ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና @kidusmikaelhikmna Channel on Telegram

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

@kidusmikaelhikmna


ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና (Amharic)

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና በቀላል የአላህ ወንጌላዊት ህዝብ የሚሆነው ተግባር በኢንተር኷ውስ መረጃና ከዛ ፊት በሳይንቲግራፊ ውይም ከማእከል ጋር ነው። ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና ለሁሉም አድራጊ ህዝብ እና ክርስቲያን የሚሆነውን ፅሁፎች ለተመሳሳይ ክብር እንዲሰጡ ቶክ ላይ ይበልጥ እንዲሆን። ይህ ተግባር በተጠናቀፍን ጊዜ ሰጥተን በፊት ተግባሩን በመረጃዎቹ እና እውነታዎቹ እንዲሁም ከሌሎቹ መልክቶቹ ከተግባር በጣም አንብብን።

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

20 Nov, 12:32


የሴት ልጅ ብልት ፈሳሽ መፍትሔ

የሴት ልጅ ብልት ፈሳሽ ሊበዛ ሊያስ ይችላል በተለያዩ ምክንያቶች፣ በጣም ሲበዛ ግን የ ማህፀን ኢንፌኮሽን ምልክት ሊሆን ስለሚችል በጊዜ ሀኪም ማማከር ተገቢ ነው።

መንስኤዎቹ

1)የወሊድ መከላከያ መድኒት ለረጅም ጊዜ የተጠቀመች ሴት ተጋላጭ ትሆናለች
2) ለ3 ጊዜ በላይ ማሶረድ
3) ሽንት ቤት ተጠቅመን ከጨረስን በሃላ ከታች ወደ ላይ ማፅዳት
4)ስፖርት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በምናረግ ጊዜ ቶሎ መታጠብ ፓንትን ቶሎ አለመቀየር
5)መጨነቅ መረብሽ ሐሳብ መብዛት
6)እንቁላል ማዘውተር አንደኛው ምክንያት ሊሆን ስለሚችል አለማብዛት
እነዚ ነገሮች ተጋላጭ ያረጋሉ።

የመሳሰሉት ለመቅረፍ መሞከር
በወር አበባ ግዜ ሊለወጥ ይችላል
በወሊድ የመለዋወጥ ባህሪ አለው

ምልክቱ
1)ማሳከክ
2)በሴክስ ጊዜ ማቃጠል
3)ሽንት ቶሎ ቶሎ መጣው ማለት
4)የፈሳሽ መልክ መቀየር ቢጫ ቡና አረንጎዴ ወይም ግራጫ እና ሽታው ይቀየራል


የቤት ውስጥ ማድረግ ያለብን ነገሮች
1)ቴምር ሳናበዛ መጠቀም ከበዛ ለስኳር እንጋለጣልን
2)የወይባ ጢስ ጥቅሙ ከፍተኛ ነው
3)በጥጥ የተሰሩ የዉስጥ ፓት መጠቀም እና በየቀኑ መቀየር
4)ሽንት ቤት ስንፀዳዳ ባክቴርያ ወደ ውስጥ እንዳይገባ ጥንቃቄ ማድረግ
5)10 ግራም የእርድ ዱቄት በግማሽ ብርጭቆ ውሃ አፍልቶ ወደ ውስጥ ዘልቆ መታጠብ
6)ነጭ ሽንኩት ዝንጅብል ሎሚ አንድ ማንኪያ አሞሌ ጨው/salt/ የምንለው አንድ ላይ በማዋሀድ በ15 ቀን 2 ጊዜ ብቻ መጠቀም ለ10 ደቂቃ እስከ 20 ደቂቃ መዘፍዘፍ አፉልቶ በውሃ መታጠብ
7)ዛፈራን ሳይበዛ በሳምንት ሁለቴ መጠቀም

ከላይ የተዘረዘሩ በቤት ውስጥ አድርጋቹ ለውጥ ከሌለው በፍጥነት የማህፀን ሐኪም ማማከር አለባችሁ።

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

18 Nov, 13:30


የጆሮ እንፌክሽን

- የጆሮ እንፌክሽን በብዛት በባከቴሪያ ወይም በቫይረስ ምከንያት የሚከሰት የህመም አይነት ነዉ፡፡የጆሮ ኢንፌክሽን ብዙ ጊዜ የላይኛውን የአየር ቧንቧ ከሚያጠቁ በሽታዎች ጋር ተያይዞ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡

- የላይኛውን የአየር ቧንቧ (እንደ ጉንፋንና አለርጂ የመሳሰሉት...) የሚያጠቁ በሽታዎች በሚኖሩ ጊዜ የጆሮን የመካከለኛውን ከፍል እና ጉሮሮን የሚያገናኘው ቱቦ (eustachian tube) ያብጥና አየር ወደ መካከለኛው የጆሮ ክፍል እንዳይገባ ያደርጋል፡፡

ይኼም በመካከለኛው የጆሮ ክፍል ውስጥ ፈሳሽ እንዲጠራቀም እና ለባከቴሪያ አመቺ የመራቢያ ሁኔታን እንዲፈጥር ያደርጋል፡፡

-ባከቴሪያ ከተራባ በኋላ በአካባቢው ያሉ ህዋሶችን በመግደል መግል እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ መግል በበዛ ቁጥር የጆሮ ታምቡርን _ በመጫን _ ህመም እንዲሁም የመስማት ችግርን ያስከትላል፡፡

የህመሙ ምልክቶች

- የጆሮ ላይ ህመም

- ከጆሮ ፈሳሽ/መግል መዉጣት

- መስማት መቀነስ

የራስ ምታት

ትኩሳት

- መንገዳገድ/ባላንስ ማጣት

- አንዳንዴም የጆሮ መጮህ እና ማዞር ይከሰታል

እነዚህ የህመም ምልክቶች በተከታታይ ቀናት/ጊዜያት ሊታዩ ይችላሉ ወይም ሊመጡ እና ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ ምልክቶቹ በአንዱ ወይም በሁለቱ ጆሮዎች ሊከሰት ይችላል፡፡ በሁለቱ ጆሮዎች ላይ ከተከሰተ ህመሙ በጣም አደገኛ ነው፡፡

