ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ @nwdnews Channel on Telegram

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

@nwdnews


የብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እና የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ እንዲሁም የሌሎች መምህራን ትምህርቶች፣ ስብከቶችና ተግሳጾች በተጨማሪም በሀገረ ስብከቱ የሚከወኑ ዓበይት ክንውኖች የሚተላለፉበት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የቴሌግራም ቻናል ነው። የቻናሉ ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በመጋበዝ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ያፋጥኑ።

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ (Amharic)

መርሐ ግብርድን የብፁዕ አቡነ ኤርምያስንና የብፁዕ አቡነ ቄርሎስን እና የሌሎች መምህራን ትምህርቶችን፣ ስብከቶችንና ተግሳጾችን በተጨማሪም ሀገረ ስብከቱ ዓበይት ክንውኖችን የሚተላለፉበት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት አዝናኝ ቴሌግራም ቻናል ነው። የቴሌግራምን ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በመጋበዝ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ያፋጥኑ።

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

03 Dec, 03:34


ዘመናዊ የአብነት ት/ቤቶችን ገንብተን ዘመኑን የሚዋጅ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድን እንድናፈራ ልገሳዎን ያድርጉ!

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

02 Dec, 14:07


#ወደ_ገላትያ_ሰዎች - የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሐተታ

ዲያቆን ኃይሌ አለልኝ (Hayle Allelgn) የተተረጎመው #ወደ_ገላትያ_ሰዎች የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሐተታ ሙሉ ገቢው በራያ ቆቦ ወረዳ ለአረቋቴ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገዳም እንዲውል ታስቦ የተዘጋጀ መጽሐፍ በስርጭት ላይ ነው!

#ዋና_አከፋፋይ፦
አርጋኖን መጻሕፍት መደብር Areganon Book Store
#አድራሻ፦
4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል 80 ሜትር ወረድ ብሎ የቀድሞ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ሕንፃ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የሚገኝበት ሕንፃ ውስጥ
#ስልክ፦
+251 912044752
+251 954838117

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

30 Nov, 15:31


https://youtu.be/sGvz5C0cVNg?si=fg-lFC8kAnKHomd2

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

30 Nov, 15:31


የመቅደስኽ ታቦት

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

30 Nov, 13:52


ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በወይብላ ምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የኅዳር ጽዮን ዓመታዊ በዓል ሲከበር እየተገነባ ስለሚገኘው አዳሪ የአብነት ት/ቤት ያስተላለፉት መልእክት።

ፕሮጀክቱን ለመደገፍ፦
ለሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት አዳሪ የአብነት ት/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት

#የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ➛ 1000268895993
#አባይ_ባንክ ➛ 2071111086582027
#ህብረት_ባንክ ➛ 2100116574227024
#ዳሽን_ባንክ ➛ 5222981650011
#አቢሲኒያ_ባንክ ➛ 15332956
#ቡና_ባንክ ➛ 1559501004676
#አዋሽ_ባንክ ➛ 01320281141100
#ብርሃን_ባንክ ➛ 1001038222028
#ኦሮሚያ_ኢንተርናሽናል_ባንክ ➛ 3662379
#አማራ_ባንክ ➛ 9900018948811

ለበለጠ መረጃ፦
➛ +251 913708168
➛ +251 924397121
➛ +251 911549205

#ለወዳጅዎ_ያጋሩ

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

12 Nov, 12:29


በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነት የጉባላፍቶ ወረዳ ቤተክህነት በ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምና በ2ኛ ሩብ ዓመት እቅድ ዙሪያ ከሰበካ ጉባኤ አመራሮች ጋር ሥልጠናና ውይይት ማድረጉን ገለጸ።

ወረዳ ቤተክህነቱ ከጥቅምት 16-29 ቀን 2017 ዓ.ም በአራት ቀጠናዎች ባካሄዳቸው የውይይት መርሐ ግብሮች የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቃነ መናብርት፣ ዋና ጸሐፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞችና ገንዘብ ያዥዎች ተሳትፈዋል።

