ ኢሳ 37፡37-38፡


ነነዌ በአሁኑ አጠራር በሰሜናዊ ኢራቅ ከተማ ሞሱል (Mosul) በሚባል ስም ትጠራለች፡፡ በወቅቱ መቶ ሃያ ሺህ ሰው ያኽል ይኖርባት የነበረ ሲሆን ከተማዋን ትንንሾቹን መንደሮች ጨምሮ ዞሮ ለመጨረስ ሦስት ቀን ይፈጃል።


ነነዌ በበደል ምክንያት እግዚአብሔር ተቆጥቶ ሊያጠፋት ይኽንንም እንዲውቁ ዮናስን እንዲያስተምር አዘዘው፡፡ ሕዝቧ ሩኅሩኅ ስለ ነበር ከንጉሡ እስከ ሕዝቡ ሕጻናት እንስሳት ሳይቀሩ የእግዚአብሔርን ፊት ፈለጉ፣ ንሰሐ ገቡ እግዚአብሔርም ራራላቸው ይቅርም አላቸው፡፡ ነቢዩ ዮናስና ናሆም የነበረውን ታሪክ ጽፈው አቆዩልን፡፡ ነቢዩ ዮናስና ነቢዩ ዳንኤል መቃብር  በዚያ የነበረ ሲሆን በአክራሪው እስልምና ISIS ሰራዊት በቅርቡ ፈራርሷል፡፡  


ኢትዮጵያ


ኢትዮጵያ ቅድመ ልደት ክርስቶስ በኖኅ የልጅ ልጅ ኩሽ የዘር ሐረግ የተመሠረተች ሀገር ስትሆን ሰሜናዊ የሀገራችን ክፍል አክሱም ከተማ የአክሱማውያን መንግሥታት መዲና ሆና ስታገለግል ኖራለች፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን በቀዳማዊ ምኒሊክ አማካኝነት ሌዋውያን ካህናትን ከታቦተ ጽዮን ጋር ከኢየሩሳሌም በማምጣት አምልኮተ እግዚአብሔርን የጀመረች በኋላም በዘመነ ክርስትና ነገሥታቷ አብርሃ እና አጽብሃ ክርስትናን በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን በጃንደረባው አማካኝነት ከኢየሩሳሌም ቀጥላ የተቀበለች በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስትናን ሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት ያደረገች ታላቅ ሀገር ናት፡፡ ሐዋ.8 ፤27


አክሱም በወቅቱ የሃይማኖትም፤ የነገሥታቱም ከተማ ከመሆኗም ባሻገር ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች ጋር የቆየ የንግድ ትስስር ነበራት፡፡ በዚያም ወቅት የመገበያያ ገንዘብን ለማሳተም በቅታለች የአክሱም ነገስታት ቀይ ባሕርን ተሻግረው አረቡን ሀገር ይገዙም ያስገብሩም ነበር፡፡ አሁንም ድረስ የታላላቅ ነገስታትና ቅዱሳንን አጽም የያዘች ስፍራ ናት፡፡ 


ምድሪቱ ተጠንቶ ያላላቀ የከርሰ ምድር ስራዎች ያሉባት ከተማ ስትሆን ሁሉንም በሆዷ ይዛለች፡፡ እንዲኽ እያልን ነነዌንና ኢትዮጵያን የሚያመሳስላቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ ማየት እንችላለን፡፡  ለምሳሌ ሁለቱም ከተሞች ታላላቅ ነገሥታት መሠረቷቸው፣ የሃይማኖትና የንግድ ማእከል መሆናቸው፣ ሁለቱም በአንድ ወቅት ፈርሰው የነበሩ መሆናቸው፣ የቅዱሳን አጽምን መያዛቸው፣ ምርምሩ ያላለቀ የአርኪዮሎጂ ምርጥ ስፍራ መሆናቸው፤ ሕዝቦቻቸው ሩኅሩኀን መሆናቸው፣ ሁለቱም የተመሠረቱት በኩሽ ዘሮች መሆናቸው፣ መምህራኖቻቸውን ሰምተው እግዚአብሔርን የሚከተሉ መሆናቸው ያመሳስላቸዋል፡፡


የዛሬ ሞሱል (ነነዌ) ግን ዛሬም እንደ ጥንቱ አክራሪ እስልምና ከጉያዋ ፈልቆ በውስጧ የሚኖሩ ጠንካራ የኢራቅ ክርስቲኖቸን በአደባባይ የሚታረዱባት፣ ለአፍታ እንኳን የመሳሪያ ፍንዳታ የማይለያት ከተማ ናት፡፡ ለምን ጸጉርሽ ታየ፤ ለምን ሙዚቃ አደመጥህ ተብሎ ወጣቶች አንገታቸው የሚቀላባት፤ የሰው ደም እንደ ውሻ ደም የሚፈስባት መሆኗን ተመልክቻለሁ፡፡ 


ከኢራቅ በመምጣት አብራኝ የምትማር ተማሪ ስለ ሀገራችን ባነሳን ቁጥር በሚዘገንን ሁኔታዎችን ታወጋኛለች፡፡ እነርሱ ትክክለኛ ሙስሊም አይደሉም የሚሏቸውን በተለይ የሺአ እስልምና ተከታይ የሆኑትን በአሰቀቂ ሆኔታ የሚገደሉባት ከተማ ናት፡፡


ሀገራችን ኢትዮጵያ ማንም ቅኝ ግዛት እንዳልገዛት፤ አባቶቻችን ዋጋ የከፈሉባት እንደሆነች ለዓለም ብንናገርም የራሷ ሰዎች በሁሉም አገዛዝ ዘመን  ጨካኝ ገዥ ሆነውባት፤ የራሳቸውን አሳብ ዜጎች በነጻነት የማያራምዱ ለእስርና ጥይት ሰለባ የሚሆኑባት፤ ሃማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው ተብሎ በስም የሚደሰኮርባት፣ በተግባር ግን "ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ" እንዳለው የጌታ ትምህርት ጋብቻ መስርተው የፍቅር እስከ መቃብር  ድርሰት ደርሰውባታል፡፡ ከዚያ ወጣን ስንል ደግሞ ባለ ጉልበቱ መንግሥት ገፍቶ ሊጥል ሴራ ላይ ያለ ይመስላል። 


ብዙ ሚሊዮን ሕዝብ የሚቀምሰው አጥቶ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በጠኔ የሚሰቃይባት፤ የተማረ አንገቱን ደፍቶ  ከተመረቀ በኋላ ከረባቱን አውልቆ ሲያስቀምጥ ያልተማረ ‘ሊቅ’ የ5ኛን 8ኛ ክፍል ‘ሊቃውንት’ አስተዳድራለሁ በሚል ስም ግፍ የሚሰሩባት፣ ስለ ሀገር እያወራ በስብሰባ ላይ የሚተኛባት፤ ሃይማኖተኛው ስለ መንጋው ደንታ ቢስ የሆነበት፣ "ተወው ሳር በሊታ ሕዝብ" ተብሎ ሩኅሩኅ ሕዝብ በመሪዎቻቸው የሚናቁባት ፣ ውሃ ሰፈራችን የለም ሲባሉ ሰው ኮካ ጠጥቶ እንደሚያድር ስፍር ቁጥር በሌላቸው ካድሬዎች ቱልቱላ የሚነዛባት፣ ጦም አዳሪ ጎዳና አዳሪ በየመንገዱ ሞልቶ ሌላው ለምሳ ዱባይ ሄዶ የሚመጣባት፡፡


ለትምህርት የወጡ ወጣቶች ታፍነው የውኃ ሽታ የሚሆኑባት ቤተ ክርስቲያ ግቢ ገብቶ ሰው የሚገደልባት። መሪዎቿ በጥቁር መስታወት ሕዝቡ እንዳያያቸው ሳይሆን እነርሱ ሕዝቡን እንዳያዩ ተሸፍነው በዘመናዊ መኪና የሚንፈላሰሱባት ሀገር ናት፡፡


ግፍን አይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን የምናልፍባት፤ አስተያየት ብንሰጥ እንትን ስለሆነ ነው፣ አነ እንቶኔ ልከውት ነው፣ የነ እንትና ጉዳይ አስፈጣሚ ነው….ብቻ የተቀጽላው ብዛቱ አይጣል ነው፡፡ ፖለቲካ አይኑን አፍጥጦ የሃይማኖት ካባ አጥልቆ በቀን ሊያፈርስ ከደጅ ቆሟል። ኢትዮጵያ በደም የምትነከር ሀገር ሆናለች። ሰው ተዘቅዝቆ ሲሰቀል ተቀጥቅጦ ሲቃጠል አይተንባታል።


 ይኽው አልበቃ ብሎን በሰለጠነው ዓለም እየኖርን ስልጣኔ ርቆን እገሌ እገሌን ቢወልድ የዘር ቆጠራ ዘርና ወንዝ የመቁጠር እሳት የሚዘንብብን ወቅት ላይ ነን፡፡ ትንሽ እንደባለ አእምሮ ማሰብ ያልዞረብ ያንንው ቅኝት ይዘን የዘረኝነት መዝሙር መዘመራችን ግርምት ነው፡፡    


 በዚኽ እሳት ዘመን የአምልኮ ስፍራ ሲቃጠል ካህናት ምዕመናን እንደ ብሉይ ኪዳን መስዋዕት የሚሰዉባት ሀገር ሆናለች። ብዙዎች ችግሩን በችግሩ ልክ እንኳ መግለጥ ፈርተዋል። ተናገሩ ካልተባሉ ምንም የማይተነፍሱ አያሳየኝ አያሰማኝ ብለው እንደ ዮናስ የመርከቢቱ የውስጥ ክፍል ዘግተው የተቀመጡ አግዚአብሔርን አንታዘዝም ያሉ አገልጋዮች  ታሪክና ሕሊና እንደ አሳ ውጧቸው ዝም ብለዋል፡፡

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Feb, 19:31


"ኢየሱስ ግን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ።በእናንተስ እንዲህ አይደለም፣ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም። ማቴ.20፡25 የተባለውን ሳታነቡት ቀርታችሁ ይሆን? 


ሰው ክብርና መብት፣ ነጻነት፣ በስደት፣ ግብረ ሰዶማዊነት እንደ እሳት ትውልዱን ሲያነደው ፈረንጆቹ እንዳይቀየሙ ተብሎ ዝም ብለዋል፡፡ ጉዳዩ ገዷቸው በአደባባይ  እንደ ነቢዩ ኤልያስ ፡ ዮሐንስ አፈወርቅ፤ ዮሐንስ መጥምቅ ጨካኞችን የሚገሰጹበት ግዜ መች ይሆን፡፡ 


በንጉሡ ጊዜ፤ በደርግ ዘመን፤ በሕወሓት፣ በብልጽግና ዘመን የወንበሩ ሰዎች ተቀየሩ እንጂ አስተሳሰቡ አሁንም ያው ነው፡፡ ግን መሪዎቻችን መቼ ነው የሚወዱን? እንድንወዳቸው የሚሰሩትስ?፡፡ “እግዚአብሔር  እንደ ተቀየመህ ማወቅ ያለብህ የምትመራው ሕዝብ አልሰማህ ሲል ነው” ያሉት አንድ የሃይማኖት መሪ ሁሌም አልረሳውም:: ለድሃ ወይስ ለማን ነው የቆምነው፡፡


 ስለ መንግስተ ሰማይ የምናስተምረውን ሰው ለምን ስለ ሰብዓዊ መብት፣ ነጻነት መስበክ ፈራን፡፡ ሰው ያልሰጠው መለኮታዊ ስጦታው ነው ፡፡ ጌታ ስለ መንግስቱ ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ ችግራቸውን ይፈታ ፣ የታመመውን ይፈውስ፣ የሞተውን ያስነሳ፣ የራበውን ያበላ፣ ግፈኛውን ይገስጽ ነበር። ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ነገሥታቱ ንሰሐ እንዲገቡ ብንነግራቸውስ፡፡ ይከፋቸዋላ፣ ይቀየሙናላ፡፡ ከውጭ ካለው ጨካኝ ውስጥ ያለው መስሎ አዳሪ ይከፋል።


ጠላት ቤተ ክርስቲያኗን አስተምህሮዋን ለማስለወጥ ድንጋይ በሚፈነቅልበት በዚህ ወቅት ከመፋቀር ይልቅ ላንስማማ ቃል ተገባብተን ጠላት ለመከላከል አቅም እስኪያጥረን ድረስ እየዛልን ትልቋን ቤተ ክርስቲያንን ማየት ተስኖን፣ በቡድን መያያዝን መርጠን ለጠላት ራሳችንን አመቻችተን፤ በቡድን ለመቋሰል አቅደን እየሰራን ነው፡፡ እንደ ክብሪት እንጨት ከአብራኳ የተከፈሉ ሰነፍ አገልጋዮች የመከራ እሳት ለኩሰው ሊያቃጥሏት ላይ ታች ይላል። ወቅቱ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና አባቶች በትጋት ያለ እረፍት መትጋት ያለበ ወቅት ነው።


ታዲያ እኛና ነነዌ በአንድ ገጽ ላይ አይደለንም ትላላችሁ? ጾሙን ከትላንት በበረታ ማንነት በፍቅር እንደ መርከቢቱ ሰዎች የተኛውን በመቀስቀስ ወደ አምላካችን መጮኽ ይኖርብናል፡፡  ከዮናስ መጽሐፍ የምንማረው ዋናው ነገር ሌላውን ሳንዘነጋ በዘመናችን በየትኛውም ዓለም ምንም እንደ ማይጠቅም እንደ ቀላል የሚታየው እውነተኛ ጾም ለአደጋ መከላከያ አማራጭ የሌለው ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠ ፍቱን መድኅኒት መሆኑን ነው።  

2010 ዓ.ም ተጻፈ


መ/ር ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Feb, 15:49


"እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።" ማቴ.24:13

‟...ዛፉ በፍሬው ይገለጣል ማቴ.12:33
ክርስትያን ነን የሚሉ ሰዎች በሥራቸው ይታወቃሉ። ሰው እስከ መጨረሻው በእምነት ኃይል መፅናቱ እንጂ ሥራውምብቻ አይፈለግምና።..”

የአንጾኪያው ቅዱስ አግናጥዮስ {+110 A.D}- [Letter to the Ephesians, 14:2; Lightfoot / Harmer / Holmes, 91

@orthodox digital library

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Feb, 03:38


"የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእውቀት አይገዛም ለጉልበት እንጂ"
እንዘጭ እንቦጭ 117

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Feb, 01:16


በጥምቀት ያገኘነው ምንድነው?

ጥምቀት አዲስ ልደት ወይም ዳግም ልደት ፣ ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር የመተባበር ሕይወት ነው። ጥምቀት አስፈላጊነቱ በክርስቲያኖች ሕይወት እጅግ ሰፊ ነው። ጥቂቱን ለመጥቀስ ብቻ ነው። 

የወራሽነት መብት 

ልጅ ያልኾነ የአባቱን መንግሥት አይወርስም። ለእግዚአብሔር ባሮቹ ሳይኾን ልጆቹ የኾንበት ወደ መንግሥቱ አባላት እንኾን ዘንድ ያደረገን ያደለን በጥምቀት ነው። “ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።” ሮሜ.8:17

ቤተክርስቲያንን መሠረተ

በእለተ ዓርብ በደሙ ከጎኑ የወጣችውን ቤተ ክርስቲያን በጥምቀት ሙሽራው ሙሽሪትን አገኛት። ቅዱስ ዮሐንስ “እነኾ የዓለም ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” ብሎ ለቤተ ክርስቲያን አሳወቃት። በጥምቀት የቤተ ክርስቲያንን መሠረት ጣለ። ያለ ዳግም መወለድ ወደ ቤተ ክርስቲያን አይገባም። የቤተ ክርስቲያን አባል የምንኾነው በጥምቀት ነው። 

አባልነቱ የቅዱሳን ኅብረት ነው። ከመላእክት፣ በሕይወት ከሌሉ ቅዱሳን፣ በተጋድሎ ካለች ቤተ ክርስቲያን ጋር ኅብረት እንፈጥራለን። 

የተጠመቀ ሰው ዘር ቀለም ቋንቋ ቦታ ቢለየው፣ የተማረ ያልተማረ ቆላፋ፣ አይሁዳዊ ፣ ግሪካዊ ቢኾን የተጠመቀ ሰው አንድ ቤተሰብ አንድ የሰውነት አካል ይኾናል። “እርሱም በሁሉም መሀይምናን ላይ ያድራል ሁላቸውንም ይቀድሳቸዋል ወንዶችን ሴቶች ጌቶችን አገልጋዮችን ቆላፋንን ግዙራንን ሁላቸውን አንድ ያደርጋቸዋል። ኹላቸውንም በአንድ ቅዳሴ ቅዱሳን ያደርጋቸዋል የአንድ የሰማያዊ አባት ልጅ ወንድማማች ያደርጋቸዋል። አንዲት ስም አለቻቸው ይህችም በአንድ መንፈስ ቅዱስ የተቀበሏት ጥምቀት ናት" (ሳዊሮስ ዘእስሙና ገጽ 57) 


ሥርየተ ኃጢአት 

በክርስቶስ ሞት የሞት ማሠሪያ ተፈታ፣ ሲኦል ባዶ ኾነ፣ ኃጢአት መውጊያ ተሰበረ። ይኽንን ቤዛነት አዳም ከተያዘበት ኃጢአት በጥምቀት ሥርየት እናገኛለን። “ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።” ሐዋ.2:38

ሠለስቱ ምዕት:-“ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን” እንዳሉት። 

 “ጥምቀት ማለት ከአዳም የወረስነውን ኃጢኣትና እኛም የፈጸምነውን በደል ひか ደምስሶ በመንፈስ ቅዱስ እንድንወለድ እንደገና የሚያደርገን የመጀመሪያው የጸጋና የእምነት ምሥጢር ነው፡፡ ይኽም የሚፈጸመው ካህኑ በጸሎተ ክርስትና መሠረት በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ በአ ጠመቀ ጊዜ ነው፡፡” (ትምህርተ ሃይማኖት ፣ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ) ገጽ 245

ቁራኝነት ይጠፋል

ሰይጣን ሰዎች ላይ ሰልጥኖ በነበረበት ወቅት ከእናት ማኅፀን ሲወጡ እየተቆራኘ ኃጢአት ሲያሠራ ቆይቶ በሲኦል ይጥል ነበር። ጌታ ያንን የእዳ ደብዳቤ ቀደደው። ስንጠመቅ ቁራኝነት ይቀራል። የተጠመቀን ሰው ሰይጣን አይቆራኘውም። “ይህንም ወድዶ ለዘለዓለም የማይኖረውን ኀላፊውን ሥራ የጠላውን ሁሉ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገብተው የክርስትና ጸሎተ ጥምቀት ይጸልዩለት የአብንና የልጁ የኢየሱስ ክርቶስንም ስም ይጥሩለት በሥጋዊት ልደቱ ቀን ዲያብሎስ በእርሱ ላይ ያሳደረው መንፈስ ርኩስ ከእርሱ ይሰደድ ዘንድ። ዳግመኛም በውኃው ላይ ይጸልዩ በዮርዳኖስ ውኃ በአንድ ወልድ ላይ የወረደውን መንፈስ ቅዱስም በላዩ ይልክ ዘንድ እግዚአብሔርን በጸሎት ይጠይቁ በውኃው ላይ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድም በውስጡ ሦስት ጊዜ በሥሉስ ቅዱስ ስም ያጥምቁት በላዩም መንፈስ ቅዱስ ያድራል ከእርሱም መንፈስ ርኩስ ይሰደዳል” ሳዊሮስ ዘእስሙናይ 83

እግዚአብሔርን ማወቅ

ያልተጠመቀ ሰው እግዚአብሔርን ማወቂያ ዓይነ ልብ አይኖረውም። እርሱን ለማወቅ ራሱ እግዚአብሔር ያስፈልገናል። ያንን ሰማያዊ እውቀት የምናገኘው በጥምቀት ነው። እግዚአብሔርን የማወቅ ጸጋ ይሰጠናል።

ትንሣኤ 

ትንሣኤ በተለወጠ አዲስ አካል ዘለዓለማዊ ኾኖ መነሣት ነው። የሚሞተው የማይሞተውን ይለብሳል። ዘለዓለማዊ ልብስ የምናገኘው በጥምቀት ነው። መጠመቅ ከሞቱና ትንሣኤው ጋር መተባበር ነውና። የተጠመቀ ሰው ከሞት በኋላ ላለው ሕይወት ይወለዳል። የሥጋ ሞቱ ጥቅም ይሆንለት ዘንድ ክርስቶስ የሞትን ሁኔታ ቀይሮታል። ይኽ በጥምቀት የምናገኘው ምሥጢር መጨረሻ ወደሌለው ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚመራን ነው።

በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን። በውሃው ውስጥ ሦስት ጊዜ በመነከር በመቃብር ከቆየበት ሞቱ ጋር እንተባበራለን። ዳግመኛም ከውሃው ውስጥ በመውጣት ከትንሣኤው ጋር እንተባበራለን።


መንፈሳዊ  እድገት 

እድገት በመሬት ላይ የወደቀ ዘርን መምሰል ነው። ዘሩ ሲሞት ሕያው የኾነ አካል ይወጣል። ብዙ ፍሬ ያፈራል። የሚሞተው ለሕይወት እንጂ በስብሶ ለመቅረት አይደለም። አካሉን ለመለወጥ ነው። መንፈሳዊ እድገትን እንድንጀምር ዘር የሚኾነው ይኽችው ጥምቀት ናት። 

ጠባቂ መልአክ ይሾምለታል

የተጠመቀ ሰው የሥላሴ ልጅ የንጉሥ ልጅ ነውና ጠባቂ መልአክ ይሾምለታል። ያልተጠመቁ ሰዎችን የሚጠብቁ መልአከ ጽልመት ነው። (ርቱዓ ሃይማኖት ገጽ 12)

 “ሐዲስ ልደት በሚገኝበት ጥምቀት ከተጠመቀበት ቀን ጀምሮ ይጠብቀው ዘንድ ክርስቶስ ጠባቂ ያደረገለት የእግዚአብሔር ቅዱስ መልአክ ወደ ሚሄድባት ወደ ገነት በምስጋናና በክብር ነፍሱን ይቀበላል እንጂ፡፡” ዘእስሙናይ 85

መንፈሳዊ ውጊያ ይጀምራል

ሰይጣን ሰውን ውጊያ የሚጀምረው ከተጠመቀ ቀን ጀምሮ ሲሆን ተጠማቂውን ይጠላዋል ይፈራዋልም። ግንባሩ ላይ የክርስቶስ ስም ተጽፎ ይታየዋል። በሰይጣን ላይ ሥልጣን ይሰጠናል። ከጥንቀት ቀጥሎ የምብቀባው ቅብዓ ሜሮን ይኽንን ማኅተመ መንፈስ ቅዱስ ይሰጠናል። 

ምሥጢራትን ሁሉ ይፈጽም ዘንድ ይፈቀድለታል

ጥምቀት ከምሥጢራት ኹሉ ቀዳሚ ነው። ምክንያቱም ማናቸውም መንፈሳዊ ሥራዎች ኹሉ በመንፈሳዊ ልደት ይጀመራሉና ነው። 

የተጠመቀ ሰው አዲስ ልደት ሕጻን ነውና መንፈሳዊ ምግብ የክርስቶስ ሥጋውና ደሙን ይመገባል። “ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ ፥ ጎኑን ለንጊኖስ የተባለ ወታደር ሲወጋው ደምና ውኃ ፈስሶበታል ፤ በዚያ ጎን በኩል [በምሥጢረ ጥምቀት) ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ገብተን ምሥጢራትን እንቀበላለን።  አውግስጢኖስ

ያልተጠመቀ ሰው የትኛውም ምሥጢራት አይፈጽምለትም። 

የመንግሥተ ሰማያት አረቦን ነው

መንግሥተ ሰማያትን እንደምንወርስ አረቦን ነው። አረቦን መያዣ ማለት ነው። ጥምቀት የመዳን መንገድ በር መግቢያ ነው። ድኅነታችንብ በጥምቀት እንጀምራለን። “ያመነ የተጠመቀም ይድናል” ማር.16:16

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Feb, 22:23


ስለ ጥምቀት

ቀደም ብዬ እንደ ጠቆምኩት እውቀትን ለማዳበር በየበዓላቱ ከሥር ከሥር እያነበቡ እየከለሱ መሄድ ቀለም ይጠራቀማል።

ስለልደትና ጥምቀት ያላቸውን ንባብ እነዚኽን መጽሐፍት ከልሻቸዋለሁ። ቢያንስ 40 በላይ አዳዲስ ነገሮችን አግኝቻለሁ። እርስዎስ ስለ ጥምቀት ምን አዲስ እውቀት ጨመሩ? ያንብቧቸው።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Feb, 21:42


እስከ መቼ

የአማራ ሕዝብ ምሑራኑን ያጣው በግልጽም በድብቅም ግድያ ነው። ዛሬም ግን የነቃ አይመስልም። የምሬት ጫፍ አልደረሰም። ቀብሮ ብቻ ይመለሳል፣ አልቅሶ ዝም ይላል።

ፍልስጥኤማውያን የሚያደርጉትን ሳይ ይገርመኛል። በእስልምና ባሕል ይሁን ሃይማኖት አላውቅም ሰው ሲሞት አያቆዩትም አያሳድሩም ቶሎ ይቀብራሉ።

ፍልስጥኤማውያን ግን እንዲኽ አያደርጉም። በእስራኤል ጦር ሲገደልባቸው። እስከሬኑን ይዘው በከተማ ይዞራሉ እየፎከሩ እየጬኹ ለመላው ዓለም ካሳዩ ብዙ ፎቶ ብዙ ምስል ካስቀሩ በኃላ ይቀብራሉ። ያንን እያየ ሕጻናት ያድጋሉ፣ ጠላታቸውን እያወቁ ያድጋሉ፣ ራሳቸውን ያዘጋጃሉ። ገና ከሕጻንነት ለፍልስጥኤም መሞትን እንደ ሃይማኖት እያጠኑ ያድጋሉ።

እነ አብይ የሐጫሉን ግድያ እንዴት እንደ ተጠቀሙበት እናስትልውሳለን። ገድለው በፎቶው ነው ሺኽ ኦርቶዶክስ ያስገደሉት። ማታገያቸው ነበር።

የዶ/ር አንዱዓለም ሞት ለአማራ ወይም ለባሕር ዳር ሕዝብ የመጨረሻ ነው ብሎ ነቅሎ ከከተናው ወታደር ይውጣልኝ ይላል ብዬ እጠብቅ ነበር። ምክንያቱን አላውቅም ዝም ብሏል። ኢትዮጵያ ግን ሐኪሟን አጣች።

የፋኖን ትግል የሕዝብ ትግል ያፋጥነዋል። እንቁ የቤተ ክርስቲያን ልጅም ነው ያጣነው። ከፕሮፌሰር አስራት የጀመረው የሕወሃት ግድያ ከኢ/ር ስመኘው የቀጠለው የአብይ ግድያ በቃ የሚባልበት ነጥብ ዛሬና ዛሬ ነው። ካልኾነ ምሑር ማምከኑን ይቀጥላል።

የዛሬ ጉልበት ነገ የለም። የዛሬ ቁጭት ነገ ፍርሃት ይኾናልና በቃ በሉት።


ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Feb, 20:10


አቃቂር  critics

የአሜሪካን የተራድኦ ኮምሽን USAID ለግዜው ሥራ እንዲያቆም ሠራተኞች ፈቃድ እንዲወጡ ተደርጓል። ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴን ፈጥሯል። ምክንያቱ ብዙና ፈርጀ ብዙ ነው።

በኢትዮጵያ በ USAID የሚሠሩ በርካታ የሰብአዊ ድጋፎች አሉ። ሠራተኞቹም ቀላል አይደሉም። የሚፈጥረው ክፍተት እንዲኽ የዋዛ  የሚታይም አይደለም። በኢትዮጵያ በሰብአዊ ድጋፍ፣ በትምህርት ፣ በጤና፣ በሰላም ዙሪያ ሥራዎችን ይሠራል። በርካታ ሀገር በቀልን ሀገር ነቀልም ትንንሽ ድርጅቶች ፈንድ የሚያገኙት ከዚኽ ድርጅት ነው።

ይኹን እንጂ አሜሪካን በዚኽ ድርጅት መልካም ብቻ አይደለም የምትሠራበት። እንደ ሰይጣን ያለ አሠራር አለው። የብርሃን መልአክ መስሎ፣ አሳቢ፣ መካሪ ደጋፊ መስሎና ድካሞችህን እያገዘ በረዥም ሰንሰለት ተብትቦ ያስርሃል። 

በትምህርት ዘርፍ ሰፊ ሥራ ይስራ እንጂ በትምህርት ውስጥ “ሥርዓተ ጾታን” በተመለከተ መርዝ አስገብቶ ትውልድ የሚገድለው የዚኽ ፕሮጀክት ክፍል ነው። 

በኢትዮጵያ በሁሉም በሚባል መልኩ የውርጃ ክሊኒክ (Abortion clinic) የዚኽ ድርጅት ፈንድ የተቋቋመ ነው። መድኃኒቶች ቁሳቁስ ስልጠና ጥናት የሚሠራው በዚሁ ፈንድ ነው። በቤተሰብ ምጣኔ ስም ወሊድ መቆጣጠሪያ ፈንድ ያደርጋል። 
በጾታ እኩልነት ስም የተመሳሳይ ጼታ ጋብቻን፣ ጾታ መቀየርን እንደ ሰብአዊ መብት እንዲታይ አጥብቆ የሚሠራ ድርጅት ነው። 

በተለያዩ ሀገራት በሰላም ዙሪያ ይሥራ እንጂ እግረ መንገዱን የስለላ፣ ውስብስብ የግጭት መንስኤ የሚኾኑ ጉዳዮችንም በመፍጠር ለወደፊት ያደራጃል። የምንጠላውን ነገር የሚሰጡን በምንወደው ነገር ጀርባ ነው የምልህ ለዚኽ ነው። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Feb, 19:11


https://www.youtube.com/live/qT-NuTEn0rY?si=uPNEtBlnSh6jpVYr

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Feb, 02:51


አብይ አሕመድ ኢትዮጵያን ለዚኽ አይነቱ ግብር ለፈረንጅ እንደሚሸጣት አትጠራጠር። አብይም ይልቅ ነው!!
የሃይማኖት ተቋማት ድምጻቸውን አጥፍተዋል። ችግሩ ሥር ሰዷል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Feb, 02:38


አሜሪካና አውሮፓን ወደ አቴስት (አምላክ ተቃዋሚነት) ያደረስቸው ፕሮቴስታንስቲዝም ነው።
ፕሮቴስታንት እግዚአብሔር በመጨረሻ የምታጣበት እግዚአብሔር ስለመኖሩ የምትጠራጠርበትና የምትክድበት መንገድ ነው። ይኽንን በቀላሉ መረዳት ከባድ ነው። የነ ሉተርን ጆን ካልቪንን መጽሐፍት ማገላበጥ ይጠይቃል።

የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስን ገልጦ ስለ ኢየሱስ እየሰበኩ ኢየሱስን እንዲያውቁት ሰይጣን የሠራው ሤራ ነው። መጨረሻ ያደረሳቸው ግብረ ሰዶማዊነት ላይ ነው። መጨረሻ ሃይማኖት የለሽ የኾነው ለዚኽ ነው።

የዚኽ ሰው ንግግር ቀላል አይደለም። ለእኛም ቤተክርስቲያን ፈተናው ቀላል አይደለም። ብዙ ሥራ እየተሠራ ነው። በውጭው ዓለም አሜሪካ በገሃድ የታዩ በሐሜትና ሸክሹክታ ስለተያዙ እንጂ ችግሩን አለ። ለመናገርም ቸግሮን ነው።

እኛ ሕንጻ ለመግዛት ልማት ምናምን እያልን ሕዝብ አላስተምልርን ለልጆች ግድ የማይሰጠን ኾነናል። በቅርብ በደንድ እናጭደዋለን።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Feb, 02:20


"እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።"
ዮሐ.1:16

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Feb, 18:50


ደውሉላቸው!!

ቤተክርስቲያን ተቋማዊ ናት። ምእመናን አጥቢያ ላይ ይገለገላሉ። ኹሉም ሰው በአጥቢያው ቤተክርስቲያን ሙሉ ምስጢራት ይፈጸምለታል። የግል ጉዳዩ ካለ ከንሰሐ አባቱ ይነጋገራል። ጥያቄውንም ከአጥቢያው መምህራን ይጠይቃል። መምህሩ እኔጋ ደውሉ አይልም። ወደ ንሰሐ አባት ነው የሚኬደው። ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ  እኔጋ ቅሩ አላላቸውም ወደ ጌታ ነው የመራቸው። 

በክፍል ውስጥ homiletics ስንማር "መድረክ ላይ ካገለገላችሁ በኋላ ሰዎችን አናግሩን እንዳትሉ፣ እሱ የእናንተ ድርሻ አይድለም። የንሰሐ አባት ነው" ያለን መምህር አልረሳውም።

እነ አጥማቂ ግርማም ደውሉልን፣ እነ ዓይነ ጥላም ደውሉልን፣ ማኅበረ ቅዱሳንም ደውሉልን? ፓስተሮቹም ያስደውላሉ። የማኅበር ጥገኛ መፍጠር ጥቅል አላማው ገንዘብ መሰብሰብ ነው። 

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Feb, 13:52


የዓርብ ጥያቄ

የረቡዕና ዓርብ ጾም ምክንያት ምንድነው?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Feb, 13:38


"ጦርነት ያለበት ሀገር ብልጽግና አይኖረውም"

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Feb, 13:03


ሕንጻ

ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጥሩ ቢሆንም ሰው ከመሥራት ግን አይበልጥም። ሕንጻውን የሚሠራው ብር እና ሰው ነው። ሕንጻ ሰብእን የሚሠራው ግን ክርስቶሳዊ ትምህርት ነው። በኦርቶዶክሳዊ አስተሳስብ የተቀረጸ ሰው በድንኳንም ቢሆን መቁረቡ ማስቀደሱ አይቀርም።

በኦርቶዶክሳዊ አስተሳስብ ያልተቀረጸ ሰው ግን በትልልቅ ካቴድራሎችም ቢሆን ስንኳን አይቆሮብበት አያስቀድስበትም። የሚበዛው ሰው እየደከመ ያለው የቱ ላይ ነው? ብዙዎች መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰ ያለው የቱ ላይ ነው?
ዘመኑ ገብቶታል ሊባል የሚችል ሰው አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ተተኪ ሰው ላይ እና ከትውልድ አደራ ላይ እየሠራ ከሆነ ነው።
@ ምሥራቀ ጸሐይ ጉባኤ ቤት 

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Feb, 03:08


Iran!!
2/6/2024

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Feb, 02:28


"ብዙ ሰዎች የቤተልሔን ሕጻናትን ባስገደለ ጊዜ ሰብአ ሰገል የሰገዱለትን ሕጻን አስገድዬዋለሁ ብለው ያስቡ ነበር። ሠላሣ ዓመት በሞላው ጊዜ በግልጽ እግዚአብሔር ልጅ መኾኑን አስመስክሮ አገልግሎት ጀመረ።"

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Feb, 18:05


አባትና ልጅ አንድ ቃል!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

02 Feb, 03:24


እንዲኽ ያለ የተምታታበት እብድ ነው ኢትዮጵያ የጣለባት። ፈልጌ አመጣኹት ንጽጽሩን!! ስሙት

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

02 Feb, 02:30


" The devil hath power to assume a pleasing shape.
"ዲያብሎስ ቆንጆ መልክ የመምሰል አቅም አለው!!

William Shakespeare, Hamlet

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

01 Feb, 21:49


ንግግር፣ ድርድር፣ ግርግር ውዥንብር!!

የሰሞኑ የእሳት አሎሎ አጀንዳ ነው። እየተቀባበለ የሚፋጅበት ነው። ከርዕሱ ጀርባ ኹለት ነገር እታዘባለሁ።

፩. መሪ ድርጅት ያለመኖር በአንድ ጥላ ሥራ አለመኾን አለመደራጀት ምን ያክል እንደሚጎዳ ማሳያ ነው። ድርጅት ኖሮ የተደራጁ ባለቤት ነን የሚሉ አባላት ቢኖሩ ተወያይተው መክረው ዘክረው ቢያወጡት ይኽ ኹሉ ግርግር ውዥንብ አይኖርም ነበር። ስለዚኽ በፓለቲካም በቤተክርስቲያንም አንድ ገዢ ኃላፊነት ወሳጅ አካል ማስፈለጉን ማሳያ ነው።

፪. አስተያየት የሚሰጠው አብዛኛው ከትግሉ አኳያ ምንም አድርጎ የማያውቀው፣ ምንም ማድረግ የማይፈልገው ትግሉን በሚዲያ ብቻ የሚደግፈው። ምንም ቅንጣት ታክል የተሳትፎ ድርሻ የሌለው ሰው የአማራን ትግል ዜና መስማትም የለበትም። ለጆሮ ቀለብ ካልኾነ በቀር። ምክንያቱም የሱ ድርሻ የሚያበረክተው ነገር ባለመኖሩ ነው። በሰላማዊ ሰልፍ አይታገል፣ በገንዘብ አይደግፍ፣ የተደራጀ ኃይል ውስጥ አይሳተፍ፣ የፓለቱካ ድርጅት ውስጥ የለ፣ ጥናት አያቀርብ፣ በሚዲያ የትግሉ አካል አይኾን። ታድያ ምን ይጠቅማል። የትግሉ አጋሮችን ቢሰማ ጥሩ ነው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

01 Feb, 13:11


ቦዶ ኾነኽ ስትዞር የሚያገኙኽ እነዚኽ አሞሮች ናቸው። ቀስሰዋል መስቀል ጨብጠዋል። በሬ ወለደ ትርጓሜ እንዲኽ ያወርዱልሃል። ፍሬ አልባ ተክል፣ ውኃ አልባ ደመናዎች

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

01 Feb, 02:49


ሰዎች የእግዚአብሔርን ድምጽ እንዳይሰሙ የሚያደርጋቸው ኃጢአት ነው። እዝነ ናቡናን ይደፍናልና ነው። ከቤት ጀምሮ እስከ ቤተ ክርስቲያን ያላስተካከልነው ሕይወት ስላለ ነው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

01 Feb, 01:38


በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በረሀብ ለተጎዱ ወገኖች ከ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ ተደረገ !

ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ /አዲስ አበባ)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነት አሳሳቢነት በአርቲስት ንብረት ገላው (እከ) አስተባባሪነት ከበጎ አድራጊዎች በማሰባሰብ በቡግና ወረዳ በረሀብ ለተጎዱ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ተደርጓል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባለፈው ወር በቡግና ወረዳ ተገኝተው በጤና ተቋማት በሕክምና ላይ የነበሩ ሕጻንትንና እናቶችን ተመልክተውና አጽናንተው ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑ ሰብዓዊ ድጋፍ አንዲደረግ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

በሀገረ ስብከቱ አሳሳቢነት አርቲስት ንብረት ገላው (እከ) ከበጎ አድራጊዎች በማስተባበር ባሰባሰበው ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት አልሚ ምግብና የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን የቡግና ወረዳ ቤተክህነት አስታውቋል።

የወረዳ ቤተክህነቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ዮሴፍ ረታ በርሀብ የተጎዱ ወገኖችን ለመታደግ በማስተባበርና በመለገስ ርብርብ ያደረጉ በጎ አድራጊዎችን ኹሉ አመስግነዋል።

በወረዳው ለችግር የተጋለጡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በጎ አድራጊ ወገኖችና ምግባረ ሠናይ ድርጅቶች ሰብዓዊ ድጋፋቸው እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።

©የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Jan, 19:04


ጥያቄ ከራሴ ለራስ

መሰደብ ለመንፈሳዊ ሕይወት ይጠቅማል? እንዴት? ስንሰደብ ደስ ይለናል? በተመሳሳይ ውርደትን የሚፈቅድ አለ? ተዋርዳችሁስ ታውቃላችሁ? ለሕይወት እድገትስ ጥቅም አለው? ወይስ ክብራችንን ማስጠበቅ መከበር?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Jan, 16:34


" ቅዱሳን መጽሐፍትን ለመረዳት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ትርጉም በማንበብ ብቻ ሳይሆን ልብን ከሥጋዊ ምግባራት በማንጻት መሳተፍ ይኖርበታል።

እነዚህ መጥፎ (ስጋዊ) ድርጊቶች ከቆሙ፥ ታዲያ የፍትወት መጋረጃን ካስወገዱ በኋላ፤ የነፍስ አይኖች የቅዱሳት መጻሕፍትን ምስጢር ያሰላስላሉ።"

+ ቅዱስ ዮሐንስ ካሲያን ሮማዊ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Jan, 16:30


የክርስቲያኖች ማኅፀን!!

የቅዱሱ አባታችን የአዳም ማኅፀን ምድር ነበረች ፤ ብፁዕ አዳም ከምድር ተገኝቶ ሕይወት ተችሮት በአምላካዊ ፍስሐ ሲኖር ያልጠበቀው ድቀት በሕይወቱ ተከስቶ፣ ከዘለዓለማዊነት ጎድሎ ቀሪ እንጥፍጣፊ ዘመኑን ምድረ ፋይድ ተብላ በምትጠራዋ ዓለም ጨርሶ፤ ተመልሶ ወደ ተገኘባት ማኅፀን ወደ ምድር ተመልሷል።

በአንዱ አዳም ምክንያት ሞት ወደ ዓለም በመግባት ልጆቹን ሥጋቸውን ለመቃብር ነፍሳቸውን ለአስጨናቂዋ ዓለም ሲኦል አሳልፎ ሲሰጥና ያለማንም ተገዳዳሪ በሰው ልጆች ላይ ነግሦ ዘመናትን ሲገፋ ኑሯል። የሰው ልጅ በራሱ ጥበብ ከዚህ አስጨናቂ የሕይወት ዑደት መውጣት እንደማይችል ተገንዝቦ ኑሮ ረድኤተ እግዚአብሔርን አንጋጦ "አንሥእ ኃይለከ ወነአ አድኅነነ" እያለ በመጠባባቅ ላይ ነበር።

የዓለም ድኅነት በመለኮታዊ እቅድ እየተቃረበ ነበር ፤ የሰው ልጅ ከደረሰበት የባሕርይ ድቀት እና ውርደት ወደ ቀደመ ክብሩ ልጅነት ፣ ወደ ቀደመ ቦታው ገነት ሊመለስ የሚችለው በእሱ ላይ የተላለፉ መለኮታዊ ፍርዶች ተፈጻሚነት ሲያገኙ ብቻ ነው። ይኽ ደግሞ እንዳይሆን ኹሉም በምልዓተ ኃጢአት ተይዞ መንፈሳዊ ቁመናው ጎብጦ ስለ ነበር ይኽን ፍርድ ሊያስወግድ የሚችል ከሰው ወገን አንዳች አልነበረም።

"እንዘ ኢኮነት ንጽሕት ድንግል እም ኢፈጠርክዎሙ ለአዳም ወሔዋን...የነጻች የተለየች የተጠበቀች ባትሆን ኑሮ (ድንግል ማርያም) አዳምንና ሔዋንን ባልፈጠርኳቸው ነበር" እንዲል አስቀድሞ በመለኮታዊ አሳብ የተለየች ንጽሕት ድንግል ማርያም ምክንያተ ድኂን ለዝንቱ ዓለም በመሆን በሥጋ ሥርዓት ይኽቺን ዓለም ተቀላቀለች ፤ ምድር ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አስተናግዳው የማታውቀውን ሰው ያየችው ቅድስት ድንግል ማርያምን ነው።

እመቤታችን፦ በእንግዳ ሥርዓት በመለኮታዊ ግብር አምላክ ወልደ አምላክ እግዚአብሔር ወልድን በተለየ አካሉ ፣ስሙ፣ አካላዊ ግብሩና ከዊኑ በተተነበየው መሠረት በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወልዳ ለዓለም ሕይወትን አስረከበች።

የሰው ልጅ እንደገና መወለድ ስላለበት እና ቀድሞ ወደ ታሰበለት ልዕልና ይመለስ ዘንድ ይገባ ስለነበር ዳግም የሚወለድባት አዲስ ማኅፀን በወልደ እግዚአብሔር ተፈጠረለት። ይህቺም ማኅፀን ጥምቀት ናት። 

አዳማዊ  ባሕርዩ የጎሰቆለ ፣ መንፈሳዊ ሕይወቱ የተበከለ፣ ኃይሉ ደካማ፣ ጸሎቱ የማይሰማ የነበረ ሰው ወደዚህች ማኅፀን ሲገባ ... ወልደ አምላክ እግዚአብሔር ክርስቶስ ኢየሱስ ሲጠመቅ በጥምቀት ማኅፀን ዘለዓለማዊነትን ፣ አዲስ ማንነትን ፣ ራሱን ሕልው እንደ ኾነ ስለሆነ የወጣው [የእሱ መጠመቅም ምክንያቱ ይህ ነው]  እያንዳንዱ ክርስቲያን ወደዚህ ማኅጸን ሲገባ ምን ሊሆን እንደሚችል ሊናገር የሚችል ከመካከላችን ይኖር ይሆን?። ሰው ልጅ ብቻ አለመኾኑ የእግዚአብሔር ልጅ መኾኑ ተመስክሮለት። 

የተጠመቀ ሰው ከሞት በኋላ ላለው ሕይወት ይወለዳል። የሥጋ ሞቱ ጥቅም ይሆንለት ዘንድ ክርስቶስ የሞትን ሁኔታ ቀይሮታል። ይህ በጥምቀት የምናገኘው ምሥጢር መጨረሻ ወደሌለው ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚመራን ነው።

በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን። በውሃው ውስጥ ሦስት ጊዜ በመነከር በመቃብር ከቆየበት ሞቱ ጋር እንተባበራለን። ዳግመኛም ከውሃው ውስጥ በመውጣት ከትንሣኤው ጋር እንተባበራለን።

ይኽን ሐዋርያው እንዲኽ ብሎ ይገልጸዋል፦ "ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን?... ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን።" ሮሜ ፮፥፫-፭

"ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ-እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።" ዮሐ ፫፥፭

ጥምቀት ማለት ክርስቶስን የምናገኝበት ድልድይ ማለት ነው። ጥምቀት የመንግሥተ ሰማያት አረቦን መያዥ ነው። ወልዳ የማታበቃ ማኅፀን፣ በወሊድ መቆጣጠሪያ የማትያዝ፣ የማታረጅ አዲስ ማኅፀን ወልዳ የሞይሞትባት ማኅፀን ጥምቀት ናት። 

እርሱ ከድንግል ማርያም የተወለደባትን ልደት እኛን  ተጠምቆ ከድንግል ጥምቀት  ወለደን ። “ክርስቶስ ተወለደ ተጠመቅ ከውኃና ከመንፈስ ወለደን” ቅዱስ ያሬድ
@Orthodox patristic

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Jan, 16:16


ታሪክን ስናስታውስ
ሁሉም ነገር ወደ ኅላም ወደፊትም ታሪክ አለ። አስተርእዮ ማርይምን ወደ ኋላ ሳስብ ይኽ ቀን ትዝ አለኝ። አቶ ሳሙኤል ሸንቁጥ እና እኔም ዲ/ን ንዋይ በጥር 21 ቀን 1990 ዓ.ም ጊንር ቅድስት ማርያም።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Jan, 15:50


የተጠመቁና ያልተጠመቁ ሰዎች

መጠመቃችን የሰጠንን ጸጋ ብዙዎች አልገባንም አልተገነዘብንም። የተገነዘብንም በጣም ጥቂቱን እሱንም በንግግር ብቻ ነው። ለዛሬ አንዱን ብቻ እናንሣ። ትርጓሜው የሳዊሮስ እስሙናይ ነው። 

መነሻዬ ይኽ ቃል ነው "ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፦ ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።”  1ኛ ቆሮንቶስ 12፥3

መጽሐፍ ቅዱስ " ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቀው የለም። ያለ ወልድም አብን የሚያውቀው የለም። ወልድም ለወደደው ይገለጥለታል" ይላል ማቴ.11:27

ወልድ ወዶ ፈቅዶ እርሱንና አባቱን መንፈስ ቅዱስን ማወቅ ለነቢያት ለቅዱሳን ሐዋርያት ለቅድስት ቤተክርስቲያን መምህራን ገለጡ። 

ዐይኖቻቸውም በእርሱ በመንፈስ ቅዱስ የበሩ ናቸው። እነርሱም በውስጣቸው ባደረ መንፈስ ቅዱስ ይኽንን ያስተውላሉ። “በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።”  1ኛ ቆሮንቶስ 12፥3

ይኽ ማለት ከነባቢት ከሥጋዊት የነፍስ ልብ መንጭቶ ከአንደበት እንደሚወጣ ቃል ነው። ከልብ የሚወጣን የቃል ትርጓሜ በውስጡ ነባቢት፣ ለባዊት፣ መንፈስ ካላቸው በቀር አያስተውሉትም። 

እንስሳት ለባዊት ነባቢት ነፍስ የላቸውም። ከነባቢት ለባዊት ነፍስ (ከሰው) የወጣን ቃል ትርጓሜ አያስተውሉም። የሚሰሙበት ጆሮ ቢኖራቸውም ቃሉን አያስተውሉም። 

በዚሁ አንጻር ያልተጠመቁ ሰዎች ለባውያት፣ መንፈስ ያሏቸው በድኖች (ያልተጠመቁ ሰዎች) እንዲሁም ተጠምቀውም የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ በውስጣቸው የሌለ (የካዱ) የእግዚአብሔርን ቅዱስ መንፈስ ቃል አያስተውሉም። 

ያልተጠመቁ ሰዎች ሰው ቢሆኑም ለባዊት ነባቢት ነፍስ ቢኖራቸውም በተጠመቁ ላይ ሁሉ ያደረው የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሱ ካደረባቸው በቀር እንስሳት የሰውን ቃል እንደማያስተውሉ የእግዚአብሔርን ቃል አያስተውሉም። በውስጣቸው የእግዚአብሔር መንፈስ የለምና። 

“ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም” 1ኛ ቆሮንቶስ 2፥14
የሰው መንፈስ ከሌላቸው (እንስሳ) ጋር እንደሚነጋገር ሰው ይሆናል። 

በተጠመቁ በሁሉ ሰው ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ አለ። እነርሱም ስለ ጥቂት እውቀታቸው ፈጥነው የእግዚአብሔር ቃልን ትርጓሜ የማያውቁ ቢሆኑም ከእግዚአብሔር መንፈስ የተራቆቱ ባዶ የኾኑ አይደሉም። እውቀታቸው ግን እንደ ሕጻን ያለ ነው። በትምህርት እና በአእምሮ ሲያድግ ግን በየጥቂት ጥቂቱ ያስተውላል።

እንዲኹም ሁሉም መሀይምናን ከክርስትና ጥምቀት ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ በውስጣቸው አለ። የእግዚአብሔርን ቃል ለመማርና ጥቂት በጥቂት ለመልመድ ያተጋቸዋል። ያን ጊዜም በውስጣቸው ባደረው የእግዚአብሔር መንፈስ ያስተውሉታል አምነውም ይቀበሉታል። ትርጓሜውንም ያውቃሉ። ሕጻን ሲማረውና ሲለምደው የሰውን የነገሩን ትርጓሜ እንደሚያውቅ በውስጡ ባለች መንፈስም አምኖ ይቀበለዋል። 

ለአባቶች ነቢያትና ሐዋርያት ወልድ የእግዚአብሔርን የተሰወረ ምስጢሩን በመንፈስ ቅዱስ ገለጠላቸው። እነርሱም መንፈስ ቅዱስ ላደረባቸው መሀይምናን ገለጡት። በጥቅምቀት የምናገኘው መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንድንማር ተምረንም እንድናውቅ የሚያግዘን እርሱ ነው ማለት ነው።

ንዋይ ካሳሁን

 

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

19 Jan, 01:27


እንዲኽም ያለ ካህን አሉ!!