የጆሮ ኢንፌክሽን ሥር የሰደደ (chronic) ወይም ከባድ (Acute) ሊሆን ይችላል፡፡

- ከፍተኛ (Acute) የጆሮ ኢንፌክሽን በጣም የሚያሠቃዩ ነገር ግን አጭር ጊዜ የሚቆዩ ናቸው፡፡

ስር የሰደደ (chronic) የጆሮ ኢንፌክሽኖች ብዙ ጊዜ አይጠፉም ወይም ብዙ ጊዜ ይደጋገማሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ጆሮ ላይ ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች

እድሜ ፡- ከ6 ወር እስከ 2 ዓመት ያሉ ህፃናቶች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸዉ

ወቅታዊ ሁኔታዎች፡- የጆሮ ኢንፌክሽን ጉንፋን በብዛት በሚከሰትበት በብርዳማ ወቅት በብዛት ይታያል፡፡

ለተበከለ አየር መጋለጥ፡- ከፍተኛ የአየር መበከል ወይም የሲጋራ ጢስ መታፈን ለጆሮ ኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

ይህን በሽታ በቤትዎ ሁነው የሚከተሉትን በመተግበር ህከምና ማድረግ ይችላሉ፡፡

ሙቅ ነገር ቦታዉ ላይ መያዝ፡- ይህ ህመሙን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

የህመም ማስታገሻ መድሃኒት፡- የህክምና ባለሙያዎች የህመም ማስታገሻ መድሃኒት ሊያዝሎት ይችላል፡፡

ፀረ ባክቴሪያ (Antibiotics)

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

15 Nov, 13:16


እግር ሽታ

በእግር ሽታ ምክንያት ሰው በተሰበሰበበት ጫማዎን ወይም ካልሲዎን ማውለቅ ይፈራሉ? የእግርዎ ጠረን ለራስዎ ጭምር ይረብሽዎታል?

ብሮሞድሮሲስ ወይም በተለምዶ የእግር ሽታ በሚባለው በሽታ ተጠቂ ይሆናሉ። በሽታው በሰው ፊት ለሃፍረት የሚያጋልጠን በሽታ ነው፡፡

ይህ በሽታ ብዙ ግዜ የሚፈጠረው እግርዎን ሲያልብዎት ነው። ካልሲ እና ጫማዎ የሚተነውን ላብ እንዳይወጣ ሲያግደው ሽታ ይፈጠራል። በእግራችን ቆዳ የሚገኙ ባክቴሪያዎች በላባችን ላይ በመመገብ ሲያድጉ ሽታው እየጨመረ ይሄዳል፡፡

ለምንድን ነው እግራችን የሚሸተው?

ማንኛውም ሰው በማንኛውም ግዜ በእግር ሽታ በሽታ ሊጠቃ ይችላል። ወቅቱ ሞቃት መሆን የለበትም። ቢሆንም በሽታው በእርጉዝ ሴቶች እና ታዳጊዎች ላይ ይስተዋላል። በእነዚህ ወቅቶች ሰውነታችን የሆርሞን ለውጥ የሚያካሂድ በመሆኑ ለበሽታው የበለጠ እንጋለጣለን፡፡

• በእግሩ ረጅም ሰአት የሚቆም ወይም የሚጨነቅ ሰው የበለጠ ስለሚያልብ ለበሽታው ተጋላጭ ይሆናል።

• የበለጠ እንድናልብ የሚያደርጉ ጫማዎች እና ካልሲዎች አሉ፡፡ እንሱን አድርገን ለረጅም ሰአት ስንቆይ ለሽታ እንጋለጣለን፡፡

ላባችን ላይ የሚያድጉት ባከቴሪያዎች ላባችን ላይ የሚገኝ ሊውሲን የተባለ ንጥረ ነገር ላይ ተመግበው አይሶቫሌሪከ አሲድ ያመነጫሉ። ይህ አሲድ ነው ጠረን እንደባከቴሪያው አይነት ጠረኑ ይበረታል። የሚፈጥረው::

ሃይፐርሃይድሮሲስ የሚባል በሽታ ካለን የበለጠ ላብ ስለምናልብ ለበሽታው ይበልጥ እንጋለጣለን።

የሰውነታችንን ንጽህና የማንጠብቅ ከሆነም እንታመማለን፡፡ እግራቸውን በየግዜው የማይታጠቡ ወይም ካልሲ የማይቀያይሩ ሰዎች በእግራቸው ላይ ለባክቴሪያው ምቹ መኖርያ ይፈጥራሉ።

በሽታውን ለማጥፋት በቤት ውስጥ ማድረግ የምንችላቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ የተወሰኑት እነሆ፡፡

1) እርሾ

እርሾ ወይም ሶድየም ባይካርቦኔት ለእግር ሽታ ፍቱን መድሃኒት ነው። በላባችን ውስጥ የሚገኘውን የኬሚካል ንጥረ ነገር በመቀየር ባክቴርያ እንዳይበራከት ያደርጋል።

ሙቅ ውሃ ውስጥ እርሾውን ከጨመርን በኋላ እግራችንን ከ15- 20 ደቂቃ ውሃ ውስጥ መጨመር። ለአንድ ሳምንት እንዲህ እያደረግን መቆየት አለብን፡፡ ካልሆነም ጫማ ከማድረጋችን በፊት ጫማና ካልሲያችን ውስጥ እርሾ በትንሹ ጣል ማድረግ እንችላለን፡፡

2) ላቬንደር ዘይት

ላቬንደር ዘይት ጥሩ ሽታ ከመኖሩም በላይ በባክቴሪያ ገዳይነቱ ይታወቃል። በጸረ ኦከሲዳንት እና ጸረ ፈንገስ ባህሪው ይታወቃል።

እግራችንን ዘይቱ ጠብ የተደረገበት ሙቅ ውሃ ውስጥ በመጨመር በሽታውን ማስወገድ እንችላለን። ከ15-20 ደቂቃ እግራችንን መዘፍዘፍ ይኖርብናል። በቀን ሁለቴ ማድረግ ያስፈልጋል።

3) አቸቶ

አቸቶ አሲዲከ ይዘት ስላለው ባከቴሪያዎች እንዳይራቡ ያደርጋል። የትኛውም አይነት አቸቶ ያገለግላል፡፡

አንድ ግማሽ ብርጭቆ አቸቶ እና 8 ብርጭቆ ሙቅ ውሃ በማቀላቀል እግራችንን ከ10-15 ደቂቃ መዘፍዘፍ በቂ ነው። በመጨረሻም የአቸቶውን ጠረን ለማጥፋት እግራችንን በሳሙና መታጠብ እንችላለን፡፡

4) የዝግባ እንጨት ዘይት

የዝግባ እንጨት ዘይት ከሚያውድ ጠረኑ በተጨማሪ ፀረ- ባከቴሪያ እና ፀረ- ፈንገስ ይዘት ያለው ዘይት ነው፡፡ የእግር ሽታን ለመከላከል ፍቱን መድሃኒት ነው።

እሱን ወይም የኮኮናት ዘይት ተጠቅሞ የእግር ባክቴሪያ መግደል ይቻላል። ቆዳም ለማለስለስ ይረዳል።

ዘይቱን በእግራችን ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ካሸን በኋላ ካልሲ አድርገን መንቀሳቀስ እንችላለን። ለአንድ ሳምነት በቀን አንዴ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

5) ቤቢ ፓውደር

ቤቢ ፓውደር ወይንም ታልከም ፓውደር _ ላባችንን መጦ እግራችንን በማድረቅ ከመጥፎ ጠረን ይከላከልልናል።

እግራችን ወይም ጫማሽን ውስጥ በትንሹ በቀን ሁለት ወይም ሶስት ግዜ በመርጨት መጥፎ ጠረን መከላከል እንችላለን።

6) ዝንጅብል

ዝንጅብል የባክቴሪያ እድገትን እና ጎጂ ንጥረ ነገሮችን በመከላከል ይታወቃል፡፡

መካከለኛ ትልቀት ያለው ዝንጅብል ካደቀቅን በኋላ ከ10-15 ደቂቃ ሙቅ ዉሃ ውስጥ እንዘፈዝፋለን፡፡ ከዛም ዝንጅብሉን ከውሃው አጥልለን አውጥተን እግራችን ላይ እንቀባለን፡፡ ከመተኛችን በፊት ማድረጉ ይመከራል። ለሁለት ሳምንት መደጋገም ያስፈልጋል።

ቆሻሻ ወይም እርጥበት የያዘ ካልሲ ማድረግ የምንቀጥል ከሆን ግን እዚህ _ የተዘረዘሩት መፍትሄዎች አይበጁንም። በዚህ ሁኔታ ለተወሰነ ግዜ ማስታገሻ ብቻ ነው የሚሆኑት። የሚበጅዎትን መፍትሄ እስከሚያገኙ እየቀያየሩ መፍትሄዎቹን መሞከር ይችላሉ፡፡

ሌላ የእግር ሽታ የምንከላከልባቸው ዘዴዎች

በየቀኑ እግራችንን በሳሙና መታጠብ። ጭቃ እና የሞቱ ሴሎችን ለማስወገድ በደንብ መፈግፈግ ይኖርብናል።

• የእግር ጥፍራችንን በየግዜው መቆረጥ

• የታችኛው እግራችንን በመዳሰስ ጠንካራ ቦታዎችን መፈለግ። ጠንካራ ቦታ ማለት የሞቱ ሴሎች ያሉበት ነው። ለማስወገድ እግራችንን ጨው በተቀላቀለበት ሙቅ ውሃ ውስጥ መዘፍዘፍ ተገቢ ነው፡፡

• በየግዜው ካልሲ መቀየር
• ከፍተት ያላቸው ጫማዎችን ማዘውተር ናቸው፡፡

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

13 Nov, 13:41


ሱስ

ሱስ ስንል ማንኛውም ነገር በሰዎች ላይ የአካላዊና ስነልቦናዊ ጥገኝነት በመፍጠር ሠዎች ለመነቃቃት፣ድብርትን - ለማስወገድ፣ጀብዱ ለመስራት፣ህመምን ለማስታገስና ከፍተኛ የደስታ ስሜትን ለመጎናፀፍ ብለው የሚያጨሷቸው፣የሚቅሟቸው፣በአፍንጫ የሚስቧቸውና በደም ስር የሚወስዷቸውን ነገሮች በሙሉ ያካትታል።ያለአነኝህ ዕፆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሲያቸውን ማከናወን ሲሳናቸው የሱሰኝነት ጠባይ እንዳላቸው ይገለፃል።ሰዎች ከላይ ዕውነታዎች በተጨማሪ ሱስ የሚያሰዙ ነገሮችን በተለያዩ ምከንያቶች ይጠቀማሉ።ከእነዚህም መካከል የጓደኛ፣የቤተሰብና የአካባቢ ተፅዕኖ እንደ ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ ይጠቀሳል።እንደ ቀልድ አንድ ብለው የጀመሩት ሲውል ሲያድር አንድ የህይወታቸው አካል ይሆንና ህይወታቸውን በማመሰቃቀል እሰከ ህይወት ህልፈት ሊያደርሳቸው ይችላል።በተለይ አምራች ሃይል በሚባሉ ወጣቶች ላይ ሱስ የሚያመጣው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም፡፡አገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ወጣቶች ያሏት እንደመሆኗ መጠን ወጣቱ በሱስ የተያዘ ከሆነ የአገሪቱ መጻኢ ዕድል የተንሰራፋ ድህነት፣ኋላቀርነት፣ወንጀልና ለሃገር ሸክም የሚሆን ዜጋ ስለሚኖር በቀጣይ ጤናማ ትውልድ ማፍራት አዳጋች ይሆናል።ወጣቶች ለረጅም ጊዜ በሱስ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ብዙ
ችግሮችና ተግዳሮቶች በፊታቸው ይደቀንባቸዋል።ወጣቶች ሱስ ውስጥ በመግባታቸው ምክንያት የሚከሰቱ ተፅዕኖዎችን ለአብነት ያክል እንመለከታለን፡፡

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

11 Nov, 09:48


የነርቭ ህመም

የነርቭ ህመም ባልተጠበቀ ሁኔታ በተለያዩ የዕድሜ ደረጃ ላይ ባሉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ህመም ነው።ምልክቶችም የሚከተሉት ናቸው

1.መደንዘዝ:ስሜታዊነርቮች/sensorynerves/መጎዳታቸውን የምናውቅበት የመጀመሪያው ምልክት የመደንዘዝ እና የመውረር ስሜት በእጅ፣ በጣት፣ በእግር፣ እና በእግር ጣቶች ላይ ሲፈጠር ነው። ስሜታዊ ነርቮች ስራቸው የስሜት መልእክት መላከ ሲሆን ጉዳት ሲያጋጥማቸው ቆይቶ ወደ መደንዘዝ የሚቀየር የመውረር ስሜት ይሰማናል። በጊዜው ተገቢ ህከምና ካላገኘ ይህ ስሜት ወደ ሌሎች የሰውነት አካሎች ሊዛመት ይችላል። ህመሙ ከጊዜ ጋር እየጨመረ የቀን ከቀን ኑሮአችንን ያስተጓጉላል። እጅ እና እግር ላይ ለሚፈጠር የመደንዘዝ ስሜት ሌሎች መንስኤዎች እግር እና እጅ ላይ የተፈጠረ ከፍተኛ ጫና፣ ለብርድ መጋለጥ፣ እንቅስቃሴ የሌለበት የአኗኗር ዘይቤ እና የቫይታሚን ቢ12 እና ማግኒዚየም እጥረት ናቸው፡።

2. ህመም:- ሌላ የነርቭ ህመም ምልከት የሚሰነጥቅ ወይም የሚያቃጥል የህመም ስሜት ነው፡፡ የዚህ አይነት ስሜት እጅ እና እግር ላይ የሚፈጠር ሲሆን ከሌላ የህመም ስሜት ይለያል። ህመሙ የሚፈጠረው ስሜታዊ ነርቮች ላይ በተፈጠረ ጉዳት ነው። ስሜት በአግባቡ ከአእምሮ ወደ ቆዳ መተላለፍ ካልቻለ የተጎዳው ቦታ ላይ ከፍተኛ ህመም ሊሰማን ይችላል። የህመሙ ቦታ በተጎዳው ክልል ዙሪያ ብቻ ወይንም ሰፊ የሰውነት ክልል ላይ ሊፈጠር ይችላል። ህመሙ ብዙ ጊዜ በምሽት ይባባሳል። ከነርቭ ጉዳት ውጪ የስኳር በሽታ፣ የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ወይም የጀርባ አጥነት ሰረሰር ላይ የተፈጠረ ጉዳት ለከባድ የህመም ያጋልጠናል።

3. የጡንቻ ድካም:- ጡንቻ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርገውን መልእክት የሚያስተላልፉ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ ድካም ይፈጥራል። አልፎም ጡንቻን የመቆጣጠር ችሎታ ሊያሳጣ ይችላል። ለጡንቻችን የሚላከው መልእከት በአግባቡ ካልተላለፈ መራመድ እንቸገራለን፡፡ በእጃችን እቃዎች ለማንሳት እና ጭብጥ አድርጎ መያዝ ይከብደናል። በነርቭ ጉዳት ምክንያት ጡንቻ ጥቅም ላይ የሚውልበት ጊዜ ሲቀንስ እራሱ እየደከመ ይመጣል። ጡንቻ መዳከም ከነርቭ ጉዳት ውጪ እንደ ፓርኪንሰን በሽታ፣ የዲስክ መንሸራተት፣ ስትሮክ የመሳሰሉ ህመሞች መንስኤው ይሆናሉ፡፡

4. የጡንቻ መሸማቀቅ:- የእንቅስቅሴ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ ሊያመጣ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ በራሱ የተጎዱት ነርቮች ላይ በሚፈጥረው እንቅስቃሴ ጉዳቱን ሊያባብስ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ የሚፈጠረው የእንቅስቃሴ ነርቮች በብዛት ሲሰሩ ነው፡፡ የመሸማቀቅ ስሜት ክብደቱ ቀላል፣ መሃከለኛም ወይንም በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል።

5. የላብ ችግር:- የሰውነት አካልን የሚረዱ ነርቮች ሲጎዱ አውቶኖሚክ ኒውሮፓቲ የሚባል ህመም ሊያስከትል ይችላል። አውቶኖሚከ ነርቮች ሲጎዱ የላብ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ላብ ሲፈጠር ሌሎች ላይ ደግሞ የላብ መቀነስ ይታያል። ላብ በአግባቡ ካልመነጨ ሰውነታችን ሙቀቱን በአግባቡ መቆጣጠር አይችልም። በከፍተኛ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት ችግሩ ይገዝፋል፡፡

6. ሽንት ቤት መመላለስ:- የሽንት ፊኛ ሽንትን በደንብ እንዲይዝ ብዙ ነርቮች አብረው መስራት አለባቸው፡፡

የነርቭ ጉዳት ሲፈጠር የሽንት ፊኛ ሽንትን ቶሎ ቶሎ ለማስወገድ ይሞክራል። የነርቭ ጉዳት የሽንት ፊኛ ጡንቻዎች የሚያደርጉትን መኮማተር እና መላላት በተገቢው መልኩ እንዳያደርጉ ያስተጓጉላል። የሽንት ፊኛ ችግር ሌላ መንስኤ ሊኖረው ይችላል።

ልጅ በወለዱ እናቶች እና የስኳር በሽታ ታካሚዎች ላይ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡

7. ከባድ ራስምታት:- ኤሌክትሪከ ንዝረት የሚመስል አጭር ጊዜ

የሚቆይ ከባድ ራስምታት የነርቭ ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል። ህመሙ የአከሲፒታል ኒውራልጂያ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል። ኦከሲፒታል ኒውራልጂያ አንገት ላይ ያለ የነርቭ መቆንጠጥ በሽታ ነው፡፡ ህመሙ የላይኛው አንገት ክፍል ወይም ጭንቅላት ጀርባ ላይ ይፈጠራል።

8. ሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር:- የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር ወይም መንገዳገድ ሌላ የነርቭ ጉዳት ምልክት ነው:: ወድቀው ሊጎዱ ስለሚችሉ ይህን ምልክት ችላ ማለት የለብዎትም፡። የነርቭ ጉዳት አእምሮ የሰውነትን እንቅስቃሴ በአግባቡ እንዳይቆጣጠር ያደርጋል። ይህ ሁኔታ ወድቀው እንዲጎዱ ሊያደርግ ይችላል። የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር የፓርኪንሰን ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።

በቤት ውስጥ ልናደርጋቸው የሚገቡ ህክምናዎችን እንሆ፦

1. የሳማ ስር፣ቅጠል፣ግንድ እና አበባውን ለያይቶ በማድረቅ እያንዳንዱን ለየብቻ በመውቀጥ ( በመፍጨት) ከሁሉም አንዳንድ ስኒ እየተለካ ከ አንድ ኪሎ ወለላ ማር ጋር ተለውሶ በየአንድ ቀን ልዩነት ህመም የሚሰማን ቦታ መቀባት

2.በነጭ ሽንኩርት እንፋሎት በቀን ሁለት ግዜ መታጠን

3.አንድ ፍሬ ነጭ ሽንኩርት ቆርጥመው በሎሚ ወይንም በግመል ወተት በቀን ሁለት ግዜ እየተጉመጠመጡ መዋጥ ይህም ለአንድ ሳምንት መቀጠል አለበት

4.አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ከአምስት ጠብታ ጥቁር አዝሙድ ጋር እየተደባለቀ ጠዋት ጠዋት ለአንድ ወር መውስድ፡።

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

08 Nov, 11:43


የሆድ ህመም

ሆድ ህመም ወይም ደዌ ማለት የሆድ ዕቃዎች መዛባት እና መታወከ ማለት ሲሆን አንጀት፣ጨጓራ፣ጉበትና ሳንባ በመታወካቸው ምከንያት የተቀበሉትን ምግብ አለመፍጨትና ወደተለያዩ የሠውነት ከፍሎች አለማስተላለፍ ነው።ይህ የሆድ ሀመም የሚከሰተው የሚበሉትን ምግብና የሚጠጡትን መጠጥ ተቆጣጥሮ ባለመውሰድ ነው ምከንያቱም ምግብም ይሁን መጠጥ ከሚወሰዱበት ጊዜ አልፎ ወደ መበላሸትና ወደ መርዝነት ከተቀየረ በኋላ ጊዜ ያለፈበትን ከመብላትና ከመጠጣት የተነሳ ተህዋስያን የምንላቸው ጀርምና ባክቴሪያ ወደ ሆድ ውስጥ ቀኑ ባለፈ _ ምግብና መጠጥ ገብተው ይከማቻሉ።ይራባሉ፤የቆሻሻ ከምችትን ይፈጥራሉ፤በዚህ ጊዜ ቁርጠትን ፣ማቅለሽለሽን፣ማስቀመጥን፣የመሳሰሉትን ሁሉ በተጠቂው ሰው ላይ እንዲቆይ ያደርጋሉ በመሆኑም ይህ ምልከት ያለባቸው ህመምተኞች መፍትሄ ወደ ሚያገኙበት ቦታ መሄድ ይኖርባቸዋል

