ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ @yaregalabegaz Channel on Telegram

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

@yaregalabegaz


This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz

https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ

“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ (Amharic)

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ በመሆኑ፣ የአብያተ ክርስቲያናት የተማረ ሁሉን አሳብ አለብንላችሁ። የእነዚህ ማህበረሰብ በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ታምሩት። በአባታችሁ፣ በፍቅርና በእምቢል ቀኖዎች ላይ ወሬው፣ በመስቀለም እና በተወላው ምዕራፍ እናወራለን። ዲቪን ያበጋዝ እናጀምራለን። ስለሆነ፣ በትኩሳት የእኛ ውይይቶችን በአጠቃላይ ዜና ማጥቃት፣ መረጃዎችን እና ለማወቅ ያለንን መረጃዎች፣ ዜናዎችን እንደ እኛ ለማቅረብ በመልኩ ማወቅና መከላከል ያቃልላችሁ።

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

13 Nov, 03:01


ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡ 

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡

#ማር_ይስሐቅ

#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ
#ዲያቆን_ሞገስ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

12 Nov, 19:37


- መጣጥፉን ከማገባደዴ በፊት ወንድሜ አረጋ አቋም ያልወሰደበት መሠረታዊ ጉዳይ ጥቂት ማለት ይኖርብኛል። ሣምራዊቷ ሴት እውነት እንደተባለችው ዘረኛ ነበረች ወይ? እዚህ ጉዳይ ላይ ከ4 አመት ገደማ በፊት የወንድሜን የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌን ኃተታ ተቃርኜ ሣምራዊቷ ሴት ዘረኛ መባሏ ስህተት መሆኑን በማስረጃ ያሳየሁበትን መጣጥፍ ፌስቡክ ላይ አጋርቼ ነበር። ይህንን ሃሳብ አሁንም መልሼ በማስረጃ substantiate ለማድረግ ተገድጃለሁ። በውይይቱ ውስጥ አይሁዳውያንና ሣምራውያን ያላቸው በቁርሾና በጥላቻ የተሞላ ታሪክ ምን እንደሚመስል በስፋት ተወያይተንበታል። የነበራቸው ልዩነት በዋናነት ነገረ መለኮታዊ / Theological እንደነበርም አንስተናል። ሣምራዊቷ ሴት ከጌታ ጋር በነበራት ውይይት ውስጥም አንዱ አቢይ መነጋገርያ ጉዳያቸው የነበረው የአምልኮ ቦታን (በገሪዛንና በኢየሩሳሌም አምልኮ መፈጸምን) ማዕከል ያደረገ የነበረው ለዚህ ነው። ይህች ሣምራዊት ሴት "አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ሣምራዊት ከምሆን ከእኔ እንዴት ውሃ ትጠይቃለህ" ማለቷን በተመለከተ ግብጻዊው የነገረ መለኮት ሊቅ ታድሮስ ማላቲ እንዲህ ይላሉ ፦

"አይሁዳውያን ሳምራውያንን ምን ያሕል እንደሚጠሉ ታውቃለች...ሣምራዊቷ ሴት በጌታችን ጥያቄ በእጅጉ ተደንቃለች። ለአንድ አይሁዳዊ ከሣምራዊት ሴት ውሃ መጠየቅ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነውና። አይሁዳውያንና ሳምራውያን ጠላቶች ናቸውና ለጥያቄው እንድትመልስለት መጠበቁም ደንቋታል። በአይሁዳውያንና በሣምራውያን መካከል ምንም አይነት ግብይት የተከለከለ ነበርና ምንም የንግድ ግንኙነት የላቸውም። ከሣምራውያን እቃ መዋስና ከእነርሱ ጋር አንድ ማእድ መጋራት በአይሁዳውያን ዘንድ በጥብቅ የተከለከለ ነበርና።>> Fr Tadros Malaty, The Gospel according to St John, Chapter 4, The conversation with the Samaritan woman

- ከላይ ከምናነበው የታድሮስ ማላቲ ኃተታ ቢያንስ ሁለት መሠረታዊ ቁም ነገሮች እንረዳለን።

1) የሴቲቱ ጥያቄ አይሁዳዊ ሣምራዊት ስሆን ሳይንቀኝ ፣ ሳይጸየፈኝ እንዴት ውሃ ይጠይቀኛል ከሚል ግርምት የመነጨ መሆኑን ነው።
2) ሌላው ቁም ነገር ታድሮስ "ለአንድ አይሁዳዊ ከሣምራዊት ሴት ውሃ መጠየቅ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነውና" ያሉት ነው። ይህም ማግለልና መጸየፍ በዚህ የታሪክ ዐውድ ብንመለከተው አይሁዳዊ የሚያደርገው እንጂ ሣምራውያን የሚያደርጉት አለመሆኑ ነው። ሰፊውን ታሪክ ስንመለከት የምንረዳው ሠማርያውያን ጽዩፋን ፣ አይሁድ የሚጸየፉ እንደሆኑ በቀላሉ እንረዳለን።

ሌላም ምንጭ እንጥቀስ

"The Samaritan woman’s surprise is therefore entirely understandable: Jesus was a Jew and she was both a Samaritan and a woman. From her perspective, she dismisses him as a Jew; later on, Jews will dismiss him as a Samaritan (8:48). But if Jesus cannot be other than alien, he nevertheless wins some Jews and some Samaritans. At this point, however, the woman is not about to be won: she cannot fathom what would possess a Jew to ask her for a drink." D.A carson, The Gospel according to john, [The commentary on the Samaritan woman]

- ይህም ምንጭ ከላይ ያልነውን ቁም ነገር ነው የሚደግምልን። ይህች ሣምራዊት ሴት አይሁዳዊ ወንድ ውሃ ሲጠይቃት ጨርሶ የማትገምተው ፣ ልትረዳውም የሚቸግራት ነገር ነው። ስለዚህም ጥያቄዋ ግርምት ፣ ግራ መጋባት ፣ ጥርጣሬ ወዘተ የተመላበት እንጂ "ደግሞ ብዬ ብዬ ለአይሁዳዊ ውሃ ልስጥ?" የሚል ትዕቢትና ዘረኝነት ጨርሶ አይታይባትም። በዋናነት ሣምራዊት በመሆኗ ሲቀጥል በማህበረሰቡ የተገፋች ምስኪን በመሆኗ ይህ አይነቱ ትዕቢትም ሊኖራትም አይችልም። ዘረኝነት anachronism ነው የምንለው ለዚህ ነው። ሴቲቱ ፍጹም ተገቢና ቅንነት ላይ የተመሰረተ ጥያቄ ነው የጠየቀችው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን ክፍል ሲተረጉም እንዲህ ይላል ፦ " አይሁዳዊ መሆኑን እንዴት አወቀች? ምናልባትም ከአለባበሱና ከንግግሩ ዘዬ (Accent) ይሆናል። ይህች ሣምራዊት ሴት ምን ያህል #ትሑት እንደሆነች ተመልከቱ። ሣምራውያን ከአይሁዳውያን ጋር ኅብረት የላቸውም አላለችም። ነገር ግን አይሁዳውያን ከሣምራውያን ጋር ኅብረት የላቸውም ስትል አደነቀች እንጂ" St John Chrysostom, Homilies 31:4] ዮሐንስ አፈወርቅ በዚህ ኃተታው ሣምራዊቷ ሴት እርሷን ነክቶ ከአይሁዳውያን እንዳይገለል እንደሳሳችለት ጭምር ይነግረናል። ታዲያ ይህችን ያለ ስሟ ስም መስጠት ፣ በዘረኝነት መክሰስ ትልቅ በደል አይደለምን? ይህንን የሚያጠናክሩ ሌሎችም ምንጮች እየጠቀስሁ ማብራርያዬን መቀጠል እችላለሁ። የተወሰኑትን ውይይቱ ላይ ያነሳናቸው በመሆኑ መድገም አስፈላጊ ላይሆን ይችላል።

