የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe @yahyanuhe Channel on Telegram

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

@yahyanuhe


﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe (Amharic)

እንኳን ወደ የሕያ ኢብኑ ኑህ ትምህርት ቤት ይላኩ! ይህ እግር ፣ ዘለፋ፣ የሃማና ስነ-ምህረት እና ፕሮፌሰር ቤት ነው። የህይወትና ሰውነት በድምቀት የሚያሳይ ሰው እና ተምሒኬ ይህ ቤት፣ ኢብን እና ኑህ, በጥቅም ህዝብ ያለ መረጃ የለውም። ምናልባት የተማሪዎችን በሀገራችን ይዞታል እና የእኛ ህይወትን በአንድነት እና አደራረግ መስለኛ እና እንዲሁም ችግር ዝናብ አሉት። በተጨማሪም የሕይወት ቤት ተሰማሁ።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

11 Jan, 20:01


የገዛ ህዝባቸውን በእምነታቸው ምክንያት ሒጃብና ሶላት ለሚከለክል የፖለቲካ ኢሊት ምርኩዝ የሆነ ግለሰብ ሌላን ሰው ሙስሊምነቱን በመጠቀም በሴኩላሪዝም ለማሸማቀቅ ሲሞክር ማየት ያስገርማል።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

10 Jan, 06:57


ዲያቆን ቴዎድሮስ አበበ ከሰሞኑ የነበረውን የ"አእላፋት መዝሙር" አስመልክቶ ተቃውሞውን አሰምቷል። የቤተ ክርስቲያኗን ስርኣት የተከተለ አይደለም የሚል ነው ወቀሳው፣ ይህ አካሔድ የምዕራባውያኑን የካቶሊክ መንገድ የሚወዱ "አፍቃሪ ካቶሊኮች" ሀሳብ እንደሆነ ገልጿል። እንዳለውም የነዚያን ግብረ ሰዶማውያን ሰዎች አካሔድ መቀበል ከሆነ ጉዳዩ እንደ ሀገር ለሌላውም ስጋት እንደሆነ ግልጽ ነው።

https://vm.tiktok.com/ZMkPxUFrC/

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

09 Jan, 07:59


የዚህ ግሩፕ አላማ በቲክቶክ የሚለቀቁ የንፅፅር ቪዲዮዎች ኮፒ ሊንክ እና ሼር ተደርገው ቫይራል እንዲወጡ ማድረግ ነው። ወደዚህ ግሩፕ የምትቀላቀሉ ሰዎች ለዚሁ ተልዕኮ ብቻ የምትፈልጉ መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል።

® https://t.me/ethiomuslimTik

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

07 Jan, 15:11


"አምላክ ከፈጠራቸው ፍጡራን ማህጸን ተወልዷል" የሚለውን ታሪክ ከልቡ የተቀበለን ሁሉ አላህ ቀናውን መንገድና አቅሉን እንዲመልስለት ዱዓየ ነው።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

06 Jan, 18:00


የባቲ ከተማ የቀድሞ ከንቲባና እና የአቢዘር ማኅበረሰብ አቀፍ ልማት ድርጅት የፕሮጀክት ኃላፊ የነበሩት አቶ አህመድ ለስራ ጉዳይ ከከሚሴ ሲመለሱ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ወደ አኼራ ሒደዋል፣ አላህ ይዘንላቸው ቀብራቸውንም ሰፊ ያድርግላቸው። ለየቲም ጉዳይ ሲባትሉ ውለው የዱንያ ፍጻሜያቸው በዚያው መንገድ ሆነ፣ አላህ ልፋታቸውን ከተቀበላቸው ያድርጋቸው።

አቢዘር ከምስረታው ጀምሮ በርካታ ፈተናዎችን የተሻገረ ተቋም ነው። ከብርቱ ወንድማችን ጀማል እልህ አስጨራሽ ጥንሰሳ ጀምሮ አላማውን የተረዱ በርካቶችን ከጎኑ አሰልፎ ሰፊ ስራዎችን እየሸፈነልን ያለ ተቋም ነው። አላህ ይቀበላችሁ፣ ወንድማችሁንም የሚተካ የተሻለ መሪ ይወፍቃችሁ።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

06 Jan, 14:30


ኦርቶዶክስን ከማደስ ወደ ማዘመን

(ሀሳቡ ላይ ብቻ አስተያየት ስጡ፣ ስድብ አይፈቀድም)

የተሐድሶ እንቅስቃሴ እንዳቆጠቆጠ ገደማ ማኅበረ ቅዱሳን አንድ አነስተኛ ጥናት አዘጋጅቶ ነበር። በወቅቱ ተሐድሶ የሚባሉ አካላት ዋነኛ መከራከሪያ የነበረው ራሳቸውን የቤተ ክርስቲያኗ አለኝታና ተቆርቋሪ አድርጎ ማቅረብ ነበር። ቤተ ክርስቲያኗን እንደሚቀበሉና ጠንካራ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖር እየታገሉ እንዳሉ አብዝተው ይገልጹ ነበር። ማኅበረ ቅዱሳን ይህንን እንዲህ ሲል ይጠቅሰዋል፦

"ተሐድሶዎች በርግጥ ኦርቶዶክሳውያን ናቸው? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውን ይቀበላሉ? ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸውስ ተሐድሶ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ ችግሮች ተፈትተው ጠንካራ የሆነች ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማየት የሚደረግ ትግል ነው?"

(የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ፥ አዘጋጅ ማኅበረ ቅዱሳን ገጽ 36)

መጽሀፉ ይህንን ጥያቄ ያነሳበት ምክንያት የተሐድሶ ሰዎች ከነሱ በላይ የቤተ ክርስቲያኗ ተቆርቋሪ የሌለ እስኪመስል ድረስ ሰፊ ሽፍን እንቅስቃሴ ያደርጉ ስለነበር ነው። መጋቢ በጋሻው እና ዘማሪ ትዝታው (በድሮ የማዕረግ ስማቸው) EBS ቴሌቭዥን ላይ በገዙት የእሁድ ጠዋት የአየር ሰአት ትልቅ ሽፋን ይሰጡ የነበሩት የእቅበተ እምነት ስራዎች ላይ ነበር። በተለይም በፕሮቴስታንት በኩል የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በመሞከር የኦርቶዶክሱን ቀልብ ለመያዝ ይጥሩ ነበር።

ኢየሱስ በዮሐንስ ወንጌል ማርያምን "አንቺ ሴት" ማለቱን ተከትሎ በፕሮቴስታንቶች ለሚነሱ ጥያቄዎች ሰፊ ውይይት በማድረግ ለመመለስ ሲሞክሩ በግሌ በወቅቱ ተመልክቻለሁ። ከዚያ እይታየ በኃላ እስኪያቆሙ ድረስ ተከታትያቸዋለሁ። ትኩረታቸው እቅበተ እምነት ተኮር ከመሆኑ ጋር "የኦርቶዶክሱ አለኝታ" ተደርገው በመሳላቸው ሳቢያ የጠዋት ፕሮግራሙን መከታተሌን አስታውሳለሁ።

እነዚህ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ መስለው መቅረባቸው ምዕመኑን በቀላሉ እንዲያሳስቱት ጠቅሟቸዋል። ማኅበረ ቅዱሳን ለዚህም ነበር በመጽሀፉ ይህንን ጉዳይ ለምዕመኑ ለማብራራት የተለያዩ አቋሞችን በመዘርዘር የተሐድሶ ሰዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አቋም እንደሚለይ ለማሳየት የደከመው። በመጽፋቸው ከዘረዘሯቸው ነጥቦች ውስጥ የተሐድሶ መለያ አድርገው ያቀረቡት የቤተክርስቲያኗን ታሪክና ትውፊት ማጣጣል ወይንም ዝቅ አድርጎ የማየት መንገድ አንዱ ነው።

የተሐድሶ ሰዎች ቤተ ክርስቲያኗን ወደ ሚፈልጉት አላማ ለማምጣት መርህ አልባ ከመሆናቸው ጋር ማንኛውም መንገድ ከመጠቀም ወደ ኃላ እንደማይሉ መጽሀፉ ይጠቅሳል። በነሱ እሳቤ በተለይም ገድላትና ድርሳናትን ማሳነስ/Undermine/ በቀላሉ ኦርቶዶክስን የማፍረስ ዘዴ ነው የሚል እሳቤ በመያዛቸው ይህኛው አካሔድ ትልቁ የስኬት መንገድ ነው። መጽሀፉ እንዲህ ይላል፦

"ስለዚህ አዲሱ ስልት “የጥንቷ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትክክል ነበረች - The ancient Orthodox was the right Church" የሚል ነው፡፡ ይህም ማለት ቤተ ክርስቲያንን ከውጭ ከመቃወም ይልቅ ውስጥ ገብቶ ምእመን፣ ካህን፣ ሰባኪ መስሎ ከፕሮቴስታንት እምነትና ባህል ውጭ ያለውን ነገር ሁሉ “ይህ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት አይደለም፣ ይህን እገሌ የጨመረው ወይም የቀነሰው ነው ´ እያሉ ቤተ ክርስቲያኗ ኦርቶዶክሳዊ ዶግማዋ፣ ቀኖናዋና ትውፊቷ በሙሉ ጠፍቶ ፍጹም የጠራች የነጣች ድሀ ፕሮቴስታንት እስክትሆን ድረስ መሥራት ነው"

(የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ፥ አዘጋጅ ማኅበረ ቅዱሳን ገጽ 45 እና 46)

ይህ የተሐድሶ መንገድ የቻለውን ያክል ምዕመን ወስዶ አገልግሎቱ ያበቃለት በመሆኑ አዲስ መንገድ ሳያስፈልግ አልቀረም። ፕሮቴስታንቶቹ ምን አይነት መንገድ እንደነደፉ በትክክል ባላውቅም በግል ካየሁት አንጻር ግን ቸርቿን ከታሪክና ትውፊቷ በማላቀቅ የማዘመን ስራ ሌላኛው አዲሱ ስትራቴጁ እንደሆነ መገመት ይቻላል።

የድሮ ምልምሎች የቤተ ክርስቲያኗ ሊቃውንት፣ መምህራንና ካህናት ሲሆኑ የአሁኖቹ ደግሞ ትምህርት ቀመስ የሚመስሉ ለቸርቿ የአለኝታነት ስሜት መፍጠርን አላማ ያደረጉ ግለሰቦች ናቸው። እነዚህ ከቀድሞዎቹ የሚለዩት ቆብና ጥምጣም ባለማድረግ እንጅ የቤተ ክርስቲያኗን ትውፊቶች ዝቅ በማድረግና ለመድረክ የማይመጥኑ አድርጎ በማቅረቡ ረገድ ልዩነት የላቸውም።

ከቀድሞዎቹ ስህተት የተማሩት ነገር ቢኖር ገድላትና ድርሳናትን በግልፍተኝነት መስደብ ልክ አለመሆኑን ነው። በቀላሉ እነዚያን መጽሀፍ ለውይይት የማይበቁ መሆናቸውን በመናገር ገሸሽ ማድረግ ከተቻለ መስደቡና ማንቋሸሹ ረጅም ጉዞን ከማሳጠር የዘለለ አስፈላጊ አለመሆኑን ነው። ይህኛው ብልጥ አካሔድ/Smart move/ ይመስላል።

በግል ለእኔ እንደ አንድ ሙስሊም ሁለቱም ተመሳሳይ ናቸው። አንድ ሰው ፕሮቴስታንትም ቢሆን ኦርቶዶክስም ቢሆን ከእምነት አንጻር የሚፈጥረው ለውጥ አለ ብየ አላምንም። እንደ ሀገር ባለን የጋራ መስተጋብር ግን የቤተ ክርስቲያኗ ትውፊት በምዕራቡ አለም በተቃኘው ዘመን አመጣሽ ጸያፍ ባህል እንዲቀየር አልመኝም። ቤተ ክርስቲያኗ ግብረ ሰዶማዊነትና መሠል ጸያፍ ተግባሮችን መቃወሟን ለመደገፍ ትውፊቷን መቀበል አይጠበቅብኝም።

በዚህ ረገድ የሀገራችን የፕሮቴስታንት ቸርቾች ተግባሩን ሊቃወሙ ይቅርና ዋናዎቹ የኛ ሀገር ቤተ ክርስቲያናት ሳይቀር በትብብር/Partner/ የሚሰሩ ከነዚሁ ደጋፊ የሆኑ የውጭ ቸርቾች ጋር ነው። እነዚህ አካላት ለችግራችን በቂ ናቸው ብየ አምናለሁ። ኦርቶዶክሱን በራሳቸው መንገድ በመለወጥ ለዚህና መሠል ምዕራባዊ ፍላጎታቸው ማዋላቸው እንደ ሀገር አደገኛውን መንገድ ከማስጀመር የዘለለ ጥቅም የለውም።

▣ ይህ መልካሙን ከመመኘት የተጻፈ የግል አመለካከት ነው

(የሕያ ኢብኑ ኑህ)

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

06 Jan, 07:14


በዛሬው እለት በኢልያና ሆቴል በተዘጋጀው "የሙስሊም ባለሙያዎች ማኅበር" የምስረታ ዝግጅት ላይ ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በተጋባዥነት የተገኘ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ ከተለያዩ አካላት ጋር ትውውቅ አድርጓል።

የሙስሊም ባለሙያዎች ማኅበር ሰፊ አላማን አንግቦ የተመሠረተ ተቋም መሆኑን ከፕሮግራሙ የተገነዘብን ሲሆን ወደፊት በሚሰራቸው ስራዎችም ማዕከላችን የራሱን በጎ አስተዋጽኦ ለማበርከት ሙሉ ተነሳሽነት እንዳለው ለመግለጽ እንወዳለን።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

Picture credit - Harun Media

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

05 Jan, 18:27


في زمنِ الجَور حُلُمٌ مَبرور
يَتراءى طَيفُهُ مِن حَولي ويَدُور
يَبعَثُ أمَلاً يَدنُو وَجِلاً
فاللَّيلُ طَغَى وتَلاشَى النُّور
يا رسُولَ الله كَم أحلُمُ لَو أَنّي
أمشِي بخُطَاك وبِذا تَرضَى عَنّي
أسْعى مَسعَاك يَغدُو همُّك هَمِّي
وأكونُ فِدا دَربِكَ هلّا تَقبَلُني
صَلَّى اللهُ وزادَ ثَناه
علَيكَ يا رسُولَ الله
يا مَن بِهُداه أسرارُ حَياة
اشفَعْ لنا يا حَبيباً لله