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

06 Nov, 08:16


ቃር

የቃር ስሜት በደረትዎ እና ጉሮሮዎ ላይ የሚሰማ የማቃጠል ስሜት ነው።አንዳንዴ የሚኮመጥጥ ስሜት አብሮት ይመጣል፡፡ሌሎች አብረውት የሚመጡ ስሜቶች ማቅለሽለሽ፣የሆድ መንፋት፣ፈስ እና መተንፈስ መቸገር ናቸው።የማቃጠል ስሜት የሚመጣው ሆዳችን ውስጥ የሚገኙትአሲዶች ወደ ላይ ወደ ሆድ ወደሚወስደው ቧንቧ ሲወጡ ነው።ይህ የሚሆነው በቧንቧውና በሆዳችን መሃል ያለው መዝጊያ በደንብ ሳይዘጋ ሲቀር ነው።ለዚህ ነው ብዙ ጊዜ የቃር ስሜት የሚሰማን ።ጮማ ነክ ወይም የተጠበሱ ምግቦች የቃር ስሜት መነሻ ምከንያት ሊሆኑ ይችላሉ።ስሜቱ በሂያታል ኸርንያ ሀመም አማካኝነትም ሊሆን ይችላል።ሂያታል ኸርኒያ የሆድ ዲያፍራማችንን አልፎ ወደ ደረታችንን የመምጣት በሽታ ነው።ቃር በእርግዝና ወቅትም የተለመደ ነው። በአኗኗር ዘይቤአችም የቃር ስሜት ሊጨምር ይችላል።የምናጨስ ከሆነ፣ቡና እና መጠጥ የምናበዛ ከሆነ፣የሚያቃጥሉ ምግቦችን የምናዘወትር ከሆነ፣ከልክ በላይ ውፍረት ከጨመርን፣ከበላን በኋላ ምንተኛ ከሆነ፣ለህመሙ ይበልጥ ተጋላጭ እንሆናለን፡፡ይሁን እንጅ አልፎ አልፎ የሚሰማ የቃር ሰሜት የተለመደ በመሆኑ የሚያሳስብ አይደለም።ሆኖም ስሜቱ በተደጋጋሚ የሚያጠቃን ከሆነ ጋስትሮኤሶፋጋል ሪፍለከስ ሀመም ይዞን ሊሆን ስለሚችል ተገቢ ህከምና ማግኘት ተገቢ ነው በመሆኑም ለዚህ በሽታ ፈውስ ለማግኘት በቤት ውስጥ ህከምናውን ማድረግ ይቻላል ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግብዓቶች የአዘገጃጀት መመሪያዎችን ተግብሮታል በመቀመም በጥንቃቄ ይውሰዱ፡፡

ሀ)የመጋገሪያ እርሾ

እርሾ ወይም ሶድየም ባይካርቦኔት በፍጥነት የቃር ስሜትን ሊያስታግስ ይችላል።እርሾ በይዘቱ ፀረ-አሲድ በመሆኑ ሆዳችን ውስጥ ያለውን አሲድ ይቀንሳል።

አዘገጃጀቱም፦

*አንድ የሻይ ማንኪያ እርሾ ከውሃ ጋር ማቀላቀል እና እንደአስፈላጊነቱ የሎሚ ጠብታዎችን በማቀላቀል በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ መጠጣት ይቻላል፡፡

ለ)አፕል ሳይደር አቸቶ

አፕል ሳይደር አቸቶ ለቃር ሰሜት ጥሩ ነው።አቸቶው የጉሮሮ ቧንቧውን መዝጊያ እንዲዘጋ በማድረግ የሆዳችን አሲድ ወደላይ እንዳይወጣ ይረዳል።ሆዳችን ውሰጥ ያለውን የአሲድ ፒ.ኤችን በመቀነስ ህመሙን ያስታግሳል።ይህን መድሃኒት በቤት ውስጥ ራስን ለማከም እንዲህ ማዘጋጀት ይቻላል።

አንድ የሻሂ ማንኪያ አቸቶው ከአንድ ብርጭቆ ሙቅ ውሃ ጋር ማቀላቀልና ትንሽ ማር ጠብ በማድረግ ከምግብ በፊት መጠጣት ነው።

ሐ)ሰናፍጭ

ሰናፍጭ የቃር ሰሜትን ለመቀነስ የሚረዳ ሌላ የምግብ አይነት ነው።የአፍ ጠረን የሚያመጣብንን አሲድ በመቀነስም ይታወቃል።ሰናፍጭ ውስጥ ያሉ እንደካልሴም ፣ማግንዜም፣ዚንከና አይረን የመሳሰሉት ንጥረነገሮች በሆዳችን ውስጥ ያለን ምግብ ለመፍጨት የሚረዱ ናቸው፡፡ከሰናፍጭ የሚዘጋጅ መድሃኒትን ማንኛውም ሰው በቤት ውስጥ ማዘጋጀት የሚችል ሲሆን ዝግጅቱም እንደሚከተለው ነው፡፡

*ሁለት የሻሂ ማንኪያ ሰናፍጭ ከአንድ ብርጭቆ ውሐ ጋር በማደባለቅ ፍሬዎችን ሳይቆረጥሙ ይዋጡ።

መ)ዝንጅብል

ዝንጅብል ሌላኛው የመድሃኒት ዓይነት ሲሆን የቃር ስሜትን በሁለት መልኩ ይቀንሳል።አንደኛ ሆድ ውስጥ ያለውን አሲድ ይመጣል።ሆዳችን ውስጥ ያለው አሲድ ወደ ላይ የመውጣቱን ዕድል ይቀንሳል።የማቃጠል ስሜትንም ይቀንሳል።አወሳሰዱም፦

ዝንጅብሉን ምግብ ሲሰሩ እንደማጣፈጫ አብረው ጨምረው መውሰድ ካልሆነም በሻይ አፍልቶ ወይም በደረቁ መውሰድ ይቻላል።

ሠ) እሬት

ከእሬት ፈሳሽ ተጨምቆ የሚወጣ ጁስ የቃር ስሜትን በማስታገሱ በብዙ ሰዎች ዘንድ ተጠቃሚነትን አግኝቷል።እሬት የቃጠሎን ስሜት ይቀንሳል።ጋስትሮ እኒቴስቲናል ትራከት የሚባለውን የሆዳችንን አካል በማከም ይታወቃል።የጨጓራ ድጋፍ ሰጭ በመሆን በምግብ ድቀት ሂደት ውሰጥ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡እንደመድሃኒት ሲወሰድ ግን ሩብ ብርጭቆ የሚያከል የእሬት ጭማቂ ምግብ ከመመገባችን ከ20-30 ደቂቃ በፊት መጠጣት ተገቢ ነው።አብዝቶ መጠጣት ግን ትቅማጥና ሆድ ቁርጠት ያመጣል።

