Minber TV @minbertv Channel on Telegram

Minber TV

@minbertv


#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ!

#ሚንበር_ቲቪን ለማግኘት

📡 በኢትዮሳት ይከታተሉ:– 👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 30000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★

Minber TV (Amharic)

ሚንበር ቲቪ የቴሌግራም አስተዳዳሪ ቤት ነጻ መሆኑን የሚገኙበት ቦታ ነው። በዚህ ቦታ የሚከበሩ ፊርማዎችን እና ክፈትፎችን ይገኛል። ሚንበር ቲቪን ለመግኘት የሚሆንን ይህንን ዌብሳይት አወዳድሮ እናረከቡ። በእርስዎ የኢትዮጵያዊው ወንድ የፍሪኩዌንሲን፣ ሲምቦልሬትን፣ እና ፖላራይዜሽን ሆሪዞንታውን እንዴት እንዳለ፣ ዝርዝርና ማስታወቂያዎች እንዲቀርበው በቴሌግራም አስተማሪነት ለሚጠቁን ሰዎች በመጠቀም እንዴት መተላለፍን በቴሌግራም እንዴት የሚከታተሉትን ይከታተል።

Minber TV

22 Jan, 18:00


በሙስሊም ዜጎቿ ብዛት የምትታወቀው ይህች ሀገር ማን በመባል ትታወቃለች?

የትላንት ጥያቄ መልስ ፡-
በዐረብኛ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ምን ይባላል?
መልስ፦  D/ ሙሐረም


በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

22 Jan, 16:17


ስንፍናና ደህነት …

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/Ox5uZsp1q8M 🔗

#ነፃ_ወግ
#ስንፍናና_ድህነት
#የድህነት_መንስኤ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

22 Jan, 14:52


"ምን ሠርተው ታወቁ የሚለው የሬዲዮ ፕሮግራም በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ተጽእኖ ፈጥሮብኛል" ይላል ዶ/ር መሐመድ ሽኩር የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደራሴና የአሚን ሆስፒታል ባለቤት። በዛሬው የቢልኮር ፖድካስት እንግዳ ሲሆን በዶ/ር ቢላል ሽኩርና በአቶ ሙኒር ኸይረዲን ቃለመጠይቅ ተደርጎለታል። በሚንበር ቲቪ ምሽት 03:00 ይጠብቁንl

#ሕይወት_ቀያሪዋ_ደብዳቤ
#Bilcor_podcast

ዕለተ ረቡዕ ጥር 14 - 2017 | ረጀብ 22 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

22 Jan, 14:42


የኢትዮጵያዊያኑን ሕይወት የቀጠፈው የጀልባ መስጠም አደጋ

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://t.me/minberkheber

Minber TV

22 Jan, 14:35


"ምን ሠርተው ታወቁ የሚለው የሬዲዮ ፕሮግራም በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ተጽእኖ ፈጥሮብኛል" ይላል ዶ/ር መሐመድ ሽኩር የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደራሴና የአሚን ሆስፒታል ባለቤት። በዛሬው የቢልኮር ፖድካስት እንግዳ ሲሆን በዶ/ር ቢላል ሽኩርና በአቶ ሙኒር ኸይረዲን ቃለመጠይቅ ተደርጎለታል። በሚንበር ቲቪ ምሽት 03:00 ይጠብቁንl

#ሕይወት_ቀያሪዋ_ደብዳቤ
#Bilcor_podcast

ዕለተ ረቡዕ ጥር 14 - 2017 | ረጀብ 22 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

22 Jan, 12:31


#ጉዞ_ወደ_ማንነት
#ክፍል_2
#ካስማ_ሾው

ዛሬ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ!

ዕለተ ረቡዕ ጥር 14 - 2017 | ረጀብ 22 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

22 Jan, 11:35


ኮድ 9/16

በቅርብ ቀን!

Minber TV

22 Jan, 10:32


በበርካታ የዳዕዋ መድረኮች በሚያቀርባቸው ሁለንተናን ሰቅዘው የሚይዙ ትምህርቶቹ በስፋት የምናውቀው ጥዑመ ልሳኑ ዳዒ ዶክተር ሰምሃር ተክሌ፤ ቤተል በሚገኘው አዲሱ የሙጀመዕ አት-ተቅዋ መስጂድ ለታዳሚዎች ዒልምን እየዘሩ ከሚገኙ ተወዳጅ ኡስታዞች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን በእጅጉ የሚያስፈልጉንን የአምልኮ፣ የሸሪዓ ድንጋጌዎችና ፊቅሃዊ ብያኔዎችን ከያዘው "አቢ ሹጃእ" ኪታብ ሰፋ ካሉ ማብራሪያዎች ጋር በማጣመር ግሩም በሆነ መንገድ ደርስ (ትምህርት) እየሰጠ ይገኛል፡፡

ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን ሚንበር ቲቪም፤ አዲስ በጀመረው "ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራሙ ይህንን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶችን የያዘውን የ "አቢ ሹጃእ" ደርስ (ትምህርት) ክፍል ሃያ አንድ ዝግጅቱን ዛሬ ምሽት ከ12፡30 ጀምሮ ለውድ ተመልካቾቹ ያቀርባል!

#ሚንበሩል_ዒልም
#አቢ_ሹጃእ
#ክፍል_21
#ዶክተር_ሰምሃር_ተክሌ

ዕለተ ረቡዕ ጥር 14 - 2017 | ረጀብ 22 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

22 Jan, 09:44


የሒጃብ ክልከላ ተቃውሞ ሠልፍ በመቐለ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/_YxvR41pOV8 🔗

#ሚንበር_ኸበር
#Minber_News
#ሒጃብ #የሒጃብ_ክልከላ
#አክሱም #መቐለ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

22 Jan, 09:06


የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ፍልስጤምን አምባሳደር ማነጋገራቸውን ጽሕፈት ቤታቸው ገለጸ

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://t.me/minberkheber

Minber TV

21 Jan, 16:14


ጤናማ አመጋገብ ብዙ በሽታዎችን ይቀርፋል!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/p6wIs_0GWBM 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #እህል_ውሃ
#አመጋገብ #nutrition #ጤና

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

21 Jan, 15:35


በአክሱም የተጣለውን የሒጃብ ክልከላ የክልሉ አስተዳደር አፋጣኝ እልባት እንዲሰጠው ነእፓ ጠየቀ

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://t.me/minberkheber

Minber TV

21 Jan, 14:49


የ“ሚንበር ኸበር” አዲስ ገፅ። ምሽት 1፡30 ከዕለቱ ዐቢይ አጀንዳ ጋር ይጠብቁን፡፡
“ስለ ሁሉም ሙስሊም በኃላፊነት”

Minber TV

21 Jan, 13:40


እውነት በዘመን ቅዝቃዜ ሞታ ቀብሯን እንዳታሳየን የሕይወት ሙቀት እየመገቡ የሚያነቋት የጋዛ ልቦች እኚሁላችሁ! የሚላችሁ እነሆ ኸበር ተስፋም ስጋትም ያዘለውን የጋዛን የተኩስ አቁም በወፍ በረር ይቃኛል።
ምሽት 02:30 በሚንበር ቲቪ

#እፎይታ_ለጋዛ!
#እነሆ_ኸበር

ዕለተ ማክሰኞ ጥር 13 - 2017 | ረጀብ 21 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

21 Jan, 11:34


በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ የሚሰናዳው እና ተማሪዎችን በቀለም ትምህርት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል እና ማበረታታት ሁለንተናዊ የሆነ የተሟላ እውቀት ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል አላማው የሆነ "ቅን ትውልድ" ፍተሻ የጥያቄ እና መልስ ውድድር ለተወዳዳሪዎች የ200,000 ብር ሽልማት ይዞ ጉዞ ቀጥሏል። ምሽት 02:00 በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#ቅን_ትውልድ
#ፍተሻ

ዕለተ ማክሰኞ ጥር 13 - 2017 | ረጀብ 21 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

21 Jan, 10:34


ከዒልም ጋር ያላቸው ጥልቅ ትውውቅ የጀመረው በልጅነታቸው ነበር፡፡ ሸይኽ ሰዒድ ዓሊ ሐቢብ ይሰኛሉ፡፡ ወጣትነታቸውን የሰዉለት የዒልም አድማስ ዛሬ ላይ በዘርፈ ብዙ ሸሪዓዊ ጉዳዮች ላይ ርቀው እንዲሄዱና ከታላላቅ ዑለሞች ተርታ እንዲሰለፉ አስችሏቸዋል፡፡ ሸይኽ ሰዒድ በመስከ ብዙ ፉኑኖች ያላቸውን የዒልም አቅም ለሰፊው ማኅበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በተፈጠረላቸው መልካም ዕድል ተጠቅመው፤ ከመግሪብ ሶላት በኋላ እስከ ዒሻእ ሶላት ድረስ በሙጀመዕ አት - ተቅዋ የሚሰጡትን "የአርበዒን ሃዲስ" ትምህርት (ደርስ) ዘወትር ማክሰኞ ምሽት ከ12፡30 ጀምሮ ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን አዲስ በጀመረው የሚንበሩል ዒልም ፕሮግራሙ #በክፍል_29 የሚያቀርብላችሁ ይሆናል፡፡

#ሚንበሩል_ዒልም
#አርበዒን_ሐዲስ
#ክፍል_29
#ሸይኽ_ሰዒድ_ዓሊ_ሐቢብ

ዕለተ ማክሰኞ ጥር 13 - 2017 | ረጀብ 21 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Jan, 16:14


ሀሜትን ቁጭ ብሎ ማዳመጥ …

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/I4Hi61vvu3I 🔗

#በይቱል_ሓቢብ
#የተፈቀዱ_ሐሜቶች_አሉን?

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Jan, 14:14


ሴኩላሪዝምና የእምነት ነጻነት በት/ቤቶች

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/WUrhR8-rcUA 🔗

#ልዩ_ዝግጅት #ሴኩላሪዝምና_የእምነት_ነጻነት_በት/ቤቶች
#ሙስሊም_ተማሪዎች #ትምህርት_እና_ሀይማኖት

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Jan, 13:20


ሙስሊም መሆኑን ያወቅኩት ዘግይቼ ነበር። ስንተዋወቅ የክርስትና እምነት ተከታይ ነበር የመሰለኝ። ሆኖም ፍቅር ውስጥ ነበርንና በየሃይማኖታችን ልንኖር ተስማምተን ትዳራችንን ቀጠልን። ኋላ ላይ ግን ለእስልምና ተረታሁ! በተረታሁበት ማግስት ግን እስልምናን ሳገኝ ባሌን አጣሁት ትላለች ። የትላንቷ ባንቺ አምላክ ቻላቸው የዛሬዋ መንገደኛዬ ሀናን ቻላቸው ዛሬ የምንመላለሰው በእሷ የሕይወት መንገድ ላይ ነው! ምሽት ከ03:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#የኒካችን_ቀን_ቀረ!
#አራስ_ልጄን_ልጥለው_ወስኜ_ነበር!
#የኔ_መንገድ

ዕለተ ቅዳሜ ጥር 10 - 2017 | ረጀብ 18 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Jan, 13:06


የሙስሊም ተማሪዎችን የሒጃብ ክልከላ የተቃውሞ ሠልፍ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዲቀላቀሉት ምክር ቤቱ ጥሪ አቀረበ

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://t.me/minberkheber

Minber TV

18 Jan, 12:47


ነገ ዕለተ እሁድ የሚተላለፈው ነፃ ወግ ፕሮግራም ዶክተር ሸምሴ ስለ ፖርኖግራፊ የዚህ ዘመን አደጋ በግልጽ ይነግረናል።
ወጣቶች በዚህ ዘመን ወለድ ቀውስ እየተጠቁ መሆኑን በተለይም ዘመናዊ ስልኮች በሚለቁት ስሜት ቀስቃሽ ምስሎች በርካታ ወጣቶች በስሜት እየተነዱ መሆኑን ይነግረናል።

ምሽት 3:00 ወላጆች ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

ነፃ ወግ | ሚንበር ቲቪ ከዴልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ጋር በመተባበር

#ነፃ_ወግ #Netsa_Weg #ፖርኖግራፊ #Pornography

★ ★ ★
Minber TV | Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Jan, 12:13


የጋዛ ተኩስ አቁም የመጨረሻ ሰዓታት

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://t.me/minberkheber

Minber TV

18 Jan, 11:14


“እኔን ከመከተል ውጪ ሌላ አማራጭ የላቸውም!”

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/zhsoI9GmWA0 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #የሸይኻችን_ሰዓት
#ክፍል_201 #ነብዩ_ሙሐመድﷺ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Jan, 10:31


የቁርኣን ተፍሲር በሐረሪ ቋንቋ - በሸይኽ የሕያ እስማዒል (ረሒመሁላህ)
ሱረቱል ሷድ 49-76

ዛሬ ምሽት 12:30 በሚንበር ቲቪ!

#ቁርኣን #ተፍሲር #ሐረሪ
#ሸይኽ_የሕያ_እስማዒል_ረሒመሁላህ 

ዕለተ ቅዳሜ ጥር 10 - 2017 | ረጀብ 18 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Jan, 08:35


SIMBOO
Akkuma torban darbee sagantaalee bohaartii fi bashannansiisoo guyyaa keessaniif ta'an Sagantaa torbee 3ffaa keenya isiniif qabannee dhufnee jirra.

Har'a sa'aa 08:00 irraa eegaluun toora Minber Tv fi YouTube Milan Media irratti nu eeggadhaa!

#siimboo
#bohaartii_sanbataa
#milanmedia
#minbertv

Guyyaa Dilbataa Amajjii 10-2017 | Rajab 18-1446

★ ★ ★
MINBAR TV | Ethiosat | 11545 | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Jan, 18:03


የአስሓማ ኢብኑ አብጀር ሌላኛው ስማቸው ማን ይባላል?
A/ አብረሃ
B/ አል ሙቀውቂስ
C/ ሳይዛና
D/ አን-ነጃሺ

የረቡዕ ጥያቄ መልስ ፡-
ሙሉ ጨረቃ ልዩ ትኩረት የተደረገበት ምስል በዋነኝነት ምንን ያመለክታል?
መልስ፦ አያም አል-ቢድ ( በሂጅራ አቆጣጠር 13ኛ፣ 14ኛውና 15ኛው ቀናት)

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

17 Jan, 17:43


Simboo
Akkuma torban darbee sagantaalee bohaartii fi bashannansiisoo guyyaa keessaniif ta'an Sagantaa torbee 3ffaa keenya isiniif qabannee dhufnee jirra.

Boru sa'aa 08:00 irraa eegaluun toora Minber Tv fi YouTube Milan Media irratti nu eeggadhaa!

#siimboo
#bohaartii_sanbataa
#milanmedia
#minbertv

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Jan, 17:33


እንደስያሚያችን ውብ ሁነን እንደተወለደችዋ ጨረቃ አብሪና አንጻባራቂነታችን ለሁሉም ይደርሰው ዘንድ ዳግም በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለናል።

እንደወትሮው  አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ፕሮግራሞቻችንን በተለመደው ሰዓታችን ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 03፡00 በተወዳጁ የቴሌቪዥን ጣቢያ (ሚንበር ቲቪ) ይከታተሉ።

"ሂላል ለልጆች"

ዕለተ ዓርብ ጥር 9 - 2017 | ረጀብ 17 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Jan, 14:14


ባሳለፍነው ቅዳሜ ጥር 3/2017 በካፒታል ሆቴል አንድ "የምርምር አውደ ጥናት" ተካሂዶ ነበር። ጥናቱን እንዲካሄድ ያደረገው ኢማን ኢስላማዊ ማኅበር በጂስራ /jisra/ ፕሮጀክት ሲሆን ጥናቱን በኃላፊነት ያከናወነው IRCC ነበር። የጥናቱ ትኩረቱ secularism and freedom of Religion in educational system of in Ethiopia የሚል ነበር። ክፍል-2 ዛሬ ምሽት ከ3:00 ጀምሮ የሚቀርብ ይሆናል።

#ሴኩላሪዝም
#የእምነት_ነጻነት_በትምህርት_ቤቶች
#ክፍል_2
#ልዩ_ዝግጅት

ዕለተ ዓርብ ጥር 9 - 2017 | ረጀብ 17 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Jan, 13:33


ባሳለፍነው ቅዳሜ ጥር 3/2017 በካፒታል ሆቴል አንድ "የምርምር አውደ ጥናት" ተካሂዶ ነበር። ጥናቱን እንዲካሄድ ያደረገው ኢማን ኢስላማዊ ማኅበር በጂስራ /jisra/ ፕሮጀክት ሲሆን ጥናቱን በኃላፊነት ያከናወነው IRCC ነበር። የጥናቱ ትኩረቱ secularism and freedom of Religion in educational system of in Ethiopia የሚል ነበር። ክፍል-2 ዛሬ ምሽት ከ3:00 ጀምሮ የሚቀርብ ይሆናል።

#ሴኩላሪዝም
#የእምነት_ነጻነት_በትምህርት_ቤቶች
#ክፍል_2
#ልዩ_ዝግጅት

ዕለተ ዓርብ ጥር 9 - 2017 | ረጀብ 17 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Jan, 12:30


የሳምንታዊው ዒዳችን ጁምዓ ኹጥባና መልዕክቶች በአግባቡ መደመጥና ወደ ህይወት መቀየር ያለባቸው መሆኑ ይታወቃል። በኹጥባ መሐል የሚከወኑ የትኞቹም ተግባራት በሃዲስ የመወገዛቸው አንዱ ምስጢርም፤ መልዕክቱን ያላንዳች መረበሽ ትኩረት ሰጥቶ በጥሞና ከመከታተል ጋር እንደሚገናኝም ዑለሞች ያስረዳሉ።

ዛሬ ቤተል በሚገኘው የሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ ተገኝተን ያሰናዳነውንና በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ "ረጀብን ለረመዳን ስንቅ" በሚል ርዕስ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የኹጥባ መልዕክት ከቀኑ 11:30 የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

#የጁሙዓ_ኹጥባ
#ረጀብን_ለረመዳን_ስንቅ
#ኡስታዝ_ካሚል_ሸምሱ

ዕለተ ዓርብ ጥር 9 - 2017 | ረጀብ 17 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Jan, 11:31


በዛሬው "መዓል ቁርአን" ፕሮግራማችን እንግዳ አብዱል መጂድ ሱለይማን አብዱል መጂድ ይባላል። በባኮ ከተማ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ቁርኣን ሃፊዝ እና መምህር ነው። ድንቅ የሆነውን ቁርአን የመሃፈዝ ጉዞውን በምልሰት እያስቃኘን የተለያዩ ገጠመኞቹን እያነሳሳን ቆይታ የምናደርግ ይሆናል። ምሽት 02:00 ሰዓት የሚተላለፈውን ፕሮግራማችንን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

#የመጀመሪያው_ፈተናችን_ሶብር
#ከቁርኣን_ጋር

ዕለተ ዓርብ ጥር 9 - 2017 | ረጀብ 17 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Jan, 11:17


በሠላሌ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ሣይንስ ተማሪ የሆነችው አሲያ ኸሊፋ የ2025 ሑዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ዓለም አቀፍ አምባሣደር ሆና መመረጧን  በያዝነው ሳምንት ሰምተናል።

በመወዳ መዝናኛ የእንግዳ ሰዓት ንዑስ መሠናዶ ላይ ጋብዘን ሰርፕራይዝ አድርገናታል። ሙሉ ፕሮግራሙን እሁድ ከሰዓት በመወዳ መዝናኛችን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ!
#መወዳ_መዝናኛ
#Meweda
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Jan, 10:32


የህይወት መመሪያችን የሆነውን ቁርአንን ለመረዳትና ለመኖር ትርጉሙን (ተፍሲር) በዘርፉ ጥልቅ ንባብና ዕውቀት ካላቸው ዑለሞች መማር ያሻል።

ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን ሚንበር ቲቪም በዕውቀት የታነጸ ማኅበረሰብን ለመገንባት እንደሚረዳ የሚታመነውንና፤ መልከ ብዙ ትምህርቶች የሚሰጡበትን "ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራም ከሥፍራው በጥራት በመቅረፅ በየዕለቱ እያቀረበ የቆየ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ ከሚሰጡ ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነውንና በተወዳጁ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እየተሰጠ የሚገኘውን የቁርኣን ተፍሲር ትምህርት (ደርስ) ዘወትር ጁምዓ አመሻሽ ከ12:30 ጀምሮ ይቀርብላችኃል።

#ሚንበሩል_ዒልም
#የቁርኣን_ተፍሲር
#ክፍል_17
#ሸይኽ_ሐሚድ_ሙሳ

ዕለተ ዓርብ ጥር 9 - 2017 | ረጀብ 17  - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Jan, 08:50


#ማስታወቂያ

ንፅህናን በሚወክለው ኢህራም ተውበን፣
እጅግ በተከበረው ሥፍራ ላይ በተልቢያ ደምቀን፣
ከሃገር ርቀን፣ ግን ደግሞ ከዓለም ሁሉ ልቀን፣
በዑምራ ክንውን ደምቀን፤ የኒያችንን የሚያስገኝልንን ዘምዘም እስክንጠግብ ጠጥተን፣ በታሪካዊ ሥፍራዎች ጉብኝት ወርቃማውን ዘመን ተዋውቀን፣ ሃጢያታችንን በአላህ ፈቃድ አራግፈን፣ ተወዳጁን መልዕክተኛ (ሰዐወ) ተመላልሰን ዘይረን፣ ደግሞም ከረውዷቸው አረፍ ብለን፣ ለወዳጅ ዘመድ ዱዓ አድርገን በድልና ስኬት እንመለሳለን!

መቼ አሉን? ከጥር 22 እስከ የካቲት 3

ከነማን ጋር ካሉን ደግሞ የኸሚስ ምሽቶቹ ተወዳጁ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሂምእና አንደበተ ርቱዕ የሖነው ወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ለእናቶች እና እህቶች ልዩ ኺድማ ደግሞ የተወዳጁ በይቱል ሐቢብ ፕሮግራም አዘጋጇን ኡስታዛ ሃስና ሸይኽ ሙስጠፋን አካተናል።

ያስታውሱ!! የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ ጥር 12 ይጠናቀቃል።

####
ከጥር 22 እስከ የካቲት 3 በመካ ለ7 በመዲና ለ4 ቀናት ቆይተን ውብ የዒባዳ ጊዜን አብረን እናሳልፋለን!!

ለምዝገባና የተሟላ መረጃ ለማግኘት
በ0965888883 ወይም 0965888884 ላይ ይደውሉልን!

ሂራ ቱር ኤንድ ትራቭል
አድራሻችን ሣር ቤት ግደይ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ያገኙናል

Minber TV

17 Jan, 08:20


የትምህርት ቢሮን አዲስ ውሳኔ ተከትሎ ወደ ትምህርት ቤት ያመሩ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ዳግም ከበር እንዲመለሱ መደረጋቸውን ተናገሩ


ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://t.me/minberkheber

Minber TV

11 Jan, 17:50


በኢስላማዊ ስነ ምግባር የታነፁ፤ በአወንታዊ አመለካከት የጎለበቱ፤ ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው፣ለሃገራቸው ብሎም ለአለም መልካም ሚናቸውን የሚወጡ ብሩህ ልጆችን ለማፍራት ጉዞ ከጀመርን እነሆ 4 ዓመታት ተቆጠሩ።

🎉🎉🎉

ዛሬም የተለምነውን ለማሳካት በአዳዲስ ፕሮግራሞችና አቀራረብ ዘወትር እሁድ መደበኛ ፕሮግራማችንን ወደናንተ ውድ ተመልካቾቻችን ለማድረስ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

ዕለተ እሁድ ጠዋት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ በሚቀርበው አዲስ ውድድር ላይ በመሳተፍ በየሳምንቱ ይሸለሙ!

#ብሩህ_ልጆች

ዕለተ ቅዳሜ ጥር 4 - 2017 | ረጀብ 11 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Jan, 15:02


የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድ አዲስ አበባ ገቡ

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://t.me/minberkheber

Minber TV

11 Jan, 12:47


ለእስልምና የነበረው ጥላቻ በቃላት መግለጽ እስኪቸግረው ድረስ ነበር። ዛሬ ላይ ግን ለእስልምና ያለው ፍቅር ልዩ ሆኗል። በስሙ የሚጠራ መስጂድ እንዳለ እና አላህን ትንሽ ነገር መጠየቅ እንደማይወድ አጫውቶናል። የትላንቱ ኃይሌ በየነ የዛሬው መንገደኛዬ ዓሊ በየነ ዛሬ የምንመላለሰው በእሱ የሕይወት መንገድ ላይ ነው። እንደዚያ ያለ ጥላቻን ንዶ በእስልምና ፍቅር እንዲረታ ያደረገው የሕይወት መንገድ እንዴት ያለ ይሆን? ምሽት ከ03:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#አላህ_የጠየቅኩትን_ሰጥቶኛል
#የኔ_መንገድ

ዕለተ ቅዳሜ ጥር 3 - 2017 | ረጀብ 11 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Jan, 12:16


ዘወትር እሁድ ከሰዓታችሁን ለማድመቅ የሚተጋው መወዳ መዝናኛችን፤ በእንግዳ ሰዓቱ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የመኪና ሥጦታ የተበረከተላቸው የታሪክ አጥኚ ፕሮፌሰር አደም ካሚል ቤት ጎራ ብሎ ግሩም የቤተሰብ ወግ ያወጋበትን እንዲሁም፤

"መወዳ ታለንት" በተሰኘው ተመልካቾች በሚሳተፉበት ንዑስ ፕሮግራም ታለንት አቅራቢው ሰርፕራይዝ የተደረገበትን

እና ሌሎች ተናፋቂ መሠናዶዎችን ይዞ ወደናንተ ውድ ተመልካቾቹ ለማድረስ ሰዓቱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

#መወዳ_መዝናኛ #Meweda
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Jan, 11:35


ለእስልምና የነበረው ጥላቻ በቃላት መግለጽ እስኪቸግረው ድረስ ነበር። ዛሬ ላይ ግን ለእስልምና ያለው ፍቅር ልዩ ሆኗል። በስሙ የሚጠራ መስጂድ እንዳለ እና አላህን ትንሽ ነገር መጠየቅ እንደማይወድ አጫውቶናል። የትላንቱ ኃይሌ በየነ የዛሬው መንገደኛዬ ዓሊ በየነ ዛሬ የምንመላለሰው በእሱ የሕይወት መንገድ ላይ ነው። እንደዚያ ያለ ጥላቻን ንዶ በእስልምና ፍቅር እንዲረታ ያደረገው የሕይወት መንገድ እንዴት ያለ ይሆን? ምሽት ከ03:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#አላህ_የጠየቅኩትን_ሰጥቶኛል
#የኔ_መንገድ

ዕለተ ቅዳሜ ጥር 3 - 2017 | ረጀብ 11 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Jan, 11:17


ከወንጀል ተውበት ማድረግ …

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/2gfQR87E38w 🔗

#ኸሚስ_ምሽት_በምልሰት
#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
#ተውበት #ኢስቲግፋር

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Jan, 10:32


የቁርኣን ተፍሲር በሐረሪ ቋንቋ - በሸይኽ የሕያ እስማዒል (ረሒመሁላህ)
ሱረቱል ሷድ 30-50

ዛሬ ምሽት 12:30 በሚንበር ቲቪ!

#ቁርኣን #ተፍሲር #ሐረሪ
#ሸይኽ_የሕያ_እስማዒል_ረሒመሁላህ 

ዕለተ ቅዳሜ ጥር 3 - 2017 | ረጀብ 11 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Jan, 09:41


ልዩ ኸበር - ፍልስጤማዊው ኦሳማ ቃሾን እንተዋወቀው

ዕለተ ቅዳሜ ጥር 3 - 2017 | ረጀብ 11 - 1446

ኦሳማ ቃሾ ይባላል፡፡ የ44 ዓመት እድሜ ያለው ፍልስጤማዊ ነው፡፡ እንደ አብዛኛው ፍልስጤማዊ የቀዬው ጉዳይ ያሳስበዋል፡፡ እንደ ሁሉም ፍልስጤማዊ ደግሞ ገና በአፍላ ዘመኑ ለታጋይነት የታጨ ነው፡፡ በፍልስጤም ሳለ የተቃውሞ ሠልፍ ላይ የሚታጣ ሰው አልነበረም፡፡ ለፍልስጤም ሲሟገት እንደ አብዛኛው የሀገሩ ሰው እስር እና ድብደባ አስተናግዷል፡፡ በዚያ ለመቆየት የቻለው ግን እ.አ.አ አቆጣጠር እስከ 2003 ብቻ ነበር፡፡ በወቅቱ ለመጨረሻ ጊዜ እስራኤል በወረራ በያዘችው ዌስት ባንክ የተካሄደ አንድ የተቃውሞ ሠልፍ ካስተባበረ በኋላ መቆየት አስጊ ስለሆነበት ወደ ስደት ሀገር ማቅናት መረጠ፡፡

እንደ አጋጣሚ ሆኖ ኦሳማ የስደት እግር የጣለው ወደ አውሮፓ ነበር፡፡ ወደ አሕጉሩ ተሻግሮ አሁን የሚኖረው በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ውስጥ ነው፡፡ ለንደን ደርሶም ቢሆን ጧት ማታ የሚብከነከነው ስለ ፍልስጤም እና ፍልስጤማዊያን ነው፡፡ በ2010 ነጻ የጋዛ እንቅስቃሴ የተሠኘ የመብት ተሟጋች ድርጅት በመመሥረት ስለ ፍልስጤም መታገል ቀጠለ፡፡ በድርጅቱ በኩል ወደ ጋዛ ሰብዓዊ ርዳታ በሚላክበት መንገድ ላይ ሲሠራ ቀይቷል፡፡ ኦሳማ መልከ ብዙ ነው፤ ፊልም ይሠራል፤ ዘጋቢ ፊልም ሲሠራ ይዋጣለታል የሚባል ነው፡፡ ፊልም ብቻ ሳይሆን ሲነግድም የሚዋጣለት ነው፡፡ በለንደን ንግድ ላይ ቢሰማራ ፍልስጤምን ማሰቡ አይቀርም፡፡ ሥያሜውን ከፍልስጤም ጋር የሚተሳሰርበትን መንገድ ይፈልጋል።

ኦሳማ ቃሾ ሲነግድ ትርፉን ለፍልስጤማዊያን እንዲደርስ የሚያደርግም ነው፡፡ ይህን አላማ ከሚያሳካባቸው ንግዶች መካከል አንደኛው የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ሆኗል፡፡ “ጋዛ ኮላ” የኦሳማ ቃሾ  የስላሳ መጠጥ ምርት ነው፡፡ ፍልስጤማዊው ጋዛ ኮላን ማምረት የጀመረው እንዲሁ ለነጋዴነት አምሮት ብቻ አይደለም፡፡ ለለስላሳ መጠጥ ምርቱ ሥያሜውን በተዋሰው ጋዛ ከተማ በእስራኤል ወታደሮች የሚደርሰውን የሰብዓዊ እልቂት በመደገፍ ሥሙ የሚነሳውን “ኮካ ኮላ”ን ለመተካት በማሰብ ነው፡፡

ለእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ የለስላሳ መጠጥ አፍቃሪ አለመሆኑን የሚናገረው ኦሳማ፤ እሱ ባይወደውም ሰዎች “የለስላሳ መጠጥ መጠቀማቸው ካልቀረ ግን በኮካ ኮላ ፋንታ ለምን ጋዛ ኮላን አይጠጡም?” በሚል ሐሳብ እንዳስጀመረው ያስረዳል፡፡ ከለስላሳ መጠጡ የሚገኘው ትርፍ ደግሞ በፍልስጤም ለወደመው አልካርማ ሆስፒታል ጥገና የሚውል ነው፡፡ ለጥገና ገንዘብ የሚያሰባስብለት አል ካርማ ሆስፒታል የወደመው በእስራኤል ወታደሮች ነው፡፡

አሁን እሱ ገንዘብ የሚያሰባስብለትን ሆስፒታል የእስራኤል ወታደሮች “ለምን እንዳወደሙት ምንም አይገባኝም” የሚለው ኦሳማ፤ “ግን ደግሞ ሌሎቹን የጋዛ መሠረተ ልማቶችም ለምን እንዳወደሟቸው ምን የተለየ ምክንያት አላቸው?” ሲል በግራ መጋባት የራሱ ጥያቄ ላይ ሌላ ጥያቄ ይሰነዝራል፡፡ ነገር ግን ሆስፒታሎቹ ሲወድሙ እጁን አጣጥፎ መቀመጥ አልፈለገም፡፡ ምንም እንኳን እኔ የማደርገው ትንሽ ቢሆንም መነሳት አለብኝ ብሎ ጋዛ ኮላን ማምረት ጀመረ፡፡ ይህን ለምን እንዳደረገ ሲጠየቅ፦ “የምንሠራው ትንሽ ቢሆንም እስከፈለግነው ማለም ተፈቅዶልናል፤ ራዕይ ሊኖረን ይገባል፤ ካልሆነ እንዴት መኖራችን ማረጋገጥ እንችላለን?” ሲል መልሷል፡፡

የኦሳማ ቃሾ ጋዛ ኮላ ፍልስጤምን በሚወክሉ ቀለማት የተዋበ ነው፡፡ ምርቱ ወደ ተጠቃሚዎች መድረስ ከጀመረበት የፈረንጆቹ 2023 አንስቶ እስካሁን ድረስ 500 ሺሕ ጠርሙስ መሸጥ ችሏል፡፡ ይህ የሚሆነው በኦንላይን አማራጮች ነው፡፡ በለንደን 24 ጠርሙስ የሚይዘው አንድ እሽግ የጋዛ ኮላ ላስላሳ መጠጥ በ30 ፓውንድ ይሸጣል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ምርቱ ከእንግሊዟ ለንደን ተሻግሮ ወደ ስፔን፣ አውስትራሊያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኩዌት ደርሷል፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ በጋዛ እና ዌስት ባንክ የሚገኙ የቃሾ ዘመዶች እና ጓደኞቹም ጭምር ገዛ ኮላን እስካሁን አልቀመሱትም፡፡ ሆኖም ከምርቱ ሽያጭ በሚገኘው ትርፍ በተገነባው ሆስፒታል ትሩፋቱን መቋደሳቸው አይቀርም።

ባለፉት ጊዜያት በፍልስጤም ምድር ለሚፈጸመው ግፍ በይፋ ጦር በማቀበል ከሚደግፉት በተጨማሪ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እስራኤልን የሚደግፉ የግፈኛ በትር አቀባዮችን ለመቅጣት የሚደረገው ትግልም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደቀጠለ ነው፡፡

በፍልስጤማዊያን የሕልውና ትግል ውስጥ እንደ ኦሳማ ሁሉ በስዊድን ማልሞ ነዋሪ የሆኑት የሑሱን ቤተሰቦችም ከዚህ ቀደም ኮካ ኮላን የሚተካ ለስላሳ መጠጥ አስተዋውቀዋል፡፡ እነ ኦሳማም ሆነ የሑሱን ቤተሰቦች እየተፋለሙ የሚገኙት በቀጥታም ይሁን እስራኤልን የሚደግፉ የግፈኛ በትር አቀባዮችን ነው፡፡ በትር አቀባዮቹ ስለ ዴሞክራሲ እና ሰብዓዊ መብት እቆረቆራለሁ የምትለው አሜሪካ ዐይነቶቹ ብቻ አይደሉም፡፡ እነ ኮካ ኮካ ኮላ ብቻም አይደሉም፡፡ ማክዶናልድ እና ስታርባክስም አሉበት፡፡ በርግጥ እነዚህ ሁሉም በጓሮ በኩል ሥራቸውን እየቀጠሉ በአደባባይ እኛ የለንበትም ብለው መከራከራቸው አልቀረም፡፡ እነርሱ ይህን ቢሉም ፍልስጤማዊያኑ የሐሰት ማስተባበያውን የሚቀበሉ አይደሉም፡፡ ለዚህም እስከ ነጻነት ድረስ በተጋድሏቸው ቀጥለዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Jan, 09:40


ልዩ ኸበር - ፍልስጤማዊው ኦሳማ ቃሾን እንተዋወቀው

በድረ ገጽ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=9709

Minber TV

11 Jan, 08:35


SIMBOO
Akkuma torban darbee sagantaalee bohaartii fi bashannansiisoo guyyaa keessaniif ta'an Sagantaa torbee 2ffaa keenya isiniif qabannee dhufnee jirra.

Boru sa'aa 08:00 irraa eegaluun toora Minber Tv fi YouTube Milan Media irratti nu eeggadhaa!

#siimboo
#bohaartii_sanbataa
#milanmedia
#minbertv

Guyyaa Sanbataa Amajjii 3- 2017

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Jan, 07:43


ሚንበር ቲቪ ከሥፍራው፦ ዓለም አቀፍ ከወለድ ነፃ ፋይናንስ ኮንፍረንስ እና ሽልማት በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ከወለድ ነፃ ፋይናንስ ኮንፍረንስ እና ሽልማት በቀጣዩ የካቲት ወር እንደሚካሄድ በዛሬው እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።

ኮንፍረንስ እና ሽልማቱን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ሣዲያ መልቲ ሚዲያ እና አልሙቲን ኮንሰልታንሲ መሆናቸውን ዛሬ ቅዳሜ ጥር 3/2017 አዘጋጆቹ በአዲስ አበባ አያ ሆቴል አሳውቀዋል።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Jan, 07:24


ሚንበር ቲቪ ከሥፍራው፦ የኢማን ኢስላሚክ አሶሲየሽን የምርምር አውደ ጥናት መድረክ

ኢማን ኢስላሚክ አሶሲየሽን ዛሬ ቅዳሜ ጥር 3/2017 የምርምር አውደ ጥናት እያከናወነ ይገኛል። በአዲስ አበባ ከተማ ካፒታል ሆቴል በተዘጋጀው የምርምር አውደ ጥናት ላይ በተለያየ ዘርፍ የሚገኙ ምሑራን እና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

"ሴኩላሪዝም እና የሃይማኖት ነፃነት በኢትዮጵያ የትምሕርት ሥርዐት፦ መስተጋብር፣ ተግዳሮቶች እና ተስፋዎች" በሚል ርእስ የተዘጋጀው ጥናት የተሠራው፤ በኢስላሚክ ሪሰርች ኤንድ ካልቸራል ሲንተር (IRCC) ነው። ይህ ጥናት አንድ ዓመት የፈጀ መሆኑም ተገልጿል።

(ሚንበር ቲቪ የጥናቱን ዝርዝር ጉዳዮች በድረ ገጽ እንዲሁም የመድረኩን ሙሉ ዝግጅት በቴሌቪዥን ይዞ እንደሚቀርብ ለማሳወቅ ይወዳል)

Minber TV

05 Jan, 16:18


ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ለ500 ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጉን አሳወቀ

ዕለተ እሑድ ታኅሣሥ 27 - 2017 | ረጀብ 5 – 1446

በተማሪዎች እና ወጣቶች ዙሪያ የሚሠራው ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ለ500 ቤተሰቦች ድጋፍ ያደረገው ከኢንተርናሽናል ኮል ኦርጋናዬዜሽን ጋር በመተባበር መሆኑን በኃላፊዎቹ በኩል ለሚንበር ቲቪ በላከው መረጃ አሳውቋል።

በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው በአባድር ትምሕርት ቤት በአባል ተማሪዎቹ በኩል እንዲደርስ የተደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ ለ500 ቤተሰቦች የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምሕርት ቢሮ ኃላፊ እና መሰናዶውን ያዘጋጀው የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ አስተባባሪዎች እንደተገኙ ታውቋል።

ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ በጎ ያደረገው አድራጎት ሥራ በዋናነት ከሚንቀሳስበት የተማሪዎችን አቅም ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ከመገንባት ባሻገር የሚያደርገው እንቅስቃሴ አካል መሆኑንም ገልጿል።

(ይህ ዜና በሚንበር ቲቪ እና በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ትብብር የቀረበ ነው)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Jan, 16:01


ሪሳላ ፖድካስት የተለያዩ የመልካም ስብእና ተምሳሌቶችን እየጋበዘ በማራኪ የአቀራረብ መንገድ ይዞ በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ አዘጋጅነት ወደናንተ መድረሱን ሊጀምር ነው።

ሪሳላ ፖድካስት ዋነኛ አላማውን ከሚጋብዛቸው እንግዶች ጋር በተለየ ሁኔታ የተማሪነት ዘመን ቆይታ፣ ኢስላማዊ እንቅስቃሴያቸውን ጨምሮ እስከ ዛሬዋ የህይወት ምዕራፋቸው ድረስ የምንቃኝበት በአይነቱ የተለየ ፖድካስት ነው!

ሪሳላ ፖድካስት ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይከታተሉ።
በዩቲዩብ ለመከታተል የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ የዩቲዩብ ገፅ ላይ ያገኙታል።

የሙስሊም ተማሪዎች ሊግን የዩቱብ ገፅ ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

🔗 https://youtube.com/@muslim_students_league 🔗

#ሪሳላ_ፖድካስት
#Risala_Podcast
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Jan, 11:32


"የተሰጠንን እድል እንጠቀም"
የሂጅራ ባንክ ባለአክሲዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ
#ክፍል_2

#ሂጅራ_ቢዝነስ
ሂጅራ ባንክ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር የቀረበ

ዕለተ እሁድ ታኅሣሥ 27 - 2017 | ረጀብ 4 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Jan, 10:10


ራይደርስ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ የተከፈለ ካፒታሉ ከ455 ሚሊዮን በላይ መድረሱን አስታወቀ 

ዕለተ እሑድ ታኅሣሥ 27 - 2017 | ረጀብ 5 – 1446

የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ እና የእርሻ ሥራ ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሠማራው ራይደርስ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ አክስዮን ማኅበር፤ 3ኛ መደበኛ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት አከናወነ። አክስዮን ማኅበሩ የተከፈለ ካፒታሉ ከ455 ሚሊዮን በላይ መድረሱን አስታውቋል።

ዛሬ እሑድ ታኅሣሥ 27/2017 በአዲስ አበባ ከተማ ዲ ሊ ኦፖል ሆቴል በተከናወነው መርሐ ግብር ላይ የአክሲዮን ማኅበሩ ባለአክስዮኖች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። በጉባዔው ላይ የአክሲዮን ማኅበሩ የ2016 አፈፃፀም፣ ፋይናንሻል ሪፖርት እና ቀጣይ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የአክስዮን ማኅበሩ የዳይሬክተርች ቦርድ ዋና ሰብሳቢ አቶ ሙኒር አደም ዓሊ ያለፈው አንድ ዓመት በአክሲዮን ማኅበሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ከባድ ፈተና የተጋፈጠበት እንደነበር ገልጸዋል። ይሁን እንጂ የገጠሙትን ተፅዕኖዎችና ፈተናዎች ተቋቁሞ ማለፍ መቻሉን አስረድተዋል። ለዚህ በማሳያ የጠቀሱት ካለፈው የሥራ ዘመን ጋር ሲነፃፀር የተከፈለ ካፒታል መጠኑ የብር የ15 ሚሊዮን እንዲሁም የባለአክስዮኖች ቁጥር በ177 ጭማሪ ማሳየቱን ነው። እንዲሁም በድርሻ ሽያጭ ፕሪሚየም ብር 18.5 ሚሊዮን እንደተመዘገበ አብራርተዋል፡፡

በሀገር ደረጃ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ከባቢያዊ ሁኔታው ፈታኝ ቢሆንም እንደ ማኅበር በተልዕኮ ደረጃ የተያዙትን ዋና ዋና ተግባራትን በማሳካት በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ፣ በእርሻ ሥራ እና ሌሎች ኢንቨስትመንቶች ላይ በመሳተፍ ውጤታማ ዓመት እንዳለፈ አንስተዋል፡፡

ራይደርስ ትሬዲንግና ማኑፋክቸሪንግ አክስዮን ማኅበር የተመሠረተው በ2014 መስከረም ወር ነው። በአሁኑ ሰዓት በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ፣ በእርሻ ሥራ፣ በሪልእስቴት እና በሌሎች ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶች ተሰማርቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። (ሚንበር ቲቪ)

Minber TV

05 Jan, 10:09


ራይደርስ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ የተከፈለ ካፒታሉ ከ455 ሚሊዮን በላይ መድረሱን አስታወቀ 

Minber TV

05 Jan, 09:44


ሚንበር ቲቪ ከሥፍራው፦ የሙስሊም ባለሞያዎች ማኅበር የማብሰሪያ መርሐ ግብር

የሙስሊም ባለሞያዎች ማኅበር የማብሰሪያ እና የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው እለት እያከናወነ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ኤሊያና ሆቴል እየተካሔደ በሚገኘው መርሐ ግብር በተለያየ ዘርፍ የሚገኙ ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንዲሁም የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።

(የመርሐ ግብሩን ዝርዝር በማኅበራዊ ትስስር መድረክ አማራጮች ይዘን የምንመለስ ይሆናል)

Minber TV

05 Jan, 09:31


#ማስታወቂያ

በወርሃ ጥር መጨረሻ፣
በታላቁ የረመዳን ወር መዳረሻ፣
ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ሲያሳርፉ፣
ወርቃማውን አጋጣሚ ከኛ ጋር ያሳልፉ!
ሂራ ቱር ኤንድ ትራቭል ወላጆች ከተደራራቢ ኃላፊነቶች ነፃ የሚሆኑበትንና ተማሪዎችም ከትምህርት የሚያርፉበትን ወቅት ታሳቢ በማድረግ ለቤተሰብ ያዘጋጀው ሶስተኛው ዙር የኅብረት የዑምራ ጉዞ፤ ከጥር 22 እስከ የካቲት 3 የሚከወን ሲሆን፤ ፓኬጁን የኸሚስ ምሽቶቹ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሂምና ወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ይመሩታል። ፓኬጁ የቤተሰብ ነውና ለእናቶችና እህቶች ደግሞ የበይቱል ሃቢብ ፕሮግራም አዘጋጇን ኡስታዛ ሃስና ሸይኽ ሙስጠፋን ይዘናል።

እንደ ቤተሰብ ተሰባስበን፣
አካልና መንፈሳችንን አሳርፈን፣
የማይረሳ ውብ ጊዜን አብረን እናሳልፋለን!
ያስታውሱ! ጉዞው የሚከወነው ለበርካታ ቤተሰቦች የእረፍት ወቅት ላይ እንደመሆኑ፤ ከወዲሁ ቀድመው ይመዝገቡ!
ለተሟላ መረጃ
096588883 ወይም 0965888884 ላይ ይደውሉ!

ሂራ ቱር ኤንድ ትራቭል
አድራሻ ሣር ቤት ግደይ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ!

Minber TV

05 Jan, 07:24


ሚንበር ቲቪ ከሥፍራው፦ የራይደርስ ትሬዲንግና ማኑፋክቸሪንግ አክስዮን ማኅበር ጠቅላላ ጉባዔ

የራይደርስ ትሬዲንግና ማኑፋክቸሪንግ አክስዮን ማኅበር 3ኛ መደበኛ እና 4ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ እያካሔደ ይገኛል። ዛሬ እሑድ ታኅሣሥ 27/2017 በአዲስ አበባ ከተማ ዲ ሊ ኦፖል ሆቴል እየተከናወነ በሚገኘው ጉባዔ ላይ የአክስዮን ማኅበሩ የ2016 አፈፃፀም፣ የኦዲት ሪፖርት እና የ2017 ዋና እቅድ ይቀርባል።

(ሚንበር ቲቪ የጠቅላላ ጉባዔውን ዝርዝር እንደሚያቀርብ ለማሳወቅ ይወዳል)

Minber TV

05 Jan, 07:16


የረመዳን ጾም ቀዳ ማውጣት

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/jVFfIQ44jjE 🔗

#ጥያቄ_አለኝ #የስአሉነክ
#ረመዳን #ጾም #ፈትዋ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 16:17


የከተማና ገጠር ልዩነት

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/F4HQZNhZe_Y 🔗

#ቅኝተ_መጻሕፍት #የመጽሐፍ_ዳሰሳ
#ከተማ #ገጠር #የኑሮ_ልዩነት #book

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 14:22


ከነገ ጀምሮ “ለሃገር ሰላም እና ደኅንነት” ሲባል በሁሉም የሰላት ወቅቶች ቁኑት እንዲደረግ የዑለማ ጉባዔ ውሳኔ አሳለፈ

ዕለተ ቅዳሜ ታኅሣሥ 26 - 2017 | ረጀብ 4 – 1446

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ፤ ከነገ ታኅሣሥ 27/2017 ጀምሮ “ለሃገር ሰላም እና ደኅንነት” ሲባል በሁሉም የሰላት ወቅቶች ቁኑት እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የጉባዔው ጽሕፈት ዛሬ ቅዳሜ ታኅሣሥ 26/2017 እንዳሳወቀው፤ ውሳኔውን ለማስተላለፉ በምክንያት የጠቀሰው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች “ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮች” መበርከታቸው ነው።

በሀገሪቱ የሰው ልጆች “ፍቅር መጥፋቱን፣ ጥላቻ መስፋፋቱን፣ የእርስ በእርስ መገዳደል መበራከቱን፣ የሰው ልጅ ከምንጊዜውም በላይ ርካሽ የሆነበትና በቀላሉ ሕይወት እየተቀጠፈ የሚገኝበት ደረጃ ላይ መደረሱንም” የዑለማ ጉባዔው ዘርዝሯል። በተጨማሪነት የተፈጥሮ አደጋዎች በመከሰት ላይ ይገኛሉ ያለው ጉባዔው፣ ለዚህ ምክንያቱ “ከጥፋቶችና ከስህተት መመለስ አለመቻል” መሆኑን ገልጿል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ በኩል የወጣው የዑለማ ጉባዔ ውሳኔ፣ ከአላህ ጋር ለመታረቅ የሰው ልጆች ከሚሠሯቸው ስሕተቶች በመታቀብ ወደእርሱ መፀፀትና ተውበት በመግባት መመለስና መማፀን እንደሚያስፈልግ ማሳሰቢያ ሠፍሮበታል።

ጉባዔው ለዚህ ሲባል ከነገ እሑድ ታኅሣሥ 27/2017 ጀምሮ እስከ ጥር 2/2017 ለስድስት ቀናት ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል። በቀጣዩ ጁመዓም በሁሉም መስጂዶች የሚደረጉ ኹጥባዎች በዚህ ዙሪያ እንዲደረጉም አሳስቧል

የምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ ውሳኔ የተሰማው በኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ የርዕደ መሬት ከተከሰተ በኋላ ነው።

የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መሥሪያ ቤት  ባወጣው መረጃ ባለፉት ሁለት ቀናት በሀገሪቱ ሰሞኑን ሲከሰቱ ከነበሩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሴከንዶች የቆየ ርዕደ መሬት ተከስቷል። ትናንት ጁመዐ ከእኩለ ሌሊት በኋላ የተከሰተው በተለይ ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

መንግሥት በዛሬው እለት እንደገለጸው ከሆነ ደግሞ፣ የርዕደ መሬት ማዕከል በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ከ80 ሺሕ በላይ ነዋሪዎችን በተለዋጭ ቦታ ለማሥፈር እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 14:22


ከነገ ጀምሮ “ለሃገር ሰላም እና ደኅንነት” ሲባል በሁሉም የሰላት ወቅቶች ቁኑት እንዲደረግ የዑለማ ጉባዔ ውሳኔ አሳለፈ

Minber TV

04 Jan, 12:35


የቁርኣን ተፍሲር በሐረሪ ቋንቋ - በሸይኽ የሕያ እስማዒል (ረሒመሁላህ)
ሱረቱል ሷድ 17-35

ዛሬ ምሽት 12:00 በሚንበር ቲቪ!

#ቁርኣን #ተፍሲር #ሐረሪ
#ሸይኽ_የሕያ_እስማዒል_ረሒመሁላህ 

ዕለተ ቅዳሜ ታኅሣሥ 26 - 2017 | ረጀብ 4 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 11:52


ባቡል ኸይር ድጋፍ የሚሰጣቸው ወገኖች ቁጥር አምስት ሺሕ መድረሱን አስታወቀ

ዕለተ ቅዳሜ ታኅሣሥ 26 - 2017 | ረጀብ 4 – 1446

ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የምገባ አቅርቦት የሚሰጣቸው ወገኖች ቁጥር አምስት ሺሕ መድረሱን በዛሬው እለት የተመሠረተበትን አምስተኛ ዓመት በማስመልከት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል።

የማኅበሩ ኃላፊዎች ዛሬ ቅዳሜ ታኅሣሥ 26/2017 ረፋድ ላይ መርሐ ግብሩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ባለፉት ዓመታት ተሠርተዋል ያሏቸው ተግባራት ላይ ማብራሪያ ከመስጠት ባሻገር ከአንድ ሳምንት በኋላ ጥር 4/2017 ስለሚከበረው የምሥረታ በዓል ገለፃ አድርገዋል።

በምሥረታው ወቅት 126 አቅመ ደካማ እና ደጋፊ የሌላቸው ወገኖችን ከጎዳና በማንሳት የምገባ አቅርቦት መስጠት በመጀመር በአሁኑ ሰዓት ይህ ቁጥር  አምስት ሺሕ ደርሷል ብለዋል።

በዋነኝነት አረጋውያንን እና ጧሪ የሌላቸውን ወገኖች ከምገባ ጀምሮ ከመደገፍ በተጨማሪ ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል።

የበጎ አድራጎት ድርጅቱን ቀጣይነት በማረጋገጥ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በተጠናከረ አቅም ለመወጣት የሁሉም ድጋፍ እንደሚያስፈልግም የድርጅቱ መሥራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሐናን ሙሐመድ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የተመሠረተው በመስከረም 2012 ነው።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 11:31


ዛሬ በህይወት መንገዷ የምታመላልሰን እናት የሂዳያን ብርሃን ካገኘች 8 ዓመታት ተቆጥረዋል። የሁለት ሴት ልጆች እናት የሆነችው ባለታሪካችን የኑሮ እና የህይወት ፈተና ሳይበግሯት ልጆቿን ለቁምነገር ለማብቃት በመትጋት ከባድ ጊዜያትን ያሳለፈች ብትሆንም፤ በህመም አልጋ ላይ እስክትውል ድረስ ማንም ሰው ስትጋፈጣቸው ስለነበሩ ከአቅሟ በላይ የሆኑ ሁኔታዎች እንዳላወቀባት አጫውታናለች።

በስክነቷ ውስጥ የሚታየው ጥብቅነቷና ኢማኗ በአላህ ላይ ያላትን መመካት ያዳበረላት እንግዳዬ ጀሚላ ''ብሞት ልጆቼን አደራ የምሰጠው ሰው የለኝም!'' እያለች ምሽት ከ03:00 ጀምሮ በህይወት መንገዷ እያመላለሰችን የምታቆየን ይሆናል።

#የኔ_መንገድ
#ብሞት_ልጆቼን_አደራ_የምሰጠው_የለኝም!

ዕለተ ቅዳሜ ታኅሣሥ 26 - 2017 | ረጀብ 4 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 10:28


Sagantaan SIMBOO guyyaa sabtii waaree booda sa'aa 8:00 irraa jalqabee karaa MINBER TV tiin Tamsaasa irra ni oola

#siimboo
#bohaartii_sanbataa
#milanmedia
#minbertv

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 09:46


መወዳ መዝናኛችን በዚህ ሳምንት ...

ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ!

#መወዳ_መዝናኛ
#Meweda
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 09:29


መንግሥት የርዕደ መሬት ማዕከል በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ከ80 ሺሕ በላይ ነዋሪዎችን በተለዋጭ ቦታ ለማሥፈር እየሠራ እንደሚገኝ አስታወቀ

ዕለተ ቅዳሜ ታኅሣሥ 26 - 2017 | ረጀብ 4 – 1446

መንግሥት የርዕደ መሬት ማዕከል በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ከ80 ሺሕ በላይ ነዋሪዎችን በተለዋጭ ቦታ ለማሥፈር እየሠራ እንደሚገኝ ያስታወቀው በዛሬው እለት ነው።

በኮሚኒኬሽን አገልግሎት በኩል ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ፤ በኢትዮጵያ ሦስት ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተለያየ መጠን ያለው የርዕደ መሬት ክስተት ማጋጠሙን አስታውቋል።

በመግለጫው የተጠቀሱት ክልሎች አፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች ናቸው። ክስተቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እና በድግግሞሽ እያደገ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፣ በዚህ ሳምንት በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጿል።

የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መሥሪያ ቤት  እንዳስታወቀው ከሆነ፣ ባለፉት ሁለት ቀናት በሀገሪቱ ሰሞኑን ሲከሰቱ ከነበሩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሴከንዶች የቆየ ርዕደ መሬት ተከስቷል። ትናንት ጁመዐ ከእኩለ ሌሊት በኋላ የተከሰተው በተለይ ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 08:44


ቢልኮር ፖድካስት | Bilcor Podcast

በቅርብ ቀን ...
በሚንበር ቲቪ

#ቢልኮር_ፖድካስት #Bilcor_Podcast
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 07:25


ሚንበር ቲቪ ከሥፍራው፦ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የትምሕርት ተሳትፎ የምክክር መድረክ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የትምሕርት ተሳትፎ የምክክር መድረክ እያካሔደ ይገኛል። ዛሬ ቅዳሜ ታኅሣሥ 26/2017 በአዲስ አበባ ስቴይ ኢዚ ሆቴል እየተከናወነ የሚገኘው መድረክ ላይ የምክር ቤቱን ከፍተኛ ኃላፊዎች ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች የተሳተፉበት ነው። ይህ መድረክ ለሁለት ቀናት የሚካሔድ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል።


★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Jan, 07:16


የድሮው የትምህርት ስርዓት …

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/NxZb8wALQL0 🔗

#ፋቲሕ_ኮንቬንሽን
#የትምህርት_ስርዓት
#እምነት

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Jan, 16:16


በሰርግ ዕለት ስለ ቀብር…

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/Y17weFuchwI 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #ልዩ_ዝግጅት
#ሰርግ #ሙሽራ #ድግስ #ቀብር

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Jan, 15:49


በአክሱም የሙስሊሞች መብት ላይ ጥሰት በፈጸሙ ግለሰቦች ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ ምክር ቤቱ ጠየቀ

ዕለተ ረቡዕ ታኅሣሥ 23 - 2017 | ረጀብ 1 – 1446

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ በትግራይ ክልል አክሱም በሙስሊሞች መብት ላይ ጥሰት በፈጸሙ ግለሰቦች ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀ። ምክር ቤቱ በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከትምሕርት ገበታ ውጪ እንዲሆኑ መደረጉ መፍትሔ ያገኛል በሚል በትዕግሥት ቢጠብቅም እልባት አለመገኘቱን ገልጿል።

ምክር ቤቱ በአክሱም በሙስሊሞች መብት ላይ ጥሰት በፈጸሙ ግለሰቦች ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ የጠየቀው ዛሬ ረቡዕ ታኅሣሥ 23/2017 በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ላይ የሚፈጸሙ የመብትና የሃይማኖት ጥሰቶችን በሚመለከት ባወጣው መግለጫ ነው።

በዚህ መግለጫ ላይ በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ሃይማኖታዊ ትንኮሳዎች የመንግሥት አካላትን ጨምሮ የሥጋት ምንጭ እየሆኑ እንደሚገኙ ተገልጿል። ከዚህ አንጻር የአክሱም ከተማ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤቶች የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ከአለባበስ ጋር በተገናኘ ለአንድ ወር ገደማ ከትምህርት ገበታ አስተጓጉለዋል ብሏል። አንዳንድ ተማሪዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚጠቅሰው መግለጫው፤ በከተማው ሙስሊሞች ለዘመናት የነበረባቸው የእምነት ነፃነት፣ የመስገጃ ቦታ ችግርና የቀብር ቦታ እጦት ወደ ባሰ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ጠቁሟል።

መግለጫው አክሎም የክልሉና የፌዴራል መንግሥት የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በዓለም አቀፍ ሕግጋትና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 27 የተቀመጡ መብቶችን የሚሸረሽሩ ተግባራትን መፈፀማቸውን አውግዟል።

ምክር ቤቱ በጠቀሰው በአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች በትምሕርት ቤቶች በተጣለው ሒጃብ ክልከላ ምክንያት ከትምሕርት ገበታ ውጪ የሆኑት ከታኅሣሥ 8/2017 አንስቶ ነው፡፡

በከተማው በተማሪዎች ላይ የሒጃብ ክልከላውን ጥለውታል የተባሉት ትምህርት ቤቶች በቀጥር ቢያንስ አምስት ናቸው፡፡ ትምሕርት ቤቶቹ “አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት”፣ “አሉሚናይ”፣ “ወርኣይ”፣ “ክንደያ” እና “ኣብርሃ ወ ኣጽብሃ” መሆናቸውም ታውቋል፡፡

በትምሕርት ቤቶቹ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሀገር አቀፍ ፈተና ቅጽ የሚሞሉበት ጊዜ ታኅሣሥ 14/2017 የጀመረ ቢሆንም፤ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከትምሕርት ገበታ ውጪ ለመሆን በመገደዳቸው መሙላት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡ በሒጃብ ክልከላው ምክንያት በተለይ “ወርኢይ” በተሰኘው ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ ሴት ተማሪዎች፤ የሴሚስተር አካፋይ (Mid semester) ፈተና ላይ መቀመጥ ሳይችሉ መቅረታቸው ታውቋል፡፡

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Jan, 15:48


በአክሱም የሙስሊሞች መብት ላይ ጥሰት በፈጸሙ ግለሰቦች ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ ምክር ቤቱ ጠየቀ

በድረ ገጽ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=9676

Minber TV

01 Jan, 15:02


#ሸይኽ_ሙሐመድ_ሮይሌ_ሐሪማ
#ካስማ_ሾው

ዛሬ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ!

ዕለተ ረቡዕ ታኅሣሥ 22 - 2017 | ጁማዱል ረጀብ 1 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Jan, 12:46


ተመልካቾቹን ለማርካት የሚሰራው መወዳ መዝናኛ በአዛን፣በቲላዋ፣በሆስቲንግ እና በግጥም ተሰጥኦቻችሁን ማውጣት ለምትፈልጉ ውድ ተመልካቾች ስቱዲዮ ቀርባችሁ ሙከራዎቻችሁን ለሕዝብ የምታቀርቡበት ዕድል ማመቻቸታችንን እናበስራለን።
. . .
ስራዎቻችሁን ለመገምገም ያመቸን ዘንድ ጥራት ባለው ካሜራ የተቀረጸ የሁለት ደቂቃ ቪድዮ ቀድማችሁ እንድትልኩ እያሳሰብን፤ ግጥሞቻችሁን ደግሞ በጉልህ በሚነበብ የኮምፒውተር ወይም በስልክ የአማርኛ የተጻፈ ከሁለት ገጽ ያልበለጠ ጽሑፍ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
. . .
ስራውን ለማቅረብ የሚመረጥ ሰው ከቀረጻ ሁለት ቀናት በፊት እንደሚነገረው ለማስታወስ እንወዳለን። ስራዎቻችሁን በቴሌግራም አድራሻችን @minbertv1 መላክ ትችላላችሁ።

#መወዳ_መዝናኛ #መወዳ_ታለንት
#ህዝባዊ_ተሳትፎ #Public_Participation #የወጣቶች_መድረክ #የተስጥኦ_መድረክ

ዕለተ ረቡዕ ታኅሣሥ 23 - 2017 | ረጀብ 1 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Jan, 12:14


… ጁሙዓ

Minber TV

01 Jan, 12:07


በአክሱም የት/ቤት ኃላፊዎች በሒጃብ ጉዳይ የተሰጠውን ትዕዛዝ በመጣስ ተማሪዎች ላይ ዳግም ክልከላ ጣሉ

ዕለተ ረቡዕ ታኅሣሥ 23 - 2017 | ረጀብ 1 – 1446

በአክሱም ከተማ የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች፤ የትግራይ ክልል ትምሕርት ቢሮ በሒጃብ ጉዳይ አዲስ ክልከላ እንደማይቀበል በመግለጽ በነባሩ አሠራር እንዲቀጥል ትዕዛዝ ቢያሳልፍም ውሳኔውን በመጣስ ተማሪዎች ወደ ግቢ እንዳይገቡ መከልከላቸው ታውቋል፡፡ “ሚንበር ቲቪ” ይህንን በከተማው በሒጃብ ክልከላ ምክንያት ከትምሕርት ቤት ከተመለሱ ተማሪዎች እና ወላጆች ማረጋገጥ ችሏል፡፡

በከተማው የሒጃብ ክልከላ ከጣሉ ትምሕርት ቤቶች መካከል በአንደኛው የምትማር ሥሟ ለደኅንነት ሲባል እንዳይጠቀስ የጠየቀች ተማሪ ለ“ሚንበር ቲቪ” እንደተናገረችው፤ የክልሉ ትምሕርት ቢሮ ለትምሕርት ቤቶቹ ደብዳቤ መጻፉን ተከትሎ ዛሬ ረቡዕ ታኅሣሥ 23/2017 ወደ ትምሕርት ቤት ቢያመሩም ወደ ውስጥ መግባት እንደማይችሉ ስለተነገራቸው እንደተመለሱ አስረድታለች፡፡ በዛሬው እለት በትምሕርት ቤቶች ዙሪያ ከፍተኛ የፀጥታ ኃይል ሥምሪት እንደነበርም ተማሪዋ እና ወላጆች ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ክልከላውን ከጣሉት መካከል በሆነው “ክንደያ ትምሕርት ቤት” ሒጃብ ለብሰው ወደ ግቢ ሊገቡ የሞከሩ ተማሪዎች ላይ ድብደባ እንደፈጸመ ተሰምቷል፡፡

የትግራይ ክልል ትምሕርት ቢሮ ታኅሣሥ 22/2017 “የትምሕርት ቤት አካሄድ ሥርዐትን በተመለከተ” በሚል ርእሰ ለአክሱም ከተማ ትምሕርት ቢሮ በላከው ደብዳቤ፤ በአክሱም ከተማ በእስልምና እምነት ተከታይ ሴት ተማሪዎች ላይ የተጣለውን የአለባበስ እገዳ በተመለከተ ከአክሱም ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ቅሬታ እንደቀረበለት በመግለጽ፤ በከተማው “የተለመደው የትምሕርት ቤት አካሄድ ሥርዐት እንዲቀጥል” ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ቢሮው የተለየ አዲስ መመሪያ እስካልወጣ ድረስ “አዲስ እገዳም ሆነ አዲስ ጥያቄ” ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በገለጸበት ደብዳቤ፤ የተማሪዎች አለባበስን በተመለከተ ግን ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል በሚል የጠቀሰው መመሪያ የለም፡፡

ሆኖም በዛሬው እለት ወደ ትምሕርት ቤቶች ያመሩ ተማሪዎችን አናስገባም ያሉ ትምሕርት ቤቶች ኃላፊዎች፤ ትምሕርት ቢሮ በግልጽ ተማሪዎቹ እንዲገቡ የሚገልጽ ደብዳቤ ባለመጻፉ ውሳኔውን እንደማይቀይሩ መናገራቸውን ሥሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችዋ ተማሪ ተናግራለች፡፡ ደብዳቤው ክልከላውን እንዲያጠናክሩ ማድረጉንም አክላለች፡፡

በአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች በትምሕርት ቤቶች በተጣለው ሒጃብ ክልከላ ምክንያት ከትምሕርት ገበታ ውጪ የሆኑት ከታኅሣሥ 8/2017 አንስቶ ነው፡፡
በከተማው በተማሪዎች ላይ የሒጃብ ክልከላውን ጥለውታል የተባሉት ትምህርት ቤቶች በቀጥር ቢያንስ አምስት ናቸው፡፡ ትምሕርት ቤቶቹ “አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት”፣ “አሉሚናይ”፣ “ወርኣይ”፣ “ክንደያ” እና “ኣብርሃ ወ ኣጽብሃ” መሆናቸውም ታውቋል፡፡

በትምሕርት ቤቶቹ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሀገር አቀፍ ፈተና ቅጽ የሚሞሉበት ጊዜ ታኅሣሥ 14/2017 የጀመረ ቢሆንም፤ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከትምሕርት ገበታ ውጪ ለመሆን በመገደዳቸው መሙላት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡ በሒጃብ ክልከላው ምክንያት በተለይ “ወርኢይ” በተሰኘው ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ ሴት ተማሪዎች፤ የሴሚስተር አካፋይ (Mid semester) ፈተና ላይ መቀመጥ ሳይችሉ መቅረታቸው ታውቋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ትናንት ማክሰኞ ታኅሣሥ 22/2017 ሊሰጥ የነበረውን መግለጫ በመሰረዝ ለሌላ ጊዜ ማዛወሩ ታውቋል። ምክር ቤቱ መግለጫውን ለሌላ ጊዜ ያዛወረው የክልሉ ትምሕርት ቢሮ ለእክሱም ትምሕርት ቤቶች የጻፈውን ትዕዛዝ ተከትሎ ነበር። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Jan, 12:06


በአክሱም የት/ቤት ኃላፊዎች በሒጃብ ጉዳይ የተሰጠውን ትዕዛዝ በመጣስ ተማሪዎች ላይ ዳግም ክልከላ ጣሉ

በድረ ገጽ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=9673

Minber TV

01 Jan, 10:32


በበርካታ የዳዕዋ መድረኮች በሚያቀርባቸው ሁለንተናን ሰቅዘው የሚይዙ ትምህርቶቹ በስፋት የምናውቀው ጥዑመ ልሳኑ ዳዒ ዶክተር ሰምሃር ተክሌ፤ ቤተል በሚገኘው አዲሱ የሙጀመዕ አት-ተቅዋ መስጂድ ለታዳሚዎች ዒልምን እየዘሩ ከሚገኙ ተወዳጅ ኡስታዞች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን በእጅጉ የሚያስፈልጉንን የአምልኮ፣ የሸሪዓ ድንጋጌዎችና ፊቅሃዊ ብያኔዎችን ከያዘው "አቢ ሹጃእ" ኪታብ ሰፋ ካሉ ማብራሪያዎች ጋር በማጣመር ግሩም በሆነ መንገድ ደርስ (ትምህርት) እየሰጠ ይገኛል፡፡

ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን ሚንበር ቲቪም፤ አዲስ በጀመረው "ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራሙ ይህንን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶችን የያዘውን የ "አቢ ሹጃእ" ደርስ (ትምህርት) ክፍል አስራ ዘጠኝ ዝግጅቱን ዛሬ ምሽት ከ12፡30 ጀምሮ ለውድ ተመልካቾቹ ያቀርባል!