- የትችታችን ማጠንጠኛ የነበረውን የሣምራዊቷ ሴት ዘረኛ ተብሎ የመከሰስ ጉዳይን ወደ ጎን ብለን አረጋ ከላይ "የሳምራውያን እና የአይሁዳውያንን ያሚያክል መናናቅና መንገድ እሰከመቀየር የሚያደርስ ንቀት ጌታችን አፍርሶ ማኅበረሰባዊ ሐፍረቷ በጠራራ ጸሐይ ብቻዋን ወደ ውኃ ጉድጓድ እስከመሄድ ያደረሳትን ሣምራዊት ቦታዋ ድረስ ሄዶ ማግኘቱ የዛሬውን የዘር ልዩነት ከንቱነት ማስተማሪያነት ሆኖ መቅረቡ እንዲያውም ድንቅ ማንጻጸሪያ እንጂ የሚያስነቅፍ ሊሆን አይችልም፡፡" ያለውን እንመልከት። በመጀመርያ ይህ ነጥብ እኛም ሆነ የተቸናቸው ሰዎች ያላሉት ነገር መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። ይህንን ሃሳብ ውይይቱ ላይ የሰማው አረጋ ብቻ ነው። ነገር ግን ይህ ሃሳብ በራሱ ትክክል አይደለም። የጌታ ወደ ሣምራዊቷ ሴት በብዙ ድካም መሄድ የዘር ልዩነትን ከንቱነት ለማሳየት አይደለም። ይህንን ለመረዳት ጌታ ከሣምራዊቷ ሴት ጋር የነበረውን ንግግር በትኩረት ማንበብ በቂ ነው። የንግግራቸው ማጠንጠኛ የነበረው ከላይ የጠቀስሁት የሥርዐተ አምልኮ ቦታ ልዩነት ነበር። ጌታም ሲመልስላት ያላት የሚከተለውን ነበር

²¹ ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል።
²² እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን።
²³ ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤
²⁴ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።

- ከዚህ ንግግር በግልጽ እንደምንረዳው የጌታችን መሠረታዊ መልእክት አይሁዳዊም ሆነ ሣምራውያን ያላቸው የአምልኮ ቦታ ልዩነት ፋይዳ እንዳበቃ ፣ አማናዊው መቅደስ እርሱ እንደሆነ እየነገራት ፣ የሐዲስ ኪዳንን ሥርዐተ አምልኮ መሠረታዊ ጭብጥ እያስረዳት ነው። ይህንን በተመለከተ የትኛውንም ትርጓሜ ማጣቀስ ይቻላል። ሁሉም ትርጓሜዎች ይህንን በመመስከር ይተባበራሉ። ስለዚህ ጌታ የዘር ልዩነትን ለመሻር አይደለም ወደ ሣምራዊቷ ሴት የሄደው። በመጀመርያ ልዩነታቸው ነገረ መለኮታዊ እንጂ የዘር አይደለም። ሲቀጥል የወንጌሉም ማዕከላዊ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

12 Nov, 19:37


መልእክት የሚነግረን ጌታ የሄደበት ምክንያት ሌላ ትልቅ ነገረ መለኮታዊ ፋይዳ ያለው ነገር መሆኑን ነው። ይህም ከላይ የጠቀስነው የሐዲስ ኪዳንን ሥርዐተ አምልኮ መሠረታዊ ጭብጥ የተመለከተ ነው።

- ለማጠቃለል ያህል ውይይቱ መነሳቱ መልካም ነው። የምንፈልገውም እርሱን ነበርና። ነገር ግን ሲሰነዘሩ ከነበሩ ብዙ አስተያየቶች መረዳት እንደቻልሁት በትክክል የተባለውን ነገር የመረዳት ፍላጎት ችግር መኖሩን ፣ የተባለውን ነገር ጨርሶ ለማዳመጥ የትዕግስት እጦት መበርከቱን ፣ ብሎም ከጭብጡ ይልቅ ሌሎች አይረቤ ጉዳዮች ላይ የመመሰጥ ዝንባሌ መኖሩን ነው። እውነቱን ለመናገር ውይይታችን ጭብጥ ተኮር ቢሆን ሁላችንም እንማማር ነበር። ጉዳዩን personal በማድረግ ወይም prejudiced ሆኖ በመናገር ምንም የምናተርፈው ቁም ነገር የሚኖር አይመስለኝም። እየተባለ ያለውን ነገር በቅጡ እንረዳ ፥ Fact ከኪሳችን አንምዘዝ ፣ ለምንለው ነገር ማስረጃ አምጥተን እንነጋገር ፣ በሃሳብ ፈንታ ግለሰብን በማጥቃት Ad hominem fallacy አንፈጽም። በተለይ ደግሞ እንደ አረጋ ካሉ ታላላቅ ወንድሞቻችን ብዙ ቁምነገር እንደምናገኝ የምናምን በመሆኑ እንዲሁ በጨበጣው በመተቸት የምናገኘውን ቁምነገር ባያሳጡን እንወዳለን። ነገር ግን ስለሰጠውም አስተያየት ፥ እርሱ የሰጠውን አስተያየት መሠረት አድርጌ ሃሳቤን በደንብ እንዳፍታታ ለፈጠረልኝ ጥሩ አጋጣሚ ወዳጄ አረጋን አመሰግነዋለሁ።

ቸር ጊዜ
3/3/2017

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

12 Nov, 19:37


The elephant in the room

አረጋ ወዳጄ ነው። በፌስቡክ ቆይታዬ እርሱም እንደተናገረው ሃሳቦች እንለዋወጥ ነበር። የተለያዩ መጻህፍትና አርቲክሎች አንዳችን ለአንዳችን በኢሜይል እንላላክም ነበር። እናወራ የነበረው ፌስቡክ ላይ ስለነበር ከፌስቡክ ከወጣሁ በኋላ ግን ከአረጋ ጋር ሙሉ በሙሉ ተጠፋፍተናል። ከረጅም ጊዜ በኋላ አረጋን ያነበብሁት ከላይ ያያያዝሁት ውይይታችንን ያሄሰበትን ጽሑፍ ፌስቡክ ላይ ያሉ ወዳጆቼ ሲያጋሩኝ ነው። ጽሑፉን አነበብሁት። በአብዛኛው ነገር አልስማማም። ምንም እንኳን ከአብዛኞቹ ሃሳቦቹ ጋር ባልስማማም ቅሉ ወዳጄ አረጋ ጊዜ ወስዶ ውይይታችንን ተመልክቶ አስተያየት በመስጠቱ ደስ ብሎኛል። አንድም የምንሻው ውይይት ማጫር የነበረ በመሆኑ አንድም ደግሞ በዚሁ አጋጣሚ ብዙ የተሳሳቱ አረዳዶችን ለማጥራት እድል የሚፈጥር በመሆኑ ነው። በብዙ ጉዳዮች ቢነቅፈንም እኔንም ሆነ ኤማሁስን በተመለከተ ስለሰጠው አድናቆትም እጅግ ላመሰግነው እወዳለሁ። በሂሱ ግን መሠረታዊ ሃሳቡን ስቶታል ብዬ ነው የማስበው። መጣጥፌ ከአረጋ ጽሑፍ ውስጥ ሃሳብ የሆኑት ላይ ብቻ ትኩረት ያደርጋል።

- ለመጣጥፌ The elephant in the room የሚል ርእስ የሰጠሁበት መሠረታዊ ምክንያት ይህ ነው። እርሱም አረጋ የክርክሩ ሰበዝ የሚመዘዝበትን መሠረታዊ መነሻ ጨርሶ የዘነጋ አስተያየት የሰጠ በመሆኑ የተነሳ ነው። ይህም ሣምራዊቷ ሴት ዘረኛ ናት የሚለው ክስ ይገባታል ወይንስ አይገባትም የሚለው መነሻ ነው። ሌሎቹ ሃሳቦች ይህንን መነሻ በተመለከተ የሃሳብ ጥራትና መግባባት ሲኖር የሚቀጥሉ ናቸው። የትችታችን መሠረታዊ ማጠንጠኛ "አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ሣምራዊት ከምሆን ከእኔ እንዴት ውሃ ትጠይቃለህ" ማለቷ ዘረኝነት ነው መባሉን በተመለከተ ነው። አረጋ ይህንን ዋና ጉዳይ ፈጽሞ ዘንግቶታል። ያቀረብናቸውንም መከራከሪያዎች እንዳላየ አልፏቸዋል። እዚህ ጉዳይ ላይ አቋሙን ግልጽ ካላደረገ ወደ ሌሎች ጉዳዮች መሄዱ ፋይዳ ቢስ ነው። የክርክሩን ፍሰት በአጭሩ ለማስቀመጥ ያህል ፦

