Venue @venuee13 Channel on Telegram

Venue

@venuee13


መድረሻ ባይኖር ፣ መጓዝ ብርቅ ነበር!
:
መራመድ ባልከፋ ፣ መድረሻም ባልጠፋ
ነገ ላይ ለመድረስ ፣ ሰው ባያጣ ተስፋ ።

Venue (Amharic)

የአርብ ከተማ የባህል ድንበር ላይ ተቀንስቀናል ። ስለእነዚህ ቅንብሳ መድረሻ ባይኖር ለሆነ እናሽፋለን። ይህ መድረሻ ይህን ተመሳሳይ ምርጫ ነበር። የሚከተሉት መራመድ ባልከፋ ፣ መድረሻም ባልጠፋ። ሌላው ነገ ላይ ለመድረስ ፣ ሰው ባያጣ ተስፋ ። ይህ መሳሪያ የዚህን መድረሻን እንዲሁም ላይ እንደዳባዝት ይረዳል። የሚከተሉት ቦታዎችን ስናገ ሹክ ።

Venue

20 Nov, 18:38


በልብ ከተሸሸጉ ህመሞች ውስጥ በተቆጠቡ ቃላት ብቻ መንገዳችንን እንድንቃኝ አወጋን። ፅሁፎቹ ቀጥተኛ አንድ ትርጉም ብቻ የላቸውም። በደንብ እናስብበት ዘንድ ለአዕምሮ ባልተቤቶች ተትቷል። እናንተ መልካሙን የምመኝላችሁ ሆይ ሰላም ለልባችሁ! 🙏🙏🙏
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

20 Nov, 18:28


« ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ የተሰበረ ልብ ያለውን አይፈልግም። ወንጀል እያለበት ተውበት(ንሰሀ) ያደረገን ለመቀበል ይኮፈሳል።
የታመመ ወይም የሚታወቅ ህመም ያለበትን ለመቀበል ብዙ ሰው ይተናነቀዋል። (ጤነኛ የተባለውን ሰው ቀደር ያወቀ ይመስል!) ሰው ጠልቼ እንዳይመስልህ ሰው የምሸሸው! »
እቅፍ የናፈቀ ህመም የተሸከመ ልቧ በቃላቶቿ ውስጥ ሲጮህ ተሰማኝ። አለቅልቃ የደፋችውን ትላንት እንዳትረሳ ይመስል ዛሬ ላይ ስትነፃ ከደፋችው የትላንት ዝቃጭ ላይ እያነሱ ሲያቆሽሿት ስብርብር የምትል ልብ ሲቃ በቃላቶቿ ውስጥ አዳመጥኩ።
« ብቻ አንተ ሰው የሚጥለውን ሁሉ አትጣል። ወደ ጌታው የሚሄድን መንገድ እንዳታስት! »
ከዚህ በላይ ቃል ማውጣት ተስኗት ተለጎመች። በእሷ ውስጥ ተቀባይነት ያጣ ድንግል ንፅህናን አየሁ። ይገርማል ለካ ሰው የሚጥለው ሁሉ ልክ አይደለም። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

20 Nov, 18:13


« የምንዋደድበት፣ የምንነፋፈቅበት ወቅት ላይ መች ተዋወቅን። ትንሽ ስንቀያየም ፍቅራችንም፣ የምር ባህሪያችንም ታየ። አየህ ምናልባት ትንሽየው መቀያየማችን ትላንታችንን እንድንጠይቅ አደረገን። ሰው መቼስ የማያልቅ ፍጥረት ነው። እያንዳንዱ እርምጃዎቹ እየገነቡት፣ እየገለጡት ይመጣሉ።
እንደው ጌታዬን እሱን በጀነት እፈልጋለሁ ብዬ ስለጠየቅኹት ልቆጭ ወይስ እዚሁ ዱንያ ላይ ብዙውን ሳንጓዝ መንገዳችን ስለተለያየ ልደሰት?»
በቃል ልትገልፀው ያቃታት ስሜት አይኗ ሲደነባበር ያወጣዋል። አይኗ በእንባ ውቅያኖስ ውስጥ ላለመስጠም ሲንደፋደፍ የልቧ የታፈነ ግለት ይወጣል።
« ብቻ አንተ ከምትወደው ጋር ስትቀያየምም፣ ስትጣላም የወደደህ ሰው ካንተ ጋር የተመኘው የነበረው ምኞት ኃጥያት እስከሚመስለው ድረስ አትጣመም። »
በእንባ የወጣውን የልቧን ቃል ከአይኗ እያሸሸች፣ አታላይ ፈገግታዋን አሳየችኝ። እሷን ካየሁ በኋላ ጀነት እንድንገኛ የተመኘኋቸውን ሰዎች ስንጣላ፣ ስንቀያየም እንዴት እንሆን ይሆን እያልኩ ሀሳብ ገባኝ። ይገርማል ለካ አንዳንዴ የተመኙት ምኞት ኃጥያት የሚመስልበትም ጊዜ ሊመጣ ይችላል! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

