ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት @tsirhatsiyon Channel on Telegram

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

@tsirhatsiyon


ይህ ጣቢያ የተከፈተው ለሰ/ት/ቤቱ አባላት መረጃዎችን ለማድረስ ነው።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት (Amharic)

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት የጠቃሚ እና ፈቃድን እንጠቀማለን ፡፡ ይህ ጣቢያ የተከፈተው ለሰ/ት/ቤቱ አባላት መረጃዎችን ለመማዶር ይችላሉ። የዚህ ጣቢያ ሰው እንዴት ይባላል። እስኪመለከት ድረስ የይሆድን ተከታዮቹን የሚለክለውን መረጃዎችን ለማጠናቀቅ ለመማዶር ስለእኛ። እኛን ለመማዶር ለመብራት ለመመልከት ለክብጂ እንስማማ። አብዛኛዎቹን እና እናት ሰ/ት/ቤቱ አዋጅዎችዎን በስም እንላክላለን።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

24 Jan, 10:57


ስማችሁ ከላይ የተዘረዘረ አባላት በ18 ለቅዱስ ጊዮርጊስ በዓል የምታገለግሉ ሲሆን ዛሬ ማታ የአገልግሎት ልብስ እንድትወስዱ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

23 Jan, 18:29


ነገ የኪዳነ ምህረት አገልግሎት ስላለ ቅድመ ቀዳማይ እና ወጣቶች ክፍል በአንድ ላይ ስለሆነ ጸሎት 11:00 ሰዓት ነው የሚጀመረው በሰዓት እንድትገኙ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

23 Jan, 14:02


ሰላም እንዴት ሰነበታቹሁ
ለሚካኤል ያገለገላቹሁ ወጣቶች ሁላቹሁም
በ16 እና 19 ማታ እንደተለመደው በሰዓ ተጌታቹሁ እንድታገለግሉ
ማሳሰቢያ፡ ያለፈቃድ የቀረ ወይም ያረፈደ ለቀጣዩ አገልግሎት አይሳተፍም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

21 Jan, 07:03


#አስደሳች_ዜና
ጥር 9 በተደረገው የፍጻሜ ውድድር ላይ እህታችን #ቤሩታዊት_አያሌው 2 ተኛ በመውጣት የሰ/ት/ቤታችንን ስም አስጠርታለች በዚሁም የምስክር ወረቀት እና ለሰ/ ት / ቤታችንም የአክሲኦን ሽልማት አስገኝታለች

ለእህታችን ረጅም የአገልግሎት ዘመንን ያድልልን🙏🙏🙏👏👏👏

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

21 Jan, 05:38


ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት pinned «📷 በብዙ አባላት ጥያቄ መሰረት በ 10 ፣ 11 እና 12 የተነሱትን የአባላት ፎቶ መውሰድ የምትፈልጉ አንድ ጊዜ 50 ብር በመክፈል ያላችሁን ፎቶ እንዳለ መውሰድ ትችላላቹ። ⚠️ ማሳሰቢያ 50 ብር የምትከፍሉት ለአንድ ፎቶ ሳይሆን ለሁሉም ፎቶ ነው (ማለት 10 ፎቶ ያለውም ፣ ከዚያ በላይ ያለውም ሰው የሚከፍለው 50 ብር ብቻ ነው)። ፎቶአችሁን በ @Mickeyas21 መጠየቅ ትችላላቹ። ድምጽ ወምስል…»

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

20 Jan, 21:29


''ሖረ ኢየሱስ እም ገሊላ ኀበ ዮሐንስ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ''

በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

ለቀጣይ አመት በሰላም ያድርሰን
ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ጥር 2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

12 Jan, 08:22


የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ የምትማሩ ልጆች ዛሬ 10፡00 መምህሩ ስለሚመጣ ማንም እንዳይቀረ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

11 Jan, 15:45


ሣልሳይ ክፍል አባላት ነገ 10፡00 ትምህርት ስላለ በሰዓት እንድትገኙ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

10 Jan, 19:42


ወረብ ላይ ያላቹ አባላት ነገ #ቅዳሜ 12፡00 እስከ 1:00 ድረስ ወረብ ጥናት ስለሚኖረን በሰዓታቹ እንድትገኙ ። እየተገኛቹ ያልሆናቹ ከትላንት ጀምሮ የወረብ አቴንዳንስ እየተያዘ መሆኑን እና ምንም አይነት ቅሬታ ማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ::

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

10 Jan, 16:12


ካልዓይ ክፍል ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ተምራችሁ ያጠናቀቃችሁ ቅዳሜ (ነገ ) 12:00 ሰዓት አዲስ ትምህርት ስለሚጀመር በሰዓት እንድትገኙ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

10 Jan, 04:49


ትላንት ዩኒፎርም አጠባ ላይ ያልተገኛቹ ልጆች ዛሬ ማለትም አርብ መጥታቹ ዩኒፎርም እንድትወስዱ እና መጥቶ ያልወሰደ ጥምቀትን እንደማያገለግል እናሳስባለን።
ንብረት ክፍል

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

08 Jan, 19:29


ከዚህ በፊት የወረብ ስልጠና ወስዳቹ ተፈትናቹ አልፋቹ ወረብ ስታቀርቡ የነበራቹ ነገር ግን አጫብር ወረብ ያልሰለጠናቹ ነገ ሐሙስ እና አርብ ከ 12:00 - 1:00 ለሁለት ቀን ለብቻቹ ስልጠና ስለሚሰጥ በሰዓቱ እንደችገኙ ።


