ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox @moa_tewahido Channel on Telegram

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

@moa_tewahido


https://t.me/defend_orthodoxy_EOTC_Followers

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox (Amharic)

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO is a Telegram channel dedicated to promoting and defending Orthodox Christianity. The channel focuses on spreading the teachings and traditions of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. MOA TEWAHIDO provides its followers with valuable insights, sermons, prayers, and discussions related to the Orthodox faith. The channel aims to educate and inspire individuals who are interested in learning more about the rich history and spiritual practices of the Orthodox Church. Whether you are a devout follower or simply curious about Orthodox Christianity, MOA TEWAHIDO welcomes you to join their community. Through engaging content and interactive discussions, MOA TEWAHIDO creates a platform for like-minded individuals to connect, share their faith, and deepen their understanding of Orthodox beliefs. By following this channel, you will have access to a supportive community that is passionate about upholding the traditions of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. Join MOA TEWAHIDO on Telegram today to discover the beauty and significance of Orthodox Christianity, and to connect with fellow believers who share your devotion to the faith. Stay informed, inspired, and empowered by becoming a part of this growing online community dedicated to defending Orthodoxy.

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

24 Jan, 16:30


https://www.youtube.com/live/XHQDX93Lcp0?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

23 Jan, 02:19


https://youtu.be/irHGOYTMm9Y?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

21 Jan, 17:23


ከተራ እና ጥምቀትን ጥቁር ለብሰው ማቅ ነስንሰው በሐዘን ያከበሩ ዘንድ የተፈረደባቸው በሀዲያ ዞን የሚገኙት የጊንብቾ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን
***

በተለያዩ ከተሞች ከተገለጡ ደማቅ የከተራ ትዕይንቶች በላይ እስከ አጥንት ዘልቆ የሚሰማ ሐዘን ቅድስት ቤተክርስትያን በሀዲያ ዞን ጊንብቾ ከተማ እያሳለፈች ትገኛለች።

የጥምቀት ማክበርያ ስፍራ ተነፍገው መከራን እየተጋፈጡ የሚገኙት የጊንብቾ ኦርቶዶክሳውያን ከተራን እንዲህ ጥቁር ለብሰው ማቅ ነስንሰው አሳልፈዋል።

ተለመነንን 🙏🙏?Kune Demelash kassaye -Arba Minchnch

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

18 Jan, 19:58


https://www.youtube.com/live/lDyIdlhm4B4?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

18 Jan, 01:18


https://www.youtube.com/live/V4TnqM1kX_I?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

16 Jan, 01:34


https://youtu.be/4e3VU02vM-w?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

14 Jan, 17:56


https://youtu.be/Vz45NCK6c0s?si=xLqE8qju02YJ4Fqh

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

14 Jan, 03:56


የማያምኑ ጳጳሳት እና ሊቃውንት እንዴት ልና ፈራ ቻልን?

መንፈሳዊነት እየተዳከመ ሙያተኛነት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት አደገ?

የእኔ ምልከታ እንሆ https://youtu.be/oUKxbVsYRC0?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

14 Jan, 03:51


የማያምኑ ጳጳሳት እና ሊቃውንት እንዴት ልና ፈራ ቻልን?

ምንፈሳዊነት እየተዳከመ ሙያተኛነት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት አደገ?

የእኔ ምልከታ እንሆ https://youtu.be/oUKxbVsYRC0?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

08 Jan, 18:28


https://youtu.be/NjQglypFD6I?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

06 Jan, 18:21


👆👆👆አምላክ ሰው የሆነለትን ፍጡሩን በዘርና በቋንቋና በእምነት ዘውግ ፈርጀው ከምድረገጽ ለማጥፋት ሕግጽፈውና ተዋቅረው ፍጅት የጀመሩትን የምትፋለሙ የአማራ ልጆች በመከራም ውስጥ ቢሆ የአምላክን የልደት በዓል ለማክበር እንኳን ከደረሳችሁ።

ወንድም: ልጅ: አባት: እናታችሁን በሕወሃትና ኦነግ ኦሮሙማ ድቅል ልጅ ብልጽግና ጭፍጨፋ የተነጠቃችሁ፤ የዘራችሁት ሰብል፣ የረባችሁት እንስሳ የወደመባችሁና በችግር ላይ የምትገኙ ወገኖቼ የጌታችን የልደቱ ብርሃን ያጽናናችሁ።

ሲራክ እንደጸለይ እንዲህ እያልን ሰውሠራሽ ሀዘናችንን በሰማያዊ ጸጋ ደስታ የበላይነት ሸፍነን እንጸልይ

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

01 Jan, 21:28


https://youtu.be/66O3t7CxqsE?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

27 Dec, 17:39


https://www.youtube.com/live/_9doP2J8SZM?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

26 Dec, 16:42


https://www.youtube.com/live/yGtRUEIJRDs?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

26 Dec, 16:36


በኢሰመጉ መታገድ ዙሪያ የተሰጠ አጭር መግለጫ ታህሳስ 17 /2017 ዓ/ም ቻናላችንን ለመቀላቀል ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑት https://t.me/ehrcow

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

24 Dec, 03:32


https://youtu.be/DZFgLyeiHZE?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

22 Dec, 05:51


Anchor ''ኦርቶዶክስ አለች ወይ? ወደ ሲኖዶሱ በበር ሳይሆን በመስኮት የገቡት ፈተና ሆነውብናል። ዳንዔል ክብረ...
https://youtube.com/watch?v=h18NN6wHACk&feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

19 Dec, 17:08


[19/12/2024, 10:07:09] Yosef Ketema: በግፍ ለሚያልቁ ልጆቻቸው ሲጮኹ የከረሙት ደጉ ካህን ታግቱ!
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የሽርካ ወረዳ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅን ጨምሮ 40 ሰዎች ታግተው መወሰዳቸው ታወቀ።
ከ2 ቀን በፊት ባለፉት አመታት በተከታታይ በወረዳው ሲጨፈጨፉ ለነበሩት ልጆቻቸው ሲጮኹ የነበሩት የሽርካ ወረዳ ቤተ ክህነት መላከ ሰላም ቀሲስ ታመነ በየነ መታገታቸውን ኢትዮ ቱንቢ ሰምታለጭ ዛሬ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ባረጋገጡት ደግሞ እሳቸውን ጨምሮ 40 ሰዎች ናቸው ታግተው የተወሰዱት። ቀጣዩ የመሠረት ሚዲያ ዘገባ ነው።
ታህሳስ 5 ቀን ማለዳ ላይ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ጋላማ ተብሎ በሚጠራው የመንግስት ጥብቅ ደን መሐል የሽርካ ወረዳ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ ቀሲስ ታመነን ጨምሮ 40 ሰዎች ከመኪና ውስጥ ተለይተዉ ታግተው እንደተወሰዱ መሰረት ሚዲያ ዘግቧል።

በዚሁ አካባቢ የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ በአንድ ቤተሰብ ዙሪያ ያሉ ዘጠኝ ሰዎች ተገድለው ማደራቸው ይታወሳል።ከሟቾቹ መሐል 70 ዓመት ያለፋቸው ሁለት አረጋውያን አባቶች እንዳሉ ያስታወቀው እናት ፓርቲ በእድሜ የገፉ እናቶችና ወጣቶችም አሉበት ብሏል፣ የሟቾች ስም ዝርዝርም ደርሶኛል ብሏል። ከወር በፊት ደግሞ በዚሁ አካባቢ 2 ሰዎች ተገድለው እና ሌሎች 8 ሰዎች ታግተው እንደተወሰዱ ይታወሳል።
[19/12/2024, 10:07:43] Yosef Ketema: በመንግሥትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ትኩረት የተነፈገው የሽርካ ኦርቶዶክሳውያን ግድያ እንደቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ !

ታኅሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኅሣሥ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳ ቤተ ክህነቱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ 20 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ግድያና እገታ እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ከታገቱት ውስጥም የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች 8 ኦርቶዶክሳውያን ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ግድያ እንደተፈጸመባቸው እንዲሁም ያሉበት እንደማይታወቅ አክለዋል፡፡ በዚህ ዕለት ብቻ ከ80 በላይ የኦርቶዶክሳውያን ከብቶች በታጣቂዎች ተወስደዋልም ተብሏል፡፡

ሀገረ ስብከቱ በየዓመቱ በሚካሄደው በ43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ2016 ዓ.ም 271 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡

በተጨማሪም ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል በጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤው ሪፖርቱ መጥቀሱ አይዘነጋም፡፡

በጀጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ለስደት መዳረጋቸውም ተገልጿል፡፡

በጠቅላይ ቤተ ክህነትም ሆነ በመንግሥት ትኩረት የተነፈገው የኦርቶዶክሳውያን ግድያ ተባብሶ ኅዳር 19 እና 20 ቀን 2017 ዓ.ም የ13 ዓመት ታዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ ተወስደው መገደላቸውንና 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ያለማንም ከልካይ በተገኙበት ሁሉ በሚገደሉበት በዚያ ሀገረ ስብከት የ45 ቀን አራስ ሕጻንን ጨምሮ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና አብያተ ክርስቲያናት ላይም ጥቃት እየተፈጸመ መቆየቱ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገብ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የኦርቶዶክሳውያን ግድያና ስደት እንዲሁም የሀብት ዝርፊያ ሰሚ ያጣና በወረዳው ተጠናክሮ የቀጠለ በመሆኑ የአካባቢው ምእመናን በትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ መሆናቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል፡፡

“የማይጠቅሙና ፋይዳ የሌላቸው ጉዳዮችን ሲዘግቡ የሚስተዋሉ ሚዲያዎች የእኛ ሞት እንደምን ቀለላቸው?” ያሉት ኦርቶዶክሳውያን ነዋሪዎች ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በወረዳችን እየተፈጸመ ያለው ግፍ ትኩረት አለመሰጠቱ እጅጉን አሳዝኖናል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሰብዓዊነት የሚሰማችሁ ግለሰቦችና የግፍ ግድያውን የምትቃወሙ ሚዲያዎች ሀብት ንብረት ባፈራንበት ወልደን ከብደን በተቀመጥንበት ሀገራችን እንዳውሬ እየታደንን ስንገደል ድምጽ ትሆኑን ዘንድ እንማጸናችዋለን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አስተያየት ሰጭዎች አክለውም መንግሥት የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት በመገንዘብ ሞታችንን ሊያስቆምና መፍትሔ ሊያመጣ ይገባዋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

©️ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

14 Dec, 00:38


https://youtu.be/fqyktdXp0zE?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

12 Dec, 17:44


https://www.youtube.com/live/cxkHdKr6WfY?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

09 Dec, 21:33


"በፊት ታጣቂዎች ፣ አሁን ደግሞ እራሱ መንግሥት እየገደለን ነው!" ነዋሪዎች! #ከደራ_እስከ_ ሽርካ! #የማያባራው_የቁማር_ፖለቲካ_ሰለባዎች! #ልዩ_ዘገባ https://youtu.be/GvGeI1MX8rw?si=91cE80Fb5xnkr5ua

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

27 Nov, 18:38


https://www.youtube.com/live/C76jBSxNC5w?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

24 Nov, 19:02


👉   ጾም ማለት ምን ማለት ነው ?

ኅዳር 15 ጾመ ነቢያት የሚገባበት ቀን ነው
ይህ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ እንደሆነ የታወቀ የተረዳ ነው የመጣው የጾም ወራት ነውና ስለ ጾም የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ መማር እና በተግባር መኖር የነጻ ፈቃድ ግዴታ ነው
ጾም ማለት ምን ማለት ነው ?
ጾም ማለት
"ተከልኦተ ብእሲ በጊዜ መብልእ
ዕውቅ" እንዲል
ከታወቀ መብል መከልከል ነው
ይህ ማለት ከሥጋ ከወተት ከእንቁላል  ወዘተርፈ በአጠቃላይ ሥጋን ከሚያለመልሙ ምግቦች መከልከል ማለት ነው
ሁለተኛ ጾም ማለት
"ጾምስ ጸባሕተ ሥጋ ይእቲ "
ጾምስ በለኝ የሥጋ ፈቃድን ለነፍስ ፈቃድ
መገበር ነው
ፈቃደ ስጋ ምንድን ነው ? ከተባለ
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይዘረዝርልናል
" የሥጋም ስራው ይታወቃል ፥
እርሱም
ዝሙት ፥
ርኵሰት ፥
መዳራት ፥
ጣዖትን ማምለክ ፥
ሥራይ ማድረግ ፥
መጣላት ፥
ኩራት  ፥
የምንዝር ጌጥ
ቅናት ፥
ቍ ጣ ፥
ዐድመኛነት ፥
መለያየት ፥
መናፍቅነት ፥
ምቀኝነት ፥
መግደል ፥
ስካር ፥
ዘፋኝነት ፥
ይህን የመሰለ ሁሉ ነው ። አስቀድሜም እንደነገርኋችሁ፥ ይህንየሚያደርግ የእግዚአብሔርን መንግሥት አያይም።
ገላ5:19-21
መጾም ከእነዚህ ከተዘረዘሩት ነው
በሌላም አንቀጽ ገና በሕገ ኦሪት ሳለ ፈቃደ ሥጋ
እና ፈቃደ ነፍስ ልቡናውን እንደጦር ሜዳ አድርገው እንደተፋለሙበት ይገልጻል
" ነገር ግን በሰውነቴ ውስጥ ያለውን ሌላ የኀጢአት ሕግ እመለከታለሁ በልቡናዬም ውስጥ ካለው ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ተሰልፈው ተዋጉ እንዲል ሮሜ 7፥23
አንድ ሰው የፈቃደ ሥጋ እና የፈቃደ ነፍስ መፋለሚያ ሰፊ ሜዳ ነው
የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ ፈቃድ አስገዝቶ በፈቃደ ነፍስ መገለጽ ደግሞ በጠባብ በር ማለፍ ነው  አምላካች ክርስቶስ እንደተናገረ
"በጠባቢቱ በር ግቡ ፤ ወደ ጥፋት የምትወስድ   ሰፊ በር ፥ ሰፊ መንገድም አለችና፥ ወደ እርሷም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ፤ ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ  ፥ መንገዷም ቀጭን ናትና፥ የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው ።
ማቴ 7፥13-14
ጠባቢቱ በር የነፍስ ፈቃድ ስትሆን
ሰፊ በር የተባለ  የሥጋ ፈቃድ ነው
የአንድ ክርስቲያን የመጀመሪያ ተጋድሎው
ፈቃደ ስጋን ማሸነፍ ነው አሸናፊነትም በሹመት በሽልማት ይገለጻል ይታወቃል
እኛም ብዙ ጊዜ ጾም ሲመጣ
ጹመናል ብለን የምናስበው
ከመብል ከመጠጥ
ከጥሉላት (ከሚያለመልሙ)
ነገሮች ነው
ነገር ግን ይህ ብቻ አይደለም
የስሜት ህዋሳትንም እንዲጾሙ
በማድረግ በራስ ላይ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ መሾም ነው
እኔ ለእኔ አንባ ገነን ንጉሥ ነኝ
በስሜት ህዋሳት ከመንገሥ
በላይም ሌላ ተአምር የለም
እንደሌለም ተገልጿል።

ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅን
እንስማው

"ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋለህን ?"