20 Nov, 17:53


« ካነሳኝ የበለጠ የጣለኝ፣ ከደገፈኝ የበለጠ የገፋኝ ይበዛል። ይኸው ልቤ ለፍቅር ቦታ አጥቶ ባዶ ሆኗል። ባዶ ሆኖ ፍቅርን መቀበል ሲከብደው ግን አይገርምም?
ባዶ ነገር ግን ብዙ ነው። የባዶ ነገር ሸክም ከባድ ነው። አህ… ይተናነቀኛል ግን እንባ አጣለሁ። መጮኽ እፈልጋለሁ ግን ድምፅ ይርቀኛል። ተናገሪ ተናገሪ ይለኛል ግን ቃል ይጠፋብኛል!
ብቻ አንተ ከእንግዲህ ሰው ልቤ ባዶ ነው ካለህ ትልቅ ሸክም እንደተሸከመ እወቅ! እውነት እልሀለሁ ባዶ ነገር ይከብዳል! »
ያለ እንባ ማልቀስ፣ ያለ ቃል መናገር፣ ያለ ድምፅ መጮህ እሷን ይመስላል።
« ምንድን ነው ልብሽን ባዶ ያደረገው? »
« ምናልባት እምነቴ፣ ምናልባት የዋህነቴ፣ ምናልባት ጥበቃዬ፣ ምናልባት ጉጉቴ፣ ምናልባት አለማወቄ፣ ምናልባት ህልሜ፣ ብዙ ምናልባት! የቱን ልጥቀስልህ……? ብቻ ተወው! »
ለካ ባዶ ነገርን መተንተን ማስረዳት ይደክማል! ደከማትና ተወው ብላ ተዝለፈለፈች።
እውነቷን መሰል ልብ ባዶ ሲሆን ሸክሙ ትልቅ ነው። ለካ ባዶ ነገር ይከብዳል። የባዶ ነገርን ክብደት በእሷ አየሁት!
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

18 Nov, 17:23


« እውነተኛ የሆኑ ታሪኮችን ማንበብ ከሚማርካቸው ሰዎች መሀል እገኛለሁ። በተለይ ወደ ኋለኛው ዘመን ላይ የተሰሩ ገድሎችን ሳነብ ለየት ያለ ስሜት ከሚሰማቸው ሰዎች ሳልመደብ አልቀርም። እስቲ በንባብ ከተገኘና ካስቀረሁት አንድ ገድል ሹክ ልበላችሁ። የጣሪቅ ቢን ዚያድን ገራሚ ገድል ላስታውሳችሁ።
እወሮፓዊቷ ሀገር ስፔን በእስልምና ሥርዓት ያሸበረቀች፣ የእውቀትና የሥልጣኔ ማዕከል የነበረች የሙስሊሞች ግዛት ነበረች።
የታሪክ መዛግብት ይህን አስደናቂ ታሪክ ከትበው አውስተዋል። አንደሉስ የስፔን እና የፖርቹጋል ግዛት በአንድ ላይ በአንድ አስተዳደር ስር የነበረበትን ወቅት ለማመልከትም እንደሆነ የታሪክ ሊቃዉንቶች ይገልፃሉ። ለማንኛውም የአሁኗ ስፔን ወርቃማዋ አንደሉስ ነበረች!
አውሮፓውያን በድንቁርና ፅልመት እየዳከሩ በነበሩበት ወቅት ከጽልመታቸው የገዘፈ ብርሀን የያዘው እስልምና በምድራቸው ፈነጠቀ። አንደሉስ በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር ገባች።
ነገሩ እንዲህ ነው የሙስሊሞችን ጦር የሚመራው ጣሪቅ ቢን ዚያድ ተራራዎችን ተሻግሮ ባህሮቹን ቀዝፎ ወደ አንደሉስ ደጃፎች ደረሰ። የአንደሉስ መሪ የነበረው ንጉስ ሮድሪክ የጣሪቅ ቢን ዚያድን ሰራዊት መገስገሱን ሲሰማ እጅግ ብዙ ሰራዊት ላከ። ጣሪቅ ቢን ዚያድ ሰራዊቱን በአንድ ላይ ካደራጀ በኋላ ባህሩን ቀዝፈው የመጡባቸውን መርከቦች እንዲቃጠሉ አደረገ። ከሰራዊቱ ፊት ለፊት ቆሞም እንዲህ አላቸው።
«እናንተ ሰዎች ሆይ ወዴት ትሸሻላችሁ ከእንግዲህ መሸሽ የለም። ከበስተኋላችሁ ባህር ከፊት ለፊታችሁ ጠላቶቻችሁ አሉ። ለአላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እውነተኛና ታጋሽ ከመሆን በቀር የሚጠቅማችሁ ነገር የለም። እዚህ ደሴት ላይ ስትሆኑ ይህን እወቁ ወላጆቹን ካጣ ሰው በላይ ሁሉን ያጣችሁ ናችሁ፣ ከፊት ለፊታችን ያለውን የታጠቀ ጠንካራ ሰራዊት ሰይፎቻችሁን አንስታችሁ በጀግንነት ካልተፋለማችሁ ምንም ሆናችሁ ትቀራላችሁ። ትኩረታችሁን የአላህን ሽልማት ማግኘት ላይ አድርጉ! በዚህ ጦርነት ላይ እኔ ሳልደርስ ብገደል እናንተ በፍፁም አታቁሙ! ወደፊት ገስግሱ! የአላህ ሱብሀነሁ ወተዓላን ቃል በዚህ ምድር ላይ ለማንገስ ተፋለሙ! »
በጣሪቅ ቢን ዚያድ የሚመራው የሙስሊሞች ጦር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የንጉስ ሮድሪክን ሰራዊት ገጠመ። ጦርነቱም በሙስሊሞች አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ሙስሊሞችም የአንደሉስ መፃዒ እድል ቀይረው በፍትሀዊነትና በጥበብ ለ903 አመታት ድረስ አስተዳደሩ።
ትንሽ ታሪኮቻችንም ገለጥ ገለጥ ስናደርግ ልባችን ረጠብ ይላልና እያነበብን! እየጠየቅን ለማለት ነው። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

17 Nov, 17:14


« በትክክለኛው መንገድ ለሚገባሽ ሰው እንዳታልቂ፣ የልብሽን ቀሚስ ላላፊ አግዳሚው አትግለቢ። አላህ ለማያዝንብሽ ግንኙነት ገላ ብቻ ተሸክመሽ እንዳትኖሪ፣ ልብሽን ዘልዛላ አታድርጊው። እቴ ከአጉራ ዘለል ፍላጎትሽ ጋር አኩኩሉ አትጫወቺ።
ልብሽ አደብ ካልያዘ ዝሙት አይከብድሽም።
እቴ ውበት እና ክብርሽን ካጣሽ፣ ዳግም መታደስ ከፈለግሽ በተውበት በር ዝለቂ። አላህ በቃ እስካላለ ድረስ ምንም የሚያበቃ ነገር የለምና ሰዎች ተስፋ ሲያስቆርጡሽ አላህ ዘንድ ተሸሸጊ። አላህ ጥፋቶችን በመላ ይምራልና ለተውበት አትኩሪ! እቴ ልብሽን ጠብቂ! የምወድሽዋ ሰላም ለልብሽ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