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

01 Jan, 14:48


በ1878 የተተረጎመው አዲስ ኪዳን፣ አሁን እጃችን ላይ በሚገኙ የመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ትርጉሞች ውስጥ የሌሉ አንቀጾች አሉት። በስፋት የሚታወቀውና ዮሀናይን ኮማ እየተባለ የሚጠራው የአንደኛ የዮሐንስ መልዕክት አንቀጽ አሁን ባሉ መጽሀፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ ባይኖርም በጥንቱ ትርጉም ውስጥ ግን ይገኛል። የዛሬው አጭር ቪዲዮ ይህንን የተመለከተ ነው፣ ተመልክተው ሼር ያድርጉት።

https://vm.tiktok.com/ZMkA5AJrW/

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

31 Dec, 19:03


ነብዩ "ﷺ" የልጅ ልጃቸውን ብልት ስመዋል በሚል በግልቡ ለሚቀርበው ክስ የተሰጠ ማብራሪያ

▣ መግቢያ

የኢንተርኔት አለም የክርስቲያን አቃቤዎች የገቡበት የምዕመን መሸሽ አጣብቂኝ በነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ስብእና ላይ ጥላሸት ይቀባልናል ብለው ያሰቡትን ማንኛውም ትርክት ከማምጣት ወደ ኃላ እንዳይሉ አድርጓቸዋል። በዚህ ረገድ ከሚጠቀሱ ትርክቶች ውስጥ ነብዩ "ﷺ" የልጅ ልጃቸውን ብልት ስመዋል በሚል የሚነሳው አንደኛው ነው። ዘገባው ሙሉ ለሙሉ ደዒፍ (ደካማ) ቢሆንም ጥቂትም ምዕመን ቢሆን ካደናገረልን በሚል ሲደጋግሙት ሰንብተዋል፣ ስለዚህ ጉዳይ እርግጡን የማያውቁ ሙስሊሞችንም ግራ ለማጋባት ሞክረዋል። ከዚህ በታች ዘገባውን እንገመግማለን።

https://hidayacomparative.org/?p=1160

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

31 Dec, 08:17


የእንግሊዝኛው የዘረኝነት ቃል የሆነው N* word (Nig**) መሠረቱ የት እንደሆነ ያውቃሉ?

እንዳለመታደል ሁኖ የቃሉ መሠረት መጽሀፍ ቅዱስ ሲሆን ቃሉም የሚገኘው በሐዋርያት ስራ 13:1 ላይ ነው። እንደሚከተለው ይነበባል፦

“በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም፦ በርናባስ፣ #ኔጌር የተባለው ስምዖን፣ የቀሬናው ሉክዮስ፣ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስ አብሮ አደግ የነበረው ምናሔና ሳውል ነበሩ።”
— ሐዋርያት 13፥1 (አዲሱ መ.ት)

በዚህ አንቀጽ ውስጥ ኔጌር የሚለው ቃል በእንግሊዝኛው Nig*er ተብሎ የተቀመጠ ሲሆን የዚህ ትርጉም መሠረት የሆነው የግሪኩ ቃል Νίγερ ነው። ይህም ማለት ትርጉሙ "ጥቁር" ማለት ነው። ግሪኩ ሲነበብም ቀጥታ ለዘረኝነት በሚውለው ቃል መሠረት neeg'-er ተብሎ ነው።

እንደ ሜሪያም ዌብስተር መዝገበ ቃላት መሠረት ቃሉ የቆዳ ቀለምን ለመግለጽ ሳይሆን የለየለት ዘረኝነትንና ጥላቻን ለመግለጽ አገልግሎት ላይ የሚውል ቃል መሆኑን ይጠቅሳል።

"..the word ranks as almost certainly the most offensive and inflammatory racial slur in English, a term expressive of hatred and bigotry..."

ባህላቸው Judeo-Christian ነው የተባሉት የክርስቲያን ሀገራት፣ የጥላቻ ቃላቸው መሠረቱ መጽሀፍ ቅዱስ መሆኑ ያሳዝናል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

25 Dec, 17:25


በቅርቡ አንድ "እፎይ" ለሚባል ሰው መልስ መስጠት ጀምሬያለሁ። ግለሰቡን የእውነትም ተከታትየው ካለማወቄ አንጻር ሰዎች መልስ እንዲሰጠው አብዝተው ቪዲዮ ሲልኩልኝ ነው በደንብ ማየት የጀመርኩት። መጀመሪያ ሳየው ጤነኛ/Stable/ አልመሰለኝም ነበር። እንደመጣለት የሚሰነዝራቸው ጸያፍ ቃላት፣ የጤነኛ የማይመስሉ አካላዊ ተግባራቱ አንድ ላይ ተደማምረው ይህ ሰው በምን ተአምር በብዙ ኦርቶዶክስ ምዕመን ዘንድ እንደ "ብጹእ" እንደታየ ደንቆኝ ነበር። "የሊቃውንት አድባር ነኝ" የምትለዋ ቤተ ክርስቲያን አቃቤዎቿ ተንጠባጥበው አልቀው የቀሩት እነዚህ ከሆኑ በእርግጥም ስለቤተ ክርስቲያኗ አሁናዊ ሁኔታ የሚጠቁመን ብዙ ነገር አለ ማለት ነው።

ወደ ዋናው አጀንዳየ ስመለስ እነዚህን ምላሽ መስጠት የጀመርኩባቸውን ቪዲዮዎች አስመልክቶ አንድ ወንድም ጋር ሀሳብ እየለተዋወጥን ነበር። በወሬያችን መሀል ተመልካች አለመኖሩ እንዳሳዘነው ነገረኝ። ግራ ተጋብቸ ቪዲዮዎቹን ገብቸ አየኃቸው፣ እይታቸውን ትቸ ቪዲዮው አስፈላጊ ነው ብለው ሼር ያደረጉ ሰዎችን ብዛት ተመለከትኩት። የአንደኛው ከ1ሺ የሚበልጥ ሲሆን የሌላኛው ደግሞ ከ2 ሺ ይበልጣል። ትምህርቱን ሼር ያደረገው ሰው ብቻ በሺ የሚቆጠር ነው። የወንድሜ የተከታታይ ማነስ ያሳዘነው ለምን እንደሆነ ገብቶኛል። ምላሽ የምንሰጣቸው ሰዎች ያላቸውን የተከታታይ መጠን በማየት ነው።

ግን መርሳት የሌለብን ተለፍቶ የተሰራን ቪዲዮ በጥንቃቄ የተመለከተ 1 ሺህ ሰው ካለ ትልቅ ነገር ነው። በየቦታው 50 የማይሞላ ሰው በአንድ ክፍል ውስጥ ለማስተማር ብዙ ኡስታዝ ተዘጋጅቶና ለፍቶ ይሔዳል። በዚህ ቴክኖሎጂ ሳቢያ 1ሺ ሰው ካየ ደግሞ ትልቅ ነገር ነው። ዋናው ጉዳይ ኢኽላሱ እንደመሆኑ መጠን እሱ ሳይሸራረፍ ካለ ስራዎች ዘመን ይሻገራሉ። እንደ አንድ ወቅት የዘመድኩን ተመልካቾች የሙቀት ሰው ሁነው በሺህ ቢከቧቸው የሆነ ቀን ሌላ የተሻለ የሙቀት አጀንዳ ሲመጣ ደግሞ ጥለዋቸው ይሄዳሉ። ከዚያ የሙቀት ተመልካች የቁምነገር ተከታታይ 100 ካሉ አጀንዳ መሆን ያለባቸው እነሱ ብቻ ናቸው።

ሰለፎች በኻለቃቸው ብዙዎቹ የሚያስተምሩት ከ10 የማይበልጥ ተማሪ ነበር። ስራቸው ግን ዘመን ተሻጋሪ ሁኖ ከምዕተ አመታት በኃላም አሁን ድረስ ተሻግሮ የማይቋረጥ ሰደቃ ሁኖላቸዋል። እኛ ከነሱ ጋር ለውድድርም የማንቀርበው ደግሞ በሚገርም ሁኔታ ከነሱ ዘመን የተሻለ ተከታታይ አለን። ህዝባችንን ወደ ሚጠቅመው ነገር ለማምጣት ከሆነም አላማችን ከወቀሳ ይልቅ ሌላ በርካታ መንገዶችን በመጠቀም መሳብ የተሻለው መንገድ ነው። የሰው ልጅ አምቢሺየስ ቢሆንም በንጽጽር ወንድሞች በኩል በተለይም በቲክቶክ እየተሰራ ያለውም ስራ መልካም የሚባል ነው፣ ነገ ደግሞ በአላህ ፍቃድ የተሻለ ይሆናል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

24 Dec, 14:10


"ሒጃብ ለብሳችሁ መማር አትችሉም" በሚል በአክሱም የሚኖሩ ሙስሊም ሴቶች ከፍተኛ እንግልት ውስጥ ናቸው። የክልሉ መጅሊስ የቻለውን ያክል ቢጥርም የሚሰማው እንዳጣ በደብዳቤ ገልጿል። እምነቱን ተንተርሶ የራስን ወገን የመጨቆን የከረመ በሽታ መቸ ይሆን የሚለቀን?ተማሪዎቹ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ከተከለከሉ 3 ሳምንት አልፏቸዋል፣ ለማትሪክ ፎርም እየተሞላ ቢሆንም ሙስሊም ተማሪዎች ግን መሙላት አልቻሉም። በዚህ አዳፋ ተግባራችሁ መጻፍ የምትፈልጉት ታሪክ ምንድን ነው?

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

22 Dec, 10:54


በደቡብ ወሎ ዞን አቅስታ የምትኖር እህታችን በመታመሟ ምክንያት ተንቀሳቅሳ መስራት አልቻለችም። ነገር ግን ቁርኣን ማቅራት ትችላለች። ከዚህ በፊትም በኦንላይን ታቀራ ነበር። አሁን መታከሚያ አጥታ ተቸግራለችና ቢያንስ አላህ ባገራላት ኢልም ቁርኣን እያስቀራች ለመድሃኒት መግዣ እንኳን እንድታገኝ መቅራት የምትፈልጉ ወይም ልጆቻችሁን ማቅራት የምትፈልጉ በዚህ ስልክ ቁጥር በመደወል አግኟት፦

09 85 33 90 51

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

22 Dec, 09:37


በቁርኣን ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከነገ ጀምሮ በአላህ ﷻ ፍቃድ በተከታታይ መመለስ እንጀምራለን። በተለይም በጥንታዊ እደ ክታባት/Manuscripts/ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች የትኩረት አጀንዳዎች ናቸው። ቲክቶክ የምትጠቀሙ ወንድምና እህቶች ተከታተሉት።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

21 Dec, 16:01


የበኒ ቁረይዛን ክስተት አስመልክቶ ተዛብቶ ለቀረበው ትችት የተሰጠ መልስ | የሕያ ኢብኑ ኑህ

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

18 Dec, 07:31


በባለፈው ስለ ኒቂያ ጉባኤና ተያይዞ ስለነበሩት የታሪክ ክፍሎቹ አውርተናል። ከኒቂያ በፊት የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በኒቂያ የእምነት መግለጫ ዙሪያ ያላቸው አስተምህሮ ስምሙ ነበርን? የሚለውንም ዳሰናል።

ዛሬ አላህ ቢፈቅድ ለክርስትናው አለም መፈጠር/መቀነን/ መሠረት ስለሆኑት ሌሎች ጥንታዊ ጉባኤያት እንዳስሳለን።

ማታ በወንድማችን አብዱልከሪም ቤት ቲክቶክ ላይ ያገኙናል።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

16 Dec, 19:35


ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" እጅ ቆርጠዋልና አዛኝ አልነበሩም በሚል ለቀረበው ትችት የተሰጠ ምላሽና ማብራሪያ

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

15 Dec, 17:46


በክርስቲያኑ አለም ዘንድ በአዲስ ኪዳን የንባብ ህየሳ/Textual Criticism/ ዘርፍ ስመ ጥር ከሆኑት ምሁራን መካከል ዶ/ር ዳንኤል ዋላስ ከፊት የሚጠቀሱ ናቸው።

በዚህ ቪዲዮ የሚነግሩንም ምናልባት ለአንዳንድ ክርስቲያኖች አዲስ ሊሆን ይችላል። የወንጌላት ጸሀፍት ተደርገው ስማቸው የተጠቀሱ ጸሀፊዎች እራሳቸው እንዳልሆኑና ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ እና ዮሐንስ የሚለው ስያሜም ከጊዜ በኃላ ወንጌላትን ለመለየት በሰዎቹ ስም ሌላ አካላት የሰየሙት እንደሆነ ይገልጻሉ።

ይህ አጻጻፍ በመጽሀፍ ቅዱስ የተለመደ ሲሆን የግለሰቦችን ስም በሐሰት በመጠቀም መጻፍ /Pseudopigraphic authors/ አጠቃቀም ነው። ዳንኤል (ዶ/ር) በዚህ ቪዲዮው የሚለንም ወንጌላትም በተመሳሳይ መልኩ የተሰየሙ እንጅ ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ አካላት አልነበሩም።

https://vm.tiktok.com/ZMkYXw9Ss/

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

14 Dec, 06:53


ሄሮድስ መጥምቁ ዮሐንስን ሊገደለው ይፈልግ ነበር? | የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች - 60

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

11 Dec, 10:32


ሁለቱ በተለያዩ የዒሻ ሰላቶች ወቅት ድንገት የተቀረጸ ድምጽ ነው፣ አካባቢያ ላይ የነበረ ቃሪዕ ቢሆንም ስሙን እንኳን አላቀውም፣ ግን ደግሞ ሁሌ ሲያሰግድ የድምጹ ውበት ይማርከኝ ነበር። ድምጹ በጥራት ተቀርጾ ሁሌ ባዳምጠው እመኝ ነበር፣ ሀሳብ ብቻ ሆነና ይህንን ሳላሳካ ከተማውን ለቀቅኩ። ባለህበት አላህ ሰላም ያድርግህ፣ ከእኔ አልፎ ባዳመጠው ሰው ልክ ሁሉ አጅር ታገኝ ዘንድ እነሆ በዚህች ጠባብ ቻናልም ቢሆን ድምጽህ ሼር አደረግኩት። ፊ አማኒላህ!

https://t.me/Qurantilawas

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

10 Dec, 18:52


የተሻረው ህግ | ግጭት - 58

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

09 Dec, 11:15


ተጎድቷል፣ ሰዎች ህክምና ቦታ ተሸክመው እየወሰዱት ነው። ፍልስጤማዊ ታዳጊ ግን አንድ ቃል ደጋግሞ ይናገራል፦

"በህይወት አለሁ (አልሞትኩት) የመግሪብ ሶላት እንዳያልፈኝ" የሚለውን ቃል ይደጋግማል። የተሸከሙት ሰዎች ህክምና እንዲያገኝ በማሰብ አካሉን ተሸክመው በመያዛቸው ሶላት ሊያልፍበት እንደሆነ ገምቶ ፍጹም ደስተኛ አይደለም።

አንገቱ አካባቢ የደረሰበትን ጉዳት ለማከም ሲሞክሩም "ይሄ (ቁስል) አይገድለኝም፣ መግሪብ እንዳያልፈኝ" ሲል ደጋግሞ ይናገራል።

ድንገት በሞትና በህይወት መካከል ውስጥ ተገኝተው እንኳን ጭንቀታቸው በቶሎ ስለመዳን አይደለም፣ በጨመረው የጥቂት ቀን እድሜያቸውም ቢሆን የሚያሳስባቸው ከአላህ ጋር ያላቸው ንግግር ነው። ሶላትን በዚያ የመከራ ጊዜያቸው ውስጥ እንኳን የልባቸው መርጊያ አድርገው ይዘውታል።

በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ሶላት መስገድ ያልገራልህ ሙስሊም ወንድሜ ኡዝርህ ምን ይሆን? ከጌታህ ጋር የሚኖርህን ስንቱን መመሳጠርስ በከንቱ መባከኑን ተረዳህ?እስከመቸ ከዚህ ደስታ በፍቃድህ ትሸሻለህ?

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

09 Dec, 06:27


From the Umayyad Mosque, the revolutionary mujahideen in Syria promised the people of Gaza "We are coming, O Quds".

"Patience, people of Gaza. Lebbeyk Ya Aqsa!!"

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

08 Dec, 04:33


ከ500ሺ በላይ የንጹሀን ነፍስ ተቀጥፈዋል፣ ህዝባቸው በአለም ዳርቻ ተበትኗል። ለሶርያውያን መርገምት የነበረው ያ ስርኣት በቀናት ውስጥ ተንኮታኮተ፣ የአላህ ተኣምሩ ብዙ ነውና የተሻለውን ደግሞ ይተካቸው..!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

07 Dec, 18:49


በአደጋ ምክንያት ለእድሳት ተዘግቶ የነበረው ስመ ጥሩ የኖትር ዳም ካቴድራል በሮች በዛሬው እለት ድጋሚ ተከፍተዋል። በመክፈቻ ስነ ስርኣቱ ላይ ትራምፕን ጨምሮ በርካታ የሀገር መሪዎች ፈረንሳይ ከትመዋል።

ቤተ ክርስቲያኑ ለአደጋ ያጋለጠው ጉዳይ በተመለከተ በውል ባይታወቅም ኤሌክትሪክ ወይንም ያልጠፋ ሲጋራ ሊሆን ይችላል የሚል በምርመራው ውጤት ላይ የተመሠረተ ጥርጣሬ አለ። ወጣም ወረደም አብዛኛው ታሪካዊ የሚባለውን ቸርች የሚያስመርቁ እንግዶች ሀይማኖት አልባ የሚባሉ ታዋቂ ስብእናዎች ናቸው። በሀይማኖታዊ ስርኣቱ ወቅትም መጠጥ እየተጎነጩ ሁኔታውን ሲከታተሉ ለተመለከተ አዝናኝ ትርኢት የሚያዩ እንጅ ሀይማኖታዊ ክስተት የሚታደሙ አይመስሉም።

በምዕራቡ አለም ያለው ሀይማኖትን ባህል የማድረግና ከዚያ የዘለለ ሚና በህይወት ውስጥ እንደሌለው የማሰብ ተግባር በሒደት የመጣባቸው እጅግ አደገኛ በሽታ ነው። ሀይማኖታዊ ስርኣቱን ከትውስታ ማጫሪያነት የዘለለ ትርጉም ሳይሰጡ ለድግሶች መጠቀም ኖርማላይዝ የተደረገ ኹነት ሁኗል። ሀይማኖት የተሰመረለት ባውንደሪ ከሌለና የዘፈቀደ ከሆነ መሠል መደበላለቅ መኖሩ የሚጠበቅ ነው።

ከአመታት በኃላ በሀገራችንም መሠል ፈተና በፕሮቴስታንቱ በኩል እንደሚመጣ ይገመታል። እንደ አማኝ ያሰመሩትና የከለሉት ይህ ነው የሚባል ጠንካራ መሠረት መፍጠር ላይ አልተሳካላቸውም። ለግብረ ሰዶማውያን ጥብቅና የሚቆሙ የአውሮፓ ሚሽነሪዎችን ተቀብሎ አብሮ የሚሰራ ቸርች ነገ ባውንደሪ ይፈጥራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ለጸያፍ ተግባራቸው መጠቀሚያ ካላደረጓቸውም መልካም ነው።


የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

07 Dec, 16:50


ዛሬ ማታ በወንድማችን አብዱልከሪም ቤት የነበረን የላይቭ ፕሮግራም በመብራት ችግር ምክንያት ለሌላ ቀን ተራዝሟል። ኢንሻአላህ ቀኑን እናሳውቃለን።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

07 Dec, 09:47


ለ11 አመት በተደረገ ትግል ከስልጣን ያልተነሳው አሳድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ግን ተአምር በሚመስል መልኩ መንበሮቹ አንድ በአንድ እየተንኮታኮቱ ነው። ኒውዮርክ ታይምስ ባወጣው ጹሁፍም የሶርያ ተቃዋሚዎች በቀናት ውስጥ እያደረጉት ያለው ግስጋሴ አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራትን ግራ መጋባት ውስጥ እንደከተተ ገልጿል።

ቻይና እና ራሺያን ጨምሮ ሀገራት ዜጎቻቸው በፍጥነት ሶርያን ለቀው እንዲወጡ እያሳሰቡ ይገኛሉ። በዛሬው እለት ስትራቴጂክ ቦታ የሆነቸውን የከበቧትን ሆምስን መቆጣጠር ከቻሉ የደማስቆ መውደቅ የቀናት ጉዳይ ብቻ እንደሆነ እየተነገረ ነው። የአላህ ውሳኔ አስደናቂ ነው..!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

07 Dec, 08:38


በእንግሊዝ ሙሐመድ የሚለው ስም ከፍተኛው መጠሪያ ሁኗል።

"..መወሳትህንም ላንተ ከፍ አድርገንልሃል.."
[ ሱረቱ አል - ኢሻራሕ - 4 ]

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

04 Dec, 07:59


የሙሴ ህግ ጠቃሚ ነውን? | ከመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች የቀጠለ

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

30 Nov, 08:41


የፕሮቴስታንት አገልጋዮች ድጋሚ ወደ ኦርቶዶክስ የመመለስ ጉዳይ

ከሰሞኑ ወደ ፕሮቴስታንት ሂደው ታዋቂ የነበሩ የቀድሞ ኦርቶዶክሶች (አንዱ ዘማሪ መሠለኝ) አሁን ደግሞ ኦርቶዶክስ መሆናቸውን ተከትሎ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ መነጋገሪያ ሁኖ ቆይቷል። በዚህ መሀል ከሁለት ቀን በፊት November 27 በእንግሊዝኛ ቋንቋ የወጣ አርቲክል አንድ ወንድሜ ላከልኝና ትኩረቴን ስቦት አነበብኩት። በጥቅሉ የሚያወራው ቤተ ክርስቲያኗ የፕሮቴስታንትና የእስልምናን ጫና ለመመከት ባለፉት አመታት የከወነቻቸውን ስራዎች ነው።

በከፍተኛ ሁኔታ የተመናመነውን ምዕመን ለመመለስ ስትራቴጂ ነድፋና አቅዳ ላለፉት አመታት የቻለችውን ያክል ተጉዛለች። በ23 አመት ውስጥ የምዕመኑ ብዛት ከ54% ወደ 43% ወርዷል። ማኅበረ ቅዱሳን ጋር በህብረት የሚሰሩ ለዚህ አገልግሎት የተቀኙ ተቋማትን ማደራጀት ችላለች። ጃንደረባው የተሰኘው የዲያቆን ሀይሌ ተቋም ለአብነት የሚጠቀስ ነው።

ጃንደረባው ከቀናት በፊት 2,000 የሚሆኑ ሰልጣኞችን በሥነ መለኮት የዲፕሎማ ስልጠና ሰጥቶ አስመርቋል። በዋናነት ስልጠናው ያተኮረውም ይህንን "ጫና" ይቋቋሙ ዘንድ እንደሆነ ተገልጿል።

▣ መውጫ

በዚህ ሁሉ ትጋት ውስጥ ምናልባት ከፍ ብሎ የሚጠቀሰው ማኅበረ ቅዱሳን የተሀድሶን እንቅስቃሴ ለመግታት የሄደበት ርቀት ነው። በዚህ ረገድ "ተሳክቶለታል" ብሎ በድፍረት መናገር ባይቻልም የማይናቅ ስራ ግን ሰርቷል። የተሀድሶ ሰዎች አብዛኛዎቹ ቆብና ቀሚሳቸውን አውልቀው አዳራሽ እንዲገኙ ማድረግ ችሏል።

እስልምናንስ በምን ያክል ስጋት ተመለከቱት?የሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ሲሆን በፕሮቴስታንቱ ደረጃ ስጋት አድርጋ አልቆጠረችውም። እንዲያም ሁኖ እስልምናን ታርጌት ያደረጉ ስራዎች መስራት ላይ ወደኃላ አላሉም።

መረጃ መልካም ነው..!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

29 Nov, 07:22


አብርሀማዊ ሐይማኖት የሚባል ነገር የለም። ቁርኣን በግልጽ "ኢብራሒም አይሁድም ሆነ ክርስቲያን አልነበረም" ብሎ ነግሮናል። ኢብራሒማዊ ሀይማኖት ከተባለም እስልምና ብቻ እና ብቻ ነው። አንዳንድ መሠረታቸው የተዛነፉ ጽንሰ ሀሳቦችን ቀስ በቀስ በሰው ህሊና ባናላምዳቸው መልካም ነው።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

28 Nov, 04:55


በመጨረሻም የሸይኻ ፋጡማ ሙስሊም አይነ ስውራን ተማሪዎች ሶላታቸውን እንዲሰግዱ ተፈቅዶላቸዋል። ጉዳያቸው አስጨንቋችሁ በየፊናችሁ ለለፋችሁ ሁሉ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈላችሁ፤ አልሐምዱሊላህ

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

26 Nov, 16:22


የሸይኻ ፋጢማ የአይነ ስውራን ት/ቤት ጉዳይን በተመለከተ መጅሊሱ አንድ እርምጃ መሄዱ መልካም ነገር ነው። ከንቲባዋ ይስተካከላል ብላ ቃል መግባቷን መጅሊሱ አሳውቋል። ጉዳዩን እንደሚከታተሉና እስከ ፍጻሜው እንደሚያደርሱት ተስፋ እናደርጋለን። የሁሉም ሙስሊም ጭንቀት የልጆቹ እንባ መታበሱ ነው። አላህ ሲስቁ እንዲያሳየን ዱዓችን ነው።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

26 Nov, 16:09


ጽንፈኛው የፕሮቴስታንት ቡድን በጉራጌ ዞን እንድብር ወረዳ ቋሻ መስጅድ አዛን አይደረግም በሚል ማይክራፎን ነቅሎ ወስዷል።

© ሀሩን ሚዲያ

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

25 Nov, 16:10


የአይን ብርሀናችንን ማጣታችን ሳያንስ የእስልምናንም ብርሀን ሊነጥቁን ነው የሚለው ንግግራቸው ለሙስሊም እንቅልፍ ይነሳል። ሙስሊም አይነ ስውራን በዲናቸው ምክንያት ተበድለዋልና በቻልነው ልክ ድምጽ እንሁን.!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

25 Nov, 12:40


"...ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን ወደ ጠባቡ መንገድ ግፏቸው.."

ለቀረቡ ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ

https://vm.tiktok.com/ZMhcTDro4/

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

24 Nov, 10:32


አንዳንድ ሰው ላመነበት የፖለቲካ ርዕዮትም ይሁን አልያም "ህዝቤ" ለሚለውም አመለካከቱ ይሁን ብቻ በአካሄዱ ግን ምንም አይነት የአኼራ ግብ ሳይኖረው ለዱንያዊ ግብ የሚያደርገው መራር ትግልና ፅናት ይገርመኛል። የያኔዎቹ ትውልዶች የሚባሉት የዘመነ ሀይለስላሴና የደርግ ፖለቲካ ሰለባዎች እስከሞት ድረስ ላመኑበት መስመር የሚያደርጉት ትንቅንቅ አስደናቂ ነው። በተቃራኒው በዚህ መነጽር ውስጥ ለትግሉ የአኼራን እውነትነት የሚያምነው ህዝቡ ሙስሊምን ለተመለከተ ሰው ደግሞ ራሱን አብዝቶ እንዲፈትሽ የሚያደርግ ነው። አኼራ ያለብን እኛ ለዑማችን ሁለንተናዊ ለውጥ ስንል ዱንያን በመናቅ በሙሉ አቅማችን መትጋትና መልፋት ፈርድ የሚሆነው በኛ ላይ አልነበረም?

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

24 Nov, 07:12


"..የአይን ብርሀናችንን ማጣታችን ሳያሳዝናቸው፣ የኢስላምንም ብርሀን ሊነጥቁን እየታገሉ ነው። ከመስጅድ መለመን የዘለለ ተጽእኖ አይፈጥሩም ብለው የኛ መሪዎችም በጠቅላላ ችላ አሉን። ነገ አላህ ፊት ግን ኢንሻአላህ ሁሉኑም እንፋረዳቸዋለን.."

የአብደላህ ኢብን ኡሙ ሙኽቱም ስራ አስኪያጅ ወንድም ከድር ከተናገረው የተወሰደ


አይነ ስውራን ሊታዘንላቸው የሚገቡ ቢሆንም በዲናቸው ምክንያት ግን የበደል ጅራፍ እያረፈባቸው ያሉ አሳዛኝ አካሎቻችን ናቸው። ከጎናቸው የሚቆም ተሰሚነት ያለው አንድ አካል እንኳን እስካሁን አለመኖሩን ከባለቤቶቹ ስትሰማ ምን አይነት አሳዛኝ ሁኔታ እንደገባን ያሳያል። ስልክ እንኳን የሚያነሳላቸው አጥተው ያሳለፉትን በለቅሶ ሲነግሩህ እንደ ኡማ ያለንበትን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ያሳዝናል፣ ይህ እንኳን አይገባችሁም ነበር..!

▣▣▣▣▣▣

ይህንን በተመለከተ ሀሩን ሚዲያ ያዘጋጀውን ልዩ መሰናዶ በሚከተለው ሊንክ መመልከት ይችላሉ፦

https://m.youtube.com/watch?v=NYpc5R0IXKA

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

23 Nov, 08:04


አንድ ሰባኪ ናቸው፣ በሰበካቸው መሀል ምዕመኑን ይጠይቃሉ፦

"ማርያም የማን ልጅ ናት?" ምዕመኑ ይመልሳል

"የእግዚአብሔር"፣

ቀጠለ "እግዚአብሔርስ የማን ልጅ ነው?"

አሁን የምዕመኑ ድምጽ ትንሽ ቀነሰ፣ አባ እራሳቸው መለሱት

"የማርያም"

ይህንን ካሉ በኃላ ግን ትንሽ ግራ ተጋቡ መሠል፣ ሲደመድሙት ምን አሉ፦ " ይሄ ሚስጥር በእርግጥ በጣም ከባድ ነው"
.
.
.
.
አባ! ታዲያ እርስዎ ከከበዶት ማን ይቅለለው?

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

23 Nov, 07:40


አንድ ወንድማችን በግል ቴሌግራም በኩል ችግር ውስጥ እንዳለና ስራ መስራት እንደሚያስፈልገው በመግለጽ መልዕክት አስቀመጠልኝ (ዝርዝሩ ስክሪን ሹቱ ላይ አለ)

የሚኖረው አሸዋ ሜዳ ነው። ከዚህ በፊት ኔትዎርክ ኬብል ዝርጋታ እንደሞከረ ነግሮኛል፣ ሽያጭ ሰራተኛነትም ሞክሯል።

ስራ ልታሰሩት የምትችሉ ወንድምና እህቶች በዚህ ስልክ ቁጥር ደውላችሁ ልታገኙት ትችላላችሁ፦

0716377504

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

21 Nov, 17:43


የእህታችን ዘሀራ የቲክቶክ አካውንት ሪፖርት ተደርጎ ስለተዘጋባት አዲስ አካውንት ከፍታለች። በሚከተለው አድራሻ ፎሎው አድርጓት፦

https://vm.tiktok.com/ZMh7NvtDN/

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

21 Nov, 11:23


ፓምፍሌቶቹ ሲዘጋጁ በዋናነት ትኩረት ያደረጉት ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖቻችንን ስለ እስልምና ማስተማር ነው። ለዚህም የመጀመሪያው ፓምፍሌት ስለ ዒሳ (ኢየሱስ) ትክክለኛ ማንነት ማሳወቅ ሲሆን በተጨማሪም የነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ስብእና ምን ይመስል ነበር የሚለውም በሁለተኛው ፓምፍሌት ተዳሶበታል።

በቀጣይ "ስለ እስልምና" በሚል ርዕስ መሠረታዊ የእስልምና መሠረቶችና ጥቅል ትምህርቶቹ በአጭር አገላለጽ ተዳሷል። በመጨረሻም የሰው ልጅ እንዴት ይድናል? በሚለው ርዕስ የሰው ልጅ ወደ አላህ በመመለስ "ንስሀ/ተውበት" አድርጎ እንዴት እንደሚድን የሚያስተምር ነው። መጽሄቶቹ ይዘታቸው ትልቅ ከመሆኑ ጋር ማራኪ ይዘት እንዲኖራቸው ጥራት ባለው የህትመት አቀራረብ ወጭ ወጥቶባቸዋል እንዲታተሙ ተደርጓል።

እስካሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ ተቋማትና ግለሰቦች ጋር በመተባበር በበርካታ ቦታዎች የተሰራጩ ሲሆን በቪዲዮው ላይ ረሕማ የተሰኘው የጎዳና ላይ ዳዕዋ ቡድን በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ሲያሰራጩ የሚያሳይ ነው። መሠል ስራዎች የሚቀጥሉ ሲሆን በዚህ ስራ ላይ አሻራዎትን በማሳረፍ የዳዕዋው አካል መሆን ይችላሉ፦
____

የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል እና የዳዕዋው አካል ለመሆን፦

https://bit.ly/4aGr93u

በቴሌግራም በኩል ሊያገኙን ከፈለጉ፦
@Hidayaislamiccenter

1000499318212
Hidaya Islamic Center

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

20 Nov, 17:26


በአካባቢየ ላይ ካለ መስጅድ የኢሻ ሶላት ተሰግዶ እንዳለቀ ከኮሚቴዎች አንዱ ተነስቶ እንደ እኛ አካባቢ ሙስሊሙ ከሰሞኑ የአካባቢው ሙስሊም የገጠመውን ችግር ተናገረ። ይኸውም ተማሪ ልጆች ከትምህርት ቤት ሲወጡ "ጌታን ተቀበሉ" የሚሉ እነሱን ታርጌት ያደረጉ ሰበካና ማደናገሪያዎች ከሰሞኑ እየቀረቡላቸው መሆኑ ነው።

ይህንን በመያዝ ከወላጅ ጋር ምክክር ሲያደርጉ ወላጅ የሰጠው መልስ ደግሞ ይበልጥ የሚያስደነግጥ ነበር። አይደለም ልጆቻቸውን ይቅርና እነሱን እራሳቸውን የቤታቸውን በር እያንኳኩ ይህንኑ ካልሰበክን እያሉ እየታገሉ መሆኑን ጠቀሱ። ሰፈሩ የሙስሊም ሰፈር (አብዛኛው ሙስሊም ነዋሪ) ከመሆኑ አንጻር ድፍረታቸው በእርግጥም ያስገርማል።

▣ ለመውጫ ያክል

በየ አካባቢያችሁ መሠረታዊ ንጽጽር ልጆቻችሁን አስተምሩ፣ የመጭው ጊዜ ፈተና እየከፋ ቢሄድ እንጅ የሚቀንስ አይሆንምና ይህ መዘናጋት በርካታ ዋጋ ያስከፍላል።

---
ምስል - ታሪኩን የሚገልጽ AI

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

20 Nov, 16:12


በተለያዩ ምክንያት ወደ የትኛውም ሀገር መጓዝ ካሰቡ እና የበረራ ትኬት ከፈለጉ ፈሲሩ ጋ ደውሉላቸው፣ ትኬት በተመጣጣኝና በአነስተኛ ዋጋ ከነሱ ጋ ከታማኝነት ጋር ታገኛላችሁ። በአጭር ሰአት የዱባይ ቪዛም ያወጡላችኃል።

- የበረራ ትኬቱን በየትም ቦታ ሆናችሁ ማስቆረጥ ትችላላችሁ።

▣ ፈሲሩ ትራቭልና ትኬት ኦፊስ

0911273017
0907710101

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

20 Nov, 07:20


የዛሬ አራት አመት በዚህች ቀን መጻፉን ፌስቡክ አስታወሰኝ፣ ይጠቅመናል አሁንም።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

19 Nov, 15:28


መካነ ኢየሱስ ቸርች በኢትዮጵያ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ውስጥ አባል የሆነ አንዱ የፕሮቴስታንት ፊርቃ ነው። መካነ ኢየሱስ ቸርች ብቻውን በሀገሪቱ ውስጥ 278 ግዙፍ የእርዳታ ፕሮጀክቶችን ያስተዳድራል። ለነዚህ ፕሮጀክቶች 1.6 ቢሊየን ብር አመታዊ በጀት ኑሯቸው የሚንቀሳቅሱ ሲሆን በአጠቃላይ 5 ሚሊየን ሰው በፕሮጀክቶቹ ታቅፏል። ለዚህ ፕሮጀክት ከቋሚ ሰራተኞች ውጭ 1,243 በጎ ፈቃደኛ አገልጋዮች አሉ። የቸርቿ አባላት ጠቅላላ ብዛት ከ8 ሚሊየን የሚበልጥ እንዳልሆነ የአለም አቀፍ አብያተ ክርስቲያናት ዳታ ያሳያል።

በተመሳሳይ የቃለ ህይወት ልማት ኮሚሽን የ2022 የበጀት ሪፖርቱን ባቀረበበት ሰነድ ላይ እንደገለጸው ለአንድ አመት አጠቃላይ ስራዎች የተጠቀመው በጀት 620 ሚሊየን ብር ነበር። በዚህ የተራድኦ ስራ አማካኝነት በዋናነት ሙስሊም በዝ አካባቢዎች ላይ መስራቱን ከሪፖርቱ መረዳት የሚቻል ሲሆን በቀጣይ አመት በተራድኦ ስራው ከ600ሺ በላይ ሰዎችን ለመድረስ አቅደው መንቀሳቀሳቸውን ሪፖርታቸው ይገልጻል።

ምስል - በቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን ስር የሚደገፉ አካል ጉዳተኛ ሙስሊሞች (ሻሸመኔ)

ምንጭ፦

- የቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን የልማት ኮሚሸን የ2022 በጀት አመት ሪፖርት

- የመካነ ኢየሱስ ኦፊሺያል መካነ ድር

- የቃለ ህይወት የልማት ኮሚሽን ኦፊሺያል የዩቲዩብ ቻናል

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

19 Nov, 09:17


የደም መሬት የተባለው ለምንድን ነው? ከይሁዳ አሟሟት ጋር ተያይዞ ያሉ ተቃርኖዎች ቀጥለዋል።

#ግጭቶች

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

19 Nov, 08:43


ኢትዮጵያ ውስጥ ስመ ጥር ከሆኑ የወንጌላውያን ኮሌጆች መካከል በአዲስ አበባ የሚገኘው ኢቫንጃሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅ (ETC) አንዱ ነው። በኮሌጁ ከሚሰጡ የማስተርስ ፕሮግራሞች አንዱ Master of Arts in Christian Muslim Relations ተጠቃሽ ነው። በዚህ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለመመረቅ በሙሉ ጊዜ ለሚከታተሉ ሁለት አመት በፓርት ታይሞ ለሚከታተሉ ደግሞ ሶስት አመት ይፈጃል።

ዲፓርትመንቱ ካካተታቸው ዋነኛ የትምህርት ትኩረቶች መካከል፦ አንድን ሙስሊም ክርስቲያን ለማድረግ በሚያግዝ መሠረት ውስጥ ሁኖ የእስልምና ታሪክን ማጥናት፣ የክርስትና እቅበተ እምነት፣ የቁርአን ተፍሲር የሀዲስ ጥናት፣ ለመጀመሪያ ዲግሪ ሚሽነሪ ተማሪዎች ስለ እስልምና ለማስተማር በቂ እውቀት ማስያዝ፣ የሙስሊሙን አለም እንቅስቃሴና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በመከታተል በሀገሪቱ ውስጥ የሚሽነሪ ስራን ለማሳለጥ የሚረዱ መንገዶችን መንደፍ ከአላማዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ። ኮሌጁ እስካሁን ከ1,800 በላይ ተማሪዎችን በዲግሪና በማስተርስ መርኅ ግብር አስተምሮ አስመርቋል።

#የሚሽነሪዎች_እንቅስቃሴ

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

17 Nov, 17:47


በይ/ጨፌ ከተማ የሚገኘው የሙስሊም መካነመቃብር ለኮሪደር ልማት እንዲፈርስ ከታዘዘው በተጨማሪ ሌላ 10 ሜትር "ለመዝናኛ አገልግሎት" በሚል እንዲፈርስ ታዟል። አጽም በክብር እንዲያነሱም አልፈቀዱላቸውም..!

በወቅቱ ይህንን የተቃወሙ ሰዎችን አስረው የነበረ ሲሆን "የእናንተ ምን ሲባል ነው የማይፈርሰው?" የሚሉ የሌላ እምነት ተከታዮችም ከንቲባውን አጅበው ብጥብጥ መፍጠራቸው ተሰምቷል።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

17 Nov, 17:04


በጃንዋሪ 20/2000 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር አንድ በአይነቱ የተለየ ወርክሾፕ በመሠረተ ክርስቶስ ቸርች አማካኝነት በአዲስ አበባ ተካሒዶ ነበር። የዚህ ወሳኝ ወርክሾፕ ዋነኛ አላማ ሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ። አንደኛው የቸርቿ አባላት ያላቸውን ተሰጥኦ ለሀይማኖታቸው እንዴት ማዋል አለባቸው? የሚል ሲሆን ሁለተኛው አላማ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለውን የእስልምና መስፋፋት እንዴት መግታት ይቻላል? የሚል ነበር።

ምንጭ፦ የመሠረተ ክርስቶስ የ2005 Global Gift Sharing Report

ምስል - 1 / በቦረና ገጠራማ አካባቢ የሚገኙ ሰዎች ተጠምቀው ቸርች ሲሰበኩ

ምስል - 2 / በቦረና ድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የመሠረተ ክርስቶስ ያደረገችው ድጋፍ

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

16 Nov, 12:05


የመሠረተ ክርስቶስ ዋና ጸሀፊ የነበረው በድሩ ሁሴን የምስራቅ ወለጋን ክርስቲያናዊ የማድረግ ሒደት በስፋት በገለጸበት የእንግሊዝኛ ጆርናሉ ቁልፍ ስኬት ብሎ የገለጸው አንድ እርምጃ ነበር። በመጀመሪያ አካባቢ ሚሽነሪ ወደቦታው በመላክ የተደረገው ሙከራ ብዙም ውጤት እንዳላመጣ ገልጾ ሁለተኛው ስራ ግን የቸርቿን አባል ከ2,500 ወደ 36,594 በአስራ ሁለት አመት ውስጥ እንዲመነድ ማድረጉን ይገልጻል። ይህም እድገት በፐርሰንት ሲገለጽ 144.2% እንደሆነ ጠቅሶታል።
...
መንገዱ ምንድን ነበር? ቀላል ስራ ነበር የተሰራው። ይኸውም የአካባቢውን ነቃ ያሉ ወጣቶች በመመልመል ወደ ከተሞች አምጥቶ እነሱን ካሰለጠኑ በኃላ ህዝባቸውን እንዲያስተምሩ እራሳቸውን ሚሽነሪ አድርጎ የመላክ ስራ ነበር። ተማሪዎቹ የአካባቢያቸውን ቋንቋ፣ ባህልና ማህበረሰባዊ ስሪት ጠንቅቀው ስለሚያውቁት ህዝቡን ወደ ሚፈልጉት ነገር ለማምጣት እጅግ በጣም ቀሏቸው ነበር። ይኸው መንገድ በሌሎች ቦታዎችም በሰፊው መተግበሩም ይወሳል።