#ሚንበሩል_ዒልም
#አቢ_ሹጃእ
#ክፍል_19
#ዶክተር_ሰምሃር_ተክሌ

ዕለተ ረቡዕ ታኅሣሥ 23 - 2017 | ረጀብ 1 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 17:05


#ማስታወቂያ

ለ ታላቁ ረመዳን ቀልባችንን ለማዘጋጀት

>  በ ረጀብ ወር ማብቂያ  እንዲሁም በ ሻዕባን ወር ጅማሮ በአንድ ጉዞ ሁለት ዑምራ ከኛ ጋር

> በታሪካዊቶ ቀን በረጀብ 27 በኢስራ ወል ሚዕራጅ ዕለት የመጀመሪያውን ዑምራ ከኛ ጋር ያድርጉ

> ቆይታችን ከ ጥር 15 - 25 ( ከረጀብ 23 እስከ ሻዕባን 3  ) የሚቆይ ይሆናል

> ጉዞው በ ዑስታዝ ናስር አሊ የሚመራ ይሆናል

ፓኬጅ ሚያካትታቸው
> የቪዛ አገልግሎት
> የአየር  ትኬት
> ምቾቶን የጠበቀ ሆቴል
> ኢንሹራስን
> የትራንስፖርት አገልግሎት
> ታሪካዊ ባታዎች ጉብኛት

> ለበለጠ መረጃና ለመመዝገብ

0988 313233
0976 838181

አል ሂያም እና ኢብራሂም ቱር ትራቪል !!

Minber TV

31 Dec, 16:14


የእንጀራ ጥቅሞች

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/J00YWOGPNNY 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #አህል_ውሃ
#እንጀራ #ጤፍ #nutrition

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 15:17


2024 የፈረንጆቹ ዓመት ከዛሬ ሌት አይሻገርም። ትውስታው ምስቅልቅሉ የሄደው የመጣው ግን ብዙ ነው። እኛም ዓመቱን በተረክ መነፅራችን ስንከርመው እነሆ 2024 ብለን ቀነጫጭበነዋል። 2025 ምን ይዞ እንደሚመጣው የሁለንተናው ባለስልጣን የጊዜ ፈጣሪ አላህ (ሱ.ወ) ብቻ ነው! ምሽት 02:30 ጀምሮ ይጠብቁን!

#እነሆ_2024!
#እነሆ_ኸበር

ዕለተ ማክሰኞ ታኅሣሥ 22 - 2017 | ጁማዱል አኺር 30 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 15:15


የምህረት ወራችን እንሆ ተቃረበ። ከምንግዜውም በላይ በመንፈስ የምንበረታበትና፤ ለፈጣሪያችን አላሁ (ሱ.ወ) የምንረታበት ውድ ሰሞናችን እየተጠጋን ነው።
በርግጥም ዋዜማው ላይ መቆም ብስራት የመኾኑን ያህል፤ ደርሰን ከኸይራት እልፍኙ እንድንመነዳም በዛው መጠን ዱዓ ማድረግ ይጠበቅብናል። የሌት ተቀን ተማፅኗችንም ከዚህ አይርቅም።
አላሁ (ሱ.ወ) ሁለት ወራት የቀሩትን ታላቁን የምህረት ወር ደርሰው፤ ከኸይር ድግሱ ከሚያጋፍሩት ያደርገን ዘንድ እንማፀነዋለን።

#የቁርኣን_ወር_የዚክር_ዓለም #ረመዳን_60_ቀናት_ቀሩት
#60days #Ramadan #ረመዷን
#اللهم_بلغنا_رمضان
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 13:15


🔴 የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት 🔴

ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣሥ 22/2017 የርችት ተኩስ ስለሚኖር ኅብረተሰቡ እንዲያውቀው ሲል አሳስቧል።

ፖሊስ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የደኅንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ በጻፈልኝ ደብዳቤ፣ ምሽት ላይ የሚተኮሰው ርችት በፈረንጆች አዲስ ዓመት ዋዜማ ምክንያት የሚደረግ ነው ብሏል። የርችት ተኩሱ ከሌሊት 6:00 እስከ 6:15 ሰዓት የሚካሔድ መሆኑ ተገልጿል።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 12:30


#ሙቀዲማህ
#ቅኝተ_መጻሕፍት
#The_Muqaddimah
#Book_review
#ክፍል_2

ምሽት ከ02:30 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ!

ዕለተ ማክሰኞ ታኅሣሥ 22 - 2017 | ጁማዱል አኺር 30 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 11:30


በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ የሚሰናዳው እና ተማሪዎችን በቀለም ትምህርት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል እና ማበረታታት ሁለንተናዊ የሆነ የተሟላ እውቀት ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል አላማው የሆነ "ቅን ትውልድ" ፍተሻ የጥያቄ እና መልስ ውድድር ለተወዳዳሪዎች የ200,000 ብር ሽልማት ይዞ ጉዞ ቀጥሏል። ምሽት 02:00 በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#ቅን_ትውልድ
#ፍተሻ

ዕለተ ማክሰኞ ታኅሣሥ 22 - 2017 | ጁማዱል አኸር 30 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 11:14


የወንጀል እድፌን ሰው ሁሉ ሲቆጥር…

አሚር ተፈሪ ይባላል። መወዳ መዝናኛችን ለተመልካቾች ያቀረበውን ዕድል ተጠቅሞ መወዳ ስቱዲዮ በመገኘት ምርጥ ግጥም አቅርቦልናል።
የተለያዩ ችሎታዎች ኖሯችሁ ዕድል ላጣችሁ በ 0948992121 ወይም @minbertv1 የቴሌግራም አድራሻችን ልታወሩን ትችላላችሁ። መልካም ዕድል!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/VC85DWBHJ1A 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #መወዳ_ታለንት

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 10:30


ከዒልም ጋር ያላቸው ጥልቅ ትውውቅ የጀመረው በልጅነታቸው ነበር፡፡ ሸይኽ ሰዒድ ዓሊ ሐቢብ ይሰኛሉ፡፡ ወጣትነታቸውን የሰዉለት የዒልም አድማስ ዛሬ ላይ በዘርፈ ብዙ ሸሪዓዊ ጉዳዮች ላይ ርቀው እንዲሄዱና ከታላላቅ ዑለሞች ተርታ እንዲሰለፉ አስችሏቸዋል፡፡ ሸይኽ ሰዒድ በመስከ ብዙ ፉኑኖች ያላቸውን የዒልም አቅም ለሰፊው ማኅበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በተፈጠረላቸው መልካም ዕድል ተጠቅመው፤ ከመግሪብ ሶላት በኋላ እስከ ዒሻእ ሶላት ድረስ በሙጀመዕ አት - ተቅዋ የሚሰጡትን "የአርበዒን ሃዲስ" ትምህርት (ደርስ) ዘወትር ማክሰኞ ምሽት ከ12፡30 ጀምሮ ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን አዲስ በጀመረው የሚንበሩል ዒልም ፕሮግራሙ #በክፍል_26 የሚያቀርብላችሁ ይሆናል፡፡

#ሚንበሩል_ዒልም
#አርበዒን_ሐዲስ
#ክፍል_26
#ሸይኽ_ሰዒድ_ዓሊ_ሐቢብ

ዕለተ ማክሰኞ ታኅሣሥ 22 - 2017 | ጁማዱል አኸር 30 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 07:14


በእርሶ እድሜ ስንት መንግስት አልፏል?

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/SnU5khn2TvM 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #የእንግዳ_ሰዓት
#አዝናኝ #አባት #እድሜ #ዘመን

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

31 Dec, 06:35


ሚንበር ቲቪ ከሥፍራው፦ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሚያዘጋጀው ከተማ አቀፍ የቁርኣን እና አዛን ውድድር

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አዘጋጀዋለሁ ላለው ከተማ አቀፍ የቁርኣን እና አዛን ውድድር ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣሥ 22/2017 ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል። ውድድሩ የሚደረገው በምክር ቤቱ ውስጥ ነው።

(ሚንበር ቲቪ የመግለጫውን ዝርዝር ጉዳዮች በድረ ገጽ፣ ማኅበራዊ መድረክ አማራጮች እንዲሁም በምሽት የሚንበር ኸበር እንደሚያቀርብ ለማሳወቅ ይወዳል)

Minber TV

27 Dec, 10:30


የህይወት መመሪያችን የሆነውን ቁርአንን ለመረዳትና ለመኖር ትርጉሙን (ተፍሲር) በዘርፉ ጥልቅ ንባብና ዕውቀት ካላቸው ዑለሞች መማር ያሻል።

ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን ሚንበር ቲቪም በዕውቀት የታነጸ ማኅበረሰብን ለመገንባት እንደሚረዳ የሚታመነውንና፤ መልከ ብዙ ትምህርቶች የሚሰጡበትን "ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራም ከሥፍራው በጥራት በመቅረፅ በየዕለቱ እያቀረበ የቆየ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ ከሚሰጡ ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነውንና በተወዳጁ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እየተሰጠ የሚገኘውን የቁርኣን ተፍሲር ትምህርት (ደርስ) ዘወትር ጁምዓ አመሻሽ ከ12:30 ጀምሮ ይቀርብላችኃል።

#ሚንበሩል_ዒልም
#የቁርኣን_ተፍሲር
#ክፍል_14
#ሸይኽ_ሐሚድ_ሙሳ

ዕለተ ዓርብ ታኅሣሥ 18 - 2017 | ጁማዱል አኸር 26 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

27 Dec, 09:22


#ማስታወቂያ

በወርሃ ጥር መጨረሻ፣
በታላቁ የረመዳን ወር መዳረሻ፣
ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ሲያሳርፉ፣
ወርቃማውን አጋጣሚ ከኛ ጋር ያሳልፉ!
ሂራ ቱር ኤንድ ትራቭል ወላጆች ከተደራራቢ ኃላፊነቶች ነፃ የሚሆኑበትንና ተማሪዎችም ከትምህርት የሚያርፉበትን ወቅት ታሳቢ በማድረግ ለቤተሰብ ያዘጋጀው ሶስተኛው ዙር የኅብረት የዑምራ ጉዞ፤ ከጥር 22 እስከ የካቲት 3 የሚከወን ሲሆን፤ ፓኬጁን የኸሚስ ምሽቶቹ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሂምና ወንድም ሙሐመድ ፈረጅ ይመሩታል። ፓኬጁ የቤተሰብ ነውና ለእናቶችና እህቶች ደግሞ የበይቱል ሃቢብ ፕሮግራም አዘጋጇን ኡስታዛ ሃስና ሸይኽ ሙስጠፋን ይዘናል።

እንደ ቤተሰብ ተሰባስበን፣
አካልና መንፈሳችንን አሳርፈን፣
የማይረሳ ውብ ጊዜን አብረን እናሳልፋለን!
ያስታውሱ! ጉዞው የሚከወነው ለበርካታ ቤተሰቦች የእረፍት ወቅት ላይ እንደመሆኑ፤ ከወዲሁ ቀድመው ይመዝገቡ!
ለተሟላ መረጃ
096588883 ወይም 0965888884 ላይ ይደውሉ!

ሂራ ቱር ኤንድ ትራቭል
አድራሻ ሣር ቤት ግደይ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ!

Minber TV

27 Dec, 07:14


ታላቁ ዓሊም ለእናቱ…

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/6Ou5f3JUjS8 🔗

#የጁምዓ_ኹጥባ #ጁምዓ_ሙባረክ!
#ኡስታዝ_ያሲን_ኑሩ #እናት #የእናት_ሐቅ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Dec, 16:14


አምባሳደሯ!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/iSIHu6360bA 🔗

#እንዴት_ልዋብ #ልዩ_ዝግጅቶች #አምባሳደሯ
#Endet_Lwab #Special_Programs

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Dec, 15:48


በአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች በሒጃብ ክልከላ ምክንያት ትምህርት ለማቋረጥ መገደዳቸውን ተናገሩ

ዕለተ ሐሙስ ታኅሣሥ 17 - 2017 | ጁማዱል አኸር 25 - 1446

በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች በተጣለው ሒጃብ ክልከላ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ ለመሆን መገደዳቸውን ተናገሩ፡፡ በከተማው በአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የሚገኙ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከታኅሣሥ 8/2017 አንስቶ ሒጃብ አድርገው እንዳይገቡ ክልከላ እንደተጣለባቸው ገልጸዋል፡፡

በአክሱም ከተማ በተማሪዎች ላይ የሒጃብ ክልከላውን ጥለውታል የተባሉት ትምህርት ቤቶች በቀጥር ቢያንስ አምስት መሆናቸውን “ሚንበር ቲቪ” ከተማሪዎች፣ ወላጆች እና ከአክሱም እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኃላፊዎች ሰምቷል፡፡ ትምህርት ቤቶቹ “አክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት”፣ “አሉሚናይ”፣ “ወርኣይ”፣ “ክንደያ” እና “ኣብርሃ ወ ኣጽብሃ” መሆናቸውን ለ“ሚንበር ቲቪ” የተናገረች ሥሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀች ተማሪ አስረድታለች፡፡

ሁለት ሳምንት ገደማ ባስቆጠረው ክልከላ ምክንያት በተለይ “ወርኢይ” በተሰኘው ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ ሴት ተማሪዎች፤ የሴሚስተር አካፋይ (Mid semester) ፈተና ላይ መቀመጥ ሳይችሉ መቅረታቸው ታውቋል፡፡

ተማሪዎቹ ከትምህርት ቤቶቹ ርእሰ መምሕራን ጀምሮ፣ ለአክሱም እስልምና ጉዳዮች እና ትምህርት ቢሮ በጉዳዩ ላይ ቅሬታ ቢያቀርቡም መፍትሔ ማግኘት እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡ የከተማው ትምህርት ቢሮ በበኩሉ፤ “ትምህርት ቤቶቹ ባስቀመጡት ሕገ ደንብ ስለሚመሩ ጣልቃ አንገባም፤ ሒጃባችን አውልቃችሁ ተማሩ” የሚል ምላሽ ሰጥቷል ተብሏል፡፡

የተማሪዎቹ ቅሬታ እንዲደመጥ አቤቱታ አቅርበንባቸዋል ካሉባቸው አካላት መካከል የአክሱም እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሊቀመንበር ኡስታዝ ዓብደላ ሙስጠፋ፤ በትግራይ “ከጦርነቱ በኋላ” ሴት ተማሪዎች ሒጃባቸውን አድርገው እንዲማሩ ይፈቀድ እንደነበር በማስታወስ፤ ሒጃባቸውን አውልቀው እንዲገቡ የሚል መመሪያ የመጣው ከርእሰ መምሕራን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ከተማሪዎች ቅሬታ በመቅረቡ ለከተማው ትምህርት ቢሮ፣ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት እና የፀጥታ ቢሮ ደብዳቤ በመጻፍ ከኃላፊዎች ጋር ለማነጋገር ሞክረው ቀድሞ በውይይት ወቅት አዎንታዊ ምላሽ የተሰጠ ቢሆንም፣ ዘግየት ብሎ የሐሳብ ለውጥ በመደረጉ መፍትሔ አለማግኘቱን ተናግረዋል፡፡

ሊቀመንበሩ ውሳኔው የተላለፈው “በሃይማኖታዊ ብያኔ” ሳይሆን ከወላጅ እና ተማሪዎች ኮሚቴ ጋር በተደረገ ስብሰባ “በድምጽ ብልጫ” መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በዚሁ ጉዳይ “ሚንበር ቲቪ” የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፍተኛ ምክር ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ የሆኑትን ሐጂ ሙሐመድ ካሕሳይን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

በአክሱም ከተማ በአሁኑ ሰዓት ተማሪዎች ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤቶች ካመሩ የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር እንደሚያውላቸው ተሰምቷል፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 17 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው በዋስትና ተለቀዋል ተብሏል፡፡ በከተማው በተለይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅጽ እንዲሞሉ የተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ በዚህ ሳምንት የጀመረ ቢሆንም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ግን በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት እንዳይችሉ የሒጃብ ክልከላ ስለተጣለ ቅጹን መሙላት እንዳልቻሉም ማወቅ ተችሏል፡፡

በአክሱም ከተማ በሙስሊም ሴት ተማሪዎች የቀረበውን ቅሬታ አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጡ “ሚንበር ቲቪ” የከተማውን ትምሕርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ፀጋ ገብረማርያምን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ምላሽ ባለመስጠታቸው ማካተት ሳይቻል ቀርቷል፡፡

በአክሱም ከተማ ከዚህ ቀደም ሙስሊሞች መስጂድ እንዳይገነቡ ክልከላ ስለተከለከሉ በተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ የሚታወቅ ነው፡፡

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Dec, 15:48


በአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች በሒጃብ ክልከላ ምክንያት ትምህርት ለማቋረጥ መገደዳቸውን ተናገሩ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9662

Minber TV

26 Dec, 15:16


🔴 የጥንቃቄ መልዕክት - የቴሌግራም አካውንቶች ምዝበራ 🔴

በዛሬው እለት የቴሌግራም አካውንቶች ምዝበራ እየተካሔደ ስለሚገኝ ተጠቃሚዎች ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት እንደሌለባቸው የኢንፎርሜሽን መረብ አስተዳደር አሳስቧል፡፡

አስተዳደሩ ምዝበራ ይፈጸምበታል ያለው የማስገሪያ (Phishing link) ከፎቶግራፍ ጋር ተያይዟል፡፡

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Dec, 12:52


እነሆ በሶለዋት ደምቃችሁ፣ ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ ጋር ተሰባስባችሁ ስትከታተሉት የቆያችሁት ተወዳጅ ፕሮግራማችን "ኸሚስ ምሽት" 200 ሳምንት ሞላው።
አልሐምዱሊላህ!!!

እንደቤተሰብ አጠጋግቶ ባቆየን "ኸሚስ ምሽት" ፕሮግራም በየሳምንቱ አዳዲስ ምልከታና ሃሳቦችን ለዛ ባለው የተለየ አቀራረብ ስትገበዩ እንደነበረ ከናንተው ይደርሱን የነበሩ መልዕክቶች ያረጋግጣሉ።

በርግጥ እንደ አዘጋጅ የሁልጊዜ ጥረትና ሙከራችን ውድ ከሆነው ጊዜያችሁ ምሽታችሁን ስታውሱን፤ በምትኩ ለናንተ የምናቀብለው
ጉዳይም ተመጣጣኝና ተቀራራቢ ዋጋ ያለው እንዲሆን ማስቻል ነበር።
በእነዚህ ወደ አራት በተጠጉ ዓመታት ይህ ተሳክቶልን ከሆነ ምስክሮቹ እናንተ የፕሮግራሙ ቤተሰቦች ናችሁና፤ እንደ ሁልጊዜውም ሃሳቦቻችሁን ታጋሩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።

ዛሬ በልዩ ዝግጅት የፕሮግራሙን ፈርጦች ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሂምንና ኡስታዝ በድር ሁሴንን እስከ ዝግጅቱ ፍጻሜ በጋራ አስቀምጠን፣ በሙንሺድ ፉዓድ መልካ የናፍቆት መድህና ነሺዳ ፋታ እየወሰድን እንቆያለን።

ምሽት ከ02:00 ጀምሮ በሶለዋት ደምቀንና ተውበን የምንከታተለውን 200ኛውን የኸሚስ ምሽት ልዩ ዝግጅት ይዘንላችሁ እንቀርባለን!!

#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_200ኛው_ኸሚስ_ምሽት!!

ዕለተ ሐሙስ ታኅሣሥ 17 - 2017 | ጁማዱል አኸር 25 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Dec, 12:15


Siimboo

Sagantaa maatii, sagantaa Bashannanaa fi boqonnaa Kan isiniif tahu sagantaa bohaartii sanbataa mata duree 'Siimboo' jedhuu qabannee gara keessanitti dhufaa jirra.

Sagantaan kun guyyaa sanbataa Tiivii Minbar irratti akkasumas toora YouTube Miidiyaa Miilaan irratti siniif dhiyaata.

Yeroo dhihootti nu eegaa !!!

Namoonni fi dhaabbileen Sagantaa kana Ispoonsara gochuu feetan lakk. Bilbilaa 0982828201 irratti nuuf bilbilaa.


t.me/milanmediaofficial
Instagram.com/milanmediaofficial
TikTok.com/milanmediaofficial


#siimboo
#bohaartii_sanbataa
#milanmedia
#minbertv

Minber TV

26 Dec, 11:59


ሚንበር ቲቪ ከሥፍራው፡- የዘምዘም ባንክ ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የዲጂታል ፋይናንሲንግ አገልግሎት ምረቃ

ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጠው ዘምዘም ባንክ፤ ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 17/2017 ሸሪዓን መሠረት ያደረገ የዲጂታል ፋይናንሲንግ አገልግሎት ምረቃ ሥነ ሥርዐት መርሐ ግብር እያካሔደ ይገኛል፡፡ ባንኩ ሥነ ሥርዐቱን እያከናወነ የሚገኘው በአዲስ አበባ ሐይሌ ግራንድ ሆቴል ነው፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የባንኩን እንዲሁም የብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

(ሚንበር ቲቪ በሥፍራው የሚከናወነውን ሥነ ሥርዐት ተከታትሎ የሚያቀርብ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል)

Minber TV

26 Dec, 11:30


እነሆ በሶለዋት ደምቃችሁ፣ ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ ጋር ተሰባስባችሁ ስትከታተሉት የቆያችሁት ተወዳጅ ፕሮግራማችን "ኸሚስ ምሽት" 200 ሳምንት ሞላው።
አልሐምዱሊላህ!!!

እንደቤተሰብ አጠጋግቶ ባቆየን "ኸሚስ ምሽት" ፕሮግራም በየሳምንቱ አዳዲስ ምልከታና ሃሳቦችን ለዛ ባለው የተለየ አቀራረብ ስትገበዩ እንደነበረ ከናንተው ይደርሱን የነበሩ መልዕክቶች ያረጋግጣሉ።

በርግጥ እንደ አዘጋጅ የሁልጊዜ ጥረትና ሙከራችን ውድ ከሆነው ጊዜያችሁ ምሽታችሁን ስታውሱን፤ በምትኩ ለናንተ የምናቀብለው
ጉዳይም ተመጣጣኝና ተቀራራቢ ዋጋ ያለው እንዲሆን ማስቻል ነበር።
በእነዚህ ወደ አራት በተጠጉ ዓመታት ይህ ተሳክቶልን ከሆነ ምስክሮቹ እናንተ የፕሮግራሙ ቤተሰቦች ናችሁና፤ እንደ ሁልጊዜውም ሃሳቦቻችሁን ታጋሩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።

ዛሬ በልዩ ዝግጅት የፕሮግራሙን ፈርጦች ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሂምንና ኡስታዝ በድር ሁሴንን እስከ ዝግጅቱ ፍጻሜ በጋራ አስቀምጠን፣ በሙንሺድ ፉዓድ መልካ የናፍቆት መድህና ነሺዳ ፋታ እየወሰድን እንቆያለን።

ምሽት ከ02:00 ጀምሮ በሶለዋት ደምቀንና ተውበን የምንከታተለውን 200ኛውን የኸሚስ ምሽት ልዩ ዝግጅት ይዘንላችሁ እንቀርባለን!!

#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_200ኛው_ኸሚስ_ምሽት!!

ዕለተ ሐሙስ ታኅሣሥ 17 - 2017 | ጁማዱል አኸር 25 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Dec, 07:14


የአይን ብርሃንሽ እንዲመለስ ዱዓ አድርገሽ ታውቂያለሽ?

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/SOrWQgC0Css 🔗

#የኔ_መንገድ #ጉዞ_ወደ_እስልምና
#journey_to_islam #ልበ_ብርሃን

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Dec, 07:03


ሚንበር ቲቪ ከሥፍራው፡- የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተና ምክር ቤቶች የትብብር ስምምነት

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተና ምክር ቤቶች የትብብር እና የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነ ሥርዐት ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 17/2017 እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የፈርማ ሥነ ሥርዐቱ በከተማው እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጽሕፈት ቤት የሚደረግ ነው፡፡

(ሚንበር ቲቪ በዚህ ጉዳይ ላይ ዝርዝር ዘገባውን ምሽት 1፡30 በ“ሚንበር ኸበር” የሚያቀርብ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል)

Minber TV

25 Dec, 18:00


በምስሉ ላይ የምትመለከቱት መስጂድ ስም ማን ይባላል?

የትላንቱ ጥያቄ መልስ:
ነቢዩ “ጀነትን ፈልጉ” ያሉት በማን እግር ስር ነው?
C/ በእናት

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

06 Dec, 07:14


በናቅኩት መድረክ ላይ... ልመሰክር ተገኝቻለሁ!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/n4_zRQ66jIk 🔗

#የኔ_መንገድ #ጉዞ_ወደ_እስልምና
#Yene_Menged #Journey_to_Islam
#ሂዳያ #guidance #ሙስሊም #Muslim

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Dec, 16:14


አሚን አሚንዬን… የሙሀመድ ኢድሪስ አዲስ መጽሐፍ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/fXB9KR0O8WU 🔗

#ኸሚስ_ምሽት
#አሚን_አሚንዬን
#አዲስ_መጽሐፍ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Dec, 14:33


ልዩ ኸበር - “ሙሐመድ” በዩናይትድ ኪንግደም ተመራጩ የወንዶች ልጆች መጠሪያ ሆነ

በዩናይትድ ኪንግደም ወላጆች ለወንዶች ልጆቻቸው “ሙሐመድ” የሚለውን መጠሪያ በቀዳሚነት እንደሚመርጡ የብሔራዊ ስታትስቲክስ መሥሪያ ቤት የ2023 ይፋዊ መረጃ ይፋ ሲያወጣ አሳውቋል። በመሥሪያ ቤቱ መረጃ መሠረት፣ በሀገሪቱ ከዚህ ቀደም ለበርካታ ልጆች ተመራጭ የነበረው መጠሪያ ኑሕ የነበረ ቢሆንም አዲሱ ሪፖርት “ሙሐመድ” ተመራጭ መሆኑን ያመለክታል።

በዩናይትድ ኪንግደም ማለትም በእንግሊዝና በዌልስ በ2022 የተመዘገበው የሙሐመዶች አሐዝ 4 ሺሕ 177 የነበረ ሲሆን፣ በ2023 ቁጥሩ 4 ሺሕ 661 ደርሷል። በአንጻሩ ኑሕ የሚል መጠሪያ ያገኙ ወንዶች ቁጥር በእነዚህ ሀገራት 4 ሺሕ 586 ነበር። ይህ ቁጥር በ2023 ዝቅ ብሎ 4 ሺሕ 382 ተመዝግቧል።

የእንግሊዙ ቴሌግራፍ ጋዜጣ አደረግኩት ባለው ዳሰሳ፣ ከሙሐመድ እና ኑሕ ውጪ አይመን እና ሐሰን የተሰኙ መጠሪያዎች ከፍተኛ ቁጥር እያስመዘገቡ ይገኛሉ። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Dec, 13:01


ተወዳጁ የቤተሰብ ፕሮግራማችን "ኸሚስ ምሽት"
ዛሬም በተለመደ ቅርፅና ይዘቱ ሰዓቱን ጠብቆ ወደናንተ ይደርሳል።

ሸይኻችን ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሂም በሰዓታቸው፤ በኢማን ጎጆ ካልተጠለልን የሚገጥሙንን መልከ ብዙ ስንክሳሮች እያወሱ አብረውን የሚያመሹ ሲሆን፤ በቢስሚከ ነህያ ጉዞ ወደ አላህ ፕሮግራማችን ደግሞ፤ ዛሬም የወረዕን ሁሉን አቀፍ ትርጓሜና ተግባራዊ ልምምድ ልዩ ልዩ መልኮች እያስቃኘን ኡስታዝ በድር ሁሴን ከኛ ጋር ምሽቱ ያሳልፋል።

እናንተም ምሽት ከ02:00 ጀምሮ በሶለዋትና በዱዓ ደምቃችሁ
በአብሮነት ከኛ ጋር  እንድታሳልፉ በአክብሮት ጋብዘናል።

#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!

ዕለተ ሐሙስ ህዳር 26 - 2017 | ጁማዱል አኸር 4 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Dec, 11:30


ተወዳጁ የቤተሰብ ፕሮግራማችን "ኸሚስ ምሽት"
ዛሬም በተለመደ ቅርፅና ይዘቱ ሰዓቱን ጠብቆ ወደናንተ ይደርሳል።

ሸይኻችን ሸይኽ ሙሐመድ ኢብራሂም በሰዓታቸው፤ በኢማን ጎጆ ካልተጠለልን የሚገጥሙንን መልከ ብዙ ስንክሳሮች እያወሱ አብረውን የሚያመሹ ሲሆን፤ በቢስሚከ ነህያ ጉዞ ወደ አላህ ፕሮግራማችን ደግሞ፤ ዛሬም የወረዕን ሁሉን አቀፍ ትርጓሜና ተግባራዊ ልምምድ ልዩ ልዩ መልኮች እያስቃኘን ኡስታዝ በድር ሁሴን ከኛ ጋር ምሽቱ ያሳልፋል።

እናንተም ምሽት ከ02:00 ጀምሮ በሶለዋትና በዱዓ ደምቃችሁ
በአብሮነት ከኛ ጋር  እንድታሳልፉ በአክብሮት ጋብዘናል።

#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!

ዕለተ ሐሙስ ህዳር 26 - 2017 | ጁማዱል አኸር 4 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Dec, 08:38


ዘምዘም ባንክ ከሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን ጋር በአጋርነት ለመሥራት ስምምነት ተፈራረመ

ዕለተ ረቡዕ ኅዳር 26 - 2017 | ጁማዱል አኸር 4 – 1446

ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ ያንክ አገልግሎት የሚሰጠው ዘምዘም ባንክ፤ ከሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን ጋር በአጋርነት ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የፊርማ ሥነ ሥርዐ መርሐ ግብሩ የተካሔደው ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 26/2017 በአዲስ አበባ ከተማ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ነው፡፡

ከባንኩ ጋር የአጋርነት ስምምነት የፈጸመው ሳንቲም ፔይ የተሰኘው የዲጂታል ፋይናንሻል ሥርዓት፤ ተግባራዊ መሆን ለተጠቃሚዎች እና ለደንበኞች በቀላሉ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱን በተመለከተ የተናገሩት የዘምዘም ባንክ ዲጂታል ኃላፊዎች፤ የባንኩ ስትራቴጂ ዕቅድ የዲጂታል ዓለምን በመቀላቀል ተወዳዳሪ መሆን ነው ብለዋል፡፡ የተፈጠረዉ ጥምረት አብር ለማደግ እና በዲጂታል የዘመናዊ ሥርዓት ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆንም ተናግረዋል።


ከዘምዘም ባንክ ጋር ስምምነት የተፈራረመው ሳንቲም ፔይ በመተግበሪያ ኪው አር ኮድ እና የፖስ ማሽን መጠቀም የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን መተግበሪያን አስመልክቶ ወይዘሮ ቅድስት አያሌው ስለ መተግበሪያው አሠራር ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

ዘምዘም ባንክ በዛሬው እለት በተመሣሣይ “ካሽ ጎ” የተሰኘውን የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ በዛሬው እለት እንደሚያስመርቅ ለ“ሚንበር ቲቪ” የላከው መረጃ ያመለክታል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Dec, 08:38


ዘምዘም ባንክ ከሳንቲም ፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን ጋር በአጋርነት ለመሥራት ስምምነት ተፈራረመ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9552

Minber TV

05 Dec, 08:10


የዓይነ ሥውራን አዳሪ ትምሕርት ቤቱ ሙስሊም ተማሪዎቹ የጀመዓ ሰላት የሚሰግዱበት ቦታ ማዘጋጀቱ መረጋገጡን የምክር ቤቱ ኃላፊ ገለጹ

ዕለተ ረቡዕ ኅዳር 26 - 2017 | ጁማዱል አኸር 4 - 1446

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ ዓይነ ሥውራን አዳሪ ትምሕርት ቤት ለሙስሊም “ተማሪዎቹ የጀመዓ ሰላት የሚሰግዱበት ቦታ ማዘጋጀቱን ማረጋገጣቸውን” ገልጸዋል፡፡

የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይህን የገለጹት ዛሬ ሐሙስ ኅዳር 26/2017 ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ትምሕርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጋር በጋራ ተደርጓል ባሉት ጉብኝት፤ ከሰሞኑ በትምሕርት ተቋሙ ትምሕርታቸውን እየተከታተሉ ስለሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች “አያያዝ እና እየተሰሙ ስለቆዩ ቅሬታዎችም” ከትምሕርት ቤቱ አስተዳደርና ከተማሪዎቹ ጋር “ሰፊ ውይይት” አካሔደናል ብለዋል፡፡

በዚህም “መሰል ችግሮች ዳግም እንዳይፈጠሩና ለተፈጠሩትም ዘላቂ መፍትሔ በመፈለግ ላይ ተግባብተናል” ያሉት ኡስታዝ አቡበከር፤ በተማሪዎች በቅሬታ ሲቀርብ የነበረውን ሙስሊም ተማሪዎቹ የጀመዓ ሰላት የሚሰግዱበት ቦታ ተመቻችቶላቸው ሰላታቸውን በወቅቱ መስገድ መቻላቸውን ለማረጋገጥ መቻላቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ“ክብርት ሸይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዐይነ ሥውራን አዳሪ ትምህርት ቤት”፤ ከዚህ ቀደም ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ሰላት እንዳይሰገዱ የጣለው ክልከላ ማንሳቱን ተማሪዎች ለሚንበር ቲቪ የገለጹት ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ኅዳር 18/2017 ነበር፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳየች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የአዲስ አበባ ትምሕርት ቢሮ ኃላፊ በትምሕርት ቤቱ ጉብኝት ያደረጉት ይህ መደረጉ ከተሰማ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው፡፡


በወቅቱ የትምሕርት ቤቱ የሰላት ክልከላ መነሳት ዜና የመጣው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በተማሪዎች የሰላት ክልከላ ጉዳይ በኃላፊዎቹ በኩል ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ውይይት ማካሔዱ ከተነገረ በኋላ ነው፡፡ የምክር ቤቱ ኃላፊ ተማረዎቹ በተመሳሳይ ክልከላ ተደርጎብናል ስላሉት የኒቃብ ጉዳይ በውይይቱ ላይ ስለመነሳቱ የገለጹት ነገር የለም፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ወር አጋማሽ በተመሣሣይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ቢያንስ አምስት ትምሕርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች “ኒቃብ ለብሳችሁ በትምሕርት ገበታ ላይ መገኘት አትችሉም” እንደተባሉ በመግለጽ ቅሬታቸው አቅርበው ከከተማው እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይህንኑ ተከትሎ ምክር ቤቱ ጥቅምት 21/2017 ከአዲስ አበባ ትምሕርት ቢሮ፣ ከሠላም እና ፀጥታ ዘርፍ እንዲሁም ከፖሊስ ጋር ውይይት ካደረገ በኋላ ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተገናኘ “ምክረ ሐሳብ” ለማቅረብ “ከስምምነት ላይ መደረሱን” አስታውቆ ነበር፡፡ ምክር ቤቱ እስካሁን ድረስ ያቀረበው ምክረ ሐሳብ ስለመኖሩ ያወጣው መረጃ የለም፡፡ (ሚንበር ቲቪ)


★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Dec, 08:09


የዓይነ ሥውራን አዳሪ ትምሕርት ቤቱ ሙስሊም ተማሪዎቹ የጀመዓ ሰላት የሚሰግዱበት ቦታ ማዘጋጀቱ መረጋገጡን የምክር ቤቱ ኃላፊ ገለጹ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9546

Minber TV

05 Dec, 07:45


የነፍስያ ድምጾች በጋዜጠኛ ዩኑስ ሙሐመድ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/P7IQ3HNiu-o 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #የግጥም_ቆይታ
#ግጥም #poem #ነሺዳ #ሕያው_አሻራ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Dec, 17:59


በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ሰው ማን ይባላሉ?

