TIKVAH-SPORT @tikvahethsport Channel on Telegram

TIKVAH-SPORT

@tikvahethsport


TIKVAH-SPORT (English)

Are you a sports enthusiast looking for a community to share your passion with? Look no further than TIKVAH-SPORT! This Telegram channel is dedicated to all things sports-related, from the latest game updates to insightful analysis and discussions. Whether you're a fan of football, basketball, tennis, or any other sport, you'll find like-minded individuals to connect with here. TIKVAH-SPORT provides a platform for sports lovers to interact, share news, and engage in friendly debates. Stay updated on the latest scores, player transfers, and tournament schedules with the help of our dedicated team of moderators. Join TIKVAH-SPORT today and be a part of a vibrant sports community that celebrates the thrill of the game!

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 12:47


አርሰናል የትሮሳርድን ውል ማራዘም ይፈልጋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የቤልጂየማዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ትሮሳርድ ውል ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም ማሰባቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ የተጫዋቹን ውል ከውድድር አመቱ መጨረሻ በፊት ለማራዘም ንግግር መጀመራቸውን ዴይሊ ሜል በዘገባው አስነብቧል።

ለአርሰናል ጥሩ ግልጋሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ሊያንድሮ ትሮሳርድ በአዲሱ ኮንትራት ትልቅ የደሞዝ ክፍያ ጭማሪ ሊደረግለት እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 12:37


ሬስ ጄምስ በድጋሜ ጉዳት አጋጠመው !

እንግሊዛዊው የሰማያዊዎቹ የመስመር ተጨዋች ሬስ ጄምስ በድጋሜ መጠነኛ ጉዳት እንዳለበት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ገልፀዋል።

“ አንድ ተጨዋች ተጎድቶብናል እሱም እንዳለመታደል ሆኖ ሬስ ጄምስ ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ኢንዞ ማርስካ ተናግረዋል።

ተጨዋቹ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው የገለፁት አሰልጣኙ በዚህ ሳምንት ለጨዋታ ዝግጁ አለመሆኑን አረጋግጠዋል።

ሬስ ጄምስ በቀጣይ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ እንደማይርቅ ተስፋ እናደርጋለን በማለት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 12:36


ልዩ የእንኳን ደህና መጡ ጉርሻ!
ደንበኛ ይሁኑ! ይወራረዱ! 100% ጉርሻ ያግኙ!
እንኳን ደህና መጡ! የመጀመሪያ ብቁ የሆነ ውርርድዎን ሲያደርጉ የተወራረዱበትን ገንዘብ መጠን እስከ 100% እንደ ጉርሻ ያገኛሉ።
አሁኑኑ Betika.et ላይ ቤቲካን ይቀላቀሉ!

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 11:07


“ ለመሰለፍ ያላቸውን መስጠት አለባቸው “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የቡድናቸው ተጨዋቾች ብዙ ሰዓት ለመጫወት ያላቸውን መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

“ ሜዳ ላይ ያለውን ሁሉ የማይሰጥ ተጨዋች አይጫወትም “ ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ ተጨዋቾች ያላቸው ትልቅ ስም ለውጥ እንደማያመጣ ያውቁታል ብለዋል።

ሜዳ ላይ ያለውን ሁሉ የማይሰጥ የቡድኑ ተጨዋች የጨዋታ ሰዓቱም ከተለመደው ያነሰ ይሆናል ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 09:05


ዩናይትድ በቀጣይ ምን ማስፈረም ይፈልጋል ?

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ የ 2025 የዝውውር መስኮት የግራ መስመር ተጨዋች ለማስፈረም ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በተለያዩ ቦታዎች መጫወት የሚችል የግራ መስመር ተጨዋች ማስፈረም እንደሚፈልጉ የዝውውር ጉዳዮችን የሚከታተለው ፋብሪዝዮ ሮማኖ አስነብቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከያዛቸው ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ የባየር ሙኒኩ አልፎንሶ ዴቪስ እና የበርንማውዙ ሚሎስ ኬርኬዝ እንደሚገኙበት ተነግሯል።

በተጨማሪም ከሶስት በላይ ተጨዋቾችን በአማራጭነት መመልከት መጀመራቸው ተጠቁሟል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 08:37


“ ሮናልዶን በአይናችን እስክናይ አላመንም ነበር “

የአል ነስሩ ተጨዋች አብዱራህማን ጋሪብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ አል ነስር ይመጣል በተባለበት ወቅት እውነት መሆኑን ማመን ከብዷቸው እንደነበር ገልጿል።

“ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ አል ነሰር ሊመጣ ነው ተብሎ ሲነገረን ከፊታችን ቆሞ በአይናችን እስከምናየው ድረስ ሁላችንም አላመንም ነበር “ ሲል ተጨዋቹ ተናግሯል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በበኩሉ “ አብዱራህማን ጋሪብ እኔን እንደ አርኣያው በማየቱ እና የእኔን ዱካ በመከተሉ ደስተኛ ነኝ።“ በማለት ተናግሯል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 08:09


አንቶኒዮ ሩዲገር ማልያው ለጨረታ ሊያቀርብ ነው !

ጀርመናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አንቶኒዮ ሩዲገር ለብሶ የተጫወተበትን የሪያል ማድሪድ ማልያ ለጨረታ ሊያቀርብ መሆኑ ተገልጿል።

አንቶኒዮ ሩዲገር ማልያውን ለጨረታ የሚያቀርበው የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸውን ጉማሬዎች ለመታደግ መሆኑ ተነግሯል።

ከጨረታው የሚገኘው ገቢ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ሴራሊዮን የሚገኙ ጉማሬዎችን ከመጥፋት ለመታደግ ይውላል ተብሏል።

የ 31ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አንቶኒዮ ሩዲገር በቅርቡ የበርሊን መካነ አራዊት የክብር አጋር እንደሆነ ይታወቃል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 07:01


ሜሲ በባርሴሎና ዝግጅት ላይ ሊገኝ ነው !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከሳምንት በኋላ 125ኛ አመት ክብረ በዓሉን እንደሚያከብር ተገልጿል።

በክብረ በዓሉ ላይ የክለቡ ታሪክ አይሽሬ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክለቡ ልሳን የሆኑ መገናኛ ብዙሃን አስነብበዋል።

የባርሴሎና 125ኛ አመት ክብረ በዓል በሚቀጥለው ሳምንት አርብ በታዋቂው ባርሴሎና ሊሴው ኦፔራ አዳራሽ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በክለቡ 125ኛ አመት ክብረ በዓል ላይ አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ትልቁ እንግዳ ሆኖ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 06:05


" ስተርሊንግ ከክረምቱ መጥፎ ፊርማዎች አንዱ ነው " ኢማኑኤል ፔቲት

የቀድሞ ፈረንሳዊ ተጨዋች ኢማኑኤል ፔቲት አርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ራሂም ስተርሊንግን ማስፈረሙ ስህተት እንደነበር ገልጿል።

" ስተርሊንግ ከክረምቱ መጥፎ ፊርማዎች አንዱ ነው " የሚለው ፔቲት "አርሰናል እሱን ማስፈረማቸው ልክ አልነበረም" ሲል ተደምጧል።

ራሂም ስተርሊንግ ባለፉት አመታት በርካታ ገንዘብ መሰብሰቡን ተከትሎ ከዚህ በኋላ ለምንም ነገር ተነሳሽነት እና ፍላጎት እንደማይኖረው ኢማኑኤል ፔቲት ተናግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 05:40


" ሜሲ የምንጊዜም ምርጡ ተጨዋች ነው " ሮድሪ

ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ አርጀንቲናዊውን ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ " የምንጊዜም ምርጡ ተጨዋች " ሲል ገልፆታል።

" ጥርጥር የለውም ሜሲ የምንጊዜም የአለማችን ምርጡ ተጨዋች ነው " ያለው ሮድሪ " አለማችን በእሱ ደረጃ ያለ ተጨዋች ተመልክታ አታውቅም።"ብሏል።