ዛሬ ከተራ ነው። በእንግድነት ለእረፍት በሄድኩበት ከተማ ከተራን በምእመናዊ ክብር ጥጌን ይዤ ታቦት አውጥተን የእለቱን ቀለም ተወርቦ የደብሩ አስተዳዳሪ እጅግ አጭር ግን ጥርት ያለችዋን መልእክት አስተላለፉ። 

ጥምቀት የእቃ አይነት የልብስ አይነት እያሳዩ በነባራዊ ኁኔታ የማይገናዘብ በዓል ሲደሰኩሩ መዋል አይደለም። ጌታ ከኹለት ሺኽ ዓመት በፊት ተጠምቋል። እኛ ግን ዛሬ እንደ ዮሐንስ ትምህርት የሕይወት ተግባር እንደ ጌታ አብነት ጽድቅ መሥራት ነው የሚጠበቅብን። ጥምቀት የታቦት ማናፈሻ በዓል አይደለም። 

እናም የደብሩ አስተዳዳሪ አባት “እኛ በዓል እናከብራለን። ማክበር ያልቻሉ አሉ። ራሃብ ጦርነት አለ። ስለኾኑም ለቤተ ክርስቲያን ከምንሰጠው ከቁርስና ምሳ ቀንሰን ፣ በጥላ ከምንሰበስበው ቀንሰን መስጠት አለብን። ጠዋት ስትመጡ ይዛችሁ ኑ” ለዚኽም ኮሚቴ አቋቁመናል ብለው ተናገሩ። የተለያዩ ፎቶዎችን በግድግዳ ላይ ሰቅለዋል። 

ለእኔ ተግባራዊ በዓል ይኽ ነው። ይኽንን መልእክት ጃንሜዳ አልሰማሁትም፣ ጎንደርም አልሰማሁትም፣ ከዋሽንግተን ዲሲ አልሰማሁም። እንዲኽ ያሉትን አበውን ምእመናንም ምስጉን ናቸው። ያልታደለው ደግሞ ምርጌጅ ክፍያ ፣ ሕንጻ ግንባታ ገንዘብ ሲለቅም ይውላል።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Jan, 20:01


እንኳን ለእናታችን ልደት አደረሳችኹ!

ዳግም የምንወለድባት ባሕረ ዮርዳኖስ ዛሬ ተወለደች። ማሕፀኗን ቀደሰች።

ብዙ እናቶች ልጆችን ይወልዳሉ። ሲወልዱ ግን ዘጠኝ ወር መጽነስ የተፈጥሮ ግዴታቸው ነው።
እንወለድባት ዘንድ ዛሬ የተወለደችው ባሕረ ዮርዳኖስ ግን ዕርግና ሳይወስናት፥ ለመውለድ ዘጠኝ ወር መጽነስ ሳያስፈልጋት በየቀኑ በየሰዐቱ...ልጆችን በክርስትና የመውለድ ጸጋ ተጎናጽፋ ዛሬ ተወለደች።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Jan, 15:56


የምወደው ልጄ እርሱ ነው እርሱን ስሙት

በዮርዳኖስ ጌታ በተጠመቀ ጊዜ ለባሕርይ ልጁ ለኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠ የባሕርይ አባቱ ምስክርነት ቃል ነው። ይኽ ቃል በደብረ ታቦርም ይደገማል። "ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፥  መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ" ሉቃ.3:21

ጌታችን ወደ ዮሐንስ ሲመጣ እንደ ሌሎቹ አይሁድ ከኃጥአን ጋር ተርታ ይዞ ተሰልፏል። አንድ ተራ አይሁዳዊ መስሏቸዋል። ወደ ዮርዳኖስ ሲወርድ የማርያም ልጅ መሆኑን ብቻ ነው ያወቁት። 

ወደ ዮሐንስ ሲቀርብ እንደ ሌሎቹ እንዲናዘዘ አልጠበቀም ወይም ተናዘዝ አላለውም። ዮሐንስ ቀድሞ መዳን የሚያስፈልገኝ እኔ ነኝ አለው "ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።  ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት" ማቴ.3:14

ቅዱስ ዮሐንስ ሌሎቹን በስመ እግዚአብሔር ያጠምቅ ነበር። አንተን በማን ስም ላጥምቅህ አለው " ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሃለነ አንተ ውእቱ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጡአተ ዓለም፣ አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ ለመልከ ጼዴቅ። የቡሩክ አብ  ልጅ ብርሃንን የምትገልጥ ቡሩክ የዓለም መድኀኒት ይቅር በለን። የዓለሙን ኃጢአት የምታስወግድ የእግዚአብሔር በግ አንተ ነህ፣  እንደ የመልከ ጼዴቅ ክህነት  አንተ የዘላለም ካህን ነህ" ብለህ አጥምቀኝ ብሎት አጥምቆታል። አብርሃም "በጉን እግዚአብሔር ያውቃል" ብሎ ነበር ዮሐንስ ግን "በጉ እነሆ" አለ።

በነዚኽ ቃላት በርካታ የሃይማኖት ጥልቀት ያለው ትምሕርት አስቀምጧል። ነገረ ድኅነትን ተንትኖበታል።  ከዚኽ በኋላ ተጠምቆ እንደወጣ " ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤  እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ" ማቴ3:16

ሰማይ ተከፈተ ሲል መጽሐፍ ቅዱስ በሰው ቋንቋ ስለተጻፈ በሚረዳን ቅርጽ እንዲታየን በመጻፉ እንጂ ሰማይ እንደ በርና መስኮት አይከፈትም አይዘጋም። መጽሐፍ በኦሪት እንደዘገበልን ተዘግቶ የነበረው ገነት እንጂ ሰማይ አልነበረም። በር ሲከፈት ውስጡ እንዲታይ የእግዚአብሔር ምሥጢር መገለጡን መናገር ነው። ሰማይ ልዕልና እግዚአብሔር ነው። አብ ከደመና "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው" አለ። 

ኃጢአት የሌለበት የሰውን ሥጋ የለበሰ ሰውና አምላክ የኾነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ምንም እንኳ እግዚአብሔር ያከበራቸው አርዕስተ አበው የላካቸው ነቢያት ቢነሡ ቢልካቸው ከኃጢአት አልተለዩም ከበደል በታች ነበሩ። እንደ ልቤ ያለው ቅዱስ ዳዊት እንኳን ብዙ በድሏል። ስለዚኽ እግዚአብሔር  በሚበዙት ደስ አልተሰኘም። 

የአብ ፈቃድ የሆነው የሰው መዳን ልጁ (ወልድም) የመጣበት ዋናው የሰው መዳን ፍጹም የሆነው ኃጢአትን የሚያስወግደው እርሱ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ "በእርሱ ደስ የሚለኝ" ብሎ መሰከረ። 

በዚኽ ብቻ ሳይበቃል "ልጄ" ብሎታል። በዮርዳኖስ ሲጠመቅ አይሁድ የማርያም ልጅ ብቻ እንዳይመስላቸው መለኮት የተዋሐደው ሥጋ መሆኑን ሊመሰክር "ልጄ" ብሎ ገለጠው። "ልጅ" የሚለው ቃል እንደ ሥጋዊ ልደት እንዳይመስለን። የማይመረመር መንክር ነው። ለዚኽም ቅዱስ ያሬድ "መንክር ስበሐተ ልደቱ" እንዲል።

የወልድ ልጅ መባል በዮሐንስ እጅ ቢጠመቅም የማይመረመር አምላክ መሆኑን ይገልጣል። ቀዳማዊ ልደቱ ከአብ ያለ እናት ከባሕርይው እንደ ተወለደ ያስረዳል። በቀዳሚ ልደቱ የአብ የባሕርይ ልጅ በደኀራዊ ልደቱ የሰው ልጅ መሆኑን ያሳያል። 

በዚኽ ምስጢር ተዋሕዶን መስክሯል። በሥጋ እየተጠመቀ "ልጄ" ብሎ መስክሮለታል። አምላክ በተዋሕዶ ሰው ሆኗልና። ከተዋሕዶ በኋላ የአብ ልጅ እና የሰው ልጅ ብሎ መክፈል አይቻልም። የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ በተዋሕዶ አንድ ሆኗልና። ሰው (ሥጋ)  በተዋሕዶ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆኗል። የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ አብ መስክሮለታል። 

ሥላሴ (ሦስትነት) በተዋሕዶ ተገለጠ። በብሉይ ኪዳን በድንግዝግዝ የነበረው ምስጢረ ሥላሴ በዮርዳኖስ ተገለጠ (አስተርእዮ)። ወደ ዮርዳኖስ ሲወርድ የሰው ልጅ ብቻ የመሰላቸው ሲመለስ ግን በተዋሕዶ የከበረ "የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ" መሆኑ ተመስክሮለት ተመለሰ። ጥንት የሌለው አምላክ ዘመን ተቆጠረለት። 

ሌሎች የእግዚአብሔር ልጅ ቢባሉ በጸጋ ልጅነት ሲሆን ከዚኽ የተለየ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ነው። አንዲት ፈቃድ፣ አንዲት ሥልጣን፣ አንዲት መንግሥት እንዳላቸው ያስረዳል። 

በስተመጨረሻም " ወሎቱ ስምዕዎ እርሱን ስሙት" ብሎ የዮሐንስ አገልግሎት ሲጠናቀቅ የጌታ ትምሕርት ይጀመራል። ሙሴ በሕግ ነቢያት በትንቢት የተናገሩለት የሁሉም ፍጻሜ እርሱ በመሆኑ ስሙት አለ። ከዚኽ በኋላ የአይሁድ ጥምቀት አለፈች ልጅነት የምታሰጥ የእኛ ጥምቀት ተመሠረተች። 

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Jan, 15:44


እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ ደረሳችኹ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Jan, 14:22


https://youtu.be/7_R9JJqeJCU?si=qpdhVn-S9BUjTqkU

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Jan, 14:20


ክርስቶስ በጥምቀቱ የወለዳቸው ልጆች እየተቀጣቀጡ እረኞች በካባ ላንቃ ተንቆጥቁጠው ጥላ ተዘርግቶላቸው "በደማቅ ኁኔታ ተከበረ" ይላሉ። ያከበረንን ቀድመን ማክበር። የጥምቀት ልጆች እያለቁ እየተራቡ በዓል!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

18 Jan, 06:35


ገሐድ 
 
ገሐድ፦መገለጥ ይፋዊ ገሀዳዊ መሆን ማለት ነው።እግዚአብሔር ወልድ በአካለ ሥጋ ለሰው ልጆች የተገለጠበት የሰው ልጆችም በጥምቀት በልጅነት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማሕፀነ ዮርዳኖስ ተወልደው በክብር የሚገለጹበት ማለት ነው።

ወልደ እግዚአብሔር በኩነት ተዋሕዶ ሰው ሁኖ የልደት መገለጡን በጥምቀቱ መገለጥ ይፋዊ ያደረገው የዲያብሎስ ሥራን አብፍሶ እርሱን ወደመምሰል ሊያሳድገን ነውና፦"ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።"፩.ዮሐ.፫፥፱ እንዲል።

ገሐድ አስተርእዮ ነው።አስተርእዮም መታየት መገለጥ ማለት ነው።

ሰው ሁሉ ለበዓለ ጥምቀት በነጭ ልብስ የሚገለጠው በብርሃነ መለኮት የተገለጸውን  አምላክ ለመቀበል እና በብርሃነ ልጅነት ለመኖር ያለውን ተስፋ ለመግለጽ ነው።

@ምሥራቀ ጸሐይ ጉባኤ ቤት

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

17 Jan, 18:16


https://youtu.be/NB4oN7QecGY?si=rM23KiCCkH_XjSic

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

17 Jan, 18:02


ተወለደ

ወደ ገነት የሚወስደው መንገድ ተከፈተ፣ እንዳይበሉ የተከለከሉት የበለስ ፍሬ የሕይወት ምግብ ሆኖ መጣ፣ በኪሩቤል የታጠረው በር ተከፈተ፣ የእባቡ መርዝ ተነቀለ፣ የኃጢአት መውጊያ ደጋኑ ተሰበረ፣ የኃጢአት ጅረት ተቋረጠ፣ ሰውን ከውድቀት የሚያነሣው የአብ ክንዱ ተላከ። 

ሰማያዊ ሙሽራ ከሰማይ መጣ፣ ክንደ ብርቱው ሙሴ የሰበከው ነቢያት የተነበዩት በመካከላችን ተገኘ። ዳዊት ሊጠጣ የተመኘው የቤተልሔም ውኃ ፈለቀ። በጨለማ ውስጥ ብርሃን በራበት፣ በኦሪት የተሰበከው አኹን ገሀድ ሆነ። ሰማይን የሠራት በበረት ተገኘ። ለኹሉ መኖሪያ የሰጠ ለራሱ ማደሪያ አጣ። ልዑሉ ዝቅ አለ። ጥበብም ቤቷን ሠራች። በደመና የሚራመድ በእናቱ እቅፍ ታየ። መለኮት ባሕርይው ያልሆነውን ሥጋን ባሕርይው አደረገ። ለሰው የሌለውን ባሕርየ መለኮትን ሰጠው። ንግሥናን ሰጥቶ ባርነትን ወሰደ። 

የእረኞች አለቃ ጠባቂ መልካም እረኛ ሆኖ መጣ። በግ እና ሊቀ ካህን ሆኖ ተገኘ። ነቢያትን የሚፈጽማቸው፣ የአዳምን ራቁትነት የሚሸፍን ልብስ ተገኘ። የሞት ምልክት ያለበት ሕጻን ተወለደ። ሊሞት ተወለደ ሊነሣ ሞተ። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

17 Jan, 16:37


ምድርን ሰማይ ያደርጋት ዘንድ እርሱ ከሰማይ ወረደ!!

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

17 Jan, 13:51


ሰብአ ሰገልን የመራው ኮከብ 

ሰብአ ሰገልን ይመራቸው የነበረውን ኮከብ ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እጅግ ንቁዎች ትጉዎች መኾንና ብዙ ጸሎት ያስፈልገናል። ከዚኽ ቀድሞ ተቃዋሚዎች የሚሉትን እናንሣ፤ ዲያብሎስም ከዚኽ ቃል የተነሣ እውነታውን ይቃወሙ ዘንድ አስታጥቋቸዋልና። 

ሰዎች እንደሚሉት "ኮከብ ቆጠራ ለእኛ ረብ ጥቅም እንዳለው ያስረዳ ዘንድ እነሆ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ተገልጦ ታይቷል። ክርስቶስ በኮከብ ቆጠራ ሕግ ከተወለደ እንዴት ኮከብ ቆጠራን አጠፋ? የሰው ልጅ ዕጣ ፈንታ በከዋክብት የተመሠረተ ነው የሚለውን ትምህርት አስወገደ? እንዴት የአጋንንትን አንደበት ዝም አሰኘ? እንዴት ስህተትን አራቀ? እንደዚኽ ያለ የጥንቆላ ሥራንስ እንዴት ገለባበጠ። 

ዳግመኛ ሰብአ ሰገል ከራሱ ከኮከቡ የተረዱት ነገር ምንድነው? ጌታችን የአይሁድ ንጉሥ መኾኑን ነውን? ኾኖም የጌታችን መንግሥቱ ከዚህ ዓለም አልነበረችም። ይህን "መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም" ሲል ለጲላጦስ ግልጽ አድርጎ ነግሮታል። 

ጦር ወይም ጋሻ የታጠቁ ጠባቂዎች አልነበሩትምና ፈረስ ወይም የበቅሎ ሰረገላ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር የያዙ ወታደሮች በዙሪያው ኾነው አላጀቡትምና። ከዚህ ኹሉ የተናቀና መናኛ ሕይወትን ይኖር ነበርና፤ ከእርሱ ጋር የነበሩት ዐሥራ ኹለት ሰዎችም ከሰዎች ኹሉ የተዋረዱና ምናምንቴዎች ነበሩና። 

ለእኔ እንደሚረዳኝ ይህ ኮከብ ከተለመዱ ከዋክብት አንዱ አይደለም፤ እንዲያውም አንድ በኮከብ አምሳል የተገለጠ የማይታይ ኃይል እንጂ ፍጹም ኮከብ አልነበረም። 

ይኽም:-

፩. በመጀመሪያ ደረጃ:- ከአካሄዱ መረዳት እንችላለን በዚህ መልኩ የሚጓዝ ተፈጥሮአዊ ኮከብ የለምና። ፀሐይን ብትጠራ፣ ወይም ጨረቃን ወይም ሌሎች ከዋክብትን ብትጠቅስ እነዚኽ ኹሉ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ሲኼዱ እናያቸዋለን ይኽ ኮከብ ግን ይኼድ የነበረው ከሰሜን ወደ ደቡብ ነበር። ፍልስጥኤምም ከፋርስ አንጻር የምትገኘው በስተደቡብ ነውና። 

፪. በኹለተኛ ደረጃ:- ከጊዜውም አንጻር አንድ ሰው ይህን መገንዘብ ይችላል። ኮከቡ ይታይ የነበረው ሌሊት ላይ ሳይሆን እኩለ ቀን ላይ ፀሐይ ብርሃንዋን እያለገሰች ሳለ ነው። ለአንድ ተፈጥሮአዊ ኮከብ ደግሞ ይህ የማይቻል ነው። ኮከብ ይቅርና ጨረቃም ብርሃንዋን በቀን አትሰጥም። የጨረቃ ብርሃን ከኮከብ ብርሃን ቢበልጥም ቅሉ የፀሐይ ብርሃን በወጣ ጊዜ ጨረቃ ትጠፋለችና። ራሷን ትሰውራለችና። የዚህ ኮከብ ብርሃን ግን ከፀሐይ ብርሃን ይልቅ ደምቆ በቀን የሚታይ ነበር። ከከዋክብት ይልቅ ጽዱል ነበርና። 

፫. በሦስተኛ ደረጃ:- ኮከቡ አንዳንድ ጊዜ የማይታይ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚታይ ነበር። ፍልስጥኤም እስኪደርሱ ድረስ ሳይሰወር እየታያቸው የመራቸው ሲኾን ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ግን ተሰውሮባቸዋል። ለሄሮድስ የመጡበትን ምክንያት ነግረውት ከእርሱ ከወጡ በኋላም እንደ ገና ራሱን ገልጦላቸዋልና። ይህ ኹሉ አኳኋኑ ደግሞ ከፍ ያለ ኃይልን ገንዘብ እንዳደረገ የሌላ ለባዊ አካል እንጂ የአንድ ተፈጥሮአዊ ኮከብ ጠባይ አይደለምና።

 እንዲያውም እርሱ ራሱ ብቻውን ሲኼድ አይታይም። ሰብአ ሰገል ሲንቀሳቀሱ የሚንቀሳቀስ እነርሱ መኼድ ሲያቆሙም እርሱም አብሮ የሚቆም ነበርና። እንደ እነርሱ መሻት የሚኼድ ነበር። ይኽውም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ የደመና ዓምድ መንገድ ሲኼዱ ይኼድ ሲያቆሙም ይቆም እንደ ነበረው ነው። 

፬. በአራተኛተኛ ደረጃ:- ሕጻኑ ባለበት ላይ ዝቅ ብሎ መጥቶ ሲቆምና በዚኽም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያመለከተበት መንገድ ይህ ተፈጥሮአዊ ኮከብ እንዳልሆነ ማንም ሊገነዘበው የሚችል ነው። እንደ ተፈጥሮአዊ ኮከብ ከሰብአ ሰገል መጥቆ በጠፈር ላይ አልተሰቀለምና። ከላይ ከጠፈር ተሰቅሎ ቢያመለክታቸው ኖሮ ቦታውን በትክክል ማወቅ ባልተቻላቸው ነበርና። 

የከብቶች ግርግምን የምታህል ጠባብ ቦታ ወይም ደግሞ በጨርቅ የተጠቀለለ ሕጻን ያለበትን ሥፍራ በትክክል ለማመልከት ለተፈጽሮአዊ (ግዙፍ) ኮከብ የማይቻል እንደ ኾነ የምታውቁት ነው። ከግዙፍነቱ አንጻር ብቻ ሳይኾን ከምጥቀቱ አንጻርም ሰብአ ሰገል ሊያዩት ይፈልጉት የነበረውን ሥፍራ ለይቶ መጠቆም የሚቻለው አይደለም።  ወንጌላዊው ይህን ሲነግረን "እነሆም ኮከቡ ሕጻኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር" ይላልና። 

እንግዲህ በዚህ ሁሉ ምክንያት ኮከቡ ከተፈጥሮአውያን ከዋክብት አንዱ እንዳይደለ ወይም ራሱን የገለጠላቸው እንደ ፍጡራን ከዋክብት ሥርዓት እንዳልኾነ አየህን? በኮከብ አምሳል የታየው ለምንድነው? የአይሁድን ልበ ቢስነት ይነቅፍ ዘንድ ወደውና ፈቅደው አላዋቂ ለኾኑበትም ምክንያት ይስጣቸው ዘንድ ነው። 

እርሱ ወደዚህ ምድር እንደሚመጣ ብዙ ጊዜ አስቀድመው ነቢያት ሲናገሩ ሱባኤ ሲቆጥሩ ምሳሌ መስለው ሲያስተምሩ ሰምተዋልና። ነገር ግን ይህን የነቢያት ትንቢት ሱባኤና ምሳሌ ሊያስተውሉ አልቻሉም። በመካከላቸው የተወለደውን ንጉሥ ይፈልጉ ዘንድ ከረቅ ሀገር እንዲመጡ አደረገ። 
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜ ማቴዎስ

የእኛ ትርጓሜ ወንጌል ከላይ የተጠቀሱትን ምክንያቶች ሁሉንም ጠቅሶ በመግቢያው "በቁሙ ኮከብ ነውን መልአክ ነው ብሎ ይጠይቅና መልአክ ነው" ብሎ ይጠቅሳል። ከላይ የተዘረዘሩትን ምክንያቶች ለመልአክ ይሰጠዋል። ትርጓሜ ወንጌል 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

17 Jan, 04:14


https://youtu.be/GecdweVR_fE?si=b9wsDSgrvmTfmhTc

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

16 Jan, 19:11


መስቀል አደባባይን በነጻ ያስረከበው ቤታችን ጥምቀትን ለቱሪዝም ከከንቲባ አዳኑ ጋር ወደፊት !!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

16 Jan, 17:22


የባሌው ድሬ ሸክ ሁሴን።
ድሬ ሼክ ሀሴን ባሌ ጎሎልቻ ወረዳ የሚገኝ ሲኾን። የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀመዝሙር አቡነ አኖሪዎስ ቦታ ነበር። በሂደት ነው ወደ እስልምና ቦታ የተቀየረው።

ዛሬ ፋሲል ግንብን ሳይ ድሬ ሸክሁሴንን ቀለም ተመሳስሎብኝ ነው። አብይ አደገኛ መርዝ ነው!! ወይስ እኔ ብቻ ነኝ የተመሳሰለብኝ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Jan, 02:58


"የጠፋ በግ አዳምን የፈለገው ባገኘውም ጊዜ የተሸከመው እውነተኛ ቸር ጠባቂያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (ተአምረ ማርያም

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Jan, 02:01


"ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።"
ማቴ.9:36

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Jan, 01:00


"መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት!"

ዘካ.11:17

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

04 Jan, 20:17


መሬት መቀጥቀጥ

ሰው መደንገጥ ያለበት መሬት ሲንቀጠቀጥ ሳይኾን መሬት በሥላሴ ሕንጻ ሰው ደም ስትጨቀይ ነበር። ምኅላ ለፈሰሰው ደም ይቅርታ መጠየቅ እንጂ ቁጣው እንዲያልፍ አይደለም። ደሞዛችን ገና አልተነካም። ምንደኛ እረኛ በላዩ ላይ ሕንጻ ቢናድበት እንኳ ቁጣ አይመስለውም። ምን በወጣቸው ይደንግጡ።
አንዱ "ቤተክርስቲያን ለምን ምኅላ አታውጅም" ሲል ሰማሁት። ሰው ደም ሲፈስ ለምን ዝም ትላለች ብሎ ነበር መጠየቅ። መነኮሳት ካህናት ምእመናን እንደ በግ ሲታረዱ ምን አሉ። ቆባቸው ካልተነካ አይነቁም። የእኛንም ክፋትና መጠላላት ልክ እንኳን መሬት መንቀጥቀጥ እሳት ያዘንባል። ገናኮ በሚገባ አልተግባባንም። ብሔራዊ ንሰሐና እርቅ ብቻ!!።

ንዋይ ካሳሁን!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

04 Jan, 01:30


ሕንጻ ሳይኾን ሰው እንገንባ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 16:32


ሕንጻ የመጣያ መድረክ ነው። አንድ ወዳጄ ካህን “ገንዘብና ሕንጻ ከመጣ ጠብ ይጀመራል” ብሎኛል። ይኽ የሚፈታው በቃለ እግዚአብሔር ነው። ልብን በማቅናት። አሜሪካ የገባ ምእመን ማንንም አይሰማም። ሁሉም ሊቅ ሁሉም ተናጋሪ ነው። የቃለ እግዚአብሔር ፍቅር ያለው የለም። “እንማር፣ እንማር” ይላሉ። አንድ ቀን ግን ጊዜ መስጠት አይፈልጉም። ይኽ የብዙኀኑ ፈተና ነው። ሕዝቡ የሚፈልገው በየሳምንቱ አዳዲስ ያላየው ያልሰማው በዩቲዩብ ያየውን ሰው ማየት ብቻ ነው። ለአንድ ሰሞን ጉድ ገድ ይላል። በሕይወቱ ግን ፈቀቅ አይልም። 

ሌላው በየቦታው እንደ ሱቅ ቤተ ክርስቲያን ከመትከል በአንድ አማካይ ቦታ ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ገዝቶ አነስ የሚሉትን በጋራ እያደረጉ ማጠቃለልና አገልግሎቱንም አገልጋዩንም ሰፊ ማድረግ። ቄሱም ምእመኑም ባኮረፈ ቁጥር፣ ቡድን ባደራጀ ቁጥር እየሄደ ቤተ ክርስቲያን እያለ መክፈት መጽደቂያ አይመስለኝም። ለዚኽ ዓይነቱን በር መክፈት አይልስፈልግም። ከዚያ ይልቅ እንዴት በአንድ ቤተ ክርስቲያን በጋራ ማገልገል ይችላል ብሎ መሥራት ነው። ብዙ ጥናት ብዙ ውይይት ይፈልጋል። ከምን በላይ ጥሩ መንፈሳዊ ምሪትም አባትም ይፈልጋል። ግዴለሽና ስለ ገዛ ኑሮው የሚጨነቅ ጵጳጳስ ይኽንን አይችለውም። 

በአንድ ወቅት እንዲኽ ያለ ውይይት ጀምሩ እኔ ዝርዝር ጥናት ላዘጋጅ ብዬ ጠይቄ ነበር። ወዳጄ ማን በኔ ጥናት ጊዜውን ያጠፋል። 

የራሱ ጉዳይ ከበረታ ይቀጥላል ካቃተው ይዘጋል እኔ ምን አገባኝ” የሚል ጨካኝ ካህን ባለበት ምን ጥቅም ይገኛል። በየንግሡ እየዞሩ ዶላር መቀበል ምንደኝነት ብቻ ነው። 

ምእመኑም ገንዘቡን እንደከሰከሰ ካህኑም በልመና በጭቅጭቅ ልቡ እየቆሰለ በነገር ብዛት ጨጓራው እየተላጠ መኖር ብቻ ነው። ካህናት ልጆቻቸውን በአግባብ አብቅተው እንኳ ራሳቸውን መተካት የቻሉ በጣት ናቸው። እንደውም ከቤተክርስቲያን ቀድመው የሚርቁት እነርሱ ናቸው።


ገዳማት እንኳ ተጠንተው የመክሮባቸው የሚቋቋሙ አይደሉም። ሁሉም በሚባል መልኩ አንድ አንድ መነኮሳት ብቻ የያዙ ናቸው። ካሊፎርኒያ “ገዳም ሊገዛ ነው” እያለ ድፍን ኢትዮጵያዊ ሲንጫጫ “ጫካ ነው እየገዛችሁ ያለው” ብለናቸዋል። ሰዉ መስሚያ የለውም። ከዚያ በኋላ ወሬው የለም። እንኳን በሽተኛ ሊያገግምበት ገዳሙንም የጀመሩት ሳይታመሙ አይቀርም። ጥናት ምክክር ብሎ ነገር የለም። አሜሪካ ስለሆነ ብቻ እንደ ፈለገ ይጀመራል ጊዜና ገንዘብ ብቻ መፍጀር ነው። 

በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ግዥና ግንባታ ላይ መርሕ የለም። ለአንዳንዱ የግድ ማስፈለጉ ካልኾነ በቀር ለብዙዎች ግን የታይታ ብቻ ነው። የሥነ ልቡና ጥቅም። የምንጨነቀው ለሕንጻው እንጂ ለውስጡ አገልግሎት እንጨነቅምም አንጠነቀቅምም። ውስጡ የሚሠራውን ማየት ነው ሕንጻ ማለት። 

የአርሜንያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአሜሪካ በሀገራቸው ካሉት በብዛት ይኖራሉ። በጣም በርካታ ቤተ ክርስቲያን ገዝተዋል። ዛሬ ግን አብዛኞቹን ዘግተዋል ሸጠዋል። ተከታይ ባለማፍራት ነው። ግብጾች በጣም ጥቂት ቤተክርስቲያን አላቸው። ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣ ኮሌጅ አላቸው። ልጆቹ ላይ ይደክማሉ። በባለሙያ የተደራጀ ከመኾኑም በላይ ሁሉም ቤተ ክርስቲያንም ኾነ ካህን በቀጥታ ከካይሮ ይታዘዛል። ማንም ከሊቀ ጳጳሱ ትዕዛዝ አይወጣም። አሜሪካ ነው ብሎ ቄሱም ምእመኑም ቤተክርስቲያን አይከፍቱም። ተጠንቶ በሲኖዶስ ሲፈቀድ ብቻ ነው። 

በስተመጨረሻም  የምእመኑ ሀብት የሞርጌጅ ጠብ ሲኖር የሎየር ሲሳይ እንዲሆን የተፈረደበት ምእመን፣ አጥቢያዊ ሃይማኖት፣ ግለሰባዊ አስተዳደርና፣ ጳጳሳዊ ስግብግብነት ሐዋርያዊ መልኩን እንዲሸፍን አዚም የተደረገበት ዘመን ላይ ደረስን እንጂ ሕንጻ የእድገታችን ማሳያ አይደለም።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 16:32


ሕንጻ በሕንጣ ላይ 

ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ አይቀርም” ያለው ጌታ ነው። የብሉይ ኪዳኑ ቤተመቅደስ የተሠራበትን ዋና ዓላማ ባጠናቀቀበት ወቅት ላይ ነበር ጌታ በአሠራሩ የተደነቁ ሐዋርያትን ሲያደንቁ አይቶ የነገራቸው። 

ሰሞኑን ለየት ባለ መልኩ በርከት ያሉ ትላልቅ የሚባሉ ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት ተገዝተው የምእመናን መገልገያ በመኾን ግምሹ ሲገዙ ግማሹ ሲመረቁ እያየሁ ነው። 


ጉዳዩ ምንም የሚከፋ አይደለም። ለአገልግሎት ምቹ ማድረግ ተገቢ ነው። 
ጉዳዩን ለማንሳት የፈለኩበት ምክንያት በአጭሩ እንዲኽ ነው። በኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥና በውጭ የሚታነጹም ኾኑ የሚገዙ አብያተ ክርስቲያናት በቀላል ገንዘብ የሚተመኑ አይደሉም። የሚገዙትም ቢኾን ለዓመታት ወጪያቸው ምእመኑን እረፍት የሚሰጡ አይደሉም። 

ይኽም ኾኖ ግን ለቤተ ክርስቲያን ከሕንጻው በላይ እጅግ አስፈላጊው ጉዳይ ግን ማንም ችላ ያለው አልያም ከንግግር ያለፈ ተግባር የለውም። 

መንፈሳዊ ሕይወት :- የሕንጻ ቤተክርስቲያን ዋና ዓላማ አማንያን ያጋራ አምልኮ ሥፍራ ኖሯቸው በክርስቶስ የሚያደርጉት ኅብረት ስፍራ ነው። ልዩና ክቡር ኅብረት። ስለኾነም ከሕንጻው የሚበልጡት ምእመናን ናቸው። መንፈሳዊ ሕይወት የሌለው በስሜቱ ብቻ ክርስትና እየተሰማው የሚኖር ምእመን ይዘን ከክርስቶስ አካል ጋር ግንኙነት የሌለው ምእመን ይዘን እንኖራለን። ሕንጻ ይሠራል እርሱ ግን አይቆርብም ራሱን አይሠራም። 

ይኽንን ሕይወት በእጅጉ ችላ የተባለ ነው። ሕንጻ መሥራት ለቤተ ክርስቲያን በአብዛኛው እንደ ግብ ተወስዷል። ፈጽሞ ስኽተት ነው። 

Fr. Josa ከ 15 ዓመት በፊት ትምህርት ላይ እያለን "የእናንተ ቤተክርስቲያን ትኩረቷ ሕንጻ ነው። እሱ አስፈላጊ ቢኾንም ዋናው ሕዝቡ ላይ ማተኮር ነው” ብሎ የነገረን ቀን ዛሬም አስበዋለሁ። 

ሌላው የሚተካ (ትክ) ትውልድን ማፍራት ጉዳይ ነው። ሕጻናትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ማምጣት ዛሬም ያልተወሰደብን ትሩፋት ነው። አስተምሮ ለነርሱ ማስረከብ ግን አልቻልንም። በእጅጉ የተዳከመ ነው። በተለይ በውጭው ያለችው ቤተ ክርስቲያን ፈጽሞ የለም በሚባል ደረጃ ላይ ነው። ጥናት ቢሠራ ውጤቱን በትክክል ማስቀመጥ ከባድ አይደለም። ልጆች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚቆዩት እስከ 18 ዓምድ ድረስ አካባቢ ወይም ኮሌጅ እስኪገቡ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ብቅ የሚል የለም። ካለም በጣት ነው። 

ልጆች ከፍ ሲሉ የሚጠሉት ነገር ቤተ ክርስቲያን መሄድ ነው። ለምን ብሎ መጠየቅ የእኛ ድርሻ ነው። ምን አጥተው ነው? ምን ስለኾነ ነው ብሎ ጥናት ይፈልጋል። ይኹን እንጂ ዋናው ከሥር ጀምሮ በልጆቹ ላይ ምንም የተደከመ ነገር የለም። ሰው የሚያጭደው የደከመበትን ሳይኾን የዘራውን ብቻ ነው። ምንም የዘራነው ነገር የለም። 

ልጆቹ በሚነጋገሩበት እንግሊዝኛ ቋሚ አገልግሎት የሚሰጥ ቤተ ክርስቲያን አላውቅም። ምናልባት አንድ ሁለት ይኖራል። ራሱን የቻለ ግን አንድ የቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን በሜሪላንድ አለ። ይኽም በልጆቹ ትልቅ ትግል የተመሠረተ እንጂ ቤተ ክርስቲያን (ሀገረ ስብከቱ ወይም አጥቢያዎች) አስባ አቅዳ ካህናት ምእመናን አስበው ያደረጉት አይደለም። 

እኔ እንኳ ለማገልገል በሞከርኩባቸው ቦታዎች ቋሚ የእንግሊዝኛ ቅዳሴ ይኑረን ልጆቹን ማብቃት ላይ እንትጋ በሚል ለማድረግ ብሞክር ጆሮ የሚሰጥ የለም። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትልቅ ቁም ነገር ወሬ ነው። እነ እገሌ ይኽንን አሉ፣ በዚኽ ወጣ በዚኽ ገባ ነው። ጃኛ የሌለበት ፍርድ ቤት ነው። 

ሦስተኛው የሕንጻው ዓላማ ምንድነው? መገዛቱን ተገዛ ግቡ ምንድነው? ይኽ በግልጽ መታወቅ አለበት። ገና ሲጀመር ምክንያት የሚሰጠው “ልጆቻችንን እናስተምራለን፣ ትምህርት ቤት እንከፍታለን” ነው። እኔ በቅርበት በተከታተልኩት መረጃ መሠረት ይኽ ፈጽሞ ነጭ ሐሰት ነው። በርከት ያሉ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል። 

የምንፈልገው የዓይናችን ማረፊያ ነው። ውስጡ ደስ የሚል፣ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ትልቁ ነው፣ አቤት ማማሩ፣ የኢትዮጵያን ሕንጻ ይመስላል ከሚል አያልፍም። ጠቅለል ሲደረግ የሞራል መጠበቂያ ነው። 

ከጥቂት ዓመታት በፊት ዳላስ አካባቢ ይመስለኛል በጣም ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ሲመረቅ ይኽንን ያክል መማሪያ ማደሪያ ክፍል ያለው ሕንጻ ተገነባ “ቅዱስ ያሬድ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተባለ” ተብሎ አዋራ አጨሱ። እንኳን ኮሌጅ ሰንበት ትምህርት ቤት የለውም። ለምን ብሎ መጠይቅ አልቻልንም። ስሜት እንጂ አቅዶ አርቆ ማስተዋል አልቻልንም። 

ታላላቅ የሚያማምሩ ሕንጻ የያዙ ዛሬም ክስ ያልተቋረጠባቸው አብያተ ክርስቲያናት አሉን። አንዳንድ ባገለገልኩባቸው አብያተ ክርስቲያናት እጅግ በሚያስደነግጥ መልኩ ሕጻናትና አዋቂ ወይም አረጋዊ ብቻ የሞላበት አይቻለሁ። “ወጣቶቹ የት ሄዱ” ብያቸዋለሁ። መልሱን አያውቁም አልያ መጠየቅም አይፈልጉም። መጀመሪያም ምእመናኑ የጽድቅ ስሜት እንጂ ክርስትና መች ገባቸውና። እንኳን ለልጅ የሚተርፍ ለራስ የሚኾን ስንቅ የለም። 

ምእመናን ከመንፈሳዊነት መቀዝቀዝ የተነሣ ትዳር በፍቺ የሚጠናቀቅበት በጣም ብዙ ነው። እንደ ቀላል ነገር ነው “ፈታሁት፣ ተገላገልኩ” የሚሉት። ቤት ገዝተው ቤተሰብ የሚበትኑ ሰዎች ምንኛ ምስኪን ናቸው። ሰይጣን ደግሞ “ፈት ናችሁ” አይላቸውም። single mom ነኝ ይላሉ። ራስን መደለል ነው። ስለ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ወገባቸውን አስረው ይደክማሉ። ይኽ ነው ቅድሚያ መታነጽ ያለበት።  ትዳር ፈቶ ቤተክርስቲያን ለማነጽ መድከም። ቤተሰብ የበተነ ቤተክርስቲያንም እረፍት የሚነሳ ነው የሚኾነው። ቄሶቹም ስለዚኽ አጀንዳ ትንፍሽ አይሉም። አንድ ቀን መድረክ ላይ “ትዳሩን የፈታ ሰውና የከሰረ ነጋዴ፣ ሰነፍ ተማሪ አታማክሩ። ውድቀታቸውን ነው የሚያጋቡባችሁ” ስል ቄሱ መኖሪያ ልታሳጣኝ ነው እንዴ" ብሎ አሳቀኝ። 

አሜሪካ በክስ የሚያልቅ ገንዘብና ጊዜ ብሎም የሚላሽቅ ክርስትናን እንኳ መፍትሔ የሚሰጥ የለም። ሁሉም እሳቱ እስኪመጣ ድረስ በሌላው ይስቃል። 

ሌላው ግላዊነት ነው። ኦርቶዶክሳዊነት ኅብረታዊነት ነው። አሜሪካ ከገባሁ ጀምሮ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ቅርጽ ማየት ማግኘት አልቻልኩም። ውስጤ እንደተፈተነ ነው። አንድ ቀን ለአንድ ሰበካ ጉባዔ ሊቀ መንበር አዲስ ሕንጻ ተገዝቶ ሲዘጋጅ ኹሉም በደስታ እየቦረቀ ለሥራ ይረባረባል። ቆመን ስለ ኦርቶዶክስ ኅብረታዊነት ማውራት ጀመርኩ። በተመስጦ ይሰማኝ ጀመር። መጨረሻ ላይ “ይኽ የምትለኝ የት ይገኛል እንዴት እናግኘው” አለኝ። በጣም አበሳጨኝ “Amazon  ኦላይን ላይ” ብዬው ንግግራችንን ዘጋነው። የሚገዛ እቃ እንጂ የምንወደው አካላችንን አስጨንቀን የምናስገዛው መስዋእትነት አንፈልግም። የቤተ ክርስቲያን ኅብረታዊነት በክህነት ማዕከላዊነት የሚመጣ ነው። ሰውየው ስነግረው እቃ ነው የመሰለው። 

ሌላው ግላዊነቱ “የእኛ ቤተ ክርስቲያን” በሚል የሚገለጸው የዳበረ ግለኝነት ነው። ለምእመኑም ለካህኑም “የእኛ ቤተ ክርስቲያን” የሚለው የራሱን አጥቢያ ማለት ነው። የሌላው ቤተ ክርስቲያን የሌላ ነው። አይመለከተውም። ሰይጣን እንዴት ያለ መርዝ እንደ ዘራብን አላውቅም። 

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 15:57


ትራምፕ ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኘውን Northon Dome ዳግም መከፈት ፕሮግራም ላይ ተገኝቶ ሕንጻ ቤተክርስቲያን መርቋል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 15:48


ከብዙ በጥቂቱ በጾመ ነቢያት ስለ ነቢያቱ ማንነት በጥቂቱ ያነሣነውን ይመስላል። እግዚአብሔር ቢፈቅድ በሚቀጥለው ትምህርታቸውና ነገረ ሥጋዌን እናያለን። በረከታቸው አይለየን። አጫጭር በመኾኑ አንብቡት።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 15:47


 ነቢዩ ሚልክያስ

ሚልክስ አንደሐጌና ዘካርያስ ከምርኮ መልስ የነበረ ነቢይ ነው። የሚልክያስ መጽሐፍ 4 ምዕራፍ ሲሆን በውስጡ ግን 23 አርዕስት ተመዝግቦበታል፡፡ ሲጀምርም በዔሳው ጥፋት በያዕቆብ ዘር በረከት ይጀምራል። “በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው።2  ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ” ሚል. 1፣ 1-6፡፡

ሁለተኛ ደረጃ በካህናት ኃጢአት በተበላሸ መስዋዕት ምክንያት እንደገና ኢየሩሳሌም እንደምትወድም መርዶ አዘል ትንበኒት ይናገራል። ሚል. 1፥6-14 ም. 2፣1-9

በሦስተኛ ደረጃም እስሩና ሁለቱን ነገድ ስለ ኃጢአት ሲወቅስ ወንድም ወንድሙን ባል ሚስቱን ሚስት ባሏን አታታል መፋታትን እግዚአብሔር እንደሚጠላ በምሳሌ አስቀምጧል ሚል.2፣10-17

በአራተኛ ደረጃም  እግዚአብሔር በኋላ ዘመን ሰው በሚሆንበት ወራት የሰው ልብ ከኃጢአት የሚያጸዳ ለእግዚአብሔር ቃል በማደሪያነት የሚያሰናዳ የሚያቀና ተስፋ የቆረጡትን በሕይወት አዘል ትምህርቱ የሚያጸናና መልክተኛው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን እንደሚልክ ስሙን ኤልያስ ብሎ ይደመድማል ሚል. 3፥1-18 ም.4:1-6