የትላንቱ ጥያቄ መልስ:

አላህ (ሱ.ወ) ሸይጧንን ከምን ፈጠረው?
መልስ፡- B/ ከእሳት

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

04 Dec, 14:30


#የምስራቁ_ኮከብ
#ክፍል_5
#ካስማ_ሾው

ምሽት ከ02:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ!

ዕለተ ረቡዕ ህዳር 25 - 2017 | ጁማዱል አኸር 3 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Dec, 14:08


የአልጀዚራው ዋኢል ደህዱህ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ያዘጋጀውን “የጀግንነት” ሽልማት አሸነፈ

ዕለተ ረቡዕ ኅዳር 25 - 2017 | ጁማዱል አኸር 3  - 1446

ከጋዛ ዘገባዎችን በማቅረብ የሚታወቀው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን የጋዛ ቢሮ ኃላፊ ዋኢል ደህዱህ የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የ2014 “የጀግንነት” ሽልማት ማሸነፍ ችሏል። የጋዜጠኛው አሸናፊነት ይፋ የተደረገው ትናንት ምሽት በአሜሪካ ዋሺንግተን በተካሔደ መርሐ ግብር ላይ ነው።

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ድርጅት፣ በዓለም ዙሪያ “የፕሬስ ነጻነትን ለመከላከል እና ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ” ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሥራዎች እውቅና በሚሰጥበት መድረክ፣ ዋኢል አሸናፊ የሆነው “በጋዛ በደረሰበት ጉዳት እና በቤተሰቦቹ ሞት ሳቢያ ዘገባውን ማሠራጨቱን አቋርጦ ባለማወቁ” መሆኑን ጠቅሷል።

በሽልማት መርሐ ግብሩ ላይ መገኘት ያልቻለው ጋዜጠኛ ዋኢል ዳህዱህ፣ በመድረኩ ላይ በድምጽ የተቀዳ መልዕክት አስተላልፏል። “በጦርነት ወቅት ከጋዛ የምናገኛቸው ዜናዎች እና ምሥሎች ወደ ቀሪው ዓለም መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለናል” ያለው ጋዜጠኛው፣ “ለዚህም ከፍተኛ ድካም፣ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች፣ ላብ እና ደም ጭምር ከፍለናል” ብሏል።

ከፍልስጤም ጋዛ ዘገባዎችን የሚያቀርበው ዋኢል ደህዱህ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በተመሣሣይ ናሽናል ፕረስ ክለብ ያዘጋጀውን ሽልማት ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

ፍልስጤማዊው ጋዜጠኛ እስራኤል በጋዛ ጦርነት ከከፈተች በኋላ ባሉ ጥቂት ሳምንታት በቀጥታ ዘገባ ላይ ሳለ በኑሰይራት የስደተኞች ካምፕ ላይ የተፈጸመው በአየር ጥቃት ባለቤቱን፣ የሰባት ዓመት ሴት ልጁንና የ15 ዓመት ልጁን ጨምሮ ሌሎች የቤተሰቡን አባላት እንደገደለ የተነገረው ነው፡፡

ዳህዱህ በታኅሣሥ ወር የአልጀዚራ ዘጋቢዎች ቡድን በተፈናቃይ ፍልስጤማውያን መጠለያ ትምሕርት ቤት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ለመሸፈን ሲሞክር ሲዘግብ ጉዳት አስተናግዷል፡፡ የ54 ዓመት ዕድሜ ያለው ዋኢል ሐማዳን ኢብራሂም ዱህዱህ፤ ጋዜጠኝነትን የጀመረው አል ቁድስ በተሰኘ ጋዜጣ ገና በ18 ዓመቱ  ነበር፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Dec, 14:07


የአልጀዚራው ዋኢል ደህዱህ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ያዘጋጀውን “የጀግንነት” ሽልማት አሸነፈ

በድረ ገጽ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=9542

Minber TV

04 Dec, 12:55


በፌዴራል ደረጃ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ለሚታዩ “የሕግ ማዕቀፍ፣ አደረጃጀት፣ የሰው ኃይል አስተዳደር ችግሮች” የመፍትሔ ሐሳብ የቀረበበት ሠነድ ተዘጋጅቷል፡፡ ሠነዱ የተዘጋጀው በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት በተቋቋመ የቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት ነው፡፡ በዚህ ሠነድ ላይ ኅዳር 22/2017 በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገውን ውይይት #ክፍል_2 ዛሬ ምሽት ከ04፡00 ጀምሮ ይቀርብላችኃል።

#የጋራ_ውይይት...
#ስለ_ሸሪዓ_ፍርድ_ቤቶች
#ክፍል_2
#ልዩ_ዝግጅት

ዕለተ ረቡዕ ህዳር 25 - 2017 | ጁማዱል አኸር 3  - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Dec, 11:30


ከ30 ዓመታት በላይ በኳታር ኖረዋል። የኳታርን ሁለንተናዊ ሥርዓት ልቅም አድርገው ያውቃሉ። አቶ ወሂብ አብዱልዋሲዕ በአዳማ ተወልደው እዚያው አድገው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በውጭ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ ተመርቀው፣ በመገናኛ ሚኒስቴር ሥር ባለው ባሕር ትራንስፖርት ተቀጥረው፣ በምጽዋ ሥራቸውን እየሠሩ ሳለ... ቀሪውን ታሪክ ምሽት ከ03:00 ጀምሮ "ኢስላም ትናንት፣ ዛሬና ነገ" የዕለቱ ልዩ ፕሮግራም ላይ ይጠብቁን።

#የሕይወት_ገጽ
#ኢስላም_ትናንት_ዛሬና_ነገ
#ልዩ_ዝግጅት

ዕለተ ረቡዕ ህዳር 25 - 2017 | ጁማዱል አኸር 3  - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Dec, 10:30


በበርካታ የዳዕዋ መድረኮች በሚያቀርባቸው ሁለንተናን ሰቅዘው የሚይዙ ትምህርቶቹ በስፋት የምናውቀው ጥዑመ ልሳኑ ዳዒ ዶክተር ሰምሃር ተክሌ፤ ቤተል በሚገኘው አዲሱ የሙጀመዕ አት-ተቅዋ መስጂድ ለታዳሚዎች ዒልምን እየዘሩ ከሚገኙ ተወዳጅ ኡስታዞች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን በእጅጉ የሚያስፈልጉንን የአምልኮ፣ የሸሪዓ ድንጋጌዎችና ፊቅሃዊ ብያኔዎችን ከያዘው "አቢ ሹጃእ" ኪታብ ሰፋ ካሉ ማብራሪያዎች ጋር በማጣመር ግሩም በሆነ መንገድ ደርስ (ትምህርት) እየሰጠ ይገኛል፡፡

ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን ሚንበር ቲቪም፤ አዲስ በጀመረው "ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራሙ ይህንን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶችን የያዘውን የ "አቢ ሹጃእ" ደርስ (ትምህርት) ክፍል አስራ ሰባት ዝግጅቱን ዛሬ ምሽት ከ12፡30 ጀምሮ ለውድ ተመልካቾቹ ያቀርባል!

#ሚንበሩል_ዒልም
#አቢ_ሹጃእ
#ክፍል_17
#ዶክተር_ሰምሃር_ተክሌ

ዕለተ ረቡዕ ህዳር 25 - 2017 | ጁማዱል አኸር 3 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Dec, 07:15


የሶሻል ሚድያ ፀብ…

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/NEtyf2fqcvs 🔗

#ቅኝተ_መጻሕፍት
#የመጽሐፍ_ዳሰሳ
#መጽሐፍ #book

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Dec, 16:15


ኢስቲግፋር… የሪዝቅ ሚስጥር!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/QO7ElrY1tp4 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #የሸይኻችን_ሰዓት
#ኢስቲግፋር #ሪዝቅ #ተውበት #በረካ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Dec, 12:35


የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች “ከባንክ፣ ከኢንሹራንስ እና ከካፒታል ማርኬት ጋር የሚነሱ አለመግባባቶችን” የመዳኘት ሥልጣን እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ የጥናት ሠነድ ላይ ውይይት ተካሔደ

የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች “ከባንክ፣ ከኢንሹራንስ እና ከካፒታል ማርኬት ጋር የሚነሱ አለመግባባቶችን” የመዳኘት ሥልጣን እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ የጥናት ሠነድ ተዘጋጅቶ በዛሬው እለት ውይይት ተካሔዷል፡፡ ሰነዱ ለፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች “በአብዛኛው በሥራ ላይ እየዋሉ ከሚገኙት የሻፊዒይና ሀነፊይ መዝሐቦች የተውጣጡ የሸሪዓ መሠረታዊ ሕግ መድብል (Codified Sharia Laws)” መዘጋጀት እንዳለበት የሚጠቁም ነው፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት በተቋቋመ የቴክኒክ ኮሚቴ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት ጋር እንዲሁም ከሕግ ባለሞያዎች የተውጣጣ ኮሚቴ እንዳዘጋጀው የተገለጸው የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ አደረጃጀት፣ የሰው ኃይል አስተዳደርን ችግሮች በመለየት የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ የተዘጋጀ ሠነድ፣፤ ዛሬ እሑድ ኅዳር 22/2017 የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ውይይት ተካሔዶበታል፡፡

በመድረክ ላይ በሠነዱ ላይ በተጨማሪነት ሊካተቱ ይገባቸዋል በተባሉ ጉዳዮች አስተያቶች ተሰንዝረዋል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የጠቅላይ ፍርደ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት እንዲሁም የእስልምና ሊቃውንት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈው የውይይት መድረክ ለግማሽ ቀን የተከናወነ ነበር፡፡

በመድረኩ ላይ ውይይት የተካሔደበትና “ሚንበር ቲቪ” የተመለከተው ባለ 50 ገጽ የጥናት ሠነድ፤ በአምስት ክፍሎች የተዘጋጀ ነው፡፡ በእነዚህ ክፍሎች የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች “መንግሥታዊ ሃይማኖት በሌላቸው (ሰኩላር) ሀገራት” ያለው ተመክሮ፣ “የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች በኢትዮጵያ”፣ “የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ የአደረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የፍትሕ አስተዳደር ችግሮች ትንተና” እንዲሁም “የመፍትሔ ምክረ ሐሳብ” የተካተተበት ነው፡፡

በተያዘው ወር መጀመሪያ ቀናት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የተረከበው የጥናት ሠነድ፤ በሥራ ላይ ባለው የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ላይ ያልነበሩ ጉዳዮችን ማካተት እንደሚገባ የሚጠቁም ነው፡፡ በ1992 የጸደቀው የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን አቋም ለማጠናከር የጸደቀው አዋጅ፤ ፍርድ ቤቶቹ ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ጋር “የወል ዳኝነት” የሚኖራቸው በውስን ጉዳዮች ላይ እንደሚሆን አስቀምጧል፡፡ ፍርድ ቤቶቹም የወል ሥልጣን እንጂ የራሳቸው ልዩ ሥልጣን እንደማይኖራቸው ጠቅሷል፡፡ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች እንዲመለከቱት በአዋጁ በቀዳሚነት የተቀመጠው “የጋብቻ፣ የፍቺ፣ የቀለብ አወሳሰን፣ አካለ መጠን ያልደረሱ ሕጻናት ሞግዚትነት”ን ነው፡፡ “የወቅፍ፣ የሥጦታ ወይም የኑዛዜ ጉዳዮችን” ደግሞ አዋጁ በሁለተኛነት ዘርዝሯል፡፡

የጥናት ሠነዱ ከጠቀሱት ጉዳዮች በተጨማሪ “የጋብቻ ውጤት፣ የፍቺ ውጤት፣ ውርስ ማጣራትና ሐብት ክፍፍል” እንዲካተቱ ጠቁሟል፡፡ በዚሁ የወል ዳኝነት ውስጥ “ሸሪዓን መሠረት ያደረገ ባንክ፣ ኢንሹራንስ፣ የሙአለ ንዋይ ገበያ (ካፒታል ማርኬት)ና ሌሎች የሸሪዓን ሕግ መሠረት አድርገው የተመሠረቱ ስምምነቶችና ግንኑነቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ አለመግባባቶችን” እንዲዳኝ ምክረ ሐሳብ ቀርቧል፡፡

በሌላ በኩል ይህ ሠነድ የፌዴራል የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኝነት መሥፈርትና ሥልጠናን በተመለከተም፤ “የሸሪዓ ሕግ አተረገጓጎምና ወጥነትና ተገማችነት እንዲኖር” በአብዛኛው ሥራ ላይ እየዋሉ ይገኛሉ ብሎ የጠቀሳቸው “ሁለቱ የሸሪዓ ሕግ አተረጓጎም ማለትም ሻፊዒይና ሀኒፊይ መዝሐቦች የተውጣጡ የሸሪዓ መሠረታዊ ሕግ መድብል (Codified Sharia Laws)” መዘጋጀት እንዳለበት ይጠቁማል፡፡

በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ ቀርቦ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጠበት የጥናት ሠነድ፤ በቀጣይም በሚዘጋጅ ተመሣሣይ መድረክ ግብዐት ለማካተት ተጨማሪ ውይይት እንደሚካሔድበት ተነግሯል፡፡ ለውይይት የቀረበው የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን የሚመለከት የጥናት ሠነድ ላይ የተሳተፉት ዳኛ አቶ ሙሐመድ አሕመድ፣ ዳኛ ሸይኽ አሕመድ አደም፣ ዶክተር ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲን፣ አቶ ሻፊ ዘለቀ እና አቶ ዓብዱልሐኪም ጀማል መሆናቸውን በሠነዱ ላይ ሠፍሮ ይገኛል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Dec, 12:34


የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች “ከባንክ፣ ከኢንሹራንስ እና ከካፒታል ማርኬት ጋር የሚነሱ አለመግባባቶችን” የመዳኘት ሥልጣን እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ የጥናት ሠነድ ላይ ውይይት ተካሔደ


በድረ ገጽ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=9525

Minber TV

01 Dec, 12:30


#ካፒታል_ማርኬት
#በግንዛቤና_በእድል_መካከል
#ኢብራሂም_አብዱልአዚዝ

ዛሬ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#ሂጅራ_ቢዝነስ
ሂጅራ ባንክ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር

ዕለተ እሁድ ህዳር 22 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 29 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Dec, 07:53


በሸሪዓ  ፍርድ ቤቶች የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት የመፍታት አላማ አለው የተባለ ውይይት እየከናወነ ይገኛል

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች  ጠቅላይ ምክር ቤት እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ጋር በጋራ በአዘጋጅት ረቂቅ የጥናት ሰነድ ላይ  ውይይት እያካሄደ የሚገኘው በአዲስ አበባ በስካይ ላይት ሆቴል ነው።

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም፣ የእስልምና ሊቃውንት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምሕረትን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በተያዘው ወር ኅዳር 2/2017 በፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የሚታዩ ችግሮችን ይቀርፋል የተባለ የጥናት ሠነድ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መቅረቡ የሚታወስ ነው። በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን መሠረት በማድረግ የቀረበውን የጥናት ሠነድ፤ ባለፈው ዓመት አጋማሽ በተቋቋመው አጥኚ ቡድን የተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

(በዚህ ዜና ላይ ከቆይታ በኋላ ተጨማሪ መረጃ ይታከልበታል)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Dec, 07:15


ንፅህና ከኢማን ነው!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/negErcpZlHk 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #ቢስሚከ_ነህያ
#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
#ንፅህና #ፅዱ_መሆን #ኢማን

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Dec, 06:15


መወዳ መዝናኛችን በዚህ ሳምንት
. . .
ግብይቱ ሀያ አመታት ገደማ እንዳስቆጠረ ይነገርለታል። እድሜያቸው ጠና ያሉ ወንዶችና ሴቶች የገበያው መሪ ተዋንያን ናቸው። ነገር ግን በዕድሜያቸው አመሻሽ ገበያውን የሚያሳልጡት እማወራና አባወራዎች የሚሸምቱትና የሚገበያዩት አይነት ለግል ፍላጎታቸው የሚያውሏቸው ሳይሆን ለአብራኮቻቸው ክፋዮች ውሃ አጣጭ ይሆኑ ዘንድ የሚያልሟቸውን ነው።
. . .
የዓለማችንን አስደናቂ የትዳር ገበያ "ዳር-ዳር" በተሰኘው ተወዳጅ የ"መወዳ መዝናኛ" ንዑስ መሠናዶ እናስቃኛችኋለን። ሌሎች ስቱዲዮና ከስቱዲዮ ውጭ ተከሽነው የተሠናዱ "የመወዳ መዝናኛ" ዝግጅቶቹን ወደናንተ ውድ ተመልካቾቻችን ለማድረስ የሰዓቱን መድረስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
. . .
ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ!

#መወዳ_መዝናኛ
#Meweda
★ ★ ★
Minber TV | Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

30 Nov, 17:30


በኢስላማዊ ስነ ምግባር የታነፁ፤ በአወንታዊ አመለካከት የጎለበቱ፤ ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው፣ለሃገራቸው ብሎም ለአለም መልካም ሚናቸውን የሚወጡ ብሩህ ልጆችን ለማፍራት ጉዞ ከጀመርን እነሆ 4 ዓመታት ተቆጠሩ።

🎉🎉🎉

ዛሬም የተለምነውን ለማሳካት በአዳዲስ ፕሮግራሞችና አቀራረብ ዘወትር እሁድ መደበኛ ፕሮግራማችንን ወደናንተ ውድ ተመልካቾቻችን ለማድረስ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

ዕለተ እሁድ ጠዋት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ በሚቀርበው አዲስ ውድድር ላይ በመሳተፍ በየሳምንቱ ይሸለሙ!

#ብሩህ_ልጆች

ዕለተ ቅዳሜ ህዳር 21 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 29 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

30 Nov, 16:15


ላትሆን አታስመስል!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/QO7ElrY1tp4 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #የሸይኻችን_ሰዓት
#ማስመሰል_እና_መሆን #አስመሳይ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

30 Nov, 13:30


መንፈሳዊ ትምህርታቸውን የጀመሩት ከቆሎ ተማሪነት ሲሆን በቲዮሎጂ (ሥነ መለኮት) የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ወስደዋል። ደረጃ በደረጃም "ከድቁና" እስከ "ቁምስና" ማዕረግ ደርሰዋል።

በአንድ አጋጣሚ ሚንበር ቲቪ ላይ "የኔ መንገድ" ፕሮግራምን ይመለከታሉ። በሰዓቱ ፕሮግራሙንም ሆነ የሂዳያ ብርሃን አግኝተው የህይወት ምልልሳቸውን ሲተርኩ የነበሩ እንግዶችን "በንቀት" ሲያዩ እንደነበርም አይሸሽጉም። ከጊዜያት በኋላ እነሆ ዛሬ "ከቁብ ባልቆጠሩት" መድረክ ላይ ተገኝተው ስላገኙት የሂዳያ ብርሃን ሊመሰክሩ፣ እርሳቸውም እንደሌሎች መንገደኞች የሄዱ ያለፉበትን ሊያጋሩን ተገኝተዋል።

የትላንቱ መልኣከ ብርሃን ቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል ረቴ የዛሬው ወንድም ሲራጅ ረቴ መንገደኛዬ ናቸው። ዛሬ ቅድመ ሂዳያ እና ድህረ ሂዳያ ስለተጓዙበት ያለ ስስት ይነግሩናል።

#የኔ_መንገድ
#በናቅኩት_መድረክ_ላይ...
#ልመሰክር_ተገኝቻለሁ!

ዕለተ ቅዳሜ ህዳር 21 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 28 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

30 Nov, 12:30


ስኬታችን የሚለካው በላይክና ሼር መሆን የለበትም ይላል ዑመር። የጻፍኩት መልዕክት ላሰብኩበት ዓላማ ደርሷል ወይ? ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ለለውጥ ጽፋችሁ ትኩረታችሁ ለውጥ ላይ እንጂ ተወደደ ተጠላ የሚለው ጭንቀታችሁ አይሁን። ፌስቡክ ላይ ስለሁሉም ነገር መናገር የለባችሁም በማይመለከታችሁ አትግቡ።

ሁሉንም ነገር እኛ መለወጥ አንችልም። ሌሎች እንደናንተ ላይቆረቆሩ ይችላልና ሁሉም ሰው ለምን እንደኔ አልተሰማውም ብላችሁ አትበሳጩ። ሙኒራ አብዱልመናን በMs League መድረክ ላይ Fiqh of Social Media መጽሐፍን አስቃኝታን ነበር። የመጽሐፉ ቅኝት ሁለተኛ ክፍል ዛሬ ምሽት 01:40 ወደናንተ ይቀርባል!

#ቅኝተ_መጻሕፍት
#የሶሻል_ሚዲያ_አባዜ
#ክፍል_2

ዕለተ ቅዳሜ ህዳር 21 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 28  - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

30 Nov, 12:00


የመተዛዘን እና የይቅርታ ወር የሆነው ረመዳን እየተቃረበ ነው። በዚህ መንፈሣዊ ጉዞ ለመታደስ ቀልባችንን ለዚህ የተቀደሰ ወር ማዘጋጀት ይጠበቅብናል። በቀሩት 90 ቀናት የዒባዳዎቻችን ቁጥር እና ጥራት በማሳደግ የአላህን ውዴታ መሻት አለብን። ንያዎቻችንን በማጥራት፣ ኢማናችንን በማጠንከርና ሰደቃ ላይ በመበርታት ራሳችንን እያዘጋጀን እንቆይ።
ይህን የዝግጅት ግዜ ሕይወታችንን ደግመን በማሰስ፣ ከጥፋቶቻችን በመመለስና አላህን በመማፀን እናሳልፍ። እነዚህን ውድ 90 ቀናት በረመዳን የሚገባንን ለማግኘት ቁርኣን ማንበብን፣ ሶላት ላይ መበርታትን እና ዚክር ማብዛትን እንለማመድ፡፡ እንዘጋጅ!

#90days #Ramadan #ረመዳን_90_ቀናት_ቀሩት
#آللّهم_بلغنا_رمضان
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

30 Nov, 11:30


የቁርኣን ተፍሲር በሐረሪ ቋንቋ - በሸይኽ የሕያ እስማዒል (ረሒመሁላህ)
ሱረቱል ሷፍፋት 114-166

ዛሬ ምሽት 12:20 በሚንበር ቲቪ!

#ቁርኣን #ተፍሲር #ሐረሪ
#ሸይኽ_የሕያ_እስማዒል_ረሒመሁላህ 

ዕለተ ቅዳሜ ህዳር 21 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 28 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

30 Nov, 10:31


በንጽጽር ትምህርቶችና መድረኮች ይበልጥ የምናውቀው ኡስታዝ ሳዲቅ ሙሐመድ (አቡ ሃይደር) እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑ ትምህርቶችን የያዘውን ኪታብ በሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ በሳምንት አንድ ቀን እያስተማረ ይገኛል።

የዛሬው የ"ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራማችን ኡስታዝ ሳዲቅ (አድ ዱሩሱል ሙሂማህ) የተሰኘውን ኪታብ ዋቢ አድርጎ የሚሰጠውን ጠቃሚ ትምህርት ምሽት ከ12:40 ጀምሮ #ክፍል_ሃያ የሚያቀርብላችሁ ይሆናል።

#ሚንበሩል_ዒልም
#ጠቃሚ_ትምህርቶች
#ክፍል_20
#ኡስታዝ_ሳዲቅ_ሙሐመድ (አቡ ሃይደር)

ዕለተ ቅዳሜ ህዳር 21 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 28 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

30 Nov, 07:30


አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጅን አክብሮታል!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/vAcw-fRIN3w 🔗

#የጁምዓ_ኹጥባ #ኹጥባ
#ሸይኽ_ሰዒድ_ዓሊ_ሐቢብ
#የሰው_ልጅ #አላህ(ሱ.ወ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV1

Minber TV

30 Nov, 06:52


ሙሐመድ ኢድሪስ ካሣ የቴሌቪዥን ተመልካቾች በሚያቀርበው ተወዳጅ መሰናዶ ያውቁታል። ከዚያ ባሻገር ገጣሚ ነው። ለሙንሺዶች በሰጣቸው ግጥሞች አድናቆት የተቸረው። በዚህ ሳምንት በአዲስ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ መምጣቱን ይፋ በማድረግ ለግጥም ወዳጆች ለምርቃቱ ደግሦ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር 21/2017) ከሰዓት እንዲታደሙ ጋብዟል። ሙሐመድ ከመጽሐፍ ምርቃቱ ሰዓታት አስቀድሞ ከ“ሚንበር ቲቪ” ድረ ገጽ ጋር በጣም አጭር ቆይታ አድርጓል።


ሚንበር ቲቪ፡- አሚን አሚንዬ እንዴት ያለ የግጥም መድበል ነው? ለኅትመት በቅቶ አንባቢ ጋር ሲደርስ ምን ስሜት ፈጠረብህ? የመገላገል ነው? (እፎይ የማለት) ወይስ ሌላ…


ሙሐመድ ኢድሪስ፡- ከ80 በላይ የሚሆኑ ከጉርምስና ዕድሜዬ ጀምሮ የተጻፉ ግጥሞች ናቸው። አንዳንዶቹ ከዚያም [ዕድሜ] አነስ ያሉ ናቸው። በ112 ገጾች ውስጥ ተሰብስበዋል። [መጽሐፉ ሲታተም] ድብልቅልቅ ስሜት ነው የተሰማኝ። በአንድ በኩል ደስ ብሎኛል፣ በሌላ በኩል ተዳፈርኩ እንዴ? ብያለሁ። የሆነ ሰዓት ላይ ደግሞ ምንም ትርጉም ያጣብኛል። የምሬን እኮ ነው! በቃ ይሄ ይሄ ነው ስሜቱ።


ሚንበር ቲቪ፡- ስለአንተ የሚናገሩ አንዳንድ ሰዎች ‘ምናባዊና ቃላት የሚታዘዙለት ገጣሚ ነው’- ይሉሃል፡፡ አንተ እሱን አገላለጽ ትጋራዋለህ? የቃላት ሐብትህ ምንጩ የት ነው?


ሙሐመድ ኢድሪስ፡- የሰዎችን ምሥክርነት ለማረም ወይም ለማስረገጥ ሥልጣኑ ያለኝ አይመስለኝም። ግን ከቃላት ጋር የተለየ ትስስር አለኝ። ቃላትን በስሜት ደረጃ፣ በሰማኋቸው ሁኔታ፣ ቦታ እና መንፈሥ ውስጥ ነው የምተዋወቃቸው። ስለዚህ እያንዳንዱ ነገር ውስጥ የምሰማቸው ቃላት በተለየ ቅንጅት ነው ትዝታዬ ውስጥ የሚነግሡት። መድረሳ የሰማኋቸው፣ ከነሺዳ የሰማኋቸው፣ ከመጽሐፍ ያነበብኳቸው፣ እናቴ ከነገረችኝ ተረት፣ አባቴ ካንጎራጎረልኝ የሆነ ስንኝ… ብቻ እንዲህ ነው በማልለው ሌሎችም አጋጣሚዎች ውስጥ ቃላትን እተዋወቃቸውና ግጥም ሆነው ያገለግሉኛል። አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ቃላትን ከተፈጥሯቸውና ትርጓሜያቸው በተለየ መልኩ ሁሉ እረዳቸዋለሁ።


ሚንበር ቲቪ፡- በግጥም መድበል ከመምጣትህ አስቀድሞ በነሺዳ ግጥሞች ትታወቃለህ…ሙስሊም ገጣሚ [በዚህ መልኩ መፈረጅ አከራካሪ ሊሆን ቢችልም]ስለ ግጥም ሲያስብ የሚያስጨንቀው ምንድን ነው? መንፈሣዊ ይዘት ላላቸው ግጥሞች ከይዘት ባሻገር ቅርጽ ቦታ አለው?



ሙሐመድ ኢድሪስ፡- እንደ አንድ ሙስሊም ሃይማኖታዊ ያልሆነውም ሕይወት የሚመራበት ሸሪዓዊ መስመር ይኖራል። እሱ ለአንድ ሙስሊም የተለየ ኪናዊ ልማድ እንዲያዳብር ያስገድደዋል። መጠበቅ ያለባቸው መለኮታዊ ድንበሮች ይኖራሉ። በማንኛውም ሞያ ውስጥ ላለ ሙስሊም ግለሰብ ይሄ ተጠባቂ ጉዳይ ይመስለኛል። ቃላትና ሐሳቦች ደግሞ ጥልቅ መሠረት ካላቸው ሸሪዓዊ ጽንሰ ሐሳቦች ጋር ሊጋጩ የሚችሉበት ዕድል አይጠፋም። እሱን ማረቅ ሊያስፈልግ ይችላል። ያም እየሆነ ግን እንደ አንድ ሰው ደግሞ የሚሰሙ ተለዋዋጭና መልከ ብዙ ስሜቶች ከሚሠራው ኪናዊ (ጥበባዊ) ሥራ ጋር አብረው የሚፈሱ ናቸው።

ቅርጽን በምን ያህል ተመሳሳይ መንገድ እንደተረዳነው ርግጠኛ ባልሆንም፣ በእኔ ዕይታ የቅርጹ ውበትና ሥምረት ይዘቱንም በጥልቀት ለመግለጽ አቅም ይሰጣል፤ በተቃራኒውም ሊሆን ይችላል። ግጥም ወይም ሌላ የጥበብ ሥራ በውበትም በቅርጽም በይዘት ተሰናስሎ መስመር ይኖርበታል።



ሚንበር ቲቪ፡- በአዲሱ መድበል ልትሰጠን የሞከርነው ምንድን ነው?


ሙሐመድ ኢድሪስ፡-. . . ልጅነቴን።



ሚንበር ቲቪ፡- የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ፋይዳ ጥያቄ የሚነሳበት ባይሆንም በዚህ ዘመን አንድ ሰው ግጥም ሲጽፍና ሲያሳትም ከደስታው/ርካታው በስተቀር ምን ሊያተርፍ ይችላል? ደስታ/ርካታ ከእንጀራ ጋር የሚስማሙት በየት በኩል ነው? እሱን አንተ በምን ልትደፍነው ሞከርክ?


ሙሐመድ ኢድሪስ፡- የሃገሩም ሁኔታ ተጨምሮበት በሥነ ጽሑፍም ሆነ ሥነ ግጥም ሕይወትን መግፋት የሚታሰብ ነገር አይደለም። አስቦ የተነሳም ይኖራል ብዬ አልገምትም። እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ከሥነ ግጥም ጋር የፈጠርኩት ውሕደትና ፍቅር እዚህ ድረስ አመጣኝ እንጂ፣ እንጀራዬ ይሆናል ብዬ ያሰብኩበት ጊዜ ብዙ አይመስለኝም። በተወሰነ ደረጃ ደግሞ እንጀራዬን አልሰጠኝም ብዬ አልደመድምም። በሚዲያ ሥራ ውስጥ ራሴን ያገኘሁት በሥነ ግጥም ላይ የነበረኝ መጠመድ ይመስለኛል። በቀጥታም ሊሆን ይችላል፣ አልያም በእጅ አዙር .
. .


ሚንበር ቲቪ፡- የግጥም መድበልህ ዛሬ ይመረቃል። ምን ተዘጋጅቷል?