በወረዳ ቤተ ክህነቱ የ2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምና በቀጣይ እቅድ አተገባበር ዙሪያ ለሰበካ ጉባኤ አመራሮች ሥልጠና መሰጠቱን ዋና ጸሐፊው መልአከ ኃይል ስጦታው ሞላ ያደረሱን መረጃ ያመለክታል።

በወረዳው ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት፣ በርካታ ተፈናቃዮችና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ማኅበራዊ ኀላፊነትን መወጣት፣ መረጃን በጥራት መመዝገብ ትኩረት የተደረገባቸው የሥልጠናና ውይይት ርዕሰ ጉዳዮች ነበሩ ተብሏል።

ሥልጠናውን የወረዳ ቤተክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅና የክፍል ኀላፊዎች የሰጡት ሲሆን ከ171 አብያተክርስቲያን የተውጣጡ የሰበካ ጉባኤ አባላት መሳተፋቸውን ወረዳ ቤተክህነቱ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ይወዳጁ ለሌሎችም ያጋሩ።

~ቴሌግራም፡ https://t.me/NWDnews

~ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia

~ድረገጽ፡ https://eotc-nw.org

~ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/EOTCNWD?mibextid=ZbWK

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

12 Nov, 11:32


~ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

11 Nov, 15:49


#ዜና_እረፍት

በተለያዩ የቤተክርስቲያን መዋቅሮች ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉት መልአከ ብርሃን ፍቅር ጸጋው ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት)

መልአከ ብርሃን ፍቅር ጸጋው በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቄትና ግዳን ወረዳ አብያተ ክህነት በተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለበርካታ ዓመታት በኃላፊነት ሠርተዋል። እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ጂንካ የጉሊላና የጋዞር ወረዳ ቤተክህነትን ለ6 ዓመታት በሥራ አስኪያጅነት ማገልገላቸውን በሕይወት ታሪካቸው ተጠቅሷል።

መልአከ ብርሃን ፍቅር ጸጋው ለጥቂት ቀናት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በተወለዱ በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሀገረ ስብከትና የወረዳ ቤተክህነት የሥራ ኀላፊዎች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ምዕመናን በተገኙበት በመቄት ወረዳ ፍላቂት ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው በሙሉ መጽናናትን ይመኛል።

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

11 Nov, 11:34


በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በቆቦና መርሣ ወረዳ አብያተክህነት በርካታ የሌላ እምነት ተከታዮች ተጠምቀው ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መቀላቀላቸው ተገለጸ።

ኅዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት)

የቆቦ ከተማ አስተዳደርና የሐብሩ መርሣ ወረዳ አብያተ ክህነት አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤያቸውን ጥቅምት 30 እና ኅዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም አካሂደዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነት ሊቀ ጳጳስ በወረዳዎቹ ተገኝተው ጉባኤያቱን መርተዋል፣ ተሳታፊዎችን አስተምረዋል፣ አባታዊ መመሪያም አስተላልፈዋል።

በጉባኤው ኹለቱም ወረዳዎች ባለፈው የአገልግሎት ዓመት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና በራስ አገዝ ልማት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ለጉባኤው ተሳታፊዎች አቅርበዋል።


የቆቦ ከተማ አስተዳደር ቤተክህነት በ2016 ዓ.ም 11 ሽህ 104 ካሬ ሜትር ቦታ ለጥምቀተ ባሕር ከከተማ አስተዳዳሩ መቀበሉን በሪፖርቱ ገልጾ ባለፈው ዓመት በዚሁ ተመሳሳይ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የጥምቀተ ባሕር ችግር እንዲፈታ በጠየቁት መሠረት ከተማ አስተዳደሩ ለዓመታት ጥያቄአቸው ምላሽ በመስጠቱ አመስግነዋል።