ጥምቀት የምታገለግሉ ወረብ ላይ ያላቹ አባላት ነገ ጀምሮ በሰዓት እየተገኛቹ እንድታጠኑ ከነገ ጀምሮ የራሱ አቴንዳንስ ቁጥጥር ይኖረዋል

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

08 Jan, 11:01


ዩኒፎርም አጠባ ስም ዝርዝር
ቀን አርብ 02/05/17

1.ኢየሩሳሌም ተስፋዬ
2.ሀሴት ሰለሞን
3.ርብቃ ተመስገን
4.ቤዛዊት ግርማ
5.ነፃነት ብርሀኑ
6.ማህሌት ዮሴፍ
7.መክሊት አስናቀ
8.ትዕግሥት ተስፋዬ
9.ያብስራ ነቢዩ
10.ሰላማዊት እንዳለ
11.ቤተልሔም አባይነህ
12.ዮርዳኖስ የሱነህ
13.ረድኤት በሀይሉ
14.ሄራኒ አብርሃ
15.ሴና ፋንታ
16.አብርሀም ወንድምአገኝ
17.ቤተልሔም ሀይሉ
18.ፍቅር ፍቃዱ
19.አየለች ተሰማ
20.ሂሩት ሚካኤል
21.ቤተልሄም ሙሉጌታ
22.የምስራች ተክሉ
23.ፍኖት ዝይን
24.ጽዮን ዘለቀ
25.ብርቱካን ባልቻ
26.ፍኖት ፍቃዱ
27.ሀና ለገሰ
28.ዮናስ ስጦታው
29.ዳዊት መለሠ
30.አለምነሽ ፀጋ
ማሳሰብያ :-ከ9:30 - 10:00 ሰአት ድረስ ያልመጣ አባል በድጋሚ እደሚመደብ እና መቅረት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

08 Jan, 11:01


ዩኒፎርም አጠባ ስም ዝርዝር
ቀን ሀሙስ 01/05/17

1.ስምረት ጌታቸው
2.ሲሳይነሽ መዝገቡ
3.ዲ/ን ገዛኸኝ ደረጃው
4.ማህሌት ዳንኤል
5.ሰላም ታደሰ
6.ቤተልሄም ፍቃዱ
7.ሻምበል ሙሉጌታ
8.ግርማ ገበየሁ
9.ሜሮን ብርሀኑ
10.ዲ/ን ሳሙኤል እንዳለ
11.ዲ/ን ብሩክ በፍቃዱ
12.መሠረት ድሪባ
13.ኢያሱ የሱነህ
14.ዳግም ጉማታ
15.ፍሬህይወት ሙላቱ
16.ሙሉወርቅ በላቸው
17.መሠረት ደጉ
18.ዘነቡ ተገኝ
19.ዲ/ን ሚኪያስ ምትኩ
20.ሀይማኖት ሄኖክ
21.ምህረት ብንያም
22.ሜላት ሀብታሙ
23.ስርጉተ ብርሀን
24.ቅድስት አለሙ
25.እድላዊት ጌታነህ
26.ቃልኪዳን ሞላ
27.አየለች ረጋሳ
28.ናርዶስ ሰለሞን
29.ተመስገን ሲሳይ
30.ኤርሚያስ ያሬድ
ማሳሰብያ :-ከ9:30 - 10:00 ሰአት ድረስ ያልመጣ አባል በድጋሚ እደሚመደብ እና መቅረት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

07 Jan, 12:04


🕯️ በዛሬው እለት የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል የሆነችው እህታችንን ነፃነት ብዙወርቅ የእናቷ ሰልስት ስለሆነ በቤታቸው ሔደን ለማፅናናት ሁላችሁም የቅድመ ቀዳማይ ክፍል እና የወጣት ክፍል አባላት 10፡00 አዳራሽ በሰአት እንድንገኝ።

ለሐዘንተኞች እግዚአብሔር መጽናናቱን ይስጥልን!

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

07 Jan, 09:59


ከፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ወረብ ጥናት ስለሚጀመር ሁላችሁም ወረብ ላይ ያላቹ አባላት እንድትገኙ

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

07 Jan, 09:55


ሖረ ኢየሱስ እም ገሊላ ኀበ ዮሐንስ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ
ወወጺዖ እም ማይ ተርኅወ ሰማይ መፅዐ ቃል እም ደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

07 Jan, 05:11


🎉 መልካም በዓል | እንኳን አደረሳችሁ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

06 Jan, 12:25


ዝክረ ልደተ እግዚእ
''ሃሌ ሉያ ንሰክብ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት''

በትላንትናው እለት የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በደብራችን በፈረንሳይ ጉራራ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
በእለቱም፦ የህብረት ዝማሬ ፣ የበገና ዝማሬ ፣ ትምህርተ ወንጌል ፣ ወረብ ፣ ወግ ፣ መንፈሳዊ ተውኔት ቀርቧል።

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

06 Jan, 10:33


ዝክረ ልደተ እግዚእ
''ሃሌ ሉያ ንሰክብ ወልደ እምዘርዓ ዳዊት''

በትላንትናው እለት የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በደብራችን በፈረንሳይ ጉራራ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
በእለቱም፦ የህብረት ዝማሬ ፣ የበገና ዝማሬ ፣ ትምህርተ ወንጌል ፣ ወረብ ፣ ወግ ፣ መንፈሳዊ ተውኔት ቀርቧል።