ሙሐመድ ኢድሪስ፡- የግጥም መጽሐፌ ዛሬ ኅዳር 21/2017 4 ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ዋሊያ መጽሐፍት ነው የሚመረቀው። በተለይ የዘመን እኩዮቼ ናቸው መድረኩ ላይ የሚኖሩት። ከዚያም ባሻገር ደግሞ ልጅነታችንን እያስታወስን የምንጨዋወትበት ነው የሚሆነው - አላህ ቢል።

ሚንበር ተቪ፡- እናመሠግናለን፡፡

Minber TV

30 Nov, 06:52


ከገጣሚ ሙሐመድ ኢድሪስ ካሣ ጋር…

ሙሉ ቆይታውን በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9511

Minber TV

29 Nov, 18:34


ልዩ ኸበር - የፍልስጤማዊያን የችሎት ተሟጋቹ ሥንብት

ዕለተ ቅዳሜ ኅዳር 21  - 2017 | ጁማዱል ኡላ 28  - 1446

“በፍልስጤም ጉዳይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ መዝገብ ለማስከፈት ሁሉም መስፈርቶች መሟላታቸው ግልጽ ሆኗል፡፡ ይህ የእኔ አስተያየት አይደለም፤ እውነታው እንደዚያ ነው፡፡ መንግሥታትም ቢሆን ከየትኛው ጎራ እንደተሰለፉ መለየት አለባቸው፡፡ ሁለት ጎራ ነው ያለው፤ ለሰብዓዊ መብቶች አጋርነታቸውን ማሳየት አልያም ከዘር ፍጅት ጋር መቆም፡፡

የእስራኤል ወታደሮች በፍልስጤም የሚፈጽሙትን ጥቃት ለማስቆም አንዳችም ነገር ሳያደርጉ ስለ ዓለም አቀፍ ሕግ እና ስለ ሰብዓዊ መብቶች መከበር የመናገር ድፍረት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ዓለም አቀፍ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ምንም ነገር ካላደረገም መጨረሻው ይሆናል፡፡ እኛ በኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ለማውጣት የሚያስችል በቂ ማስረጃ ሰብስበናል፡፡”

ይህ የተናገሩት ፈረንሳዊው የሕግ ባለሞያ ጋይልስ ዲቬርስ ናቸው፡፡ ዴቨርስ በርካታ ዓመታትን ያሳለፉት ለፍልስጤማዊያን በፍርድ ቤት ሲሟገቱ ነው፡፡ የእስራኤል ወታደሮች በሚሰነዝሩት ርሕራሄ በጎደለው የቦንብ ጥቃት፤ ጉዳት የደረሰባቸውን በሺሕዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ፍልስጤማዊያንን ዶሴ ሰብስበው ችሎት ፊት ሲሟገቱ ኖረዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን ንግግር በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ቀርበው ያደረጉት ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ነበር፡፡ የሕግ ባለሞያው ይህን የተናገሩት ለዓለም አቀፍ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት እርሳቸው በመሪነት ቆመው ከሌሎች ሦስት ጠበቆች ጋር የእስራኤልን ወንጀል ለማጋለጥ ለሙግት በተዘጋጁበት ወቅት ነበር፡፡ ጋይልስ ዲቬርስ ለፍርድ ቤቱ ዶሴ ያሰባሰቡት የእስራኤል ባለሥልጣናት የፈጸሙትና እየፈጸሙ የሚገኙት የዘር ፍጅት መሆኑን ተከራክረው ለመርታት ነበር፡፡

በወቅቱ የ67 ዓመት እድሜ የነበራቸው ፈረንሳዊው የሕግ ባለሞያ፤ በችሎት ፊት ሙግታቸው ቢያሸንፉ የመጨረሻ ግብ አድርገው ያስቀመጡት፤ ያለፉትን ዓመታት በፍልስጤማዊያን ላይ ሕጻን - አዋቂ ሳይመርጥ እጅግ አስከፊ ወንጀሎችን ሲፈጽም የቆየውን የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትር በችሎት ፊት ማቆም ነው፡፡ ብርቱው የሕግ ባለሞያ ዲቬርስ ለዚህ መንገዳቸው ከጎናቸው በርካቶችን ማሰለፍ ስለነበረባቸው ይህንኑ አደረጉ፡፡ 800 አባላት ያሉትን ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሞያዎች ኔትወርክ መመሥረት ቻሉ፡፡

ጋይልስ ዲቬርስ ከባልደረቦቻቸው ጋር ቀን ከሌት የለፉበት ጉዳይ ያለፉትን ወራት ስለፍትሕ በሚቆሙ ሰብዓዊ ፍጡራን ሲጠበቅ የነበረ ነው፡፡ እንደመታደል ሆኖ እነ ጋይልስ ዲቬርስ ልፋታቸው አንዲሁ መና አልቀረም፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት ኅዳር 12/2017 ከሰዓት ላይ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዜናውን ይፋ አደረገ፡፡ ዜናው በቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ መቆረጡን የሚገልጽ ነበር፡፡ መቀመጫውን ኔዘርላንድስ ሔግ ያደረገው ዓለም አቀፍ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት፤ ማዘዣውን ሲያወጣ ከቤንያሚን ኔታንያሁ በተጨማሪ በመከላከያ ሚኒስትሩ ዮቭ ጋላንት ላይ የእስር ማዘዣ ቆርጧል። ኔታኒያሁና የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትሩ ላይ የወጣው ማዘዣ ጋይልስ ዲቬርስ ሲጠይቁት እንደነበረው በጋዛ ፈጽመውታል በተባለው “የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ በሚፈፀም ወንጀል” ምክንያት የተቆረጠ ነው።

ጉዳዩን የያዙት ዳኞች፤ ሁለቱ ግለሰቦች ቢያንስ ከባለፈው ዓመት መስከረም መጨረሻ ቀናት ወዲህ ባሉት አስራ አራት ወራት ገደማ፤ “በጋዛ ለሚገኙ ንጹሐን ሕልውና አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ማለትም ምግብን፣ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ እና መድኃኒቶችን እንዲሁም የሕክምና አቅርቦቶችን ነዳጅ እና ኤሌክትሪክ ጭምር እንዳያገኙ ሆን ብለው መከልከላቸውን ለማመን የሚያስችሉ በቂ ምክንያቶች እንዳሉ ተገንዝበናል” በማለት የእስር ማዘዣውን ያስፈለገበትን ምክንያት አስረድተዋል፡፡

ይህ ቀን የፈረንሳዊው የሕግ ባለሞያ ጋይልስ ዲቬርስ ሕልም በእውን የተገለጠበት ነበር፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ ግን ዲቬርስ ዜናውን ሲሰሙ ዕድሜ ሕመም ደርቦባቸው አልጋ ላይ ነበሩ፡፡ በርግጥ ባልደረቦቻቸው እንዳሉት ከሆነ ያለፉትን ጊዜያት ሕይወታቸውን ሊያሳጣቸው ከሚችል ሕመም ጋር እየተጋፈጡ ነበር የፍርድ ቤቱን ጉዳይ የሚከታተሉት፡፡ ከሕግ ባለሞያ ከመሆናቸው አስቀድሞ  ሕክምና ያጠኑት ሰው፤ ጤናቸው ተቃውሶ ፋታ አልሰጥ ቢላቸውም በፍልስጤማዊያን ጉዳይ የሚተኙ አልሆኑም ነበር፡፡

በቅርብ ጓደኛቸውና በሌላኛው ፈረንሳዊ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያ ዓብዱልመጂድ ሜራሪ ‹‹ለሰብዓዊነት እና ለመርህ የታመኑ›› ተብለው የሚገለጹት ጋይልስ ዲቬርስ፤ ከዚህ ቀደም ለሕይወታቸው አስጊ የሚባል የቀዶ ጥገና ለማድረግ ሆስፒታል አልጋ ላይ ሆነው እንኳን በመጨረሻው ሰዓት ያነሱ የነበረው የፍልስጤማዊያንን ጉዳይ ነው፡፡ በሌላ አጋጣሚ በፍልስጤማዊያን ንጹሐን ጉዳይ እንባ አውጥተው ሲያለቅሱ መመልከቱንም ዓብደልመጂድ ያስታውሳል፡፡

እኒህ የተከበሩ የሕግ ባለሞያ ባለፈው ሳምንት የኔታንያሁ የእስር ማዘዣ ዜና ይፋ ሲደረግ፤ አልጋ ላይ ሆነው ከሕመማቸው ጋር እየታገሉ የነበረ ቢሆንም፤ ሰውዬው ላይ እስር ማዘዣ መውጣቱን ሰምተው ተደስተዋል፡፡ ለዓመታት የለፉለት ጉዳይ ቢያንስ ግማሽ መንገድ ተጉዟል፡፡ ከፈረንሳይዋ ሊዮን ከተማ የወጡት ጋይልስ ዲቬርስ፤ ሲጠብቁት የቆዩት ጉዳይ መሳካቱን ሲያውቁ ግን “በምድር ቆይታ ከዚህ በላይ ማሳካት የሚሹት አልነበረም ወይ?” በሚያስብል ሁኔታ ብዙ አልቆዩም፡፡ በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ከምድር ሕይወት ሕይወት የመሸኘታቸው አሳዛኝ ዜና በቤተሰቦቻቸው በኩል ይፋ ተደረገ፡፡ ለ ሞንድ የተሰኘው የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን እንዳስነበበው ከሆነ፤ ከመሔዳቸው በፊት ልጃቸውን ጠርተው ‹‹በል ይበቃል፤ አሁን በሰላም ልሒድ›› ብለውታል፡፡

ከሽኝታቸው በኋላ ለሚድል ኢስት ሞኒተር የተናገረው የቅርብ ጓደኛቸው ዓብዱልመጂድ ሜራሪ፤ የኔታንያሁ የእስር ማዘዣ ለጋይልስ ዲቬርስ “የ15 ዓመታት ልፋት የተበረከተ ሥጦታ ነው” ብሏል፡፡ የእነ ኔታንያሁ ጉዳይ በእስር ማዘዣ መውጣት በቃ የሚባል አለመሆኑንም በዚሁ ያስታወሰው ሜራሪ፤ እውነተኛውና አስቸጋሪው ሥራ ከዚህ በኋላ ያለው መሆኑን በመጠቆም ለዚህ ደግሞ ስለፍልስጤማዊያን ሲለፉ የቆዩትን የጋይልስ ዲቬርስን ብርታት መዋስ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት በመስጠት ተናግሯል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)


★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Nov, 18:01


በሕዝቦቹ ተቆጥተው በመሄድ በሌሊት የዓሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ የገቡት ነቢይ ማን ናቸው?
A/ ነቢዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ)
B/ ነቢዩላህ ዩኑስ (ዐ.ሰ)
C/ ነቢዩላህ አዩብ (ዐ.ሰ)
D/ ነቢዩላህ ሱለይማን (ዐ.ሰ)

የትላንቱ ጥያቄ መልስ:

ከመላእክት ሁሉ እጅግ ግዙፍና የስድስት መቶ ክንፍ ባለቤት የሆኑት ማን ናቸው?
መልስ: - D/ ጂብሪል (ዐ.ሰ)

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

18 Nov, 17:09


🔻 መንፈስን የሚያድስ ቲላዋ
🔻 በማስተር ሀምዛ ሰይድ
🔻 ሱረቱል ዋቂዓህ 77 - 96
🔻 تلاوة هادئة ❤️
🔻 سورة الواقعة ٧٧ - ٩٦
🔻 ماستر أستاذ حمزة سعيد

🔗 https://youtu.be/HqPSsO0CdQo 🔗

Follow us | ይከታተሉን | تابعونا
using our username @MinberAlQurraa on
Facebook | YouTube | Telegram |X |Instagram | TikTok | Spotify

Minber TV

18 Nov, 16:14


የሙንሺድ ኢምራን ጧሂር አዲስ ሥራ!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/4nSuU74F3m0 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #አዲስ_ነሺዳ #nashida #nasheed #ኢምራን_ጧሂር

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Nov, 13:30


ለሃያ ዓመታት ያህል ያልተቋረጠ የዕውቀት፣ የተራድኦና የማኅበራዊ ልማት አገልግሎትን በመላ አገራችን እየሰጠ ዛሬ ላይ የደረሰው አንጋፋው ኢማን ኢስላማዊ ማህበር፤ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የወቅፍ ፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሩን ምክንያት በማድረግ በትላንትናው ዕለት የመሠረት ድንጋይ ማኖርና የመስክ ጉብኝት አከናውኗል።
"የትውልድ ቅርስ" በሚል መሪ ቃል ተዘጋጅቶ የነበረውን ቆይታ ዛሬ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ እናቀርብላችኃል።

#የትውልድ_ቅርስ
#ልዩ_ዝግጅት

ዕለተ ሰኞ ህዳር 9 - 2016 | ጁማዱል ኡላ 16 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Nov, 11:31


ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው የዒባዳ ተግባራት የተለያዩ ሃሳቦችን ሲያጋራን የቆየው "በይቱል ሐቢብ" ፕሮግራማችን፤ ባሳለፍነው ሳምንት "ሶብር ምንድ ነው?" በሚል ርዕስ ሲያስቃኘን ቆይቷል።

በዛሬው ዝግጅታችን ደግሞ "የሶብር ዓይነቶች" በሚል ርዕስ እህቶች እየተመለከቱ ይቆያሉ። ምሸት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#በይቱል_ሐቢብ
#የሶብር_ዓይነቶች?

ዕለተ ሰኞ ህዳር 9 - 2016 | ጁማዱል ኡላ 16 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Nov, 09:45


የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ከቢላል መስጂድ እና መካነ መቃብር ለኮሪደር ልማት የጠየቀውን “ተጨማሪ መሬት” የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተቃወመ

ዕለተ ቅዳሜ ኅዳር 9 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 16 – 1446

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፤ በጌድዮ ዞን በምትገኘው የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ከቢላል መስጂድ እና መካነ መቃብር ለኮሪደር ልማት የጠየቀውን “ተጨማሪ መሬት” በመቃወም ደብዳቤ መጻፉ ታወቀ፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ለርእሰ መስተዳደሩ ጽሕፈት፣ ለክልሉ ሰላም እና ፀጥታ አካል እንዲሁም ለክልሉ የሃይማኖት ፎረም በጻፈው ደብዳቤ ላይ ለኮሪደር ልማት ይፈለጋል ተብሎ ከተቀመጠው ውጪ ተጨማሪ 10 ሜትር በከተማዋ አስተዳደር መጠየቁን አግባብነት የለውም ብሏል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፋሪስ ጀማል ለ“ሚንበር ቲቪ” እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ ዛሬ ሰኞ ኅዳር 9/2017 በኃላፊዎች በኩል ተቃውሞውን ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በደብዳቤ ያቀርባል፡፡

የምክር ቤቱ ተቃውሞ የመጣው የከተማዋ ለ50 ዓመታት በዘላቂ ማረፊያነት ሲያገለግል የቆየው የቢላል መስጂድና መካነ መቃብር፤ ለመንገድ ማስፋፊያ ተፈልጓል ከተባለው አምስት ሜትር ገደማ ተጨማሪ የመካነ መቃብሩን “አስር ሜትር” ተፈልጓል መባሉ በይርጋ ጨፌ አስተዳደር ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ተጨማሪ ያለውን መሬት የጠየቀው “ለመዝናኛ ሥፍራ” መሆኑም ተነግሯል፡፡

የከተማዋ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለከተማ አስተዳደሩ በጻፈው ምላሽ፤ ለኮሪደር ልማት “ከመንገድ ጀምሮ የተቀመጠውን የርቀት ደረጃ ስታንዳርድ ጠብቆ እንዲከናወን ቦታውን በማጽዳት ለልማት እንደሚያስረክብ” በመግለጽ፤ “ከዚህ ውጭ የሆነውን የከተማው አስተዳደር ውሳኔ ሕዝቡ እንደሚቃወምና በሸሪዓ ሕግ መሠረት በመቃብር ሥፍራው ምንም ዐይነት መዝናኛም ሆነ ሃይማኖቱ የማይፈቅዳቸው ነገሮች” እንደማይሠሩ በጥብቅ ገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ ተቃውሞን ቢገልጽም ኅዳር 4/2017 የይርጋ ጨፌ ከንቲባ አቶ ታደለ ጥላሁን “በግብረ ኃይል ለማስፈረስ” ሥፍራው ላይ መገኘታቸውን የጌዴኦ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት፤ ለከተማው አስተዳደር ጽሕፈት ቤት እና ለጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በጻፈው ደብዳቤ ላይ አስታውቋል፡፡ በእለቱ ሕዝበ ሙስሊሙ በሥፍራው ተገኝቶ የተቃውሞ ድምጹን ማሰማቱን የገለጸው ምክረ ቤቱ፤ “ግጭት ውስጥ ሊያስገባ” ነበር ባለው ድርጊት 14 ሰዎች ታስረው ከአንደኛው በስተቀር ምሽት ላይ መለቀቃቸውን አመልክቷል፡፡

በምክር ቤቱ ደብዳቤ ላይ መመልከት እንደተቻለው፤ ከቢላል መስጂድ እና መካነ መቃብር ቀድሞ ይፈርሳል ከተባለው የፊት አጥር በተጨማሪ ከጎን አስር ሜትር ፈርሷል፡፡ ይህን የማፍረስ ተግባር በመቃወም በሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት በኩል ከከተማው ከንቲባ ጋር ውይይት ቢደረግም “ምንም የሚቀየር ነገር የለም” በሚል እየተገለጸ እንደሚገኝ ምክር ቤቱ በደብዳቤው ላይ አስፍሯል፡፡

የይርጋጨፌ ከተማ ከንቲባ መቀመጫቸውን ከኢትዮጵያ ውጪ ላደረጉ መገናኛ ለመገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፤ “ለአምስት ጊዜ ያህል ስብሰባ አድርገው መቃብሩን ለማንሳት ስምምነት ተደርሶ በ10 ቀናት ውስጥ አጽም ወደ ዘላቂ ማረፊያ እንዲዘዋወር ተስማምተናል” ሲሉ ገልጸዋል። ነገር ግን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፋሪስ ጀማል፤ በደረሱን ሪፖርቶች የተደረሰ ስምምነት አለመኖሩን ማወቅ ችለናል ሲሉ የከንቲባው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ለ“ሚንበር ቲቪ” አስረድተዋል፡፡

የከተማው አስተዳደር የጠየቀውን ሥፍራ “አንስታችሁ አስረክቡኝ” በማለት ያስቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ፤ እሑድ ኅዳር 8/2017 ድረስ መሆኑ ታውቋል፡፡ ሆኖም ፕሬዝዳንቱ መቃብር ተቆፍሮ፣ አጽም ወጥቶ፣ ሸሪዓው በሚፈቅደው መልኩ አጽድቶ ለማስረከብ ስምምነት ስለሚያስፈልግ የሚቀድመው ይህ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በይርጋ ጨፌ የሚገኘው ቢላል መካነ መቃብር፤ በስሩ መስጂድ የያዘ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

18 Nov, 09:42


የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ከቢላል መስጂድ እና መካነ መቃብር ለኮሪደር ልማት የጠየቀውን “ተጨማሪ መሬት” የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተቃወመ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9445

Minber TV

17 Nov, 16:14


የነቢዩኡመት ላደረገን ጌታ ምስጋና ይገባው!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/vgTciUme9cI 🔗

#ኸሚስ_ምሽት
#የሸይኻችን_ሰዓት
#Khemis_Meshit
#አልሀምዱሊላህ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Nov, 10:18


ኢማን እስላማዊ ማኅበር የዋና መሥሪያ ቤት እና የኮሌጅ የወቅፍ ሕንጻ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር አከናወነ

ዕለተ እሑድ ኅዳር 7 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 14 - 1446

ከ20 ዓመታት በላይ በትምሕርት እና በማኅበራዊ አገልግሎት ላይ ሲሠራ የቆየው ኢማን እስላማዊ ማኅበር የሚገነባውን የዋና መሥሪያ ቤት እና የኮሌጅ የወቅፍ ሕንጻ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ያከናወነው በዛሬው እለት ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እንዲሁም የክልል ምክር ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ማኅበሩ የዋና ጽሕፈት ቤቱን ግንባታ ያስጀመረው አምፎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ዛሬ እሑድ ኅዳር 8/2017 ይፋ የተደረገው የግንባታ ሒደት በ500 ካሬ ሜትር ላይ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ከእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ኃላፊዎች ውጪ የማኅበሩ ደጋፊዎች እና ቤተሰቦች ተሳታፊ ሆነዋል። በተቋሙ ታሪክ ትልቅ እርምጃ ነው የተባለው የሕንጻ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ሙስሊሙ ማህበረሰብ፣ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል፡፡ የሕንጻ ግንባታው የመሠረት ሥራው ተጠናቆ በአሁኑ ሰአት 10 በመቶ ያክል እንደተጓዘ ተገልጿል፡፡

በ1995 የተመሠረተው ኢማን ኢስላማዊ ማህበር የሙስሊሙን ማህበረሰብ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊች ግሮችን በመቅረፍና ኢስላማዊ አስተምህሮን በማስፋፋት ሃላፊነት የሚሰማውና በኢስላማዊ እሴቶች የታነጸ እንዲሁም በሀገሪቱ ልማት ላይ ንቁ ተሳትፎ ያለውን ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት በሚል የተቋቋመ መሆኑን ይገልጻል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ

Minber TV

17 Nov, 07:14


ቲላዋ በቃሪእ ዓብዱራሕማን ሙሐመድ
ሱረቱ አል-ዒምራን (190-191)

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/w7mGL5b1vG8 🔗

#ከቁርአን_ጋር #ማዓል_ቁርአን
#ቁርአን #ቲላዋ #Quran #recitation

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

16 Nov, 17:30


በኢስላማዊ ስነ ምግባር የታነፁ፤ በአወንታዊ አመለካከት የጎለበቱ፤ ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው፣ለሃገራቸው ብሎም ለአለም መልካም ሚናቸውን የሚወጡ ብሩህ ልጆችን ለማፍራት ጉዞ ከጀመርን እነሆ 4 ዓመታት ተቆጠሩ።

🎉🎉🎉

ዛሬም የተለምነውን ለማሳካት በአዳዲስ ፕሮግራሞችና አቀራረብ ዘወትር እሁድ መደበኛ ፕሮግራማችንን ወደናንተ ውድ ተመልካቾቻችን ለማድረስ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

ዕለተ እሁድ ጠዋት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ በሚቀርበው አዲስ ውድድር ላይ በመሳተፍ በየሳምንቱ ይሸለሙ!

ዕለተ ቅዳሜ ህዳር 7 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 14 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

16 Nov, 16:14


አስፈሪው የጃፓን ድልድይ!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/BONlKLm_wQo 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #ዳር_እስከ_ዳር
#Meweda_Meznagna #Dar_Eske_Dar
#ጃፓን #ድልድይ #Japan #bridge

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

16 Nov, 15:46


ሚንበር ቲቪ፤ ለሐሚልተን ቲቪ የሦስት መቶ ሺሕ ብር የገንዘብ ድጋፍ ለመለገሥ ቃል ገባ

ዕለተ ቅዳሜ ኅዳር 7 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 14 - 1446

ሚንበር ቲቪ፤ በዛሬው እለት በሸገር  ሲቲ በፉሪ ክፍለ ከተማ ያስገነባውን ስቱዲዮ እና ዋና ቢሮ ላስመረቀው ሐሚልተን ቲቪ የሦስት መቶ ሺሕ ብር የገንዘብ ድጋፍ ለመለገሥ ቃል የገባው በዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አዩብ አደም በኩል ነው።

ዛሬ ቅዳሜ ኅዳር 7/2017 በተከናወነው የሐሚልተን ቲቪ የምርቃት መርሐ ግብር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የተሳተፉበት ነበር። በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ትኩረታቸውን በእስላማዊ ጉዳዮች ላይ ያደረጉ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሐሚልተን ቲቪ የቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ጣቢያው አዲስ ባስገነባው ስቲዲዮ በ4 ቋንቋዎች “በጥራት እና በፈጠራ የላቁ ፕሮግራሞችን እንደሚያቀርብ” ገልፀዋል። የተጠቀሱት ቋንቋዎች አፋን ኦሮሞ፣ አማርኛ፣ ሲዳምኛ እና ሶማሊኛ ናቸው።

በዛሬው መርሐ ግብር ላይ ለቴሌቪዥን ጣቢያው ከተለያዩ አካላት እና ግለሰቦች የገንዘብ ድጋፍ ቃል ተገብቷል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

16 Nov, 13:22


"ፈጣሪን ማን ፈጠረው?" በሚል ጥያቄ የናወዘች ነፍስ! ገና በለጋ ዕድሜዋ የሱስን ዓለም የተቀላቀለች፤ ዳንሰኛና ተዋናይት ነበረች። ዛሬ ግን መንገዷን አግኝታ የሰከነች ነፍስ ባለቤት ሆናለች። የትላንቷ ሄርሜላ ተስፋዬ የዛሬዋ መንገኛዬ ሂዳያ ተስፋዬ!! ዛሬ ምሽት ከ03:00 ጀምሮ የምንመላለሰው በእርሷ የህይወት መንገድ ላይ ነው!!

#ገነትን_ሳጣት_የገሃነም_አለቃ_ጋር_ሄድኩ!
#የኔ_መንገድ

ዕለተ ቅዳሜ ህዳር 7 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 14 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

12 Nov, 11:30


በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ የሚሰናዳው እና ተማሪዎችን በቀለም ትምህርት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል እና ማበረታታት ሁለንተናዊ የሆነ የተሟላ እውቀት ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል አላማው የሆነ "ቅን ትውልድ" ፍተሻ የጥያቄ እና መልስ ውድድር ለተወዳዳሪዎች የ200,000 ብር ሽልማት ይዞ ጉዞ ቀጥሏል። ምሽት 02:00 በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#ቅን_ትውልድ
#ፍተሻ

ዕለተ ማክሰኞ ህዳር 3- 2017 | ጁማዱል ኡላ 10 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

12 Nov, 10:40


ልዩ ኸበር - ቢን ሰልማን፣ ኤርዶጋን እና አል ሲሲ በሪያድ ጉባዔ

ዕለተ ማክሰኞ ኅዳር 3 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 10 – 1446

የሙስሊም ሀገራት መሪዎች ሰኞ ኅዳር 2/2017 በሳዑዲ ዐረቢያ መዲና ሪያድ ያከናወኑትን ጋዛን እና ሊባኖስን የተመለከተ ጉባዔ አጠናቀዋል፡፡ የዐረብ ሊግ እና የእስላማዊ ትብብር ሀገራት ድርጅት አባላትን በጋራ ያሰባሰበው ጉባዔ ሲጠናቀቅ የወጣው መግለጫ፤ እስራኤል በወረራ የያዘቸውን የፍልስጤም መሬት በመልቀቅ እንድትወጣ ጥሪ የቀረበበት ነው፡፡

በስብሰባው መዝጊያ የተነበበው ይህ መግለጫ የፍልስጤም መሬት ድንበሩ እ.አ.አ ከ1967 በፊት በነበረው እንዲጸና ተጠይቋል፡፡ በጉባዔው የተሳተፉት የ57 ሀገራት መሪዎች የፍልስጤም ሉዓላዊ ሀገርነት እውን እንዲሆን በመጠየቅ ለትግበራውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመውን መጠነ ሠፊ ጥቃት ያወገዘው የሙስሊም ሀገራት መሪዎች ጉባዔ፤ “አስከፊ እና አስደንጋጭ” ሲል የጠራውን ጥቃት “ከዘር ፍጅት” ጋር የሚተካከል ነው ብሎታል፡፡

የጉባዔው አስተናጋጅ ሳዑዲ ዐረቢያ በልዑል አልጋ ወራሽ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ተወክላ ድምጽዋ ተሰምቷል፡፡ በዚህ ንግግር ቢን ሰልማን የእስራኤልን ጥቃት ለመጀመሪያ ጊዜ “የዘር ፍጅት ነው” ሲሉ ጠርተውታል፡፡ በተጨማሪም ስለ መስጂደል አቅሷ ያነሱት አልጋ ወራሹ፤ “[እስራኤል] በመስጂደል አቅሷ ላይ ርኩሰት ፈጽማለች” በማለት የወራሪ ወታደሮችን ድርጊት ኮንነዋል፡፡ ከጋዛ ውጪ የእስራኤል ወታደሮች በሊባኖስ የሚፈጽሙት ጥቃትም በቢን ሰልማን ንግግር ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማኅረሰብ ድርጊቱን እንዲያስቆም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በጉባዔው ላይ ሌላኛው ተናገሪ የነበሩት የግብጹ ፕሬዝዳንት ዐብዱልፈታህ አልሲሲ ናቸው፡፡ አል ሲሲ በንግግራቸው የጋዛን ጉዳይ ቢያነሱትም እንደ ቢን ሰልማን የእስራኤልን ጥቃት “የዘር ፍጅት ነው” ከማለት ተቆጥበዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን ከማድረግ ቢቆጠቡም “ታቅዶበት የሚፈጸም ነው” ያሉትን ድርጊት ከማውግዝ ግን ወደ ኋላ አላሉም፡፡ አክለውም “የፍልስጤምን ጉዳይ ለመቀልበስ የሚሞክሩትን፣ በግዳጅ የሚያፈናቅሉትንም ሆነ ጋዛን ለኑሮ ለማትመች የሚደረገውን ጥረት ሁሉ የምንቃወመው መሆኑን ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በዐረብ ሊግ እና የእስላማዊ ትብብር ሀገራት ድርጅት ጥምረት በተሰናዳው ጉባዔ ላይ የተናገሩት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋንም እንዲሁ በጋዛ የሚሰነዘረውን ጥቃት በማውግዝ፣ የእስራኤልን “ፍልስጤማዊያንን የማጥፋት እቅድ” ኮንነው ለእቅዱ የሚንቀሳቀሱትን አስጠንቅቀዋል፡፡ ኤርዶጋን በንግግራቸው ያነሱት ሌላኛው ጉዳይ ለእስራኤል “ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ወታደራዊ እና ሞራላዊ ድጋፍ” ይሰጣሉ ያሏቸውን ምዕራባዊያን ሀገራትን ነው፡፡ በሌላ በኩል በፍልስጤማዊያን ላይ ለሚፈጸመው የዘር ፍጅት የሙስሊሙ ዓለም በአንድነት መቆም አለመቻሉንም ሊስተካከል የሚገባው ጉዳይ መሆኑን በመናገር በትብብር እንዲቆሙ በመድረኩ ላይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሪያዱ የሙስሊም እና ዐረብ ሀገራት ጉባዔ የተከናወነው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ዶናልድ ትራምፕ መሆናቸው ይፋ ከተደረገ አንድ ሳምንት እንኳ ሳይሞላ መሆኑ በተለያዩ ተንታኞች ዘንድ የተለያየ አስተያየት እንዲሰጥበት አድርጓል፡፡

ለአል ዐረቢያ የተናገሩት የኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ተንታኙ አና ጃኮብስ፤ ጉባዔው የቀጣናው ሀገራት ከትራምፕ አስተዳደር የሚፈልጉት ምን እንደሆነ “ፍንጭ የሰጡበት ጥሩ አጋጣሚ ነው” ብለዋል፡፡ የተንታኙን አስተያየት የሚጋራ የሚመስል አስተያየት በኢራን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሪዛ አሪፍ በጉባኤው ላይ ተስተጋብቷል፡፡ አሪፍ በመድረኩ ዓለም ትራምፕ በጋዛ እና በሊባኖስ በንጹሐን ሰዎች ላይ የተከፈተውን ጦርነት “በአስቸኳይ ያስቆማሉ በሚል እየጠበቀ ይገኛል” ብለዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9424
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

12 Nov, 10:39


ልዩ ኸበር - ቢን ሰልማን፣ ኤርዶጋን እና አል ሲሲ በሪያድ ጉባዔ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9424

Minber TV

12 Nov, 10:31


ከዒልም ጋር ያላቸው ጥልቅ ትውውቅ የጀመረው በልጅነታቸው ነበር፡፡ ሸይኽ ሰዒድ ዓሊ ሐቢብ ይሰኛሉ፡፡ ወጣትነታቸውን የሰዉለት የዒልም አድማስ ዛሬ ላይ በዘርፈ ብዙ ሸሪዓዊ ጉዳዮች ላይ ርቀው እንዲሄዱና ከታላላቅ ዑለሞች ተርታ እንዲሰለፉ አስችሏቸዋል፡፡ ሸይኽ ሰዒድ በመስከ ብዙ ፉኑኖች ያላቸውን የዒልም አቅም ለሰፊው ማኅበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በተፈጠረላቸው መልካም ዕድል ተጠቅመው፤ ከመግሪብ ሶላት በኋላ እስከ ዒሻእ ሶላት ድረስ በሙጀመዕ አት - ተቅዋ የሚሰጡትን "የአርበዒን ሃዲስ" ትምህርት (ደርስ) ዘወትር ማክሰኞ ምሽት ከ12፡30 ጀምሮ ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን አዲስ በጀመረው የሚንበሩል ዒልም ፕሮግራሙ #በክፍል_19 የሚያቀርብላችሁ ይሆናል፡፡


#ሚንበሩል_ዒልም
#አርበዒን_ሐዲስ
#ክፍል_19
#ሸይኽ_ሰዒድ_ዓሊ_ሐቢብ

ዕለተ ማክሰኞ ህዳር 3 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 10 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

12 Nov, 07:15


የአይጥ ጥብስ ለመክሰስ!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/BONlKLm_wQo 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #ዳር_እስከ_ዳር
#Meweda_Meznagna #Dar_Eske_Dar
#አይጥን_ለምግብነት #አይጥ #rats

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Nov, 18:00


ረሱል ሰ.ወ አላህ ሱ.ወ የዲን እውቀት ስጠው ትርጓሜውንም አስተምረው ብለው የለመኑለት ሰሐባ?
A/ ዓብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ)
B/ ዓብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ)
C/ አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ)
D/ ዓብደላህ ኢብን አባስ (ረ.ዐ)

የትላንት ጥያቄ መልስ:

የእጁጅ እና መእጁጅ ላይ ግድብ የሰራው መሪ ማን ይባላል?
መልስ ፦ B/ ዙልቀርነይን

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

11 Nov, 15:11


የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሸይኽ ጋሊ ሙኽታርን ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡን አስታወቀ

ዕለተ ሰኞ ኅዳር 2 - 2016 | ጁማዱል ኡላ 9 – 1446

የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሔድ የቆየውን ስድስተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሲያጠናቅቅ፤ ሸይኽ ጋሊ ሙኽታርን ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡን አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ አዲስ ፕሬዝዳንት የመረጠው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጀማል ሙሳ “በገዛ ፍቃዳቸው የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ” በማቅረባቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ ጥቅምት 30/2017 እና ኅዳር 1/2017 ባካሔደው ጉባኤ ፕሬዝዳንቱን በሸይኽ ጋሊ ሙኽታር በአዲስ መተካቱን ሲገልጽ፣ ሸይኽ ጣሂር ዓብዱልቃድርን በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም ሸይኽ ዚያድ ዓሊን ምክትል ፕሬዝደንት አድርጎ መምረጡንም የምክር ቤቱ የሚዲያ እና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኡስታዝ ሹዓይብ ሸምሱ ለ“ሚንበር ቲቪ” ተናግረዋል፡፡

በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ቅዳሜ እና እሑድ የተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ የ2016 በጀት አፈጻጸም ሪፖርት የተደመጠበት እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ የጸደቀበት እንደነበርም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባ ፍሬንድሺፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል የተከናወነው የሰባተኛ ዓመት ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ከነበረበት ጊዜ “ዘግየት ብሎ መደረጉን” ያነሱት ኡስታዝ ሹዐይብ፤ ለዚህ ምክንያት ሆኗል ያሉት “የግምገማ ውጤቶች እስኪስተካከሉ ድረስ” ጊዜ በመውሰዱ ነው፡፡

ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች እና ከተሞች ከእያንዳንዱ ሦስት ሰው ተሳታፊ ሆኖበታል በተባለው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአጠቃላይ ከ43 ዞኖች እና ከተሞች 127 ተወካዮች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡ በምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሥራ አፈጻጸም እና ቀጣይ እቅዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው የጸደቀ ሲሆን፣ የአዳዲስ አመራሮች ምርጫ የተከናወበት ሆኖ ማለፉንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡

የአመራሮችን ምርጫ የተደረገው ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ጀማል ሙሳና ምክትሎቻቸው “በፍቃደኝነት” እንዲሁም “በሕመም ምክንያት” የሥራ መልቀቂያ በማቅረባቸው ነው ተብሏል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በጉባኤው ፊት ቀርበው “ከእኔ የተሻለ ሰው መምጣት አለበት” ማለታቸውን የሚዲያ እና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዶክተር ማሕሙድ ሑሴን ከለቀቁ ወደ አምስት ወር ገደማ በመሆኑ በምክር ቤት ይኸው በይፋ መቅረቡ አክለዋል፡፡ ሸይኽ ሙሳ ዐብዱረሕማንም እንዲሁ በሕመም ምክንያት ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ በማቅረባቸው ሦስቱንም ኃላፊዎች መተካት ግዴታ ሆኗል ተብሏል፡፡

መልቀቂያው የቀረበለት ጉባኤው በሥራ አስፈጻሚው በኩል ሦስት ዕጩዎችን በማቅረብ አባላት ድምጽ እንዲሰጡበት ማድረጉ ሲገለጽ፣ በዚህም ከፍተኛ ድምጽ አግኝተዋል የተባሉት ሸይኽ ጋሊ ሙኽታር ሸይኽ ጀማል ሙሳን እንዲተኩ ተመርጠዋል ተብሏል፡፡ ሸይኽ ጋሊ ከአባላት አግኝተውታል የተባለው ድምጽ ሃምሣ ነው፡፡

አዳዲስ አመራሮችን መምረጡን ያሳወቀው የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ በቀጣይ በጀት ዓመት ቅድሚያ የሚሠጣቸውን ጉዳዮች በተመለከተ የ100 ቀናት እቅድ እያዘጋጀ መሆኑን አሳውቋል፡፡

የምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ የተከናወነው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮ ጠቅላይ ምክር ቤት፤ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ካካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በኋላ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳዮ ከፍተኛ ምክር ቤቶች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ካስተላለፈ በኋላ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Nov, 15:11


የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሸይኽ ጋሊ ሙኽታርን ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡን አስታወቀ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9414

Minber TV

11 Nov, 13:07


የሙስሊሙ ዓለም መሪዎች በጋዛ እና ሊባኖስ ጉዳይ በሪያድ ከተማ መምከር ጀመሩ

ዕለተ ሰኞ ኅዳር 2 - 2016 | ጁማዱል ኡላ 9 – 1446

የእስላማዊ ትብብር ሀገራት ድርጅት እና የዐረብ ሊግን ያጣመረው ልዩ የምክክር ጉባዔ ትኩረቱን በጋዛ እና በሊባኖስ ላይ በማድረግ መካሔድ ጀምሯል፡፡ እሑድ ኅዳር 1/2017 በሳዑዲ ዐረቢያ ሪያድ መካሔድ በጀመረው ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ከተማዋ መግባታቸው ታውቋል፡፡

በመክፈቻው መርሐ ግብር ላይ የጉባዔው አስተናጋጅ ሳዑዲ ዐረቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ንግግር አድርገዋል፡፡ በዚህ ንግግር ወቅት አልጋ ወራሹ እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ በጋዛ የምትፈጽመውን ጥቃት አውግዘዋል፡፡ በሳዑዲ እየተካሄደ የሚገኘው ጉባዔ አምና በተመሳሳይ ወቅት የተከናወነ ሲሆን፣ የአሁኑ የዚያን ጊዜው ተከታይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሳዑዲ የዜና አገልግሎት ስለ ጉባዔው ይዞት በወጣው ዘገባ ጉባዔተኞቹን ያሰባሰበው “እየተባባሰ የመጣው” በፍልስጤም እና በሊባኖስ እየተፈጸመ የሚገኘው ጥቃት ነው፡፡ የዜና ኤጀንሲው ከጉባዔው የተለያዩ ውጤቶች እንደሚጠበቅም ዘርዝሯል፡፡

ከተዘረዘሩት መካከል ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ያላቸው “የንጹሐንን ጥቃት ማስቆም፣ ለፍልስጤማዊያንና ለሊባኖስ ሕዝቦች ድጋፍ ማድረግ፣ በጉዳዩ ላይ ወጥ አቋም መያዝ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቀጣናው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ርምጃዎችን እንዲወስድ ጫና ማሳደር” ተካተዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን በዛሬው እለት ሪያድ መግባታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያመለክታል፡፡ ኤርዶጋን ሪያድ ሲደርሱ የመዲናዋ አሚር ፈይሰል ቢን ባንዳር ቢን ሡልጣን አቀባበል አድርገውላቸዋል ተብሏል፡፡ በጉባዔው ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት ፕሬዝዳንቱ፣ እስራኤል በጋዛ የምትፈጽውን ጥቃት ለማስቆም “በሙስሊም ሀገራት መካከል ትብብር እንዲደረግ” ጥሪ ያስተላልፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ዘገባዎቹ አመልክተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በተከናወነው ተመሳሳይ ጉባኤ ቱርኪዬን ጨምሮ ሳዑዲ ዐረቢያ እና ግብጽን ያካተተ “የጋዛ ኮንታክት ግሩፕ” የተሰኘ ጥምረት ተመሥርቶ ነበር፡፡ ኳታር፣ ፍልስጤም፣ ኢንዶኔዥያ እና ናይጄሪያ የተካተቱበት ይህ ስብስብ በጋዛ ጉዳይ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ሲመከር መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ፍልስጤም እና እስራኤል ሁለት ሀገር እንዲሆኑ ሲቀሰቅስ ቆይቷል፡፡


እስራኤል ባለፉት አስራ አራት ወራት በጋዛ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 43 ሺ 500 ንጹሐን ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል፡፡ በተጨማሪም ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Nov, 13:04


የሙስሊሙ ዓለም መሪዎች በጋዛ እና ሊባኖስ ጉዳይ በሪያድ ከተማ መምከር ጀመሩ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9411

Minber TV

11 Nov, 12:37


ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው የዒባዳ ተግባራት የተለያዩ ሃሳቦችን ሲያጋራን የቆየው "በይቱል ሐቢብ" ፕሮግራማችን፤ ባሳለፍነው ሳምንት "ኢሣር... ከራሥ የተሻገረ ውዴታ" በሚል ርዕስ ሲያስቃኘን ቆይቷል።

በዛሬው ዝግጅታችን ደግሞ "ሶብር ምንድ ነው?" በሚል ርዕስ እህቶች እየተመለከቱ ይቆያሉ። ምሸት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#በይቱል_ሐቢብ
#ሶብር_ምንድ_ነው?

ዕለተ ሰኞ ህዳር 2 - 2016 | ጁማዱል ኡላ 9 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

11 Nov, 08:48


ከኅዳር 26 እስከ ታህሳስ 7 ከታዋቂው ሸይኽ አብራር ሽፋ እና ተወዳጇ የበይቱል ሐቢብ ፕሮግራም አቅራቢ ኡስታዛ ኸይሪያ በድሩ ጋር ለመጓዝ የመጀመሪያውን ዙር ምዝገባ ጀምረናል።

ለህይወት አዲስ ጣዕም ሰጥቶና፣ መንፈስና አካልን በወጉ አሳርፎ፤ እጅግ በተሳካ ሁኔታ የተከወነው የመጀመሪያው ዙር የሂራ ትራቭል የኅብረት ዑምራ ፓኬጃችን፤ ጨርሶ የሚዘነጋ አለመሆኑን አብረውን የተጓዙ መንገደኞችቻን ምሥክሮች ናቸው!!!

አብረውን ይጓዙ

ለተሟላ መረጃ በ 0965888883 ወይም በ 0965888884 ይደውሉልን!

ሂራ ቱር ኤንድ ትራቭል!
አድራሻችን ሣር ቤት ግደይ ህንፃ አንደኛ ፎቅ እንገኛለን!!

Minber TV

10 Nov, 16:14


እሷ እንደ ፀሃይ ሁር አል-ዓይን እንደ ኮከብ!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/Y742Y6ka4as 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #የሸይኻችን_ሰዓት
#ዱንያ_እና_አኺራ #ሁር_አል_ዓይን

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

10 Nov, 12:31


የሲራራ አዋርድ ዳኛ ከሆነው ኢዘዲን ካሚል ጋር
የተደረገ ልዩ ቆይታ ዛሬ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#ሂጅራ_ቢዝነስ
ሂጅራ ባንክ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር

ዕለተ እሁድ ህዳር 1 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 8 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

10 Nov, 11:30


ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ለግሉ፣ ለሐገሪቱ ደግሞ 47ኛ ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጧል። የከርሞ ደጋፊዎቹን በአዲስ የድጋፍ መስመር የቀየረው ባለጠጋው ትራምፕ በተወጠረው የዓለም ፖለቲካ ላይ ውጥረትን ወይስ መርገብን ይዞ ይቀጥላል የሚለውን እንቆቅልሽ የከረመ ያየዋል። ምሽት ከ03:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#ትራምፕ
#እነሆ_ኸበር

ዕለተ እሁድ ህዳር 1 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 8 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

10 Nov, 11:15


ሳድግ ሰሓባ መሆን እፈጋለው!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/0hws2Y4WAJs 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #መዲና_ሰማይ_ስር
#ሰሓባ #ሰሓባዎች #ልጆች_ማስተማር

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

09 Nov, 17:30


በኢስላማዊ ስነ ምግባር የታነፁ፤ በአወንታዊ አመለካከት የጎለበቱ፤ ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው፣ለሃገራቸው ብሎም ለአለም መልካም ሚናቸውን የሚወጡ ብሩህ ልጆችን ለማፍራት ጉዞ ከጀመርን እነሆ 4 ዓመታት ተቆጠሩ።

🎉🎉🎉

ዛሬም የተለምነውን ለማሳካት በአዳዲስ ፕሮግራሞችና አቀራረብ ዘወትር እሁድ መደበኛ ፕሮግራማችንን ወደናንተ ውድ ተመልካቾቻችን ለማድረስ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

ዕለተ እሁድ ጠዋት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ በሚቀርበው
አዲስ ውድድር ላይ በመሳተፍ በየሳምንቱ ይሸለሙ!

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 30 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 7 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

09 Nov, 16:15


ዱንያን ንቆ ለአኺራው የሰራ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/Y742Y6ka4as 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #የሸይኻችን_ሰዓት
#ዱንያ #አኺራ #አቡ_ደርዳእ #Abu_al_Darda

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

09 Nov, 12:31


የቁርኣን ተፍሲር በሐረሪ ቋንቋ - በሸይኽ የሕያ እስማዒል (ረሒመሁላህ)
ሱረቱል ሷፍፋት 1-28

ዛሬ ምሽት 12:30 በሚንበር ቲቪ!

#ቁርኣን #ተፍሲር #ሐረሪ
#ሸይኽ_የሕያ_እስማዒል_ረሒመሁላህ 

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 30 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 7 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

09 Nov, 11:30


ትውልድና እድገቷ እዚሁ አዲስ አበባ ነው። የጓደኛዋ ድንገቴ አሟሟት አስደንግጧት ነፍሷን ለማዳን የሰለመችው የዛሬዋ መንገደኛችን ''ሰላት መፅናኛዬ ነው!" ትለናለች። ባሳለፍነው ሳምንት የቀጠለ... #ክፍል_2 ምሽት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#ሰላት_መፅናኛዬ_ነው!
#የኔ_መንገድ

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 30 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 7 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

09 Nov, 10:42


ኤርዶጋን ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እስራኤል በጋዛ የምትሰነዝረውን ጥቃት ለማስቆም የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ጠየቁ

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 30 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 7 - 1446

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል በጋዛ የምትሰነዝረውን ጥቃት ለማስቆም የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ጠየቁ። ኤርዶጋን ትራምፕ አሜሪካ ለእስራኤል የምትሰጠውን የጦር መሣሪያ ድጋፍ ያስቆማሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ይህን የጠየቁት ወደ ሀንጋሪ የሚያደርጉትን ጉዞ አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው። ከጋዛ በተጨማሪም እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትሰዝረውን ጥቃትም ተመራጩ ፕሬዝዳንት እንዲያስቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ከጋዜጠኞች ጋር በነበረው ቆይታ ትራምፕ የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሲከተሉ የቆዩትን ፖሊሲ ትራምፕ ማስቀጠል እንደሌለባቸው ተናግረዋል። የፕሬዝዳንት ባይደን ፖሊሲ የቀጣናውን ችግሮች አባብሶታል የሚል እምነት እንዳላቸውም አስረድተዋል።

በአሜሪካ ምርጫ ሪፐብሊካን ፓርቲን የወከሉት ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ፉክክሩን  ማሸነፋቸው ይፋ የተደረገው በሳምንቱ አጋማሽ ነበር። ውጤቱን ተከትሎ ኤርዶጋን ለትራምፕ በመደወል የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ለጋዜጠኞች ነግረዋቸዋል።

የትራምፕ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ እንደ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ሁሉ በአሜሪካን ሀገር የሚገኘው የመብቶች ተሟጋቹ ዘ ካውንስል ኦፍ አሜሪካን ኢስላሚክ ሪሌሽንስ፤ ተመራጩ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሙስሊሞችን በተመለከተ የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ጠይቋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ኒሐድ አዋድ ባወጡት መግለጫ፤ በምርጫው የትኛውም ግለሰብ ቢያሸንፍ ችግር እንደማይሆን በመጠቆም፣ “መሠራት ያለበት ጉዳይ መኖሩን” አጽንኦት ሰጥተው ጽፈዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ “በምርጫው ወደ ሥልጣን የወጡ ባለሥልጣናት ሙስሊም መራጮች ያነሷቸውን ጉዳዮች በቅንነት እንዲያጤኑት እንጠይቃለን፣ ይህ ለተመራጩ ፕሬዝዳንት ትራምፕም ይሠራል” ብለዋል።

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቃለ መሐላ ፈጽመው የፕሬዝዳንትነት መንበሩን ከጆ ባይደን ይረከባሉ ተብሎ የሚጠበቀው ጥር 12/2017 ነው፡፡

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

09 Nov, 10:40


ኤርዶጋን ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እስራኤል በጋዛ የምትሰነዝረውን ጥቃት ለማስቆም የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ጠየቁ

በድረ ገጽ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=9406

Minber TV

09 Nov, 10:30


በንጽጽር ትምህርቶችና መድረኮች ይበልጥ የምናውቀው ኡስታዝ ሳዲቅ ሙሐመድ (አቡ ሃይደር) እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑ ትምህርቶችን የያዘውን ኪታብ በሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ በሳምንት አንድ ቀን እያስተማረ ይገኛል።

የዛሬው የ"ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራማችን ኡስታዝ ሳዲቅ (አድ ዱሩሱል ሙሂማህ) የተሰኘውን ኪታብ ዋቢ አድርጎ የሚሰጠውን ጠቃሚ ትምህርት ምሽት ከ02:00 ጀምሮ #ክፍል_አስራ_ስምንት የሚያቀርብላችሁ ይሆናል።

#ሚንበሩል_ዒልም
#ጠቃሚ_ትምህርቶች
#ክፍል_18
#ኡስታዝ_ሳዲቅ_ሙሐመድ (አቡ ሃይደር)

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 30 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 7 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

08 Nov, 18:01


በበድር ዘመቻ ወቅት የተማረኩት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አጎት ማን ናቸው?
A ሐምዛ (ረ.ዐ)
B/ ዓባስ (ረ.ዐ)
C/ ዙበይር (ረ.ዐ)
D/ ዓሊይ (ረ.ዐ)

የትላንት ጥያቄ መልስ:

የኦቶማን ቱርኮች የመጨረሻ ኸሊፋ ማን ነው?
መልስ: - A/ ሱልጣን E. ዓብዱልመጂድ 2ተኛ

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

08 Nov, 17:31


እንደስያሚያችን ውብ ሁነን እንደተወለደችዋ ጨረቃ አብሪና አንጻባራቂነታችን ለሁሉም ይደርሰው ዘንድ ዳግም በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለናል።

እንደወትሮው  አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ፕሮግራሞቻችንን በተለመደው ሰዓታችን ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 03፡00 በተወዳጁ የቴሌቪዥን ጣቢያ (ሚንበር ቲቪ) ይከታተሉ።

#ሂላል_ለልጆች

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 29 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 6 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

08 Nov, 16:31


ልዩ ኸበር - የጥንቱን ፍለጋ፡ ከአንደሉስ እስከ መካ

ከሠላሳ አራት ዓመታት በፊት ነው - እ.አ.አ በ1990፡፡ ስፔናዊው ራፋኤል ፈርናንዴዝ ከእስልምና ጋር ተዋወቀ፡፡ መምሕሩና የጂኦግራፊ አጥኚው ሰው አላህ ልቡን ወደ እውነት ስለመራው ደስታው ወደር አልነበረውም፡፡ ደስታው በትኩሱ ሳለ ለጌታው የገባው ቃል እንዲህ የሚል ነበር - “ሐጅ የማደርገው በፈረስ ተጉዤ ነው”፡፡ ይህ ለወቅቱ ጉልበታም ወጣት በአንድ ጊዜ የሚቻል አልነበረም፡፡ ጉልበት ብቻ አይደለም፣ ጊዜ እና ገንዘብ የሚጠይቅ ቃል ኪዳን ነበር፡፡ ጉልበት፣ ጊዜ እና ገንዘብ ቢሟላም ጽናት የሚጠይቅም ነበር፡፡ ስለዚህ መታገስ ነበረበት፡፡

ከ35 ዓመታት በኋላ የዚያን ጊዜው ወጣት ራፋኤል ፈርናንዴዝ፤ በእስልምና ሥሙ ዓብደላህ ተብሎ የሚጠራ ሆኗል፡፡ አብዱላህ በዩኒቨርሲቲ ባጠናው ጂኦግራፊ፣ በዲግሪ ላይ ሌላ ዲግሪ እየደረበ የዶክትሬት ማዕረግ ላይ ደርሷል፡፡ በትምሕርት ረዥም ርቀት በመጓዝ ብቻ ሳይወሰን ወጣት ሳለ ቃል ኪዳን ገብቶ ያልፈጸመውን ሐጅን በፈረስ ጀርባ ተንጠላጥሎ ወደ ቅዱሳኑ ሥፍራዎች የመድረስ ውጥን ለማሟላት ዝግጁ ሆኗል፡፡

ዓብደላህ በዚህ መልኩ ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ሲነሳ አርዓያ ያደረገው ከ500 ዓመታት በፊት በአንደሉስ ምድር የነበሩ በጀግንነት የሚያወድሳቸውን አያት ቅድመ አያቶቹን ነው፡፡ በርግጥ የፈረስ ግልቢያ መውደዱ፣ ከዚያም ሲያልፍ በአንዳንድ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ማሸነፉ ይህን መንገድ እንዲመርጥ አስችሎታል፡፡ በጉዞው አያት ቅድመ አያቶቹንም አብሮ ያስታውሳል፡፡ ዓብዱላህ የቅድመ አያቶች አንደሉስ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ሥፍራዋ ከፍ ያለ መሆኑንም ያውቃል፡፡ እነርሱ ያን ጊዜ የጌታን ትእዛዝ ለመሙላት ፀሐይ እና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው ሀገራትን አቋርጠው ከ8 ሺሕ ኪሎ ሜትር በኋላ ሳዑዲ ዐረቢያ እንደሚደርሱም ከድርሳናት አንብቧል፡፡

ዓብዱላህ ፌርናንዴዝ ያለፉት ዓመታት ይህን ገድል ለመድገም የተጋበት ነበር፡፡ የጉዞ እቅድ ነደፈ፣ ራሱን የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ በማድረግ ይህን ፅናት የሚጠይቅ ጉዞ በማድረግ በርትተው የሚያበረቱን ባልንጀሮች መፈለግ ጀመረና የሕልሙን ተጋሪዎች አገኘ፡፡ እነዚህ የሕልም ተጋሪዎቹ ሙሐመድ ሚስባሂ፣ እስማኢል ጎንዛሌዝ፣ ዑመር ከሪም፣ ሙጃሂድ ኤስፒኖ፣ ዑመር ሚላኒሮ እና ዓብዱልቃድር ሃርካሲ ሆኑ፡፡ ዓብዱላህ ሕልሙን የሚጋሩትን ሰዎች ከማግኘት ውጪ ሌሎች መሟላት የሚኖርባቸው ሎጂስቲክሶችን ለማግኘት እንቅስቃሴውን ቀጠለ፡፡ ሰዎቹን 8 ሺሕ ኪሎ ሜትር አቆራርጠው ሳዑዲ ዐረቢያ ምድር ላይ የሚያደርሱ ብርቱ ፈረሶችን መፈለግ ተጀመረ፡፡ የትኞቹ ዝርያዎች የተሻለ ብርታት፣ ቅልጥፍና እና ጉልበት አላቸው ብሎ መምረጥ ስለነበረበትም በማፈላለግ የዐረቢያ ዝርያ ያላቸው ፈረሶችን ለጉዞው ተስማሚ ሆኖ አገኛቸው፡፡ ፈረሶቹን ማሠልጠንና ምግባቸውን እየመረጡ ጡንቻቸው እንዲፈረጥም ማድረግ የእለት ተእለት ሥራው ሆነ፡፡ ብርታት የሚጨምሩ ተግባራት ሲደረጉ የነበሩት ለፈረሶቹ ብቻ ግን አልነበረም፡፡ የጉዞው ተሳታፊዎችም ይህንኑ ሲከውኑ ቆዩ፡፡ በዚህ ሒደት የሕክምና ባለሞያዎች የሚያስፈልገውን እገዛ እያደረጉ ቆይተዋል፡፡

ቀጣዩ ሒደት የነበረው የፈረሶቹን ጉልበት መለካት ነበር፡፡ እነ ዓብዱላህም ወደፊት የሚጠብቃቸውን ብርታት የሚጠይቅ ጉዞ የሚሞክሩበት ቀን ተቆረጠ፡፡ ለሙከራው የተመረጠው የሰሜናዊ ስፔን ክፍል ነበር፡፡ 2021 ክረምት የመጀመሪያው የፈረስ ጉዞ ተጀመረ፡፡ ዓብዱላህ እና የሕልም ተጋሪዎቹ ለአስራ ስድስት ቀናት ባደረጉት የፈረስ ላይ ጉዞ 700 ከሎ ሜትር መሸፈን ቻሉ፡፡ የፈረሱም የሰውም ጉልበት ተፈተሸ፡፡ ስለ ጉዞው እነ ዓብዱላህ ሲናገሩ “ፈታኝ ቢሆንም ስኬታማ ነበር” ይላሉ፡፡ ጉልበት ከሚፈትሸውና ከሌላው ሁሉ “ጠንካራ ወዳጅነት እንዲኖረን አድርጎናል” ብለዋል፡፡ ይህ ሲጠናቀቅ ሌላ አንድ ዓመት ጠብቀው ሁለተኛው ጉዞ ማድረግ ነበረባቸው፤ አደረጉት፡፡ በአጎራባች ፖርቹጋል በኩል ከሰሜን ወደ ደቡብ የተደረገው የፈረስ ላይ ጉዞ በ2022 የተደረገ ነበር፡፡ ይህ ጉዞ እንደቀደመው ጊዜ 16 ቀናት ሲፈጅ፤ የሸፈኑት 600 ኪሎ ሜትር ነው፡፡ ይህ ቁጥር ቀድሞ ከተመዘገበው ያነሰ ነው፡፡ እነ ዓብዱላህ ለዚህ ሰበብ የሆነው የአየር ሁኔታው በጣም ደረቅ መሆኑ እንዲሁም “በማናውቀው ሀገር እና ቋንቋ ጉዞውን ማድረጋችን ነው” ሲል ያስታውሳሉ፡፡ ይህ ቢሆንም ለቀጣይ ጉዞ በርካታ ስንቅ የተያዘበት ነበር ይላል፡፡

አሁንም ይህ ብርታት የሚጠይቅ ልምምድ እንደቀጠለ ነው፡፡ ከወራት በፊት ከአንደሉስያ ምእራባዊ አካባቢ የተነሱት እነ ዓብዱላህ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ከረር ባለ ፀሐይ ውስጥ ትግላቸውን ቀጥለዋል፡፡ ቀኑ ከረር ያለ ፀሐይ ቢያስተናግድም ሌሊቱ እጅግ በጣም ቀዝቃዛ የሚባል ስለነበር ከሁለቱ የልምምድ ጉዞዎች ለየት ያለ አጋጣሚ ማስተናገድ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ በዚህ የአየር ጠባይ 420 ኪሎ ሜትር ሸፍነው ተመለሱ፡፡ በተለይ በምሽት በደረሱበት እሳት እያቀጣጠሉ መሞቅ ግድ ነበር፡፡ በፈረስ ላይ ከአንደሉስ ምእራብ አቅጣጫ ወደ ምሥራቅ ተጉዘው ግራናዳ ሲደርሱ የተወሰኑ ሰዎች አቀባበል አደረጉላቸው፡፡

አሁን ልምምዱ አበቃ፡፡ የፈረስ ላይ የሐጅ ተጓዦቹ ቀድመው እቅድ ሲያወጡ አላህ ቢፈቅድ መድረስ የሚፈልጉት በዚህ ዓመት በሚከናወነው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ነው፡፡ ሆኖም ከፊታቸው ስምንት ሺሕ ኪሎ ሜትር መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከደቡባዊ ስፔን ተነስተው፣ ዐስር ሀገራትን ያቆራርጣሉ፡፡ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ስሎቬንያ፣ ክሮሽያ፣ ቦስንያ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ኮሶቮ፣ ሰሜን ሜቄዶንያ፣ ቡልጋሪያ፣ ቱርክ ደርሰው ቀይ ባህርን በጀልባ ተሳፍረው ግብጽ መድረስ ይኖርባቸዋል፡፡ ከግብጽ ደግሞ ቅዱሳኑን ሥፍራዎች ወደያዘችው ሳዑዲ ዐረቢያ መጓዝም አለ፡፡

ይህ 35 ዓመት ያስቆጠረን ቃል ኪዳን ለመሙላት የሚደረገው ጉዞ ከ23 ቀናት በፊት ተጀመረ፡፡ ዶክተር ዐብዱላህ ፌርናንዴዝ ዝግጅቱን ሲጀምሩ ከስድስት ሰዎች ጋር የነበረ ቢሆንም እንደ አለመታደል አሁን የጉዞው ተሳታፊዎች አራት ቀርተዋል፡፡ የእንስሳት ሐኪም፣ ነርስ፣ ምግብ አብሳይ እና ሌሎች ጉዳዮችን የሚያስፈጽሙ ሰዎችም በመኪና ይከተሏቸዋል፡፡ ሕልም የሚመስለው ለአላህ የተገባን ቃል ኪዳን የመሙላት ጉዞ እነ ዓብዱላህ ጥንት አያት ቅድመ አያታቻቸው እንዳደረጉት መነሻውን በአንደሉስ ውስጥ በሚገኘው አልሞናስቴር መስጂድ አድርጓል፡፡ ተጓዦቹ የእለቱ የት እንደደረሱ ኢንስታግራም እና ፌስቡክን በመሳሰሉ ማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ያጋራሉ፡፡ እስከ ትላንት ሐሙሰ ድረስም 935 ኪሎ ሜትር መጓዝ የቻሉት እነ ዓብዱላህ፤ ቀሪ ከ7 ሺሕ በላይ ኪሎ ሜትሮችን ለቃል በመታመን እና ቅዱሳኑን ሥፍራዎች በመናፈቅ ቀጥለዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9384

Minber TV

08 Nov, 16:31


ልዩ ኸበር - የጥንቱን ፍለጋ፡ ከአንደሉስ እስከ መካ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9384

Minber TV

08 Nov, 16:15


9 ዓመታትን በአስመራ!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/uq_Yn7QXVEs 🔗

#የሕይወት_ገጽ #አስመራ #ኤርትራ
#የሕይወት_ታሪክ #መምህር #life_story

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

08 Nov, 14:31


የዛሬው የመኣል ቁርኣን እንግዳችን አብዱል አዚዝ ሙሔ ይባላል። በለጋ እድሜው ቁርኣንን በነዘርም በሒፍዝም በአንዴ የሃፈዘ ሲሆን አሁን ላይ የ5ኛ ዓመት የኮተም ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነው። የተለያዩ ማህበረሰብ ተኮር የለውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ይሳተፋል። ውብ የሆኑ የመድረሳ ተውስታዎችን በምልሰት እያስቃኘን ቆይታ የምናድርግ ይሆናል። ምሽት ከ02:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#አንድ_ሐዲስ_ሕይወቴን_ቀየረው
#ከቁርኣን_ጋር

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 29  - 2017 | ጁማዱል ኡላ 6 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

08 Nov, 13:31


#ኢስላም_እና_ሳይንስ
#ክፍል_8
#ምሕዋር
ዛሬ ምሽት 12:00 በሚንበር ቲቪ!

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 29 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 6 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

08 Nov, 12:30


የሳምንታዊው ዒዳችን ጁምዓ ኹጥባና መልዕክቶች በአግባቡ መደመጥና ወደ ህይወት መቀየር ያለባቸው መሆኑ ይታወቃል። በኹጥባ መሐል የሚከወኑ የትኞቹም ተግባራት በሃዲስ የመወገዛቸው አንዱ ምስጢርም፤ መልዕክቱን ያላንዳች መረበሽ ትኩረት ሰጥቶ በጥሞና ከመከታተል ጋር እንደሚገናኝም ዑለሞች ያስረዳሉ።

ዛሬ ቤተል በሚገኘው የሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ ተገኝተን ያሰናዳነውንና በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የቀረበውን إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ ۗ "አላህ ዘንድ ትክክለኛ እምነት ኢስላም ብቻ ነው።" በሚል ርዕስ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የኹጥባ መልዕክት ከቀኑ 11:30 የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

#የጁሙዓ_ኹጥባ
#አላህ_ዘንድ_ትክክለኛ_እምነት_ኢስላም_ብቻ_ነው።
#ኡስታዝ_ካሚል_ሸምሱ

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 29  - 2017 | ጁማዱል ኡላ 6 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

08 Nov, 11:30


ዛሬ በ"ጥያቄ አለኝ" ፕሮግራማችን ከምንዳስሳቸው የጥያቄ ሃሳቦች መካከል "ሙስሊም ላልሆነ ሰው ሩቃ ማድረግ ይቻላልን?" በሚል የተጠየቀ ጥያቄን ጨምሮ የ"ጥያቄ አለኝ" ፕሮግራም ዛሬ ይህንንና ሌሎች ከተመልካቾች የደረሱ ጥያቄዎችን አካቶ ምሽት ከ03:00 ጀምሮ ለሁለንተናዊ ከፍታ በሚተጋው ሚንበር ቲቪ የሚቀርብላችሁ ይሆናል።

#ጥያቄ_አለኝ?
#ሙስሊም_ላልሆነ_ሰው_ሩቃ_ማድረግ_ይቻላልን?

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 29  - 2017 | ጁማዱል ኡላ 6 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

08 Nov, 11:14


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለሳሃቢዩ አደራ ያሉት ነገር

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/JYf2xLMPl-M 🔗

#ሚንበሩል_ዒልም #አርባዒን_ሀዲስ
#ሀዲስ #ቡኻሪ #ሸይህ_ሰዒድ_ዓሊ_ሐቢብ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Nov, 16:15


ቁርአን እንዴት እስካሁን ተጠብቆ ሊቆይ ቻለ?

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/vUxwgEd20-U 🔗

#ከቁርአን_ጋር #ማአል_ቁርአን
#with_the_Quran #Quran

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Nov, 11:30


በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ የሚሰናዳው እና ተማሪዎችን በቀለም ትምህርት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል እና ማበረታታት ሁለንተናዊ የሆነ የተሟላ እውቀት ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል አላማው የሆነ "ቅን ትውልድ" ፍተሻ የጥያቄ እና መልስ ውድድር ለተወዳዳሪዎች የ200,000 ብር ሽልማት ይዞ ጉዞ ቀጥሏል። ምሽት 02:00 በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#ቅን_ትውልድ
#ፍተሻ

ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 26 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 3 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Nov, 10:30


ከዒልም ጋር ያላቸው ጥልቅ ትውውቅ የጀመረው በልጅነታቸው ነበር፡፡ ሸይኽ ሰዒድ ዓሊ ሐቢብ ይሰኛሉ፡፡ ወጣትነታቸውን የሰዉለት የዒልም አድማስ ዛሬ ላይ በዘርፈ ብዙ ሸሪዓዊ ጉዳዮች ላይ ርቀው እንዲሄዱና ከታላላቅ ዑለሞች ተርታ እንዲሰለፉ አስችሏቸዋል፡፡ ሸይኽ ሰዒድ በመስከ ብዙ ፉኑኖች ያላቸውን የዒልም አቅም ለሰፊው ማኅበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በተፈጠረላቸው መልካም ዕድል ተጠቅመው፤ ከመግሪብ ሶላት በኋላ እስከ ዒሻእ ሶላት ድረስ በሙጀመዕ አት - ተቅዋ የሚሰጡትን "የአርበዒን ሃዲስ" ትምህርት (ደርስ) ዘወትር ማክሰኞ ምሽት ከ12፡30 ጀምሮ ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን አዲስ በጀመረው የሚንበሩል ዒልም ፕሮግራሙ #በክፍል_18 የሚያቀርብላችሁ ይሆናል፡፡


#ሚንበሩል_ዒልም
#አርበዒን_ሐዲስ
#ክፍል_18
#ሸይኽ_ሰዒድ_ዓሊ_ሐቢብ

ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 26 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 3 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Nov, 09:05


ቢቢሲ፤ በዘገባዎቹ “ለእስራኤል ወገንተኝነት አሳይቷል” ባሉ ባልደረቦቹ ወቀሳ ተሰነዘረበት

ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 26 – 2017 | ጁማዱል ኡላ 3 – 1446

በእንግሊዝ ለንደን ከተማ መቀመጫውን ያደረገው ብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ቢቢሲ)፤ በዘገባዎቹ ለእስራኤል ወገንተኝነት አሳይቷል ባሉ ከ100 በላይ ባልደረቦች ወቀሳ ቀርቦበታል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ባልደረቦች ወቀሳ የሠፈረበትን ደብዳቤ ካሰባሰቡት ፊርማ ጋር አያይዘው ለኃላፊዎች መላካቸው ታውቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጁመዐ ለቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ቲም ዴቪ እና ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ዲቦራህ ተርኔስ በደረሰው ደብዳቤ፤ የጣቢያው ባልደረቦች በጋዛ ጉዳይ አሳይቶታል ባሉት ውገና “የጋዜጠኝነት መሠረታዊ መርህ” ተጥሷል ሲሉ ከሰዋል፡፡

የ230 የቢቢሲ ባልደረቦች ፊርማ በሠፈረበት ደብዳቤው ላይ በጣቢያው ውስጥ ከጋዜጠኝነት በተጨማሪ በሌሎች ዘርፎች የሚሠሩ ሠራተኞችም መካተታቸውን የሚድል ኢት ዐይ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ወቀሳውን ያቀረቡ ባልደረቦች ቢቢሲ ፋይናንስ ከሕዝብ የሚሰበሰብ መሆኑን በመጥቀስ የሞራል ጥያቄ በማንሳት ተከራክረዋል፡፡

ፊርማውን ያሳሰቡ ባልደረቦች ቢቢሲ የጋዛን ጉዳይ በሚመለከት በሚሠራቸው ዘገባዎች ከርእስ አመራረጥ ጀምሮ የዜና ዳራ አሰጣጥን በተመለከቱ ጉዳዮችም አካሔዱ ትክክለኛ አለመሆኑን በመጥቀስ አሠራሩን እንዲፈትሽ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም የእስራኤል ባለሥልጣናት የሚፈጽሙትን ጥቃት በሥሙ እንዲጠራም ጠይቀዋል፡፡

የእንግሊዙ መገናኛ ብዙኃን በባልደረቦቹ ለሚቀርብት ወቀሳ ተደጋጋሚ ማስተባበያ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው ማስተባበያም “ስህተት ስንሠራ አልያም በዘገባዎች ላይ ለውጥ በምናደርግበት ጊዜ የምንሠራው በግልጽነት ነው” ሲል ጥቅል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በጋዛ ጉዳይ በሚያቀርባቸው ዘገባዎች ቅሬታ ቀረበበት ቢቢሲ፤ ከባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር አንስቶ የገንዘብ አሰባሰብ ዘዴውን በመቀየር በሀገሪቱ ከእያንዳንዱ አባወራ በዓመት 169.50 ፓዉንድ የሚሰበስብ ነው፡፡ እ.አ.አ በ1922 ብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ካምፓኒ በሚል ሥያሜ የተመሠረተው ጣቢያው፤ በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ 21 ሺሕ ሠራተኞችን ይዟል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

05 Nov, 09:04


ቢቢሲ፤ በዘገባዎቹ “ለእስራኤል ወገንተኝነት አሳይቷል” ባሉ ባልደረቦቹ ወቀሳ ተሰነዘረበት


በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9363

Minber TV

05 Nov, 07:15


“ሶብር” በመወዳ ስቱድዮ!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/cdp0jfA_F_c 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #ነሺዳ #ቶፊቅ_ዩሱፍ
#ሶብር #neshida #nasheed #Tofik_Yusuf

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Nov, 18:15


ሐምዛ(ረ.ዐ) መቼ እስልምናን ተቀበሉ?

