በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw @betremariyamabebaw Channel on Telegram

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

@betremariyamabebaw


አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw (Amharic)

በትረማርያም አበባው (Betremariam Abebaw) ትክክለኛ መረጃና መዝሙር አሳልፈን ለእግዚአብሔር አቀድም አእኵቶቶ የሚሆን ታሪክን በመዝሙርና በትረማርያም ይሻወራል። በታካል የቴሌግራም መረጃዎችን እና ተረትና ስንጡትን ይስማማል። እሱን ጠቅላለሁ እና እንደደም አስቀምጥለው የሚያገኙበት ስልክና የጀምሮ ቤተሰቦች እንዲቀጥል ምክንያት አስተያየታል።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Feb, 23:01


💗 መዝሙረ ዳዊት ክፍል 8 💗

💗መዝሙር ፸፩፡- ልዑል እግዚአብሔር ብቻውን ተአምራትን እንደሚያደርግ

💗መዝሙር ፸፪፡- እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ
-እግዚአብሔርን መከተል እንደሚሻል

💗መዝሙር ፸፫፡- እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ እንደሆነና በምድርም መካከል መድኃኒትን እንዳደረገ
-በጋንና ክረምትን የሚያፈራርቅ እግዚአብሔር እንደሆነ

💗መዝሙር ፸፬፡- በእግዚአብሔር ላይ ዐመፃን መናገር እንደማይገባ

💗መዝሙር ፸፭፡- እግዚአብሔር ግሩም እንደሆነ

💗መዝሙር ፸፮፡- ዳዊት እግዚአብሔርን አሰብኩት ደስ አለኝም እንዳለ
-የእግዚአብሔር ፍለጋው እንደማይታወቅ

💗መዝሙር ፸፯፡- የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ ኃይሉንና ያደረገውን ተአምራት መናገር እንደሚገባ
-እግዚአብሔር መሓሪ እንደሆነ

💗መዝሙር ፸፰፡- ዳዊት ስለስምህ ክብር አቤቱ ታደገን፣ ስለስምህም ኃጢአታችንን አስተሥርይልን እንዳለ

💗መዝሙር ፸፱፡- እግዚአብሔር ፊቱን ካበራልን እንደምንድን

💗መዝሙር ፹፡- ከእግዚአብሔር ውጭ ሌላ አምላክ ማምለክ እንደማይገባ

💗የዕለቱ ጥያቄ💗
፩. ስለ ልዑል እግዚአብሔር ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ብቻውን ተአምራትን ያደርጋል
ለ. ቸር ነው
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/Gzf4fQdXzvM?si=AwO4nm9rIh0Bgeol

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Feb, 22:50


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 139 💙💙

▶️፩. መዝ.67፥31 ላይ "መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" ይላል። መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ ሲል ምን ማለት ነው? ከሌሎች ሀገሮች ተለይታ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘርጋለች ለምን ተባለ?

✔️መልስ፦ መኳንንተ ግብጽ እጅ መንሻቸውን ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዳሉ ማለት ነው። ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ማለትም በንግሥት ሳባ አማካኝነት እጅ መንሻን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ትሄዳለች ማለት ነው። በሀገሪቱ ሰዎችን መናገር ነው።

▶️፪. መዝ.69፥2 "ጠላቶቼ ይታመሙ ከፊትህም ይጥፉ" ይላል። መዝ.62፥9-10 ላይ ደግሞ "እነርሱ ግን ነፍሴን ለከንቱ ፈለጓት ወደ ምድር ጥልቅ ይግቡ" ይላል። መዝ.67፥1-2 ላይ እና መዝ.68፥22-23 ላይ ስናነብም ቅዱስ ዳዊት ጠላቶቼ እንዲህ ይሁኑ የሚላቸው ያኔ ሲያሳድዱት የነበሩትን ነው ወይስ አጋንንትን ነው? ይህስ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ካለን ጋራ አይጋጭም ወይ?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። በብሉይ ኪዳን የጠሏቸውን መጥላት በደል አልነበረም። ስለዚህ ዳዊት ጠላቶቼ ይጥፉ እያለ ጸልዩዋል። በሐዲስ ኪዳን ግን አፍቅሩ ጸላእተክሙ (ጠላቶቻችሁን ውደዱ) የሚል ሕግ አለና ከሰው ወገን ማንንም እንድንጠላ አልተፈቀደም። በሐዲስ ኪዳን ይህንን የመዝሙረ ዳዊት ክፍል ስንደግም አጥፋቸው የምንላቸው አጋንንትንና እግዚአብሔር በሚያውቀው ከክፋታቸው የማይመለሱትን ነው። ይህ ለሁለቱም ይጠቅማልና። ክፉ ሰው ቶሎ ቢሞት ይጠቀማል። በክፋቱ ቆይቶ ፍዳው ከሚጸና ፍዳው ይቀልለት ዘንድ ቶሎ ቢያርፍ ይሻለዋልና።

▶️፫. "ረዳቴ ሆነኸኛልና በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና" ይላል (መዝ.62፥7)። በክንፎችህ ጥላ ሲል የእግዚአብሔር ክንፎች አሉት ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ለእግዚአብሔር ክንፍ ኖሮት አይደለም። ክንፎችህ እያለ የሚገልጸው ረድኤቱን ነው። ደራሲ ከመ ዖፍ አፍኅርቲሃ ትሴውር በክንፋ እንዳለ ወፍ ልጆቿን በክንፎቿ እንደምትሠውር ሁሉ እግዚአብሔርም በቸርነቱ በረድኤቱ ከመከራ ሁሉ ያድነናልና ይህን ለመግለጽ በወፍ ግሥ የተነገረ ነው።

▶️፬. "ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል። በእርሱ የሚምል ሁሉ ይከብራል ሐሰትን የሚናገር አፍ ይዘጋልና" ይላል (መዝ.62፥11)። በእግዚአብሔር የሚምል ይከብራል የሚለው ሐሳብ በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ደግሞ ሰው በራሱ እንኳን መማል እንደማይችል የሚናገር እናገኛለንና አይጋጭም ወይ?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። በብሉይ ኪዳን በሐሰት መማል እንደማይገባ ተገልጿል (ዘፀ.20)። በእውነት መማል ግን የሚቻል እንጂ ኃጢአት አልነበረምና ዳዊት በእርሱ የሚምል ይከብራል አለ። በሐዲስ ኪዳን ግን በእውነትም በሐሰትም መማል ስለማይገባ ፈጽማችሁ አትማሉ ስለተባለ አሁን ላይ ዳኛ ሳያዝዘን በእውነትም ቢሆን መማል ፈጽሞ አይገባም።

▶️፭. መዝ.63፥3 "ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል" ይላል። ሕይወት ብሎ ከምሕረቱ ጋር ያወዳደራት የእርሱን ሕይወት ነው ወይስ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ስለትሩፋን የተነገረ እንደመሆኑ ሕይወት ያላት በባቢሎን ተማርከው የሚኖሩ ሰዎችን ሕይወት ነው። ስለዚህ ምሕረትህ ከሕይወት ይሻላልና ማለት በባቢሎን ብዙ ዘመን ከመኖር በይቅርታህ ኢየሩሳሌም ገብቶ አንድ ቀን አድሮ መሞት ይሻላል ማለቱ ነው።

▶️፮. መዝ.67፥16 ላይ "እግዚአብሔር ያድርበት ዘንድ የወደደው ተራራ ይኽ ነው" ይላል። ያ የተወደደ ተራራ የተባለ ምንድን ነው? እዚሁ ምዕራፍ ቁጥር 18 ላይ "ያድሩ ዘንድ ይክዱ ነበርና" ያለው እነማንን ነው?

✔️መልስ፦ በዚህ አግባብ እግዚአብሔር ያድርበት ዘንድ የወደደው ተራራ የተባለ ትሩፍ እስራኤላዊ ነው። እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ በረድኤት ከእስራኤል ጋር ነበርና። ያድሩ ዘንድ ይክዱ ነበር የተባሉ እስራኤላውያን ናቸው። ተስፋ ሚጠት፣ ሚጠት ባይኖርላቸው ኖሮ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ክደው ጣዖትን ያመልኩ እንደነበረ የሚያሳውቅ ነው።

▶️፯. መዝ.68፥15 ላይ "የውኃ ማዕበል አያስጥመኝ ጥልቁም አይዋጠኝ። ጒድጓዶችም አፋቸውን በእኔ ላይ አይክፈቱ" ያለው ጒድጓዶችም የተባሉ እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ መዝሙር 68 ስለመቃብያን የተነገረ ትንቢት ነው። ከላይ ያለው ዓረፍተ ነገር ለመቃብያን ሲነገር ጣዖት አምላኪው አንጥያኮስ ፈጽሞ እንዳያጠፋኝ አድርገኝ ተብሎ ይተረጎማል። ጉድጓዶች የተባሉ እነ አንጥያኮስ ናቸው።

▶️፰. "ለሰይፍ እጅ ዐልፈው ይሰጣሉ የቀበሮም ዕድል ፈንታ ይሆናሉ" ይላል (መዝ.62፥10)። የቀበሮ ዕድል ምን ዓይነት ነው?

✔️መልስ፦ የቀበሮ ዕድል ፋንታ ይሆናሉ ማለት በሰይፍ አልቀው ተገድለው ሬሳቸውን የሚያነሣው ጠፍቶ ቀበሮ ይበላዋል ማለት ነው።

▶️፱. "በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ። እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ ሰልፍን የሚወዱትን አሕዛብን በትናቸው" ይላል (መዝ.67፥30)። ከዚህ ላይ የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ የበሬዎችና የወይፈኖች ጉባኤ የተባሉ እስራኤላውያን ናቸው። ገሥጻቸው ማለት በአሕዛብ ተማርከው እንዳይቀሩ አስተምራቸው ማለት ነው።

▶️፲. መዝ.62፥1 ላይ "እንጨትና ውኃ በሌለበት ምድረበዳ ሥጋየን ላንተ እንዴት ልዘርጋልህ?" ይላል። ቢብራራ።

✔️መልስ፦ ይህ ስለትሩፋን የተነገረ ነው። እንጨትና ውሃ በሌለበት ምድረበዳ ማለት ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉ ዕፀዋት በሌሉበት በባቢሎን መሥዋዕትን እንዴት ልሠዋልህ? ማለት መሠዋት አልቻልኩም ማለት ነው።

▶️፲፩. "ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? መድኀኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና" ይላል (መዝ.61፥1)። እዚህ ላይ መድኃኒቴ ያላት እመቤታችንን ነው ብለን መናገር እንችላለን ወይስ አንችልም?

✔️መልስ፦ ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? የሚለው በአሉታ የተጠየቀ አዎንታዊ መልስ ያለው ነው። ይህ ማለት በአጭሩ ነፍሴ ለእግዚአብሔር ትገዛለች ማለት ነው። መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናት ማለት ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት ማለት ነው። ትርጓሜው ላይ ለድንግል ማርያም ሰጥቶ አልተረጎመውም ነገር ግን አክሊለ ምክሕነ ወቀዳሚተ መድኃኒትነ በሚለው አግባብ በጸጋ በምልጃዋ የምታድነን ስለሆነች ሌላ መተርጉም ተርጉሞት ቢገኝ መልካም ምሥጢር ነው።

▶️፲፪. መዝ.66፥3-5 አሕዛብ እግዚአብሔርን እንደሚያመሰግኑት እና በእርሱም ደስ እንደሚላቸው ይናገራል። ይህ ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ አሕዛብ የሚላቸው እስራኤላውያንን ነው። ሕዝብ የሚለው ውስጠ ብዙ (ብዛትን አመልካች ቃል) የብዙ ብዙ ሲሆን አሕዛብ ይላልና ከዚህ አሕዛብ ያላቸው ራሳቸውን እስራኤላውያንን ነው።

▶️፲፫. መዝ.67፥4 "ወደ ምዕራብ ለወጣው መንገድን አብጁ" ይላል። ከዚህ ላይ ምዕራብ ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ ምዕራብ ያለው ባቢሎንን ነው። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም እንደመለሳቸው ያመለክታል። በተጨማሪም በምሥጢር ሊቃውንት ምዕራብን ሲኦል ብለውታል። ከሲኦል እግዚአብሔር ነፍሳትን አውጥቶ ወደ ገነት እንደመለሳቸው ለመግለጽ ነው።

▶️፲፬. መዝ.67፥13 ላይ ''በርስቶች መካከል ብታድሩ ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክንፎች በቅጠልያ ወርቅም እንደ ተለበጡ ላባዎቿ ትኾናላችኹ'' የሚለውን ቢያብራሩልኝ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Feb, 22:50


✔️መልስ፦ በርስቶች መካከል ብታድሩ ማለት የከነዓን ሰዎች ወደ ወረሷት ወደሴም ዕፃ ብትደርሱ እንደ ርግብ ክንፎች በቅጠልያ ወርቅም እንደተለበጡ ላባዎቿ ትሆናላችሁ። ይህም ማለት ወርቅ ጽሩይ እንደሆነ ልብን የምታጠራ ሕግን ታገኛላችሁ ማለት ነው።

▶️፲፭. መዝ.67፥17 ላይ የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የተባሉ እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የሚባሉት በእግዚአብሔር ሕግ የሚመሩ እስራኤላውያን ናቸው።

▶️፲፮. መዝ.67፥18 "ምርኮን ማርከኽ ወደ ሰማይ ወጣኽ። ስጦታኽንም ለሰዎች ሰጠኽ። ያድሩ ዘንድ ይክዱ ነበርና'' የሚለውን ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ምርኮን ማርከህ ወደ ሰማይ ወጣህ ማለት ለጊዜው እስራኤላውያንን ከባቢሎን ምርኮኝነት አውጥተህ በዘሩባቤል አማካኝነት ወደ ኢየሩሳሌም መለስካቸው ማለት ነው። በሌላ አገላለጽ (ኦ ክርስቶስ) ነፍሳትን ከሲኦል አውጥተህ ወደ ገነት አገባሀቸው ማለት ነው። ስጦታህንም ለሰዎች ሰጠህ ማለት ሚጠተ ሥጋን ለእስራኤል ሰጠህ፣ ሚጠተ ነፍስን ደግሞ ለነፍሳት ሰጠህ ማለት ነው። ሚጠትን ባትሰጥ ኖሮ ይክዱ ነበር ማለት ከመከራው ጽናት የተነሣ ከአምልኮተ እግዚአብሔር ይወጡ ነበር ማለት ነው።

▶️፲፯. መዝ.67፥20 ላይ "የሞት መንገድ የእግዚአብሔር ነው'' ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የሞት መንገድ የእግዚአብሔር ነው ማለት የሰውን ነፍሱን ከሥጋው የመለየት ሥልጣን የእግዚአብሔር ነው ማለት ነው።

▶️፲፰. መዝ.67፥21 ላይ ''በጠጉራቸው ጫፍም በደላቸው ይኼዳል'' ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ማለት ማዕበል ሞገዱ በራሳቸው ላይ ይሔዳል ማለት ነው። ይኸውም ለበደሉ እስራኤላውያን ታላቅ መከራ ይመጣባቸዋል ማለት ነው። በሌላ አገላለጽ የምእመናን ኃጢአታቸው በክርስቶስ ይቅር ይባላል ማለት ነው።

▶️፲፱. መዝ.67፥22 ላይ ''ወጥቼ እመለሳለኹ'' ይላል። ቢብራራ።

✔️መልስ፦ ይህ ስለክርስቶስም ያስተረጉማል። (ይቤ ክርስቶስ) ወደ ሰማይ ዐርጌ እመለሳለሁ ይላል። ይህም ማለት በምጽአት መጥቶ ፍርድ እንደሚሰጥ ያመለክታል።

▶️፳. መዝ.67፥23 ላይ ''እግሮችኽ በደም ይነከሩ ዘንድ የውሻዎችኽ ምላስ በጠላቶች ላይ ነው'' ማለቱ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እግሮችህ በደም ይነከሩ ዘንድ የተባለ ክርስቶስ በመስቀል እግሮቹ ተቸንክረው በደም እንደሚነከሩ ያመለክታል። ሰላም ለአጽፋረ እግርከ በደመ ቅንዋት እለ ተጠምዓ እንዳለ ደራሲ። የውሾችህ ምላስ በጠላቶች ላይ ነው ማለት ውሻ ለጌታው ታማኝ እንደሆነ በአንተ የሚያምኑ ምእመናን አንደበት በአጋንንት ላይ ነው ማለት ነው።

▶️፳፩. "ቀንድና ጥፍር ካበቀለ ከእንቦሳ ይልቅ እግዚአብሔርን ደስ ያሠኘዋል" ይላል (መዝ.68፥31)። ምን ማለት እንደሆነ ቢያብራሩልን?

✔️መልስ፦ ቀንድና ጥፍር ያበቀለ እንቦሳ የተባለው ለቤተ መቅደስ የሚሠዋውን መሥዋዕት ነው። ከዚህ መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል የተባለ ግን ከፍ ብሎ እንደተገለጠው ምስጋና መሆኑን ያመለክታል።

▶️፳፪. ''በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ" ሲል ምን ማለት ነው? ቢብራራልኝ (መዝ.67፥33)።

✔️መልስ፦ በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ ማለት ትሩፋንን ይዞ ከፋርስ ባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ለወጣ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ ማለት ነው። በሌላ አገላለጽ ነፍሳትን ከሲኦል ወደ ገነት ለመለሰ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ ማለት ነው።

▶️፳፫. መዝ.68፥6 ''የእስራኤል አምላክ ሆይ የሚሹኽ በእኔ አይነወሩ'' ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ማለት እግዚአብሔር ሆይ አንተን በሕግ በአምልኮ የሚሹህ ነቢያት ካህናት የእኔ መከራ አይድረስባቸው ይላል ዳዊት።

▶️፳፬. መዝ.70፥6 ''በማሕፀን ውስጥም አንተ ሸሸግኸኝ'' ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ በማሕፀን ውስጥ ሸሸግኸኝ ማለት በጽንስነቴ እንዳልሞት አንተ ጠበቅኸኝ ማለት ነው።

▶️፳፭. መዝ.70፥7 ''እንደ ጥንግ ኾንኹ" ሲል ጥንግ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ጥንግ የሚባለው እንደ ኳስ ክብ የሆነች በጣም ትንሽ ነገር ስትሆን በገና ጨዋታ ተጫዋቾች የሚጫወቱባት የሚለጓት ነገር ናት።

▶️፳፮. መዝ.62፥8 ላይ "ነፍሴ በዃላኽ ተከታተለች እኔንም ቀኝኽ ተቀበለችኝ" ይላል። ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች ማለት በአምልኮ አንተን ተከተለች ማለት ነው። ስለዚህም ቀኝህ ተቀበለችኝ ማለት ረድኤትህን ሰጠኸኝ ማለት ነው።

▶️፳፯. መዝ.64፥2 "ሥጋ ዅሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል" ይላል። ሥጋ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሥጋ ብሎ የጠቀሰው ሰውን ነው። ሰውን አንዳንድ ጊዜ ሥጋ አንዳንድ ጊዜ ነፍስ ብሎ ይጠራዋልና ነው። ስለዚህ ሰው ሁሉ፣ ሥጋዊ ደማዊ ፍጥረት ሁሉ ወደ አንተ ይመጣል ማለት ጸሎቱን ያቀርባል ማለት ነው።

▶️፳፰. መዝ.65፥18 "በልቤስ በደልን አይቼ ብኾን ጌታ አይሰማኝም ነበር" ይላል። ይህ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ዳዊት ይህንን የተናገረው ስለትሩፋን ነው። ከትሩፋንም ስለአስቴርና ስለመርዶክዮስ ነው። መርዶክዮስ በልቡናዬ ቂም በቀል፣ በቃሌ መበደል፣ በእጄ መግደል ቢኖር እግዚአብሔር ልመናዬን ባልሰማኝም ነበር ይላል።

▶️፳፱. "እስከ መቼ በሰው ላይ ትቆማላችሁ? እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድላላችሁ" ይላል (መዝ.61፥3)። እንዳዘነበለ ግድግዳ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድላላችሁ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ያዘነበለን ግድግዳና የፈረሰን አጥር ሌላ ሰው እንዳይጎዳ እንደምታፈርሱት ሁሉ መቃብያንን ለምን ትገድሏቸዋላችሁ ብሎ ዳዊት ይናገራል። ደግ ሆነው ሳለ መግደል አይገባችሁም ነበር ማለቱ ነው።

▶️፴. "ነገር ግን የሰው ልጆች ከንቱ ናቸው። የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው። በሚዛንም ይበድላሉ። እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው" ይላል (መዝ.61፥9)። በሚዛንም ይበድላሉ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ በሚዛን ይበድላሉ ማለት በሚዛን ያታልላሉ ማለት ነው። ይኸውም በታናሽ ሚዛን ሰጥተው በታላቅ ሚዛን ይቀበላሉ ወይም በታላቅ ተቀብለው በታናሽ ይሰጣሉ ማለት ነው። ምሥጢሩ ሕግን ያሳብላሉ ማለት ያፈርሳሉ ማለት ነው።

▶️፴፩. "የባሕሩን ጥልቀት የሞገድንም ጩኸት ታናውጣለህ" ይላል (መዝ.64፥7)። ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የባሕርን ጥልቀት የሞገድንም ጩኸት ታናውጣለህ ማለት በጥልቅ ባሕር ሞገድ ፈርዖንን አሰጠምክ ማለት ነው።

▶️፴፪. "ትልሟን ታረካለህ። ቦይዋንም ታስተካክላለህ። በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ። ቡቃያዋንም ትባርካለህ። በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ። ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ። ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ። ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ። በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም" ይላል (መዝ.65፥10-12)። የዚህ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከላይ ያለው ስለዚህች ዓለም የተነገረ ነው። እግዚአብሔር ትልሟን በዝናም አርክቶ፣ ወንዞቿን አስተካክሎ ምድር ቡቃያን እንደምታወጣ ያመለክታል። በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ ማለት በቸርነትህ ዘመን የተገኘውን ዓመት ትባርካለህ በዘመኑ የሚገኘውን እህሉንም ታበዛለህ ማለት ነው። ተራሮች ይረካሉ፣ ኮረብቶች በደስታ ይታጠቃሉ ማለት አብበው ለምልመው ያሸበርቃሉ ማለት ነው። ማሰማሪያዎች መንጎችን ለበሱ ማለት አውራ በጎች ሴት በጎችን ይንጠላጠሏቸዋል ማለት ነው። ሸለቆዎች በእህል ተሸፈኑ፣ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Feb, 22:50


ማለት በልምላሜ ተሸፍነው ደስ ያሰኛሉ ማለት ነው። በምሥጢር ስለክርስቶስና ስለትሩፋን የሚተረጎምበት መንገድም አለ። (የበለጠ አንድምታ ዳዊትን ይመልከቱ)።

▶️፴፫. "ሰማያዊ ንጉሥ በላይዋ ባዘዘ ጊዜ በሰልሞን ላይ በረዶ ዘነበ። የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው። የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው። የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ? እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው። በእውነት እግዚአብሔር ለዘላለም ያድርበታል" ይላል (መዝ.68፥14-17)። የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምን ይሆን?

✔️መልስ፦ ይህ ማለት እግዚአብሔር ሰልሞን በሚባል ሀገር ላይ በረዶን አዘነበ ማለት ነው። የእግዚአብሔር ተራራ፣ የጸና ተራራ፣ የለመለመ ተራራ የተባሉ ትሩፋን ናቸው። በሌላ አተረጓጎም ምእመናን ናቸው። እግዚአብሔር በትሩፋን እስራኤላውያን በረድኤት እንዳደረ ለምእመናን ደግሞ ልጅነትን ሰጠ ማለት ነው።

▶️፴፬. "ወጣቱ ብንያም በጕልበቱ በዚያ አለ። ገዦቻቸው የይሁዳ አለቆች የዛብሎን አለቆችና የንፍታሌምም አለቆች። አቤቱ ኃይልህን እዘዝ። አቤቱ ይህንም ለእኛ የሠራኸውን አጽናው" ይላል (መዝ.68:27-28)። ይህ መቼና ሰለምን የተዘመረ ነው?

✔️መልስ፦ ከብንያም ነገድ የሚወለዱትን ሁሉ ብንያም ብሎ መጥራት በመጽሐፍ ቅዱስ የተለመደ ነው። የይሁዳ አለቆች፣ የዛብሎን አለቆች፣ የንፍታሌም አለቆች ያላቸውም በዳዊት ዘመን የነበሩ ከእነርሱ ተወልደው ነገዱን በአለቅነት የሚመሩትን ሰዎች የሚያመለክት ነው። የተዘመረው በዳዊት ነው። ለምን ተዘመረ ለሚለው በእርሱ ዘመን ለነበሩ ለእነዚህ ነገድ ተወላጅ ሰዎች ነው።

▶️፴፭. "አቤቱ  ውኃ እስከ ነፍሴ ደርሶብኛልና አድነኝ። በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቋሚያም የለኝም። ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ። በጩኸት ደከምሁ ጕሮሮዬም ሰለለ። አምላኬን ስጠብቅ ዓይኖቼ ፈዘዙ" ይላል (መዝ.69፥1-3)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ስለመቃብያን የተነገረ ነው። ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ ከባድ መከራ ደረሰብኝ ለማለት የተገለጹ ናቸው። አምላኬን ስጠብቅ ዓይኖቼ ፈዘዙ ማለት ረድኤቱን ስጠባበቅ ቆየሁ ማለት ነው።

▶️፴፮. "በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጕር በዙ። በዓመፅ የሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ። በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ" ይላል (መዝ.69፥4)። በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ያልተበደርኩትን ተበድረሀል እያሉ አስከፈሉኝ ማለት ነው። ወይም ያልቀማሁትን ቀምተሀል ብለው አስከፈሉኝ ማለት ነው።

▶️፴፯. "ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና እፍረትም ፊቴን ሸፍናለችና። ለወንድሞቼ እንደ ሌላ ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው። የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና። ነፍሴን በጾም አስመረርኋት ለስድብም ሆነብኝ። ማቅ ለበስሁ ምሳሌም ሆንሁላቸው። በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ ወይን የሚጠጡ እኔን ይዘፍናሉ" ይላል (መዝ.69፥7-12)። ይህን ንባብ ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ይህ ስለመቃብያን የተነገረ ነው። መቃብያን ስለእግዚአብሔር ስም ስድብን እንደታገሡ፣ እፍረትን እንደተቀበሉ ያስረዳል። እንዲሁም በሦስቱ ከሓድያን ካህናት መከራ መቀበላቸውን ለመግለጽ ለወንድሞቼ እንግዳ ሆንኩባቸው ብለዋል። መቃብያን አንጥያኮስ በቤተ መቅደስ የጣዖት መሥዋዕት ሲሠዋ አይተው ለእግዚአብሔር ሕግ መቅናታቸውን ለመግለጽ የቤትህ ቅንዐት በላኝ አሉ። በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ ወይን የሚጠጡ እኔን ይዘፍናሉ ማለት የአንጥያኮስ ወገኖች ወይን እየጠጡ ሲጫወቱ በመቃብያን ይተርቱ ነበርና ነው።

▶️፴፰. "እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፤ ከሚጠሉኝና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ። የውኃው ማዕበል አያስጥመኝ። ጥልቁም አይዋጠኝ። ጕድጓድም አፉን በእኔ ላይ አይዝጋ" ይላል (መዝ.69፥14-15)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ስለ መቃብያን የተነገረ ነው። ረግረግ፣ ጉድጓድ፣ ጥልቅ የተባሉ አንጥያኮስና ሠራዊቱ ናቸው። እነዚህ ከሚያመጡት መከራ አድነን እያሉ መቃብያን ይጸልያሉ ማለት ነው።

▶️፴፱. "ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ። ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ። ማዕዳቸው በፊታቸው ለወጥመድ ለፍዳ ለዕንቅፋት ትሁንባቸው። ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ። ጀርባቸውም ዘወትር ይጕበጥ። መዓትህን በላያቸው አፍስስ። የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው። ማደሪያቸው በረሃ ትሁን በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ" ይላል (መዝ.69፥21-25)። ይህን ንባብ ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ይህ ስለክርስቶስ የተነገረ ነው። ክርስቶስ ሰውን ለማዳን በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ አይሁድ ሐሞት እንዳጠጡት ያመለክታል። ከዚያ ቀጥሎ ያለው እርግማን በክፉዎች አይሁድ ይድረስባቸው ማለት ነው። ይህም ብዙው በ70 ዓመተ ምሕረት በጥጦስ ደርሶባቸዋል።

▶️፵. "ነገር ግን ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ በጥሜም ሮጥሁ" ይላል (መዝ.61፥4)። በጥሜም ሮጥሁ ይልና ዕብራይስጡ ሐሰትን ይወድዳሉ ይላል የትርጉም ለውጥ አያመጣም?

✔️መልስ፦ በጥሜም ሮጥኩ ማለት በደል ሳልሠራ ወደ ጽርዕ ተማረክሁ ማለቱ ነው። ማየ ኃጢአትን አለመጠጣቱን በጽምእ መስሎ ተናገረ። ዕብራይስጡ ሐሰትንም ይወዳሉ ያለው በምሥጢር ክብሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ ካለው ጋር አንድ ስለሆነ የትርጉም ለውጥ አያመጣም።

▶️፵፩. "አቤቱ ፈትነኸናልና ብርንም እንደሚያነጥሩት አንጥረኸናልና። ወደ ወጥመድ አገባኸን። በጀርባችንም መከራን አኖርህ። በራሳችን ላይ ሰውን አስረገጥኸን። በእሳትና በውኃ መካከል አለፍን ወደ ዕረፍትም አወጣኸን" ይላል (መዝ.65፥10-12)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ዳዊት ስለእስራኤላውያን ከቀድሞ ጀምሮ የነበረውን እያወሳ ይናገራል። ስለዚህ ብርን እንደሚያነጥሩት አንጥረኸናል ማለት በመከራ ፈትነኸናል ማለት ነው። ወደ ወጥመድ አገባህን ማለት ወደ ግብፅ ወሰድከን ማለት ነው። በጀርባችን መከራን አኖርክ ማለት በዚያ መከራን እንድንቀበል አደረግከን ማለት ነው። በእሳትና በውሃ መካከል አለፍን ወደ እረፍትም አወጣህን ማለት ባሕረ ኤርትራን አሻግረህ ወደ ከነዓን አገባህን ማለት ነው።

▶️፵፪. "ከዕጣንና ከወጠጤዎች ጋራ ለሚቃጠል መሥዋዕት ፍሪዳን አቀርባለኹ። ላሞችንና ፍየሎችን እሠዋልኻለኹ" ይላል (መዝ.65፥15 )። ወጠጤ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ወጠጤ የሚባለው ከግልገልነት ከፍ ያለ ከአውራነት ያነሠ መካከለኛው ወንድ ፍየል ነው።

▶️፵፫. "እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም ፊቱንም በላያችን ያብራ" ይላል (መዝ.66፥1)። ፊቱንም በላያችን ያብራ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ፊቱን በላያችን ያብራ ማለት ረድኤቱን ይግለጽልን ረድኤቱን ይስጠን ማለት ነው።

▶️፵፬. "እግዚአብሔርን በጉባኤ ጌታችንንም በእስራኤል ምንጭ አመስግኑት" ይላል (መዝ.67፥26)። በእስራኤል ምንጭ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ የእስራኤል ምንጭ ያለው የኤርትራ ባሕርን ነው። ስለዚህ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ያሻገረ እግዚአብሔርን በጉባኤ አመስግኑት ማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው

✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Feb, 15:14


በቅዱሳት ገድላትና ድርሳናት ዙሪያ እንዲሁም በጥንተ አብሶ ዙሪያ

፩፦ እስካሁን በተመለከትኩት ገድላት አያስፈልጉም መወገድ አለባቸው የሚል ንግግርም ጽሑፍም ከኦርቶዶክሳውያን አልሰማሁም። ምክንያቱም ገድላትና ድርሳናት የወንጌል ትርጉሞች ናቸው። የቅዱሳን ሕይወት የሚታይ የሚዳሰስ የወንጌልን ቃል በተግባር የሚያሳይ ነውና።

፪፦ ነገር ግን በአንዳንድ ገድላትና ድርሳናት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ብዙ ስሕተቶች ሊገኝባቸው ይችላል። ይህ እንዳይፈጠር የሊቃውንት ጉባኤያችን ጠንክሮ ማዕከላዊ የቅዱሳት መጻሕፍት ኅትመት ቢኖረውና በዚያ ቢታተሙ መልካም ነው። ብሔርን ከብሔር የሚያጣሉ፣ ጥላቻን የሚያስተላልፉ ሐሳቦች በግል በሚታተሙት ገድላት ይስተዋላል።

፫፦ ለምሳሌ ቡና ይጠጣል ወይስ አይጠጣም የሚለው ክርክር ምንጩ ገድልና ድርሳን ነው። ለምሳሌ እኔ ከአምስት የገድላትና የድርሳናት መጻሕፍት ቡና እንደማይጠጣ የሚገልጽ አግኝቻለሁ። በተማርኩባቸው ጉባኤ ቤቶችና በየትኛውም የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት ቡና አይጠጣም የሚለው ሐሳብ ተቀባይነት የለውም። ታዲያ ጉባኤ ቤቶች ይህንን ሐሳብ ቀጥታ የመቀበል ግዴታ አለባቸውን?

፬፦ ባለፈው መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚእ አሰፋ (የጠቅላይ ቤተክህነት የትምህርትና ሥልጠና ክፍል ኃላፊ) ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በነበረው ሥልጠና እንደማሳያ ብለው ብዙ የተአምረ ማርያም ቅጅዎችን እንዳዩ ገልጸውልን ነበር። እና በአንዱ የብራና ተአምረ ማርያም ቅጂ አጼ ቴዎድሮስን እጅግ በጣም አክፋፍቶ የሚገልጽ እንዳገኙ ገልጸውልን ነበር። አስተውሉ በአንዱ ቅጂ ነው የተገኘ እንጂ በሁሉ አይደለም። ትክክልነቱ ምን ያህል ነው? የሚለው ጥናት ይጠይቃል።

፭፦ ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ ላይ ዮሐንስ አሥር ጊዜ ከተለያዩ እናቶችና አባቶች እንደተወለደ የሚገልጽ አግኝቻለሁ። ዮሐንስ መጀመሪያ የተወለደ ከአዳምና ከሔዋን ሲሆን ስሙም ያን ጊዜ "ሔና" ነበረ ይላል። ከዚያ በየዘመናቱ እየተወለደና መጨረሻ ላይ ከዘካርያስና ከኤልሳቤጥ ተወለደ ይላል። ይህ በአንድ ወቅት ደብረ ሊባኖስ ገዳም ግጭት ፈጥሮ ነበር። በወቅቱ በገዳሙ የነበሩት የንታ ብሩክ ይህ መስተካከል አለበት ሲሉ አንዳንድ ከመጻሕፍት ሩቅ የነበሩ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር ስለሌለ እንዳለ እንቀበላለን አሉ። ነገሩ ግን ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር መመርመር አለበት። ይህ በአንዳንድ የገድለ ዮሐንስ መጥምቅ ቅጂዎች አይገኝም።

፮፦ ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ላይ እስከ ዕለተ ምጽአት የጎጃም ሕዝብ ይቅር እንደማይባል ይገልጻል። በሌሎች ገድሎችና ድርሳኖች ለምሳሌ በገድለ አቡነ ሰላማ፣ በድርሳነ ኡራኤል፣ በገድለ ተከሥተ ብርሃን፣ በገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ ደግሞ እስከ ዕለተ ምጽአት ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ ብለው እግዚአብሔርን የሚያመልኩና እግዚአብሔርም የሚወዳቸው በሃይማኖታቸውና በምግባራቸው የተመሰከረላቸው የጎጃም ሰዎች ናቸው ይላል። እና የትኛውን እንቀበለው? መመርመር አለበት። ራእየ ማርያም ላይ ሻን*ቅላ ለዘለዓለም እንደማይጸድቅ የሚናገር አለ። በእውነት ይህን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት የተናገረችው? ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ጋር አይጋጭም?

፯፦ እንደዚህ እርስ በእርሱ የሚጋጩ ጉዳዮች ገድላት ላይና ድርሳናት ላይ ይስተዋላሉ። ይህ በተለያየ ምክንያት ነው። አንዳንድ መምህራን ሚሲዮናውያን ኢትዮጵያውያንን ለማለያየት ያስገቧቸው ናቸው ይላሉ። ይህ ሁሉ ቢሆንም ገድላትና ድርሳናት የሚታረሙት እየታረሙ በማዕከላዊነት በጠቅላይ ቤተክህነት ቢታተሙ እነዚህን ችግሮች መቅረፍ ይቻላል።

፰፦ በጥንተ አብሶ ዙሪያ ለምሳሌ ማኅበረ ቅዱሳን ባሳተመው ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በጻፉት መጽሐፍ የሰው ልጅ ከጥንተ አብሶ የሚላቀቅ ሲጠመቅ ነው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ጥንተ አብሶ በክርስቶስ መሰቀል ተወግዷል። ከዚህ በኋላ ሰው ቢኮነን እንኳ ራሱ በሠራው ኃጢአት እንጂ በጥንተ አብሶ አይደለም ይላሉ። (በጉባኤ ቤቶች ያለው አስተምህሮ ይህኛው ነው። በክርስቶስ መስቀል የውርስ ኃጢአት ጠፍቷል የሚል ነው። የእኔም አቋም ይህ ነው)። ጥንተ አብሶ የሚለው የግእዝ ቃል ሲሆን የበደል መጀመሪያ ማለት ነው። ይኸውም አዳምና ሔዋን የሠሩት በደል ነው። ይህ በደል ለአዳምና ለሔዋን ብቻ ይነገራል። የእነርሱ የበደል ውጤት (መርገም) ከእነርሱ ወደሚወለዱት ልጆች ተላልፏል። ይህን ውጤቱን የውርስ ኃጢአት እንለዋለን። ቅድስት ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት የለባትም። ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል እንዲል ከማኅፀን ጀምሮ ራሱ እግዚአብሔር ጠብቋታልና።

፱፦ በሚዲያ ዞር ዞር ስል ሕዝቤ ለሁለት ተቧድኖ ይቧቀሳል። በሁለቱም ወገን ያለው በእመቤታችን ንጽሕናና ቅድስና ይስማማል። ጠቡ በቃላት ያለመግባባት ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ሁሉም ጽንፍ ይዞ የአንዱ ደጋፊና የአንዱ ነቃፊ ሆኖ በየራሱ ትርጉም ክፉ ስም ይሰጣጣል እንጂ ቆም ብሎ አንዱ አንዱን ለማዳመጥ ጊዜ ቢሰጣጡ ተመሳሳይ አረዳድ ላይ ይደርሱ ነበር። አንዳንዱ ደግሞ ስለጉዳዩ የሚያውቀው ነገር የለም። ነገር ግን በደጋፊነትና በነቃፊነት ጎራ ይተራመሳል። የዚህ መፍትሔው ከፍ ያሉ ጉዳዮች ላይ ዝም ብሎ ማዳመጥ የተሻለ ነው።

፲፦ ወቅት እየጠበቁ የሚያከራክሩ ጉዳዮች አሁንም ብዙ አሉ። ለምሳሌ የልደት ጾም በዘመነ ዮሐንስ ህዳር 15 ይጀመራል ወይስ 14? ጥምቀት ሰኞ ሲውል ቅዳሜና እሑድ ይጾማል ወይስ እሑድ ብቻ የመሳሰሉ ጉዳዮች ይነሳሉ። (እነዚህን የጠቀስኳቸው ታዋቂ ስለሆኑ እንጂ ሌላም ቀኖናዊ ያልሆኑ ከፍ ያሉ ብዙ ጉዳዮች አሉ። ለጊዜው ከዚህ አልጠቅሳቸውም)። አሁን ዘመኑ የሚዲያ ስለሆነ ሁሉም የየራሱን አብነት እየያዘ ከሚወጋገዝ በማዕከላዊነት ሊቃውንት ተሰብስበው ወጥ የሆነ እይታ እንዲኖር ማድረግ ግድ ይላል። የሊቃውንት ጉባኤ ከዘመኑ መቅደም አለበት። EOTC Tv ከአሉባልታና ከጳጳሳት ውዳሴ ወጥቶ ዘመኑን የሚመጥንና ጥያቄዎችን ቀድሞ የመመለስ ሥራ ሊሠራ ይገባል።

ኦርቶዶክሳዊው መንገድ ጉዳይ ተኮር ነው። ክርስቶስ ኃጢአትን እንጂ ኃጢአተኛን አልጠላም ብሏል። ይህ ጉዳይን በጉዳይነቱ መሞገት እንደሚገባ ያስረዳናል። ሁሉም ሰው የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ከውስጥም ከውጭም ጠላቶች መጠበቅ አለበት። ሲጠብቅ ግን እውነትን መሠረት አድርጎ እንጂ በተሳሳተ ፍረጃ፣ ስምን በማጥፋት፣ በስድብ ሊሆን አይገባም።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 18:51


💓 መዝሙረ ዳዊት ክፍል 7 💓

💓መዝሙር ፷፩፡- እግዚአብሔር አምላካችን ረዳታችንም መድኃኒታችንም እንደሆነ
-ዳዊት ክብሬ በእግዚአብሔር ነው እንዳለ
-ይቅርታ የእግዚአብሔር እንደሆነ
-እግዚአብሔር ለሁሉ እንደ ሥራው እንደሚከፍለው

💓መዝሙር ፷፪፡- ንጉሥ በእግዚአብሔር ደስ እንደሚለው

💓መዝሙር ፷፫፡- ጻድቅ በእግዚአብሔር ደስ እንደሚለው ልባቸውም የቀና እንደሚከብሩ

💓መዝሙር ፷፬፡- የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ እንደሆነ

💓መዝሙር ፷፭፡- እግዚአብሔርን ማመስገን እንደሚገባ
-ለእግዚአብሔር ነውር የሌለበትን ንጹሕ መሥዋዕትን መሠዋት እንደሚገባ

💓መዝሙር ፷፮፡- እግዚአብሔር በቅን እንደሚፈርድ

💓መዝሙር ፷፯፡- የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው መባሉና እግዚአብሔር ያድርበት ዘንድ የወደደው ተራራ ይህ ነው መባሉ
-እግዚአብሔር አምላክ ቡሩክ እንደሆነና የማዳን አምላክ እንደሆነ
-ኢትዮጵያ እጆቿን እንደምትዘረጋ መነገሩ

💓መዝሙር ፷፰፡- ሰውነትን በጾም ማድከም እንደሚገባ
-የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው እንደሚሆን

💓መዝሙር ፷፱፡- ዳዊት እኔን ለማዳን ተመልከት ብሎ እንደጸለየ

💓መዝሙር ፸፡- እግዚአብሔርን የታመነ እንደማያፍር
-የእግዚአብሔርን ጽድቅና ማዳኑን መናገር እንደሚገባ

💓የዕለቱ ጥያቄ💓
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው
ሀ. እግዚአብሔር ለሁሉ እንደ ሥራው ይከፍለዋል
ለ. ይቅርታ የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው
ሐ. የጻድቃን ክብራቸው በእግዚአብሔር ነው
መ. ሁሉም

https://youtu.be/CkLLLI35xzw?si=LiCaoW2TYeso3NED

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 17:48


Tiktok
ልክፈተው እንጂ ተጠቅሜበት አላውቅም

፩ኛ፦ ቅድሚያ የጀመርነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መጨረስ ስለሚገባ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱን ከግማሽ በላይ አጥንተናል። ለ2300 አካባቢ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል። አሁንም ተሳታፊው ጨምሮ ትምህርቱ እንደቀጠለ ነው።

፪ኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ እስኪያልቅ ከዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ውጭ የሆኑ ጥያቄዎችን አልመልስም። ጊዜ ስለሚያጥረኝ ነው እንጂ የሁሉን ጥያቄ ብመልስ ደስ ይለኝ ነበር።

፫ኛ፦ ለሐሰተኛ ክሶች፣ ለስድቦች፣ ለስም ማጥፋቶች ብዙ ጊዜ መልስ መስጠት አይገባም። ቢያንስ ይህን የሚያደርጉ ሰዎች እውነታውን ልባቸው ያውቀዋል። በረከት ስለሚገኝበት በዝምታ ማለፍ ጥሩ ነው።

፬ኛ፦ ለምሁራን (በዘመናዊው በኩል ላሉ ምሁራንም፣ በአብነቱ በኩል ላሉ ምሁራንም) ታላቅ ክብር አለኝ። ብዙ ጊዜ ጉዳይ ተኮር ናቸው። የሚሞግቱ ጉዳዩን ነው። ለሰው ስሜት ያላቸው ጥንቃቄ ያስቀናኛል። ክብር ለአዋቂዎቻችን።

፭ኛ፦ እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር ስለሆነ ከእያንዳንዱ ጉዳይ ጀርባ ያለውን ስሜታችንን እንመርምር። እግዚአብሔር የሚወደው ሥራ ላይ እናተኩር።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 16:53


Dr. Samuel Seifu
Dr. Mule Dereje
Dr. Samuel Gebretsadik
እንኳን ደስ አላችሁ። እናንተን የመሳሰሉ ዶክተሮች ስላሉን እንደ ሀገር ደስተኞች ነን።

ሐመረ ኖህ ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ በአዲስ አበባ ተከፈተ

ሐመረ ኖህ ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክጨ ትናንት የካቲት 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ መገናኛ ማራቶን የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው ራሄም ህንፃ ላይ በይፋ ተመርቆ ስራውን መጀመሩን አሳወቀ።

በህክምና ሙያተኞች አማካኝነት የተመሠረተው ክሊኒኩ የሙያ ስነምግባር የተሞላ አገልግሎትን መርሁ አድርጎ፡በተጓዳኝ አቅም ለሌላቸውን ዜጎች በጎ ፈቃድ አገልጎሎት ለመስጠት የተቋቋመ መሆኑን በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።

ዶክተር ሳሙኤል ሰይፉ የሐመረ ኖህ ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ መስራች እና የአፍ ውስጥ ፣ የፊት እና የመንጋጋ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ፤እንደገለፁት ክሊኒኩ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን ያሟላ ሲሆን ለህብረተሰቡም ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን እና በቀጣይም በዘርፉ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የክሊኒኩ መስራች ከሆኑት መካከል አንዱ የሆኑት ዶክተር መለሰ ብዙአየሁ ደግሞ እንደገለፁት ክሊኒኩ በዘመናዊ መሳሪያዎች መደራጀቱንና በየወሩ በ16ኛው ቀን ነጻ የህክምና አገልግሎት እንደሚደረግ ገልጸዋል። በተጨማሪም የክሊኒኩ መከፈትን አስመልክቶ ከዛሬ የካቲት 10 እስከ የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ወደክሊኒኩ ለሚመጡ ታካሚዎች አስቀድሞ 0976 16 00 16 ላይ በመደወል የ50 በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግ ጨምረው ገልጸዋል።

በመክፈቻው መርሐግብሩ ላይ ፣ በዘርፉ ዕውቅ የሆኑ ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 15:07


▶️፳፱. "ቍጣቸው እንደ እባብ መርዝ ነው እንደ ምድር አውሬም ጆሮዋ የተደፈነ ነው" ይላል (መዝ.57፥4)። ጆሮው የተደፈነ የምድር አውሬ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ጆሮው የተደፈነ የምድር አውሬ የተባለ እባብ ነው። ይህም ለእባብ ተፈጥሯዊ ጆሮ የለውም ለማለት ሳይሆን እባብ ከሰይጣን ጋር ተባብሮ አዳምና ሔዋንን ስላሳተ ከስብሐተ እግዚአብሔር መከልከሉን ለመግለጽ ነው። የሰይጣንን ቃል መስማት ስብሐተ እግዚአብሔርን አለመስማት ነውና።

▶️፴. "ለንጉሥ ከቀን በላይ ቀን ትጨምራለህ ዓመታቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሆናሉ" ይላል (መዝ.60፥6)። ለንጉሥ ቀንን ትጨምራለህ ሲል ምን ማለት ነው? የሚጨመርስ ለንጉሥ ብቻ ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ስለዘሩባቤል የተነገረ ትንቢት ነው። የዘሩባቤልን የንግሥና ዘመን ታበዛለህ ማለቱ ነው። 49 ዓመት ገዝቷልና። ዳዊት ሲናገር የመጣው ስለትሩፋን ስለሆነ ከዚህ ላይ ዘሩባቤልን አነሣ እንጂ እርሱ እግዚአብሔር ባወቀ እድሜያቸውን የሚጨምርላቸው ከነገሥታት ውጭም ብዙ ሰዎች አሉ።

▶️፴፩. "ገለዓድ የእኔ ነው ምናሴም የእኔ ነው ኤፍሬም የራሴ መጠጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው።
ሞዓብ መታጠቢያዬ ነው። በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እዘረጋለሁ። ፍልስጥኤም ይገዙልኛል" ይላል (መዝ.59፥7-8)። ምሥጢሩን ቢያብራሩልን።

✔️መልስ፦ የገለዓድ ነገድ፣ የምናሴ ነገድ፣ የኤፍሬም ወገን፣ የይሁዳ ወገን ሁሉ ንጉሥ ስለሆንኩ ገንዘቤ ነው ይላል ዳዊት። ሞዓብ መታጠቢያዬ ነው ማለት አገልጋዬ ነው ማለት ነው። በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እዘረጋለሁ ማለት ኤዶምያስ የድካም ማረፊያዬ ናት ማለቱ ነው። ቀጥሎም ፍልስጥኤምም ይገዙልኝ ነበር ይላል ዳዊት።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 15:07


▶️፲፭. "ነፍሴን ከሞት እግሮቼን ከመውደቅ አድነሃልና በሕያዋን ብርሃን እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ" ይላል (መዝ.55፥13)። በሕያዋን ብርሃን እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ ሲል ምን ለማለት ይሆን?

✔️መልስ፦ ይህም ስለመቃብያን የተነገረ ነው። የመቃቢስ ልጆች ሰማዕትነትን ቢቀበሉም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ገብተው እንደ መላእክት እያመሰገኑት እንደሚኖሩ የሚያሳውቅ ነው። የሕያዋን ብርሃን የተባለች መንግሥተ ሰማያት ናት።

▶️፲፮. "ቍጣቸው እንደ እባብ መርዝ ነው። እንደ ምድር አውሬም ጆሮዋ የተደፈነ ነው። አዋቂ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ። እግዚአብሔር ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ይሰብራል። እግዚአብሔር የአንበሶቹን መንጋጋቸውን ያደቅቃል። እሳት ወደቀች። ፀሐይንም አላዩአትም። እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ። ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይነጥቃችኋል" ይላል (መዝ.57፥4-9)። የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የእባብ መርዝ እንደሚጎዳ የኃጥኣን ቁጣቸው ይጎዳል ማለት ነው። እባብ የሰይጣን ተባባሪ እንደሆነች ኃጥእ ሰውም የሰይጣን ተባባሪ እንደሆነ ያመለክታል። ጆሮዋ ተደፈነ ማለት ጆሮው የተደፈነ እንደማይሰማ ኃጥኣንም ስብሐተ እግዚአብሔርን አይሰሙም ማለት ነው። እግዚአብሔር የአናብስቶችን መንጋጋቸውን ይሰብራል ማለት የነገሥታትን ሥልጣን ያጠፋል ማለት ነው። እሳት ወደቀች ማለት መከራ ረኃብ መጣች ማለት ነው። ፀሐይንም አላዩአትም ማለት የራበው ሰው ስልት ይዞት ቀና ብሎ እንደማያይ ለመግለጽ የተነገረ አነጋገር ነው። እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ ማለት በደላችሁ በዛ ማለት ነው።

▶️፲፯. "እነሆ በአፋቸው አሰምተው ይናገራሉ። ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ ማን ይሰማል? ይላሉ" ይላል (መዝ.58፥6-7)። ምን ለማለት ነው? ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ በአፋቸው አሰምተው ይናገራሉ ማለት በአንደበታቸው የማይገባ ነገር ይናገራሉ ማለት ነው። ሰይፍ በከንፈሮቻቸው አለ ማለት የሚጎዳ ነገርን ይናገራሉ ማለት ነው።

▶️፲፰. "ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ በከተማም ይዙሩ። እነርሱም መብል ለመፈለግ ይበተኑ። ያልጠገቡ እንደ ሆነም ያንጎረጕራሉ" ይላል (መዝ.58፥14-15)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በከተማ ዞረው ዞረው የሚበሉት አጥተው ይደሩ ማለት ነው። እርግማን ነው። ሳይጠግቡ አድረው እንደሚያንጎራጉሩ የሚገልጽ ነው።

▶️፲፱. "አቤቱ ጣልኸን አፈረስኸንም። ተቈጣኸን ይቅርም አልኸን። ምድርን አናወጥሃት አወክሃትም። ተናውጣለችና ቍስሏን ፈውስ። ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው። አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን" ይላል (መዝ.59፥1-3)። አፈረስኸን፣ ምድርን አናወጥሃት አወክሃትም፣ አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን ሲል ምን ማለት ነው? ስለምን የተነገረ ቃል ነው?

✔️መልስ፦ አፈረስኸን፣ ምድርን አናወጥሃት አወክሃትም፣ አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን ማለት እስራኤላውያን ሀገራቸው ፈርሳ ተማርከው ወደ ባቢሎን መሄዳቸውን የሚያመለክት ነው። አስደንጋጩንም ወይን አጠጣህን ማለት ተማርከን መከራን እንድንቀበል አደረግከን ማለት ነው። ስለመቃብያንም ስለትሩፋንም የተነገረ ቃል ነው።

▶️፳. "ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል? ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?" ይላል (መዝ.59፥9)። ጽኑ ከተማ ያለው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ቀድሞ ጽኑ ከተሞችን እነኢያሪኮን አሳልፈህ ወደ ሀገራችን እንድንገባ አደረግከን። አሁን ግን በመከራ ላይ ነው ያለን ለማለት ትሩፍ የተናገረው የኀዘን ንግግር ነው።

▶️፳፩. በዳዊት ዘመን ቅኔ ነበረ ወይ?

✔️መልስ፦ ቅኔ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ የኢትዮጵያ ሀብት ብቻ እንደሆነ ታላቁ ሊቅ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ገልጸዋል። እንደቅኔ ሰምና ወርቅ ያለው አነጋገር በመጽሐፍ ቅዱስ ያለ ቢሆንም የቅኔን ዜማ ልክ ያልጠበቀ ስለሆነ ቅኔ ለመባል ይጎድለዋል። ስለዚህ በዳዊት ጊዜ ቅኔ መኖሩን የሚያሳይ ምንም ማስረጃ አላገኘሁም። በሀገራችንም ቅኔ ተጀመረ የሚባለው ዋሸራ በእነዘሱቱኤል እንደሆነና በኋላ ደግሞ ዮሐንስ ገብላዊና ተዋነይ እንዳስፋፉት ነው የሚነገር። ይህ ታሪክ እውነት ከሆነ ዘሱቱኤል በሐዲስ ኪዳን የነበረ ሊቅ እንደሆነ ስለሚነገር ቅኔ በዳዊት አልነበረም ወደሚል ድምዳሜ ያደርሰናል። የሆነ ሆኖ ግን ይህ ታሪክ ስለሆነ በየጊዜው በተገኙና በሚገኙ ማስረጃዎች (Evidences) ሊከለስ ይችላል።

▶️፳፪. መዝ.58፥5 ላይ "አሕዛብን ሁሉ ጎብኛቸው ይቅርም በላቸው። ዐመፅ የሚያደርጉትን ሁሉ ግን አትማራቸው" ይላል። ሁለቱ ዓረፍተ ነገር አይጋጭም ወይ? ሙሉ ቃሉ ቢብራራ?

✔️መልስ፦ አሕዛብን ጎብኛቸው ያለው እስራኤልን ጎብኛቸው ለማለት ነው። ሕዝብ ሲበዛ አሕዛብ ይሆናልና (የብዙ ብዙ)። ስለዚህ እስራኤላውያንን በረድኤት ጎብኛቸው ዐመፅን የሚያደርጉ ሌሎችን ግን ይቅር አትበላቸው ማለት ነው።

▶️፳፫. "ኃያል ሆይ በክፋት ለምን ትኮራለህ ሁልጊዜስ በመተላለፍ" ይላል (መዝ.51፥1)። ኃያል ሆይ ተብሎ የተጠራው ማን ነው?

✔️መልስ፦ ኃያል ሆይ ለምን ትኮራለህ የተባለ በሕዝቅያስ ላይ የተዘባበተ ሰናክሬም ነው።

▶️፳፬. "ጻድቃን አይተው ይፈራሉ በእርሱም ይሥቃሉ እንዲህም ይላሉ" ይላል (መዝ.51፥6)። ጻድቃን አይተው ይፈራሉ ካለ በኋላ እንደገና ደግሞ ይሥቃሉ ሲል አይጋጭም ወይ? የሚስቁትስ ከምን አንጻር ነው?

✔️መልስ፦ ጻድቃን አይተው ይፈራሉ የተባሉት ሕዝቅያስ የሚመራቸው ሁለቱ ነገድ የሰናክሬምን መጥፋት አይተው በፍርሀት ለእግዚአብሔር ይገዛሉ ማለት ነው። በእርሱም ይስቃሉ ማለት ከእጄ የሚያድናችሁ ማን ነው ብሎ በተናገረ ሰናክሬም ይዘባበታሉ ማለት ነው። ስለዚህ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የተነገሩ ስለሆኑ አይጋጩም። የሚስቁት በእግዚአብሔር ላይ በተገዳደረ በሰናክሬም ትዕቢት ነው።

▶️፳፭. "እንግዳዎች ቁመውብኛልና ኃያላንም ነፍሴን ሽተዋታልና። እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም" ይላል (መዝ.53፥3)። እንግዳዎች እና ኃያላን የተባሉት እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ ይህም ስለሕዝቀያስ የተነገረ ነው። እንግዳዎች እና ኃያላን የተባሉትን ሕዝቅያስንና ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት የመጡ ሰናክሬምና ሠራዊቱ ናቸው።

▶️፳፮. "በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ" ይላል (መዝ.54፥6)። የዚህን ምስጢር ቢያብራሩልን።

✔️መልስ፦ ርግብ ከአንድ አስቸጋሪ ቦታ ተነሥታ ወደ መልካም ቦታ እንደምትሄድ እኔም ከመከራው አርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍ የሚያሻግር ረድኤት ማን በሰጠኝ ይላል መቃቢስ። የናፍቆት አነጋገር።

▶️፳፯. "በሕይወት ሳሉም ወደ ሲኦል ይውረዱ" ይላል (መዝ.54፥15)። በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ ሲኦል ያለው መቃብርን ነው። በሕይወት ሳሉ እንደ ዳታንና እንደ አቤሮን ወደ መቃብር ይውረዱ ማለት ነው።

▶️፳፰. "ኃጥኣን ከማሕፀን ጀምረው ተለዩ ከሆድም ጀምረው ሳቱ ሐሰትንም ተናገሩ" ይላል (መዝ.57፥3)። ከማሕፀን ጀምረው ሐሰትን ተናገሩ ሲል ምን ማለት ነው? እንዴት ከማሕፀን መናገርና ስሕተት መሥራት ይችላሉ?

✔️መልስ፦ ማንኛውም ሕፃን በማሕፀን ሳለ ክፋትን ስለማያውቅ ሳተ አይባልም። ለነቢያት ግን የክፉ ሰዎች የኋላ ሥራቸው ተገልጾላቸው የኋላውን ለጽንስ አድርገው ይናገራሉ። ኋላ ክፉ የሚሠራበት ተሥዕሎተ መልክእ የሚፈጸም በማኅፀን ሳለ ነውና።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 15:07


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 138 💙💙

▶️፩. "ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል በኀጢአተኛው ደምም እጁን ይታጠባል" ይላል (መዝ.57፥10)። ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ጻድቅ ንጉሥ ጠላቶቹን ባጠፋ ጊዜ ደስ ይለዋል ማለት ነው። በፍትሕ ሥጋዊ ንጉሥ በትክክለኛ ምክንያት ጠላቶቹን ቢቀጣና ቢያጠፋ በደል አይሆንበትምና። ከዚህ መተርጉማን በተለየ የጠቀሱት ይሁዳ መቅብዩ የሚባልን ሰው ታሪክ ነው። ጠላቶቹን ሲገድል ውሎ በሰይፉ የገደላቸው የጠላቶቹ ደም በእጁ ተዘፍቆ እጁም ከሰይፉ ጋር ተጣብቆ ነበር። በኋላ በውሃ ታጥቦ እጁን ከሰይፉ አስለቅቆታልና ይህን ለመግለጽ ነው። ይህ ይሁዳ ለመቃብያን የተበቀለ ሰው ነው።

▶️፪. "ከፊትህ አትጣለኝ። ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ" ይላል (መዝ.51፥11)። ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ሲል ምን ተብሎ ይተረጎማል?

✔️መልስ፦ መንፈስ የሚለው በብዙ ይተረጎማል። ከዚህ ላይ ከብዙ ትርጉሙ በአንዱ ማለትም በረድኤቱ በጸጋው ይተረጎማል። ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ማለት ረድኤትህን ከእኔ አትለየው ማለት ነው።

▶️፫. መዝ.59፥4 ላይ "ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው" ይላል። ንባቡን ቢያስረዱን።

✔️መልስ፦ ይህ በብዙ ይተረጎማል። አንደኛው ለሚያመልኩህ ሰዎች ከመከራ ይድኑ ዘንድ ልዩ ረድኤትን፣ ተአምራትን ሰጠሀቸው ማለት ነው። ይህ ለመስቀልም ይተረጎማል። ጌታ ሆይ ለሚያመልኩህ ለምእመናን አጋንንትን የሚያሸንፉበትን መስቀልን ምልክት አድርገህ ሰጠሀቸው ማለት ነው።

▶️፬. "ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ። አቤቱ መልካም ነውና ስምህን አመሰግናለሁ" ይላል (መዝ.53፥6)። ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የምንወደውን ነገር ለእግዚአብሔር ብሎ መሠዋት የጽድቅ መንገድ እንደሆነ የሚገልጽ መንገድ ነው።

▶️፭. መዝ.50፥7 ላይ "በሂሶጵ እርጨኝ እነጻማለሁ። እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ" ይላል። ሂሶጵ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሂሶጵ በብሉይ ኪዳን የመንጻት ሥርዓት ወቅት ደም ወይም ውሃ ለመርጨት ያገለግል የነበረ ቀጫጭን ቅርንጫፎችና ቅጠሎች ያሉት ተክል ነው።

▶️፮. "እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ" ይላል (መዝ.54፥3-4)። ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ በእግዚአብሔር ታመንሁ አልፈራም ይላል (መዝ.26፥1)። እኔ ግን ፈራሁ ካለ በኋላ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል ይላልና አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ዳዊት መጀመሪያ ፈርቶ ነበር። በኋላ ግን በእግዚአብሔር ታምኖ ፍርሀትን አስወግዷል። ሥጋዊ ፍርሀቶች ሁሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ይርቃሉና።

▶️፯. "እነሆ እውነትን ወደድህ። የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ። በሂሶጵ እርጨኝ እነጻማለሁ። እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ" ይላል (መዝ.50፥6-7)። የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ ሲል ይህ ስውር ጥበብ ምንድን ነው? እርጨኝና አጠበኝ ሲልስ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የማይታይ ስውር ጥበብ የተባሉ የእግዚአብሔር ትእዛዛት ናቸው። ኅቡዕ ጥበብ መባሉ በገቢር ለአሕዛብ የተሰወረ ለምእመናን የተገለጠ ስለሆነ ነው።

▶️፰. "ልቤ ጨካኝ ነው። አቤቱ ልቤ ጨካኝ ነው። እቀኛለሁ እዘምራለሁ። ክብሬ ይነሣ። በገናና መሰንቆም ይነሡ። እኔም ማልጄ እነሣለሁ" ይላል (መዝ.56፥7-8)። ልቤ ጨካኝ ነው፣ ክብሬ ይነሣ፥ እኔም ማልጄ እነሣለሁ ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ልቤ ጨካኝ ነው ማለት ሕግህን ለመጠበቅ ትጉሕ ነው የታመነ ቆራጥ ነው ማለት ነው። ክብሬ ይነሣ ማለት ደግሞ ክብሬ ይመለስልኝ ማለት ነው። ማልጄ እነሣለሁ ማለት ዘወትር ለምስጋና እነሣለሁ ማለት ነው።

▶️፱. "ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው። አቤቱ ጋሻዬ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም" ይላል (መዝ.59፥11)። ቁጥር 13 ላይ ደግሞ "በቍጣ አጥፋቸው። እንዳይኖሩም አጥፋቸው" ይላል። አይጋጭም? ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው ሲልስ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው ማለት ምናልባት መመለስ ቢችሉ አታጥፋቸው ማለቱ ነው። ከላይ አጥፋቸው ማለቱ የማይመለሱ ከሆነ አጥፋቸው ማለቱ ነው። ስለዚህ የተነገረበት ዐውድ የተለያየ ስለሆነ አይጋጭም።

▶️፲. "አቤቱ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት። የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ" ይላል (መዝ.50፥18)። ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ጽዮንን አሰማምራት ማለት በጽዮን ሕዝቡን መናገር ነው። በባቢሎን የሚኖሩ ትሩፋንን ወደ ሀገራቸው ወደ ጽዮን መልሰህ አከናውናቸው ማለት ነው። የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ ያለው እነ ነህምያ የሚያደርጉትን እንዲያከናውንላቸው በትንቢት መናገሩ ነው። መተርጉማን ለምእመናንም ተርጉመውታል። እግዚአብሔር ሆይ ምእመናንን ከሲኦል መልሰህ ልጅነትን ሰጥተህ ወደ ገነት አግባቸው ማለት ነው።

▶️፲፩. "መድኃኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን በሰጠ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል" ይላል (መዝ.53፥6)። ስለምን የተነገረ ቃል ነው? ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ በዚሁ ኃይለ ቃል ተገልጿል። በባቢሎን ተማርከው ስለሚመለሱ እስራኤላውያን የተነገረ ነው። ቀጥሎም ከምርኮ ሲመለሱ ደስ እንደሚላቸው ነው የተገለጠው።

▶️፲፪. "ጠላትስ ቢሰድበኝ በታገሥሁ ነበር። የሚጠላኝም ራሱን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር" ይላል (መዝ.55፥12)። ይህ ግልጽ ስላልሆነልኝ ቢያስረዱኝ።

✔️መልስ፦ የሚወዱትን ሰው ይናገሩታል እንጂ ጠላት ምንም ቢናገር መታገሥ ወይም መሸሽ እንደሚገባ የሚያመለክት ነው። ዳዊት ሌላ ጠላት ቢነሣብኝ በታገሥኩት ነበር ነገር ግን ሳኦል ቢነሣብኝ ወገኔ ስለሆነ የምነቅፍበትን ጉዳይ ቀጥታ እነግረዋለሁ ማለቱ ነው። ይህም ያላሳደጉትን ውሻ ጆሮ መቆንጠጥ እንደማይቻል ሁሉ ያላስተማሩትንና ያልቀረቡትን ሰው መገሠጽ ተገቢ አለመሆኑን ያስረዳናል።

▶️፲፫. "አንተ ግን እኩያዬ ሰው ባልንጀራዬና የልቤ ወዳጅ መብልን ከእኔ ጋር በአንድነት ያጣፈጥህ በአንድ ልብ በእግዚአብሔር ቤት ተራመድን" ይላል (መዝ.54፥14)። ዳዊት ማንን ነው እንደዚህ ያለው? መብልን ከእኔ ጋር በአንድነት ያጣፈጥህ፣ በአንድ ልብ በእግዚአብሔር ቤት ተራመድን ሲልስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ዳዊት እንዲህ ያለው ሳኦልን ነው። ሳኦል በዳዊት ከመቅናቱ በፊት ወዳጅ እንደነበሩና ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት በአንድነት ያድርጉ እንደነበር ያመለክታል።

▶️፲፬. "ከእርሱ ጋር ሰላም በነበሩት ላይ እጁን ዘረጋ። ኪዳኑንም አረከሱ። አፉ ከቅቤ ይልቅ ለዘበ። በልቡ ግን ሰልፍ ነበረ። ቃሎቹም ከዘይት ይልቅ ለሰለሱ። እነርሱ ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው" ይላል (መዝ.55፥20-21)። እዚህ ላይ ኪዳኑንም አረከሱ ያላቸው እነማንን ነው? የትኛውን ኪዳን ነው? እነርሱ ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው ያላቸውስ ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ ዳዊት ስለመቃብያን የተናገረው ነው። አንጥያኮስ ለእግዚአብሔር እሰግዳለሁ ብሎ ቢገባም በኋላ ጣዖትን በማምለክ ቃል ኪዳኑን እንዳፈረሰ የሚገልጽ ነው። መጀመሪያውንም በአፉ ለእግዚአብሔር እሰግዳለሁ አለ እንጂ በልቡ አለማመኑን ያስረዳል። ቃሉን ቢያለሰልስም ሽንገላ ስለነበር ምላሶቹ እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው አለ። ያ እንዲጎዳ በሽንገላ መቃብያንን ማጥፋቱን ለመግለጽ የተነገረ ቃል ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 05:17


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 137 💙💙

▶️፩.መዝ.44፥9 "በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" ይላል። የንባቡ ትርጓሜ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደሆነ አባቶቻችን አስተምረውናል። ለቤተ ክርስቲያን እንጂ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አይተረጎምም የሚሉ መ*ና//ፍ*ቃንም አሉና እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ ይህ ቃል በብዙ ይተረጎማል። ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያምም፣ ለቅድስት ቤተክርስቲያንም ይተረጎማል። በመሠረቱ መና*/ፍ--ቃ*ን ለቤተክርስቲያን ይተረጎማል የሚለውንስ ከምን አገኙት? መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ባይ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ቀጥታ ቃል በቃል ለቤተክርስቲያን ይተረጎማል አይልም። ለቤተክርስቲያንም ለድንግል ማርያምም እንደሚተረጎም የሚነግረን ከቀድሞ ጀምሮ ሲወርድ ሲወራረድ የመጣው የእኛው አንድምታ መጽሐፍ ነው። ትርጉሙም በቀኝህ ትቆማለች ማለት በሰጠሀት ክብር ጸንታ ትኖራለች ማለት ነው።

▶️፪. መዝ.44፥9 ላይ "የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርኽ ናቸው። በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝኽ ትቆማለች" ይላል። የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርኽ ናቸው ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የንጉሦች ሴት ልጆች የተባሉ ምእመናን ናቸው። ምእመናን ለክብርህ ይገዛሉ ማለት ነው። በሌላ አተረጓጎም የእመቤታችን የመንፈስ ቅዱስ ልጆች ለጌትነትህ ይገዛሉ ማለት ነው።

▶️፫. መዝ.44፥14 "በዃላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ። ባልንጀራዎቿንም ወደ አንተ ያቀርባሉ።
በደስታና በሐሴት ይወስዷቸዋል። ወደ ንጉሥ ዕልፍኝም ያስገቧቸዋል" ይላል። ሙሉው ቢብራራልኝ?

✔️መልስ፦ ለንጉሡ ለእግዚአብሔር ደናግሉን ይወስዱለታል ማለት ነቢያት ሐዋርያት አስተምረው እግዚአብሔርን አያመልኩ የነበሩ አሕዛብን አሳምነው የእግዚአብሔር ልጆች ያደርጓቸዋል ማለት ነው። ወደ ንጉሥ እልፍኝ ያገቧቸዋል ማለት ወደ ቤተ መቅደስ ወደ መንግሥተ ሰማያት ያገቧቸዋል ማለት ነው።

▶️፬. መዝ.48፥12 "ሰው ግን ክቡር ኾኖ ሳለ አያውቅም እንደሚጠፉ እንስሳዎች መሰለ" ይላል። እንደሚጠፉ እንስሳዎች መሰለ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ለእንስሳት ትንሣኤ የላቸውም። ስለዚህ ኑሯቸው በዚህ ምድር ብቻ የተወሰነ ነው። ሰውም ዘለዓለማዊውን ሐሳብ ትቶ በዚህ ምድር ያለጾም ያለ ሥርዓት እንደ እንስሳ ከኖረ እንስሳ መሰለ ይባላልና በዚህ አግባብ የተነገረ ነው።

▶️፭. መዝ.49፥12 "ብራብም ለአንተ አልነግርኽም። ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና" ይላል። እግዚአብሔር ይራባልን?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በባሕርይው ረኃብ የሌለበት አምላክ ነው። ከዚህም ለመግለጽ የተፈለገው እግዚአብሔር አልራብም እንጂ የምራብ ብሆኖ ኖሮ እንኳ ዓለም በምሉ በጥቅሉ የእኔ ገንዘብ ነው ማለቱ ነው።

▶️፮. መዝ.45፥7 ላይ "የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋራ ነው። የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው" ይላል። ይህን ያለው ማነው?

✔️መልስ፦ ዳዊት ስለሕዝቅያስ የተናገረው እንደሆነ በአርእስቱ ተገልጿል።

▶️፯. ዋላ ወደ ውሃ ምንጭ እንደሚናፍቅ አቤቱ እንዲሁ ነፍሴ ወዳንተ ትናፍቃለች ይላል (መዝ.41፥1)። ዋላ የምትባለው ምን አይነት እንስሳ ናት ትንሽ ስለ እሷ ቢብራራልን።

✔️መልስ፦ ዋላ ያለው በሀገራችን ዋልያ የሚባለው የእንስሳት ዝርያ ነው።

▶️፰. "በፏፏቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ ዐለፈ" ይላል (መዝ.41፥7)። ምን ማለት እንደሆነ ቢብራራ።

✔️መልስ፦ የኤርትራ ባሕር የዮርዳኖስን ወንዝ ትጠራለች ማለት ነው። ይኸውም ወንዞች አፍ ኖሯቸው ይጠራራሉ ለማለት ሳይሆን እስራኤላውያን የኤርትራ ባሕር ተከፍሎላቸው እንደተሻገሩ የዮርዳኖስ ባሕርም ተከፍሎላቸው ተሻገሩ እያሉ ሰዎች ያወራሉ ይናገራሉ ለማለት ነው። ማዕበልህና ሞገድህ በላዬ አለፈ ማለት ባሕሩ ሲከፈል ግራና ቀኝ መቆሙን ያመለክታል።

▶️፱. "በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ በምድርም ሁሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ" ይላል (መዝ.44፥16)። ማንን ነው ልጆች እንደተወለዱላት የሚናገረው?

✔️መልስ፦ ለጊዜው ስለኢየሩሳሌም የተነገረ ነው። ፍጻሜው ለምእመን (ለቤተ ክርስቲያን) የተነገረ ነው። በሐዋርያት ፈንታ ሰብዓ አርድእት፣ በሰብዓ አርድእት ፈንታ ሊቃውንት ተተኩልሽ ማለት ነው።

▶️፲. "ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል" ይላል (መዝ.49፥2)። ከጽዮን ይመጣል ሲል ከማን ነው?

✔️መልስ፦ ጽዮን ያላት ኢየሩሳሌምን ነው። ጌታ በኢየሩሳሌም ተወልዶ ዓለምን እንደሚያድን ያመለክታል። ሁለተኛ ጽዮን ያላት ድንግል ማርያም ናት። ጸወነ ሥጋ ጸወነ ነፍስ ናትና። ከድንግል ማርያም ተወልዶ ዓለምን ያድናል ማለት ነው።

▶️፲፩. "እነሆ በዐመፃ ተፀነስሁ እናቴም በኀጢአት ወለደችኝ" ይላል (መዝ.50፥5)። ነቢዩ ዳዊት በዐመፃ የተፀነሰ ነበር?

✔️መልስ፦ አዎ። የዳዊት እናቱ ሁብሊ አባቱ እሴይ ይባላሉ። አንድ ጎልማሳ ጎረቤት አላቸው። ዓይኑ ሲፈቅዳት አይቶ መንገድ እሔዳለሁና ስንቄን አሰናጅልኝ አላት እሴይ። አሰናድታ ሰጥታው ይዞ ሄዶ ሌሊት ተመልሶ መጥቶ ጎረቤቱን መስሎ ሳይታወቅ ተገናኝቷት ሄዷል። በዚያ ጊዜ ዳዊት ስለተፀነሰ በዐመፃ ተፀነስኩ አለ።

▶️፲፪. መዝ.፵፱፥፳፫ "የከበረች መሥዋዕት ታከብረኛለች። እግዚአብሔር ማዳኑን ያሳየባት መንገድ በዚያ አለች" ይላል። ያሳየባት መንገድ የተባለች ማን ናት?

✔️መልስ፦ መንገድ ያላት ከላይ የገለጻትን በንጹሕ ሆኖ መሥዋዕትን ማቅረብን ነው። መሥዋዕት ማቅረብ እግዚአብሔር ማዳኑን የሚያሳይባት መንገድ ተብላለች።

▶️፲፫. መዝ.፵÷፩ "ዋልያ ወደ ውኃ ምንጭ እንደ ሚና*ፍ-ቅ እንዲሁ ነፍሴ ወደ እግዚአብሔር ትናፍ*ቃለች" ይላል። ንጽጽሩ ቢብራራ።

✔️መልስ፦ ዋልያ የውሃ ምንጭ ባለበት መኖርን ይወዳል። እንደዚሁ ሁሉ በባቢሎን የተማረከ ትሩፍ የእኔ ሰውነት ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት አድሮባት በሚኖር በኢየሩሳሌም መኖርን ወደደች ይላል። የናፍ*ቆት አነጋገር።

▶️፲፬. መዝ.፵፩÷፫ ዘወትር "አምላክህ ወዴት ነው?" ይሉኛልና። ይህን ዳዊት ስለእነማን ተናግሮታል?

✔️መልስ፦ መዝሙር 41ን ዳዊት ስለትሩፋን የተናገረው መዝሙር ነው። ትሩፋን በባቢሎን ተማርከው ሳሉ ባቢሎናውያን ፈጣሪ ካላችሁ እስኪ ከእኛ ያድናችሁ እያሉ ይዘባበቱባቸው ነበርና ነው።

▶️፲፭. "ይህን ሳስብ ነፍሴ ወደ ውስጥ ፈሰሰች" ይላል (መዝ.፵፩÷፬)። ምን ማለቱ ነው? ዝቅ ብሎ ከዚሁ ቁጥር ላይ በዓልን የሚያደርጉ ሰዎች በምስጋናና በደስታ ቃል ሲያመሰግኑ ተሰሙ ይላል። በዚህ አገባብ በዓል የተባለው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ነፍሴ ወደ ውስጥ ፈሰሰች ማለት ታወከችብኝ ማለት ነው። የውሃ መፍሰስ የውሃ ሁከት ውጤት ነውና መስሎ ተናግሮታል። ቀጥሎ ያለው እስራኤላውያን በዓላትን በደስታ ያከብሩ እንደነበረ የሚገልጽ ነው። በዓል የተባለው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሠራላቸው የምስጋና ዕለት ነው።

▶️፲፮. መዝ.፵፩÷፮ "በዮርዳኖስ ምድር በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስብሃለሁ" ሲል ጥምቀቱንና ደብረታቦርን ሲናገር ነው?

✔️መልስ፦ አዎ በምሥጢር ምድረ ዮርዳኖስ ያለው መጠመቅን ሲያመለክት አርሞንኤም ያለው በደብረ ታቦር የታየው የጌታ ብርሃን እስከ አርሞንኤም ደርሶ ነበርና ነው።

▶️፲፯. መዝ.፵፩ ÷፱ ላይ "ጠላቶቼ ሁሉ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ" ሲል ምን ለማለት ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 05:17


✔️መልስ፦ ውሆቻቸው የተባሉ ሰናክሬምና ሠራዊቶቹ እየደነፉ እስራኤልን ሊያጠፉ መጡ ማለት ነው። ተራሮች ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ከመገለጡ የተነሣ ነገሥታት ጠፉ ማለት ነው። የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ ማለት ከሰማይ የወረደ ቅዱስ ገብርኤል ድንግል ማርያምን በማብሠር ደስ ያሰኛታል ማለት ነው። አሕዛብ ተናወጡ ማለት በጌታ ከድንግል ማርያም መወለድ አጋንንት ደነገጡ ጠፉ ማለት ነው።

▶️፳፱. "እግዚአብሔር ትልቅ ነው። በአምላካችን ከተማ በተቀደሰ ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው። በሰሜን ወገን በመልካም ስፍራ የቆመ የምድር ሁሉ ደስታ የጽዮን ተራራ ነው። እርሱም የትልቁ ንጉሥ ከተማ ነው" ይላል (መዝ.47፥1-2)። የአምላካችን ከተማ የተባለች ማን ናት?

✔️መልስ፦ የአምላካችን ከተማ የተባለች ኢየሩሳሌም ናት። እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥበት ታላቁ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ነበረና።

▶️፴. "በኃይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለህ። እንደ ሰማን እንዲሁ አየን በሠራዊት ጌታ ከተማ። በአምላካችን ከተማ" ይላል (መዝ.47፥7-8)። ግልጽ አይደለም ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ በኃይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለህ ማለት በመዓትህ እነሰናክሬምን ታጠፋለህ ማለት ነው። ከዚያ በኋላ ያለውም አንድ ወገን ነው። እነሰናክሬምን አጥፍተሀቸው አየን ማለት ነው።

▶️፴፩. "አቤቱ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው። የአይሁድም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ። ጽዮንን ክበቧት። በዙሪያዋም ተመላለሱ። ግንቦቿንም ቍጠሩ። በብርታቷ ልባችሁን አኑሩ። አዳራሿን አስቡ። ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ" ይላል (መዝ.47፥11-13)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አቤቱ ስለፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው ማለት የእስራኤል ሰዎች ፈርደህ አሕዛብን ስላጠፋህላቸው ደስ ይላቸዋል ማለት ነው። ሕዝቅያስ ጽዮንን ክበቧት ማለቱ በምስጋና ክበቧት ማለቱ ነው። ሰናክሬም ስለሞተ በዙሪያዋም ተመላለሱ ማለቱ በአደባባይዋ በቤተ መቅደስ ጸልዩ ማለት ነው። ግንቦቿን ቁጠሩ ማለት ከእስራኤል ንብረት ሰናክሬም ያጠፋው ምንም ጥፋት የለም ማለት ነው። ስለዚህ በብርታቷ ልባችሁን አኑሩ ማለት በእግዚአብሔር ታመኑ ማለት ነው።

▶️፴፪. "አፌ ጥበብን ይናገራል። የልቤም አሳብ ማስተዋልን። ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ። በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ። ኃጢአት ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?" ይላል (መዝ.48፥3-5)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ የዳዊት አፍ ጥበብን እንደተናገረና ልቡም አስተዋይ እንደነበረ የሚገልጽ ነው። ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ ማለት ከወግ ከታሪክ ያገኘሁትን እናገራለሁ ማለቱ ነው። ነገሬን በበገና እገልጻለሁ ማለት በዝማሬ ሐሳቤን አስተላልፋለሁ ማለቱ ነው። ኃጢአት ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ? ማለት ንስሓ እያለ ለምን እጨነቃለሁ ማለቱ ነው። ንስሓ የገቡ ሰዎች ፍርሀት የለባቸውምና።

▶️፴፫. "ወንድም ወንድሙን አያድንም። ሰውም አያድንም። ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም" ይላል (መዝ.48፥7)። ስለምን የተነገረ ቃል ነው? ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም ሲልስ?

✔️መልስ፦ ይህ ስለኃጥእ ሰው የተነገረ ነው። በእግዚአብሔር ፍርድ ጊዜ ወንድም ወንድሙን አያድንም ማለት ነው። ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም ማለት የሰው ሀብቱ ሥልጣኑ ከእግዚአብሔር ፍርድ አያድነውም ማለት ነው።

▶️፴፬. "እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚሄዱ ናቸው። እረኛቸውም ሞት ነው። ቅኖችንም በማለዳ ይገዟቸዋል። ውበታቸውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች" ይላል (መዝ.48፥14)። ትርጓሜው ምን ይሆን?

✔️መልስ፦ ይህም ስለኃጥኣን የተነገረ ነው። እንደ በጎች ወደ ሲኦል ይሄዳሉ እረኛቸውም ሞት ነው ሲል ሲኦል ያለው ከዚህ መቃብርን ነው። በግ እንደሚሞት ይሞታሉ ማለት ነው። ቅኖችም በማለዳ ይገዟቸዋል ማለት እስኪሞቱም ድረስ ለማንም የማያዳሉ ደዌያት (በሽታዎች) ያሰቃዩዋቸዋል ማለት ነው። ውበታቸውም በሲኦል ታረጃለች ማለት ነፍሳቸውም በሳኦል ትሰቃያለች ማለት ነው።

▶️፴፭. "የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ። ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት። ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል" ይላል (መዝ.49፥1-2)። ምድርን ጠራት ሲልና ከጽዮን ይመጣል ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ምድርን ጠራት ማለት በወቅቱ የዘሩባትን እንዳታበቅል አደረጋት ማለት ነው። እግዚአብሔር ከጽዮን ይመጣል ማለት በኢየሩሳሌም ተወልዶ ዓለምን ያድናል ማለት ነው። በሌላ አገላለጽ ድንግል ማርያምን ጽዮን ስለሚላት ከድንግል ማርያም ተወልዶ ዓለምን ያድናል ማለት ነው።

▶️፴፮. "አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም። እሳት በፊቱ ይቃጠላል። በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ። በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል። ከእርሱ ጋር ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡለት። ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ" ይላል (መዝ.49)። በዚህ ንባብ ውስጥ እሳትና ዐውሎ የተባሉ ምንድን ናቸው? ዝም አይልም፣ ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙትን ቅዱሳኑን፤ ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ ሲልስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ እሳትና ዐውሎ የተባሉት እግዚአብሔር በመዓቱ የሚያመጣቸው መቅሠፍቶች ናቸው። እግዚአብሔር መጥቶ ዝም አይልም ማለት ከድንግል ማርያም ተወልዶ ያስተምራል ክፉዎችንም ይገሥጻል ማለት ነው። ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙት ቅዱሳኑን ማለት ደጋግ ካህናትን ማለት ነው። ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ ማለት ተዘርግተው በመታየት የእግዚአብሔርን ቸርነቱን ያሳውቃሉ ማለት ነው።

▶️፴፯. "ስለ ቍርባንህ የምዘልፍህ አይደለሁም። የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው። ከቤትህ ፍሪዳን ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም" ይላል (መዝ.49፥8-9)። የዚህ  ንባብ ዋና ሐሳቡ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በንጽሕና የሚቀርብ መሥዋዕትን እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይቀበላል ማለት ነው። ከመሥዋዕት ይልቅ ግን ለእግዚአብሔር መታዘዝና እግዚአብሔርን ማመስገን ይሻላል ማለት ነው። ይህንንም ቁጥር 14 ላይ ገልጾታል።

▶️፴፰. "ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው። ለእናትህም ልጅ ዕንቅፋት አኖርህ። ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ። እኔ እንደ አንተ እሆን ዘንድ ጠረጠርህ። እዘልፍሃለሁ በፊትህም እቆማለሁ" ይላል (መዝ.50፥20-21)። ለእናትህም ልጅ ዕንቅፋት አኖርህ ሲል ምን ማለት ነው? እዚህ ላይ ተናጋሪው ማነው?

✔️መልስ፦ ይህ ስለክፉ ሰው የተነገረ ቃል ነው። ክፉ ሰው ሰውን ያማል ማለት ነው። ለሌላው ሰው እንቅፋትን ያስቀምጣል ማለት አምቶ ለአሚታ ይሰጣል ማለት ነው። ተናጋሪው ዳዊት ነው።

▶️፴፱. "ነፍሳችን በመሬት ላይ ተጎሳቍላለችና። ሆዳችንም ወደ ምድር ተጣብቃለችና" ይላል (መዝ.43፥25)። ሆዳችንም ወደ ምድር ተጣብቃለች ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሆዳችን ወደ ምድር ተጣብቃለች ማለት እስራኤላውያን በምርኮ ሳሉ ረኃብ ጸንቶባቸው ምድር ምድር ያዩ ነበርና ነው። የራበው ሰው ቀና ብሎ ማየት ይከብደዋልና ይህን ለመግለጽ ነው።

▶️፵. "ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ። እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለኹ። አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው። ውበትኽ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል። ሞገስ በከንፈሮችኽ ፈሰሰ። ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባረከኽ" ይላል (መዝ.44፥1-2)። እንዲህ እያለ የተናገረው ማነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 05:17


✔️መልስ፦ ጠላቶቹ ሰውነቱን እየጠመዘዙ እየቆለመሙ በዚያውም ላይ ስድብን ይሰድቡት ነበርና ይህን ለመግለጽ ነው።

▶️፲፰. መዝ.፵፪÷፫ ላይ "ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ እነርሱ ይምሩኝ" ይላል። ብርሃንህንና ጽድቅህን ያላቸው እነማንን ነው?

✔️መልስ፦ ብርሃንህን ጽድቅህን ብሎ የገለጸው አንድ ወገን ረድኤተ እግዚአብሔርን ነው። በሌላ መልኩ ይህ መዝሙር ስለትሩፋን የተነገረ ስለሆነ ከባቢሎን የሚያወጡን ዮሴዕ ዘሩባቤልን ላክልን ማለት ነው። ሊቃውንት በትርጓሜ አብ ሆይ ብርሃንህን ወልድን ጽድቅህን መንፈስ ቅዱስን ላክልን ማለት ነው ብለውም ተርጉመውታል።

▶️፲፱. "እኔን ለማየት ቢገባ ከንቱን ይናገራል። ልቡ ኃጢአትን ሰበሰበለት። ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም" ይላል (መዝ.41፥6)። ይሄን ንባብ ግልጽ ቢያደርጉልኝ።

✔️መልስ፦ ዳዊት ይህን ስለሕዝቅያስ ተናግሮታል። ይህም የሕዝቅያስ መታመም ስላስደሰተው ሰው ይናገራል። ሕዝቅያስን ሊያይ ሲገባ ይድን ብላችሁ ነው እያለ ተስፋ ለማስቆረጥ ይጥራል። ይህ ሰው በፈጣሪ ሥራ ስለገባ ልቡ ኃጢአትን ሰበሰበ ተብሏል። ወደ ሜዳ ወጥቶም ሕዝቅያስ ይድን ብላችሁ ነውን ይልቅስ ሌላ አንግሡ እያለ ስለሚናገር ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም ተብሏል።

▶️፳. "እግዚአብሔር በቀን ቸርነቱን ያዝዛል። በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል። የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው" ይላል (መዝ.42፥8)። ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው ማለት ሕይወትን ለሰጠኝ ለእግዚአብሔር እሳላለሁ ማለት ነው።

▶️፳፩. "ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል። ለዘለዓለም ብርሃንን አያይም" ይላል (መዝ.48፥19)። ለዘለዓለም ብርሃንን አያይም ማለቱ ክርስቶስ ሙታንን ከሲኦል ማውጣቱን አይቃረንም?

✔️መልስ፦ ዘለዓለም በሁለት መልኩ ይተረጎማል። ብዙ ዘመንን ዘለዓለም ማለት የተለመደ ነው። ሰሎሞን ለዘለዓለም እንደሚነግሥ በመጽሐፈ ዜና መዋዕል ተነግሯል። ብዙ ዘመን (አርባ ዓመት) እንደሚነግሥ ለመግለጽ ነው። ሁለተኛው ፍጻሜ የሌለው ዘለዓለም አለ። ይህ ለክርስቶስ የባሕርይ ንጉሥነት ይነገራል። ስለዚህ በዚህ ጥያቄ የተጠቀሰው ፍጻሜ ያለው ዘለዓለም ስለሆነ አይቃረንም።

▶️፳፪. "አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ። ለያዕቆብ መድኃኒትህን እዘዝ። በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን። በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን" ይላል (መዝ.43፥4-6)። ያዕቆብ አስቀድሞ ሞቶ እያለ ዳዊት ለያዕቆብ መድኃኒትህን እዘዝ ሲል ምን ማለት ነው? በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን የሚለውን ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ በያዕቆብ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን መግለጹ ነው። እስራኤላውያን የያዕቆብ ልጆች ናቸውና በእርሱ ስም ያዕቆብ ብሏቸዋል። በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን ማለት በአንተ በእግዚአብሔር ረድኤት ጠላቶቻችንን እናጠፋለን ማለት ነው።

▶️፳፫. "ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል። እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል። አቤቱ ንቃ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ ለዘወትርም አትጣለን" ይላል (መዝ.43፥22-23)። ዳዊት ይህን የተናገረው በዘመኑ ስለነበረው ሁኔታ ነው ወይስ ትንቢት ነው? እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል። ንቃ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ ሲልስ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ መዝሙር ስለመቃብያን የተጻፈ ነው። መቃብያን በእግዚአብሔር ስላመኑ በአንጥያኮስ መገደላቸውን ያመለክታል። ይህ እስከ ምጽአት የሚነሡ ምእመናንንም የሚመለከት ነው። ምእመናን በእግዚአብሔር ስም ስላመንን፣ በእግዚአብሔር ስም ስላስተማርን፣ በእግዚአብሔር ስም ውሉደ እግዚአብሔር ተብለን ስለተጠራን አሕዛብ አጋንንንት መከራ እንደሚያመጡብን ያመለክታል። ንቃ ለምንስ ትተኛለህ የሚለው እግዚአብሔር የሚተኛ ሆኖ አይደለም። ረድኤት አለመስጠቱን በመተኛት መስሎ ነቢዩ ተናገረ እንጂ። ተነሥ ማለቱም ኃጢአታችንን ይቅር ብለህ ረድኤትን ስጠን ማለቱ ነው።

▶️፳፬. "ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ። እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ። አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው። ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል። ሞገስ በከንፈሮችህ ፈሰሰ። ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባረከህ። ኃያል ሆይ በቍንጅናህና በውበትህ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ" ይላል (መዝ.44፥1-3)። ስለ ማን የተዘመረ ነው? ንባቡ ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ይህ መዝሙር ስለክርስቶስ የተነገረ ነው። ውበትህ ከሰው ልጆች ሁሉ ያምራል መባሉ ውብ ስለነበረ ነው። ይህም ይታወቅ ዘንድ ጌታን ከሚከተለው ከአምስት ገበያ ያህል ሕዝብ አንዱ ገበያ የሚሆነው መልኩን ለማየት የሚመጣ ነበር። ምገስ ከከንፈሮችህ ፈሰሰ ማለት ሥርየተ ኃጢአት በአንደበትህ በዝቶ ተነገረ ማለት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባረከህ ማለት በተዋሕዶ አከበረህ ማለት ነው።

▶️፳፭. "አምላክ ሆይ ዙፋንህ ለዘላለም ነው። የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው" ይላል (መዝ.44፥6)። የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው ማለት ጌትነትህ ባሕርያዊ ነው። የጌትነትህም ሥልጣን ቀዳማዊ ነው ማለት ነው።

▶️፳፮. "የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው። በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች። ልጄ ሆይ ስሚ እዪ። ጆሮሽንም አዘንብዪ። ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ" ይላል (መዝ.45፥9-10)። ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ያለውን ግልጽ ቢያደርጉልኝ። በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ሲልስ ምንን ለመግለጽ ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሲነገር በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ማለት ንጽሐ ሥጋን፣ ንጽሐ ነፍስን፣ ንጽሐ ልቡናን ገንዘብ አድርጋ ማለት ነው። ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ማለት እንደ አባቶችሽ በዘር በሩካቤ አትወልጂም በድንግልና ትወልጃለሽ እንጂ ማለት ነው።

▶️፳፯. "የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል። የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትህ ይማለላሉ። ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው ልብሷ የወርቅ መጎናጸፊያ ነው። በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ። ባልንጀሮቿንም ወደ አንተ ያቀርባሉ። በደስታና በሐሴት ይወስዷቸዋል። ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቧቸዋል። በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ። በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ። ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ" ይላል (መዝ.45፥12-17)። የጢሮስ ሴቶች ልጆች ያላቸው እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ የጢሮስ ሴቶች ልጆች የተባሉት ምእመናን ናቸው። ምእመናን ምግባርንና ሃይማኖትን አስተባብረው ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ ማለት ነው።

▶️፳፰. "ውኆቻቸው ጮኹ ተናወጡም። ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ። የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ። ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ። እግዚአብሔር በመካከሏ ነው አትናወጥም። እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል። አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተመለሱ። እርሱ ቃሉን ሰጠ። ምድርም ተንቀጠቀጠች" ይላል (መዝ.46፥3-6)። የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 05:17


✔️መልስ፦ ይህን የተናገረው ዳዊት ሲሆን የተናገረው ትንቢት በእንተ ክርስቶስ ነው።

▶️፵፩. "በልብሶችኽ ዅሉ ከርቤና ሽቱ ዝባድም አሉ። ከዝኆን ጥርሶች አዳራሽ ደስ ያሠኙኻል" ይላል (መዝ.44፥8)። ይህ የተነገረው ለማን ነው? ከርቤና ሽቱ፣ ዝባድ፣ የዝኆን ጥርሶች አዳራሽ ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ ይህ የተነገረ ስለክርስቶስ ነው። ከርቤ፣ ሽቱ፣ ዝባድ፣ የዝሆን ጥርስ የተባሉና በእነዚህ የተመሰሉ ምእመናን ናቸው። ምእመናን ምግባር ትሩፋት ሠርተው ክርስቶስን ደስ ያሰኙታል ማለት ነው።

▶️፵፪. "ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል። የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ" ይላል (መዝ.49፥23)። እንዲህ ብሎ የተናገረው ማን ለማን ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ለካህናትና ለምእመናን የተነገረ ነው። የተናገረው ተናጋሪው ደግሞ ዳዊት ነው።

▶️፵፫. "ብልኀተኛዎች እንዲሞቱ ሰነፎችና ደን*ቈ//ሮዎች በአንድነት እንዲጠፉ ገንዘባቸውንም ለሌላዎች እንዲተዉ አይቷል" ይላል (መዝ.48፥10)። ብልኀተኛዎች እንዲሞቱ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ብልኀተኞች የተባሉ ጻድቃንም በሞተ ሥጋ ይሞታሉ ማለት ነው። እነርሱ እንደሚሞቱ ሁሉ ኃጥኣንም ይሞታሉ የኃጥኣን ሞት ግን የከፋ ሞት ነው ለማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Feb, 03:30


💞 መዝሙረ ዳዊት ክፍል 6 💞

💞መዝሙር ፶፩፡- ሰው በክፋቱ መኩራትና ሁል ጊዜ መበደል እንደማይገባው

💞መዝሙር ፶፪፡- ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም እንደሚል

💞መዝሙር ፶፫፡- መልካም ነውና እግዚአብሔርን ማመስገን እንደሚገባ

💞መዝሙር ፶፬፡- እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠርም እንደነበረ

💞መዝሙር ፶፭፡- ዳዊት በእግዚአብሔር ቃሌን አከብራለሁ የተናገርኩትም በእግዚአብሔር ዘንድ ይከብራል እንዳለ

💞መዝሙር ፶፮፡- ወደሚረዳን ወደ እግዚአብሔር መጮህ እንደሚገባ

💞መዝሙር ፶፯፡- ኃጥኣን ከማኅፀን ጀምረው እንደተለዩ

💞መዝሙር ፶፰፡- ዳዊት በምሕረትህም በማለዳ ደስ ይለኛል እንዳለ

💞መዝሙር ፶፱፡- እግዚአብሔር ለሚፈሩት ምልክትን እንደሰጣቸው

💞መዝሙር ፷፡- እግዚአብሔር ለሚፈሩት ርስትን እንደሰጣቸው

💞የዕለቱ ጥያቄ💞
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በሰው መታመን ከንቱ ነው
ለ. እግዚአብሔር ለሚፈሩት ርስትን ይሰጣቸዋል
ሐ. ሀ እና ለ
መ. ሁሉም

https://youtu.be/Hugp0WZ1RXs?si=fQ56ERHDOpCsd3qO

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Feb, 22:04


✝️ መዝሙረ ዳዊት ክፍል 5 ✝️

✝️መዝሙር ፵፩፡- እግዚአብሔር ይቅር ባይ እንደሆነ

✝️መዝሙር ፵፪፡- ዳዊት ከዐመፀኛና ከሸንጋይ ሰው አድነኝ እንዳለ

✝️መዝሙር ፵፫፡- ሁል ጊዜ በእግዚአብሔር እንደምንከብር

✝️መዝሙር ፵፬፡- የአምላክ ዙፋን ለዘለዓለም እንደሆነና በትረ መንግሥቱም በትረ ጽድቅ እንደሆነ

✝️መዝሙር ፵፭፡- አምላካችን መጠጊያችን ኃይላችን ረዳታችን እንደሆነ

✝️መዝሙር ፵፮፡- ለእግዚአብሔር በደስታ ቃል እልል ማለትና በእጅ ማጨብጨበ እንደሚገባ
-እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ እንደሆነ

✝️መዝሙር ፵፯፡- እግዚአብሔር ታላቅ እንደሆነ

✝️መዝሙር ፵፰፡- ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ እንዳላወቀና እንስሳትን እንደመሰለ

✝️መዝሙር ፵፱፡- እግዚአብሔር በግልጥ እንደሚመጣና ዝም እንደማይል
-ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕትን መሠዋት እንደሚገባ

✝️መዝሙር ፶፡- ዳዊት ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ እንዳለ
-የእግዚአብሔር መሥዋዕት የዋህ መንፈስ እንደሆነ

✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️
፩. ስለ ልዑል እግዚአብሔር ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ጽድቅን ይወዳል
ለ. ዐመፃን ይጠላል
ሐ. ዙፋኑ ዘለዓለማዊ አይደለም
መ. በትረ መንግሥቱ በትረ ጽድቅ ነው
፪. ንጉሥ ዳዊት ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም እንስሳትን መሰለ ሲል እንስሳትን መምሰል ምን ማለት ነው?
ሀ. በአራት እግር መሄድ
ለ. ቀንድ ማብቀል
ሐ. በግብረ እንስሳ መኖር
መ. ሀ እና ለ

https://youtu.be/HZS60WLSMXc?si=rZEo5vCEfTJBO5ne

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Feb, 20:35


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 136 💙💙

▶️፩. መዝ.34፥10 ላይ "አጥንቶች ሁሉ እንዲህ ይሉሃል" ሲል ትርጉሙን ቢያስረዱን።

✔️መልስ፦ አጥንቶቼ ያላቸው ከዚህ ወገኖቼ ለማለት ነው።

▶️፪. መዝ.36፥29 "ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ። በእርሷም ለዘለዓለም ይኖራሉ" ይላል።
ምድርን የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ጻድቃን ለዘለዓለም ወርሰዋት የሚኖሩ መንግሥተ ሰማያትን ነው። ከዚህም ምድር ብሎ የጠቀሳት መንግሥተ ሰማያትን ነው። ምድር አልፋ በምድር የምትተካ ስለሆነች መንግሥተ ሰማያትን ምድር ብሏታል።

▶️፫. "ጥሩርና ጋሻ ያዝ። እኔንም ለመርዳት ተነሥ። ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ። ነፍሴን መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት" ይላል (መዝ.34፥2-3)። እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ጥሩር፣ ጋሻና ሰይፍ የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ጥሩር፣ ጋሻ የተባሉት ለእግዚአብሔር ሲነገሩ ሥልጣን ተብለው ይተረጎማሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ በባሕርይ ሥልጣንህ እርዳኝ ማለት ነው።

▶️፬. መዝ.40፥9 "እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሳ" ይላል። ንባቡን ቢያስረዱን።

✔️መልስ፦ ይህ ውለታ ቢስነትን ለመግለጽ የተነገረ ቃል ነው። አንዳንዱን እንጀራ አብልተኸውና ተንከባክበኸው እርሱ ግን በሌላ ጊዜ ረግጦህ ሊሄድ ይችላልና ይህን ለመግለጽ ነው። በምሥጢር ለይሁዳ ተነግሯል። ጌታ አክብሮ ሐዋርያ አድርጎ ቢሾመውም ሐዋርያ አድርጎ የሾመውን ጌታ ክዶ በመሳም አሳልፎ ሸጦታልና።

▶️፭. "በጠላቶቼ ዘንድ ተነወርኹ ይልቁንም በጎረቤቶቼ ዘንድ ለሚያውቁኝም ፍርሀት ሆንሁ" ይላል (መዝ.30፥11)። ለሚያውቁኝም ፍርሀት ሆንሁ ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የፍርሀት አብነት ሆንኩ ማለቱ ነው።

▶️፮. "በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ እግዚአብሔር ይመስገን" ይላል (መዝ.30፥21)። የተከበበ ከተማ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የተከበበ ከተማ ያለው ብዙ የሆነ መከራውን ነው። ከተማ ሲከበብ በውስጧ የሚኖሩ ሰዎች እንደሚጨነቁ መከራም ሰውነትን ያስጨንቃልና በዚህ አግባብ የተነገረ ነው።

▶️፯. "አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ። ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ" ይላል (መዝ.31፥7)። እዚህ ላይ ተናጋሪው ማን ነው?

✔️መልስ፦ ከላይ ዳዊት ስለ እግዚአብሔር ሲናገር መጥቶ ነበር። ቀጥሎ ያለውን ይህንን የተናገረው ደግሞ ራሱ እግዚአብሔር ነው።

▶️፰. "የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። ጽድቅንና ፍርድን ይወድዳል፤ የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች" ይላል (መዝ.32፥4-5)። በዚህ ንባብ ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል፣ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና የሚሉትን ግልጽ ቢያደርጉልኝ።

✔️መልስ፦ ከዚህ የእግዚአብሔር ቃል የተባለ አካላዊ ቃል ወልደ እግዚአብሔር ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት የሚለው ግብረ ባሕርይ ስለሆነ ቀጥታ ቸርነት ተብሎ ይተረጎማል። በቸርነቱ ምድርን መፍጠሩን ይገልጻል። ሥራው ሁሉ በእምነት ነውና ማለት ሥራው ሁሉ ሃይማኖት ነው በአዎንታ ይደረጋል ማለት ነው።

▶️፱. "የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘላለም ይኖራል። የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው" ይላል (መዝ.32፥11)። የእግዚአብሔር ምክርና የልቡም አሳብ የሚሉት ምን ተብለው ይተረጎማሉ?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ምክር የተባለው ቀጥታ ይተረጎማል። ዘለዓለማዊ ምክሩን ያመለክታል። የልቡ ሐሳብ የተባለውም በግብረ ባሕርይ እግዚአብሔር የሚያስበው ሐሳብ ማለት ነው። ይህ ሐሳብም ዘለዓለማዊ ነው እንጂ በየዘመኑ የሚቀንስና የሚጨምር አይደለም።

▶️፲. "እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል። ከእነርሱም አንድ አይሰበርም" ይላል (መዝ.34፥20)። ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ከዚህም አጥንቶቻቸው የተባሉ ወገኖቻቸው ለማለት ነው። የጻድቃን ወገኖች ጉዳት እንደማይደርስባቸው የሚያመለክት ቃል ነው።

▶️፲፩. "ስለ በጎ ክፋትን መለሱልኝ። ነፍሴንም ልጆችን አሳጧት። እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ። ነፍሴንም በጾም አደከምኋት። ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ። ለወዳጄና ለወንድሜ እንደማደርግ አደረግሁ። ለእናቱም እንደሚያለቅስ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግሁ። በእኔ ላይ ተሰበሰቡ ደስም አላቸው። ግፈኞች በእኔ ላይ ተሰበሰቡ እኔም አላውቅሁም። ቀደዱኝ አልተውኝምም። ፈተኑኝ በሣቅም ዘበቱብኝ። ጥርሳቸውንም በእኔ ላይ አንቀጫቅጩ" ይላል (መዝ.34፥12-16)። ዳዊት ይሄን መችና ሰለእነማን የተናገረው ነው? ነፍሴንም ልጆችን አሳጧት፤ እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥ ቀደዱኝ አልተውኝምም ሲልስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ መቼ እንደተናገረው ዝርዝር ጉዳይ አላገኘሁም። ዳዊት ይህን መዝሙር የዘመረው ግን ስለኤርምያስና ስለጌታ ክርስቶስ እንደሆነ መተርጉማን ገልጸዋል። ነፍሴንም ልጆችን አሳጧት ማለቱ ኤርምያስ ሲማረክ የቀለም ልጆቹ ባሮክና አቤሜሌክ ተለይተውት ቀርተዋልና ይህን ለመግለጽ ነው። እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኩ ያለውም ኤርምያስ ነው። ኢየሩሳሌም ትማረካለች እያለ ሲናገር የቀለም ልጆቹ ይህ ነገር እንዳያገኘን ጸልይልን ይሉት ስለነበር ማቅ ለብሶ እንደጸለየላቸው ለመግለጽ ነው። ቀደዱኝ አልተውኝምም ማለቱ እስራኤላውያን የሐሰተኛ ነቢያትን ቃል እየሰሙ ኤርምያስን ይገርፉት ነበርና ገረፉኝ መከራ አደረሱብኝ ማለቱ ነው።

▶️፲፪. "አቤቱ ምሕረትህ በሰማይ ነው። እውነትህም ወደ ደመናት ትደርሳለች" ይላል (መዝ.35፥5)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ምሕረትህ በሰማይ ነው ማለት ምሕረትህ ሰማይን በመፍጠር ታወቀ ማለት ነው። እውነትህም ወደ ደመናት ትደርሳለች ማለት ደግሞ ቸርነትህ ደመናትን በመፍጠር ታወቀ ማለት ነው።

▶️፲፫. "ከቤትህ ጠል ይጠጣሉ። ከተድላም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ። የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና። በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን" ይላል (መዝ.35፥8-9)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከቤትህ ጠል ይጠጣሉ ማለት ከቤተ መቅደስ የተገኘውን አሥራት በኵራት ቀዳምያት አግኝተው ደስ ይላቸዋል ማለት ነው። ከተድላም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ ማለት ደስ ታሰኛቸዋለህ ማለት ነው። የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነው ማለት ሕይወት ከእግዚአብሔር የሚገኝ መሆኑን መግለጽ ነው።

▶️፲፬. "ኃጢአተኛ ጻድቁን ይመለካከተዋል ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል። እግዚአብሔር ይሥቅበታል። ቀኑ እንደሚደርስ አይቷልና። ኃጢአተኞች ሰይፋቸውን መዘዙ። ቀስታቸውንም ገተሩ። ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ" ይላል (መዝ.36፥12-14)። እግዚአብሔር ይስቅበታል ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በኃጥኣን የሚስቅ የሚሳለቅ ሆኖ አይደለም። በበደላቸው ምክንያት ረድኤቱን ይከለክላቸዋል። ቸል ይላቸዋል ማለት ነው።

▶️፲፭. "ኃጥእን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። ብመለስ ግን አጣሁት። ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም" ይላል (መዝ.37፥35-37)። ምን ተብሎ ይተረጎማል?

✔️መልስ፦ ዳዊት "ኃጢአተኛ ሳኦልን ገንኖ ከብሮ አየሁት። ጥቂት ቆይቼ ብመለስ አጣሁት" ማለቱ ነው። ይኸውም ሳኦል በበደሉ ምክንያት ብዙ ሳይነግሥ መሞቱን ያመለክታል። ቀጥታም መተርጎም ይችላል። ይኸውም ማንኛውም ኃጢአተኛ መጀመሪያ በሀብት፣ በዕውቅና፣ በሥልጣን ከፍ ብሎ ሊታይ ይችላል። በኋላ ግን ይዋረዳል ለማለት ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Feb, 20:35


▶️፲፮. "ከስንፍናዬ የተነሣ ቍስሌ ሸተተ በሰበሰም። እጅግ ጎሰቈልሁ ተዋረድሁም ሁልጊዜም በትካዜ እመላለሳለሁ። ነፍሴ ስድብን ተሞልታለችና ለሥጋዬም ጤና የላትምና። ታመምሁ እጅግም ተቸገርሁ ከልቤ ውዝዋዜም የተነሣ ጮኽሁ። አቤቱ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው ጭንቀቴም ከአንተ አይሰወርም። ልቤ ደነገጠብኝ ኃይሌም ተወችኝ የዓይኖቼም ብርሃን ፈዘዘ። ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ከቍስሌ ገለል ብለው ቆሙ ዘመዶቼም ርቀው ቆሙ" ይላል (መዝ.37፥5-11)። ዳዊት ይሄን የተናገረው ስለራሱ ነው? ከስንፍናዬ የተነሣ ቍስሌ ሸተተ በሰበሰም፤ ከልቤ ውዝዋዜም የተነሣ ጮኽሁ፣ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው ሲልስ ምን ለማለት ይሆን?

✔️መልስ፦ አዎ ዳዊት ይህንን የተናገረው ስለራሡ ነው። ከስንፍናዬ የተነሣ ቁስሌ ሸተተ በሰበሰም የሚለው ሰንፌ በሠራሁት ኃጢአቴ ምክንያት ሰውነቴ ሸተተ ማለቱ ነው። ልቡናዬ ተወዛወዘ ማለት ልቤ ተሸበረ ማለት ነው። ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው ማለት ፈቃደ ልቤን ኃጢአቴን አንተ ታውቃለህ ማለት ነው።

▶️፲፯. "ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ። ከማሰቤም የተነሣ እሳት ነደደ" ይላል (መዝ.38፥3)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ልቤ ሞቀብኝ ማለት ተናደደብኝ፣ ተናገር ተናገር አለብኝ ማለት ነው። ከማሰቤ የተነሣ እሳት ነደደ ማለት ተናድጄ የማይገባ ነገር ተናገርኩ ማለት ነው።

▶️፲፰. "መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድህም ሥጋን አዘጋጀህልኝ። የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልሻህም። በዚያን ጊዜ አልሁ እነሆ መጣሁ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፏል" ይላል (መዝ.40፥6-7)። ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፏል ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ በመጽሐፍ ራስ ተጽፏል ማለት የብሉይ ኪዳን ዋና ራስ መጽሐፍ የሚባለው ኦሪት ነው። ስለዚህ በኦሪት ንጹሓን ሆናችሁ መሥዋዕት ሠዉ ተብሎ ተጽፏል ማለት ነው።

▶️፲፱. መዝሙረ ዳዊት ተለይቶ ሲተኛ የሚጸለይ አለው እንዴ?

✔️መልስ፦ ስትተኙ በተለየ ከመዝሙረ ዳዊት ይህንን ጸልዩ የሚል አላገኘሁም። ጠዋት መዝሙር 62ን፣ በሠርክ መዝሙር 140ን መጸለይ እንደሚገባ ፍትሐ ነገሥት ላይ ተገልጿል። እኒህም ከሰዓቱ ጋር ልዩ ምሥጢር ስላላቸው ተለይተው ተጠቀሱ እንጂ በማናቸውም ጊዜ ከማናቸውም የመዝሙር ክፍል በንጹሕ ልብ ብንጸልይ ሰማያዊ ዋጋን እናገኝበታለን።

▶️፳. መዝሙረ ዳዊት በአርእስት ይከፈላል? ከተከፈለ ስንት አርእስት አለው?

✔️መልስ፦ አዎ። መዝሙረ ዳዊት አሥር አርእስት አለው። እነዚህም በእንተ ርእሱ፣ ተግሣጽ ለኩሉ፣ በእንተ ክርስቶስ፣ በእንተ መነናውያን፣ በእንተ ሕዝቅያስ፣ በእንተ ሰሎሞን፣ በእንተ ኤርምያስ፣ በእንተ መቃብያን፣ በእንተ ትሩፋን፣ በእንተ ዘለፋ ካህናት ናቸው።

▶️፳፩. "በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና ርጥበቴም ለበጋ ትኵሳት ተለወጠ" ይላል (መዝ.31፥3)። ይኼንን የተናገረው ከምን አንጻር ነው?

✔️መልስ፦ ይህን ዳዊት በትንቢት ስለሕዝቅያስ የተናገረው ነው። እጅህ ከብዳብኛለች ማለቱ መዓትህ ጸናብኝ ማለት ነው። ይህን የተናገረው ሕዝቅያስ ታላቅ ሕመምን ታምሞ ነበርና ነው።

▶️፳፪. "ስለዚህ ቅዱስ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወዳንተ ይለምናል ብዙ የጥፋት ውሃም ወደ እርሱ አይቀርብም" ይላል (መዝ.31፥5)። በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይለምናል ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ምቹ ጊዜ ያለው ንስሓ የምንገባበትን ጊዜ ነው። ሰው ንስሓ ሲገባ ከኃጢአት የተለየ ስለሚሆን ቅዱስ (የተለየ) ይባላል። ንስሓ ገብተው የሚጸልዩት ጸሎት መልካም ነውና ሰው ንስሓ ገብቶ ወደ አንተ ይጸልያል ማለት ነው። ይህም በጸናው መናገር ነው እንጂ ሌላውም ቢሆን ከበደል ለመውጣት መጸለይ ይገባዋል።

▶️፳፫. "የባሕርን ውሃ እንደ ረዋት የሚሰበስበው ቀላዮችንም በመዝገቦች የሚያኖራቸው" ይላል (መዝ.32፥7)። ረዋት የሚባለው ምንድን ነው?
ቀላዮችንም በመዝገብ የሚያኖራቸው ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ረዋት በቀድሞ ዘመን የውሃ መጠጫ የነበረ ነው። ቀላዮችን በመዝገብ የሚያኖራቸው ማለት ውሃዎችን በአንድ ቦታ (በውቅያኖስ) የሚወስን የሚሰበስብ ማለት ነው።

▶️፳፬. "መንገዳቸው ድጥና ጨለማ ይሁን የእግዚአብሔርም መልአክ ያሳድዳቸው" ይላል (መዝ.34፥6)። ይኸንን መናገር እንደርግማን አይቆጠርም ወይ?

✔️መልስ፦ የሚገባ ርግማን አለ። ከኃጢአቱ የማይመለስን ሰው ይረግሙታል። ከዚህም ዳዊት የረገማቸው በሰው ላይ ክፉ ለማምጣት የሚመክሩ ሰዎችን ስለሆነ በብሉይ ኪዳን በደል አልነበረም። በሐዲስ ኪዳን ግን የሚረግሙንን እንድንመርቅ ታዝዘናል።

▶️፳፭. "እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ ነፍሴንም በጾም አደከምኋት ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ" ይላል (መዝ.34፥13)። ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ጸሎቴ ወደ ብብቴ ተመለሰ ማለት ጸሎቴ እኔን ወደ መጥቀም ተመለሰልኝ ማለት ነው። ይህም ያለ ዋጋ የሚቀር ጸሎት እንደሌለ ያመለክታል።

▶️፳፮. "አቤቱ እስከ መቼ ድረስ ታይልኛለህ ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው ብቸኝነቴንም ከአንበሳዎች አድናት" ይላል (መዝ.34፥17)። ብቸኝነቴንም ከአንበሶች አድናት ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ብቸኝነቴን አይተህ ማለት ብቻዬን መሆኔን አይተህ በአናብስት ከተመሰሉት ክፉ ሰዎች አድነኝ ማለት ነው።

▶️፳፯. "ኃጥእ ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት" ይላል (መዝ.36፥35)። ኃጥእ ሰው እንዴት ሊለመልም ይችላል?

✔️መልስ፦ ዝቅ ብሎ ቁጥር 36 ላይ በተመለስኩ ጊዜ አጣሁት ተብሏል። ክፉ ሰው በዚህ ምድር ለአጭር ጊዜ በሥጋዊ ሀብት፣ ዕውቅናና፣ ሥልጣን ከፍ ሊል ይችላል። ይህንን ለመግለጽ ለምልሞ አየሁት ይላል። ነገር ግን በዚህ ጸንቶ ስለማይኖር በተመለስኩ ጊዜ አጣሁት ተብሏል።

▶️፳፰. ቅድስናና ጽድቅ አንድ ነው? አንድ ሰው ጻድቅ ለመባል መስፈርቱ ምንድን ነው? በሕይወት እያሉ የቅድስና ክብር ይሰጣል? እንዴትስ ነው የሚረጋገጠው?

✔️መልስ፦ ሁለቱም ምሥጢሩ አንድ ነው። ጻድቅ እውነተኛ ማለት ነው። ቅዱስ ሲል ደግሞ ጻድቅንም ሌሎችንም መልካም ምግባሮች አስተባብሮ የያዘን ለመግለጽ እንጠቀምበታለን። አንድ ሰው ጻድቅ ለመባል መሥፈርቱ ጻድቅ መሆን ነው። በሕይወት ዘመኑ ያከናወናቸው መልካም ምግባራት፣ ከሞተ በኋላም በተለያዩ ተአምራት ደግነቱ ሲረጋገጥ ቅዱስ ተብሎ ይሰየማል። ሰው ሳይሞት ቅዱስ ተብሎ አይሰየምም።

▶️፳፱. "አቤቱ የሚበድሉኝን በድላቸው። የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው። ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ። ነፍሴን መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት። ነፍሴን የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጎስቈሉም። ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይፈሩ ወደ ኋላቸውም ይበሉ። በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይሁኑ። የእግዚአብሔርም መልአክ ያስጨንቃቸው። መንገዳቸው ዳጥና ጨለማ ይሁን። የእግዚአብሔርም መልአክ ያሳድዳቸው" ይላል (መዝ.34፥1-6)። ይህን የሚመስሉ ብዙ ንባባት በጸሎት መጽሐፎች ውስጥም አለ እና ለሰው መጥፎ መመኘት አይሆንም? ጠላቶቻችሁን ውደዱ ከሚለው ጋር አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ሁለት ዓይነት ጸሎት አለ። ባለማወቅ የሚበድሉንን ይቅር እንዲላቸው መለመን፣ እያወቁ የሚያጠፉትንና የማይመለሱትን ደግሞ አጥፋቸው ብሎ መጸለይ ይገባል። ጌታ በመስቀል ባለማወቅ ለሚያጠፉት አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሎ ይቅርታ ሲያደርግ ለማይመለሱት ግን ቀድሞ ሲያስተምር ወዮታ እንዳለባቸው ገልጿልና ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Feb, 20:35


▶️፴. “እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ። ነፍሴንም በጾም አደከምኋት። ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ” ይላል (መዝ.35፥13)። ነፍሴን በፆም አደከምኳት ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ነባቢት ነፍስ በጾም ትበረታለች እንጂ አትደክምም። ነፍሴን በጾም አደከምኳት ማለት ሰውነቴን በጾም አደከምኳት ማለት ነው። ከዚህ ላይ ነፍስ ያላት ሰውነትን ነው።

▶️፴፩. “አቤቱ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ” ይላል (መዝ.38፥4)። ከዘመን ቁጥር አያይዤ ጥያቄዬ የሞታችንን ቀን እግዚአብሔር ቆርጧታል? የአሟሟታችን ዓይነትስ አጋጣሚ ነው ወይስ የእግዚአብሔር አሳብ? ከዚህም ጋር አያይዤ በቤተክርስቲያን (በእምነት ዐይን) አጋጣሚ የሚባል አለ?

✔️መልስ፦ ሰው የሚሞተው እግዚአብሔር ይሙት ሲል እንደሆነ በመጽሐፈ ዕዝራ ተገልጿል። ስለዚህ ሰው ለምን ያህል ዘመን እንደሚኖር ዕድሜው በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው። የአሟሟታችን ዓይነት ምን እንደሆነ የሚያውቀው እግዚአብሔር ነው። በቤተክርስቲያን አጋጣሚ፣ ዕድል የሚባል ነገር የለም። ሁሉም በተሰጠው ነጻ ፈቃድ መልካም እየሠራ ይኑር። እግዚአብሔር ደግሞ የሥራውን ይከፍለዋል።

▶️፴፪. "ቍጥር የሌላት ክፋት አግኝታኛለችና። ኀጢአቶቼ ያዙኝ ማየትም ተስኖኛል። ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ ልቤም ተወኝ" ይላል (መዝ.39፥12)። ልቤም ተወኝ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ልቤም ተወኝ ማለት ማሰብ ተሳነኝ፣ አእምሮዬ ተለየኝ ማለት ነው።

▶️፴፫. "ጎለመስኹ አረጀኹም ጻድቅ ሲጣል ዘሩም እኽል ሲለምን አላየኹም" ይላል (መዝ.36፥25)። ዘሩም እኽል ሲለምን አላየኹም ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ዘሩም ማለት የጻድቁ ልጁ የልጅ ልጁ እህል አይቸገርም ማለት በእግዚአብሔር ረድኤት ይኖራል ለማለት ነው።

▶️፴፬. "ከዝምታ የተነሣ እንደ ዲ*ዳ ኾንኹ። ለበጎ እንኳ ዝም አልኹ ቍስሌም ታደሰብኝ" ይላል (መዝ.38፥2-5)። ለበጎ እንኳ ዝም ማለት ተገቢ ነውን?

✔️መልስ፦ በጎ ነገርን መናገር መልካም ነው። ዳዊት ለበጎ ነገር ዝም አልኩ ካለ በኋላ ውጤቱን ቀጥሎ ሲነግረን ወተሐደሰኒ ቍስልየ መከራዬ ጸናብኝ ብሏል። ስለዚህ መልካም ነገርን መናገር ይገባል። ሰሚ በሌለበት ከሆነ ግን ዝም ማለት ተገቢ ነው።

▶️፴፭. "መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድኽም። ሥጋን አዘጋጀኽልኝ። የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልሻኽም" ይላል (መዝ.39፥6)። ሥጋን አዘጋጀኽልኝ ሲል ምን ማለት ነው? መሥዋዕቱን ያልወደደው ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ሰዎች በኃጢአት ሆነው የሚያቀርቡትን መሥዋዕት አይቀበልም። ስለዚህ ከዚህ ላይ መሥዋዕቱን ያልወደደበት ምክንያት ከኃጢአት ሳይነጹ የሚያቀርቡትን መሥዋዕት ነው። ሥጋን አዘጋጀህልኝ ማለት ንጹሕ ሁን አልከኝ ማለቱ ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Feb, 17:36


፩ኛ፦ ጠንቅቀን በማናውቀው ጉዳይ ላይ መናጆ/አንጃ ሆነን አስተያየት አለመስጠት መልካም ነው።

፪ኛ፦ የዕውቀታችንን ምንጭ መመርመር መልካም ነው። ከልምድ ነው? ከመጽሐፍ ነው? ከመምህር ነው? ከመሰለኝ ነው? ከምንድን ነው?

፫ኛ፦ የሰውን አለማወቅ እንደ Advantage ተጠቅሞ ማታለል አይገባም። ለምሳሌ ማንኛውም ክርስቲያን ንስሓ ገብቶ ሥጋውን ደሙን መቀበል ይገባዋል። ወደ ገጠር ስንሄድ ግን ወጣት አይቆርብም እያሉ አንዳንድ ሰዎች ሲከለክሉ ይስተዋላል። ይህ ስሕተት ነው። አንዱ መምህር ሄዶ ንስሓ እየገባችሁ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ ቢል ሰው ከልምዱ ተነሥቶ ሊጠላው ይችላል። የተናገረው ግን እውነት ነው። ሌላ እወደድ ባይ መምህር አዎ ወጣት መቁረብ የለበትም ብሎ ሕዝቡ የሚያቀርባቸውን አመክንዮዎች ቢያቀርብ ሕዝቡ ደስ ሊለው ይችላል። ሕዝቡም የዚህ ደጋፊ ሊሆን ይችላል። መማር እንደዚህ ነው ሊልህ ይችላል። እውነታው ግን የላይኛው ነው። በዚህ ጊዜ ከሕዝቡ የሐሰት ፈጠራ ይልቅ እግዚአብሔራዊውን እውነት ተናግሮ ከመሸበት ማደር ይገባል።

፬ኛ፦ ፈሪሳዊነትን እናስወግድ። ፈሪሳውያን በእግዚአብሔር ቃል ላይ የራሳቸውን ወግ እየጨመሩ ያስተምሩ ነበር። ለወጋቸው መጽሐፋዊ ወይም ቅዱስ ትውፊታዊ የሆነ ማስረጃ የላቸውም። ግን ሕዝቡ ወጋቸውን እንደ ጽጽቅ እንዲያይላቸው ይጥሩ ነበር።

፭ኛ፦ ክፉ ነገሮችም፣ መልካም ነገሮችም በትውፊት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊተላለፉ ይችላሉ። እኛ ቅዱስ ትውፊትን መቀበል አለብን። ቅዱስ ትውፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ የሚቃረን ከሆነ ትውፊት ቢሆንም እንኳ ቅዱስ ትውፊት ስላልሆነ አንቀበለውም።

፮ኛ፦ እግዚአብሔር ልብን የሚመረምር ስለሆነ ከእያንዳንዱ ሐሳባችን፣ ንግግራችን፣ ተግባራችን ጀርባ ያለውን ጉዳይ መመርመር ይገባናል። ከፍቅር ተነሥተን ነው? ከጥላቻ ተነሥተን ነው? ለሃይማኖታችን ከማሰብ ነው? ከአንጃነት ነው? ከምቀኝነት ነው? ከቅንዐት ነው? እግዚአብሔርን ከመውደድ ነው? በጠቅላላው ልባችንን እንፈትሽ። በእያንዳንዱ ንግግራችን፣ በእያንዳንዱ ሐሳባችን፣ በእያንዳንዱ ተግባራችን በእግዚአብሔር ፊት እንመዘንበታለንና።

፯ኛ፦ አንዳንዱ ሊሳደብ፣ ክፉ ስም ሊሰጥ ይችላል። አንዳንዱ ደግሞ ሊዋሽ ይችላል። በዚህ ጊዜ ስድቡን ቸል ብሎ ጉዳዩ ላይ ማተኮር መልካም ነው። ታግሠው ሲቀበሉት የበረከት ምንጭ ነውና። (አንዳንዱ የማስረዳት አቅም ሲያጥረው ስድብን እንደ አማራጭ ሊጠቀም ይችላል። ስለዚህ የሰውየውን ድክመቱን መረዳትና ንቆ መተው መልካም ነው)።

፰ኛ፦ ንግግሮችን፣ ጽሑፎችን ከነዐውዳቸው ለመረዳት መጣር ይገባል።

፱ኛ. ሟች መሆናችንን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም። መቼ እንደምንሞት ስለማናውቅ ከመሞታችን በፊት መሥራት አለብን ብለን ያሰብነውን ጉዳይ ለመፈጸም መትጋት ይገባናል።

፲ኛ፦ አጥፍተን ከነበረ ይቅርታ ማለትን እንልመድ። ትሑት ልቡናን ገንዘብ እናድርግ። ፈሪሀ እግዚአብሔርን እናስቀድም።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Feb, 19:05


💜 መዝሙረ ዳዊት ክፍል 4 💜

💜መዝሙር ፴፩፡- በልባቸው ሽንገላ የሌለባቸው ሰዎች ብፁዓን እንደሆኑ
-የኃጥኣን መቅሠፍታቸው ብዙ እንደሆነ
-በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ይቅርታ እንደሚከባቸው

💜መዝሙር ፴፪፡- ለቅኖች ክብር እንደሚገባቸው መገለጹ
-እግዚአብሔርን በመሰንቆና በበገና ማመስገን እንደሚገባ
-የእግዚአብሔር ቃል እውነት እንደሆነ
-እግዚአብሔር ጽድቅንና ምጽዋትን እንደሚወድ
-እግዚአብሔር አምላክ የሚሆንለት ሕዝብ ብፁዕ እንደሆነ
-ንጉሥ በሠራዊት ብዛት እንደማይድን

💜መዝሙር ፴፫፡- ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ያበራላችኋል እንደተባለ
-የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ እንደሚሰፍርና እንደሚያድናቸው
-በእግዚአብሔር የሚታመን ብፁዕ እንደሆነ
-አንደበትን ከክፉ መከልከል እንደሚገባ
-ሰላምን መሻትና መከተል እንደሚገባ
-የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃኑ ጆሮዎቹም ወደ ልመናቸው ናቸው መባሉ

💜መዝሙር ፴፬፡- እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ታላቅ እንደሆነ

💜መዝሙር ፴፭፡- ኃጢአተኛ ራሱን የሚያስትበትን ነገር እንደሚናገር

💜መዝሙር ፴፮፡- በክፉዎች ላይ ዐመፃንም በሚያደርጉ ላይ መቅናት እንደማይገባ
-በእግዚአብሔር መታመንና መልካምንም ማድረግ እንደሚገባ
-ለእግዚአብሔር መገዛትና እርሱን ማገልገል እንደሚገባ
-መዓትን መተው ቁጣን መጣል እንደሚገባ
-እግዚአብሔር ጻድቃንን እንደሚደግፋቸውና ርስታቸውም ዘለዓለማዊ እንደሆነ
-ከክፉ መሸሽ መልካምንም ማድረግ እንደሚገባ
-እግዚአብሔር ለንጹሓን እንደሚበቀልላቸውና የኃጥኣንን ዘር ግን እንደሚያጠፋ
-የጻድቅ አፍ ጥበብን ይማራል አንደበቱም ጽድቅን ይናገራል መባሉ
-ቅንነትን መጠበቅ ጽድቅን ማየት እንደሚገባ
-እግዚአብሔር ጻድቃንን እንደሚረዳና እንደሚያድናቸው

💜መዝሙር ፴፯፡- ዳዊት አቤቱ በመዓትህ አትቅሠፈኝ እንዳለ

💜መዝሙር ፴፰፡- ዳዊት በአንደበቴ እንዳልስት አፌን እጠብቃለሁ እንዳለ
-የሰው ልጅ ከንቱ እንደሆነ እና በጥላ እንደሚመሰል
-ተስፋችን እግዚአብሔር እንደሆነ

💜መዝሙር ፴፱፡- መታመኛው የእግዚአብሔር ስም የሆነ ሰው ብፁዕ እንደሆነ

💜መዝሙር ፵፡- ለድኻና ለምስኪን የሚያስብ ብፁዕ ነው እንደተባለ

💜የዕለቱ ጥያቄዎች💜
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ለቅኖች ክብር ይገባ
ለ. በእግዚአብሔር መመካት ያስኮንናል
ሐ. በልቡ ሽንገላ የሌለበት ሰው ብፁዕ ነው
መ. ሁሉም
፪. እግዚአብሔርን አመስግኑት የተባለው በምንድን ነው?
ሀ. በመሰንቆ
ለ. ዐሥር አውታር ባለው በገና
ሐ. በእልልታ
መ. ሁሉም
፫. የጽድቅ ሥራ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. አንደበትን ከክፉ መከልከል
ለ. በሥጋዊ ሠራዊት መመካት
ሐ. በእግዚአብሔር መታመን
መ. ሰላምን መሻት
፬. ስለ ጻድቅ ሰው ትክክል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. የጻድቅ አፍ ጥበብን ይማራል
ለ. የጻድቅ አንደበት ጽድቅን አይናገርም
ሐ. እግዚአብሔር ለጻድቃን ይበቀልላቸዋል
መ. ሀ እና ሐ

https://youtu.be/FLhRqX1zbpk?si=yOrUWzWKkXcX0dBf

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Feb, 18:56


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 135 💙💙

▶️፩. መዝ.21፥6 ላይ "እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም" ይላል። ዳዊት ለምን እንዲህ አለ?

✔️መልስ፦ ይህ የቅዱስ ዳዊት የትሕትና ቃል ነው። እኔ ትል ነኝ ማለቱ ትል እንደሚሞት የምሞት ነኝ ማለቱ ነው። ትል የተናቀ እንደሆነ የተናቅሁ ነኝ ማለቱ ነው።

▶️፪. መዝ.፳፰፥፩ ላይ ''የአማልክት ልጆች'' የተባሉ እነማን ናቸው? አማልክትስ እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ የአማልክት ልጆች የሚላቸው ካህናትን ነው። አማልክት የተባሉም ካህናት ናቸው። አማልክት ዘበጸጋ ናቸውና። የካህናት ልጆች የሆናችሁ ካህናት ማለቱ ነው። ክህነት በብሉይ ከሌዊ ወገን ነበርና። የሌዊ ወገን ከሆነ አባትም ልጅም ካህናት ናቸውና።

▶️፫. መዝ.22፥5 ላይ "ራሴን በዘይት ቀባህ" ይላል። ዘይት የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ መዝሙር 22 ስለትሩፋን የተነገረ ነው። እስራኤላውያን በባቢሎን ተማርከው በነበረ ጊዜ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተስፋ ያደርጉ ነበር። ተስፋውን ዘይት ብሎታል። ይህን መተርጉማነ ብሉይ ሊቃውንት ለሐዲስ ትንቢት አድርገው ዘይትን ልጅነት ብለው ተርጉመውታል።

▶️፬. መዝ.፳፫፥፯ ላይ ''እናንተ መኳንንቶች በሮችን ክፈቱ። የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ። የክብርም ንጉሥ ይግባ'' ይላል። ከዚህ ላይ መኳንንት፣ በር፣ የዘላለም ደጅ የተባሉ ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ ይህ በብዙ ተተርጉሟል። ከብዙው አንዱ መኳንንት የተባሉ የገነት ጠባቂ መላእክት ናቸው። በሮችን ክፈቱ መባሉ ተዘግታ የነበረች ገነት ትከፈት ማለት ነው። የክብር ንጉሥ ይግባ የተባለ ክርስቶስ ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ እየመራ ወደ ገነት ለማግባቱ ምሳሌ ነው።

▶️፭. መዝ.፳፪፥፬ ላይ ''በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል'' ይላል። በትር እና ምርኲዝ የተባሉ ምንድን ናቸው? ቃሉስ ያጸናኑኛል ነው ወይስ ያጽናኑኛል?

✔️መልስ፦ በትርና ምርጕዝን መተርጉማነ ብሉይ በብዙ ተርጉመውታል። ከብዙው አንዱ በትርና ምርኩዝ የተባለ የክርስቶስ ሥጋና ደምና ነው። የክርስቶስን ሥጋና ደም መቀበል አጋንንትን አርቆ እኛን በመልካም ሥራ ያጸናናልና። ቃሉ ያጸናኑኛል ነው። አጸና፣ አጸናና ከሚለው ግሥ የወጣ ነው። አጽናና አረጋጋ ከሚለው የወጣ ስላልሆነ ያጽናኑኛል አላለም።

▶️፮. መዝ.21፥12-17 "ብዙ በሬዎች ከበቡኝ፥ ብዙ ውሾች ከበቡኝ" ይላል። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ለጊዜው ዳዊት ያሳደዱትን እነ አቤሴሎምን በበሬ፣ በውሻ መስሎ ተናግሯል። ስለክርስትስ ትንቢት ሲሆን ደግሞ በበሬና በውሻ የተመሰሉት አይሁድ ናቸው።

▶️፯. መዝ.27፥8 "ለመሲሑ የመድኃኒቱ መታመኛ ነው" ይላል። አልገባኝም ቢያብራሩት።

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ቀብቶ ላነገሠው ለንጉሡ ለዳዊት የታመነና ድኅነቱን የሚያደርግለት ነው ማለት ነው።

▶️፰. መዝ.28፥6 ላይ "ተወዳጅ ግን አንድ ቀንድ እንዳለው ርኤም ነው" ይላል። ርኤም ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ርኤም በበርሃ በዱር የሚኖር የበሬ ዓይነት እንስሳ ነው።

▶️፱. መዝ.፳፮፥፲ ላይ ''አባቴና እናቴ ጥለውኛልና'' ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ለዳዊት ሲነገር በእናትና በአባቴ ሩካቤ በማኅፀን ተፀነስኩ ማለቱ ነው። ቀጥሎ እግዚአብሔር ተቀበለኝ ማለቱ በሕይወት አቆየኝ ማለቱ ነው። እናት አባት ቢጸንሱ ቢወልዱ እንኳ በሕይወት ማቆየት የእግዚአብሔር ሥራ ነውና።

▶️፲. መዝ.፳፰፥፫ ላይ ''የእግዚአብሔር ድምፅ በውኆች ላይ ነው'' ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ቅዱስ ዳዊት መዝሙር 28ን ስለሕዝቅያስ ተናግሮታል። በዚህ አግባብ ውሆች ያላቸው ሕዝቅያስን ሊያጠፉ መጥተው የነበሩ እነሰናክሬምን ነው። የእግዚአብሔር ድምፅ በእነርሱ ላይ ነው ማለት እነሰናክሬም እንዲጠፉ እግዚአብሔር መናገሩን መግለጽ ነው።

▶️፲፩. መዝ.፳፰፥፭ ላይ 'ዝግባን ይሰብራል/የሊባኖስን ዝግባ'' ሲል ምን ለማለት ነው? መዝ.፳፰፥፮ ላይስ ''እንደ ሊባኖስ ላም'' ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ዝግባ ያለው ሰናክሬምንና ሠራዊቱን ነው። እግዚአብሔር እነዚህን ያጠፋል ማለት ነው። የሊባኖስ ላም የሚለው የደጋ ላም ለማለት ነው። የደጋ ላም ድርቅ በሆነ ዘመን የሚበላው አጥቶ ይከሣል። በደጋ ላም የተመሰለ ሰናክሬምም ሠራዊቱ አልቆ ጥቂት ብቻ ሆኖ ወደ ሀገሩ መመለሱን ለማመልከት ነው።

▶️፲፪. የ፳፻ ዕትም መዝ ፴፥፲፰ ላይ ''በጻድቅ ላይ ሽንገላን የሚናገሩ ከንፈሮች ወዮላቸው'' ሲል የስልኩ ግን ''ዲ*ዳ ይኹኑ'' ይላል ይኽ ተገቢ ነውን?

✔️መልስ፦ ሁለቱም ምሥጢሩ ተመሳሳይ ነው። ወዮታ አለባቸው ብሎ መከራ እንደሚደርስባቸው ገልጿል። የስልኩ የሚደርስባቸውን መከራ በስም ጠቅሶ ዲ*ዳ ይሁኑ አለ። ዲ*ዳ ይሆናሉ ሲል ነው።

▶️፲፫. መዝ.28፥6 ላይ "እንደ ጥጃ ሊባኖስን አንድ ቀንድ እንዳለው አውሬ ልጅ ስርዮንን ያዘልላቸዋል" ሲል ስርዮን ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ስርዮን አንድ ቀንድ ያለው ውብ ፍጥረት ነው።

▶️፲፬. መዝ.28፥10 "እግዚአብሔር የጥፋት ውሃን ሰብስቧል። እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ኾኖ ይቀመጣል" ይላል። የጥፋትን ውሃን ሰብስቧል ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የጥፋት ውሃን ሰብስቧል ማለት እግዚአብሔር ሰናክሬምን ከነሠራዊቱ ለጥፋት በለኪሶን ይሰበስበዋል ማለት ነው። እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል ማለት ለዘለዓለም ንጉሥ ነው ማለት ነው።

▶️፲፭. "በእጃቸው ተንኰል አለባቸው ቀኛቸውም መማለጃ ተሞልታለች" ይላል (መዝ.25፥10)።
በእጃቸው ተንኮል ሞልቷል ካለ በኋላ መማለጃ ደግሞ በቀኛቸው አለ ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በእጃቸው ተንኮል አለባቸው ያለው በእጃቸው ነፍስን ይገድላሉ ማለት ነው። መማለጃ በቀኛቸው አለ ማለቱ ደግሞ ከመግደል በተጨማሪ ጉቦን (መማለጃን) በመቀበል ይበድላሉ ማለት ነው።

▶️፲፮. "እንደ ሞተ ሰው ከልብ ተረሳሁ እንደ ተበላሸ ዕቃም ሆንሁ" ይላል (መዝ.30፥12)። የሞተ ሰው ብሎ የተናገረው በሥጋ ያረፈን ሰው ነው ወይስ በነፍስ የጎሰቆለን ሰው? ከልብ ተረሳሁ ያለውስ ከምን አንጻር ነው? ክፉ ሰውም ሆነ መልካም ሰው ከሞተ በኋላ ይረሳልን?

✔️መልስ፦ በሥጋ የሞተ ሰው ለጥቂት ጊዜ ይታወሳል እንጂ ሁልጊዜ ስለማይታወስና ስለሚረሳ እንደሞተ ሰው ተረሳሁ አለ። መልካም ሰው ከሞተ በኋላ አይረሳም። በቅድስናው በመልካምነቱ ሲወሳ ይኖራል። ኃጥእ ሰው ግን ከሞተ በኋላ አይወሳም ይረሳል።

▶️፲፯. "አቤቱ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ" ይላል (መዝ.29፥3)። ከሲኦል አወጣሃት ብሎ እንደገና ደግሞ ጉድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ሲኦል የሚለው መቃብርን ነው። ሰውነቴን ሙቼ ወደ መቃብር ከመውረድ አዳንካት ማለት ነው። ወደ ጉድጓድም እንዳልወርድ አዳንከኝ ማለት ነፍሴን ወደ ሲኦል ከመውረድ (ወርዳ ከመቅረት) አዳንካት ማለት ነው። በክርስቶስ ትንሣኤ መቃብር ውጦ ማስቀረት የማይችል ሆኗልና። ጻድቃነ ብሊትም ከሲኦል ወደ ገነት ተመልሰዋልና ይህን ለመግለጽ ነው።

▶️፲፰. "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ። አምላኬ በቀን ወደ አንተ እጠራለሁ አልመለስህልኝም። በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም " ይላል (መዝ.22፥1-2)። በሌላ ቦታ ደግሞ "እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል" ይላል (መዝ.4፥3)። ሁለቱ አይጋጭም?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Feb, 18:56


✔️መልስ፦ አዎ ቅዱስ ዳዊት በዕለተ ዓርብ በክርስቶስ የሚደርሰውን ሕማም መከራ በትንቢት መነጽር ተገልጾለት አይቶት ጽፎታል። ነቢያት ቀጥታ ወደፊት የሚሆነው ነገረ ክርስቶስ ተገልጾላቸው ቀጥታ የጻፉት ነገር ደረቅ ሐዲስ እየተባለ ይጠቀሳል።


© በትረ ማርያም አበባው

✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Feb, 18:56


✔️መልስ፦ እግዚአብሔር የሰዎችን ልመና የሚሰማበትም የማይሰማበትም ጊዜ አለ። እግዚአብሔር ጸሎትን ሰማ ማለት ረድኤትን ሰጠ ማለት ነው። አልሰማም ማለት ደግሞ የጸሎት ፍሬ የሆነውን ረድኤትን አልሰጠም ማለት ነው። በንጹሕ ልብ ሆነን ብንለምነው ይሰማናል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እርሱ ራሱ ብቻ በሚያውቀው ምክንያት ይተወናል። ስለዚህ ሁለቱም የሚሆኑበት የየራሳቸው አግባብ ስላለ አይጋጭም።

▶️፲፱. መዝ.፳፱፥፲፩ ላይ "ማቄን ቀድደህ ደስታን አስታጠቅኸኝ" ይላል። ማቅ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከእንስሳት ጸጉር የሚሠራ ሲለብሱት ምቾት የማይሰጥ ልብስ ነው።

▶️፳. "ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ። በጕሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ። ወደ ሞትም አሸዋ አወረድኸኝ" ይላል (መዝ.21፥15)። ወደ ሞትም አሸዋ አወረድኸኝ ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የሞት አሸዋ ያለው መቃብርን ነው። ወደ መቃብር አወረድከኝ ማለት ነው።

▶️፳፩. "ከአንበሳ አፍ አድነኝ ብቻነቴንም አንድ ቀንድ ካላቸው። ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ። በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ" ይላል (መዝ.21፥21-22)። ብቻነቴንም አንድ ቀንድ ካላቸው ሲል ምን ማለት ነው? ዳዊት ወንድሞቼ ያላቸውስ እነማንን ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ ቀንድ ያለው ሥልጣንን ነው። ዳዊት በአንድ ሥልጣኑ ከሚመካ ከአቤሴሎም አድነኝ ማለቱ ነው። ዳዊት ወንድሞቼ የሚላቸው ሁለቱን ነገድ ማለትም ነገደ ይሁዳንና ነገደ ብንያምን ነው። ከእርሱ ጋር በአንድ ክፍለ ሀገር የሚኖሩ ናቸውና።

▶️፳፪. "ችግረኞች ይበላሉ ይጠግቡማል። እግዚአብሔርንም የሚሹት ያመሰግኑታል። ልባቸውም ለዘላለም ሕያው ይሆናል" (መዝ.21፥26) የሚለውንና "የምድር ደንዳኖች ሁሉ ይበላሉ ይሰግዳሉም። ወደ መሬት የሚወርዱት ሁሉ በፊቱ ይንበረከካሉ። ነፍሴም ስለ እርሱ በሕይወት ትኖራለች" (መዝ.21፥29) የሚለውን  ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ መዝሙር 21 ቁጥር 26 ላይ ነዳያን ያላቸው ነቢያት ካህናቱን ነው። የራሳቸው ሥጋዊ ርስት የላቸውምና። ይበላሉ ይጠግቡማል ማለቱ አሥራቱን በኵራቱን በልተው ይኖራሉ ማለት ነው። መዝሙር 21 ቁጥር 29 ላይም የምድር ደንዳኖች ያላቸው ነቢያት ካህናቱን ነው። አንድ ወገን ነው።

▶️፳፫. "በለመለመ መስክ ያሳድረኛል። በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል" ይላል (መዝ.22፥2)። ከዚህ ላይ የለመለመ መስክና የዕረፍት ውኃ ያላቸው ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ በተክል በለመለመች በኢየሩሳሌም ያኖረኛል ማለት ነው። የለመለመ መስክ እና የዕረፍት ውሃ ያላት ኢየሩሳሌምን ነው።

▶️፳፬. "ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል?" ይላል (መዝ.23፥3)። የእግዚአብሔር ተራራና የቅድስናው ስፍራ የተባሉ ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ተራራ ያላት ኢየሩሳሌምን ሲሆን የቅድስናው ሥፍራ የተባለው ደግሞ ቤተ መቅደስ ነው።

▶️፳፭. መዝሙረ ዳዊት ለኛ የጸሎት መጽሐፋችን እንደሆነ ይታወቃል። በምን ምክንያት ሆነ ወይም ሌሎቹ ለምን አልሆኑም? ከዚህ ጋር አያይዤ ባለ አምስት መቶ ባለ 700 የሚባል አለና (ካልተሳሳታኩ) ለምን ተባለ?

✔️መልስ፦ መዝሙረ ዳዊት ለእኛ የጸሎት መጽሐፋችን እንዲሆን ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14 ላይም ተገልጿል። የሆነበት ምክንያት ከሌለው በተለየ በብዛት ምስጋናን፣ ጸሎትን፣ ተአምኖ ኃጣውእን አካቶ ስለያዘ ነው። የመዝሙሩ ብዛት 150 ነው። 500ም፣ 700ም አለ የሚሉ ካሉ እኔ አይቼው ስለማላውቅ እንዲህ ነው ማለት አልችልም። እኛ ከአባቶቻችን በተቀበልነው መሠረት 150 እንደሆነ አምነን ተቀብለን ለሌላውም እናስተላልፋለን።

▶️፳፮. "የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ" ይላል (መዝ.26፥13)። ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔርን ተድላ ደስታውን ሕያዋን በተባሉ በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ ምድር በኢየሩሳሌም እንደማይ አምናለሁ ማለት ነው።

▶️፳፯. "ሕዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ። ጠብቃቸው ለዘላለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው" ይላል (መዝ.27፥9)። ይህን ቃል ዛሬም ካህኑ በቅዳሴ መጨረሻ ላይ ይናገረዋል። ርስትህንም ባርክ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ርስትህ የሚላቸው ሁለቱን ነገደ እስራኤል ነው። አሁን በሐዲስ ኪዳን ካህኑ ሕዝበከ ርስተከ የሚላቸው አንድ ወገን ምእመናንን ነው። እስመ ንሕነ መዋርስቲሁ ለእግዚአብሔር እንዲል።

▶️፳፰. "ቅዱሳን ሆይ ለእግዚአብሔር ዘምሩ። ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ። ቍጣው ለጥቂት ጊዜ ነው። ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን። ልቅሶ ማታ ይመጣል። ጠዋት ግን ደስታ ይሆናል" ይላል (መዝ.29፥4-5)። የቅድስናውም መታሰቢያ ያለው ምኑን ነው? ልቅሶ ማታ ይመጣል ጠዋት ግን ደስታ ሲልስ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የቅድስናው መታሰቢያ ያለው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ የሚመሰገነውን የስሙን ምስጋና መታሰቢያ ነው። በማታ ልቅሶ ይደረጋል ማለት በኦሪት ልቅሶ ይደረጋል ማለት ነው ልጅነት አልተሰጠምና። ጠዋት ደስታ ይሆናል ሲል በወንጌል ደስታ ይሆናል ማለቱ ነው። በወንጌል ልጅነት ተሰጥቷልና።

▶️፳፱. "ወደ ጥፋት ብወርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ? አፈር ያመሰግንሃልን? እውነትህንም ይናገራልን?" ይላል (መዝ.30፥9)። ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ እኛ ብንሞት የእኛ ሞት ለእግዚአብሔር ምንም ጥቅም የለውም ማለቱ ነው። እኔ ብሞት መቃብር የእኔን ሥጋ ስላገኘ ያመሰግንሀልን ይላል አያመሰግንህም ለማለት ነው። እውነትህንም ይናገራልን ማለት አይናገርም ማለት ነው።

▶️፴. “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ” ይላል (መዝ.22፥1)። ይህ ቃል ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ ትንቢት እንደሆነ ይነገራል። "እኔን ከማዳንህና ከጩኸቴ ሩቅ ነህ" የሚለው ትርጓሜው ምንድን ነው? ከዚህ ጋር አያይዤ ኢየሱስ ክርስቶስ (ከተዋሕዶ በኋላ) ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የጸለየው በሥጋው ነው በመለኮቱ? ለምንስ ለሥጋውና ለመለኮቱ የሚናገሩ ሆኑ?

✔️መልስ፦ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ አምላኬ አምላኬ ማለቱ የሰውን ሁሉ ጩኸት ስለሰው ቤዛ ሆኖ የጮኸው ነው። የአዳምን ጩኸት ቤዛ አዳም ሆኖ ጮኾለታል። ከጩኸቴ ሩቅ ነህ ማለቱ 5500 ዘመን ሰው ሳይድን በሲኦል መቆየቱን ለመግለጽ የዘመኑን ርዝመት ለመግለጽ ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ክርስቶስ ያደረገው ሥራ በተዋሕዶ የተሠራ እንጂ እየለዩ የሥጋ የመለኮት ብሎ መናገር የለም። መለኮት በሥጋ ሞተ ሲባል እንኳ አዋሐጅ ፊደል "በ"ን እየጠቀስን እንናገራለን። እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሞተ በሥጋ ወሐይወ በመንፈስ እንላለን እንጂ ሞተ ሥጋ ወሐይወ መንፈስ ብለን ምንታዌን በሚያሳይ አነጋገር አንናገርም።

▶️፴፩. "እንደ ነጣቂና እንደሚጮኽ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ። እንደ ውኃ ፈሰስሁ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ። ልቤ እንደ ሰም ሆነ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ። ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጕሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አሸዋ አወረድኸኝ። ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም። ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ" ይላል (መዝ.22፥13-18)። መምህር እነዚህ የመዝሙር ንባቦች ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገሩ እንደሆነ እኛ እናውቃለን ሲፈጸም አይተናል ወይ ደግሞ ተተርጉሞልናል። ዳዊትስ ይህን ስለክርስቶስ እየተናገረ መሆኑን ያውቀው ነበር? ወይም እኛ አሁን የምንረዳውን ያውቅ ነበር?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Feb, 05:13


💙 መዝሙረ ዳዊት ክፍል 3 💙

💙መዝሙር ፳፩፡- እግዚአብሔር በቅዱሳን እንደሚኖር
-እግዚአብሔር ያመኑበትን እንደሚያድን
-እግዚአብሔር የምትፈሩት አመስግኑት እንደተባለ
-እግዚአብሔርን የሚሹት እንደሚያመሰግኑት

💙መዝሙር ፳፪፡- እግዚአብሔር በጽድቅ መንገድ እንደሚመራ
-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ካለ ምንም እንደማያስፈራን

💙መዝሙር ፳፫፡- ምድር በመላዋና ዓለምም በእርሷ የሚኖረውም ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ
-እግዚአብሔር የክብር ንጉሥ፣ የኃያላን አምላክ እንደሆነ

💙መዝሙር ፳፬፡- የእግዚአብሔር ምሕረት ለዘለዓለም እንደሆነ
-እግዚአብሔር ቸር፣ ጻድቅም እንደሆነና ለየዋሃን ፍርድን እንደሚያስተምራቸው
-እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነፍሱ በመልካም እንደምታድር

💙መዝሙር ፳፭፡- ዳዊት እንዳልደክም በእግዚአብሔር አመንኩ ማለቱ

💙መዝሙር ፳፮፡- ዳዊት እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው እንዳለ
-እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግ እንደሚገባ

💙መዝሙር ፳፯፡- እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይላቸው እንደሆነ

💙መዝሙር ፳፰፡- የእግዚአብሔር ቃል ኃያል እንደሆነ

💙መዝሙር ፳፱፡- ለእግዚአብሔር መዘመር እንደሚገባ

💙መዝሙር ፴፡- በትዕቢትና በመናቅ በጻድቅ ላይ ዐመፃን የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ወዮታ እንዳለባቸው
-እግዚአብሔር ጽድቅን እንደሚሻ
-በእግዚአብሔር የምናምን ሰዎች ሁሉ ልባችንን ማፅናትና መታገሥ እንደሚገባን

💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ይቀበላል የተባለው የቱ ነው?
ሀ. ልቡ ንጹሕ የሆነ ሰው
ለ. ለባልንጀራው በሽንገላ ያልማለ
ሐ. በነፍሱ ላይ ከንቱን ያልወሰደ
መ. ሁሉም
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. እግዚአብሔር የክብር ንጉሥና የኃያላን አምላክ ነው
ለ. ምድር በሞላዋና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔር አይደሉም
ሐ. የእግዚአብሔር ምሕረት ለዘለዓለም ነው
መ. ሀ እና ሐ
፫. ስለ ልዑል እግዚአብሔር ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ይቅርታና እውነት ነው
ለ. እግዚአብሔር ቸርም ጻድቅም ነው
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም
፬. እግዚአብሔርን ስለሚፈራ ሰው ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ነፍሱ በመልካም ታድራለች
ለ. ዘሩ ምድርን ይወርሳል
ሐ. ሀ እና ለ
መ. ሁሉም
፭. ወዮላቸው ከተባሉት መካከል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በትዕቢት በጻድቅ ላይ ዐመፃን የሚናገሩ
ለ. በመናቅ በጻድቅ ላይ ዐመፃን የሚናገሩ
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/YSo5iCU6Z-s?si=ajlMdZpQAKr64uTS

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Feb, 20:03


✔️መልስ፦ ሰኰና ልቡናዬ በአምልኮተ ጣዖት በገቢረ ኃጢአት እንዳይሰነካከል እግረ ልቡናዬን በአምልኮትህ አጽናው ማለት ነው። ሰኰና ማለት ተረከዝ ማለት ነው። ውሳጣዊውን የልብ ተረከዝ በአፍኣዊው ተረከዝ ገልጾት ነው።

▶️፳፱. "ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ። በቀኜ ነውና አልታወክም" ይላል (መዝ.16፥8)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ቅዱሳን ሲበቁ ሁልጊዜም እግዚአብሔርን በዘፈቀደ ያዩታልና ነው። ዳዊትም በኋላ በቅቶ እግዚአብሔርን ያይ እንደነበር ገለጠልን። በቀኜ ነውና አልታወክም ማለት እግዚአብሔር ይረዳኛልና አልፈራም ማለቱ ነው።

▶️፴. "ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም። የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ። ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ። በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ" ይላል (መዝ.16፥10-11)። ይህ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ ትንቢት ነው ሲባል እሰማለሁና ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ለጊዜው ዳዊት ለዘመኑ የተናገረው ቢሆንም ይህ ቃል ስለክርስቶስም ይናገራል። ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም ሲል ሲኦልን መቃብር ብሎ ይተረጉማል። ክርስቶስ በመቃብር ፈርሶ በስብሶ አይቀርም አምላክ እንደመሆኑ በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ያመለክታል። የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ ማለት ስለሥጋ እንግድነት የተነገረ ነው። ሟች ሥጋ ቃልን በመዋሐዱ የባሕርይ አምላክ ሆኗልና የባሕርይ አምላክ ሆንኩ ማለት ነው። በቀኝህ የዘለዓለም ፍሥሓ አለ ማለት ከዕርገት በኋላ ክርስቶስ በአምላካዊ ግብር ጸንቶ መኖሩን ያመለክታል።

▶️፴፩. "ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጎበኘኸኝ። ፈተንኸኝ ምንም አላገኘህብኝም። የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው። ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ" ይላል (መዝ.16፥3-4)። እዚህ ላይ ዳዊት ሊናገረው የፈለገው ሐሳብ ምንድን ነው ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ዳዊት እግዚአብሔርን ልቤን ፈተንከው ማለቱ ጠላቱን ሳኦልን በእጄ ጥለህ ይገድለው ይሆን አይሆን ብለህ ፈተንከኝ ማለቱ ነው። ፈተንከኝ ምንም አላገኘህብኝም ማለቱ ጠላቶቼን በእጄ ብትጥላቸውም ስላልገደልኳቸው ከበደል አላገኘህብኝም ማለት ነው። ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ ማለቱ ጠላቱን ሳኦልን አግኝቶ አለመግደል ጭንቅ ነውና አፍቅሮ ጸላእትን ለመጠበቅ ይህንን አለፍኩ ማለቱ ነው።

▶️፴፪. "አንጀታቸውን በስብ ቋጠሩ። በአፋቸውም ትዕቢትን ተናገሩ" ይላል (መዝ.16፥10)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ አንጀታቸውን በስብ ቋጠሩ ማለት ክፉ ምክር መከሩብኝ ማለት ነው። በአፋቸውም ትዕቢትን ተናገሩ ማለት ይህ የዕሴይ ልጅ አይደለምን እያሉ ጠላቶቼ የንቀት የትዕቢት ቃልን ተናገሩ ማለት ነው።

▶️፴፫. "ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ። ልጆቻቸው ብዙ ናቸው የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ" ይላል (መዝ.16፥14)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከሰወርከው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብክ ማለት በመከራ ቀጣሀቸው ማለት ነው። ልጆቻቸው ብዙ ናቸው የተባሉ የገባዖን ልጆች ናቸው። እስራኤላውያንን በሸበተ እንጀራ አታለው ከመከራ ቢተርፉም ውሸት እያደረ ስለሚገለጽ ውሸታቸው ሲገለጽ እስራኤላውያን ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን ለቤተ እግዚአብሔር እንጨት ለቃሚ ውሃ ቀጂ እንዲሆኑ ስለወሰኑባቸው ይህንን ለመግለጽ ነው። (ይህን ታሪክ ኦሪት ስንማር ስላየነው አስታውሱት)።

▶️፴፬. "ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ። ከቍጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊቱም የሚበላ እሳት ነደደ፥ ፍምም ከእርሱ በራ። ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥ ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ። በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ። መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ፥ በዙሪያውም ድንኳኑ፥ በደመናት ውስጥ የጨለማ ውኃ ነበረ። በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ። እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጎደጎደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ። ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፤ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።አቤቱ ከዘለፋህ ከመዓትህም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ" ይላል (መዝ.18፥7-15)። ዳዊት ይህን ያለ መቼ ስለሆነው ነገር ነው?

✔️መልስ፦ ቅዱስ ዳዊት ይህን ሁሉ የተናገረው ስለልዑል እግዚአብሔር ታላቅነትና ከቀድሞ ጀምሮ ስላደረጋቸው ታላላቅ ሥራዎች ለመግለጽ ነው።

▶️፴፭. "በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ። የባዕድ ልጆች ደለሉኝ። የባዕድ ልጆች አረጁ። በመንገዳቸውም ተሰናከሉ" ይላል (መዝ.18፥44-45)። የባዕድ ልጆች ያላቸው እነማንን ነው? ደለሉኝ፣ አረጁ ሲልስ ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ የባዕድ ልጆች ያላቸው እነሳኦልን ነው። መንግሥትነት ለነገደ ብንያም ሳይሆን ለነገደ ይሁዳ ቀድሞ የተሰጠ በመሆኑ ከሌላ የነገሡትን እንደ ባዕድ ቆጥረዋቸዋል። ደለሉኝ ማለቱ ሳኦል ዳዊትን ብዙ ጊዜ ለመግደል እንደሸነገለው የሚገልጽ ነው። አረጁ መባሉ እነሳኦል ጠፉ ማለት ነው።

▶️፴፮. "እስከ መቼ በነፍሴ እመካከራለኹ ትካዜስ እስከ መቼ ዅልጊዜ ይኾናል እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይጓደዳል?" ይላል (መዝ.12፥2)። እስከ መቼ በነፍሴ እመካከራለኹ ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ እስከ መቼ በነፍሴ እመካከራለሁ ማለት እስከ መቼ በሰውነቴ አዝኜ ተክዤ እኖራለሁ ማለት ነው።

▶️፴፯. "ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም" ይላል። በዐራጣ ማበደር ምን ማለት ነው? ወለድ ማስከፈል ትክክል ነው?

✔️መልስ፦ በአራጣ ማበደር ማለት ከዓይነታው በተጨማሪ ተበዳሪው ትርፍ እንዲከፍል ተዋውሎ ማበደር ማለት ነው። ክርስቲያን ወለድ ማስከፈል ፈጽሞ አይገባውም። ስለዚህ ወለድ ማስከፈል ትክክል አይደለም።

▶️፴፰. "የእግዚአብሔር ፍርሀት ንጹሕ ነው ለዘለዓለም ይኖራል። የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው" ይላል (መዝ.18፥9)። የእግዚአብሔር ፍርሀት ንጹሕ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ፍርሀት ያለው ፈሪሀ እግዚአብሔር ለማለት ነው። የአማርኛው ትርጉም አሻሚ አድርጎት ነው እንጂ እግዚአብሔርን መፍራት ንጹሕ ነው ማለት ያነጻል ማለት ነው። እንጂ እግዚአብሔር ምንም ፍርሀት የሌለበት አምላክ ስለሆነ በእርሱ ፍርሀት እንዳለበት የሚገልጽ አይደለም።

▶️፴፱. "ስሕተትን ማን ያስተውላታል ከተሰወረ ኀጢአት አንጻኝ። የድፍረት ኀጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያኽን ጠብቅ። የዚያን ጊዜ ፍጹም እኾናለኹ ከታላቁም ኀጢአት እነጻለኹ" ይላል (መዝ.18፥12-13)። የተሰወረ ኀጢአት፣ የድፍረት ኀጢአት፣ የትልቅ ኀጢአት እና የትንሽ ኀጢአት ልዩነታቸውን ቢያስረዱን?

✔️መልስ፦ የተሰወረ ኃጢአት ማለት እኛ የዘነጋነው ወይም ባለማወቅ የሠራነው እግዚአብሔር የሚያውቀው የእኛ ኃጢአት ነው። የድፍረት ኃጢአት ማለት ሰው እንደሚያስቀጣና መከራን እንደሚያመጣ እያወቀ በድፍረት የሚሠራው ኃጢአት ነው። የኃጢአት ትንሽ ትልቅ የለውም ሁሉም ፍዳን መከራን በማምጣት አንድ ናቸው። ነገር ግን በሚያመጡት ፍዳ ቅለትና ክብደት መጽሐፈ መነኮሳት ታላቅ የሚላቸው ዝሙትን፣ ግድያንና የመሳሰሉትን ነው። ታናሽ የሚላቸው የኀልዮ ኃጢአቶችን ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Feb, 20:03


✔️መልስ፦ ሳልሳቀቅ እንድሄድ አደረግከኝ ማለት ነው። ጠላት ያለበት ሰው ሰው አየኝ አላየኝ ብሎ ይሔዳል እንጂ መልቶ አስፍቶ አይሄድም። ዳዊት ግን አረማመዴን አሰፋህልኝ ማለቱ በረድኤተ እግዚአብሔር ታምኖ ያለፍርሀት መኖሩን ለመግለጽ ነው።

▶️፲፯. መዝ.፲፭/፲፮፥፯ ላይ "የመከረኝን እግዚአብሔርን እባርካለኹ ደግሞም በሌሊት ኵላሊቶቼ ይገሥጹኛል" ይላል። እግዚአብሔርን እባርካለኹ ሲል ምን ማለት ነው? እግዚአብሔርን የሰው ልጅ ሊባርከው ይችላልን?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔርን እባርካለሁ ማለት እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ማለት ነው። እንጂ ሰው እግዚአብሔርን ቀድሶ በቅድስናው ላይ፣ ባርኮ በቡሩክነቱ ላይ ይጨምርለታል ማለት አይደለም።

▶️፲፰. መዝ.፲፮/፲፯፥፲፫ "አቤቱ ተነሥ ቀድመኽ ወደ ታች ጣለው ነፍሴን ከኀጢአተኛ በሰይፍኽ አድናት" ይላል። እግዚአብሔር ስዎችን የሚጠብቅ በሰይፍ ነውን? የሌሎች እምነት ተከታዮች በተደጋጋሚ ሰይፍ የሚለውን ቃል ሲያገኙ እግዚአብሔር ሰይፍ አለው ሰይፍን እንድትይዙ ያዛችኋል ይላሉና እዚህ ላይ ሰይፍ የሚለው ቢብራራ።

✔️መልስ፦ ለእግዚአብሔር ሰይፍህ እየተባለ የተገለጠው ሥልጣኑና በሥልጣኑ የሚያመጣው ቅጣት ነው። ሰይፍ ያለው ሥልጣኑን ነው። ሰይፍ አካልን እንደሚለያይ እግዚአብሔርም በሥልጣኑ ኃጥኣንን ከጻድቃን በሞት በምጽአት በመከራና በመሳሰሉት ይለያልና።

▶️፲፱. መዝ.፲፯፥፰-፲ ላይ "ከቍጣው ጢስ ወጣ ከፊቱም የሚበላ እሳት ነደደ ፍምም ከእርሱ በራ። ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም። ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ። በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ በነፋስም ክንፍ በረረ" ይላል። እግዚአብሔር ምሉእ ሆኖ ሳለ ወዴት ነው የሚበረው? ይህ ከቁጥር 8 ጀምሮ ያለው ሁሉም ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ከቁጣው ጢስ ወጣ ማለት በቁጣው እግዚአብሔር ሀገርን ማቃጠሉን መግለጽ ነው። ሀገር ሲቃጠል ጢስ፣ እሳት፣ ፍም ይወጣልና። እሳት ነደደ ፍምም ከእርሱ በራ የሚለው አንድ ወገን ነው። ሰማያትን ዝቅ ዝቅ አደረገ ማለት ኃያላንን፣ መላእክትን በመኖሪያቸው ሰማይ ይላቸዋልና በእነርሱ ረዳኝ ማለት ነው። ጨለማ ከእግሩ በታች ነበር። ጨለማ ሥውር እንደሆነ ሁሉ በሥውር ረዳኝ ማለት ነው። በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ ማለት በዘፈቀደ በእነርሱ እንደሚገለጽ መንገር ነው። በነፋስ ክንፍ በረረ ማለት ፈጥኖ ረዳኝ ማለት ነው። ፈጥኖ መርዳቱን ለመግለጽ በረረ አለ እንጂ እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ምሉእ ስለሆነ ከአንዱ ወደ አንዱ የሚበር ሆኖ አይደለም።

▶️፳. መዝ.19 የሚናገረው ቅዱስ ዳዊት ነው እና ማንን ነው የሚመርቀው?

✔️መልስ፦ ራስን አርቆ መናገር ልማደ መጽሐፍ ስለሆነ ዳዊት ስለራሱ ተናግሮታል። ጌታ ሐዋርያትን ሰዎች ማን ይሉኛል ለማለት ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ እንደጠየቃቸው ያለ ነው። በተጨማሪም ዳዊት መዝሙሩን ሲጽፍ በዋናነት ስለአሥር አርእስቶች ነው። ከእነዚህ መካከል መዝሙር 19ኝን ስለሕዝቅያስ ተናግሮታል።

▶️፳፩. መዝሙረ ዳዊት ሁሉንም ቅዱስ ዳዊት አይደለም የጻፈው ሌሎች አባቶችም ጽፈውታል ይባላል? እውነት ነው? እውነት ከሆነስ ዳዊት የጻፈው ስንት ምዕራፍ/ቁጥር ነው ሌሎችስ የጻፉት እነማን ይባላሉ? ስንት ምዕራፍ ጽፈዋል?

✔️መልስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትም የሚለው እንዲሁ ነው። ሙሉውን ዳዊት እንዳልጻፈው ገልጿል። በዝርዝር ይህን ዳዊት ጽፎታል። ይህን ደግሞ እርሱ አልጻፈውም ብሎ ከመግለጽ ግን ተቆጥቧል። ሌሎቹ ጸሓፍያን እነማን ናቸው ለሚሉት ዳዊት ራሱ ከመደባቸው ከ288ቱ መዘምራን መካከል እንደሆኑ ፍንጭ ይጽፋል። መጽሐፍ ቅዱሱ በዚህ ዙሪያ ዝርዝር ጉዳይ ስላልጻፈልን አለማወቅ ይገድበናል።

▶️፳፪. "በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው" ይላል (መዝ.11፥6)። የእግዚአብሔር ቃላት ያላቸው አሠርቱን ትእዛዛት ነው ወይስ ሌላ? የነጹ ናቸው ሲልስ ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ ቃለ እግዚአብሔር ያለው አካላዊ ቃልን ነው። ለዚያ ነው ሊቃውንቱ ሲያትቱ ከሐሰት ከዝርውነት ንጹሕ ነው ብለው ያተቱት። ይህ ማለት ጻድቅ አካላዊ ነው ማለት ነው። ለትምህርተ እግዚአብሔር ቢጠቀስም ይሆናል። የእግዚአብሔር ትምህርት ሐሰት የሌለበት ንጹሕ የሚያነጻ ነውና። የነጹ ናቸው ማለት ጉድፍ የሌለባቸው የጠሩ ናቸው ማለት ነው።

▶️፳፫. "በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ" ይላል (መዝ.11፥8)። ምን ለማለት ይሆን?

✔️መልስ፦ በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ማለት ክብር የሌለው ወራዳ ሰው ከፍ ባለ ጊዜ ማለት ሀብትን ሥልጣንን ዕውቅናን ባገኘ ጊዜ ክፉ ሰዎች በዙሪያው ይመላለሳሉ ማለት ነው።

▶️፳፬. "የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ" ይላል (መዝ.13፥2)። እግዚአብሔር የሰውን ሥራ ሁሉ የሚያውቅ ሆኖ እያለ "ያይ ዘንድ፣ ከሰማይ ተመለከተ" ሲል እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ሁሉን ያያል። ሁሉንም ይመለከታል። ሁሉን ማየቱንና መመልከቱን እንድንረዳ በሰውኛ ያይ ዘንድ፣ ተመለከተ ተብሎ ተገልጿል። ምሥጢሩ በዘመኑ የነበሩ የሰዎችን ምግባር መረመረ ማለት ነው።

▶️፳፭. "ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ ያዕቆብ ደስ ይለዋል። እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል" ይላል (መዝ.13፥10)። ስለምን የተነገረ ቃል ነው? ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ስለእስራኤላውያን የተነገረ ነው። ከዳዊት ንግሥና በኋላ ዘመን እስራኤላውያን በኃጢአታቸው እንደሚማረኩና በኋላም ከምርኮ እንደሚመለሱ ለዳዊት ተገልጾለት ተናግሮታል። እግዚአብሔር ምርኮን ሲመልስ እስራኤላውያን ደስ ይላቸዋል ማለት ነው። ከጽዮን መድኃኒትን ማን ይሰጣል ብሎ ጠይቋል። በኋላ መድኃኒትን የሚሰጥ እግዚአብሔር መሆኑን ቀጥሎ ገልጾታል።

▶️፳፮. "አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?" ይላል (መዝ.14፥1)። እዚህ ላይ ድንኳንና የተቀደሰ ተራራ የተባሉ ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ በዚህ አግባብ ድንኳን ያለው የእግዚአብሔርን ረድኤት ሲሆን የተቀደሰ ተራራ የተባለች ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት። ነቢይ በባቢሎን ምርኮ ሆኖ በኢየሩሳሌም ማን ያድር ይሆን ብሎ ሲጠይቅ መንፈስ ቅዱስ ቀጥለው ከቁጥር ሁለት ጀምሮ የተዘረዘሩትን መልካም ሥራዎች የሚሠራ ሰው ከምርኮ ወጥቶ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለስ ገልጿል።

▶️፳፯. "ፈቃድህ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው። ወደ ሌላ ለሚፋጠኑት መከራቸው ይበዛል። የቍርባናቸውን ደም እኔ አላፈስሰውም። ስማቸውንም በከንፈሬ አልጠራም" ይላል (መዝ.15፥3-4)። ፈቃድህ ያለው ምኑን ነው? ዳዊት የቍርባናቸውን ደም እኔ አላፈስሰውም ስማቸውንም በከንፈሬ አልጠራም ሲልስ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ፈቃድህ ያለው መከራ እንደሆነ መተርጕማን ገልጸዋል። በቅዱሳን የሚያመጣባቸው መከራ ጸጋቸው ይበዛ ዘንድ ነው። ቅዱሳንም ሳያጕረመርሙ ደስ ብሏቸው ይቀበሉታል። ዳዊት የጣዖታትን እንኳንስ ግብራቸውን ልሠራ ስማቸውን እንኳ አልጠራም ማለቱ ነው። የቍርባናቸውን ደም አላፈስስም ማለቱ ለጣዖት አልሠዋሁም ከጣዖት አምላኪዎችም ጋር አልተባበርኩም ማለቱ ነው።

▶️፳፰. መዝ.፲፮፥፭ ሰኰናዬ እንዳይናወጥ አረማመዴን በመንገድህ አጽና ሲል ሰኰና ምንድን ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Feb, 20:03


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 134 💙💙

▶️፩. መዝ.15፥2 ላይ "እግዚአብሔርን አልሁት አንተ ጌታዬ ነህ በጎነቴን አትሻትምና" ይላል። በጎነቴን አትሻትምና ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሰው ክፉ ሥራ ቢሠራ ራሱ ይጎዳል። በጎ ሥራ ቢሠራ ደግሞ ራሱ ይጠቀማል። የሰው ክፉ ሥራ እግዚአብሔርን የሚጎዳው ነገር የለም። የሰው በጎ ሥራም ለእግዚአብሔር የሚጠቅመው ነገር የለም። ይህን ለመግለጽ በጎነቴን አትሻትም አለ።

▶️፪. መዝ.17፥35 ላይ "ቀኝህም ተቀበለኝ" ይላል። ቀኝህም የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ለእግዚአብሔር ቀኝ ሲነገር ረድኤት፣ ሥልጣን ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ ቀኝህም ተቀበለኝ ማለት ሥልጣንህ ረድኤትህ ተቀበለኝ ማለት ነው።

▶️፫. መዝ.17፥46 የመድኃኒቴ አምላክ ሲል ምን ማለት ነው? መድኃኒቴ ወይም አምላኬ አልያም መድኃኒቴና አምላኬ ቢል ያሰኬዳል። መድኃኒቴ እና አምላኬ አንድ ወገን ስለሆኑ እንዴት የመድኃኒቴ አምላክ ይላል?

✔️መልስ፦ የመድኃኒቴ አምላክ ማለት ድኅነቴን የሚያደርግልኝ አምላክ ማለት ነው። ለብቻው መድኃኒቴ ብሎ ከመጣም ያስኬዳል የሚያድነን እርሱ ነውና። ለብቻው አምላኬ ብሎ ቢመጣም ያስኬዳል ፈጥሮ የሚገዛን እርሱ ነውና። የመድኃኒቴ አምላክ ብሎ ሲመጣ ግን ድኅነትን የሚያደርግልኝ አምላክ ተብሎ ይተረጎማል።

▶️፬. መዝ.18፥2 ላይ ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ትናገራለች ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ዕለት አፍ ኖሮት ለቀጣዩ ዕለት ነገርን ነገረው ማለት አይደለም። ነገር ግን ሰው በዕለተ እሑድ በዕለተ ሰኑይ እነዚህ ፍጥረታት ተፈጠሩ እያለ የሚናገር ስለሆነ የሰውን ነገር ለዕለት አድሎ ተናገረ። ይህንን ሊቃውንት በምሥጢር የሐዲስ መምህራን ለሐዲስ ምእመናን፣ የብሉይ መምህራን ለብሉይ ምእመናን ነገረ እግዚአብሔርን አስተማሩ ማለት ነው ብለውታል።

▶️፭. መዝ.17፥46 ላይ የመድኃኒቴ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል ሲል ምን ማለት እንደሆነ ያብራሩልን።

✔️መልስ፦ እግዚአብሔርን ብዙ ቦታ ላይ ከፍ ከፍ ይበል ሲል ቢገኝ ከፍ ያለ ዐቢይ ነው ማለት እንደሆነ መረዳት ይገባል። እንጂ ከፍ ያላለ ሆኖ በእኛ ንግግር ከፍ የሚል ነው ማለት አይደለም።

▶️፮. ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር ሲል ማን ነው የመዘምራን አለቃ የተባለው?

✔️መልስ፦ የመዘምራን አለቃ የተባለ አሳፍ ነው። ዳዊት ደብተራ ኦሪትን (ቤተ መቅደስን) በተራ እንዲያገለግሉ 288 መዘምራንን መድቧል። እና አሳፍ በተራው ሊዘምረው ዳዊት የተናገረው መዝሙር ይህ ነው ለማለት የተገለጸ ነው።

▶️፯. መዝ.18፥8 ላይ "የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው። ልብንም ደስ ያሰኛል" ይላል። መና*ፍ//ቃ-ን ብዙውን ጊዜ ሥርዓት ምን ያደርጋል? ሥርዓት አያድንም! ይላሉና ይህ እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ ሥርዓትን የሠራ እግዚአብሔር መሆኑ ከተገለጸ ከእግዚአብሔር ሐሳብ የሚቃረኑ ሐሳቦችን መቀበል አይገባም። የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ማለት ከጥሩ መዳረሻ የሚያደርስ ነው ማለት ነው። እግዚአብሔር በሠራልን ቅን ሥርዓት አለመሄድ ግን ከጥሩ መዳረሻ እንዳንደርስ ያደርገናል።

▶️፰. መዝ.11፥1 አቤቱ ደግ ሰው አልቋልና ከሰው ልጅ መተማመን ጠፍቷና ሰዎች እርስ በእርሳቸው የሽንገላን ነገር እንደሚናገሩ ይናገራል። ይህ ቃል የተነገረው ትንቢት ነው ወይስ በዚያን ዘመን ሰዎች ይበድሉ ነበር?

✔️መልስ፦ ከአርእስቱ ይህንን ትንቢት በእንተ ሳምኒት ዘመን (ስለ ስምንተኛው ሺ የተነገረ ትንቢት) ብሎታል። በተጨማሪም ዳዊት በዘመኑ ስለደረሰበት ነገር ተናግሮታል። አንዳንድ ትንቢቶች ሁለትና ከዚያ በላይ ሐሳብን ማስተላለፍ የሚችሉ ናቸው። ዳዊት አቤቱ ደግ ሰው አልቋል ያለው ከአሳዳጁ ከሳኦል ወገን ደግ ሰው አልቋል ማለቱ ነው። ከሰው ልጅ መተማመን ጠፍቷል ያለው በዘመኑ በእርሱ የደረሰበት ጉዳይ ነው።

▶️፱. መዝ.፲፭፥፬ ላይ ''ደዌያቸው በዛ ከዚያም በኋላ ተፋጠኑ በደም ማኅበራቸው አልተባበርም" ይላል። የእነማን ደዌ ነው የበዛው? ተፋጠኑ ሲልስ?