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

03 Jan, 15:19


ነገ ቅዳሜ 12 ሰዓት የእሑድን ዝማሬ የመጨረሻ ስለምናጠና ሁላችሁም እንድትገኙ

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

01 Jan, 11:56


🎉 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አስደሳች ዜና
የአእላፍ ዝማሬ ጉዞ

የፊታችን ሰኞ ታህሳስ 28 በቦሌ ደብረ ሳሌም መድሐኔዓለም ቤ/ክ  ከቀኑ 9ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው የአእላፋት ዝማሬ ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉ ምእመናን የ ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት  የትራንስፖርት አቅርቦት ስላዘጋጀ የምትሄዱ ምእመናን ከወዲሁ በሰ/ት/ቤቱ መዝሙር ቤት እንድትመዘገቡ  እናሳስባለን

ዋጋ - 200 ብር ብቻ

ያለው ቦታ ውስን ስለሆነ በቶሎ ይመዝገቡ
ለበለጠ መረጃ
0934469482
0910726773

አዘጋጅ፦ ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

30 Dec, 09:43


🔅 ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባዔ

ዝክረ ልደት


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

'' ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የኾነ ተወልዶላችዃልና።'' (ሉቃ 2፥11)

በዕለቱ የሚቀርቡ
- ያሬዳዊ ወረብ
- ትምህርተ ወንጌል
- የበገና ዝማሬ
- ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች
- የህብረት (የአእላፍ ዝማሬ)

አዘጋጅ፦ ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት ከስብከተ ወንጌል ጋር በመተባበር

ታህሣሥ 2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

30 Dec, 08:17


እንኳን ደስ አላችሁ

በሰንበት ትምህርት ቤታችን ለ3 ወር ልዩ የኪነጥበብ ስልጠና ሲሰለጥኑ የነበሩ አባላት በትላንትናው ዕለት ተመርቀዋል።

በእለቱም፦
እጅግ ማራኪ ሁሉንም ያስደመመ ልዩ የመመረቂያ ድራማ አቅርበዋል። እንዲሁም መነባነብ ፣ የህብረት ዝማሬ እና የተለያዩ መርሐ ግብራትን አቅርበዋል።

በመጨረሻም ትምህርታቸውን አጠናቀው ለተመረቁ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ተሰቷቸዋል።

እንዲሁም በ 2016 ዓ.ም መልካም የስራ አፈጻፀም ላሳዩ ንዑሳን አባላት የማበረታቻ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።

ከእህት ደብር ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የኛን ሰንበት ተናሪዎች ለማስተማር/ለማሰልጠን ለመጣው ወንድማችን አሸናፊ የምስጋና ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ታኅሣሥ 21/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

26 Dec, 19:46


⚠️ጥብቅ ማሳሰቢያ
የፊታችን ታህሳስ 27 ለሚኖረን ዝክረ ልደት መርሐ ግብር የህብረት ዝማሬ ጥናት ላይ ሁላችንም አባላት በህብረት ዝማሬ እንደምናቀርብ ይታወቃል ስለሆነም የፊታችን እሑድ 12 ሰዓት በመዝሙር ጥናት ሰዓት ከ ቅ/ ቀዳማይ ክፍል ጋር የመጨረሻ ጥናት እና የሰልፍ ስርዓት ስለምንይዝ ከዚህ በታች በተቀመጡት የሠልፍ ምድቦች እራሳችሁን በመመልከት በዕለቱ በመገኘት የመጨረሻ ጥናታችሁን እንድታደርጉ እንድትገኙ እናሳስባለን በማትገኙ አባላት ላይ ባለፈው እሑድ ባስተላለፍነው መሠረት ከፊት በሚኖሩት አገልግሎቶች ላይ ጥምቀትንም ጨምሮ ማታገለግሉ መሆኑን እንገልፃለን ።

#ሰልፍ_1

አቶ ተስፋ ፀጋዬ
ወ/ሮ ዝናሽ ኃይሉ
ዮርዳኖስ ታደሰ
ቃልኪዳን እንዳለ
አለሙ ጉልማ
ትንሣኤ አሊ
አበራሽ ዳጨው
መስከረም ብርሃኑ
ጌታቸው ማሞ
ብንያም ዮናስ
በቃል ተካልኝ
ፌቨን በሃይሉ
ዘኤልሻዳይ ክብሩ
ቃልኪዳን መስፍን
ስምረት ጌታቸው



#ሰልፍ_2

ቤተልሄም ወ/ማርያም
ዘበነ ሙላቱ
ቤሩታዊት አያሌው
ንግሥት ሽፈራው
ኪሩቤል ታከለ
ሀብታሟ ሲሳይ
በቀለ ባልቻ
ኤደን ፍቃዱ
ሲሳይነሽ መዝገቡ
ናሁሰናይ ነዲ
ፀደንያ ዳንኤል
መቅደስ አያሌው
መሰረት በቀለ
ዘላለም መኮንን
ዲ/ን ገዛኸኝ ደረጃው



#ሰልፍ_3

ሰላማዊት ተስፋዬ
ማንዴላ መኮንን
ፋሲል ወንድዬ
አወቀ ጌትነት
ማህሌት ዳንኤል
ሮዳስ መንገሻ
ሰላም ታደሰ
ገነት ዝይን
ቤተልሄም ፍቃዱ
መሰለ ሰንደቅ
ቅድስት ታዴ
ሻምበል ሙሉጌታ
ያኔት ካሳሁን
ሩሃማ መስፍን
ግርማ ገበየሁ