እንደ ኢሳይያስና ዘካርያስ መጽሐፍ የሚልክያስ መጽሐፍ የብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን ነው። ሚልክያስ ቅድመ ልደተ ክርቶስ በ430 ዓመተ አለም እንደነበረና በዚህ በመከረኛው አለም ሲንገላታ ኖሮ ጥር 8 ቀን አርፏል ይለናል ዜና አበው፡፡ ሚልክያስ ነቢየ አሕዛብ ወሕዛብ ነው፡፡
@አበው ነቢያት ቀደምት ወደኀርት

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 15:42


ነቢዩ  ሚልክያስ

ሚልክያስ ማለት “መልእክተኛዬ” ወይም “የእኔ መልአክ” እንደማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሊቃውንት ሚልክያስ የነቢዩ ስም እንዳልሆነ ይገልጻሉ፡፡ 

እንደነዚህ ሊቃውንት አገላለጽ ሚልክያስ በመጽሐፉ ውስጥ የተገለጸውና ወደፊት ይመጣል የተባለው መልእክተኛ ነው እንጂ በእንደዚህ ዓይነት ስም ማለትም “የእኔ መልአክ" በማለት አንድ አይሁዳዊ ቤተሰብ ልጁን ይሰይማል ብሎ ማመን ያስቸግራል። “
እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡” ሚል 3፡1

እነዚህ ሊቃውንት በወቅቱ ከነበረው የአይሁዳውያን ባህል፣ ሃይማኖትና የአኗኗር ሁኔታ መነሻ በማድረግ ወደዚህ መደምደሚያ ይድረሱ እንጂ የነቢዩ ስም ማን ሊሆን እንደሚችል ምንም ዓይነት አስተያየት አይሰጡም፡፡ መጽሐፉ ስለ ሚልክያስ የግልም ሆነ ቤተሰባዊ ሕይወቱ ወይም ከየትኛው ወገንና ከየትኛው ቤተሰብ እንደሆነ ምንም ዓይነት መረጃ ስለማይሰጥ ይህ ነው ብሎ በተጨባጭ ሁኔታ ስለ ሕይወቱ መናገር ያዳግታል፡፡

 ሚልክያስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ምዕተ ዓመት 620-515 ዓ.ዓ. ኢየሩሳሌም ውስጥ እንደኖረና የነቢይነት ተግባሩን እንዳከናወነ ከመጽሐፉ እንረዳለን፡፡ 

በዚህ ወቅት የቤተ መቅደሱ ዳግመኛ ግንባታ ተጠናቆ የነበረ ሲሆን ካህናቶች አገልግሎታቸው ማከናወን የጀመሩበት ሕዝቡም ኑሮውን በተረጋጋና በተደራጀ ሁኔታ ይኖር የነበረበት ወቅት ነው። “
በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡” ሚል 1፡10፤3፡1 

ነገር ግን ካህናቶችም ሆኑ በወቅቱ የነበረው ሕዝብ ፍቅሩ የቀዘቀዘ ፣ የአምልኮ ሕይወቱም የተዳከመና የተሰላች፣ በማኅበራዊ ሕይወትም ግዴለሽነት የበዛበት ወቅት ነበር፡፡ 

በተጨማሪም በወቅቱ ከሕዝቡ መካከል ባዕዳን ሴቶች እያገቡ ኑሮአቸውን በዘፈቀደ የሚመሩ አይሁዳውን እንደነበሩ ከመልእክቱ እንረዳለን፡፡ ነቢዩ ሚልክያስም ይህንን መነሻ በማድረግ ሕዝቡ ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ሆነው እንዲኖሩ የነቢይነት መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡ በመልእክቱም ሕዝቡ እግዚአብሔርን በታማኝነት ስላላመለኩ፣ የጋብቻ ቃል ኪዳናቸውን ስለጣሱና ከባዕዳን ሴቶች ጋር ስለተጋቡ እንዲሁም ፍትሕን ስላጐደሉ ይህንን መረን የወጣና የተበላሸ አካሄዳቸውን ትተው ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ማደስ እንዳለባቸው ነቢዩ ይናገራቸዋል፡፡

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 15:33


ነቢዩ ዘካርያስ

ዘካርያስ የሚለው ስም “ዛካር”ማስታወስ፣ መዘከር እና “ያህ” ከእግዚአብሔር መጠሪያ ስሞች አንዱ የሚሉትን የሁለት ቃላቶች ጥምር ሲሆን ትርጓሜውም “እግዚአብሔር አስታወሰ” ወይም “እግዚአብሔር አሰበ ማለት ነው፡፡ 

ምንአልባት ዘካርያስ የባቢሎን የስደት ኑሮ መጨረሻ አካባቢ 539 ዓ. ዓ. ተወልዶ ወላጆቹ በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር እኛን ሕዝቦቹ ከስደትና ከጉስቁልና ኑሮአችን ነፃ ሊያወጣን አሰበን፤ እኛን ሕዝቦቹ አስታወሰን ከሚለው ጋር በተያያዘ መልኩ የተሰየመ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡ 

ዘካርያስ የዒዶ ልጅ መሆኑን ቢገለጽም በሌላ መልኩ ደግሞ የቤሬክያ ልጅ እንደሆነም ተነግሯል። ዘካ 1፡1 ስለዚህ ወላጅ አባቱ ዒዶ ወይም ቤሬክያ መሆኑን በትክክል ባይታወቅም እንደነ ቅዱስ ጀሮም ያሉ ሊቃውንቶች ግን ቤሬክያ የዘካርያስ ወላጅ አባቱ ዒዶ ግን መንፈሳዊ አባቱ ሊሆን እንደሚችል መላ ይመታሉ፡፡ 

ሌሎች ሊቃውንቶች ደግሞ የመጽሐፉ የመጀመርያው ክፍል ዘካ 1-8 በዒዶ ልጅ ዘካርያስ የተጻፈ ሲሆን ሁለተኛው ክፍል ዘካ8-14 ደግሞ በቤሬክያ ልጅ ዘካርያስ የተጻፈ ነው፤ በኋላ ግን መጽሐፉ ወደ አንድ ጥንቅር ወይም በአንድ መልክ በተዋቀረ ጊዜ ዒዶና ቤሬክያ እንደ አባት በአንድነት ተጠቅሰዋል በማለት መላ ምታቸውን ያቀርባሉ፡፡ 

ነቢዩ ዘካርያስ የኖረውና የነቢይነት ተግባሩን የተወጣው ነቢዩ ሐጌ በኖረበትና የነቢይነት ተግባሩን ባከናወነበት ተመሳሳይ ወቅት ነው፡፡ 

ዘካርያስ ለነቢይነት አገልግሎት እንዴት እንደተጠራ፣ የቤተሰባዊ ኑሮው ምን እንደሚመስል፣ የት እንደኖረና የነቢይነት አገልግሎቱ የት እንደተወጣ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ 

ነገር ግን በመጽሐፉ ስለ ኢየሩሳሌምና ቤተ መቅደስዋ እንዲሁም በውስጥዋም ስለሚኖሩ እቃዎች፣ ስለ ሕገ እግዚአብሔር፣ ስለ ይሁዳ ሕዝቦች፣ በቤተ መቅደስ ስለሚያገለግሉት ሊቀ ካህናቶችና የአገልግሎት ልብሶቻቸው ብዙ ትኩረት ሰጥቶ ስለሚናገር የነቢይነት ተግባሩን የተወጣው በኢየሩሳሌም አካባቢ እንደሆነና እሱም ከወገነ ክህነት በኩል ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡ 

በእርግጥ ዘካርያስ ኢየሩሳሌምንና አካባቢዋ በደንብ እንደሚያውቀው ከመጽሐፉ በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ እንደ መጽሐፈ ነህምያ አገላለጽ ደግሞ ዘካርያስ ከይሁዳ ዘርና ከሌዋውያን ወገን እንደነበረ እንረዳለን። ነህ 11


ዘካርያስ እስራኤል ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ በኋላ ከነቢዩ ሐጌ ጋር የነበረ ነቢይ ነው ዕዝ .5፣1-5።  የዘካርያስ መጽሐፍ ተመዝግበውበታል ወይም አርዕስት አሥር ራዕያት የነቢያት መጽሐፍ ተመሳሳይነት ቢኖረውም የዘካርያስ መጽሐፍ በሚስበራዊ ርቀቱ ከሕዝቅኤልና ዳንኤል መጽሐፍ እንዲሁም የሐዲስ ኪዳን የትንቢት መጽሐፍ ከሆነው ከራዕየ ዮሐንስ ይጎራበታል።

ዘካርያስ ያያቸው አስደናቂ ራዕያት የሚከተሉት ናቸው:-

1. መጋላና ሐመር አንበላይ ፈረሶች ም 1፣ 8-17 እነዚህም የኢየሩሳሌምን ምሕረታዊ ተስፋ ሰላምና ፀጥታ ጥጋብና ደስታን ያመለክታሉ።

2. አራት ቀንዶች ም.1፥18-21 እነዚም በቀንድ የተመሰሉ ኢየሩሳሌምን የደመሰሱ ንብረቷን የወረሱ ኅብረተሰቧን ያፈለሱ ኃያላን የአሕዛብ ነገዞታት እንደነበሩ መልአክ ተርጉሞለታል፡፡

3. አራት ጠራቢዎች ም2፣ 1 እነዚህም መላእክት ናቸው በቀንድ የተመሰሉ ኢየሩኄምን ያጠፋ የአሕዛብን ነገሥታት ያጠፋ አራቱ ሊቃነ መላıክት መሆናቸው ተተርጉሟል::

4. የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰው ይህ በሰው የተመሰለው መላዕ ነው ይኸውም የኢየሩሳሌምን ልማት የእግዚአብሔርን ረድኤት ያመለክታል። ምዕ..2፣1-5

5. የኢያሱ ወይም የዮሴዕ በሰይጣን መከሰስ። እንደዚሁም ሰይጣኑን በሚያደርገው ተንኮል በመልአከ ምህረት መወቀስ። ምዕ.3፣1-10

6. ባለሰባት መቅረዝ የወርቅ ማብሪያ ከሁለት የወይራ ዛፎች ጋር ሰባቱ መቅረዞች በዘሩባቤል የተሰራውን የቤተመቅደስ ፍጹም ክብር ሲያጠይቅ። ም.4፥1-14

 ሐጌ 2 ፣1-10 በሁለት የወይራ ዛፎች የተመሰሉት ንጉሡ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህናቱ የሴዕ ናቸው ሐጌ 6፥1-10

2. በራሪ የመጽሐፍ ጥቅል ርዝመቱ ሃያ ክንድ ወርዱም አስር ክንድ ምዕ5፣1-5 የዚህንም የመጽሐፍ ትርጓሜ መልአኩ እንደነገረው በሌቦችና በሀሰተኞች ላይ እግዚአብሔር መርገም አዘል ከባድ መዓት እንደሚያመጣባቸው በከፋ መቅሰፍት እንደቀጣቸው እንደ እርዝማኔው የመከራቸውን ብዛት ያስቃያቸውን ጽንአት ይገልጻል።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 15:14


 ነቢዩ ሐጌ

ሐጌ አሥሩና ሁለቱ ነገድ ከዝርወት ተሰባስበው ከምርኮ ተመልሰው ዘሩባቤልን አንግሠው በተስፋ ምድር በእግዚአብሔር ሀገር በኢየሩሳሌም ባልተረጋጋ ሰላም በነበሩበት ዘመን የተነሳ ነቢይ ለመሆኑ ከታሪካዊና ትንቢታዊ መጽሐፉ ለመረዳት አያዳግትም ዕዝ.5፣1-5።

እስራኤል ሕገ ኦሪትን በሕገ ጣኦት ለውጠው በሠሩት ኃጢአት ተማርከው ክብራቸውን ተገፈው በአረማውያን ሀገር በባርነት ቀንበር ሲማቅቁ በነበሩበት ጊዜ ፈጣሪያቸውን ከዚህ ከባርነት ቀንበር ካወጣኸን ላገራችንም ካበቃኸን ለስምህ መጠሪያ ቤተመቅደስ ሳንሠራ ኑሮ አንጀምርም ብለው ተስለው ነበር።

ነገር ግን ታሞ የተነሳ ፈጣሪውን ረሳ እንዲሉ እግዚአብሔር ስዕለታቸውን ስምቶ ግፋቸውን ተመልክቶ ከምርኮ ቢመልሳቸው ለሀገራቸው ቢያበቃቸው የገቡትን ውል ቤተመቅደስን ሳይሰሩ የራሳቸውን ቤት ሲሰሩ እግዚአብሔር ተመልክቶ በሐጌ አድሮ “የኔ ቤት ፈርሶ እናንተ በአማረ ቤት ብትኖሩ ሰላም የላችሁም ትበላላችሁ አትጠግቡም ትጠጣላችሁ አትረኩም ትለብሳላችሁ አይሞቃችሁም ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር  ከመስጠት ምድርም የዘራችሁባተን ከማብቀል የተከላችሁባትንም ከማጽደቅ ትከለከላለች፡፡” በአጠቃላይ በንብረታችሁ ላይ ልማትን ሳይሆን ጥፋትን ትርፍን ሳይሆን ኪሳራን አመጣለሁ። ገንዘቡን በቀዳዳ ከረጢት እንዳስቀመጠ ሰው ገንዘባችሁ እንደዚያ ይሆናል እያለ በመጀመሪያ ያስጠነቅቃል። ሐጌ 1 ፣1-12።

እስራኤልም ይህን እግዚአብሔር በሐጌ የነገራቸውን ቃል ተቀብለው እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን ትንሽ ትልቅ ሳይሉ በሕብረት በፈጣሪያቸው ረድኤት የታዘዙትን ሠሩ። ሐጌ.  1 ፣12-15።

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔርም በማንኛውም ነገር በረድኤት አንደማይለያቸው የሚያስፈልጋቸውን ለማግኘት ቢያመለክቱ እንደሚሰጣቸው ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል ይላል። 

በሦስተኛ ደረጃ በርዕስነት ያሰፈረው ገናናው የአሕዛብ መንግስት እንደሚፈረካከስ በየጊዜው የተዘረፈው ወርቅና ብር ንዋየ ቅድሳት እንደሚመለስ ከቀድሞው ቤተመቅደስ በሁሉ ነገር እንደሚበልጥ በወርቅና በብር እንደሚያጌጥ ያዘኑት መጽናኛ የሰላም መገኛ እንደሚሆን ብሥራት መዝግቧል ሐጌ . 2፥5-9

በአራተኛ ደረጃ ቤተመቅደስን ሳይሠሩ የነበረውንና ከተሠራ በኋላ ያለውን በረከት ማለት የአዝመራውን ምርት የስንዴውን ዛላ የወይኑን ዘለላ ምን ያህል ለውጥ እንዳሳየ የትርፋቸው ብዛት የጎተራቸውን ሙላት በረከስ ዕቃና ባልረከሰ ዕቃ መካከል ያለውን ልዩነት እየመለሰ ያነጻጽራል ሐጌ. 2፣10-19::

በአምስተኛ ደረጃም ሲያጠቃልል በአሕዛብ መንግሥታት ውድቀት በዘሩባቤል ድኅነት ይደመድማል። ሐጌ. 2፣ 20-23:: 

ይህ የሐጌ መጽሐፍ ዋናው መልክቱ የሰውን ከንቱ ሀሳብ ምን እንደሚመስል ማስረዳት ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ ሰራተኞች በከንቱ ይደክማሉ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል ይላል መዝ. 126 + 1-2 ፣ 


ሐጌ ከፈጣሪው ጋር ለብዙ ጊዜ የተነጋገረ ነቢይ ለመሆኑ መጽሐፉ ምስክር ነው በዚህም ስለሐጌ ማንነት መረዳት ይቻላል ሐጌ ነቢየ አሕዛብ ወሕዝብ ነው። ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ536 ዓመተ አለም እንደነበረና በዚህ በመከረኛው ዓለም ሲንገላታ ኖሮ ታህሳስ 20 አርፏል ይለናል ዜና አበው።
@አበው ነቢያት ቀደምት ወደኀርት

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 15:00


ነቢዩ ሐጌ

ሐጌ የሚለው ቃል “ሐግ” ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም “ክብረ በዓል" ማለት ነው፡፡ ሐጌ ምንአልባት በአንድ የአይሁድ ክብረ በዓል ወቅት በመወለዱ ምክንያት ወላጆቹ ሐጌ ብለው ሰይመውት ሊሆን ይችላል፡፡ 

ከትንቢተ ሐጌ ውጭ ሐጌ የሚለው ስም በብሉይ ኪዳን ውስጥ በሁለት ቦታዎች ተጠቅሶ ይገኛል (ዕዝ 5፡1፤ 6፡14)፡፡ 
መጽሐፉ ውስጥ ስሙ ከመጠቀሱ ውጪ ስለ ራሱም ሆነ ስለ ቤተሰባዊ ሕይወቱ ምንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ ስለሌለ ማንነቱ በደንብ ለመረዳት ያስቸግራል፡፡ 

የመልእክቱ ይዘት በማየት አንዳንድ ሊቃውንት ሐጌ ካህን ሊሆን እንሚችል መላ ቢመቱም የራሳቸው ጥናት ያደረጉ ሌሎች ሊቃውንት ግን ይህንን መላምት በመቃወም ሐጌ ከካህናት ወገን እንዳልነበር የተለያዩ ማረጋገጫዎች ያቀርባሉ።
እንዲያውም ሐጌ አገር ወዳድ፣ ፖለቲከኛና የሕዝብ እንቅስቃሴ መሪ እንደነበር ያረጋግጣሉ፡፡ የዚህም ዋና ምክንያታቸው ሐጌ ኢየሩሳሌም እንድትገነባ ቤተ መቅደስዋም እንድትታነጽ ሕዝቡን በተለያየ መልኩ እያስፈራራ ብዙ ቅስቀሳ አድርጓል፤ ይህ ደግሞ በወቅቱ ኢየሩሳሌም የሃይማኖታዊና የፖለቲካዊ አስተዳደር ዋና ማዕከል እንድትሆን የወቅቱ መሪዎች በተለይም የፖለቲካ ሰዎች ጽኑ ምኞት ስለነበር ነው፡፡ 

ነቢዩ ሐጌ የኖረውና የትንቢት ቃሉን ያስተላለፈው በ520 ዓ.ዓ በኢየሩሳሌም ውስጥ ለነበሩት አይሁዶች ነው፡፡ በዚህ ወቅት አይሁዳውያን ከባቢሎን የስደት ሕይወት ተመልሰው ኑሮአቸውን በመመሥረትና በማጠናከር ሂደት ላይ ነበሩ፡፡ 

በእርግጥ በ539 ዓ.ዓ የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ ባቢሎናውያንን በማሸነፍ ምርኮኞች ሆነው በስደት ይኖሩ የነበሩትን ወደ አገራቸው ወደ ይሁዳ እንዲሁም ወደ ዋና ከተማቸው ወደነበረችው ኢየሩሳሌም መመለስ ለሚፈልጉ አይሁዳውያን ፈቃድ ሰጥቶ ነበር፡፡ 

ከስደት ተመላሾቹ ምንም እንኳ በደንብ ያልተደራጁና ብዙም ሀብት ባይኖራቸውም በባቢሎናውያን ፈርሶ የነበረውን ቤተ መቅደስ ዳግመኛ መገንባትና ማነጽ ጀምረው ነበር፡፡ ነገር ግን ሳምራውያኖች በብርቱ ስለተቃወምዋቸው  እነርሱም በሞራልና በገንዘብ የአቅም ደረጃ በደንብ ካለመጠናከራቸው የተነሣ ተቃዋሚዎቻቸውን የመቋቋም ኃይል ስላልነበራቸው ሥራውን ለማቋረጥ ተገደዱ፤ ወደ ፍጻሜም ሳያደርሱት ለ16 ዓመታት ያህል የግንባታ ሥራው በእንጥልጥል ተቋርጦ ቀረ። ዕዝ 3-4፡

በ520 ዓ.ዓ ንጉሥ ዳርዮስ ቀዳማዊ የፋርስ ንጉሥ የነበረውን የቂሮስ ልጅ ካምቢስስ ተክቶ ሥልጣኑን በደንብ ካጠናከረ በኋላ ሌሎች በዛ ያሉ አይሁዳውያን በንጉሥ ዘሩባቤል እየተመሩ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡ 

ይህ ቡድን ከበፊተኞች ይልቅ የተጠናከረ፣ ቤተ መቅደስም ለመገንባት መንፈሱ ከበፊተኞቹ ይልቅ የበረታና በመሪዎችና በሊቀ ካህናትም ጭምር የተመራ ስለነበር ወደ ግንባታው ተግባር ለመግባት ወሰኑ፡፡ 

በእርግጥ እነዚህ አይሁዳውያን የነቢዩ ኤርምያስን ምክር በመከተል በባቢሎን ውስጥ በነበራቸው ሕይወት የተደራጁ ፣ ንብረት ያፈሩና የባቢሎናውያንን የአኗኗር ዘይቤ ተቀብለው ትዳር መስርተው ይኖሩ የነበሩ ናቸው።ኤር 29፡5-6

 ንጉሥ ቂሮስ በ439 ዓ.ዓ አይሁዳውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ፈቃድ ቢሰጣቸውም እነዚህ ሁለተኞቹ ቡድኖች ከነበራቸው ሀብትና ንብረት እንዲሁም ከመሠረቱት የተደራጀ ቤተሰባዊ ሕይወት አኳያ ወደ ይሁዳ ለመመለስ አልተጣደፉም ነበር፡፡ በኋላ ግን ወደ ዋና መዲና ወደ ነበረችው ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ ይጀምራሉ።

 በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር የትንቢት ቃል ወደ ነቢዩ ሐጌ መጣ፤ እሱም የነቢይነት መልእክቱን ከዚህ ከግንባታው ሥራ ጋር በተያያዘ መልኩ ማከናወን ጀመረ። በእርግጥ ነቢዩ ሐጌ ከዚህ ከቤተ መቅደስ የዳግም ግንባታ ሥራ መቋረጥ ጋር በተያያዘ መልኩ የነቢይነት ተግባሩን እንደጀመረ ከመጽሐፉና ከሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች እንረዳለን ዕዝ. 5:11 6:14

@ነቢይ ማነው

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Jan, 01:18


ሕንጻ በሕንጣ ላይ!! እመጣበታለኹ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

02 Jan, 16:50


"ንቃት ወይም መንቃት የሚገኘው ከፍርሃትህ በላይ ነው። ፍርሃትን ሳትሻገር ንቃት አይገኝም"

ንዋይ ክሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 20:58


"ቤተ ክህነቱን ከጳጳሳት ቅኝ ገዥነትና ከማኅበረ ቅዱሳን አዳካሚነት ማላቀቅ ካልተቻለ ለውጥ አንጠብቅም"

እኔው ንዋይ ነኝ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 20:48


ነቢዩ  ናሆም

ናሆም ማለት “መጽናናት” ማለት ነው፡፡ ናሆም ከይሁዳ ከተሞች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ከሚገመተው ልዩ ስሙ ኤልቶሽ ከተባለ መንደር እንደሆነ ቢገለጽም ይህ መንደር የት እንደሚገኝ ትክክለኛ የሆነ ተጨባጭ መረጃ ስለሌለ ማወቅ አልተቻለም። “እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፤ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።”  ናሆ 1፡2 

መጽሐፉ ውስጥ ናሆም መቼ እንደኖረና የነቢይነት ተግባሩም መቼና በማን ዘመነ መንግሥት ጊዜ እንደተወጣ፣ ከየትኛው ወገን ወይም ቤተሰብ እንደሆነ፣ የራሱ ቤተሰባዊ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበርና መጽሐፉም መቼና የት ቦታ እንደተጻፈ ምንም ዓይነት ፍንጭ ከመጽሐፉ አናገኝም፡፡

 ቢሆንም መጽሐፉ ውስጥ በተካተቱት ጥቂት መረጃዎች መሠረት ነቢዩ ናሆም ይሁዳ ውስጥ በተለይም ኢየሩሳሌም አካባቢ እንደኖረና የነቢይነት ተግባሩም እዛው ኢየሩሳሌም አካባቢ እንደተወጣ ይታመናል። ናሆም ከዮናስ የቀረውን የነነዌን ታሪክ ይናገራል። “እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።” ናሆ 1፡15

በእርግጥ ናሆም ስለ ይሁዳ በጎነት ወይም ይሁዳን በመልካም አቀራረብ እየገለጸና መልካም ዜናን እያበሰረ ደጋግሞ ይናገራል፡፡ በተጨማሪም መጽሐፉ ውስጥ ዓመት በዓሎቻቸውንና ስእለቶቻቸውን ለእግዚአብሔር ማቅረባቸውን የሚያበረታታ ይንጸባረቅበታል፡፡ ስለዚህ ናሆም ምንአልባትም ቤተ መቅደስ አካባቢ የሚኖርና የነቢይነት ተግባሩንም እዛው ቤተ መቅደስ ውስጥ ይወጣ እንደነበር ይታመናል። “እግዚአብሔርም ከስምህ ማንም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይዘራ ስለ አንተ አዝዞአል፤ ከአምላኮችህ ቤት የተቀረጸውንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል አጠፋለሁ፤ አንተም የተጠቃህ ነህና መቃብርህን እምሳለሁ።” ናሆ. 1:14

ናሆም የአሦር ዋና ከተማ ስለነበረችው ስለነነዌ ውድቀት ሲናገር ከተማዋ እጅግ በጣም በልጽጋ እንደነበረች፣ ዙርያዋም በቅጽሮች የታጠረችና የጦር ሹማምንቶችዋም ገናና ስለነበሩበት ወቅት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ 

ይህ የነነዌ የብልጽግናና የኃያልነት ጊዜ የነበረው በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በመሆኑ ነቢዩ ናሆም በዚህ ወቅት በተለይም በ620 ቅልክ አካባቢ እንደኖረና የትንቢት ቃሉ እንዳስተላለፈ ይታመናል። “የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቶአል፤ ምሽግን ጠብቅ፥ መንገድንም ሰልል፤ ወገብህን አጽና፥ ኃይልህንም እጅግ አበርታ።  ዘራፊዎች ዘርፈዋቸዋልና፥ የወይናቸውንም አረግ አጥፍተዋልና እግዚአብሔር የያዕቆብን ክብር እንደ እስራኤል ክብር ይመልሳል።”  ናሆ 2፡1-12

በተጨማሪም ለግብጽ እንደ ዋና ከተማ ታገለግል ስለነበረችው ስለ ቴብስ ከተማ በ663 ዓ.ዓ በአሦራውያን እጅ ስለመውደቅዋ ስለሚጠቅስ የነቢይነት ተግባሩም ከዚህ ወቅት ብዙም ባልራቀ ጊዜ ውስጥ ሊወጣ እንደሚችል ይታመናል፡፡ 

በእርግጥ ከታሪክ እንደምንረዳው ነነዌ በ612 ዓ.ዓ ወድቃለች፤ ስለዚህ ናሆም የተናገረው ትንቢት ከዚያ በፊት ስለሆነ የኖረውም ከ660 እስከ 612 ዓ.ዓ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡ በሌላ በኩል ናሆም ስለ ይሁዳ መልካም ነገር ብቻ ትኩረት ሰጥቶ ስለሚናገር አንዳንድ ሊቃውንት ናሆምን እንደ ሐሰተኛ ነቢይ ወይም እንደ “አፍቃሪ አይሁድ” አድርገው ይቆጥሩታል፤ ምክንያቱም ብዙ ነቢያቶች ስለ ይሁዳና ስለ ይሁዳ ሕዝብ በጎ ነገሮች ቢናገሩም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ የይሁዳን ሕዝብ ከመተቸትና ከመውቀስ ተቆጥበው አያውቁም፡፡ 

ናሆም ግን የይሁዳን ሕዝብ በጎነት ከመናገር አልፎ የይሁዳን ሕዝብ ጠላቶች እንደ እግዚአብሔር ጠላቶች አድርጎ ካቀረባቸው በኋላ እግዚአብሔርም እንደሚበቀላቸው ይተነብያል።

በእርግጥ የአሦር መንግሥት ኃያል ሆኖ በኖረባቸው ዓመታት እጅግ በጣም ጨካኝ ጦረኛና ጎረቤቶቹንም ሰላም በመንሣት የታወቀ ነበር፡፡ የአሦር መንግሥት በደረሰበት ቦታ ከተማዎች ማቃጠል፣ ወንዶች ለባርነት ሥራ ማስገደድ፣ ሴቶችና ሕፃናት ላይ በደል መፈጸም እንዲሁም ሌሎች የጭካኔ ተግባራት በመፈጸመ የታወቀ ነበር፡፡ ለዚህም ነው ነቢዩ ናሆም ስለ አሦር ዋና ከተማ ስለነበረችው ነነዌ በመውቀስ የትንቢት ቃሉን የሚናገረው፡፡

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 17:21


ነቢዩ ዮናስ

ዮናስ ከታሪከ ነገሥት መረዳት እንደሚቻለው በካልዕ ኢዮርብአም ዘመነ መንግሥት በሰማርያ የነበረ የዋህ ነቢይ ነው 2ነገ. 14፣25

ዮናስ ነቢየ አሕዛብ ወሕዝብ እንደመሆኑ መጀመሪያ የስማርያውን ንጉሥ ኢዮርብአምን ጠቃሚ ምክር በመለገስ የእሥራኤልን ድንበር ከሔማት እስከ አረባ ባህር ድረስ እንዲይዝ አድ አድርጓል 2 ነገሥ. 14፣25-26::

እግዚአብሔር የነነዌን ሕብረተሰብ በሰሩት ኃጢአት በከባድ መዓት እንዳያጠፋቸው ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ባይመ መለሱ እንደሚያጠፋቸው ዮናስን ሂደህ ፈጣሪያችሁ በተወሰነ ሰዓት ሊያጠፋችሁ ተዘጋጅቷል ብለህ ከኃጢአታቸው እንዲመለ ምከር አስተምር ትንቢት ተናገር ባለው ጊዜ የዋሁ ዮናስ በኑሮ ሂደት የፈጣሪውን ቸርነት በመረዳት ጨክነህ ላታ ታጠፋቸው ምን ያደክመኛል በማለት እግዚአብሔር በዓለም ምሉዕ መሆኑን በባለማስተዋል ይመስላል ባፈጣሪው ፊት ለመኮብለል እግዚአብሔር ወደሌለበት ከእግዚአብሔ አብሔር ፊት ለመሰወር ወደሌላ ሀገር ለመጓዝ በየዋህነት ተሰልፏል ይላል አስደናቂ ታሪኩ ም. 1፣1-14::

ዮናስ ወደነነዌ ሄዶ ለማስተማር ትንቢት ለመናገር ፈቃደኛ ሆኖ ሳለ አልሄድም ያለበትን ምክንያት ሲገልጽ በሀገሬ ሳለሁ ፈርቼ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን አንተ ቸርና ይቅር ባይ ምህረትህም የበዛ ከክፉም ነገር የተነሳ የምትጸጸት አምላክ እንደሆንክ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደተርሴስ ልኮበልል ፈጥ ነበር በማለት ያብራራል ም. 4÷2-3 

የዋሁ ዮናስ የፈራው የእግዚአብሔርን መዓት ሳይሆን እነዚህ ከዚህ በላይ የተናገራቸው የእግዚአብሔር የስሙ ትርጓሜዎችን ነበር ዘፀ. 23+21: 

ዮናስ ወደነነዌ ለመላክ ፈቃደኛ ባይሆንም የእግዚአብሔር ዕቅድ አልቀረም። ተሳፍሮበት የነበረ ነበረውን መርከብ በማዕበል በማናወጥ ተሳፋሪዎችንም በማስደንገጥ ደንገጥ በዚህም ምክንያት ተሣፋሪዎች ከሰጥመት ለማምለጥ ዕጣ ተጣጥለው በዮናስ እንዲወጣበት ከመርከብ አውጥተው ወደባሕር እንዲጥሉት ከዚያም ባልታሰበ መንገድ በመርከብ ሳይሆን በአሣ ሆድ እንደሚሄድ ሳያስበው ግዑዙ ፍጥረት ዓሣው በፈጣሪው ትዕዛዝ ዮናስን በሆዱ ቋጥሮ የሦስት ቀን ጎዳና በባሕር ውስጥ በመገስገስ በዮናስ ላይም ምንም ኣደጋ ሳያደርስ በሰላም ሀገረ ነነዌ ሲደርስ በፈጣሪው ትዕዛዝ ከባሕሩ አሻግሮ ከየብስ አራግፎት ዮናስና ዓሣው ግዳጃቸውን እንደተወጡ የዮናስና መጽሐፍ በተኣምርነት መዝግቦ ያስነብበናል:: ም. 1፣4-16 

ዮናስ በዓሣ ሆድ ተጭኖ በሚጓዝበት ጊዜ በመርከብ ሳለ ተኝቶ እንደነበር የተኛ አይደለም በባሕሩ ውስጥ የታየውን እየመዘገበ በአንክሮ እየተገነዘበ ከፈጣሪው ጋር በጸሎት እየተነገረ ከሥነ ፍጥረት ጋር እየተከራከረ ጎዳናውን ፈጽሟል ም. 2፣1-11።

በዓሣ ሆድ ተጉዞ ያስተማረ ትንቢትም የተናገረ በቅዱስ መጽሐፍ የመጀመሪያ ነቢይ ነው ከዓሣ ሆድ ከ ከወጣ ወደነነዌ ከተማ ገብተህ አስተምር ባለው ጌዜ ዮናስ እንደቀድሞው ሳያንገራግር የታዘዘውን ተናግሯል።

የነነዌ ሰዎችም የሚድኑ ናቸውና የዮናስን አስደንጋጭ ትምህርት መዓታዊ ትንቢት ሳያቃሪ ያቃልሉ ይህ ነገር ሊሆን አይችልም ሳይሉ ከመሪ እስከ ተመሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው ፈጣ እንደ ፈጣን መልስ አንድ ልብ መ በመስጠት ምንም ከኃጢአቱ ባይኖሩበት መከራው ስለማይቀር ቀርላቸው ሕፃናቱን ከጡት ከብቶቹንም ከመሰማራት ለሦስት ቀናት ያለ ምግብ ዘግተው ማቅ ለብሰው በላያቸው አመድ ነስንሰው ነስንሰው በጾምና ጸሎት ሁሉም በእያሉበት ወደፈጣሪያቸው ጩኸዋል ፈጣሪያቸውም ጾማቸውንና ሰውነታቸውን እንደአዋረዱ ተመልክቶ ጩኸታቸውንም ሰምቶ መዓቱን ወደ ምሕረት ቁጣውን ትዕግስት በመለወጥ ይቅር ብሏቸዋል ም. 3÷1-10 


ዮናስ የተናገረው  ትንቢት  በሰዎች የተባበረ ጩኸት በእግዚአብሔር ምሕረት ባለመፈጸሙ ከሕይወት ሞት ይሻላል ከእኔ ውሰድ እያለ ይበሳጫል እግዚአብሔርም በውኑ ቆጣ ዘንድ ይገባሃልን ብሎታል።  ዮና.3፣1-4

ፈጣሪ ሲያስረዳው ፈ ለፍጥረቱ ምን ያህል እንደሚያዝንና እንደሚራራ ፈልጎ ለዮናስ አንድ ቅል አብቅሎ በልምላሜዋ ከፀሐይ ሙቀት በማዳን አስደስቶታል። እንደገናም  ያችን ቅል በትል አለበልቶ በማድረቅ አሳዝኖታል፡፡ ዮናስም በቅሏ መድረቅ ሲያዝን እግዚአብሔር ተመልክቶ ለምን ታዝናለህ ላልተከልሃትና ውሃ ላላጠጣሃት ሌሊት በቅላ ሌሊት ለደረቀች ቅል ቅል ስታዝን እኔ ለፍጥረቶቼ አላዝንምን ብሎታል። 


ቀደም ሲል በነቢዩ ዳዊት አድሮ ስለመሐሪነቱ ወሐሪነቱ ሲናገር አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ሔር ለሚፈሩት ይራራል። 

 
ከዮናስ መጽሐፍ የምንማረው ፍሬ ጉዳይ አንድ ነገር ነው ሌላውን ሳንዘነጋ ይኸም በዘመናችን በየትኛውም ክፍለ ዓለም ምንም እንደማይጠቅም እንደቀላል ነገር የሚታየው እውነተኛ ጾም ለአደጋ መከላከያ አማራጭ የሌለው ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠ መድኃኒት መሆኑን ነው::

ሌላው በዮ በዮናስ ታሪካዊ መጽሐፍ የሠፈረው በመጀመሪያውና በመጨረሻው ባለማወቅ የዋሁ ዮናስ እንደጓደኛ ከፈጣሪው ጋር ሲከራከር የእግዚአብሔርን ቸርነት ያስረዳናል፡፡ ዮናስ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ 850 ዓመተ ዓለም እንደነበረና በዚህ መከራ በማይለየው ዓለም ሲንገላታ ኖሮ መስከረም 25 ቀን አርፏል ይለናል ዜና አበው።

ስለ ክርስ ስቶስ ትንሳኤ በዓሣ ሆድ የነበረበት በምሳሌነት ተጠቅሷል ማቴ. 12÷39-41። ዮናስ በሕይወተ ሥጋ ሣለ ሰማርያና ነነዌን ብቻ ነበ ነበር ያስተማረ ከሞተ በኋላ ግን ዛሬ የሚያስተምረው ዓለም አቀፋዊ ነው:: ፈቃደኛ ከተገኘ፡፡
@አበው ነቢያት ቀደምት ወደኀርት

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 16:42


 ነቢዩ ዮናስ

ዮናስ ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ “ርግብ” የሚለውን ትርጓሜ ይገልጸዋል፡፡ ዮናስ ከዐሥራ ሁለቱ ታናናሽ ነቢያት አንዱ ሲሆን የኖረውም ከክርስቶስ ልደት በፊት በስምንተኛው ክፍለ ዘመን ከ786-746 አካባቢ እንደሆነ ከመጽሐፉ ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡ 

በእርግጥ ዮናስ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመን የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ዮናስም ኢዮርብአም ሶርያውያንን አባርሮ የእስራኤል ድንበር እንደሚመልስ ትንቢት ተናገረ፡፡

በዚህም ዮናስ ከቀደምት ወይም ከመጀመሪያዎቹ ነቢያቶች ከእነ አሞጽና ኢሳይያስ በተመሳሳይ ወቅት የኖረ ነቢይ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። “የጋትሔፌር በነበረው በአማቴ ልጅ በባሪያው በነቢዩ በዮናስ እጅ እንደ ተናገረው እንደ እስራኤል አምላክ እንደ እግዚአብሔር ቃል የእስራኤልን ድንበር ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።”2 ነገ 14፡25

ገና ከመጽሐፉ መግቢያ ዮናስ የአማቴ ልጅ መሆኑንና መኖርያውም በገሊላ በጋትሔፌር ከተማ እንደነበር ቢገለጽም ስለሌላው ቤተሰባዊ ሕይወቱ ግን ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። “የእግዚአብሔርም ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ” ዮና 1፡1

ዮናስ የነቢይነት ተግባሩን የሚጀምረው እስራኤል ውስጥ ሲሆን የሚያጠናቅቀው ግን አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሕዝብ ይኖሩባት የነበረው ነነዌ ከተማ ውስጥ ነው፡፡

ነነዌ  በጤግሮስ ወንዝ ዳር በናምሩድ የተመሠረተች ጥንታዊት ከተማ ስትሆን ለአሦር ደግሞ እንደ መናገሻ፣ ሰፊና ውብ የነበረች ከተማ ናት። “አሦርም ከዚያች አገር ወጣ፤ ነነዌን፥ የረሆቦትን ከተማ፥ ካለህን፥ በነነዌና በካለህ መካከልም ሬሴንን ሠራ፤ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት።” ዘፍ 10፡11-12

ለብዙ ዘመናት የአሦር ንጉሠ ነገሥት የእስራኤል ተቀናቃኝ ጠላት ሆኖ የኖረ መንግሥት ነው፡፡ የከተማው ቅጽር ርዝመት ዐሥራ ሁለት ኪ.ሜ እንደነበርና በውስጥዋም ብዙ ሕንጻዎች ተሠርተውባት ነበር “እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው” ዮና 4፡11

የባቢሎን መንግሥት ከክርስቶስ ልደት በፊት በ612 ከተማዋን ይዞ አፈረሰው፡፡

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 16:28


እግዚአብሔር ንግግር የጀመረበት ቃል
"እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ" የሚለው ነው። ዘፍ.1:3

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 13:52


የጥንቶቹ ብፁዓን እንዲኽ ነበሩ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 13:44


  አርዶ የሚበላው እረኛ 

እረኛ ምንደኛ ሲኾን ለበጉ እንደማይራራ መጽሐፉ ነግሮናል። ምክንያት የሱ አይደሉምና። እሱም ቅጥረኛ ነው። ግድ ይለውም ይለናል። 

የ አርባ (40) ዓመት የሕወሃት ፓለቲካ የትግራይን ሕዝብ ሃይማኖትም ሃገርም አሳጣው። ከአንድ ቤተሰብ የኤርትራ ሕዝብ ከጣልያንና በአሜሪካ በእንግሊዝ ተንኮል ቃየንና አቤል አደረጉት። ሁለት ሕዝብ አስመስለው ሰበኩትና አለያዩት። 

ኢትዮጵያን ከመሠረቱ የመራ ያቀና ሕዝብ ተጨቁነሃል ተበድለሃል ብለው ሰበኩትና ነጻ አውጪ ኾኑበት። ከማን ነው ነጻ የምወጣው ብሎ አልጠየቀም ነጻ አወጣንህ ብለው መንግሥት ኾኑ ሁለት ጦርነት ፈጠሩለት። ሀገር ትሆናለህ ብለው “ትግራይ ትስእር” አሉት። ሚሊየኑን አስፈጁት። እጅ እግር የሌለው ወጣት ጧሪ ቀባሪ የሌለው አረጋውያንን አሳቀፉት። 
ዛሬ መሪዎቹ ገዳያቸውን ፈጣሪ አድርገው ደጅ በመጥናት መሥዋዕት ለማቅረብ ደጅ ይጠናሉ። 

በዘር የመነኮሱት ብልጣ ብልጦቹ ደግሞ “ጳጳስንልህ” አሉት። ጳጳሱም ክህነት የለው፣ መንግሥቱም ጉልበት የለው። ሁለት ጨካኝ እረኛ እጅ ወደቀ። ምንደኛ እረኛ ቢሸጠው ለገንዘብ የገዛው ባለቤት  ቢያርደው ሊበላው ነው። ሁለቱም ለበጉ ጠላት ናቸው። በጉ ከሞት አያመልጥም። 

የዋህ ምእመን ገንዘቡን እያመጣ “ጸልዩልኝ” እያለ እንኳን በጸሎት ሊጠቅመው አርዶ ለሚበላው ምንደኛና ዘረኛ ክህነት አለው ብሎ ገንዘብ ይሰጣል። የሚበላው አጥቶ ጠኔ የሚደፋው ወንድሙ እያለ በመኪና ለሚዞር ምንደኛ ገንዘብ ያሳቅፏል። የትግራይ ወጣት የሞተው “ትግራይ ትስእር” ብሎ ነው ይላል። እሱም የጰጰሰው “ትግራይ ትስስር” ብሎ ነው። አንዲት ሃይማኖት የት አለ?፣ የማይከፈለው ክርስቶስስ ወዴት አለ?። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 13:20


ወዴት እየሄድን እንደ ኾነ አልያ ምን እየኾንን እንደኾነ ላልገባችሁ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 13:14


የጎዳናችን ቁልቁለት ጅማሮ

እንዴት እዚኽ ደረስን የሚል ካለ። መጀመሪያ የቤተ መንግሥቱንም የቤተ ክህነቱንም እረኞች በሲአይኤ እና ሞሳድ ተልዕኮ አዕምሯቸው የታጠቡ ተስፈንጣሪ ወጣቶች ግልብ አብዮት አንቀው ገደሏቸው። አንድ ትልቅ ኢትዮጵያን ታሪክ አዳፈኑ በሕዝቡም ፍርሃትን ፈጠሩ ያልተለመደ የማይታወቅ እንግዳ ነገር ተከሰተ። 

ቤተ ክርስቲያን የልማት ጸር ፣ የአድሃሪዎች ናት አሉ። “ፓለቲካና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው” በሚል የሁለቱን አስተሳሰብ ከሰው ልብ ውስጥ አራራቁት። ሥጋና ነፍስ አንድ አይደሉም እንዲል ምንታዌነትን አስጠኑት። እሱም ተሳካ። 

ኹለተኛው መንገድ ነጻ አውጪዎች መጥተው  “መንግሥት በሃይማኖት፣ ሃይማኖት በመንግስት ጣልቃ አይገባም” በሚል ደግሞ ሌላ ማስፈራሪያ ሀረግ አመጡ። ይበልጥ ፓለቲካን የሚፈራ ሃይማኖተኛ ሆኖ ፓለቲካው እንዳይቀርብ አደረጉት። ይኽም ተሳካ። 

በስተመጨረሻም ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው ሲኖዶሱን እርስ በርሱ ለያዩት። ይኽም ተሳካ። እና ምን ቀረ? ክርስቲያን እና ቤተ ክርስቲያን ራሱ መኖር የለበትም ነዋ? ይኽም በሂደት ላይ ነው። መርከብን የሚያሰጥመው ውኃ ወደ መርከብ ውስጥ መግባት ሲጀምር ነው። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Dec, 01:51


ሰርጌላ ላቭሮቭ አሜሪካ ኦርቶዶክስን ከዓለም ለማጥፋት እንዲሁም የዛሬ 4 ዓመት ነበር የዪክሬንን ቤተክርስቲያን ከራሺያ ለመነጠል እየሠራች መኾኑን የተናገሩት። ደግሞም አደረጉት።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

30 Dec, 23:03


ተደራጅቶ ተቀናጅቶ በየቀኑ ያለ ማቋረጥ የአብይ መንግሥት የሚወድቅበትን፣ ቤተ ክርስቲያን የምትጠበቅበትን መንፈሳዊ ተጋድሎ የማያደርግ ማንም ኦርቶዶክሳዊ ካህንም ይኹን ምእመን ተንበርክክኮ ለአብይ በመንግሥቱ ላይ እንዲቆይ እድሜ መርዘም የሚለምን ያክል ነው። አብይንና መንግሥቱን በመጥላት ብቻ ለውጥ አይመጣም። ለውጥ በተጋድሎ እንጂ በተአምር አይደለም።

መቀናጀት መደራጀት ምን ማለት እንደኾነ ብዙ ጊዜ እኔና መ/ር ፋንታሁን በማስረዳት ደክመናል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

30 Dec, 19:50


በዋሽንግተን ዲሲ ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሰማዕትነት እየተቀበሉ ላሉ ኦርቶዶክሳውያን ጸሎተ ፍትሐት አድርገናል። በጣም ጥሩ ጉባዔም ነበረን።
የመከረኞች ጉዳይ ግድ የሚላቸው ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በመገኘት ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል።
ሰልፍ የፓለቲከኛ ነው ይሉ የነበሩ አፈ ጻድቅ ካህናትና ምእመናን ባይገኙም ግድ የሚላቸው በርካታ ካህናትና ምእመናን ተገኝተዋል።

"መከራውን እኩል እስኪያግባባን ድረስ እልቂቱ ስደቱ ረሃቡ ይቀጥላል" ቆሞስ አባ ኃይለ ሚካኤል።

https://youtu.be/pxWsZJ6EYCo

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

30 Dec, 19:45


https://youtu.be/pxWsZJ6EYCo

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

30 Dec, 15:55


የሠለስቱ ደቂቅ የነገረ መለኮት ትርጓሜ 

በሠለስቱ ደቂቅ ምስጋና ሰይጣን የሰው ልጆችን ድል መንሳቱን የእግዚአብሔር ልጅም ወደ ሲኦል መውረዱን በኃይሉም ከችግራቸው ስለማዳኑ የገለጠበት ምስጢር ነው። 