✔️መልስ፦ በጠቅላላው ኃጥኣንን ለመግለጽ ነው። ደዌ ያለው በግሥ ተናግሮት ነው እንጂ ኃጢአት ለማለት ነው። ተፋጠኑ ማለት ኃጥኣን ኃጢአትን ለመሥራት ፈጠኑ ማለት ነው።

▶️፲. መዝ.፲፭፥፮ ላይ ''ይይዙኝ ዘንድ ገመድ ጣሉብኝ ርስቴ ግን ተያዘልኝ'' የሚለው ቢብራራ።

✔️መልስ፦ ይህን የተናገረው ዳዊት ነው። እነሳኦል እኔን ይይዙኝ ዘንድ ምክር መከሩብኝ ጦር አዘመቱብኝ ማለት ነው። ርስቴ ግን ተያዘልኝ ማለቱ እነ ሳኦል ቢያሳድዱኝም ከሳኦል ቀጥየ የምነግሥ እኔ ነኝ ማለቱ ነው። ርስቴ ያላት መንግሥቱን ነው።

▶️፲፩. መዝ.፲፭፥፯ ላይ ''በሌሊት ኩላሊቶች ይገሥጹኛል'' ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የግእዙ የተሻለ ትርጉም ነው። ወዓዲ ሌሊተኒ ገሠጸኒ ኵልያትየ ይላል። ባለቤቱን እግዚአብሔር አድርጎ ኵልያትየን ተሳቢ ያደርገዋል። ይህም በኵላሊት መላውን ሕዋሳት ወክሎ መናገሩ ነው። ሳኦልን በሌሊት ገድዬ፣ አትግደል የሚለውን ሕግ አፍርሼ በፍዳው እንዳልያዝ አትግደል የሚለውን ሕግ አሳስቦ ሰውነቴን የጠበቀልኝ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ማለት ነው።

▶️፲፪. መዝ.፲፭፥፲፩ ላይ ''በቀኝኽም የዘላለም ፍስሓ አለ'' ይላል። ቀኝ ሲል ምን ማለት ነው? መዝ.፲፮፥፯ ላይ ''ቀኝህን ከሚቃወሟት'' የሚለውም ቢብራራ።

✔️መልስ፦ ቀኝ የሚለው ሥልጣን፣ ክብር ተብሎ እንደጊዜ ግብሩ ይተረጎማል። ለድንግል ማርያም ወትቀውም ንግሥት በየማንከ ተብሎ ሲነገር ነቢረ የማን (በቀኝ መቀመጥ) ምልጃን ያመለክታል። ለክርስቶስ ሲነገር በአብ ቀኝ ተቀመጠ ሲል በአምላካዊ ሥራ ጸንቶ መኖርን ያመለክታል። ከዚህ ቀኝህን ከሚቃወሟት የሚለው ሥልጣንህን ከሚቃወሟት ማለት ነው። በቀኝህ የዘለዓለም ፍሥሓ አለ ሲል ቀኝህ ያለው ክብርህ ለማለት ነው።

▶️፲፫. መዝ.፲፯፥፲፮ ላይ ''ከአርያም ላከ ወሰደኝም ከብዙ ውኆችም አወጣኝ'' ይላል። ላከ የተባለው ማነው የተላከውስ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር እጁን ከአርያም ላከ ማለት ረድኤቱን ሰጠ ማለት ነው። ከብዙ ውኆች አወጣኝ የሚለውም ከብዙ መከራ አዳነኝ ማለት ነው። ይህንን መተርጉማን ለነገረ ክርስቶስም ተርጉመውታል። ከአርያም ላከ ማለት አብ ልጁን ለተዋሕዶ ሰጠ ማለት ነው። ከብዙ ውኆች አዳነኝ ማለትም ወልድ ሥጋን ተዋሕዶ ሰውን ከአጋንንት፣ ከክፉ ፍትወታት አዳነ ማለት ነው።

▶️፲፬. መዝ.፲፯፥፴፬ ላይ ''ለክንዴም የናስ ቀስት አደረገ'' የሚለው ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የናስ ቀስት እንደማይበጠስና ጠንካራ እንደሆነ ሁሉ እጆቼ ቢወጉ ቢመክቱ እንዳይደክሙ የሚያደርጋቸው እግዚአብሔር ነው ይላል ዳዊት።

▶️፲፭. መዝ.17÷25-26 "ከጻድቅ ሰው ጋር ጻድቅ ትሆናለህ። ከቅን ሰው ጋርም ቅን ትሆናለህ። ከንጹሕም ሰው ጋር ንጹሕ ትሆናለህ። ከጠማማ ጋር ጠማማ ትሆናለህ" ይላል። ከጠማማ ጋር ጠማማ ትሆናለህ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ከደግ ሰው ጋር የዋለና ያደረ ሰው የደጉ ሰው ምግባር ስቦት እርሱም ደግነትን ተምሮ ደግ ይሆናል ማለት ነው። ከጠማማ ጋር ጠማማ ትሆናለህ የሚለው ደግሞ ከክፉ ሰው ጋር የዋለ ያደረ ሰው የክፉ ሰዎች ክፋት ተጋብቶበት እርሱም ክፋትን ይሠራል ማለት ነው።

▶️፲፮. መዝ.17፥36 አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ ሰኮናዬም አልደከመም ሲል ምን ማለት ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Feb, 04:04


መዝሙረ ዳዊት ክፍል 2

መዝሙር ፲፩፡- ደግ ሰው እንዳለቀ፣ ከሰው ልጆች መተማመን እንደጎደለ መገለጹ
-ሰዎች እርስ በእርሳቸው በሽንገላ ነገር ከንቱ ነገርን እንደሚናገሩ
-እግዚአብሔር የሽንገላ ከንፈሮችን እንደሚያጠፋቸው
-የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ነው መባሉ

መዝሙር ፲፪፡- የረዳንን እግዚአብሔርን ማመስገን እንደሚገባ

መዝሙር ፲፫፡- ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም እንደሚል
-እግዚአብሔር ለድኾች ተስፋቸው እንደሆነ

መዝሙር ፲፬፡- በቅንነት የሚሄድ፣ ጽድቅንም የሚያደርግ፣ በልቡም እውነትን የሚናር፣ በአንደበቱ የማይሸነግል፣ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ ሰው በተቀደሰው ተራራ እንደሚኖር

መዝሙር ፲፭፡- የእግዚአብሔር ፈቃዱ በምድር ባሉት ቅዱሳን እንደተገለጠ

መዝሙር ፲፮፡- ዳዊት እገዚአብሔርን ክብርህን በማየት እጠግባለሁ እንዳለው

መዝሙር ፲፯፡- እግዚአብሔር ኃይላችን፣ አምባችን፣ መድኃኒታችን፣ ረዳታችን እንደሆነ
-ዳዊት እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ከጠላቶቼ እድናለሁ እንዳለ
-ሰው ከጻድቅ ሰው ጋር ጻድቅ፣ ከቅን ሰው ጋር ቅን፣ ከጠማማ ጋር ጠማማ እንደሚሆን
-የእግዚአብሔር መንገዱ ንጹሕ እንደሆነ መገለጡ
-እግዚአብሔር ሕያውና ቡሩክ እንደሆነ

መዝሙር ፲፰፡- ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር እንደሚናገሩ
-የእግዚአብሔር ሕግ ንጹሕ እንደሆነና ነፍስንም እንደሚመልስ
-የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን እንደሆነ
-የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ እንደሆነና ዐይኖችንም እንደሚያበራ
-የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት እንደሆነ

መዝሙር ፲፱፡- በእግዚአብሔር በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንደምንል

መዝሙር ፳፡- እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ከፍ ያለ እንደሆነ

የዕለቱ ጥያቄዎች
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ነው
ለ. እግዚአብሔር ሽንገላን ይጠላል
ሐ. የሽንገላ ንግግር ጽድቅ ነው
መ. ሀ እና ለ
፪. ከሚከተሉት ውስጥ በተቀደሰው ተራራ የሚኖር ተብሎ የተገለጸው የትኛው ነው?
ሀ. በቅንነት የሚሄድና ጽድቅን የሚያደርግ
ለ. በአንደበቱ የማይሸነግልና በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ
ሐ. በልቡ እውነትን የሚናገር
መ. ሁሉም
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከእግዚአብሔር በቀር የባሕርይ አምላክ የለም
ለ. እግዚአብሔር ሕያውና ቡሩክ ነው
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም
፬. ስለ እግዚአብሔር ሕግ፣ ትእዛዝ እና ሥርዓት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ንጹሕ ነው
ለ. ብሩህ ነው
ሐ. ቅን ነው
መ. ሁሉም

https://youtu.be/9mQ3FG38JLA?si=0PK5Z1JYFPohJPNT

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Feb, 21:21


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 133 💙💙

▶️፩. መዝሙረ ዳዊት በ2000 እትም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እና የስልክ አፕ ላይ ያለው አንድ አንዴ ምዕራፉ ይለያያል። እንዲሁም አንዱ መምህር የሚጠቅሰውን ተመሳሳይ ቃል ሌላ መምህር ደግሞ ሌላ ምዕራፍ ላይ ቀጥሎ ያለውን ሲጠቅስ ይታያል። በተጨማሪም የሆነ መዝሙር ተጠቅሶ በቅንፍ እየተባለም ይነገራልና ልዩነቱ ከምን የመጣ ነው?

✔️መልስ፦ እውነት ነው። ሁለት ዓይነት አቆጣጠር አለ። አንደኛው ሰባው ሊቃውንት በተረጎሙበት መንገድ የሚቆጠር ነው። ይኸውም በሀገራችን የምንጠቀመው የመዝሙረ ዳዊት ቁጥሮች ማለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ የዕብራይስጡን መንገድ የያዘ አቆጣጠር ነው። የዕብራይስጡ መዝሙር ዘጠኝን ለሁለት ይከፍለዋል። ከቁጥር 1 እስከ ቁጥር 20 ያለውን መዝሙር ዘጠኝ ይለዋል። መዝሙር ዘጠኝ ከቁጥር 21 እስከ ቁጥር 38 ያለውን መዝሙር አሥር ይለዋል። ከዚህ በኋላ እስከ መዝሙር 146 ድረስ የዕብራይስጡ ከእኛ አንድ አንድ እየጨመረ ይሄዳል። ስለዚህ ጸሓፍያን የሁለቱንም ለመግለጽ በቅንፍ የሚገልጹበት ሁኔታ አለ። መዝሙር 147 ከእኛ በመዝሙር 146 የተገለጸውንና በመዝሙር 147 የተገለጸውን በአንድ ላይ ጨምሮ ቁጥሩን 20 አድርጎ ይጽፋል። በመዝሙር 148፣ በመዝሙር 149 እና በመዝሙር 150 ግን ሁለቱም ቅጂዎች ተመሳሳይ ናቸው።

▶️፪. «ተቆጡ ነገር ግን አትበድሉ» ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሁለት ዓይነት ቁጣ አለ። አንደኛው የሚገባና እግዚአብሔር የሚወደው ቁጣ ነው። ይኸውም ሕፃናት የተማሩትን ሲገድፉ፣ መና*ፍ//-ቃ*ን ሃይማኖታችንን ሲነቅፉ መቆጣት ይገባል። ከዚህ ውጭ ግን መቆጣት ስለማይገባ ቀጥሎ ነገር ግን አትበድሉ ተብሏል።

▶️፫. መዝ.2፥4 "በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል ጌታም ይሣለቅባቸዋል" ይላል። ጌታም ይሳለቅባቸዋል የተባሉት እነማን ናቸው? ጌታስ እንደ ሰው ይሳለቃልን?

✔️መልስ፦ ጌታም ይሳለቅባቸዋል የሚለው ቃል የተነገረው ስለኃጥኣን ነው። ጌታ እንደሰው የሚሳለቅ ሆኖ አይደለም። በሰው ልማድ በሰውኛ ይሳለቅባቸዋል ተብሎ ተገለጸ እንጂ ፍሬ ነገሩ ይፈርድባቸዋል ማለት ነው።

▶️፬. "ትእዛዙን እናገራለሁ እግዚአብሔር አለኝ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ። ለምነኝ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ። በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ። እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ" ይላል (መዝ.2፥7-9)። አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ የተባለው ማን ነው? ለምነኝ የተባለውስ ማን ነው? ትጠብቃቸዋለህ ተብሎ ለምን ትቀጠቅጣቸዋለህ ተባለ አይጋጭም? ከሆነስ ወልድን በሥጋው ወልዶታል?

✔️መልስ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኩህ የተባለ ክርስቶስ ነው። ተናጋሪው አብ ነው። ወልድ ቅድመ ዓለም ከአብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ተወልዷልና። ለምነኝ ማለቱ ወልድ አብን የሚለምን ሆኖ አይደለም ቅድመ ተዋሕዶ የሚለምን የነበረ ሥጋን እንደተዋሐደ ለማስረዳት የተነገረ ነው። ሥጋ ቃልን በተዋሕዶ ገንዘብ በማድረግ የሕዝብና የአሕዛብ ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነው። ስለዚህ ስለሥጋ እንግድነት ለምነኝ ተባለ። ቅድመ ተዋሕዶ ምንም የሌለው ሥጋ በተዋሕዶ የሁሉ ገዥ ባለቤት ሆኗል። ለምነኝ የተባለ ተለማኙ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ደግሞ የሦስቱም መጠሪያ ነው። አንሰ ሶበ እቤ እግዚአብሔር እብል በእንተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እንዲል። ትጠብቃቸዋለህ የተባለ ደጋጎችን ነው። ትቀጠቅጣቸዋለህ የተባለ ደግሞ አጋንንትን ክፉ ሰዎችን በሥልጣንህ ፈርደህ ታጠፋቸዋለህ ማለት ነው። በጊዜ ተዋሕዶ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብ ለቃል ስለሆነ የቃል ወልድነት ለሥጋ ገንዘቡ ስለሆነ ሥጋ ወልድ ተብሎ መጠራቱን ለመግለጽ ዮም ወለድኩከ ብሏል። ወልድየ ረሰይኩከ (ልጄ አደረግሁህ) ማለት ነው።

▶️፭. “ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው። በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው” ይላል (መዝ.8፥5)። ከመላእክት በጥቂት ያነሰበት በምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ይህ የተነገረው ስለክርስቶስ ትንቢት ነው። ክርስቶስ ከመላእክት ጥቂት አነሰ መባሉ በሥጋ በመሰቀሉ፣ ሕማምን በመቀበሉ ነው። በመላእክት ሕማመ ሥጋ የለባቸውምና። እንጂ በክብር ከመላእክት ያንሣል ማለት አይደለም። እርሱ የመላእክት ጌታ ነውና።

▶️፮. መዝ.2፥9 "እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀጠቅጣቸዋለህ" ይላል። ንባቡን ቢያስረዱን።

✔️መልስ፦ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ አጋንንትን እንደሚያጠፋ የሚገልጽ ቃል ነው። የሸክላ ዕቃ ከተሰበረ አይጠገንም። ከደቀቀ ደቀቀ ነው። ጌታም አጋንንትን በሞቱ በመስቀሉ እንዳጠፋልን የሚገልጽ አነጋገር ነው።

▶️፯. መዝ.3፥5 "እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም አንሥቶኛልና ተነሣሁ" ይላል። ንባቡን ቢያስረዱን።

✔️መልስ፦ ምሥጢሩ ስለክርስቶስ የሚናገር ነው። እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም ያለው በመስቀል ተሰቅሎ መሞቱን ያመለክታል። ሞት በእንቅልፍ ይመሰላልና። እግዚአብሔር አንሥቶኛልና ተነሣሁ ማለቱ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን ከሙታን መካከል መነሣቱን ያመለክታል። እግዚአብሔር አንሥቶኛል የሚለው በማስነሣት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ስለሆኑ አብ አስነሣው፣ መንፈስ ቅዱስ አስነሣው፣ በራሴ ሥልጣን ተነሣሁ ቢል ምሥጢሩ አንድ ስለሆነ ነው። አንሣኢ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ፣ ተንሣኢ ቃል በሥጋ ነው።

▶️፰. መዝ.8፥4 "ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጎበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?" ይላል። ንባቡን ቢያስረዱን።

✔️መልስ፦ ሰው በበደሉ ምክንያት እግዚአብሔርን ደጋግሞ ያሳዘነ ሆኖ ሳለ የሰውን ሥጋውን ነፍሱን ተዋሕደህ ታስነሣው ዘንድ ሰው ምንድን ነው ማለት ነው። በመጠይቅ አድርጎት ነው እንጂ ፍሬ ነገሩ በአሉታ ሲገለጽ ሰው በደለኛ ስለሆነ ይጎበኝ ዘንድ አይገባም ነበር ነገር ግን አንተ ቸር ስለሆንክ የሰውን ሥጋ ነፍስ ተዋሐደህ አዳንከን ማለት ነው።

▶️፱. መዝ.8፥5 "ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው" ይላል። እዚህ ላይ ከለልኸው ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ከለልከው ማለት አከበርከው ማለት ነው። ግእዝ ቀመስ አማርኛ ነው። ከለለ-ጋረደ፣አከበረ ከሚለው ቃል አክሊል፣ ተክሊል የሚሉ ባዕድ ዘሮች ይወጣሉ። ምሥጢሩ የሁለቱም ክብርን ያመለክታሉ። በአጭሩ በምስጋና ዘውድ ከለልከው ማለት አከበርከው ማለት ነው።

▶️፲. ንጉሥ ዳዊትን ጨምሮ ልጁ ሰሎሞንም ሌሎችም በሕይወት ታሪካቸው ስለ ዘማሪነታቸውና ጥበባቸው ተጽፏል። ስለ ጸሓፊነታቸው (ደራሲነታቸው) የተጻፈ አይመስለኝም። ጸሓፊ እንደሆኑና ስንት መጽሐፍ እንደጻፉ መች እንደጻፉ ለምን አልተነገረም?

✔️መልስ፦ ስለብዙ ቅዱሳን ታሪክ ስናነብ ሁሉ ነገራቸው አልተጻፈም። የአንዳንዶች ጥቂት ንግግሮቻቸው፣ ጥበቦቻቸው ተጽፎ ሲመጣልን የብዙዎች ግን አልተገለጸልንም። ዳዊትና ሰሎሞን ጸሓፍያን፣ ደራስያን በመንፈስ ቅዱስ እንደሆኑ ራሱ የጻፉት መጽሐፍ ምስክር ስለሆነ በተግባር የሚታይ ስለሆነ ለምን በቃል አልተነገረም አያሰኝም።

▶️፲፩. Psalms 1:5 Therefore the ungodly shall not stand in the judgment ሲል ኃጥኣን ለፍርድ ሳይቀርቡ ነው ወደ ሲኦል የሚወርዱት እንዴ?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Feb, 21:21


✔️መልስ፦ አይደለም። shall not stand in the judgment የሚለው በእግዚአብሔር ፊት የሚያቆም የባለሟልነት መልካም ሥራ የላቸውም የሚለውን ለመግለጽ ነው እንጂ በሞትም በምጽአትም ጊዜ ለፍርድ ቀርበው እግዚአብሔር ፈርዶባቸው ወደመከራ መቀበያ ቦታ ይገባሉ።

▶️፲፪. መዝ.9፥23 ኃጢአተኛ በነፍሱ ፈቃድ ይወደሳል። ዐመጸኛም ይባረካል ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አንዳንድ ኃጢአተኞችና ዐመፀኞች በክፉ ሥራቸው ርቀት፣ በረቀቀ ሤራ አካሄዳቸው ምንም እንኳ ያደረጉት ነገር ስሕተት ቢሆንም በአካሄዳቸው የሚያደንቃቸው ሰው ስላለ ያን ለመግለጽ ነው።

▶️፲፫. “በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ። እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ” ይላል (መዝ.2፥9)። እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ የሚለው እንዴት ይተረጎማል?

✔️መልስ፦ ሽክላ ሠሪ በጥራት ያልወጡ ሸክላዎች ካሉ ሰባብሮ አድቅቆ እንደገና ሌላ አዲስ ዕቃ ይሠራባቸዋል። እንደዚሁ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከአንዲት ባሕርየ ነፍስ የተፈጠረ ሰው ቢያጠፋ ሞት ፈረደበት። እንደገና በመስቀል ተሰቅሎ አዳነውና ወደቀደመ ቦታው መልሶ አድሶታል። ወብኪ ተሐደሰ አዳም ቀዳሜ ኵሉ ፍጥረት እንዲል።

▶️፲፬. "አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ? የምድር ነገሥታት ተነሡ። አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰሪያቸውን እንበጥስ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል" ይላል (መዝ.2፥1-3)። የአሕዛብ ማጕረምረም ምንድን ነበር? ወገኖች የተባሉስ እነማን ናቸው?ማሰሪያቸውን እንበጥስ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል ሲልስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ መዝሙር ሁለት ስለክርስቶስ የተነገረ ትንቢት (ትንቢት በእንተ ክርስቶስ) ነው። አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ ያለው አይሁድ ጌታን ስቀለው ስቀለው እያሉ ለምን ይናገራሉ ማለት ነው። የምድር ነገሥታት ተነሡ ማለት በክርስቶስ ስቅለት ዙሪያ ሄሮድስ፣ ጲላጦስ መከሩ ማለት ነው። ማሰሪያቸውን እንበጥስ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል የሚለው አይሁድ የምእመናንን ሕጋቸውን ሕገ ወንጌልን እናጥፋ ማለታቸውን የሚገልጽ ነው። ማሰሪያ ብዙውን አንድ እንደሚያደርግ ሕግም ሕዝብና አሕዛብን አንድ ያደርጋልና ነው።

▶️፲፭. "በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል። በመዓቱም ያውካቸዋል። እኔ ግን ንጉሤን ሾምኩ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ" ይላል (መዝ.2፥5-6)። በዚያን ጊዜ ያለው መች ማለት ነው? እኔ ግን ንጉሤን ሾምኩ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ ሲል ተናጋሪው ማነው? (ራሱ ዳዊት ነው እንዳንል ዳዊት ንጉሥ አልሾመም። እግዚአብሔር አብ ነው እንዳንል ንጉሤን ይላልና) ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በዚያን ጊዜ ያለው ከአርባ ዓመት በኋላ ማለትም በሰባ ዓመተ ምሕረት ነው። በዚህ ጊዜ ጥጦስ የተባለ ንጉሠ ሮም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ኢየሩሳሌምን አጥፍቷታልና። ሁለተኛው በዚያን ጊዜ ያለው በምጽአት ጊዜ ነው። ያንጊዜ ኃጥኣንን ሑሩ እምኔየ ርጉማን ብሎ ወደዘለዓለም ስቃይ ይመራቸዋልና። ንጉሤን ሾምኩ የሚለውን ቃል ግን በተሻለ የሚገልጸው ግእዙ ነው። "አንሰ ተሠየምኩ ንጉሠ በላዕሌሆሙ" ይላል። በእነርሱ ላይ ንጉሥነት ተሾምኩ ማለት ነው። ተሿሚው ሥጋ በተዋሕዶ ነው። ሥጋ ቃልን በመዋሐዱ ንጉሠ ነገሥት የባሕርይ ንጉሥ ሆኗልና ተሾምኩ ይላል። በዚህ ጊዜ ሿሚው ማን ነው ከተባለ ሥጋ በተዋሕዶ አምላክ ይሆን ዘንድ የሦስቱም አካላት የአንድነት የባሕርይ ግብር ነው። አማርኛው "ንጉሤ" ማለቱ በባለቤትነት ለመግለጽ ነው። ያነገሥኩት ለማለት ነው። በተቀደሰው ተራራ በጽዮን ላይ ሾምኩት ሲል ጽዮን የተባለች በምሥጢር ድንግል ማርያም ናት። አምላክ ሰው ሰው አምላክ የሆነው በእርሷ ማኅፀን ስለሆነ በጽዮን ሾምኩት ብሏል። በተጨማሪ ጽዮን የተባለች ኢየሩሳሌም ናት። ይህም ጌታ በኢየሩሳሌም ማስተማሩን ይገልጻል።

▶️፲፮. "በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል" ይላል (መዝ.3፥4)። እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ አለ። እዚህ ላይ የተቀደሰ ተራራ ያለው ምኑን ነው?

✔️መልስ፦ የተቀደሰ ተራራ የተባለች ለቅዱሳን በዘፈቀደ (በወደደ) የሚገለጽባትን ሰማያዊት መቅደሱን (መንበረ ስብሐትን) ነው። በምድር ደግሞ የተቀደሰ ተራራ የተባለችው ቤተክርስቲያን ናት። እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ያለና የሚኖር ስለሆነ የሁሉን ጸሎት በሁሉ ቦታ ቢደረግም የሚሰማ ቢሆንም በተለየ ጸጋውን የሚያድልባት ስለሆነ ቤተክርስቲያንን የተቀደሰች ተራራ ይላታል።

▶️፲፯. "እናንት የሰው ልጆች እስከ መቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ? እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ ዕወቁ" ይላል (መዝ.4፥3-4)። ልብ ማክበድ ምንድን ነው? እግዚአብሔር በጻድቁ ተገለጠ ሲባልስ?

✔️መልስ፦ ልብ ማክበድ ማለት የተሳሳተ ነገርን ይዞ በስሕተት ጸንቶ መቆየት ማለት ነው። በእውነት ላለማመን በሐሰት ጸንቶ መቆየት ማለት ነው። እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተገለጠ ዕወቁ የሚለው በጻድቁ በኖኅ በሌሎችም ቅዱሳን በተአምራትና በሌሎችም መልካም ነገሮች እንደሚገለጥ የሚገልጽ ነው።

▶️፲፰. "የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ። በእግዚአብሔርም ታመኑ። በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። አቤቱ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ" ይላል (መዝ.4፥5-6)። ይህ የጽድቅ መሥዋዕት የተባለ ምንድን ነው? የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ ሲልስ?

✔️መልስ፦ የጽድቅ መሥዋዕት የተባለ እውነት ነው። የጽድቅ መሥዋዕትን ሠዉ ማለት እውነትን ተናገሩ ማለት ነው። ሠዉ የሚለው ቃል በቅኔ መንገድ የተነገረ ነው። በቅኔ መንገድ ሰም ለወርቅ ማሠሪያ አንቀጽ ያተርፍለታል። ስለዚህ ሰሙ መሥዋዕትን ሠዉ ይሆንና ወርቁ እውነትን ተናገሩ ይላል ማለት ነው። የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ የሚለው የአካልህ መኖር ለእኛ ተገለጠ ማለት ነው።

▶️፲፱. "በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ። በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እጠብቃለሁም" ይላል (መዝ.5፥3)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በጠዋት መጸለይ እንደሚገባ የሚያሳስብ ቃል ነው። በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ ማለቱ ጸሎት አቅርቤ ጸሎቴን ትሰማኛለህ ማለት ነው። በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ ያለውም በማለዳ መሥዋዕትን እሠዋለሁ ጸሎትን እጸልያለሁ ማለት ነው።

▶️፳. "በሞት የሚያስብህ የለም በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?" ይላል (መዝ.6፥5)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በሞት የሚያስብህ የለም ማለት ሰው ከሞተ በኋላ ሥጋዊ ልመናን ማለትም ዝናም ለዘር ጠል ለመከር የሚልህ የለም ማለት ነው። በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው የሚለው በአሉታ ሲተረጎም የሚያመሰግንህ የለም ማለት ነው። ከዚህ ሲኦል ያለው መቃብርን ነው። በመቃብር ሥጋዊ ልመናን የሚያመሰግን የለም ማለት የዓመት ልብስ የዕለት ጉርስ ሰጠኝ ብሎ የሚያመሰግን የለም ማለት ነው።

▶️፳፩. "አቤቱ በመዓትህ ተነሥ በጠላቶቼ ላይ በቍጣ ተነሣባቸው። አቤቱ አምላኬ ባዘዝኸው ትእዛዝ ንቃ" ይላል (መዝ.7፥6)። እንደዚህ ርግማን የሚመስል ነገር ጠላቶቼ እንዲህ ይሁኑ (አጥፋቸው፤ ቅሠፋቸው) የሚል በዚህ በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ብዙ ቦታ ተጽፎ ይገኛል። ዳዊት በጠላቶቹ ላይ ክፉ ነገር እንዲያመጣባቸው እግዚአብሔርን የለመነው ይመስላል። እኛ ይህንና መሰሎቹን መዝሙራት ስንጸልይ ምን ብለን እንረ'ዳቸው? ባዘዝኸው ትእዛዝ ንቃ ሲልስ ምን ማለት ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Feb, 21:21


✔️መልስ፦ ባዘዝከው ትእዛዝ ንቃ የሚለው ትእዛዝ አዝዘህ ትእዛዝህን በማይፈጽሙ ሰዎች ፍረድባቸው ለማለት ነው። ዳዊት በዘመኑ ጠላቶቼ ያላቸው በንግሥናው ጊዜና ከዚያም በፊት በከንቱ በጠላትነት የተነሡበትን ሰዎችን ጨምሮ ነው። ጠላቶቻችንን እንዲያጠፋልን እኛም እንጸልያለን። እያወቁ የሚበድሉንን እርሱ ባወቀ እንዲያጠፋቸው፣ ባለማወቅ የሚበድሉንን እርሱ ባወቀ እንዲምርልን እንጸልያለን። በዋናነት በሐዲስ ኪዳን ላለን ሰዎች ዋና ጠላቶቻችን አጋንንት ስለሆኑ እነርሱን አጥፋልን ብለን እያሰብን እንጸልያለን።

▶️፳፪. "የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል። በእነርሱም ላይ ወደ ከፍታ ተመለስ" ይላል (መዝ.7፥7)። ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በምድር ላይ በክፉዎች እንደክፋታቸው ቢፈርድባቸው ለደጋጎች እንደ ደግነታቸው ቢፈርድላቸው የአሕዛብ ጉባኤ ይከብሀል ማለት ሁሉ ያምንብሀል ማለት ነው። በእነርሱም ላይ ወደ ከፍታ ተመለስ ማለት ፍረድ ማለት ነው።

▶️፳፫. "እግዚአብሔርን እንደ ጽድቁ መጠን አመሰግናለሁ። ለልዑል እግዚአብሔርም ስም እዘምራለሁ" ይላል (መዝ.7፥17)። እንደ ጽድቁ መጠን ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ እንደ ጽድቁ መጠን ማለት እግዚአብሔር እውነተኛ እንደመሆኑ ለእውነተኛነቱ እውነተኛ በመሆኑ ምስጋና አቀርባለሁ ማለት ነው።

▶️፳፬. "ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ። ስለ ጠላትህ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት" ይላል (መዝ.8፥2)። ስለዚህ ንባብ ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ይህም ትንቢት በእንተ ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ በዕለተ ሆሳዕና በአህያይቱ ውርንጭላ ተጭኖ ሲሄድ ሕፃናት ሆሳዕና በአርያም ለዳዊት ልጅ ምስጋና ይገባል እያሉ አመሰግነዋል። ለዳዊት ይህ በመጽሔተ ትንቢት ተገልጾለት ተናግሯል። ጠላትህን ለማጥፋት ያለው አጋንንትን ለማጥፋት ማለት ነው። ክርስቶስ ከጽንሰቱ ጀምሮ የአጋንንትን ሥራ በብዙ መልኩ አፈራርሷልና።

▶️፳፭. "ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ በጽዮን ልጅ በደጆቿ በማዳንህ ደስ ይለኛል" ይላል (መዝ.9፥14)። በጽዮን ልጅ በደጆቿ ያለው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የጽዮን ልጅ የሚላት ኢየሩሳሌምን ነው። ዳዊት ስለእግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ምስጋና ማቅረቡን ያመለክታል። ኢየሩሳሌምን የጽዮን ልጅ ማለቱ ጽዮን ቀድሞ ከነበራት ጥቂት ቦታ ተጨምሮባት ኢየሩሳሌም ተብላ ስለተመሠረተች ነው።

▶️፳፮. "ኃጥኣን እንዲህ አይደሉም። ነገር ግን ነፋስ ከገጸ ምድር ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው። ስለዚህ ዝንጉዎች በፍርድ ኃጥአንም በጻድቃን ምክር አይቆሙም" ይላል። ይህ ቃል ቢብራራ?

✔️መልስ፦ ትቢያ ነፋስ ከወሰደው በኋላ ከዚህ ደረሰ እንደማይባል ሁሉ ኃጥኣንም በዚህ ምድር ምንም እንኳ አለሁ አለሁ ቢሉም በሞት እንደሚነጠቁና በእግዚአብሔር ፍርድ እንደሚቀጡ ያመለክታል።

▶️፳፯. "የኃጢአተኛንና የክፉን ክንድ ስበር። የኃጢአቱንም ብድራት ክፈል ሌላ እስከማይገኝ ድረስ" ይላል (መዝ.10፥15)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የክፉ ሰዎችን ሥልጣን አጥፋ ማለት ነው። ክንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ሥልጣን ተብሎ ይተረጎማል። የኃጢአቱንም ብድራት ክፈል ማለት እንደ ኃጢአቱ ፍረድበት ማለት ነው።

▶️፳፰. "ለእግዚአብሔር በፍርሀት ተገዙ። በረዓድም ደስ ይበላችኹ" ይላል። ረዓድ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ረዓድ ርዕደ ተንቀጠቀጠ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ዘመድ ዘር ነው። ትርጉሙ መንቀጥቀጥ ማለት ነው። በአጭሩ ለእግዚአብሔር በመንቀጥቀጥ ተገዙ ማለት ነው።

▶️፳፱. "በእግዚአብሔር ታመንኹ ነፍሴን እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ተቅበዝበዢ እንዴት ትሏታላችኹ" ይላል (መዝ.10፥1)። እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ተቅበዝበዢ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ዳዊት ከሳኦል ቀጥሎ እንደሚነግሥ ብዙዎች ያውቁ ነበር። እና በዚህ ወቅት ከዳዊትም ከሳኦልም ለመወዳጀትና በሁለቱም ለመከበር አንዳንዶች ዳዊት በዚህ አደረ ብለው መረጃ ለሳኦል ይነግሩታል። ዳዊት ደግሞ በይፋ ሲነግሥ ይሾመናል ብለው ሳኦል ሊያሳድድህ ነው ይሉታል። በዚህ ጊዜ ዳዊት በእግዚአብሔር ታምኛለሁ እንደወፍ ከተራራ ተራራ እንድሸሽ ለምን ትነግሩኛላችሁ ብሎ ይገሥጻቸው ነበርና ይህን ለመግለጽ የተነገረ ቃል ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Feb, 17:01


💜 መጽሐፈ ኢዮብ ክፍል 8 💜

💜ምዕራፍ ፴፮፡-
-በጥበብ ብርቱና ኃያል የሆነ እግዚአብሔር እንደሆነ
-እግዚአብሔር ፍርድን ለጻድቃን እንደማያዘገይ
-የእግዚአብሔር የዘመኑ ቁጥር እንደማይመረመር

💜ምዕራፍ ፴፯፡-
-እግዚአብሔር ለፍጥረታት በየጊዜው ምግባቸውን እንደሚያዘጋጅ

💜ምዕራፍ ፴፰፡-
-እግዚአብሔር በደመናና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን እንዳናገረው

💜ምዕራፍ ፴፱፡-
-እግዚአብሔር ብዙ ነገሮችን እየጠቀሰ ኢዮብን እንደገሠጸው

💜ምዕራፍ ፵፡-
-ኢዮብ ከአንተ ጋር መናገር አይቻለኝም ብሎ ዝም ብሎ እግዚአብሔርን ይሰማ እንደነበር

💜ምዕራፍ ፵፩፡-
-እግዚአብሔርን ተከራክሮ በሕይወት የሚኖር እንደሌለ

💜ምዕራፍ ፵፪፡-
-ኢዮብ እኔ አፈርና አመድ እንደሆንኩ አውቃለሁ ማለቱ
-እግዚአብሔር ሦስቱን የኢዮብ ወዳጆች ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት በጎችን ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ እርሱ የሚቃጠል መሥዋዕትን ያሳርግላችሁ ኢዮብም ስለ እናንተ ይጸልይ እኔም ፊቱን እቀበላለሁ ስለ እርሱ ባይሆን ባጠፋኋችሁ ነበር እንዳላቸው
-ኢዮብ እንደዳነና እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋላውን እንደባረከለት

💜💜💜የዕለቱ ጥያቄዎች💜💜💜
፩. ስለ ልዑል እግዚአብሔር ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. የዘመኑ ቁጥር አይመረመርም
ለ. ለእንስሳት በየጊዜው ምግባቸውን ያዘጋጃል
ሐ. እርሱ ያልፈጠራቸው አንዳንድ ፍጥረቶች አሉ
መ. ሀ እና ለ
፪. እግዚአብሔር ሦስቱን የኢዮብ ወዳጆች ይቅር ያላቸው በምን ምክንያት ነው?
ሀ. ኢዮብ ስለጸለየላቸው
ለ. በራሳቸው ጸሎትና መሥዋዕት
ሐ. ኢዮብን በመገሠጻቸው
መ. ለ እና ሐ

https://youtu.be/6eV8vkxYAtQ?si=0kB440uVHQCv4CLq

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Feb, 16:46


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 131 💙💙

▶️፩. "ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ። እንግዲህስ ቈንጆይቱን እንዴት እመለከታለሁ?" ይላል (ኢዮ.31፥1)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ ማለት ዓይኔ የሌላ ሰው ሚስት አይታ እንዳትበድል (እንዳታመነዝር) ከዐይን ምንዝር ከለከልኳት ማለት ነው። እንግዲህስ ቆንጆይቱን እንዴት እመለከታለሁ የሚለው እንግዲህ ከሚስቴ ውጭ ያለችን ቆንጆ አልመለከትም ማለቱ ነው።

▶️፪. "ሚስቴ ለሌላ ሰው ትፍጭ። ሌሎችም በእርሷ ላይ ይጎንበሱ" ይላል (ኢዮ.31፥10)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ኢዮብ እንዲህ ካደረግሁ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብኝ እያለ የተናገረው ቃል ነው። ፍሬ ሐሳቡ ኃጢአትን ብሠራ ሚስቴ ለሌላ ሰው ትፍጭ ማለት የሌላ ሰው ሚስት ሆና ታገልግል ማለት ነው።

▶️፫. "ፀሐይ ሲበራ ጨረቃ በክብር ስትሄድ አይቼ ልቤ በስውር ተታልሎ አፌም እጄን ስሞ እንደ ሆነ" ይላል (ኢዮ.31፥26-27)። ምንን ለመግለጽ ነው?

✔️መልስ፦ ፍሬ ነገሩ ቀን በፀሐይ ሌሊት በጨረቃ በድዬ ከሆነ ማለት ነው። አፌም እጄን ስሞ እንደሆነ የሚለው አገላለጽ አፌን ዝም ለማሰኘት እጄን ጭኜ እንደሆነ ማለት ነው። መናገር ያለብኝን ሳልናገር ቀርቼ እንደሆነ ለማለት ነው።

▶️፬. "እርሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ እንደ ሆነ ትልሞቿም በአንድ ላይ አልቅሰው እንደ ሆነ" ይላል (ኢዮ.31፥38)። እርሻና ትልም የተባሉ ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ እርሻዋ በእኔ ላይ ጮኻ እንደሆነ ማለት በእርሻዋ ዘር ሳልዘራባት ቀርቼ እንደሆነ ማለት ነው። ትልሞቿ በአንድ ላይ አልቅሰው እንደሆነ ማለት ድንበር ገፍቼ እንደሆነ ማለት ነው። እርሻ ትልም ያለው በቁሙ እርሻ ትልምን ነው።

▶️፭. "እርሱ ልቡን ወደ ራሱ ቢመልስ፥ መንፈሱንና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፥ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል" ይላል (ኢዮ.34፥14-15)። ለእግዚአብሔር ልብ፤ መንፈስና እስትንፋስ ሲባል እንዴት ይተረጎማል?

✔️መልስ፦ ለእግዚአብሔር ልብ፣ መንፈስ፣ እስትንፋስ የሚሉት ቃላት ሲነገሩ በሁለት መልኩ ይተረጎማሉ። አንደኛው አካላዊ ልብ አብ፣ አካላዊ እስትንፋስ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ይተረጎማል። ሁለተኛው ከዚህ ከተጠቀሰው ኃይለ ቃል በተነገረው መልኩ ሲቀርብ በአፍኣዊ ግብር ለፍጡራን ይተረጎማል። ለምሳሌ እግዚአብሔር ለፍጡራን ሕይወት ነው ወይም እስትንፋስ ነው ሲባል ፍጡራን ሕያው ሆነው የሚኖሩት በእርሱ ነው ማለት ነው። ልብ ነው ሲባል ደግሞ ፍጡራን በእግዚአብሔር ለባውያን ሆነው መኖራቸውን መግለጽ ነው። መንፈስ ነው የሚለው የእግዚአብሔርን ረቂቅነት ያመለክታል።

▶️፮. "በኃጢአቱም ላይ ዐመፅን ጨምሯልና፥ በእኛም መካከል በእጁ ያጨበጭባልና" ይላል (ኢዮ.34፥37)። በእጁ ያጨበጭባል ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በእጅ ማጨብጨብ ትእምርተ ፍሥሓ (የደስታ ምልክት) ነው። ኃጥእ ሰው ኃጢአት ሠርቶ በኃጢአቱ ለጊዜው በሰዎች መካከል መደሰቱን የሚገልጽ ቃል ነው።

▶️፯. "ከራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ የኤሊሁ ቍጣ ነደደ። ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው" ይላል (ኢዮ.32፥2)። ሰው ራሱን ከፍ ማድረጉ ኃጢአት አይሆንበትምን?

✔️መልስ፦ ኢዮብ ራሱን ከእግዚአብሔር አስበልጦ ጻድቅ ነኝ አላለም። ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበር የሚለው አገላለጽ በእግዚአብሔር ፊት ምንም በደል የለብኝም ይል ነበር ማለቱ ነው። የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ግን በገቢር ባትሠራ በኀልዮ ንጹሕ አትሆንም ብሎ ገሥጾታል። እግዚአብሔርም የኤሊሁን ተግሣጽ ወዶለታል። በየትኛውም መሥፈርት ሰው በትሕትና መኖር እንጂ ራሱን ከፍ ማድረግ አይገባውም።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Feb, 11:12


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 130 💙💙

▶️፩. ምድር በውሃ ላይ እንደጸናች ዳዊት ይናገራል። ኢዮ.26፥7 ላይ ግን በባዶ ላይ እንደተንጠለጠለች ይናገራል። አይጋጭም ወይ? በምድር እና ከመሬት በታች ያለው ውሃ ምን ያህል ይራራቃሉ?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ምድር በውሃ ላይ ጸንታ ትኖራለች። በመሬትና በውሃ መካከል ደግሞ ምንም ዓይነት ክፍተት (Space) የለም። በመጽሐፈ ኢዮብ ምድር በባዶ ላይ እንደተንጠለጠለች መገለጹ ከመሬት በታች ያሉትን ውሃውንም፣ እሳቱንም፣ ነፋሱንም የምድር አካል አድርጎ ቆጥሮ ነው። ይኸውም በባዶ ላይ ተንጠለጠለች ማለት ከእነዚህ በታች ሌላ ዓለም የለም። በእግዚአብሔር ዓለምነት ትኖራለች ለማለት ነው። እግዚአብሔር ዓለማተ ዓለም መባሉ ለዚህ ነውና።

▶️፪. "ለዝናብም ሥርዓትን፥ ለነጎድጓድ መብረቅም መንገድን ባደረገ ጊዜ በዚያን ጊዜ አያት፥ ገለጣትም፤ አዘጋጃትም፥ ደግሞም መረመራት" ይላል (ኢዮ.28፥26-27)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አያት፣ ገለጣት፣ አዘጋጃት እየተባለች የተገለጸች ለጊዜው ምድር ናት። በምሥጢር ለሥጋዌ ይተረጎማል። በተጨማሪም የመንፈስ ቅዱስ ለምእመናን በመሰጠት ይተረጎማል።

▶️፫. "በማስተዋሉም ረዓብን ይመታል። በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ። እጁም በራሪይቱን እባብ ወጋች" ይላል (ኢዮ.26፥12-13)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በማስተዋሉ አጋንንትን እንደሚያጠፋ፣ የሰማያት ውበት ከእግዚአብሔር የተገኘ እንደሆነ፣ በራሪ እባብ የተባለ ዲያብሎስን በመስቀሉ ያጠፋም እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ረዓብ ዘማን ዝሙት ያሠራ የነበረውን ጋኔን ያጠፋ ማለት ነው። በስመ ኀዳሪ ይጼዋዕ ኀዳሪ ወበስመ ማኅደር ይጼዋዕ ማኅደር በሚለው ነው።

▶️፬. "ድንጋይዋ እንደ ሰንፔር ወርቋም እንደ አፈር የሆነ መሬት አለች። መንገዷን ወፍ አያውቀውም የንስርም ዐይን አላየውም። የትዕቢተኞች ልጆች አልረገጧትም። ደቦል አንበሳም በውስጧ አላለፈባትም" ይላል (ኢዮ.28፥6-8)። ሰንፔር ምንድን ነው? የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሰንፔር የዕንቍ ዓይነት ነው። የከበረ ድንጋይ ነው። ትርጉሙ ወርቅ እንደ አፈር በዝቶ የሚገኝበት ሀገር አለ ማለት ነው። ንስር ወፍ የተባለ ዲያብሎስ ነው። ስለዚህ ዲያብሎስ ያላሳሳታት ሰብእና ጻድቃን (የጻድቃን ሰውነት) አለች ማለት ነው። በተጨማሪም ሰይጣን የማይገባባት ገነት መንግሥተ ሰማያት አለች ማለት ነው። የትዕቢተኞች እግር አልረገጣትም ማለት አጋንንት ወደ መንግሥተ ሰማያት አይገቡም ማለት ነው።

▶️፭. ስለ ጥበብ እየተናገረ ሄዶ "በሰው ሁሉ ተረስታለች ከሰማይ ወፎችም ተሰውራለች። ሞትና ሲኦል ወሬዋን በጆሮዎቻችን ሰማን ብለዋል" ይላል (ኢዮ.28፥21)። ከሰማይ ወፎችም ተሰውራለች የሚለው ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው? ሞትና ሲኦል ሰማን ሲሉስ እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ የሰማይ ወፎች የተባሉ አጋንንት ናቸው። ጥበብ መንፈሳዊ ከአጋንንት ተሰውራለች ማለት አጋንንት ጥበብ መንፈሳዊ የላቸውም። ሞት ሞት ነው። ሲኦል ያለው መቃብርን ነው። ሞትና ሲኦል የጥበብን ወሬዋን ሰማን አሉ ይላል። ሞትና ሲኦል የተባሉ ሄኖክና ኤልያስ ናቸው። በሞት ሞት፣ በሲኦል ሲኦል ሆነውበታልና። ሄኖክና ኤልያስ የጥበብን የወልድን የጸጋ መንፈስ ቅዱስን ዜናቸውን ሰማን አሉ ማለት ነው።

▶️፮. ኢዮ.28፥19 ላይ የኢትዮጲያ ቶጳዛዮን አይተካከላትም ይላል። ቶጳዝዮን ማለት ምሳሌው ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ሉል አይተካከላትም። በጥሩም ወርቅ አትገመትም ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ቶጳዝዮንን ሉል ብሎ ይተረጉመዋል። የዕንቍ ዓይነት ነው። ጥበብ ከዕንቍ ትበልጣለች ማለት ነው። በጥሩም ወርቅ አትገመትም ማለት ጥበብ ከወርቅም በላይ ናት ማለት ነው።

▶️፯. "ስለዚህም ሕማሜ መሰንቆ ልቅሶዬም በገና ሆነብኝ" የሚለው ትርጉሙ ቢብራራ?

✔️መልስ፦ መሰንቆና በገና እንደሚያጫውቱ ሁሉ መከራ አጫወተኝ ማለት ነው። ይኸውም መከራ ጸናብኝ ልቅሶዬም በዛ ማለት ነው።

▶️፰. "ሙታን ሰዎች ከውሆች በታች፥ በውሆችም ውስጥ ከሚኖሩ በታች ይንቀጠቀጣሉ። ሲኦል በፊቱ ራቁቷን ናት። ለጥፋትም መጋረጃ የለውም" ይላል (ኢዮ.26፥5-6)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በእግዚአብሔር ፊት ሁሉ የተገለጠ መሆኑን ለመግለጽ ሲኦል በፊቱ ራቁቷን ናት ተብሏል። የሰውን ክፉ ሥራ ሁሉ አይቶ የሚፈርድ ስለሆነ ለጥፋትም መጋረጃ የለውም ተብሏል። የሁሉም ጥፋት በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጠ ነው ማለት ነው። ሙታን ሰዎች ያላቸው ከዚህ ላይ ኃጥኣንን ነው። ከውሆች በታች ይንቀጠቀጣሉ ማለት በሲኦል ይሰቃያሉ ማለት ነው።

▶️፱. "ሰው በእጁ ያጨበጭብበታል። ከስፍራውም በፉጨት ያስወጡታል" ይላል (ኢዮ.27፥23)። ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ስለ ኃጥእ ሰው የተነገረ ነው። ኃጥእን ሰው ሞት ድንገት ሲመጣበት አጋንንት በፉጨት ያስወጡታል ማለት ይሳለቁበታል ማለት ነው። ኃጥኡ በእጁ ያጨበጭባል መባሉ ቢነደው ቢቆጨው ያጨበጭባል አለ። ትእምርተ ቁጭት ነው። ቢነደው አጨበጨበ ማለት ነው።

▶️፲. "ሰው ለጨለማ ፍጻሜን ያደርጋል። የጨለማውንና የሞት ጥላን ድንጋይ እስከ ወሰኑ ድረስ ይፈላልጋል። ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ይቈፍራሉ። ከሰውም እግር ተረሱ። ከሰዎችም ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ። እንጀራ ከምድር ውስጥ ይወጣል። በእሳትም እንደሚሆን ታችኛው ይገለበጣል" ይላል (ኢዮ.28፥3-5)። ይህ ንባብ ግልጽ አልሆነልኝም ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ኃጥእ ሰው ሲሞት ፍጻሜው የሲኦል ጨለማ መሆኑን ይገልጻል። ሰው ከሚኖርበት ርቀው መውረጃ ቆፈሩ፣ ከሰው እግር ተረሱ፣ ከሰዎች ርቀው እየተንጠለጠሉ ይወዛወዛሉ የሚለው ሁሉም አንድ ወገን ነው። ክፉ ሰዎች ከጻድቃን ሰዎች ተለይተው ኃጢአትን ዝሙትን እንደሚሠሩ ያመለክታል። እንጀራ ከምድር ውስጥ ይወጣል። የተባለው መሬት እህልን ታበቅላለች ማለት ነው። በእሳትም እንደሚሆን ታችኛው ይገለበጣል ማለት ከመሬት በታች እሳት መኖሩን መግለጽ ነው። በተጨማሪም የብሉይ ሊቃውንት በትርጓሜ ልበ መምህራን በእሳተ መንፈስ ቅዱስ ይሞቃል ብለውታል።

▶️፲፩. "በነፋስ አነሣኸኝ በላዩም አስቀመጥኸኝ። በዐውሎ ነፋስ አቀለጥኸኝ" ይላል (ኢዮ.30፥22)። ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ይህን የተናገረው ኢዮብ ነው። ነፋስ ያለው መከራውን ነው። በነፋስ አነሳኸኝ ማለት በመከራ መታኸኝ ማለት ነው። በላዩ አስቀመጥከኝ ማለት በመከራው አቆየኸኝ። በዐውሎ ነፋስ አቀለጥከኝ ማለት ጽኑ ደዌን አመጣህብኝ ማለት ነው።

▶️፲፪. "ለቀበሮ ወንድም ለሰጎንም ባልንጀራ ሆንሁ" ይላል (ኢዮ.30፥29)። እዚህ ላይ ቀበሮና ሰጎን የምን ምሳሌዎች ናቸው?

✔️መልስ፦ ይህን ያለውም ኢዮብ ነው። ቀበሮና ሰጎን ከሰው ተለይተው በዱር እንደሚኖሩ ሁሉ ኢዮብንም ሲታመም ከሰው ለይተው ሜዳ ቀሳ አውጥተውት ስለነበረ አመሳስሎ ተናገረ።

▶️፲፫. "እርሱ ያዘጋጀው ይሆናል። ነገር ግን ጻድቅ ይለብሰዋል። ብሩንም ንጹሓን ይከፋፈሉታል" ይላል (ኢዮ.27፥17)። ይሄ ነገር ሃሳቡ ኃጢአተኛ የሠራውን ጻድቁ ይጠቀመዋል ነው አይደል? እንዲህ ከሆነ በራስህ ሠርተህ ብላ ከሚለው ሕግ ጋር አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ጻድቃን ሠርተው ይበላሉ። ኃጥኣን ሲሞቱ ደግሞ ጻድቃን ገንዘባቸውን ወርሰው ይኖራሉ። ርስትን መውረስ ምንም በደልነት የለውምና።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Feb, 11:12


▶️፲፬. "መንገዴ በቅቤ ይታጠብ በነበረ ጊዜ፥ ድንጋዩ የዘይት ፈሳሽ ያፈስስልኝ በነበረ ጊዜ" ይላል (ኢዮ.29፥6)። ምንን ለመግለጽ የተነገረ ቃል ነው?

✔️መልስ፦ የኢዮብን የቀድሞ ባዕለጸጋነት ለመግለጽ ነው። ላሞቹ ግትን አግተው በየተራራው ወተታቸው ይፈስ ነበርና ይህን ለመግለጽ ነው። ድንጋዩ የዘይት ፈሳሽ ያፈስስልኝ በነበረ ጊዜ ሲል ደግሞ የዘይት ግብር ሲመጣ በየተራራው ይፈስ ነበርና ይህን ለመግለጽ ነው።

▶️፲፭. ኢዮ.27፥8 በእግዚአብሔር የማያምን የማይድን መሆኑ የታወቀ ሆኖ ሳለ እንዴት እንጃ ብሎ ስለአለመዳኑ እርግጠኛ መሆን አልቻለም?

✔️መልስ፦ በእግዚአብሔር የማያምን አይድንም። እንጃ ማለቱ ጥርጣሬው ከሰዎች የመነጨ ነው። ይኸውም ካመኑ ሊድኑ ይችላሉና። መጨረሻ ላይ ይመኑ አይመኑ የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ ጸሓፊው የዕውቀት ውሱንነቱን እንጃ በማለት ገልጾታል።

▶️፲፮. ኢዮ.27፥9 በእግዚአብሔር የማያምን ሰው ጸሎት ይሰማልን?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ፍጥረታት ሁሉ ይመግባል። ለሁሉ ፀሐይን፣ ጨረቃን፣ ዝናምን ያወጣል። እግዚአብሔር የሁሉንም ጸሎት ይሰማል። እግዚአብሔር በልጅነት የሚሰጡ ጸጋዎችን የሚሰጥ ግን በተለየ ለሚያምን ሰው ብቻ ነው። ከእነዚህ ጸጋዎች ውጭ ያሉ ጸጋዎችን ግን ለለመነው ሁሉ ይሰጣል።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Feb, 10:38


እንኳን ደስ አለህ ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው
ዐይነ ልቡና
ዐይነ ልቡናን ረቂቁን ለማየት እድል ነበረኝ። እጅግ በጣም ጥሩ መጽሐፍ ነው። ነገረ ክርስቶስን እና ነገረ ማርያምን እንዲሁም ስለክህነትና ጥምቀት በጥሩ መንገድ የሚያብራራ መጽሐፍ ነው። በየጊዜው የሚጠየቁ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ልቡናን የሚያሳርፍ መጽሐፍ ነው።

ይህን መጽሐፍ አድነው ፈጥነው በእጅዎ ያስገቡ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Feb, 04:05


✝️ መጽሐፈ ኢዮብ ክፍል 7 ✝️

✝️ምዕራፍ ፴፩፡-
-ኢዮብ እግዚአብሔር ቅንነቴን ያውቃል ማለቱ

✝️ምዕራፍ ፴፪፡-
-ኢዮብ በሦስቱ ወዳጆቹ ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ሦስቱ ወዳጆቹ ከመናገር ዝም እንዳሉ
-ከአውስጢድ ሀገር የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ኢዮብንም ሦስቱን የኢዮብ ወዳጆችንም እንደተቆጣ

✝️ምዕራፍ ፴፫፡-
-ኤሊዩስ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ያስተምረኛል እንዳለ

✝️ምዕራፍ ፴፬፡-
-ጆሮ ቃልን ጉረሮ ምግብን እንደሚለይ መገለጹ
-በመከከላችን ምን እንደሚሻል እንወቅ መባሉ
-እግዚአብሔር ሁሉን እንደሚያይ መነገሩ

✝️ምዕራፍ ፴፭፡-
-ኢዮብ ራሱን በማጽደቁ ኤልዩስ እንደተቃወመው

✝️✝️✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️✝️✝️
፩. ኢዮብንና ሦስቱን የኢዮብ ወዳጆች የተቆጣቸው የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ማን ነው?
ሀ. በልዳዶስ
ለ. ኤሊዩስ
ሐ. ኤልፋዝ
መ. ሶፋር
፪. ከሚከተሉት ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ የሚለው ቃል የሚገኝ የት ነው?
ሀ. ኢዮ.32፣9
ለ. ኢዮ.33፣4
ሐ. ኢዮ.34፣3
መ. ኢዮ.31፣39
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. እግዚአብሔር ሁሉን አያይም
ለ. እግዚአብሔር ሁሉን ያያል
ሐ. እግዚአብሔር አስተዋይ ነው
መ. ከእግዚአብሔር የሚሰወር የለም

https://youtu.be/Sjtsb5p7xNQ?si=1hnOCtvGM2Ncbxf0

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

09 Feb, 09:08


ከሌላው በተለየ በዶክተር አንዱዓለም ሞት ያዘንንበት ምክንያት

፩. ትሕትና ምንድን ነው? መልካምነት ምንድን ነው? ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቀንና ለማስረዳት በጣም ብዙ ጊዜ የሚፈጅብን ከሆነ ትሕትናና መልካምነት ማለት የዶክተር አንዱዓለም ሰብእና ነው ብለን በቀላሉ እሱን አሳይተን ማስረዳት እንችል ስለነበር። ወደፊት ለሚነሣው ትውልድም ተግባራዊ ክርስትናን ያስተምርልን ነበር ብለን ነው ቁጭታችን።

፪. ማወቅ ምንድን ነው ብሎ ለሚጠይቀን ማወቅማ እንደ ዶክተር አንዱዓለም ነው ብለን ዕውቀትን በአካል ለማሳየት ዋና አርአያችን ስለነበረ ነው። በነገራችን ላይ በተመረቀባቸው የትምህርት ሂደቶች ሁሉ የወርቅ ሜዳሊስት ነበር። ይህ ደግሞ ሊደገም እንጂ ሊሻሻል የማይችል ታላቅ ሪከርድ ነው።

፫. ባህርዳር ዩንቨርሲቲ ዶክተር አንዱዓለም ሁልጊዜ እንዲታወስልንና በቋሚነት አርአያነቱ ለትውልዱ ሲነገር እንዲኖር የወሰናቸው ውሳኔዎች ደስ የሚያሰኙ ናቸው።

፬. ብዙ ዓለማቀፋዊ ጥሪዎችን ትቶ ሀገሩን ከፍ ለማድረግ ሲጥር በአጭር ተነጠቅን። ልጆቹን ባለቤቱን ለመርዳት በባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ አማካኝነት በዶክተር አንዱዓለም የቅርብ ጓደኞች የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች አሉ። በዚያ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።

፭. ሞት ለሁሉም ሰው የተሠራ ሕግ ነው። ሁላችንም ሟች ነን። ለቀጣዩ ትውልድ ግን የዶክተር አንዱዓለም መልካምነቶች ሲነገሩ ቢኖሩ ቀጣዩ ትውልድ ያተርፍባቸዋል።


የጥምር ሂሳብ ቁጥር ስም:-

1- ዶ/ር ኃይለማርያም አወቀ እንግዳው
2- ዶ/ር አምሳሉ ወርቁ መኮንን
3- ዶ/ር መኳንንት ይመር አድማሴ

የጥምር ሂሳብ ቁጥር:-

1. የንግድ ባንክ= 1000 676 116 978
2. የአዋሽ ባንክ= 013 200 903 947 800
3. የአቢሲኒያ ባንክ= 218 081 487
4. የአማራ ባንክ= 9900 037 383 825

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

09 Feb, 05:36


🧡 መጽሐፈ ኢዮብ ክፍል 6 🧡

🧡ምዕራፍ ፳፮፡-
-ኢዮብ ስለ እግዚአብሔር ታላቅነት መናገሩ

🧡ምዕራፍ ፳፯፡-
-ኢዮብ አንደበቴ ዐመፅን አይናገርም እንዳለ
-በእግዚአብሔር የማያምን እንደማይድን

🧡ምዕራፍ ፳፰፡-
-ብር የሚወጣበት ቦታ እንዳለ መነገሩ
-ብረት ከመሬት ውስጥ እንደሚወጣ መነገሩ

🧡ምዕራፍ ፳፱፡-
-ኢዮብ ያደረገውን መልካም ሥራ መዘርዘሩ

🧡ምዕራፍ ፴፡-
-ኢዮብ መከራውን እያሰበ መናገሩ

🧡🧡🧡የዕለቱ ጥያቄ🧡🧡🧡
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው
ለ. ከክፉ መራቅ ማስተዋል ነው
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/5gvFM10jyvU?si=41j3h4OUb4rYadWY

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

08 Feb, 19:12


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 129 💙💙

▶️፩. "ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን?" ይላል (ኢዮ.22፥3)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ማለት የእግዚአብሔር ደስታ ባሕርያዊ ነው በእኛ ጻድቅ መሆንና አለመሆን የሚለዋወጥ ደስታ አይደለም ማለት ነው። እኛ ንጹሕ ጻድቅ ብንሆን የምንጠቀመው እኛ ነን። እኛ ክፉ ኀጥእ ብንሆን የምንጎዳው እኛ ነን። እኛ ጻድቅ ብንሆን እግዚአብሔር የሚያገኘው ልዩ ደስታ የለምና። እኛ ኃጥእ ብንሆንም እግዚአብሔር የሚያገኘው ልዩ ኀዘን የለምና።

▶️፪. "በውኑ ኃጢአተኞች ሰዎች የረገጧትን የዱሮይቱን መንገድ ትጠብቃለህን?" ይላል (ኢዮ.22፥15)። የዱሮይቱ መንገድ ያላት ምንድን ናት?

✔️መልስ፦ እኔጋ ያለው ቅጂ ጻድቃን ሰዎች የረገጧትን ይላል። ጻድቃን ሰዎች የረገጧት የተባለች የእግዚአብሔር ሕግ ናት። በሕግ ጸንተው መኖራቸውን መግለጽ ነው። ዕብራይስጡ ኃጥኣን ሰዎች የረገጧትን ትጠብቃለህን እንደሚል ከግርጌ ማስታዎሻ (foot note) ተጽፏል። የኃጥኣን ሕግ ከእግዚአብሔር ሕግ በተቃራኒ መሥራት ነው። ለሰይጣን ከእግዚአብሔር ሕግ በተቃራኒ የሆኑ አሥር ሕግጋት አሉት እንደሚለው ያለ ነው። የኃጥኣን ክፉ ሥራ በመንገድ ተመስሏል። ብፁዕ ብእሲ ዘኢሖረ በምክረ ረሲዓን ወዘኢቆመ ውስተ ፍኖተ ኃጥኣን እንዲል። በየትኛውም ቢገለጽ በጥያቄ መልክ የቀረበ ስለሆነ መሠረታዊ የሐሳብ ልዩነት አያመጣም።

▶️፫. "የወርቅን ዕቃ በአፈር ውስጥ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል" ይላል (ኢዮ.22፤24)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የሚያስመኩ የሆኑ እነዚህን የወርቅ ዕቃዎቸና የኦፊርን ወርቅ ቢጥል ሁሉን የሚችል አምላክ ይረዳዋል። አምላኩ ወርቅ (ገንዘብ) ይሆነዋልና ሁሉን ያገኛል ማለት ነው።

▶️፬. "እነሆ በምድረ በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች መብልን ፈልገው ወደ ሥራቸው ይወጣሉ። ምድረ በዳውም ለልጆቻቸው መብልን ይሰጣቸዋል። ራቁታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ። በብርድ ጊዜ መጎናጸፊያ የላቸውም" ይላል (ኢዮ.24፥5-7)። ምን ለማለት ነው? ምሳሌዎች ከበድ ያሉ ናቸውና በአጠቃላይ በዚህ ምዕራፍ ሊተላለፍ የተፈለገው ዋና ሐሳብ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ ባለማወቅ እንደ እንስሳ ሆነ ካለው ከቅዱስ ዳዊት ቃል ጋር ይመሳሰላል። እንስሳት የጾም፣ የመሥዋዕት፣ የበዓላትና የመሳሰሉት ሕጎች የሏቸውም። ስለዚህ ክፉ ሰዎችም እነዚህን ሕጎች ካልጠበቁ በሜዳ አህያ እንደሚመሰሉ ያመለክታል። ራቁታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ ማለቱም ዘማውያን መሆናቸውን ያመለክታል። ልብስ አለመልበስ የዝሙት ምልክት ነውና። ዋና ሐሳቡ ኃጥኣን ያለ ሕገ እግዚአብሔር ስለሚኖሩ በሜዳ አህያ መመሰላቸው ነው።

▶️፭. "ከአፉም ሕጉን ተቀበል በልብህም ቃሉን አኑር" ይላል (ኢዮ.22፥22)። ከሙሴ በፊት የነበሩ ሕዝቦች በሕገ ልቦና አልነበረ የሚመሩት እንደሱ ከሆነ እንዴት ሕጉን ተቀበል ይለዋል?

✔️መልስ፦ ሕግ የሚባለው አድርግ አታድርግ የሚለው ነው። ከአፉም ሕጉን ተቀበል በልብህም ቃሉን አኑር ማለት እግዚአብሔር በአፉ የተናገረውን ነገር እመን፤ አምነህም ቃሉን በልብህ መርምር ማለት ነው። አሥሩ ሕግጋት ለሙሴ በኋላ ዘመን ተጽፈው ቢሰጡትም ከዚያም በፊት ሳይጻፉ በሕገ ልቡና የሚታወቁ አዳም ለልጆቹ ያስተማራቸው ሕጎች ነበሩ። እነዚህን የሚያመለክት ቃል ነው።

▶️፮. "ከድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያ ይወቅራል ዐይኑም ዕንቍን ሁሉ ታያለች" ሲል መንዶልዶያ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ መንዶልዶያ ማለት መፍሰሻ ቦይ ወይም ቧንቧ ማለት ነው።

▶️፯. "ሰው ወደ ቡላድ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል ተራራውንም ከመሠረቱ ይገለብጣል" ይላል። ቡላድ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ቡላድ ድንጋይ ጥይት የሚመስል ሹል ነገር ያለው የድንጋይ ዓይነት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Feb, 18:21


💛 መጽሐፈ ኢዮብ ክፍል 5 💛

💛ምዕራፍ ፳፩፡-
-የኃጥኣን መብራት እንደምትጠፋና መቅሠፍትም እንደምትመጣባቸው

💛ምዕራፍ ፳፪፡-
-ማስተዋልንና ዕውቀትን የሚያስተምር እግዚአብሔር እንደሆነ

💛ምዕራፍ ፳፫፡-
-ኢዮብ በተገሠጽኩ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብኩት እንዳለ

💛ምዕራፍ ፳፬፡-
-የአመንዝራ ዓይን ድንግዝግዝታን እንደሚጠብቅ

💛ምዕራፍ ፳፭፡-
-ሰው ፈራሽ በስባሽ እንደሆነ መገለጹ

💛💛💛 የዕለቱ ጥያቄ 💛💛💛
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳቸዋል
ለ. በኃጥኣን መቅሠፍት ትመጣባቸዋለች
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/2ZdBnjJZ3RU?si=HMgUh1D1K9K2VrTj

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Feb, 18:08


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 128 💙💙

▶️፩. ኢዮ.19፥22 "ስለ ምን እናንተ እንደ እግዚአብሔር ታሳድዱኛላችሁ?" ይላል። እንደ እግዚአብሔር ማለቱ ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ መከራው እንዲመጣበት ያደረገ እግዚአብሔር ነው። እና እግዚአብሔር መከራ እንዳደረሰብኝ እናንተስ ለምን ክፉ ቃል እየተናገራችሁ ታሳድዱኛላችሁ ማለቱ ነው ኢዮብ ሦስቱን ወዳጆቹን።

▶️፪. ኢዮ.19፥26 "ይህ ቍርበቴም ከጠፋ በኋላ
በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ ዐውቃለሁ" ይላል። እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ ማለቱ ነፍሱ ከሥጋው በምትለይበት ጊዜ ነው?

✔️መልስ፦ በሁለቱም ያስተረጉማል። አንደኛው በኋላ ተፈውሼ እግዚአብሔርን ሀብት ሰጥቶኝ በመግቦቱ አየዋለሁ ማለቱ ነው። ሁለተኛው እግዚአብሔርን አየዋለሁ ማለቱ ሰው ሆኖ በሥጋ ሲመጣ በነፍሴ በሥጋ አየዋለሁ ማለት ነው።

▶️፫. "አሁን ግን የዕብድ ቁርጥራጭና ብጥስጣሽ አደረከኝ። እኔንም መያዝህ ምስክር ሆነችብኝ ሐሴትም በእኔ ላይ ተነሣች በፊቴም ተከራከረችኝ" ይላል (ኢዮ.16፥8-9)። የንባቡ ትርጓሜ ምንድን ነው? እኔንም መያዝህ ምስክር ሆነችብኝ ሲልስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ እኔንም መያዝህ ምስክር ሆነችብኝ ማለት በመከራ መቅጣትህ ለኃጢአቴ ምስክር ሆነች ማለቱ ነው። እንደ እብድ ቁርጥራጭና ብጥስጣሽ አደረግኸኝ የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። የእብድ ቁርጥራጭና ብጥስጣሽ በጣም የተቆራረጠና የተበጣጠሰ እንደሆነ የእኔንም ሰውነቴን በሕመም በጣጠስከው ቆራረጥከው ማለት ነው።

▶️፬. "ተዘልዬ ስኖርም ጣለኝ። የራስ ጠጉሬን ይዞ ነጨው። እንደ አላማም አድርጎ አቆመኝ እንደ ጉበኛም ተመለከተኝ። በጦር ከበቡኝ
ኩላሊቴንም ወጉኝ። እነርሱም አልራሩልኝም
ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሱ" ይላል (ኢዮ.16፥13-15)። ይህ ስለማን ነው የሚያወራው? ትርጓሜውስ?

✔️መልስ፦ ቃሉ የሚያወራው ስለኢዮብ ነው። ኢዮብ ስለራሱ የተናገረው ነው። በጦር ከበቡኝ፣ ኩላሊቴን ወጉኝ፣ አልራሩልኝም ያላቸው አጋንንት እና እርሱን ለማሳመም በአካሉ ወጥተውበት የነበሩ ትሎች ናቸው። ሐሞቴን በምድር አፈሰሱት ያለው ሐሞቱ የፈሰሰ ሰው እንደማይድን እኔም ሳልድን ቀረሁ አለ ኢዮብ። በእርግጥ ኢዮብ እንዲህ ይበል እንጂ በኋላ በእግዚአብሔር ቸርነት ከሕመሙ ድኗል።

▶️፭. ኢዮ.17፥3 "አሁንም አንተ መያዣ ሆነህ ተዋሰኝ። ከእኔ ጋራ አጋና የሚመታ ማን ነው" ይላል። አጋና ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አጋና መምታት ማለት ሥልጣን መከልከል ማለት ነው። አጋና ያለው ሥልጣንን፣ ጥበቃን ነው።

▶️፮. "በቁርበቴ ላይ ማቅ ሰፋሁ። ቀንዴንም በመሬት ላይ አኖርሁ" ይላል (ኢዮ.16፥15)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ቀንዴን በመሬት ላይ አኖርኩ ማለት ኃይሌን በመከራ አጣሁ ማለት ነው። በዚህ አግባብ ቀንድ ኃይል ተብሎ ይተረጎማል። በቁርበቴ ላይ ማቅ ሰፋሁ ያለው መከራ አገኘኝ ማለት ነው። ማቅ መልበስ የመከራ ምልክት ነውና።

▶️፯. "ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው የልጆቹ ዓይን ይጨልማል" ይላል (ኢዮ.17፥5)። የልጆቹ ዓይን ይጨልማል ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ በባልንጀራው ላይ ክፉ ሥራን የሚሠራ ሰው በልጆቹ ላይ መከራን ያመጣል ማለት ነው። በልጅ ከመቀጣት የበለጠ ቅጣት የለምና።

▶️፰. "የሞትም በኵር ልጅ ብልቶቹን ይበላል" ይላል (ኢዮ.18፥13)። የሞት በኵር ልጅ የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እኔ ባሉኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች እንዲህ የሚል አላገኘሁም። የሆነ ሆኖ ግን ሐሳቡ ተቀራራቢ ነው። አሁን ሞት የሚወልድ የሚዋለድ ሆኖ አይደለም። ሰው ከሞተ በኋላ ቀጥለው የሞት በኩር የተባሉ ትሎች አካሉን ይበሉታል ማለት ነው። የሞት በኵር ልጅ የተባሉ በአጭሩ ዕፄያት (ትሎች) ናቸው።

▶️፱. "ልጆቹ ድሆቹን ያቈላምጣሉ። እጁ ሀብቱን ይመልሳል" ይላል (ኢዮ.20፥10)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህን ቃል አሜናዊው ሶፋር ስለ ኃጢአተኛ ሰው የተናገረው ነው። የኃጢአተኛ ሰው ልጆቹ ድኾቹን ያቆላምጣሉ ማለቱ ከድኻ በታች ይሆናሉ ለማለት ነው። በእርግጥ እኔ በያዝኳቸው ቅጅዎች ቃል በቃል እንዲህ ባይልም የመሠረታዊ ሐሳብ ልዩነት ስለሌለ ትርጉሙ አንድ ነው። እጁ ሀብቱን ይመልሳል ማለት የመጣለትን የነበረውን ጸጋ ያጣል ማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Feb, 18:52


💟 መጽሐፈ ኢዮብ ክፍል 4 💟

💟ምዕራፍ ፲፮፡-
-ኢዮብ እኔ ብናገር ቁስሌ አይድንም ዝም ብልም ሕመሜ ይብስብኛል እንዳለ
-ኢዮብ ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ትድረስ እንዳለ

💟ምዕራፍ ፲፯፡-
-ኢዮብ ደስታዬን ተማምኛት ነበር ነገር ግን ጠፋችብኝ እንዳለ

💟ምዕራፍ ፲፰፡-
-አውኬናዊው በልዳዶስ ኢዮብን መከራው ይገባሃል እንዳለው

💟ምዕራፍ ፲፱፡-
-ኢዮብ ዘመዶች አልተረዱኝም የሚያውቁኝም ረሱኝ እንዳለ

💟ምዕራፍ ፳፡-
-አሜናዊው ሶፋር ኢዮብን በዕውቀትም ከእኔ አትሻልም እንዳለው

💟💟💟የዕለቱ ጥያቄዎች💟💟💟
፩. ከሚከተሉት ውስጥ የኢዮብ ንግግር ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ጌታ ሆይ በክፉ ቁስል መትተኸኛልና እንግዲህ በአንተ አላምንም
ለ. ብናገር ቁስሌ አይድንም ዝም ብልም ሕመሜ ይብስብኛል
ሐ. ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ትድረስ
መ. ደስታዬን ተማምኛት ነበር ነገር ግን ጠፋችብኝ
፪. ከሚከተሉት ውስጥ በታመመ ጊዜ ኢዮብ የተናገረው የትኛው ነው?
ሀ. ወንድሞች ተለዩኝ ከእኔ ይልቅም ባዕዳንን ወደዱ
ለ. ጓደኞቼ አላዘኑልኝም
ሐ. ዘመዶች አልተረዱኝም ስሜንም የሚያውቁኝ ረሱኝ
መ. ሁሉም

https://youtu.be/9AMJS1w0j0E?si=RWVP4hp8RtUAVRhc

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Feb, 18:37


እንደምታውቁት በጣም ብዙ ዓይነት መንጋ አለ። የፖለቲካ መንጋ፣ የአጥማቂ ነን ባይ መንጋ፣ የሰባክያን መንጋ፣ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መንጋ፣ የመሳሰሉት። ሁሉንም መንጋዎች የሚያመሳስላቸው መንጋ የሆኑለት አካል ተሳስቶ እንኳ ስሕተቱን በማስረጃ ብትነግራቸው አይቀበሉህም። እንዲያውም ስሕተቱን ጽድቅ ለማድረግ ሲደክሙ ታያለህ።

፩. ስሕተቱን ትተህ መልካም ጎኑን ብቻ አጉልተህ ከጻፍክ መንጋዎቹ ምን ይሉሃል መሰለህ። እንዳንተ ዓይነት ጠቢብ ሰዎችን ያብዛልን😀፣ እግዚአብሔር ይባርክህ፣ መማር ማለት እንዲህ ነው😀 እና የመሳሰሉ ሙገሳዎችን ያጎናጽፉሀል። የጻፍከው እውነታውን ሳይሆን መንጋነታቸውን የሚያጸና ስለሆነ ነው። ይህ Part ያዝናናል። በቃ ስሕተቷን ላለማመን ሰዎች ሲደክሙ ሳይ አንጀቴን ይበሉታል😀። ሰው ሁሉ ወድዶን እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ከማድረግ ሰው ሁሉ ጠልቶን እግዚአብሔር የሚወደውን ማድረግ ይበልጣል። ለእውነት እንኑር።

፪. የአንድን ሰው መልካም ጎኑን ትተህ ስሕተቱን ብቻ እየነቀስክ የምታወራ ከሆንክ ደግሞ ችግር አለብህ ማለት ነው።

፫. ከመንጋነት እንውጣ። ለእያንዳንዱ ነገር ሚዛናችን የእግዚአብሔር ቃል ይሁን። ከመምህራን መልካም ትምህርታቸውን እየወሰድን ክፉ ነገራቸውን እንተወው። ቢቻል መጥፎ ነገራቸውን እንዲያስተካክሉ መንገር። ካልተመለሱም ለእግዚአብሔር መተው ጥሩ ነው።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Feb, 18:02


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 127 💙💙

▶️፩. "ከሴትም የሚወለደው ሰው የሜዳ አህያን ይመስላል" ይላል (ኢዮ.11፥12)። የሜዳ አህያን ይመስላል ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሰው የሜዳ አህያን መምሰሉ እንደሜዳ አህያ መብላቱ መጠጣቱ፣ እንደሜዳ አህያ መሞቱን ለማመልከት ነው። ሰው ሟች መሆኑን አስቦ እንዳይኮራና እንዳይታበይ የተነገረ የትሕትና ቃል ነው።

▶️፪. "ጸሎትህ እንደ አጥቢያ ኮከብ ይሆናል" ይላል (ኢዮ.11፥17)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የንጋት ኮከብ ሲወጣ የቀንን መምጣት የሚያበስር ስለሆነ ደስ ያሰኛል። እንደዚሁ ሁሉ ጸሎትህም ደስ የሚያሰኝ ጸጋን ክብርን ያሰጥሀል ማለት ነው።

▶️፫. "አሁን ግን እንስሶችን ጠይቅ ያስተምሩህማል። የሰማይንም ወፎች ጠይቅ ይነግሩህማል። ለምድር ንገራት እርሷም ትተረጉምልሃለች። የባሕር ዓሣዎች ያስረዱሃል" ይላል (ኢዮ.12፥7-8)። በዚህ መጽሐፍ ዐውድ ምንድን ነው የሚያስተምሩን ምንድን ነው የሚተረጉሙልን?

✔️መልስ፦ አሁን እንስሳት ተጠይቀው የሚመልሱ እንደ ሰው ነባብያን ሆነው አይደለም። የእነርሱን አኗኗር በማየት የእግዚአብሔርን ታላቅነት እንድንረዳ ለማጠየቅ ነው። ፍጥረታትን በጥልቀት ማየት ወደፈጣሪያቸው በማድረስ ያስረዳናልና ነው።

▶️፬. "ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች ሰው ማን ነው?
ጻድቅ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ማን ነው?
እነሆ በቅዱሳን እንኳ አይታመንም
ሰማይም በፊቱ ንጹሕ አይደለም" ይላል (ኢዮ.15፥14-15)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እነሆ በቅዱሳን እንኳ አይታመንም የተባለው የነገሩ ባለቤት ንጽሕና ነው። የመላእክት ንጽሕናቸው አይታመናቸውም ማለት ነው። የወደቁ መላእክት ስላሉ እነርሱን ለማመልከት ነው። መላእክት እንኳ እስከ መሳት ከደረሱ ሰው ንጹሕ ነኝ ብሎ መመካት አይገባውም። ንጽሕና የባሕርይው ስላልሆነ ድቀት ሊያገኘው ይችላልና ማለት ነው።

▶️፭. መጽሐፈ ኢዮብ ከየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ምድብ ይመደባል?

✔️መልስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኚዎች የጥበብና የመዝሙር ከሚባሉት መድበውታል።

▶️፮. የኢዮብ ሦስቱ ወዳጆች ኢዮብን ገሠጹት እንጂ ክፉ አልተናገሩትም። ለምን ኢዮብ አልወደዳዋቸውም እግዚአብሔርም አልወደዳቸውም።

✔️መልስ፦ ተግሣጹ የውሸት ነበር። መጨረሻ ላይ እንደምናገኘው ራሱ እግዚአብሔርም ገሥጿቸዋል። በወዳጄ በኢዮብ ላይ ክፉ ነገርን ስላደረጋችሁ ኢዮብ ይጸልይላችሁ ነበር ያላቸው። የተናገሩት ንግግር ኢዮብን ኃጢአተኛ ነህ ለማለት የተናገሩት ነበር እንጂ እውነትን መሠረት ያደረገ አልነበረም።

▶️፯. "በእርግጥ እናንተ ዓይነተኞች ሰዎች ናቸሁ። ጥበብም ከእናንተ ጋር ይሞታል" ይላል (ኢዮ.12፥2)። ዓይነተኞች ሰዎች ምን ማለት ነው? እዚህ ላይ ጥበብ የተባለ ምንድን ነው? ይሞታል ሲልስ?

✔️መልስ፦ ዓይነተኞች ሰዎች ማለት ዋና ዋና ሰዎች ማለት ነው። ከዚህ ጥበብ የተባለው የዕውቀት ፍሬ የሆነው ብልህነት ነው። ይሞታል ማለት ዋና ሰዎች ሆናችሁ ሳለ ጥበብ ግን ከእናንተ ጨርሶ ጠፍቷል የለም ማለት ነው።

▶️፰. "በሽምግልና ጊዜ ጥበብ፥ በዘመንስ ርዝመት ማስተዋል ይገኛል" ይላል (ኢዮ.12፥12)። ዳዊት ደግሞ "ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ" ይላል (መዝ.119፥100)። ሁለቱ ንባብ እንዴት ይስማማል ምን ለማለትስ ነው?

✔️መልስ፦ ሰው በዕድሜ እየበሰለ ሲመጣ በዕድሜው ብዛት የሚያውቀው ዕውቀት አለ። ለምሳሌ የገጠር አባቶች የተጣላን ያስታርቃሉ። ዩኒቨርስቲ ገብተው Psychology ተምረው አይደለም። በሕይወት ዘመናቸው በቆይታቸው የተረዱት ብዙ ዕውቀት ስላለ ነው። ይህን ለመግለጽ በመጽሐፈ ኢዮብ በሽምግልና ጥበብና ማስተዋል ይገኛል ብሎ ተናገረ። ዳዊት ደግሞ ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልኩ ብሏል። በእርግጥ ከዚህ ንግግር ውስጥ በጥልቀት ስንመለከተው ዳዊትም የሽማግሌዎች ማስተዋል እንዳላቸው አመልክቷል። ከእነርሱ ይልቅ ብሎ በንጽጽር ማምጣቱ ይህን ያሳያል። አንዳንድ ሰው በጸሎት፣ በጾም፣ በመንፈሳዊ ሥራ፣ በትምህርት ሽማግሌዎች ካላቸው ጥበብ የበለጠ ጥበብ ሊኖረው ይችላል። መጽሐፈ ኢዮብ የሽማግሌዎች ጥበብ እንዳላቸው ተናገረ እንጂ በእድሜ ከእነርሱ ያነሱ ሰዎች በፍጹም በጥበብ ሊበልጧቸው አይችሉም ስላላለ አይጣላም።

▶️፱. "የመረረ ነገር ጽፈህብኛልና። የሕፃንነቴንም ኃጢአት ታወርሰኛለህ" ይላል (ኢዮ.13፥26)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የመረረ ነገር ጽፈህብኛል የሕፃንነቴንም ኃጢአት ታወርሰኛለህ ማለት በሕፃንነቴ በሠራሁት ኃጢአት መከራን አደረስክብኝ ማለት ነው። እንጂ በሰማይ የሚጻፍ ጽሑፍ የተጻፈ ጽሑፍ ኖሮ አይደለም።

▶️፲. "በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን?" ይላል (ኢዮ.14፥13-14)። ሰው ሕያው እንደሆነ ይታወቃል። በአጠቃላይ ይሄ ጥቅስ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርከኝ ከሚለው ቃል ሲኦል ያለው መቃብርን ነው። ኢዮብ በዚህ ምድር ከምሰቃይ ሞቼ በመቃብር ባርፍ ይሻለኛል አለ። በትንሣኤ ዘጉባኤ እስኪነሣ ድረስ በአፀደ ነፍስ ዕረፍት አግኝቶ በኋላም ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት ይገባልና። በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን ያለው በትንሣኤ ዘጉባኤ ነው እንጂ ከዚያ በፊት የሞተ ሰው ዳግመኛ ሞት የሌለበትን ትንሣኤ አይነሣም ማለት ነው።

▶️፲፩. ኢዮብ.14፥5 ላይ በምድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር የሚለው ቀጥሎ ከተጠቀሰው ዘመኑ የተቆጠረ ነው የሚለውን አንዳንዶች አንድስ እንኳ ንጹሕ የለም ከሚለው ከቁጥር 4 ጋር ያያይዙታል ለምሳሌ st.augustine , Father Hecechius of Jerusalem ,Father Caesarius, Bishop of Arless ,origen of alexandria, st.basil the great etc ይህ grammaticaly ትክክል ነው?

✔️መልስ፦ በእርግጥ እነዚህ ከላይ የጠቀሷቸው አባቶች በዚህ ዙሪያ የጻፉትን አላነበብኩትም። የሆነ ሆኖ ሐሳቡን ከላይኛው ማለትም ከቁጥር 4 ጋር ያያይዙታል ብለውኛል። ካያያዙት መልካም። እኛም በትርጓሜ የምናያይዘው ከቁጥር 4 ጋር ነው። በግእዙ "ወመኑ ይነጽሕ እምርስሐት ወኢመኑሂ" ካለ በኋላ "ወዘአሐተ ሰዓተ ሐይወ በዲበ ምድር" ይላል። ይህ ደግሞ ትኤምኀክሙ ቅድስት ቤተክርስቲያን ካለ በኋላ ወማርቆስ ወልድየ ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው። ይኤምኀክሙ ለማለት ነው። በአጭሩ ከቁጥር አራት ጋር የሚያያዝና ከዚያ የቀጠለ ሐሳብ መሆኑን እኛም እንናገራለን።

▶️፲፪. "ከአባቶቻቸው ተቀብለው የተናገሩትን ያልሸሸጉትንም እገልጥልሃለሁ ስማኝ። ያየሁትንም እነግርሃለሁ" ካለ በኋላ የተናገረው ነገር ዋና ሐሳቡ ምንድን ነው? (ኢዮ.15፥19)።

✔️መልስ፦ ከቁጥር 20 ጀምሮ እስከ ቁጥር 35 ያሉት ሐሳቦች ናቸው። ፍሬ ሐሳቡ ኃጥእ ሰው ስለሚደርስበት ነገር ያትታል። ያው ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ኢዮብን እንደ ኃጥእ ቆጥረው በነገር እያቆሰሉት ስለነበር ነው።

▶️፲፫. ኢዮ.12፥12 ላይ በመኖር ብዛት ዕውቀት ይገኛል። ሲል ኢዮ.32፥7 በዓመታት ብዛት ሰዎች ጥበብን አያውቋትም ይላል አይጋጭም ወይ?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Feb, 18:02


✔️መልስ፦ በመኖር ብዛት የሚገኝ ዕውቀት አለ። ብዙ ማወቅና ጥበበኛ መሆን ግን ይለያያል። አንድ ሰው አዋቂ ነው ማለት ስለጉዳዩ ማብራራት፣ መናገር ይችላል ማለታችን ነው። ጠቢብ ነው ማለት ደግሞ የዕውቀትን ፍሬ ማለትም ሥነ ምግባርን ገንዘብ አድርጓል ማለት ነው። ሰው እግዚአብሔርን ካልፈራ፣ ሥነ ምግባር ከሌለው አዋቂነቱ ጠቢብ አያሰኘውም። ሰይጣንም አዋቂ ነው። ነገር ግን ዕውቀቱ ለድኅነት ስላላበቃው ጠቢብ ነው ማለት አይቻልም።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Feb, 13:34


በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት በ“ሃሎ መምህር” እንዲመለስልዎ የሚፈልጉትን ሃይማኖታዊ ጥያቄ በስልክ ቁጥር 0111 55 32 32  በመደዎል ይጠይቁ፡፡ ለጥያቄዎ ማብራሪያ እና መልስ ከመምህራን ያገኛሉ፡፡

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Feb, 07:52


ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ
---------------------------------------------
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ከዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራር አካላት ጋር የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በተለይ ቤተሰቦቹ ሊደገፉ በሚችሉባቸውና ሃኪሙ በህይዎት ዘመኑ ያከናወናቸው ልዩ ሙያዊ አስተዋጽኦችን መዘከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡

ዶ/ር አንዱአለም ምንም እንኳን የተሰጠውን ጸጋ ሳይሰስት በመጠቀም ለበርካቶች የዘርፉ ባለሙያዎችና በሙያው ላገለገላቸው በርካታ ህሙማን የቅን አገልጋይነት ተምሳሌት የነበረ እንቁ ባለሙያ ቢሆንም ገና በ37 ዓመቱ የተቀጠፈ በመሆኑ ለህጻናት ልጆቹና ቤተሰቡ ትቶ ያለፈው ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት የሌለው መሆኑን፣ የቀረቡለትን በርካታ ዓለምአቀፍ የስራ ቅጥር ግብዣዎች ባለመቀበል ወገኑን ለማገልገል ቆርጦ የነበረ ባለሙያ ከመሆኑም በላይ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ክፍል የነበረውን ልዩ አበርክቶና የቀዶ ጥገና ክፍሉን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሻሻል እየጣረ የነበረ እና እውን ለማድረግ ጫፍ ላይ ደርሶ ያለፈ መሆኑን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የነበረውን ሞያዊ አቅም ተጠቅሞ ራሱን ለተገልጋዮች በቅንነት ሰጥቶ ያለፈ ታላቅ ባለሙያ እንደነበረ የስራ ባልደረቦቹ ፣ተማሪዎቹ እና አገልግሎቱን ያገኙ ደምበኞቹ የሚመሰክሩለት ድንቅ ሃኪም የነበረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በጥልቀት ገምግሟል፡፡
በመሆኑም፡
የዶ/ር አንዱአለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤
ባለቤቱ ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ አቅም ያላት በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የምትቀጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች፤
ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሰራው እሱ በመሆኑና ክፍሉን እስከ ህልፈቱ ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረ በመሆኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በስሙ ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም፤
የዶ/ር አንዱአለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነቱን በቋሚነት ለመዘከርና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆምለት፤
በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስሙ BDU Talent Scholarship እንዲቋቋም፤
ለ40ኛ ቀኑ መታሰቢያ የሚደርስ ስለ ዶ/ር አንዱአለም የህይዎት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ የወሰነ ሲሆን ይህ ውሳኔም ቀድሞ በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በኋላም ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይሁንታን አግኝቶ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
በሌላ በኩል በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ በኩል የሚሰሩ ዝርዝር ስራዎችን የሚከታተል የስራ ባልደረቦቹን ያቀፈ አንድ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
በመጨረሻም የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን የግፍ ግድያ አስመልክቶ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደ ተቋም ፍትህ አጥብቆ የሚሻ ሲሆን ክስተቱ የአንድ ጊዜ አጋጣሚ ብቻም ሳይሆን ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ያጣውን በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ አቶ አድነው በለጠን ጨምሮ እየተደጋገመ የመጣና ለሕብረተሰቡ አገልጋይ የሆኑ እንቁ ሃኪሞቻችንን ደህንነት እንዲሁም የማሕበረሰቡን የጤና አገልግሎት በእጅጉ እየተፈታተነ ያለ አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ ተገቢውን እና ጥልቅ ምርመራ አድርገው በግድያው ላይ እጃቸው ያለበትን አካላት በአፋጣኝ ለህግ እንዲቀርቡ እንዲደረግ እየጠየቀ ይህ ጉዳይ በቋሚነት መፍትሄ በሚያገኝበት መንገድ ላይ ዩኒቨርሲቲው በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶችን የሚያደርግ መሆንን ይገልጻል፡፡

© ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Feb, 05:35


💗 መጽሐፈ ኢዮብ ክፍል 3 💗

💗ምዕራፍ ፲፩፡-
-አሜናዊው ሶፋር ኢዮብን ንግግር አታብዛ፣ በሥራዬ ንጹሕ ነኝ በፊቱም ጻድቅ ነኝ አትበል እንዳለው

💗ምዕራፍ ፲፪፡-
-የሕያዋን ሁሉ ነፍስ በእግዚአብሔር እጅ እንደሆነ መነገሩ
-በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል ምክርና ማስተዋል እንዳለ

💗ምዕራፍ ፲፫፡-
-ኢዮብ ሦስቱን ወዳጆቹን ጥበብ ከእናንተ ጠፍታለች፣ ሽንገላን ትናገራላችሁ እንዳላቸው

💗ምዕራፍ ፲፬፡-
-የሰው ልጅ በዚህ ምድር የሚኖረው የሕይወት ዘመኑ ጥቂት እንደሆነ መገለጡ
-ሰው ከሞተ በኋላ እንደሚተላ መነገሩ

💗ምዕራፍ ፲፭፡-
-ቴማናዊው ኤልፋዝ ኢዮብን ጥቂት ብትበድል ተገረፍክ እንዳለው
-የኃጥእ ሰው ዕድሜው በጭንቅ እንደሚያልፍ

💗💗💗የዕለቱ ጥያቄዎች💗💗💗
፩. አሜናዊው ሶፋር ኢዮብን ምን አለው?
ሀ. ንግግር አታብዛ
ለ. በሥራዬ ንጹሕ ነኝ አትበል
ሐ. በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ነኝ አትበል
መ. ሁሉም
፪. በዚህ ዓለም የምንኖረው ኑሮ በምን ተመስሏል?
ሀ. በአበባ
ለ. በጥላ
ሐ. ሀ እና ለ
መ. ሁሉም
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ስለኃጢአተኛ ሰው ትክክል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. መከራና ጭንቀት ይመጡበታል
ለ. ውርደት ይመጣበታል
ሐ. ገነት ይገባል
መ. ሁሉም

https://youtu.be/gAsPbuAhyLE?si=vvoCLvJ6NB28JL5F

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Feb, 16:51


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 126 💙💙

▶️፩. ስለግሪክ ሰባው ሊቃውንት መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስለ ዕብራይስጥ እና ስለ ግእዙ መጽሐፍ ቅዱሶች ቢነግሩን የኅዳግ ማስታዎሻዎችን ለመረዳት ያግዘናል። ብዙ የተራራቁ የሚመስሉ ትርጓሜዎችና ጭማሪዎች አሉና።

✔️መልስ፦ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ነው። ነገር ግን በብዙ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ወደ ሌላ ቋንቋ ሲተረጎም በቋንቋው ውስንነት ምክንያት መጀመሪያ ከተጻፈበት ቋንቋ ጥቂት የቃል ልዩነት ሊፈጠር ይችላል። መሠረታዊ ሐሳቡ ግን በሁሉም ቋንቋ የተተረጎመው አንድ ዓይነት ነው። የኅዳግ ማስታዎሻዎቹ ሙሉ ሐሳቡን ለማግኘት ይረዱናል። ዕብራይስጡ እንዲህ ይላል፣ ግእዙ እንዲህ ይላል፣ ግሪኩ እንዲህ ይላል ማለቱ የትርጉምና የሐሳብ ለውጥ አያመጣም። የአገላለጽ፣ የአተረጓጎም ልዩነት ካልሆነ መሠረታዊ የሐሳብ ልዩነት የለባቸውም።

▶️፪. "ሰው ምንድን ነው? ከፍ ከፍ ታደርገው ዘንድ ልቡናውንም ትጎበኘው ዘንድ ማለዳ ማለዳስ ትጎበኘው ዘንድ" ይላል (ኢዮ.7፥17)። እኔም ይህን ብጠይቅ ደስ ይለኛል ሰው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሰው እግዚአብሔርን እያመሰገነ ለዘለዓለማዊ ደስታ የተፈጠረ፣ በእግዚአብሔር አርአያና መልክ የተፈጠረ የጸጋ ገዢ ነው። አፈጣጠሩ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከአምስተኛ ባሕርየ ነፍስ ነው። የፈጣሪውን ትእዛዝ አፍርሶ ሞት የተፈረደበት የነበረ ቢሆንም ወልደ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በመልእልተ መስቀል ተሰቅሎ ወደቀደመ የክብር ቦታው መልሶታል። አሁንም ተጠምቆ፣ ምግባር ትሩፋት ሠርቶ ወዶ ገነት እንዲገባ ነጻነት የተሰጠው ክቡር ፍጥረት ነው።

▶️፫. ኢዮ.6፥4 "ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው። መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች የእግዚአብሔር ድንጋጤ በላዬ ተሰልፏል" ይላል። መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ የአምላክ ፍላጻ፣ መርዝ የተባሉት አንድ ወገን በኢዮብ የደረሱ በሽታዎች ናቸው። መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች ማለት ሰውነቴ የሕመምን መራራነት ቀመሰች ማለት ነው።

▶️፬. "ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ  እንዲሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግመኛ አይወጣም" ይላል (ኢዮ.7፥9)። ሞቶ ሲኦል የገባ ሰው ከሲኦል የሚወጣበት ጊዜ አለ ይባላልና ቢያብራሩልኝ። የቅዱሳን ምልጃስ የሞተን ሰው ነፍስ ከሲኦል ያወጣል? መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ቢሰጡኝ።

✔️መልስ፦ በቅዱሳን አማላጅነት ሰው ከሲኦል ወጥቶ ወደ ገነት ሊገባ ይችላል። የቅዱሳን ምልጃ የሞተን ሰው ከሲኦል ያወጣል። ይህን ሥልጣን የሰጣቸው ደግሞ እግዚአብሔር ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ እገሌ ሲኦል ነበረ በቅዱሳን ምልጃ ወጥቶ ወደገነት ገባ የሚል ቃል በቃል የተጻፈ አላገኘሁም። በቅዱሳት ገደላትና በድርሳናት ነው ይህ የሚገኘው።

▶️፭. "ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል?" ይላል (ኢዮ.9፥2)። ኢዮ.1፥1 ላይ ደግሞ ኢዮብ ፍጹም እንደነበር ተጽፏል። ታዲያ ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ መሆን ይችላል? የሚለው አነጋገር አንጻራዊ አነጋገር ነው። ይህ ማለት ሰው ቅዱስ መሆን የሚችለው በእግዚአብሔር ቸርነት እንጂ በራሱ ቅዱስ መሆን እንደማይችል የሚያመለክት ቃል ነው። በሌላ አገላለጽ እንደ እግዚአብሔር በባሕርይው ቅዱስ የሆነ የለም ማለት ነው። በጸጋ ግን ጻድቃን መሆን ይቻላል። ኢዮብ በጸጋ ነው ቅዱስ የሆነው እንጂ በባሕርይው ቅዱስ አይደለምና።

▶️፮. "መቅሠፍቱ ፈጥኖ ቢገድል፥ በንጹሐን ፈተና ይሳለቃል" ይላል (ኢዮ.9፥23)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እንዲህ የሚያደርግ ኃጥእ ሰው ነው። ኃጢአተኛ ሰው በንጹሓን ፈተና ይሳለቃል። እግዚአብሔር ግን በንጹሓን ፈተና ደስ ይለዋል። ክብርን የሚያገኙበት ነውና።

▶️፯. "ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ይላል (ኢዮ.10፥18)። መምህር ይሄ ግን ማማረር አይደለም?

✔️መልስ፦ ኢዮብ በዚህም የተናገረው ይህ ሁሉ መከራ ከሚደርስብኝ ወዲያው በሕፃንነቴ በሞትኩ በተሻለኝ ነበር እያለ ነው። በማኅፀን እያለሁ ብትገድለኝ ይሻለኝ ነበር ነው ያለ። በራሱ ሰውነት ላይ ፈረደ እንጂ እግዚአብሔርን ያለማክበርና የማማረር ስሜትን አላሳየም።

▶️፰. "ምድርንም ሆነ ሰማይን የሚደግፍ ባላ (ምሰሶ) የለምና" ይላል (ኢዮ.26፥7)። ስለምን ምሰሶ ነው ኢዮብ.9፥6 ላይ የሚያወራው?

✔️መልስ፦ ምድርንም ሆነ ሰማይን የሚደግፍ ምሰሶ የለም ማለት የፍጥረታት ሁሉ መሠረታቸውም ምሰሷቸውም እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል። ኢዮ.9፥6 ላይ መሠረቶቿና ምሰሶዎቿ ያለው ከመሬት በታች ያሉ ማያትን፣ እሳትን፣ ነፋስን ነው። ለእነዚህም መሠረት ግን እግዚአብሔር ስለሆነ ከላይ ያለ ምሰሶ ይኖራሉ ተብለዋል።

▶️፱. ኢዮ.9፥16 "ቢመልስልኝ ኖሮ እንደሰማኝ አላምንም ነበር" ሲል ባይመልስለት ነው እንዴ እንደሰማው የሚያምን? ተቃራኒ ሆነብኝ

✔️መልስ፦ እንደሱ ማለት አይደለም። ቢመልስልኝ ኖሮ እንደሰማኝ አላምንም ነበር ማለት እግዚአብሔር በቸርነቱ እንጂ በመልካም ሥራዬ ምክንያት ሰማኝ አልልም ነበር ማለቱ ነው።

▶️፲. "አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ በራእይም ታስደነግጠኛለህ" ይላል (ኢዮ.7፥14)። እንዲህ እያለ የተናገረው ማንን ነው? የሚያስፈራራው ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ኢዮብ እንዲህ እያለ እየተናገረ ያለው እግዚአብሔርን ነው። በሕልም ታስፈራራኛለህ ማለቱ ሰይጣን በኢዮብ ላይ የፈለገውን እንዲያደርግ ስለፈቀደለት ሰይጣን ደግሞ በተለያዩ አምሳሎች ያስፈራራኛል ማለቱ ነው። የሚያስፈራው ለምንድን ነው? የሚለው የኢዮብ ትዕግሥት ለእኛ ትምህርት እንዲሆነን የኢዮብን ትዕግሥት እኛ እንድንረዳ ነው።

▶️፲፩. "ነገር ግን ሁለት ነገር አታድርግብኝ የዚያን ጊዜ ከፊትህ አልሰወርም" ይላል (ኢዮ.13፥20)። እነዚህ ሁለት ነገሮች ያላቸው ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ ከዚያው ቀጥሎ የተናገራቸው ናቸው። እጅህን ከእኔ አርቅ የሚለውና ግርማህም አታስደንግጠኝ የሚሉት ናቸው።

▶️፲፪. "ከታመኑ ሰዎችም ቋንቋን ያርቃል የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል" ይላል (ኢዮ.12፥20)። ቋንቋን ያርቃል ሲል ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የቋንቋ መሠረታዊ ዓላማው ለመግባባት ነው። ከታመኑ ሰዎችም ቋንቋን ያርቃል መባሉ እንዳይግባቡ ያደርጋል ማለት ነው። ከዚህ የታመኑ ሰዎች የተባሉ እስራኤል ናቸው። በኋላ በድለው እንዳይግባቡ ይሆናሉ ማለት ነው።

▶️፲፫. "የሜዳ አህያ ግልገል ሰው ሆኖ ቢወለድ ያን ጊዜ ከንቱ ሰው ጥበብን ያገኛል" ይላል (ኢዮ.11፥12)። ንባቡን ያስረዱኝ መምህር።

✔️መልስ፦ የሜዳ አህያ ግልገል ሰውን አይወልድም። ከንቱ ሰው ጥበብን አገኘ ማለት የሜዳ አህያ ሰውን ወለደ ማለት ነው እንደማለት ነው። በጠቅላላው የቃሉ ፍሬ ሐሳብ የሜዳ አህያም ሰውን አይወልድም። ከንቱ ሰውም ጥበብን አያገኝም ማለት ነው።

▶️፲፬. "ወንድሞቼ እንደ ፈፋ እንደሚያልፍ ፈፋ ሐሰተኛዎች ሆኑብኝ" ይላል። ፈፋ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ፈፋ ማለት ትንሽ ዥረት ማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Feb, 03:48


💓 መጽሐፈ ኢዮብ ክፍል 2 💓

💓ምዕራፍ ፮፡-
-ኢዮብ እግዚአብሔር አልጎበኘኝም አልተመለከተኝም እንዳለ
-ኢዮብ ሦስቱን ወዳጆቹን አስተምሩኝ እኔም አዳምጣችኋለሁ የተሳሳትኩትም ካለ አስረዱኝ እንዳላቸው

💓ምዕራፍ ፯፡-
-የሰው ሕይወት በምድር ላይ እንደ ጥላ እንደሆነ

💓ምዕራፍ ፰፡-
-አውኬናዊው በልዳዶስ ኢዮብን ወደ እግዚአብሔር ገሥግሥ ሁሉንም ወደሚችለው አምላክ ጸልይ እንዳለው
-የዝንጉ ሰው ተስፋ እንደምትጠፋ
-እግዚአብሔር የዋሁን ሰው እንደማይጥለው

💓ምዕራፍ ፱፡-
-እግዚአብሔር ታላቅ፣ ጠቢብ፣ ኃይለኛ እንደሆነ
-የኃጥኣን ሞታቸው ክፉ እንደሆነ መነገሩ

💓ምዕራፍ ፲፡-
-ኢዮብ እግዚአብሔርን እጆችህ ፈጠሩኝ ሠሩኝም እንዳለ

💓💓💓የዕለቱ ጥያቄዎች💓💓💓
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. አሁን እየኖርንባት ያለችዋ ምድር ዘለዓለማዊት ናት
ለ. እግዚአብሔር የሚወደውን ይገሥጻል
ሐ. የሰው ሕይወት በምድር ላይ እንደ ጥላ ፈጥኖ ያልፋል
መ. ለ እና ሐ
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. እግዚአብሔር የዋሁን አይጥለውም
ለ. እግዚአብሔር የቅኖችን ከንፈሮች ምስጋና ይሞላል
ሐ. እግዚአብሔር የዝንጉዎችን መባ አይቀበልም
መ. ሁሉም
፫. ስለ ልዑል እግዚአብሔር ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ታላቅ ነው
ለ. ጠቢብ ነው
ሐ. በአካል የማይኖርበት ቦታ አለ
መ. ኃያል ነው

https://youtu.be/VIpnNjgVx4w?si=aqN4LBWBpI1TJm6z

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Feb, 20:28


▶️፲፩. ኢዮ.1፥11-12 "ነገር ግን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ዳብስ። በእውነት በፊትህ ይሰድብሀል። እግዚአብሔርም ሰይጣንን እነሆ ለእርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው። ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ ይላል። እዚህ ላይ እግዚአብሔር በሰይጣን ታዘዘ አያስብልም ወይ?ምክንያቱም ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ። የኢዮብን ያለውን ሁሉ ገደለበት ይህን እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በሰይጣን አይታዘዝም። ነገር ግን እግዚአብሔር ሰይጣን ያሰበው ሐሳብ ከንቱ መሆኑን እኛ እንረዳ ዘንድ በኢዮብ የፈለገውን እንዲያደርግ አሰናብቶታል። ሰይጣንም በኢዮብ ትዕግሥት ተሸንፎ ሐሳቡ ከንቱ መሆኑ ታወቀ።

▶️፲፪. ኢዮብ እስራኤላዊ ነው? የኖረበትስ ዘመን መቼ ነው? ከእነ ዳዊት እና ከባቢሎን ምርኮ በፊት ወይስ በኋላ ነው?

✔️መልስ፦ ኢዮብ የኖረበት ዘመን መጨረሻ ምዕራፍ ላይ ተገልጿል። ኢዮብ ከአብርሃም አምስተኛ ትውልድ ላይ የሚገኝ ነው። ከባላቅ በኋላ የነገሠ እንደሆነ ተገልጿል። አውስጢድ የት ትገኝ እንደነበረ ተጨማሪ ነገር መጽሐፍ ቅዱሱ ስላልገለጸ አለማወቅ ይገድበናል። ታሪኩ የተደረገው ከባቢሎን ምርኮ በፊት እንደሆነ ግን ከባላቅ በኋላ ኢዮብ መንገሡ ማስረጃ ይሆነናል።

▶️፲፫. ሰይጣን ወደ ሰማይ ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊት መቆም ይችላል?

✔️መልስ፦ አይችልም። ወደሰማይ ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊትም አልቆመም። ሲጀመር እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ያለ ስለሆነ ፊቱ በሰማይ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ሰይጣን በእግዚአብሔር ፊት ቆመ መባሉ በኢዮብ መከራን ለማድረስ ከእግዚአብሔር ፈቃድን አገኘ ማለት ነው።

▶️፲፬. መጽሐፈ ኢዮብ ላይ ዋኔን የሚል ቃል አለ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ዋኔን ከርግብ አነስ የምትል የወፍ ዝሪያ (ቡላል) ናት።

▶️፲፭. "መንፈስም በፊቴ አለፈ። የሥጋዬ ጠጕር ቆመ። እርሱም ቆመ መልኩን ግን ለመለየት አልቻልሁም" ይላል (ኢዮ.4፥15-16)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ይህን የተናገረው ከኢዮብ ጓደኞች አንዱ ነው። መንፈስም በፊቴ አለፈ፣ የሥጋዬ ጠጉር ቆመ ማለቱ የኢዮብን ቁስል አይቶ እንደሞተ ሰው ያህል ድንግጦ እንደቆመ ያመለክታል። መልኩን መለየት አልቻልኩም ያለው የኢዮብን መልክ ነው። ኢዮብ ሰውነቱ በቁስል ስለተመታ የቀድሞውን ኢዮብ አይመስልም ነበርና ይህን ለመግለጽ ነው።

▶️፲፮. "ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤ የአምላክ ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ። ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ። እግዚአብሔርም ሰይጣንን ከወዴት መጣህ? አለው። ሰይጣንም ምድርን ሁሉ ዞርኋት በእርሷም ተመላለስሁ ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ" ይላል( ኢዮ.1፥6-7)። እግዚአብሔር ሰይጣንን ከወዴት መጣህ ሲለው መቼስ የመጣበት ተሰውሮበት አይደለምና ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ሊያናግር ሲሻ ይጠይቃል። አዳምን ወዴት አለህ ብሎታል። ነቢዩ ኤርምያስንም ምን እንደሚያይ እያወቀ ኤርምያስ ኤርምያስ ምን ታያለህ ብሎታል። ሰይጣንንም ሊያናግረው ሲሻ ከወዴት መጣህ ብሎታል እንጂ ከየት እንደመጣ ጠፍቶት አይደለም።

▶️፲፯. "እግዚአብሔርም ሰይጣንን እነሆ ለእርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው። ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ" ይላል (ኢዮ.1፥12)። ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ ሲል ምን ለማለት ነው? ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ ሲልስ?

✔️መልስ፦ ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ ማለት ለጊዜው ንብረቱን አጥፋ እንጂ እርሱን ምንም አታድርገው ማለቱ ሲሆን ለኋላው ደግሞ አትግደለው እንጂ በሕመም መፈተን ትችላለህ ማለት ነው። ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ ማለት በኢዮብ መከራን ለማድረስ ፈቃድ አገኘ ማለት ነው።

▶️፲፰. "የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀች። በጎቹንም አቃጠለች ጠባቂዎችንም በላች። እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው" ይላል (ኢዮ.1፥16)። የእግዚአብሔር እሳት ይላልና ይህን ፈተና እግዚአብሔር አመጣበት ወይስ ሰይጣን አመጣበት? ብዙ ጊዜ ሰው ችግር ውስጥ ሲገባ (በሕይወቱ ሲፈተን) ሰይጣን ተፈታተነኝ ይላል። በዚሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ እፈትናቸዋለሁ/እፈትናለሁ ያለበት ጊዜ አለ። ፈተናው ከእግዚአብሔር ይሁን ወይስ ከሰይጣን እንዴት ይታወቃል?

✔️መልስ፦ እሳት በተፈጥሮ የእግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ሰይጣን በተፈጥሮ የእግዚአብሔር በሆነው እሳት የኢዮብን ንብረት አጥፍቶበታል። ለምሳሌ ድንጋይ የእግዚአብሔር ነው። ነገር ግን ቃየል አንሥቶ አቤልን ገድሎበታል። እንደዚሁ በኢዮብ መከራውን ያመጣበት ሰይጣን ነው። መከራን ሲያመጣበት ግን በተፈጥሮ የእግዚአብሔር ገንዘብ በሆነ ነገር ንብረቱን አጥፍቶበታል። እግዚአብሔር የሚፈትንበት ወቅት አለ። እግዚአብሔር የሚፈትነን ግን ከፍ እንድንል ነው። ወርቅን በእሳት ሲፈትኑት ጥራቱ ከፍ እንደሚል። አንድን ፈተና ከእግዚአብሔር ይሁን ወይም ከሰይጣን ይሁን በምን እናውቃለን ለሚለው በቅድስና በንጽሕና ነው የሚታወቅ እንጂ ማንኛውም ሰው አያውቀውም። የሆነ ሆኖ ከማንም ይምጣ ከእኛ የሚጠበቀው ግን በድለን ከነበረ ንስሓ መግባትና መከራውን በትዕግሥት መቀበል ነው።

▶️፲፱. "ሰይጣንም መልሶ እግዚአብሔርን ቁርበት ስለ ቁርበት ነው። ሰው ያለውን ሁሉ ስለ ሕይወቱ ይሰጣል" ይላል (ኢዮ.2፥4)። ቁርበት ስለ ቁርበት ነው ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ቁርበት ስለቁርበት፣ ዓይን ስለዓይን፣ ጥርስ ስለጥርስ የመሳሰሉ ቃላት ቁርበት የወሰደ ቁርበት እንዲመልስ፣ ዓይን ያጠፋ ዓይኑ እንዲጠፋ፣ ጥርስ የሰበረ ጥርሱ እንዲሰበር የሚያመለክቱ የብሉይ ኪዳን ሕጎች ናቸው።

▶️፳. "ከዚያም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ። ያ ቀን ጨለማ ይሁን። እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው። ብርሃንም አይብራበት" ይላል (ኢዮ.3፥1-4)። ከዚያ "በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም" ይላል (ኢዮ.2፥10)። ሁለቱ ንባብ እንዴት ይታረቃል? ኢዮብ አማራሪ እንዳልሆነ በብዛት እንደምሳሌ ይጠቀሳል። የተወለደበትን ቀን ረገመ ሲባል በዚያች ዕለት እግዚአብሔር ባወቀ እንዲወለድ አድርጎታልና የፈጠረው እግዚአብሔርን አማረረው ማለት አይቻልም? አንዳንድ ሰው ሲከፋው የ40 ቀን ዕድሌ እያለ ብሶቱን ይገልጻል። ከዚህ ጥቅስ አንጻር ይሄ ሰው ያችን ሰው የሆነበትን ዕለት ረገመ ወይስ በዚያች ዕለት ሰው ያደረገውን እግዚአብሔርን አማረረ ነው የሚባለው?

✔️መልስ፦ ኢዮብ የተወለደባትን ቀን በመርገሙ ማንንም አልበደለም። ዕለት ግእዛን የላትም። አትናገርም፣ አትሰማም፣ ሕይወት የላትም። ቢመርቋትም አትጠቀምም፣ ቢረግሟትም አትጎዳም። ስለዚህ ኢዮብ ማንንም ስላልበደለ የሚጋጭ ነገር የለውም። እግዚአብሔርን እግዚአብሔር ሰጠ፣ እግዚአብሔር ነሣ እያለ ምስጋናውን አላቋረጠም። ዕለቲቱን መርገም እግዚአብሔርን ከመርገም አይቆጠርም። ዕለቲቱን የረገማት እንኳ እግዚአብሔርን ላለመርገም በማሰብ ነው። የአርባ ቀን እድሌ የሚለው ገለጻ ስሕተት ነው። እድል የሚባል ነገር በሃይማኖት የለም። በአርባ ቀን ተሥዕሎተ መልክእ ይፈጸማል። ስለዚህ ጽድቅንም ኃጢአትንም ለመሥራት የሚያበቁት አካላት ተቀርጸው የሚያልቁበት እንጂ እድል የሚታደልበት ቀን አይደለም። እግዚአብሔር ለሁሉም የመዳንን እድል ሰጥቷል። ያን መርጦ መኖር የሁሉም ሰው ድርሻ እንጂ ለጥቂቶች እንደ እድል የደረሰ ወይም የተሰጠ አይደለም።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Feb, 20:28


▶️፳፩. ኢዮ.1፥6 "ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ። የአምላክ ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ። ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ" ይላል። የአምላክ ልጆች ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ የአምላክ ልጆች ያላቸው ቅዱሳን መላእክትን ነው። የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርጉ የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆቹ ናቸውና።

▶️፳፪. ጻድቃን በዚህች ምድር የሚሠቃዩት ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ መከራ ከበዛ ዘንድ ጸጋ ይበዛልና ጸጋቸው ይበዛ ዘንድ በዚህ ምድር ሥቃይን ይቀበላሉ። ይኸውም በሰማይ ዋጋቸው ይበዛ ዘንድ ነው።

▶️፳፫. መከራ ሁል ጊዜ የኃጢአት ቅጣት ነው?

✔️መልስ፦ መከራ ሁል ጊዜ የኃጢአት ቅጣት አይደለም። ለምሳሌ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ ስትሰደድ ብዙ መከራዎችን ተቀብላለች። ክርስቶስ በመስቀል መከራን ተቀብሏል። ንጹሐ ባሕርይ እርሱ መከራ የተቀበለ መከራ ለሚቀበሉት ሰማዕታት አብነት ለመሆን ሲሆን ድንግል ማርያምም የተቀበለችው ጸጋዋ ይበዛ ዘንድ ነው። ስለዚህ ሰዎች በንጽሕና ሳሉም መከራን ሊቀበሉ ይችላሉ። በድለው መከራ የሚመጣባቸውም አሉ። ይኸውም ጥፋታቸውን አምነው እንዲጸጸቱ ለተግሣጽ ነው።

▶️፳፬. "በእውኑ ደንገል ረግረግ በሌለበት መሬት ይበቅላልን ወይስ ቄጠማ ውሃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን" ይላል። ደንገል ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ደንገል በባሕር ዳር፣ በውሃ ውስጥ የሚበቅል ወፍራም የሣር ዓይነት ነው።

▶️፳፭. እግዚአብሔር ለምን ኢዮብን ሰይጣን እንዲፈትነው ፈቀደለት?

✔️መልስ፦ የኢዮብ ትዕግሥት፣ የሰይጣን ሐሰት ለትውልዱ ይገለጽ ዘንድ ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Feb, 20:28


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 125 💙💙

▶️፩. "የእግዚአብሔር መላአክት በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ ሰይጣንም ከእነርሱ ጋር መጣ" ይላል (ኢዮ.1፥6)። ሰይጣን ቅዱሳን መላእክት በሚወጡበት ስፍራ ይገባ ይወጣ ነበር? ሰይጣን ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚነጋገረው ከመላእክት ጋር ይነጋገራል? እዚህ ላይ በሰዎች ዘንድ ሰይጣንን መቃወም ማራቅ እናደርጋለን። በመላእክት ዘንድስ እንዴት ነው ኑሮው? ያሸሹታል? ያቀረቡታል?

✔️መልስ፦ ሰይጣን ባለበት ኅሡር (ጎስቋላ) ቦታ ሆኖ፣ ቅዱሳን መላእክትም ባሉበት ክቡር ቦታ ሆነው ተናግረዋል። ቅዱሳን መላእክት የኢዮብን ደግነት ተናግረዋል። ሰይጣን ደግሞ ምቀኝነቱን አንጸባረቀ። ለኢዮብ ሁሉን ስለሰጠኸው ነው እንጂ አያመሰግንህም ነበር አለ። እግዚአብሔር ግን የኢዮብን ጻድቅነት ለእኛ ሊገልጽልን ፈልጎ ሰይጣን ያሰበውን እንዲያደርግ ፈቀደለት። መላእክት በራሳቸው ዓለም ማለትም በኢዮር፣ በራማ፣ በኤረር ይኖራሉ። ሰይጣናት ደግሞ በአየር፣ በዚህች ምድር፣ በሲኦል ይኖራሉ። መላእክት ለተልዕኮ ወደዚህች ዓለም ሲመጡ ሰይጣናት ይፈራሉ ይደነግጣሉ። በእነርሱ ፊት ቆመው ለመናገርም አቅሙ የላቸውም። ቅዱሳን መላእክት ሰይጣንን ያሳድዱታል እንጂ አያቀርቡትም። እግዚአብሔርም ቢሆን ሰይጣንን አላቀረበውም። ሰይጣን ባለበት ወራዳ ቦታ ሆኖ ሐሳቡን ተናገረ እንጂ።

▶️፪. "እግዚአብሔር ሰይጣንን አለው በባሪያዬ በኢዮብ ላይ የምታስበው እንዳይኖር ተጠንቀቅ" ይላል (ኢዮ.1፥8)። ይህ ዓይነት ንግግር የመጠራጠር ዓይነት አለው? ለምን እንደዚያ ተባለ? ከዚህ ጋር እግዚአብሔር ከሰይጣን ጋር እንዲህ ዓይነት ስምምነት ያደርጋል? ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚወደው ቤቱን ስለባረከለት እንዳልሆነ ያውቃል። ታዲያ ለሰይጣን ለምን ይህን ሥልጣን ሰጠው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር አስቀድሞ ሁሉን ስለሚያውቅ በንግግሩ ምንም የመጠራጠር ዓይነት የለም። በባሪያዬ በኢዮብ ላይ የምታስበው እንዳይኖር ማለቱ ደግ ነው እንጂ ምንም ክፋት እንደሌለበት ተረዳ ማለቱ ነው። ሰይጣን የእግዚአብሔር አንዱ ፍጥረት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ከሰይጣን ጋር አቻ ለአቻ ስምምነት አያደርግም። በኢዮብ ላይ መከራ ለማድረስ እንኳ ሰይጣን ስለማይችል ከእግዚአብሔር ፈቃድ ነው የጠየቀው። እግዚአብሔርም ትውልዱ የኢዮብን ትዕግሥት አስቦ እንዲማርበት በማለት ፈቅዶለታል። ስለዚህ ለሰይጣን ይህን ሥልጣን የሰጠው እኛ ከኢዮብ ሕይወት እንድንማር ነው።

▶️፫. "የተጠራጠርሁት ነገር መጥቶብኛልና ያሰብሁትም ደርሶብኛል" ይላል (ኢዮ.3፥35)። በዚህ ንባብ "ግእዙ ያልተጠራጠርሁት፣ ያላሰብሁት" ይላል ብሎ በግርጌ ማስታወሻ ተጽፏል። በእነዚህ ቃላት ትልቅ የትርጉም ልዩነት አላቸውና እንዳለ ለምን አልተተረጎመም? እንደዚህ ሲሆንስ ሐሳቡን አያዛባውም? ከግርጌ ማስታዎሻዎች ጋር ከሌላ በዕብራይስጥ እንደዚያ ይላል በግእዝ እንዲህ ይላል ተብሎ ይገለጻል። ለምን ከመጽሐፍ ቅዱስ መገኛ ቋንቋ ቀጥታ አልተተረጎመም? ከግእዝ ከተወሰደ የግእዙን ትርጉም ከዕብራይስጥ ከሆነ የዕብራይስጡን?

✔️መልስ፦ የአማርኛ መተርጉማን የተጠራጠርሁት ብለው መተርጎማቸው ከምን አንጻር እንደሆነ እኔም አልገባኝም። በእርግጥ በቃል በቃል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም አንዳንድ ጊዜ ሐሳቡን ይዞ ስለሚተረጎም የቃላት ልዩነት ሊኖር ይችላል። ከአርእስቱ ጀምረን ስንመለከተው ያልጠረጠርኩት፣ ያላሰብኩት መከራ ደረሰብኝ የሚለው ነው ሙሉ ሐሳቡን የሚይዘው። ምክንያቱም ኢዮብ ቀድሞ ይህ ሁሉ መከራ እንደሚደርስበት አላወቀምና ያላሰብኩት፣ ያልጠረጠርኩት የሚለው ነው የሚያስኬድ። የአማርኛና የሌሎች ቋንቋ መተርጉማን የተጠራጠርኩት፣ ያሰብኩት ብለው መጻፋቸው ከምን አንጻር እንደሆነ ስላላወቅሁት ስሕተት ነውም ልክ ነውም ማለት አልችልም። አንዳንድ ጊዜ የቃል በቃል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ ሐሳቡን ይዞ የሚተረጎምበት ወቅት ስላለ በሐሳብ አንድ ሆኖ በቃል የሚለያይበት ሁኔታ ሊኖር ይችላልና።

▶️፬. "ነገር ግን ሌዋታንን ለመግደል የተዘጋጀ ያችን ቀን የሚረግማት ይርገማት" ይላል (ኢዮ.3፥8)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሰማይና ምድር ሲያልፍ በአድማስና በናጌብ መካከል በዐቢይ ውቅያኖስ የምትኖረዋ ሌዋታንም ታልፋለች። ኢዮብ ሌዋታንን የሚያሳልፋት እግዚአብሔር የተወለድኩባትን ቀን ይርገማት ማለቱ ነው።

▶️፭. የኢዮብ ሚስት ለኢዮብ እግዚአብሔርን ሰድቦ እንዲሞት የጠየቀችው ሰይጣን ያጣችውን አስታውሷትና አድሮባት እንደሆነ የሚነገር ታሪክ ነበር። ከዚህ አልተጻፈም ከየት የተገኘ ነው?

✔️መልስ፦ መቼም ሰይጣን ያደረበት ሰው ካልሆነ በቀር እግዚአብሔርን ስደበው የሚል የለም። ቢያንስ በዚህ ሰዓት የኢዮብ ሚስት የሰይጣንን ሐሳብ የተሸከመች ሆና ተገኝታለች። ያጣችውን አስታውሳ ይህን እንዳለችው ራሱ መጽሐፈ ኢዮብም ያስረዳል (ኢዮ.2፥9)። ስለዚህ ስለተጻፈ መልሰው ይመልከቱት። አንድምታው ደግሞ ልትለምን ሄዳ ሰይጣን የሰውን ልቡና እንዳጸናባትና እንደመከራት ያስረዳል። ለተጨማሪ የኢዮብን አንድምታ ይመልከቱ።

▶️፮. "እነሆ አገልጋዮቹንም አይተማመናቸውም መላእክቱንም በጭንቅ ይጠራጠራቸዋል" ይላል (ኢዮ.4፥18)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የነገሩ ባለቤት ልቡናቸው ንጽሕናቸው ነው። የመላእክት ልቡናቸው ንጽሕናቸው አይተማመናቸውም ማለት ንጹሕ ሆነው ተፈጥረው ሳለም የወደቁ መኖራቸውን ለመግለጽ ነው።

▶️፯. "ስድስት ጊዜ ከክፉ ነገር ያድንሃል በሰባተኛውም ጊዜ ክፋት አትነካህም" ይላል (ኢዮ.5፥19)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ስድስት ያለው ሠላሳውን ዓመት በአምስት በአምስት ከፍሎ ነው። ኢዮብ ሠላሳ ዓመት ነው የታመመው። ስለዚህ ለሠላሳ ዓመት ከታመምክ በኋላ በሰባተኛው ማለት በሠላሳ አንደኛው ዓመት ትፈወሳለህ ማለት ነው።

▶️፰. "ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሷል" ይላል። ጓል ለብሷል ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ጓል የሚባለው የተድበለበለ አፈር ነው።

▶️፱. ኢዮ.3፥1 ጀምሮ ኢዮብ የተናገረው ማማረር የሚመስል ነገር እናገኛለን። ቀደም ብሎ ግን እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ በማለት ተናግሮ ነበር። ታዲያ ከዚያ በኋላ ለምን ማማረር በሚመስል መልኩ እንደዚያ አለ? ንባቡን ቢያስረዱን?

✔️መልስ፦ ኢዮብ እግዚአብሔርን አላማረረም። በሽታው ሲጸናበት የተወለደባትን ቀን ነው የረገማት። አሁን ዕለቲቱ የምትጎዳ ሆና አይደለም። ግእዛን የሌላትን ዕለት ረገመ። በጭንቅ በሽታ ሆኖ ግእዛን የሌላትን የማትጎዳ ዕለትን ረገመ እንጂ እግዚአብሔርን አላማረረም።

▶️፲. የኢዮብ ወዳጅ የሆነው ቴማናዊው ኤልፋዝ ኢዮብን ለማጽናናት ከሌሎች ወዳጆቹ ጋር እንደመጣ በምዕራፍ 2 ተገልጿል። በምዕራፍ 4 እና 5 የተገለጸው ኢዮብ ይህ ሁሉ መከራ የመጣበት በኃጢአቱ ምክንያት እንደሆነ ነው የሚገልጸው? ከሆነስ ለምን?

✔️መልስ፦ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ከተናገሩት ውሸትም ነበረበት። ለዚያም ነው መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር የገሠጻቸው። ኢዮብ ኃጢአት ሳይሠራ ነው መከራ የመጣበት። ይኸውም መከራ ከበዛ ዘንድ ጸጋ ይበዛልና በኋላ ጸጋው ይበዛለት ዘንድ ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Feb, 15:20


የኔታ ገብረ መድኅን እንደጻፉት

ብዙ ጊዜ በጉባኤ ቤት ደረጃ ደቀ መዛሙርቱ ከሚቸገሩባቸው ነገሮች አንዱ ደቀ መዛሙርቱ ሲታመሙ ህክምና ማግኘት አለመቻላቸው ነበር።

ዶክተር አንዷለምና ጓደኞቹ ግን አይደለም የማከሚያ ቦታቸው ሂደን ይቅርና ወደ ጉባኤ ቤት በመምጣት ያክሙን ነበር።

መነኮሳትን እና ደቀ መዛሙርትን በሙያችን የማከም ሀላፊነት አለብን ብለው ባላቸው ጊዜ በየጉባኤው እየዞሩ የድርሻቸውን ተወጥተዋል።

የጤና አጠባብቃችን ምንም መሆን እንዳለበት በተወደደ ጊዜያቸው ጉባኤ ቤት እየተመላለሱ አስተምረውናል።

ሰማዕቱ ዶክተር ደግሞ የተለየ ትሁት ወንድም ነበረ።ተማሪ ታሞብኛል ምን ይሻላል? ስለው ወደዚህ ከመምጣቱ በፊት በስልክ ልጠይቀው አገናኘኝ ይለኛል።ከዚያም ወደ ሆስፒታል የሚያስሄድ ጉዳይ ከሆነ በዚህ ቀን ይምጣ ይላል።በሌለ ጎኑ ደቀ መዛሙርትን የሚያክምልን ወጪው በራሱ ሁኖ በነጻ ብቻ ነው።

ይሄንን ትሁት ወንድም ማጣት እጅጉን ያማል፣ያበሳጫል፣ያሳዝናል።
ሃይማኖተኛ እና እውነተኛ ሰዎች ታሪካቸው ብዙ እድሜያቸው ግን አጭር ነው።
ትንሿን እድሜያቸውን ለእውነት እና ለቅንነት ስለሚኖራት ትርፍ ያልተሠራበት እድሜ የላቸውም።

በቅንነት እና በአገልግሎት ሲፋጠኑ በግፍዕ የሚሞቱ የሕያዋን ሰማዕታት ደማቸው እንደ አቤል እና ዘካርያስ ደም ግፈኞቹን ይካሰሳል።

ፍትሀ እግዚአብሔር በጊዜው ጊዜ መድረሷ አይቀርምና ግፈኞች ለንጹሓን ሰማዕታት በቀዱት የግፍዕ ፅዋ መጠጣታቸው አይቀርም።

ከጥንት ጀምሮ የእግዚአብሔር አሠራሩ ልሚዱ እንዲህ ነውለጻድቁ ፈርዶ ዋጋውን በኃጥኡ ፈርዶ ፍዳውን ማምጣት። "እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት"ራእ.፲፰፥፮ እንዲል።በግፍዕ የተገደለውን የሰማዕቱን ደም የሀገራችን ቤዛ ያድርገው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Feb, 07:18


የዶ/ር አንዱዓለም ዳኘን ቤተሰብ ለማገዝ ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ ለዚሁ ዓላማ ተብሎ የተከፈተው የጥምር የባንክ ሂሳብ ቁጥር መረጃ ይህ መሆኑን እያሳወቅን ስለምታደርጉት እገዛ በቅድሚያ እናመሰግናለን::

Account Holder Names:

Dr. Hailemariam Awoke
Dr. Amsalu Worku
Dr. Mequanint Yimer

Bank: Commercial Bank of Ethiopia (CBE), Bahir Dar Branch

Account No:

1000676116978

© College of Medicine and Health Science, Bahir Dar University

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Feb, 05:33


💞 መጽሐፈ ኢዮብ ክፍል 1 💞

💞ምዕራፍ ፩፡-
-ኢዮብ አውስጢድ በሚባል ሀገር ይኖር እንደነበር
-ኢዮብ ቅን፣ ንጹሕና ጻድቅ፣ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ከክፉ ሥራ ሁሉ የራቀ ነበር
-ኢዮብ ሰባት ወንዶች ልጆችና ሦስት ሴቶች ልጆች እንዲሁም ብዙ ሀብት እንደነበረው
-ኢዮብ ስለ ልጆቹ በቁጥራቸው የኃጢአት መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ያቀርብ እንደነበር
-ሰይጣን የኢዮብን ልጆች እንደገደላቸውና ንብረቱንም ሁሉ እንዳጠፋበት

💞ምዕራፍ ፪፡-
-ሰይጣን በኢዮብ ላይ ደዌን እንዳመጣበት
-የኢዮብ ሚስት ኢዮብን እግዚአብሔርን ስደበውና ሙት እንዳለችው
-ኢዮብ መከራ በደረሰበት ጊዜ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በከንፈሩ እንዳልበደለ
-የኢዮብ ወዳጆች ኢዮብን ሊጎበኙት እንደመጡ

💞ምዕራፍ ፫፡-
-ኢዮብ የተወለደባትን ቀን እንደረገመ
-ሞት ለሰው ዕረፍቱ እንደሆነ

💞ምዕራፍ ፬፡-
-ቴማናዊው ኤልፋዝ ኢዮብን በመከራ ሳለህ ነገር አታብዛ እንዳለው
-ቴማናዊው ኤልፋዝ ኢዮብን አንዳች እውነት አድርገህ ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ባልደረሰብህም ነበር እንዳለው

💞ምዕራፍ ፭፡-
-እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ እንደሆነ
-የአምላክን ተግሣጽ መናቅ እንደማይገባ

💞💞💞የዕለቱ ጥያቄዎች💞💞💞
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ኢዮብ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ኢዮብ የሚኖር ኢትዮጵያ ነበር
ለ. ኢዮብ ቅን ንጹሕና ጻድቅ ነበር
ሐ. ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነበር
መ. ኢዮብ ከክፉ ሥራ ሁሉ የራቀ ነበር
፪. ከሚከተሉት ውስጥ መጨረሻ ላይ የተከናወነው የትኛው ነው?
ሀ. የኢዮብ ልጆች መሞታቸው
ለ. የኢዮብ ንብረት መዘረፉ
ሐ. የኢዮብ መታመም
መ. የኢዮብ ግመሎች መማረካቸው
፫. ኢዮብ ከታመመ በኋላ ሚስቱ ኢዮብን ምን አለችው?
ሀ. እግዚአብሔርን ስደበውና ሙት
ለ. እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ
ሐ. እግዚአብሔርን አመስግነው
መ. ለ እና ሐ
፬. በታመመ ጊዜ ኢዮብን ሊጠይቁት ከመጡት ሦስት ወዳጆቹ ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ቴማናዊው ንጉሥ ኤልፋዝ
ለ. ሊቀ ነቢያት ሙሴ
ሐ. አውኬናዊው መስፍን በልዳዶስ
መ. አሜናዊው ንጉሥ ሶፋር

https://youtu.be/YoOGwroAT20?si=jcIpFPwOqutp_JQj

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Feb, 18:16


አንዳንዴ በምድር መኖር አሰልቺ ይሆንብህና ደጋግ ሰዎችን ስታይ ግን መኖርን ትወዳለህ። መኖርን ከሚያስመኙህ ሰውነትን በትክክል ከምታይባቸው ሰዎች አንዱ ዶ/ር አንዱዓለም ነበር።

እንግዲህ ምን እንላለን። እግዚአብሔር ከደጋጉ አባቶች ጋር በገነት ያኑርልን። ደግነት፣ ቅንነት፣ እርጋታ፣ ትሕትና ሥጋ ለብሰው በአንተ ይታዩ ነበር።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Feb, 15:44


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 124 💙💙

▶️፩. "የጻድቅም የኃጥእም ነፍስ ብትሆን ከሥጋዋ በተለየች ጊዜ ከእግዚአብሔር ብቻ በቀር ነፍስ የምትሄድበትን ጎዳና የሚያውቅ የለም" ይላል (3ኛ መቃ.9፥4)። ጻድቅ ከሆነ ነፍሱ ወደ ገነት ኃጥእ ከሆነ ደግሞ ነፍሱ ወደ ሲኦል እንደምትሄድ እየታወቀ ነፍስ የምትሄድበትን ጎዳና የሚያውቅ የለም ለምን አለ?

✔️መልስ፦ የጻድቅ ሰው ነፍስ ወደ ገነት፣ የኃጥእ ሰው ነፍስ ወደ ሲኦል እንደሚገቡ ይታወቃል። ማን ኃጥእ፣ ማን ደግሞ ጻድቅ እንደሆነ የሚያውቀው ግን እግዚአብሔር ነው። ነፍስ ከሥጋዋ ከተለየች በኋላ በየት በኩል አድርጋ ወደ ገነት እንደምትገባ ወይም ወደ ሲኦል እንደምትገባም ከእግዚአብሔር በቀር የሚያውቅ የለም ማለት ነው። ማን ጻድቅ እንደሆነ ማን ደግሞ ኃጥአ እንደሆነ የሚያውቅ ደግሞ እግዚአብሔር ብቻ ነው። መላእክትም ነፍስን ወደ እግዚአብሔር የፍርድ ቦታ የሚወስዷት የእርሱን ቃል ሰምተው ነውና።

▶️፪. "ከእግዚአብሔር ወደሚያርቅ ወደ ከንቱ ፈቃድ እንዳይሆንባችሁ በእናንተ ጽኑ ነቀፋ መቀማጠል መብልንና ተድላን ደስታንም መውደድ በእናንተ አይገኝ። ያለልክ የጠገበች ሰውነት የእግዚአብሔርን ስም አታስብምና የዲያብሎስ ሀብት ያድርባታል እንጂ። በእርሷ መንፈስ ቅዱስ አያድርባትምና ተድላ ደስታውን መውደድ በእናንተ አይገኝ" ይላል። በምድር ተድላን ደስታን መውደድ ኀጢአት ነው?

✔️መልስ፦ ያለልክ መብላት፣ ሰማያዊውን ሕይወት ዘንግቶ በምድር ላይ ብቻ ተድላ ደስታን መውደድ (ንብላዕ ዮም ወንሙት ጌሠመ ማለት) አዎ ኃጢአት ነው። ኃጢአት ማለት ማጣት ማለት ነው። ምድራዊ ተድላ ደስታን የሚወድ ሰው ሰማያዊውን ተድላ ደስታ ያጣልና።

▶️፫. "እግዚአብሔርን ሕጉን ለሚጠብቁ ለአባቶቻቸው በአዘጋጀው ቤት በመንግሥተ ሰማይም መወደድንና ክብርን ይሰጣቸዋል፡፡ በአምልኮቱና በሕጉም ጸንተው ለኖሩ ከሕጉም ላልወጡ ለተንከባከባቸው ለመገባቸው ሥርዓቱንና ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ ለአገነናቸው ለአሳደጋቸው ለአባቶቻቸው በአዘጋጀው ቦታ በመንግሥተ ሰማይ መወደድንና ክብርን ይሰጣቸዋል። እኔም ጠላታቸውን በማድከም ሰውነታቸውንም በመጠበቅ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ለወዳጆቹ የሚያደርገውን አየሁ" ይላል (3ኛ መቃ.9፥17)። አየሁ፣ ይሰጣቸዋል እያለ የተናገረው ማን ነው?

✔️መልስ፦ እንዲህ እያለ የተናገረው የመጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ጸሓፊ ነው።

▶️፬. "በሥልጣኑ በቃሉ ያለ አባትና ያለ እናት ይፈጠራሉና የሞቱ ሰዎች አይነሡም የምትል አንተ ስውረ ልቡና እውቀት ጥበብ ካለህ የሞቱ ሰዎች በፈጣሪያቸው በእግዚአብሔር ቃል እንዴት አይነሡም ትላለህ" ይላል (3ኛ መቃ.10፥6)፡፡ ያለ አባትና ያለ እናት ይፈጠራሉ ሲል ምን ማለት ነው ቢያብራሩልን?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ያለ እናት ያለ አባት መፍጠር እንደሚችል በአዳም በመላእክት ይታወቃል። ለአዳም ለመላእክት እናት አባት የላቸውምና። ስለዚህ ሰውንና መላእክትን ያለ አባት ያለ እናት መፍጠር የሚችል እግዚአብሔርን ሙታንን ማስነሣት ይሳነዋል ማለት ተገቢ አለመሆኑን ለማስረዳት የቀረበ ቃል ነው።

▶️፭. "ዓለሙን ሁሉ ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ከሕጉ ከሥርዓቱ የወጣ የለም" ይላል (3ኛ መቃ.9፥2)። ከጥንተ ጠላታችን ከዲያብሎስ ጀምሮ እስካሁን ብዙዎች (አሕዛብም ይሁኑ ወይም እኛ የምናምን ግን ሕጉን የማንጠብቅ) እያለን ከሕጉ ከሥርዓቱ የወጣ የለም ለምን አለ?

✔️መልስ፦ ከዚህ ሕግ ያለው አድርግ አታድርግ ብሎ ለነባብያን ፍጥረታት የተናገረውን ሳይሆን የተፈጥሮ ሕግን ነው። የተፈጥሮ ሕግን የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ነው። ፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር በሠራላቸው የተፈጥሮ ሕግ ይኖራሉ ለማለት ነው። ይህም ለመሆኑ ቀጥሎ "የንስርን መብረር፣ የእባብን መኖሪያና የመሳሰሉትን በመጥቀሱ ይታወቃል።

▶️፮. 3ኛ መቃ.9፥21 የሰዎች ይቅር ባይነት (ዘፍ.50፥17፤ ዘፀ.10፥17፤ ማቴ.6፥14) እና የመልአክ ይቅር ባይነት (ዘፀ.23፥21) ከእግዚአብሔር ይቅር ባይነት በምን ይለያል?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ወይም መሓሪነት የባሕርይ ነው። ይህም ማለት ለመሓሪነቱ ሌላ ምክንያት የለም። የሰዎችና የመላእክት ይቅር ባይነት ግን ከፈጣሪ የተሰጠ (የጸጋ) ነው። ስለዚህ ልዩነቱ የእርሱ የእግዚአብሔር የባሕርይ፣ የሰዎችና የመላእክት ደግሞ የጸጋ በመሆን ነው።

▶️፯. 3ኛ መቃ.9፥33 ራቁታቸውን ይቆማሉ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ራቁታቸውን ይቆማሉ ያለው በትንሣኤ ጊዜ ሰው ሁሉ ሲነሣ (ጻድቃንም ኃጥኣንም) ሌላ ልብስ ይዘው አይነሡም። ራቁታቸውን ይነሣሉ ለማለት ነው። ልክ አዳም በገነት ሳለ እንደነበረው ራቁታቸውን ይነሣሉ እንጂ። ሲነሡ ግን የጻድቃን አካል እንደ ፀሐይ ስለሚያበራ ኃፍረታቸው አይታይም። የኃጥኣንም አካል እንደ ቁራ የጠቆረ ሆኖ ስለሚነሣ ኃፍረታቸው አይታይም።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Feb, 05:11


💙 ሦስተኛ መጽሐፈ መቃብያን ክፍል 2 💙

💙ምዕራፍ ፮፡-
-የምንሞትበትን ቀን ማሰብ እንደሚገባ
-እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎችን አጋንንት እንደሚፈሯቸው
-ኃጥኣን ዘመናቸው ሳያልፍ ንስሓ መግባት እንደሚገባቸው
-ያለ ልክ የጠገበች ሰውነት እግዚአብሔርን እንደማታስብ
-ያለ ልክ መብላትና መጠጣት ማመንዘርም እንደ እሪያ መሆን እንደሆነ
-በልክ የሚበላ ሰው በእግዚአብሔር መሠረት እንደ አድማስ የጸና እንደሚሆን
-እግዚአብሔርን የማይወዱ ሰዎች ቃሉን እንደማይጠብቁና ልቡናቸውም የቀና እንዳልሆነ

💙ምዕራፍ ፯፡-
-በእግዚአብሔር የሚያምኑ ሰዎች ፍርሃት እና ድንጋጤ እንደሌለባቸው

💙ምዕራፍ ፰፡-
-ኢዮብ በደረሰበት መከራ ልቡን እንዳላሳዘነ መገለጹ
-ወደእኛ ከሚላኩ ጠላቶች ብንታገሥ ብፁዓን እንደሆንን መነገሩ

💙ምዕራፍ ፱፡-
-ፍጥረታት ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆኑና እርሱም እንደሚመግባቸው መነገሩ
-ነፍሳችን ከሥጋችን ሳትለይ የፈጣሪያችንን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድንፈጽም

💙ምዕራፍ ፲፡-
-ስለትንሣኤ ሙታን መነገሩ
-ለሰው ጌጡ ንጽሕና፣ ጥበብና ዕውቀት፣ ያለ መቅናትና ያለ ምቀኝነትና መዋደድ እንደሆነ
-ክፉ ላደረገብህ ሰው ክፉ ነገር አለማድግ እና መታገሥ እንደሚገባ
💙💙💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙💙💙
፩. አጋንንት የሚፈሯቸው እነማንን ነው?
ሀ. ብዙ ገንዘብ ያላቸው ሰዎችን
ለ. እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎችን
ሐ. ብዙ ምድራዊ ሠራዊት ያላቸውን
መ. ሀ እና ሐ
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የጻድቃን ነፍሳት በመላእክት ይባቤ ደስ ይላቸዋል
ለ. የኃጥኣንን ነፍሳት አጋንንት ይዘባበቱባቸዋል
ሐ. ጻድቃን ይህንን ዓለም ስለናቁት ደስ ይላቸዋል
መ. ሁሉም
፫. በእግዚአብሔር ስለሚያምኑ ሰዎች ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ፍርሃትና ድንጋጤ የለባቸውም
ለ. ልቡናቸው የቀና (ቅን) አይደለም
ሐ. ሰላም የላቸውም
መ. ለ እና ሐ
፬. በመጽሐፈ መቃብያን መሠረት የሰው ጌጥ ከተባሉት መካከል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ያለመቅናትና ያለምቀኝነት መዋደድ
ለ. ጥበብና ዕውቀት
ሐ. ንጽሕና
መ. ሁሉም

https://youtu.be/7_mvKBWeQLE?si=WwSn8ZWi4j8bc9qk

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Feb, 18:19


▶️፲፪. "ምልክቶችንም ባሳየኋቸው ጊዜ በባልንጀሮቻቸው ልቡና አድራለሁ። በልቡናቸውም እየራሱ የሆነ የምልክት ነገርን አሳድራለሁ የቃላቸውንም ምልክት አሳይቼ አሳትኳቸው" ይላል (3ኛ መቃ.1፥11)። እነዚህ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

✔️መልስ፦ ምልክቶቹን ቀጥሎ ጠቅሷቸዋል። በከዋክብት አካሄድ፣ በደመና መውጣት፣ በእሳት ማናፋት፣ በአውሬዎችና በወፎች ጩኸትና በመሳሰሉት መነሻነት እንደሚያስት ተገልጿል።

▶️፲፫. "ከእኔ ጋራ የተሰደዱ ሰይጣናት የተባሉ የሥልጣናትን ዘውድ ለነእርሳቸው ስጣቸው። ከእኔ ከሠራዊቶቼም ምድረ በዳ በሆነች በዙፋኔ በቀኝህ አስቀምጣቸው" ይላል (3ኛ መቃ.1፥20)። የሥልጣናትን ዘውድ ለነእርሳቸው ስጣቸው ሲልና በዙፋኔ በቀኝህ አስቀምጣቸው ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሰይጣን መቀባጠር ልማዱ ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር አፉን ከፍቶ፣ ፊቱን ጸፍቶ አናግሮታል። በሰይጣን በቀድሞው መልካም ቦታ ጻድቃን ሰዎች እንደሚገቡበት የሚያመለክት ቃል ነው። በቀድሞ የክብር ዙፋኔ አስቀምጣቸው ማለት ታስቀምጣቸዋለህ ማለት ነው።

▶️፲፬. "እኔም የአዳምን ልጆች በሁሉ እተንኰልባቸዋለሁ። እነርሱን ማሳት ከተቻለኝ በበጎ ሥራ ይጸኑ ዘንድ አልተዋቸውም። የአዳምን ልጆች ሁሉ እተነኰልባቸዋለሁና የዚህን ዓለም ተድላ ደስታ አጣፍጥላቸዋለሁም። መጠጥንና መብልን ልብስንም በመውደድ ነገርንም በመውደድ በመንሣትና በመስጠትም ቢሆን" ይላል። መጠጥንና መብልን ልብስንም በመውደድ ነገርንም በመውደድ ሲል ቢያብራሩልን?

✔️መልስ፦ ሰይጣን ሥጋዊ ምግብን፣ ሥጋዊ መጠጥን፣ ሥጋዊ ልብስን በማስወደድ፣ ለወንዱ ሴትን በፍትወት በማስወደድ፣ ለሴቷ ወንድን በፍትወት በማስወደድ ከሰማያዊው ሕይወት ለማስቀረት ይጥራል ማለት ነው።

▶️፲፭. "አንተ በተመካህ ጊዜ እግዚአብሔር ክፉ ሥራህን አይቶ አንተ ከሠራዊቶችህ ጋራ እግዚአብሔርን ክደሃልና ሳያጓድል ስሙን ያመሰግን ዘንድ አዳምን ፈጠረው" ይላል (3ኛ መቃ.2፥11)። ለአዳም የመፈጠሩ ምክንያት የሳጥናኤል  ክሕደት ነው እንዴ? ሳጥናኤል የካደው በተፈጠረበት ዕለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ ሳጥናኤል ቢክድ በእርሱ ቦታ አዳም ተፈጥሯል። ሳጥናኤል የካደ በተፈጠረበት ዕለት በዕለተ እሑድ ነው።

▶️፲፮. 3ኛ መቃ.2፥14 ላይ "ስለዚህ ነገር በተዋረዱ ሰዎች ይመሰገን ዘንድ አዳምን ከመሬት ፈጠረው" ይላል። የሰው ልጅ (አዳም) እንደተፈጠረ ወዲያውኑ ትእዛዙን አፍርሷል። ታዲያ በተዋረዱ ሰዎች ይመሰገን ዘንድ አዳምን ከመሬት ፈጠረው ለምን  አለ?

✔️መልስ፦ አዳም እንደተፈጠረ ወዲያውኑ ትእዛዙን አልሻረም። ሰባት ዓመት ከሁለት ወር ከአሥራ ሰባት ቀን እግዚአብሔርን ከመላእክት ጋር እያመሰገነ በገነት ኖሯል እንጂ። በኋላ ወድቋል። ንስሓ ገብቶ መልሶ እግዚአብሔርን የሚያመሰግን ሆኗል። እስከ ዕለተ ምጽአት የሚነሡ ጻድቃንም እግዚአብሔርን እያመሰገኑት ይኖራሉ።

▶️፲፯. "የበለስ ፍሬን ከበላች በኋላ መጥታ የእግዚአብሔር መጀመሪያ ፍጥረቱ አዳምን አሳተችው የፈጣሪዋን ትእዛዝ ስለ ተደፋፈረች በእርሱም በልጆቿም ሞትን አመጣች" ይላል (3ኛ መቃ.3፥6)። መጀመሪያ ሔዋን በልታ ከዚያ በኋላ ነው ለአዳም እንዲበላው የሰጠችው? አዳም ዕፀበለስ መሆኑን ራሱ አውቆ ከበላ ለምን "አዳምን አሳተችው" ተባለ?

✔️መልስ፦ ዕፀ በለስን እንብላ የሚለውን ሐሳብ ለአዳም የነገረችው ለመጀመሪያ ጊዜ ሔዋን ስለሆነች (መነሻ ምክንያት ስለሆነች) አዳምን አሳተችው ተብላለች። እንጂ እርሱ ራሱም ዕፀ በለስ መሆኑን እያወቀ ነው የበላው።

▶️፲፰. "የአዳም ምስጋና ከመላእክት ምስጋና ጋራ አንድ ሆነ ምስጋናቸውም የተካከለ ሆነ" ይላል (3ኛ መቃ.4፥11)። የመላእክት ምግባቸው እግዚአብሔርን ማመስገን ነው ይባላል። አዳም ደግሞ ሰው ነውና ይበላል ይጠጣል። ምንም እንኳ አብዝቶ ቢያመሰግን እንደ መላእክት ምስጋና ይሆናል እንዴ? ምስጋናቸውም የተካከለ ሆነ ለምን አለ?

✔️መልስ፦ የተካከለ ነው መባሉ በብዛት፣ በሰዓት ሳይሆን ዋጋ በማሰጠት ነው። መላእክት እግዚአብሔርን በማመስገናቸው በክብር ላይ ክብር፣ በዕውቀት ላይ ዕውቀት እየተጨመራቸው እንደሚኖሩ ሰውም እግዚአብሔርን በማመስገኑ በክብር ላይ ክብር በዕውቀት ላይ ዕውቀት ይጨምራል ማለት ነው።

▶️፲፱. "እርሱ ከመደረጉ በፊት ሁሉን ያውቃልና ትእዛዙንም እንድታፈርስ ሳይፈጥርህ አወቀህ ዓለም ሳይፈጠር በእርሱ ዘንድ የተሰወረ ምክር አለና በካድኸው ጊዜ ባርያው አዳምን በመልኩ በምሳሌው ፈጠረው" ይላል (3ኛ መቃ.4፥14)። የተሰወረ ምክር የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ የተሰወረ ምክር ያለው የእግዚአብሔርን ባሕርያዊ ዕውቀት ነው። እግዚአብሔር ሳጥናኤልን ገና ሳይፈጥረው ጀምሮ እንደሚስት ያውቅ እንደነበረና እርሱ ሲስት አዳምን በምትኩ ይፈጥረው እንደነበረ ያውቅ ነበር። ይህንን ዕውቀት ነው የተሰወረ ዕውቀት ያለው። የተሰወረነቱ ለእኛ ነው። እስኪገለጥ ድረስ ይህ ለፍጡራን ስውር ነበርና።

▶️፳. 3ኛ መቃ.4፥35 ዲያብሎስ እና ሠራዊቶቹ (አጋንንት) ንስሓ ሊገቡ ይችላሉን? ንስሓ የማይገቡ ከሆነስ እያወቀ ጸሓፊው ለምን በንስሓ ተናዘዝ ይላል?

✔️መልስ፦ ትዕቢት ወጥሯቸው ነው እንጂ ንስሓ እንዳይገቡ የሚከለክላቸው ሌላ ነገር የለም። ስለዚህ አሁንም አጋንንት ዕቡይነታቸውን ትተው ንስሓ ቢገቡ ይጠቀሙ ነበር። ካልገቡም ራሳቸውን ይጎዳሉ እንጂ ሌላ ማንንም አይጎዱም።

▶️፳፩. 3ኛ መቃ.1፥21 ዲያብሎስ ሰውን ከአመድ እና ከመሬት እንደተፈጠረ ይናገራል ከአመድ ግን አልተፈጠረም። ታዲያ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሰው ከመሬትና አመድ ተፈጠረ የሚለው ያው ከመሬት ተፈጠረ ለማለት ነው። አንድ ወገን ነው የተለየ ነገር አይደለም። ሰው ከመሬት፣ ከነፋስ፣ ከውሃ፣ ከእሳት ተፈጥሯል። ከመሬት ብቻ ተፈጠርክ ቢል ስሕተት ነበር። ከተፈጠረበት አንዱን ጠቅሶ ከዚያም መፈጠሩን መግለጽ ግን ምንም ስሕተት የለውም። አመድ ያለው ያው መሬቱን ነው።

▶️፳፪. 3ኛ መቃ.2፥22 ሰው ሥጋ (body) ነፍስ (soul) ልቡና (spirit) አለው ይላል። አንዳንድ ሊቃውንት ደግሞ ሰው ነፍስ እና ሥጋ ያለው (dichotomy) ነው እንጅ trichotomy አይደለም ምክንያቱም ነፍስ እና ልቡና የአንድ ነገር ሁለት መጠሪያዎች ናቸውና ይላሉ። እርስዎ የነፍስ እና የመንፈስ ልዩነቱ ምንድን ነው ይላሉ?

✔️መልስ፦ ሰው ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋና ከአንዲት ባሕርየ ነፍስ የተገኘ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው። ሰው ነፍስና ሥጋ ያለው አንድ ነው። ስለዚህ አተያያችንን ካስተካከልነው ሁለቱም ትክክል የሚሆንበት አግባብ አለ። Dichotomy ሰው ነፍስና ሥጋ አለው የሚል ነው። Trichotomy ደግሞ ሰው ሥጋ፣ ነፍስና መንፈስ አለው የሚል ነው። መንፈስ የሚለው ብዙ ጊዜ የነባቢት ነፍስን ለባዊነቷን ነው። Dichotomy ባልን ጊዜ የነፍስን ለባዊነት (መንፈስን) ከነፍስ ጨምረን መቁጠር ነው። በሌላ አገላለጽ ለቀድሶ ሥጋ ወነፍስ ወመንፈስ ሲል ይገኛል። በዚህ ጊዜ ደማዊት ነፍስን፣ ነባቢት ነፍስን፣ ሥጋን ለብቻው ቆጥሮ Trichotomy ይላል። ይህንኑ Dichotomy ባለ ጊዜ ደማዊት ነፍስንና ሥጋን በአንድ ቆጥሮ፣ ነባቢት ነፍስን ለብቻዋ ይቆጥራል። ስለዚህ Dichotomy ወይም Trichotomy ብንል ከምን አንጻር እንደተናገርነው መለየት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Feb, 18:19


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 123 💙💙

▶️፩. "ያሳትኋቸው ሰዎች ከእኔ ጋር በእሳት ይጨመሩ ዘንድ ከፈጠረኝ ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን አለኝ" ይላል (3ኛ መቃ.1፥16)። ብዙ ጊዜ ዲያብሎስ ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚነጋገርና እንደሚጠይቅ የሚነግሩን ንባቦች አሉ። በምን ዓይነት አኳኋን ነው ፊቱ የሚቀረበው? እዚህ ላይ ደግሞ ዲያቢሎስ እንደ ተገዳዳሪ አቻ ኃይል ያለው አያስመስለውም ወይ? እንዲህስ እንዲያደረግ ለምን ተፈቀደለት?

✔️መልስ፦ ዲያብሎስ በጣም ደካማ ፍጡር ነው። በራሱ ጥፋት የወደቀ መልአክ ነው። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ያፈነገጡ ሰዎች ከሰይጣን ጋር እየተሰቃዩ እንደሚኖሩ ለማሳወቅ የተነገረ ነው። በሲኦል ኃጥእ ሰውም ሰይጣንም ሁሉም ይሰቃያሉ እንጂ አንዱ ብቻ አይሰቃይም። ዲያብሎስ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር የሚያበቃ ምንም ነገር የለውም። እግዚአብሔር የዲያብሎስን ፈቃድ ዐውቆ የዲያብሎስ ፈቃድ የእኛ ጥፋት እንደሆነ ሊያሳውቀን ነው በቅዱሳኑ አድሮ የነገረን። ሰይጣን ቃል ኪዳን አለኝ ያለው ያጠፉ ሰዎችም እንደእኔ ይሰቃያሉ ማለቱ ነው። እግዚአብሔር የበደለ ሰውንም ሲኦል ስለሚያስገባ ይህን ለመግለጽ የተነገረ ነው። እንጂ እግዚአብሔር ሰውን አሳስት ብሎ ልዩ ፈቃድ አልሰጠውም። ሰይጣን ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ነው በራሱ ላይ ፈርዶ ተግቶ ሰውን ለማሳሳት የሚጥር። ልዩ ቃል ኪዳንም አልተሰጠውም እንደ አንተ ያመፁት በሲኦል ይቃጠላሉ ተባለ እንጂ።

▶️፪."እንደ በገና በተለያዩ ብዙ ስልቶች የሚያመሰግኑ አስር ሕሊናትን ፈጠረለት" ይላል (3ኛ መቃ.2፥23)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው? ለአዳም የተፈጠረለት አሥር ኅሊናት ምን ምን ናቸው? የሰው ሕሊና (ማሰቢያ) አንድ አይደለምን?

✔️መልስ፦ አሥር፣ መቶ፣ ሺህ፣ እልፍ ወዘተ የመሳሰሉ ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ተብለው ይተረጎማሉ። ለአዳም ፍጹም የሚያስብ ሕሊና መሰጠቱን ይገልጽልናል። እንጂ በቁጥር አሥር ሐሳቦች ብቻ ተሰጡት ማለት አይደለም። የሰው ማሰቢያ ኅሊና አንድ ነው።

▶️፫. "ለአዳም ግን ክፉ የሆኑ አምስት አሳቦችና በጎ የሆኑ አምሰት አሳቦች አሥር አሳቦች ተሰጡት" ይላል (3ኛ መቃ.3፥1)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው? እነዚያ አምስት ክፉ አሳቦችና አምስት በጎ አሳቦች ምን ምን ናቸው?

✔️መልስ፦ አምስት የአሥር ግማሽ ነው። አሥር ፍጹም ተብሎ እንደሚተረጎም ከዚህ ቀደም አይተናል። የአዳም ፍጹም ኅሊናው እንደ ነጭ ልብስ መሆኑን ለመግለጽ ነው። ነጭ ልብስ ቀይ ቀለም ቢቀቡት ቀይ ይሆናል። ጥቁር ቀለም ቢቀቡት ጥቁር ይሆናል። ስለዚህ ለአዳም ክፋትም ደግነትም የሚስማማው አካል እንደተሰጠው ለመግለጽ አምስት ክፉ ሐሳቦች፣ አምስት በጎ ሐሳቦች ተሰጡት አለ። እንጂ እግዚአብሔር ክፉ ሐሳብን ፈጥሮ ለአዳም ሰጠው ማለት አይደለም።

▶️፬. "ጌታውም አዳምን ይቤዠው ዘንድ አለው። አንተንም ያሳፍርሃል። በጉንም ከተኩላው አፍ ያድነዋል" ይላል (3ኛ መቃ.4፥1)። ይህ ንባብ ስለማን ነው የሚናገረው? አዳም በዚህ መጽሐፍ በግ እየተባለ ተጠርቷል በምን ምክንያት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ንባብ የሚያስረዳን አዳምን ወልደ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ እንደሚያድነው ነው። አዳም በበግ፣ ሰይጣን በተኵላ ተመስለዋል። ተኵላ በግን እንደሚበላ ሰይጣንም አዳምን አሳስቶ ከገነት አስወጥቶታልና።

▶️፭. ይህ መጽሐፈ መቃብያን ብዙ አሳቦች አሉት ብዙ ጊዜ በሰባክያን ትምህርትና በመጽሐፍ ሲጠቀስ አይታይም (በኔ መረዳት)። በምን ምክንያት ነው? በቤተክርስቲያናችንስ ይህን መጽሐፍ ጠቅሶ ያስተማረ አባት አለ?

✔️መልስ፦ ቅዱሳን ሊቃውንት በጣም ይጠቅሱት የነበረ መጽሐፍ ነው። ለምሳሌ ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስን ብንመለከተው ስለትንሣኤ ሙታን የገለጸው በከመ ይቤ መቃቢስ ብሎ ባይጠቅስ እንኳ ሐሳቦቹ ከመጽሐፈ መቃብያን ጋር በእጅጉ የተቀራረቡ ናቸው። ቅዱሳን ሠለስቱ ምእትም በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ሁለት እንደገለጹት መጽሐፈ መቃብያን ከመጻሕፍት አምላካውያት አንዱ ነው። ስለዚህ በዚህ እንደተጠቀሰ ያስተውሉ። ስለዚህ ቅዱስነቱ ከተነገረ ጠቅሶ ማስተማር የመምህር የሰባኪ ድርሻ ነው።

▶️፮. 3ኛ መቃ.1፤15 "ለበታቼ አልሰግድም በማለቴ" ይላል ሰይጣን። የጠፋው በዚህ ምክንያት ነውን?

✔️መልስ፦ ሰይጣን ውሸታም ነው። ሰይጣን የወደቀው አምላክ ሳይሆን አምላክ ነኝ ብሎ በመዋሸቱ እንጂ ለአዳም አልሰግድም በማለቱ አይደለም።

▶️፯. 3ኛ መቃ.2፤8 ላይ ነቢይ የተባለው ማን ነው?

✔️መልስ፦ ስሙ አልተገለጸም። ከሌላም መጽሐፍ አላገኘሁትም።

▶️፰. 3ኛ መቃ 3፥8 "ይተክሉ ዘንድ እግዚአብሔር በሰጣቸው በገነት ፍሬና በምድር ፍሬ ይረጋጉ ዘንድ" ይላል። ይህ እንዴት ሊያረጋጋ ይችላል?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ከገነት ቢያስወጣቸውም ተርበው እንዲሞቱ ግን አላደረገም። ምግብ በመስጠት አረጋጋቸው ማለት ነው። ምግብ የሚሆኑ ፍሬያት ያረጋጋሉ መባሉ ረኃብን ስለሚያርቁ ነው። ልጆች ያረጋጋሉ መባሉ ልጆች አባቶቻቸውን በመርዳት ደስ ያሰኛሉና ነው።

▶️፱. 3ኛ መቃ.1፥2 "ማደሪያዬም ላደረኳቸው ሰዎች ምልክትን አሳያቸዋለሁ በከዋክብት አካሄድም ቢሆን፣ በደመና መውጣትም እሳት ማናፋትም ቢሆን" ይላል። በደመና መሄድ ሰይጣናዊ ነው ማለት ይቻላል? እነ ተዋነይ በጥበብ ወይንስ እንደሚባለው በሰይጣናዊ ግብር በደመና ይሄዱ የነበረው?

✔️መልስ፦ በደመና መሄድ ሁሉ ሰይጣናዊ አይደለም። ሐዋርያው ቶማስ በደመና ተጭኖ እየሄደ ያስተምር ነበርና። ይህ ሲሆን በእግዚአብሔር ረድኤት ነው። በሰይጣን ተንኮል በደመና ተጭኖ መሄድ ግን ኃጢአት ይሆናል። ባለቅኔው ተዋነይ በደመና ይሄድ እንደነበር እንዲሁ ይነገራል። በእግዚአብሔራዊ ጥበብ ይሆን በምን ይሆን የተገለጸ ነገር አላገኘሁም። በደመና ይሄድ ነበር ለሚለው ራሱ አፈ ታሪክ እንጂ ታሪካዊ ማስረጃ ማግኘት አልቻልኩም።

▶️፲. 3ኛ መቃ.1፥1 "ግፈኛና አሳች የፈጣሪዉንም መንገድ የሚፃረር ዲያብሎስን ስለሚበቀለው በኋላ ዘመን ስለሚመጣው ቸርና የዋህ የግብጽ ደሴቶች ደስ ይላቸዋል" ይላል። ይህ መቼ የሚሆን ነው? ክርስቶስ ሲወለድ ነው? የግብጽ ደሴቶችን ለይቶ ለምን ደስ ይላቸዋል አለ?

✔️መልስ፦ አዎ ይህ ስለክርስቶስ መወለድ የተነገረ ትንቢት ነው። የግብጽ ደሴቶች ደስ ይላቸዋል ያለው ክርስቶስ ወደ ግብጽ ተሰዶ የግብጽን ጣዖታት እንደሚያጠፋ ለመግለጽ ነው። ለይቶ የግብጽ ደሴቶችን የጠቀሰ ክርስቶስ ከእናቱ ጋር የተሰደደ በተለየ ወደ ግብጽ ስለሆነ ነው።

▶️፲፩. 3ኛ መቃ.5፥10 "በንጹሕ ልቡናህም እሰጣለሁ ባልክ ጊዜ አጋንንት እንደ ውሾች ደጅ ይጠኑሀል። ሁሉንም ያስረሱሀል ብትነሣም ልትሰጥ ብትወድም የማይጠቅምህንና የማትበላዉን ገንዘብ ታደልብ ዘንድ የዚህ ዓለም ገንዘብ ያስጎመጅሃል። ይሰበስባሉ የሚሰበስቡለትንም አያውቁም ተብሏልና" ይላል። ሰው እሰጣለሁ ብሎ የሚያስበዉ መጀመሪያ በንጹሕ ልቡ አይደለም ወይ? እዚህ ቢያብራሩልኝ መምህር።

✔️መልስ፦ ይህ እሰጣለሁ እያለ ለማይሰጥ ክፉ ሰው የተነገረ ቃል ነው። ይህንንም ከቁጥር 4 ጀምረን ስናነበው እንረዳዋለን። በንጹሕ ልቡ አስቦ የሚሰጥን ሰው እግዚአብሔር ይወደዋል። እሰጣለሁ እያለ እያሰበ በተግባር የማይሰጥ ሰው ግን ክፉ ሰው ስለሆነ ተገሥጿል።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Feb, 04:44


መልካምነት፣ ትሕትና፣ ምሁርነት ማን እንደ አንተ
የአንተን ሞት መስማት ልብ ይሰብራል።

ዶ/ር Andualem Dagne (በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊስት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር)

በምድር መኖር አሰልቺ ይሆንብህና አንዳንድ ደጋግ ሰዎችን ስታይ ግን መኖርን ትወዳለህ። መኖርን ከሚያስመኙህ ሰውነትን በትክክል ከምታይባቸው ሰዎች አንዱ ዶ/ር አንዱዓለም ነበር።

እግዚአብሔር በአፀደ ነፍስ ከደጋጉ አባቶች ጋር ያኑርህ
ለልጆችህና ለባለቤትህ ለእህታችን Bezaye Girma (ቤዛዬ ግርማ) ፈጣሪ መጽናናትን ይስጥልን።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Feb, 00:50


💚 ሦስተኛ መጽሐፈ መቃብያን ክፍል 1 💚

💚ምዕራፍ ፩፡-
-ዲያብሎስ ግፈኛና አሳች የፈጣሪውንም መንገድ የሚጻረር እንደሆነ
-ዲያብሎስ በገንዘብና በመልከ መልካም ሴቶች ምክንያት ብዙ ሰዎችን እንደሚያሳስት
-ዲያብሎስ በሟርተኞች እያደረ ብዙዎችን እንደሚያሳስት
-የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማይጠብቁ ሰዎች ከዲያብሎስ ጋር ለዘለዓለም በገሃነም እንደሚኖሩ

💚ምዕራፍ ፪፡-
-ሰይጣን ማሳት ያልቻላቸው ሰዎች መንግሥተ ሰማያትን ወርሰው እንደሚኖሩ
-ዲያብሎስ በብዙ መልኩ ሰውን እንደሚያሳስት

💚ምዕራፍ ፫፡-
-እግዚአብሔር ያመሰግነው ዘንድ ለዲያብሎስ አንድ ኅሊና ሰጥቶት እንደነበረና ዲያብሎስ ግን እንደሳተ መነገሩ
-እግዚአብሔር ለአዳም አሥር አሳቦች እንደሰጠው መገለጡ
-አዳምና ሔዋን በዲያብሎስ ምክር ከገነት እንደወጡ መነገሩ

💚ምዕራፍ ፬፡-
-ጌታ አዳምን እንደሚቤዠው መነገሩ
-እግዚአብሔር አዳምን በመልኩና በምሳሌው እንደፈጠረው
-አዳም በንስሓ ወደ እግዘአብሔር እንደተመለሰ

💚ምዕራፍ ፭፡-
-የፈጠረንን ልዑል እግዚአብሔርን ማወቅ እንደሚገባ
-በእጅ ሥራ መመገብ እንጂ ቅሚያ ተገቢ እንዳልሆነ
-ከብዙ የኃጢአተኞች ገንዘብ በእውነት ያለ ጥቂት ገንዘብ እንደሚሻል

💚💚💚የዕለቱ ጥያቄዎች💚💚💚
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ስለ ዲያብሎስ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የፈጣሪውን መንገድ የሚጻረር ነው ሐ. ግፈኛና ትዕቢተኛ ነው
ለ. ሰውን የሚያሳስት አሳሳች ነው መ. ሁሉም
፪. ዲያብሎስ ሰውን በምን ሊያሳስት ይችላል?
ሀ. መጠጥንና ስካርን በማብዛት ሐ. ስድብንና ቁጣን በማብዛት
ለ. ቧልትንና ቀልድን በመናገር መ. ሁሉም
፫. ዲያብሎስ ሔዋንን እንዴት አሳታት?
ሀ. በእባብ ልቡና አድሮ በመምከር ሐ. ሀ እና ለ
ለ. አስገድዶ ዕፀ በለስን አፏ ላይ በማስገባት መ. ሁሉም

https://youtu.be/VsC0psPVEcg?si=VUnnUJhg9em-J1Z0

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Feb, 15:40


25ኛ PDF (ኻያ አምስተኛ ስስ ቅጂ)
በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

መጽሐፍ ቅዱስን በተከታታይ ማጥናት ከጀመርን አራት ወር ሆኖናል። በዚህም እስካሁን ወደ ሁለት ሺ ለሚጠጉ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል። የሁሉም ጥያቄዎች በPDF በዚሁ ቴሌግራም ቻናሌ ተለቋል። በእግዚአብሔር ቸርነት ሦስተኛ መጽሐፈ መቃብያንን ነገ ማለትም ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንጀምራለን። የንባቡ ሕግ ለመድገም ያህል እንደሚከተለው ነው።

1ኛ፦ በቀን አምስት አምስት ምዕራፍ ማንበብ (አምስት አምስት እያነበብን ሳለ በምዕራፉ መጨረሻ አካባቢ አንድ፣ ሁለት ወይም ሦስት ምዕራፎች ከተረፉ መጨረሻ ላይ ስድስት፣ ሰባት ወይም ስምንት ምዕራፍ ማንበብ)።

2ኛ፦ ከዕለቱ ምዕራፎች ምን ያህል እንደተረዳን ለማወቅ በየዕለቱ የምጠይቃቸውን ጥያቄዎች በኮሜንት መመለስ።

3ኛ፦ ካነበባችሁት የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያልገባችሁንና ግልጽ ያልሆነላችሁን ጉዳይ መጠየቅ። በፌስቡክ በሚሴንጀር፣ ወይም በቴሌግራም የሕይወት መጽሐፍ በሚለው የመወያያ ግሩፕ https://t.me/betremariamabebaw መጠየቅ ትችላላችሁ። ጊዜን ለመቆጠብ ያህል ጥያቄ መጠየቅ የሚቻለው ከዕለቱ የንባብ ምዕራፎች ብቻ ነው።

4ኛ፦ ጥያቄያችሁ ግልጽ እና የሚነበብ ይሁን። በምናነበው ምዕራፍ ውስጥ ከሓድያን፣ መና*ፍ//ቃ*ን፣ ኤቲስት ወይም ሌሎች የሚጠይቋችሁ ጉዳይ ካለ አምጡት ጠይቁት። ቤተክርስቲያን ለሁሉም ምላሽ አላት።

5ኛ፦ በቀን አምስት ምዕራፍ ለማንበብ ጊዜ የሚያጥራችሁ ሰዎች ካላችሁ ደግሞ የየዕለቱን በድምፅ በዩቲይብ ቻናሌ ስለምለቀው እየሄዳችሁም፣ እየሠራችሁም ማዳመጥ ትችላላችሁ። የዩቲይብ ቻናሌ We belong to Christ ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።


በዚህ መሠረት እያነበብን ከዚህ ደርሰናል። አዲስ መከታተል የሚፈልግ ካለ ወይም ጀምሮ ያቋረጠ ካለ ደግሞ ካለንበት ጀምሮ እያነበበ ያልገባውን እየጠየቀ መቀጠል ይችላል። ከዚህ ቀደም ጠይቃችሁኝ ምላሽ የሰጠሁባቸውን ጥያቄዎች መልሰው ሲጠየቁ አልመልስም። PDF ስላለ ከዚያ ማየት ይቻላል። ማንበብ፣ መማር፣ መጠየቅ የሚፈልግ ካለ ይምጣ። ሼር በማድረግ አሳውቁት።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Feb, 14:46


▶️፲፩. 2ኛ መቃ.20፥2-4 "ለጎዳናችንም ስንቅ ባልያዝን ጊዜ ለሰውነታችንም ልብስ በሌለን ጊዜ ለእጃችን ምርጉዝ ለእግራችንም ጫማ በሌለን ጊዜ ድጥም ጎጣጉጥም ቢሆን ጨለማም ቢሆን እሾህም አሜከላም ቢሆኝ የውሃም ጥልቅ የጕድጓድም ጥልቅ ቢሆን " ሲል ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ስንቅ፣ ልብስ፣ ለእጃችን ምርጉዝ ካልያዝንና ለእግራችን ጫማ ከሌለን እኒህ ሁሉ ሳይኖሩን መንገዱ ድጥ ጎጻጉጽ ጨለማ ከሆነ በእሾህ በአሜኬላ፣ በጉድጓድ ገብተን እንደምንጎዳ ሁሉ ሁሉ ምንም መልካም ሥራ ሳንሠራ ኖረን ኃጥኣን ሆነን ሳለ ብንሞት አጋንንት ወደ ታላቅ መከራ ይወስዱናል ማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Feb, 14:46


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 122 💙💙

▶️፩. 2ኛ መቃ.16፥2 በትንሣኤ የምንለብሰው ሥጋ የሁላችንም ተመሳሳይ ነው? ረቂቅ ወይስ ግዙፍ ነው? አካሉ የጎደለ ሰው በትንሣኤ ሙሉ አካል ይዞ ነው የሚነሣው? ትንሣኤ በምንለብሰው ሥጋ አጭር፣ ረጅም፣ ወፍራም፣ ቀጭን፣ ጥቁር ቀይ ነውን?

✔️መልስ፦ ምንም እንኳ ይዘነው የምንነሣው አካል አሁን ያለንን አካል ቢሆንም ያን ጊዜ ግን ይህ አሁን ያለን አካል የሁሉም ተመሳሳይ ቁመናና መልክን ይዞ እንዲነሣ እግዚአብሔር ያደርገዋል። ይህም ማለት ፍጹም ሌላ አካል ሳይሆን ያንኑ አካል አዲስ አድርጎ ያስነሣዋል ማለታችን ነው። ስለዚህ ያን ጊዜ አጭር፣ ረጅም፣ ወፍራም፣ ቀጭን፣ ጥቁር፣ ቀይ ተብሎ የሚለያይ አይኖርም። ሁሉም በተመሳሳይ መልክና ቁመና ይነሣል። አካሉ የጎደለ ሰውም ያን ጊዜ ሙሉ አካል ሆኖ ይነሣል። አዲስ አካል ይገጠምለታል ማለት አይደለም። ከነበረው አካል እግዚአብሔር የጎደለውን ሞልቶ ያስነሣዋል ማለት ነው። የሚነሣው ሥጋ የግዙፍ ረቂቅ ነው። መዳሰስ የሚችል ግዙፍ ቢሆንም ረቂቅነትንም ገንዘብ ያደረገ አካልን ይዘን እንነሣለን። ለዚህ አብነቱ ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ ከትንሣኤ በኋላ ተዳሷል፣ ታይቷልና። ረቂቅ ብቻ ሆነን ብንነሣ ኖሮስ በኵረ ትንሣኤያችን ክርስቶስም ከትንሣኤ በኋላ ባልታየ ባልተዳሰሰ ነበር። አሁን ምንም እንኳ ነፍስ ብትኖርም በሥጋ መደበኛነት እንደምንኖር ሁሉ ከትንሣኤ በኋላ ደግሞ ምንም እንኳ ሥጋ ቢኖርም በነፍስ መደበኛነት እንኖራለን።

▶️፪. በትንሣኤ ወንዶች የሠላሳ ዓመት ሰው ሴቶች የአሥራ አምስት ዓመት ሰው ሆነው ይነሣሉ ብለው ያስተማሩ የጥንት የቤተ ክርስቲያን አባቶች አሉን? እነማን?

✔️መልስ፦ በሐተታ በቅዳሴ አትናቴዎስ ተገልጿል። ከቀድሞ አባቶች ቃል በቃል በዘር የተጻፈ ግን እስካሁን አላገኘሁም። የሆነ ሆኖ መተርጉማንም ትውፊትን ይዘው ስለሚተረጉሙ ወንዶች የሠላሳ ዓመት ሴቶች የአሥራ አምስት ዓመት ቁመናን ይዘው እንደሚነሡ ተገልጿል። "አልቦ አሜሃ ሐፂር ወነዊህ። ያን ጊዜ አጭር ረጅም የለም። ሐተታ፦ ወንዱ በአቅመ አዳም የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሴቲቱ በአቅመ ሔዋን የአሥራ አምስት ዓመት ቆንጆ ሆነው ይነሣሉ። ጸሊም ወቀይሕ። ያን ጊዜ ቀይ ጥቁር የለም። አላ አሐዱ አካል ወአሐዱ ኅብር። አንድ አካል አንድ መልክ ሆነው ይነሣሉ እንጂ። ጻድቃን ክርስቶስን መስለው ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርተው ይኖራሉ። ኃጥኣን ዲያብሎስን መስለው ከቁራ ሰባት እጅ ጠቁረው ይነሣሉ" እንዲል (ቅዳሴ አትናቴዎስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 31)።

▶️፫. "የስንዴ ቅንጣት ግን እግዚአብሔር የፈጠራት ነባቢት ነፍስ ያደረችበት የአዳም አምሳል ነው" ይላል (2ኛ መቃ.17፥6)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው? የስንዴ ቅንጣት ለብቻ የአዳም አምሳል ለምን ተባለች?

✔️መልስ፦ መጽሐፈ መቃብያን ምሥጢረ ትንሣኤን በስንዴ ቅንጣት (ፍሬ) መስሎ ይገልጻል። አንዲት የስንዴን ፍሬ በእርሻ መካከል ብንዘራት በርጥበት፣ በሙቀት አማካኝነት ትበሰብስና ታበቅላለች። አብቅላ አብባ አፍርታ ወደ ጎተራ ትገባለች። እንደዚሁ ሁሉ ሰው ከሞተ ከበሰበሰ በኋላ በዕለተ ምጽአት እግዚአብሔር ተነሥ ሲለው ይነሣል ማለት ነው።

▶️፬. አንድ መጽሐፍ ብሉይ ኪዳን የሚባለው የተጻፈበት ዘመን ነው ወይስ ሌላ? ከዚህ አያይዤ ይህ የመጽሐፍ ክፍል በብሉይ ኪዳን ዘመን ለመጻፉ ማስረጃው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ቀድመው የተጻፉ በመሆናቸው ብሉይ ተብለዋል። መጽሐፈ መቃብያን ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ለመሆኑ ማስረጃው ቅዱሳን ሊቃውንት በፍትሐ ነገሥት የብሉይ ኪዳን ክፍሎች ብለው ከጠቀሱልን አንዱ ስለሆነ ነው (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 2)።

▶️፭. "እግዚአብሔር የዘራቸው ሥጋና ነፍስ ተዋሕደው ይነሣሉ እንጂ በጎ ሥራ የሠሩ ሰዎች ክፉ ሥራ በሠሩ ሰዎች አይለወጡም። ክፉ ሥራም የሠሩ ሰዎች በጎ ሥራ በሠሩ ሰዎች አይለወጡም" ይላል (2ኛ መቃ.16፥8)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ አልገባኝም ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ይህ ማለት በትንሣኤ ጊዜ በዚህ ምድር ክፉ ሲሠራ የነበረው ኃጥእ ሲነሣ ጻድቅ ሆኖ አይነሣም። ያው ኃጥእ ሆኖ ይነሣል። በዚህ ምድር መልካም ሥራን ሲሠራ የነበረ ጻድቅ ሲነሣም ኃጥእ ሆኖ አይነሣም። ያው ጻድቅ ሆኖ ይነሣል ማለት ነው። በትንሣኤ ጊዜ ጻድቁ ኃጥእ፣ ኃጥኡ ጻድቅ ሆነው ተለዋውጠው አይነሡም። ጻድቁም ጻድቅ ሆኖ ይነሣል ኃጥኡም ኃጥእ ሆኖ ይነሣል ማለት ነው።

▶️፮. የእጅና የእግራችን ጥፍር የራሳችንም ጸጉር የትንሣኤ ሙታን ምሳሌ ሁነው ተጠቅሰዋል (2ኛ መቃ.16፥1-2)። እንዴት ምሳሌ ሆነው እንደተጠቀሱ ቢያብራሩልኝ?

✔️መልስ፦ ጸጉራችንን ብንላጨው እንኳ መልሶ ያበቅላል። ጥፍራችንንም ብንቆርጠው መልሶ ያወጣል። እንደዚሁ ሁሉ እኛም ምንም እንኳ ብንሞት በትንሣኤ መልሰን እንደምንነሣ ያስረዳል። ጸጉር ተላጭቶና ጥፍር ተቆርጦ የሚወጣው ጸጉርና ጥፍር አዲስ ነው። እንደዚሁ ሁሉ እኛም ሞተን ስንነሣ ምንም እንኳ የነበረንን ሥጋ ይዘን የምንነሣ ብንሆንም ነገር ግን ሞት፣ ረኃብ፣ ጥም የማይስማማው ሐዲስ ሆኖ እንደሚነሣ ያስረዳናል።

▶️፯. 2ኛ መቃ.17፥8 ወይን ይበላል እንዴ?

✔️መልስ፦ አዎ ፍሬው ከመጠመቁ በፊት (ሳይጠመቅ) ልክ እንደ ቀጋ እንደ አጋም ሁሉ ፍሬው ይበላል።

▶️፰. "የጨለማ ዳርቻ ወደ ሆነ ጥርስ ማፋጨትና ልቅሶ ወዳለበት" ይላል (2ኛ መቃ.16፥12)። ብዙ ቦታ ስለ ገሃነም ሲገልጽ "በዚያ ጥርስ ማፋጨትና ልቅሶ ይሆናል" የሚሉ ቃላት አብረው ይጠቀሳሉ። በገሃነም ውስጥ ጥርስ ማፋጨት ሲባል ምን ማለት ይሆን?

✔️መልስ፦ ማልቀስና ጥርስ ማፋጨት የመጨነቅ፣ የኀዘን ምልክቶች ናቸው። ሰው ሲፈራ፣ ሲጨነቅና ጤናው ሲቃወስ ጥርሱ እርስ በእርሱ ይፋጫል። በምጽአት ጊዜም ኃጥኣን የዘለዓለም ስቃይ ሲፈረድባቸውና ወደ ገሃነም ሲገቡ በኀዘን፣ በፍርሀትና በጭንቀት ሆነው እያለቀሱ፣ ጥርሳቸውን እያፋጩ ይኖራሉ ማለት ነው።

▶️፱. "እነርሳቸው ጥቋቁሮች ናቸውና ወደ ጨለማም ይመሩናልና ፊታቸውን አናይም"  ይላል (2ኛ መቃ.20፥6)። ጥቋቀሮች ናቸውና ካለ በኋላ ፊታቸውን አናይም ይላል አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። በብርሃን ነው እንጂ በጨለማ የሰው ማንነት አይታወቅም። እንደ ጨለማ ጥቋቁሮች ከመሆናቸው የተነሣ ፊታቸው አይታይም ማለት የጥቁርነታቸውን መጠን አጉልቶ የሚያሳይ አነጋገር ነው። ጥቋቁሮች ከመሆናቸው በተጨማሪ የሚመሯቸውም በብርሃን ሳይሆን በጨለማ ስለነበር መልካቸው አይታወቅም ተብሏል። "ወኢንሬኢ ገጾሙ እስመ ጽልመት እሙንቱ ወውስተ ጽልመት ይመርሑነ" ያለው ለዚህ ነው።

▶️፲. "የእግዚአብሔርን ፈቃድ ካደረጉ ከሴትና ከአዳም ተወልደዋልና በእግዚአብሔር ቃል ያመኑ በትእዛዙም ፀንተው የኖሩ" ይላል (2ኛ መቃ.21፥24)። አዳም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አፍርሶ ዕፀ በለስን በልቶ እያለ እንዴት የእግዚአብሔርን ፈቃድ አደረገ አለው?