"እንኪያስ በዘፈን የደነቆረ ጆሮህን መዝሙር እንዲሰማ አድርገው
ሴትን በመመኘት የታወረ ዓይንህን
ፈጣሪውን እንዲያይ አድርገው
በስርቆት የሰለለ እጅህን በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርገው
ወደኅጢአት ቤት በመኼድ ሽባ
የሆነ እግርህን ወደ እግዚአብሔር
ቤት እንዲሮጥ አድርገው
ሐሜትን በማውራት ዲዳ
የኾነ ከንፈርህን መልካም
እንዲናገር አድርገው
ከተአምራት ሁሉ የበለጠ
ተአምር ይኼ ነውና ። " ይለናል
ስለዚህ ጾም ማለት
ተአምር ማለት በህዋሳት መንገሥ
ከፈቃዳተ ሥጋ መፍለስ
በቅዱሱ እግዚአብሔር መቀደስ
ከብልየተ ስጋ (በኀጢአት ካረጀ ሥጋ) መታደስ
ማለት ነው።

አብርሃም ፈቃዴ

ክፍል ሁለት ይቀጥላል ..........

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

21 Nov, 04:53


ነገረ ባንዳ ን — በቅጡ መረዳት ይቀረናል። ይህን ተምህርት እናስተውል

https://youtu.be/bmVmjaOvz4k?si=2D1VcOrrdRbIeTC2

ክፍል 2 https://www.youtube.com/watch?v=fyxGy0JjnsI

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

16 Nov, 06:12


Addisu Media አንዳንድ ነገሮች //ቤተ ክርስቲያንን ለመታደግ..." Friday Nov 15, 2024
https://youtube.com/live/omUhktJReaQ?feature=shared

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

13 Nov, 23:08


Enat Party condemns massacre in East Shoa : 38 burned to death locked in their house. Read more
https://borkena.com/2024/11/02/enat-party-condemns-massacre-in-east-shoa-38-burned-to-death-locked-in-their-house/ @zborkena #Ethiopia #News #humanrights 

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

10 Nov, 12:00


የብልጽግና የባህልና ማንነት አፓርታይድ! ኦርቶዶክስ ጠልናትና ፍጅ*ትን ከስውር ሴራነት ወደ ግልጽ ፖሊሲነት ያወጣው...
https://youtube.com/live/tkm9iCzZGfA?si=fqXEOThFcv6tbBnu

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

07 Nov, 16:31


ከገሀዱ ጦርነት ጀርባ! ያልተነገረለት #በጽንስ #በህጻናት #በሐኪሞች ላይ የሚካሄደው ውጊያ! ያለውን ብቻ ሳይሆን ...
https://youtube.com/watch?v=-TJKyNVAAqw&si=pyuB4p3tvEjKdk_R

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

05 Nov, 11:05


https://www.facebook.com/share/p/kLyhjwm8MW35yNeS/

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

03 Nov, 10:37


https://www.youtube.com/live/LXND-yjyqgQ?si=WYDr_5BqR-cXyBha

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

30 Oct, 10:50


MK TV || ወቅታዊ ጉዳዮች || 421 አብያተ ክርስቲያናትን ያወደመው ጦርነት
https://youtube.com/watch?v=drPa6zeYucg&si=Gq2FOqDgskG_xyGJ

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

27 Oct, 19:13


https://www.youtube.com/live/tK2dl8f8u4Y?si=Ypp6og50YrlXlPlV

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

26 Oct, 19:27


https://www.youtube.com/live/kO5NtvB0p3w?si=FTiSy7MGNx6gjYiR

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

24 Oct, 10:58


EOTC TV | ዐውደ ስብከት | እውነትን ተጸየፉ
https://youtube.com/watch?v=4fiF6OEPCic&si=UIyq9TavGaKn4tR4

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

23 Oct, 18:40


https://www.youtube.com/live/vPrNhwiAho4?si=YGnIiPJ1BDd2sj3v

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

22 Oct, 20:26


https://youtu.be/QMlC_WffDiM?si=QuWjzMm13UZxHDvu

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

22 Oct, 11:47


ኡኡኡኡኡኡ

ይሰሙ እንደኾን ብዬ ነው። ለምነን አባብለን ሥራቸው ተነጥፈን፣ ተመካክረን አልሰሙንም። ዛሬ ላይ ለአንድ አባት ብቻ ነው የልቤን ኀዘን የነገርኳቸው። "ትሰሙናላችሁ ብዬ አይደለም ነገር ግን ምን ያክል እንደምናዝን እንዲይልውቁ ብቻ ነው.... " ብዬ ነው የነገርኳቸው። አኩርፌም አዝኜም ከማናችሁም ርቄያለኹ ነው ያልኳቸው።

ለድሮው ቢኾን "ይኽ ቢኾንስ እንዲኽስ ብታደርጉ እያልኩ የማዋውየው ከግማሹ በላይ ነበሩ። አይሰሙም አልሰሙም። ዛሬም ስንጮኽ ከሰሙን ብዬ ነው።
ኦርቶዶክሳውያን እያለቁ ነው። ቢያንስ በአብይ ፍጅት 3 ሚሊየን ኦርቶዶክሳውያን አልቀዋል። ስደተኛው ረሃብተኛው 20 ሚሊየን ይበልጣል። ሰሜኑን እየሰበረው ነው። ግድ የላችሁም ስሙን።
አዲስ አበባ በወራት ውስጥ ሕንጻ ብቻ ታቅፋችሁ ትቀራላችሁ። መጨረሻ ቤተ ክህነቱም ሕንጻ አይቀርለትም። መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ አጥሩና ቤተልሔሙ ይፈርሳል። ምልክት ተደርጎበታል።
አዲስ አበባ የሚተርፍ ክርስቲያን የለም። ነቅሎ ያባርረዋል። አብይን የማውገዝ ጉልበት ብታጡ እንኳ ለሕዝቡ ተጋድሎ አውጁለት መከራውን በጋራ እንካፈላለን በሉት። ስቃዩን በግልጽ ተናገሩና ተቀላቀሉለት። እያለቀሰ ቤተክርስቲያንን ጥሎ እየተሰደደ ነው። መንግሥት ይስማን ብላችሁ አትጨነቁ ከምእመናችሁ ጋር ኹኑ። ጦርነቱን በግልጽ አውግዙ አትለምኑ። ተደራደሩብ፣ ተነጋገሩ እያላችሁ አታውሩ። አብይን አቁም ብላችሁ አውግዙት። ቀጥታ ጦርነቱ መካከል ሂዱ።
ዘንድሮ ጥር ጥምቀት ጃንሜዳ ለጥምቀት የሚወጣ ታቦት አለ? ክርስቲያን አለ? ከምእመኑ ጎን ኹኑ። ተቃጠል ብሎኝ ነው እንጂ ምን በወጣችሁ ትሰማላችሁ። ካድሬ ቢደውል ዳንኤል ቢደውል ይሰማል።

እናንተ ስለ ቅያሬ፣ ስለ በጀት፣ ስለ መኪና መግዣ ፣ ስለ ኮሪደር መአት ተወያዩ።

ንዋይ ካሳሁን

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

21 Oct, 22:09


https://www.youtube.com/live/2ApOvhi6RY4?si=zXM2t3x92UFKx_jN

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

19 Oct, 15:11


f

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

19 Oct, 15:11


https://youtu.be/t5rRyw8-HqE?si=_FKBTwjV6Y49ht0-

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

19 Oct, 03:30


11. ሙስና፣ ዘረኝነት፣ ጎሠኝነት፣ ቡድነኝነት፣ አድሎዓዊነትና ግለኝት በተመለከተ በጋራ በአንድ ድምጽ በመነሣት ይህንን ክብረ ነክና አጋላጭ፣ ለቤተ ክርስቲያን እድገትና ለሐዋርያዊ ተልእኮ እንቅፋት፣ የቤተ ክርስቲያን ማንነት ለሌላቸው ግለሰቦች መደበቂያ፣ በጥቂት ግለሰቦች በደልና ጥፋት በንጽሕና በቅድስና የሚያገለግሉ፣ ካህናትንና ሠራተኞችን የሚያሳፍሩ፣ ምእመናንን የሚያሸማቅቁ በመሆናቸው እነዚህን ክፉ ደዌያት ስም አጠራራቸውን ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለማስወገድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በጥናትና በቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ፣ የጥፋት በራቸውን በዘላቂነት የሚዘጋ ሥልት እንዲቀይስ ጉባኤው ያሳስባል ፡፡

12. በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት እስከ አሁን ቤተ ክርስቲያን በፈረሱባት ሕንጻዎችና ቤቶች ምትክ ቦታ በመስጠት ጉዳቷን ለመቀነሰ የተደረገውን ጥረት ጉባኤው እያደነቀ፤ በተሰጡት ይዞታዎች ላይ በአጭር ጊዜ ግንባታውን በማካሄድ የአባቶችቻንን አሻራ መልሶ በመትከል፣ ይዞታውን ማስከበርና የተቋረጠውን ገቢ ማስቀጠል እንዲቻል ብርቱ ጥረት እንዲደረግ ጉባኤው እያሳሰበ፤ የኮሪደር ልማት የተባለው ጉዳይ በሌሎች የክልል ከተሞችም እየተስፋፋ ስለሆነ በቀጣይ ለሚነሡ የይዞታ ጥያቄዎች ለሚከሰቱ ችግሮች ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ፡፡

13. አዳዲስ አማኞችን አሳምኖ ለሥላሴ ልጅነት ማብቃት፣ የአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት መተከል፣ መታነጽና መባረክ የታየው ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ እመርታ ሁሉን ያስደሰተ በመሆኑ ከዚህ በበለጠ አጠናክረን ለመሥራት ቃል እንገባን፡፡

14. የቅዱስ ባኮስ የቅድስና ዕውቅና ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ስትዘግበው የቆየ ቢሆንም ጽላት ተቀርፆ እንዲከበር መደረጉ አስደሳች ሲሆን ለሀገር በረከት፣ ለትውልድ የመንፈሳዊ ሕይወት አርአያ፣ ለቅድስና ፍኖት የሆኑ ነገርግን የማይታወቁ የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ቅዱሳን ታሪክና ገድል በማጥናት እንዲዘከሩ እንዲደረግ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

15. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የተከፈቱ መንፈሳውያን ኮሌጆችና የካህናት ማሠልጠኛዎችም በአጥጋቢ ሁኔታ ሥራ መጀመራቸው፣ በዚህ ዘርፍ በእጥፍ እየጨመረ የመጣው ዕድገትና ውጤት ጉባኤው ያደነቀ ሲሆን ወደ ሥራ ለመግባት በሂደት ላይ ያሉት በርካታ መንፈሳዊ ኮሌጆች እየተስፋፉ ያሉ የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ዘመናዊ የትምህርት ተቋማት በአጠቃላይ ሁሉም ትምህርትን የሚመለከት ጉዳይ በትምህርት ኮሚሽን ተቋቁሞ ጥናት በማድረግ እንዲስፋፉ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

16. በሰላም መታጣትና በቀኖና ጥሰት ምክንያት መላው ወለጋ አህጉረ ስብከት ለበርካታ ወራት ከማእከሉ ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ በቅርቡ በሀገረ ሰብከቱ ሊቀ ጳጳስ ወደ መዋቅር መመለሳቸው ጉባኤውን በእጅጉ አስደስቷል፤ ስለሆነም ቀሪ ሥራዎች ተጠናቀው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እንዲጠበቅ፣ በሌሎችም አካባቢዎች ለተፈጠሩት የመዋቅር ጥሰቶች ቀኖናዊ መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤ ያሳስባል፡፡

17. ሐዋርያዊትና የክርስቶስ አገልጋይ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ቋንቋን በማክበር ታገለግልበታለች እንጅ በቋንቋም አትገደብም፤ ስለዚህ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ሐዋርያዊ ተልእኮ መፈጸሟ እንደተጠበቀ ሆኖ ለወደፊት የሁሉም መዓረገ ክህነት ሢመት፣ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር ሥራ የኀላፊነት ምደባዎች፣ መሠረት እምነትን፣ ቀኖና ቤተክርስቲያንን፣ ዕውቀትና ሙያዊ ብቃትን ብቻ መሠረት ያደረገ ይሆን ዘንድ ጉባኤው በጥብቅ ያሳስባል፡፡

18. ሰበካ ጉባኤን ማጠናከር፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን ማደራጀት፣ አብነት ትምህርት ቤቶች ማጎልበትና ማስፋፋት፣ ሕጎችና ደንቦችን በማዘጋጀት የተደረገውን ጥረት የሚያስመሰግን ሆኖ አሁን ወቅቱን የጠበቁ ሕጎችና ደንቦችን በማውጣት ሁሉም እንዲሠራበት ማድረግን፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ የራስ አገዝ ልማትን ማሳደግና በገቢ ራስን መቻል፣ በጸደቀው የዐሥር ዓመቱ መሪ ዕቅድ መሥራት የቤተ ክርስቲያናችን ዓይነተኛ ተልእኮ በመሆኑ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ለመፈጸም ቃል እንገባለን፡፡

19. የቤተ ክርስቲያናችን የውጭ ሀገር አገልግሎት እየሰፋና እያደገ መምጣቱ በጉልህ የሚታይ ሲሆን ይህ እድገትና አደረጃጀት እንዲጠናከር፤ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሳትፎ የበለጠ እንዲያድግ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

20. ከውይይትና ከብፁዓን አበው መልእክቶች እንደተሰጠው መመሪያ የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና ለመመለስ፣ ለሀገራንችን ሰላምና ደኅንነት ለሰው ልጆች ሁሉ መልካም ግንኙነት የጋራ ጸሎት በኅብረት ይደረግ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ እንዲሰጥበት ጉባኤ በአክብሮት ይጠይቃል፡፡

በመጨረሻም እስከ ዛሬ ስንሰበሰብበት ከነበረው መቃረቢያ አዳራሽ ወጥተን ይህ ዛሬ የተገኘንበት አዳራሽ በአጭር ጊዜ አሁን ባለበት ደረጃ እንዲህ ጸድቶና ተውቦ የ43ኛውን አጠቃላይ ጉበኤ እንዲከናወንበት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አመራር መስጠታቸው ቁርጠኝነት ካለ ብዙ መሥራት እንደሚቻል ያሳየ፣ የሥራ ክትትልና አፈጻጸም አድናቆታችንን በመግለጽ ሐዋርያው እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖርና እንዳለው የአዳራሹ ቀሪው ሥራ ተጠናቆ በቅርቡ እንደሚመረቅ ተስፋችንን እንገልጻለን፡፡

ይህ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸም ያደረጉ በቅዱስነታቸው አባታዊ ርእሰ መንበርነት፣ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በሳልና የተረጋጋ አመራር ሁሉም መርሐ ግብሮች በተያዘላቸው ሰዓትና ጊዜ ተጠናቀው እንዲፈጸሉ የመሩንን አባቶች በረከታችሁ ይድረሰን እያልን፡፡

የጉባአው ዋና አዘጋጅ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ኀላፊና መላው ሠራተኞች፣ ሁሉም ተባባሪ አካላት በገንዘብም በጉልበትም ትብብር ያደረጉ ሁሉ በአጠቃላይ ጉባኤው አመስግኗል፡፡

ከሁሉም በላይ ለዚህ ለ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ ያደረሰንና ያስፈጸመን የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአሔር ምስጋና ይግባው አሜን ሎቱ ስብሐት ወባርኰት ወጥበብ፣ ወአኰቴት፣ ወኃይል ወጽንዕ ለአምላክነ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ቴሌቪዥን

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

19 Oct, 03:30


የአቋም መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ የአቋም መግለጫ
በአባቶችሽ ፈንታ ሚዲያ

“ትውልደ ትውልድ ይንእዱ ምግባሪከ ወይዜንዉ ኃይለከ - የልጅ ልጅ ሥራህን ይናገራሉ፤ ያመሰግናሉ፣ ከሃሊነትህን ይናገራሉ ያስተምራሉ” መዝ 144 ቁ 4

ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ዓለምአቀፋዊት የሆነቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ረጅም ዘመናትን ሰማያዊውን ጥበብንና ምድራዊውን ዕውቀትን በማስተማር፣ የሀገርና የወገንን እምነትና ፍቅር ምንነት ከተግባር ጋር፣ ሰላምና አንድነትና በማስፈን፣ ለሰው ልጅ ዘለዓለማዊ ድኅነት ሌሌት ከቀን ያለማቋረጥ ሰዓት ሳይገድባት፣ መልክዓ ምድር ሳይገድባት፣ የሰው ባሕልና ቋንቋ ሳይወስኗት፣ ትውልድን፣ ከትውልድ፣ ዘመንን ከዘመን፣ ሰማያውያን ከምድራውያን፣ ፍጡራንን ከፈጣሪ ስታገናኝ ኖራለች፡፡ ለሰው ዘር ጥበብን፣ ለትወልድ ታሪክና ትውፊትን፣ ስትቀምር፣ ነፃነትና ሰብዓዊ ክብርን በዐውደ ምኅረቷ ስታውጅ፣ በአባቶችና በሊቃውንት በሕየወት ሰሌዳ፣ በደመቀ ቀለም በቃልም በመጽሐፍም ስታስተጋባ እስከ አሁን አለች ወደፊትም ትኖራለች፡፡

ከዚህ መሠረታዊ የታሪክ ዕሴት በመነሣት ለዛሬው 43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ደርሰናል፡፡

በዚሁ ጉባኤው በቆየባቸው ቀናት ውስጥ የቅዱስነታቸውንና የብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ አባታዊ መልእክቶች፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሪፖርት፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር አህጉረ ሰብከት ዘገባዎች፣ ከውይይት ሐሳቦች፣ ከአበው ሊቃነ ጳጳሳት መልእክቶች፣ ከቡድን ውይይትና ዘገባ በመነሣት ከቃለ ጉባኤ ሐሳብ በተጨማሪ በቅዱስ ሲኖዶስ ትኩረት ተሰጥቶባቸው በአጀንዳ ተቀርጸው ውይይትና ምክክር ተደርጎባቸው ውሳኔና መመሪያ ይደረግባቸው ዘንድ እኛም ለተፈጻሚነቱ የራሳችንን ድርሻ መወጣት እንድንችል ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የአቋም መግለጫ አቅርበናል፤

1. በጉባኤው መክፈቻ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ያስተላለፉፉልንን ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎታል፣ ለተግባራዊነቱ ቃል ይገባል ፡፡

2. ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፉልንን አባታዊ መልእክት ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል እንገባለን፤፡፡

3. በብዙ የሀገራችን ክፍል ባለው የሰላም እጦት የተፈጠሩት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት የካህናት፣ የመነኮሳትና የምእመናን ሞትና ስደት በጥብቅ እያወገዝን በዚህ ታሪክ የማይረሳው በምድር ወንጀል፣ በመንፈሳዊው ዓለምና በሰማይ ኃጥያት የሆነ እኩይ ተግባር የተሰማራችሁ ሁሉ ወደ ርኃራኄ ልብ እንድተመለሱ ጉባኤው በአጽንኦት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

4. የሰላም ዕጦት ጉዳይ ምንም እንኳ ዓለም አቀፍ ቢሆንም ሀገራችንም በተከሰተው ግጭትና ጦርነት ምክንያት ሰላም ካጣች ሰንብታለች፣ ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ በዓለም የሚደነቅ፣ ለሀገር ተገን የሚሆን አስደነቂ ውሳኔ እንደሚወስን ተስፋችን ጽኑ ነው፣ ጸሎታችንም ነው፤ የአገልጋዮች እንባ የሚታበስበት፣ ለነገ ታሪክ የትውልድ ተወቃሽ ከመሆን ይልቅ፤ የሰላምና እርቅ ምሳሌ የምንሆንበት ከፍተኛ የሰላም ሥራ ልዩ የሆነ የሰላም ኮሚቴ ተቋቁሞ ዘላቂ ሰላምን ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚያመጣ ሥራ እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፡፡

5. የዚህን ዓለም ተድላ ንቀው፣ ዳዋ ለብሰው ጤዛ ልሰው በገዳም ተወስነው ድምጸ አራዊቱን ግርማ ሌሊቱን ታግሰው ለመላው የሰው ዘር የሚጸልዩ ይህን ይደግፋሉ ያንን ይቃወማሉ የማይባሉ ገዳማውያን መነኮሳት ከየበዓታቸው ተጎትተው ወጥተው የተገደሉበት ሁኔታ በሀገራችን መከሰቱ ጉባኤውን እጅግ አሳዝኖታል፤ ይህ ጉዳይ ቀጣይነቱ እየታየ ስለሆነ የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን የሕግ ሥራ በመሥራት የሰው ልጅ ከአምላክ የተሰጠውን የመኖር መብት፣ የእምነት ነፃነት፣ የመዘዋር ተፈጥሯዊና ሰብዓዊ መብት በሀገራች እንዲከበር ያሳስባል፡፡

6. በታሪካችን ያላየነው ከአባቶቻችን ያልሰማነው በመጻሕፍት ያላነበብነው ከኢትዮጵያ ባሕልና ሥነ ልቡና ውጪ በሆነ መንገድ ሰዎችን ለገንዘብ ሲባል ማገት በተለይም ፊትና ኋላ፣ ግራና ቀኝ፣ እሳትና ውኃ ያለዩ ሕጻናት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው፣ ወጣቶችና አረጋውያን ሳይቀር እያተገቱ የሚሰቃዩበትና የሚደፈሩበት ሁኔታ የገጠመንን ፈተና ክብደቱን የሚያሳይ መሆኑ ይህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፡፡

7. ጥላቻና የጥፋት ቅስቀሳዎች፣ በዜጎች መካከል አለመተማመንና መለያየት፣ ለሀገር አንድነትና የሕዝብ አብሮነት ጠንቅ፣ ለወደፊቱ አስጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች የበዙበት፣ የትውልዱ የወደፊት በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ የመኖር ዋስትና እየጠፋ፣ በርካታ ወጣቶች በስደትና በመፈናቀል ላይ ያሉበት ሁኔታ በመኖሩ የጥላች ንግግር፣ ዘለፋና ያልተገባ ትችትና መናናቅ ማንንም የማያንጽ ክፉ ትምህርት፣ ለሀገርም፣ ለሕዝብም የማይጠቅም ሁሉንም የሚያጠፋ ስለሆነ በእንዲህ ያለ ተግባር መገናኛ ብዙኃን በመጠቀም የተሰማራችሁ፣ ሁሉ በሚያፋቅርና በሚያዋድድ ተግባር እንድትሰማሩ ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፣ ቅዱስ ሲኖዶስም ለዚሁ ትኩረት ሰጥቶ መመሪያና ውሳኔ ያወጣ ዘንድ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡

8. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 20 በእንተ ሰማዕታት የጌታችንን ትምህርት መሠረት በማድረግ በተሠራው ቀኖና ካህናትና ምእመናን ሰማዕትነትን የተቀበሉበትን ቀን መዘከርና ማክበር፣ የከበረ አጽማቸውን በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን በክብር ማስቀመጥ፣ ቤተሰቦቻቸውንና በእነሱ ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ የሰማእታት ቤተሰብ በሚል መርዳት የተደነገገ ቀኖና ነው፤ ይህን በማድረግ የሰማዕትነት ዋጋን እናገኛለን፣ ቤተ ክርስቲያነን እናጸናለን፤ በዚህ ቀኖና መሠረትና ከሰብዓዊ ርኅራሄ በመነሣት በሰማዕትነት የተለዩን ወገኖች መታሰቢያቸው እንዲደረግ፣ ቤተሰቦቻቸውና ጉዳተኞችን ወላጆቻውን ያጡ የካህነትና የምእመንና ጨቅላ ሕጻናትና ያልደረሱ ልጆች፣ ያለጧሪ የቀሩ አረጋውያን የቤተ ክርስቲያንን እንክብካቤ በጥብቅ ይፈልጋሉ፤ ለዚህ መፍትሔ እንዲሆን በውጭና በሀገር ውስጥ ያሉ አህጉረ ሰብከት ያካተተ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት እያሳሰብን ለተግባራዊነቱም ሁላችንም ቃል እንገባለን፡፡

9. በአንዳንድ አካባቢዎች ሕግንና የአምልኮ ነፃነት ሰብዓዊ መብትን በመጣስ የመስቀል ደመራና የባሕረ ጥምቀት ቦታ መወሰድ ሃይማኖታዊ አለባበስና መስቀል መያዝን በመከልከል የአንገት ማዕተብን መበጠስ፣ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እንግልትና ወከባ መፍጠር አሳዛኝ በመሆኑ ድገርጊቱን አጥብቀን እየተቃወመን በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይት እንዲደረግበት ጉባኤው ያሳስባል፡፡

10. ቤተ ክርስቲያን እንኳንስ ተናግራ ሰማች ሲባል የሚያስደነግጥ ግርማና መታፈር፣ መከበርና መወደድ የነበራት በመሠረተችው ሀገር የምትሳደድበት፣ የመሪዎቿ አባቶች ጥሪ የማይከበርበት፣ የሰላም ጥሪ ድምጽዋ የማይሰመባት፣ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በመፈተሸ ክብርና ልዕልናዋ እንዲመለስ በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይትና ጥልቅ ምክክር እንዲደረግ መፍትሔም እንዲፈለግለት ጉባኤ ያሳስባል፡፡

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

18 Oct, 08:32


https://youtu.be/xHFjvTTaI0k?si=uEtLMPN4HTDz0wsw ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! ያስተዋውቁ!
https://t.me/tunbi_media
🎥💻📺🎙 YouTube በዩቲዩብ ዝግጅቶቻችንን 👁👁👂🏽👂🏽ይታደሙ!
www.youtube.com/@TunbiMedia_
በራምብል
rumble.com/c/c-3688912
በቲክቶክ
tiktok.com/@ethiotunbi

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

18 Oct, 08:27


      የግል ምልከታየ
ዕቅበተ እምነት ላይ እንጂ ተቋማዊ ጥበቃ ላይ ብቻ ማተኮር ማደክደክ ነው።
  ላይኛው ተቋም ለእውነት ሥራ ዝግጁ አይለም።
ከትናንት እስከ አሁን  በቤተ ክርስቲያን ላይ ለደረሰው ውስጣዊ መከራ ተቋሙ የችግር ባለቤት ሳይሆን ራሱ ችግር ነው።
በተለይም የውጭ መከራዎችን እንደ እባብ ሰይጠንን ተጭኖ እየመጣ አዳማውያንን የሚያስትበት ቤት ከሆነ ሰነባብቷል።
ህልው ሁኖ አጀንዳ የሚሰጣችሁ ማን ነው?ይሄንን የማያውቅ ሰው ይኖራል? ካላ በጣም ፈዛዛ ነው።
ይልቅስ እንደ ባለቅኔው የጥፋት መልእክቱ ደርሶና የላካችሁ ሰውየ ደኅና ነውወይ? አትሏቸውም?
ይሄንን የምጽፈው በግል ሁኖ አንዳንድ የቤቱን ተንኮል ያልተረዱ የዋሓን ምእመናን ዛሬም ሲደናገሩ በማየቴ ነው።
የማይፈወሰው ድውይ የማይመለሰው ጊጉይ ሁኖ መድኃኒቱን እያማሰነ እንደገና በደዌ እያመረቀዘ የጥፋት ቫይረስ ተሸካሚ ሁኖ ከተገለጸ ቆይቷል።
አሁንም የአትርሱኝ ጩኸት ወዲያ ወዲህ ሲያወራ ቢሰማም ምእመናንን ዕረፍት ለመንሳት፣ለማደናገር፣የንትርክ አጀንዳ ለመስጠት፣ለሥርዓቱ ጥበቃ ይጠቅማል ተብሎ የተሰጠውን የተልእኮ ዓላማ ለመፈጸም ሲባል..ነው እንጂ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚመለከተው ሁኖ አይደለም።
ይሄ ጉዳይ በደንብ ተነጋግረውበት ተወያይተውበት የአትርሱኝ አስታውሱኝ አጀንዳ እንጂ የእውነት አይደለም።ሁሉም የሚሠሩት አብረው ነው።
ዋናው ጉዳይ ምእመናንን ማደናገር፣ዕረፍት መንሳት፣እምነቱን እንዲተው ማወክ፣ሥርዓቱን መጫን፣ምእመናንን ማሳቀቅ፣ጭር ሲል አልወድም...ነው።
ቢያንስ ሞቱ እንግልቱ ይቅርና ምእመናን ሀዘናቸውን እንኳን ዕርም አውጥተው እንዳያዝኑበት ዲሪቶውን አምጥቶ ይጭንባቸዋል።
እኔ በግሌ ከነነዌ ምህላ እና ከሐምል 9/1015 ዓ.ም.ጀምሮ ጨርሸ ትቻቸዋለሁ።ረቂቅ ውንብድናውን እስከ ጥግ አይቸዋለሁ።
እኔ ግን የለውጥ መንገዱን እስካገኘው እፈልገዋለሁ።ከሕይወቴ አብልጬጬ እጨነቅለታለሁ።ሁልጊዜም ቤተ ክርስቲያን የደረሰባትን ሳስበው አንጀቴ ይላወስብኛል።
ወደ መፍትሄው ብቻ ዓይናችንን እናዙር።
የቤቱ ስም የእኛ ነው ሥራው ግን የአጥፊዎች ነው።
ሁለንተናው ኦርቶዶክሳዊ እስኪሆን ድረስ ዓይናችንን ወደ መፍትሄው ብቻ እናዙር።

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

16 Oct, 19:12


https://www.youtube.com/live/4upYe2px7ao?si=rajqcZr8nDDTpq6M

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

12 Oct, 18:27


https://www.youtube.com/live/HBerkzDgFvc?si=ip-tBu_7_J_25xel

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

07 Oct, 07:07


https://youtu.be/t3FDb2-8aAs?si=4H9mQ14_qglfA6tJ

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

05 Oct, 19:11


https://www.youtube.com/watch?v=TQBr8kNh4yo

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

03 Oct, 17:06


👆🏾 የቀጠለ

በዚህ ግምገማ መሠረት በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ላለፉት 50፥ 30፥ 6 ተደማሪ (የ3 አምላክ የለሽ ምንግሥት) ዓመታት የተንሠራፋውን ሙስና ለማሸነፍ መዋቅሩን በየደረጃው አንዲመሩ የደረጉ አባቶች እና ሠራተኞች አመጣጥ፥ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጤንነት፥ የሕይወት ፍልስፍና መመዝና ይገባል። ሙስና የሰው ተግባር ነው። ሰው ሚሰኛ የሚሆነው ሕሊናው ብቻ ሳይሆን እምነቱም ሲበላሽና በቁስ ፍተወት ሲታወር ነው። ሌሎች ቀድሞውኑ ለሆዳቸው የተካኑና የተጠጉ እምነት የለⶄች ሊሆኑ ይችላሉ። ሌሎቹ በሕወሃት ሠልጥነው ቤተ ክርስቲያንን ለማፈራረስ የገቡ ናቸው። ሕወሃት ብቻውን እንዳይጠየቅበት የፖለቲካ አሽከሮቹ ብአዴንና ኦፒዲኦ የቤተ ክርስቲያን ተሿሚዎች እየመለመለ በኮታ እንዲያⶄም በማድረግ በኃጢያቱ አሳትፏቸዋል። ወሊሶና አክሱም ጫካ የሚሿሿሙት መሠረታቸው የፖለቲካና የጎሣ ኮታ ደርሷቸው አባት የተባሉ መነኮሳትና ጳጳሳት ናነው።

አሁን አጣሪ ኮሚቴ ብለው ቅዱስ አባታችን ኃላፊነት የሰጧቸው ወድም እኅቶቻችን ይህን ከላይ የተገለጠውን መሠረታዊ ብልሽት አንዲያስተካክሉ ሙሉ ኅልጣን ካልተሰጣቸው ከንቱ ድካም ነው።
ይህ የተወሳሰብ ሙስና በኮሚቴ ምርመራ አይጠፋም።

እንደ እኔ ዐሳብ መፍትሔ ለማግኘት ከተፈለገ በመጀመሪያ የሚከተሉትን ከባድ ውሳኔዎች መወሰን ይጠይቃል
1. ላለፉት 50 ዓመታት በሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት አንጻር የተጣሱት ቀኖናን ተመርምረው ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ማድረግ
2. በተጣሰው ቀኖና እና በፖለቲካ ኮታ መሠረት የተⶄሙት አባቶች መሻር ወይንም ወደ ገዳም ሄደው በጸሎት አንዲወሰኑ ማድረግ
3. ሲኖዶሲን የመነኮሳት ብቻ ሳይሆን የሊቃውንትና የምእመናን ጭምር ማድረግ
4. ከተማ ጠከተሙ መነኮሳትን ሁሉ ወደ ገዳም ባዕታቸው በመሰብሰብ የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር በሕግ ካህንና በባለሙያ ምእመናን ጥምረት እንዲመራ ማድረግ
5. ጎሠኛ ካህናትን፥ ኤጲስቆጶሳትን መሻር
6. የተገለጠና በምእመናን ደረጃ የታወቀ የክህነትንና ምነኩስና ሕይወት የማይፈቅዳቸውን ስነ ምግባራዊ ብልሽት ያደቀቃቸውን በመሻር በቀኖና መወሰን
7. ዐዓለም አቀፍ የሊቃውንት፥ የበገረ መለኮት ምሁራን፥ የምእመናንና የአኀት አቢኣተክርስቲያናት ድጋፍ ያለበት ጉባዔ በማዘጋጀት ራስን እንደ አዲስ ማስተካከል
ከዚህ ውጭ የሆነ ሙከራ ሁሉ ለፖሊስ ተሰጥቶ ሌባን በወንጀል መክሰስ አንጂ በአጣሪ ኮሚቴ መፍታት አይቻልም።

አግዚአብሔር የተሻለ መፍትሔ ይግለጥልን
ፋንታሁን ዋቄ
https://t.me/Wakie_EOTCissues

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

03 Oct, 17:06


👆🏾👆🏾👆🏾 ይህን ዜና በሚመለከት ጠንካራ አስተያየት አለኝ። ቤተ ክህነቱና አደራ የተጣለባቸው የኮሚቴ አባላት ያጤኑት‼️‼️‼️

መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ሙስና በኮሚቴ አይጠፋም!!
አህያውን ፍርቶ ዳውላዉን ይባላል በእኛ በኢትዮጵያውያን፥ ሌሎቹ ደግሞ በከንቱ ጥላ መደብደብ (shadow boxing) ይሉታል።⁉️

የዛሬው ዜና አስገራሚ ነው። እንዲህ ይላል፦
“በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለውን የሙስናና ብልሹ አሰራር በዝርዝር በማጥናት የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት አጥኚ ኮሚቴ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተቋቁሙ የሥራ መመሪያ ተቀብሏል። “ [በአጭሩ የተጠቀሰ ነው]
መስከረም 23 ቀን 2017
ይህን አይነት ኮሚቴ ከ2004 ጀምሮ እናውቃለን። 12 ዓመታት ስንት ኮሚቴ ተቋቁሞ ፈርሷል። በዚህ ሂደት ሁለንተናዊ ሙስና ተጠናክሮ ቀጥሏል። አሁንም በዚህ ኮሚቴ የሚመጣ መፍትሔ አይኖርም።

ምክኒያቴን ላቅርብ፦


በቤተ ክህነት ውስጥ በተወሳሰበ አደረጃጀት፥ በተባለሸ አስተሳሰብና የእምነት ዝለት፥ በፖለቲካና ጎሠኛ ቁርኝት በወደቁ ሰዎች ምክንያት የተንሰራፉ ስድስት አይነት የሙስና አይነቶች አሉ

በመጀመሪያ በቤተ ክህነት መዋቅር አውድ ውስጥ ሙስና ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ በቀላሉ የሚከተሉትን መለየት ይቻላል፦

1. ቁምስናን፥ ክህነትን በእጅ መንሻ፥ በጎሣ ዘውግ ማደል (መዋቅሩ የሕወሃት፥ የኦፒዲኦ፥ የብአዴን የኮታ ጳጳሳት መⶄም ምክንያት ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ የማይገዳቸው ምንደኞች እጅ መውደቁ)፥ የከተማ መነኮሳት መፈጠርና የገነዝብና የሰው አስተዳዳሩ በመሆን ሙስናን እየለማመዱ ወደ ጵጵሳ ማደግ ባህል መስፈን፤=== በዚህ ምክኒያት የሚከተሉት 5 የሚስና አይነቶች ተንሰራፍተዋል፦
2. በአስተዳደራዊና ሃይማኖታዊ ሥልጣን እና/ወይንም የሙያ ኃላፈነትን በመጠቀም ከቀኖና ቤተክርስቲያን፣ ከአስተዳደር መመሪያዎች ውጭ ሰዎችን መሾምና መሻር ወይንም በሕግ ያልተፈቀደ ጥቅም ማካፈል

3. አስተዳደራዊና ሃይማኖታዊ ሥልጣን እና/ወይንም የሙያ ኃላፈነትን በመጠቀም አንድን የታወቀን የመንግሥት ወይንም የቤተክርስቲያን ወይንም ተቀባይነት ያለውና ከቅድስና ሕይወት ጋር የሚስማማ ባህላዊ አሠራርን በመጣስ የግል ጥቅምን ወይንም የአንድኘ ቡድን ጥቅም ለማሳካት መንቀሳቀስ

4. ቃል የገቡበትን አስተዳደራዊና ሃይማኖታዊ ሥልጣን እና/ወይንም የሙያ ኃላፊነት በሚፃረር መንገድ ንብረትንና ገንዘብን ማባከን ወይንም ለግል ጥቅም ማዋል ወይንም ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት ውጤት እንዲያስገኙ ለሥራ የተሰለፈውን የሰው ኃይል ውጤታማ እንዳይሆን በተለያዩ መንገዶች ማሰናከል፣ እውቀታቸውን ማባከን ወስጥ የተሳተፈ ማንኛውም ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሙስና እንደፈፀመ ይቆጠራል

5. የሃይማኖታዊ አገልግሎት ኃለፊነትንና ሥልጣን በተገቢው መንገድ መወጣት የሚያስችል ሁኔታ እያለ: ነገር ግን ለግል የሥጋ ፈቃድ በማድላት ወይንም ሆን ተብሎ ከአፅራረ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር የቤተክርስቲያናችንን ተከታዮች በመናፍቃን ያስነጠቀ ወይንም በቀጥታ ወደ ሌላ የእምነት ድርጅት እንዲፈልሱ ያስትማረ፣ ወይንም በንግግርና ኢክርስቲናዊ አርአያነት ባለው በኑሮ የሚገለጥ ተግባሩ ምእመናንን ወደ ሌላ እምነት ወይንም ወደ ክህደት የገፋ ወይንም ነፍሳት እንዲጠፉ ያመቻቸ ግለሰብም ይሁን ቡድን ሙስና እንደፈፀመ ይቆጠራል

