በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 2:1-7፡ "ወተወሊዶ እግዚእ ኢየሱስ" - "ኢየሱስም በይሁዳ ቤተልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና፥ እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋራ፤ የካህናትንም አለቃዎች የሕዝቡንም ጻፊዎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው። እነርሱም፦ አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ከይሁዳ ገዢዎች፡ ከቶ አታንሺም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና፥ ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፏልና፥ በይሁዳ ቤተልሔም ነው አሉት። ከዚህ፡በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ።ወደ፡ቤተ፡ልሔምም፡እነርሱን፡ሰዶ፟፦ኺዱ፥ስለ፡ሕፃኑ፡በጥንቃቄ፡መርምሩ፤ባገኛችኹትም፡ጊዜ፡እኔ፡ደግሞ፡መጥቼ፡እንድሰግድለት፡ንገሩኝ፡አላቸው። እነርሱም፡ንጉሡን፡ሰምተው፡ኼዱ፤እንሆም፥በምሥራቅ፡ያዩት፡ኮከብ፡ሕፃኑ፡ባለበት፡ላይ፡መጥቶ፡እስኪቆም፡ድረስ፡ይመራቸው፡ነበር። ኮከቡንም፡ባዩ፡ጊዜ፡በታላቅ፡ደስታ፡እጅግ፡ደስ፡አላቸው። ወደ፡ቤትም፡ገብተው፡ሕፃኑን፡ከእናቱ፡ከማርያም፡ጋራ፡አዩት፥ወድቀውም፡ሰገዱለት፥ሣጥኖቻቸውንም፡ከፍተው፡እጅ፡መንሻ፡ወርቅና፡ዕጣን፡ከርቤም፡አቀረቡለት። ወደ፡ሄሮድስም፡እንዳይመለሱ፡በሕልም፡ተረድተው፡በሌላ፡መንገድ፡ወደ፡አገራቸው፡ሄዱ። እነርሱም፡ከኼዱ፡በዃላ፥እንሆ፥የጌታ፡መልአክ፡በሕልም፡ለዮሴፍ፡ታይቶ፦ሄሮድስ፡ሕፃኑን፡ሊገድለው፡ይፈልገዋልና፥ተነሣ፥ሕፃኑንና፡እናቱንም፡ይዘኽ፡ወደ፡ግብጽ፡ሽሽ፥እስክነግርኽም፡ድረስ፡በዚያ፡
ተቀመጥ፡አለው።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