1) ሣምራዊቷ ሴት "አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ሣምራዊት ከምሆን ከእኔ እንዴት ውሃ ትጠይቃለህ" ማለቷ ዘረኝነት ነው "ውሃ ሲጠይቃት ዘር መጠየቅን ምን አመጣው ፥ ሳምራዊቷ ሴት ዘረኛ ናት" የሚል ሰፊ ተቀባይነት ያለው ሃሳብ አለ።
2) ይህ ሃሳብ ከታሪክና ከአበው ድጋፍ አለው ወይ የሚለውን አጠየቅን።
3) ታሪክም አበውም የሚነግሩን በተቃራኒው መሆኑን demonstrate አደረግን።

- በዋናነት የክርክራችን ፍሰት ከላይ በጠቀስኋቸው 3 ነጥቦች ይጠቃለላል። ስለዚህ እኛ ያነሳነውን ሃሳብ ለመተቸት መጀመርያ ሣምራዊቷ ሴት በዘረኝነት የምትወነጀል ናት ወይ የሚለው ላይ አቋም መውሰድ ግዴታ ነው። በቤቱ ውስጥ በገሃድ ሲንጎማለል ቢታይም አረጋ የዘነጋው ትልቁ ዝሆን ይሄ ነው። ይህንን በተመለከተ ምንም አቋም ያልወሰደው አረጋ የሚከተለውን ይለናል።

"ቃላቱና እጠቃቀሙ ይለያይ እንጂ በጥንት የነበረን ክስተት ከአሁኑ ጋር አገናዝቦ መልእክት ማስተላለፍ አንዲያውም ጎብዝ የሚያሰኝና ትርጉም የሚሰጥ ነገር ነው፡፡ ችግር የሚሆን የነበረው ብቸኛ ትርጉም ይኸ ነው፣ ያኔ የተነገረው ለዛሬው ለእኛ ጠብና ልዩነት አስተማርያ ነው ቢባል ነበር፡፡ የሳምራውያን እና የአይሁዳውያንን ያሚያክል መናናቅና መንገድ እሰከመቀየር የሚያደርስ ንቀት ጌታችን አፍርሶ ማኅበረሰባዊ ሐፍረቷ በጠራራ ጸሐይ ብቻዋን ወደ ውኃ ጉድጓድ እስከመሄድ ያደረሳትን ሣምራዊት ቦታዋ ድረስ ሄዶ ማግኘቱ የዛሬውን የዘር ልዩነት ከንቱነት ማስተማሪያነት ሆኖ መቅረቡ እንዲያውም ድንቅ ማንጻጸሪያ እንጂ የሚያስነቅፍ ሊሆን አይችልም፡፡"

- አረጋ የክርክራችን መነሻም ሆነ መድረሻ ፈጽሞ እንዳልገባው የሚያሳብቀው ይህ አስተያየቱ ነው። ትችቱ ሙሉ በሙሉ dislocated የሆነ ትችት ነው። ምክንያቱም እኛ የተቸናቸው ጸሐፍያን ነጥብ ጌታ ይህችን ሴት አድካሚ የሦስት ቀን መንገድ ተጉዞ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ማግኘቱ የዘር ልዩነትን ሲሽር ነው የሚለው ፈጽሞ አይደለም። ይልቁንም ከላይ የጠቀስነውን የሣምራዊቷን ሴት "አይሁዳዊ ስትሆን ሣምራዊት ከምሆን ከእኔ ውሃ እንዴት ትጠይቃለህ" የሚለውን አነጋገር ነው።

እዚህም ላይ የሃሳባቸውን ፍሰት በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ ልሞክር።

1) ሣምራዊቷ ሴት ውሃ ስትጠየቅ "አይሁዳዊ ስትሆን" ብላ የዘር ጥያቄ ውስጥ የምትገባ ዘረኛ ናት።
2) ጌታም ጥያቄዋ የዘር ስለነበረ ምንም አስተያየት ሳይሰጥ አለፋት።
3) እኛም በዚህ ዘመን "አንተ አማራ ስትሆን ኦሮሞ ከምሆን ከእኔ ፣ ጉራጌ ስትሆን ወላይታ ከምሆን ከእኔ ፣ ትግሬ ስትሆን አማራ ከምሆን ከእኔ እንዴት ውሃ ትጠይቃለህ ወዘተ" የምንለው ነፍሳችን በዘረኝነት ስለቆሰለች ነው።

- ከላይ በቅደም ተከተል መነሻውንና ድምዳሜውን ተቀምጧል። ስለዚህም በዘመናችን ያለውን ዘረኝነት ከሣምራዊቷ ሴት አነጋገር አንጻር ለመናገር (ውሃው ሣምራዊ ነው ወይስ አይሁዳዊ? የቆሰለች ነፍስ ስለዘር ታወራለች የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ) መጀመርያ ሣምራዊቷ ሴት ዘረኛ ናት የሚለውን መነሻ መቀበል የግድ ነው። ይህንን መነሻ ካልተቀበልን ከድምዳሜው ጋር ጨርሶ ልንስማማ አንችልም። ወዳጄ አረጋ የዘነጋው መሠረታዊ ቁም ነገር ይሄ ነው። ከላይ የጠቀስሁት ይህ አስተያየቱ እውነት ውይይታችንን በደንብ ተከታትሎታል ወይ? ወይስ እስቲ የሚሉትን ብለው ይጨርሱና እተቻቸዋለሁ እያለ ነው የሰማን አሰኝቶኛል። ምክንያቱም እኛ እየተቸን ያለነው ሣምራዊቷ ሴት ያለ በደሏ በዘረኝነት መከሰሷና ይህ ታሪክ ሊል ያልፈለገውን ነገር በግድ ቆንጥጦ የማናገርን ስሁት አካሄድ እንደነበረ ደጋግመን አንስተናልና። ጥንት የነበረን ክስተት ከዛሬ ጋር አገናዝቦ መተረክ ችግር አለው የሚል ነገር ፈጽሞ አልተናገርንም። ይልቁንም የዛሬን ሁነቶች እንዲደግፉልን ያመጣናቸው ጥንታዊ ምሳሌዎች ዛሬ ካለው ሁኔታ ጋር በትክክል የሚገጥሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ከዚህም ሲሻገር መሠረታዊ መልእክታቸው ምን እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል የሚለውን ደጋግመን ስናጸና ነበር። የዛሬን ሁነቶች መሠረት አድርጎ ታሪክን ወደ ኋላ ለመተርጎም መሞከር Anachronism ይባላል። ይህም ታሪክ Anachronize ተደርጓል የሚል ሙግታችንን በውይይቱ ላይ አቅርበናል። አረጋ ግን መነሻውን ሙሉ በሙሉ ላለማየት እየጣረ የነበረ በመሆኑ ዋናውን ቁም ነገር ሳይነካው ነው የቀረው።

- ከላይ ባቀረብሁት ኃተታ መሠረት ይህንን ታሪክ የዘረኝነትን እኩይነት ለማስተማር ሣምራዊቷ ሴት የጠየቀችው ጥያቄ የዘረኝነት ነው እርሷም ደንበኛ ዘረኛ ናት የሚለውን መነሻ (premise) መቀበል ያስፈልጋል። አረጋ እዚህ ጉዳይ ላይ ቁርጥ አቋም አልወሰደም። ስለዚህ ታሪክ ከዘረኝነት አንጻር መጠቀስ ይገባዋልም ፣ አይገባውምም ለማለት ምንም መሠረት የለውም። ምክንያቱም የመነሻው/premise (ሣምራዊቷ ሴት ዘረኛ ናት የሚለውን ማለት ነው) ትክክል መሆን አለመሆን ላይ ምንም ሳይሉ መደምደሚያውን (Conclusion) መደገፍ ምንም ስሜት ሊሰጥ አይችልምና።

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

12 Nov, 12:42


ለቅዱሳን የተሰጠ ቃልኪዳን ለመዳናችን ያለው አስተዋጽኦ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

12 Nov, 10:51


ፈውስ እና ድኅነት

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

11 Nov, 11:46


ነገረ ቤተክርስቲያን በሣምራዊቷ ሴት" በሚለው ውይይታችን ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን ስለመቃኘት ፦

- ከአንድ ወር ገደማ በፊት በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አራት ላይ ያለውን ሣምራዊቷ ሴት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያደረገችውን ተዋስዖ ያተትንበት ውይይት በኤማሁስ በኩል ቀርቦ የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ውይይቱ አየር ላይ ከዋለ በኋላ ከዚህም ከዚያም የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ይስተዋላል። ደጋግመን እንደምንለው አስተያየቶቹ መሰረታዊ ጭብጡን ወደ ጎን ያደረጉና ፣ የተባለውን ነገር ትተው ባልተባለ ነገር ላይ የሚያተኩሩ ሆነው ይገኛሉ። ይህ መሆኑ ደግሞ ጭብጥ ተኮር የሆነ ፣ በቅንነት ሃሳቡን ለመረዳት የሚሞከርበትና substance ያለው ተቃራኒ ሃሳብ አምጥቶ የሚሞገትበት ጠቃሚ ውይይት እንዳይደረግ ያግዳል። ስለዚህም እዚህና እዚያ ያሉ ጉንጭ አልፋ ጉዳዮች ላይ በከንቱ መጠመድና መባከን ይፈጠራል። ውይይት ምንጊዜም ቢሆን ጭብጥ ተኮር መሆን አለበት። ወደ ሁነቶችና ወደ ግለሰቦች ከተቀነሰ ውይይት ሳይሆን ተርታ ሃሜት ነው የሚሆነው። በቅርቡ የውስጣዊ ተዋስዖን አስፈላጊነት በተመለከተ ባደረግነው ውይይት ላይ ይህንን ነጥብ በስፋት የሄድንበት በመሆኑ እዚህ ላይ ልደክምበት አልሻም።

- ሣምራዊቷን ሴት በተመለከተ የተወያየነው ውይይት በሦስት መሠረታዊ ሃሳቦች የተዋቀረ ነው። የመጀመርያው ክፍል ይህንን የወንጌል ክፍል ለመረዳት እጅግ አስፈላጊ የሆነው የሣምራውያንና የአይሁዳውያንን ማንነት ፣ በመካከላቸውም የነበረው ታሪካዊ ግንኙነት ምን ይመስል እንደነበረ ያነሳንበት ክፍል ነው። ሁለተኛው ደግሞ የዚህ ታሪክ ትርጓሜና ፋይዳ ምን እንደሆነ ያተትንበትና የወንጌሉ መሠረታዊ ጭብጥ ምን እንደሆነ በስፋት ለማብራራት የሞከርንበት ክፍል ነው። ሦስተኛው ክፍል ደግሞ ይህን ታሪክ በተመለከተ ከታሪክ መዛግብትም ሆነ ከአበው ትርጉም አንጻር አድራሻ የማይገኝላቸውን አተያዮች ያሄስንበት ክፍል ነው። የውይይቱ መሠረታዊ መዋቅር ይህን ይመስላል።

- የወይይቱ አወቃቀር ምን እንደሚመስል ያነሳሁበት መሠረታዊ ምክንያት ብዙ አስተያየት ሰጪዎች የውይይቱ ማዕከላዊ ጭብጥና ማጠንጠኛ ምን እንደሆነ ፈጽሞ የዘነጋ አስተያየት ሲሰጡ ስለታዘብሁ ነው። ይህ ታሪክ የዘረኝነትን መጥፎነት ከማስተማር አንጻር ዋቢ የመሆኑ ነገር ለምን ትክክል እንዳልሆነ ያነሳንበት ክፍል ከውይይቱ አስር ደቂቃ እንኳን ያልወሰደና እንደ ኅዳግ ማስታወሻ የታከለ ነገር እንጂ የውይይቱ ማዕከላዊ መልእክት እርሱ እንዳልሆነ ተስቷል።
በርግጥ ይህን ጉዳይ በራሱ ጉዳይ ብናደርገውም በራሱ ምንም ነውር የለበትም። (ይህንን ጉዳይ ጉዳይ አድርጌ ወንድማችን ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የኤፍራጥስ ወንዝ በሚል ርእስ ባሳተመው እስትግቡዕ ውስጥ ሣምራዊቷን ሴት በሚመለከት የጻፈው ላይ ያቀረብሁት ሂስ እዚሁ ቻነል ላይ ይገኛል። ፍላጎቱ ያለው ሰው ወደ ኋላ ሄዶ ሊመለከተው ይችላል) ነገር ግን የውይይቱ ዋና ማጠንጠኛ ሳምራዊቷ ሴት የቤተክርስቲያን ምሳሌ መሆኗ ፣ ጌታም በውሃ ዳር ያጫት መሆኑ በአበው ዘንድ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ማውሳት መሆኑ ውይይቱን በደንብ የተከታተለ ሁሉ በቀላሉ የሚገነዘበው ነገር ነው።

ሣምራዊቷ ሴት ዘረኛ ናት የሚለው ፍጹም ሃሳዊ ውንጀላ ለምን ተገቢ እንዳልሆነ በውይይቱ ውስጥ አንድ ፥ ሁለት ተብለው የሚቆጠሩ መከራከሪያዎች አንስተን ሞግተናል። ምንም እንኳን ቀዳሚው የውይይታችን አጀንዳ እርሱ ባይሆንም ሣምራዊቷ ሴት ይህ ውንጀላ ይገባታል የሚል ቢኖር ማስረጃ ጠቅሶ ይሞግተን ብለን challenge አድርገን ነበር። ነገር ግን ይህን በማድረግ ፈንታ ከጀርባ ያላችሁ ፍላጎት ሌላ ነው ፥ እገሌን ለማጥቃት ነው ወዘተ የሚሉ ከጭብጡ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ነገሮች ይነገራሉ። ይህም ቀድሜ እንዳልሁት ስልጡን የሆነ ፣ ሃሳብና ማስረጃ ላይ ያተኮረ ውይይት ላለመዳበሩ ትልቅ ምክንያት ይመስለኛል። ስለዚህም አንደኛ ውይይቱ በተደረገበት ዐውድ ይደመጥ። ማዕከላዊ መልእክቱን ያገለለ አረዳድ ትክክል አይደለምና። ሁለተኛ ያነሳችኋቸው ነጥቦች ትክክል አይደሉም የሚል ቢኖር አንድ ሁለት ብለን ላነሳናቸው መከራከርያዎች አንድ ሁለት ብሎ ይሞግተን።

ብዙዎች የማይስማሙት ያለመስማማት መብታቸውን ለመጠቀም ያህል ብቻ ይመስላል። ምክንያቱም አልስማማም ያለ ሰው አልስማማም የሚል አቋም ሳይሆን የማይስማማባቸውን ነጥቦች ማቅረብ ነው ያለበት። ከሃሳብ ጋር እንጂ ከአቋም ጋር ሙግት አይገጠምምና። ሦስት በተዋስዖዎቻችን ውስጥ ቀናነት (good faith) ይኑር። አንድ ሰው አለመስማማቱን ሲገልጽ ቢያንስ ውይይቱን አዳምጦ መሆን መቻል አለበት። ውይይቱን ፈጽሞ ሳያዩ አስተያየት መስጠት በጣም አሳፋሪ ነው። ባጭሩ ጭብጥ ላይ በማተኮር ፍሬያማ ውይይት ለማድረግ እንሞክር።

ለዝግጅት የተጠቀምንባቸው ይህንን ታሪክም በስፋት ለመረዳት ለሚሻ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ማጣቀሻዎች ፦

1) ወንጌል ቅዱስ ንባቡና ትርጓሜው
2) አባ ምሥራቅ ጥዩ - የዮሐንስ ወንጌል ማብራርያና አስተንትኖ
3) Raymond E. Brown, The Gospel according to john, a new translation with introduction and commentary
4) Tadros Malaty, The Gospel according to St John, part one, chapters 1-8
5) D.A carson, The Gospel according to john
6) John Behr, John the theologian and his paschal gospel, a prologue to theology
7) David H. Stern, Jewish new testament commentary
8) Sister Thomas Aquinas Goggin, S.C.H (Translator), Saint John Chrysostom, commentary on saint John the apostle and the evangelist, homilies 48-88

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

11 Nov, 08:53


አንድ አንድ ሰው የሃይማኖት መርኆ የሚቀርጸው ከዕቅበተ እምነት እና መናፍቃንን ከማሳፈር ወይም ከመብለጥ አንጻር ብቻ ሲኾን ጥልቅ ለኾነው ኦርቶዶክሳዊ ነገረ መለኮት ዓለምን መፈተሽ ለሚያስችለው ኦርቶዶክሳዊ ንጻሬ ዓለም ደንታ የሌለው ይኾናል። የእንደዚኽ አይነቱ ሰው የኹል ጊዜ ፍላጎት ነገር ኮሽ በማይልበት ቤተ ክርስቲያን መኖርን መናፍቃኑን ማስቀናት ነው። ተባብሮ የውጭ ጠላት እንደማሳፈር እንደ ደላው ሰው በውስጥ ተዋስዖ ማድረግን እንደ ቅብጠት ይቆጥረዋል። ይህ ሰው ቤተ ክርስቲያን በዘመናት እንዴት እውነትን ከሀሰት እየለየች እንደተሻገረች የገባው አይመስልም። በዚህ ምክንያት በውስጥ የሚደረግን ተዋስዖ አጥብቆ ይጸየፋል።

ሌላኛው አይነት ሰው ደግሞ ስለ ትክክለኝነቱ ከመጨነቅ ይልቅ ተያያዥ ጉዳዮች ያሳስቡታል። የግል ጉዳዩ የሚወደው ሰባኬ ወንጌል ዘመዱ የኾነ ጳጳስ ወይም ያስቀጠረው ጳጳስ... ወ.ዘ.ተ ቀስፎ ስለሚይዘው የውስጥ ተዋስዖን ይጸየፋል።

ከዚህ ውጭ የኾነው እምነቱን በመጠየቁ የሚያጣው የሚመስለው የእምነቱን ጉዳይ ለተወሰኑ ሰዎች ሰጥቶ እነሱን እያመነ መኖር የሚፈልግ ሰነፍ ሰው ነው። አብዛኛው ሰው የእምነት ፍርሃት አለበት። ለዚህ ማሳያው የምንዘምራቸው መዝሙራት ሳይቀሩ "አንተ ባታውቅም ኦርቶዶክስ መልስ አላት" የሚል አሳብ ያላቸው ናቸው። ለእንደዚህ ዓይነት ሰው በውስጥ የሚደረግ ተዋስዖ ስጋት ነው።

ውስጣዊ ተዋስዖ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አካል አይደለምን?
እንደ ተለመደው አሳብ አስተያየት ትለመናላችኹ።
ኤማሁሳውያኑ በመንገድ እንዲኽ ተወያዩበት


ኢዮብ ወንድወሠን

https://youtu.be/VYm1SakDhR8?si=lDnLABDv8OcolyqA

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

10 Nov, 20:48


ቤተ ክርስቲያናችን በዘመናችን ከገጠሟት ተግዳሮቶች መሀከል አንዱ ምናልባትም ዋናው የውስጥ አቅሟ (ሰብአዊም ሆነ ቁሳዊ ሀብቷ) ለዋና ዓላማዋ መዋል አለመቻሉ ነው የሚል ጽኑ አቋም አለን። ውስጣዊ ጥንካሬ የቆምንበትን ዓላማ ከዳር የሚያደርስ፣ የውጪውንም ፈተና ማሸነፍ የሚቻልበትን አቅም ፈጣሪ ነው። ነገር ግን ውስጣዊው አቅም እንዲህ በቀላሉ የሚመጣ ነገር አይደለም። ጨከን ብሎ መነጋገር እና መተማመን ይፈልጋል። ከዚሁ አንጻር ውስጣዊ ተዋሥኦን በተመለከተ ግራ ቀኙን ለመቃኘት የሞከርንበትን ይኼን ቪዲዮ ያድምጡ፤ የተዋሥኦውም አካል ይሁኑ።

https://youtu.be/VYm1SakDhR8?si=lDnLABDv8OcolyqA

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

08 Nov, 18:48


https://youtu.be/rT2byvf-n1w?si=Hnn7Pq0xXwBDvhHx

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

08 Nov, 17:28


https://youtu.be/tzpIxaBQPxk?si=yU6oclKF5o1nFT2-

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

08 Nov, 08:29


ክፍል አምስት እነሆ!

https://emmauspresset.com/1013/

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

07 Nov, 17:51


Dn. Yaregal Abegaz

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

06 Nov, 05:49


ተዝካረ ስቅለቱ ለእግዚእነ

እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን::

ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቤተ ክርስቲያናችን ጌታችን በመስቀሉ ስለፈጸመልን የማዳን ሥራ “ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ”በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው እያለች እየዘመረች ታስበዋለች።

ከዚህም በተጨማሪ ጥቅምት ፳፯ በወርኀ ጽጌ ውስጥ ያለ በመሆኑ “ …እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ” እያለች የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን መድኃኒት የሆነው ጌታ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣት እንደሆነ በመመስከር ትዘምራለች ።

መጋቢት ፳፯ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን ዐርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርዓት ሠርተዋል፡፡መጋቢት ፳፯ ቀን በዐቢይ ጾም ስለሚውልና በወቅቱም ኀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለች ።

ጲላጦስ አይሁድን ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ ቢላቸው በርባንን ፍታልን ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ግን ስቀለው አሉ። ጲላጦስም በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ሁሉ ንጹሕ ነኝ ብሎ ባደባባይ እጁን ታጠበ። አይሁድ ደሙ በኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ። እርሱም በርባንን ፈታላቸው ጌታንም አሳልፎ ሰጣቸው። ማቴ ፳፯ ፥፳፭

መጋቢት ፳፯ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል። የተሰቀለው የክብር ባለቤት ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀዷል፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯ )፡፡

ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ ጋር ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መ.ክ.ዘ የነበሩትን አቡነ መብዓ ጽዮንን ታስባለች፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ በዕለተ ዓርብ የተቀበልከውን መከራ ግለጽልኝ ››ብለው በጸለዩ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተቀበላቸውን መከራዎች ሁሉ አሳያቸው፡፡

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስን መከራ ካዩበት ቀን ጀምሮ ሕማሙን መከራውን ግርፋቱን እስራቱን በጠቅላላ አሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በማሰብ ጀርባቸውን በአለንጋ ይገርፉ ፤ ራሳቸውን በዘንግ ይመቱ ነበር፡፡

የጌታችንን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ዘወትር ስለሚያለቅሱ ዐይናቸው ጠፍቶ ነበር፡፡ ነገር ግን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የብርሃን ጽዋ ይዛ መጥታ ዐይናቸውን ቀብታ አድናቸዋለች፡፡ በዚህ የተነሣ ‹‹በትረ ማርያም›› እየተባሉ እንደሚጠሩ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ በዚህ መሠረት ጥቅምት ፳፯ ቀን ለአቡነ መብዓ ጽዮን ቃልኪዳን የገባበት ቀን በመሆኑ በየዓመቱ ጥቅምት ፳፯ ቀን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱ ጋር ይከበራል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Mahibere kidusan