#ሰልፍ_4

ፌሽን ፍቃዱ
የአብሥራ አዳነ
ሲሳይ ጌታቸው
ሜሮን ብርሃኑ
እፀገነት ብሩ
ዩርዳኖስ ዘሪሁን
የአብሥራ ዳኛቸው
ዲ/ን ሳሙኤል እንዳለ
ቡሩክ በፍቃዱ
ቤዛዊት ቸርነት
መሰረት ድሪባ
ናርዶስ ታሪኩ
ዲ/ን ኪሩቤል አራጋው
ተስፋነሽ በቀለ
ሰብለ ወንጌል ሰለሞን


#ሰልፍ_5

አለም ፀሐይ ሰለሞን
መሰረት በዳዳ
ቤተልሄም ካህሳይ
ኢያሱ የሱነህ
ወይንሸት አበበ
ዳግም ጉማታ
ሀይማኖት ሀብታሙ
ፍሬሕይወት ሙላቱ
ትዕግስት ፍቃዱ
ሜሮን ብዙአየሁ
ትዕግስት ደመቀ
ሙሉ ወርቅ በላቸው
ነፃነት አለምነው
ሙሉሴት ታዬ
ፍሬሕይወት እንግዳሰው
መሰረት ደጉ
ዘነቡ ተገኝ

የዝማሬው መሪዎች
1 ዲ / ን ያዕቆብ ጌታቸው
2 ዲ / ን ዮናስ ፋሲክ
3 ተስፋዬ ሲሳይ
4 መቅደላዊት ከበደ
5 ሳምኬት ፋሲል
6 ኢየሩሳሌም ተስፋዬ
7 ሀሴት ሰለሞን
8 ሜላት ሀብታሙ
9 ነፃነት ብርሃኑ

⚠️ከዚህ በላይ ስማቹ የተዘረዘረ አባላት እስከ ጥምቀት ላለው አገልግሎት የወጣ ስም ዝርዝር መሆኑን እንገልግለን ቅሬታ ያላቹ አባላት አባላት አስተዳደር ክፍልን እስከ እሑድ ድረስ ማቅረብ ትችላላቹ ከእሑድ በኋላ የሚመጣ የቅሬታ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

25 Dec, 19:21


የነገ ሐሙስ መዝሙር ጥናት ሁለችሁንም አገልግሎት ላይ ያላቹ አባላት የሚመለከት ስለሆነ መዝሙሮቹን በደንብ አጥንታችሁ እንድትገኙ

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

25 Dec, 11:02


ቅድመ ቀዳማይ ዩኒፎርም ያላጠባቹ ሐሙስ 10:00 ሰአት ላይ መጥታቹ እንድታጥቡ መቅረት የተከለከለ ነው

ንብረት ክፍል

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

22 Dec, 18:06


🎓 የምርቃት መርሐ ግብር

በጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት ኪነጥበብ ክፍል ባዘጋጀው 1ኛ ዙር ልዪ የቲያትር ስልጠና ትምህርታቸውን በተገቢው ሰልጥነው የጨረሱ ተማሪዎች ምርቃት።

የምርቃቱ ቀን፦ ዕለተ እሑድ ታኅሣሥ 20/2017 ዓ.ም

ቦታ በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ

በዕለቱም፦ ትምህርተ ወንጌል
- ዝማሬ
- መነባነብ
- ግጥም
- በላልበልሃ
- ድራማ
እና የተለያዩ መርሐ ግብራት ይቀርባሉ

⚠️ እርሶም ተጋብዘዋል መቅረት የተከለከለ ነው!!!

📍 ቦታ ፈረንሳይ ጉራራ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን።

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ታኅሣሥ 14/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

21 Dec, 10:47


⚠️ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ

ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት አባል የሆነው ህፃን በእምነት ምስክር እድሜው 12 ዓመት የሚሆን በዕለተ ረቡዕ 9/04/2017 ከትምህርት ቤቱ እንደወጣ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር በመሆን ስላልተመለሰ ያገኛችሁት ሰዎች ለሰንበት ትምህርት ቤቱ እንድታሳውቁን ስንል በትህትና በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ከታች ባለው ስልክ ይደውሉልን
📞 0942073757

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

20 Dec, 19:26


ዐቢይ መንፈሳዊ ጉባኤ
ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም በጠዋት እና በማታ መርሐ ግብር

''ነፍሴ አንተን ተጠማች'' መዝ፦ 63 ፥ 1

ከታላላቅ ሰባኪያን እና ዘማሪያን ሃር
⌚️ሠዓት
ጠዋት ከ 1:00 ጀምሮ እስከ
ማታ ከ 10:30 ጀምሮ

አዘጋጅ፦ የደብሩ ስብከተ ወንጌል ክፍል

📍ፈረንሳይ ጉራራ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

⚠️ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (link) በመንካት የደብሩን የቴሌግራም እና ፌስቡክ ድህረ ገፅ በመከተል በየቀኑ የሚለቀቁ መረጃዎችን ይከታተሉ።

ቴሌግራም፦ https://t.me/kmgl16
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=61563805325526

ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

17 Dec, 08:33


ሀሌ ሀሌሉያ (በሰማይ በምድር)
ሀሌ ሀሌሉያ (2)
በሰማይ በምድር ምሕረት ሆኗልና
ሃሌ ሃሌሉያ አሜን ሀሌሉያ
መላእክት ዘመሩ አመሰገኑት
እየተደነቁ በአምላክ ቸርነት (2
ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት አሉ
እረኞችም አብረው እርሱን አከበሩ (2)
ዓለምን ለመፍጠር ከተጠበበት
ይበልጣል ከሁሉም እኛን ያዳነበት (2)
በዳግማዊት ሔዋን ከእመቤታችን
በረቂቅ ጥበቡ ተወልዶ አዳነን (2)
ሁላችሁም ግቡ ከቤተልሔም
ታገኙታላችሁ በከብቶች ግርግም (2)
ኢየሱስ ክርስቶስ ወኃቤ ሰላም
ሞታችንን ወስዶ ሕይወትን ሰጠን (2)
ወልደ እግዚአብሔር መጣ ከላይ ከሰማይ
ፍቅር አወረደው ከመንበሩ ላይ
አልተጸየፈም መሆን በግርግም
ትሕትናው ደነቀኝ የመድኃኔዓለም (2)

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

17 Dec, 08:17


እነዚህ ዝማሬዎች በህብረት በቅድመ ቀዳማይ ና ወጣት ክፍል አባላት የሚዘመሩ ናቸው ሁለችሁም በደንብ አጥንታችሁ እንድትገኙ

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

17 Dec, 08:11


ሰላም እንደምን ቆያቹ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በአል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የዝማሬ እና ኪነ ጥበባዊ መርሒ ግብሮች እንደምናዘጋጅ ይታወቃል ስለሆነም በዚህኛው ዓመት በታህሳስ 27 ለየት ባለ መልኩ ለማክበር ዝግጅት እያደረግን እንገኛለን ።
በዕለቱም የወረብ አገልግሎት በ ቅድመ ቀዳማይ ክፍል አባላት
✝️ ትምህርተ ወንጌል
የበገና ዝማሬ በ1ኛ እና 2ኛ ዙር የበገና ተመራቂዎች
የልደት በአልን የሚያወሱ ሥነ - ጽሑፍ እና ወግ
የህብረት ዝማሬ በቅድመ ቀዳማይ እና ወጣት ክፍል አባላት

⚠️ማሳሰቢያ
ሁላችሁም አገልግሎት ላይ ያላቹ አባላት በምትመደቡበት መርሐ ግብር ዝግጅት ላይ የሚመለከታቸው ክፍሎች በሚያዟቹ እና በሚቀጥሩአቹ ቀን በመገኘት እንድትዘጋጁ እና በዚህ በልደት በዓል ዝማሬ አገልግሎት ላይ ሁለችሁም አባላት የቅድመ ቀዳማይ እና ወጣት ክፍል አባላት የምትሳተፉ ሲሆን ያልተሳተፋቹ አባላት ለጥምቀትም እንደማትሳተፉ ከወዲሁ እናሳውቃለን ።

ጽ/ጽ /ሰ/ት/ቤት
ጽ/ቤት

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

16 Dec, 04:10


እንኳን ደስ አላችሁ

በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት በ2016 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርቱን ሲከታተሉ የነበሩ የ4ኛ ፣ 6ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በሀገረ ስብከቱ የተዘጋጀውን ፈተና በማለፋቸው በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት የምርቃት መርሐ ግብሩ ተካሂዷል።

ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም
ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

02 Dec, 12:37


ከላይ የተለቀቀውን ሊንኩን በመንካት ሙሉ ቪዲዮውን በማየት የሰንበት ትምህርት ቤቱን የዩቲዩብ ገጽ ያበረታቱ።

በተጨማሪም #like #share በማድረግ የሰንበት ትምህርት ቤቱን የዩቲዩብ ገጽ ያበረታቱ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

02 Dec, 12:18


https://youtu.be/9XVYaKCX6R8?si=1GUilbz1biXIluKA

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

24 Nov, 07:54


ዛሬ 10:00 ትምህርት እንደጠበቀ ነው።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

23 Nov, 14:29


የሳልሳይ ክፋል አባላት የነገረ ቅዱሳን ትምህርት ስትማሩ የነበራችሁ መምህሩ ነገ የፈተናው ውጤት ለመስጠት 4፡00 ስለሚመጣ በሰዓት እንድትገኙ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

23 Nov, 13:06


የምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን መምህሩ ዛሬ መምጣት ስለማይችል ዛሬ 12:00 ኮርስ የለም።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

22 Nov, 06:28


ከላይ የተለቀቀውን ሊንኩን በመንካት ቪዲዮውን በማየት የሰንበት ትምህርት ቤቱን የዩቲዩብ ገጽ ያበረታቱ።

በተጨማሪም #like #share በማድረግ የሰንበት ትምህርት ቤቱን የዩቲዩብ ገጽ በጋራ እናሳድግ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

22 Nov, 06:28


https://youtu.be/QeYBnPGJo38?si=ghsEhnCbHB_IOdHk

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

22 Nov, 03:13


በዛሬው እለት በደብራችን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን የሊቀ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን አመታዊ ክብረ በዓል ተከብሮ ውሏል።

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ህዳር 12/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

21 Nov, 19:02


https://youtu.be/xrDQMrPi0aw

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

21 Nov, 13:47


በዛሬው እለት በደብራችን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን የሊቀ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን አመታዊ ክብረ በዓል ተከብሮ ውሏል።

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ህዳር 12/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