ምንጭ፦ Contextualization of the gospel among th Oromo tribe of the eastern Wollega region: The Meserete Kirstos Church Experience - Bedru Hussein

Picture - Bedru Hussein

https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

16 Nov, 11:07


የምስራች ከቁርአን ቀጥሎ ትልቁን ኪታብ ሶሂሁ አልቡኻሪን መቅራት ለምትፈልጉ ሁሉ

ለመመዝገብ


አኅት ዘሃራ ሙስጠፍን፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት ዝሃራ ኢማምን ፦ @Zehar678
ያናግሩ

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

15 Nov, 11:11


ኦክቶበር 6፣ 2006 የመሠረተ ክርስቶስ ቸርች አንድ ውሳኔ አሳለፈች። ይኸውም ከአንድ በላይ ሚስት ያገቡ ሰዎች ቸርቿን መቀላቀል ቢፈልጉ ሚስቶቻቸውን ሳይፈቱ የቸርቿ አባል እንዲሆኑ የሚያስችል ውሳኔ ነው። በቸርቿ የሀይማኖት መመሪያ መሠረት ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው። ነገር ግን አንድ ሰው ከአንድ በላይ ሚስት ኑሮት ቸርቿን መቀላቀል ቢፈልግ ሌሎች ሚስቶቹን ፈቶ በአንዷ ብቻ ይወሰን? ወይንስ ሁሉኑም ሚስቶች እንዳገባ ሳይፈታቸው ይጠመቅና የቸርቿ አባል ይሁን? የሚለው በሰፊው ካከራከረ በኃላ በስተመጨረሻ ከነሚስቶቹ ሳይፈታቸው አባል ይሁን በሚለው ተወሰነ። ትዳሩም ህጋዊ ተደርጎ እንዲወሰድ ተደረገ።

የዚህ ውሳኔ ዋነኛ ምክንያት ሙስሊሞች ወደ ቤተ ክርስቲያኗ እንዲመጡ መንገድ ለመክፈት ነበር። በዚህ ሒደት ውስጥ የእምነቱ "መመሪያ" አጣብቂኝ ውስጥ ቢገባም ሙስሊሙ ወደነሱ ከመምጣቱ አንጻር መመሪያው ኮምፕሮማይዝ ቢደረግም ችግር ስለሌለው ይህ ውሳኔ ተወሰነ። የሰውየውን ሌሎች ሚስቶች እና የነሱን ልጆች ከማጣትም ህጉን አላልቶ ሙስሊሙን መውሰድ የተሻለ ነው በሚል ታምኖበት ነው። ባይሆን ሰውየው ግን ቸርቿን ከተቀላቀለ በኃላ ያሉት ሚስቶች "በቂ ስለሆኑ" ሌላ ሚስት እንዳያገባ ይከለከላል።

Holly Blosser Yoder, "Landmark Decisions in Ethiopia,"Mennonite Weekly Review 84, no. 46 (November 2006)


https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

14 Nov, 17:28


በተለያዩ ጊዜያት ቃሪኦችን ሳዳምጥ የሚማርኩኝን ለብቻ በአንድ ቻናል የመሰብሰብ ልምዱ አለኝ። እነዚያን ቂርአቶች የምሰበስበው ለራሴ ለማዳመጥ ስለሚያስደስቱኝ ብቻ ነበር። ከቀናት በአንዱ ቀን የአጎቴ ልጅ ሳዳምጥ አገኘኝና ብቻየን ያለሁበት ቻናል ውስጥ እንድጨምረው ጠየቀኝ። ችግር ስላልነበረው ሊንክ ልኬለት ጆይን አለ። ይህ ወንድሜ በቂርአቶች ተማርኮ በተደጋጋሚ ሳገኘው እያዳመጠ ነበር የማገኘውና ትልቅ ትምህርት ሰጠኝ። ይህንን ጉዳይ ለራሴ ብቻ ከማደርገው ለሌላም ሰው ሼር ባደርገው ለኔም ለቃሪኦችም ተጨማሪ አጅር የሚያስገኝ መልካም ስራ መሆኑ ገባኝ። አሏህ ﷻ ወስኖ ከዚህ አለም በሞት ስለይም ሰደቀቱል ጃሪያ ይሆንልኛልና ከመልካም ስራ መሳነፍ ልክ እንዳልሆነ ተረዳሁ። ስታዳምጡ ዱዓ ማድረግ አትርሱ፥ ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ
...
https://t.me/Qurantilawas

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

14 Nov, 16:34


ውሸት በከበበው በዚህ ሁሉ ምድር አንድ መጽናኛ እውነት አለን፣ ጌታችን ሆይ! ቃልህን ከልብ እንወዳለን፣ ዲንህን ከምንም አስበልጠን እንወዳለን። ደካሞች ነንና በስራ ግን የምንታበይበት አንድ ስንኳ የለንም..! ይህችኑ ውዴታችንን በእውነተኛው ቀን ለእዝነትህ መጠጊያ አድርግልን።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

14 Nov, 08:24


በዛሬው አጭር የኦዲዮ መልዕክታችን የኦሮሞ ህዝብን በተለይም የጅማን ሙስሊም ለማክፈር በማሰብ ጉዞ ጀምረው በመሀል ሀድያ ስለቀሩት ምዕራባውያን ሚሽነሪዎች ከታሪክ ምዕራፋቸው የተወሰነ እናወሳለን።

https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

14 Nov, 04:53


መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በደርግ ዘመን በገጠማት ፈተና ከእስር ጀምሮ ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል ያስቀጠሏት መሪዎቿ 6 እንደሆኑ የመሠረተ ክርስቶስ ኢንሳይክሎፒዲያ ይገልጻል። ከነዚህ ውስጥ 2ቱ፣ ኸሊፋ ዓሊ እና ሸምሰዲን አብዶ የተሰኙ የከፈሩ ሰዎች ነበሩ።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

13 Nov, 06:56


ወንድማችን ኡስታዝ አቡ ዩስራ በዋናነት የንጽጽር ትምህርቶችን የሚያቀርብበት ቻናል ይህ ነው። ጆይን በማድረግ ተጠቃሚ ሁኑ፦

https://t.me/Abuyusra3

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

13 Nov, 06:54


መሳሳት የማይደክማቸው ሰዎች!


ቁርዓን 3:44

ይኸ ወደ አንተ የምናወርደው የኾነ ከሩቅ ወሬዎች ነው፡፡ መርየምንም ማን እንደሚያሳድግ ብርኦቻቸውን (ለዕጣ) በጣሉ ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም፡፡ በሚከራከሩም ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም፡፡


ذَٰلِكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلْغَيْبِ نُوحِيهِ إِلَيْكَۚ وَمَا كُنتَ لَدَيْهِمْ إِذْ يُلْقُونَ أَقْلَٰمَهُمْ أَيُّهُمْ يَكْفُلُ مَرْيَمَ وَمَا كُنتَ لَدَيْهِمْ إِذْ يَخْتَصِمُونَ

የኢየሱስ እናት መርየም (ዐ.ሰ) በቁርኣን ውስጥ በስሟ የተሰየመ ምእራፍ መኖሩን አስመልክቶ "ይሄ ምን ያስገርማል ታዲያ? ቁርኣን እኮ ብዙ አስገራሚ እና አስቂኝ የምእራፍ ስሞች የያዘ መፅሀፍ ነው" በማለት አንዳንድ ክርስቲያኖች ሲሳለቁ ከርመዋል።

ከዚህ በፊት የኢየሱስ (ዐ.ሰ) ስም   ከነብዩ ሙሐመድ (ዐ.ሰ.ወ) ስም ይበልጥ በቁርኣናችሁ ተጠቅሷል፣ ነብያችሁ ግን በስም ከ 4 ግዜ በላይ አልተጠቀሰም እያሉ ሲያደርቁን የነበሩ ሰዎች ዛሬ ተገልብጠው የማርያምን ስም መጠቀስ ለማንቋሸሽ የሄዱበት ርቀት ይገርማል።

የኢየሱስ እናት ስሟ መጠቀሱ እንዲሁ ትርጉም አልባ ገለጻም አልነበረም። ከዚህ ጋ ተያይዞ ለየት የሚያደርገውን ሁለት ምክንያቶችን ልጥቀስ።

① በአረቦች  እና በእስራኤላያውያን  መካከል ያለው አለመግባባት ዘመናትን የዘለቀ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ነብዩ (አሰወ) በነበሩበት ዘመን ጥላቻውም በግልፅ ይንፀባረቅ ነበር። ታዲያ በዚሁ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ነብዩ (ዐ.ሰ.ወ) በዚያ ዘመን ከምዕተ አመታት በፊት የነበረችውንና አይሁዳዊቷን ማርያምን እንዴት ሊያሞግሷት ቻሉ?


② ነብዩ (ዐ.ሰ.ወ) በአጠገባቸው ሚስቶቻቸው ወይንም ሴት ልጆቻቸው እያሉ እንዴት ቢያንስ አንድ ምእራፍ እንኳን በነሱ ስም አልሰየሙም? ከዚያም በተጨማሪ በቁርኣኑ ውስጥ ስማቸውን እንኳን ገልጸው ለማሞገስ እንዴት አልሞከሩም?

ዋናው ነጥብ በምእራፍ ስም መሰየሙ አለመሰየሙ አይደለም፣ መሠረታዊ መልዕክቱ ቁርኣን የሰጣት ክብር ነው። ይህ ደግሞ ከመለኮታዊ መልዕክት የወጣና የግል ዝንባሌ የተጨመረበት ቢሆን ፈጽሞ ሊደረግ የሚችል አልነበረም።

https://t.me/Abuyusra3

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

12 Nov, 07:18


እ.ኤ.አ. በ1962 የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኝ የሆኑ ወጣት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አንድ ፍላጎት አሳደሩ። ይኸውም እንግሊዘኛ የሚያስተምር መምህር ፈልገው ወደ ዶ/ር ሮህሬር እሸልማን መጡ። ዶክተሩ ሚሽነሪ ነበረና እንግሊዝኛ ለማስተማር አንድ መስፈርት አስቀመጠላቸው። ይኸውም የዮሐንስ ወንጌልን እንደ መማሪያ መጽሐፋቸው/Text book/ እስከተጠቀሙ ድረስ እንግሊዝኛ ሊያስተምራቸው ተስማማ። ተማሪዎቹ ተስማሙ፣ ትምህርቱም ተጀመረ። እንደ አናባፕቲስት ገለጻ ከሆነ ብዙም ሳይቆይ ከእንግሊዝኛው ትምህርት ይልቅ ለወንጌል የበለጠ ፍላጎት ተፈጠረባቸው። ❝..ምንም እንኳን ቅዱሳት መጻሕፍት የመጨረሻ ሥልጣን እንዳላቸው ቢገነዘቡም፣ እነዚህ ተማሪዎች በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመቆየት ይፈልጉ ነበር። ምክንያቱም በወቅቱ ወንጌላውያን ከውጭ አገር ሚስዮናውያን ጋር ተያይዞ በአሉታዊ መልኩ ይገለጹ ስለነበር እነሱን መቀላቀል ትክክል ነው ብለው አላመኑም❞

ተማሪዎቹ ይህን በማሰብ መሠረተ ክርስቶስን ሳይቀላቀሉ የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን መስርተው ሰማያዊ ብርሃን ወይም ሰማያዊ ፀሐይ” ብለው ሰየሙት። መሠረተ ክርስቶስ ግን ከእነዚህ ተማሪዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ጠብቆ ነበር እና መርዳት በሚችልበት ጊዜ ረድቷቸዋል። በኃላም የሙሉ ወንጌል እንቅስቃሴ እንዲመሠረት መሠረት ጥለው እንቅስቃሴውን በዩንቨርሲቲ ደረጃ ጭምር እንዳሰፉት ይነገርላቸዋል።
.
.
እያለ ታሪኩ ይቀጥላል...

ምንጩ፦

Global Anabaptist Mennonite Encyclopedia Online. March 2010. Web.

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

11 Nov, 11:07


እዚህ ላይ መርከዛችሁን ከሞላችሁ ውስጥ ስልክ ቁጥር የተሳሳታችሁ አላችሁ። በዚህ ምክንያት ልናገኛችሁ አልቻልንም። ስለዚህም በተቻለ መጠን በሁለት ቀናት ውስጥ ፎርሙን እንደ አዲስ አስተካክላችሁ ለመሙላት ሞክሩ።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

08 Nov, 07:04


ሻውዚን ነፋሕነ
..
በነገራችን ላይ ይህንን ቃል በቪዲዮ ላይ ሲናገር የነበረው ሰባኪው የፈጠረው ቃል አይደለም። ሰባኪው ከሰሞኑ በቲክቶክ ሲጠይቁትም የእሱ ቃል አለመሆኑን ተናግሯል። ልክ ነው፣ አልተሳሳተም። ንግግሩ በተዓምረ ጽዮን ማርያም ድርሳን ውስጥ የሚገኝ ቃል ነው..! ድርሳኑ እስልምናን በመሳደብ የሚታወቅ ሲሆን በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ነብዩ ሙሐመድን "ﷺ" ዲያቢሎስ አዘዛቸው በሚል የቀረበ ቃል ነው። መጽሀፉ በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ይታመንበታል ወይ? የሚል ጥያቄ ካላችሁ መልሱ "አዎ" ነው።

📎 https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

06 Nov, 08:50


ሪፐብሊካኖች ሙስሊሞችን ይጠላሉ፣ ዲሞክሮቶች ደግሞ እስልምናን ይጠላሉ። They are the same.