በቆቦና ሐብሩ መርሣ ወረዳ አብያተክህነት ባለፈው ዓመት በኹሉም አብያተክርስቲያን ከ150 በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተጠምቀው ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ኅብረት መቀላቀላቸውን በሪፖርታቸው አመላክተዋል።

በመርሣ ከተማ ፈለገ አክሊል መርሶ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤልና በደብረ ጽዮን ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ማርያም አብያተክርስቲያን ከ320 በላይ ሕጻናትን የዘመናዊ ትምህርት በማስተማር ለሀገር ግብረ ገብ ትውልድ በማፍራት የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑ ተገልጿል።

የወረዳ አብያተ ክህነቱ በ2017 ዓ.ም በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ዘርፎች የሚያከናውኗቸውን ተግባራት እቅድ ለጉባኤው አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነት ሊቀ ጳጳስ በጉባኤያት ለተሳተፉ የአብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ሀገረ ስብከቱ በተያዘው ዓመት ትኩረት ያደረገባቸው ጉዳዮችና በምሥጢራት አፈጻጸም በተለይም በቅብዓ ሜሮንና ቅብዓ ቅዱስ ልዩነትና አጠቃቀም ዙሪያ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል።

የአፈጻጸም ሪፖርቱንም ሆነ የቀጣይ እቅድ ከፈጻሚ አካላት (አጥቢያዎች) ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ መወያየቱ ለተግባራዊነቱ በር ይከፍታል ብለዋል ብፁዕነታቸው።

ወረዳ አብያተክህነቱ ባካሄዱት ዓመታዊ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በቤተክርስቲያን አገልግሎት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰበካ ጉባኤያት፣ ተቋማትና ግለሰቦች የእውቅና ሽልማት አበርክተዋል።

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

11 Nov, 06:36


አርዮስፋጎስ

ይህ የቴሌግራም ቻናል በወልድያ ደብረ ሲና ተክለሃይማኖት ቤ/ያን የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህርና የሀገረስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ሃላፊ የሆኑት የመጋቤ ሐዲስ ኤርምያስ አዳነ ነው።
➛ አርዮስፋጎስ ማለት ፦ግሪካዊ ቃል ሲሆን ለሕዝብ ይፋ የሆነ የምርምር አደባባይ ማለት ነው።
➛ ቻናሉ በመንፈሳዊ ምርምር እንጅ በሥጋዊ ምርምር ልንረዳቸው የማንችል ጥልቅ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች፣
➛ ስብከቶች እና ጽሑፎች የሚለቀቁበት እንዲሁም
➛ ሌሎች ተከታታይ ትምህርቶችን የሚያስተምሩበት የቴሌግራም ቻናል ነውና ይቀላቀሉ ሌሎችንም ይጋብዙ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

https://t.me/Ariosfagos1271

https://t.me/Ariosfagos1271

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

07 Nov, 14:32


የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ጥገና  መዘግየት በቅርሱ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋትን አስከትሏል።

ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከጥቅምት 24-27 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ሐዋርያዊ ጉዞ አድርገዋል።

ብፁዕነታቸው የቅዱስ ላሊበላ ደብር የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት፣ የእድር አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በመሪ እቅድ አተገባበር፣ በቅርሱ ጥገናና እንክብካቤ ዙሪያ አወያይተዋል።

የቅዱስ ላሊበላ አብያተክርስቲያናት መጠለያ አለመነሣቱና የቅርሱ ጥገና መዘግየት እንዲሁም በአካባቢው የሚተኮሰው ከባድ መሣሪያ ያስከተለው ንዝረት በቅርሱ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑን ተሳታፊዎች አንሥተዋል።

የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ አስተዳዳሪ መ/ር አባ ሕርያቆስ ጸጋዬ (ቆሞስ) በበኩላቸው አካባቢው የጦርነት ቀጠና ቢሆንም ቤተክርስቲያኗ በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የአስተዳደር ዘርፎች ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንድታስፋፋ ታልሞ የተዘጋጀውን መሪ እቅድ ለማሳካት ደብሩ የአስተዳደር ደንብና መዋቅር እያጠና መሆኑን አብራርተዋል።

