Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ። @finotehiwott Channel on Telegram

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

@finotehiwott


የቀጨኔ መድኀኔ ዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ (Amharic)

እንኳን ለበጎ ሀይቅና ነዋሪዎች! በዚህ ቦታ ያለን ሰንበት ትምህርት ቤት ወይም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አሉበት። Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት እንደገና አመሰግናለን። ስለዚህ ከላይ በፌስቡክ እናገርላለን። ከዚህ በላይ ከእኛ ጋር በሚሰማበት ዕለት ይህንን ሰንበት ትምህርት ቤት ከግምትና ከታች ለመደጋገም ይህንን ቦታን እንከፍላለን። ለአንዲት ሀይቅ እና አካልታ፣ ለሙሉ ማህበረሰብ ቤትአማራ ቦታ ውስጥ በላይ እንዲገልፅላቸው በተመሳሳይ ሁኔታ ለመምረጥ ለአገርኛ የሥራ መረጃ ዋና ዋና ሊከተለው ይገባል። ለበጎ ሀይቅና ነዋሪዎች በድምፅ እንዲህ ያለው ምክር ከቶ አይመንህቡም።

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

11 Jan, 17:06


መዝሙር ዘዘመነ ልደት
http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

11 Jan, 10:11


http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

10 Jan, 14:55


http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

10 Jan, 14:54


#ጥር_4_ተዝካረ_ፍልሰቱ (በዓለ ስዋሬው ) #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ሐዋርያ ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፤ ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ

ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ
በተለያዩ ቅጽል ስሞች የሚጠራ፤ ጌታቸችንን ሥነ ስቅለት የሳለ፡፡
ከ81ዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 5ቱንና ሌሎች መጻሕፍትን (ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤
#ብዙ ደቀ መዛሙርትን ያስተማረ፤

ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡
✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤)
✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤)
✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /መጽሐፈ ሰዐታት/

፨#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ፤

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ፤
ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡
ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡
ወልደ #ዘብድዮስ ፥
ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥
ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ ፥
ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥ (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡)
ዮሐንስ #ወንጌላዊ ፥
ዮሐንስ #ድንግል
ዮሐንስ #ታዎሎጎስ ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡

1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) ፣ 2. ዮሐንስ ድንግል ፣3. #ዮሐንስ_ፍንው፣4. #ዮሐንስ_ካህን ፣ 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ ፣
6. ዮሐንስ ሥርግው፣7. #ዮሐንስ_ምዑዝ8. ዮሐንስ ቅኑይ ፣ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት ፣ 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ ፣ 11. #ዮሐንስ_ክቡር12. ዮሐንስ ጻድቅ ፣ 13. #ዮሐንስ_ረድእ፣ 14. ዮሐንስ ማኅቶት፣ 15. #ዮሐንስ_ድንግል፣ 16. ዮሐንስ ንጹሕ ፣ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ ፣18. ዮሐንስ መረግድ፣ 19. #ዮሐንስ_ዕንቈ ፣ 20. ዮሐንስ መልአክ ፣21. #ዮሐንስ_ኪሩብ ፣22. #ቁጽረ ገጽ

#ስዋሬው፤
ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡

ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ተጋድሎን አርገጐ ዓለምን ሁሉ ዞሮ ካስተማረ ቦኃላ በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መርጦ መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ አዘዘ ከዚያም ወረዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም ነበር ፡፡ እየጸለየ ወደ ከተማም አሰናበታቸው፡፡

በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝብ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዘ ሁሉም እንደየ ስራቸው ጌታ እንደሚከፍላቸው ነገራቸው ፡፡ካዛም እንዲህ አለ እኔ ከሁላችሁም ደም ንፁሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራቹ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩም አላቸው ፡፡ እነርሱም እጅና እግሮቹን ስመውት ትተውት ሄዱ ሲመለሱም ልብስና ጫማ እንጂ ምንም አላገኙም እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡

ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘጠና ዓመትም ኖረ፤ እንደባላሟሎቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አለቀመሰም፡፡ ‹‹ያ ደቀ መዝሙር አይሞትን እንዲል ›› ዮሐ 21 ስለ ድንግልናውና ስለንጽሕናው ይህ ሁሉ ሆነ፡፡
በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን አሜን

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

09 Jan, 16:06


http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

09 Jan, 16:05


በኋላ ግን የቤተክህነቱ ባለሥልጣናት ታቦቱን ከአስገባን ዘንድ ንግሥትን ጠርተን ማሳየት ግዴታችን ነው፤ ከአዩት ደግሞ በቤቱ አነስተኛነት መቆጣታቸው አይቀርምና ከዚህ ከፍ ያለ ቤት ብንፈልግ ይሻለናል በማለት በፀበሉ ቦታ ላይ በዘመኑ የተሻለ ነው ተብሎ የሚገመተውን የነጋድራስ ሠርፀ ወልድ ፎቅ ቤትን በማስለቀቅ ጥቅምት 4 ቀን 1914 ዓ.ም. ግርማዊት ንግሥተ ነግሥታት ዘውዲቱ በተገኙበት ለ፪ኛ ጊዜ ታቦተ ቅዱስ ዮሐንስ ከመጀመሪያ የሳር ክዳን ጎጆ ቤት ወደ ሁለተኛው ፎቅ ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡
የመጀመሪያው ሕንፃ ክብ ቤ/ን (ዛሬ የእመቤታችን ቤ/ን ያለበት) የመሠረት ድንጋይ በፊታውራሪ አባ ይሬ ቦታ ላይ በ1924 ተጣለ፤ ከ2ት ዓመታት በኋላም በ1926 ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ አልቆ ንግሥት ባሉበት ተመርቋል፤ ንግሥቲቱም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ አንሶ በመሠራቱ ቅር ተሰኝተዋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ታላቅ ቤ/ንን እሠራለታለሁ እስከዚያው ድረስ ከመቃኞው ወደ አዲሱ ክቡ ቤ/ን ይግባ ብለው ገብቷል፡፡ ንግሥቲቱም ያሰቡትን ቤ.ን ሳይሠሩ በ1922 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ዐርፈዋል፡፡

✧ #የአዲሱ_ሕንፃ_ቤተ_ክርስቲያን_መሠራት፡፡
የዐፄ ኀይለ ሥላሴ ልጅ የሐረሩ መስፍን ልዑል መኮንን የተወለደው በዮሐንስ እለት ሲሆን የክርስትና ስሙም አርአያ ዮሐንስ ነው፡፡ አርአያ ዮሐንስም ቅዱስ ዮሐንስን በስሙ የተሰየመበት በመኾኑ ከብላታ ተሰማ ደባልቄ ጋራ በመሆን አባቱ አፄ ኀይለ ሥላሴን የደብረ ነጐድጓድ ቅ/ዮሐንስ ቤ/ንን በአዲስ መልክ አሻሽለው እንዲሠሩለት ይጠይቃቸዋል፡፡ ነገር ግን አባቱ እኛ እንሠራዋለን የሚል መልስ ሰጡት፤ ለጉዳዩ ብዙም ትኩረት ሳይሰጡት፥ ሕንፃውም ሳያሠራ ቆየ፡፡

ብዙም ሳይቆይ መስፍኑ ልጃቸው በቅዱስ ዮሐንስ እለት በግንቦት 4/1949ዓ.ም. አረፈ፡፡ ንጉሡም የልጃቸውን ምኞት ባለመፈጸማቸው ተጸጽተው፤ ልጃቸው ባረፈ በ12ኛው ቀን ወደ ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ን በመምጣት የቤተ ክርስቲያኑን ጥንተ ታሪኩን ጠይቀውና ተረድተው፥ ቤተ ክርስቲያኑን ተሳለመውና አፀዱንና ቅጥሩን ተመልክተው የልጃቸውን ራዕይ ለማሳካት በዘመናዊ አሠራር አዲስ ቤ/ን እንደሚያንፁ ቃል ገቡ፡፡
በቃላቸው መሠረትም አፄ ኀይለ ሥላሴ ራሳቸው ተገኝተው በ1960 የመጀመሪያ መቃኞ ቤተ ክርስቲያን ባለበት ቦታ ላይ የመሠረት ደንጊያ ተጣለ፡፡ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ አርቴክት ኢጣሊያዊ ነው፡፡ በዐፄ ኀይለ ሥላሴ የገንዘብ ሥጦታም ከ3 ዓመታት በኋላ በ1963 ሕንፃው አልቆ ተመረቀ፤ የሕንፃ ሥራው የተጓተተበት ምክንያትም በ1960 በጄኔራል መንግሠቱ ንዋይና በወንድሙ ግርማሜ ንዋይ መሪነት በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት የሕንፃው ሥራ እየተቋረጠ እንደገና ሲጀምር ጊዜ በመውሰዱ ነው፡፡
ታቦተ ዮሐንስ ከመጀመሪያው ክብ ቤተ ክርስቲያን ወጥቶ በልዩና ባመረ ኹኔታ፥ በመስቀልኛ ቅርጽ፥ በዘመናዊ አሠራር (በአዲስ አበባ በአሠራሩ አምሳያ በሌለው) ወደተሠራው ሕንፃ ቤ/ን ገባ፡፡ በመጀመሪያ በተሠራው የክብ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም ከታቦተ ዮሐንስ ጋር ታቦተ ማርያም አብራ በድርብነት ትኖር ነበርና፤ #በ1963 ታቦተ ዮሐንስ አዲስ ወደታነጸው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ ታቦተ ማርያም ደግሞ በዚሁ በቀድሞው ክብ ቤ/ን ቆየች፤ ስያሜዋም መካነ ጎልጎታ ማርያም ኾነ፤ በዚህም ምክንያት የደብሩ ሙሉ መጠሪያ ስያሜ ደብረ ነጐድጓድ ዮሐንስ ብቻ በመባል ፈንታ #ደብረ_ነጐድጓድ_ዮሐንስ_ወመካነ_ጎልጎታ_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን ሆነ።

✧ #የቤተ_ክርስቲያኑ_አስተዳደር
ከ1922 እስከ 1960 ድረስም የተዳደረው በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ን ሥር ሲኾን የሚያስተዳድሩት አለቃውም ኾነ ገበዙ የገነተ ጽጌ አለቃና ገበዝ ነበሩ፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ በተመሠረተበት ወቅት የሚያገለግሉት በ2ት ምድብ የተመደቡ ሰሞንኛ 10 አገልጋይ ካህናት ብቻ ነበሩ፡፡ ርስት ጉልት ስላልተጎለተለት አገልጋዮቹ የሚተዳደሩትም በደመወዝ ነበር፡፡ ደመወዛቸውም የቀሳውስት በወር 10ብር፥ የዲያቆናት በወር 5 ብር ሲኾን ገንዘቡ የሚከፈለውም ከቤተ ክህነት ለቤተ ክርስቲያኑ ከተበጀተ ገንዘብ ነበር፡፡

✧ #ጠበል_ቤት_
በጠበል ቤቱ ግቢ ውስጥ 9ኝ ጠበሎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም፤
1ኛ) የሥላሴ ጠበል፤
2ኛ) የእግዚአብሔር አብ ጠበል፤
3ኛ) የመድኀኔ ዓለም ጠበል፤
4ኛ) የእመቤታችን የማርያም ጠበል፤
5ኛ) የኪዳነ ምሕረት ጠበል፤
6ኛ) የቅዱስ ሚካኤል ጠበል፤
7ኛ) የቅዱስ ገብርኤል ጠበል፤
8ኛ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ጠበል፤
9ኛ) የአቡነ ተክለሃይማኖት ጠበል ናቸው፡፡

#በደብሩ_የሚከበሩ_ክብረ_በዓላት፤
✧ ጥር 4፤ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በዓለ ሥዋሬው፤
✧ መስከረም 21፣ ኅዳር 21፣ ጥር 21፣ ግንቦት 21፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል፤
ኅዳር 12፣ ሰኔ 12፤ የቅዱስ ሚካኤል በዓል፡፡

✧ #ታቦተ_ሕጉ_ወጥቶ_ባይከበርም #የሊቁ_የቅዱስ_ዮሐንስ_አፈ_ወርቅ_ታቦትም_ይገኛል፡፡
አምላካችን ደብሩን ይጠብቅልን፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

08 Jan, 17:22


http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

08 Jan, 17:22


#ጥር ፫፤
የደብረ_ሊባኖስ_ገዳምን_የመሠረቱና_በስማቸው_የተሠየመላቸው እና የእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳምን_ጸበል_ያፈለቁ የታላቁ አባት አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ በዓለ ዕረፍት ነው ።

#በአ.አ. #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት ቀድሞ በቅዳሴና በውዳሴ ታቦተ ሕጋቸው ሲከበር የቆየው የአቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ታቦተ ሕጋቸው #ቅዳሜ_ጥር 3/2017 ዓ.ም.
ሰባተኛ ጊዜ_ታቦተ_ሕጋቸው_ወጥቶ_ይከብራል፡፡ (ሁላችሁም እንድትገኙ ገዳሟ ጥሪዋን አስተላልፋላች)፡፡

አባ ሊባኖስ #የደብረ_ሊባኖስ_ገዳምን_የመሠረቱና_በስማቸው_የተሠየመላቸው፤
፠ ቅዱስ ላሊበላ ከ11ዱ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱን በስማቸው ያነፀላቸው፡፡
፠ #ከደረቅ_ዐለት_ላይ_ውሃ_እያፈለቁ_ድውያንን_የሚፈውሱ_ተአምረኛ_አባት
፠ በኤርትራ አካለ ጉዛይ ገዳመ መጣዕ፣ በአኵሱም ከተማ አጠገብ፣ በላስታ ላሊበላ፣ ደብረ ወርቅ አቡነ ሊባኖስ ገዳም፣ እንዲሁም ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በአ.አ. እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ገዳም ክብረ በዓል የሚከበርላቸው።

፠ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ሊድሯቸው ሲሉ መመነን በመፈለጋቸው መልአክ በሌሊት መጥቶ ወደ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡
፠ አባ ጳኩሚስም ሥርዐተ ገዳምን፥ አስኬማ መላእክትን፥ ቅናተ ዮሐንስን አስተማሯቸው፤ አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡
፠ ቀድሞ የመራቸው መልአክ ከአባ ጳኩሚስ ‹‹ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድሎህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ›› አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአኵሱም ተቀመጡ፡፡
፠ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው (ቀድሞ የዋልድባን ገዳም ባስፋፉ አባቶች የተመሠረተችውን #የእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳምን እስፋፍተው፡፡) ተመልሰው ወደ አኵሱም ሄዱ፡፡
፠ በአኵሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ፥ ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአኵሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል ‹‹ተራ ውሃ ነው›› ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ ‹‹አምላከ አባ ሊባኖስ›› ብሎ አመሰገነ፡፡ (ስዕላቸው የሚገልጸው ይህንን ተአምር ነው፡፡)
፠ ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው ‹‹ምትሃት ነው የሚያሳየው›› ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡
፠ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአኵሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ፤ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው ‹‹አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን›› ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡

፠ ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ (የአሁኗ ደብረ ሊባኖስ) መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው ‹‹ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ (አቡነ ተክለ ሃይማኖት) ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኮሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል›› አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡
፠ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አኵሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም ‹‹ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ›› አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹ሊባኖስ ዘመጣዕ›› የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው አፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡

፠ ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ አፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡
፠+፠ በመጨረሻም ጥቅምት 2 ቀን ተፀንሰው ፤
፠+፠ ሐምሌ 3 ቀን ተወለደው፤
፠+፠ በ140 ዓመታቸው ጥር 3 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡
፠+፠ ቅዳሴ ቤታቸው ደግሞ ሐምሌ 3 ነው፡፡ ይኸውም ለመጀመሪያ ጊዜ በዐፄ ገብረ መስቀል ጊዜ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተመረቀበት ዕለት ነው፡፡
* እኛም ለክብረ በዓሉ የሚሆነውን ከዋይዜማው ጀምሮ ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት እነሆ ብለናል፡፡

#እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም

፠ እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት በ485 ዓ.ም. የሸዋ አባቶች የዐብዩ መድኀኔዓለምንና የበረከት ኪዳነ ምሕረት ታቦትን ይዘው ለ3 ወራት የተሰባሰቡባት ስትሆን፤ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እንጦጦ ላይ አስቀምጠውና ገዳሟን መሥርተው፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ይዘው ወደ ዋልድባ በመሄድ ቀድሞ ጌታችን የገደመውን ገዳም ለ2ኛ ጊዜ አስፋፍተውታል፡፡
፠ ከ16 ዓመታትት በኋላ በ500 ዓ.ም. ደግሞ አቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ከአኵሱም ወደ ሸዋ ሲመጡ ሐመረ ኖኅን በገዳምነት ገድመው ጠበሏን አፍልቀው ሕሙማንን ፈውሰው ተመልሰዋል፡፡
፠ በ197 ዓ.ም. አንድ ምዕመን ለአቡነ ተክለሃይማኖት አስፈቅደው፤ ገድላቸውን ከአኵሱም አጽፈው በማምጣት ማኅሌቱ እንዲቆም፣ ገድላቸው እንዲነበብ፤ 50 ብር እየከፈሉ የጻድቁን ዝክር እንዲገለገል አስደርገዋል፡፡
፠ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ይመስገን፨

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

08 Jan, 05:28


#ጥር ፫፤ #የአቡነ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው ፲፩ ገዳማትና አድባራት፡፡

(አባ ሊባኖስ በሃገራችን ላይ 80 ገዳማትን መሥተዋል)
በ79 ገዳማትና አድባራት ላይ ሲከበሩ ዐበይቶቹ የሚከተሉት ናቸው፤

#በአዲስ_አበባ_የሚከብርባቸው_፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ እንጦጦ፤
ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ ጊዮርጊስ (4 ኪሎ) (ከመርካቶ) → ሽሮ ሜዳ → እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት፡፡
#ለቅምሻ_በአጭሩ፤ #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም
፠ እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት በ485 ዓ.ም. የሸዋ አባቶች የዐብዩ መድኀኔዓለምንና የበረከት ኪዳነ ምሕረት ታቦትን ይዘው ለ3 ወራት የተሰባሰቡባት ስትሆን፤ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እንጦጦ ላይ አስቀምጠውና ገዳሟን መሥርተው፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ደግሞ ይዘው ወደ ዋልድባ በመሄድ ቀድሞ ጌታችን የገደመውን ገዳም ለ2ኛ ጊዜ አስፋፍተውታል፡፡
፠ ከ16 ዓመታትት በኋላ በ500 ዓ.ም. ደግሞ አቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ከአኵሱም ወደ ሸዋ ሲመጡ ሐመረ ኖኅን በገዳምነት ገድመው፥ ጠበሏን አፍልቀው፥ ሕሙማንን ፈውሰው ተመልሰዋል፡፡
፠ በ1967 ዓ.ም. አንድ ምዕመን ለፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት አስፈቅደው፤ ገድላቸውን ከአኵሱም አጽፈው በማምጣት ማኅሌቱ እንዲቆም፣ ገድላቸው እንዲነበብ፤ 50 ብር እየከፈሉ የጻድቁን ዝክር እንዲገለገል አስደርገዋል፡፡
፠ ባለውለታዋን ዘንግታ የቆየችው እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳምም ከ በኋላ በዕለተ እሑድ ጥር 3/2012 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ታቦተ ሕጉን አውጥታ አክብራለች፨

፪. አያት ጣፎ መካነ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ን፡፡ (በድርብነት ይከበራል)
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አያት 2 ኮንዶሚንየም
ትራንስፖርት፤ ከመገናኛ → አያት(በሲኤምሲ) አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ
ወይም ከመገናኛ በኮተቤ ጣፎ /አባ ኪሮስ ጋር ወርደው/ በባጃጅ (በታክሲ) ያገኙታል፡፡

#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከብርባቸው_፱ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ደብረ ወርቅ ገዳመ መጣዕ አቡነ ሊባኖስ፤ (በ523 ዓ.ም. በጻድቁ በአቡነ ሊባኖስ የተገደመና በአፄ ገብረ መስቀል የታነጸ፥ ገደል ወገብ ላይ የታነፀና የሚያስደንቅ፡፡) (የጻድቁ የከበረ አጽም የሚገኝበት፥ ሙት ያስነሳበት፥ ዕውር ያበራበት ገዳም ነው)
አድራሻ፤ ደቡብ ኤርትራ፥ አካለ ጉዛይ አውራጃ፥ ሃም ታርካ፡፡
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ (በአውሮፕላን) → ኤርትራ → አካለ ጉዛይ → ሃም ታርካ፡፡

፪. አኵሱም አጠገብ የሚገኝ አባ ሊባኖስ፤ (ጻድቁ የዋሻ በዓት ሠርተው የጸለየበት፥ 7ት ዓይነት ጠበል ያፈለቀበት፤ አንዲት እናት ውኃ ነው ብላ ብትዳፈር ልጇ ሞቶባት እንደ ኤልያስ ያስነሳበት፥ የአከባቢው ካህናት ቢያድሙበት እንደ ኤልያስ በዚህ አካባቢ ላይ ለ3ት ዓመት ዝናብ እንዳይዘንብ የከለከለበት ኋላ ደግሞ በይቅርታ ቢጠይቁት ዝናብ ያዘነበበት ነው)
(ልጅ ያጡ የሚወልዱበት መታሻ ደንጊያ ያለበት፥ ከዐለት ላይ የሚፈልቅ ተአምረኛ ጠበል ያለበት)
(ገዳሙ ዋሻና ለእኅቶች ደግሞ ክብ ሕንፃ ቤ/ን አለ)
አድራሻ፤ አኵስም ሃገረ ስብከት
ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ በጎንደር/በሽሬ/ → አኵስም → የ10 ብር ትራንስፖርት(የ2ሰዐት የእግር መንገድ) ወይም
ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ በደሴ/ወልድያ/መቀለ/ → አኵስም → የ10 ብር ትራንስፖርት(የ2ሰዐት የእግር መንገድ)

፫. ተንቤን አምበራ አቡነ ሊባኖስ (በአፄ ገብረ መስቀል የታነፀ)
አድራሻ፤ ትግራይ
ትራንስፖርት፤ ከአኵሱም → ተንቤን

፬. ላስታ ላሊበላ ቤተ አባ ሊባኖስ (ቅዱስ ላሊበላ ለ23ት ዓመታት ካነጻቸው አንዱ፥ በላስታ ከሚገኙት 11ዱ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ አንዱ የኾነና ከ11ዱ ሙሉ ለሙሉ ከተራራ ላይ ተፈልፍሎ ባለመውጣቱ በአሠራሩ ልዩ የኾነ)
አድራሻ፤ ሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ላስታ፥ ላሊበላ ከተማ፡፡
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ በደሴ/በጋሸና/ → ላሊበላ
ወይም ከአ.አ. (በአውሮፕላን) → ላሊበላ
ወይም ከጎንደር (ባህር ዳር) /በወረታ/ /ደብረ ታቦር/ /ጋሸና/ → ላሊበላ
ወይም ከመቀለ በወልድያ መስመር/ጋሸና/ → ላሊበላ

፭. ዛራ ሐሙሲት አካባቢ የሚገኘው አባ ሊባኖስ (ቅዱስ ላሊበላ ለ23ት ዓመታት ካነጻቸው አንዱ)
አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት
ትራንስፖርት፤ ከባህር ዳር /በጎንደር መስመር/ → ሐሙሲት

፮. ጎንደር ግራርጌ (ቆላ ድባ) ፈለገ ሕይወት አቡነ ሊባኖስ፤ (በአፄ ገብረ መስቀል እንደተመሠረተ የሚነገርለት፥ አጸዱ እጅግ በጣም የሚማርክ /ዕድሜ ጠገብና አርስ በእርሱ የገጠመ 4 ትላልቅ ወርካና 4 ጽድ የሚገኝበት፤ ወርካውን ፈልፍለው መነኰስ ይኖሩበት የነበረው ለምስክር ቆሞ የሚገኝበት፥ 1ዱ ጽድ በ1880 አካባቢ ወድቆ እስካሁን ዝናብና ፀሐይ እየፈራረቀበት ሳይበሰብስ የሚገኝበት)፤ ውሎ ቅዳሴ የሚቀደስበት፤ የአከባቢው ገበሬ እህሉን ወደ ጎታው ከቅዳሴ በኋላ የሚያስገባበት የበረከት ቃል ኪዳን የተሰጠው ምድር፡፡
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደንቢያ ወረዳ፥ ቆላ ድባ ከተማ፡፡
ትራንስፖርት፤ ከጎንደር (አዘዞ) → ወደ ጎርጎራ መስመር (በደረስጌና በቆላ ድባ መሃል ላይ ያገኙታል) (በ25 ኪ.ሜ አስፓልቱ ዳር)

፯. በመንዝ ቀያ ሀገረ ገራዴ አባ ሊባኖስ አፅመ ቅዱሳን ዋሻ (ፈዋሽ ጠበልና አስገራሚ ዋሻ ያለበት)፡፡
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ፥ ዘመሮ ከተማ፥ በንዲ ቀበሌ፡፡
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ዘመሮ → 9 ኪ.ሜ ያህል እንደተጓዙ በንዲ ቀበሌ (ከአዲስ አበባ 328 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል)

፰. መንዝ ላሎ አንጀትላ አቡነ ሊባኖስ ገዳም፤
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መንዝ፥ ዘብር፥ ላሎ፥ አንጀትላ፡፡
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ዘብር(247 ኪ.ሜ.) → የ2ት ሰዐት የእግር መንገድ → የአንጀትላ አቡነ ሊባኖስ ገዳም፡፡

፱. *** ነገር ግን የመሠረቱት፥ ለ40 ዓመታት በዓት ሠርተው የኖሩበትና፥ በስማቸው የሚጠራው ታላቁ ገዳም ደብረ ሊባኖስ ግን ባለፉት 10ር ዓመታት ውስጥ ገድላቸውን በግእዝና በአማርኛ ከማሳተም የዘለለ የሚጠበቅበትን ሥራ አልሠራም፡፡
(ያልጠቀስናቸው ካሉ በውስጥ አሳውቁን)
/ #ክብረ_በዓላት #Feasts /
/ #ገዳማትና_አድባራት #Monasteries_and_Churches /

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

07 Jan, 14:42


ያለመሰልቸት መድኃኔዓለምን ሲያገለግሉ የኖሩት መምሬ ዋለ አባተ አረፍተ ዘመን ገታቸው በዛሬው እለት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

    "እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ አቡነ ወልደ ጊዮርጊስ"
ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ያድልልን የአባታችንንም ነፍስ ከደጋግ አባቶች ጋር ያሳርፍልን።

http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

06 Jan, 11:53


http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

02 Jan, 10:37


ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እና አካባቢው - 1951 ዓ.ም

ኢቲሳ በሰሜን ሸዋ በቀድሞው ቡልጋ አውራጃ የሚገኝ እና ከ800 ዓመት በፊት እ.ኤ.አ በ1215 ዓ.ም አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱበት ታሪካዊ ቦታ ነው።

University of Monash/Asian Collections/Forsyth, Elliott Christophe Photographs:
https://repository.monash.edu

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

01 Jan, 08:14


http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

01 Jan, 07:44


http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

01 Jan, 05:48


እንኳን አደረሳችኁ
በዓለ_ልደቱ_ለሐዲስ_ሐዋርያ_ፀሐይ_ማር_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ታኅሣሥ 24 1196 ዓም በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ጽላልሽ እቲሣ ተወልደው በአጠገቡ በምትገኛዋ ደብረ አጋዕዚት ክርስትና_ተነሡ፡፡
#አባታቸው ቅዱስ ጸጋ ዘአብና እናታቸው ቅድስት እግዚእ ኀረያ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው በአካባቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻንና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡
#በ7ት ዓመታቸው ከግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ ከዮዲት ጉዲት በኋላ ሃገራችን ሰሜኑና ደቡቡ ተቆራርጧል፤ የሐሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ሐዲስ ሐዋርያ ያስፈልግ ነበርና አምላካችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ጠራ፡፡
#አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት ከአባታቸው ጋር አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር  ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው በሸዋና በዳሞት በስብከተ ወንጌል አገለገሉ፡፡ ከዚያም፤
#በመጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ላይ ገዳማቸውን ደብረ ጎል ገድመው ወደሚገኙት ታላቁና ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወደኾኑት ጻድቅ አባት አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ዐሥር ሁለት ዓመታት በትምህርትና በሥራ (በአርድእትነት) አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር፡፡
#በ1216 ዓ.ም. አካባቢ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገሳም ገብተዋል፤ በዚሁ ገዳምም ከመመንኰሳቸው በፊት ሰባት ዓመት ከመነኰሱም በኋላ ሦስት ዓመት በድምሩ ለ10 ዓመታት በትምህርት፣ በእደ ጥበብ ሥራ፣ በአገልግሎትና ሥርዓተ ምንኩስናን እያጠኑ ቆይተዋል፡፡
#ከሐይቅ ወጥተው በዘመኑ በሥርዐተ ምንኩስናና በትምህርት ብሎም በጥበበ እድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ወደ ነበረው ወደ ደብረ ዳሞ በመሄድ በየገዳሙ አበምኔት ከሆኑት ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ መንፈሳዊ ትምህርት ፣ ሥርዐተ ምንኩስናና ጥበበ እድ ሲማሩ ለ12 ዓመታት ቆዩ ፡፡ ያነጹት ፍልፍል ድንጋይ ዋሻ፣ መጻሕፍት ሲጽፉ ቀለማቸውን ያስቀምጡባቸው የነበሩትን ሽንቁሮች ዛሬም በደብረ ዳሞ ማየት ይቻላል፡፡
#በደብረ ዳሞ የነበራቸውን ቆይታ ጨርሰው በገመድ ሲወርዱ ሰይጣን በቅንዐት መጥቶ ገመዱን በጠሰባቸው እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ወቅት የሚበሩበትን እንደ መላእክት ክንፍ ሰጣቸው፡፡
#ለአምስት ዓመታት #አኵስምን_ዋልድባን እንዲሁም ሎሎች የትግራይ ገዳማትን እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ቆዩ
#ከሸዋ በወጡ በሃያ ሁለት ዓመት (እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ሲሆን) ለበለጠው ክብር እና ርእይ በግብጽ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ተሻገሩ፡፡
#ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ በሐይቅ በኩል አድርገው ደብረ ጎልን ተሳልመው በሚዳ እና በመርሐ ቤቴ በኩል ወደ ሸዋ በመምጣት ከዮዲት ዘመን በኋላ በመንፈሳዊ ሕይወት የተጎዳውን ሸዋን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በመዘዋወር ለዐሥር ዓመታት ያህል አስተምረዋል፡፡
#አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ፣ የደከመው በረታ፣ የጠፋውም ተገኘ፡፡ ሐዋርያትን ለማፍራት እንዲችሉ አንድ ገዳም ለመመሥረትና ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር አሰቡ፡፡ እናም ወደ ደብረ አስቦ ገዳም ገቡ ፡፡ ቦታውን አስተካክለው እና ከደብረ ዳሞ እና ከሐይቅ የተከተሏቸውን ጥቂት ደቀ መዛሙርት ይዘው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ልክ እንደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሁሉ ሦስቱን ነገሮች ያካተተ አገልግሎት ጀመሩ፡፡ ምንኩስና፣ ትምህርትና ሥራ፡፡ መነኮሳቱ መንፈሳዊ ትምህርት ይማራሉ፤ በሕገ ገዳም ይመራሉ፤ ለራሳቸው እና ለአካባቢው ሕዝብ ርዳታ የሚሆን እርሻ ያርሳሉ፡፡
#ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ገዳማቸውን አደራጅተው፣ ስብከተ ወንጌልንም አስፋፍተው ካደላደሉ በኋላ በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አስቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ፡፡
#አገልግሎታቸውን ፈጽመው ነሐሴ 24 ቀን 1297 ዓ.ም. በ99 ዓመታቸው ዐረፉ፡፡
✤✤ #እቲሣ_ገዳም_
#በቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃና አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተመሠረተ፤ ሲመሠረትም በታቦተ ኢየሱስና አርባዕቱ እንስሳ ነው፤
#ሊቀ ካህናት አበይድላ ከአኵስም 300 ታቦታትና 300ካህናት ይዞ መጥቶ በጽላልሽ የተቀመጠባት ናት፤
#ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱባት (የተወለዱባት ጠፍጣፋ ደንጊያ አሁንም በቦታው አለች)፣
#አባታቸውና ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእኀረያ የተወለዱበት፤ ኋላም ክብሩ አጽማቸው ያረፈበት ነው፡፡
#ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ጸልዮባታል፤
#ቅዱስ ላሊበላ 7 ዓመት ጸልዮባታል፤
#ተሰዓቱ ቅዱሳን 20 ዓመት የጸለዩበት፤
#ሐርቤ በሚባለው ቦታ ላይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 7 ዓመት ጸልየውበታል፤
#ታቦተ ጽዮን 12 ዓመት (ከ9ሺህ ሕዝብ) ጋር መጥታ ኖራበታለች፤
#በአምሳለ ሲዖል የተሠራ አስደናቂ የጨለማ ዋሻ ያለበት ነው፤
#ብዙ የታሪክ ቅርስ ያለበት ነው፤
#በቅዱስ ሚካኤልና ጸጋ ዘአብ ቤተ ክርቲያን ውስጥ ካየን በኋላ፤ እዚሁ ቦታ በሚገኘው ፈዋሽ ጠበል ተጠምቀንና ጠጥተን ጕዟችንን ወደ
ቦታው ከአ.አ በቅርብ ርቀት በደብረ ብርሃን መንገድ አሌልቱ ከተማ ላይ በመታጠፍ ይገኛል፡፡
#ሥርዐተ_ማኅሌቱን እንደየደብራችሁ ይትበሃል እንድትጠቀሙበት (በላይ ቤትና በታች ቤት) (#ዘአባጃሌ_ተክለ_ሃይማኖትና_ዘአደባባይ_ተክለሃይማኖት) አዘጋጅተነዋል፡፡
ጸሎትና በረከታቸው ፤ ረድኤትና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

06 Dec, 13:54


@finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

06 Dec, 13:54


#ዘመነ_አስተምህሮ

በቤተ ክርስቲያናችን የወቅት አከፋፈል ሥርዓት #ከኅዳር_፮ እስከ #ታኅሣሥ_፯ ቀን የሚገኘው ወቅት ‹#ዘመነ_አስተምህሮ› ይባላል፡፡ ቀጣዩ ወቅት (ዘመነ ስብከት) ዕለተ ሰንበትን ጠብቆ የሚገባ በመኾኑ ይህ ወቅት አንዳድ ጊዜ እስከ ታኅሣሥ ፲፫ ቀን የሚዘገይበት ጊዜም አለ፡፡ ‹ዘመነ አስተምህሮ› የሚለው ሐረግ ትርጕሙም በሃሌታው ‹#ሀ› (‹#አስተምህሮ› ተብሎ) ሲጻፍ የቃለ እግዚአብሔር ማስተማሪያ ማለትም የትምህርተ ወንጌል ዘመን ማለት ነው፡፡ ሥርወ ቃሉም ‹‹መሀረ/አምሀረ – አስተማረ፤ ለመምህር ሰጠ፤  መራ፤ አሳየ፤ መከረ፤አለመደ››  ወይም ‹‹ተምህረ – ተማረ፤ ለመደ›› የሚለው የግእዝ ግስ ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፭፻፸፱)፡፡ 

ይኸውም የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ ርኅራኄ፣ ትዕግሥትና የማዳን ሥራውን የሚመለከት ትምህርት በስፋት የሚቀርበበት ጊዜ ነው፡፡

ቃሉ በሐመሩ ‹‹#ሐ›› (‹#አስተምሕሮ› ተብሎ) ሲጻፍ ደግሞ የምሕረት፣ የይቅርታ ዘመን ማለት ነው፡፡ ሥርወ ቃሉም ‹‹መሐረ – ይቅር አለ፤ ዕዳ በደልን ተወ›› ወይም ‹‹አምሐረ – አስማረ፤ ይቅር አሰኘ፤ አራራ፤ አሳዘነ›› የሚለው የግእዝ ግስ ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፭፻፹፬)፡፡

ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ዘመነ አስተምሕሮ ስለ እግዚአብሔር ቸርነትና ርኅራኄ፤ እርሱ በደላችንን ዅሉ ይቅር እንደሚለን እኛ ምእመናንም እርስበርስ ይቅር መባባል እንደሚገባን ትምህርት የሚሰጥበት ጊዜ ነው፡፡

በቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት እንደ ተቀመጠው በዘመነ አስተምሕሮ ውስጥ የሚገኙ ሰንበታት (እሑዶች)

1ኛ. #አስተምሕሮ፣ (ከኅዳር ፮–፲፪)
2ኛ. #ቅድስት፣ (ከኅዳር ፲፫–፲፱)
3ኛ. #ምኵራብ፣ (ከኅዳር ፳–፳፮)
4ኛ. #መጻጉዕ፤ (ከኅዳር ፳፯ እስከ ታኅሣሥ ፫) እና
5ኛ. #ደብረ_ዘይት፤ (ከታኅሣሥ ፬ – ፮) ተብለው ይጠራሉ፡፡

ከመጀመሪያው ሳምንት (ከአስተምሕሮ) በቀር የአራቱ እሑዶቹ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ የሰንበታቱ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ጋር ተመሳሳይ ይኹን እንጂ በእነዚህ ሳምንታት ሌሊት የሚዘመሩ መዝሙራት፣ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ #ምንባባትና_የሚቀርቡ_ትምህርቶች ግን #በምሥጢር_ይለያያሉ፡፡

ትምህርቶቹ ይለያያሉ ስንልም በዚህ ወቅት የሚነገረው ምሥጢርና ይዘት በወቅቱ ላይ የሚያተኵር መኾኑን ለመግለጽ ነው እንጂ በየትኛውም ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን የሚቀርበው ትምህርት አንዱ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው። ሳምንታቱን በዚህ መልክ የከፋፈለውም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ይህንንም ከመጽሐፈ ድጓው መመልከት ይቻላል (ድጓ ዘአስተምህሮ)፡፡
የአራተኛ ሳምንት መጻጉዕን መዝሙር እና ምንባባት እነሆ ብለናል...
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Dec, 15:14


t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Dec, 12:14


በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም እና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከ1983ዓ.ም ጀምሮ ያለመሰልቸት በትሩፋት ሲያገለግሉ የነበሩት መዘምር መኮንን አበራ ከዚህ ዓለም ድካም በዛሬው ዕለት አርፈዋል ስርዓተ ቀብራቸውም ሲያገለግሉ በቆዩበት ደብር በቀጨኔ ደብረሰላም መድኃኔዓለም በ25/03/2017ዓ/ም  ከ8-9 ይፈፀማል ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ያድልልን የአባታችንንም ነፍስ ከደጋግ አባቶች ጋር ያሳርፍልን።

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Dec, 11:00


t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Dec, 10:59


#ኅዳር_26
#_ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተማርያም፡፡

፠ አቡነ_ሀብተማርያም በሽዋ (የራውዕይ /ቡልጋ/) ከአባታቸው ፍሬ ቡሩክ ከእናታቸው ቅድስት ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡
፠ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መናኝ ነበረች፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡
፠ ጻድቁ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ ይህንንም በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል፤ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡
፠ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ መንነዋል፤ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኰሱ በኋላም ብዙ ትርፋትንና ተጋድሎን ሠሩ፡፡ ለአብነትም፤
*ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ፤
*በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ፤
*በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ፤
*ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ነው፤
*በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ፤
*ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ፥ ክቡር ደሙን ይጠጣሉ፤
*በልባቸው ውስጥ በፍጹም ቂምን፥ መከፋትን አላሳደሩም፡፡
* ረአዬ ኅቡዓት በመባል ይታወቃሉ፡፡
* በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርኩት ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡
* ‹‹#ጽድቅና_ትሩፋት_እንደ_ሀብተ_ማርያም፠››
፠ ጌታችን ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔዱ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው፤
* ‹‹ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ፤ ስለ ምናኔህ፣ ስለ ተባረከ ምንኵስናህ፣ ስለ ንጹሕ ድንግልናህ፣ ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ፣ ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ፣ ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ፡፡››
* በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን፤ 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ፡፡ በስምህ የሚለምኑ፤ በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ ‹አማንየ በርእስየ› ብዬሃለሁ›› አላቸው፡፡
* ቅዱሳን መላእክትም ‹‹ሀብተ ማርያም ወንድማችን›› ሲሉ አቀፏቸው፡፡ ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው፡፡ ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች፡፡ በዝማሬም ወሰዷት፡፡
✤ ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤
1ኛ. #_መብረቅ፣
2ኛ. #_ቸነፈር፣
3ኛ. #_ረሃብ፣
4ኛ. #_ወረርሽኝ፣
5ኛ. #_የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
፠ በተሰጣቸው ቃል ኪዳንም ከላይ ያሉትን 5ት መቅሰፍቶች የሚያርቁ በመሆናቸው፤ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን በደብረ ሊባኖስ ገዳም እነዚህ 5ቱ መቅሰፍቶች እንዳይቀርቡ የሀብተማርያም ካህናት ከኅዳር 1-7(10) ማዕጠንት ያጥናሉ፤ ደብረ ሊባኖስ ገዳምም ለደብረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማርያም ገዳም 1ድ በሬ ስጦታን ያበረክታሉ፡፡
፠ በዛሬው ዕለት በኅዳር 26 ባረፈ ጊዜ፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው፤ በዝማሬ ፥ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በጻድቁ መቃብር ቀበሩት፡፡
(ከወርቅ ንፁህ ፥ ከብርም የጠራ ፥ ከሁሉ የሚበልጥ ፥ የተመረጠ ፥ ሀብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡)
#_በዛሬዋ ዕለት #በናግራን ያሉ ክርስቲያኖች በ6ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት የኾኑበት ዕለትም ነው፡፡

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Dec, 08:13


፠ ጻድቁ በአጠቃላይ 44 ዓመታትን ማለትም፤
* 20 ዓመት በይትባረክ ዘመነ መንግሥት
* 15 ዓመት በይኵኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት
* 9 ዓመት በአግብዓ ጽዮን ዘመነ መንግሥት የኖሩ ሲኾን፤ ለ44 ዓመታት በገዳም ቆይታቸው ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም፥ ለሰውነታቸውም(ለጎናቸውም) ምኝታን አላስለመዱትም፡፡
‹‹እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ፤
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ፡፡›› እንዲል፡፡
ጻድቁ በሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩም የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር፡፡
** የማረፊያው እለት በደረሰ ጊዜ ደቀመዛሙርቱና ሰዎች ተሰባሰቡ፤ በደብረ ነጐድጓድ ያደገውን ተክለ ኢየሱስን መምህር አድርጎ ሾመላቸው እነርሱንም ባርኳቸው፤ ኅዳር 26 በ1286ዓ.ም. በእለተ እሑድ ጧት ፀሐይ ስትወጣ ዐረፈ፤ ደቀ መዛሙርቱም እንደሚገባ አድርገው በፍየል ሌጦ አድርገው ገንዘው በክብር ቀበሩት፡፡

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Dec, 08:13


#ኅዳር_26_ #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ፤

#_ከደብረ_ዳሞ_ቀጥሎ_በሃገራችን_ሁለተኛውን_መካነ_አእምሮ(#University)#የመሠረተ፤
#_በሃገራችን_ወርቃማ_ዘመን_ተብሎ_የሚታወቀውን_ዘመን_ፋና_ወግቶ_የጀመረ_
#_መጻሕፍትን በእጁ በመጻፍ ለትውልድ የታሪክ አሻራን ያሳረፈ
#_የሐይቅ_እስጢፋኖስ_ገዳምን_ዳግመኛ_ያቀናና_ያስፋፋ፥
#በደብረ ዳሞ አስኬማ ዘመላእክትን የተማረ
#እንደ እስጢፋኖስ ጸጋን ጽድቅንና ሞገስን የተመላ፥ በሥራው ፍጹም የኾነ፥
#የመጀመሪያውን_የዐቃቤ_ሰዐት_ማዕርግ_ያገኘ፡፡
#_ለቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል ፥ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ ፥ #አቡነ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫና_ #ለሌሎችም_በርከካታ_ቅዱሳን_ወላዴ_አእላፍ_ቅዱሳን_የኾነ፡፡
* በበጌምድር ዳኅና(አሁን ስማዳ) ገብርኤል በተባለ ቦታ ከአባታቸው ዘክርስቶስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ ነሐሴ 26 ሰኞ ተጸንሰው፤ ግንቦት 26/1205 ዓ.ም. ረቡዕ በቅዱስ ነአኵቶ ለአብ ዘመነ መንግሥት ተወለዱ፡፡ ወንድሞቻቸው ገብረ ጽዮንና ስቡሕ አምላክ ይባላሉ፡፡
*እስከ 30 ዓመታቸው ድረስ በእናት አባታቸው ቤት እያገለገሉና ትምህርት እየቀሰሙ ቆዩ፤ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾላቸው ወደ 5ኛው የደብረ ዳሞ አበምኔት ዳግማዊ አቡነ ዮሐኒ ዘንድ እንዲሄዱ በራዕይ ነገራቸው፤ በመንገድም ሲሄዱም የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን አግኝተው ይምጻአ ምሕረት የሚባል ዲያቆንን አስከትለው ወደ ደብረ ዳሞ እንዲሄዱ መልአኩ ባዘዛቸው መሠረት ወደ ገዳሙ አቀኑ፡፡
*በደብረ ዳሞ ቆይታቸውም እህልን በመፍጨትና ለገዳሙ ንግድን (ሩቅ መንገድንና አስጨናቂ ኹኔታዎችን በማለፍ ) ይነግዱ ነበር፡፡ እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጻፍ (በመገልበጥም) ትጉህ ጸሓፊ ናቸው፤ ይህ ይታወቅ ዘንድ በቅርብ የደብረ ዳሞ ዕቃ ቤት እስከተቃጠለበት ድረስ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በእጃቸው የጻፉት ወንጌል ይገኝ ነበር፡፡
*37ዓመት ሲኾናቸው ከአባ ዮሐኒ ሥርዐተ አስኬማ ዘመላእክትን ከተቀበሉ በኋላ መልአኩ ወደ ሐይቅ እንዲሄዱ በገለጻላቸው መሠረት በ1237 ዓ.ም. ወደ ሐይቅ በመምጣት በሐይቁ ዳር በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤ.ክ. ለ6ወራት አገለገሉ፤ በዚሁ ደብር የሚገኘው ‹‹#ሔር_አምላክ_›› የተባለ ካህንም የጻድቁን ታሪካቸውን ጠይቆ ከተረዳ በኋላ ወደ ደሴቱ አስገባቸው፤ የአካባቢው ሕዝብም አገልግሎታቸውንና መንፈሳዊ ተጋድሏቸውን አይተው ንጉሡ ይትባረክ ዘንድ በመሄድ የገዳሙ አበምኔት እንዲያደርገው ጠየቁት እርሱም ሾመው፡፡ ጻድቁም ይህን ገዳም በዮዲት ጉዲት ከጠፋ ከ300 ዓመታት በኋላ ዳግም አቅንቶታል፡፡
*እርሳቸውም ደሴቲቷም ስለወደዷት ከገዳሟ ላለመውጣት፤ የባሕሩን ወደብም ላለመርገጥ ብፅዓት ገብተው 20 ዓመታት ያህል እንደኖሩ፤ አፄ ይኵኖ አምላክ እንደነገሠ ጻድቁ ወደ ንጉሡ እንዲመጡ ላከበቸው፤ እርሳቸው ግን ከሐየቁ እንደማይወጡ ብፅዓት እንዳለባቸው፤ ንጉሡ ወደ እርሳቸው እንዲመጣ ላኩበት፤ ንጉሡም በበቅሎ እስከ ጉልበቱ ድረስ ወደ ባሕሩ ገብቶ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ኂሩተ አምላክና ኀረየነ ክርስቶስ ከሚባሉ ደቀመዛሙርቶቹ ጋር በታንኳ (በጀልባ) መጥተው ተጨዋወቱ፤ ንጉሡም ምን ላደርግልህ ትወዳለህ ሲላቸው፤
* ገዳሟ የወንዶች ገዳም እንድትኾን ነው አሉት፤ ንጉሡም በቦታው ያሉትን ሴቶች ይህ ቦታ የወንዶች ገዳም ብቻ እንዲኾን ስለወሰንኩ የፈቀዳችሁ ከእኔ ጋር በከተማዬ መኖር አሊያ በፈቀዳችሁትና በመረጣችሁት ቦታ መኖር ትችላላችሁ የምትፈልጉትንም ኹሉ እሰጣችኋለሁ በማለት ሥርዐት አበጁለት፡፡ ደሴቲቱን ለቀው እየሄዱ ካሉት ሴቶች መካከልም አንዲቷ ምጧ ደርሶ ነበረና በደሴቱ ጫፍ ወለደች ቦታውም ‹‹#ምጥ_ገበታ_›› ተባለ፡፡ ዛሬ ክብረ በዓል የሚከበረው በዚሁ ምጥ ገበታ በተባለው ቦታ ነው፡፡ (ከምጥ ገበታ በስተምዕራብ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ፤ በስተሰሜን ምዕራብ መካነ አእምሮ (University)፤ በስተሰሜን የሴቶች ገዳም ይገኛል)
* በንግግራቸው ሳሉም እባብና አለቅት በንጉሡን በቅሎ እግር ላይ ተጠመጠሙ፤ ጻድቁም መርዛማነት ያላቸው እንስሳት በዚህ ገዳም ሰውን እንዳይጎዱ አወገዟቸው፤ የደወልም ድምፅ ተሰማ ንጉሡም አሁን ስንት ሰዐት ነው የደወል ድምፁስ ምንድን ነው ብሎ ጻድቁን ጠየቀ፤ ጻድቁም ፱ኝ ሰዐት በመኾኑ ደወሉ ከገዳሙ የተደወለ መኾኑን ነገሩት ንጉሡም ለጻድቁ #የዐቃቤ_ሰዐት_ ማዕርግን ሰጣቸው (በአሁኔ ሰዐት ዐቃቤ ሰዐት የጠቅላይ ሚንስትሩ ዋና አማካሪ ከሚለው ጋር የተካከለ ነው)፡፡ (ምንም እንኳን እርሳቸው በሹመቱ ለመጠቀም ባይፈልጉም)፤ ከተከታያቸው ከአባ ዘኢየሱስ አንስቶ እስከ 16ኛው መጀመሪያ አጋማሽ ድረስ በሐይቅ መምህራን እጅ ቆይቷል፤ ኋላ የንጉሦች መናገሻ ከሸዋ ወደ ጎንደር ሲዛወር በቦታ ርቀት ምክንያት ይህ ሹመት በገጽ የሚሰጥ ሹመት ሁኗል፡፡)
✤ንጉሡ ይኵኖ አምላክ ለገዳሟ የሚከተለውን ሥርዐት ሠርተው መደ መናገሻቸው፤ ጻድቁም ወደ ደሴታቸው ተመለሱ ፤