የባሎን ዶር አሸናፊው ሮድሪ ሜሲን በተቃራኒ መግጠም አስቸጋሪ መሆኑን በመግለፅ " ከእሱ እግሮች ኳስን መንጠቅ እጅግ ከባድ ነው።" በማለት ተናግሯል።

በሮናልዶ እና በሜሲ ያለውን ልዩነት ለመረዳት ከሁለቱም ጋር መጫወት በቂ ነው ያለው ሮድሪ " ሁለቱም ትልቅ ተጨዋቾች ናቸው ነገር ግን ሰፊ ልዩነት አላቸው።" ብሏል።

" ከሮናልዶ ጋር ስትጫወት ሳጥን ውስጥ ኳሶችን እንዳያገኝ ለማድረግ ትጥራለህ ከሜሲ ጋር ግን የትም ቢሆን ኳሱ በጭራሽ እሱ እግር ላይ እንዳይደርስ ለማድረግ ትሞክራለህ።" ሮድሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 05:25


ፒያሴንዛ በአንድ ቀን ሁለት አሰልጣኝ አሰናብቷል !

የጣልያን አራተኛ ሊጉ ክለብ ፒያሴንዛ በአንድ ቀን ውስጥ ሁለት አሰልጣኞችን ማሰናበቱ ተገልጿል።

ክለቡ ማክሰኞ ጠዋት አሰልጣኙን አሰናብቶ አሰልጣኝ ሲሞኒ ቤንቲቮግሊዮ የሾመ ሲሆን አሰልጣኙ ቡድኑን ለአንድ ጊዜ ብቻ አሰልጥነው ከሰዓት መሰናበታቸው ተነግሯል።

ፒያሴንዛ አዲሱን አሰልጣኝ በአንድ ቀን ያሰናበተው የክለቡ ደጋፊዎች የልምምድ ማዕከሉን ሰብረው በመግባት አሰልጣኙ እንዲሰናበት በመጠየቃቸው መሆኑ ተገልጿል።

አሰልጣኙ ከዚህ በፊት የጨዋታ ማጭበርበር ፈፅመዋል በሚል የተቀጡ መሆናቸው የክለቡን ደጋፊዎች እንዲያስቆጣ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

በአንድ ቀን ውስጥ ሶስተኛ አሰልጣኝ የሾመው ፒያሴንዛ በመጨረሻም በ 24 ሰዓታት ውስጥ ሶስት አሰልጣኞች የመሩት የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።

ፒያሴንዛ ከአመታት በፊት በጣልያን ሴርያ ተወዳዳሪነቱ ይታወቃል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 05:01


ሁዋን ማታ የክለብ ባለቤት ሆኗል !

የቀድሞ የቼልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሁዋን ማታ የአሜሪካው ክለብ ሳን ዲዮጎ አክሲዮን ድርሻ ባለቤት መሆኑ ተገልጿል።

ሁዋን ማታ አሁን ላይ በተጨዋችነት እየገለገለ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር የክለብ ባለድርሻ መሆን የቻለ የመጀመርያው ተጨዋች ሆኗል።

" የዚህ ክለብ አካል መሆን በመቻሌ ደስተኛ ነኝ ለደጋፊዎች ክለቡን ትልቅ ደረጃ ላይ ለማድረስ ያለእረፍት እንደምንሰራ ቃል ልገባላቸው እወዳለሁ።"ሲል ሁዋን ማታ ተናግሯል።

የአለም ዋንጫ አሸናፊው ሁዋን ማታ በአሁኑ ሰአት በአውስትራሊያው  ክለብ ዌስተርን ሲድኒ ወንደረርስ በመጫወት ላይ ይገኛል።

@Tikvahethsport               @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 04:51


ሲቲ ወሳኝ ተጨዋቾቹ ልምምድ ሰርተዋል !

እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆን ስቶንስ ከጉዳቱ በማገገም ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

ከሀገራት ጨዋታ በኋላ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ የሚጠበቀው ኬቨን ዴብሮይን በተመሳሳይ የቡድን ልምምዱን መሰራት ችሏል።

በተጨማሪም ጃክ ግሪሊሽ እና ማኑኤል አካንጂ ወደ ቡድን ልምምድ የተመለሱ ሌሎች የማንችስተር ሲቲ ተጨዋቾች መሆናቸው ተዘግቧል።

ማንችስተር ሲቲ የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 2:30 ከቶተንሀም ጋር የፕርሚየር ሊግ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 04:51


#Wanaw_Premium
🔥ዋናው ስፖርት ከትጥቅም በላይ ነው ስንል በምክንያት ነው ውብ ህብረትን ከሀገር አልፎ ኡጋንዳም እያጎናጸፈ ይገኛል🤩🔥
የአፍሪካችን ኩራት!!!🔥

Call us!
📞 8289


Chat With Us
🤖 Wanaw Bot

Follow Us
Website|Instagram|Facebook|TikTok|X|Youtube|Telegram

🏅 ዋናው ወደፊት...
🌍Made In Africa🌍

TIKVAH-SPORT

21 Nov, 04:51


iPhone 16 Pro Max
•256GB = 189,000 Birr
•512GB = 219,000 Birr

iPhone 15 Pro Max
•256GB = 154,000 Birr
•512GB = 164,000 Birr

Contact us :
0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@Heyonlinemarket

TIKVAH-SPORT

20 Nov, 19:06


“ የሊቢያ ፖሊሶች ተጨዋቾችን ደብድበዋል “ የቤኒን አሰልጣኝ

የቤኒን ብሔራዊ ቡድን ከሊቢያ ጋር በነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ ወቅት ጥቃት እንደደረሰበት የቡድኑ አሰልጣኝ ጌርኖት ሮህር ተናግረዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ በሊቢያ በነበረው ቆይታ ባልተገባ መልኩ ከመልበሻ ቤት እንዳይወጣ ተደርጎ እንደነበር ተዘግቧል።

የቡድኑ አሰልጣኝ ጌርኖት ሮህር ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃል የሊቢያ ፖሊሶች የቤኒን ተጨዋቾች እና አሰልጣኝን በዱላ መደብደባቸውን አስታውቀዋል።

የቢኒን ብሔራዊ ቡድን ከሊቢያ ጋር ያደረገውን ጨዋታ አቻ መውጣቱን ተከትሎ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ማረጋገጡ አይዘነጋም።

ሊቢያ በቅርቡ በናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ላይ ባደረጉት ያልተገባ ድርጊት በፎርፌ ሶስት ነጥብ እና ሶስት ጎል እንደተሰጠባቸው ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

TIKVAH-SPORT

20 Nov, 18:12


“ የሳውዲ ሊግን ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአል ነስር ጋር የሊጉን ዋንጫ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

የሳውዲ አረቢያን ሊግ የተመለከተ ዘጋቢ ፊልም በኔትፍሊክስ ለእይታ ሲቀርብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዘጋቢ ፊልሙ አስተያቱን ሰጥቷል።

ሮናልዶ ካነሳቸው ሀሳቦች መካከልም :-

- “ እዚህ ያለሁት ለማሸነፍ ነው ወደ አል ነስር የመጣሁት ቡድኑን ለማሻሻል እና ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ነው።

- የሳውዲ አረቢያ ሊግ ዋንጫ እንደማሸንፍ እና አል ነስርን እንደማሻሽል ተስፋ አደርጋለሁ።

- ወደዚህ የመጣሁት ለገንዘብ እንደሆነ ይናገራሉ ነገርግን ስህተት ነው እዚህ የመጣሁት የእግርኳስ ፍቅር ስላለኝ ነው።

- የሳውዲ አረቢያ ሰዎች በጣም ተግባቢ እና ጥሩ ሰው ናቸው ደግነታቸውን መክፈል እፈልጋለሁ።

- እኔ አሁንም ለመፎካከር ብቁ ነኝ ሰዎች ሁልጊዜም ሮናልዶን ይጠራጠራሉ በመጨረሻ ያልተጠበቀ ነገር ይመለከታሉ።“ ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe