የካቲት ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
በዚች ዕለት ቅዱስ ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ሶምሶን ላከው የፍልስጥዔም ሰዎች ሊገድሉት በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ ድል እስከ አደረጋቸውና እስከ ገደላቸው ድረስ ቅዱስ ሚካኤል ረዳው ኃይልንም ሰጥቶ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰዎችን ገደለ።
ተጠምቶም ለሞት በተቃረበ ጊዜም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ተገለጠለትና አጸናው እግዚአብሔር ከአህያ መንጋጋ አጥንትም ውኃን አፈለቀለትና ጠጥቶ ዳነ።
ዳግመኛም ከሚስቱ ጋር ተስማምተው ዐይኖቹን አሳወሩ የራሱንም ጠጉር ላጩ አሠሩትም ከዚህም በኋላ ለጣዖቶቻቸው በዓልን በአዘጋጁ ጊዜ ሶምሶንን ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ወሰዱት በዚያም ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ተሰብስበው ነበር።
የከበረ ሚካኤልም ተገለጠለትና ኃይልን መላው የዚያንም ቤት ምሰሶዎች ነቀላቸው ቤቱም በላያቸው ወድቆ ከእርሱ ጋር ሁሉንም ገደላቸው ጅ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘለዓለሙ!