Tofik Bahiru @fiqshafiyamh Channel on Telegram

Tofik Bahiru

@fiqshafiyamh


fiqshafiyamh (English)

fiqshafiyamh is a Telegram channel dedicated to sharing inspiring and thought-provoking content that aims to uplift and empower its followers. The channel, managed by the creative mind of Tofik Bahiru, offers a unique blend of motivational quotes, insightful readings, and beautiful imagery to brighten up your day. Tofik Bahiru, a passionate individual with a desire to spread positivity and wisdom, curates each post with care and attention to detail, ensuring that every message resonates with those who come across it. Whether you're looking for a boost of motivation, a moment of reflection, or simply some inspiration to get through the day, fiqshafiyamh has something for everyone. Join this thriving community today and let the uplifting content fill your feed with positivity and encouragement.

Tofik Bahiru

10 Nov, 14:14


ሰይዲና አቡሁረይራ [ረዲየላሁ ዐንሁ] የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል: ‐
«አላህ ጀነትን ከፈጠረ በኋላ ጂብሪልን [ዐለይሂ ሰላም] «ሂድና ተመልከታት!» አለው።

ጂብሪል ተመለከታትና እንዲህ አለ: ‐ «በልቅናህ እምላለሁ! ስለርሷ የሰማ ማንም ሰው ወደርሷ መግባቱ አይቀርም።»

ከዚያም አላህ ነፍስ በምትጠላው ነገር ከበባትና «ሂድና ተመልከታት» አለው። ሂዶ ተመለከታትና «በልቅናህ እምላለሁ! ማንም እርሷ ውስጥ አይደባም ብዬ ሰጋሁ!» አለ።

እሳትን የፈጠረ ጊዜም ጂብሪልን «ሂድና እያት» አለው። ሄዶ ተመለከታትና «በልቅናህ እምላለሁ! ስለርሷ የሰማ ማንም ሰው እርሷ ውስጥ አይገባም።» አለ።

ከዚያም አላህ ነፍስ በምትወዳቸው [እኩይ] ስሜቶች ከበባትና «ሂድና ተመልከታት» አለው።

ጂብሪልም ተመለከታትና እንዲህ አለ: ‐ «በልቅናህ እምላለሁ! ማንም ሰው እርሷ ውስጥ ከመግባት አይተርፍም ብዬ እሰጋለሁ።» አለ።»
ኢብኑ አቢዱንያ ዘግበውታል።

Tofik Bahiru

03 Nov, 09:23


ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ክፍል ሠላሳ አንድ:‐ የዒድ ሶላት (ሶላቱል‐ዒደይን)
📆 ጥቅምት 24/ 2017 ዓ. ል.

Tofik Bahiru

01 Nov, 18:49


በርካቶቻችን በቀልብ ድርቀት ፈተና ውስጥ ወድቀን በጭካኔ ህመም እየተሰቃየን ይሆናል።
አንዳንድ ሰዎች ግን ፈተናቸው ተቃራኒ ነው። በቀልብ ልስላሴና በቀልብ ቅጥነት ስር ወድቀው የሚሰቃዩ አሉ። የነርሱ ስቃይ ከባድ ነው!
:
መከረኛ በሆነው በዚህ ዓለም ውስጥ ቀልበ ቀጭን መሆን ከባድ ነው። የሰብዓዊው ፍጡር እንግልት በጠናበት በዚህ ዓለም እዚህም እዚያም ለሚወድቀው ነፍስ ማዘን መራር ነው። ፀሀይ ወጥታ እስከምትጠልቅ ስንት ዓይነት የሰዎችን ስቃይና ሰቆቃ እናያለን?
ቀልበ ቀጭኖች የሌሎችን ስቃይ እንደራሳቸው ስቃይ ይመለከታሉ። በሰው ሃሳብ ይብሰለሰላሉ። በጭንቀታቸው ይብሰከሰካሉ። በሰዎች ህመም ይታመማሉ። ከምላሳቸውና ከኪሳቸው እምባቸው ይቀድማል።
ሩኅሩኅ ናቸው። ለሰዎች መልካምን ይመኛሉ። በሰው ላይ በሚደርስ ክፉ ነገር ይጨነቃሉ። ሰዎች በእጦት ከተረበሹ እነርሱም ያላቸውን ሰጥተው በእጦት ከሚሰቃዩት ጋር ራሳቸውን ይቦድናሉ። የሚሰጡት ካጡም መለገስ ባለመቻላቸው በመቆጨት በለቅሶ ይመለሳሉ።
:
እነዚህ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው። በህይወቴ ከሦስት የማይበልጡ ሰዎች ከነዚህ እንደሚመደቡ እመሰክርላቸዋለሁ። ምቾትን አያውቋትም። በእርግጥ በዓለሙ ስቃይ ይሰቃያሉ። ነገርግን ስቃያቸው ቢበረታም የጀነት ናቸው። እንደውም ያለ ሂሳብ ጀነት ከሚገቡት የበሯ ከፋቾች ናቸው! በክብር የሚገቡበት የግል በርም ሳይኖራቸው አይቀርም!
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ልባቸው እንደ ወፍ ልብ የሆኑ ሰዎች ጀነት ይገባሉ!»
በዚህ ሐዲስ ላይ «የወፍ ልብ ያላቸው» የተባሉት ሩኅሩኅ ሰዎች ናቸው ተብሏል በአንድ ተፍሲር።
አላህ ርኅራኄን ይስጠን!
https://t.me/fiqshafiyamh

Tofik Bahiru

01 Nov, 09:22


ከተወዳጁ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በስተቀር ማንም ሰው በዱንያ ያንተ ቅርብ ወዳጅ ቢሆን እንኳን በቂያማ ቀን ስላንተ ሊጨነቅና ሊያስብ አይችልም።
እርሳቸው ግን በቂያማ ቀን የፍጥረት ሁሉ መሸሸጊያ፣ የኡመታቸው መጠጊያ ናቸው።
#ፊዳሁ አቢ ወኡሚ

Tofik Bahiru

28 Oct, 17:42


አላህ ስላዘነልን ሲሳያችንን በእጁ አደረገ።…
ከተወለድን ጀምሮ እስከ ሞት ድረስ የተመደበልንን ሲሳይ በአንድ ጊዜ በእጃችን ቢሰጠን ኖሮ ብዬ አሰብኩ። የምንበላውን፣ የምንጠጣውን፣ የምንጓጓዝበትን፣ መኖሪያ ቤታችንን… በአንድ ላይ እንካችሁ ቢለን የምንለፋው ልፋት አስፈራኝ። በዚህ ነገር ውስጥ ያለው የአላህ እዝነት ታወሰኝ።
:
… ትልቅ መጋዘን ያስፈልገን ነበር። መቆጣጠርና ማስተዳደሩም መከራ ነው። ከቦታ ወደ ቦታ ስንንቀሳቀስ የሚሆነውን ደግሞ አስቡት!…
ለምሳሌ: የኑሮ አድራሻውን ከአፍሪካ ወደ ምስራቅ ኢሲያ የሚለውጥ ሰው ምን ዓይነት ከባድ ሸክም ይኖርበታል?!…
ሪዝቃችንን ማስተዳደር ራሱ የጭንቀት ምንጭ ይሆንብን ነበር። የሚበላሸው እንዳይበላሽ፣ የሚሰረቀው እንዳይሰረቅ…
:
… ትካዜንም ይፈጥራል። ሰውየው በእጁ ያለውን ሪዝቅ መጨረሱ የሞት ቀጠሮው መድረሱን ያመለክተዋል። ከመጨረሻዋ ጉርሻ በኋላ አይኖርም። ሟች ነው!
ስለዚህ በሚጠቀመው ሪዝቅ ልክ እድሜውም እያለቀ መሆኑን ይረዳል። በሲሳዩ ከመደሰት ይልቅ ይሳቀቃል።
:
አላህ ሲሳይን ከመስጠቱ በላይ ሪዝቃችንን በእጁ ማድረጉ ደግሞ የእዝነቱ ጥግ ነው!
ያ #ረዝ‐ዛቅ! ያ #ረሕማን!

Tofik Bahiru

27 Oct, 18:39


«ምርጡ ሙእሚን»
===========
አንዳንዴ አላህ በማይመቹ ሰዎች ይፈትንሀል። ለምን?
በውስጥህ ያለን የሆነ እንከን ለማስተካከል። ስብእናህን በሆነ መንገድ ለመለወጥ።…
ጭፍን ፅንፈኛ ይገጥምህና ትእግስት ትማራለህ። ራስ ወዳድ ጉረኛ ይገጥምህና ጥበብና ብልሀት ትማራለህ።… የተለያየ ክፉ የሚባል ጠባይ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ይገጥሙሀል። በዚያውም አላህ ያንተን ጠባይ ያርቃል። ለምሉእነት ያቀርብሀል።…
ሁሉንም ሰው በህይወትህ ውስጥ የኸዲርን ሚና እንዲጫወት ማድረግ ትችላለህ። እንደ ሙሳ ምን ልማር ማለት ብቻ ነው የሚጠበቅብህ። ይህ ሰው በህይወቴ ውስጥ በማለፉ ከአላህ በኩል ለኔ የተላለፈው መልእክት ምንድን ነው ብሎ ማሰላሰል!…
:
አንዳንዴ በተቃራኒው አስደናቂ ስብእና የተላበሱ ግሩም ሰዎች ይገጥሙሃል። ላንተ ያላቸው አበርክቶ ከፍተኛ የሆኑ፣ የሚወዱህ የምትወዳቸው፣ የሚያከብሩህ የምታከብራቸው… የነበሩ!…
በድንገት ግን በአስደንጋጭ ሁኔታ ነገራቸው ይለወጥና ሌላ ሰው ይሆኑብሃል!
ለምን?…
ሰዎች አንተን ለማቅናት የአላህ መልክተኞች ስለሆኑ ነው!
ሰዎች ሁሉ መልካሞች ከሆኑ ትእግስትን እንዴት ትማራለህ?!
ሁሉም ላንተ የተመቹ ደጋጎች ከሆኑ ይቅር ባይነትና ቻይነትን የት ታገኛለህ? ሁሉም አስተዋዮች ከሆኑ በጥበብ መኗኗርና አይቶ ማለፍን ከየት ትማራለህ?
ከመጀመሪያው የነዚህኞቹን ክፋት ብታስተውል ኖሮ ትርቃቸው ነበር። ስለዚህ የክፋት መርዛቸውን አትቀምስም። ዐፉታን አትማርም።
:
አኩራፊ ሰው ቃላትን እየመረጥክ በጥንቃቄ መናገርን ያስተምርሃል። ከመናገርህ በፊት እንድታስብ ያስገድድሀል። አስቦ መናገርን የመሰለ ምርጥ ጠባይን ተላበስክ ማለት ነው! ምላስህን መጠበቅ ቻልክ!
:
ብዙዎቻችን ልባችን ጠባብ ነው። ሰዎችን ከነልዩነታቸው ከተለያዩ ቀለማቶቻቸው ጋር ልባችን ውስጥ ቦታ ማግኘት አይችሉም። በቅድሚያ ለራሳችን ባስቀመጥነው ጠባይ የመረመርናቸውን ብቻ ማቅረብ እንሻለን። አላህ ደግሞ ልባችንን ማስፋት ይፈልጋል። ቀልባችን ለሁሉም የሰው ልጆች የፍቅር ምንጭ ይሆን ዘንድ ይከጅላል።
:
በሀሳብና በጠባይ የተለዩን ሰዎች ሁሉ ለቀልቦቻችን መድኃኒት የተሸከሙ ፈውሶቻችን ናቸው። አላህ በመሰሎችህና በሚመቹህ ሰዎች ብቻ ተከበህ እንድትኖር ያደርግ ነበር። ነገርግን አይጠቅምህም!
:
በስተመጨረሻም ሁላችንም የጎደፍን ሰዎች ነን!
ነውራችን ተሸፍኖልን ወይም ልበ‐ሰፊዎች ታግሰውን ከዙርያችን ፍቅርና እዝነት እያገኘን እንኖራለን!
የአላህ ነቢይ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል: ‐ «በሰዎች መካከል እየኖረ ክፋታቸውን ችሎ የሚያሳልፍ ሙእሚን በሰዎች መካከል የማይኖርና ክፋታቸውን ከማይታገሰው ሙእሚን በላይ የተመረጠ ነው።»
https://t.me/fiqshafiyamh

Tofik Bahiru

24 Oct, 19:50


ሶላት ዐለን‐ነቢይ [ﷺ] እና ጁሙዐን ምን አገናኛቸው?
========

የሳምንቱ ሌሊቶች በታላቅ የዒባዳ ዘርፍ [በተሀጁድ ሶላት] መለዮ ሲደረግላቸው ለአላህ ነቢይም [ﷺ] ከዒባዳ ውስጥ ከእርሳቸው ጋር የሚያያዝ ድርሻ ተደረገላቸው። የጁሙዐ ሌሊት ላይ ልዩ የሶለዋት ድግስ ተደነገገ። የእለቱም ሶለዋት የተለየ እንዲሆን ተደረገ።

ይህ የአላህ ልማድ ነው። ምንጊዜም ወደ ዒባዳ እንድንዞር ሲያዝዝ ሁሉንም የዒባዳ ዘርፍ እርሱን ከመዝከር ጋር የሚወዳቸውን ነብይ [ﷺ] ማስታወስም እንዲካተትበት ያደርጋል።

ሸሃዳ የኢስላም መግቢያ፣ የመድኅን ሰርተፍኬት ነው። ሁለት ክፍል አለው። አንዱ የአላህ፤ ሌላኛው የነቢይ [ﷺ]

አዛን ውስጥ አላህን እንደምናወሳው እርሳቸውንም እንዘክራለን።

ሶላት ውስጥ ከአላህ ጋር እንደምናወራው እርሳቸውንም እንድናወራ ታዘናል።

ሌሎችም የዒባዳ ዘርፎች የአላህን ልእልና በመሰከርንበት ግብር የርሳቸውንም ከፍታ እንድናስብ የሚያደርግ ክፍል አይጠፋቸውም።

አላህ ነቢዩን [ﷺ] በጣም ይወዳቸዋል። ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ የበላይ፣ የኸልቅ ሁሉ ዓይነታ አድርጓቸዋል። ለዚህ ማሳያም ከየዒባዳው አይነት ለርሳቸው ዝክር የሚሆን ክፍል ይመድባል። ወደ አላህ የሚያደርስ ብቸኛው መንገድ መሆናቸውን ለማሳበቅ፣ በኡመታቸው ላይ ያላቸው መብት ግዙፍ መሆኑን ለማሳየት፣ ውለታቸው የማያልቅ መሆኑን ለማስገንዘብ ሁሌም እርሱ በተወሳ ቁጥር እንዲወሱ ያደርጋል።
አላህ እርሳቸውን ይወዳል። የሚወዳቸውንም ይወዳል!…

Tofik Bahiru

24 Oct, 18:37


ሙት ወገኖቻችንን ከመልካም ምንዳችን አናጋራቸው!
:
ሙስሊም ዐኢሻን [ረዐ] በማጣቀስ እንደዘገቡት: — «አንድ ሰው ነቢዩን [ﷺ] እንዲህ በማለት ጠየቃቸው: ‐ «እናቴ በድንገት ሞተች። ነገርግን መናገር ችላ ቢሆን ኖሮ ሶደቃ ታደርጋለች ብዬ እገምታለሁ። ብመፀውትላት ምንዳውን አገኝ ይሆን?»
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] «አዎን።» በማለት መለሱ።»
:
ኢማም ነወዊይ [ረሒ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «በዚህ ሐዲስ መሰረት ለሞተ ሰው ምፅዋት ማድረግ እንደሚወደድ መገንዘብ ይቻላል። ምንዳውም ለሟች ይደርሰዋል። መፅዋቹም ምንዳ ይኖረዋል። ይህ በሙሉ ሙስሊሞች ያለ ልዩነት የተስማሙበት ነጥብ ነው።»
ሸርሕ ሶሒሕ ሙስሊም፥ ቅፅ 11፥ ገፅ 84
https://t.me/fiqshafiyamh

Tofik Bahiru

24 Oct, 18:36


ኢማም ሰኻዊይ እንደሚሉት ሶላት ዐለን‐ነቢይ ማድረግ ለወላጆች መልካም ከመዋል ይቆጠራል። ምክንያቱም ለነቢዩ ﷺ ሶለዋቱን የሚያደርሰው መላኢካ «ሙሐመድ ሆይ እገሌ የእገሌ የእገሊት ልጅ ሶለዋት አድርጎብሃል።» ይላል። በልጅ በረካ አባትና እናት ይጠራሉ።
:
በአላህ መልክተኛ ﷺ ፊት በተከበረው የመላኢካ ልሳን ወላጆችን ማስጠራት በእርግጥም ከፍ ያለ ውለታ ነው!
:
ጁሙዐ ከዐስር በኋላ ሰማንያ ሶለዋት እንዳይረሳ!
https://t.me/fiqshafiyamh

Tofik Bahiru

21 Oct, 18:14


ዓሚር ኢብኑ በህደላ [ረሒ] ሐጃጅ ኢብኑ ዩሱፍ በስቅላት በገደላቸው ሰዎች አጠገብ ሲያልፉ በልባቸው እንዲህ አሉ: ‐ «ጌታዬ ሆይ! በዳዮችን መቻልህ ተበዳዮችን ጎዳ!»
:
ከዚያም ወደቤታቸው ተመልሰው ሲተኙ በህልማቸው ቂያማ ቆሞ ተለመከቱ። እርሳቸው ጀነት የገቡ ይመስላቸዋል።. በስቅላት የተገደለውን ሰውም ከሁሉም ከፍ ካሉት የላይኛዎቹ የጀነት ሰዎች ዘንድ የሚያዩት መሰላቸው። ከወዲያ ደግሞ እንዲህ የሚል አዋጅ ይነገራል:‐ «በዳዮችን መቻሌ ተበዳይን ከበላይኞቹ የበላይ አድርጎታል!»
:
ተበዳይ ተሰቅሎ ሲገደልኮ በገሀድም እግሮቹ ከሰቃዮቹ አናት በላይ ነው!

Tofik Bahiru

20 Oct, 16:35


መልካም ነገሮች የሚኖሩት ክስተቶች ላይ ሳይሆን በልባችን ውስጥ ነው። መልካም ዐይን ሲኖረን በሁሉም ነገር ላይ ያለውን ውበት እናያለን።
ሰይድ አቡበክርና አቡጀህል በእኩል አንድን ክስተት አይተዋል፤ ሰይዳችን ሙሐመድን [ﷺ]።
ዐይናቸውና ልባቸው ግን ተለያይቷል። አቡበክር በንፁህ ልብ ውበትን ለማየት በታደለ ዐይን አዩ። አቡጀህል በቆሻሻ ልብ ውበትን ማየት በማይችል ዐይን አየ።
ውሳኔያቸውም ተለያየ!
መልካሙን እይ። ክፉን ሸፍን።
ከፈለጉ ሞኝ ነው ይበሉህ፤ አንተ ግን በጎ አስብ!
:
t.me/fiqshafiyamh

Tofik Bahiru

19 Oct, 17:24


ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ክፍል ሠላሳ:‐ የፍርሃት ሶላት (ሶላቱል‐ኸውፍ)
📆 ጥቅምት 09/ 2017 ዓ. ል.

Tofik Bahiru

19 Oct, 02:20


በሰሞኑን ክስተት ተከታታይና የተለያዩ ስሜቶች ሲፈራረቁብኝ ቆይተዋል። የመጨረሻው ትእይንት ግን የሚደንቅ ነው!
አንበሳው! በከባድ ሁኔታ ቆስሎ፣ በደም ተጨማልቆ ተቀምጧል። የቀረችውን እስትንፋስ እንኳን በቢላሽ ማሳለፍ አልፈለገምና በእጁ በቀረችው ዱላ ጠላቶቹን ለመምታት ሰነዘራት!…
«በአንዳችሁ እጅ ችግኝ እያለ ቂያማ ቢደርስና ቂያማው ከመቆሙ በፊት መትከል ከቻለ ይትከላት።» የአላህ መልክተኛ []

ይህ ትእይንት ከፊልም የተቀነጨበ ተውኔት አይደለም። በጠላቱ ሳይቀር የተመሰከረ የእውን ክንውን ነው!
:
የተመለከትነው ክስተት ጥልቅ ምክርና አስተምህሮን አዝሏል። ለበርካቶች የመንፈስ ምግብና የትጋት ምንጭ ይሆናል ተብሎም ይታሰባል። በአላህ መንገድ ለመሰዋት መናፈቅ በእውነተኞች ልብ ውስጥ የሚዘልቅ ጥልቅ ነገር እንጂ የምላስ ወግ እንዳልሆነ ያስረዳል!
:
በተረፈው ሰውየው የሕያ ነው። ስሙ ህያውነትን ያሳያል። የሸሂዱ ነቢይ የሕያም [ﷺ] ስም ነው። ሸሂድ ደግሞ ጌታው ዘንድ ህያው ነው!
አላህ ይቀበለው! መሬታቸውን ለተቀሙ፣ ለዲናቸውና ለክብራቸው ለሚፋለሙ ድኩማን ወንድሞቻችንም ድሉን ይስጥ!
አሚን!

Tofik Bahiru

16 Oct, 18:50


በርካታ በሮችን አንድ በአንድ ስታንኳኳ አይቶሃል። የሀብታም በር፤ የባለስልጣን በር፤ የባለ ዝና በር፤ የዘመድ በር፤… በየበሩ ስትወድቅ፣ በየመንገዱ ስትሰናከል አይቶሃል። አንዱ ሲያስከፋህ፣ ሌላው ሲያስደነግጥህ፣ ሦስተኛው ሲያሾፍብህ፣ ሌላኛው ሲያሴርብህ… ተመልክቷል።
ቀጥ ብለህ ስትቆም፣ ስትንዳለጥ፣ ስትወድቅ፣ ስትነሳ፣ ስትለፋ፣ ስታለቅስ… በመንገድህ ሁሉ የርሱን ደጃፍ እየዘለልክ ስትባትል አይቶሃል።  የርሱን ደጃፍ የምትረግጥበትን ቀን እየጠበቀ ነው። ከሁሉም ደጃፍ መፍትሄን አጥተህ በተሰበረ ልብ፣ በለቅሶ ተሞልተህ፣ በሀፍረት ተውጠህ፣ ተፀፅተህ በርሱ ግቢ የምትነጠፍበትን ቀን በናፍቆት ይጠብቃል።
:
«ሁሉም ቢገፉህ እኔ ደጋፊህ ነኝ!
ፍጥረት ቢጠሉህም እኔ ወዳጅህ ነኝ!
ቢያቆስሉህ እኔ ሀኪምህ ነኝ!
ከጎናቸው ቢያርቁህም እኔ ቅርብህ ነኝ!
ወደኔ ና!
ወደ እልፍኜ ጎራ በል!
ምንጊዜም ስትፈልገኝ አለሁ!
ከኔ ውጪ ሌላን አትጥራ! ምላሽ ከመስጠት አልታክትም! እኔ እበቃሀለሁ! ችግርህን እቀርፋለሁ! ጭንቀትህን እፈታለሁ! አግዝሃለሁ! እረዳሃለሁ! ስታስበኝ አስብሀለሁ! ስትለምነኝ እሰጥሀለሁ!»
እያለ!…
:
ስለ ''አል‐ወዱድ'' [ﷻ] ነው የማወራው!

Tofik Bahiru

16 Oct, 05:07


ፍየል አርደው ስጋዋን በሙሉ ሶደቃ አደረጉና አንዲት እግር ብቻ ቀረች። የአላህ ነቢይ [ﷺ] ስጋው የት እንደደረሰ ሲጠይቁ «ሁሉም [ተሶድቆ] አንድ እግር ብቻ ቀረ።» አሏቸው፤ በኛ ቋንቋ።.…
እርሳቸውም  «ሁሉም ቀረ [አለ]። አንድ እግሯ ሲቀር።» አሉ፤ በአኺራ አፍ!
:
ጀሊሉም «እናንተ ዘንድ ያለ አላቂ ነው። አላህ ዘንድ ያለ ግን ቀሪ ነው።» ብሏል።
:
ወዳጆቼ እየተረዳዳን!