ከአዳም ከተፈጠረ እስከ ክርስቶስ ልደት ድረስ ያለውን ከዚያም እስኪሰቀልና ወደ ሲኦል ወርዶ እስኪያድናቸው በምድር የሚኖርባቸውን ዘመናት ይነግረናል። ይኽም የዳንኤል አራተኛው ራእይ ነው። 
"የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት" ት. ዳን 1:1

የእስራኤል ልጅች በፈርኦን በባርነት መኖራቸው የአዳም ልጆች ለሰይጣናት በባርነት ለመኖራቸው ምሳሌ እንደሆነ እግዚአብሔርን ስለመድፈራቸው ናቡከደነጾር የእስራኤልን ልጆች እንደ ማረካቸው ከቅድስት ሀገራቸው እስከ ሀገሩ ባቢሎን እንዳፈለሳቸው እርሱም ከሠራዊቱ ከከለዳውያን አስገድዶ እንዳስገዛላቸው ነቢዩ ዳንኤል አመለከተ። 

"ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው። የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፥ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል" ት.ዳን. 3:1-5 

እግዚአብሔርን ስለ መደፋፈራቸው አዳምና ዘሩን ሰይጣን እንዳማረካቸው ከቅድስት ገነት አውጥቶ የጨለማ ምድር እስከ ሆነው እስከዚህ ዓለም አውርዷቸው እንደ ነበር ይኽችውም የሹመት ሀገሩ ናት። 

ናቡከደነጾር የእስራኤልን ልጆችና ከአህዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩትን ከበሮ መለከት መሰንቆንና በገናን ጸናጽልንም በመስማት በዘፈን ላቆመው ምስል እንዲሰግዱ አደረገ። ላቆመው ምስልም እንዲሰግዱ እንደ አሳታቸው እንዲሁ ሰይጣን ለእርሱ ባርያ ሆነው ለትእዛዙ እንዲገዙ እስኪጠፉ ድረስ የአዳም ልጆችን በዚህ ኅላፊው የዓለም ፍትወት አሳታቸው። ኅላፊ ፍትወት ማለት ተድላ ዘፈን ደስታ ማለት ነው።

ናቡከደነጾር ያልታዘዙት ላቆመው ምስልም ያልሰገዱትን ሠለስቱ ደቂቅን በእቶን እሳት ውስጥ እንደ ጣላቸው እንደዚሁ ሰይጣን ትእዛዙን ያልሰሙትን ጻድቃን ሁሉ አብርሃም ይስሐቅን ያእቆብን ከጻድቃን ከሌሎችንም ነቢያት ስለ አባታቸው አዳም ሕግ ማፍረስ ወደ ሲኦል ጣላቸው። 
"ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡንም፦ ናቡከደነፆር ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም።……..ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ፥ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ" ት.ዳን. 3:16-20

እሳቱ ግን የናቡከደነጾርን ሠራዊት እንዳቃጠላቸው ሠለስቱን ደቂቅ አላቃጠላቸውም። ለሰይጣን የታዘዙትን እንዳቃጠለቻቸው ጻድቃንን በሲኦል ውስጥ አላቃጠላቸውም። 
"መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፥ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች፥ ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፥ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ"  ት.ዳን.3:27

እሳቱ ከሠለስቱ ደቂቅ እንደ ራቀ እንዳላቃጠላቸው እንደ ቀዝቃዛ ጠል ሆነላቸው። ይኽም ስለ ባለ ጻጋውና ስለ ደሃው ሲናገር አልአዛርም በአብርሃም አጠገብ እንደ ነበር ተናገረ። ሉቃ 16:19

ቅዱሳን ጻድቃን በእረፍትና በቅዝቃቄ ሁኔታ ከሐድያን በእሳት ኩነኔ መኖራቸውን ዳንኤል በሦስቱ ወጣቶች ተናገረ። 

አዛርያም "ለሕዝቡ ሁሉ ኃጢአት በእግዚአብሔር ታምኖ በእሳት እቶን ውስጥ በመቆም እንዲህ አለ "አቤቱ ባመጣህብን ነገር ሁሉ እንደ ጻድቅ ነህ ፍርድህም የእውነት ፍርድ ነው። እኛ ግን በደልን ሐጢአት ሠራን ዐመጽንም" 

እንዲሁም ጻድቃን አበው በሲኦል ውስጥ ስለ ሁሉ የአዳም ዘር ኃጢአትና ሕግ ስለማፍረሳቸው የሚታመኑ ሆኑ።  
እስከ እለት ሞታቸው ድረስ አመኑት። ስለዚህም "ከዚህ እንጨት ከበላህ ሞትን ትሞታለህ" ባለው ጊዜን እግዚአብሔርን ሐሰተኛ ያደረገው የአዳም ኃጢአት ተተወች። "ይህችን በበላህ ግዜ አምላክ ትሆናለህ" ያለውን የሰይጣንን ቃል ባመነ ጊዜ አዳምና ልጆቹ ባሪያ ሆኑ። ዘር ሁሉ ወደ ሲኦል ወደቁ። 

አብርሃም ይስሐቅ ያእቆብ በእግዚአብሔር በማመናቸው ቃል የገባላቸውን የከነዓንን ምድር አላወረሳቸውም። ከከነዓን የምትበልጠውን መንግሥተ ሰማያትን ሰይጣን ከእርሷ የወደቀባትን ከፍተኛውን  ስፍራ አወረሳቸው እንጂ። 

በአዳም ላይ የሚገባውን ፍርድ ተሸክሞ በራሱ ይቤዥው ዘንድ ሊገድለው እስኪደፋፈር ድረስ መለኮቱን ከዲያብሎስ ይሰውር ዘንድ ከእርሱም ስለ ቤዛነቱ በፍትሕ ይወስዳቸው ዘንድ ነው። 

ስለ አብርሃም ይስሐቅ ያእቆብ እምነት ሕግ ስለማፍረሱ የመጣበት የአዳም ኃጢአቱ ተተወ። ስለዚህ አዛርያ በእቶን እሳት ውስጥ ስለ አዳምና ዘሩ ማለደ። ስለ ወዳጁ ስለ አብርሃም ስለ ባለሟሉ ስለ ይስሐቅ ስለ ቅዱሱ ያእቆብ ብሎ ይቅር ይላቸው ዘንድ በጽድቃቸው የገባላቸውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ ለመነ። 

እግዚአብሔር የአዛርያን ጸሎት ሰማ የእግዚአብሔር ልጅም ዝቅ ብሎ ወደ እነርሱ ወደ ሲኦል እንደ ሚወርድና እንደ ሚያድናቸው ገለጠ። ወደ እሳቱ ከነአዛርያ ጋር መልአክ እንደ ወረደ በተናገረ ጊዜ "መልአክ" ብሎ ጠራው። በኋላም የእግዚአብሔር ልጅ ብሎ ገለጠው። 

ናቡከደነርም "በእስር ውስጥ ተፈተው የሚመላለሱ አራት ሰዎችን አያለሁ አራተኛውም እንደ እግዚአብሔር ልጅ ይመስላል።" ዝቅ ብሎ ሰው እስከ ኾነ ድረስ ወደ እነርሱ ወደ ሲኦል እንደማይወርድ ገለጠ። 

አዛርያ ጸሎቱን በጨረስ ጊዜ ከአዳም ጀምሮ እስከ መምጫው ያሉትን ዓመታት መጠን ገለጠ። የንጉሡ ሠራዊትም ነበልባሉ አርባ ዘጠኝ ክንድ ከፍ ከፍ እስኪል ድረስ እሳቱን አነደዱ። አርባ ዘጠኝ ክንድ የሚለው ሰይጣንን ሠራዊቱ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዓመት በሲኦል እሳት ውስጥ ያቃጥሏቸው ዘንድ በዓለም ላይ እንደ ሰለጠኑ ማስረዳቱ ነው። እርባ ዘጠኝ ክንድ አንዱ ክንድ ስለ መቶ ዘመን ነው። 

ይህም ማለት የሰይጣናት እሳት በዚያ ዘመን ልክ እንደ ሆነች ጻድቃን በሲኦል እንዳልተቃጠሉ ሠለስቱ ደቂቅን እንዳላቃጠላቸው የሰይጣናትን ሕዝብ ከሐድያን አይሁድን ታቃጥላቸው ነበር። በእሳት ውስጥ ያመሰግኑት ነበር። 
"ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ እስመ ለአለም ምሕረቱ" እግዚአብሔርን አመስግኑት ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና" እየደጋገሙ ሠላሣ ሦስት (33) ጊዜ አመስገኑት ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ከልደት ጊዜ እስከ ስቅለቱ ጊዜ ወደ ሲኦል እስከ መውረዱ ጊዜ ምድር ላይ የኖረበት የሠላሳ ሦስት ዓመት ምልክት ነው። 

ስለዚህም ሠላሳ ሦስት ጊዜ ብለው ከፈጸሙ በኃላ እንዲህ አሉ። አመስግኑ ልዕልናውን ጨምሩ ከሲኦል አድኖናል ከሞት እጅም አስጥሎናልና ከሚነድ ነበልባል መካከልና ከእሳት እቶንም ታድጎናልና። አዳምንና ዘሩን ከሲኦል ያዳናቸው በሠላሳ ሦስት ዓመት እንደ ሆነ አሳየ። 

ከስቅለቱ በኋላ ያመኑበትን እርሱን ያመሰግኑ ዘንድ አዘዛቸው ምሕረቱ እስከ ዘለዓለም እንደ ምትኖርላቸውም ተረዱ። ከሰዎች የኦሪትን ሕግ በወንጌል እንደ ለወጠ አይለውጣትም። የሚያመሰግን ሰው "እግዚአብሔርን ባርኩት" ሲል ቡሩካን መኾናቸው ተናገረ። አምልኳቸውም የተባረከች ነች። እነርሱም ቡሩካን ናቸው። 
ቅዱስ ሳዊሮስ ዘእስሙናይ 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

30 Dec, 15:55


ይኽ በዓል የቅዱስ ገብርኤል ብቻ አይደለም። ጠለቅ ያለ የነገረ ሥጋዌ ትምህርት ነው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

29 Dec, 09:06


መልክዐ ኢየሱስ

ሰላም ለህሊናከ ዘይሄሊ ሠናያተ። ለውሉደ ሰብእ ምህረተ። ክርስቶስ ብርሃን ዘአሰሰልከ ጽልመተ። ላዕለ ኪሩቤል ነቢረከ ዘትሬኢ ቀላያተ። ስቡህኒ ወልዑል አንተ።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

29 Dec, 06:46


ሥጋ ለባሽ ነን እንጂ ሥጋ አይደለንም። ለኃጢአት አርነት ራሳችንን አንስጠው። ሰው ነን። ሰው ደግሞ መልክአ ሥላሴ ነው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

28 Dec, 19:49


ዘርና ጎሣ የሰበሰባቸው ልብስና ቆብ ካህን ያደረጋቸው ምንደኞች!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

28 Dec, 18:49


ድሮ ድሮ እኛም እንዲኽ ነበረን!!

ዓለም በአንድነት ለማጥፋት የሚታገለውን ኦርቶዶክስነት አላስነካ ያላቸው ፑቲን ነው!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

28 Dec, 17:34


Global Ethiopia – Global Alliance for the Right of Ethiopians
https://globalethiopia.org/

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

28 Dec, 10:19


ገብርኤል ማለት

፩. እግዚአብሔር ኃያል ነው
፪. እግዚእ ወገብር ጌታና አገልጋይ ማለት ነው። 
፫. እፁብ ድንቅ :- ድንቅ መካር የተባለ ክርስቶስን መወለድ ያበሰረ ነው። ብስራት ሶምሶንን ሲያበስር ድንቅ መካር መሳ.13 
፬. መልአከ ኪዳኑ ለቃል፣ ለእግዚአብሔር  ይባላል። የቃል ኪዳኑ መልአክ ማለት ነው ሁሉን ኪዳን ይዞ የመጣ እሱ ነው። ኪዳነ ምህረትን ይዞ መጣ።

የተጨነቁትን አጽናኝ፣ መካኖችን የሚያበስር፣ ያዘኑትን የሚያረጋጋ፣ መብረቅን የሚያዝ ነው።

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

28 Dec, 09:58


ምሪት

የእግዚአብሔር ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው፣ ወዴትስ እንደሚሔዱ ምንስ ማድረግ እንዳለባችው ምሪት ይሰጣሉ። ዮሴፍ እመቤታችንን ሊተዋት ባሰበ ጊዜ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ድንግሊቱን ለመጠበቅ መውሰድን እትፍራ ሲለው እናያለን። ሐዋርያው ፊሊጶስንም በጋዛ መጽሐፍን እየመረመረ የነበረውን ጃንደረባውን ያጠምቅ ዘንድ የላከው  የእግዚአብሔር መልአክ ነው። የእግዚአብሔር ሕዝብ ለአርባ ዘመን በሲና በረሃ ሲጓዝ ቀኑን በደመና ሌሊቱን በብርሃን ፋና ከፊትና ከኋላ ሆኖ የመራው የእግዚአብሄር መል አክ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል። ዛሬም ይህንንው እውነት በብዙ የሕይወት ገጠመኝ የምናየው ተግባራቸው ነው።

+ ማዳንና መታደግ

ሰዎች በመከራ ሥጋ በመከራ ነፍስ ሲያዙ በሰይጣን ወጥመድ ሲወድቁ፣ ክፉ ሰዎች ከመከሩባቸው፡ ካደረሱባቸው ችግር ቅድሳን መላእክት ሲያድኑ፣ ሲታደጉ የሚናገር ምንባብ በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በገድላትና በድርሳናት በስፋት ተጠቅሷል። ሰለስቱ ደቂቅን በናቡከደነጾር እጅ ከገቡበት እሳት ያወጣ፣ ሐዋርያት በታሰሩ ጊዜ የእስር ቤቱን ደጅ ከፍቶ ያዳናቸው፣ ዳናኤልን ከአንባሳ መንጋጋ የታደገው፣ አፎምያን ከሰይጣን ያስጣለ፣ የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የለወጠ እግዚአብሔር መልአክትን በመላክ  ነው። ት. ዳን. 3:1 ። ሐዋ.5፡19። 12:6

+ ምልጃና ጸሎት ማሳረግ

ከቅዱሳት መላእክት ተግባር መካከል አንዱ ምልጃ ሲሆን የሰውን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ፣ እግዚአብሔር የመለሰውን ምላሽ ወደ ሰው ማምጣትም ድርሻቸው ነው። እስራኤላውያንን ተቆጥቶ የቀጣቸውን መልአኩ ሲያማልድ 
 “የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ”  በዚህ ልመና ወስጥ ስለ እስራኤም ሕዝብ ሲያማልድ እናያለን። ቅዱስ ገብርኤልም ስለ ስሙ ሲያስታውቅ  “መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤” በማለት  የተናገረው በእግዚአብሄር ፊት መቆም ማለት ማማለድ መለመንን ያሳያል። ሉቃ.1:19

የቅዱሳን መላእክትን ተግባር በአጭሩ ለማቅረብ ያክል እንጂ ከዚህም የሰፋ በመሆኑ በሰፊው ለማወቅ ለመነሻ ግንዛቤ ይህንን ከጠቀስን ቅዱሳት መጻህፍትን መመርመር ሊቃውንትን በመጠየቅ በስፋት መገንዘብ ይገባል።  እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እግዚአብሔር ባለበት መላእክት፤ መላእክት ባሉበት እግዚአብሔር እንዳለ ታስተምራለች። ንጉሥ ባለበት ጭፍራ እንዲኖር ማለት ነው። 

በአጠቃላይ የቅዱሳት መላእክትን ተግባርም ይሁን አገልግሎት ሰፊ በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ሰፊ ቦታ አለው። በቤተ ክርስቲያን ቀን ተወስኖላቸው፣ መጻህፍት ተጽፈው፡ ታቦት ተቀርጾላቸው መልክ ተደርሶላቸው፣ ሰዕላቸው ተስሎ፣ የጸጋ ስግደት እየተደረገላቸው፣ በታላቅ ክብር  ይከበራሉ።

የቅዱሳን መላእክት ረዳኤት አይለየን

  ንዋይ ካሳሑን

https://youtu.be/UyrgbRTA8YY?si=OM9V4J7nBB47aUK3

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

28 Dec, 09:57


የመላእክት ክብራቸው፦

የመላእክት ክብራቸው ከፍ ያለ ነው። በብርሃን የተመሉ በመሆናቸው ብዙ ጊዜ ሲገለጡ መጻህፍት “ብርሃን ሆነ” የሚል ገጸ ንባብ ማየት የተለመደ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ “ ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች” ራዕ.18:1 እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚገባው ተገለጠ የተባለው አንድ መልአክ ሲሆን ምድር ግን እንደ በራች ያመለክታል። በዚህም ምን ያህል ክብር እንዳላቸው ያሳያል። 

ማኑሔ የተባለው ሰው ሚስቱ እንደምትወልድ ካነጋገረው በኋላ መልአክ መሆኑን ሲያውቅ “ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ።ማኑሄም ሚስቱን፦ እግዚአብሔርን አይተናልና ሞት እንሞታለን አላት።” በማለት ተናገረ። ማሳ.13:21 መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳን በቅዱሳን መላእክት ፊት የቆመ አልያ መላእክት የተገለጠለት ሁሉ በፊታቸው መቆም አይችልም ነበር። ኢያሱ፣ ዘካርያስ፣ ዳንኤል፣ የቤተልሔም እረኞች እንደ ምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው።

የመላእክት ተግባራቸው:-

በመግቢያው ለመጥቀስ እንደተሞከረው በጥቅሉ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የሚያገለግሉ፣ የሚላኩ መናፍስት  ሲሆኑ። ተግባራቸውን በመዘርዘር ለማየት ያሕል፦ 

+ አምልኮና ምስጋና ፦

 የቅዱሳን መላዕክት ተቀዳሚ ተጠቃሽ ተግባር ውስጥ እንዱ ምስጋና ነው። ያለ ማቋረጥ፣ ያለ እረፍት የእግዚአብሔርን ክብር፣ ቅድስና ኃያልነት አመስጋኝ ናቸው። የኢትዮጵያ ሊቃውንት “የመላእክት ምግባቸው ምስጋና ነው” ይላሉ። ያውም አመስግነው በቃኝ የማይሉ።  

ነቢዩ አሳይያስ ሲናገር “ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።” ይላል።ኢሳ.6:2

+ መልእክተኛ

የእግዚአብሔርን ምህረትም ይሁን ቁጣ ወደ ሰው፤ የሰውን  ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በማድረስ ያገለግላሉ። እግዚአብሔር ወደ ሰው ምህረት አልያ መቅሰፍት ሊልክ ይችላል። እንዲሁም የሰው ልጅ ጸሎትን ወደ እግዚአብሔር ያደርጋል። ይህንን በማከናወን ደግሞ መላእክት የመላከለኛነትን ሥራ ሲያከናውኑ ይታያል። 

የሰዶም ሰዎች እግዚአብሔርን ሲበድሉ ሕዝቡን ሊቀጣ ከተማዋን ሊያቃጥል መላእክቱን ወደ ከተማዋ ሰደደ። ሎጥን እጁን ይዘው ሲያወጡት ከተማዋን ግን በእሳት ዲን እንዳቃጠሏት እናነባላን። ለሎጥ የድኅነት፤ ለሰዶም ሰዎች የመዓትን መልእክት ይዘው መጡ። “ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፦ ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር” ዘፍ.19:1-38

ብዙ ጊዜም የደስታ ብስራትን ይዘው መጥተው መልዕክት ሲያደርሱ እናያለን። አጋር በበረሃ ጉዞዋ መንገድ እየመራ ልጅዋ በውሃ ጥማት እንደማይሞት፣ ካህኑ ዘካርያስ ሚስቱ ኤልሳቤጥ እንደምትወልድ፣እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመንፈስ  ቅዱስ ግብር የተነሳ ወንድ ልጅ እንደምትወልድ፣ እረኞች የአለም ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም መወለዱን ፣ሔደውም የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ማዳን እንዲመለከቱ የምስራቹን የነገሩት ቅዱሳን መላእክት ናቸው። ዘፍ.6፡  ሉቃ.2 ፡8።  ሉቃ.1:13

የጌታን ትንሳኤ በመጀመሪያ የታወቀው ለመላእክቱ ሲሆን ለሰዎችም ያበሰሩት፣ እርገቱን ወደላይ ቀና ብለው ይመለክቱ ለነበሩ ሐዋርያትን በማጽናናት እያዩት እንዳረገ እያዩት እንደሚመጣ የተናገሩት መላእክት ናቸው። እንዲሁም ለፍርድ ዳግም በሚመጣ ጊዜ መምጣቱን የሚያውጁት፣ ሙታንን  የሚያነቁት፣ ፍጥረትን የሚሰበስቡት፣ ምድር እንድታልፍ መለከት የሚነፉት፣ በግርማ መንግስቱ ሲገለት በመላእክት ታጅቦ መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ያስራዳሉ።  ማቴ 28:5    24:31  ሉቃ.

https://youtu.be/UyrgbRTA8YY?si=OM9V4J7nBB47aUK3

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

28 Dec, 09:56


ቅዱሳን መላእክት"

መላእክት በግሪክኛው ቋንቋ "መልእክተኛ" በእብራይስጥ "አገልጋይ" የሚል ትርጉም የያዘ ቃል ሲሆን: መልእክተኛ መባላቸው ከሰው ወደ እግዚአብሔር፣ ከእግዚአብሔር ወደ ሰው ለምህረት ይሁን ለቅጣት የሚላኩ ፈጻምያነ ፈቃደ እግዚአብሔር ናቸው። 

 እንዲሁም አገልጋይነታቸውም በዋናነት የሰውን ልጅ ነው።  መላእክት የሰውን ልጅ በገነት ጀምሮ ያገለልሉት እንደነበር ሁሉ ከእግዚአብሔር በተጣላ ጊዜም ከገነት ያስወጡት ቅዱሳን መላእክት ናቸው። “አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ።” በማለት ይገልጣል። ዘፍ.3፡24

አብርሃም ለልጁ ለይስሃቅ ሚስትን በፈለገና አገልጋዩ ኢያውብርን ሲልከው መላእክት እንደሚረዱት ነግሮት ነበር። “ከአባቴ ቤት ከተወለድሁባት ምድርም ያወጣኝ፦ ይህችንም ምድር እሰጥሃለሁ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፥ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ። ዘፍ.24:7 እና 40 በአጠቃላይ የሚታዘዙ መንፈሳዊ አካል ናቸው።

የመላእክት ተፈጥሮ፦

የተለያዩ መጻህፍት የቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮን በተመለከተ ሁለት ዓይነት አስተሳሰብ ሲያንጸባርቁ ይታየል። ነገር ግን ከነገረ መለኮቱ አስተምህሮ ሚዛን አንጻር ለመመልከት ያህል፦
+ መላእክት ተፈጥሮአቸው ከእሳት እና ከውኃ ነው የሚሉ አሉ። 
ይኽ ግን የማያስኬድበት ምክንያት ሲኖር ባህርያቸው ከእሳት ከነፋስ የሆነ ከሆነ በእሳትነት ባህርይ ውኃ ውስጥ፤ በውኃ ባሕርይ እሳት ውስጥ መግባት አይችሉም ነበር ያሰኛል። ለምሳሌ የሰው ተፈጥሮው ከመሬት፣ ከውኃ፣ ከነፋስ ሲሆን ውኃ ውስጥም ሆነ እሳት ውስጥ መኖር አልያ መቆየት አይችልም። ሌላው ምክንያት እሳትም ነፋስም በምጽአት የሚጠፉ ባህርያት ናቸው። ተፋጥሮ ስለሆኑ ማለት ነው። ከዚህ ተፈጥረው ቢሆን ጠፊ ሊሆኑ ነው የሚል ጥያቄን ያስነሳል።

+ በመሆኑም ሁለተኛው አስተምህሮ የመላዕክት ተፈጥሮ ከእሳት እና ከነፋስ ሳይሆን “እንደ ነፋስ እና እንደ እሳት ነው” የሚል ነው። ይኽንንም ሲያብራሩ ነፋስም ሆነ እሳት ታላላቅ የኃይል ሥራ የሚሰሩ ስለሆነ በዚህ ተመስለዋል። መጽሐፍ ቅዱስም ይኽንን ሲደገፍ “መላእክቱን መናፍስት አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ ይላል”  ። ዕብ.1:7

መላእክት ተፈጥሯቸው ራቂቅ ሲሆኑ አጥንትና ሥጋ የላቸውም። አያገቡም፣ አይጋቡም። ጌታ ይኽንን ሲናገር “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም”ሲል ተናግሯል። ማቴ.22:30 በመሆኑም የተፈጥሮ ጾታ የላቸውም ወንድ ሴት ናቸው አይባሉም።  በተጨማሪም አይሞቱም (immortal)አይባዙም፣ ሰማይና ምድር እንደሚያልፉ መላእክት አያልፉም።

መላእክት በቀዳሚ ቀን በእለተ እሁድ ተፈጥረዋል። ቅዱስ ጄሮምና የሚላኑ አምብሮስም "እግዚአብሔር መላእክትን ከሚታየው ዓለም በፊት ፈጠራቸው" ብለዋል። ቅዱስ አትናቴዎስም "እግዚአብሔር ከፍቅሩ የተነሳ  የማይታዩትን ፍጥረታትን ፈጠረ ።ይኽም መልካም እንደሆነ አየ በመቀጠልም የሚታየውን አለም ፈጠረ። በሁለቱም መካከል መልካም ግንኙነት አደረገ" በማለት ይገልጣል።

 በጸሎተ ሃይማኖትም ላይ የሚታየውን እና የማይታየውን ሲል ከማይታዩ ፈጥረታት መካከል መላእክት ይጠቀሳሉ። ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ስለ መላእክት ሲጽፍ “መላእክት ሲወዱ በተለያየ መልክ መገለጥ ይችላሉ፡ ሲገለጡም በባህርያቸው ሳይሆን በሰው መልክም ሊገለጡ ይችላሉ ይላል፡፡  ጦቢት 12:9

https://youtu.be/UyrgbRTA8YY?si=OM9V4J7nBB47aUK3

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

28 Dec, 09:56


https://youtu.be/UyrgbRTA8YY?si=OM9V4J7nBB47aUK3

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

28 Dec, 04:10


ደስ ብሎኛል

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በተገኙበት በግፍ ሰማዕትነትን ለተቀበሉ የሸርካ ሰማዕታት ጸሎተ ፍትሐት በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም አድርገናል። የተዋጣለት ጉባዔ ነበር።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

27 Dec, 21:26


https://youtu.be/UyrgbRTA8YY

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

27 Dec, 20:21


ንቁ ማኅበራዊ ሕይወት social life ያላቸው የሚባሉ ሰዎች፣ ብቸኛ አልያ አነስተኛ ግንኙነት ካላቸው ሰዎች በላይ የውስጥ ሁከት chaos ያለባቸው ናቸው። የውስጡን ጩኽት ማፈን የሚጠቀሙበት መንገድ ማኅበራዊ ሕይወት ነው። ብቻቸውን መኾን ይቸገራሉ፣ ራሳቸውን ይፈሩታል"

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

27 Dec, 14:37


 ነቢዩ  ኢዩኤል

ኢዩኤል የሚለው ስም በዕብራይስጥ “ጆኤል” ሲሆን “ጆ” ወይም “ኢዩ” የሚለው የቃሉ የመጀመሪያ ክፍል ከነናዊ የሆነ የእግዚአብሔር መጠርያ መለኮታዊ ስም ሲሆን “ኤል” ደግሞ ማለት “እግዚአብሔር አምላክ ነው” አምላክ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኢዩኤል ማለት ነው፡፡ 

ነቢዩ ኢዩኤል መቼ እንደኖረ፣ የትና ከየትኛው ቤተሰብ ተወልዶ እንዳደገ፣ ለነቢይነት እንዴት እንደተጠራና የነቢይነት ተግባሩ መቼ እንደተወጣ በአጠቃላይም ስለ ሕይወት ታሪኩ ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ 

በእርግጥ በመጽሐፉ መጀመሪያ የወላጅ አባቱ ስም ባቱኤል እንደሆነ ተነግሯል። “ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።” ኢዩ 1፡1

ነገር ግን ከየት እንደሆነ፣ በማን ዘመነ መንግሥት ትንቢት መናገር እንደጀመረና እንዳስተማረ ምንም ዓይነት መረጃ አይሰጥም፡፡ 

በአጠቃላይ ነቢዩ ከመልእክቱ በስተጀርባ ተከልሎ ወይም በመልእክቱ ውስጥ ተሸፍኖ ይገኛል፡፡ መጽሐፉ ውስጥ የነቢይነት ተግባሩን የተወጣበት ጊዜ ለመገመት የሚያስችል ምንም ዐይነት መረጃ ባይኖርም ከመልእክቱ ይዘት በመነሣት ሊቃውንቶች መጽሐፉ የተገኘው ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራተኛው ወይም በአምስተኛው መቶ ምዕተ ዓመት አካባቢ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ፡፡ 

በእርግጥ ነቢዩ በትንቢት ቃሉ ውስጥ ይሁዳና ኢየሩሳሌምን በተደጋጋሚ ሲጠቅስ ከ721 ዓ.ዓ በፊት ጠቀሜታቸው እጅግ በጣም ጎልቶና በነቢያቶች በተደጋጋሚ ይጠቀሱ የነበሩትን ስለ እስራኤልና ሰማሪያ ምንም አይናገርም፡፡ ከዚህ በመነሣት መጽሐፉ ሰማርያ በአሦራውያን ተሸንፋ ከወደቀች በኋላ ማለትም ከ722 ዓ.ዓ በኋላ ሊጻፍ እንደሚችል ይገመታል፡፡ 

በተጨማሪም ነቢዩ ኢዩኤል ጽዮንን ሰባት ጊዜ፣ ኢየሩሳሌምን ስድስት ጊዜ እንዲሁም ይሁዳን ስድስት ጊዜ በመጥቀስ ለአይሁዳውያን በተለይም ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ 

በመሆኑም ኢዩኤል የነቢይነት አገልግሎቱን የተወጣው ኢየሩሳሌም ውስጥ ሲሆን መልእክቱም በወቅቱ ወራሪዎችን በመፍራት በስጋት ይኖሩ ለነበሩት ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የተላለፈ ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ ሊቃውንት መላ ይመታሉ፡፡ ይሁን እንጂ መጽሐፉ ከሚሰጠው እጅግ በጣም ውስን የሆነ መረጃ ምክንያት የኖረበትና ያስተማረበት ወቅት እንዲሁም መጽሐፉ የተጻፈበት ጊዜና ቦታ በትክክል ይህ ነው ብሎ መወሰን አልተቻለም፡፡ 

መጽሐፉ በፋርስ ዘመነ መንግሥት ወቅት እንደተጻፈ የሚገምቱ ሊቃውንት ቢኖሩም ለግምታቸው ግን በሐዋር ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው ያምናሉ፡፡ ትንቢተ ኢዩኤል በአዲስ ኪዳን በሐዋርያት ሥራ ውስጥ በቅዱስ ጴጥሮስ አማካይነት ተጠቅሶ ስለሚገኝ በአዲስ ኪዳን አንባቢዎች ዘንድ ይታወቃል።  

 ነቢዩ ኢዩኤል

ኢዩኤል በመጀመሪያ ትንቢቱ ተስፋ በሚያስቆርጥ ሕልውናን በሚያናውጥ በአንበጣና በተምች መዓት ከአንበሳ መንጋጋ በሚጠነክር ለቁጥርም በሚያስቸግር የአሕዛብ ጦር ሠራዊት በሰዎቿ ክፋት ኢየሩሳሌም እንደምትወረር ማንኛውም ንብረቷ እንደሚመዘበር የአዝመራቸውም ዓይነት በከባድ ድርቅ በመመታት በበቀለበት ያለ ፍሬ ጋሽቦ እንደሚቀር ነዋሪዎቿ የሚበሉት ስንዴና የሚጠጡት ወይን ካህኑም ለመሥዋዕት የሚያቀርበው ቁርባን እንደሚጠፋ ካስረዳ በኋላ ቀጠል አድርጎ በዕድሜና በአስተሳሰብ የበሰሉ አረጋውያንና መሥዋዕት አቅራቢ ካህናትን ማቅ ታጥቃችሁ ከአመድ ላይ ተኝታችሁ በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪያችሁ አልቅሱ እንባችሁንም አፍሱ ከጥፋታችሁም ተመለሱ ከኃጢአታችሁም ተቀደሱ በማለት ጥብቅ የመርዶ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። “ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፤ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፤ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው። በተሃ ወይን ጠጃችሁ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ ሰካራሞች፥ ነቅታችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉ፥ ዋይ በሉ።” ኢዩ.1፣1-14: 

ቀጥሎም በዚሁ በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ስለመከራው ጽንአት ሲዘረዘር ለዚያ ቀን ወዮ ከዝናም መታጣት የተነሣ የተዘራው በመሬት ይበሰብሳል ጎተራውም በባዶነት ይፈርሳል ባልሠሩት ኃጢአት በሰዎች ክፋት ላሞችና በጎች የሚበጥሱት ቅጠል በማጣት ከረሀብ የተነሳ አሰምተው ይጮኻሉ በተሰማሩበትም ረግፈው ይቀራሉ ገበሬዎች ከአዝመራቸው እረኞች ከመንጋቸው ባዷቸውን ወደቤታቸው ይመለሳሉ እያለ በምሬት የመርዶ መርዶ ይናገራል።ኢዩ.1፣15-20 ም.2፣1-12

ኢዮኤል በመከራ ጊዜ ስለጾምና ጸሎት አስፈላጊነት እንዴት እንደሆነ ለማስረዳት ከአንዴም በላይ ለሦስት ጊዜ መላልሶ መዝግቧል። “የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፤ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።14  ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፤ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።” ኢዩ.1:13-14 9 ምዕ. 2፣12. ምዕ. 2፣15-17::

አምላካችንም ሰው ሆኖ በሚያስተምርበት ወራት ለተከታዮቹ ሲመክር ቀንደኛው ጠላት ሠይጣን ያለጾምና ጸሎት ድል እንደማይመታ ነግሯቸዋል። ነቢያትም ሆነ ሐዋርያት ስለጾም አስፈላጊነት መላልሰው ዘግበዋል:: ማቴ.17፥21።

በሁለተኛ ደረጃም የጾሙበትንና ያዘኑበትን ዋጋቸውን እግዚአብሔር ከአረማውያን ጦር እንዳዳናቸው አዝመራም በእጥፍ እንደሚሰጣቸው የአዝመራቸውን ብዛት የደስታቸውን ዓይነት ያብራራል። “የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”ኢዩ. ም. 2፣12-27

በሦስተኛም ደረጃ ስለመንፈስ ቅዱስ ሲገልጽ በዘመነ ሥጋዌ በአመኑት ላይ ወርዶ ትንቢት እንደሚናገሩ ራዕይ እንደሚያዩ እውነተኛ ሕልም እንደሚያልሙ በትንቢትነት መዝግቧል ይህም ትንቢት በዘመነ ሐዋርያት ተፈጽሟል።
“ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ”ኢዩ..2÷28-30
የሐዋ . 2፣15-22:

ከዚያ ወዲህ ግን በየዘመናቱ በሰይጣን እየተነዱ ሰዎችን ለማወናበድ ራዕይ አይተናል ሕልም አልመናል በአዲስ ቋንቋ እንናገራለን እያሉ ሲንተባተቡ ይደመጣሉ ማቴ7፣15-23 ም. 24÷24-25:: 

 ኢዮኤል ስለ ክርስቶስ ሰው መሆንና መድኃኒትነት በትንቢቱ ሲያበስር እግዚአብሔርም እንደተናገረ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ይገኛል በማለት መዝግቧል። “እንዲህም ይሆናል፤ የእግዚአብሔር ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምስራች የሚሰበክላቸው ይገኛሉ።”ኢዩ. 2፣32:: 
ስለክርስቶስ መድኃኒትነት ቅዱስ መጽሐፍ በትንቢትም ሆነ በመልዕክት በስፋት መዝግቧል አንድ ሁለት እንመልከት፡፡

@አበው ነቢያት ቀደምት ወደኀርት

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

27 Dec, 14:26


ነቢዩ  ኢዩኤል

ኢዩኤል የሚለው ስም በዕብራይስጥ “ጆኤል” ሲሆን “ጆ” ወይም “ኢዩ” የሚለው የቃሉ የመጀመሪያ ክፍል ከነናዊ የሆነ የእግዚአብሔር መጠርያ መለኮታዊ ስም ሲሆን “ኤል” ደግሞ ማለት “እግዚአብሔር አምላክ ነው” አምላክ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኢዩኤል ማለት ነው፡፡ 

ነቢዩ ኢዩኤል መቼ እንደኖረ፣ የትና ከየትኛው ቤተሰብ ተወልዶ እንዳደገ፣ ለነቢይነት እንዴት እንደተጠራና የነቢይነት ተግባሩ መቼ እንደተወጣ በአጠቃላይም ስለ ሕይወት ታሪኩ ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ 

በእርግጥ በመጽሐፉ መጀመሪያ የወላጅ አባቱ ስም ባቱኤል እንደሆነ ተነግሯል። “ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።” ኢዩ 1፡1

ነገር ግን ከየት እንደሆነ፣ በማን ዘመነ መንግሥት ትንቢት መናገር እንደጀመረና እንዳስተማረ ምንም ዓይነት መረጃ አይሰጥም፡፡ 

በአጠቃላይ ነቢዩ ከመልእክቱ በስተጀርባ ተከልሎ ወይም በመልእክቱ ውስጥ ተሸፍኖ ይገኛል፡፡ መጽሐፉ ውስጥ የነቢይነት ተግባሩን የተወጣበት ጊዜ ለመገመት የሚያስችል ምንም ዐይነት መረጃ ባይኖርም ከመልእክቱ ይዘት በመነሣት ሊቃውንቶች መጽሐፉ የተገኘው ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራተኛው ወይም በአምስተኛው መቶ ምዕተ ዓመት አካባቢ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ፡፡ 

በእርግጥ ነቢዩ በትንቢት ቃሉ ውስጥ ይሁዳና ኢየሩሳሌምን በተደጋጋሚ ሲጠቅስ ከ721 ዓ.ዓ በፊት ጠቀሜታቸው እጅግ በጣም ጎልቶና በነቢያቶች በተደጋጋሚ ይጠቀሱ የነበሩትን ስለ እስራኤልና ሰማሪያ ምንም አይናገርም፡፡ ከዚህ በመነሣት መጽሐፉ ሰማርያ በአሦራውያን ተሸንፋ ከወደቀች በኋላ ማለትም ከ722 ዓ.ዓ በኋላ ሊጻፍ እንደሚችል ይገመታል፡፡ 

በተጨማሪም ነቢዩ ኢዩኤል ጽዮንን ሰባት ጊዜ፣ ኢየሩሳሌምን ስድስት ጊዜ እንዲሁም ይሁዳን ስድስት ጊዜ በመጥቀስ ለአይሁዳውያን በተለይም ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ 

በመሆኑም ኢዩኤል የነቢይነት አገልግሎቱን የተወጣው ኢየሩሳሌም ውስጥ ሲሆን መልእክቱም በወቅቱ ወራሪዎችን በመፍራት በስጋት ይኖሩ ለነበሩት ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የተላለፈ ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ ሊቃውንት መላ ይመታሉ፡፡ ይሁን እንጂ መጽሐፉ ከሚሰጠው እጅግ በጣም ውስን የሆነ መረጃ ምክንያት የኖረበትና ያስተማረበት ወቅት እንዲሁም መጽሐፉ የተጻፈበት ጊዜና ቦታ በትክክል ይህ ነው ብሎ መወሰን አልተቻለም፡፡ 

መጽሐፉ በፋርስ ዘመነ መንግሥት ወቅት እንደተጻፈ የሚገምቱ ሊቃውንት ቢኖሩም ለግምታቸው ግን በሐዋር ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው ያምናሉ፡፡ ትንቢተ ኢዩኤል በአዲስ ኪዳን በሐዋርያት ሥራ ውስጥ በቅዱስ ጴጥሮስ አማካይነት ተጠቅሶ ስለሚገኝ በአዲስ ኪዳን አንባቢዎች ዘንድ ይታወቃል።  

ይቀጥላል
ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

27 Dec, 14:25


"የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናት ከወለሉና ከመሠዊያው መካከል እያለቀሱ፦ አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብ መካከል፦ አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ? ይበሉ።" ኢዩ.2

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

27 Dec, 09:13


ፍኖተ አዕምሮ 

መነሻህ ሰው መኾን ነው። አዕምሮ ለብዎ (ማስተዋል) ያለው እግዚአብሔር መልኩን የሳለበት ፍጡር ነው። ሰው ማንነቱን ማወቅ ሲያቅተው ራሱን በእውቀትም በሕይወት መንገድም መረዳት ሲያቅተው ድንቁርናውን ተጠቅሞ ሰይጣንም ሰውም የፍላጎቱ መፈጸሚያ ባርያ ያደርገዋል። 


ባርያ ማለት የራሱ መብት የሌለው፣ በሌላው አካል ተጽዕኖ ውስጥ የወደቀ፣ የራሱ እውቀት፣ ውሳኔ፣ ተግባር የሌለው ማለት ነው። አንተ መወሰን ሳትችል በራስኽ ላይ ሌላ ወሳኝ ይመጣብሃል። ነጻ የሚወጣ ሰው መጀመሪያ ራሱ ከራሱ ነው ነጻ መውጣት ያለበት። የባርነት መንፈስ ያለበት ሰው ነጻ ቢያወጡት እንኳ ነጻ የወጣው ለሌላው ባርያ ለመኾን አለቃ ለመቀየር ብቻ ነው። የሀሳቡ መሠረት ይኽ ነው። 

ራሱ ማሰብ ለገዛ ራሱ ማሰላሰል ይኽንን ማሰላሰል የሚያግዘው ደግሞ እውቀት ነው። ለማወቅ ደግሞ ቀዳሚው መንገድ ንባብ ነው። ማንነቱን ታሪኩን መገንዘብ። ያለበትን መተንተን። ያኔ ራሱ ለራሱ ለማሰብ ይጀምራል። የራሱ ሐሳብ፣ የራሱ መንገድ፣ አማራጭ ይዞ የመቅረብ፣ በአመክንዮ ማስረዳት፣ በስሜት መገንዘብ ያዳብራል። ካልኾነ በየመንገዱ በየሚዲያው ያነበበው ፕሮፓጋንዳዊ እውቀት እየጠለፈው፣ የድንቁርና ጭልፊት ይመታዋል። 

ብዙ እውቀቶቻችን በሳይንስ ስም ተሸፍነው መልካም ስም ተቀብተው እንደ እባብ ነድፈውናል። ሳናውቃቸው የጎዱን ብዙ ናቸው። አለማወቅ የጎዳንን ያክል እንኳ ሰይጣን እንኳ አልጎዳንም። ንባብ ድንቁርናን ይገልጣል። አለማወቅን ይጎዳታል። 


ወደ ዛሬው ዋና ነጥብ ልሻገር:-

ምንም ማድረግ እንደማንችልና መፍትሔው ኹሉ ከእኛ ውጭ እንደ ኾነ ለምን ይሰማናል። ጥያቄውን በአካል ላገኘሁት ሰው ሁሌ አነሣዋለሁ። መልስ ሲሰጡኝ እያደራጀሁ እሰማዋለሁ። 
አንደኛ ራሳቸው ያሰቡትን ሳይሆን የሰሙትን እንደ መፍትሔ ይነግሩኛል። ኹለተኛም ለሌላ ባርነት ራስን ለማዘጋጀት መፍትሔ ያልኾነን ነገር መፍትሔ ይሉታል። ሦስተኛ በየትኛውም መልኩ ራሳቸውን የችግሩ ተጠቂም የመፍትሔ አካልም አድርገው አይቆጥሩም። ችግሩ ቢደርስባቸውም እንኳ መፍትሔው ሌላ እንጂ እነርሱ እንዳልኾኑ ያስባሉ። ዋና የችግሩ ምክንያት ደግሞ ይኽ ነው። 

መደንዘዙ መፍዘዙ የመጣው ከዚኽ ዓይነት እሳቤ ነው። እንዲኽ አይነት ሰው መብቱን ነጻነቱን ለሌላው ይሰጣል። ከማለቃቀስ ውጭ አቅም የለውም። እንቅልፍ ያጣል ይወራጫል የሕልም ሩጫ ይሮጣል ስንዝር ግን አይሄድም። መጨረሻም ተስፋ ይቆርጣል። ችግሩን አልሰማም አላይም ማለት ይጀምራል። አለመስማቱና አለማየቱ ችግሩን አይቀርፈውም። 

መፍትሔው:- አርቆና አጥብቆ ማንበብ ቢያቅተው አንብበው ተረድተው ለሚናገሩ ሰዎች ለሚያምናቸው ሰዎች ጆሮ ሰጥቶ መስማት። ይኽም ቢኾን አጥብቆ የሚሰማ ሰምቶ የሚረዳ በጣም ጥቂት ነው። የሰማውን አገናዝቦ አሰናስሎ እውቀት ገንዘብ ማድረግ ያዳግተዋል። 

የራሱ መጠነኛ መረዳትና መገንዘብ ራሱ ስለ ራሱ ማሰብ ከቻለና የራሱን ድርሻ ካወቀ ከሌሎች ሥራ ከጀመሩት ጋር መቀላቀል። ከእንጦጦ ቆርቆሮ ላይ የወረደች የዝናብ ጠብቃ በቀጭን ቦይ ትወርዳለች። ቁልቁለቱን ወርዳ ከሌሎች ጋር እየተባበረች አቅም እያገኘች አባይ ትደርሳለች። ሰፈር የቀረ ውኃ ጸሐይ ልብጭ ሲል ይደርቃል። 

በግል አስብና በጋራ ተደራጅ ያልኩት ይኽንን ነው። ሰንበት ትምህርት ቤት አንዱ ዋና መወያያ መድረክ ነው። መዝሙር የፕሮግራም ማሟያ ከምታጠና ሊያጠፋኽ የመጣውን ጠላት በመምከር ተጋድሎ ጀምር። ከራስኽ ድንቁርና ራስኽን ነጻ አውጣ። 
ቄሶች ከቄሶች ጋር ምከሩ። ሄሮድስ ዙሪያ የተሰበሰቡ መጽሐፍ አዋቂ የተባሉት የኦሪቱ ቄሶች የንጉሡን ፍትፍት እየበሉ መጽሐፍቱን ማነብ ትተው አዋራ ጠጥተው አሕዛብ (ሰብአ ሰገል) “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው” ብለው ሲጠይቁት ሄሮድስ ግራ ገባው። ካህናቱን ሊቃውንቱን ጠርቶ ሲጠይቃቸው ደንግጠው መጽሐፍ ማገላበጥ ጀመሩ። ቀድመው ማወቅ የነበረባቸው ሰዎች ሥራቸውን ትተው አሕዛብ ቀደሟቸው። እኛም የተፈጸመብን ይኽ ነው። 

ታቦት ስለመደረብ፣ በዓል በማድመቅ፣ መዝሙር በማጥናት፣ አዳካሚ አጽናኝ በመስማት፣ አባይ ጠንቋይ አጥማቂ በመከተል ራሳችንን አደነዝዝን። ነጻነታችንን ከነጻ አውጪ የምንጠብቅ ኾንን። 

ሃምሳ ሺኽ የዜና ትንታኔ ብትሰማ፣ የተጻፈ ስታነብ ብትውል ራስህን የመፍትሔ አካል አድርገህ ካልተደራጀኽ እመን ለመጥፋት ወስነሃል ማለት ነው። መጀመሪያ ጎንህ ያለውን ሰው ያንተ አይነት ስሜት እንዳለው ጠይቀው፣ በጋራ ተነጋገር ቁጥርህን አብዛ ሐሳብህን ለሌሎች አብረህ ለሚውሉ “እናገለግላለን” ለሚሉ አጋራ፣ ያኔ መፍትሔው ላይ ታተኩራለህ ማለት ነው። ጭላንጭል ማየት ትጀምራለኽ። 

ለችግርህ ሰበብ ምክንያት እየሰጠህ መፍትሔው ሌሎች እጅ ነው ብለኽ ከተቀመጥክ አበቃልህ። ላንተ ካንተ የቀረበ ማንም የለም። በግል አስብ በጋራ ለመሥራት ተደራጅ። ብዙ ሚሊየን ሰው በጋራ ካላሰበ ብቻውን “ምንም ማድረግ አልችልም” ካለ ሚሊየን ሳይሆን አንድ ሰው ብቻ ነው። ሚሊየን የሚባለው በጋራ የሚደመር ሲኾን ብቻ ነው። በግሉ ሚሊየንም አንድ ነው። 

እነ እገሌ አሉ፣ እነ እገሌ ይሠሩታል፣ ፋኖ አለልኝ የሚል ሰው እጅግ ደካማ ከመኾኑም በላይ የጠላት ያክል አደገኛ ነው። እሱ ቆሞ ሌላው ሲተጋ የሚተጋው ሰው እንደሚደክም አለመገንዘቡ ነው። ብዙ ሰው ሌላውን ጠባቂ ሲሆን ጥቂቶች አቅማቸው እየቀነሰ ይሄድና ያቆማሉ። ብዙ ሰው መፍትሔ ጠባቂ ጥቂቶች መፍትሔ አምጪ ሲኾኑ ትርፉ መውደቅ ነው። አንተም የመፍትሔ አካል ነህ። 

ጉንዳን ትልቁን ኩይሳ የሚሰራው በእያንዳንዱ ጉንዳን ተግባር እንጂ በጥቆቶች ጥረት አይደደም። ንብ ማር የምታመርተው በጋራ ነው። ተግባሩ ግን ግላዊ ጥረትን በጋራ በማድረግ ነው።

ሺኽ ጊዜ ብታውቅ ሺኽ መጽሐፍ ብታነብ ምን ብትተነትን በጋራ ካልሠራኽ ውጤት የለውም። "ብቻውን ኾኖ ያሸነፈ ብቻውን ኾኖ የተፈራ የለም" ኦርቶዶክሳዊነት ግብረታዊነት ነው። በል ዛሬ ጀምር። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

27 Dec, 00:17


"በግል አስቦ በጋራ መሥራት"

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

26 Dec, 19:29


ነቢዩ ሚክያስ

ሚክያስ የሚለው ስም ሚካያ ከሚለው የተገኘ ሲሆን ሚ (ማን)፣ ካ (እንደ)፣ ያህ (የእግዚአብሔር መጠሪያ ስም) ሲሆን ትርጓሜውም “ማን እንደ እግዚአብሔር” ማለት ነው፡፡ በእርግጥ ነቢዩ ሚክያስ ከስሙ ጋር በሚመሳሰል መልኩ በትንቢት ቃሉ ሲናገር “አንተን የሚመስል አምላክ የለም፤ ዘላለማዊ ፍቅርህን ለእኛ ለማሳየት ስለምትደሰት ቁጣህ ብዙ ጊዜ አይቆይም ይላል” ሚክ 7፡18

ሚክያስ የይምላ ልጅ ሲሆን ከኢየሩሳሌም ደቡብ ምዕራብ በ32 ኪ.ሜ ያህል ርቃ ከምትገኘው ሞሬሼት ከምትባለው መንደር እንደሆነና የነቢይነት መልእክቱም በአክአብ ዘመነ መንግሥት በኢየሩሳሌምና በሰማርያ ለነበሩት ነዋሪዎች ያደረሰ ነቢይ ነው። 3፡1-12

ሚክያስ በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመንም የነቢይነት አገልግሎቱን የተወጣ መልእክተኛ ነው። 
በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታምና በአካዝ በሕዝቅያስም ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው፥ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው፥ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።” ሚክ 1:1፡14

ሚክያስ በስምንተኛው ክፍለ ዘመን የነቢይነት ተግባራቸው ከተወጡት ጥንታውያን ከሚባሉት አራቱ ነቢያቶች ማለትም ነቢዩ ኢሳይያስ፣ አሞጽና ሆሴዕ ጋር የሚመደብ ነቢይ ነው፡፡ 

ከዚህ የምንረዳው ሚክያስ የነቢይነት አገልግሎቱ የጀመረው በንጉሥ ኢዮአታም (ከ750-732 ቅልክ) ጊዜ ሆኖ በንጉሥ አካዝ ጊዜም (735 ዓ.ዓ በኋላ) እንደቀጠለ ነው፡፡ ከመጽሐፉ ይዘት እንደምንረዳው ደግሞ በሕዝቅያስ ዘመን ከተደረገው ሃይማኖታዊ ተሐድሶ በፊት የነበረው ማኅበራዊ ሁኔታ ስለሚያንጸባርቅ ነቢዩ በንጉሥ ሕዝቅያስ ጊዜም የነቢይነት ተግባሩን ተወጥቶም ሊሆን ይችላል፡፡

ሚክያስ የሞሬሼት ተወላጅ ከመሆኑ ውጪ ስለ ቤተሰባዊ ሕይወቱና እንዴት ለነቢይነት እንደተጠራ ከመጽሐፉ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ 

ከሌሎች ነቢያቶች ለየት ባለ መልኩ በወላጅ አባቱ ስም ከመጠራት ይልቅ ሰባ አንድ (71) በትውልድ መንደሩ ስም “የሞሬሼቱ ነቢይ” በመባል ይጠራል”፡፡ 

በወቅቱ ሞሬሼት አንዲት ትንሽ መንደር ስለነበረች ሚክያስ ከነገሥታት ወይም ከነቢያት ቤተሰብ ሳይሆን ከዚህ መንደር ነዋሪዎች ከነበሩት ውስጥ የተገኘ እንደሚሆን ሊቃውንቶች ይገምታሉ፡፡ በእርግጥ ሚክያስ በትንቢቱ ሀብታሞች፣ የሕዝብ መሪዎች፣ ሐሰተኛ ነቢያቶች፣ ካህናቶች፣ ዳኞችና ባለሥልጣናትን ይወቅሳል፡፡ 

በዚህም ምክንያት ሚክያስ ከእነዚህ ወገኖች ሊሆን እንደማይችልና ቤተሰቡ የማኅበረሰቡ ተበዳይ ክፍል ሊሆን እንደሚችል ሊቃውንቶች ያክላሉ፡፡ 

ከትንቢተ ሚክያስ ውጪ ነቢዩ ሚክያስ በትንቢተ ኤርምያስ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል ሽማግልዎችም ተነሥተው እንዲህ አሉ ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን የሞሬሼቱ ነብይ ሚክያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተናገረውን የትንቢት ቃል ለሕዝቡ አውጆ ነበር። ኤር 26፡17-19

በእርግጥ ሚክያስ የነቢይነት አገልግሎቱ መወጣት የጀመረው ከሰማርያ ውድቀት (722 ዓ.ዓ) በፊት ነው፡፡ በትንቢቱም አስቀድሞ ሰማርያ በኋላም ኢየሩሳሌም  እንደሚፈርስ ተነበየ፡፡ “ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌምም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።” ሚክ.3:12

በአንጻሩ ደግሞ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ መንጋ እንደሚሰበስብ “ያዕቆብ ሆይ፥ ሁለንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፤ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።” ሚክ 2፡12፤ 7፡14

 ኢየሩሳሌምን አጽንቶ እንደሚሠራና “በመጨረሻውም ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛብም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።”ሚክ 4፡1

 አሕዛብም እግዚአብሔርን ለመፈለግ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንደሚወጡ የወደፊቱ የተስፋ ቃል ተናገረ “ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።” ሚክ 4፡2፤ 7:16)፡፡

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

26 Dec, 14:39


አለ በየአይነቱ ዘይት፣ ጨው፣ ቲሸርት፣ ውኃ... መቁጠሪያ....

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

26 Dec, 14:38


እንዲኽ ነው እንግዲኽ!!

ጳጳስ ብለን፣ አባት ብለን ፣ይመሩናል ይመክሩናል ብለን የሰበሰብናቸው ከዚኽ የተለዩ አይደሉም። ቤተ ክርስቲያንን ለጠንቋዩ አብይ አስረክበው አፋቸውን ሸብበው የጎሳ ፌደራሊዝም ሲኖዶስ ከመሠረቱ በኋላ ውጭ መጥተው ዋናውን የዶላር ማተሚያ እንዲኽ ያስተዋውቁልሃል። ካናዳ በል ቻለው።

የመልአከ አንከርት ዋና ኪስ ማደለቢያ ኾኗል።
ቤታችን በነዚኽ ዓይነት ጳጳሳት እና ካህናት መከራ እያየች ነው።

መንፈስ ቅዱስ ሲለይኽ በአቢይ መንፈስ ስትጋለብ እንዲኽ ነው። እስከ ዛሬ ይኽ ኹሉ የካህን የመናንያን የአብነት ተማሪዎች የምእመናን ደም በዐይናቸው ፊት ሲፈስ የት ነበሩ? ምነው ዝም አሉ። ዛሬስ ምን ትዝ ቢላቸው ነው ስለ ጠንቃዩ ሊሰብኩን ብቅ ያሉት። Good luck.

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

26 Dec, 14:06


አውቀህ ግባበት ወዳጄ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

26 Dec, 14:05


ለልዩ እጥበትም አገልግሎት እንሰጣለን!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

26 Dec, 14:04


መርጣችሁ ተቀቡ። በጠርሙስ ወይስ በብልቃጥ፣ የተልባ ወይስ የወይራ ዘይት? በሔኖክ ወይስ በግርማ ወይስ በዳንሳ? የጾም ቅባት በየዓይነቱ።
አይ ኦርቶዶክሳውያን እንዲህ ከርታታ ይብዛበት።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Dec, 05:08


https://youtu.be/DZFgLyeiHZE?si=9nobrS_ekJr5IxaG

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Dec, 02:24


በዓል ምንድነው? ንግሥስ ምንድነው?

ተሰብስበን ማስቀደስ፣ ከበሮ እየመቱ መዘመር፣ ነጫጭ  ጥበብ ለብሶ ፏ ብሎ መዋል፣ የምግብ አይነት አዘጋጅቶ በዓል በዓል ድባብ መፍጠር። 

ታቦት ወጣ ብሎ እልልልል ማለት፣ አዲስ አልባሳት አሰፍቶ ጉድ ማሰኘት፣ ለቤተ ክርስቲያን ማሳደሻ ፣ መሬት መግዣ፣ ሞርጌጅ መክፈት ሚሊየኖችን መሰብሰብ? ሺኽዎች መኪናዎች ወደ ንግሥ መሄድና ድምቅ ብሎ መዋል? 
ምንድነው በዓል? ለበረከት የተዘጋጀ ዳቦ መብላት። በጧፍ ብርሃን ድምቅ ማድረግ፣ ድክም ብሎ መጥቶ መተኛት። 

ሚሊየኖት ሞትና ሕይወት መካከል ኾነው በረሃብ እያጣጣሩ፣ ሚሊየኖች የጦርነት ድምጽ እየሰሙ ባሉበት፣ በአንድ ጉድጓድ ብዙዎች ተረሽነው ሲቀበሩ። ቤት ፈርሶባቸው መኖሪያ ሲያጡ እያየን እልልልል የሚል ድምጽ ከየት ነው የሚወጣው? 

ወይስ በዓላችንን ለኀዘን፣ ድኆችን ለማገዝ፣ በጦርነት በረሃብ ብርድ ላይ ለወደቁት ልብስ ምግብ የምናቀርብበት? ታቦት አውጥቶ ንግሥ ወይስ ክርስቶስ ለሞተለት ሰው አንድ ቁም ነገር ማድረግ። ንግሥ እሱ ነው። በዓል እሱ ነው። እግዚአብሔር እጣንን የናቀበት፣ ካህናትን የናቀበት ጾምን የናቀበት አምልኮን የናቀበት ብዙ አጋጣሚዎች አሉ። የእኛን ለመነጻጸሪያ እንመልከተውና ራስን ለመልካሙ በዓል እናዘጋጅ። ዛሬ ክርስቶስ የሚወለደው አንተ ውስጥ ነው። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Dec, 02:16


ከሀገር ውስጥ እስከ ሀገር ውጭ እንዴት ባለ ምትሐታዊ አዚም ነው የሰጠም ነው? ወይስ አንተን አንቺን አይመለከትኽም?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Dec, 00:27


"ፍርሃታችንን እየፈራን እግዚአብሔርን የፈራን ይመስለናል።"

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

23 Dec, 23:49


ሰማዕት ማነው?

የዚኽች ምስኪን ኦርቶዶክሳዊ ደም አያችሁ። ነጭ ለብሰን መዝሙር አጥንተን የምንዘምር ወይስ እንዲኽ ደም ፈሷት የተዘነጋችው እናት?
እኛ ለበዓል ሥጋ ለመብላት እንዘጋጃለን። እሷ ደሟን ታፈሳለች። የሚያጽናናት እንኳ የለም!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

23 Dec, 20:30


ክህነት ወዴት አለሽ?

ርዕዮተ ዓለም ወለድ የጎጥ "ጳጳሳት "

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

23 Dec, 18:43


https://youtu.be/h18NN6wHACk?si=4G_tHQE7tOBAKuU5

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

23 Dec, 18:43


ደጋግማችሁ ስሙት!! ይኽ ነው መስመራችን (ኦርቶዶክሳዊ ተጋድሎ)

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

23 Dec, 16:30


መጪው ዓርብ ታኅሣሥ ፲፰ ዓርብ 6pm

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

23 Dec, 15:40


 ነቢዩ ሆሴዕ

ሆሴዕ የሚለው ስም “ሆሻ-ያ” ከሚለው ስም ጋር ተዛማጅነት ያለው ሲሆን ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ረድቷል” ማለት ነው፡፡ “ሆሻያ” የሚለው ስም በተቀራራቢነት ኢየሱስ እና ኢያሱ ከሚሉት ስሞች ጋር ስለሚዛመድ “እግዚአብሔር ያድናል” በሚለውም ጭምር ይተረጐማል፡፡

ዳግማዊ ኢዮርብአምከሞተ በኋላ መንግሥቱ ተዳክማ፥ በ722 ከክ.በ. በአሦር እጅ ወደቀች። የእግዚአብሔር ሕዝብ አንድ በመሆኑ ሆሴዕ በትንቢቱ ስለ ይሁዳም ተናግሯል፤ 2፥2።  በዚያን ዘመን አሞጽ፥ ኢሳይያስና ሚክያስ ትንቢት ይናገሩ ነበር።

ሆሴዕ የብኤር ልጅ እንደሆነ ተገልጿል። “በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስም ዘመን በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።” ሆሴ 1፡1 

ነብዩ ሆሴዕ ሰማርያ በሰባት መቶ ሃያ አንድ (721) ዓመተ ዓለም ተሸንፋ ከመፍረስዋ በፊት የእስራኤል የፖለቲካ ሕይወት ባልተረጋጋበትና እጅግ በጣም አስቸጋሪ በነበረበት ጊዜ በተለይም ከ755 እስከ 725 ዓ.ዓ ገደማ በእስራኤል ግዛት ወይም በሰሜናዊው መንግሥት ውስጥ የትንቢት ቃል ያስተላለፈ ነቢይ ነው። 

ይህ ወቅት በፖለቲካዊ አለመረጋጋት የሰፈነበት፣ የድኾችን መብት የተረገጠበት በአጠቃላይ የሕዝቡ ሕይወት ሃይማኖታዊ አኗኗር የተናጋበት ወቅት ነበር፡፡

 በዚህ ፈታኝ በሆነና የኑሮ ብልሹነት በተንሰራፋበት ወቅት ነው የነቢይነት መልእክቱን ለሰሜኑ ግዛት (ለእስራኤል ሕዝብ) ያስተላለፈው። 

 በዚህ ጊዜ በደቡባዊ መንግሥት ወይም በይሁዳ ግዛት ውስጥ ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝና ሕዝቅያስ በንጉሥነት ሲመሩ ነቢዩ ኢሳይያስ ደግሞ በዚሁ በይሁዳ ሕዝብ ማእከላዊ ቦታ ወይም መናገሻ በነበረችው ኢየሩሳሌም ውስጥ የነቢይነቱን ተግባር ያከናውን ነበር፡፡ 

ሆሴዕ ለነቢይነት እንዴት፣ የት እንደተጠራና የነቢይነት ሥራውን እንዴት እንደጀመረ ምንም አይናገርም፡፡ ስለ ነቢይነት ጥሪው ከመተረክ ይልቅ እግዚአብሔር በሆሴዕ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን ማስተላለፍ ሲጀምር ወይም እግዚአብሔር ለብኤር ልጅ ለሆሴዕ የገለጠለት የትንቢት ቃል ይኽ ነው በማለት የነቢይነት ቃሉ ቀጥታ ማስተላለፍ ይጀምራል።  “እግዚአብሔር መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ሆሴዕን፦ ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና ሂድ፤ ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች ለአንተ ውሰድ አለው። ሆሴ. 1:1-2

ነቢዩ ሆሴዕ ከሚጠቅሳቸው ነገሥታቶች፣ መንደሮች፣ የአምልኮ ቦታዎች እንዲሁም አጐራባች አገሮች በምናይበት ጊዜ አብዛኛው የነቢይነት መልእክቱን ያስተላለፈው በሰሜናዊ ግዛት ወደነበሩት ሕዝቦች ወይም ለእስራኤላውያን ነው፡፡ 

ከእነዚህም ውስጥ ለመጥቀስ ያህል የሰሜኑ መንግሥት መሪ የነበረው ዳግማዊ ኢዮርብዓም ይገኝበታል፡፡ ከቦታዎች መካከል ደግሞ ምጽጳና ታቦር ፣ ገባዖንና ራማ፣ ጌልገላ፣ ቤቴል እና ሰማርያ ይገኙበታል፡፡ 4፡15፣ 5፡8 8:5

የኖረውና መልእክቱንም ያስተላለፈው ለእስራኤል ሕዝብ ቢሆንም ትምህርቱ ውስጥ የይሁዳንም ሕዝቦች አልፎ አልፎ ያካትታል ሆሴ 6፡4-11፤ 8:14፤ 12፡2

ትንቢቱ ውስጥ የተጠቀሱትና ነቢዩ ያስተማረባቸው ልዩ ልዩ ቦታዎች በምናይበት ጊዜ ነቢዩ ሆሴዕ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በቀላሉ ይንቀሳቀስ እንደነበር እንረዳለን፡፡

መጽሐፉ ካካተታቸው የተወሰኑ መረጃዎች በመነሣት ስለ ነቢዩ ሆሴዕ ቤተሰባዊ ሕይወት በተወሰነ መልኩ ቢሆንም መናገር ይቻላል፡፡ ሆሴዕ ባለትዳር የነበረና ሚስቱም ጎሜር በመባል እንደምትታወቅ ተገልጿል። ሆሴ 1:3

ሆሴዕና ጎሜር በትዳር ሕይወታቸው አይዝራኤል፣ ሎሩሐማ እና ሎዓሚ የሚባሉ ሁለት ወንዶችና አንድ ሴት ልጅ ወልደዋል። ሆሴ 1፡2-9

 ጎሜር ባለቤትዋ ነቢዩ ሆሴዕ ትታ ከውሽማዋ ጋር ትኖር በነበረ ጊዜ በእግዚአብሔር ትእዛዝ አማካኝነት ሆሴዕ ወደ ጎሜር በመሄድ በዐሥራ አምስት ብርና በመቶ ኀምሳ ኪሎ ገብስ ገዝቶ በድጋሚ ወደ ቤቱ እንደመለሳት ይናገራል። “እግዚአብሔርም፦ የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳ፥ እግዚአብሔር እንደሚወድዳቸው አንተም ውሽማዋን የምትወድደውን አመንዝራይትን ሴት ውደድ አለኝ።  እኔም በአሥራ አምስት ብርና በአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ተኩል ገብስ ገዛኋት።” ሆሴ 3፡1

በእርግጥ ይህንን የሆሴዕ ሚስት ለትዳርዋ ታማኝ ባትሆንም ነቢዩ አባብሎ ወደ ቤትዋ እንድትመለስ የማድረጉን ሂደት በመጠቀም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ማስተላለፍ የፈለገው መልእክት ስለነበረው መሆኑን ከትንቢቱ ቃል እንረዳለን። “እርስዋም፦ ውሽሞቼ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።15  እኔን ረስታ ውሽሞችዋን እየተከተለች፥ በጕትቾችዋና በጌጥዋም እያጌጠች ለበኣሊም ያጠነችበትን ወራት እበቀልባታለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር” ሆሴ 2፡14-23

የሆሴዕ ሚስት የጎሜር ማመንዘር ለእስራኤል መንፈሳዊ አመንዝራነት (ለአምልኮተ ጣዖት) ምሳሌ ሆነ። ሆሴዕም ሚስቱን ወዶ እንዲመልሳት ታዝዞ ነበር። እግዚአብሔር እስራኤልን በጽድቅና በምሕረት በገዛ ፈቃዱም ወደደ፤ 1፥1-3:5

የሆሴዕ ዋና መልእክት የእግዚአብሔር የማይለወጥ ፍቅር ሲሆን ዋና ጥሪው ሕዝቡ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ በመመለስ እንዲያውም ነው። 2፥23-24፤ 14፥4 (መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት)


ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

23 Dec, 13:16


ቀን ይለፍ ዝም በል!!

የብዙዎች ምክር ይኽ ቀን ይለፍ ዝም በል። ዝቅ ያለ እና ዝም ያለ ነው ይኽንን ቀን የሚያልፈው? ይላሉ።

ቀኑ እስሲያልፍ እድሜ ያልፋል፣ ታሪክ ያልፋል፣ ወገን ያልፋል፣ ኦርቶዶክሳውያን ያልፋሉ፣ የክርስትና አሻራ ዎች ያልፋሉ፣ እውነት ራሷ በውሸት ተተክታ እውነት መስላ ታልፋለች፣..እና ማን በመሰከራት እውነት ላይ ነው ነገን መረዳት የምንችለው? ሲባሉ።
እንግዲህ ነገርሁህ ለአንተ ብየ ነው ይላላሉ።

ያለ እውነት፣ ያለ ክስትና፣ ያለ ታሪክ፣..በምድር ላይ ብዙ ዓመት ኑሮ እንጀራ ለመብላት ሲባል ብቻ ዝም ማለት አይከብድም?

በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርሁ ፍትሐዊ ሰው ነኝ ማለት ይቻላል?

"የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና። ስለዚህ  ሞቱ በእኛ  ይሠራል።" ፪ቆሮ.፬፥፲-፲፪

@ምስራቅ ጸሐይ ጉባዔ ቤት

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

23 Dec, 13:11


አኹን ባለንበት ወቅት ቤተክርስቲያን ለገባችበት መከራና ፈተና መንገድ በመጥረግ፣ ፈተናውን እንደ ኦርቶዶክሳዊ ባለመጋደልና ለጠላት አሳልፎ በመስጠት ለገባንበት ውድቀት ኹሉ ቀደምት ተጠያቂ ሦስቱ አባቶች ናቸው!! ሌላው እንደየ ድርሻው ይደርሰዋል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

22 Dec, 19:33


አንድ የቁጭት ሐሳብ መጣልኝ። ስትፈቅዱ ብቻ መጻፍ እችላለሁ።

ቄሮ VS ማ.ቅ MK የሚል!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

22 Dec, 15:47


ምን ለማለት ፈልጌ ይኾን? ፎቶዎቹን የለጠፍኩት?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Dec, 14:13


                በማፌዝ ማፋዘዝዝ

ነጠላ በመላበስ ብቻ የቤተ ክርስቲያን ችግሩን ለመፍታት ማሰብ በቤተ ክርስቲያን ማፌዝ ነው።
በየዓውደ ምህረቱ በመለገስ ብቻ ችግሩን እፈታለሁ ማለት በምእመናን ሞት መሳለቅ ነው።
ተሰልበው የሚሰልቡ ስልብ ልቦች ራሳቸው ችግር ናቸው እንጂ ችግር ፈቺ አይደሉም።
ሕይወታችሁ አያገባንም ገንዘባችሁን  ግን እንፈልገዋለን በማለት ወንጌል ለትውልድ ትቀጥላለች?

"መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።"ማቴ.፳፫፥፲፫ ያለው ቃል እንዳይደርስብን ያስፈራል።

@ምሥራቀ ጸሐይ ጉባዔ ቤት

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 21:19


https://youtu.be/cDbclFnEdgQ?si=hQHZmwGnnxtFup9Y

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 18:46


መንቃት ምንድነው?

ንቃት ማግኘት ሲሆን ለማግኘት መፈለግ የንቃት ሂደት ጥረት ነው። በትክክል ማግኘት እሱ መንቃት ነው። ሁለት ምሳሌ እንጥቀስ:-

የጠፋው ልጅ ልጅነቱን አቃለለ፣ የአባቱ ቤት ሰለቸው፣ ውጭው ናፈቀው የቤቱ ክብር አል ታይ አለው። ሰውነቱን በውጭው መረጃ ማስደሰት ፈለገ። ለግዜው ቢደሰትም ጨለማ ድንቁርና ዋጠው። ከቤቱ ርቆ ሄደ ከከተማ ሰዎች “ከሠለጠኑት” ከሙዚቃው ከድግሱ ከጭፈራው ሁሉ ተካፈለ። 

የሚያስደስተው ነገር ጠፋ እረፍት አጣ። መጨረሻ ግን አንድ ስሜት ወደ ልቡ ገባ “ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ” ይኽ ለመንቃት ሐሳብ መጣበት ያወጣ ያወርድ ምን ሊያደርግ እንደሚችል አሰበ። የንቃት ሂደት ነው። የመጣበትን መንገድ ገመገመ ጥፋቱን ኪሳራውን ተረዳ። መጨረሻ ግን “ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።” አባቱ እቅፍ ገባ። ይኽ ነው የመንቃት ሂደትና መንቃት። ወደ ቀደመ ክብሩ የመመለስ ያጣውን ማስመለስ ነው። 

ሌላው መንቃት ፈልጎ ማግኘት ነው። አንዲት ሴት ድሪም ጠፋባት አፋልጉኝ ብላ ጎረቤት አሳተፈች። ልብ በሉ የጠፋባት ብቻ ሳትሆን ለማፋለግ ጎረቤት ተሳትፏል። “ወይም አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፥ መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?” 

መብራት አብርተዋል፣ ቁሻሻ ጠርገዋል፣ ተመሳስይ እቃ እየጠረጠሩ አይተው ጥለዋል። በስተመጨረሻ ግን አገኘችው “ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ፦ የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች።” ሉቃ.15:8

መንቃት የጠፋብንን መፍትሔ በትክክል ማወቅ ማግኘት ነው። 

ይኽንን መንቃት awakens በግል በቤተክርስቲያን በሀገር መተንተን ያስፈልጋል። ጥቂት ማፋለጊያ መሣሪያ መጀመሪያው የጠፋብን እንዳለ ማወቅ ነው፣ ከዚያ ምን እንደጠፋን ማወቅ በንባብ በዳሰሳ አዋቂ በመጠየቅ ብዙ ወደ ኋላ መጓዝ ይጠይቃል። 
ሌላው እኛ ፈልገን ማግኘት ካልቻልን የሚያፋልገንን መጥራት ነው። እርዳታ ማግኘት ነው። ፈልጎ ካገኘው ጋር መተባበር መሰብሰብ መሰልጠን መጋፈጥ ነው። ንቃት መዝለል አይደለም። ራቅ ያለ ግብን ዛሬ ላይ ሆኖ አሻግሮ ማየት ነው። 

የአኹኑን ዙሪያ ገባ ማጤን ወዴት እየሄድን እንደሆነ መተንተን ወደፊት ሊኾን የሚችለውን ዛሬ ላይ ቆሞ ማየት ነው። ይኽ መነሻ ሐሳብ ነው።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 18:27


መንቃት ያልኾነው ምንድነው!!

ጠጉሩን እያጨባረረ አራዳ ነኝ ማለት ንቃት አይደለም፣ ፌስቡክና ቲክቶክ ከፍቶ አፍ መክፈት መንቃት አይደለም፣ መረጃ መሰብሰብ መንቃት አይደለም። ነጠላ ለብሶ መዝሙር ማጥናት በከበሮ ልብ እስኪጠፋ መዝለል መንቃት አይደለም። ተሰብስስቦ ጉዞ መሄድ መንቃት አይደለም።

ጠርብ ጠርብ የሚያክል ጧፍ እየለኮሱ ነቅተናል እያሉ መዘመር ንቃት አይደለም። አዲስ ትውልድ ለመፍጠር ኮርስ፣ ዝማሬ እያሉ መንከራተት መንቃት አይደለም።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 16:45


መንቃት wake up

መንቃት ምን ማለት ነው። አንድ ሰው ነቅቷል ሲባል መገለጫው ምንድነው?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 15:33


ሕማም suffering

ፍቅር ሕማምን አያጠፋውም ያስችለዋል አንጂ። ማንም ቢኾን የሌላውን ሕመም መካፈል አይፈልግም። እናት ልጇ ሲታመም የልጇን ሕመም ለእኔ ያድርገው እያለች ታቅፈዋለች።

እኛ በኃጢአት ዋጋ የምንሰቃየውን እርሱ ሕመማችን በመሸከም ወደ መስቀል ወጣ። የሕማም ሰው ተባለ።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 13:46


መጽሐፍ ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ትክክሉንና እውነቱን ይነግረናል።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰው እውነቱንን ይነግረናል።
መጽሐፍ ስለ መልካም ተግባራት እውነቱን ይነግረናል። 
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰይጣን እውነቱን ይነግረናል።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተፈጥሮ እውነቱን ይነግረናል። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 13:42


በድንገት ይኽንን ወሬ ማውራት የጀመርኩት በሥራ አጋጣሚ ያገኘሁት ልጅ ነው። ከዚያች ቅጽበት በፊት አላውቀውም። ግማሽ ቀን ስልጠና ነበረን ሻይ እረፍት ላይ ነው ያገኘሁት። “Are you habesha” በሚለው ቋንቋ ተግባባን። 

“አየሩ እየቀዘቀዘ መጣ አይደል አልኩት። አዎ ይበርዳል አለኝ። eyes breaking መኾኑ ነው። 
ስለ ሃይማኖቴ አያውቅም በአካልም አያውቀኝም። 
በአጋጣሚ “ሐዋዝ የሚባለው ዘማሪ ተመለሰ አይደል” አለኝ። ወሬ ለመጀመር ፈልጎ መሰለኝ። “እኔ እንጃ አላውቅም” አልኩት። “ሐዋዝ ዘማሪውን አታውቀውም” አለኝ። አላውቀውም አልኩት። ፌስቡኩ ተጨናንቋል አለኝ። ስልኩን በጣቱ እየነካካ “እኔ ፌስቡክ የለኝም ፌስቡክ ሳይሆን የሰው አእምሮ ነው የሚጨናነቀው የአሊጎሪዝሙ ሰይጣን እንዲያ ነው አልኩት” አጀንዳውን አዘበራረቅሁበት። 

ቀጠለ ኢትዮጵያ ቅዱስ ዑራኤል ሰንበት ተማሪ ነበርኩ እዛው ነው ከልጅነቴ ያደኩት እዚህም አገለግላለሁ አለኝ። ብዙም አላወራሁም። የት ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው አለኝ። በአጭሩ እኔ የትም አልሄድም አልኩት። ትንሽ ቅር አለው። ቀዝቀዝ ሲል ይሰማኛል። ተጠራጠረኝ አንገቴን አየ፣ እኔ በአገልግሎት ስም ጥላ shadow የሠራበትን ጎን እየፈለኩ ነበር። 

“ጴንጤ ኾኖ ነበር አኹን ግን ተመለሰ” ብሎኝ ወዳቋረጠው አጀንዳ ተመለሰ። እኔ በጉዳዩ ሐሳብ ለመስጠት ምንም ፍላጎት አላሳየሁትም። ቀጠለ ቀጠለ ሌላም ሌላም። ሰውን እንደ መስማት ጥሩ ነገር የለም። እኔ የመስማት ልምድ ችግር አለብኝ። ግን ብዙ ልምምድ እያደረኩ ነው። ብዙ ርቀት እንደ ሄድኩ እገምታለሁ። ሰማሁት። 

ስለ “መውደቅ” ነገርኩት እሱም ስለመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቃቅስልኛል ይሰብከኛል። ቀስ ብዬ “የኾነ ምሳሌ ድሮ የሰማሁ ይመስለኛል” ብዬ ጥቅስ ጠቀስኩለት። ምን አለኝ ዮሐንስ 12 ላይ አልኩት።
ስልኩን ፓስዋርድ ጠቅ ጠቅ አድርጎ ከፈተና አወጣው ምን ይላል አለኝ። ቀስ ብዬ አንብበው አልኩት። ማንበብ ጀመረ። እኔ በየ ቁጥሮቹ እያስቆምኩ ነጥቦቹን እንዲያስተውል እያብራራሁ ቀጠልኩ። ታሪኩ የሆሳዕና ታሪክ ነው። ተረረም አድርጎ ሊያነብ ፈለገ እኔ ደግሞ አንድ በአንድ ቁጥሮቹን እየደገምኩ ጨረሰልኝ። 

“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።” አገኛት። ለምን ይኽንን ለግሪክ ሰዎች እንደተናገረ ጠቅሼ ስለ መውደቅ ጠቀለልኩለት። የግሪኮችን ወሬም ምን እንደኾነ ፍልስፍናዋን ጨመርኩበት። 

እኔ እስከ ዛሬ እንዲኽ እንደ ኾነ አላውቅም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን አስተውዬ አንብቤ አላውቅም አለኝ። “የጽድቅ ስሜት እንዴት እንደሚፈጠርና የልምድ አገልግሎት ጎጂነቱን ልንገረው አልንገረው እያልኩ ሙግት ውስጤ ገጠመ። ብዙ ላለማውራት ራሴን አቀብኩ። አገልጋይ ከሆንክማ ዋናው ንባብ መጽሐፍ ቅዱስ ነው አልኩት። ሆሳዕና እለት ከበሮ ለመንታት ለመዝለል  እንጂ ምስጢሩን ማስተዋል መች ለመድክና ልለው አስቤ ሆሆሆ ምን አግብቶኝ ብዬ ጭጭ። 

ፓስዋርድህን ካላወክ የመከፈት ስልክ የለም ብዬ አመክንዮውን በአጭር አቋረጥኩበት። 
እረ በአጭር ደቂቃ ብዙ ቁም ነገር ነገርከኝ አለኝ። ስልክህን ስጠኝ ሲለኝ “እኔ ስልክ ማውራት ፍላጎቴ በእጅጉ ስለ ቀነሠና ዳተኛ ሰነፍ ስለኾንኩ ይቅርብህ ትበሳጭብኛለህ ብዬ አሜል አድርግልኝ እሱ ይሻለኛል አልኩት። ወደ ስልጠናው ግቡ ተባልን። 

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 13:33


ወድቆ ማፍራት 

ሰው ውድቀት ይፈራል። እውነት ነው መውደቅ ከባድ ነው። ይሰብራል ያማል። ግን የማይወድቅ ደግሞ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፍጥረት ከነገረን በኋላ ቀጥሎ የሚነግረን አሳዛኙን የሰውን ውድቀት ነው። 

መውደቅ ብዙ ጉዳይን የያዘ ውስብስብ የሕይወት ጉዞ ነው። በስልጠና በክትትል በጥያቄና መልስ ካልኾነ በቀር በፊት ለፊት ቢጻፍ ሁሉም ሰው ከራሱ አቅጣጫ ስለሚተረጉመው አዛብቶ አጣሞ ሊረዳው ስለሚችል መጻፉን አልመረጥኩትም። እንደ ግለሰቡ ውድቀትና ከውድቀቱ በኋላ ስላለው ውጤት አንጻር ውድቀት ሊተነተን ይችላል። 

ውድቀታቸው የመነሻ መጀመሪያ የኾናቸው ብዙ ሰዎች አሉ። 
ቅዱስ ጳውሎስ ከነበረው ኃይለኛ ስልጣን በብርሃን ኃይል ሲመታ ወደቀ። ይኽ የቅዱስ ጳውሎስ የመነሻው መጀመሪያ ኾነ። መነሣቱ የጀመረው ዓይነ ስውር በመኾኑ ነው። 

ውድቀታቸውም የመሠበርና የሕይወት ፍጻሜ የኾነባቸውም አሉ። እነ ዴማስና ይሁዳ ውድቀታቸው ለሕይወታቸው መበላሸት መጨረሻ ኾነ። 

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መውደቅ ድንቅ ምሳሌ ነግሮናል። “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።” ዮሐ.12:24
ስንዴ ለማፍራት መውደቅ አለባት። ካልወደቀች አታፈራም። መውደቅ ብቻ ሳይሆን መሞት መበስብሰብ አለባት። ከዚያ ሞት ውስጥ ነው አዲስ ሕይወት ብቅ የሚለው። አንዳንዴ ይኽ እውን የሚኾንበት የህይወት ጎዳና አለ። 

ይኽ ቃል የስንዴ ቅንጣት ክርስቶስ ነው። ሞቶ በሞቱ ድል ሲነስቶ ሲነሣ ሙታንን ያስነሳቸዋል። ሰውም በሞት በኩል ወደ ትንሣኤ ይመጣል ማለቱ ነበር። 

ንዋይ ካሳሁን 

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 11:48


ከእውነት ጋራ ለመጣላት የሐሰት ወገን መሆን ይጠይቃል። ከእውነትም ከሐሰትም መካከል ላይ መኖር ግን አይቻልም። የሰው ልጅ ከሁለት በላይ ምርጫ የለውም።

መኖር- መሞት
ኅዘን- ደስታ
ሲኦል-ገነት
እውነት-ሐሰት
ሰይጣን- መልአክ....
ማዕከላዊ ልኹን ቢባል እንኳን ቁጥሩ ከፈዘዙት የዲያብሎስ ነገድ አይነቶች ነው።

@ምሥራቀ ጸሐይ ጉባዔ ቤት

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 11:36


ራስን መፈተኛ ነው!!
የጌታ ጥያቄ የሰው የሕይወቱ ቁልፍ ጥያቄ

"ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል"

ሰዎች ምን ይሉሃል?
ጓደኞችህ ማን ነህ ይሉሃል?
አንተስ ራስህን ማን ትለዋለኽ?
ድርጊቶችኽስ ማን ነህ ይሉሃል? ልዩነቱን ፈልጎ መሙላትስ?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Dec, 01:50


"ስንፍናን ትኅትና አታድርጓት"

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Dec, 22:05


"ጠላት ቅጥርህን ሲሻገር ካላወቅህ ችግሩ ያንተ ነው። ጠላትህን እወቀው እወቅበት ተከላከለው ግን ውደደው። እባብን የምንፈራው ስለምንጠላው ነው"

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Dec, 21:52


"ጠላት ቅጥርህን ሲሻገር ካላወቅህ ችግሩ ያንተ ነው። ጠላትህን እወቀው እወቅበት ተከላከለው ግን ውደደው"

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Dec, 16:13


ማነው ገዳዩ?

ዳኒ "እሺ የኦርቶዶክስ አማኞችን የሚገድለው መንግሥት ነው" ምስክርነቱን ሰጥቶናል። ሌላ ገዳይ ማን ይኾን? የሚገድለው ይታወቃል አለን። ለምን ሌላ ካለ አይናገርም?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Dec, 16:01


"ሰይጣን ጽድቅህን እያስታወስክ ኃጢአትህን እንድትዘነጋ ያሳስብሀል"

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Dec, 15:37


"ጽድቅኽንና መልካም ድርጊቶችኽን እርሳ ክፋትህን ኃጢአትህን አስታውስ"

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21 Nov, 02:31


https://youtu.be/2S46vQLgXPM?si=gFVG0StGNg5c0Mow

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21 Nov, 02:17


ትንቢት!!

አብይ እድሜ ካገኘ መርካቶ መካከል ቤተ ክርስቲያን እና መስጊድ በጋራ የያዘ ትልቅ የአምልኮ ስፍራ ይገነባል!!

ንዋይ ካሳሁን
ኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 21:45


https://youtu.be/2S46vQLgXPM?si=hgyFT9A5_EFr3MFH

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 20:32


ኦሪትና ሐዲስ በንጽጽር

በምድረ በዳ ሙሴ ከእባብ መርዝ እንዲድኑ እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞ ያዘጋጀው የነሐስ እባብ መጨረሻው ምን ኾነ?። የምሳሌውስ ፍጻሜ ምን ነበር? ከነ ማስረጃው።
ቢያንስ የ20 ሰው መልስ እጠብቃለኹ።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 19:51


ከግብጽ ሲወጡ ሙሴ በምድረ በዳ የመራቸው ከ600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ነበሩ። ከነዓን የገቡት ግን ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 19:23


ምርጫ ነው!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 19:17


Dogmatic personality
ሰውነቱ፣ አኗኗሩ፣ ሐሳቡ ዶግማዊ የኾነ ማለት ነው። አቋም አይቀይርም፣ ሐሳብ አያሻሽልም፣ ነገሮችን በተለየ መንገድ አያይም፣ ከሚፈልገው ነገር ውጭ መስማት መሞከር አይፈልግም።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 18:02


እነዚኽ እስረኞች የሚሰቃዩት ታስረው የሚገደሉት ኦርቶዶክስ አማኞች ናቸው። የእስሩ ትእዛዝ የአብይ ነው!! ማስቆም ካልቻልን ገና ብዙ ስቃይ እናያለን።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 17:51


ይኽ ዜና ታስታውሳላችሁ?

ወይስ አብይ ባደረገብን አዚም ረስተን እንደ ትክክል ቆጥረነዋል። በነገራችን ላይ የዚኽ ንግግር ውጤት የሃምሳ ሰዎች እስሩ መጨረሻ ምን ደረሰ? የገረመኝ ደግሞ ዜናውን አንባቢው ራሱ "የጊቢ ጉባዔ ፍሬ" ከሚባሉት አልጫ ኦርቶዶክሳውያን መካከል መኾኑ ነው። አይ እንጀራና ሃይማኖት!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 16:55


መጽሐፍ ቅዱስ እንማር

ከእስር ቤት ቀጥታ ወደ ንግሥና የተወሰደው ሰው ዮሴፍ ነው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 16:52


መጽሐፍ ቅዱስ እንማር

ሁለት ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በ ወሊድ ላይ እያሉ ሞተዋል፦

1. ራሄል ቢንያምን ስትወልድ ሞተች (ዘፍ 35፤ 16-19)

2. የፌንያስ ሚስት ኢካቦድን ስትወልድ ሞተች (1ሳሙ 4፤ 19-22)

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 15:45


"እንደ ሐሞት እስክትመር ድረስ እውነትን ተናገር" መጽሐፈ ወቅሪስ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 14:46


ቤተ ክህነትም፣ ሀገረ ስብከቱም፣ ማኅበረ ቅዱሳንም ይኽንን አይነግሩንም እርዳታ ግን ይለምኑባቸዋል። ፕሮጀክት ይቀርጸባቸዋል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 14:36


ወንድሜ ዳንኤል ጥቂቶች የምናውቀውን ብዙዎች የማያውቁትን ጉዳይ በጥቂቱ የነገረን። በአጭሩ ቤተክህነትም ማኅበረ ቅዱሳንም ሕወሃት ይመራው እንደ ነበር ከእርሱ በላይ ምስክር የለም። ይኽንን ለማስረዳት በእጄ ያለ ዶክመንት አለ። የማኅበሩ አባላት 95% የኢህአዴግ አባላት መኾናቸውን። ሳላቀርበው ዳኒ በአጭሩ ነገረልኝ።
ዛሬስ ነው ጥያቄው? በዳንኤል የማይዘወር ማኅበረ ቅዱሳን አለ?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 13:37


የሰውን መገኛ ተልዕኮ እና መድረሻ በግልጽ የሚናገር መጽሐፍ "መጽሐፍ ቅዱስ" ብቻ ነው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 13:34


በመጽሐፍ ቅዱስ ከሴቶች ብዙ ጊዜ የተጠቀሰችው "ሳራ" ስትሆን ከሃምሳ (50) ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች። "ራሄል" ደግሞ ኹለተኛዋ ስትሆን ከአርባ (40) ጊዜ በላይ ተጠቅሳለች።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Nov, 13:32


መጽሐፍ ቅዱስ እውነታዎች

አኹን በምድር ላይ የሚታየው ሕዝብ ኹሉ የመጣው ከኖህ ሦስት ልጆች ከሴም፣ ከካምና፣ ከያፌት ነው።

"ኖኅም ሦስት ልጆችን ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ።" ዘፍ.6:10

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

19 Nov, 20:39


ኦሪትና ነቢያትን ለመሻር አልመጣኹም


ሕግን የፈጸመው ግን በአንድ መንገድ ብቻ አይደለም፤ በኹለተኛና በሦስተኛ መንገድም ጭምር ነው እንጂ፡፡ የመጀመሪያው መንገድ በኦሪት የተሰጡትን ትእዛዛት ኹሉ ባለማፍረስ ፈጽሞአቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ ኹሉንም ለመፈጸሙ እርሱ ራሱ ለመጥምቁ ዮሐንስ ምን እንዳለው አድምጥ፣ እንዲህ ያለውን፡- “እንዲህ ጽድቅን ኹሉ መፈጸም ይገባናልና" (ማቴ.3፡15)፡፡ 

ለአይሁድም፡- “ስለ ኃጢአት ከእናንተ የሚወቅሰኝ ማን ነው?" ብሎአቸዋል (ዮሐ.8፡46)፡፡ ዳግመኛም ለደቀ መዛሙርቱ፡- “የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም ምንም አያገኝም” ብሎአቸዋል ዮሐ.14፡30፡፡ ነቢዩም ይህን በማስመልከት ገና ከመጀመሪያው፡- “ኃጢአትን አላደረገም” ብሎአል። ኢሳ.53፡9

“ሕግን ፈጽሞአል” የምንልበት አንዱ መንገድ እንግዲህ በዚህ ረገድ ነው፡፡ ሌላው “ሕግን ፈጽሞአል" የምንልበት መንገድ ደግሞ በእኛ በኩል የሚፈጽመው ነው። ዕፁብ ድንቅ የሚያሰኘውም ይህ ነው፡- ሕግን የፈጸመው እርሱ ብቻ ሳይኾን እኛም እንድንፈጽመው ሰጥቶናልና፡፡ 

ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ግልፅ ሲያደርገው፡- “የኦሪት ጽድቅ ፍጻሜስ ለሚያምኑበት ኹሉ በክርስቶስ ማመን ነው' ብሎአል። ሮሜ.10፡4 ዳግመኛም፡- “በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ" አለ ሮሜ.8፡3-4። ጨምሮም፡- “እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አንሽርም፤ ሕገ ኦሪትን እናጸናለን እንጂ" ብሎአል። ሮሜ.3፡31

 ሕገ ኦሪት ትጥር የነበረው ሰውን ጻድቅ ለማድረግ ነበርና፡፡ ነገር ግን ኃይል ስላልነበራት እርሱ መጥቶ በእምነት ሕግ ኃይልን እንድታገኝ አድርጎ የምትሻውን እንድትፈጽም አደረጋት፡፡ ኦሪት በጽሕፈት ያልተቻላትን በእምነት ሕግ ማከናወን እንድትችል አደረጋት፡፡ “እኔ ሕግን ልሽር አልመጣሁም” ያለው ለዚህ ነውና፡፡

አንድ ሰው አጥብቆ የሚጠይቅ ከኾነ ሕግ የተፈጸመበትን ሦስተኛ መንገድም ያገኛል፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው? ቀጥሎ ሊሰጣቸው ባለው ሕገ ሐዲስ ነው፡፡

ቀጥሎ የሚሰጣቸው ትእዛዛቱ የቀደሙትን ትእዛዛት የሚሽሩ ሳይኾኑ ይበልጥ የሚያጸኑ ነበሩና፡፡ ለምሳሌ “አትግደል” የሚለው ሕግ “አትቈጣ' በሚል ሕግ ይበልጥ ጸና (ጠነከረ) እንጂ አልተሻረምና፡፡ ሌሎችም እንደዚሁ ይበልጥ ጸንተዋል፤ ፍጹማን ኾነዋል፡፡

በመኾኑም እንደምትመለከተው ከዚህ በፊት ማንም በማያስተውለው መልኩ ይህንኑ ዘር በልቡናቸው እርሻ ላይ ስለ ዘራ የኦሪትንና የወንጌል ትእዛዛትን ማነጻጸር በሚጀምርበት አንቀጽ ላይ ሲደርስ ኦሪትን እየተቃወመ እንደ ኾነ ማንም እንዳያስብ ለዚህ የሚኾን መድኃኒት ሰጣቸው፡፡ በምሥጢርም ቢኾን ቀድሞውኑ በተናገረው ይህን ዘር ዘርቶባቸው ነበርና፡፡ ለምሳሌ፡-

“በመንፈስ ድኾች የኾኑ ብፁዓን ናቸው" ያለው ልንቈጣ እንደማይገባን ከተናገረው ጋር ተመሳሳይ ነውና፤

“ልበ ንጹሃን ብፁዓን ናቸው” የሚለው “ወደ ሴት አይቶ" ካለመመኘት ጋር ተመሳሳይ ነውና፤

“ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቈፍረው በሚሰርቁት ዘንድ" መዝገብ አለመሰብሰብ “የሚምሩ ብፁዓን ናቸው” ከሚለው ጋር አንድ ኅብረ መልክ አለውና


“የሚያዝኑ”፣ “ሲነቅፉአችሁ” እና “ሲያሳድዱአችሁ" በእኔም የሚለው “በጠበበው ደጅ” ከመግባት ጋር የሚስማማ ነውና፤

“ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው” የሚለውም “ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ኹሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው” ማለት እንጂ ሌላ ምንም አይደለምና፤

“የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው” ብሎ የተናገረውም፥ በመሠዊያው ላይ መባን ትቶ በመኼድ አስቀድሞ ከወንድም ጋር መታረቅ እንደሚገባ ከተናገረውና “ከባለጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ” ካለው ጋር ከሞላ ጎደል ያው ነውና፡፡


@የማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ተርጓሚ ገ/እግዚአብሔር ኪዶ)

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

19 Nov, 17:55


እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ” ማቴ.5፡17

እንዲኽ ብሎ የተናገረው ለምንድን ነው? “ሕግንና ነቢያትን ለመሻር መጥተሃል” ብሎ ማን ጠረጠረው? ወይም ማን ልትሽር መጥተሃል ብሎ ከስሶት ነው ይኽን መልስ የሰጠው? አስቀድሞ በተናገረው ነገር እንደዚህ ያለ ጥርጣሬ አልተነሣምና፡፡ ሰዎች የዋሃን፣ ትሑታን፣ ርኅሩኀን፣ ልበ ንጹሃን እንደዚሁም ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ እንዲኾኑ ማዘዝ ማስተማር እንዲያውም ሕግንና ነቢያትን ማጽናት እንጂ መሻርን አያመለክትምና፡፡

ታዲያ ጌታችን ይህን ያለው ከምን አንጻር ሊኾን ይችላል? ይህንን የተናገረው እንዲሁ ወይም በከንቱ አልነበረም፡፡ ይልቁንም ቀጥሎ በብሉይ ከተሰጡት ትእዛዛት ይልቅ አሁን ጠንከር የሚሉ ትእዛዛትን ሊሰጣቸው ስለ ኾነ፥ ለምሳሌ “ለቀደሙት አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፥ እኔ ግን እላችኋለሁ ቍጣም ቢኾን አትቈጡ” ብሎ ሊነግራቸው ስለ ኾነ። ማቴ.5፡22 

ግሩምና ልዑል የኾነ ትምህርት ሊያስተምራቸው ስለ ኾነ፥ ስማዕያኑ ይኽን እንግዳ ነገር ሲሰሙ በነፍሳቸው እንዳይታወኩ ወይም የሚያስተምራቸውን ነገር እንዲሁ ወደ መቃወም እንዳይገቡ ብሎ አስቦ አስቀድሞ ልቡናቸውን በዚኽ መንገድ ሲያዘጋጅ ነው፡፡

አይሁድ፥ ምንም እንኳን ሕጉን የማይፈጽሙት የነበሩ ቢኾኑም በሕሊናቸው ግን ክብር ነበራቸውና፡፡ ምንም እንኳን ዕለት ዕለት በገቢር ይሽሩት የነበሩ ቢኾኑም፥ በፊደል ደረጃ ምንም እንዲነካ አይሹም ነበርና፤ ከተጻፈው በላይ ማንም እንዲጨምርበት አይፈልጉም ነበርና፡፡ እንዲያውም ለልማት ያይደለ ለባሰ ጥፋት ኾነባቸው እንጂ ከተሰጣቸው ሕግ ጋርም (እርሱን ለመጠበቅ ብለው አስበው) ሌላ የራሳቸውን ወግ ጨምረዉበት ነበርና፡፡ እንደዚኽ በማድረግ ለምሳሌ ለወላጆች ሊሰጥ ይገባው የነበረው ክብር ለራሳቸው ይወስዱት ነበርና፡፡ ሌሎችም እንደዚሁ እነርሱ ሕጉን ላለመፈጸማቸው ነጻ የሚያደርጋቸውን አለአግባብ ይጨምሩ ነበርና፡፡

ስለዚኽ በመጀመሪያ ደረጃ ጌታችን ክርስቶስ ከካህናት ወገን ስላልነበረ ዕብ.7፡11 በተጨማሪም ቀጥሎ ሊነግራቸው ያሉት ሕጎች የቀደመውን ሕገ ኦሪትን የሚሽሩ ሳይኾኑ የሚያጠነክሩ ቢኾኑም ቅሉ ከአፍአ ሲታዩ ጭማሪ ስለሚመስሉ፥ እነዚህ ኹሉ ነገሮች ሊያውኩአቸው እንደሚችሉ ዐውቆ እነዚህን ወርቃማ ሕጎች (ወንጌልን) በሕሊናቸው ጓዳ በልቡናቸው ሰሌዳ ከመጻፉ በፊት፥ የሚጻፉበትን የልቡናቸው ጽላት ወለወለው፤ ሰነገለው፡፡ 

አስቀድሞ በልቡናቸው ጽላት ላይ የነበረውና ሊሰጣቸው ላለው ሕግ ዕንቅፋት ሊኾን የነበረውስ ምንድን ነበር?

 እንደ እነርሱ አሳብ ጌታችን እነዚህን ሕጎች ሲናገር የነበረው ሕግንና ነቢያትን ከመሻር አንጻር ነበር፡፡ ጌታችን እንግዲህ የፈወሰው ይህን ጥርጣሬአቸውን ነበር፡፡ ይህን ያደረገውም እዚህ ብቻ ሳይኾን ሌላም ቦታ ላይ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ተቃዋሚ እንደ ኾነ አድርገው ይቈጥሩት ስለ ነበር፥ ለምሳሌ “ሰንበትን አያከብርም” ይሉ ስለ ነበር፥ እንደዚህ ያለ ጥርጣሬአቸውን ሊፈውስላቸው ሽቶ አንዳንድ ጊዜ ጸሎት አቀረበ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ምሳሌ “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል፥ እኔም ደግሞ እሠራለሁ” በማለት ለባሕርዩ እንደሚስማማ አድርጎ ፈጸመ። ዮሐ.5፡17

አንዳንድ ጊዜ ግን (ጸሎት አቀረበ እንዳልሁት የመሰለ) በውስጣቸው እጅግ ከፍ ያለ አትሕቶ ርእስ ያለባቸውን ነገሮች ይፈጽም ነበር፡፡ ለምሳሌ በሰንበት የጠፋ በግን ስለ ማውጣት ሲናገር ማቴ.12፡11 ሕጉ ይጸና ዘንድ መደፍረሱን ሲጠቁም፣ ስለ መገረዝም ሲጠቅስ ያው ጥርጣሬያቸውን ሲፈውስ ነው።

በመኾኑም የእግዚአብሔር ተቃዋሚ እንደ ኾነ አድርገው እንዳያስቡት ሽቶ ብዙ ጊዜ ለመለኮታዊ ባሕርይው የማይስማሙ ቃላትን (በአትሕቶ ርእስ) ሲናገር እናየዋለን፡፡

በመኾኑም ለባሕርይው የማይስማሙና እጅግ ዝቅ ባለ መንገድ የተናገራቸው ብዙ ናቸው፡፡ እዚህም ላይ ከአፍአ ሲታይ ጭማሪ የሚመስልን ሕግ ሊናገር ስለ ኾነ አስቀድሞ በሕሊናቸው ሊፈጠር የሚችለውን ጥርጣሬ ያስወግድ ዘንድ ብዙ ነገሮችን ተናገረ፡፡ “ሕግን አልሻርሁም” ብሎ የተናገረው አንድ ጊዜ ብቻ አይደለምና፡፡ ይህን ደግሞ ደጋግሞ ተናግሮታል እንጂ፡፡ በዚሁም ላይ ሌላና ታላቅ የኾነ ነገር ጨምሮ ተናግሮአል፤ “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ" በሚለው ቃል ላይ፡- “ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም” ሲልም ጨምሮ ተናግሮአል፡፡

ይህ ቃሉም የአይሁድን እልኸኝነት ብቻ ሳይኾን “ብሉይ ኪዳን የዲያብሎስ (የክፉ አምላክ) ሕግ ነው" ብለው የሚናገሩ ሐራ ጥቃዎችንም አፋቸውን የሚዘጋ ነው። ጌታችን የመጣው ዲያብሎስን ለመሻር ከኾነ᎙ ይህ ሕግ ያልተሻረው ይልቁንም በእርሱ በራሱ በጌታችን የተፈጸመው እንዴት ነው? በቂ የነበረ ቢኾንም ቅሉ “ለመሻር አልመጣሁም አላለምና፤ ልፈጽም እንጂ" በማለት የመቃወም ሳይኾን ይበልጥ የማጽናት ኃይለ ቃል ተናግሮአልና፡፡

“ያልሻረውስ እንዴት ነው? ሕግንና ነቢያትን የፈጸመው እንዴት ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ ስለ እርሱ የተባለውን በሥራ ሲያከናውነው ነቢያትን ፈጽሞአቸዋል፡፡ ስለ ኾነም ወንጌላዊው በተለያየ ቦታ ላይ፡- “በነቢይ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ኾኖአል” ብሎአል፡፡ ለምሳሌ ጌታችን ሲወለድ ማቴ.1፡22-23፣ ሕፃናት “ሆሣዕና በአርያም'' እያሉ ሲዘምሩና በአህያ ላይ ሲቀመጥ ማቴ.21፡5-16፣ እንደዚሁም እነዚህን በመሰሉ በሌሎች ብዙ ኹኔታዎች ላይ ጌታችን በሥራው ነቢያትን ፈጽሞአቸዋል፤ እርሱ ባይመጣ ኹሉም አይፈጸሙም ነበርና፡፡
ይቀጥላል 

@የማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ተርጓሚ ገ/እግዚአብሔር ኪዶ)

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

19 Nov, 16:18


ስሜትህን ሳይሆን እውነትን ተከተል

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

14 Nov, 14:56


እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ የምኖር አንድ ምእመን ወይም ወጣት ሰንበት ተማሪ ብሆን በተለይ አማራ ክልል ያለሁ ወጣት አልያ ሰንበት ተምሪ ብሆንና ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅመውን ለማድረግ ምርጫ ብወስድ ወይም ባደርግ ወጣቱን ሰነበተ ተማሪውን በቤተ ክርቲስያን ዙሪያ ያሉትን ማኅበራት አስተባብሬ ስልጠና ወስጄ ታጥቄ ቤተክርቲስያንን አብነት ተምሪዎችን ለመጠበቅ ጫካ እንደምንገባ ቅንታት አልጠራጠርም። ቆሜ ነጠላ ለብሼ ከበሮ እየመታሁ አልያ "ማርያም ኀዝዘነ ልቡነ ታቀልል" እያልኩ አላለቃቅሳም።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

14 Nov, 13:38


ጸረ ብልጽግና ቤተ ክርስቲያን

የምትደግፈው መሪና ምሪት ከሌለኽ መቃወምህ ብቻ አሸናፊ አያደርግኽም። ይልቁንም ሳታውቀው የጠላትህ ደጋፊ ነው የምትሆነው። የምትነጋገርበት የምትወስንበት መዋቅር አለኽ ወይ? የምትደግፈው መፍትሄ ጠቋሚ አለኽ? ወይስ ቁጭ ብለኽ በዜና እየሰማኽ መቃወም ብቻ ነው? ይኽ ከሆነ ጥሩ የጠላት ደጋፊ ነኽ። 

ሲኖዶስን ብቻ መቃወም መፍትሔ አይደለም። የምትፈልገው ለውጥ እንዲመጣ ምን እየሠራኽ ነው። ሥራው ከግልኽ ይጀምራል። ሌሎችን መቀላቀል ማደራጀት ይጠይቃል። በጥልቀት ማሰብ ይፈልጋል። የተናጠልም የጋራም ሥራ ውጤት ነው። በጋራ ሆን መምክር የግድ ይላል። ብቻውን ሆኖ የተፈራ ብቻውን ሆኖ ያሸነፈ ብቻውንም የተከበረ ማንም የለም። 

“እኔ ውስጥ ውስጡን ነው የምሠራው” የሚልኽ ሰው ውሸቱን ከመኾኑም በላይ መደበቁን ምክንያት እየነገረኽ ነው። 
አብይ በየመድረኩ የሚያደርገው ንግግር የሞኝ ንግግር አይምሰልኽ። “በኢትዮጵያ ክርስትና ብልጽግናን አላመጣም አልጠቀመንም” ሲልኽ ቁጭ ብለኽ ትበሳጫለኽ። ምን እያለን እንደ ኾነ እንኳ ማላመጥ አልቻልንም። ሕንጻዋ ቢፈርስ በመንግሥት አቤቱታዋ ባይሰማ ስለማትጠቅም ነው እያለኽ ነው።ጥሪዋን አትቀበሉ እያላቸው ነው። ከቀበሌ እስከ ክልል። ኦርቶዶክስን በሏት ደብድቧት ማለት ነው። ምክንያቱም ጸረ ልማት ናት። መሬት በወረራ ይዛለች ቀሟት እያለኽ ነው። 

የእርሱ ዓላማ ማፍረስ ነው። የማይፈርስ ነገር የለም። በቅርብ የሚፈርሱ ብዙ ናቸው። ያንን ደግሞ “የሚያስቆመን የሚቆምም ነገር የለም” ብሏል። 
በኢትዮጵያ ከደርግ ጀምሮ የጨቋኝ መጠቀሚያ ናት በማለት ቤተ ክርስቲያን ጎታች ናት፣ የበዝባዦች መሣሪያ ናት በማለት ኖረዋል። 

ይኽ በእንዲኽ እንዳለ ካህኑም ምእመኑም በፍጹም አይቃወምም። በተለይ ኹሉንም ለማድረግ ነጻናት ያለው በውጭ የሚኖረው ክርስቲያን እንኳ እንደ ሞተ ዝንብ ኾኗል። የምንችለውን ኹሉ በር በማንኳኳት መሥራት ሲገባ ስለ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሀገር እንመካከር ሲባል ፓለቲካ ነው ይልሃል። ስንፍናውን ቅድስና አድርጎ ይዞታል። 

“ዋናው መጸለይ ነው” የሚለኝ አላጋጭም አለ። ማነው አትጸልይ ያለው? ጸሎት አይጠቅምም ያለው ማነው። እንዲኽ የሚል ሰው ደግሞ የሚጸልይም አይደለም። የማኅበረሰብ ደመ ነፍሳዊ ሐሳብ ተጠቂ ነው። 

ገበሬ ሳያርስ ዋናው ጸሎት ብቻ ነው ብሎ ቢቀመጥ የሚሰበስበው አዝመራ የለም። ዓመቱን ሙሉ መዝሙር ላጥና ሰንበት ትምህርት ቤት ልማር እያለ የሚዞር ተማሪ ሰኔ ላይ ውጤት መጠበቅ ዘበት ነው። 

እንዴት ያለ ድንቁርና ነው ያሰጠመን። እንዴት ትንሽ እንኳ አይቆረቁረንም። 
ግማሹ ሲኖዶስ ይጠብቃል፣ ሌላው ማኅበረ ቅዱሳን አለልኝ ባይ ነው። ሌላው ፋኖን ይጠብቃል። ይኽ ወረርሽኝ በሽታ ነው። 

ሰው አመዛዛኝ ሕሊና አለው። ኃጢአት ያልኾነውን ኹሉ መንገድ መሄድ ይኖርበታል። ቤተ ክርስቲያንን እያጠፉ ካሉ ጳጳሳት ምንም አትጠብቁ፣ ከማኅበራችሁ ምንም አትጠብቁ እንደ አጥቢያ ምን እናድርግ ብላችሁ ተመካከሩ። በአግባብ ማመጽ ካልቻልክ አላግባብ ማመጽኽ አይቀርም። ያኔ ፈውስ የለኽም። 

ጣልያን ኢትዮጵያን ሲወር እንዲኽ ነው የኾነው። አብዛኛውን ሕዝብ እያጨበጨበ ጣልያንን ተቀብሏቸዋል። ብዙዎችም “ይኽ የክርስቲያን መንግሥት ነው ተቀበሉ” ብለዋል። ጥቂት አርበኞች እነ አበበ አረጋይ፣ በላይ ዘለቀ…መ/ር ገብረ ኢየሱስ ጉባዔ ቤት አጥፈው በየአካባቢው ወደ ጫካ ገብተው መፋለም ጀመሩ። ይኽ ነው አምስት ዓመት በተጋድሎ እንዲያሳልፉ ያደረጋቸው።
ተኝተህ መና ስትጠብቅ በዐይንኽ ፊት ኹሉም ነገር ፈርሶ ብልጭልጭ ፎቅ ታያለኸ። ጸልይ፣ ምክር፣ መክት። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

14 Nov, 13:07


ደብረ ዘይት ወዳሉ ወዳጆቼ ለሰላምታ ደውዬ ነበር። ስለ ቤተክርስቲያን ስለ ሀገር ስለ ኑሮ አወራን። ደብረ ዘይት 20% ብቻ ቤት ሲቀር 80% ከተማው ኹሉም ፈራሽ ነው ተብሏል አሉኝ። እኛም ቀናችንን እየጠበቅን ነው። እየፈረሰባቸው ያሉ ቤተሰቦቻችን ጉዳይ ልብ ይነካል ብለውኛል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

13 Nov, 23:05


በአብይ ድሮን እያለቁ ያሉት እኒኽ ንጹሐን የአማራ ሕዝቦች ናቸው።
እያረሱ የሚበሉ፣ እግዚአብሔርን እንጂ ከመንግሥት ምንም የማይጠብቁ ናቸው። ሰንበት ቤተክርስቲያን ይስማሉ። ኑሯቸውን ይኖራሉ። አብይ ግን እየጨፈጨፋቸው ነው። ለነዚኽ ድምጽ ያለመኾን ግፍ ብቻ ሳይኾን የአብይ ደጋፊነት ነው።
በነገራችን ላይ በዚኽ ስድስት ዓመት ስድስት ሚሉየን ኢትዮጵያውን አልቀዋል። አማራ ሦስት ሚሊየን በላይ።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

13 Nov, 18:58


የሕይወት ባሕር


ንሰሐ ወደ  ክርስቶስ ሕይወት ባሕር መግባት ነው። ከነኃጢአታችን ገብቶ መታጠብ ነው። ዘሎ ገብቶ መንጻት ነው። አንተ ክርስቶስ የውበት ባህር ነህ። ሰው ሁሉ ገብቶ ታጥቦ የሚወጣበት የሚነጻበት ባሕር ሰው ሁሉ ቢገባበት የማይደፈርስ ባህር እርሱ ነው። የተቀባናቸው ሽቱዎች ከሞት አያድኑም፣ ይልቁንም በሽታ ያመጣሉ። በክርስቶስ ስንታጠብ ለሕይወት እንነጻለን። ነፍሳችን ትደሰታለች። ስንናዘዘ ነፍስ ትነጻለች። ለክብራችን አንጨነቅ። 

ፓሊስ እጅ የገባ ወንጀል አይደመሰሰም። ክርስቶስ እጅ የገባ ደብዳቤ ባሕር የገባ ወረቀት ነው። ስንበላው ደረቅነታችን ይለመልማል።  ፍሬ አልባ የሆነውን ያለመልማል። የሕይወት ውኃ ነው። ስሙ ቁርባኑ ቃሉ ሲፈስብን ሕይወት እናፈራለን። 
ስለ እግዚአብሔር የተጻፈ ንባብ በመሸምደድ አያድንም እየጸለዩ የማይቆርቡ ካልኾነ። ከመማር በኋላ መመገብ ይገባል። ፍቅር ያለው አዘውትሮ ክርስቶስን ይመገበዋል። 

ኃጢአታችን የሚደምሰስበት ዓለት ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ የሕይወት ባሕር ነው። 

ንሰሐ መግባት ከክርስቶስ ግርፋት መሳተፍ ነው። ኃጢአተኛ ነኝ ስንል ስድቡን እንሳተፋለን። ኃጢአተኛ ተብሏል። ቀኖና ግርፋቱ በረከት እንጂ ለኃጢአት ቅጣት አይበቃም። 

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

13 Nov, 15:17


ዲያቆናት ኾነን የምንይዛት ሚዳቋ ናት። ቤተክርስቲያኑና ቤተልሔሙ በጫካ የተከበበ ነበር። መምሬ ኃይለ ሥላሴ "አንተ ዲያቆን በጌታ ልደት የዘለችውን ሚዳቋ" እንዳታጠምድ ይሉኝ ነበር። ❤️❤️

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

13 Nov, 14:48


ለኹሉም ትምህርት እንዴት እንግዳ እንደኾንን ይገርመኛል። አንዳንድ መምህራንማ "ተማርን" ባለ ቁጥር እየደነቆሩ ይሄዳሉ መሰለኝ ገበሬ አስደንግጥ መልስ ይሰጣሉ። ከማን ተማሩ ምንድነው ያነበቡት ያሰኛል።
የረቀቀ ትምህርት ቢያከራክር ግድ የለም። ትክክልም ነው። ተራ ያውም ጥቅም እንኳ የሌለው እንዴት ግራ ይገባናል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

13 Nov, 14:28


ያኖሩት እንቅርት እንዲባል ከሦስት ዓመት በፊት የተጻፈች ናት👆👆👆

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Nov, 17:14


ሕልምኽን መንፈሳዊ ማድረግ

አልጫነት ከመሠረቱ የሚመሠረተው በተረትና በሕልም ነው። በዚኽ ወጣትነት ጊዜ ጎንበስ ብሎ ቃለ እግዚአብሔር የምትማርበት እድሜ ነው። ነጠላ ለብሶ ያለጨ (አልጫ የኾነ) ማለት ይኽ ነው። ጊቢ ጉባዔ ተማርኩም ብሎ አልጫ የሚኾነው እንዲኽ ነው። 

ሕልም አየሁ ብላ ባል ልትመርጥ ነው። ያውም ዩቲበኛ ናት። live ቀራጩ ደግሞ ካሜራ ማን ሳይኾን ራሱ “ጊዮርጉስ” መኾኑ ነው። በጣም ያሳዝናል። ጠያቁው ደግሞ ይገርማል ተመስጦ እንደ እውነት መስማቱ። 

አርፋችሁ ቃለ እግዚአብሔር ተማሩ። መንፈሳዊነት የሚመስል የጽድቅ ስሜታችሁን ፈትኑ አጥፋት። መሠረታችሁ ቃለ እግዚአብሔር ላይ ይኹን። ደመነፍሳዊ ሕልሙን ሰይጣን የሚጠቀምበት ስለኾነ ተዉት። 

አርሴማ ታየችኝ፣ ማርያም ታየችኝ እያልክ ገዳም ለገዳም መዞር መንፈሳዊ ስሜት በመፍጠር አትባዝን። ሰይጣን ሲጫወትብህ ይኖራል። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Nov, 16:56


"ቤተ ክርስቲያን እኛን ጣለባት እኛም ተባብረን አጠፋናት። ካህናት ነን አገልጋይ ነን ብለን ወደ መቃብር እያወረድናት ነው። ☺️☺️☺️

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

09 Nov, 14:14


አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው ያጸኗት ቤተክርስቲያን በካባ ለባሽ አላዋቂ ካህናትና ምእመናን የምዕራባውያን የተሟጠጠ የሞራል ዝቅጠት ቆሻሻ መጣያ እየኾነች ነው።
እንዲኹም ምእመናን በአሜሪካ በግልጽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ እፍረት ራሳቸውን በዚኽ ግብረ ሰይጣን እያስተዋወቁ እኛም በዝምታና በተባባሪነት ዝም እያልን ነው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Nov, 21:26


ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴን የሰማችሁ ለመጽናናት ሊቀ ብርሃናትን ስሟቸው። ትፈወሳላችሁ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Nov, 21:25


https://youtu.be/pehRwV0R8Ko?si=6GVUSMMxCjDSfexq

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Nov, 15:55


እንዲኽ ሲነቅዝ እርስዎ ወረብ እየውወረቡ ያጅቧቸው የነበሩ አልነበሩ ወይ?
ለአቡነ ጳውሎስን ለምን ይኽንን አላሏቸውም?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Nov, 15:54


ብሳና ይነቅዛል ወይ?

ብሳና የእንጨት አይነት ነው። እናም አንዱ ምን ብሎ ይጠይቃል “ብሳና ይነቅዛል ወይ ብሎ አንዱን ጠየቀው መላሹም “መንቀዝን ለእንጨቶች ኹሉ ያስተማረው ማን ኾነና” አለው። 

ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም በዚኽ ቃለ ምልልሳቸው እዚኽ ግባ የሚባል ቁም ነገር ባይኖረውም በርካታ ገዳዮችን ነካክተዋል። በብዛት እንቶ ፈንቶ ንግግር ነው። 

በእውነቱ ለመናገር በቤተ ክርስቲያን የዜማ ትምህርት ጥርት አድርገው ከተማሩት የአቋቋም መምህራን መካከል ናቸው። ኹሌም ሲያዜሙ ማኅሌት ሲቆሙ ብሰማቸው የማልጠግባቸው ሊቅ ናቸው።

ጉዳዩ ግን ሰው ያለ ሙያው ሲገባ የሚፈጥረው ምስቅልቅል ማሳያ ናቸው። ቤተ ክርስቲያንን የገደሉት ጳጳሳት እያንቆለጳጰሱ የሚያጅቡ ሊቃውንት ናቸው።

በጨዋታ መካከል ኃይለ ሥላሴ የሚደብቁት ነገር የለም። እርሳቸው እንዳሉት ንግግር ላይ ብዙም አይደብቁም። በጣም ሰላምተኛና ተጫዋች ከሰው ለመግባባት የማይቸገሩ ናቸው። ሁሉንም ሰው “ዋይ አንተ ወንድማችን” በመባል ይታወቃሉ። እኔም አብረን ቤተክህነት በሠራሁበት ጊዜ የማውቀው ነው። 

ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ወያኔ አዲስ አበባ ስትገባ ክላሽ በካባ ሥር ይዘው ቤተ ክህነት ከገቡት ጥቂት ካህናተ ሕወሃት መካከል ናቸው። ክህነት ወይም ቅስናም የላቸውም። በቅርቡ ነው መስቀል እንኳ መያዝ የጀመሩት። ሥራቸውን እንኳን እግዚአብሔር ሰውም እኛም እናውቀዋለን። ዝም ቢሉ ይሻል ነበር።

ኪራይ ቤቶች ሳሉ በርካታ ቤቶች ተመልሰዋል። ይኽ ጠቅላላ የቤተ ክርስቲያን የሥራ ሂደት እንጂ አርሰው ቆፍረው ያመጡት አይደለም። ደግሞም በወቅቱ ተደማጭ ናቸው። ሲናገሩ እንደ ካህን ብቻ አይደለም። “ዋይ አንተ ክላሽ ይዘን ተዋግተን ነው ነጻ ያወጣናችሁ” ሊሉም ይችላሉ። 

ብዙ ጊዜ በጨዋታም “ትግል ላይ እያለን” ማለት ይቀናቸዋል። 
ይኽ የተለየ ውዳሴ የሚፈልግም አይደለም። መንግሥት የነጠቃትን ማስመለስ የተቀጠሩበት ደሞዝ የሚበሉበት ሥራ ነው። ባለ ሥልጣናቱም የሚታዘዟቸው ካህን ስለኾኑ ብቻ አይደለም። 

ሊቀ ካህናት ቤቶችን አስመለስኩ ይበሉ እንጂ ራሳቸው የሸጧቸው ቤቶችን ግን አልነገሩንም። ሊነግሩንም አይችሉም። የሚችሉትን ያክል የድርሻቸውን ወስደው ቤቶችን ቸብችበዋል። 

በጣም የሚደንቀው ግን ቤተ ክርስቲያን እድሜ ልካቸውን ስትንከባከባቸው ከፍተኛ ደሞዝ እየከፈለቻቸው እንደ ተበደሉ መናገራቸው ነው። ሰው ሥራ የሚሠራበት ጊዜ ሲያልቅ ጡረታ ይወጣል። ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ጡረታ የወጡት እኔ እዚያው ቤተ ክህነት እያለሁ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ ነው። ብፁዕ አቡነ ፊሊጾስ ሥራ አስኪያጅ ሳሉ ነው። 

ደብዳቤ በደረሳቸው ጊዜ ቁልፍ ይዘው ይጠፋሉ። ቢሮው ይታሸጋል። እሳቸውም ሌላ ወረቀት ይዘው መጥተው ያሽጉታል። በጆሮዬ እየሰማሁ “ለአሻጊም ሌላ አሻጊ አለበት” ሲሉ ሰምቻለሁ። በግብ ግብ የሚችላቸው የለም። ላቷን የተማመነች በግ ማለት ነው። 

ይኹን እንጂ ሊቀ ካህናት በጊዜያዊነት በሚል ከጡረታ በኋላ ቤተክህነት ቀጥሮ እያሠራቸው ቆይቶ በአቡነ ያሬድ ቅጥሩ ተቋርጦ ወጥተዋል። አኹንም የጡረታ ደሞዝ ያገኛሉ። 

ቤተክህነት ያገለገሉ እሳቸው ብቻ ጡረታ የወጡ እሳቸው ብቻ ማስመሰላቸው ይገርማል።

እነ መልአከ ታቦር ተሾመ ዘሪሁን፣ እነ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል፣ እነ ሊቀ ካህናት ብርሃኑ ገብረ አማኑኤል፣ እነ መልአከ ሰላም ዳኛቸው፣ እነ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል፣ እነ ራደ ዓሥራት .... ሁሉም በጡረታ ነው የተሰናበቱት። ምንም አላሉም አመስግነው ነው ቤታቸው የገቡት። 

ታድያ የሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ምንድነው የሚለየው። አዋራ ለማስነሳት ካልኾነ በቀር። በትግራይነቴ እያሉ ማሳበብ። 

በአኹን ሰዓት የቤተ ክህነት የጡረታ ደሞዝ፣ ቅድስት ማርያም፣ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሙያቸው ማሕሌት እየቆሙ ደሞዝ ይከፈላቸዋል። ቤተ ክርስቲያን ከዚኽ በላይ ምን ታድርግላቸው። የእሳቸው መምህራንኮ በረሃብ ነው የሞቱት። አብነት ትምህርት ቤት በረሃብ እየተፈታ ነው። 

ለመኾኑስ የሲኖዶሱ ደካማነት ዛሬ እንዴት ተገለጠላቸው እሳቸው ሠላሳ ዓመትኮ ቤተክህነት ነው የኖሩት። ያኔ ሙስና አልነበረም? ለመኾኑ ሙስና የተጀመረው አቡነ ጳውሎስ እየሰበሰቡ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በበተኗቸው ወሮበሎች አይደለም እንዴ። ከማርስ የመጣ አስመሰሉት። 

ቤተ ክርስቲያን ለዛሬ የደረሰችበት ውድቀት መነሻው ትናንት ነው። ዘረኝነቱ ጎጠኝነቱ የጎሣ ጳጳሳት መሾም የተጀመረው በአቡነ ጳውሎስ ነው። ዛሬ ቤተ ክርስቲያንን በአፍጢም የደፉት ኹሉም የአቡነ ጳውሎስ ተሿሚዎች ናቸው። እሳቸውን ዘወትር እያነሱ ጻድቅና ንፁሕ ማድረግ በራሱ ውሸት ነው። 

“ጳጳሳት ሕግ አውጪ ተርጓሚና አስፈጻሚ ኾነዋል ትክክል አይደለም” ያሉት ትክክል ነው። ግን መቼ ነው የተጀመረው። አቡነ መርቆሬዎስን አባሮ ፓትርያርክ የተሾመው በማን ዘመን ነው። ወያኔ አይደለች። ማነው ቤተክህነት የሙስና ማሽን የተከለው አቡነ ጳውሎስ አይደሉም?።

ከትናንት ጀምሮ የተተከለ በሽታ የዛሬ ማስመሰልና ራስን ንፁህ ማድረግ ትክክል አይደለም። 

ክላሽ አንግተው ቤተ ክርስቲያን ገብተው ሲያበቁ ማመስገን ባይችሉ በአፍጥጢሙ መድፋት ትክክል አይደለም። 
ትግሬ ነኝ በማለት እንዲታዘንላቸው ፈልገው ነው። የዛሬውን ጥላቻ የወለደው የትናንት ሥራቸው ነው። ወያኔ የትግራይ ሕዝብ ያበረከተው ጥላቻን ነው። ዘሩ የተዘራው ሠላሳ ዓመት ነው። 

ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ እነ አባ ሠረቀን ጳጳሳት መኾናቸውን እንደሚቀበሏቸውም ከዚኽ በፊት በዓልን ሄደው መቀሌ ማክበራቸው ቢታወቅም። ቀኖና ጥሰው መወገዛቸውን አይቀበሉም። ይኽ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መክፈል ላይ ትልቁን ሥራ እየሠሩ መኾናቸውን ማስረጃም ነው። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Nov, 13:22


ከስሜት ይልቅ ለእውነት መቆሜን እቀጥላለኹ።
በጣም በስሱ እነካካዋለሁ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

08 Nov, 12:46


"እግዚአብሔር እውቀት ሳይኾን ባሕሪያዊ ማንነት ነው"

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Nov, 23:46


ቤተ ክህነታችን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Nov, 20:35


ዐይናችሁን ገብሩልኝ

ሰው ሲታወር የሚያደርገውን አያውቅም። አጋንንት ልቡን ይሰቅረዋል። ሰው እንስሳ መስሎ ይታየዋል። 

ናዖስ የአሞን ንጉሥ ነው። ሳኦል በኢያቢስ ገለዓድ ላይ አሸንፎታል። ትእቢተኛን ሌላ ከሱ ከፍ ያለ ትዕቢተኛ ልኮ ያስተነፍሰዋል። ቆይቶ የቅዱስ ዳዊት ጓደኛም ኾነ። 1 ሳሙ. 11:1


ናዖስ ለጦርነት የሄደባቸው የኢያቢስ ሰዎች ናዖስን እንዳትወጋን ከእኛ ጋር ቃል ኩዳን አድርግ ብለው ሽምግልና ላኩበት። በጦርነት ከብቦ ከሚያጠፋቸው ስ እርሱ ገዥ እነርሱ ባሮች ኾነው ለመገዛት ፈቀዱ። “የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፦ ቃል ኪዳን አድርግልን፥ እኛም እንገዛልሃለን አሉት።” 1.ሳሙ.11:1

ይኽ የኢያቢስ ሰዎች መገዛታቸውን የተመለከተው ናዖስ ኹሉም ሰዎች ቀኝ ቀኝ ዓይናቸውን እያወጡ እንዲገብሩለት ጠየቀ። 
ግፈኞች እንዲኽ ናቸው። ዓይን የሌላቸው ሕዝቦች ምን ያደርጉለታል። ሌላው እነዚያ ዕውራን እያለ ቢስቅባቸው ምን ይጠቀማል። 

ዐይን ከጠፋ እንደ ባሕር ዛፍ አያቆጠቁጥም። በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ያሳየው ጭካኔ ነው። “አሞናዊውም ናዖስ፦ ቀኝ ዓይናችሁን ሁሉ በማውጣት ቃል ኪዳን አደርግላችኋለሁ፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ ስድብ አደርጋለሁ አላቸው።” 1. ሳሙ.11:2

ሕዝቡ በናዖስ ንግግር በጣም ተረበሹ አዘኑ አለቀሱ። ወደ ሳኦል ላኩበት እርሱን ከገደልክልን እኛ ላንተ እንገዛለን አሉት። ሳኦልን በላያቸው አነገሡት። 

ናዖስንና ሠራዊቱን እንደ በሬ በሰይፍ እየቆራረጠ አጠፋቸው። “በነጋውም ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ወገን አደረጋቸው፤ ወገግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካከል ገቡ፥ ቀትርም እስኪሆን ድረስ አሞናውያንን መቱ፤ የቀሩትም ተበተኑ፥ ሁለትም በአንድ ላይ ሆነው አልቀሩላቸውም።” 1. ሳሙ.11:11

አቢይ ናዖስ ገና ዐይናችሁን ገብሩልኝ ይለናል። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

07 Nov, 14:02


ንጉሠ መዓት ሳኦል

ሳኦል ለዕብራውያን የመጀመሪያ ንጉሥ ሲሆን ለዘመነ ነገሥትም የመጀመሪያ የንጉሥ ነቢይ ነው::

ከጊዜ በኋላ የሚጥል ርኩስ መንፈስ ያደረበት የንጉሥ እብድ በመጥፎ ሥራውም የማይወደድ የሰይጣን ባልደረባ ታሪከ ለመልካም ሥራ በምንም ዓይነት የማይረባ መሪ እንደነበር ዜና ነገሥት ይናገራል::

እንዲህ ሰይጣን የሚጫወትበት የአዕምሮ ችግር, ያለበት ሰው በእሥራኤል ላይ ሊሾም የቻለው እስራኤል ጠግቡው በመሥፍን አድሮ ከጠላት የሚታደጋቸው ከክፉ ነገር የሚጠብቃቸው ፈጣሪያቸውን ንቀው አሕዛባዊ መንግሥት ፤ እንደ አሕዛብ ንጉሥ አንግሥልን ብለው ደገኛው ሳሙኤልን

ስለአስቸገሩት ከፈጣሪው ጋር ተነጋግሮ የጥጋብ ማብረጃ የሚሠራውን የማያውቅ በግብርና በአገዛዝ የሚያስጨንቅ ሳዖልን አንግሶላቸዋል፡

ሳኦልን የመሰሉ ባለሥልጣኖች በየዘመናቱ የሚነሡት የፈጣሪ ቁጣ ሙሆኑን ከሳዖል መረዳት አያዳግትም፡፡ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ተቀብቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ላይ የነገሠው እንዲህ እንደነበር ሳሙኤል መዝግቦልናል፣ 1 ሳሙ. 9፥1-26 ፡፡

ሳኦል በዘመነ መንግሥቱ አንደኛ ከጥጋቡ የተነሣ የሰው ዓይን ያስገብር የነበረ ጨካኙ ዓሞናዊው ናዖስን፣ 1ኛ ሳሙ 11: 1-12

ሁለተኛም ከጭካኔው የተነሳ መጣ ሲባል ያረገዙት የሚያስወርዳቸው ወላጆችን የሚያመክናቸው በአጠቃላይ የእሥራኤልን ሴቶች ልጅ አልባ ያደረገ አማሌቃዊውን መሪ አጋግን፣1 ሳሙ 15:1-35

ሦስተኛም ስድስት ክንድ ከስንዝር የኃጢአት ቅልብ የጣዖት ድልብ የነበረ ረአይታዊ ጎልያድን በዘመኑ እንዲገደል አድርጓል።1.ሳሙ 17: 1-58

እነዚኽን ኃያላን ከገጸ ምድር ያጠፋ ታላቅ የጦር መሪ እንደነበር ስለ ሳዖል ዜና ነገሥት ይመሰክራል። ሳኦል ከዚኽ ባሻገር ሰላማውያን ሕፃናትንና ወላጆችን እንዲሁም አረጋውያንን በመግደል በዘመኑ ብቸኛ ሰው ነው። ሰማንያ አምስት ካህናትን ሽማግሌዎችን ሕጻናትን ገድሏል።
ንጉሡም ዶይቅን፦ አንተ ዞረህ በካህናቱ ላይ ውደቅባቸው አለው። ኤዶማዊውም ዶይቅ ዞሮ በካህናቱ ላይ ወደቀ፥ በዚያም ቀን የበፍታ ኤፉድ የለበሱትን ሰማንያ አምስት ሰዎች ገደለ። የካህናቱም ከተማ ኖብን በሰይፍ ስለት መታ፤ ወንዶችንና ሴቶችንም፥ ብላቴኖችንና ጡት የሚጠቡትን፥ በሬዎችንና አህዮችንም በጎችንም በሰይፍ ስለት ገደለ።” 1ኛ ሳሙ 22÷1-23

እንደ ሳኦል የአዕምሮ ችግር የነበረባቸው ሰው በላ አምባገነኖች የሰይጣን ቡችሎች በርካቶች ናቸው። 

ደገኛው ሳሙኤል ለሳኦል ፈጣሪው ይቅር እንዲለው መላልሶ በልቅሶ የተደገፈ ልመና አቅርቦለት ነበር፡፡ ፈጣሪው ግን አትዘንለት ነው ያለው። 1ኛ ሳሙ. 16.1-6
ምልጃ የማይቋቋመው ኃጢአት ከመሥራት ፈጣሪዬ ሰውረኝ እንበል፡፡

ሳኦል በዚህ ችግር ውስጥ እያለ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ1083 ዓመት እሥራኤልን ቀጥቅጦ በመግዛት በገዛ ሰይፉ ተወግቶ ሞት አይቀርምና ሞቷል ይለናል ዜና ነገሥት።

ሳሙኤል ደገኛ ነቢይ እንደመሆኑ በሳዖል ምክንያት ለዕብራውያን የሚከተለውን ይመክራል ቀደም ሲል በዘመነ መሳፍንት የቅርብ ረዳታቸው ፈጣሪያቸውን ትተው የመሰላቸውን ስለ አመለኩ ለጠላት አሳልፎ አስረከባቸው መከራው ሲጸናባቸው ከኃጢአት ተመልሰው ወደ ፈጣሪያቸው ቢያመለክቱ ጌዴዎንን ባርቅንና ዲቦራን ዮፍታሄን ሳሙኤልን ሾመላቸው አሁንም ሳዖልን አስነስቶ ከጠላት ታድጓች ኖል ጣዖት እንዳታመልኩ ጣዖት ካመለካችሁ ግን እናንተንና ንጉሣችሁን እግዚአብሔር ያጠፋችኋል በማለት ያስጠነቅቃል።

ፍልስጥኤማውያንን ፈርቶ የሳሙኤልን መምጣት ሳይጠብቅ ውሥዋዕትን በማቅረብ በደለ። በአማሌቅ ላይ በተላከ ጊዜ በሙሉ ልቡ ለእግዚአብሔር አልታዘዘም።  ሳሙኤልም “መንግሥትህ አይጸናም። እግዚአብሔር ናቀህ” አለው  ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ክፉ መንፈስ አደረበት። "የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው።" ይላል 1 ሳሙ.16:14

እግዚአብሔር ዳዊትን ለንጉሥነት መምረጡን ባስተዋለ ጊዜ ሳኦል በዳዊት ላይ ቀና በልዩ ልዩ ተንኰል ሊገድለው እየሞከረ ፥ ያሳድደው ነበር። 1ሳሙ. 18: 6-20   ዳዊትን ስለ ረዳው ካህኑን አቤሜሌክንና ሌሎችንም አስገደለ 1ሳሙ. 22: 6-23

ዳዊትን ያሳድድ ነበር እንጂ አልያዘውም   ሁለት ጊዜ ዳዊት ሳኦልን ሳይገድል ራራለት ፤ ሳኦልም መጸጸቱን ገልጦ በድያለሁ አለ።1 ሳሙ. 24: 17 -21 

በመጨረሻም ሞቶ የነበረውን ሳሙኤልን ለመጠየቅ ፡ መናፍስት ጠሪ ወደ ሆነች ሴት በድ ብቅ ሄደ። ሳሙኤል አንተና ልጆችህ ነገ ትሞታላችሁ ባለው ጊዜ በምድር ላይ ወደቀ።

"ሳኦልም ባሪያዎቹን፦ ወደ እርስዋ ሄጄ እጠይቅ ዘንድ መናፍስትን የምትጠራ ሴት ፈልጉልኝ አላቸው፤ ባሪያዎቹም፦ እነሆ፥ መናፍስትን የምትጠራ አንዲት ሴት በዓይንዶር አለች አሉት። ሳኦልም መልኩን ለውጦ ሌላ ልብስም ለብሶ ሄደ፥ ሁለትም ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፥ በሌሊትም ወደ ሴቲቱ መጡ። እርሱም፦ እባክሽ፥ በመናፍስት አምዋርቺልኝ፥ የምልሽንም አስነሽልኝ አላት።" 1ሳሙ 28 1: 20 

በማግሥቱ በፍልስጥኤማውያን ሲሸነፍ ራሱን ገደለ። በእውነትም የሳኦል ውድቀት አሳዛኝ ከመሆኑ በላይ የሚያስፈራ ማስጠንቀቂያ ነው። 
ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በእግር በእግራቸው ተከትለው አባረሩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን ሜልኪሳንም ገደሉ።  ሰልፍም በሳኦል ላይ ጠነከረ፥ ቀስተኞችም አገኙት፤ እርሱም ከቀስተኞቹ የተነሣ እጅግ ተጨነቀ።  ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፦ እነዚህ ቈላፋን መጥተው እንዳይወጉኝና እንዳይሳለቁብኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበርና እንቢ አለ። ሳኦልም ሰይፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።  ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል እንደ ሞተ ባየ ጊዜ እርሱ ደግሞ በሰይፉ ላይ ወደቀ፥ ከእርሱም ጋር ሞተ።” 1. ሳሙ.31:2

ሳሙኤል እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ቢሾመው እርሱ ግን እጅግ ክፉ ኾነ የንጉሥ እብድ ኾነ ከካህን እስከ ሕጻን ኹሉ ይገድል ነበር። በስተመጨረሻ መናፍስትን ይጠይቅ በየሟርተኞች ስፍራ ይዞር ጀመር በስተመጨረሻ ራሱን አጠፋ። የክፉ ሰዎች አሟሟት ይኽ ነው። 
ምንጭ :- አበው ቀደምት ወደኀርት 
             መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበቃላት 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Nov, 22:27


Ethiopia: End the month-long arbitrary detention of thousands in Amhara Region - Amnesty International
https://www.amnesty.org/en/latest/news/2024/11/ethiopia-end-the-month-long-arbitrary-detention-of-thousands-in-amhara-region/

በአብይ የተዘጋጀው የመሰቃያ ቦታ!! ሺዎች እየተሰቃዩበት ሲኾን  ከፍተኛ  የኦርቶዶክስ የአማራ ማሰቃያ ስፍራ ነው። የሚቀር ሰው ዘር የለም!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Nov, 19:14


ባለ ችንካር ምልክቱ ሰው

ኢየሱስ በቆሰለ ትከሻው መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ አድካሚውን ጉዞ ጀመረ። ከእርሱ ጋራ የሚሰቀሉ ሁለት ክፉ አድራጊዎች ነበሩ። የቤተ መቅደስ ካህናት የተፈረደበት ሆኖ ስላገኙት ከኢየሩሳሌም አጋዙት። የኃጢአት መስዋዕት በግ ከከተማው መውጣት ነበረበት። ዘሌ 16:27 

ለኃጢአት መስዋዕት የሆነ ክርስቶስ ከኢየሩሳሌም ተባረረ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከተማዋ ክብሯን አጣችና በሰማያዊ ኢየሩሳሌም ተተካች። እርሱን ሊከተል የሚፈልግ ሁሉ መስቀሉን ተሸክሞ እንዲከተል አሳስቦ ነበር። 

በጣም ደክሞ የነበረ ኢየሱስ በመንገድ ይሞታል ብለው ስለፈሩ ጠላቶቹ ስምዖን የሚባለውን የቀሬና ሰው በማስገደድ መስቀል እንዲሸከም አደረጉ። ጌታችን መስቀሉን በማንኛውም ሰው ላይ ሲያደርግ ይኽ የመጀመሪያ ነበር። መስቀል ለሰው ከባድ ቢሆንም ስምዖን ቀሬናዊ መስቀል በመሸከም እድለኛ ሆነ አንደኛ ክብር አገኘ። 

ጌታችን ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ ሲሄድ ብዙ ሴቶች ተከትለውታል። በመስቀሉ ስር አራት ሴቶች አንድ ከሐዋርያት ወንድ ተገኘ። ሰዎች ስቀለው እያሉ ጮኹ ሴቶች ግን አለቀሱ። ጌታ ለሱ ሳይሆን ለኢየሩሳሌም አልቅሱ አለ። ጌታ ሕማማቱን መስበክ ጀመረ። ወደ ስቅለት ስፍራ ሲደርሱ ልብሱን ገፈፉት። 

በዚያ ጊዜ ልብሱ በደም ተነክሮ ከሥጋው ጋር ተጣብቆ ነበር። መስቀሉ በተዘጋጀ ጊዜ በሦስት ቋንቋዎች ሞትና ንጉሥነት በጊዜው በታወቁ በሦስት ቋንቋዎች ታወጀ። በኋላም በነዚኹ ቋንቋ ወንጌል ተጻፈ። ዮሐ.19:20

የጠፋውን በግ ለመፈለግ የሚሮጡ እግሮቹ በምስማር ታሠሩ። በትንቢት የተነገረው ሁሉ ፍጻሜውን አገኘ። ቅዱስ ዳዊት ምስማርና መዶሻ በጌታ ላይ ስለሚኖራቸው ድርሻ ተንብዮ ነበር። 

ስቅለት ከቅጣት ሁሉ በላይ ስለ ነበር ስሜት የሚያደነዝዝ መጠጥ መስጠት ልማድ ነበርና አቀረቡለት። ጌታ ግን አልተቀበለውም። የአስታራቂነቱን ሥራ የሚፈጽመው ስቃዩን በሙሉ በመቀበል  እንጅ በድንዛዜ አይደለም። ከርቤ በልደቱ መባዕ ተቀበለ በሞቱ ጊዜ የመጣበትን ዓላማ የሚያደነዝዘውን ከርቤ አልተቀበለም። አባቱ የሰጠውን ጽዋ እንደሚጠጣ ለቅዱስ ጴጥሮስ ነግሮት ነበር። መስቀል ላይ ከፍ ብሎ የተሰበሰበውን ሕዝብ አየ። እናቱን ለአዳም ዘር አስረከበ። ለሰቃዮቹ አዘነ።

ዛሬ የክርስቶስን መስቀል ተሸካሚዎች ክርስቲያኖች ናቸው። አማራ፣ ነፍጠኛ፣ ክርስቲያን፣ ባለ ማዕተብ ተብለው እንደ ስምዖን መስቀል ተሸካሚዎች። ሰቃዮች  ክርስቲያን ከሆንክ የራሳቸው ወገንም ብትሆን አይምሩህም። ምክንያቱ ደግሞ የተሸከምከው መስቀል በራሱ ሞት ይጠራብሀል። ያሰቅቅ ይሆናል። ሰብአዊ መብቴ ተጣሰ ትል ይሆናል። ጌታ ከስቅለቱ በኋላ መስቀሉን ላንተ ማቀበሉን አትርሳ። የማንም ጎሳ ወገን ሁን የክርስቶስ መስቀል ብቸኛው መለያህ ነው። "ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው" ሮሜ 8:36

የሌለ በደልህ ለሞትህ እንደ ምክንያት ሲጻፍልህ የጌታ ሞት ትዝ ይበልህ። ለትውልድ የሚታይ የሞትህ ደብዳቤ "ክርስቲያን ስለሆነ" የሚለው ነው። ልጆችህ ዘመዶችህን ሲጠይቁ ክርስቲያን "በመሆኑ ሞተ' ሲሉህ ነፍስህ ደስ ይላታል። በሌብነት፣ በበሽታ፣ በመኪና አደጋ በትንታ ከምትሞት በግፍ መሞትህ ቢያስጨንቅም የተጠራህበት ስም በራሱ ሞት ይጠራብሃልና ደስ ይበልህ። 

የሀገራችን ፖለቲካ ትልቁንና የመጨረሻውን  ችንካር የሚቸነክረው አንተና አንተ (ቤተ ክርስቲያን) ላይ ነው። ባለ ችንካር ሰዎች ነን። ሞታችንን ተሸክመን የምንዞር ነው። ለክርስቲያኖች ደስ የሚል ቀን የሚመች ዓለም ይኖራል ብለህ ካሰብክ ገና መጻሕፍትን አልመረመርክም። ቀኖች ክፉዎች ናቸው ነው የሚለው። 

"የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን" 2ቆሮ.4:10

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

06 Nov, 18:43


ሰልፍ ለውጥ አያመጣም ለሚሉ ሰዎች አንዱ ውጤቱ ይኽንን መፍጠር ነው!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Nov, 20:01


አይደለም ወይ?