✔️መልስ፦ ምንም እንኳ አዳም ዕፀ በለስን በመብላት እግዚአብሔርን በድሎ የነበረ ቢሆንም ንስሓ ገብቶ ከፈጣሪው ጋር ስለታረቀና ቀሪ የሕይወት ዘመኑን በመልካም ሥራ ስላሳለፈ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አደረገ ተብሏል። ሰው በደሉን በንስሓ አርቆ ምግባር ትሩፋት በመሥራት የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ይችላልና።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Feb, 01:52


💖 ሁለተኛ መጽሐፈ መቃብያን ክፍል 4 💖

💖ምዕራፍ ፲፮፡-
-ምሥጢረ ትንሣኤን በጸጉር፣ በጥፍር መረዳት እንደሚቻል
-በጎ ሥራን የሠሩ ሰዎች የሕይወት ትንሣኤን እንደሚነሡ
-ክፉ ሥራን የሠሩ ሰዎች የደይን ትንሣኤን እንደሚነሡ

💖ምዕራፍ ፲፯፡-
-ትንሣኤ በስንዴ ቅንጣት ተመስሎ መነገሩ

💖ምዕራፍ ፲፰፡-
-የሙታንን መነሣት የማያምኑ ሰዎች በዕለተ ትንሣኤ ጊዜ እንደሚጸጸቱ

💖ምዕራፍ ፲፱፡-
-ምድር መኳንንትን፣ ታላላቆችን፣ ክቡራንን፣ የተዋቡ ሴቶችንና መልካማ ቆነጃጅትን ሳይቀር፣ ደም ግባት ያላቸውን፣ ምሁራንን፣ ቃላቸው የሚያምረውን፣ ዜማቸው ደስ የሚያሰኙትን፣ ጽኑዓንን፣ ኃያላንን ሁሉ በሞት እንደሰበሰበቻቸው መገለጹ
-ምግባችንን ከመሬት እንደምናገኝና ስንሞት ደግሞ ሥጋችንን፣ ደም ግባታችንን መሬት እንደምትበላው መገለጹ
-የጻድቃንን ነፍሳት ይቀበሉ ዘንድ ወደ ሕይወት ብርሃን ቦታም ይወስዱ ዘንድ ወደ ደጋጉ የሚላኩ ረቂቃን መላእክተ ብርሃን እንደሆኑ

💖ምዕራፍ ፳፡-
-በዕለተ ትንሣኤ በምድር የሠራነው ሥራችን ሁሉ እንደማይሰወርና እንደሚገለጥ

💖ምዕራፍ ፳፩፡-
-በሞት እንደምናልፍ ገንዘባችንም እንደሚያልፍ መረዳት እንደሚገባ

💖💖💖የዕለቱ ጥያቄዎች💖💖💖
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትንሣኤን የሚያስረዳ ምሳሌ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የእጅ እና የእግር ጥፍር
ለ. የራስ ጸጉር
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ስለጻድቃን ትንሣኤ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የደይን ትንሣኤን ይነሣሉ
ለ. የሕይወት ትንሣኤን ይነሣሉ
ሐ. ወደ ዘለዓለም ቅጣት ይሄዳሉ
መ. ምሕረት ወደሌለበት ገሃነም ይገባሉ
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ሰው በሕይወተ ሥጋ ሳለ ምግቡን ከመሬት ያገኛል ሲሞት ሥጋው ወደመሬትነት ይለወጣል
ለ. የጻድቃንን ነፍሳት መላእክተ ብርሃን ወደ ሕይወት ብርሃን ይወስዷቸዋል
ሐ. የኃጥኣንን ነፍሳት መላእክተ ጽልመት ዘለዓለማዊ ቅጣት ወዳለበት ቦታ ይወስዷቸዋል
መ. ሁሉም

https://youtu.be/b_WkfJ2qEPo?si=Kf-c7IoYfv4Dg94i

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Jan, 15:46


▶️፲. "ይህንንም ነገር ተናግሮ ሳይጨርስ ስሙ ጥልምያኮስ የሚባል መልአከ ሞት ወርዶ ልቡን መታው በዚያችው ሰዓት ሞተ" ይላል (2ኛ መቃ.12፥13)። በመቃብያን ቀዳማዊ ላይ ግን  ጺሩጻይዳን የወባ ትንኝ ነክሳው እንደሞተ ነበር የተገለጸውና አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። በብሉይ ኪዳን ማንኛውም ሰው በማንኛውም በሽታ ቢታመምም ነፍሱ ከሥጋው የሚለየው ግን በመልአከ ሞት አማካኝነት ነበር። ስለዚህ ጺሩጻይዳን ወባ ነከሰችውና በጣም ታመመ። በእርሷ ምክንያት ለሞት ደረሰ። ነፍሱን ከሥጋው ደግሞ መልአከ ሞት ለየው። ስለዚህ ምንም የሚጋጭ ነገር የለውም። አንዱ ከአንዱ ጋር የተያያዘ ነውና። ሰው በበሽታ ታሞ ቢሞት የሞቱ መንሥኤ በሽታው ቢሆንም በኋላ ነፍስ ከሥጋ የሚለይ ግን መልአከ ሞት ነው። ስለዚህ የጺሩጻይዳንን ሞት መነሻ ምክንያት ሲያይ በወባ ትንኝ ሞተ ሲባል፣ ነፍሱን ከሥጋ የለየውን ሲያይ በመልአከ ሞት ሞተ ተብሏል።

▶️፲፩. "ሳምራውያን ግን ሥጋችን ትቢያ ይሆናልና አይነሣም ይላሉ" ይላል (2ኛ መቃ.14፥2)። በሌላ ደግሞ "ሰዱቃውያን ግን ነፍሳችን ከሥጋችን ከወጣች በኋላ ከሞቱ ሰዎች ጋራ አንነሣም ለሥጋና ለነፍስም ከሞት በኋላ መነሣት የላቸውም ከሞትንም በኋላ አንነሣም ይላሉ" የሚል አለ (2ኛ መቃ.14፥7)። የሁለቱ ሐሳብ ልዩነት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የሰዱቃውያን ትምህርት ሰው ሲሞት ነፍሱ እንደ ጉም ተና ትጠፋለች፣ ሥጋውም ፈርሶ በስብሶ ይቀራል የሚል ነው። የሳምራውያን ትምህርት ደግሞ ነፍስ ትኖራለች እንጂ አትጠፋም። ሥጋ ብቻ ነው ፈርሶ በስብሶ የሚቀር የሚል ነው።

▶️፲፪. 2ኛ መቃ.14፥16 ላይ "ሥጋህም ከነፍስህ ተለይቶ ከኖረ በኋላ እንደ አባታችን እንደ አዳም ሥጋ ሰባት እጥፍ ሆኖ የእግዚአብሔር የቸርነቱ ጠል ታስነሣሃለች" ያለው ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ሰባት እጥፍ የሚለው ፍጹም ለማለት ነው። እስመ ኍልቍ ሳብዕ ፍጹም በኀበ ዕብራውያን እንዲል። ስለዚህ በምጽአት ጊዜ ምንም ምን ሳይጎድል አካልህ ይነሣል ማለት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መተርጉማን ይህን በጥሩ ተርጉመውታል። ግእዙ "ወሥጋከኒ ተአቲቶ ከዊኖ ምስብዒተ በከመ ሥጋሁ ለአቡነ አዳም ታነሥአከ ጠለ ምሕረቱ ለእግዚአብሔር" የሚለውን "ሥጋህም ከነፍስህ ከተለየ በኋላ እንደ አባታችን እንደ አዳም ሥጋ ፍጹም ሆኖ በእግዚአብሔር በቸርነቱ ጠል ይነሣል" ብለው ተርጉመውታል።

▶️፲፫. "ሥጋዎችም ሬሳቸው በወደቀባት ቦታ ይሰበሰባሉ ነፍሳት የሚኖሩባቸው ቦታቸውም ይከፈታሉ ነፍሳትም ቀድሞ ወደ ተለዩበት ወደ ሥጋ ይመለሳሉ" ይላል (2ኛ መቃ.14፥33)። በትንሣኤ ዘጉባኤ ነፍስና ሥጋ መጀመርያ በተለያዩበት ቦታ (ውሃ ያሰጠመውም ውሃ ውስጥ፣ አውሬ የበላውም የተበላበት ቦታ ላይ፣ ወዘተ) ይዋሓዳሉ ማለቱ ነው? እንደዚያ ከሆነ "በደብረ ጽዮን ከበጎቹ ጋር በቀኝ ያቁመን" የምንለው ጸሎት ምን ይሆን?

✔️መልስ፦ አዎ ቀጥታ የተገለጸው እንዲህ ነው። ሰው ሬሳው ከወደቀበት ሆኖ እንደሚነሣ በግልጽ ተጽፏል። "ወይትጋብኡ ሥጋት ውስተ መካናቲሆሙ ኀበ ወድቀ አብድንቲሆሙ" ያለው ለዚህ ነው። ቀሪ የትንሣኤን አፈጻጸም ስንደርስበት የምናውቀው ይሆናል። ከየወደቁበት ሆነው ከተነሡ በኋላ ጻድቃንን በቀኙ፣ ኃጥኣንን በግራው ያቆማቸዋል። ስለዚህ እኛንም በቸርነቱ በቀኙ ያቁመን እንላለን። በቀኙ ያቁመን ማለት የዘለዓለም ሕይወትን ይስጠን ማለት ነው። በግራ አቆማቸው ማለት ወደ ዘለዓለማዊ የመከራ ቦታ እንዲሄዱ ፈረደባቸው ማለት ነው። በደብረ ጽዮን እግዚአብሔር ነግሦልን ይኖራል ማለት በመንግሥተ ሰማያት ነግሦልን ይኖራል ማለት ነው።

▶️፲፬. 2ኛ መቃ.14፥1 አይሁድ በትንሣኤ ሙታን አያምኑም እንዴ? በተጨማሪ በኦሪት የተጻፉ ስለ ትንሣኤ ሙታን የሚያትቱ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው? (2ኛ መቃ.14፥25)።

✔️መልስ፦ መላው አይሁድ ባይሆኑም ዛሬ እንብላ እንጠጣ፣ ነገ እንሞታለን፣ በዚያም የምናየው የለም የሚሉ የአይሁድ ክፍሎች እንደነበሩ መጽሐፈ መቃብያን በግልጽ ጽፎልናል። በኦሪት ትንሣኤ ሙታን እንዳለ የሚያስረዱ ብዙ ምሳሌዎች አሉ። ከእነዚህም አንዱ የሣራ አርጅቶ መውለድ ነው። ይህን የመሰሉ ብዙ ምሳሌያዊ ትምህርቶች አሉ። ሙሉ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በመክብባቸው ኦሪት ስለሚላቸው ዳዊትም "እስመ ኢተኀድጋ ውስተ ሲኦል ለነፍስየ" ብሎ ሰውነቴን በመቃብር አትተዋትም ብሏል። በዚህም ትንሣኤ ሙታን መኖሩን አስረድቷል። በመጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ላይም በስፋት ትንሣኤ ስለመኖሩ ተገልጿል።

▶️፲፭. 2ኛ መቃ.14፥6 ጳውሎስ ያለው የትንሣኤ ሙታን አረዳድ ከፈሪሳውያን ጋር ተመሳሳይ ነውን? (የሐዋ.ሥራ 23፥6)።

✔️መልስ፦ አይመሳሰልም። ቅዱስ ጳውሎስ ፈሪሳዊ ነኝ ያለው በግብሩ ሳይሆን በትውልዱ ነው። እንጂ እርሱማ ትንሣኤ ሙታንን የሚያምን ስለትንሣኤ ሙታንም በስፋት ያስተማረ ታላቅ ሐዋርያ ነው (ዕብ.6፥2)።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Jan, 15:46


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 121 💙💙

▶️፩. 2ኛ መቃ.11፥6 "በሥጋና በነፍስ ሕያዋን ሳሉ ከከብቶቻቸውና ከድንኳኖቻቸው ጋራ ወደ ሲኦል አወረዳቸው" ይላል እንስሳት ሲኦል ይወርዳሉን?

✔️መልስ፦ ሲኦል መካነ ነፍሰ ኃጥእ ናት። በሲኦል የሚኖሩ የበደሉ ሰዎችና አጋንንት ናቸው። እንስሳት፣ አዕዋፋት፣ አራዊትና ሌሎችም ደማውያን ፍጥረታት ሲኦል አይኖሩም። ከዚህ ጥቅስ "በሥጋና በነፍስ ሕያዋን ሳሉ ከከብቶቻቸውና ከድንኳኖቻቸው ጋራ ወደ ሲኦል አወረዳቸው" ያለው ወደ መቃብር ወረዱ ማለት ነው። መቃብርን ሲኦል ስለሚለው ነው። ከነቤታቸውና ከነእንስሳቸው ስለሚቀበሩ መቃብሩን ሲኦል ብሎት መሆኑን ያስተውሉ።

▶️፪. "በምድር ላይ ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን መደሰት ይሻላል" ይላል (2ኛ መቃ.13፥4)። ከዚህ አያይዤ መጠየቅ የፈለኩት ሰማዕትነትን በተመለከተ ነው። አንድ ክርስቲያን የሞት ሰማዕትነትን ቢሸሽ ወይም ከሞት ሸሽቶ ቢሰደድ እንደ ኀጢአት ይቆጠርበታል? በሃይማኖት ምክንያት ከሚመጣ ሞት ወይም መከራ ሸሽቶ ከአካባቢ ርቆ ለመኖር ቢወስንስ ኀጢአት ነው?

✔️መልስ፦ ኃጢአት አይሆንበትም። በክርስትና ሁለት ዓይነት ሕይወት አለ። ሁለቱንም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳይቶናል። አንደኛው ሞትን ከፈራን መሰደድ እንደምንችል የሚያሳይ ነው። ጌታ ወደ ግብጽ የተሰደደ ለሚሰደዱት አብነት ለመሆን ነው። ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን እንዳለ ደራሲ። በእርግጥ እርሱ አርአያ ለመሆን ተሰደደ እንጂ ፈርቶ አልተሰደደም። ከፈራን እንድንሸሽ ራሱ ጌታ "በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ" ብሎ ገልጾልናል (ማቴ.10፥23)። ሁለተኛው ለመሞት የቆረጠ ካለ ደግሞ ሰማዕት እንዲሆን ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ሞቶ አሳይቶናል።

▶️፫. "ስሙ ጥልምያኮስ የሚባል መልአከ ሞት ወርዶ ልቡን መታው" ይላል (2ኛ መቃ.12፥13)። ይህ መልአክ ቅዱስ ነው ርኩስ? መልአከ ሞትስ ቁጥሩ አንድ ነው?

✔️መልስ፦ መልአከ ሞት የሚባል ራሱ ሰይጣን ነው። ሰይጣን ደግሞ ርኩስ ነው እንጂ ቅዱስ አይደለም። ሰይጣን የሚባሉ በሰይጣን ስም የሚጠሩ አጋንንት ሁሉ ናቸው። ስለዚህ ቁጥራቸውም ብዙ ነው። መጽሐፍ ግን በግብር አንድ ከሆኑ ዘንድ በአንዱ የሁሉን ግብር ይገልጻል። ለምሳሌ ሰይጣን የብርሃን መልአክ እንደሚመስል ሲጻፍ ለአንዱ ብቻ የተነገረ ሳይሆን ለሁሉ የተነገረ ነው። ቃል በቃል መልአከ ሞትን ሰይጣን ሲለው "እስመ ደቂቅ ተሳተፉ በሥጋ ወደም። ውእቱኒ ተሳተፎሙ በዝንቱ ወከመ ቢጾሙ ኮነ ሎሙ። ከመ በሞቱ ይስዐሮ ለመልአከ ሞት ዘውእቱ ሰይጣን" ይላል (ዕብ.2፥14)። ትርጉሙም "ልጆች በሥጋና በደም አንድ ናቸውና እርሱ ደግሞ በዚህ ከእነርሱ ጋር አንድ ሆነ። ለእነርሱም እንደ ወንድም ሆነላቸው። መልአከ ሞትን በሞቱ ይሽረው ዘንድ ይኸውም ሰይጣን ነው" ማለት ነው።

▶️፬. "የተናገረው ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይደረግለት ነበር" ይላል (2ኛ መቃ.11፥6)። ለሙሴ እግዚአብሔር እንዲናገር ተናግሮት ሳለ "እንደ እግዚአብሔር ቃል ይደረግለታል" ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ቃል ከተነገረ ይደረጋል። እግዚአብሔር ተናግሮ ሳይደረግ የቀረ የለም። ሙሴም በጸጋ ከእግዚአብሔር ቃልን (ትምህርትን) ስለተቀበለ እግዚአብሔር በባሕርይው ሁሉን እንደሚያደርግ ሁሉ ለሙሴም በጸጋ ሁሉ ይደረግለት ነበር ማለት ነው።

▶️፭. "ካህናቱን ይሾማቸዋልና በእነርሱ ዘንድ እንደ እግዚአብሔር አስመሰለው" ይላል (2ኛ መቃ.11፥5)። በእነርሱ ዘንድ እንደ እግዚአብሔር አስመሰለው ሲባል ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በባሕርይው እንደሚከበር፣ ካህናትንም እንደሚሾም ሁሉ ሙሴ ደግሞ ከእግዚአብሔር በተቀበለው ጸጋ አሮንንና ካህናትን መሾሙንና በካህናት ዘንድ በጸጋ መከበሩን ለመግለጽ እንደ እግዚአብሔር አስመሰለው ተብሏል።

▶️፮. "በሞትህ ጊዜ የተያዝክባት የሲዖል ገመድ በአንገትህ አለችና ሳትወድ ይፈረድብሃል" ይላል (2ኛ መቃ.14፥11)። ከዚህ ከዘላለማዊ ፍርድ አያይዤ ለፍርድ ዙፋን የሚቀርቡት አምነው ምግባር ያልሠሩት ብቻ ናቸው ወይስ ያላመኑትም ናቸው?

✔️መልስ፦ ሰው የሆነ ሁሉ በዕለተ ምጽአት ይነሣል። ሰው ሆኖ ትንሣኤ የሌለው የለም። ሃይማኖት ያልነበራቸው ከሓድያንም፣ ሃይማኖት ኖሯቸው ምግባር ያልሠሩ ኃጥኣንም፣ ሃይማኖት ኖሯቸው ምግባር ትሩፋት የሠሩ ጻድቃንም ሁሉም ይነሣሉ።

▶️፯. "በአንገትህ የታሠረች ያች ገመድ ለእናትህ ማሕፀን ከሲኦል ግንድ ለአንተ ትበቅላለች። አንተም ባደግህ ጊዜ እርሷም ታድጋለች" ይላል (2ኛ መቃ.14፥12)። ከዚህ ጋር አያይዤ
በእናታቸው ማሕፀን እያሉ የሚሞቱ ትንሣኤ ሙታን ያገኛሉ? ለፍርድስ ይቆማሉ? ከቆሙስ እንዴት ባለ መልኩ?

✔️መልስ፦ ተሥዕሎተ መልክእ የተፈጸመለት ሁሉ በትንሣኤ ጊዜ ይነሣል። ሳይወለዱ በውርጃ የወረዱ ሕፃናት ሁሉ ይነሣሉ። ነፍስ የነበረው ሰው ሁሉ ይነሣል። ማንኛውም የሰው ጽንስ ገና ሲጸነስ ከእናትና ከአባቱ ሥጋን እንደሚነሣ ሁሉ ነፍስንም ይነሣል። ስለዚህ ከጽንስ ጀምሮ ነፍስ ያለው ሰው ስለሆነ ይነሣል። ክርስቶስን ሰው ሆነ የምንለው በተጸነሰ ጊዜ ነው። የተጸነሰበትን ቀን ማለትም መጋቢት 29ን ዕለተ ትስብዕት (ሰው የሆነባት ዕለት) ብለን እናከብራታለን። ስለዚህ ማንኛውም ሰው ከተጸነሰ በኋላ ሰው ስለሚባል ሳይወለድ ቢሞት እንኳ በትንሣኤ ጊዜ ይነሣል። እንዴት ባለ መልኩ ይነሣሉ ለሚለው ያኔ ስንደርስ እናውቀዋለን። መጽሐፍ ሁሉም ወንድ የሠላሳ ዓመት ቁመና ኖሮት ሴት የአሥራ አምስት ዓመት ቁመና ኖሯት ይነሣሉ ብሎናል።

▶️፰. "ያን ጊዜ በነፋስ ውስጥ ያለ ነፋስ ባሕርይህም ቢሆን፥ በውኃ ውስጥ ያለ ውኃ ባሕርይህም ቢሆን፤ በመሬት ውስጥ ያለ መሬት ባሕርይህም ቢሆን፤ በእሳት ውስጥ ያለ እሳት ባሕርይህም ቢሆን ይመጣል። በአንተ ያደረች በጨለማ የምትኖር ነፍስም ብትሆን ትመጣለች" ይላል (2ኛ መቃ.14፥19)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሰው ሲሞት ነፍሱ ከሥጋው ትለያለች። ተለይታም ኃጥእ ከነበረ ሲኦል ይቆያል። ጻድቅ ከነበረ ገነት ይቆያል። ሥጋችን ደግሞ ከአራቱ ባሕርያት የተገኘ እንደመሆኑ የመሬት ባሕርይ ወደ መሬትነት፣ የነፋስ ባሕርይ ወደ ነፋስነት፣ የእሳት ባሕርይ ወደ እሳትነት፣ የውሃ ባሕርይ ወደ ውሃነት ይመለሳል። በዕለተ ምጽአት በዳግም ትንሣኤ ጊዜ ሙታን ሲነሡ አራቱ ባሕርያት ከሞት በፊት ወደነበሩበት የሰውነት ማንነት ይመለሳሉ። የኃጥእ ነፍስም ከጨለማ ከሲኦል ወጥታ ከአራቱ ባሕርያት ጋር ተዋሕዳ ትነሣለች። የጻድቅ ነፍስ ደግሞ ከብርሃን ከገነት ወጥታ ከአራቱ ባሕርያት ጋር ተዋሕዳ ትነሣለች። ከዚያ ዘለዓለማዊ ፍርድ ይደረጋል ማለት ነው።

▶️፱. "በሙሴ ወንበር ተቀምጠህ በቃልህ የሙታን ትንሣኤ የለም ትላለህ" ይላል (2ኛ መቃ.14፥24)። በሙሴ ወንበር ተቀምጠህ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የሙሴን መጻሕፍት ተቀብለው የሚያስተምሩ ሰዎች በሙሴ ወንበር የተቀመጡ ይባላሉ። ፈሪሳውያን፣ አይሁድ፣ ሳምራውያን፣ ሰዱቃውያን ሁሉ የሙሴን መጻሕፍት ተቀብለው ነገር ግን በመጻሕፍቱ መሠረታዊ ፍሬ ሐሳብ የማያምኑ ስለነበሩ በሙሴ ወንበር ተቀምጣችሁ ትንሣኤ ሙታን የለም ትላላችሁ ተብለው ተገሥጸዋል (ማቴ.23፥2)።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Jan, 08:03


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 120 💙💙

▶️፩. "ወደ አራስና ሳትነጻ በደሟ ወዳለች ሴት መሄድ" እንደ ኀጢአት በብሉይ ኪዳን ተቆጥሯል (2ኛ መቃ.9፥21)። አንዲት ሴት ስትወለድ ማን ያርሳታል ወይስ ራሷ እንድትሠራው ነው? በሐዲስ ኪዳንስ ያለው እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ ወደ አራስና ሳትነጻ በደሟ ወዳለች ሴት መሔድ አይገባም ብሎ የገለጸው ከዚህ በአራስነቷ ወይም በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋር ግንኙነት አይገባም ማለት ነው እንጂ እንኳን ማርያም ማረችሽ ለማለት አራስን ለመጠየቅ መሔድ አይገባም ማለት አይደለም። በእርግጥ በብሉይ ኪዳን አራስ ቤተ መቅደስ እስከምትገባና ሌላም ሴት በወር አበባዋ ወቅት ሳለች እንደ ርኵስት ትታይ ነበር። እና እርሷን ሰላም ማለትና መንካትም ያረክስ ነበር። በሐዲስ ኪዳን ግን ሰላምታም አይከለከልም። መስቀል መሳለምም ትችላለች። ቤተክርስቲያን ውስጥ መግባትና መቁረብ ብቻ አይፈቀድላትም።

▶️፪. እግዚአብሔር እስራኤላውያን ሲበድሉ የአሕዛብን ነገሥታት አስነሥቶ ያስማርካቸዋል። መልሶ ደግሞ የአሕዛብን ነገሥታት በዚያ ድርጊታቸው ይኮንናቸዋል ይሄ ነገር እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ ማንኛውም ሰው በደለኛ ከሆነ በበደሉ ይቀጣል። አንድ ጻድቅ ሲያጠፋ እግዚአብሔር በኃጥእ እጅ ሊጥለው ይችላል። ይህም ተጸጽቶ ንስሓ እንዲገባ ነው። ኃጥእ ራሱ ግን ባደረገው በደል ይቀጣል። ለምሳሌ ይሁዳ ጌታን በሠላሳ ብር የሸጠው ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ነው። ንጹሕ ሰውን አሳልፎ መሸጥ ኃጢአት መሆኑን ይሁዳም ያውቅ ነበር። ብሩ በልጦበት እስከ መካድ ደረሰ። አሁን በዚህ ጊዜ ተሰቅሎ ዓለምን ማዳን የጌታም ፈቃዱ ስለሆነ የይሁዳን ክፋት እርሱ ለሌሎች መዳኛ አድርጎ ለውጦታል። ይሁዳ ግን ክፋትን ስለሠራ ተጠያቂ ሆኖ በበደሉ ተቀጥቶበታል። የአሕዛብ ነገሥታት እስራኤላውያንን እየማረኩ ሲበድሏቸው ኖረዋል። አሕዛብ ክፋትን ስላደረጉ በክፋታቸው ይቀጣሉ። እስራኤላውያንም በክፋታቸው ይቀጣሉ። ክፋት ሆኖ የማያስቀጣ ነገር እንደሌለ ሁሉ መልካም ሥራ ሆኖ የሚያስጎዳም የለምና።

▶️፫. አንደኛ መቃብያን ላይ ያለው መቃቢስ ታሪኩ አልተገለጸም ነበር። ሁለተኛ መቃብያን ላይ ነው የተገለጸው። እንደዚህ ከሆነ ለምን ከሁለተኛ መቃብያን አልጀመረም? አንደኛና ሁለተኛ መቃብያንስ ልዩነቱ ምንድን ነው? ታሪኩ ስለተመሳሰለብኝ ነው ።

✔️መልስ፦ ምንም እንኳ ታሪካቸው ተቀራራቢ ቢሆንም ሁለቱም መጻሕፍት የተጻፉት ስለተለያዩ ሰዎች ነው። አንደኛ መቃብያን የተጻፈው ስለመቃቢስ ዘብንያምና ስለ ልጆቹ ሲሆን ሁለተኛ መቃብያን የተጻፈው ደግሞ ስለ መቃቢስ ዘሞዓብ ነውና።

▶️፬. "ክሣደ ልቡናውን በማጽናትና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን እምቢ እንዳለ" ይላል (2ኛ መቃ.9፥3)። ይሄ ንባብ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ቅዱሳን መላእክት አዳም በእግዚአብሔር አርዓያና መልክ የተፈጠረ መሆኑን ሲሰሙ እግዚአብሔር በባሕርይው ስለማይታይ አምሳሉን አዳምን ለማየት ይጓጉ ነበር። እናም ቅዱሳን መላእክት አዳምን አይተው ሲያከብሩትና ደስ ሲሰኙ ሰይጣን ግን ክፉ ቅንዐትን ቀንቷል። የዲያብሎስን አለመደሰትና አለማክበር አለመስገድ ብሎ ገልጾታል።

▶️፭. "አሳዝነውታልና ክፉ ሥራ የሠሩ ሰዎችንም አስነሥቶ ፈርዶ ወደ ገሃነም ይወስዳቸዋል" ይላል (2ኛ መቃ.9፥16)። መቼም ፍርድ ሲባል የመጨረሻው ቀን (ምጽአት) ነው። መምህር እዚህጋ አንድ ነገር ግልጽ ቢያደርጉልኝ። ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ከዲያቢሎስ አገዛዝ (ባርነት) ነጻ አወጣ። አንዳንድ መመህራን "ሲኦል ተመዘበረች ባዶ ቀረች" ይላሉ። ከሲዖል ያወጣቸው በስሙ (በእግዚአብሔር  አምላክነት) አምነው የሞቱትን የአዳም ልጆች ብቻ ነው ወይስ በአምላክነቱ ሳያምኑ የሞቱትን አሕዛብንም ጭምር ነው? ለዘለዓለም ወደ ገሃነም የሚገቡ ሲኦል ውስጥ የቀሩ ነፍሳት ነበሩ?

✔️መልስ፦ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ከዚያ በፊት የነበሩ ሕዝብና አሕዛብን በጠቅላላው የአዳም ልጆችን አድኗል። መድኃኔዓለም መባሉ አንዱ በዚህ ነው። ስለዚህ ከዚያ በፊት አምነው የሞቱትም ሳያምኑ የሞቱትም ከሲኦል ወጥተው ወደ ገነት ገብተዋል። እንጂ ያን ጊዜ ሲኦል የቀሩ ነፍሳት አልነበሩም። በመቅድመ ወንጌል ወኀደጎሙ ለእኩያን የሚለውን ሲያትት አጋንንትን በሲኦል እንደተዋቸው ይናገራል። የሰው ልጆች ግን ሁላቸውም ወጥተዋል። ከስቅለት በኋላ ያለን ሰዎች ደግሞ አምነን በመጠመቅና መልካም ሥራን በመሥራት ወደ ገነት እንድንገባ ነጻ ፈቃድ ተሰጥቶናል። ነጻ ፈቃዳችንን ለበጎ እንጠቀምበት። ከስቅለት በኋላ ግን ክፋት ሠርቶ ሲኦል የሚገባ ሰው በኋላ ዘመን ወደ ዘለዓለማዊ ገሃነም እንደሚገባ ተገልጿል (ማቴ.25)።

▶️፮. መቃብያን ማለት ምን ማለት ነው? የመጽሐፈ መቃብያን ጸሓፊስ ማን ነው?

✔️መልስ፦ መቃብያን ማለት የመቃቢስ ዘሮች ማለት ነው። የእነርሱን ታሪክ ስለሚናገር የመጽሐፉ ስም በእነርሱ መቃብያን ተብሏል። የመጽሐፈ መቃብያን ጸሓፊ ከዚሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማን እንደሆነ አልተገለጸም። በሌላ የታሪክ መጽሐፍ ካለ ከዚያ ይፈልጉት። ያስጻፈው መንፈስ ቅዱስ ለመሆኑ ግን መጻሕፍት አምላካውያት ከሚባሉት በመመደቡ ታውቋል (ፍት.ነገ.2)።

▶️፯. በለዓም ንጉሡ ባላቅ እስራኤልን እንዲረግምለት ብዙ እጅ መንሻ ቢያቀርብለትም የእግዚአብሔርን ቃል በማክበር ጥያቄውን እንዳልተቀበለ ተገልጿል (2ኛ መቃ.10፥12)። ብዙ ጊዜ ትምህርት ሲሰጥ ግን በለዓም በበጎ ጎን ሲነሣ አልሰማም። በአሉታዊ ሁኔታ በበለዓም መንገድም ሄደዋልና ተብሎም ሌላ ስፍራ ላይ ተጠቅሷል እንጂ። ይህ ሀሳብ እንዴት ይታረቃል?

✔️መልስ፦ በለዓም ጠንቋይ ነው። እስራኤላውያን ሊረግም ሲሄድ እንኳ እግዚአብሔር አፉን ከፍቶ ፊቱን ጸፍቶ ነው አልረግምም ያሰኘው። ፈርቶና ተገዶ ነው እንጂ የእግዚአብሔርን ቃል አክብሮና በእግዚአብሔር አምኖ አልነበረም አልራገምም ያለ። ክፉና ተንኮለኛ ሰው እንደነበረ የሚያሳየን ባይራገም እንኳ ክፉ ምክር መክሮ እስራኤላውያን እንዲጎዱ በማድረጉ ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Jan, 05:08


💝 ሁለተኛ መጽሐፈ መቃብያን ክፍል 3 💝

💝ምዕራፍ ፲፩፡-
-ሙሴ ሕዝቡን ሲመራ እንዳልተበሳጨ መገለጡ
-የእግዚአብሔርን ቃል ካልተላለፍን ፈቃዳችንን እንደሚያደርግልን መገለጡ

💝ምዕራፍ ፲፪፡-
-የእግዚአብሔርን ፈቃድ የማያደርጉ ሰዎች ወዮታ እንዳለባቸው
-ክፋትን የሚሠሩትን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚያጠፋቸው
-ጺሩጻይዳን እንደሞተ

💝ምዕራፍ ፲፫፡-
-ይህ ዓለም እንደሚያረጅና እንደሚያልፍ ተድላውም ለዘለዓለም እንደማይኖር ዐውቀው ያመኑ የመቃቢስ ልጆች ለጣዖት የተሠዋውን መሥዋዕት አንበላም በማለታቸው በሰማዕትነት ሰውነታቸው ለሞት እንደሰጡ
-ከንጉሥ ቁጣ የእግዚአብሔር ቁጣ እንደሚከፋ መነገሩ

💝ምዕራፍ ፲፬፡-
-ስለ ፈሪሳውያን፣ ስለ ሳምራውያን እና ስለሰዱቃውያን አስተምህሮ መነገሩ

💝ምዕራፍ ፲፭፡-
-ጻድቃን በዳግም ምጽአት ጊዜ በደስታ እንደሚኖሩ መገለጹ
-በዕለተ ምጽአት ሁሉ እንደ ሥራው እንደሚከፈለው
-ኃጥኣን በዕለተ ምጽአት ቀድሞ በሠሩት ክፉ ሥራ እንደሚጸጸቱና እንደሚያለቅሱ

💝💝💝የዕለቱ ጥያቄዎች💝💝💝
፩. እኛ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስንፈጽም እግዚአብሔር ለእኛ ምን ያደርግልናል?
ሀ. መልካም ፈቃዳችንን ያደርግልናል
ለ. በመከራችን ጊዜ ቸል አይለንም
ሐ. ኃጢአታችንን ያስተሠርይልናል
መ. ሁሉም
፪. ጺሩጻይዳንን የገደለው ማን ነው?
ሀ. መቃቢስ ዘይሁዳ
ለ. መቃቢስ ዘሞዓብ
ሐ. ጥልምያኮስ የተባለ መልአከ ሞት
መ. መብክዩስ
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ይህች ዓለም የምታልፍና የምታረጅ ናት ተድላዋም ለዘለዓለም አይኖርም
ለ. የመቃቢስ ልጆች መከራ ሲጸናባቸው የጣዖት መሥዋዕትን በልተዋል
ሐ. በምድር ላይ ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል
መ. እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው
፬. ከሚከተሉት ውስጥ በትንሣኤ ጊዜ ሥጋችን ትቢያ ይሆናልና አይነሣም ነፍሳችን ግን ትነሣለች የሚሉት የትኞቹ ናቸው?
ሀ. ፈሪሳውያን
ለ. ሳምራውያን
ሐ. ሰዱቃውያን
መ. ሀ እና ለ

https://youtu.be/YErG3SRvW6w?si=LNRHXlMbYejy4GyZ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

30 Jan, 05:25


💛 ሁለተኛ መጽሐፈ መቃብያን ክፍል 2 💛

💛ምዕራፍ ፮፡-
-የእግዚአብሔር ጠላት ጺሩጻይዳን የሐሰት ካህናትንና የጣዖታቱን አገልጋዮች እንደሾመ፣ እነዚህም ለጣዖታት መሥዋዕትን ይሠዉ እንደነበር
-የመቃቢስ ልጆች ለጣዖታት አንሰግድም በማለታቸው እንደታሰሩና እንደተሰደቡ
-የመቃቢስ ልጆች በሰማዕትነት በእሳት ተቃጥለው እንደሞቱ

💛ምዕራፍ ፯፡-
-ሰማዕት ከሆኑ በኋላ የመቃቢስ ልጆች ለጺሩጻይዳን በራእይ ተገልጠው እንዳስፈራሩት

💛ምዕራፍ ፰፡-
-ጺሩጻይዳን በኩራትና በልብ ተንኮል እንደሄደ

💛ምዕራፍ ፱፡-
-ሰው ነገ መሬትና አመድ የሚሆን እንደመሆኑ መኩራት እንደማይገባው መነገሩ
-ኃጥኣን በጻድቃን ምክር ይኖሩ ዘንድ እንደማይወዱ መገለጹ
-ጻድቃን እግዚአብሔር ከማይወደው መንገድ ሁሉ እንደሚርቁ መነገሩ

💛ምዕራፍ ፲፡-
-ነገሥታትና መኳንንት በሰይጣን ጎዳና መሄድ እንደማይገባቸው መገለጹ
-ነገሥታትና መኳንንት እግዚአብሔርን መፍራት እንደሚገባቸው መገለጹ

💛💛💛የዕለቱ ጥያቄዎች💛💛💛
፩. የመቃቢስ ዘሞዓብ ልጆች ለጣዖት አንሰግድም ስላሉ ምን ተደረገባቸው?
ሀ. በጣዖታውያን ተሰደቡ
ለ. በጣዖታውያን ታሰሩ
ሐ. በእሳት ተጥለው ሰማዕት ሆኑ
መ. ሁሉም
፪. ስለጺሩጻይዳን ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ለድኻ አይራራም ነበር
ለ. እግዚአብሔርን ያመልክ ነበር
ሐ. ለጣዖት ይሰግድ ነበር
መ. ትዕቢተኛ ነበር
፫. ከሚከተሉት ውስጥ የኃጥኣን መንገድ የተባለው የቱ ነው?
ሀ. ፍቅርና ሰላም
ለ. ቅሚያና ክዳት
ሐ. ጾምና ጸሎት
መ. ትሕትናና የውሃነት

https://youtu.be/aAD-FgWCdMM?si=yZS0O3KKZPHg7-Yy

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

29 Jan, 19:37


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 119 💙💙

▶️፩. "መስጊዳቸውን፣ ጥንቆላቸውንና ጣዖቶቻቸውን" ይላል (2ኛ መቃ.3፥20)። "መስጊዳቸውን" የሚለው ቃል በዚህ መጽሐፍ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘሁት (ካልተሳሳትኩ)። ይሄ ደሞ መጽሐፉ መች ነው የተጻፈው የሚል ጥያቄ ይወልዳል? እስልምና ከመነሣቱ በፊት መስጊድ ነበር?

✔️መልስ፦ በግእዝ ሰገደ ከሚለው ቃል ምስጋድ የሚል ባዕድ ዘር ይወጣል። ትርጉሙ መስገጃ፣ መሰገጃ ማለት ነው። ይህንን ዐረብኛው መስጊድ ይለዋል። ስለዚህ እስልምና ከመነሣቱ በፊትም ጣዖታዊ ሰው ለጣዖት የሚሰግድበት ልዩ ቦታ ስለነበረው ያን ቦታ መስጊድ ማለት የተለመደ ነበር። ስለዚህ እስልምና ከመነሣቱ በፊትም ለጣዖት የሚሰገድባቸው ብዙ ቦታዎች ስለነበሩ እነርሱን ለመግለጽ የብሉይ ጸሓፊዎች መስጊድ ብለዋቸዋል።

▶️፪. "እርሱ ልዩ ሞዓባዊ ሲሆን አይሁድ የሚከለክሉትን ምግብ ይከለክል ነበር" ይላል (2ኛ መቃ.4፥15)። "ልዩ ሞአባዊ" ሲል ምን ማለቱ ነው? በሐዲስ ኪዳን አንድ ሰው ወደ ክርስትና ቢመጣ ቀድሞ የነበረውን የምግብ ሥርዓት መተው አለበት?

✔️መልስ፦ መቃቢስ ልዩ ሞዓባዊ መባሉ ሞዓባውያን ጣዖት ሲያመልኩ እርሱ በኋላ ተለይቶ በእግዚአብሔር ያመልክ ስለነበረ ነው። በሌላ አተረጓጎም በነገድ ከእስራኤላውያን የተለየ ሆኖ ሳለ በአምልኮ እንደ እስራኤላውያን ሆኖ ስለተገኘ ልዩ ሞዓባዊ ተብሏል። በሐዲስ ኪዳን አንድ ሰው ወደ ክርስትና ቢመጣ ክርስትና ከሚከለክላቸው ምግቦች መከልከል ግዴታው ነው። ክርስትና ለጣዖት የታረደን፣ ደምን፣ ሞቶ ያደረን፣ ጥሬ ሥጋን መብላትን ይከለክላል። ስለዚህ ከእነዚህ መከልከል ግዴታው ነው። ሌላው ግን የባህል ጉዳይ ስለሆነ እንደየባህሉ የመቀጠል ነጻ ክርስቲያናዊ ፈቃድ አለው።

▶️፫. "ከዚህም በኋላ የከለዳውያን ንጉሥ ጺሩጻይዳን መጣ። ሀገራቸውንም ሁሉ አጠፋ" ይላል (2ኛ መቃ.5፥4)። እስካሁን ባነበብነው እስራኤሎች በባዕድ እንዲወረሩ የሚሆነው እግዚአብሔርን በረሱበት ዘመን ነበር። በዚህ ታሪክ የመቃቢስ ልጆች በሥርዓት እየኖሩ አልነበረም ወይ? እግዚአብሔር እንዴት አሳልፎ ሰጣቸው?

✔️መልስ፦ መከራ በሁለት መልኩ ይመጣል። አንደኛው ሰዎች ኃጢአት ሲሠሩ ለተግሣጽ እግዚአብሔር መከራን የሚያመጣባቸው ጊዜ አለ። እስራኤላውያን ሲበድሉ የተለያዩ መከራዎች ይደርስባቸው የነበረው በዚህ አግባብ ነው። ሁለተኛው ሰዎች ምንም በደል ሳይበድሉ ጸጋቸው ይበዛ ዘንድ እግዚአብሔር የሚያመጣባቸው መከራ ነው። የመቃቢስ ልጆች የደረሰባቸው መከራ ይህ ነው። ሰማያዊ ዋጋቸው ይበዛ ዘንድ ነው መከራ የመጣባቸው። መከራን በትዕግሥት ቢቀበሉት የጸጋ ምንጭ ይሆናልና።

▶️፬. "አሁን ስለወለድካቸው ልጆችህ እግዚአብሔር ኀጢአትህን ይቅር አለህ" ይላል (2ኛ መቃ.3፥5)። የመቃቢስ ልጆች እግዚአብሔርን ያመልኩ ነበር?

✔️መልስ፦ መቃቢስ ስለወለድካቸው ልጆችህ እግዚአብሔር ኃጢአትህን ይቅር አለህ መባሉ ልጆቹ በኋላ ሰማዕት ሆነው እንደሚያርፉ እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለሚያውቅ በእነርሱ የኋላ ግብር ይቅር እንዳለው የሚያመለክት ቃል ነው። ምክንያቱም መቃቢስ ልጆቹን ያስተማራቸው ንስሓ ከገባ በኋላ ነው። እነርሱም ኖሩ የተባለው አባታቸው ባስተማራቸው ሥርዓት ነውና (2ኛ መቃ.5፥1)። ስለዚህ ይህ ቃል መቃቢስ ካመነ በኋላ ልጆቹም እንዳመኑ ያመለክታል።

▶️፭. መቃቢስ ቀድሞ እግዚአበሔርን የማያመልክ እንደነበረ ይታወቃል። እስካሁን ባነበብናቸው የእስራኤል ታሪኮች እግዚአብሔር መከራ ሲያመጣባቸው ከመከራ እንዲድኑ በንስሐ ወደ እርሱ እንዲመለሱ የእስራኤልን ሕዝብ ነበር የሚያስጠነቅቀው። በዚህ ታሪክ ግን መቃቢስ በባለ ራእዩ ራእይ ሲገሥጸው አይተናል ለምን ሕዝቡን ንስሓ አስገብቶ ከመከራ አላዳናቸውም ነበር?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በመግቦቱ ለሁሉም የንስሓ ጊዜን ይሰጣል። ስለዚህ ለሕዝቡም ብዙ ጊዜ ነቢያትን እየላከ ከበደላቸው እንዲመለሱ አስተምሯል። ምክሩን ሰምተው ተግባራዊ ያደረጉት ግን በየዘመኑ ጥቂቶች ናቸው። ከዚህም መቃቢስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ አምኖ ንስሓ ገብቶ አርፏል። ስለዚህ እግዚአብሔር የእነርሱን መታመን አይቶ ያዳናቸው አሉ። በክፋታቸው በጸኑት ደግሞ መከራን አምጥቷል።

▶️፮. "ስለ እነዚህ ልጆች ከአንተ ጋር ያለውን ቃል ኪዳኔን እጠብቃለሁ" ይላል (2ኛ መቃ.3፥10)። "ካንተ ጋር ያለውን ቃል ኪዳኔን" ሲል መቃቢስ ቃል ኪዳን ነበረው? መቃቢስ በቀድሞ ሕይወቱ እግዚአብሔርን የሚያመልክ ነበር?

✔️መልስ፦ መቃቢስ በቀድሞ ሕይወቱ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አልነበረም። በኋላ ግን ንስሓ ገብቶ እግዚአብሔርን የሚያመልክ ሆኗል። እግዚአብሔርም ለመቃቢስ ቃል ኪዳን የገባለት ከተመለሰ በኋላ ነው። እግዚአብሔር ለመቃቢስ የገባለት ቃል ኪዳን እንዳለ በዚሁ ተገልጿል። ምን የሚል ቃል ኪዳን እንደነበረ ግን መጽሐፍ ቅዱሱ ዝርዝር ጉዳዮችን ስላልጻፈልን አለማወቅ ይገድበናል።

▶️፯. 2ኛ መቃ.1፥9 ላይ "ኢየሩሳሌምንም እንደ ተክል ጠባቂ ጎጆ አደረጓት በውስጧም ድምፅ አሰማባት" ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በገጠር ተክል የሚጠብቅ ሰው ጊዜያዊ ጎጆ ሠርቶ ይጠብቃል። ተክሉ ከተሰበሰበ በኋላ ጎጆዋን ያፈርሳታል። ስለዚህ የተክል ጠባቂ ጎጆ ማለት ሁልጊዜ የማትኖር ቶሎ የምትፈርስ ማለት ነው። ኢየሩሳሌምን እንደ ተክል ጠባቂ ጎጆ አደረጓት ማለት አፈረሷት ማለት ነው። በውስጧም ድምፅ አሰማባት የሚለው እግዚአብሔር የማይወደውን ሥራ አደረገባት ማለት ነው።

▶️፰. 2ኛ መቃ.5፥6 "አውሬ የነከሰውንና ደሙን፣ በክቱን አባላ መትተው የጣሉትን" ይላል። አባላ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አባላ መትተው የጣሉትን ማለት አንገቱን ወይም ቋንጃውን ቆርጠው የጣሉትን እንስሳ ሥጋውን መብላት አይገባም ማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

29 Jan, 12:45


፩. አንዳንድ ቀን የሞቱ ሰዎችን የfacebook ገጽ አያለሁ። ከዕድሜያቸው ቀንሰው ዋጋ ሰጥተው የጻፉት ምን ነበር? ያ ያደረጉት ነገር ከሞት በኋላ ላለው ሕይወት አንዳች ቁም ነገር ኖሮት ይሆን? ለሰው ጠቅሞ ይሆን? እግዚአብሔር የሚወደው ነበር ይሆን?

፪. አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሞቱ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ እሰማለሁ። ዋጋ ሰጥተው የተናገሩት ነገር ከዘለዓለማዊው ሕይወት ጋር ግንኙነት ነበረው ይሆን? ለምን ነበር በዚህ ምድር የደከሙት? ቃለ መጠይቃቸው ላይ ትኩረት ያደረጉት በምን ጉዳይ ነበር? ያ ጉዳይ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ አሁን ለሄዱበት ዓለም አዎንታዊ ሚና ነበረው ይሆን?

፫. የሞቱ ሰዎችን መጻሕፍትና የምርምር ውጤቶች (Researches) አነባለሁ። በዚህ ዓለም የደከሙለት ጉዳይ ከዘለዓለማዊው ሕይወት ጋር የተገናኘ ነበር? የትኩረታቸው ዋና ማዕከል ምን ነበር?

፬. ቤተክርስቲያን ስትሔዱ የብዙዎችን መቃብር አስባችሁት ታውቃላችሁ? አንዳንዶቹ ዕቅዳቸውን ሳይቋጩ ያረፉ ናቸው። አንዳንዶቹ ለምን እንደሚኖሩ ሳያውቁ ያረፉ ናቸው። አንዳንዶች አሁን እኛ ባለንበት ሁኔታ (መጥፎ ወይም መልካም) ሆነው ያረፉ ናቸው።

ሰው ሞትን መዘንጋት የለበትም። ስለዚህ እስካለ ድረስ ለሰው በጎ አስተዋጽኦ አበርክቶ ቢያልፍ መልካም ነው። እግዚአብሔር አድርጉ ያለንን አድርገን ለማለፍ ሕጉን በየዕለቱ እያነበብን እየተገበርን ብንኖር መልካም ነው። ለመሞት አንድ ቀን እንደቀረው ሰው ሆነን እንኑር። ሰውን እንደራሳችን እንውደድ። የእግዚአብሔርን ሕግ እንጠብቅ። ጎበዝ ዕድሜያችንን ለቁም ነገር እናውላት። ሁሉም ኃላፊ ነውና የማያልፈው ላይ ትኩረት እናድርግ። መሞታችን ካልቀረ ደግ ሥራ እየሠራን እንሙት።

© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

29 Jan, 06:09


🧡 ሁለተኛ መጽሐፈ መቃብያን ክፍል 1 🧡

🧡ምዕራፍ ፩፡-
-ሞዓባዊው መቃቢስ እስራኤልን ከሌሎች አሕዛብ ጋር ሆኖ እንዳጠፋቸው
-እስራኤላውያን ቢበድሉ መቃቢስ ዘሞዓብን እንዳስነሳባቸው
-መቃቢስ ዘሞዓብ እግዚአብሔር የማይወደውን የክፋት ሥራ ሁሉ እንዳደረገ

🧡ምዕራፍ ፪፡-
-ንስሓ ካልገባ በመቃቢስ ዘሞዓብ የልብ በሽታና የተለያዩ መከራዎች እንደሚደርሱበት ነቢይ መናገሩ
-መቃቢስ ስለኃጢአቱ ማቅ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት እንዳለቀሰ

🧡ምዕራፍ ፫፡-
-እግዚአብሔር የመቃቢስን ንስሓ ተቀብሎ ይቅር እንዳለው
-ንስሓ የሚገቡ ሰዎች ብፁዓን እንደሆኑ መገለጹ

🧡ምዕራፍ ፬፡-
-እግዚአብሔር በተለያዩ ሰዎች እያደረ እስራኤላውያንን ይረዳቸው እንደነበረ
-መቃቢስ በጎ ሥራን መሥራት እንደጀመረና መንገዱን ያቀና እንደነበር

🧡ምዕራፍ ፭፡-
-መቃቢስ እንደሞተና ልጆቹ በሥርዓት እንዳደጉ፣ ገንዘባቸውን ለድሆች ይመጸውቱ እንደነበር

🧡🧡🧡የዕለቱ ጥያቄዎች🧡🧡🧡
፩. ሞዓባዊው መቃብስ ስለሠራው ሥራ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከሴቶች ሆድ ያለውን ፅንስ አውጥቷል
ለ. እግዚአብሔር የማይወደውን ክፉ ሥራ ሠርቷል
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም
፪. መቃቢስ ዘሞዓብ በሠራው ክፉ ሥራ ምክንያት ንስሓ ካልገባ የልብ በሽታ፣ እከክና ቁርጥማት እንደሚመጣበት የተናገረው ማን ነው?
ሀ. ሚክያስ
ለ. ረአይ የሚሉት ነቢይ
ሐ. ዮናስ
መ. ናሆም
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የሚጠራጠሩ ሰዎች ንስሓ ለመግባት አይጨክኑም
ለ. በፍጹም ልቡናቸው ንስሓ የሚገቡ ሰዎች ብፁዓን ናቸው
ሐ. ከሳቱ በኋላ ንስሓ የገቡ ሰዎች የእግዚአብሔር ናቸው
መ. ሁሉም
፬. መቃቢስ ዘሞዓብ ንስሓ ከገባ በኋለ ምን አደረገ?
ሀ. ከቤቱ ጣዖትን አስወገደ
ለ. ሟርተኞችን፣ ጠንቋዮችንና ጣዖት የሚያመልኩ ሰዎችን አስወገደ
ሐ. የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ሥርዓቱንና ሕጉን ጧትና ማታ ይመረምር ነበር
መ. ሁሉም
፭. ስለ መቃቢስ ዘሞዓብ ልጆች ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ስሙ ብኤል ፌጎር የሚባል ጣዖትን ያመልኩ ነበር
ለ. እግዚአብሔርን ይፈሩት ነበር
ሐ. ገንዘባቸውን ለድኾች ይመጸውቱ ነበር
መ. ባልቴቶችንና የሙት ልጆችን እየረዱ ያረጋጓቸው ነበር
፮. ብኤል ፌጎር ስለተባለው ጣዖት ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ይበላና ይጠጣ ነበር
ለ. ትንፋሽና ዕውቀት የሌለው የሰው እጅ ሥራ ነው
ሐ. መልካምም ክፉም አያደርግም
መ. ለ እና ሐ

https://youtu.be/LOHKuokmjRw?si=6IEk7GL2SEJx7qbA

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

27 Jan, 15:57


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 117 💙💙

▶️፩. "በስድስተኛዪቱም ቀን ከብቶችንና አውሬዎችን ሌሎችንም ፈጠረ ሁሉንም ፈጥሮ አዘጋጅቶ አዳምን በምሳሌውና በመልኩ ፈጠረው" ይላል (1ኛ መቃ.27፥11)። መምህር በደንብ ግልጽ ያልሆነልኝ ነገር አለ። እግዚአብሔርን በባሕርይው  መላእክትስ እንኳን ቢሆኑ ማንማ ያየው የለም ይባላል። ሰው ደሞ የተለያየ መልክ አለው። ግን ሀሉም ሰው (ነጩም ጥቁሩም) እግዚአብሔርን ይመስላል ይባላል። ታዲያ አዳምን በምሳሌውና በመልኩ ፈጠረው ስንል ምሳሌና መልክ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ እውነት ነው እግዚአብሔርን በባሕርይው ያየው አንድስ እንኳ የለም። ወደፊትም የሚያየው የለም። አዳምን በምሳሌውና በመልኩ ፈጠረው የሚለው በዋናነት እግዚአብሔር በባሕርይው የሚገዛውን ፍጥረት አዳም በጸጋ እንዲገዛው አደረገው ማለት ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው ምሳሌ ከሚመሰልለት ያነሰ ስለሆነ ሰው እግዚአብሔርን ይመስላል ሲባል በገዢነት ይመስለዋል ማለት ነው። በተጨማሪም እግዚአብሔር በባሕርይው ለባዊ፣ ሕያው፣ ነባቢ እንደሆነ ሁሉ ሰው ደግሞ በጸጋ ለባዊ ነባቢ ሕያው ነውና በዚህ ይመስለዋል። ሌላው የእግዚአብሔር አካል በሁሉ ያለ ረቂቅ ቢሆንም የሰውን አካል ይመስላልና ይኸውም ለእግዚአብሔርም እጅ እግር፣ ራስ፣ ዓይን እና የመሳሰሉት ሌሎችም አካላት እንዳሉት ተጠቅሷልና ነው። ለሰውም በጸጋ እነዚህ ነገሮች ስላሉት እግዚአብሔርን ይመስላል ተብሏል።

▶️፪. "እግዚአብሔር በአባታችን በአዳም ተቈጣ ከገነትም አስወጥቶ ሰደደው። ያርሳት ዘንድ ጥሮ ግሮም የድካሙን ዋጋ ይበላ ዘንድ ትእዛዙን ባፈረስ ጊዜ ስለእርሱ ረገማት። አሜከላና እሾህን የምታበቅል ያችንም ምድር ሰጠው" ይላል (1ኛ መቃ.27፥19)። አሜከላና እሾህን የምታበቅል ያችንም ምድር ሰጠው ሲል እሾህና አሜከላ አዳም ከመበደሉ በፊት ቀድመው እንደ ሌሎች ዕፀዋት በሦስተኛው ቀን የተፈጠሩ ነበሩ እንዴ? ወይስ አዳም ስለበደለ ብቻ ከበደል በኋላ መሬት ያበቀለቻቸው ናቸው?

✔️መልስ፦ በዚህ ዙሪያ ሁለት እይታዎች (Speculations) አሉ። አንደኛው የዕፀዋት እሾህ ባሕርያዊ የሆነና ከዕለተ ፍጥረታቸው ጀምሮ ያለና የነበረ ሲሆን ስለዚህ እሾህና አሜከላ ያብቅሉብህ ማለት ፍትወታት እኩያት (ክፉ ምኞቶች) ይሠልጥኑብህ ማለት ነው የሚል ነው። ሁለተኛው የብሉይ መተርጉማን እንዳለ ወስደው የተረጎሙት ነው። ይህም ማለት ዕፀዋት አስቀድሞ እሾህ አልነበራቸውም። ከዚህ ርግማን በኋላ እሾህ እንዳወጡ ተናግረዋል ማለት ነው። አንድም በሰው ሆድ ውስጥ ተሐዋስያን ይኑሩ ማለት ነው ብለውታል። ሁለቱንም እይታዎች አክብረን እንይዛለን።

▶️፫. "አዞዎችንና ዓሣ ነባሪዎችን አሽኮኮዎችና ጉማሬዎችን አቆስጣንም" ይላል፡፡ አቆስጣ ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አቆስጣ ከአራዊት ወገኖች የሆነ የሚናከስ ፍጥረት ነው።

▶️፬. "ዳግመኛ ደግ ልጅ ሴት ተወለደ። አዳም ስድሳ ልጆችን ወለደ ከነእርሳቸው ደጋጎች ሰዎችና ክፉዎቸ ሰዎች አሉ" ይላል (1ኛ መቃ.28፥6)፡፡ አዳምና ሔዋን የወለዷቸው ልጆች ብቻ ናቸው ስድሳ?

✔️መልስ፦ አዎ አዳም ከሔዋን በጠቅላላ የወለዳቸው ልጆች ስድሳ (ስሳ) ናቸው።

▶️፭. "በሦስተኛው ቀን እግዚአብሔር በምድር ላይ አትክልቱን ሥሩን ሁሉ እንጨቶችንም በየወገናቸው የሚያፈሩ ፍሬዎችንም ሲያዩት ያማረ የደኅንነት እንጨትንም ፈጠረ" ይላል (1ኛ መቃ.27፥6)። የደኅንነት እንጨት ሲል ምን ዓይነት እንጨት ነው?

✔️መልስ፦ የደኅንነት እንጨት የሚለው ዕፀ ሕይወትን ነው። ግእዙ በደንብ ገልጾታል። "ወዕፀ ሕይወት ዘሠናይ ለርእይ" እንዲል።

▶️፮. "ወንድሙን አቤልን ስለ ገደለ እግዚአብሔር በቃየል ፍርድን ፈረደ ደሙንም ስለ ጠጣች እግዚአብሔር ምድርን ተቈጣት" ይላል (1ኛ መቃ.28፥3)። የበደለ ቃኤል ብቻ ሆኖ እያለ ደሙንም ስለ ጠጣች እግዚአብሔር ምድርን ተቈጣት ለምን አለ?

✔️መልስ፦ የምድር መረገም ጉዳቱ ለሰው ስለሆነና ምድርን መርገም ቃኤልን የመርገም አንድ አካል ስለሆነ ነው እንጂ ተነጥሎ የሚታይ አይደለም።


© በትረ ማርያም አበባው

✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

27 Jan, 10:16


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 116 💙💙

▶️፩. "ደስታቸው እንደምትበር ወፍ ነውና" ይላል (1ኛ መቃ.25፥15)። ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የምትበር ወፍ ፈጥና እንደምትሄድ (እንደምታልፍ) ሁሉ የኃጥኣንም ደስታቸው ፈጥና ታልፋለች አትጸናላቸውም ማለት ነው።

▶️፪. "እርሱ ሕያዋንንና ሙታንን ከኖባና ከሳባ ከኢትዮጵያና ከሕንደኬ" ይላል (1ኛ መቃ.25፥9)። ሳባና ሕንደኬ ይለያያሉ? ከኢትዮጵያና ሕንደኬ ሲልስ የተለያዩ ሀገሮች ናቸው እንዴ?

✔️መልስ፦ ሕንደኬ የሚላት ሕንድን ነው። ሳባ የሚላት ደግሞ የመንን ነው። ኢትዮጵያ የሚላት ደግሞ ሀገራችንን ነው። ስለዚህ የተለያዩ ሀገሮች ናቸው። የመን የኢትዮጵያ አካል የነበረችበት ዘመን ግን እንደነበረ በትውፊት ይነገራል።

▶️፫. 1ኛ መቃ.24፥8 ላይ"ክፉ ሰዎች ልብሳቸውን ለውጠው ይመጣሉ። ከመብላት ከመጠጣት በብርና በወርቅም ከማጌጥ እግዚአብሔርም የማይወደውን ሥራ ሁሉ በኃጢአት ጸንቶ ከመኖር በቀር በነእርሳቸው ዘንድ ሌላ ሕግ የለም"ይላል።  በዚህ ንባብ "ልብሳቸውን ለውጠው ይመጣሉ" ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በሌላ ክፉ ሥራ ይመጣሉ በክፋት ላይ ክፋት ይጨምራሉ ማለት ነው። ይህም እንደ አንዳንድ ሌቦች ነው። ሰርቀው ወዲያው ሌላ ልብስ ቀይረው ይመጣሉ። ይህም ሌባ ሆነው ሳለ ሌብነታቸው እንዳይታወቅ ነው።

▶️፬. "የዓለምንም ገንዘብ በሰሙ ጊዜ በዐይናቸው ሳያዩት የራሳቸው ገንዘብ ያደርጉታል። በዐይናቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለምና በዐይናቸው ባዩት ጊዜ በአፋቸው የበሉት ይመስላቸዋል" ይላል (1ኛ መቃ.24፥12)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ደግሞ ስስታምነታቸውን ለመግለጽ ነው። በዐይናቸው ባዩት ጊዜ በአፋቸው የበሉት ይመስላቸዋል ማለት አንዳንዱ ሰው ምግብ ቀርቦለት ምንም ሳይበላው ገና በዐይኑ ቀውለል ቀውለል እያለ ስስታምነቱን ያሳያል ማለት ነው። የዓለምንም ገንዘብ የራሳቸው ገንዘብ ያደርጉታል የተባለው የእነርሱ ያልሆነን ገንዘብ እየሰረቁ ኃጢአት ይሠራሉ ማለት ነው።

▶️፭. "እኔ እግዚአብሔር ከአድማስ እስከ አድማስ ምሉእ ነኝና ፍጥረቱም ሁሉ በሥልጣኔ ተይዟልና በሰማይና በምድር በጥልቅና በባሕርም ከሥልጣኔ የሚያመልጥ የለም" ይላል (1ኛ መቃ.25፥4)። መምህር ስለአድማስና ናጌብ ሰፋ አድርገው ቢያብራሩልኝ። ከአድማስ እስከ አድማስ ሲል ከአድማስ ባሻገር እግዚአብሔር በሥልጣኑ የሚገዛው ሌላ ፍጥረት (ዓለም) የለም እንዴ?

✔️መልስ፦ ናጌብ የሚባለው በመሬት ዙሪያ ያለ እስከ ሰማይ የማይደርስ ከሰማይ ዝቅ ያለ ተራራ (ቅጽር) ነው። ከናጌብ ቀጥሎ ዐቢይ ውቅያኖስ የሚባል አለ። ይህም ከዓለም የተሰወረ ዓለም ያልደረሰበት ዓለም ነው። ግዙፋኑ ፍጥረታት እነ ሌዋታን የሚኖሩበት ክፍለ ምድር ነው። ከዚያ ቀጥሎ አድማስ አለ። አድማስ ሰማይና ምድር የሚገናኙበት ቦታ ነው። እግዚአብሔር ከአድማስ እስከ አድማስ ይገዛል ማለት በምድር ያሉ ፍጥረታትን ሁሉ ይገዛል ማለት ነው። ከአድማስ ባሻገር ዓለም እንዳለ የሚገልጽ መጽሐፍ አላገኘሁም። ከአድማስ በኋላ ያለ እግዚአብሔር ነው። በሰማያት ያሉትንም በምድር ያሉትንም ሁሉንም ፍጥረታት የሚገዛ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን ይተርፋታል እንጂ አትተርፈውምና። ስለዚህ በያዛት ዓለምም ህልው ሆኖ ከያዛት ዓለም ውጭም በምልአት ኖሮ ፍጥረታትን ሁሉ ይገዛል ያስተዳድራል።

▶️፮. "ከአዜብ ነፋሰ ይነሣል በመስዕም ያለ ድርቅ ይጸናል ኋላ በፍጻሜ ዘመን ወደእርሷ የሚመጣ ከእግዚአብሔር መፈራት ገናንነትም የተነሣ የኤርትራ ባሕር ተሰምታ ትጠፋለች። በእርሱ የሞቱትንና ያሉትን ሰዎች ይገዛልና ከሳባ እና ከኖባ ከሕንደኬና ከኢትዮጵያም ወሰናቸውና አውራጃቸውም ጋራ ሁሉ ተሰምታ ትጠፋለች" ይላል (1ኛ መቃ.25፥8-9)። የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ ነው። በእርሱ የሞቱትንና ያሉትን ሰዎች ይገዛልና የተባለ ክርስቶስ ነው። በስሙ አምነው የሞቱትንና ያሉትን የሚገዛ እርሱ ነውና። ሌሎችን እርሱ የማይገዛ ሆኖ አይደለም። የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እግዚአብሔር በሚወዳቸው መጠራት ደስ ስለሚለው ነው። የሁሉ አምላክ ሆኖ ሳለ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ የያዕቆብ አምላክ ነኝ እንዳለው ያለ ነው። የኤርትራ ባሕር በእግዚአብሔር ግርማ ፊት መቆም እንደማትችል ለመግለጽ ትጠፋለች ተብሏል። ምድር ከቃሉ የተነሣ ትንቀጠቀጣለች እንደሚለው ያለ ነው።

▶️፯. "የክፉ ሰዎች ዐመፃቸው እንደ ጥቅል ነፋስ የበደለኞች ጉባኤያቸውም እንደ ጉም ሽንት ነውና ይልቁንም በየጊዜው ወደሱ የሚለምኑ የንጹሓንን ልመና ይቀበላል" ይላል (1ኛ መቃ.25፥14)። ጥቅል ነፋስና የጉም ሽንት ብሎ የገለጻቸው ምንን ለማመልከት ነው?

✔️መልስ፦ ጥቅል ነፋስ ለአንድ አፍታ ብዙ መስሎ ቢታይም ትንሽ ቆይቶ እንዳልነበረ ይሆናል። ጉምም ብዙ ቢመስልም ከዘነበ በኋላ ወዴት እንደሄደ አይታወቅም ይጠፋል። ክፉ ሰዎችም ያለን ቢመስላቸውና ብዙ ቢመስሉም እንደ ጉም ሽንትና እንደ ጥቅል ነፋስ ወዲያው ይጠፋሉ ማለት ነው።

▶️፰. "የሌላውን ገንዘብ ይበሉ ዘንድ ከጠላታቸው የዘረፉትን ገንዘብ በልተው ይጠግቡ ዘንድ እንስሳትን በጎችንና ላሞችንም ይዘርፉ ዘንድ የሌላውንም ማዕድ ይበሉ ዘንድ የጠላቶቻቸውንም ልጆች ምርኮ ይወስዱ ዘንድ ደስ ያሰኘዋል" ይላል። የጠላትን ገንዘብ መውሰድ (መማረክ) በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ በጦርነት ገጥሞ የጠላትን ገንዘብ መማረክ በብሉይም የነበረ በሐዲስም ያለ ነው። ሰው መጀመሪያውን ባይጣላና በሰላምና በፍቅር ቢኖር መልካም ነበር። ነገር ግን አለመግባባት አይሎ ወደ ጦርነት ቢያድግ በፍትሕ ሥጋዊ (በነገሥታት አስተዳደር) ምርኮ ሊፈቀድ ይችላል። ይህ በራሱ ሕግ የሚዳኝ ስለሆነ ኃጢአትነት የለውም። በፍትሕ መንፈሳዊ (በካህናት አስተዳደር) ግን መታረቅና ሰላም መፍጠር እንጂ ምርኮ የለም።

▶️፱. "ከጉድጓዱ እንደ ወጣ ፍለጋውም እንደማይገኝ ወደ ቤቱም እንደማይመለስ አሽን ፈጥነው ይጠፋሉና በሕይወታቸውም ሳሉ በጎ ሥራን ስላልሠሩ እግዚአብሔር ተቈጥቶ በያዛቸው ጊዜ ለሰውነታቸው ወዮላት" ይላል። አሽን ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አሸን የሚባለው ክረምት ሊገባ ሲል ከመሬት የሚወጣ ሁለት ክንፍ ያለው አካሉ ምስጥ የሚመስል ፍጥረት ነው።

▶️፲. 1ኛ መቃ.23፥2 ቃኤል ወንድሙን አቤልን የገደለው በሴት ቀንቶ ነው ይላል። ነገር ግን በዘፍ.4፥1-8፣ ኩፋ.5፥9፣ ዕብ.11፥4 እና 1ኛ ዮሐ.3፥12 ባለው እግዚአብሔር የአቤልን መሥዋዕት ስለተቀበለና የቃኤልን ስላልተቀበለው እንደገደለው ያስረዳል። ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ሁለም ትክክል ነው። አቤልና ቃኤል መጀመሪያ በሚስት ተጣሉ። አዳም የአቤልን መንትያ ለቃኤል፣ የቃኤልን መንትያ ለአቤል አጋብቷቸው ነበር። ነገር ግን የአቤል ሚስት የነበረችው የቃኤል መንትያ በጣም ውብ ስለነበረች ቃኤል የእኔን ውብ መንትያ ለምን ለአቤል ይሰጠዋል ብሎ ተቆጣ። ይህን ጊዜ አዳም መሥዋዕት ሠዉና መሥዋዕቱን እግዚአብሔር የተቀበለለት ይሁን አላቸው። ከዚያ መሥዋዕት ሠዉ። መሥዋዕት ሲሠዉ ቃኤል እግዚአብሔር አይበላ ምን ይሠራለታል ብሎ ግርድ ግርዱን አቀረበ። አቤል ደግሞ እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ስለሆነ ንጹሕ ነገር ይፈልጋል ብሎ ቀንዱ ያልከረከረ፣ ጸጕሩ ያላረረ የዓመት ጠቦት አቀረበ። እግዚአብሔርም የአቤል የልቡን ንጽሕና ተመልክቶ የአቤልን መሥዋዕት ተቀበለ። ወነጸረ እግዚአብሔር ላዕለ አቤል

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

27 Jan, 05:14


💟 መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ክፍል 6 💟

💟ምዕራፍ ፳፮፡-
-የሰው ራሱ የጽድቅ ፍሬ እንደሆነ እና ፍሬ የሌለው በጎ ሥራ እንደሌለ መገለጹ

💟ምዕራፍ ፳፯፡-
-እግዚአብሔር ዓለምን እንደፈጠረ፣ ምድርን በውሃ ላይ እንዳጸናት

💟ምዕራፍ ፳፰፡-
-ከአዳም ደጋግ ልጆች ነቢያት ነገሥታትና ክፉዎች ልጆች እንደተወለዱ

💟ምዕራፍ ፳፱፡-
-እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ቸል እንደሚላቸው መገለጹ

💟ምዕራፍ ፴፡-
-እግዚአብሔር እንደ ሕጉ የማይሄዱ ነገሥታትን ልጆች ከመንግሥትነት እንደሚከለክላቸው መናገሩ
-እግዚአብሔር ያላከበሩኝን፣ ሕጌንም ያልጠበቁትን ከሰጠኋቸው ስጦታ እለያቸዋለሁ ማለቱ

💟💟💟የዕለቱ ጥያቄዎች💟💟💟
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ፍሬ የሌለው በጎ ሥራ የለም
ለ. ሰው ጽድቅን ሲሠራ ቅንነትን ያፈራል
ሐ. እግዚአብሔር ለሚጸልይ ሰው የአንደበቱን ዋጋ ይሰጠዋል
መ. ሁሉም
፪. ስለ ልዑል እግዚአብሔር ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ለፈጠረው ፍጥረት ሁሉ መሓሪና ይቅር ባይ ነው
ለ. ለፈጠራቸው ደማውያን ፍጥረታት ሁሉ ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/2dQxH87vVC0?si=hAR4ZRyT0cL-3MP9

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

26 Jan, 07:58


እንኳን ለሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ።

የሰማዕቱ በረከት ይደርብን።

ሰማዕት ማለት እውነትን በመመስከር እስከ ሞት የታመነ ማለት ነው። ሰማዕትነትን ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ባርኮ ሰጥቶናል። ቅዱሳን ፍቅረ እግዚአብሔርን እስከ ሰማዕትነት ደርሰው ገለጹ።

ሰማዕታት ለክርስቶስ ፍቅር ሲሉ የደረሰባቸውን ምድራዊ መከራ ሁሉ ናቁት። የዚህን ዓለም ክብር ናቁት። አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም። ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ። ወተዐገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት። ስለመንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሡ (ቅዱስ ኤፍሬም፣ ውዳሴ ማርያም)።

ሰማዕትነት ፍኖተ ክርስቶስ ነው። ሰማዕትነት መስቀለ ክርስቶስን መሸከም ነው። ዓለሙ ሁሉ ወዶን እግዚአብሔር ከሚጠላን ዓለሙ ሁሉ ጠልቶን እግዚአብሔር ቢወደን ይሻላል። ነገራችንን ምን ያህል ሰው ይወደዋል ብሎ ከመናገር ይልቅ እግዚአብሔር የሚወደው ነወይ የሚለው ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።

እንደ ሰማዕታት
ለእውነት
በእውነት እንኑር

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

26 Jan, 05:30


💜 መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ክፍል 5 💜

💜ምዕራፍ ፳፩፡-
-ዳዊት በእግዚአብሔር በመታመኑ ከሳኦልና ከሌሎችም ጠላቶቹ እጅ እንደዳነ መነገሩ
-ድል መንሣት ከእግዚአብሔር እንደሆነ መገለጡ
-እግዚአብሔር ሕጉን በማይጠብቅ ሰው ላይ መከራን እንደሚያመጣበት መገለጡ

💜ምዕራፍ ፳፪፡-
-በእውነት መፍረድ፣ ቸር፣ የዋህና ቅን መሆን እንደሚገባ መገለጹ

💜ምዕራፍ ፳፫፡-
-በቃየል መንገድ መሄድ እንደማይገባ

💜ምዕራፍ ፳፬፡-
-ጌዴዎን እግዚአብሔርን በመታመኑ በጥቂት ሠራዊት ብዙ የአሕዛብን ሠራዊት ድል እንደነሣ

💜ምዕራፍ ፳፭፡-
-ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ የሚገዛና የሚያስተዳድር እግዚአብሔር እንደሆነ
-ደም ግባት፣ ገንዘብ ኃላፊ እንደሆነ መገለጹ

💜💜💜የዕለቱ ጥያቄዎች💜💜💜
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ድል መንሣት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው
ለ. በእግዚአብሔር መታመን ከጠላት ያድናል
ሐ. በእግዚአብሔር ከመታመን በሠራዊት መታመን ይሻላል
መ. በእግዚአብሔር የታመነ በሕይወት ይኖራል ይከብራልም
፪. እግዚአብሔር ሕጉን የማይጠብቅን ሰው ምን ያደርገዋል?
ሀ. በጠላቱ እጅ ይጥለዋል
ለ. ፍሬያትን በመስጠት ደስ ያሰኘዋል
ሐ. ዝናምን በጊዜው ያዘንምለታል
መ. ለ እና ሐ
፫. ጌዴዎን በጥቂት ሠራዊት በጣም ብዙ የሆኑ የአሕዛብን ሠራዊት ለማሸነፍ የረዳው ምንድን ነው?
ሀ. በእግዚአብሔር መታመኑ
ለ. ለጣዖታት መሥዋዕትን መሠዋቱ
ሐ. ኃይለኛና ጉልበታም መሆኑ
መ. ለ እና ሐ

https://youtu.be/VDY0NiNL-vs?si=rOAjlK3DROrTS4f9

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Jan, 16:23


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 115 💙💙

▶️፩. 1ኛ መቃ.18፥7 ከጥፋት ውሃ በኋላ ከ120 ዓመት በላይ የኖረ አለ አይደል?

✔️መልስ፦ አዎ አለ። ነገር ግን ከጥፋት በኋላ ጥቂቶች ብቻ እንጂ አብዛኛው ከ120 ዓመት በላይ አልኖረም። በብዙው ተናግሮ ነው። ከጥፋት ውሃ በፊት ግን አብዛኛው ከ120 ዓመት በላይ ይኖር ነበር።

▶️፪. "በኪሩቤል ሠረገላ የሚቀመጥ እጅግ የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክት በፊቱ የሚቆሙ የሠራዊት ጌታ የሚመሰገንባት የእግዚአብሔርን ከተማ ለማጥፋት ተባብረዋልና" ይላል (1ኛ መቃ.16፥9)። ያች የእግዚአብሔር ከተማ የተባለችው ማን ናት?

✔️መልስ፦ በብሉይ ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ከተማ የሚላት የዳዊት የመንግሥቱ መቀመጫ የነበረችውን ጽዮንን (ኢየሩሳሌምን) ነው።

▶️፫. "አባቶቻቸው መላእክት ሳሉ ከመላእክት ጋር በሰማይ ያመሰግኑ ነበር" ይላል (1ኛ መቃ.18፥3)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው? መላእክት ሳሉ ሲልስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ደቂቀ ሴት በመልካም ሥራ ጸንተው ይኖሩ ስለነበር መላእክት እስከመባል ደርሰው ነበር። ስለዚህ መላእክት ሳሉ ማለት በግብረ መላእክት በመልካም ሥራ ጸንተው ሳሉ ለማለት ነው።

▶️፬. አጋንንት ከደቂቀ ሴት የሚለዩት በምንድን ነው? አንዳዴ ሲወራ ጋኔን ልጇን አዝላ አየን ሲሉ ይሰማልና ከዚህ 1ኛ መቃ.18፥4 ካለው ጋር ያለውን ግንኙነት ያስረዱኝ? እንዲሁም የቃየን ልጆች በበዙ ጊዜ ከበሮና በገናን ሳንቲንና መሰንቆን ሠሩ ዘፈንና ጨዋታውንም ሁሉ አደረጉ ይላልና ሳንቲ ምንድን ነው? (1ኛ መቃ.19፥1)።

✔️መልስ፦ ደቂቀ ሴት ሰዎች ናቸው። መጀመሪያ በመልካም ሥራቸው መላእክት እስከመባል ደርሰዋል። ቀጥለው ክፉ ሥራ በመሥራታቸው አጋንንት ተብለዋል (ልቡሳነ ሥጋ አጋንንት) ማለት ነው። ደቂቀ ሴት ሥጋ ያላቸው በክፋታቸው ምክንያት አጋንንት የተባሉ ናቸው እንጂ ከመጀመሪያውም ረቂቃን ሆነው የተፈጠሩ አይደሉም። ልቡሳነ ሥጋ አጋንንት ይወልዳሉ ይዋለዳሉ ስለዚህ ልጅ አዝለው ሊታዩ ይችሉ ይሆናል። ሳንቲ የሚባለው ዋሽንት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Jan, 15:57


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 114 💙💙

▶️፩. "ክሣደ ልቡናውን የሚያጸና የሚመካ ፈጣሪውን የማያውቅ ሐሳዊ መሲሕ ከእነርሱ ይወለዳልና ወዮላቸው" ይላል (1ኛ መቃ.13፥2)። ሐሳዊ መሲሕ የሚወለድበት ወገን በእውኑ ይታወቃል እንዴ? ከገዳም ይወጣል የሚሉ ሰዎችም አሉና በአጠቃላይ ስለሐሳዊ መሲሕ ስፋ አድርገው ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ሐሳዊ መሢሕ ከነገደ ዳን እንደሚወለድ በቅዱሳት መጻሕፍት ተገልጿል። አንዲት ሴት መነንኩ ብላ ወደ ገዳም ስትሄድ ከመቃብረ አረሚ አግኝቷት አንድ ጎልማሳ ይደፍራታል። በዚህ ጊዜ ትጸንሳለች። እርሷም ትዕቢት ይዟት በድንግልና ጸነስኩ ብላ ትዋሻለች። ልጁ ይወለዳል። የሚወለደው ልጅ ላይኛው ከንፈሩ ትልቅ፣ ዓይኑን ደም የሰረበው ነው (ዘላዕላይ ከንፈሩ የዐቢ እንዲል)። ይህም ሰው በሰይጣናዊ ምትሐት እየታገዘ የተለያዩ ተአምራትን እያደረገ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር (ለ42 ወር) ብዙ ሰዎችን ያስታል። ከዚያ በኋላ እነ ኤልያስ እነ ዕዝራ እነ ሄኖክ ከብሔረ ሕያዋን መጥተው ሐሰተኛነቱን ይነግሩታል። እርሱም ይገድላቸዋል። ሰማዕት ይሆናሉ። ከዚያ በኋላ ጎግ ማጎግ የሚባሉ ኃያላን ሠራዊት የዓለምን ሕዝብ በጦር ይጨርሱትና ጥቂት ሰዎች ይቀራሉ። እነዚያ ለጥቂት ዘመን በዚህች ምድር ከኖሩ በኋላ ዳግም ምጽአት ይሆናል። ጻድቃን ወደ ዘለዓለም ደስታ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ። ኃጥኣን ወደ ዘለዓለም ኀዘን ወደ ገሃነመ እሳት ይገባሉ።

▶️፪. 1ኛ መቃ.13፥8 ላይ "ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እኔ ፈርጄ አጠፋለሁ ብሏልና ከምጽአት በኋላ ግን ለዲያብሎስ ሥልጣን የለውም" ሲል በምን ላይ ነው ሥልጣን የሌለው? ከምጽአት በኋላ ከእርሱ ጋር በገሃነመ እሳት በሚኖሩት ላይ ሥልጣን የለውም እንዴ?

✔️መልስ፦ ዲያብሎስ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ የቻለውን ያህል ለማሳሳት ይሞክራል። ከምጽአት በኋላ ግን ማንንም አያሳስትም። እርሱና በእርሱ ትምህርት የተሳሳቱት ሁሉ በገሃነመ እሳት እየተቃጠሉ ይኖራሉ። በገሃነመ እሳት እርሱም ከሚቃጠሉትና ከሚሰቃዩት አንዱ ሆኖ ይኖራል እንጂ ለእርሱ የተለየ ሥልጣን አይኖረውም።

▶️፫. "እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት ላይ ኮርቷልና ፈጥኖም የወደደውን ሁሉ በአንድ ሰዓት አድርጓልና ታናሽ ጠላት ዲያብሎስን የጌታ ሞት ያጠፋዋል" ይላል (1ኛ መቃ.13፥7)። በፈጠረው ፍጥረት ላይ ኮርቷልና፣ በአንድ ሰዓት አድርጓልና ሲል ምን ለማለት ነው?  ይሄ ንባብ ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ የወደደውን በአንድ ሰዓት አድርጓል ማለት አንድ ጊዜ ክዷል ማለት ነው። በካደ ጊዜ የሆነውን ድርጊት ለማስታዎስ ነው። በፈጠረው ፍጥረት ላይ ኮርቷልና ማለት እግዚአብሔር ከፍ አድርጎ ቢፈጥረው ሌሎችን ፍጥረታት እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መታበዩን መግለጽ ነው። ኩራት የትዕቢት መገለጫ ነውና።

▶️፬. 1ኛ መቃ.12፥1 ላይ ያለው በየትኛው የትንቢት ክፍል ተጽፏል?

✔️መልስ፦ ኢየሩሳሌም በበደሏ ምክንያት እንደምትማረክ ነቢያቱ እነኤርምያስን ጨምሮ ተናግረዋል። ከዚህ ላይ የመቃብያን ጸሓፊ ነቢይ ብሎ ቢገልጽም ስሙን ግን አልነገረንም። ኢየሩሳሌም በበደሏ ምክንያት እንደምትማረክ ግን ኤርምያስ "በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ። ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ። ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ። ሁሉም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ" ብሏል (ኤር.23፥14)።

▶️፭. 1ኛ መቃ.12፥7 ላይ "የወይናቸው ተክል የሲዖል ውኃን ጠጥቷልና ሐረጋቸውም በሐሩር ነፋስ ፀንቷልና" ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ጉዳዩ ቀጥታ ስለወይንና ስለተክል ለመናገር ሳይሆን ምሳሌያዊ አገላለጽ ነው። የሲኦል ውኃ ያለው ክፋትን ነው። የሲኦል ውሃን ጠጥቷልና ሲል ክፋትን ሠርቷልና ማለት ነው። በሐሩር ነፋስ ጸንቷል ያለው የሐሩር ነፋስ በጣም ሞቃት ስለሆነ ተክልን ያደርቃል። በዚህ ምክንያት ተክሉ ልምላሜ ፍሬ አይገኝበትም። ስለዚህ ምግባር የላቸውም መልካምነት አይገኝባቸውም ማለት ነው።

▶️፮. "ክፉ ሰዎች የማረኩትን ምርኮ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ደጋጎች ይካፈላሉ" ይላል (1ኛ መቃ.12፥4)። የንባቡ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ክፉ ሰዎች በክፋታቸው ብዙ ገንዘብ ቢሰበስቡ እንኳ ያንን ገንዘብ ሳይበሉት ያልፉና ሌሎች ደጋግ ሰዎች ወርሰውት ይኖሩበታል ማለት ነው።

▶️፯. "ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ኃይሌን እገልጽ ዘንድ ለቁጣዬ አምሳል አደረግሁት" ይላል (1ኛ መቃ.13፥2)። "ለቁጣዬ አምሳል አደረግሁት" ሲል ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በቁጣ የሚመጣ ቅጣት ከፍ ያለ ነው። ስለዚህ የቁጣ አሞሳል ማለት እገሌን ቢያጠፋ እግዚአብሔር ተቆጥቶ እንዲህ አደረገው እኛም ብናጠፋ እንዲህ ያደርገናል እንድንል የሚያደርግ ማለት ነው። ሌላው የቁጣውን ውጤት አይቶ ከክፉ ሥራው እንዲመለስ የሚያደርግ ስለሆነ የቁጣ አምሳል ተብሏል። እግዚአብሔር ቁጣውን በእኛ ላይ ክፉ ሰዎች ሲነግሡ ዝም በማለት ሊገልጽ ይችላል። በዚህ ጊዜ እነዚያ ክፉ ነገሥታት የቁጣ አምሳል ይባላሉ።

▶️፰. "ምሥጢር እንዳያዩ ዓይነ ልቡናቸው ታውሯልና እንዳይሰሙ እግዚአብሔር የሚወደው ፈቃዱንም እንዳያደርጉ ጆሯቸውም ደ*ንቁ-ሯልና በሥራቸው እግዚአብሔርን አላወቁም ልቡናቸውም አንደ ሰዶም ሕግ ማደሪያ ነው። ወገናቸውም የጣፈጠ ፍሬን የሚያፈራ የገሞራ ወይን ወገን" ይላል (1ኛ መቃ.12፥2)። የጣፈጠ ፍሬን የሚያፈራ የገሞራ ወይን ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የገሞራ ወይን (ወይነ ገሞራ) ያለው ውስጠ ወይራ ነው። ወይን ብሎ በግሥ ተናገረው እንጂ የገሞራ ክፋት ማለት ነው። የጣፈጠ ፍሬ ማለቱም ኃጢአት ሲሠሩት የጣፈጠ እንደሚመስልና ቆይቶ ግን መራራ መሆኑን ለማሳየት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Jan, 10:10


ጽድቅ መስሎ ከሚሠራ ክፋት እንራቅ ማለት ነው
ክፉ ሥራን ግራ ሲለው
የጽድቅ ሥራን ቀኝ ይለዋል
ታዲያ ወደ ግራ አትበል ማለት ክፉ ሥራን አትሥራ ማለት ከሆነ ወደ ቀኝ አትበል ማለትስ መልካም ሥራን አትሥራ ማለት ነውን ቢሉ አይደለም። መልካም ሥራን ሁልጊዜም ልንሠራው የሚገባን ነገር ነው። ታዲያ ወደ ቀኝ አትበል ማለት ምን ማለት ነው? ከተባለ ጽድቅ መስሎ ከሚሠራ ክፋት ራቅ ማለት ነው። ይኸውም፦
በቀናዒነት ስም ከተደበቀ ስድብ
በፍቅር ስም ከተደበቀ ዝሙት
በተግሣጽ ስም ከተደበቀ ጽርፈት
በአስተዋይነት ስም ከተደበቀ ፍርሀት
በፍትሕ ስም ከተደበቀ ጥላቻ
በዘመድ ፍቅር ከተደበቀ ዘረኝነት
መራቅ ይገባል ማለት ነው። አንዳንዱ አጥፊዎችን ፊት ለፊት ጥፋታቸውን ላለማውገዝ ፈርቶ ዝም ይላል። ይህ ብቻ አይደለም ዝምታውን ከጥበብ እንድንቆጥርለት ይጥራል። ይህ መቆም አለበት። አንዳንዱ ፍትሕን ለማስፈን ሕግን ለማረጋገጥ በሚል ሰበብ የሚጠላቸውን ሰዎች ለማሰር ወይም ለመቅጣት ይጠቀምበታል። ይህም ትልቅ ስሕተት ነው። ችግር ፈጣሪዎችን ፊት ለፊት ስሕተታቸውን መግለጽ ከሁላችንም ይጠበቃል። በዚህ ጊዜ ያለስድብ ጉዳዩን ብቻ በመሞገት መሆን ይገባዋል። ስድብ የሚጎዳው ተሳዳቢውን ነው እንጂ ተሰዳቢው ዝም ካለ በረከትን የሚያገኝበት ነው። የአንድን ችግር እውነተኛ መልኩን ማሳየት እንጂ የችግሩን ግዝፈት ለማሳየት ጨመርመር እያደረጉ ማውራት አይገባም። እውነትን ለመግለጽም እውነትን ቀጥታ መንገር እንጂ ድሪቶ መጨመር አያስፈልግም። የእውነትን ውበት የሚያደበዝዙ ድሪቶዎች አያስፈልጉም። ግነትም ማኮሰስም አይገባም። ኦርቶዶክሳዊ ቀጥ ያለ ነው። አይጠማዘዝም።

በደንብ በጥልቀት መመርመር ያለብን ጉዳይ ግን ከንግግራችን፣ ከተግባራችን ጀርባ ያለውን መነሻ ሐሳብ ነው። ለምሳሌ ከአንድ ሰው ጋር በሆነ ጉዳይ ስለማትግባቡና ስለምትጣሉ ያ ሰው ቢሰርቅና አንተ ደግሞ ሌባ መንግሥተ ሰማያትን አይወርስም ብትል ንግግርህ እውነት ነው። ይህን ትክክለኛ ንግግር የተናገርከው ያን የተጣላሀውን ሰው ለማናደድ አስበህ ከሆነ ግን ጽድቅ መስሎ የሚሠራ ክፋትን እየሠራህ መሆኑን ልትረዳው ይገባል። ለዚያ ነው ከእያንዳንዱ ንግግራችንና ጽሑፋችን ጀርባ የተደበቀ ጥላቻ ወይም ከንቱ ውዳሴ እንዳይኖር መመርመር አለብን የምንለው። አይሁድ ጌታን የሰቀሉት ለጌታ እንቀናለን ብለው ነው። ሽፋኑ ቅዱስ ቅንዐት ነበረ። ነገር ግን በጥልቀት ሲመረመር ምቀኝነት ነበር። እና ከእያንዳንዱ ተቃውሟችን ጀርባ ያለውን ጉዳይ መመርመር ጥሩ ነው። ለቤተ ክርስቲያን አስባለሁ በሚል ሽፋን ቤተክርስቲያንን እየጎዳናት እንዳይሆን በጥልቀት ስሜትን መመርመር ይገባል። ትክክል እያደረግን መስሎን እያጠፋን እንዳይሆን ራሳችንን ብንመረምር መልካም ነው።

ክፋትን ማረምና መቃወም ከሁላችንም ይጠበቃል። ስናርምና ስንቃወም ግን በኦርቶዶክሳዊነት መንፈስ ሆነን ካልሆነ የክፋቱ ተባባሪ እንሆናለን። ጉዳይን መሞገት እንጂ ባለጉዳዩ ጋር ጠብ አያስፈልግም። ማንንም መፍራት አያስፈልግም። ሁሉም ወደ አመድነት የሚለወጥ ነው። ስለዚህ ማንኛውንም ሰው ማክበርና መውደድ እንጂ መፍራት አይገባም። ክፉ ሥራ በታዋቂነት፣ በምሁርነት፣ በሥልጣን፣ በሀብትና በመሳሰሉት ተደብቃ መጥታ እንዳትሸውደን በጥልቀት ማሰብ ይጠበቅብናል። አጥፍተን ከነበረ ይቅርታ መጠየቅን እንልመድ እንጂ በእልህ በጥፋታችን መቀጠል የለብንም። የተሰበረ ልብን ገንዘብ እናድርግ። ከራሳችን ጋር ጦርነት እንግጠም። ራሳችንን እናሸንፍ። ልብንና ኩላሊትን መርምሮ የሚፈርድ አምላክ ስላለ ከእያንዳንዱ ድርጊታችን ጀርባ ያለውን ሐሳብ እንመርምር። በወንድማማችነት፣ በባለቤትነት ስሜት ሆነን እናስብ። ሁሉንም ሰው እንደራሳችን በማሰብ እንናገር። እውነትን አጋንነን በመናገር ሰበብ የውሸት ስልታዊ ደጋፊ እንዳንሆን እንጠንቀቅ። እውነትን ስንናገር ምንም ግነት አያስፈልግም።

© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Jan, 07:23


የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም ለማስከበርና
የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየተሰራ ነው።
************

ጥንታዊት፣ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማስፋፋት በምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሌሎችን መብትና ጥቅም ባለመንካት በትዕግሥትና በማስተዋል የምትጓዝ አገራዊ ኃላፊነት የሚሰማት ሰላምን አብዝታ የምትሰብክ መንፈሳዊት ተቋም መሆኗ ይታወቃል።

ቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮቷን ለማስፋፋት በተጓዘችባቸው አያሌ ዓመታት አገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ፊደላትና የራሷ የቀን አቆጣጠር ባለቤት እንድትሆን ያስቻለች፣በሊቃውንቶቿ የመጠቀ እውቀት አማካኝነት የሥነ ጥበብ፣ የሥነ ስዕል፣ የዕጽዋትና የጠፈር ምርምርና ጥናቶችን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ለዓለም ያበረከተች ጥንታዊት ተቋም ስለመሆኗም አያሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ይሁን እንጂ ይህች ለአገረ መንግስት መመስረትና መጽናት፣ ለእውቀት መስፋፋት፣ ለአብሮነት መጎልበት፣ ትውልድን በሥነ ምግባር ቀርጻ ፍቅርና አንድነትን በተግባር የሰበከች እናት ቤተክርስቲያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ፣ በአስተምህሮቿ፣በዕምነቷ፣በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል።

ስለሆነም በተደጋጋሚ እየተፈጸሙባት የሚገኙትን እነዚህን እኩይ ተግባራት ከዚህ በላይ በዝምታና በትዕግስት ማለፍ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ የሚያደርጋት ከመሆኑም በላይ መብቷን በእጅጉ የሚጋፋ፣ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቶቿን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።

ስለሆነም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ማጥናት፣መከታተልና ሕግን መሰረት ያደረገ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድግ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘችው ወቅታዊ ሁኔታውን በዝርዝር በማጥናት ተቋማዊ እልባት የሚያገኝበትን መንገድ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ያደረገች ሲሆን የቤተክርስ
ቲያናችን የሕግ አገልግሎት መምሪያም በሕግ አግባብ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ፍትሕ ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብና በማደራጀት ክስ መመስረት የሚያስችለውን ሁኔታ በማመቻቸት ወደ ተግባር ለመለወጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ከዚህ ጎን ለጎንም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በጠቅላይ ቤተክህነት ከሚገኙ መምሪያዎች መካከል ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን መምሪያዎች በማካተት የተቋቋመው ኮሚቴም ዝርዝር ጥናቶችን በሚገባ በማጥናትና ችግሮቹን ለይቶ ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ በማቅረብ በቤተክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ አስተዳደር አማካኝነት ተቋማዊ አቋም የሚወሰድበትና በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የማያዳግም መፍትሔ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል ሥራ በመሥራት ላይ መሆኑን እየገለጸች በሁለቱም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ በተከታታይ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲገለጽ የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እያስታወቀች በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምዕመናንና ምዕመናት በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት የሚደረግ
ላቸውን ጥሪ ተቀብለው ለቤተክርስቲያናችን መብት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እናት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ጥር ፲፯ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Jan, 04:16


💗 መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ክፍል 4 💗

💗ምዕራፍ ፲፮፡-
-ከእስራኤላውያን ውጭ ከነበሩ ሕዝቦችም እግዚአብሔርን የሚያውቁ እንደነበሩ መገለጹ

💗ምዕራፍ ፲፯፡-
-የኤዶምያስና የአማሌቅ ሠራዊት እግዚአብሔርን የማያመልኩ እንደነበሩ መገለጹ
-ሰብልያኖስ ለሰው ልጅ ክፋትን እንደሚያስተምር መነገሩ

💗ምዕራፍ ፲፰፡-
-ወደ እግዚአብሔር እንደምንሄድ ማስብ እንደሚገባን

💗ምዕራፍ ፲፱፡-
_የቃየን ልጆች ለብዙ ጊዜ ጨዋታንና ዘፈንን እንዳደረጉ
-ቃየን አቤልን ከገደለ በኋላ ለአቤል የተወሰነችለትን ሚስት እንዳገባ

💗ምዕራፍ ፳፡-
-እግዚአብሔር የጻድቃንን ፍሬ እንደሚያበዛ መነገሩ

💗💗💗የዕለቱ ጥያቄዎች💗💗💗
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ለሰው ልጆች ክፋትን የሚያስተምር ማንኛው ነው?
ሀ. መልአኩ ሚካኤል
ለ. መልአኩ ሰብልያኖስ
ሐ. መልአኩ ሩፋኤል
መ. መልአኩ ዑራኤል
፪. የእግዚአብሔር መንገድ ተብሎ ከተገለጹት መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ሙቶ ያደረውን እንስሳ መብላት
ለ. ትሕትናና የውሃት
ሐ. ወንድምን አለማበሳጨት
መ. ከሰው ሁሉ ጋር መፋቀር
፫. ስለ ጻድቃን ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ስም አጠራራቸው ለበጎ ነገር እስከ ዘለዓለም ይኖራል
ለ. እግዚአብሔር በመከራቸው ጊዜ ረዳት ይሆናቸዋል
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/FVTbAAs2gRU?si=qlGFO6hw__vUIePr

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

24 Jan, 19:19


የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ በአስደናቂ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው። እግዚአብሔር ያስፈጽመን።
#ለመጨረሻ #ጊዜ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ እስኪያልቅ ሌላ ጥያቄ አትጠይቁኝ። ጊዜ ስለማላገኝ ነው። በየዕለቱ ከምናነባቸው ክፍሎች መጠየቅ ይቻላል። የትላንቱን ዛሬም አትጠይቁ። ሙሉ ጊዜ ቢኖረኝ ማናቸውንም ጥያቄ በተቀበልኩ ነበር። ጥናቱ ካለቀ በኋላ የፈለጋችሁትን ትጠይቃላችሁ። እስከዚያ ሌላ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ ውጭ ጥያቄ ካላችሁ ሌላ መምህራንን ጥይቁ።

ይህን መጻፍ ያስፈለገበት ምክንያት አንዳንዶቻችሁ ይህን ደጋግሜ ብናገርም ስላላቆማችሁና ዝም ስላችሁ እየተከፋችሁ ስለሆነ ነው። የየዕለቱን በዕለቱ ጠይቁኝ።

መጽሐፍ ቅዱስን ከግማሽ በላይ አንብበናል። በእያንዳንዱ ክፍል ብዙ የሕይወት መመሪያን አግኝተናል። እስከ 2000 የሚደርሱ ጥያቄዎችን ጠይቃችኋል። በጣም ደስ የሚል ነው። እስካሁን ያልጀመራችሁም ካለንበት ጀምራችሁ መቀጠል ትችላላችሁ። ነገ አንደኛ መቃብያን ከምዕራፍ 15 እስከ ምዕራፍ 20 ነው።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

24 Jan, 05:18


💓 መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ክፍል 3 💓

💓ምዕራፍ ፲፩፡-
-ክፉዎች በክፋታቸው እንደሚፈረድባቸውና እንደሚያለቅሱ መገለጡ

💓ምዕራፍ ፲፪፡-
-እስራኤል እግዚአብሔርን እንዳሳዘነች መገለጧ

💓ምዕራፍ ፲፫፡-
-ለኃጢአተኞች ወዮታ እንዳለባቸው መገለጹ
-ዲያብሎስ በትዕቢቱ እንደተዋረደ መገለጹ
-ቅዱሳን መላእክት በልብ ትሕትና እግዚአብሔርን እንደሚያመሰግኑት መገለጹ
-ቅዱሳን መላእክት ከእግዚአብሔር ትእዛዝ እንዳይወጡና እንዳይተላለፉ ሕሊናቸውን እንደሚጠብቁ መገለጹ

💓ምዕራፍ ፲፬፡-
-እግዚአብሔር ምድርን በማየ አይኅ ከቃየን ልጆች ኃጢአት ሁሉ እንዳነጻት መገለጹ
-ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ፣ ሌሎች አማልክትን አለማምለክ፣ የባልንጀራን ገንዘብ አለመመኘት፣ እግዚአብሔርን ፈጽሞ መውደድ እንደሚገባ መገለጹ

💓ምዕራፍ ፲፭፡-
-መቃቢስ፣ መብክዩስ እና ይሁዳ እስራኤላውያንን ከንጉሠ ምድያም ከአክራንድዮስ እንዳዳኗቸው

💓💓💓የዕለቱ ጥያቄዎች💓💓💓
፩. በዕለተ ትንሣኤ ወደ ገሃነም እንዲሄዱ የሚፈረድባቸው ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው?
ሀ. ጣዖት አምላኪዎች
ለ. አመንዝራዎች
ሐ. ሌቦችና ትዕቢተኞች
መ. ሁሉም
፪. ስለልዑል እግዚአብሔር ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ፈራጅ ነው
ለ. ኃይል ነው
ሐ. ገዢ ነው
መ. ሁሉም
፫. ስለ ቅዱሳን መላእክት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በትሕትና ሆነው እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል
ለ. ከእግዚአብሔር ትእዛዝ እንዳይወጡ ኅሊናቸውን ይጠብቃሉ
ሐ. ሀ እና ለ
መ. በትዕቢታቸው የተዋረዱ ናቸው
፬. አክራንድዮስ ንጉሠ ምድያም በእስራኤል ላይ በተዘባበተ ጊዜ ከእስራኤል ሄደው ገጥመው ካሸነፉት ሦስቱ ሰዎች መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. መቃቢስ
ለ. ስምዖን
ሐ. ይሁዳ
መ. መበክዩስ

https://youtu.be/EU9-GZcvhsE?si=5FmFqEofPOv4xQe-

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Jan, 18:47


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 113 💙💙

▶️፩. "ከእግዚአብሔር አንደበት በሚወጣ ቃል ነው እንጂ ሰው የሚድን በእህል ብቻ አይደለም ብሎ ሙሴ እንደ ተናገረ ዳግመኛም የእግዚአብሔር ቃል ሰውን ሁሉ ከመቃብር ያስነሣዋል" ይላል (1ኛ መቃ.7፥26)። "የእግዚአብሔር ቃል" ሲል እግዚአብሔር ወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ማለት ነው ወይስ እንዴት ይተረጎማል?

✔️መልስ፦ ከአንደበት የሚወጣ ቃል ዝርው ቃል ነው። እግዚአብሔር ለነቢያት ያሰማቸው ድምፅ ዝርው ነው እንጂ አካላዊ አይደለም። ቦርፎሪኮን ተብሎ ይጠራል። የእግዚአብሔር ቃል ሰውን ሁሉ ከመቃብር ያስነሣዋል የሚለው አካላዊው ቃል እግዚአብሔር ወልድን ቢያመለክትም ይሆናል። ትምህርተ እግዚአብሔርን፣ ሕገ እግዚአብሔርን፣ ትእዛዘ እግዚአብሔርንና የመሳሰሉትን ቃለ እግዚአብሔር ይላቸዋልና። ሲሲተ ልብ ቃላቲሁ ለእግዚአብሔር ባለ ጊዜ ምሥጢሩ ትእዛዛቲሁ ትምህርታቲሁ ሕገጋቲሁ ማለት እንደሆነ ሁሉ ማለት ነው። በዚህ ጊዜ አካላዊ አለመሆኑን የሚያስረዳን "ቃላቲሁ" የሚለው ቃል ነው። በአካላዊነት ያለ ቃል አንድ ስለሆነ አንድን በሚያመለክት አገላለጽ ቃሉ ይላል እንጂ ቃላቲሁ አይልምና ነው።

▶️፪. "እግዚአብሔር ጻድቃንን መጥራቱ ለክብር ኃጥኣንንም ለመከራ ነውና ኃጢአተኛውን ያጎሳቁላል ጻድቃንን ግን ያከብራል" ይላል (1ኛ መቃ.7፥32)። መቼስ  እግዚአብሔር አስቀድሞ አይፈርድም (የሰውን ዐጣ ፈንታ አይወስንም) ይባላልና ለምን ጻድቃንን ለክብር ጠራ ኃጥአንንም ለመከራ ነውና ተባለ? ከዚህ ጥቅስ አንጻር ዳዊት "ኃጥኣን ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ። ከሆድም ጀምረው ሳቱ። ሐሰትንም ተናገሩ" (መዝ.58፥3) ያለው እንዴት ይተረጎማል?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር የሰውን ነጻ ፈቃድ ያከብራል። ሰው በነጻ ፈቃዱ ክፋትን መርጦ በክፉ ሥራ ጸንቶ ቢኖር የክፋቱን ዋጋ ይሰጠዋል። መልካምነትን መርጦ በመልካም ሥራ ጸንቶ ቢኖር የመልካምነቱን ዋጋ ይሰጠዋል። እግዚአብሔር ጻድቃንን ያከብራል የተባለው ነጻ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው መልካምነትን የመረጡትን ያከብራቸዋል ማለት ነው። ክፉ የሠሩ ኃጥኣንን ደግሞ ያጎሳቁላል ተብሏል። ኃጥኣን ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ ማለትም እግዚአብሔር ሰዎችን ማን ጽድቅ እንደሚሠራና ማን ደግሞ እንደማይሠራ ሁሉን አዋቂ በመሆኑ አወቃቸው ማለት ነው። እንጂ ኃጢአት እንዲሠሩ አድርጎ ፈጠራቸው ማለት አይደለም። እንዲያ ቢሆን ኖሮስ በኃጥእነታቸው ባልተቀጡ ነበር። ኃላፊነቱን እነርሱ አይወስዱምና።

▶️፫. "አንተ ልበ በካና ደ*ን-ቆሮ የሞቱ ሰዎች የማይነሡ ይመስልሃልን? በሙታን ትንሣኤ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አንደበት መለከት በተነፋ ጊዜ ሳትነሣ በመቃብር አትቀርምና እንዲህ ያለ ነገር አታስብ" ይላል (1ኛ መቃ.9፥7)። በብሉይ ኪዳን ሰውን ደ*ን-ቆሮ ብሎ  መሳደብ እንዴት ተቻለ? "በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አንደበት መለከት በተነፋ ጊዜ" ሲል ይህ መለከት አሁን እኛ የምናውቀው የሚነፋው መለከት ነው ወይስ ሌላ ትርጓሜ አለው?

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም መሳደብ አልተፈቀደም። ከዚህ ላይም ተለይቶ የተሰደበ የለም። ትንሣኤን አለማመን ድ*ንቁ-ርና መሆኑን ተናገረ እንጂ። ትንሣኤን የማያምን ሰውም ደን*-ቆሮ መሆኑን ገለጠ። ደን*ቆ-ሮን ደን*ቆ-ሮ ማለት እውነት እንጂ ስድብ አይደለምና። አንድ ሰው "ሌባ መንግሥተ ሰማያትን አይወርስም" ብሎ ቢናገር ተሳደበ አይባልም። ይህ እውነት ነውና። አንድ ሰው አንድን ሰው ያልሆነውን እንደሆነ አድርጎ ሌባ ቢለው ግን ኃጢአት ይሆንበታል። በቅዱስ ሚካኤል አንደበት መለከት በተነፋ ጊዜ የሚለው በዚህ ምድር እንደምናየው ያለ የሚነፋ መለከት ኖሮ አይደለም። አዋጅ በተናገረ ጊዜ ለማለት ነው። ሚካኤል ከፈጣሪው ተቀብሎ የሚያውጀውን አዋጅ መለከት ብሎ ጠርቶት ነው።

▶️፬. "የቀደሙ ሰዎች ከአዳም ጀምሮ ከሴትና ከአቤል ከሴምና ከኖኅ ከይስሐቅና ከአብርሃም ከዮሴፍና ከያዕቆብ ከአሮንና ከሙሴም ጀምሮ በአባቶቻቸው መቃብር ይቀበሩ ዘንድ ነው እንጂ በሌላ ቦታ ይቀበሩ ዘንድ ያልወደዱ ለምንድን ነው? አጥንታቸውስ ጣዖት ከሚያመልኩ ከክፉዎች ከአረማውያንም አጥንት ጋራ እንዳይቈጠር አይደለምን በሌላ ቦታ ይቀበሩ ዘንድ ያልወደዱ ለምንድን ነው?" ይላል (1ኛ መቃ.10፥1-2)። አንድ ሰው በሕይወቱ እያለ የሠራው ሥራ እንጂ  የሚያድነው ከሞተ በኋላ የትም ቢቀበር ምን ይጠቅመዋል እንዴት ከአረማውያን ጋር ሊቆጠር ይችላል?

✔️መልስ፦ አንድ ሰው ከአረማውያን ጋር ስለተቀበረ አረማዊ ይሆናል ማለት አይደለም። በብሉይ ዘመን አባቶች አፅማችንን ለይታችሁ ከወገኖቻችን ጋር ቅበሩ እያሉ የተናገሩት በዕለተ ትንሣኤ ኃጥኣንና ጻድቃን ተለይተው በኃጥኣን እንደሚፈረድባቸው ለጻድቃን እንደሚፈረድላቸው ትምህርት ለመስጠት ነው። ከግብፅ ወደ ከነዓን መልሱን ያሉት ደግሞ ወደ ከነዓን ለመሄድ እንዲፋጠኑ ለመግለጽ ነው።

▶️፭. 1ኛ መቃ.7፥2 "አምልኮቱንና ዘጠኙን ትእዛዝ ጠብቅ" ይላል። ዘጠኙ ትእዛዝ ያላቸው እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ ዘጠኙ ትእዛዛት የሚላቸው "ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልኩ" ከሚለው ውጭ ያሉትን ዘጠኙን ነው። ይህንን ለብቻው "ኢታምልክ" ብሎ ይገልጸዋል።

▶️፮. መቃቢስ የነበረበት ዘመን መቼ ነው? በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ወይስ በኋላ ነው?

✔️መልስ፦ የነበሩበት ዘመን መቼ እንደነበረ እስካሁን አላገኘሁትም።

▶️፯. 1ኛ መቃ.6፥9 በመንግሥተ ሰማያት አትክልት አለ እንዴ?

✔️መልስ፦ መንግሥተ ሰማያት ዐይን ያላያት ከመታሰብ በላይ ነች። ከዚህ ከመጽሐፈ መቃብያን ብዙ ዕንቍዎች፣ ወርቅ፣ ዕፀዋት እንዳሉ ተገልጿል። እንደምናውቀው ዓይነት ወርቅና ዕፀዋት እንዲሁም አዕናቍ ይሁኑ አይሁኑ ግን ከመታሰብ በላይ ስለሆነች በቸርነቱ ይቅር ብሎን ያኔ ወደ መንግሥቱ ቢያስገባን የምናውቃት ናት። እንጂ አሁን አናውቃትም።

▶️፰. "በምድር እንዳለ የመንግሥታቸው ክብር በሰማይ እንዳለ በምድርም እንደሚያከብሯቸውና እንደሚሰግዱላቸው በሰማይም ከፍ ከፍ ይላሉ" ይላል (1ኛ መቃ.6፥12)። በሰማይ የሚኖረን አኗኗር የሥልጣን ሥርዓት አለው ወይስ ሁሉም በእኩልነት ይኖራሉ?

✔️መልስ፦ በሰማይ በመንግሥተ ሰማያት በገነት የሁሉም ንጉሥ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው። በሰማይ አንዱ የአንዱ ገዢ አይሆንም። ነገር ግን በክብር መለያየት አለ። ኮከብ እምኮከብ ይኄይስ ክብሩ እንዲል ባለመቶ ፍሬ፣ ባለስሳ ፍሬ፣ ባለሠላሳ ፍሬ የተባሉ በክብር የሚለያዩ ይኖራሉ። ነገሥታት በምድር ሳሉ ሕዝቡን በፍትሓዊነትና በእውነት ካስተዳደሩ በሰማይም ከብረው እንደሚኖሩ ለመግለጽ በዚያ ከፍ ከፍ ይላሉ ተብሏል።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Jan, 18:35


ክቡራን ፎቶዋ ተገኝቷል።

ሰማይ ጠቀስ😀😀😀

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Jan, 16:36


አዲስ አበባ ስሄድ ሁል ጊዜ ፍግግ የምታሰኘኝ ፎቅ

የካ አካባቢ ያለች "ሰማይ ጠቀስ" የምትባለዋን ሕንፃ ሳያት ሁል ጊዜ ታስቀኛለች። ከአጠገቧ ከእርሷ የሚበልጥ ፎቅ አለ። እና ባለቤቶቹ "ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ" ብለዋታል።

ያችን ሕንፃ ሳይ በብዙ ነው የምተረጉማት

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Jan, 06:21


ጎፋ መካነ ሕያዋን ሥራ ላይ ናቸው።

የተልዕኮ ትምህርት በተጠናከረ መንገድ በሰንበት ትምህርት ቤት ደረጃ እየተሠራ ነው። በፎቶው የምትመለከቱት በአራቱ ሰንበት የሚማሩ ተማሪዎች ናቸው። ወጣቶችን ትምህርተ ወንጌል እያስታጠቁ ነው። ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ያስተማራቸውን የካቲት 2 2017 ዓ.ም የ3ተኛ ሰንበት ተማሪዎችን ያስመርቃል። በእነርሱ ምትክ ምዝገባ ተጀምሯል። ይመዝገቡ።

-ለመመዝገብ ሊንኩን ይከተሉ https://t.me/+voq-zJahBeVjM2Q0

-በተደራጀ መንገድ ተጨባጭ ሥራ የሚሠሩ፣ በእቅድ የሚመራ የተልዕኮ ትምህርት አገልግሎትን ይደግፉ።

-ቦታ ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Jan, 04:39


💞 መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ክፍል 2 💞

💞ምዕረፍ ፮፡-
-እግዚአብሔር ፈቃዱን የሚያደርጉ ነገሥታቱን እንደሚያነግሥ
-የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርጉ ነገሥታት በመንግሥተ ሰማያት እንደሚኖሩ
-ደጋግ ነገሥታት በዚህ ዓለም ሳሉ በጎ ሥራን እንደሚሠሩ መገለጹ
-ክፉ ነገሥታት የድኾችን ጩኸት ቸል እንደሚሉና የተገፋውን ሰው እንደማያድኑ

💞ምዕራፍ ፯፡-
-ንጉሥ እግዚአብሔር እንደሾመው በሚገባና በእውነት መፍረድ እንደሚገባው
-ንጉሥ የእግዚአብሔርን ቃል መስማትና ትእዛዙንም ማድረግ እንደሚገባው
-ምድራዊ መንግሥት ኃላፊ እንደሆነ መገለጡ

💞ምዕራፍ ፰፡-
-ትንሣኤ ሙታን በተክልና በአዝርዕት ፍሬ፣ በሰው መተኛትና መንቃት፣ በፀሐይ መግባትና መውጣት መመሰሉ
-በትንሣኤ ለሁሉም እንደሥራው እንደሚከፈለው ማሰብ እንደሚገባና መስነፍ እንደማይገባ
-የእግዚአብሔር የሕይወት ጠል ካልወረደ ሙታን እንደማይነሡ መገለጹ

💞ምዕራፍ ፱፡-
-በዕለተ ትንሣኤ ተራሮችና ኮረብቶች፣ ወንዞችና ጥልቆች እንደ ጥርጊያ ጎዳና እንደሚሆኑና ሥጋ ለባሽም ሁሉ ትንሣኤን እንደሚነሣ መገለጹ

💞ምዕራፍ ፲፡-
-እግዚአብሔር ሰውን ካለመኖር ወደ መኖር እንዳመጣው ሁሉ የሞተውን ሰውም እንደገና እንደሚያስነሣው መገለጡ

* 💞💞💞የዕለቱ ጥያቄዎች💞💞💞
፩. ስለደጋግ ነገሥታት ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. የድኻውን ጩኸት ቸል ይላሉ
ለ. የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይፈጽማሉ
ሐ. ከሞት በኋላ በመንግሥተ ሰማያት ይኖራሉ
መ. በዚህ ዓለም ሳሉ በጎ ሥራን ይሠራሉ
፪. ስለ ክፉ ነገሥታት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከሞት በኋላ ወደ ሲኦል ይወስዷቸዋል
ለ. በእውነትና በሚገባ አይፈርዱም
ሐ. የተራቡትን አይመግቡም የተጠሙትንም አያጠጡም
መ. ሁሉም
፫. በመጽሐፈ መቃብያን መሠረት ከሚከተሉት ውስጥ ለትንሣኤ ሙታን ምሳሌ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የፀሐይ መግባትና መውጣት
ለ. የአዝርዕትና የአትክልት ፍሬ መፍረስና መብቀል
ሐ. የሰው መተኛትና መንቃት
መ. ሁሉም
፬. ስለ መጨረሻው ትንሣኤ ሙታን ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. እንሳስትና አራዊት ከሙታን ይነሣሉ
ለ. አዕዋፋት ከሙታን መካከል ይነሣሉ
ሐ. ሰው የሆነ ሁሉ ከሙታን ይነሣል
መ. ከሰው መካከል ኃጥኣን ሞተው ይቀራሉ እንጂ በትንሣኤ ጊዜ አይነሡም

https://youtu.be/Zur_v_AqO3o?si=kRHN17IQxJfvcMRB

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

22 Jan, 19:40


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 112 💙💙

▶️፩. 1ኛ መቃ.1፥11 "ሰው ግብር እም ግብር እንጅ እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው እንዴ የተፈጠረው?

✔️መልስ፦ በዚህ ጥቅስ ሰው ካለመኖር ወደ መኖር እንደመጣ ይነግረናል እንጂ ግብር እምግብር ወይም እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ እንደሆነ አይገልጽም። ግእዙም ወገብሮ ወሣረሮ እምኀበ ኢሀልዎ ይላል። ግብር እምግብር የተፈጠሩትም እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ የተፈጠሩትም ቀድሞ አለመኖር ስለሚቀድማቸው ኢሀልዎ ይነገርላቸዋልና። ከተጠየቀ አይቀር ግን ሁለት ሐተታዎች ይታተታሉ። አንደኛው የሰውን ነፍሱን ሲመለከት እምኀበ አልቦ ሊል ይችላል። ሁለተኛው መገለጫውን ሲያይ እምኢሀልዎ ሊል ይችላል። ከዕለተ ዓርብ በፊት ሰው አሁን ያለውን ቁመና መስሎ አልተገለጠም ነበርና ነው። ሥጋውን ሲመለከት ደግሞ ቀድሞ ከተፈጠሩ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ስለመጣ ግብር እምግብር ይላል።

▶️፪. 1ኛ መቃ.5፥8 ሲዖል ከገቡ መውጣት የለባትም ሲል 1ኛ መቃ.7፥30 ግን እግዚአብሔር ከሲዖል የሚያወጣበት ሁኔታ እንዳለ ይናገራል አይጋጭም ወይ?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ከዚህ ሲኦል ያለው ገሃነምን ነው። ሲኦልን በኋላ ግብሩ ገሃነም ይለዋል። በኋላ ወደ ገሃነም የሚገቡት አስቀድሞ ሲኦል የነበሩት ናቸውና። ሲኦል ያለ ሰው እስከ ምጽአት ባለው ጊዜ በቅዱሳን ቃል ኪዳን በልዑል እግዚአብሔር ቸርነት ወደ ገነት የመመለስ እድል ሊኖረው ይችላል። ከዚህ ሲዖል ከገቡ መውጣት የለም ያላቸው ግን ይህ ለማይደርሳቸው ሰዎች ነው። በእርግጥ 1ኛ መቃ.7፥30 ላይ እግዚአብሔር ከሲዖል ስለሚያወጣበት ሁኔታ አይናገርም። ሁለቱም ችሎታውን የሚገልጹ መንታ ሐሳቦች ናቸው። ወደ ሲዖል አወርዳለሁ አንድ፣ ዳግመኛም ወደ ሰማይ አወጣለሁ ሁለት።

▶️፫. 1ኛ መቃ.5፥23 እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ከዓለት ውሃ እንጂ ማር አፍልቆላቸዋልን?

✔️መልስ፦ አዎ። ውሃንም አፍልቆላቸዋል ማርንም አፍልቆላቸዋል። ወሐፀኖሙ በመዓር እምኰኵሕ እንዲል። ዘዳ.32፥13 ላይም ተገልጿል።

▶️፬. "መልካቸው ፈጽሞ ያማረ ሁለቱም ሰዎች በፊታቸው ቁመው በታዩዋቸው ጊዜ እንደ መብረቅ የሚያስፈሩ የእሳት ሰይፎች ወርደው አንገታቸውን ቆርጠው በገደሏቸው ጊዜ ያን ጊዜ እንደ ቀደመው ደኅነኞች ሁነው ተነሡ" ይላል (1ኛ መቃ.2፥27)፡፡ መች አግኝተዋቸው ነው የገደሏቸው አልገባኝም ቢያስረዱኝ።

✔️መልስ፦ ዝርዝር ጉዳዩን መጽሐፍ ቅዱሱም አልገለጸውም። ነገር ግን ሦስቱ የመቃቢስ ልጆች አብያ፣ ሲላ እና ፈንቶስ ትንሣኤ እንዳለ ተረድተው ሰማዕት እንዲሆኑ ሁለት ሰዎች ወዲያው ሞተው ሲነሡ አይተዋቸዋል። ስለሞቱትና ወዲያው ስለተነሡት ሰዎች ግን ተጨማሪ ጉዳይ አልተገለጸም። ሁለቱን የገደሏቸውም ከሰማይ የወርዱ የእሳት ሰይፎች ናቸው እንጂ ሰዎች አይደሉም።

▶️፭. መጽሐፈ መቃብያን በአማርኛውና በግሪኩ መካከል ያለውን ልዩነት ቢያስረዱን በተጨማሪም ቀደምት የቤተክርስቲያን አባቶች ከእርሱ ጠቅሰው አስተምረው ይሆን?

✔️መልስ፦ የግሪኩን መጽሐፍ ቅዱስ አላነበብኩትም። ሲጀምር ግሪክኛ ቋንቋም ጭራሽ አላውቅም። ስለዚህ ንጽጽር ሠርቼ ይህ ልክ ነው ይህ አይደለም ለማለት የሚያበቃ ዕውቀት የለኝም። ነገር ግን ግእዙና አማርኛው ስመለከተው የተቀራረበ ነው። ስለዚህ የያዝኩትን ትክክል ነው ብየ አምኜ አስተምረዋለሁ። የሚቃረነውን ጉዳይ ለይታችሁ ብታመጡትና ብናየው እላለሁ። ከመጽሐፈ መቃቢስ ጠቅሰው እነማን አስተማሩ የሚለውም ሰፊ ጥናት የሚጠይቅ ስለሆነ በአጭር ጊዜ እነእገሌ ብየ ለመጥቀስ እቸገራለሁ።

▶️፮. 1ኛ መቃ.4፥13 ሰው በሕይወት ሳለ (አሁን የለበሰውን ሥጋ ይዞ) በኃጢአቱ ምክንያት ሲዖል ሊወርድ ይችላልን?

✔️መልስ፦ መቃብርንም ሲዖል ስለሚለው ነው እንጂ ሲዖል መካነ ነፍስ ስለሆነ በሲዖል የሚኖሩት ኃጥኣን ነፍሳት ናቸው። ስለዚህ በሕይወት ሳለሁ ወደ ሲኦል አታውርዱኝ ማለት ወደ መቃብር አታውርዱኝ ማለት ነው።

▶️፯. ፩ኛ መቃ.፩፥፲፫ "ልቡናቸውም እንደ አመድ የሆነ የአዳም ልጆች በሚታመኑባቸው በጣዖቶቹ ይፈረድባቸዋል" ሲል ልቡናቸው እንደ አመድ የሆነ ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ አመድ ነፋስ የሚበትነው ባለበት የማይጸና ቀላል እንደሆነ ሁሉ ልቡናቸው በአንድ በእግዚአብሔር በማመን ጸንቶ መኖር ሲገባው ወደ ጣዖታት የሚበተን ማለት ጣዖታትን ለማምለክ የሚያዘነብል ሆነ ለማለት ነው።

▶️፰. ፩ኛ መቃ.፪፥፲፱ "የሰውን ሥጋ የሚበላ ነው" ይላል። (literally) የሰው ሥጋ ይበላ ነበር ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የግእዙም የአማርኛውም መጽሐፍ ቅዱስ ቃል በቃል ነው ያስቀመጡት። ስለዚህ ጺሩጻይዳን ይህንን ያደርግ ነበር ማለት ነው።

▶️፱. ፩ኛ መቃ.፫፥፴፰ "ደስታ ወደሚገኝበት ወደ ገነት ወሰዷቸው" ይላል። ገነት ዝግ ሆና ሳለ ወደ ገነት ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ምንም እንኳ ጻድቃን በብሉይ ኪዳን በሲዖል ይኖሩ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በረድኤተ እግዚአብሔር ተጠልለው የሲኦል እሳት አያገኛቸውም ነበር። ጻድቃንሰ ውስተ እደ እግዚአብሔር ወኢለከፈቶሙ እሳተ ገሃነም እንዲል መጽሐፈ ጥበብ። ይህንን ገነት ብሎት ነው። ከሌሎች ኃጥኣን ነፍሳት በተሻለ ምቾት መኖራቸውን ለመግለጽ እንዲህ አለ። ገነት ማለት ምቹ ቦታ ተብሎም ይተረጎማልና።

▶️፲. "የሲላና የአብያ የፈንቶስ ሁለቱ ወንድሞቻቸው መጥተው ካሠሯቸው እሥራት ፈትተው እነዚህ ተጠራጣሪና ወንጀለኞች እንዳያገኙን ኑ እንሽሽ አሏቸው" ይላል። የመቃቢስ አምስት ልጆች ነበሩት? የሁለቱ ወንድሞቻቸው ስማቸው ማን እና ማን ነው?

✔️መልስ፦ አዎ ለመቃቢስ አምስት ልጆች እንደነበሩት ተጽፏል። የሁለቱን ወንድሞቻቸውን ስሞቻቸውን ግን መጽሐፍ ቅዱስ ስላልጻፋቸው አለማወቅ ይከለክለናል።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

22 Jan, 03:44


✝️ መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ክፍል 1 ✝️
✝️ምዕራፍ ፩፡-
-ጺሩጻይዳን ክፋትን የሚወድ፣ በፈረሶቹ ብዛትና ከሥልጣኑ በታች ባሉ በጭፍራዎች ይመካ እንደነበረና የሚያመልካቸው ብዙ ጣዖታት እንደነበሩት
-ጺሩጻይዳን በልቡናው ድንቁርና ጣዖታት ኃይልንና ብርታትን የሚሰጡት ይመስለው እንደነበር መገለጹ
-ጣዖታቱን የሚያገለግሉ ካህናት መሥዋዕቱን እነርሱ እየበሉ ጣዖቶቹ የሚበሉ አስመስለው ይነግሩት እንደነበር መገለጹ
-ጺሩጻይዳን ጣዖታቱ የፈጠሩት፣ ጣዖታቱም የሚመግቡትና የሚያነግሡት ይመስለው እንደ ነበር መገለጹ
-ጣዖታትን ሙታን ሊሏቸው እንደሚገባ መገለጹ
-ጺሩጻይዳን ትዕቢተኛ እንደነበር፣ በወንዶች አምሳል የተሠሩ ሃምሳ እና በሴቶች አምሳል የተሠሩ ሃያ ጣዖቶች እንደነበሩት መገለጹ
-ጺሩጻይዳን ጣዖታቱን የማያመልኩ ሰዎች እንዲቀጡ አዋጅ ማወጁ

✝️ምዕራፍ ፪፡-
-መቃቢስ ከነገደ ብንያም የተወለደ እንደሆነና መልከ መልካም ልጆች እንደነበሩት መገለጹ
-የመቃቢስ ልጆች እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ስለነበሩ ለጺሩጻይዳን ጣዖታት አንሰግድም ማለታቸው

✝️ምዕራፍ ፫፡-
-እግዚአብሔር የመቃቢስን ልጆች ሰማዕትነትን እንዲቀበሉ መንገሩ
-ከመቃቢስ ልጆች ሦስቱ አብያ፣ ሲላ፣ ፈንቶስ እንደሚባሉ መነገሩ
-የመቃቢስ ልጆች ጣዖታትን አናመልክም በማለታቸው በጺሩጻይዳን የተለያዩ መከራዎች እንደደረሱባቸው
-የመቃቢስ ልጆች መከራችን ሲበዛ ዋጋችን ይበዛል ማለታቸው

✝️ምዕራፍ ፬፡-
-ጺሩጻይዳን የመቃቢስን ልጆች በድን እንዲቃጠል ማዘዙ
-እሳት የመቃቢስን ልጆች በድን ማቃጠል እንዳልቻለ ባሕርም ማስጠም እንዳልቻለ
-በጺሩጻይዳን ግዛት የሚኖሩ ሰዎች ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ይሠዉ እንደነበር መገለጹ

✝️ምዕራፍ ፭፡-
-ጺሩጻይዳን በወባ ትንኝ አማካኝነት እንደሞተ
-እግዚአብሔር በተለያዩ ዘመናት ያደረጋቸው መልካም ነገሮች በጥቂቱ መጠቀሳቸው

✝️✝️✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️✝️✝️
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ስለጺሩጻይዳን ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በፈረሶቹ ብዛትና በጭፍራዎቹ ጽናት ይመካ ነበር
ለ. በመዓልትና በሌሊት መሥዋዕት የሚሠዋላቸው ብዙ ጣዖታት ነበሩት
ሐ. ጣዖታቱ ኃይልንና ብርታትን የሚሰጡት ይመስለው ነበር
መ. ሁሉም
፪. ስለጺሩጻይዳን የጣዖታት ካህናት ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. መሥዋዕቱን ራሳቸው እየበሉ ጣዖታቱ እንደሚበሉ እየተናገሩ ይዋሹ ነበር
ለ. ሌሎች ሰዎችም ለጣዖታቱ መሥዋዕትን እንዲሠዉ ያበረታቱ ነበር
ሐ. ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በትክክለኛው አምላክ ያምኑ ነበር
መ. ሀ እና ለ
፫. ስለመቃቢስ ልጆች ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. መልከ መልካሞችና እጅግ ብርቱዎች እንዲሁም ደጋጎች ነበሩ
ለ. እግዚአብሔርን ያመልኩ ስለነበር ሞትን አይፈሩትም ነበር
ሐ. ለጺሩጻዳይን ጣዖታት አንሰግድም ብለው ሰማዕትነትን ተቀብለዋል
መ. ሁሉም
፬. ስለመቃቢስ ልጆች በድን ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ጺሩጻይዳን በድናቸውን በእሳት ሲያቃጥለው ወደ አመድነት ተለውጠዋል
ለ. በድናቸውን ወደ ባሕር ሲጥለው ሰጥሞ ቀርቷል
ሐ. በድናቸውን ባሕር ማስጠም አልቻለችም እሳትም ማቃጠል አልቻለችም
መ. ሀ እና ለ
፭. ጺሩጻይዳን የሞተው በምንድን ነው?
ሀ. ጦር ሜዳ ሄዶ በጦር ተወግቶ
ለ. የወባ ትንኝ ነክሳው በወባ ትንኝ ምክንያት
ሐ. ጠላቶቹ መርዝ አጠጥተው ወደ ገደል ጥለውት
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/oUeOYog2AQ4?si=MO8ZBPuxhSxLWFCf

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Jan, 05:35


💓መጽሐፈ አስቴር ክፍል 1💓

💓ምዕራፍ ፩፦ መርዶክዮስ በንጉሡ በአርጤክስስ አደባባይ ያገለግል እንደነበረ
-መርዶክዮስ ሕልም እንዳየ
-መርዶክዮስ የንጉሡን ሕይወት እንዳዳነ
-ሐማ የንጉሡ የአርጤክስስ ባለሟል እንደነበረ
-ንጉሡ አርጤክስስ ግብዣ እንዳደረገና ንግሥት አስጢን በግብዣው እንዲልተገኘች በዚህም ምክንያት እንደተገደለች

💓ምዕራፍ ፪፦ አስቴር ከብዙዎች ሴቶች ተመርጣ ንግሥት እንደሆነች
-አስቴር የመርዶክዮስ የአጎቱ ልጅ እንደነበረች

💓ምዕራፍ ፫፦ መርዶክዮስ ለሐማ አይሰግድ እንደነበረ
-ሐማ አይሁድን ለማጥፋት እንዳስፈቀደ
-ሐማ መርዶክዮስ ስላልሰገደለት መቆጣቱ

💓ምዕራፍ ፬፦ መርዶክዮስ የአይሁድን የጥፋት አዋጅ ሰምቶ እንዳዘነ
-መርዶክዮስ አስቴርን ንጉሡን ለምነሽ አድኚን እንዳላትና እንደጸለየ

💓ምዕራፍ ፭፦ አስቴር ንጉሥ አርጤክስስን እና ሐማን ግብዣ እንደጠራች

💛የዕለቱ ጥያቄዎች💛
፩. አርጤክስስ በስንት ሀገሮች ላይ ነበር ነግሦ የነበረው?
ሀ. በ27
ለ. በ127
ሐ. በ17
መ. በ157
፪. መርዶክዮስ ለሐማ ያልሰገደበት ምክንያት ምንድን ነበር?
ሀ. መርዶክዮስ ሐማን ይንቀው ስለነበረ
ለ. መርዶክዮስ ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ስለነበረ
ሐ. ከእግዚአብሔር በቀር ለማንም አልሰግድም ብሎ
መ. ሀ እና ለ
፫. ከንጉሡ ከአርጤክስስ ግብዣ ባለመገኘቷ ምክንያት የተገደለችው የንጉሡ የአርጤክስስ ሚስት ማን ነበረች?
ሀ. አስጢን
ለ. አስቴር
ሐ. ዮዲት
መ. ሣራ

https://youtu.be/AIK4obEy3vg?si=1MCGqlnYXELg6zs8

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Jan, 17:51


ከስምዐ ጽድቅ ሚዲያ ጋር የነበረን ቆይታ እነሆ።

ስምዐ ጽድቅ ሚዲያን ሰብስክራይብ ያድርጉ።

https://youtu.be/7djGRvBNmZk?si=fYIn2C9wUyf6zFPQ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Jan, 15:39


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 109 💙💙

▶️፩. ቢትወደድ የሚለው ቃል ፍች ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ቢትወደድ ማለት በንጉሡ ከሁሉ በላይ የሚወደድ ባለሥልጣን ማለት ነው።

▶️፪. ዮዲ.፲፪፥፰ ላይ "ሌሊትም ወጥታ በምንጩ ውሃ ትጠመቅ ነበር" ይላል የምን ጥምቀት ነው?

✔️መልስ፦ ለምን ትጠመቅ እንደነበረ ምክንያቱን መጽሐፍ ቅዱሱ አይገልጽም። የልጅነት ጥምቀት እንዳልሆነ ግን ይታወቃል። የልጅነት ጥምቀት የተሰጠው ከጌታ ልደት በኋላ ነውና።

▶️፫. የብሉይ ኪዳን ሰዎች ግድያን እንደጽድቅ መውሰዳችን ራሳችን በመረዳት ወይስ እግዚአብሔር ጽድቅ ነው ብሎ ነው?

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን በግፍ መግደል ኃጢአት ነበር። ነገር ግን በግፍ የገደለ ሰውን መግደል ፍትሓዊ ስለነበረ እንደጽድቅ ይቆጠር ነበር።

▶️፬. ዮዲ.፲፩፥፲፱ ላይ "በመካከሏም ዙፋንህን ትዘረጋለህ እረኛቸውም እንደበተናቸው በጎች ፈጽመህ ትከብባቸዋለህ ውሻም አይጮህብህም" የሚለው ሽንገላ አይሆንም?

✔️መልስ፦ ጠላትን ለማጥፋት እና ከጠላት ለመዳን መስሎ መቅረብ ሽንገላ አይሆንም። ዮዲት የእስራኤልን ጠላት ሆሎፎርኒስን ለማጥፋት ሰላማዊ መስላ ቀርባ ገድለዋለች። ዳዊት ከንጉሥ አንኩስ ለመዳን እብድ መስሎ ታይቷል። ንጹሓንን ለማጥፋት ንጹሕ መስሎ መቅረብ ነው ሽንገላ።

▶️፭. ጾመ ድኅነት እና ጾመ ዮዲት የዕለት ግንኙነት አለው?

✔️መልስ፦ ጾመ ድኅነት በሐዲስ ኪዳን የመጣ ጾም ነው። ይኸውም ረቡዕ እና ዓርብን መጾም ነው። ጾመ ዮዲት በብሉይ ኪዳን የነበረና ዮዲት የጾመችው ጾም ነው። ስለዚህ በዘመን አይገናኙም።

▶️፮. ዮዲ.16፥20-21 ከፍርድ ቀን በኋላ የሥጋ ቅጣት አለ እንዴ?

✔️መልስ፦ በትንሣኤ ጊዜ ነፍስ ከሥጋ ጋር ተዋሕዳ ትነሣለች እንጂ ሥጋ ፈርሶና በስብሶ አይቀርም። ስለዚህ ገሃነም የገባ ሰው መከራ የሚደርስበት ከነሥጋው ስለሆነ ወይፌኑ እሳተ ወዕፄ ዲበ ሥጋሆሙ ተብሏል።

▶️፯. "ባግዋም እያለቀሰና እየቃሰተ በታላቅ ቃል ፈጽሞ ጮኽ ልብሱንም ቀደደ" ይላል። አሕዛብም ሲያዝኑ ልብስ መቅደድ ለአሕዛብ ልምዳቸው ነበር ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ። በብዙዎች ሀገሮች ልብስን መቅደድ ትእምርተ ኀዘን (የኀዘን ምልክት) ነው። ስለዚህ ከአሕዛብ ወገን የነበረው ባግዋ ልብሱን ቀድዷል።


© በትረ ማርያም አበባው

✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Jan, 05:03


💞መጽሐፈ ዮዲት ክፍል 3💞

💞ምዕራፍ ፲፩፦ ዮዲት እስራኤላውያን ፈጣሪያቸውን ካልበደሉ ሰይፍ ሊያጠፋቸው እንደማይችል መናገሯ
-የዮዲት ቃል ሆሎፎርኒስን ደስ እንዳሰኘውና ከሠራዊቱ ጋር በጥበቧ እንደተደነቀ

💞ምዕራፍ ፲፪፦ ዮዲት በሆሎፎርኒስ ግብዣ ራሷ ካመጣችው ምግብ እንደተመገበች
-ዮዲት መንገዷን ያቃናላት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ትጸልይ እንደነበር

💞ምዕራፍ ፲፫፦ ዮዲት የሆሎፎርኒስን አንገት እንደቆረጠች

💞ምዕራፍ ፲፬፦ እስራኤላውያን የሆሎፎርኒስን ቸብቸቦ ይዘው ጠላቶቻቸውን እንደገጠሙ

💞ምዕራፍ ፲፭፦ አሦራውያን ደንግጠው እንደሸሹ
-እስራኤላውያን ዮዲትን እንደመረቋት

💞ምዕራፍ ፲፮፦ የዮዲት የምስጋና መዝሙር መገለጹ
-ዮዲት በእስራኤል ዘንድ ስለሚጨነቁት ሰዎች ስትል የመበለትነት ልብሷን እንደተወች፣ ሽቱ እንደተቀባች

💛የዕለቱ ጥያቄዎች💛
፩. ሆሎፎርኒስን የገደለ ማን ነው?
ሀ. ባግዋ
ለ. ዮዲት
ሐ. ዖዝያን
መ. ምናሴ
፪. ዮዲት ሆሎፎርኒስን ከገደለች በኋላ እስራኤላውያን ጦርነቱን አሸንፈዋል። ጦርነቱን ካሸነፉ በኋላ ስለሆነው ነገር ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ዮዲት ዘንባባ በእጇ ያዘች
ለ. እስራኤላውያን ለዮዲት የወይራ ጉንጉን አደረጉላት
ሐ. ዮዲት የሴቶች መሪ ሆና ዘመረች
መ. ሁሉም

https://youtu.be/tvYRPT7Z4DM?si=94Pr_ifqycZpQO68

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Jan, 19:03


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 108 💙💙

▶️፩. ዮዲ.9፥8 ቤተ መቅደሱ ከተሠራ በኋላ ደብተራ ኦሪት አገልግሎት ትሰጥ ነበር እንዴ?

✔️መልስ፦ አትሰጥም ነበር። ቤተ መቅደስ ቢሠራም የቀድሞዋ ደብተራ ኦሪት በክብር ተቀምጣ ትኖር ስለነበረ ነው እንጂ ከቤተ መቅደስ መሠራት በኋላ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ቤተ መቅደስ እንጂ ደብተራ ኦሪት አልነበረችም።

▶️፪. ዮዲ.8፥6 በበዓላት፣ በሰንበት፣ በመባቻ፣ በሰንበት ዋዜማ እና በመባቻ ዋዜማ መጾም በብሉይ ኪዳን የተከለከለ ነበር እንዴ?

✔️መልስ፦ ዋዜማ የሚለው ከሠርክ ጀምሮ ያለውን ጊዜ ነው። ይኸውም ለምሳሌ ዓርብ ከ12 ሰዓት በኋላ ወደ ቅዳሜ ስለሚቆጠር በዓል ነበር። የሰንበት ዋዜማ ያለው ይህንን ነው። የመባቻ ዋዜማ ያለውም ይህንኑ ነው። በሐዲስ ኪዳን ከቀዳም ሥዑር ውጭ ቅዳሜና እሑድ መጾም እንደማይገባ ሁሉ በብሉይ ኪዳንም በበዓላት መጾም አይገባም ነበር። በተለየ በጾም ይከበር የነበረው በዓል በጥቅምት ይከበር የነበረው ዮሴፍ የተሸጠበት መታሰቢያ በዓል ነበር።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Jan, 08:43


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 107 💙💙

▶️፩. የጨረቃ አቆጣጠር ምን ዓይነት ነው? ከእኛ አቆጣጠር ይለያል?

✔️መልስ፦ በጨረቃ አቆጣጠር አንድ ዓመት 354 ቀን ነው። በሀገራችን የተለመደው አቆጣጠር በፀሐይ አቆጣጠር ነው። ይሁን እንጂ በዓላትን ስናወጣና ስናሰርቅ (ዘመኑን አስበን እግዚአብሔርን ስናመሰግን) ሠርቀ ወርኅን እያወጣን ጭምር ነው። አሁን በፀሐይ አቆጣጠር ዓለም ከተፈጠረ 7517 ዓመት ነው። ይህንን በጨረቃ ለማወቅ ከፈለግን ደግሞ በ11 አባዝተን በ354 አካፍለን እናገኘዋለን። በ11 ያባዛንበት ምክንያትም ጨረቃ ከፀሐይ በዓመት 11 ቀን አንሳ ስለምታበራ ነው። 11×7517፥354= 233.58 ይሆናል። በተጨማሪም ሌላ ትርፍ ቀን በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ስለምትመጣ 0.25×7517= 1879.52 ይሆናል። በየስድስት መቶ ዓመት ደግሞ አንድ ቀን ትተርፋለች። ስለዚህ 7517፥600= 12.53 ይሆናል። 1879.52+12.53= 1892.05 ይሆናል። ይህንን በጨረቃ ዓመት ለመቀየር በ354 ስናካፍለው 5.34 ይሆናል። ከላይ ካለው 233.58 ጋር ሲደመር 238.92 ይሆናል። ይህንን ብናጠጋጋው 239 ይሆናል። ይህንን ከ7517 ጋር ስንደምረው 7756 ዓመት አካባቢ ይሆናል።

▶️፪. "የጉበኛ ቤቱን አቆመ" ይላል (ዮዲ.1፥3)። የጉበኛ ቤት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ጉበኛ ማለት ሰላይ ማለት ነው። ስለዚህ የጉበኛ ቤት አቆመ ማለት የሰላይ ቤት ሠራ ማለት ነው።

▶️፫. የመጽሐፉ ስያሜ ለምን መጽሐፈ ዮዲት ተባለ?

✔️መልስ፦ ዮዲት ለእስራኤላውያን ያደረገችላቸውን በጎ ነገር ስለሚናገርና ስለእርሷ የቅድስና ታሪክም የሚገልጽ ስለሆነ የመጽሐፉ ስም በስሟ ተሰይሟል።

▶️፬. ዮዲ.1፥7 ላይ "የፋርስ ንጉሥ ናቡከደነፆር" ይላል። ናቡከደነፆር የፋርስ ወይስ የባቢሎን ንጉሥ?

✔️መልስ፦ ፋርስንም ባቢሎንም ደርቦ ይገዛ ስለነበር ናቡከደነፆር የሁለቱም ንጉሥ ነበር።

▶️፭. "የኔን የባሪያህን ቃል ከሰማህ እግዚአብሔር ላንተ ፍጹም ሥራ ይሠራልሃል። ለዓለም ሁሉ የነገሠ ናቡከደነፆር በሕይወት ይኖራልና ሰውን ሁሉ ታድን ዘንድ የላከህ አንተም ቢትወደዱ በሕይወት ትኖራለህና" ይላል። እግዚአብሔር ብላ እየጠራችው ያለው ማንን ነው?

✔️መልስ፦ ዮዲት ለሆሎፎርኒስ ስትነግረው ምንም እንኳ ሆሎፎሮኒስ ጣዖት አምላኪ ቢሆንም እግዚአብሔር ያለችው ግን ሰማይንና ምድርን የፈጠረውን ራሱን እግዚአብሔርን ነው እንጂ ሌላ አይደለም።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Jan, 05:44


እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ

መልካም በዓል

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Jan, 03:55


✝️መጽሐፈ ዮዲት ክፍል 2✝️

✝️ምዕራፍ ፮፦ ሆሎፎርኒስ አክዮርን ለእስራኤላውያን ተላልፎ እንዲሰጥ ማድረጉ

✝️ምዕራፍ ፯፦ ሆሎፎርኒስ የእስራኤላውያንን የውሃ ምንጭ እንደያዘ
-እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር እንደጮሁ

✝️ምዕራፍ ፰፦ ዮዲት ደግ ሴት እንደነበረች

✝️ምዕራፍ ፱፦ ዮዲት እንደጸለየች

✝️ምዕራፍ ፲፦ ዮዲት አጊጣ፣ ጥሩ ልብስ ለብሳ ወደ ሆሎፎርኒስ እንደሄደች

💛የዕለቱ ጥያቄዎች💛
፩. የናቡከደነፆር ሠራዊት ናቡከደነፆርን ምን ይሉት ነበር?
ሀ. የዓለሙ ሁሉ ጌታ
ለ. እግዚአብሔር
ሐ. አምላክ
መ. ሁሉም
፪. ስለዮዲት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በበዓላትና ካልሆነ በስተቀር አትበላም ነበር
ለ. መልከ መልካምና እጅግ ደመ ግቡ ነበረች
ሐ. እግዚአብሔርን ፈጽማ ትፈራ ነበር
መ. ሁሉም

https://youtu.be/QcBGfs-MFrI?si=_S68Ip0K4IT2C4Q-

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Jan, 18:36


በአጭር ጊዜ ብዙ ነገሮችን የተረዳሁበት ቀን
with መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ።

በመጽሐፈ ሄኖክና በአክሲማሮስ በስፋት ስለሚነገሩት ጨረቃ፣ ከዋክብት በTelescope እና በሌሎችም መሣሪያዎች እገዛ በጥቂቱም ቢሆን ለመረዳት ሞክሬያለሁ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Jan, 04:47


💜መጽሐፈ ዮዲት ክፍል 1💜

💜ምዕራፍ ፩፦ ናቡከደነፆርና ንጉሠ ሜዶን አርፋክስድ ጦርነት እንደገጠሙ
-ንጉሥ አርፋክስድ እንደተሸነፈ

💜ምዕራፍ ፪፦ ናቡከደነፆር ትእዛዙን ያልተቀበሉትን በጦርነት ማጥፋቱ

💜ምዕራፍ ፫፦ አንዳንድ ሀገሮች ለአንተ እንገዛለን ብለው የሰላም መልእክተኞችን ወደ ናቡከደነፆር መላካቸው
-ሆሎፎርኒስ አሕዛብን ሁሉ እንዳጠፋ

💜ምዕራፍ ፬፦ እስራኤላውያን ሆሎፎርኒስ በአሕዛብ ላይ ያደረገውን ሰምተው እንደፈሩ መገለጹ
-የእስራኤል ልጆች ሊቀ ካህናቱና የሕዝብ አለቆች ያዘዟቸውን እንዳደረጉ

💜ምዕራፍ ፭፦ እስራኤል በጽድቅ መንገድ ካሉ ሆሎፎርኒስ በጦርነት እንደማያሸንፋቸው የአሞን ልጆች ሹም እንደነገረው

💛የዕለቱ ጥያቄዎች💛
፩. የናቡከደነፆር ከእርሱ በታች ያለ ቢትወደዱ ማን ይባል ነበር?
ሀ. ሆሎፎርኒስ
ለ. አስራዶን
ሐ. አርፋክስድ
መ. ሰናክሬም
፪. ሆሎፎርኒስ እስራኤልን ለመዋጋት ወደ እስራኤል በሄደ ጊዜ የእስራኤል የካህናት አለቃ ማን ይባል ነበር?
ሀ. ፊንሐስ
ለ. ኢዮአቄም
ሐ. አልዓዛር
መ. አሮን
፫. ሆሎፎርኒስ እስራኤልን ለማጥፋት ሲመጣ የእስራኤል ካህናት ምን አደረጉ?
ሀ. በወገባቸው ማቅ ታጠቁ
ለ. መሥዋዕት አቀረቡ
ሐ. ወደ እግዚአብሔር ጮኹ
መ. ሁሉም
፬. እስራኤላውያን በጽድቅ መንገድ ካሉ ሆሎፎርኒስ ጦርነቱን እንደማያሸንፍ የነገረው የአሞን ልጆች ሹም ማን ነበር?
ሀ. አክዮር
ለ. አስራዶን
ሐ. አሕሻዊሮስ
መ. ሴኬም

https://youtu.be/bAw_F-VB7T8?si=SS2SIRPDhTWObTZ3

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

16 Jan, 16:55


አዲስ መጽሐፍ
#መስተዋድድ
በመ/ር ያሬድ ዘርአብሩክ
0941555550

እናመሰግናለን Yared Zera-buruk

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

16 Jan, 14:49


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 106 💙💙

▶️፩. ጦቢ.12፥18 ለመላእክት ምስጋና አይገባምን?

✔️መልስ፦ ለቅዱሳን መላእክት ምስጋና ይገባል። ለእነርሱ የሚገባው ምስጋና ግን የጸጋ ምስጋና ነው እንጂ የባሕርይ ምስጋና አይደለም። የባሕርይ ምስጋና የሚገባው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። በባሕርይው ምስጉን እግዚአብሔር ብቻ ነውና።

▶️፪. ጦቢ.13፥16 መጽሐፈ ጦቢት የተጻፈው ከኢየሩሳሌም መታደስ በፊት ነው ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ። ገና እስራኤላውያን በምርኮ ሳሉ የተጻፈ መጽሐፍ ነው።

▶️፫. "ከነነዌ ውጣ ነቢዩ የተናገረው ነገር በግድ ይደረጋልና" ይላል (ጦቢ.14፥8)። ነነዌ የጠፋችው ከኢየሩሳሌም ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ነው? ናቡከደነፆር የነነዌን ጥፋት ሰምቶ ደስ ያለው በምን ምክንያት ነው?

✔️መልስ፦ ነነዌ በናቡከደነፆር ዘመነ መንግሥት እንደጠፋች ተገልጿል። ናቡከደነፆር የነነዌ ሰዎችን ይጠላ ስለነበር ነነዌ ስትጠፋ ተደስቷል።

▶️፬. መጽሐፈ ጦቢት ከ፷፮ቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የለም። ለመሆኑ ይህን ሌሎች ፲፭ቱን ትተን ፷፮ ብቻ ማንበብ ተገቢ ነውን? ወይም ሁለቱንም መያዝና ማንበብ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ይፈቀዳል? ወይስ የተፈቀደልን ፹ አሐዱን ብቻ ነውን? ይህንን በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ቢያብራሩልን።

✔️መልስ፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና 81 ነው። ይኸውም በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 2 በእንተ መጻሕፍት አምላካውያት ተብሎ ተገልጿል። ስለዚህ 81ዱንም መቀበልና ማንበብ ተገቢ ነው። በሁሉም የእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ እንዲሁም መግቦቱ ተገልጿልና።

▶️፭. ጦቢ.፲፬፥፬ ልጄ ወደ ሜዶን ሂድ ትጠፋ ዘንድ እንዳላት እያለ የተናገረውን ለልጁ ነገረው። ጦቢትና የዮናስ በአንድ ዘመን የነበሩ ናቸውን?
ቀጥሎ ጦቢ.፲፬፥፲፭ አባቱም እንደ ነገረው ሳይሞት የነነዌን ጥፋት ሰማ ሲል ምን ማለት ነው? የተማርነው ንስሓ እንደገቡና ከጥፋት እንደዳነች ነውና ግልፅ ቢያደርጉልን።

✔️መልስ፦ አዎ ጦቢትም ዮናስም በአንድ ዘመን በእስራኤል የምርኮ ዘመን የነበሩ ሰዎች ናቸው። የነነዌ ሰዎች ንስሓ በመግባታቸው ለጊዜው መከራው ርቆላቸው ነበር። በኋላ መልሰው ክፉ ሥራን በመሥራታቸው በሌላ ዘመን ጠፍተዋል።

▶️፮. ጦቢ.12፥19 "እኔ ግን ተገለጥሁላችሁ መልኬንም አያ ችሁ ከእናንተ ጋራ አልበላሁም አልጠጣሁም" ይላል። ጦቢ.6፥5 ላይ ደግሞ "ያም ልጅ መልአኩ እንዳዘዘው አደረገ ዓሣውንም ጠብሰው በሉ። ሁለቱ ሁሉ ገሥግሠው ሄደው ወደ በጣኔስ ደረሱ" ይላል። ሁለቱ አይጋጭም።

✔️መልስ፦ አይጋጭም። መልአኩ በላ መባሉ ምግብ ለባሕርይው የሚስማማው ሆኖ ወይም አስፈልጎት በላ ማለት አይደለም። ሥላሴ በአብርሃም ቤት በሉ እንደተባለው ያለ ነው። ይህም እሳት ቅቤ በላ እንደሚባለው ያለ ነው። በባሕርይው ምግብ ስለማይፈልግ አልበላሁም አልጠጣሁም አለ። በተገለጸበት አምሳል መብላቱን ሲያይ በላ አለ። እሳት ቅቤ በላ ሲባል መቼም ቅቤው ለእሳቱ ጥቅም ሰጠ ማለት አይደለም። ቅቤውን አቀለጠው አጠፋው ማለት ነው። ከዚህም መልአኩ በላ መባሉ የቀረበውን ምግብ የበላ መስሎ ቢታይም ለአካሉ ሳይዋሐደው አጠፋው ማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

16 Jan, 06:22


💙መጽሐፈ ጦቢት ክፍል 3💙

💙ምዕራፍ ፲፩፦ የጦቢት ዓይን በዓሣ ጉበት ምክንያት እንደዳነና ጦቢትም እግዚአብሔርን እንዳመሰገነ

💙ምዕራፍ ፲፪፦ እነ ጦቢት አዛርያ መልአኩ ሩፋኤል እንደሆነ መረዳታቸው
-መልአኩ እነጦቢትን እንደመከራቸው
-መልአኩ ሩፋኤል ጦቢት መልካም ባደረገ ጊዜ ሁሉ በረድኤት ከእርሱ ጋር እንደነበረ መገለጹ

💙ምዕራፍ ፲፫፦ ጦቢት እግዚአብሔርን እንዳመሰገነ

💙ምዕራፍ ፲፬፦ ጦቢት ፈሪሀ እግዚአብሔርን እንደጨመረ መገለጹ
-ነነዌ እንደምትጠፋ ዮናስ የተናገረው ትክክል ስለሆነ ወደ ሜዶን ሂድ ብሎ ጦቢት ጦብያን እንደመከረው


💛የዕለቱ ጥያቄዎች💛
፩. ጦቢት የልጁ የጦቢያን ሚስት ሣራን ባያት ጊዜ ምን አላት?
ሀ. እንኳን በደህና ገባሽ
ለ. ወደ እኛ ያመጣሽ እግዚአብሔር ይመስገን
ሐ. እግዚአብሔር አባትሽንና እናትሽን ይባርክ
መ. ሁሉም
፪. መልአኩ ሩፋኤል እነ ጦቢትን ምን አላቸው?
ሀ. እግዚአብሔርን አመስግኑ
ለ. መከራ እንዳታገኛችሁ በጎ ሥራን ሥሯት
ሐ. የእግዚአብሔርን ሥራ በክብር ተናገሩ
መ. ሁሉም
፫. ስለምጽዋት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ምጽዋት ከሞት ታድናለች
ለ. ምጽዋት ከኃጢአት ታነጻለች
ሐ. ምጽዋት ታጸድቃለች
መ. ሁሉም
፬. በነነዌ ጥፋት ደስ ያለው ማን ነው?
ሀ. ናቡከደነፆር
ለ. አሕሻዊሮስ
ሐ. ሀ እና ለ
መ. ሁሉም

https://youtu.be/dpWSeqy9ERY?si=2loOBoLNnb8Z6cjY

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Jan, 15:02


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 105 💙💙

▶️፩. ዓሣን መብላት በተመለከተ ዓሣ ከውሃ እንደወጣ እንደሚሞት እና ሳይባረክም ነፍሱ ብትወጣ መብላት ይቻላል? የሚያጠምደው ሰው ማንነትስ እንዳይበላ ያደርገዋል? ምሳሌ አጥማጁ አሕዛብ ቢሆን?

✔️መልስ፦ በዚህ ዙሪያ የተጻፈ አላገኘሁም። ነፍሱ ሳይወጣ የታረደውን ብቻ ብሉ ወይም አትብሉ የሚል አላገኘሁም። አጥማጁ አሕዛብ ይሁንም አይሁንም ግን የሚያመጣው ለውጥ የለም። ማንኛውም ቢያመጣው ባርከን አቡነ ዘበሰማያት ብለን ስንበላው ይቀደሳልና።

▶️፪. ቁጥር 14 ላይ "አሁንም እኔ ብቸኛ ልጃቸው ነኝ" ካለ በኋላ ቁጥር 16 ላይ "ሁለቱም ወጥተው ሄዱ ሌላው ልጃቸውም ተከተላቸው" ይላል (ጦቢ.5፥14-16)። ቢያስታርቁልኝ።

✔️መልስ፦ ሌላው ልጃቸውም ተከተላቸው የሚለው የትርጉም ስሕተት ነው። እንጂ ግእዙ "ወተለዎሙ ከልበ ወልዶሙ" ብሎ የተከተላቸው ውሻው ነው እንጂ ሌላ ልጅ ኖሮ ያ ልጅ አይደለም።

▶️፫. "መልአኩም ክፉ ጋኔን ያደረበት ቢኖር ወይም የረከሰ ረቂቅ ጋኔን ያደረበት ቢኖር ጉበቱንና ልቡን ለዚያ ሰው በፊቱ ያጤሱለታል። ሴትም ብትሆን ያጤሱላታል ከዚያ በኋላ አይታመምም" ይላል። ይህ የዓሣ ልብ እና ሐሞትን በመጽሐፉ ለተጠቀሰው አገልግሎት መጠቀም በሐዲስ ኪዳን አለ?

✔️መልስ፦ ለጊዜው ለሣራ ወለተ ራጉኤልና ለጦቢት ጥቅም ሰጥቷል። ለቀጣይ ግን የእነርሱን ችግር የመሰለ ችግር ለገጠመው ሁሉ መፍትሔው ይህ ይሆን አይሆን ግን የተገለጸ ነገር አላገኘሁም። የእነርሱ መፈወስ ተአምራዊም ጭምር ነበርና። ተአምር ደግሞ ሁል ጊዜ አይደረግም።

▶️፬. መጽሐፈ ጦቢት ላይ የተጠቀሰችው ነነዌ በኋላ ነቢዩ ዮናስ ሰብኳት በንስሓ የተረፈችው ከተማ ናት?

✔️መልስ፦ አወ ራሷ ናት። ከብዙ ዘመን በኋላ እንደገና በድላ ተቃጥላለች።

▶️፭. ጦቢ.11፥16 "ጦቢት ግን በፊታቸው እግዚአብሔርን አመሰገነ ፤ እግዚአብሔር ይቅር ብሎታልና" ይላል። ጦቢት እግዚአብሔርን አሳዝኖ ነበርን?

✔️መልስ፦ ጦቢት እግዚአብሔርን አላሳዘነውም። እግዚአብሔር ይቅር ብሎታል ማለት ከበሽታው አድኖታል ማለት ነው። እግዚአብሔር ይማርህ ስንል ከሕመምህ ያድንህ እንደምንለው ያለ ነው። ጦቢት ዓይኑ ላይ ብልዝ ወጥቶበት ስለነበር በኋላ በመዳኑ እግዚአብሔር አዳነው ለማለት ይቅር አለው ተብሏል።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Jan, 12:59


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 104 💙💙

▶️፩. ጦቢ.2፣1 "በሰባተኛው ሱባዔ በተቀደሰችው የበዓለ ኀምሳ ዕለት ለእኔ መልካም ነገር አደረጉልኝ እበላም ዘንድ ተቀመጥሁ" ይላል። በዚያ ዘመን በዓለ ኀምሳ የተባለው የምን በዓል ነው? አሁን ላይ የምናከብረው በዓለ ኀምሳ በዚያን ጊዜ ይከበር ነበር ማለት ነውን?

✔️መልስ፦ በዚያ ዘመን በዓለ ኃምሳ ይባል የነበረው በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ነበረ። ይህም የፋሲካውን በግ ካረዱ በኋላ ለ50 ቀን የሚያከብሩት በዓል ነበር።

▶️፪. ጦቢ.2፣4 የጦቢት ልጅ በገበያው ላይ የወደቀ ሬሳ እንዳለ ሲነግረው "እኔም እህል ሳልቀምስ ተነሣሁ ፀሐይም እሰኪገባ ድረስ ወደ አንዱ ቤት አገባሁት" ይላል። እዚህ ጋር ተያይዞ እኔ ባደኩበት ማኅበረሰብ ሰው ከሞተ አፈር ሳይቀምስ እህል አይበላም። ይህ ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር እንዴት ይታያል? የሞተው ሰው ሳይቀበር እህል የበላ ሰውስ ኃጢአት ይሆንበታልን?

✔️መልስ፦ በሀገራችን ያለው ይህ ትውፊት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ መሆኑን እንረዳለን። ይህ ትውፊት ነው። አንድ ሰው እህል ቀምሶ ቢያስቀብር በደል ይሆንበታል የሚል ግን አላገኘሁም።

▶️፫. ጦቢ.2፣9 "በዚያችም ሌሊት ከቀብር ተመለስኩ ረክሼም ሰለነበር በእድሞው ስር አደርሁ" ይላል። በብሉይ ኪዳን ሰው መቅበር ያረክስ ነበር ማለት ነውን?

✔️መልስ፦ አዎ በብሉይ ኪዳን ሬሳ መንካት ያረክስ ነበረ። ሰው የሞተ ሰውን ሲቀብር ደግሞ ሬሳውን መንካት ስለሚኖርበት ጦቢት ረክሼ ነበር ብሏል።

▶️፬. ጦቢት ምዕራፍ አራት ላይ ጦቢት መልአኩ ሩፋኤልን ከየት ወገን እንደሆነ እና ስሙን እንዲነገረው ሲጠይቀው የታላቁ የአናንያ ዘመድ አዛርያ ነኝ ያለዉ ለምንድን ነው? በመላእክት ዘንድስ ቃላቸው ይታበላልን? ለምን መልአክ ሆኖ ሳለ የሰው ልጅ ነኝ አለው?

✔️መልስ፦ መልአኩ በሰው አምሳል ሆኖ የሰው ልጅ ነኝ ያለው በአዛርያ አምሳል ስለተገለጸ የአናንያ ዘመድ አዛርያ ነኝ ብሏል። ስለዚህ በተገለጸበት ስለተናገረ ውሸት ነው አንለውም። የአናንያ ዘመድ ነኝ ማለቱ በረድኤት አናንያን ይረዳ ስለነበረ ነው።

▶️፭. ጦቢ.፩÷፳፩ "ሁለቱ ልጆቹ እስኪገድሉት ድረስ ሸሽተውም ወደ አራራት ተራራ እስኪሄዱ ድረስ 55 ቀን ከቤት አልወጣሁም" ይላል የአማርኛው። የግሪክ ሰባ ሊቃውንት ግን 50 ይላል። የትኛው ነው ትክክል?

✔️መልስ፦ የግእዙም ፶፭ ይላል። እንግዲህ ምናልባት የግሪኩ የተረፈ ትቶ በሚለው ባህለ መጻሕፍት ፶ አድርጎ ጽፎት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ 55 የሚለውን እንያዝ።

▶️፮. ጦቢ.፪÷፱ "ረክሸም ስለነበር በእድሞው ሥር አደርሁ" ይላል። እድሞ ምንድን ነው? ረክሼ ነበር ሲል የሰው ሬሳ ስለነካ ነውን? የሰው ሬሳስ በሐዲስ ኪዳን እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ እድሞ የሚባለው በድንጋይና በአፈር የተገነባ የቤተ ክርስቲያን ወይም የቤት አጥር ነው። ወይም ጣራው በአፈር የተሠራ ቤት ነው። በብሉይ ኪዳን የሰው ሬሳ የነካ እንደ ርኩስ ይታይ ነበር። በሐዲስ ኪዳን ግን የከበረ ስለሆነ ታጥቦና ፍትሐት ተደርጎለት ከሊቀ ካህናቱ ጀምሮ ሁሉም ይስሙታል።

▶️፯. ጦቢ.፭÷፲፮ "ሌላው ልጃቸውም ተከተላቸው" ይላል አማርኛው። ግሪክ ሰባ ሊቃውንት "የወጣቱ ሰው ውሻ ተከተላቸው" ይላል። የተከተላቸው ሰው ነው ወይስ ውሻ? ትክክለኛው ትርጉምስ አማርኛው ነው ወይስ የግሪኩ?

✔️መልስ፦ የአማርኛው የትርጉም ስሕተት ነው እንጂ ግእዙም የሚለው "ወተለዎሙ ከልበ ወልዶሙ" ነው። ይኸውም የወጣቱ ሰው ውሻ ተከተላቸው ከሚለው የግሪኩ ቅጂ ጋር አንድ ነው።

▶️፰. ጦቢ.1፥20 ላይ "ከሚስቴ ሐናና ከልጄ ጦብያ በቀር ያስቀሩልኝ የለም" ይልና ጦቢ.2፥1 ላይ ደግሞ ወደ ሀገሬም በተመለስኩ ጊዜ ሚስቴን ሐናንና ልጄን ጦብያን መለሰልኝ ይላል። እነዚህ አይጋጩም ወይ መጀመሪያ አሰቀረ ይልና ተመልሶ ደግሞ መለሰኝ ይላል ይህ እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ግእዙ ወደ አማርኛ ሲተረጎም በትክክል ስላልተተረጎመ ነው እንጂ ግእዙ "ወአልቦ ዘአትረፉ ሊተ ዘእንበለ ሐና ብእሲትየ ወጦብያ ወልድየ" ይላል። እንበለ ደግሞ "ሳይቀር" ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ ልጄና ሚስቴ ሳይቀሩ ሁሉንም ወሰዱብኝ ማለት ነው። በኋላ መለሱልኝ ያለም ለዚህ ነው።

▶️፱. ጦቢ.1፥21 "የሸሹት ተራራ አራራት ተራራ" ይላል። ይህ ተራራ የኖኅ መርከብ ያረፈበት ተራራ ነው?

✔️መልስ፦ መጽሐፍ ቅዱሱ በዚህ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ስላልገለጸልን ነውም አይደለምም ማለት አይቻልም።

▶️፲. ጦቢ.5፥4 "እርሱም ሰውን ሊፈልግ ሄዶ መልአኩን ሩፋኤልን አገኘው። ነገር ግን መልአክ እንደ ሆነ አላወቀም" ይላል። ወረድ ብሎ ከአባቱ ጋር እጅ ተነሳሱ ይላል። መላእክት ግን የሚዳሰስ አካል የላቸውም። በሰው አምሳል ሲገለጹ የራሳቸው የሆነ የሚዳሰስ አካል አላቸው? ቢያብራሩልን መምህር።

✔️መልስ፦ በእርግጥ እጅ ተነሣሡ ማለት ሰላም ተባባሉ ማለት ነው። ሰላም መባባል ደግሞ በቃልም መደረግ ይችላል። ለጠቅላላ ዕውቀት ግን መላእክት በተለያዩ አምሳላት ሲገለጹ መገለጣቸው እንደ ሰይጣን ምትሐታዊ (የውሸት) ስላልሆነ በሚገለጡበት አካል ሆነው ይታያሉ። ይህንንም እግዚአብሔር ያደርግላቸዋል። በተለያዩ አምሳላት እንዲታዩ የፈቀደላቸው እግዚአብሔር የመሰሉትን ነገር አማናዊ አድርጎ ለሌላው እንዲታይ ያደርገዋል።

▶️፲፩. "አንተ ወንድሜ ደኅና ነህን አገርህንና ወገንህን አውቅ ዘንድ መርምሬአለሁና አገሬንና ወገኔን መረመረኝ ብለህ አትንቀፈኝ። ነገር ግን አንተ በእውነቱ ከደግ ከከበረ ወገን የተወለድህ ነህ። እኔም አናንያን አውቀዋለሁ አናንያንና ኢታያንን አውቃቸዋለሁ። የታላቂቱ የሴምዩ ልጅ አዛርያንም አውቀዋለሁ አለው። እንሰግድ ዘንድ ከነእርሳቸው ጋራ አብረን ኢየሩሳሌም ሄደን ነበር። የእህላችንን አሥራትና ከከብቶቻችን መጀመርያ የተወለደውን ወስደን ነበር። ነገር ግን በአባቶቻችን በደልን" ይላል። በአባቶቻችን በደልን ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ተርጓሚው አሻሚ አድርጎ ተርጉሞት ነው እንጂ ግእዙ "ወኢአበስነ አበሳ አበዊነ" ይላል። ይኸውም የአባቶቻችንን በደል አልበደልንም ማለት አባቶቻችን የሠሩትን ኃጢአት እኛ አልሠራንም ማለት ነው።

▶️፲፪. "የአሥራቱን መጀመሪያና እህሉንም ሁሉ ለሚያገለግሉ ለአሮን ልጆች እሰጣቸው ነበር። የሁለተኛውን ዘመን አሥራት ግን እሸምተው ነበር። ምጽዋቱንም አወጣጥቼ በዓመት በዓመት ወደ ኢየሩሳሌም እሄድ ነበር። ሦስተኛውንም አሥራት የአባቴ እናት ዲቦራ እንዳዘዘች ለድኖች እሰጥ ነበር" ይላል። የመጀመሪያው፣ ሁለተኛውና ሦስተኛውን አሥራት ልዩነታቸው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የመጀመሪያው ለካህናት የሚሰጥ ነው። ሁለተኛው ምጽዋት ነው። ሦስተኛው ለነዳያን የሚሰጥ ነው። ሁለተኛው ለነዳያንም ለሌሎችም ሊሰጥ ይችላል።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Jan, 02:16


መጽሐፈ ጦቢት ክፍል 2

ምዕራፍ ፮፦ መልአኩ ሩፋኤል ጦብያን የዓሣውን ጉበትና ሐሞት እንዲይዝ መንገሩ

ምዕራፍ ፯፦ መልአኩ ሩፋኤልንና ጦብያን ሣራ ወለተ ራጉኤል ተቀብላ ደስ እንዳሰኘቻቸው

ምዕራፍ ፰፦ አስማንድዮስ የተባለው ጋኔን ከሣራ ወጥቶ እንደሄደ
-ጦብያና ሣራ እንደጸለዩ
-የሣራ አባት ራጉኤል ጦብያና ሣራ ደህና መሆናቸውን ሲያውቅ እግዚአብሔርን እንዳመሰገነ
-ራጉኤል አስቆፍሮት የነበረውን መቃብር እንዳስደፈነው

ምዕራፍ ፱፦ ሩፋኤል የአደራውን ገንዘብ እንደተቀበለ

ምዕራፍ ፲፦ ጦብያ ከሄደበት ሀገር በቀጠሮው መሠረት ስላልመጣ እናቱና አባቱ ጦብያ እንዳዘኑ መገለጡ

💛የዕለቱ ጥያቄዎች💛
፩. መልአኩ ሩፋኤል ጦብያን ጉበቱንና ሐሞቱን ያዝ ያለው ዓሣ የተገኘው ከምን ወንዝ ነበር?
ሀ. ከጤግሮስ ወንዝ
ለ. ከኤፌሶን ወንዝ
ሐ. ከግዮን ወንዝ
መ. ከኤፍራጥስ ወንዝ
፪. የጦቢት ዓይን የዳነው በምንድን ነበር?
ሀ. በዓሣ ልብ
ለ. በዓሣ ጉበት
ሐ. በዓሣ ሐሞት
መ. በዓሣ ቅርፊት
፫. ራጉኤል ልጁን ሣራን ምን አላት?
ሀ. አማቶችሽን አክብሪ
ለ. በአንቺ መልካሙን እንስማ
ሐ. የሰማይ ጌታ በጎ ነገር ያድርግላችሁ
መ. ሁሉም

https://youtu.be/mtFH7B4FQjY?si=K6Hq8qrFBLMnG8m4

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Jan, 09:52


"ኵሉ ይሰግድ ለሥላሴ
ወይትቀነይ ኵሉ ለመንግሥተ ሥላሴ"

እንኳን አደረሳችሁ ክቡራን

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Jan, 23:25


💚መጽሐፈ ጦቢት ክፍል 1💚

💚ምዕራፍ ፩፦ ጦቢት ነገዱ ከንፍታሌም እንደሆነ
-ጦቢት በጽድቅና በቅንነት መንገድ እንደሄደ
-ምጽዋትን ያደርግ እንደነበር
-ጦቢት ጦብያን እንደወለደ

💚ምዕራፍ ፪፦ ጦቢት የአሕዛቡ ንጉሥ ይገድላቸው የነበሩትን ሰዎች ሳይፈራ ይቀብራቸው እንደነበር
-በጦቢት ዓይን ላይ ወፍ ኩስ ቢጥልበት ዓይኑ እንደበለዘ

💚ምዕራፍ ፫፦ ጦቢት እንደጸለየ
-የራጉኤል ልጅ ሣራ ስታገባ ባሎቿን አስማንድዮስ የሚባል ሰይጣን ይገድልባት እንደነበረ መገለጹ
-ሣራ እንደጸለየች

💚ምዕራፍ ፬፦ ጦቢት ልጁን ጦቢያን ከዝሙት እንዲጠበቅ፣ ከትዕቢት እንዲጠበቅ፣ ምጽዋት እንዲሰጥ፣ እንደመከረው
-ስለምጽዋትና ስለምጽዋት ጥቅሞች መገለጹ

💚ምዕራፍ ፭፦ ጦቢት ጦብያን ከመልአኩ ሩፋኤል ጋር እንደላከው


💛የዕለቱ ጥያቄዎች💛
፩. የጦቢት ነገዱ ከማን ነው?
ሀ. ከዛብሎን
ለ. ከንፍታሌም
ሐ. ከይሳኮር
መ. ከአሴር
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ስለጦቢት ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. በጽድቅና በቅንነት መንገድ ይሄድ ነበር
ለ. ምጽዋትን ይመጸውት ነበር
ሐ. ደማሊ የሚባል ጣዖት ያመልክ ነበር
መ. ሀ እና ለ
፫. ጦቢት ዓይኑ የበለዘ የነበረው በምን ምክንያት ነበር?
ሀ. አስራዶን የተባለ ንጉሥ በጥፊ ስለመታው
ለ. አኪአኪሮስ በጨለማ ቤት ስላሰረው
ሐ. ወፍ ዓይኑ ላይ ኩስ ስለጣለበት
መ. ሀ እና ለ
፬. የጦቢት ሚስት ማን ትባል ነበረ?
ሀ. ዮዲት
ለ. ሐና
ሐ. አድና
መ. ሣራ
፭. የጦቢትን ዓይን ብልዙን ያጠፋለት እና አስማንድዮስ የተባለውን ሰይጣን ከሣራ ያራቀላት መልአክ ማን ነው?
ሀ. ራጉኤል
ለ. ሩፋኤል
ሐ. ፋኑኤል
መ. አፍኒን
፮. ጦቢት ልጁን ጦብያን ምን ብሎ መከረው?
ሀ. በአመፅ መንገድ አትሂድ
ለ. በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ጽድቅን ሥራ
ሐ. ከገንዘብህ ምጽዋት ስጥ
መ. ሁሉም
፯. በመጽሐፈ ጦቢት መሠረት ስለምጽዋት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በመከራ ቀን ከሞት ታድናለች
ለ. በልዑል ፊት መልካም ስጦታ ናት
ሐ. ወደ ጨለማ ከመሄድ ትጠብቃለች
መ. ሁሉም

https://youtu.be/v1yW7k_XvSY?si=Pj1l07FfZC7dZnxJ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Jan, 12:20


ሐዋርያ እንደ ዮሐንስ

ጥቡዕ ነው ከፈጣሪው ውጭ የሚፈራው የለም።
ወደር የለሽ ሊቅ ነው ነገረ መለኮትን አስፍቶ ጽፏል።
መናኝ ነው ሰው ሁሉ የናቀውን ልብስ ይለብሳል።
ታማኝ ነው እስከ መስቀል ጌታውን ተከትሏል።
በምጡቅ አእምሮው ምክንያት በንስር ይመሰላል።
እውነተኛ ነው ይሁዳ ሌባ እንደነበረ ነግሮናል።
በቅድስናው ምክንያት ፍቁረ እግዚእ እስከ መባል ደረሰ
በነገረ መለኮት ዕውቀቱ ታዖሎጎስ ተባለ
ፍጥሞ ደሴት ሳለ የዓለም ፍጻሜ ምሥጢር ተገልጾለት በመጻፉ አቡ ቀለምሲስ (ረአዬ ኅቡዐት) ተባለ።

የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ በረከት ይደርብን።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Jan, 08:41


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 101 💙💙

▶️፩. ዕዝ.ሱቱ.8፥17 ላይ መንግሥተ ሰማያት የተዘጋጀችው ከዚህ ዓለም መፈጠር በፊት ነው ሲል ማቴ.25፥34 ላይም ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ ይላልና እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ መንግሥተ ሰማያት የተፈጠረችው በዕለተ እሑድ ነው። ማቴዎስም፣ ዕዝራም ዓለም ሳይፈጠር እያሉ መጻፋቸው ሰውን ዓለም ብሎ ስለሚተረጉመው ነው። እስመ አፍቀሮ እግዚአብሔር ለዓለም ሲል እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና ማለት ነው። በዚህ አግባብ ዓለም የተባለው ሰው ነው። ሰው የተፈጠረ በዕለተ ዓርብ ሲሆን መንግሥተ ሰማያት የተፈጠረችው ደግሞ በዕለተ እሑድ ነው። ይህንን ለመግለጽ ነው ዓለም ሳይፈጠር የተባለችው።

▶️፪. ዕዝ.ሱቱ.8፥9 መልአኩ እንዴት ትእዛዜን ያቃለሉ እኔን የማይፈሩ ገሀነም ይወርዳሉ ይላል እርሱ አምላክ አይደለምና?

✔️መልስ፦ መልአኩ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ስለሆነ እርሱ የተናገረው ቃል እግዚአብሔር በል ያለውን ነው። መልአኩ ይናገረው እንጂ የቃሉ ባለቤት እግዚአብሔር መሆኑን ልብ ማድረግ ይገባል።

▶️፫. ዕዝ.ሱቱ.9፥21 ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ የሚል እነ ዘሩባቤል ሠርተውት የለም ወይ?

✔️መልስ፦ ይህ እነ ዘሩባቤልና ራሱ ዕዝራም ጭምር ቤተ መቅደስን ከመሥራታቸው በፊት የነበረውን ሁኔታ የሚገልጽ ነው። የሠሩት እነርሱ በአንድነት ነውና።

▶️፬. ዕዝ.ሱቱ.9፥45 ላይ ሠላሳ ዘመን መካን የሆነችው የሚለው አልገባኝም ቢብራራ።

✔️መልስ፦ ሠላሳ ዘመን ያለው ሦስት ሺ ዓመት እንደሆነ ከዚሁ ተገልጿል። ጽዮን ወይም ኢየሩሳሌም ናት። መካን ሆነች መባሏ ለሦስት ሺ ዓመት መሥዋዕት አልተሠዋባትም ማለት ነው።

▶️፭. ዕዝ.ሱቱ.13፥44 ዕዝራ ያጻፈው የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ነውን? እንዲያ ከሆነስ ከእርሱ በፊት ይህን ያህል (24) መጻሕፍተ ብሉያት ተጽፈው ነበርን?

✔️መልስ፦ አዎ በትውፊት እንደሚነገረው ዕዝራ ከእርሱ በፊት ጠፍተው የነበሩትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ተገልጸውለት ጽፏል። ከእርሱ በኋላ ደግሞ ሌሎች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ተጽፈዋል ማለት ነው።

▶️፮. "በሞትን ጊዜ ከእኛ ከእያንዳንዳችን ነፍሳችን በምትወጣበት ጊዜ ቁርጥ ፍርዱን የሚያደርግበት ጊዜው እስኪደርስ ድረስ ይጠብቁናል ወይስ ከዛሬ ጀምሮ ይፈርድብናል" ይላል። የዚህ ጥያቄ መልስ ቢብራራ?

✔️መልስ፦ በሞትን ጊዜ እግዚአብሔር ጊዜያዊ ፍርድን ይሰጠናል። በምጽአት ጊዜ ደግሞ ቁርጥ ፍርድ ይፈርድልናል ወይም ይፈርድብናል ማለት ነው።

▶️፯. "በፍርድ ቀን ጻድቃን በልዑል ዘንድ ለኃጥኣን መለመን ይችላሉን" ይላል። የዚህ ጥያቄ መልሱ ቢብራራ።

✔️መልስ፦ በፍርድ ቀን ጻድቃን ለኃጥኣን አይለምኑም። ልመና ወይም ምልጃ ያለውና የሚኖረው እስከ ዕለተ ምጽአት ብቻ ነው። ምጽአት የፍርድ ቀን ነው እንጂ የልመና ቀን አይደለም።

▶️፰. "ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይምን። ግናያቱ እንደጠፋ ምስጋናችን እንደቀረ ዘመራ ዘውዳችን እንደወደቀ" ይላል። ግናያቱ እና ዘመራ ዘውዳችን ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ግናያት ማለት ልዩ ማኅሌት፣ ልዩ ምስጋና ማለት ነው። ዘመራ ዘውድ ማለት የክብር ዘውድ የምስጋና ዘውድ ማለት ነው።

▶️፱. "ይህ ሠላሳ ዘመን መካን ሆንኩ ያለችህም መሥዋዕት ሳይሠዉ በዚህ ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሦስት ሺ ዘመን ኑረዋልና ይህ ነው" ይላል።  መሥዋዕት ሳይሠዉ የተባለው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው?

✔️መልስ፦ አዎ።

▶️፲. "ትርጓሜው ይህ ነው እግዚአብሔር ለኋላ ዘመን የጠበቃቸው የጥፋት መጀመሪያ የሚደረግባቸው አጀም ሮም ናቸው። አንተ እንዳየኸውም ብዙ ጸብ ክርክር ይደረጋል" ይላል። አጀም ሮም እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ የሀገር ስሞች ናቸው።

▶️፲፩. "በእነዚያ በአርባው ቀኖች ሃያ አራት መጻሕፍት ተጻፉ" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.13፥9)። ሃያ አራቱ መጻሕፍት ምን ምን ናቸው?

✔️መልስ፦ በዝርዝር እኒህ እኒህ ተብለው አልተገለጹም። ከዕዝራ ዘመን በፊት የተጻፉ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት እንደሆኑ ግን በትውፊት ይነገራል።

▶️፲፪. "ያየኸው የሕልምህም ትርጓሜው ይህ ነው ስለዚህ ነገር ላንተ ብቻ አሳየውህ። ግዳጅህን ትተህ የእኔን ግዳጅ ተከትለሃልና ሕጌንም ፈልገሃልና" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.12፥12)። ግዳጅህን ትተህ የኔን ግዳጅ ተከትለሃልና ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሥጋዊ ፈቃድህን ትተህ ፈቃደ እግዚአብሔርን ፈጽመሀልና ማለት ነው። ሥጋ ልብላ ልብላ እያለ ቢያስቸግርም ዕዝራ ግን ብዙ ጊዜ እየጾመ ስለነበር በዚህም ምክንያት ግዳጅህን ትተህ የእኔን ግዳጅ ተከትለሀል ተብሏል።

▶️፲፫. ዕዝ.ሱቱ.9፥21-22 የታቦተ ጽዮን መማረክ እንደሆነና ባቢሎናውያን ማርከው ወስደዋታል ብለው ለሚከራከሩን ሰዎች መልሳችን ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የቃል ኪዳናችን ታቦት እንደተማረከች የሚለው ግልጽ ነው። አዎ ተማርካ ነበር። ቀድሞ ጽላቶቹ ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል። ታቦቱ ማለትም ጽላቱ የሚቀመጡበት ማደሪያቸው ግን በቤተ መቅደስ ነበረ። ያ በባቢሎናውያን ተማርኮ ነበር ማለት ነው።

▶️፲፬. "እንደ አውሎ ነፋስ የሆኑ አሕዛብን በኀጢአታቸው የሚዘልፋቸው እርሱ ወልድ ነው" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.12፥37)። እንዲሁም "በምድር ካሉት ወልድን ማወቅ የሚችል ማንም የለም" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.12፥52)። እነዚህ ንባቦች ስለእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው? ከሆኑ ደግሞ በብሉይ ኪዳን ስለ ቅድስት ሥላሴ በስም "አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ" ተብሎ ይታወቁ ነበር?

✔️መልስ፦ አዎ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚለው በብሉይ ኪዳንም ለጥቂቶች ይታወቅ ነበር። ወልድ እንደሚታወቅ ማስረጃው ይህ ነው። የመንፈስ ቅዱስ ስም ይታወቅ እንደነበረም "የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ" ተብሎ በኢዮ.33፥4 ተገልጿል። የአብ ስምም ይታወቅ እንደነበረ አኮኑ ዝንቱ አብ ፈጠረከ ተብሎ ተገልጿል።

▶️፲፭. "ሠላሳ ዘመን መካን ሆንኩ ያለችህም ይህ ነው የሚያቀርቡት መሥዋዕት ሳይኖር ዓለም ሦስት ሺህ ዘመን ኖሯልና። ከሦስት ሺህ ዓመት በኋላም ሰሎሞን ከተማን ሠራ ያን ጊዜም ቍርባንን አቀረበ ያችም መካን ሴት የወለደችው ልጅ ነው" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.9፥45-46)። ከሰሎሞን በፊት ብዙዎች መሥዋዕት አቅርበው አይደል ለምን እንዲህ አለ?

✔️መልስ፦ ቤተ መቅደስ ተሠርቶ መሥዋዕት የቀረበበትን ዘመን ለመግለጽ ነው። ከዚያ በፊት ቤተ መቅደስ አልተሠራም ነበርና።

▶️፲፮. "አባቶቻችንም ሕግህን ተቀብለው አልጠበቁምና በሥርዐትህም አልጸኑም። የሕግህ ፍሬ ግን አልጠፋም የአንተ ገንዘብ ስለሆነ ይጠፋ ዘንድ አይቻልምና" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.8፥33)። ሕግህን ተቀብለው አልጠበቁም ይላልና ታዲያ እዚህ ላይ የሕግህ ፍሬ ግን አልጠፋም የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አባቶቻችን ሕግህን አልጠበቁም እንጂ ሕጉ ግን ነበረ ማለት ነው። በተጨማሪም አብዛኞች ሕግን ባለመጠበቅ ቢስቱም ጥቂቶች ግን ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ይኖሩ ስለነበረ የሕግህ ፍሬ ግን አልጠፋም ተብሏል።

▶️፲፯. "በዓለም የሆነው ሁሉ አስቀድሞ በቃል ኋላም በመገለጥ እንደ ሆነ እንዲሁም የልዑል ዓለም መጀመሪያ በቃል በተአምርና በኃይል ኋላ ግን በሥራና በድንቅ ነው" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.8፥5)። ይሄ ንባብ ቢብራራልኝ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Jan, 08:41


✔️መልስ፦ በዚህች ዓለም እግዚአብሔር አስቀድሞ የተናገረው በኋላ በመገለጥ የሆኑ ብዙ ጉዳዮች ነበሩ። አሁንም በቃል የሚነገሩና እየተነገሩ ያሉ ወደፊት የሚገለጡ ምጽአትን የመሳሰሉ ምሥጢሮች አሉና ይህንና የመሳሰሉትን የሚገልጽ አነጋገር ነው።

▶️፲፰. "ዓለም ለዐሥር ክፍል ተከፍሏልና እስከ ዐሥርም ድረስ ደርሷልና። የዐሥረኛው እኩሌታ ቀርቷልና" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.13፥11)። ይህ ንባብ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የዓለምን ዕድሜ እግዚአብሔር ባወቀ ለአሥር ክፍል ከፍሎታል ማለት ነው። ከአሥሩ ክፍል ደግሞ የአሥረኛው እኩሌታ ክፍል እንደቀረ ተናግሯል።

▶️፲፱. "ከዚሀም በኋላ ሁሉም የየራሳቸውን ቃል ጻፉ አትመውም ከንጉሡ ከዳርዮስ መከዳ በታች አኖሩት" ይላል። መከዳ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ መከዳ ማለት ትራስ ማለት ነው።

▶️፳. "ከሰው ለይተው ይወስዱሃልና ከዚህም በኋላ ዓለም እስኪያልፍ ድረስ እንዳንተ ያሉት ባሉበት ቦታ ከልጆቼ ጋር ትኖራለህ" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.13፥9)። ዕዝራ ሱቱኤል አልሞተም?

✔️መልስ፦ አዎ ዕዝራ ወደ ብሔረ ሕያዋን ከሄዱት ከእነ ኤልያስ፣ ከእነ ሄኖክ ጋር በብሔረ ሕያዋን ይኖራል እንጂ እስከ አሁን አልሞተም።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Jan, 06:55


✔️መልስ፦ ምሥጢሩ ስለክርስቶስ ነው። ክርስቶስ አነ ውእቱ ሐረገ ወይን ብሏልና። ወንዝ መባሉም አፍላገ ማየ ሕይወት ዘይውኅዝ እምከርሡ ተብሏልና ነው። እንዲሁም አንድ ወንዝ ዮርዳኖስ ነው። ጌታ ተጠምቆበታልና። ለእኛ አንድ ወንዝ ማየ ገቦ ነው። ከጎኑ ከፈሰሰ ውሃ እስከ ዕለተ ምጽአት እየተጠመቅን ልጅነትን እናገኛለንና።

▶️፳፰. "መልሼም እንዲህ አልሁት የመጀመሪያው ዓለም ምልክቱ ጊዜውስ ምንድን ነው? ፍጻሜውስ መቼ ነው? የሁለተኛውስ ዓለም መጀመሪያው መቼ ነው?" ሲል የመጀመሪያውና የሁለተኛው ዓለም ያላቸው የትኞቹን ዓለማት ነው?

✔️መልስ፦ የመጀመሪያው ዓለም የተባለ ይህ እየኖርንበት ያለው ዓለም ነው። ሁለተኛው ዓለም ከምጽአት በኋላ ጻድቃን በመንግሥተ ሰማያት ኃጥኣን በገሀነም የሚኖሩበት ዓለም ነው።

▶️፳፱. ዕዝ.ሱቱ.4፥21 ላይ "ዓመት የሆናቸው ሕፃናት ፈጽመው ይናገራሉ። የጸነሱ ሴቶችም የሦስት ወርና የአራት ወር ሕፃናትን ይወልዳሉ ሕያዋንም ሆነው ይነሣሉ" ሲል ምን ተብሎ ይተረጎማል?

✔️መልስ፦ የመጨረሻው ሰዓት ሊደርስ ሲል የአንድ ዓመት ሕፃን ሳይቀር መናገር ይጀምራል ማለት ነው። የጸነሱ ሴቶች የሦስት ወርና የአራት ወር ሕፃናትን ይወልዳሉ መባሉ በመጨረሻው ሰዓት ጽንስ የሚያስወርዱ ሰዎች እንደሚበዙ ያመለክታል። ሕያዋን ሆነው ይነሣሉ መባሉ ሰው ተስእሎተ መልክእ ከተፈጸመለት በኋላ ቢሞትም በዕለተ ትንሣኤ ይነሣል ማለት ነው።

▶️፴. "የማትታይ ምድርም ዘርዕ ተዘርቶባት ትታያለች። ውስጣቸው ሙሉ የነበሩ ቤቶችም ባዷቸውን ይገኛሉ። ነጋሪት ይሰማል የሰማውም ሁሉ ይደነግጣል" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.4፥22-23)። የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የማትታይ ምድርም ዘርዕ ተዘርቶባት ትታያለች ማለት እስከ አሁን የማትታይ መንግሥተ ሰማያት በምጽአት ጊዜ ትገለጣለች ማለት ነው። ምድር ያላት ምድር አልፋ በምድር ምትክ የምትተካ ስለሆነች ነው። በተጨማሪም በምድር በተሠራው መልካም ሥራ የምትወረስ ስለሆነች ነው። ውስጣቸው ሙሉ የነበሩ ቤቶች ባዷቸውን ይገኛሉ ያለው ምድር ታልፋለች፣ ገነት ታልፋለች፣ ሲኦል ታልፋለች ማለት ነው። በእነዚህ የነበሩ ፍጥረታትም ያልፋሉ፣ ነፍሳትም ወደ ገሃነመ እሳት ወደ መንግሥተ ሰማያት ሄደው ሲኦልና ገነት ባዷቸውን ይቀራሉ ማለት ነው።

▶️፴፩. "ያንጊዜም የፈጠርሃቸውን ሁለቱን እንስሳት ጠበቅህ ያንዱን ስሙን ብሔሞት አልከው የሁለተኛውንም ስሙን ሌዋታን አልከው" ይላል።  ስለ ብሔሞትና ሌዋታን ሰፋ አድርገው ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ብሔሞትና ሌዋታን በናጌብና በአድማስ መካከል ባለው ቦታ የሚኖሩ ግዙፋን ፍጥረታት ናቸው። ብሔሞት በየብስ ይኖራል። ሌዋታን በውሃ ትኖራለች። መሬትን ዙሪያዋን ከበው የሚኖሩ ግዙፋን ፍጥረታት ናቸው። ብዙ ብዙ እየተመገቡ የሚኖሩ ናቸው።

▶️፴፪. "ከዚህ በኋላ ልጄ መሲሑ ይፈጽማል አእምሮ ያለው ሰውም ሁሉ ይፈጽማል" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.5፥29)። ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ልጄ መሢሑ የተባለ ክርስቶስ ነው። ክርስቶስ የአብ ልጅ ነውና። መሢሑ ይፈጽማል ማለት ፈርዶ መንግሥተ ሰማያትን ለሚወርሱት መንግሥተ ሰማያትን፣ ገሃነመ እሳትን ለሚወርሱት ገሃነመ እሳትን አውርሶ ይፈጽማል ማለት ነው። አእምሮ ያለው ሰውም ሁሉ ይፈጽማል ያለው የሚወርሰውን ወርሶ ይፈጽማል ማለት ነው።

▶️፴፫. "የሞትስ ነገር እንዲህ ነው ከልዑል ዘንድ የትእዛዝ ቃል ከመጣ በኋላ እገሌ ይሙት ባለ ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ትለያለች" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.6፥9)።   አብዛኛውን ጊዜ ሰው ሲሞት መቼም እግዚአብሔር  ገደለው አይባልምና በሕመም፣ በአደጋ ወይም ራሱን አጥፍቶ ነፍሱ ከሥጋው ትለያለች። ራሱን ያጠፋን ሰው (ታንቆ ወይም ራሱን መርዞ) ከዚህ ንባብ አንጻር እግዚአብሔር ይሙት ብሎት ነው ማለት ይቻላል?

✔️መልስ፦ የሰውን የሞት ቀን የሚወስን እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር እንዳይሞት ከፈቀደ ሰው መርዝ ጠጥቶ ወይም ራሱን አንቆ እንኳ ሳይሞት ሊተርፍ ይችላልና። እግዚአብሔር እንዲሞት ከፈረደበት ግን ይሞታል። መታነቅ ወይም መርዝ መጠጣት ግን ኃጢአት ስለሆነ እግዚአብሔር በዚህ ክፉ ሥራ በሰው ይፈርዳል። እግዚአብሔር መታነቅን ወይም መርዝ መጠጣትን አይፈቅድምና። ሰው ይህን ክፉ ሥራ ካደረገ ግን እግዚአብሔር በዚያው ነፍሱን ከሥጋው ሊለየው ይችላል።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Jan, 06:55


✔️መልስ፦ የጨረቃ በቀን ማብራት፣ የፀሐይ በሌሊት ማብራት፣ ከእንጨት ደም መፍሰስ፣ የድንጋይ መጮህ ያልተለመደ ነገር ነው። ዕለተ ምጽአት ሲቃረብ ብዙ ያልተለመዱ እንግዳ ነገሮች፣ ክፋቶች ይደረጋሉ ማለት ነው።

▶️፲፮. "ከተፈጠሩ ወፎችም ሁሉ አንድ ርግብን ለአንተ ለየህ። ከተፈጠሩ እንስሳትም ሁሉ አንድ በግን መረጥህ። ከምድር አሕዛብ ሁሉ አንድ ሕዝብን ለራስህ መረጥክ" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.3፥26)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ርግብ ማየ አይኅ መጉደሉን ያበሰረች በመሆኗ ከወፎች ሁሉ የተከበረች ወፍ ናት። ይህን ለመግለጽ ከወፎች ርግብን ለየህ ተብሏል። በብሉይ ኪዳን ምንም እንኳ ርግብ የምትበላ ባትሆንም ለመሥዋዕትነት ግን ትቀርብ ነበር። መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዷል። በግን መረጥክ መባሉም ከእንስሳት ሁሉ ለመሥዋዕትነት በተለየ የተመረጠ በግ መሆኑን ለመግለጽ ነው። ለይስሐቅ ቤዛ ሆኖ የመጣ በግ ነው፣ እኛን ለማዳን የመጣው ክርስቶስም የእግዚአብሔር በግ ተብሎ ተገልጿልና በግን መረጥክ ተብሏል። ከአሕዛብ ሕዝብን መረጥክ መባሉ ክርስቶስ ሕዝብ ከተባሉ እስራኤላውያን መወለዱን ያመለክታል።

▶️፲፯. "ኤሳው የዚህ ዘመን ፍጻሜ ምሳሌ ነው። ያዕቆብ የአዲሱ ዘመን መጀመሪያ ነው" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.4፥9)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ኤሳው መጀመሪያ ተወልዷል። ያዕቆብ ደግሞ ቀጥሎ ተወልዷል። ኤሳው የዚህ ዓለም ምሳሌ መባሉ መጀመሪያ ሰዎች የሚኖሩበት ዓለም ይህ ነው ማለት ነው። ያዕቆብ የአዲሱ ዘመን ምሳሌ መባሉ ከኤሳው ቀጥሎ ያዕቆብ እንደተወለደ ከዚህ ዓለም ኑሮ ቀጥሎ ዘለዓለማዊው ኑሮ ስለሚቀጥል ነው።

▶️፲፰. ዕዝ.ሱቱ.፩ ፥፯ "ከዚህም በኋላ በእርሱና በልጆቹ ላይ ሞትን አመጣህ" ይላል። ቢብራራልን ሞትን ያመጣ ሰው አይደለምን? እግዚአብሔር ሞትን እንደማያመጣ ተምረናል ግልጽ ቢደረግልን።

✔️መልስ፦ ሞትን በፈቃዱ ያመጣው ሰው ነው። ሰው ኃጢአት ባይሠራ ኖሮ ሞት አይኖርም ነበር። ነገር ግን ኃጢአት ከሠራ ሞት እንደሚኖር ተገልጿል። የኃጢአት ውጤት ሞት እንዲሆን የተፈጥሮውን ሕግ የሠራው ግን እግዚአብሔር ነው። ሕጉን የሠራው እግዚአብሔር በመሆኑ ሞትን አመጣህ ተብሏል። ነገር ግን አዳም ባይበድል ሕጉ ተፈጻሚ አይሆንም ነበረ። ሰው ሕጉን ሽሮ ሕጉ ስለተፈጸመበት ደግሞ ሰው ሞትን አመጣ ተብሏል።

▶️፲፱. ጌታችን የሚመጣበትን ቀን ዘመኑ እንደማይታወቅ መልአኩ ለዕዝራ በምሳሌ ነግሮታል። ታዲያ በአስተምህሮ ግን ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ፣ ጳጉሜ ፫፣ ዕለተ ሰንበትና ደብረ ዘይትም እየተባለ ተምረናል። ይህ አስተምህሮ አይጋጭም ወይ? ቢያብራሩልን።

✔️መልስ፦ ጳጕሜን 3 የዕለተ ምጽአት መታሰቢያ ነው እንጂ ምጽአት የሚሆንበት ጊዜ አይደለም። እግዚአብሔር የሚመጣበት ጊዜ አይታወቅም። ነገር ግን መጋቢት 29፣ ዘመነ ዮሐንስ፣ ዕለተ እሑድ መሆኑ ተገልጿል። ብዙ ዘመነ ዮሐንስ፣ ብዙ መጋቢት 29፣ ብዙ ዕለተ ሰንበት ስላለ በየትኛው እንደሚሆን አይታወቅም ማለት ነው። ታወቀ የሚባለው ሁሉም ተለይቶ ቢታወቅ ነበረ እንጂ አሁን ግን ተለይቶ ስለማይታወቅ አይታወቅም ተብሏል።

▶️፳. መልአኩ ለዕዝራ በራእይ ከ፫ ወር በኋላ ምድርን ስትታወክ ታያታለህ ብሎታል። እንዲህ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ስለምጽአት የተነገረ ነው። ዕዝራ የነበረበት ዘመን ዓለም ከተፈጠረ 5000 ዓመት አካባቢ ሆኖት ነበረ። ከሦስት ወር በኋላ ያለው ከ3000 ዓመት በኋላ ማለት ነው። ይኸውም የጎደለ ሞልቶ ነው። በስምንተኛው ሺ ሰዎች እርስ በእርስ ይጣላሉ፣ ምድር ትጠፋለች ማለት ነው።

▶️፳፩. ዕዝ.ሱቱ.፫፥፴፰ ዕዝራ መልአኩን አቤቱ ጌታዬ ብሎ ማነጋገሩ ከምን አንጻር ነው ትርጉሙ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የአክብሮት አነጋገር ነው። ሣራ አብርሃምን ጌታዬ ትለው የነበረ ለእርሱ ያላትን ክብር ለመግለጥ እንደነበረ ሁሉ ዕዝራም ለመልአኩ ያለውን ክብር ለመግለጥ ጌታዬ ብሎታል።

▶️፳፪. ዕዝ.ሱቱ.2፥28 ላይ "ስለ እርሷ የጠየቅኸኝ ክፋት ተዘርታለችና መከራዋም አልደረሰምና" ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ክፋት ተዘርታለች ማለት ሰዎች ክፋትን እየሠሩ ይገኛሉ ማለት ነው። መከራዋ አልደረሰም ማለት ክፉ የሠሩት እንደክፋታቸው የሚፈረድባቸው በምጽአት ስለሆነ የምጽአት ፍርድ ገና አልተደረገም ማለት ነው።

▶️፳፫. "ስለዚህ የጻድቃን ነፍሳት በማደሪያቸው ሁነው ጠየቁ በዚህ እስከ መቼ ድረስ እንኖራለን? የዋጋችንስ መከር መቼ ይደርሳል? አሉ። መልአኩ ኢይሩማኤልም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው እንደ እናንተ ያሉት ጻድቃን ቍጥራቸው በተፈጸመ ጊዜ ነው" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.2፥35-36)። የጻድቃን ነፍሳት ማደሪያ የተባለ ምንድን ነው? እንደ እናንተ ያሉት ጻድቃን ቍጥራቸው በተፈጸመ ጊዜ ነው ሲልስ መች ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ የጻድቃን ነፍሳት ማደሪያ የተባለ እስከ ዕለተ ምጽአት ጻድቃን በጊዜያዊነት የሚኖሩበት ገነት ነው። እንደ እናንተ ያሉት ጻድቃን ቁጥራቸው በተፈጸመ ጊዜ ማለት እስከ ምጽአት ድረስ የሚነሡ ጻድቃን አሉና ጻድቅ በዚህች ምድር ጻድቅ እስኪጠፋ ድረስ ማለት ነው። ጻድቅ ሙሉ በሙሉ በምድር ከሚኖሩት ሲጠፋ ምጽአት እንደሚሆን የሚያሳይ አነጋገር ነው።

▶️፳፬. "እኔም ቆምሁ እነሆም ምድጃ በፊቴ እየነደደ ሲሄድ እየሁ ከዚህም በኋላ እሳቱ በሄደ ጊዜ እነሆ ጢሱ ቀረ። ከእርሱም በኋላ ውኃን የተመላች ደመና በፊቴ ሄደች ታላቁና ብዙ የሆነ ዝናምንም ታዘንማለች ታላቁ ዝናምም ካለፈ በኋላ ካፊያው ቀረ" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.2፥48-49)። እሳት፣ ጭስ፣ ደመና፣ ዝናምና ካፊያ የምን ምሳሌዎች ናቸው?

✔️መልስ፦ ከዚህ እኒህ ሁሉ መጠቀሳቸው የዘመናትን ርዝመት ለመግለጽ ነው እንጂ የተለየ ምሳሌ የላቸውም። ከዝናም ካፊያ፣ ከእሳት ጢስ እንደሚያንስ ሁሉ የወደፊቱ ዘመን ያንሳል ማለቱ ነው። በደመና የተመሰለው በዚህ አግባብ ዘመን ነው።

▶️፳፭. "በእነዚያም በሰባቱ ቀኖች ይህን የነገርሁህን ሥራቸውን ሁሉ ያዩ ዘንድ ለሰባት ቀን ነጻ ናቸው። ከዚያም በኋላ ወደ ቦታቸው ይመለሳሉ አለኝ" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.6፥32)። ነፍስ ከሥጋ ከተለየች በኋላ ወደ ሲኦል ወይም ወደ ገነት ሳትገባ ሰባት ቀን ትቆያለች ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ እንደዚህ ለማለት አይደለም። በዚሁ ምዕራፍ ከቁጥር 22 እስከ ቁጥር 31 የተገለጹትን ሥርዓታት ወደ ገነትና ወደ ሲኦል እየተመላለሰ ያያል ማለት ነው እንጂ ከገነትና ከሲኦል ውጭ ሌላ ሦስተኛ መካነ ነፍስ ኖሮ በዚያ ይቆያሉ ማለት አይደለም።

▶️፳፮. "ከሴቶችም ባለ ምልክት ይወለዳል። የሚጣፍጠውም ውኃ መራራ ይሆናል። ያንጊዜም ጥበብ ትሰወራለች ምክርም ወደ ማደሪያዋ ትመለሳለች" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.3፥8-9)። ምን ለማለት ይሆን?

✔️መልስ፦ ጥበብ ትሠወራለች የተባለው ከሰው ክፋት የተነሣ መንፈሳዊ ጥበብ ይቀንሳል ማለት ነው። የሚጣፍጠው ውሃ መራራ ይሆናል ማለት በክፋት ምክንያት ጽድቅ ይጠላል ማለት ነው። ከሴቶች ባለምልክት ይወለዳል የሚለው ምጽአት ሲቀርብ ሸብተው የሚወለዱና የተለያየ አርዓያ ያላቸው ሰዎች ይወለዳሉ ማለት ነው። በተጨማሪም ዓለምን የሚያስት ላዕላይ ከንፈሩ ትልቅ የሆነ አንድ ዓይና ሐሳዊ መሢሕ ይወለዳል ማለት ነው።

▶️፳፯. ዕዝ.ሱቱ.3፥23-26 ባለው ንባብ ውስጥ አንድ የወይን ሐረግ፣ አንድ ወንዝ የተባሉ የምን ምሳሌዎች ናቸው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Jan, 06:55


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 100 💙💙

▶️፩. ዕዝ.ሱቱ.3፥45 ላይ አንድ ላይ ይላል። 1ኛ ተሰ.4፥16 እንደሚነግረን ደግሞ በክርስቶስ የሞቱት አስቀድመው ነው የሚነሡት ይላል እና አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ሙታን የሚነሡት በአንድ ጊዜ ነው። 1ኛ ተሰ.4፥16 ላይ የተገለጠው አስቀድመው ይነሣሉ መባሉ የሕይወት ትንሣኤን ይነሣሉ ለማለት ነው እንጂ ከኃጥአን ቀድመው ይነሣሉ ለማለት አይደለም።

▶️፪. ዕዝ.ሱቱ.6፥26 ጻድቅ ከሞተ በኋላ በመልአክ ይጠበቃል?

✔️መልስ፦ ጻድቅ ሰው ከሞተ በኋላ በነፍስ የሚጠብቀው እግዚአብሔር ነው። ከዚህ በመላእክት ይጠበቃሉ ተብሎ መገለጹ ገነትን የሚጠብቁ መላእክት ስላሉ በማደሪያው ኀዳሪው ተገልጾ ነው።

▶️፫. ዕዝ.ሱቱ.4፥21 ከትንሣኤ ዘጉባኤ በፊት የጸነሱት ከትንሣኤ በኋላ ይወልዳሉን?

✔️መልስ፦ ከትንሣኤ በኋላ መጽነስ፣ መውለድ መዋለድ የለም። ከዚህ ላይም የተገለጠው ከትንሣኤ በፊት ስለሚደረገው ነው እንጂ ከትንሣኤ በኋላ ስለሚሆነው አይደለም።

▶️፬. ዕዝ.ሱቱ.1፥6 ምድር ሳትጸና ሲል ምን ለማለት ነው? በጭቃነት ሳለች እንዳይባል እግዚአብሔር ከአዳም መፈጠር በፊት በነፋስ አድርቋታልና።

✔️መልስ፦ ምድር ሳትጸና ማለት ከተፈጠረች ብዙ ቀን ሳይሆናት ማለት ነው። አዳም ምድር ከተፈጠረች ገና በ46ኛ ቀኗ ወደ ገነት ገብቷልና።

▶️፭. ዕዝ.ሱቱ.1፥17 "ሰማያትን ዝቅ አደረግህላቸው። ምድርንም አነዋወጥህላቸው" ይላል። ንባቡ አልገባኝም።

✔️መልስ፦ ሰማያትን ዝቅ አደረግህላቸው ማለት መናን አወረድክላቸው፣ በመልአክ መራሐቸው ማለት ነው። ምድርንም አነዋወጥክላቸው ማለት ባሕረ ኤርትራን ከፈልክላቸው፣ ነገሥታተ አሕዛብን እንዲያሸንፉ አደረግሃቸው፣ ውሃን ከጭንጫ አፈለቅህላቸው ማለት ነው።

▶️፮. ዕዝ.ሱቱ.1፥18 አራቱ ተአምራት ምን ምን ናቸው?

✔️መልስ፦ ከዚሁ ተገልጸዋል። የእሳት፣ የንውጽውጽታ፣ የበረድ፣ የነፋስ ናቸው።

▶️፯. ዕዝ.ሱቱ.1፥29 እግዚአብሔር ወዳጆቹን ትቶ እንዴት ጠላቶቹን ይጠብቃል?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ፍጥረታቱን ሁሉ ይጠብቃል። በተለየ ረድኤተ ነፍስን የሚሰጥ ደግሞ ለጻድቃን ነው። ከዚህ የተገለጸው እስራኤላውያን መማረካቸው ነው። ዕዝራ ከዚህ ጥቅስ ያቀረበው ለምን እኛን እንድንማረክ አደረግኸን፣ አሕዛብ ግን ሳይማረኩ ቀሩ የሚል ነው።ወዳጆችህን ትተህ ኃጥኣንን ትጠብቃለህን የሚለው እንደ ጥያቄ የቀረበ እንጂ እውነታ አይደለም። መልሱም የእስራኤል መማረክ የተመረጡ ሕዝቦች ሆነው ሳለ ጣዖት በማምለካቸው እንደሆነ እንዲረዱት ነው። ደጋግ ሆነው የተማረኩት ጸጋ ይበዛላቸው ዘንድ አብረው ተማርከዋል። ሌሎቹ ደግሞ ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ለቅጣት ተማርከዋል።

▶️፰. ዕዝ.ሱቱ.4፥41-42 ነፋስ በመጀመሪያው ቀን አይደል የተፈጠረው? ውሃውስ የተከፈለው ሰኞ አይደለም ወይ?

✔️መልስ፦ ነፋስ የተፈጠረው በመጀመሪያው ቀን በዕለተ እሑድ ነው። ውሃውም የተከፈለው በዕለተ ሰኞ ነው። ከዚህ በሁለተኛው ቀን ነፋሳትን ፈጠርክ ማለቱ በዕለተ እሑድ የተፈጠረውን ነፋስ ከፋፍለህ በተለያዩ ቦታዎች ወሰንከው ማለት ነው። ይኸውም ሐኖስን የሚሸከመውን ረቂቁን ነፋስ ባቢልን በላይ አደረግከው፣ ምድርን የሚሸከመውን ነፋስ ከመሬት በታች አደረግህ ማለት ነው። አራቱን ነፋሳተ ምሕረትና ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ለየህ ማለት ነው።

▶️፱. ዕዝ.ሱቱ.5፥30 የዓለም እድሜ 7000 ነውን?

✔️መልስ፦ አይታወቅም። ከዚህም ከሰባት ቀን በኋላ ሰው ይነሣል ነው የሚለው። ከሰባት ቀን በኋላ መቼ የሚለውን ግን አይገልጽም። ከሰባት ሺህ ዓመት በኋላ እንደሚሆን ተገልጿል። ከዚያ በኋላ ግን መች መሆኑን ስላልተገለጸ የዓለም ዕድሜ 7000 ብቻ አለመሆኑን እንረዳለን።

▶️፲. አገራችን ኢየሩሳሌም በጠፋች በሠላሳ ዘመን ዕዝራ እባል የነበርኩ እኔ ሱቱኤል በባቢሎን ነበርኩ በመኝታዬም እኔ ተኝቼ ነበር። ፊቴ ግን ተገልጦ ነበር በልቡናዬም አሳብ ይወጣ ይወርድ ነበር። ሱቱኤል ምን ማለት ነው? የመጽሐፈ ዕዝራ እና የመጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ጸሓፊ ራሱ ዕዝራ ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ የተጠቀሱት የሁለቱም መጻሕፍት ጸሓፊው አዎ ራሱ ዕዝራ ነው። ሱቱኤል የሚለው የዕዝራ ተጨማሪ ስም ነው። ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቄርሎስ መምህረ ዓለም፣ ኤፍሬም አፈ በረከት፣ ናጣሊስ ማኅቶት ብሩህ እንደሚባለው ያለ ነው።

▶️፲፩. "በልዑል ዘንድ የተዘጋጀ መዝገብ ለአንተ አለህና። ነገር ግን እስከ ኋለኛው ቀን ድረስ አልገልጥልህም" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.6፥8)። መልአኩ ከሚፈረድባቸውና ከከሓድያን ጋር እንደማይቆጠር ለዕዝራ ከነገረው ታዲያ እስከ ኋለኛው ቀን ድረስ አልገልጥልህም ያለው ምኑን ነው?

✔️መልስ፦ ከዚሁ ተገልጿል። መዝገቡን ነው አልገልጥልህም ያለው። ዕዝራ እስከ ምጽአት መቃረብ ድረስ በብሔረ ሕያዋን ኖሮ በኋላ መንግሥተ ሰማያት ይገባል። ከከሓድያን ጋር እንደማይቆጠር ነገረው እንጂ ይህንን አልገለጠለትም ነበረና ነው።

▶️፲፪. "እመን አትፍራ በኋላ ዘመን እንዳትጠራጠር ስለቀደመው ስለክፉዉም አሳብህ አትቸኩል አለኝ። ከዚህ በኋላ የነገረኝ ሦስቱን ሱባዔ እጨርስ ዘንድ ዳግመኛ ሰባት ቀን እያለቀስኩ ጾምኩ" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.4፥34)። ክፉዉም አሳብህ የተባለው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የቀደመው ክፉ ሐሳብህ የተባለው ለዝንጉዎች የምትራራ፣ ወገኖችህን የምትጥል እያለ የተናገረውን ነው። የእግዚአብሔርን ፍርድ ለማወቅ መፈለጉ ነው። በኋላ ግን መልአኩ በተለያየ መልኩ ስላስረዳው ዕዝራም ሐሳቡን ትቶታል።

▶️፲፫. "በሦስተኛይቱ ቀን ውሃውን በሰባተኛይቱ ዕጣ በምድር ይወሰን ዘንድ አዘዝከው። ያርሱ ዘንድ ዘርም ይዘሩ ዘንድ በፊትህም ጸንተው ይኖሩ ዘንድ የምድር ስድስተኛይቱ ዕጣ ደረቅ ሁኖ ይቅር አልህ" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.4፥42)። ሰባቱ ዕጣዎች እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ ከዚሁ ገልጾታል። ስድስቱ ዕጣ ደረቅ ይሁን ተብሎ የተገለጸው ሰው የሚያርሰው የሚቆፍረው የብሱ ነው። አንዱ ዕጣ ያለው ደግሞ ዐቢይ ውቅያኖስ ያለበትን ነው። በሌላ አገላለጽ ሰባቱ የመሬት ክፍሎች የሚባሉት እኛ የምንኖርባት መሬት፣ ግሩማን አራዊት የሚኖሩበት ቦታ፣ ናጌብ፣ ዐቢይ ውቅያኖስ፣ አድማስ፣ ሌዋታን የምትኖርበት ዓለም፣ ብሔሞት የሚኖርበት ዓለም ናቸው።

▶️፲፬. "በስድስተኛይቱም ቀን በፊትህ እንስሳን የሰማይ ወፎችንና የምድረ በዳ አውሬዎችን ታስገኝ ዘንድ ምድርን አዘዝካት" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.4፥53)። ከፍ ብሎ ግን ቁጥር 47 ላይ በ5ተኛ ቀን ዓሣዎችን እና ወፎችን ያስገኝ ዘንድ አዘዝክ ይላል አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። በአምስተኛው ቀን የተፈጠሩት ዓሣዎች፣ ወፎች፣ እንስሳት፣ አራዊት ከውሃ የተፈጠሩ ናቸው። በስድስተኛው ቀን የተፈጠሩት ደግሞ ከየብስ የተፈጠሩ ናቸው። በሥነ ፍጥረት አቆጣጠር እንኳ ከውሃ የተፈጠሩት እንስሳት፣ አራዊት፣ አዕዋፋት፣ ዓሣት ሦስት ተብለው ሲቆጠሩ ከየብስ የተፈጠሩት እንስሳት፣ አራዊት፣ አዕዋፋት፣ ዓሣት ደግሞ ለብቻቸው ሦስት ተብለው ይቆጠራሉና።

▶️፲፭. "ልዑል ሕይወትህን ከሰጠህ ከሦስት ወራት በኋላ ምድርን ስትታወክ ታያታለህ ፀሐይም ድንገት በለሊት ያበራል። ጨረቃም ድንገት በቀን ያበራል። ከእንጨቶችም ደም ይፈሳል ድንጋይም ትጮሃለች" ይላል (ዕዝ.ሱቱ.3፥4)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Jan, 03:11


💚 መጽሐፈ ዕዝራ ካልእ ክፍል 1 💚

💚ምዕራፍ 1፦ ኢዮስያስ የፋሲካውን በግ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳመጣና እስራኤላውያን እንደ ሥርዓቱ የፋሲካን በዓል እንዳከበሩ
-ኢዮስያስን በሥራው በፈጣሪው ፊት የቀና እንደነበር
-እስራኤላውያን እንደተማረኩ

💚ምዕራፍ 2፦ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ ቤተ እግዚአብሔርን ለመሥራት እንደተነሳሳ

💚ምዕራፍ 3፦ ሦስቱ የንጉሡ ጠባቂዎች በንጉሥ ዳርዮስ ፊት የሚወደድ ቃል ለመናገር እንደተወዳደሩ

💚ምዕራፍ 4፦ ስለንጉሥ አሸናፊነት፣ ስለሴት አሸናፊነት፣ ስለእውነት አሸናፊት በየተራ አቅራቢዎቹ እንደገለጹ
-እውነት ሁልጊዜ እንደምታሸንፍ መነገሩ
-የኢየሩሳሌምና የቤተመቅደስ ሥራ እንዲከናወን ዳርዮስ እንደፈቀደና ለሠሪዎች ምግብ እንዲሠፈርላቸው ማድረጉ

💚ምዕራፍ 5፦ ከምርኮ ስለተመለሱት ሰዎች የስም ዝርዝር


💚 የዕለቱ ጥያቄዎች 💚
፩. ከሚከተሉት ውስጥ በንጉሥ ዳርዮስ ዘንድ አብልጦ የተወደደው ሐሳብ የትኛው ነበር?
ሀ. ወይን ያሸንፋል
ለ. ንጉሥ ያሸንፋል
ሐ. እውነት ታሸንፋለች
መ. ሕዝብ ያሸንፋል
፪. ሴቶች ያሸንፋሉ ከሁሉም ይልቅ እውነት ታሸንፋለች የሚለውን ቃል ለዳርዮስ ያቀረበው ማን ነው?
ሀ. ዘሩባቤል
ለ. ዕዝራ
ሐ. ነህምያ
መ. ኢዮስያስ
፫. ሁለተኛው ቤተመቅደስ በእነዘሩባቤል አማካኝነት ሲሠራ የሲዶናና የጢሮስ ሰዎች የዋንዛ እንጨቶችን ከሊባኖስ በየት በኩል በመርከብ ያገቡላቸው ነበር?
ሀ. በኤርትራ ባሕር
ለ. በኢዮጴ ባሕር
ሐ. በቀይ ባሕር
መ. በሙት ባሕር

https://youtu.be/xeS5zgxMG9Q?si=_2Tx-EWY5XCNWg2b

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

11 Jan, 14:11


https://youtu.be/KK2c904av4o?si=-1ZfBxLce9R6nefL

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

11 Jan, 04:21


መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ተፈጸመ።

ነገ መጽሐፈ ዕዝራ ካልእ ይጀምራል። የሚገራርሙ ጥያቄዎች ተጠይቀዋል። የትላንቱንና ዛሬ የተጠየቁትን እንዲሁም የሚጠየቁትን በኋላ እመልሳለሁ። ሱቱኤል ላይ ቀሪ ጥያቄ ካላችሁ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት አምጡት።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

11 Jan, 04:16


✝️ መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ክፍል 2 ✝️

✝️ ምዕራፍ 8፦ ዛሬ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ቸል ያሉ ያንጊዜ መከራን እንደሚቀበሉ
-ሄኖክ ዳግመኛ ሰባት ቀን ቢጾምና ቢጸልይ፣ ግንብ ወዳልተሠራባት ምድረ በዳ ቢሄድና ከእንጨት ፍሬ ብቻ ቢበላ፣ ሥጋ ባይበላ ወይን ባይጠጣ ወደ ልዑል ሁልጊዜ ቢጸልይ ምሥጢር እንደሚገለጥለት መነገሩ
-ዕዝራ ጽዮንን በምታለቅስ ሴት አምሳል በራእይ ማየቱ

✝️ምዕራፍ 9፦ ዕዝራ የደረሰባቸውን መከራ መዘርዘሩ

✝️ምዕራፍ 10፦ ዕዝራ በንስር አምሳል ራእይ እንዳየ

✝️ምዕራፍ 11፦ ዕዝራ ከዱር በወጣ አንበሳ አምሳል ራእይን እንዳየ

✝️ምዕራፍ 12፦ ዕዝራ ሌላ ራእይን እንዳየ

✝️ምዕራፍ 13፦ ዕዝራ ሌላ ራእይን እንዳየ፣
-በኋላ ዘመን እውነት እንደምትጠፋ፣ ሐሰት እንደምትጸና መነገሩ
-ዕዝራ በአርባ ቀናት ኻያ አራት መጻሕፍትን እንዳስጻፈ


✝️ የዕለቱ ጥያቄዎች ✝️
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ስለኃጥኣን ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በመጨረሻው ፍርድ መከራን ይቀበላሉ
ለ. በዚህ ዓለም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ቸል ብለው ይኖራሉ
ሐ. ሰፊውን ዓለም በጠባብ ዓለም ለውጠውታል
መ. ሁሉም
፪. ሄኖክ የበለጠ ምሥጢር እንዲገለጥለት ምን አድርግ ተባለ?
ሀ. ወደ ምድረ በዳ ሂድ
ለ. ጹም፣ ጸልይ
ሐ. ሥጋ አትብላ፣ ወይን አትጠጣ
መ. ሁሉም
፫. ለዕዝራ ባዘነችና በምታለቅስ ሴት አምሳል የተገለጠችለት ማን ናት?
ሀ. ጽዮን
ለ. ባቢሎን
ሐ. ግብጽ
መ. ፋርስ
፬. ዕዝራ ክርስቶስን በምን አምሳል አየው?
ሀ. በንስር
ለ. በአንበሳ
ሐ. በነምር
መ. በርግብ

https://youtu.be/uRKZfeONw_w?si=Q5ijXtBqo5Kg90vF

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Jan, 08:05


ራሳችንን ቆም ብለን እንመርምር።

ከእያንዳንዱ ንግግራችን ጀርባ ያለው ዋና ሐሳብ ምንድን ነው? እውነት ያንን ሐሳብ እግዚአብሔር ይወደዋል?

አይሁዳዊ ኅሊናን እናስወግድ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Jan, 01:55


መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ክፍል 1

ምዕራፍ 1፦ ዕዝራ ሌላ ስሙ ሱቱኤል እንደሆነ
-ዕዝራ የሚያስደነግጥ ራእይ እንዳየ

ምዕራፍ 2፦ የሰው እእምሮ ውሱንነት መነገሩ
-ስለዛፎችና ስለባሕር ምሳሌ
-ዓለም የጻድቃንን ተስፋ ማስቀረት እንደማይችል መነገሩ

ምዕራፍ 3፦ ስለ ዓለም ፍጻሜ መነገሩ
-ብዙዎች ያልጠረጠሩት እንደሚነግሥ መነገሩ
-በብዙ ሀገሮች ሽብር እንደሚሆን መነገሩ

ምዕራፍ 4፦ በምጽአት ክፋት እንደምትደመሰስ፣ ተንኮልም እንደምትጠፋ፣ ሞት ድል እንደሚነሡ መነገሩ
-ዕዝራ ዳግመኛ ሰባት ቀን ቢጾምና ቢጸልይ የበለጠ ሞሥጢር እንደሚያይ መነገሩ

ምዕራፍ 5፦ ጻድቃን ሰፊውን ዓለም ተስፋ አድርገው ጠባቡን እንደሚታገሡት፣ ኃጥኣን ግን ጠባቡን ታምነው ሰፊውን እንደማያገኙት መነገሩ
-የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የጠበቁ ብፁዓን እንደሆኑ መነገሩ

ምዕራፍ 6፦ እግዚአብሔር እገሌ ይሙት ባለ ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው እንደምትለይ
-የፍርድ ቀን ለአንድ ጊዜ እንደሆነች መነገሩ

ምዕራፍ 7፦ ዕዝራ ራእይ እንዳየና እንደጸለየ


የዕለቱ ጥያቄዎች
፩. "ሱቱኤል" እየተባለ የተጠራው ማን ነው?
ሀ. ዘካርያስ
ለ. ዕዝራ
ሐ. ሐጌ
መ. ዘሩባቤል
፪. ስለዓለም ፍጻሜ መጨረሻ ምልክት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የጽድቅ መንገድ ትሠወራለች
ለ. ሃይማኖት ከሀገር ትጠፋለች
ሐ. በደል ይበዛል
መ. ሁሉም
፫. ስለ ፍርድ ቀን ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የፍርድ ቀን የዚህ ዓለም መጨረሻ ናት
ለ. የፍርድ ቀን ለአንድ ጊዜ ናት
ሐ. ያኔ አንዱ ለአንዱ መለመን አይችልም
መ. ሁሉም

https://youtu.be/7C5M7e01eV4?si=vMbPGoMk2Ou_DB44

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

09 Jan, 19:19


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 99 💙💙

▶️፩. "የሕዝቡም አለቃዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከቀሩትም ሕዝብ ከዐሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም ዘጠኙም በሌላዎች ከተማዎች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ" ይላል። ዐሥሩ ክፍል እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ አሥሩ ክፍል የተባሉት እስራኤላውያን ሁሉ ናቸው። ከአሥሩ አንዱ ክፍል የተባሉት በኢየሩሳሌም ከተማ የተቀመጡት ናቸው።

▶️፪. "በመዝሙርም፣ በጸናጽልም፣ በበገናም፣ ለማድረግ ወደ እስራኤልም ያመጧቸው ዘንድ ሌዋውያኑን ፈለጉ" ይላል (ነህ.12፥27)። የመዘመርና የዜማ መሣሪያዎችን የመያዝ ሥልጣን ለሌዋውያን ብቻ ነበር?

✔️መልስ፦ አዎ ለሌዋውያን ብቻ የተሰጠ ሥርዓት ነበር። እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ የተመረጡ የሌዊ ነገዶች ናቸው። የዜማ መሣሪያዎችን የሚጠቀሙ በተለየ የተመረጡ መዘምራንም ነበሩ።

▶️፫. "ቆመውም ኀጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን ኀጢአት ተናዘዙ" ይላል (ነህ.9፥2)። ኑዛዜያቸው በአደባባይ ወይንስ በየግል ለካህናቱ ነበር? ከዚህ ጋር አያይዤ አንድ ሰው ቤተ ክርስቲያን ሄዶ በእግዚአብሔር ፊት ስለ ኀጢአቱ ቢያለቅስና ቢናዘዝ እንደ ንስሓ ይቆጠርለታል? ወይስ ለካህን የግድ ማሳየት አለበት?

✔️መልስ፦ እንደተናዘዙ ተገልጿል። እንዴት አንደተናዘዙ ዝርዝር ጉዳዩን ግን መጽሐፍ ቅዱሱ አይገልጽም። በየግል ይሆን በማኅበር የተናዘዙት አልተገለጸም። አሁን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ አንድ ሰው ኃጢአት ከሠራ የግድ ንስሓ አባት ላይ ሄዶ ንስሓ መግባት ይገባዋል።

▶️፬. ነህምያ እና ዕዝራ የተለያዩ ናቸው? ሲያገለግሉት የነበረው ንጉሥ ተመሳሳይ ነበር? ነህምያ ቤተ መቅደሱ ሲሠራ ነበር ወይስ ቅጥሩን ብቻ ነው የሠራው?

✔️መልስ፦ ነህምያና ዕዝራ በአንድ ዘመን ይኖሩ የነበሩ የተለያዩ ሰዎች ናቸው። ስለ ነህምያ ቅጥር እንደሠራ ነው መጽሐፍ ላይ የተጻፈው። ቤተ መቅደሱ ሲሠራ ይኖር ወይም አይኖር የተገለጸ ነገር አላገኘሁም። አዎ ሁለቱም ተማርከው በነበሩበት ሀገር ንጉሡ ያው አርጤክስስ ነበር።

▶️፭. ወደ ባቢሎን የተማረኩት ሁለቱ ነገድ ነገደ ይሁዳና ነገደ ብንያም ብቻ ናቸው? አሥሩስ?

✔️መልስ፦ ወደ ባቢሎን ተማርከው የነበሩት ሁሉም ናቸው። መጀመሪያ አሥሩ ነገድ ተማረኩ። ቀጥለው ሁለቱ ነገድ ተማርኩ። ሲመለሱ በአንድነት ተመልሰዋል።

▶️፮. እነ ዘሩባቤ፣ ነህምያ፣ ዕዝራ፣ ነቢዩ ኤርምያስ የነበሩበት ዘመን ተመሳሳይ ነበር? ከሆነ እንዴት አብረው አልተነጋገሩም?

✔️መልስ፦ አዎ በተመሳሳይ ዘመን የነበሩ ነቢያት፣ ካህናት ናቸው። አብረው ይነጋገሩ እንደነበረ ወይም እንዳልነበረ የተገለጸ ነገር አላገኘሁም። ሁሉም ግን ቤተ መቅደስ እንዲሠራ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ተጽፏል።

▶️፯. መጽሐፈ ነህምያ የእስራኤል ልጆች እያለ ያነሣል። ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ እስራኤልና ይሁዳ አንድ ሆነዋል? ይሄ መጽሐፍ የሚተርከው ከምርኮ ስለተመለሱት ይሁዳ ነው ወይስ እስራኤልና ይሁዳ ተብለው ከመከፈላቸው በፊት እንደነበረው ስለ ሙሉ እስራኤላውያን? ተማርኮ የነበረስ ሙሉ እስራኤል ነበር እንዴ?

✔️መልስ፦ ተማርከው የነበሩት ሁሉም ናቸው። ከምርኮ በኋላ በአንድ ሀገር፣ በአንድ ንጉሥ እየተዳደሩ ኖረዋል።

▶️፰. "ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተማዎቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውሃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ። እግዚአብሔርም ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓፊውን ዕዝራን ተናገሩት" ይላል። በውሃው በር ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የውሃ በር የሚባለው ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውሃ ለማስገባት የሚጠቀሙበት በር ነበር።

▶️፱. “በየጊዜውም ለእንጨት ቍርባን ለበኵራቱም ሥርዓት አደረግሁ። አምላኬ ሆይ፥ በመልካም አስበኝ” ይላል (ነህ.13፥31)። የእንጨት ቁርባን ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሁለተኛው ቤተ መቅደስ ከታነጸ በኋላ እንጨት እንደ መብዓ ለቤተ መቅደስ ይሰጥ ነበረ። ያንን የእንጨት ቁርባን ይለዋል።

▶️፲. "በዚህም ወር በኻያ አራተኛው ቀን የእስራኤል ልጆች ጾመው ማቅም ለብሰው በላያቸውም ትቢያ ነስንሰው ተከማቹ" ይላል። በምን ምክንያት ነበር እንደዚህ የሆኑት?

✔️መልስ፦ ከምርኮ በኋላ እስራኤላውያን የቀድሞውን ሕገ በዓላት ሲሰሙ፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ሲሰሙ እስከዛሬ ባጠፉት ጥፋት ተጸጽተው፣ ተናዝዘው በቀድሞው በደላቸው አልቅሰዋል፣ ማቅ ለብሰዋል።

▶️፲፩. ነህ.10፣38 ላይ “ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን። ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት” ይላል። የአሥራቱን አሥራት ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት ሲል ቀሪውስ ቤተ እግዚአብሔር አይገባም ማለት ነው? ወይስ ለምን አገልግሎት ነው የሚውል?

✔️መልስ፦ ሁሉም አሥራት ወደ ቤተ መቅደስ ይመጣል። ከዚያም የሌዊ ወገኖች በአሥራቱ ይተዳደራሉ። ሌዋውያን ደግሞ ከተቀበሉት አሥራት የአሥራት አሥራት ለቤተ መቅደስ ያወጡ ነበረ። ያ አገልግሎቱ ለድኻ አደጎች፣ ለመጻተኞች ነበር።

▶️፲፪. ነህ.12 ላይ “እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር። የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ። ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ” ይላል። ግልጽ ቢያደርጉልኝ ሌዋውያን እና የአሮን ልጆች ክህነታቸው ይበላለጣል ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ። ምንም እንኳ የአሮን ልጆችም ሌዋውያን ቢሆኑም ከሌሎች ሌዋውያን ግን ከፍ ያለ መዓርግ ነበራቸው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

09 Jan, 08:33


የእስጢፋኖስ መንገድ
ለእውነት እስከ ሞት መታመን።
እኒህ ድንጋይ ያነሡትኮ አላዋቂነታቸው ሸፍኗቸው እንጂ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የሚነግራቸውን ሰው አይገድሉትም ነበር።

ብንችል እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ እንሁን። አርአያ እናድርገው። ባንችል ግን ቢያንስ ዘለዓለማዊ የሕይወት ትምህርት በሚያስተምሩን ላይ ድንጋይ አናንሳ።

ድንጋይ ለእስጢፋኖስ የሰማዕትነትን ክብር ያገኘበት ሲሆን፣ ድንጋይ ላነሡት ደግሞ የሕይወት ትምህርትን የሚነግራቸውን ሰው ያጡበት ነው።

የንግግራችን፣ የሐሳባችን፣ የድርጊታችን ማዕከል ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን። እውነት ሐሳባችን ወይም ንግግራችን ወይም እያንዳንዱ ተግባራችን ወደ ዘለዓለማዊው ሕይወት ለምናደርገው ጉዞ ግብአት ይሆናል??! ራስን ቆም ብሎ መመርመር ይገባል።

የሰማዕቱ በረከት ይደርብን

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

09 Jan, 03:53


💜 መጽሐፈ ነህምያ ክፍል 2 💜

💜ምዕራፍ 8፦ ዕዝራ የእግዚአብሔርን ሕግ ለሕዝቡ እንዳነበበ
-እስራኤላውያን የዳስ በዓልን እንዳከበሩ

💜ምዕራፍ 9፦ እስራኤላውያን ስለኃጢአታቸው ማዘናቸውና ኃጢአታቸውን መናዘዛቸው
-ዕዝራ የባለፈውን ዘመን እያስታወሰ እንደጸለየ

💜 ምዕራፍ 10፦ እስራኤላውያን ቃል ኪዳን እንዳደረጉ

💜ምዕራፍ 11፦ እስራኤላውያን በየርስታቸውና በየከተማቸው እንደተቀመጡ

💜ምዕራፍ 12፦ የሌዋውያን ስም ዝርዝር መጻፉ

💜ምዕራፍ 13፦ እስራኤላውያን በሙሴ መጽሐፍ መሠረት ከአሕዛብ መለየታቸው
-እስራኤላውያን ሰንበትን በሚገባ እንዲያከብሩ መነገሩ


💜 የዕለቱ ጥያቄ 💜
፩. በመጽሐፈ ነህምያ መሠረት ለእስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ሕግ ያነበበላቸው ማን ነበር?
ሀ. ነህምያ
ለ. ዕዝራ
ሐ. ቀድምኤል
መ. ሐናንያ

https://youtu.be/gXqIL6W5ogA?si=yUFE4r50F7nCLzwI

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

08 Jan, 18:18


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 98 💙💙

▶️፩. ነህምያ የሠራው ቤተ መቅደሱን ወይስ የኢየሩሳሌምን ቅጥር?

✔️መልስ፦ ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንዳሠራ ነው የተጻፈው። ቅጽሯን ነው በ52 ቀን ያጠናቀቀ።

▶️፪. "እነርሱም በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ። የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሷል በሮቿም በእሳት ተቃጥለዋል አሉኝ" ይላል። የፈረሰው የኢየሩሳሌም ቅጥር ብቻ ነው ወይስ ቤተ መቅደሱም ነው።

✔️መልስ፦ ቤተ መቅደሱም ቅጥሩም ፈርሶ ነበር። ቤተ መቅደሱ መሠራቱን በመጽሐፈ ዕዝራ ተመልክተናል። በዚህ በመጽሐፈ ነህምያ ደግሞ ቅጥሩ መሠራቱ ተገልጿል።

▶️፫. ነህ.3፥1-2 ላይ "የበግ በርና የዓሣ በር" ተብለው የተጠቀሱት ምን ዓይነት በሮች ናቸው?

✔️መልስ፦ የበግ በር የሚባለው በጎችን ወደ ኢየሩሳሌም ከተማዋ አደባባይ ለማስገባት ያገለግል የነበረ በር ነው። የዓሣ በር የሚባለው ደግሞ በአጠገቡ ዓሣ ይሸጥበት የነበረ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ የሚያስገባ ሌላ በር ነው። ስለነበር የተሰጠ ስም ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

08 Jan, 12:11


የአእላፋት ዝማሬ አዘጋጆች እና በዚህ ውብ ሥርዓት ለተገኛችሁ
እግዚአብሔር ረጅም እድሜን ይስጥልን

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

08 Jan, 10:42


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 97 💙💙

▶️፩. "ሌዋውያንንም እንዲያገለግሉ ዳዊትና አለቃዎቹ ከሰጧቸው ናታኒም ውስጥ ሁለት መቶ ሃያ ናታኒም አመጡ እነዚህም ሁሉ በስም በስማቸው ተጠሩ" ይላል (ዕዝ.8፥20)። ናታኒም ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ለቤተ እግዚአብሔር የተሰጠ አገልጋይ ማለት ነው።

▶️፪. ዕዝ.6፥17 እና ዕዝ.8፥35 ላይ የተጠቀሱት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ቁጥራቸው ይለያያል። አይጋጭም ወይ?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ዕዝ.8፥35 ላይ የቀረበው እስራኤላውያን በምርኮ ከነበሩበት ሀገር ስለተመለሱ ያቀረቡት መሥዋዕት ነው። ዕዝ.6፥17 ያለው ደግሞ ቤተ መቅደስ በመሠራቱ ለቅዳሴ ቤቱ የቀረበ መሥዋዕት ነው። ለተለያዩ ሁነቶች የቀረቡ መሥዋዕቶች ስለሆኑ አይቃረንም።

▶️፫. ዕዝ ፱፥፲፩ ፡፲፪ "አሁንም ትበረቱ ዘንድ የምድሩንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ ልጆቻችሁም ለዘለዓለም ይወርሷት ዘንድ" ይላል። የሚወርሱት ርስት ስለከነዓን ነው ወይስ ስለመንግሥተ ሰማያት ስለየትኛው ርስት ነው የነገራቸው?

✔️መልስ፦ ለጊዜው የተነገረው ስለከነዓን ነው። ለዘለዓለም ትወርሷት ዘንድ የሚለው ለብዙ ዘመን ወርሳችኋት ትኖሩ ዘንድ ማለቱ ነው። ፍጻሜው ስለመንግሥተ ሰማያት ነው። መልካም ሥራን ሠርታችሁ፣ በእግዚአብሔር አምናችሁ ዘለዓለማዊት መንግሥተ ሰማያትን ውረሷት ማለት ነው።

▶️፬. “ሚስቶቻቸውን ይፈቱ ዘንድ እጃቸውን ሰጡ” ይላል (ዕዝ.10፥19)። እዚህ ላይ አንድ ሰው ከአሕዛብ ወይንም ከመ*ና-ፍ/ቃን ቢያገባ በኋላ በሃይማኖት ምክንያት መፋታት ይገባል?

✔️መልስ፦ መጀመሪያውንም በሃይማኖት የማትመስለውን/የማይመስላትን ማግባት አይገባም። ከተጋቡ በኋላ አንዱ ሃይማኖቱን ቢተው ግን ወደ ትክክለኛ ሃይማኖቱ እንዲመለስ ደጋግመው ይምከሩት። ካልተመለሰ መፋታት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

08 Jan, 04:42


💟 መጽሐፈ ነህምያ ክፍል 1 💟

💟ምዕራፍ 1፦ ነህምያ የኢየሩሳሌም ቅጥር መፍረሱን ሰምቶ እንዳዘነና እንደጸለየ

💟ምዕራፍ 2፦ ንጉሡ አርተሰስታ የነህምያን ማዘን አይቶ ለምን እንዳዘነ መጠየቁ
-ንጉሥ አርተሰስታ ለነህምያ የኢየሩሳሌምን ከተማ እንዲሠራ መፍቀዱ
-ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ለመሥራት እንዳስተባበረ

💟ምዕራፍ 3፦ እስራኤላውያን የኢየሩሳሌም ከተማን ቅጥሮቿንና ቤቶቿን መሥራት እንደጀመሩ

💟ምዕራፍ 4፦ ነህምያ ጠላቶቹን እንደተቋቋመ፣
-እስራኤላውያን ጠላት ቢነሣባቸውም ሰይፍ በወገባቸው ታጥቀው ይሠሩ እንደነበረ

💟ምዕራፍ 5፦ ረኃብ በእስራኤል መከሠቱ

💟ምዕራፍ 6፦ ጠላቶች በነህምያ ላይ ሴራ ማሴራቸው
-የኢየሩሳሌም ቅጥር ተሠርቶ መጠናቀቁና የእስራኤል ጠላቶች ሁሉ ይህንን ሰምተው መደናገጣቸው

💟 ምዕራፍ 7፦ ከስደት የተመለሱ የአይሁድ ስም ዝርዝር መገለጡ


💟 የዕለቱ ጥያቄዎች 💟
፩. የኢየሩሳሌምን መፍረስ ሰምቶ በማዘኑ ንጉሥ አርተሰስታ የይለፍ ደብዳቤ ሰጥቶ ኢየሩሳሌምን ይሠራ ዘንድ የፈቀደለት የንጉሡ የጠጅ አሳላፊ ማን ነበር?
ሀ. ዕዝራ
ለ. ነህምያ
ሐ. ሰንባላጥ
መ. ጦብያ
፪. እስራኤላውያን ኢየሩሳሌምን እንዳይሠሩ ጠላቶች በተነሡባቸው ጊዜ ምን አደረጉ
ሀ. ሥራውን ትተው ጠላቶቻቸውን ገጠሙ
ለ. በወገባቸው ሰይፍ ታጥቀው ሥራቸውን ቀጠሉ
ሐ. ለጠላቶቻቸው ጉቦ ከፍለው ሥራቸውን ቀጠሉ
መ. ሀ እና ሐ
፫. ነህምያ ያሠራው የኢየሩሳሌም ቅጥር በስንት ተሠርቶ ተጠናቀቀ?
ሀ. በሁለት ዓመት
ለ. በአምሳ ሁለት ቀን
ሐ. በአርባ ስምንት ቀን
መ. በአራት ዓመት

https://youtu.be/Li-yqbLNZbQ?si=UxRlc0O2kaRBBOVl

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Jan, 18:49


መጽሐፈ ነሕምያን ከምዕራፍ 1 እስከ ምዕራፍ 7 እናጥና።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Jan, 18:29


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 96 💙💙

▶️፩. ዕዝ.2፥65 "ወንዶችና ሴቶች መዘምራንም ነበሯቸው" ይላል። በብሉይ ኪዳን የሴቶች መዘምራት አገልግሎት እንዴት ነበር? በጉባኤ ላይ መዘመር ይችሉ ነበር? በሐዲስ ኪዳንስ 1ኛ ቆሮ.14፥34 ላይ "ሴቶችም በቤተ ክርስቲያን ዝም ይበሉ። ሊታዘዙ እንጂ ሊናገሩ አልተፈቀደምና ኦሪትም እንዲህ ብሏልና ለሴት በቤተ ክርስቲያን መናገር ክልክል ነው" ይላል። አሁን ላይ ሴቶች በዐውደ ምሕረት ሲያገለግሉ እናያለን። በመ*ና_ፍ/*ቃን ዘንድ ደግሞ በስብከት ጭምር ሲሳተፉ እናያለን። በአጠቃላይ ይህ ነገር እንዴት ይታያል መምህር?

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን ሴቶች ነቢያት፣ መዘምራት ይሆኑ ነበር። ነገር ግን ሲዘምሩ የሴቶች መሪ ሆነው ነው እንጂ የወንዶችም መሪ ሆነው አይደለም። በብሉይ ኪዳን ዮዲትም ማርያም እኅተ ሙሴም የሴቶች መሪ ሆነው እንደዘመሩ ነው የተጻፈ። በሐዲስ ኪዳን ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ዝም ይበሉ ተብሏል። ወንዶች ባሉበት ጉባኤ መስበክም ዘማሪት ሆኖ ዐውደ ምሕረት ላይ መውጣትም አይገባም።

▶️፪. ዕዝ.1፥9-10 የተዘረዘሩት ቁጥር 2499 እና ዕዝ.1፥11 ላይ የተጠቀሰው ድምር 5400 እኩል አይደለምሳ?

✔️መልስ፦ 5400 የተባሉ በዝርዝር ካልተገለጹት ከሌሎች የወርቅ ዕቃዎች ጋር ተደምሮ ነው።

▶️፫. ዕዝ.1፥10 ዳካ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ትልቅ ሰሐን እንደማለት ነው

▶️፬. ጠላቶች ለንጉሥ አርተሰስታ ደብዳቤ ሲልኩ
"አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጡ ጌታቸው ንጉሥ ይወቅ" ብለው ነውና የጻፉት "ጌታችን" በማለት ፋንታ ለምን "ጌታቸው" ብለው ጻፉ?

✔️መልስ፦ ራስን አርቆ መናገር ልማደ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ጌታቸው ያለው ጌታችን ለማለት ነው።

▶️፭. "የአምላካችንን ቤት መሥራት ለእኛና ለእናንተ አይደለም" ይልና "እኛ ራሳችን ግን ቂሮስ እንዳዘዘን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ቤት እንሠራለን" ይላል (ዕዝ.4፥3)። መሥራቱ "ለእኛና ለእናንተ አይደለም" ካለ በኋላ "እኛ እንሠራለን" ሲል አልገባኝም።

✔️መልስ፦ ፀረ ይሁዳና ፀረ ብንያም የነበሩ ጠላቶች ቤተ መቅደስን ከእነዘሩባቤል ጋር ሆነው ለመሥራት ፈልገው ነበር። በዚህ ጊዜ እነዘሩባቤል እኛና እናንተ በአንድነት አንሠራም። ቤተ መቅደስን መሥራት የሚገባን እኛ ብቻ ነን ብሏል። ይህን ለመግለጽ የተጻፈ ነው።

▶️፮. የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እግዚአብሔርን ያመልክ ነበር? የእግዚአብሔር መንፈስ የማያምኑትን ስዎች ሲያነሳሳ ፈቃዳቸውን አስገድዶ ነው ወይስ እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ ቂሮስ ንጉሠ ፋርስ እግዚአብሔርን ያመልክ ነበር። መንፈስ ቅዱስ እንደ በለዓም እንደ ቀያፋ ያሉትን ሰዎች ፊታቸውን ጸፍቶ አፋቸውን ከፍቶ ያናግራቸዋል። እግዚአብሔር አያስገድድም ነገር ግን ተናጋሪዎቹ ሳይረዱት ራሳቸው ፈቅደው እንዲናገሩት ያደርጋል። ምሳሌ ቀያፋ አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል ያለው ራሱ ወዶና ፈቅዶ ነው። ነገር ግን ራሱ ወዶ ቢናገረውም ይህ ሐሳብ የእግዚአብሔር ሐሳብ ስለሆነ አፉን ከፍቶ አናገረው ተብሏል።

▶️፯. "የአምላካቸው ዐይን ግን በአይሁድ ሽማግሌዎች ላይ ነበረ። ይህም ነገር ወደ ዳርዮስ እስኪደርስ ድረስ መልሱም በደብዳቤ እስኪመጣ ድረስ አልከለከሏቸውም" ይላል (ዕዝ.5፥5)። የአምላካቸው ዐይን ግን በአይሁድ ሽማግሌዎች ላይ ነበረ ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የአምላካቸው ረድኤት አልተለያቸውም ነበረ ማለት ነው።

▶️፰. ዕዝ.2፥64 ከላይ ያለውን ስንደምረው ግን 42360 አይመጣም።

✔️መልስ፦ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ያልተዘረዘሩትን ጨምሮ 42360 ብሏል እንጂ ከላይ ያሉትስ ተደምረው ይህን አያህሉም። 2,172+372+775+2,812
+1,254+945+760+642
+623+1,222+666+2,056
+454+98+323+112+223
+95+123+56+128+42+743
+621+122+223+52+156
+1,254+320+725+345
+3,630+973+1,052+1,247
+1,017+74+128+139+392+652= 29,818 ይሆናል። ከእነዚህ ጋር ያልተጠቀሱትም ተደምረው 42360 ተብለዋል።

▶️፱. ዕዝ.3፥12 የፊቱን ቤተ መቅደስ የሚያውቁ ሽማግሌዎች ለምን እንደገና በመሠራቱ ያለቅሳሉ መደሰት ሲገባቸው?

✔️መልስ፦ የደስታ ለቅሶ ነው እንጂ የኀዘን አይደለም። በጣም ደስ ስላላቸው የደስታ እንባ አነቡ ማለት ነው።

▶️፲. ዕዝራ ቀዳማዊ የተባለው መጽሐፈ ዕዝራን ነው ወይስ ዕዝራ ሱቱኤልን ነው?

✔️መልስ፦ ዕዝራ ቀዳማዊ የሚባለው ይህ መጽሐፈ ዕዝራ ነው።

▶️፲፩. የዕዝራና የኤርምያስ ታሪክ በአንድ ወቅት ዘመን የነበረ ታሪክ ነው?

✔️መልስ፦ አዎ በአንድ ዘመን የነበሩ ናቸው። ሁለቱም በምርኮ የነበሩ ሲሆኑ ሁለቱም በምርኮ ሳሉ ትንቢትን ይናገሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው።

▶️፲፪. "ከቴልሜላ ከቴላሬሳ ከክሩብ ከአዳን ከኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም" ይላል (ዕዝ.2፥59)። አብረው ወጡ እንጂ እስራኤላውያን አይደሉም ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ እስራኤላውያን ነን ብለው መጥተዋል። ነገር ግን የትውልድ ሐረጋቸውን በቅደም ተከተል ማሳወቅ አልቻሉም።

▶️፲፫. ዕዝ.2፥62-63 "እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ። ነገር ግን አልተገኘም ከክህነትም ተከለከሉ። ሐቴርሰታም በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳን አትበሉም አላቸው" ይላል ሲል ካህናት እንዳይሆኑ ተከለከሉ ወይስ ክህነት ኖሯቸው ከማገልገል ተከለከሉ?

✔️መልስ፦ በስም የካህናት ዘሮች ነን ብለው ካህናት እንደሆኑ አስበው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን የትውልድ መጽሐፍ አቅርቡ ሲባሉ ማቅረብ ባለመቻላቸው ከክህነታቸው ተሽረዋል። ይህን ለመግለጽ የተነገረ ነው።

▶️፲፬. ትውልዳቸውን ፈለጉ መባሉ በእውኑ የማን ልጆችና የልጅ ልጆች መሆናቸው ጠፍቶባቸው ነው? ኡሪምና ቱሚም የቦታ ወይስ የሰው ስሞች ናቸው?

✔️መልስ፦ ኡሪምና ቱሚም በደረት ኪስ ይደረጉ የነበሩ እንደ መዓድን ያሉ ናቸው። ሊቀ ካህናቱ በደረት ኪሡ ይይዛቸው ነበር።

▶️፲፭. ፋርስና ባቢሎን የአንድ ሀገር ስሞች ናቸው?

✔️መልስ፦ ፋርስ በአሁኑ ጊዜ ኢራን የሚባለው ቦታ ነው። ባቢሎን በአሁኑ ጊዜ ኢራቅ ናት። በዚያን ዘመን ሁለቱም በአንድነት ይገዙ ስለነበረ ነገሥታቱ የፋርስ ወይም የባቢሎን ይባሉ ነበር።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Jan, 13:23


እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ

የመጽሐፈ ዕዝራ ጥያቄዎችን የትላንትናዎችንም የዛሬዎችንም ዛሬ እመልሳለሁ። የቀረ ጥያቄ ካላችሁ አምጡት።

መልካም በዓል

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Jan, 04:11


🧡 መጽሐፈ ዕዝራ ክፍል 2 🧡

🧡ምዕራፍ 6፦ ዳርዮስ በባቢሎን ቤተ መዛግብት ያሉ መጻሕፍት እንዲመረመሩ ማዘዙ
- ቤተ መቅደስ ተሠርቶ መጠናቀቁ

🧡ምዕራፍ 7፦ ዕዝራ ለእስራኤል ሥርዓትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ እንደነበር
-ንጉሥ አርተሰስታ (አርጤክስስ) የእግዚአብሔርን ቤት በሚሠሩ አገልጋዮች ግብርና ቀረጥ እንዳይጣልባቸው ማዘዙ

🧡ምዕራፍ 8፦ ከባቢሎን ስለወጡት አይሁድ መነገሩ
-እስራኤል ጾምን እንዳወጁ፣ እግዚአብሔርን እንደለመኑና እርሱም እንደሰማቸው

🧡ምዕራፍ 9፦ ዕዝራ እስራኤላውያን ከአሕዛብ ጋር ተጋብተው ባየ ጊዜ እንዳዘነና እንደጸለየ

🧡ምዕራፍ 10፦ እስራኤላውያን ከአሕዛብ ሚስቶቻቸው (ባሎቻቸው) እንደተለዩ


🧡 የዕለቱ ጥያቄዎች 🧡
፩. ሁለተኛው ቤተ መቅደስ ተሠርቶ የተጠናቀቀው መቼ ነው?
ሀ. በንጉሡ ቂሮስ መንግሥት በመጀመሪያው ዓመት
ለ. በንጉሡ ዳርዮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት
ሐ. በንጉሡ ቂሮስ መንግሥት በስድስተኛው ዓመት
መ. በንጉሡ ዳርዮስ በመጀመሪያው ዓመት
፪. በመጽሐፈ ዕዝራ መሠረት የእግዚአብሔርን ቤት በሚሠሩ ሰዎች ግብርና ቀረጥ እንዳይጣል ያደረገው ንጉሥ ማን ነው?
ሀ. ንጉሥ አርጤክስስ
ለ. ንጉሥ አርተሰስታ
ሐ. ንጉሥ ሰናክሬም
መ. ሀ እና ለ

https://youtu.be/fiB6iAmS8V4?si=UYaMrTadcC6JM7iL

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Jan, 14:47


እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ
"አንበሳ ተንሥአ እምገዳም
ውእቱኬ ወልድ ውእቱ"
ድንግል ማርያም ገዳመ ዕዝራ ናት። ዕዝራ ከገዳም አንበሳ ሲወጣ አይቷል። አንበሳ የተባለ ክርስቶስ ነው።

አንበሳ ሲጮኽ አራዊት ጸጥ ይላሉ። ክርስቶስ ሲናገር አጋንንት ይጠፋሉ። በጨለማ ለነበረች ዓለም ብርሃን ተወለደላት። በባርነት ለነበረች ዓለም ነጻነቷን የሚያጎናጽፋት አምላክ በሥጋ ተወለደላት።

ዮም ተወልደ እግዝእነ
ዮም ተወልደ አምላክነ
ዮም ተወልደ ቤዛነ
ዮም ተወልደ ሕይወትነ
ዮም ተወልደ ትምክህትነ
ዮም ተወልደ ፍሥሓነ

የጌታ ልደት ለእኛ ለሰው ልጆች ሁሉ ልዩ ቀን ናት።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Jan, 03:56


💛 መጽሐፈ ዕዝራ ክፍል 1 💛

💛ምዕራፍ 1፦ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ ቤተ እግዚአብሔርን ለመሥራት እንዳሰበ
- ናቡከደነፆር ማርኳቸው የነበሩ የቤተ መቅደስ ንዋያትን ንጉሥ ቂሮስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመለሳቸው

💛ምዕራፍ 2፦ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ የአይሁድ ስም ዝርዝር መጻፉ

💛ምዕራፍ 3፦ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱና የሰላትያል ልጅ ዘሩባቢል እና ወንድሞቻቸው መሠዊያን እንደሠሩ

💛ምዕራፍ 4፦ የእግዚአብሔር ቤት ሥራ እንደተቋረጠ

💛ምዕራፍ 5፦ የቤተ እግዚአብሔር ሥራ እንደገና መሠራት እንደተጀመረ



💛 የዕለቱ ጥያቄዎች 💛
፩. ከምርኮ በኋላ ቤተ እግዚአብሔርን መጀመሪያ ለመሥራት ያሰበው የፋርስ ንጉሥ ማን ነበር?
ሀ. ሚትራዲጡ
ለ. ቂሮስ
ሐ. ሲሳብሳር
መ. ናቡከደነፆር
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ቤተ መቅደሱ እንደገና በሚሠራበት ዘመን ለእስራኤላውያን ትንቢት ይናገሩ ከነበሩ ነቢያት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ሐጌ
ለ. ኤልያስ
ሐ. ዘካርያስ
መ. ሀ እና ሐ
፫. በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ መልካም ፈቃድ ተጀምሮ የነበረው ቤተ መቅደስ ሥራው ተስተጓጎለ። እንደገና የቤተ መቅደስ ሥራው እንዲቀጥል ያደረገው የፋርስ ንጉሥ ማን ነው?
ሀ. ዳርዮስ
ለ. አስተርቡዝናይ
ሐ. ተንትናይ
መ. ኢዮሴዴቅ

https://youtu.be/H0NQUPVpo3E?si=LHTUms8wxN9GsGY7

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Jan, 19:15


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 95 💙💙

▶️፩. ሄኖ.42፥5 ሲዖል (ገሃነም) ላይ የተጠቀሰው የማይጠፋ እሳት (unquenchable fire) በቀጥታ (literally) የለም አይደል? ሲዖል በጨለማ የተከበበ ቦታ ነውና እሳት ደግሞ ብርሃን አለውና።

✔️መልስ፦ ገሃነም ላይ የማይጠፋ እሳት አለ። እሳትነቱ ግን እኛ እንደምናውቀው እሳት ያለ አይደለም። ረቂቅ እሳት ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለዚያ ሲናገር እሳት ነው ግን ብርሃን የለውም ብሎታል። ብርሃን የሌለው ክፉ እሳት ነው ማለት ነው።

▶️፪. "ከኃጥኣንም ጋር አንድ ሆናችሁ እንደ ሄለይም ያለቅሳሉ" ይላል (ሄኖ.36፥22)። ሄለይም ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ዔሊ ማለት ነው።

▶️፫. "ጠልም ከእናንተ ወርቅንና ብርን ተቀብሎ እንዲወርድ ለዝናም እጅ መንሻ ስጡ" ይላል (ሄኖ.38፥35)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከላይ ጀምረን ዐውዱን ስንመለከተው ፍሬ ሐሳቡ ለዝናም እጅ መንሻ ብንሰጠው እግዚአብሔር ካላዘነበው በስተቀር መዝነም አይችልም ማለት ነው።

▶️፬. "ያፈራውን ስንዴ የምትበሉ ከላምም ጡት የተገኘ ወተቱንም የምትጠጡ የተዋረዱትንም ሰዎች በኃይላችሁ የምትረጋግጧቸው ለእናንተ ወዮላችሁ። የኃጢአታችሁን ፍዳ ፈጥናችሁ ትቀበላላችሁና ሁል ጊዜ ውኃን ለምትጠጡ ሰዎች ወዮላችሁ የሕይወት መገኛ ሕጉን ትታችኋልና ፈጽማችሁ ትጠፋላችሁ" ይላል (ሄኖ.36፥26-27)። ያፈራውን ስንዴ የምትበሉ፣ ከላምም ጡት የተገኘ ወተቱንም የምትጠጡ፣ ሁል ጊዜ ውኃን ለምትጠጡ ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ እነዚህ ሁሉ ኃጢአት ሆነው አይደለም። ከድኻ ቀምታችሁ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ብትበሉና ብትጠጡ ወዮላችሁ ለማለት ነው።

▶️፭. ሄኖ.42፥15 ኃጥኣን በሲዖል (በገሃነም) እና ጻድቃን በገነት (በመንግሥተ ሰማይ) ይተያያሉ?

✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ የተጠቀሰው በዕለተ ምጽአት ጻድቃን ከፀሐይ ሰባት እጥፍ አብርተው ንዑ ኀቤየ ሲባሉ፣ ኃጥኣን ደግሞ ከቁራ ሰባት እጥፍ ጠቁረው ሑሩ እምኔየ ሲባሉ ይተያያሉ ለማለት ነው። እንጂ ጻድቃንም በመንግሥተ ሰማያት ሲኖሩ ገሃነምን፣ ኃጥኣንም በገሃነም ሲኖሩ መንግሥተ ሰማያትን ያያሉ ማለት አይደለም።

▶️፮. "ከከበሩ መላእክትም በደናግልና በሕጋውያን ላይ ጠባቂዎችን ይሰጣል። እነርሱም ክፋት ሁሉ ኃጢአትም ሁሉ ጨርሶ እስኪጠፉ ድረስ እንደ ዓይን ብሌን ይጠብቋቸዋል። ቢተኙም ብዙ እንቅልፍን ይተኛሉ የሚፈሩትም ነገር የላቸውም (ሄኖ.38፥7)። ቢተኙም ብዙ እንቅልፍን ይተኛሉ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ በዚህ ዐውድ ብዙ እንቅልፍ የተባለው ብዙ ዕረፍት፣ ብዙ ተድላ ደስታ ያደርጋሉ ለማለት ነው። ቢተኙም ብዙ እንቅልፍን ይተኛሉ ማለት ቢሞቱም ዕረፍተ ነፍስን ያገኛሉ ማለት ነው። እንቅልፍ ምሥጢሩ እረፍት ነውና።

▶️፯. ሄኖ.41፥6 ላሜህ መላእክት እንደማይዋለዱ አያውቅም ነበር? (ማቴ.22፥30)።

✔️መልስ፦ ለጊዜው ለላሜህ ስለመሰለው ተናግሯል እንጂ መላእክት አይዋለዱም። ላሜሕ ግን ባለማወቁ የሚወልዱ መስሎት ነበር።

▶️፰. ሄኖ.42፥15 አንድ ሰው ሲሞት ኃጥእ ቢሆን አስቀድሞ [መልካም ቢሠራ ኖሮ የሚያገኛትን] ገነትን ይጎበኝ እና በኋላ ነው ሲዖል የሚወርድ። ጻድቃንም አስቀድመው ሲዖልን [እየዞሩ] አይተው በኋላ ገነት ይገባሉ የሚል ነገር አንብቤ ነበር ይህ ትምህርት ትክክል ነው?

✔️መልስ፦ እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን ልክ ናቸው ወይም አይደሉም ብለን ለመናገር መሞት አለብን። ባጭሩ ስንሞት ስለምናውቀው ትክክል ይሁን አይሁን ያን ጊዜ እናየዋለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ የሚል አላገኘሁም። ከሌሎች መጻሕፍት ካለም በገለጽኩት መሠረት ስንሞት እናውቀዋለን።

▶️፱. "ተራራው ወንድ ባሪያ እንዳልነበረ እንግዲህም ወዲህ እንደማይሆን ኮረብታም ለሴት ሴት ባሪያ እንዳይደለች ለእናንተ ማልሁላችሁ" ይላል (ሄኖ.37፥17)። የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ኮረብታም ተራራም በባሕርያቸው መገዛት የለባቸውም። እንደዚሁ ኃጢአትም የባሕርይ ሆና አልተፈጠረችም ማለት ነው። ይህንን ነገርኳችሁ ለማለት ነው።

▶️፲. ሄኖ.37፥19 "በእጇ በሠራችው ሥራ ልጅ ሳትወልድ ትሞታለች እንጂ ለሴትም መምከን አልተሰጣትም ነበር" ሲል ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ምክነት በበሽታ ምክንያት ወይም በኃጢአት ምክንያት ይከሠታል ማለት ነው።

▶️፲፩. "በጻድቃንም እጆች አልፋችሁ ትያዙ ዘንድ እንዳላችሁ ዕወቁ። አንገቶቻችሁንም ቆርጠው ይገሏችኋል ከዚያም አስቀድመው አይራሩላችሁም" ይላል (ሄኖ.37፥28)። ይህ ንባብ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ኃጥኣን ጻድቃንን ሲበድሏቸው ኖረዋል። በዚያ በደላቸው ምክንያት እግዚአብሔር በኃጥኣን ላይ ፍዳን ያመጣል። ይህን ለመግለጽ የተነገረ ምሳሌያዊ አገላለጽ ነው።

▶️፲፪. ሄኖ.37፥34 "የቀኑ ነገሮችንም ለምትለዋውጧቸው ለናንተ ወዮላችሁ" ሲል የቀኑ ነገሮች የተባሉ ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ የቀኑ ነገሮችን ማለት ቅን ነገሮችን ለውጣችሁ በክፋት ለምትኖሩ ቅንነት ለሌላችሁ ሰዎች ወዮላችሁ ማለት ነው። መልካም ሥራዎችን ሁሉ የቀኑ ነገሮች ይላቸዋል።

▶️፲፫. "ሰውነታችሁ በጽኑ መከራና በጨለማ በሚነድ በሚያላልብ መከራም ወደ ጽኑ መቻያ ትገባለች ጽኑ መቻያም ለልጅ ልጅ ዘመን ትደረጋለች" ይላል (ሄኖ.40፥11)። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ "መቻያ" ተብሎ ብዙ ጊዜ ተጽፏልና ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ መቻያ ማለት ባጠፋ ሰው ላይ ቅጣትን ማስተላለፍ ማለት ነው።

▶️፲፬. የመጽሐፉ መጨረሻ ላይ "ሄኖክ ተሠውሮ ያየው በዚህ ተፈጸመ" ይላል። ገና ሳይሠወር አይደለም ወይ ራእይ ያየ?

✔️መልስ፦ መጽሐፉ የሄኖክ ሥውር ራእይ ተፈጸመ ይላል እንጂ ከተሠወረ በኋላ ያየው ራእይ ተፈጸመ አይልም። ራእዩን ያየው ገና ሳይሠወር ነው። ያየውን ራእይ ጽፎ ለሰው ከሰጠ በኋላ ነው የተሠወረው።

▶️፲፭. ሄኖ.፴፮÷፲፭ "እንዳትፈቱ ሆናችሁ ግዝትን ለምትገዝቱ ለእናንተ ወዮላችሁ" ሲል አልገባኝም ቢብራራ?

✔️መልስ፦ በማይገባ ለምታወግዙ ወዮላችሁ ማለት ነው።

▶️፲፮. ሄኖ.፴፮÷፳፮-፴፯ "የስንዴውን ፍሬ የምትበሉ÷ ከምንጩ መነሻ ኃይልን የምትጠጡ÷ የተዋረዱትንም በኃይላችሁ የምትረግጧቸው ወዮላችሁ። ሁልጊዜ ውኃን የምትጠጡ ወዮላችሁ! ፍዳን ፈጥናችሁ ትቀበላላችሁና" ይላል። ኃይል ይበላል እንዴ? የስንዴ ፍሬ መብላት÷ ውኃ መጠጣት በደል የሚሆንበት ጊዜው አለ እንዴ? በዚህ ገጸንባብ ስንዴ÷ ኃይልና ውኃ አንድምታቸው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ጾም ገድፋችሁ ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ሁሉ የምትበሉ የምትጠጡ ወዮላችሁ ማለት ነው። እንጂ ጾም ሳንገድፍ ብንበላቸው በደል ይሆኑብናል ማለት አይደለም። ኃይልን የምትጠጡ ያሉ በኃይል ቀምታችሁ የምትጠጡ ለማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Jan, 01:30


🧡 መጽሐፈ ሄኖክ ክፍል 8 🧡

🧡ምዕራፍ 36፡- ሄኖክ ልጆቹን ጽድቅን ውደዷት በእርሷም ሂዱ እንዳላቸው

🧡ምዕራፍ 37፡- ኃጥኣን እንደሚፈረድባቸው፣ ክፉ ሥራን የሚሠሩ ሰዎች ወዮታ እንዳለባቸው
-ሐሰት ነገርንና የዝንጉዎች ነገርን መጻፍ እንደማይገባ

🧡ምዕራፍ 38፡- ለኃጥኣን ወዮታ እንዳለባቸው

🧡ምዕራፍ 39፡- የሰማይ ልጆች ሁሉ ሰማይን እንዲረዱ፣ የልዑልን ሥራ እንዲረዱ መነገራቸው
-ኃጥኣን ልዑልን እንደማይፈሩትና በዚህም ምክንያት መከራ እንደሚመጣባቸው

🧡ምዕራፍ 40፡- ለጻድቃን በጎው ነገር ሁሉ፣ ደስታውና ክብሩ እንደተዘጋጀላቸው

🧡ምዕራፍ 41፡- ኖኅ እንደተወለደ እግዚአብሔርን ማመስገኑ

🧡ምዕራፍ 42፡- ጻድቃን እያበሩ እንደሚኖሩ

🧡የዕለቱ ጥያቄዎች🧡
፩. ዐመፅንና ግፍን የሚሠሩ ሰዎች ምን ይሆናሉ?
ሀ. ፈጥነው ይጠፋሉ
ለ. ሰላም የላቸውም
ሐ. በሰይፍ ይወድቃሉ
መ. ሁሉም

https://youtu.be/gLneokEtzoM?si=7YlPfFaPVRiNf1EL

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Jan, 18:06


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 94 💙💙

▶️፩. "የእስራኤል ገዢ እግዚአብሔርም በእነርሱ በወገኖቻቸውም ሁሉ ደስ አለው" ይላል። ደስ አለው ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በባሕርይው ደስታ ነው። ለእርሱ ኀዘን አይስማማውም። አንዳንድ ጊዜ አዘነ ተብሎ ተጽፎ ቢገኝ እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ በሰውኛ ስለሆነ በሰውኛ ተገልጾ እንጂ በባሕርይው ኀዘን ኖሮበት አይደለም። ስለዚህ ደስ አለው ሲባል እንደ አዲስ የደስታ ስሜት ተሰማው ለማለት ሳይሆን ሁልጊዜም ደስተኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው።

▶️፪. ሄኖ.፴፭÷፴፭ የምድር ወርዷና ርዝመቷ ምን እንደሆነ ማወቅ የሚችል ሰው ሁሉ ማነው? ወርዷና ርዝመቷ በመጽሐፍ አይታወቅምን?

✔️መልስ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ አልተገለጸም። በሳይንስም ቢሆን ግምት እንጂ ትክክለኛ ርዝመቷና ወርዷ አይታወቅም። በመንፈሳዊ መጻሕፍትም ወርዷ ይህን ያህላል፣ ርዝመቷ ይህን ያህላል የሚል እስከዛሬ አላገኘሁም።

▶️፫. ሄኖ.33፥21 እስራኤላውያን በባቢሎን ምርኮ የቆዩት 70 ዘመን (10 ሱባኤ) ሲሆን እዚህ ላይ ግን 12 ይላል ለምን?

✔️መልስ፦ አስቀድሞ ኤልያቄም ለናቡከደነፆር ሦስት ዓመት ተገዝቷል። ቀጥሎ ሴዴቅያስ 11 ዓመት ተገዝቷል። ይህ 14 ይሆናል። በባቢሎን ደግሞ 70 ዓመት ተገዝተዋል። በጠቅላላ 84 ዓመት ሲሆን በሱባኤ 12 ይሆናል።

▶️፬. ሄኖ.33፥3 ጌታ ሰዎች እንዲጠፋ ይፈልጋልን?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ፈታሒ በጽድቅ ስለሆነ መጥፋት ያለበትን ያጠፋል። ስለዚህ በፈታሒነቱ መጥፋት ያለበትን ስለሚያጠፋ አዎ ያጠፋል።

▶️፭. ሄኖ.32፥72 እግዚአብሔር ነቢያትን የላከው ከታናሹ በግ (ከሰሎምን) መንገሥ በኋላ ነው እንዴ? ከዚያ በፊት አልላከላቸውም ነበር? (ኤር.7፥25)።

✔️መልስ፦ ነቢያት ከዚያም በፊት ተነሥተዋል። ከዚህ የተጠቀሰው ኢሳ.7፥25 የሚገልጽልንም ይህንኑ ነው። ሄኖ.32፥72ም ከሰሎሞን ጀምረው ብቻ እንደተነሡ አያመለክትም።

▶️፮. ሄኖ.31፥9 መልአኩ እንዴት ይገዳደሉበት ዘንድ ሰይፍ ይሰጣቸዋል?

✔️መልስ፦ ለጊዜው ሄኖክ ይህን በራእዩ አይቷል። መላእክት ከፈጣሪ ከታዘዙ ሰይፍን ይሰጣሉ። መጥፋት ያለበትን እነርሱ ራሳቸውም በሰይፍ ያጠፋሉ። ለሌላውም እንዲያጠፋበት ሊሰጡ ይችላሉ። ለቅዱሱ ለቴዎድሮስ በናድሌዎስ ሰይፍ እንደሰጡት (ገድለ ቴዎድሮስ በናድሌዎስን ይመልከቱ)።

▶️፯. ሄኖ.33፥39 ላይ ያለው 58 ሱባኤ የሚመጣው እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ 23ቱ የሮማ ነገሥታት እስከሚገዙበት የነበረው ዘመን ነው። የሮማውያን ዘመነ መንግሥታቸው 400 ዘመን ነው። ይህ በሱባኤ 57 ሱባኤ ከአንድ ዓመት ይተርፋል። ከአምሳ ስምንተኛው አንድ ዓመት ከተጀመረለት ብሎ 58 ይለዋል።

▶️፰. ሄኖ.35፥12 ብዙዎች በትሕትና ራሳቸውን እንደ ጭንጋፍ እንደ ትል ሲቆጥሩ ሄኖክ ግን ራሱን ከሰው ሁሉ ክቡር እያለ መጥራቱ ለምንድን ነው?ሰው ያመስግንህ እንጂ አንተ አይደለህም ይላልና መጽሐፍ (ምሳ.27፥2)።

✔️መልስ፦ ነቢያት መንፈስ ቅዱስ ሲያድርባቸው የመንፈስ ቅዱስን ቃል ይናገራሉ። ሄኖክ መታበይ ፈልጎ አይደለም እንደዚያ ያለው በላዩ ያለ መንፈስ ቅዱስ ስለሄኖክ ክቡርነት ተናግሮ ነው እንጂ። በኋላ ዘመን ድንግል ማርያም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይለኛል እንዳለችው ያለ ነው። ሁለቱንም መንፈስ ቅዱስ አናግሯቸው ነው።

▶️፱. ሄኖ.32 ያለው ራእይ ከአብርሃም ጀምሮ ስለእስራኤል ነው የሚያወራው?

✔️መልስ፦ ስለአብርሃምም ስለሌሎችም ያወራል።

▶️፲. "ሰባውን ነገሥታት ጠራ። ይጠብቋቸውም ዘንድ እኒህ እስራኤልን ጠብቁ ብሎ በእነዚህ እጅ ጣላቸው" ይላል። ሰባው ነገሥታት እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ ሰባ ነገሥታት የተባሉት 47 የጽርዕ (የግሪክ) ነገሥታትና 23 የባቢሎን ነገሥታት እንደሆኑ መተርጉማን በትርጓሜ ገልጸዋል።

▶️፲፩. "ለሐዋርያትም ታላቅ ሥልጣን እስኪሰጣቸው ድረስ ደርሼ አየሁ። ሐዋርያትም ከዕውቀት ምድረ በዳ ወደ ሆኑ ወደ አሕዛብ ሁሉ ሊያጠፏቸው ወጡ" ይላል። ሊያጠፏቸው ወጡ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ያላመኑትን በተአምራት ሊያጠፏቸው ማለት ነው። ጴጥሮስ ሐናንያና ሰጲራን፣ ሌሎችም ሐዋርያት አንዳንድ ክፉዎችን በተአምራት እንደሚያጠፏቸው የተነገረ ትንቢት ነው።

▶️፲፪. ሄኖ.፴፩÷፲፩ "ኀፍረታቸው እንደ ፈረሶችም ኀፍረት የሆነ ታላቅ ከዋክብትንም ሁሉ ሰብስቦ ያዘ። ሁሉንም እጅ እና እግራቸውን አስሮ በምድር ጉድጓድ ጣላቸው" ይላል። በዚህ ራእዩ
ኀፍረታቸው እንደ ፈረሶችም ኀፍረት የሆነ የተባሉ ምንድን ናቸው? ጣዩስ ማነው?

✔️መልስ፦ ኀፍረታቸው እንደፈረሶች እየተባሉ የተገለጹት ወደ ደቂቀ ቃኤል የወረዱ ደቂቀ ሴት ናቸው። በምድር ጉድጓድ ጣላቸው የተባለ እግዚአብሔር ነው። ይኸውም በበደላቸው ምክንያት እንደፈረደባቸው ለመግለጽ ነው።

▶️፲፫. ሄኖ.33፥14 ላይ "ከዚያም በኋላ እኒህ በጎች ወደ ቤተ መቅደስ ይገቡም እንደ ሆነ አይገቡም እንደ ሆነ እነሱን ማየት አልተቻለኝም" ሲል ከዚያ በኋላ ያለው ነገር ለሄኖክ በራእይ አልተገለጸለትም ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሄኖክ ፍጡር እንደመሆኑ ዕውቀቱ ወሰን አለበት። ራእይ ሲያይም ከፍሎ አይቷል እንጂ ሁሉን አላየም። ስለዚህ ማየት ያልተቻለውን አላየም ማለት ነው። አዎ እግዚአብሔር ስላልገለጸለት አላየም።

▶️፲፬. "መጽሐፉም በበጎች ጌታ ፊት ተነበበ። ጌታም መጽሐፊቱን በጁ አንሥቶ አንብቦ አጥፎ አኖራት" ይላል (ሄኖ.33፥20)። ይህ እንዴት ይተረጎማል?

✔️መልስ፦ የሚነበብ መጽሐፍ ኖሮ አይደለም። መጽሐፍ ሲገለጥ መልክአ ፊደሉ እንደሚታይ እግዚአብሔር ምሥጢርን ለሄኖክ ገለጠለት ማለት ነው። ጌታ አንብቦ አጥፎ አኖራት ማለት የሰዎችን ኃጢአት እያወቀ እንደታገሣቸው ለመግለጽ ነው።

▶️፲፭. ሄኖ.33፥30 ላይ "እረኞችም እስከ ነገሡበት ዘመን ደርሼ አየሁ። ሠላሳ ሰባት እረኞችም እንደዚህ አድርገው ይጠብቁ ነበር" ካለ በኋላ ቁጥር 39 ላይ "ሃያ ሦስትም እረኞች እስከ ተሾሙበት ዘመን ድረስ ደርሼ አየሁ አምሳ ስምንት ሱባኤን በየሹመቻቸው ተሾመው ጨረሱ" ይላል። ቁጥሩ አልተለያየም?

✔️መልስ፦ ሠላሳ ሰባቱ የጽርእ ነገሥታት ናቸው። ሃያ ሦስቱ የሮማውያን ነገሥታት ናቸው። ስለዚህ የተለያዩ ሀገራት ነገሥታት ስለሆኑ አይቃረንም።

▶️፲፮. "ከእኒህም ከበጎች በአንዱ ላይ ትልቅ ቀንድ እስኪበቅል አየሁ። ዐይኖቻቸውም ተገለጡ" ይላል (ሄኖ.33፥44)። ይህ ቀንድ የበቀለለት ማነው?

✔️መልስ፦ ይህ ትልቅ ቀንድ ያበቀለለት የተባለው ክርስቶስ ነው። ቀንድ ሥልጣን ነው። በአምላካዊ ሥልጣኑ ፍጥረቱን እንደሚያስተዳድር ለመግለጽ የተነገረ ነው።

▶️፲፯. ሄኖ.33፥21 ላይ "ከእነዚህም ከበጎች ሦስቱ ተመልሰው መጡ ወዳገራቸውም ገቡ" ይላል። እነዚህ ሦስቱ እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ ሦስቱ የተባሉ ከምርኮ የተመለሱት ኤርምያስ፣ ነሕምያ፣ ካልእ ዕዝራ ናቸው።

▶️፲፰. "የበጎች ጌታ እግዚአብሔርም ከዚህም ከቀደመው ቤት ፈጽሞ የሚበልጥ አዲስ የሆነ ቤትን አምጥቶ እስኪሠራ ድረስ ደርሼ አየሁ። ያንንም ቤት አምጥቶ አስቀድማ በፈረሰችው ቤት ቦታ አጸናው" ይላል (ሄኖ.34፥15)። መላእክት አውጥተው የጣሉት አሮጌና አዲስ ቤት የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አሮጌ ቤት የተባለ የኦሪት ሕግ ነው። አዲስ ቤት የተባለ የወንጌል ሕግ ነው። እንዲሁም አሮጌ ቤት የተባለች ደብተራ ኦሪት ስትሆን አዲስ ቤት የተባለች ቤተክርስቲያን ናት።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Jan, 18:06


▶️፲፱. ሄኖ.34፥26-27 ላይ "አንድ ነጭ ላም ተወልዶ አየሁት ቀንዶቹም ታላላቆች ናቸው። በጎችና አሕዛብም ሁሉ ፈርተው በየጊዜው ይለምኑታል" የተባለ ማን ነው?

✔️መልስ፦ ነጭ ላም የተባለ ክርስቶስ ነው። ንጹሐ ባሕርይ መሆኑን ለመግለጽ ጸዓዳ ላሕም ተብሏል።

▶️፳. "ከዚህም በኋላ በአሥረኛይቱ ሱባዔ ሰባት እጅ የሚሆን የዘላለም ፍርድ ይደረግባታል" ይላል (ሄኖ.35፥5)። የዘላለም ፍርድ ይላልና ገና ያልተፈጸመ ራእይ ነው? ከሆነ አሥረኛይቱ ሱባዔ ማለት መች ነው?

✔️መልስ፦ የጎደለ ሞልቶ የተረፈ ትቶ መቁጠር ልማደ መጻሕፍት ስለሆነ ነው እንጂ ምጽአት የሚደረገው ከሰባት ሺህ እስከ ስምንት ሺህ ባለው ዓመት መሆኑን ያመለክታል።

▶️፳፩. ሄኖ.35፥17 "ባለማወቅ የተሠራች ኃጢአትም እስከዘላለሙ ትጠፋለች" ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ከምጽአት በኋላ ኃጢአት አይሠራም ለማለት ነው። ኃጢአት የሠሩትም ፍዳቸውን እየተቀበሉ ይኖራሉ። ጽድቅ የሠሩትም ዘለዓለማዊ ደስታን ገንዘብ አድርገው ይኖራሉ። ሁሉም ቀድሞ በሠራው እየተጸጸተ ወይም እየተደሰተ ይኖራል እንጂ አዲስ በደልን አይበድልምና ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Jan, 04:31


💛 መጽሐፈ ሄኖክ ክፍል 7 💛

💛ምዕራፍ 31፡- ሄኖክ ስለማየ አይኅ ራእይን ማየቱ

💛ምዕራፍ 32፡- ሄኖክ ሌላ ራእይን እንዳየ

💛ምዕራፍ 33፡- ሄኖክ ሌላ ራእይን እንዳየ

💛ምዕራፍ 34፡- ምድር በማየ አይኅ እንደምትጠፋ ሄኖክ መናገሩ

💛ምዕራፍ 35፡- ሄኖክ ልጆቹ በጽድቅ መንገድ እንዲሄዱ መምከሩ

💛የዕለቱ ጥያቄ💛
፩. ሄኖክ ለልጆቹ ለእነ ማቱሳላ ምን ብሎ መከራቸው?
ሀ. በጽድቅ መንገድ እንዲሄዱ
ለ. በእውነት እንዲኖሩ
ሐ. ሕግን እንዲወዷት
መ. ሁሉም

https://youtu.be/zDXrJqHv2-M?si=ouPQ0yqnwQUGzNp9

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Jan, 17:54


✔️መልስ፦ ሰዎች ከዋክብትን ፈጣሪዎች ናቸው ብለው አምልከዋቸው ይጎዳሉ ማለት ነው። ሌላው የወቅቶች መጋቢ ከዋክብት እያሉ ሰዎች የሉም ብለው ይዋሻሉ ማለት ነው።

▶️፲፪. ሄኖ.28፥31 ላይ ምልክኤል ስለሚመግብበት ወራት ሲገልጽ "በጎችም ይንጠላጠላሉ ይጸንሳሉም" ይላል። በእነዚያ ወራት ብቻ ነው በጎች የሚጸንሱት ማለት ይቻላል ወይስ አብዛኛው በጎች ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ምልክኤል የሚመግበው ወር የመጸው ወቅት (የጥቢ ወቅት) ነው። በብዛት በጎች የሚጸንሱበትን ጊዜ ለማመልከት የተነገረ ነው። ሣሩ፣ ውሃው ሁሉ ነገር ለእንስሳት የተመቸ ወቅት ስለሆነ በወቅቱ የሚጸንሱ በጎችም ብዙ መሆናቸውን ለመግለጽ ነው። እንጂ በሌሎች ወሮችም በጎች ይጸንሳሉ።

▶️፲፫. ሄኖ.፳፮÷፩ "የፀሐይ ስሙ እንዲህ ነው የአንዱ ኦርያሬስ ሁለተኛውም ቶማስስ ይባላል" ይላል። ፀሐይ ከሚለው ስሟ ሌላ ስም ነው?

✔️መልስ፦ አዎ ፀሐይ ፀሐይ ከሚለው ስሟ በተጨማሪ ቶማስስ፣ ኦርያሬስ ትባላለች ማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Jan, 17:54


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 93 💙💙

▶️፩. "እነሆ ላም ከምድር ወጣ ያም ላም ነጭ ሆነ። ከእርሱም በኋላ አንዲት ሴት ጥጃ ወጣች" ይላል (ሄኖ.30፥4)። ላም ካለ በኋላ በወንድ አንቀጽ ወጣ፣ ነጭ ሆነ ይላልና ምሥጢሩ ምንድን ነው? አጠቃላይ እዚህ ምዕራፍ ላይ የተጠቀሱት ሴት ጥጃ፣ ጥቁር ጥጃ፣ ቀይ ጥጃ፣ ጥቋቁር ጊደሮች፣ ነጭ በሬ፣ ነጫጭ ላሞች፣ ከሰማይ የወደቀ አንድ ኮከብ፣ ብዙ ኮከቦች፣ ዝሆኖች፣ ግመሎችና አህዮች የተባሉ ምሳሌያቸው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በግእዝ ቋንቋ ላሕም ብሎ ላምም ተብሎ ይተረጎማል በሬም ተብሎ ይተረጎማል። ላም ብሎ በወንድ አንቀጽ የጠቀሰው በሬ ለማለት ነው። በዚህ የሄኖክ ራእይ ላም የተባለ አዳም ነው። ነጭ ሆነ መባሉም ባለአእምሮ (ባለዕውቀት) ሆነ ማለት ነው። ከዚያ በኋላ አንዲት ሴት ጥጃ ወጣች የተባለች ሔዋን ናት። ከአዳም ጎን ወጥታለችና። ጥቁር ጥጃ የተባለው ቃኤል ነው። ኃጥእነቱን ለመግለጽ ጥቁር ተባለ። ቀይ ጥጃ የተባለ አቤል ነው። አቤል ደሙ በቃኤል ፈስሷልና ቀይ ጥጃ ተባለ። እንደ ገና ነጭ በሬ ተወለደ መባሉ ሴት መወለዱን ለመግለጽ ነው። ጥቋቁር ጊደሮች የተባሉት ከአዳም የሚወለዱ ኃጥኣን ልጆቹ ናቸው። ነጫጭ ላሞች የተባሉት ደጋግ ልጆች ናቸው። ከሰማይ የወደቀ አንድ ኮከብ የተባለ ስማዝያ ነው። ብዙ ኮከቦች የተባሉ ከስማዝያ ጋር ከደብር ቅዱስ የወረዱት ደቂቀ ሴት ናቸው። ዝሆኖች፣ ግመሎች እና አህዮች የተባሉት ከደቂቀ ሴትና ከደቂቀ ቃኤል የተወለዱት ረጃጅም ሰዎች (ረዓይት) ናቸው።

▶️፪. "መጽሐፊቱን አነበብኋት በእርሷም የተጻፈውንም ሁሉ አነበብሁ የሰዎችንም ሥራ ሁሉ ተመለከትሁት የዚህ ዓለም ዘመን እስኪያልፍ ድረስ በዚህ ዓለም ያለ ከሥጋዊ ከደማዊ የተወለደውን ሁሉ አየሁ" ይላል (ሄኖ.27፥11)። እዚህ ላይ መጽሐፊቱን አነበብኋት ከሥጋዊ ከደማዊ የተወለደውን ሁሉ አየሁ የሚለው ምንን ለመግለጽ ነው?

✔️መልስ፦ በሰማይ ሰሌዳ ኖሮ አይደለም። ወደፊት የሚደረገውና ባለፈው የተደረጉት ነገሮች ከእግዚአብሔር ተገለጡልኝ ሲል ሄኖክ መጽሐፊቱን አነበብኳት ብሏል።

▶️፫. "ምግብናቸውን የሚጠብቁ ከዋክብትን የሚመሩ የከዋክብት ስማቸው ይህ ነው" ይላል (ሄኖ.28፥15)። ምግብናቸውን ሲል ምን ማለቱ ነው? ከዚህ ጋር ተያይዞ የከዋክብት ሻለቆች መጋቢዎች ሲባልስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ምግብና የሚለው ለፀሐይ፣ ለከዋክብት፣ ለጨረቃ ሲነገር የሚያበሩበት ጊዜ ማለት ነው። ለምሳሌ ዘፍ.1፥16 ላይ ፀሐይ ቀንን ይመግባል ይላል። በቀን ያበራል ለማለት ነው። ጨረቃና ከዋክብት ሌሊቱን ይመግባሉ ይላል። በሌሊት ያበራሉ ለማለት ነው። የከዋክብት መሪዎች፣ ሻለቆች፣ መጋቢዎች እያለ የሚጠቅሳቸው በተለያዩ ጊዜያት ከሌሎች በተለየ በወቅታቸው ጎልተው የሚያበሩ ከዋክብት ናቸው።

▶️፬. ሄኖ.27÷1 "በኃጥኣንም ወራት ክረምቶች ያጥራሉ። በእርሻቸውና በመሰማሪያቸው ያለ አዝመራቸውም በኋላ ይደርሳል" ይላል። በኃጥኣንም ወራት ክረምቶች ያጥራሉ ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ በምድር ላይ ኃጥኣን ሲበዙ እግዚአብሔር የተፈጥሮ ሕግን እንዲዛባ ያደርገዋል። ከግንቦት ከሰኔ ጀምሮ ይዘንም የነበረውን ዝናብ አሳጥሮ በሐምሌ በነሐሴ እንዲዘንም ያደርገዋል ማለት ነው። አዝመራውም በኋላ ይደርሳል መባሉ በግንቦት በሰኔ ካልተዘራና በሐምሌ በነሐሴ ከተዘራ ዘግይቶ ይደርሳል ማለት ውጤታማ አይሆንም ማለት ነው።

▶️፭. "ለዘመን ምልክት ሊሆን እስከ አሥራ አምስት ቀን ብርሃኑን ፈጽሞ ያገኛል ሦስት አምስት ክፍለ ብርሃንም ይሰጠዋል ጨረቃም በፀሐይ ሰባተኛ ክፍለ ብርሃን ያበራል። ሕፀፅ በሚያደርግበትም ጊዜ በመጀመሪያይቱ ቀን አሥራ አራተኛውን እጅ ክፍለ ብርሃን ያጣል በሁለተኛይቱም ቀን አሥራ ሦስተኛይቱን ያጣል" ይላል። ሕፀፅ ምን ማለት ነው? ክፍለ ብርሃንም ይሰጠዋል እና ያጣል ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሕፀፅ የሚለው ቃል ሐፀ-ጎደለ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን መጉደል ማለት ነው። ጨረቃ ከወጣች ጀምሮ ብርሃኗ እየጨመረ ይሄዳል። በአሥራ አምስት ቀን ጨረቃ ሙሉ ትሆናለች። ከዚያ በኋላ ደግሞ ብርሃኗን እያጎደለች ሄዳ እስከ መጥፋት ትደርሳለች። እንደገና ከፀሐይ ብርሃንን ወስዳ እየጨመረች ትሄዳለች። ይህ ዑደት እስከ ዕለተ ምጽአት ይቀጥላል። ክፍለ ብርሃን ይሰጠዋል የሚባለው ጨረቃ ከተወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በየጥቂቱ በየጥቂቱ ብርሃን እየተጨመራት ይሄዳል ለማለት ነው።

▶️፮. "የከዋክብት ሥርዐትም ሁሉ በኀጢአተኞች ላይ ይለወጥባቸዋል። በምድር ላይም የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ላይ አእምሯቸውን ይለውጣሉ" ይላል (ሄኖ.27፥7)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ላይ አእምሯቸውን ይለውጣሉ ማለት ባለማወቅ ከዋክብትን የሚያመልኩ ሰዎች ይነሣሉ ማለት ነው። የከዋክብት ሥርዓት በኃጥአን ይለወጣል ማለቱ የተፈጥሮ ዑደታቸውን እግዚአብሔር እንደሚለውጠው ያስረዳል።

▶️፯. "ሰማይ ሲወርድና ሲነጠቅ በምድርም ላይ ሲወድቅ አየሁ። በምድርም ላይ በወደቀ ጊዜ ምድርን በታላቅ ጥልቅ እንደምትሰጥም አየኋት። ተራሮች በተራሮች ላይ ሲሰቀሉ ኮረብቶችም በኮረብቶች ላይ ሲሰጥሙ ረዣዥም ዛፎችም ከግንዶቻቸው እየተነቀሉ ሲወድቁ በጥልቅ ወንዝም ሲሰጥሙ አየኋቸው" ይላል (ሄኖ.29፥4-6)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሄኖክ ያየው ራእይ ስለሆነ በራእዩ ቀጥታ ከላይ የተጠቀሱትን አይቷል። እኒህ ሁሉ ምሥጢራቸው አንድ ነው። ማየ አይኅ ተነሥቶ መሬት እንደምትገለባበጥ ለመግለጽ የተነገረ ነው።

▶️፰. ያለ ፀሐይ ብርሃን በቀር ሌላ ብርሃን ምንም ምን የላትምና በሃያ በሃያ ቀን ሌሊት ሰው መስሎ ቀን ሰማይ መስሎ ይታያል። ሰው መስሎ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ጨረቃ ሠርቅ ባደረገ በኻያ በኻያ ቀን ከአሥራ አምስት በኋላ ጥቂት ብርሃን ስለሚነሣው ሰው መስሎ ይታያል። ጥቂት መመሳሰልን መሠረት አድርጎ ሰው መስሎ ይታያል ተብሏል።

▶️፱. ጨረቃ ባንዱ ዘመን ከኮከቦች ሥርዓትና ከፀሐይ የሚያንሰው ጠንቅቆ ቢቈጥሩት አምስት ቀን ይሆናል። አምስት ቀን ሲባል ቢያብራሩልን?

✔️መልስ፦ አምስት ቀን ያንሣል ያለው የጳጉሜንን ወር ነው። እንደሚታወቀው በሁለት ወር አንድ ጊዜ ጨረቃ ጠፍ ትሆናለች። በአሥራ ሁለት ወር ስድስት ቀን ይሆናል። እንዲሁ ጠፍ የምትሆንባቸው ትርፍራፊ ደቂቃዎች አምስት ቀን ይሆናሉ። በጠቅላላው በዓመት ጨረቃ ከፀሐይ አሥራ አንድ ቀን አንሳ ታበራለች።

▶️፲. "ሰሌዳውም ሁሉ በተቃጠለ ጊዜ ብርሃኗ በሰማይ ይፈጸማል በዚያች ቀን በእርሷ ብርሃን ይሳልባታልና መጀመሪያይቱም ጨረቃ የተወለደችበት ቀን ትባላለች" ይላል (ሄኖ.26፥20)። ሰሌዳውም ሁሉ በተቃጠለ ጊዜ ሲል ሰሌዳ የተባለ የጨረቃ አንድ ክፍል ነው እንዴ? መቃጠል ሲልስ?

✔️መልስ፦ ጨረቃ ብርሃኗን የምታገኘው ከፀሐይ ነው። የፀሐይ ብርሃን ደግሞ ሙቀትም አለው። ብርሃን አግኝታ ብሩህ ስትሆን ሙቀቱም ስላረፈባት በተቃጠለች ጊዜ ተብሎ ተገልጿል። ፍሬ ነገሩ ጨረቃ ከፀሐይ የሚገባትን ብርሃን ሁሉ ወስዳ በምልአት ማብራቷን ለመግለጽ ነው።

▶️፲፩. "ከእነርሱም ጋር አራት ቀን ይገባሉ። ስለእነርሱም ሰዎች ይሳሳታሉ። በዓለሙ ቁጥርም አይቆጥሯቸውም ይስቷቸዋልና" ይላል (ሄኖ.28፥8)። ስለእነርሱም ሰዎች ይሳሳታሉ ሲል ምን ለማለት ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Jan, 04:36


💟 መጽሐፈ ሄኖክ ክፍል 6 💟

💟ምዕራፍ 26፡-
ፀሐይ በተጨማሪም ኦርያሬስ፣ ቶማስስ ተብሎ እንደሚጠራ
-ጨረቃ ደግሞ አሶንያ፣ ዕብላ፣ ብናሴ፣ ኤራዕ ተብሎ እንደሚጠራ

💟ምዕራፍ 27፡-
በኃጥኣን ወራት ክረምቶች እንደሚያጥሩ፣ ዝናም እንደሚከለከል መነገሩ

💟ምዕራፍ 28፡-
ጻድቃን ብፁዓን እንደሆኑ መነገሩ
-ስለዕለት መጋቢ ከዋክብት፣ ስለወር መጋቢ ከዋክብት፣ ስለአራቱ ወቅቶች መጋቢ ከዋክብት መነገሩ

💟ምዕራፍ 29፡-
ሄኖክ እግዚአብሔርን እንዳመሰገነና እንደጸለየ

💟ምዕራፍ 30፡-
ሄኖክ ሌላ ሕልምን እንዳየ ለልጁ ለማቱሳላ መንገሩ

💟የዕለቱ ጥያቄዎች💟
፩. ከሚከተሉት ውስጥ የፀሐይ ሌላ ስሙ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ኤራዕ
ለ. ኦርያሬስ
ሐ. አሶንያ
መ. ዕብላ
፪. በሰሌዳ ክበብ መጠን ፀሐይ ከጨረቃ…………..?
ሀ. ይበልጣል
ለ. ያንሳል
ሐ. እኩል ነው
መ. መልስ የለም
፫. ከሚከተሉት ውስጥ አራቱን የዓመቱን ክፍለ ዘመናት ከሚለዩት አራቱ ዐበይት ከዋክብት ውስጥ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ምልኤል
ለ. ኢየሱሳኤል
ሐ. አንድርናኤል
መ. ኢይሉማኤል
፬. በምድር ያሉ አበቦች ሁሉ የሚያብቡት የትኛው ኮከብ በሚመግብበት ወቅት ነው?
ሀ. ምልክኤል
ለ. አስፋኤል
ሐ. ሕልመልመሌክ
መ. ናርኤል

https://youtu.be/Sjqec27cznY?si=HmnwPUohziFdH5G4

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Jan, 16:18


▶️፲፪. ከዚህ ጋር ተያይዞ በየሀገራቱ የቀንና የሌሊት መፈራረቅ ለምን ነው ፀሐይ በሰማይ ስትጓዝ በአንዱ ጨላማ በአንዱ ብርሃን ይሆናልና?

✔️መልስ፦ በመሬት ዙሪያ ናጌብ የሚባል ንዑስ ተራራ አለ። ከዚያ ቀጥሎ ውቅያኖስ፣ ከዚያ ቀጥሎ አድማስ አለ። ፀሐይ ሁልጊዜም ታበራለች። ስለዚህ ከምሥራቅ ወጥታ ስታበራ ውላ በምዕራብ ትገባለች። ከዚያ በሰሜን ዙራ በምሥራቅ ትወጣለች። ወደመሬት ዳርቻ ያሉ ሀገሮች በምሥራቅ ስትወጣ ናጌብ ብርሃኗን ስለሚወስንባቸው ጨለማ ይሆናል። በምሥራቅ በኩል ረጅም ገደል ቢኖር ፀሐይ ስትወጣ ከገደሉ አጠገብ ላሉ ቆይታ እንደምትደርሳቸው ማለት ነው። በወዲያ በኩል ስትሄድም እንዲሁ እየሆነ በአንዱ ጨለማ በአንዱ ብርሃን እየሆነ ይኖራል ማለት ነው (ሄኖ.21፥12)።

▶️፲፫. ሠርቅ እና ሠርቀ ወርኅ ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሠርቅ የሚለው ቃል ሠረቀ ወጣ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ መውጣት ማለት ነው። ሠርቀ ወርኅ ማለት ደግሞ የጨረቃ መውጣት ማለት ነው። ጨርቃ ጠፍታ እንደ አዲስ ስትወጣ ሠርቀ ወርኅ ሆነ ይባላል።

▶️፲፬. መስዕ፤ አዜብ፤ ሊባ፤ ባሕር
የተባሉት እያንዳንዳቸውን የአቅጣጫ ጠቋሚዎች ቢያብራሩልን ማለቴ እንደ ምሥራቅ፤ ምዕራብ፤ ሰሜን፤ ደቡብ አቅጣጫቸው ግልጽ አልሆነልኝም።

✔️መልስ፦ መስእ ሰሜን ምሥራቅ ማለት ነው። አዜብ ደቡብ ምዕራብ ማለት ነው። ሊባ ደቡብ ምሥራቅ ማለት ነው። ባሕር ሰሜን ምዕራብ ማለት ነው።

▶️፲፭. "ገናና ፀሐይ በዚያ ይወርዳልና ይልቁንም ለዘላለሙ የከበረ እግዚአብሔር በዚያ ይወርዳልና ሁለተኛውንም ነፋስ ስሙን አዜብ ይሉታል" ይላል (ሄኖ.25፥20)። ለዘላለሙ የከበረ እግዚአብሔር በዚያ ይወርዳልና ሲል ምን ለማለት ይሆን?

✔️መልስ፦ ደብረ ሲና ያለች በአዜብ በኩል ናትና እግዚአብሔር በዘፈቀደ እንደሚገለጥባት ለመግለጽ ይወርዳል ተብሏል።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Jan, 16:18


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 92 💙💙

▶️፩. "በታወቁባቸው ዘመኖችም በተከፈቱ ጊዜ ከእነርሱ በምድር ላይ ድርቅ ይወጣል" ይላል (ሄኖ.24፥9)። የከዋክብት ዑደት ምድር ላይ ተጽእኖ አለው ማለት ነው? እያንዳንዱ ሰው በሚወለድበት ወራት የሚወጡ ከዋክብት አሉት? ከዋክብት የሚወጡበት ወራት የሰው ባሕርያት ላይስ ተጽእኖ አላቸው?

✔️መልስ፦ የከዋክብት ዑደት ተፈጥሮ ላይ የሚያመጣው የየራሱ ተጽእኖ አለ። የሕልመልመሌክ፣ የምልኤል፣ የምልክኤል፣ የናርኤል በየዘጠና አንድ ቀኑ መውጣት ወቅቱን ይቀይረዋል። የበጋ፣ የክረምት፣ የመጸው፣ የጸደይ መለዋወጥ ከከዋክብት ጋር የተያያዘ ነውና። ለምሳሌ ሕልመልመሌክ ምግቡ እሳት ነው። ስለዚህ በበጋ ወቅት ሙቀት መበርታቱ ከዚህ ጋር ይያያዛል። በየወሩ የሚወጡ የየወር መጋቢ ኮከቦችም አሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የየዕለት ኮከቦችም አሉ። የእነዚህ መውጣት በተፈጥሮ ላይ በሙቀት፣ በቅዝቃዜ፣ በዝናምና በመሳሰሉት ላይ ለውጥ ያመጣሉ። እኒህን መሠረት አድርገው በሚመጡ የሰው ሥጋዊ ሕይወት ላይም ተጽእኖ አላቸው። የሰው ባሕርይ ላይ ግን የሚያመጡት ልዩ ነገር የለም። ፍካሬ ከዋክብትን የመሳሰሉ የጥንቁልና መጻሕፍት ላይ የተጻፉ ብዙ ስሕተቶች አሉ። እነዚህን ዓይነት መጻሕፍትን መቀበል አይገባም።

▶️፪. በዘመናችን የምናያቸው አጥለቅላቂ ጎርፎች አውሎ ነፋሶች የዘመን ዑደት ውጤቶች ናቸው? እነዚህስ በተፈጥሮ ሚዛን መዛባት የመጡ ወይስ የፈጣሪ ቁጣ?

✔️መልስ፦ ተፈጥሮ የእግዚአብሔር ታዛዥ ናት። እግዚአብሔር እኛን ለመቅጣት የሚያመጣቸው መቅሠፍቶች አሉ። እንዲሁም በተፈጥሮ ዑደት የሚፈጠሩ ጎርፎች አሉ። ለምሳሌ በክረምት ዝናም አለ። የብዙ ዝናም ውጤት ደግሞ ጎርፍ ነው። ስለዚህ ሰው ቸል ብሎ ከወንዝ ዳር ቤቱን ሠርቶ የጎርፍ መከላከያ ሳይሠራ ጎርፍ ቢበላው ሰው በራሱ ቸልታ የፈጠረው መቅሠፍት መሆኑን ልብ ማድረግ ይገባል። ስለዚህ በፈጣሪ ቁጣ የሚመጡም አሉ። የተፈጥሮ ዑደትን መሠረት አድርገው የሚመጡም አሉ።

▶️፫. ሄኖ.21፥19 "ቀኒቱ 10 ሌሊቱ 8 በድምሩ 18 ሰዓት ነው" ይላል። ቀሪው 6 ሰዓትስ?

✔️መልስ፦ በሄኖክ አቆጣጠር አንድ ቀን ለ18 እኩል ክፍሎች የተከፈለ ነው። እኛ በለመድነው አከፋፈል አንድ ቀን ለ24 እኩል ክፍሎች የተከፈለ ነው። በሄኖክ አቆጣጠር አንዱ ክፍል እኛ በለመድነው ሰዓት አንድ ሰዓት ከኻያ (1፡20) ነው። ስለዚህ ቀሪ 6 ሰዓት የለም። በሄኖክ አቆጣጠር አንድ ሰዓት የሚባለው 80ው ደቂቃ ነው። ስለዚህ 80 ደቂቃ በ18 ሲባዛ 1440 ደቂቃ ይሆናል። የእኛ 24 ሰዓትም በ60 ሲባዛ 1440 ይሆናል። በአጭሩ የሄኖክ 18 ሰዓትና እኛ የለመድነው 24 ሰዓት ተመሳሳይ ነው።

▶️፬. "አንዱም አንዱም በየወገናቸው እንዳሉ አንዱም አንዱ በየዘመናቸውና በየሥልጣናቸው አንዱም አንዱም በየመውጫቸውና በየስማቸው ከኔ ጋራ ያለ መሪያቸው የሚሆን የከበረ መልአኩ ዑርኤል ባሳየኝ በየወራታቸውም ጸንተው እንዲኖሩ የሚናገር መጽሐፍ ይህ ነው" ይላል። የመልአኩ ስም ዑርኤል ነው ወይስ ዑራኤል?

✔️መልስ፦ በሁለቱም ስም ይጠራል። ዑርኤልም ይባላል ዑራኤልም ይባላል። በግእዝ ቋንቋ ዑራኤል ሲል ተጣይ ንባብ ሲሆን ዑርኤል ሲል ሰያፍ ይሆናል (ለጠቅላላ ዕውቀት)።

▶️፭. "በተመለሰም ጊዜ ስሳውን ከንትሮስ ሊፈጽም ይመለሳል" ይላል (ሄኖ.2፥11)። ከንትሮስ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከንትሮስ ፀሐይ የምትመላለስበት ክፍለ ሰማይ ነው። ይህም ማለት ሊቃውንት ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ያለውን ፀሐይ የምትመላለስበትን የሰማይ ክፍል በእኩል ስልሳ ክፍሎች ይከፍሉታል። ይኸውም ሐሳባዊ ክፍል ነው በሰማይ የተሰመረ መስመር ኖሮ አይደለም። ያ ሐሳባዊ ክፍለ ሰማይ ከንትሮስ ይባላል።

▶️፮. "ስሙ መስዕ የሚባል አራተኛውም ነፍስ ከሦስት ይከፈላል" ይላል (ሄኖ.25፥22)። አዜብና መስዕ ሲል የአቅጣጫ ስም ወይስ የነፋስ ስም ነው?

✔️መልስ፦ የአቅጣጫ ስምም ይሆናሉ። የነፋስ ስምም ይሆናሉ። ስምንት ነፋሳተ መዓትና አራት ነፋሳተ ምሕረት በአጠቃላይ በምድር ዳርቻ 12 የነፋሳት መውጫዎች (መዛግብት) አሉ። ሦስቱ በአንድ አቅጣጫ ሦስቱ በአንድ እያለ በአራቱም አቅጣጫ ሦስት ሦስት አሉ። ከሦስቱ ሁለቱ ነፋሳተ መዓት ሲሆኑ አንዱ ነፋሰ ሞሕረት ነው። ስለዚህ ነፋሱ በመውጫ አቅጣጫው ተሰይሟልና ለዚህ ነው።

▶️፯. "ነገ ሠርቅ ሊያደርግ ከፀሐይ ጋራ ያድራል። ፀሐይም በወጣ ጊዜ ጨረቃ ከእርሱ ጋራ አብሮ ይወጣል ነገ በሚቀበለው ብርሃን እኩሌታ ዛሬም ይቀበላል" ይላል። ፀሐይ እና ጨረቃ እኩል ሰዓት ይወጣሉ?

✔️መልስ፦ ጨረቃ ጠፍ ሲሆን ከፀሐይ ጋር አድሮ ብርሃንን ከፀሐይ ይሰበስባል። አዎ ፀሐይና ጨረቃ በእኩል ሰዓት የሚወጡበት ጊዜ አለ።

▶️፰. ሄኖ.21፥53 ላይ "በተመለሰም ጊዜ ስድሳውን ከንትሮስ ሊፈጽም ይመለሳል ተመልሶም ይወጣል ለዘለዓለም የሚኖር ታለቅ ብርሃን ይህ ነው" ሲል ጌታችን ይህችን ዓለም ሊያሳልፍ ሲመጣ ብርሃናት አያልፉም ለዘለዓለም ይኖራሉ ማለት ነው ወይስ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ሁለት ትርጉም አለው። አንደኛው ብዙዉን ዘመን ዘለዓለም ማለት የተለመደ ስለሆነ ፀሐይ ደግሞ እስከ ዕለተ ምጽአት እያበራ ስለሚኖር ለዘለዓለም የሚኖር ተብሏል። ሁለተኛው በምሥጢር የእውነት ፀሐይ የሚባል ጌታ ስለሆነ ጌታ ዘለዓለማዊ ነው ማለት ነው።

▶️፱. ሄኖ.22፥5 ላይ ስለ ጨረቃ ሲናገር "የብርሃኑ ሁኔታ በተስተካከለም ጊዜ የብርሃኑ መጠን ከፀሐይ ሰባተኛ እጅ ይሆናል" ይላል። ሄኖ.21፥56 ላይ ደግሞ ስለ ፀሐይ ሲናገር "ብርሃኑ ከጨረቃ ይልቅ ሰባት እጅ ያበራል" ይላልና ሁለቱ ሐሳቦች እንዴት ነው የሚታረቁት?

✔️መልስ፦ ጨረቃ ብርሃኑ ሙሉ ሲሆን የፀሐይን አንድ ሰባተኛ ያህል ያበራል ማለት ነው። ይህ ማለት ፀሐይ ከጨረቃ ይልቅ ሰባት እጥፍ ያበራል ማለት ነው። ሄኖ.21፥56 ላይ ሰባት እጅ ያለው ሰባት እጥፍ ለማለት ነው። ሄኖ.22፥5 ላይ ሰባተኛ እጅ ያለው አንድ ሰባተኛ ለማለት ነውና አይቃረንም።

▶️፲. ሄኖ.፳፩÷፮-፯ "የፀሐይ መውጫና መግቢያ መስኮቶች የጨረቃ መውጫና መግቢያ መስኮቶች ናቸው" ይላል። እንዴት ነው አብረው በአንድ ጊዜ በአንድ መስኮት ይገናኛሉ ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ በአንድ መስኮት ይወጣሉ በአንድ መስኮት ይገባሉ ማለት ነው። ስለሚገናኙም ነው ጨረቃ ከፀሐይ ብርሃንን በየጊዜው የምትወስደው።

▶️፲፩. ሄኖ.፳፩÷፳፪ "ያንጊዜም ቀኒቱ ሁለት እጅ ትረዝማለች ሌሊቲቱም ታጥራለች ሰባት ክፍልም ትሆናለች" ይላል። ጠቅለል ባለመልኩ የየወራቱ የቀንና የሌሊት ሰዓት በፀሐይና ጨረቃ አወጣጥ እንዴት ይሰላል?

✔️መልስ፦ በመስከረም ሌሊቱና ቀኑ እኩል ነው። በጥቅምት ሌሊቱ 13 ሰዓት ቀኑ 11 ሰዓት ነው። በህዳር ሌሊቱ 14 ቀኑ 10 ነው። በታኅሣሥ ሌሊቱ 15 ቀኑ 9 ይሆናል። በዚሁ የገና ፀሐይ የሚባለው ቶሎ የሚመሽ ለማለት እንደሆነ አስተውል። ከዚያ ጥር ቀኑ 10 ሌሊቱ 14 ይሆናል። የካቲት ቀኑ 11 ሌሊቱ 13 ይሆናል። በመጋቢት ሌሊቱና ቀኑ ይተካከላሉ ማለት 12: 12 ይሆናሉ። በሚያዝያ ቀኑ 13 ሌሊቱ 11 ይሆናል። በግንቦት ቀኑ 14 ሌሊቱ 10 ይሆናል። በሰኔ ቀኑ 15 ሌሊቱ 9 ይሆናል። የሰኔ ቀን ቶሎ የማይመሽ ለዚህ ነው። በሐምሌ ቀኑ 14 ሌሊቱ 10 ይሆናል። በነሐሴ ቀኑ 13 ሌሊቱ 11 ይሆናል። በጨረቃ ሲቆጠር ደግሞ ጨረቃ በሁለት ወር አንዴ ትጠፋለች። በጠቅላላው በዓመት ከፀሐይ 11 ቀን አጉድላ ታበራለች።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Jan, 15:47


✍️ሐመር መጽሔት በጥር  ወር እትሟ!✍️
✍️".. እኛም ጥምቀትን እንፈልጋለን የሚሉ ምእመናን  ብዙ ናቸው ..) #ሐመር #መጽሔት  በጥር  በ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዐምድ  ✍️      
                   ༺ ༻ 
  #የኅትመት ዘመን ፦#ጥር ፳፻፲፯  ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
•  ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት  ቁጥር-፩    #ጥር  ፳፻፲፯  ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን " #ጥምቀትን የተጠሙ ነፍሳት "በሚል ዐቢይ መልእክት
አገልግሎቱን ከሚፈልጉት ምእመናን ቍጥር ጋር ባለመጣጠኑ የተጠመቁትም  ምእመናን የሚያነሡት ጥያቄ  “አጠመቃችሁን ነገር ግን እግዚአብሔርን የምናመልክበት፣ ሥጋ ወደሙን የምንቀበልበት ቤተ ክርስቲያን የለንም፤ የሚያስተምሩን መምህራን፣ ቀድሰው የሚያቈርቡን ካህናትና ዲያቆናትም የሉንም” የሚለውን ነው።በአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት ሥር የሚገኙ አንዳንድ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለአብነት ያህል ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ትጉሃን ሰንበት ትምህርት ቤት፣ የዘነብ ወርቅ ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት፣ የቤተል ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት እና እንደእነዚህ ያሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በቋንቋ የሚሰብኩ ሰባክያንን አገልግሎቱ ከሚፈለግበት አካባቢ እያስመጡ ያሠለጥናሉ፤ የአገልግሎት ተሞክሯቸውንም እያሳዩ ይገኛሉ። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ይህን ከሠሩ ሁሉም ቢተባበሩ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት ይቻላል። መልካም እየሠሩ ያሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን አብነት በማድረግ ሁሉ ለእንደዚህ ያለው ተግባር መረባረብ “እኛም መጠመቅ እንፈልጋለን” ብለው ጥሪ ለሚያቀርቡ ምእመናን የድርሻቸውን ምላሽ ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል።
“እኛም መጠመቅ እንፈልጋለን፤ እኛም እንደ እናንተ ኦርቶዶክስ መሆን እንፈልጋለን” ብለው ለሚጣሩት ወገኖቻችን ፈጥኖ ከመድረስ አኳያ ያለውን ጫና (ተግዳሮት) ሁሉም የየድርሻውን ቢወጣ የእነዚህን ጥምቀትን የተጠሙ ነፍሳት ጥያቄዎችን በሚገባ መመለስ  እንደሚቻል ሐመር በመልእክት ዐምድ ታስነብባለች።
.#ዐውደ ስብከት  ሥር” # “ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል" በሚል ርእስ  ባልንጀራ የሚለውን ቃል ትርጉምና አከፋፈል ፣ከክፉ ባልንጀራ መራቅ አሰፈላጊ  እንደሆነና ክፋት ለሰው ልጅ የባሕርዩ  እንደአልሆነ ና ለማሳያ ያህል የተወሰኑትን በማንሳት ከክፉ ባልንጅርነት ተጠብቀን በመልካም ባልንጅረነት እንድንጠቀም መንገድ ታሳያለች ።
  #በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# “ቃል ሥጋ  ሆነ” (ዮሐ.፩፥፲፬)  ክፍል ሁለት  " በሚል ዐቢይ ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው  ጌታ ለምን እንደተወለደ  በዝርዝር ተዳሶበታል።
#ዐቢይ ጉዳይ  ዐምድ  ሥር  ደግሞ “# የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ችግር በመፍታት ረገድ የምእመናን ድርሻ   " በሚል ርእስ  ዓለምን ሊሞላ በሚገባው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ቦታ ሊጠባቸው አይገባም፡፡ ‹‹ክርስትናችሁን ጠብቁ፣ ሲሞላላችሁ ጸበል ረጭተን፣ አጥምቀን፣ አቊርበን እናስተናግዳችኋለን፤›› ብቻ ተብለው የሚገፉ፣ ዘልቀው የመጡ ብቻ ተጨንቀውም ቢሆን በአገልግሎቱ ውስጥ ብልጭ፣ ብልጭ እንዲሉ ብቻ ማድረግ ሕዝባውያን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍቅርና ቅርበት እንዲኖራቸው አያደርግም፡፡ ስለዚህ ከዚህ የተሻገረ ተሳትፎ እንደሚፈልጉ  ያሳያል።
በአፈጻጸም  ችግር ምእመናን የሰበካ ጉባኤ ተወካይ ሁነው ተመርጠው ግን ቢሮ አካባቢ ባሉት ሠራተኞች  ሥራው  ይያዝና የተመረጡ የሰበካ ጉባኤ አባላት አዝነው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዕውቀትና በሙያ ምንምአገልግሎት ሳይሰጡ ከተመረጡበት የፈቃድ አገልገሎት  እንደሚወጡ፤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት  ቤተ ክርስቲያን አባላት የሆኑ ምእመናን በተወሰነ መልኩ በሰበካ ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ። ይሁን እንጂ ብዙ ጊዜ ለቍጥር መሙያ ያህል እንጂ በወሳኝነት ሚና ላይ ሲሳተፉ  ብዙ እንደማይታዩ ታስነብባለች ፡፡ሙሉውን ጥር ሐመር ያንብቡ !
•  #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር  ደግሞ  "#“ድኾችንና ጦም አዳሪዎችን…ጥራ” "በሚል ርእስ 
በርካታ ሰዎች ቤታቸው ፈርሶባቸው፣ ሀብት ንብረታቸው ተወስዶባቸው፣  ሲያበሉ ሲያጠጡ የነበሩ አሁን አብሉኝ አጠጡኝ የሚሉ ሆነው፣ እንግዳ ሲቀበሉ የነበሩት የሚቀበላቸው አጥተው በየመጠለያው ወድቀው፣ አንዳንዶች ደግሞ ያንኑም እያጡት  በችግር ላይ ችግር ተደራርቦባቸዋልና እንደነዚህ ያሉትን በፍቅር ማስተናገድ እጅግ የበለጠ ዋጋ  እንዳለው በአጽንዖት ታሰተምራለች።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የስደተኞች መጠጊያ ጁባ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን " ክፍል ሁለት በሚል ርእስ  ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ያለውን ግንኙነት ፣ ከሀገረ ስብከቱ ጋር ያለውን ግንኙነት ፣ በሀገር ውስጥ ካሉ ተቋማት ጋር ያለ ግንኙነት ፣የነበሩ ተግዳሮቶችን  ታስቃኛለች ።
•  #በነገዋ  ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ  ሥር “ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን" በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ክፍል ሁለት   በሚል ርእስ ስለ መንፈሳዊ ማኅበራት በዓለማውያን ዘንድ ፣ መንፈሳውያን ማኅበራት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ መንፈሳውያን ማኅበራት የአገልግሎት ተሳትፎ፤ በእኛ ዘመን ለጽዋ ማኅበር የሰጠነው ትርጉም መስተካከል እንዳለበት  በተለይም በአሁኑ ዘመን መልካም ማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሚያስፈልግበት ወቅት ይህንን ብናደርግ ትርጉም  እንደሚኖረው  ሰፊ ጉዳይይዛለች።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "#ጥሪ" ክፍል -፩"በሚል የሴቶች አለባበስን  በተለይም ራቁታቸውን ስለሚሄዱ  ለመንፈሳዊ ሕይወት አጠራራችን እንደሚለያይ ታስነብባለች።
•  #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “በዐልና አከባበሩ- # ክፍል ፪ " በሚል ርእስ #“በዓልንና የበዓል  አከባበርን” በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆኑትን መጋቤ ሐዲስ ኀይለ እግዚእ አሰፋ ጋር የተደረገ የመጨረሻ   ጥያቄና መልስ ይዛለች  ። ለምሳሌ፦የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን በዓል አንድነትና ልዩነት ።፤የበዓል አከባበር እንዴት መሆን እንዳለበት ፤በዓል ማክራችን ለምን እንደሚጠቅመን ፣ባናከብርስ ምን እንደሚቀርብን፣በዓል አከባበር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ፤እነዚህን ችግሮች እንዴት መፍታት እንደሚቻል ከሊቁ ጋር የተደረገውን ምልልስ ይዛለች
   ሐመር መጽሔት #፴፪  ኛ ዓመት   ቁጥር ፩  በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org  #ሐመር #መጽሔት  ዝግጅት  ክፍል

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Jan, 05:17


💖 መጽሐፈ ሄኖክ ክፍል 5 💖

💖ምዕራፍ 21፡- ለፀሐይ በምሥራቅ ስድስት በምዕራብ ስድስት መውጫና መግቢያ እንዳለው

💖ምዕራፍ 22፡- ጨረቃ ከፀሐይ ብርሃንን እየተቀበለ እንደሚያበራ መነገሩ

💖ምዕራፍ 23፡- በሄኖክ አቆጣጠር አንድ ዓመት በፀሐይ 364 በጨረቃ ደግሞ 354 ቀናት እንደሆኑ መነገሩ

💖ምዕራፍ 24፡- ፀሐይ ከከዋክብት ይልቅ እንደሚያበራና ከዋክብትን እንደሚበልጣቸው

💖ምዕራፍ 25፡- በምድር ዳርቻ ለነፋሳት የተከፈቱ 12 መስኮቶች እንዳሉ

💖የዕለቱ ጥያቄዎች💖
፩. በሄኖክ አቆጣጠር አንድ ቀን ስንት ክፍል ነው?
ሀ. አሥራ ስምንት ክፍል
ለ. ኻያ አራት ክፍል
ሐ. አሥራ ሁለት ክፍል
መ. ሠላሳ ክፍል
፪. በሄኖክ የጨረቃ አቆጣጠር አንድ ዓመት ስንት ቀናት ናቸው?
ሀ. 364
ለ. 254
ሐ. 354
መ. 264
፫. በምድር ዳርቻ ከሚገኙት ከአሥራ ሁለቱ የነፋሳት መስኮቶች የበረከትና የሰላም ነፋሶች የሚወጡባቸው ስንት ናቸው?
ሀ. አራት
ለ. ስምንት
ሐ. አሥር
መ. ሰባት
፬. ነፋሳተ መዓት በነፈሱ ጊዜ ምን ይሆናል?
ሀ. ድርቅ፣ ውርጭ፣ ኩብኩባ፣ ዋግ ይመጣል
ለ. ቅንነት፣ ሰላም፣ ሕይወት፣ በረከት ይሆናል
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/PnkfVtOIKWA?si=ySqxDKNHYhQZrSMZ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Jan, 22:03


▶️፲፭. "ሦስተኛውም ስሙ ጋድርኤል ነው መትቶ መግደልን ሁሉ ለሰው ልጅ ያስተማረ ይህ ነው" ይላል (ሄኖ.19፥19)። መትቶ መግደልን ሁሉ ለሰው ልጅ ያስተማረ ጋድርኤል ከሆነ ጋድርኤል ከማስተማሩ በፊት ቃኤል አቤልን የገደለው ማን አስተምሮት ነው? ቀጥሎ ቁ.20 ላይ "ሔዋንንም ያሳታት እሱ ነው" ይላልና ሔዋን የሳተችው ገና የሴት ልጆች ሳይወለዱ አይደል እንዴ?

✔️መልስ፦ ለቃኤል ሰው እንዴት እንደሚገደል ያስተማረው ጋድርኤል የተባለው ሰይጣን ነው። ቀድሞ የነበሩት ረቂቃን አጋንንት ልክ ሰይጣን በእባብ አድሮ ሔዋንን እንዳሳታት በሴት ልጆች አድሮ በኋላም ያሳተ የቀድሞዎቹ ሰይጣናት ስለሆኑ ነው።

▶️፲፮. ሄኖ.19፥29 ላይ "የአውሬ መንከስን ስሙ ጨካኝ የሚባል የአውሬ ልጅ እርሱ በቀትር ጊዜ የሚደረጉ ሥራዎችን ሁሉ አስተማረ አለ" ይላል። በዋናነት እዚህ ላይ ያስተማረው ምንድን ነው አልገባኝም።

✔️መልስ፦ ሰይጣን በእባብ አድሮ ሰውን እንዲናደፍ እንዳስተማረ የሚገልጽ ነው።

▶️፲፯. "እግዚአብሔር በዚህ ዓለም በጌትነት በኖረ ጊዜ ለቅዱሳን የገለጠው የመሐላ ፍጻሜ የክስብኤል የስሙ ቁጥር ይህ ነው። ስሙም ቤቃ ይባላል ይኸውም አጋንንት ያንን የተሠወረ ስሙን ይሰሙት ዘንድ ቅዱስ ሚካኤልን የተሠወረ ስሙን ግለጥላቸው አለው" ይላል (ሄኖ.20፥1-2)። እግዚአብሔር በዚህ ዓለም በጌትነት በኖረ ጊዜ ሲል ምን ማለት ነው? መቼስ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም በጌትነቱ ያልነበረበት ጊዜ የለ። ለቅዱሳን የገለጠው የመሐላ ፍጻሜ፣ የክስብኤል የስሙ ቁጥር ቤቃ፣ በአጠቃላይ ይህ ንባብ ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ክስብኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ማለት ነው። እግዚአብሔር በዚህ ዓለም በጌትነት በኖረ ጊዜ ማለት በማኅፀነ ማርያም በክብር ባደረ ጊዜ ማለት ነው። በአጭሩ ሰው በሆነ ጊዜ ማለት ነው። ሰው ያልሆነበት ዘመን ደግሞ ነበረ። ቤቃ ማለት ቀዳሚሁ ቃል (በመጀመሪያ ቃል ነበር) ማለት ነው። ለቅዱሳን የገለጠው የመሓላ ፍጻሜ ማለት ለነቢያት እወርዳለሁ እወለዳለሁ እያለ የነገራቸውን ትንቢት ከድንግል ማርያም በመወለድ መፈጸሙን ያሳውቀናል።

▶️፲፰. "ይኸንንም ስም ከሃሊ የሚሆን አምላክ በቅዱስ ሚካኤል እጅ አኖረው የዚህም ስም የተሠወሩ ምሥጢሮቹ እኒህ ናቸው። ፍጥረታቱም ሁሉ በመሐላው ጸና" ይላል (ሄኖ.20፥5)። በቅዱስ ሚካኤል እጅ አኖረው ሲባል ምን ማለት ነው?የዚህም ስም የተሠወሩ ምሥጢሮቹ የተባሉስ ምንድን ናቸው? ፍጥረታቱም ሁሉ በመሐላው ጸና መባሉስ የምን መሐላ ነው?

✔️መልስ፦ በቅዱስ ሚካኤል እጅ አኖረው ማለት ቅዱሳን መላእክት የእግዚአብሔር ስም ተገልጦላቸው እንደሚያመሰግኑት የሚገልጽ ነው። የእግዚአብሔር ምሥጢሮቹ ያላቸውን ቀጥሎ ዘርዝሯቸዋል። ፍጥረታት ሁሉ የተፈጠሩና ጸንተው የሚኖሩት በእነዚህ የእግዚአብሔር ስሞች እንደሆነ ተገልጿል።

▶️፲፱. "በዚያም ቦታ የነጐድጓድ የቃሉ ቦታዎች ይጠበቃሉ የመብረቅም ብርሃን ይጠበቃል። በዚያም ቦታ የውርጭና የበረድ ቦታዎች የጉምም ቦታዎች የጤዛና የዝናም ቦታዎች ይጠበቃሉ። እነዚያም ሁሉ በመላእክት ጌታ ፊት አምነው ያመሰግናሉ በፍጹም አእምሯቸው ያመሰግናሉ" ይላል (ሄኖ.20፥13-15)። በነጎድጓድ፣ በመብረቅ፣ በውርጭና፣ በበረድ፣ በጉም፣ በጤዛና በዝናም የተመሰሉ ምንድን ናቸው? እነዚህ ቦታዎች ይጠበቃሉ ማለትስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ቀጥታ በቁሙ ነው የሚተረጎመው የነጎድጓድ፣ የመብረቅ፣ የውርጭ፣ የበረድ፣ የጉም፣ የጤዛ፣ የዝናምና የመሳሰሉ ቦታዎች በእግዚአብሔር ስም ተጠብቀው እንደሚኖሩ የሚገልጽ ነው። ያመሰግናሉ መባላቸው ሰው እነርሱን አይቶ እነርሱን የፈጠረ እግዚአብሔርን ስለሚያመሰግን የተነገረ ነው።

▶️፳. ገሃነም መውረድ መጋዝ እየተባለ የተጠቀሱ ተደጋጋሚ ክፍሎች በመጽሐፈ ሄኖክ ተጠቅሰዋል። ይህ ጊዜያዊ ሲዖል ወይስ ዘላለማዊ ፍርድ የሚሰጥበት ገሃነም ለማለት ተፈልጎ ነው? ሁለቱ ማለትም ሲዖል እና ገሃነም ቃላቱ በዚህ መጽሐፍ interchangeably ተጠቅሰዋል ማለት እንችላለን?

✔️መልስ፦ ሲዖል ጠፍቶ በሲዖል የሚተካ ገሃነም ስለሆነ ሲዖልን ገሃነም ሲለው ይገኛል። ሲዖል ሰማይና ምድር በምጽአት ሲያልፉ ያልፋል። ገሃነም ግን ለዘለዓለም የኃጥኣን መኖሪያ ነው።

▶️፳፩. መጽሐፈ ሄኖክ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አይደለም ማለት ነው? እንደዚያ ከሆነ እንዴት አሁን ከሌሎች የብሉይ መጻሕፍት ጋር እናጠናዋለን? ሐዋርያትስ ስለትንቢተ ሄኖክ ጠቅሰው እያለ ከቀኖና መጻሕፍት አለመቆጠሩ እንዴት ይታያል ግልጽ ቢያደርጉልኝ?

✔️መልስ፦ በቀኖና አዎ አይደለም። ያልሆነው ግን መጽሐፉ ስሕተት ስላለበት አይደለም። ፈላስፎች የእኛን መጽሐፍ የመሰለ ነው ብለው ደንበኛውን ሕገ ወንጌል ከመቀበል እንዳይከለከሉ ሐዋርያት ከቀኖና አውጥተውታል። ከቀኖና ቢያወጡትም ግን የመጽሐፉ ደግነት የታወቀ ስለሆነ በከመ ይቤ ሄኖክ እያሉ ጽፈዋል። ከሌሎች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጋር ታትም የምናጠናውም የመጽሐፉን ደግነቱን ሐዋርያት ስለነገሩንና የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ነው።

▶️፳፪. የተፈረደባቸው ደቂቀ ሴት ወይም በመጽሐፉ የተገለጹት ፍርድ የተቀበሉ የሴት ልጆች በጊዜያዊነት ነው የተፈረደባቸው በኋላ በዳግም ምጽአት የመጨረሻውን ፍርድ (ገሃነም) ይቀበላሉ ብለውን ነበር ወደኃላ መመለስ ካልሆነብኝ ክብር ይግባውና በጌታችን በዕለተ ዓርብ የብሉይ ኪዳን ነፍሳት እንደተሰበከላቸው እና ነጻ እንደወጡ ይታወቃል ይህ ፍርድ ከዚህ አንጻር እንዴት ይታያል።

✔️መልስ፦ የወረዱት ደቂቀ ሴት ከሰውነት ወርደው በፈቃዳቸው አጋንንት ሆነዋል። ስለዚህ ለአጋንንትም ቢሆን ሙሉ ፍርድ የሚፈረድባቸውና ወደዘለዓለማዊው ገሃነም የሚገቡት በዕለተ ምጽአት ነው። አጋንንትም ቢሆኑ ዕቡያን (ትዕቢተኞች) ሆነው ነው እንጂ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እንደሞከረችው ይቅርታ ቢጠይቁ ከገሃነም የመዳን እድል ነበራቸው። ግን ዕቡያን ስለሆኑ ክርስቶስ ሠምራንም እንቢ ብለዋታልና። ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ያዳነ የሰው ልጆችን እንጂ አጋንንትን አይደለም። ስለዚህ የሰው ልጆች ከሲኦል ሲወጡ አጋንንት ግን ከሲዖል አልወጡም። ወኀደጎሙ ለእኩያን ሲል መቅድመ ወንጌል አጋንንትን በዚያው በሲዖት ተዋቸው ለማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Jan, 22:03


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 91 💙💙

▶️፩. "እንደ መላእክት ንጹሓን ጻድቃን ሁነው ይኖሩ ዘንድ ነው እንጂ ሰው በእንዲህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም። በጥቁር ቀለምና በቀይ ቀለም ጽፈው ሃይማኖታቸውን ሊያጸኑ ሰው ለእንዲህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም ነበርና ስለዚህ ነገር ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘላለሙ እስከዚያችም ቀን ድረስ ብዙ ሰዎች ይስታሉ አለ" ይላል (ሄኖ.19፥7)። በጥቁር ቀለምና በቀይ ቀለም መጻፍ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ የተጠቀሰው በቀይ ቀለም፣ በጥቁር ቀለም እየጻፉ የሚያሟርቱ ሰዎች እንደሚጎዱ ነው። በሌላ አተረጓጎም ደግሞ ሰው የተፈጠረው እንደ መላእክት በሕገ ልቡና ጸንቶ እንዲኖር እንጂ በተጻፈ ሕግ እንዲመራ አልነበረም። በሕገ ልቡና መኖር ሲያቅተው የተጻፈች ሕግ ሕገ ኦሪት ተሰጠችው። በሕገ ኦሪት መጽደቅ ባይችል ሕገ ወንጌል ተሰጥታዋለችና።

▶️፪. "ለአለቆች ቅጣት ስለ ተሠወረች ስለ ፍርድ ጭንቀትም ያበሳጨኛል" ሲል ምን ለማለት ነው (ሄኖ.19፥2)። መላእክት በባሕርያቸው ይበሳጫሉን?

✔️መልስ፦ በመላእክት ብስጭት የለም። ነገር ግን መላእክት ለእኛ ለሰዎች እንደ ታላቅ ወንድም ያስቡልናል። አንድ ሰው ለአንድ ሰው መከራ እንዳይደርስብህ ተጠንቀቅ እያለው ባለመጠንቀቅ መከራ ቢደርስበት ያ ያስጠነቀቀው ሰው ምክሩ ባለመጠበቁ በሰውየው ጥፋት እንደሚበሳጭ ሁሉ ቅዱሳን መላእክትም የሰው ልጅ እንዳይጠፋ በተለያዩ ጊዜያት እየተገለጡ እውነትን ቢናገሩም ሰው እነርሱን ባለመስማቱ መጥፋቱን በሰውኛ ለመግለጽ የተነገረ ነው እንጂ በመላእክትስ ብስጭት የለም።

▶️፫. ሄኖ.19፣19 ላይ "ሦስተኛውም ስሙ ጋድርኤል ነው። በመምታት መግደልን ሁሉ ለሰው ልጆች ያስተማረ ይህ ነው ሔዋንንም ያሳታት እርሱ ነው" ሲል መልአክ ነው ማለት ነው ይህን ያስተማራቸው ወይስ ከደቂቀ ቃየን ወገን ነው ግልጽ ቢያደርጉልኝ? ከደቂቀ ቃየን ነው እንዳንል ሔዋንን ያሳታት ይላልና?

✔️መልስ፦ ከደቂቀ ቃኤልና ከደቂቀ ሴት የተወለዱት እንዲሁም ከደብር ቅዱስ ወርደው ከደቂቀ ቃኤል ጋር የበደሉት ደቂቀ ሴት ሰዎች ነበሩ። በኋላ ግን በክፉ ሥራቸው ከረቂቃን አጋንንት ጋር አንድ ሆነዋል። ስለዚህ በእነርሱ አድረው ክፉ ይሠሩ የነበሩ አጋንንት ዓለም ሲፈጠር ጀምረው የነበሩ ናቸው። ጋድርኤል ሔዋንን ያሳታት ነው መባሉ ለዚህ ነው።

▶️፬. ሄኖ.17፣22 "ቅዱስ ስምህን ማመስገን ማክበር ከፍ ከፍ ማድረግና መቀደስ የምትችል የብርሃን መንፈስ ሁላ ታመሰግነዋለች" ሲል ምን ማለት ነው? የብርሃን መንፈስ የተባለች ማን ናት?

✔️መልስ፦ የብርሃን መንፈስ የተባለችው ዕውቀት ያላት የሰው ልቡና ናት።

▶️፭. ሄኖ.16፣13 ላይ "የማይታየውን ምድረ በዳ በደረቱ የሚይዝ ስሙ ብሔሞት የሚባለው ተባዕት አንበሪ ነው" ሲል ምድረ በዳን የመሸከም አቅም ስላለው ነው ወይስ ምን ለማለት ነው ቢያብራሩልኝ?

✔️መልስ፦ በእርግጥ ብሔምት በዓለማችን ላይ በጣም ትልቁ ሕይወት ያለው ደማዊ ፍጥረት ነው። ብሔሞት የሚገኘው በናጌብና በአድማስ መካከል ባለ በየብስ ቦታ ነው። ብሔሞት ያረፈበትን ቦታ ብሔሞት ስለሸፈነው (ስለያዘው) አይታይም። ይህን ለመግለጽ የተነገረ ነው እንጂ ብሔሞት ቦታውን ተሸክሞታል ማለት አይደለም።

▶️፮. ሄኖ.17፥47 "ከዚያም ከሰው ልጅ ጋር ይኖራሉ ይበላሉ ይጠጣሉም ያርፋሉም ለዘለዓለሙም ይነሣሉ" ይላል። ንባቡ አልገባኝም ይብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ምሳሌያዊ አነጋገነር ነው። በልቶ፣ ጠጥቶ፣ ተኝቶ የተነሣ ሰው ደስ እንደሚለው ደስ ይላቸዋል ለማለት ነው። በአጭሩ ደስ ይላቸዋል ለማለት ደስታቸውን ለመግለጽ እኛ በምናውቀው የተነገረ እንጂ ቀጥታ የሚተረጎም አይደለም።

▶️፯. "ዋግንም የሚጠብቅ መልአክ ክፉ ስለሆነ ለብቻው ጠባቂ አለው" ይላል (ሄኖ.16፥29)። ለክፉ መልአክ ጠባቂ አለው?

✔️መልስ፦ ለመልአክ መልአክ የለውም። አልቦቱ መልአክ ለመልአክ እንዲል ቄርሎስ። አገላለጹ እንደሱ አይደለም። ክፉ ስለሆነ የተባለ ዋግ ነው። ለክፉው ለዋግም ጠባቂ መልአክ አለው ለማለት ነው። ክፉነቱ ለእኛ ነው እንጂ በተፈጥሮውስ ዋግም ቢሆን ነውር የለበትም። ስለዚህ እግዚአብሔር ለብቻው ጠባቂ መልአክን ሹሞለታል።

▶️፰. "እነሱ ባያስተምሩ ከመሬቱ ትቢያ ብር እስኪ እንዴት ይገኝ ነበር" ይላል (ሄኖ.18፥2)። ብር የተባለው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ብር ማለት ከመሬት ተቆፍሮ የሚገኝ የመዓድን ዓይነት ነው። በክብር ከነሐስ ከፍ ያለ ከወርቅ ዝቅ ያለ መዓድን ነው።

▶️፱. "እነዚህ ውሃዎች በእነዚያ ወራት ለነገሥታቱ ለጸኑም ሰዎች ለከበሩም ሰዎች በዚህ ዓለም ለሚኖሩም ሰዎች ለሥጋና ለነፍስ ድኅነት ለሰውነታቸውም መቻያ ይሆናሉ" ይላሉ (ሄኖ.18፥33)። ውሃዎች የተባሉት ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ መቻያ ይሆናሉ ማለት መቀጣጫ ይሆናሉ ማለት ነው። የማየ አይኅ ውሃን ለመግለጽ ነው። ውሃዎች ብሎ ያበዛው ከሰማይም ከምድርም መንጭተው ክፋት የሠሩትን ሰዎች አጥፍተዋልና ነው። በክፋታቸው ለጸኑ፣ በክፋታቸው ለከበሩ ሰዎች መቅጫ ማየ አይኅ መጥቷልና።

▶️፲. ሄኖ.16፣39 ላይ "እነዚህ ሁለቱ አንበሪዎች በታላቋ የእግዚአብሔር ቀን የእግዚአብሔር መቅሠፍት ከንቱ እንዳትሆን ይበሉ ዘንድ የተዘጋጁ ናቸው" ይላል ምንን ለመብላት ነው የተዘጋጁት በእግዚአብሔር መቅሠፍት የሚጠፉትን ነውን ወይስ ሌላ ነገር ነው?

✔️መልስ፦ የኃይለ ቃሉ ፍሬ ሐሳብ ብሔሞትና ሌዋታን በጣም ግዙፋን ፍጥረታት ናቸው። በቀን በቀን ብዙ ሺህ እንስሳትን አራዊትን ተመግበው ነው የሚኖሩት። እና እነርሱን የሚመግብ እግዚአብሔር ይመግበናል ብለው በማይታመኑ ሰዎች መቅሠፍት ይመጣል ማለት ነው።

▶️፲፩. ሄኖ.16፥1 ሄኖክ ይህን መጽሐፍ የጻፈው መቼ ነው ከተሠወረ በኋላ ነውን?

✔️መልስ፦ ከመሠወሩ በፊት ነው። ነገር ግን እርሱ የጻፈውን ልጆቹ ያነቡት ስለነበረ በኋላ የልጆቹና የልጅ ልጆቹ ሐሳብ አልፎ አልፎ ተጽፎ ይገኛል።

▶️፲፪. ሄኖ.18፥28 አያቴ ሄኖክ ሲል ጸሐፊው የሄኖክ አያት ነውን?

✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ አያቴ ሄኖክ እያለ የሚናገረው ኖኅ ነው። ሄኖክ የኖኅ አያት ነውና። ስለዚህ በሄኖክ ቃል ላይ በተጨማሪ ኖኅም የበቃ ስለነበረ አንዳንድ ነገሮችን ጽፏል።

▶️፲፫. "አስታራቂ ማወቅ ትችሉ እንደ ሆነ ዓይኖቻችሁን ግለጡ ሥልጣናችሁንም አንሡ አለ" ይላል (ሄኖ.17፥26)። ይህ ቃል ምንን ለመግለጽ የተነገረ ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ነገሥታትና ገዢዎች በሄኖክ አድሮ ያስተላለፈው መልእክት ነው። አስታራቂ ማወቅ ትችሉ እንደሆነ ማለት መሢሑ ክርስቶስን እንዲያውቁ እንዲያስተውሉ ለማሳሰብ የተነገረ ቃል ነው።

▶️፲፬. ሄኖ.18፥42 ላይ "ከዚህ በኋላ አያቴ ሄኖክ የተሰጡትን ነገሮች ሁሉ ምልክት በመጽሐፍ ጽፎ ሰጠኝ ለእርሱም የተሰጡትን ነገሮች የኔ ነገር በተጻፈበት መጽሐፍ ጽፎ አንድ አድርጎ ሰጠኝ አለ" ሲል ከላይ ጀምሮ በራእይ ያየውን ሁሉ እየተናገረ ያለው ኖኅ ነበር እንዴ?

✔️መልስ፦ ኖኅም ያየው አለ። ሄኖክም ያየው አለ። በመጽሐፈ ሄኖክ ውስጥ አብዛኛው የሄኖክ ቃል ቢሆንም አልፎ አልፎ የጻድቁ የኖኅ ቃልም ይገኝበታልና ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Jan, 04:47


💝 መጽሐፈ ሄኖክ ክፍል 4 💝

💝ምዕራፍ 16፡- ሌዋታን በባሕር፣ ብሔሞት በየብስ እንደሚኖር መገለጡ

💝ምዕራፍ 17፡- በሰማይ ያሉ ሠራዊት ከእግዚአብሔር ትእዛዝን እንደሚቀበሉ

💝ምዕራፍ 18፡- ኖኅ በማየ አይኅ እንደማይጠፋ ሄኖክ ለኖኅ መንገሩ

💝ምዕራፍ 19፡- የሳቱ እና ያሳቱ የደቂቀ ሴት ስም ዝርዝር መጻፉ

💝ምዕራፍ 20፡- ለውሃዎች ሕይወታቸው ነፋስ እንደሆነ መነገሩ

💝የዕለቱ ጥያቄዎች💝
፩. ብሔሞት የሚባለው ታላቅ አንበሪ የሚኖረው ከየት ነው?
ሀ. ከመሬት በታች ካለው ውሃ
ለ. በመሬት ዙሪያ ካለ የብስ
ሐ. ከሰማይ በላይ ባለ ውሃ
መ. በመሬት ዙሪያ ካለ ውሃ
፪. እግዚአብሔርን ለዘለዓለም ይክበር ይመስገን እያሉ ከሚያመሰግኑት መካከል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. አፍኒን
ለ. ሚካኤል
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ጽንስ ማስወረድን ያስተማረው ማን ነው?
ሀ. ጥራኤል
ለ. ካሳድያዕ
ሐ. ጋድርኤል
መ. ፔንሙዕ

https://youtu.be/BymCKtTN_8w?si=Z6bz1LD7x5nHEQUM

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Dec, 19:06


✔️መልስ፦ ስለወልደ እግዚአብሔር የተነገረ ነው። በኋላ ዘመን ሰው ስለሚሆን መልኩ እንደ ሰው መልክ ነው ተብሏል። ፊቱም ከቅዱሳን መላእክት እንደ አንዱ ነው ማለት እንደ ገብርኤል ነው ማለት ነው። ወደ ምሥጢር ሄዶ ተረጎመው። ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ ገብርኤል ማለት ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነውና።

▶️፲፰. ሄኖ.፲፫÷፯ ላይ "እንዳይወድቁ እርሱን ይመረጐዙ ዘንድ ለጻድቃንና ለቅዱሳን በትር ይሆናል" ይላል። በትር ይሆናል የተባለ ማን ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ነው።

▶️፲፱. ሄኖ.11፥2 ላይ "መንግሥት እንዴት እንደምትከፈል ሰዎችም በሠሩት ሥራቸው ዋጋቸው እየተመዘነ እንዲሰጣቸው አየሁ" ይላል። የመንግሥት መከፈል የተባለ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የመንግሥት መከፈል የተባለው በዕለተ ሞት በዕለተ ምጽአት ኃጥኣን ከጻድቃን ተለይተው እንደሚኖሩና ጻድቃን ወደ መንግሥተ ሰማያት ኃጥኣን ወደ ገሀነመ እሳት እንደሚሄዱ የሚገልጽ ነው።

▶️፳. "የመላእክት ጌታን ስም የካዱ ኃጥኣንም ሁሉ ከመንግሥተ ሰማይ ወጥተው ሲሰደዱ ዓይኖቼ አዩ። መላእክት ስበው ያወጧቸዋል" ይላል (ሄኖ.11፥4-5)። የጌታን ስም የካዱ ሲጀመር እንዴት መንግሥተ ሰማያት ገቡ? መንግሥተ ሰማያት ከገቡ በኋላ መውጣት የለም ለዘለዓለም እንደመላእክት በደስታ ሲያመሰግኑ መኖር እንጂ ይባላልና ከዚህ ንባብ ጋ እንዴት ይታረቃል?

✔️መልስ፦ መጀመሪያም ኃጥኣን መንግሥተ ሰማያት አልገቡም። ስበው ያወጧቸዋል ማለት መጀመሪያውኑም እንዳይገቡ ያደርጓቸዋል ተብሎ ይተረጎማል እንጂ መንግሥተ ሰማያት መጀመሪያም ገብተው ቢሆን ኖሮስ እዚያ ከገቡ በኋላ መውጣት ስለሌለ ባልወጡ ነበር።

▶️፳፩. "በነፋሳት ጌታም ትእዛዝ አንዱ ሁለተኛውን ያየዋል። ለእነርሱ ዕረፍታቸው ምስጋናቸው ነውና ፈጽመው ያመሰግናሉ ከምስጋናውም አያርፉም ለሚያበራ ፀሐይም ብዙ መለዋወጥ አለውና ለበጎዎች በረከት ነው ለክፉዎችም መርገም ነው" ይላል (ሄኖ.11፥15-16)። አንዱ ሁለተኛውን ያየዋል ሲል ምን ለማለት ነው? ለሚያበራ ፀሐይም ብዙ መለዋወጥ አለውና ለበጎዎች በረከት ነው ለክፉዎችም መርገም ነው የሚለው ቢብራራ።

✔️መልስ፦ ጨረቃና ፀሐይ በሰሌዳ ሰማይ በብዙ መልኩ በአንፃር ስለሚተያዩ አንዱ ሁለተኛውን ያየዋል ተብሏል። ፀሐይ ለበጎዎች በረከት ነው ማለት ለማያመልኩት በረከት ነው ማለት ነው። ለክፉዎች መርገም ነው ማለት ፀሐይን አምላክ ነው ብለው ለሚያመልኩት መርገም ነው ማለት ነው።

▶️፳፪. "ጥበብ የምታድርበት ቦታን አላገኘችም ማደሪያዋም በሰማይ አለ። ጥበብ በሰው ልጆች ልታድር ወጣች በሰው ዘንድ ማደሪያ አላገኘችም ጥበብ ወደ ማደሪያዋ ወደ መላእክት ልቡና ተመለሰች በመላእክትም መካከል አደረች" ይላል (ሄኖ.12፥1-2)። ጥበብ የምታድርበት ቦታን አላገኘችም ማለት ምን ማለት ይሆን? ወደ ማደሪያዋ ወደ መላእክት ልቡና ተመለሰች በመላእክትም መካከል አደረች ሲልስ?

✔️መልስ፦ ጥበብ የምታድርበትን ቦታን አላገኘችም ማለት ሕግን ሰው አልጠበቃትም ማለት ነው። ወደማደሪያዋ ወደመላእክት ልቡና ተመለሰች ሲል በመላእክት መካከል አደረች ማለት መላእክት ሕግን ጠብቀው ይኖራሉ ማለት ነው።

▶️፳፫. ሄኖ.12፥3 ላይ "ዐመፃ ከመዛግብት ወጣች ያልወደደችውን አገኘች። ዝናም በምድረ በዳ ጠል በተጠማች ምድር እንዲያድር እሷም በእነርሱ አደረች" ይላል። ይህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ዐመፃ ከመዛግብት ወጣች ማለት ክሕደት ከዲያብሎስ ከአጋንንት ተገኘች ማለት ነው።

▶️፳፬. ሄኖ.12፥40 ላይ "የጻድቁም ደም በመላእክት ጌታ ፊት ተወደደ" ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የሰማዕታት ደም በከንቱ ፈስሶ አይቀርም ዋጋ ያሰጣል ማለት ነው። እንዲሁም ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ያፈሰሰው ደም ለምዕመናን መዳኛ ስለሆነ ተወደደ ማለት ነው።

▶️፳፭. "በዙሪያውም ብዙ የጥበብ ምንጮች ይከቡታል። የተጠሙ ሰዎችም ሁሉ ከእርሱ ይጠጣሉ ይማራሉ ጥበብንም ይመላሉ" ይላል (ሄኖ.13፥2)። ምንጭ የተባለ ምንድን ነው?የተጠሙ ሰዎችም ሁሉ ከእርሱ ይጠጣሉ ይማራሉ ጥበብንም ይመላሉ ሲልስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ምንጭ የተባለ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ምንጮች ሲል ብሉይ ኪዳን ሐዲስ ኪዳን ማለት ነው። የተጠሙትም ሰዎች ከእርሱ ይጠጣሉ ማለት ከዕውቀት ከትምህርት የተጠሙ ሰዎች እኒህን ተምረው ያውቃሉ ማለት ነው። ጥበብንም ይሞላሉ ማለት ብሉይ ሐዲስን የተማሩ ሰዎች ጥበብ ሥጋዊን ጥበብ መንፈሳዊን ገንዘብ ያደርጋሉ ማለት ነው።

▶️፳፭. "ፈጽመው በተጨነቁባት ቀን ሰውነታቸውን አላዳኑምና ይችን ዓለም የሚገዟት ሰዎችና የዚህ ዓለም ነገሥታት በእጃቸው ስለ ሠሩት ክፉ ሥራቸው በዚያ ወራት አንገታቸውን የደፉ ሆኑ። በመረጥኋቸው በጻድቃንም እጅ ይጥሏቸዋል" ይላል (ሄኖ.13፥13-14)። በመረጥኋቸው በጻድቃንም እጅ ይጥሏቸዋል ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በጻድቃን እጅ ይጥላቸዋል ማለት ኃጥኣን ጻድቃንን ሲበድሉ ይኖራሉ ጻድቃንም ታግሠዋቸው ይኖራሉ። እግዚአብሔር ደግሞ ኃጥኣን ጻድቃንን ስለበደሉ የሚፈርድባቸው ስለሆኘ በጻድቃን እጅ ይጥላቸዋል አለ እንጂ በጻድቃን እጅ ይጠፋሉ ማለት አይደለም።

▶️፳፯. ሄኖ.፲፪ "ጥበብ የምታድርበት ቦታ አላገኘችም። ማደሪያዋም በሰማያት ነው አለ" ይላል። ማደሪያ አላገኘችም የሚለውና ማደሪያዋ በሰማያት ነው የሚለው አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ማደሪያ አላገኘችም የተባለው በምድር ነው። አዳም ሕግን አለመጠበቁን ለመግለጽ የተነገረ ነው። ማደሪያዋ በሰማያት ነው ማለት ደግሞ መላእክት ሕግን ጠብቀው እንደቀጠሉ ለመግለጽ ነውና።

▶️፳፰. "የወዳጆቼ የሁለቱ ነገድ አገር ግን ለፈረሶቻቸው መሰናክል ትሆናለች" ይላል (ሄኖ.15፥17)። ሁለቱ ነገድ የተባሉ እነማን ናቸው? ከቁ 21 ላይ "በውስጧም ይቀበራሉ ሁለቱን ነገድ ከመበደላቸው የተነሣ ሲኦል ትውጣቸዋለች" ይላል። ቁጥር 17 ላይ ወዳጆቼ  ብሎ እዚህ ላይ ደግሞ በደለኛ እንደሆኑ ይገልጻልና አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ሁለቱ ነገድ የተባሉት ነገደ ብንያምና ነገደ ይሁዳ ናቸው። ወዳጆቼ ያላቸው በቀድሞ ሥራቸው ነው። ከእነርሱ ኢዮስያስ፣ ሕዝቅያስና ብዙ ደጋግ ነቢያት ስለተነሡ ስለእነዚያ ወዳጆቼ ብሏቸዋል። እንደገና በኋላ ሌሎች ሰዎች ጣዖት አምልከው ስለበደሉት ሲኦል ባቢሎን ትውጣቸዋለች ብሏል።


© በትረ ማርያም አበባው

✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Dec, 19:06


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 90 💙💙

▶️፩. ሄኖ.12፥18 ከገጸ ምድር አጠፋቸዋለሁ ማለት ከመንግሥተ ሰማያት እንደሚለያቸው ነው ወይስ ወደ አለመኖር (annihilation) ሊመልሳቸው?

✔️መልስ፦ ከመንግሥተ ሰማያት እንደሚለያቸው መናገር ነው እንጂ ወደ አለመኖር መመለስ አይደለም።

▶️፪. ሄኖ.12፥20 እንደ ሰው መልክ ፊቱም እንደ መላእክት ይላል የሰው እና የመላእክት ተስዕሎተ መልክዕ አንድ ነው እንዴ?

✔️መልስ፦ መላእክት ረቂቅ ቢሆኑም ብዙ ዓይነት ኅብረ መልክእ እንዳላቸው በመጽሐፈ አክሲማሮስ ተገልጿል። የአንዳንዶች መላእክት ተስዕሎተ መልክእ ምንም እንኳ ረቂቅ ቢሆን ከሰው ጋር ተመሳሳይ ነው።

▶️፫. ብሉየ መዋዕል ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ብሉየ መዋዕል ማለት ዘመንን የሚያስረጅ ማለት ነው። እንደሚታወቀው ዘመን ፍጥረታትን ሁሉ ያስረጃል። በፈጣሪ ግን እርጅና ስለሌለበት ዘመናትን ያስረጃል እንጂ አያረጅም። ይህን ለመግለጽ ብሉየ መዋዕል ይባላል።

▶️፬. "ከሰማያት በላይ ያለው ውሃ ግን ተባዕታይ ነው። ከምድር በታች ያለችው ውሃም አንስታይ ናት" ይላል (ሄኖ.14፥32)። የንባቡ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከላይ ያለው ውሃ ተባዕታይ ነው የሚለው ምሳሌያዋ አነጋገር ነው። ከደብር ቅዱስ የወረዱት ወንዶች ናቸው ማለት ነው። ከታች ያለው ውሃ አንስታይ ነው ማለት ደቂቀ ሴት የተገናኟቸው ደቂቀ ቃኤል ሴቶች ናቸው ማለት ነው። እንዳለም በቁሙ ይተረጎማል። በሰማይ ያለው ውሃ ተባዕታይ ይባላል። በማየ አይኅ ጊዜ ምድርን ለማጥፋት ሲመጣ ኃይል ነበረው ማለት ነው። ወንድ ደግሞ ከሴት ይልቅ ኃያል ስለሆነ ነው። ከታች የመነጨው ከላይኛው አንጻር ኃይሉ ደካማ ስለነበረ አንስታይ ተብሏል።

▶️፭. "እነዚህ ሁሉ በአስታራቂው ፊት በእሳት ፊት እንዳለ አደሮማር ይሆናሉ" ይላል (ሄኖ.15፥7)። አደሮ ማር ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አደሮ ማር ግራር ላይና ሌሎችም ላይ የሚወጣ እንደ ሙጫ ያለ ነው።

▶️፮. ሄኖ.15፥3 ላይ ጌታ ማየ አይኅን የማያመጣው የሰማይ ዘመን ያህል ለዘላለም ነው (ዘፍ.9፥15) ይላል። የሰማይ ዘመን ማለት ለዘላለም ማለት ነውን?

✔️መልስ፦ አዎ። የሰማይ ዘመን ማለት በሰማይ የምንኖረው ዘመን ብዙ እንደሆነ ሁሉ ለዘለዓለም ማየ አይኅን አምጥቼ አላጠፋም ማለቱ ነው።

▶️፯. ሄኖ.12፥2 ጥበብ ክርስቶስ ያደረው በሰው ልጅ ወይስ በመላእክት? እዚህ ላይ ጥበብ የተባለው ክርስቶስ ሳይሆን ሕጉ ነው ከተባለ ሕጉ እንዴት ጥበብ ተባለ?

✔️መልስ፦ ጥበብ ክርስቶስ ያደረው በሰው ነው። በዚህ ጊዜ ኅድረት ሥጋዌ ተብሎ ይተረጎማል። ኢነሥኦ ለዘነሥኦ እመላእክት አላ እምዘርዐ አብርሃም ንሕነ እንዲል ጳውሎስ። ጥበብ ሕግ ተብላ ትተረጎማለች። ሕግ ጥበብ መባሏ ሰውን ወደ እውነት ወደ ሕይወት መርታ የምታደርስ ስለሆነ ነው። ማደሪያዋ በመላእክት አለ ማለት መላእክት ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው ይኖራሉ ማለት ነው።

▶️፰. "ከዚያም የምድርን ትቢያ ይጠግባሉ" ይላል (ሄኖ.11፥7)። የንባቡ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ትርጉሙ በምድር ትቢያዎች ላይ ዝናም ይዘንባል ማለት ነው።

▶️፱. "መብረቅ መብረቅን ይወልዳል። አመላለሳቸውም በመልኮቻቸው ቁጥር ነው። ሃይማኖታቸውንም እርስ በርሳቸው ይጠብቃሉ" ይላል (ሄኖ.12፥7)። ሃይማኖታቸውንም እርስ በርስ ይጠብቃሉ ሲል ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ምሳሌ ነው። መብረቅ መብረቅን ይወልዳል ማለት መምህር መምህርን ይወልዳል ማለት ነው። ሃይማኖታቸውንም እርስ በእርስ ይጠብቃሉ ማለት መምህርና ደቀመዝሙር በሃይማኖት ጸንተው ይኖራሉ ማለት ነው።

▶️፲. ከጨዋነት ወደ ነቢይነት መመለሳቸው በመልአከ ዑቃቢያቸው ቁጥር ነው ሃይማኖታቸውንም እርስ በእሳቸው ይጠብቃሉ (ሄኖ.12፥2)። ከጨዋነት ወደ ነቢይነት መመለሳቸው ሲባል ምን ማለት ነው? መልአከ ዑቃቢ ምን ዓይነት መልአክ ነው?

✔️መልስ፦ አንድ ሰው ተምሮ መምህር ነቢይ ይሆናል። ይህን ጊዜ ከጨዋነት ወደ ነቢይነት ይሸጋገራል። ይህ የሚሆነው ደግሞ በመልአከ ዑቃቢ ነው ማለት በመምህር አጋዥነት ነው ማለት ነው። እንደገና መልአከ ዑቃቢ ማለት ቃል በቃል ጠባቂ መልአክ ማለት ነው። ለእያንዳንዱ ሰው ከፈጣሪ ዘንድ ጠባቂ መልአክ ይመደብለታል።

▶️፲፩. "እጆቻቸው ክፉ ሥራን ይሠራሉ ዕዳ ሊሆንባቸው ኃጥኣን የደከሙበትን ጻድቃን ይበሉታል" ይላል (ሄኖ.14፥3)። ኃጥኣን የደከሙበትን ጻድቃን ይበሉታል ሲል ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ኃጥአን ሀብት ንብረት እያከማቹ ቢኖሩም የኋላ ኋላ እነርሱ ሞተው ገንዘባቸውን ጻድቃን ይወርሱታል ይበሉታል ማለት ነው።

▶️፲፪. "በዚያ ቦታ ዓይኖቼ ዙሀዎችን ቁጥር የሌላቸው የብረት ማሠሪያዎችን አድርገው ሲያሥሯቸው አዩ" ይላል። ዙሀዎች ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ዙሃ የሚባለው ከመሬት ውስጥ የሚገኝ የብረት አፈር ነው። ጠገራ ተብሎም ይተረጎማል። ጠገራ መዓድኑ ብር ነው።

▶️፲፫. "ፀሐይ በዚህ ዓለም እንዲያበራ ብርሃነ መለኮቱ ያበራልና ድ*ን-ቁር*ናም ጠፍቷልና የማይቈጠር ጸጋ ክብር ይሰጣል። አስቀድሞ ድን*-ቁር*ና ጠፍቷልና። ጻድቃን በዘመኑ ቁጥር ወደ መንግሥተ ሰማያት አይገቡም" ይላል (ሄኖ.15፥36)። ጻድቃን በዘመኑ ቁጥር ወደ መንግሥተ ሰማያት አይገቡም ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ጻድቃን በዘመኑ ቁጥር መንግሥተ ሰማያት አይገቡም ማለት በሚገቡበት ቦታ የዘመን ገደብ ወይም መጠን የለም ለዘለዓለም ይኖራሉ ማለት ነው።

▶️፲፬. ሄኖ.12፥12 "ወደ ሰማይ አይወጡም ወደ ምድርም አይወርዱም። የመላእክትን ጌታ ስም የሚክዱ ፍጹም መከራ ለሚደረግበት ቀን እንደዚህ የሚጠብቁ የኃጢአተኞች እድል እንዲህ ይሆናል። በዚያች ቀን ክርስቶስ በጌትነቱ ዙፋን ይቀመጣል" ይላል። ክርስቶስ የሚለው ስም በብሉይ ኪዳን ይጠሩት ነበር በተደጋጋሚ እዚህ መጽሐፍ ሲያነሣው አየሁ ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ አዎ በትንቢት ክርስቶስ እንደሚመጣ ይታወቅ ስለነበረ ነቢዩ ሄኖክም ደጋግሞ ጠርቶታል። ሌሎች ነቢያትም ለምሳሌ ዕዝራ መቅደስ ትትሐነፅ እስከ ክርስቶስ ንጉሥ ወእምዝ ትትመዘበር ብሎ ተናግሯል። ሌሎችም በብዙ መልኩ ተናግረዋል።

▶️፲፭. ሄኖ.14፥3 "የብረት ተራራን የናስ ተራራን የብር ተራራን የወርቅ ተራራን የዕይር ተራራን የርሳስ ተራራን አዩ" ይላል። የዕይር ተራራ ይላልና ዕይር ምን ዓይነት ቁስ ነው እርሳስስ?

✔️መልስ፦ ዕይር የሚለው ብርትን (መዳብን) ነው። የብርት ተራራ (የመዳብ ተራራ) ለማለት ነው። እርሳስም ሰማያዊና አመድማ የሆነ ከባድ የመዓድን ዓይነት ነው።

▶️፲፮. ሄኖ.11፥5 ላይ መላእክት ስበው ያወጧቸዋል ይላል። ከምን ወደምን ነው ስበው የሚያወጧቸው?

