Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) @ibnumunewor Channel on Telegram

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

@ibnumunewor


كناشة ابن منور

كناشة ابن منور (Arabic)

تعتبر قناة 'كناشة ابن منور' هي واحدة من أفضل القنوات على تطبيق تيليجرام التي تهتم بتقديم المعلومات القيمة والمفيدة للمستخدمين. تضم القناة مجموعة متنوعة من المواضيع تتناول أحدث الأخبار والمعلومات العامة في مجالات مختلفة. إذا كنت تبحث عن مصدر موثوق للمعرفة والمعلومات، فإن 'كناشة ابن منور' هي القناة المثالية لك. فهي تقدم تحليلات عميقة ومواضيع متنوعة تلبي اهتمامات جميع القراء

من هو ابن منور؟ إذا كنت تتساءل عن شخصية ابن منور، فهو شخصية مشهورة بسبب مشاركته المستمرة للمعرفة والثقافة مع الجمهور. يعتبر ابن منور خبير في مجال الأخبار والشؤون العامة، وهو يسعى دائمًا إلى تقديم المعرفة بطريقة ممتعة وسهلة الفهم عبر قناته على تطبيق تيليجرام

ما هي قناة 'كناشة ابن منور'؟ إنها قناة تليجرام تهدف إلى تقديم المعلومات بشكل شيق وطرح تحليلات عميقة للمواضيع المختلفة. تتميز القناة بتنوع محتواها واهتمامها بتلبية احتياجات المستخدمين من جميع الفئات العمرية والاهتمامات

إذا كنت تبحث عن مصدر موثوق للمعلومات والتحليلات العميقة، فإن 'كناشة ابن منور' هي القناة التي تحتاج إليها. انضم اليوم واحصل على الوصول إلى أحدث الأخبار والتحليلات الشيقة التي تقدمها القناة.

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

10 Jan, 20:52


📌የዳዕዋ ፕሮግራም

☞ውድ የተከበራቹ ወንድም እና እህቶች በአሏህ ፍቃድ
ነገ ማለትም ቅዳሜ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ የዳዕዋ ፕሮግራም
በመርከዝ ኢማሙ አህመድ በአካል ተገኝታቹ እንድትታደሙ ስንጋብዛቹ በታላቅ ደስታ ነው

በአካል መገኘት ለማችሉ በቴሌግራም ቀጥታ ስርጭት  መከታተል ትችላላቹ

ተጋባዣ ዱዓቶች
↓↓↓↓↓↓
🎤ኡስታዝ ሳዳት ከማል

🎤ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🎤ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ


ዳዕዋው የሚተላለፍበት ቻናል
https://t.me/MedrestuImamuAhmed
https://t.me/MedrestuImamuAhmed
https://t.me/MedrestuImamuAhmed

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

10 Jan, 20:05


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 1️⃣8️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6718
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

10 Jan, 16:52


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

10 Jan, 15:51


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

10 Jan, 15:01


ዛሬ የአልዐቂደቱል ዋሲጢያህ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።

• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6718

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

10 Jan, 08:35


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"እናንተ ነጋዴዎች ሆይ! አደራ ውሸትን ተጠንቀቁ።" [ሶሒሑ ተርጊብ፡ 1793]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

10 Jan, 08:13


ኢትዮጵያ ውስጥ መቻቻል እንዳለ ለማሳየት ፖለቲከኛውም፣ ጋዜጠኛውም፣ አር ቲስቱም፣ አክቲቪስቱም፣ መሀይሙም፣ ምሁሩም እንቁጣጣሽ፣ ጥምቀትና ገና የሚያከብሩ "ሙስሊሞችን" ማቅረብ / መጥቀስ የተለመደ ነው። በተቃራኒው የሙስሊም ዒዶችን የሚያከብሩ ክርስቲያኖችን ግን ሲያቀርቡ ወይም ሲጠቅሱ ገጥሞኝ አያውቅም። ለምን? ሙስሊሙ የእምነቱን ህግጋት ጥሶ የነሱን በአላት ማክበሩ ከመቻቻል ትርጓሜ ጋር ምን የሚገናኝ ነገር አለው?

እውነት ይሄንኑ የተንሻፈፈ አረዳድ መቻቻል አድርገው ካሰቡት ለምን ሙስሊሞችን ብቻ ነጥለው ያቀርባሉ? እንዲህ አይነቱ "ከባልሽ ባሌ ይበልጣል ሽሮ አበድሪኝ" አይነት የብልጠት ጨዋታ አይደብርም ወይ? ደግሞ'ኮ ሙስሊሙ የገዛ ወገኑን ከእንዲህ አይነት ተግባራት እንዲርቁ ሲያስተምር እንደ ማክረርና ፅንፈኝነት ሊቆጥሩ ዳር ዳር ሲሉ ማየት ነው የሚገርመው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

09 Jan, 19:33


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 1️⃣7️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

09 Jan, 16:42


Live stream finished (53 minutes)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

09 Jan, 15:49


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

09 Jan, 15:23


ዛሬ የምንነሳው ከዚህ ነው ኢንሻአላህ

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

09 Jan, 15:15


ዛሬ የአልዐቂደቱል ዋሲጢያህ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።

• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6718

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Jan, 16:52


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Jan, 15:46


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Jan, 15:21


ዛሬ የምንነሳው ከዚህ ነው ኢንሻአላህ

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Jan, 14:46


ዛሬ የአልዐቂደቱል ዋሲጢያህ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።

• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6718

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Jan, 14:43


https://t.me/BerekahJobs

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Jan, 09:31


በአሕ ^ባሽ ስብከት ለተሸወዳችሁ ወገኖች!
~
አላህ ከዐርሽ በላይ ነው የሚለውን ዐቂዳ ከጊዜ በኋላ የመጣ እንግዳ እምነት አድርገው ሲሞሏችሁ አትሸወዱ። የቀደምት ዑለማኦችን ንግግር ተመልከቱ። ከዚህ በፊት በሂጅራው አቆጣጠር ከ300 አመት በፊት የሞቱ ዓሊሞችን ኢጅማዕ ዝርዝር አሳልፌያለሁ። አሁን ደግሞ ከዚያ በኋላ ግን ከኢብኑ ተይሚያ መምጣት በፊት ያለፉ ዓሊሞችን እጠቅሳለሁ።

1. አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይ (324 ሂ.) የአህሉ ሱናን ኢጅማዕ ሲዘረዝሩ ዘጠነኛው ኢጅማዕ ላይ እንዲህ ብለዋል፡-
وأجمعوا على... أنه تعالى فوق سماواته على عرشه دون أرضه، ... وليس استواؤه على العرش استيلاء كما قال أهل القدر؛ لأنه عز وجل لم يزل مستولياً على كل شيء
“የላቀው አላህ ... በምድሩ ሳይሆን ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ እንደሆነም ኢጅማዕ አድርገዋል። የኢስቲዋኡ ፍቺ ቀደሪያዎች (ሙዕተዚላዎች) እንደሚሉት መቆጣጠር ማለት አይደለም” ብለዋል። [ሪሳላህ ኢላ አህሊ ሠግር፡ 130 - 131]

2. አቡ አሕመድ አልከርጂይ አልቀሷብ (360 ሂ.) ከዐርሹ ላይ መሆኑን መካድን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡-
مكابرة العقول ومقابلة الأمة عالمهم وجاهلهم بالخلاف فيما ليس فيه لبس ولا إشكال
“ይሄ ህሊናን መቃረን፣ መድበስበስና ችግር በሌለው ጉዳይ ላይ ከአዋቂ እስከ መሀይም ህዝበ ሙስሊሙ ጋር በልዩነት መላተም ነው።” [ኑከት፣ ቀሷብ፡ 1/429]

3. አቡበክር አልኢስማዒሊይ (371 ሂ.)፡- የሐዲሥ ምሁራንን ጥቅል ዐቂዳ ባሰፈሩበት ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡-
ويعتقدون أن الله تعالى مدعو بأسمائه الحسنى وموصوف بصفاته التي سمى ووصف بها نفسه ووصفه بها نبيه ﷺ، خلق آدم بيده، ويداه مبسوطتان ينفق كيف يشاء، بلا اعتقاد كيف، وأنه عز وجل استوى على العرش، بلا كيف.
“የላቀው አላህ እራሱን በሰየመባቸው፣ እንዲሁም መልእክተኛው ﷺ እሱን በጠሩበትና በገለፁበት መልካም ስሞቹና መገለጫዎቹ የሚጠራና የሚገለፅ እንደሆነ፤ ኣደምን በእጁ እንደፈጠረ፣ - አኳኋን ሳይሰጡ - እጆቹ የተዘረጉ እንዳሻው የሚለግስባቸው እንደሆኑ፣ እርሱ - ዐዘ ወጀለ - ያለ እንዴት ከዐርሹ በላይ ከፍ ያለ እንደሆነ ያምናሉ።” [ኢዕቲቃዱ አኢመቲል ሐዲሥ፡ 49 - 50]

4. ኢብኑ አቢ ዘይድ አልቀይረዋኒይ አልማሊኪይ (386 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
“ምሁራኖች ከተስማሙባቸው ሃይማኖታዊ ጉዳዮች፣ እንዲሁም ቢጥጣሱ ቢድዐና ጥመት ከሆኑት ሱናዎች ውስጥ አንዱ እርሱ፡-
فوقَ سماواتِهِ على عَرْشِهِ دونَ أرضِهِ وأنَّهُ في كُلِّ مكانٍ بِعِلْمِهِ
“በምድሩ ሳይሆን ከሰማያቱ በላይ ከዐርሹ ላይ እንደሆነና በእውቀቱ ግን በሁሉም ቦታ እንደሆነ ማመን ነው።” [አልጃሚዕ፣ አልቀይረዋኒይ፡ 107 - 108]

5. ኢብኑ በጧህ አልዑክበሪይ (387 ሂ.) ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
أجمعَ المسلمونَ مِنَ الصَّحابةِ والتَّابعينَ، وجميعُ أهلِ العلمِ مِنَ المؤمنينَ أنَّ الله تباركَ وتعالى على عَرْشِهِ، فَوْقَ سَمَاواتِهِ، بائِنٌ منْ خَلْقَهِ، وعِلْمُهُ مُحِيطٌ بجميعِ خَلْقِهِ
“ሙስሊሞች ሁሉ ከሶሐቦችና ከታቢዒዮች፣ ከአማኞች የሆኑ ሁሉም ምሁራኖች የላቀው አላህ ከፍጡሩ ተለይቶ ከሰማያቱ በላይ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል። እውቀቱ ሁሉንም ፍጡሮቹን ያካበበ ነው።” [አልኢባናህ፣ ኢብኑ በጧህ፡ 7/136]

6. ኢብኑ አቢ ዘመኒን አልማሊኪይ (399 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
وَمِنْ قَوْلِ أَهْلِ اَلسُّنَّةِ: أَنَّ اَللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ خَلَقَ اَلْعَرْشَ وَاخْتَصَّهُ بِالْعُلُوِّ وَالِارْتِفَاعِ فَوْقَ جَمِيعِ مَا خَلَقَ، ثُمَّ اِسْتَوَى عَلَيْهِ كَيْفَ شَاءَ، كَمَا أَخْبَرَ عَنْ نَفْسِهِ فِي قَوْلِهِ: ﵟ‌ٱلرَّحۡمَٰنُ ‌عَلَى ‌ٱلۡعَرۡشِ ‌ٱسۡتَوَىٰﵞ
“ከአህሉ ሱና አቋሞች ውስጥ አላህ - ዐዘ ወጀለ - ዐርሹን እንደፈጠረና ከፈጠረው ሁሉ ለይቶ በላይ በመሆንና ከፍ በማለት ለይቶታል የሚለው ነው። ከዚያም እንደሻው በሱ ላይ ከፍ አለ። {አረሕማን ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ} ሲል ስለ ራሱ እንደተናገረው።” [ኡሱሉ ሱና፣ ኢብኑ አቢ ዘመኒን፡ 88]

7. አቡ ዐምር አዳኒይ (440 ሂ.) ረሒመሁላህ፡-
የአህሉ ሱናን መዝሀብ ዐቂዳዊ ነጥቦች ባሰፈሩበት ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡-
ومنْ قولهم: إنَّهُ سُبْحَانَهُ فَوْقَ سماواتهِ مستوٍ عَلَى عرشه، ومُسْتَوْلٍ على جميعِ خلقهِ، وبائنٌ منهم بذاتهِ، غيرُ بائنٍ بعلمهِ، بلْ علمهُ محيطٌ بهم
“ከአቋሞቻቸውም ውስጥ እርሱ ጥራት ይገባውና ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ ከፍ ብሎ ነው ያለው የሚለው ነው። በሁሉም ፍጡሮቹ ላይ ተቆጣጣሪ ነው። በዛቱ ከነሱ የተለየ ሲሆን በእውቀቱ ግን የተለየ አይደለም። ይልቁንም እውቀቱ እነሱን ያካበበ ነው።” [አሪሳለቱል ዋፊያህ፡ 129 - 134]

8. አቡ ዑሥማን አሷቡኒይ (449 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
ويعتقدُ أهلُ الحديثِ ويشْهدونَ أنَّ الله سبحانه وتعالى فوقَ سَبْعِ سَمَاوَاتٍ على عَرْشِهِ كمَا نطقَ بهِ كتابُهُ، ... وعلماءُ الأمَّةِ وأعيانُ الأئمَّةِ مِنَ السَّلفِ رحمهمُ الله لم يختلفوا في أنَّ اللهَ تعالى على عَرْشِهِ، وعَرْشُهُ فَوْقَ سَمَاوَاتِهِ، يُثْبتونَ لهُ منْ ذلكَ ما أثبتهُ الله تعالى ويؤمنونَ بهِ ويُصدِّقونَ الرَّبَّ جلّ جلاله في خبرهِ، ويُطْلقونَ ما أَطْلقهُ سبحانه وتعالى من استوائهِ على العرشِ ويُمرُّونهُ على ظاهِرِهِ
“የሐዲሥ ተከታዮች: የጠራውና ከፍ ያለው አላህ - ቁርኣኑ እንደተናገረው - ከሰባቱ ሰማያ በላይ ዐርሹ ላይ እንደሆነ ያምናሉ፤ ይመሰክራሉ። … የህዝበ ሙስሊሙ ምሁራን፣ የቀደምት ታዋቂ ኢማሞች - አላህ ይዘንላቸውና - የላቀው አላህ ከዐርሹ በላይ በመሆኑና ዐርሹም ከሰማያቱ በላይ በመሆኑ ላይ አልተወዛገቡም። በዚህ ላይ የላቀው አላህ ያፀደቀውን ለሱ ያፀድቃሉ። ያምኑበታልም። ልቅናው ከፍ ያለውን ጌታም በንግግሩ ያምኑታል። የጠራውና የላቀው አላህ ከዐርሹ በላይ ስለመሆኑ የተናገረውን ያስተጋባሉ። በይፋዊ (በዟሂር) መልእክቱም ያስኬዱታል። [ዐቂደቱ ሰለፍ ወአስሓቢል ሐዲሥ፡ 36 - 37]

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Jan, 09:31


9. ኢብኑ ዐብዲል በር አልማሊኪ (463 ሂ.)፡-
“አላህ የት ነው?” የሚለውን ሐዲሥ አውስተው እንዲህ ብለዋል፡-
فَعَلَى ذَلِكَ جَمَاعَةُ أَهْلِ السُّنَّةِ وَهُمْ أَهْلُ الْحَدِيثِ وَرُوَاتُهُ الْمُتَفَقِّهُونَ فِيهِ وَسَائِرُ نَقَلَتِهِ كُلُّهُمْ يَقُولُ مَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى فِي كِتَابِهِ ﵟ‌ٱلرَّحۡمَٰنُ ‌عَلَى ‌ٱلۡعَرۡشِ ‌ٱسۡتَوَىٰﵞ وَأَنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ فِي السَّمَاءِ وَعِلْمَهُ فِي كُلِّ مَكَانٍ
“የአህለ ሱና ጀማዐ በዚህ ላይ ነው ያሉት። እነሱም የሐዲሥ ባለቤቶች፣ ዘጋቢዎቹ፣ በሱ ላይ አዋቂዎቹና ሌሎችም አቀባባዮቹ በሙሉ የላቀው አላህ በመፅሐፉ {አረሕማን ከዐርሽ በላይ ከፍ አለ} ያለውን ያስተጋባሉ። አሸናፊውና የላቀው አላህ በሰማይ እንደሆነና እውቀቱ በሁሉም ቦታ እንደሆነም እንዲሁ።” [አልኢስቲዝካር፡ 7/337]
وفيه دليلٌ على أنَّ اللهَ عزَّ وجلَّ في السَّماءِ على العَرْشِ، مِنْ فَوْقِ سَبْعِ سَمَاوَاتٍ، كما قالتِ الجماعةُ، وهوَ منْ حجَّتهم على المعتزلةِ، والجهميَّةِ، في قولهم: إنَّ الله عزَّ وجلَّ في كلِّ مكانٍ، وليسَ على العرشِ
“በዚህ ውስጥ አህሉ ሱና ወልጀማዐ እንዳሉት አላህ - ዐዘ ወጀል - ከሰባት ሰማያት በላይ ዐርሹ ላይ እንደሆነ ማስረጃ አለ። ይሄ አላህ - ዐዘ ወጀል - ‘ሁሉም ቦታ ነው፤ እንጂ ዐርሽ ላይ አይደለም’ በሚሉት ሙዕተዚላና ጀህሚያ ላይ ከሚጠቅሱ ማስረጃ ነው።” [አተምሂድ፡ 7/129]

10. ኢስማዒል ብኑ ሙሐመድ አተይሚይ (532 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
أهل السّنة يَعْتَقِدُونَ أَن الله ... عَلَى الْعَرْش كَمَا قَالَ تَعَالَى: {ٱلرَّحۡمَٰنُ ‌عَلَى ‌ٱلۡعَرۡشِ ‌ٱسۡتَوَىٰ} وَأَنه ينزل كل لَيْلَة إِلَى السَّمَاء الدُّنْيَا كَمَا جَاءَ فِي الحَدِيث
“የሱና ሰዎች የላቀው አላህ {አረሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ} እንዳለው በዐርሹ ላይ እንደሆነ በየሌሊቱም ወደ ቅርቢቷ ሰማይ እንደሚወርድ ያምናሉ። [አልሑጃ፣ ተይሚይ፡ 2/432]

11. የሕያ ብኑ አቢል ኸይር አልዐምራኒይ (558 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
عندَ أصحابِ الحديثِ والسُّنةِ أنَّ الله سبحانهُ بذاتهِ، بائنٌ عَنْ خَلْقِهِ، على العرشِ استوى فوقَ السَّمواتِ
“የሐዲሥና የሱና ተከታዮች ዘንድ የሚታመነው አላህ ጥራት ይገባውና በዛቱ ከፍጡራን ተነጥሎ ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ እንደሆነ ነው።” [አልኢንቲሷር፣ ዐምራኒይ፡ 2/607]

12. ኢብኑ ሩሽድ አልማሊኪይ (595 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
القولُ بالجهةِ: وأمَّا هذهِ الصِّفَةُ فلمْ يزل أهلُ الشَّريعةِ منْ أولِ الأمرِ يثبتونها لله سبحانه وتعالى، حتَّى نَفَتْها المعتزلةُ ثمَّ تبعهم على نفيِّها متأخرو الأشعريةِ، ... وظواهرُ الشَّرعِ كلُّها تقتضي إثباتَ الجهةِ
“በ(ላይ) አቅጣጫ ማመን፡ ይህቺ መገለጫ ከመጀመሪያው ዘመን ጀምሮ የሸሪዐ ባለቤቶች ለአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ከማፅደቅ ወደ ኋላ ብለው አያውቁም። ሙዕተዚላዎች እስከሚያስተባብሏትና የኋለኛው ዘመን አሽዐሪዮች በማስተባበል ላይ እስከሚከተሏቸው ድረስ ማለት ነው። … የሸሪዐ ግልፅ ማስረጃዎች እንዳለ የ(ላይ) አቅጣጫን ማፅደቅን ያመላክታሉ።” [መናሂጁል አዲላህ ፊ ዐቃኢዲል ሚላህ፣ ኢብኑ ሩሽድ፡ 176]

አላህ ከዐርሽ በላይ ነው ለሚለው አንዳች ማስረጃ ባይኖር እንኳን “... ከላይም፣ ከአለም ውጭም፣ ከአለም ተነጥሎም አይደለም” ብሎ ለማመን ወይ የቁርኣን ወይ የሐዲሥ ወይ ደግሞ የኢጅማዕ ማስረጃ ማቅረብ ግድ ነበር። ይህም ይቅር። ቢያንስ ከሶሐቦች፣ ከታቢዒዮችና ከአትባዑ ታቢዒን ይህን የሚያስረዳ ሀሳብ ማቅረብ ነበረባቸው። ይህንን የሚያሳይ ደግሞ ቅንጣት የላቸውም። ይልቁንም የቁርኣንም፣ የሐዲሥም፣ የኢጅማዕም ማስረጃዎች ያሉት ከነሱ ተቃራኒ ነው። እኛ እንደምናቀርበው ተፃራሪ ማስረጃ ቢያቀርቡ ሁለቱም ተፈትሾ፣ ተመዝኖ ሚዛን የሚደፋው ይታይ ይባል ነበር። እነሱ ግን ባዶ ኪሳቸውን እያፏጩ መጥተው የኡማውን ኢጅማዕ እንደ ዋዛ ሊንዱ ነው የሚገላገሉት። የጌታ ቃል፣ የመልእክተኛው ንግግር፣ የቀደምቶች ኢጅማዕ በአንድ ቃል ያስተጋቡትን ሐቅ በ‘ተእዊል’ም ይሁን በሌላ ማመሀኛ ለማስተባበል መሞከር ድርቅና እንጂ ምን ሊባል ይችላል?!

እንግዲህ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ቁርኣኑም፣ ሐዲሡም፣ ኢጅማዑም አረጋገጠ። ከዚህ በኋላ ግራ ቀኝ ማማተር ከሙስሊም ይጠበቃል ወይ?! ዐብዱላህ ብኑ ዐዲይ አሷቡኒይ “ወይ ቁርኣን፣ ሱናና ኢጅማዕ ነው። ካልሆነ ግን (እንደ መነኩሴዎች) ዝናር መታጠቅ፣ ቢጫ መልበስና ጂዝያ መክፈል ነው የሚቀረው” ይላሉ። [ዘሙል ከላም፡ 1/27] አደገኛ ምርጫ! በነዚህ አካላት የተሸወድክ ወገኔ ሆይ! ግዴለህም ንቃ። መንቃትህ የሚጠቅመው አንተን ነው። አላህ ልብህን ለሐቅ ክፍት ያድርግልህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Jan, 20:36


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 1️⃣4️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Jan, 16:47


Live stream finished (55 minutes)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Jan, 15:51


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Jan, 15:51


Live stream finished (1 minute)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Jan, 15:50


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Jan, 13:39


ዛሬ የአልዐቂደቱል ዋሲጢያህ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።

• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Jan, 03:21


ዘሀቢይ እንዲህ ይላሉ፦
"ጀግንነት እና ቸርነት ወንድማማቾች ናቸው። ገንዘቡን ያልቸረ ሰው ነፍሱን አይቸርም።" [ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ፡ 8/366]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

06 Jan, 19:47


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 1️⃣4️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

06 Jan, 16:50


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

06 Jan, 15:48


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

06 Jan, 14:26


ዛሬ የዐቂደቱል ዋሲጢያ ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ።

• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

06 Jan, 13:02


ደርስ
~
* መንሀጁ ሳሊኪን
* ክፍል:- 4️⃣3️⃣
* የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ
* የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

06 Jan, 08:06


የአፋልጉኝ ማስታወቂያ❗️

አሰላሙ ዓለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረቱህ
    ከላይ በፎቶ የምትመለከቱት ሰዉ ስሙ
ዘገየ ማህሙድ ሹምየ ይባላል
   ሀገሩ ሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ (ድሬ ሮቃ)  ቀበሌ 024
   ወደ አድስ አበባ እንደወጣ አልተመለሰም ቆየት ብሏል ከወጣ።
እናም ይሄን ሰው ያለበትን የሚያውቅ
በነዚህ ቁጥሮች አሳውቁን
0984197003
0554276873
ወይም በዚህ username
@bin_husein

ሼር አርጉት አፋልጉን ምንዳው ከአሏህ ነው ።

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

06 Jan, 08:06


ሙሓደራ 219

ስለ ወቅታዊ መሬት መንቀጥቀጥ አጭር ምክር

🚦 የቂያማ ምልክት 

🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ሓቲም)

https://t.me/UstazKedirAhmed/8288

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

06 Jan, 04:02


ደርስ
~
* መንሀጁ ሳሊኪን
* ክፍል:- 4️⃣2️⃣
* የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ
* የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

05 Jan, 17:41


ይሄ ሐሰን ታጁ የሚያስተዋውቀው ሰው "አላህ በቁርኣን እንደገለፀው ከዐርሹ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን ከኢስላም እያስወጣ የሚናገር ተክ - ፊሪይ ነው። ይሄ አቋም የ "ሙፍቲ" ዑመር አቋም ነው። እነ ሐሰን ታጁ ሰዎችን ከተለያዩ ክፍላተ ሃገራት እያስመጡ በህቡእ እያደራጁ በዚህ ቆ - ሻ ሻ አስተሳሰብ በማጥመቅ ላይ በሰፊው ተሰማርተዋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

05 Jan, 14:48


*የዱንያ ነገር!!*
~
ዐሊይ ኢብኑል ሀይሠም እንዲህ ይላሉ:–

"አምሳያ ያላየሁለት የዘመን መገለባበጥ፣ የጊዜ መለዋወጥ አይቻለሁ።
★ የአልፈድል ብኑ ረቢዕ ንብረት በአንድ ሺህ ግመል ተጭኖ አይቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተደብቄ አይቻለሁ። በውስጧ መድሃኒቶቹ ተጨምረው።

★ አልሐሰን ብኑ ሰህልን ደግሞ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተመልክቻለሁ። ከዚያ ግን ንብረቱ በአንድ ሺ ግመል ላይ ተጭኖ አይቼዋለሁ።"

||

ዱንያ እንዲህ ነች። መርጋት የማታውቅ ወላዋይ!!
♣️ ሃያላን ይዋረዳሉ። ደካሞች ይነግሳሉ።
♣️ ሀብታሞች ጎዳና ላይ ይወድቃሉ። ምንዱባን በሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይንፈላሰሳሉ።
♣️ ሳር ቅጠሉን የተፀየፈው ጨፍጫፊ አረመኔ አለም ጠባው ከአይጥ ጎሬ ሲያደፍጥ ታየዋለህ። የትላንቱ ተሳዳጅ ተራውን ሲያሳድድ ትመለከታለህ።

® ይሄው ነች ዱንያ!! ብልጭ ብላ ድርግም፣ ቦግ ብላ እልም የምትል። ሁሌ ሳቅ የለም! ሁሌ ድል የለም።
|
♣️ በድር ላይ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩ፣ ጥጋብ ያስከራቸው ቁረይሾች፣ 70 መኳንንቶቻቸው ትላንት ሲያሳድዷቸው በነበሩ ሶሐቦች ሰይፍ ተበልተው፣ ሌላ 70 ደግሞ በምርኮ አስረክበው የሐዘን ማቅ ለብሰዋል። መካ በዋይታ ተንጣለች።
|
♣️ ኡሑድ ሌላ ቀን ነው። ሌላ ተራ!! አጋሪዎች የፈነደቁበት፣ እነ ሐምዛን፣ እነ ሙስዐብን ጨምሮ ከ70 በላይ ታላላቅ ጀግኖች ወድቀው ሌላ 70 የቆሰሉበት፣ አሳዝኝ ክስተት እውን የሆነበት ቀን። ሶሐቦች አካላቸው በስለት፣ ልባቸው በሐዘን ቢቆስል ጊዜ አላህ እንዲህ ሲል አሳሰባቸው: –

(إِنْ يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ الْقَوْمَ قَرْحٌ مِثْلُهُ ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسَ)
"ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ እናም እነዚህን ቀናት በሰዎች መካከል (በመልካምና በሌላ) እናቀያይራቸዋለን፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 140]

|||

ዱንያ አመሏ ነው። ዛሬም እንዲሁ ናት።
ግን ማነው የሚማረው? ግን ማነው የሚመረምረው? ግን ማነው የዱንያን ከንቱነት ተገንዝቦ ለዘላለም ቤቱ ከልብ የሚጨነቀው?
እስከ መቼ ነው የምናንቀላፋው?
እስከ መቼ ነው የምንዘናጋው?
እስከ መቼ ነው በከንቱ የምንባዝነው?
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
ኢላሂ ልብ ስጠን!
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

04 Jan, 18:27


የችግሩ መንስኤ ክፋት ነው። የቅንነት መጥፋት ነው። እንጂ አገሪቱ የጋራ ናት፤ እኩል የመጠቀምም የመወሰንም መብት አላቸው የሚል እምነት ቢኖር ኖሮ ማንም በእብሪት እየተነሳ የራሱን ውሳኔ ባላሳለፈ ነበር። ዋናው ችግር ግን ከላይ ነው። ዋና ወሳኝ ክፍሎች ላይ ቁርጠኝነት ቢኖር ሁሉም ባይሆን እንኳ ብዙ ቦታዎች ችግሩ ይቀረፍ ነበር። ግን ምን ዋጋ አለው? መርፌ ከለገመ ቅቤ አይወጋም።
የጊዜ ጉዳይ እንጂ መብታችን ሳይሸራረፍ የሚከበርበት ጊዜ እንደሚመጣ እናምናለን፣ ኢንሻአላህ። ብቻ ትዝብት ነው ትርፉ። በታሪክ ጥቁር መዝገብ ላይ ስምን ከማኖር በበጎ መታወስ ይሻል ነበር። ዛሬ እያሳለፍነው ያለው ተጨባጭ ትናንት አባቶቻችን ምን አይነት ዘግናኝ ዘመን እንዳሳለፉ የሚጠቁም ነው፡፡ "ለዓለም ምሳሌ የሚሆን መቻቻል ... " የሚለው ፉገራ እንዴት እንደሚያስጠላ!

ሰውየው አብዛኞች ዘንድ የሌለ ሚዛናዊነት ስላሳየን አላህ ሂዳያ ይስጥልን። እናመሰግናለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

04 Jan, 15:13


ፖለቲከኛ ሆደ ሰፊ ሲሆን ጥሩ ነው
~
በዚህ ባንዲራ ሰበብ ወንድሞች እየታሰሩ እንደሆነ ከአንድ ወንድም መረጃ ደረሰኝ። በዚህ ፖስት አንዱ ማስተላለፍ የፈለግኩት ነጥብ ይሄ ነው። ጥንቃቄ እንድታደርጉ።
በርግጥ ይህንን ባንዲራ እኔም አልወደውም። ይህን ብቻ ሳይሆን ቢጫውና ቀዩ ቀለማት የተጣመሩባቸው ባንዲራዎች ሁሉ የየትኛውም አካል ቢሆኑ አልወዳቸውም፡፡ ይሄ የግል ስሜቴ ነው።

ግን ፖሊቲከኞች (ፖሊሶች) በዚህ ሰበብ ሰዎችን ማሳደድ ለምን? መንግስትን በምትወክሉበት ስልጣን ላይ ሆናችሁ ግለሰባዊ የሚመስል እልህ ባታሳዩ መልካም ነው። በተለጠፈው ምስል በዋናነት ማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት "በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው በደል ይቁም። ፍትህ ይስፈን" የሚል ነው። በዚህ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ አይኑን የጨፈነ አካል ኮከብ አለ የለም እያለ ሰው ሲያሳድድ ማየት የሚገርም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

04 Jan, 06:27


ዝንጀሮ የራሷ መላጣ አይታያትም!
~
ልጅቷ
“የሰለጠነችው”
ነጮቹ ሲያብዱ አይታ - ማሰብ ያቆመችው
ከፈረንጆች በላይ - የፈረነጀችው
ልብስ ባልጠፋበት - ባለንበት ዘመን
ልብሶቿ ሸሽተዋት - እሩቧን ብትቀር
እርቃንነት ለምዳ - መልበስ የሚደንቃት
ሀሩር የሚበርዳት - ቁር የሚወብቃት
ከልብሶቿ ቀድሞ - ህሊና አምፆባት
ጎንበስ ብላ አየችኝ - የኔ ሱሪ አጥሮባት
አቤት!
እስኪ እዩ ይሄን እብደት!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ታህሳስ 04/2006)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

04 Jan, 04:42


ቅናት አያረጅም!
~
የአዛንና የሶላት ሰዓት አጭር ነው። በጥላቻ ስትሞላ ግን 5ቱ ደቂቃ አምስት ሰዓት ይሆንብሃል። ሰፈራችን ላይ የሱብሕ አዛን 11፡25 አካባቢ ተደረገ። ሶላቱ ደግሞ ሩብ ጉዳይ አካባቢ። ሁሉም ቢደመር 20 ደቂቃ አይሞላም። ከማዶ የሚሰማው የቤተ ክርስቲያን ድምፅ ግን እስካሁን አልተቋረጠም። ይሄ የየሰፈሩ እውነታ ነው። ግን የራስ እንትን አይገማም።

የዚች ሃገር ትልቁ ችግር ቅናት ነው። ሙስሊም ተማሪዎችን በአለባበስ ምክንያት ከትምህርት ገበታ የሚገፋው አስተማሪ ከክልከላው ጀርባ ያደፈጠው ምክንያቱ ምቀኝነት ነው። ሌላው እንዲሁ ሽፋን ነው። የራሱን ማስለበስ ሲያቅተው ሌሎች ላይ ይዘምታል። "ለሙስሊሞች ሒጃብ ከተፈቀደ እኛም ነጠላ እንለብሳለን" የሚለው የምቀኛ ሰፈር ልጆች መፈክርም የታወቀ በሽታ ነው፣ ቅናት። "ለሙስሊሞቹ መስገጃ ከተፈቀደ ለኛም መፀለያ ይፈቀድልን" የሚለው የምቀኝነት ልክፍትም የተለመደና ዝነኛ ህመም ነው።

ምቀኝነት እየተጋተ ያደገ አካል አድጎ አርጅቶ፣ በምርኩዝ እየሄደ፣ የሌሎችን ሃገራት ሁኔታ እያየ እንኳ አይለወጥም። እንዲያውም እየባሰበት ይሄዳል። ወደው አይደለም "ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም" የሚሉት። በቅናት የገረጣ ፊት በቅባት አይወዛም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Jan, 19:12


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 1️⃣3️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Jan, 16:48


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Jan, 15:46


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Jan, 14:50


ዛሬ የዐቂደቱል ዋሲጢያ ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ቦታው ላይ መገኘት የማይችል በዚህ የቴሌግራም ቻናል መከታተል ይችላል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

* የኪታቡን pdf ፋይል የሚፈልግ በዚህ ማግኘት ይችላል፦
https://t.me/IbnuMunewor/6718

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Jan, 11:23


የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
(من رأى منكم منكرا فليغيره بيده فإن لم يستطع فبلسانه فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان).
"ከናንተ መጥፎን ነገር የተመለከተ በእጁ ይቀይረው (ያስወግደው)። ካልቻለ በምላሱ። ካልቻለ ደግሞ በልቡ። ይሄ ግን ደካማው ኢማን ነው።" [ሙስሊም: 186]
ከሐዲሡ የሚወሰዱ ቁም ነገሮች:–

① ከመጥፎ መከልከል ነፍስ ወከፋዊ ሃላፊነት እንደሆነ፣
② ከመጥፎ መከልከል የተለያዩ ደረጃዎች ስላሉት ሁኔታዎችን እና ተገቢ እርምጃዎችን መለየት እንደሚያስፈልግ፣
③ በእጅ ወይም በአንደበት ጥፋትን ለማስወገድ አቅም እንደሚያስፈልግ፣
④ ጥፋትን በልቡም የማይጠላ ሰው ኢማኑ ከዝቅተኛ ወለልም በታች በመውረዱ ከባድ አደጋ ላይ እንደሆነ
⑤ ኢማን ከልባዊ እምነት ባለፈ ተግባርንም እንደሚጨምር
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Jan, 03:45


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 1️⃣2️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Jan, 16:49


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Jan, 15:45


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Jan, 14:40


ዛሬ የዐቂደቱል ዋሲጢያ ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ቦታው ላይ መገኘት የማይችል በዚህ የቴሌግራም ቻናል መከታተል ይችላል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

* የኪታቡን pdf ፋይል የሚፈልግ በዚህ ማግኘት ይችላል፦
https://t.me/IbnuMunewor/6718

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Jan, 03:42


ከዒልም አንራቅ፡ ልባችን እንዳይሞት
~
ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"የሸሪዐ እውቀት ለልብ ምግቡ፣ መጠጡ እና መድሃኒቱ ነው። ህይወቱ በሱ ላይ ነው የቆመው። ልብ እውቀትን ካጣ ያኔ ሙት ሆኗል።" [ሚፍታሑል ዳ ሪ ሰዓደህ፡ 1/344]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Jan, 19:36


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 1️⃣1️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Jan, 16:49


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Jan, 15:44


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Jan, 15:04


ዛሬ የዐቂደቱል ዋሲጢያ ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ቦታው ላይ መገኘት የማይችል በዚህ የቴሌግራም ቻናል መከታተል ይችላል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

* የኪታቡን pdf ፋይል የሚፈልግ በዚህ ማግኘት ይችላል፦
https://t.me/IbnuMunewor/6718

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Jan, 05:48


የገና በዓል የዒሳ ዐለይሂ ሰላም የመውሊድ በዓል ነው። ስለዚህ ሃይማኖታዊ በዓል ነው ማለት ነው። ስለዚህ የነብዩን ﷺ የመውሊድ በዓል ማክበር ቢድዐ እንደሆነው ሁሉ የዒሳን መውሊድ ማክበርም በተመሳሳይ ቢድዐ ነው። ከቢድዐነቱም ባሻገር ሙስሊም ባልሆኑ አካላት አጉል መመሳሰል ነው። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
በነገራችን ላይ የልደት ቀንን አመት እየጠበቁ ማክበር በኢስላም ብቻ ሳይሆን በክርስትናም የለም። ይልቁንም ይሄ ተግባር ከጣኦ. ታውያን የተኮረጀ ልማድ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Jan, 04:59


የእርዳታ ጥሪ
~
ወዳጄቼ ተወልጀ ባደግኩባት ከተማ የተከሰተ አሳዛኝ ክስተት ነው
እናት ቤቴ በሀዘን ተውጧል የቀረኝ አንዱን ልጄን አድኑልኝ ትላለች
የእርዳታ ጥሪ ልጆቼን ተነጠኩ አንዱን ገደሉብኝ አንዱን አድኑልኝ ትላለች እናታችን

ወንድማችን ኡመር ሀሰን ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ሉማሜ ከተማ የአባቱ የቀብር ስነ ስራአት ላይ ለመገኘት በመሄድ ላይ እያለ መንገድ ላይ ባጋጠማቸው እገታ ታላቅ ወንድሙም ወዲያዉኑ የተገደለ ሲሆን እሱም እንደታገተ ይታወቃል አጋች አካላትም ልጁን ለመውሰድ የምትፈልጉ ከሆነ 2 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን ቤተሰቦቹም አቅም ስለሌላቸው የአቅማቹሁን እንድትረድን ስንል በፈጣሪ ስም እንማፀናለን

የአካውን ባለቤት ስም
ኢብራሂም ሀሰን (ታላቅ ወንድም)
ንግድ ባንክ
1000270990057

አቢሲንያ
131756399

ለበለጠ መረጃ 0934181613

የአቅማችሁን በማገዝ እና ይህንን መልእክት ሼር በማድረግ አግዙን።

መልእክቱ ከወንድማችን Hussen Oumer የተወሰደ ነው።

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Jan, 04:04


ከ1400 ዓመታት በፊት ትግራይ ውስጥ ከዛሬው የተሻለ የሃይማኖት ነፃነት ነበር። መካ ውስጥ በገዛ ወገኖቻቸው የተገፉ የተንገላቱ ሙስሊሞች ባህር አቆራርጠው የተሰደዱት ወደ ሐበሻ ነበር። "እዚያ ከሱ ዘንድ ማንም የማይበደልበት ፍትሃዊ መሪ አለ" ተብሎ በነብዩ ﷺ የተመሰከረለት ድንቅ መሪ ነበር፣ ነጃሺ። ያኔ በግዛቱ ውስጥ ማንም እንዳይነካቸው ዋስትና ሰጥቷቸው ነበር ለስደተኛዎቹ ሙስሊሞች።
ዛሬ ከ1400 ዓመታት በኋላ በ21ኛው ክ/ዘመን ሙስሊም ለጋ ልጆች፣ ከሩቅ የመጡ እንግዶች ሳይሆኑ ተወላጆች፣ ሻሽ ካልጣላችሁ ተብለው በእምነታቸው ተለይተው ከትምህርት ገበታ ተገፍተዋል። ይበልጥ መሰልጠን ሲገባ ጭራሽ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ መሄድ የሚያሳዝንም፣ የሚያሳፍርም፣ የሚገርምም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Dec, 19:46


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 1️⃣0️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Dec, 17:51


የምንችለውን እናስተምር
~
ኢብኑል ሙባረክ - ረሒመሁላህ - "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ትሰራ ነበር?" ተብለው ተጠየቁ።
"ሰዎችን አስተምር ነበር" አሉ።
[አልመድኸል ኢለሱነን፣ አልበይሀቂይ፡ 309]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Dec, 16:48


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Dec, 15:45


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Dec, 15:45


Live stream finished (1 minute)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Dec, 15:43


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Dec, 13:20


ዛሬ የዐቂደቱል ዋሲጢያ ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ቦታው ላይ መገኘት የማይችል በዚህ የቴሌግራም ቻናል መከታተል ይችላል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

* የኪታቡን pdf ፋይል የሚፈልግ በዚህ ማግኘት ይችላል፦
https://t.me/IbnuMunewor/6718

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Dec, 19:05


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 0️⃣9️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Dec, 16:46


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Dec, 15:44


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Dec, 14:11


ዛሬ የዐቂደቱል ዋሲጢያ ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ቦታው ላይ መገኘት የማይችል በዚህ የቴሌግራም ቻናል መከታተል ይችላል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

* የኪታቡን pdf ፋይል የሚፈልግ በዚህ ማግኘት ይችላል፦
https://t.me/IbnuMunewor/6718

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Dec, 12:52


ይሄ የአደንዛዥ እፅ ውጤት ነው። ወጣቶች ተጠንቀቁ። አንዴ ከገባችሁበት መውጫው ከባድ ነው። ወላጆች ልጆቻችሁን ተከታተሉ። ጠብቁ። በጊዜ ጉዳቱንና ሐራምንቱን አስተምሯቸው። እንዳታጧቸው። በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች፣ በግል ኮሌጆች እና በዩኒቨርሲቲዎች አደንዛዥ እፅ መጠቀም እንደተስፋፋ ይወራል።
=
የቴለግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Dec, 11:53


ከቂብላ ጋር የተያያዙ ነጥቦች
~
1- ብይኑ፦ ወደ ቂብላ (ከዕባ) መዞር ከሶላት ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ነው። ያለ ቂብላ አቅጣጫ የተሰገደ ሶላት ተቀባይነት የለውም።
2- የሚጠበቀው መጠን፦ በቦታው ማለት ከዕባ ዘንድ ያለ ሰው ከዕባን ቀጥታ መቅጣጨት አለበት። መስጂደል ሐራም የሚፈፀመው የሶላት ሶፍ ክብ የሚሆን በዚህ የተነሳ ነው። በሩቅ የሆነ ሰው ግን በደፈናው አቅጣጫውን መያዝ በቂው ነው።
3- የቂብላን አቅጣጫ ያላወቀ ሰው ምን ያድርግ? የቂብላን አቅጣጫ ያላወቀ ሰው በግምት ከመቆሙ በፊት ጥረት ማድረግ አለበት። የሚያጣራበት መንገድ ወይም የሚጠይቀው ሰው እያለ በተጋነነ መልኩን ቂብላን የሳተ ሰው ሶላቱን እንደገና መስገድ ይኖርበታል። ትንሽ መልቀቅ ችግር የለውም።
4- ቂብላን መለየት የሚችልበት መንገድ ካጣስ? ከአካባቢው ርቆ መንገድ የወጣ በፀሐይ፣ በጉም እና መሰል ነገሮች ቂብላን መለየት ካልቻለ እና የሚጠቁመው ሰው ካጣ ወይም በአስቸጋሪ ሁኔታ ታስሮ ቂብላን መለየትም መጠየቅም ያልቻለ ሰው ገምቶ ይሰግዳል። ኋላ እንደተሳሳተ ቢያውቅ እንኳ ሶላቱን መድገም አይጠበቅበትም።
5- መጓጓዣ ላይ ያለ ሰው የሚሰግደው ሶላት ሱና ሶላት ከሆነ ቂብላን ባይጠብቅም የጉዞውን አቅጣጫ ይዞ መስገድ ይችላል። ሲጀምር ወደ ቂብላ ዙሮ ቢጀምር በላጭ ነው። ከዚያ በኋላ የጉዞውን አቅጣጫ ይዞ ሶላቱን መቀጠል ይችላል። ለግዴታ ሶላት ግን እስከቻለ ድረስ ወርዶ ቂብላ ጠብቆ መስገድ አለበት። በጉዞው አለመመቸትም ይሁን በሌላ አስገዳጅ ምክንያት ቂብላ መጠበቅ ካልቻለስ? ከተቻለው ለተክበሪተል ኢሕራም አንዴ ወደ ቂብላ ይዞራል። እሱም ካልተቻለ ባለበት ሁኔታ ይሰግዳል።
6- መንቀሳቀስ የማይችል ህመምተኛ የሚቻል ከሆነ በሌሎች ሰዎች እገዛ ወደ ቂብላ እንዲዞር ይደረግና ይሰግዳል። ምንም የማይቻልበት ሁኔታ ከገጠመ ባለበት ሆኖ ይሰግዳል።
=
የቴለግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Dec, 17:10


ደርስ
~
• ኪታቡ:- አልቀዋዒዱል አርበዕ
• ክፍል:- 1️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡ ሶፍት ኮፒ በpdf:- https://t.me/IbnuMunewor/6487
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል መከታተል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Dec, 16:28


Live stream finished (55 minutes)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Dec, 15:32


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Dec, 12:31


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ዛሬ የአልቀዋዒዱል አርበዕ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።

* ቦታ :- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
* ጊዜ :- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
* የኪታቡ ሶፍት ኮፒ በpdf:- https://t.me/IbnuMunewor/6587
* ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Dec, 07:31


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ይሄ ኪታብ የሚገኝበትን የምታውቁ ብትጠቁሙኝ። በተለይ ሃገር ውስጥ ካለ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Dec, 07:11


ጫት
~
ጫት የዲን፣ የጤና፣ የኢኮኖሚ፣ የቤተሰብ፣ የማህበራዊ ህይወት፣ የሃገር እድገት ፀር ነው። በጫት የተነሳ ትውልዱ ወኔው የፈሰሰ፣ ሞራሉ የላሸቀ የወጣት ጡረተኛ ሆኗል። በጫት ሱስ በደነዘዙ ቤተሰቦች ጭካኔ የተነሳ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ለአመታት በሰው ሃገር ደክመው ያጠራቀሙት ጥሪት እንደ ዋዛ መና ቀርቷል። የጫት ጉዳት ከሚገለፀው በላይ የከፋ ነው።
ለችግሩ መባባስ አንዱ ሰበብ ደዕዋ ላይ ያሉ ሰዎች የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ባገናዘበ መልኩ ተገቢ ትኩረት ሰጥተው አለማስተማራቸው ነው። አሁንም በሚገባ ልንነቃ ይገባል። የወገናችን ጉዳት የሚያመው ሁሉ! በሚችለው መድረክ ሁሉ ከዚህ መርዛማ ቅጠል ሰዎችን ሊያስጠነቅቅ ይገባል። በዚህ ቅጠል የተለከፉ ወገኖችን ከሱስ ማውጣት ቢያቅተን እንኳ ቢያንስ ልጆቻቸውን በሚጠብቁበት መልኩ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ብናደርግ ቀላል ስኬት አይደለም።
~
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Dec, 05:36


ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚታዩ እውነታዎች ውስጥ አንዱ ብዙ ወጣት ስለተውሒድ፣ ስለሺርክ፣ ስለ መሰረታዊ ጉዳዮች ሲወራ እንዳላየ ሆኖ ያልፋል። በጉዳዩ ላይ ለወሬ የሚበቃ ግንዛቤ የለውም። ሌላው ቀርቶ ስለሶላት፣ ስለፆም፣ ስለጦሀራ እንኳ የረባ ግንዛቤ የለውም። ስለ ጀናባ፣ ስለ ሐይድ ጥቆማ ቢሰጥ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች የግንዛቤውን መጠን ያሳዩሃል።
የፖለቲካ ጉዳይ ሲነሳ ግን ጥግ የደረሰ ድፍረት ይታይበታል። የሃገር ውስጡ አልበቃ ብሎ የዓለምን ፖለቲካ ሊተነትን ይነሳል። ስለገባው አይደለም እንዲህ የሚሆነው። በመሰለኝ የሚያወራ የበዛበት ጉዳይ ስለሆነ ነው የልብ ልብ የሚሰማው። ስለዲን ቢያወራ ማስረጃ ይጠየቃል። የዘመኑ የፖለቲካ ትንተና ግን በአመዛኙ እንዲህ አልተለመደም።
ይበልጥ የሚገርመው ግን ይሄ አይደለም። በተውሒድና በሺርክ ጉዳይ ወላእና በራእ የማያውቀውና የማይጥመው ፍንዳታ ሁሉ የሱን ጥራዝ ነጠቅ ትንታኔ መሰረት አድርጎ የፖለቲካ ወላእና በራእ የሚመሰርት መሆኑ ነው። ለተውሒድ ውግንና የለውም። ሲያሾፍ ሁሉ ልታገኘው ትችላለህ። ሺርክንም አይፀየፍም። የሺዐ እና የሱፊያን ሺርክ አይቶ ይጠላል ብለህ ስታስብ እሱ ያንተ የጠነከረ አቋም መያዝ ነው የሚያስከፋው። ሺርኩ ካለባቸው አካላት በላይ ሺርኩን የምትቃወመውን አንተን ነው አምርሮ የሚተቸው። ፖለቲካው ላይ ሲሆን ግን የወደደውን እንድትወድ የጠላውን እንድትጠላ ይፈልጋል። ካልሆነ ይፈርጅሃል። እንዲህ አይነቱ ጥራዝ ነጠቅ ነው የሱና ዑለማኦችን ሊዳኝ እየተነሳ ያለው።

ማስታወሻ፦
ምስሉ ከፅሁፉ ጋር ግንኙነት የለውም። ፖለቲካው ላይ በእውቀት ሳይሆን በድፍረት፣ በጥልቅ ንባብ ሳይሆን በምርቃና የሚራኮተውን ጀማ ሳይ ትዝ ብሎኝ ነው። በርግጠኝነት ዑለማኦችን ቅጥረኛ እያለ ከሚወርፈው ነውረኛ መንጋ የደላላ ጀማዐ ይሻላል።
=
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 18:50


السلام عليكم ورحمةالله وبركاته

ተቀርቶ ያለቀ የኡሱሉ_ሰላሳ ደርስ በኢብኑ ሙነወር

ፒዲኤፍ t.me/IbnuMunewor/6486

ክፍል 1↓↓
t.me/IbnuMunewor/6473

ክፍል 2↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6474

ክፍል 3↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6488

ክፍል 4 ↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6497

ክፍል 5↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6504

ክፍል 6↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6524

ክፍል 7 ↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6534

ክፍል 8↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6541

ክፍል 9 ↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6550

ክፍል 10↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6559

ክፍል 11↓↓↓
t.me/IbnuMunewor/6585

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 17:26


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
የሠላሠቱል ኡሱል ኪታብ ደርስ ዛሬ ተጠናቋል። አልሐምዱ ሊላህ። ኢንሻአላህ ከነገ ጀምሮ የአልቀዋዒዱል አርበዕ ደርስ ይከተላል። መከታተል የምትፈልጉ ኪታቡን ብትይዙ መልካም ነው። የማታገኙ የ pdf ፋይል አያይዣለሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 17:23