ያለ ተግባር ብቻውን ደም በማልቀስ ድንጋይ በመንከስ  የቤተ ክርስቲያን ችግር አይወገድም። አውጥቶ አውርዶ ራስን ሰጥቶ ነገን ተንብዮ በመሥራት ነው እንጂ።

የዘመናት ወረቱን እንደተቀማ ነጋዴ አንገት ደፍቶ ልቡናን አሙቶ ተስፋን አጥቶ በመቆዘም ችግሩ አይፈታም። ትናንትን መሠረት አድርጎ ለነገ የሚደርስ የዓላማ የተግባር ዘርን በመዝራት ነው እንጂ።

እንዲያው ላይሆን ከንቱ እስኪሞት ድረስ እንጀራ ከመፈለግ እስኪሞቱ ድረስ የቤተ ክርስቲያንን ዕረፍት መፈለግ  የተሻለው ዓላማ ነው።

ምክንያቱም መኖራችን እንኳን የሚታወቀው ለፍትህ ለእውነት  እሺ ፦ ለጥፋት እና ለውድመት ግን እንቢ ማለት ስንችል ነው።
ሁሉም ዘመዶች ሁሉም ወገኖቻችን የምቾት ጊዜ ጌጦች ናቸው እንጂ የፍትሕ የእውነት ጊዜ ማደንዘዣዎች  ማስቀየሻዎች አይደሉም።

@ ምሥራቀ ጸሐይ ጉባኤ ቤት

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Nov, 16:16


ሰው መኾን :- ቅውም ማንነት state of bing "እነት" ነው
ብሔር:- ማኅበረሰባዊ ስሪት social construction

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Nov, 15:37


በማን ስልጣን ይኽንን አደረገ?

አብይ በሥልጣኑ ዘመን ገና ስድስት ዓመቱ ነው። ነገር ግን ስልሣ ዓመት የገዛን ያክል ነው ሸክም የኾነብን። አብይ ሥልጣን ላይ ያቆየው ምንድነው?

የሕዝብ ተቀባይነት ኖሮት ነው? አዎ ጥቂት ዓመት በሕዝብ ተደግፏል። አኹን ላይ የቀረ የለም። እሱን መስማት ማየት አይፈልግም። 

ከሥሩ ጠንካራ አመራር አለ? ግማሹን በእርግጫ ግማሹን በጥፊ የሚመታቸው ሚኒስትሮች ነው ያለው። እንደ ሳሎን ውሻ እግሩ ስል የሚቅለሰለስ ብቻ ነው። 

የሚከተለው ርዕዮተ ዓለም ነው? አብይ ርዕዬተ ዓለምም እቅድም የለውም። ውሎና አዳሩ መቃዥት ነው። እንኳን ሀገር እድር የመምራት ብቃት እንኳ የለውም። 


ጥሩ ፓለቲከኛ ኾኖ ነው? በፍጹም አይደለም። ሚናውን የማያውቅ የሚናገረውን እንኳ የማያውቅ ነው። የእርሱ ፓለቲካ ማባላት፣ ማፍረስ፣ መግደል ብቻ ነው። 

ኢትዮጵያን ስለሚወድ ኾኖ ነው? አይደለም። በቃሉ እየደለለ በየቀኑን ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ሰው ነው። በተናገረ ቁጥር ነው ሃገሩን የሚሰድበው። ለማኝ ሕዝብ፣ የማያልፍለት ሕዝብ፣ መሪውን የሚበላ፣ ብልጽግናን የሚጠላ ይለዋል። ለማኝ ሕዝብ ካልክ እሱ የለማኝ ሀገር መሪ መኾኑን እንኳ አያወቅም።

የገነባው ሠራዊት ነው? አይደለም። ፍርስርሱ የወጣ መሄጃ ያጣ ሠራዊት ነው። 

ሰላማዊ መሪ ኾኖ ነው? በፍፁም!! ቀን ከሌሊት ግድያ ስደት ማፈናቀል ለቅሶ ጩኽት መስማት የሚናፍቅ ገዳይ ናዚ ነው።

ሀገሩን ሙሉ በጦርነት ሲያነደው፣ ከከተማ እስከ ገጠር ሲያፈራርሰው ሰው እንዴት ዝም ጭጭ አለ? ማንን ተማምኖ ነው። ታስሮ እንደሚገረፍ ልጅ እንዴት ተሳሰረ?

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Nov, 13:04


https://youtu.be/Uutz00ORs6I?si=3-Rd_S9LDqZNZ9xN

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Nov, 01:31


አብይኮ ልዩ ነው

አብይ ጉደኛኮ ነው። ጳጳሳቱ ወያኔ ተመልሳ ልትመጣ ነው ብለው ነጩ ቤተመንግሥት ገብተው ለምነዋል።

ዛሬ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጧፍ እየነደደች ጭጭ። አብይ ምን መርፌ ነው የወጋቸው😄
የርዕዬተ ዓለም ጳጳሳት። ከግማሽ በላዩ ቦሌ እንዳይደርስ ተባሯል፣ ግማሹም አዋሽ አርባ እንዳልገባ ብለው ተቀምጠዋል። አብይማ ልዩ ነው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

05 Nov, 01:18


በጥንቁልና መንፈስ ከሚያምኑት መካከል ብፁዕ አቡነ ናትናኤል (ዴንቨር ኮሎራዶ) ሊቀ ጳጳስ። በምንኩስና በሆሳዕና ጀምሮ የሚተዋወቁ ሲኾን። በጥንቁልናው ሳይታወቅባቸው የሚሠሩ ናቸው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

04 Nov, 23:01


እንዲኽ ነው እንግዲኽ!!

ጳጳስ ብለን፣ አባት ብለን ፣ይመሩናል ይመክሩናል ብለን የሰበሰብናቸው ከዚኽ የተለዩ አይደሉም። ቤተ ክርስቲያንን ለጠንቋዩ አብይ አስረክበው አፋቸውን ሸብበው የጎሳ ፌደራሊዝም ሲኖዶስ ከመሠረቱ በኋላ ውጭ መጥተው ዋናውን የዶላር ማተሚያ እንዲኽ ያስተዋውቁልሃል። ካናዳ በል ቻለው።

የመልአከ አንከርት ዋና ኪስ ማደለቢያ ኾኗል።
ቤታችን በነዚኽ ዓይነት ጳጳሳት እና ካህናት መከራ እያየች ነው።

መንፈስ ቅዱስ ሲለይኽ በአቢይ መንፈስ ስትጋለብ እንዲኽ ነው። እስከ ዛሬ ይኽ ኹሉ የካህን የመናንያን የአብነት ተማሪዎች የምእመናን ደም በዐይናቸው ፊት ሲፈስ የት ነበሩ? ምነው ዝም አሉ። ዛሬስ ምን ትዝ ቢላቸው ነው ስለ ጠንቃዩ ሊሰብኩን ብቅ ያሉት። Good luck.

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

04 Nov, 15:51


አጋግና  አጋጋውያን 

አማሌቃውያን በሰማርያ በረሃ የሚኖሩ ወራሪ ሕዝቦች ናቸው። ከኢየሩሳሌም በደበብ በኩል ሲኖሩ ከሙሴ ጀምሮ እስከ ሕዝቅያስ ድረስ ኢየሩሳሌምን የሚቃወሙ ነበሩ። ዘጸ.17

አማሌቅ ኤሊፋዝ (የኤሳው ልጅ) የተወለደ ነው። የኤሳው ትውልድ ውስጥ ጎሳ ነው። አማሌቃውንያ ከእስራኤላውያን በዝምድና ሩቅ ናቸው። እስራኤልን ለማጥፋት በመጀመርያ የተነሡ ሕዝቦች ናቸው። 
አማሌቅ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ስም የሚነሳባቸውን ሁሉንም ነገር ለማጥፋት ቆርጠው የተነሡ ነበር። 

በንጉሡ ሳኦል ዘመን እግዚአብሔር አማሌቃውያን ውጋ አለው። በተደጋጋሚ የመለኮት ትዕዛዝ በሳሙኤል አማካኝነት ደርሶታል። "አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል" 1.ሳሙ.15:8

አማሌቃውያን እግዚአብሔርን ባለመፍራት ብዙ ክፉ ዘር ዘርተዋል። ምንም እንኳ እግዚአብሔር ብዙ ቢታገሳቸውም ጥጋበኛ መቀጣቱ አይቀርምና ፍርድ መጣባቸው። 

አጋግ የአማሌቃውያን ንጉሥ ነው። እጅግ ጨካኝ ከመኾኑ የተነሣ ሕጻናትን በመግደል ይደሰት ነበር። እርጉዝ እናቶችን በሕይወት ሳሉ በሰይፍ ሆዳቸውን እየሰነጠቀ የጽንሱ አቀማመጥ እንዴት ነበር እያለ ያያል በስቃያቸው ይቀልድ ነበር። 
ሳኦል አስር ሺኽ ሠራዊት አዘጋጅቶ ዘመተ "ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብጽ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው" 

ሳኦል የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን ከነ ሕይወቱ ማረከው። እግዚአብሔር በሳኦል አልተደሰተም። ማንንም እንዳትምር ሰውንም እንስሳውንም አጥፋ ብሎት ነበር። ሳኦል ግን ከሰው ክፉውን አጋግን ከእንስሳቱ የደለቡትን የአማሌቅ ንብረት ይዞ መጣ እግዚአብሔር አዘነበት። 

እግዚአብሔር ለሳሙኤል ማዘኑን ነገረው ሳኦልን ናቀው። ለምን እንስሳቱን እንደተዋቸው ሲጠየቅ "ለእግዚአብሔር መስዋዕት ይሆናሉ ብዬ ነው አለ" 

እግዚአብሔር አጋግን በሳሙኤል እጅ ሊቀጣው አዘዝው። ደም አፍሳሽ የሚሞተው ደሙ ፈሶ ነው። ደም ማፍሰስ ደም መፍሰስን ይወልዳል። ዘፍ.9:6

ሳሙኤል አጋግን አምጡልኝ አለው። አጋግ ፍርሃት ፍርሃት አለው መቆም አቃተው። ሞት ሸተተው። "ሳሙኤልም፦ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ አለ። አጋግም እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋግም፦ በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን? አለ" 1.ሳሙ.15:32

በሠራዊት በወታደር በመሳሪያ የተከበበ ኹሉ ጀግና አይደለም ሴትና ሕጻናት የገደለ ኹሉ ጀግና አይደለም። ጀግና ማለት ብቻውን ኾኖ በልበ ሙሉነት የሚቆም ማለት ነው። አጋግ ብቻውን ሲኾን ጉልበት ከዳው። በደሉ ታየው። 
የሞት አስከፊነት በትክክል ገባው። "በውኑ ሞት እንደዚኽ መራር ነውን" አለ። ጀግና  ሰው በሰው ሞት ይማራል ፈሪ ሰው በራሱ ሞት ይማራል። 

ብዙ መሪዎች በጦር ሠራዊት ሲከበቡ በመሳሪያ ታጥረው ሲናገሩ ጀግና ይመስላሉ እንጂ ለብቻ ሲያዙ የመጨረሻ ፈሪ ናቸው። 

"ሳሙኤልም፦ ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች አለ፤ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቈራረጠው" ይላል

ሳሙኤል አጋግን በሰይፍ እንደ መስዋዕቱ ቆራረጠው። የአጋግ ታሪክ ተደመደመ።

ዛሬ አጋጋውያን በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቆመው ይፎክራሉ የቤተ ክርስቲያን ጉልላት መስቀል ታቦት ማዕተብ አያሳየን እያሉ ነው። 
የእግዚአብሔርን በዓል ማየት አይፈልጉም። 
አጋጋውያን በሳሙኤል እጅ ገብተዋል። በሕጻናትና እርጉዞች ላይ የሰነዘሩት ስለት በራስቸው አንገት ተሰንዝሯል። 

አጋግ የሰይጣን ቋሚ ግብረ አበር ነበር። ሳሙኤል እንደ መስዋዕት በግ አወራረደው። 
የእኛ አባቶች በአማሌቅ ገንዘብ ይራኮታሉ። ጵጵስና ሹመት የአማሌቅን ገንዘብ እንደ ማትረፍ ተቆጥሯል። ገንዘብ አማሌቅ ኾኖብናል። እግዚአብሔር የአማሌቅን ንብረት ወደ መቅደሱ ወደ ከተማው እንድዲገባ አይፈልግም። 

አጋጋውያን ዋጋቸውን ማግኘታቸው ጥርጥር የለውም። ሴቶችን ልጅ አልባ ሲያደርጋቸው ወላጅን ገድሎ ልጆችን የሙት ልጅ። ልጆችን ገድሎ ወላጅን ያለ ቀባሪ አስቀርቶ ነበር። ሌላው ሲያልቅ እሱና መኳንንቱ ይስቁ ነበር። እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነውና መጣበት ታሪኩን በክፉ ሞት ደመደመው። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

04 Nov, 15:34


አዚም ያደረገብን ማነው?

በጽሑፍም ኾነ በንባብ  ረገድ ነገረ መለኮት ላይ ብቻ ባተኩር የምደሰትበት ርዕስ ነው። ይኹን እንጂ ነገረ መለኮት የምናገርበት አውድም የሃይማኖት መፈጸሚያ ሀገርና ቤተ ክርስቲያን እየፈረሱ እጅን በገዛ ፈቃዳችን ለባርነት መስጠት ተገቢ ባለመኾኑ ቤተ ክርስቲያንንም ሀገርንም መከላከል መጠበቅ ተመሳሳይ ናቸው።

ሰው ሲወለድ ከነርስቱ ይወለዳል። ሲወለድ ሰው ነው። ሲወለድ ግን ተፈጥሮ የምታድለው ነገር አለ። የሚወለድባቸው ቤተሰቦቹ፣ የተወለደበት ሀገር የተወለደበት ቀን ይዞ ይመጣል።

በቆይታ ቋንቋ ይማራል፣ ባሕል ውስጥ ይቀላቀላል፣ ሃይማኖት ይቀበላል። ይኽ እየተሰናሰለ የሰውየው ማንነት እየተሠራ ይሄዳል። ብሔር ወይም ጎሳ ከዚኹ ባሕል ውስጥ የሚሠራ አንድ ንዑስ ማንነት ነው እንጂ ተፈጥሮ አይደለም። ቋንቋም ልምምድ እንጂ ተፈጥሮ አይደለም።

ሰው እያደገ ሲሄድ መማር ማምለክ መገበያየት ማረስ መሥራት ስለሚያስፈልገው መሬት ሀብት ያስፈልገዋል። ሰው መንፈስ ብቻ አይደለም አካላዊም ነው። ለግዙፉ አካል ግዙፍ ሀብትም መሬትም ይኖረዋል። አኹን ይኽንን አካላዊ ሀብት መሬት ሀገር ማሳጣት ላይ ነው። 

አኹን ላይ በጽሑፍ ረገድ ብጽፍ ብዬ የምመኘው ጽሑፍ ብዙ የለም። ደስ ብሎኝ የጻፍኳቸው ከዚኽ በላይ ሌላ ባልጽፍ ደስ የሚሉኝን ነገር መለኮት ጽሑፎችን ጽፌያለኹ። ጽፌ ያለጠፍኳቸው ብዙ ናቸው። ደመ ነፍሴ የሚከለክለኝ ጽኁፍ ብዙ ነው። በንቁ አዕምሮ ጽፌ ደመ ነፍሴ ይከለክለኛል። አንዳንዱ ደግሞ ቀን ይጠብቃሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ማጠናከር ይፈልጋሉ። እኔ መረጃ መስጠት ላይ አላተኩርም ጠባይን ማረቅ ማቃናት ለውጥ ማምጣት ላይ፣ ራስን በማየት ላይ ነው። ለዚኽም ነው ብዙ ሰው ሊወደው የማይችለው። ሰው የሚወደው መረጃ እንጂ ቁም ነገር አይደለም። 


ነገር ግን መጻፍ የማላቆመው ሃገርና ቤተ ክርስቲያን የሚያሳጣኝን ጸረ ሰው፣ ጸረ ነባር፣ ጸረ፣ መንግሥት መዋጋት ስላለብኝ ነው። የምዋጋው ከሰው ልብ ክፋትን ማስወጣት መጋደያ መሣሪያ እውቀት መንገድ በመስጠት ነው።

ሰው ትክክለኛ መጋደያ መሣሪያ ሲያገኝ አሰለጠንከው ማለት ነው። ሰውየው ያንን ሲጠቀመው እየታገለ ነው ማለት ነው። ሰምቶ ዝም ካለ ራሱን ለባርነት አዘጋጅቷል ሸጧል ማለት ነው። 

ሌላው ትምህርት በሰው ልብ የተተከለን ስንፍና፣ ግድ የለሽነትን ይነቅላል። በዚኽ ምክንያት በጥቂቱ ለመጻፍ እሞክራለሁ። የሰሞኑ አጀንዳ  የክፋትን ሥራ ማሳየት ላይ ያተኩራል። በቅርቡ "ለምን ፈዘዝን" በሚል ጥያቄ አንስቼ ነበር። ለዚያ መልስ መንደርደሪያ መስጠት ነው።

መልሱን የነገርኳቸው ሦስት ሰዎች መጠራጠርና መደንገጥ እየኹባቸው። እረ አይኾንም እንደማለት። ነገሩን ማጣጣል። ግን መሞገት አልቻሉም። አንድ የአደባባይ ሊቅ ግን “ለምን ሕዝቡ ፈዘዘ ብዬ ለጠየኳቸው ጥያቄ መልሴን በዝርዝር አስረዳኋቸው "ምን ስትል ይኽንን እሰብክ እንዴትስ እዚኽ ሐሳብ ላይ ደረስክ አሉኝ" ለአንድ ሰዓት አወራኋቸው። ከዚኽ ውጭ መልስ ያለው አይመስለኝም አሉ። እኔም አሉኝ የምላቸውን ማስረጃዎች አቀረብኩላቸው።

በአደባባይ መልሶች እነዚያን በግልጽ አልጽፍላችሁም። ትምህርቶቹን የመሪዎችን ልምምድ በግልጽ እስከ አኹን ያሉትን ለማንሳት እሞክራለኹ።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

04 Nov, 15:33


ትናንት የነበረን የዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ እጅግ ስኬታማ በርካታ ሕዝብ የተገኘበት። የሪፐብሊካን ተመራጮች ተገኝተው ለቤተክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ እንደሚታገሉ ቃል የገቡበት ነው።

ለመታገል የቆረጡ አምስት ካህናት ተገኝተዋል። ጥሩ መልእክትም አስተላልፈዋል። ሳምንትም ይቀጥላል።

ቪዲዮውን በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ድንቁርናዬ ምክንያት አቀራረጹ አልተስካከልም ሳስተካክል እለጥፈዋለሁ።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

03 Nov, 14:27


https://youtu.be/PBrTj0HmpjY?si=SzYHGP7n7S7u9HQG

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

02 Nov, 19:47


https://youtu.be/8493M7cheYQ?si=6LA_2Yzs3cLzMXe9

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

02 Nov, 17:53


የሃገሬ መጥፋት ያሳስበኛል። መገደሉ መሰደዱ ጦርንቱ የሚያሳስባችሁ። ቤተክርስቲያን መውደሟ መድከሟ መከፋፈሏ የሚያሳስባችሁ ኑ!!
የጽድቅ ስሜታችሁ እንደሚጠፋ የሚሰማችዂ ጣድቃኖች አትምጡ። ጥድቃችሁን ተንከባከቡ።

የብልጽግና ካህናንትና ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን የሀገርን ጉዳይ ለመረጃ ያክል የምትፈልጉ አትምጡ።

ሰልፉ ለወገን ድምጽ ለመኾን የስቃይ ስሜቱን በሁለት ሰዓት ቆይታ ለመጋራት እንጂ ለመረጃ ያክል አይደለምና።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

02 Nov, 14:32


መፍትሔው ይኼ ነው። እጅህ ላይ ባለው በራስኽ ራስኽን መከላከል ነው። ትእቢተኛ የሚገባው ቋንቋ በመጣበት መንገድ ማስተናገድ ነው።
ውኃ አትጠጣም ካለኽ የመጠጣት መብትኽን ማስጠበቅ ነው።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

02 Nov, 13:23


የዛሬ ፬ ዓመት ዱባይ ላይ ያደረገው ንግግር ነው። የሞጣ መስጊድን በሚመለከት ተጠይቆ ነው።

አብይ ይደበቀን ነገር የለም። በዚኽ ንግግሩ
፩. ሽማግሌዎቹን ጠርቶ ከብሄር ግጭቱ ቀጥሎ ወደ ቤተክርስቲያን ቃጠሎ እንደሚሄድ ነግሯቸዋል። በቅርቡ ዳንኤል ክብረት በሰጠው ቃለ ምልልስ "አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ግጭት የሚሰማበት ቦታ የለም" ያለው ማረጋገጫ ነው።

፪. ሱዳን ውስጥ የትኛው ቤተክርስቲያን ነው ሙስሊሞች የሰገዱት ?

፫. ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈርስ ሕንጻ ጥቅም እንደሌለው ቀድሞም ያቀደበት መኾኑን ነግሮናል።

፬. ከተቻለ አንድ ትልቅ ሕንጻ ተሠርቶ ክርስቲያን ሙስሊሙ በጋራ አርብና እሑድ ተካፍሎ እንዲጸልይበት ማሰቡን ይገልጻል።

እኛኮ ልዩ ሰዎች ነን። ቁጭ ብለን መፍትሔ አምጪ ነጻ አውጪ የምንጠብቅ።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

02 Nov, 00:35


እስቲ ከልብ እናስብ

የአዲስ አባባ ወጣት በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ዙፋኑን ነቅንቆ ሃገሪቱን እነቃንቆ ማውረድ ችሏል።
በደርግ ዘመን በወጣትነት በርዕዮተ ዓለም ተከፋፍሎ ለመጠፋፋት የወጣትነት እድሜውን ለመስጠት ወደ ኋላ አላለም።
ሕወሃት በአጋዚ ጦር ሳያስፈራው ምክንያት እየጠበቀ በታላላቅ በዓላት ሳይቀር በድንጋይ በመወርወር ጎማ በማቃጠል። በገፍ እየሞተ እንኳ ኢህአዴግን አዳክሟል።

በጎንደር በባሕር ዳር በርካታ ወጣቶች የአጋዚን ጦር በድንጋይ ገጥሞ ብዙ ታግሏል።
ዛሬ ላይ ያ ወጣት ክላሽ መትረየስ ስናይፐር ታጥቋል።
የአዲስ አበባ ወጣት ብርቱካን ሚደቅሳን ለማስፈታት ምርጫ ተጭበርበረ ብሎ ባዶ እጁን ኢህአዴግን አንቀጥቅጧል፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪው እረፍት አልነበረውም።


ታድያ

ዛሬ ምን ኾኖ ነው ባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረ ብርሃን ዝም ጭጭ ያለው?
የአዲስ አበባ ወጣት እንኳን ቤቱ ሊፈርስ ቀርቶ በሰፈሩ ፓትሮል መኪና እንኳ ካለፈ ከባድ ጠብ ያንሡ ነበር።

አብይ ስድስት ዓመት ሙሉ ቤት ዘግቶ በጦርነት ሲፈጀው። ቤቱን ሲያፈስር እያለቃቀሰ ሰፈር ሲለቅ ምን ኾኖ ነው?
ከቄስ እስከ ሼኽ ከተማረ እስከ ገበሬ ምን አዚም አደረገበት? ፓርላማ ላይ እንደፈለገው ሲናገር እንኳን ጦርነት ያለበት ሀገር ቀርቶ ንቀቱ አይጣል ነው።

የዚኽ ጥያቄ ምላሽ ምን ይመስላችኋል። እንዴት አንድ ደፋር እንዲኽ መከራ ያሳየናል?። የእኔን ምላሽ ዘግይቼ እመጣበታለኹ።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

01 Nov, 14:46


ጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ምእመናን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

01 Nov, 14:14


ከአዲስ አበባው ሲኖዶስ የመቀሌው የሕወሃት ውላጅ የተሻለ ሰርቷል😂

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

01 Nov, 13:54


Kickout

አባትና ልጆች ተገናኝተዋል😂 ያዝልቅላቸው። ከዚያ ተያይዘው 4 ኪሎ ይመጣሉ። መካከል ላይ ያሉት እነ አማራ የሚሉትን ጳጳሳት kickout እናደርጋችኋለን እንዲሉ እነ ሳዊሮሳውያን።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

01 Nov, 12:59


ኦርቶዶክስ ለብልጽግና አትመችም። ስለዚኽ አፍርሼ ለብልጽግና እንድትመች አድርጌ እሠራታለሁ ነው።

ይኽንን ንግግር በአመክንዮ ሙግት አቅርቡ!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

01 Nov, 12:57


ችግሩን አንስተው 420 መነኮሳትን የገደለውን አብነት ተማሪዎችን የሚረሽነውን በግልጽ አስቀምጠው መፍትሔው ገዳዩን ለመታገል ያደረጉት ውይይት መስሎኝ ሰማሁት።
ዓላማው ግን ለምን እንገደላለን የሚገድለን የመንግሥት ወታደር ነው የሚል ሳይኾን፣ "ግጭት፣ ወቅታዊ ጉዳይ" በሚል ነው የሚያድበሰብሱት።
ዓላማው ገዳዩን ትቶ ለለቅሶ መድረሻ ስንዴና ዘይት ይዞ መግዣ መጠየቅ ነው።
ችግራችን በዚኽ አይፈታም። ገዳዩን ማስቆም ብቻ ነው። ለውጭ ሀገር በሚኾን መልኩ የተዘጋጀ የልመና ፕሮግራም ነው። ለአሜሪካና አውሮፓ።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Oct, 18:01


ድንግል ማርያምን ማሰብ

ሠላሳ ዓመት ሲሞላው ለእናቱን “አባቴ ለላከኝ ዓላማ ወደ አደባባይ ልወጣ ነው” አላት። እናቱን ትቶ ወደ ማስተማር ወጣ። አንድ ልጇ ከስሯ መለየቱ ሌላ ኀዘን ሌላ ጦር ነው። 

እስራኤልን ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ከሰሜን ወደ ደቡብ በእግሩ እየተዘዋወረ አስተማረ። ከሦስት ዓመት በኋላ በአደባባይ ሊሰቀል ወደ ፍርድ ተወሰደ፣ ልብሱን ገፈው ገረፉት፣ ደሙን ያፈሱት ጀመር። ይኽንን ከቤቷ ተጠርታ መጥታ ስታይ በእውን የሚኾን አልመሰላትም፣ ሊያስገርፈው የሚችል ምንም በደል የለበትም። መከራውን ሕልም እንዲኾን መሰላት፣ ነገሩ ግን እውን መኾኑን ተረዳች አብራ ተሰቃየች። 

በኢየሩሳሌም መሬት ላይ ሲጎትቱት ፊቱን ስታይ ልጇ መኾኑን መልኩን መለየት እንኳ አይቻልም ነበር። በደም ተለውሷል። 

ርኅራኄ የሌለው የሮማ ወታደሮች ግርፋት ልቧ ስር ደርሶ እርሷንም ይሰማት ይገርፋት ነበር። ልብ የሌላቸው የአይሁድ ካህናት ጨካኞች ነበሩ። ድንጋጤ ውስጧ ገብቷል። “እውን ልጄ ነው? እውን ዐይኔ እያየ ነው ይኽንን” አለች። ይኽ በልቧ የሚያልፍ እሾክ ነው። 

የእግዚአብሔር እቅድ ለሚሆነው ኹሉ ታማኝ ኾና ቆመች። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ለአንዲት ቅጽበት ፈቀቅ አላለችም። ልጇን ወደ ጎልጎታ ተከተለችው። ጎልጎታ በእብራይስጥ የራስ ቅል ማለት ነው። በቆመ መስቀል ላይ ልጇ ተሰቅሎ ታያለች። ሰውነቱ ተበጣጥሷል፣ ፊቱ በደም ተሸፍኗል። መልኩን አትለየውም። በዐይኗ ፊት ልጇ በሥጋ ሞተ። 

አረጋዊው ስምዖን በቤተ መቅደስ ያላት ኹሉም ተፈጸመ። “በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።” ሉቃ.2:35

ይኽ ኹሉ ሲኾን ዝም ነው ያለችው። አላመረረችም፣ አልተቆጣችም፣ አልተቀየመችም፣ እግዚአብሔር ይኽንን አደረከኝ ብላ አላማረረችም። ይኽንን ኹሉ በልቧ ታኖረው ነበር። ለእግዚአብሔር ምን ያኽል መታመኗን ያሳያል።  “ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር።” ሉቃ.2:19

አንዲት ስህተት አልፈጸመችም ኃጢአት አልሠራችም። ሰው ኾና ኃጢአት ያልተገኘባት ንፁሕ ናት። 
በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።  በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በልጆች መካከል ነው።"

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Oct, 17:17


አሳስቢ

ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ ።
ድንግል ሆይ በቤተ ልሔም ካአንቺ የተወለደውን መውለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም አሳስቢ።

ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋራ መሰደዱን አሳስቢ።

ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደው ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ አሳስቢ።

ድንግል ሆይ ረኃብና ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ።

ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ።

ለጻድቃን ያይደለ ለኃጣን አሳስቢ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ።

ቅዳሴ ማርያም

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Oct, 16:52


ተገላቢጦሽ
እመቤታችንን ስደት እናስባለን
ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ናት።

እኛ ግን ዝላይ፣ ደስታ ላይ ነን። አበባ ይዘን መዝለል ላይ ነን። ይኽንን ጉዳይ ስናገር ፬ ዓመት ሞላኝ። ማገናዘብ አልቻልንም። ወቅቱን ማንበብ አልቻልንም። ማልቀሻ ጊዜውን መዝለያ ማድረጋችን።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Oct, 15:07


ድንግል ማርያምን ማሰብ

እመቤታችን መልአኩ እንደ ነገራት ጸነሰች። 
በኦሪቱ ሕግ ሳታገባ ብትጸንስ በድንጋይ ያስወግራል። ይኽም ሌላ በልቧ የገባ ኀዘን ነው። በዚኽ ነገር ኹሉ ደግሞ ዝም ነው የምትለው። ነገሩን ለማንም አትናገረውም። 
ለመልአኩ የመለሰችው “ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች።” የሚል ቃል ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ፍቃድ ተቀበለች። 

ጌታን በቤተልሔም ወለደችው። የእግዚአብሔር ልጅ ልጇ ኾነ። የሰማይ ስጦታ ተሰጣት። ወንድ ልጅ ወልጃለሁ በልጄ ደስ ይለኛል ሳትል ገና ኹለት ዓመት ሲሞላው በሔሮድስ አማካኝነት ሌላ የመከራ ዜና ሰማች። ልጇን ሊገድለው እንደሚፈልግ። በግብጽ የበረሃ ልብ ውስጥ ልታልፍ ተነሳች። “እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።” ማቴ.2:13

ሔሮድስ ወታደሮቹን ላከባቸው። ጌታ፣ እመቤታችን፣ ቅዱስ ዮሴፍ፣ ሰሎሜ ከሔሮድስ ያመልጡ ዘንድ ስደት ጀመሩ። ወታደሮቹ ይከተሏቸው ስለ ነበር ምንም እረፍት አልነበራቸውም። ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ከበረሃ ወደ በረሃ ይሸሹ ነበር። ሦስት ዓመት ከስድስት ወር በመከራ አሳለፈች። ንጉሥ ከነሠራዊቱ ያሳድሳታል ልጇንና እርሷን ሊገድል። ዓለም ሊገድላት የሚፈልጋት ብቸኛ ሴት ናት ። ሊያድናት ሊታደጋት የመጣ ማንም የለም። ኹሉም በር ይዘጋባታል። 

በዝምታ ምን ያክል ግዜ አለቀሰች፣? ምን ያኽል እንባ በጉንጯ በዝምታ ወረደ?፣ ምን ያኽል መገፋትን ምን ያኽል መነቀፍን በዝምታ ታገሰች። ይኽ ኹሉ ለዓለም ድኅነት በእርሷ በኩል ያልፍ ስለ ነበር ነው። 

ሰይጣን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚወዱትን ይጠላል ይዋጋል። የሚወዱትን ይኽንን ያክል ከጠላ እናቱን ምን ያኽል እንደሚጠላት መረዳት ያስፈልጋል። ሰይጣን እንደ እመቤታችን የሚጠላው ሰው የለም። የሰይጣንን ራሱን የሚቀጠቅጠውን ወልዳለችና። የእግዚአብሔርን እቅድ ያቆም ዘንድ የሚችለውን ያኽል ተዋግቷታል። ነገር ግን ጸንታ ቆመች። 

ያለፈችበት መንገድ ኹሉ ከአንዱ ጨለማ ወደ ሌላው ጨለማ ዋሻ ተንከራተተች። ማለቂያ 
የሌለውን ጨለማ ለእኛ መዳን አለፈችበት። ሔሮድስ ሲሞት ተመለሰች። “ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦  የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።” ሉቃ.1:19

ናዝሬት ገብተው ተቀመጡ “በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።” ማቴ.2:23

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

31 Oct, 11:53


ድንግል ማርያምን ባሰብኩ ጊዜ

እመቤታችንን ማን ምን እንደኾነች የሚያውቃት እርሱ ልጇ ብቻ ነው። ከእግዚአብሔር ጸጋና ከመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ነው ቅዱሳን እመቤታችንን ክብሯን የተናገሩት። ማወቅም የምንሞክረው በዚኽ መንገድ ብቻ እንጂ ፍጥረት እመቤታችንን በሙሉ ለማወቅ ይቸገራል። ድንግልናዋ፣ ኀዘኗ፣ ትኅትናዋ፣ ተጽእኖ መፍጠሯ፣ ቅድስናዋ ይደንቃል።  


“በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።  በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በልጆች መካከል ነው።” መኃ.2:2

በመጽሐፍ ቅዱስ በምልክት symbolic ወይም በምሳሌ የተጻፉ መጽሐፍት ኹለት ናቸው አንዱ መኃይልየ ሰሎሞን ሲኾን ኹለተኛው ዮሐንስ ራዕይ ነው። 

ኹለቱ መጽሐፍት በምልክት የተጻፉበት ምክንያት እግዚአብሔርን ወይም አምላክን መግለጥ የሚችል አቅም ያለው ቃል ስለሌለ ነው። እውነተኛ የእግዚአብሔር ፍቅር ምን እንዴት እንደኾነ መግለጽ የሚችል ቃል የለም። ብቸኛ መግለጫ መንገዱ ምሳሌያዊ ነው። የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጽ ቃል የለም ራዕይም የሚያሳየን ይኽንን ነው። 

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ልዩ ሰው በመኾኗ መግለጽ የሚቻለው በምሳሌ ነው። 

የእመቤታችን ኀዘን

እመቤታችን ከልደቷ ጀምሮ በመንግሥተ ሰማያት እስከ ገባችበት ጊዜ ያለው ሕይወቷ በኀዘን የተሞላ ጉዞ ነበር። ከቅዱሳን ቤተሰቦች ነው የተወለደችው። ልጅ እንዲሰጣቸው በሽምግልናቸው ሐናና ኢያቄም ተስለው ነው ያገኟት። በተአምር ልጃቸው ማርያምን ሰጣቸው ወለዱ። ስሟ ማርያም ተባለ። ትክክለኛ ቋንቋው አረማይኩ።“መርየም” የሚል ነው። ሕይወቷ ሁሉ እርሷም በኹለንተናዋ ለእግዚአብሔር የተሰጠች ናት። 

ስሟ መሠረቱ በአረማይክ ወይም በእብራይስጥ “ሙራ” ከሚለው ቃል ነው። ሙራ ማለት ዕጽ (ተክል) ሲሆን ሲቀምሱት መራራ ነው። በእሳት ላይ ሲያቃጥሉት ግን መግለጽ የማይቻል እጅግ መልካም መዓዛ ያለው እእንጨት ነው።

የእመቤታችንንም ነገር ሲሰሙት በአራት መዓዝነ ዓለም ሽታው ይደርሳል።  ሕይወቷን ሙሉ በእሳት ውስጥ በመቃጠል አልፋለች። የሦስት ዓመት ሕጻን  እያለች ወላጆቿ በተሳሉት መሠረት ቤተመቅደስ ወስደው ሰጧት። ሴት ልጅ ከሰጠህን ለቤተ መቅደስ አገልግሎት እንሰጣለን ብለው ነበር። መስዋዕት ትኾን ዘንድ ሰጧት። 
ዘፍ.3:15

በቤተ መቅደስ ካሉት ኹሉ ትንሿ ሕጻን እርሷ ናት። “በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።” መኃ.2:2

እሾኽ ይዋጋል ይኽ በእመቤታችን ከሚደርሰው ኀዘን መካከል ነው። ለእመቤታችን የመጀመሪያው ኀዘን በሕጻንነት ከወላጅ መለየቷ ነው። እናትና አባት ምን ማለት እንደኾነ ጣዕሙን ሳታውቅ ተለያት። 

ቤተ መቅደስ አሥራ ኹለት  ዓመት ኖረች። ይኽ እድሜ ደግሞ ለአቅመ ሔዋን የምትደርስበት ስለኾነ ከቤተመቅሰ መውጣት አለባት። ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ነበር አልወጣችም። 
እመቤታችን በቤተመቅደስ ሰዎችን ትትታዘዛለች፣ ታገለግላለች፣ ታጸዳ ነበር። እመቤታችን ቤተመቅደስ ባሳለፈችበት ጊዜ ኹሉ አገልጋይ ነበረች። 

ቤተ መቅደስ ዘወትር ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው የእንስሳት መስዋዕት የሚያቀርቡበት ደም የሚያፈሱበት ነው። እመቤታችን ያን የደም መስዋዕትን የሚያስቀረውን ልጇን ልትወልድ ምድሩን ከደም ልታነጻ እያጠበች ነበር። 

እመቤታችን ከቤተመቅደስ በአሥራ አምስት ዓመቷ ስትወጣ ወላጆቿ በሞት ተለይተዋታል። ሌላው ኀዘን ይኽ ነው። በመካከለኛው ምስራቅ ባሕል አንዲት ልጃገረድ ሳታገባ ብቻዋን መኖር እንደ ነውር ይቆጥረዋል። ካላገባች ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀል አትችልም። 

ቅዱስ ዮሴፍ በጣም ሽማግሌ ነው። ጠባቂዋ ይኾን ዘንድ ተሰጠችው። መልአኩም እርሷን ነገራት “ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።  መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤  ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።  ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።” አላት። ሉቃ.1:34

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

30 Oct, 20:14


የመፈታት፣ የመበተን፣ የመራቆት፣ የመቅለል፣ የመዝረክረክ፣ የመዋረድ ፣ ቅጥር የመፍረስ ዘመን!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

30 Oct, 00:00


ወይ 3H

ትንሽ ፈታ ብላችሁ ተኙ። ከዛሬ ፬ ዓመት ገደማ ምነው ዳንኤል ጠበል ቢወስደው ብዬ ነበር። ራሱ ዳንኤል ጠበል የሚወሰድ ኾኑ።

በደንብ እንድንስቅ ነው ለካ ቤት የሚያፈርሰው፣ በድሮን የሚገለን።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

29 Oct, 22:18


የቤተሰብ ጠላቶች

፩ ሰይጣን
፪ ግለሰባዊ ጠባይ፣ እውቀት፣ ብስለት ማጣት
፫ ሥልጣኔ

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

29 Oct, 20:35


ስለ ቁልቢ ገብርኤል

ብዙ ሰው የሚያውቀው አይመስለኝም ካወቀም አይናገረውም ይንሾካሾካል። በተለይ ልጅ መውለድ አንችልም ያሉ ሰዎች "ቀልቢ ገብርኤል ሄዳችሁ ግቢው ውስጥ ግብረ ሥጋ ግንኙነት አድርጉ" የሚል ወሬ ከሰው ይሱማሉ።
ይኽ ከፍተኛ የአጋንንት ሥራ ነው። መናፍስት ቦታውን ሲዋጋ ሰዉን በንግስ ስም ዩሚያረክስበት መንገድ ነው።
ሰይጣን ቁልቢ ላይ ድል ስለኾነ በዚኽ ምክንያት ሰዉን ያረክሰዋል። ቁጣን ይጠራል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

25 Oct, 16:55


"መልካም ሰዎችን የተሳሳተና መጥፎ መረጃ ብትሰጣቸው ውጤቱም የተሳሳተ ነው"

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

25 Oct, 15:19


የሕወሃት ፍልፍል የዘር መነኮሳት!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

25 Oct, 13:25


ዓርብ

የፍጥረት መካተቻ ሰው ነው። እግዚአብሔር ሰውን የፍጥረታት ዘውድ አድርጎ ሲፈጥረው ደስ ተሰኘ። ሰማይና ምድርን ፈጥሮ ደስ አላለውም፣ አንበሳና ነብር ፈጥሮ ደስ አላለውም። ደስ ያለው ሰውን ሲፈጥር ደስ አለው። የእግዚአብሔር ልብ ያረፈው በሰው መፈጠር ነው። እግዚአብሔር ደስ የተሰኘው መልኩን ሲፈጥር ሲያይ ነው። "እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው" ዘፍ.1:27

እባብ፣ ፈረስ፣ ጅብ ተፈጥሯል ይኽ ሀሉ ለሐሳቡ ማካተቻ ለሆነ ሰው መጠቀሚያ ነው። ሰው ሲፈጠር ፍጥረት ይካተታል። ሰው ሲፈጠር የእግዚአብሔር ምክር ይካተታል። እግዚአብሔር ሰውን ሲያገኝ ልቡ አረፈ። ከእሁድ እስከ ሐሙስ በፈጠረው መልካም ቢሆኑም ልቡ አላረፈም። እግዚአብሔር ሰው በሆነ ሰው ያርፋል።