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

04 Nov, 17:51


❝....ላለፉት 3 ዓመታት ወንጌላውያን የቢዝነስ መሪዎችን ሲያሠለጥን፣ ሲያስታጥቅና የኅብረት ጊዜዎችን ሲያዘጋጅ የቆየው ኅብረታችን በክርስቲያኑ ነጋዴ ማኅበረሰብ መካከል የበለጠ ኅብረት፣ ትስስር እና ልቀት እንዲኖር ተግተን ልንሠራ ቆርጠን ተነሥተናል...❞

- ከኅብረቱ መግለጫ የተወሰደ

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

04 Nov, 15:02


ዑለሞች የነብያት ወራሾች ናቸው። እነዚህን ዑለሞች መግደል እስልምናን የማጥቃት ምልክት ነው፣ ሰሜን ሸዋ ላይ የተገደሉት ዓሊምና ቤተሰባቸው የዚህ ተግባር ማሳያ ነው..!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

02 Nov, 06:01


ሰሜን ሸዋ ደራ ላይ ታላቅ አሊም ከ12 ቤተሰቦቻቸው ጋር ተገድለዋል። አጋች ታጣቂዎች ከአንድ ወር በፊት አግተዋቸው 2 ሚሊየን ብር ጠይቀው 1.4 ተከፍሏቸው ነበር፣ ቀሪው እስኪከፈል ግን አልጠበቁም። ሙሉ ቤተሰብ ጨፈጨፉ፣ ያውም አሊምና የአሊም ቤተሰብ..! እጅግ በጣም ያሳዝናል። ኢናሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን፣ አላህ ይዘንላቸው፣ ለቤተሰባቸውም ሰብሩን ይወፍቅ። ፍትሕን የምንጠይቀው ከአላህ ነውና የግፋችሁን ውጤት ሳይውል ሳያድር ያሳየን..!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

01 Nov, 11:17


በኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ውስጥ ከመነሻው ጀምሮ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን የተተቸ፣ የተወገዘ ከዚያም አልፎ በጠቅላይ ሚንስትር ደረጃ ሳይቀር ስሙ በክፉ ተነስቶ "የተወነጀለ" ተቋም ኦርቶዶክስ ውስጥ አላውቅም። ድኅረ ደርግ ድርጀቱ ከተመሰረተ ጀምሮ ያሳለፋቸውን ሒደቶች ማጥናት ለሚፈልግ ብዙው መረጃ ለማግኘት ምቹ ነበርና ከጓደኞቼ ጋር በቅርበት ለማየት ችለናል። ከድርጅቱ ቀደምት መስራቾች ጀምሮ አሁን እስካሉት ድረስ ለእስልምና ያላቸው አሉታዊ አመለካከት የሚታወቅ ቢሆንም ድርጅቱን ለማቆም የከፈሉት መስዋዕትነት ግን የሚካድ አይደለም።

ተቋሙ እንዲበረታ የግል ኢጓቸውን ከማፈን ጀምሮ ግለሰቦች ያልገነኑበት ተቋም እንዲሆን በሲኖዶሱ አጋዥነት (ኃላ ተቃርኖ ውስጥ ቢገቡም) ሰፊ ስራ ለመስራት ሞክረዋል። ሰንበት ት/ቤቶችን ማደራጀት፣ የግቢ ጉባኤዎችን መምራትና ማገዝ፣ ኦርቶዶክስ ገጥሟት የነበረውን የተሀድሶ ፈተና በመታገል ረገድ የሰሩት ስራ ቀላል አልነበረም። አሁን ላይ በተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት የምታዮቸው ታዋቂ ግለሰቦች ሁሉ በአንድ ወቅት በአንድ ላይ የተሰባሰቡበትና በሙያቸው ድርጅቱን ያገዙበት ነበር።

በመዋቅር ደረጃ እንደ ኢትዮጵያ ሰፊ ቅርንጫፍ በመክፈት፣ ከፍተኛ ፋይናንስ በማንቀሳቀስ፣ ሰፊ የሰው ኃይል በመምራትና የተደራጀ የሚዲያና ኮሚንኬሽን በማዋቀር ከሲኖዶሱ ያልተናነሰ ኔትዎርክ በመላ ሀገሪቱ መፍጠር ችለዋል። እንደ አንድ ተቋም በተለይም ለእምነቱ ሰዎች ሞዴል መሆን የሚችል የተቋም ግንባታን ሰርተው አሳይተዋል።

የዛሬ 10 አመት ገደማ የሙስሊሙ የዳዕዋ እንቅስቃሴ ከወትሮው ከፍ ያለበት ጊዜ ነበር። በመሀል የመጡት የመንግስት ጭቆናዎች መነቃቃቱ ላይ ውሀ ቢቸልሱበትም ባልታሰበ መልኩ ደግሞ ለጭቆናው የተሰጠው ግብረ መልስም ሌላ የመነቃቃት ምዕራፍን የፈጠረ ነበር። ያንን ጥንካሬና አንድነት እንዲሁም መስዋዕትነት ለተመለከተ ሰው ከጥያቄው መልስ በኃላ ሁሉም ነገር ይቀዛቀዛል ብሎ የጠበቀ ያለ አይመስለኝም።

መሪዎቹም ሆኑ ከጀርባ የነበሩ አስተባባሪዎች ያንን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ወደ ተቋም ለማምጣት የተሻለ እድሉም አቅሙም ነበራቸው። ተቋም መገንባቱን መጅሊሱ ላይ ብቻ ተውነውና አጋዥ ተቋማትን የመፍጠሩ ሒደት ላይ ተዘናጋን። ለዚህ በርካታ የግል ምክንያቶች/ኡዝሮች ሊነሱ ይችላሉ፣ እድሉን በማባከን በኩል ግን የሚለውጡት ነገር የለም። በተበታተነ መልኩ ከሚደረጉ ያልጠረቁ ስራዎች በተሻለ ግለሰብ ያልገነነባቸው አሰባሳቢ ድርጅቶች እውን ቢሆኑ መልካም ነበር። ዘመንም ትውልድም መሻገር የሚችሉት "ተቋም" ሲሆኑ ነው። መጭው ጊዜም አንዳለፉት አመታት እንዳይባክን ዱዓ እናድርግ.! አንዳንድ የሚባክኑ እድሎች ድጋሚ በቀላሉ አይገኙም።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

30 Oct, 16:29


ዶ/ር ቶማስ ላምቤ አንድ ግለሰብ ናቸው። ከ100 አመት በፊት የተከበረ የህክምና ሙያቸውንና የሞቀ ኑሯቸውን ጥለው የጅማ ህዝብ "ኢየሱስን ሳያውቅ ሊሞት ነው" በሚል ቁጭት ክርስቲያን ሊያደርጉት አዲስ አበባ ገቡ። በወቅቱ በነበረው የኦርቶዶክስ ሀገረ መንግስት ምክንያት "ወንጌል ለመስበክ" ፍቃድ ማግኘት አልቻሉምና በብላቴ ጌታ ህሩይ ምክርና እገዛ "ለመዝናናት" በሚል ሰበብ አስፈቅደው የጅማ ጉዟቸውን ጀመሩ።

ጉዞው በእግር ስለነበርና መንገዱም በደንብ ግልጽ ስላልነበረ ጅማ ያሰቡት ሰው መንገድ በመሳሳታቸው ምክንያት ራሳቸውን ሀድያ ሆሳዕና አገኙት። በወቅቱ በሆሳዕና ደጃዝማች መሸሻን አገኟቸው፣ በህክምና ስራቸው ቀድመው ይተዋወቁ ነበርና ደጃዝማቹ ሀገረ ግዛቱ ላይ የጤና ተቋምና መሠል የማኅበራዊ ግልጋሎት ቦታዎችን እንዲሰሩላቸው ተማጸኗቸው። አስከትለውም የወላይታና የሲዳማ ሀገረ ገዥዎችም "ለእኛም እባክዎትን" ሲሉ ተማጸኗቸው።

ጅማን በልባቸው ቢያረግዙም "እዚህም ለጊዜው ወንጌል መስራት ጥሩ ነው" በሚል ሀሳብ በሶስቱ አካባቢዎች "Instititional model" ተብሎ በሚጠራው መንገድ እየተዘዋወሩ ህክምናና ሰበካውን ተያያዙት። በኃላም እሳቸው ያቋቋሙት "አቢሲኒያ ፍሮንቲየር ሚሽን" እና በወቅቱ ስመ ጥር የነበረው "ሱዳን ኢንቲርየር ሚሽን" በጋራ በመጣመር ሶስቱን አካባቢዎች ከሞላ ጎደል ፕሮቴስታንት ማድረግ ቻሉ።

ልብ ብላችኃል?ዶ/ር ቶማስ አንድ ሰው ናቸው፣ ብቻቸውን ሶስት ሰፋፊ አካባቢዎችን በጽናት "ማክፈር" ቻሉ። በዚያ የመኪና መንገድ እንኳን በሌለበት አስቸጋሪ ጊዜ በትጋት ስራቸውን ሰሩ። አንድ ሰው ቢሆኑም ማስተባበር የሚችሉበት እድል፣ ገንዘብ እና በስልጣን ካሉ ሰዎች ጋ ያለ ቅርበትን፤ ሁሉኑም በሚገባ ተጠቅመውበት ዘመን መሻገር የሚችል ስራ ሰሩ።

እኛ አሁን ላይ ስንት "አንድ ሰው" አለን?ጥቂት ያልሆኑ በርካታ "አንድ ሰዎች" አሉን። ሰውን ማስተባበር፣ ገንዘብ የማዘጋጀት፣ ዳዒውን በተቋም በኩል ሰፊ ስራ እንዲሰራ ለማድረግ ወራት እንኳን የማይፈጅባቸው ጥቂት የማይባሉ "አንድ ሰዎች" አሉን። ለምን አልተሰራም?አላውቅም፣ ምናልባት እድሉ ካለፈ በኃላ በየፊናው እንወቃቀስ ይሆናል..! አላህ ግን ይጠይቀናል፣ የሰጠን እድልና አቅም ባለመጠቀማችንና በማባከናችን እያንዳንዳችንን ያለ ጥርጥር ይጠይቀናል።

https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

30 Oct, 12:35


ከዚህ በፊት የተለቀቀው ፖስት ላይ የነበረው ሊንክ ስላስቸገረ ተቀይሯል፣ አዲሱን ይጠቀሙ..!

እስልምና ላይ ጥያቄ ያጫረባችሁ ጉዳይ ኑሮ ጥያቄ መጠየቅና መልሱን ማግኘት ለምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች በተቀመጠው ቡት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።

ጥያቄ ስትጠይቁ ግን የሚከተሉትን ከግምት አስገቡ፦

❐ በተቻለ መጠን ጥያቄያችሁ ረጅም ጹሁፍ ፍርዋርድ ከማድረግ በዘለለ ስፔስፊካሊ ጥያቄ የፈጠረባችሁን ክፍል ብቻ አጭር አድርጎ ማስቀመጥ ላይ ያተኩር።

❐ ቮይስ ሪከርድ ወይንም ቪዲዮ ሪከርድ ከሆነም ከ1 ደቂቃ ያልበለጠ ይሁን፣ በተቻለ መጠን ጥያቄውን አጭርና ግልጽ በሆነ መልኩ ለማቅረብ ሞክሩ።

❐ ፈትዋ ነክ ጉዳዮችን አትጠይቁ፣ እነሱን በተለያዩ መንገዶች ምላሽ የሚሰጡ ዑለሞች ስላሉ ለነሱ አቅርቡ። በዚህ ክፍል ንጽጽር ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎችን ብቻ ለመጠየቅ ሞክሩ።

❐ ጥያቄዎችን የምመልሰው በቅደሞ ተከተል ስለሆነ በትዕግስት መጠበቅ ላይ አደራ እላችኃለው። በቻልኩት ልክ ሁሉንም በተራ ለመመለስ ስለምሞክር በመሀል እየመጣችሁ "የኔ ለምን አልተመለሰም" በሚል ወቀሳና ስድብ አትሰንዝሩ። በአላህ ﷻ ፍቃድ ሆንብየ የምተወው ምንም ጥያቄ አይኖርም። ስለዚህ በዚያ መልኩ ለመጠባበቅ ሞክሩ ኢንሻአላህ።

▣ ከጥያቄ በተጨማሪ አስተያየት ካላችሁም ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

https://t.me/Yahyanuhe1

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

29 Oct, 16:52


"አውልቀው ይማሩ"

እንደ ሙስሊም አንድ ሰው በአንድ አስተምህሮ ዙሪያ የተለያየ አቋም ሊኖረው ይችላል። ለአብነት ኒቃብን በተመለከተ "ኒቃብ ፈርድ ነው" ብሎ የሚያስብ ሊኖር ይችላል። አልያም "ሙስተሀብ ነው" ብሎ የሚያምንም ሊኖር ይችላል። ነጥቡ ግን እሱ አይደለም፤ ዋናው ነገር እንደ አንድ የሀገሪቱ ዜጋ "ፍላጎታችን ኒቃብ ለብሶ መማር ነው" ብለው የሚያምኑ ሰዎች መብታቸው እስከምን ድረስ ነው? የሚለው ይመስለኛል።

"ኒቃብ እለብሳለሁ" የምትል እንስት ተማሪ ሀገሪቱ እሷን ያማከለ የመብት ማዕቀፍ የለውም?እንደ ዜጋ ለእሷ የሚሰጥ የመብት ከለላ የለም? ይህንን ጥያቄ የጠየቀ ሰው ሁሌም እንደ ባዕድ ዜጋ ምርጫ አልባ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ "ኒቃብ አውልቃ ትማር" የሚለው መልስ እስከመቸ ነው ብቸኛ ምርጫዋ ሊደረግ የሚገባው?