ደርስ
~
• ኪታቡ:- ሠላሠቱል ኡሱል
• ክፍል:- 1️⃣1️⃣ (የመጨረሻ)
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡ ሶፍት ኮፒ በpdf:- https://t.me/IbnuMunewor/6487
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል መከታተል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 16:35


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 15:33


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 14:29


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ዛሬ የሠላሠቱል ኡሱል ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።

* ቦታ :- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
* ጊዜ :- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
* የኪታቡ ሶፍት ኮፒ በpdf:- https://t.me/IbnuMunewor/6487
* ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 13:08


ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም ለሁለተኛ ጊዜ የተፈታች ሴት ዒዳዋ እስካልተጠናቀቀ ድረስ ለባሏ ፊቷን መግለጥ፣ መዋዋብ፣ ከሱ ጋር ማውራት፣ ተገልሎ መቀመጥ ትችላለች። ግንኙነት የሚፈፀመው ግን ከመለሰ በኋላ ወይም በመመለስ ኒያ ሲሆን ነው።
ዒዳዋ ካላለቀ በቀላሉ መመለስ ይችላል። ዒዳዋ ከተጠናቀቀ በኋላ መመለስ ቢፈልግ ግን አዲስ ኒካሕ ነው በወሊይና ሁለት ምስክር የሚያስረው።
ለሶስተኛ ጊዜ ከፈታ ግን ከዚህ በኋላ መመለስ የሚችለው በትክክለኛ ኒካሕ ሌላ ሰው አግብታ ግንኙነት የተፈፀመበት ጋብቻ ሆኖ ከተፈታች ብቻ ነው። በሃገራችን የተለመደው ለቀድሞ ባሏ ሐላል ለማድረግ ታስቦ የሚፈፀም ጊዜያዊ ጋብቻ እጅጉን የተወገዘ ተግባር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 10:12


የወላጅ የገቢ ምንጭ ሐራም ቢሆንስ?
~~
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–
"የወላጅ የገቢ ምንጭ ሐራም ከሆነ ሊመክሩት ግድ ይላል።
~ ወይ በራሳችሁ ልትመክሩት ይገባል፣ ይህንን ማድረግ የምትችሉበት መንገድ ከኖረ ማለት ነው።
~ ወይ ሊያሳምኑት በሚችሉ የእውቀት ባለቤቶች ታገዙ።
~ ወይ ደግሞ ምናልባት ከሐራም ስራው እንዲርቅ ካሳመኑት ጓደኞቹን መጠቀም ነው።

ይህ ነገር ካልተሳካ ግን በሚያስፈልጋችሁ መጠን መመገብ ትችላላችሁ። በዚህ ሁኔታ ላይ ወንጀል አይኖርባችሁም።
ነገር ግን የገቢ ማግኛው ሐራም ከሆነ አካል ዘንድ መመገብ በመፈቀዱ ላይ ብዥታ ስላለበት በመሰረታዊነት ከሚያስፈልጋችሁ የበዛ ልትወስዱ አይፈቀድም።"

ምንጭ:– ፈታወል ኢስላሚያ: 3/45
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 08:17


እነዚህ ፈፅሞ ሙስሊሞች አይደሉም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Dec, 05:16


የሶሪያ ነገር
~
የሶሪያ ተቃዋሚዎች ሰሞኑን በበሻር አልአሰድ መንግስት እና ተባባሪዎቹ ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት እያደረሱ ነው። እየተዋጉ ስላሉት አካላት ጠለቅ ያለ መረጃ የለኝም። ሆኖም ግን ቢሆንላቸው ከበሻር የማይሻል የለም።
እስከዛሬ በነበረው ጦርነት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሶሪያውያን አልቀዋል። በዚህ እልቂት ላይ የኢራንና የሩሲያ መንግስት ጦሮች፣ የሒዝበላት ጦር ሚና ከበሻር ጦር ብዙም የተለየ አይደለም። ሁሉም እጃቸው በንፁሃን ደም የተጨማለቀ ነው። አሁንም ሽንፈት ከገጠመ ከባድ እንደሚሆን ይገመታል። አላህ ያብጀው።

በርግጥ የተቃዋሚዎቹ አቅምና ዝግጅት ባይታወቅም የበሻርና የአጋሮቹ ተጨባጭ ከትናንቱ በብዙ መልኩ ይለያል። ከፊሎቹ የራሳቸው ጉዳይ በቂ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል። ከፊሎቹ ጡንቻቸው ዝሏል። ትናንት በሻርን ከውድቀት ያተረፉት ሩሲያ፣ ኢራንና ሒዝበላት በቀድሞው አቅማቸውና ትኩረታቸው መጠን አይደሉም። ቢሆንም በሻርን እንደ ዋዛ ችላ ይሉታል ተብሎ አይታሰብም። የጋራ ትብብራቸው ደግሞ ትርጉም ይኖረዋል። ራሺያ የአየር ድብደባዋን አጠናክራ ቀጥላለች። ከዒራቅ ጀምሮ የሺ0 ቡድኖችም እየተጠራሩ ነው። የበሻር መውደቅ እንደ ሀገር ለኢራን ትርጉሙ ከባድ ነው። ምናልባትም የመጨረሻዋ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል። በሊባኖስ፣ በዒራቅ፣ በየመን ያላትን ተፅእኖ ከማዳከም አልፎ ሊያጠፋው ይችላል። እንዲያውም አንድምታው ከዚህም ሊያልፍ ይችላል። ስለዚህ የሞት ሞቷን ትታገላለች እንጂ ለአፍታ ችላ አትልም።

ሒዝበላት ሙሉ ለሙሉ ተፍረክርኳል ባይባልም ክፉኛ ቆስሏል። ትናንት ሶሪያውያንን የጨፈጨፈበት አቅሙ በነበረበት መጠን የለም። ይሄ ጦርነት ግን ለሱ የህልውና ጉዳይ ነው። ከእስ ራኤል ጋር ካለው ጦርነት የበለጠ እንጂ ያነሰ ትኩረት ይሰጠዋል ተብሎ አይጠበቅም።
ስለዚህ የኢራን መንግስት እና በተለያዩ ሃገራት ያሉ የሺ0 ቡድኖች በሻርን ለማትረፍ እስከ ደም ጠብታ ሊታገሉ ይችላሉ።
ስጋቴ ምናልባት ተቃዋሚዎቹ የረባ አቅምና መደራጀት ከሌላቸው አፀፋው ይበልጥ እንዳይከፋ ነው። አላህ የሶሪያን ህዝብ ከበሻር ይገላግለው። ኸይሩንም ይምረጥለት።

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Dec, 18:28


ደርስ
~
* መንሀጁ ሳሊኪን
* ክፍል:- 3️⃣8️⃣
* የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ
* የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Dec, 17:06


ልጅህን አባት ያለው የቲም አታድርገው!
~
ልጆች ከአላህ የተሰጡ አማናዎች ናቸው። አማናን ባግባቡ አለመጠበቅ ነውር ነው። ዘመኑ እንደምናየው ከባድ ነው። የልጆችን ህይወት የሚያበላሹ ነገሮች በጣም በዝተዋል። የአደጋ ስጋት ሲጨምር ጥንቃቄያችን መጨመር ነበረበት። እኛ ግን ይበልጥ እየተዘናጋን ነው። በገዛ ገንዘብህ፣ እጅህ ላይ ባለው ሞባይል፣ ቤትህ ውስጥ ባለው ቴሌቪዥን ልጆችህን እያጠፋሃቸው እንዳይሆን ተጠንቀቅ። ልጅህ ልጅ ነው። የነገ ህይወቱን ሳይሆን የዛሬ ደስታውን ነው የሚያየው። ቅፅበታዊ ኩርፊያውን ፈርተህ፣ የእለት ደስታውን ብቻ እያየህ የጠየቀውን ሁሉ አትስጥ። የሚያስፈልገውን እንጂ የሚፈልገውን ሁሉ አታድርግ።
ትንፋሽ እስከሚያጣ አስጨንቀው እያልኩህ አይደለም። ግን ዛሬ ቁርኣን ካልቀራ፣ ዲኑን ካላወቀ፣ ትምህርት ካልተማረ መቼ ሊማር ነው? አባትነት ልጆችን ቆፍጠን ብሎ በስርአት ለማሳደግ ካልሆነ ምን የረባ ትርጉም አለው? አኺራውንም ይሁን ዱንያውን በተመለከተ ስለ ነገ ህይወቱ አንተ ካልተጨነቅክለት ማን ይጨነቅለት? አባትነትህ ለዚህ ካልሆነ ለምን ይሁን?
ስለ ልጅህ ስታስብ ልብሱና ጉርሱ ላይ አትቁም። ነጣ ገረጣ፣ ከሳ ኮሰሰ፣ ሳቀ አኮረፈ ላይ ብቻ አታተኩር። "ለነገ ምን ይዟል?" በል። ለሃላፊነት አዘጋጀው። ህይወት ከባድ ትምህርት ቤት ናት። ብዙ መውጣት መውረድ አላት። ነገ ምን እንደሚገጥመው አታውቅም። ሁሌ አብረኸው አትሆንም። ብትሆንም አቅምህ ውስን ናት። ጥገኝነትን አታለማምደው። ካንተ የተሻለ እንጂ ያነሰ እንዲሆን አትተወው። ከመስመር ወጥቶ ከሆነ በጊዜ ወደ ቦዩ መልሰው።
ይጫወት ፋታ ስጠው። ግና ቁም ነገረኝነትን አስተምረው። ያለበለዚያ አካሉ ቢያድግም ከልጅነት ስነ ልቦና አይወጣም። በሰላሳ አመቱም የሰው እጅ የሚጠብቅ ጥገኛ ይሆናል። ሌሎችን በሚጦርበት እድሜው ተዘፍዝፎ በአዛውንቶች ይጦራል። ከእህቱ እየነጠቀ ሱስ የሚያሳድድ ጅል ፈጥረት ይሆናል።
ባጭሩ ለልጅህ የእውነት አባት ሁነው። ከልብ አንፀው። መኖርህ በልጅህ አስተዳደግ ላይ ትርጉም ያለው ልዩነት ይኑረው። ልጅህን በአደብ፣ በእውቀት ተከትኩቶ እንዲያድግ ካላገዝከው በህይወት እያለህ የቲም አድርገኸዋል። የአባትን መኖር ትርጉም ነፍገኸዋል። የምታሳድገው ልጅ የቤተሰብ ማፈሪያ፣ የማህበረሰብ እዳ፣ የሃገር ሸክም ከሆነ በሃገርም በወገንም ላይ ትልቅ በደል ነው የፈፀምከው። ይሄ ህዝብ ጀርባውን ያጎበጠው ብዙ ሸክም አለበት። ሌላ ሸክም አትጨምርበት። ለራስህም ቢሆን ነገ በፀፀት እጅህን ከመንከስህ በፊት ዛሬ ሃላፊነትህን ባግባቡ ተወጣ። አባት ሁን። አባት!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Dec, 14:53


አዲስ ወደ ሱና የሚገቡ ሰዎች ራሳቸውንም ሌሎችንም እንዳይጎዱ በጥንቃቄ መያዝ ያስፈልጋል። የሆነ ቡድን ውስጥ የቆዩ ሰዎች ሱና ውስጥ ረዘም ያለ ጊዜ ካልቆዩ የመንሀጅ ግንዛቤያቸው ግልብ ነው፣ የላይ ላይ። ቁንፅል ነገሮችን በያዙ ማግስት በድፍረት የተሞላ ወዝጋባ አካሄድ በማራመድ ፊትና ሊያስነሱ ስለሚችሉ መጠንቀቅ ይገባል። በተለይ በሃገራችን አብዛኞቹ (ሁሉም አላልኩም) ፊትና የሚያራግቡት አካላት ሱና ላይ የቆዩ አይደሉም። ተክ .ፊር፣ ኢኽዋን፣ ሱፊያ፣ ተብሊግ ውስጥ የነበሩ ናቸው። ታዲያ ከራሳቸው ግልብ ግንዛቤ በላይ የጎዳቸው በዙሪያቸው ያልለ አጉል አጨብጫቢ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Dec, 04:05


እምቢ በይ እታለም!
(ከካ|ፊ- ር ጋር ትዳር ለሚያስቡ እህቶች)
~
ለአላፊ ደስታ ስትይ ………. ለምትከስመው ጠውልጋ
ትዳር ከምትመሰርቺ ………. ኢስቲንጃ ከሌለው ጋ
ለዚች ጤዛ ዱንያ ብለሽ ………. ብልጭ ብላ ለምትጠፋ
ከለጋሱ ጌታ ዘንዳ ………. ከትንኝ ክንፍ ለማትሰፋ
እያለቀስን መጥተን ሳለ ………. እያለቀስን ለምንለቃት
አኺራችንን አስበን ………. ምናለ ግን ብንንቃት?!!

እቱ ከጌታችን ጋራ ………. ነገ ከባድ ሂሳብ አለ
አስፈሪ ጭንቅ የሚያይበት ………. መናጢ ሁሉ ያልታደለ
ዛሬ ከመስመሩ ለቆ ………. ወደ ጥፋት ያጋደለ
ከእርኩ -ሳን ጋር ተጣምሮ ………. በክህ -ደት ላይ የዋለለ
ነገን በዛሬ የሸመተ ………. የዋህ እራሱን ያታለለ
“ያ ለይተኒ” የሚልበት ………. ነገ የቁጭት ቀን አለ፡፡

ይልቅ ስሚኝ እህት አለም፡

ትዳር የጌታ ሲሳይ ነው ………. ከባለ ዐርሹ የሚወሰን
ስለቋመጥን ብቻ ሳይሆን ………. ፈቃዱ ሲኖር የሚደርሰን
“ይታደሉታል እንጂ ………. አይታገሉትም” ነው ነገሩ
ውሳኔው ከላይ እስኪወርድ ………. ከዱዓ ጋር ይሶብሩ፡፡
እንጂ ከእንጨት አምላኪ ጋ
እንጂ “አንድም ሶስትም” ከሚል ዜጋ
በስሜት ናላው ዞሮ ………. ሊያጠምድሽ መረብ ቢዘረጋ
ማር በሚተፋ ምላሱ ………. በስልት ወዳንቺ ቢጠጋ
ምናባዊ ሐሴት አይተሽ ………. ጉም ለመጨበጥ መንጠራራት
ለተስፋ ዳቦ እየቋመጥሽ ………. አትሁኚ የ’ሳት እራት፡፡

በሚታዩሽ ብልጭልጮች ………. እራስሽን አትደልይ
ባለ ገ -ዳይ መርዙ እባብም ………. ለስላሳ ነው አስተውይ፡፡
ይልቁንም ረጋ ብለሽ ………. ከአፅናፍ ማዶ ተመልከቺ
ጤፍ በሚቆላ ምላሱ ………. በተኩላ እንዳትረቺ
ለዚች አጭር ህይወት ስትይ ………. ኣኺራሽ ላይ አትሸፍቺ፡፡

ለዚህ ብላሽ ፈራሽ ገላ
ለዚህ ከንቱ ገ -ልቱ አተላ
ዛሬ እጅሽን አትዘርጊ
ነገ እንዳትጠወልጊ፡፡
ሶላት ቁርኣኑ ተትቶ
ሒጃብ አደቡ ተዘንግቶ
በላኢላሀ ኢለላህ ቦታ ………. “አንድም ሶስትም” ተተክቶ
ግንባር ለመስቀል ሲዋረድ ………. የሐያሉ ሱጁድ ቀርቶ
ከቤትሽ ግድግዳ ላይ ………. የፈረንጅ ስእል ተለጥፎ
ሐያእ ግብረ-ገብነትሽ ………. ከአካልሽ ላይ ተገፎ
ከግንባርሽ ላይ ነጥፎ ………. ከልብሽ ላይ ተንጠፍጥፎ
መስጂድ የለመዱ እግሮችሽ ………. ወደ ከኒሳ ሲያመሩ
ጠላ ኮረፌ እየጠመቅሽ ………. ሰካራሞቹ ሲያጓሩ
ይሄ እውን የሆነ እለት
ያኔ ሆነሻል የቁም ሙት!
.
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 21/2008)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Dec, 03:42


እዚህ ላይ ደግሞ በግልፅ ቃል 0ሊይ ጌታ ነው እያሉ ነው። ከሺ0 ቡድኖች ውስጥ 0ሊይ ጌታ ነው የሚሉ በተጨባጭ እንዳሉ አንድ መረጃ ነው። እነዚህ ፈፅሞ ዑዝር የማያስተናግዱ ከሃዲዎች ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Dec, 03:31


በቅርቡ እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አንዱ አፍቃሪ ሺ0 የሆነ ሰው "ዐሊይ ጌታ ነው የሚል ሺ0 የለም፣ እየዋሹባቸው ነው" ሲል ነበር። ለሺ0 ያለው ውግንና ወይም ድንቁ -ርናው ሸፍኖበት እንጂ ይሄ በግልፅ የሚታወቅ ነው።

ይሄው በዚህ ቪዲዮ ላይ የሚታዩት ሺዐዎች ሙሐመድን እና ሌሎቹንም ነቢያት የላካቸው ዐሊይ ነው እያሉ ነው። እነዚህ ፈፅሞ ዑዝር የማያስተናግዱ ከሃዲዎች ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Nov, 17:13


ለሚያስተውሉ ብቻ!
~
ኢብኑ ከሢር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ሐንበልዮች ከጥንት እስከ ዛሬ በአሽ .ዐሪያ ላይ መናገራቸው የተለመደ ነው።" [አልቢዳያ ወኒሃያ፡ 15/153]

ማሳሰቢያ፦
1- ሐንበልዮች ማለት በጊዜው አነጋገር የሰለፎችን አቋም በማንፀባረቅ የሚታወቁት አህሉል ሐዲሥ ናቸው።
2- አሽዐሪዮች ማለት የዛሬ አሕባሾችና መሰሎቻቸው ናቸው።

ከአሽዐሪያ ብልሹ አካሄድ ማስጠንቀቅ እና የተሳሳተ አካሄዳቸውን ማጋለጥ ከጥንት ጀምሮ የአህሉል ሐዲሥ አቋም እንደሆነ መገለፁን አስተውሉ። ዛሬ ሚዛኑ ተገልብጦ ስለዚህ ጉዳይ መናገር በጠርዘኝነት ያስፈርጃል። ዛሬ ሐቅን በመሸፋፈን አንድነትን እናረጋግጣለን ብለው የሚያስቡ የዋሆች የነገሱበት ዘመን ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Nov, 12:07


ጦለበተል ዒልም የሆናችሁ እነዚህን የድምፅ ቅጂዎች ብታዳምጧቸው ትጠቀማላችሁ ኢንሻአላህ።

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Nov, 12:05


#العلم_والدعوة_إلى_الله #محاضرات_وكلمات
#سلسلة_محاضرات_في_المنهجية_العلمية_للشيخ_وسام_الكحلاني
عدد المواد الصوتية ٦👇👇

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Nov, 08:02


ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ
~
እውነቱን ለመናገር አንዳንድ ችግሮቻችንን እራሳችን ነን የምናውሰበስባቸው። እንዴት 80%፣ 90% ሙስሊም የሆነ ህዝብ "ተጨቆንኩ፣ ተበደልኩ" ብሎ ያለቅሳል?! ወላሂ! 100% ሙስሊም በሆነ ህዝብ ውስጥ በአንድ ተል ካሻ ግለሰብ እምነት ተኮር በደል ሲፈፀም አይቻለሁ። በአንድ ሰው! ሰው እንዴት በዚህ መጠን ራሱን ያስደፍራል?! "የተናቀ መንደር በአህያ ይወረራል" ይባላል። በዚህ ደረጃ ራሳችንን ካስደፈርን ጩኸት አያምርብንም የሚሆነውን መቀበል ነው። "ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!"