በደብሩ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠትና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን ለማሻሻል የሚያግዝ የአስተዳደር ደንብ በባለሞያዎች እየተዘጋጀ ስለመሆኑም አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት የማጠቃለያ አባታዊ መልእክት በፈተናዎች ውስጥ ብንሆንም እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የተዘጋጀውን የሀገረ ስብከት ሥልታዊ እቅድ እስከ አጥቢያ ድረስ ማውረድ ተችሏል ብለዋል።


በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ባላቸው ምሁራን የተዘጋጀውን የ10 ዓመት መሪ እቅድ ተገንዝበን መተግበር ከቻልን ኹሉም ጥያቄዎቻችን መልስ ያገኛሉ ብለዋል ብፁዕነታቸው።

በቅዱስ ላሊበላ ቅርስ ደኅንነት፣ በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግሥት ስምምነት የተጀመረው የዘላቂ ላሊበላ ቅርስ ጥገና ፕሮጀክት መዘግየት፣ በመዳረሻ ልማትና ማስተዋወቅ ዙሪያ ከባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር
ባለፈው ሳምንት ውይይት በማድረግ የመፍትሔ አቅጣጫ መቀመጡንም ብፁዕነታቸው ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው ለሦስት ቀናት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት፣ በማስተማርና አባታዊ መመሪያ በማስተላለፍ በቅዱስ ላሊበላ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናቀው ወደ መንበረ ጵጵስናቸው በሰላም ተመልሰዋል።

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ይወዳጁ ለሌሎችም ያጋሩ።

~ቴሌግራም፡ https://t.me/NWDnews

~ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia

~ድረገጽ፡ https://eotc-nw.org

~ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/EOTCNWD?mibextid=ZbWK

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

06 Nov, 17:27


በጦርነቱ ፈርሶ የነበረውን የደብረ ዘቢጥ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ለመገንባት የመሬት ቁፋሮ ተጀመረ።

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት መቄት ወረዳ ቤተክህነት በ2014 ዓ.ም በጦርነት ሙሉ በሙሉ ወድሞ የነበረው የደብረ ዘቢጥ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የመልሶ ግንባታ ሥራ ተጀምሯል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አብያተክርስቲያናት መልሶ ለመገንባት ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው በግል ገንዘባቸው ለመገንባት  ቃል የገቡት አቶ አሸናፊ ታደሰ (ወ/ጻድቅ)ና ባለቤታቸው ወ/ሮ ራሄል አረጋ (እኅተ ማርያም) ቁፋሮውን አስጀምረዋል።

የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በዚሁ ቤተክርስቲያን መቃረቢያ ዛሬ ተከብሮ ውሏል።


ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቤተክርስቲያኑን ለመገንባት ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ባርከው ማኖራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

06 Nov, 16:31


https://youtu.be/eeta659mpeg

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

04 Nov, 15:21


በላስታ ወረዳ ከጎብኝዎች በሚገኝ ገቢ የሚተዳደሩ አብያተ ክርስቲያናት ገቢያቸው በመቀነሱ በአገልግሎት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረባቸው መሆኑን ተናገሩ።

ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም  (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት)

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የላስታ ወረዳ ቤተክህነት 37ኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤውን ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ መምህር አባ ሕርያቆስ ፀጋዬ (ቆሞስ)ና የሀገረ ስብከቱ የሥራ የክፍል ኀላፊዎች በተገኙበት ትናንት በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ቤተ አብርሃም ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።

የላስታ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ይሄይስ ተመስገን ባለፈው የአገልግሎት ዓመት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና የራስ አገዝ ልማት የተከናወኑ ተግባራት የአፈጻጸም ሪፖርት ለጉባኤው አቅርበዋል።