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

03 Nov, 19:50


የማርክሳዊነት የገደል ማሚቱዎች

'ወደ ርስታችን ያልተመለስንበት ኢዮቤልዩ' የተሰኘውን ጽሑፍ መሠረት አድርጎ ጥቅምት 17 ፣ 2017 ዓ.ም. በዐውደ ፋጎስ የውይይት ክበብ የተደረገ አቅርቦት ።

https://youtu.be/kiG8GWoTlW8?si=jKY1v3A3cSCu1NHB

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

03 Nov, 09:40


ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን አምጣ የወለደችው የመምህረ ወንጌል የዲ/ን ያረጋል አበጋዝ የተወሰኑ የመጽሐፍ
ቅጂዎች ስላሉን ማግኝት ትችላላችሁ።
በግዮን መጽሐፍ መደብር ደርዛቸውን የጠበቁ ነባርና አዳዲስ መጽሐፍቶችን ያገኛሉ። ለበለጠ መረጃ
በ0913083816/0931144330

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

01 Nov, 15:13


https://youtu.be/GfpAu4o5Qpw?si=bhAmTetLPoA4oHGY

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

01 Nov, 09:11


https://youtu.be/SXZqXgQFLow?si=7FMXEs-NJp3Gmw0A

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

01 Nov, 08:07


ይህ የዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ድንቅ መጽሐፍት ፤ከሳይንስ፤ ጋር የተገናኙ፤ ፍልስፍናዊ ፤ጉዳዮች ፤ከክርስትናዊ ፤ በሰፊው የሚዳስስ ፤መጽሐፍ ነው።

እያለቀ ስለሆነ እንዳያመልጥዎት የተወሰነ ቅጂዎች አሉን ይጎብኙን ግዮን ፤መጻሕፍት፤ መደብር ፤ዘወትር በልዩ ቅናሽ እንጠብቃችኋለን።

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

31 Oct, 14:54


Rock and Sand: An Orthodox Appraisal of the Protestant Reformers and Their Teachings

Book by Josiah B. Trenham

This book has been written for three purposes. First, to provide the Orthodox reader with a competent overview of the history of Protestantism and its major traditions, from its beginnings in the 16th century to the present day. This overview relies heavily upon the Reformer’s own words as well as the creeds of various Protestant faiths, in order to avoid misrepresentation and caricature. Second, to acquaint Orthodox and non-Orthodox readers with a narrative of the historical relations between the Orthodox East and the Protestant West. Finally, to provide a summary of Orthodox theological opinion on the tenets of Protestantism.

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

30 Oct, 18:09


ሰዎች ላይ እንዳልፈርድ ምን ላድርግ?
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

29 Oct, 09:52


ምስጢር ከሚፈስበት፣ከሚቀዳበት ከጉባኤ ቤት የተሰጠ የምስጢር መአድን አቅርብንላችኋል። "ከመዝ ነአምን" በመምህር የኔታ ገብረ መድኀን እንየው የተበረከተ።  የጉባኤ ቤት ምስጢር የፈሰሰበት መጽሐፍ ነው።
መጽሐፍን እኛ ዘንድ በግዮን መጽሐፍት መደብር ዘወትር በልዩ ቅናሽ ያገኙታል።ገቢው ሙሉ ለሙሉ ለምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት የሚውል ነው። አንድም ከበረከቱ እንሳተፍ አንድም ምስጢሩን ከየኔታ እንቅዳ።

አድራሻ:-መ/ገ/ጽ/ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን
ለበለጠ መረጃ 0913083816 /0931144330

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

28 Oct, 08:47


" ለራስ ጥቅም ሌሎችን ማስቀደም "

     በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

በዚህ ጽሑፍ አንድ ሰው ራሱን ለመጥቀም እንዴት ማድረግ እንዳለበት ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር ለማየት እንሞክራን።ለዚህ ጉዳይ አስተማሪ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንዳስሳለን

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

27 Oct, 13:39


Modern Orthodox Thinkers: From the Philokalia to the Present

By Andrew Louth, one of the most respected authorities on Orthodoxy, introduces us to twenty key thinkers from the last two centuries.

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

26 Oct, 18:39


አሐቲ ድንግልን ነገ እሁድ ሱቃችን ክፍት ስለሆነ ከ3 ሰዓት ጀምሮ እስከ 8 ሰዓት በግዮን መጻሕፍት ታገኙታላችሁ።

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

26 Oct, 14:11


Paulos Mar Gregroios

Meaning and Nature of Diakonia:

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

26 Oct, 05:26


አሐቲ ድንግል ዛሬ ቅዳሜ ከስዓት በግዮን መጻሕፍት ታገኙታላችሁ።

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

23 Oct, 19:07


እግዚአብሔር በመጽሀፍ ቅዱስ "ክፋትን እፈጥራለሁ" ሲል ምን ማለቱ ነው?

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

22 Oct, 12:02


የማርክሳዊነት የገደል ማሚቶዎች
=====================
በ "ያ" ትውልድ የተጻፉ መጻሕፍት እና የተደረጉ ጥናቶች ፣ ውይይቶች እና መጠይቆችም ነበሩ ።  ዳሩ ግን በዚያን ጊዜም ሆነ አሁን በመሠረታዊነት መነሣት የነበረባቸውን ማርክሳዊም ሆነ ተዛማጅ ፍልስፍናዊ ጉዳዮችን በሚገባ አንሥተው  በጥልቀት ተወያይተውባቸዋል ለማለት አያስደፍርም ። አሁንም ቢሆን የደፈረሰው አልጠራም ። ሐሳቦቻችንም ሆኑ ሩጫዎቻችን ቦታ ቦታ አልያዙም - መደምደሚያም ባይሆን መሰብሰቢያ ምዕራፍ አላገኙም ። 

በ "ያ"  ትውልድ ዋና ገዢ ሐሳብ ማርክሳዊነት ነበር ። ከደርግ ዘመን በኋላ ደግሞ በተቃራኒው ማርክሳዊነት እንደ ርእዮት ተቀባይነት ያጣ መስሏል ። ነገር ግን አሁን ያሉ ተዋሥኦዎች የማርክሳዊነትን መነሻዎች በውስጣቸው ያቀፉ ሆነው ይገኛሉ ። ወይም ማርክሳዊነትን አንቀበልም ቢሉም እንኳን ግቦቻቸው ማርክሳዊነት የእኔ ናቸው ከሚላቸው ግቦች እምብዛም ፈቀቅ ያላሉ ሆነው ይገኛሉ ።

  እንደምመለከተው ከሆነ ፥ ተዋሥኦዎቻችን - ተዋሥኦ ሊባሉ ከቻሉ - ከመሠረታዊ ጥያቄዎች ተፋትተዋል ። ብዙ ጊዜ ዐቢይ ጉዳያችን “ወቅታዊው” እና “ተግባራዊው” ነገር ነው ። መሠረታዊ እና ሐሳባዊ ፣ ረቂቅ የሆኑትን ጥያቄዎች ጉዳይ ማድረግን ከሥራ ፈትነት ቆጥረነዋል ። ነገር ግን ተዋሥኦዎቻችን ፍሬ ያፈሩ ዘንድ እንዲህ ወዳሉት ጥያቄዎች መመለስ እንዳለባቸው አምናለሁ ። በዚህ አቅርቦትም ለማጠየቅ የምሞክረው ይህን ነጥብ ነው ።
Synopsis by  በርናባስ ሽፈራው
ቀን :- እሁድ በ17/02/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ላይ
ቦታ :- በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) አዳራሽ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

22 Oct, 04:55


አገልግሎትን የተረዳንበት መንገድ እንኳን ለሰማዩ ለምድራዊነት የማይመጥን ነው!

አገልጋይነት እና አገልግሎት ምንድን ነው? በተለይ በዚህ ዘመን የኢትዮጽያ ቤተ ክርስቲያን አንዱ እና ዋነኛው ችግር "አገልጋይ" ከተባሉ ሰዎች የሚመነጭ አይመስላችኹም?

በተለይ በእንደዚህ አይነት ጊዜ ወደ መሠረታዊው የነገረ መለኮት እሳቤ ወደ አበው ትርጓሜ እና አረዳድ ወደ ከበረው የጌታ ትምህርት መለስ ብሎ ጉዳዩን መዳኘት እና እልባት መስጠት ብቻ እና ብቻ መፍትሔ ይኾናል።

አገልግሎትን የተረዳንበት መንገድ እንኳን ለሰማዩ ለምድሩም ማፈሪያ ያደረገን ከኾነ ለምን አንጠይቅም? "አገልግሎት ምንድን ነው?"
ለውይይት ማጫሪያነት ኤማሁስ አገልግሎትን እንደዚ በአጭሩ ፈክራለች።
እንደ ተለመደው ለውይይት ክፍት ነው መድረኩ!

ኢዮብ ወንድወሰን

https://youtu.be/S92e2ZjnF5M?si=yxkFjyNRY7xFZVkR

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

20 Oct, 18:23


በዚህ ውይይታችን ስለ 'አገልግሎት' ለመነጋገር የመረጥነውን የወንጌል ክፍል ማለትም ማቴ 20÷20-28 ለመረዳት የሚያስፈልገውን መሠረታዊ ዓውድ ከማንሳት በመጀመር ፦

- አገልግሎት (Diakonia) ምንድነው? ዘመናዊ የነገረ መለኮት ምሁራን 'አገልግሎት' ን ከቅዳሴ በኋላ ያለ ቅዳሴ (liturgy after the liturgy) ይሉታል ምን ማለት ነው? የሚለውንና

- አገልግሎትን እውነተኛ አገልግሎት (authentic diakonia) የሚያሰኙት ምን ምን ናቸው? የሚለውን ጨምሮ ሌሎችንም ነጥቦች በብዙ ያይደለ በጥቂቱ አንስተናል።ሃሳብ አስተያየታቹ አይለየን።

መልካም ቆይታ!

https://youtu.be/S92e2ZjnF5M?si=7souBSHH1vmU4SyX

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

20 Oct, 06:18


ኤጲስ ቆጶስ የሚለው ማዕረግ በጥንቱ የሮማ ቤተሰባዊ መዋቅር ውስጥ 'አንድ ሮማዊ ጌታ በሚያስተዳድረው ቤት ውስጥ የሚሠሩ አገልጋዮች አለቃ - master of slaves' የሚጠራበት ስም ነበር። ክርስቲያኖች ስሙን ከዚያ ነበር የወሰዱት። በእግዚአብሔር ቤት ካሉ አገልጋዮች መሀከል አንዱ ግን ታላቁ አገልጋይ ስም ኤጲስ ቆጶስ መባሉ የጥንቶቹ ተምኔት ምን እንደሆነ በግልጥ ያሳያል። ዛሬ ይኼ የአገልጋይነት መንፈስ የሚገኘው የት ይሆን? የሚለው የእኛ የቤት ሥራ ነው። አገልግሎትን በተመለከተ የተወያየነውን እንደ ወትሮው እንድታዳምጡ፣ አሳባችሁንም እንድታጋሩን ግብዣችን ነው።

https://youtu.be/-M_tj2UM-oE?si=45QsJ9fFkpY9620M

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

19 Oct, 07:58


https://youtu.be/DDu6pzl94eg?si=CeEWPbrekzeqKJyd

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

18 Oct, 08:24


https://youtu.be/-M_tj2UM-oE?si=MCde2OEO46zQ_u9s

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

16 Oct, 17:22


የግል ምልከታየ
ዕቅበተ እምነት ላይ እንጂ ተቋማዊ ጥበቃ ላይ ብቻ ማተኮር ማደክደክ ነው።
ላይኛው ተቋም ለእውነት ሥራ ዝግጁ አይለም።
ከትናንት እስከ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ ለደረሰው ውስጣዊ መከራ ተቋሙ የችግር ባለቤት ሳይሆን ራሱ ችግር ነው።
በተለይም የውጭ መከራዎችን እንደ እባብ ሰይጣንን ተጭኖ እየመጣ አዳማውያንን የሚያስትበት ቤት ከሆነ ሰነባብቷል።
ህልው ሁኖ አጀንዳ የሚሰጣችሁ ማን ነው?ይሄንን የማያውቅ ሰው ይኖራል? ካላ በጣም ፈዛዛ ነው።
ይልቅስ እንደ ባለቅኔው የጥፋት መልእክቱ ደርሶና የላካችሁ ሰውየ ደኅና ነውወይ? አትሏቸውም?
ይሄንን የምጽፈው በግል ሁኖ አንዳንድ የቤቱን ተንኮል ያልተረዱ የዋሓን ምእመናን ዛሬም ሲደናገሩ በማየቴ ነው።
የማይፈወሰው ድውይ የማይመለሰው ጊጉይ ሁኖ መድኃኒቱን እያማሰነ እንደገና በደዌ እያመረቀዘ የጥፋት ቫይረስ ተሸካሚ ሁኖ ከተገለጸ ቆይቷል።
አሁንም የአትርሱኝ ጩኸት ወዲያ ወዲህ ሲያወራ ቢሰማም ምእመናንን ዕረፍት ለመንሳት፣ለማደናገር፣የንትርክ አጀንዳ ለመስጠት፣ለሥርዓቱ ጥበቃ ይጠቅማል ተብሎ የተሰጠውን የተልእኮ ዓላማ ለመፈጸም ሲባል..ነው እንጂ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚመለከተው ሁኖ አይደለም።
ይሄ ጉዳይ በደንብ ተነጋግረውበት ተወያይተውበት የአትርሱኝ አስታውሱኝ አጀንዳ እንጂ የእውነት አይደለም።ሁሉም የሚሠሩት አብረው ነው።
ዋናው ጉዳይ ምእመናንን ማደናገር፣ዕረፍት መንሳት፣እምነቱን እንዲተው ማወክ፣ሥርዓቱን መጫን፣ምእመናንን ማሳቀቅ፣ጭር ሲል አልወድም...ነው።
ቢያንስ ሞቱ እንግልቱ ይቅርና ምእመናን ሀዘናቸውን እንኳን ዕርም አውጥተው እንዳያዝኑበት ዲሪቶውን አምጥቶ ይጭንባቸዋል።
እኔ በግሌ ከነነዌ ምህላ እና ከሐምሌ 9/1015 ዓ.ም.ጀምሮ ጨርሸ ትቻቸዋለሁ።ረቂቅ ውንብድናውን እስከ ጥግ አይቸዋለሁ።
እኔ ግን የለውጥ መንገዱን እስካገኘው እፈልገዋለሁ።ከሕይወቴ አብልጬጬ እጨነቅለታለሁ።ሁልጊዜም ቤተ ክርስቲያን የደረሰባትን ሳስበው አንጀቴ ይላወስብኛል።
ወደ መፍትሄው ብቻ ዓይናችንን እናዙር።
የቤቱ ስም የእኛ ነው ሥራው ግን የአጥፊዎች ነው።
ሁለንተናው ኦርቶዶክሳዊ እስኪሆን ድረስ ዓይናችንን ወደ መፍትሄው ብቻ እናዙር።

ገብረመድኅን እንየው

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

16 Oct, 17:14


መንፈሳዊነት ምንድን ነው ?


፩. መንፈሳዊነት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ኅብረትና አንድነት ነው፡፡

፪. መንፈሳዊነት ስሜትን፣አእምሮንና መንፈስን ሲገዛ ነው፡፡

፫. መንፈሳዊነት ጥረት፣ተጋድሎ፣ ውጣ ውረድ ነው

፬. መንፈሳዊነት ጊዜና ቦታ የማይወስነው ነው፡፡

፭. መንፈሳዊነት የኑሮ ሁኔታ የማይወስነው ነው፡፡

በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

15 Oct, 07:20


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት አምስት ቀን የታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት) የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ዕረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ላይ በዐቢይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሐዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሐዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

14 Oct, 15:42


Life after Death According to the Orthodox Tradition offers an accessible and well organized synthesis of the ancient Christian understanding of death and the afterlife. French philosopher and patrologist Jean-Claude Larchet draws both from Scriptures and a multiplicity of early Christian writings, both Greek and Latin, in demolishing false conceptions such as reincarnation, whilst setting forth with clarity an authentically Christian understanding.

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

13 Oct, 19:06


በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 4 የሳምራዊቷን ሴት ከጌታ ጋር የነበራትን ንግግር መሠረት አድርገን የቅዱሳት መጻሕፍት ፍካሬ (Biblical Hermeneutics) እንዴት መሆን አለበት? የሚለውንና ሌሎችንም ርእሰ ጉዳዮች በጥቂቱ ዳሰንበታል።የትኩረት ነጥቦቻችንም፦

- የመጀመሪያው ታሪካዊ ዓውድ (Historical Context) ሲሆን ሳምራውያን እነማን ናቸው? ከአይሁዳውያን ጋር የነበራቸው መሠረታዊ ልዩነት ምንድነው? እና መሠል ነጥቦች ተዳሰውበታል።

- ሁለተኛ የወንጌሉ ክፍል ዋና ጭብጥ ምንድነው? የሚለው ሲሆን ነገረ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ነገረ አምልኮ ወይም ነገረ ቤተ-መቅደስ (Worship and Temple theology) የተዳሰሰበት ነው። '....his encounter with the Samaritan woman (4.1–42) also provides a number of images relating Jesus to the Temple as the place of worship...'{1} እንዲል።

- ሦስተኛ በታሪኩ ላይ የሚስተዋሉ የተዛቡ (distorted) አመለካከቶችን ከታሪካዊው እውነታ እና ከወንጌሉ መሠረታዊ ጭብጥ በመነሳት ያኄስንበት ነው። ተመልካታችሁ ሃሳብ አስተያየታችሁን ስጡን።

ሠናይ ቆይታ!



1.John Behr, John the Theologian and His Paschal Gospel (Oxford University Press, 2019), 144.

https://youtu.be/f2aunKpPPBY?si=x1PP7owrI-fBT5cT

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

11 Oct, 05:53


https://youtu.be/9MpqBWzz4-I?si=oMzNy6bsZmm1cPCS

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

09 Oct, 15:42


https://youtu.be/KwMMbJnxeV4?si=de1djVkY58LAswLZ

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

09 Oct, 06:06


እንኳን አደረሰን!

ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ

++++++++++++++++++++++++++++++++++++

በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ንጉሡ መልኳ (ሥነ ላህይዋ) ውብ የሆነች ብላቴና ሊያገባ ወዶ መልእክተኞችን መርጠው ያመጡለት ዘንድ ላከ። እነርሱም መላ ሀገሪቱን ሲያስሱ ከቆዩ በኋላ ንጽሕት ቅድስት አርሴማ እናታችንን በአንድ በሮሜ ባለ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር አገኟትና ሥዕሏን ስለው ለንጉሡ ላኩለት። ብፅዕት እናታችን ቅድስት ንጽሕት መርዓተ ክርስቶስ ቅድስት አርሴማም ሥነ ላህይዋ እጅጉን ልዩ የሆነ መልከ መልካም ነበረች።

ንጉሡም ይህን ሥዕል እንዳየ በልቡ በእጅጉ ፈቀዳ፤ እንዲያመጡለትም አዘዘ። ይህን እንደሰሙ እኒያ ደናግልና ቅድስት አርሴማ የገዳሙም እመምኔት የሆነችው ቅድስት አጋታ ሸሽተው ወደ አርማንያ ሄዱ። በዚያም ሳሉ ንጉሥ ድርጣድስ የሚገዛው ግዛቱ ነበርና ከንጉሡ ድዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛቸው። እርሱም በመልከ መልካምነቷ በእጅጉ ተስቦ እንዲህ ያለችቱንማ ለራስ ነው እንጂ ማን ሞኝ አለ በሚል ለንጉሡ ድዮቅልጥያኖስ መሥጠቱን ትቶ ለራሱ እዚያው አኖራት። ከደናግሉም ጋራ ካሠራቸው በኋላ ቅድስት እናታችንን ብዙ ሊያታልላት ሞከረ። እርሷ ግን በመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ጥብዓት ያለባት ራሷንም ለቸሩ አምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ ያደረገች ናትና ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች። ንጉሡም ደጋግሞ ቢሞክር አልሆንለት አለ። በኋላም እመ ምኔቷን እንድታባብላት ላካት፤ እመ ምኔቷ ግን ይበልጡኑ አጽናናቻት፤ ‹‹አይዞሽ! እንዲ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ›› ብላ እንዲያውም ይበልጥ አስጨከነቻት። በኋላም ንጉሡ በግድ ይዞ ሊሄድ ቢል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባት ነበርና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለውን ብርቱ ንጉሥ ከመሬት ፈጠፈጠችው። ንጉሡም አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ አፈረ።

ንጉሡም በዚህ ሁሉ ተቆጥቶ ቅድስት አርሴማን ሥቃይዋን ሊያበዛባት ወዶ እኒያን ደናግል እርሷን ፊት ለፊታቸው አሠራትና አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው። እርሷ ግን ‹‹አይዟችሁ!›› እያለች ታጽናናቸው ነበር። የሚደንቀው ትሰቀቃለች ብሎ ያደረገላት ነገር እንዲያውም ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከትበት ነበር። በኋላም ‹‹አንቺንስ እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም›› ብሎ እጅግ ብዙ ሥቃያትን አሠቃያት። ከእነዚህም አንደኛው ሁለቱን ድንግል ጡቶቿን ቆረጠ፤ ይህም አልበቃ ብሎት ሁለቱን ዐይኖቿን አወጣ፤ እርሷም እንዲህ ሳለች እመቤታችን ንጽሕት ድንግል ማርያም የብርሃን ልዩ ዐይኖችን ሰጠቻት። በመጨረሻም ማሠቃየትን በሰለቸ ጊዜ ከእኒያ ከቀሩት ደናግል ጋራ በመስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገቷን ሰየፈና ሁላቸውም የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ። እኒህም ቁጥራቸው ሰባ አምስት ወንዶችና ሠላሳ ዘጠኝ ሴቶች ነበሩ።

ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከ። ቅዱስ ጎርጎርዮስም ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር። (ይኸውም በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ ይገራል)። በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፤ የቅዱሳን ደናግል እና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዕፅም ፍልሠታቸው በዚህ በቅዱስ ጎርጎርዮስ እንዲደረግ ሆነ፤ ይህም ታኅሣሥ ስድስት ቀን ነው፡፡ እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው። ከዚያም በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው እንዲሁ ያከበሩበት ነውና እናከብረው ዘንድ ይገባናል።

ለእግዚአብሔር አምላካችን በዚህች ድንቅ የክርስቶስ ሙሽራ ቅድስት አርሴማ እና በደናግሉም ሁሉ ጸሎት ይማረን፤ ለዘላለሙ አሜን።

ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሣር ዘወርኃ መስከረም

Mahebre kidusan

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

07 Oct, 10:24


Emmaus press application

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

06 Oct, 18:39


- ማኅሌት ወይም የምስጋና ነገረ መለኮታዊ ትርጓሜ (Theology of Doxa) ምንድን ነው?

- ምስጋና ስንል ምን እያልን ነው? ውስጡ ምን ምን ነገሮች አሉት?

- ዘመን ምንድነው? ዘመነ ጽጌስ?

- ተፈጥሮ በማኅሌት ጽጌ ? አባ ጽጌ ድንግል ተፈጥሮን ለማንሳት ለምን ፈለገ? The conception of Creation as a Sacrament....እና ሌሎችም ሃሳቦች እንደመግቢያ ተዳሰውበታል። ተመልክታችሁ ሃሳብ አስተያየት ትሰጡን ዘንድ ግብዣችን ነው።

https://youtu.be/JUQJQqQdHhE?si=l5PAEAItfVbX5nRC

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

06 Oct, 10:46


https://emmauspresset.com/1002/

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

06 Oct, 05:26


ፈሪሳዊነት

https://youtu.be/Dh1Ssdk5HrM?si=lVwKnrIYraZvrYNI


#ዲያቆን_ብርሀኑ_አድማስ

22,260

subscribers

377

photos

96

videos