ለማንኛውም እስከዛሬ ከደረሱ እልፍ ክስተቶች ትምህርት እንውሰድ። በሰፈር መፈታት የሚችልን ጉዳይ አገር አቀፍ አጀንዳ ካደረግነው መፍትሄ የማግኘት እድሉ በጣም ይመነምናል። የአንዳንዶቹ ችግሮች መፍትሄው አዲስ አበባ አይደለም። ክልልም አይደለም። እዚያው ነው። ችግሩ የተከሰተበት ሰፈር። ጎንደርም አፋርም ለሚደርስ ትንኮሳ ምላሻችን እኩል ለቅሶ ብቻ ነው መሆን ያለበት? ስለዚህ አካባቢያዊ ችግሮችን ገና ሳይጎመሩ መነጋገሪያ ሳይሆኑ በፊት አስተማሪ በሆነ መልኩ አካባቢያዊ መፍትሄ እናብጅላቸው። الحر تكفيه الإشارة

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Nov, 07:03


#በመላ ሃገሪቱ ባሉ ከተሞች ከህዳር 18/ 2004 ጀምሮ የተሰሩ "ህገ ወጥ" የከተማ ቤቶችን በማፍረስ መንግስት መሬቶቹን እንደሚረከብ በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሬት ማኔጅመንት ዴስክ ኃላፊው አቶ ገብሩ ባየብኝ ገለፁ የሚል ዜና አየሁኝ። ህዝቡኮ እንኳን ተጨማሪ መከራ ወድቆበት አሁንም የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አቅቶታል። የሚገርም ነው መቼም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Nov, 04:36


"ተቃጠልን'ኮ ባለቤት"
~
ሰውየው እንግዳ ሆኖ ከሰው ቤት ያርፋል። ሚስት የእንግዳው መኖር እንኳ ሳይከብዳት ባለቤቷን ከፍ ዝቅ አድርጋ ታዋርደዋለች። ባል ዋጥ አድርጎ ዝም ይላል። አቶ እንግዳ ግን ራሱን መቆጣጠር አልቻለም። ተነስቶ ሚስትን ከባሏ ፊት ጠፍጥፎ ጠፍጥፎ ለቀቃት። ባለቤት በገዛ ቤቱ ገላጋይ ሆነ።
"ምነው እንግዳ?" አለው ግራ ቢገባው።
"ተቃጠልን'ኮ ባለቤት!" አለ እንግዳው።
.
.
.
አሁን ይህንን ምን አስታወሰኝ? ባንክ ቤት ገብቼ ቁጭ ብያለሁ። አንዷ ልጇን ይዛ ገባች። ልጁ በጣጣጣም የተንቀዠቀዠ ነው። ቤቱን ባንድ እግሩ አቆመው። ሁሉን ነገር አተራመሰው። እናት ወረቀት አንስታ ልትፅፍ ስትል እጇ ላይ ያለውንም ጠረጴዛው ያለውንም በሙሉ መሬት ላይ በተነው። የወደቀውን እንኳ ሳታነሳ ወደሌላው ጥግ ሄደች። እዚያም በተመሳሳይ በተነው። እንዲሁ ላመል ያህል "ተው" ትለዋለች። እሱም አይተው፣ እሷም ጠንከር አትል። ከባንኩ ሰራተኛ ዘንድ ሆና አቀፍ አድርጋ ለመፃፍ እየሞከረች ነው። ልጁ አሁንም እየታገለ ነው። ግርርርም አለኝ። ልናገራት አፌ እያደረስኩ ዝም አልኩ።

እኔ ምለው! "እኔ በሶፍት እየታሰርኩ በፓስታ እየተገረፍኩ ነው ያደግኩት" የሚሉት'ኮ ቀልድ ነበር የሚመስለኝ። ይሄ ነገር እውነት ነው'ንዴ? እንዴዴዴ! ልጆቻችሁን ቆንጥጡ እንጂ። ይሄን ያህል ጨው አይደሉ! አይሟሙ! አዎ ልጅን ጨካኝ አያያዝ መያዝ አይገባም። ግን ደግሞ አሪፍና ዘመናዊ አስተዳደግ ማለት ልጅን ማጨማለቅ ማለት አይደለም። ኧረ ከፈረንጅና ከዐረብ የምትቀዱትን እየለያችሁ! ይሄ አስተዳደጋቸውን ሁሉ ማበላሸት ነው።

ደግሞም "እንዲህ ሆኜ" "እንዲህ ተደርጌ" ሲሏችሁም ያሉትን ሁሉ አትመኑ። የልጅ ወሬ ይዛችሁ ከሰው ጋር አትጣሉ። አንዱ "ልጄ ተበደለብኝ" ብሎ አስተማሪ ላይ ሽጉጥ እንዳወጣ ሰምቼ በጣም ገርሞኛል። እዚህ ላይ "ከልጁ በፊት አባትን ነበር መቅጣት" ያስብላል። ልጆች የጠየቁትን ሁሉ አትስጡ። ያሉትን ሁሉ አታድርጉ። "አይሆንምን"ም ይወቁ። ህይወት ብዙ "አይሆንም" አላት። እናንተ ብታቀብጧቸው ነገ ብዙ ልትፈትናቸው ትችላለች። ሁሉን የለመደ ትንንሹን ሁሉ እንደ በደል ይቆጥራል። በአንድ ወቅት አንድ ወንድሜ የሚገርም ነገር ነገረኝ። ልጅ እናቱን መኪና እንድትገዛለት ጠየቀ። ገዛችለች። ትንሽ ቆይቶ ሌላ ሞዴል (እንደዛ ነው ኣ የሚባለው?) ጠየቀ። "ይገዛልሃል ግን ትንሽ ቆይ" አለችው፡፡ "አሁን ካልሆነ" ብሎ ፍርጥም አለ። እሷ "አይሆንም" አለች። ገብቶ ራሱን አጠፋ። በቃ! እንደተበደለ ነው የተሰማው።
እና ልጆቻችሁን ለማዘን እንኳ የማይመቹ አታድርጓቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

29 Nov, 17:57


ደርስ
~
• ኪታቡ:- ሠላሠቱል ኡሱል
• ክፍል:- 1️⃣0️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡ ሶፍት ኮፒ በpdf:- https://t.me/IbnuMunewor/6487
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል መከታተል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

29 Nov, 14:13


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ዛሬ የሠላሠቱል ኡሱል ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።

* ቦታ :- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
* ጊዜ :- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
* የኪታቡ ሶፍት ኮፒ በpdf:- https://t.me/IbnuMunewor/6487
* ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

29 Nov, 11:36


ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት
~
ለሙስሊም ወንዶች ከነ ጭራሹ ሃይማኖት የሌላቸውን ሴቶች ማግባት ፈፅሞ አይፈቀድላቸውም። ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ባጠቃላይ ማግባትም እንዲሁ የተፈቀደ አይደለም። ከዚህ ተለይቶ የሚወጣው ራሳቸውን ከዝሙት የሚጠብቁ ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት ብቻ ነው። ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት እንደሚፈቀድ ግን ቁርኣን ውስጥ ተጠቅሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ)
“ከነዚያ ከናንተ በፊት መፅሐፍ ከተሰጡት (አይሁድና ክርስቲያን) ሴቶች ጥብቆቹም (ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው።)” [አልማኢዳህ፡ 5]
.
ይህንን መነሻ በማድረግ ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ጋብቻ የሚመሰርቱ ሙስሊም ወንዶች አሉ። ነገር ግን እዚህ ላይ የቁርኣኑን መልእክት በደንብ ማጤን ያስፈልጋል። ጋብቻ የተፈቀደው በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ ራሳቸውን ከዝሙት ከጠበቁ ሴቶች ጋር ነው። ይሄ ሁኔታ ባልተሟላበት ዝም ብሎ ልብ ስላዘነበለ ብቻ ወይም ፍቅር ላይ ስለወደቁ ብቻ የሚፈፀም ልቅቅ ያለ ህግ አይደለም። ስለዚህ የቁርኣኑን መልእክት ለስሜታዊ ዝንባሌያችን ምርኩዝ እንዳናደርግ መጠንቀቅ ይገባል።
.
በዚህ ዘመን ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ከጋብቻ በፊት ያለ ህይወታቸው እጅግ የተጨመላለቀ እንደሆነ በተጨባጭ እያየን ነው። ዝሙቱ ቀርቶ ከትዳር ውጭ መውለዱ እንኳ እንደ ‘ኖርማል’ እየተቆጠረ ነው። ሰፊ እውቅና ያላቸው ሰዎች ሳይቀሩ ህዝብ በሚከታተለው ሚዲያ ላይ ቀርበው “ትዳር የለኝም፣ ግን ልጅ አለኝ” ሲሉ ምንም አይሰቀጥጣቸውም። ልጅ እንዳላቸው የሚታወቁ ግን ትዳር ባለመመስረታቸው የተነሳ ዛሬም “ወይዘሪት እንትና” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙ ናቸው። ባጭሩ ከትዳር በፊት የዝሙት ህይወት ማሳለፍ ብዙዎቹ ዘንድ ነውርነቱ ቀርቷል። እንዲያውም “ዝሙት” መባሉ ቀርቶ “ከጋብቻ በፊት ግንኙነት” እየተባለ ነው እየቀረበ ያለው። ይሄ ከጋብቻ በፊት ያለ ግንኙነት ምናልባት በስሱ ከተነቀፈም በፀያፍነቱ እየተኮነነ ሳይሆን ለቀጣይ ህይወት መሰናክል እንዳይሆን ያክል ብቻ ተራ የግል አስተያየት ሆኖ ነው የሚቀርበው። በዝሙትነቱ ሳይሆን ለሴቷ ከሚያስከትለው ጥቅምና ጉዳት አንፃር ብቻ ነው የሚቃኘው። ዝሙት፣ ማመንዘር ይህን ያክል ቀሏል። እንዲያውም ብልግና እንደ አራድነት፣ ጨዋነት ደግሞ እንደ ፋራነት እየተቆጠረ ነው።
ቁርኣናችን ደግሞ ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻን የፈቀደው “ከዝሙት የተጠበቁ መሆናቸው” ከታወቁት ጋር ብቻ ነው። ይሄ መስፈርት ባልተሟላበት ከነሱ ጋር ትዳር መፈፀም አይፈቀድም። ይሄ አንድ ነው።

ሁለተኛ:- ልጆችህን በኢስላማዊ ስርአት የምታሳድግበት ሁኔታ መኖር አለበት። አንዲት ሙስሊማ ያልሆነች ሴት ከዝሙት የተጠበቀችና ግብረ ገብ ብትሆን እንኳ በዚህ ዘመን ልጆችህን እርሷ በምትፈልገው እምነትና መንገድ ላይ ማሳደግ ብትሻ የሚያግዳት ገደብ የለም። በዚህ የተነሳ ልጆች እምነታቸው ሊቀየር ይችላል። ይሄ በተጨባጭ እየገጠመ ያለ ዘግናኝ ጥፋት ነው። ሙስሊማት ካልሆኑ ሴቶች ጋር ትዳር ፈፅመው ከዚያ ልጆቻቸው የከ'ፈ'ሩ ስንቶች ናቸው? አንዳንዶቹ እንደዋዛ ልጆቹ 18 አመት ሲሞላቸው ሃይማኖታቸውን ይመርጣሉ ይላሉ። ይሄን ሁሉ አመት ኢስላምን አልተማረም፣ ሶላት የለም፣... ። በዚያ ላይ ለልጆች ከአባቶች ይልቅ እናቶች የበለጠ የቀረቡ ናቸው። ጊዜው አይነቱ የበዛ የሞራል ዝቅጠት የተንሰራፋበት ነው። ከስነ ምግባር ለተኳረፈ ትውልድ ከኢስላም ይልቅ ሌሎች እምነቶች ሊቀርቡት ይችላል። በነዚህና መሰል ምክንያቶች የተነሳ ልጆቹ ኢስላምን የመያዛቸው እድል የመነመነ ይሆናል። እንዲህ አይነት ከባቢ ባለበት ደግሞ ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት አይፈቀድም።

ሶስተኛ፦ ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦችም ባሻገር በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈፅሙ አካላት የራሳቸውም እምነት ጭምር አደጋ ላይ የመውደቅ እድሉ ሰፊ ነው። ወንድ ተከትለው የሚከ - ፍሩ እንዳሉ ሁሉ ሴት ተከተለው የተበላሹ ብዙ ናቸው። ይሄ የከፋው አደጋ ነው።
.
ስለዚህ እነዚህ መስፈርቶች ባልተሟሉበት እና ስጋት በተደቀነበት ሁኔታ ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም የሚፈቀድ አይደለም። ታላቁ የዘመናችን የሐዲሥ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአባኒይ ረሒመሁላህ ቀደም ብለው የተጠቀሱትን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች በመጥቀስ በዚህ ዘመን ከክርስቲያን ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም እንደማይቻል አጥብቀው ያሳስባሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ቁ. 523]

እንዲያውም ኢስላም ከሙስሊማት ውስጥ እንኳ አላህን መፍራትና ግብረ ገብነት ያላቸውን ሴቶች እንዲያገቡ ነው ወንዶችን የሚያነሳሳው። ይህንን ህግ መጠበቅ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ለሚወለዱ ልጆችም፣ ለሙስሊሙ ማህበረሰብም፣ ለኢስላምም ውለታ መዋል ነውና ተገቢውን ትኩረት ልንሰጠው ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

29 Nov, 05:25


ሙስሊም ካልሆነ ወንድ ጋር አጉል ቅርርብ ውስጥ የገባችሁ እህቶች በጊዜ ከሰመመናችሁ ውጡ። በፍቅር ምርቃና እንደ ዋዛ ያቆራረጡት አደገኛ መንገድ መመለስ ሲያስቡ ዳገቱ ልብን ሊፈትን ይችላል። ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው። መጨረሻችሁ ኩ- ፍ- ር ከመሆኑ በፊት በጊዜ ንቁ። ርቀቱ ሲጨምር መመለሻው ይከብዳል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

18 Nov, 16:34


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

18 Nov, 15:28


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

18 Nov, 12:42


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ዛሬ የሠላሠቱል ኡሱል ኪታብ ደርስ እንጀምራለን፣ ኢንሻአላህ።
ቦታ :- አሸዋ ሜዳ መስጂደል ዋሊደይን
ጊዜ :- ከመግሪብ እስከ ዒሻ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

18 Nov, 05:49


የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦
"ሱጁድ ላይ ተስተካከሉ። አንዳችሁ እንደ ውሻ ክንዶቹን አያንጥፍ።" [ቡኻሪይ ዘግበውታል።]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

17 Nov, 17:57


ኹፍ ወይም ካልሲ በጦሀራ የለበሰ መስሎት አብሶ የሰገደ ሰው ኋላ ላይ በጦሀራ ሆኖ እንዳልለበሰው ካስታወሰ ውዱኡንም ሶላቱንም መመለስ አለበት። ማለትም እንደገና ውዱእ አድርጎ መስገድ ይኖርበታል። ያለ ውዱእ የተሰገደ ሶላት ዋጋ የለውምና።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