ኒቃቧን ለብሳ መማር የምትችልበትን የአሰራር ማዕቀፍ ማዘጋጀት ምን ያክል ከብዶ ነው ለዘመናት ሙስሊም ሴቶች በዚህ ጥያቄ መከራቸውን የሚያዩት?የቀናነት ችግር ከሌለ በስተቀር በጣም ኢምንት የሙስሊም ቁጥር ያለባቸው ሀገራት ሳይቀር አመቻምቸውና መብታቸውን ሳይጨፈልቁ የሚፈጽሙትን ቀላል ተግባር በዚህ ደረጃ የትውልድ መከራ አናደርገውም ነበር።

በመጅሊሱም በኩል ይሁን በምሁራኑ በኩል ትኩረት መደረግ ያለበት ይህ ይመስለኛል። ዘላቂ የህግ ማዕቀፍና የአሰራር ሒደት እንዲዘጋጅለት ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል። የዛሬ 30 አመት የነበረ ችግር ላይ ዘንድሮም መከራከር አድካሚና ጉልበት ጨራሽ ነው።

https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

27 Oct, 12:14


በተለያዩ ምክንያት ወደ የትኛውም ሀገር መጓዝ ካሰቡ እና የበረራ ትኬት ከፈለጉ ፈሲሩ ጋ ደውሉላቸው፣ ትኬት በተመጣጣኝና በአነስተኛ ዋጋ ከነሱ ጋ ታገኛላችሁ። በአጭር ሰአት የዱባይ ቪዛም ያወጡላችኃል።

- የበረራ ትኬቱን በየትም ቦታ ሆናችሁ ማስቆረጥ ትችላላችሁ።

▣ ፈሲሩ ትራቭልና ትኬት ኦፊስ

0911273017
0907710101

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

26 Oct, 18:26


ህይወት ማለት በአላህ መንገድ ላይ የተኖረው ብቻ ነው። ከዚያ ውጭ ያለው ሁሉ ቅጽበታዊ ከሆነው በቀር እርካታ ቢስና ትርጉም አልባ ነው..!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

26 Oct, 12:09


የእስራኤል ወታደሮች ናቸው፣ ንጹሀን ላይ የለመዱት መሳርያ ወንዶቹ ጋ ሲሆን እንዳሰቡት አልሆነላቸውም።

https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

26 Oct, 10:56


"እስራኤል ሀያልነቷን የሚያሳይ ጥቃት ትሰነዝራለች" ነበር ያሉት፣ አይ እስራኤል..! ርችት እራሱ ቢልኩ ከዚህ የተሻለ ይፈነዳል።


https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

24 Oct, 08:20


ጣልያናዊው ጓድ ፍራንኮ ፎንታና የፍልስጤማውያን ሰቆቃ ሲያንገሸግሸው ለነጻነታቸው ሊታገል በ1970ዎቹ ፍልስጤም ምድር የከተመ ሰው ነበር። በወቅቱ የነበሩ ሙጃሒዶችን በተለይም በሮኬት ተኩስ ካገዙ ወታደራዊ ጠበብቶች መካከል ነበር። በመጨረሻም በጣልያን ያፈራውን ንብረት ሁሉ በመሸጥ ለትግሉ አበረከተ።

ይህ ቀና ሰው በስተመጨረሻም አላህም ﷻ ሒዳያውን ወፍቆታል። በ2005 እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ለፍልስጤማውያን ህዝቦች ነጻነት ሲታገል እድሜውንም፣ ህይወቱንም፣ ንብረቱንም ሰውቷል። በመጨረሻ ጊዜዎቹ ከተናገረው ውስጥ፦

"ምናልባት እኔ የፍልስጤማውያንን ነጻነት ለመመልከት አልታደልኩ ይሆናል፣ ግን ያለምንም ጥርጥር ልጆቼና የልጅ ልጆቼ የፍልስጤማውያንን ነጻነት ያያሉ። ያኔም ለዚህች የተባረከች ምድር የከፈልኩትን መስዋዕትነት ይረዳሉ"

አላህ ﷻ ይዘንለት፣ ያለምንም ጥርጥር ቁድስ ከወራ*ሪዎቿ ነጻ ትሆናለች - ኢንሻአላህ..!

https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

23 Oct, 16:20


ከተወሰነ ወራት በፊት አንድ ስሙን የማልጠቅሰው ኢስላማዊ ተቋም ሙስሊም በዝ አካባቢ ላይ ለወጣቶች ስልጠና አዘጋጅቶ ነበር። ይህንን ስልጠና ስፖንሰር ያደረገውና በርዕሱ ዙሪያ ስልጠና እንዲሰጥ ያመቻቸው ደግሞ በሚያስደነግጥ ሁኔታ የሚሽነሪ ድርጅት ነው።

ኢስላማዊ ተቋሙ ስለ ድርጅቱ በቂ መረጃ ከሌለው በሚል ወንድሜ አብዱረሒም አህመድ ጋ ተመካከክረን ለድርጅቱ አመራሮች እንዲደርስ አደረግን። ከዚያ በኃላ ተቋሙ ከሚሽነሪ ድርጅቱ ጋር ያለውን አሰራር ያቁም አያቁም ባላቅም በይፋ ያየነው ነገር አልነበረምና እንዳቆመ በማሰብ ጉዳዩን ለጊዜው ገታ አደረግነው።

እንዳሰብነው በዚህ ብቻ ቢቆም ግን መልካም ነበር። ይህ የሚሽነሪ ድርጅት አሁን ደግሞ በአንድ አካባቢ ከሚሰሩ ኢስላማዊ ተቋማት ጋር በህብረት መስራቱን ገልጾ አየን። በዚህኛው ስራው ላይ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የመጅሊስ አመራሮችንም ጭምር አሳስቶ ተሳታፊ እንዳደረጋቸውም ጭምር አስተዋልን። አመራሮቹን ሆን ብለው ከፊት አምጥተው በማያቁት ነገር ቡራኬ እንዲፈጽሙላቸው አድርገዋል።

የሚሽነሪ ተቋማቱ ይህኛው መንገድ ያዋጣናል ብለው የመጡ ይመስላሉ። ሙስሊሞቹ ስለነሱ እንደማናውቅ በመገመትም ይሁን ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ በሚሰጡን ደጎስ ያለ የገንዘብ ድጋፍ እንታተለላለን ብለው በመገመት በተለይም ሙስሊም በዝ አካባቢዎች ላይ ወጥመዳቸውን ዘርግተዋል።

ኢስላማዊ ተቋማት ላይ የምትሰሩ አካላት በተቻላችሁ መጠን አብራችሁ የምትሰሯቸውን አካላት ማንነት ለማጣራት ሞክሩ። ባለማወቅ የሴራቸው መጠቀሚያ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። በተለይም ተቋማቱ የግብረ ሰናይ ድርጅት ሁነው ግን መሠረታቸው የውጭ ሀገር ከሆነ በደንብ ለማጣራት ሞክሩ።

ድርጅቱንና አታሎ የሰራቸውን ስራዎች አስመልክቶ በቀጣይ በአላህ ﷻ ፍቃድ በዝርዝር የምንጽፍ ይሆናል።


https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

23 Oct, 11:51


ዛሬ ኢንሻአላህ ለ2 ሰኣት ገደማ የሚቆይ ፕሮግራም በቲክቶክ ይኖረናል። በአጀንዳው ዙሪያ ምላሽ ወይንም ማብራሪያ መስጠት የምትፈልጉ ክርስቲያኖች በፕሮግራሙ ላይ ትገኙ ዘንድ ተጋብዛችኃል።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

22 Oct, 07:49


የእድሜ ልክ ልፋታችሁ በአንድ ጀንበር ሲወድም ህመማችሁን ለመጠገን ቃልም ይጠፋል። አላህ ሰብሩን ይወፍቃችሁ፣ የሪዝቁ ባለቤት በተሻለና በእጥፉ ይተካችሁ።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

21 Oct, 08:50


የጀርመን፣ የብሪታንያ እና የአሜሪካ መንግስታት ይህንን ሚሳኤል ለአሸባሪው የጽዮናውያን ወራሪ ሀይል በጋዛ ውስጥ ያልታጠቁ ፍልስጤማውያንን ለመግደል ቢልኩትም ሚሳኤሉ ግን ቤት ላይ ወድቆ ሳይፈነዳ ቀረ። የፍልስጤም ሙጃሒዶች እንደገና ተጠቅመውበት የአሸባሪውን የጽዮናውያን ታንኮች አፈነዱበት።

🔻🇵🇸

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

20 Oct, 17:36


ከአዲስ አበባና እና ሸገር ሲቲ ከተማ ውጭ በሚገኙ መርከዞች ያላችሁ ፎርሙን አትሙሉ፣ ይህ ፎርም የሚመለከተው አዲስ አበባና ሸገር ሲቲ ላሉ መርከዞችና የዲን ትምህርት ተቋማት ብቻ ነው።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

20 Oct, 17:34


የቀረው እድል የሁለት ተቋማት ብቻ ነው..! ቀሪው አራት ተሟልቷል።

ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የቀረበ የትምህርት እድል

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በተለያዩ አካባቢዎች ከሚሰጣቸው የንጽጽራዊ ሀይማኖት ስልጠናዎች በተጨማሪ፣ በአዲስ አበባ እና በሸገር ሲቲ የሚገኙ የተለያዩ መርከዞችና ኢስላማዊ የትምህርት ተቋማትን አወዳድሮ ከፊል የትምህርት እድል ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።

የንጽጽር ትምህርት ስልጠናው ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ለአንድ አመት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ማዕከሉ ባዘጋጀው ስርአተ ትምህርት/Curriculum/ መሠረት በዘርፉ ልምድ ባላቸው ኡስታዞች አማካኝነት ይሰጣል።

በዚህ የትምህርት እድል ለመስጠት የታቀደው የመርከዞችና የትምህርት ተቋማት ብዛት 6 ሲሆን በዚህ ዘርፍ ተማሪዎቻቸውን ማብቃት ለሚፈልጉ ተቋማት ባስቀመጥነው መስፈርት መሠረት አወዳድረን እድሉን እንሰጣለን።

በዚህም መሠረት በተቋማችሁ ውስጥ የኃላፊነት ወይንም የውሳኔ ሰጭነት ሚና ያላችሁ ወንድምና እህቶች ብቻ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ፎርም በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፦

https://bit.ly/4dvInRv

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

19 Oct, 18:42


ሂዝቡላህ የኔታንያሁን ቤት ያለምንም ከልካይ በድሮን መምታት ችሏል። ድሮኑ ኔታንዮህን ቀጥታ አገኘውም አላገኘውም በዚህ ጥቃታቸው ያስተላለፉት መልዕክት ግን ጠንካራ ነው። እስራኤል ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን የሀገሪቱን መሪ መኖሪያ ቤት በቀላሉ ከ70 ማይል ርቀት ኢላማውን ጠብቀው ማጥቃት ከቻሉ፣ እስራኤል ውስጥ ለማጥቃት የሚቸግራቸው ምንም ኢላማ የለም ማለት ነው።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

18 Oct, 18:56


በሀድያ ዞን ሆሳዕናን ጨምሮ በርካታ የሚሽነሪ ት/ቤቶች አሉ። በዞኑ ያለው የሙስሊም ት/ቤት ግን አንድ ብቻ ነው። እሱም በሻሸጎ ወረዳ ቦኖሻ ከተማ የሚገኘው ኑር ት/ቤት ነው። በዚህ ት/ቤት በሚሽነሪ ት/ቤቶች ሊማሩ የነበሩ በርካታ ሙስሊም ልጆች ይማሩበታል።

ይህ ት/ቤት ግን በርካታ ወጭዎች ገጥመውት እየተንገዳገደ ይገኛል። ሁሉኑም ወጭዎች መሸፈን እንኳን ቢከብድ አሁን ላይ አንገብጋቢ ማነቆ የሆነባቸውን የመምህራን ደሞዝ ተባብረን እንድንሸፍንላቸው ለመማጸን ወደ እናንተ መጣሁ። የአንድ አመት የመምህራን ደሞዝ 600ሺ ብር ነው። ይህ በእርግጥ በአንድ ሰው ሊሸፈን ይገባው የነበረ ቢሆንም በአቅማችን ልክ ሁላችንም አኽለል ኸይር በመሆን እንድንሸፍነው እጠይቃችኃለው።

ከዚህ በታች የተቋሙን አካውንት አስቀምጣለሁ፣ ከ100 ብር ጀምሮ የአቅማችሁን በመነያት የኸይር ስራው ተጋሪ ይሁኑ፣ ከቻሉ ያስገቡበትን ደረሰኝ ኮሜንት ላይ በማስቀመጥ ለሌላውም መነሳሳት ይፍጠሩ፦

1000655472006
ቦኖሻ ከተማ አስተዳደር እ/ጉ የግንባታ ማንቀሳቀሻ አካውንት

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

18 Oct, 14:32


🤲 መስጅድ አል-ነበዊ

የሕያ ሲንዋር በጋዛ ከተገደለ ከአንድ ቀን በኋላ ኢማሙ በዛሬው የጁምዓ ኹጥባ አላህ ፍልስጤማውያንን ድል እንዲያጎናጽፋቸውና እና ሰማዕቶቻቸውን እንዲቀበል ዱዓ አድርገዋል።

https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

18 Oct, 14:30


የሕያ ሲንዋርን ለጠቆማቸው በርካታ ገንዘብ እንደሚሰጥ ወራሪው ኃይል ቃል ገብቶ ነበር። በመካከላቸው በቅርበት አብሯቸው ሲኖር አንድም የጋዛ ነዋሪ ግን አሳልፎ አልሰጠውም። የጋዛ ህዝብ ምን ያክል ይወደው እንደበር ግልጽ ነው። ህዝቡ እስከ መጨረሻው ድረስ ለትግሉና ለጠላቱ ያለው አቋም ቅንጣት የተዛነፈ አልነበረም።


https://t.me/Yahyanuhe

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

18 Oct, 11:47


አንድ ጅሀድ ውስጥ ያሉ ሼይኽ በቀለጠ ውጊያ መሀል ለሚዲያ ቃለ መጠይቅ ይሰጣሉ። በድምጽ የሚሰጥ ኢንተርቪው ቢሆንም ከጀርባ ያለው የመሳርያ ተኩስ በከፍተኛ ድምጽ ይሰማል። ጋዜጠኛው በመጨነቁና በመፍራቱ ጥያቄዎቹን በቅጡ መሰደር ሁሉ አልቻለም። በዚህ ሁሉ መሀል መልስ የሚሰጡት ሸይኽ ግን ከጀርባቸው መሳርያ የሚያፏጭባቸው አይመስሉም። ፈጽሞ በተረጋጋ ድምጽ ለተጠየቁት ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ። እያንዳንዱ ንግግራቸው ከመሳርያው ድምጽ ተነጥሎ በጆሮ ኩልል ብሎ ይገባል።

ሰው ሁለት አይነት እንደሆነና የመጃሒዶች ደረጃ ፈጽሞ የተለየ እንደሆነ ሙሉ ክስተቱ ያስረዳል። የጅሀድ ሰዎችን ቁርኣኑ "ወንዶች" ሲል ጠራቸው። እነዚህ የት እንደሚገኙ ሲነግረንም "ወይ ቃላቸውም ጠብቀው በጅሀድ ላይ ተገድለዋል፣ አልያም ሞታቸውን በጉጉት የሚጠባበቁ ናቸው" ከዚህ ውጭ እዚህ ምድር ላይ ሲኖሩ ለማሳካት የሚመኙት ሌላ ህይወት የለም። ያለቻቸው ህይወት ልክ እንደኛው አንድ ናት፣ እሷንም ከአላህ ጋር ሊገበያዩባት አይሳሱም። ታዲያ እነዚህ ከማን ጋ ይወዳደራሉ?

