➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
◉ክፍል 21
▪️ሆዴ ሰፊነታቸዉ ከባለፈ የቀጠለ(1)
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭
➧ከዚህ በኋላ እዚያዉ ግብፀ ዉስጥ ፊታቸዉን ወደ ማስተማር አዞሩ። ይሄ በእንድህ እያለ በ711 ሂ.የሆኑ ሰዎች መስጂድ ዉስጥ ለብቻቸዉ አድርገዉ ደበደቧቸዉ።
➧ነገሩን የሰማዉ ብዙ ህዝብ ጦር ይዞ ተነሳ።ከፊሉ በእግረኛ ከፊሉ ደግሞ ፈረሰኛ ነዉ።የሰዎቹ ማንነት እድነግሯቸዉ ሸይኹን ጎተጎቱ። አንዱ መጥቶ"አለቃዬ"ይሄዉ ይሄ ሁሉ ህዝብ ተሰብስቧል።ሙሉ ግብፀን እንድያወድሙ ብታዛቸዉ ያደርጉታል!!አለ።ለምን ሲባል?አሉት። ላንተ"ሲባል አላቸዉ።"ይሄ ተገቢ አይደለም አሉት።
➧ሌሎቹ ተነሱና እነዚህን የበደሉህን ሰዎች እያንዳንዱነ ከቤታቸዉ እየሄድን እንገድላቸዋለን።፣ ቤታቸዉንም እናፈርሰዋለን!!ምክንያቱም ሰዉ በጥብጠዋል።ይህን ፈተናም ቀሴቅሰዋል አሉ።"ይሄ እኮ አይፈቀድም አሉ እሳቸዉ።
➧ይህስ እነሱ የሰሩት የሚፈቀድ ነዉ!?ይሄ የምንታገሰዉ ጉዳይ አይደለም።የግድ ወደ እነሱ ሄደን በሰሩት እንጋደላቸዋለን አሉ።
➧ኢብኑ ተይሚያ ግን ይከለክሏቸዋል ፣ ይቆጦቸዋል።ሰዎቹ በጣም ሲጎተጉቱ ጊዜ"እንግድህ ሀቁ የኔ ነዉ ወይ የናንተ ነዉ፣ወይንም ደግሞ የአላህ ነዉ። ሀቁ የኔ ከሆነ እኔ ይቅር ብያለሁ።
➧ሀቁ የእናንተ ከሆነና የማትሰሙኝና የማታማክሩኝ ከሆነ የፈለጋችሁትን ስሩ።ሐቁ የአላህ ከሆነ ግን አላህ ሐቁን ከፈለገ በፈለገዉ መልኩ ይይዛል አሉ።
➧ሰዎቹ "ይሄ ባንተ ላይ የፈፀሙት ለነሱ ሐላል ነዉ?አሉ።
ኢብኑ ተይሚያህ "ይሄ የፈፀሙት ነገር የሚመነዱበት አጁር የሚያገኙበት ነዉ አሉ።
➧ሰዎቹ፦"አጁር የሚያገኙ ከሆነ አንተ ሐሠት ላይ አነሱ ግን ሐቅ ላይ ናቸዉ ማለት ነዉ።ስለዚህ ስማቸዉ፣በሚሉትም ላይ ተስማማ"አሉ።
➧ኢብኑ ተይሚያህ፦ጉዳዩ እንደምታስቡት አይደለም። እነሱ ምናልባተ ሐቅን ለመረዳት ጥረዉ በጦረታቸዉ የተሳሳቱ ሊሆኑ ይችላል።እዉነትን ለማግኘት ጥሮ የተሳሳተሰዉ አጂር እንዳለዉ ይታወቃል አሉ።
➧ሰዎቹ፦"እሺ ተነስና አብረን ወደ ካይሮ እንሂድ አሉ።
➧ኢብኑ ተይሚያህ፦አይሆንም አሉ።የዐስር ወቅት ሲጠይቁ እንደተቃረበ ነገሯቸዉ።ለዐስር ሶላት ወደዚያዉ ወደ ተደበደቡበት መስጂድ አመሩ።"አለቃ!ሰዎቹ ሊገድሉህ ወስነዋል።መስጂድ ዉስጥ ደግሞ ከሌላ ቦታ በተለየይህን ማድረግ ይመቻቸዋል።
➧ስለዚህ ባለህበት ስገድ"አላቸዉ አንዱ።ፈቃደኛ ስላልሆኑ እዚያዉ ለመስገድ ተነሱ።ብዙ ህዝብ ተከተላቸዉ።መንገዱ ተጨናነቀ።አንዱ መንገድ ዳር ወዳለ መስጂድ እየጠቆመ ህዝቡ በግፊ እንዳይሞት ይቀንስ ዘንድ ለአፍታ በዚህ መስጂድ ገብተህ ተቀመጥማ አላቸዉ። ገቡና ቆሙ።
➧ሰዉ ቀለል ሲል ወደ ጥንታዊ ትልቁ መሰጂድ ጉዟቸዉን ቀጠሉ። መንገድ ላይ ቼዝ የሚጫወቱ ሰዎች አገኙ።ቼዙን አንስተዉ በመገልበጥ በታተኑት። ጉዟቸዉን ቀጥለዋል። ሰዎቹ ከአሁን አሁን ገደሏቸዉ እያሉ ነዉ።
➧ወይም መስጂድ ሲገቡ ከነጓደኞቻቸዉ ቆልፈዉባቸዉ ይገድሏቸዋል ብለዉ ሰግተዋል። መስጂድ ደረሱ። ሁለት ረከዐዎች ሰገዱ። ዐስር ተሰገደ። ከዚያም ተነስተዉ "አልሐምዱሊላሒ ረቢል ዓለሚን"ብለዉ ንግግራቸዉን ከፈቱ።
➧ ፈተና የተነሳበት ርእስ አንስተዉ አሰከ መግሪብ አዛን ድረስ ተናገሩ።
✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል....................