ረ)ማስቲካ

ስኳር ያልያዘ ማስቲካ ማኘከ የቃር ሰሜትን ለማጥፋት ይረዳል።ማስቲካ ማኘክ በአፋችን ምራቅ ይበልጥ እንዲመነጭ ያደርጋል።ምራቃችንን ይበልጥ አልካላይን በማድረግ ሆዳችን ውስጥ ያለውን አሲድ ያቀዘቅዛል።በ2005 በዴንታል ምርምር ጆርናል የታተመ ጥናት እንደሚለው ከምግብ በኋላ ለ30 ደቂቃ ማስቲካ ማኘከ አሲዲከ ፖስትፕራንዲያል ኤሶፋጋል ሪፍለክስን እንደሚቀንስ ይተነትናል።አሲዲቲን ለመከላከል ከምግብ በኋላ ለ30 ደቂቃ ማስቲካ ያኝኩ፡፡

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

04 Nov, 11:44


ቆረቆር

ብዙን ጊዜ ህፃናትን ያጠቃል፡፡ በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን፡፡ይህ Anthropophilic ወይም Zoophilic በተሰኘ ፈንገስ አማካኝነት የሚመጣው ቆረቆር የተሰኘው የራስ ቅል በሽታ በሌላ ስሙ የራስ ቅል የቀለበት ትል( Scalp ringworm) ተብሎ ይታወቃል፡፡ ከሌሎች የቆዳ በሽታዎች ይልቅ በጣም ተላላፊ ነው፡፡

የበሽታ ምልከቶች
1. መጀመሪያ ሲወጣ ትንሽ ክብ መሳይና ቅርፊት ያለበት እባጭ ሆኖ ነው፡፡ ይህም ቁስል በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሰፋል፡፡

2. ቁስሉም በሙሉ በሰፋ ጊዜ ነጣ ይልና እንደ ቀለበት ከብ ወይም እንደ አንቁላል ሞላላ ይሆንና ቅርፊት ይዞ በዙሪያው የተወሰነ ዳርቻ ይኖረዋል፡፡

3. አብዛኛውን ጊዜ ብዙ ቁስሎች በአንድ ጊዜ በአንድ ቦታ ላይ ይወጣሉ፡፡

4. ቁስሉ መጀመሪያ እንደወጣ በፀጉሩ ለማወቅ አይቻልም፤ቆይቶ ግን ቁስሉ ከወጣበት ቦታ ላይ የሚበቅለው ፀጉር ይደርቃል፡፡ ወዝ የለሽ ይሆንና እየተሰበረ ሲወድቅ በቀላሉ ሊመዘዝ የሚችል የፀጉር ቁራሽ በራስ ላይ ይቀራል፡፡

5. ራስን ሁልጊዜ ያሳከካል እንግዲህ ይህን በሽታ በቤታችን ውስጥ እንዲህ አክመን መፈወስ ስለምንችል መፍትሄዎን እንሆ!

መፍትሔ፦

1.ቁስሉ ባለበት ቦታ ላይ የበቀለውን ፀጉር መላጨት፣መቁረጥ፣ወይም _ መንቀልና ራስን ደህና አድርጎ በሳሙና ካጠቡ በኃላ አሥር ፐርሰንት አሞንያ ያለበት የሜርኩሪ ቅባት ወይም የኃይዌት ፊልድ ቅባት የሚባለውን በቀን ሁለት ጊዜ መቀባት

2. ህከምናው በሚሰጥበት በመጀመሪያው ሳምንት ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን ቅባት በቀን ሁለት ጊዜ በመስጠት ፈንታ በቀን አንድ ጊዜ ቲንከቻር ኦፍ አዮዲን መቀባት የበለጠ ይረዳል፡፡ አንድ ሳምንት ካለፈ በኃላ ቅባቱን መቀባት ነው፡፡ነገር ግን ቅባቱ ከመቀባቱ በፊት አዮዲኑ ጨርሶ መወገድ አለበት፡፡

3. Griseofulvin e Terbinafine እና itraconazole የተሰኙ የሚዋጡ መድኃኒቶች በሽታውን ለማስወገድ ወሳኝ ::

በሽታውን እንዴት እንከላከል?

1. የራስ ቁስል ካለበት ሰው ጋር አለመነካካት ወይም እሱ የነካቸውን ዕቃዎች አለመንካት

2. የሌላን ሰው ልብስ፣ ኮፍያ፣ማበጠሪያና የፀጉር ብሩሽ አለመጠቀም

3. ድመቶችና ውሾች ሳይታወቅባቸው ይህን በሽታ የሚያመጡትን ሕዋሳት እንደሚያመላልሱ አለመዘንጋት ነው፡፡ ይሁን እና ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በተለይ ከልጆች ወደ ልጆች የሚተላለፈው በጣም ቀላልና በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ አካባቢን የሚሸፍን ሲሆን በአገራችን ጭምር የዚህ በሽታ ዋነኛ የመተላለፊያ መንገድ ተደርጎ ይነገራል፡፡

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

01 Nov, 11:28


ጭርት

ጭርት በፈንገስ ምከንያት በቆዳ ላይ የሚከሰት የኢንፌክሽን ዓይነት ነው፡፡የጭርት መገለጫው ክብ ሆኖ ዳር ዳሩ ቀይና መሀሉ የዳነ የሚመስል ሲሆን የማሳከክ ስሜት ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል።ጭርት ከአንዱ ወደ ሌላው ሠዉ በቆዳ ለቆዳ ንከኪ በቀላሉ የሚተላለፍ የህመም ዓይነት ነዉ።

ጭርት ቅርፊታማና ጠፍጣፋ ሁኖ በቆዳ ላይ የሚወጣ እና አንዳንዴ የማሳከከ ባህሪና ቀላ ያለ ቁስለት ያለዉ ፣ከብ ሁነ ጠርዝ ጠርዙ ቀይ መልክ የሚኖረዉ እና ቀስ በቀስ እየሰፋ የሚመጣ የቆዳ ላይ ህመም ነዉ።ቆዳዎ ላይ የወጣ ሽፍታ ሁኖ በሁለት ሳምንት ውስጥ የማይድን ከሆነ የጤና ባለሙያን ማማከር ተገቢ ነው።