A/ 1ኛ ዓመተ ሂጅራ
B/ 10ኛ ዓመተ ነብይነት
C/ 5ኛ ዓመተ ነብይነት
D/ 2ኛ ዓመተ ሂጅራ

የትላንት ጥያቄ መልስ:

ከግዴታ ሰላት ቀጥሎ በላጩ ሰላት የትኛው ነው?
መልስ፡- A/ የለይል ሰላት

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

04 Nov, 16:15


የነብያት ታሪክ በኡስታዝ ሰዒድ ሙሐመድ ያሲን

በቅርብ ቀን በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Nov, 15:16


ሚንበር መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን፤ ከሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ዕለተ ሰኞ ጥቅምት 25 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 2 - 1446

“ሚንበር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን”፤ ከሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመው በዛሬው እለት ነው፡፡ ሰኞ ጥቅምት 25/2017 የተደረገው ስምምነት፤ በሁለቱ ተቋማት መካከል ከዚህ ቀደም በተለይ በወጣቶች ዙርያ “እስከዛሬ የነበረውን የሥራ ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ” መሆኑ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን በሚንበር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን በኩል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አዩብ አደም እና የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዓብዱልመጂድ ጀማል ፈርመዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ከ“ሚንበር ቲቪ” ስድስት ምሰሶዎች ውስጥ ወጣቶችን በሁሉም መስክ ማብቃት (Empowerment) አንደኛው መሆኑን በመጥቀስ፤ የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ በዚህ መስክ በጥምረት ለመሥራት ወደ “[ጣቢያችን] በመምጣቱና እኛም አጋር በመሆናችን ኩራት ይሰማናል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ትብብር “ወደፊት ማኅበረሰብ ሊያጋጥመው የሚችለውን ተግዳሮት ለመጋፈጥ ወጣቶች መፍትሔ አመንጪ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል” በማለትም ስምምነቱ በረዥም ጊዜ ሊኖረው የሚችለውን ፋይዳ አስረድተዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመው የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ፤ በሚንበር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ስር በሚተዳደረው “ሚንበር ቲቪ” ለተማሪዎች እና ወጣቶች የሚሰናዱ ዝግጅቶችን ሲያቀርብ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በጣቢያው ሲቀርቡ ከነበሩ ፕሮግራሞች መካከል ከአንድ ዓመት በላይ ወደተመልካቾች የደረሰው “የመጻሕፍት ዳሰሳ” እና “ቅን ትውልድ” ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዓብዱልመጂድ ጀማል ስምምነቱ ይህንኑ “ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ጠቃሚ” እንደሚሆንም ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

የሚንበር መልቲ ሚዲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አዩብ አደም፤ በስምምነቱ መሠረት ሚንበር ቲቪ የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ለሚሠራቸው ፕሮግራሞች ቴክኒካዊ ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ ሞያዊ እገዛዎችን እንደሚያደርግ በመግለጽ፤ ጥምረቱን ለወጣቶች “ጠቃሚ ነው” ብለውታል፡፡ አያይዘውም የተቋማት በጋራ መሥራት መለመድ ያለበት ጉዳይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ እንደ ተቋም ከዚህ ቀደም ከሌሎች ጋር በጋራ የመሥራት ልምድ እየዳበረ የመጣ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ጣቢያው የአመራርነት ሥልጠና እና በምርምር ላይ ከተሰማራው ከ“ቢልኮር” ጋር ሲሠራ መቆየቱንም በምሣሌነት አንስተዋል፡፡ በዛሬው ስምምነት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በጋራ ስለ መሥራት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ “የብቻ ጉዞ የትም አያደርስም” ያሉት አቶ አዩብ አደም፤ ተቋማት ይህንኑ አሠራር ቢተገብሩት መልካም እንደሚሆን በመግለጽ የትብብር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ከሚንበር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመው የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ፤ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች በሚያዘጋጀው ሽልማት እንዲሁም የተለያዩ ሥልጠናዎችን ለወጣቶች በመስጠት ይታወቃል፡፡

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

04 Nov, 15:16


ሚንበር መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን፤ ከሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9356

Minber TV

04 Nov, 11:30


ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው የዒባዳ ተግባራት የተለያዩ ሃሳቦችን ሲያጋራን የቆየው "በይቱል ሐቢብ" ፕሮግራማችን፤ ባሳለፍነው ሳምንት "ተዋዱእ ወይም መተናነስ" በሚል ርዕስ ሲያስቃኘን ቆይቷል።

በዛሬው ዝግጅታችን ደግሞ "ኢሣር... ከራሥ የተሻገረ ውዴታ" በሚል ርዕስ እህቶች እየተመለከቱ ይቆያሉ። ምሸት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#በይቱል_ሐቢብ
#ኢሣር...
#ከራሥ_የተሻገረ_ውዴታ

ዕለተ ሰኞ ጥቅምት 25 - 2016 | ጁማዱል ኡላ 2 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

03 Nov, 12:30


#ሃላል_ፔይ
የመጀመሪያው ሸሪዓ ላይ የተመሠረተ ዲጅታል
ፋይናንሲንግ አገልግሎት ምን ይዞ መጣ?

ዛሬ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#ሂጅራ_ቢዝነስ
ሂጅራ ባንክ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር

ዕለተ እሁድ ጥቅምት 24 - 2017 | ጁማዱል ኡላ 1 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

03 Nov, 12:27


ለህይወት አዲስ ጣዕም ሰጥቶና፣ መንፈስና አካልን በወጉ አሳርፎ፤ እጅግ በተሳካ ሁኔታ የተከወነው የመጀመሪያው ዙር የሂራ ትራቭል የኅብረት ዑምራ ፓኬጃችን፤ ጨርሶ የሚዘነጋ አለመሆኑን አብረውን የተጓዙ መንገደኞችቻን ምሥክሮች ናቸው!!!

አሁን ደግሞ ከኅዳር 26 እስከ ታህሳስ 7 ከታዋቂው ሸይኽ አብራር ሽፋ ጋር ለመጓዝ የመጀመሪያውን ዙር ምዝገባ ጀምረናል።

ለሴት የዑምራ ተጓዦቻችን ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ሂራ ትራቭል በሁለተኛው ዙር ጉዞው ተወዳጇ የበይቱል ሐቢብ ፕሪግራም አቅራቢ ኡስታዛ ኸይሪያ በድሩን አካቶ ይጠብቃችዃል።

በማይረሳውና በተሟላ የዑምራ ፓኬጃችን ይጓዙ!

ለተሟላ መረጃ በ 0965888883 ወይም በ 0965888884 ይደውሉልን!
ሂራ ቱር ኤንድ ትራቭል!
አድራሻችን ሣር ቤት ግደይ ህንፃ አንደኛ ፎቅ

Minber TV

03 Nov, 07:08


መወዳ መዝናኛችን በዚህ ሳምንት ...

ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ!

#መወዳ_መዝናኛ
#Meweda
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

02 Nov, 16:15


ውዱ ማድረግ ሱና የሚሆንባቸው ሁኔታዎች

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/--LOVaJW6Ow 🔗

#ሚንበሩል_ዒልም #Minberul_Ilm
#ዶክተር_ሰምሃር_ተክሌ #ሱና #sunnah

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

02 Nov, 12:30


የቁርኣን ተፍሲር በሐረሪ ቋንቋ - በሸይኽ የሕያ እስማዒል (ረሒመሁላህ)
ሱረቱል ያሲን 62-68

ዛሬ ምሽት 12:30 በሚንበር ቲቪ!

#ቁርኣን #ተፍሲር #ሐረሪ
#ሸይኽ_የሕያ_እስማዒል_ረሒመሁላህ 

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 23 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 30 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ!

Minber TV

02 Nov, 12:08


በደራ ወረዳ የመስጂድ ኢማም የነበሩት የሸይኽ ሙሐመድ መኪን ግድያ ምክር ቤቱ አወገዘ

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 23 - 2017 | ረቢዕ አል- ሳኒ 30 - 1446

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በገንደ ዐረብ መንደር የመስጂድ ኢማም የነበሩት ሸይኽ ሙሐመድ መኪን ግድያ በማውገዝ መግለጫ አውጥቷል፡፡ “በታጣቂዎች” ተፈጽሟል በተባለው ጥቃት የተገደሉ የኢማሙ ቤተሰብ አባላት ብዛት 13 ደርሷል ተብሏል፡፡ 

በምክር ቤቱ መግለጫ መሠረት የመስጂድ ኢማም የነበሩት ሸይኽ ሙሐመድ መኪን የተገደሉት ትናንት ጁመዓ ጥቅምት 22/2017 ነው፡፡ “ሚንበር ቲቪ” ይህንኑ ከቅርብ ቤተሰብ ማረጋገጥ ችሏል፡፡ እንደ ቤተሰብ ምንጭ ከሆነ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን ለረዥም ዓመታት ካገለገሉበት መስጂድ ከ20 ቀናት በፊት የፈጅር ሰላት አሰግደው ሲወጡ በታጣቂዎች ታግተው ማስለቀቂያ ገንዘብ ተጠይቆባቸው ነበር፡፡ 

ከእርሳቸው በተጨማሪም ባለቤት እና እናታቸውን ጨምሮ ለታገቱት የተጠየቀው ገንዘብ 2.5 ሚሊዮን ብር እንደነበር ያስታወሱት የቅርብ ቤተሰብ፣ ከተጠየቀው ገንዘብ 1.5 ሚሊዮን ብር ለኢማሙ ተጠይቆ ቢከፍሉም ከግድያው ማትረፍ እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡ ከታገቱት ውስጥ የሸይኽ ሙሐመድ ባለቤት እና እናት ተለቀዋል ተብሏል፡፡ 

ታጣቂዎቹ ኢማሙ ላይ ግድያውን የፈጸሙት ትናንት ሌሊት መሆኑንም ምንጩ አስረድተዋል፡፡ የሸይኽ ሙሐመድ አስከሬን በገበሬ ማሣ ውስጥ መገኘቱ ሲገለጽ፤ ማንነታቸውን መለየት በቻሉ የአካባቢው ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዐታቸው በዚያኑ ዕለት እንደተፈጸመ ታውቋል፡፡ ከአንድ ቤተሰብ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር እስካሁን ድረስ 13 መድረሱም ነው የተገለጸው፡፡ 

ታጣቂዎቹ በአሁኑ ሰዓት ኢማሙ ሲያሰግዱ የቆዩበትን መስጂድ ጥሰው በመግባት ፀያፍ ተግባራትን እየፈጸሙ እንደሚገኙም ተሰምቷል፡፡ ግድያውን በተመለከተ እስካሁን ድረስ በአካባቢው የሚገኘው የመንግሥት የፀጥታ መዋቅር በይፋ ያለው ነገር የለም፡፡

በጉዳዩ ላይ ዛሬ እኩለ ቀን መግለጫ ያወጣው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፤ “ዑለሞችና ኢማሞችን በመግደል የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ የለም” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫው፤ ኢማሞች “የማኅበረሰብ መንፈሣዊ መሪዎች፤ የምድራችን አብሪ ከዋክብት፤ የቅን መንገድ አመላካቾች” መሆናቸውን በመጥቀስ፣ “የሚከውኑት በጎ ምግባር ታውቆ ሊከበሩና ሊደገፉ ሲገባቸው” ሕይወታቸውን መንጠቅ አግባብነት የሌለው ተግባር ነው ሲል ግድያውን ኮንኗል፡፡ “ፀያፍ” ያለውን ይህን ተግባር ፈጻሚዎች “እኩይ ማንነታቸውን ከማጋለጡ ውጪ የሚያስገኘው ምንም ዓይነት ትርፍ” እንደሌለም ገልጿል፡፡ 

የሐጂ አሕመድ መስጅድ እና ሐሪማ ኸሊፋ በመሆን በርካታ ደረሶችን እያስተማሩ የነበሩት ኢማም ሸይኽ ሙሐመድ መኪን፣ የታላቁ ዓሊም ሸይኽ አሕመድ ደራ የልጅ ልጅ እንዲሁም የሐጂ ሙሐመድ ወሌ የወንድም ልጅ ናቸው፡፡

ሸይኽ ሙሐመድ መኪን የተገደሉበት ደራ ወረዳ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ ላይ የሚገኝ አካባቢ ነው። የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

02 Nov, 12:07


በደራ ወረዳ የመስጂድ ኢማም የነበሩት የሸይኽ ሙሐመድ መኪን ግድያ ምክር ቤቱ አወገዘ

በድረ ገጽ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=9351

Minber TV

02 Nov, 11:30


ትውልድና እድገቷ እዚሁ አዲስ አበባ ነው። የጓደኛዋ ድንገቴ አሟሟት አስደንግጧት ነፍሷን ለማዳን የሰለመችው የዛሬዋ መንገደኛችን ''ሸሃዳ ስይዝ በሕይወት የምቆይ አልመሰለኝምና የወደፊት የትዳር አጋሬንም ሆነ ቤተሰቤን አላሰብኩም ነበር። ሕይወት ስትቀጥል ግን ከመስለሜ ጋር በእሱ ፍቅር ተፈተንኩ !'' ትለናለች። ምሽት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#አላህን_ሳውቀው_እሱን_ከዳሁት!
#የኔ_መንገድ

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 23 - 2017 | ረቢዕ አል- ሳኒ 30 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

02 Nov, 11:15


ዋትስአፕ... መጨረሻው ሀሳብ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/V9UKRco324c 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #የሸይኻችን_ሰዓት
#ዋትስአፕ #ማህበራዊ_ሚድያ
#WhatsApp #social_media

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

02 Nov, 10:31


በንጽጽር ትምህርቶችና መድረኮች ይበልጥ የምናውቀው ኡስታዝ ሳዲቅ ሙሐመድ (አቡ ሃይደር) እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑ ትምህርቶችን የያዘውን ኪታብ በሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ በሳምንት አንድ ቀን እያስተማረ ይገኛል።

የዛሬው የ"ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራማችን ኡስታዝ ሳዲቅ (አድ ዱሩሱል ሙሂማህ) የተሰኘውን ኪታብ ዋቢ አድርጎ የሚሰጠውን ጠቃሚ ትምህርት ምሽት ከ02:00 ጀምሮ #ክፍል_አስራ_ሰባት የሚያቀርብላችሁ  ይሆናል።

#ሚንበሩል_ዒልም
#ጠቃሚ_ትምህርቶች
#ክፍል_17
#ኡስታዝ_ሳዲቅ_ሙሐመድ (አቡ ሃይደር)

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 23 - 2017 | ረቢዕ አል- ሳኒ 30 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

02 Nov, 08:48


እውነትን መቀበል

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/XJF3K64g4QU 🔗

#በይቱል_ሃቢብ #Beytul_Habib
#ሀቅ #ሀቅን_መቀበል #እውነት #እውነታ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

02 Nov, 07:12


በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ በአዋሽ ፈንታሌ መከሰቱን ባለሞያዎች ገለጹ

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 23  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 30 – 1446

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አካባቢ ትናንት ጁመዐ ጥቅምት 22/2017 ከቀን አንስቶ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ለመንግሥት ቅርበት ላላቸው መገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት፣ በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳ እና አካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ከትናንት ቀን አንስቶ ነው።

ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከሌሊቱ 6:13 ላይ የዕለቱ ከፍተኛ የተባለው በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመዝገቡን የገለጹት ባለሞያው፣ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ድረስ መሰማቱን ጠቁመዋል።

በአካባቢው ባለፉት ሳምንታት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው። ባለሞያው እንደሚሉት መጠኑ አነስተኛ ስለሆነ ሥጋት አይሆንም።

በአፋር ክልል ባለፉት ሳምንታት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። በክልሉ ከዛሬው አስቀድሞ ከሳምንት በፊት ጥቅምት 16/2017 ተከስቷል። ጥቅምት 7/2017 በተመሳሳይ ከመተሐራ ከተማ በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ 34 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ የሚታወስ ነው። በወቅቱ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ንዝረት ያስከተለ ነበር።

ጥቅምት 6/2017 እንዲሁ በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በዚሁ አካባቢ ተከስቶ ነበር። በአፋር አዋሽ አካባቢ ባለፉት አምስት ሳምንታት ቢያንስ ዘጠኝ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Nov, 17:59


ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ረመዳንን ምን ያህል ግዜ ጾመዋል?
A/ 4
B/ 9
C/ 5
D/ 7

የትላንት ጥያቄ መልስ:

ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለአስር ዓመታት ያገለገለ ሰሓባ ማን ነው?
መልስ፡- C/ አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ)

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

01 Nov, 15:25


ልዩ ኸበር- “ፍልስጤማዊያን የነጻነት ታጋዮች” እና ዕድሜ ጠገቡ የእስራኤል ጋዜጣ

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 22 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 29 – 1446

“ሀአሬትስ” በእስራኤል የሚገኝ ዕድሜ ጠገብ ጋዜጣ ነው፡፡ በ1918 የተመሠረተው ጋዜጣው ለአንባቢያን የሚደርሰው በእንግሊዝኛ እና በሂብሩ ቋንቋዎች ነው፡፡

በዋነኝነት የእስራኤል መሠረት ያለው ጋዜጣው ራሱን ‘ግራ ዘመም አስተሳሰብ ላይ የቆመ’ በሚል የሚገልጽ ነው፡፡ በኤዲቶሪያል ፖለሲው መነሻቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ ሰዎችን ጨምሮ ‘ለጭቁኖች ድምጽ እሆናለሁ’ የሚለው “ሀአሬትስ”፤ ደፈር ብሎ የእስራኤሉን ቤንያሚን ኔታንያሁን አስተዳደር ይተቻል ተብሎም የሚነገርለት ነው፡፡

ጋዜጣው በዚሀ ሰሞን ከዚሁ ከቤንያሚን ኔታንያሁ አስተዳደር ጋር ተላትሟል፡፡ በእለቱ ፍልስጤማዊያን ላይ የቦንብ ጥቃት ከሚሰነዝረው አስተዳደር ጋር የተላተመው አሳታሚው ባደረገው ንግግር ነው፡፡ የጋዜጣው አሳታሚ አሞስ ሾከን ባለፈው እሑድ በለንደን ባደረገው ንግግር ላይ “ፍልስጤማዊያን የነጻነት ታጋዮች” የሚል ሐረግ ተጠቅሟል፡፡ እንደ ሚድል ዐይ ዘገባ ከሆነ ይህን መጠቀሙ በእስራኤል ባለሥልጣት አልተወደደለትም፡፡ አልተወደደለትም ብቻ ሳይሆን ያልገመተውን አስከትሎበታል፡፡ በዚህም የእስራኤል ባለሥልጣናት ስፖንሰር ከመከልከል ጀምሮ ጋዜጣውን ያይጎዳል ያሉትን ሁሉ ቅጣት ጥለዋል፡፡

ጉዳዩ መነጋገሪያ ከሆነና የእስራኤል ባለሥልጣናትም ቁጣቸውን ከገለጹ በኋላ የጋዜጣው አሳታሚ ‘እኔ የነጻነት ታጋይ የሚል ሐረግ ስጠቀም ምናልባት ሐማስን ለማለት ፈልጌም መስሏችሁ ከሆነ አይደለም፤ እኔ የጠቀስኩት ሌሎችን ነው’ ቢልም ሰሚ አላገኘም፡፡ የእስራኤል የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ሽሎሞ ካርሂ በጋዜጣው ላይ ሊጣሉ ይገባል ያለውን ቅጣት የያዘ ዶሴ ለአስፈጻሚው ልኳል፡፡ በዚህም ወትሮም ለሕጻናት እንኳ ጥቂት የማይራሩት የእስራኤል ባለሥልጣናት “ለልጃቸውም” ቢሆን የሚመለሱ እንደማይሆኑ አሳይተዋል እየተባለ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9346

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Nov, 15:25


ልዩ ኸበር- “ፍልስጤማዊያን የነጻነት ታጋዮች” እና ዕድሜ ጠገቡ የእስራኤል ጋዜጣ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9346

Minber TV

01 Nov, 14:30


ዛሬ በ"ጥያቄ አለኝ" ፕሮግራማችን ከምንዳስሳቸው የጥያቄ ሃሳቦች መካከል "የመጀመሪያ ባለቤቴን ሳላሳውቅ... ሌላ ትዳር ብመሠርትስ?" በሚል የተጠየቀ ጥያቄን ጨምሮ የ"ጥያቄ አለኝ" ፕሮግራም ዛሬ ይህንንና ሌሎች ከተመልካቾች የደረሱ ጥያቄዎችን አካቶ ምሽት ከ03:00 ጀምሮ ለሁለንተናዊ ከፍታ በሚተጋው ሚንበር ቲቪ የሚቀርብላችሁ ይሆናል።

#ጥያቄ_አለኝ?
#የመጀመሪያ_ባለቤቴን_ሳላሳውቅ...
#ሌላ_ትዳር_ብመሠርትስ?

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 22  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 29 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Nov, 13:30


በዛሬው የመኣል ቁርኣን ቆይታችን ተወዳጅ የሆነው የሀገራችን ቃሪዕ ኡስታዝ ሰዒድ ዓሊ 30 ጁዙን ቁርኣን በምን መልኩ የድምጽ ቀረጻ እንደተከናወነ፣ ተግዳሮት የሆኑበትን የተለያዩ ጉዳዮች እያነሳሳ ያወጋናል።

በተጨማሪም ቁርኣን እንዴት የሰው እጅ ሳይገባበት ተሰብስቦ እስካሁን እንደቆና በሰሃቦች ጊዜ እንዴት እንደ ተፃፈ እያብራራን ቆይታ የምናደርግ ይሆናል። ምሽት ከ02:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#ድምጽን_መቅረጽ_ያለው_ፈተና
#ከቁርኣን_ጋር

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 22  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 29 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TVወ

Minber TV

01 Nov, 12:30


የሳምንታዊው ዒዳችን ጁምዓ ኹጥባና መልዕክቶች በአግባቡ መደመጥና ወደ ህይወት መቀየር ያለባቸው መሆኑ ይታወቃል። በኹጥባ መሐል የሚከወኑ የትኞቹም ተግባራት በሃዲስ የመወገዛቸው አንዱ ምስጢርም፤ መልዕክቱን ያላንዳች መረበሽ ትኩረት ሰጥቶ በጥሞና ከመከታተል ጋር እንደሚገናኝም ዑለሞች ያስረዳሉ።

ዛሬ ቤተል በሚገኘው የሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ ተገኝተን ያሰናዳነውንና በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የቀረበውን "መሽሸፈን ተፈጥሯዊ ነው፤ ሒጃብ ደግሞ ግዴታ ነው።" በሚል ርዕስ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የኹጥባ መልዕክት ከቀኑ 11:30 የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

#የጁሙዓ_ኹጥባ
#መሽሸፈን_ተፈጥሯዊ_ነው፤
#ሒጃብ_ደግሞ_ግዴታ_ነው።
#ኡስታዝ_ካሚል_ሸምሱ

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 22  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 29 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TVወ

Minber TV

01 Nov, 11:30


#ኢስላም_እና_ሳይንስ
#ክፍል_7
#ምሕዋር
ዛሬ ምሽት 12:00 በሚንበር ቲቪ!

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 22 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 29 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

01 Nov, 11:15


ፈተና የበዛብን አላህ ስለሚጠላን አይደለም!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/CgW5koI8Hgw 🔗

#የጁምዓ_ኹጥባ #ኹጥባ
#ፈተና #ፊትና #ጥላቻ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

27 Oct, 16:15


ወላጆቻችንን ሃያእ ማድረግ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/rNBAmI_1Y-U 🔗

#በይቱል_ሀቢብ #Beytul_Habib
#ወላጆች #የወላጅ_ሀቅ #ሃያእ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

27 Oct, 12:32


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በነገው እለት ሊጀመር ነው

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚያከናውነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ነገ ሰኞ በይፋ ሊጀመር መሆኑን አስታወቀ። በመድረኩ ከ2 ሺሕ በላይ ተወካዮች እንደሚገኙ ተገልጿል።

ኮሚሽኑ ይህን ያስታወቀው ዛሬ እሑድ ጥቅምት 17/2017 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ምክክሩን አስመልክተው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) እና ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌጡ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ከነገ ጥቅምት 18/2017 ጀምሮ በክልሉ የሚካሄደውን የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ የምታስተናግደው ወላይታ ሶዶ ከተማ ነች። በዚህም ከ96 ወረዳዎች የተመረጡ የህብረተሰብ ወኪሎችን ጨምሮ ከ2 ሺሕ በላይ ተወካዮች ይሳተፋሉ።

በክልሉ በሚከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት የማኅበረሰብ ወኪሎችን ጨምሮ፣ በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግሥት አካላት፣ የተለያዩ ተቋማትና ማኅበራት ተወካዮች እንዲሁም የተፅእኖ ፈጣሪ ተወካዮች በአጀንዳ ሐሳብ ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

የደቡብ ኢትዮጵያ የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የሚካሄደው፣ በሶማሌ ክልል የተከናወነው ተመሣሣም መድረክ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። በክልሉ ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ የተጠናቀቀው ጥቅምት 13/2017 ነበር። በእለቱ የምክክር ባለድርሻ አካላት የክልሉን አጀንዳ ለኮሚሽኑ አስረክበዋል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

27 Oct, 12:31


#ሃላል_ፔይ_አዲስ_ነገር_ከሂጅራ_ባንክ
ዛሬ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#ሂጅራ_ቢዝነስ
ሂጅራ ባንክ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር

ዕለተ እሁድ ጥቅምት 17 - 2017 | ረቢዕ አል- ሳኒ 24 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

27 Oct, 11:53


ልዩ ኸበር - ሙስሊም አሜሪካዊያን መራጮች እና ትራምፕ

ዕለተ እሑድ ጥቅምት 17 - 2017 | ረቢዕ አል- ሳኒ 24 - 1446

ሊካሔድ ከዐሥር ቀናት በታች በቀሩት የአሜሪካ ምርጫ የመጨረሻዎች የምርጫ ቅስቀሳ መድረኮች እንደቀጠሉ ነው። የምርጫው ተዋናዮች የዴሞክራቲክ ፓርቲዋ ካማላ ሐሪስ እና የሪፐብሊካን ፓርቲው ዶናልድ ትራምፕ 'እኔ እበልጥ - እኔ እበልጥ' እየተባባሉ ነው።

አንዱ ሌላውን ለመጣልና ለማብጠልጠል የሚጠቀሟቸው ቃላትም ጠንከር እያሉ ነው። ሰዎቹ ቃላት የሚመርጡት እርስ በእርስ ለመወራወር ብቻ አይደለም። በምረጡኝ ቅስቀሳው ለድምጽ ሲጪዎች 'እኔ እበጃችኋለሁ' ለማለትም አማላይ ቃላት ያዘንማሉ።

የኋለኛውን ማድረጉ በዘንድሮው ምርጫ የማጠቃለያ ቀናት ቀድሞ ሙስሊሞችን በተመለከተ ጥሩ መናገር ለማይሆንላቸው ለትራፕም የቀናቸው ይመስላል። ትራምፕ በ2016 በዚህ ወቅት የሚናገሩት የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ከተቆናጠጡ ሙስሊሞች አሜሪካ እንዳይገቡ ገደብ ስለመጣል ነበር። አሁን ግን እየሆነ ያለው እንደዚያ ጊዜው አይደለም።

ትራምፕ ትናንት ምርጫ ቅስቀሳ ባካሔዱበት ሚቺጋን የሙስሊሞችን ሥም በክፉ ማንሳት በመተው "የተከበሩ" ሲሉ የጠሯቸውን የእስልምና መምሕራን ወደ መድረኩ ሲጋብዙ ተስተውለዋል። ሰውዬው ከመድረኩ አስቀድሞም በርካታ የዐረብ እና ሙስሊም መሪዎችን አግኝተው ማነጋገራቸውን ሲኤንኤን ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቦ ነበር። የ78 ዓመቱ አዛውንትም ይህንኑ ለሚቺጋን ታዳሚዎች አረጋግጠዋል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እንደጻፉት ከሆነ፣ ውዝግብ በማሳደድ የሚታወቁት ትራምፕ ሙስሊም የሃይማኖት መምሕራን ፊት የሰጧቸው የጋዛን ጉዳይ እንደ እጅ መንሻ ስላቀረቡ ነው።

ተፎካካሪያቸው ዴሞክራቲክ ፓርቲን የጋዛን ጉዳይ መፍታት ተስኖታል በሚል የሚተቹት የቀድሞው ፕሬዝዳንት፣ እኔን ከመረጣችሁ በጋዛ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በመካከለኛውን ምሥራቅ ሰላም አሰፍናለሁ በሚል ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ በተለይ በርካታ ሙስሊም መራጮችን በምትይዘው ሚቺጋን የሚገኙ ሙስሊሞችን ልብ ሊያሸፍት ይችላል በሚል መላ ምት እየቀረበ ነው።

ሰሞንኛ መረጃዎች ይህን ቢያመለክቱም ቀድሞ እንደወጡት ከሆነ ሙስሊሞች መራጮች በ2024 ምርጫ ካማላ ሐሪስ የሚወክሉትን ዴሞክራቲክ ፓርቲንም ሆነ ሪፐብሊካኖችን ከመምረጥ ለሦስተኛ አማራጭ ድምጻቸውን ቢሰጡ ይወዳሉ። የአሁኑ የትራምፕ ነገርም የቢቸግር አማራጭ ሆኖ ነው።

ትናንት በሚቺጋን ትራምፕ ጋዛን ጠረጴዛው ላይ ለድርድር ያቀረቡት ትራምፕ፣ በአካባቢው ሙስሊም መሪዎች 'ድምጽ ስጡት' በሚል ቅስቀሳ ተደርጎላቸዋል። ከሚቺጋን ሙስሊም ማኅበረሰብ መሪዎች መካከል ታዊቂው ኢማም ቢላል አልዙሃይሪ እንዲያውም 'ትራምፕን መምረጥ፣ ሰላምን መምረጥ' ነው ብለዋል።

የሚቺጋን የሙስሊም ማኅበረሰብ መሪዎች እዚህ ትራምፕን መምረጥ ሰላምን መምረጥ ነው ሲሉ፣ በሌላ ጫፍ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሰዎች 'ከትራምፕ አደገኛነት ራሳችሁን ጠብቁ' ሲሉ ቀስቅሰዋል። ይህ የተስተጋባው ከካማላ ሐሪስ ጋር በዴሞክራቶች መድረክ የተገኙት በቀድሞዋ የሀገሪቱ ቀዳማይ እመቤት ሚሼል ኦባማ ነው።

የ2024 የአሜሪካ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት ለጥምቅት 26/2017 ነው። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

27 Oct, 11:52


ልዩ ኸበር - ሙስሊም አሜሪካዊያን መራጮች እና ትራምፕ


በድረ ገጽ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=9317

Minber TV

27 Oct, 07:15


ወለድ ለምን ሀራም ሆነ?

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/tPBnyf-6q1Q 🔗

#ጥያቄ_አለኝ #ፈትዋ #ጥያቄ
#ሸሪዓ #ወለድ #ሀራም

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Oct, 16:15


የየመን ህዝቦች ብሎ ማለት…

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/5kQm2vAC5Aw 🔗

#ሚንበሩል_ዒልም #የቁርአን_ተፍሲር
#የመን #ረሱል_(ሰ.ዐ.ወ) #ሀዲስ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Oct, 14:34


በአዋሽ አካባቢ በዛሬው እለት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተሰማ

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 16 - 2017 | ረቢዕ አል- ሳኒ 23 - 1446

በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 16/2017 ከሰዓት በኋላ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ሚንበር ቲቪ ከአካባቢው ባለሥልጣን ሰምቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች መሰማቱ ታውቋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦችን በሚመዝግበው “ቮልካኖ ዲስከቨሪ” የተባለ ድረ ገጽም ከሰዓት 9 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ገደማ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተመዘገበ አስፍሯል። ነገር ግን የተከሰተው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል ሲለካ ምን ያህል እንደተመዘገበ ይፋዊ መረጃ አልወጣም።

ሚንበር ቲቪ ያናገራቸው ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ያስተናገደው የዱላሳ ወረዳ የሰገንቶ ቀበሌ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሡልጣን ካሚል ኮንቴ፣  የመሬት መንቀጥቀጡ በዛሬው መከሰቱን አረጋግጠዋል። እንደ ሥራ አስኪያጁ ከሆነ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በመጠን ከፍተኛ ሆኖ የተሰማ ነው።

በአፋር ክልል ባለፉት ሳምንታት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። በክልሉ ከዛሬው አስቀድሞ ጥቅምት 7/ 2017 በተመሳሳይ ከመተሐራ ከተማ በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ 34 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ የሚታወስ ነው። በወቅቱ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ንዝረት ያስከተለ ነበር።

ጥቅምት 6/2017 እንዲሁ በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በዚሁ አካባቢ ተከስቶ ነበር። በአፋር አዋሽ አካባቢ ባለፉት አምስት ሳምንታት ቢያንስ ስምንት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000

Minber TV

26 Oct, 11:31


የዛሬው መንገደኛችን በመንፈሳዊ ህይወት ራሱን የቃኘ ፤ እድሜውን ለመንፈሳዊ ትምህርትና አገልግሎት የሰጠ መሪጌታ ነበር። በድቁና 13 ዓመታት በመሪጌታነት 4 ዓመታትን አገልግሏል። ዛሬ ግን በአላህ የሂዳያ ችሮታ እስልምናን መኖር ጀምሯል። የትላንቱ መሪጌታ ይርጋ ደረሰ የዛሬው መንገደኛዬ ኢብራሒም ደረሰ። ምሽት ከ03:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#ነፍሴን_ለማዳን_ራሴን_ስገርፍ_ነበር!
#የኔ_መንገድ

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 16 - 2017 | ረቢዕ አል- ሳኒ 23 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Oct, 10:30


በንጽጽር ትምህርቶችና መድረኮች ይበልጥ የምናውቀው ኡስታዝ ሳዲቅ ሙሐመድ (አቡ ሃይደር) እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑ ትምህርቶችን የያዘውን ኪታብ በሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ በሳምንት አንድ ቀን እያስተማረ ይገኛል።

የዛሬው የ"ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራማችን ኡስታዝ ሳዲቅ (አድ ዱሩሱል ሙሂማህ) የተሰኘውን ኪታብ ዋቢ አድርጎ የሚሰጠውን ጠቃሚ ትምህርት ምሽት ከ02:00 ጀምሮ #ክፍል_አስራ_ስድስት የሚያቀርብላችሁ  ይሆናል።

#ሚንበሩል_ዒልም
#ጠቃሚ_ትምህርቶች
#ክፍል_16
#ኡስታዝ_ሳዲቅ_ሙሐመድ (አቡ ሃይደር)

ዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 16 - 2017 | ረቢዕ አል- ሳኒ 23 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

26 Oct, 07:15


የሚንበር ቲቪ የአራተኛ ዓመት ማስታወሻ

“ሁለንተናዊ ከፍታ” ላይ የመድረስ ራዕይ በመሰነቅ የሚንቀሳቀሰው ሚንበር ቲቪ ጁመዓ ጥቅምት 8/2017 ከተመሠረተ አራተኛ ዓመቱን ደፍኗል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ጣቢያው በዋነኛነት በሳተላይት እንዲሁም ዘመን በደረሰበት የዲጂታል አማራጭ ሁሉ ወደ ውድ ተመልካቾቹ ሲደርስ ቆይቷል፡፡ በዚህም እንደ ጣቢያ ይዞት ከተነሳው ራዕይና ሊደርስበት ከሚናፍቀው ከፍታ ለመድረስ ሲተጋ ነበር። ...

