ዛሬ በኅዳር 8/2017 ዓ.ም በነበረን የቅዱስ ገብርኤል የጥምቀት የቃና ዘገሊላ እንዲሁም የቅዱስ ጊዮርጊስ የመዝሙር ጥናት የመክፈቻ መርሐግብር ከ110 በላይ ነባር እና አዳዲስ አባላት በተገኙበት ተከናውኗል የሰ/ት/ቤቱን ጥሪ ሰምታችሁ ለተገኛችሁ ሁሉ አምላከ ቅዱሳን ያክብርልኝ
በመርሐግብሩም
👉መምህር ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።
👉የመዝሙር መምህራን ዝማሬ እንዲሁም በበገና ክፍል ዝማሬ በበገና የቀረበ ሲሆን
👉ቀሲስ ያሬድ መለሰ በመርሐግብሩ ተገኝተው ቡራኬ በመስጠት የመዝጊያውን ጸሎት አከናውነውልና።
በዕለቱ በተለያየ ምክንያት ያልተገኛችሁ አባላት ከነገ ጀምሮ የጥናት መርሐግብሩ የሚቀጥል መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።
👉ለነባር አባላት ከዓርብ ውጪ ከ12:00--1:30
👉ለአዳዲስ አባላት ከ11:00 ጀምሮ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mezmur_fere
👆👆👆👆👆👆👆
ጆይን በማድረግ አዲሱን የመዝሙር ክፍል ቻናል ይቀላቀሉ።
መዝሙር ክፍል
08/03/2017 ዓ.ም