ላስታ ወረዳ ቤተክህነት የበርካታ ውቅር፣ ፍልፍልና የዋሻ ውስጥ አብያተክርስቲያናት መገኛ  ቢሆንም ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝና የእርስ በርስ ጦርነት ሳቢያ የጎብኝዎች ቁጥር በመቀነሱ ችግር እንደገጠማቸው በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል።

በአካባቢው በተከሰተ ተደጋጋሚ ውጊያ ምክንያት በማይተኩ ቅርሶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከተዋጊ ኃይሎች ጋር በመነጋገር የከፋ ጉዳት ባይደርስም አሁንም ከፍተኛ ስጋት ላይ መሆናቸውን በሪፖርቱ ተገልጿል።

ከሀገረ ስብከት በወረደላቸው የእቅድ መነሻ በወረዳ ቤተክህነቱ፣ በአድባራት፣ በገዳማትና በአጥቢያ አብያተክርስቲያናት የሚከናወኑ  መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች 16 ግቦችና ዝርዝር ዓበይት ተግባራት ያሉት የ2017 ዓ.ም እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በዘርፉ እውቀትና ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች ተዘጋጅቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ተገምግሞና ጸድቆ እስከ ታችኛው የቤተክርስቲያኗ መዋቅር የወረደው የ10 ዓመት መሪ እቅድ ሳይሸራረፍ እንዲተገበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሊሰጥ እንደሚገባ ተሳታፊዎች አሳስበዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለጉባኤው ተሳታፊዎች ትምህርትና አባታዊ መመሪያ ያስተላለፉ ሲሆን የቤተክርስቲያንን የእምነት አቋምና ትውፊቱን ከባሕል ለይተው የሚያስተምሩ የመጻሕፍት ትርጓሜና የነገረ መለኮት መምህራንን በማሳተፍ ለምእመናን ተገቢውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ማዳረስ ይገባል ብለዋል።

አክለውም የአብነት መምህራንንና ደቀመዛሙርትን መደገፍ፣ መከታተል ለቤተክርስቲያን ተተኪ አገልጋዮችን ለማፍራት ደግሞ የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ሃይማኖታቸውን አውቀው እንዲመሰክሩ ማስተማር፣ ማስፋፋትና ማጠናከር ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል።

የምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን ምንነትና አፈጻጸም በተመለከተ በተለይም ምሥጢረ ሜሮንና ምሥጢረ ቀንድልን አስመልክተው ለጉባኤው ተሳታፊዎች ማብራሪያ የሰጡት ብፁዕነታቸው በሀገረ ስብከታችን የዲቁና፣ ቅስናና ቁምስና ሥልጣነ ክህነት የሚቀበሉ አገልጋዮች የክህነትን ምንነት የተረዱና ለሌሎችም ማስረዳት የሚችሉ መሆናቸው ተረጋግጦ እንዲላኩና ብቁ አገልጋዮችን ለማፍራት ኹሉም የድርሻውን እንድወጣ አሳስበዋል።

በጠቅላላ ጉባኤው ከ166 አድባራት፣ ገዳማትና አጥቢያ አብያተክርስቲያናት የተውጣጡ 230 የሰበካ ጉባኤያት ሊቃነመናብርት፣ ጸሐፊያንና የገዳማት አበዎምኔታት ተሳትፈዋል።

በተጠናቀቀው የአገልግሎት ዓመት መልካም አፈጻጸም ላስመዘገቡ ገዳማት፣ አድባራት እንዲሁም በቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ድጋፍ ላደረጉ የመንግሥት ተቋማትና ለማኅበረ ቅዱሳን የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

01 Nov, 16:13


የመቄት ወረዳ ቤተክህነት በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ዙሪያ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መስጠቱን አስታወቀ።

ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት)

በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነት የመቄት ወረዳ ቤተ ክህነት ትናንት ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮችና አባላት ሥልጠና ሰጥቷል።