የመተላለፊያ መንገዶች፦

1.ከሰው ወደ ሰዉ፦ጭርት አብዛኛውን ጊዜ የሚተላለፈው ኢንፌክሽን ካለው ሰው ጋር ቀጥታ የቆዳ ንከኪ በሚኖርበት ወቅት ነው፡፡

2.ከእንሰሳት ወደ ሠዉ፦ጭርት የያዘው እንሰሳት ካለ እና ንከኪ ከነበረዎ ጭርት ሊተላለፍብዎ ይችላል።ለምሳሌ ከውሻ፣ ከድመት፣ ከላም ወዘተረፈ

3. ከእቃ ወደ ሠው፦የቆዳ ላይ ጭርት ያለበት ሰው በጭርት እጁ ዕቃውን ቢይዘውና ሌላ ሰው ያንን ዕቃ ቢነካው ጭርት ሊተላለፍ ይችላል።ለአብነት ያከል ልብስ፣ፎጣ፣የአልጋ አንሶላ፣የፀጉር ማበጠሪያና የጥርስ ብሩሾች ይጠቀሳሉ፡፡

4.ከአፈር ወደ ሰው፦አንዳንዴ ጭርት ከተበከለ አፈር ወደ ሰው ሊተላለፍ ይችላል።ይህ የሚሆነው ከተበከለ አፈር ጋር ለረጅም ጊዜ ንከኪ ካለ ነው፡፡

ለጭርት የሚያጋልጡ ነገሮች፡-

1.እድሜያቸው ከ15 ዓመታት የሆኑ ህፃናት
2.እርጥበታማ ፣እምቅ አየርና በተፋፈገ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ
3.በጭርት በተያዘ ሰው ወይም እንሰሳት ጋር የቅርብ ግንኙነት /ንክኪ ካለ
4.የፈንገስ ኢንፌክሽን ካለው ሰው ጋር አልባሳት፣አንሶላ፣ፎጣ በጋራ የሚጠቀም ከሆነ
5.በጣም ጥብቅ ያሉና አየር በቀላሉ የማይዘዋወርባቸው አልባሳትን የሚያዘወትሩ ከሆነ ናቸው፡፡

የጭርት መከላከያ ዘዴዎች፦

ጭርት በብዛት የሚከሰት በቀላሉ የሚተላለፍና የህመሙ ምልክቶች ሳይታዩ ወደ ሌላ ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ መሆኑ በሽታውን መከላከል ከባድ ያደርገዋል ነገር ግን የሚከተሉትን መንገዶች መተግበር ችግሩ እንዳይከሰት ሊያደርግ ይችላል።ከእነዚህም መካከል፦

*እራስንና ሌሎችን ማስተማር
*ንፅህናዎን መጠበቅ፣እርጥበትን መከላከል
*የታመሙ እንሰሳትን አለመንካት
*የግል መገልገያ የሆኑ ቁሳቁሶችን በጋራ ያለመጠቀም ናቸው::

በመሆኑም የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል በቤት ውስጥ ህከምና ራስዎን ማከም ስለሚችሉ ቀለል ካሉ የጭርት ህመሞች መፈወስይችላሉ።ለምሳሌ ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ ከሬሞችን፣ሎሽኖችን(ኬቶኮናዞልና ተርቢናፌን)የሚባሉ ሎሽኖችን መጠቀም ተመራጭ ነው፡፡
▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com

ቅዱስ ሚካኤል የባህል ሕክምና

30 Oct, 08:30


ለምፅ በሽታ

የለምፅ በሸታ የሚከሰተው በቆዳ ውስጥ ያሉት ቀለም የሚያመነጩ የሚላኒን ህዋሳት እጥረት ነው።በሽታው በቆዳ ላይ ነጣ ያሉ ነጠብጣቦች እንዲወጡ ወይም የተወሰነ የቆዳ ከፍል እንዲነፃ ያደርጋል።ይህ በሸታ በየትኛውም የቆዳ አካባቢ ላይ ሊፈጠር ይችላል ነገር ግን አብዛኛውን ግዜ በፊታችን ላይ ፣ በአፍ ዙርያ ያለውን ቆዳ፣ ዓይን ቆብ አካባቢ፣በእጃችን _ በጣት ላይ፣በእጅ አንጓ፣ ብብት፣ ብሽሽት፣ ብልት፣እንዲሁም _ በአፍ ውስጥ ክፍል ከሚጠቁት መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሱ የሰውነት ክፍሎች ናቸው። በተጨማሪም የፀጉር ስር፣ የራስ ቆዳ አናት ላይ ሊከሰት ይችላል።በቆዳ ውስጥ በሚላኒን እጥረት ፀጉር ወደ ነጭ ወይም ግራጫ እንዲቀየር ያደርጋል።ከቆዳ ስር የደም ስሮች ካሉ የተጠቃው ክፍል ከነጭነት ይልቅ የሮዝማን ቀለም ይይዛል።

▪️ማንኛውንም ለመድሀኒትነት የሚውሉ እፀዋቶችን እዚህ ቅዱስሚካኤል የባህል ህክምና ማእከል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

»ለበለጠ መረጃ፦ ወደ ቅዱስ ሚካኤል የባህል ህክምና በመምጣት ሀኪም ሰለሞን አዳሙን ያማክሩ
»አድራሻ፦አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

»ዱባይ መታከም ለምትፈልጉ ውምጲም አካባቢ ቀጠሮ በማስያዝ መምጣት ይችላሉ።
»ስልክ፦0989020202 ወይም 0911810736
website፦www.hakimsolomon.com