ለወንዙ ገደብ በሰጠ
ለውቅያኖሱ ማረፊያ የሰፈረለት
ማዕበል ወጀቡን በቃሉ ገሳጭ
ባህሩን እንደመስታወት በስጋ ረጋጭ
መልኮትን ከስጋ ጋራ አንድ አድርጎ ያዋሃደ ፣
ጠፈር ሃኖስ ዋኖሱን ትቶ እንደምን ዮርዳኖስ ሄደ ?!
እንደምን ዮርዳኖስ ሄዴ?!
በእሳት አጥማቂ ተብለህ በወዳጅህ ተሰብኮልህ፣
የህይወት ሁሉ ወሃ ሆነህ?!
ዮርዳኖስ በምኑ ሳበህ?
እንዴት ወደ ወሃ ሄድህ አንተ ዮርዳኖስ ምን ምስጢር አለህ?።
ዋ ዮርዳኖስ !
አንቺ የወንዞች ሁሉ ንጉስ !
ዋ ዮርዳኖስ !
የቀላያት ሁሉ ዳኛ ፣
የማያት ሁሉ እረኛ !
የምድር የዳርቻዋ አድባር ፣
የፍጥረተ ወንዝ በኩር !
ዋ ዮርዳኖስ !
እንደምን ሸሸሽ ወደኋላ ፣
እንደምን ቆምክ ካለ ባላ፣
እንደው !
ስንቱ ጉድ ተሰማልን ፣
ስንት እንግዳ አስተናገድን ፣
በፍጥረቱ በውልደቱ ስንደመም ፣
ሌላ መንክር ተገለጠ በዮርዳኖስም ፣
ቤተልሔም ሲደመሙ ሰባ ሰገል፣
አሁን ደግሞ ምን ያቅርቡ ? ለፍቅሩ ቃል፣
አይ ዮርዳኖስ !
ምን ምስጢር አለ የቀበርኸው?
ታላቁ ጌታን ና ግባ ያልኸው?!
አይ ዮርዳኖስ!
.....
እስኪ ኑ #ዮርዳኖስ ሲያፈገፍግ እዩ
ዮሐንስ ሲያጠምቅ ክርስቶስን ሲያዩ!
...✍Solomon Adugna
January ,2024