✔️መልስ፦ ቀጥታ የሚተረጎም አይደለም። ስበው ያወጧቸዋል ማለት ኃጥኣንን መንግሥተ ሰማያት አያስገቧቸውም ማለት ነው።

▶️፲፯. ሄኖ.12÷19-20 "በዚያም ብሉየ መዋዕልነት ያለውን አየሁ ራሱም እንደ ባዘቶ ነጭ ነው" ይላል። መልኩ እንደ ሰው መልክ የሆነ ሌላም ከእርሱ ጋር አለ። ጸጋንም የተመላ ነው። ፊቱም ከቅዱሳን መላእክት እንደ አንዱ ነው" ይላል። ከላይ የተገለጹት በሙሉ ስለማን ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Dec, 05:48


💗 መጽሐፈ ሄኖክ ክፍል 3 💗

💗ምዕራፍ 11፡-
ሄኖክ የሰማያትን ምሥጢሮች እንዳየ፣ የፀሐይን የጨረቃን ጎዳና እንደተመለከተ

💗ምዕራፍ 12፡-
ሄኖክ የሰማይ ከዋክብትን እንዳየ፣ ሄኖክ እግዚአብሔርን በራእይ እንዳየው
-ክርስቶስ እንደሚወለድ ሄኖክ ትንቢት መናገሩ

💗ምዕራፍ 13፡-
እግዚአብሔር ጻድቃንን በስሙ እንደሚያድናቸው

💗ምዕራፍ 14፡-
ኃጥኣን ወደ ገሃነም እንደሚጣሉ ሄኖክ በራእይ ማየቱ

💗ምዕራፍ 15፡-
ሰዎች ከሰዎች ጋር እንደሚጣሉና ጦርነትን እንደሚያነሡ መነገሩ
-ጻድቃን በዘለዓለማዊ የሕይወት ብርሃን እንደሚኖሩ

💗የዕለቱ ጥያቄዎች💗
፩. እግዚአብሔር ለሄኖክ በምን አምሳል ተገለጸለት?
ሀ. ጸጕሩ እንደባዘቶ ነጭ በሆነ ሰው አምሳል
ለ. ዙፋን ላይ በተቀመጠ ንጉሥ አምሳል
ሐ. በርግብ አምሳል
መ. ሀ እና ለ
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ጻድቃን ይህንን ዓለም ጠልተው ንቀውታል
ለ. ንስሓ የማይገባ በእግዚአብሔር ፊት ይጠፋል
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከሰማያት በላይ ያለው ውሃ ተባዕታይ ይባላል
ለ. ከምድር በታች ያለ ውሃ አንስታይ ይባላል
ሐ. ከሰማያት በላይ ያለው ውሃ አንስታይ ይባላል
መ. ሀ እና ሐ

https://youtu.be/6pPl_y_ZfeU?si=BgC5_gk7gn_kCP2K

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

30 Dec, 17:55


💙💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 89 💙💙

▶️፩. "ሰባተኛውም ተራራ በእነዚህ መካከል ነው ቁመታቸው እንደ አፍርንጊ ወምበር ሁሉም ይመሳሰላሉ" ይላል። አፍርንጊ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የግእዝ ድርሳናት አፍርንጊ የሚሉት ፈረንጅ፣ የፈረንጅ ሀገር ለማለት ነው። "ጀ" የሚባል ፊደል በግእዝ ቋንቋ ስለሌለ ፈረንጅ ለማለት አፍርንጊ ይላሉ።

▶️፪. "በዚያ ወራት ሄኖክ ቁጣና ቅናት የተጻፈባቸው መጽሐፎችን ሁከትና ችኮላም የተጻፈባቸው መጽሐፎችን ያዘ" ይላል። ቁጣና ቅናት የተጻፈባቸው መጻፎች ሲል ምን ዓይነት ይዘት ያላቸው መጽሐፎች ናቸው?

✔️መልስ፦ አሁን እንዲህ ያለው በሰማይ የተጻፉ መጻሕፍት ኖረው አይደለም። የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ለሄኖክ ተገልጾለት ጽፏል እንጂ። ቁጣና ቅንዐት የተጻፈባቸው ማለት እግዚአብሔር ቀናዒ አሞላክ መሆኑን መግለጽ ነው። ቁጡ መባሉም በትክክል ፈርዶ የሚያጠፋ ስለሆነ ነው። ሁከትና ችኮላ የተጻፈባቸው መጽሐፎች መባሉ ለሄኖክ ወደፊት የሚሆነው ሁከት ተገልጾለት እንዳወቀው የሚገልጽ ነው። እንጂ የተጻፉ መጻሕፍት ኖረው አይደለም።

▶️፫. "የክብር ጌታ ምድርን በበጎ ሊጎበኛት በወረደ ጊዜ የሚቀመጥበት ዙፋኑ ነው" ይላል (ሄኖ.7፥15)። ስለ መስቀሉ ዛፍ እያወራ ነው? ወይስ ሌላ?

✔️መልስ፦ ይህ ለጊዜው በሙሴ ዘመን የብሉይ ኪዳን ሕግ ስለሚሰጥበት ስለደብረ ሲና ተራራ የተነገረ ነው። በምሥጢር ግን ለቀራንዮ፣ ለመስቀል፣ ለድንግል ማርያም ያስተረጉማል።

▶️፬. "ይህ ቦታ እንዴት የሚያስፈራ ነው? ለማየትም ደዌ ነው አልሁ" ይላል (ሄኖ.6፥17)። ለማየትም ደዌ ነው ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ሲያዩትም ስለሚያስደነግጥ በሽታ ይሆናል ያማል ማለት ነው።

▶️፭. ሄኖ.፰÷፮ "በዚያም የፍርድ እንጨቶችን አየሁ" ይላል። የፍርድ እንጨት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሥርዓት ሕግ የተሠራባቸውን እንጨቶች አየሁ ማለቱ ነው። በምሥጢር ደግሞ የሚያስፈርዱብንን ሕገጋት አየሁ ማለት ነው።

▶️፮. ሄኖ.፮÷፬ ራጉኤል ስለዓለምና ብርሃናት የሚበቀል ነው ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሰይጣን የብርሃን መልአክ እንደሚመስል ቅዱስ ጳውሎስ ጽፎልናል። ስለዚህ የብርሃን መልአክ የሚመስሉ አጋንንትን የሚበቀል ለማለት ራጉኤል ብርሃናትን የሚበቀል (ብርሃናት ሳይሆኑ ብርሃናት የሚመስሉትን የሚበቀል) ተብሏል።

▶️፯. ሄኖ.፮÷፮ ሠረቃኤል በሰውነታቸው ላይ ኃጢአት በሚሠሩ በሰዎች መናፍስት ላይ የተሾመ ነው። የሰው መናፍስት አሉ እንዴ? ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ መንፈስ ብሎ ሰውነት ይላል። ስለዚህ በሰዎች ሰውነት ላይ የተሾመ ማለት ነው። ይኸውም አእምሮ ያጡ፣ ያበዱ ሰዎች ቢኖሩ ራሳቸውን የበለጠ እንዳይጎዱ በእነርሱ ላይ የተሾመ ማለት ነው።

▶️፰. ሄኖ.፮÷፯ ገብርኤል በእባቦች ላይና በኪሩቤል ላይ የተሾመ ነው። በሥልጣን ከኪሩቤል ይበልጣል? ወይስ በእነሱ ላይ መሾሙ ምንድን ነው? በእባቦች ላይ የተሾመ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ገብርኤል በእባቦች ላይ የተሾመ መባሉ እባቦች በሰው ላይ ብዙ ጉዳት እንዳያደርሱ የተሾመ ማለት ነው። በኪሩቤል ላይ የተሾመ መባሉ የነገደ መላእክት የአለቃ አለቃ ሁለት አሉ። እነዚህም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ናቸው። ገብርኤል በራማ የአርባብ አለቃ ሲሆን በኢዮር በኪሩቤል ላይም አለቃ ተደርጎ ተሹሟልና ነው። ሚካኤል ከኃይላት በተጨማሪ የሱራፌል አለቃ እንደሆነው ያለ ነው።

▶️፱. "የአራቱ ገጻት ቃላትም በክብር ጌታ ፊት ሲያመሰግኑ ሰማሁ" ይላል (ሄኖ.10፥4)። አራት ገጻት ቃላት እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ የአራቱ ገጻት ቃላት ያለው የአራቱን መላእክት የምስጋና ቃል ሰማሁ ማለቱ ነው።

▶️፲. ሄኖ.9÷2 ያለዚህ የአበው ነገራቸው ከዘጠኙ ሕገጋት ኢታምልክ ይበልጣል ማለት ነው። እኛም በኋላ የተነሣን ሰዎች ከዘጠኙ ሕገጋት ኢታምልክ ትበልጣለች ማለትን አንከለክልም ይላል። ኢታምልክ ሲል ምን ማለት ነው ? ደግሞስ ሕገጋት ያለው የትኞቹን ሕገጋት ነው?

✔️መልስ፦ ኢታምልክ የሚለው ከአሥሩ ሕገጋት የመጀመሪያው ሕግ ነው። ሙሉው ኢታምልክ ባዕደ አምላከ ዘእንበሌየ ይላል። ትርጉሙ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልክ ማለት ነው። ሕገጋት ያላቸው ሌሎቹ ዘጠኙ ደግሞ ከዚህ ቀጥለው ያሉት አትስረቅ፣ አትግደል፣ አታመንዝር እያሉ የሚጠቀሱት ቀሪዎቹ ናቸው።

▶️፲፩. "ከዚያም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ በምዕራብ ወዳለ ወደ ሌላ ቦታ ሄድሁ። ሳያርፍ እየሮጠ የሚነድን እሳትንም አየሁ እኔ እንዳየሁት ፈጽሞ ሲሮጥ ይኖራል እንጂ በሌትና በቀን ከሩጫው አይገታም አያርፍም ሲል ነው። ያን ጊዜ ከኔ ጋራ ያለ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ራጉኤል መለሰልኝ ወደ ምዕራብ ሊሮጥ ሩጫውን ያየኸው ይህ የሚነድ እሳት ነው ይኸውም ለሰማይ የሚያበራ ፀሐይ ነው" ይላል (ሄኖ.6፥39-40)። በምድር ያለ ነገር እንዴት ለሰማይ ሊያበራ ይችላል? ወይስ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ፀሐይ ያለው በሰማይ ነው። ስለዚህ በሰማይም በምድርም ያበራል ማለት ነው። በሌትና በቀን ያበራል መባሉ በአንዱ ሌሊት በሆነበት ሀገር በሌላው ቀን ወይም ጠዋት ሆኖ ሲያበራ ይገኛልና ነው።

▶️፲፪. ሄኖ.7፥15 ላይ "ይህ ተራራ የተመሰገነ የገነነ የዘለዓለም ንጉሥ የሚሆን የክብር ባለቤት ይህችን ዓለም በበጎ ሊጎበኛት በወረደ ጊዜ የሚቀመጥበት ዙፋኑ ደብረ ሲና ነው" ሲል ስለ ዳግም ምጽአቱ የሚያመለክት ቃል ነው ወይስ ለሙሴ ስለመገለጹ?

✔️መልስ፦ ለጊዜው ለሙሴ ስለመገለጹ የተነገረ ነው። ፍጻሜው ግን ለድንግል ማርያም ማኅፀን፣ ለመስቀል፣ ለቀራንዮ ያስተረጉማል።

▶️፲፫. "ለደጋጎች ለተዋረዱም ሰዎች ከዚህ እንጨት ፍሬ ይሰጣቸዋል ለተመረጡም ሰዎች ደኅንነት ይሰጣል" ይላል (ሄኖ.7፥17)። እዚህጋ የተገለጸው የእንጨት ፍሬ ለደጋጎችና ለተመረጡ ሰዎች ድኅነትን ይሰጣል ሲል ምን ማለት ነው? አዳም ከወጣ በኋላ መቼስ በገነት መብላት የለ።

✔️መልስ፦ ጉዳዩ ስለእንጨትና ፍሬ የተነገረ ሳይሆን በምሳሌ የተነገረ ነው። ሕገ እግዚአብሔርን በመጠበቅ የሚገኝ ክብር ለጻድቃን ይሰጣል ማለት ነው። "ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙሓዘ ማይ" እንዳለው ያለ ነው (መዝ.1)።

▶️፲፬. "በዚያም ቦታ ሳለሁ በፀሐይ መውጫ በኩል የተከፈቱ ሦስት የሰማይ ደጃፎችን አየሁ። በታናናሽ ደጃፎችም ላይ ከነዚህ ደጃፎች በእያንዳንዱ ታናናሾች የሰማይ ኮከቦች ይገቡበታል" ይላል ሄኖ.8፥43-44። ይሄ ንባብ ትርጓሜው ምን ይሆን?

✔️መልስ፦ ቀጥታ መተርጎም ነው። ሄኖክ በምሥራቅ በኩል ሦስት የሰማይ ደጃፍ አይቷል። በዚያ ደግሞ ከዋክብት ሲወጡ ሲገቡ አይቷል።

▶️፲፭. ሄኖ.10፥8 "ሰይጣናትን አስወጥቶ ሲሰዳቸው አራተኛውንም ቃል ሰማሁ" ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ አራተኛው ቃል የተባለው ከዚህ መልአኩ ፋኑኤል እንደሆነ መተርጕማን ገልጸዋል።


© በትረ ማርያም አበባው


✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Dec, 19:19


✔️መልስ፦ የሀገሩን ሠራዊት አስገድሎ ስለመጣ ከዚህ በኋላ በማን ልትነግሥ ነው ብለው ገድለውታል።

▶️፲፰. "ኢሳይያስም እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይኾንልኻል። ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይኼድ ዘንድ ወይም ዐሥር ደረጃ ወደ ዃላ ይመለስ ዘንድ ትወዳ፟ለኽን አለ" ይላል። ትርጉሙ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የተለየ ምሥጢር የለውም። በወቅቱ ሕዝቅያስ እንደሚፈወስ ለመግለጽ ተአምር ተደርጎለታል። ተአምሩ ደግሞ ከነበረው ሰዓት ወደኋላ አሥር ሰዓት መመለስ ነበረ።

▶️፲፱. "ራፋስቂስ ግን ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወዳንተና ወደ ጌታኽ ልኮኛልን ከእናንተ ጋራ ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደተቀመጡት ሰዎች አይደለምን አላቸው" ይላል። ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የትዕቢት አነጋገር ነው። ትዕቢተኛ ሸንትህን ነው የማጠጣህ ኩስህን ነው የማበላህ ብሎ እንደሚታበየው ያለ ነው።

▶️፳. "በንጉሡም በሕዝቅያስ በዐሥራ አራተኛው ዓመት የአሶር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደተመሸጉት ከተማዎች ዅሉ ወጣ ወሰዳቸውም" ይላል። ከፍ ብሎ ግን የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር ነው ነው የሚለው አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ስልምናሶር ቀድሞ የነበረ የአሦር ንጉሥ፣ ሰናክሬም ደግሞ በኋላ የነበረ የአሦር ንጉሥ ነው።

▶️፳፩. ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ። ከፊቱም ጣላቸው። ከይሁዳም ነገድ ብቻ በቀር ማንም አልቀረም። ለምን ይሁዳ ተለይቶ ቀረ?

✔️መልስ፦ ይሁዳ በሃይማኖት በምግባር ከእስራኤል የተሻሉ ስለነበሩ ነው። ለጊዜው ይህ ይሁን እንጂ እነርሱም ቢሆን በድለው በኋላ ተማርከዋል።

▶️፳፪. "ነገር ግን በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ ደግሞም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብ ርኵሰት ልጁን በእሳት አሳለፈው " ይላል (2ኛ ነገ.16፥3)። ልጁን በእሳት አሳለፈው ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ልጁን በእሳት ሠዋው ማለት ነው።

▶️፳፫. "በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን አሳረገ፥ የመጠጡንም ቍርባን አፈሰሰ፥ የደኅንነቱንም መሥዋዕት ደም ረጨ" ይላል (2ኛ ነገ.16፥13)። ንጉሡ አካዝ ይህን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ነው ያቀረበው ወይስ ለጣዖት? ከላይ "በመስገጃዎችና በኮረብቶቹ ላይ በለመለመውም ዛፍ ሁሉ በታች ይሠዋና ያጥን ነበር" ስለሚል ግልፅ አልሆነልኝም።

✔️መልስ፦ ለጣዖት ነው የሠዋው።

▶️፳፬. "በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ ነገር ግን ከእርሱ አስቀድሞ እንደ ነበሩት እንደ እስራኤል ነገሥታት አይደለም "ይላል (2ኛ ነገ.17፥2)። ነገር ግን ከእርሱ አስቀድሞ እንደ ነበሩት እንደ እስራኤል ነገሥታት አይደለም ሲል ምን ማለት ነው ከጥቂቶች በቀር አስቀድመው የነበሩትስ ቢሆን መቼ እግዚአብሔርን ደስ አሰኙትና?

✔️መልስ፦ ከቀደሙት ይሻላል ለማለት የተነገረ ቃል ነው።

▶️፳፭. "እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፥ የሚሄድበትም መንገድ ተከናወነለት፤ በአሦርም ንጉሥ ላይ ዐመፀ፥ አልገበረለትም" (2ኛ ነገ.18፥7) ካለ በኋላ "የይሁዳም ንጉሥ ሕዝቅያስ በድያለሁ፥ ከእኔ ተመለስ፤ የምትጭንብኝን ሁሉ እሸከማለሁ ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ ሦስት መቶ መክሊት ብርና ሠላሳ መክሊት ወርቅ ጫነበት ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤት መዛግብት የተገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው" ይላል (2ኛ ነገ.18፥14-15)። ሁለቱ አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም ሕዝቅያስ ደግ ሰው ነበረ። ነገር ግን ፍጹም ስላልነበረ በድሎም ነበረ። መጀመሪያ በአሦር ንጉሥ ላይ ዐምፆ ነበረ። በኋላ ግን ፈርቶ ለመገበር ተስማማ። በስምምነቱ መሠረትም ከቤተ መንግሥቱና ከእግዚአብሔር ቤት ያገኘውን ብር ገብሮለታል።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Dec, 19:19


💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 66 💙

▶️፩. "የሴፌርዋይም ሰዎች ለሴፌርዋይም አማልክት ለአድራሜሌክና ለአኔሜሌክ ልጆቻቸውን በእሳት ይሠዉ ነበር" ይልና "እግዚአብሔርንም ይፈሩ ነበር" ይላል (2ኛ ነገ.17፥41)። ሁለቱ ተጋጩብኝ ጣዖት እያመለኩ እግዚአብሔርን መፍራት ይቻላልን?

✔️መልስ፦ አይቻልም። ሁለቱንም ቀላቅለው ያመልኩ ነበር ማለት አሁንም በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተጠምቀው ክርስቲያን ነንም ብለው ነገር ግን ቆሌ፣ የቤት አምላክ፣ አቴቴ ወዘተ እያሉ ደግሞ ሌላ እንደሚያመልኩ ዓይነት ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እናመልካለን ይላሉ። በጎን ደግሞ ሌላ ጣዖት ያመልኩ ስለነበረ እንዲህ አለ። ከዚያ በኋላ ነቢይ ሄዶ ከእግዚአብሔር ውጭ ሌላ አታምልኩ ብሎ አስተምሯቸዋል። "ወኢታምልኩ ባዕዳነ አማልክተ ዘእንበለ እግዚአብሔር አምላክክሙ" እንዲል።

▶️፪. "የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሃቅ ሊወጋህ መጥቷል" ይላል (2ኛ ነገ.19፥9)። ይህ ታሪክ ዝርዝሩ በእኛ ይታወቃል?

✔️መልስ፦ በእኛ ሀገር ስለቲርሐቅ የኢትዮጵያ ንጉሥ እንደነበረ የሚናገር እንጂ ስለጦርነቱ ምክንያትና ዝግጅት እንዲሁም በዘመኑ ስለነበረው የአስተዳደር፣ የአኗኗርና የመሳሰሉት ነገር ዝርዝር ጉዳይ የያዘ መጽሐፍ እስከዛሬ አላገኘሁም። አላነበብኩም አላውቀውም።

▶️፫. "ትሞታለህ እንጅ በህይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል" ይላል (2ኛ ነገ.20፥1)። የሕዝቅያስ ኃጢአት ምን ነበር ምንስ ነው የሚያስተካክለው?

✔️መልስ፦ ሕዝቅያስ የሰናክሬም ሠራዊት በመልአኩ አማካኝነት ሲጠፉለት ሐሰተኛ ነቢያት እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ብሎ በዘመኑ የነበረው ነቢይ ኢሳይያስ ትንቢት ሲናገር ሐሰተኛ ነቢያት ትንቢቱን አሳስተው ድንግል የተባለች ኢየሩሳሌም ናት ወንድ ልጅ የተባልክ አንተ ነህ ብለው በሐሰት ሲነግሩት ሕዝቅያስ እሆንን ብሎ አሰበ። እግዚአብሔርም ሕዝቅያስን በዚህ ትዕቢቱ እንዲታመም አድርጎታል። ቤትህን አስተካክል ማለት ንስሓ ግባ ከክፉ ሥራህ ተመለስ ማለት ነው።

▶️፬. ኢሳይያስ ለሕዝቅያስ በቤቱ ያሉት ወደ ባቢሎን እንደሚፈልሱና ልጆቹም ተማርከው የንጉሥ ጃንደረቦች እንደሚሆኑ ሲነግረው ለምን
"እግዚአብሔር የተናገረው ቃል መልካም ነው" አለ?

✔️መልስ፦ ምንም ቢሆን ምን እግዚአብሔር የተናገረውና የሚናገረው ቃል ሁልጊዜም መልካም ስለሆነ እንዲህ አለ። በውስጡ ግን ተአምኖ ኃጣውእ አለበት። ሕዝቅያስ በደሉን አምኖ እግዚአብሔር ያዘዘበትን መከራ በአኰቴት መቀበሉን ያሳየናል።

▶️፭. "ከተነሱብኝ ከሶርያ እና ከእስራኤል ንጉሥ አድነኝ" ይላል (2ኛ ነገ.16፥7)። በወቅቱ ነገዶቹ የየራሳቸው ንጉሥ ነበራቸው ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የያዕቆብ ልጆች ለሁለት ተከፍለው ይኖሩ ነበር። አሥሩ ነገድ ለብቻው ሀገር መሥርቶ የሀገሩን ስም እስራኤል የከተማዋን ስም ሰማርያ ብለው ይኖሩ ነበር። ሁለቱ ነገድ ማለትም ነገደ ይሁዳና ነገደ ብንያም ደግሞ ሀገሩን ይሁዳ ከተማውን ኢየሩሳሌም ብለው ይኖሩ ነበር።

▶️፮. 2ኛ ነገ.18፥3 ላይ "ሕዝቅያስ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አደረገ" ይላል። 2ኛ ነገ.18፥14 ላይ ደግሞ ለሰናክሬም "በድያለሁ ከእኔ ተመለስ አለው" ይላል። በደሉ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከዚህ ላይ ሕዝቅያስ በድያለሁ ብሎ ተናግሯል እንጂ በደሉ ምን እንደነበረ አልተገለጸም።

▶️፯. 2ኛ ነገ.19፥21 ላይ ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሰድቦሻልና ንቆሻልምና ይላሉ። ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ የተባለች ማን ናት?

✔️መልስ፦ ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ የምትባለው ኢየሩሳሌም ናት። በሀገሪቱ ሰዎችን መናገሩ ነው። ሰናክሬም የኢየሩሳሌምን ንጉሥና ሕዝብ በመናቁ እግዚአብሔር እንዳጠፋው የሚገልጽ ሙሉ ታሪኩ ነው።

▶️፰. የደማስቆ ንጉሥ እግዚአብሔርን ያመልክ ነበር? ንጉሥ አካዝ በደማስቆ ያየው የየትኛውን መሠዊያ ነው የእግዚአብሔርን ወይንስ የጣዖትን? አርያስ የማን ካህን ነው?

✔️መልስ፦ አያመልክም ነበረ። ንጉሥ አካዝ ያየው መሠዊያ የጣዖት መሠዊያ ነበር። አርያም ካህነ ጣዖት ነበረ።

▶️፱. "እርሱም የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቷል የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ደግሞ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ" ይላል (2ኛ ነገ.19፥9)። በዚያ ጊዜ የኢትዮጵያ ግዛት (ወሰን) እዚያ ድረስ ይደርስ ነበር እንዴ?

✔️መልስ፦ በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ ግዛት ከየት እስከ የት እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱሱ አይገልጽም። ስለዚህ አላውቀውም።

▶️፲. "ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ" ይላል (2ኛ ነገ.19፥28)። "ከኢየሩሳሌም ቅሬታ ከጽዮንም ተራራ የዳነ ይወጣልና" ይላል (2ኛ ነገ.19፥31)። የእነዚህ ንባቦች ትርጓሜ አልገቡኝም?

✔️መልስ፦ ስናግ የፈረስ መግቻ ነው። ስናግ ፈረስን እንደሚገታ ገትቼ እመልስሃለሁ ማለት ነው (በኢሳይያስ አማካኝነት ለሰናክሬም የተነገረ ቃል ነው)። የሁለተኛው ጥቅስ ሐሳብ ከሰናክሬም የዳነው ሁለቱ ነገድ በኢየሩሳሌም ይኖራል ማለት ነው።

▶️፲፩. ዐሥሩ ነገድ በፊት እንደተማረኩ አይተናል። ከዚያ በኋላ ግን ሰናክሬም ከ185000 ሠራዊቱ ጋር ሲጠፋ እንዴ አሥሩ ነገድ ነጻ አልወጡም። ነጻ የወጡትስ መቼ ነው?

✔️መልስ፦ ሰናክሬም ቢሞትም በሰናክሬም ምትክ ልጁ አስራዶን ስለነገሠ ነጻ መውጣት አልቻሉም። ነጻ የወጡት ከ70 ዓመት በኋላ በእነዘሩባቤል አማካኝነት ነው።

▶️፲፪. 2ኛ ነገ.16፥7-9 ላይ የአሦር ንጉስ ቴልጌልቴልፌልሶር የይሁዳን ንጉሥ እንደረዳው ሲናገር 2ኛ ዜና መዋ.28፥20-21 ግን አልረዳውም ይላል አይጋጭም ወይ?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ረአሶንን በመግደል ረድቶታል። ይህንን ሲያይ መጽሐፈ ነገሥት እንደረዳው ተገለጸ። ግን ደግሞ አካዝ ቴልጌልቴልፌልሶርን በጣም ፈርቶት ስለነበረ ብዙ እጅ መንሻን ሰጥቶታል። ስለዚህ በእጅ መንሻ የሆነ ስለሆነ አልረዳውም ተባለ። በተጨማሪም የረአሶን ጠላትነት የጋራ ስለነበረ ነው።

▶️፲፫. 2ኛ ነገ.17፥21 በዚህ ሰዓት ኢዮርብአም ወልደ ናባጥ አልሞተም እንዴ?

✔️መልስ፦ ሞቶ ነበር። ነገር ግን ጸሓፊው ታሪክ እየተረከ ስለሆነ የነበረውን እየተረከ ነው። ከዚህ ቀድሞ የሠራው ታሪኩ ነው የተነገረ እንጂ አሁንም እንዳለ አልተገለጸም።

▶️፲፬. ናባጥ የኢዮርብአም አባት መሆኑ በተለያዩ ቦታዎች የተጠቀሰ ሲሆን 1ኛ ነገ.14፥20 ግን ናባጥ የኢዮርብዓም ልጅ ነው ይላል ልጁን በአባቱ ስም ሰይሞት ነው እንዴ?

✔️መልስ፦ የኢዮርብዓም አባቱም ናባጥ ይባል ነበረ። ናባጥ የሚባል ልጅም ነበረው።

▶️፲፭. 2ኛ ነገ.18፥5 ከእርሱ በፊት እንደእርሱ ያለ የይሁዳ ንጉሥ አልተገኘም ሲል ከዳዊት በልጦ ነው? ወይስ ከሮብዓም ጀምሮ ቆጥሮ ነው?

✔️መልስ፦ ቃሉ የሚለው ከይሁዳ ነገሥታት ከእርሱ በፊትም ከእርሱ በኋላም አልተነሣም ነው። ይሁዳ የሚባለው ደግሞ ሁለቱ ነገድ ብቻ ነው። ዳዊት ደግሞ የይሁዳ ብቻ ንጉሥ ሳይሆን የ12ቱም ነገደ እስራኤል ንጉሥ ነበረ። ስለዚህ ከሮብዓም ጀምሮ ካሉት እንደሆነ ግልጽ ነው።

▶️፲፮. 2ኛ ነገ.19፥2 በብዙ ቁጥር ሊቃነ ካህናት አለ። በአንድ ዘመን ከአንድ በላይ ሊቀ ካህናት አለ እንዴ? አንድ ሳይሞት ሌላ አይተካምና።

✔️መልስ፦ ሊቀ ካህናቱ አንድ ነው። በመዓርግ ከእርሱ ዝቅ ከሌሎች ካህናት ደግሞ ከፍ ያሉትንም ሊቃነ ካህናት ስለሚላቸው በዚህ አግባብ የተነገረ ነው።

▶️፲፯. 2ኛ ነገ.19፥37 ሰናክሬምን እንዴት የገዛ ልጆቹ ይገድሉታል እርሱን ከመታደግ ይልቅ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Dec, 03:45


💗፪ኛ ነገሥት ክፍል 4💗

💗ምዕራፍ 16፡-
አካዝ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አለማድረጉ

💗ምዕራፍ 17፡-
ሆሴዕ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ እንዳደረገ
-እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን እንዳደረጉ
-የአሦር ንጉሥ በእስራኤል ሀገር ሌላ ሰዎችን እንዳሰፈረና እነዚያን ሰዎች አንበሳ እንዳስቸገራቸው እንዲሁም የአሦር ንጉሥ የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲያስተምሯቸው ካህናትን መላኩ

💗ምዕራፍ 18፡-
ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን እንዳደረገ
-ሙሴ የሠራውን የነሐስ እባብ እስራኤላውያን ስላመለኩት ሕዝቅያስ ማጥፋቱ

💗ምዕራፍ 19፡-
ንጉሡ ሕዝቅያስ ከሰናክሬም ይድን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ እንደጸለየ
-የእግዚአብሔር መልአክ አሦራውያንን ማጥፋቱ

💗ምዕራፍ 20፡-
ሕዝቅያስ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል እንደተባለ
-ሕዝቅያስ ንስሓ በመግባቱ 15 ዓመት እንደተጨመረው
-ነቢዩ ኢሳይያስ ጸልዮ ጥላውን ዐሥር ደረጃ ወደኋላ እንደመለሰው
-ሕዝቅያስ ለባቢሎኑ ንጉሥ ለመሮዳህ በቤተ መዛግብቱ ያለውን ንብረት ሁሉ እንዳሳየው

✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️
፩. የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር ዐሥሩን ነገደ እስራኤል ወደ አሦር ሲያፈልሳቸው በወቅቱ የነበረው የእስራኤል ንጉሥ ማን ነበር?
ሀ. ፋቁሔ
ለ. ሆሴዕ
ሐ. ሴሎም
መ. ዔላ
፪. ሙሴ የሠራውን የነሐስ እባብ እስራኤላውያን ቢያመልኩት ያጠፋው የይሁዳ ንጉሥ ማን ነው?
ሀ. አሜስያስ
ለ. ኢዮአክስ
ሐ. ሕዝቅያስ
መ. ኢዮአታም
፫. የእግዚአብሔር መልአክ ያጠፋቸው እስራኤልን ለመውረር የመጡ አሦራውያን ብዛት ስንት ነው?
ሀ. 18500
ለ. 18000
ሐ. 185000
መ. 19200

https://youtu.be/giG1Fe4y4UA?si=8MDKNDGDfhXZnkQi

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Dec, 03:37


✝️ መዝሙረ ዳዊት ክፍል 24 ✝️
✝️መዝሙር ፵፩
ዋልያ የውሃ ምንጮችን እንደሚወድ እንደዚሁም ሁሉ የእኔም ሰውነት እግዚአብሔርን ናፈቀች ወደደች፡፡ ሰውነቴ ሕያወ ባሕርይ ፈጣሪዬን ናፈቀች ወደደች፡፡ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው የተናገሩት ሐዋርያት ወረደ ተወለደ ብለው ያስተማሩት አንድ ሆነ፡፡ መከታዬ ፈጣሪዬ ነው፡፡
✝️መዝሙር ፵፪
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ዐመፀኛ ከዳተኛ ከሚሆን ከብልጣሶር አድነኝ፡፡ አንተ ፈጣሪዬ ብዋጋ ኃይሌ ነህና፡፡ ጠላቶቼ ባስጨነቁኝ ባስጠበቡኝ ጊዜ ብርሃነ ረድኤትህን ላክልኝ፡፡ ቸርነትህን አድርግልኝ፡፡ ፈጣሪዬ ሆይ መሰንቆ እየመታሁ እገዛልሃለሁ፡፡ አንድም በሃይማኖት በምግባር ጸንቼ እገዛልሃለሁ፡፡
✝️መዝሙር ፵፫
መቃብያን ማለት ዕጉሣን በስደት ፅኑዓን በምግባር ወበሃይማኖት ማለት ነው፡፡ አንጥያኮስ አልዓዛርን አስጠርቶ አንተ ጽዩፍ ነህ ሲሉ እሰማለሁና ለእኔና ለአንተ መሥዋዕተ በግዕ ትሠዋለህ፡፡ መሥዋዕተ እሪያ ሠውተህ በቀኝ እጅህ ቢላዋ በግራ እጅህ ሥጋ ይዘህ የበላህ መስለህ ሕዝቡን አሳምንልኝ አለው፡፡ አልዓዛርም ፈጣሪዬ የሃይማኖት አብነት ቢያደርገኝ የክሕደት የጥብዐት አብነት ቢያደርገኝ የክፋት አብነት እሆናለሁን አይሆንም አለው፡፡ ይመለስ እንደሆነ ብሎ ለክህነት የደረሱ ሰባት ልጆች ነበሩት ከፊቱ በሰይፍ አስመትቷቸዋል፡፡ የማይመለስ ሆነ ሚስቱን በኩላብ አሰቅሎ በሰይፍ አስመታት፡፡ የማይመለስ ቢሆን በቁመቱ ልክ ሻሽ ጠምጥሞ በሰም ጠምቶ ብረት ምጣድ አግሎ በራሱ ላይ ደፋበት፡፡ ተንጠቅጥቆ ሞቷል፡፡ ጌታ ሆይ በአንተ አምነን ጠላቶቻችንን ድል እንነሣለን፡፡ አባቶቻችን በሥልጣንህ በኃይልህ በረድኤትህ ነው እንጂ በጦራቸው አንደበት በፈረሳቸው አንገት ከነዓንን እንዳልወረሷት አውቄ እኔም በሥልጣንህ በኃይልህ በረድኤትህ ነው እንጂ በጦሬ አንደበት በፈረሴ አንገት የምታመን አይደለሁም፡፡ በእግዚአብሔር ንከብር ኵሎ አሚረ፡፡ በእግዚአብሔር አምነን ዕለት ዕለት ከብረን ገንነን እንኖር ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ስም ስላመንን፣ በእርሱ ስም ስላስተማርን፣ በእርሱ ስም ስለተጠራን ዘወትር መከራ ያመጡብናል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Dec, 15:12


▶️፲፭. "የሠራዊቱም አለቃ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ተማማለበት፥ በሰማርያም በንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአርጎብና ከአርያ ጋር መታው "(2ኛ ነገ.15፥25)። አርጎብና አርያ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የሀገር ስሞች ናቸው።

▶️፲፮. 2ኛ ነገ.14፥25 ይህ ዮናስ በአሳ አንባሪ ሆድ የነበረው ነው?

✔️መልስ፦ አዎ ራሱ ነቢዩ ዮናስ ነው።

▶️፲፯. 2ኛ ነገ.11፥1 እሷ ለመንገሥ ብላ ነው ሌሎችን የገደለችው?

✔️መልስ፦ አወ ለመንገሥ ብላ እንደሆነ ቁጥር 3 ላይ ተገልጿል። የልጇን መሞት ምክንያት አድርጋ ሌሎችን ገድላ እርሷ ነግሣለች። ሌሎችን የገደለቻቸው እነርሱ እንዳይነግሡባት ሰግታ ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Dec, 15:12


💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 65 💙

▶️፩. "የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ የሊባኖስ ኵርንችት፥ ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ" ይላል (2ኛ ነገ.14፥9)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው? የሊባኖስ ኵርንችት፤ የሊባኖስ ዝግባ፤ የሊባኖስ አውሬ የተባሉ ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ ዮአስ አሜስያስን በኩርንችት፣ ራሱን በዝግባ መስሎ የተናገረው እንቆቅልሽ ነው። ዮአስ የሊባኖስ አራዊት ብሎ የመሰላቸው ደግሞ የራሱን ሠራዊት ነው።

▶️፪. "የእግዚአብሔርም ሰው ተቆጥቶ አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መትተኸው ኖሮ ሶርያን እስክታጠፋው ድረስ በመታኸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶርያን ትመታለህ አለ" ይላል (2ኛ ነገ.13፥19)። ንጉሡ ምድሩን በመታው ቁጥር ብዛት ድል እንደሚያደርግ ያውቅ ነበር? ምድሩን መምታትስ አላማው ምንድን ነው? ሲጀመር ይሄ ትንቢት ነው ወይስ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ከትንቢት ዓይነቶች አንዱ ነው። ነቢያት በሚታይ ነገርም በማይታይ ነገርም ትንቢትን ሊናገሩ ይችላሉ። ንጉሡ ከፍ አድርጎ አምስት ጊዜ ወይም ስድስት ጊዜ ምድርን መትቶ ቢሆን ኖሮ ሶርያን ስድስት ጊዜ ይመታ ነበረ። በነገራችን ላይ ይህ መሠረቱ እምነት ነው እንጂ ሳይንሳዊ አመክንዮ የለበትም። ሙሴ እጁን ሲዘረጋ እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ያሸንፉ ነበረ። ይህ የሆነው እግዚአብሔር በወቅቱ እጅ መዘርጋትን ማሸነፊያ መንገድ ካደረገው እንደሚሆን ነው። ከዚህ የተጠቀሰውም ይህ ነው። ምድር መምታትን የማሸነፊያ ጊዜያትን መንገድ አድርጎታል። ሦስት ጊዜ በመምታቱ ሦስት ጊዜ እንዲያሸንፍ አድርጎታል ማለት ነው። ንጉሡ ግን ይህን ቀድሞ ያውቅ እንደነበረ ወይም እንዳልነበረ የተገለጸ ነገር አላገኘሁም።

▶️፫. "ምሥራቁን መስኮት ክፈት አለ ከፈተውም። ኤልሳዕም ወርውር አለ ወረወረውም። እርሱም የእግዚአብሔር መድኃኒት ፍላጻ ነው። በሶርያ ላይ የመድኃኒት ፍላጻ ነው። እስክታጠፋቸው ድረስ ሶርያዊያንን በአፌቅ ትመታለህ አለ" ይላል (2ኛ ነገ.13፥17)። ኤልሳዕ እንደ ነቢይነቱ በቃል ብቻ ሶርያውያንን እንደሚያጠፋቸው መናገር እየቻለ ፍላጻ እንዲወረውር ያዘዘው ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ነቢያት ከእግዚአብሔር ያገኙትን ምሥጢር በተግባርም፣ በቃልም፣ በምሳሌም ያሳያሉ። ከዚህ ነቢዩ ኤልሳዕ ያደረገው ትንቢቱን በምሳሌ መግለጽና ማሳየት ነው።

▶️፬. "እግዚአብሔርም ንጉሡን ቀሠፈው እስከሚሞትበትም ቀን ድረስ ለምጻም ኾነ በተለየ ቤትም ይቀመጥ ነበር። የንጉሡም ልጅ ኢዮአታም በንጉሥ ቤት ላይ ሠልጥኖ ለአገሩ ሕዝብ ይፈርድ ነበር" ይላል። ምን አድርጎ ነው የተቀሠፈው?

✔️መልስ፦ የኢዮአታም አባት ዖዝያን የተቀሠፈ ንጉሥ ሆኖ ሳለ የክህነት ሥራን እሠራለሁ ብሎ በድፍረት የሚያጥንበት ጥና ይዞ በማጠኑ ነው (2ኛ ዜና መዋ.26፥20)።

▶️፭. 2ኛ ነገ.15፥1 ላይ የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ ሲል 2ኛ ዜና መዋ.26፥1እና ኢሳ.7፥1 ግን የአሜስያስ ልጅ ኦዝያን ይላል ትክክለኛው የቱ ነው?

✔️መልስ፦ ሁለቱም ትክክል ነው። ለአንድ ሰው ሁለትና ከዚያ በላይ ስሞች ሊኖሩት ይችላሉ። በመጽሐፈ ነገሥት ዓዛርያስ የተባለው በመጽሐፈ ዜና መዋዕልና በትንቢተ ኢሳይያስ ዖዝያን የተባለው ሰው ነው።

▶️፮. 2ኛ ነገ.11፥21 እንዴት ሰው በሰባት ዓመቱ በትክክል ሀገርን ያስተዳድራል?

✔️መልስ፦ በሁለት መልኩ ያስተዳድራል። አንደኛው የመንግሥቱን ሥራ የሚያከናውኑት ተወራጅ መኳንንት ካሉ በስም ንጉሥ ሆኖ አስተዳደሩን ሌሎች ያስተዳድሩለታል። ሁለተኛው ተአምራዊ ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰባት ዓመት ሕፃንም ጥበብን ሰጥቶ ሀገርን እንዲያስተዳድር ያደርገዋል።

▶️፯. "ስሟንም ዮቅትኤል አላት" ይላል፡፡ ምን ማለት ነው? ኤል የሚል ስለቀጸለች ስመ አምላክን ትወክላለችን?

✔️መልስ፦ ትርጉሙ ምን እንደሆነ አልተገለጸም።

▶️፰. "የቀረውም የዘካርያ ነገር እነሆ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተጽፏል" ይላል። ከላይ ግን ስሙን ዘካርያስ ይለዋል የቱ ነው ትክክል?

✔️መልስ፦ ሁለቱም ትክክል ነው። እንዲህ ዓይነት የስም ለውጦች ከቋንቋ ቋንቋ ሲገለበጡ የሚፈጠሩ ልዩነቶች ናቸው። ለምሳሌ በግእዝ ቋንቋ "ሸ" የሚባል ፊደል የለም። ስለዚህ ሻባ የሚለውን ቃል የግእዝ መዛግብት ሳባ ሊሉት ይችላሉ። ሲተረጎም የተጻፈበት እናት ቋንቋውን ያህል አይሆንም። ግእዙና እንግሊዘኛው መጽሐፍ ቅዱስ ሁለቱንም አንድ አድርጎ ይገልጸዋል እንጂ አይለያየውም። እንግሊዘኛው ሁለቱንም 'Zechariah' ይለዋል። ግእዙ ደግሞ ሁለቱንም 'አዜኬርያስ' ይለዋል።

▶️፱. 2ኛ ነገ.13፥17" በአፌቅ ትመታለህ አለ" ይላል። አፌቅ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የሀገር ስም ነው።

▶️፲. "በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ አልተጻፈምን" እያለ ብዙ ቦታዎች ላይ ይጠቅሳል ይህ ለሁለተኛ ሰው የተላከ መልእክት ይመስላል። እና መጀመሪያ ለማን ወይም ወደ ማን ነው የተጻፈው?

✔️መልስ፦ አማርኛውና እንግሊዘኛው አሻሚ አድርጎ ጽፎት ነው እንጂ "በእስራኤል የነገሥታት ታሪክ ተጽፏል" ማለት ነው። ግእዙ በጥራት ተርጉሞታል። "ወኵሉ ዘገብረ ናሁ ዝ ውእቱ ዘጽሑፍ ውስተ መጽሐፈ ነቢያቲሆሙ ለነገሥተ እስራኤል" እንዲል (2ኛ ነገ.15፥21)። የነገሥታት ታሪክ የተጻፈው ለጊዜው የሀገራቸውን ታሪክ ያውቁ ዘንድ ለእስራኤላውያን ሲሆን ፍጻሜው ግን የተለያዩ ትምህርቶችን እናገኝበት ዘንድ ለሁላችንም የተጻፈ ነው።

▶️፲፩. ዮአስም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ ኢዮርብዓምም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ። ዮአስም በሰማርያ ከእስራኤል ነገሥታት ጋራ ተቀበረ። ኤልሳዕም በሚሞትበት በሽታ ታመመ። የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለቀሰና አባቴ ሆይ አባቴ ሆይ የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኛዎች አለ። የቅደም ተከተል ስሕተት የለበትም?

✔️መልስ፦ የቅደም ተከተል ስሕተት የለበትም። መጀመሪያ ኤልሳዕ ሞተ። ከዚያ ዮአስ ሞተ።

▶️፲፪. ነገር ግን በእርሷ ኼዱ እንጂ እስራኤልን ካሳተው ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልራቁም። ደግሞም የማምለኪያ ዐጸድ በሰማርያ ቆሞ ቀረ። በእርሷ ኼዱ ሲል በጣኦት አምልኮ ፀኑ ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ። ኢዮርብዓም ጣዖት ሠርቶ ብዙውን አስቷል። ሌሎቹም በእርሷ ሄዱ ማለት እንደ ኢዮርብዓም ጣዖትን አመለኩ ማለት ነው።

▶️፲፫. ካህናቱም ከሕዝቡ ገንዘቡን አንወስድም በቤቱም ውስጥ የተናዱትን አንጠግንም ብለው እሺ አሉ። ግን ዝቅ ብሎ የተናዱትን እንዳስጠገኑ ተገልጿልና አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። ሕዝቡ የሚያዋጣውን ገንዘብ ካህናት ለራሳቸው ይጠቀሙት ነበረ። በኋላ ኢዮአስ ሕዝቡ ለእናንተ የሚሰጠውን ገንዘብ አትቀበሉ ገንዘቡ ለቤተ መቅደስ መጠገኛ ይሁን አላቸው። ካህናቱም እሺ በግላችን ከሕዝቡ ተቀብለን አንጠግንም። ከዚያ ይልቅ ኢዮአስ ባሠራው ሳጥን በተሰበሰበው ገንዘብ እንሠራለን እንጠግናለን ማለታቸው ነው።

▶️፲፬. "ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውየው ድኖ በእግሩ ቆመ"ይላል (2ኛ ነገ.13፥21)። ሆን ብለው ነው በኤልሳዕ መቃብር የጣሉት ወይስ በድንገት አደጋ ጣዮችን አይተው ስለደነገጡ?

✔️መልስ፦ በድንገት አደጋ ጣዮችን ሲያዩ በሌላ መቃብር ሊቀብሩት የነበረውን ሰው ባያደርሳቸው በኤልሳዕ መቃብር አኖሩት። የኤልሳዕም ዐፅም የሞተውን ሰው አስነሣው። የጻድቃን ዐፅም በረከትን ረድኤትን እንደሚያሰጥ በዚህ ታወቀ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Dec, 03:42


💝፪ኛ ነገሥት ክፍል 3💝

💝ምዕራፍ 11፡-
ጎቶልያ የንጉሡን ዘሮች እንዳጠፋች

💝ምዕራፍ 12፡-
ካህኑ ዮዳሄ ያስተምረው በነበረ ዘመን ሁሉ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር እንዳደረገ

💝ምዕራፍ 13፡-
የሰማርያ ንጉሥ ኢዩአካዝ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን እንዳደረገ
-ከኢዮአካዝ ቀጥሎ የነገሠው ዮአስም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ እንዳደረገ
-ነቢዩ ኤልሳዕ እንደሞተ

💝ምዕራፍ 14፡-
አሜስያስ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን እንዳደረገ
-የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ለአሜስያስ የሊባኖስ ኵርንችት ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው ብሎ ወደሊባኖስ ዝግባ ላከ፡፡ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ” ብሎ በምሳሌ እንደላከለት
-የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን እንዳደረገ

💝ምዕራፍ 15፡-
የእስራኤል ንጉሥ ዘካርያስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ እንዳደረገ
-በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር እንደመጣና ከእስራኤላውያን ብዘዎችን ወደ አሶር እንዳፈለሳቸው

✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️
፩. ከጎቶልያ በኋላ የነገሠው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን እንዲያደርግ ያስተምረው የነበረው በዘመኑ የነበረው ካህን ማን ነው?
ሀ. ዮዳሄ
ለ. አዛሄል
ሐ. ኢዮሣፍጥ
መ. ሳሜር
፪. የአሥሩ ነገደ እስራኤል ዋና ከተማቸው ማን ነበረች?
ሀ. ሰማርያ
ለ. ቤተ ልሔም
ሐ. ኢየሩሳሌም
መ. ቀራንዮ
፫. በእስራኤል ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን ከእስራኤላውያን መካከል ገለዓድንና ገሊላን እንዲሁም ሌሎችን ሀገሮች ሁሉ የወሰደና ወደ አሶር ያፈለሰ የአሶር ንጉሥ ማን ነው?
ሀ. ወልደ አዴር
ለ. ቴልጌልቴልፌልሶር
ሐ. ስልምናሶር
መ. አስራዶን

https://youtu.be/DVAXO5tKJW4?si=v92mDF4FxYpQSY46

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Dec, 03:34


✝️ መዝሙረ ዳዊት ክፍል 23 ✝️
✝️መዝሙር ፴፯
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ በነፍስ በሥጋ አታጥፋኝ፡፡ አቤቱ በአንተ አምኛለሁና ልመናዬን ስማኝ፡፡ የጠላቶቼ መዘበቻ አታድርገኝ፡፡ ኃጢአት ስለሠራሁ አዝናለሁ፡፡ አቤቱ ፈጣሪዬ በመከራው አትጣለኝ በረድኤትም አትለየኝ፡፡ እኔን ወደ መርዳት ተመልከት፡፡
✝️መዝሙር ፴፰
ለአንደበቴ አርምሞን ትዕግሥትን ገንዘብ አደረግሁ፡፡ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግሁ፡፡ ለበጎ ነገር ዝም አልኩ፡፡ ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመላለሳል፡፡ ጥላ ጠዋት ሰባ ሰማንያ ክንድ ይሆናል፡፡ በቀትር ጊዜ ከዚህ ደረሰ አይባልም፡፡ ሰውም ታይቶ ይጠፋልና፡፡ ነገር ግን እንደ ጥላ መሆን ሳለ እንኑር እንክበር በማለት ይታወካሉ፡፡ አሁንስ አለኝታዬ ማን ነው እግዚአብሔር አይደለምን? አቤቱ መዓትህን ሁሉ ከእኔ አርቅልኝ፡፡ አቤቱ ከኃጢአት አርፍ ዘንድ በንስሓ አሳርፈኝ፡፡
✝️መዝሙር ፴፱
እግዚአብሔርን በጸሎት በቀኖና ደጅ ጸናሁ፡፡ ከቁጣ ወደ ትዕግሥት ከመዓት ወደ ምሕረት ተመልሶ ልመናዬን ሰማኝ፡፡ በአንደበቴ እንግዳ ምስጋናን እንዳመሰግነው አደረገኝ፡፡ ብፁዕ ብእሲ ዘስመ እግዚአብሔር ትውክልቱ፡፡ እምነቱ በእግዚአብሔር ስም የሆነለት ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ አቤቱ ቸርነትህን በብዙ ጉባዔ ነገርኩ፡፡ ይቅርታህ ቸርነትህ ሁልጊዜ ያግኙኝ፡፡
✝️መዝሙር ፵
በነዳይ በምስኪን ላይ ያለውን መከራ አስቦ ምግቡን በከርሠ ርኁባን፣ መጠጡን በጕርዔ ጽሙዓን፣ ልብሱን በዘባነ ዕሩቃን የሚያኖር ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ እንዲህ ያለውን ሰው እግዚአብሔር ከዕለተ ሞት ከዕለተ ምጽአት ያድነዋል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Dec, 16:01


💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 64 💙

▶️፩. "ልጄንም ቀቅለን በ*ላነው" ይላል (2ኛ ነገ.6፥28)። በአንድ ወቅት እንዲህ ዓይነት ነገር አጋጥሞ ነበር። አንድ አውሮፕላን ተከስክሶ የወደቀበት ቦታ እጅግ አስቸጋሪ ገደል እና ምንም ዓይነት ምግብ ባልነበረበት ቦታ የተረፉት ሰዎች የሞቱ ሰዎችን ሥጋ በ-ል*ተው እንደተረፉ የሚነገር ታሪክ አንብቢያለሁ። በወቅቱ የእነርሱን ሥጋ መብላታቸው ኃጢአት ነበረ ወይስ አይደለም? በእኛ ቤተክርስቲያን እንዲህ አይነት ነገር እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ ፍጹም ኃጢአት ነው። የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርዓያ የተፈጠረ ክቡር ፍጥረት ነው። ሲሞትም አፅሙ በክብር ፍትሐት ተደርጎለት በቤተክርስቲያን ይቀበራል። ስለዚህ ሰው የፈለገ ቢራብ የሞተ ሰውን አካል ለመ*ብ-ላት እንኳን ሊያደርገው ሊያስበው አይገባም። ስለዚህ እነዚያ ከአውሮፕላን የተረፉ ሰዎች ያደረጉት እንደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ፍጹም ኃጢአት ነው።

▶️፪. "እግዚአብሔር በምድር ላይ ረኃብ ጠርቷልና" ይላል (2ኛ ነገ.8፥1)። እግዚአብሔር በምድር ላይ መከራ የሚጠራው በምን ምክንያት ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር መከራን በብዙ መንገድ ያመጣል። አንዳንድ ጊዜ ኃጢአተኞችን ለመገሠጽና ከክፉ ሥራቸው ተጸጽተው እንዲመለሱ ለተግሣጽ መከራን ሊያመጣ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የጻድቃን ዋጋቸው ይበዛ ዘንድ ምንም ሳይበድሉ መከራን እንዲቀበሉ ያደርጋል። መከራ የጸጋ መገኛ ነውና። እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ እንዲሉ። ስለዚህ መከራ በኃጢአት ምክንያትም ሊታዘዝብን ይችላል። ሳንበድል ጸጋን እናገኝ ዘንድም ሊታዘዝብን ይችላል።

▶️፫. የሚመጣውን ነገር አስቀድሞ መናገር ጉዳት የለውም ወይ? ምክንያቱም አዛሄል ወልደ አዴርን እንደሚነግሥ ባያውቅ ላይገለው ይችል ካልነበረስ? እንደሚነግሥ ማወቁ ገፊ ምክንያት ሁኖበት ቢሆንስ?

✔️መልስ፦ ነቢያት የተናገሩት የሚሆነውን ነው እንጂ እንዲሆን አልተናገሩም። ነቢያት አዛሄል በራሱ ፈቃድ ተነሣሥቶ የሚያደርገውን አስቀድመው አውቀው ተናገሩ እንጂ ለአዛሄል ድርጊት የእነርሱ ንግግር መነሻ አልሆነም። እነርሱ ባይናገሩትም አዛሄል በፈቃዱ ያንን ማድረጉ አይቀርም ነበር። በልቡ ሽቶ የሚያደርገው ነገር አስቀድሞ ተገልጦላቸው ተናገሩ እንጂ የእነርሱ ንግግር አዲስ መሻትን አሳድሮበት ከመግደል አላደረሰውም። ሽቶ እንደሚገድል ቀድመው አውቀው ተናገሩ እንጂ።

▶️፬. በሰማርያም ታላቅ ረኃብ ኾኖ ነበር እነሆም፥ የአህያ ራስ በአምሳ ብር፥ የርግብም ኩስ የጎሞር ስምንተኛ የሚኾን በአምስት ብር እስኪሸጥ ድረስ ከበቧት። የአህያ ራስ ይበላ ነበረ ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አህያ በብሉይ ኪዳን ርኩስ ከተባሉትና ኦሪት ዘሌዋውያን ላይ በተገለጸው መሠረት ከማይበሉት መካከል ነበረች። የሰማርያ ሰዎች ሲራቡ ሕግ አፍርሰው ነው እንዲህ ያደረጉት። ስለዚህ አይበላም ነበረ። እነርሱ ግን ሲርባቸው ሕግ አፍርሰው በልተዋል።

▶️፭. ኤልሳዕ ቅርፊቱን ሲጥለው ብረቱ መንሳፈፉ ድንቅ ተአምር ቢሆንም ይሄ ለነገረ ክርስቶስ ምሥጢራዊ ምሳሌ ይኖረው ይሆን?

✔️መልስ፦ አዎ አለው። ይህ ድርጊት ለክርስቶስ ትንሣኤ ምሳሌ ይሆናል። ብረቱ ወደ ውሃው ገባ። ኤልሳዕ ቅርፍቱን ሲጥልበት ቅርፍቱ ሰጥሞ ብረቱ ተንሳፈፈ። ብረቱ የአዳም ምሳሌ ነው። አዳም ትእዛዘ እግዚአብሔርን በማፍረሱ ሞት ተፈርዶበት ይኖር ነበር። ቅርፍቱ የክርስቶስ ምሳሌ ነው። ቅርፍቱ መስጠሙ ክርስቶስ በሥጋ የመሞቱ ምሳሌ ነው። ቅርፍቱ ሰጥሞ ብረቱን ማውጣቱ ክርስቶስ በሞቱ አዳምን ከሲኦል የማውጣቱ ምሳሌ ነው። ሞተ ክርስቶስ በሞተ ዚኣነ ከመ ይቅትሎ ለሞት በሞቱ እንዳለ ሊቅ። ምሳሌ ዘሐጽጽ መሆኑን ግን ልብ አድርግ።

▶️፮. "ከዚያም በኋላ በነገው ለሐፍ ወስዶ በውሃ ላይ ነከረው በፊቱም ላይ ሸፈነው ሞተም" ይላል (2ኛ ነገ.8፥15)። ለሐፍ ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ለሐፍ እንደ ብርድ ልብስ ያለ የአልጋ ልብስ ነው።

▶️፯. በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ አባቱ ዖዝያን እንዳደረገ ዅሉ እንዲሁ አደረገ። ይህ ዖዝያን በልዑለ ቃል ኢሳይያስ ጊዜ የነበረ ነው?

✔️መልስ፦ አዎ። ኢሳይያስ አፍሮ ያልገሠጸውና በኋላ በዚህ ምክንያት ሀብተ ትንቢት ተነሥቶት የነበረ በዚህ ዖዝያን ምክንያት ነበረ።

▶️፰. አዛሄል ኤልሳዕን ትኩር ብሎ አየውና አፈረ ይላል አንዳንዴ ማፈር ያስፈልጋል ወይስ እንዴት ነው? የሚታፈር የማይታፈር ነገር በምን በምን ነው?

✔️መልስ፦ የሚገባ ኀፍረትና የማይገባ ኀፍረት አለ። የሚገባ ኀፍረት ኃጢአትን ከመሥራት ማፈር ነው። ይኸውም እነእገሌ ኃጢአትን በመሥራታቸው ከፈጣሪያቸው ተጣሉ ብሎ አስቦ እግዚአብሔርን ፈርቶ ክፉ ነገርን ላለመሥራት ማፈር ተገቢ ኀፍረት ነው። የማይገባ ኀፍረት ቤተክርስቲያን ስትሰደብ፣ ምእመናን ሲገደሉ፣ ከሓድያን የክሕደት ትምህርትን በክርስቶስ ላይ ሲናገሩ፣ መና*ፍ-ቃ+ን ቅዱሳንን ሲሳደቡ አፍሮ ዝም ማለት ነው። ይህ ማፈር ተገቢ ያልሆነ ማፈር ነው። ስለክርስቶስ ለመመስከርም ማፈር አይገባም።

▶️፱. ፪ኛ ነገ.፰ ስለ ወልደ አዴር መዳንስ ትድናለህ ነገር ግን እግዚአብሔር እንድትሞት አሳይቶኛል ይላል ይሄ ነገር አይጋጭምን?

✔️መልስ፦ የቅጂ ስሕተት ነው እንጂ ትክክለኛው መዳንስ አትድንም ትሞታለህ ነው የሚል። "ሐይወሰ ኢተሐዩአ አንተአ ወአይድዐኒ እግዚአብሔር ከመ ሞተ ትመውት" እንዲል።

▶️፲. "እርሱም አትግደላቸው፤ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኸውን ትገድል ዘንድ ይገባሃልን? (2ኛ ነገ.6፥22)። ኤልሳዕ በጸሎቱ ዕ*ውር አድርጎ እንዲያዙ (እንዲማረኩ) አደረገ እንጂ የእስራኤል ንጉሥ መች በሰይፍና በቀስት ማረካቸው?

✔️መልስ፦ ይህ በሁለት መንገድ ይተረጎማል። አንደኛው የተማረከም ቢሆን አይገደለም። በጦርነት መካከል አንድ ሰው እጅ ሰጥቶ ከተማረከ በኋላ መግደል አይገባም። ሁለተኛው ግን የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ አሻሚ አድርጎት ነው እንጂ ኤልሳዕ ንጉሡን በሰይፍህና በቀስትህ የማረካቸው እስካልሆኑ ድረስ በእነርሱ ሕይወት ላይ ማዘዝ አይገባህም ማለቱ ነው። ኤልሳዕ በተአምራት ዓይናቸውን አሳውሮ አመጣቸው እንጂ ንጉሡ እንዳልማረካቸው ግእዙ እትም በግልጽ ያስቀምጠዋል። "ኢትቅትሎሙ ዘአኮ በኲናትከ ፄወውኮሙ ወዘአኮ በቀስትከ። አላ በኲናትከ ወበቀስትከ ዘፄወውከ ኪያሆሙ ትቀትል። ወአቅርብ ሎሙ እክለ ወማየ ቅድሜሆሙ ወይብልዑ ወይስተዩ ወይእተዉ ኀበ እግዚእሙ" እንዲል።

▶️፲፩. "እርሱም እግዚአብሔር ያልረዳሽን እኔ እንዴት እረዳሻለሁ? ከአውድማው ወይስ ከመጥመቂያው ነውን? አለ" ይላል (2ኛ ነገ.6፥27)። ከአውድማው ወይስ ከመጥመቂያው ነውን? ሲል ምን ለማለት ነው? እግዚአብሔር ያልረዳሽን እኔ እንዴት እረዳሻለሁ? ሲልስ ንጉሡ በእግዚአብሔር ላይ እያፌዘ ነው?

✔️መልስ፦ ንጉሡ በእግዚአብሔር ላይ እያፌዘ አይደለም። እንዲያውም እርሱ ማድረግ የማይችለውን እግዚአብሔር ማድረግ እንደሚችል እየመሰከረ ነው። እግዚአብሔር ካልረዳ ንጉሥ ከእግዚአብሔር በታች ስለሆነ መርዳት የማይችል ደካማ መሆኑን ነው የመሰከረው። ንጉሡ ከአውድማም ከመጥመቂያም እንዳልሰጥሽ የለም እያላት ነው።

▶️፲፪. "የአክዓብም ቤት ሁሉ ይጠፋል፤ በእስራኤልም ዘንድ የታሰረውንና የተለቀቀውን ወንድ ሁሉ ከአክዓብ አጠፋለሁ" ይላል (2ኛ ነገ.9፥8)። በዚህ ንባብ የታሰረና የተለቀቀ ወንድ ማለት ምን ማለት ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Dec, 16:01


✔️መልስ፦ የታሰረውን የተባለው ባሪያውን ለማለት ነው። የተለቀቀውን ማለት ከባርነት ነጻ የሆነውን ማለት ነው። ምሥጢሩ በጠቅላላው የአክአብን ልጆች ሁሉ አጠፋለሁ ማለት ነው።

▶️፲፫. "ኢዩም ወደ ኢይዝራኤል መጣ። ኤልዛቤልም በሰማች ጊዜ ዓይኗን ተኳለች፥ ራሷንም አስጌጠች፥ በመስኮትም ዘልቃ ትመለከት ነበር" ይላል (2ኛ ነገ.9፥30)። እዚህ ላይ ኤልዛቤል መኳሏና ማጌጧ ለምን ነበር?

✔️መልስ፦ ኤልሳቤጥ የተከበለችና ያጌጠች ጠላቴ ነው ብላ ያሰበችውን ኢዩን ለማብሸቅ ደስ አይበለው ብላ ነው።

▶️፲፬. "ነቢዩ ኤልሳዕ ግያዝን ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው" ይላል። እነ ማንን ነው?

✔️መልስ፦ በእሳት ሠረገላ የተቀመጡ ቅዱሳን መላእክት ናቸው። ግያዝ ስላልበቃ አይታዩትም ነበረ። ኤልሳዕ ግን ያያቸው ነበረ። እነ ኤልሳዕን የሚረዱ በነኤልሳዕ ዙሪያ መላእክት ከትመው ነበረና እነርሱ (መላእክት) ከእኛ ጋር ስላሉ አትፍራ አለው ግያዝን።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Dec, 03:55


💖፪ኛ ነገሥት ክፍል 2💖

💖ምዕራፍ 6፡-
ኤልሳዕ ወደውሃው የገባውን ብረት ቅርፊት ወደውሃው ጥሎ ቅርፊቱን አጥልቆ ብረቱን እንዳወጣው
-የሶርያ ንጉሥ በድብቅ የመከረውን ምክር ኤልሳዕ በሀብተ ትንቢቱ ያውቅ እንደነበር
-ኤልሳዕ ጸልዮ ለግያዝ ዙሪያቸውን ያሉትን የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች እንደገለጸለት
-ኤልሳዕ ግያዝን እኛ ጋር ያሉት እነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ እንዳለው
-በሰማርያ ታላቅ ረኃብ ደርሶ እንደነበር

💖ምዕራፍ 7፡-
እግዚአብሔር ሶርያውያንን የፈረስ ድምፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰምቷቸው ሸሽተው እንደሄዱ

💖ምዕራፍ 8፡-
አካዝያስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ እንዳደረገ

💖ምዕራፍ 9፡-
ኢዩ በእስራኤል ላይ እንደነገሠ

💖ምዕራፍ 10፡-
ኢዩ የጣዖት ካህናትንና አገልጋዮችን ሁሉ እንደገደለ


✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️
፩. የሶርያውን የሠራዊት አለቃ ተከትሎ ሄዶ ገንዘብ የተቀበለና በዚህም ምክንያት በኤልሳዕ ርግማን ለምጻም የሆነ ሰው ማን ነው?
ሀ. ንእማን
ለ. ኢዮሣፍጥ
ሐ. ግያዝ
መ. አክአብ
፪. ናቡቴን ያስገደለችው ኤልዛቤልን ያስገደለ የሰማርያ ንጉሥ ማን ነው?
ሀ. ኢዮራም
ለ. ኢዩ
ሐ. አካዝያስ
መ. ዘንበሪ
፫. ከሚከተሉት ውስጥ የሰማርያው ንጉሥ ኢዩ ያደረገውን ድርጊት የሚገልጽ የቱ ነው?
ሀ. የአክአብን ወገኖች አስገደለ
ለ. የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስን ዘመዶች ገደለ
ሐ. የጣዖት ካህናትን አጠፋቸው
መ. ሁሉም

https://youtu.be/kgJxvBvNFyw?si=WbCZZHdH89QZell6

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Dec, 03:48


✝️ መዝሙረ ዳዊት ክፍል 22 ✝️
✝️መዝሙር ፴፭
ክፉ ሰው በአንደበቱ የሚናገረው ነገር ሁሉ ዐመፃ ክዳት ሽንገላ ነው፡፡ ክፉ ሰው ኃጢአትን ቢሠራት ቢሠራት አይሰለቻትም፡፡ አቤቱ ጌታ ሆይ ይቅርታህ ሰማይን በመፍጠርህ ታወቀ፡፡ ቸርነትህም ደመናትን በመፍጠር ታወቀ፡፡ ፍርድህ እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ የአዳም ልጆች በክንፈ ረድኤትህ አምነው ተጠብቀው ይኖራሉ፡፡
✝️ምዕራፍ ፴፮
ሰርቀው ቀምተው አስረው ፈትተው በሚኖሩ ሰዎች አትቅና፡፡ በእነዚህ መቅናት እኔም የእነርሱን ሥራ ልሥራ ማለት ነውና፡፡ ጣዖት በሚያመልኩ ሰዎች አትቅና፡፡ እንደ ሣር ፈጥነው ከብዕላቸው ይለያሉና፡፡ እንደ ጎመን ቅጠል ፈጥነው ይወድቃሉ፡፡ አንተ ግን በእግዚአብሔር እመን በጎ በጎውን ሥራ ሥራ፡፡ በእርሱ እመን እርሱም የለመንከውን ያደርግልሀል፡፡ ቁጣን ተዋት፡፡ ክፉ የሚያደርጉ ተነቃቅለው ይጠፋሉ፡፡ ቅኖች ኀዳግያነ በቀል መንግሥተ ሰማያትን ወርሰዋት ይኖራሉ፡፡ በፍጹም ተድላ ደስታ ደስ ይላቸዋል፡፡ ሰርቀው ቀምተው ሸፍጠው ተሟግተው ከሰበሰቡት ከባለጸጎች ብዙ ብዕል ይልቅ ወጥቶ ወርዶ ነዶ በርዶ በእውነት የተገኘ ጥቂት የድኃ ገንዘብ ይበልጣል፡፡ የባለጸጎች ገንዘብ ፈጥኖ ይጠፋልና፡፡ ጻድቅ መምህር ከእግዚአብሔር ትምህርትን ይበደራል፡፡ ሐዲስ የተማረ እንደሆነ ሐዲሱን እያስተማረ ብሉዩን ይማራል፡፡ ብሉይ የተማረ እንደሆነ ብሉዩን እያስተማረ ሐዲሱን ይማራል፡፡ የሰው ሥራው ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋውን ተቀብሎ ይጠብቀዋል፡፡ ከልጅነት እስከ ሽበት ደረስኩ ጻድቅ ሰው ሲጎዳ አላየሁም፡፡ ከክፉ ሥራ ተለይ በጎውን ሥራ ሥራ፡፡ እግዚአብሔር እውነትን አንድም እውነትን የያዘ ሰውን ይወድዳል፡፡ ጻድቃንን በመከራው አይጥላቸውምና ለጊዜውም ቢጥላቸው እንደ ጣላቸው አይቀርምና፡፡ በነፍስ በሥጋ ይጠብቃቸዋል፡፡ ለንጹሓን ይፈርድላቸዋል፡፡ የጠቢብ ሰው አንደበቱ ጥበብን አንድም ሕግን ይማራል፡፡ እግዚአብሔር በሃይማኖት ለፈተና መከራ ቢያመጣብህ መከራውን ታግሠህ ተቀበል ሕጉን ጠብቅ፡፡ እንዲህ ያደረግህ እንደሆነ በነፍስ በሥጋ ያከብርሃል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Dec, 17:05


💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 63 💙

▶️፩. 2ኛ ነገ.4 ላይ የተጠቀሰው ዘይቱ እና ማድጋው ምሳሌነቱን ቢያስረዱን?

✔️መልስ፦ እንዳለ ንባቡን መረዳት ነው። ሴትዮዋ ተቸግራ ነበረ። ነቢዩ ኤልሳዕ ችግሯን አራቀላት። የተለየ ምሥጢር የለውም። ነገር ግን በምሳሌ ዘየሐጽጽ ለሚመስል ነገር ልንመስለው እንችላለን።

▶️፪. በ1ኛ ነገ.22፥42 ላይ ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም ላይ 25 ዓመት ነገሠ ይላል ወረድ ይልና ቁጥር 51 ላይ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ17 ኛው ዓመት አካዝያስ በእስራኤል ላይ 2 ዓመት ነገሠ ይላል። አኹን በ 2ኛ ነገ.1፥17 ላይ ደግሞ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮሳፍጥ ልጅ በኢዮራም በ2ኛው ዓመት የአካዝያስ ወንድም ኢዮራም ነገሠ ይላል። በ2ኛ ነገ.3፥1 ላይ ደግሞ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ18ኛ ዓመት ይላል። ይህ እንዴት ነው አይጋጭም ሀሳቡ ማለት የኢዮሳፍጥ ልጅ በነገሠ በ2ኛው ዓመት ብሎ እንደገና ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ18 ዓመት የአካዝያስ ወንድም ኢዮራም ነገሠ ይላልና።

✔️መልስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጅ ስሕተት ነው እንጂ አንድምታው በ25ኛው ነው የሚል። ይኸውም የነገሠበትንና መጨረሻውን ትቶ ቆጦሮ እንጂ ነው። "ወኢዮራም ወልደ አክአብ ነግሠ ለእስራኤል በሰማርያ አመ ዕሥራ ወኀምስቱ ዓመተ መንግሥቱ ለኢዮሳፍጥ ንጉሠ ይሁዳ" ነው የሚል ትክክለኛው። ስለዚህ በዚህ መልኩ አይጋጭም ማለት ነው።

▶️፫. ኤልሳዕ ግያዝን "ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታገኝ ሰላም አትበል፤ እርሱም ሰላም ቢልህ አትመልስለት፤ በትሬንም በሕጻኑ ፊት ላይ አኑር" አለው ይላል። ሰላምታን ለምን ከለከለው?

✔️መልስ፦ በጸሎት መካከል ሰው ሰላም ቢለን ዝም ማለት እንደሚገባን የሚያስረዳ ቃል ነው። የግያዝ ተልዕኮ በጸሎት ተመስሏል። በጸሎት የሚሹትን እንደሚያገኙ ሁሉም ግያዝም የሚሻውን ያገኝ ዘንድ ይህን ተልዕኮ ሲፈጽም ማንንም እንዳያናግር ተነግሮታል።

▶️፬. "በቤቴልም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ወጥተው። እግዚአብሔር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው አውቀሃልን? አሉት። እርሱም። አዎን አውቄአለሁ ዝም በሉ አላቸው" ይላል (2ኛ ነገ.2፥3)። የነቢያት ልጆች ኤልያስ ወደ ሰማይ እንደሚነጠቅ እንዴት አውቁ?

✔️መልስ፦ ለነቢያት ምሥጢሩን የሚገልጽ እግዚአብሔር ነው። ከእግዚአብሔር ሳያገኙ አይናገሩም። ስለዚህም ኤልያስ እንደሚያርግ እግዚአብሔር ገልጦላቸው ተናግረዋል።

▶️፭. "የእግዚአብሔር ሰው ሆይ በምንቸቱ ውስጥ መርዝ አለ" ይላል (2ኛ ነገ.4፥40)። ሰው ሳይሞት ወይም ሳይታመም እንዴት መርዝ መኖሩን አወቁ?

✔️መልስ፦ ቀምሰው አውቀውታል። በጥቂቱ ሲቀምሱት እንደመርዝ ሲመራቸው አይተዋልና መርዝ አለ ብለዋል። ኤልሳዕ ደግሞ ዱቄት ጨምሮ ፈውሶታል።

▶️፮. ዓይነ ርግብ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከሐር ክር የሚሠራ የመስኮት መሸፈኛ ነው። ሴቶችም ፊታቸውን ለመሸፈን ይጠቀሙበታል። በአጭሩ እንደ ፎጣ እንደ መጋረጃ ያለ ነው።

▶️፯. "የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ያፈርሁ ባልሆነ ኖሮ አንተን ባልተመለከትሁና ባላየሁ ነበር" ይላል (2ኛ ነገ.3፥14)። ለኢዮሳፍጥ ኤልሳዕ እንዲህ ለምን አለለት?

✔️መልስ፦ኢዮሳፍጥ ደግ ስለነበረ ለእርሱ ብየ እንጂ ለአንተ ለእስራኤሉ ንጉሥ ለኢዮራም ባልመለስኩልህ ነበረ ብሎታል። ትእምርተ ጸብዕ ነው። ኢዮራም ጣዖት ስላመለከ በዚህ ኤልሳዕ አለመውደዱን ገልጿል።

▶️፰. ኤልያስ ኤልሳዕን እንዳይከተለው የፈለገ ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የኤልሳዕ መሻት ለእኛ ይታወቅ ዘንድ ነው። ደቀ መዝሙር መምህሩን እስከ መጨረሻው መከተል እንዲገባው ለእኛ ትምህርትን ይሰጠን ዘንድ ነው። ኤልሳዕ በረከትን ለማግኘት ምን ያህል ቁርጠኛ እንደሆነ እኛ እንድንረዳ ነው። በዚህም የኤልሳዕን የልቡናውን ትጋት የሃይማኖቱን ጽናት አወቅን።

▶️፱. "እርሱም አስቸጋሪ ነገር ለምነሃል፤ ነገር ግን ከአንተ ዘንድ በተወሰድሁ ጊዜ ብታየኝ ይሆንልሃል፤ አለዚያ ግን አይሆንልህም አለ" ይላል (2ኛ ነገ.2፥10)። አስቸጋሪ ነገር ለምነሀል ያለው ኤልያስ ያን ለማድረግ ይከብዳል ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ አስቸጋሪ ነገር ለምነሀል ማለት ድንቅ ነገር ታላቅ ነገር ለምነሀል ማለት ነው። አስቸጋሪ መባሉ ይህ በእግዚአብሔር እንጂ በሰው ኃይል መደረግ አይችልምና ነው።

▶️፲. "አሁንም ባለበገና አምጡልኝ አለ። ባለ በገናውም በደረደረ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ መጣችበት" ይላል (2ኛ ነገ.3፥15)። እዚህ ላይ የበገናው ሚና ምንድን ነው? የእግዚአብሔር እጅ የተባለስ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ኤልሳዕ በገና ሲደረደር ሀብተ ትንቢትን ጸጋን ያገኝ ነበረና በገና ደርድሩልኝ አለ። የእግዚአብሔር እጅ የተባለ የእግዚአብሔር ረድኤቱ ነው።

▶️፲፩. "በነጋውም የቍርባን ጊዜ ሲደርስ እነሆ ውኃ በኤዶምያስ መንገድ መጣ ምድሪቱም ውኃ ሞላች" ይላል (2ኛ ነገ.3፥20)። የቁርባን ጊዜ የተባለ የመሥዋዕት ጊዜ ነው?

✔️መልስ፦ አዎ የቍርባን ጊዜ የሚለው የመሥዋዕት ጊዜ ነው። ለእግዚአብሔር የሚቀርበው የእህሉ ቍርባን፣ የእንስሳትን ደግሞ መሥዋዕት ይባላልና።

▶️፲፪. "በዚያም ጊዜ በእርሱ ፋንታ ንጉሥ የሚሆነውን የበኵር ልጁን ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በቅጥሩ ላይ አቀረበው። በእስራኤልም ዘንድ ታላቅ ቍጣ ሆነ። ከዚያም ርቀው ወደ ምድራቸው ተመለሱ" ይላል (2ኛ ነገ.3፥27)። የበኵር ልጁን ለመሥዋዕት በማቅረቡ እስራኤል ለምን ተቆጣ?

✔️መልስ፦ ልጅን ለጣዖት መሥዋዕት ማድረግ (ማረ*ድ) በእግዚአብሔር ሕግ ፈጽሞ የተከለከለ ስለሆነ እስራኤላውያን ተቆጥተዋል።

▶️፲፫. "ገብተሽም ከአንቺና ከልጆችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፥ ወደ እነዚህም ማድጋዎች ሁሉ ዘይቱን ገልብጪ፤ የሞላውንም ፈቀቅ አድርጊ አለ" ይላል (2ኛ ነገ.4፥4)። በሩን ዝጊ ማለቱ ምሥጢሩ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የተለየ ምሥጢር የለውም። እግዚአብሔር የሰውን ንብረት በምክንያትም ያለምክንያትም ይባርካል። በዚህ ጊዜ ለእርሷ በሩን ዝጊ መባሏ ይህን መታመኗን ምክንያት አድርጎ ያበረክትላት ዘንድ ነው።

▶️፲፬. "እርሱም መባቻ ወይም ሰንበት ያይደለ ዛሬ ለምን ትሄጂበታለሽ? አለ። እርሷም ደኅና ነው አለች" ይላል (2ኛ ነገ.4፥23)። በዘመኑ ሰው ወደ ነቢይ የሚሄደው በመባቻ ወይም በሰንበት ብቻ ነበር ማለት ነው?

✔️መልስ፦ በዋናነት በዐበይት በዓላት ጊዜ ይሄድ ነበር። በሌላው ጊዜም ግን ከመሄድ አይከለከሉም ነበረ። ለዚህም ማስረጃ በዚህ አንቀጽ የተጠቀሰችው ሴት ናት። ነገር ግን በእኛም ሀገር በሌላውም ቀን ከመሄድ ሳይከለከል በብዛት በዋናነት በበዓላት ሁሉም ወደቤተክርስቲያን እንደሚሄድ ሁሉ ያለ ነው። በዚያ ልማድ ባል ሚስቱን ዛሬ የምትሄጅው ለምንድን ነው ያለው ከበዓላት ውጭ በብዛት ባለመለመዱ ነው።

▶️፲፭. "መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ። አፉንም በአፉ ዓይኑንም በዓይኑ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት የሕፃኑም ገላ ሞቀ" ይላል (2ኛ ነገ.4፥34)። ዛሬም አንዳድ  የፕሮቴስታንት ፓስተሮች የሞተ እናስነሣለን እያሉ ይህን ዓይነት ነገር ሲያደርጉ እናያለን። ለመሆኑ እንዲህ ማድረግ  የመጸለይ ምልክት ነው ወይስ ምንድን ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Dec, 17:05


✔️መልስ፦ አሁን ላይ የመጸለይ ምልክት እጅን ዘርግቶ ዓይንን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ነው። ቅዱሳን በብዙ መንገድ የሞተ ሰውን አስነሥተዋል። ኤልሳዕ አፉን በአፉ ዓይኑን በዓይኑ እጁን በእጁ አድርጎ በመጸለይ የሞተ አስነሥቷል። ሰባት ጊዜ ይህን ማድረጉ በፍጹም ጸሎት የሞተው እንደሚነሣ ለማስረዳት ነው። አንዳንድ ፓስተሮች ይህን ያደርጋሉ የተባለው ቢያደርጉም የሞተ ሲያስነሡ አላየንም። የሞተን ለማስነሣት መጀመሪያ በኅሊናው ፍጹም እምነት ሊኖረው ይገባል። ከኤልሳዕ ሙት ከማስነሣቱ ጀርባ ፍጹም እምነት ነበረና።

▶️፲፮. ንዕማን ነቢዩ ኤልሳዕን አፈር የለመነው ለምንድን ነው? (2ኛ ነገ.5፥18-18)። ምናልባት ከቤተክርስቲያን የምንቀባው እምነት ከዚህ ጋር ይገናኝ ይሆን?

✔️መልስ፦ ንእማን ኤልሳዕን አፈር የለመነበት ምክንያት የተቀደሰ አፈር ስለሆነ የንእማን ጌታ ለጣዖት ሲሰግድ ንእማን ይህንን የተቀደሰ አፈር ምክንያት አድርጎ ለእግዚአብሔር ይሰግድ ዘንድ ነው። ንእማን የወሰደው አፈር አሁን በቤተክርስቲያን ለምንቀባው እምነት ምሳሌ ይሆናል። ጌታም አፈሩን በምራቁ ለውሶ ዕው*-ሩን አድኖታል። አሁን የምንጠቀመው እምነት የዚህም ምሳሌ ነው።

▶️፲፯. "ብሩንና ልብሱን፥ የወይራውንና የወይኑን ቦታ፥ በጎችንና በሬዎችን፥ ወንዶችንና ሴቶችን ባሪያዎች ትቀበል ዘንድ ይህ ጊዜው ነውን?" ይላል (2ኛ ነገ.5፥26)። ግያዝ ሁለት መክሊት ብርና ሁለት መለወጫ ልብስ ነው የተቀበለው። ታዲያ  ኤልሳዕ ግያዝ ያልተቀበለውን ለምን እንዲህ አለ?

✔️መልስ፦ እውነት ነው ግያዝ ከንእማን የተቀበለው ገንዘብ ሁለት መክሊት ብርና ልብሶችን ነው። ነገር ግን ግያዝ ከንእማን በተቀበለው ገንዘብ የወይን ቦታን፣ ባሪያዎችን፣ በጎችን፣ በሬዎችን የሚገዛበት ስለሆነ ነቢዩ ኤልሳዕ ነቢይ እንደመሆኑ ፍጻሜውን አይቶ ተናገረ። ቀጥሎም በግያዝ ለምጽ እንደሚወጣበት ተናገረ።

▶️፲፰. ብዔልዜቡል ምንድን ነው? ቃሉስ የማን ነው?

✔️መልስ፦ ብዔልዜቡል ማለት የዝንብ ጌታ ማለት ሲሆን በአቃሮን የሚኖሩ ሰዎች ያመልኩት የነበረው ጣዖት ስም ነው። ዝንብን የፈጠረ ነው ብለው ያስቡ ስለነበረ የዝንብ ጌታ አሉት። ቃሉ የዕብራይስጥ ነው።

▶️፲፱. 2ኛ ነገ.2፥9 ሳልወሰድ ጠይቀኝ የሚለው ከተወሰደ በኋላ ቢጠይቀው ምንም አይሰጠውም ማለት ነው? ጳውሎስም ሞቶ ከክርስቶስ ጋር ከሚኖር የእርሱ በሥጋ መኖር ለምዕመናን እንደሚጠቅማቸው ይናገራል (ፊልጵ.1፥23-24)። ስለዚህ ቅዱሳን ከእኛ ከተለዩ በኋላ የሚያማልዱን መሆኑ የታወቀ ከሆነ ለምን ኤልያስ ሳልወሰድ ይላል?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ጸጋውን በብዙ መልኩ ይሰጣል። በምክንያትም ያለምክንያትም ይሰጣል። ኤልሳዕ የኤልያስን ጸጋ ኤልያስን ሲያርግ በማየት ተቀብሏል። ሌሎች ሰዎችም በተለያዩ ምክንያቶች ጸጋን አግኝተዋል። ከተወሰደ በኋላ ቢጠይቀው አይሰጠውም ነበር ወይ ለሚለው መልስ መስጠት አንችልም። ምክንያቱም ድርጊቱ አልሆነም። ባልሆነ ነገር ላይ አስተያየት መስጠት አይቻልምና። ምልጃ በአፀደ ነፍስም በአፀደ ሥጋም አለ። ይህንን የሚነግረን ይኸው የኤልሳዕ ታሪክ ነው። ኤልሳዕ ኤልያስ ካረገ በኋላ የኤልያስን ስም ጠርቶ የዮርዳኖስን ውሃ ከፍሏልና (2ኛ ነገ.2፥14)።

▶️፳. 2ኛ ነገ.2፥16 በፊት እንደሚያርግ ሲናገሩ ቆይተው አሁን ወድቆ እንደሆን የሚሉ ለምንድን ነው? እነዚህ ሰዎች እውነተኛ ነቢያት ናቸውን?

✔️መልስ፦ አዎ እውነተኛ ነቢያት ናቸው። ነገር ግን የሰው ልጅ ዕውቀት የጸጋ ስለሆነ ሁሉን አያውቅም። እንደሚያርግ ያውቁ ነበረ። ካረገ በኋላ የት ሆነ የሚለው ግን ስላልተገለጠላቸው እንፈልገው ብለዋል። መንፈስ ቅዱስ በሠረገላ ሠውሮ ወደዮርዳኖስ አውርዶት ይሆናል የሚል ግምት ስለነበራቸው ካልፈለግን ብለው ነበር። ነገር ግን እነርሱ እንዳሰቡት ስላልሆነ ቢፈልጉትም አላገኙትም።

▶️፳፩. 2ኛ ነገ.3፥13 ነቢያት በዘር ነው የሚያገለግሉት እንዴት? ለምን የአባትህን እና የእናትህን ነቢያት ጠይቅ ይላል?

✔️መልስ፦ ይህ የቁጣ አነጋገር ነው። ለእስራኤል ንጉሥ ሐሰተኛ ካህናት ሐሰተኛ ነቢያት ስለነበሩት ወደእነዚያ ሂድ ብሎታል። ምሥጢሩ እነርሱ መፍትሔ እንደማይሰጡህ እወቅ ማለቱ ነው። እንጂ በቅዱሳን ነቢያትስ የዘር ነቢያት አልነበሩም። ሁሉም የእግዚአብሔር ነቢያት ነበሩ እንጂ። እግዚአብሔር ደግሞ የሁሉ አምላክ እንጂ የአንድ ዘር አምላክ አይደለም።

▶️፳፪. 2ኛ ነገ.5፥14 ሰውነቱ እንደ ትንሽ ብላቴና ሆኖ ተመለሰ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ታድሶ፣ ድኖ፣ ተፈውሶ ተመለሰ ማለት ነው።

▶️፳፫. ንዕማን እየተጠራጠረ ተጠምቆ እንዴት ዳነ?

✔️መልስ፦ ንእማን እየተጠራጠረ እንደተጠመቀ አልተገለጸም። መጀመሪያ ነቢዩ ዳስሶ ያድነኛል ብሎ በኅሊናው ስሎ መጥቶ ነበር። ነቢዩ ግን በዮርዳኖስ ተጠመቅ ሲለው ቀድሞ በኅሊናው ያላሰበውን ቢነግረው ለወንዝ ለወንዝማ የሀገሬ ወንዞች አይሻሉም ነበርን ብሏል። በኋላ በሌሎች ሰዎች ምክር አማካኝነት በዮርዳኖስ ተጠምቆ ድኗል። ሲጠመቅ እንደተጠራጠረ አልተገለጸም። ቢጠራጠርም ሥጋዊ ፈውስን ማግኘት እምነትን ብቻ ስለማይጠይቅ ችግር አይፈጥርም። የማያምኑ ሰዎች ታመው ሲድኑ በዘመናችንም እናያለንና። ምክንያቱም ይህ እግዚአብሔር ለአማኙም ለኢአማኙም የሚያደርገው መግቦት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Dec, 04:30


🧡፪ኛ ነገሥት ክፍል 1🧡

🧡ምዕራፍ 1፡-
አካዝያስ በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ በዐይነ ርግቡ ወድቆ እንደታመመና እድን እንደሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ ብሎ መልእክተኞችን እንደላከ
-ነቢዩ ኤልያስ መልእክተኞችን በመንገድ አግኝቷቸው ትሞታለህ በሉት ብሏቸው እንደተመለሱ
-ኤልያስ ከአካዝያስ የተላኩ መልእክተኞችን ከእሳት ሰማይ እያወረደ እንደገደላቸው
-ኤልያስ በእግዚአብሔር ቃል እንደተናገረው አካዝያስ እንደሞተ

🧡ምዕራፍ 2፡-
ኤልያስ መጠምጠሚያውን ጠቅልሎ የዮርዳኖስን ውሃ ቢመታው የዮርዳኖስ ውሃ ወዲያና ወዲህ እንደተከፈለ
-ኤልያስ በእሳት ሠረገላና በእሳት ፈረስ ወደሰማይ እንዳረገ
-ኤልያስ ኤልሳዕን ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን እንዳለው
-ኤልሳዕ ኤልያስን መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ እንዳለው
-ኤልሳዕ አዲስ ማሰሮ ጨውም ጨምራችሁ አምጡልኝ ብሎ በዚያ ውሃውን እንደፈወሰው
-ኤልሳዕን አንተ ራሰ በራ ብለው የሰደቡት ልጆች በድብ እንደተበሉ

🧡ምዕራፍ 3፡-
የአክአብ ልጅ ኢዮራም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ እንዳደረገ
-ኤልሳዕ ባለበገና አምጡልኝ እንዳለ፣ ባለበገናውም በደረደረ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ ወደ ኤልሳዕ ይመጣ እንደነበር

🧡ምዕራፍ 4፡-
ኤልሳዕ የአንዲትን ድኻ ሴት ገንዘብ እንዳበረከተላት
-ኤልሳዕ በጸሎቱ የሞተውን ሰው እንዳስነሣ

🧡ምዕራፍ 5፡-
የሶርያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃ ንዕማን በዮርዳኖስ ውሃ ተጠምቆ ከለምጹ እንደዳነ
-ግያዝ ከኤልሳዕ ተደብቆ ሄዶ ከንዕማን ገንዘብ እንደተቀበለ

✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️
፩. አካዝያስ በሰማርያ በሰገነቱ ሳለ በዐይነ ርግቡ ወድቆ በታመመ ጊዜ እድን ይሆንን ብሎ እንዲጠይቁ መልእክተኞችን የላከ ወደማን ነው?
ሀ. ወደ አቃሮን አምላክ ወደ ብዔልዜቡል
ለ. ወደ እግዚአብሔር ካህናት
ሐ. ወደ ነቢዩ ኤልያስ
መ. ለ እና ሐ
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ኤልያስ በእሳት ሠረገላና በእሳት ፈረስ ወደ ሰማይ ዐርጓል
ለ. ኤልያስ የዮርዳኖስን ወንዝ በመጠምጠሚያው ከፍሎት ተሻግሯል
ሐ. ኤልያስ ሲያርግ የዐውሎ ነፋስ ንውጽውጽታ ነበረ
መ. ሁሉም
፫. ኤልሳዕን ልጆች “አንተ ራሰ በራ ውጣ” እያሉ ቢያፌዙበት ልጆች ምን ሆኑ?
ሀ. ልጆች በረከትን አገኙ
ለ. ልጆችን ሁለት ድቦች መጥተው ሰባበሯቸው
ሐ. ኤልሳዕ መረቃቸው
መ. መልስ የለም
፬. ከሚከተሉት ውስጥ ስለነቢዩ ኤልሳዕ ትክክል የሆነው የቱ ነው፡፡
ሀ. የአንዲትን ድኻ ገንዘብ ባርኮ አብዝቶላታል
ለ. የሱማናዊትን ሴት ልጇን ከሞት አስነሥቶላታል
ሐ. በመራራው ምግብ ላይ ዱቄት ጨምሮ ምግቡ ላይ የነበረውን መርዝ አጥፍቷል
መ. ሁሉም
፭. ሶርያዊው የሠራዊት አለቃ ከለምጹ የዳነ በምንድን ነው?
ሀ. ከዕፀዋት በተቀመመ መድኃኒት
ለ. በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቅ
ሐ. ሥጋ አብዝቶ በመብላት
መ. ወተት በመጠጣት

https://youtu.be/LruU80nSKH4?si=w5Iv2o-pRLQZLY9E

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Dec, 04:22


✝️መዝሙረ ዳዊት ክፍል 21 ✝️
✝️መዝሙር ፴፬
ዳዊት ይህን መዝሙር ስለኤርምያስ ተናግሮታል፡፡ ኤርምያስ እስራኤልን ቢመክራቸው ቢያስተምራቸው ምክሩን ትምህርቱን የማይቀበሉት ሆነ፡፡ ጌታ ሆይ ሰውነቴን ረዳትሽ እኔ ነኝና አይዞሽ በላት፡፡ ሰውነቴን ለማጥፋት የሚሿት ሁሉ ይፈሩ ይዋረዱ፡፡ የእኛ ሰውነት ግን በእግዚአብሔር አምና ደስ ይላታል፡፡ ጌታ ሆይ የሐሰት ምስክሮች በጠላትነት ተነሱብኝ፡፡ በእኔ ላይም የማላውቀውን ነገር ተናገሩብኝ፡፡ ጸሎት ያለዋጋ አይቀርም፡፡ አቤቱ የምትፈርድልኝ መቼ ነው፡፡ አቤቱ በብዙ ሰዎች ጉባኤ እገዛልሃለሁ፡፡ ሳልጣላቸው በግፍ የሚጣሉኝ ደስ አይበላቸው፡፡ አቤቱ ከእኔ በረድኤት አትራቅ፡፡ በእኔ መከራ ደስ የሚላቸው ይፈሩ ይዋረዱ፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Dec, 19:39


💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 62 💙

▶️፩. 1ኛ ነገ.18፥22 "ኤልያስም ሕዝቡን አለ ከእግዚአብሔር ነቢያት አንድ እኔ ብቻ ቀርቻለሁ" ይላል። በጊዜው ሌሎች የእግዚአብሔር ነቢያት አልነበሩም ማለት ነው? አብድዩ ሸሽጎ እንጀራ እና ውሃ ይመግባቸው የነበሩ ነቢያት አልነበሩምን?

✔️መልስ፦ ነቢዩ ኤልያስ ብቻውን የቀረ መስሎት ስለነበረ ብቻዬን ቀርቻለሁ ብሏል። ነገር ግን አብድዩ በዋሻ ደብቆ ይመግባቸው የነበሩ ሌሎች ነቢያትም በዘመኑ ነበሩ።

▶️፪. "ከእሳቱም በኋላ እንደ ፉጨት ያለ ቀጭን ድምፅ ሆነ በዚያም እግዚአብሔር ነበር" ይላል (1ኛ ነገ.19፥12)። የንባቡ ትርጓሜ አልገባኝም። በነፋስ በምድር መናወጥ በእሳት በዚያ ያልነበረ በፉጨት እንዴት ሊኖር ቻለ?

✔️መልስ፦ እንደፉጨት ያለ ቀጭን ቃል የተባለ ነቢዩ ኤልሳዕ መሆኑን መተርጉማን ገልጸዋል። በዚያ እግዚአብሔር ነበረ ማለት እግዚአብሔር በኤልሳዕ አድሮ ረድኤትን ይሰጥ ነበር ለማለት ነው። በነፋስ የተመሰለው ወልደ አዴር ነው። በምድር መናወጥ የተመሰለው አዛሄል ነው። በእሳት የተመሰለው መቅሠፍት ነው። በእነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ረድኤቱን አይሰጥም ነበረ ማለት ነው። ረድኤት አለመስጠቱን አለመኖር ብሎ ተርጉሞት እንደሆነ ልብ ማድረግ ይገባል።

▶️፫. 1ኛ ነገ.16፥5-20 "የቀረውም ነገር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ ነው" ይላል። ይህ ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል ወይስ በሌላ የታሪክ መጽሐፍ ነው። ካልተገኘ ለምን በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጻፈም?

✔️መልስ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝ አለ። ለምሳሌ በመጽሐፈ ነገሥት ያልተገለጹ በሕጹጻን (በመጻሕፍተ ዜና መዋዕል) የተገለጹ ይኖራሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ የማይገኝ በዘመናቸው በነበረ ሌላ መጽሐፍ ተመዝግቦ የነበረም ይኖራል። ለምን በመጽሐፍ አልተጻፈም ለሚለው ሁሉ በመጽሐፍ ቢጻፍ ዓለም ባልበቃች ነበርና ነው። ስለዚህ ከብዙው በጥቂቱ የመዳን ዕውቀትን ይሰጡን ዘንድ ጥቂቶች ብቻ ተጽፈውልናል።

▶️፬. ኤልያስ የእግዚአብሔር ነቢይ ሲሆን ነቢያተ ሐሰቶችን በቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ እየወጋ ገደላቸው ይላል። ይህ ኃጢአት አይሆንበትምን።

✔️መልስ፦ ሳሙኤል አጋግን መግደሉ፣ ኤልያስ ነቢያተ ሐሰትን ማስገደሉ የጠመመን ከማቅናት ተቆጥሯል እንጂ በደል አይደለም። በብሉይ ሕግ ሐሰተኛ ነቢይ ቢኖር እንዲገደል ስለሚያዝዝ ኤልያስ ያስፈጸመው ሕጉን ነው። በሐዲስ ኪዳን ግን በፍትሕ መንፈሳዊ ከባዱ ቅጣት ውግዘት ነው እንጂ መግደል አይደለም።

▶️፭. 1ኛ ነገ.፲፱÷፲፩ "በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮችን ሰነጠቀ። እግዚአብሔር ግን (በነፋሱ፥ በምድር መናወጥ፥ በእሳቱ) ውስጥ አልነበረም። እግዚአብሔር የሌለበት ቦታ አለን?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በአካል የሌለበት ቦታ የለም አይኖርም። ምሉዕ በኵለሄ ነውና። ከዚህ ጥቅስ እግዚአብሔር አልነበረም መባሉ በአካል ሳይሆን በረድኤት ነው። በረድኤት አልነበረም ማለት ደግሞ በበደላቸው ምክንያት አይረዳቸውም ነበረ ማለት ነው። በነፋስ፣ በምድር መናወጥ የተመሰሉ ሰዎች መሆናቸውን ከላይ ተመልክተናል።

▶️፮. "በሰባተኛውም ጊዜ እነሆ የሰው እጅ የምታህል ታናሽ ደመና ከባሕር ወጥች አለ" ይላል (1ኛ ነገ.18፥44)። እመቤታችን በታናሸ ደመና ትመስላለችና ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ድንግል ማርያም የደመና ኤልያስ ምሳሌ ናት። ከደመና ውሃ እንደሚገኝ ሁሉ ከድንግል ማርያምም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ክርስቶስ ተወልዷልና ነው። ጥማችንን የሚያጠፋ የሕይወት ውሃ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወለደልን።

▶️፯. "በቀትርም ጊዜ ኤልያስ አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ ምናልባት ዐሳብ ይዞታል ወይም ፈቀቅ ብሏል ወይም ወደ መንገድ ኼዷል ወይም ተኝቶ እንደ ኾነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል እያለ አላገጠባቸው" ይላል። አላገጠባቸው ሲል ምን ለማለት ነው? በሌሎች እምነት ማላገጥ ተገቢ ነው?

✔️መልስ፦ ካህናተ ሐሰት ከእግዚአብሔር የተላኩ መስለው የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያታልሉ ክፉዎች ነበሩ። ስለዚህ ኤልያስ አላገጠባቸው መባሉ የያዙት እምነት ሰው ሠራሽ መሆኑን ሕዝቡ እንዲረዳ ነበረ። አሁንም ቢሆን የሌላ እምነት ሰዎች እምነታቸው የተሳሳተ መሆኑን እንናገራለን። ነገር ግን የእምነት ግጭት እንዳይፈጠር ሁሉም የሌላውን ሳይጋፋ የየራሱን እምነት ያስተምራል። በኤልያስ ዘመን የነበረው ሁኔታ ግን ከአሁኑ የተለየ ነው። በእግዚአብሔር አምልኮ ተቀላቅለው ሐሰታቸውን የሚሰብኩ ስለነበሩ ገልጦ ስሕተታቸውን መንገር ተገቢ ስለነበረ ተናግሯል። ለዚያ ነው ከፍ ብሎ እስከ ማእዜኑ ተሐነክሱ በክልኤሆን ጌጋያቲክሙ ያለው። በውስጥ እየኖረ የሚያሳስት አካል ካለ ገልጦ በአደባባይ መገሠጽ ይገባል። በኦሪት አካሉ ሙሉ ለምጽ የሆነ አይለይም ነበረ። አንዲት ለምጽ ያለበት ግን ተለይቶ ይቆይ ነበረ። ለምጽ አለብህ ተብሎም በካህኑ ይመሰከርበት ነበረ። ኤልያስ ያደረገው እንደዚህ ካህን ነው። በውስጥ ሆነው የሚያታልሉትን በግልጽ ነግሯቸዋል። አላገጠባቸው ማለት ጥቅል ሐሳቡ የያዙት አምልኮ ከንቱ መሆኑን መሰከረባቸው ማለት ነው።

▶️፰. ሰባት ጊዜ ተመላለስ አለው ይላል በሰባተኛውም ጊዜ ደመና ማየቱ ምሥጢሩ ለምን ይሆን?

✔️መልስ፦ ሰባት ቁጥር በዕብራውያን ፍጹም ነው። ስለዚህ በፍጹም ትጋት ጸጋ ክብር እንደሚሰጥ ለማጠየቅ ሰባት ጊዜ ተመላልሷል።

▶️፱. ኤልያስ ታላቅ ነቢይ ሲሆን ለምን በመጀመሪያ ለእኔ አስቀድመሽ እንጎቻ አድርጊልኝ አለ?

✔️መልስ፦ በኤልያስ ረኃብ ጸንቶበት ስለነበረ አስቀድመሽ ጋግረሽ አምጪልኝ ብሏል። ታላቅ ነቢይ ቢሆንም ረኃብን ተርቧልና። አስቀድሚልኝ ማለቱ ከእነርሱ ይልቅ ተርቦ ስለነበረ እንጂ ራስ ወዳድ ሆኖ አልነበረም።

▶️፲. የኤልያስ ወደ ሰራፕታ መሄድ መበለቷን ማግኘቱ ልጇን መፈወሱ ሊመጣ ካለው ለሐዲስ ኪዳን ምሳሌና ምሥጢር ያገናኘው ይሆን?

✔️መልስ፦ ልጇን ከሞት ማዳኑ ትንሣኤ ሙታን እንዳለ ማስረጃ ሆኗል። ከዚህ የተለየ ምሥጢር እንዳለው ግን በብሉያቱ ትርጓሜ የተገለጸ ነገር አላገኘሁም።

▶️፲፩. "ኢዮሣፍጥ ግን እንጠይቀው ዘንድ ሌላ የእግዚአብሔር ነቢይ በዚህ አይገኝምን አለ" ይላል (1ኛ ነገ.22፥7)። ኤልያስ በዚህ ጊዜ የት ሄዶ ነው ሚክያስን የጠሩት።

✔️መልስ፦ በዘመኑ ነቢይ ኤልያስ ብቻ ነው አልተባለም። ስለዚህ ለምን ኤልያስን አልጠሩም ለምን ኤልሳዕን አልጠሩም እያልን መላምት አንፈጥርም። ሚክያስም ነቢይ ስለነበረ እርሱን ጠርተዋል። እርሱም የሚገባቸውን ነግሯቸዋል። በሁሉም ነቢያት አድሮ የሚናገር እግዚአብሔር መሆኑን ልብ ማድረግ ይገባል።

▶️፲፪. በናቡቴ አቅራቢያ የነበሩ ሽማግሌዎች ኤልዛቤል ንፁሐን እንደምታስገድለው እያወቁ ለምን ገደሉት? በእግዚአብሔር የሚያምኑ ሁነው ሳለ ሰውን ያህል ነገር እንደዚህ የንግሥትን ቃል ተቀብለው ለምን ተገበሩት?

✔️መልስ፦ በየዘመናቱ አድር ባይና ፈሪ ሰዎች ነበሩ አሁንም አሉ። እነዚህ ሰዎች ለእውነት ሳይሆን የሚቆሙት ለጊዜያዊ ጥቅም ነበረ። ሞት እንዳለ የዘነጉ፣ እግዚአብሔርን የማይፈሩ ሰዎች ናቸው። እንዲህ ዓይነት ሰዎች ስለነበሩ ንጹሑን ናቡቴን አስገድለውታል።

▶️፲፫. "እግዚአብሔርም በምን አለው እርሱም ወጥቼ በነቢያቱ ዅሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እኾናለኹ አለ። እግዚአብሔርም ማሳሳትስ ታሳስተዋለኽ ይኾንልኻልም ውጣ እንዲሁም አድርግ አለ" ይላል። መንፈስ የተባለው በዚህ ጽሑፍ ማነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Dec, 19:39


✔️መልስ፦ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ ብሎ የተናገረው ሰይጣን ነው። ሐሰተኛ መንፈስ ያለው ሐሰተኛ ትምህርት ነው። ሰይጣን ሐሰተኛ ትምህርት ለሐሰተኛ ነቢያት እየተናገረ እንደሚያሳስት የሚያመለክት ቃል ነው። ስለዚህ በዚህ አገባብ መንፈስ ትምህርት ነው። ኢትእመንዋ ለኵላ መንፈስ ካለው ጋር አንድ ነው።

▶️፲፬. "ከነቢያትም ወገን አንድ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ባልንጀራውን ምታኝ አለው። ሰውየውም ይመታው ዘንድ እንቢ አለ። እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማኽምና እነሆ ከእኔ በራቅኽ ጊዜ አንበሳ ይገድልኻል አለው። ከእርሱም በራቀ ጊዜ አንበሳ አግኝቶ ገደለው" ይላል። ስላልመታው ኀጢአት ይሆንበታል?

✔️መልስ፦ ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። ግደለኝ ብሎ ሄደበት ማለት ወልደ አዴር አክአብን ግደለኝ ብሎ ሄደበት ማለት ነው። እንቢ አለው ማለት አክአብ ወልደ አዴርን አልገድልህም ብሎ ተማምሎ ሰደደው። እንቢ ያለውን አንበሳ ሰብሮ ገደለው ማለት አክአብን እግዚአብሔር አጠፋው ማለት ነው።

▶️፲፭. የሰራፕታዋ ሴት ማን ናት? የሰራፕታዋ ልጅ ማን ነው?

✔️መልስ፦ የሰራፕትዋ ሴት ከዚህ ስሟ አልተገለጸም። ልጇ ግን ነቢዩ ዮናስ እንደነበረ በትውፊት (በትርጓሜ) ይነገራል።

▶️፲፮. "የእስራኤል አምላክ የተራሮች አምላክ ነው እንጅ የሸለቆ አምላክ አይደለም" ይላል (1ኛ ነገ.21፥23)። የንባቡ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ይህን የተናገሩት እስራኤላውያን ሳይሆኑ በዘመኑ የነበሩ ሶርያውያን ናቸው። እነርሱም የመሰላቸውን ተናገሩ እንጂ ነገሩ እንደተናገሩት አይደለም። እግዚአብሔር የሁሉ አምላክ ነው። የሰማይም፣ የምድርም፣ የደጋም፣ የቆላም፣ ለሚታየውም፣ ለማይታየው፣ ለፍጥረት ሁሉ አምላክ ነው።

▶️፲፯. "አመንዝራ ሴቶችም በደሙ ታጠቡበት" ይላል (1ኛ ነገ.22፥38)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አክአብ ቆስሎ ሲሄድ ከወንዙ ደሙ ነጠበበት። ከዚያ በወንዙ ውሃ ሴቶች ታጥበውበታል። ይህን ለመግለጽ የተነገረ ቃል ነው።

▶️፲፰. "በኮረብቶች ላይ ያሉትን መስገጃዎች አላራቀም" ይላል (1ኛ ነገ.22፥43)። ይህ ንባብ በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት ለሄዱት ተገልጿል ያላራቁበት ምክንያት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ቦታው ቢርቃቸውና ባያውቁት ነው ያላጠፉት። በኋላ ግን ኢዮስያስ አጥፍቶታል።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Dec, 04:35


💟፩ኛ ነገሥት ክፍል ፬💟

💟ምዕራፍ 16፡-
ባኦስ እንደሞተና ልጁ ኤላ በምትኩ እንደነገሠ
-ኤላ ሞቶ በፋንታው ዘምሪ እንደነገሠ
-ዘንበሪና ታምኒ በንግሥና እንደተጣሉና ታምኒን ገድሎ ዘንበሪ እንደነገሠ
-ኢዮሳፍጥ በአባቱ በአሳ መንገድ እንደሄደና የእግዚአብሔርን ሕግ እንደጠበቀ
-ኢዮሳፍጥ ሞቶ ልጁ ኢዮራም እንደነገሠ

💟ምዕራፍ 17፡-
ነቢዩ ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ ስለመከልከሉ
-ለኤልያስ ቁራዎች በየጠዋቱና በየማታው እንጀራና ሥጋ ያመጡለት እንደነበር
-ከፈፋው ይጠጣ እንደነበር፣ በኋላ ግን ዝናብ ስለቀረ ፈፋው እንደደረቀ
-ኤልያስ ወደሰራፕታዋ መበለት ሄዶ ምግብ እንደበላ
-ነቢዩ ኤልያስ እንደተናገረው እንደእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ የሰራፕታዋ ሴት ዱቄትና ዘይት አለመጉደሉ
-ኤልያስ ሞቶ የነበረውን የሰራፕታዋን ልጅ ጸልዮ እንዳዳነው፡፡

💟ምዕራፍ 18፡-
-አብድዩ ነቢያትን በዋሻ ደብቆ ይመግባቸው እንደነበር
-አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን እንዳለው፣ ኤልያስ ግን እኔ ሳልሆን ጣዖትን እያመለካችሁ እናንተ ናችሁ ማለቱ
-ኤልያስ እስራኤላውያንን እስከመቼ በሁለት ሐሳብ ታነክሳላችሁ እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፣ በዓልም አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ ማለቱ
-የጣዖቱ የበአል ነቢያት በአል ሆይ ስማን እያሉ የሠሩትን መሠዊያ እያነከሱ ቢዞሩም ምንም ድምፅ ሳያገኙ መቅረታቸው፣ እንደልማዳቸው ደማቸው እስኪፈስ ድረስ ገላቸውን በጦርና በሰይፍ ቢቧጭሩም ምንም ድምፅ አለማግኘታቸው
-ኤልያስ መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ ከሰማይ እሳት ወርዶ መሥዋዕቱን መብላቱ፣ ሕዝቡም ይህንን ተአምር አይተው እግዚአብሔር በእውነት እርሱ አምላክ ነው ማለታቸው፣ ነቢያተ ሐሰትንም ከበው መግደላቸው

💟ምዕራፍ 19፡-
-ነቢያተ ሐሰትን ኤልያስ እንዳስገደላቸው ሰምታ የአክዓብ ሚስት ኤልዛቤል ኤልያስን ልትገድለው እንደፈለገች፣ ኤልያስም እንደሸሸና እግዚአብሔርን እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ ማለቱ፣ በደደሆ ዛፍ በታች ተኝቶ ሳለ መልአክ ዳሰሰውና ተነሥተህ ብላ ብሎ የተጋገረ እንጎቻና በማሰሮ ውሃ መስጠቱ፣ በልቶ ሁለተኛ ሲተኛም መልአኩ ቀስቅሶ የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነሥተህ ብላ ማለቱ፣ ኤልያስ ያንን በልቶ ኃይል ሆኖት እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እንደሄደ
-ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ኤልያስን እንደተከተለው

💟ምዕራፍ 20፡-
ኤልዛቤል ናቡቴን በግፍ እንዳስገደለችው
-ኤልያስ አክዓብ ናቡቴን ገድሎ በመውረሱ የናቡቴን ደም ውሾችችና ጅቦች በላሱበት ቦታ አክዓብም እንደሚሞት መንገሩ፣ አክዓብም መጸጸቱ

💟ምዕራፍ 21፡-
የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴር ሰማርያን እንደከበባትና እንደወጋት ነገር ግን እንደተሸነፈና ወልደ አዴርም በፈረስ እንዳመለጠ

💟ምዕራፍ 22፡-
ነቢዩ ሚክያስ አክዓብ እንደሚሸነፍ ትንቢት መናገሩ፣ አክዓብ ግን በእኔ ክፉ ነገርን የሚናገር ነቢይ ስለሆነ ጦርነቱ እስኪያልቅ ብሎ ነቢዩ ሚክያስን አስሮ እንዳቆየውና ከጦርነቱ ሲመለስ ሊገድለው እንዳሰበ፣ አክዓብ ግን ነቢዩ ሚክያስ እንደተናገረው በጦርነቱ እንደሞተ
-ሰይጣን በነቢያተ ሐሰት እያደረ ሰዎችን እንደሚያሳስት መገለጹ



የዕለቱ ጥያቄዎች
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ስለነቢዩ ኤልያስ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በእግዚአብሔር ስም ምሎ ዝናብ እንዳይዘንብ አድርጓል
ለ. በኮራት ፈፋ ሳለ ቁራዎች የሚበላውን ምግብ ያመጡለት ነበር
ሐ. የሰራፕታዋ እናት ልጅ በሞተ ጊዜ ጸልዮ ከሞት አስነሥቶታል
መ. ሁሉም
፪. እግዚአብሔር ኤልያስን “በእስራኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ቀብተህ አንግሠው” ያለው ማንን ነው?
ሀ. አዛሄል
ለ. ናሚሶን
ሐ. ኢዩ
መ. ሣፋጥ
፫. የአባቶቼን ርስት አልሰጥም በማለቱ በአክዓብ ሚስት በኤልዛቤል ትእዛዝ ሰጪነት በድንጋይ ተደብድቦ የተገደለው ሰው ማን ነው?
ሀ. ናቡቴ
ለ. ወልደ አዴር
ሐ. ሴዴቅያስ
መ. ዮዳሄ
፬. አክዓብ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ሊዘምት ሲል ነቢዩን ቢጠይቀው ነቢዩ አክዓብ እንደሚሸነፍ ነገረው፡፡ አክዓብ ግን የእኔን ሽንፈት ለምን ይናገራል ብሎ ከጦርነት እስክመለስ ብሎ አሳሰረው፡፡ ይህ ነቢይ ማን ነው?
ሀ. ሚልክያስ
ለ. ኢዩ
ሐ. ሚክያስ
መ. አኪያ
፭. ኤልያስ ነቢያተ ሐሰትን ስላስገደለ ኤልዛቤል ልትገድለው በፈለገች ጊዜ ሸሸ፡፡ ሸሽቶ ከደደሆ ዛፍ በታች አንቀላፍቶ ሳለ ጎኑን ዳስሶ የተጋገረ እንጎቻና የማሰሮ ውሃ ሰጥቶት የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነሥተህ ያለው ብላ ያለው ማን ነው?
ሀ. አብድዩ
ለ. መልአክ
ሐ. ቁራ
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/GG1mqUi2Nys?si=fC6kKw7fDpAIY5lE

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Nov, 16:18


እስካሁን የተማማርናቸው ትምህርቶች በPDF በቴሌግራም ቻናሌ ተለቀዋል። አንደኛ ሳሙኤል ላይ የጠየቃችኋቸው ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ነገ ይለቀቃል።

1. መጻሕፍተ ሊቃውንት ተከታታይ ትምህርት
2. መጻሕፍተ መነኮሳት ተከታታይ ትምህርት
3. ነገረ ክርስቶስ
4. ኦሪት ዘፍጥረት ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
5. ኦሪት ዘፀአት ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
6. ኦሪት ዘሌዋውያን ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
7. ኦሪት ዘኍልቍ ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
8. ኦሪት ዘዳግም ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
9. መጽሐፈ ኢያሱ ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
10. መጽሐፈ መሳፍንት ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
11. መጽሐፈ ሩት ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
12. ተከታታይ የግእዝ ትምህርት

እና ሌሎችንም አሁን በቴሌግራም ቻናሌ እለቃቸዋለሁ። ገብታችሁ አውርዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። እስካሁን የተማማርናቸውን ማንበብ ለሚፈልግ ሼር አድርጉለት።

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Nov, 15:27


✝️ የጥያቄዎች መልስ ክፍል 52 ✝️

▶️፩. "ካህኑም ለዳዊት መልሶ ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን የተቀደስ እንጀራ አለ፤ ብላቴኖቹ ከሴቶቹ ንጹሐን እንደ ሆኑ መብላት ይቻላል አለው። ካህኑም በእርሱ ፋንታ ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ ከእግዚአብሔር ፊት ከተነሣው ከገጹ ኅብስት በቀር ሌላ እንጀራ አልነበረምና የተቀደሰውን እንጀራ ሰጠው" ይላል (1ኛ ሳሙ.21፥4-6)። ከላይ ቁጥር 1 ላይ ዳዊት ወደ አቤሜሌክ ብቻውን እንደሄደ ይናገራል። እዚህ ላይ ደግሞ "ብላቴኖቹ" ብሎ ከዳዊት ጋር አብረው ስላሉት ይገልጻልና ሀሳቡ እንዴት ይታረቃል? በሐዲስ ኪዳን ተረፈ መሥዋዕት መብላት የሚችሉ እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ ቁጥር 1 ላይ ዳዊት ወደ አቤሜሌክ እንደሄደ ይናገራል። ብቻውን ሲሄድ ግን አብረውት የነበሩ ሰዎችን ፌላሌምሌሞንም በተባለ ድብቅ ቦታ አቆይቷቸው ነው። ብቻውን ሄዶ አቤሜሌክን ምግብ እንዳለው የጠየቀው ለተደበቁት ሰዎችም ጭምር እንዲሆን ነበር። ካህኑ አቤሜሌክም ይህንን ተረድቶ አንተም ብላቴኖችህም ንጹሕ ከሆናችሁ ብሉ ብሎታል። በሐዲስ ኪዳን ተረፈ መሥዋዕትን የሚበሉት የቆረቡ የቀደሱ ካህናት ናቸው።

▶️፪. "በፊታቸውም አእምሮውን ለወጠ፥ በያዙትም ጊዜ እንደ እብድ ሆነ፥ በበሩም መድረክ ላይ ተንፈራፈረ፥ ልጋጉም በጢሙ ላይ ይወርድ ነበር" ይላል (1ኛ.ሳሙ 21፥13)። ዳዊት ሆን ብሎ ለማምለጥ ሲል ያደረገው ነው ወይስ እግዚአብሔር እንዲያመልጥ ስለፈለገ እንዲህ አድርጎት ነው?

✔️መልስ፦ ዳዊት ራሱ የዘየደው ዘዴ ነው። እብድ ሳይሆን እብድ መስሎ ታየ። ንጉሠ ጌትም እብድ ለምን እገድላለሁ ብሎ ንቆ ትቶታል። እግዚአብሔርም ዳዊት ያደረገውን ጥበብ ምክንያት አድርጎ ዳዊትን ከእንኩስ ንጉሠ ጌት አድኖታል።

▶️፫. "ከአሥር ቀንም በኋላ እግዚአብሔር ናባልን ቀሠፈው፥ እርሱም ሞተ" ይላል (1ኛ ሳሙ.25፥38)። እግዚአብሔር ቀሠፈው ሲል ዳዊት ለምኖት ስላልሰጠው ነው? ሰው በሀብቱ ማዘዝስ ልማድ አይደለም ወይ?

✔️መልስ፦ ሰው በሀብቱ የማዘዝ ሥልጣንና ነጻነት አለው። ናባልንም እግዚአብሔር የቀጣው ወይም የቀሠፈው ለምን በገንዘብህ አዘዝክ ብሎ አይደለም። እግዚአብሔር የቀባውን ዳዊትን ስላቃለለና ስለተሳደበ ነው። እግዚአብሔር ያከበረውን መናቅ እንደሚያስቀሥፍ በናባል ሕይወት አወቅን።

▶️፬. 1ኛ ሳሙ.25፥43 "ሳኦል ግን የዳዊትን ሚስት ልጁን ሜልኮልን ሀገሩ ሮማ ለነበረው ለያሚስ ለፈሊጥ ሰጣት" ይላል። በዳዊት በንግሥናው ሁሉ ከዳዊት ጋር አብራው አልነበረችም ወይ?

✔️መልስ፦ ሳኦል ዳዊትን አምርሮ ይጠላው ስለነበር ለዳዊት ሚስቱ እንድትሆን ያጋባትን ልጁን ሜልኮልን ሳይቀር ለሌላ ሰው ዳረበት። በሌላ ጊዜ ግን ዳዊት ከሮማዊው ከፌልጢ ቀምቶ እንደገና ሚስቱ አድርጓታል። ዳዊት ሳኦል ሞቶ ከነገሠ በኋላ ሜልኮል ሚስቱ ሆና ኖራለች።

▶️፭. "ካህኑን አቤሜሌክ በኖብም ያሉት ካህናት" ይላልና በብሉይ ኪዳን በአንድ ዘመን ስንት ካህናት ሊኖሩ ይችላሉ ሊቀ ካህናቱ ማን ነበር? የትስ ይኖራል?

✔️መልስ፦ ሊቀ ካህናቱ አንድ ነው። በመዓርግ ከሊቀ ካህናቱ በታች ያሉ ካህናት ብዙ ናቸው። በዘመኑ የነበረው ሊቀ ካህናቱ አቤሜሌክ ሲሆን ይኖር የነበረውም ታቦተ እግዚአብሔር ባለችበት ቦታ አካባቢ ነበር። ሌሎች ካህናት በ48ቱ የመማጸኛ ከተሞች ሁሉ ይኖራሉ።

▶️፮. "ሳኦልም ወገቡን ይፈትሽ ዘንድ ወደዚያ ዋሻ ገባ" ይላል እና ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ወገብን መፈተሽ ማለት ሽንት ቤት መጸዳዳት ማለት ነው። ሽንት ቤት እየተጸዳዳ ነበር ከሚለው ይልቅ ወገቡን እየፈተሸ ነበር የሚለው ጥሩ ነው አገላለጹ። ሽንት ቤት የሚለው ጸያፍ ስለሆነ ሊቃውንት ቀይረው ወገብን መፈተሻ (አንበሳ መደብ) ብለውታል።

▶️፯. "አኹንስ በእጅኽ ምን አለ አምስት እንጀራ ወይም የተገኘውን በእጄ ስጠኝ አለው" ይላል። ምሳሌነቱ ምንድን ነው መምህር?

✔️መልስ፦ መተርጉማን በአንድምታው የተለየ ትርጉም አልሰጡትም። ዳዊት እንዲሁ ካለው ከተገኘው ስጠኝ ብሎ አምስት እንጀራ ካለ ብሎ አዝዞታል። ምሳሌ ግን ስለማያልቅና ዙሮ ዙሮ ዘየሐጽጽ ስለሆነ ሌላ መተርጉም በአምስቱ አዕማድ መስሎ ቢናገር ላይነቀፍ ይችላል።

▶️፰. 1ኛ ሳሙ.24፥15 "አሁንም የእስራኤል ንጉሥ ማንን ለማሳደድ ወጥተሀል? አንተስ ማንን ታሳድዳለህ? የሞተ ውሻን ታሳድዳለህን? ወይስ ቊንጫን ታሳድዳለህን? እንግዲህ እግዚአብሔር ዳኛ ይሁን" ይላል። ክቡር ዳዊት እነዚህን ምሳሌዎች ምንን ለመግለጽ ተጠቀማቸው?

✔️መልስ፦ ዳዊት ራሱን በውሻ በቀበሮ መመሰሉ ውሻ ወይም ቀበሮ የተናቀ እንደሆነ እኔስ የተናቅሁ አይደለሁምን ለማለት ነው። በሌላ አተረጓጎም ደግሞ ውሻን ጨክነው ቢያሳድዱት ዙሮ እንደሚናከስ ሁሉ እኔንም ጨክነህ ብታሳድደኝ ዙሬ እዋጋሀለሁ ሲለው ነው። ዳዊት ራሱን በቁንጫ መመሰሉ ደግሞ ቁንጫ ፍንጥር ፍንጥር (እንጣጥ እንጣጥ) እያለች እንደማትያዝ ሁሉ ኤኔም ከአንዱ ተራራ ወደ አንዱ ተራራ እያልኩ ስለምሄድ ሳኦል ሆይ አትይዘኝም ሲለው ነው።

▶️፱. ዳዊት ካህኑን አቤሜሌክ እንጀራ እንደለመነው እና አቤሜሌክ ከተቀደሰው እንጀራ ከሴት ንጹሕ እንደሆኑ መብላት እንደሚችሉ ነገረው ግን "ነገር ግን ሰውነቴ ንጽሕት ስለሆነች ነው እንጂ ይህች መንገድ የነጻች አይደለችም" ይላል። ትርጉሙ ምንድን ነው? ደግሞ ንጹሕ የሆኑ ስዎች ሰዎች ሁልግዜ የሚመገቡት አይደለም ወይ?

✔️መልስ፦ ዳዊት ይህች መንገድ ንጽሕት አይደለችም ያለው ከነገደ ሌዊ ሳይወለዱ ንጹሕ እንጀራ መብላት አይገባም ነበረ ነገር ግን ስለራበኝ እኔም ንጹሕ ስለሆንኩ በላሁ ማለቱ ነው። ያንን ንጹሕ እንጀራ የሚበሉት ሌዋውያን ነበሩ። ዳዊት ግን ከነገደ ይሁዳ ሆኖ ሳለ መብላቱን ሲያይ ንጹሕ መንገድ አይደለም አለ። ነገር ግን ደግሞ ሦስት ቀን ሙሉ ከሚስቶቻቸው ተለይተው ስለበሉ ንጹሕ ነን አለ።

▶️፲. 1ኛ ሳሙ.24፥4 "ዳዊትም የሳዖልን መጎናጸፊያ በቀስታ ቀደደ" ይላል። እንዴት ነው ልብሱን አስቀምጦት ነበር ወይስ እንደለበሰው ነው?

✔️መልስ፦ ሳኦል ልብሱን እንደለበሰው አንበሳ መደብ ሊቀመጥ ወደ ዋሻ ገባ። ወደ ዋሻ ውስጥ የሚገባ ሰው ወደ ውስጥ ያለውን ለማየት ስለሚቸገር አላያቸውም እንጂ ከውስጥ ግን እነ ዳዊት ነበሩ። እና ሳኦል ልብሱን እንደለበሰ ወገቡን ሲፈትሽ ዳዊት ከልብሱ ቀድዶ ሳኦል ከዋሻ ከወጣ በኋላ አሳይቶታል።

▶️፲፩. 1ኛ ሳሙ.፳፩÷፱ "የጎልያድ ሰይፍ እነሆ በመጎናጸፊያ ተጠቅልላ አለች" ሰይፍ ለዛውም የፍልስጤማዊው በቤተ መቅደስ (በካህን ቤት) ይቀመጣል ወይ? መቼ ነው ቤተ መቅደስ (ከካህኑ ቤት) ያስቀመጡት? በአሁኑ ዘመንስ (በሐዲስ ኪዳን) ሰይፍ፣ ሽጉጥ ቤተ መቅደስ ይኖራል ወይ? በካህናት ቤትስ ማስቀመጥ ይቻላል ወይ?

✔️መልስ፦ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በዳዊት አድሮ ከፍልስጥኤማዊው ከጎልያድ እንዳዳናቸው እንዲያስታውሱበት በደብተራ ኦሪት ሰይፉ ተቀምጦ ነበር። አሁንም በሀገራችን የነገሥታት ሰይፍ፣ ጋሻ፣ ልብስ በቅርስነት ተቀምጦ እንዳለው ያለ ነው። በሐዲስ ኪዳንም በብሉይ ኪዳንም ለቅርስነት ለማስታዎስ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ አገልግሎት ቤተ መቅደስ ውስጥ ሰይፍም ሽጉጥም ሌላም መሣሪያ አይቀመጥም።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Nov, 04:56


💝 ፩ኛ ሳሙኤል ክፍል ፭ 💝

💝ምዕራፍ 21፦
-ዳዊት ወደካህኑ ወደአቤሜሌክ ሄዶ የተቀደሰ እንጀራ እንደበላ
-አቤሜሌክ የጎልያድን ሰይፍ ለዳዊት እንደሰጠው
-ዳዊት በጌት ንጉሥ በአንኩስ ፊት እብድ መስሎ ከመገደል እንደተረፈ

💝ምዕራፍ 22፦
-ሳኦል ዳዊትን ስለረዱ ካህኑን አቤሜሌክንና ሌሎችንም ካህናት በዶይቅ እንዳስገደላቸው

💝ምዕራፍ 23፦
-ዳዊትና ሰዎቹ ቂኦላን ከፍልስጥኤማውያን እጅ እንዳዳኑ

💝ምዕራፍ 24፦
-ሳኦል በዋሻ ውስጥ በዳዊትና በዳዊት ሰዎች እጅ ወድቆ እንደነበረና ዳዊት ግን ልብሱን ብቻ በቀስታ ቆርጦ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን አላነሣም ብሎ ሳኦልን አለመግደሉ፣ ሳኦልም በኋላ ሲያውቅ ዳዊትን እኔ ክፉ በመለስኩልህ ፋንታ በጎ መልሰህልኛልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ እንዳለውና እግዚአብሔር መልካሙን ይመልስልህ ብሎ እንደመረቀው

💝ምዕራፍ 25፦
-ሳሙኤል እንደሞተ
-የዳዊት ሰዎች የዳዊትን መልእክት ለናባል እንዳደረሱ፣ ናባል ግን ዳዊትን እንደተሳደበና እንደናቀ፣ ዳዊትም ሰይፉን ታጥቆ ወደናባል እንደሄደ፣ ወደናባል ሳይደርስ የናባል ሚስት ቀድማ ደርሳ ምሕረትን ለናባል እንደለመነችለት፣ ዳዊት በአቤግያ ልመና ምክንያት ናባልን አለመግደሉ፣ ናባል ዳዊት መጣ ሲሉት ደንግጦ እንደሞተ፣ ዳዊት አቢግያን ሚስቱ እንዳደረጋት


✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️
፩. ዳዊት ከሳኦል ሸሽቶ ባመለጠ ጊዜ የተቀደሰ እንጀራንና የጎልያድን ሰይፍ የሰጠው ካህን ማን ነው?
ሀ. አብያታር
ለ. ነቢዩ ጋድ
ሐ. አቤሜሌክ
መ. አኪጦብ
፪. ዳዊት እብድ መስሎ በመታየት ከመገደል የተረፈው ከማን ነው?
ሀ. ከቂኦላ ሰዎች
ለ. ከጌት ንጉሥ ከአንኩስ
ሐ. ከዚፍ ሰዎች
መ. ከንጉሡ ከሳኦል
፫. ዳዊት ሰይፍ ታጥቆ ናባልን ሊገድል ሲሄድ ምግብ ይዛ ቀድማ አግኝታ ለናባል ምሕረትን ለምና ናባልን ከዳዊት ሰይፍ ያዳነችው ሴት ማን ናት?
ሀ. አቤግያ
ለ. ሜሮብ
ሐ. አኪናሆም
መ. ሜልኮል

https://youtu.be/59wse28ZHBA?si=p4SOnLRbTDW_YhZ2

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Nov, 04:46


✝️ መዝሙረ ዳዊት ክፍል 10 ✝️
✝️መዝሙር ፲፩
ዳዊት ይህንን መዝሙር የስምንተኛው ሺህ ነገር ተገልጾለት ጸልዮታል፡፡ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ከስምንተኛው ሺህ ዘመን ሰው በጎ ቸር ጠፍቷልና አድነኝ፡፡ አፄ ናዖድ የስምንተኛው ሺህ ነገር ተገልጾላቸው ከጊዜው አታድርሰኝ ከእህል ከውሃው አታቅምሰኝ እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ ይኸውም ሊታወቅ ስምንተኛው ሺህ በመስከረም ሊገባ በነሐሴ ሰባት ቀን አርፈዋል፡፡ በከዳተኛ አንደበት የሚነጋገሩትን ሰዎች እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፡፡ መቀባጠር የምታበዛ አንደበትንም ነቃቅሎ ይጥላታል፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ አንደበትን መስጠቱ እርሱን ልናመሰግንበት ነው እንጂ ሰውን ልንሰድብበት አይደለም፡፡ ቃለ እግዚአብሔር ቃል ንጹሕ፡፡ ቃለ እግዚአብሔር ከሐሰት ከዝርውነት ንጹሕ ነው፡፡ ብረቱን ሰባት ጊዜ ከከውር ወደ ከውር ያፀሩት እንደሆነ ከብር መዓርግ ይደርሳል፡፡ ብሩ ከወርቅ ወርቁ ከዕንቊ መዓርግ ይደርሳል፡፡ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ጠብቀን፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Nov, 17:29


💝የጥያቄዎች መልስ ክፍል 49💝

▶️፩. የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እስራኤል ስትመለስ በባዶ እንዳይሰዱ የመከሯቸው ጠንቋዮች ናቸው እና እግዚአብሔር በጠንቋይ ሰው ልቦና ያድራል?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በጠንቋይ ሰው ልቡና አያድርም። ነገር ግን ልክ እንደ ጠንቋዩ በለዓም ሁሉ አፋቸውን ከፍቶ ፊታቸውን ጸፍቶ ለታቦተ ጽዮን መገበር እንደሚገባቸው አናግሯቸዋል።

▶️፪. "አምስት የወርቅ እባጮች" ይላልና ትርጓሜው ምንድነው?

✔️መልስ፦ አምስት የወርቅ እባጮች የሚለው ታቦተ ጽዮን በሀገራቸው ሳለች መቅሠፍት ወርዶባቸዋል። አንዱ መቅሠፍት ብልታቸው አብጦ መጨጊያ መጨጊያ አህሎ ነበር። እና ያንን ለማስታዎስና በኃጢአታችን ምክንያት ይህ ደረሰብን ሲሉ የወርቅ የአካላቸውን እባጭ የመሰለ ሠርተው ለታቦተ ጽዮን ገብረዋል።

▶️፫. "ውሃ ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት በምድር ላይ አፈሰሱ በዚያም ቀን ጾሙ" ይላልና ውሃ በምድር ላይ ማፍሰስ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ውሃ የማፍሰሱ ትርጉም ውሃ ከፈሰሰ በኋላ እንደማይመለስ ሁሉ እኛም ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮ እግዚአብሔር ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ ከተመለስን በኋላ ወደ አምልኮ ጣዖት ወደ ገቢረ ኃጢአት አንመለስም ሲሉ በእግዚአብሔር ፊት ውሃውን ወደ ምድር አፍስሰውታል።

▶️፬. "በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን ናቁ" ይላልና የእስራኤል ንቀት ምንድን ነው? እና እስራኤል ንጉሥ መፈለጋቸውን ነው?

✔️መልስ፦ በመሳፍንት ዘመን በመስፍኑ አድሮ ይገዛቸው የነበረ እግዚአብሔር ነው። መስፍኑ ሳሙኤል፣ ከሳሙኤል በላይ ያለው ንጉሥ ግን እግዚአብሔር ነበረ። እና እስራኤል ንጉሥ አንግሥልን ሲሉ እግዚአብሔር በመስፍኑ አድሮ አይንገሥብን ማለታቸው ስለነበረ ነው እኔን ናቁ ያለ እግዚአብሔር።

▶️፭. "ሳኦልም አጎቱን አህያዎች እንደ ተገኙ ገለጠልን አለው። ነገር ግን ሳሙኤል የነገረውን የመንግሥትን ነገር አላወራለትም" ይላል። ለምን ነበር ያልነገረው?

✔️መልስ፦ የአህዮችን መጥፋት አጎቱም ያውቅ ስለነበረ መጥፋታቸውን ነገረው ተብሏል። የመንግሥትን ነገር ግን አጎቱም ስላልጠየቀው እርሱም አልመለሰለትም።

▶️፮. "ከሳሙኤልም ዘንድ ለመኼድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ለወጠለት። በዚያም ቀን እነዚህ ምልክቶች ዅሉ ደረሱለት" ይላል። እግዚአብሔር ሌላ ልብ ለወጠለት ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሌላ ልብ ለወጠለት ማለት አላዋቂ የነበረውን ሳኦል እግዚአብሔር ዕውቀት ጨመረለት፣ ባለአእምሮ አደረገው ማለት ነው።

▶️፯. "ሳኦልም ብላቴናውን እነሆ እንኼዳለን። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሰው ምን እናመጣለታለን እንጀራ ከከረጢታችን አልቋልና እጅ መንሻም የለንምና ለእግዚአብሔር ሰው የምናመጣለት ምን አለን አለው" ይላህ። ለነቢይ መባ እጅ መንሻ ማምጣት ግዴታ ነበር?

✔️መልስ፦ ኦሪት በእግዚአብሔር ነቢይ ፊት ያለእጅ መንሻ አትቁም ስለምትል በሕጉ መሠረት እንዴት ያለእጅ መንሻ ወደነቢይ እንቀርባለን ብለዋል። በነቢይ ፊት እጅ መንሻ ይዞ መቅረብ ግዴታ ይሆን አይሆን ግን የተጻፈ ነገር አላገኘሁም አላውቀውም።

▶️፰. "የሚፈርድልንም ንጉሥ ስጠን ባሉት ጊዜ ነገሩ ሳሙኤልን አስከፋው። ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ" ይላል። ለምን ነበረ ሳሙኤል የተከፋው?

✔️መልስ፦ ሳሙኤል የተከፋው ምስፍና ከእኔ ቀረ ብሎ አልነበረም። ከዚህ ቀደም እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በነቢይ፣ በካህን፣ በመስፍን አድሮ ይረዳቸው ነበር። እንደ ንጉሥ እግዚአብሔር ሲሆን ከእግዚአብሔር በታች ደግሞ መስፍኑ ይገዛቸው ነበረ። የእግዚአብሔርን ንጉሥነት አምነው መቀጠል ሲገባቸው ሌላ ንጉሥ አንግሥልን ሲሉ ከእንግዲህ እግዚአብሔር ላይረዳቸው ይችላል ብሎ ስላሰበ ነው ሳሙኤል የተከፋው።

▶️፱. "ወደ እግዚአብሔርም ታቦት ውስጥ ተመልክተዋልና የቤት ሳሚስን ሰዎች መታ" ይላል (1ኛ ሳሙ.6፥19)። መምህር እዚህ ላይ ግልፅ ያልሆነልኝ ነገር አለ ቁ.15 ላይ ሌዋውያን ታቦቱን እንዳወረዱትና በድንጋይ ላይ እንዳስቀመጡት ይናገራል። ምናልባት ያኔ ሌዋውያን ሲከፍቱት አይተው ይሆን የቤትሳሚስ ሰዎች የተመቱት ወይስ  "የቤትሳሚስ ሰዎችም በሸለቆው ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ዓይናቸውንም ከፍ አድርገው ታቦቱን አዩ፥ በማየታቸውም ደስ አላቸው" ባለው ነው የተመቱት?

✔️መልስ፦ 1ኛ ሳሙ.6፥19 ላይ ተጎዱ የተባሉት ታቦተ እግዚአብሔርን እያዩዋት ተመልክተዋት ያልተቀበሉ ሰዎች (የኢያኮንዩ ልጆች) ናቸው። በሳሚስ ቤት የነበሩ ልጆች ግን ደስ ብሏቸው ስለተቀበሏት መቅሠፍት አልደረሰባቸውም። (የግእዙን መጽሐፍ ቅዱስ ወይም የአንድምታውን መጽሐፍ ቅዱስ ተመልከት)

▶️፲. "እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው። በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ" ይላል (1ኛ ሳሙ.8፥7)። እዚህ ላይ የሳሙኤል ልጆች ፍርድን ስላጣመሙ ሕዝቡ ሳሙኤልን ሌላ የሚፈርድልን ንጉሥ ስጠን አሉት እንጂ የሕዝቡ ጥፋት ምን ስለሆነ ነው "እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና" የተባለው?

✔️መልስ፦ እውነት ነው የሳሙኤል ልጆች በድለው ነበረ። መፍትሔው ደግሞ እነርሱን ቀጥቶ ሌላ መስፍን መሾም እንጂ እንደአሕዛብ ልማድ ንጉሥ አንግሥልን ማለት አልነበረም። እግዚአብሔርም እኔን ናቁ ማለቱ በመስፍኑ አድሬ ነግሼባቸው የምኖረውን እኔን የባሕርይ ንጉሥን ትተው ፍጡር ንጉሥ ፈለጉ ብሎ ነው። እግዚአብሔርም ናቁኝ ማለቱ ኅሊናቸውን አውቆ ነው። በሳሙኤል አንጻር ሌላ ንጉሥ ይንገሥልን ይበሉ እንጂ በኅሊናቸው የናቁት እግዚአብሔርን ነበረ።

▶️፲፩. "የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፥ ዕጣውም በማጥሪ ወገን ላይ ወደቀ። የማጥሪንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፥ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለጉትም፥ አላገኙትምም" ይላል (1ኛ ሳሙ.10፥21)። አስቀድሞ ቁ.1 ላይ ሳሙኤል ቀብቶ አንግሦት እያለ ከነገሠ በኋላ ዕጣ ማውጣቱ ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እውነት ነው ሳሙኤል ሳኦልን አስቀድሞ ሹሞታል። ነገር ግን ሕዝቡ ልሹምብህ ከሚባል የመረጥከውን ሹም ቢባል ይመርጣል። ስለዚህ በሳኦል መመረጥ እንዳያጉረመርሙና የእግዚአብሔርም ፈቃድ መሆኑን ለማሳየት እንደገና በዕጣ ለሳኦል ሲደርሰው ሁሉም ተመልክተዋል።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Nov, 14:48


እንቋዕ አብጽሐክሙ
እግዚኡ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል።
እምኵሎሙ መላእክት መላእክት ይትለዐል መንበሩ።

የመልአኩ ረድኤት አይለየን።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Nov, 04:41


💛 ፩ኛ ሳሙኤል ክፍል ፪ 💛

💛ምዕራፍ 6፦
-የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን ሀገር ሰባት ወር እንደተቀመጠችና በዚህ ምክንያት በሀገሩ አይጦች መብዛታቸው
-ለታቦተ ጽዮን የበደል ካሣ ሰጥተው በሠረገላ አድርገው ወደሌላ ሀገር መላካቸው
-ታቦተ ጽዮን በሠረገላ በሁለት ላሞች እየተሳበች ስትመጣ በአጨዳ የነበሩት የቤትሳሚስ ልጆች ደስ ብሏቸው እንደተቀበሏት፥ የኢያኮንዩ ልጆች ግን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመልክተው ከቤትሳሚስ ሰዎች ጋር አለመቀበላቸው

💛ምዕራፍ 7፦
-ሳሙኤል እስራኤላውያንን ከጣዖት አምልኮ እንዲርቁ መናገሩ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልኩ መንገሩ
-እስራኤላውያን ሳሙኤልን ወደእግዚአብሔር ጸልይልን ማለታቸው፣ ሳሙኤልም መሥዋዕትን መሠዋቱ
-ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ገጥመው መሸነፋቸው

💛ምዕራፍ 8፦
- የሳሙኤል ልጆች ፍርድ ማድላታቸው፣ መማለጃ መብላታቸው
-እስራኤላውያን ሳሙኤልን ንጉሥ አንግሥልን ማለታቸው

💛ምዕራፍ 9፦
-ሳኦል የአባቱ አህዮች ጠፍተው ሊፈልግ መሄዱ
-ሳኦል አህዮች ያሉበትን ይጠቁመው ዘንድ ወደሳሙኤል መሄዱ
-እግዚአብሔር ለሳሙኤል ሳዖልን እንዲያገግሠው መንገሩ

💛ምዕራፍ 10፦
- ሳሙኤል ሳኦልን ቀብቶ እንዳነገሠው


✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️
፩. ፍልስጥኤማውያን ለታቦተ ጽዮን የበደል ካሣ ምን ሠጡ?
ሀ. የአካላቸውን እባጭ የመሰለ ወርቅ
ለ. የወርቅ አይጦች
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም
፪. ታቦተ ጽዮን በሠረገላ በሁለት ላሞች እየተሳበች ስትመጣ በአጨዳ ላይ እያሉ አይተዋት ደስ ብሏቸው የተቀበሏት እነማን ናቸው?
ሀ. የቤትሳሚስ ሰዎች
ለ. የኢያኮንዩ ልጆች
ሐ. ሀ እና ለ
መ. ሁሉም
፫. ሳሙኤል ፍልስጥኤማውያንን ከአሸነፈ በኋላ አንድ ድንጋይ ወስዶ በመሴፋና በአሮጌው ከተማ መካከል አኖረው ይላል። ይህን ድንጋይ ምን ተብሎ ተጠራ?
ሀ. አቤንኤዜር
ለ. ዕብነ ረድኤት
ሐ. ሀ እና ለ
መ. ሁሉም

https://youtu.be/UDFMrAeXA38?si=1gheWK2NuolFwbZy

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Nov, 04:33


✝️መዝሙረ ዳዊት ክፍል 7✝️
✝️መዝሙር ፭
መዝሙር 5 ስለትሩፋን የተጻፈ ነው፡፡ ትሩፋን የሚላቸው አሥሩ ነገድ ተማርከው በኢየሩሳሌም የቀሩ ሁለቱ ነገድ ናቸው፡፡ አንድም ሁሉም ተማርከው አበው አልቀው የቀሩ ውሉድ ናቸው፡፡ አቤቱ ልመናዬን ስማኝ፡፡ ጌታ ሆይ የእኔ ንጉሤም ፈጣሪዬም አንተ ነህ፡፡ እግዚኦ ምርሐኒ በጽድቅከ፡፡ ሰውን መበደል እግዚአብሔርን ማሳዘን ነው፡፡
✝️መዝሙር ፮
ዳዊት በቤርሳቤህ ምክንያት ያስገደለው ኦርዮ የጌታ ምሳሌ ነው፡፡ ኦርዮ ጦማረ ሞቱን ይዞ ከኢየሩሳሌም ወደ አራቦት እንደሄደ ጌታም ከሊቶስጥራ ወደ ቀራንዮ መስቀሉን ተሸክሞ ሄዷልና፡፡ በቀድሞው ዘመን ነቢያት ዘመነ ሣህል ወርኀ ሰላም ነው ሲሉ ኩፋር ለብሰው ኩፋር ጠምጥመው በአምባላይ ፈረስ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታያሉ፡፡ ዘመነ ፀብዕ ወርኀ ኀዘን ነው ሲሉ ከል ለብሰው ከል ጠምጥመው ዘገር ይዘው ይታያሉ፡፡ ዳዊት ኦርዮን በማስገደሉ ተጸጽቶ ጉድጓድ ምሶ አመድ ነስንሶ ማቅ ለብሶ ንስሓ ገባ፡፡ በእንባው የበቀለ ሰርዶ ሰውነቱን ተብትቦ ይዞት ብላቴኖቹ በመቀስ እያረፉ አውጥተውታል፡፡ ዳዊት በነፍሱ ይቅር ሲባል በሥጋው ግን ኃጢአት ያለፍዳ አይነፃምና ልጁ እንዲያሳድደው ሆኗል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Nov, 18:50


💝የጥያቄዎች መልስ ክፍል 48💝

▶️፩. "ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ" ይላል። በዚህ አገባብ ቀንድ የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የሳሙኤል እናት የሐና እንደ በሬ እንደ ላም ቀንድ ነበራት ለማለት አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ቀንድ እየተባለ የሚጠራ ሥልጣን ነው። ስለዚህ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለቷ ሥልጣኔ ከፍ ከፍ አለ ለማለት ነው።

▶️፪. "ስለዚህም የዔሊ ቤት ኃጢአት በመሥዋዕትና በቍርባን ለዘላለም እንዳይሠረይለት ለዔሊ ቤት ምያለሁ" ይላል (1ኛ ሳሙ.3፥14)። ይህ ነገር ከእግዚአብሔር መሓሪነትና ይቅር ባይነትጋ አብሮ ይሄዳል ወይ ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር መሓሪነት አያጠያይቅም። በባሕርይው ቸር መሓሪ እግዚአብሔር ብቻ ነው። የዔሊ ወገኖች ከበደላቸው ቢመለሱ እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል። ነገር ግን እንደማይመለሱ አውቆ አይሠረይላቸውም አለ።

▶️፫. "የእግዚአብሔርም ታቦት ተማረከች፥ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ" ይላል (1ኛ ሳሙ.4፥11)። በዚህ ዘመን ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በአክራሪ ኃይሎች ይቃጠላሉ፤ ታቦታትና ንዋየ ቅድሳት ይዘረፋሉ፤ አገልጋይ ካህናት ይገደላሉ። አንዳንድ ሰዎች እንዴት ታቦት ካህን ባልሆነ ያውም በማያምን ሰው እጅ ይያዛል? እውነት የምትሰግዱለት ታቦት የሆነ ኃይል ካለው ለምን አይቀሥፍም? ወይስ  ለምን ሌላ ተአምር ሠርቶ አያጠፋቸውም? ይላሉና ከዚህ ጥቅስ ተነሥተው ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ፈታሒ (ፈራጅ) ብቻ ሳይሆን መሓሪም ነው። አንድ ሰው አጥፍቶ ሳለ እንኳ ወዲያው አያጠፋውም በንስሓ ይመለስ ዘንድ በድሎም ዝም ይለዋል። የእርሱ ማደሪያ የሆነው ታቦት ብቻ ሳይሆን እርሱን ራሱን ኢየሱስ ክርስቶስን ይሁዳ ስሞ ሲሸጠው ሲሰቅሉት እንደሚታረድ በግ ዝም እንዳለ ተገልጿል። ይህ ሁሉ የእግዚአብሔርን መሓሪነት ሰው እንዲረዳ ነው። ታቦተ ጽዮን መማረኳ ስለሁለት ነገር ነው። አንደኛ እስራኤላውያን ስለበደሉ በእርሷ መማረክ አዝነው ንስሓ እንዲገቡ ነው። ሁለተኛ ተማርካ የአሕዛብን አማልክት እነዳጎንን እንድትሰባብርና አሕዛብ የሚያመልኳቸው አማልክት የእጅ ሥራዎች መሆናቸውን አሕዛብ እንዲረዱ ነው። ስለዚህ ታቦት የሚሰርቅ ሰው ያልተቀሠፈ እግዚአብሔር መሓሪ ስለሆነ የንስሓ እድሜ እየሰጠው እንጂ ወዲያው ማጥፋት አቅቶት እንዳልሆነ ሊረዳው ይገባል።

▶️፬. "የእግዚአብሔርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ አለው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በግብጽ በፈርዖን ቤት ባሪያ ሳለ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ" ይላል (1ኛ ሳሙ.2፥27)። የእግዚአብሔር ሰው የተባለው ነቢይ ነው ወይስ ማነው?

✔️መልስ፦ ስሙ ከዚህ ያልተጻፈ ነቢይ ነው። መተርጉማን በሰው አምሳል ስለታየ ነው እንጂ መልአክ ነው ብለዋል።

▶️፭. "እነሆ፥ ለቤትህ ሽማግሌ እንዳይገኝ፥ ክንድህን የአባትህንም ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል። በእስራኤል በረከት ሁሉ፥ በማደሪያዬ ጠላትህን ታያለህ በቤትህም ለዘላለም ሽማግሌ አይገኝም። ከመሠዊያዬ ያልተቈረጠ ልጅህ ቢገኝ ዓይንህን ያፈዝዘዋል፥ ነፍስህንም ያሳዝናል ከቤትህም የሚወለዱ ሰዎች ሁሉ በጎልማስነት ይሞታሉ" ይላል (1ኛ ሳሙ.2፥31-33)። ክንድ የተባለ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ክንድ የተባሉ ወገኖች ናቸው። ክንድህን ማለት ወገንህን ማለት ነው፣ የአባትህንም ቤት ክንድ ማለት ደግሞ የአባትህን ወገኖች ማለት ነው። ዘርህን ወገንህን የማጠፋበት ቀን ይመጣል ለማለት የተነገረ ቃል ነው።

▶️፮. "ዔሊም በስፍራው ተኝቶ ሳለ፥ የእግዚአብሔር መብራት ገና ሳይጠፋ፥ ሳሙኤልም የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር መቅደስ ተኝቶ ሳለ" ይላል
(1ኛ ሳሙ.3፥3)። ታቦት ባለበት መቅደስ ውስጥ መተኛት በዛን ዘመን ሥርዓት ነበር? አሁን በዚህ ዘመን ላለን ሰዎችስ በሕንፃ ቤተ ክርስቲያን (በቅኔ ማኅሌት፣ በቅድስት) ውስጥ መተኛት ይፈቀዳል ወይ? አንዳንድ ካህናት ታቦቱ ባለበት መቅደስ ወስጥ ሳይቀር ገብተው የሚተኙ (የሚያንቀላፉ) አሉና ከዚህ ጥቅሰ አንፃር ሥርዓቱን ቢነግሩኝ።

✔️መልስ፦ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር መቅደስ ተኝቶ ነበር መባሉ ከቅጽሩ ውስጥ ሆኖ በዙሪያው ተኝቶ ነበር ለማለት ነው እንጂ በደብተራ ኦሪት ውስጥ ተኝቶ እንደነበረ የሚገልጽ አይደለም። በሕንፃ ቤተክርስቲያን ውስጥ መተኛት ፈጽሞ አይገባም። በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 1 ላይ እንደተገለጸው ቤተክርስቲያን የጸሎት ቤት ናት እንጂ የመኝታ ቤት አይደለችም። በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉም ንቁሕ ሆኖ ቃለ እግዚአብሔርን በንቃት መከታተል፣ በንቃት መጸለይ ይገባዋል እንጂ መተኛት ፈጽሞ አልተፈቀደም። መቅደስ ውስጥ ገብተው የሚተኙ ካሉም ስሕተት ነው መታረም አለበት።

▶️፯. "የውስጥ አካላቸውን በእባጭ መታ"
ይላልና ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የውስጥ አካላቸውን በእባጭ መታ ማለት ብልታቸውን (መሽኛቸውን) በእባጭ መታ ማለት ነው።

▶️፰. "በዚያንም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ክቡር ነበር፤ ራእይም አይገለጥም ነበር" ይላል። ራእይ አይገለጥም ሲል ምን ማለቱ ነው እግዚአብሔር ስዎችን እንዴት ነበር የሚያናግራቸው?

✔️መልስ፦ በዚያን ዘመን እግዚአብሔር ማንንም እንዳላናገረ የሚገልጽ ቃል ነው። በራእይም በሌላም መንገድ ለሕዝቡ አልተገለጠም አልተናገረም ነበር። ስለዚህ በዚያን ወቅት ያናገረው ሰው አልነበረም ማለት ነው።

▶️፱. "ከተሸከሙትም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በታላቅ ድንጋጤ በከተማዪቱ ላይ ኾነች። ከታናሹም እስከ ታላቁ ድረስ የከተማዪቱን ሰዎች መታ ዕባጭም መጣባቸው" ይላል። ማን ነበር ታቦቱን የሚሸከመው?

✔️መልስ፦ ታቦቷን በሠረገላ ስለነበር የሚያደርጓት በሠረገላ አድርገው በላሞች ነበር የሚያስጎትቷት እንጂ በተለየ ታቦተ እግዚአብሔርን የሚሸከም አልነበረም። ወደእስራኤል ስትመጣ ግን ሌዋውያን ይሸከሟት ነበር።

▶️፲. "እግዚአብሔርም ማሕፀኗን ዘግቶ ነበርና ጣውንቷ ታስቈጣት ታበሳጫትም ነበር" ይላል። ጣውንቷ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ጣውንት ማለት ጎባን ማለት ነው። ለምሳሌ አንዲት ሴት ያገባችውን ባል ሌላ ሴት ብታገባው አንዷ ለአንዷ ጎባን ናቸው ይባላል። የወንድም እንዲሁ ነው። አንዱ ያገባት የነበረችን ሴት ሌላ ሲያገባት ጎባን ሆኑ ይባላል።

▶️፲፩. ወራት የባሰባት ሴት ማለት ምን ለማለት ነው? እንዲሁም መካኗ ሰባት ወልዳለች ይላልና ሐና የወለደቻቸው ስንት ናቸው?

✔️መልስ፦ ወራት የባሰባት ሴት ማለት መከራ የተደራረበባትና በዚህም ምክንያት ያዘነች ሴት ማለት ነው። ሐና ከሳሙኤል በኋላ ሦስት ወንዶች ልጆችንና ሁለት ሴቶች ልጆችን ወልዳለች። ሳሙኤል ምስፍናን ከክህነት አንድ አድርጎ ይኖር ስለነበር ስለሁለት ተቆጥሮ ነው መካኗ ሐና ሰባት ወልዳለች የተባለው። በሌላ አገላለጽ ሰባት በዕብራውያን ፍጹም ተብሎ ይተረጎማል። ስለዚህ ፍጹም ደግ ልጅ ሳሙኤልን ወለድኩ ስትል ሐና መካኗ ሰባት ወልዳለች ብላ ስለራሷ ተናግራለች።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Nov, 13:40


ሰአሉ ለነ ሐና ወኢያቄም።
ዘወለድክምዋ ለማርያም ቤዛዊተ ኵሉ ዓለም።

እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ሐና ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Nov, 04:12


💟 ፩ኛ ሳሙኤል ክፍል ፩ 💟

💟ምዕራፍ 1፦
-ሕልቃና ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሠዋ ዘንድ ከከተማው ከአርማቴም በየዓመቱ ይወጣ እንደነበረ
-ሐና ልጅ ስላልነበራት ወደ እግዚአብሔር እንደጸለየችና ልጅ ከወለደች ለእግዚአብሔር እንደምትሰጠው መሳሏ
-ዔሊ ሐናን በሰላም ሂጂ የእስራኤል አምላክ ከአንቺ ጋር ይሁን ብሎ እንደመረቃት
-ሐና ወንድ ልጅ እንደወለደችና ስሙንም ሳሙኤል እንዳለችው

💟ምዕራፍ 2፦
-ሐና በጸሎቷ የእግዚአብሔርን ቅዱስነት፣ ጻድቅነት፣ ዐዋቂነት፣ ጸሎትን የሚሰማ መሆኑን፣ የጻድቃንን ዘመን እንደሚባርክ መግለጿ
-ሐና ኃይለኛ በኃይሉ፣ ሀብታም በሀብቱ፣ ጥበበኛ በጥበቡ መመካት እንደሌለበት በጸሎቷ መግለጿ
-የካህኑ የኤሊ ልጆች ክፉዎች እንደነበሩ መገለጹ
-ካህኑ ኤሊ ልጆቹ መበደላቸውን ሰምቶ አለመገሠጹ

💟ምዕራፍ 3፦
-ሳሙኤል እግዚአብሔርን ያገለግል እንደነበር
-እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንደጠራው
-ኤሊ ልጆቹን ባለመገሠጹ በእርሱና በልጆቹ መቅሠፍት እንደሚመጣ እግዚአብሔር ለሳሙኤል መግለጡ

💟ምዕራፍ 4፦
-ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን መግጠማቸውና ማሸነፋቸው
-ፍልስጥኤማውያን ታቦተ ጽዮንን መማረካቸው፣ አፍኒንና ፊንሐስን መግደላቸው
-ኤሊ የታቦተ ጽዮንን መማረክ ሲሰማ ከወንበሩ ወድቆ እንደሞተ

💟ምዕራፍ 5፦
-ፍልስጥኤማውያን ታቦተ ጽዮንን ማርከው ወደዳጎን ቤት ማስገባታቸውና በዳጎን አጠገብ ማስቀመጣቸው
-ዳጎንን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ማግኘታቸው፣ የዳጎን ራስ ሁለቱ እጆቹም ተቆርጠው እየራሳቸው ወድቀው እንደነበር
-በታቦተ ጽዮን ምክንያት የማረኳት ሀገር ሰዎች መታመማቸው


✝️የዕለቱ ጥያቄዎች✝️
፩. የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በደላቸው ምን ነበር?
ሀ. የእግዚአብሔርን ቍርባን ይንቁ ነበር
ለ. በደብተራ ኦሪት ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋር ይተኙ ነበር
ሐ. ሀ እና ለ
መ. መልስ የለም
፪. ታቦተ ጽዮንን ዳጎን ከተባለው ጣዖት ጎን ባስቀመጧት ጊዜ ምን ሆነ?
ሀ. ዳጎን በግንባሩ ወድቆ ተገኘ
ለ. የዳጎን እጆች ተቆርጠው ወድቀው ተገኙ
ሐ. የዳጎን ራስ ተቆርጦ ወድቆ ተገኘ
መ. ሁሉም
፫. የነቢዩ ሳሙኤል እናት ማን ትባላለች?
ሀ. ፍናና
ለ. ሐና
ሐ. ሕልቃና
መ. ኢካቦድ

https://youtu.be/agl5uXy6Tpc?si=zjp5zt5pNE2Gsp4G

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Nov, 04:01


🌹መዝሙረ ዳዊት ክፍል 6🌹
🌹ምዕራፍ ፫
ሰይጣን ያስጀመረውን አያስፈጽምም፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ዘውዴ አንተ ነህ፡፡ ዘውድ እንዲያስከብር የምታስከብረኝ አንተ ነህ፡፡ ልመናዬን ወደ እግዚአብሔር አቀረብኩ፡፡ (እርሱም) በሰማያዊት መቅደሱ ሆኖ ልመናዬን ሰማኝ፡፡
🌹ምዕራፍ ፬
ሳዶቅ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ ሰው ሙቶ መቃብር ከገባ በኋላ ፈርሶ በስብሶ ይቀራል ነፍሱም እንደ ጉም ሽንት በንና ትቀራለች የሚል ነው፡፡ የእርሱን ባህል የያዙ ሁሉ ሰዱቃውያን ተብለዋል፡፡ ማኒ ገንዘብ ጠፋበት ገንዘቡም አህያ ነው፡፡ በጾም በጸሎት በቀኖና ስኖር እንዴት የእኔ ገንዘብ ይጥፋ ብሎ በጸሎቱ ተመክቶ የሐሰት መሥዋዕት ሠውቶ ቀኖና ገባ፡፡ ገንዘቤ አህያዬ ቢገኝ ሠራዒ መጋቢ አለ እላለሁ ባይገኝ ግን የለም እላለሁ አለ፡፡ ጌታም በትሕትና ቢለምኑት ነው እንጂ በሐሰት ቢለምኑት አይሰማምና ይገኝ የነበረውን አጠፋበት ይቀርብ የነበረውን አራቀበት፡፡ ሱባኤው ሲፈጸም አልባቲ ሠራዒ ወመጋቢ ለዛቲ ዓለም፡፡ ለዚህች ዓለም ሠራዒ መጋቢ የላትም ብርሃናት በልማድ ይመላለሳሉ፣ አፍላጋት በልማድ ይፈሳሉ፣ ክረምትና በጋ ቀንና ሌሊት በልማድ ይፈራረቃሉ፣ ሰውም በልማድ ይወለዳል በልማድ ይሞታል ብሎ ተነሣ፡፡ መዝሙር 4ን ዳዊት የጻፈው ለማኒ ምላሽ ነው፡፡ የሚገባ ቁጣ ሕፃናት የተማሩትን እንዳይገድፉ፣ ከሓድያን ሃይማኖትን እንዳይነቅፉ መቆጣት ነው፡፡ የክርስቶስን ሥጋውን ደሙን ከመቀበላችን የተነሣ ሃይማኖት ፀናልን፣ ጸጋ ክብር ጸናልን፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Nov, 19:24


💖የጥያቄዎች መልስ ክፍል 47💖

▶️፩. "ወደዚህ ቅረቢ ምሳም ብዪ፥ እንጀራሽንም በሆምጣጤው አጥቅሺ" ይላል (ሩት 2፥14)። በሆምጣጤው ጥቀሽ ሲል ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሆምጣጤ የሚባለው መራራነት ያለው የከረመ ወይን ወይም የሚያሰክር መጠጥ ነው። በዚህ እያጣቀስሽ ብዪ ማለት ነው።

▶️፪. "ዋርሳ መሆኔ እውነት ነው፤ ነገር ግን ከኔ የሚቀርብ ዋርሳ አለ" ይላል (ሩት 3፥12)። ከእኔ የሚቀርብ ዋርሳ አለ ሲል ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ዋርሳ በእስራኤል ባህል መሠረት አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት የሟቹ ወንድሙ ወይንም የቅርብ ዘመዱ የሟቹን ሚስት አግብቶ በሕግ ለሟቹ ዘር የሚተካበት መንገድ ነው።

▶️፫. ሩት ፩፥፲፭ "ኑኃሚንም እነሆ ባልንጀራሽ ወደ ሕዝቧና ወደ አማልክቷ ተመለሰች አንችም ደግሞ ከባልንጀራሽ ጋራ ተመለሽ አለቻት" ይላል። ሩትና ዖርፋ ቀድሞ በእግዚአብሔር አያምኑም ነበር ማለት ነው? ዝቅ ብሎም ሩት ለኑኃሚን አምላክሽ አምላኬ ይሆናል ብላለች እንዲህስ ከሆነ ለምን ከማያምኑጋ ተጋቡ በመጀመርያ።

✔️መልስ፦ የአቤሜሌክ ልጆች ሩትንና ዖርፋን ሲያገቡ ወደአይሁዳዊ እምነት ቀይረዋቸው ይሁን አይሁን የተገለጸ ነገር አላገኘሁም። ባሎቻቸው ሲሞቱ ዖርፋ ከወገኖቿ ጋር ወደጣዖት አምልኮዋ እንደተመለሰች ተገልጿል። ሩት ግን አምላክሽ አምላኬ ይሆናል ብላ ኑኃሚንን ተከትላታለች። መጀመሪያውንም ሳያምኑ አግብተዋቸው ከሆነ ሕገ ኦሪትን ሽረው አግብተዋቸው ነበረ ማለት ነው። አሳምነው አግብተዋቸው ከሆነም መልካም አድርገው ነበረ ማለት ነው። ነገር ግን በዚህ ዙሪያ እንዴት እንደነበረ ተጨማሪ የተጻፈ ስላላገኘሁ አላውቀውም።

▶️፬. ሁሉን የሚችል አምላክ አስመርሮኛልና መራራ በሉኝ እንጅ ኑኃሚን አትበሉኝ ስትል። እግዚአብሔር ሰዎችን ያስመርራል?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ሰውን አያስመርርም። ነገር ግን ረድኤቱን ባይሰጥ ስለሆነ ይህ ሁሉ የደረሰባት ረድኤት መንሣቱን ከማስመረር ቆጥራ ኑኃሚን እንዲህ አለች። መራራ ሕይወትን ስለኖረች የራሷን መመረር ለመግለጽ የተናገረችው ነው።

▶️፭. "ኑኃሚንም ምራቶቿን ኺዱ ወደእናቶቻችኹም ቤት ተመለሱ በእኔና በሞቱት እንዳደረጋችኹ እግዚአብሔር ቸርነት ያድርግላችኹ" ይላል። ምንድን ነበር በእርሷ እና በሞቱት ያደረጉት?

✔️መልስ፦ ዖርፋና ሩት ኑኃሚን ቀሪ ልጆች እንደሌሏት እያወቁ ተከትለንሽ እንሄዳለን ማለታቸው ይህ ትልቅ የቸርነት ሥራ ነው። እናታቸውን መንከባከብ ለሞቱት ልጆቿም እንደማሰብ ስለተቆጠረላቸው ነው እንዲህ መባሉ።

▶️፮. "እነርሱም ተቀመጡ። ቦዔዝም የቅርብ ዘመዱን ከሞዐብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቢሜሌክን ጢንጦ ትሸጣለች" ይላል (ሩት 4፥3)። ጢንጦ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ጢንጦ የሚባለው የመሬት ርስት ድርሻ ነው።

▶️፯. “ቦዔዝም፦ እርሻውን ከኑኃሚን እጅ በምትገዛበት ቀን፥ ለሞተው በርስቱ ስሙን እንድታስነሣለት ከሟቹ ሚስት ከሞዓባዊቱ ከሩት ደግሞ ትገዛለህ አለ” ይላል (ሩት 4፥5)። ለሞተ ሰው በርስቱ ስሙን እንድታስነሣለት የሚለው ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በዋርሳ ሕግ የቅርብ ዘመድ የሟቹን ሚስት ካገባ በኋላ የሚወለደው ልጅ በሕግ በሞተው ሰው ይጠራል። ልጁን የወለደው ሌላ ሰው ቢሆንም ነገር ግን ወልዶ ስሙ እንዲነሣለት (እንዲታወስለት) አደረገ ማለት ነው።

▶️፰. "መቤዠት ብትወድድ ተቤዠው፤ መቤዠት ባትወድድ ግን ከአንተ በቀር ሌላ ወራሽ የለምና፥ እኔም ከአንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ አለው። እርሱም። እቤዠዋለሁ አለው" ይላል (ሩት 4፥4)። በዚህ ዐውድ "መቤዠት" ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ መቤዠት ማለት በዚህ አግባብ ሚስቱን አግብተህ ስለእርሱ ለእርሱ በእርሱ ስም የሚጠራ ልጅ ውለድለት ማለት ነው።

▶️፱. ሩት 4፥6 ላይ የራሴን ርስት እንዳላበላሽ ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ሁለት ሚስት አግብቼ ማስተዳደር እንዳያቅተኝ ለማለት የተናገረው ነው። ርስቴ ሲበዛ እንዳይጠፋብኝ ማለቱ ነው። ርስት ሲበዛ ይጠፋልና።

▶️፲. "እንግዲህ ታጠቢ፥ ተቀቢ፥ ልብስሽን ተላበሺ፥ ወደ አውድማውም ውረጂ፤ ነገር ግን መብሉንና መጠጡን እስኪጨርስ ድረስ ለሰውዮው አትታዪው" ይላል (ሩት 3፥3)። የዘመኑ የአለባበስና የቅባት አጠቃቀም ሁኔታ (አጠቃላይ ለማጌጥ የሚደረጉ ነገሮች) ከዚህ ጥቅስ አንፃር ተቀባይነት የለውም ወይ? ለማጌጥ መሆን ያለበትስ (የሚፈቀደው) እስከምን ድረስ ነው?

✔️መልስ፦ አለባበስ፣ መታጠብ፣ ሽቱ መቀባትና ሌሎችም ኃጢአት የሚሆኑት ለዝሙትና ለትዕቢት የሚጋብዙ፣ ሌላውን የሚያሰናክሉ ሆነው ከተገኙ ነው። ከዚህ መሠረታዊ ሐሳብ ሳናፈነግጥ ብንታጠብ፣ ብንለብስ ምንም ችግር የለውም። የዘመኑ አለባበስም መለካት ያለበት በዚህ ሂደት ነው። ለፍትወት የሚዳርግ ከሆነ መተው ይገባል።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Nov, 10:05


💙💙💙 የዕለቱ ጥያቄዎች 💙💙💙
፩. እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ቢበድሉ የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎም መታቸው። በኋላ እንደገና ወደእግዚአብሔር ሲጸልዩ እግዚአብሔር መስፍን አስነሥቶ የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን መስፍኑ ገደለላቸው። ይህ መስፍን ማን ነው?
ሀ. ጎቶንያል
ለ. አዶኒቤዜቅ
ሐ. ናዖድ💙
መ. አቢኒሔም
፪. ሲሣራን በካስማ (በመዶሻ) መትቶ የገደለው ማን ነው?
ሀ. ዲቦራ
ለ. ባርቅ
ሐ. ኢያዔል💙
መ. ሔቤር
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ዲቦራ ሕዝበ እስራኤልን ትገዛ ነበረ
ለ. ዲቦራ ነቢይት ነበረች
ሐ. የእስራኤል ልጆች ለፍርድ ወደ ዲቦራ ይመጡ ነበረ
መ. ሁሉም💙
፬. ጌዴዎን ምድያማውያንን ገጥሞ ድል ከማድረጉ በፊት ምን አደረገ?
ሀ. ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ
ለ. የጣዖት መሠዊያዎችን አፈራረሰ
ሐ. በተባዘተ የበግ ጸጉር ላይ ምልክትን ያደርግለት ዘንድ እግዚአብሔርን ጠየቀ
መ. ሁሉም💙
፭. ጌዴዎን ምድያማውያንን ያሸነፈ ከእርሱ ጋር ስንት ተዋጊዎችን ይዞ ሄዶ ነው?
ሀ. 22,000
ለ. 300💙
ሐ. 10,000
መ. 32,000
፮. እስራኤላውያን ጌዴዎን ከምድያማውያን ስላዳናቸው አንተም ልጅህም የልጅ ልጅህም ደግሞ ግዙን ሲሉት ምን ብሎ መለሰላቸው?
ሀ. እኔ እገዛችኋለሁ
ለ. እግዚአብሔር ይገዛችኋል💙
ሐ. ልጄ ይገዛችኋል
መ. የልጅ ልጄ ይገዛችኋል
፯. በጌዴዎን ልጅ በኢዮአታም ምሳሌ ዛፎች ተሰብስበው ንገሽልን ሲሏት እሺ ያለችው ማን ናት?
ሀ. ወይራ
ለ. በለስ
ሐ. ዶግ💙
መ. ዝግባ
፰. ሰባ ወንድሞቹን ገድሎ በእስራኤል ላይ ገዢ የሆነና በኋላ ሴት በወፍጮ መጅ አናቱን መትታው ቆስሎ ሳለ ጋሻ ዣግሬውን ሴት ገደለችው እንዳልባል ግደለኝ ያለ ማን ነው?
ሀ. ገዓል
ለ. አቤድ
ሐ. አቤሜሌክ💙
መ. ኢዮአታም
፱. ዮፍታሔ የአሞን ልጆችን ጦርነት ሊገጥም ሲሄድ በደህና ከተመለስኩ ከቤቴ ደጅ ወጥቶ የሚቀበለኝን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አደርገዋለሁ ብሎ ተስሎ ነበረ። በደህና ሲመለስ ከቤቱ ደጅ ወጥቶ የተቀበለውና ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያደረገው ማንን ነው?
ሀ. የሚወዳትን አንዲት ልጁን💙
ለ. ያሳደገውን በግ
ሐ. ወይፈኖችን
መ. የልጁን በጎች
፲. መልአከ እግዚአብሔር ለማኑሄ ሚስት ምን አላት?
ሀ. ሶምሶንን በጸነሰሽበት ወቅት የወይን ጠጅን አትጠጪ
ለ. ሶምሶን ሲወለድ በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስ
ሐ. ሶምሶን ከማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ እንደሚሆን ነገራት
መ. ሁሉም💙
፲፩. ስለሶምሶን ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የአንበሳ ደቦል ገድሎ በሌላ ጊዜ ከሞተው አንበሳ አፍ ማር አግኝቶ በልቷል
ለ. 300 ቀበሮዎችን ሰብስቦ በየመካከላቸው ችቦ አስሮ የፍልስጥኤማውያንን እህል አቃጥሏል
ሐ. በአህያ መንጋጋ 1000 ሰው ገድሎ በተጠማ ጊዜ ከአህያው መንጋጋ ውሃ ወጥቶለት ጠጥቶ ከጥሙ አረፏል
መ. ሁሉም💙
፲፪. የሶምሶን ኃይሉ የደከመና በፍልስጥኤማውያን እጅ የተያዘው መቼ ነው?
ሀ. በሰባት ባልደረቀ ርጥብ ጠፍር በታሰረ ጊዜ
ለ. በሰባት አዳዲስ ገመዶች በታሰረ ጊዜ
ሐ. ጸጉሩን በተላጨ ጊዜ💙
መ. የራሱን ጸጉር ከድር ጋር ጎንጉነው በችካል በተከሉት ጊዜ
፲፫. ፍልስጥኤማውያን ሶምሶንን ከያዙት በኋላ ምን አደረጉት
ሀ. ዓይኖቹን አወጡበት
ለ. ወደጋዛ አውርደው በእግር ብረት አሰሩት
ሐ. በግዞት አድርገው እህል ያስፈጩት ነበረ
መ. ሁሉም ዠ💙
፲፬. ሶምሶን ስለገደላቸው ሰዎች ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በሕይወቱ ከገደላቸው በሞቱ የገደላቸው ይበዛሉ💙
ለ. በሞቱ ከገደላቸው በሕይወቱ የገደላቸው ይበዛሉ
ሐ. በሞቱ የገደላቸውና በሕይወቱ የገደላቸው ብዛታቸው እኩል ነው
መ. በሕይወቱ የገደላቸው በሞቱ ከገደላቸው ይበዛሉ

፲፭. አቤሜሌክ ሚስቱን ኑኃሚንንና ልጆቹን ይዞ ወደ ሞዓብ የተሰደደ በምን ምክንያት ነበር?
ሀ. በሀገሩ ጦርነት ስለነበረ
ለ. በሀገሩ ረኀብ ስለሆነ💙
ሐ. በሀገሩ በሽታ ስለሆነ
መ. ሁሉም
፲፮. ኑኃሚን ወደሀገሯ ወደቤተልሔም ስትመለስ ሕዝብሽ ሕዝቤ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል ብላ የተከተለቻት የልጇ ሚስት ማን ናት?
ሀ. ሩት💙
ለ. ዖርፋ
ሐ. ራኬብ
መ. ራሔል
፲፯. ሩትን አግብቶ ኢዮቤድን የወለደ ማን ነው?
ሀ. አሚናዳብ
ለ. ቦዔዝ💙
ሐ. ዕሤይ
መ. ነአሶን

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Nov, 05:13


💛መጽሐፈ ሩት💛

💛ምዕራፍ 1፦
-መሳፍንት ይገዙ በነበረ ጊዜ በሀገሩ ላይ ረኀብ መሆኑ፣ አቤሜሌክም ከሚስቱና ከሁለት ልጆቹ ጋር ከይሁዳ ቤተልሔም ተነሥቶ ወደሞዓብ ምድር መሄዱ፣ የሚስቱ ስም ኑኃሚን እንደሆነ
-አቤሜሌክ በተሰደደበት ሀገር መሞቱ፣ ልጆቹ ከሞዓብ ሴቶችን አግብተው እንደኖሩና ትንሽ ቆይተው እንደሞቱ
-ኑኃሚን ከሁለት ምራቶቿ ጋር ብቻዋን መቅረቷ፣ በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቧን እንደጎበኘ መስማቷና ወደሀገሯ ለመመለስ መወሰኗ፣ ምራቶቿን ግን መርቃ ወደወገኖቻችሁ ተመለሱ ማለቷ፣ የአንዱ ልጇ ሚስት ዖርፋ ወደወገኖቿ መመለሷ
-ሩት ኑኃሚንን ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ ሕዝብሽ ሕዝቤ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል በምትሞችበትም እሞታለሁ ብላ ተከትላት መሄዷ

💛ምዕራፍ 2፦
-ሩት ከቦዔዝ እርሻ አጫጆች ኋላ ኋላ እየሄደች በእርሻ ውስጥ መቃረሟ፣ ቦዔዝም ቃርሚያ ለመቃረም ወደሌላ እርሻ አትሂጂ ከዚሁ ቃርሚ እንዳላት፣ ለኑኃሚን ያደረገችላትን መልካም ነገር ሰምቶ እንደመረቃት፣ የተጠበሰ እሸት እንደሰጣት፣ የቃረመችውን ወቅታ ወደኑኃሚን እንደወሰደችው

💛ምዕራፍ 3፦
-ኑኃሚን ሩትን ታጥበሽ፣ ተቀብተሽ ወደ ቦዔዝ አውድማ ውረጂ እንዳለቻት፣ ሩት አማቷ ያዘዘቻትን ሁሉ እንዳደረገች፣ ቦዔዝ ስድስት መሥፈሪያ ገብስ ሠፈሮ ለሩት እንደሰጣት

💛ምዕራፍ 4፦
-ቦዔዝ ሩትን እንዳገባት፣ ሩትም ከእርሱ ወንድ ልጅን እንደወለደችና ስሙንም ኢዮቤድ እንዳለችው፣ ኢዮቤድ የዳዊትን አባት እሴይን እንደወለደ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. አቤሜሌክ ሚስቱን ኑኃሚንንና ልጆቹን ይዞ ወደ ሞዓብ የተሰደደ በምን ምክንያት ነበር?
ሀ. በሀገሩ ጦርነት ስለነበረ
ለ. በሀገሩ ረኀብ ስለሆነ
ሐ. በሀገሩ በሽታ ስለሆነ
መ. ሁሉም
፪. ኑኃሚን ወደሀገሯ ወደቤተልሔም ስትመለስ ሕዝብሽ ሕዝቤ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል ብላ የተከተለቻት የልጇ ሚስት ማን ናት?
ሀ. ሩት
ለ. ዖርፋ
ሐ. ራኬብ
መ. ራሔል
፫. ሩትን አግብቶ ኢዮቤድን የወለደ ማን ነው?
ሀ. አሚናዳብ
ለ. ቦዔዝ
ሐ. እሴይ
መ. ነአሶን

https://youtu.be/T5X6QaQfO6k?si=Hvj6l_FtldcL3DuB

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Nov, 05:08


💙መዝሙረ ዳዊት ክፍል 5💙
💙መዝሙር ፪
ለምንት አንገለጉ አሕዛብ የሚለው ዓይነት ደረቅ ሐዲስ ይባላል፡፡ ለዳዊት የክርስቶስ ስቅለት ተገልጾለት የጻፈው ነው፡፡ ከንቱ ማለት አስበውት ሳይሠሩት የቀረ ነው፡፡ አብ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ብሎ የመሰከረለት ወልድን ዕሩቅ ብእሲ ማለት አብን ዕሩቅ ብእሲ ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ለወልድ ከመሰከረለት በኋላ ዕሩቅ ብእሲ ማለት መንፈስ ቅዱስንም የዕሩቅ ብእሲ ሕይወት ማለት ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፀወነ ሥጋ ፀወነ ነፍስ ፀወነ ጻድቃን ወኃጥኣን ናትና ጽዮን ትባላለች፡፡ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክ ወንጌልን ፍጽምት ሕግ በሉ፡፡ ክርስቶስን ዕሩቅ ብእሲ ወንጌልን ዲቃላ ሕግ አትበሉ፡፡ ለእግዚአብሔር በመፍራት በመንቀጥቀጥ ተገዙ፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Nov, 14:37


PDF
መጽሐፈ መሳፍንት ላይ ለጠየቃችኋቸው ጥያቄዎች መልሶች በPDF ቀጥሎ ለቅቄዋለሁ። ገብታችሁ አውርዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Nov, 12:58


ጓዴ
እንኳን አደረሰህ!
እንኳን ደስ አለህ!
መምህር እንዳልክ (ኢያሱ)። ለዚህች ልዩ ቀን ያደረሰህ እግዚአብሔር ይመስገን።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Nov, 12:47


✔️መልስ፦ ይህ ሽማግሌ ግብረ ሰዶማዊነትን በጣም እንደተጸየፈ ያስረዳል። የሀገሪቱ ሰዎቹ በወንዱ ላይ ግብረ ሰዶምን ሊፈጽሙበት ነበረ። ሽማግሌው ግን ይህ አይገባም ተፈጥሮም የሚነግረን ወንድ ለሴት ሴት ለወንድ ነው ስለዚህ ወንድ እንደመሆናችሁ ለእናንተ የሚገቡ ሴቶች ናቸው ብሎ ሴት ልጁንና ዕቁባቱን ሰጥቷቸዋል። እነርሱም ማደሪያቸውን አመንዝረውባት ለሞት ተዳርጋለች።

▶️፲፬. ጋለሞታ እና ዕቁባት ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ጋለሞታ ማለት አግብታ የፈታች ወይም ባሏ የሞተባት ሴት ናት። ዕቁባት ማለት ደግሞ በኦሪት ዘመን አንድ ባል ከሕጋዊ ሚስቱ በተጨማሪ እንደሚስት ሆነው የሚያገለግሉት ሴቶች ናቸው።

▶️፲፭. "እርሱም እስራኤልን 20 ዓመት ገዛቸው" ይላል እና ታሪኩ ሹመት ያልነበረው እና በግሉ መንቀሳቀስ የነበረ እንጅ ሲገዛ እነርሱም ሲገዙ አልታየም እና ለምን ገዛቸው ተባለ?

✔️መልስ፦ የአገዛዙ ሁኔታ እኛ ከለመድነው ስለተለየ እንጂ እንደተባለው ሶምሶን እስራኤላውያንን 20 ዓመት ገዝቷቸዋል። የአንድ ገዢ ዋና ሥራ ሀገሩን ከጠላት መጠበቅ ነው። ሶምሶንም የእስራኤልን ጠላቶች ሲፋለም የኖረ ገዢ ነው።

▶️፲፮. "ልባቸውንም ደስ ባለው ጊዜ በፊታችን እንዲጫወት ሶምሶንን ጥሩት አሉ። ሶምሶንንም ከግዞት ቤት ጠሩት በፊታቸውም ተጫወተ ተዘባበቱበትም በምሰሶና በምሰሶም መካከል አቆሙት" ይላል። ከማን ጋራ እና ምን ዓይነት ጨዋታ ነው?