19 Nov, 17:48


https://t.me/FerensaySundaySchoolUnity

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

18 Nov, 17:26


ይህ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ ለምትማሩ ልጆች የአሳይመንት ዋቢ መጻሕፍት ናቸው::


# የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች (ዳንኤል ክብረት)
# ቅዱሳን መካናት በኢትዮጵያ (ዘመድኩን በቀለ)
# ተድባበ ማርያም (በደብሩ የታተመ)
# የግራኝ አህመድ ወረራ (በተክለ ጻድቅ መኩሪያ)
# የኢት/ያ ቤተ ክርስቲያን ትላንትናና ዛሬ ( በኢ/ኦ/ተ/ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት)
# የመርጡለ ማርያም ገዳም ታሪክ (በገዳሙ ሰ/ጉባኤ የታተመ)


የቀረውን በራሳችቹ ፈልጉ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

15 Nov, 03:21


ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረ የካልዓይ ክፍል አባላት እሁድ የቤተ ክርስትያን ታሪክ በኢትዮጵያ የምትፈተኑ ስለሆናችሁ እንድትዘጋጁ።

1. ሀብታም ታርቆ
2. ፋሲካ አመሉ
3. ዳግማዊት ብርቅነህ
4. ህሊና ብርቅነህ
5. ማህሌት አታላይ
6. ቤተልሔም ሙሉጌታ
7. ሒሩት ሚካኤል
8. ሎታ ፍታወቅ
9. ትዕግስት ፍቃዱ
10. የምስራች ገላነህ
11. ሜሮን ኢያሱ
12. ፈለቀች በቀለ
13. ሳምራዊት አሰፋ
14. እፀብድንቅ ደመቀ
15. ሐይማኖት ሐብታሙ
16. ፍሬህይወት እንግዳሰው
17. መሰረት አዲሱ
18. መድሓኒት ጥላሁን
19. ምህረት ሙሉጌታ
20. ዝኑ ሙሉጌታ
21. ቅድስት ሞገስ
22. ታድላ ገበየሁ
23. ጽዮንማርያም ግርማ
24. አርሚያስ አስታጥቄ
25. ሔኖክ ወንደሰን
26. ተመስገን ወንድሙ
27. ፍኖት ዝይን
28. ቤሩታዊት አያሌው
29. ኢያሱ የሱነህ
30. ተስፋዬ ማስረሻ
31. ጠጅቱ ተዋበ
32. ትዕግስት ደመቀ
33. ሙሉወርቅ በላቸው
34. ናሁሰናይ ነዲ
35. ነፃነት አለምነው

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

14 Nov, 13:22


☝️ ስም ዝርዝራችሁ የተጠቀሰ አባላት በተመደባችሁበት ዕለት በሰዓት መታችሁ እንድታገለግሉ ማርፈድ ሆነ መቅረት በፍጹም የተከለከለ ነው።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

14 Nov, 13:18


እሑድ [ኅዳር ፰/፳፻፲፯.ዓ.ም]12:30  ጠዋት የሰርግ አገልግሎት የግቢ ውስጥ አገልግሎት
1.ፋሲል ወንድዬ
2. አወቀ ጌትነት
3. ግርማ ገበየሁ
4. መስከረም ብርሃኑ
5. አበራሽ ዳጨው
6.ሻምበል ሙሉጌታ
7. ሩሐማ መስፍን
8. ያኔት ካሣሁን
9. ሲሳይ ጌታቸው
10. መቅደስ አያሌው
11. የአብሥራ ዳኛቸው
12. መስከረም በዳዳ
13. መሰረት በቀለ
14. ዳግም ጉማታ
15.ቤተልሔም ወ/ማርያም
16. ሳምኬት ፋሲል
17.ጸደንያ ዳንኤል
18. ሮደስ መንገሻ
19. ማኅሌት ዳንኤል
20. ኤደን ፈቃዱ
21. ሀብታሟ ሲሳይ
22. ሥምረት ጌታቸው
23. ቃልኪዳንመስፍን
24. የአብሥራ ንጋቱ
25. ኪሩቤል ታከለ
26 የአብስራ አዳነ
እሑድ [ኅዳር ፰/፳፻፲፯.ዓ.ም] ረፋድ
4፡30  የሰርግ አገልግሎት ከግቢ ውጪአገልግሎት

1. መስከረም ብርሃኑ
2. አበራሽ ዳጨው
3. ዘበነ ሙላቱ
4. ዓለሙ ጉልማ
5. በቀለ ባልቻ
6. ብንያም ዮናስ
7. ሰብለወንጌል ሰሎሞን
8. ዓለምፀሐይ ሰሎሞን
9. መቅደላዊት ከበደ
10. ቤተልሔም ወ/ማርያም
11. ዲ.ን ያዕቆብ ጌታቸው
12. ዲ.ን ሳሙኤል እንዳለ
13. ዲ.ን ኪሩቤል አራጋው
14. ዲ.ን ገዛኸኝ ደረጃው
15. ፌቨን በኃይሉ
16. ዘላለም መኮንን
17. ተስፋነሽ በቀለ
18.ቤሩታዊት አያሌው
19. ጸዳንያ ዳንኤል
20.ቤዛዊት አበባው
21. ገነት ዝይን

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

14 Nov, 13:18


ሰኞ {ኅዳር ፱/ ፳፻፲፯ ዓ.ም } ሠርክ 11:30 የሠርግ አገልግሎት {ከግቢ ውጪ }

1. ዓለሙ ጉልማ
2. በቀለ ባልቻ
3. ብንያም ዮናስ
4. ዘላለም መኮንን
5. ዲ.ን ያዕቆብ ጌታቸው
6. ዲ.ን ሳሙኤል እንዳለ
7. ዲ.ን ኪሩቤል አራጋው
8. ዲ.ን ገዛኸኝ ደረጃው
9. ፀደንያ
10. ዘበነ ሙላቱ
11. ፋሲል ወንድዬ
12. ቤተልሔም ወ/ማርያም
13. መቅደላዊት ከበደ
14. ሳምኬት ፋሲል

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

13 Nov, 06:23


https://youtu.be/IyHuRwC19H0?si=4Hdeeofg6Orj0tAq

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

12 Nov, 17:00


ለቅድመ ቀዳማይ አባላት በሙሉ ከነገ ጀምሮ ከ 10:00 - 11:30 የወረብ ጥናት ስላለ በሰዓት እንድትገኙ።

መዝሙር ክፍል

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

11 Nov, 18:49


ከላይ የተለቀቀውን ሊንኩን በመንካት ቪዲዮውን በማየት የሰንበት ትምህርት ቤቱን የዩቲዩብ ገጽ ያበረታቱ።

በተጨማሪም #like #share በማድረግ የሰንበት ትምህርት ቤቱን የዩቲዩብ ገጽ ያበረታቱ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

11 Nov, 18:47


🛑 የ2017 የጽርሐ ጽዮን የዜማ መሳሪያ ተመራቂ ተማሪዎች የቀረበ መዝሙር በክራር
https://youtube.com/watch?v=Id7V53YCN8U&si=qxnOXw1zWU1HISye

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

11 Nov, 07:44


'' አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ፤ አሥር አውታር ባለው በበገና እዘምርልሃለሁ።''
(መዝ፦ 143 ፥ 9)

እንኳን ደስ አላችሁ

የ2017 የ 2ተኛ ዙር የጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት የበገና እና የክራር ሰልጣኝ ተማሪዎች በሙሉ።

የአገልግሎት ዘመናችሁን ልዑል እግዚአብሔር ይባርክላችሁ።

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ህዳር 2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

10 Nov, 15:27


እንኳን ደስ አላችሁ

''ዐሥር ፡ አውታር ፡ ባለው ፡ በገና ፡ እዘምርልኻለኹ።''
(መዝ 143፥9)

🛑 በዛሬው ዕለት በጉራራ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት ለ 2ተኛ ዙር ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን የበገና እና የከራር ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በእለቱም፦
- መዝሙር በተመራቂ ተማሪዎች ቀርቧል።
- ለተመራቂ ተማሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በደብሩ አስተዳደር በመልአከ ብስራት መዓዛ ፈንታዬ ተበርክቶላቸዋል።
- ከተመራቂ ተማሪዎች ለመምህራን የምስጋና ስጦታም ተበርክቷል።

እንዲሁም ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ትልቅ ድጋፍ ስታደርግ የቆየችው ለእህታችን ለወ/ሮ ትዕግሥት ኢዶሳ የምስጋና ስጦታ ከጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት ተበርክቷል።

በመጨረሻም ለተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ የአገልግሎት ዘመናችሁን ልዑል እግዚአብሔር ይባርክላችሁ።

'' እንሆ፥እግዚአብሔርን፡የሚፈራ፡ሰው፡እንዲህ፡ይባረካል። ''
(መዝ 127፥4)

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ህዳር 1/2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

05 Nov, 10:29


ቅድመ ቀዳማይ ክፍል አባላት ዛሬ 11:00 ሰዓት ወረብ ጥናት ስላለ ወረብ ላይ ያላችሁ አባላት በሰዓቱ እንድትገኙ።

መዝሙር ክፍል

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

05 Nov, 09:42


Channel photo updated

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

03 Nov, 15:04


የሰርግ የምርቃት ፎቶ እንዲሁም ቅዱሳን ስነ ስዕላትን
ለወዳጅ ዘመድዎ ስጦታ መስጠት እና ማሰራት ከፈለጉ በሚፈልጉት ስፋት እና ቁመት ማሰራት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ 0965 89 62 03

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

01 Nov, 16:58


ለሣልሳይ እና ራብዕይ ክፍል አባላት በሙሉ እሁድ ማለትም በ24/02/2017 ለሁለቱም ክፍሎች የተጀመሩት ትምህርቶች ስለተጠናቀቁ አዲስ ትምህርት ስለሚጀመር 10፡00 ሰዓት እንድትገኙ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

27 Oct, 10:44


ዛሬ እሁድ ማለትም በ17 - 02- 2017 ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በሰ/ት/ቤታችን አዳራሽ ልዮ የፀሎት እና በተጋባዥ መምህራን የትምህርት መርሐ ግብር ስለ ተዘጋጀ ከቅድመ ቀዳማይ ጀምሮ እስከ ራብዓይ ክፍል ያላችሁ አባላት በሰዓቱ እንድትገኙ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

26 Oct, 08:26


ምስጢርተ ቤተ-ክርስቲያን የምትማሩ ዛሬ 12:00 ትምህርት ስላለ ማንም እንዳይቀር።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