17 Nov, 16:36


« ብዙ ሰዎች የተውበት(ንሰሀ) ትልቅነት ገና በደንብ በጥልቀት አልተረዱም። የተውበትን ትልቅነት ለወሬ ማድመቅያ፣ ለስብከቶች አፍ መሟሻ ከማዋል በዘለለ እውነተኛ ተውበት ያደረጉትን ለማክበር እና ለመቀበል ብዙ ሰው ያመነታል።
እረፉ ተውበት አይናቅም። ብታውቁ ተውበትን አለማክብር የአላህን ቀደር መሟገት ነው።
እናንተ ወደ አላህ ተመላሾች ሆይ ሁሉም ሰዎች ተውበታችሁን ባይቀበሉ አትዘኑ። የተውበትን ትልቅነት፣ ልቅና የሚያውቁት እነዝያ የአላህን እዝነት የተረዱት እንጂ እውነቱን የማይነሩት አይደሉም።
የአላህ ባሮችን ተውበት የምትንቅ ልብ ወየውላት! ወደ አላህ የተመለሱ ሰዎችን ተውበት የምታጣጥል ነፍስ የአላህን ቀደር እያስተባበለች እንደሆነ ትወቅ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

17 Nov, 16:20


ምንም ቢሆን ሰላም ለልባችሁ ይሁን! 🙏🙏
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

16 Nov, 17:37


የማከብራችሁ ሰላም ለልባችሁ! 🙏🙏🙏
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

16 Nov, 17:29


« አንቱ ሰው እስቲ ምከሩኝ? »
« የኔ ልጅ አንድ ሰው ነበር። እሱም ዝሙት ፈፀመና ስላረካኸኝ ተመስገን ጌታዬ አለ። »
« ጌታውን እንዴት ቢንቀው ነው? »
« አለማወቅ ጌታን ያስንቃል። የኔ ልጅ ጌታህን እንዳትንቀው እወቀው! »
« አንቱ ሰው እወዶታለሁ! »
« ከጌታህ ዘንድ ክብር አትጣ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

16 Nov, 17:23


« ልብ በደንብ የሚያውቀው ዘንድ ነው መመለስን የሚሻው፣ ከርሞ ከርሞ የሚመለስበት ያው አለሁበት የሚለው መዘውተርያው ላይ ነው።
መጠጥ ጠጥቶ የሚሰክረውን ሰካራም ማለት ችለን፣ የልቡ መመሰቃቀል ለሚያንገዳግደው እንደምን ስያሜ አጣን?
ሰው አይሰክርም ብቻ በመጠጥ
ይሰክራል በደንብ ታሞ ሲያገጥ። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

16 Nov, 16:45


« ጌታዬን በደንብ እንዳውቅ ሰበብ የሆነኝ ሰው ከሰዎች ሁሉ በላጩን ውለታ ውሎልኛልና ባለ ዕዳው ነኝ። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

16 Nov, 08:40


አንዳንዴም ከቃላት ውጪ በምስል ሀሳቦቻችንን ለመግለፅ ስንሞክር!
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

15 Nov, 18:27


ሰላም ለልባችሁ! 🙏🙏🙏
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

15 Nov, 06:26


« አዛኙ እንያ ልዕለ ምግባር፣ የመልካም ነገሮች ሁሉ ፊት ቀደም፣ ፈገግታቸው ልብን በትፍስህት የሚያጥለቀልቅ፣ ንግግራቸው ዘመን አዝማናት ቢነጉድ እየጠለቀ፣ እየረቀቀ የሚያስገርም፣ እንያ የውበት ባለሟል፣ የአፍቃሪዎች አውራ፣ የሰውነት ሚዛን ልኬት፣ እንያ አይጠገብ ሰርክ ተናፋቂ፣ ፈፅሞ ቀልብ ሰብረው የማያውቁት ንፁሁ ነብይ እንዲሀ ብለው ዱዓ ያደርጉ ነበር።
አላሁመ ፈአዩ ማ ሙዕሚነን ሰበብቱሁ፣ ፈጀዓል ዛሊከ ለሁ ቁርበተን ኢለይከ የውመል ቂያማ። አላህ ሆይ የትኛውንም ሙዕሚን በንዴትም ይሁን ሌላ ነገር ለመግለፅ የተናገርኳቸው እንደሆነ ያ ንግግሬን የውመል ቂያማ አንተ ዘንድ የሚያቃርባቸው አድርግልኝ።
መገን አላህ የወደደውን ማስወደድ ከእርሱ በቀር ማን ያውቅበታል? (ማንም)
ይህን ዱዓ ያደረጉበትን አንድ ቅፅበት እስቲ አንስተን እናውጋ።

