- ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 21/2017
በዳዕዋ ስራዎቻቸውና በሙስሊሙ ማኅበረሰብ አወንታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በስፋት በመሳተፍ የሚታወቁት ኡስታዝ አቡበከር አህመድና ኡስታዝ ያሲን ኑሩ የሀሩን ሚድያ አዲስ አበባ ስቱድዮን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው ወቅታም ሀሩን ሚዲያ ላለፉት ሰባት ዓመታት በሚዲያው ዘርፍ እየሰራቸው ያሉትን ስራዎች አስመልክቶ በሚድያው የአዲስ አበባ ስቱድዮ ስራ አስኪያጅ አቶ ባህሩ አባስ አማካኝነት ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
ኡስታዞቹ በመልዕክታቸውም ሀሩን ሚድያ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመረጃ ክፍተት በመሙላት እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሚድያውን በተለያየ መንገድ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።
© ሀሩን ሚድያ