25 Oct, 09:48


የፊታችን እሁድ ማለትም በ17 - 02- 2017 ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በሰ/ት/ቤታችን አዳራሽ ልዮ የፀሎት እና በተጋባዥ መምህራን የትምህርት መርሐ ግብር ስለ ተዘጋጀ ከቅድመ ቀዳማይ ጀምሮ እስከ ራብዓይ ክፍል ያላችሁ አባላት በሰዓቱ እንድትገኙ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

24 Oct, 19:34


የቤተ - ክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ የምትማሩ ከዚህ በላይ የተለቀቀውን pdf መምህሩ ለእሁድ አንድትዘጋጁ የላከው ነው።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

22 Oct, 08:04


ነገ እሮብ እና ሐሙስ የወረብ ጥናት ስላለ ሁላችሁም ወረብ ላይ ያላችሁ አባላት 12:00 አንድትገኙ።

መዝሙር ክፍል።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

21 Oct, 10:57


🎓 እንኳን ደስ አለሽ 🎉

የምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ።

- ንግሥት ሽፈራው (Department of accounting and finance)

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ጥቅምት 2017 ዓ.ም

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

21 Oct, 07:50


https://t.me/+3z5aXMIeRng1NjA0

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

21 Oct, 07:50


ሁላችሁም አባላት ይህንን የአባልነት ፎርም እየሞላችሁ በsoftcopy ከዚህ በታች የተቀመጠውን ማስፋንጠሪያ(Link) እየተጠቀማችሁ የተከፈተው ግሩፕ ላይ ላኩ።

ይንን ፎርም መሙላት የምትችሉት አባላት ቋሚ ሆናችሁ አገልግሎት ላይ ያላችሁ ብቻ ናችሁ።

አባላት አስተዳደረ ክፍል።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

20 Oct, 19:31


ሰላም እንዴት አመሻቹሁ
የፍቃድ ደብዳቤ እንድታስገቡ ብለን ተናግረን የነበር ሲሆን አንድ አንድ አባላት ያስገባቹሁት ደብዳቤ ግን ማስረጃ ያልተሟላ ስለሆነ ተማሪዎችም ሰራተኞችም የትምህርት እና የመስሪያ ቤት መታወቂያ እና እንዲሁም ተማሪዎች የትምህርት ፕሮግራም ሰራተኞች የመስሪያ ቤት ደብዳቤ አድርጋቹሁ የሰንበት ትምህርት ቤታችን ነገ እና ከነገ ወዲያ መዝሙር ቤት እንድታስቀምጡ ።

ማሳሰቢያ:-ከማክሰኞ ያሳለፈ ተቀባይነት የለዉም
አባላት አስተዳደር ክፍል

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

18 Oct, 12:02


ዩኒፎርም አጠባ የተመደባቹ አባላት ዛሬ አርብ 10:00 ሰአት እንድትገኙ ማርፈድም ሆነ መቅረት አይቻልም።

ንብረት ክፍል

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

17 Oct, 07:54


ዛሬ ወረብ ጥናት ስላለ ወረብ ላይ ያላችሁ ሁላችሁም አባላት 12:00 እንድትገኙ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

15 Oct, 18:08


ሰላም እንደምን አመሻችሁ
የማዕከላውያን ክፍል አባል እና የእህታችን የቅ/ቀዳማይ ክፍል አገልጋይ እህታችን ኢየሩሳሌም ተስፋዬ ታናሽ ወንድም  የሆነው ወንድማችን ህፃን ዮርዲያኖስ ተስፋዬ ሰልስት ስለሆነ ስ/ ት/ቤታችን በመኖሪያ ቤታቸው የጸሎት መርሐ ግብር እና የጧፍ ማብራት ስነ ስርዓት ከ 11፡ዐዐ ጀምሮ ስላዘጋጀን ወጣት ክፍል ያላችሁ እንዲሁም የቅድመ ቀዳማይ ክፍል አባላት 10፡ዐዐ ቤተ-ክርስቲያን ሁላችንም ተገኝተን እንሔዳለን በሰዓት ድረሱ።

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

14 Oct, 16:35


ዩኒፎርም አጠባ የተመደባቹ አባላት አርብ 10:00 ሰአት ስለተቀየረ ማርፈድም ሆነ መቅረት አይቻልም።

ንብረት ክፍል

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

14 Oct, 06:49


😭የሐዘን መግለጫ😭
የማዕከላውያን ክፍል አባል እና የ ቅ/ቀዳማይ ክፍል አገልጋይ እህታችን ኢየሩሳሌም ተስፋዬ ታናሽ ወንድም የሆነው ወንድማችን ህፃን ዮርዲያኖስ ተስፋዬ ባደረበት ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም ድካም ስላረፈ ሥርዓተ ቀብሩም ዛሬ ጥቅምት 4 በደብረ ፀሐይ ቅ/ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ከቀኑ 6 ሰዓት ስለሚፈፀም ሁላችሁም አባላት በቀብር ሥርዓቱ ላይ እንድትገኙ !

የቅድመ ቀዳማይ ክፍል አባላት 5 ሰዓት ላይ አዳራሽ በመገኘት የአገልግሎት ልብስ ለብሳቹ ሥርዓተ ቀብሩን እንድታጅቡ !

ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት

13 Oct, 18:32


በዛሬው እለት ነባር የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት የነበረ ጉባኤ።

''መሰባሰባችንን አንተው እርስ በእርሳችን እንመካከር'' (ዕብ ፲፥፳፭)

ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት
ጥቅምት 2017 ዓ.ም

1,784

subscribers

4,375

photos

21

videos