ኡሙ ሱለይም ጋር የምትኖር አንዲት የቲም ልጅ ነበረች። ረሱል ለረጅም ጊዜ አላዯትም ነበርና ልክ ሲያዩዋት አንቺ ነሽ?
ለቀድ ከቢርቲ ላ ከቢረ ሲኑኪ አሏት። ትልቅ መሆን እስክታቆሚ ያህል ትልቅ ሆነሻል። ረሱሉላህ ለውጧን ተመልክተው አድገሻል ማለታቸው ነበር። ይህች ትንሽዬ ልጅ ግን ከረሱል ከተለየች በኋላ እያለቀሰች ወደ ቤት ተመለሰች።
ኡሙ ሱለይም ተመልክታት ማ ለኪ ያ ቡነየቲ ምን ሆነሻል የኔ ልጅ ስትል ጠየቀቻት።
ዳዓ አለየ ነብየላህ ነብዩ በኔ ላይ ዱዓ አደረጉብኝ ከዚህ በኋላ አላድግም፣ ከዚህ በኋላ አላረጅም ስትል መለሰች።
ይህች የቲም ትንሽዬ ልጅ ነብዩ ዱዓ ስላደረጉብኝ ከዚህ በኋላ ወይ ቶሎ መሞት ነው አልያም ባለችበት እድሜ ትልቅ ሰው ሳትሆን እንደምትኖር ነበር የተሰማት። ለዚህም አለቀሰች። ነብዩን ግን አልተቀየመችም። ገና በልጅነቷ እውነተኛ መሆናቸውን ተመልክታለቻ። ደጉን እንስፍስፉን ነብይ ማን ይቀየማል? (ለስሜቱ ባርያ የሆነ ጠማማ ቢሆን እንጂ!)
ኡሙ ሱለይም ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ምን ያህል የቲሞችን እንደሚወዱና እንደሚንከባከቡ ታውቃለች። የልጅቷ እንደዚህ መሆን የሆነ ችግር ሳይኖር አይቀርም ብላ ነገሩን ለማጣራት ወደ ሀቢቡላህ ዘንድ አቀናች። እየተጣደፈች ወደ ረሱል ጋር ስትመጣ ረሱል ተመልክተዋት ማ ለኪ ያ ኡሙ ሱለይም ምን ሆነሻል የሱለይም እናት አሏት።
አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ የቲም ልጄን ረግመዋታል እንዴ? አለቻቸው። ( እዚህ ጋር እንያ ለሚያስተነትኑት ረሱሉላህ ምን ያህል አቅራቢ እና ሰዎችን እንደሚረዱ፣ ሰዎችም ረሱሉላህን ለማናገር ነፃነት እንደሚሰማቸው ይረዳሉ።)
ረሱልም ኡሙ ሱለይም ሆይ ምንድን ነው የምትዪው አሏት። ነብዩ ዱዓ አድርገውብኛል ከዚህ በኋላ አላድግም እያለች ነው ስትላቸው ነብዩላህ ፈገግ አሉ። (ምን ያምር ፈገግታ! አላህ አላህ!)
ኡሙ ሱለይም ሆይ በእኔና በጌታዬ መሀል ምንም ብናገር የተናገርጉት ነገር ለዛ ሰው የማይገባው ቢሆን እንኳ የውመል ቂያማ ወደ አላህ መቃረብያ መልካም ነገር እንደሚያደርግላቸው አታውቂምን! አሏት!
ሰርክ ተገልፀው የማያልቁ፣ ዝንት ቢያወሷቸው የማይጠገቡ የፍጥረታት እንቁ የሆኑት ነብያችን እንዲህ ናቸው።
ይህን ልብ ይሏል! ብዙዎች ፍቅርን ተጠቅመው አፈቀሩ። እንያ ፍቅር ግን ፍቅርን ሆኑ። በእርግጥም ፍጥረታት ፍቅር መሆንን ከእሳቸው ሊማሩ ተጉ። አንዳቸውም ግን ፍቅርን ማፍቀር እንጂ ፍቅርን መሆን አልተቻላቸውም። ከፍጥረታት ውስጥ የፍቅር የረቂቅነት ጥልቀት ሚዛን ልኬታውን ያሟሉት ፍቅርን የሆኑት ፍቅር የሚናፍቃቸው ንፁሁ ፍቅር ብቻም ሆኑ። በእርግጥም ፍቅር የልቅና ስሙ ሙሀመድ አለይሂ ሰላም እንጂ ሌላ አይደለም።
አል ወዱድም እንደሳቸው ያላቀው፣ ፍቅር ሲነሳ እንደ ንፁሁ ፍቅር መወሳቱን ከፍ ያደረገው አንድም ፍጥረት የለም።
መገን አላህ ከእርሱ በቀር የሚወደውን ማስወደድ ማን ያውቅበታል? (ማንም)
የአላህ ሰላም እና እዝነት በታማኙ፣ ቀልቦችን በፍቅር በዳበሱት፣ በሰናይ ምግባር አቻ በማይገኝላቸው፣ በኸዲጀቱ አፍቃሪ የፍጠረታት እንቁ በሆኑት፣ በመጨረሻው እና በመደምደምያው ነብይ በረሱሉል አሚን ላይ ይሁን! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