ሥልጠናው በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥና ሰንበት ት/ቤቶችን ለማጠናከር መዘጋጀቱን ወረዳ ቤተ ክህነቱ አስታውቋል።

በሥልጠናው የወረዳ ቤተ ክህነቱ የሥራ ኅላፊዎችና ሠራተኞች፣ የአድባራት አሰተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮችና አባላት፣ የሰበካ ጉባኤ ተወካዮች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ፍላቂት ወረዳ ማእከልና የቀጠና ተወካዮች፣ የወረዳው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፣ የአብነት መምህራንና ደቀመዛሙርት ተሳትፈውበታል።

በመርሐ ግብሩ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት አተገባበርና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አሁናዊ ሁኔታ ዙሪያ መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ማቋቋም፣ ማጠናከርና መከታተል ለነገ የማይባል ሥራ በመሆኑ የቤተክርስቲያን ተረካቢ ወጣቶችና ሕጻናት በሰንበት ትምህርት ቤት ተኮትኩተው እንዲያድጉ ኹሉም የድርሻውን እንዲወጣ የወረዳ ቤተክህቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወሀቤ ሀብታት ፍሥሐ ዓለሙ አሳስበዋል።

ሥርዓተ ትምህርቱን ለመተግበርና ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማጠናከር ሥልጠናው አቅም እንደፈጠረላቸው የጉባኤው ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያግኙን፤ ይወዳጁ ለሌሎችም ያጋሩ።

~ቴሌግራም፡ https://t.me/NWDnews

~ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia

~ድረገጽ፡ https://eotc-nw.org

~ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/EOTCNWD?mibextid=ZbWK

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

19 Oct, 16:58


የሊቀ ትጉሃን ባሕታዊ አባ መፍቀሬሰብእ ኪዳነ ወልድ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት)

የሊቀ ትጉሃን ባሕታዊ አባ መፍቀሬሰብእ ኪዳነ ወልድ ሥርዓተ ቀብር ብፁዕ አቡነ ቄርሎስና ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳሳት፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ከቅዱስ ላሊበላ ፣ ከተድባበ ማርያም ፣ ከግሸን ደብረ ከርቤ እና ከደሴና ከኮምቦልቻ ዙሪያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት እና ምእመናን በተገኙበት በሐይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ እና ቅዱስ እስጢፋኖስ አንድነት ገዳም ተፈጽሟል።

©ተዋሕዶ ሚዲያ ማእከል
ፎቶ፦ ከማኅበራዊ ሚዲያ

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

19 Oct, 10:41


የሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነት
በሥራ አፈጻጸም 1ኛ በሞዴል አህጉረ ስብከት ደግሞ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)

43ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ዐለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ሲጠናቀቅ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በ2016 ዓ.ም የተሻለ የሥራ አፈጻጸም በማስመዝገቡ በምድብ "ሀ" ከተደለደሉት አህጉረ ስብከት 1ኛ ደረጃ፤ ከኹሉም አህጉረ ስብከት ደግሞ 2ኛ ሞዴል ሀገረ ስብከት በመሆኑ ሽልማት ተበርክቶለታል።

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ፍሥሐ ጌታነህ ከቅዱስ ፓትርያርኩ እጅ ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ለተመዘገበው ስኬት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ የሀገረ ስብከት፣ የወረዳ አብያተ ክህነት፣ የአድባራትና ገዳማት አገልጋዮች፣ በተለያዩ ፕሮጀክቶቻችን በእውቀት፣ በገንዘብና በጉልበት የምታገለግሉ ሁሉ እንኳን ደስ አለን።

በማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያግኙን፤ ይወዳጁ ለሌሎችም ያጋሩ።

~ቴሌግራም፡ https://t.me/NWDnews

~ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia

~ድረገጽ፡ https://eotc-nw.org

~ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/EOTCNWD?mibextid=ZbWK

5,747

subscribers

2,272

photos

6

videos