17 Nov, 10:21


መርካቶ ዛሬም ቃጠሎ ደረሰ እየተባለ ነው። ግራ የገባ ነገር። ለማንኛውም ነጋዴዎች አደጋውን በመከላከልም ይሁን ጉዳትን በመቀነስ ላይ ማድረግ የምትችሉት ጥንቃቄ ካለ አስቡበት። እቃ መቀናነስ፣ በተለየ ትኩረት የሚፈልጉ በጣም ውድ እቃዎችን ወይም ዶክመንቶችን ማራቅ ሊሆን ይችላል። ብቻ የሚቻላችሁ ካለ አስቡበት። መርካቶ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አካባቢዎች ያላችሁ ትኩረት አድርጉ።
የተጎዳችሁን አላህ ይተካችሁ። ሌሎቻችሁን አላህ ይጠብቅላችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

17 Nov, 04:19


ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ በሑዘይፋ መስጂድ የሚሰጠው ደርሳችን እንደተጠበቀ ነው።

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

16 Nov, 17:34


አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ቀጥሎ ያሉት በመርከዘ ተውሒድ ለክረምት ተማሪዎች የቀረቡ የሹሩጡ ሶላት ኪታብ ደርሶች ናቸው። አንድ ወይም ሁለት የቀሩ ደርሶች አሉ። ሰሞኑን ቀድቼ አሟላለሁ፣ ኢንሻአላህ ። ከዚህ በፊት የተቀዱ የሹሩጡ ሶላት ደርሶችን አታሰራጯቸው። በየትኛውም ጊዜ እርምት የሚሻ ነገር ያስተዋለ አካል እንዲያካፍለኝ እጠይቃለሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

16 Nov, 14:26


ረስቶ ያለ ውዱእ የሰገደ ሰው ሶላቱን እንደገና ይሰግዳል። ምክንያቱም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا تقبل صلاة بغير طهور
"ያለ ውዱእ ሶላት ተቀባይነት የላትም።" [ሙስሊም]

لا تقبل صلاة أحدكم إذا أحدث حتى يتوضأ
"ያንዳችሁ ሶላት - ውዱእ ካጠፋ - ውዱእ እስከሚያደርግ ድረስ ተቀባይነት የለውም።" [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]

* ሳያውቅ ወይም ረስቶ በተነጀሰ ልብስ ወይም ጫማ ከሰገደ በኋላ ያስታወሰ ግን ሶላቱን አይመልስም። መሀል ላይ ካስታወሰ የሚመቸው ከሆነ የተነጀሰውን ጥሎ ባለበት መቀጠል ይችላል። ማስረጃው ነብያችን ﷺ በአንድ ወቅት እያሰገዱ እያሉ ጂብሪል ጫማቸው ላይ ነጃሳ እንዳለ ሲናግራቸው አወለቁ። ሶላታቸውን እንደገና ከመጀመር ይልቅ ባለበት መቀጠላቸው ያላወቀ ሶላቱ እንደማይበላሽ ይጠቁመናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

16 Nov, 09:56


❶⓪❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4999
❶⓪❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5004
❶⓪❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5012
❶⓪❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5017
❶❶⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5025
❶❶❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5029
❶❶❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5047
❶❶❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5063
❶❶❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5066
❶❶❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5072
❶❶❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5081
❶❶❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5087
❶❶❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5112
❶❶❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5120
❶❷⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5133
❶❷❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5147
❶❷❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5154
❶❷❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5159
❶❷❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5183
❶❷❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5189
❶❷❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5196
❶❷❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5221
❶❷❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5223
❶❷❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5243
❶❸⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5250
❶❸❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5259
❶❸❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5288
❶❸❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5295
❶❸❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5304
❶❸❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5315
❶❸❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5319
❶❸❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5332
❶❸❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5338
❶❸❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5354
❶❹⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5364
❶❹❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5365
❶❹❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5372
❶❹❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5400
❶❹❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5406
❶❹❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5431
❶❹❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5437
❶❹❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5452
❶❹❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5462
❶❹❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5664
❶❺⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5689
❶❺❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5693
❶❺❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5722
❶❺❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5740
❶❺❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5755
❶❺❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5796
❶❺❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5801
❶❺❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5818
❶❺❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5820

❶❺❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5854
❶❻⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5859
❶❻❶:
https://t.me/IbnuMunewor/5864
❶❻❷:
https://t.me/IbnuMunewor/5868
❶❻❸:
https://t.me/IbnuMunewor/5879
❶❻❹:
https://t.me/IbnuMunewor/5886
❶❻❺:
https://t.me/IbnuMunewor/5917
❶❻❻:
https://t.me/IbnuMunewor/5927
❶❻❼:
https://t.me/IbnuMunewor/5944
❶❻❽:
https://t.me/IbnuMunewor/5949
❶❻❾:
https://t.me/IbnuMunewor/5974
❶❼⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/5984
❶❼❶;
https://t.me/IbnuMunewor/6015
❶❼❷:
https://t.me/IbnuMunewor/6025
❶❼❸:
https://t.me/IbnuMunewor/6057
❶❼❹;
https://t.me/IbnuMunewor/6073
❶❼❺:
https://t.me/IbnuMunewor/6095
❶❼❻:
https://t.me/IbnuMunewor/6103
❶❼❼:
https://t.me/IbnuMunewor/6136
❶❼❽:
https://t.me/IbnuMunewor/6158
❶❼❾:
https://t.me/IbnuMunewor/6182
❶❽⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/6191
❶❽❶:
https://t.me/IbnuMunewor/6217
❶❽❷:
https://t.me/IbnuMunewor/6224
❶❽❸:
https://t.me/IbnuMunewor/6265
❶❽❹:
https://t.me/IbnuMunewor/6266
❶❽❺:
https://t.me/IbnuMunewor/6303
❶❽❻:
https://t.me/IbnuMunewor/6304
❶❽❼:
https://t.me/IbnuMunewor/6315
❶❽❽:
https://t.me/IbnuMunewor/6320
❶❽❾:
https://t.me/IbnuMunewor/6366
❶❾⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/6367
❶❾❶:
https://t.me/IbnuMunewor/6396
❶❾❷:
https://t.me/IbnuMunewor/6405
❶❾❸:
https://t.me/IbnuMunewor/6439
❶❾❹:
https://t.me/IbnuMunewor/6445

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

16 Nov, 09:56


Samira umu Ismail:
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ተቀርቶ የተጠናቀቀውን የሪያዱ ሷሊሒን ሙሉ ደርስ እነዚህን ሊንኮች በመጫን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ:- ⤵️
የኪታቡ ሶፍት ኮፒ  በpdf ለማግኘት :
https://t.me/IbnuMunewor/3505
ክፍል :--
❶:
https://t.me/IbnuMunewor/3490
❷:
https://t.me/IbnuMunewor/3508
❸:
https://t.me/IbnuMunewor/3514
❹:
https://t.me/IbnuMunewor/3536
❺:
https://t.me/IbnuMunewor/3541
❻:
https://t.me/IbnuMunewor/3572
❼:
https://t.me/IbnuMunewor/3581
❽:
https://t.me/IbnuMunewor/3620
❾:
https://t.me/IbnuMunewor/3625
❿:
https://t.me/IbnuMunewor/3649
❶❶:
https://t.me/IbnuMunewor/3656
❶❷:
https://t.me/IbnuMunewor/3684
❶❸:
https://t.me/IbnuMunewor/3691
❶❹:
https://t.me/IbnuMunewor/3723
❶❺:
https://t.me/IbnuMunewor/3731
❶❻:
https://t.me/IbnuMunewor/3769
❶❼:
https://t.me/IbnuMunewor/3775
❶❽:
https://t.me/IbnuMunewor/3809
❶❾:
https://t.me/IbnuMunewor/3813
❷⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/3837
❷❶:
https://t.me/IbnuMunewor/3853
❷❷:
https://t.me/IbnuMunewor/3870
❷❸:
https://t.me/IbnuMunewor/3874
❷❹:
https://t.me/IbnuMunewor/3931
❷❺:
https://t.me/IbnuMunewor/3941
❷❻:
https://t.me/IbnuMunewor/3944
❷❼:
https://t.me/IbnuMunewor/3952
❷❽:
https://t.me/IbnuMunewor/3968
❷❾:
https://t.me/IbnuMunewor/3973
❸⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/3995
❸❶:
https://t.me/IbnuMunewor/3999
❸❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4013
❸❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4018
❸❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4041
❸❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4047
❸❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4058
❸❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4064
❸❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4085
❸❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4091
❹⓪
https://t.me/IbnuMunewor/4103
❹❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4107
➍➋:
https://t.me/IbnuMunewor/4122
➍➌:
https://t.me/IbnuMunewor/4129
➍➍:
https://t.me/IbnuMunewor/4143
➍➎:
https://t.me/IbnuMunewor/4150
➍➏:
https://t.me/IbnuMunewor/4166
➍➐:
https://t.me/IbnuMunewor/4167
➍➑:
https://t.me/IbnuMunewor/4173
➍➒:
https://t.me/IbnuMunewor/4175
➎⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4194
❺❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4201
❺❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4216
❺❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4218
❺❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4254
❺❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4264
❺❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4486
❺❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4489
❺❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4511
❺❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4516
❻⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4534
❻❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4539
❻❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4547
❻❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4560
❻❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4566
❻❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4570
❻❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4577
❻❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4579
❻❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4588
❻❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4591
❼⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4639
➐❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4643
❼❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4660
❼❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4665
❼❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4675
❼❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4676
❼❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4709
❼❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4713
❼❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4722
❼❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4723
❽⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4730
❽❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4731
❽❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4746
❽❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4751
❽❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4771
❽❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4776
❽❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4798
❽❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4801
❽❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4821
❽❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4828
❾⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4857
❾❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4864
❾❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4874
❾❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4880
❾❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4904
❾❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4908
❾❻:
https://t.me/IbnuMunewor/4922
❾❼:
https://t.me/IbnuMunewor/4930
❾❽:
https://t.me/IbnuMunewor/4947
❾❾:
https://t.me/IbnuMunewor/4951
❶⓪⓪:
https://t.me/IbnuMunewor/4962
❶⓪❶:
https://t.me/IbnuMunewor/4967
❶⓪❷:
https://t.me/IbnuMunewor/4972
❶⓪❸:
https://t.me/IbnuMunewor/4980
❶⓪❹:
https://t.me/IbnuMunewor/4985
❶⓪❺:
https://t.me/IbnuMunewor/4989

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

14 Nov, 16:30


Live stream finished (56 minutes)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

14 Nov, 15:33


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

14 Nov, 15:02


ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ደርሱ የሚተላለፈው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ነው:-

https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

14 Nov, 09:54


💥ወደድንም ጠላንም ከተማ ዉስጥ ተቀምጠን ኡዝር ቢል ጀህል አለ? ወይስ የለም?

እያልን ከመነታረክ ወደ ገጠሩ ክፍል ጠልቀን በመግባት ይከፍራል ወይስ አይከፍርም?
እያልን የምንጨቃጨቅበትን የዋህ ማህበረሰብ ንፁሁን ኢስላም ማስተማር በእጅጉ የበለጠ ነዉ‼️

👉https://t.me/murselseid

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

14 Nov, 06:43


ከጭፍን ተከታይነት መጠንቀቅ
~
ከሱና ሰዎች አበይት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ የፈለገ ቢገንኑ ለዑለማዎች ጭፍን ወገንተኛ አለመሆን ነው፡፡ የፈለገ ብንወደው ማንም ቢሆን የተናገረው ሁሉ ልክ አይሆንም፡፡ ስለሆነም ለማንም ጭፍን ወገንተኛ ልንሆን አይገባም፡፡ ዑለማዎቻችንን ስለወደድናቸው ብቻ ንግግራቸውን ሁሌ እንደወረደ አንወስድም፡፡ ይህንን በተግባር ያስተማሩን ራሳቸው ዑለማዎቹ ናቸው፡፡ ለአብነት ያክል የአራቱን መዝገቦች ኢማሞች ንግግሮች ላስፍር፡-

[ሀ] የአቡ ሐኒፋ ንግግሮች፡-

1. “አንድ ሐዲሥ ትክክለኛ ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
2. “ከየት እንደወሰድነው ካላወቀ ለማንም አቋማችንን ሊወስድ አይፈቀድለትም፡፡”
3. “ማስረጃዬን ያላወቀ ሰው በኔ ንግግር ፈትዋ ሊሰጥ ሐራም ነው፡፡”
4. “እኛ ሰዎች ነን፡፡ አንድ ንግግር ዛሬ እንናገርና ነገ ከሱ እንመለሳለን፡፡”
5. “የላቀውን አላህ መፅሐፍና የመልእክተኛውን ﷺ ንግግር የሚፃረር ንግግር ከተናገርኩኝ የኔን ንግግር ተውት፡፡”

[ለ] የማሊክ ንግግሮች፡-

1. “እኔ ሰው ነኝ፡፡ እስታለሁ፣ አገኛለሁ፡፡ ስለዚህ እይታየን ተመልከቱ፡፡ ቁርኣንና ሱና ጋር የገጠመውን በሙሉ ያዙት፡፡ ቁርኣንና ሱና ጋር ያልገጠመውን ተውት፡፡”
2. “ከነብዩ ﷺ በስተቀር ንግግሩ የሚያዝለት ወይም የሚመለስበት ያልሆነ አንድም የለም፡፡”
3. “ከነብዩ ﷺ በኋላ ከንግግሩ የሚያዝና የሚተው ያልሆነ አንድም የለም፡፡ ነብዩ ﷺ ሲቀሩ፡፡"

[ሐ] የሻፊዒይ ንግግሮች፡-

1. “አንድ የነብዩ ﷺ ሱና የተገለፀለት ሰው ለማንም ንግግር ሲል እሷን (ሱናዋን) መተው እንደማይፈቀድለት ሙስሊሞች በሙሉ ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡”
2. “በኪታቤ ውስጥ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ሱና የሚፃረር ነገር ካገኛችሁ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ሱና ተከተሉ፡፡ የኔን ንግግር ተውት፡፡”
3. “ሐዲሥ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ከሆነ መዝሀቤ እሱ ነው፡፡”
4. “እኔ ከተናገርኩት በተቃራኒ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ትክክለኛ ዘገባ የመጣበት ርእስ ሁሉ እኔ በህይወት ሳለሁም ሆነ ሞቼ ከሱ ተመልሻለሁ፡፡”

[መ] የአሕመድ ንግግሮች፡-

1. “የአውዛዒይ ግላዊ አስተያየት (ረእይ)፣ የማሊክም ግላዊ አስተያየት፣ የአቡ ሐኒፋም ግላዊ አስተያየት ሁሉም አስተያየት ነው፣ እኔ ዘንድ፡፡ መረጃ ያለው ከነብዩ ﷺ እና ከሶሐቦቹ ቅሪት ዘንድ ነው፡፡”
2. “ማሊክንም፣ ሻፊዒይንም፣ አውዛዒይን፣ ሠውሪይን በጭፍን አትከተል፡፡ እነሱ ከያዙበት ያዝ፡፡”

እነዚህንና መሰል ወርቃማ ንግግሮችን ከሸይኹል አልባኒይ “ሲፈቱ ሶላቲ ነቢይ” ኪታብ መግቢያ ላይ እናገኛለን፡፡

ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! እኛ ከዚህ ምን እንማራለን? ለየትኛውም ዓሊም ጭፍን ተከታይ አንሁን። ከላይ ያለፉትን ንግግሮች በአንክሮ እናስተውል፡፡ የህይወታችን ቋሚ መመሪያም እናድርጋቸው፡፡ “ማሊክንም፣ ሻፊዒይንም፣ አውዛዒይንም፣ ሠውሪይንም በጭፍን አትከተል” የሚለውን የኢማሙ አሕመድ ንግግር እናስተውል። እነዚህን የኡማው ከዋክብት በጭፍን መከተል ካልተፈቀደ ከነሱ በእጅጉ የሚያንሱትንስ በጭፍን መከተል ይፈቀዳልን? ጤነኛ ለሆነ ሰው መልሱ አይጠፋውም፡፡ እናም ተመሳሳይ ነገር ልበል፡፡
- ኢብኑ ተይሚያንም፣ ኢብኑል ቀይምንም፣ ዘሀቢይንም፣ ኢብኑ ከሢርንም፣ … በጭፍን አትከተል፡፡
- ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወህሃብንም፣ ዐብዱረሕማን ብኑ ሐሰንም፣ ዐብዱለጢፍ ኣሊ ሸይኽንም፣ ሰዕዲይንም፣ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ኢብኑ ባዝንም፣ አልባኒይንም፣ ኢብኑ ዑሠይሚንንም፣ ሙቅቢልንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- ፈውዛንንም፣ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድንም፣ ሙሐመድ አማን አልጃሚይንም፣ ረቢዕ አልመድኸሊይንም፣… በጭፍን አትከተል፡፡
- በሰፈርህ፣ በአካባቢህ፣ በሃገርህ ያሉ መሻይኾችንም፣ ተማሪዎችንም የፈለገ ብትወዳቸው በጭፍን አትከተል፡፡ የተወሰኑትን ከሌሎች ለይተህ የሐቅ መለኪያ ሚዛን አታድርጋቸው፡፡ ማንም ይሁን ማን፡፡
እዚህ ላይ ይህ ፅሑፍ ዑለማን ከማክበርና ትንታኔያቸውን ከመጠቀም ጋር የሚፃረር የሚመስለው ካለ የፅሑፉን መልእክት ፈፅሞ አልተረዳም፡፡ የዚህ ፅሑፍ አላማ ግለሰቦችን የሐቅ መለኪያ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል ፈተና መጠንቀቅ እንደሚገባ ማሳሰብ ብቻ ነው፡፡ እንጂ የቁርኣንና የሐዲሥን ማብራሪያ የምንወስደው ከዑለማዎች እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን የአንዱ ዐሊም ትንታኔ ከሌላው የሚፃረርበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም በጭፍን ልንከተል እንደማይገባ የሚያሳይ ነው፡፡ ዛሬ ግን ታላላቅ መሻይኾችን ቀርቶ በአካባቢያቸው የሚገኙ ዝቅ ያሉ አስተማሪዎችን ጭምር በጭፍን በመከተል የወደዱትን የሚወዱ፣ የጠሉትን የሚጠሉ፣ የነኩትን የሚነኩ፣ የፈቀዱትን የሚፈቅዱ፣ የከለከሉትን የሚከለክሉ፣ ያስጠነቀቁትን የሚያስጠነቅቁ ብዙ ናቸው፡፡ የሚከተሏቸው ሰዎች በሆነ ምክንያት አቋም ሲቀይሩም ያለምንም ማገናዘብ ሰልፋቸውን በመቀየር ዥዋዥዌ ይጫወታሉ፡፡ ይሄ ፈፅሞ ሊሆን አይገባም፡፡ አላህ ማስተዋሉን ያድለን፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 07/2010)
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

* የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

14 Nov, 03:43


መልእክተኛው እየሱስ
~
* በጊዜው የነበሩ ሰዎች ነብይ እንደሆነ ነበር የሚያውቁት። “ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ።” (ዮሐንስ 6፡ 14)
* ባሪያ እንደሆነ ነው ያስተማረው። “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።” (ዩሐንስ 13፡16)
* እሱን የሚያመልኩት መለኮታዊ ሳይሆን ሰውሰራሽ ስርአት የሚከተሉ ናቸው። "ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።" (ማቴዎስ 15፡8-10)
* እየሱስ አምላክ ሳይሆን አምላኩን የሚማፀን ባሪያ ነው። “በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው።” (ማርቆስ ወንጌል 15:34)

* ወንጌል የእየሱስ ንግግር አይደለም። እሱ ተላኪ እንጂ ላኪ አይደለም። "የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የኔ አይደለም።" (ዮሐንስ ወንጌል 14:24)
"እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።" (ዮሐንስ ወንጌል 12:49)
* እየሱስ ታዛዥ እንጂ የራሱ ስልጣን የለውም። ሙታን መፈወስ፣ ለምፃሞችን ማዳን፣ ተአምራትን ማሳየት በራሱ አቅም የተፈፀሙ አይደሉም። "እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም። እንደሰማሁ እፈርዳለሁ፤ ፍርዴም ቅን ነው፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።" (ዮሐንስ ወንጌል 5:30)

ስለዚህ የእየሱስን መልእክተኛነት በመቀበል ወደ እየሱስ አምላክ ተመለሱ። የእየሱስን ትእዛዝ ጠብቁ። "እየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፡ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ እስራኤል ሆይ ስማ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው።" (ማርቆስ 12:29)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

13 Nov, 19:29


አስቸኳይ ማስታወቂያ


መረከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዓሪ ለአዳሪ የቁርአን ሒፍዝ ፕሮግራም ኡስታዞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል  ።

ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1, ቁርአንን መርከዝ ዉስጥ በጥሩ ተጅዊድ እና ሙራጅዓ የሀፈዘ ::
2, የቁርአን ሽሀዳ ያለውና መርከዝ ዉስጥ አስተምሮ የሚያዉቅ ::
3, መሰረታዊ የተጅዊድ ህግጋቶች ላይ ግንዛቤ ኖሮት ማስተማር የሚችል ።
4, የስለፊያን ዳዕዋ የተረዳ, ኪታቦችን የቀራና የ ማስተማር ልምድ ያለው ።
5,  ለተማሪዎች በሁለንተናው ጥሩ አርአያ መሆን የሚችል እና የማስተማር ልምድ ያለው
6,  እድሜው ከ 23 ዓመት በላይ የሆነ ::

7, ብዛት : 2

እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ከታች ባለው ዩዘር ኔም ያናግረን ።⤵️⤵️⤵️

📞 0930547776

@AbulAbasNasirMuhammed

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

13 Nov, 17:17


ሐላል ሪዝቅ ጋሻ ነው።
~
ሱፍያን አሠውሪይ እንዲህ ይላሉ :-
"ባለፈው ዘመን ገንዘብ ይጥጠላ ነበር። ዛሬ ግን የሙእሚን ጋሻ ነው።"

[ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ፡ 7241]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

13 Nov, 16:12


ፊቅህ ኪታብ ስትቀራ አንድም ضمير ወደየት እንደሚመለስ ሳታዉቅ እንዳታልፍ አደራ

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

13 Nov, 07:13


"ተውሒድ የኢማን መሰረት ነው። እርሱ በጀነትና በእሳት ሰዎች መካከል መለያ ነው። እርሱ የጀነት ዋጋ ነው። የማንም እስልምና ያለሱ ዋጋ አይኖረውም። የመጨረሻ ንግግሩ ላ ኢላሀ ኢለላህ የሆነ ሰው ጀነትን ገባ።"
[መጀሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ተይሚያ፡ 24/235]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

13 Nov, 03:40


ለኢማምነት መሸቀዳደም አይገባም
~
ኢማምነቱ ሰጋጆች ዘንድ የማይፈለግ የሆነ ሰው ነፍሲያውን ተቆጣጥሮ አርፎ ሊቀመጥ ይገባል። ተከታዮቹ የጥላቻቸው ሰበብ የራሳቸው ክፋት ከሆነ ከቁም ነገር አያገባም።
ሸሪዐዊ ምክንያት ካልኖረ በስተቀር ራስን በሰዎች ላይ ኢማም አድርጎ ለማንገስ መሸቀዳደም አይገባም። ካልሆነ የሚመለከታቸው አካላት ሊያሳርፉት ይገባል። ሱፍያን አሠውሪይ እንዲህ ይላሉ፦
"አንድ ሰው በሶላት ሰዎችን ለመምራት ሲጓጓ ካየኸው ወደኋላ አድርገው።" [ሙስነድ ኢብኑል ጀዕድ፡ 1787]

በቦታው ይበልጥ አዋቂ ካለ ቦታውን ለሱ መልቀቅ፣ እሱን ማስቀደም ይገባል። ቦታው ላይ መደበኛ ኢማም ካለ ስልጣኑ የሱ ነው። ከሰው ቤት ሄደን ከሆነ ስልጣኑ የባለቤቱ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

13 Nov, 03:29


ደርስ
~
* መንሀጁ ሳሊኪን
* ክፍል:- 3️⃣5️⃣
* የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ
* የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

12 Nov, 16:41


#ኺላፍ ባለበት ጉዳይ ላይ ሌሎችን ማሸማቀቅ ይቻላልን ?

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሓፊዘሁላህ

      ~  t.me/Darutewhide

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

12 Nov, 13:51


ለየትኛውም ዓሊም ጭፍን ተከታይ አትሁን። ይሄ ጉዳይ አልባኒ ወይም ፈውዛን ወይም ረቢዕ ወይም ሐጁሪ ጋር ሲደርስ የሚቀየር አይደለም። ዓሊምን ማክበርና በስሙ ርካሽ ቡድናዊ ንግድ ማራመድ የተለያዩ ናቸው።
ከሌሎች ዓሊሞች በተለየ አንድን ዓሊም ማስፈራሪያ ወይም የወላእና በራእ ማጠንጠኛ ከሚያደርግ ስብስብ ራስህን አርቅ። በሱና ስም ስለተጮኸ እንዳትሸወድ። እራሱን በመጥፎ ስም የሚጠራ አንጃ የለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

12 Nov, 12:13


አንድ ሰው ሶላት ውስጥ ሆኖ የተነጀሰ ልብስ እንደለበሰ ካስታወሰ
* በቀላሉ የተነጀሰውን ጥሎ መቀጠል የሚችል ከሆነ (ለምሳሌ ጃኬቱ፣ ጥምጣሙ ሊሆን ይችላል) የተነጀሰውን ከጣለ በኋላ ሶላቱን ባለበት ይቀጥላል።
* የተነጀሰውን ልብስ ጥሎ ለመቀጠል የማይመች ከሆነ ከነነጃሳው ሶላቱን ሊቀጥል አይገባም። ስለዚህ ከሶላቱ በመውጣት እንደገና አስተካክሎ ከለበሰ በኋላ ሶላቱን እንደ አዲስ ይጀምራል።
* የልብሱን ነጃሳ መሆን ያወቀው ሶላቱን ካጠናቀቀ በኋላ ከሆነ ወይም ቀድሞ ቢያውቅም ረስቶት ኖሮ ሶላቱን ከጨረሰ በኋላ ካስታወሰ ሶላቱ ምንም ችግር የለበትም። ስለሆነም እንደገና አይሰግድም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

12 Nov, 08:00


ዚክር የነፍስ ምግብ
~
በቅርቡ በግምት የስምንት ሰዐት መንገድ ከአንድ ሾፌር ጋር ተጓዝኩ፡፡ ጉዞው ለኔ በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ጉዞዎች እጅግ ልዩ ሆኖብኛል፡፡ ሾፌሩ ከኔ ጋር ከተለዋወጣቸው ጥቂት ቃላት ውጭ ይሄን ሁሉ ሰዐት ስንጓዝ ዚክር ላይ ነበር፡፡ ወላሂ እጅግ በጣም ነው የገረመኝ፡፡ እሱን አይቼ እኔም ዚክር እጀምርና ብዙም ሳልቆይ እራሴን ከሆነ የሀሳብ ባህር ውስጥ ስንቦጫረቅ አገኘዋለሁ፡፡ እመለሳለሁ፡፡ ዳግም እራሴን ከሌላ ቦታ አገኘዋለሁ፡፡ ሱብሃነላህ! እራሴን ታዘብኩት አልላችሁም፡፡ ነገሩ ከዚያም በላይ ነው የሆነብኝ፡፡ እራሴን ተጠየፍኩት፡፡ በወንድሜ በጣም ቀናሁኝ፡፡ አላህ በተውሂድና በሱና ላይ ያፅናው ብያለሁ፡፡
ግን ወንድሞችና እህቶች ስራችን ብለን ቁጭ ብለን ዚክር ላለማረጋችን አዋጣም አላዋጣም ምክንያት ይኖረን ይሆናል፡፡ አሰልቺ ረጃጂም ጉዞዎችን ስናደርግ አሁንም አሁንም ከማዛጋት፣ አስቀያሚ ማስታወቂዎች ላይ ከማፍጠጥ፣ … ዚክር ብናረግ ምን ነበረበት? ሱብሓነላህ! አንዴ ሱብሓነላህ ሳንል ስንት መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠናል?! ስንት ረጃጅም ሰአቶችን በከንቱ አሳልፈናል? አራት መቶ አምስት መቶ ኪሎ ሜትሩ ይቅር፣ የአራትና አምስት ሰዐት መንገዱም ይቅር፤ ኧረ ሌላው ቀርቶ የፒያሳ መገናኛ፣ የመርካቶ አየር ጤና መንገድም ይቅር እሩቅ ነው እንበል። በአንዲት አጭር ፌርማታ ስንትና ስንት ዚክር ማድረግ፣ ስንት አጅር ማፈስ አይቻልም? እውነት በዚክሩ የሚገኘው አጅር በገንዘብ ቢቀየር እንዲህ እንዘናጋ ነበር? አቤት የኛ ነገር!
እስኪ አንድ ደቂቃ በማይፈጁ ዚክሮች የሚገኘውን አጅር ያስቡ

- “ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ ሱብሐነላሂል ዐዚም”
በሐዲስ እንደተነገረው እነኚህ ለምላስ የሚቀሉ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አረሕማን ዘንድ የተወደዱ ቃላት ናቸው፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማለት ይቻላል? ሰላሳና አምሳ ኪሎሜትሮችን ስንጓዝስ?
- “ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ” ከጀነት ድልብ ሀብቶች ውስጥ አንዷ ነች፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማለት ይቻላል?
- የነብዩ (ﷺ) ባለቤት ጁወይሪያ ከፈጅር ሶላት እስከ ረፋድ ዚክር ስታደርግ ቆይታ “እኔ ካንቺ በኋላ አራት ከሊማዎችን ሶስት ጊዜ ደጋግሜ ብያለሁ፡፡ ብትመዘን እስካሁን አንቺ ካልሺው ትበልጣለች አሏት፡፡(ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ ዐደደ ኸልቂሂ፣ ወሪዷ ነፍሲሂ፣ ወዚነተ ዐርሺሂ፣ ወሚዳደ ከሊማቲሂ)
- አንዴ በነብዩ (ﷺ) ላይ ሶላት ያወረደ አላህ በሱ ላይ 10 ሶለዋት ያወርድበታል፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማድረግ ይቻላል? … እነኚህ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ውድ የኢስላም ወንድሞችና እህቶች! ኢስላም እኮ ሂወት ነው፡፡ ጁሙዐ ወይም ረመዳን ብቻ ተጠብቆ ሽር ጉድ የሚባልበት ድግስ አይደለም፡፡ “የኢስላም ድንጋጌዎች በዙቡኝ” ያላቸውን ሰው “ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ” ብለው አይደል ያመላከቱት ነብዩ (ﷺ)? ጌታችን እንዲህ ይላል፡
(ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَتَطۡمَىِٕنُّ قُلُوبُهُم بِذِكۡرِ ٱللَّهِۗ أَلَا بِذِكۡرِ ٱللَّهِ تَطۡمَىِٕنُّ ٱلۡقُلُوبُ)
(እነዚያ ያመኑት ልቦቻቸውም አላህን በማስታወስ የሚረኩ ናቸው፡፡ አዋጅ! አላህን በማስታወስ (የአማኞች) ልቦች ይረካሉ።) (አረዕድ፡ 28)

ነብያችን (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፡ "ጌታውን የሚያስታውስና የማያስታውስ ምሳሌ የህያውና የሙት ምሳሌ ነው።" [ቡኻሪና ሙስሊም]
አሁን እኛ ህያዋን ነን ወይስ የቁም ሙት? በጊዜ እናሳችንን እናስተካክል።
የአላህ ሰዎች ሀይላቸውም፣ ምግባቸውም፣ እስትንፋሳቸውም፣… ዚክር ነው፡፡ ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ እንደ ኢብኑ ተይሚያ ዚክር የሚያበዛ አላየሁም፡፡ በአንድ ወቅት ፈጅር ከሰገዱ ጀምሮ ዚክር ያደረጋሉ፡፡ ባሉበት ሁኔታ ላይ እያለ ሰዐቱ በጣም ሄደ፣ ረፈደ፡፡ በሁኔታቸው ተገርሜ እያየኋቸው ነው፡፡ እንደተገረምኩ ገብቷቸዋል፡፡ ዘወር ብለው እንዲህ አሉኝ፡- ይሄ ምግቤ ነው፡፡ እሱን ካላገኘሁ ብርታት አይኖረኝም። (ቃል በቃል አይደለም ያሰፈርኩት።)
“ጌታችን ሆይ! አንተን ለማስታወስ፣ አንተን ለማመስገን እንዲሁም አንተን ባማረ መልኩ ለመገዛት አግዘን፡፡”

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 21/2005)
የቴሌግራም ቻላል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

12 Nov, 04:16


ሶላት የረሳ ሰው ሲያስታውስ ይሰግዳል። የመጀመሪያውን በማስቀደም ቅደም ተከተሉን ይጠብቃል። ለምሳሌ ዙህርን ረስቶ የዐስር ወቅት ከገባ በኋላ ቢያስታውስ መጀመሪያ ዙህርን ይሰግዳል። ከዚያ ዐስርን ያስከትላል።
ዐስርን መስገድ ከጀመረ በኋላ ካስታወሰ ግን የጀመረውን ያጠናቅና ከዚያ ዙህርን ይሰግዳል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

11 Nov, 17:00


ሸሪዐ ሸፋን ብቻ ነው
~
የኢኽዋነል ሙስሊሚን ቡድን ዋና አላማ ኢስላማዊ ኺላፋን መመለስ ነው የሚሉ የዋሆች አሉ። ከዐረብ መሪዎች ጋር የሚያጋጨውም ይሄ ነው ይላሉ። ወላሂ ወቢላሂ ወተላሂ! ይሄ አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው። ኢኽዋንን ከዐረብ መሪዎች ጋር የሚያፋጠው የኩርሲ ጉዳይ ነው። እንጂ ፈፅሞ ኢስላማዊ ስርአት የመዘርጋት ህልም የለውም። ከ90 ዓመት በላይ በኖረበት ግብፅ ምድር ራሱ ለስልጣን የከፈለውን መስዋእትነት ሩብ ያህል እንኳ ሰዎችን ከሺርክ ለማውጣት አልሰራም። ባለስልጣናትን መግደል፣ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ማውደም፣ ህዝብን ወደ ነውጥ መጥራት ነው ቀዳሚ ስራው።

ቡድኑ ከፍተኛ ባለ ስልጣናትን ከሃገር መሪዎች ነቅራሺን፣ አንዋር ሳዳትን ገድ.ሏል። ሙባረክን ለመግ.ደል ሞክሯል። መንግስትም የመረሩ የአፀፋ እርምጃዎችን ወስዶበታል። የቡድኑን መስራች ሐሰን አልበናን፣ ሰዪድ ቁጥብን፣ ... ገድሎበታል። እልፎችን አስሯል። እነዚህ አካላት የተገደሉት የመንግስትን ስልጣን ለመቀናቀን ሲሉ ነውጥ በማራመዳቸው እንጂ ሸሪዐ ለመዘርጋት ብለው አይደለም።