14 Nov, 17:45


በስተመጨረሻ በልባችሁ ከምትሸከሙት ነገር ጋር ትቀራላችሁ። ለልባችሁ ክብር እየሰጣችሁ። ብቻ አብሽሩ። ሰላም ለልባችሁ! 🙏🙏🙏
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

14 Nov, 09:18


« የስነ ምግባር ብልሹነትን ከሚያመለክቱ ነገሮች አንዱ ሰዎችን በደንብ ስንግባባቸው እና ካወቅናቸው በኋላ ስንንቃቸው ነው።
ሰውየው የጠበቃችሁትን ያህል ካልሆነ በክብሩ ላይ ድንበር ማለፍ የተፈቀደ አይደለም። ሰው ለሚወደው፣ የተለየ ቦታ የሰጠው ሰው ዘንድ ነፃነቱን ይጠቀማል። ለሌሎች የማያሳያቸው አስቂኝም አናዳጅ ባህሪውን ያንፀባርቃል። (እየተረዳን እንጂ ወገን!)
አንዳንድ ሰዎች ያወቁን ከመሰላቸው ቅፅበት ጀምሮ ንቀታቸው ብቅ ይላል። (እረፉዋ!)
ዛሬ በለስላሳነታቸው፣ በይቅር ባይነታቸው የምናውቃቸው ሰዎች ፈፅሞ መጨከን የማይችሉ አይምሰለን።
አንድ ነገር ፈፅሞ መርሳት የሌለብን ነገር አለ። ይህም የትኛውም ሰው ጨካኝ እና አረመኔ መሆን ይችላል። መጨከን ለጥቂት ሰዎች ብቻ የተሰጠ አይደለም።
አንዳንዴ ከጨከኑብን ሰዎች የበለጠ ፈፅሞ አይጨክኑብንም ብለን ያልናቸውን ሰዎች ጭካኔ መጠንቀቅ ይኖርብናል። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

14 Nov, 08:45


« ሌሎች ሰዎች ለማድረግ የሚከብዳቸው እና የሚሰለቻቸው ነገር ለእናንተ ገር ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ሀሳቦችን በፅሁፍ ማዋቀር ለኔ ያን ያህል ከባድ ሆኖብኝ አያውቅም። እንደውም አሁን አሁን የሆነ የገራልኝ ነገር ነው እንጂ የስነ ፅሁፍ ችሎታ የለኝም ብዬ ማመን ላይ ደርሻለሁ። እናንተስ ምን ስትሰሩ፣ ወይም ስታደርጉ ያን ያህል ሸክም ወይም አሰልቺ ሆኖ አይሰማችሁም?
አሁን ዋናው ጥያቄ አላህ እንድትሰሩት ገር ባደረገላችሁ ነገር ምን እያደረጋችሁ፣ ምን እየሰራችሁ ነው? (በጣም ተራ ጥያቄ ሊመስላችሁ ይችላል። ነገር ግን በጥልቀት ካሰባችሁበት ብዙ ነገራችሁን እንድትፈትሹ ያደርጋችኋል።) እስቲ አስቡበት! ሀሳብ ካላችሁም አካፍሉን! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13

Venue

13 Nov, 17:25


ሌላው ይደርሳል። ውስጣችሁ ብቻ ሰላም ይሁን! ሰላም ለልባችሁ! 🙏🙏🙏
:
@Venuee13
@Venuee13