... በአራት ዓመታት ጉዞ ውስጥ ለነበሩት የሚንበር ቲቪ መሥራች ባለድርሻዎች እንዲሁም እስካሁን ድረስ በአንድነት የዘለቁ ታላላቅ የንግድ ድርጅቶችን በተመልካቾቻችን ሥም ለማመሥገን እንወዳለን። ምሥጋናው ለጉዟችን ስንቅ አቀባይ ስለነበራችሁ እና የቀጣይ ሕልማችን ተጋሪ እንደምትሆኑ ስለምናውቅም ነው። በተለያዩ መንገድ ብርታት ለሆኑን የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች እና ለተመሣሣይ ዓላማ የተሰለፉ የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞችንም እናመሠግናለን። ሚንበር ቲቪ መቀመጫው አዲስ አበባ ከተማ ቢሆንም እንደ ራሳቸው ቤት በመቁጠር ከመላው ዓለም ሀገሮች አብረውን ለዘለቁ የዲያስፖራ ቤተሰቦቻችንም ምሥጋናችን ይድረስ፡፡

ሚንበር ቲቪ - አራተኛ ዓመቱን ሲያከብር ሁልጊዜም እንደሚለው ነገ ላይ ለመድረስ በትጋት እየሠራ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።

ሚንበር ቲቪ - ሁለንተናዊ ከፍታ
4ኛ ዓመት
ዛሬም እንደ ትላንት - በትጋት!


★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

25 Oct, 18:02


ሁሉም ነብያት የሰሩት የስራ መስክ ምንድነው? 
A/ እረኝነት   
B/ ንግድ   
C/ ልብስ ስፌት   
D/ ግንበኝነት

የትላንት ጥያቄ መልስ:

መካ የተከፈተችው በስንተኛው ዓመተ ሂጅራ ነው? 
መልስ: - A/ 8

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

25 Oct, 16:24


ልዩ ኸበር - ፍልስጤም ዩሱፍም አላት!

በይት ላሂያ ከተማ የምትገኘው በጋዛ ሰሜናዊ ክፍል ውስጥ ነው፡፡ ከተማይቱ ለም አፈር ታድላለች። ስለዚህ መሬቷ ላይ የወደቀ ሁሉ ፍሬ ያፈራል ይባልላታል። የአካባቢው ነዋሪዎች የመስኖ ውሃ ተጠቅመው በግብርና መስክ ላይ መሠማራታቸውም ለዚሁ ነው፡፡ በይት ላሂያ በተለይ በእንጆሪ ምርት ታዋቂ ነች፡፡

ዩሱፍ አቢ ረቢዕ ተወልዶ ያደገው በዚህች ከተማ ነው፡፡ ቤተሰቡም እንደ አብዛኛው የአካባቢው ሰው ከግብርና ጋር ያለው ቁርኝት ከፍተኛ ነው፡፡ የዩሱፍ ወላጆች ኑሯቸውን የመሠረቱት በግብርና ላይ ስለሆነ እርሱም ገና በትንሽ እድሜው ከግብርና ጋር ተዋውቆ እንደ ገበሬ እያሰበና ግብርናን እየወደደ የማደግ እድል አስገኝቶለታል፡፡ በዚህ መንገድ የመጣው ዩሱፍ በእድሜ ደረስኩ ሲል ወደ ከፍተኛ ትምህርት የመግባት እድል ሲያገኝም በዲግሪ ደረጃ ያጠናው ግብርናን ነው፡፡ በዚህም ዩሱፍ የእለት ጉርሱን፤ የዓመት ልብሱን የሚሸፍነውም በግብርና ሆነ፡፡ አሁን ዩሱፍ እድሜው 24 ብቻ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱንም  ያጠናቀቀው ከአንድ ዓመት በፊት ነበር።

ዩሱፍ ትምህርቱን ባጠናቀቀበት የ2023 ጥቅምት ወር እርሱን ጨምሮ ለፍልስጤማዊያን ከባድ ሆኖ ያለፈ ወር ነበር፡፡ በርግጥ ጥቅምት አሁንም አልፏል አይባልም፤ ለዩሱፍ፣ ለቤተሰቡ እና ለፍልስጤማዊያን ቀን ቀናት ወልዶም፤ ወራት ተጠራቅመው ዓመት ደፍነውም ቢሆን የተቀየረ ነገር የለም፡፡

እ.አ.አ ጥቅምት 8/2023 በእስራኤል ወታደሮች መዝነብ የጀመረው ቦምብ የአቡ ረባእንና ቤተሰቡን ኑሮ በድንገት ቀየረው፡፡ በበይት ላሂያ የኖረው ዩሱፍ፤ ከዚህ ቀን በኋላ ራሱን ያገኘው በጀበሊያ የተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ ሆነ፡፡ ሲለፋበት የኖረው የገበሬ ማሳም በእስራኤል ቦንብ እንዳልነበረ ሆኖ ወደመ፡፡

ለእነ ዩሱፍ ሕይወት እንደማንኛውም ተፈናቃይ መሆኑ ግድ ነበር፡፡ ከረጂነት ወደ ተረጂነት፤ ከለፍቶ አዳሪነት በሸራ የተወጠረ ዳስ ውስጥ ደግ ቀን እንዲመጣ እየተመኙ ሕይወትን መግፋት ሥራቸው ሆነ። ነገር ግን ለገበሬው ዩሱፍ ይህ የሚዋጥ አልነበረም፡፡ አውጥቶ አውርዶ አንድ ነገር መወሰን ነበረበት፡፡ ለዚህ ወሳኔው መነሻ የሆነው በጋዛ የሚመለከተው የወገኖቹ ስቃይ ነው፡፡

በተፈናቃይ መጠለያዎች የተመለከታቸው ሰዎች ልክ እንደሱ ሥራ የነበራቸው፣ የእለት ጉርሳቸውን የሚሸፍኑ፤ አንዳንዶቹም ከራሳቸው አልፈው ለሌላ የሚተርፉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን በጣቢያው ሕይወት እንደ ድሮው አይደለም፡፡ በቀን ሦስት ጊዜ አልያም ሁለት ጊዜ የፈለጉትን አግኝቶ መመገብ ከባድ ነው፡፡ የእስራኤል ወታደሮች የረድኤት ኮሪደሮችን ዘግተዋቸው ምግብ ከእነ አካቴው ማግኘትም ፈታኝ መሆኑን መመልከቱ የሚታገሰው ስላልሆነ መላ ዘየደ፡፡ ይህን ለመወሰን ግን ወደ ቀድሞ ከተማው በይት ላሂያ መሄድ ነበረበት፡፡ እንዳሰበው ወደ ቀድሞ ቤቱ በማቅናት ከቦንብ የተረፈውን ማሳ ተመለከተ። አብሮት ከተጓዘው ወንድሙ ጋር እዚያ ሄዶ ካገኘው የተራረፈውን ለቃቅሞ ሲመለስ በሚያውቀው የግብርና ሥራ ወገኖቹን መታደግ እንዳለበት በመወሰን ነበር፡፡ ዩሱፍ እና ወንድሙ በድሮ ሠፈራቸው ለመኖር ባይችሉም ወደ ግብርና ተመልሰን በተገኘው መሬት ያገኘነውን ተክለን ከራሳችን ጓሮ ሌሎችን መመገብ አለብን አሉ፡፡ በውጥን ብቻ አልቀሩም፤ አደረጉት፡፡

ዩሱፍ አቡ ረቢዕ ቲአርቲን ለመሳሰሉ መገናኛ ብዙኃን በሰጠው ቃለ ምልልስ መጀመሪያ በቤታችን ጣሪያ ላይ አፈር ጎዝጉዘን የተከልነው ኢጂፕሽያን ስፒናች እና ዱባ ነው ብሏል፡፡ ወንድማማቾቹ ለተከሉት ዘር ያገኙት ቀድሞ ከነበራቸው ማሳ ነው፡፡ ለዩሱፍና ወንድምየው ውጥን መሬት እንደ እስራኤል ወታደሮች አልጨከነችም፤ የተከሉት ፍሬ አፈራ፡፡ ቀስ በቀስ የተክሎቹ ብዛትም በቁጥር ጨመረ፡፡ ከጓሮ ሰብስበው በጥቂት ገንዘብ የሚሸጡላቸው የሀገሩ ሰዎች ቁጥርም እንደዚያው፡፡

በርግጥ የተክሎቹ ዐይነት እንዲሁም ምርት ‘ጊዜ እስኪያልፍ እንዝለቅበት’ በሚል ካልሆነ በቂ እንዳልሆነለት ዩሱፍ ይናገራል፡፡ በተለይ ባለፈው ዓመት ረመዳን ወር ለእኛ ፈታኝ ነበር ብሏል ወደ ኋላ አስታውሶ፡፡ ቢሆንም እርሱም ሆነ ፍልስጤማዊያኑ ከመጾም አላጎደሉም፡፡ በሌሎች አርሶ አደሮች እገዛ ጭምር የአተር፣ ዱባ፣ ባቄላና ሌሎችንም ተክሎች ማምረት መቻሉን የሚናገረው ዩሱፍ፤ መጀመሪያ አካባቢ ከወጪው አንጻር የሚያቀርቡበት ዋጋ ከፍተኛ እንደበር በማስታወስ፤ በኋላ ግን ምርት ሲጨምር ዋጋው ቅናሽ ማሳየቱን ይገልጻል፡፡

ይህ የዩሱፍ ተግባር በተፈናቃዮች ዘንድ ያስገኘለት ከበሬታ ከፍተኛ ነው፡፡ በጋዛ ላገኙት ጋዜጠኞች ሥራውን የሚቀጠለው አንድም እስራኤልን ለመበቀል መሆኑን ነግሯቸዋል፡፡ ምክንያቱን ሲያስረዳም ወታደሮቹ የፍልስጤማዊያን መጠቀሚያ የሆኑ የእርሻ መሬቶችን በተጠና መንገድ ማውደማቸውን በማስታወስ ነው፡፡

ከቲአርቲ ጋር ከሦስት ወር በፊት በነበረው ቆይታው ይህንኑ ያንጸባረቀው ዩሱፍ፤ በዚህ ሁሉ የቦንብ ዝናብ ‘ብዙ ጊዜ በሕይወት እሰነብታለሁ የሚል እምነት የለኝም፤ ሆኖም እነሱን የምፋለምበትን መንገድ ሁሉ አደርጋለሁ’ ብሏል፡፡ ዩሱፍ የምሰነብት አይመስለኝም የሚለው ከዚህ ቀደም ከቦንብ ስለተረፈም ጭምር ነው፡፡

የበይት ላሂያው ልጅ ዩሱፍ አቢ ረቢዕ ይህ ንግግር እንዲሁ ሥጋት ብቻ ሆኖ አልቀረም፡፡ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከባልደረቦቹ ጋር የእስራኤል ድሮን ሕይወቱን ነጠቀው፡፡ ዩሱፍ ቀድሞ ለጋዜጠኞች ‘እንስሳት እንኳ ሊኖሩበት የሚከብድ ነው’ ካለው ሕይወት ተለየ፡፡ ብርቱው ሰው በመታከት ሥሜት ውስጥ ስለነበሩበት ሥፍራ ይህን ቢልም ‹‹ያለንበትን ሁኔታ መቀበል አለብን፤ ነገ የተሻለ ይሆናል›› እያለ የሀገሩን ሰዎች ማበረታታት አላቆመም ነበር፡፡ ለቲአርቲ ጋዜጠኞች የብርታቱ ምንጭ ቁርኣን መሆኑንም ነግሯቸዋል፡፡ ዩሱፍ በዚህ ሳምንት በዚህ መንገድ ዓለምን ቢሰናበትም ፍልስጤማዊያን እናቶች አንድ ጀግና ሲወድቅ፤ ሌላ ጀግና እየወለዱ ሕይወት በፍልስጤም ምድር ቀጥሏል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
 
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

25 Oct, 16:24


ልዩ ኸበር - ፍልስጤም ዩሱፍም አላት!

Minber TV

25 Oct, 16:15


አላህን ያገኘ ሰው ያጣው የለም!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/S9xt2fr0ZTk 🔗

#ከቁርአን_ጋር #ማዓል_ቁርአን
#ሰው_ይቀያየራል #አላህ_ግን_አንድ_ነው!

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

25 Oct, 14:30


#ኢስላም_እና_ሳይንስ
#ክፍል_6
#ምሕዋር
ዛሬ ምሽት 12:00 በሚንበር ቲቪ!

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 15 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 22 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

25 Oct, 13:30


ዛሬ በ"ጥያቄ አለኝ" ፕሮግራማችን ከምንዳስሳቸው የጥያቄ ሃሳቦች መካከል "የቴሌኮም አክሲዮን መግዛት ይቻላል?" በሚል የተጠየቀ ጥያቄ ጨምሮ የ"ጥያቄ አለኝ" ፕሮግራም ዛሬ ይህንንና ሌሎች ከተመልካቾች የደረሱ ጥያቄዎችን አካቶ ምሽት ከ03:00 ጀምሮ ለሁለንተናዊ ከፍታ በሚተጋው ሚንበር ቲቪ የሚቀርብላችሁ ይሆናል።

#ጥያቄ_አለኝ?
#የቴሌኮም_አክሲዮን_መግዛት_ይቻላል ?

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 15  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 22 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

25 Oct, 12:44


በመርካቶ ሸማ ተራ ሱቆቻቸው ለተቃጠሉባቸው ወገኖች በሙሉ የተደረገ ዱዓ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/is1Fcwch1Qc 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #የሸይኻችን_ሰዓት
#መርካቶ #ሸማ_ተራ
#merkato #shema_tera
#ዱዓ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

25 Oct, 12:32


የሳምንታዊው ዒዳችን ጁምዓ ኹጥባና መልዕክቶች በአግባቡ መደመጥና ወደ ህይወት መቀየር ያለባቸው መሆኑ ይታወቃል። በኹጥባ መሐል የሚከወኑ የትኞቹም ተግባራት በሃዲስ የመወገዛቸው አንዱ ምስጢርም፤ መልዕክቱን ያላንዳች መረበሽ ትኩረት ሰጥቶ በጥሞና ከመከታተል ጋር እንደሚገናኝም ዑለሞች ያስረዳሉ።

ዛሬ ቤተል በሚገኘው የሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ ተገኝተን ያሰናዳነውንና የኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የቀረበውን "ትዕግስት" በሚል ርዕስ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የኹጥባ መልዕክት ከቀኑ 11:00 የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

#የጁሙዓ_ኹጥባ
#ትዕግስት
#ኡስታዝ_ካሚል_ሸምሱ

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 15  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 22 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TVወ

Minber TV

25 Oct, 11:30


በዛሬው መኣል ቁርኣን ፕሮግራማችን ከተወዳጁ ዳኢ እና ሙረቢ ኡስታዝ አብዱልመጂድ ጋር ካሳለፍነው ሳምንት የቀጠለ... ቆይታ ይኖረናል። በቆይታችን ከቁርኣን ጋር በተያያዘ "ለምን ይሆን ቁርኣንን ያልተረዳነው?" በሚል ርዕስ ቁርኣንን የማንበብ አስፈላጊትን እያነሳሳን ቆይታ የምናደርግ ይሆናል። ዛሬ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ ይጠብቁን!

#ለምን_ይሆን_ቁርኣንን_ያልተረዳነው?
#ከቁርኣን_ጋር

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 15 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 22 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

25 Oct, 10:30


የህይወት መመሪያችን የሆነውን ቁርአንን ለመረዳትና ለመኖር ትርጉሙን (ተፍሲር) በዘርፉ ጥልቅ ንባብና ዕውቀት ካላቸው ዑለሞች መማር ያሻል።

ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን ሚንበር ቲቪም በዕውቀት የታነጸ ማኅበረሰብን ለመገንባት እንደሚረዳ የሚታመነውንና፤ መልከ ብዙ ትምህርቶች የሚሰጡበትን "ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራም ከሥፍራው በጥራት በመቅረፅ በየዕለቱ እያቀረበ የቆየ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ ከሚሰጡ ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነውንና በተወዳጁ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እየተሰጠ የሚገኘውን የቁርኣን ተፍሲር ትምህርት (ደርስ) ዘወትር ጁምዓ አመሻሽ ከ12:30 ጀምሮ ይቀርብላችኃል።

#ሚንበሩል_ዒልም
#የቁርኣን_ተፍሲር
#ክፍል_5
#ሸይኽ_ሐሚድ_ሙሳ

ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 15 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 22 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

25 Oct, 07:15


በወንጀሎቻቸው ያዝናቸው!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/nHEcwKebPVM 🔗

#የጁምዓ_ኹጥባ #ኡስታዝ_ያሲን_ኑሩ
#ወንጀላችን_በዝቷል!! #ችግር_እና_መከራ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

24 Oct, 16:15


ሰላተል ጀናዛን የሚሰግድ ሰው ያለው ትልቅ ምንዳ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/pXzLBgMVhUE 🔗

#ሚንበሩል_ዒልም #አስፈላጊ_ትምህርቶች
#ጀናዛ #የጀናዛ_ሀቅ #ሰላተል_ጀናዛ #ሀዲስ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

24 Oct, 13:41


ጥቅምት ተወልዶ ጥቅምት ላይ ተፍረምርሞ ጥቅምት ላይ እንደ እሳት ተግ እንዳለ የፅናት እሸት ሆኖ ከጀግንነት ጋር የምድር ዜናው ተባበለ! ከበትረ ሞገሱ ጋር ጀግና የሚለውን ቃል በስሙ እያንጣጣን እኛ በትውስታው እንዘልቃለን! ምሽት 01:45 ይጠብቁን!

#ከጥቅምት_እስከ_ጥቅምት
#እነሆ_ኸበር

ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 14  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 21 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

24 Oct, 13:06


ቬትናም የመጀመርያውን ብሔራዊ የሐላል ኮንፍረንስ አካሔደች

ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 14 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 21 - 1446

በደቡብ ምሥራቅ እስያ ውስጥ የምትገኘው ቬትናም የመጀመሪያውን ብሔራዊ የሐላል ኮንፍረንስ አካሔዳለች፡፡ በኮንፍረንሱ ላይ ከቬትናም እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት የተውጣጡ የሐላል ሠርተፊኬት ሠጪ ድርጅቶች ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በውጭ ጉዳይ፣ የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የግብርና እና የከተማ ልማት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በጋራ ያዘጋጁት ኮንፍረንስ የተካሔደው በሳምንቱ አጋማሽ ነው፡፡ ኮንፍረንሱ የተከናወነው በ2030 በቬትናም ጠንካራ የሐላል ኢንዱትሪ ዘርፍ ለመገንባት እና ዓለም አቀፍ ጠንካራ ትብብር ለመመሥረት በሚል ዓላማ የተደረገ ነው፡፡

ኮንፍረንሱ የሀገር ውስጥ ተሳታፊዎችን በአካል ከማገናኘቱ በተጨማሪ በመይነ መረብ በርካቶችን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ጽፈዋል፡፡ እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ያሳተፈው ኮንፍረንስ፤ በውጪ ሀገራት የሚገኙ የሐላል ንግድ ላይ የተሠማሩ ድርጅቶችም ተወካዮቻቸውን የላኩበት ሆኖ አልፏል፡፡

በኮንፍረንሱ ላይ የተናገሩት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋም ሚንህ፤ በቬትናም የሐላል ዘርፉን ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ፤ ዘርፉ ለወደፊቱ የዓለም አቀፍ በተለይ ደግሞ ከሙስሊሙ ዓለም ጋር ለሚኖረው የኢኮኖሚ ትብብር ምሰሶ የመሆን አቅም ያለው ነው ብለውታል፡፡

ዓለም አቀፉ የሐላል ኢንዱስትሪ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ከ2028 በፊት 10 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይገመታል። በአሁኑ ወቅት ከዓለም የሕዝብ ቁጥር የሙስሊሞች ቁጥር አንድ አራተኛ የሚገመት ነው፡፡ ይህ ቁጥር በ2050 ወደ 2 ነጥብ 8 ቢሊዮን እንደሚደርስ የሚገመተው ሲሆን፣ በየጊዜው መጨመሩ እምቅ አቅም እንደመሆንም ዘርፉ ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9307
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 16:15


አዝናኝ ነገሮችን በምልክት የመግለፅ ጨዋታ 😂

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/WAlL2WtMriQ 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #ፋታ_በጫዋታ
#አስቂኝ #አዝናኝ #funny #entertaining

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 13:15


ለሙስሊሙ ዓለም የተላለፈው ጥሪ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/6Zvy92l0a1k 🔗

#ሚንበር_ኸበር #Minber_Kheber
#ሙስሊም #ኢስላም #Muslim #Islam

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 12:31


እንደስያሚያችን ውብ ሁነን እንደተወለደችዋ ጨረቃ አብሪና አንጻባራቂነታችን ለሁሉም ይደርሰው ዘንድ ዳግም በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ልንል መሆኑን ስንገልጽ ደስታዎን በመጋራት ነው።

እንደወትሮው  አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ፕሮግራሞቻችንን በተለመደው ሰዓታችን ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 03፡00 በተወዳጁ የቴሌቪዥን ጣቢያ (ሚንበር ቲቪ) ላይ ይከታተሉ።

"ሂላል ለልጆች"

ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 7  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 14 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 11:31


190 ውብ ሳምንታት!
ዛሬ የጣቢያችን አራተኛ ዓመት ነው።

የተወዳጁ ኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን ደግሞ 190 ኛ ሳምንት መሰናዶው! ይህ የአላህ ፈቃድና ችሮታ ያልተለየው ጉዟችን፤ እንደ አዘጋጅ በርካታ አዳዲስ ጉዳዮችን የገበየንበት ሲሆን፤ እናንተም እንደ ቤተሰብ እጅግ ጠቃሚ ነገሮችን ስትሸምቱ እንደቆያችሁ እናምናለን።

በኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን የማይጠገብ አንደበትን ከተቸሩት ሸይኻችን በእንባና ሳቅ የታጀቡ ታሪኮችንና  አያሌ ቁምነገሮችን ቀስመናል። ወዲህ ደግሞ የአላህን ስም በጥልቅ ሲያስተዋውቀን ከርሞ፤ ወደ አላህ የሚደረገውን ጉዞ ደረጃ በደረጃ እያስቃኘን ከኛ ጋር ከዘለቀው ኡስታዝ በድር ሁሴን ልሳን በየምዕራፉ የህይወት ዘመን ስንቃችንን ቋጥረናል።

በተናፋቂው የመዲና ሰማይ ሥር ንዑስ ፕሮግራማችን "አብዮት" ተብሎ ሊወሳ በሚችል መልኩ ስለ ተወዳጁ መልዕክተኛ (ﷺ) ናፍቆትና ጥልቅ ውዴታ ከእንግዶቻችን የትውስታ ማኅደር እየጨለፍን መዲናን እንደ አዲስ አስናፍቀናል። በአላህ እገዛ በሃገር ውስጥና በመላው ዓለም በርካታ ቤተሰቦችን ያፈራንበት ተወዳጅ ፕሮግራማችን፤ ዛሬም በሸይኻችን ጣፋጭ ትምህርትና በኡስታዝ በድር አስገራሚ ገጠመኞች ተሰናድቶ ሰዓቱን ሳያዛንፍ ወደናንተ ይደርሳል!

#190_ውብ_ሳምንታት!
#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!!

ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 7  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 14 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 11:15


ኸሚስ ምሽት በዚህ ሳምንት ...

#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!!

ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 7  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 14 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 10:44


የመሬት መንቀጥቀጥና ተመሣሣይ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሚደረጉ ዱዓዎች፦

اللهم أعوذ بك من التردي والهدم والغرق والحرق، وأعوذ بك أن يتخطبني الشيطان عند الموت وأعوذ بك أن أموت في سبيلك مدبرا أو أموت لديغا

بسم الله الذي لا يضر مع اسمه شيء في الأرض ولا في السماء وهو السميع العليم

اللهم لا تقتلنا بغضبك، ولا تهلكنا بعذابك، وعافنا قبل ذلك

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 10:30


በመልከ ብዙ ተሳትፎዎቹ የምናውቀው ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በርካታ ወንድምና እህቶችን አስተባብሮ በአጭር ጊዜ ለተሟላ አገልግሎት ያበቃው የቤተሉ ሙጀመዕ አት-ተቅዋ መስጂድ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ድረስ ተከታታይነት ያላቸውን የተለያዩ አስፈላጊ ደርሶች (ትምህርቶች) ለምዕመናኑ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን፤ እኛም እንደ ጣቢያ ይህንን እጅግ ጠቃሚ ደርስ በጥራት በመቅረጽ አዲስ በጀመርነው የ"ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራማችን ምሽት ከ12፡30 ጀምሮና በዛው ዕለት በድጋሚ ከ4፡30 ጀምሮ በማሳየት ትምህርቱ በርካታ ቁጥር ላለው ተመልካች በቲቪና በሚንበር የዩቱብ ገፃችን ተደራሽ እንዲሆን ሰፊ ሽፋን በመስጠት ላይ እንገኛለን፡፡

የዛሬው ተረኛ ትምህርት አቅራቢያችን ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ሲሆን፤ የተወዳጁን መልዕክተኛ (ﷺ) ዜና መዋዕል (ሲራ) በወጉ ሰንደው እንደያዙ ከሚነገርላቸው ድርሳናት መካከል አንዱ የሆነውንና፤ ከሁሉም ሙስሊም ቤት የመፅሐፍት መደርደሪያ ላይ ጨርሶ መጥፋት እንደሌለበት የሚነገርለትን "ረሒቀል መኽቱም" #ክፍል_13 ውብ መፅሐፍ ዋቢ አድርጎ የተወዳጁን ነቢይ (ﷺ) ሁለንተናዊ የሕይወት እንቅስቃሴ በግሩም ሁኔታ እያስቃኘን ይቆያል፡፡

#ሚንበሩል_ዒልም
#ሲራ
#ረሒቀል_መኽቱም
#ክፍል_13
#ኡስታዝ_ካሚል_ሸምሱ

ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 7  - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ 14 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 09:07


አንድ ሚሊዮን የቁርኣን ቅጂ የማሠራጨት ዓላማ ያለው ዘመቻ በለንደን ይፋ ሊደረግ ነው

ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 7 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ-14 1446

የእንግሊዝ መዲና ለንደን በሳምንቱ መጨረሻ በምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የሰላም እና የአንድነት አውደ ርዕይ ላይ አንድ ሚሊዮን የቁርኣን ቅጂ የማሠራጨት ዓላማ ያለው ዘመቻ ይፋ ሊደረግ ነው፡፡ አውደ ርዕዩ 50 ሺሕ ሰዎች ይሰተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለ7ኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ዓለም አቀፍ የሰላም እና የአንድነት አውደ ርእይ ላይ አንድ ሚሊዮን የቁርኣን ቅጂዎች እንደሚቀርቡ ያስታወቀው መቀመጫውን ማሌዥያ ያደረገው ሬስቱ ፋውንዴሽን የተሰኘ እስላማዊ ማዕከል ነው፡፡

የፋውንዴሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ዳቱክ ዓብዱለጢፍ ሚራሳ፤ ቅዱስ ቁርኣን የማሠራጨት ዘመቻው በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ማኅበረሰቦች ውስጥ የቅዱስ ቁርኣንን መልዕክት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ግንዛቤን የማሳደግ ራዕይ ያዘለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሥራ አስፈጻሚው በአውደ ርዕዩ ላይ የሚሠራጩት የቅዱስ ቁርኣን ቅጂዎች የኅትመት ጥራት ከፍተኛ እንደሚሆንም አክለዋል፡፡ ዳቱክ ዓብዱለጢፍ፤ በእንግሊዝ ውስጥ የቁርኣን ቅጂዎቹን ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለም ጠቅሰዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የሰላም እና አንድነት አውደ ርዕይ በለንደን ከተማ የሚካሔደው በመጪው ቅዳሜ እና እሑድ ነው፡፡ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሔደው አውደ ርዕይ ከዐሥር ዓመታት መቋረጥ በኋላ እንደ አዲስ ተመልሶ የሚከናወን ነው፡፡ 50 ሺሕ ሰዎችን ያሳትፋል ተብሎ የሚገመተው አውደ ርዕይ የተለያዩ ባሕሎችን በማዋሐድ ስለ ሰላም እና አንድነት የሚቀነቀንበት መሆኑን አዘጋጆቹ ይገልጻሉ፡፡

የተለያዩ መርሐ ግብሮችን የሚያካትተው አውደ ርዕይ ላይ፤ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ፖለቲከኞች፣ የማኅበረሰብ እና የአስተሳሰብ መሪዎችን የሚሳተፉበት የፓናል ውይይት ይቀርብበታል ተብሏል። በአውደ ርዕዩ ላይ ከሁሉም የሐላል ኢኮኖሚ ዘርፎች የተውጣጡ ምርቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ዝግጅቱን በመላው ለሚገኙ ሙስሊሞች በቀጥታ ለማስተላለፍ ኃላፊነቱን የወሰደው መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ኢስላም ቻናል ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 09:07


አንድ ሚሊዮን የቁርኣን ቅጂ የማሠራጨት ዓላማ ያለው ዘመቻ በለንደን ይፋ ሊደረግ ነው

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9274

Minber TV

17 Oct, 07:15


"ሂላል ለልጆች" አዝናኝ እና አስተማሪ የልጆች ፕሮግራም በአዲስ መልኩ ወደ እናንተ መቅረብ ይጀምራል።

በቅርብ ቀን በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#ሂላል_ለልጆች #በቅርብ_ቀን
#የልጆች_ፕሮግራም #ለልጆች

ዕለተ ሐሙስ ጥቅምት 7 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ-14 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

17 Oct, 04:00


በአዋሽ ፈንታሌ ለሦስተኛ ጊዜ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ተሰማ

በአዋሽ ፈንታሌ ትናንት ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ለሦስተኛ ጊዜ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ተሰምቷል።

ይህንኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለብሔራዊ ጣቢያ ገልጸዋል። በአዋሽ ፈንታሌ የተከተሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተሰማው ምሽት 5፡11 ደቂቃ ላይ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እንደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ አረጋግጠዋል።

በአካባቢው ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴው አሁንም እንዳልቆመ  ተነግሯል።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

16 Oct, 18:01


ከነብዩ ሰ.ዐ.ወ ሞት በኋላ በስድስት ወር የተከተለቻቸው (የሞተች) ልጃቸው ማን ናት?
A/ ዘይነብ (ረ.ዐ)
B/ ፋጢማ (ረ.ዐ)
C/ ኡሚ ኩልሱም (ረ.ዐ)
D/ ሩቂያ (ረ.ዐ)

የትላንት ጥያቄ መልስ:

የሂጅራ አቆጣጠር የጀመረው በስንተኛው ዓመተ ልደት ነው? መልስ: - B/ 622

በዙርያችን ያሉ ሰዎች እየተዝናኑ እንዲማሩበት ሼር ማድረግ እንዳይረሳ።
@minbertv

Minber TV

16 Oct, 12:34


የዛሬው የሕይወት ገጽ እንግዳችን በአዲስ አበባ 1933 ተወለዱ ጣሊያን እንደወጣ ፈትህ ት/ቤት እስከ አራተኛ ክፍል ተምረው በአጋጣሚ ኮኮብ ጽባሕ ት/ቤት ሔደው ከሁለተኛ ክፍል ጀመሩ። ከዚያ ወጡና በአጋጣሚ ዑመር ሠመተር  8ኛ ክፍልን ተማሩ። ሚኒስትሪን በከፍተኛ ውጤት አልፈው እርሻና ቴክኒክ ለመማር ቢፈልጉም በአጋጣሚ ሐረር ሄደው መምሕራን ማሰልጠኛ ተቋም ገቡ ተመርቀውም ወጡ ቀሪ ሕይወታቸውን ምሽት ከ3:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#በአጋጣሚ
#የሕይወት_ገጽ

ዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 6 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ-13 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

16 Oct, 12:18


በድሬዳዋ በማረፍ ላይ የነበረ አውሮፕላን ላይ ጢስ መታየቱን አየር መንገዱ ገለጸ

ዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 6 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ-13 1446

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የበረራ ቁጥሩ ET248 ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ ጢስእንደታበት ገልጿል፡፡ አየር መንገዱ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ፤ ጢስ የታየበት አውሮፕላን በረራውን ያደረገው ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ነው፡፡

አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አየር ማረፊያ በሰላም አርፏል ያለው አየር መንገዱ፤ መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ እንደተቻለ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ፤ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

16 Oct, 11:45


የጥንታዊ እስላማዊ ሥልጣኔ መናኸሪያ እና ሕያው ሙዚየም የሆነችው የዒልም ሃገሯ ሐረር፤ በአገራችን ሐሪማዎችና መሻኢኾች ዙሪያ ልዩ ዝግጅት እያቀረበ በሚገኘው "ካስማ ሾው" ተጎብኝታለች። ዛሬ ምሽት ከ02:00 ጀምሮ ጥንታዊቷን ሐረር አብረን እንቃኛት።

#ጥንታዊቷ_ሀረር
#ካስማ_ሾው

ዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 6 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ-13 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

16 Oct, 10:31


በበርካታ የዳዕዋ መድረኮች በሚያቀርባቸው ሁለንተናን ሰቅዘው የሚይዙ ትምህርቶቹ በስፋት የምናውቀው ጥዑመ ልሳኑ ዳዒ ዶክተር ሰምሃር ተክሌ፤ ቤተል በሚገኘው አዲሱ የሙጀመዕ አት-ተቅዋ መስጂድ ለታዳሚዎች ዒልምን እየዘሩ ከሚገኙ ተወዳጅ ኡስታዞች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን በእጅጉ የሚያስፈልጉንን የአምልኮ፣ የሸሪዓ ድንጋጌዎችና ፊቅሃዊ ብያኔዎችን ከያዘው "አቢ ሹጃእ" ኪታብ ሰፋ ካሉ ማብራሪያዎች ጋር በማጣመር ግሩም በሆነ መንገድ ደርስ (ትምህርት) እየሰጠ ይገኛል፡፡

ለሁለንተናዊ ከፍታ የሚተጋው ጣቢያችን ሚንበር ቲቪም፤ አዲስ በጀመረው "ሚንበሩል ዒልም" ፕሮግራሙ ይህንን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶችን የያዘውን የ "አቢ ሹጃእ" ደርስ (ትምህርት) ክፍል አስራ ሁለት ዝግጅቱን ዛሬ ምሽት ከ12፡30 ጀምሮ ለውድ ተመልካቾቹ ያቀርባል!

#ሚንበሩል_ዒልም
#አቢ_ሹጃእ
#ክፍል_12
#ዶክተር_ሰምሃር_ተክሌ

ዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 6 - 2017 | ረቢዕ አል-ሳኒ-13 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

15 Oct, 16:15


ዱንያ እና አኺራ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/dHCgR9cBMMs 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #ቢስሚከ_ነህያ
#ዱንያ #አኺራ #dunya #akhira

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

Minber TV

15 Oct, 15:12


በአዲስ አበባ የሕዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደርጓል። አዲሱን ታሪፍ ከሥር ያገኙታል።