የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን @jimmadiocese Channel on Telegram

የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን

@jimmadiocese


ይህ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን (ሕጋዊ የቴሌግራም ገጽ) ነው።

አማራጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ድምጽ !

የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን (Amharic)

በአማርኛ ፍቃድ: nnየጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ድምጽ፣ ሥራን እና የቴሌግራም ተመልከተናል። ስለምንድን ነገር ነው? ጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን ለምን ይበልጥ ነው? ይህ ቻናል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር የተጠናቀ መገናኛ ብዙኃን ነው። እዚህ በዚህ ቻናል በኢትዮጵያ የሆነውን ጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን ይጨለሱ።

የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን

06 Nov, 15:28


የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የተዝካረ ስቅለቱ መታሰቢያ በዓለ ንግሥ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በጅማ መንበረ ጵጵስና ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ !


⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም (ጅማ፤ ኢትዮጵያ)
@የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን!!

የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የተዝካረ ስቅለቱ መታሰቢያ በዓለ ንግሥ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጅማ፣ የየም፣ የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ክቡር መልዐከ ሠላም ተስፋ ሚካኤል አሰፋ የጅማ እና የየም አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱ የመመሪያ ኃላፊዎች፣ የአድባራት እና የገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና በርካታ ምእመናን በተገኙበት በጅማ መንበረ ጵጵስና ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን

06 Nov, 07:52


ተዝካረ ስቅለቱ ለእግዚእነ

እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን::

ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቤተ ክርስቲያናችን ጌታችን በመስቀሉ ስለፈጸመልን የማዳን ሥራ “ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ”በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው እያለች እየዘመረች ታስበዋለች።

ከዚህም በተጨማሪ ጥቅምት ፳፯ በወርኀ ጽጌ ውስጥ ያለ በመሆኑ “ …እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ” እያለች የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን መድኃኒት የሆነው ጌታ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣት እንደሆነ በመመስከር ትዘምራለች ።

መጋቢት ፳፯ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን ዐርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርዓት ሠርተዋል፡፡መጋቢት ፳፯ ቀን በዐቢይ ጾም ስለሚውልና በወቅቱም ኀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለች ።

ጲላጦስ አይሁድን ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ ቢላቸው በርባንን ፍታልን ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ግን ስቀለው አሉ። ጲላጦስም በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ሁሉ ንጹሕ ነኝ ብሎ ባደባባይ እጁን ታጠበ። አይሁድ ደሙ በኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ። እርሱም በርባንን ፈታላቸው ጌታንም አሳልፎ ሰጣቸው። ማቴ ፳፯ ፥፳፭

መጋቢት ፳፯ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል። የተሰቀለው የክብር ባለቤት ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀዷል፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯ )፡፡

ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ ጋር ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መ.ክ.ዘ የነበሩትን አቡነ መብዓ ጽዮንን ታስባለች፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ በዕለተ ዓርብ የተቀበልከውን መከራ ግለጽልኝ ››ብለው በጸለዩ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተቀበላቸውን መከራዎች ሁሉ አሳያቸው፡፡

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስን መከራ ካዩበት ቀን ጀምሮ ሕማሙን መከራውን ግርፋቱን እስራቱን በጠቅላላ አሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በማሰብ ጀርባቸውን በአለንጋ ይገርፉ ፤ ራሳቸውን በዘንግ ይመቱ ነበር፡፡

የጌታችንን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ዘወትር ስለሚያለቅሱ ዐይናቸው ጠፍቶ ነበር፡፡ ነገር ግን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የብርሃን ጽዋ ይዛ መጥታ ዐይናቸውን ቀብታ አድናቸዋለች፡፡ በዚህ የተነሣ ‹‹በትረ ማርያም›› እየተባሉ እንደሚጠሩ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ በዚህ መሠረት ጥቅምት ፳፯ ቀን ለአቡነ መብዓ ጽዮን ቃልኪዳን የገባበት ቀን በመሆኑ በየዓመቱ ጥቅምት ፳፯ ቀን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱ ጋር ይከበራል፡፡

ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት

1,708

subscribers

5,052

photos

7

videos