✔️መልስ፦ ሶምሶን ለፍልስጥኤማውያን ጨዋታ ያሳያቸው ነበረ ወይም ይዘፍንላቸው ነበረ ለማለት ነው። ተማራኪ እንደመሆኑ ማራኪዎቹ አድርግ ያሉትን ያደርግ እንደነበረና ማራኪዎቹ ይዘባበቱበት እንደነበረ የሚገልጽ ቃል ነው።

▶️፲፯. እስራኤላውያን ምንድን ነው እንደዚህ ከጣዖት ጋር ያጣበቃቸው? ማለት ጣዖቱ ፍላጎታቸውን ይሰጣቸው ነበር?

✔️መልስ፦ የእስራኤል ሕዝብ አሽቸጋሪ ሕዝብ ነበረ። ውለታ የዋለላቸውን፣ ከጽኑ አገዛዝ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን ረስተው ምንም ነገር የማያደርግላቸውን የተጠረበ ጣዖትን እያመለኩ በተደጋጋሚ እግዚአብሔርን ሲያሳዝኑት ኖረዋል። ከእግዚአብሔር ያጡት ነገርም የለም አልነበረም። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ዙሪያቸውን ያሉ አሕዛብ ጣዖት ያመልኩ ስለነበረ ይህ ተጽእኖ እያሳደረባቸውም ጭምር ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Nov, 12:47


💖የጥያቄዎች መልስ ክፍል 46💖

▶️፩."በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው በዙ" ይላል (መሳ.16፥30)። ሶምሶን የጌታቻን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ ሲነገር እሰማለሁና ከዚህ ጥቅስ አንጻር ቢያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ሶምሶን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ከዚህ በፊት ግን መረዳት ያለብን ምሳሌ ከሚመሰልለት ያነሰ መሆኑን ነው። ይህንን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ተናግሮታል። የሀገራችን ሊቃውንትም ይህንን ለማስገንዘብ ምሳሌን ዘየሐጽጽ ብለው ይቀጽሉለታል። አንድ ነገር ለአንድ ነገር በጥቂት ነገር ስለተመሳሰለ ምሳሌ ሊመሰል ይችላል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ምድር በሥጋ እየተመላለሰ ሲያስተምር አጋንንትን ከሰዎች ያስለቅቃቸው ነበረ። ነገር ግን በዚህች ምድር ሲመላለስ ካጠፋቸው አጋንንት ይልቅ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ያጠፋቸው አጋንንት ይበዛሉ። ሶምሶንም በሕይወተ ሥጋ ሳለ ካጠፋቸው ሰዎች ይልቅ በሞቱ ያጠፋቸው ይበዛሉ። በሌላ መልኩ ሶምሶን ከሞተ አንበሳ አፍ ሳይጸየፍ ማር በልቷል። ከአህያ መንጋጋ የመነጨ ውሃንም ሳይጸየፍ ጠጥቷል። ጌታም የሰውን ሥጋ ሳይጸየፍ ተዋሕዶ ሰውን አድኖታል። በዚህና በዚህ ሶምሶን የጌታ ምሳሌ ነው ይባላል።

▶️፪. "የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ እግዚአብሔርንም ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋራ ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ውጡ አለ" ይላል። ግን እግዚአብሔር አዟቸው ከሆነ እንዴት ተሸነፉ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በሚያውቀው ከእነርሱም መሞት የነበረባቸው ክፉዎች ሰዎች ስለነበሩ እንዲሸነፉ አድርጓቸዋል። ከእነርሱ መሞት የነበረባቸው ሰዎች ከሞቱ በኋላ በሦስተኛው ግጥሚያ እንዲያሸንፉ አድርጓል።

▶️፫. “የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጌ ከእጄ ስለ ልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ” ይላል (መሳ.17፥3)። ይህች ሴት ጣዖት የምታመልክ ናት ወይስ እግዚአብሔርን?

✔️መልስ፦ ይህች ሴት ጣዖት አምላኪ ናት። ጣዖቷን እግዚአብሔር እያለችው ነው። ነገር ግን እርሷ ጣዖቷን እግዚአብሔር ወይም አምላክ ብትለውም ከወርቅ ጥፍጥፍ የሠራችው ጣዖት ነው።

▶️፬. “ሰውየውም ሚካ የአምላክ ቤት ነበረው” ይልና “ሚካም ሌዋዊ ካህን ስለ ሆነልኝ እግዚአብሔር መልካም እንዲሠራልኝ አሁን አውቃለሁ አለ” ይላል (መሳ.17፥13)። ሚካ እግዚአብሔርን ያመልክ ነበር ወይ?

✔️መልስ፦ መልሱ ከዚህ ከፍ ብሎ እንደተመለሰው ጥያቄ ነው። የሚያመልኩትን ጣዖት በራሳቸው እግዚአብሔር እያሉት ነው እንጂ ሚካም ያመልክ የነበረው ጣዖትን ነበረ። ሌዋዊውም የጣዖት አገልጋይ ሆኖ ክብሩን አዋረደ እንጂ የጣዖትም የእግዚአብሔርም አገልጋይ አልሆነም። ሚካ የጣዖት አገልጋይ ካህን ሆነ እንጂ።

▶️፭. “እስከዚያም ቀን ድረስ ለዳን ነገድ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልደረሳቸውም ነበርና በዚያ ዘመን የሚቀመጡባት ርስት ይሹ ነበር” ይላል (መሳ.18፥1)። ለሁሉም እስራኤላውያን ነገዶች ርስት ደርሷቸው ሳለ ለምን ለዳን ነገዶች ርስት አልደረሳቸውም ተባለ?

✔️መልስ፦ የዳን ወገኖች ከነገደ ሮቤል ጋር በዮርዳኖስ ማዶ መውረሳቸውን መጽሐፈ ኢያሱን ስንማማር አይተናል። ነገር ግን የወረሱት ብዙ ስላልነበረ ሌላ ተጨማሪ ርስት መፈለጋቸውን ለመግለጽ ከዚህ ላይ ርስት አልደረሳቸውም ተብሎ ተገልጿል።

▶️፮. አንድ ሰው ሌዋዊ ሆኖ እንዴት ከይሁዳ ነገድ ሊሆን ይችላል? (መሳ.17፥7)።

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት ክህነት ከነገደ ሌዊ ለሚወለዱ ሰዎች እንዲሠጥ ሥርዓት ተሠርቷል። ከዚህ ላይ የተጠቀሰው ሰውም ካህነ ጣዖት እንጂ ካህነ እግዚአብሔር አይደለም። ካህንን ሌዋዊ ማለት ልማድ ስለሆነ ምንም እንኳ የጣዖት አገልጋይ ካህን ቢሆንም ሌዋዊ ተብሏል።

▶️፯. መሳ.21፥14 "በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ተመለሱ፤ ከኢያቢስ ገለዓድም ሴቶች ያዳኗቸውን ሴቶች አገቧቸው። ነገር ግን የሚበቁ ሴቶች አላገኙም" ይላል። ካገቧቸው በኋላ እንዴት ነው የሚበቁ አልተገኙም የሚባለው?

✔️መልስ፦ የሚበቁ ሴቶች አላገኙም ማለት ወንዶች በዝተው ሴቶች አንሰው ስለነበረ። ከተጋቡ በኋላ ሴቶች አንሰው ሳያገቡ የቀሩ ወንዶች ነበሩ ለማለት ነው።

▶️፰. መሳ.16፥18 "ደሊላም የልቡን ሁሉ እንደ ገለጠላት ባየች ጊዜ፦ የልቡን ሁሉ ገልጦልኛልና ይህን ጊዜ ደግሞ ኑ ብላ ላከችና የፍልስጥኤማውያንን መኳንንት ጠራች። የፍልስጥኤማውያን መኳንንትም ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርሷ መጡ" ይላል። እንደበፊቱ እንዳላታለላት በምን እርግጠኛ ሆና ነው የልቡን ነግሮኛል ያለችው?

✔️መልስ፦ ይህንን የምታውቀው ደሊላ ናት። ደሊላ በምን ከልቡ እንደነገራት እንዳወቀች ተጽፎ አላገኘሁም አላውቀውም።

▶️፱. መሳ.18፥5 "እነርሱም፦ የምንሄድበት መንገድ የቀና መሆኑን እናውቅ ዘንድ እባክህ እግዚአብሔርን ጠይቅልን አሉት" ይላል። እነርሱ ስለምን ጣዖትን ታገለግላለህ ብለው መገሠጽ እያለባቸው እንዴት ጭራሽ ከካህነ ጣዖት እግዚአብሔርን እንዲጠይቅላቸው ያስባሉ?

✔️መልስ፦ ጣዖታቸውን እንደ አምላክ ስላዩት እግዚአብሔር አሉት እንጂ ከዚህ የተጠቀሰው ዋናው ፈጣሪ እግዚአብሔር አይደለም። አለመሆኑም ዝቅ ብሎ የጣዖት ዕቃዎችን ወሰዱ ተብሎ በመገለጹ ይታወቃል። እነርሱም በጣዖት የሚተማመኑ ነበሩ። ሰውየውም የጣዖት አገልጋይ ነበረ።

▶️፲. መሳ.19፥29 "ወደ ቤቱም በመጣ ጊዜ ካራ አነሣ፥ ዕቁባቱንም ይዞ ከአጥንቶቿ መለያያ ላይ ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ሰደደ" ይላል። ሳይቆርጥ ለአንዱ ነገድ ቢልክ ዜናው በ12ቱ ነገድ ይሠማ የለምን ለምን ከ12 ቆራርጦ ለ12 ነገድ መላክ አስፈለገ?

✔️መልስ፦ ለሁሉም አጽንዖት ለመስጠትና በእስራኤል ሀገር እንዲህ ያለ ግፍ ተደረገ ለማለት ለ12 ቆራርጦ ለእያንዳንዱ ነገድ ልኮታል። ለአንዱ ነገድ ከመላክ ለ12 ነገድ መላክ ለመልእክቱ የበለጠ ጉልበት ይሰጠዋልና ነው።

▶️፲፩. ሶምሶን እንዴት አራት ጊዜ ተታለለ? የእግዚአብሔር እቅድ ወይስ የእርሱ እንዝህላልነት?

✔️መልስ፦ በሰዎች መታለል ውስጥ የእግዚአብሔር እቅድ የለም። የእግዚአብሔር እቅድ ሁሉ መልካም ነገርና ጽድቅ ነው። ስለዚህ ሶምሶን የተሰጠውን ነጻ ፈቃድ ተጠቅሞ በራሱ እንዝህላልነት አራት ጊዜ ተሸወደ ተታለለ ማለት ነው። እንጂ እግዚአብሔር እንዲታለል አላደረገውም።

▶️፲፪. "ይህን ብር የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጌ ከእጄ ስለ ልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም  ለአንተ እመልሰዋለሁ አለች" ይላል (መሳ.17፥3)። ምስል ብሎ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ ይላልና ግልፅ  ቢያደርጉልኝ።

✔️መልስ፦ ጣዖቷን እንደ አምላክ ስላየችው እግዚአብሔር አለችው እንጂ ልጅቷ የሠራቸው ምስል ጣዖት ነው።

▶️፲፫. "ድንግል ልጄና የእርሱም ዕቁባት፥ እነሆ፥ አሉ፥ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዷቸው እንደ ወደዳችሁም አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አታድርጉ አላቸው" ይላል (መሳ.19፥24)። ሽማግሌው ሰውየውን ብቻ አድኖ ዕቁባቱን ግን አሳልፎ የሰጣትና ለሞት የዳረጋት ለምንድን ነው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Nov, 06:57


💟መጽሐፈ መሳፍንት ክፍል ፬💟

💟ምዕራፍ 16፦
-ሶምሶን ደሊላን እንዳገባ
-ፍልስጥኤማውያን ሶምሶን በምን እንደሚሸነፍ ጠይቃ እንድትነግራቸው ደሊላን ገንዘብ እንሰጥሻለን ብለው መጠየቃቸው
-ሶምሶን ለደሊላ ስለኃይሉ ሦስት ጊዜ ዋሽቶ እንደነገራት፣ በአራተኛው ግን የኃይሉን ምንጭ በትክክል እንደነገራትና ጸጉሬ ከተላጨ ኃይሌን አጣለሁ እንዳላት፣ አስተኝታም ጸጉሩን እንዳስላጨችውና የእርሱም ኃይሉ እንደደከመ
-ፍልስጥኤማውያን ሶምሶንን ይዘው ዓይኑን እንዳወጡትና በእግር ብረት እንዳሠሩት፣ በግዞት ሆኖሞ እህል ይፈጭ እንደነበረ
-ፍልስጥኤማውያን ለጣዖታቸው መሥዋዕት ሊሠዉ መሄዳቸው፣ ሶምሶንን ጠርተው እንደተዘባበቱበት፣ የሶምሶን ጸጉሩ እንደገና አድጎ ስለነበረ የሚመራውን ሰው እንድደገፋቸው ምሰሶዎች ጋር ውሰደኝ ማለቱ
-ሶምሶን ጸልዮ ምሰሶዎቹን በሙሉ ኃይሉ ቢገፋቸው ቤቱ በቤቱ ውስጥ ባሉ ሰዎች ሁሉ መውደቁና ሁሉም መሞታቸው ሶምሶንም መሞቱ
-ሶሞሶን በሕይወቱ ከገደላቸው በሞቱ የገደላቸው መብዛታቸው

💟ምዕራፍ 17፦
-በኤፍሬም ሀገር ሚካ የተባለ ሰው ጣዖት እንዳስቀረጸና አንዱን ሌዋዊም የጣዖቱ ካህን እንዳደረገው

💟ምዕራፍ 18፦
-የዳን ነገድ የተቀረጸውን የሚካን ጣዖት ለራሳቸው እንዳቆሙ

💟ምዕራፍ 19፦
-በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ማዶ የተቀመጠ አንድ ሌዋዊ እንደነበረና ከይሁዳ ቤተልሐም ሚስት እንዳገባ
-ይህ ሌዋዊ ከሚስቱ ጋር እንግዳ ሆኖ ከአንድ ሽማግሌ ቤት እንዳደረ፣ የኢያቡሴዎን ሰዎች ሽማግሌውን ሰው ወደቤትህ የገባውን ሰው እንድረስበት አውጣልን እንዳሉት፣ ሌዋዊውም ዕቅብቱን እንዳወጣላቸውና እንዳዋረዷት፣ ሌሊቱን ሙሉ እስኪነጋ ድረስ እንዳመነዘሩባት፣ ጠዋት ሞታ መገኘቷ፣ ሌዋዊውም በሕይወት ያለች መስሎት "ተነሺ እንሂድ" ማለቱ፣ መሞቷን ሲያውቅ ሰውነቷን ለአሥራ ሁለት ቆራርጦ ፍረዱኝ ብሎ ለእያንዳንዱ ነገድ መላኩ

💟ምዕራፍ 20፦
-የእስራኤል ልጆች ሁሉ ከነገደ ብንያም ጋር መግጠማቸው፣ ለመጀመሪያ ጊዜና ደግመውም ለሁለተኛ ጊዜ ነገደ ብንያም ከእስራኤላውያን ብዙ እንደገደሉ፣ በሦስተኛው ነገደ ብንያም እንደተሸነፈ

💟ምዕራፍ 21፦
-በእስራኤል ንጉሥ እንዳልነበረና ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ እንደነበረ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. የሶምሶን ኃይሉ የደከመና በፍልስጥኤማውያን እጅ የተያዘው መቼ ነው?
ሀ. በሰባት ባልደረቀ ርጥብ ጠፍር በታሰረ ጊዜ
ለ. በሰባት አዳዲስ ገመዶች በታሰረ ጊዜ
ሐ. ጸጉሩን በተላጨ ጊዜ
መ. የራሱን ጸጉር ከድር ጋር ጎንጉነው በችካል በተከሉት ጊዜ
፪. ፍልስጥኤማውያን ሶምሶንን ከያዙት በኋላ ምን አደረጉት
ሀ. ዓይኖቹን አወጡበት
ለ. ወደጋዛ አውርደው በእግር ብረት አሰሩት
ሐ. በግዞት አድርገው እህል ያስፈጩት ነበረ
መ. ሁሉም
፫. ሶምሶን ስለገደላቸው ሰዎች ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በሕይወቱ ከገደላቸው በሞቱ የገደላቸው ይበዛሉ
ለ. በሞቱ ከገደላቸው በሕይወቱ የገደላቸው ይበዛሉ
ሐ. በሞቱ የገደላቸውና በሕይወቱ የገደላቸው ብዛታቸው እኩል ነው
መ. በሕይወቱ የገደላቸው በሞቱ ከገደላቸው ይበዛሉ

https://youtu.be/g8nqjr4WdxQ?si=Gi0zYhN_so5rqquc

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Nov, 06:53


💙መዝሙረ ዳዊት ክፍል 4💙
💙መዝሙር ፩
በረሲዓን ምክር ጸንቶ ያልኖረ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ ረሲዓን የሚላቸው እንጨት ጠርበው ድንጊያ አለዝበው የሚያመልኩ ናቸው፡፡ በኃጥኣን ጎዳና ያልሄደ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ ኃጥኣን የሚላቸው ሠርቀው ቀምተው አሥረው ፈትተው ቋንጃ ቆርጠው ነፍስ ገድለው የሚኖሩ ናቸው፡፡ በመስተሳልቃን አደባባይ ያልተቀመጠ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ መስተሳልቃን የሚላቸው ዓይኑ በፈረጠ እጅ እግሩ በተቆረጠ የሚዘብቱ ናቸው፡፡ ፈቃዱ ሕገ እግዚአብሔር የሆነለት ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ ሕጉንም በመዓልት በሌሊት የሚመለከት ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ እንዲህ ያለው ሰው በፈሳሽ ውሃ እንደተተከለች ዕፅ ይሆናል፡፡ ሰውነቱ በረድኤተ እግዚአብሔር ተጠብቆለት የሚኖር ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ የጀመረውን የሚፈጽም ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ መፈጸም እንጂ መጀመር አያስመሰግንምና፡፡ ኃጥኣን ግን ነፋስ ከመሬት እንደሚጠርገው ትቢያ ናቸው፡፡ ዕፀ ከንቱ በነግህ ትበቅላለች በሠለስት ታብባለች በቀትር ታፈራለች በተስዓት ትደርቃለች በሠርክ ኳኰርኳ ብላ ትወድቃለች፡፡ ዕፀ ከንቱ የሰው ምሳሌ ናት፡፡ ኃጥኣን ጻድቃን በመከሯቸው ምክር ጸንተው አይኖሩም፡፡ የጻድቃን ምክር ፍቅር፣ ትሕትና፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ሰጊድ፣ ምጽዋት ነው፡፡ የኃጥኣን ምክር ስርቆት፣ መግደል፣ ዝሙት ነው፡፡ እግዚአብሔር የጻድቃንን ሥራ ይወዳል፡፡ የኃጥኣንን ሥራ ግን አይወድም፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Nov, 04:32


💜መጽሐፈ መሳፍንት ክፍል ፪💜

💜ምዕራፍ 6፦
-የእስራኤል ልጆች እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ መሥራታቸውና በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በምድያም እጅ አሳልፎ እንደሰጣቸው
-የእስራኤል ልጆች መከራ ስለደረሰባቸው ወደእግዚአብሔር መጮኻቸው፣ እግዚአብሔርም በጌዴዎን አማካኝነት እስራኤልን መርዳቱ
-ጌዴዎን መሥዋዕትን መሠዋቱ፣ የሠዋበትን ቦታም የእግዚአብሔር ሰላም እንዳለው፣ የጣዖታትን መሠዊያዎች እንዳፈረሰ
-ጌዴዎን በአውድማ ላይ የተባዘተ የበግ ጸጉር እንዳኖረ፣ እግዚአብሔር በመጀመሪያ በተባዘተው ጸጉር ብቻ ጠል ማውረዱ፣ ቀጥሎ በሌላው ጠል አውርዶ በተባዘተው የበግ ጸጉር ጠል አለማውረዱ

💜ምዕራፍ 7፦
-ጌዴዎን የፈራ ይመለስ ብሎ አዋጅ መንገሩ
-ጌዴዎን ውሻ እንደሚጠጣ ውሃ በምላሱ የሚጠጣውንና በጉልበቱ ተንበርክኮ የሚጠጣውን ወደጦር ሜዳ እንዳልወሰደው
-ጌዴዎን 300 ሰዎችን ይዞ ምድያማውያንን ድል እንዳደረገ
- ጌዴዎን ኃይል የእግዚአብሔር ሰይፍ የጌዴዎን በሉ እንዳለ

💜ምዕራፍ 8፦
-የኤፍሬም ሰዎች ለጦርነት ለምን አልጠራህንም ብለው ጌዴዎንን መጠየቃቸው
-እስራኤላውያን ጌዴዎንን ከምድያም እጅ አድነህናልና አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም ደግሞ ግዙን ማለታቸው። ጌዴዎን ግን እኔ አልገዛችሁም እግዚአብሔር ይገዛችኋል እንጂ እንዳላቸው።
-በጌዴዎን ዘመን ምድሪቱ (እስራኤል) አርባ ዓመት እንዳረፈች
-ጌዴዎን ሸምግሎ እንዳረፈ
-ጌዴዎን ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን ጣዖት ማምለካቸው

💜ምዕራፍ 9፦
-የጌዴዎን ልጅ አቤሜሌክ ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ እንደገደላቸው
-የጌዴዎን ትንሹ ልጁ ኢዮአታም በገሪዛን ተራራ ላይ ቆሞ እንዳለቀሰ፥ ዛፎች ተሰብስበው ወይራን ንገሽልን አሏት ከሚለው ጀምሮ ዛፎች ዶግን ንገሽልን አሏት እስከሚለው ድረስ ያለውን መስሎ እንደተናገረ
-የሰቂማ ሰዎች አቤሜሌክን እንደከዱት
-አቤሜሌክን አንዲት ሴት በወፍጮ መጅ አናቱን እንደመታችው፣ ሴት ገደለችው እንዳይባልም ጋሻ ዣግሬውን በሰይፍ ግደለኝ ብሎት በሰይፍ እንደሞተ

💜ምዕራፍ 10፦
-ከአቤሜሌክ ሞት በኋላ ቶላ እስራኤልን ለማዳን እንደተነሣ፣ ከእርሱ በኋላ ኢያዕር እንደተነሣ
-የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደገና ስለበደሉ እግዚአብሔር ለፍልስጤማውያን አሳልፎ እንደሰጣቸው


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ጌዴዎን ምድያማውያንን ገጥሞ ድል ከማድረጉ በፊት ምን አደረገ?
ሀ. ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ
ለ. የጣዖት መሠዊያዎችን አፈራረሰ
ሐ. በተባዘተ የበግ ጸጉር ላይ ምልክትን ያደርግለት ዘንድ እግዚአብሔርን ጠየቀ
መ. ሁሉም
፪. ጌዴዎን ምድያማውያንን ያሸነፈ ከእርሱ ጋር ስንት ተዋጊዎችን ይዞ ሄዶ ነው?
ሀ. 22,000
ለ. 300
ሐ. 10,000
መ. 32,000
፫. እስራኤላውያን ጌዴዎን ከምድያማውያን ስላዳናቸው አንተም ልጅህም የልጅ ልጅህም ደግሞ ግዙን ሲሉት ምን ብሎ መለሰላቸው?
ሀ. እኔ እገዛችኋለሁ
ለ. እግዚአብሔር ይገዛችኋል
ሐ. ልጄ ይገዛችኋል
መ. የልጅ ልጄ ይገዛችኋል
፬. በጌዴዎን ልጅ በኢዮአታም ምሳሌ ዛፎች ተሰብስበው ንገሽልን ሲሏት እሺ ያለችው ማን ናት?
ሀ. ወይራ
ለ. በለስ
ሐ. ዶግ
መ. ዝግባ
፭. ሰባ ወንድሞቹን ገድሎ በእስራኤል ላይ ገዢ የሆነና በኋላ ሴት በወፍጮ መጅ አናቱን መትታው ቆስሎ ሳለ ጋሻ ዣግሬውን ሴት ገደለችው እንዳልባል ግደለኝ ያለ ማን ነው?
ሀ. ገዓል
ለ. አቤድ
ሐ. አቤሜሌክ
መ. ኢዮአታም

https://youtu.be/5HtpnO5QJCo?si=CfGBlbqDrbt63qDc

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Nov, 04:24


💙መዝሙረ ዳዊት ክፍል 2💙
ዳዊት መዝሙሩን በዋናነት ስለዐሥር ነገሮች ዘምሮታል፡፡ እነዚህም፦
፩.ተግሣጽ ለኵሉ (መዝ.1፣1)
፪.በእንተ ክርስቶስ (መዝ.2፣1)
፫.በእንተ ርእሱ (መዝ.3፣1)
፬.በእንተ መነናውያን (መዝ.4፣1)
፭.በእንተ ትሩፋን (መዝ.5፣1)
፮.በእንተ ሕዝቅያስ (መዝ.13፣1)
፯.በእንተ ኤርምያስ (መዝ.34፣1)
፰.በእንተ መቃብያን (መዝ.43፣1)
፱.በእንተ ዘለፋ ካህናት (መዝ.49፣1)
፲.በእንተ ሰሎሞን ወልዱ (መዝ.71፣1)
ናቸው። በእነዚህ በአሥሩ አርእስት ደግሞ አምስት ነገር አለባቸው፡፡ እነዚህም፦
፩.ተግሣጽ ለኵሉ (መዝ.1)
፪.ምዕዳን (መዝ.37)
፫.ጸሎት (መዝ.101)
፬.ትንቢት (መዝ.109)
፭.አኰቴት (መዝ.29) ናቸው፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Nov, 17:17


💖የጥያቄዎች መልስ ክፍል 43💖

▶️፩. እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ስለበደሉ ነበር በባርነት እንዲኖሩ የተደረጉት። ይሁዳ ሲነሣ ንስሓ እንደገቡ አልተጻፈም እና እግዚአብሔር እንዴት ረዳቸው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ረድኤት ለሚያስፈልገው ረድኤትን ይሰጣል። ደግሞም ሁሉም ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱስ ስላልተጻፈ ንስሓ ገብተው ነበር ወይም ንስሓ አልገቡም ነበር ለማለት አይቻልም። እግዚአብሔር ግን ረድኤት እንደሚያስፈልጋቸው አውቆ ነገደ ይሁዳን አስነሥቶ ረድቷቸዋል።

▶️፪. ከዚህ ቀደም አንድን ከተማ ሲይዙ ማንንም ሳያስቀሩ ይገድሉ ያጠፉ ነበር። በዚህ ምዕራፍ ግን አላጠፉም ምክንያቱ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አጥፉ የተባሉትን አጥፍተዋል። ግደሉ የተባሉትንም ገድለዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ባወቀ የሚጠፉትን እንዲጠፉ ካደረገ በኋላ ሌሎቹን ለጊዜው እንዲድኑ አድርጓቸዋል።

▶️፫. "በዚያም ወራት ነብይቱ የለፊዶ ሚስት ዲቦራ እስራኤልን ትገዛ ነበር" ይላል (መሳ.4፥4)። እስካሁን ሴት መሪ አልነበራቸውም እንደ ንግሥት ሆና ነው? ይህን ቃል ቢያብራሩልኝ። የመጀመሪያዋ እስራኤልን የገዛች ሴት ንግሥት ነች ወይስ ከዚያ በፊት ሌላ ንግሥት ነበረች?

✔️መልስ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ባየነው ታሪክ አዎ እስካሁን ሴት መስፍን ሆና እንደገዛች አልተገለጸም ነበረ። ነገር ግን የዓለም ታሪክ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ የተጻፈው ስላልሆነና ያልተጻፉ ብዙ ጉዳዮች ስላሉ ከዚያ በፊት አልነበረም ብሎ መደምደም አይቻልም። ትገዛ ነበረ መባሉ ፍርድ ትሰጥ ነበረ ማለት እንደሆነ ተጽፏል። ስለዚህ የመሪነት ሚና እንደነበራት የሚገልጽ ቃል ነው።

▶️፬. መሳ.4፥4 "በዚያም ወራት ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ እስራኤልን ትገዛቸው ነበረች" ይላል። ነብይነት ለሴትም ለወንድም የተሰጠ ነው ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ እግዚአብሔር በማንኛውም ሰው ላይ ሀብተ ትንቢትን አሳድሮ ያስተምራል። ስለዚህ ሴት ሆነው ነቢያት የነበሩ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጹ አሉ። በጌታ ልደት ዘመንም ነቢይት ሐና የምትባል እንደነበረች ተገልጿል።

▶️፭. እግዚአብሔር እስራኤላውያን በጊዜው እያስከፉት ጣዖት እያመለኩ ተቆጥቶ መልሶ ይቅር የሚላቸውን ንስሓ መግባትን እና ታጋሽነቱን ለማስተማር ነው?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ይቅር ባይነቱና ትዕግሥቱ የባሕርይው ነው። እስራኤላውያን ግን አስቸጋሪ ሕዝብ ስለነበሩ ነጻ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው ይበድሉ ነበረ። እንደገና መከራ ሲበዛባቸው ይቅርታን ይለሞናሉ። እግዚአብሔርም ቸር ስለሆነ ይቅር ይላቸው ነበረ።

▶️፮. መሳ.፪፥፬-፭ "የእግዚአብሔር መልአክ ይህን ቃል ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ድምፃቸውን አንሥተው አለቀሱ። የዚያም ስፍራ ስም መካነ ብካይ ተብሎ ተጠራ ይላል መካነ ብካይ ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ መካነ ብካይ የግእዝ ቃል ነው። የልቅሶ ቦታ ማለት ነው።

▶️፯. መሳ.2፥11-13 "የእስራኤል ልጆች እግዚአብሔርን ትተው በዓሊምን እና አስታሮትን አመለኩ" ይላል። በዓሊም እና አስታሮትን ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ በዓሊምና አስታሮት የጣዖት ስሞች ናቸው።

▶️፰. መሳ.3፥31 ሴሜጋር ከፍልስጥኤማውያን ጋር ስድስት መቶ ሰው በበሬ መውጊያው ገደለ ሲል በሬ መውጊያ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ የበሬ መውጊያ ቀንድ ነው። ስለዚህ እንደበሬ ቀንድ ባለ መውጊያ ማረሻ ገደላቸው ማለት ነው።

▶️፱. ''ምናልባት በሰገነቱ ውስጥ ወገቡን ይሞክር ይሆናል አሉ። እስኪያፍሩም ድረስ እጅግ ዘገዩ የሰገነቱንም ደጅ እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ መክፈቻውን ወስደው ከፈቱ እነሆም ጌታቸው በምድር ወድቆ ሞቶም አገኙት'' ይላል። ወገቡን ይሞክር ይሆናል ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ወገቡን ይሞክር ይሆናል ማለት ሽንት ቤት እየተጠቀመ ይሆናል ማለት ነው። ሽንት ቤት ላለማለት የተሻለ ቋንቋ አንበሳ መደብ ይባላል። የገጠር ሰው ወገቤን ልፈትሸው ይላል ሽንት ቤት ልጠቀም ሲል ነው። (እኔም ሁሉም የሚያውቀው የተሻለ መግለጫ ስላጣሁ በዚህ ገልጨዋለሁ። አንባቢ ሆይ ይህ ጸያፍ ከሆነብህ አስቀድሜ ይቅርታ እላለሁ)።

▶️፲. ኢያዔል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ኢያዔል የአንዲት ሴት ስም ነው። ትርጉሙ ምን እንደሆነ ግን አላውቀውም።

▶️፲፩. መሳ.1፥21 "ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን የብንያም ልጆች አላወጧቸውም ኢያቡሳውያንም ከብንያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀምጠዋል" ይላል። ኢያ.15፥63 ላይ ግን የይሁዳ ልጆች ስላላስወጧቸው ከይሁዳ ልጆች ጋር እንደሚገኙ አይተን ነበር አይጋጭም ወይ።

✔️መልስ፦ ነገደ ብንያምና ነገደ ይሁዳ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ነገዶች ናቸው። ስለዚህ ኢያቡሳውያን በሁለቱም መካከል ስለነበሩ መጽሐፈ ኢያሱ ላይ ነገደ ይሁዳን ሲጠቅስ መጽሐፈ መሳፍንት ላይ ደግሞ ነገደ ብንያምን ጠቅሷል። ስለዚህ አይጋጭም።

▶️፲፪. መሳ.1፥19 "እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበር። ይሁዳም ተራራማውን ሀገር ወረሰ በሸለቆው የሚኖሩትን ግን የብረት ሠረገሎች ነበሯቸውና ሊወርሳቸው አልቻለም" ይላል። የብረት ሠረገሎች ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ ሠረገላ ለጭነት፣ ለጦርነት የሚያገለግል በፈረስ የሚሳብ ተሽከርካሪ (መንኰራኵር) ያለው ነው። (እንደ ጋሪ ያለ ነው)። የብረት ሠረገላ ደግሞ የበለጠ ጽኑዕ ስለሆነ በሸለቆው የሚኖሩት እርሱን ይዘው ስለነበረ ነገደ ይሁዳ እንደሌሎቹ ሊያሸንፏቸው አልቻሉም ነበረ ማለት ነው።

▶️፲፫. መሳ.፫፥፲፭ 'ናዖድን'' ሁለት እጆቹ ቀኝ የሆነለትን አዳኝ አስነሣላቸው ይለዋል። ሁለት እጁ ቀኝ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ቀኝ እጅ ከግራ እጅ ይልቅ አጥብቆ ይመታል አርቆ ይወረውራል። የናዖድ ሁለቱም እጆቹ ቀኝ ነበሩ ማለቱ ሁለቱም ጽኑዕ ነበሩ ማለት ነው። በሁለቱም እጆቹ ጠላትን ማጥቃት ይችል እንደነበረ ለመግለጽ ነው። ግራ እጁም የቀኙን ያህል ይሠራ እንደነበረ ለመግለጽ ነው።

▶️፲፬. መሳ.1፥1-2 "እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች፦ ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን በፊት ይወጣልናል? ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም፦ ይሁዳ ይውጣ፤ እነሆ፥ ምድሪቱን በእጁ አሳልፌ ሰጥቻለሁ አለ" ይላል። እግዚአብሔር በማን በኩል ነው የእስራኤልን ልጆች ያናገራቸው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር እንደተናገራቸው ተገልጿል። በማን አማካኝነት ነገራቸው የሚለው ግን በዚህ ስላልተገለጸ አላውቀውም።

▶️፲፭. ከካሌብ የእርሻ ቦታ ለመቀበል በመጽሐፈ ኢያሱ መካሪዋ ዓክሳን ናት (ኢያ.፲፭፥፲፰)። በመጽሐፈ መሳፍንት ደግሞ ጎቶንያል ነው ይላል (መሳ.፩፥፲፬)። አይጋጩም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም በመጽሐፈ መሳፍንት ጎቶንያል ሚስቱን አባቷን ካሌብን እንድትለምነው መከራት እንጂ እርሱ ራሱ አልጠየቀም። መምከሩ ነው የተገለጸው። ከመጽሐፈ ኢያሱም ዓክሳን አባቷን መጠየቋን የሚገልጽ ስለሆነ አይጋጭም።

▶️፲፮. "እግዚአብሔርንም ትተው በዓልን እና አስታሮትን አመለኩ" ይላል (መሳ.፪፥፲፫)። አንዳንድ ሰዎች በዓል የሚለው በአልፋው አ ከተጻፈ ጣዖት የሚል ትርጉም ይሰጣል ይላሉ (መልክዓ ፊደል)። እዚህ ጋር ደግሞ "በዓል" ራሱ ጣዖት እንደሆነ ይገልጸዋል እንዴት ነው እስኪ ያብራሩት?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Nov, 17:17


✔️መልስ፦ አብዐለ አከበረ ከሚለው የግእዝ ቃል በዓል የሚል ዘመድ ዘር ይወጣል። ትርጉሙ ክብር እንደማለት ነው። በግእዝ ሰዋስው ይህ ነው። ከዚህ ለመለየትና ጣዖቱን ለመግለጽ ደግሞ በኣል እንደሆነ ይነገራል። እኔ ካሉኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ሁሉም ጣዖቱን ለመግለጽ አልፋው "አ"ን ተጠቅመዋል።

▶️፲፯. ሴቶች በእስራኤላውያን ዘንድ ከቁጥር እንኳን የማይገቡ ሲሆን እንዴት ዲቦራ እስራኤልን ልትገዛ ቻለች? (መሳ.፬፥፬)።

✔️መልስ፦ ከቁጥር አለመግባታቸው የንቀት አይደለም አልነበረም። እግዚአብሔር ባወቀ የሠራው ሥርዓት ነበረ። ዲቦራ ነቢይት ነበረች። ሀብተ ትንቢትን ደግሞ እግዚአብሔር ለሚገባው ይሰጠዋል። ስለዚህ የመፍረድን ሥልጣን ሰጥቷታል። እንዳትገዛ የሚል ከልካይ ሕግ ስላልነበረ ልትገዛ ችላለች። ኖሮ ከነበረም እግዚአብሔር ካለ አለ ነው። ከፈቀደ ፈቀደ ነው።

▶️፲፰. "ይሁዳም ወንድሙን ስምዖንን፦ ከነዓናውያንን እንወጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ወደ ዕጣዬ ውጣ፥ እኔም ደግሞ ከአንተ ጋር ወደ ዕጣህ እሄዳለሁ አለው። ስምዖንም ከእርሱ ጋር ሄደ" ይላል (መሳ.1፣3)። እነ ይሁዳና ስምዖን እስካሁን በሕይወት አሉን?

✔️መልስ፦ ይሁዳና ስምዖን ከሞቱ ብዙ ዘመን ሆኗቸው ነበረ። ነገር ግን ከእነርሱ የተወለዱት ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው በጠቅላላው ዘሮቻቸው በእነርሱ ስም ይጠሩ ስለነበረ ነው። ስምዖንና ይሁዳ ማለቱ ነገደ ስምዖንና ነገደ ይሁዳ ለማለት ነው።

▶️፲፱. መሳ.1፣12 "ካሌብም ቅርያትሤፍርን ለሚመታና ለሚይዝ ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ አለ" ይላል። በስልክ በአፕሊኬሽን ካለው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ "ቅርያትሤፍር" ይላልና ትርጉሙ "ሀገረ-መጻሕፍት" ካለው ጋር ተመሳሳይ ይሆን? ቃሉስ የምን ቋንቋ ነው?

✔️መልስ፦ አዎ ትርጉሙ ቃላዊ ይሁን ዐውዳዊ አልተገለጸም እንጂ ቅርያትሤፍርን ሀገረ መጻሕፍት ብሎ ተርጉሞታል። ይኸውም የወግ የታሪክ ሀገር ማለት እንደሆነ የግእዙ መጽሐፍ ቅዱስ ገልጾታል። መነሻ ቋንቋው የምን እንደሆነ ግን አላውቀውም።

▶️፳. "አዶኒቤዜቅም የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣት የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበር፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ አለ" ይላል (መሳ.1፥7)። አዶኒቤዜቅ "እግዚአብሔር መለሰልኝ" ሲል በእግዚአብሔር መኖር ያምን ነበር እንዴ?

✔️መልስ፦ የአዶኒቤዜቅ እምነቱ ምን እንደነበረ አልተገለጸም። ነገር ግን ቀድሞ በሠራው ክፉ ሥራ ፋንታ እርሱንም በጠላት እጅ አሳልፎ ሲሰጠው እግዚአብሔር አሳልፎ ሰጠኝ ብሏል። እግዚአብሔር አሳልፎ ሰጠኝ ማለቱ በኋላ አምኖ ይሆን ወይም ከቀድሞ ጀምሮ አምኖ ይሆን የተገለጸ ነገር አላገኘሁም።

▶️፳፩. "የእግዚአብሔርም መልአክ ከጌልገላ ወደ ቦኪም ወጥቶ እንዲህ አለ። እኔ ከግብፅ አውጥቻችኋለሁ፥ ለአባቶቻችሁም ወደ ማልሁላቸው ምድር አግብቻችኋለሁ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ለዘላለም አላፈርስም" ይላል (መሳ.2፥1)። መልአኩ ነው ወይስ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያደረገ?

✔️መልስ፦ መልአክ ማለት የእግዚአብሔር መልእክተኛ ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ለሰዎች የሚያስተላልፍ ማለት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር በል ያለውን ብሏል። ከግብፅ አውጥቻችኋለሁ ማለቱ የእግዚአብሔርን ሥራ መናገሩ ነው እንጂ እርሱ እንዳወጣቸው የሚገልጽ አይደለም። መልአኩ በመላክ ('ላ' ጠብቆ ይነበብ) ትእዛዙን መፈጸሙን ለመግለጽ የተነገረ ቃል ነው። መልአክ ታዝዞ (ተልኮ) ቀን በደመና ሌሊት በዐምደ እሳት ይረዳቸው ነበረና።

▶️፳፪. "ኢያሱም ሕዝቡን ባሰናበተ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ምድሪቱን ሊወርሱ ወደ እየርስታቸው ሄዱ" ይላል (መሳ.2፥6)። ኢያሱ ሙቶማ ይሁዳ መሪ ሆኖ መስሎኝ? ኢያሱ ከሞተ በኋላ ብሎ ጀምሮ ለምንድን ነው እዚህ ላይ ወደ ኋላ የተመለሰው? መልአኩ የተናገራቸው ኢያሱ እያለ ነው እንዴ? የትረካው ሂደት ስላልገባኝ ነው።

✔️መልስ፦ ቀድሞ የተደረገውን መልሶ ለመግለጽ ደግሞት ነው። እንጂ ኢያሱ የሞተ ቀድሞ ነው።

▶️፳፫. "ከእነዚያም በኋላ እግዚአብሔርን ለእስራኤልም ያደረገውን ሥራ ያላወቀ ሌላ ትውልድ ተነሣ" ይላል (መሳ.2፥10)። በኋላ ደግሞ "የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ" ይላል (መሳ.3፥9)። እግዚአብሔርን ካላወቁት እንዴት ጮኹ አለ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔርን ያላወቀ ማለት በሕግ በአምልኮት እርሱን ያልተከተለ አስቀድሞ ለአባቶቻቸው ያደረገውን መልካም ሥራ ያላስተዋለ አመፀኛ ሕዝብ ተነሣ ማለት ነው እንጂ ፈጣሪ እርሱ መሆኑን ፈጽሞ የማያውቅ ትውልድ ተነሣ ለማለት አይደለም። በኋላ መከራ ሲጸናባቸው አድነን ብለው ወደ እግዚአብሔር መጮኻቸውም ለዚህ ነው።

▶️፳፬. "በዚያ ጊዜም ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ በእስራኤል ላይ ትፈርድ ነበረች። የእስራኤልም ልጆች ወደ እርሷ ለፍርድ ይወጡ ነበር" ይላል (መሳ.4፥4-5)። እዚህ ጋ ያለው ፍርድ  እንዴት ያለ ነው?

✔️መልስ፦ ሥጋዊ ፍርድ ነው። ሙሴ በሕዝቡ ላይ ይፈርድ እንደነበረ ያለው ዓይነት ፍርድ ነው።

▶️፳፭. "ቄናዊውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኦባብ" ይላል (መሳ.4፥11)። ይህ ሙሴ እስራኤላውያንን ሲመራ የነበረው ነው ወይስ የስም መመሳሰል ነው?

✔️መልስ፦ አዎ እስራኤልን ሲመራ የነበረው ሙሴ ነው።

▶️፳፮. መሳ.5፥24 "ኢያዔል ከሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን" ይላል። እንዲሁም ደግሞ ሲሣራን መግደሏ፤ እነዚህ ሁለቱ በሐዲስ ኪዳን ምናልባት ለእመቤታችን ምሳሌ መሆን ይችሉ ይሆን?

✔️መልስ፦ ኢያዔል ከሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን መባሏ በዘመኗ ካሉ ሴቶች ሁሉ ይልቅ ነው። እንጂ ከእርሷ በፊት ከነበሩትና ከእርሷ በኋላ ከተነሡት ሁሉ ይልቅ የተባረከች መሆኗን አይገልጽም። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ከእርሷ በፊት ከነበሩትም፣ በዘመኗ ከነበሩትም፣ እስከ ዓለም ፍጻሜ ከሚነሡትም ሁሉ ይልቅ የተባረከች ስለሆነች ምሳሌው ሕፀፁ ስለሚጎላ ሊቃውንትም ምሳሌ አድርገው በትርጓሜ አላስቀመጡልንም።


© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Nov, 05:46


ጫማ ወደቤተክርስቲያን ስንገባ ለምን እናወልቃለን?

ቅዱስ ሳዊሮስ ወደቤተክርስቲያን ገብተን ሥጋውን ደሙን በምንቀበልበት ጊዜ ጫማ እንድንጫማ፣ ዝናር እንድንታጠቅ፣ ኩፌት እንድንደፋ ያስተምረናል። ሙሴ ደግሞ ወደቅዱሱ ተራራ በቀረበ ጊዜ "ሙሴ የምትረግጣት ምድር ቅድስት ናትና ጫማህን አውልቅ ተብሏል"።

ቅዱስ ሳዊሮስ ሥጋውን ደሙን በምንቀበልበት ጊዜ ጫማ እንድንጫማ፣ ዝናር እንድንታጠቅ፣ ኩፌት እንድንደፋ መንገሩ ምሥጢሩ ሃይማኖትን ይዘን፣ ምግባር ትሩፋትን ሠርተን፣ ፍቅርን ገንዘብ አድርገን ሥጋውን ደሙን መቀበል እንደሚገባ መግለጹ ነው። እንጂ በቁሙ ጫማ እንድናጠልቅ መንገሩ አይደለም። አንድም ሹራቡን ሲያይ ጫማ ተጫሙ አለ ተብሎ ይገለጻል።

ሙሴ ጫማህን አውልቅ መባሉ የምትሄድባት ምድረ ግብፅ ጽንዕት ናትና ፍርሀትን ከልቡናህ አውልቅ (ጣል) ማለቱ ነው። አንድም ፋል የሚባል ጥንቁልና ለምዶ ነበርና እርሱን ትተህ በአምልኮተ እግዚአብሔር ጽና ማለቱ ነው። በዋናነት ግን ወደቤተክርስቲያን በምትገቡበት ጊዜ ጫማችሁን አውልቁ ማለት ነው። እንኳንስ ቤተክርስቲያን ቃለ እግዚአብሔር ከሚነገርበት ጉባኤ ቤት ሲገባ እንኳ ጫማን አውልቆ መግባት ይገባል።

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Nov, 05:20


💚መጽሐፈ መሳፍንት ክፍል ፩💚

💚ምዕራፍ 1፦
-ኢየሩሳሌም በይሁዳ ነገድ እንደተያዘች
-የካሌብ ወንድም ጎቶንያል ዳቤርን መያዙ
-እግዚአብሔር ከይሁዳ ጋር በረድኤት እንደነበረ

💚ምዕራፍ 2፦
-ከትውልድ በኋላ እግዚአብሔርንና ለእስራኤልም ያደረገውን ሥራ ያላወቀ ሌላ ትውልድ እንደተነሣ።
-እስራኤላውያን አምልኮተ እግዚአብሔርን እንደተዉ፣ በዓሊምን፣ በአልንና አስታሮትን እንዳመለኩ፣ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ለጠላቶቻቸው አሳልፎ እንደሰጣቸው፣ በኋላ መሳፍንትን እንዳስነሣላቸውና እንዳዳናቸው
-እግዚአብሔር መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ እግዚአብሔር ከመስፍኑ ጋር እንደነበረ

💚ምዕራፍ 3፦
-እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ለመፈተን አሕዛብን እንደተዋቸው፣ ይህም ጦርነት እንዲያስተምሯቸው እንደሆነ
-የእስራኤል ልጆች ክፉ ሥራን እንደሠሩ፣ በዚህም ምክንያት እስራኤል በጦርነት እንደተመታች
-የእስራኤል ልጆች ወደ እግዚአብሔር እንደጮሁና እግዚአብሔርም ናዖድን እንዳስነሣላቸው

💚ምዕራፍ 4፦
-እስራኤላውያን በበደላቸው ምክንያት እግዚአብሔር ለአሦር ንጉሥ የሠራዊት አለቃ ለሲሣራ አሳልፎ እንደሰጣቸው
-እስራኤላውያን ወደእግዚአብሔር እንደጮሁና በዲቦራና በባርቅ አማካኝነት እንዳዳናቸው
-ሲሣራን የሔቤር ሚስት ኢያዔል በካስማ መትታ እንደገደለችው

💚ምዕራፍ 5፦
-ዲቦራና ባርቅ እንደዘመሩ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ቢበድሉ የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎም መታቸው። በኋላ እንደገና ወደእግዚአብሔር ሲጸልዩ እግዚአብሔር መስፍን አስነሥቶ የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን መስፍኑ ገደለላቸው። ይህ መስፍን ማን ነው?
ሀ. ጎቶንያል
ለ. አዶኒቤዜቅ
ሐ. ናዖድ
መ. አቢኒሔም
፪. ሲሣራን በካስማ (በመዶሻ) መትቶ የገደለው ማን ነው?
ሀ. ዲቦራ
ለ. ባርቅ
ሐ. ኢያዔል
መ. ሔቤር
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ዲቦራ ሕዝበ እስራኤልን ትገዛ ነበረ
ለ. ዲቦራ ነቢይት ነበረች
ሐ. የእስራኤል ልጆች ለፍርድ ወደ ዲቦራ ይመጡ ነበረ
መ. ሁሉም

https://youtu.be/v1HZO_VZQqs?si=nq4AYEiquDxQ9d9o

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

14 Nov, 05:13


💙መዝሙረ ዳዊት ክፍል 1💙
ይህን መዝሙረ ዳዊት መነኮሳት፣ ካህናት፣ መዘምራን በዜማ በንባብ በቤተክርስቲያን በመዓልትም በሌሊትም ሳያቋርጡ እንዲጸልዩበት ምእመናንም ከሌላው ጸሎት ይልቅ እርሱን መላልሰው እንዲጸልዩ ታዝዘዋል፡፡ ዳዊት ማለት ልበ አምላክ፣ ኅሩይ፣ መስተሳልም፣ መስተፋቅር (የሚያዋድድ) ማለት ነው፡፡ እስራኤል አሥራቱን በኵራቱን ሳያወጡ መሥዋዕት አይሠዉም ነበረ፡፡ ልብስን ቀዶ ትቢያ ነስንሶ መሄድ በእስራኤል ባህል ትእምርተ ኀዘን ነው፡፡ ከሰው ቤት ማዘዝ አይገባም፡፡ ቢጠቅምም ባይጠቅምም ባለቤት ያውቃል እንጂ እንግዳ አያውቅምና፡፡ ቆርሶ ያላጎረሱትን ቀዶ ያላለበሱትን ብላቴና ማዘዝ አይገባም፡፡ ከመሥዋዕት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መስማት ይሻላል፡፡ የሳሙኤል አጋግን መግደል፣ የፊንሐስ ክስቢንና ዘምሪን መግደል ያጠመሙትን ከማቅናት ያጎደሉትን ከመምላት ተቆጥሮላቸዋል እንጂ እዳ አልሆነባቸውም፡፡ ሰው የመልክን ደም ግባት ያያል እግዚአብሔር ግን የልቡናን ቅንነት ያያል፡፡ ሳሙኤል ዳዊትን በቅብዐት ቀብቶ አነገሠው፡፡ ዳዊትም ሲቀባ ሰባት ሀብታት አድረውበታል፡፡ እነዚህም፦
፩.ሀብተ መንግሥት
፪.ሀብተ ክህነት
፫.ሀብተ ኃይል
፬.ሀብተ መዊዕ
፭.ሀብተ በገና
፮.ሀብተ ፈውስ
፯.ሀብተ ትንቢት ናቸው፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Nov, 19:02


ሰማዕታት ለእርሱ ያላቸውን ፍቅር ጀርባቸውን ለግርፋት፣ አንገታቸውን ለሰይፍ በመስጠት ገለጡ።

መነኮሳት ለእርሱ ያላቸውን ፍቅር ፍርኵታ ለፍርኵታ ከዋሻ ዋሻ በመሄድ፣ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ ግርማ ሌሊት ድምፀ አራዊትን ታግሠው ኖሩ።

ሊቃውንት ኃይለ ቃል ጠቅሰው ከሓድያንን ረትተው ስለእርሱ በማስተማር ፍቅራቸውን ገለጡ። ማሕሌታውያን ስቡሕ ውዱስ ብለው እርሱን ሌት ከቀን በማመስገን ፍቅራቸውን ገለጡ።

ክርስቲያኖች ሁሉ የእርሱ ልጆች እንደመሆናቸው ትምህርቱን ጠብቀው በመኖር ፍቅራቸውን ይገልጣሉ። እርሱ ናዝራዊ እንደተባለ በእርሱ ናዝራውያን ይባላሉ። እርሱ ክርስቶስ እንደተባለ እነርሱ ክርስቲያን ይባላሉ። ክርስቲያን እንደ ንስር ከፍ ብሎ የሚበር አስተሳሰቡ ልዑል ነው።

አነ ዘክርስቶስ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Nov, 16:16


PDF
በእግዚአብሔር ቸርነት መጽሐፈ ኢያሱን ተማምረን ጨርሰናል። መጽሐፈ መሳፍንት ነገ ይጀመራል። በቀን አምስት አምስት ምዕራፍ እናጠናለን። ከአምስቱ ምዕራፍ ውስጥ ያልገባችሁን ጉዳይ ትጠይቁኛላችሁ
ሙስሊሞች
ፕሮቴስታንቶች
እምነት የለሾች (ኤቲስቶች)
እና የተለያዩ አካላት በየቀኑ ከምናጠናቸው ጥያቄዎች ከጠየቋችሁ አምጧቸው። በደንብ አብራርተን እናስረዳቸዋለን። እስከ ትንሣኤ ድረስ እስከ ራእየ ዮሐንስ ተማምረን እንጨርሳለን። ከዘፍጥረት ጀምሮ ለጠየቃችኋቸው ጥያቄዎች መልስ በPDF ቀጥሎ በቴሌግራም ቻናሌ ለቅቄዋለሁ። ጥያቄ ስትጠይቁ የዕለቱን በዕለቱ ጠይቁ። ከባለፈው ጥያቄ ካላችሁ PDFውን ተመልከቱ። ለሚመጣው ጥያቄ ካላችሁ ስንደርስበት ጠይቁ።

መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት መጽሐፍ ነው። የሕይወት መልእክት ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው። እናንብብተ ያልገባንን በሥርዓት በትሕትና እንጠይቅ።

© በትረ ማርያም አበባው ካሣ

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Nov, 15:00


" ..በዚህ ወቅት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በስፋት የሚሰማውን ብልሹ አሠራር ማረምና ለቀጣዩ አገልግሎት መልክ ማስያዝ የካህናቱ ትልቅ ድርሻ ነው፡ ፡ ፡"#ሐመር መጽሔት
                                                                   ༺ ༻
                        #የኅትመት ዘመን ፦#ኀዳር  ፳፻፲፯ ዓ.ም ቁ.፲ ፩
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል #በየወሩ የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
                           ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
  • ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር -፲፩ ኀዳር  ፳፻፲፯ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ “#እናንተ ግን የሌቦችና የቀማኞች ዋሻ አደረጋችሁት፤” በሚል ዐቢይ ርእስ በሁሉም መስክ ከወሬ ባለፈ ብልሹ አሠራርንና ዘረኝነትን በተግባር የሚፀየፍ አገልጋይ በታሰበው መጠንና ፍጥነት መፍጠር እንዳልተቻለ ፤በተቀደሰው ሥፍራ የጥፋት ርኵሰትን ማከናወን ሊቋቋሙት የማይችሉትን የእግዚአብሔር ቍጣ በራስ ላይ መጥራት ነው።
       ሲገሠጹም ከመመለስ ይልቅ ለምን ታወቀብኝ ብሎ ሌላ በደል ለመጨመር መሯሯጣቸውና የእግዚአብሔርን ትዕግሥት መፈታተን መሆኑን አለመረዳታቸው ደግሞ ሌላው ጉዳይ እንደሆነ ፤ ችግር ዳር ሆኖ በማውራት፣ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በማንሸራሸር፣ ከንፈር በመምጠጥና በተናጠልም እዚህም እዚያም በማለት የሚፈታ እንዳልሆነ ልንገነዘብና ሁላችንም ተገቢውን ሥራ ልንሠራ  እንደሚገባ ፤  በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለአጥፊዎች መከታ፣ ሽፋንና ዋሻ የሆኑ አካላትም ከእነርሱ ጋር ከተሳሰሩበት ምድራዊ ማሰሪያ ይልቅ አባታቸው እግዚአብሔርና እናታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደምትበልጥባቸው አስታውሰው አካሄዳቸውን በማስተካከል ከእውነት ጐን እንዲቆሙ ጥሪዋን  ታስተላልፋለች።
.           #ዐውደ ስብከት ሥር  ‹‹ወዳጄ በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ ነሽ››(መኃ.፪፥፪) በሚልርእስ ከመዝሙራት ሁሉ በሚበልጥ መዝሙሩ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ቅዱሳን ጻድቃን ስለ እውነተኞቹ ምእመናን (ክርስቲያኖች)፣ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር ወዘተ. የተናገረው ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ትንቢቱን ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር ተናግሮታል፡    መሆኑን ያሳያል።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ  (ዕብ.፲፫፥፰)" በሚል ዐቢይ ርእስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ክርስቶስን በኦሪት፣በነቢያት ፣በወንጌል፣ እንዴት እንደምስብከው ሰፊ ትምህርት ይሰጣል፡፡ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዓተ አምልኮቷ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በልዩ ልዩ መልኩ ታስረዳለች።
         በሥርዓተ ቅዳሴዋ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን እንደምትሰብከው ሁሉ ሥርዓተ ቅዳሴዋን እና ማኅሌት በምትፈጽምባቸው ንዋየ ቅድሳትም ትሰብከዋለች ።ቤተ ክርስቲያንን ሳያውቋት ሰዎች ስሟን እንዲሁ እናጠፋለን ብለው የሚያስቡበትን ልቡናቸውን ሽህ ጊዜ እንደገና መልሰው መላልሰው ሊያስቡበት ይገባል ። ይህን ሁሉ ቤተክርስቲያን ስታስተምር እየታየች ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ አታስተምርም ማለት ባላዩት ምስክር መሆን፤ ለራሱ ሳያውቅ እኔ ላሳውቅህ ማለትና ከአንተ ይልቅ እኔ ስለ አንተ አዋቂ  ነኝ እንደ ማለት ይቆጠራል፡፡
       #ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “‹‹ወይሠረዉ መፍቀርያነ ወርቅ፤ ወርቅን የሚወዱ ይነቀሉ›› (ቅዳሴ እግዚእ ቁ.፭) በሚል ዐቢይ  ርእስ የወቅቱ የቤተ ክህነታችን ፈተና በጥልቀት ትዳስሳለች ።በአሁኑ ዘመን አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ባለሥልጣናት እንደ መንፈሳዊ መሪነት ሚናቸውን መወጣት ተስኗቸው  እንደሚታዩ በመረጃ ትሞግታለች፡፡አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን መሪዎች ብዙውን ጊዜ ከእግዚአብሔር አገልጋይነት ይልቅ እንደ ምድራዊ ምንደኛ፣ እንደ ፖለቲከኛ፣ እንደ ቢዝነስ ሰው ያለ የአካሄድ ዝንባሌን የሚያሳዩም መኖራቸውን ትጠቁማለች፡፡
          ሙሉውን #ከመጽሔቱ ይነበብ
         #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ጭንቀት ክፍል_፪ "በሚል ርእስ መጋቤ ሐዲስ #አእምሮ ደምሴ #የኳታር ጸርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ መ/ር ደግሞ  መንፈሳዊ ጭንቀት ስለሰማያዊው እና ዘለዓለማዊው ሕይወት መጨነቅና ማሰብ እንደሆነ በጥልቀት ያስተምራሉ፡፡ከመንፈሳዊ ጭንቀቶች ስቀምጣሉ፡፡ ሙሉውን ከሐመር  መጽሔት ታገኛላችሁ፡፡
  • #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “ከገነተ ልዑል እስከ መንበረ ልዑል”በሚል ዐቢይ ርእስ በሚል ርእስ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረቱ ምክንያቶችና የአመሠራረት ሁኔታውን የሰንበትትምህርት ቤቱ አመሠራረት፣ የሊቃውንት አሻራ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን  ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም የምረቃ  መጽሔትን በምንጭነት በመጠቀም ታስቃኛለች ።
          • #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳውያን ምሩቃን ለቤተ ክርስቲያን ያላቸው አስተዋፅኦ" በሚል ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በመላው ዓለም በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግቢ ጉባኤያትን በመመሥረት ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ ዶግማ እና ቀኖና እንዲሁም ሥርዓት እንዲያውቁ፣ ራሳቸውንም ከክፉ ነገር በመጠበቅ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ማነጽ እንዲችሉ አገልገሎቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ያሳያል ። የግቢ ጉባኤ ተመራቂዎች ከምረቃ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ያላቸው ድርሻ ዘርፈ ብዙ ቢሆንም ዓበይት የሆኑትን ሐመር መጽሔት ታስቃኛለች፡፡
          #በኪነ ጥበብ ዐምድ "#በፍላጻ የተወጋ ልብ-ክፍል ፩ "በሚል እጅብ ባሉ ሀገር በቀል የተፈጥሮ ዛፎች በተከበበ ዐፀደ ቤተክርስቲያን ውስጥ መጸለይ እጅግ ይወዳል፡፡ ከዚያ ውጣ ውጣ አያሰኘውም፡፡ አንድ ቀን እንደልማዱ ሲጸልይ ቆይቶ ጸሎቱን ሲያበቃ ከአንድ ዛፍ ሥር አረፍ አለ፡፡ እጅግ የሚያስደስት መዐዛ ቢያውደው የትመጣውን ለማወቅ ከአንገቱ ተቃንቶ ዙሪያውን ሊቃኝ ጀመረ በማለት ግሩም የኪነጥበብ ጹሑፍ  ታስነብባለች ።
                 • #በጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምዳችን “ወርኀ ጽጌን” ክፍል አንድን በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ ይሰጡን ዘንድ መጋቤ ሐዲስ ተስፋ ሚካኤል ታከለን በወርኃ ጥቅምት ዝግጅታችን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ቀጣይና የመጨረሻውን ክፍል ደግሞ ጌታ ወደ ግብፅ የተሰደደበት ምክንያት ለምንድ ነው?
                በስደቱ ጊዜ እነ ኮቲባ ወደ ዝንጀሮና ጦጣ እንደተለወጡ ይነገራል ከሥነ ፍጥረት አንጻር ይስማማልን? የስደት ዐቢይ ምክንያቶችን እና ስደቱን ለምን በወርኀ ጥቅምት እናስባለን? ከወቅቱ ጋር የተሳሰረ ምሥጢር  አለው የሚሉ ጉዳዮችን በሊቃውንት ምላሽ  ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Nov, 13:46


💖የጥያቄዎች መልስ ክፍል 42💖

▶️፩. "የነሮቤል" ነገድ የሠሩት የእግዚአብሔር መሠዊያ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሄር እስከሆነ ድረስ ለምን ተቃዎሙት?

✔️መልስ፦ አስቀድመው ዘጠኙ ነገድና ግማሹ የምናሴ ነገድ የመሰላቸው ሌላ የጣዖት አምልኮ ነበረ። የጣዖት አምልኮ መስሏቸው ስለነበረ ተቃወሟቸው። በኋላ ግን ልጆቻችን ከዮርዳኖስ ማዶ ካሉት እስራኤላውያን ጋር ምን ኅብረት አለን ብለው በጠየቁን ጊዜ እንድንመልስላቸው ለቤተ እግዚአብሔር የተሠራውን የሚመስል መሠዊያ ለእግዚአብሔር ሠራን አሉ። ሌሎች ነገዶችም ይህን በሰሙ ጊዜ ደስ ብሏቸው ተቃውሟቸውን ትተዋል።

▶️፪. እስራኤላውያን ካህኑ ፊንሐስ እስከነበረ ድረስ እግዚአብሔርን ያመልኩት ነበር። ከዛ ምን ተፈጠረ? ከፊንሐስ ሞት በኋላ ካህንን አልሾመላቸውም ነበር?

✔️መልስ፦ ለፊንሐስ የተሰጠው የክህነት ዘመን 300 ዓመት ነበረ። ከእርሱ በኋላም እንደ ኤሊ ያሉ ሌሎች ካህናት ተነሥተው ነበረ። ነገር ግን ካህናት ቢኖሩም በየጊዜው ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ሕግ እያፈነገጠና በእግዚአብሔር እያመፀ በተለያዩ መከራዎች ይቀጣ ነበረ።

▶️፫. "ካልተከላችኋቸውም ከወይን እና ከወይራ በላችሁ" ይላል (ኢያ.24፥13)። ወይራ ይበላል እንዴ?

✔️መልስ፦ ከወይራ ዘይት ይገኛል። እና ያንን ዘይት ሰጠኋችሁ ለማለት ነው።

▶️፬. ''ኢያሱም ሕዝቡን እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና እርሱም ቀናተኛ አምላክ ነውና እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም መተላለፋችሁንና ኀጢአታችሁን ይቅር አይልም'' ይላል (ኢያ.24÷19)። 'እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም' ሲል ምን ለማለት ነዉ?

✔️መልስ፦ በእግዚአብሔር አምልኮ ላይ ጣዖት አምልኮን እንዳይጨምሩ ለማስገንዘብ የተነገረ ቃል ነው። ፈጥሮ የሚገዛን እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ጣዖትን ፈጣሪዬ ማለት ትልቅ በደል ነው። ስለዚህ ጣዖትን የሚያመልኩ ሰዎች እግዚአብሔርን ማምለክ እንደማይችሉ በግልጽ የተነገረ ቃል ነው።

▶️፭. "ነገር ግን የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዋውያን በመካከላችሁ እድል ፈንታ የላቸውም" (ኢያ.18፥7) የሚለውና "በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማርያቸው ነበሩ" ( ኢያ.21፥41) የሚለው ሁለቱ ግልፅ አልሆንልህ አለኝ (ተጋጨብኝ) ቢብራራልኝ።

✔️መልስ፦ ሌዋውያን ርስት የላቸውም ተባሉ እንጂ መኖሪያ የላቸውም አልተባለም። ሰዎች እስከሆኑ ድረስ መኖሪያ ያስፈልጋቸዋል። ስለዚህ ሌዋውያን ይኖሩባቸው ዘንድ ከአሥራ ሁለቱ ነገድ ርስቶች የተወጣጡ 48 ከተማዎች ተለይተውላቸዋል። እነዚህ እንደ ርስት ሳይሆን እንደመኖሪያ የተለዩ ቦታዎች ናቸው። የእነዚህ ቦታዎች ርስትነትም ለሌዋውያን ሳይሆን ለእግዚአብሔር ነው።

▶️፮. "እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን" ይላል (ኢያ.24፥15)። እዚህ ላይ "ቤቴ" ያለው ምኑን ነው?

✔️መልስ፦ ቤቴ ማለቱ ወገኖቼ ለማለት ነው። እኔና ወገኖቼ ማለት የኢያሱ ቅርብ ዘመዶች እና ኢያሱ እግዚአብሔር በማምለክ እንደሚጸኑ የተናገረበት ነው።

▶️፯. "ኢያሱም ሕዝቡን እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፥ እርሱም ቀናተኛ አምላክ ነውና እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም" ይላል (ኢያ.24፥19)። "እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም....ኃጢያታችሁን ይቅር አይልም" ያለው ለምንድን ነው እያመለኩት አይደለም ወይ? በእውኑ እግዚአብሔር ይቅር ባይስ አይደለም ወይ?

✔️መልስ፦ ጉዳዩ ጣዖት ካመለካችሁ እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም ለማለት የተነገረ ነው እንጂ አሁን እያመለካችሁኝ አይደለም ማለት አይደለም። ኃጢአታችሁን ይቅር አልልም ማለቱም ጣዖትን በማምለክ ከጸኑ ኃጢአታቸው ይቅር እንደማይባል የሚያስረዳ ቃል ነው እንጂ ከጣዖት አምልኮ ተመልሰው እግዚአብሔርን ቢያመልኩ የቀድሞ በደላቸውን ይቅር ይባላሉ።

▶️፰. "ኢያሱም ለሕዝቡ እነሆ የተናገረንን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ሰምቷልና ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፤ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል አላቸው" ይላል (ኢያ.24፥27)። በሰውኛ ድንጋዩን ሰምቷል ሲል ምን ለማለት  ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ይስማ ካለው እንደ ቢታንያ ድንጋዮች ማናገር ማሰማት ይችላልና በወቅቱ ኢያሱ ድንጋዩን ምስክር አድርጎታል።

▶️፱. እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን ማለት ምን ማለት ነው? እግዚአብሔርን መፍራት በምን ይገለፃል?

✔️መልስ፦ እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን ማለት እኔና ወገኖቼ እግዚአብሔርን እናመልካለን ማለት ነው። እግዚአብሔርን መፍራት የሚገለጸው እርሱን ብቻ በማምለክና ያዘዘውን ትእዛዝ በመፈጸም ነው።

▶️፲. "እነሆም ዛሬ የምድርን ዅሉ መንገድ እኼዳለኹ እናንተም እግዚአብሔር ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ዅሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችኹ ዅሉ በነፍሳችኹም ዅሉ ዕወቁ ዅሉ ደርሶላችዃል ከእርሱም አንድ ነገር አልቀረም" ይላል። የምድርን ዅሉ መንገድ እኼዳለኹ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የምድርን ሁሉ መንገድ እሄዳለሁ ማለቱ ማንኛውም ምድራዊ ሰው የሚሞተውን ሞት እሞታለሁ ማለቱ ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Nov, 12:13


💙💙💙 የዕለቱ ጥያቄዎች 💙💙💙

፩. ኢያሱ ኢያሪኮን ይሰልሏት ዘንድ ሰላዮችን በስውር ልኮ ነበረ። ሰላዮቹ ወደኢያሪኮ ሲገቡ ከማን ቤት ገቡ?
ሀ. ረዓብ💙
ለ. ርብቃ
ሐ. ራኄል
መ. ሣራ
፪. ኢያሱ ይሰልሏት ዘንድ ወደኢያሪኮ የላካቸው ሰዎች ስንት ናቸው?
ሀ. ዐሥራ ሁለት
ለ. ሁለት💙
ሐ. ዐሥር
መ. ስድስት
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የዮርዳኖስ ወንዝ እስራኤል እስኪሻገሩ ድረስ ደርቋል
ለ. ሰላዮች ከቤቷ ገብተው የነበሩባት ሴት እንዳትጠፋ ቀይ ሐር በመስኮት እንድታደርግ ነገሯት
ሐ. የዮርዳኖስ ወንዝ ሁሉም እስራኤላውያን ከተሻገሩ በኋላ መልሶ ሞልቷል
መ. ሁሉም💙

፬. እስራኤላውያን ታቦቱን ሲከተሉ በታቦቱና በእነርሱ መካከል ርቀቱ ምን ያህል እንዲሆን ታዘዙ?
ሀ. 400 ክንድ
ለ. 1000 ክንድ
ሐ. 2000 ክንድ💙
መ. 100 ክንድ
፭. እርም የሆነውን ነገር ከኢያሪኮ በቤቱ አስቀምጦ በዚህ ምክንያት እስራኤል በጋይ ሰዎች እንዲሸነፉ ያደረገው ሰው ማን ነው?
ሀ. አካን💙
ለ. ከርሚ
ሐ. ዘንበሪ
መ. ዛራ
፮. ያረጀ ልብስ ለብሰው የሻገተና የደረቀ ምግብ ይዘው ከሩቅ ሀገር መጣን ብለው ዋሽተው ኢያሱን ያታለሉትና ኢያሱም በኋላ ተንኮላቸውን አውቆ የእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቀራጮችና ውሃ ቀጂዎች ያደረጋቸው የየት ሀገር ሰዎች ናቸው?
ሀ. የኢያሪኮ
ለ. የገባዖን💙
ሐ. የጋይ
መ. የአሞራውያን
፯. ኢያሱ ጠላቶቹን እስኪያጠፋ እግዚአብሔር ፀሐይን በገባዖን ያቆማት ለስንት ቀን ነው?
ሀ. ለሦስት ቀን
ለ. ለሁለት ቀን
ሐ. ለአንድ ቀን💙
መ. ለሰባት ቀን
፰. የሌዊ ነገዶች እንደሌሎች ነገዶች ከምድረ ርስት ያልተካፈሉ ለምንድን ነው?
ሀ. ኃጢአተኞች ስለሆኑ
ለ. ርስታቸው እግዚአብሔር ስለሆነ💙
ሐ. ጥቂት ስለሆኑ
መ. ከሌሎች ነገዶች ተለይተው ስለሚናቁ
፱. ከያዕቆብ ልጆች ከእርሱ ሁለት ነገዶች የተወለዱለት ማን ነው?
ሀ. ይሁዳ
ለ. ሌዊ
ሐ. ዮሴፍ💙
መ. ብንያም
፲. ኢያሱ ለካሌብ ርስት እንዲሆነው የሰጠው ከተማ ማን ትባላለች?
ሀ. ኬብሮን💙
ለ. አርቦቅ
ሐ. ሀ እና ለ
መ. የሲና ተራራ
፲፩. ከሚከተሉት ውስጥ የብንያም ነገድ ርስት የሆነው ከተማ የቱ ነው?
ሀ. ኤፍራታ
ለ. ኢያሪኮ
ሐ. ገባዖን
መ. ሁሉም💙
፲፪. እስራኤላውያን ዕጣ ሲጣጣሉ ቤርሳቤህ ከተማ ለማን ነገድ ደረሰች?
ሀ. ለዛብሎን ነገድ
ለ. ለስምዖን ነገድ💙
ሐ. ለንፍታሌም ነገድ
መ. ለኤፍሬም ነገድ
፲፫. ከሚከተሉት ውስጥ የመማፀኛ ከተማ የሆነችው የቷ ናት?
ሀ. ሴኬም
ለ. ኬብሮን
ሐ. ኤርሞት
መ. ሁሉም💙
፲፬. ልጆቻቸው ከእስራኤል ልጆች አምላክ ምን አላችሁ እንዳይሏቸው ፈርተው በዮርዳኖስ አጠገብ መሠዊያ የሠሩ እነማን ናቸው?
ሀ. ነገደ ሮቤል
ለ. ነገደ ጋድ
ሐ. እኩሌታው ነገደ ምናሴ
መ. ሁሉም💙
፲፭. ኢያሱ በስንት ዓመቱ ሞተ?
ሀ. በ85 ዓመቱ
ለ. በ40 ዓመቱ
ሐ. በ110 ዓመቱ💙
መ. በ120 ዓመቱ
፲፮. አልዓዛር ሲሞት በእርሱ ምትክ ሊቀ ካህናት የሆነው ማን ነው?
ሀ. አሮን
ለ. ፊንሐስ💙
ሐ. ሳዶቅ
መ. ዔሊ

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Nov, 04:11


💞መጽሐፈ ኢያሱ ክፍል ፭💞

💞ምዕራፍ 21፦
-ለሌዋውያን ስለተሰጡ ከተሞች

💞ምዕራፍ 22፦
-የሮቤል፣ የጋድ፣ የመ*ን-/ፈ*ቀ ምናሴ ነገዶች በዮርዳኖስ አጠገብ መሠዊያ መሥራታቸው

💞ምዕራፍ 23፦
-ኢያሱ ሕዝቡን በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን እንዲጠብቁ መንገሩ

💞ምዕራፍ 24፦
-ኢያሱ ከቀድሞ ጀምሮ የተደረገውን እንደተረከ
-ኢያሱ እግዚአብሔርን ፍሩት ብሎ ለሕዝቡ መናገሩና እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን ማለቱ
-እስራኤላውያን የአሕዛብን አማልክት እንዳመለኩ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ልጆቻቸው ከእስራኤል ልጆች አምላክ ምን አላችሁ እንዳይሏቸው ፈርተው በዮርዳኖስ አጠገብ መሠዊያ የሠሩ እነማን ናቸው?
ሀ. ነገደ ሮቤል
ለ. ነገደ ጋድ
ሐ. እኩሌታው ነገደ ምናሴ
መ. ሁሉም
፪. ኢያሱ በስንት ዓመቱ ሞተ?
ሀ. በ85 ዓመቱ
ለ. በ40 ዓመቱ
ሐ. በ110 ዓመቱ
መ. በ120 ዓመቱ
፫. አልዓዛር ሲሞት በእርሱ ምትክ ሊቀ ካህናት የሆነው ማን ነው?
ሀ. አሮን
ለ. ፊንሐስ
ሐ. ሳዶቅ
መ. ዔሊ

https://youtu.be/V0Ac1VRgasY?si=7zfRZJycIDOIe7QA

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Nov, 03:28


PDF PDF ቀጥሎ
ተፈጸመ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ተከታታይ ትምህርት።

መዝሙረ ዳዊት ተከታታይ ትምህርት ነገ ይቀጥላል። ይህኛው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ በተለየ ከአንድምታው መጽሐፍ አጫጭር ማስታዎሻዎችን ብቻ በመጻፍ የምንማማረው ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን ደግሞ ዛሬ መጽሐፈ ኢያሱን እንጨርስና ነገ መጽሐፈ መሳፍንትን እንጀምራለን።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ በቀን አምስት አምስት ምዕራፍ እያነበብን ያልገባንን በመጠየቅ በመጠያየቅ የሚዘልቅ ነው። ጠይቁ እንጠያየቅ።

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

13 Nov, 03:03


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 43🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፵፫
እግዚአብሔር ሰማይን ያለባላ ከፍ አድርጎ በሕዋ አጸናው፡፡ ዐቢይ ውእቱ እግዚአብሔር፡፡ የከዋክብት ብርሃናቸው የሰማይ ጌጥ ነው፡፡ እግዚአብሔርም በፈጠረው በሰማይ ሆነው ለሀገር ያበራሉ፡፡ የእግዚአብሔር ገናናቱ እጅግ ግሩም ነው፡፡ እግዚአብሔርን አመስግኑ ገናናነቱንም ተናገሩ፡፡
🧡ምዕራፍ ፵፬
ንወድሶሙ ለዕደው ክቡራን ለአበዊነ በመዋዕሊሆሙ፡፡ እግዚአብሔር ብዙ ክብርን ሰጥቷቸዋልና የከበሩ ሰዎች አባቶቻችንን እናመስግናቸው፡፡
🧡ምዕራፍ ፵፭
ሙሴ የቀድሞ ስሙ ምልክአም ነበረ መልአክ ማለት ነው።

ከምዕራፍ 44 ጀምሮ እስከ ምዕራፍ ፶ የቀድሞ አባቶችን ታሪክ የያዘ ነው፡፡ የሁሉንም አባቶች ታሪክ በየቦታው ስለምንማማረው ከዚህ አልደግመውም። ምዕራፍ ፶፩ ደግሞ ጸሎተ ኢያሱ ወልደ ሲራክን የያዘ ነው፡፡

አነሳስቶ ላስጀመረን
አስጀምሮ ላስፈጸመን
ልዑል እግዚአብሔር
ምስጋና ይገባል

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Nov, 14:09


💖የጥያቄዎች መልስ ክፍል 41💖

፩. የዮሴፍ ልጆች ኤፍሬምና ምናሴ እኛ ብዙ ሕዝብ ስለሆነ እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከን ብለው ተጨማሪ ርስት የጠየቁት እግዚአብሔር የባረካቸው የሌዊን ልጆችን አይደል ምን ማለታቸው ነው?

✔️መልስ፦ የክህነት በረከት የባረካቸው ሌዋውያንን ብቻ ነው። ከክህነት ውጪ ባሉ በረከቶች ግን በነገዶች መካከል ልዩነት የለም። ስለዚህ ከዚህ ላይ የተጠቀሱት ነገደ ኤፍሬምና ነገደ ምናሴ ተባረኩ መባላቸው ከክህነት ውጪ ያለ ሌላ በረከት ነው።

▶️፪. አሁን እየተደረገ ያለው የእናት አባት ሀብትና ርስት ክፍፍል ከእስራኤላውያን የተወሰደ ነው?

✔️መልስ፦ አሁን በተለያዩ የመንግሥት ሕገ ደንቦች ያለው የርስት ክፍፍል ከተለያዩ ሀገሮች ልምዶች፣ ከባህላዊ እሴቶች፣ ከሃይማኖታዊ እሴቶችና ከመሳሰሉት የተዘጋጀ ነው። ፍትሐ ነገሥት ላይ ያለው በእንተ ርስት የሚለው አንቀጽ አብዛኛው ከዚሁ ከብሉይ ኪዳን የተወሰደ ነው። አሁን እንደ ሀገር ግን የተለያየ ባህል፣ ቋንቋ፣ እምነት ያለን በመሆናችን በርስት ዙሪያ ያለው ሕግም ሁሉን ያማከለ ነው እንጂ ከመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የተቀዳ ነው ማለት አይቻልም።

▶️፫. "በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ፤ ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመለሳል፥ ወደ ከተማውም ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣባትም ከተማ ይገባል" ይላል (ኢያ.20፥6)። ከዚህ ላይ ገዳዩ በመማፀኛ ከተማ የሚቆየው በማህበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቀርብ ድረስ ወይስ ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ? ወይስ ሁለቱም እስኪሆን? ከታች ቁጥር  9 ላይ ደሞ "...ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው" ይላልና ከተሞቹ ለሁለቱም (በድንገት ሰውን ለገደለና ለመጻተኛ) ነው የሚያገለግሉት? ከሆነስ  "በመካከላቸው ለሚቀመጥ" ስለሚል ያላጠፏቸው በመካከላቸው የሚኖሩ አሕዛብ ስላሉ ለእነሱ ነው ወይስ አዲስ ለሚመጡ?

✔️መልስ፦ በመማፀኛ ከተማዎች ሌዋውያን፣ መጻተኞችና ባለማወቅ ወንጀል የሠሩ ሰወች ይኖሩበታል። ባለማወቅ ወንጀል የሠሩ ሰዎች ሊቀ ካህናቱ እስኪሞት ድረስ በመማፀኛ ከተማ እንዲቆዩ ሥርዓት ተሠርቶ ነበረ። ነገር ግን ሆን ብለው ወንጀል ሠርተው ወደመማፀኛ ከተሞች ሸሽተው የገቡ ሰዎች ካሉ የመማፀኛ ከተማ ነዋሪዎች ፍርድ እስኪሰጠው ወንጀለኛውን አቆይተው አሳልፈው ለዳኛ ይሰጡታል። በመካከላቸው የሚቀመጡ መጻተኞች የተባሉት ተቸግረው ወደእስራኤል መጥተው የሚኖሩ ከእስራኤላውያን ውጪ ያሉ ሌሎች ሰዎች ናቸው። አሕዛብ የሚባሉት ግን ሀገር መሥርተው ዙሪያቸውን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው።

▶️፬. "በዮርዳኖስ ማዶ ካለው ከገለዓድና ከባሳን አገር ሌላ ለምናሴ ዐሥር ዕጣ ኾነ" ይላል። ለምን ለምናሴ ዐሥር ዕጣ ኾነ?

✔️መልስ፦ ይህ የዕጣው ምክንያት ነው። ዕጣ ሲወጣ አሥር ከተሞች እንደደረሳቸው የሚናገር ቃል ነው። ለሌሎችም በዕጣ አሥርም አምስትም የደረሰው ሊኖር ይችላል። ለምሳሌ ለካሌብ ወልደ ዮፎኒ ብዙ ዕጣዎች ደርሰውታል። ስለዚህ ይህ ሕገ ዕፃ ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

12 Nov, 10:39


Mr. X= የአህያ ሥጋ መብላት ኃጢአት ነው።
Mr. Y= በሐዲስ ኪዳን መብላትም አለመብላትም የጽድቅ ምልክት አይደለም። አያጸድቅም አያስኮንንም።

Mr. X= በባህላችን እንኑርበት ለምን ብሉ አልከን።
Mr. Y= በአስተምህሮ ደረጃ የሚበሉ ካሉ ኃጢአት አይሆንባቸውም አልን እንጂ መች ብሉ አልን?

Mr. X= ብሉ ብላችሁ አታስገድዱን።
Mr. Y= hahahahahahahaha (ይህ ነገር የአህያ ጩኸት መሰለ መሰለኝ)።

ጎበዝ መገለባበጥ ጥሩ አይደለም። በነገረ ክርስቶስ ዙሪያ ጳጳሱ የተናገሩት ለብቻው የሚታይ ነው (በግሌ መልስም ሰጥቼበታለሁ)። በምግብ ዙሪያ የተናገሩት ግን የጠራ እውነት ነው። እርሳቸውኮ የኢትዮጵያ ሕዝብ መብላት አለበት አላሉም። ሲጠየቁ የሚበሉ ካሉ ኃጢአት አይደለም ነው ያሉት። ያስገደዱበት ቦታ የለም። ያስገደዱበት ብቻ ሳይሆን ብላ ብለው የማይበላውን ሰው የመከሩበት ቦታ የለም።

ማስታዎሻ፦ አንዳንዶች ደግሞ በዚህ ወቅት ይህ አጀንዳ መሆን የለበትም ይላሉ። አዎ መሆን አልነበረበትም። ነገር ግን አጀንዳ ሆኖ ከመጣ ደግሞ እውነታውን ገልጦ ማለፍ እንጂ መልመጥመጥ አይገባም። አንዳንዶች ደግሞ ሥጋ አልቸገረንም ሰላም ነው ያጣን ይላሉ። እንዴት እንደምታስቡ አይገባኝም። ለእናንተ እጦትኮ አይደለም ቃሉ እየተነገረ ያለው። መጽሐፍ በጉዳዩ ምን ይላል የሚለውን ነው እያብራራን ያለነው።

ኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ ምን ይላል የሚለውን መግለጥ አስፈላጊ ነው። ከርእሱ ውጭ የሆኑ ጉዳዮችን በዚህ ማምጣት አይገባም።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Nov, 05:16


💝መጽሐፈ ኢያሱ ክፍል ፪💝

💝ምዕራፍ 6፦
-እስራኤላውያን የኢያሪኮን ግንብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሰባት ቀን መዞራቸው፣ በሰባተኛው ቀን ሰባት ጊዜ መዞራቸው፣ ካህናት ቀንደ መለከቱን እንዲነፉና ሕዝቡም እንዲጮሁ መታዘዛቸው
-የኢያሪኮ ከተማ ቅጥር መፍረሱ
-እስራኤላውያን እርም የሆነውን ከኢያሪኮ እንዳይወስዱ መታዘዛቸው
-ረዓብ ዘማ ከነዘመዶቿ ከኢያሪኮ መትረፏ

💝ምዕራፍ 7፦
-አካን ወልደ ከርሚ እርም በሆነው ነገር መበደሉና በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መቆጣቱ፣ በዚህም ምክንያት በጋይ ሰዎች መሸነፋቸው፣ እስራኤል አካን ወልደ ከርሚንን በድንጋይ ወግረው መግደላቸውና በእሳት ማቃጠላቸው
-ኢያሱ እስራኤላውያንን በመካከላችሁ እርም የሆነውን ነገር ካላጠፋችሁ ትሸነፋላችሁ ማለቱ

💝ምዕራፍ 8፦
-እስራኤላውያን የጋይን ከተማ መደምሰሳቸው
-ኢያሱ በጌባል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መሠዊያን እንደሠራና የእግዚአብሔርን ሕጉን ለእስራኤላውያን እንዳነበበ

💝ምዕራፍ 9፦
-የገባዖን ሰዎች ያረጀ ልብስ ለብሰው፣ የደረቀና የሻገተ ምግብ ይዘው ዋሽተው ኢያሱን እንዳታለሉት፣ ኢያሱም በኋላ እውነታውን ሲያውቅ እንደረገማቸውና በኋላ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቀራጮችና ውሃ ቀጂዎች እንዳደረጋቸው

💝ምዕራፍ 10፦
-አሞራውያን የአቅራቢያ ነገሥታቶችን ይዘው እስራኤልን እንደገጠሙና በእስራኤል እንደተሸነፉ
-እግዚአብሔር ኢያሱ ጠላቶቹን እስኪያጠፋ ፀሐይን ማቆሙ
-ኢያሱ ሌሎች ከተሞችንም አሸንፎ መያዙ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. እርም የሆነውን ነገር ከኢያሪኮ በቤቱ አስቀምጦ በዚህ ምክንያት እስራኤል በጋይ ሰዎች እንዲሸነፉ ያደረገው ሰው ማን ነው?
ሀ. አካን
ለ. ከርሚ
ሐ. ዘንበሪ
መ. ዛራ
፪. ያረጀ ልብስ ለብሰው የሻገተና የደረቀ ምግብ ይዘው ከሩቅ ሀገር መጣን ብለው ዋሽተው ኢያሱን ያታለሉትና ኢያሱም በኋላ ተንኮላቸውን አውቆ የእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቀራጮችና ውሃ ቀጂዎች ያደረጋቸው የየት ሀገር ሰዎች ናቸው?
ሀ. የኢያሪኮ
ለ. የገባዖን
ሐ. የጋይ
መ. የአሞራውያን
፫. ኢያሱ ጠላቶቹን እስኪያጠፋ እግዚአብሔር ፀሐይን በገባዖን ያቆማት ለስንት ቀን ነው?
ሀ. ለሦስት ቀን
ለ. ለሁለት ቀን
ሐ. ለአንድ ቀን
መ. ለሰባት ቀን

https://youtu.be/aXVuEhv-MeE?si=flZ2tGGUzNKArhab

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

10 Nov, 05:09


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 40🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፴፯
በተሾምክ በተሸለምክ ጊዜ ወዳጅህን አትዘንጋ ገንዘብንም ካገኘህ ስጠው፡፡ ለሴት የሚያስቀናትን ነገር አትናገር፡፡ የሰልፍንም ነገር ከፈሪ ጋር አትማከር፡፡ የትርፍን ነገር ከቅርብ ነጋዴ ጋራ አትማከር፡፡ የምጽዋትንም ነገር ከንፉግ ሰው ጋር አትማከር፡፡ ልጄ በሕይወተ ሥጋ ሳለህ ሰውነትህን በሥራ ፈትናት፡፡ የሚጎዳትንም ሥራ አውቀህ አታሠራት፡፡
🧡ምዕራፍ ፴፰
ባለመድኃኒቱን አክብረው፡፡ አንድም ቄሱን አክብረው፡፡ እግዚአብሔር መድኃኒትን ከምድር ፈጥሯልና፡፡ ልጄ ሕመምህን ቸል አትበል፡፡ አድነኝ ብለህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ እርሱም ያድንኻል፡፡ ኃጢአትን በንስሓ ተዋት፡፡ እጅህን ከመግደል ቃልህንም ከመበደል ከልክል፡፡ ልብህንም ከዐመፅ ሁሉ ንጹሕ አድርግ፡፡ ብኪ ወልድየ ላዕለ ዘሞተ፡፡ ወበከመ ግዕዙ ግበር ሎቱ ተዝካሮ፡፡ ልጄ ለሞተ ሰው አልቅስ እንደ ሀገሩም ልማድ አዝነህ መታሰቢያውን አድርግለት፡፡ እንደ ሀገሩም ልማድ አልቅስለት፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

09 Nov, 17:26


በመጀመሪያ እንኳን ለማኅሌተ ጽጌ የመጨረሻ ሳምንት አደረሳችሁ። በመቀጠል መጽሐፍ ቅዱስን በተከታታይ ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምረን እየተማማርን እንገኛለን። አምስቱን የሙሴ መጻሕፍት ተማምረን መጽሐፈ ኢያሱን ጀምረነዋል። ደግሞም እስከ ራእየ ዮሐንስ ድረስ እንማማረዋለን (በዚህ መልኩ እስከ ትንሣኤ እንደምንጨርስ ተስፋ አደርጋለሁ)። በቀን አምስት አምስት ምዕራፎች አጥንተን በቀኑ ካጠናናቸው ምዕራፎች ግልጽ ያልሆነልንን መጠየቅ ነው። ከዚያ የጥያቄዎች መልስ ምሽት ላይ ይለቀቃል።

ጥያቄያችሁ ግልጽ ይሁን። እንዲሁም ከዚህ ቀደም ከተማማርናቸው የተጠየቀውን መልሳችሁ አትጠይቁ። PDF በዚሁ የቴሌግራም ቻናሌ ስላለ መልሱን ከPDF ማግኘት ትችላላችሁ። ሁሉንም በየቦታው ስለምንማማረው ከየዕለቱ አምስት አምስት ምዕራፎች ውጪ የሆነ ጥያቄ አትጠይቁ። አንዳንዶች ደግሞ ጥያቄያችሁ በሌላ ሰው ጥያቄ ተካቶ ሊመለስ ስለሚችል ሙሉውን ለማንበብ ሞክሩ። ትምህርቱ በጽሑፍ በቴሌግራም ቻናሌና በፌስቡክ ይለቀቃል። በድምፅ ደግሞ በዩቲይብ ቻናሌ ይለቀቃል።

የሕይወት መጽሐፍ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን እናንብብ።

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

09 Nov, 16:58


የጥያቄዎች መልስ ክፍል 38

▶️፩. ኢያሱ ነቢይ ነው ወይንስ ንጉሥ?

✔️መልስ፦ ነቢይም ንጉሥም ተብሎ መጽሐፍ ላይ ተጽፎ አላገኘሁም። ኢያሱ ከሙሴ ቀጥሎ እስራኤላውያንን የመራ መስፍን ነው።

▶️፪. ኢያ.1፥1 ላይ ረዓብ ሰላዮችን በተቀበለች ጊዜ የጸደቀችው በሥራዋ [ያዕ.2፥25] ወይስ በእምነት [ዕብ.11:31]።

✔️መልስ፦ በእምነትም በምግባርም ነው። እምነቷ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ አሳልፎ ይሰጣችኋል ማለቷ ሲሆን። ምግባሯ ደግሞ ሁለቱን ሰላዮች ደብቃ በማዳኗ ይገለጻል።

▶️፫. ኢያ.5፥6 ላይ የሰባ ሊቃናቱ ቅጅ (septuagint [LXX]) እስራኤል በበረሃ የቆዩት 42 ዓመት ነው ይላል። ከዘኁ.32፥13 ላይ ግን አርባ ይላል። ለምን ተለያየ?

✔️መልስ፦ የሰባ ሊቃናቱን ቅጂ አላየሁትም ነገር ግን የግእዙ መጽሐፍ ቅዱስና ትርጓሜው ሁለቱም ተመሳሳይ ፵ ነው።

▶️፬. ኢያሪኮ ከዮርዳኖስ ማዶ ነው? ከሆነስ እነዚያ ሁለት ሰላዮች አእላፋት እስራኤል በተአምራት የተሻገሩትን ወንዝ እንዴት እነርሱ ተመላለሱበት? (ኢያ.፫፥፲፮)።

✔️መልስ፦ እንዴት እንደተመላለሱበት የተገለጸ ነገር አላገኘሁም። አላውቀውም። ኢያሪኮ ከዮርዳኖስ ማዶ ናት። በየትኛው ማዶ እንዳለች ግን ስላላየኋት አላውቅም።

▶️፭. በሕዝቡ መካከል ሆነው እግዚአብሔር ሙሴን ተናገረው እግዚአብሔርም ኢያሱን ተናገረው ይላል (ኢያ.4፥15)። እንዴት ብሎ ነው የሚያናግራቸው? ድምፅ አውጥቶ እንዳልል ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ይፈራሉ።

✔️መልስ፦ በምን መልኩ ያነጋግራቸው እንደነበረ ከዚህ ክፍል ስላልተገለጸ አላወቅሁም።

▶️፮. ''በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት በስፍር ሁለት ሺሕ ክንድ ያህል ይሁን በዚህ መንገድ በፊት አልሄዳችሁበትምና የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ ብለው አዘዙ'' ይላል። ይህ ሕግ በሐዲስ ኪዳንም ጸንቷል አይደል? ሁለት ሺህ ክንድ ሲል ምን ያህል ርቀት ይሆናል በሜትር? በበዓላት ላይ የምቸገርበት ጉዳይ ስለሆነ ነው።

✔️መልስ፦ ሁለት ሺ ክንድ ያው በክንድ መቁጠር ነው። ሁለት ክንድ አንድ ሜትር ቢሆን ወደ1000 ሜትር ገደማ ማለት ነው። በሐዲስ ኪዳን በዚህ ዙሪያ የተገለጸ ነገር አላገኘሁም። ነገር ግን ለክብረ ታቦት ከካህናት በኋላ ብንቆም መልካም ነው።

▶️፯. "ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎችን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ተከለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ" ይላል (ኢያ.4፥9)። ..."እስከዛሬ ድረስ በዚያ አሉ" ሲል ዛሬ ማለት አሁንም (እኛ በምንኖርበት በዚህ ጊዜም) አሉ ማለት ነው ወይስ ይህ መጽሐፍ እስከተጻፈበት ድረስ ነው?

✔️መልስ፦ ይህ መጽሐፍ ማለትም መጽሐፈ ኢያሱ እስከሚጻፍበት ዘመን ነበሩ ለማለት ነው። ጸሓፊ የጊዜውን ተናገረ።

▶️፰. "የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ" ይላል (ኢያ.5፥15)። ከላይ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ይላልና ያ የኢያሪኮ አጠገብ ስፍራ የተቀደሰ ነበር ወይስ የትኛውን ነው የተቀደሰ ያለው?

✔️መልስ፦ ለጊዜው መልአኩ ለኢያሱ የተገለጸበት ቦታ ስለሆነ ነው የተቀደሰ ነው የተባለው። በምሥጢር ደግሞ መተርጉማን የምትሄድባት ኢያሪኮ ጽንዕት ናትና ፍርሃትን ከልቡናህ አውልቅ (አርቅ/አጥፋ) ማለት እንደሆነ አትተዋል።

▶️፱. በቤቷ መስኮት ቀይ ፈትል ለምልክት እንድታስር ነገሯት (ኢያ.2፥18)። ምሥጢር ይኖረው ይሆን? ካለው ቢብራራ?

✔️መልስ፦ ለጊዜው እስራኤላውያን ሌሎችን ሲያጠፉ እርሷን እንዳያጠፏት መለያ እንዲሆናቸው ነው። መተርጉማን ደግሞ ይህንን በሥጋው በደሙ መስለውታል። ረዓብ ቀይ ፈትል በመስኮቷ አድርጋ ከጥፋት እንደዳነች ሁሉ ምእመናንም ንስሓ ገብተው ሥጋውን ደሙን ተቀብለው ለመዳናቸው ምሳሌ ነው።

▶️፲. የኤርትራ ባሕር እና ቀይ ባሕር አንድ ናቸው?
ወይስ የተለያዩ?

✔️መልስ፦ ባሕረ ኤርትራ እየተባለ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸው ቀይ ባሕር ነው። ስለዚህ አይለያዩም።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

09 Nov, 04:31


💗መጽሐፈ ኢያሱ ክፍል ፩💗

💗ምዕራፍ 1፦
-ኢያሱ እስራኤላውያንን ዮርዳኖስን አሻግሮ ምድረ ርስት ማግባቱ
-እግዚአብሔር ኢያሱን ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ እንዲሁ ከአንተ ጋር እኖራለሁ እንዳለው

💗ምዕራፍ 2፦
-ኢያሱ ሁለት ሰላዮችን በስውር ወደኢያሪኮ መላኩ
-ሰላዮቹ ረዓብ ወደምትባለዋ ዘማ ቤት መግባታቸው፣ የኢያሪኮ ሰዎች ሲፈልጓቸው ረዓብ እንደደበቀቻቸው
-ሰላዮች ቸርነት እንዲያደርጉላት ረዓብ መጠየቋ
-ሰላዮቹ ረዓብን ስንመጣ ቀዩን ፈትል በመስኮት እሰሪው እንዳሏት

💗ምዕራፍ 3፦
-እስራኤላውያን ሌዋውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ተነሥታችሁ ተከተሉት መባላቸው፣ በእናንተና በታቦቱ መካከል ሁለት ሺህ ክንድ ይሁን መባላቸው።

💗ምዕራፍ 4፦
-ሕዝበ እስራኤል ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ ለመታሰቢያ 12 ቀላል ድንጋዮችን እንዲያነሱና እንዲወስዷቸው መታዘዛቸው።
-የካህናት እግር ወደዮርዳኖስ ወንዝ ሲገባ የዮርዳኖስ ውሃ ደረቀና ሕዝቡ መሻገሩ፣ ሕዝቡ ተሻግሮ ከጨረሰ በኋላ ዮርዳኖስ መልሶ መሙላቱ

💗ምዕራፍ 5፦
-ኢያሱ የእስራኤልን ልጆች እንዲገርዝ መታዘዙ፣ በምድረ በዳ የተወለዱት ሁሉ አልተገረዙም ነበረና።
-መልአክ ለኢያሱ እንደተገለጸለትና ኢያሱም እንደሰገደለት (የጸጋ ስግደት)
-መልአክ ኢያሱን የቆምክበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ ማለቱ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ኢያሱ ኢያሪኮን ይሰልሏት ዘንድ ሰላዮችን በስውር ልኮ ነበረ። ሰላዮቹ ወደኢያሪኮ ሲገቡ ከማን ቤት ገቡ?
ሀ. ረዓብ
ለ. ርብቃ
ሐ. ራኄል
መ. ሣራ
፪. ኢያሱ ይሰልሏት ዘንድ ወደኢያሪኮ የላካቸው ሰዎች ስንት ናቸው?
ሀ. ዐሥራ ሁለት
ለ. ሁለት
ሐ. ዐሥር
መ. ስድስት
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የዮርዳኖስ ወንዝ እስራኤል እስኪሻገሩ ድረስ ደርቋል
ለ. ሰላዮች ከቤቷ ገብተው የነበሩባት ሴት እንዳትጠፋ ቀይ ሐር በመስኮት እንድታደርግ ነገሯት
ሐ. የዮርዳኖስ ወንዝ ሁሉም እስራኤላውያን ከተሻገሩ በኋላ መልሶ ሞልቷል
መ. ሁሉም

፬. እስራኤላውያን ታቦቱን ሲከተሉ በታቦቱና በእነርሱ መካከል ርቀቱ ምን ያህል እንዲሆን ታዘዙ?
ሀ. 400 ክንድ
ለ. 1000 ክንድ
ሐ. 2000 ክንድ
መ. 100 ክንድ

https://youtu.be/FueDllqUvmM?si=geawjNCde8-HGSly

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

09 Nov, 04:11


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 39🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፴፭
አለቃ አድርገው ቢሾሙህ ራስህን አታስታብይ፡፡ ለሰው ሁሉ ምሥጢርህን አትንገር፡፡ በየፈርጁ የሚነገር ነገር ደስ ያሰኛል፡፡ ሌላ ሰው ሲናገር ሳታስፈጽም ጠለፍ አድርገህ አትናገር፡፡ በቃልህ ተናግረህ አትበድል፡፡ ፈጣሪህን አመስግነው እርሱም በረከተ ሥጋንና በረከተ ነፍስን አብዝቶ ይሰጥሀል፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈራው ለሕጉ ይገዛል፡፡ በእግዚአብሔር ያመነ ሰው የሚያጣው የለም፡፡
🧡ምዕራፍ ፴፮
እግዚአብሔርን የሚፈራን ሰው ክፉ መከራ አያገኘውም፡፡ ቢያገኘውም ለፈተና ነው እንጂ በኃጢአቱ አይደለም፡፡ ከዚያውም ፈጥኖ ይድናል፡፡ ብእሲሰ ጠቢብ ያፈቅር ሰሚዐ መጻሕፍት፡፡ ብልህ ሰው መጻሕፍትን መስማት ይወዳል፡፡ የእህልን ሁሉ ጣዕም ጉረሮ ለይቶ ያውቀዋል፡፡ እንደዚህም ሁሉ የብልህ ሰው ልቡ የሐሰትን ነገር ለይቶ ያውቃል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

08 Nov, 14:44


የጥያቄዎች መልስ ክፍል 37

▶️፩. "በቤተ ፌጎርም አቅራቢያ በናባው ምድር ቀበሩት" ይላል (ዘዳ.34፥6)። ሙሴን የቀበሩት እነማን ናቸው? ከዚያ "እስከዛሬ ድረስ መቃብሩን የሚያውቅ የለም" ይላል (ዘዳ.34፥7)።

✔️መልስ፦ ሙሴን የቀበሩት መላእክት ናቸው። እስከ ዛሬ ድረስ መቃብሩን የሚያውቅ የለም የተባለው ከሰው የሚያውቅ የለም ማለቱ ነው እንጂ የቀበሩት መላእክትስ ያውቁታል። መቃብሩ ያልታወቀውም እስራኤላውያን በዐፅሙ እንዳያመልኩ ነው።

▶️፪. “ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንድትረክሱ፥ ካዘዝኋችሁም መንገድ ፈቀቅ እንድትሉ አውቃለሁና። በእጃችሁም ሥራ ታስቈጡት ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ስላደረጋችሁ በኋለኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገኛችኋል” ይላል (ዘዳ.31፥29)። በኋለኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገኛችኋል የተባለውስ መቼ ነው?

✔️መልስ፦ ሙሴ ሊሞት ሲል ለእስራኤላውያን የተናገረው ቃል ነው። በኋለኛው ዘመን ያላቸው እርሱ ከሞተ በኋላ ስለሚመጣው ዘመን ነው። ክፉ ቢያደርጉ የተለያዩ መከራዎች እንደሚደርስባቸው ነው የነገራቸው። ለጊዜው በእርሱ ዘመን ያሉ ሰዎች እግዚአብሔርን ቢበድሉ የሚደርስባቸውን ሲያሳውቅ ፍጻሜው ግን ለሁሉም ሰው የተነገረ ነው። ማለትም ማንኛውም ሕዝብ ክፉ ቢሠራ መከራ እንደሚደርስበት የተነገረ ነው። በዚያን ዘመን ይህን የነገራቸው ስለትንሣኤ ሙታን ሳይሆን በዘመናቸው ስለሚገጥማቸው ነገር ነው።

▶️፫. “በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውኃ ስለ በደላችሁኝ፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል ስላልቀደሳችሁኝ” ይላል (ዘዳ.32፥51)። ይህ አንቀጽ ሙሴ ከንዓን እንዳይገባ ያደረገው በደል ነው። ታዲያ እኔ ግልጽ የማይሆንልኝ ለምን ምሕረት አልተደረገለትም? እሽ እግዚአብሔር ባወቀ ካልን አሁን ላይ መምህራን ጭምር የሰው ልጅ በምድር የበደለው ነገር ቢኖር የዛችን ቅጣት ወይም መከራ በምድር ሳይሞት በፊት ያገኘዋል ይላሉ ይህን እንዴት ያዩታል? ንስሓ ስንገባስ ለነፍሳችን ብቻ ነው በሥጋችንስ መከራ እንዳያገኘን አያደርግም?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር መሓሪ ነው። ፈታሒም ነው። ስለዚህ መሓሪነቱንና ፈታሒነቱን አስማምቶ እርሱ ባወቀ ለሙሴ የሚገባውን አድርጓል። ሰው ሁሉ በምድር ስለሠራው ኃጢአት በምድር ይከፈለዋል የሚለው ግን የተሳሳተ አስተምህሮ ነው። እንዲያ ከሆነ ነዌ ለምን በምድር ሳይከፈለው ቀረ?። ለሌሎች ትምህርትና ተግሣጽ እንዲሆን በምድር የሚከፈለው ሊኖር ይችላል፣ ሙሉ ቅጣቱን በሰማይ ያገኝ ዘንድ በምድር ምንም የማይቀጣ ሊኖር ይችላል። ምንም ሳይበድል በዚህ ምድር ሥጋዊ መከራ የሚያጋጥመው ሊኖር ይችላል። ኃጢአት ሠርቶ በምድር የተቀጣ ሰው በሰማይ ፍርዱ ሊቀንስለት ይችላል። በምድር ያልተቀጣ በሰማይ ጽኑ ቅጣት ሊጠብቀው ይችላል። ሁሉንም የሚያውቀው እግዚአብሔር ነው። ንስሓ መግባት ከሥጋም ከነፍስም መከራ ያድናል።

▶️፬. "እግዚአብሔር ከሲና መጣ በሴይርም ተገለጠ። ከፋራን ተራራ አበራላቸው ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ። በስተቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው" ይላል። የእሳት ሕግ ምንድን ነበረ?

✔️መልስ፦ የእሳት ሕግ ያለው ምኑን እንደሆነ አላወቅሁትም። በትርጓሜ ትምህርትም የእሳት ሕግ አይልም። መላእክት ወእለ ምስሌሁ ነው የሚል። ምናልባት መላእክትን እሳት ብሏቸው እንደሆነ የአማርኛው ትርጉም አላወቅሁም።

▶️፭. "የላሙንም ቅቤ የመንጋውም ወተት ከጠቦት ስብ ጋራ የባሳንንም አውራ በግ ፍየሉንም ከስንዴ እሸት ጋራ በላህ። ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ። ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ ሲባል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ የወይኑን ዘለላ ሲጨምቁት የሚገኘውን ፈሳሽ ለመግለጽ ነው።

▶️፮. "በዚያም ቀን ቍጣዬ ይነድድባቸዋል እተዋቸውማለሁ ፊቴንም እሰውርባቸዋለሁ። ለአሕዛብ መብል ይሆናሉ። በዚያም ቀን በእውነት እግዚአብሔር በእኛ መካከል የለምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገኘን እስኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገርና ጭንቀት ይደርስባቸዋል" ይላል (ዘዳ.31፥17)። ለአሕዛብ መብል ይሆናሉ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ለጠላቶቻቸው ምግብ ይሆናሉ ማለት ምግብ በእጅ እንደሚበላ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ ማለት ነው።

▶️፯. ዘዳ.32፥8 "ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ የአዳምን ልጆች በለየ ጊዜ፥ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቍጥር፥ የአሕዛብን ድንበር አቆመ። የአሕዛብ ድንበር እንደ መላእክት ቁጥር አደረገ ሲል ምን ለማለት ነው? ማለቴ የመላእክት ቁጥር ስለማይታወቅ።

✔️መልስ፦ መላእክት ብዙ እንደሆኑ ሁሉ ሰዎችንም አበዛኋቸው ማለት ነው።

▶️፰. በኦሪት የበግ ወተት ይጠጣል እንዴ? ስብስ ይበላል እንዴ? ዘዳ.32፥14 ላይ የበግ ወተት እና ስብ መገብኋችሁ ስለሚል።

✔️መልስ፦ ስብ አይበላም። የጠቦት ስብ ያለው ሥጋውን ነው። የበግ ወተትን ግን እንደሚጠጣ ከዚህ ተናግሮታል።

▶️፱. ዘዳ.33፥6 "ሮቤል በሕይወት ይኑር፥ አይሙት፤ ቍጥሩም ብዙ ይሁን" ይላል። ሮቤል ሲጀመር አልሞተም ወይ? እንዴትስ ይበዛል?

✔️መልስ፦ ሮቤል ሞቶ ነበረ። ነገር ግን በሕይወት ሳለ ከአባቱ ዕቅብት ደርሶ ስለነበረ ጌታ ሆይ ዕዳ አታድርግበት ሲል ነው (ይህ የፍትሐት ምሳሌ ነው)። በተጨማሪ ግን ከዚህ ሮቤል የተባለው ከእርሱ የሚወለደውን ሕዝብ (ነገድ) ነው።

▶️፲. ዘዳ.33፥22 "ስለ ዳንም እንዲህ አለ፦ ዳን የአንበሳ ደቦል ነው፤ ከባሳን ዘልሎ ይወጣል" ይላል። የአንበሳ ደቦል ይሁዳ አይደለም ወይ (ዘፍ.49፥9)።

✔️መልስ፦ ይሁዳን የአንበሳ ደቦል ብሎ የመረቀው ያዕቆብ ነው። ከዚህ ደግሞ ዳንን የአንበሳ ደቦል ብሎ የመረቀው ሙሴ ነው። ሁሉም ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። አንድ ቃል ለብዙ ነገሮች ምሳሌ መሆን ስለሚችል ምንም ችግር የለውም።

▶️፲፩. የእስራኤል ትምክህት ሰይፍ ነው ሲል ምን ማለት ነው (ዘዳ.33፥29)።

✔️መልስ፦ይህ ማለት በሰይፋቸው አሕዛብን ወግተው በረድኤተ እግዚአብሔር ተጠብቀው ይኖራሉ ማለት ነው።

▶️፲፪. ዘዳ.34፥10 "እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም" ይላል። እግዚአብሔር ለሙሴ እንዳንተ ያለ ነቢይ ከወገኖቻቸው አስነሣለሁ ብሎ የለምን (ዘዳ.18፥18)። የሚነሣው ነብይ ፍጻሜው ክርስቶስ ቢሆንም ለጊዜው ግን የሚነሣው ማን ነው?

✔️መልስ፦ ሙሴ ሊቀ ነቢያት ነው። ከነቢያት ሁሉ ታላቅ ስለነበረ እንደእርሱ ያለ አልተነሣም ተብሏል። እንደሙሴ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል የተባለ ኢያሱ ነው። ከዚህ እንደአንተ የሚለው በጥቂት መመሳሰል ስላለ ነው። በጥቂት መመሳሰልን በእንደ መግለጽ ደግሞ ልማደ መጻሕፍት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

08 Nov, 13:28


💙💙 የጠየቅኋችሁ ጥያቄዎች መልስ💙💙
፩. እስራኤላውያን ከግብጽ ተነሥተው ምድረ ርስት እስኪገቡ ምን ያህል ዘመን ተጓዙ?
ሀ. 40 ቀን
ለ. 40 ዓመት💖
ሐ. 19 ቀን
መ. 19 ዓመት
፪. እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተራራ ለእስራኤላውያን ሲገለጥ በጊዜው ምን ዓይነት ተአምር ተደርጓል?
ሀ. ከተራራው እስከ ሰማይ ድረስ እሳት ይነድ ነበረ
ለ. ድቅድቅ ጨለማ ነበረ
ሐ. አውሎ ነፋስ ነበረ
መ. ሁሉም💖
፫. በዕለተ ሰንበት ከሥራ እንዲያርፉ የታዘዘላቸው እነማን ናቸው?
ሀ. ባለቤቶች
ለ. አገልጋዮች
ሐ. እንስሶች
መ. ሁሉም💖
፬. የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብንጠብቅ ምን እንጠቀማለን?
ሀ. በሕይወት እንኖራለን
ለ. መልካም ይሆንልናል
ሐ. ዕድሜያችን ይረዝማል
መ. ሁሉም💖
፭. የመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ሲጠፉ ሙሴ እንደገና እንዲቀርጻቸው የታዘዙ ጽላቶች ስንት ናቸው?
ሀ. ሁለት የድንጋይ ጽላት💖
ለ. አራት የድንጋይ ጽላት
ሐ. ሦስት የድንጋይ ጽላት
መ. አምስት የድንጋይ ጽላት
፮. ስለእግዚአብሔር ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ኃያል ነው
ለ. በፍርድ የማያዳላ ነው
ሐ. አምላክ ነው
መ. ሁሉም💖
፯. አምላካችን እግዚአብሔር ስንት ነው?
ሀ. ሁለት
ለ. አንድ 💖
ሐ. አራት
መ. አምስት
፰. ለእስራኤል በረከት የተላለፈበት ተራራ ማን ነው?
ሀ. ጌባል
ለ. ገሪዛን💖
ሐ. ኮሬብ
መ. ሲና
፱. ዐሥራት የሚባለው ከስንት ስንት ነው?
ሀ. ከመቶው ሁለት
ለ. ከመቶው አንድ
ሐ. ከዐሥር አንድ💖
መ. ከዐሥር አምስት
፲. ከእንስሳት መጀመሪያ የሚወለደውን ለእግዚአብሔር መሥጠት እንደሚገባ ተነግሯል። ይህ ስጦታ ምን ይባላል
ሀ. ቀዳምያት
ለ. በኵራት💖
ሐ. ዐሥራት
መ. ብፅዐት
፲፩. እስራኤላውያን አዝመራ በተሰበሰበ ጊዜ ሰባት ቀን እንዲያከብሩት የታዘዘ በዓል ምን ይባላል።
ሀ. በዓለ ሠዊት
ለ. የመከር በዓል
ሐ. የዳስ በዓል💖
መ. በዓለ ፋሲካ
፲፪. ከሚከተሉት ውስጥ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በመካከላችሁ እንዳይገኝ ያላቸው የትኛውን ነው?
ሀ. ሟርተኛ
ለ. ጠንቋይ
ሐ. መተተኛ
መ. ሁሉም💖
፲፫. ከሚከተሉት ውስጥ ጦርነት በሆነ ጊዜ ወደሰልፉ መሄድ አይገባውም የተባለ የትኛው ነው?
ሀ. አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ሰው
ለ. ሚስት አጭቶ ያላገባ ሰው
ሐ. ፈሪና ልበ ድንጉጥ
መ. ሁሉም💖
፲፬. ከሚከተሉት ውስጥ እስራኤላውያን በብሉይ ኪዳን እንዲያደርጉት የታዘዘ ትእዛዝ የቱ ነው?
ሀ. ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ
ለ. ለወላጆቹ የማይታዘዝ ልጅ ይገደል
ሐ. ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ የተገኘ ይገደል
መ. ሁሉም💖
፲፭. አንዲት ለጋብቻ የታጨች ድንግል ሴት ብትኖርና ያች ሴት በራሷ ፈቃድ ከሌላ ወንድ ጋር በዝሙት ብትገኝ አብሯት የተኛው ሰው እና የእርሷ በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት ፍርዳቸው ምንድን ነው?
ሀ. በስቅላት መገደል
ለ. በድንጋይ ተወግረው መገደል💖
ሐ.በሰይፍ ተመትተው መገደል
መ. በግርፋት ቀጥቶ መተው
፲፮. በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት ሰው ሲሰርቅ የተገኘ ሰው ፍርዱ ምንድን ነበረ?
ሀ. መታሰር
ለ. መገደል💖
ሐ. መገረፍ
መ. ገንዘብ መክፈል
፲፯. በጌባል ተራራ ከተላለፉት 12 ርግማኖች መካከል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ወላጆቹን የሚያቃልል ርጉም ይሁን
ለ. ፍርድን የሚያጣምም ርጉም ይሁን
ሐ. ባልንጀራውን በተንኮል የሚመታ ርጉም ይሁን
መ. ሁሉም💖
፲፰. ከሚከተሉት ውስጥ ተገቢ ያልሆነውን ነገር ይረግሙ ዘንድ በጌባል ተራራ የቆሙትን ብቻ ስም ዝርዝር የያዘው የትኛው ነው
ሀ. ስምዖን፣ሌዊ፣ይሁዳ፣ይሳኮር፣ዮሴፍ፣ብንያም
ለ. ሮቤል፣ጋድ፣አሴር፣ዛብሎን፣ዳን፣ንፍታሌም💖
ሐ. ይሁዳ፣ሮቤል፣ዮሴፍ፣ዳን፣ይሳኮር፣ሌዊ
መ. ዮሴፍ፣ብንያም፣ንፍታሌም፣ስምዖን፣ጋድ
፲፱. በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት የዐሥራት ገንዘብ ለእነማን መሆን ይገባዋል?
ሀ. ለድኻዎች
ለ. ለሌዋውያን
ሐ. ለመበለቶች
መ. ሁሉም💖
፳. ሙሴ የሞተ የት ነው?
ሀ. በምድረ ግብጽ
ለ. በባሕረ ኤርትራ
ሐ. በሞዓብ ምድር💖
መ. ምድረ ርስት እስራኤል
፳፩. ስለ ልዑል እግዚአብሔር ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. እግዚአብሔር የታመነ ነው
ለ. እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ሕያው ነው
ሐ. እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው
መ. ሁሉም💖
፳፪. ሙሴ እስራኤላውያንን ሲመርቃቸው "የአንበሳ ደቦል" ያለው የማንን ነገድ ነው?
ሀ.ነገደ ጋድ
ለ. ነገደ አሴር
ሐ. ነገደ ዳን💖
መ. ነገደ ይሁዳ

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

08 Nov, 04:51


ኦሪት ዘዳግም ክፍል ፯

ምዕራፍ 31፦
-ኢያሱ በሙሴ ምትክ ሕዝቡን መርቶ ወደምድረ ርስት እንዲያስገባቸው መነገሩ

ምዕራፍ 32፦
-እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ፣ መንገዱ የቀና፣ የታመነ፣ ጻድቅና ቸር፣ ለዘለዓለም ሕያው እንደሆነ
-አባትን ሽማግሌን ስላለፈው ነገር መጠየቅ እንደሚገባ

ምዕራፍ 33፦
-ሙሴ እስራኤላውያንን መባረኩ
-ሙሴ በሞዓብ ምድር እንደሞተ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ሙሴ የሞተ የት ነው?
ሀ. በምድረ ግብጽ
ለ. በባሕረ ኤርትራ
ሐ. በሞዓብ ምድር
መ. ምድረ ርስት እስራኤል
፪. ስለ ልዑል እግዚአብሔር ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. እግዚአብሔር የታመነ ነው
ለ. እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ሕያው ነው
ሐ. እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው
መ. ሁሉም
፫. ሙሴ እስራኤላውያንን ሲመርቃቸው "የአንበሳ ደቦል" ያለው የማንን ነገድ ነው?
ሀ.ነገደ ጋድ
ለ. ነገደ አሴር
ሐ. ነገደ ዳን
መ. ነገደ ይሁዳ

https://youtu.be/eO8wQbo_WHE?si=KO2r2ChqCUnguH4K

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

08 Nov, 04:29


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 38🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፴፪
ምጽዋትን የመጸወተ ሰው ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕትን መሠዋቱ ነው፡፡ ፈቃዱ ለእግዚአብሔር ከመ ኢትግበር እኩየ ወሥምረቱ ከመ ትትገሐሥ እምዐመፃ፡፡ ሳትታጠብ ወደ ቤተ እግዚአብሔር አትግባ፡፡ የጻድቅ ሰው መሥዋዕቱ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል፡፡ ደስ ብሎህ እግዚአብሔርን አመስግነው፡፡ የድሀ ጸሎት ከደመና አልፋ ትሄዳለች ማለት ፈጥና ትሰማለች፡፡
🧡ምዕራፍ ፴፫
የሁሉ አምላክ አቤቱ ይቅር በለን፡፡ መፈራትህን አምልኮትህንም ሁሉ በአሕዛብ ሁሉ አሳድር፡፡
🧡ምዕራፍ ፴፬
በጎ ልብንና የጣፈጠን ምግብ የሚጠላ የለም፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው አይከብርም፡፡ በፍቅረ ንዋይ የተጎዱ ሰዎች ብዙዎች ናቸው፡፡ ከፍቅረ ንዋይ ንጹሕ የሆነ ባለጸጋ ክቡር ነው፡፡ ክፉ ማድረግ ሲቻለው ክፉ ያላደረገ ሰው ቢኖር የተመሰገነ ነው፡፡ ስታላምጥ ምላስህን አታጩህ ባልንጀራህ ይጸየፍሀልና፡፡ መጥኖ የሚበላ ሰው እንቅልፉ ጤና ነው፡፡ ደመ ወልደ እግዚአብሔርን ንስሓ ገብቶ በጊዜው መቀበል ያማረ ነው፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Nov, 14:38


የጥያቄዎች መልስ ክፍል 36

▶️፩. የመንግሥት ሠራተኛ የግል ሠራተኛ (ነጋዴ)፣ ከደመወዝ በተጨማሪ ደግሞ በአበል፣ በresearch፣ ወይም መጽሐፍ በመጽሐፍ፣ በስጦታ---ወዘተ ገቢ ይገኛልና ከየትኛው ነው አሥራት ሚወጣው? ለማን ነው የምንሰጠው? ለቤተክርስትያን መሆኑ ግልጽ ነው። ነገር ግን ብዙዎቹ ከመንፈሳዊነት ወጥተው ንግድን፣ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑን ማዘመንን (የእኛ ቤተ ክርስቲያን ከ---ብምን ያንሳል?) ሲባል አይቻለሁ። ወደገጠሩ እንኳ ሳንሄድ ከዚያው ከጎን ያለው ቤተክርስቲያን እና ካህናቱ እጅግ ተቸግረው እነሱ ግቢውን በሚሊዮን ብር ወጭ አድርገው እንደሠሩት አይቻለው---ሪፖርትም ሲያቀርቡ። መቼ ነው የምንከፍለው? እኔ ራሴ ችግረኛ ስለሆንኩ አሥራት እፈልጋለሁ፣ እናቴ አሥራት ትፈልጋለች---ስለዚህ የራሴን ወይም የቤተሰቤን ችግር ሳልፈታ አላወጣም፣ በዚህ እግዚአብሔርም አይጠይቀኝም እላለሁና። በተለይ ደግሞ በዚህ ኑሮ እና ጦርነቱ ችግሩን ባባባሱበት ወቅት። ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን አሥራት ከምን፣ ለማንና መቼ ነው የምናወጣው?

✔️መልስ፦ አሥራት ለሁሉም ምእመን የታዘዘ ነው። ለካህናት ሳይቀር የታዘዘ ነው። ከሚያገኙት ገንዘብ ከአሥር አንድ መስጠት ለሁሉም የተፈቀደ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ የጻፈም፣ ስጦታ የተቀበለም፣ አበል ያገኘም፣ ነጋዴም፣ መምህርም ሁሉም ከአገኙት ገንዘብ ከአሥር አንዱ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ነው። እኛ አሥራት ብለን ለቤተክርስቲያን ከሰጠን በኋላ የቤተክርስቲያኗ ካህናት አላግባብ ቢያባክኑት (ተገቢ ባልሆነ ነገር ወጪ ቢያደርጉት) ራሳቸውን እግዚአብሔር ይጠይቃቸው። እኛ ግን ምንም ክፉ ቢሆኑ አሥራት እናስገባለን። አሥራቱን እግዚአብሔርን አክብረን ለእግዚአብሔር ነው ያወጣነውና ክብር አይቀነስብንም። ምንም ችግረኞች ብንሆን ካገኘየው ገንዘብ ከአሥር አንዱ ለእግዚአብሔር ስለሆነ ቢቸግረንም መስጠት ይገባናል። ካህናት ከተቀበሉ በኋላ በየአጥቢያቸው ያሉ የተቸገሩ ምእመናን ካሉ ከተዋጣው አሥራት አስበው መሥጠት ይገባቸዋል። ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታ ብንሆን አሥራት የእግዚአብሔር ስለሆነ መክፈል መንፈሳዊ ግዴታችን ነው።

▶️፪. "ዓሥራት በምታወጣበት በሦስተኛው ዓመት የፍሬህን ሁሉ አሥራት አውጥተህ በፈጸምህ ጊዜ በአገርህ ደጅ ውስጥ ይበሉ ዘንድ ይጠግቡም ዘንድ ለሌዋዊው ለመጻተኛውም ለድኻ አደጉም ለመበለቲቱም ስጣቸው" ይላል። በሐዲስ ኪዳንስ አሥራትን ለመጻተኛውም ለድኻ አደጉም መስጠት ይቻላል?

✔️መልስ፦ አሥራት በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም የሚሰጥ ለቤተ እግዚአብሔር (ለቤተ ክርስቲያን) ነው። ለቤተ ክርስቲያን ከገባ በኋላ ካህናት ከፋፍለው ለራሳቸው፣ ለድኻዎች፣ ለመጻተኞች ይሰጣሉ። ስለዚህ እኛ ለቤተ እግዚአብሔር ብቻ እንሰጣለን። እንደሁኔታው ከፋፍለው መስጠት ግን የካህናት ድርሻ ነው።

▶️፫. "በመዓቱ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ኾነች ባዩ ጊዜ" ይላል። አዳማና ሲባዮ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዳማና ሲባዮ ከሰዶምና ገሞራ ጋር አብረው የጠፉ የሀገር ስሞች ናቸው።

▶️፬. "እግዚአብሔር ግን አስተዋይ ልብ የሚያዩ ዐይኖች የሚሰሙም ዦሮዎች እስከ ዛሬ ድረስ አልሰጣችሁም" ሲል ምን ለማለት ነው

✔️መልስ፦ ታላላቅ ተአምራት አድርጎ ቢያድናችሁም እናንተ ግን ይህንን ባለማስተዋላችሁ ረድኤትን ነሳኋችሁ ማለት ነው።

▶️፭. ዘዳ.27፣14 "ሌዋውያንም ከፍ ባለች ድምፅ ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገራሉ" ብሎ ርግማንን ይናገራል። ነገር ግን ሌዊ በገሪዛን ተራራ ሕዝቡን ከሚባርኩት መካከል ነው። እንዴት ከሚረግሙት መካከል ሌዋውያን ተጠቀሱ?

✔️መልስ፦ በቦታ አዎ ሌዋውያን ሕዝቡን ከሚባርኩት ጋር በደብረ ገሪዛን ነበሩ። ቃሉን የተናገሩትም ካሉበት ቦታ (ደብረ ገሪዛን) ሆነው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ነው። ሁለቱንም ወክለው የቡራኬውንም የርግማኑንም ቃላት የሚናገሩ ካህናት ስለሆኑ ሌዋውያን ናቸው። የርግማን ቃላትን ሲናገሩ በደብረ ጌባል ያሉት አሜን ይላሉ። የቡራኬ ቃላትን ሲናገሩ በደብረ ገሪዛን ያሉት አሜን ይላሉ።

▶️፮. ከአሥራ ሁለቱ ሕጎች ዕውሩን ከመንገድ ፈቀቅ የሚያደርግ ርጉም ይሁን ሲል ፈቀቅ ማለት ያስነሣ ማለት ነው? ቢብብራራ?

✔️መልስ፦ ትክክለኛውን መንገድ አስትቶ በተሳሳተ መንገድ ዕው*ርን የመራ ርጉም ይሁን ለማለት ነው።

▶️፯. ዘዳ.28፥24 በማይታዘዝ ላይ የሚደርስ እርግማንን ሲዘርዝር "....እስክትጠፋም ድረስ ከሰማይ አፈር ይወርድብሃል" ይላል። አፈር ከሰማይ አለ እንዴ? ትርጉሙ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከሰማይ አፈር የለም። ነገር ግን በነፋስ አቧራውን አስነሥቶ መልሶ ጭጋግ አድርጎ ያዘንበዋልና ይህን ለመግለጽ ነው።

▶️፰. ዘዳ.28፥63 "....እንዲሁ እግዚአብሔር ሲያጠፋህ፥ ሲያፈርስህም ደስ ይለዋል" ይላል። በውኑ እግዚአብሔር በእስራኤል መጥፋት ደስ ይለዋልን?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በትክክለኛ ፍርዱ ሁልጊዜም ደስተኛ ነው። በፍርዱ ኀዘን የለበትም። ስለዚህ በበደላቸው ምክንያት ሲቀጣቸውም ንስሓ ሲገቡ ይቅር ሲላቸውም በትክክለኛ ፍርዱ ስለሆነ ምንም ሕፀፅ የለበትም። ይህን ፈታሒ በጽድቅ መሆኑን ለመግለጽ የተነገረ ቃል ነው።

▶️፱. አሥራት ከፋዩ ለሚከፍለው መንፈሳዊ ተቋም አገልጋዮች እምነት ቢያጣባቸው ማለት የመንፈሳዊ አግልጋዮቹ ላይ የከፋ ያገጠጠ ገሐድ የወጣ መዋቅራዊ ኢ-ሃይማኖታዊ ምግባር በዘር፣ በቡድን፣ በጥቅም መተሳሰር ብሎም አንድ ሲኖዶስን ለሥጋዊ ጥቅም ለሚከፋፍል መዋቅር፣ ከፀረ ሃይማኖት መንግሥት ጋር ሲተባበር በፍሬው ቢታወቅ፣ ምዕመኑን ለነፍሱ ድኅነት (መዳን) መጨነቅ ሳይሆን ለገቢ ምንጭነት የሚጠቀም መዋቅራዊ አገልጋይ ግልጽ ሁኖ ቢያይና ሲረዳ አንድ ምዕመን አልከፍልም ቢል በደል ይሆንበታልን? መጽሐፍ ምን ይላል?

✔️መልስ፦ ተቀባይ ካህናት ምንም ያህል በደለኞች ቢሆኑ አሥራቱን መክፈል ለማንኛውም ምእመን ይገባዋል። አሥራቱን የሚከፍለው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለመጠበቅ ነውና። ካህናቱ በደለኞች ቢሆኑና የወጣውን አሥራት ተገቢ ባልሆነ ቦታ ቢያውሉት ራሳቸው ይጠየቁበት።

▶️፲. ዘዳ.20፥2 "አምላክህ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ቀዳምያትን ውሰድ፤ በእንቅብም አድርገው" ይላል። እንቅብ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እንቅብ ከአክርማ ከስንደዶ ወይም ከግራምጣ የሚሠራ የእህል መያዣ ወይም መስፈሪያ ነው።

▶️፲፩. ዘዳ.26፥10 "አሁንም እነሆ አቤቱ አንተ የሰጠኸኝን ማርና ወተት የምታፈስሰውን የምድሪቱን ፍሬ ቀዳምያት አቅርቤያለሁ። አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ስገድ" ይላል። የበኵራትና የቀዳምያት ልዩነት እንዴት ነው? ከዚህ ጋር ተያይዞ ምድርን አርሶ፥ እንስሳትን አርብቶ የማይኖር ነጋዴና የመንግሥት ሠራተኛ የሚከፍለው በኵራትና ቀዳምያት አለ? ካለስ ምኑንና እንዴት ነው የሚከፍለው? አሥራትስ እንዴት ነው የሚከፍለው? ማለቴ ነጋዴውም የመንግሥት ሠራተኛውም በየወሩ ወይስ ከዓመት አንዴ ነው አሥራት የሚያወጣው ቢብራራ?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Nov, 14:38


✔️መልስ፦ ቀዳምያት የሚባለው ከአዝርእት፣ ከማር፣ ከእህልና ከመሳሰሉት መጀመሪያ የደረሰውን ለቤተ እግዚአብሔር መስጠት ነው። በኵራት የሚባለው ከሰው፣ ከእንስሳት መጀመሪያ የተወለደውን ለእግዚአብሔር መስጠት ነው። የመንግሥት ሠራተኛ ከብት ከሌለው የከብት በኵራት አይጠየቅም። ባለው ነው የሚጠየቀው። አሥራት ግን ሁሉም ሰው ግዴታው ነው። ምክንያቱም በየትኛውም የሥራ መስክ ካገኙት ገንዘብ ከአሥር አንዱ የእግዚአብሔር ነውና። አሥራት ሲከፍል ደግሞ እንደተመቸው ነው ከዓመት አንዴም የዓመቱን መክፈል ይችላል። ወይም ከወር አንዴም የየወሩን በየወሩ መክፈል ይችላል።

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Nov, 13:17


ለመፍቀርያነ ግእዝ

ይህ የአፄ ገላውዴዎስ የእምነት መግለጫ ነው። በዘመኑ ሥነ ጽሑፍ ምክንያት አንዳንድ የሰዋስው ግድፈቶች ቢኖሩ እንኳ ሐሳቡን ለመረዳት ሞክሩ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Nov, 11:02


አንድ የራሴ መርሕ አለኝ። የማላውቀውን እጠይቃለሁ። የማላውቀውን ስጠየቅም አላውቀውም እላለሁ። የማውቀውን ደግሞ ማንንም ሳልፈራና ሳላፍር እናገራለሁ። አንዳንዱ ሰው በማስረጃ መሞገት ሲያቅተው የስድብ ክር ይመዛል። ክፉ ስም ያወጣልሀል። ያልሆንከውን ነህ ይልሀል። አንዳንዱ ደግሞ የተጻፈውን መሞገት ሲያቅተው ከተጻፈው ሐሳብ ውጭ ሌላ የራሱ ዐውድ ፈጥሮ ራሱ ለፈጠረው ዐውድ ምላሽ ያዘጋጃል። ወይም ሞራላዊ ዐውድ ይፈጥራል። ለምሳሌ ጦርነት ላይ ሆነን እንዴት ይህንን ታነሣለህ? ይልሀል። ነገር ግን ጉዳዩን በጉዳይነቱ አንሥቶ መሞገት እንጂ ሌላ ዓለም ውስጥ ገብቶ ጊዜ መፍጀት አይገባም።

ብዙ ጊዜ ለሐሰተኛ ክሶች፣ ከዐውድ ለአፈነገጡ ጉዳዮች መልስ አልሰጥም። የያዝኩትን ጉዳዩን ብቻ እያብራራሁ እቀጥላለሁ። ስለሁለት ምክንያት ይህን አደርጋለሁ። አንደኛው ለተሳሳተው ሰው የማርያም መንገድ ለመስጠት ነው። ሰው በዕውቀት እጥረት የተሳሳተ ነገር ቢናገር ወደፊት ሲያውቅ ይረዳዋል በማለት የው። ስሕተታቸውን በተከታታይ እነርሱ በጻፉት ልክ ብናገራቸው ወደፊት እውነታውን ሲያውቁት እልህ ይዟቸው ከድኅነት ወጥተው እንዳይቀሩ ስለምፈልግ ነው። አንዳንዶች ማስረጃ ስናቀርብባቸው እልህ ይዟቸው ሃይማኖተ አበው ተሳስቷል ይታረም ያሉ ስለገጠሙኝ ነው። አንዳንዶች ደግሞ የተጻፈውን ላለመቀበል ሌላ ዐውድ ፍለጋ ሲባክኑ ስላየሁ ነው። ሁለተኛው ለሐሰተኛ ክሶች መልስ አልሰጥም። ምክንያቴ በረከት አገኝባቸዋለሁ ብዬ ስለማስብ ነው። አንዳንዶች በአስተያየት መስጫውም ፎቶዬን ወይም የጻፍኩትን ጽሑፍ ለጥፋችሁ ተገቢ ያልሆኑ ቃላትን ስትጽፉ ዝም የምላችሁ በዚህ እሳቤ ነው። ከእናንተ እጥፍ የሆነ ቃል ብናገራችሁ ኀዘንን ትጨምራላችሁ ብየ ስለማስብ ዝም እላለሁ። በእናንተ ላይ ኀዘን ላለመጨመር ዝም እላለሁ። የክርስትና አስተምህሮም ይህ ነው። ሰዎች እውነታውን እስኪረዱ ድረስ ድካማቸውን መሸከም ነው።


እኛ የማናውቀው ጉዳይ ከገጠመን ከሚያውቁት መጠየቅ ነው እንጂ ስሕተት ነው ብለን መደምደም የለብንም። እኛ የማናውቀው ነገር ሁሉ ስሕተት ነው አይባልም። ማንኛውንም አስተምህሮ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት፣ በቅዱሳን ሊቃውንት አስተምህሮ መመዘን ይገባል። ለሁሉም ነገር መለኪያችን ኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ ይሁን። ማንንም ፈርቼ እንደማላውቅ የምታውቁኝ ታውቁኛላችሁ። ክፉ ቃል ስታነገሩኝ ዝም የምላችሁ ፈርቻችሁ ሳይሆን ብመልስላችሁ እኔም እናንተም ስለማልጠቀም ስለማትጠቀሙ ነው። ሁላችንም ስለምንናገረው ቃል በእግዚአብሔር ፊት ምላሽ እንሰጥበታለን። ዳኛው እርሱ ይዳኘናል። ይህንን አስበን መነጋገር ይገባል። እውነታውን በንጹሕ ኅሊና ለመረዳት እንሞክር። ከምቀኝነት ከቅንዐት ከዘረኝነት ከአንጃነት ንጹሕ እንሁን።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Nov, 05:59


መ/ር ሥሙር አላምረው Simur Alamrew በጥቂት ቃላት ብዙ ምሥጢርን ማስተላለፍ ዋና ጸጋቸው ነው። ይህ እርሳቸው ያዘጋጁት መጽሐፍ ድጋሚ በመታተሙ ደስታችን ወደር የለውም።

ይህን የሊቁን መጽሐፍ ገዝተን እንጠቀምበት። ሁለተኛ መጽሐፍ እንዲጽፉልን እንገፋፋቸው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Nov, 04:41


💝ኦሪት ዘዳግም ክፍል 6💝
💝ምዕራፍ 26፦
-ምድር ከምትሰጠው ፍሬ ሁሉ ቀዳምያትን ወደቤተ እግዚአብሔር መውሰድ እንደሚገባ
-ዐሥራትን ለሌዋዊ፣ ለመጻተኛ፣ ለድኻ፣ ለመበለት መስጠት እንደሚገባ

💝ምዕራፍ 27፦
-እስራኤላውያን ድንጋይ ወስደው በዚያ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጽፈው በጌባል ተራራ እንዲያስቀምጡትና በዚያም መሠዊያ እንዲሠሩ መታዘዛቸው
-ሕዝቡን ይባርኩ ዘንድ በገሪዛን ተራራ ላይ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍና ብንያም እንዲቆሙ መነገሩ። ይረግሙ ዘንድ ደግሞ በጌባል ተራራ ሮቤል፣ ጋድ፣ አሴር፣ ዛብሎን፣ ዳንና ንፍታሌም እንዲቆሙ መነገሩ
-ዐሥራ ሁለት ርግማኖች መነገራቸው

💝ምዕራፍ 28፦
-የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ከሁሉ በላይ ከፍ እንደሚያደርግ፥ በረከትን እንደሚያስገኝና ረድኤትን እንደሚያሰጥ
-የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አለመጠበቅ መርገምን፣ ረኃብን፣ በሽታን፣ ጭንቀትን፣ ቸነፈርንና የተለያዩ መከራዎችን እንደሚያመጣ

💝ምዕራፍ 29፦
-እስራኤላውያን በአርባው ዓመት ጉዟቸው የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ እንዲሁም እንጀራ እንዳልበሉ

💝ምዕራፍ 30፦
-ወደ እግዚአብሔር መመለስ እንደሚገባ
-እግዚአብሔር ኃጢአትን ይቅር እንደሚል
-እግዚአብሔር ያዘዘው ትእዛዝ ከባድ እንዳልሆነ
-እግዚአብሔርን መውደድ ቃሉን መስማት እንደሚገባ


💝የዕለቱ ጥያቄዎች💝
፩. በጌባል ተራራ ከተላለፉት 12 ርግማኖች መካከል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ወላጆቹን የሚያቃልል ርጉም ይሁን
ለ. ፍርድን የሚያጣምም ርጉም ይሁን
ሐ. ባልንጀራውን በተንኮል የሚመታ ርጉም ይሁን
መ. ሁሉም
፪. ከሚከተሉት ውስጥ ተገቢ ያልሆነውን ነገር ይረግሙ ዘንድ በጌባል ተራራ የቆሙትን ብቻ ስም ዝርዝር የያዘው የትኛው ነው
ሀ. ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍ፣ ብንያም
ለ. ሮቤል፣ ጋድ፣ አሴር፣ ዛብሎን፣ ዳን፣ ንፍታሌም
ሐ. ይሁዳ፣ ሮቤል፣ ዮሴፍ፣ ዳን፣ ይሳኮር፣ ሌዊ
መ. ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ስምዖን፣ ጋድ
፫. በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት የዐሥራት ገንዘብ ለእነማን መሆን ይገባዋል?
ሀ. ለድኻዎች ሐ. ለመበለቶች
ለ. ለሌዋውያን መ. ሁሉም

https://youtu.be/IqSI1HwQjj0?si=k__Pch1P94SuK-2e

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

07 Nov, 04:31


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 37🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፴፩
ደ*ን-ቆ*ሮ ሰው ሐሰተኛ ሕልምን በከንቱ ተስፋ ያደርጋታል፡፡ ከመ ዘይፀብጥ ጽላሎተ ወከመ ዘይዴግን ነፋሰ ከማሁ ዘይትአመን ሕልመ፡፡ ሕልምን የሚያምን ሰው ጉም ዘገን ነፋሰ ወግ ይባላል፡፡ ከእሪያ በግ አይወለድም፡፡ ሕልም ብዙዎችን ሰዎች አስቷል፡፡ እርሱንም ተስፋ አድርገው ጠፍተዋል፡፡ እውነተኛ ሕልም ፈጥኖ ይደርሳል፡፡ ብዙ መከራን የተቀበለ ሰው ጥበብን ያውቃል፡፡ ብዙ መከራን የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርትን ይማራል፡፡ እግዚአብሔርን የምትፈራው ሰውነት ሕይወተ ሥጋን ሕይወተ ነፍስንም ታገኛለች፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውን የሚያስፈራው የለም፡፡ እርሱም አይደነግጥም አለኝታው እግዚአብሔር ነውና፡፡ እግዚአብሔርን የምትፈራው የምታመልከውም ሰውነት የከበረች ናት፡፡ ሰርቀው ቀምተው የሚያቀርቡት መሥዋዕት ርኩስ ነው፡፡ ክፉዎችም ሰዎች ያቀረቡት መባ የተጠላ ነው፡፡ ባልና ሚስትን የለየ ሰው ባልንጀራውን እንደገደለ ያለ ነው፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Nov, 15:57


✔️መልስ፦ የሞተ ሰው በሞተበት ቀን እንዲቀበር ለመታዘዙ ይህ ጥቅስ መነሻ ይሆነናል። ሲቀበር ማስቆረብ ስለሚገባ ከቁርባን ውጭ ከሞተ በማግሥቱ መቅበር ነው። በፊት ከሞተ በዚያው መቅበር ነው። ነገር ግን ይህ የክርክር ምንጭ አይሆንም። ለፍትሐት በሚያመችበት ሁኔታ ካህናት በስምምነት በፈለጉት ጊዜ ሊያደርጉት ይችላሉ። የሟቹ አካል በሕያዋኑ ላይ ምንም ዓይነት ተጽእኖ የማይፈጥር ከሆነ ማለት ነው።

▶️፳. ዘዳ.22፣5 "ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና" ይላል። በዝርዝር ይህን ይህን አይልበሱ በማለት ፈንታ "ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ" ነው ያለውና ሴቶች "ሱሪ" እንዳይለብሱ ሲከለከሉ፣ ሱሪ የወንድ ስለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለህ የሚል ምላሽ ይሰጣሉ። ካልተሳሳትኩ ሌላ አገር ላይ ያሉ ክርስቲያን ወንዶችም ቀሚስ የዘወትር ልብሳቸው የሆኑ እንዳሉ እሰማለሁና ሴቶች የተከለከሉት ምን ዓይነት ልብሶችን ነው?

✔️መልስ፦ እንደየሀገሩ ባህል መልበስ ነው። በሀገሩ ባህል የወንድ የተባለ ልብስ ካለ ያንን ሴት እንዳትለብሰው መሆን ነው። በሀገሩ ባህል የሴት የተባለ ልብስ ካለ ያንን ወንድ እንዳይለብሰው መሆን ነው። ስለዚህ መለኪያችን የልብሱ ስም ሳይሆን ትውፊት ነው። በተጨማሪም ለዝሙት የማያነሳሳ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ጥብቅ ያለ ቀሚስ ሆኖ የሰውነትን ቅርጽ እያሳየ ለዝሙት የሚያነሳሳ ከሆነ አይፈቀድም። ስለዚህ መለኪያችን ከላይ በጠቀስኩት መልኩ ይሁን።

▶️፳፩. ዘዳ.22፣20-21 "ነገሩ ግን እውነት ቢሆን፥ በብላቴናይቱም ድንግልናዋ ባይገኝ፥ ብላቴናይቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያውጧት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባቷም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ" ይላል። ድንግልና በተለያየ ምክንያት ያለተራክቦ ሊፈርስ ይችላል። ይህ አጋጣሚ አሁን ላይ በተክሊል በተጋቡ ሰዎች ቢያጋጥም እንዴት ሊታይ ይችላል?

✔️መልስ፦ ድንግልና ማለት ተደንገለ ተጠበቀ ከሚለው የግእዝ ቃል የሚገኝ ሲሆን መጠበቅ ማለት ነው። ለዚህ መሥፈርቱ ግንኙነት ማድረግ አለማድረግ ነው እንጂ መድማት አለመድማት አይደለም። ግንኙነት ካደረጉ ባይደማም ሁለቱም ድንግልናቸውን አጡ ይባላል። አንዲት ሴት ከማንም ጋር ግንኙነት ሳታደርግ ከኖረች በየትኛውም ምክንያት ድንግል ናት። የአካሏ ጅማት ሳይሆን የሚታየው ከዚህ ቀደም ግንኙነት ማድረግ አለማድረጓ ነው። ስለዚህ ድንግል ሆነው ከተጋቡ በፍቅር መኖር ነው እንጂ ሌላ ጥርጣሬ አያስፈልግም።

▶️፳፪. መበለት የምትባለው ምን ዐይነት ሴት ናት? (ዘዳ.24፥17)።

✔️መልስ፦ አግብታ የፈታች ሴት ወይም ባሏ የሞተባት ብቻዋን የምትኖር ሴት ማለት ነው።

▶️፳፫. ዘዳ.25፥2 "የግርፋቱም መጠን እንደ ኀጢአቱ ይሁን ይልና ቁጥር ፫ ላይ ግርፋቱም ፵ ይሁን" ይላል። ኃጢአቱ ፵ ባይሞላስ?

✔️መልስ፦ የግርፋቱን መጠን የሚወስነው ዳኛው ነው። ነገር ግን ዳኛው ሲወስን የመጨረሻው የግርፋት መጠን አርባ ብቻ እንዲሆን ነው የታዘዘው። አርባ የተባለው የኃጢአቱ ብዛት ሳይሆን የግርፋቱ ቅጣት ብዛት ነው። እንደ ኃጢአቱ ሁኔታ ከ40 በታችም ሊገረፍ ይችላል።

▶️፳፬. ዘዳ.21÷12 "እርሷም ራሷን ትላጫለች ጥፍሯንም ትቈረጣለች። በሌላ ክፍሎች ግን ሴት ልጅ ፀጉሯን እንዳትላጭ ይናገራል ይህን እንዴት ይታያል አይቃረንም ወይ? ደግሞም ከሌላ ነገድ/ወገን እንዳይጋቡ ተነግሯል ይህስ እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ ሴት ልጅ ጸጉሯ ክብሯ ስለሆነ አለመላጨት ይገባታል። በኀዘን ምክንያትም እንዳትላጭ ከዚህ ቀደም ተነግሯል። ከዚህ ላይ ጥፍሯን ትቆረጥ ጸጕሯን ትላጭ የተባለው ግን ለጋብቻ ዝግጅት ነው እንጂ ለኀዘን አይደለም (አዲስ ወታደር ጸጕሩን እንደሚላጭ ያለ ነው)። እግዚአብሔር ይህንን ያዘዘበትን ምክንያት ግን አላውቀውም። በሐዲስ ኪዳን አንዲት ሴት ጸጉሯን ካሳደገች ሁልጊዜም በሻሽ መሸፈን አለባት። በሻሽ መሸፈን ካልፈለገች ግን መላጨት እንደሚገባት ተነግሯል።

▶️፳፭. ዘዳ.22 ÷12 "በምትለብሰው በልብስህ በአራቱ ማእዘን ዘርፍ አድርግ" ይላል። ለምን ዘርፍ እንዲያደርጉ ታዘዙ ምሳሌ አለው?

✔️መልስ፦ ሰማያዊ ዘርፍ እንዲያደርጉ ነው የታዘዙት። ምክንያቱ ደግሞ ሰማያዊ የሚመስል ባሕረ ኤርትራን እንዳሻገራቸው እንዲያስቡ ነው።

▶️፳፮. "ፍሬ ዘሩ የተቀጠቀጠ፣ አባለዘሩም የተቆረጠ፣ ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ" ይላል (ዘዳ.23፥1-2)። እነዚህ ሰዎች በራሳቸው ፈቃድ አይደለምና የተቀጠቀጠው፣ የተቆረጠው እና የተደቀሉት (እስካሁን ባየነው መሠረት ኃጢአት አልሠሩም) እና ምን አልባት ከትእዛዝ ባሻገር ምሥጢር ይኖረው ይሆን?

✔️መልስ፦ አዎ አለው። በጠቅላላው ነውረ ሥጋ ያለበት፣ ከአካሉ የጎደለ ነገር ያለበት ሰው እንዳይገባ በብሉይ ኪዳን ሥርዓት ተሠርቷል። ምክንያቱም ቤተ እግዚአብሔርን እንዳያስነቅፍ ነበረ።

▶️፳፯. ዘዳ.23፥19-20 ለሁለት ዓይነት ሰዎች የወለድ ነገር ይናገራል። ወለድ እና ክርስትና በሐዲስ ኪዳን (ወለድ ከዘመድ፣ ከባዕድ፣ ከባንክ---ጋር) እንዴት ይታያል።

✔️መልስ፦ ለተቸገረ ሰው ስናበድር ምንም ዓይነት ወለድን መቀበል አይገባም። ለዘመድም ለባዕድም። የባንኩ ጉዳይ ግን ከዚህ የተለየ እንደሆነ ከላይ ተመልሷል።

▶️፳፰. ዘዳ.25÷9 "ዋርሳይቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል፡ ስትል ጫማውን ከእግሩ ታውጣ፥ በፊቱም እንትፍ ትበልበት" ይላል። ይህ ጥቅስ ወንዱን በጋብቻ ማስገደድ አይሆንም ወይ?

✔️መልስ፦ በእርሷ ብቻ ተወስኖ እንዲኖር የሚያስገድድ ሕግ በብሉይ አልነበረም። ማስገደድ ቢሆን ኖሮ ይህ ሥርዓት ባልተሠራ ነበረ። በግድ አግባት ይባል ነበረ እንጂ። ከዚህ ግን አልተባለም። የጫማ ፈቱ ቤት እንዲባል የተወሰነውም ለወንድሙ ዘር ስላላስቀረለት ነው።

▶️፳፱. “አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል” ይላል (ዘዳ.24፥16)። በሌላ ሰው በደል እንደማንጠየቅ ይናገራል። ነገር ግን በአዳም እና በሔዋን የመጣ ኃጢአት ለልጅ ልጆች ተርፏል እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ የአዳም ኃጢአት ወደልጆቹ አልተላለፈም። የተላለፈ ኃጢአቱ ሳይሆን ፍዳው ነው። ይህ የሆነው ደግሞ የአዳም ውድቀት ባሕርያዊ ጉስቁልናን ስላስከተለ ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Nov, 03:23


💜ኦሪት ዘዳግም ክፍል ፭💜

💜ምዕራፍ 21፦
-ሰው ተገድሎ በሜዳ ቢገኝና ገዳዩ ባይታወቅ መደረግ ስላለበት ሥርዓት መነገሩ
-በሌዋውያን ቃል ክርክር ሁሉ ጉዳትም ሁሉ እንደሚቆም መነገሩ
-ስለተማረኩ ሴቶች፣ ስለበኵር ልጅ መነገሩ
-ለአባቱና ለእናቱ የማይታዘዝ ልጅ እንዲገደል መነገሩ

💜ምዕራፍ 22፦
-የጠፋ በግ ወይም በሬ ቢኖር ለባለቤቱ መመለስ እንደሚገባ መነገሩ
-ሴት የወንድን ልብስ ወንድም የሴትን ልብስ መልበስ እንደማይገባው መነገሩ
-ድንግልናን መጠበቅ እንደሚገባ መነገሩ
- ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ የተገኘ እንዲገደል መታዘዙ

💜ምዕራፍ 23፦
-በብሉይ ሕግ ፍሬ ዘሩ የተቀጠቀጠ፣ አባለዘሩ የተቆረጠና ዲቃላ ወደቤተ እግዚአብሔር እንዳይገቡ መነገሩ
-አሞናዊና ሞዓባዊ ወደእግዚአብሔር ቤት እንዳይገቡ መነገሩ
-ጠላቶችህን ልትወጋ በወጣህ ጊዜ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰውነትህን ጠብቅ መባሉ
-ከእስራኤል ሰዎች አመንዝራ እንዳይገኝ መነገሩ
-ወለድ መውሰድ ተገቢ እንዳልሆነ መነገሩ

💜ምዕራፍ 24፦
-ስለጋብቻ ፍቺ መነገሩ
-አዲስ ሚስት ያገባ ሰው ወደጦርነት መሄድ እንደማይገባው መነገሩ
-ሰው የሰረቀ ሰው እንዲገደል መታዘዙ
-የሠራተኛን ደመዎዝ መከልከል እንደማይገባ
-አባቶች ስለልጆቻቸው ፋንታ፣ ልጆችም ስለአባቶቻቸው ፋንታ መገደል እንደማይገባቸው

💜ምዕራፍ 25፦
-ለጻድቁ እንዲፈረድለት ለበደለኛ እንዲፈረድበት መነገሩ
-በደለኛን ከአርባ በላይ መግረፍ እንደማይገባ
-እህልን ስታበራይ በሬውን አፉን አትሰረው መባሉ
-በብሉይ ኪዳን ሕግ ወንድም ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ እንዲወልድለትና የተወለደው ልጅ በሞተው ወንድሙ አባት ተብሎ እንዲጠራ መነገሩ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ከሚከተሉት ውስጥ እስራኤላውያን በብሉይ ኪዳን እንዲያደርጉት የታዘዘ ትእዛዝ የቱ ነው?
ሀ. ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ
ለ. ለወላጆቹ የማይታዘዝ ልጅ ይገደል
ሐ. ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ የተገኘ ይገደል
መ. ሁሉም
፪. አንዲት ለጋብቻ የታጨች ድንግል ሴት ብትኖርና ያች ሴት በራሷ ፈቃድ ከሌላ ወንድ ጋር በዝሙት ብትገኝ አብሯት የተኛው ሰው እና የእርሷ በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት ፍርዳቸው ምንድን ነው?
ሀ. በስቅላት መገደል
ለ. በድንጋይ ተወግረው መገደል
ሐ.በሰይፍ ተመትተው መገደል
መ. በግርፋት ቀጥቶ መተው
፫. በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት ሰው ሲሰርቅ የተገኘ ሰው ፍርዱ ምንድን ነበረ?
ሀ. መታሰር
ለ. መገደል
ሐ. መገረፍ
መ. ገንዘብ መክፈል

https://youtu.be/_tgbjuT30rY?si=5E65kFAxqi5IquJr

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

06 Nov, 03:11


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 36🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፳፱
ምጽዋትን የሚመጸውት ሰው ለእግዚአብሔር ማበደሩ ነው፡፡ ለባልንጀራህ በተቸገረ ጊዜ አበድረው፡፡ ደግ ሰው ለወዳጁ ይዋሰዋል፡፡ ጠብንና ክርክርን ለማጥፋት መዋስ ደግ ነው፡፡ ለታናሹም ለታላቁም ሥራህን ቃልህንም በጎ አድርግ፡፡
🧡ምዕራፍ ፴
በልጁ መሠልጠን ኋላ ደስ ይለው ዘንድ ልጆቹን የሚወድ ሰው ቁጣንና ቅጣትን ቸል አይልም፡፡ ልጁን ያስተማረን ሰው ሁሉ በማስተማሩ ያመሰግኑታል፡፡ ልጁን ያስተማረ ሰው ጠላቱን ያስቀናዋል፡፡ በወዳጆቹም በጠላቶቹም ዘንድ በልጁ መማር ደስ ይለዋል፡፡ ልጅህን ብታደላድለው ብታቀማጥለው አንተኑ መልሶ ያዋርድሀል፡፡ ከታመመ ሰው ባለጸግነት በድህነት ያለ ጤነኛ ይሻላል፡፡ ልብህን አታበሳጭ፡፡ የሰው ሕይወቱ የልብ ደስታ ነው፡፡ የልብም ደስታ ዘመንን ያረዝማል፡፡ ብዙዎችን ሰዎች ኀዘን አጥፍቷቸዋል፡፡ ቅንዐትና ብስጭት ቁጣም ዕድሜን ያሳጥራሉ፡፡ አለጊዜውም ያስረጃሉ፡፡ ከሰው ሳትመክር የምትሠራው ሥራ አይኑር፡፡ ነገር ግን ቢመክርህም ሥጋዊን ደማዊንም ሰው ሁሉ አትመነው፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Nov, 18:48


የጥያቄዎች መልስ ክፍል 34

▶️፩. ''ሁልጊዜ አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራት ትማር ዘንድ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን የወይን ጠጅህንም የዘይትህንም ዐሥራት የላምህንና የበግህንም በኵራት ብላ'' ይላል። አሥራትና በኵራት ለእግዚአብሔር ነው መሥዋዕት የሚቀርበው ወይስ ሕዝቡ ይበሉታል?

✔️መልስ፦ በማኅበራዊ ሚዲያ አንዳንዶች እግዚአብሔር አይበላውም ስለዚህ ለእግዚአብሔር ተብሎ አሥራት ለምን ይወጣል ብለው የሚከራከሩ ሰዎች አሉ። ይህ ትልቅ ስሕተት ነው። እኛም እግዚአብሔር ይበላዋል ብለን አይደለም አሥራት በኵራትን የምናወጣው። እኛን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኙን ካህናት ናቸው። ስለዚህ የገባው አሥራትና በኵራት ለካህናት ምግብና ሌላም ነገር ያገለግላል ማለት ነው። አሥራት በኵራት ለእግዚአብሔር ቀረበ ሲባል ርስታቸው እግዚአብሔር ለሆኑ ካህናት ሆነ ማለት ነው።

▶️፪. "በዓመት ሦስት ጊዜ፥ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል" ይላል። (ዘዳ.16፥16) ይላል። ከዚህ በፊት ካጠናኋቸው በዓላት እና ቀናቱ ጋር ሳየው ተምታቶብኛል እና እስከሚውሉባቸው ቀናት ያስረዱኝ።

✔️መልስ፦ ፩ኛ. የፋሲካ በዓል ነው ይኸውም ከሚያዝያ 14 እስከ ሚያዝያ 21 ነው። የሚከበረው ያልቦካ ቂጣ እየተበላ ስለሆነ በዓለ ናዕት (የቂጣ በዓል) እየተባለም ይጠራል። ፪ኛ. የመከር በዓል ወይም በዓለ ሰዊት ነው። ይኸውም ከፋሲካ በኋላ ሰባት ሱባኤ ቆጥረን (7*7=49) ይሆናል በ50ኛው ቀን የሚከበር በዓል ነበረ። የመለከት በዓል ጥቅምት 1 የሚከበር በዓል ነበረ። የዳስ በዓል አዝመራ ከተሰበሰበ በኋላ ለሰባት ቀን የሚከበር በዓል ነበረ። ከጥቅምት 15 ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀን እስከ (ጥቅምት 22) የሚከበረ በዓል ነበረ።

▶️፫. "አምላክህ እግዚአብሔርም የሚጠላውን ሐውልት ለአንተ አታቁም" ይላል (ዘዳ.16፥22)። በዚህ ኃይለ ቃል አንጻር በየቤተክርስቲያኑ የፓትርያርክ/ጳጳሳት፣ ዘፋኞች፣ መሪዎች በመቃብራቸው ላይ የሚቆም ሐውልት እና በልዩ ልዩ ቦታም ለሀገርና ቤተክርስቲያን ውለታ የዋሉ ቅዱሳን ሰማዕታት እና አርበኞች ሐውልት በሐዲስ ኪዳን እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ ይህ አንቀጽ የአምልኮት (የጣዖት) ሐውልትን እንዳናቆም የሚከለክል አንቀጽ ነው። የመላእክት፣ የጳጳሳት፣ የዘፋኞችና የመሳሰሉት ሐውልት ግን በቤተክርስቲያን መሠራት የለበትም። ምክንያቱም የሃይማኖታችን አበጋዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ ይህን አላደረገም። ሐዋርያትም እንዲህ አላደረጉም። ከእነርሱ ያላገኘነውን ነገር ለምን እናደርጋለን። ከቤተክርስቲያን ውጭ ላሉ በአደባባይ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሐውልት መሠራቱ ግን ከሃይማኖት ጋር የሚገናኝ ስላልሆነና መልካም አበርክቷቸውን ሕዝቡ ጠይቆ እንዲረዳ በማሰብ ሊደረግ ይችላል። በዚህ ዙሪያ ሀገራዊ ስምምነት ነው የሚጠይቅ እንጂ ከእምነት ጋር አይያያዝም።

▶️፬. "በመንግሥቱም ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ ይህን ሕግ ለራሱ በመጽሐፍ ይጻፍ" ይላል (ዘዳ.17፥18)።
"ይህን ሕግ" ሲል ፲ቱ ትዕዛዛትን ማለቱ ነው ወይስ በዚያን ጊዜ ከ፬ቱ የሙሴ መጻሕፍት ለነገሥታት ማስተዳደሪያ ተብሎ የተውጣጣ እንደ ፍትሐ ነገሥት ያለ ነበረ?

✔️መልስ፦ ኦሪት ዘዳግምን ነው። ኦሪት ዘዳግም ከአራቱ ብሔረ ኦሪት የተወጣጣ ነውና። በኦሪት ዘዳግም አሥሩ ትእዛዛት ደግመው ተነግረዋል። ስለዚህ ንጉሡ አሥሩን ትእዛዛት ይጠብቅ ዘንድ ኦሪት ዘዳግምን ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ ይጽፋል ማለት ነው።

▶️፭. "ሌዋውያን ካህናት፥ የሌዊም ነገድ ሁሉ" ይላል (ዘዳ.18፥1)። ሌዋዊያን ካህናት አሮንና ዘሮቹን። የሌዊ ነገድ ያላቸው ደግሞ ጌድሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ እና ዘሮቻቸውን ነው አይደል?

✔️መልስ፦ ሌዋውያን ካህናት የሚባሉት የክህነትን መሥፈርት የሚያሟሉ ወንዶች የሌዊ ዘሮች ናቸው። የሌዊ ነገድ ሁሉ የሚላቸው ግን ሕፃናቱንም ሴቶችንም ሁሉንም ከሌዊ ወገን የሚወለዱትን ያካተተ ነው።

▶️፮. "ከተሸጠው ከአባቶቹ ከብት ዋጋ ሌላ እንደ ባልንጀሮቹ ከመብል ድርሻውን ይወስዳል" ይላል (ዘዳ.18፥6-8)። ይህ ሙሉ ገጸ ንባቡ አልገባኝም።

✔️መልስ፦ አንድ ሌዋዊ አስቀድሞ ከሚኖርበት ቦታ ወጥቶ ወደሌላ ቦታ ቢሄድ። ሲሄድ ቀድሞ ከነበረበት ድርሻውን ወስዶ ቢሄድ። ከሄደበት ሀገር ከድርሻው በተጨማሪ ከዚህ በኋላ ሲያገለግል ድርሻውን እየተቀበለ ማገልገል እንደሚገባው የሚገልጽ አነጋገር ነው።

▶️፯. ዘዳ.20፥5-7 "አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ፣ ወይን ተክሎ ፍሬውን ያልበላ እና ሚስት ያጨ" የተባሉት ሰዎች ከጦርነቱ እንዲመለሱ የተከለከሉት፥ በሙሉ ልብ መዋጋት ስለማይችሉ እንደፈሪዎቹ ለማኅበሩ የሽንፈት ምክንያት እንዳይሆኑ ነው ወይስ ሌላ ምሥጢር ይኖረዋል?

✔️መልስ፦ ስለርኅራኄ ነው። አዲስ ቤት ሠርቶ፣ ሚስት አጭቶ ሳያስመርቅ ሳያገባ ጦርነት ሄዶ ቢሞት ያሳዝናልና ለርኅራኄ ሲባል ጦርነት እንዳይሄዱ ሥርዓት ተሠርቷል። ትእምርተ ርኅራኄ ነው። የታጨችውም አገባዋለሁ ብላ አስባ በጦርነት ቢሞትባት ኀዘኗ ጽኑ ይሆናልና ነው።

▶️፰. “የመከራን እንጀራ፥ ቂጣ እንጀራ፥ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ” (ዘዳ.16፥3)። የመከራ እንጀራ ብላ ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የመከራ እንጀራ የተባለው ሊጡ ሳይቦካ እርሾ የሌለበት እንጀራ ነው። የመከራ የተባለው እስራኤላውያን በጉዞ ሳሉ በድካም ሳሉ ይመገቡት ስለነበረ። እርሱን እያሰቡና ከግብፅ መከራ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን እያሰቡ እንዲበሉት የታዘዘ ምግብ ነው። ቂጣም እንዲሁ ነው። ፋሲካን ሲያከብሩ ይህንን እየበሉ እንዲያከብሩ ታዝዘዋል።

▶️፱. "ፈረሶችን አያብዛ ሕዝቡንም ወደ ግብፅ እንዳይመልስ" ይላል (ዘዳ.17፥16)። ፈረሶችን አያብዛ ሲል ምን ማለቱ ነው ዙሪያቸው በጠላት ተከቦ እያለ? ወደ ግብፅስ የመመለስ ፍላጎት ነበራቸው?

✔️መልስ፦ ይህ አንቀጽ እስራኤላዊ ያልሆነ መሪ እንዳይሾሙ የታዘዙበት አንቀጽ ነው። ምክንያቱን ሲያስቀምጥ ደግሞ ለራሱ ፈረሶችን እንዳያበዛ የሚል ነው። ፈረስ በብዛት ለጦረኞች ያገለግል ነበረ። ስለዚህ የራሱን ጦር አብዝቶ እስራኤላውያንን ዳግመኛ ወደባርነት ቀንበር እንዳያስገባቸው ለማለት ነው። ወደ ግብፅ እንዳይመልስ የሚለው በግብር ነው። ግብፅ ሳሉ በባርነት ይገዙ እንደነበረ በባርነት እንዳይገዙ ለማለት ነው።

▶️፲. "ልቡም እንዳይስት ሚስቶችን ለእርሱ አያብዛ ወርቅና ብርም ለእርሱ እጅግ አይብዛ" ይላል (ዘዳ.17:17)። በብሉይ ኪዳን የነበሩ ነገሥታት ከዚህ የራቁ ነበሩ የፈጸሙት ነበሩ ወይ የብዙ ሚስቶች ጉዳይ ደግሞ ብዙ ጊዜ እነ ንጉሥ ሰሎሞን "ብዙ ሴት በማግባት ድንግል ማርያምን ከእነርሱ እንድትወለድ" ፍላጎት እንደነበራቸው ይነገራል እና አያይዘው ቢመልሱልኝ።

✔️መልስ፦ ንጉሥ ሰሎሞን ሴት ወዳድ እንደነበረ ተጽፏል። በዚህም ምክንያት ሴት ተከትሎ ጣዖት እስከማምለክ ደርሶ ነበረ። በኋላ ንስሓ ገብቶ እንደተመለሰ ይነገራል እንጂ። ሚስቶችን አያብዛ የተባለው ወደፊት ሰሎሞን እንደገጠመው እንዳይገጥመው ነው። ማለት እነርሱን ተከትሎ ጣዖትን እንዳያመልክ ነው። ብዙ ሚስት ቢያገቡም ግን በዚያን ዘመን የሚከለክላቸው ሕግ አልነበረም። ስለዚህ ድንግል ማርያም ከእነርሱ እንድትወለድ ከመፈለግ አድርገውት ከነበረም በጎ ሐሳብ ነው። በሐዲስ ኪዳን ግን አንድ ወንድ ለአንድ ሴት እንጂ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ማግባት እንደማይገባው ተገልጿል።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Nov, 18:48


▶️፲፩. ዘዳ.16፥8 ላይ ደግሞ ስድስት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ፤ ሰባተኛው ቀን ግን መውጫው ስለሆነ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በዓል ይሁን፤ ለነፍስም ከሚሠራው በቀር ሥራን ሁሉ አታድርግበት ይላል። የፋሲካው በዓል 7 ቀን አይደለም እንዴ? ከ7ቱስ የተለየ ክብር ያለው ቀን ነበር ማለት ነው? በቀሩት ስድስት ቀናትስ ለነፍስ ከሚውል ሥራ በቀር ይሠራባቸው ነበረ? በሐዲስ ኪዳን ስናከብር የሥጋ ሥራን በተመለከተ ቢያብራሩልኝ? ለምሳሌ በዘመናችን ቅዳሜ የታወቀ የገበያ ቀን ሁኗል። ይህ በዓልን አያስሽርምን? የሰንበት ውሃ ስለሚባለው ቢያብራሩልኝ ማለቴ ቅዳሜና እሑድ አይቀዳም ይባላልና። ታዲያ በዘመናችን ውሃውን በሰንበት ከማጠራቀሚያው ወደየቤታችን ቧንቧ ይላካልና እየቀዳን እንጠቀማለን። በውኑ ስንበትን ሽረናልን? ቢብራራ? ከሆነስ መፍትሔው? በሰንበት ምግብ አዘጋጅቶ መመገብስ ስንበትን መሻር ነውን? በሰንበት የማይሠሩ በሌሎች ዐቢይ በዓላትስ ይሠራሉን?

✔️መልስ፦ በሰባቱም ቀን በዓል የሚከበረው የፋሲካ በዓል ስለሆነ ነው። የመጨረሻዋን ቀን ደግሞ የበዓል መውጫ ስለሆነች በልዩ ሁኔታ እንዲያከብሯት ስላዘዘ ባዘዘው መልኩ ትከበራለች። ይህ ይበልጣል ይህ ያንሳል የሚል ግን አላገኘሁም። ሰባቱም ቀን በዓል ስለሆኑ ሥጋዊ ሥራን እንዳይሠሩባቸው ታዝዘዋል። በሐዲስ ኪዳንም ቅዳሜ፣ እሑድ፣ በጌታ በዓላት፣ በእመቤታችን በዓል እና በሚካኤል በዓል መንፈሳዊ ሥራ እንጂ ሥጋዊ ሥራ እንዳይሠራባቸው ታዝዟል። በሌሎች ቀን ግን ውግዘት የለም። መሥራት የፈለገ መሥራት ይችላል። የገበያ ቀንም ከላይ በጠቀስናቸው የበዓላት ዕለታት እንዳይሆን ፍትሐ ነገሥት ይገልጻል። ስለዚህ ማስተካከል ነው። ቅዳሜና እሑድ በዓል ስለሆነ በሌላው ቀን ቀድቶ ማስቀመጥ ይገባል። ነገር ግን ውሃ አልኖር ብሎ ቅዳሜና እሑድ ቢመጣ ቀድተን ማስቀመጥ እንችላለን። (የዕለት ምግብና መጠጥን ለማዘጋጀት አልተከለከለም)። ስለዚህ የሚበላውን እንጀራና ወጥ በሰንበት ቢያዘጋጅ ሰንበትን ሻረ አያሰኝም።

▶️፲፪. ዘዳ.16፥17 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ባዶ እጅህን አትታይም ሲል በአዲስ ኪዳንም ይሠራልና ቢብራራ? ማለቴ የግድ ወደ ቤተክርስቲያን ስንሄድ በበዓላትም በአዘቦትም ገንዘብ መያዝ አለብን?

✔️መልስ፦ አሥራት በኵራት መንፈሳዊ ግዴታ ስለሆነ ወደቤተ እግዚአብሔር ይዘን መምጣት ይገባናል። ባዶ እጅህን አትታይ ማለት አሥራት በኵራትህን ክፈል ማለት ነው። እነዚህን ከከፈለ በኋላ ራሱን ችሎ፣ ቤተሰቡን አስተዳድሮ፣ የተቸገሩ ዘመዶቹን ረድቶ የሚተርፈው ከሆነ የተቻለውን ያህል መብዓ ወደቤተክርስቲያን ይዞ ይመጣል። ካልተቻለው ግን ንጹሕ ልቡን ይዞ ወደእግዚአብሔር ቤት እንዲመጣ ለማለት ነው።

▶️፲፫. ዘዳ.16፥22 "አምላክህ እግዚ አብሔርም የሚጠላውን ሐውልት ለአንተ አታቁም" ሲል ቢብራራ። የሚወደውና የሚጠላው ሐውልት አለን? በዚያውም የዘመናችን የመቃብር ርስት ለቤተክርስቲያን ልማት እንቅፋት ሲሆን ተመልክቻለሁ። እረ እንዲያውም የጠብ መነሻም ሁኖ አይቻለሁና በእውነት ሐውልት የተፈቀደ ነውን? ትልቅ ቤት ተሠርቶ ርስቴ ነው ማለት ይቻላልን? አንዳንድ ካቴድራሎችም የመቃብር ቤት የገቢ ምንጭ እያደረጉ ነው ባለሀብት የመቃብር ርስት በገንዘብ እየገዛ አለና እንደ ሐዲስ ኪዳን አስተምህሮ መጽሐፍ ምን ይላል?

✔️መልስ፦ የሚጠላውን ሐውልት አታቁም ተብሏል። የሚወደው ሐውልት እንዳለ አልተገለጸም። ሐውልት መሥራትን ከጌታ ከሐዋርያት ከሊቃውንት ስላላገኘነው ተገቢ አይደለም መቅረት አለበት። የመቃብር ርስት የለም። ቤተክርስቲያን የሁሉ ናት። ሁሉም ይቀበርባታል እንጂ ባለርስቶች የሚቀበሩባት ሌላው የማይቀበርባት አይደለችም። ሲጀመር ቅጽረ ቤተክርስቲያን ባለቤትነቱ ለምእመናን ሁሉ ነው እንጂ በቅጽሯ ውስጥ የተለየ ርስት ያለው ምእመን መኖር የለበትም። ካለውም ስሕተት ነው መስተካከል አለበት።

▶️፲፬. ዘዳ.18፥10-11 የአሕዛብን ልማድ ሲገልጽ "ሞራ ገላጭ" ይላል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሞራ የሚባለው የቀለጠ የበሬ ወይም የበግ ስብ ነው። በዚህ የሚጠነቁል ሰው ሞራ ገላጭ ይባላል።

▶️፲፭. ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ ይላል። ሙታንን መሳብ ምን ማለት ነው? ሙታንን በምን ኃይልና ሥልጣን ነው የሚስቡት? ከአምላክ ፈቃድ ውጭ ዲያብሎስን ሙታንን መጥራት/መሳብ ይችላል ወይስ በምትሐት ነው ቢብራራ?

✔️መልስ፦ ሙታን ሳቢ የሚባለው የሞቱ ሰዎችን በምትሐት የሚጠራ ነው። ሙት አስነሺ የሚባሉት ናቸው። በትክክል ሙት የሚያስነሡ ግን አይደሉም። ሰይጣናት በምትሐት በመልክ የሞተውን ሰው መስለው ስለሚነጋገሩ ነው እንዲህ ያለው። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሞተውን ሰው ሥጋ ያቆሙትና የሞተው ሰው የተነጋገረ እንዲመስል ከንፈሩን እያንቀሳቀሱ በውስጡ ይናገራሉ። በአጭሩ በአጋንንት ኃይል የሞተውን የሚመስልን ሰው አስነሥተው የሚያነጋግሩ ናቸው። በትክክል የሞተን ማስነሣት የሚችል እግዚአብሔር ነው።

▶️፲፮. የአሕዛብን ልማድ ከአየን አይቀር በዘመናችን ደብተራ እየተባሉ ዐውደ ነገሥት የሚባል መጽሐፍ እየተጠቀሙ ኮከብ እየቆጠሩ ትውልዱን ከእግዚአብሔር የሚለዩት ነገር መሠረቱ ምንድን ነው? መጽሐፉስ የት ተገኘ? ማህበራዊ ሚዲያውም በዚህ የነገሠ ነውና በሰፊው ቢብራራ?

✔️መልስ፦ ለጥንቁልና፣ ለምትሐት፣ ኮከብ ለመቁጠር መሠረቱ ሰይጣን ነው። ይህን ከሚያደርጉ ሰዎችም መራቅ ይገባል። ዐውደ ነገሥት የጥንቆላ መጽሐፍ ነው። ደብተራ የሚባሉት ግን ቤተክርስቲያንን ሌት ከቀን በማኅሌት የሚያገለግሉ ሊቃውንት መጠሪያ ነው እንጂ ለጠንቋዮች መጠሪያ አይደለም። በደብተሮች በስማቸው የሚነግዱ አጭበርባሪዎችን መራቅ ይገባል።

▶️፲፯. ዘዳ.20፥1 ጀምሮ ስለጦርነት የተሰጠውን መመሪያ ያትታል። ይህ ምዕራፍ አትግደል ከሚለው ጋር አይጋጭም? ቢብራራ?

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን የተፈቀደ ግድያና ያልተፈቀደ ግድያ ነበረ። አንድን ሰው በጥላቻ ተነሣሥቶ መግደል ታላቅ ኃጢአት ነበረና አትግደል አለ። ነገር ግን በተገቢ ጦርነትና በፍርድ ጊዜ ሞት የሚገባውን በሕጉ መሠረት መግደል ኃጢአት አይሆንም ነበረ።

▶️፲፰. ዘዳ.19፥12 በባለደሙም እጅ አሳልፈው ይሰጡታል ይሞታልም ይላል ስለ ነፍሰ ገዳይ ሲገልጽ። ይህ በዘመናችንም በሰፊው ሰዎች ይፈጽሙታልና እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ በአመፅ አንድን ሰው የገደለ ሰው ወደመማፀኛ ከተሞች ቢገባም ከሞት አይድንም። በሕጉ መሠረት በአመፅ የገደለ ይገደል ነበረና። በሐዲስ ኪዳን ግን ጠላትህን ውደድ የሚል ሕግ አለና በይቅርታ ታርቆ መኖር ነው እንጂ ባለደም እየተባባሉ መገዳደል አይገባም።

▶️፲፱. “ሰባት ሳምንትም ትቈጥራለህ፤ መከሩን ማጨድ ከምትጀምርበት ቀን ጀምሮ ሰባት ሳምንት መቍጠር ትጀምራለህ" ይላል (ዘዳ.16፥9)። በዓለ ሰዊት የሚከበረው ከፋሲካ በኋላ ባለው 50ኛ ቀን ነው ወይስ መከር ማጨድ በተጀመረ በ50ኛው ቀን? ማጨድ በተጀመረ ከሆነስ ሰዎች ማጨድ የሚጀምሩት በተለያየ ቀን ቢሆን በዓሉም በተለያየ ቀን ሊከበር ነው?

✔️መልስ፦ ከፋሲካ በኋላ በ50ኛው ቀን ይከበራል። በትርጓሜ ቤት አንድ ወገን የሚባል ብሂል አለ። ስለአንድ ጉዳይ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ አገላለጾች ካሉ ለማስረዳት ነው። ሰባት ሳምንት ትቆጥራለህ የተባለውና መከሩን ማጨድ ከምትጀምርበት ቀን ጀምሮ ሰባት ሳምንት ትቆጥራለህ የተባሉት አንድ ወገን ናቸው። ሰዎች በየግላቸው የአጨዳ መርሐ ግብር ቢኖራቸውም በዓሉ ግን የሚከበረው አማካይ ጊዜን መሠረት አድርጎ ሁሉም በአንድ ቀን ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Nov, 18:48


▶️፳. ምስክሮች በአንድ እንዳይሆን የተከለከለው እና በሁለት ወይም በሦስት የሚጸናው ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ከአንድ ሁለት ከሁለት ሦስት ሰው የተሻለ ይታመናልና ነው። ይህም ሆኖ ግን ሦስቱም ሊዋሹ ስለሚችሉ የነገሩን እውነትነት ዳኛው በብዙ መንገድ ፈትኖ መረዳት አለበት። ሳይረዳና በቂ ማስረጃ ሳያገኝ በማንም መፍረድ አይገባውም።

▶️፳፩. ከእስራኤላውያን ጋር አብረው የሚኖሩ መጻተኞች ወይም እንግዶች በኦሪት ሕግ ቢያምኑ ኖሮ ተገርዘው እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ የሚመጡበት አግባብ ነበረ?

✔️መልስ፦ አዎ ከሌላ ሀገር የመጡ ሰዎች ቢኖሩ ተገርዘው እግዚአብሔርን የሚያመልኩበት ሥርዓት ነበረ።

▶️፳፪. ''አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና የበከተውን ሁሉ አትብላ ይበላው ዘንድ በአገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ትሰጠዋለህ ወይም ለእንግዳ ትሸጠዋለህ'' ሌሎች ያላመኑ የበከተውን ይበሉ ዘንድ ተፈቅዶ ነበር ማለት ነውን?

✔️መልስ፦ ለአላመነ ሰው ሕግ የለውም። ሕግ የሚሠራው ለአመነ ሰው ነው። ለተቆረጠ አንገት ጸጉር ምን ይሠራለታል። የፊቱ ውበትስ ምን ይጠቅመዋል!? ስላላመኑ ማንኛውንም ነገር ቢበሉ ያው ከአለማመናቸው ጋር ተደምሮ ይቀጡበት ነበረ። ለአመነ ግን በሥርዓቱ መቀጠል መንፈሳዊ ግዴታው ነበረ።

▶️፳፫. ዘዳ.20፥14 "ነገር ግን ሴቶቹንና ሕፃናትን እንስሶቹንም በከተማይቱም ያለውን ምርኮ ሁሉ በዝብዘህ ለአንተ ትወስዳለህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የጠላቶችህን ምርኮ ትበላለህ» ካለ በኋላ ከቁጥር 16-18 ደሞ ኃጢአት እንዳያሠሩህ አጥፋቸው ይላል። 14 ላይ የተቀመጡት ምን ዓይነቶቹን ነው አትግደል ማርክ የተባለው?

✔️መልስ፦ ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ ከብቶችን አትግደል ማርክ ተብሏል። ተዋጊ ወንዶችን ግን እንዲገድል ነው የታዘዘው።

▶️፳፬. "ሰው ከባልንጀራው ጋራ እንጨት ሊቈርጥ ወደ ዱር ቢኼድ፤ ዛፉንም ሊቈርጥ ምሣሩን ሲያነሣ ብረቱ ከእጀታው ቢወልቅ፤ ባልንጀራውንም እስኪሞት ድረስ ቢመታው፤ ደም ተበቃዩ ነፍሰ ገዳዩን በልቡ ተናዶ፟ እንዳያሳድደው፤ መንገዱም ሩቅ ስለኾነ አግኝቶ እንዳይገድለው፤ ከእነዚህ ከተማዎች ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖራል። አስቀድሞ ጠላቱ አልነበረምና ሞት አይገ፟ባ፟ውም" ይላል። አንድ ሰው አስቀድሞ ጠላቱ ያልነበረውን ሰው ቢገድል ኃጢአት አይደለም ማለት ነው?

✔️መልስ፦ በአመፅ ያይደለ ጥይት ተባርቆበት፣ ወይም ሳያስበው በሌላ መንገድ ሰው ቢሞትበት አስቦበት ስላልገደለው ሸሽቶ ወደመማፀኛ ከተሞች ገብቶ ይድናል ለማለት ነው። ጠላቱ ያልነበረውን ሰው አስቦ ሆን ብሎ ከገደለው ኃጢአት ይሆንበታል። ሳያስብ ከድንገት ቢሞትበት ግን ወደመማፀኛ ከተሞች ገብቶ መዳን ይችላል ለማለት ነው።

▶️፳፭. “ለሌዋውያን ካህናት፥ ለሌዊም ነገድ ሁሉ ከእስራኤል ጋር ድርሻና ርስት አይሆንላቸውም፤ በእሳት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕቱንና ርስቱን ይበላሉ” ይላል (ዘዳ.18፥1)። ካህናት ርስታቸው እግዚአብሔር እንደሆነ ይነገረናል ወይም ሀብታቸው ምዕመናን እንደሆኑ ይነገራል። በሐዲስ ኪዳንስ እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ በሐዲስ ኪዳንም ካህናት ሰውን ከእግዚአብሔር የሚያገናኙ ድልድዮች ናቸው። ስለሆነም መጽሐፍ የፈቀደላቸውን ይበላሉ። ይኸውም አሥራቱን በኵራቱን ተቀብለው እነርሱ ደግሞ ተግተው እያስተማሩ ይኖራሉ።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Nov, 15:52


#መድኃኔዓለም
፩. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርጋታው የተነሣ "የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጧፍ ክርም አያጠፋም" ተብሏል (ማቴ.12፥20)። የእርጋታ መምህር ነው።

፪. የትሕትና መምህር ነው።"ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ" እንዲል (ማቴ.11፥29)።

፫. የይቅርታ መምህር ነው። በመስቀል ተሰቅሎ ይቅርታን ለሰው ልጅ ያደለ እርሱ ነው። "ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ" እንዲል (ሉቃ.23፥34)።

፬. የሰላም፣ የፍቅር፣ የትዕግሥት፣ የሰማዕትነት በጠቅላላው የመልካም ሥራዎች ሁሉ መምህር እርሱ ነው። እርሱን ሁልጊዜ ማሰብ ለነፍስ ዕረፍት ነው። እኛም ዋና አብነታችን እርሱ ስለሆነ መልካም ሥራዎችን ሁሉ አባታችንን እርሱን መስለን እንሥራ።

ለዚህች ልዩ ቀን እንኳን አደረሳችሁ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Nov, 04:22


💝ኦሪት ዘዳግም ክፍል ፬💝

💝ምዕራፍ 16፦
-በዓለ ፋሲካን ማክበር እንደሚገባ መነገሩ
-ከፋሲካ በኋላ ሰባት ሳምንት ቆጥሮ፣ መከሩን ማጨድ ከጀመሩበት ቀን ሰባት ቀን ቆጥሮ የሰባት ሱባዔ በዓል ማድረግ እንደሚገባ (ይህ የመከር በዓል) ነው።
-ከአውድማና ከወይን ጭማቂ ፍሬ በተሰበሰበ ጊዜ ሰባት ቀን የዳስ በዓል ማድረግ እንደሚገባ
-በዓመት ሦስት ጊዜ (በቂጣ በዓል፣ በሰባቱ ሱባዔ በዓል፣ በዳስ በዓል) ወንድ ሁሉ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ እንዲታይ መነገሩ
-ለሕዝቡ ቅን ፍርድን መፍረድ እንደሚገባ፣ ጉቦ መቀበል እንደማይገባ፣ እውነተኛውን ፍርድ መከተል እንደሚገባ
-እግዚአብሔር የሚጠላውን (የጣዖት) ሐውልት አትትከል መባሉ።

💝ምዕራፍ 17፦
-ነውር ያለበትን በሬ ለእግዚአብሔር አትሠዋ መባሉ
-በሀገራቸው ጣዖት የሚያመልክ ቢገኝ እንዲገድሉት እስራኤላውያን መታዘዛቸው
-ሞት የሚገባቸው ሰዎች በሁለት ወይም በሦስት ምስክር መገደል ይገባቸዋል እንጂ በአንድ ምስክር መግደል ተገቢ እንዳልሆነ
-እስራኤላውያን ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ መባላቸው
-ማናቸውም ሰው ቢኮራ ወይም ዳኛውን ባይሰማ ሞት እንደሚገባው መነገሩ
-እስራኤላውያን ከራሳቸው መካከል ማንገሥ እንጂ ከሌላ ንጉሥን ማንገሥ እንደማይገባቸው መነገሩ
-በእስራኤል የነገሠ ንጉሥ ኦሪት ዘዳግምን ወስዶ በዕድሜ ዘመኑ ሁሉ እንዲያነበው መነገሩ፣ እግዚአብሔርን መፍራት እንደሚገባው መነገሩ

💝ምዕራፍ 18፦
-ለሌዋውያን ርስታቸው እግዚአብሔር ነውና ሌላ ርስት እንዳይኖራቸው መነገሩ
-ሟርተኛ፣ ሞራ ገላጭ፣ አስማተኛ፣ መተተኛ፣ ጠንቋይ፣ መናፍስትን ጠሪ በመካከላቸው እንዳይገኝ እግዚአብሔር ለእስራኤል መንገሩ
-እንደሙሴ ያለ ነቢይ እንደሚነሣ መነገሩ
-ከእግዚአብሔር ሳይላክ ተልኬያለሁ የሚል ነቢይ እንዲገደል መነገሩ

💝ምዕራፍ 19፦
-ሰው ባልንጀራውን ጠልቶ፣ ሸምቆ፣ በእርሱ ላይ ተነሥቶ ቢገድለውና በመማጸኛ ከተማዎች ቢማጸን የከተማው ሽማግሌዎች ይዘው በባለደሙ እጅ አሳልፈው ይሰጡትና እንዲሞት ይደረጋል መባሉ
-ድንበር ማፍረስ እንደማይገባ መነገሩ
-ነፍስ በነፍስ፣ ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በእግር መመለስ እንደሚገባ መነገሩ

💝ምዕራፍ 20፦
-በጦርነት ጊዜ የጠላትን ብዛት አይቶ መፍራት እንደማይገባ መነገሩ
-ጦርነት መሄድ ስለሌለባቸው አካላት መነገሩ
-ከጦርነት በፊት የሰላም አማራጮችን መጠቀም እንደሚገባና ስለጦርነት ሕግ መነገሩ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. እስራኤላውያን አዝመራ በተሰበሰበ ጊዜ ሰባት ቀን እንዲያከብሩት የታዘዘ በዓል ምን ይባላል።
ሀ. በዓለ ሠዊት
ለ. የመከር በዓል
ሐ. የዳስ በዓል
መ. በዓለ ፋሲካ
፪. ከሚከተሉት ውስጥ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በመካከላችሁ እንዳይገኝ ያላቸው የትኛውን ነው?
ሀ. ሟርተኛ
ለ. ጠንቋይ
ሐ. መተተኛ
መ. ሁሉም
፫. ከሚከተሉት ውስጥ ጦርነት በሆነ ጊዜ ወደሰልፉ መሄድ አይገባውም የተባለ የትኛው ነው?
ሀ. አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ሰው
ለ. ሚስት አጭቶ ያላገባ ሰው
ሐ. ፈሪና ልበ ድንጉጥ
መ. ሁሉም

https://youtu.be/1P3XK4xeTEw?si=ZDDjZuKYGYGj6Ps-

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

05 Nov, 04:16


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 35🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፳፯
ሥራውን መርምረህ ሳትረዳው ሰውን አታመስግነው፡፡ ጽድቅ ከሚሠሯት ጋር ትኖራለች፡፡ ኃጢአት የሚሠሯትን ሰዎች ታድናቸዋለች፡፡ ብልህ ሰው ዘወትር ጥበብን ያስተምራል፡፡ የባልንጀራውን ምሥጢር ያወጣ ሰው ባልንጀራው አያምነውም፡፡ እንግዲህም እንደልቡ የሚያምነው ወዳጅ አያገኝም፡፡ ወደሰማይ ደንጊያ የሚያጉን ሰው ተመልሳ ወደራሱ ትወርዳለች፡፡ ቁጣና ብስጭት የተጠሉ ናቸው፡፡ በክፉ ሰው ዘንድ ግን ተወደው ይኖራሉ፡፡
🧡ምዕራፍ ፳፰
መከራ ቢመጣበት ሳይቆጣና ሳይበሳጭ ለሚታገሥ እግዚአብሔር በቀሉን ይመልስለታል፡፡ ኃጢአቱንም ያስተሠርይለታል፡፡ ባልንጀራህን ይቅር ካልክ እግዚአብሔር ይቅር ይልሀል፡፡ ሞትን መፍረስንና መበስበስን አስበህ ሕጉን ጠብቅ፡፡ ትዕቢትን የሚያበዛት ሰው ቁጣን ያበዛታል፡፡ ቁጣን ባትታገሣት ትበዛለች ብትታገሣት ግን ትጠፋለች፡፡ የነገረ ሠሪ አንደበት አጥንት ይሰብራል፡፡ ሲኦል ኃጥኣንን እንጂ ጻድቃንን አታገኛቸውም፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Nov, 14:39


▶️፲፬. "አምላክህ እግዚአብሔር --- የመረጠው ስፍራ ከአንተ ሩቅ ቢሆንም--- እንደ ሰውነትህም ፈቃድ ሁሉ በአገርህ ደጅ ውስጥ ብላው" ይላል (ዘዳ.12፥21)። እንዲህ ሲል አምላክ የመረጠው ቦታ ሩቅ ከሆነ፥ "ከተቀደሰው ነገር፣ ስእለት፣ የሚቃጠል መሥዋዕትህን፥ ሥጋውንና ደሙን" ውጭ ያለውንና "ሰውነቱ የወደደችውን" በአገርህ ደጅ ውስጥ (ወይም ከሚመችህ ቦታ) መብላት (መሥዋዕት ማቅረብ) ትችላለህ እያለው ነው?

✔️መልስ፦ ሥጋው ደሙ የሚለው የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት ስለሆነ ከዚህኛው ጋር የሚታይ አይደለም። ነገር ግን እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ይመገቧቸው የነበሩ ምግቦችን ለምሳሌ የፋሲካውን በግ ባሉበት ቦታ አርደው በልተው እግዚአብሔርን ማመስገን ይችሉ እንደነበረ የሚገልጽ ነው። መሥዋዕትና ስእለት ነክ ጉዳዮች ግን እግዚአብሔር በመረጠው ቦታ ብቻ ይቀርቡ ነበረ።

▶️፲፭. "ሚዳቋና ዋልያ እንደሚበሉ እንዲሁ ብላው ንጹሕ ሰው ንጹሕም ያልሆነ ይብላው" ይላል (ዘዳ.፲፪÷፳፪)። ሚዳቋና ዋልያ ይበላሉ ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ ይበላሉ። ዋላ ያለው ዋልያ ነው።

▶️፲፮. “ነገር ግን ደሙ ነፍሱ ነውና፥ ነፍሱንም ከሥጋው ጋር መብላት አይገባህምና ደሙን እንዳትበላ ተጠንቀቅ” ይላል (ዘዳ.12፥23)። ነፍሳችን ደማችን ላይ ነው ያለችው? ካልሆነም የት ናት?

✔️መልስ፦ ደማችን ራሱ ነፍሳችን ነው። ለሰው ልጅ ሁለት ነፍስ አለው። ደማዊት ነፍስ እና ሕያዊት ነፍስ። ደማዊት ነፍስ የሚላት ለእንስሳት እንዳላቸው ያለች ነፍስ ስትሆን በሞት እንዳልነበረች ትሆናለች። በአጭሩ ደማችን ራሱ ነፍሳችን ነው። ነባቢት ነፍስ (ለባዊት ነፍስ) የምታድረው በደም ነው። የአንድ ሰው ደሙ ከሰውነቱ ፈሶ ካለቀ ነባቢት ነፍስ በሰውነት አትኖርም ትለያለች። ደማችን (ደማዊት ነፍስ) በአካላችን ሁሉ እንዳለች ሁሉ ነባቢት ነፍስም ደምን ምክንያት አድርጋ ከኵለንታ አካላችን ጋር ተዋሕዳ ትኖራለች።

▶️፲፯. “እኔ የማዝዝህን ነገር ሁሉ ታደርገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምር፥ ከእርሱም ምንም አታጕድል” ይላል (ዘዳ.12፥32)።
ሕገጋት ቀኖና ናቸው ካልን በየወቅቱ እንደአስፈላጊነቱ ይሻሻላሉ። ታዲያ በእርሱ ላይ አትጨምር፥ ከእርሱም ምንም አታጕድል ከሚለው ጋር አይጋጭም?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። በእርሱ ላይ አትጨምር ከእርሱም ምንም አታጉድል የተባለው ዶግማዊ አስተምህሮዎች ላይ ነው። ቀኖናት ግን ከዘመን ዘመን ከቦታ ቦታ ሊቀየሩ ወይም ሊታደሱ ይችላሉ። ለምሳሌ በሐዋርያት ዘመን ቤተክርስቲያን ስላልነበረ ሐዋርያት በየደረሱበት ያቆርቡ ነበረ። ቤተክርስቲያን ከተሠራ በኋላ ግን ቁርባን ታቦት ካለበት ወይም ከቤተክርስቲያን እንዲሆን ሆኗል። በአዳም ጊዜ እህት ወንድም ተጋብተዋል። በኋላ ግን እህት ወንድሟን ወንድምም እህቱን እንዳያገባ ሥርዓት ተሠርቷልና።

▶️፲፰. እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነው ማለት ምን ማለት ነው? ማመንዘር ምንድን ነው? ቆንጆ ሰውን አይቶ ይቺ ልጅ ቆንጆ ናት ወይም ታምራለች ብሎ ማሰብ ወይም መናገር እንደ ማመንዘር ይቆጠራል? እንዴት?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነው። ጎልማሳ በሚስቱ፣ ንጉሥ በመንግሥቱ ሲመጡበት እንደማይወድ ሁሉ እግዚአብሔርም በአምላክነቱ ሲመጡበት ይቀናል። ይህ ቅንዐት ግን ቅዱስ ቅንዐት ነው። ማመንዘር ማለት የራስ ያልሆነችን የሌላ ሚስት የሆነችን ሴት ለእኔ ብትሆን ብሎ መመኘት ነው። ይህ ኃጢአት ነው። ከዚህ ስሜት ወጥቶ የሰዎችን ቁንጅና አስቦ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርን ማመስገን ግን በደል አይሆንም።

▶️፲፱. "እንደ ሰማይ ዘመን በምድር ላይ ዘመናችሁ የልጆቻችሁም ዘመን ይረዝም ዘንድ በቤትህ መቃኖች በደጃፍህም ላይ ጻፈው" ይላል። የሰማይ ዘመን ሲል ምንን ለማጠየቅ ነው?

✔️መልስ፦ ሰማይ ከተፈጠረ ጀምሮ እስካሁን ብዙ ዘመን ሳያልፍ እንዳለና እንደኖረ ሁሉ የልጆቻችሁ እድሜም ይረዝማል ማለቱ ነው።

▶️፳. ከእንግዳ ላይ ያበደርከውን መፈለግ ትችላለህ በወንድምህ ላይ ያለውን ሁሉ ግን እጅህ ይተወዋል ይላል። ወንድምህ አና እንግዳ ያላቸው እነማንን ነው? ሰባተኛው ዓመትስ የዕዳ የምሕረት ዘመን አልነበረም ወይ? እንዴት እንግዳውስ ይክፈል ተባለ?

✔️መልስ፦ እንግዳ የሚላቸው እስራኤላዊ ያልሆኑ ነገር ግን በስደተኛነት ወይም በሌላ ምክንያት በእስራኤል የሚኖሩ ሰዎች ናቸው። ወንድምህ እየተባሉ የተገለጹት ደግሞ ሁሉንም ነገደ እስራኤል ነው። በሰባተኛው ዓመት ለወንድሞቹ ሞሕረት እንዲያደርግ ታዝዟል። ከቻለ ለእንግዶችም ምሕረት ማድረግ ይችላል። ነገር ግን ከእንግዶች ቢቀበልም በደል እንደማይሆንበት እግዚአብሔር ባወቀ ሥርዓት ሠርቶላቸዋል።

▶️፳፩. ዘዳ.11፥28 "በረከትም፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰሙ ነው፤ መርገምም ፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬ ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አማልክት ብትከተሉ ፥ ብታመልኳቸውም ነው" ይላል። መከተል እና ማምለክ አንድ አይደለም ወይ?

✔️መልስ፦ አንድ ወገን ናቸው። መከተልም ማምለክም አንድ ነው። እግዚአብሔርን ትታችሁ ጣዖታትን ፈጽማችሁ ብታመልኩ ትጎዳላችሁ ለማለት ነው። ተመሳሳይ መልእክት ያላቸው ቃላት ተከታትለው ሲመጡ አጽንዖት ለመስጠት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Nov, 14:39


የጥያቄዎች መልስ ክፍል 33
▶️፩. “ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አትንጩ፥ በዓይኖቻችሁም መካከል ራሳችሁን አትላጩ” ይላል (ዘዳ.14፥1-2)። ይህ ነገር በሀገራችን በስፋት የሚታይ ነገር ነው አሁንም። እና የአሕዛብ ልማድ ነበር ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ። ይበልጥ እንዲያውም አሁን በሐዲስ ኪዳን ለሞተ ሰው አካልን መንጨት፣ ጸጕርን መላጨት ተገቢ አይደለም። እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲኦልስ አሸናፊነትህ ወዴት ነው እያልን በሞት እንሳለቅበት ዘንድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ሞትን አጥፍቶልናል። ሞተ ክርስቶስ በሞተ ዚኣነ ከመ ይቅትሎ ለሞት በሞቱ እንዳለ ሊቅ። በሐዲስ ኪዳን ለሞተ ሰው ግብዒ ነፍስየ ውስተ ዕረፍትኪ (ነፍሴ ሆይ ወደዕረፍትሽ ግቢ) እያልን እየዘመርን ትንሣኤን ተስፋ በማድረግ እንቀብረዋለን እንጂ መላጨት ፊትን መንጨት አይገባም።

▶️፪. በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ከሌሎች (አሕዛብ) ጋር እንዴት ነው የሚኖር የነበረው? በተለይ ከመቻቻል እና አንዱ የሌላውን ከማክበር አንጻር ?

✔️መልስ፦ በኦሪት ሕግ ሌላ እምነት ያላቸው ሰዎች በእስራኤላውያን መካከል እንዲኖሩ አይፈቀድም ነበረ። በሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ሌላ እምነትን ሲሰብክ ቢገኝ በድንጋይ ተወግሮ ይገደል ነበረ። ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር የነበረው ግንኙነት ግን እነዚያም ሳይገቡ እነዚህም ሳይገፉ በያሉበት ጸንተው ይኖሩ ነበረ።

▶️፫. ዘዳ.14፥12 ላይ "ሊበሉ የማይገባቸው ግን እነዚህ ናቸው ንስር፣ ገዴ፣ ዓሣ አውጭ" ይላል። ዓሣ አውጭ ማለት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ዓሣ አውጭ የሚባለው እንደ ንስር ያለ ዓሣን ከባሕር አውጥቶ የሚበላ የወፍ ዝርያ ነው።

▶️፬. ዘዳ.12፥23 "ደምን እንዳትበላ ተጠንቀቅ ደሙ ነፍሱ ነውና ነፍስም ከሥጋ ጋር አይበላምና በምድር ላይ እንደውሃ አፍስሰው እንጅ አትብላው" ይላል። አሁንም ደም የሚበሉ አሉ ይህ እንዴት ይታያል።

✔️መልስ፦ ደም በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም እንዳይበላ ታዝዟል። ምክንያቱንም ከዚሁ ደሙ ነፍሱ ነውና ብሎ ገልጾታል። እስመ ነፍስ ተኀድር በደም እንዲል። ስለዚህ ባለማወቅ ሰዎች ደሙን አርግተው ቆልተው ሊበሉ ይችላሉ። ስሕተት ስለሆነ እንዳይበሉ ማስተማር ነው።

▶️፭. ዘዳ.11፥23 "እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣል ከእናንተም የሚበልጡትን የሚበረቱትንም አሕዛብ ትወርሳላችሁ" ይላል። አሕዛብን ትወርሳላችሁ የሚለው አልገባኝም ቢብራራ።

✔️መልስ፦ እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው የወረሱት ምድር ቀድሞ ብርቱዎች አሕዛብ ይኖሩበት የነበረ ነው። ይህን ለመግለጽ ነው።

▶️፮. ዘዳ.12፣23 "ነገር ግን ደሙ ነፍሱ ነውና፥ ነፍሱንም ከሥጋው ጋር መብላት አይገባህምና ደሙን እንዳትበላ ተጠንቀቅ" ይላል። ካቶሊኮች "ደም የሌለው ሥጋ የለም" በማለት ሥጋውን ብቻ ያቀብላሉ። ከዚህ ክፍለ ንባብ አንጻር ትክክል ናቸው ሊያስብል አይችልም?

✔️መልስ፦ እውነት ነው ሥጋ ደም አለው። ነገር ግን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዬ ደም ስላለው ሥጋዬን ብቻ ብሉ አላለም። ሁለቱንም ዘርዝሮ ሥጋዬን ብሉ፣ ደሜን ጠጡ ብሎ ተናገረ እንጂ። ስለዚህ ጌታ ካዘዘው ውጭ ሌላ ፍልስፍናዊና ሳይንሳዊ መንገድን ስለተጠቀሙ እንዲህ የሚያደርጉ ካሉ ትክክል አይደሉም።

▶️፯. የኦሪት ዘዳግም መጻፍ መሠረታዊ ዓላማው ምንድን ነው? ከዚህ በፊት ያየናቸውን መድገም እንጅ አዲስ ነገር ያለው አልመሰለኝም።

✔️መልስ፦ መሠረታዊ ዓላማው ሙሴ ለአበው የተናገረውን ሕግና ትእዛዝ ጠቅለል አድርጎ ለልጆቻቸው ለመንገር ነው። ከሌሎች የኦሪት ክፍሎች በተለየ ዘዳግም ትረካና ምግባር ላይ ያተኩራል። ከግብፅ ጀምሮ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ለልጆች ደግሞ መግለጽ ስላስፈለገ ተጽፏል።

▶️፰. ዘዳግም የተጻፈው ምድረ ርስትን ሳይወርሱ ነው (ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ ስላረፈ)። ታዲያ ምድረ ርስትን ስለመውረሳቸው እንዴት ርግጠኛ ሆኖ ጻፈ? ነው ሌላ ሰው ነው የጻፈው?

✔️መልስ፦ ኦሪት ዘዳግምን መጨረሻውን ክፍል ሙሴ ሳይሆን ሌላ ሰው (ኢያሱ) ጽፎታል። ምክንያቱም ሙሴም ሞተ ብሎ ሳይሞት ስለራሱ አይጽፍምና። መውረሳቸውን ግን ነቢይ ነውና ያለፈውንም የሚመጣውንም በእግዚአብሔር መንፈስ አውቆ አስረግጦ ይናገራል።

▶️፱. ይቅርታ ይደረግልኝና ሙሴ ከመወለዱ ከብዙ ዘመን በፊትስ (በሥጋ ያልነበረበትን ዘመን) ያለውን ከዘፍጥረት ጀምሮ እንዴት ሊጽፍ ቻለ?

✔️መልስ፦ ነቢይ ማለት በዘመኑ በጊዜው ያልነበረበትንና የማይኖርበትን ጉዳይ ከመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ የሚጽፍ የሚናገር የሚያስተምር ማለት ነው። ስለዚህ ሙሴ ስላልነበረበት ዘመን እግዚአብሔር የዓለምን አፈጣጠር ገልጾለት ጽፏል። ይህ ብቻ ሳይሆን ከሞተ በኋላ ስለሚሆነው የክርስቶስ መወለድም ስቅልተ ትሬእያ እስራኤል ለሕይወትከ ብሎ ተናግሯል።

▶️፲. "አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፥ ሕጉንም ሥርዓቱንም ፍርዱንም ትእዛዙንም ሁልጊዜ ጠብቅ" ይላል (ዘዳ.11፥1)። ሕግ፣ ሥርዓት እና ትእዛዝ ከ10ሩ ውጭ ያሉ ናቸው ወይስ ሌላ?

✔️መልስ፦ ሕግ የሚለው ከአሥሩ ትእዛዛት የመጀመሪያውን "ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልክ" የሚለው ነው። ትእዛዝ የሚላቸው ደግሞ ዘጠኙን ነው። ሥርዓት የሚለው ከእነዚህ ውጭ ያሉት እንደ መሥዋዕት አቀራረብ፣ አለባበስና የመሳሰሉት ናቸው። በሌላ አገላለጽ ሥርዓት የሚለው አሥሩንም ትእዛዛት በአንድ ላይ ነው።

▶️፲፩. "---እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው---" ይላል (ዘዳ.11፥4)።
"እስካዛሬ" የሚለው እስራኤላውያን ምድረ ርስት ከገቡ በኋላ ዳግመኛ የተነሱባቸው ጠላቶች ነበሩ ወይስ እነ ፈርዖንን ፍጹም አጠፋቸው ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ በእርግጥ እስራኤላውያን ምድረ ርስት ከገቡ በኋላም ዙሪያቸውን አሕዛብ ነበሩ። ስለዚህ በተለያዩ ጊዜያት እየመጡ መከራ እንዳደረሱባቸው ቀጥለን ከምናየው መጽሐፈ ኢያሱና ከመጽሐፈ መሳፍንት ተገልጿል። እግዚአብሔርም እስከዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው ማለት "እስከ ዛሬ" የሚለው ግን እነፈርዖንን ጠፍተው መቅረታቸውን ለመግለጥ ነው። እነፈርዖንንና ከፈርዖን በኋላ የተነሡ ጠላቶቻቸው መጥፋታቸውን ይገልጻል።

▶️፲፪. "---የምትጠብቋትና የምታደርጓት ሥርዓትና ፍርድ እነዚህ ናቸው" ይላል (ዘዳ.12፥1)። የሚጠብቁት እና የሚያደርጉት ፍርድ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሥርዓትና ፍርድ አንድ ወገን ናቸው። አሥሩን ትእዛዛት ለመግለጽ የተነገሩ ናቸው። በሌላ አገላለጽ ሥርዓት ሥርዓት ዘጠኙ ሕገጋት፣ ፍርድ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ የሚለው እንደሆነ መተርጉማን ገልጸዋል።

▶️፲፫. "---እኛ በዚህ ዛሬ የምናደርገውን ሁሉ አታደርጉም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ዕረፍትና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና" ይላል (ዘዳ.12፥8-9)። ሁለቱ ማለቴ ወደ ዕረፍቱና ርስታቸው ገና ስላልገቡ ሲያደርጉት የነበረው እና ከገቡ በኋላ ደግሞ እንደዚያ ያላይደለ ልዩ እንዲያደርጉት የታዘዙት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በጉዞ ሳሉ በጉዞው ምክንያት በዓል አከባበራቸው፣ መብዓ አሰጣጣቸውና በጠቅላላ አምልኮታቸውን ለመፈጸም የሚያከናውኗቸው ተግባራት ጥቂቶች ነበሩ። ምድረ ርስት ከጠቡ በኋላ ግን መብዓም ሲሰጡ አብዝተው የሚሰጡ ሆነዋልና ይህን ለመግለጽ ነው። በጉዞ ሳሉ አነስተኛ የነበረው ከጉዞ በኋላ በዝቶ መደረጉን ለመግለጽ ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Nov, 04:31


🧡ኦሪት ዘዳግም ክፍል ፫🧡

🧡ምዕራፍ 11፦
-የእግዚአብሔርን ሕጉን፣ ሥርዓቱን፣ ትእዛዙን በዘመን ሁሉ መጠበቅ እንደሚገባ
-እስራኤል እግዚአብሔር የሚጎበኛት ሀገር እንደሆነችና የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በእርሷ ላይ እንደሆነ መገለጡ
-እስራኤል ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ መታዘዛቸው
-የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መስማት በረከት፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አለመስማት መርገም እንደሆነ መገለጡ

🧡ምዕራፍ 12፦
-የጣዖት አማልክቶችን ማቃጠል እንደሚገባ
-እስራኤላውያን በምድር ሲኖሩ ሌዋውያንን ቸል ማለት እንደማይገባቸው
-ደምን መብላት እንደማይገባ

🧡ምዕራፍ 13፦
-ሕልም አላሚ ወይም ነቢይ ነኝ ባይ ሌሎች አማልክትን እንከተል ቢል መስማት እንደማይገባ፣ እግዚአብሔርን ለማስካድና ሌላ አማልክት እንዲያመልኩ ያደረገ ሰው ነቢይ ካለ እንዲገደል መነገሩ

🧡ምዕራፍ 14፦
-ለሞተ ሰው ፊትን መንጨት፣ ራስን መላጨት እንደማይገባ
-ርኩስን ነገር መብላት እንደማይገባ መነገሩ፣ ንጹሕ የሆነን መብላት እንደሚገባ
-ዐሥራት መስጠት እንደሚገባ

🧡ምዕራፍ 15፦
-ሰው ቢቸገር መርዳት፣ ማበደር እንደሚገባ
-ለሚለምን ሰው እጅን መዘርጋት እንደሚገባ
-በኵራትን ለእግዚአብሔር መስጠት እንደሚገባ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ለእስራኤል በረከት የተላለፈበት ተራራ ማን ነው?
ሀ. ጌባል
ለ. ገሪዛን
ሐ. ኮሬብ
መ. ሲና
፪. ዐሥራት የሚባለው ከስንት ስንት ነው?
ሀ. ከመቶው ሁለት
ለ. ከመቶው አንድ
ሐ. ከዐሥር አንድ
መ. ከዐሥር አምስት
፫. ከእንስሳት መጀመሪያ የሚወለደውን ለእግዚአብሔር መሥጠት እንደሚገባ ተነግሯል። ይህ ስጦታ ምን ይባላል
ሀ. ቀዳምያት
ለ. በኵራት
ሐ. ዐሥራት
መ. ብፅዐት

https://youtu.be/I8wA5yz2zSQ?si=mQOGo-rT5OP4UXx0

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

04 Nov, 04:27


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 34🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፳፭
ፍቅረ እግዚአብሔርንና ፍቅረ ሰብእንም በመያዝ ያማርሁ የተወደድሁም ሆኜ ጸናሁ፡፡ ትዕቢተኛ ድሃን፣ ንፉግ ባለጸጋን፣ ዕውቀት የሌለው ሴሰኛ ሽማግሌን ሰውነቴ ጠላች፡፡ ታላላቆች ሰዎች ጥበብን መማር ይገባቸዋል፡፡ የመምህራን ዘውዳቸው ብዙ ትምህርት ነው፡፡ ዘውድ እንዲያስከብር ያስከብራቸዋልና፡፡ መመኪያቸውም እግዚአብሔርን መፍራትና ማምለክ ነው፡፡ ልባም ሴትን ያገባ ሰው ክቡር ነው፡፡ በቃሉ ክፉ ተናግሮ ያልሳተ ሰው ያማረ ነው፡፡ ከቁስል ሁሉ ይልቅ የልብ ቁስል ይጸናል አይታገሙት አይበጡትምና፡፡ ከክፉ ሴት ጋራ ከመኖር ከአናብስትና ከአናምርት ጋራ መኖር ይሻላል፡፡ አራዊት ቢያጠፉት በሥጋ ብቻ ነው፡፡ እርሷ ግን በሥጋም በነፍስም ታጠፋዋለችና፡፡
🧡ምዕራፍ ፳፮
ደግን ሴት ባሏ ያመሰግናታል፡፡ ዘመኑም እጥፍ ይሆንለታል፡፡ ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች፡፡ ክፉ ሴት ለልብ ቊስል ነች፡፡ ሞገሳ ለብእሲት ያስተፌሥሖ ለምታ፡፡ የሴት መወደዷ ባሏን ደስ ያሰኘዋል፡፡ ደግ ሴት የእግዚአብሔር እድል ፈንታው ነች፡፡ ሰውንና እግዚአብሔርን የምታፍር ሴት በበጎ በረከት ላይ የሚገኝ በጎ በረከት ነች፡፡ ለምትታገሥ ሴት ዋጋ የላትም ማለት በወርቅና በብር አትገኝም፡፡ ደግ ሴት በቤቷ ውስጥ ሆና ለባሏ ብቻ ታጌጣለች፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Nov, 16:11


የዩቲይብ ቻናሌ ሰብስክራይበሮች 6000 ሞልታችኋል። 10,000 (አሥር ሺ) ሲሞላ ያን ተወዳጁን የነገረ ክርስቶስ ትምህርት በቪድዮ በታገዘ ገለጻና ጥያቄና መልስ (በተጠየቅ) እንማማረዋለን። እስከዚያው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በቀን በቀን አምስት አምስት ክፍል በድምፅ እየለቀቅሁበት እቆያለሁ። በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም የግእዝ ቋንቋን በተከታታይነት ተማምረንበታል። ገብቶ ከክፍል 1 ጀምሮ መልሶ ማዳመጥ ይቻላል።

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- We belong to Christ ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ ሼር በማድረግ ይተባበሩ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Nov, 15:31


PDF ቀጥሎ
ኦሪት ዘኍልቍ ላይ ለጠየቃችኋቸው ጥያቄዎች መልሶቻቸው በpdf ከዚህ ቀጥሎ ለቅቄዋለሁ። ጥያቄ በደንብ ጠይቁ። እስከ የዮሐንስ ራእይ ድረስ ያልገባችሁን እየጠየቃችሁ በቀን አምስት አምስት ምዕራፍ እያነበብን እንዘልቃለን። I hope እስከ ትንሣኤ እንጨርሳለን።

ጥያቄ ስትጠይቁ ደግሞ ግልጽ አድርጉት። አንዳንዶቻችሁ ጥቅሱን ትጠቅሱና አብራራልን ትሉኛላችሁ። ግልጽ ያልሆነላችሁ የትኛው ክፍል እንደሆነ ስለማላውቀው ግልጽ ያልሆነላችሁን ይህ ምንድን ነው በሉኝ። አንዳንዶች ደግሞ ወይ አልፋችሁ ወይም ደግሞ ባለፈው ከተማማርነው ስትጠይቁ አልመልስም። ምክንያቱም በወቅቱ መጠየቅ ነው። ጊዜ ለመቆጠብ። አንዳንዶች ደግሞ ከዚህ ቀደም የተጠየቀውን ትጠይቃላችሁ። ተመልሶ በpdf በዚሁ የቴሌግራም ቻናሌ ስለሚገኝ ከፍ ብላችሁ እዩት። አንዳንዶች ደግሞ ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ ትጠይቁኛላችሁ። መልስ አዘጋጅቼ ለመላክ እንዲያመቼኝ ቀጣዩን የዕለቱን ትምህርት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀሞራችሁ እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ባለው ብቻ ጠይቁኝ።

ያቋረጣችሁ ካላችሁም ለስንፍናና ለምክንያት እድል አትስጡት አሁን ካለንበት ጀምራችሁ እየተከታተላችሁ ጠይቁ። ሰፋፊ ክፍል የሆኑትን የብሉይ ኪዳን ክፍሎች እየተማማርናቸው ነው። ሐዲስ ኪዳን ላይ ስንደርስ ነገረ ክርስቶስን በስፋት እንማማራለን። የሐዲስ መሠረቱ ብሉይ ስለሆነ ብሉያቱን በደንብ እናጥና መጀመሪያ ብየ ነው እንጂ ከሐዲስ መጀመር እንችል ነበረ።

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Nov, 14:13


የጥያቄዎች መልስ ክፍል 32
▶️፩. ዘዳ.10፥20 "አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ እርሱንም አምልክ ከእርሱም ተጣበቅ በስሙም ማል" ይላል። በድጋሜ ዘዳ.6፥13 "አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ እርሱንም አምልክ በስሙም ማል" የሚል አንብቤያለሁ። ነገር ግን በየአብያተ ክርስቲያናት ላይ መማል ክልክል እንደሆነና መማል ቢያስፈልግ እንኳን እውነት ወይም ሐሰት ብለን እንድንምል ነው የምንማረው አይጋጭም ወይ?

✔️መልስ፦ አይጋጭም። መሓላ ሁለት መንገዶች አሉት። በሐዲስ ኪዳን ፈጽመህ አትማል ተብሏል። ነገርን እውነት ወይም ሐሰት ማለት እንደሚገባ ተገልጿል። ነገር ግን በሁለት ሰዎች መካከል ጠብ ተነሥቶ በጉዳዩ ዳኛ አዝዞን ማሉ ብንባል መማል ይፈቀዳል። ቅዱስ ጳውሎስ "ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፥ ለማስረዳትም የሆነው መሐላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል" እንዲል (ዕብ.6፥16)። ስንምል ግን በስመ እግዚአብሔር እንጂ በስመ ጣዖት መሆን እንደሌለበት ተገልጿል።

▶️፪. ዘዳ.7፥4 ላይ "እስራኤል ሆይ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው አምላክህም እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ፤ በፍጹም ኃይልም ውደድ ሲል ያዕቆብን ነው ወይስ እስራኤላውያን ነው እስራኤል ሆይ የሚለው?

✔️መልስ፦ ሁሉንም እስራኤላውያንን የሚያመለክት ቃል ነው። ለጊዜው ለእስራኤል ዘሥጋ ይነገሩ እንጂ ቃሉ ግን ለሰው ልጅ ሁሉ የተነገረ አምላካዊ እውነታ ነው።

▶️፫. ዘዳ.7፥13 "ላይ የሆድህን ፍሬ፤ የመሬትህንም ፍሬ፤ እህልህን ይባርክልሃል" ይላል የሆድህን ፍሬ ሲል ልጅህን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ የሆድ ፍሬ የተባሉ ልጆች ናቸው። መዝሙረኛው ዳዊት "ናሁ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር ውሉድ፤ ዕሤተ ፍሬሃ ለከርሥ" እንዳለ (መዝ.127፥3)።

▶️፬. "በፍፁም ልብህ፣ በፍፁም ነፍስህ እና በፍፁም ኃይልህ" የሚሉት ኃይለ ቃላት ቢብራሩልን?

✔️መልስ፦ ነፍስ የሚለው ኵለንታ አካለ ነፍስን ነው። በተለያየ አተረጓጎም ደግሞ ምኞትን ሐሳብን ሁሉ ያካተተ ሆኖ ይገኛል (የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግሥን ይመልከቱ)። ኃይል የነፍስ ግብረ ባሕርይ ነው። ልብ የነፍስ ከዊናዊ ግብር ነው። በምሥጢር ግን ሁሉም አንድ ወገን ናቸው። እግዚአብሔርን በኵለንታ ማንነታችን መውደድ እንዳለብን መግለጥ ነው።

▶️፭. “በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ” ይላል (ዘዳ.6፥8)። በዚህ ጥቅስ ምክንያት ልጠይቅና አሁን ላይ አንገታችን ላይ የምናስራቸው አንዳንዴ የመላእክት ስሞች አንዳንዴ ሌላ አይነት ክታቦች አግባብ ናቸው? መቼስ ነው የተጀመሩት ስለ ክታብ በሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያንስ ምን ይመስላል?

✔️መልስ፦ እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይዘነጉ በቤት መቃኖቻቸው በቤታቸው ደጃፍ እንዲጽፉ በተጨማሪም ክታብ አድርገው በአንገታቸው እንዲያሥሩ ተነግረዋል። አሁንም አንዳንዶች ፍቅራቸውን ለመግለጥ የቅዱሳን ሥዕል ያለበትን መስቀል፣ የእግዚአብሔር ቃል የተጻፈበት ልብስ ሲለብሱ ይስተዋላል። ኦሪት አፍኣዊ (ውጫዊ) ሕግ ስለነበረች ሰማዕትነቷም አፍኣዊ ነበረ። ሐዲስ ኪዳን ግን ውሳጣዊ ስለሆነች በአንገት ከመጻፍ ከፍ ባለ መንገድ ቃለ እግዚአብሔርን በልብ ሰሌዳነት ጽፎ እስከ ሞት መታመንን ትጠይቃለች። ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ክቡር የሆነውን ቃለ እግዚአብሔር ክቡር በሆነ ቦታ መጥራት ይገባል። ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን በክታብ መልኩ አስሮ ከመሄድ በልብ ሰሌዳነት ጽፎ መያዝ ይገባናል። መስቀልን ብቻ በአንገታችን አስረን በመስቀሉ የተደረገልንን ድንቅ ሥራ እያሰብን እንኑር።

▶️፮. "በውዕየት፥ በፈተና በምኞት መቃብርም እግዚአብሔርን አስቆጣችሁት" ይላል (ዘዳ.9:22)። "ውዕየት" ትርጉሙ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ውዕየት የግእዝ ቃል ነው። ውዕየ=ተቃጠለ ከሚለው የግእዝ ቃል ውዕየት የሚል ሳቢ ዘር ይወጣል። ሳቢ ዘር ደግሞ ብዙ ጊዜ በአድራጊና በተደራጊ ንዑስ አንቀጽ ይፈታል። ስለዚህ ውዕየት ማለት መቃጠል፣ ማቃጠል ማለት ነው።

▶️፯. ዘዳ.10፥22 «አባቶችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁንም አምላክህ እግዚአብሔር ብዛትህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አደረገ» ይላል። በሐዋ. ሥራ 7፥14 ላይ ደግሞ «ዮሴፍም አባቱን ያዕቆብንና ሰባ አምስት ነፍስ የነበረውን ቤተ ዘመድ ሁሉ ልኮ አስጠራ» ይላል። እንዴት ሊሆን ቻለ ቢያብራሩልን።

✔️መልስ፦ እነያዕቆብ ሰባ ሆነው ነው ወደ ግብፅ የወረዱት። ወደ ግብፅ ሲወርዱ ግን የኤርንና የአውናንን አፅም ይዘው ነው የወረዱት። በግብፅ ደግሞ ዮሴፍና ሁለቱ ልጆቹ ኤፍሬምና ምናሴ አሉ። ዮሴፍን፣ ኤፍሬምን፣ ምናሴን፣ ኤርን፣ አውናንን ጨምሮ ከቆጠረ 75 ይሆናል። እነዚህን ሳይቆጥር ከሆነ ደግሞ 70 ይላል። ስለዚህ እርስ በእርሱ አይቃረንም።

▶️፰. በፀሐይ የሚያበስሉ በሽንብራ ጥላ የሚጠለሉ የሚባሉት ረዐይቶች የዔናቅ ዘር ናቸውን?

✔️መልስ፦ አይደሉም። ረጃጅሞቹ በፀሐይ የሚያበስሉ አጫጭሮቹ በሽንብራ ጥላ የሚጠለሉ የተባሉ ከደብር ቅዱስ ከወረዱት ከሴት ልጆችና በምድረ ፋይድ ከነበሩት የቃኤል ልጆች ግንኙነት የተገኙ ናቸው። እነርሱም በማየ አይኅ ጠፍተዋል። የኤናቅ ዘር የተባሉት ግን ረጃጅሞችና ኃያላን ስለነበሩ ይህንን ለመግለጽ ረዐይት ተብለዋል። የስም መመሳሰል ነው እንጂ እንደነዚያ አይደሉም።

▶️፱. "እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ። ስብሰባ ተደርጎ በነበረበት ቀን እግዚአብሔር በተራራው በእሳት ውስጥ ሆኖ የነገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር" ሲል ከሁለቱ ጽላቶች ከአሥርቱ ትእዛዛት ውጭ የተጻፈ ነበር ወይ?

✔️መልስ፦ በጽላቶቹ ከአሥሩ ትእዛዛት ውጭ የተጻፈ አልነበረም። ነገር ግን እግዚአብሔር ለሙሴ የነገረው ቃል ሁሉ ምሥጢሩ ከአሥሩ ትእዛዛት የወጣ ስላልሆነ እንዲህ አለ።

▶️፲. ሙሴ ሁለቱን ጽላቶች መስበሩ ኃጢአት ሆኖ አልተቆጠረበትምን?

✔️መልስ፦ አልተቆጠረበትም። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጠላት የሆነውን ጣዖት አድቅቆበታልና።

▶️፲፩. ሙሴ የጥጃውን ምስል አቅልጦ አድቅቆ በተራራ በሚወርድ ወንዝ እንደጨመረው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። አቅልጦ እስራኤላውያንን እንዳጠጣቸውም ይነገራል ይህ እንዴት ይስማማል?

✔️መልስ፦ ሙሴ በጽላቱ ጣዖቱን ፈጭቶታል። የፈጨውን በውሃ በጥብጦ ሲያጠጣቸው ፍቅረ ጣዖት የነበረበት ሰው ከከንፈሩ የወርቅ ለምጽ ወጥቶበታል። በዚህ ተለይተው ተገድለዋል። በውሃ መበጥበጡን ሲያይ በተራራ በሚወርድ ወንዝ ጨመረው ብሏል።

▶️፲፪. ሙሴን ታቦት ሥራ ይለዋል። ታቦትና ንዋየ ቅድሳትን ባስልኤል እንዲሠራ ሙሴ ያዘዋል ይህ እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ በባለቤትነት ታቦትን እንዲሠራ የታዘዘ ሙሴ ነው። ሙሴ ግን መሥራት ስለማይችል ጠቢበኞቹ ባስልኤልና ኤልያብ ሠርተውለታል። የሰሎሞንን ቤተመቅደስ የሠሩት ሌሎች ሲሆኑ በአሠሪው በሰሎሞን እንደተጠራ ሁሉ የታቦትም እንዲሁ ነው። ሙሴ እንዳሠሪ እነባስልኤል እንደሠራተኛ ማለት ነው።

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

03 Nov, 12:35


#የፈርዖን #ንስሓ
ፈርዖን በእስራኤላውያን ላይ መከራ ባጸና ጊዜ መከራ መጣበት። መከራ ሲመጣበት መከራው ይራቅልኝ እንጂ እስራኤልን እለቃቸዋለሁ እያለ ይናገራል። ሙሴ ጸልዮ መከራውን ሲያርቅለት እንደገና እስራኤላውያን ይበድላቸው ነበረ። እንዲህ እያለ አንዴ ተጸጸትኩ ሲል አንድ ጊዜ ክፉ ሲሠራ ቆይቶ በመጨረሻ በኤርትራ ባሕር ሰጥሟል።

በፈርዖን ንስሓ ድኅነት የለበትም። ድኅነት ያለበት የጴጥሮስ ንስሓ ነው። ጌታውን መካዱ ትዝ ሲለው አለቀሰ። ከዚያ በኋላ ተዘቅዝቆ እስከ መሰቀል የደረሰ መታመንን ገንዘብ አደረገ። በአፍ ሰላም እያሉ በልብ መካድ ይሁዳዊ ክፉ ጸባይ ነው።

ጴጥሮሳዊ ንስሓን ገንዘብ እናድርግ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Nov, 23:47


💖ኦሪት ዘዳግም ክፍል ፪💖

💖ምዕራፍ 6፦
-እስራኤል ሆይ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ ነው ተብሎ መነገሩ
-እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ ውደድ መባሉ
-እናት አባት የእግዚአብሔርን ቃል ለልጆቻቸው ማስተማር እንደሚገባቸው መነገሩ
-በማናቸውም ሁኔታ የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማር እንደሚገባ መገለጹ
-እግዚአብሔርን መፍራት እርሱንም ብቻ ማምለክ እንደሚገባ መነገሩ
-እግዚአብሔርን መፈታተን እንደማይገባ

💖ምዕራፍ 7፦
-በዘመኑ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር የመረጠው ቅዱስ ሕዝብ መሆኑ
-የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ በረከትን እንደሚያስገኝ

💖ምዕራፍ 8፦
-ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንደማይኖር መገለጡ
-እስራኤላውያን እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ነገር ረስተው እንዳይበድሉ መነገሩ
-እግዚአብሔርን ማሰብ እንደሚገባ

💖ምዕራፍ 9፦
-ሙሴ እስራኤል በቀደመ ጉዟቸው የገጠማቸውንና የተደረገውን ነገር መተረኩ

💖ምዕራፍ 10፦
-እግዚአብሔርን መፍራት፣ እግዚአብሔርን መውደድ እንደሚገባ
-እግዚአብሔር አምላከ አማልክት፣ የጌቶች ጌታ፣ ታላቅ አምላክ፣ ኃያል፣ በፍርድ የማያዳላ መሆኑ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. የመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ሲጠፉ ሙሴ እንደገና እንዲቀርጻቸው የታዘዙ ጽላቶች ስንት ናቸው?
ሀ. ሁለት የድንጋይ ጽላት
ለ. አራት የድንጋይ ጽላት
ሐ. ሦስት የድንጋይ ጽላት
መ. አምስት የድንጋይ ጽላት
፪. ስለእግዚአብሔር ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ኃያል ነው
ለ. በፍርድ የማያዳላ ነው
ሐ. አምላክ ነው
መ. ሁሉም
፫. አምላካችን እግዚአብሔር ስንት ነው?
ሀ. ሁለት
ለ. አንድ
ሐ. አራት
መ. አምስት

https://youtu.be/xDmItKe08sY?si=dsJ6rxYRgKOALv0N

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

02 Nov, 16:46


የጥያቄዎች መልስ ክፍል 31

▶️፩. እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነው ሲባል ጣዖት ሲያመልኩ ይቀናል ለማለት ነው ወይስ ለጥፋተኞች ቀጭ አምላክ መሆኑን ለመግለጽ ነው?

✔️መልስ፦ አዎ ጥፋተኞችን እንደጥፋታቸው የሚቀጣ አምላክ ነው ማለት ነው። የፈጠራቸው አምላክ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ እንደነርሱ ፍጡር የሆነውን ማምለካቸው ተገቢ አለመሆኑን ለመግለጽ ነው። ቅዱስ ቅንዐትን እግዚአብሔር ይቀናል።

▶️፪. ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው ይላል በብሉይ ኪዳን ሌላ በዓላት አልነበሩም? ስድስት ቀን ሁሌም ሥራ ነበረ?

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን ሌሎችም በዓላት ነበሩ። በዓለ ሠዊት፣ በዓለ መጸለት፣ በዓለ ፋሲካ የሚባሉ በዓላት ነበሩ። በብሉይ ኪዳን እሑድ የሥራ ቀን ነበረ። ስድስቱን ቀን ከላይ የጠቀስናቸው በዓላትና ሌሎችም በዓላት ካልዋሉባቸው ይሠሩ ነበረ። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጸነሰባት፣ ትንሣኤን የተነሣባት ዕለት በመሆኗ እሑድንም ጨምረን እናከብራታለን።

▶️፫. እግዚአብሔር ስድስት ቀን ሥራ ያለው ዛሬም ነው ወይ። "የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነዉ" ካለውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተከሰሰው ስንበትን ሽሯል በመባል አልነበረም ወይ? ትንሽ ማብራሪያ ቢሰጥ።

✔️መልስ፦ አዎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰንበት ጌታ ነው። ሰንበትን ግን ሽሯል ያሉት በምቀኝነት ነበረ። አይሁድ ኦሪት ያላዘዘችውን ትእዛዝ በበዓላት አከባበር ላይ የራሳቸውን ወግ ጨምረው ያከብሩ ነበረ። በሰንበት ሰውን ማዳን ሰንበትን መሻር አይደለም። አይሁድ ግን ጌታን ሰንበትን ሻረ ያሉት የታመሙትን በዕለተ ሰንበት በመፈወሱ ነበረ።

▶️፬. “የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና” ይላል (ዘዳ.5፥11)። በተለይ በአሁኑ ዘመን ፈተና የሆነብን ነገር ይህ የአምላክን ስም በከንቱ ማንሳት ነው እናም ንስሓ ብንገባም አይምረንም ማለት ይሆንን? ደግሞስ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ንስሓ ከገባን ማንኛውም ኃጢአት ይቅር ይባልልናል። አዎ አሁን ማርያምን፣ ጊዮርጊስን፣ እግዚአብሔርን...ወዘተ እያሉ የሚምሉ ሰዎች ተበራክተዋል። ግን ስሕተት ነው መታረም አለበት። የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት ማለት ለምስጋና መጥራት ሲገባ በዋዛ ፈዛዛ፣ በቀልድ፣ በውሸትና በመሳሰሉት መጥራት ማለት ነው።

▶️፭. “ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር እርሱ ግን ያያታል እግዚአብሔርን ፈጽሞ ተከትሏልና የረገጣትን ምድር ለእርሱ ለልጆቹም እሰጣለሁ ብሎ ማለ” ይላል (ዘዳ.1፥36)። ከዚህ ላይ ለምን ኢያሱን አልጠቀሰውም?

✔️መልስ፦ ዝቅ ብሎ ቁጥር 38 ላይ ስለሚጠቅሰው።

▶️፮. አሥርቱ ትእዛዛት በዚያን ጊዜ ለነበሩት ለእስራኤላውያን ወይንስ ለሁላችንም በዚህ ዘመንም ለምንኖርም ሕግ ተደርገው ተሰጥተዋል? ሕግ 'ቀኖና ወይንስ ዶግማ?' ክርስቶስ በዚች ምድር ሲያስተምር አሥርቱን ትእዛዛት አስተምሯልን?

✔️መልስ፦ አሥሩ ሕገጋት አሁን ላለን ክርስቲያኖችም ዋና መመሪያና ሕግ ናቸው። ጌታ ሲያስተምር ትእዛዜን ጠብቁ ያላቸው በዋናነት አሥሩን ትእዛዛት ነው። እነዚህም ቁጥራቸው ከዶግማም ከቀኖናም ነው። ለምሳሌ አትስረቅ የሚለው ትእዛዙ ዶግማ ነው። የሰረቀ ይህን ያህል ጊዜ ይጹም ይስገድ ብሎ መወሰን ደግሞ ቀኖና ነው።

▶️፯. “እኔ የእግዚአብሔርን ቃል እነግራችሁ ዘንድ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር፤ እናንተ በእሳቱ ምክንያት ፈርታችኋልና፥ ወደ ተራራውም አልወጣችሁምና” ይላል (ዘዳ.5፥5)። በብሉይ ሰው እና መላእክት መካከለኛ (mediators)ነበሩን?

✔️መልስ፦ አዎ ነበሩ። ነገር ግን ምልጃቸው የሚያድን ከሥጋ መቅሠፍት ብቻ ነበረ። ሙሴ አማልዷል። መላእክትም ይማልዱ እንደነበረ ትንቢተ ዘካርያስ ላይ ተገልጿል።

▶️፰. “ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ፥ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ” ይላል (ዘዳ.4፥19)። ለሰማይ ሠራዊት (መላእክት) መስገድ አይቻልም እንዴ?

✔️መልስ፦ መላእክትንም ቢሆን እናከብራቸዋለን እንጂ አናመልካቸውም። አክብረን የጸጋ ስግደት እንሰግድላቸዋለን እንጂ የአምልኮት ስግደት አንሰግድላቸውም። የአምልኮት ስግደት የሚገባው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው።

▶️፱. “ታደርጉትም ዘንድ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን አሥሩን ቃላት ነገራችሁ፤ በሁለቱም በድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው” ይላል (ዘዳ.4፥13)። በሁለቱም ላይ አሥሩን ትእዛዛት ነው ወይስ እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ የተወሰኑትን በአንድ ገጽ ሌሎችን በሌላ ገጽ ጽፏቸዋል።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Nov, 18:21


💛ኦሪት ዘዳግም ክፍል ፩💛

💛ምዕራፍ 1፦
--የወንድሞቻችንን ነገር መስማት እንደሚገባ፣ በጽድቅ መፍረድ እንደሚገባ
-ፍርድ የእግዚአብሔር ስለሆነ ማዳላት እንደማይገባ
-ሙሴ ከቀድሞ ጀምሮ እግዚአብሔር ለእስራኤል ያደረገውን መተረኩ

💛ምዕራፍ 2፦
-ሙሴ በአርባው ዓመት የእስራኤል ጉዞ እግዚአብሔር ያደረገላቸውን መልካም ሥራ መግለጡ

💛ምዕራፍ 3፦
-ሙሴ ቀድሞ በጉዟቸው ጊዜ የተደረገውን ነገር ለሕዝቡ መተረኩ

💛ምዕራፍ 4፦
-ሕዝበ እስራኤል የተደረገላቸውን ነገር ለልጅ ልጆቻቸው እንዲነግሩ መነገራቸው
- እስራኤላውያን የተቀረጸን ምስል (ጣዖትን)፣ ፀሐይን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትን በጠቅላላው ፍጥረታትን እንዳያመልኩ መነገሩ
-እግዚአብሔር የሚበላ እሳት፣ ቀናተኛ አምላክ እንደሆነ መነገሩ
-እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ከበደሉና ጣዖት ካመለኩ የተለያዩ መከራዎች እንደሚደርሱባቸው መነገሩ
-እስራኤል ከእነርሱ በፊት ስለነበረው ስለቀደመው ታሪክ እንዲጠይቁ መነገራቸው
-ከእግዚአብሔር ሌላ አምላክ እንደሌለ መነገሩ

💛ምዕራፍ 5፦
-ዐሥሩን ትእዛዛት ሙሴ ለሕዝቡ መንገሩ
-በሕይወት እንድትኖሩ መልካምም እንዲሆንላችሁ በምትወርሱትም ምድር እድሜያችሁ እንዲረዝም እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ መባላቸው


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. እስራኤላውያን ከግብጽ ተነሥተው ምድረ ርስት እስኪገቡ ምን ያህል ዘመን ተጓዙ?
ሀ. 40 ቀን
ለ. 40 ዓመት
ሐ. 19 ቀን
መ. 19 ዓመት
፪. እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተራራ ለእስራኤላውያን ሲገለጥ በጊዜው ምን ዓይነት ተአምር ተደርጓል?
ሀ. ከተራራው እስከ ሰማይ ድረስ እሳት ይነድ ነበረ
ለ. ድቅድቅ ጨለማ ነበረ
ሐ. አውሎ ነፋስ ነበረ
መ. ሁሉም
፫. በዕለተ ሰንበት ከሥራ እንዲያርፉ የታዘዘላቸው እነማን ናቸው?
ሀ. ባለቤቶች
ለ. አገልጋዮች
ሐ. እንስሶች
መ. ሁሉም
፬. የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብንጠብቅ ምን እንጠቀማለን?
ሀ. በሕይወት እንኖራለን
ለ. መልካም ይሆንልናል
ሐ. ዕድሜያችን ይረዝማል
መ. ሁሉም

https://youtu.be/KHCids4utrs?si=4m7JkB5-avJviRGK

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Nov, 18:06


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 32🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፳፩
ልጄ ሆይ የበደልከው በደል ቢኖር ብትስትም ዳግመኛ እንዳትበድል ዕወቅ፡፡ ስለቀደመውም በደልህ ወደንስሓ ተመለስ፡፡ ከዘንዶና ከአንበሳ እንደሚሸሽ እንደዚሁ ሁሉ ከኃጢአት ራቅ፡፡ ሁለት ልሳን ያለው የተሳለ ሰይፍ በሁለት ወገን እንዲቆርጥ እንደዚሁ ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለምም በወዲያኛውም ዓለም ትጎዳለች፡፡ ለብልህ ሰው የተሳተው ይታወቀዋል፡፡ ልቡናውን በዕውቀት ያጸና ሰው የእግዚአብሔርን ሕግ ይጠብቃል፡፡ እግዚአብሔርንም የመፍራት ፍጻሜዋ ክብር ነው፡፡ የብልህ ሰው ነገሩ በአደባባይ ይሰማል፡፡ ሰነፍ ሰው ሲስቅ አፉን ከፍቶ ይንካካል፡፡ ብልህ ሰው ግን በጭንቅ ከንፈሩን ይገልጣል (ፍግግ ብቻ ይላል)፡፡ የብልሆች ሰዎች ነገራቸው በልክ ነው፡፡ ኃጥእ ሰው ክፉ ሥራ ሠርቶ ጋኔን አሳተኝ ቢል ራሱን መስደቡ ነው፡፡
🧡ምዕራፍ ፳፪
ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ኀፍረት ነው፡፡ በትርና ቁጣ ሁሉን ያሰለጥናል፡፡ ብኪ ላዕለ ዘሞተ እስመ ኀለፈ ብርሃኑ፡፡ ወብክዮ ለአብድ እስመ አምሰጦ ልቡ፡፡ ለሞተ ሰው ታለቅስ ዘንድ የተገባ ነው ንስሓ የለውምና፡፡ ለሰነፍ ሰው ግን በሕይወቱ ሳለ አልቅስለት ከሞት ይልቅ ሕይወት ከፍቶበታልና፡፡ ንስሓ ለማይገባ ኃጥእ ባለ በዘመኑ ሁሉ አልቅስለት፡፡ ከባልንጀራህ ጋር የተጫወትከውን ምሥጢር አታውጣ፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Nov, 14:17


💙የጥያቄዎች መልስ ክፍል 30💙

▶️፩. ‹‹በለዓምን ደግሞ በዚያው ጦርነት ሰይፍ ገደሉት›› ይላል (ዘኍ.31፥8)። በለዓም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ያደረገ ነውና ለምን ገደሉት?

✔️መልስ፦ በለዓም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አላደረገም። ለሞዓባውያን ክፉ ምክርን መክሮ እስራኤላውያን እንዲጎዱ አድርጓቸዋል። ስለዚህ ገደሉት።

▶️፪. ‹‹እነርሱ በበለዓም ምክር ፌጎር ምክንያት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲስቱ›› ይላል (ዘኍ.31፣16)። ለበቀል ያበቃው ምክር ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በለዓም እስራኤላውያንን የሚጎዳ ምክር ለባላቅ እንደነገረው በዚህ ይታወቃል። ምክሩ ምን የሚል እንደነበረ ግን አላገኘሁም። በውጤቱ እንደምናስተውለው ግን ሴቶቻቸውን በማግባታቸው እስራኤላውያን መቀሠፋቸው ተገልጿል። ስለዚህ ሴቶች መሰናክል እንዲሆኗቸው በለዓም ስለመከራቸው እንደሆነ ተገልጿል።

▶️፫. ''ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺሕ ወደ ጦርነት ሰደደ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ሰደዳቸው የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም መለከት በእጁ ሰጠው'' ይላል,(ዘኍ.31፥6)። ከሌዊ ወይንም ከካህናት ወገን ለጦርነት ይሰለፋሉ ማለት ነው? ፊንሐስ ወደ ጦርነት እንዴት ሄደ?

✔️መልስ፦ ካህናት ለጦርነት መሰለፍ አይገባቸውም። ፊንሐስ ወደጦርነት የሄደው በደብተራ ኦሪት ይኖር የነበረውን መለከት እንዲነፋ ነው። ሌዌውያን ወደጦር ሜዳ የሚሄዱ ከንዋየ ቅድሳት አብሮ የሚሄድ ካለ በዚያ ምክንያት ነው። ለጦርነት ታቦት ይዘውም ሲወጡ ታቦቱን ለመሸከም አብረው ይሄዱ ነበረ።

▶️፬. ወንድ የማያውቁትን ሴቶች ልጆች ሁሉ ግን አድኗቸው የተባለው በምን ምክንያት ነው?

✔️መልስ፦ እንዲያገቧቸው። በዋናነት ግን እግዚአብሔር ስላዘዘ ነው።

▶️፭. ወደ ከነዓን ምድር ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ በዚያችም ምድር የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ አጥፏቸው የተባሉት ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ባወቀ በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች መጥፋት ይገባቸው ስለነበረ ነው። ቦታውን ደግሞ አስቀድሞ ለእስራኤል ርስት እንደሚሆን አስቀድሞ እግዚአብሔር ተናግሮ ነበረ።

▶️፮. ለሌዋውያን የተሰጣቸው ከተሞች በአራቱም አቅጣጫ ሁለት ሽህ ክንድ የሆነበት ምሥጢር አለው? ወይስ እንዲሁ የተደረገ ቁጥር ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ስላዘዘ ነው። ጥያቄው እግዚአብሔር ለምን አዘዘ ከሆነ ግን አላውቀውም።

▶️፯. የእስራኤል ልጆች ርስት ከነገድ ወደ ነገድ ምንም አይተላለፍ የተባለው ለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ርስት እንዳይደበላለቅ ነው። አባቶችን የሚወርሱ ልጆች ናቸውና።

▶️፰. አንድ ሰው ሲኖር እግዚአብሔር በጻፈለት ነዉ የሚኖረዉ የሚባል እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ ሰው ክፉዉን ከደጉ የሚለይ ኅሊና ያለው ሆኖ ስለተፈጠረ ራሱ በመረጠው አኗኗር ይኖራል እንጂ እግዚአብሔር አያስገድደውም። እግዚአብሔር የሰውን ሁሉ መጨረሻ ገና ሳይፈጥረው ያውቀዋል። ሰው ምን እንደሚያደርግም ያውቀዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ የሚያደርገውን እንዲያደርግ እግዚአብሔር አያስገድደውም። ሰው በነጻ ፈቃዱ መርጦ የሚያደርገውን እግዚአብሔር ያውቃል እንጂ።

▶️፱. ዘኍ.33፥38 "ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ" ይላል። ከዚህ በፊት አሮን ምድረ ርስት ሳይገባ እንደሞተ አይተናል። ስለዚህ እስራኤል ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከነዓን አልገቡም ማለት ነው?ማለትም ከነዓን የገቡ በ40ኛው ዓመት መሆኑ ይታወቃል ወሩ እና ቀኑ መቼ ነው?

✔️መልስ፦ እስራኤላውያን ወደ ምድረ ርስት የገቡት አርባው ዓመት ሲፈጸም ነው። አሮን ሞተ የተባለው ደግሞ አርባው ዓመት ሳይፈጸም ገና በአምስተኛው ወር ነው። በ41ኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ከአሥረኛው ቀን ጀምረው ገብተዋል። ዮርዳኖስን ከተሻገሩ ምድረ ርስት ነውና። ነገር ግን በአንድ ጊዜ ሁሉንም አልወረሱም ከገቡ በኋላም የተለያዩ ጦርነቶችን አድርገዋል።

▶️፲. ዘኍ.36፥8 "ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ሰው የአባቶቹን ርስት ይወርስ ዘንድ፥ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአባቷ ነገድ ባል ታግባ" ይላል። አንዲት ሴት ከነገደ ስምዖን ብትሆን የምታገባው የግድ ከነገደ ስምዖን ነው ወይስ ከ12ቱ ነገደ እስራኤል መርጣ ነው? ማለቴ ርስት እንዳይተላለፍ ስለሚል።

✔️መልስ፦ አዎ በየነገዱ እንዲጋቡ ሥርዓት ተሠርቷል። ይኸውም ርስት እንዳይፋለስ ነው።

▶️፲፩. ዘኍ.31፥15-16 "ሙሴም አላቸው፦ በውኑ ሴቶችን ሁሉ አዳናችኋቸውን? እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር እግዚአብሔርን ይበድሉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ" ይላል። ሴቶች ምን አድርገው ነው እንቅፋት የሆኑት?

✔️መልስ፦ ለእስራኤል ልጆች መሰናክል ስለሆኑ ነው። ይህም በክስቢና በዘንበሪ ታውቋል። እስራኤላውያን ወንዶች የሞዓብን ሴቶች ተከትለው አመንዝረዋልና።

▶️፲፪. ምርኮኞችን ለራስ መውሰድ ተገቢ ነው?

✔️መልስ፦ በብሉይ ሕግ ምርኮኛ ባሪያ ሆኖ ለማረከው ሰው ያገለግል ነበረ። ወንዶችም የማረኳቸው ሴቶች ከነበሩ ማግባት የፈለጓቸውን ከባርነት ነጻ አውጥተው ያገቧቸው ነበረ።

▶️፲፫. ዘኍ.31፣7 "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፥ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ" ይላል። በዘፍጥረት እንዳየነው ደግሞ ምድያም ዛሬ ሱዳን ላይ የሚገኝ ያኔ የኢትዮጵያ ክፍል ነው። ታዲያ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ጋር ተዋጉ ማለት እንችላለን?

✔️መልስ፦ ምድያም የኢትዮጵያ ክፍል እንደነበረች ተገልጿል። ነገር ግን የኢትዮጵያ ክፍል እንደነበረች ተገልጿል እንጂ የኢትዮጵያ ሌላ ስሟ ምድያም እንደነበረ አልተገለጸም። ከዚህ ኃይለ ቃልም ከምድያም ጋር እንደተዋጉ ነው የተነገረው እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር አይልም።

▶️፲፬. የዮሴፍ ልጆች ኤፍሬምና ምናሴ እንደነገድ የሚቆጠሩበት የተለየ ነገር ምን ኖሮ ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ለየብቻቸው እንዲቆጠሩ ስላዘዘ ነው።

▶️፲፭. በለዓም ጣዖት አምላኪ ከሆነ እንዴት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ ይለናል?

✔️መልስ፦ በለዓም መሥዋዕትን የሠዋው ለእግዚአብሔር አልነበረም። በጥንቆላ በለመደው ሥርዓት ነው መሠዊያን አዘጋጅቶ መሥዋዕት ያቀርብ የነበረው። እግዚአብሔር ግን በለዓም ሐሰተኛ መሥዋዕትን ቢያቀርብም ተገልጦ አስጠንቅቆታል።

▶️፲፮. የሮቤል የጋድ እና የምናሴ ነገድ ከነዓንን አልወረሱም ምክንያቱም ምድያም ስለቀሩ። ነገር ግን አሥሩ ነገዶች ከነዓንን እንደተከፋፈሉ ይናገራል። የሌዊ ነገድ ርስት አልተሰጠውም ። እንዴት ከአስራ ሁለት አብልጦ ቆጠራቸው?

✔️መልስ፦ ከአሥራ ሁለት አልበለጡም። የሌዊ ነገድ ርስቱ እግዚአብሔር ስለሆነ ርስት አልተሰጠውም። የሮቤል፣ የጋድ እና የምናሴ እኩሌታ ወንድሞቻቸውን ምድረ ርስትን አውርሰው ተመልሰዋል። ብዙ እንስሶች ስለነበራቸው ከምድረ ርስት ይልቅ ለእንስሳት ምቹ ቦታ ነው ብለው ገለዓድንና ሌሎችንም ቦታዎች እንዲሰጧቸው እነሙሴን ጠይቀዋል። በጠየቁት መሠረት እነሙሴም ፈቅደውላቸዋል። 12ቱ ነገድ የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Nov, 14:17


፩. ነገደ ሮቤል
፪. ነገደ ስምዖን
፫. ነገደ ይሁዳ
፬. ነገደ ንፍታሌም
፭. ነገደ ይሳኮር
፮. ነገደ ዛብሎን
፯. ነገደ አሴር
፰. ነገደ ጋድ
፱. ነገደ ዳን
፲. ነገደ ብንያም
፲፩. ነገደ ምናሴ
፲፪. ነገደ ኤፍሬም
ነገደ ሌዊ ርስቱ እግዚአብሔር ነው ስለተባለ እንደሌሎች ባለርስቶች አልተቆጠረም። ስለዚህ ከ12ቱ ሁለቱ ማለትም ነገደ ሮቤልና ነገደ ጋድ ከዮርዳኖስ ማዶ ሲቀሩ 10ሩ ወርሰዋታል። ነገደ ሞናሴ ግማሹ ስለገባ ስለአንድ ተቆጥሮ ነው አሥር መባሉ። መጽሐፍ የተረፈ ትቶ የጎደለ ሞልቶ መናገር ልማዱ ነውና።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Nov, 12:10


🧡🧡🧡የጠየቅኋችሁ መልሶቻቸው🧡🧡🧡
፩. ከነገደ ሌዊ ውጭ ያሉ ነገዶች የተቆጠሩት ከስንት ዓመት በላይ የነበሩት ናቸው?
ሀ. ከ25 ዓመት እስከ 50 ዓመት
ለ. ከአንድ ወር በላይ
ሐ. ከ20 ዓመት በላይ🧡
መ. ከ25 ዓመት በላይ
፪. ዐሥራ አንዱ ነገድ ሲቆጠሩ አንደኛው ነገድ ግን ለጊዜው እንዳይቆጠርና ለእስራኤል ልጆች በኵሮች ምትክ እንዲሆን እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዘው ማንኛው ነገድ ነው?
ሀ. ነገደ ሌዊ🧡
ለ. ነገደ ይሁዳ
ሐ.ነገደ አሴር
መ. ነገደ ምናሴ
፫. ታቦቱን እንዲጠብቁ የታዘዙ የማን ልጆች ናቸው?
ሀ. የጌድሶን ልጆች
ለ. የአብዩድ ልጆች
ሐ. የቀዓት ልጆች🧡
መ. የሜራሪ ልጆች
፬. ራሱን ለእግዚአብሔር የተለየ አድርጎ የተሳለ ሰው ሊያደርገው የሚገባ ሥርዓት ምንድን ነው?
ሀ. የሚያሰክር መጠጥ አለመጠጣት
ለ. ጸጉሩን አለመላጨት
ሐ. ወደሬሳ አለመቅረብ
መ. ሁሉም🧡
፭. መለከቶች እንዲነፉ የታዘዘው መቼ መቼ ነው?
ሀ. በወር መባቻ
ለ. በበዓላት ዘመን
ሐ. እስራኤላውያን ወደ ጦርነት ሲወጡ
መ. ሁሉም🧡
፮. የአሮን ልጆች የእስራኤልን ሕዝብ ሲባርኩ ምን ይሉ ነበረ?
ሀ. እግዚአብሔር ይባርክህ
ለ. እግዚአብሔር ሰላምን ይስጥህ
ሐ. እግዚአብሔር ይራራልህ
መ. ሁሉም🧡
፯. ሙሴ ሰባ ሽማግሌዎችን መርጦ ከተመረጡት ውስጥ 68ቱ ወደ ደብተራ ኦሪት ሄደው የእግዚአብሔር መንፈስ ሲወርድባቸው ሁለቱ ግን ከሰፈር ቀርተውም የእግዚአብሔር መንፈስ ወርዶባቸው ትንቢት ተናግረዋል። ማንና ማን ናቸው?
ሀ. አሮንና ሖር
ለ. አውሴና ካሌብ
ሐ. ኤልዳድና ሞዳድ🧡
መ. ሙሴና አውሴ
፰. ከነዓንን እንዲሰልሉ ከተላኩት 12ቱ ሰላዮች የሰለልናትን ሀገር ሰዎች ማሸነፍ እንችላለንና እንውረሳት ያለ ማን ነው?
ሀ. ካሌብ🧡
ለ. ጉዲኤል
ሐ. ሰሙኤል
መ. ዓሚሄል
፱. እስራኤላውያን በልብሳቸው ዘርፍ እንዲያደርጉት የታዘዘ ፈትል ምን ዓይነት ቀለም ያለው ነው?
ሀ. ነጭ
ለ. ሰማያዊ🧡
ሐ. ቀይ
መ. ጥቁር
፲. ሳይፈቀድለት ጥናዎቹን ወስዶ አጥናለሁ ብሎ በሙሴና በአሮን ስላጉረመረመ ምድር ተከፍታ የዋጠችው ማን ነው?
ሀ. ቆሬ
ለ. ዳታን
ሐ. አቤሮን
መ. ሁሉም🧡
፲፩. በደብተራ ኦሪት ተቀምጣ ሳለ ለምልማ፣ አብባ፣ አፍርታ የተገኘች የማን በትር ናት?
ሀ. የሙሴ
ለ. የአሮን🧡
ሐ. የኤፍሬም
መ. የምናሴ
፲፪. ሕዝቡ ለደብተራ ኦሪት ከሚሰጠው ለሌዋውያን እንዲሆናቸው የታዘዘላቸው ምንድን ነው?
ሀ. ቀዳምያት
ለ. በኵራት
ሐ. ዐሥራት
መ. ሁሉም🧡
፲፫. እስራኤላውያንን ይረግምለት ዘንድ በለዓምን የጠየቀው ማን ነው?
ሀ. ሴዎን
ለ. ባላቅ🧡
ሐ. አግ
መ. የኤዶም ንጉሥ
፲፬. እስራኤላውያን የእባብ መቅሠፍት ከወረደባቸው ጊዜ በኋላ በእባብ የተነደፉት የዳኑት ምንን አይተው ነው?
ሀ. የነደፋቸውን እባብ
ለ. የናስ እባብ🧡
ሐ. የሙሴን በትር
መ. የአሮንን በትር
፲፭. ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ብሎ ትንቢት የተናገረ ማን ነው?
ሀ. በለዓም🧡
ለ. አሮን
ሐ. ሄኖስ
መ. ካሌብ
፲፮. እስራኤላውያን ዳግመኛ ሲቆጠሩ ከነገደ ሌዊ ውጭ ያሉት ከ20 ዓመት በላይ ወንዶች ስንት ነበሩ?
ሀ. 603,550
ለ. 22,000
ሐ. 601,730🧡
መ. 23,ዐዐዐ
፲፯. ከሙሴ ቀጥሎ ሙሴ ከሞተ በኋላ ሙሴን ተክቶ እስራኤላውያንን እንዲያስተዳድር የተሾመው ማን ነው?
ሀ. ካሌብ
ለ. ኢያሱ🧡
ሐ. ፊንሐስ
መ. አልዓዛር
፲፰. ስለስእለት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ሚስት መጀመሪያ ባሏ ካልፈቀደ ስእለቷ ይጸናል
ለ. ልጅ መጀመሪያ አባቷ ካልፈቀደ ስእለቷ ይጸናል
ሐ. የተሳለ ሰው ስእለቱን መፈጸም ይገባዋል
መ. ሀ እና ለ🧡
፲፱. ከእስራኤል ነገዶች በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ አንጻር በምሥራቅ በኩል ያለውን ቦታ የወረሱ እነማን ናቸው?
ሀ.የነገደ ምናሴ እኩሌታዎች
ለ. ነገደ ጋድ
ሐ. ነገደ ሮቤል
መ. ሁሉም🧡
፳. ባለማወቅ ነፍስ የገደለ ሰው ሸሽቶ እንዲያመልጥባቸው የተደረጉ የመማጸኛ ከተሞች ስንት ነበሩ?
ሀ. 42
ለ. 6🧡
ሐ. 48
መ. 12
፳፩. ባለማወቅ ገድሎ ወደመማጸኛ ከተሞች ሸሽቶ ስለገባው ሰው ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ማኅበሩ ከባለደሙ እጅ ያድኑታል
ለ. ታላቁ ካህን እስኪሞት ከመማጸኛው ከተማ መውጣት የለበትም
ሐ. ታላቁ ካህን ከሞተ በኋላ ወደርስቱ ምድር ይመለሳል
መ. ሁሉም🧡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Nov, 05:21


💞ኦሪት ዘኍልቍ ክፍል ፯💞

💞ምዕራፍ 31፦
-እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ምድያማውያንን እንዲወጉ መታዘዛቸው፣ እነርሱ ግን ወንዶችን ሲወጉ ሴቶችን ማርከው በማምጣታቸው መቅሠፍት መሆኑ

💞ምዕራፍ 32፦
-የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች ከዮርዳኖስ ማዶ ያለውን ሀገር ወርሰው እንደኖሩ

💞ምዕራፍ 33፦
-ከግብፅ ጀምሮ ስለነበረው ጉዞ ጠቅለል ተደርጎ መገለጹ

💞ምዕራፍ 34፦
-ስለተስፋይቱ ምድር ወሰኖች መነገሩ
-ምድረ ርስትን እንደተከፋፈሏት

💞ምዕራፍ 35፦
-ለሌዋውያን ከተሞች መሰጠታቸው፣ ከተሰጡት ከተሞች ስድስቱ የመማፀኛ ከተሞች እንዲሆኑ መነገሩ፣ ከመማጸኛ ከተሞች በተጨማሪ 42 ከተሞች እንደተሰጡ
-ባለማወቅ ነፍስ የገደለ ሰው ቢኖር ወደመማጸኛ ከተሞች ገብቶ እንዲሸሽ መታዘዙ፣ ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስም ከዚያው እንዲቆይ መነገሩ፣ ታላቁ ካህን ከሞተ በኋላ ግን ወደርስቱ እንዲመለስ መነገሩ
-በአንድ ምስክር ማናቸውንም ሰው መግደል እንደማይገባ
-ምድርን የሚያረክሳት ደም ነውና የምትኖሩባትን ምድር በነፍስ ግድያ አታርክሷት መባሉ

💞ምዕራፍ 36፦
-እስራኤላውያን በየርስታቸው እንዲኖሩ መነገሩ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ከእስራኤል ነገዶች በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ አንጻር በምሥራቅ በኩል ያለውን ቦታ የወረሱ እነማን ናቸው?
ሀ.የነገደ ምናሴ እኩሌታዎች
ለ. ነገደ ጋድ
ሐ. ነገደ ሮቤል
መ. ሁሉም
፪. ባለማወቅ ነፍስ የገደለ ሰው ሸሽቶ እንዲያመልጥባቸው የተደረጉ የመማጸኛ ከተሞች ስንት ነበሩ?
ሀ. 42
ለ. 6
ሐ. 48
መ. 12
፫. ባለማወቅ ገድሎ ወደመማጸኛ ከተሞች ሸሽቶ ስለገባው ሰው ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ማኅበሩ ከባለደሙ እጅ ያድኑታል
ለ. ታላቁ ካህን እስኪሞት ከመማጸኛው ከተማ መውጣት የለበትም
ሐ. ታላቁ ካህን ከሞተ በኋላ ወደርስቱ ምድር ይመለሳል
መ. ሁሉም

https://youtu.be/iKm5U3B2Za8?si=lrhitb0rDGBSO61m

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

01 Nov, 05:11


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 31🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፲፱
ከዐሠርቱ ቃላት አንዲቱን የሚያፈርስ ብዙ ጸጋንና ክብርን ያጣል፡፡ መጠጥ ብልሆችን ሰዎች ያስታል፡፡ የነገሩትን ነገር ሳያስተውል ፈጥኖ የሚያምን ሰው ልቡ ቀሊል ነው፡፡ ኃጢአትን የሚሠራ ሰው ራሱን ይበድላል፡፡ ብዙ መናገርን የሚጠላ ሰው ኃጢአቱን ያሳንሳታል፡፡ የሰማኸውን ነገር አውጥተህ አትናገር፡፡ ቀሊል ሰው የሰማውን እስኪናገር ድረስ ይቸኩላል፡፡ ክፉ ትምህርትን የሚያስተምር ሰው ብልህ አይደለም፡፡
🧡ምዕራፍ ፳
ለበጎ ነገር ሳይሆን ለውዳሴ ከንቱ የሚቆጣ ሰው አለ፡፡ ነገርንም አከናውኖ መናገር ሲቻለው የማይናገር ሰው አለ፡፡ ሰውን ከመንቀፍ መቆጣት ይሻላል፡፡ ሁሉን እያወቀ ዝም የሚል ሰው አለ፡፡ በመቀባጠሩም ብዛት ራሱን የሚያስጠላ ሰው አለ፡፡ የሚናገረውን ነገር አያውቅምና ዝም የሚል ሰው አለ፡፡ ለነገሩም ጊዜ እስኪያገኝለት ድረስ ዝም የሚል አለ፡፡ ብልህ ሰው ለነገሩ ጊዜ እስኪያገኝለት ድረስ ዝም ይላል፡፡ ዕውቀት የሌለውና ደፋር ሰው ግን እንዳገኘ ይቀባጥራል፡፡ ሰነፍ ሰው ወዳጅ ለምኔ ይላል፡፡ በአንደበትህ ክፉ ነገር ተናግረህ ከምትሰናከል በእግርህ ተሰናክለህ ብትወድቅ ይሻልሀል፡፡ ክፉ በመናገር ክፉ መከራ ፈጥኖ ይመጣልና፡፡ አገኝ አጣውን የሚናገር ሰው ራሱን ያስነቅፋል፡፡ ለነገሩም መወደድ (ሞገሰ ቃል) የለውም፡፡ የውሸትና የስርቆት ፍጻሜያቸው ሞትና ጉስቁልና ነው፡፡ ነገር አዋቂ ሰው ነገሩ ከሩቅ ሀገር ይሰማል፡፡ የተማሩትን ትምህርት ካላስተማሩት ጥቅም የለውም፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Oct, 18:18


እህት ሔቨን በቃሏ መሠረት ለጉባኤ ቤታችን ለመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ጉባኤ ቤት መጻሕፍትን ሰጥታናለች። የቀትር ጤዛ የሚለውን የራሷን መጽሐፍም አበርክታልናለች።

እናመሰግናለን።
ሔቨን ዮሐንስ ተፈሪ
Heaven Yohannes

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Oct, 14:13


💙የጥያቄዎች መልስ ክፍል 29💙

▶️፩. የሌዊ ነገድ ልጆች እንደ ተቆጠሩና ቁጥራቸውም 23 ሺህ አንደሆነ ተነግሯል። ነገር ግን ርስት ያልተሰጣቸው ለምንድን ነው? የትስ ይኖራሉ?

✔️መልስ፦ ርስታቸው እግዚአብሔር ነው። የሚኖሩት ደግሞ በሁሉም ነገድ መካከል በተለየላቸው 48 ከተማዎች ነው። ርስታቸው እግዚአብሔር ስለሆነ ለቤተ እግዚአብሔር ተብሎ የሚወጣው ገንዘብ የእነርሱ ሆኖ ይኖራሉ ማለት ነው።

▶️፪. "ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቆጠሩም" ይላል (ዘኍ.26፣62)። ንባቡ አልገባኝም?

✔️መልስ፦ ርስት እንዲወርሱ ከሌሎች ነገዶች ጋር አልተቆጠሩም ማለት ነው። የሌዋውያን ርስታቸው እግዚአብሔር ነውና። እንጂ ከእስራኤላዊነት ወጡ ለማለት አይደለም።

▶️፫. በዓለ ናዕት፣ በዓለ ሰዊት፣ በዓለ መጥቅዕ፣ የዳስ በዓል የሚሉ የበዓል ቀናት አሉና ትርጉማቸው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በዓለ ናዕት ማለት የቂጣ በዓል ማለት ነው። ከፋሲካ ማግሥት (ሚያዝያ 15) ጀምረው ለሰባት ቀን ቂጣ እየበሉ የሚያከብሩት በዓል ነው። በዓለ ሠዊት የእሸት በዓል ማለት ነው። ከፋሲካ ጀምሮ 49 ቀን ቆጥረው በ50ኛው ቀን የሚከበር በዓል ነው። በዓለ መጥቅዕ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያ ቀን (ጥቅምት 1) የሚያከብሩት በዓል ነው። የዳስ በዓል የሚባለው ደግሞ ከጥቅምት 15 ጀምሮ ለሰባት ቀን የሚከበር በዓል ነው።

▶️፬. ዘኍ.26፥10 "ያም ወገን በሞተ ጊዜ ምድሪቱ አፏን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ በዚያም ጊዜ እሳቲቱ ሁለት መቶ አምሳውን ሰዎች አቃጠለቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ" ይላል። ምድሪቱ አፏን ከፍታ ከቆሬ ጋራ ዋጠቻቸው ወይስ ለምልክት ተቃጥለው ተርፈዋል ለምልክት ሆኑ ሲል ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?

✔️መልስ፦ ለምልክት ሆኑ ማለት ሌላውም ሰው ለበወደፊቱ ሳይመረጥ በድፍረት የክህነት ሥራ እሠራለሁ ቢል እንደነርሱ እንደሚቀሠፍ ማስተማሪያ ምልክት ሆኑ ማለት ነው። ምድር ሁሉንም ውጣቸዋለች (ዘኍ.16፥40)።

▶️፭. እስራኤላውያን ድጋሜ የተቆጠሩበት ምክንያት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በምድረ በዳ የሞቱ አባቶቻቸው ልጆቻችን ይሞታሉ ብለው በሐሰት ተናግረው ስለነበረ በእነርሱ ምትክ ልጆች ምድረ ርስት እንደገቡ ለማሳወቅ ነው። ዋናው ምክንያት ግን እግዚአብሔር ዳግመኛ ይቆጠሩ ስላለ ነው።

▶️፮. ስእለት የሚሰጠው በዓመት ወይስ በዕለት ምሳሌ በአንድ የእግዚአብሔር በዓል ወይም የቅዱሳን በዓል ቢሳል በዕለቱ ወይስ በወር ወይም በዓመት ነው መሰጠት ያለበት? የተሳለው ስእለት ባይፈጸም ስእለቱን አለመሰጠት ይችል ይሆን?

✔️መልስ፦ እንደተሳለው ስእለት ዓይነት ይለያያል። እስከ ወር እሰጣለሁ ብሎ ከተሳለ እስከ ወር ባለው መስጠት ነው። እስከ ዓመት ካለ ዓመቱ ሲደርስ መስጠት ነው። ለስእለቱ ቅድመ ሁኔታ ካዘጋጀ እንደቅድመ ሁኔታው ማድረግ ነው። ምሳሌ ልጅ ከወለድኩ ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ ብሎ የተሳለ ሰው ቢኖር ካልወለደ አምጣ አይባልም።

▶️፯. ''ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል እርሷም በአባቷ ቤት ሳለች በብላቴንነቷ ጊዜ ራሷን በመሐላ ብታስር አባቷም ራሷን ያሰረችበትን መሐላ ስእለቷንም ቢሰማ አባቷም ዝም ቢላት ስእለቷ ሁሉ ይጸናል ራሷንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል'' ሲል ይህ ገጸ ንባብ ሀሳቡ አልገባኝም። ምን አልባት ሴቲቱ ስእለት ለመሳል የአባት ወይንም የባሏን ፍቃድ ያስፈልጋት ይሆን?

✔️መልስ፦ አወ። ባል ያላት ሴት በስእለቷ ባሏም ከተስማማ ስእለቷ ይፈጸማል። ባል የሌላት ከአባቷ ጋር የምትኖር ልጅም (ሴት ልጅም ወንድ ልጅም ቢሆኑ) በስእለታቸው አባታቸው ከተስማማ ስእለታቸው ይፈጸሜል። ካልተስማሙ ግን አይሆንም ማለት ነው።

▶️፰. ''እግዚአብሔር ስለ እነርሱ፦በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ ብሎ ተናግሯልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው ስንኳ አልቀረም'' ይላል። ከ600,000 በላይ ሕዝብ ሞተው ሁለቱ ማለትም ካሌብ እና ኢያሱ ብቻ ነው ምድረ ርስት የገቡት ወይንስ የእነርሱን ነገድ ጨምሮ ነው?

✔️መልስ፦ ከ600,000 በላይ ሕዝብ ተብለው የተቆጠሩት በመጀመሪያው ቆጠራ ከ20 ዓመት በላይ የሆናቸው ተቆጥረው ነው። እነዚህ ሁሉ ቢበድሉ ከካሌብና ከኢያሱ በቀር ሁሉም በምድረ በዳ ሞቱ። ከ20 ዓመት በታች የነበሩት እድሜያቸው ከፍ ሲል እንዲሁ ከ600,ዐዐዐ በላይ ሆኑ። ስለዚህ የመጀመሪያዎቹ ሞተው በብዛት ከእነርሱ ጋር የሚቀራረቡ ልጆቻቸው ምድረ ርስትን ወርሰዋል ማለት ነው።

▶️፱. “ለብዙዎቹ እንደ ብዛታቸው፥ ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣቸዋለህ። ለሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን ርስታቸው ይሰጣቸዋል” ይላል (ዘኍ.26፥54)። እንደገና ደግሞ “ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ” ይላል (ዘኍ.26፥55)። ከላይ እንደ ቁጥራቸው መጠን ይላል ከታች ደግሞ በዕጣ ይላል እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ ቦታው በዕጣ ከተከፋፈለ በኋላ እንደየሰው ብዛት ስለተከፋፈሉት ነው። መጀመሪያ በዕጣ ተከፈለ። ከዕጣው በኋላ ለእያንዳንዱ ለማከፋፈል ደግሞ እንደየብዛቱ ተከፋፍሏል ማለት ነው።

▶️፲. “እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አልቀደሳችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የመሪባ ውኃ ነው” ይላል (ዘኍ.27፥14)። የክርክር ውኃ ምንድን ነበር? ዐመፃቸውስ? ሙሴ ምድረ ርስትን እዳልወረሰ መቃብሩን እስራኤላውያን እንዳላዩት ይነግረናል። የእነዚህ ምክንያቶች ምን ይሆኑ?

✔️መልስ፦ የክርክር ውሃ የሚባለው እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ላይ በአጉረመረሙ ጊዜ የፈለቀ ውሃ ነው። እነሙሴም በዚህ ጊዜ ተበሳጭተው ስለነበረ እግዚአብሔርን አላመሰገኑትም ነበረ። በዚህም ምክንያት ወደምድረ ርስት ሳይገቡ ቀርተዋል። ሙሴ የተቀበረ በናባው ተራራ ነው። የቀበሩትም መላእክት ናቸው። መቃብሩ ያልታወቀው ቢታወቅ ኖሮ እስራኤላውያን ሊያመልኩት ይችሉ ስለነበረ እግዚአብሔር ባወቀ ሠውሮታል።

▶️፲፩. (ዘኍ.27፣8) "ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ሰው ቢሞት ወንድ ልጅም ባይኖረው፥ ርስቱ ለሴት ልጁ ይለፍ" ይላል። ወንድ ልጅ ካለ ግን ለሴት ልጅ አይተላለፍም ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ርስት ለሴት ልጅም ለወንድ ልጅም እኩል ነው። ለአንድ አባት አንድ ሴት ልጅና አንድ ወንድ ልጅ ቢኖረውና ቢሞት የሚካፈሉት እኩል ነው። (በተጨማሪ ፍትሐ ነገሥት በእንተ ርስትን ይመልከቱ)። በመቆጠር ጊዜ ነው ሕፃናትና ሴቶች የማይቆጠሩት እንጂ በርስት መቆጠራቸውን ለመግለጽ ነው።

▶️፲፪. ሙሴ ከነዓን አልደረሰም ማለት እንችላለን?

✔️መልስ፦ አዎ አልደረሰም። ከነዓንን በርቀት ነው አይቷት በናባው ተራራ ሞቶ የተቀበረ።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Oct, 11:56


የእግዚአብሔር ስጦታ & መሠረታዊ የግእዝ ቋንቋ መማሪያ
@ጎንደር ማኅበረ ቅዱሳን ሱቅ (ማራኪና መስቀል አደባባይ ካሉት ሱቆች) ያገኟቸዋል።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Oct, 03:57


💚ኦሪት ዘኍልቍ ክፍል ፮💚

💚ምዕራፍ 26፦
-እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ዳግመኛ መቆጠራቸውና ከ20 ዓመት በላይ የሆኑት የ12ቱ ነገድ ወንዶች ልጆች ብዛት 601,730 (ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ እንደነበሩ።
-እስራኤላውያን ምድረ ርስትን በእጣ እንዲከፋፈሏት መነገሩ
-የሌዊ ነገዶች ከአንድ ወር ጀምሮ በላይ ያሉ ወንዶች ልጆች 23,000 (ኻያ ሦስት ሺ) እንደነበሩ

💚ምዕራፍ 27፦
-የሰለጰአድ ሴት ልጆች የሞተውን የአባታቸውን ርስት ይገባናል ብለው ጠይቀው እግዚአብሔር እንደፈቀደላቸው
-አባት ቢሞት ልጆች እንዲወርሱት፣ ልጆች ከሌሉት ወንድሞቹ እንዲወርሱት፣ ወንድሞች ከሌሉት ከወገኑ የቀረበ ዘመድ እንዲወርሰው መነገሩ
-ሙሴ በጺን ምድረ በዳ ባለው በቃዴስ በነበረው የክርክር ውሃ እግዚአብሔርን ስላላከበረው ምድረ ርስት እንደማይገባና በናባው አሻገር ባለው ተራራ ሆኖ ከርቀት አይቷት እንደሚሞት መነገሩ
-ኢያሱ ከሙሴ ቀጥሎ እንዲያስተዳድር መሾሙ

💚ምዕራፍ 28፦
-እስራኤላውያን በበዓላት ቀን ለእግዚአብሔር መባ፣ ቁርባን፣ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ መነገሩ
-በዘወትር፣ በሰንበት፣ በመባቻ፣ በፋሲካና በበዓለ ናዕት፣ በበዓለ ሠዊት ስለሚቀርቡ የመሥዋዕት አቀራረቦች መገለጡ

💚ምዕራፍ 29፦
-በበዓለ መጥቅዕ፣ በኃጢአት ማስተሥረያ ቀን፣ በዳስ በዓል ቀን ስለሚቀርቡ የመሥዋዕት አቀራረቦች መገለጡ

💚ምዕራፍ 30፦
-ሰው ከተሳለና ለእግዚአብሔር ከማለ ቃሉን መፈጸም እንደሚገባው
-ስለ ስእለት ሥርዓት መነገሩ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. እስራኤላውያን ዳግመኛ ሲቆጠሩ ከነገደ ሌዊ ውጭ ያሉት ከ20 ዓመት በላይ ወንዶች ስንት ነበሩ?
ሀ. 603,550
ለ. 22,000
ሐ. 601,730
መ. 23,ዐዐዐ
፪. ከሙሴ ቀጥሎ ሙሴ ከሞተ በኋላ ሙሴን ተክቶ እስራኤላውያንን እንዲያስተዳድር የተሾመው ማን ነው?
ሀ. ካሌብ
ለ. ኢያሱ
ሐ. ፊንሐስ
መ. አልዓዛር
፫. ስለስእለት ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ሚስት መጀመሪያ ባሏ ካልፈቀደ ስእለቷ ይጸናል
ለ. ልጅ መጀመሪያ አባቷ ካልፈቀደ ስእለቷ ይጸናል
ሐ. የተሳለ ሰው ስእለቱን መፈጸም ይገባዋል
መ. ሀ እና ለ

https://youtu.be/j_aNlsCw-10?si=zqRyeDRkI7DnXouY

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

31 Oct, 03:47


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 30🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፲፯
የሚመጸውት ሰው ከመንግሥተ ሰማያት አይከለከልም፡፡ በንስሓ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፡፡ ኃጢአትንም ተዋት፡፡ ትዕቢትህንም ትተህ በንስሓ ወደልዑል እግዚአብሔር ተመለስ፡፡ ርኵስን ሁሉ ጥላ፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነቱ ብዙ ነውና በሕይወት ሳለህ አመስግነው፡፡ ንስሓ ገብተው የሚለምኑትንም ይቅር ይላቸዋልና ንስሓ ግባ፡፡
🧡ምዕራፍ ፲፰
እግዚአብሔር ባሕቲቱ ጻድቅ፡፡ እውነተኛ የባሕርይ አምላክ እርሱ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ባሕርዩን መርምሮ ያወቀ የለም፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረው ጊዜ ይህን ያህል ዘመን ኑር ብሎ የተወሰነ ዘመን ይሰጠዋል፡፡ የሰጠውንም ዘመን በጨረሰ ጊዜ በሞት ያሳርፈዋል፡፡ ንፉግ ሰው ልቡን ደስ ሳይለው ይሰጣል፡፡ ክፉን ነገር ሳትናገር አስቀድመህ መርምር፡፡ ሳትታመም ባለመድኃኒቱን ወዳጅ አድርገው፡፡ ገሀነም ሳይፈረድብህ ንስሓ ግባ፡፡ ስለትህንም ፈጥነህ ስጥ እንጂ አታዘግይ፡፡ በጎንም ሥራ ሳትሞት ሥራት፡፡ በተቆጣህ ጊዜ ዕለተ ሞትህን አስብ፡፡ ፍዳህንም የምትቀበልበትን ቀን አስብ፡፡ ከቁጣህም ተመልሰህ ይቅር በል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

30 Oct, 15:37


💙የጥያቄዎች መልስ ክፍል 28💙

▶️፩. ዘኍ.22፥22-23 "እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ ሰዎቹ ይጠሩህ ዘንድ መጥተው እንደ ሆነ ተነሣ ከእነርሱም ጋራ ኺድ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ታደርጋለህ አለው። በለዓምም ሲነጋ ተነሣ አህያዪቱንም ጭኖ ከሞዓብ አለቃዎች ጋራ ሄደ። እርሱም ስለ ሄደ እግዚአብሔር ተቈጣ" ይላል። ከእነርሱም ጋራ ኺድ ካለው በኋላ እግዚአብሔር ለምን ተቆጣ ትንሽ ግር ስላለኝ ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በለዓምን እንዲሄድ ያዘዘው እግዚአብሔር የነገረውን ብቻ እንዲናገር ነበረ። ነገር ግን በለዓም በመንገድ ሳለ የሚረግመውን እርግማን እያሰበ ሄደ። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ተቆጥቶታል።

▶️፪. "እስራኤል" የሚለውን ንባብ በብዙ ቁጥር እና በነጠላ ቁጥር ሲነበብ አይቻለሁ እና ምክንያት አለው ወይንስ የመጻሕፍት ባህል ነው?

✔️መልስ፦ የያዕቆብ ሌላ ስሙ እስራኤል ነው። ያዕቆብን አስቦ ሲናገር በነጠላ ሊናገር ይችላል። በግእዝ ቋንቋም ያዕቆብን አስቦ ሲናገር ገቢር ሲሆን እስራኤልሀ ይላል። ከያዕቆብ የተወለዱትን ሕዝቦች ሲመለከት ደግሞ በብዛት ይናገራል። በዚህ ጊዜ በግእዝ ቋንቋም ገቢር ሲሆን እስራኤለ ይላል።

▶️፫. “እርሱም ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ እግዚአብሔርም እንደሚነግረኝ እመልስላችኋለሁ አላቸው” ይላል (ዘኍ.22፥8)። በለዓም ጠንቋይ ሁኖ ሳለ እንዴት እግዚአብሔር የሚነግረኝን ሊል ቻለ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በክፉዎችም አድሮ ትንቢቱን ሊናገር ይችላል። በቀያፋ አድሮ ስለክርስቶስ ሲናገር ይህ ሁሉ ሰው ከሚሞት አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል አለ። በእርሱ ሞት ሰው ሁሉ የሚድን ስለሆነ። በበለዓምም አድሮ እግዚአብሔር ትንቢቱን ተናግሯል። በዚህ ጊዜ አፉን ከፍቶ ፊቱ ጸፍቶ አናገረው ይባላል። በለዓም ጻድቅ ስለሆነ አይደለም እግዚአብሔር የነገረው። ነገር ግን ሊራገም የሄደውን እንዲመርቅ እግዚአብሔር አስገድዶ አናግሮታል።

▶️፬. “እግዚአብሔርም በለዓምን፦ ከእነርሱ ጋር አትሂድ፤ የተባረከ ነውና ሕዝቡን አትረግምም አለው” ይላል (ዘኍ.22፥12)። እግዚአብሔር አምላክ ለጠንቋዮችም ይገለጣል ማለት ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ለማንኛውም ሰው ሊገለጥ ይችላል። መገለጡ በብዙ መንገድ ነው። ለቅዱሳን በቅድስናቸው ምክንያት ሊባርካቸው በመዓርግ ላይ መዓርግን እንዲጨምሩና ደስ እንዲላቸው ይገለጣል። ለክፉዎች ደግሞ ከክፉ ሥራቸው እንዲመለሱ ለማስጠንቀቅ ሊገለጥ ይችላል። ለበለዓም የተገለጠለት በዚህኛው በሁለተኛው መንገድ ነው። በለዓም ሊራገም ሲሄድ ሕዝቡ የተባረከ ስለሆነ እንዳይረግም ሊያስጠነቅቀው ተገልጦለታል።

▶️፭. "ወደ ምድያማዊት ሴት ወሰደ እነርሱም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያለቅሱ ነበር" ይላል (ዘኍ.25፥6)። ከዚህ ደግሞ "ያም የእስራኤልን ሰው ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ" ይላል (ዘኍ.25:8)። ፊንሐስ የገደላቸው ከድንኳኑ ውጭ ነው ውስጥ?

✔️መልስ፦ እነርሱም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያለቅሱ ነበረ የተባለ እነ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ናቸው። ሕዝቡ በሠራው ኃጢአት አዝነው ማልቀሳቸውን ይገልጻል። ቁጥር 28 ላይ ያለው ደግሞ እስራኤላዊውና ምድያማዊት ሴት ወደእስራኤላዊው ድንኳን ገብተው ዝሙት ሲሠሩ ፊንሐስ ስላገኛቸው ለእግዚአብሔር ቀንቶ እንደገደላቸው ያስረዳል።

▶️፮. "ለእርሱም ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም የክህነት ቃል ኪዳን ይሆንለታል" ይላል (ዘኍ.25፥13)። ደም በእጁ ያለበት (ደም ያፈሰሰ) የእግዚአብሔር ካህን እንዳይሆን ይደረጋል። እና ፊንሐስ እንዴት ካህን ሊሆን ቻለ? ነው ንባቡ እርሱን አያጠቃልልም?

✔️መልስ፦ በሐዲስ ኪዳን አዎ አንድ ካህን ጦር አንስቶ ሌላ ሰውን ከገደለ ክህነቱ ይሻራል። በብሉይ ኪዳን ዘመን ግን ይህ ሕግ አልነበረም። ለዚያም ነው ፊንሐስ ለእግዚአብሔር ቀንቶ ሰው ገድሎ ለብዙ ዘመን ካህን እንዲሆን ያደረገው።

▶️፯. ይህን ሕዝብ አሳልፈህ በእጆቻችን ብትሰጠን እርሱንና ከተሞቹን ሕርም ብለን እናጠፋቸዋለን ብለው ስእለት ተሳሉ ይላል። ሕርም ምንድን ነው ትርጉም?

✔️መልስ፦ አንድም ሳናስቀር (ሳናስተው) ሁሉንም እናጠፋቸዋለን ማለት ነው። ሕርም የግእዝ ቃል ነው። ሐረመ ተወ ከሚለው የግእዝ ቃል ሕርም የሚል ዘመድ ዘር ይወጣል።

▶️፰. እስራኤልን እንዲረግም ተጠርቶ የነበረው ሟረተኛው በለዓም እንዴት ነው እስራኤልን የባረከው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር እስራኤልን ባርክ ብሎ ስላዘዘው።

▶️፱. በለዓም ጠንቋይ ነው ወይስ ነቢይ? ትውልዱስ ከማን ነው?

✔️መልስ፦ ጠንቋይ ነበረ። በለዓም የቢዖር ልጅ እንደሆነ ተገልጿል። ሀገሩም ፋቱራ እንደምትባል ተገልጿል።

▶️፲. በመጽሐፍ ቅዱስ በጣም interesting ከሆኑ ታሪኮች አንዱ የበለዓም ታሪክ ነው። በለዓም ሟርተኛ እንደሆነ ይገልጽና መልሶ እግዚአብሔር አናገረው ይላል። ወደ ባላቅ እንዲሄድ ይፈቅድለትና መልሶ ለምን ሄድክ ይለዋል። መንገዱን በመልአክ ይዘጋበትና ይገሥጸዋል። በጣም የሚገርመው ደግሞ ከዚህ በፊት ተናግራ የምታቅ ይመስል ከአህያ  ጋር ያወራል። በመንፈሰ እግዚአብሔር ታግዞ እስራኤልን ይመርቃል ትንቢት ይናገራል። 
እስራኤልን እንዳሰናከለም ተደርጎ ይወቀሳል። ለመሆኑ እንዴት አንድ ሰው ሟርተኛም ከእግዚአብሔር ጋርም የሚነጋገር ነብይ ይሆናል?

✔️መልስ፦ በለዓም ሟርተኛ ነው። የእግዚአብሔር ነቢይ አይደለም። እግዚአብሔር ግን በክፉ ሰዎች አድሮም አፋቸውን ከፍቶ ፊታቸውን ጸፍቶ ያናግራቸዋል። ትንቢቱንና ቡራኬውን በለዓም ወዶ ያደረገው አይደለም። የበለዓም መደበኛ ሥራው ጥንቆላ ነበረ። በኋላም ቢሆን እግዚአብሔር ያዘዘውን ሳያደርግ ለሞዓብ ሰዎች ክፉ ምክር መክሮ እስራኤላውያንን እንዲያታልሉና እንዲጠፉ አድርጓቸዋል።

▶️፲፩. "እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ ሰዎቹ ይጠሩህ ዘንድ መጥተው እንደ ሆነ ተነሣ ከእነርሱም ጋራ ኺድ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ታደርጋለህ አለው። በለዓምም ሲነጋ ተነሣ አህያዪቱንም ጭኖ ከሞዓብ አለቃዎች ጋራ ሄደ" ይላል። በዚህ መሠረት ከሄደ ታድያ የእግዚአብሔር ቁጣ እንዴት መጣ? ንባቡ አልገባኝም?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በለዓምን የምነግርህን ቃል ብቻ ታደርጋለህ ቢለውም በለዓም ርግማንን እያሰበ በመሄዱ እግዚአብሔር ተቆጥቶታል።

▶️፲፪. ''እግዚአብሔር ከግብጽ አውጥቷቸዋል ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው'' ሲል አንድ ቀንድ ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ቀንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን፣ ክብር ተብሎ ይተረጎማል። አንድ ቀንድ ያለው እንስሳ ባለችው አንድ ቀንድ ከብሮ (ራሱንም አስከብሮ) እንደሚኖር ሁሉ እግዚአብሔር ደግሞ እስራኤልን በሥልጣኑ ከግብፅ አውጥቶ ክብር እንደሆናቸው ለመግለጽ ነው።

▶️፲፫. ''የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የሟርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ ወደ በለዓምም መጡ የባላቅንም ቃል ነገሩት'' ይላል። የሟርቱ ዋጋ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ባላቅ ንጉሠ ሞዓብ በለዓም እስራኤልን እንዲረግምለት ጠይቆት ነበረ። ሲረግምለት ደግሞ የረገመበትን ወይም ያሟረተበትን ዋጋውን እንደሚሰጠው በዋጋ ጠይቆታል። የሟርቱ ዋጋ ያለው ይህንን ነው። ባላቅ ለበለዓም የላከለት እጅ መንሻ ነው።

▶️፲፬. ''የካህኑም የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ባየው ጊዜ ከማኅበሩ መካከል ተነሥቶ በእጁ ጦር አነሣ'' ይላል። የፊንሐስ ጉዳይ አትግደል ከሚለው ትእዛዝ ጋር እንዴት ይታያል? ስለ እግዚአብሔር ቅንዓትስ መግደል በሐዲስ ኪዳን እንዴት ይታያል?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

30 Oct, 15:37


✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን የተለያዩ ሕጎችን የሻረ ሰው እንዲገደል ሥርዓት ተሠርቶ ነበረ። አንድ እስራኤላዊ ከአሕዛብ ጋር ግንኙነት ካደረገ ሁለቱም እንዲገደሉ ሥርዓት ነበረ። ፊንሐስ ያደረገው በሥርዓቱ መሠረት ነው። በሐዲስ ኪዳን ግን የመጨረሻው ቅጣት ውግዘት ነው። እንጂ መግደል አልተፈቀደም። ክፉ ንጉሥ ተነሥቶ ከሆነ ግን እርሱን አጥፍቶ ደግ ንጉሥ ማንገሥ በሐዲስም የተቻለ ነው። ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ መክስምያኖስን አጥፍቶ መንገሡ ተገቢ ነበረና። ይህም ሆኖ ግን ለካህናት ማንንም ሰው ጦር አንሥተው መግጠምና መግደል አልተፈቀደላቸውም። ካህን ያልሆኑ ምእመናን ግን ይህን ቢያደርጉ በደል አይሆንባቸውም።

▶️፲፭. "ዛሬ ሌሊት በዚኽ እደሩ እግዚአብሔርም የሚነግረኝን እነግራችኋለሁ" ይላል (ዘኍ.22፥8)። በለዓም ሟርተኛ ሲሆን እንዴት ይህንን ቃል ተጠቀመ? እንዴትስ ተገለጠለት? እንዴትስ አምላኬ ብሎ እግዚአብሔርን ጠራው? የእግዚአብሔርስ መንፈስ እንዴት በርሱ ላይ ሊመጣ ቻለ?

✔️መልስ፦ በለዓም ጠንቋይ ነው። ነገር ግን ሊረግም ሲነሣ እግዚአብሔር ተገልጦለት ይህንን በል ስላለው ነው። በተፈጥሮ የሁሉም አምላክ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የበለዓምን አፉን ከፍቶ ፊቱን ጸፍቶ እግዚአብሔር የገለጠልኝን እናገራለሁ እንዲል አደረገው። የእግዚአብሔር መንፈስ በፈለገው ሰው ላይ አድሮ መናገር ይችላል። በዚህ እደር በዚህ አትደር ብለን እኛ አስተያየት የምንሰጠው አይደለም። በበለዓም ላይ ያደረ ግን በለዓም ቅዱስ ሆኖ አይደለም። በክፉዎችም አድሮ ትንቢትን እንደሚናገር እኛ እንድንረዳ ይህን አደረገ።

▶️፲፮. “እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፥ ከነዓናውያንንም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱንም ከተሞቻቸውንም እርም ብለው አጠፉ፤ የዚያንም ስፍራ ስም ሔርማ ብለው ጠሩት” ይላል (ዘኍ.21፥3)። እግዚአብሔር ሊያወርሳቸው ካለው ከተሞች አንዷ ከንዓን ነች? ከሆነች ስለምን ያጠፏታል? ጉዟቸውስ እንዴት አላበቃም?

✔️መልስ፦ ያጠፏት ከነዓንን ሀገሪቷን ሳይሆን አስቀድመው በከነዓን የሚኖሩ ሰዎችንና ንብረቶቻቸውን ነው። ጉዟቸው የሚያበቃው ለአባቶቻቸው ለአብርሃምና ለይስሐቅ እንዲሁም ለያዕቆብ የማለላቸውን ምድረ ርስት ሙሉ በሙሉ ሲወርሱ ነው። ስለዚህ የሚቀራቸው ቦታ ስለነበረ ጉዟቸው አላበቃም።

▶️፲፯. “ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ” ይላል (ዘኍ.21፥9)። የነሐሱ እባብ የክርስቶስ ምሳሌ ይደረጋል? ምንድን ተብሎ?

✔️መልስ፦ አወ። መጀመሪያ የነደፋቸው እባብ የዲያብሎስ ምሳሌ ነው። እባብ በመርዙ እንደሚጎዳ ዲያብሎስም በክፉ ሥራው ይጎዳልና። ሙሴ የሰቀለው የነሐስ እባብ ደግሞ የክርስቶስ ምሳሌ ነው። የነሐስ እባብ መርዝ እንደሌለው ክርስቶስም ምንም በደል የሌለበት ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ነውና። የነሐስ እባቡ ተሰቅሎ የታመሙት ሁሉ ሲያዩት እንደዳኑ ሁሉ ክርስቶስም በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ የሰው ልጅ ሁሉ ዳነ። የነሐስ እባቡን ማየት ከሥጋ በሽታ ሲያድን ክርስቶስን ማየት ግን ከሥጋም ከነፍስም በሽታ ያድናል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማመን የመዳን መሠረት ነው።

▶️፲፰. ዘኍ.፳፬፥፲፱ "ከያዕቆብ ኃያል ሰው ይወጣል ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል" ይላል። ይህ ትንቢት የተነገረለት ለማን ነው?

✔️መልስ፦ ለጊዜው ከያዕቆብ የሚወለደው ንጉሥ ዳዊት የቀሩትን ጠላቶች ያጠፋቸዋል ማለት ነው። ለዳዊት የተነገረ ነው። ፍጻሜው ግን ከያዕቆብ ወገን የሚወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ አጋንንትን ያጠፋቸዋል ማለት ነው። ለክርስቶስ የተነገረ ነው።

▶️፲፱. “የእግዚአብሔርም መልአክ፦ አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ” ይላል (ዘኍ.22፥32)። በለዓም አብሮ እንዲሄድ እግዚአብሔር አዞታል። ታዲያ ከዚህ መልአኩ ለምን መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነው አለው?

✔️መልስ፦ እውነት ነው በለዓም እንዲሄድ እግዚአብሔር ፈቅዶ ነበረ። የፈቀደለት ግን እስራኤልን እንዲመርቅ ነበረ። በለዓም ግን በመንገድ ሳለ ርግማንን እያሰበ ሄደ። በዚህ ጊዜ መልአኩ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ተገለጸለትና መንገድህ ጠማማ ነው ብሎታል። በለዓም በተነገረው አካሄድ ቢሄድ ኖሮስ መንገድህ ጠማማ ነው ባልተባለ ነበረ።

▶️፳.“በለዓምም እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርክ ዘንድ እንዲወድ ባየ ጊዜ፥ አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ይሻ ዘንድ አልሄደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና” ይላል (ዘኍ.24፥1)።
ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና ምን ማለት ነው? መነነ እንዴት ነው?

✔️መልስ፦ ወደምድረ በዳ ፊቱን አቀና ማለት ወደምድረ በዳ ሄደ ማለት ነው። እንጂ መነነ ማለት አይደለም።

▶️፳፩. ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበረ ሲል ሞዓብ ሀገር ነው ወይንስ ሰው?

✔️መልስ፦ የሎጥ ልጆች አባታቸውን አስክረው አሳስተው ከእነርሱ ጋር እንዲገናኝ አድርገው ጸነሱና ሞዓብንና አሞንን ወለዱ። ሞዓብ የሎጥ ልጅ (የልጅ ልጅ) ነው። የዚህ የሞዓብ ልጆች በዝተው ሀገር ሆነዋል። ስለዚህ ሀገሪቱን በአባታቸው ስም ሞዓብ ብለዋታል። ስለዚህ ሞዓብ የሀገርም ስም ሆኗል የሰው ስምም ነበረ።

▶️፳፪. መራገም ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ ነው ማለት ይቻላላል? ልክ እንደ በለዓም።

✔️መልስ፦ በለዓም የሚራገም የነበረ በጉልበቱ እንጂ እግዚአብሔር ፈቅዶለት አልነበረም። እግዚአብሔር አንደበትን የፈጠረ እንድናመሰግንበት እንጂ እንድንራገምበት አይደለም። እግዚአብሔር የረገመው የተረገመ ነው። እግዚአብሔር የባረከው የተባረከ ነው። እግዚአብሔር ርገም ብሎ ያዘዘው ሰው ካለ ርግማኑ ከእግዚአብሔር ታዝዞ ስለሚሆን ጸጋ ይሆናል። በጥንቁልናና በራስ ፈቃድ ከተደረገ ደግሞ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ ሳይሆን ሰው በራሱ የፈጠረው ስሕተት ይሆናል።

▶️፳፫. Application Bible ላይ "ኤዶምያስም ርስቱ ይኾናል። ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይኾናል። እስራኤልም በኀይል ያደርጋል። ከያዕቆብም የሚወጣ ገዢ ይኾናል። ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል" ይላል። አዲሱ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጠላቱ "ኤሳው" ይላል ለምን ተለያዩ?

✔️መልስ፦ የኤሳው ሌላ ስሙ ኤዶም ነው። ስለዚህ እየተናገረ ያለው ስለአንድ ሰው ስለሆነ ተለያየ አያሰኝም። መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ቋንቋ ሲተረጎም በተለይ በስሞች ላይ መጠነኛ ልዩነት ሊኖር ይችላል። በሐሳብ ግን ሁሉም አንድ ነው።

▶️፳፬. እስራኤል የበሉት መናና እመቤታችን ኅብስተ መና ትመገብ ነበር ከሚለው ጋር አንድ ነው?

✔️መልስ፦ ተመሳሳይ ነበረ ወይም ተመሳሳይ አልነበረም የሚል በዚህ ዙሪያ መጽሐፍ ላይ አላገኘሁም። ስለዚህ አላውቀውም።

▶️፳፭. ዘኍ.፳፩፥፳፰ "እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ" ይላል። እሳት እና ነበልባልን ለያይቶ ከሁለት ከተማ ወጣ ብሎ የገለጸበት ምክንያት ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ነበልባልና እሳት አንድ ወገን ናቸው። የተለያዩ አይደሉም።


© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

30 Oct, 04:44


💗ኦሪት ዘኍልቍ ክፍል ፭💗

💗ምዕራፍ 21፦
-ሕዝበ እስራኤል እግዚአብሔርንና ሙሴን በማማታቸው በእባብ እንደተነደፉ፣ በኋላ በድለናል ብለው በደላቸውን አምነው ይቅርታ እንደጠየቁ፣ እግዚአብሔር ሙሴን የናስ እባብ እንዲሰቅል ማዘዙ፣ የናስ እባቡን አይቶ በእባብ የተነደፈው ሁሉ እንደዳነ
-እስራኤላውያን ንጉሥ ሴዎንንና ንጉሥ አግን ከነሠራዊታቸው ማሸነፋቸው

💗ምዕራፍ 22፦
-ባላቅ የእስራኤልን ሕዝብ አይቶ እንደፈራና እንዲረዳው በለዓም የተባለ ጠንቋይን መጥራቱ
-ባላቅ በለዓምን እስራኤልን እንዲረግምለት መጠየቁ
-በለዓም ወደ ባላቅ ሲሄድ ባላቅ የነበረባት አህያ መልአኩን የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ እንዳየችውና በለዓም ግን ባለማየቱ አህያይቱን ወደፊት እንድትሄድለት መምታቱ፣ በኋላ መልአኩን እርሱም እንዳየው

💗ምዕራፍ 23፦
-የእግዚአብሔር መንፈስ በበለዓም አድሮ እስራኤላውያንን እንደመረቀ
-በለዓም እስራኤልን የሚመርቁ የተመረቁ፣ እስራኤልን የሚረግሙ የተረገሙ ይሁኑ ብሎ እንደተናገረ

💗ምዕራፍ 24፦
-በለዓም ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ብሎ ትንቢት እንደተናገረ

💗ምዕራፍ 25፦
-እስራኤላውያን ከሞዓባውያን ጋር እንዳመነዘሩ፣ እስራኤላውያን ለሞዓብ አማልክቶች እንደሰገዱ፣ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር እንደተቆጣ
-ፊንሐስ ለእግዚአብሔር ቀንቶ ዘንበሪንና ከስቢን በመግደሉ መዓተ እግዚአብሔርን መመለሱ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. እስራኤላውያንን ይረግምለት ዘንድ በለዓምን የጠየቀው ማን ነው?
ሀ. ሴዎን
ለ. ባላቅ
ሐ. አግ
መ. የኤዶም ንጉሥ
፪. እስራኤላውያን የእባብ መቅሠፍት ከወረደባቸው ጊዜ በኋላ በእባብ የተነደፉት የዳኑት ምንን አይተው ነው?
ሀ. የነደፋቸውን እባብ
ለ. የናስ እባብ
ሐ. የሙሴን በትር
መ. የአሮንን በትር
፫. ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ብሎ ትንቢት የተናገረ ማን ነው?
ሀ. በለዓም
ለ. አሮን
ሐ. ሄኖስ
መ. ካሌብ

https://youtu.be/ifU9K_ls6CA?si=NKJAtGVM0czkoCdv

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

30 Oct, 04:37


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 29🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፲፭
ጥበብ ከትዕቢተኞች የራቀች ናት፡፡ ሐሰተኞችም ሰዎች አያስቧትም፡፡ የክፉ ሰው የአንደበቱ ነገር የሚወደድ አይደለም፡፡ የሚናገረው ነገር እግዚአብሔርን በመፍራት አይደለምና፡፡ እግዚአብሔር ሰው ኃጥእ ይሆን ዘንድ አይወድም፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ክፉና በጎን በሚያውቅ ግዕዛን ፈጥሮ በወደደው ሊኖር ተወው፡፡ እነሆ እግዚአብሔር የወደድከውን ትሠራ ዘንድ ክፉንና በጎን ለይቶ የሚያውቅ ግእዛን ሰጠህ፡፡ ሕይወትም ሞትም በሰው ፊት ይኖራል፡፡ ከእሊህም የመረጠውን ሥላሴ ይሰጡታል፡፡ ይህም ማለት ጽድቅን ቢሠራ ሕይወትን ይሰጡታል፡፡ ኃጢአትን ቢሠራ ሞትን ያመጡበታል ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጥበቡ ረቂቅ ነው፡፡ ዕውቀቱም ጥልቅ ነውና ሁሉን መርምሮ ያውቃል፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአትን ይሠራ ዘንድ ያዘዘው ሰው የለም፡፡ ይበድልም ዘንድ ማንንም አያሰናብትም፡፡
🧡ምዕራፍ ፲፮
በክፉ ልጅ ደስ አይበልህ፡፡ ከሺህ ክፉዎች ልጆች አንድ ደግ ልጅ ይሻላል፡፡ ክፉ ልጅን ከመውለድ ልጅ ሳይወልዱ መሞት ይሻላል፡፡ በአንድ ብልህ ልጅ ሀገር ትጸናለች፡፡ በክፉዎች ብዛት ግን ትጠፋለች፡፡ ኃጥእ ሰው ከፍዳ አያመልጥም፡፡ ጻድቅ ሰው ግን የትዕግሥቱን ዋጋ አያጣም፡፡ ምጽዋት ሁሉ ይቅርታን ያመጣል፡፡ ኃጢአትን ሠርተህ ከእግዚአብሔር አመልጣለሁ በሰማይም የሚያገኘኝ የለም አትበል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

29 Oct, 15:57


💙የጥያቄዎች መልስ ክፍል 27💙

▶️፩. "የሚያነጻውን ውኃ የሚረጭ ሰው ልብሱን ያጥባል፤ የሚያነጻውንም ውኃ የሚነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል"ይላል (ዘኍ.19፥21)። የሚያነጻው ውኃ ርኩሱን ይቀድሳል፤ ንጹሑን ደግሞ ያረክሳልሳ እንዴት ነው አልገባኝም።

መልስ፦ ብዙ ጊዜ በርኵሰት የኖረውን ሰው ካህኑ በሚያነጻው ውሃ ረጭቶ ከርኵሰቱ ያነጻዋል። ሲያነጻው ግን ካህኑ ደግሞ ለአጭር ጊዜ (እስከ ሠርክ ብቻ) የሚያነጻውን ውሃ በመንካቱ ርኩስ እንደሚሆን ተነግሯል። ለአንዱ መንጫ የሆነው ሌላውን እስከ ሠርክ ርኵስ የሚያደርግ ሆነ። ለምን ሆነ ከተባለ እግዚአብሔር ባወቀ።

▶️፪."ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ---ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል---" ይላል (ዘኍ.20፥14)። ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል ያለው የኤዶምያስ ንጉሥ ኤሳው (ዘሮቹ) ነው እንዴት?

መልስ፦ የኤሳው ሌላ ስሙ ኤዶም ነው። የእርሱ የልጅ ልጆች ሀገር መሥርተው በስሙ ኤዶም (ኤዶምያስ) ብለዋታል። ስለዚህ የኤዶም ንጉሥ እየተባለ የሚጠራው የኤሳው ዘሮች ሀገርን የሚገዛውን ለመግለጽ ነው።

▶️፫. "በመሪባ ውኃ ዘንድ በቃሌ ላይ ስለ ዐመፃችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባም" ይላል (ዘኍ.20፥24)። ያ ዐመፅ ምን ብለው እንደሆነ በግልጽ አልገባኝም።

መልስ፦ በውኃ ምክንያት እስራኤላውያን እግዚአብሔርን የተፈታተኑበት ነው (ዘፀ.17፥7)። የእነሙሴ በደልም ተበሳጭተው ለሕዝቡ እግዚአብሔርን ሳያመሰግኑ ውኃን በመስጠታቸው ነው።

▶️፬. “እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፥ ለመለመችም፥ አበባም አወጣች፥ የበሰለ ለውዝም አፈራች” ይላል (ዘኍ.17፥8)። "ለሌዊ ቤት የሆነችው የአሮን በትር" ይላልና አልገባኝም አሮን የሌዊ ወገን ነው? ክህነትስ ለአሮን እና ለልጆቹ ብቻ የተሠጠበት ምክንያት ምንድን ነው?

መልስ፦ አዎ። አሮን የሌዊ ወገን ነው። የሌዊ ወገኖች እነርሱ ስለሆኑና ነገደ ሌዊ ደግሞ እግዚአብሔርን በክህነት እንዲያገለግል በእግዚአብሔር በመመረጡ።

▶️፭. ዘኁ.፲፰ ÷፩ "እግዚአብሔርም አሮንን አለው አንተ ከአንተም ጋራ ልጆችኽና የአባቶችኽ ቤት የመቅደስን ኀጢአት ትሸከማላችኹ አንተም ከአንተም ጋራ ልጆችኽ የክህነታችኹን ኀጢአት ትሸከማላችኹ" ይላል። የመቅደስንና የክህነታችሁን ኀጢአት ትሸከማላችኹ ሲል ምን ማለት ነው?

መልስ፦ የክህነት ኃጢአት የተባለው በተሰጣቸው የክህነት አገልግሎት ማድረግ እየቻሉ ባለማድረጋቸው የሚጠየቁበት ነው። ለምሳሌ ንዋየ ቅድሳቱን ሕዝቡ እንዳይነካው መጠበቅ የሌዋውያን ሥራ ነው። ነገር ግን ቸል ብለው ሳለ በቸልተኝነት ሕዝቡ ንዋያተ ቅድሳትን ቢነካና ሕዝቡ ቢቀሠፍ ተጠያቂ የሚሆኑት ካህናት ናቸው። ይህንን ነው የክህነትና የመቅደስ ኃጢአት ያለው።

▶️፮. “በእግዚአብሔር ፊት ለአንተ ከአንተም ጋር ለዘርህ የጨው ቃል ኪዳን ለዘላለም ነው” ይላል (ዘኍ.18፥19)። የጨው ቃል ከዳን ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፦ ጨውም በመሥዋዕት ላይ ስለሚቀርብ መሥዋዕቱን መባውን የጨው ቃል ኪዳን ብሎት ነው እንጂ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት መብዓ ለአንተ ይሁን ማለት ነው።

▶️፯. ከሁሉም ተለይቶ በሌዊ በትር ላይ የአሮን ስም ለምን ተጻፈ?

መልስ፦ እግዚአብሔር ስላዘዘ

▶️፰. ዘኁ.18፤4 ከባዕድ ወገን የሆነ ሰው ወደ አንተ አይቅረብ ሲል ከሌዋውያን ውጭ ለማለት ነው? ቢብራራልኝ።

መልስ፦ አዎ በደብተራ ኦሪት ላይ የተሾሙ ካህናት ናቸው። እነዚህም ነገደ ሌዊ ናቸው። ከእነርሱ ውጭ በክህነት አገለግላለሁ ብሎ ሌላ አካል እንዳይገባ ማለት ነው።

▶️፱. እግዚአብሔር በክርክር ውኃ ዘንድ ስለ አሳዘናችሁኝ ለእስራኤል ልጆች ወደ ሰጠኋት ምድር አትገቡም ካለ በኋላ አሮንን ለምን ከሙሴ ተለይቶ እንዲሞት ሆነ? ከአሮን ልብሱን አውጡ ልጁንም አልዓዛርን አልብሰው ሲል ምን ማለት ነው?

መልስ፦ ሞት በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ነው። ሁሉም እግዚአብሔር ባሰበው ቀን ይሞታል። አሮንም ሙሴም ምድረ ርስትን ሳይወርሱ ነው የሞቱት። ስለዚህ እግዚአብሔርን እገሌን ለምን ቶሎ እንዲሞት አደረግከው እገሌን ለምን አቆየኸው ማለት አንችልም። ይህ የእርሱ ሥራ ነው። ከአሮን ልብሱን አውጡ ማለት የሊቀ ካህናትነት ልብሱን አውጥታችሁ ለአልዓዛር አልብሱትና አልዓዛር በሞተው በአሮን ምትክ ሊቀ ካህናት ሆኖ ያስተዳድር ማለት ነው።

▶️፲. ሙሴም የኤልያብን ልጆች ዳታንንና አቤሮንን እንዲጠሯቸው ላከ፤ እነርሱም፥ ''አንመጣም ፤ በምድረ በዳ ትገድለን ዘንድ፥ በእኛም ዘንድ አለቃችን ትሆን ዘንድ ወተትና ማር ከምታፈስሰው ምድር ያወጣኸን አነሰህን? አንተ አለቃ ነህን? ደግሞስ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር አገባኽንን? እርሻንና የወይን ቦታንስ አወረስኸንን? የእነዚህ ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም'' አሉ:: ማርና ወተት ከምታፈስሰው ምድር ያወጣኽን አነሰኽን? የሚሉት ግብፅን ነው?

መልስ፦ ግብፅን አይደለም። ይህ ቃል በአጭሩ አንተ ሙሴ ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድረ ርስትን አወርሳችኋለሁ ብለህን ነበረ። አንተ ግን አላወረስከንም ለማለት ነው እንጂ ግብፅን ምድረ ርስት እያሏት አይደለም። ከግብፅ ሲወጡ ምድረ ርስትን ተስፋ አድርገው ነበረ የወጡት ነገር ግን በበደላቸው ምክንያት ብዙ ዘመን ሲቆዩ በሙሴ ላይ ያንጎራጎሩት እንጉርጉሮ ነው።

▶️፲፩. የእነዚህን ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? ሲል ምን ለማለት ነው?

መልስ፦ ዓይኖቻቸውን ታወጣለህን ማለት የሰዎችን ዓይን በሞት ታጠፋለህን ማለት ነው።

▶️፲፪. ዘኍ.20፥12 “እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር ይህን ማኅበር ይዛችሁ አትገቡም አላቸው” ይላል። እግዚአብሔር በመረጣቸው ሙሴና አሮን እንዲኽ እስከሚናገር ድረስ ያደረሰው የሙሴና የአሮን የተለየ ጥፋት ምን ነበር?

መልስ፦ ምክንያቱ ከዚሁ ጥቅስ ላይ ተገልጿል። መሪ ሆነው ሳለ ተበሳጭተው እግዚአብሔርን በወቅቱ ስላልቀደሱት (ስላላመሰገኑት) ነበረ።

▶️፲፫. ከዚህ በፊት ካነበብናቸው ምዕራፎች ሬሳም ሆነ ሌላ ርኩስ ነገር የነካ እስከ ማታ ይረክሳል በበነገታው ይነፃል ዘኍልቍ ላይ ግን እስከ ሰባት ቀን ይላል ልዩነቱ ምንድን ነው/እንዴት ይታያል?

መልስ፦ እንደርኵሰቱ ዓይነት ይለያያል። ለምሳሌ በማርያም እኅተ ሙሴ ሰባት ቀን የወሰነባት እግዚአብሔር ነው። እስከ ሠርክ የሚያረክሱ ርኵሰቶች እስከ ሠርክ ያረክሳሉ። ሌላውም እንደርኵሰቱ ዓይነት በተመደበለት ጊዜ ይፈጸማል። እርስ በእርሱ የሚቃረን የለውም።

▶️፲፬. እነ ቆሬ የተቀጡት ምድር ተከፍታ ከነሕይወታቸው ዋጠቻቸው ሲል ምን ለማለት ነው ቢያብራሩልኝ።

መልስ፦ ሰው ከሞተ በኋላ ነው ወደመሬት የሚቀበር። የሚቀብረውም ሌላ ሰው ነው። እነቆሬን ግን ሌላ ቀባሪ ሳያስፈልግ ከነሕይወታቸው ሳሉ ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው እግዚአብሔር አደረገ ማለት ነው።

▶️፲፭. ሌዋውያንና አሮን ምንድን ነው ልዩነታቸው እሱ ሌዋዊ አይደለም?

መልስ፦ አሮንም ሌዋዊ ነው። ልዩነቱ አሮን ሊቀ ካህናት ሲሆን ሌሎች ሌዋውያን የእርሱ ተወራጅ ካህናት ናቸው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

29 Oct, 13:16


https://youtu.be/jeyEQqhsK-M?si=BmSRvypDHMEpXe_8

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

29 Oct, 04:27


💟ኦሪት ዘኍልቍ ክፍል ፬💟

💟ምዕራፍ 16፦
-ቆሬ ከዳታን፣ ከአቤሮን፣ ከአውናንና ከእስራኤል ከተመረጡ 250 ሰዎች ጋር ሆኖ በሙሴና በአሮን ላይ መነሣቱ፣ በድፍረት ተነሥተውም ጥናዎችን ይዘው እናጥናለን ማለታቸው፣ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር መቅሠፍትን እንዳወረደባቸው ከብቶቻቸውን፣ ቤቶቻቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን ሁሉ ምድር ተከፍታ እንደዋጠቻቸው
-ሙሴ በመጸለዩ መቅሠፍቱ እንደቆመ

💟ምዕራፍ 17፦
-ሙሴ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድና ከነገደ ሌዊ አንድ አንድ በትር ወስዶ በደብተራ ኦሪት እንዲያስቀምጥ መታዘዙ
-የአሮን በትር ለምልማ፣ አብባ፣ የበሰለ ለውዝ አፍርታ መገኘቷ

💟ምዕራፍ 18፦
-በእስራኤል ልጆች ላይ መዓት እንዳይመጣባቸው የሌዊ ነገዶች የደብተራ ኦሪትን ሕግና ሥርዓት እንዲጠብቁ መታዘዛቸው
-በኵራት፣ ክፍለ መሥዋዕት፣ ቀዳምያት፣ ዐሥራት የሌዋውያን ፈንታ እንዲሆን መታዘዙ
-ሌዋውያን የዐሥራት ዐሥራት እንዲያወጡ መታዘዛቸው

💟ምዕራፍ 19፦
-ንጹሕ የሆነች ቀይ ጊደርን ካህኑ አልዓዛር ከሰፈር ውጭ ወስዶ በንጹሕ ስፍራ ላይ በፊቱ እንደሚያርዷት፣ አልዓዛር ከደሟ በጣቹ ወስዶ በምስክሩ ድንኳን ፊት ሰባት ጊዜ እንደሚረጨው፣ ጊደሪቱን በፊቱ እንደሚያቃጥሏት፣ ንጹሕ ሰው የጊደሯን አመድ ከንጹሕ ቦታ እንደሚያስቀምጠውና ይህም የእስራኤል መንጫ እንዲሆን መታዘዙ
-የሞተ ሰውን በድን የነካ ሰው ሰባት ቀን ርኩስ እንደሚሆን፣ ርኩሱን ሰው የሚነካ ሰው ደግሞ እስከ ሠርክ እንደሚረክስ

💟ምዕራፍ 20፦
-ማኅበረ እስራኤል በውሃ ጥም በተቸገሩ ጊዜ ሙሴ በበትሩ ከድንጋይ ውሃ አፍልቆ ሕዝቡን እንዳጠጣቸው
-አሮን እንደሞተና በእርሱ ምትክ ልጁ አልዓዛር እንደተሾመ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ሳይፈቀድለት ጥናዎቹን ወስዶ አጥናለሁ ብሎ በሙሴና በአሮን ስላጉረመረመ ምድር ተከፍታ የዋጠችው ማን ነው?
ሀ. ቆሬ
ለ. ዳታን
ሐ. አቤሮን
መ. ሁሉም
፪. በደብተራ ኦሪት ተቀምጣ ሳለ ለምልማ፣ አብባ፣ አፍርታ የተገኘች የማን በትር ናት?
ሀ. የሙሴ
ለ. የአሮን
ሐ. የኤፍሬም
መ. የምናሴ
፫. ሕዝቡ ለደብተራ ኦሪት ከሚሰጠው ለሌዋውያን እንዲሆናቸው የታዘዘላቸው ምንድን ነው?
ሀ. ቀዳምያት
ለ. በኵራት
ሐ. ዐሥራት
መ. ሁሉም

https://youtu.be/XRcJ6mdbPGA?si=HVdVSbo2pBj6doTJ

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

29 Oct, 04:22


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 28🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፲፫
የማትችለውን ሸክም አንስተህ እሸከማለሁ አትበል፡፡ ታላቅ ሰው ያዘዘህን ስለታላቅነቱ እሺ በለው ቢጠራህ አቤት ቢልክህም ወዴት በለው፡፡ እንዲህም ያደረግህ እንደሆነ እጅግ ይወድሀል፡፡ ከታላቅ ሰው እጅግም አትራቅ እጅግም አትቅረብ፡፡ እጅግም የራቅህ እንደሆነ ይረሳኻልና እጅግም የቀረብህ እንደሆነ ይሰለችኻልና፡፡ ኃጢአትን ሳይሠሩ የሚገኝ ባለጸግነት ደግ ነው፡፡
🧡ምዕራፍ ፲፬
በአፉ ክፉ ተናግሮ ያልተሰናከለ ሰው ክቡር ነው፡፡ ነገር ለማያውቅ ሰው ሹመት አይገባውም፡፡ ለንፉግም ሰው ገንዘብ አይገባውም፡፡ የደኻውን ልመና እንዳይሰማ ፊቱን የሚመልስ ሰው ነፍሱን ቸል ማለቱ ነው፡፡ ተዘከር ከመ ኢይጐነዲ ዕለተ ሞት፡፡ ሞት እንደማይዘገይ አስብ፡፡ ዕለተ ሞትም ይቀራል ብለህ አያጠራጥርህ፡፡ ሳትሞት ለባልንጀራህም ለወገንህም በጎ አድርግ፡፡ ሰው ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃል ያፈጃል፡፡ ሰው እኩሌታው ሲወለድ እኩሌታው ሲሞት ይኖራል፡፡ ሥራ ሁሉ ያረጃል ያፈጃልም፡፡ ሠሪውም እንደ ሥራው ያልፋል ይጠፋልም፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

28 Oct, 16:42


💙የጥያቄዎች መልስ ክፍል 26💙

▶️፩. “በመካከላቸውም የነበሩ ልዩ ልዩ ሕዝብ እጅግ ጎመጁ፤ የእስራኤል ልጆች ደግሞ ያለቅሱ ነበር፦ የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል?” ይላል (ዘኍ.11፥4)። “በመካከላቸውም የነበሩ ልዩ ልዩ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ" ይላልና ምን አይተው ነው? ንባቡ አልገባኝም።

✔️መልስ፦ ጎመጁ ማለት በጣም ተመኙ ማለት ነው። ምኞት ደግሞ ታይቶም ሳይታይም ሊሆን ይችላል። ሥጋ ለመብላት ነው የጎመጁት።

▶️፪. “ሕዝቡንም በላቸው፦ የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል? በግብፅ ደኅና ነበረልን እያላችሁ ያለቀሳችሁት ወደ እግዚአብሔር ጆሮ ደርሷልና ለነገ ተቀደሱ፥ ሥጋንም ትበላላችሁ እግዚአብሔርም ሥጋን ይሰጣችኋል፥ ትበሉማላችሁ” ይላል (ዘኍ.11፥18)። "ወደ እግዚአብሔር ጆሮ ደርሷልና ለነገ ተቀደሱ" ይህ ንባብ የሕዝቡ ምሬት ልክ እንደሆነ አይመሠክርም? ታዲያ እግዚአብሔር ለምን ተቆጣ?

✔️መልስ፦ ወደእግዚአብሔር ጆሮ ደርሷል ማለት መጀመሪያ አልደረሰም ማለት አይደለም። ማንኛውንም ነገር እግዚአብሔር ከመሆኑ በፊት ያውቀዋልና። ወደእግዚአብሔር ጆሮ ደረሰ ማለት የፈለጉትን ለመስጠት ጊዜው ደረሰ ማለት ነው። የሕዝቡ ምሬት እግዚአብሔርን እስከመውቀስ የደረሰ ነበረ። በተገቢው መልኩ በትሕትና አይደለም ልመናቸውን ያቀረቡት። ስለዚህ እግዚአብሔር ተቆጣ ማለት ቀጣቸው።

▶️፫. “አንድ ጎበዝ ሰው እየሮጠ መጥቶ፦ ኤልዳድና ሞዳድ በሰፈር ትንቢት ይናገራሉ ብሎ ለሙሴ ነገረው” ይላል (ዘኍ.11፥27)። ከዚህ ንባብ በላይም ሽማግሌዎች ትንቢት እንደተናገሩ ተፅፏል ትንቢታቸው እውነተኛ ነበር ወይንስ ሐሰተኛ ነቢያት ነበሩ?

✔️መልስ፦ ትንቢታቸው እውነተኛ ነበረ። ምክንያቱም ትንቢቱን የገለጸላቸው እግዚአብሔር ስለሆነና በትክክል ሙሴ በእግዚአብሔር ታዝዞ የመረጣቸው ስለሆነ ነው። ኤልዳድና ሞዳድ ምንም እንኳ ከሌሎቹ ጋር ወደምስክሩ ድንኳን ባይሄዱም በመመረጣቸው ብቻ መንፈሰ እግዚአብሔር ተገልጦላቸው ትንቢትን ተናግረዋል።

▶️፬. “ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳያኝኩትም፥ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ መቅሠፍት እጅግ መታ” ይላል (ዘኍ.11፥33)። እግዚአብሔር ራሱ መና ካወረደላቸው ለምን ሕዝቡን በመቅሠፍት መታ?

✔️መልስ፦ ባሕር ከፍሎ፣ ከፈርዖን ጽኑ አገዛዝ ነጻ አውጥቷቸው ሳለ፣ እንደማር የሚጣፍጥ መናን አውርዶ እየመገባቸው ሳለ በተራ ምግብ እግዚአብሔርን ስላሳዘኑና በእግዚአብሔር ላይ ስላንጎራጎሩ በመቅሠፍት መትቷቸዋል።

▶️፭. ማርያም እና አሮን በሙሴ ሚስት ላይ ምን ተናገሩ? ለመናገር ምክንያታቸው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሚስቱ ከአሕዛብ ወገን ናት ብለው ነው ያንጎራጎሩ።

▶️፮. ሐሜቱን (ነገሩን) የተናገሩት ማርያም እና አሮን ሁነው ሳለ እግዚአብሔር አምላክ ለምን ማርያምን ነጥሎ በለምፅ መታት?

✔️መልስ፦ አሮን ካህን ስለሆነ የካህንን ነውር በአደባባይ መግለጽ እንደማይገባ ሲያስተምረን ውስጥ ውስጡን አሳምሞ ትቶታል። ማርያም ግን ካህን ስላልሆነች ለሌላው መቀጣጫ ትሆን ዘንድ በውጭ ለምጽ መትቷታል።

▶️፯. "ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር” ይላል (ዘኍ.13፥13)። የመላእክት ስም ለሰው ልጅ መሠየም ይፈቀዳል? በዚህ ዘመን አንዳንድ ክርክሮችን ስለሠማሁ ነው።

✔️መልስ፦ የሚከለክል ነገር አላገኘሁም። በዮሐንስ ራእይም ሚካኤል የሚባል ሰው ነበረ። ነገር ግን ስሙ እንደ ግብሩ ባለመሆኑ ተነቅፏል። የመላእክት ስም የእግዚአብሔርን ግብረ ባሕርይ የሚገልጽ ነው። ለምሳሌ ሚካኤል ማለት እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው ማለት ነው። ሚክያስም እንዲሁ ነው። ስለዚህ በመጻሕፍት መሠረት በእግዚአብሔር ስም ነው መጠራት የማይገባ እንጂ በሌሎቹ ሲከለከል አላገኘሁም።

▶️፰. “በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን ኔፊሊም፥ የዔናቅን ልጆች፥ አየን፤ እኛም በዓይናችን ግምት እንደ አንበጣዎች ነበርን፥ ደግሞም እኛ በዓይናቸው ዘንድ እንዲሁ ነበርን አሉ” ይላል (ዘኍ.13፥33)። የኔፊሊ ሕዝቦች በኖኅ ዘመን አልጠፉም? እነዚህ ሕዝቦች ምን ዓይነት ናቸው?

✔️መልስ፦ ረጃጅምና ጽኑ አርበኞችን ኔፍሊም እያለ ስለሚገልጻቸው ነው እንጂ ደቂቀ ቃየል በማየ አይኅ ጠፍተዋል። እኒህም ኃያላን ስለሆኑ ኔፍሊም ተብለው በስም ተመሳስለው ነው እንጂ እነዚህ የደቂቀ ቃየል ልጆች አይደሉም።

▶️፱. ሥጋ ማን ያበላናል? (ዘኁ 11፥4) ያሉት እውነት ሥጋ አጥተው ነው? እንደዚያ ከሆነ ለኀጢአት መሥዋዕት እና ለደኅንነት መሥዋዕት የሚሆነውን ከየት እያገኙት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ ሥጋ አጥተው ነው። ምግባቸው ለአርባ ዘመን ያህል መና ነበረ። መናው ግን በብዙ ዓይነት መልኩ ይሠራ ነበረ። ሥርዓተ መሥዋዕቱ የተሠራው በዋናነት ምድረ ርስት ከገቡ በኋላ እንዲያከናውኑት ነው።

▶️፲. (ዘኁ.14፥18) ላይ "ኀጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ" ይላል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ኃጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ ማለት በትክክል የበደሉ ሰዎችን የሚቀጣ ማለት ነው። ይኸውም ከበደሉ ለበደላቸው ቅጣት እንደሚያዘጋጅ ለመግለጽ ነው። ፈታሒነቱን ለመግለጽ ነው። የኃጢአተኛን ፍዳውን እከፍላለሁ ሲል ነው።

▶️፲፩. ምድሪቱን እንደሰለሉባቸው እንደነዚያ አርባ ቀኖች ቁጥር...ይላል (ዘኁ.14፥34)። ሰላዮቹ 40 ቀን ቆይተው ነው? እንደዚያ ከሆነ የወይኑ ዘለላ እንዴት ሳይደርቅ?

✔️መልስ፦ አወ አርባ ቀን ቆይተዋል። ዘለላ ቆርጠው እንደመጡ ተነገረ እንጂ ስለዘለላው መድረቅ አለመድረቅ የተነገረ ነገር የለም። ደርቆ ከነበረም ፍሬውን፣ በተአምራት አልደረቀ ከነበረም ዘለላውን አቅርበዋል። መጽሐፉ ስለዘለላው የተናገረው ነገር የለም። ለእስራኤላውያን እንኳ ፍሬውን እንደአሳዩ ነው የተነገረው።

▶️፲፪. እግዚአብሔር ሙሴን ከእስራኤል ሽማግሌዎች ሰባ ሊቃውንት እንዲመረጥ ያዘዘበት ምክንያት ምንድን ነው ምሥጢሩ?

✔️መልስ፦ ምሥጢሩ ሙሴን በአስተዳደር እንዲያግዙት ነው። በዚያው ተገልጿል። ወይፀውሩ ምስሌከ ክበዶሙ ለእሉ ሕዝብ ወኢትሥራሕ ባሕቲትከ ሎሙ እንዲል (ዘኍ.11፥17)።

▶️፲፫. ሙሴን ኢትዮጵያዊቱን ሴት በማግባቱ ማርያምና አሮን ያሙት በምን ምክንያት ነው? ለምን አገባት ነው ወይስ በሌላ ነው?

✔️መልስ፦ ያሙት እኛን ከአረማውያን አትጋቡ ይለናል እርሱ ግን ኢትዮጵያዊትን አግብቷል ብለው ነው። እኛን ከሴት አድራችሁ ወደደብተራ ኦሪት አትግቡ ይለናል እርሱ ግን ይገባል ብለው ነው ያሙት።

▶️፲፬. እግዚአብሔር ሁሉንም በእርሱ ኃይል ማወቅ እየቻለ ለምን ሙሴን ወደ ከነዓን ሰላይ ላክ አለው? ምሥጢሩ ምንድን ነው? የተላኩትስ የሰለሉትን ምድር ለእስራኤል ልጆች አስፈሪ አድረገው ለምን ተናገሩ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር የራሱን ሥራ ይሠራል። ሲሠራ ደግሞ በተለይ ሰውን ለመጥቀም ሲፈልግ የነጻነት አምላክ ስለሆነ የሰዎችን ፈቃድ አይቶ ነው። የሰዎች ፈቃድ ደግሞ ትእዛዙን በመፈጸም ይገለጣል። ስለዚህ እስራኤላውያን ወደከነዓን እንዲገቡ የእርሱ ፈቃድ ነው። የእነርሱ ፈቃድ ደግሞ የታዘዙትን በመፈጸም መገለጥ ነበረበትና ሁሉን እያወቀ ድርሻቸውን እንዲወጡ 12 ሰላይ ተመርጦ እንዲሰልሉ ተደረገ። የተላኩት 10ሩ አስፈሪ አድርገው መናገራቸው የራሳቸው ድክመትና እግዚአብሔርን ያለማመን ውጤት ነው። ሁለቱ ግን ሕዝቡ ባይሰማቸውም እውነታውን ለሕዝቡ አቅርበው ነበረ።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

28 Oct, 16:42


▶️፲፭. “ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል” ይላል (ዘኍ.14፥21)። እግዚአብሔር ሙሴን ሲያነጋግር ከሦስቱ አካል ማን ነበር የሚያናግረው? በዚህ ጥቅስ ላይ 'እኔ' ብሎ ስለሚናገር ነው ይህን ጥያቄ ያነሳሁት።

✔️መልስ፦ በትርጓሜ በብሉይ ኪዳን የተነገሩትን ለአብ ሰጥቶ አድሎ ይነገራል። ነገር ግን አድሎ መናገር እንጂ አንዱ በአንዱ አለ። ሦስቱ አካላት በግብረ ባሕርይ አንድ ስለሆኑ የሦስቱም ነገር ነው። ያ የአንዱ ንግግር በመንፈስ ቅዱስ ሕያውነት ሕያው ተሁኖ በአብ ልብነት የታሰበ በወልድ ቃልነት የተነገረ ነውና።

▶️፲፮. ''እግዚአብሔር በደመናው ወረደ ተናገረውም በእርሱም ላይ ከነበረው መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አደረገ መንፈሱም በላያቸው ባደረ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ ከዚያ በኋላ ግን አልተናገሩም'' ሲል መንፈስን ወስዶ ማለት ምን ለማለት ነው።

✔️መልስ፦ ሀብተ ትንቢትን ወስዶ ማለት ነው። መንፈስ ብዙ ትርጉም አለው። (ነገረ ክርስቶስ ብየ ካዘጋጀሁት PDF) ይመልከቱ። ሀብተ መንፈስ ቅዱስን መንፈስ ይለዋል። ትንቢት ደግሞ አንዱ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ከዚህ መንፈስ ተብሎ ተገልጿል።

▶️፲፯. ''እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ በምሳሌ አይደለም የእግዚአብሔርንም መልክ ያያል በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አልፈራችሁም አለ'' ይላል። የእግዚአብሔርን መልክ ማየቱን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ማየት እንደማያድነው ከተነገረው ጋር እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔርንም መልክ ያያል ማለት ጌትነቴን በዘፈቀድኩ ያያል ማለት ነው። ይኸውም ለሙሴ ሊታይና ሊረዳ በሚችል መልኩ በዘፈቀደ (እርሱ እግዚአብሔር በወደደ) የታየውን መታየት ለመግለጽ ነው። በባሕርይው ግን እግዚአብሔርን ያየው የለም። የሚገርመው ወደፊትም የሚያየው አይኖርም (ዮሐ.1፥18)።

▶️፲፰. ዘኍ.11፥4-6 ላይ ጸሎት በሚመስል መልኩ ሥጋን ሽተዋል፤ ቁጥር10 ላይ "የእግዚአብሔር ቁጣ እጅግ ነደደ፣ ሙሴም ተቆጣ" ሲል ቁጥር 18 ላይ ደግሞ ጸሎታችሁ ተሰምቷልና ተዘጋጁ አላቸው። ከበሉ በኋላ ለሚያመጣባቸው መቅሠፍት እና ሊገድላቸው ከሆነ ለምን ጸሎታቸውን ሰምቶ የሚበሉት ድርጭት አዘጋጀላቸው?

✔️መልስ፦ ሥጋን ሲሹ እግዚአብሔርን በትሕትና አልጠየቁም። እግዚአብሔር የሰጣቸውን ነጻነት አማርረው በግብፅ የምንገዛው መገዛት ይሻለን ነበር አሉ። ይህንም ያሉት የግብፁ አኗኗር የተሻለ ስለነበረ አይደለም። በእግዚአብሔር ማጉረምረም ስለፈለጉ ነው እንጂ። የእስራኤል ሕዝብ አስቸጋሪ ሕዝብ ነበረ። በዚህ ከንቱ አነጋገራቸውና አስተሳሰባቸው እግዚአብሔር መቅሠፍትን አምጥቶባቸዋል። ስለዚህ ምግቡን አቅርቦ ቀሥፏቸዋል። ፍላጎታቸውን ፈጽሞ በማጉረምረማቸው ደግሞ ቀጥቷቸዋል።

▶️፲፱. ዘኍ.13፥25 "ምድሪቱንም ሰልለው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ" ይላል። እነዚህ 40 ቀናት የሄዱበት ሲደመር የሰለሉበት ሲደመር የተመለሱበት ሆኖ ሳለ የ40ቀናት መንገድ 40 ዘመን ፈጀባቸው እየተባለ በተደጋጋሚ በመጽሐፍት መምህራንም ሲነገር ሰምቻለው። ነገር ግን ንባቡ ላይ ትክክለኛው የመንገዱ ርቀት የስንት ቀን እንደኾነ አይናገርም። በተጨማሪም 40 ዘመን ተጓዙ ሳይሆን 40 ዘመን በበረሃ ኖሩ ብሎ ማስተማር ትርጉም የሚሰጥ ይመስላል። እስኪ መምህር ያብራሩልኝ።

✔️መልስ፦ ሰላዮቹ 40 ቀን ሰልለው እንደተመለሱ ተነግሯል። እስራኤላውያንን በማንጎራጎራቸውና በመበደላቸው ግን አንድ ቀን የሚፈጀው ጊዜ ዓመት እንዲፈጅባቸው ተነግረዋል። ይህ የሚገኘው ቀጥሎ ካለው ምዕራፍ ነው። ዘኍ.14፥34 "እምአርብዓ አሐቲ ዕለት ዓመተ ትከውን ብክሙ በእንተ ኃጢአትክሙ ወይኩንክሙ አርብዓ ዓመ" ተብሎ በግልጽ ተቀምጧል። 40 ዘመን ያለው 40 ዓመት ነው። አሐቲ ዕለት ዓመተ ትከውን ብክሙ ብሎ በግልጽ ተናግሯልና።

▶️፳. ዘኍ.11÷18 ላይ ለነገ ተቀደሱ ሥጋንም ትበላላችሁ እግዚአብሔርም ሥጋን ይሰጣችኋል ትበሉማላችሁ ብሎ ለሙሴ ነገርው ሙሴም ለሕዝቡ ነገራቸው። ቁጥር 33 ላይ ደግም ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳያኝኩትም የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ መቅሠፍት እጅግ መታ ሥጋው ገና በጥርሳቸው ሳለ የእግዚአብሔር ቁጣ መጣባቸው ይላል? እሱ አይደል ትበላላችሁ ተዘጋጁ ያላቸው አይጣረስም ወይ ቁጥር 18 እና 33 ያለው?

✔️መልስ፦ አይጣረስም። መብላት ፈለጉ። መብላት ሲፈልጉ ግን በትሕትና መጠየቅ ሲገባቸው በማንጎራጎር ጠየቁ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሁለቱንም አሳካላቸው። ምግብ ፈልገው ነበረ ምግብ አቀረበላቸው። አንጎራጉረው ስለነበረ ደግሞ መቅሠፍቱን አበላቸው።

▶️፳፩. ድርጭት ምንድን ነው? ሥጋ ነውን?

✔️መልስ፦ ከዚህ ድርጭት የሚለው ዓሣውንና የባሕር ዶሮውን ነው። የእነዚህን ሥጋ አበላቸው ማለቱ ነው።

▶️፳፪. ዘኁ.፲፩፥፳፭ ሰብዓው ሊቃናት ለምን ተመረጡ?

✔️መልስ፦ በአስተዳደር ሙሴን እንዲያግዙት

▶️፳፫. ዘኍ.፲፪፥፲፭ ማርያም እኅተ ሙሴ ከሰፈር ውጭ ለሳምንት መቆየቷንና መዳኗን ይገልፃል። ሰንበትን የሻረውም ከሰፈር ውጭ እንደወገሩት እንደገደሉት ይገልፃል በኦሪት የማይረባውን ያልተገባውን ከሰፈር ወጭ እንደሚጣል ይገልፃል። ክርስቶስንና ሌሎች ቅዱሳን አባቶቻችንም ከሰፈር ወጭ አውጥተው መከራ እንዳደረሱባቸው ይገለፃል። ስለዚህ ከሰፈር ውጭ መሆኑ በኦሪት ምክንያቱ ምንድን ነው? ከሰፈር ውጭ ይህ የብሉዩ ከሐዲስ ጋር ምሥጢር ካለው ወይም ምሳሌነት ካለው ቢያብራሩልን?

✔️መልስ፦ ሰፈሩን እንዳያረክሱ ተብሎ ነው የረከሱ ሰዎች ከሰፈር ውጭ እንዲቆዩ የነበረው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም በደለኛ ነው ብለው ከሰፈር ውጭ ሰቀሉት። ነገር ግን እርሱ ንጹሐ ባሕርይ ነው። በምሥጢር አዳም ከገነት ወጥቶ በምድር (በአፍኣ) ይኖር ነበረ። አዳምን ለመካስ ክርስቶስ ደግሞ ከሰፈር ውጭ በኢየሩሳሌም በቀራንዮ ተሰቀለ። በዚህም አዳምን ወደገነት መለሰው።

▶️፳፬. ዘኁ፲፪፥፩ ሙሴ ያገባት ኢትዮጲያዊት ሴት ማን ናት? ከየትስ ልናገኘው እንችላለን?

✔️መልስ፦ ሲፓራ። ምንጭ ዘፀ.2፥21

▶️፳፭. አሥራ አንዱ አሳሾች ከነዓንን ለማሰስ አርባ ቀን ፈጀባቸው በማጉረምራቸውም አንዱ ቀን እንደ አንድ ዓመት አርባ ቀን እንደ አርባ ዓመት እንዲሆንባቸው ተረግመዋልና። ከግብፅ ከመጀመሪያው ጉዞ እስከ ከነዓን ለመግባት ስንት ዓመት ፈጀባቸው?

✔️መልስ፦ በጠቅላላው አርባ ዓመት ፈጅቶባቸዋል።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

28 Oct, 04:51


💓ኦሪት ዘኍልቍ ክፍል ፫💓

💓ምዕራፍ 11፦
-ሕዝቡ በክፋት በእግዚአብሔር ላይ እንዳጉረመረሙና እግዚአብሔርም ተቆጥቶ በእሳት እንዳቃጠላቸው
-ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮ መዓተ እግዚአብሔርን እንዳራቀ
-እስራኤላውያን መና ሰለቸን ማለታቸውና ግብጽ ሳሉ ይበሉት የነበረውን ምግብ እንደተመኙ
-ሙሴ ሰባ ሽማግሌዎችን እንደመረጠና በእነርሱ ላይም የእግዚአብሔር መንፈስ አርፎባቸው ትንቢት እንደተናገሩ፣ ከሰባው ሁለቱ ግን ከሰፈር ቀርተው እንደነበረና ቢሆንም ግን መንፈስ እንዳረፈባቸውና ትንቢት እንደተናገሩ
-እስራኤላውያን ሥጋን ተመኝተው በእግዚአብሔር ላይ ባጉረመረሙ ጊዜ እግዚአብሔር የድርጭት ሥጋን በነፋስ እንዳመጣላቸው፣ ሥጋውን እየበሉ ሳለም መቅሠፍተ እግዚአብሔር ወርዶ እንዳጠፋቸው

💓ምዕራፍ 12፦
-ሙሴ ኢትዮጵያዊቱን ሴት በማግባቱ እህቱ ማርያምና ወንድሙ አሮን እንደአሙት፣ በዚህም ምክንያት ማርያም ለምጻም እንደሆነች፣ በኋላ ሙሴ ጸልዮ ፈውስን ከእግዚአብሔር እንዳሰጣት
-ሙሴ በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የዋህ ሰው እንደነበረ
-ሙሴ የታመነ አገልጋይ መሆኑን እግዚአብሔር መግለጹ

💓ምዕራፍ 13፦
-ሙሴ የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ 12 ሰዎችን መላኩ፣ የተላኩት ሰዎችም ሰልለው መጥተው የወይን ዘለላ፣ ሮማን፣ በለስ ተሸክመው እንደመጡ
-ሙሴ ከነገደ ኤፍሬም የሚወለደውን አውሴን ኢያሱ ብሎ እንደጠራው
-ሰላዮቹ ስለከነዓን አጋንነው በመናገራቸው ሕዝቡ እንደፈራ፣ ካሌብ ግን ማሸነፍ እንችላለንና እንውጣ ማለቱ

💓ምዕራፍ 14፦
-የእስራኤል ልጆች በሙሴና በአሮን ላይ ማጉረምረማቸው፣ በእግዚአብሔር ላይ ያመፁት ሰዎች እንደተቀሠፉ
-ኢያሱና ካሌብ ከነዓንን ማሸነፍ እንደሚችሉ መናገራቸው፣ በዚህም ምክንያት ሌሎች ሲጠፉ ካሌብና ኢያሱ መትረፋቸውና ምድረ ርስትን እንደሚወርሱ መነገሩ
-ሙሴ ለሕዝቡ እንደለመነና እግዚአብሔርም ሕዝቡን ይቅር እንዳለ
-ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል ስላልሰሙ ምድረ ርስትን እንደማይወርሱ መነገሩ
-እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስላልሆነ ጠላቶቻችሁን አትግጠሙ እየተባሉ አንሰማም ብለው የገጠሙት እንደተሸነፉ

💓ምዕራፍ 15፦
-እስራኤላውያን ወደምድረ ርስት ሲገቡ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲያቀርቡ መታዘዛቸው
-ላልታወቀ ኃጢአት መሥዋዕት እንዲሠዋ መታዘዙ
-ትዕቢትን የሚያደርግ ሰው እግዚአብሔርን ሰድቧልና ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ መባሉ
-በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም የተገኘው ሰው እንዲገደል መፈረዱ
-እስራኤላውያን በልብሳቸው ዘርፍ ሰማያዊ ፈትል እንዲያደርጉ መታዘዙ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ሙሴ ሰባ ሽማግሌዎችን መርጦ ከተመረጡት ውስጥ 68ቱ ወደ ደብተራ ኦሪት ሄደው የእግዚአብሔር መንፈስ ሲወርድባቸው ሁለቱ ግን ከሰፈር ቀርተውም የእግዚአብሔር መንፈስ ወርዶባቸው ትንቢት ተናግረዋል። ማንና ማን ናቸው?
ሀ. አሮንና ሖር
ለ. አውሴና ካሌብ
ሐ. ኤልዳድና ሞዳድ
መ. ሙሴና አውሴ
፪. ከነዓንን እንዲሰልሉ ከተላኩት 12ቱ ሰላዮች የሰለልናትን ሀገር ሰዎች ማሸነፍ እንችላለንና እንውረሳት ያለ ማን ነው?
ሀ. ካሌብ
ለ. ጉዲኤል
ሐ. ሰሙኤል
መ. ዓሚሄል
፫. እስራኤላውያን በልብሳቸው ዘርፍ እንዲያደርጉት የታዘዘ ፈትል ምን ዓይነት ቀለም ያለው ነው?
ሀ. ነጭ
ለ. ሰማያዊ
ሐ. ቀይ
መ. ጥቁር

https://youtu.be/ge6h5A4QFfI?si=RJwCrwhOED6NpTir

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

28 Oct, 04:37


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 27🧡
🧡መጽሐፈ ሲራክ
🧡ምዕራፍ ፲፩
ድኻ በጥበቡ ይከብራል፡፡ በመኳንንትም መካከል ይቀመጣል፡፡ መልኩ አማረ ብለህ ለመልከ መልካም ሰው አታድላለት፡፡ መልከ ክፉውንም ሰው መልኩ ከፋ ብለህ አትንቀፈው፡፡ ንብ ከአዕዋፍ ሁሉ ተለይታ በመልክ ስትከፋ ማሯ ከሁሉ ይልቅ ይጣፍጣል፡፡ በልብስህ ጌጥ አትኩራ፡፡ በተሾምክበትም ወራት ራስህን አታስታብይ፡፡ ሳትመረምር አትንቀፍ፡፡ አስቀድመህ ነገሩን ጠይቀህ ተረዳ እንጂ፡፡ በሰው ነገር ጥልቅ ብለህ አትግባ፡፡ የእግዚአብሔር ረድኤቱ ጻድቃንን ትጠብቃቸዋለች፡፡ በገንዘብህ ዕወቅበት ከእግዚአብሔርም ታረቅበት፡፡ በሥራህም ጸንተህ ኑር፡፡ እግዚአብሔር ለጻድቃን ዋጋቸውን አብዝቶ ይሰጣቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለሰው እንደሥራው ዋጋውን ይከፍለዋል፡፡ በጎ ቢሠራ ዋጋውን ይሰጠዋል፡፡ ክፉ ቢሠራ ፍዳውን ያመጣበታል፡፡ ፍጻሜውን ሳታይ ሰውን ዕፁብ ዕፁብ አትበለው፡፡ ያገኘኸውን ሰው ሁሉ ሳትመረምር አትሹም፡፡ ተንኮለኛ ሰው በጎ ያደረግህለትን ያህል ክፉ ነገር ይመልስልኻል፡፡ ነውርም ሳይኖርብህ ነውረኛ ያደርግኻል፡፡
🧡ምዕራፍ ፲፪
እሾማለሁ ባልክ ጊዜ የምትሾመውን ሰው መርምረህ ዕወቅ፡፡ ለድኻ በጎ አድርግለት፡፡ ጠላትህን አንድ ጊዜ ብታምነው ሁልጊዜ አትመነው፡፡ ከብረት ዝገት እንደማይጠፋ ከልቡ ክፋት አይጠፋምና፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

27 Oct, 16:37


መሥዋዕት ግን መሥዋዕቱ የሚቀርብባቸውን ምክንያቶች መሠረት ያደረጉ አከፋፈሎች ናቸው። የኃጢአት መሥዋዕት ሰው ኃጢአት ሠርቶ ከነበረ ሥርየትን ለማግኘት የሚያቀርበው መሥዋዕት ነው። የደኅንነት መሥዋዕት የሚባለው ደግሞ ከሚመጣው ችግር ከአባር ከቸነፈር ለመዳን ሲሉ የሚያቀርቡት መሥዋዕት ነው።

▶️፲፭. "ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው" ይላል (ዘኁ.8፥7)። ይህ ውኃ አሮን/ሙሴ ጸልየውበት ነው ወይስ እንደ መናው ከእግዚአብሔር ተሰጥቷቸው ነው ኃጢአትን የሚያነጻው?

መልስ፦ ካህናት ሕዝቡን ለማንጻት የሚያዘጋጁት ልዩ ውኃ ነው።

▶️፲፮. "የእስራኤልም ልጆች በሌዋውያን ላይ እጃቸውን ይጫኑባቸው" ይላል (ዘኁ.8፥10)። ከታች ደግሞ "ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ይሠሩ ዘንድ ገቡ" ይላል (ዘኁ.8፥22)። ይህ የመንጻት (መቀደስ) ሥርዓት የተደረገላቸው ለሁሉም ነው ወይስ ተመርጠው የክህነትን ሥርዓት ለሚሠሩት ብቻ?

መልስ፦ የክህነት ሥራ ለሚሠሩት ብቻ ነው። ይህንኑ ግልጽ የሚያደርግልን ከዚሁ ያለው ቃል ነው አገልግሎታቸውን ይሠሩ ዘንድ ገቡ የሚለው ማለት ነው። እጃቸውን የጫኑባቸው ምክንያቱ ከዚህ በላይ ባለ ጥያቄ ተመልሷል።

▶️፲፯. "ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው በሬሳ ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ---በሁለተኛው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ ያድርጉት" ይላል (ዘኁ.9፥10-11)። ይህ ሥርዓት (በሁለተኛው ወር መሆኑ) ሩቅ የሄዱትም በአንድ ወር ውስጥ ተመልሰው ከረከሱት ጋር እንዲያከብሩ ነው ወይስ ከዋናው ሲለየውና ሁሉም በአሉበት ሆነው እንዲያከብሩት የተሠራ?

መልስ፦ የፋሲካን በዓል ለማድረግ በዋና ጊዜው (ሚያዝያ 14) በተለያዩ ምክንያቶች ማክበር ላልቻሉ ሰዎች የተሠራ ሥርዓት ነው እንጂ ለሁሉም የተሠራ አይደለም። በሁለተኛው ወር ማለትም ግንቦት 14 እንዲያከብሩ ታዝዘዋል። ለምን በዚህ ጊዜ ታዘዙ እርሱ እግዚአብሔር ባወቀ አድርጎታል። ስለዚህ የታዘዘው አካል በታዘዘለት ቀን ለማክበር የራሱን ድርሻ ይወጣ። ሩቅ ሀገርም ይሁን የትም ይሁን። የፋሲካ በዓል በፈለጉት ቦታ የሚከበር አይደለም። እግዚአብሔር በመረጠው ቦታ በደብተራ ኦሪት የሚከበር ስለሆነ ከደብተራ ኦሪት ውጭ በያሉበት ማክበር አይችሉም።

▶️፲፰. ዘኁ.9፥15 ጀምሮ ስለደመናውና ጉዟቸው ይናገራል። 40ቀን ይወስዳል የተባለው የምድረ ርስት ከነዓን ጉዞ 40 ዘመን የወሰደባቸው በኃጢአታቸው ምክንያት እግዚአብሔር ደመናው ቶሎ እንዳይነሳ እያደረገ እየቀጣቸው ስለነበር ማለት ነው?

መልስ፦ አዎ በኃጢአታቸው ምክንያት ነው 40 ቀን የሚፈጀው መንገድ 40 ዘመን የፈጀባቸው።

▶️፲፱. "እንደ ዓይኖቻችንም ትሆንልናለህና አትተወን" ይላል (ዘኁ.10፥31)። ይህ የዮቶር ልጅ መቼ መጥቶ ከእነርሱ ጋር መኖር ጀምሮ ነው? እንደ ዓይኖቻችንም ትሆንልናለህ አትተወን ሲል ምን ማለቱ ነው?

መልስ፦ መቼ ጀምሮ እንደተከተላቸው መጽሐፉ የሚገልጸው ነገር የለም። እንደ ዓይኖቻችን የሚለው ዓይን መልካሙን መንገድ ከክፉው መንገድ እንደሚለይ አንተም ሽማግሌ ስለሆንክ በምክርህ ትጠቅመናለህ ለማለት የተናገረው ምሳሌያዊ አነጋገር ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

27 Oct, 16:37


💙የጥያቄዎች መልስ ክፍል 25💙

▶️፩. “ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፦ ሰው ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ የናዝራዊነት ስእለት ቢሳል” ይላል (ዘኍ.6፥2)። ናዝራዊነት ምንድን ነው? ምንስ ይሠራል?

መልስ፦ ናዝራዊነት የሚባለው ራሱን ለእግዚአብሔር የተለየ ስእለት አድርጎ ማቅረብ ነው። ናዝራውያን የሚባሉት ደግሞ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር የለዩ (ለእግዚአብሔር የሰጡ) ሰዎች ናቸው።

▶️፪. “ለቀዓት ልጆች ግን መቅደሱን ማገልገል የእነርሱ ነውና፥ በትከሻቸውም ይሸከሙት ነበርና ምንም አልሰጣቸውም” ይላል (ዘኍ.7፥9)።
"በትከሻቸው ይሸከሙት ነበርና" ምንም አልተሰጣቸውም ለምን ተባለ የበለጠ መሸከም ከባድ ሥራ አልነበረም?

መልስ፦ በአጭሩ ድርሻቸው ስላልሆነ ነው ያልሰጣቸው። እግዚአብሔር ያዘዘላቸው የንዋየ ቅድሳት ሥራ ነውና።

▶️፫. ብዙ ጊዜ ታቦትን "የምስክሩ ታቦት" ተብሎ ተደጋግሞ ተጠርቷል እና ለምን ይህን ስያሜ ያዘ?

መልስ፦ ደብተራ ኦሪት አምልኮተ እግዚአብሔር ስለሚመሰከርባት ነው የምስክሩ ድንኳን የተባለችው። የምስክሩ ታቦት ያለውም ታቦቱ የእግዚአብሔር አምልኮት ስለሚመሰከርበት ነው።

▶️፬. “ከእስራኤል ልጆች መካከል ሌዋውያንን ወስደህ አንጻቸው” ይላል (ዘኍ.8፥6። ሌዋውያን እንዲነፁ ያደረገ ኃጢአታቸው ምንድን ነው?

መልስ፦ በዚህ አገባብ አንጻቸው ማለት ቀድሳቸው ለያቸው ማለት ነው እንጂ ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው ማለት አይደለም።

▶️፭. “ሌዋውያንንም በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው፤ የእስራኤልም ልጆች በሌዋውያን ላይ እጃቸውን ይጫኑባቸው” ይላል (ዘኍ.8፥10)። ይህን ንባብ አልተረዳሁትም። እጅ የሚጭኑት ካህናት ናቸው እና እስራኤላውያን ሁሉ ካህናት ናቸው?

መልስ፦ አይደሉም። ለመባረክ ከሆነ እጅ የሚጭኑት ካህናት ናቸው። ከዚህ ኃይለ ቃል ላይ የምናገኘው ግን ሕዝበ እስራኤል በካህናት ላይ እጃቸውን እንደጫኑ ነው። ትርጉሙም በእናንተ ምክንያት ኃጢአታችን ይሠረይልናል ብሎ መመስከር ነው።

▶️፮. ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር ሲታገል ጉልበቱ (ወርቹ) ቆስሎ ስለነበር እስራኤል ወርች አይበሉም የሚል ነገር የሰማሁ (ያነበብሁ) መስሎኝ ነበር። አሁን ደግሞ ወርቹ የካህናት ድርሻ ነው ይላል። ቢያብራሩልኝ።

መልስ፦ አዎ ወርች አይበሉም ነበረ። ነገር ግን በዘመናቸው ያልበሉት በራሳቸው ምክንያት እንጂ እግዚአብሔር አይበላም ብሎ ከልክሏቸው አልነበረም። ስለዚህ በኋላ ሕገ ኦሪት ስትሠራ ወርቹ የካህናት ድርሻ እንዲሆን ሥርዓት ተሠርቷል።

▶️፯. "ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን የተለየ ያድርግ። ከወይን ወይም ከሌላ ነገር የሚገኘውን ሖምጣጤ አይጠጣ የወይንም ጭማቂ አይጠጣ የወይን እሸት ወይም ዘቢብ አይብላ" ይላል (ዘኁ.፮፥፫)። እኛ ባለንበት ዘመን ዘቢብ የሚበሉ ሰዎች እንዳሉ ሰምቻለሁና ጥያቄ ስለፈጠረብኝ ነው ከዚህ ጋር አያይዘው ቢመልሱልኝ።

መልስ፦ ዘቢብ ወደቤተክርስቲያኗ ከገባ በኋላ ስለሚቀደስ ለአገልግሎት በሚውልበት መንገድ እንጂ ከዚያ ውጪ ማንም ማን መብላት አይገባውም። ቤተክርስቲያን ከመግባቱ በፊት ግን እንደሌላው ልክ እንደስንዴው ሁሉ ገበሬው አምርቶ ለግል ጥቅሙ ሊያውለው ይችላል። ምንም በደል የለበትም። ከላይ ከተጠቀሰው ናዝራውያን በስእለታቸው ወቅት እንዳይጠጡ እንጂ ለማንኛውም ሰው የተከለከለ አይደለም አልነበረም።

▶️፰. ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድርበትን ስፍራ ይፈልግላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ቀደማቸው" ይላል (ዘኁ.10፥33)። ድንኳኑ ካልተተከለ የማያርፉ ከሆነ ሦስት ቀን ሌሊትም ቀንም ያለማቋረጥ ነው የተጓዙት ማለት ነው?

መልስ፦ ጉዞው በተከታታይነት ያለእንቅልፍ የተደረገ ይሆን ወይስ እየተጓዙ እያረፉ ሦስት ቀን የተደረገ ይሆን የተገለጸ ነገር የለውም። ስለዚህ እንዲህ ነው እንዲያ ነው ለማለት አልችልም። አላውቀውም።

▶️፱. ሬሳ እንዴት እያረከሰ ነው ወደ ሬሳ አትቅረቡ የሚል?

መልስ፦ በዘመኑ አዎ ሬሳ እንደሚያረክስ እግዚአብሔር ነግሯቸዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ያረክሳል ካለ ያረክስ ነበረ ማለት ነው። በሐዲስ ኪዳን ግን ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቷል። ሥጋ ሁሉም በትንሣኤ ይነሣል። ስለዚህ ትንሣኤን ተስፋ አድርገን ሬሳን አጥበን ገንዘን ስመን እንሸኘዋለን። ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ሕግ ሬሳ ርኵስ አይደለም።

▶️፲. ለቀዓት ልጆች ለምስክሩ ድንኳን ሥራ የሚያገለግል ያልተሰጣቸው ለምንድን ነው?

መልስ፦ በወቅቱ እግዚአብሔር ስላልፈቀደላቸው።

▶️፲፩. የራጉኤል/ዮቶር ልጅ ኦባብ ከነ ሙሴ ጋር ሔደ ወይስ ቀረ? ምናልባት በአንድምታ ወይም በትውፊት የሚያውቁት ከሆነ (ዘኁ.10፥29)።

መልስ፦ ከዚህ ኃይለ ቃል የኢዮባብ መሄድ ወይም አለመሄድ አልተገለጠም። በመጽሐፈ መሳፍንት ላይ ግን አብሮ እንደሄደና በዚያም ለልጆቹ ርስት እንደተሰጣቸው ተገልጿል። ስለዚህ ከነሙሴ ጋር አብሮ ሄዷል።

▶️፲፪. ዘኍ.6፥5 "ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ" ሲል ምን ማለት ነው? ናዝራዊነት ጊዜያዊ ስዕለት (ሱባዔ እንደመግባት) ነው ወይስ እንደ ምንኩስና ዓይነት?

መልስ፦ እንደሱባኤ ጊዜያዊም ሊሆን ይችላል እንደ ምንኵስና እስከ ዕለተ ሞትም ሊሆን ይችላል። የተሳለው ሰው ስእለት ይወስነዋል። የተሳለው እስከ ዕለተ ሞቴ ካለ እስከ ዕለተ ሞቱ ናዝራዊ ሆኖ ይኖራል ከተከለከሉት ነገሮችም ተከልክሎ ይኖራል። የተሳለው ለጥቂት ወራት ከሆነ ወራቱን እስኪፈጽም ከተከለከሉት ነገሮች ተከልክሎ ይቆያል። ከፈጸመ በኋላም መሥዋዕትን እንደ ሕጉ ያቀርባል።

▶️፲፫. ዘኁ.7፥1 እና ዘኍ.7፥10-11 ሁለቱም መሠዊያውን ቀድሰዋልና የሙሴና የአለቃዎቹ መቀደስ ልዩነት አለው? ሙሴስ ካህን ወይስ ነቢይ? ከአሮን ጋር በክህነት ደረጃ የሚለያዩት እንዴት (በምን) ነው?

መልስ፦ አንድን ነገር ካህናት ቀደሱት ሙሴ ቀደሰው ሲባል ለአገልግሎት ለየው ለዩት ማለት ነው። ክህነት የሌላቸው አካላት ቀደሱት ሲባል አመሰገኑት፣ መረቁት እንደ ማለት ነው። ሙሴ ካህንም ነቢይም ነው። በክህነቱ አሮንን ሹሞታል። አሮንን ከሾመ በኋላ በብዛት በአስተዳደር ሥራው ላይ ይታወቃል። በትርጓሜ መጻሕፍት ሙሴ የፓትርያርክ አሮን የጳጳስ ምሳሌ መደረጋቸው ለዚህ ነው።

▶️፲፬. የእህል ቁርባን፣ የሚወዘወዝ፣ የኀጢአት መስዋዕት፣ የደኅንነት መስዋዕት እና የሚቃጠል መስዋዕት እስካሁን በደንብ አልገቡኝም።
በኦሪት የነበሩት ጠቅላላ የመስዋዕት ወይም ቁርባ ዓይነቶች (ብዛት) ስንት ናቸው? የእያንዳንዱ ጥቅማቸው እና እንዴት(መቼ) እንደሚቀርቡ ቢነገረን? ከላይ ከተጠቀሱት የቁርባን ዓይነቶችስ ካህናቱ ወይም ህዝቡ የሚበሉት አለ? ካለስ የትኛውን ዓይነት መስዋዕት/ቁርባን ማን ይበላው ነበረ?

መልስ፦ የእህል ቁርባን የሚለውና የሚወዘወዝ መሥዋዕት የሚለው አቀራረብን ማለት የሚቀርበውን መሠረት አድርጎ የተነገረ ነው። ሰው በማናቸውም ምክንያት ወደእግዚአብሔር የሚያቀርበው እህል ከሆነ የእህል ቁርባን ይባላል። የሚያቀርበው እንስሳ ከሆነ የሚወዘወዝ መሥዋዕት ይባላል። የሚቃጠል መሥዋዕት የሚለው ደግሞ ከቀረበው መሥዋዕት በእሳት የሚቃጠል ነገር ያለውን መሥዋዕት ነው። ለምሳሌ አንዲት ላም ለመሥዋዕት ከቀረበች በኋላ ሥጋዋ በየመልኩ ከተዘጋጀ በኋላ ከማይበሉት ክፍሎች እንደስብ ያሉትን በመሠዊያው ማቃጠል ነው። በጠቅላላው በመሠዊያው በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ከሆነ የሚቃጠል መሥዋዕት ይባላል። የደኅንነት መሥዋዕትና የኃጢአት

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Oct, 14:56


ጥያቄ ጠይቁ እንጂ!!!
መጽሐፍ ቅዱስን በቀን በቀን አምስት አምስት ምዕራፍ ማንበብ ከጀመርን ጥቂት ቀናት አስቆጥረናል። ጥያቄ የሚጠይቀው ሰው ግን ቀንሷል። በደንብ ጠይቁ። ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራእየ ዮሐንስ እንማማራለን። I hope እስከ ትንሣኤ አንብበን እንጨርሳለን። ስለዚህ የሌላ እምነት ሰዎች የሚጠይቋችሁን፣ ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች የሚጠይቋችሁን፣ እናንተም ስታነቡ ግልጽ ያልሆነላችሁን ጠይቁ። በዚህ መልኩ ከዘለቅን የመጽሐፍ ቅዱስ ተጠያቂ እንሆናለን ማለት ነው።

በሁሉም ስለምንደርስበት ሁሉንም በየቦታው ጠይቁ። ሐዲስ ኪዳን ላይ በተለይም ነገረ ክርስቶስን በተመለከተ ጉዳይ ለ348 ጥቅሶች ማብራሪያ በPDF በቴሌግራም ቻናሌ ተለቋል። ስንደርስበት ደግሞ የበለጠ እንጠያየቅበታለን።

ስትጠይቁ ደግሞ ጥያቄያችሁ ግልጽ ይሁን። ጠይቃችሁኝ ያልመለስኩላችሁ ካለ ወይ ጥያቄው ግልጽ አልሆንልኝ ብሎ ነው ወይም ደግሞ ተቀራራቢ ጥያቄዎችን በሌላ ጥያቄ መልሻቸዋለሁ ብየ ካሰብኩ ነው። አንዳንድ ጥያቄዎቻችሁ ጥቅሱን ትጽፉና ግልጽ አልሆነልኝም ትላላችሁ። ከዚህ ይልቅ ግልጽ ያልሆነላችሁ የቃል ወይም የሐሳብ ጥያቄ ካለ ምን ማለት ነው ብላችሁ ለይታችሁ ጠይቁኝ።

ኦሪት ዘሌዋውያን ላይ ጠይቃችሁኝ የመለስኩላችሁ መልሶች በPDF በቴሌግራም ቻናሌ አሁን ለቅቄዋለሁ። ገብታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። አስተያየቶቻችሁን አይቻቼዋለሁ። እያንዳንዱ ክፍል ሲያልቅ ጠቅለል ያለ መርሐ ግብር ቢኖር ብላችሁኛል። ሐሳቡ ጥሩ ነበረ። ጊዜ ግን ስለማይኖረኝ መጀመሪያ በዚህ መልኩ እንጨርስና በኋላ ሁሉንም ጠቅለል ጠቅለል እያደረግን እንወያይባቸዋለን ብየ ነው እንጂ ቸል ብየው አይደለም። አንዳንዶች ደግሞ ጥያቄ አትድገሙ። ዘፍጥረት ላይ ተጠይቄ የመለስኩትን ደግማችሁ ብትጠይቁ አልመልሰውም። ከዚህ ቀደም የመለስኩት በPDF ስላለ ተመልከቱት።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Oct, 13:30


💙ክፍል 23 የጥያቄዎች መልስ💙

▶️፩. “ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ከዘርህ በትውልዳቸው ነውር ያለበት ሰው ሁሉ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ” ይላል (ዘሌ.21፥17)። ይህ ንባብ አልገባኝም። አካል ጉዳተኞች ካህን መሆን አይችሉም? በዘራቸው የተገለሉትስ ? አሁንስ በዚህ ዘመን?

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን ሕግ አካል ጉዳተኞች ካህን መሆን አይችሉም ነበረ። በሐዲስ ኪዳን ግን የክህነት አገልግሎት የሚፈልገውን የሚያስችል አካላዊ ቁመና ካለ (ማለትም ቄስ ለመሆን ዙሮ ማጠን፣ ጠንቅቆ ማንበብ፣ መፈተት) ከቻለ ይሾማል። በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ባወቀ በዘር በተለየ የሌዊ ዘር ካህን እንዲሆን መርጧል። ለምን መረጠ እግዚአብሔር ራሱ በሚያውቀው ምክንያት ነው። በሐዲስ ኪዳን ግን በዘር የሚደረግ ሹመት የለም።

▶️፪. “ከእነዚህም ከእንግዳ ሰው እጅ ለአምላካችሁ እንጀራ አታቅርቡ ርኵሰትም ነውርም አለባቸውና አይሠምሩላችሁም” ይላል (ዘሌ.22፥25)። አንድ ሰው "ነውር" ካለበት ሰው ተበድሮ ወይንም በስጦታ ተቀብሎ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረብ አይችልም ማለት ነው?

✔️መልስ፦ አዎ አይችልም ነበረ። ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ዘመን ነውር ያለበት ሰው መሥዋዕት እንዳያቀርብ እግዚአብሔር ስላዘዘ ነው።

▶️፫. “ምድርም ለእኔ ናትና፥ እናንተም ከእኔ ጋር እንግዶችና መጻተኞች ናችሁና ምድርን ለዘላለም አትሽጡ” ይላል (ዘሌ.25፥23)። "ምድርን ለዘለዓለም አትሽጡ" ሲባል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ እስከ ዕለተ ምጽአት ለልጅ ልጆቹ እየተላለፈ ይኖራልና ለዘለዓለም አለ። ለራሱ ለሰውየው ደግሞ እስከ ዕለተ ሞት ድረስ ርስትን መሸጥ አይገባውም ማለት ነው።

▶️፬. “የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ት*በ*ላላችሁ፤ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ት*በላላች*ሁ” ይላል (ዘሌ.26፥29)። የዚህ ንባብ ትርጓሜ አልገባኝም?

✔️መልስ፦ በአጭሩ ትቸገራላችሁ ማለት ነው።

▶️፭. “ማናቸውም ሰው ሰውን ለእግዚአብሔር ሊሰጥ ቢሳል አንተ እንደምትገምተው መጠን ስለ ሰው ዋጋውን ይስጥ” ይላል (ዘሌ.27፥2)። ለእግዚአብሔር ሰውን እንደ ስለት መስጠት ይቻላል? ወይስ ንባቡ ስለምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አዎ በስእለት ሰውን ለእግዚአብሔር መሥጠት ይቻል ነበረ። ድንግል ማርያም እንኳ የስለት ልጅ እንደነበረች ተጽፏልና።

▶️፮. ካህናት ከራሳቸው ወገን ድንግሏን ያግቡ የሚለው ከሥጋ ዘመድ ወይስ በሃይማኖት የሚመሳሰሉትን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ ከራሳቸው ወገን ያለው ከራሳቸው ነገድ ያግቡ ለማለት ነው እንጂ የቅርብ ዘመዳቸውን ያግቡ ለማለት አይደለም። በሃይማኖት የምትመስላቸውን ከእነርሱ ነገድ የሆነችን ሴት እንዲያገቡ በዘመናቸው ሥርዓት ተሠርቶላቸው ነበረ።

▶️፯. ካህን ወደ ሞተ ሰው ሁሉ አይግባ በአባቱም ወይም በእናቱ አይርከስ ሲል እንዴት ነው የሞተ ሰው የሚያረክስ? በብሉይ ኪዳን ሰው ሲሞት ፍትሐት አልነበረም?

✔️መልስ፦ የሞተ ሰውን መንካት በብሉይ ዘመን ርኵሰት እንደሆነ ተገልጿል። ስለዚህ በዘመኑ እግዚአብሔር ያረክሳል ስላለ ያረክስ ነበረ ማለት ነው። በፍትሐት ዙሪያ ከመጻሕፍተ ብሉያት አላገኘሁም። ነገር ግን ለሞተው ሰው በየጊዜው ሽቱ የመቀባት ልምድ ነበረ። ለሞቱት መጸለይም ነበረ። ሙሴ ይሕየወኒ ሮቤል ወልድየ ወኢይሙተኒ ብሏልና። የፍትሐት ጥቅም ነፍሳዊ ነው። በነፍስ ደግሞ በብሉይ ድኅነት አልነበረም።

▶️፰. የዳስ በዓል ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አዝመራ በተሰበሰበ ጊዜ ለሰባት ቀን የሚከበር በዓል ነው።

▶️፱. የሰሎሚት ልጅ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ የተሳደበው በምን ምክንያት ነው? ምን አደረገ ብሎ ነው? ምሥጢሩስ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ምሥጢሩ እግዚአብሔርን መስደብ ተገቢ እንዳልሆነ መግለጥ ነው። በምን ምክንያት እንደሰደበው ግን ስላልተገለጸ አላውቀውም። በእርግጥ እግዚአብሔርን ለመስደብ ምንም ምክንያት አይገኝም የለም።

▶️፲. በኢዮቤልዩ ዘመን አትዝሩ፥ የገቦውንም አትጨዱ የተቀደሰውን በእርሱ አትልቀሙ ይላል ኢዮቤልዩ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ኢዮቤልዩ በየአምሳ ዓመቱ የሚከበር በዓል ነው።

▶️፲፩. የተቀደሰውን ስሜን እንዳያረክሱ ሲል እርሱ ይቀድሳል እንጂ የእነርሱ ርኵሰት እንዴት ስሙን ሊያረክስ ይችላል?

✔️መልስ፦ የእግዚአብሔር ስም በፍጡራን ድርጊት የሚረክስ፣ በፍጡራን ድርጊት የሚቀደስ አይደለም። የእግዚአብሔር ስሙ ቅዱስ ነው። ቅዱስነቱ ደግሞ የባሕርይ ነው ማለት በዘመን ብዛት በሁኔታዎች የሚለዋወጥ አይደለም። እንዲህ ከሆነ ስሜን እንዳያረክሱ ማለት ስሜን እንዳይሳደቡ ወይም ስሜን እንዳያሰድቡ ማለት ነው።

▶️፲፪. አንድ ሰው የአካል ጉዳት ቢኖረው በአዲስ ኪዳን ክህነት መቀበል ይችላል?

✔️መልስ፦ ዙሮ ማጠን የሚችል አንካሳ ከሆነ፣ በደንብ ማንበብ የሚችል አንድ ዓይና ከሆነ፣ መፈተት የሚችል ከሆነ በሐዲስ ኪዳን ክህነት መቀበል ይችላል። በጠቅላላው የክህነት አገልግሎት የሚፈልጋቸውን ሥራዎች ማከናወን የሚችል ከሆነ በሐዲስ ኪዳን ሰው ክህነት መቀበል ይችላል።

▶️፲፫. በዓለ ሠዊት የሚከበረው ከበዓለ ፋሲካ ሰባት ሱባኤ ቆጥረን ነው?

✔️መልስ፦ አዎ።

▶️፲፬. ማናቸውም ሰው ከባለ ግዳጅ ሴት ጋር ቢተኛ ይላል (ዘሌ20፥18)። ከባለ ግዳጅ ሴት ሲል ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ግዳጅ የሚለው ሴቶች በየወሩ የሚፈሳቸው ደም (የወር አበባ) ነው። ግዳጅ አለው በየወሩ በግድ ይመጣልና ነው።

▶️፲፭. እስራኤል ወተት እና ማር የምታፈስ የተባለችበት ምክንያት ምንድን ነው? (ዘሌ20፥24)።

✔️መልስ፦ ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር ነው። ማርና ወተት ደስ እንደሚያሰኙ ሁሉ ተድላ ደስታ ወደሚገኝባት ወደእስራኤል ትገባላችሁ ለማለት ነው። በአጭሩ ማርና ወተት የሚፈስባት ማለት ተድላ ደስታ የሚደረግባት ማለት ነው።

▶️፲፮. ተዘልላችሁ ትኖራላችሁ ማለት ምን ማለት ነው? (ዘሌ25፥18)።

✔️መልስ፦ በተድላ በደስታ (በዕረፍት) አርፋችሁ ትኖራላችሁ ማለት ነው።

▶️፲፯. እግዚአብሔር መለኮታዊ ሲሆን ነፍሴም የሚልበት ምክንያት ምንድን ነው? (ዘሌ26፥30)።

✔️መልስ፦ በዚህ አገባብ ነፍሴ ሲል ባሕርይዬ (ግብረ ባሕርይዬ) ተብሎ ይተረጎማል። እግዚአብሔር ክፉ ሥራን እንደማይወድ ለመግለጽ የተናገረው ቃል ነው።

▶️፲፰. ዘሌ.21፥18-20 "ዕ_ው*ር፥ ወይም ዐንካሳ ወይም አፍንጫ ደፍጣጣ ወይም ትርፍ አካል ያለው ወይም እግረ ሰባራ ወይም እጀ ሰባራ ወይም ጎባጣ ወይም ድንክ ወይም ዐይነ መጭማጫ ወይም ዕከካም ወይም ቋቍቻም ወይም ጃንደረባ ነውረኛ ዅሉ አይቅረብ" ይላል። ፈጣሪ የልብ ንጽሕናን እንጂ ደም ግባትን ያያል እንዴ? እሱ በአምሳሉ የፈጠረውንስ ያለያያል እንዴ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር የልብ ንጽሕናን ይመለከታል። መሥፈርቱም የልብ ንጽሕና ነው። በብሉይ ኪዳን ዘመን ግን በተለየ የሥጋ ንጽሕና ያላቸው ሰዎች ወደደብተራ ኦሪት እንዲቀርቡ ሥርዓት ተሠርቶ ነበረ። ደብተራ ኦሪት ከሥጋ መቅሠፍት ብቻ ታድን ስለነበረ ወደእርሷ የሚቀርቡትም የሥጋ ንጽሕና እንዲኖራቸው ትፈልግ ነበረ። እግዚአብሔርም እርሱ ባወቀ በዘመኑ ይህ ሥርዓት እንዲሠራ አድርጓል። በሐዲስ ኪዳን ግን ቤተክርስቲያን የነፍስ ድኅነትን ስለምትሰጥ ከሥጋ ንጽሕና ይልቅ የነፍስ ንጽሕናን ከእያንዳንዱ ሰው ትፈልጋለች።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Oct, 11:57


💙💙💙 የዕለቱ ጥያቄዎች 💙💙💙
፩. በደብተራ ኦሪት ይቀርብ ስለነበረው የእህል ቁርባን ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከመልካም ስንዴ ዱቄት ይቀርባል
ለ. እርሾ ይደረግበታል💙
ሐ. በጨው ይጣፈጣል
መ. ከመሥዋዕቱ የተረፈውን የአሮን ልጆች ይበሉታል
፪. ስለኃጢአት መሥዋዕት ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. በስንዴው ዱቄት ዘይት አይፈስበትም
ለ. በስንዴው ዱቄት ዕጣን አይጨመርበትም
ሐ. በስንዴው ዱቄት ዘይት ይፈስበታል💙
መ. ሀ እና ለ
፫. በሕገ ኦሪት አንድ ሰው ኃጢአትን ቢሠራና እግዚአብሔር ይቅር እንዲለው ቢፈልግ ምን ማድረግ ይጠበቅበት ነበረ?
ሀ. መጀመሪያ በበደሉ መጸጸት
ለ. መሥዋዕት የሚሆን በግ ወደካህኑ መውሰድ
ሐ. የክርስቶስን ሥጋና ደም መቀበል
መ. ሀ እና ለ💙
፬. እግዚአብሔር ያላዘዘውን ሌላ እሳት በእግዚአብሔር ፊት በማቅረባቸው የሞቱት የአሮን ልጆች ማንና ማን ናቸው?
ሀ. አብዩድና ይታምር
ለ. አልዓዛርና ናዳብ
ሐ. አብዩድና ናዳብ💙
መ. አልዓዛርና ይታምር
፭. አሮንና ልጆቹ ከታዘዙት ትእዛዛት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ወደ ደብተራ ኦሪት ሲገቡ ወይንና ጠጅ እንዳይጠጡ💙
ለ. ራሳቸውን መንጨት እንደሚገባቸው መነገሩ
ሐ. ሲያዝኑ ልብሳቸውን እንዲቀዱ መነገሩ
መ. ለ እና ሐ
፮. እስራኤል እንዳይበሉት እግዚአብሔር ካዘዛቸው መካከል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ስብ
ለ. ደም
ሐ. የተጠበሰ ሥጋ
መ. ሀ እና ለ💙
፯. እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የማይበሉ ብሎ ከጠቀሳቸው እንስሳት መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. በግ💙
ለ. ግመል
ሐ. ጥንቸል
መ. እርያ
፰. የሚበሉ እንስሳት ወይም አዕዋፋት ምን ዓይነት ናቸው?
ሀ. ከእንስሳት የሚያመሰኩ ሰኰናቸው የተሰነጠቀ
ለ. በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ክንፍና ቅርፊት ያላቸው
ሐ. ከእንስሳት የሚያመሰኩ ሰኰናቸው ያልተሰነጠቀ
መ. ሀ እና ለ💙
፱. አንዲት እናት ሴት ልጅን ስትወልድ ከወለደች በስንተኛ ቀኗ መሥዋዕት ይዛ ወደ ደብተራ ኦሪት ትመጣለች?
ሀ. በ7
ለ. በ14
ሐ. በ80💙
መ. በ40
፲. ከሚከተሉት ውስጥ ዘመድና ዘመድ መጋባት እንደሌለባቸው የሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው።
ሀ. ዘሌ.16፥1-34
ለ. ዘሌ.18፥1-23💙
ሐ. ዘሌ. 15፥1-20
መ. ዘሌ. 10፥3-8
፲፩. ከሚከተሉት ውስጥ የተከለከለ ሩካቤ የትኛው ነው?
ሀ. ዘመድ ከዘመዱ ጋር
ለ. ወንድ ከወንድ ጋር
ሐ. ሰው ከእንስሳት ጋር
መ. ሁሉም💙
፲፪. ከዐሥሩ ትእዛዛት መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ
ለ. እናትና አባትህን አክብር
ሐ. አትስረቅ
መ. መልስ የለም💙
፲፫. የእስራኤላውያን በዓለ ፋሲካ የሚውለው መቼ ነው?
ሀ. ሚያዝያ 1
ለ. ሚያዝያ 21
ሐ. ሚያዝያ 14💙
መ. ሚያዝያ 7
፲፬. ከሚከተሉት ውስጥ እስራኤል ከሚያከብሯቸው በዓላት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በዓለ ሰንበት
ለ. በዓለ ሠዊት
ሐ. በዓለ ፋሲካ
መ. ሁሉም💙
፲፭. እስራኤል በዓለ መጥቅዕን መቼ እንዲያከብሩ ተነገሩ?
ሀ. መስከረም 12
ለ. ጥቅምት 1💙
ሐ. ሚያዝያ 1
መ. ግንቦት 12
፲፮. ኢዮቤልዩ የሚባለው በየስንት ዓመቱ የሚመጣ ነው?
ሀ. በየ25 ዓመት
ለ. በየ50 ዓመት💙
ሐ. በየ75 ዓመት
መ. በየ100 ዓመት

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Oct, 04:34


#ኦሪት #ዘሌዋውያን #ክፍል 5
💚ምዕራፍ 21
-ስለሞተ ሰው ተብሎ ራስን መላጨት፣ ጺምን መላጨት፣ ሥጋን መንጨት እንደማይገባ
-ነውረ ሥጋ ያለበት ሰው መባ ያቀርብ ዘንድ መቅረብ እንደማይገባው

💚ምዕራፍ 22
-ከአሮን ዘር ለምጽ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት ሁሉ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሰው እንዳይበላ መነገሩ
-የሞተውን፣ አውሬም የሰበረውን መብላት እንደማይገባ
-ነውረ ሥጋ የሌለበትን መሥዋዕት ማቅረብ ይገባል

💚ምዕራፍ 23
-ሰንበትን ማክበር እንደሚገባ
-በዓለ ፋሲካንና በዓለ ናዕትን ማክበር እንደሚገባ
-በኵራትን ለቤተ እግዚአብሔር መስጠት እንደሚገባ
-በዓለ ሠዊትን፣ በዓለ መጥቅዕን ማክበር እንደሚገባ መነገሩ

💚ምዕራፍ 24
-በመቅረዙ ላይ ያሉ መብራቶችን እስኪነጋ ማብራት እንደሚገባ መነገሩ
-የእግዚአብሔርን ስም መስደብ ቅጣቱ መገደል እንደሆነ

💚ምዕራፍ 25
-እስራኤል ስድስት ዓመት ሠርተው በሰባተኛው ዓመት እንዲያርፉ መነገሩ
-እስራኤል ሃምሳኛውን ዓመት ኢዮቤልዩ ብለው እንዲያከብሩት መነገሩ
-የእግዚአብሔርን ትእዛዙን በረከትን እንደምናገኝ
-ርስትን መሸጥ እንደማይገባ
-በወለድ ማበደር ተገቢ እንዳልሆነ

💚ምዕራፍ 26
-ለጣዖት መስገድ እንደማይገባ
-በእግዚአብሔር ሥርዓትና በትእዛዙ መኖር እንደሚገባ
-ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ውጭ መሄድ ጥፋትን እንደሚያስከትል

💚ምዕራፍ 27
-ስለ ስእለት ተገልጿል።
-ዐሥራት ለእግዚአብሔር እንደሚገባ


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. የእስራኤላውያን በዓለ ፋሲካ የሚውለው መቼ ነው?
ሀ. ሚያዝያ 1
ለ. ሚያዝያ 21
ሐ. ሚያዝያ 14
መ. ሚያዝያ 7
፪. ከሚከተሉት ውስጥ እስራኤል ከሚያከብሯቸው በዓላት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በዓለ ሰንበት
ለ. በዓለ ሠዊት
ሐ. በዓለ ፋሲካ
መ. ሁሉም
፫. እስራኤል በዓለ መጥቅዕን መቼ እንዲያከብሩ ተነገሩ?
ሀ. መስከረም 12
ለ. ጥቅምት 1
ሐ. ሚያዝያ 1
መ. ግንቦት 12
፬. ኢዮቤልዩ የሚባለው በየስንት ዓመቱ የሚመጣ ነው?
ሀ. በየ25 ዓመት
ለ. በየ50 ዓመት
ሐ. በየ75 ዓመት
መ. በየ100 ዓመት

https://youtu.be/rQ-JsHo3Tlk?si=z8u0NqggyU0Isr0i

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

25 Oct, 04:16


✝️መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 24✝️
✝️መጽሐፈ ሲራክ
✝️ምዕራፍ ፬
ያዘነች ሰውነትን አታሳዝን፡፡ የተከዘውንም ልቡና አታስደንግጥ፡፡ በብዙ ሰዎች ዘንድ የተወደድክ ሁን፡፡ ለደኻው ልመናውን በጆሮህ ሰምተህ ቢኖርህ ስጠው ባይኖርህም ወንድሜ ቀን ይመልስህ ብለህ በገርነት በጎ ቃል መልስለት፡፡ ሰው ነገሩን ሲነጋገር ሳታስፈጽመው ጠለፍ አድርገህ አትናገር፡፡ ኃጢአትህን ለመምህረ ንስሓህ መናገርን አትፈር፡፡ የውሃ ምላትንም እንደ አንበሳ ተጋፍቼ እሻገራለሁ አትበል፡፡ ወኢታትሕት ርእሰከ ለብእሲ አብድ ወኢታድሉ ለገጸ ዐቢይ፡፡ ሰነፍን ሰው ባልንጀራ አታድርገው፡፡ እስከ ትበጽሕ ለሞት ተበአስ በእንተ ጽድቅ እስመ እግዚአብሔር አምላክከ ይትበአስ በእንቲኣከ፡፡ ሃይማኖትን ለማጽናት ለሞት እስክትደርስ ደርሰህ ተከራከር፡፡ ፈጣሪህ እግዚአብሔር በአንተ አድሮ ይከራከርሀልና፡፡
✝️ምዕራፍ ፭
ገንዘብህን ለአዝማሪና ለዘዋሪ አትበትን፡፡ እግዚአብሔር ብዙ ዘመን ይታገሣል፡፡ በኃጢአትህ ላይ ኃጢአትን አትጨምር፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነቱ ብዙ ነው ይቅር ይለኛል እያልክ ኃጢአትን አትሥራ፡፡ ቸርነትም መቅሠፍትም ከእርሱ ይገኛልና፡፡ እግዚአብሔር ቢታገሥህ የተወኝ መስሎህ ንስሓ መግባትን አትተው፡፡ ከዛሬም ነገ ከነገም ሣልስት ስትል ንስሓ እገባለሁ እያልክ ቀንን አታሳልፍ፡፡ ሞት ድንገት ይመጣልና ፍዳህም ከመቅሠፍት ጋራ በመጣች ጊዜ ትጨነቃለህና፡፡ አንተ ባለአእምሮ ምሥጢርህን ለሁሉ አትንገር፡፡ ነገርን ሁሉ ለመስማት ቸኩል ለመመለስ ግን ዳ በል፡፡ በታላቁም በታናሹም ሰው ዘንድ በጎ ሰው ሁን፡፡
✝️ምዕራፍ ፮
ቅጠል ከፍሬ እንዲቀድም ሃይማኖትም ከምግባር ይቀድማል፡፡ ነገር አዋቂ አንደበት ወንድሜ ወንድሜ ማለት ያበዛል፡፡ በጎም አንደበት ወዳጁን ያበዛል፡፡ ወዳጅ መስሎ ጠላት የሚሆን የወዳጅ ጠላት አለ፡፡ ለሆዱ ብሎ ወዳጅ የሚያደርግህ ሰው አለ፡፡ ወዳጅ መስለው ከሚጠሉህ ጠላቶችህ ራቅ፡፡ ጠላቶችህንም ጠብቃቸው ዕወቅባቸው፡፡ የታመነ ወዳጅ የሚያድን መድኃኒት ነው፡፡ የመጽሐፍን ነገር ሁሉ ፈጥነህ ስማ፡፡


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

24 Oct, 13:45


✔️መልስ፦ የሚያመሰኳ ማለት የሚያመነዥክ ማለት ነው። ምሳሌ በሬ፣ በግ ይጠቀሳሉ። የማያመሰኳ ማለት የማያመነዥክ ማለት ነው። ምሳሌ እሪያ።

▶️፲፬. ኦሪት ዘሌዋውያን ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሌዋውያን ሊያደርጉት የሚገባውን ሥርዓት የሚናገር ማለት ነው። ሌዋውያን የሚባሉት የብሉይ ኪዳን ካህናት ናቸው።

▶️፲፭. ሰው የወንድሙን ሚስት ቢያገባ ርኩሰት ነው ይላል ከዚህ በፊት እንዳየነው አንድ ሰው አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ለስሙ መጠሪያ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ይውለድ ይላል። ይህ እንዴት ይስማማል?

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን ሥርዓት አንድ ሰው በሕይወት የወንድሙን ሚስት ማግባት እንደማይገባውና ካገባ ግን ርኵሰት እንደሆነ ተነግሯል። ከሞተ በኋላ ግን ለወንድሙ በሕግ ዘር ያስቀርለት ዘንድ አግብቷት ልጅ እንዲወልድ ታዝዟል። ስለዚህ በሕይወት እያለና ከሞት በኋላ ስላለው የተነገሩ ስለሆነ የሚቃረን ነገር የለውም። በሐዲስ ኪዳን ግን በሕይወት ሳለም ከሞተ በኋላም የወንድምን ሚስት ብቻ ሳይሆን የወንድምን ሚስት ወንድሞች ማግባት የለበትም አልተፈቀደም።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

24 Oct, 13:45


💙ክፍል 22 የጥያቄዎች መልስ💙

▶️፩. “የመለቀቅም ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያስተሠርይበት ዘንድ፥ ለመለቀቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰድደው ዘንድ በሕይወቱ በእግዚአብሔር ፊት ያቆመዋል” ይላል (ዘሌ.16፥10)። ወደ ምድረ በዳ ፍየሉ ለምን ይለቀቃል ትርጉሙ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ፍየሉ ሳይታረድ በነጻ እንደተለቀቀ መሥዋዕት ያቀረበው ሰውም ከኃጢአቱ ነጻ መሆኑን ለመግለጽ ነው። የሰውየውን ኃጢአት ፍየሉ ተሸክሞ ወደምድረ በዳ ይሄድ ነበረና።

▶️፪. “ይህም የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፤ በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስተሥረያ ይሆንላችኋልና በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት" ይላል (ዘሌ.16፥29-30)። ራሳችሁን አስጨንቋት ሲል አልገባኝም?

✔️መልስ፦ ሰባተኛ ወር የተባለው የጥቅምት ወር ነው። ጥቅምት 10 ዮሴፍ የተሸጠበት ቀን መታሰቢያ ናት። ስለዚህ እስራኤላውያን በኀዘን ሆነው በጾም እንዲያከብሯት ነው ሥርዓቱ የተነገረው። ራሳችሁን አስጨንቋት ማለቱ በዓሉን በጾም በኀዘን አክብሩት ማለት ነው።

▶️፫. “ከዘርህም ለሞሎክ በእሳት አሳልፈህ አትስጥ፥ የአምላክህንም ስም አታርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ይላል (ዘሌ.18፥21)። ሞሎክ ምንድን ነው? "ዘርህን ለሞሎክ እሳት አሳልፈህ አትስጥ" ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ ሞሎክ የአሞን ዘሮች ያመልኩት የነበረ ጣዖት ስም ነው። ዘርህን ለሞሎክ አትስጥ ማለት ልጅህን ሞሎክን እንዲያመልክ አታድርገው ማለት ነው።

▶️፬. “ወደ አገሩም በገባችሁ ጊዜ፥ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁም ጊዜ፥ ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ፤ ሦስት ዓመት እንዳልተገረዘ ይሆንላችኋል፤ አይበላም” ይላል (ዘሌ.19፥23)። "ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቆጥሩታላችሁ" ሲል አልገባኝም?

✔️መልስ፦ ያልተገረዘ ርኵስ ይባል እንደነበረ እንዳልተገረዘ ትቆጥሩታላችሁ ማለቱ እንደ ርኵስ ትቆጥሩታላችሁ ማለት ሲሆን በአጭሩ አትብሉት ማለት ነው። ወይን ከተተከለ በኋላ በሦስተኛው ዓመት አፍርቶ ቢገኝ እንኳ ለምድረ በዳ አዕዋፋት ይተው ነበረ። በአራተኛው ዓመት ግን እንዲበሉት ታዝዟል።

▶️፭. “የራስ ጠጕራችሁንም ዙሪያውን አትከርክሙት፥ ጢማችሁንም ዙሪያውን አትቍረጡት” ይላል (ዘሌ.19፥27)። ይህ ንባብ አልገባኝም። ፂም መቆረጥ ለምን ተከለከለ? በሐዲስ ኪዳንስ ተፈጻሚ ነውን?

✔️መልስ፦ ወንድ ልጅ መታወቂያው ስለሆነ ጺሙን እንዳይቆርጥ እግዚአብሔር አዝዟል። ይህ በሐዲስ ኪዳንም የቀጠለ ሥርዓት ነው። (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 11 በእንተ ሕዝባውያን ላይ ተገልጿል)።

▶️፮. በእኅቷ ላይ እንዳትቀና ሚስትህ በሕይወት ሳለች የእኅቷን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ ይላል (ዘሌ 18፥8)። ከሞተች በኋላስ ይቻላል ማለት ነው?
በዚያውም አንድ ጥያቄ አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት እኅት ማግባት ይችላል? (በሐዲስ ኪዳን)።

✔️መልስ፦ ከሞተች በኋላ ስላለው ነገር የተገለጸ ነገር የለም። በሐዲስ ኪዳን ግን አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት እኅት ማግባት አይገባውም። የጋብቻ ዝምድና ይፈርሳልና (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 24ን ይመልከቱ)። ባለማወቅ እስከዛሬ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በኋላ እንዳይሆን ማስተማር ነው።

▶️፯. አብዛኞቹ እንስሳት አይበሉም። ለሰው መጠቀሚያ ያልሆኑት በተለይ ነፍሳት እና ተሳቢ እንስሳት ለምን ተፈጠሩ?

✔️መልስ፦ ፍጥረታት ሁሉ ለሰው ጥቅም ተፈጥረዋል። ጥቅም የሚሰጡበት መንገድ ግን የተለያየ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ አህያን ባንበላው እንኳ በጭነት እንጠቀምበታለን። ሌሎችም ፍጥረታት ምንም እንኳ ሁሉም ለምግብነት ባያገለግሉ ነገር ግን በተለያየ መንገድ ሰውን ለመጥቀም ተፈጥረዋል። ስለዚህ እንዴት ለጥቅማችን ማዋል እንዳለብን መመርመር የእኛ ድርሻ ነው።

▶️፰. የደኅንነት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ስትሠዉ ንጹሕ አድርጋችሁ ሠዉት በምትሠዉበት ቀን በነጋው ይበላል እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል ሲል ምሳሌ በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚነሣ ለማሳየት ወይስ ሌላ ነው ትርጉሙ?

✔️መልስ፦ ምሳሌ ዘየሐጽጽ ስለሆነ ይህንን መሠረት አድርገን ለክርስቶስ ምሳሌ ልናደርገው እንችላለን። ለጊዜው ግን ከእግዚአብሔር ስለታዘዙ ነው እንዲህ ያደረጉት።

▶️፱. ደም ካልተበላ፤ የሥጋ ሕይወት ሁሉ ደም ከሆነ ሥጋ መብላት ለምን ተፈቀደ? (ሥጋ መብላት ከተፈቀደ?)። የሥጋ ሕይወት ሁሉ ደም ነው ሲባልስ ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ የሥጋ ሁሉ ሕይወት ደም ነው ማለት እንስሳትና ደማውያን ፍጥረታት የሚንቀሳቀሱትና ሕይወት ያላቸው ሆነው የሚቆዩት በደመ ነፍሳቸው ነው ማለት ነው። በአጮሩ የእንስሳት ነፍሳቸው ደማቸው ነው ማለት ነው። ሥጋ መብላት የተፈቀደው ደሙ ከደረቀ ወይም በእሳት ከበሰለ በኋላ ነው። ደሙ ሳይደርቅ ወይም በእሳት ሳይበሰል ግን እንዳይበላ ሥርዓት ተሠርቷል።

▶️፲. ዘሌ.፲፱፥፲፱ "ሥርዓቴን ጠብቁ፤ በበሬህ በባዕድ ቀንበር አትረስ፤ በወይንህ ቦታ የተለያየ ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ ኀፍረት ነውና አትልበስ" ይላል። የተለያየ ዘር አትዝራ የሚለው የአዝርዕት ዓይነት ወይስ ሌላ?
ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ የሚለው ቀለሙን ወይስ ምንድን ነው? እንዴት ኀፍረት ይሆናል?

✔️መልስ፦ አዎ ለጊዜው የተለያየ አዝርዕት በአንድ እርሻ ሲዘራ ለመሰብሰብ ያስቸግራል። በተጨማሪም አንዱ ተክል ሌላውን ፍሬያማ እንዳይሆን ያደርገዋልና ስለዚህ ነው። ምሳሌው ምሥጢሩ ደግሞ የሕግ ማደሪያ በሆነ ልቡናህ ሕገ እግዚአብሔርንና ሕገ ጣዖትን በአንድ ላይ አታስቀምጥ ማለት ነው። የልብሱም እንዲሁ ያስተረጉማል። ለጊዜው ሁለት ዓይነት ቀለም ያለበት ልብስ እንዳይለብሱ ታዝዘዋል። ኀፍረት የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ኀፍረት ነው ስላለው ነው።

▶️፲፩. ዘሌ.16፥29-30 “ይህም የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፤ በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስተሥረያ ይሆንላችኋልና በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት፥ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። የዘላለም ሥርዓት ከሆነ አሁን የት አለ። ወይስ እንደግዝረት በምትክ ተፈጽሟል?

✔️መልስ፦ በኦሪት ዘሌዋውያን ብዙ ቦታ ላይ የዘለዓለም ሥርዓት እየተባሉ የተጠቀሱት እስከ ብሉይ ኪዳን ፍጻሜ ተብለው ይተረጎማሉ። ለምሳሌ ግዝረትንም የዘለዓለም ሥርዓት ብሎታል። ዘለዓለም በመጽሐፍ ቅዱስ ሦስት አተረጓጎም አለው። አንደኛው መነሻም መድረሻም የሌለው ሲሆን ይህ ለእግዚአብሔር ብቻ ይነገራል። ሁለተኛው መነሻ ያለው መድረሻ ግን የሌለው ሲሆን ይህ ለሰውና ለመላእክት ይነገራል። ሦስተኛው መነሻም መድረሻም ያለው ነው። ይህ ስለግዝረትና ስለ ሌሎችም የብሉይ ኪዳን ሥርዓቶች ይነገራል።

▶️፲፪. ዘሌ.20፥27 “ሰው ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይ ይውገሩአቸው፤ ደማቸው በላያቸው ነው” ይላል። መናፍሥት ፆታ አላቸውን?

✔️መልስ፦ የጽሑፉ ሐሳብ ሰው (ወንድ ልጅ) ወይም ሴት (ሴት ልጅ) መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ይገደሉ የሚል ነው። ሴት የተባለችው መናፍስቱን የምትጠራዋ ጠሪ ናት መናፍስቱ ደግሞ ተጠሪ ናቸው። መናፍስት ጾታ የላቸውም። የልቡሳነ ሥጋ አጋንንት ግን ጾታ አላቸው።

▶️፲፫. የሚያመሰኳ እና የማያመሰኳ ሲል ምን ማለቱ ነው? ለምሳሌ ያክል እነማን ናቸው?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

24 Oct, 04:23


#ኦሪት #ዘሌዋውያን #ክፍል 4
ምዕራፍ 16
-አሮን ስለራሱ፣ ስለሕዝቡ መሥዋዕት መሠዋቱ

ምዕራፍ 17
-ደምን መብላት እንደማይገባ
-የሥጋ ሁሉ ሕይወት ደም እንደሆነች

ምዕራፍ 18
-ከዘመድ ጋር መጋባት እንደማይገባ
-ሰው ከእንስሳት ጋር ሩካቤ መፈጸም እንደሌለበት
-የተመሳሳይ ጾታ ሩካቤ ፈጽሞ እንደማይፈቀድ

ምዕራፍ 19
-እግዚአብሔር እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ማለቱ
-አጥርቶ ማጨድ እንደማይገባ
-መስረቅ፣ መዋሸት እንደማይገባ
-ባልንጀራን እንደራስ መውደድ እንደሚገባ
-ሥርዓትን መጠበቅ እንደሚገባ
-የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ እንደሚገባ

ምዕራፍ 20
-እናት አባትን መሳደብ እንደማይገባ
-ሕገ እግዚአብሔርን መጠበቅ እንደሚገባ
-ከእንስሳት ጋር ሩካቤ የፈጸመም ተመሳሳይ ጾታ ጋር ሩካቤ የፈጸመም እንዲገደሉ መነገሩ

💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ከሚከተሉት ውስጥ ዘመድና ዘመድ መጋባት እንደሌለባቸው የሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው።
ሀ. ዘሌ.16፥1-34
ለ. ዘሌ.18፥1-23
ሐ. ዘሌ. 15፥1-20
መ. ዘሌ. 10፥3-8
፪. ከሚከተሉት ውስጥ የተከለከለ ሩካቤ የትኛው ነው?
ሀ. ዘመድ ከዘመዱ ጋር
ለ. ወንድ ከወንድ ጋር
ሐ. ሰው ከእንስሳት ጋር
መ. ሁሉም
፫. ከዐሥሩ ትእዛዛት መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ
ለ. እናትና አባትህን አክብር
ሐ. አትስረቅ
መ. መልስ የለም

https://youtu.be/A_W5uVrCNXk?si=dQWDpuIIGdsz4FiL

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

24 Oct, 04:16


💟መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 23💟
💟መጽሐፈ ሲራክ
💟ምዕራፍ ፪
ወልድየ ለእመ ሖርከ ትትቀነይ ለእግዚአብሔር አስተዳሉ ነፍሰከ ለሕማም፡፡ ልጄ ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ወደምናኔ ብትሄድ ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ፡፡ ዕፀበ ገዳም እንዳለብህ አውቀህ ሂድ፡፡ ሁለተኛም ልጄ ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ወደሰማዕትነት ብትሄድ ዓይንህን ለፍላት እጅ እግርህን ለስለት አዘጋጅ፡፡ ይህ እንዳለብህ አውቀህ ሂድ ሲል ነው፡፡ በትምህርት የሚወልደውን ሁሉ ልጄ ይላል፡፡ ልብህንም አቅንተህ መከራውን ታገሥ፡፡ ትልዎ ለእግዚአብሔር ወኢትኅድጎ ከመ ትብዛኅ ሕይወትከ በደኃሪትከ፡፡ የመጣብህን መከራ ሁሉ በምስጋና ተቀበል፡፡ ወርቅን በእሳት እንዲፈትኑት ጻድቁንም ሰው ሥላሴ በመከራ ይፈትኑታል፡፡ ርእዩ ቀደምተ ዓለም፡፡ ከእናንተ አስቀድሞ የነበሩትን እዩ፡፡ እግዚአብሔር ቸር ርኅሩኅ ነውና ኃጢአትን ይቅር ይላል በመከራም ቀን ያድናል፡፡ ለሚጠራጠር ልብ ወዮለት፡፡ ለክፉዎች ሕዋሳት ወዮላቸው፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ቃሉን አይዘነጉም የሚወዱትም ሕገጋቱን ይጠብቃሉ፡፡ ሰውን ፈርተን በገሀነም ከምንወድቅ እግዚአብሔርን ፈርተን በዐላውያን እጅ ብንወድቅ ይሻለናል፡፡
💟ምዕራፍ ፫
አባቱን የሚያከብር ኃጢአቱ ይሠረይለታል፡፡ ዘያከብር አባሁ ይትኀደግ ሎቱ ኃጢአቱ፡፡ ሰው አባቱንና እናቱን ካከበረ ረድኤት አይለየውም፡፡ ረድኤትም ካልተለየው ኃጢአትን አይሠራምና፡፡ አባቱን የሚያከብር ልጆቹ ሲያከብሩት አይቶ ደስ ይለዋል፡፡ በጸለየም ጊዜ ፈጣሪው ፈጥኖ ይሰማዋል፡፡ አባቱንና እናቱን የሚያከብር ዘመኑ ይረዝምለታል፡፡ በረከቱ ያድርብህ ዘንድ ቢኖርህ ሰጥተህ ባይኖርህ በጎ ተናግረህ አባትህን አክብረው፡፡ የአባት ምርቃት የልጆችን ቤት ያጸናል፡፡ የእናትም መርገም ሥር መሠረትን ያጠፋል፡፡ እስመ በክብረ አቡሁ ይከብር ሰብእ ወኀሣሩ ለሰብእ በአስተሐቅሮታ ለእሙ፡፡ አባትህ በማርና በወተት በፍትፍትም ማሳደጉ አይዘንጋህ፡፡ አባቱን የማይረዳ እናቱንም የሚያሳዝናት በእግዚአብሔር ዘንድ ሑር እምኔየ የሚባል ርጉም ነው፡፡ ወልድየ በሃይማኖትከ ያስተርኢ ምግባሪከ ወያፈቅሩከ እደው ጻድቃን፡፡ ራስህን አዋርድ ዋጋህንም በእግዚአብሔር ዘንድ ታገኛለህ፡፡ የማይቻልህን ነገር አትመርምር፡፡ ባሕርየ ሥላሴን እመረምራለሁ አትበል፡፡ የምትነድ እሳትን ውሃ ያጠፋታል፡፡ ኃጢአትንም ምጽዋት ያስተሠርያታል፡፡


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Oct, 14:40


💙ክፍል 21 የጥያቄዎች መልስ💙

፩. “ከእነርሱም እነዚህን ትበላላችሁ፤ አራቱን ዓይነት አንበጣዎች በየወገናቸው” ይላል (ዘሌ.11፥22)። አንበጣ ይበላል? አሁንም የሚበሉት ክርስቲያኖች አሉ?

✔️መልስ፦ ከእነርሱም እነዚህን ትበላላችሁ ያለው ከላይ ይህን ከመጻፉ በፊት ባለው ቁጥር የጠቀሳችውን ነው እንጂ ቀጥለው ያሉትን አይደለም። አንበጣ አይበላም። እንደማይበላም ከዚሁ ጽሑፍ ቀጥሎ ተገልጿል።

፪. ዘሌ.11፥37-38 "ከበድናቸውም በሚዘራ ዘር ላይ አንዳች ቢወድቅ እርሱ ንጹሕ ነው። ነገር ግን በዘሩ ላይ ውኃ ቢፈስስበት፥ ከዚህ በኋላ ከበድናቸው አንዳች ቢወድቅበት፥ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው" ይላል። ርኵሰቱ ከውሃ ጋር የተገናኘበት ምክንያት ምንድነው?

✔️መልስ፦ ከበድኑ ላይ ውሃ ሲፈስበት እዥ ይሆናል። ከእዡ ላይ እንዳይዘራ ተከልክሏል። ከበድን እዥ የበለጠ ያስጸይፋልና ነው። ዘር ከተዘራ በኋላ የአንድ ርኩስ የተባለ በድን ቢወድቅ ግን ምድሪቱ ቀድሞ ንጹሕ ስለነበረች ንጹሕ ነው ተብሏል።

፫. እንደ ኦሪቱ ሴት ልጅ በዚህ ዘመን ስትወልድ የረከሰች ናት ትባላለች? መስቀል መሳለም አትችልም የሚሉ አሉ? የአዋለደ ሰውስ ቤተክርስቲያን መግባት ይከለከላል? እርሷስ በስንት ቀኗ ነው ጠበል የምትረጨው (ሲጀመር ግዴታ ነው ለምን?)። የወለዱ ሴቶች ካጠገባቸው ብረት ነክ ያደርጋሉ እና ሰውም አይለያቸውም ይሄስ በዘልማድ ነው ወይስ ሥርዓት ነው? የወለደች ሴት ትጦማለች?

✔️መልስ፦ ሴት ስትወልድ ርኩስ አትባልም። የእግዚአብሔር አርዓያ የሆነ ልጅን በመውለዷ ትደነቃለች ትከበራለች እንጂ ርኩስ ናት አይባልም። በወር አበባ ጊዜ፣ በአራስነት ጊዜ ርኩስ ነን የሚሉ ሰዎች አሉ። ስሕተት ነው ይታረም። ደም መፍሰሱ እስኪያቆም ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ የተከለከሉም ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ደም ብቻ የሚፈተትባት ስለሆነች የፍጡር ደም እንዳይፈስባት በማሰብ ነው። ስለዚህ የወለደች ሴት መስቀል መሳለም ትችላለች። የአዋለደ ሰውም ታጥቦ ቤተክርስቲያን መግባት ይችላል። ለመቁረብ ግን ወንድ ያወለደ ከ20 ቀን በኋላ፣ ሴት ያዋለደ ከ40 ቀን በኋላ እንዲሆን ሥርዓት ተሠርቷል። የወለደች ሴት በልማድ በ10 ቀኗ ትጠመቃለች። የተጸለየበት ውሃ ለማንኛውም ሰው ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። ነገር ግን ልማድ እንጂ ሥርዓት አይደለም። ክርስትናው ሲደርስ ራሷ ታጥባ ቤተክርስቲያን መግባት ትችላለች። የወለዱ ሴቶች ብረት ነክ ማድረግም ቤተክርስቲያናዊ መነሻ የለውም። የወለደች ሴት ሕመሟ ጽኑ ካልነበረና ለመጾም በቂ አካላዊ ቁመና ካላት መጾም ይገባታል።

፬. የወለደች ሴት ወለደች እንጂ መች ኀጢአት ሠራችና ነው የኀጢአት መሥዋዕት የምታመጣው?(ዘሌ.12፥6)።

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን ዘመን የአራስነት ደም እንደ ርኵሰት ስለሚታይ ከእርሱ ለመንጻት ነው መሥዋዕት የምታቀርበው እንጂ በደል ሆኖ አይደለም አልነበረም።

፭. የቈረቈር ደዌ ምንድን ነው? (ዘሌ.13፥31)።

✔️መልስ፦ እንደ ቋቁቻ ያለ የበሽታ ዓይነት ነው።

፮. እስከ ማታ ርኩስ ነው ማለት እሰከ ቀኑ ማታ ወይስ አስከ ዕድሜ መጨረሻ ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ እስከ ቀኑ ማታ።

፯. ሴት ልጅ ስትውልድ ወንድ ከሆነ ከደሟ እስክትነጻ 33 ቀን ሴት ከወለደች 66 ቀን ትቆይ ይላል። ይህ ሕግ በአዲስ ኪዳንም አለ? ምክንያቱም ክርስትና እስኪያስነሱ ወደ ቤተክርስቲያን አይሄዱምና።

✔️መልስ፦ በሐዲስ ኪዳን ያለው የጥምቀት ሥርዓት ነው። ቀኑም ወንድ እስከ 40 ቀን ሴት እስከ 80 ቀን ነው እንጂ 33 እና 66 አይደለም።

፰. “ከደሟም እስክትነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቀመጥ። የመንጻቷ ቀንም እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰን ነገር አትንካ፥ ወደ መቅደስም አትግባ" ይላል (ዘሌ.12፥4)። “ሴት ልጅም ብትወልድ እንደ መርገሟ ወራት ሁለት ሳምንት ያህል የረከሰች ናት፤ ከደሟም እስክትነጻ ድረስ ስድሳ ስድስት ቀን ትቀመጥ” ይላል (ዘሌ.12፥5)። እነዚህ ሁለት ጥቅሶች ወንድ ልጅ በ40 ቀን ሴት ልጅ በ80 ቀን ክርስትና ለመነሣታችን ምሳሌ ይሆናሉ ወይስ ምንድን ነው ከአሁኑ ጋር ቀናቶች ስለተመሳሰሉ ነው?

✔️መልስ፦ አዎ በምሳሌነት የብሉዩ ሥርዓት ለሐዲሱ ሥርዓት ምሳሌ ይሆናል። አሁንም ሴት ወንድ ስትወልድ በ40ኛ ቀኗ ሴት ስትወልድ በ80ኛ ቀኗ ወደ ቤተክርስቲያን መግባቷ የብሉዩ ምሳሌ ነው። ተጨማሪ ምሳሌ ሔዋን ከመሬት ተፈጥራ በ80ኛ ቀኗ ወደ ገነት ገብታለች። አዳምም በተፈጠረ በ40ኛ ቀኑ ወደ ገነት ገብቷል። ቤተክርስቲያን የገነት ምሳሌ በመሆኗ በዚህ አምሳል በ40ና በ80 ቀን እናጠምቃለን እንጠመቃለን።

፱. ዘሌ.14፥54-56 "ይህም ሕግ ነው ለሁሉ ዓይነት ለምጽ ደዌ፥ ለቈረቈርም፥ በልብስና በቤትም ላለ ለምጽ፥ ለእባጭም፥ ለብጕርም፥ ለቋቁቻም" ይላል። አሁን ላይ በተለይ የቆዳ በሽታ ያለብን ሰወች እንሸማቀቃለን። አሁን ላይ ይህ ጥቅስ እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ በሐዲስ ኪዳን ሥርዓት ሥጋዊ በሽታ የንጽሕና ወይም የርኵስነት መለኪያ አይደለም። ብዙ ቅዱሳን ከገድላቸው ጽናት የተነሣ ሰውነታቸው አብጦ፣ አካላቸው ቆስሎ በሰማዕትነት አርፈዋል። ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን በዋናነት የነፍስ በሽታ እንጂ የሥጋ በሽታ ነውር አይደለም።

፲. የማይበሉ እንስሳት ለምንድን ነው ርኩሳን የተባሉ በእግዚአብሔር ፍጥረት ርኩስ እንዴት ኖሮ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ በተፈጥሮው መልካም ነው። ከዚህ ላይም ርኩስ እየተባሉ የተገለጹት በተፈጥሯቸው ሳይሆን እግዚአብሔር ባወቀ ለሰው ሰውነት ተስማሚ ሆነው ስላልተገኙና ሰው ስላልበላቸው ነው ርኵስ የተባሉት። በአጭሩ ስለማይበሉ ርኵስ ተባሉ እንጂ በተፈጥሯቸው ርኵስ ስለሆኑ አይደለም። በተፈጥሮ ሁሉም መልካም ነውና።

፲፩. በአዲስ ኪዳን የሚበሉ የማይበሉ ተብሎ የተቀመጠው በምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በሐዲስ ኪዳን የሚበሉ የማይበሉ የተባሉት ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 23 ላይ የተገለጹት ናቸው። በተጨማሪም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳይበሉ ብሎ የከለከላቸው ናቸው። እነዚህም ሙቶ ያደረው፣ ታንቆ የሞተውን፣ ለጣዖት የታረደውን፣ ደምን እንዳንበላ ታዝዘናል። ስለሌላው ግን የተጻፈ ነገር የለም።

፲፪. ካህኑ በቡሉይ ኪዳን ለምጽ ቢወጣበት ምን ይደረግ ነበር?

✔️መልስ፦ ለምጽ የወጣባቸው ሰዎች በሚዳኙበት ሥርዓት ይዳኝ ነበረ።

፲፫. "በእነዚህም ርኩስ ትሆናላችሁ፤ የእነርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው" ይላል (ዘሌ.11፥24)። በነጋታው ንጹሕ ይሆናል ማለት ነው? ልብሱን ባያጥብስ?

✔️መልስ፦ አዎ በነጋታው ንጹሕ ይሆናል። ልብሱን ካላጠበና በነጋታውም ከለበሰው ግን ከርኵሰቱ አልነጻም ይባላል።

፲፬. ዘሌ.15፣6 "ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው በተቀመጠበት ነገር ላይ የሚቀመጥበት ሰው ልብሱን ይጠብ፥ በውኃም ይታጠብ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው" ይላል። እስከ ማታ ድረስ ሲል ምን ማለት ነው? በቀጣዩ ቀን ያለምንም ነገር ንጹሕ ይሆናልን?

✔️መልስ፦ በቀጣዩ ቀን ታጥቦ ንጹሕ ይሆናል ማለት ነው። በዕለቱ ግን ቢታጠብም ንጹሕ እንደማይሆን ተነግሯል።

፲፭. ዘሌ.12፣2-5 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው ‘ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት፤ እንደ ሕመሟ መርገም ወራት ትረክሳለች......."። ወንድ ብትወልድ ለ7፣ ሴት ብትወልድ ለ 14 ቀናት የረከሰች ናት ተብሎ የተለያየበት ምክንያት?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Oct, 14:40


✔️መልስ፦ ወንድ ስትወልድ ከሚፈሳት ደም ይልቅ ሴት ስትወልድ የበለጠ ደም ስለሚፈሳት ነው።

፲፮. ለምጽ ያለበት ሰው ሰውየውን ነው ካህኑ ርኩስ የሚለው ወይንስ የለምጹን ቦታ ብቻ ነው? ደዌው በቤቱ ግንብ ላይ ቢሰፋ ካህኑ ደዌ ያለባቸው ድንጋዮችን እንዲያወጡ ከከተማም ወደ ውጭ ወደረከሰው ቦታ እንዲጥሏቸው ያዛል ይላል። ቤት ግዑዝ አይደለ እንዴት በደዌ ተመታ ይባላል?

✔️መልስ፦ ለምጹን ነው ርኵስ የሚለው። ለምጹ ያረፈበት ሰውም በዚህ ምክንያት ረክሷል ይባላል። በቤት ላይም እንደለምጽ ያለ ወይም የተለየ ሽበት ሊያጋጥም ይችላል። ያንን ነው ለምጽ ወይም ደዌ ያለው እንጂ ቤት አይታመምም።

፲፯. ብሉይ ኪዳን መማራችን ምንድን ነው ጥቅሙ?

✔️መልስ፦ የሰው ልጅ ዋና መመሪያ ሕጎች ዐሥሩ ትእዛዛት ያሉ በብሉይ ኪዳን ስለሆነ ነው። በተጨማሪም ከየት መጣን የሚለውን የሚነግረን የተፈጥሮን ሙሉ ትርጉም የሚነግረን ብሉይ ኪዳን ነው። ማን እንደፈጠረን፣ ከፈጠረን በኋላ እግዚአብሔር በየዘመናቱ ከእኛ ከሰው ልጆች ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳንና የቸርነት ሥራ ለመረዳት ይጠቅመናል። ይህ ብቻ ሳይሆን ክርስቶስን የተቀበልነው በብሉይ በትንቢት በምሳሌ ሲነገር ቆይቶ ስለመጣ ነው። እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ የሆነ ነገርን አልተቀበልንም።

፲፰. የዓሣ ሥጋ አይበላምን? ከማይበሉት ብሎ ጠቅሶታል።

✔️መልስ፦ ይበላል። ከማይበሉትም አልጠቀሰውም። ከሚበሉት ወገን ከሰውነቱ ላይ ገለፈት (ቅርፍት) ያለው ተብሎ የተገለጸው ዓሣ ነው።

፲፱. ሴት ልጅ ከወለደች በኋላ የመንጻቷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ መሥዋዕት ወደ ካህኑ ታምጣለት እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል ያስተሠርይላትማል ይላል (ዘሌ.፲፪)። ሰለወለደች ኃጢአት አለባት ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ስለወለደች ኃጢአት አለባት አይባልም። ስትወልድ የፈሰሳት የአራስነት ደም ግን በብሉይ ርኩስ ተብሎ ይገለጽ ስለነበረ ከእርሱ ስለመንጻቷ መሥዋዕት ታቀርብ እንደነበረ የሚገልጽ ነው።

፳. በርኩስና በንጹሕ መካከል የሕይወት ነፍስ ካላቸውም በምትበሉትና በማትበሉት መካከል እንድትለዩ ነው። ይህ የመብል መለያየት በሐዲስ ኪዳን ቀጥሏል? የአበው ቅዱሳን ሐዋርያት ትምህርት ምን ይመስላል?

✔️መልስ፦ ወንጌል የምግብ ሕግ አይደለችም። ስለዚህም ይህን ብሉ ይህን አትብሉ ብላ አትገልጽም። ሆኖም ከብሉይ ኪዳን ከተከለከሉት በተለየ አሁንም እንዳንበላቸው የታዘዙ እንዳለ ከዚሁ ከፍ ብሎ ከተጠየቀው ጥያቄ ላይ ተገልጿል።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Oct, 13:21


ጉባኤ ቤታችን የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም የመጻሕፍተ ሐዲሳትና የመጻሕፍተ ሊቃውንት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት መጻሕፍትን እያሰባሰበ ይገኛል። ከፎቶው ላይ የምትመለከቱትን የመጽሐፍ መደርደሪያ አዘጋጅቶ በስጦታ የምታበረክቱልንን መጻሕፍት እየተጠባበቀ ይገኛል። ስለሆነም መጻሕፍትን ለግሡ። ማንኛውንም ዓይነት መጻሕፍት መለገሥ ይቻላል። መንፈሳዊ መጻሕፍት፣ የታሪክ መጻሕፍት፣ የልብ ወለድ መጻሕፍት፣ የስነ ልቡና መጻሕፍት፣ ሳይንሳዊ መጻሕፍት..... ሌሎችንም መጻሕፍት ማስገባት ትችላላችሁ።

ለተጨማሪ መረጃ
የጉባኤ ቤቱን መምህር መጋቤ ሐዲስ የኔታ ቃለ ሕይወት በዛን ያነጋግሩ። በምን መልኩ መጽሐፍ እንደምታበረክቱ ደግሞ መ/ር ማኅቶት እሸቴን ያነጋግሩ። ስልክ ቁጥር፦ 0918105917

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Oct, 13:07


የሚከተሉትን የቴሌግራም ቻናሎች ይቀላቀሉ።

1ኛ፦ መምህር ሲሳይ (የመጻሕፍተ ብሉያትና የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ መምህር)። እስካሁን በማኅበራዊ ሚዲያ መጥተው አያውቁም ነበረ። ከዚህ በኋላ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ሊያስተምሩን በቴሌግራምና በfacebook መጥተዋል። ጓደኛ እናድርጋቸው። (የሰው ልጅ ማን ነው የሚለውን መጽሐፍ ያበረከቱልን መምህር ናቸው)።

የፌስቡክ ገጻቸው Memher Sisayi https://www.facebook.com/profile.php?id=61566909047225

የቴሌግራም ቻናላቸው መምህር ሲሳይ ተስፋ https://t.me/memhirsisay

2ኛ፦ መምህር ማኅቶት እሸቴ፦
የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/MEBspiritualeducationtraining21

3ኛ፦ መምህር ፍሬው እውነቱ
የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/firewewunetu

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Oct, 05:17


#ኦሪት #ዘሌዋውያን #ክፍል 3
💙ምዕራፍ 11
-ስለሚበሉ እና ስለማይበሉ እንስሳት መነገሩ
-የተሰነጠቀ ሰኰና ያለውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ አርዶ መብላት እንደሚገባ፣ የማያመሰኳውንና የተሰነጠቀ ሰኰና የሌለው ግን እንደማይበላ
-ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ክንፍና ቅርፊት ያላቸው እንደሚበሉ፣ ቅንፍና ቅርፊት የሌላቸው ግን እንደማይበሉ

💙ምዕራፍ 12
-ሴት ወንድ ልጅ ስትወልድ በስምንተኛው ቀን መገረዝ እንደሚገባ፣ በአርባኛው ቀን ወደ ደብተራ ኦሪት መሥዋዕት ይዛ መምጣት እንደሚገባት፣ ሴት ስትወልድ ደግሞ ወደ ደብተራ ኦሪት በሰማንያኛው ቀን መምጣት እንደሚገባ

💙ምዕራፍ 13
-ለምጽ የወጣበት ሰው ርኵስ ይባል እንደነበረ

💙ምዕራፍ 14
-የለምጽ ደዌ ከለምጻሙ ላይ ቢጠፋ ካህኑ ስለሚነጻው ሰው መሥዋዕት ያቀርባል።

💙ምዕራፍ 15
-ከሰውነቱ ዘር የሚፈስሰው ሰው ቢኖር ርኩስ እንደሆነ፣ የሚተኛበት መኝታም ርኵስ እንደሆነ
-ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት እንዲሁም በግዳጇ (በወር አበባዋ) ሰባት ቀን እንደምትቀመጥ


💜የዕለቱ ጥያቄዎች💜
፩. እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የማይበሉ ብሎ ከጠቀሳቸው እንስሳት መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. በግ
ለ. ግመል
ሐ. ጥንቸል
መ. እርያ
፪. የሚበሉ እንስሳት ወይም አዕዋፋት ምን ዓይነት ናቸው?
ሀ. ከእንስሳት የሚያመሰኩ ሰኰናቸው የተሰነጠቀ
ለ. በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ክንፍና ቅርፊት ያላቸው
ሐ. ከእንስሳት የሚያመሰኩ ሰኰናቸው ያልተሰነጠቀ
መ. ሀ እና ለ
፫. አንዲት እናት ሴት ልጅን ስትወልድ ከወለደች በስንተኛ ቀኗ መሥዋዕት ይዛ ወደ ደብተራ ኦሪት ትመጣለች?
ሀ. በ7
ለ. በ14
ሐ. በ80
መ. በ40

https://youtu.be/W6RjHJzxKVY?si=G8to_KdnUc0TPkaV

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

23 Oct, 05:10


መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ክፍል 22
መጽሐፈ ሲራክ
ሲራክ የግብር ስሙ ሲሆን ዋና ስሙ ኢያሱ ነው፡፡ ይህ ኢያሱ ሲራክ እግዚአብሔርን ጥበብ ሥጋዊ ጥበብ መንፈሳዊ ግለጽልኝ እያለ ሲጸልይ ይኖር ነበር፡፡ በኋላ ተገልጾለት ይህንን መጽሐፍ ጽፏል፡፡ የተነሣውም እስራኤል ከባቢሎን ከተመለሱ በኋላ በዘሩባቤል ዘመን ነው፡፡
ምዕራፍ ፩
የአእምሮ ጠባይዕ መገኘቷ ከእግዚአብሔር ነው፡፡ የሕግ መገኘቷ ከእግዚአብሔር ነው፡፡ የወልድ መገኘቱ ከእግዚአብሔር አብ ነው፡፡ ወልድ ሰው እንዲሆን መታሰቡ ዓለም ሳይፈጠር ነው፡፡ ለአንድ ሰው ዐሥር ደጃፍ ያለው ቤት ይኖረዋል፡፡ ዘጠኙን ዘግቶ አንዱን ቢተወው አያድኑትም በአንዱ ደጃፍ ሌባ ገብቶ ያጠራቀመውን ከብቱንም ሰውንም ይወስድበታል፡፡ ሰውም ከዐሥሩ ሕግጋት አንዷን ቢያፈርስ ይጎዳል፡፡ ጻድቅ ሰው በክብር በባለሟልነትም ይኖራል፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት ማምለክ የነፍስ ክብር ነው፡፡ የሚያስመካም ነው፡፡ ትምክህት እንደ ኤልያስ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት የልብ ደስታ ነው፡፡ ፍጹም የሥጋና የነፍስ ደስታን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ፍጻሜው ያምርለታል፡፡ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የፍቅር የአደራ እናታችን ናት፡፡ የጥበብ ዘውዷ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡ ቁጡ አመፀኛም ሰው እስኪሞት ድረስ ምግባርንና ሃይማኖትን ሠርቶ አይጸድቅም፡፡ በተቈጣ ጊዜ ፈጥኖ ይጠፋልና፡፡ ጊዜዋ እስኪያልፍ ድረስ ቁጣን ታገሣት፡፡ ጊዜ እስክታገኝ ድረስ ነገርህን አትናገር አይሰማልህምና፡፡ ኃጥእ ሰው እግዚአብሔርን የሚፈራውን ጻድቁን ይንቀዋል፡፡ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ከወደድክ ሕጉን ጠብቅ፡፡ ጥበብ ዕውቀት ይሉሀል እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡ ራስህን አታኩራ እንዳትዋረድ ሰውነትህም እንዳትጠፋ፡፡ ምነዋ ብኮራ ትለኝ እንደሆነ ሠውረህ የሠራኸውን እግዚአብሔር ይገልጽብሀል፡፡ በብዙዎች ሰዎች መካከልም ያዋርድሀል፡፡


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

21 Oct, 14:06


💙ክፍል 19 የጥያቄዎች መልስ💙

▶️፩. እግዚአብሔር አትሥሩ ካላቸው አንዲቱን ቢተላለፍ ባያውቅም ያ ሰው በደለኛ ነው ይላል ካላወቀ እንዴት በደለኛ ይሆናል?

✔️መልስ፦ አለማወቅ ከተጠያቂነት እንደማያድን ያረጋግጥልናል። የእግዚአብሔርን ሕግ ማንኛውም ሰው አውቆ መዳን ይገባዋል።

▶️፪. ስብና ደም አትብሉ በምትኖሩበት ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው። ስብ ደግሞ በሁሉም ዘንድ በተለይ በገጠሩ ተወዳጅ ምግብ ነው ቢብራራ።

✔️መልስ፦ ስብ በዘመናቸው እንዳይበሉ ታዝዘዋል። በሐዲስ ኪዳን ግን መጻሕፍት ደምን ሲከለክሉ እንጂ ስብን ሲከለክሉ አላገኘሁም።

▶️፫. እንስሳት ደመ ነፍስ ስለሆኑ ደማቸው አይበላም ስቡ ግን ለምን እንዳይበላ ተከለከለ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር እንዳይበላ መከልከሉ ራሱ ምክንያት ይሆናል። ሌላው ምክንያት ተጨማሪ ነው።

▶️፬. የኃጢአት መሥዋዕትና የደኅንነት መሥዋዕት ሁለቱ ምንድን ነው ልዩነታቸው? አንድ ሰው ኃጢአቱ ከተሠረየለት ዳነ አይባልም?

✔️መልስ፦ ኃጢአቱ ከተሠረየለት ዳነ ይባላል። የኃጢአት መሥዋዕት ሰው ኃጢአት ከሠራ በኋላ ለኃጢአቱ ሥርየት የሚያቀርበው መሥዋዕት ነው። የደኅንነት መሥዋዕት ግን ሰው በኃጢአት ምክንያት የሚያቀርበው አይደለም።

▶️፭. ዘሌ.5:8 ላይ ሁለቱ ዋኖሶች ወይም ርግቦች ለምን አንገቱን አይቆርጠውም ተባለ?

✔️መልስ፦ የሚቆረጡት እንዲቆረጡ የማይቆረጡት እንዳይቆረጡ እግዚአብሔር ስላዘዘ።

▶️፮. ካህናት እንስሳትን ለመሥዋዕትነት ሲያቀርቡ ለምንድን ነው እጃቸውን የሚሠዋው ነገር ላይ የሚጭኑት?

✔️መልስ፦ ኃጢአታችን በአንተ ይሠረያል ለማለት ነው።

▶️፯. ዘሌ.2፥2 "ወደ አሮንም ልጆች ወደ ካህናቱ ያመጣዋል፤ ከመልካም ዱቄቱና ከዘይቱም አንድ እፍኝ ሙሉና ዕጣኑን ሁሉ ወስዶ ካህኑ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል" ይላል። ለመታሰቢያ የሚለው ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ሰዎች በተለያየ ምክንያት መሥዋዕት ለመሠዋታቸው መታሰቢያ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ የሚኖር ማለት ነው። ያ በጎ መዓዛ ስለሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወደድ ተገልጿል።

▶️፰. አጥንት መስበር በሐዲስ ኪዳን አይፈቀድም?

✔️መልስ፦ አጥንት አትስበሩ የተባለው ለዘመናቸው ነው። በአምሳል ደረጃ ደግሞ የክርስቶስ አፅም ላለመሰበሩ ምሳሌ ሆኖ አልፏል። በሐዲስ ግን አርዳችሁ ስትበሉ የበጉን አጥንት አትስበሩ የሚል ሥርዓት አላገኘሁም።

▶️፱. ማንኛውም ሰው ሳይታወቀው ርኩስ ነገር ቢነካ የረከሰም አውሬ በድን የረከሰም ከብት በድን ቢነካ፣ በማንኛውም ርኩስ ቢረክስ ነገሩ በታወቀው ጊዜ በደል ይሆንበታል ይላል። ከዚህ በፊት ይህ ርኩስ ይህ ቅዱስ ተብሎ የተለየ ነገር አለ? ነገሩ ባይታወቅስ?

✔️መልስ፦ የሚበሉትን ንጹሕ፣ የማይበሉትን ርኵስ ማለት የተጀመረው በኖኅ ጊዜ ነው። ነገሩ ከታወቀው በደል ይሆንበታል የተባለው ርኵስ የሆነን ነገር መዳሰስ በደል እንደሆነ ስለተገለጸ ነው። ስለዚህ የማንጻት ሥርዓቱን ሲፈጽም በታዘዘው ጊዜ መሠረት መሥዋዕት ያቀርባል። ባይታወቀውም ርኵስ የተባለን ከነካ ርኵስ ነው። ስላልታወቀው ግን ደብተራ ኦሪት ሊቀርብ ይችላል።

▶️፲. ካህኑም ከደሙ በጣቱ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል። ሲል በጣት ምን ያህል ሊወስድ ይችላል በቀንዶችስ የሚሆን ደም እንዴት በጣት ይወሰዳል?

✔️መልስ፦ በጣቱ ይውሰድ ማለት በአጭሩ የመሠዊያውን ቀንድ በደም ይቅባው ማለት ነው።

▶️፲፩. እርሾ ያለበት ነገር ማርም ለእግዚአብሔር የእሳት ቁርባን ይሆን ዘንድ አታቀርቡምና ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የእህል ቁርባን ሁሉ እርሾ አይሁንበት። እነዚህንም የበኩራት ቁርባን አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ እንደ ጣፋጭ ሽታ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠሉም። የትኞቹን በኩራት ነው?

✔️መልስ፦ የበኵራት ቁርባን የሚባለው ከዐሥር አንድ ለእግዚአብሔር ሲቀርብ፣ በኵራትን ለእግዚአብሔር ሲያቀርቡ የሚሠውት መሥዋዕት ነው።

▶️፲፪. ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር መባ ሲያቀርብ መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች ታቀርባላችሁ። ከላሞች መንጋ ቢሆን ነውር የሌለበት ተባቱን ያቀርባል ይላል። ከላሞች ወገን ብሎ ተባቱን ሲል ቢብራራ?

✔️መልስ፦ ወይፈኑን፣ ጥጃውን ሁሉ የላም ወገን ስለሚለው ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

21 Oct, 04:26


#ኦሪት #ዘሌዋውያን #ክፍል 1
✝️ምዕራፍ 1
-እስራኤል ለእግዚአብሔር መባ የሚያቀርብ ሰው ቢኖር መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች አቅርቡ መባላቸው
-የሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለበት ተባዕት እንዲሆንና ሲያቀርቡም በምስክሩ ድንኳን ፊት እንዲሆን መነገሩ
-መሥዋዕቱ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ እርሱም ያስተሰርይለት ዘንድ እጅን በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ መጫን እንደሚገባ
-መሥዋዕቱ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚታረድ

✝️ምዕራፍ 2
-ማንኛውም ሰው ቍርባን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲሆን ቢያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ስንዴ ዱቄት እንዲሆን መነገሩ፣ በዱቄቱም ላይ ዘይትን ማፍሰስ ዕጣንን መጨመር እንደሚገባ
-ከመሥዋዕቱ የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ እንደሚሆኑ
-ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የእህል ቁርባን ሁሉ እርሾ እንዳይሆንበት መነገሩ
-የሚቀርበው መሥዋዕት ሁሉ በጨው እንደሚጣፈጥ

✝️ምዕራፍ 3
-ስለ ደኅንነት መሥዋዕት አቀራረብ

✝️ምዕራፍ 4
-ስለኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት አቀራረብ
-እስራኤላውያን ኃጢአት ከሠሩ ስለሠሩት ኃጢአት ነውር የሌለበትን ወይፈን ለእግዚአብሔር እንደሚያቀርቡ

✝️ምዕራፍ 5
-ሰው ዐውቆም ሳያውቅም ኃጢአትን ቢሠራና በሥራው ቢጸጸት እግዚአብሔር ኃጢአቱን ይቅር እንደሚልለት

💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. በደብተራ ኦሪት ይቀርብ ስለነበረው የእህል ቁርባን ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከመልካም ስንዴ ዱቄት ይቀርባል
ለ. እርሾ ይደረግበታል
ሐ. በጨው ይጣፈጣል
መ. ከመሥዋዕቱ የተረፈውን የአሮን ልጆች ይበሉታል
፪. ስለኃጢአት መሥዋዕት ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. በስንዴው ዱቄት ዘይት አይፈስበትም
ለ. በስንዴው ዱቄት ዕጣን አይጨመርበትም
ሐ. በስንዴው ዱቄት ዘይት ይፈስበታል
መ. ሀ እና ለ
፫. በሕገ ኦሪት አንድ ሰው ኃጢአትን ቢሠራና እግዚአብሔር ይቅር እንዲለው ቢፈልግ ምን ማድረግ ይጠበቅበት ነበረ?
ሀ. መጀመሪያ በበደሉ መጸጸት
ለ. መሥዋዕት የሚሆን በግ ወደካህኑ መውሰድ
ሐ. የክርስቶስን ሥጋና ደም መቀበል
መ. ሀ እና ለ

https://youtu.be/OHgIIdn0O9k?si=mKKFJSVUE4kfo4xw

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

21 Oct, 04:19


🌻መጻሕፍተ 🌻ሰሎሞን 🌻ወሲራክ 🌻ክፍል 20
🌻መኃልየ 🌻ሰሎሞን
🌻ምዕራፍ ፩
እግዚአብሔርን በመርዓዊ (በሙሽራው) ቤተ እስራኤልን በመርዓት (በሙሽራዪቱ) መስሎ ሰሎሞን የተናገረው ቃል ይህ ነው፡፡ መኃልየ መኃልይን ጦር ያልጠፋለት ምሥጢሩን የማያውቅ ሰው ሊጸልየው አይገባም፡፡ ሁለቱ ጡቶችሽ ደስ ያሰኛሉ ማለት ቤተ እስራኤል ሆይ ሁለቱ ጽላቶችሽ ደስ ያሰኛሉ ማለት ነው፡፡ ጌታ ሆይ ደናግለ ልቡና አሕዛብ ወደዱህ፡፡ ከወደኋላህ ስበው አስቀሩህ ማለት በምግባር በሃይማኖት ተከተሉህ፡፡ በመዓዛ ዕፍረትከ ንረውፅ፡፡ በዐሥሩ ቃላተ ኦሪት እንኖራለን፡፡ አብአኒ ንጉሥ ውስተ ጽርሑ፡፡ ንጉሥ እግዚአብሔር ከፋርስ ከባቢሎን አውጥቶ ወደቤተ መቅደስ አገባኝ፡፡ ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ብኪ፡፡ በአንቺ መመለስ በአፍኣ በውስጥ ደስ ይለናል ይላሉ ነቢያት፡፡ አንድም መርዓት ቤተ ክርስቲያን፣ መርዓዊ ክርስቶስ ነው፡፡ ሁለቱ ጡቶቿ ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን ናቸው፡፡ ናርዶስ ወሀበ መዓዛሁ፡፡ ነቢያት አስተማሩ፡፡ እስራኤል ለእግዚአብሔር ምግባር ሃይማኖት አቀረቡ፡፡
🌻ምዕራፍ ፪
እኔ የምድረ በዳ አበባ ነኝ፡፡ ከአበባም በቆላ ያለ የሱፍ አበባ ነኝ፡፡ በእሾህ መካከል ያለ የሱፍ አበባ ያማረ የተወደደ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያን ሆይ አንቺም ለእኔ እንደዚያ የተወደድሽ ነሽ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ፡፡ ጽጌ ክርስቶስ በሀገራችን ተገለጸ፡፡ አንድም በእኛ በሥጋ ተገለጸ፡፡ አንድም የክርስቶስን ሥጋውን ደሙን የምንቀበልበት ጊዜ ደረሰ፡፡ ተንሥኢ ወንዒ ቅርብትየ እንቲኣየ ሠናይት ርግብየ፡፡ አቅራቢያዬ መልካም ርግቤ የኔ ሆይ ምእመን ፈጥኖ የሚራዳ ክርስቶስ ወደጻፋት ወንጌል ነይ፡፡
🌻ምዕራፍ ፫
ሁለቱ ጡቶችሽ ወተትን ያፈሳሉ ማለት ሁለቱ ጽላቶችሽ ሕገጋትን ያስገኛሉ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ከአብርሃም ልጆች ለይቶ እመቤታችንን ማደሪያው አደረገ፡፡ ፃኣ ትርኣያ አዋልደ ጽዮን ለንጉሥ ሰሎሞን በአክሊል ዘአስተቀጸለቶ እሙ፡፡ የእናቱ የማርያም ዘመዶች አይሁድ ያቀዳጁትን አክሊለ ሦክ ደፍቶ ንጉሥ ክርስቶስን ታዩ ዘንድ ኑ፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Oct, 12:02


💙💙💙 የጥያቄዎች መልስ💙💙💙
፩. የፈርዖንን ክፉ ትእዛዝ ባለመቀበላቸው እግዚአብሔር መልካም ያደረገላቸው አዋላጆች ማንና ማን ናቸው?
ሀ. ሲፓራና ዮስቲና
ለ. ፎሓና ሰሎሜ
ሐ. ሲፓራና ፎሓ💙
መ. ሰሎሜና ዮስቲና
፪. የሙሴ ሚስት ስሟ ማን ነው?
ሀ. ዮካብድ
ለ. ሲፓራ💙
ሐ. ፎሓ
መ. ዲቦራ
፫. እግዚአብሔር ለሙሴ ማን ነኝ አለው?
ሀ. የአብርሃም አምላክ
ለ. ያለና የሚኖር
ሐ. የይስሐቅ አምላክ
መ. ሁሉም💙
፬. እግዚአብሔር ለፈርዖን አምላክ አደርግሀለሁ ወንድምህ አሮንም ነቢይ ይሆንልሀል ያለው ማንን ነው?
ሀ. ያዕቆብን
ለ. ሙሴን💙
ሐ. ኢያሱን
መ. ሖርን
፭. የፈርዖን ጠንቋዮች ማድረግ ያቃታቸው ምትሐት ምን ነበር?
ሀ. በትራቸውን እባብ ማድረግ
ለ. የወንዙን ውሃ ደም ማድረግ
ሐ. በአስማታቸው ቅማል ማውጣት💙
መ. ጓጉንቸር እንዲወጣ ማድረግ
፮. እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አፀና ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. ፈርዖንን ክፉ አደረገው
ለ. ረድኤቱን ነሣው💙
ሐ. ጨካኝ እንዲሆን አደረገው
መ. ሀ እና ሐ
፯. እስራኤላውያን የፋሲካውን በግ አርደው የቤቱን መቃንና ጉበን የበጉን ደም ቀብተው የዳኑት ከምን መቅሠፍት ነው?
ሀ. ከአንበጣ መንጋ
ለ. ከበረዶ
ሐ. ከተናካሽ ዝንብ
መ. ከሞተ በኵር💙
፰. እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከፋሲካ በኋላ የቂጣ በዓልን ለስንት ቀን እንዲያከበሩ አዘዛቸው?
ሀ. ለዐሥራ አራት ቀን
ለ. ለዘጠኝ ቀን
ሐ. ለሰባት ቀን💙
መ. ለዐሥራ አንድ ቀን
፱. እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የዓመቱ መጀመሪያ ወር እንዲሆናቸው የነገራቸው ወር ማን ነው?
ሀ. መስከረም
ለ. ሚያዝያ💙
ሐ. ጥር
መ.ታኅሣሥ
፲. እስራኤላውያን የሁለት ቀን የሚሆን መና እንዲሰበስቡበት የታዘዘ ዕለት ማን ነው?
ሀ. ማክሰኞ
ለ. ቅዳሜ
ሐ. ዓርብ💙
መ. እሑድ
፲፩. እግዚአብሔር በምድረ በዳ ለአባቶቻቸው ያደረገውን ቸርነት ልጆች እንዲረዱ በመሶበ ወርቅ ሙሴ ያስቀመጠው መና ምን ያህል ነው?
ሀ. ሦስት ጎሞር
ለ. አንድ ጎሞር💙
ሐ. አራት ጎሞር
መ. ሰባት ጎሞር
፲፪. እስራኤላውያን እንዲያሸንፉ የሙሴን እጆች በግራና በቀኝ ይደግፉ የነበሩ ማንና ማን ናቸው
ሀ. ኢያሱና አሮን
ለ. አሮንና ሖር💙
ሐ. ሖርና ኢያሱ
መ. ዮቶርና ኢያሱ
፲፫. በብሉይ ኪዳን ሕግ በግ የሰረቀ ሰው በአንድ በግ ፋንታ ቅጣቱ ምን ነበረ?
ሀ. አራት በግ💙
ለ. አምስት በግ
ሐ. ሁለት በግ
መ. ዘጠኝ በግ
፲፬. በብሉይ ኪዳን ሕግ አባቱንና እናቱን የሰደበ ቅጣቱ ምን ነበረ?
ሀ. መታሰር
ለ. መገደል💙
ሐ. መገረፍ
መ. መደብደብ
፲፭. ሙሴ የመጀመሪያውን የቃል ኪዳን ታቦት ለመቀበል በተራራ ላይ ለምን ያህል ቀን ቆየ?
ሀ. አርባ💙
ለ. ሰማንያ
ሐ. ሠላሳ
መ. ሰባት
፲፮. በቀን በቀን በደብተራ ኦሪት መሠዊያ ላይ ስንት ጠቦቶች ይቀርቡ ነበረ?
ሀ. ሦስት
ለ. አራት
ሐ. ሁለት💙
መ. አምስት
፲፯.በደብተራ ኦሪት በታቦቱ ፊት መብራት እንዲበራ የታዘዘ መቼ ነው?
ሀ. ሁልጊዜም
ለ. ከጠዋት ጀምሮ እስከ ሠርክ
ሐ. ከማታ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት
መ. ከማታ ጀምሮ እስከ ማለዳ💙
፲፰.በደብተራ ኦሪት ስለነበረው መሠዊያ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ርዝመቱ አምስት ክንድ ነው
ለ. ወርዱ አምስት ክንድ ነው
ሐ. ከፍታው ሦስት ክንድ ነው
መ. ሁሉም💙
፲፱. ደብተራ ኦሪትን ይሠራ ዘንድ ጥበብ ተሰጠው የተባለ ማን ነው?
ሀ. ባስልኤል
ለ. አሮን
ሐ. ኤልያብ
መ. ሀ እና ሐ💙
፳. ሙሴ በጽላቱ ላይ የጻፋቸው የቃል ኪዳን ቃሎች (ትእዛዛት) ስንት ናቸው?
ሀ.10💙
ለ. 6
ሐ.12
መ. 7
፳፩. ሙሴ እግዚአብሔርን "የእስራኤልን ኃጢአታቸውን ይቅር ትላቸው እንደሆነ ይቅር በላቸው፣ ያለዚያ ግን ከጻፍከው መጽሐፍ ደምስሰኝ" ብሎታል። ይህ ቃል የት ይገኛል?
ሀ. ዘፀ.34፣11
ለ. ዘፀ.32፣32💙
ሐ. ዘፀ.35፣9
መ. ዘፀ.33፣23
፳፪. ደብተራ ኦሪት እስራኤል ከግብጽ ከወጡ በስንተኛው ዓመት ተተከለች?
ሀ. በመጀመሪያው ዓመት
ለ. በሁለተኛው ዓመት💙
ሐ. በሦስተኛው ዓመት
መ. በአራተኛው ዓመት
፳፫. በሥርየት መክደኛው ስንት ኪሩቤል እንዲሣሉ ተደረገ?
ሀ. አራት
ለ. ዐሥራ ስድስት
ሐ. ሁለት💙
መ. ኻያ አራት
፳፬. ንዋየ ደብተራ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. መቅረዝ
ለ. ታቦት
ሐ. መስቀል💙
መ. ሀ እና ለ

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Oct, 11:57


💙ክፍል 18 የጥያቄዎች መልስ💙

▶️፩. “ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ የዘረጉ ሆኑ፥ የሥርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ሸፈኑ፥ እርስ በርሳቸውም ተያዩ፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ መክደኛው ተመለከቱ” ይላል (ዘፀ.37፥9)።
ይህ ንባብ በወርቅ ስለተሠሩት ኪሩቤል ነው? ወይስ አማናዊ ነው?

✔️መልስ፦ ስለምስሎቹ የተነገረ ነው። ሙሴ እንዲያ አድርጎ እንዲስላቸው ስለታዘዘ ከላይ በተገለጸው መልኩ አድርጎ ቀርጿቸዋል። ስለዚህ ስለምስሎቹ የተነገረ እንጂ ስለአማናውያን ኪሩቤል የተነገረ አይደለም። አማናውያን ኪሩቤል ረቂቅ ስለሆኑ በዓይነ ሥጋ አይታዩምና።

▶️፪. የተሰጠው ወርቅ ሁሉ ለድንኳኑ ሥራ ሁሉ የተደረገው ወርቅ እንደ መቅደሱ ሰቅል 29 መክሊት 730 ሰቅል ነበረ ይላል። ሰቅልና ዲድርክም የሚሉት ቃላት የምን መለኪያ ናቸው?

✔️መልስ፦ ሰቅል የብር፣ የወርቅ መለኪያ ሚዛን ነው። ዲድርክም ደግሞ የሳንቲም (የገንዘብ) ዓይነት ነው።

▶️፫. ድንኳኑን የእግዚአብሔር ክብር ስለሞላው ሙሴ ወደ ድንኳኑ ይገባ ዘንድ አልቻለም ይላል ለምን ነው ያልገባው?

✔️መልስ፦ ምክንያቱ ከጥያቄው ተገልጿል። የእግዚአብሔር ክብር ስለሞላው መግባት አልቻለም ተብሏል። የእግዚአብሔር ክብር ሙላት ሙሴን እንዳይገባ ከልክሎታል።

▶️፬. ባለፉት ምዕራፎች ሙሴ የመገናኛውን ድንኳን ሠርቶ እንደነበር አይተናል። በዚህ ምዕራፍ የተሠራው ሌላ ነው? ስንት ደብተራ ድንኳን ነበሩ?

✔️መልስ፦ ባለፉት ምዕራፎች እንዲሠራ መታዘዙንና የሥራው ዐቅድ (Plan) ምን መሆን እንዳለበት ነው የተነገረው እንጂ በተግባር አልተሠራም ነበረ። ከዚህኛው ምዕራፍ የተነገረው ደግሞ ተግባራዊ ሥራው መጠናቀቁን ሲሆን የባለፈው ምዕራፍ የሚነግረን ደግሞ ዕቅዱን ነው።

▶️፭. "ባስልኤልም ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ፤ ርዝመቱም ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ" ይላል (ዘፀ.37፥1)። ታቦት መሥራት የሚችለው ማን ነው (በብሉይም በሐዲስም) ባስልኤል ክህነት ነበረው?

✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን ታቦት እንዲሠራ የታዘዘው ባስልኤል ነው። ባስልኤል ደግሞ ነገዱ ከነገደ ይሁዳ ስለነበረ ክህነት አልነበረውም። ታዲያ ለምን እንዲሠራ ተፈቀደለት ከተባለ እግዚአብሔር እንዲሠራ ስለፈቀደለት ነው። በሐዲስ ኪዳን ማን ታቦት ይቅረጽ ለሚለው ካነበብኳቸው መጻሕፍት ላይ ማስረጃ አላገኘሁም።

▶️፮. (ዘፀ.39፥11-13) ላይ የተጠቀሱት ሉር፥ ሰንፔር፥ አልማዝ፤ ያክንት፥ ኬልቄዶን፥ አሜቴስጢኖስ፤ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያሰጲድ የሚሉት ቃላት ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ የመዓድናት (የዕንቍ) ዓይነቶች ናቸው። አዕናቍ ናቸው።

▶️፯. "በእነርሱም ላይ በጥልፍ ሥራ ኪሩቤልን አደረጉባቸው" ይላል (ዘፀ.36፥8)። የመራቸው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ይነገራል። ታድያ ለምን ይሆን ኪሩቤል በመቅደስ ውስጥ የተሠሩት?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ኪሩቤል እንዲሠሩ ስላዘዘ ነው።

▶️፰. “የቅብዓቱንም ዘይት ወስደህ ማደሪያውን በእርሱም ያለውን ሁሉ ትቀባለህ፥ እርሱንም ዕቃውንም ሁሉ ትቀድሳለህ፤ ቅዱስም ይሆናል” ይላል (ዘፀ.40፥9)። ይህ ቅባትና ቅብዐ ሜሮን አሁን ላይ ቤተ ክርስቲያን የምትገለገልበት ከሙሴ ጀምሮ የኖረ ነው ወይስ ይለያያል?

✔️መልስ፦ ይለያያል። የሐዲስ ኪዳኑ ቅብዐ ሜሮን መነሻው ፍልሀተ ሜሮን ሲደረግ የክርስቶስ ደምም ነበረበት። በብሉይ ኪዳን ግን የክርስቶስ ደም አልነበረምና ነው። ስለዚህ የብሉዩ ቅብዐትና የሐዲሱ ቅብዐ ሜሮን የተለያዩ ናቸው። በምሳሌነት ግን የብሉዩ የቅብዐ ሜሮን ምሳሌ ነው።

▶️፱. ሙሴ ካህን ነበር?

✔️መልስ፦ ሙሴ ነገዱ ከነገደ ሌዊ ስለሆነ አዎ ካህን ነበረ። ነገር ግን አሮንን በደብተራ ኦሪት ላይ ከሾመ በኋላ በዋናነት ሥራው አስተዳደር ላይ ያተኮረ ነበረ። በምሳሌ ደረጃም ሙሴ የፓትርያርክ ምሳሌ ነው።

አነሳስቶ ላስጀመረን ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይገባል። ነገ ኦሪት ዘሌዋውያን ይጀምራል።

© በትረ ማርያም አበባው

🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Oct, 09:32


💙ፍካሬ ሞት ወሕይወት💙
አንዳንዱ ሰው ሞትን ማሰብ አይፈልግም። ማሰብ ስላልፈለገ ግን ሞት አይቀርለትም። ከአንድ ጓደኛዬ ጋር "ሞት ካልቀረ የመኖር ትርጉሙ ምንድን ነው?" በሚለው ዙሪያ ስናወራ ይህንን ጥያቄ ለሌላ ጓደኛዬ ጠየቅሁት አለኝ። ያ ልጅ ጃንቦ እየጠጣ ሳለ "ሞት ካልቀረልን ለምንድን ነው የምንኖረው" ብየ ስጠይቀው ሞትን ሲያስብ ጨነቀውና "እባክህ ተወኝ ጃንቦዬን ልጠጣበት" አለኝ ብሎ ነገረኝ።

ሞት ካልቀረልን የመኖር ጥቅሙ ምንድን ነው? ለምንስ እንኖራለን? የምንሞትበትን ቀን አናውቀውም። በምን እንደምንሞትም አናውቅም። ከመቶ ዓመት በፊት የነበሩ ብዙዎች አሁን የሉም። ከመቶ ዓመት በኋላም አሁን ካለኖች አብዛኞች በሥጋ አንኖርም። በሥጋ ወደአለመኖር እንሸጋገራለን። ሞት ካልቀረልን ታዲያ የመኖር ጥቅሙ ምንድን ነው? እኔ የመኖር ጥቅም ብየ የማስበው ከሞት በኋላ ለሚኖረው ዘለዓለማዊ ሕይወት መዘጋጃ እንዲሆነን የሚል ነው።

በዚህች ምድር ምንም ያህል ዘመን እንኑር ለእውነት መኖር፣ ለነጻነት መኖር፣ ለእውነት መሞት፣ ለነጻነት መሞትን የመሰለ ደግ ነገር ግን የለም። ቅዱስ ቂርቆስ በዚህች ምድር የኖረው ለ3 ዓመታት ብቻ ነው። ነገር ግን ለእውነት ስለሞተ በዘለዓለማዊው ዓለም አሸብርቆ ይኖራል። ብዙ ክፉ ሰዎች (ሌቦች፣ ዘረኞች፣ ውሸታሞች፣ ራስ ወዳዶች፣ ሐሜተኞች፣ አመንዝራዎች እና የመሳሰሉት) ብዙ ዘመን በዚህ ምድር ኖረው ነበረ። ግን ከሞት አላመለጡም። ወደዘለዓለም የሥቃይ ቦታም ሄደዋል።

ውሸትን ይዞ፣ አድር ባይ ሁኖ፣ ሰማዕትነትን ፈርቶ፣ ሞትን ፈርቶ ከወንጀለኞች ጋር ተስማምቶ በዚህች ምድር አንድ ሺህ ዓመት ከመኖር ይልቅ እውነትን ይዞ፣ ለነጻነት ታግሎ፣ ለትክክለኛ ነገር ኑሮ፣ ውሸትን ተቃውሞ እንደቂርቆስ በዚህች ምድር ጥቂት ዘመን ኑሮ መሞት በብዙ እጥፍ ይበልጣል። ለትክክለኛ ነገር ኑሮና ታግሎ የሞተ ሰው ብፁዕ ነው። ምክንያቱም የማይቀርለትን ሞት ቁምነገር ሠርቶ አሳምሮታልና ነው። ሞትን አስበን መሥራት ይገባናል። እንዳይቆጨን ከሞት በፊት መሥራት ያለብንን መሥራት እንጀምር። ዛሬ ወይም ነገ እንደምንሞት አስበን እንሥራ። አበባ መርገፉ ካልቀረ ፍሬን ይተካ። ዕፀዋት አበባቸውን አርግፈው ፍሬን ያፈራሉ። የዚህች ዓለም ኑሮ እንደአበባ አንድም እንደ ጠዋት ጥላ ዘመኗ አጭር ነው።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Oct, 05:01


#ኦሪት #ዘፀአት #ክፍል 8
💜ምዕራፍ 36
-ደብተራ ኦሪት መሠራቷ

💜ምዕራፍ 37
-የቃል ኪዳኑ ታቦትና መቅረዙ መሠራታቸው

💜ምዕራፍ 38
-መሠዊያ መሠራቱ

💜ምዕራፍ 39
-የልብሰ ተክህኖ መሠራት

💜ምዕራፍ 40
-ደብተራ ኦሪትና በውስጧ ያሉት ንዋያት ተሠርተው መፈጸማቸው
-ድንኳኗ የእግዚአብሔርን ክብር እንደተሞላች


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ደብተራ ኦሪት እስራኤል ከግብጽ ከወጡ በስንተኛው ዓመት ተተከለች?
ሀ. በመጀመሪያው ዓመት
ለ. በሁለተኛው ዓመት
ሐ. በሦስተኛው ዓመት
መ. በአራተኛው ዓመት
፪. በሥርየት መክደኛው ስንት ኪሩቤል እንዲሣሉ ተደረገ?
ሀ. አራት
ለ. ዐሥራ ስድስት
ሐ. ሁለት
መ. ኻያ አራት
፫. ንዋየ ደብተራ ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. መቅረዝ
ለ. ታቦት
ሐ. መስቀል
መ. ሀ እና ለ

https://youtu.be/whcT_dVNDQs?si=A55n-DUWRmZj0GR1

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

20 Oct, 04:46


💐መጻሕፍተ 💐ሰሎሞን 💐ወሲራክ 💐ክፍል 19
💐መጽሐፈ 💐መክብብ
💐ምዕራፍ ፲
የብልህ ሰው ልቡናው በቀኙ ነው አለ ቀና ነገርን ያስባል፡፡ የአላዋቂ ሰው ልቡና በግራ ነው አለ ጠማማ ነገርን ያስባል፡፡ ሁሉን የሚያስብ ሰው አላዋቂ ነው፡፡ ንስሓ ብዙ ኃጢኣትን ያስተሰርያል፡፡ ለባልንጀራው ጉድጓድ የሚቆፍር ሰው በቆፈረው ጉድጓድ ይወድቃል፡፡ ሰማያዊ ሕግን የሚያፈርስ ሰው ሰማያዊ ሕግን በማፍረሱ መከራን ይቀበላል፡፡ ዕውቀት ሰውን ታበረታዋለች፡፡ የብልህ ሰው መወደዱ በአፉ በተናገረው ነገር ነው፡፡ አላዋቂ ሰው ነገርን ያበዛል፡፡ ንጉሥሽ ሕፃነ አእምሮ የሆነ ሀገር ሆይ ወዮልሽ፡፡ አንድም ንጉሥሽ ሕፃነ አእምሮ ዲያብሎስ የሚሆን ስብእና ኃጥኣን ወዮልሽ፡፡ ንጉሥሽ የአብ ልጅ ክርስቶስ የሚሆን ሰብእና ጻድቃን ሆይ ንዕድ ክብርት ነሽ፡፡ የክርስቶስ ሥጋው ደሙ በመንፈስ ቅዱስ ሕያዋን የሆኑትን ሰዎች ደስ ያሰኛቸዋል፡፡
💐ምዕራፍ ፲፩
ብርሃነ ፀሐይን ማየት ለዓይነ ሥጋ ያማረ ነው፡፡ ስለሠራኸው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር ለፍርድ እንደሚያቀርብህ ዕወቅ፡፡ ከልቡናህ መዓትን አርቅ፡፡ ትምክህትንም ከሰውነትህ አርቅ፡፡
💐ምዕራፍ ፲፪
ክፉ ቀን ሳይመጣብህ በሕፃንነትህ ወራት እግዚአብሔርን አስበው አለ ሞት ሳይመጣብህ አስበው፡፡ የሰውነትህ ደም ግባቱ ሳይለወጥ ፈጣሪህን አስብ፡፡ በሞት መሬት ወደመሬትነቱ ይመለሳል፡፡ ሰው በሥጋ በነበረ ጊዜ ስለሠራው ሥራ ሁሉ ምላሽ ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔርን ፍራ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፡፡ ፍጥረቱን ሁሉ እግዚአብሔር ለፍርድ ያቀርበዋል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Oct, 14:14


#እግዚአብሔርን #እንድናገኝ #ከሰፈር #እንውጣ

ዘፀ.33፥7 "ሙሴም ድንኳኑን እየወሰደ ከሰፈር ውጭ ይተክለው ነበር፤ ከሰፈሩም ራቅ ያደርገው ነበር፤ የመገናኛውም ድንኳን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርንም የፈለገ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ወዳለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይወጣ ነበር"።

በዘረኝነት እሳቤ፣ በሰፈርተኝነት እሳቤ ውስጥ ተሁኖ እግዚአብሔር አይገኝም። ደብተራ ኦሪት የቤተክርስቲያን ሞሳሌ ናት። ደብተራ ኦሪት ከሰፈር ውጭ ነበረ የምትተከል። እግዚአብሔርን የፈለገ ከሰፈር ወጥቶ ነበረ የሚያገኘው። የደብተራ ኦሪት ምሳሌ በሆነችው ቅድስት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን ለማግኘት የፈለግን ሰዎች ከሰፈር እንውጣ። ከሰፈር ከጎጥ ከብሔር ሳይወጡ እግዚአብሔር አይገኝም። በተለይ ጳጳስ ሆኖ፣ መነኩሴ ሆኖ ሰፈር ለሰፈር ሲርመጠመጥ ማየት ያቆስላል። በሰፈር ሚዛን በኮታ ጵጵስና መሾም ያደማል። ከሰፈር እንውጣ ጎበዝ። የቤተክርስቲያን ተቋማት ላይ የሚሠሩ ሰዎች ሰፈርን መሠረት አድርገው ሲሠሩ አያበሳጭም??። ከሰፈር ሳንወጣ እግዚአብሔርን ማግኘት አንችልም። ከሰፈር እንውጣ።

ከላይ ከጻፍኩት ጋር የማይገናኝ ግን ግልጽ ያልሆነልኝ ጥያቄ አለ። እስኪ የምታውቁ መልሱልኝ። ጳጳስ ሆኖ የሲኖዶስ አባል ያልሆነ አለ ወይ? ብዙ ጊዜ ስናስተዋውቅ ብፁዕ አቡነ እገሌ የእገሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንላለን ለምን? በሀገረ ስብከት ውስጥስ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሚባል አለ ወይ? የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መባል አይበቃውም? "ዋና" የምትለዋ ቃል መጨመሯ አስፈላጊነቷ ምንድን ነው?

ስብከት ላይ የሰላምታ ጋጋታ ቢቀርስ? ለምሳሌ "ሁላችሁም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እንደምን አላችሁ" ብሎ ሰላምታ አቅርቦ ቀጥታ ወደርእስ ገብቶ ማስተማር አይቻልም ወይ? በእግዚአብሔር አደባባይ ፍጻሜው ያልታወቀ ሰውን ማሞጋገሱ ምን ይጠቅማል?

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Oct, 12:16


💙ክፍል 17 የጥያቄዎች መልስ💙

▶️፩. “ሕዝቡም ሁሉ በጆሮዎቻቸው ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብረው ወደ አሮን አመጡለት” ይላል (ዘፀ.32፥3)። አሮን የእግዚአብሔር ካህን ሆኖ ሳለ እንዴት ጣዖት ሠራላቸው? ከግብፅ ያወጣቸው እግዚአብሔር እንደሆነ እያወቀ ለምን ጣዖት ነው አለ? ከዛስ በኋላ አሮን በክህነቱ ቀጠለ?

✔️መልስ፦ አሮን ወርቃችሁን ጌጣችሁን አምጡ ያላቸው እስራኤላውያን ገንዘብ ወዳድ ስለሆኑ ለገንዘባቸው ሲሉ ዝም ይላሉ ብሎ አስቦ ነበረ። ነገር ግን ጣዖትን የማምለክ ፍቅራቸው ከፍ ስላለ ገንዘባቸውን ሰጡ። ከዚያም ወርቁ ቀልጦ ቢጠፋልኝ ብሎ ቢያቃጥለው ሳይጠፋ ቀረ። ከዚያ ዓይን ጆሮ አበጅቶ ሠራላቸው። ፈርቶም የጥጃ ምስል አቁሞ እነሆ አምላካችሁ አላቸው። ፈርቶ ነው እንዲህ ያደረገው። በኋላ ሙሴ ጣዖቱን አጥፍቶታል። እግዚአብሔርም ቸር ስለሆነ ያለፈውን በደሉን ሳይቆጥር አሮን በክህነቱ እንዲቀጥል አድርጎታል።

▶️፪. “እርሱም፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእናንተ ሰው ሁሉ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፥ በሰፈሩም ውስጥ በዚህና በዚያ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፥ የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም ይግደል አላቸው” ይላል (ዘፀ.32፥27)። የሌዊ ልጆችን ለምን እንዲገድሉ ተመረጡ? ያጠፉት ሕዝቡ በሙሉ ሆነው ሳለ ተመርጠው የተገደሉት እነማን ናቸው? ለምን?

✔️መልስ፦ የሌዊ ልጆች በተለየ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ ስለተመረጡ ነው። እስራኤላውያን ያመለኩትን ጥጃ ሙሴ በያዘው ጽላት ፈጨው። አደቀቀው። የደቀቀውን በውሃ በጥብጦ ለእስራኤል አጠጣቸው። ያን ጊዜ ፍቅረ ጣዖት ያደረባቸው ሰዎች በአካላቸው ላይ ወርቅ የመሰለ ለምጽ ወጣባቸው። ለምጽ ያልወጣባቸው ለምጽ የወጣባቸውን ገደሏቸው ማለት ነው። የጣዖት ፍቅራቸው ከፍ ያለ ሰዎች ናቸው የተገደሉት። ሌላውን እግዚአብሔር ምሮታል።

▶️፫. “አንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆንህ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ በአንተ መካከል አልወጣምና በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ” ይላል (ዘፀ.33፥1-3)። ከላይ ስንነጋገር የእግዚአብሔር መልአክ ካለ እግዚአብሔር እንዳለ አይተን ነበር። ታዲያ እኔ አልመጣም መልአክ እሰድዳለሁ ለምን አለ?

✔️መልስ፦ በህልውና እግዚአብሔር የሌለበት ቦታ የለም። የማይኖርበት ቦታም አይኖርም። አምላክ ምሉእ በኵለሄ ነውና። ከዚህ ላይ መልአኬን እልካለሁ ያለው መልአኩ ይረዳሀል ማለት ነው። መልአክ ቀን በዐምደ ደመና ሌሊት በዐምደ እሳት ይመራቸው ነበረ። በመሠረቱ በመልአኩ አድሮ የሚረዳቸውም እግዚአብሔር ነበረ። ታዲያ እግዚአብሔር በአንተ መካከል አልወጣም ማለቱ ምን ማለት ነው? ከተባለ ከዚህ ቀደም ሕዝቡ እንዳንጠፋ ሙሴ ይናገረን እንጂ እግዚአብሔር አይናገረን እንዳሉት ያለ ነው። አሁን ሙሴ የሚናገረው እግዚአብሔር ያልነገረውን ሆኖ አይደለም። እግዚአብሔር በዘፈቀደ በግልጥ ሲታይ ሕዝቡ የሚጠፉ የሚቸገሩ ስለሆነ ከእርሱ ይልቅ መልአኩ እንዲረዳቸው አደረገ።

▶️፬. “ሙሴም ድንኳኑን እየወሰደ ከሰፈር ውጭ ይተክለው ነበር፤ ከሰፈሩም ራቅ ያደርገው ነበር፤ የመገናኛውም ድንኳን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርንም የፈለገ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ወዳለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይወጣ ነበር” ይላል (ዘፀ.33፥7)። የመገናኛ ድንኳኑን ከሰፈር ውጭ ለምን አደረገው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ከሰፈር ውጭ እንዲያደርገው ስላዘዘው።

▶️፭. “የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ” ይላል (ዘፀ.34፥7)። ይህ ንባብ አልገባኝም በአባቶች ጥፋት ልጆች ይቀጣሉ?

✔️መልስ፦ ከዚህ ቀደም ተጠይቆ ተመልሷል። ልጆች አባቶቻቸውን መስለው ክፋት ከሠሩ እንደሚቀጡ፣ አባቶቻቸውን መስለው ጽድቅ ከሠሩም እንደሚባረኩ ለመግለጽ ነው። እንጂ ልጅየው ጻድቅ ሆኖ አባትየው ኃጥእ ቢሆን በአባቱ ኃጢአት ልጁ ይቀጣል ማለት አይደለም።

▶️፮. “የአህያውንም በኵር በጠቦት ትዋጀዋለህ፤ ባትዋጀውም አንገቱን ትሰብረዋለህ” ሲል (ዘፀ.34፥20) ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ሽጠህ ዋጋውን ትሰጣለህ ማለት ነው።

▶️፯. “በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ እንጀራም አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። በጽላቶቹም አሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ” ይላል (ዘፀ.34፥28)። አሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች የጻፈ ማነው እግዚአብሔር ወይስ ሙሴ?

✔️መልስ፦ ጽላቱን የቀረጸው ሙሴ ሲሆን ጽሑፎችን የጻፋቸው ደግሞ እግዚአብሔር ነው። ጽላቱን ማዘጋጀቱን ለመግለጽ ሙሴ ጻፈው ይላል። ጽሑፉን የጻፈውን ለማመልከት ደግሞ እግዚአብሔር ጻፈው ይላል።

▶️፰. "ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለኽ ንገራቸው እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር እንደ ኾንኩ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ ዘንድ ለልጅ ልጃችሁ ምልክት ነውና ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ" ይላል (ዘፀ.31:13)። በብሉይ ኪዳን ቅዳሜ ብቻ አይደለም እንዴ ሰንበት የነበረው? ሰንበቶቼን ሲል ምን ማለቱ ነው?

✔️መልስ፦ የዓመቱን ቅዳሜዎች በአንድ ላይ ቆጭሮ ሰንበቶቼ ብሏል።

▶️፱. ዘፀ.33:11 ላይ እግዚአብሔርም ሰው ከባልንጀራው ጋራ እንደሚነጋገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋራ ይነጋገር ነበር ይልና ከታች ደግሞ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልኽም አለ ይላል። መጀመሪያ እንዴት ነው ያየው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ሰው አያየኝም ያለው በባሕርይው እንደማይታይ ለመግለጽ ነው (ዮሐ.1፣18)። ሙሴ አየው ተነጋገረው የተባለው ደግሞ በዘፈቀደ (እግዚአብሔር ለሙሴ መታየት በሚችልበት መገለጥ) ነው።

▶️፲. እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሚያዘው መሠረት መና ከሰማይ እያወረደ ውሃ ከዐለት እያፈለቀ አብልቶ አጠጥቶ ከግብፅ ምድር ያወጣንን ሙሴን ለምን አናውቀውም አሉ?

✔️መልስ፦ አናውቀውም ማለታቸው ለጊዜያው የት እንደሄደ አላወቅንም ማለታቸው ነበረ። ከተራራ ሄዶ አርባ ቀን ሲሠወራቸው ጊዜ የተናገሩት ቃል ነው። እንጂ በመልክ በስም በአካል አለማወቅን አያመለክትም።

▶️፲፩. እግዚአብሔር ሙሴን ጀርባዬን ታያለህ ፊቴ ግን ለአንተ አይታይም ማለቱ ትርጉሙ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በዘፈቀደ እታይሀለሁ እንጂ በባሕርይዬ አታየኝም ማለት ነው። እንዲሁም ሰው ሆኜ በሥጋ ታየኛለህ እንጂ በመለኮት መቼም መች አታየኝም ማለቱ ነው።

▶️፲፪. በማደሪያዎቻችሁ ውስጥ በሰንበት ቀን እሳትን አታንድዱ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ሲል የዕለት ምግብ መሥራት አይቻልም ወይስ ሌላ ነው ትርጉሙ?

✔️መልስ፦ ቅዳሜ የሚበሉትን ምግብ ዓርብ እንዲያዘጋጁ ስለታዘዙ ነው እንዲህ መባሉ። አሁን በሐዲስ ኪዳንም የቻለ ምግቡን ቀድሞ ማዘጋጀት ነው። ካልቻለ ደግሞ የዕለት ምግብ የሆኑ ጉዳዮችኝ ቢያዘጋጅ በደል አይሆንበትም።

▶️፲፫. ዘፀ.34፥11 "በዚህ ቀን የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ እኔ አሞራዊውን ከነዓናዊውንም ኬጢያዊውንም ፌርዜዎናዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም በፊትህ አወጣለሁ" ይላል። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት እስራኤላውያን በግብፅ በነበሩበት ጊዜ ሀገረ እስራኤል ተቀምጠው ነው?

✔️መልስ፦ አዎ። በኋላ እግዚአብሔር እነዚህን አጥፍቶ እስራኤላውያንን አውርሷቸዋል።

▶️፲፬. የመጀመሪያዎቹን ጽላት ይዞ ሲወርድ አርባ ቀን ቆየ ይላል እና ሁለተኛ ጽላት ቀርፆ ወጥቶ ሲወርድ አርባ ቀን ቆየ (34፡28) ይላል 80 ቀን ማለት ነውን?

✔️መልስ፦ አዎ። በመጀመሪያው 40 ቀን ቆየ። የመጀመሪያው ጽላት ሲሰበር እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ አርባ ቀን ቆይቶ ተቀብሏል።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Oct, 12:16


▶️፲፭. በሰባተኛውም ቀን ከሥራው ስላረፈና ስለተነፈሰ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘላለም ምልክት ነው። ይላል ስላረፈና ስለተነፈሰ ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር አረፈ ተነፈሰ ማለት መፍጠርን አቆመ ማለት ነው። ፍጥረት ተፈጥሮ ያለቀ በዕለተ ዓርብ ነው። ከዚያ በኋላ ያለው በመዋለድ የበዛና የሚበዛ ነውና።

▶️፲፮. ዘፀ.31፣15 "በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል" ይላል። ይህ ሕግ ከሐዲስ ኪዳን ሰንበት አከባበር አንጻር እንዴት ይታያል? ጥቅል ሕግጋትስ ከብሉይ ወደ ሐዲስ ስንመጣ ቀለሉ ወይንስ ከበዱ?

✔️መልስ፦ ሕገጋት ለመተግበር የማያስቸግሩ ልዝብና ቀላል እንደሆኑ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሯል። ስለዚህ በዚህ ጊዜ ከበዱ በዚህ ጊዜ ቀለሉ ተብሎ አይነገርላቸውም። በሐዲስ ኪዳን ሰንበትን መሻር ቅጣቱ መገደል አይደለም። ይህ አንድ ኃጢአት ስለሆነ ነፍሳዊ ቅጣትን እንደሚያስከትል እንናገራለን እንጂ። በብሉይ የሥጋ ሞትን ያስከትል ነበረ። አሁን ደግሞ የነፍስ ሞትን ያስከትላል።

▶️፲፯. ዘፀ.34፣15 "በዚያች ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፥ እነርሱ አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና በሠዉላቸው ጊዜ እንዳይጠሩህ፥ ከመሥዋዕታቸውም እንዳትበላ" ይላል። እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?

✔️መልስ፦ አሞራውያን፣ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ ፌርዜዎናውያን፣ ኢያቡሳውያን..... እና የመሳሰሉት ቀድሞ በኋላ እስራኤላውያን በነበሩበት ቦታ የነበሩ ናቸው።

▶️፲፰. ዘፀ.34፣23 "በአንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በእስራኤል አምላክ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት በዓመት ሦስት ጊዜ ይታይ" ሲል ምን ማለት ነው? ሦስት ጊዜስ መቼ መቼ ነው?

✔️መልስ፦ ወደምስክሩ ድንኳን ቢያንስ በዓመት ሦስት ጊዜ እንዲመጡ የሚያዝዝ ነው። እነዚህ ሦስቱ ቀናት ደግሞ የእስራኤላውያን በዓላት ሲሆኑ በዓለ ፋሲካ፣ በዓለ ሰዊትና በዓለ መጸለት ናቸው።

▶️፲፱. ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እንጀራም አልበላም ውሃም አልጠጣም ይላል። ይህ የሆነው የመጀመሪያወቹን ፅላቶች ከመቀበሉ በፊት ነው ወይንስ በኋላ?

✔️መልስ፦ በሁለቱም ጾሟል።

▶️፳. ዘፀ.32፣17 "ኢያሱም እልል ሲሉ የሕዝቡን ድምፅ ሰምቶ ሙሴን፦ "የሰልፍ ድምፅ በሰፈሩ ውስጥ አለ አለው" ይላል። ካህናትን ወደከለከለበት ቦታ ከሙሴ ጋር ኢያሱን ለምን ጠራው?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ለኢያሱ ስለፈቀደለት።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Oct, 09:37


#ስም #ቢቀርስ
በቤተክርስቲያን በአሁኑ ሰዓት ብዙ ሊቀ ሊቃውንት የሚባሉ፣ ብዙ መጋቤ ሐዲስ የሚባሉ፣ ብዙ መጋቤ ብሉይ የሚባሉ፣ ብዙ ሊቀ ጠበብት የሚባሉ፣ ብዙ ሊቀ መዘምራን የሚባሉ፣ ብዙ ሊቀ ምሁራን የሚባሉ፣ ብዙ መልአከ..... የሚባሉ አሉ።

እኔ የማስበው እስካሁን ስም የተሰጣቸው ሰዎች በተሰጣቸው ይቀጥሉ (ስማችሁ ተነሥቷል ሲባሉ ቅር እንዳይላቸው)። ከዚህ በኋላ ግን ለሌሎች ሰዎች ባይሰጥ ባይ ነኝ። በቃ መጠሪያ ስማችን ብቻ ይበቃል። ለቅዱሳን ሊቃውንት ያልተሰጠ ስም ተሸክመን ምን ይሠራልናል?!።

ሁለት ሰዎች ነበሩ። እና ለአንዱ "መልአከ ፀሐይ" የሚል ስያሜ ይሰጠዋል። በዚህ ጊዜ ሌላኛው ፀሐይን የሚጋርዳት ደመና ነው። ስለዚህ እኔን ደግሞ "መልአከ ደመና" በሉኝ አለ ይባላል።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Oct, 04:26


#ኦሪት #ዘፀአት #ክፍል 7
💚ምዕራፍ 31
-ባስልኤልና ኤልያብ ደብተራ ኦሪትንና ሌሎችንም ንዋያተ ቅድሳት እንዲሠሩ በእግዚአብሔር መመረጣቸው
-እስራኤላውያን ሰንበትን እንዲያከብሩ እግዚአብሔር መናገሩ
-እግዚአብሔር ሁለቱን የምስክር ጽላት ለሙሴ እንደሰጠው

💚ምዕራፍ 32
-ሙሴ በተራራው እንደቆየ ባዩ ጊዜ እስራኤላውያን አሮንን አማልክትን ሥራልን እንዳሉትና እንደሠራላቸው
-እግዚአብሔር ሙሴን ሕዝብህ በደሉኝ እንዳለው
-ሙሴ ለእስራኤላውያን እንዳይጠፉ እግዚአብሔርን እንደማለደና እግዚአብሔርም የሙሴን ምልጃ ተቀብሎ እስራኤልን ሳያጠፋቸው መቅረቱ
-ሙሴ እስራኤላውያን ያመለኩትን ጣዖት በእሳት እንዳቀለጠውና ፈጭቶ እንዳደቀቀው ከዚያም እስራኤላውያንን እንዳጠጣቸው
-ሙሴ እግዚአብሔር እስራኤልን ይቅር እንዲል መለመኑና ይቅር ካላላቸው ግን ከሕይወት መጽሐፍ እንዲደመስሰው መጠየቁ


💚ምዕራፍ 33
-ሙሴ እግዚአብሔርን ፊትህን አሳየኝ እንዳለውና እግዚአብሔር ግን ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም እንዳለው
-እግዚአብሔር ሙሴን ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም እንዳለው

💚ምዕራፍ 34
-እግዚአብሔር ሙሴን ሁለት የድንጋይ ጽላት እንደፊተኞቹ አድርጎ እንዲቀርጽ መንገሩና በጽላቶቹ ትእዛዛቱን እንደጻፈባቸው

💚ምዕራፍ 35
-እስራኤላውያን ለደብተራ ኦሪትና ለሌሎችም ንዋያት መሥሪያ በፈቃዳቸው ለእግዚአብሔር መስጠታቸው


💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. ደብተራ ኦሪትን ይሠራ ዘንድ ጥበብ ተሰጠው የተባለ ማን ነው?
ሀ. ባስልኤል
ለ. አሮን
ሐ. ኤልያብ
መ. ሀ እና ሐ
፪. ሙሴ በጽላቱ ላይ የጻፋቸው የቃል ኪዳን ቃሎች (ትእዛዛት) ስንት ናቸው?
ሀ.10
ለ. 6
ሐ.12
መ. 7
፫. ሙሴ እግዚአብሔርን "የእስራኤልን ኃጢአታቸውን ይቅር ትላቸው እንደሆነ ይቅር በላቸው፣ ያለዚያ ግን ከጻፍከው መጽሐፍ ደምስሰኝ" ብሎታል። ይህ ቃል የት ይገኛል?
ሀ. ዘፀ.34፣11
ለ. ዘፀ.32፣32
ሐ. ዘፀ.35፣9
መ. ዘፀ.33፣23

https://youtu.be/HQs4UUxMKi0?si=NAyi6iQRY0efRwPP

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

19 Oct, 04:21


🌹መጻሕፍተ 🌹ሰሎሞን 🌹ወሲራክ 🌹ክፍል 18
🌹መጽሐፈ 🌹መክብብ
🌹ምዕራፍ ፭
ወደቤተ እግዚአብሔር በሄድክ ጊዜ እግርህን ጠብቅ ማለት ወዲያ ወዲህ አትበል፡፡ አንድም እግረ ልቡናህን ወስነህ ጸልይ፡፡ የመምህራንን ትምህርት ለመስማት ወደጉባዔያቸው ቅረብ፡፡ ይኩን ነገርከ ኅዳጠ፡፡ ነገርህ ጥቂት ይሁን፡፡ ብዙ ነገር ከንቱ ነውና፡፡ ስለት ከተሳልክ በኋላ አታስቀር፡፡ እግዚአብሔርን በደዌህ ጊዜ ትፈራው እንደነበረ አሁንም እንደቀድሞው አንድ አድርገህ ፍራው፡፡ ሰው ከእናቱ ማኅፀን ዕራቁቱን እንደወጣ በሞት ራቁቱን ይሄዳል፡፡
🌹ምዕራፍ ፮
ሰው ሁሉ ወደመቃብር ይሄዳል፡፡
🌹ምዕራፍ ፯
ሽቱ ከመቀባት በጎ ስም ይሻላል፡፡ ጻድቃን ከተወለዱበት የሞቱበት ቀን ይሻላል፡፡ መወለዳቸው መከራ ለመቀበል ነው ሞታቸው ግን ለሕይወት ነውና፡፡ ሕያው የሆነ ሰው ሁሉ በጎ ነገርን ያስብ፡፡ ሞት መቃብር እያለ በዋዛ በፈዛዛ መኖር ከንቱ ነው፡፡ በቃልህ ለመቆጣት አትቸኩል፡፡ ቁጣ ባላዋቆች ልቡና ታርፋለችና፡፡ የእግዚአብሔር ሥራውን ተመልከት፡፡ ንስሓ ገብተህ በተድላ በደስታ ኑር፡፡ እግዚአብሔርን ፍራው አምልከው፡፡
🌹ምዕራፍ ፰
የሰው ጥበቡ ፊቱን ያበራዋል፡፡ እስመ ለኵሉ ግብር ቦ ጊዜ፡፡ ለሥራው ሁሉ ጊዜ አለው፡፡ ከፀሐይ በታች በልቶ ጠጥቶ ደስ ካለው በቀር ለሰው በጎ ነገር የለምና፡፡
🌹ምዕራፍ ፱
የጠቢባን የጻድቃን ሥራቸው በእደ እግዚአብሔር ተይዞ እንዳለ ልቡናዬ መረመረች፡፡ በሰው ሁሉ ከንቱ ሞት አለ፡፡ ከሞተ አንበሳ ሕያው የሆነ ውሻ ይሻላል፡፡ ከሞተ ኃጥእ ያለ ኃጥእ ይሻላል፡፡ ሕያዋን እንደሚሞቱ አውቀው ንስሓ ይገባሉና፡፡ የክፉዎች ፍቅራቸው ጥላቻቸው ቅንዐታቸው እነሆ በሞት ይጠፋል፡፡ በየጊዜው ልብስህ ንጹሕ ይሁን፡፡ ደስ ብሎህ ንስሓ ገብተህ የክርስቶስን ሥጋውን ደሙን ተቀበል፡፡ በየጊዜው ሕዋሳትህ ንጹሓን ይሁኑ፡፡ ሰው የሞት ጊዜውን አያውቅም፡፡ ትኄይስ ጥበብ እምኃይል፡፡ ትኄይስ ጥበብ እምንዋየ ሐቅል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Oct, 15:55


💙ክፍል 16 የጥያቄዎች መልስ💙

▶️፩. “አቆስጣ፣ በፍታም፣ ኩላቦቻቸው” ይላል (ዘፀ.26፥14-3)። የእነዚህ ቃላት ትርጉማቸው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ አቆስጣ የእንስሳ ስም ነው። በፍታ ኩታ (ጋቢ) ማለት ነው። ኩላብ ለማንጠልጠያነት የሚያገለግል ከእንጨት የሚዘጋጅ ነገር ነው።

▶️፪. “በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል” ይላል (ዘፀ.28፥30)። ኡሪምና ቱሚም ትርጉማቸው ምንድን ነው? "በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ" ሲባልስ? "አሮን የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል" ሲባል ትርጉሙ ምንድነው?

✔️መልስ፦ ኡሪምና ቱሪም የከበሩ የድንጋይ ዓይነቶች ናቸው። በአሮን ልብ ላይ ናቸው ማለቱ በደረቱ (በልቡ) በኩል ባለ ኪሱ ይይዛቸው ነበረ ለማለት ነው።

▶️፫. “ሰቅሉ ሀያ ኦቦሊ ነው” ይላል (ዘፀ.30፥14)
አቦሊ ምን አይነት መስፈሪያ ነው?

✔️መልስ፦ በእስራኤል የነበረ የገንዘብ ስም ነው።

▶️፬. ኦሪት ዘፀአት ምዕራፍ 26 ስለ ድንኳን አሠራር ያትታል። ታድያ በስደት ላይ እንዳሉ እንዲሠሩ ነው ወይስ ርስታቸውን ከወረሱ በኋላ እንዲሠሩ ነው የታዘዙት ማለት በስደት ከሆነ ሲያርፉ እየተከሉ ሲንቀሳቀሱ እየነቀሉ መሄድ አይከብድም?

✔️መልስ፦ በሁለቱም ነው። በስደት ላይ እያሉም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት፣ ከእግዚአብሔር ረድኤትን ለማግኘት ደብተራ ኦሪት ሄደው ይለምኑ (ይጸልዩ) ነበረ። ምድረ ርስት ከነዓን ከገቡ በኋላም የሰሎሞን ቤተ መቅደስ እስከሚሠራ ድረስ በደብተራ ኦሪት ያገለግሉ ይገለገሉ ነበረ። ለመትከል ለመንቀልም አይቸገሩም ነበረ። ምክንያቱም ለዚህ አገልግሎት ብቻ የተመደቡ ብዙ ሰዎች ነበሩ።

▶️፭. ዘፀ.29፡1 ነውር ያለባቸው እና የሌለባቸው ወይፈን እና አውራ በጎች መለያቸው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ነውር ያለባቸው የሚባሉት ጅራታቸው የተቆረጠ፣ ጸጉራቸው ያረረ፣ አንድ ዓይናና በጠቅላላው ከአካላቸው የጎደለ ነገር ያለባቸው እንስሳት ናቸው። ነውር የሌለባቸው የሚባሉት ከአካላቸው ምንም የጎደለ ነገር የሌለባቸው በሁሉ ነገር ንጹሓን የሆኑ ናቸው።

▶️፮. ዘፀ.28፡42 የተልባ (ተቆልቶ ተወቅጦ የሚጠጣውን ከሆነ) እግር እንዴት ልብስ ሊሆን እንደሚችል ቢያብራሩልን።

✔️መልስ፦ ከተልባ ከፍሬው ሳይሆን ከልጡ የሚሠራ ልብስ ነው። ከተልባ ልጥ የሚሠራ የልብስ ዓይነት ነው።

▶️፯. የሥጋ ሜንጦ ምንድነው? (ዘጸ 27፡3)

✔️መልስ፦ ሜንጦ የሚባለው ባለጣት የሥጋ መስቀያ እንጨት ነው።

▶️፰. ዘፀ 28፥14 ላይ ሁለት ቋዶችንም ከጥሩ ወርቅ እንደ ተጎነጎነ ገመድ አድርገህ ሥራ ይላል ቋዶች ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ እንደ ማተብ ያለ ነው።

▶️፱. ዘፀ.29፤40 ላይ ኢን እና ኢፍ የሚሉት ቃለት ምን ማለት ናቸው?

✔️መልስ፦ የመስፈሪያ ስሞች ናቸው። ኢፍ ቁና ነው። ኢን ትንሽ ገንቦ ነው።

▶️፲. እስራኤላውያን በጉዞ ላይ እያሉ ለምን ደብተራ ኦሪት መሥራት አስፈለገ። ነው ወይስ ደብተራ ኦሪቱ ተንቀሳቃሽ ነው?

✔️መልስ፦ በጉዞ እያሉ የእግዚአብሔርን ረድኤት ለማግኘት እንዲረዳቸው ደብተራ ኦሪትን ሠርተዋል። ደብተራ ኦሪቱም ተንቀሳቃሽ ነበረ።

▶️፲፩. አሮንም የእስራኤል ልጆች በሚያቀርቡትና በሚቀድሱት በቅዱስ ስጦታቸው ሁሉ ላይ ያለውን ኃጢአት ይሸከም ሲል ምን ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ መሥዋዕት ሠውቶ ኃጢአታቸውን ያስተሥርይ ማለት ነው።

▶️፲፪. የተካኑና የተቀደሱ ይሆኑ ዘንድ ማስተሥረያ የሆነውን ይብሉት ሌላ ሰው ግን አይብላው የተቀደሰ ነውና ይላል የተቀደሰን ነገር ሌላው መብላት የለበትምን?

✔️መልስ፦ ቀደሰ ለየ ማለት ነው። የተቀደሰ ማለት የተለየ ማለት ነው። ይህም ምግብ የአሮን ልጆችና በጠቅላላው ካህናት ብቻ እንዲበሉት የተለየ ምግብ ነው። እግዚአብሔር እነርሱ ብቻ ይበሉት ዘንድ ሥርዓት ሠርቶላቸዋል። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ቸል ብሎ ሌላው ቢበላው በእግዚአብሔር ዘንድ ያስቀጣዋልና ነው።

▶️፲፫. "የማስተሥርያውን ገንዘብ ከእስራአል ወስደህ ለመገናኛው ድንካን ማገልገያ ታደርገዋለህ። በእግዚአብሔር ፊት ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን ለእስራአል ልጆች መታሰቢያ ይሁን" ይላል (ዘፀ.30፥1)። በኦሪት ለነፍስ የሚሆን ማስተሥርያ እንደምን ያለ ነው? በእግዚአብሔር ፊት ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን ብሏልና ቢብራራ። ለምንድን ነው ለኃጢአት ማስተሥርያ ይህ የእንስሳትን ደም እና ሥጋችውን ማቃጠል ያስፈለገው?

✔️መልስ፦ ይህን ማድረግ ያስፈለገ እግዚአብሔር ስላዘዘ ነው። እግዚአብሔር ካዘዘ አዘዘ ነው። በወቅቱ በዘመኑ በዚህ መልኩ ኃጢአትን ይቅር እላለሁ ብሏል። እስራኤላውያንም እንዳዘዛቸው አድርገዋል። ጥቅሙ ከሥጋዊ መከራ ለመዳንና በነፍስ ደግሞ ምንም ሁሉም ሲዖል ቢገቡ በእደ እግዚአብሔር ለመያዝ ያበቃቸዋልና ነው።

▶️፲፬. ልብሰ ተክህኖ በብሉይ ኪዳን በተለየያ ሕብር ይሠራ ነበር በአዲስ ኪዳን እንዴት ነው ነጭ ብቻ ነው የተፈቀደው በመጽሐፈ ቅዳሴ እንዲህ የሚል አለና?

✔️መልስ፦ አወ በሐዲስ ኪዳን የክህነት ልብስ ነጭ እንዲሆን ተሠርቷል። ስለዚህ ነጭ መልበስ ይገባል። በብሉይ ኪዳን ለነበሩ ሰዎችም በታዘዙት መልኩ አድርገዋል። በሐዲስ ኪዳን ያለን ሰዎችም በታዘዝነው መልኩ በነጭ ማድረግ ይገባናል።

▶️፲፭. በብሉይ የነበሩ ንዋየ ቅድሳት በምንድን ነው ተባርከው ቅዱስ የሚሆኑት?

✔️መልስ፦ በልዩ ቅብዐት ተቀብተው ንዋየ ቅድሳት ይሆኑ ነበረ።

▶️፲፮. "ለአሮንም ክህነት የታረደውን በግ ፍርምባ ወስደህ ለሚወዘወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ትወዘውዘዋለህ፤ እርሱም የአንተ ወግ ይሆናል" ይላል (ዘፀ.29፥26)። "ፍርምባ "ምንድን ነው

✔️መልስ፦ ፍርምባ የሚባለው የበግ ወይም የበሬ ወይም የሌላ እንስሳ በፊት እግሮቹ መካከል ያለው የሥጋ ክፍል ነው።

▶️፲፯. ዘፀ.28፥35 "በማገልገል ጊዜም በአሮን ላይ ይሆናል፤ እርሱም እንዳይሞት ወደ መቅደሱ በእግዚአብሔር ፊት ሲገባና ሲወጣ ድምፁ ይሰማል" ይላል። የሻኩራዎቹ መንጠልጠል ድምፅ ማሰማት እንዴት ከሞት ይታደገዋል?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር የመዳኛ ምክንያት ካደረገው ማንኛውም ነገር ያድናል። በወቅቱ እግዚአብሔር የሻኵራዎች ድምፅ ከሞት መዳኛ አድርጎት ስለነበረ ከሞት ይታደግ ነበረ።

▶️፲፰. ድንኳኑ የመገናኛ ታቦቱ የምስክር ታቦት የተባለው ለምንድን ነው? (ዘፀ.27፥21)።

✔️መልስ፦ አምልኮተ እግዚአብሔር ስለሚመሰከርባት ነው።

▶️፲፱. አሮን ካህን የሆነው መቼ ነው? ከሌዊ ዘር ሲወለድ ነው ወይስ ሙሴ ቀብቶ ሲሾመው ነው?

✔️መልስ፦ ሙሴ ቀብቶ ሲሾመው ነው ካህን የሆነው። ከእርሱ በኋላ ነው ከሌዊ የተወለዱት ሁሉ ካህን እንዲሆኑ ሥርዓት የተሠራው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Oct, 08:34


ሲያዩህም እግረኛ ነገር ነህ😁
አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አምስት ኪሎ በERA (Ethiopian Road Authority) ስፖንሰር Geotechnical Engineering (MSC) እየተማርኩ ሳለሁ (አልጨረስኩትም Withdrawal ሞልቼ ነበረ ጉባኤ ቤት የገባሁ)። ከቅድስት ማርያም እስከ ጦር ኃይሎች በእግር የመሄድ ልምድ ነበረኝ😁። አልፎ አልፎ ሜክሲኮ ድረስ ተሳፍሬ ከዚያ በእግሬ እሄዳለሁ።

አንድ ቀን በእግሬ እየነካሁት ሳለ የታክሲው ረዳት ሜክሲኮ ሜክሲኮ ይላል። የት ነህ ብሎ መንገድ እየሄድኩ ጠየቀኝ። ሜክሲኮ ነኝ አልኩት። ታዲያ ና ግባ ታክሲው ሜክሲኮ ነው አለኝ። አልገባም በእግሬ ነው የምሄድ አልኩት።

ከዚያ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው😁?!

ሲያዩህም እግረኛ ነገር ነህ😁 ብሎኝ ሄደ። ብቻዬን እየሳቅሁ በእግሬ ነካሁት።

እኔና ታክሲ ብዙም አንዋደድም። አንድ ቀን ደግሞ ታክሲ ውስጥ ገብቼ ከኋላ ወንበር አካባቢ መስኮቱን ከፍቼ ቁጭ አልኩ። ከውጭ የሆነ ልጅ ቆሟል። ታክሲው መንቀሳቀስ ሲጀምር በመስኮቱ እጁን ሰዱ በቦክስ ፊቴን አስተካከለልኝ። (ይህ ሞኛሞኝ ፊት ሲያየው ቦክስ ባሳርፍበት ብሎ መሰለኝ😁)።

እና ምን ለማለት ነው። ታክሲ ተወደደ ብላችሁ ማማረር ብቻ ሳይሆን በእግር መሄድንም ልመዱ ለማለት ነው።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Oct, 04:34


#ኦሪት #ዘፀአት #ክፍል 6
✝️ምዕራፍ 26
-እግዚአብሔር ለሙሴ የደብተራ ኦሪትን አሠራር ማሳየቱ

✝️ምዕራፍ 27
-እግዚአብሔር ለሙሴ የመሠዊያውን አሠራር እንደነገረው
-የመብራት ዘይትን በደብተራ ኦሪት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ እንዲያበሩ መታዘዛቸው

✝️ምዕራፍ 28
-እግዚአብሔር ለሙሴ ስለልብሰ ተክህኖ አሠራር መንገሩ

✝️ምዕራፍ 29
-አሮንና ልጆቹ ክህነት እንደተሾሙ
-በደብተራ ኦሪት ስለሚቀርበው መሥዋዕት መነገሩ

✝️ምዕራፍ 30
-የመታጠቢያ ሰን እንዲሠራ እግዚአብሔር ለሙሴ መንገሩ

💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. በቀን በቀን በደብተራ ኦሪት መሠዊያ ላይ ስንት ጠቦቶች ይቀርቡ ነበረ?
ሀ. ሦስት
ለ. አራት
ሐ. ሁለት
መ. አምስት
፪.በደብተራ ኦሪት በታቦቱ ፊት መብራት እንዲበራ የታዘዘ መቼ ነው?
ሀ. ሁልጊዜም
ለ. ከጠዋት ጀምሮ እስከ ሠርክ
ሐ. ከማታ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት
መ. ከማታ ጀምሮ እስከ ማለዳ
፫.በደብተራ ኦሪት ስለነበረው መሠዊያ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ርዝመቱ አምስት ክንድ ነው
ለ. ወርዱ አምስት ክንድ ነው
ሐ. ከፍታው ሦስት ክንድ ነው
መ. ሁሉም

https://youtu.be/nFwg7QAfWT0?si=xS2sTFthGxvoX8VM

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

18 Oct, 04:27


🌻መጻሕፍተ 🌻ሰሎሞን 🌻ወሲራክ 🌻ክፍል 17
🌻መጽሐፈ 🌻መክብብ
🌻ምዕራፍ ፪
እኔ በልቡናዬ አስቤ ደስ ብሎህ ና ልምከርህ አልሁ፡፡ ንስሓ ገብተህ ጸጋ ክብርን ውረስ፡፡ ወይን ሰውን በፍቅር እንድትስብ ሰውነቴን ጥበብ ሳበችው፡፡ ቤት ሠራሁ፣ በወይኑ ቦታ ወይን ተከልሁ፣ የተክል ቦታ አበጀሁ፣ የሚያፈሩ እንጨቶችን ሁሉ በየወገናቸው ተከልሁ፣ የኩሬ ውሃዎችን አበጀሁ፣ ብዙ ወርቅን ብርን ሰበሰብሁ፣ ከሰዎች ጋር ተድላ ደስታን አደረግሁ እነሆ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡ የብልህ ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው፡፡ አላዋቂ ሰው ግን በድን*_ቁ*ር-*ና ጸንቶ ይኖራል፡፡ አዋቂውንም አላዋቂውንም አንድ ሞት እንደሚገናኛቸው አወቅሁ፡፡ እስመ ናሁ መዋዕል ይመጽእ፡፡ እነሆ መዋዕለ ሞት ይመጣል፡፡ ወኵሉ ይትረሣእ፡፡ ሁሉ በሞት ይዘነጋል፡፡ ሰው ያጠራቀመውን ከብቱን ላልደከመበት ሰው ይሰጣል፡፡
🌻ምዕራፍ ፫
ቦ ለኵሉ ዘመን፡፡ ለሁሉ ዘመን አለው፡፡ ከሰማይ በታች ላለ ሥራ ሁሉ ጊዜ አለው፡፡ ለመጽነስ ጊዜ አለው፣ ለሚወልዱበትም ጊዜ አለው፣ ለሕይወት ጊዜ አለው፣ ለሞትም ጊዜ አለው፣ ለዝምታ ጊዜ አለው፣ ለመናገርም ጊዜ አለው፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረቱ ሁሉ ሠናይ ያማረ ነው፡፡
🌻ምዕራፍ ፬
የአንዱን ሀብት አንዱ ላያገኘው ባልንጀራ በባልንጀራ መቅናቱ ከንቱ ነው፡፡ በሐሰት ከሚሆን ሁለት እፍኝ በእውነት አንድ እፍኝ በጎ ነው፡፡ አንዱ ቢወድቅ አንዱ ያነሣዋልና ከአንድ ሰው ሁለት ሰዎች ይሻላሉ፡፡ ከሦስት ሆኖ የተፈተለ ፈትል ፈጥኖ አይቆረጥም፡፡

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Oct, 16:17


በክርስትና ሕይወት ከሰው ጋር የሚደረግ የጎንዮሽ ግጥሚያ የለንም። ሰው ለሰው ጠላቱ አይደለም። ጥላቻን ወደሰው ልጅ የሚዘራው ሰይጣን ነው። በጉዞ ጊዜ ጓደኛችን ወደኋላ እንዳይቀርብን ድካሙን አስቦ መሸከም መልካም ነው። ሰው ሲደክመው ሊነጫነጭ ይችላል። ግን አሸናፊ ይሆን ዘንድ ንጭንጩን ታግሠን አዎንታዊ አስተዋጽኦ (Positive influence) ማድረግ ይገባናል። አይሁድ ጌታን ባለማወቅ ቢሰቅሉትም መከራውን ታግሦ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሎ ይቅርታን ሰበከላቸው።

ግላዊ ጊዜያዊ ጥቅም ከዘለዓለማዊው ሕይወት እንዳይከለክለን እንጠንቀቅ። እከብር ባይ ልቡናን እናስወግደው። የክርስቶስን መስቀሉን እንሸከም። መስቀሉን መሸከም ማለት ሰዎች የሚያደርሱብንን ክፋት በትዕግሥት ማሳለፍ ማለት ነው። ብንችል በቀና ልቡና ሰዎችን ካሉበት ክፋት ለማውጣት እንሞክር። ሁላችንም እርስ በእርስ አስፈላጊዎች ነን። ደግ ብንሆን የእግዚአብሔር መንግሥት ለሁላችንም ይበቃናል። ምቀኝነትን፣ ቅንዐትን፣ ዘረኝነትን አምርረን እንጥላቸው። ካሰብነው ደግ ዓለም የሚያስቀሩን ክፉ ሥራዎች ናቸውና። ወደ ደጉ ዓለም ለመድረስ እንድንበቃ እርስ በእርስ እንዋደድ። የዚህች ዓለም ክብሯም፣ ዝናዋም፣ ሥልጣኗም፣ ሹመቷም ሁሉም ኃላፊ ነው። የማታልፈዋን ደግ ዓለም ለመውረስ በኃላፊ ነገሮች አንጠላ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙዎች የፈለገውን ያህል ክፉ ቃል ቢናገሩኝ አልመልስም እየመለስኩም አይደለም። ምክንያቴ ደግሞ አጥፍቼ ከነበረ የደረሰብኝ ዘለፋና ክፉ ቃል የጥፋቴ ውጤት እንደሆነ አስባለሁ። ሳላጠፋ እንዲሁ ከሆነ ደግሞ ዝም በማለቴ በረከትን አገኝበታለሁ ብየ አስባለሁ። ቀድሞ እንኳ ልክ ልኩን ልንገረው ብየ አስብና እንዲሰማው የሚያደርግ ቃል እናገር ነበረ😁። ግን ሳስበው ይህ ምንም ጥቅም የለውም። ማንኛውንም ሰው የተናገረኝን ክፉ ቃል ወደመልካም እንዴት መለወጥ እንዳለብኝ ነው አሁን ላይ የሚያሳስበኝ። ትተናት ለምንሄዳት ዓለም ክፉ ቃል መነጋገሩ ጥቅም የለውም። ብንችል ያን ሰው ወደመልካም መንገድ መምራት ነው። ካልቻልን ደግሞ የማንኛውም ሰው ክፋቱ እኛንም እንዳይስበን ጉዟችን ላይ ትኩረት ማድረግ ነው።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Oct, 15:03


እንደ እድለኝነት ነው የማየው
አሁን በሕይወተ ሥጋ ያላችሁትን በሙሉ ፈጣሪ በአንድ ዘመን ስላኖረን እንደታላቅ እድል ነው የማየው። መቼም በአንድ ዘመን ያኖረን በአንድነት መሥራት የሚገባን ሥራ እንዳለ ሲጠቁመን ነው። እንዲያ ከሆነ ደግሞ የሁላችንም አንድ ተመሳሳይ ጠላት እንዳለን ይሰማኛል። ስለዚህ ተደጋግፈን ያንን ጠላት መግጠም ይገባናል። ስለዚህ ሁላችንም አንዳችን ለአንዳችን አስፈላጊ ነን ብየ አስባለሁ። እንዲያ ከሆነ ቅንዐት ምቀኝነት በእኛ ዘንድ የለም። ወደመንግሥተ ሰማያት ለምናደርገው ጉዞ አንዳችን ለአንዳችን አስፈላጊዎች ነን። ስለዚህ መበረታታት ይገባናል እንጂ መሰዳደብ መጠላላት አይገባንም ባይ ነኝ።

እኔ ያ የጋራ ጠላት ነው ብየ የማስበው ሰይጣን ነው። ሰይጣን በውሸት፣ በሐሜት፣ በሌብነት፣ በዘረኝነት፣ በራስ ወዳድነትና በመሳሰሉት ይፈትነናል። ስለዚህ ሰይጣንንና የሰይጣንን ገንዘቦች አምርረን መታገል ይኖርብናል። ሰይጣንን ለመዋጋት ይረዳን ዘንድ ሰባክያን ሲሰብኩ፣ መጽሐፍ ሲጽፉ ደስታዬ ወደር የለውም። አሸናፊ ሆነን ወደአንዲት ዘለዓለማዊት ሀገር ለመሄድ አስፈላጊ ነገር ሰጥተውናልና። እግዚአብሔርንና ወዳጆቹ ቅዱሳንን እንድንወድ ሰይጣንን እንድንጠላ ታላቅ አስተዋጽኦ አድርገውልናልና። ጥላቻን፣ ቂምን፣ ቅንዐትን፣ ምቀኝነትን ከእኛ እናርቅ። ይቅርታን፣ ፍቅርን፣ ትሕትናን፣ ትዕግሥትን ገንዘብ እናድርግ።

© በትረ ማርያም አበባው

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Oct, 14:32


✔️መልስ፦ መግደል ኃጢአት መሆኑን ኦሪት ዘፀአት ምዕራፍ 20 ላይ ተማምረናል። ነገር ግን አንዱ አንዱን ሰው በቀላል ግጭት ከድንገት ሳያስበው ቢሞትበት የገደለው ሰው ሸሽቶ "የመማጸኛ ከተማ" ወደተባሉት ቦታዎች ቢሸሽ ከዚያ ገብቶ ማንም እንዳይገድለው ነው ሥርዓት የተሠራው። ሕንፃ ሥላሴን መግደል ተገቢ አይደለም። ሞት የሚገባውን በፍርድ መግደል ግን ፍትሓዊ ስለሆነ ችግር የለውም ነበረ።

▶️፲፭. ዘፀ.21፣28 "በሬም ወንድን ወይም ሴትን እስኪሞቱ ድረስ ቢወጋ በሬው ይወገር" ይላል። ሕግ የሚወጣው ተጠብቆ ይድን ዘንድ አስተዋይ ልቡና ላለው ፍጥረት ይመስለኛል። ለበሬ እንዴት?
ስለ ተዋጊ በሬስ ይህን ያህል ተተንትኖ የተጻፈው ምን ያህል አንገብጋቢ ጉዳይ ቢሆን ነው?

✔️መልስ፦ በሬው እንዲገደል ሥርዓት የተሠራው ወደፊትም ሌላ ሰው ወግቶ እንዳይገድል ነው። ከእንስሳ ይልቅ ሰው የከበረ ስለሆነ ሌላ ሰውን ወግቶ እንዳይገድል ታስቦ ነው ይገደል ማለቱ። እግዚአብሔር ለሰው ይህን ያህል የሚያስብ ቸር አምላክ መሆኑን እንድንረዳ ነው።

▶️፲፮. ዘፀ.23፣11 "በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት፣ አሳርፋትም" የተባለው ከመዝራት ነው ፍሬዋን ከመልቀም? ምሳሌነቱስ?

✔️መልስ፦ ከመዝራትም ፍሬዋን ከመልቀምም ነው። ፍሬዋ ለመጻተኞች ለድኾች እንዲሆን ነው የታዘዘው።

▶️፲፯. የሰው በሬ የሌላውን ቢገድል ባለቤቱ በሞተው ፈንታ በሬ ይስጥ የሞተውን እርሱ ይውሰድ ይላል። የሞተ ይበላልን? ሌላ ቦታ አውሬ የገደለውን ለውሻ ጣሉት እንጂ አትብሉት ይላል። የማይበላው አውሬ ከገደለው ነውን?

✔️መልስ፦ የሞተውን በሬ እርሱ ይውሰደው ማለት ሥጋውን ይብላው ማለት አይደለም። የሞተ በሬ ለማንም እንደማይጠቅም ሁሉ ባለቤቱ ይክሰር ማለት ነው። መክሰር ብቻ ሳይሆን አስቀድሞ ተዋጊነቱን እያወቀ ባለመጠበቁ ሌላ ንጹሕ በሬ ለተጎጂው ይስጥ ማለት ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Oct, 14:32


💙ክፍል 15 የጥያቄዎች መልስ💙

▶️፩. “ዕብራዊ ባሪያ የገዛህ እንደሆነ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፥ በሰባተኛውም በከንቱ አርነት ይውጣ” ይላል (ዘፀ.21፥2)። "በከንቱ አርነት" አውጣው ሲባል ያገለገለበትን ሳይከፍለው ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ አይደለም በነፃ ይውጣ ለማለት ነው። በከንቱ ያገኛችሁትን በከንቱ ስጡ (በከንቱ ዘነሣእክሙ በከንቱ ሀቡ) ሲል በነፃ ያገኛችሁትን በነጻ ስጡ ማለት እንደሆነ ማለት ነው። በነጻ አሰናብተው ገንዘብም ሌላም ነገር አታስከፍለው ማለት ነው።

▶️፪. “ጌታው ሚስት አጋብቶት እንደ ሆነ ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆች ብትወልድለት፥ ሚስቱና ልጆቿ ለጌታው ይሁኑ፥ እርሱም ብቻውን ይውጣ” ይላል (ዘፀ.21፥4)። ይህ አልገባኝም ለምን እንዲህ ዓይነት ሥርዓት ሠራላቸው? ፍትሓዊ ነው ወይ?

✔️መልስ፦ ሚስቱና ልጆቹ ለጌታው ይሁኑ ያለው ጌታውን በማገልገል ይቆዩ ለማለት ነው እንጂ ጌታው ሚስቱ ያድርጋት ማለት አይደለም። ባሏ ነጻ ሲወጣ ባልነቱን ይተዋል ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ፍትሕ በእኛ ትንሽ ሕሊና የሚመረመር አይደለም። እርሱ ባወቀ ይህ መልካም ነው ብሎ ለጊዜው በጊዜው ሥርዓት አድርጎ ሠርቶታል።

▶️፫. ዘፀ.21:8-9 "ሰውም ሴት ልጁን ለባርነት ቢሸጥ ባሪያዎች እንደሚወጡ እርሷ አትውጣ። ጌታዋን ደስ ባታሰኘው በዎጆ ይስደዳት፤ ስለ ናቃት ለሌላ ወገን ሰዎች ይሸጣት ዘንድ አይገባውም" ይላል። ይህ ሕግስ እግዚአብሔር ሰው እንደ "እቃ እንዲሸጥ" ያዝዛልን?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ሁሉም ሰው በነጻነት እንዲኖር ፈጥሮታል። ነገር ግን የተለያዩ ችግሮች ሰውን ለባርነት ይዳርጉታል። ከሰው ልጆች ተለይቶ እንዲሸጥና እንዲገዛ የተደረገ ዘር የለም። ነገር ግን ለምሳሌ አንድ ሰው ንብረቱን በተለያየ መልኩ ሲያጣ ነፍሱን ለማትረፍ ለሌላው ሰው አገልጋይ (ባርያ) ሆኖ ምግቡን ያገኛል። በደንብ ከተደላደለ በኋላ ከባርነት ተላቆ ነጻ ይሆናል። ስለዚህ መሸጥ ያለው መግዛት ያለው ሰው ነፍሱን ለማትረፍ ወዶ ለሌሎች ሰዎች አገልጋይ መሆኑን ለመግለጽ ነው። በሰውየው ነጻነት የሚከናወን እንጂ እንደከብት እንደዕቃ ዓይነት የሚከናወን አይደለም።

▶️፬. በኦሪት ሕግ የኃጢአት ሥርየት እንዴት ያገኛሉ?

✔️መልስ፦ በኦሪት ሕግ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ በኃጢአቱ ተጸጽቶ መሥዋዕት ሠውቶ ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል። ነገር ግን ይህም የሚጠቅመው ከሥጋዊ መቅሠፍት ለመዳንና ከሞት በኋላም በእደ እግዚአብሔር ለመያዝ ነበረ እንጂ ፍጹም ነፍሳዊ ድኅነትን አያገኝም ነበረ።

▶️፭. ዘፀ.21፡8 "ለእርሱ ከታጨች በኋላ ጌታዋን ደስ ባታሰኘው በዎጆ ይስደዳት" ሲል ዎጆ ምንድነው?

✔️መልስ፦ ዋጆ ማለት ምትክ ክፍያ ቤዛ ማለት ነው። በዋጆ ይስደዳት ሲል በእርሷ ምትክ በገንዘብ ወይም በሌላ ዓይነት ክፍያ ተቀብሎ ይስደዳት ማለት ነው።

▶️፮. "ፀሐይ ግን ከወጣችበት የደም ዕዳ አለበት የገደለው ይገደል" ይላል (ዘፀ.22፡3)። ገድሎት ሳይናገር ፀሐይ ብትወጣበት ነው ወይስ ቀን ሲምስ (ሲሰርቅ) ቢገኝ ለማለት ነው?

✔️መልስ፦ አንድ ሰው አንድን ሰው ሌሊት ሊሰርቀው መጥቶ ሳለ ሌባውን ባለቤቱ ቢገድለው ኃጢአት አይሆንበትም ነበረ። ፀሐይ ከወጣ በኋላ ባለቤቱ በሌባው ሲሰርቅ ቢደርስበት ግን ሌባውን ሰዉ ሁሉ ስለሚያየው በምስክር ዳኛ እንዲፈርድበት አይግደለው ተብሏል።

▶️፯. ዘፀ.23፡19 "ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል" ማለት ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ ይህ ትእምርተ ርኅራኄ ነው። የእናቱን ጡት ሲጠባ ያደገውን ወይፈኑንና እናቱን በአንድ ቀን አትረዷቸው ማለት ነው። እናትና ልጅ የሆኑ እንስሳት በአንድ ቀን እንዳይታረዱ ለማለት ነው። የኀዘን የርኅራኄ ምልክት ነው።

▶️፰. ማስቸገር ካልሆነብኝ የብሉይ ኪዳኑ ታቦት፤ ኅብስተ ገጹ የሚቀመጥበት ገበታ፤ ባለ ስድስት ቅርንጫፍ መቅረዝ እና መኮስተሪያ የሚባሉትን በምስል ካለዎት ቢለቁልን በተለይ መቅረዙን በምስል ካልሆነ መረዳት አቅቶኛል።

✔️መልስ፦ ጥሩ ሠዓሊ አይደለሁም። ስለዚህ ሥዕል መሣል የምትችሉ ሰዎች ካላችሁ የመጽሐፍ ቅዱሱን ሐሳብ ይዛችሁ ብትስሉልን።

▶️፱. ዘፀ.23፤34 "በፍርድ ለድሃው አትራራ"ይላል። ቁ.6 ላይ ደግሞ በፍርድ የድሃውን ፍርድ አታጣምም ይላል ሐሳቡ ተለያየብኝ ቢብራራ?

✔️መልስ፦ ሁለቱም ትክክል ነው። በፍርድ ጊዜ በደል የሠራው ድኻው ሆኖ ከተገኘ እንዲፈረድበት በፍርድ ለድኻው አትራራ ተብሏል። በፍርድ ጊዜ ባዕለጸጋ በድሎ ድኻው እውነተኛ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ የድኻውን ፍርድ በጉቦ ወይም በሌላ ምክንያት አታጣምም ተብሏል። ሁለቱም ሐሳባቸው ትክክለኛ ፍርድ ይፈረድ ማለት ነው።

▶️፲. “ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በሥርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ” ይላል (ዘፀ.25፥18)። ቢብራራልን።

✔️መልስ፦ ኪሩቤል ረቂቃን መላእክት ናቸው። ነገር ግን ለሙሴ በተገለጹለት መንገድ እንዲሳሉ ተደረገ።

▶️፲፩. ዘፀ.25፥36 "ጕብጕቦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከእርሱ ጋር አንድ ይሁኑ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተቀረጸ ከጥሩ ወርቅ ይደረግ" ሲል ጕብጕቦቹ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ጉብ ጉብ ያለ ማለት ወጣ ወጣ ያለ ማለት ነው። ከግንዳቸው ወጣ ያሉ እንደማለት ነው። ከቅርንጫፎቹ ጫፍ ላይ ጉብ ያሉ ለማለት ነው።

▶️፲፪. ዘፀ.25:18 ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በሥርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ። ሙሴ በወቅቱ ሥዕል ነው ምስል ነው የሠራው? ሥዕል ከሆነ ሳለ እንጂ ሠራ ይባላልን? በብሉይ ኪዳን የነበረው ሥዕልና የሐዲስ ኪዳኑ ሥዕል ልዩነት ካለው ቢያብራሩልኝ?

✔️መልስ፦ ሙሴ የሠራው ምስል ነው። የሐዲስ ኪዳን ሥዕል ግን መሠረቱ ወንጌላዊው ዮሐንስ ለጢባርዮስ ቄሳር የሳለለት ሥዕል ነው። ከዚያም በፊት በስቅለት ጊዜ ለቬሮኒካ በደሙ የመልኩን ሥዕል ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሻሿ በደሙ የሣለው የራሱ መልክ ነው። ስለዚህ ይህኛው ከቅርጽ የተለየ በቀለም በደም ብቻ የሆነ ስለሆነ የሐዲስ ኪዳኑ ሥዕል ነው።

▶️፲፫. ዘፀ.21፣2 ጀምሮ ባርያን ስለመግዛትና ስድስት ዓመታትን አገልግሎ በሰባተኛው አርነት ይውጣ" የሚለው ከሰዎች እኩልነት/በእግዚአብሔር አምሳል ከመፈጠር/ ጋር እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ ሰው ሁሉ በተፈጥሮ እኩል ነው። ሁሉም በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯል። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች አንዱ ሰው ለአንዱ ሰው ይገዛል። ከእነዚህም ምክንያቶች መካከል በፍትሐ ነገሥት በፍትሕ ሥጋዊ ጦርነት አንዱ እንደሆነ ይገልጻል። በጦርነት ጊዜ ማራኪው ተማራኪውን አገልጋዩ እንዲሆን ያደርገዋል። ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ችግር ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው የሚበላው አጥቶ ቢቸገር ለሌላው ሰው አገልጋይ ሆኖ በሰባተኛው ዓመት ነጻ ይወጣል። አይ ጌታዬን በማገልገል እቀጥላለሁ ካለ አፍንጫውን ተፎንኖ ጌታውን እያገለገለ ይኖራል። ስለዚህ ባርነት በወቅቱ ከሞት መትረፊያ መንገድ ነበረ ማለት ነው።

▶️፲፬. ዘፀ.21፣13 "ነገር ግን እግዚአብሔር ድንገት በእጁ ቢጥለው ገዳዩ የሚሸሽበትን ስፍራ እኔ አደርጋለሁ" የሚለው ሕንፃ ሥላሴን ከማፍረስ አንጻር እንዴት ይታያል? ለዚህ ዘመንስ ያለው አንድምታ?

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Oct, 04:51


#ኦሪት #ዘፀአት #ክፍል 5
ምዕራፍ 21
-ስለባርነት ሥርዓት መገለጹ
-ሰውን የገደለ ሰው በብሉይ ሕግ ይገደል እንደነበረ
-እናቱንና አባቱን የሚሳደብ በብሉይ ሕግ በሞት ይቀጣ እንደነበረ
-በተለያየ ዐመፅ ያሉ ሰዎች ስለሚቀጡበት ቅጣት መነገሩ

ምዕራፍ 22
-አንድ ሰው በሬ በግ ቢሰርቅ በአንድ በሬ ፋንታ አምስት በሬዎችን፣ በአንድ በግም ፋንታ አራት በጎች እንዲከፍል መደረጉ
-ስለሌባ ቅጣት መነገሩ
-የሰውን አዝመራ ያስበሉ ሰዎች ቅጣት መነገሩ
-ያልታጨችን ድንግል አታሎ ከእርሷ ጋር የተኛ ሰው ሚስት አድርጎ እንዲይዛት
-ከመተተኛ ጋር አንድ መሆን እንደማይገባ
-ከእንስሳት ጋር ግንኙነት የፈጸመ ቅጣቱ ሞት እንደነበረ

ምዕራፍ 23
-ሐሰተኛ ወሬን መቀበል እንደማይገባ
-ፍርድን ለማጣመም ከብዙ ሰው ጋር መጨመር እንደማይገባ
-የጠላትህን ገንዘብ ጠፍቶ ብታገኘው መመለስ እንደሚገባ
-በፍርድ ጊዜ ማዳላት እንደማይገባ
-ጉቦ የዓይናማዎችን ዓይን እንደሚያሣውር
-በስደተኞች ላይ ግፍን ማድረግ እንደማይገባ
-ስድስት ዓመት ምድርን ዘርቶ በሰባተኛው ዓመት ምድርን ከማረስ መከልከል እንደሚገባ በብሉይ ኪዳን መነገሩ
-በዓመት ሦስት ጊዜ ለእግዚአብሔር በዓል ማድረግ እንደሚገባ
-በእግዚአብሔር ፊት ባዶ እጅን መታየት እንደማይገባ
-በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዱ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዲታይ መታዘዙ
-የምድርን ፍሬ በኵራት ለእግዚአብሔር መስጠት እንደሚገባ
-እግዚአብሔርን ቢያመልኩት እንደሚባርክ

ምዕራፍ 24
-እስራኤላውያን እግዚአብሔር ያለንን እናደርጋለን ማለታቸው
-እግዚአብሔር ለሙሴ ጽላትን እንደሚሰጠው መንገሩ

ምዕራፍ 25
-እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር መባ እንዲያቀርቡ መታዘዛቸው
-ጽላቱ የሚቀመጥበትን ታቦት ሙሴ እንዲሠራ መታዘዙ
-ሙሴ መቅረዝን እንዲሠራ መታዘዙ

💙የዕለቱ ጥያቄዎች💙
፩. በብሉይ ኪዳን ሕግ በግ የሰረቀ ሰው በአንድ በግ ፋንታ ቅጣቱ ምን ነበረ?
ሀ. አራት በግ
ለ. አምስት በግ
ሐ. ሁለት በግ
መ. ዘጠኝ በግ
፪. በብሉይ ኪዳን ሕግ አባቱንና እናቱን የሰደበ ቅጣቱ ምን ነበረ?
ሀ. መታሰር
ለ. መገደል
ሐ. መገረፍ
መ. መደብደብ
፫. ሙሴ የመጀመሪያውን የቃል ኪዳን ታቦት ለመቀበል በተራራ ላይ ለምን ያህል ቀን ቆየ?
ሀ. አርባ
ለ. ሰማንያ
ሐ. ሠላሳ
መ. ሰባት

https://youtu.be/QbK8DstElDM?si=3rVbnnl62lnHGos6

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

17 Oct, 04:43


💐መጻሕፍተ 💐ሰሎሞን 💐ወሲራክ 💐ክፍል 16
💐መጽሐፈ 💐መክብብ
💐ምዕራፍ ፩
መክብብ ሰሎሞን ከንቱ ነው ከንቱ ነው ሁሉ ከንቱ ነው አለ፡፡ ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካሙ ሁሉ ለሰው ትርፉ ምንድን ነው? እኖራለሁ እንዳይል እኩሉ ይሞታል እኩሉ ይወለዳል፡፡ ትውልድ የኀልፍ ወትውልድ ይመጽእ፡፡ ዓይን በማየት አይጠግብም፡፡ ጆሮም በመስማት አይጠግብም፡፡ ከፀሐይ በታች አንድም ከሰማይ በታች የተፈጠረውን ፍጥረት ሁሉ አየሁ እነሆ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡ በጥበብ ብዛት ብዙ ኀዘን አለ፡፡ ዕውቀትንም ያበዛ ሰው ብዙ መከራን አብዝቷል፡፡ የአዋቂ በዳይ ተብሎ ይፈረድበታልና፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

16 Oct, 14:53


ይህ በመምህር ሐዲስ ዓለሙ የተዘጋጀው በቅዳሴ ዙሪያ የተጻፈ ድንቅ መጽሐፍ ነው። መ/ር ሐዲስ ከክቡር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ የመጻሕፍት ትርጓሜን የተማሩ መምህር ናቸው።

መጽሐፋቸውን በመግዛት ደግመው ደጋግመው ይጽፈልን ዘንድ እናበረታታቸው።

ስ.ቁ= 0923703505 (መ/ር ሐዲስ)

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

16 Oct, 13:23


💙ክፍል 14 የጥያቄዎች መልስ💙

▶️፩. “እንዲህም ሆነ፤ በመሸ ጊዜ ድርጭቶች መጡ፥ ሰፈሩንም ከደኑት፤ ማለዳም በሰፈሩ ዙሪያ ጠል ወድቆ ነበር” ይላል (ዘፀ.16፥13)። "ድርጭቶች" ምንድን ናቸው?

✔️መልስ፦ የወፍ ዓይነቶች ናቸው።

▶️፪. “ኀፍረተ ሥጋህ በእርሱ እንዳይገለጥ ወደ መሠዊያዬ በደረጃ አትውጣ” ይላል (ዘፀ.20፥26)። የዚህ ንባብ ትርጓሜው ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ በቤተ እግዚአብሔር መራቆት (ራቁትን መሆን) እንደማይገባ የሚያስረዳ ነው።

▶️፫. መንሱት ደግሞም ጋእዝ ማለት ትርጉሙ ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ሁለቱም የግእዝ ቃላት ናቸው መንሱት ጥፋት ፈተና ማለት ነው። ጋእዝ ክርክር ጠብ ማለት ነው።

▶️፬. እስራኤላውያን በአርባ አመት ወይስ በሦስት ወር ነው ወደ ሀገራቸው የደረሱ ቢብራራልኝ?

✔️መልስ፦ በአርባ ዓመት።

▶️፭. ዮቶር የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ ሲል ምን ማለት ነው?

✔️መልስ፦ በኋላ እግዚአብሔር ለእስራኤል ያደረገውን ከሙሴ ሰምቶ አምኗል። አምኖም መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር አቅርቧል።

▶️፮. ዘፀ.16፡14 "እንደ ውርጭ ነጭ ሆኖ ድንብላል የሚመስል ደቃቅ ነገር በምድረ በዳ ታየ። ውርጭ ነጭ ነው እንዴ? ያ የወረደው መና የሚታይ ነው እኔ እስከማውቀው ድረስ ውርጭ የሚታይ አይመስለኝም ታድያ እንዴት እንደ ውርጭ ብሎ በምሳሌነት ለማስረዳት ሞከረ?

✔️መልስ፦ ሙሴ በታየው መልኩ ጽፏል። ሙሴ ውርጭን ነጭ መስሎ አይቶታል። ውርጭ ረቂቅም ቢሆን አካል አለው። ያ አካሉ ለሙሴ ተገልጾለት ጽፏል። ቃሉ ግን ምሳሌ ነው። ምሳሌ ደግሞ ሁልጊዜም ሕፀፅ አለበት። እግዚአብሔርን በፀሐይ ስንመስለው ፀሐይ ግዙፍ ነው እግዚአብሔር ረቂቅ ነው። በጥቂት ነገር ለማስረዳት ብቻ እንመስላለን እንጂ።

▶️፯. አንዳንድ ትልልቅ ሰዎች (በዕድሜ) ዛሬም ድረስ የዓርብ ውሃ የሚሉት ነገር አለ። ታዲያ ሙሴ ያዘዘውን ያን ለሰንበት ቀን አስቀድመው ሁለት እጥፍ እንዲሰበስቡ ያለውን ትእዛዝ መሠረት አድርገው ይመስለኛል። ግን በሐዲስ ኪዳን ተቀባይነት አለው?

✔️መልስ፦ ሰንበትን ማክበር በሐዲስ ኪዳንም የቀጠለ በዓል ነው። ስለዚህ በሰንበት ሥጋዊ ሥራ ውሃ መቅዳት እንጨት መፍለጥ ስለማይቻል ለቅዳሜና ለእሑድ የሚበቃን ውሃ ዓርብ ላይ መሰብሰብ ምንም ችግር የለውም።

▶️፰. "አሁንም በፍጹም ብትታዘዙኝና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ እነሆ ከአሕዛብ ሁሉ እናንተ የተወደደ ርስቴ ትሆናላችሁ፤ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆንም" ይላል (ዘፀ.19፥5)። ማዳላት አይሆንበትም ወይ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በትክክል የሚፈርድ ፈታሒ አምላክ ነው። ስለዚህ ባለችን ጥቂት ኅሊና ተመራምረን ያዳላል ማለት አይቻልም። እርሱ ባወቀ ለሁሉ እንደየሚገባው ሰጥቶታል ይሰጠዋል።

▶️፱. ሙሴም አሮንን። አንድ ማድጋ ወስደህ ጎሞር ሙሉ መና አግባበት፥ ለልጅ ልጃችሁም ይጠበቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው አለው" ይላል (ዘፀ.16፥33)። መናው እስከ ማን ተላለፈ ?

✔️መልስ፦ መናው እስከ ክርስቶስ ልደት ቆይቷል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሲወለድ እንደ ሰም ቀልጦ ጠፍቷል። አማናዊው መና ክርስቶስ ተወልዷልና።

▶️፲. "እግዚአብሔርም። ሂድ፥ ውረድ፤ አንተ አሮንም ከአንተ ጋር ትወጣላችሁ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ወደ እግዚአብሔር ይወጡ ዘንድ አይተላለፉ አለው" ይላል (ዘፀ.19:24)። ካህናቱ የተባሉ እነማን ናቸው የአሮን ልጆች ናቸው? ለምንስ እንዳይወጡ ታዘዙ?

✔️መልስ፦ ካህናቱ የተባሉት የአሮን ልጆች ናቸው። እንዳይወጡ የታዘዙበት ምክንያት እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ተብሎ ከዚሁ ተገልጿል።

▶️፲፩. ጎሞር ምንድን ነው?

✔️መልስ፦ ጎሞር ማለት ቁና ማለት ነው

▶️፲፪. ዘፀ.20 ላይ ከተዘረዘሩት 10ሩ ትእዛዛት ውስጥ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚለው ይካተታል ወይ?

✔️መልስ፦ አዎ ይካተታል። የሚገኘው ግን ኦሪት ዘሌዋውያን ምዕራፍ 19 ላይ ነው።

▶️፲፫. “ከሰማይ እንጀራ አዘንብላችኋለሁ። ሕዝቡም በየቀኑ እየወጡ ለዕለት የሚበቃቸውን ይሰብስቡ፤ በዚህም ትእዛዞቼን ይጠብቁ እንደ ሆነ እፈትናቸዋለሁ” ይላል (ዘፀ.16፥4)። ሳይፈትናቸው ማወቅ እየቻለ መፈተን ለምን አስፈለገ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል። ያለፈተና ከፍ ወዳለ መዓርግ ማደግ አይቻልም። ስለዚህ እስራኤልን በመከራ ፈትኖ በረከቱን ያበዛላቸው ዘንድ ፈትኗቸዋል።

▶️፲፬. ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት ሙሴም ለምን ትጣሉኛላችሁ እግዚአብሔርንስ ስለምን ትፈታተናላችሁ ይላል። የተጣሉት ከሙሴ ጋር ነው እግዚአብሔርን ለምን ትፈታተናላችሁ ሲል ግልፅ ቢደረግልኝ?

✔️መልስ፦ ሙሴ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው። የሚናገረውም እግዚአብሔር የነገረውን መልእክት ነው። ስለዚህ ተላኪውን መናቅ ላኪውን መናቅ ስለሆነ እንዲህ ብሏል። መልእክተኛው ሙሴን መፈታተን ላኪውን እግዚአብሔርን መፈታተን ነውና።

▶️፲፭. ሙሴም መጣ የሕዝቡን ሽማግሌወች ጠርቶ እግዚአብሔር ያዘዘውን ተናገረ ሕዝቡም በአንድ ቃል እግዚአብሔር ያለውን እናደርጋለን አሉ። ሙሴም የሕዝቡን ቃል ወደ እግዚአብሔር አደረሰ ይላል። እግዚአብሔር ሕዝቡ ነገራቸውን ለሙሴ ከመመለሳቸው ከመናገራቸው በፊት በልባቸው ያለውን ያውቃል ግን ከአንድ መስሪያ ቤት ወደ ሌላ መስሪያ ቤት መልዕክትን እንደሚቀበል ከሙሴ ተቀበለ ለዚህ ነገር ገለጻ ቢሰጠኝ?

✔️መልስ፦ እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው ከመፍጠሩ በፊት ያውቀዋል። ነገር ግን ለቅዱሳን ቢለሟልነትን ስለሰጣቸው እርሱ ቢያውቅም እነርሱ እንዲነግሩት ያደርጋል። ይህም በእርሱ ዘንድ ያላቸውን ክብር እኛ እንድንረዳ ነው።

▶️፲፮. ለሚጠሉኝ እስከ ሦስት እና እስከ አራት ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢኣት በልጆች ላይ የማመጣ ሲል ልጅ በአባቱ በደል ይጠየቃልን? በዘመነ ሐዲስ የዚህ ሰው በደል ከራሱ ወይንስ ከወላጆቹ ካለው ጋርስ እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ ልጅ በአባቱ በደል እንደማይጠየቅ ነቢዩ ሕዝቅኤል በትንቢቱ ገልጾታል። ነገር ግን አባቶቻቸውን መስለው የሚበድሉትን እንደ አባቶቻቸው እንደሚቀጣ ለመግለጽ እንዲህ አለ። ከዚህ የተገለጸው ይህ ነው። አባቶቻቸውን መስለው ስለሚበድሉ ሰዎች የተነገረ ነው።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

16 Oct, 05:23


ስለእርሳቸው ሲወራ ነው እንጂ በአካል እንኳ አላውቃቸውም። ነገር ግን ለምሳሌ ወደሌላ ሩቅ ሀገር ቢሄዱና ከድንገት የሄዱበት ሀገር አካባቢ የቤተክርስቲያን ቅጽር ካቡ ተንዶ ቢያገኙት ሳያስተካክሉት አያልፉም ነበረ ሲባል ሰምቻለሁ።

እኛኮ ቤተክርስቲያንንም በሰፈር ለማበላለጥ የምንጥር ድኩማን ሰዎች ነን። ቤተክርስቲያን አንዲት መሆኗን ተረድተው የትም አካባቢ ላለች ቤተክርስቲያን እኩል ፍቅር የነበራቸው አባ መፍቀሬ ዛሬ እንዳረፉ ሰማሁ።

እግዚአብሔር በአፀደ ገነት ያኑርልን።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

16 Oct, 03:38


#ኦሪት #ዘፀአት #ክፍል 4
💙ምዕራፍ 16
-እስራኤላውያን በምግብ ምክንያት በሙሴና በአሮን ላይ ማንጎራጎራቸው
-እግዚአብሔር ካዘዛቸው ውጭ ምግብ ያሳደሩ ሰዎች ምግቡ እንደተበላሸባቸው
-እስራኤል ከሰማይ የወረደላቸውን መና አርብ አርብ የቅዳሜውን ጨምረው እንዲሰበስቡና ቅዳሜ ግን ምንም እንዳይሰበስቡ መነገሩ
-በሰንበት ቅዳሜ መና ሊሰበስቡ የወጡ ሰዎች መና እንዳላገኙ
-መና መልኩ እንደ ድንብላል ነጭ ሲሆን ጣዕሙ ደግሞ እንደማር እንጀራ እንደሆነ
-ሙሴ የወርቅ መሶብ ወስዶ አንድ ጎሞር ሙሉ መና ለልጅ ልጆች ይጠበቅ ዘንድ ማስቀመጡ
-እስራኤላውያን ከነዓን እስኪገቡ ድረስ ለአርባ ዓመት መና እንደበሉ

💙ምዕራፍ 17
-ሙሴ ከዓለት ላይ በተአምራት ውሃ አፍልቆ ሕዝቡን እንዳጠጣ
-ኢያሱ ከአማሌቃውያን ጋር እንደተዋጋ
-ከአማሌቃውያን ጋር በነበረው ጦርነት ሙሴ እጁን ሲያነሣ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ እንደነበረ፣ እጁን ሲያወርድ ግን አማሌቃውያን ድል ያደርጉ እንደነበረ
-እስራኤላውያን እንዲያሸንፉ የሙሴ እጅ ሲከብድባቸው ድንጋይ ወስደው በበታቹ አኑረው ግራና ቀኝ ሆነው አሮንና ሖር ይደግፉት እንደነበረ

💙ምዕራፍ 18
-አማቱ ዮቶር የሙሴን ሚስትና ልጆቹን ይዞ ወደሙሴ መሄዱ
-ዮቶር እግዚአብሔር ለእስራኤል ያደረገውን ተአምር ሰምቶ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን መሠዋቱ
-ሙሴ በሕዝቡ ላይ ይፈርድ እንደነበረ
-ዮቶር ሙሴን አማካሪዎችን እንዲሾምና በፍርድ እንዲያግዙት መምከሩ፣ ሙሴም የዮቶርን ምክር ሰምቶ ተግባራዊ ማድረጉ

💙ምዕራፍ 19
-እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ሕዝቦች እንደሚሆኑ መነገሩ
-እስራኤላውያን ሁሉም ራሳቸውን አንጽተው ልብሳቸውን አጥበው በሦስተኛው ቀን እግዚአብሔር በሲና ተራራ እንደተገለጠላቸው
-እስራኤላውያንን ወደሲና ተራራ ከመቅረባቸው በፊት ሦስት ቀን ከሴቶቻቸው ጋር እንዳይገናኙ እግዚአብሔር ማዘዙ፣ እንዳይቀሠፉ ተራራውን ማንም እንዳይነካው ማዘዙ
-በሲና ተራራ ነጎድጓድና መብረቅ ከባድም ደመና፣ የበረታ የቀንደ መለከት ድምፅም እንደተሰማ በዚህም ምክንያት ሕዝቡ እንደደነገጠ
-ሙሴ ወደተራራው ራስ እንደሄደና ከእግዚአብሔር ጋር እንደተነጋገረ

💙ምዕራፍ 20
-ከእግዚአብሔር ውጭ አምላክ እንደሌለ
-የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት እንደማይገባ
-ሰንበትን ማክበር እንደሚገባ
-ዕድሜያችን ይረዝም ዘንድ አባትና እናትን ማክበር እንደሚገባ
-መግደል፣ መስረቅ፣ ማመንዘር፣ በባልንጀራ ላይ በሐሰት መመስከርና የባልንጀራን ገንዘብ መመኘት እንደማይገባ
-ሕዝቡ ፈርተው ሙሴን አንተ ከእኛ ጋር ተናገር። ነገር ግን እንዳንሞት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አይናገር እንዳሉ
-መሥዋዕትን ሲሠው እግዚአብሔር እንደሚባርክ

💚የዕለቱ ጥያቄዎች💚
፩. እስራኤላውያን የሁለት ቀን የሚሆን መና እንዲሰበስቡበት የታዘዘ ዕለት ማን ነው?
ሀ. ማክሰኞ
ለ. ቅዳሜ
ሐ. ዓርብ
መ. እሑድ
፪. እግዚአብሔር በምድረ በዳ ለአባቶቻቸው ያደረገውን ቸርነት ልጆች እንዲረዱ በመሶበ ወርቅ ሙሴ ያስቀመጠው መና ምን ያህል ነው?
ሀ. ሦስት ጎሞር
ለ. አንድ ጎሞር
ሐ. አራት ጎሞር
መ. ሰባት ጎሞር
፫. እስራኤላውያን እንዲያሸንፉ የሙሴን እጆች በግራና በቀኝ ይደግፉ የነበሩ ማንና ማን ናቸው
ሀ. ኢያሱና አሮን
ለ. አሮንና ሖር
ሐ. ሖርና ኢያሱ
መ. ዮቶርና ኢያሱ

https://youtu.be/N8Fpk1f1eLk?si=r03gGDH6eHfrzKBK

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

16 Oct, 03:37


🌻መጻሕፍተ 🌻ሰሎሞን 🌻ወሲራክ 🌻ክፍል 15
🌻ምዕራፍ ፰
ሰውን የምትወድ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ጥበብ የአንተ ገንዘብ ናት፡፡ ጌታ ሆይ ያለአንተ ለሁሉ የሚያስብ ሌላ ፈጣሪ የለም፡፡ ፍርድህን የሚቃወመው ማንም የለም፡፡ ፈታሒ በጽድቅ ነህና፡፡ ሁሉን መፍጠርህ ይቅር ትል ዘንድ ይቅር እንድትል ያደርግሀል፡፡ ከመከራ በንስሓ ይድን ዘንድ ለሰው ልጅ ዘመንን ፍኖተ ንስሓን ሰጠኸው፡፡
🌻ምዕራፍ ፱
አብ ሆይ የአንተ ሥልጣን ሁሉን ትሠራለች፡፡ እስራኤልን ባሕርን በእግር ተሻግረው እንዲድኑ፣ ኖኅን ባሕርን በመርከብ ተሻግሮ እንዲድን አደረግህ፡፡ ኖኅን በሐመር እስራኤልን በእግር አዳንክ፡፡ የዝሙት መጀመሪያው ጣዖት ልሥራ ብሎ ማሰብ ነው፡፡ እግዚአብሔር ታጋሽ፣ የዋህ (ኀዳጌ በቀል)፣ ፈጣሪ ነው፡፡
🌻ምዕራፍ ፲
ለክፋት የሚደክም ሰው ከጭቃ ከንቱ ጣዖትን ይሠራል፡፡ የእንደዚህ ያለው ሰው ልቡናው አመድ ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘመንን መስጠቱ ንስሓ ሊገቡበት ትሩፋት ሊሠሩበት ነው፡፡
🌻ምዕራፍ ፲፪
ጌታ ሆይ በወገኖችህ በጻድቃን ደገኛ ብርሃን ነበረ፡፡ ለወገኖችህ ለምእመናን ድኅነትን አደረግህ፡፡ ምእመናንን ለሚጣሉ ለአጋንንት ጥፋትን አድርገህ ወገኖችህ ምእመናንን በልጅነት ተቀበልካቸው፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

15 Oct, 15:03


✔️መልስ፦ ቀይ ባሕር አሁን ያለው ቀይ ባሕር ነው። በአሁኑ ሰዓት ከማን ሀገር ምን ያህል ወሰን እንደሚጋራ የዓለምን ካርታ (World Map) አይቶ ምን ያህል ርቀት (Distance) እንዳለው ማረጋገጥ ይቻላል።

▶️፳፰. የሙሴ እህት ማርያም ከበሮ አንሥታ ዘምራለች። በአሁኑ ዘመን እኅቶች በዓውደ ምሕረት ወጥተው ከበሮ መምታት ይፈቀዳል ወይ? አንድ አንዴ ማርያም እኅተ ሙሴ ከብሮ ይዛ አመስግናለች እና አይከለከሉም የሚባል ነገር አለ ከፍትሐ መንፈሳዊ አንጻር እንዴት ይታያል?

✔️መልስ፦ ማንኛዋም ሴት እግዚአብሔርን ማመስገን ትችላለች። ከምስጋና የሚከለክል መጽሐፍ የለም። ነገር ግን የምስጋናው ሥርዓት ሴት በሴቶች መካከል እንድትዘምር ነው እንጂ ወንዶች ባሉበት ጉባኤ እንድትዘምር አይደለም። ለዚሁም ማስረጃ ማርያም እኅተ ሙሴ ስታመሰግንም ሴቶች ተከተሏት ተብሎ በሴቶች መካከል እንደዘመረች መገለጹ ነው። ቅዱስ ጳውሎስም ሴት በቤተክርስቲያን ዝም እንድትል ማስተማሩ ነው።

▶️፳፱. ''እንግዳ ሰውም በመካከላችሁ ቢቀመጥ ለእግዚአብሔርም ፋሲካን ሊያደርግ ቢወድ፟ አስቀድሞ ወንድ ሁሉ ይገረዝ ከዚያም ወዲያ ይቅረብ ያድርግም እንደ አገር ልጅም ይሆናል ያልተገረዘ ሁሉ ግን ከእርሱ አይብላ'' ይላል። ሴቶች አይገዘሩም ነበር? ካልተገረዙ የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለመሆናቸው በምን ይለዩ ነበር?

✔️መልስ፦ ስለሴቶች ግርዛት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አላገኘሁም። በዚህ ዙሪያ ሁለት እይታዎች አሉ። አንደኛው ትእዛዙ ለወንድ ተደርጎ ይገለጽ እንጂ ሴቶችንም ይመለከታል የሚል ሲሆን ሌላኛው ግን የተገለጸው ተለይቶ ወንዶች ይገረዙ ስለተባለ ሴቶቹን አይመለከትም ማለቱ ነው የሚል ነው። የሴቶች ማመን በምን ይገለጽ ነበረ ከተባለ የተጻፈ ነገር አላገኘሁም አላውቀውም። ነገር ግን እነርሱም አማኞች እንደነበሩ መጻሕፍት ላይ በብዛት ተገልጿል።

▶️፴. የአህያውን በኵር በጠቦት ትዋጀዋለህ። የሰውንም በኵር ሁሉ ከልጆችህ መካከል ትዋጀዋለህ። ይህ ምን ለማለት ነው።

✔️መልስ፦ አህያ ለቤተ እግዚአብሔር አይሰጥም። ስለዚህ የአህያ በኵር ካለ በበግ ተክቶ መስጠት ይገባል ማለት ነው። የሰውንም በኵር በገንዘብ ትቀይረዋለህ ማለት ነው።

▶️፴፩. ወገብ መታጠቃቸው፤ መጫማታቸው፤ በትር ይዘው ደግሞ እየቸኮሉ መብላታቸው ለምን ይሆን?

✔️መልስ፦ ለጊዜው ተቻኵለው እንዲወጡ ነው። ፍጻሜው ምሳሌ ሲሆን ፍቅርን ሃይማኖትን ይዛችሁ፣ ምግባር ትሩፋት ሠርታቸው፣ ንጽሕናን ገንዘብ አድርጋችሁ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ ማለት ነው።

▶️፴፪. ዘፀ.13፥6 "ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላለህ፥ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር በዓል ይሆናል። ሰባተኛው ቀን የትኛው ነው? ቀዳሚት ሰንበትን ነው ሌላ?

✔️መልስ፦ ሰባተኛ ቀን የተባለው ቂጣ መብላት ከጀመሩበት ከሚያዝያ 14 እስከ ሚያዝያ 21 ያለው ጊዜ ሲሆን ሰባተኛው ቀን ማለት የመጨረሻው ቀን ማለት ነው እንጂ ቅዳሜን ለማለት አይደለም።


© በትረ ማርያም አበባው


🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።