6. ማንኛውም የሃይማኖት አባት፣ የሥራ ኃላፊ፣ ሠራተኛና ምእምን በተሰጠው የአገልግሎት እድሎች በመጠቀም ለምእመናን በክርስትና አኗኗር መፅናትና ለመንፈሳዊ ሕይወት መጎልበት እንዲያገለግሉ ታስበውና ታምነው በቀደሙትና አሁን ባሉት አባቶችና መምህራን የተዘጋጁ ንዋየቅድሳትን፣ የቤተክርስቲያን ሥዕሎችን፣ የዜማና የተለያዩ የሥነጥበብ ውጤቶችን፣ የመንፈሳዊ ትምህርት ማስፋፊያ መጻሕፍትን፣ ለመንፈሳዊ አገልግሎት የተለዩ ቦታዎችን፣ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ታሪካዊ ቅርሶችን፣ በዓላትን ወዘተ ለቁሳዊ የግልና የቡድን ብልፅግና ብሎ ወደ ቁሳዊ ሸቀጥነት ቀይሮ ለገበያ ያቀረበ፣ ወይንም ለሥጋዊ መገልገያነት ያዋለ ወይንም ለአገልግሎት በማይውሉበት ሁኔታ እንዲገኙ አድርጎ የሰወረ ሁሉ ሙስናን እንዳደረገ ይቆጠራል


ለ) በቤተ ክህነታችን ውስጥ ስምንት የሙስና ድርጊቶች የተገለጡባቸው መንገዶች አሉ

1. የቀኖና ጥሰት
2. ምእመናን በሚመለከት ከክህነት ኃይልና ሥልጣን የበለጠ በፖለቲካ ሥልጣንና በፖሊስ ኃይል የሚተማመኑ አባቶች መብዛት
3. የገንዘብ ብክነት፥ የንብረት ብክነት
4. የማይንቀሳቀሱ ሀብታትን ያለአግባብ ተግባር ላይ መዋል
5. የፍትህ መታጣት ወይንም ያለአግባብ መዘግየት
6. አድሎዎ ያለበት የሰው ቅጥር፣ የእደገትና የዝውውር ሁኔታ
7. የአባትነትን ቦታውን ይዞ በተግባር የፖለቲካና የብሔረሰብ ካድሬነት ሚና መውሰድ
8. ምእመናንን ባለማስተማር፣ ንስሐ ባለመስጠት፣ በክፉ አርአያነትና ብልሹ ሥነምግባር፣ ማሰናከል ወይንም በተለያዩ ምክኒያቶች ምእመናን መለያየት፣ ለኑፋቄ መዳረግ
9. ለግል ጥቅም ሲባል ምእመናንን በቡድንና በአካባቢ በመከፋፈልና ማጋጨት
10. የጎኃ ሲኖዶስና ጳጳሳትን ለመሾም በሚያበቃ ደረጃ የተከፋፈሉ የመነኮሳት ሠራዊት በከተማ መከማቸት

(ሐ) ጎላ ብለው የሚታዩ የሙስና መንስዔዎች

1. የሥርዓት፣ የአቅም እና የሙያ ችግሮች
2. ክህነትን ለሥጋዊ ኑሮ ታሳቢ አድርጎ ከመንፈሳዊ ተልእኮው ነጥሎ መጠቀም፥
3. ዘረኝነትና ቡደንኘት በመዋቅሩ ውስጥ መንሰራፋት
4. መንፈሳዊ ዝለት መበርታትና ቁሳዊነት መንገስ
5. የገንዘብ አሰባሰብ፣ አያያዝና አጠቃቀም ኃላቀር መሆንና ተገቢው ዘመናዊ ሙያዊ፣ የቴክኖሎጂና
6. የቁጥጥር ዘዴዎችን በሙሰኛ ኃላፊዎች ውሳኔ ሥር ማዋል እና እንደሚገባው አለመጠቀም
7. የንብረትና የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር ሥርዓትና ቁጥጥር የዘመኑን ሰው ፈተና የሚከላከል ሆኖ አለመደራጀቱና
8. የንብረትና የሰው ኃይል ልማትና አስተዳደር በብቁና በቂ ሠራተኞች አለመመራት
9. የቅጥር የዝውውር፣ የእድገት፣ የሙያ ምዘናና፣ የሰው ኃይል ምጣኔ፣ የሰው ኃይል አስተዳደር፣ የሰው ኃይል የአገልግሎት ውጤት መለኪያዎችን በሚመለከት ግልፅ የሆነ ሥርዓትና መመሪያ፣ የመመሪያውን ተግባራዊነት የሚቆጣጠር መዋቅር አለመኖርና የቁጥጥር ሥርዓት ደካማነት

👇🏾👇🏾👇🏾 ቀጥሏል

https://t.me/Wakie_EOTCissues

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

03 Oct, 17:06


ተቋሟዊ የሆነ የተደራጀ ሌብነትን በኮሚቴ ማጥፋት አይቻለም። መፍትሔው ሌላ ነው። ሌላ ጊዜ እንወያይበታለን።

ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

03 Oct, 17:06


https://www.facebook.com/share/QEdcUjcsiNYqeT15/?mibextid=xfxF2i


ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአጣሪ ኮሚቴው የሥራ መመሪያ ሰጡ።
*************

"ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም።"
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ

መስከረም ፳፫ ቀን፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም.
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
=============

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለውን የሙስናና ብልሹ
አሰራር በዝርዝር በማጥናት የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው አጥኚ ኮሚቴ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትና ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን የሠራቸውን ሥራዎች ሪፓርት በማቅረብ በቀጣይ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ በመወያየት የሥራ መመሪያ ተቀብሏል።

ኮሚቴው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚስተዋለው የመልካም አስተዳደር ችግር ከውስጥ አልፎ በአደባባይ መነጋገርያ በመሆኑ በጥናት ላይ በተመሠረተ አግባብ ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችልና የቤተ ክርስቲያናችንን ክብር በሚመጥን መልኩ እንዲደራጅ የሚያደርግ የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ የሚያስችለውን ዕቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መግባቱን የኮሚቴው ሰብሳቢ መ/ሰ ቆሞስ አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ (ዶር)
እና ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርኩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰጡት አባታዊ የሥራ መመሪያ "ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም። ያሉ ሲሆን ስለሆነም ሕግና ሥርዓትን አክብራችሁ፣ በእውነተኝነት ለቤተክርስቲያን፣ለእግዚአብሔርና ለራሳችሁ ብላችሁ ሳታፍሩና ሳትፈሩ ሥራችሁን ሥሩ። ሥራው ታማኝነት"ጥብዓት" ያስፈልጋል ብለዋል።

ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጋር ሆናችሁ በጋራ ሥሩ ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ጠንከር ያለ መድኅኒት ሊሆን የሚችል ጥናት ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር እንደምታቀርቡ እምነቴ የጸና ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም የተላካችሁበት ሥራ ያለ ውጤት የሚቀር መሆን የለበትም። ቤተክርስቲያን የተዋረደችበት ጊዜ ማብቃት አለበት ያሉት ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያናችን ራሷን አንጽታ ለሌሎች መልካም አብነት መሆን አለባት ካሉ በኋላ ዓለማዊያን የሚሰሩት ሥህተት እንዳይኖር በተግባር የምታስተምር ተቋም እንጂ በሙስና የምትታማ መሆን የለበትም ብለዋል።

ልጆቼ እውነቱን ለማውጣት ታጥቃችሁ ሥሩ በሙስና ህመም ለምትሰቃየው ቤተክርስቲያን መድኃኒት ፈልጉላት በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንመረመርም ማለት ራሱን ችሎ ወንጀል ነው ካሉ በኋላ ይህ ሥራ ለእናንተም ታሪክ ነው። እውነትን መሰረት አድርጋችሁ በመሥራት ታሪክ አስመዝግቡ ብለዋል።

በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይም ወደ እዚህ ተቋም የሚገቡ ሁሉ ይህን ያህል ጊዜ ቆይተን ይህን ያህል ይዘን እንውጣ የሚሉ እንጂ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩና የሚያስቡ እንዳልሆኑ ይታወቃል ካሉ በኋላ የተሰጣችሁን ኋላፊነት በትጋት ፈጽሙ ብለዋል።
በመጨረሻም ሥራችሁ ሁሉ የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን እንጸልያለን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

3,050

subscribers

129

photos

35

videos