መኳንንት፣ መሳፍንትና ነገሥታት የሰጡትን የገዳሙን ርስት ጉልት ማንም እንዳይነካ፤
ሴቶች ወደ ገዳሙ እንዳይገቡ (የአባቶች መነኰሳትና የባሕታውያን ብቻ መኖሪያ እንዲኾንና እኅቶች እንዳይቀላቀሉ በማሰብ)
መነኰስ ያልኾነ ማንም በሐይቅ ገዳም ቤትን እንዳይሠራ፡፡
፠ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በሃገራችን አንጋፋና ቀደምት በኾነው ደብረ ዳሞ መካነ አእምሮ (University) የተማሩ እንደመኾናቸው፤ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሲመለሱም በሃገራችን በትምህርት መካነ አእምሮነቱ ዋናና ግንባር ቀደምቱን፤ በርካታ ሊቃውንትን ቅዱሳንን ያፈለቀውን የሐይቅ እስጢፋኖስ መካነ አእምሮ መሠረቱ፤ በዚህም የኢትዮጵያን ወርቃማ ዘመን መሥራች ነው፤ ልጆቻቸውም ይህን ወርቃማ ዘመን አስቀጥለውታል፡፡ በቆብ የወለዷቸው ቅዱሳን ሊቃውንት ብዙ ቢኾኑም ለአብነት ያህል ዐበይቶቹ፤
✤ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል (ምድረ ዐማራን፣ ሸዋንና ደቡብን፤ ምድረ ትግራይን ያስተማሩ፤ የአቡነ ተክለሃይማኖት የመጀመሪያ መምህር የኾኑ)
✤ አቡነ ተክለሃይማኖት (ሐዲስ ሐዋርያ ተብሎ የተሰየመ፤ በሐይቅ ከመመንኰሳቸው በፊት 7 ዓመታት፣ ከመነኰሱ በኋላ 3 ዓመታት ተቀምጠዋል)
✤ አባ ሕዝቅያስ (ከምድረ ወግዳ ይዞ እስከ ጎጃም ያስተማሩ)
✤ አባ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት (በጸበላቸው የእንጨት ቅርፊትን እንደ ደንጊያ መቁጠሪያ የሚያደርጉ፣ በድንጋይ ሠረገላ የሚጓጓዙ)
✤ እጨጌ አባ አሮን ዘደብረ ዳሪት (ከምድረ ዋድላ አንስቶ እስከ ዳውንት፤ ከበጌምድር እስከ ደምቢያ የሰበከ)
✤ አባ ገብረ ናዝራዊ ዘበለሳ (ምድረ ትግሬን ያስተማረ)
✤ አባ ኂሩተ አምላክ ዘዳጋ (እንደ መምህሩ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በእስጢፋኖስ ስም በጣና ላይ የዳጋ እስጢፋኖስ ገዳምን የመሠረተ፤ ምድረ ሳርክን ይዞ እስከ ጋዝጌ፤ መላዋን የአላፋና ጣቁሳ እና የአገው ምድርን ያስተማረ)
✤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ዘደብረ ባሕርይ) (የኢትዮጵያ መብራት)፤ አብዛኛዋን የኢትዮጵያ ምድር ያስተማረና ቤተ ክርስቲያንን ከ40 በላይ በሚደርሱ ድርሳናቱ ያስጌጠ፡፡ 
✤ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፡፡
✤✤ እንዲሁም ንጉሡ ይኵኖ አምላክ (ከንግሥናው በፊት በልጅነቱ ያደገውና የተማረው ከጻድቁ ዘንድ ነው፡፡)

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Dec, 05:53


ቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕሉ ሲያሸበሽብ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፤ ጣርማ በር ወረዳ፤ ጋሹ አምባ ቀበሌ፤ አርማንያ ቅዱስ መርቆሬዎስ፡፡
t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

29 Nov, 15:31


መዝሙር ዘሰንበት
እም ፳ ለኅዳር እስከ ፳፮ለኅዳር ዘምኩራብ

http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

28 Nov, 09:03


t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

28 Nov, 09:02


እንኳን ለኅዳር ጽዮን ማርያም (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ በሁሉም ቦታ የሚባለውን የኅዳር ፳፩ ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፤ ዚቁንና ወረቡን እንደ የደብራችሁ የአቋቋም ይትበሃል ትቆሙ ዘንድ፤ የላይ ቤት በሚቆባቸው አድባራት ዚቅ ዘግምጃ ቤት የሚለውን ተመልከት፤ የታች ቤት በሚቆባቸው አድባራት ዚቅ ዘበዓታ የሚከለውን ተመልከት፡፡ በተጨማሪ የሸዋ ወረብን (እንደ አዲስ አለም ማርያምና እንጦጦ ማርያም ባሉት) የሚባለውን አብረን አዘጋጅተነዋል፡፡
ኅዳር 21 የታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ) ዓመታዊ ክብረ በዓል የምናከብረው፤
1.በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ የተመለሰችበትን፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6)
2. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23)
3. በቀዳማዊ ምኒልክ ቀዳማዊ ንጉሥ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት:: (ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …)
4, በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም መካናት በስደት ከልጇጋር ባርካ አኵስም ጽዮን መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ (ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ..)
5.በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ አማካኝነት መስዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵስም ጽዮን፤ ጽዮን ማርያም ተብላ 12 መቅደሶች ያሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤት የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡
6. ነቢያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክዕና አምሳል (ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፥ በአምሳለ ብእሲት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ፣ ……) ያዩበት
6.1 እረኛው ሔርማ ጻድቅ ቤተ ክርስቲያንን በአምሳለ ብእሲት በራእይ የተመለከተበት
6.2 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ዘሀገረ ሮሜ የሚዘከርበት
7. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ትሰደድ ነበርና:: ተመልሳ ስትታነጽም (ከዮዲት ወረራ በኋላ፤ ከግራኝ ወረራ በኋካ አፄ ፋሲል፤ በአዲስ መልክ አፄ ኃይለ ሥላሴ ካነጹ በኋላ) ቅዳሴ ቤቷ የተከከበረው ኅዳር 21 ቀን ስለኾነ፡፡
(የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት)
• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 http://tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

26 Nov, 04:42


የዓለም ኹሉ መምህር የኾነው #ሊቁ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባረፈ በ35 ዓመቱ (በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን) በዛሬዋ ዕለት ኅዳር 17 ሥጋው ፈልሶ በቊስጥንጥንያ በክብር ያረፈበት ነው፤ የቅዱሱ ሥጋውም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል፡፡
✣✣✣ስለ ቀዳማዊው ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዳግማዊው ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ) እንዲህ ብሎ ገልጾታል፡፡
✤አፈ ዕንቊ
✤አፈ ጳዝዮን ፤(/ስለ እመቤታችን ፍቅር/ የወር አበባ ያላትን ሴት አንቀጸ ሥጋ ለመሳም ያላፈረ)
✤አፈ ባሕርይ (በድርስቶቹ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስጌጣት)
✤አፈ መዐር
✤አፈ ሦከር (በቃሉ ጣፋጭነት ምእመናንን የሚያለመልማቸው)
✤አፈ አፈው /ሽቱ/ (በትምህርቱ መዐዛ የምሥጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው)
✤አፈ ርኄ
✤አፈ ሰይፍ (በውግዘቱ ሥልጣን ከሀዲዎችን የሚቆርጥ)
✤አፈ መጥባሕት
✤የማይነዋወጥ ዐምድ
✤የማይፈርስ መሠረት
✤ከሞገዶች መነሣት የተነሣ የማይሰበር መርከብ
✤በሃይማኖት ባሕር ውስጥ የሚዋኝ ዋናተኛ
✤የማይፈርስ ግንብ
✤በጠላት ፊት የሚፀና አዳራሽ
/መጽሐፈ ምሥጢር፣ ዘጌና ምንባብ/

በተጨማሪም፤ በሚከተሉት ስሞችም ይጠራል፡፡
፨አፈ ወርቅ /የእመቤታችን ስዕል አፍ አውጥታ ነው ዮሐንስ አፈወርቅ ብላ የሰየመችው/
፨አፈ በረከት
፨ልሳነ ወርቅ
፨የዓለም ሁሉ መምህር
፨ርዕሰ ሊቃውንት
፨ዐምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
፨ሐዲስ ዳንኤል
፨ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው ሊቀ ጳጳሳት)
፨መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
፨ጥዑመ ቃል

~~ ምስጋና ለአምላካችን ይሁንና ንስጥሮስ በምፍቅናው የአንዲት ሴትን ኀፍረት ሥጋ ገልጦ እግዚአብሔር ወልድ በዚህ ማሕፀን ተፀንሶ አልተወለድም ብሎ በሕዝቡ ፊት ተናገረ፤
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም፤
* ‹‹እኔ እግዚአብሔር .. በዚህ ሥጋ ከሴት እንደተወለደ አምናለሁ፤
* እኔ እግዚአብሔር በመዋለጃ ማኅፀን እንደተወሰነ አምናለሁ፤
* እኔ እግዚአብሔር በድንግልና ወተት እንዳደገ፣ በሕፃናትም ሥርዐት ሕፃናትን እንደመሰላቸው፣ ከብቻዋ ከኀጢአትም በቀር የሰውን ሕግ ሁሉ እንደፈጸመ አምናለሁ፡፡›› ብሎ የዚህችን ሴት ኀፍረተ ሥጋ ስለ እመቤታችን ፍቅር ብሎ ሳመ፤ ከእመቤታችን ሥዕል አንደበትም ከዚህ በኋላ ስምህ ዮሐንስ ብቻ ሳይኾን ‹‹ዮሐንስ አፈወርቅ›› ይሁን ብላ ሰይመችው፤ አርሱም ‹‹እሰግድ ለኪ፥ እሰግድ ለኪ ወእዌድሰኪ … ›› ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የሚነበበውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት፡፡

*በ347 ዓ.ም. በሶርያ ዋና ከተማ በአንጾኪያ ሲኾን የተወለደው፤ አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ አትናስያ ይባላሉ፡፡
*ገና የ15 ዓመት ሕፃን ሳለ በሕፃንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) በሙሉ ተምሮ ተመልሷል፤ በዚህም በመንፈሳዊውም ኾነ በዘመናዊው ይፍልስፍና ይህ ቀረህ የማይባል ሊቅ ኾነ፡፡
*ቅዱሱ በ16 ዓመቱ ኃብትና ንብረቱን ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ፤ በበርሃ ሳለም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጥተው፤ ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጡት፡፡ የመጻሕፍት ድርሰት ተገለጹለት፤ በዚህም ቅዱስ በትጋትና በንቃት እጆቹ ታመው በክር አስሮ እስኪጽፍ ድረስ ዐሥር ሺህ የሚደርሱ ድርሳናትን መልዕክታትንና ትርጓሜያትን ጻፈ፡፡
ከዚህ በኋላ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ፤ በቅድስናው ወደውታልና የቊስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት፡፡ በሚያስተምርበት ጊዜም ከጣዕመ ትምህርቱ የተነሣ ሕዝቡ ተመስጠውና ተደመው ይሰሙት ነበር፤ ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር፡፡
በሠርጓ ቀን በሞት ሊወስዳት የመጣውን መልከአከ ሞት ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ ገዝቶ 10 ዓመት አቁሞታል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ.ም. አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ::
/ምንጭ፤ መጽሐፈ ምሥጢር፣ ማኅሌተ ጽጌ፣ ተአምረ ማርያም፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ በዲ.ን. ያረጋል አበጋዝ፣ የቃል ትምህርት፣ የዲ.ን. ዮርዳኖስ መጽሐፈ ገጽ፣ በእንተ ምክንያተ ሐውልታት በገብረእግዚአብሔር ኪደ/

✤✤ #በአንበሳ ላይ የምትጫነው ኢትዮጵያዊቷ #ቅድስት_ወለተ_ጴጥሮስ ዕረፍቷ ነው፡፡
* በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ ኢትዮዽያ ደዋሮና ፈጠጋር አካባቢ ሲኾን የተወለደችው፤ አባቷ ባሕር አሰግድና እናቷ ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡

* በወግ በማዕረግ ባል አገባች፤ ግን ወዲያው አፄ ያዕቆብ ገደሉባት፤ ወላጆቿም ግድ ብለው ስዕለ ክርስቶስ የተባለ የሱስንዮስን የጦር መሪ አጋቧት 24 ዓመት እስኪኾናት ድረስም 3ት ልጆችን ወለደች፡፡ አፄ ሱስንዮስ ካቶሊክ በኾነ ጊዜ ባሏ ወደ ንጉሡ እምነት ወደ ካቶሊክነት ገባ፡፡ ልጆቿም እግዚአብሔርን የማያስደስቱ ከኾነ በሞት ውሰዳቸው ብላ ለፈጣሪ በመንገሯ ሦስቱም ልጇቿ ሞቱ፤ ባሏም ክዶ ወደ ካቶሊክነት ስለገባ ተለይታው ወደ ጣና ገዳማትና ወደ ታላቁ ገዳም ዋልድባ ገብታ ብዙ ተጋደለች፡፡

* ንጉሡንም በካቶሊክ እምነቱ ከሌሎች ቅዱሳን ጋራ ኾና ስለተቃወመችው 2 ጊዜ ወደ በርሃ አግዟታል፤ ወደ ጉሙዝ ባጋዛት ወቅት ወደ እሳት ውስጥ ቢከታትም እሳቱ ሳያቃጥላት ወጥታለች፡፡
* ፋሲል ነግሶ ሃይማኖት ተመልሶ ሃገር ሲረጋጋ ወደ ምጽሌ ከዚያም ወደ መንዞ መጥታ 7ት ገዳማትን አቅንታለች፡፡ ከ700 በላይ ለሚኾኑ መነኰሳትና መነኰሳይያት እመ ምኔት ኾናም አስተዳድራለች፡፡ ምግቧም የመረረ ቅጠልና ኮሶ ነበረ፡፡ በስተመጨረሻም የሬማ መድኀኔ ዓለምን አቅንታ በተወለደች በ50 ዓመቷ ብዙ ቃል ኪዳንን ተቀብላ በ1630ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ዐርፋ በዚሁ ገዳም በክብር አርፋለች፤ በበዓለ ዕረፈቷም የብርሃን ምሰሶ ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ታይቷል፡፡ ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ሰማዕትም ጻድቅም ናት፡፡ /ምንጭ ገድለ ወለተ ጴጥሮስ፣ የዲ.ን ዮርዳኖስ መጽሐፈ ገጽ/
(ጽሑፎቹን ከቃል ትምህርት፣ ከመጻሕፍትና ከመጽሐፈ ገጽ አውጣትቶ ለጻፈልን ወንድማችን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የዳግማዊ ዮሐንስ አፈወርቅ (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)ና የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ረድኤት በረከታቸው ይደርበት፡፡) እኛንም አንባቢዎቹን በረከታቸው ትድረሰን፡፡

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

24 Nov, 18:22


ለቀጣይ ሦስት ዓመታት (ከ 2017 - 2019 ዓ.ም ) ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉኃን ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያንን የሰበካ ጉባኤ አባል በመሆን ለመምራት የተመረጡ ከካህናት ፣ ከምዕመናን እና ከሰንበት ትምህርት ቤት የተወከሉ ።

መልካም የአገልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ!
t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

24 Nov, 07:09


#ማር_ሚና (#ቅዱስ_ሚናስ_ገዳም)

ከራሱ አልፎ ለሀገርና ለወገኖቹ የተረፈ ፣በተባበረ ክንድ በረሃን ለምለም ያደረገ ተፈጥሮን በጥረት ያሸነፈ፣ የቅዱሳን አጽም ማረፊያ የሆነ ታላቅ ገዳም።

በታችኛው ግብጽ ይገኛል። ከፍተኛ የሆነ በረሃማነት ያለው ገዳም ነው። ይህ ገዳም ጥብቅ የሆነ ገዳማዊ ሥርዓትና የመነኮሳት አቀባበል ያለውና ከ120 በላይ መነኮሳትን የያዘ ነው። ገዳሙ 34 የተለያዩ ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን ከ1500 በላይ ሠራተኞችን ቀጥሮ የሚያሠራና ከግብጽ ገዳማት 1ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ገዳም ነው። ገዳሙ በጣም በረሃማ ቢሆንም የሚያመርተውን ምርት ወደ ተለያዩ ሀገራት export በማድረግ ለሀገሪቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ገዳም ነው። በሀገሪቷ መንግሥትም ልዩ ትኩረትና ጥበቃም ይደረግለታል። ገዳሙ ከሚያገኘው ገቢም በቀን ከ600 በላይ ለተቸገሩ ወገኖቹ በቋሚነት ርዳታ ያደርጋል።

በተጨማሪም ከንጉስ አፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር የቅርብ ወዳጅነት እንደነበራቸው የሚነገርላቸውና የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆኑትን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስን የሾሙትን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ቅዱስ አጽም ፣የቅዱስ ሚናስና የቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያዊ ተረፈ አጽም በገዳሙ ይገኛል።
ዲ.ን አንድነት ተ

Facebook 👉 የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

23 Nov, 10:42


ኅዳር 15 እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#ቅዱስ_ሚናስ (#ማር_ሚና)

ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው። በግብጻውያን ልዩ ቦታ አለው ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም። ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው። በተለይ ለታመመ ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ ባለ በጎ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው።

ቅዱስ ሚናስ ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው። በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ፣ በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ፣ በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ፣ ሃብትን ክብርን ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ፣ በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ በአላውያን ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ኅዳር 15 በሰማዕትነት ያረፈበት ሲሆን ሰኔ 15 ደግሞ ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው።

#በአንድ_ወቅት፦
ዐሥራ ስምንት ቀሳውስት በሥራ ጉዳይ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛን ለማነጋገር መርዩጥ ወደ ሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ጉዞ ጀመሩ። ቀሳውስቱ በጉዞአቸው መንገድ ስተው ሲባዝኑ ከአንድ የበረሓ ሰው ጋር ተገናኙ።

የበረሓው ሰው መርዩጥ የሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ለመሄድ መንገድ እንደሳቱ ቀድሞ ተረድቶ ነበርና "የማር ሚናስን ገዳም ነው የምትፈልጉት? በማለት ይጠይቃቸዋል። እነርሱም ችግራቸውን እንዴት እንዳወቀ በልባቸው እያደነቁ "አዎን" አሉት። የበረሓው ሰውም እየመራ ከገዳሙ አደረሳቸው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛም ወደ በር ወጥተው ተቀበሏቸው።

ከዚያም "ምነው ዘገያችሁ? መንገድ ሳታችሁ እንዴ?" ብለው እንደ ቀልድ ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን! በጣም ተቸግረን ሳለን ይህ የበረሓ ሰው ደርሶልን መንገዱን አሳየን" ብለው ወደ ሰውየው ለማመልከት ዘወር ሲሉ እርሱ በአካባቢው የለም። አቡነ ቄርሎስም "መንገድ እንደጠፋችሁ ስለተረዳሁ ሚናስን ልኬላችሁ ይዟችሁ የመጣው እርሱ ነው" አሏቸው።

አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን!!

• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 http://tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

23 Nov, 08:44


መዝሙር ዘሰንበት
እም ፲፫ ለኅዳር እስከ ፲፱ ለኅዳር ዘቅድስት

http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

22 Nov, 12:20


#ጾመ_ነቢያት_ (#የገና_ጾም_)

፠ ከ7ቱ አጽዋማት (ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ፍልሠታ፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ነነዌ ና ጾመ ገሃድ) መካከል አንዱ ነው፡፡
፠ ኅዳር 15 ቀን ተጀምሮ እስከ ልደት ለአርባ ሦስት ቀናት የሚጾም ጾም ነው፡፡
፠ ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፤
† ፩. #ጾመ_አዳም_፤ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ; በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ፤ አለቀሰ (እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ) ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡›› የሚል ነው፡፡ /ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ/ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡

† ፪. #ጾመ_ነቢያት_፤ ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስ፣ ቅዱስ ዳንኤል ና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዘዳ 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3፣ መዝ. 68:10, 108:24) ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል::

† ፫. #ጾመ_ሐዋርያት_፤ ሐዋርያት ‹‹ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?›› ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡
† ፬. #ጾመ_ማርያም_፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ‹‹ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?›› ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና ‹‹ጾመ ማርያም›› ይባላል፡፡

† ፭. #ጾመ_ፊልጶስ_፤ ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡

† ፮. #ጾመ_ስብከት_፤ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡

† ፯. #ጾመ_ልደት_፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡

   ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ፡፡

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

21 Nov, 15:37


http://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

12 Nov, 20:20


https://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

12 Nov, 20:19


#ኅዳር_6፤ ደብረ ቊስቋም፤ #እመቤታችን_ከልጇ_ጋር_ስደትን_የጀመረችበት_ዕለት_ነው፡፡

**ድንግል ማርያም ከልጇና ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋርለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) (1275 ቀናት) ከተሰደደች በኋላ #ግንቦት_24_ደግሞ_በዓተ_ግብጽ_ (ወደ ግብጽ ወደ ደብረ ቊስቊም ገብታ ያረፈችበት ቀን ነው)።
ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ፤ ወፍም ቤቷን ሰራች፡፡ መዝ. ፹፫፥፫ ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማው ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንድ አምላክ ልጇን አዝላ፤ በአንዲት አህያ ላይ ተቀምጣ፤ ጥቂት ስንቅ ቋጥራ፤ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች፡፡ ከገሊላ ተነሥታ በጭንቅ፣ በመከራ፣ በረሃብና በጥም፣ በሐዘንና በድካም፣ በእንባ ተጕዛ በዚህች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታ በሥደት እጅግ ብዙ መከራ ተቀብላለች::
† የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
† ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
† የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
† የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
† የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
† እመ አምላክ ተራበች፣ ተጠማች፣ ታረዘች፣ ደከመች፣አዘነች፣ አለቀሰች፣ እግሯ ደማ፣ ተንገላታች::
     ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳን ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ:: አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና::

#መድኃኔ_ዓለም_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ለምን_ተሰደደ? #ለምን_ስደቱን_ወደ_ግብፅና_ኢትዮዽያ_አደረገ?

1. ፠ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና(ኢሳ 19፥1፣ ዕን. 3፥7)
2. ፠ምሳሌውን ለመፈጸም፤ የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም፥ ያዕቆብ (እሥራኤል):፥ ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::
3. ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19፥1)
4. የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::
5. ሰው መሆኑ በአማን (በእውነት) እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::
6. ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና
7. የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

     እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) (1275 ቀናት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ::

፠ በመጀመርያ ድንግል ማርያም ከርጕም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነበር:: በዚያም የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች፡፡
፠ በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች:: ‹‹እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ፡፡›› እንዲል:: (እሴብሕ ጸጋኪ)
፠ ቀጥላም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው) ዐረፈች፤
፠ ከደብረ ቢዘን ደብረ ሐዊ፣ በደብረ ዳሞ፣ አኵሱም፣ ደብር ዐባይ፣ ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ቆይታለች፤
፠ በዋልባም ቆይታቸው ልጇ ገዳሙን በኢትዮጵያ በብጨኝነት ራሱ የገደመውን ገዳም መሥርቶ እየባረከ ወደ ጣና ሄደዋል፡፡
፠ በጣና ገዳማትም፤ በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ100 ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሸዋ ሔዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች::
፠ ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች፤ በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሀገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች፡፡
፠ በደብረ ኤረር ተራራ ላይም ከልጇ ኢትዮጵያን በዐሥራትነት ተቀብላለች፡፡
ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል::
     እመቤታችን የሄሮድስን ሞት ከሰማች በኋላ ቊስቋም ከሚባል ተራራ ላይ ሆና ደስታዋን አብረዋት መከራን ከተቀበሉት ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር አከበረች፡፡ ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ኅዳር 6 ቀን ቊስቋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል፤ ሐሴትንም አድርገዋል::

***ኅዳር 5 ለኅዳር 6 ከዋይዜማው ጀምሮ የሚባለውን ሙሉ ሥርዐተ ማኅሌትም እነሆ ብለናል፤ መልካም የማኅሌት ሌሊት ይሁንልን፡፡

#የቊስቋም_ክብረ_በዓልን_በየት_ሊየከብሩ_ዐስበዋል???

#በመላው_ዓለም_የቊስቋም_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
(ሌሎች ያልጠቀስናቸው አብያተ ክርስቲያናት ካሉ አሳውቁን)

#በአዲስ_አበባ_የቊስቋም_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #መንበረ_ንግሥት_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ_፤
(#፫፻፷፭ት #ቀናት_ሙሉ_ዝክር_በማኅበረ_ሰላም_መድኀኔዓለም_የሚዘከርባት_ቤ/ክ)
አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ እንጦጦ፥ ቊስቋም፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ/ጊዮርጊስ  (መርካቶ) (4 ኪሎ) → ሽሮሜዳ (መነን) → ቊስቋም፤

፪. #ደብረ_ናዝሬት_ቅዱስ_ዮሴፍ_ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ቦሌ ክለ ከተማ፥ ደጃዝማች መርዕድ መንገድ፥ ቀለበት መንገድ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) (ከላጋር) (ከ4 ኪሎ) → ቦሌ → ሳሪስ /ቃሊቲ ቀለበት መንገዱ ላይ/
ወይም፤ ከሳሪስ አቦ → ቦሌ /በቀለበት መንገድ/

፫. #ቃሊቲ_ደብረ_ገነት_ቅዱስ_ሚካኤልና_ደብረ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ (ቃሊቲ ቊስቋም)
አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) (ከላጋር) (ከ4 ኪሎ) → ቃሊቲ መናኸሪያ → ሰፈረ ገነት
ወይም፤ ከሳሪስ አቦ → ቦሌ /በቀለበት መንገድ/

፠፨፠ #እንዲሁም_በድርብነት_የሚከበርባቸው_፤
፬. #ኮልፌ_ደብረ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ_ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት፥ ጠሮ፥ አራት መንታ፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ/አቡነ ጴጥሮስ ዐደባባይ/ → ዊንጌት → ጠሮ፡፡
ወይም፤ ከመርካቶ ኮልፌ አጣና ተራ → ጠሮ

፭. #ማኅደረ_መለኮት_ወይብላ_ቅድስት_ማርያም_ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ የሺ ደበሌ፡፡
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → የሺ ደበሌ፡፡

፮. #ላፍቶ_ደብረ _ኢያሪኮ_መድኀኔ_ዓለምና_መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ_ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ላፍቶ ፤
ታክሲ፤ ከመገናኛ → ሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡

፯. #መዝገበ_ምሕረት_ፋኑኤልና_ቊስቋም_ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ካራ ፥ አጀንባ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት (ከሜክሲኮ) → አየር ጤና → ካራ፡፡

፰. #ጉለሌ_ሸጎሌ_ኪዳነ_ምሕረት_ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ አዲሱ ገበያ ፥ ቶታል፥ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል (ወደ ዊንጌት በቀለበት መንገገዱ ትንሽ ሄደው)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (አስኮ) → አዲስ ገበያ /ጸዮን ሆቴል/፤

#በኢትዮጵያ_ደረጃ_የሚከብርባቸው_ #፭ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #ደብረ_ፀሐይ_ፋርጣ_ቊስቋም _ቤ/ክ፤ (በ1254 ዓ.ም. የተመሠረተች)
አድራሻው፤ ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ/ወልድያ → ፋርጣ፡፡
ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር → ወረታ → ፋርጣ፤

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

12 Nov, 20:19


፪. #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም_፤
አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤
ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎጃም (በመርጡለ ማርያም) → መካነ ሰላም ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤
ወይም፤ ከአ.አ. ቦሌ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሐ ቤቴ ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፡፡

፫. #አምባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም፤
አድራሻው፤ ዋግኽምራ ሀገረ ስብከት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → ሰቆጣ (ዋግኽምራ)፡፡

፬. #ጎንደር_ደብረ_ፀሐይ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ ቸቸላ (ሆስፒታል አጠገብ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር ከተማ → ሆስፒታል → ቊስቋም፤

፭. #ደሴ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ደሴ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ ከተማ፡፡

#ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከብርባቸው_ #፩ #ጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #ግብፅ_ቊስቋም _ማርያም_ገዳም_፤
(#እስከ_ቅርብ_ዘመናት_በግብፅ_የኢትዮጵያ_ርስት_የነበረ_)
አድራሻው፤ ግብፅ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ → ግብፅ → ገዳመ ቊስቋም፤

• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 http://tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

07 Nov, 07:51


ታላቁ ገዳማችን አሰቦት ደብረ ወገግንና ደብረ ኪሩብን ለመሠረቱት ለአባታችን ለአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ በዓለ ዕረፍት (ጥቅምት 29) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡

✤✤ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ፡
፠ በታላቁ አባት አቡነ ተክለሃይማኖት ‹እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ጣዖታትን የሚሰብር፣ የሚያጠፋ፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኀጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ› ተብሎ በተነገረለት ትንቢታዊ ብሥራት ከደጋግና ከበቁ አባታቸው እንድርያስና ከእናታቸው አርሶንያ ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም. በቡልጋ ተወለዱ፤ ሲወለዱም መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡
፠ስማቸውን ሳሙኤል በብለው የሰየሟቸውና ክርስትናም ያነሷቸው፤ ኋላም መዓርገ ምንኵስናን የሰጧቸው አቡነ ተክለሃይማኖት ናቸው፡፡
፠ ብዙ ጻድቃንን (አቡነ ተክለሃይማኖትን፣ ታዴዎስ ዘደብረ ድኁኃን፣ ሮማኖስ ዘደብረ ዋምን፣ አቡነ አኖሬዎስ ዕንቈ ባሕርይ ዘመረግድ ወመስተጋድል ወምግባር ንጹሕን) በሥጋ የሚዛመዱ ናቸው፡፡
፠  ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና አባቱ ዓምደ ጽዮን ለሠራው ክፉ ሥራ ‹‹መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ›› ብሎ ለመነውና የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡
፠፠  አቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል፤
* በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡
* ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡
* ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፥
* ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፥
* በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፥
* ይህን ኀላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፥
* በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፥
* በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ፤
* ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግም ይታወቃሉ፤ ከእነዚህም ጥቂቶቹ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሎአቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት (በጥቅምት 29) በኦጋዴን ዘርዘር በተባለ ቦታ በሰላም አርፈዋል፤ ከ7 ወራት በኋላ ሠምረ ክርስቶስ የተባለ ልጃቸው ሥጋቸውን አፍልሶ በደብረ ወገግ በክብር አሳርፎታል፡፡
፠ የአሰቦት ደብረ ወገግን (ምስራቅ ሐረርጌ) ና ደብረ ኪሩብ (አፋር) ገዳምን የመሠረቱ፥ ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና፤ የመሠረቱት ገዳም የምሥጢርና የብዙ ስውራን መኖሪያ የኾነላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡
፠ ከአቡነ ተክለሃይማኖት በኋላ ከተሾሙት 12ቱ ንቡራነ ዕድ አንዱ ናቸው፤ ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነው፡፡
፠  ‹‹ደብረ ወገግ›› ከ2-5 ዓ.ም. እመቤታችን ከነልጇ ስተሰደድ ለ6 ወር የተቀመጠችበት ሲኾን፤ ደብረ ወገግ የሚለው ስያሜ የተገኘው ከመላእክት ነው፡፡ ድርሳነ ዑራኤል በሰፊው እንደሚያትተው ቅዱስ ዑራኤል በ34ዓ.ም. የጌታችንን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን እየረጨ ሲቀድሳት የያዘውን ጽዋ በደብረ ወገግ ላይ ቆሞ ሳለ ነው ጨልጦ ያንጠፈጠፈው፡፡ ያንጊዜም ደብረ ወገግን የብርሃን ውጋገን ሲያጥለቀልቀው መላእክትም ቦታውን ‹‹ደብረ ወገግ›› (የብርሃን ተራራ) ብለው ሰይመውታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ‹‹ወደፊት ፈጣሪውን የሚያገለግል ታላቅ ጻድቅ ይወጣባታልና ይህችን ቦታ ባርካት›› ብሎ ቅዱስ ዑራኤልን በነገረው መሠረት ባርኳት አርጓል፡፡
✤✤ ደብረ ወገግ፤
፠  በደብረ ወገግ ቦታ ላይ ብዙ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ መታየቱን የበቁ ገዳማውያን ብቻ ሳይሆኑ በከተማ ያሉና ለመሳለም ወደ ቦታው የሄዱ ደገኛ ሰዎችም በዐይናቸው ያዩትን ይናገራሉ፡፡ በገዳሙ ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡
፠ ገዳሙ በግራኝ ወረራ ወቅት ከጠፋ በኋላ እንደገና መልሶ የቀናው በ1911ዓ.ም. በታላቁ ሊቅና መናኝ በአለቃ ገብረ መድኅን ነው፡፡ በ1912 ዓ.ም. የአቡነ ሳሙኤልን ቤተ ክርስቲያንን በሣር ክዳን ሠሩ፤ በዓመቱ በ1918 ዓ.ም. ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን መሥራት ጀምረው ፍጻሜውን ሳያዩ እርሳቸው ቢያርፉም፤ በ1919 ዓ.ም. የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተጠናቋል፡፡ በ1929 ዓ.ም. በሶማልያ በኩል በገባው የፋሽስት ኢጣልያ ጦር ገዳሙ ተዘርፏል፥ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንም ፈርሷል፡፡ በወቅቱ በገዳሙ ከነበሩት ከ500 በላይ መነኰሳት መካከል ከፊሉ ታቦቱን ይዘው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሲሸሹ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ሞቃዲሾ ተወስደው ታስረዋል፡፡ ከጣሊያን ወረራ በኋላ መነኰሳቱ በ1936 ዓ.ም. ተሰባስበው ወደ አሰቦት መጡ፡፡ ከ22 ዓመት በኋላ ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ በ1952 ዓ.ም. ተሠራ፡፡ በደርግ ዘመነ መንግሥት ሶማሊያ ኢትጵያን ስትወርር ገዳሙ ላይ አደጋ ለመጣል የመጡ ጠላቶች በተአምራት ያለቁበት ነበር፤ የጃራ ጦር የሚባሉ ገዳሙን ለማጥፋትም መጡ ጠላቶች እንዲሁ በተአምራት አብደው የተመለሱበት ታላቅ ገዳም ነው፡፡ ግንቦት 16 ቀን 1984 ዓ.ም. በአክራሪ ኃይል የገዳሙን መነኰሳትና የአካባቢው ምዕመናን ላይ የከፋ አደጋ ጥሏል፤ ብዙዎችም ሰማዕት ሁነዋል፡፡
በአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም ውስጥ የተሰወሩ እጅግ በርካታ ቅዱሳን ስለመኖራቸው በገድለ አቡነ ሳሙኤል መቅድም ውስጥ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ አሁንም ሆነ ወደፊት በቦታው ላይ የተሰወሩት ቅዱሳን ለገዳማውያኑም ሆነ በዓለም ለሚኖሩ ምግባርን ከሃይማኖት አስተባብረው ለያዙ ሰዎች እየተገለጡላቸው ይታዩዋቸዋል፣ መልእክትም ይነግሯቸዋል፡፡ እንዲሁም ስውራኑ ባሉበት ቦታ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ዕጣን ይሸታል፣ ቀንና ሌሊት አራዊት ሲሰግዱበትና ሲጠብቁት ይታያል፡፡ ለአብነትም በ1972ዓ.ም. ሐምሌ 7 ብዙ ሰው እያያቸው አባ መዘምር የተሠወሩበት ታለቅ ገዳም ነው፡፡
የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘፍቅዳቲሁ ራብዕ፤
ውእቱ ልኩእ ዲበ ረቀ ሰማይ ሳብዕ፡፡
ሊቀ ካህናት ሳሙኤል ዘደብተራ ሐዲ ምሥዋዕ፤
አስተስሪ ኀጣውእየ በደመ ነቢብ በግዕ፤
ለቤዛ ሙታን ዘሞተ በግፍዕ፡፡
(ሳሙኤል ሆይ ቊጥሩ ዐራት ለኾነ በሰባተኛው የሰማይ ብራና(ወረቀት) ለተጻፈ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፤ የሐዲስ መሠዊያ አገልጋይ፥ የካህናት አለቃ ሳሙኤል ሆይ፤ ለሰዎች ቤዛ ለመኾን በግፍ በሞተ በነባቢ ክርስቶስ ደም ኀጢአቴን አስተሥርይ፡፡)
/ታሪኩን ለዘገበልን ወንድማችን አምላከ አቡነ ሳሙኤል በረድኤት በበረከት በጤና ይጠብቅልን፡፡/

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Nov, 17:27


ሥርዐተ ማኅሌት ዘጥቅምት ፳፯
በዓለ መድኀኔዓለም ወመብዓ ጽዮን

ልዩ አዋጅ ዘጥቅምት መድኀኔዓለም

የጥቅምት መድኀኔዓለም የማኅሌቱ ሥርዐት ‹‹የመልክአ መድኀኔዓለምን›› እና ‹‹የመልክአ መስቀልን›› የሚከተል ነው፡፡

‹‹የመልክአ መድኀኔዓለም››ን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ‹ዘአዲስ አበባ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም የሚለውን እንዲከተሉ፤

‹‹የመልክአ መስቀል››ን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ‹ዘጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም›› የሚለውን እንዲከተሉ እናሳስባለን፡፡

✤ መልካም በዓል ✤
https://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Nov, 11:09


ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ (ስብስብ 3)፤

የ114 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የልጅ ኢያሱ ደብር፤ ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ፡፡ (ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመችው፡፡)

የሰላም አምላክ የፍቅር ጌታ መድኀኔዓለም ያደረባት ደብረ ሰላም ብዙ ነገሮች አሏት፤

የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤

ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ደብሩን አገልግለው ወደ ሌላ ደብር የሚዛወሩ ካህናት ኹሌም በዓይናቸው የደብሩ ፍቅር ውልብ የሚልባቸው፤ ምዕመናኑ በአጸዱና በግርማ ሞገሱ ኹሌም የሚደነቁበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡

#አጽዶቹ ሳይቀሩ በቁጥር በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት።

በጣሊያን ወረራ ወቅት እንኳን አንድም ቀን አገልጎሎት ያልቋረጠበት፤ 365 ቀን በሰዓታቱ፣ በማኅሌቱ፣ በመቅደሱ ያለ ማቋረጥ የምስጋና ወንዝ የሚፈስበት፤ ሁልጊዜ ወር በገባ ከ፩ አስከ ፯ ምሕላ የሚደርስበት።

አረጋውያኑ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት በአዘቦት ቀን ለቅዳሴ እና ለጸሎት የሚገኙበት፤ የስውራን ቅዱሳን አባቶች መናሐሪያ የሆነ፤

ከጥንት ዘመን እስከ ዛሬ መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ በብቸኝነት የሚቀድስበት ደብር

#ፍጹም መንፈስ ቅዱስ የረበበት ታላቅ እና ልዩ ደብር ነው፡፡

✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም፤ በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

04 Nov, 09:06


Share
https://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

01 Nov, 11:09


፩ኛ ዙር ዓመት ፭ኛ ሳምንት
ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ ቤት
https://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

01 Nov, 11:09


ዘጥቅምት ፳፬፤ ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)

(፩ኛ ዙር ዓመት፤  ፭ ሳምንት፥ ዘጥቅምት ፳፬)
በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት፤ ወቅዱስ ፊልጶስ ሰማዕት፤ ወዕረፍቱ ለአቡነ ዲዮስቆሮስ ካልዕ፤ ወልደታ ለቅድስት ሐና እመ ሳሙኤል፤ ወዕረፍቱ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ እኁኁ ለቅዱስ ባስልዮስ።

✤ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤
✤ የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው

✤ የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡

✤በማኅሌት በምትቆሙ ጊዜ በጸሎታችሁ ደብራችንን ደብረ ሰላምን፤ ሰ/ት/ቤታችንን ፍኖተ ሕይወትን እና በውስጧ ያሉ አገልጋዮቿን አስቡልን፡፡✤

• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 http://tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

29 Oct, 18:50


#ጥቅምት_20_በዓለ_ልደቱ_ለኤልሳዕ_ነቢይ
#በዓሉ_በእንጦጦ_ራጉኤል_ይከብራል።

ኤልሳዕ የስሙ ትርጒም “እግዚአብሔር ደኅንነት ነው” ማለት ነው፡፡ነቢዩ ኤልሳዕ እጅግ ባለጠጋ የሆነ ሰው ነበር።

ከዕለታት በአንደኛ ዕለት በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነቢዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የኤልያስ መንፈስ እጥፍ ድርብ ሆኖ አድሮበት ለረጅም ጊዜ እግዚአብሔርን አገለገለ፣ ብዙ ተአምራትንም አደረገ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ኢያሪኮ ከተማ በሚገባበት ጊዜ በከተማዋ የሚኖሩ ሰዎች ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ እነርሱ እንደመጣ ባዩ ጊዜ “የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነው ውኃው ግን ክፉ ነው ምድሪቱም ፍሬዋን ትጨነግፋለች” አሉት፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ይህን ልመና ለኤልሳዕ ያቀረቡት እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ነገርን ሁሉ መለወጥ እንደሚችል ይታመኑ ስለነበር ነው፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ የሰዎቹን ችግር ከተረዳ በኋላ የከተማውን ሰዎች አዲስ ማሰሮ እና ጨው እንዲያመጡለት አዘዘ፡፡ ሰዎቹም ኤልሳዕ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አዲስ ማሰሮ በውስጡ ጨው አድርገው አመጡለት፤ ነቢዩ ኤልሳዕ ወደ ውሃው ምንጭ ወደ አለበት ስፍራ መጥቶ ጨው ጣለበት እና “እግዚብሔር እንዲህ ይላል ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ ከዚህም በኋላ ሞትና ጭንገፉ አይሆንበትም” ብሎ ለከተማው ሰዎች ተናገረ፡፡ ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ውኃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል፡፡ የኢያሪኮ ከተማ ሰዎች ከዛ ጊዜ ጀምሮ ንጹሕ ውሃ መጠጣት ጀመሩ፡፡ የምድሪቱንም ፍሬ ተመገቡ፡፡ እግዚአብሔር በነቢዩ አልሳዕ ድንቅ ነገር ሰለአደረገላቸው ዘወትር ያመሰግኑ ነበር፡፡

እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች።

ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳዕ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነቢይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት19 ላይ በስፋት ተጽፏል ጥቅምት 20 ልደቱ ሲሆን ሰኔ 20 ቀን ደግሞ በዓለ እረፍቱ ነው።

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/

• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

26 Oct, 14:29


Orthodox_Quotes

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

25 Oct, 15:35


፩ኛ ዙር ዓመት ፬ኛ ሳምንት
ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ ቤት
https://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

25 Oct, 15:34


ዘጥቅምት ፲፯፤ ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)

(፩ኛ ዙር ዓመት፤  ፬ ሳምንት፥ ዘጥቅምት ፲፯)
በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት፤ ወቅዱስ ፊልጶስ ሰማዕት፤ ወዕረፍቱ ለአቡነ ዲዮስቆሮስ ካልዕ፤ ወልደታ ለቅድስት ሐና እመ ሳሙኤል፤ ወዕረፍቱ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ እኁኁ ለቅዱስ ባስልዮስ።

✤ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤
✤ የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው

✤ የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡

✤በማኅሌት በምትቆሙ ጊዜ በጸሎታችሁ ደብራችንን ደብረ ሰላምን፤ ሰ/ት/ቤታችንን ፍኖተ ሕይወትን እና በውስጧ ያሉ አገልጋዮቿን አስቡልን፡፡✤

• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

24 Oct, 08:13


ተሰአሎ ለአቡከ ወይነግረከ፤ ወለሊቃውንቲከ ይዜንዉከ፡፡ (አባትህን ጠይቅ ይነግርሃል፤ ሊቃውንትን ጠይቅ ያስታውቁህማል፡፡)
የኹሉንም ሳምንታት ማኅሌተ ጽጌ ቀድሞ ከአባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ዚቁን፤ ታላቁ ሊቅና ቅዱስ አባ ጽጌ ድንግል ከደረሰው ማኅሌተ ጽጌ ጋር እያስማሙ አቀናብረው ያቀረቡልን ዐበይት የላይ ቤትና የታች መምህራን፡፡ እነርሱም፤
✤✤ የላይ ቤቱን፤ መምህር ተክለማርያምና ሊቀ ማዕምራን ወመጋቤ ሐዲስ ወ/ሰንበት ባይነሳኝ፤ (ሁለቱም የቀለም ቀንድ የኾኑ ሊቃውንት የመጻሕፍተ ሐዲሳት ዋና ምስክርና የመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ዋና አስተዳዳሪ የነበሩ ናቸው፡፡)
✤✤ የታች ቤቱን፤ መምህር ክፍሌ ወልደ ጻድቅ ና መጋቤ አእላፍ ሄኖክ ወልደሚካኤል /ሁለቱም ሊቃውንት የደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ በዓታ የአቋቋም ዋና ምስክርና የደብሩ አስተዳዳሪ የነበሩ ናቸው።/

• Facebook 👉 https://www.facebook.com/

• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

20 Oct, 16:53


Channel photo updated

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

20 Oct, 16:28


#ዳሕምሞ_ #ደብረ_ዳሞ_
መላእክትም ለአረጋዊ እንደባልንጀራ አንደ ጓደኛ ሆኑት፤ እሳቸውን ለመጐብኘትና በረከት ለማግኘት አባቶች ብቻ ሳይሆኑ ንጉሡ አጼ ገብረመስቀልም ወደእሳቸው ይመጣ ነበር፡፡ እሱም እሰከዛሬ ምስክር ሁኖ የሚገኘውንና በእመቤታችን ስም የተሰየመውን ድንቅ ገዳም ሲያንጽ ለእንሳሳቱ መመላለሻ እንዲሆን ተራራን አሠራ፤ ሕንጻው ቅዱስ ያሬድ በተገኘበት ተመረቀች፤ ኋላ ግን ንጉሡ ከአረጋዊ ተባርኮ ሲመለስ ‹‹ተራራውን ላፍርሰው፤ ወይስ ልተወው?›› አለ፤  አቡነ አረጋዊም በግዕዙ ‹‹#ዳሕምሞ_›› አሉት፡፡  በአማርኛ ቋንቋ ‹‹የሰራኸውን ደረጃ ናደው ፥ አፍርሰው እንጂ አትተወው›› ማለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አካባቢው ዳሞ ገዳሙ ደግሞ ደብረዳሞ ተባለ፡፡ አቡነ አረጋዊም ንጉሡን ‹‹ስለዘንዶው ጅራት ፈንታ ሰዎች ይወጡበት ዘንድ ገመድ አብጅ፡፡ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ እንዲሆንና ይህን ድንቅ ሥራ እያየ በፍጥረቱ ሁሉ አንደበት እግዚአብሔር ይመሰገን ዘንድ፡፡›› አሉት፤ ለመወጣጫ ይሆን ዘንድ ገመድ ተሰራለት፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ገመዱ የታሠረበት ግንድ እስካሁን ከ1500 ዓመታት በላይ አለ፤ ኋላ በ13ኛው ክፍለ ዘመን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለ12 ዓመታት በደብረ ዳሞ ቆይተው በዚሁ ገመድ ሲወርዱ ነው ሰይጣን ቀንቶ ገመዱን ቢበጥስባቸው እግዚአብሔር አምላክ ክንፍ የሰጣቸው፡፡
ደብረዳሞ ዙርያው ገደል ሆኖ የጠረጴዛ ቅርጽ ያለው ያለው አምባ ሲሆን 500*1000 ሜትር የሚሆን ስፋት አለው፡፡ ከባህር ወለልም በላይ 2216ሜ. ከፍ ይላል፡፡ ወደ ገዳሙ መውጣት አና መውረድ የሚቻለው 16ሜ. በሚረዝመው በአምሳለ ዘንዶ በተሰራው ገመድ ብቻ ነው፡፡
   ንጉሡም ከተራራው እንደወረደ እንደታዘዘው አፈረሰ፡፡ አሁን የምናየው ዓይነት ገመድንም አዘጋጅቷል፤ የገመዱም ስመ ‹‹ዘንዶ›› ይባላል፡፡ በዚህ ገዳም ሴቶች በአፀደ ሥጋ እያሉ አይገቡም፤ ካረፉ በኋላ ግን እንደ አባ ጳኩሚስ ገዳምና ሥርዓት ከተከዜ ማዶ ከሚኖሩ የሴት መነኮሳት መካከል አንዲቱ የሞተች እንደሆነ ወደ ወንድሞች መነኰሳት አምጥተው በነሱ ዘንድ በሚገኘው የመቃብር ቦታ ይቀብሯቸው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የአቡነ አረጋዊ እናት የነበረችው ልጂ በሕፃንነቱ ሳለ መመንኰሱን አውቃ ከልጇ ሕይወቱን ተምራ ገና ከመጀመሪያ ወደ አባ ጳኵሚስ ገዳም ሄዳ መንኵሳ ነበርና በቅድስና በትሕትና ደናግሉ በፍቅር ስታስተዳድር ኖራ መንፈሳዊ ግዳጇን በጐ አገልግሎቷን ፈጽማ ጥር 4 ቀን ስታርፍ ለመቀበሪያዋ ይሆን ዘንድ አባታችን አቡነ አረጋዊ ባሰራላት አዲስ መቃብር ተቀብራለች፡፡
• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

18 Oct, 16:33


፩ኛ ዙር ዓመት ፫ኛ ሳምንት
ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ ቤት
https://t.me/finotehiwott

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

18 Oct, 16:32


ዘጥቅምት ፲፤ ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)

(፩ኛ ዙር ዓመት፤ ፫ኛ ሳምንት፥ ዘጥቅምት ፲)
በዓለ መስቀል ወቅዱስ ሰርጊስ ወሊቀጳጳሳት አውማንዮስ ወቀሲስ ዮሐንስ ሰማዕት።

✤ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤
✤ የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው

✤ የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡

✤በማኅሌት በምትቆሙ ጊዜ በጸሎታችሁ ደብራችንን ደብረ ሰላምን፤ ሰ/ት/ቤታችንን ፍኖተ ሕይወትን እና በውስጧ ያሉ አገልጋዮቿን አስቡልን፡፡✤

• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

15 Oct, 07:02


የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የዘመነ አበው ቀደምት ማኅሌት

ዛሬ በአፀደ ነፍስ ያሉ አባቶቻችን ሊቀ መዘምራን ሰምረ ወሌ፣ ሊቀ ጉባኤ አድማሱ ውበቱ ፣መምህር መርአዊ፣ መጋቤ ምስጢር መንግስቱ፣ሊቀ ጠበብት ምሕረቱ፣መዘምር ዘውገ እርገጤ፣ መዘምር ንጉሴ ሀብተ ወልድ፣መምሬ ታፈሰ፣ሊቀ አበው መኮንን፣ሊቀ አበው ሽፈራው፣መምሬ ካሳ፣መምሬ እስጢፋኖስ..... የሚገኙበት የዛሬዎቹ አበው በውርዝውና ዘመናቸው ሳሉ... በትውስታ ወደኋላ የጎተተን ማኅሌት

የአባቶቻችን በረከት ይደርብን

.Facebook...
https://www.facebook.com/
.Telegram... https://t.me/finotehiwott
http://tiktok.com/@finotehiwot
.YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

13,183

subscribers

11,572

photos

61

videos