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

18 Oct, 04:34


የእስራኤል ጦር በለቀቀው የድሮን ፉቴጅ የመጨረሻ የሲንዋርን ሰአታት ማሳየት ችሎ ነበር። በታንክና ከባድ መሳርያ ተኩስ ባደረሱበት ጥቃት አንድ እጁን አጥቶ እንኳን በስናይፐር እስከተገደለበት ቅጽበት በጽናት እየተዋጋቸው ነበር። ህዝቡን ማግዶ ከኃላ የሚቀር መሪ አልፈጠሩም፣ ከዋሻ ጀርባም ወታደር እየላከ አልተዋጋቸውም። ፊት ለፊታቸው ተዋድቋል፣ አልሸሸም፣ አልዞረም። ሲያገኙት ከነ መሳርያው ነው። እየሞተ ሳይቀር ድል አደረጋቸው..!እናትማ እናንተን ወልዳለች..!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

17 Oct, 17:21


የሕያ ሲንዋር 25 ዓመታትን በአይሁድ እስር ቤት አሳልፏል። ህክምና እንዳያገኝ ከልክለውት ለጥቂት ከሞት ተርፏል። በዘመናችን ከተደረጉ ጅ*ሀ*ዶች ውስጥ ከፍ ያለው የሆነውን ይህንን ጅ*ሀ*ድ ዋሻ ውስጥ በአመራርነት ብቻ ማሳለፍ አልፈለገም። ከሚመራቸው ሙጃሒዶች ጋር አብሮ ሲታገል መሳርያውን እንደተንተራሰ አርፏል። አላህ ከሸሒዶች ይቀበለው፣ ሺዎችን የሚተካ ሸሒድነትም ያድርግለት..! የፍልስጤም ትግል በመሪዎች ሞት እየበረታ እንጅ እየቀነሰ አልሔደምና የድል ጊዜውን ያቅርብላቸው፣ አሚን!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

17 Oct, 16:00


a wounded lion is still a lion.

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

15 Oct, 16:57


ከአመታት በፊት ዳዕዋ ለማድረግ ፈተና ነበር። በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ግን የዳዕዋዎች ብዛትና መነቃቃት መልካም ነበር። አሁን ላይ በሚያሳዝን ሁኔታ ዳዕዋው በጥቂት ሰዎች ጫንቃ ላይ ብቻ ጭላንጭሉን እያየን ነው። የነገን አላህ ያውቃል..! ገጠሩ ከምንጊዜውም በላይ የአክፍሮተ ሀይላት አደጋዎች አንዣበውበታል። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እንደምናየው አይደለም፣ መሬት ላይ ያለው ነገር ፈጽሞ የተለየ ነው። በተቻለ መጠን ጥረቶች ቢኖሩም ቀረብ ብለን ስናየው ግን በተቃራኒ በኩል የሚሰራው ሰፊ ስራ ያስደነግጣልም፣ የኛን ሁኔታ ላስተዋለ ደግሞ ተስፋ ያስቆርጣል። ከጊዜያዊ ምቾታችን ስንባንን እንዳያረፍድብን ያሰጋል።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

15 Oct, 10:21


https://hidayacomparative.org/?p=739

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

15 Oct, 08:11


ከሰሞኑ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በተገኙበት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አንድ ንግግር አድርገው ነበር። በንግግሩ ላይ ከንቲባው በስሜት ተውጠው ሰበካ ሲያደርጉ ታይተዋል። በእርግጥ ሰበካ ማድረጋቸው አልያም የግል ሀይማኖታቸውን መግለጻቸው እንደ ግል የሚወቀስ ላይሆን ይችላል።

የሀዋሳ ህዝብን እንደ መሪ ወክለው በተገኙበት መድረክ ግን "ብቸኛው መፍትሄ ኢየሱስ ነው" የሚል ቃል ሲናገሩ እንደ መንግስት ኃላፊነታቸውም ስህተትና ሴኩላሪዝሙን የጣሰ ወንጀል ነው። ይህንን የማያምነው የሌላ እምነት ተከታይ በሳቸው ቢሮ ውስጥ ያለውን ቦታ በቀላሉ የሚጠቁም አደገኛ ንግግር ነው።

በእርግጥ በከተማው ሴኩላሪዝም እየተፋቀ በሒደት ወደለየለት የሀይማኖት መር ከተማ እያዘገመ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ሒደት ውስጥ ከፕሮቴስታንቱ ውጭ ያለው የእምነት ተከታይ የሚደርስበትን ቢሮክራሲያዊ መጉላላት በተደጋጋሚ የምንሰማው እውነታ ነው።

ከተማዋ በአደባባይ "ኢየሱስ መፍትሄ ነው" የሚል ከንቲባ ቢኖራትም "መዳን በእስልምና ነው" የሚል አንድ ምዕመን ግን ድምጹን ከፍ አድርጎ መናገር የማይችልባት ከተማ ናት።

የደቡቡ የለየለት ፕሮቴስታንታዊ ሞናርኪ እንደ ሀገር የወደፊቱ ፈተናችን ነው..!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

13 Oct, 18:04


አልሐምዱሊላህ...!

በሀድያ ዞን ወረዳዎችን ማዕከል ባደረገ መልኩ ቦኖሻ ላይ የነበረው ኮርስ በሰላም ተጠናቋል፣ አልሐምዱሊላህ። ባለፉት 6 ወራት ውስጥ በሀድያ ዞን ብቻ ሶስት ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች መሠረታዊ የንጽጽር ኮርሶችን በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አማካኝነት መስጠት ተችሏል።

ይህኛው ስራ በአካባቢው በዳዕዋ ለመስራት በማሰብ በቅርቡ ከተመሰረተው አል-ሰባት የንጽጽር ማዕከል ጋር በመተባበር የተሰራ ሲሆን ከትምህርቱ በተጨማሪ ለወደፊት የዳዕዋ ስራዎቻቸው የልምድ ልውውጦችም የተካሔዱበት ነበር። እንደ ሁሉም አካባቢዎች ለሰልጣኞች የሚያሰራጩት ፓምፍሌትና በጋራ የሚያጠኗቸው መጽሀፍትም ተበርክቶላቸዋል። በአሏህ ﷻ ፍቃድ መሠል ስልጠናዎችና የዳዕዋ ስራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል እና የዳዕዋው አካል ለመሆን፦

https://bit.ly/4aGr93u

በቴሌግራም በኩል ሊያገኙን ከፈለጉ፦
@Hidayaislamiccenter

1000499318212
Hidaya Islamic Center
አጭር የንግድ ባንክ ቁጥር - 8212

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

12 Oct, 10:38


ወደ ደቡብ በተለይ ከወራቤ ጀምሮ እስከ ሀላባ ያለው መንገድ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ክፉኛ ተበላሽቷል። ውስጡን ያሉ የሀድያ ወረዳዎችም ተመሳሳይ የመንገድ ችግር አለባቸው። በዚህ መሀል ወላድ እናትን ጨምሮ አስቸኳይ ህመም ለሚገጥመው ሰው ፈተናዎቹ ከባድ ናቸው። የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራው ወይንም ቢጠግነው የማኅበረሰቡን ስቃይ ማቃለል ይቻል ነበር።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

10 Oct, 13:26


ቀኑን ባላስታውሰውም በአንድ ወቅት በሆሳዕና ከተማ ሊዘጋጅ የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት እዚሁ ፌስቡክ ላይ በነበረ ዘመቻ ምክንያት ተሰረዘ። የዘመቻውም ምክንያትም "ሀድያ የወንጌላውያን መሬት ስለሆነች ሙዚቃ አይዘፈንባትም" የሚል ነበር።

በወቅቱ ሙዚቃውን ማስቆማቸው እንደ መልካም ነገር ተወስዶ ስለነበር "ዘፋኙን ብቻ ሳይሆን ምዕመኑንም ከሙዚቃ እንዲያግዱ" በማበረታታት ብዙው ሰው በተግባራቸው ተደስቶ ነበር። በግሌ መሳሳቴ የገባኝ ግን ዘግይቶ ነበር።

ለአንድ የዳዕዋ ስልጠና በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ በነበርንበት ወቅት ጀለብያ መልበሴን የተመለከቱ አንድ ትልቅ ሰው ቀለል አድርገው "ይሄ የእግዚአብሔር ምድር ነው" አሉኝ። በተዘዋዋሪ ምድሩ የወንጌላውያን መሆኑንና አንድ የሙስሊም ልብስ የለበሰ ሰው በዚህ ምድር መገኘቱ ያሳሰባቸው የሚመስል ነው። በወቅቱ ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር።

ከሰሞኑ በሀዋሳና ወላይታ ሊዘጋጅ የታሰበ የሙዚቃ ኮንሰርትን በተመሳሳይ ድምጸት እነዚሁ ሰዎች ለማገድ ሞክረዋል። የሙዚቃ ኮንሰርት አለመካሔዱ እንደ አንድ ሙስሊም በግሌ የምደግፈው ነው። ተቃውሞዬም እገዳው ላይ ሳይሆን ከእገዳው ጀርባ ያለው ቀስቃሽ ምክንያት/Motive/ ጋር ነው።

እነዚሁ ሰዎች ከተሞቹን የራሳቸው ብቻ አድርገው ከነሱ አመለካከት ውጭ ያለ አካል በህጉ መሠረትም ቢሆን የራሱን ተግባር እንዲከውን ያልፈለጉት "ምድሪቷ የእግዚአብሔር ምድር ናት" ብለው ስለሚያምኑ ነው። የእግዚአብሔር ያሉት ምድር ላይ አዛን መስማት ባለመፈለግ ሙስሊሞችን በተደጋጋሚ ሲበድሉ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። በከተማው በነበርንበት ወቅት የሰማናቸው ግፎች ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ነበሩ።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መስጅድና መቀበሪያ ተከልክለው ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉ ሙስሊሞችን ለቅሶ በሀሩን ሚዲያ መሰናዶ ውስጥ አይተናል። ይህንን ለመዘገብ የሄዱ ጋዜጠኞች ለጥቂት ከእስር ተርፈው ያመለጡትም በዚሁ ዞን ነው።

ሙዚቃውን አለመፈለግ መብታችሁ ነው፣ ከዚህ ክልከላ ጀርባ ያለው ሞቲቫችሁ ግን አደገኛ ነው። በዚህ ተግባራችሁ "ሌላኛውን አክሱም" ሳትፈጥሩ በፊት መጠንቀቁ ይበጃልና "አካሔዳችሁን አስተካክሉ" ማለት ያስፈልጋል።

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

09 Oct, 17:42


አልሐምዱሊላህ፣ 90ሺ ገደማ ተከታታይ የነበረው ፔጄ ከአንድ አመት እገዳ በኃላ በዛሬው እለት መለቀቁን ፌስቡክ ገልጾልኛል..!

የዛሬ አመት ገደማ ፌስቡክ ላይ አንድ የወቅቱን ጉዳይ የተመለከተ ነገር ጻፍኩ፣ ትንሽ ቆይቶ ፌስ*ቡክ ጹሁፌን በማ*ጥፋት ማስጠንቀቂያ ሰጠኝ፣ ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ነበርና ሌላ ተመሳሳይ ሀሳብ እንዲሁ በሰፊው ጻፍኩ፣ በዚህ ጊዜ የወሰደው እርምጃ ግን ሙሉ ለሙሉ ፔጁን መጠቀም እንዳልችል የሚያደርግ ነበር። በዚህ ደረጃ አሁንም የቀጠለውን የወቅቱን ግ*ፍ ለመሸፈን ሰፊ ርቀት እንደሚጓዙ ለመረዳት ግን ምንም ጥሰት የሌለውን ግን ደግሞ በደ*ልን የሚያወግዝ ጹሁፍ ስለተለጠፈ ብቻ ፔጁን ለአንድ አመት አገዱት። ደጋግሜ አፒል ባስገባም ብዙ ሰው ዘንድ ይደርስ የነበረውን ይህንን አካውንት መመለስ አልቻልኩም ነበር። ከአመት በኃላ ፔጁን መልቀቃቸውን አሳወቁኝ። "ለምን ሲባል እስካሁንስ?" ብለን መጠየቅ ቅንጦት ነውና ቀሪ ጊዜ መልዕክት ለማድረስ ስለፈቀዱልን አመስግነን መቀጠል ነው። በስተመጨረሻ ፔጁ መለቀቁ መልካም ነገር ነው፣ በዚያ በኩል እንደገና ለመገናኘት መልካም እድል ነውና አልሐምዱሊላህ..!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

08 Oct, 05:04


https://youtu.be/LsG0Ka4rJoA?si=GI8u6QFC0QSaaQVm

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

06 Oct, 18:00


አጋጣሚ ከቤት ውጭ ብርድ ላይ ስለነበርኩ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ብርዱ ራሴን ያዞረኝ ነበር የመሠለኝ፣ ግን እንደዚህ አይነት ራስ ምታት የሚፈጥር የቅጽበት ብርድ ፈጽሞ ገጥሞኝ ስለማላቅ በጤናየ ዙሪያ ህመም ነው በሚል እየተጠራጠርኩ ነበር። በደቂቃዎች ልዩነት ቤት ስገባ ነው የመሬት መንቀጥቀጥ መሆኑንና ይህ ስሜት የኔ ብቻ እንዳልነበር የተረዳሁት። ከሰከንዶች በላይ ቆይቶ ቢሆን ምን ነበር የሚፈጠረው?የሚለውን ማሰብ ያስጨንቃል። አላህ ከድንገተኛ አደጋ ይጠብቀን..!

16,749

subscribers

1,089

photos

240

videos