ዛሬ  ሰው ግማሹ እባብ፣ ዘንዶ፣ ቀብር፣ ጅብ፣እባብ፣ ምስጥ ሆነናል። ሰው ከሆንን የእግዚአብሔር ልብ ያርፋል። እግዚአብሔር ሰው ይፈልጋል። እረፍቱ ሰው ነው።
ሰው ሲናቅ፣ ብረት ሲወደድ እግዚአብሔር ያዝናል። መሬት ከሰው ይልቅ ተወደደ። እግዚአብሔር ለመላእክት ለእንስሳ አልሞተም እግዚአብሔር የሞተው ለሰው ነው።  ሰው ስንሆን ሀገር ያርፋል። እግዚአብሔር ዓለምን ለመቀደስ አንድ ሰው ይበቃዋል። 

ሰው የፍጥረት ዘውድ ነው። የሰማና ምድር ዘውድ ሰው ነው። የእግዚአብሔር የልቡ ማደሪያ ነን። ሳንቲም ጭቃ ውስጥ ቢወድቅ አይጣልም፣ ምንም ብንቆሽሽ አይጥለንም። ለእግዚአብሔር የማይገዛ ሕዝብ ገዥዎች ጨካኞች ይሆኑበታል። መንፈሳዊ ሰው እሳትን ያለ ውሐ፣ ጦርነትን ያለመሳሪያ ያሸንፋል፣ ባሕርን ያለ መርከብ ይሻገራል፣ መርዝን ያለመሻሪያ ያጠፋል እሾኽን ያለ ጫማ ያደቃል። ያለ ጋሻ ይመክታል፣ ያለ ጦር ያሸንፋል ያለ ሠራዊት ይነግሳል። 

ዓርብ የፍጥረት መካተቻ ነው። በእግዚአብሔር ፊት መጣል ነው ክፉ። እግዚአብሔር ከጣለ የሚያነሳ የለም። ሰው ሲጥል እግዚአብሔር ያነሳል።

ዓርብ ማለት የመና መካተቻ ነው። እስራኤላውያን የአርባ  ቀን ጉዞ አርባ ዓመት ተጓዙ። በበደላቸው ምክንያት ረዘመ። ዛሬ ኃጢአታችን በዝቶ መከራችን ከብዷል።  በዚኽ ግዜ ዛርም ሰው ለበዓል ይዘፍናል። 

እስራኤላውያን ፊንቆን ሲደርሱ ይመግባቸው የነበረ መና ቆመ። ተካተተ። ከነአን ሲደርሱ እሸቱ ሲቀምሱ መና ቆመ። በልተውት የማያድነው ሞትን ያላጠፋ ምግብ ቀረ። የዘለአለም እንጀራ ጀመረ ማለት ነው። ለመስዋዕት ፍየል ማረድ፣ በሬ፣ርግብ ማረድ ቀርቶ ክርስቶስ የታረደበት ሆነ። የረሃብ መካተቻ የምግብ መጀመሪያን ቀን ነው። የነፍስ ምግብ የተጀመረበት ነው። የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ የተባለበት ነው። 

ጥም ይብቃ ብሎ ደሙን ያጠጣበት ረሃብ ይብቃ ብሎ ስጋውን የመገበበት ቀን ዓርብ ነው። ረሃባችን ያለቀው ዓርብ ነው። ዓርብ የፍዳ መካተቻ ነው። በለስ በመብላታችን የእሳት የበረዶ እዳ ተፈርዶብን ነበር ዛሬ እዳችን ተከፍሎ ያለቀበት ነው። ቁስላችን ቆስሎ ውድቀታችን ወድቆ እዳችን ከፍሎ ጨረሰልን። "በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው" ኢሳ.53:4

ጌታ ዓርብ ሁሉም ተፈጸመ አለ። የሞት ሥልጣን ያበቃበት፣ የሞት ግዛቱ ያበቃበ፣ ትንቢተ ነቢያት የተፈጸመበት ነው፣ የዲያብሎስ ሰንሰለቱ ተበጠሰ፣ መንጋጋው ወለቀ፣ መራቆት አለቀ፣ የነጻነት ቀናችን ዓርብ ነው። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

25 Oct, 08:08


እናባርራችኋለን

"አኹን ከዚኽ በፊት እንደ ተደረገው አንባራርም። እኛ አባረናችሁ ቤተ ክህነቱን እንቆጣጠረዋለን። እናንተን ነቅለን እንጥላለን። እኛን አባረራችሁን። ክህነታችንን ነጠቃችሁን በትግራይ ላይ ግን ምንም አላደረጋችሁም። ከዚኽ በኋላ የራሳችን ፓትርያርክ መርጠን የምንቀልበት ሁኔታ ይፈጠራል።"
በሲኖዶሱ ላይ የተናገሩት ነው

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

25 Oct, 08:02


አቡነ ሄኔክን ማንሳት አትችሉም። ካነሣችሁ እንጣላለን።

ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረ ሚካኤል

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

25 Oct, 01:04


በትግራይ ክልል የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት የራሳቸውን ሲኖዶስ ማቋቋማቸውን ገለጹ
https://amharic.voanews.com/a/7837941.html

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

25 Oct, 00:56


የዳስ በዓል ሱኮት (sukkot)

እሥራኤላውያን በሀገራቸው እንዲያከብሯቸው ከታዘዙት ሦስት ዓበይት በዓል መካከል እንዱ የዳስ በዓል ሲኾን በእብራይስጥ ሱኮት ይባላል። ዳስ ማለት ነው። 
ዳስ ማለት ከቤት ውጭ የሚሠራ ጊዜያዊ መጠለያ ነው። እስራኤላውያን ከግብጽ ወጥተው በምድረ በዳ አርባ ዘመን መኖራቸውን ለማስታወስ ከቤታቸው ወጥተው ዳስ ሠርተው በዓል ያከብሩ ነበር። (ዮሐስን ወንጌል ትርጓሜ መ/ር ስቡሕ።)

የበዓሉ መነሻ ያዘዘው እግዚአብሔር ነው። “እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦34  ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባተኛው ወር ከአሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የዳስ በዓል ይሆናል።” ዘሌ.23:33

ከሦስቱ ታላላቅ በዓላት የመጨረሻው የመሰብሰቢያ በዓል ወይም የዳስ በዓል ተብሎ ይጠራ ነበር። ቲሽሪ ወይም ኢታኒም ይባል በነበረው ሰባተኛ ወር ከ15 ኛው እስከ 21ኛው ቀን የሚውል ሲሆን ከእኛ የጥቅምት ወር መጀመሪያ ጋር አንድ ነው።
የዳስ በዓል ግን በሰባተኛው ወር በእኛ መስከረም መጨረሻና ጥቅምት መጀመሪያ የሚከበር ነው ። የዳስ በዓል ዓላማው የእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ ላይ አርባ ዓመት መጓዛቸውን የሚያስቡበት ነው። ይህንም በዓል የሚያከብሩት ከቤታቸው ወጥተው ለሰባት ቀን የዳስ ጎጆ ሠርተው ነው። እግዚአብሔር በምድረ በዳ ውስጥ ሰማይን ጣራ ፣ ምድረ በዳውን ቀዝቃዛ አድርጎ እንዴት እንደተንከባከባቸው የሚያስቡበት ነው ። ይህ በዓልም የመኸር መክተቻ ወራት ላይ የሚውል ነው ። 

እስራኤል አርባ ዓመት ሲጓዙ ይጠለሉ የነበረው በዳስ እንጂ ቋሚ መኖሪያ ቤት እየሠሩ አልነበረም። 
በዚህ ወቅት የአምላክ ሕዝቦች ከቤታቸው ውጭ ወይም በጣሪያቸው ላይ ከዛፍ ቅርንጫፎችና ቅጠሎች በተሠሩ ዳሶች ውስጥ ይቀመጡ ነበር። ይህም እስራኤላውያን በየዕለቱ ለሚያስፈልጓቸው ነገሮች በአምላክ መታመንን የተማሩባቸውንና ከግብጽ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመድረስ በጉዞ ያሳለፏቸውን 40 ዓመታት ያስታውሳቸው ነበር።​ ዘሌ.23:34 ዘዳ.8:15
በዚኽ በዓል አይኹድ ለሰባት ቀን በዳስ የሚያከብሩት ሲኾን አኹን ግን በተለይ በአሜሪካ ምኩራብ ውስጥ ያከብራሉ። በውጭም ድንኳን ጥለው ሲያከብሩ ዛሬ ተመልክቻለሁ። 

በበዓሉ ዘንባባ፣ ትርንጎ፣ አደስ፣ ዝግባ በአንድነት አስረው በማስቀመጥ ያከብራሉ። 

የዳስ (ጎጆው) ሥጋችንንና ዓለምን ይገልጣሉ። ሥጋችን ፈራሽ ድንኳን ተብሏል ። 2 ቆሮ.5 ፡ 1-5። ድንኳን በጥሩ ካስማ ቢቆምም ንውጽውጽታ አያጣውም። ሥጋም ቢማሩ ፣ ቢሰበስቡ ጭንቀት አያጣውም። ዓለምም በእንግዳ ወሬዎች ስትናጥ የምትውል ድንኳን ናት ። ድንኳን ምንም ዕድሜው ቢረዝም ለሦስት ቀን ነው ። በዚህ ዓለም ብንቆይም ለጥቂት ዘመን ነው ። ዓለምም ኃላፊ ነው ። የዳስ በዓል ፈራሹን ሥጋና ዓለም ያስታውሰናል ። የመጨረሻው መኸር ደግሞ ምጽአትን ያሳስበናል ። ከምጽአት በፊት ብዙ መኸሮች አሉ። አጠቃላዩና የመጨረሻው መኸር ግን ዳግም ምጽአት ነው ። የዳስ በዓል የመጨረሻው በዓልም ነው ። በዚኽ ዓለም ላይ የሚቀረን የመጨረሻው በዓልና ጉባዔ ዕለተ ምጽአት ነው ።
“የአይሁድም የዳስ በዓል ቀርቦ ነበር” ይላል ። ዮሐ. 7:1። የዳስ በዓሉ ትርጉሙም ዓላማውም ይህ ነው።

ንዋይ ካሳሁን



 

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

25 Oct, 00:32


Al Jazeera English on X: ""Being ethnic Amhara is becoming a death sentence in some parts of the country." Mass protests took place in Ethiopia's northern Amhara region denouncing civilian killings and criticising the govt’s inability to curb worsening ethnic violence https://t.co/gZgfXIeRt5 https://t.co/s0Bl6v0brL" / X
https://x.com/AJEnglish/status/1544646878733672448

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Oct, 19:39


ድሮን በየቀኑ እሳት የሚዘንብባት ኢትዮጵያ። ባዶ ልትቀር በየገጠሩ አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉባት አብነት ተማሪዎች የሚረሸኑበት ኢትዮጵያ ግን ምንም አይዘገብባትም። ሕዝብ የሚፈለገው ለገንዘብ ነው። ኢትዮጵያ ስለ ኮሪደር ልማት አውሩ።

አብይ ይቀየማል፣ ዳንኤል ያኮርፋል፣ አቡነ ሳዊሮስ ይቆጣሉ።
ኢትዮጵያ እሳት እየዘነበ ስለ ቤሩት።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Oct, 19:39


https://youtu.be/dpXSkAjUGKQ?si=oF4QitSb8WUaSC0z

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Oct, 17:14


አሐቲ ይእቲ (አንዲት ናት)

በዚኽ ወቅት ያልከሸፍንበት ነገር የለም። በመከራ ቀን መገኘት በጣም ከባዱ ነገር ነው። በውጭው ዓለም በተለይ በአሜሪካ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ይገኙበታል። በይበልጥ ደግሞ በዋሽንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጁንያ በመቶ ሺኽ የሚቆጠር ምእመናን ይኖራሉ። 

The Washington, D.C., Maryland, and Virginia (DMV) area is home to one of the largest Ethiopian populations outside of Ethiopia. Estimates suggest that around 250,000 to 300,000 Ethiopians live in the DMV area, making it one of the largest Ethiopian communities in the United States.

ታድያ በዚኽ መከራ ወቅት ለሀገርም ለቤተ ክርስቲያንም በቆረጠ ልብ የሚጋደል የሚገኝ ካህንም መምህራንም ምእመናንም በቁጥር በጣም ውስን ናቸው። ንግሥና ጠብ ሲኖር ብቻ ነው ግልብጥ ብለው የሚወጡት። 

በተለይም አሜሪካ ተወልደው አልያ አድገው የሀገሩን ባሕል፣ ሥርዓት፣ ቋንቋ አውቀው ለመብታቸው ሀገሩ በሚፈቅደው ለመሞገት ደግሞ ከአዲሱ ትውልድ 2nd generation ፍጹም የለም። እዚኽ ሀገር ተወልደው ስለ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሀገር የሚናገርም የሚጽፍም የለም። 

ስለ ፍልስጥኤም ግን መብት ይቆማሉ።  አብዛኞቹ McDonald እና Starbucks አይጠቀሙም። ምክንያቱም የፍልጥኤምን ጦርነት አሜሪካንን ብዙ ገንዘብ ደግፈዋል በማለት። 

ወላጅ ወንድ ልጆቹን ጭኑ ሥር አስቀምጦ ጠጉር እየጎነጎነ ሹሩባ ይሠሯቸዋል። መኝታ ለማንጠፍ ልብሳቸውን ለማጠብ እንኳ አስንፈው ያሳድጋሉ። 

ሄርሜላ መስፍን ግን በእጅጉ ልዩ ናት። ካወቅኋት ጀምሮ እረፍት የላትም። በየሰልፉ ትገኛለች። ትሞግታለች። ትናንትና በተወካዮች ምክር ቤት ለሴኔት የሚወዳደሩ አሜሪካኖችን ከሌሎች ጋር በመኾን አናጋግራለች። አጀንዳውን ከፍ እንዲል አድርጋለች። 

ሄርሜላ አንዲት ናት ( አሐቲ ይእቲ)። እግዚአብሔር ብድራትንሽ ይክፈልሽ። እንዳንቺ ያለ ጠንካራ ልብ ያላቸው ወጣቶችን ይስጠን። ሄርሜላም ሰንበት ተማሪውም ቤተ ክርስቲያን እያገለገልኩ ነው ይላል አይደል?። 

https://youtu.be/RFIOnmhVozQ?si=vPv4eDFeQ5q0J4uX

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Oct, 16:21


ወይ ይኼ ሰላም !!

የሰላም ሚኒስቴር ሲገርመኝ ሲኖዶስም ውስጥ "የሰላም ኮሚቴ" የሚባል አለው። ሀገራዊ ሽግግሩን የሚያሳልጡ ናቸው። ሰላም ያሳጡን እነማን ኾኑና። ጨርሶኮ ካድሬያዊነት ወርሶናል። 😔😔

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Oct, 15:28


ሲኖዶስ

የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ጉዳይ ውይይት አድርጎ ተጠንቶ ለግንቦት ይቅረብ ብሏል!!😂😂😂

ደኽና ናችኹ ምእመናን?

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Oct, 14:11


https://youtu.be/HeDKo2FTEVE?si=B7VE76NyF4IlRvpB

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

24 Oct, 12:48


አይመለከተኝም

በማይመለከተኝ አጀንዳና ርዕስ ምን አገባኝ። ባለቤት ይኖረዋል ባይኖረውም አይመለከተኝም የሚባል ነገር ሊኖር ይችላል። 

እናም ከማይመለከተን ርዕስ መካከል የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ጉዳይ ነው። የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንደ ርዕስ በየዕለቱ የሚወያይ ማነው? የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚመለከተው ማንን ነው?

ለካህናቱ የቤተክርስቲያን ሕልውና ርዕሱ አይደለም አይመለከተውም። ለሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች አጀንዳቸው አይደለም። ምእመናንም ምን አገባቸው አይመለከታቸውም። ለማኅበረ ቅዱሳን ጉዳዩ አይደለም። 
እና እኛን የሚመለከተን ምን ይኾን? የየዕለት አጀንዳችን ምን ይኾን?

ለሲኖዶሱ በጀት ማጽደቅና ስለ ጳጳስ ዝውውር፣ ስለሙስና። ለቄሶቹ ቅዳሴ አይታጎል፣ ጠበል መርጨት፣ ወላድ መጠየቅ፣ ለሰንበት ተማሪው መዝሙር ማጥናት፣ ዘጥዘጥ ማለት፣ ወሬ ማመላለስ፣ ለማኅበረ ቅዱሳን ስለ ድርጅቱ መጽናት ይጨነቅ፣ ቆሎ ትምህርት ቤት እያለ ገንዘብ ይሰብስብ፣ ለምእመኑ ሕንጻ ማነጽ ቦታ መግዛት፣ ንግሥ ማድመቅ ናቸው። 

የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ጉዳይ ማን ይኾን የሚመለከተው። እኔ እንጃ ፋኖ ሲመጣ ይስተካከላል መሰለኝ። ፋኖ ኹሉን ቻይ ስለኾነ ያስተካክለዋል አይደል? እንደዛ መሰለኝ እያልን ያለነው። ወይም አብይ አሮጌዋን አፍርሶ ለእኛ በምትመጥን መልኩ ሠርቶ ይሰጠናል። አዳነች አቤቤም አካባቢውን ካጸዳች በኋላ መጥታ ታስቀድሳለች። አብይም ንጹሕ ቦታ መናፈቻ ከሠራልን በኋላ አመሻሽ ላይ ከሥራ ሲወጣ ሥላሴ ወይም ግቢ ገብርኤል ብቅ ብሎ ይሳለማል። 
እኔው ነኝ የማወራው!!

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

22 Oct, 17:54


https://youtu.be/_5CmwUBrmnc?si=zLMbRlChzrQiHCM4

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

22 Oct, 17:54


ማትረፍ ከፈለጋችሁ የምመክራችሁ አንዱ ይኽንን ዩቲዩብ ነው። ተከተሉት!!

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

22 Oct, 16:23


ይስማችሁም አልስማችሁም!!

አብይ ይስማም አይስማም እናንተ ግን ሥራ ሥሩ። የትግራይ ጦርነት በመታለልም ይኹን በቸልታ አልያ በክፋት ብዙ ምእመናን በማለቅ ተባባሪ ኾነን አልፏል። አማራ ክልል እሳት እየዘነበ ነው።

አብይ አሰማም!! ቀጥታ ግን "ካላናገርከን ስብሰባ አንጀምርም" በሉት። ቆራጥ አጥቶ ነው እንጂ ፈሪ ነው። ፈሪ ግን ጨካኝ ነው። ቀጥ ብላችሁ "ጦርነት ዛሬውኑ አቁም አቁም፣ አንተን የምንለምንበት ጊዜ አብቅቷል። በቀጣይ ቀን እናወግዛለን፣ አልያ ከፈለክ ሰብስበህ እሰረን" በሉት። ኢትዮጵያ ያኔ ትፈወሳለች። ተስፋ ይለመልማል። ካልኾነ ግን በቃላት እየተክበሰበሳችሁ ምንም አታመጡም። ተያይዞ መፍረስ ብቻ ነው።

እኔኮ ነኝ በውስጤ የምለው።

https://youtu.be/T9i0k8-Wiyw?si=W48GRrHNbIwIUj2l
ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

22 Oct, 13:45


ቅጽል

በጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተጠሩበት ቅጽል


የወንጌል ገበሬ
የጸሎት አባት
ትጉህና የዋህ
የልማት አርበኛ
የድሆች አባት
ደከመኝ ስለቸኝ የማይሉ
ቆራጥ አመራር ሰጪነት የሚሉ ናቸው!!

እውነቱ ግን በእጅጉ ከዚኽ የራቀ ነው የአደባባይ ኩሸት

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

22 Oct, 12:42


ኃጢአትንም ጽድቅንም የሠሩት በጋራ ነው ቅጣትም ሽልማትም የሚያገኙት በጋራ ነው።

ገማልያም ይኽንን ምሳሌ ተነግሯል:- ዐይነ ስውር እና እግረ ልምሾ ሰው መንገድ ሲሄዱ ይርባቸዋል። ፍራፍሬ ሰርቀው ሊበሉ ያስባሉ እና እንዴት ያድርጉ ዐይነ ስውሩ ፍሬውን አያይም ልምሾው ደግሞ ዛፉ ላይ አይደርስም። ተመካከሩና ዐይነ ስውሩ ልምሾውን ሰው እሽኮኮ ብሎት ወደ ተክሉ ገብተው ቆርጠው በሉ። ባለቤቱ ዳኛ ፊት አቅረባቸው። ዳኛው ማነው የሰረቀው ብሎ ይፍረድ? አንዱ በማየት አንዱ በመሄድ ተባብረዋል። ኹለቱንም ቀጣቸው። ዕውር ያለ ልምሾው ልምሾው ያለ  ዕውሩ ምንም ሊያደርጉ አይችሉም። ስለዚኽ ዳኛው ልምሾውን ሰው ዐይነ ስውሩ ትከሻ ላይ አስቀምጦ በጋራ ፈረደባቸው። ጽድቅን ባደረጉበት በጋራ ይሸለማሉ፣  ኃጢአትንም በሠሩበት መንገድ በጋራ ይፈረድባቸዋል። 

ነፍስ እንደገና ወደ አካሏ ትመለሳለች። አካልም እንደ ገና ሕያው ይኾናል። ይኽ ዳግም ትንሣኤ የምንለው ነው። ከትንሣኤ በኋላ ግን ፍጹም ምድራዊ እውቀቸው ይጠፋል ይቀየራል እንደ መላእክት ስለ ምስጋና ይኾናል። ቤተሰብ ሚስትና ባል እናትና ልጅ አይተዋወቁም። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

22 Oct, 12:41


መጸነስና መሞት በንጽጽር

በጽንስ ወቅት ነፍስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግዙፉ ዓለም ጋር ትገናኛለች። ወሊድ በጣም ሕመም ያለው ክስተት ነው። ቅዱስ ዳዊት “አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።” ይላል መዝ.27:10


ቅዱስ ዳዊት “አባቴና እናቴ ተዉኝ” ሲል ይኽ በጽንስ ግዜ ስለነበረው ነገር ነው የተናገረው። ቅዱስ ዳዊት የእግዚአብሔር ነቢይ የተቀባ ነው። ወደ ኋላ ሄዶ በማኅጸን ስለ ኾነው ነገር አስታወሰ። 

ቅዱስ ዳዊት በእናትና በአባቱ በሩካቤ እንደተገኘ ያውቃል። ዳዊት በማኅጸን በተጸነሰ ጊዜ ተጸንሶ ሲያገኝ ከየት መጣሁ ብሎ እንደ መጠየቅ ነው። እናቱም ተኝታለች አባቱም ተኝቷል ዳዊት ግን ጽንስ ኾኗል። እኔን ለመፍጠር ኃላፊነቱ የማን ነው? ከየት መጣኹ እያለ ይጠይቃል። ብቻውን በማኅጸን ነበር። ጥያቄውን ይጠይቅና መልሱን መንፈስ ቅዱስ ይነግረዋል። “እግዚአብሔር ተቀበለኝ” ይላል። ኹሉም እንዲከናወን ያደረገው እርሱ ነው ይላል። 

እናትና አባቴ ደክሟቸው ተዉኝ ያለው ተኝተው ነበር ነው። እግዚአብሔር ግን ይንከባከበኝ ነበር። ይኽ ለመጀመሪያ ጊዜ ነፍስና ሥጋ ሲገናኙ ነው። ሰው የኾነበትን ቅጽበት። 

ከጽንሱ ከ40 ቀን በኋላ አካሉ ኹሉ ተሰርቶ ያልቃል። በሦስተኛው ወራት አካላት ተግባራቸውን ይጀምራሉ። አዕምሮ ወደ ጭንቅላት mind to brain ፣ መስማት ወደ ጄሮ hearing to ear ፣ ማየት ወደ ዐይን vision to eye ይሄዳሉ። መክሊታቸውን ያገኛሉ። ከአካል ጋር ይያያዛሉ። settling in ቀስ በቀስ ሙሉ ሰው ኾኖ ዘጠኝ ወር ያድጋል። 

ቅዱስ ዳዊት ይቀጥልና “በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ እንኳ አንተ ከእኔ ጋር ነኽና ክፉውን አልፈራም“ ይላል። መዝ.22:4 

የሞት ጥላ ያለው መወለድን (ልደትን ነው) ምክንያቱም በጣም ምቹ ከኾነው ሕይወት ከማኅጸን ውጭ ወደ ኑሮ ዓለም እየመጣ ነው። በነዚኽ መካከል በሸለቆ ውስጥ ያልፋል። አደገኛ መንገድ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ችሎ ሊተነፍስ ነው። በጣም አስፈሪ መንገድ ነው። ይኽ ጠባቡ የማኅጸን በር ምጥ ነው። 

በዚኽ ሸለቆ ውስጥ ሲያልፍ እግዚአብሔር ብቻ ነው ማሳለፍ የሚችለው። ሞትን ሊያይ ይችላል በዚኽ ሸለቆ። 

ሞትን መጋፈጥ ከመወለድ ጋር ተመሳሳይ ነው birth and death. ልደትም ለሞት የቀረበ ተሞክሮ ወይም ልምምድ ነው። በዚያ መካከል እግዚአብሔር ብቻ ነው ሊጠብቅ የሚችለው። በመወለድም በሞትም ወቅት የሚያሳልፈው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ተመሳሳይ ናቸው። አስፈሪ ነገር ያልፋሉ። ከጽንስ 30 ቀን በኋላ ልጁ ፍጹም ነው። ነፍስ ከሥጋ ፍጹም ስምም ትኾናለች። 

በሞትም ጊዜ ተመሳሳይ ነው። ሞት በቅጽበት የሚኾን አይደለም። ደረጃ አለው። 

ብዙ ሰዎች ከሞታቸው 40 ቀን በፊት ሞት እየመጣ መኾኑን ያውቁታል። አስተውለው ስለማያውቁ ነው። ስሜት አላቸው። የሞትን ሽታ ይሸታቸዋል። ሞት በአስፈሪ ኹኔታ አይመጣም። ለዚኽ ነው ቅዱሳንም አንዳንድ ሰዎች ሞታቸውን አውቀው ኑዛዜ ያደርጋሉ፣ ይሰናበታሉ፣ ስለሞታቸው ይናገራሉ። እየመጣ መኾኑን ይታወቃቸዋል። 

ሞት በጣም አስደንጋጭ ነው። ለክርስቲያኖች ግን ሞት አስደንጋጭ አይደለም። ሂደቱ ግን ቀስ ብሎ ነው የሚከናወነው። መጀመርያ ስሜት ይፈጠራል። ነፍስ ከሥጋ እንደ ተለየች ወዲያው ሥጋን ጥላው አትሄድም። ሥጋዋ ባለበት ስፍራ ትቆያለች። ሰባት ቀን ድረስ ከሥጋው ውጭ አካሉ ላይ ትቀመጣለች። ቶሎ ትታው አትሄድም። ለዚኽ ነው ሰባት ቀን ኀዘን የመቀመጥ ባሕል የመጣው። በአይሁድ seven days of shivah ይሉታል። ቋሚ ሰዎች የሚሰማቸውን ኀዘን ነፍስም ይሰማታል። ነፍስ የሚሰማትን ነው እኛ የሚሰማን። 
ዮሴፍ ለአባቱ ያዕቆብ ሲሞት ሰባት ቀን አለቀሰ። “በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ መጡ፥ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።" ዘፍ.50:10

ሦስት ቀን በጣም ከባድ ኀዘን ነው። ኀዘንተኛው ምግብ እሺ አይለውም፣ እንቅልፍ ያጣል፣ በጣም ግራ ይገባዋል። አስፈሪ ግን አይደለም ኀዘኑ ግን ጽኑዕ ነው። አራቱ ቀን ኀዘኑ እየቀነሰ ይሄዳል። በሰባተኛው ቀን ነፍስ ደግማ ከሥጋ ጋር እንደማትዋሐድ ታውቃለች። ሥጋን ለቃ ትሄዳለች። በዚኽ ምክንያት ኀዘንተኞች መቀመጥ ያቆማሉ። ነፍስ ተረጋግታለች። ለራስህ ግን ማዘንህ ይቀጥላል። 

30 ቀን በኋላ በሰማያት መኖር ትጀምራለች። ቢበዛ 12 ወር ነፍስ በምድር የነበራትን ትዝታ እየቀነሰች ትመጣለች። ይኽ ወቅት የሽግግር ወቅት ነው። ከምድራዊ ኑሮ ወደ ሰማያዊ ኑሮ ይቀየራል። ይኽ ኁኔታ ሲኦልም ገነትም ሊኾን ይችላል። እንደ ነፍስ ጽድቅ ኹኔታ። ወደ ደስታ አልያ ወደ ለቅሶ ይቀየራል። ገነት ከገባች ደስታን መደሰት ትጀምራለች። አይታው ሰምታው ወደ ማታውቀው ደስታ። ሲኦልም የገባችው አይታው ሰምታው ወደማታውቀው ስቃይ። የገነትም ደስታ ቀስ በቀስ እያደገ እያደገ ይመጣል። 

ሕጻን ልጅ በምጥ ወደ ዓለም እንደሚመጣ ወደ ሞትም በምጥ ነው የሚኬደው። ነፍስ ወደ ሰማይ የሚደረግ ጉዞ መኾኑን ታውቃለች። ነፍስ በምድር ላይ የኾነውን ነገር ሙሉውን ታውቀዋለች። ትውስታዋ አለ። የኖረችው ምድር ላይ ነው። የኾነውን ኹሉ ታውቃለች። እውቀቷ፣ የነፍስ ረቂቅ አካሏ አይጠፋም። በተለይ ቤተሰቧን አትረሳም፣አይጠፋም። 
በምድር ስላሉት ታስባለች። እንደውም ከሥጋ በኋላ ነፍስ ቀድሞ ከነበራት በላይ መስማት ማየት መገንዘብ ትችላለች።  ከሥጋ መለየት በኋላ ከፍ ትላለች። በሥጋ አካል አትገደብም። ስሜቷም ከምድር ይልቅ ከፍ ያለ ስሜት አላት። ለደስታም ይኹን ለስቃይ። ስለ እኛም ይጸልያሉ። 
ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።” 1 ቆሮ.13:12

ባለጠጋው ነዌ ከሞተ በኋላ በሲኦል ሳለ ወንድሞቹን አስቧቸዋል። “እርሱም፦ እንኪያስ፥ አባት ሆይ፥ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና” ሉቃ.16:27


ሙሉ በሙሉ ትውስታ memory የሚጠፋው ከዳግም ምጽዓት በኋላ ነው። ነፍስ አትሞትም። ሞት ማለት ሥጋ ነፍስን ሲለቃት ማለት ነው። የሚሞተው ሥጋ ነው። ነፍስ ሕያውነቷ ይቀጥላል። ሥጋና ነፍስ ሲለያዩ ነው ሞት የምንለው። 
በገነት ያለችም ነፍስ እንዲኹ ቤተሰቦቿን እያሰበች እርሷ ወዳለችበት እንዲመጡ ትመኛለች ትጸልያለች። “ሙታን ይስዕሉ ለሕያዋን” የሚለው ይኽንን ነው

በሞት የማናዝንበት ምክንያት ምድራዊ ሕይወት አጭር መኾኑን ማወቃችን ነው። ሞትም ጊዜያዊ ነው። ነፍስ ተመልሳ ሥጋን ለመዋሐድ ትጠብቃለች። የዛሬ ኹለት ሺኽ የሞተ ሰው ነፍስ ተመልሳ ወደ ሥጋዋ ለመመለስ ትጠቃለች። አካሏ ነው። The Resurrection of body. 
ይቀጥላል

ንዋይ ካሳሁን


👇

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

22 Oct, 12:41


ይኽንን ጽሑፍ በጥንቃቄ ያንብቡት ጊዜ ሲገኝ የማስረጃ ጥቅሶችን ማጣቀሻዎችን አቀርባለሁ። 👇

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21 Oct, 23:41


ስንፍናችን ገደብ የለውም "መግለጫ አይጠቅምም፣ ሰልፍ አይጠቅምም" የምንል ነን። እነርሱ ግን መግለጫ ምንም አያመጣም ብለው አይንቁትም ። አቅሙን ያውቁታል።

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21 Oct, 22:54


አሐቲ ድንግል

የሊቀ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን አዲሱ መጽሐፍ ነው። ለወትሮው መጽሐፍ ሲወጣ ሰው የሙያመጣልኝን ማፈላለግ እጀምር ነበር።

የልብን ፍላጎት የሚያውቅ ወዳጅ መቼስ ጥቂት ነው። እናም ለሥራ ወደ አሜሪካ ያቀናው ወንድሜ ፕ/ር እንግዳ አበበ ሰላም ሊለኝ ደውሎ መምጣቱን ነገረኝ። አሐቲ ድንግልን አምጥቼልሃለኹ ሲለኝ ደነቀኝ። ምን ይባላል የልብ ወዳጅ ማለት ይኽ አይደል። ድንግል ትስጥልኝ።

የመጽሐፉን ሽፋን፣ ምስጋናውን አበርክቶውን፣ አርዕስት ማውጫ ይዘቱን አነበብኩት።

የአባን መጽሐፉን ያዘጋጁበትን ምክንያት አመሻሹን አነበብኩት። እንቅልፍ አልመጣ ሲል አንድ ምዕራፍ ቀመስኩለት። መጽሐፍ ሳይነበብ ስለተደራረበብኝ አሁን አልጀምረውም።

ንባብ ጊዜ ይፈልጋል። ጊዜ ስል ሰዓት ሳይኾን የንባብ ፍላጎት መምጣት ማለት ነው። በጣም ከባዱ ነገር የንባብ ድባብ መፍጠር ነው። ያውም በአሜሪካ። ወቅቱ ንባብ እንቢ የሚልበት ወቅት ነው። ቀድሞ የጀመርኩትስ ስጨርስ ለማንበብ ነው። ንባብ ዲሲፒሊን ይፈልጋል።

መጽሐፉ ይደንቃል አባታችን የጻፉበትን መንፈስ ያሰቡበትንም ምክንያት ሳነብ መጽሐፉ ታላቅ ድካም የተደከመበት ነው።

መጽሐፉ ጥም ቆራጭ ተጠቃሽ መጽሐፍ ነው። አንብቤ ስጨርስ በዝርዝር እመለስበታለሁ።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21 Oct, 17:28


https://youtu.be/tbTBIgAmf1Q

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21 Oct, 16:29


ኡኡኡኡኡኡ

ይሰሙ እንደኾን ብዬ ነው። ለምነን አባብለን ሥራቸው ተነጥፈን፣ ተመካክረን አልሰሙንም። ዛሬ ላይ ለአንድ አባት ብቻ ነው የልቤን ኀዘን የነገርኳቸው። "ትሰሙናላችሁ ብዬ አይደለም ነገር ግን ምን ያክል እንደምናዝን እንዲይልውቁ ብቻ ነው.... " ብዬ ነው የነገርኳቸው። አኩርፌም አዝኜም ከማናችሁም ርቄያለኹ ነው ያልኳቸው።

ለድሮው ቢኾን "ይኽ ቢኾንስ እንዲኽስ ብታደርጉ እያልኩ የማዋውየው ከግማሹ በላይ ነበሩ። አይሰሙም አልሰሙም። ዛሬም ስንጮኽ ከሰሙን ብዬ ነው።
ኦርቶዶክሳውያን እያለቁ ነው። ቢያንስ በአብይ ፍጅት 3 ሚሊየን ኦርቶዶክሳውያን አልቀዋል። ስደተኛው ረሃብተኛው 20 ሚሊየን ይበልጣል። ሰሜኑን እየሰበረው ነው። ግድ የላችሁም ስሙን።
አዲስ አበባ በወራት ውስጥ ሕንጻ ብቻ ታቅፋችሁ ትቀራላችሁ። መጨረሻ ቤተ ክህነቱም ሕንጻ አይቀርለትም። መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ አጥሩና ቤተልሔሙ ይፈርሳል። ምልክት ተደርጎበታል።
አዲስ አበባ የሚተርፍ ክርስቲያን የለም። ነቅሎ ያባርረዋል። አብይን የማውገዝ ጉልበት ብታጡ እንኳ ለሕዝቡ ተጋድሎ አውጁለት መከራውን በጋራ እንካፈላለን በሉት። ስቃዩን በግልጽ ተናገሩና ተቀላቀሉለት። እያለቀሰ ቤተክርስቲያንን ጥሎ እየተሰደደ ነው። መንግሥት ይስማን ብላችሁ አትጨነቁ ከምእመናችሁ ጋር ኹኑ። ጦርነቱን በግልጽ አውግዙ አትለምኑ። ተደራደሩብ፣ ተነጋገሩ እያላችሁ አታውሩ። አብይን አቁም ብላችሁ አውግዙት። ቀጥታ ጦርነቱ መካከል ሂዱ።
ዘንድሮ ጥር ጥምቀት ጃንሜዳ ለጥምቀት የሚወጣ ታቦት አለ? ክርስቲያን አለ? ከምእመኑ ጎን ኹኑ። ተቃጠል ብሎኝ ነው እንጂ ምን በወጣችሁ ትሰማላችሁ። ካድሬ ቢደውል ዳንኤል ቢደውል ይሰማል።

እናንተ ስለ ቅያሬ፣ ስለ በጀት፣ ስለ መኪና መግዣ ፣ ስለ ኮሪደር መአት ተወያዩ።

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21 Oct, 16:08


ከሞት በኋላ ያለ የነፍስ ግብግብ 

ሰው ሲሞት ነፍሱ ከሥጋው ትለያለች። መንፈሱ ከነፍስ ጋር ወደ ሰማይ ትሄዳለች። ሞት እንዲኽ ቀላል አይደለም። ይኽንን ለመረዳት በጥቂቱ የብሉይ ኪዳንን የነፍስ ኹኔታ እንመልከት። 

ሰው እንደ ተወለደ ሳጥናኤል ከጭፍሮቹ አንዱን ይልክና ይቆራኘዋል። በዚኽም ሰውየው ክፋት እንዲሠራ ያስጨክነዋል። ጣኦት እንዲያመልክ ወደ እግዚአብሔር ዞር እንዳይል ያደርገዋል። 

ሰውየው ሲሞት ደግሞ ሳጥናኤል እየተገለጸ ጽልመት ፊቱን እያሳየ ብዙ ያሰቃየዋል ያስፈራራዋል። በዚኽም ሰውየው ላብ አልቆ ደም እስኪወጣው ድረስ ይጨነቃል እያንፈራገጠ መሬቱን ይቆፍራል። በስተመጨረሻ ደሙ ይደርቃል ነፍሱ ትለያለች። ወደ ሲኦል እያዳፋ ይወስድና ወደ ስቃይ ይወስዳታል። 

በሐዲስ ኪዳን የተጠመቀ ክርስቲያንን ሰይጣን አይቆራኘውም። ለሰይጣን ተላልፎ እንዳይሰጥ የሥላሴ ልጅነት ይጠብቀዋል። ሰይጣን ያንን ሰው አጥብቆ ይጠላዋል። የተጠመቀ ቀን ለማሳሳት መድከም ይጀምራል። በሞተ ጊዜ ጭንቀት የለበትም። ጦርነቱ ነፍሱ ከወጣች በኋላ ይቀጥላል። ጠባቂ መላእክት መካከልና በሰይጣን መካከል ይኾናል። ሰይጣን ይኽች ነፍስ የእኔ ናት ይላል መዝገብ እየገለጠ ይከራከራል። አየሩን ላለማሳለፍ ከፍተኛ ውጊያ ያደርጋሉ። “በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው።” ኤፌ.2:1

መላእክት ደግሞ ደግ ሥራዋን እየጠቀሱ ሊያሳልፏት ይከራከራሉ። ሰይጣናት ወደ ሥጋዋ መልሰን እናሰቃያት እያሉ ይዋጋሉ። ነፍስ በመካከል ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ትወድቃለች። በዚኽ መልክ ከፍተኛ ውጊያ ተደርጎ ነው ነፍስ የምታልፈው። 
የኹሉም የብሉይ ኪዳን ነፍሳት በዚኽ መልክ ያለፈች ስትኾን የሙሴ ነፍስ ግን የተለየ ጥበቃ ተደርጎላታል። ሙሴን ቅዱስ ሚካኤል ሰይጣን ነፍሱን እንዳይወስዳት ተከራክሯል። ሰይጣን  ሰው ገድሏል የእኔ ነፍስ ናት ቢልም “እግዚአብሔር ይጣልኽ” እያለ ገሰጸው። 

ርቱዓ ሃይማኖት ስለ ሙሴ ሥጋ ሲናገር እንዲኽ ይላል:- ሙሴ በሚሞትበት ጊዜ ግን ሚካኤል ነፍሱን ያዛት፤ መልአከ ሞትም ፈጽሞ አልነካውም፡፡ ሰይጣን የሙሴን ነፍስ ሲያሳርጋት በተመለከተው ጊዜም እኔ መጥቼ የሞት ጽዋን ሳላጠጣት ለምን አወጣሃት አለው፡፡

ምንም ዓይነት የሞት ጻዕር አልነካውምና፡፡ አንተ በይውህና፣በሰላም ነፍሱን አውጥተሃልና፡፡ የአማፂው፤ የወንጀለኛው የአዳም ልጅ ነውና፡፡ ሚካኤል ግን የስድብን ቃል በሰይጣን ላይ ይሳደብ ዘንድ አልደፈረም፡፡ እግዚአብሔር ይገስጽህ አለው እንጂ። ያን ጊዜም ሰይጣን ሸሸ፡፡ ሚካኤልም የሙሴን ነፍስ ወደ እግዚአብሔር ዐሳረጋት፡፡ ስለዚህም ጌታችን "ሞትን የማይቀምሱ ከዚህ አሉ" አለ፡፡ ማቴ.17:28

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21 Oct, 15:23


https://youtu.be/wwv5uMQtZP4?si=a6GyVYW37rN9ruE8

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21 Oct, 12:11


ይረርም ይምረርም

ቤተ ክርስቲያን እንደ ተቋማዊ መዋቅር ቤተ ክህነት እንለዋለን። ይምረርም ይረርም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ ተቋሟ ይኽ ባሳለፍነው ሳምንት 43ኛ ዓመት ጉባኤውን ያካሄደው ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ነው። ይኽ ጉባዔ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተቋም ከአጥቢያ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከዚያም ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ ያለ መዋቅራዊ ሰንሰለት የያዘ ነው።
በዚኽ መዋቅር ውስጥ የማይካተት ነገር ቤተ ክርስቲያን የላትም። ምእመኑም ካህኑም፣ አገልግሎቱም ቅርሱም ሕንጻውም፣ ይዞታውም፣ ገንዘቡም መዋቅሩ ይኽ ነው። 

ይኽንን ያነሣሁበት ምክንያት በሚገባውም በማይገባውም ቤተ ክህነት እያልን ስንወቅስና ስንተች ቀላል ነገር እንዳይመስለን ለማስገንዘብ ነው። የቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ ምሰሶ ወይም የጀርባ አጥነት ማለት ነው። የቤተ ክርስቲያን የጀርባ አጥንት ምሰሶዋ ይኽ ከአጥቢያ እስከ መንበረ ፓትርያርክ ያለው የዕዝ ሰንሰለት እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን እንዳልኾነም ማወቅ ይጠቅማል። ሌላው ኹሉ ቢደረትና ቢደረብ እዚኽ ላይ የተለጠፈ ነው። 

ይኽ ተቋም ጠንካራ ከኾነ ቤተ ክርስቲያን ጠንካራ ትኾናለች። ይኽ መዋቅር ጠንካራ ካልኾነና ሥራውን በአግባብ ካልሠራ ቤተ ክርስቲያን ደካማ ትኾናለች። ቀደም ባሉት ጊዜያት ማለትም 1950ዎች በፊት ይኽ መዋቅር አይነት አይደለም የነበረው። ይኽንን ቅርጽ የያዘው በተለይ የደርግ መምጣት ጀምሮ ነው የዛሬውን ቅርጹን የያዘው። ከዚያ በፊት መዋቅራዊ ቅርጹ የተለየ ነው። 

ደርግ ሲመጣ የቤተ ክርስቲያን ርስት ጉልቷን ሐብቷን ኹሉ በመንጠቁ ምን ማድረግ ይሻላል በሚል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን መሠረት የጣለ ነው። ቤተ ክርስቲያን ምእመናኑን አስተባብራ ገንዘብ ከራሷ እየሰበሰበች አገልግሎቷን ታስቀጥል የሚል ነው። ያ ነው እስከ ዛሬ ቀጥሎ 43ኛ ዓመት ጉባዔውን ያካሄደው። 

በብዙ የውስጥም የውጭም ፈተና በተለይም የውስጥ አሰራርን ካለመጠንከር በመነሣት ይኽ መዋቅር በእጅጉ የተጎዳ መዋቅራችን ነው። አቅሙም አቋሙም የደከመ ስለኾነ ነው ወቀሳም ከሰሳም የምናበዛው እንጂ ስለማያስፈልገን ስለማይጠቅመን አይደለም። 

አሉበት የምንለው መዋቅራዊ ፈተና እንዲኽ በቀላሉ የምንዘልቀው አይደለም። ራሱን የቻለ ሰፊና ጥልቅ ጥናት ይፈልጋል። ይኽም ኾኖ ይኽ መዋቅር ባይኖር ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዘመን መምራት ጭርሱኑ አይታሰብም። የተበተነ ጨው በለው። ቤተ ክርስቲያን እንድትቀጥል ከፈለግንም የምናሻሽለው የምንለውጠው ይኽንን መዋቅር ይኽንን ተቋም ብቻ ነው። ምንም ላይ ብንንጠለጠል ይኽ ምሰሶ ሲያጎነብስ አብሮ ማጎንበስ ሲሰበር መዘርገፍ አይቀርም። ምክንያቱም የድሮው ሳይኾን ያለንበት መዋቅር ይኽ ስለኾነ ነው። 

ታላላቅ አድባራት፣ ገዳማት፣ አብነት ትምህርት ቤቶች፣ መንፈሳዊ ኮሌጆች የካህናት ማሰልጠኛዎች ኹሉም በዚኽ መዋቅር ሥር የሚመሩና የሚተዳደሩ ናቸው። ይኽ ጠቅላላ መዋቅር የሚመራበት ሕግ ደግሞ አንዱ "ቃለ አዋዲ" በመባል ይታወቃል። ሲኖዶስ የሚመራበት ደግሞ "ሕገ ቤተክርስቲያን" ይባላል።

የእኽል ክምር የሚበላሸው አንዴ ከአከማመሩ ብልሽት ከአናቱ ዝናብ ሲገባው ነው። አልያም እኽቱ ደርቆ ሳይወጣለት ታጭዶ ከተከመረ ነው። 

ቤተ ክህነት ከአናቱ ተበላሸ ማለት ከላይ ውኃ እንደ ገበበት ክምር ቁጠሩት። እስከ ታች አጥቢያ ድረስ ይበላሻል። የገጠመን ችግር ይኽ ነው። ከላይ የሚገባው ልፍስፍስነት ግዴለሽነት፣ ሙስና፣ ደካማ አሰራር መንፈሳዊነት መጉደል እስከ ታች ይዘልቃል። በጥቅሉ ቤተ ክርስቲያን ትደክማለች ብሎም ትጠፋለች። ነገም ከነገ ወዲያም ማዘመን፣ መፈተሽ ማሻሻል መለወጥ የሚገባው ይኽንን ነው። 

ንዋይ ካሳሁን

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Oct, 20:16


የእኽታችን እህተ ማርያም (ሔርሜላ ጌታቸው) ሽኝት

"ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን፦ እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።"

ማቴ.22:31

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

20 Oct, 16:56


https://youtu.be/3KnRJTHWmpw?si=yN5yKBe7TUyN4mWp

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

19 Oct, 17:20


ተቃውሞ ማለት ባለጋራ ሜዳ ላይ ሄዶ መግጠም ማለት ብቻ ሳይኾን በራስህ ስፍራ ላይ ተገቢውን ዝግጅትና ሥራ መሥራት ማለት ነው። ትልቁ የማጥቂያ መንገድ ይኽ ነው። ከዚያ እንደ ባላጋራኽ አይነት ወደ እርሱ ትሄድበታለኽ።