እንጂ ቡድኑ ሶሻሊዝም ፋሽን በነበረበት ጊዜ ይህንን የኩ.ፍ.ር ስርአት ደግፎ ተጉዟል። ወደ ስልጣን በተቃረበበት ጊዜ የራሳቸው አባል የነበረው ጀማል ዐብደናሲር ቀድሟቸው የሶሻሊዝም ስርአት ሲዘረጋ ጊዜ ደግሞ ከአሜሪካና እንግሊዝ ጎን ተሰልፈው ፀረ ሶሻሊዝም ትግል ሊያራምዱ ሞክረዋል። ምእራባውያኑ ቤተ መንግስት እንዲያስገቧቸው በማሰብ ነበር ያለ ወትሯቸው ፀረ ሶሻሊዝም አቅጣጫ የያዙት። የትግላቸው ዛቢያ የሚያልሟት ኩርሲ ብቻ ናት።
እንጂ ህልማቸውም ፍላጎታቸውም የሸሪዐ አስተዳደር መዘርጋት እንዳልሆነ ይሄው ራሳቸው ይመሰክራሉ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

10 Nov, 04:58


* የራስን ብሄር በተለየ ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ የሌሎችን ብሄር የሚያንቋሽሹ፣ ሰዎች በብሄራቸው ተለይተው ጥቃት ሲደርስባቸው ለአጥፊዎቹ የሚከላከሉ ፖስቶችን ወይም ኮሜንቶችን ሼር፣ ላይክ የምታደርጉ፣
* ዘር ላይ ያነጣጠሩ ዘረኛ ቀልዶችን በሳቅ የምታጅቡ፣
* በየትኛውም መልኩ ለዘር ተኮር ጥላቻ ድጋፍ የምታደርጉ አካላት የወንጀሉ ተካፋይ ናችሁ።
* የራሳችሁ ዘር ላይ ቢፈፀም የማትወዱትን ሌላው ላይ ሲሆን የምታደርጉት ከሆነ የዘረኝነት በሽታ ላይ ወድቃችኋል። "ተዋት! እሷ ጥንብ ነች!"
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

10 Nov, 03:27


ሸይኽ ዐብዱልከሪም አልኹዶይር እንዲህ ይላሉ፦
"ልብ ሳይገነዘብ እንዲሁ በምላስ ጫፍ የሚፈፀሙ ዚክሮች ይጠቅማሉ። ነገር ግን ምላስ ከልብ ጋር የተዋሀዱባቸው ዚክሮች የሚኖራቸውን ያክል ውጤትና ምንዳ አይኖራቸውም።" [አተዕሊቃቱ ሰኒያህ፡ 116]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

09 Nov, 17:58


የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

09 Nov, 11:34


የጉዞ ማስታወሻ
~
በቅርቡ ለሳምንት ያክል በአንድ የአፍሪካ ሃገር ውስጥ ቆይታ አድርጌ ነበር። ጉብኝቱ ላይ የተገኘሁት በአንድ በሙስሊሞች ዙሪያ ሰፋፊ ኸይር ስራዎችን በመስራት ላይ በተሰማራ ወዳጅ ያላሰብኩት ግብዣ ተደርጎልኝ ነው። በቆይታዬ ላይ እንዲሁ ትኩረቴን የሳቡኝን ነገሮች ማንሳት ወደድኩኝ።

1- ኢስላምን ለማስፋፋት፣ ሙስሊሞችን ለማገዝ ሃብታቸውን በማፍሰስ፣ ከሃገርና ከቤተሰብ ርቀው ደፋ ቀና የሚሉ 0ረቦችን ተመልክቻለሁ። ከኛ ጋር የማይቀራረብ ምቾት የለመዱ ከመሆናቸው ጋር ሁለ ነገራቸውን ጥለው ለዲን መስዋእትነት ሲከፍሉ ሳይ የኛ ስንፍና ፍንትው ብሎ ነው የታየኝ። እኛኮ በገዛ ሃገራችን ውስጥ በየገጠሩ እየወጣን የረባ እንቅስቃሴ አናደርግም። ባለንበት ከተማ ውስጥ እንኳ የረባ ትጋት የለንም። እኛኮ አላህ ከሰጠን ሃብት ለደዕዋ የምንዘረጋው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። እኛኮ ከስራችን እንቅፋታችን ይበዛል።

2- ሌላው የገረመኝ ነገር በሃገሪቱ ውስጥ በረጅም ዘመናት ኢስላምን ረስተው ከነጭራሹ ሃይማኖት አልባ የሆኑ ህዝቦች መኖራቸውን መስማቴ ነው። ይሄ አስደንጋጭ ነገር ነው። ወደኛ ተመልሼ ሳስብ ተቀራራቢ እውነታዎች እንዳሉ ነው የገባኝ። ሰሜን ሸዋ ላይ በርካታ ዐረብኛ ፅሁፍ የተተከለባቸው መቃብሮች አሉ። የጥንት አርጎባዎች መቃብር ናቸው። ዛሬ አካባቢው ኦርቶዶክስ ነው። ሃዲያዎች በአብዛኛው ወደ ጴን .ጤነት ተቀይረዋል። ደቡብ ጎንደር ላይ እምነት አልባ የሆኑት አውራ አምባዎች የእስልምና ታሪካቸው የሩቅ አይደለም። እነዚህ የለየላቸው ክስተቶች ናቸው። በደርግ የሶሻሊዝም ፋሽን ከኢስላም የራቁት ቀላል አይደሉም። ዛሬም በየ ገጠሩ እጅግ ብዙ ወገናችን ሙስሊም ነው ለማለት በሚከብድ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። አጥብቀን ካልሰራን ብዙ የባሱ ነገሮች ይከሰታሉ።

3- የኛ ሃገር ሙስሊም ተጨባጭ ከብዙ ሃገራት አንፃር ሲታይ ከነ እንከኑ የተሻለ እንደሆነ ያለኝን ግምት አሁንም ከፍ አድርጌያለሁ። በጀማዐ ሶላት ታዳሚ ብዛት፣ በሴቶች አለባበስ፣ በወጣቱ ዲናዊ ንቅናቄ፣ ... ሌላው ቀርቶ ከብዙ የዐረብ ሃገራት ሳይቀር የተሻለ ነው። ይሄ አላህን ልናመሰግንበት የሚገባ ነው። ቀጥሎም ለዚህ ለውጥ አሻራቸውን ያሳረፉ መሻይኾች፣ ዱዓቶች ለኢትዮጵያ ሙስሊም ባለ ውለታ ናቸው።

4- በሄድኩበት ሃገር ሌላው ያስተዋልኩት የደዕዋውን እንቅስቃሴ የሚመሩት እንዳለ የመዲና ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ምሩቆች ናቸው። ይሄ የዚህን ትልቅ ተቋም ትልቅ አበርክቶ የሚያሳይ ነው። በኛ ሃገር ደዕዋ ላይም የመዲና ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ጥሩ አስተዋጽኦ አለው። ይሁን እንጂ ደዕዋው ላይ ካሉት ይልቅ ለአመታት ሲማሩ ቆይተው ባክነው የሚቀሩት ይበዛሉ።

5- ሌላው የጃሚ0 ትምህርት በቂ የዒልም ትጥቅ እንደማያስታጥቅ ነው ከብዙዎች አቅም የተረዳሁት። ከሃገር ውጭ ትምህርት ላይ ያላችሁ ወገኖች በግል እየጣራችሁ ራሳችሁን በሚገባ እንድታበቁ አደራ እላለሁ። ካልሆነ ግን የማይጠቅም ስምና ጉራ ነው የሚተርፋችሁ።

6- ሌላኛው በሄድኩበት ሃገር ያየሁት ሙስሊሞች ሰፊ ነፃነት ያላቸው መሆኑ ነው። ከመንግስት በኩል ጫና የለባቸውም። ዐረቦች በነፃነት ሙስሊሞችን ያገለግላሉ። በሙስሊሞች ለሙስሊሞች የተገነቡ የወንዶች ትምህርት ቤቶች፣ የሴቶች ትምህርት ቤቶች፣ የአይታም ማዕከላት፣ ሌሎችም ተቋማት ውስጥ መስጂዶች አሉ። የመንግስት ኃላፊዎች ባሉበት ምረቃ ላይ ቁርኣን ሲቀራ፣ አዛን ሲደረግ የጎሪጥ የተመለከተው አካል የለም። እኛ ጋር ያለውን ክፋት ርቀቱን አሰብኩኝ።

7- የሃገሪቱ ሙስሊሞች በቁጥራቸውም፣ በዲንም ይሁን በአካደሚ በተማረ የሰው ሃይላቸውም፣ በኢኮኖሚያቸውም፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ባላቸው ተሳትፎም በጣም ከኛ ያነሱ ናቸው። ከእኛ ባነሰ አቅም ላይ ሆነው ተፍ ተፍ ሲሉ ሳያቸው ግን እኛ አቅማችንን እንደሚገባ እንዳልተጠቀምን ነው የተሰማኝ።

8- ሌላው የደነቀኝ ነገር ሌሎች ህዝቦችን ወደ ኢስላም መጣራት በጣም ቀላል መሆኑ ነው። አንድ ሰው ጎዳና ላይ ደዕዋ ቢያደርግ ብዙ ሰው ሊሰልም ይችላል። ቋሚ ክትትል ካልተደረገ ግን በሌላ ጊዜ ቢመለስ እነዚያን ሰዎች ኢስላም ውስጥ አናገኛቸውም። በቀላል እንደገቡ በቀላል ይወጣሉ፡፡ ሰፊ ስራ ለመስራት ደግሞ የአቅምም፣ የሰው ሃይልም ውስንነት አለ። በኛም ሃገር ተጨባጭ ተግቶ የሚሰራ ጠፍቶ እንጂ በአንዳንድ አካባቢዎች ሰዎችን ማስለም ከባድ ነገር አይመስለኝም።

9- በሄድኩበት ሃገር ፈርጣማ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው ነገር ግን በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሺ0ዎች አሉ። ደግነቱ ሌሎች ሃገራት ላይ እንደሚታየው ወደ ቡድናቸው የመጣራት ተነሳሽነት የላቸውም። መስጂዳቸው ጭር ያለ ነው። ከህዝቡ እጅግ ዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታና ሰፊ መሀይምነት አንፃር ሲታይ ጠንከር ያለ ስብከት ቢኖራቸው አደጋቸው ከባድ ነበር። በነገራችን ላይ ቁጥራቸው እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ሃገራችን ውስጥ በኢራን ኤምባሲ ድጋፍ በህቡእ የሚንቀሳቀሱ ሺዐዎች አሉ።

10- ሌላው የድርጅቶችን አስፈላጊነት በሚገባ አይቻለሁ። ለሙስሊሙ ህዝብ ድጋፍ እያደረጉ ያሉት ዐረቦች በድርጅት የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ያለ ህጋዊ ተቋም (ጀምዒያህ) ምንም አይነት የበጎ አድራጎት ስራዎችን መስራት እንደማይችሉ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። በህቡእ ለሚንቀሳቀሱ አካላት የሚሄዱ ገንዘቦችን ለመቆጣጠር ሲሉ መንግስታት የፋይናንስ ፍሰቶችን በጥብቅ ይቆጣጠራሉ። እነዚህ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በርከት ያሉ ትምህርት ቤቶችን፣ መስጂዶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ የህክምናና የሙያ ማሰልጠኛዎችን፣ የአይታም ማዕከሎችን በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ፣ በኤሺያ፣ በአሜሪካ አቋቁመዋል። የመጠጥ ውሃ ጉድጓዶችን ይቆፍራሉ። ሰፋፊ እርዳታዎችን ያከፋፍላሉ። እነዚህን ስራዎች የሚሰሩት በሚሄዱበት ሃገር ከተከፈቱ ህጋዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ነው።
=
ቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

09 Nov, 06:39


ምንኛ ደስ የሚያሰኝ ርብርብ ነው! ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የሚችለውን እያደረገ ነው። በዚህ የመስጂድ ግንባታ ላይ የሶደቀቱን ጃሪያ ድርሻ እንዲኖረው የሚሻ ያቅሙን በማገዝ ለኣኺራው ስንቅ ያስቀምጥ።
መስጅደል ፉርቃን በወረባቦ ወረዳ ዋና ከተማ ቢስቲማ ላይ እየተሰራ ያለ መስጂድ ነው። መስጂዱ ለከተማው ድምቀት ነው። ከዚያ በላይ ግን ለከተማውም በዙሪያው ላሉ ቀበሌዎችም ጥሩ የደዕዋ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፣ ኢንሻአላህ።

መርዳት ለምትፈልጉ ከታች በተለጠፈው አካውንት ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።
#ወረባቦ ፉርቃን መስጂድ
ንግድ ባንክ - 1000401221957
አቢሲኒያ - 64828638
ዳሽን - 2935824167011

መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩን። ምናልባት በናንተ በኩል ተሳትፎ የሚያደርግ ቢኖር ከአጅሩ ተካፋይ ትሆናላችሁ።
{ مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ }
"ሌሎችን ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የተገበረውን ሰው አምሳያ ምንዳ ይኖረዋል።"
=
ቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

09 Nov, 04:14


እዚያ ጋ ሰው ይታየኛል!
~
"ሰው ሞልቶ ሰው ጠፋ … ሚዛን የሚደፋ
ለእውነት የሚቆም … ላገር የሚለፋ"
እላለሁ እንደ ሰው
ሆዴን ሆድ ሲብሰው።

"ሴት ይርመሰመሳል … ሚስት ነው የጠፋ"
እላለሁ አንዳንዴ
ወንዶችን ወክየ … ቆሜ ሳንቀላፋ።

"ወንድ ይተራመሳል … ግን ባሎች የታሉ?"
እያሉ 'ሚጮሁ … እልፍ ሴቶች አሉ።

ሰው ሁሉ ሰው አድዳኝ … በሆነበት ምድር
ሰው ያልተገኘበት … አለን አንዳች ምስጢር።

ገባኝ ገባኝ

ለካስ ሰው "ነፍ" ነው … "ሰው" ከሰው ለለየ
ክፉን ብቻ ሳይሆን … ጥሩውንም ላየ።

ለካስ ሚስቶች አሉ … ባል ሆኖ ለመጣ
ሐያእ ለሚገባው … ላልሆነ ፈጣጣ።

ለካስ ባል በሽ ነው … ባልነት ለገባት
እራሷን ረስታ እንጂ … ዞራ የዞረባት።

ምልከታ ከራስ ይጀምር!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 16/2011)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Nov, 19:46


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣9️⃣2️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 640፣ ሐዲሥ ቁ. 1866
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Nov, 16:33


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Nov, 15:31


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Nov, 14:59


ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ደርሱ የሚተላለፈው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ነው:-

https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Nov, 11:51


ትላንት ከዝሙት ስለመጠንቀቅ ማሳሰቢያ የፃፍኩት ዐረብ ሃገር ላይ እየተፈፀሙ ስላሉ ጥፋቶች የሚገልፁ አስደንጋጭ ጥቆማዎችን ከተለያዩ ወንድሞች ስላየሁ ነው። ከላይ ያያያዝኩት መልእክት ወንድማችን ከኔ ፖስት ስር ያስቀመጠው እጅግ አስደንጋጭ ትዝብት ነው። እንዲህ አይነት ወጥመዶች ወንጀሉ መቋጫ እንዳይኖረው ነው የሚያደርጉት። የመፍትሄው ሁሉ ቁንጮ አላህን መፍራት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Nov, 05:59


የኢኽ^ዋን ምሽጎችን ማንኮታኮት
(ተከታታይ፣ ክፍል-3)
ሰይድ ቁጥብን ለማያውቀው
~
1. ሰይድ ቁጥብ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን አይቀበልም። ኢስቲዋእን ልክ አሕባሾች እንደሚያደርጉት በጀህ^ሚያ፣ በሙዕ^ተዚላና በአሻ^ዒራ ተፍሲር ነው የፈሰረው። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 4/2328፣ 5/2807፣ 6/3480] በዚህ ጉዳይ የአሕ^ባሽን ጥመቶች ለማጋለጥ የምትታትሩ ወንድሞችና እህቶች ሆይ! የጥመት ቡላና ዳለቻ የለውም! የሰይድ ቁጥብን ጥመትም እንዲሁ አትርሱ።

2. ሰይድ ቁጥብ አደገኛውን የ“ወሕደተል ውጁድ” በተጨማሪም የጀህ^ሚያዎችን፣ የቀ^ደ^ሪያዎችንና የጀ^ብ^ሪያዎችን ዐቂዳ አስፍሯል። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 4/2249፣ 5/2719፣ 6/4002]

3. ሰይድ ቁጥብ {የኡሉሂያ ጉዳይ የውዝግብ አጀንዳ አልነበረም። ይልቁንም የሩቡቢያ ጉዳይ ነው የውዝግብ አጀንዳ የነበረው። መለኮታዊ ተልእኮዎች (ሪሳላዎች) ሲጋፈጡት የነበረውም ይህን ነው። የመጨረሻው ተልእኮም (ሪሳላም) ይጋፈጠው የነበረው ይህ ነው} ይላል። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 4/1846]
እውነታው ግን በነቢያትና በህዝቦቻቸው መካከል የነበረው ፍጭት ዋና መንስኤው ተውሒደል ኡሉሂያን አለመቀበላቸው ነበር። እንጂ ተውሒደ ሩቡቢያህ አልነበረም። ለምሳሌ የመካ ሙሽሪኮች የአላህን ፈጣሪነትና ጌትነት ያውቁ ነበር። ችግራቸው እሱን በብቸኝነት ለማምለክ ፈቃደኞች አለመሆናቸው ነው።

4. ሰይድ ቁጥብ ላኢላሀኢለላህ ማለት “በመፍጠርና በመምረጥ ተጋሪ የለውም ማለት ነው” ይላል። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 5/2707] ይሄም ግልፅ ስህተት ነው። ላኢላሀኢለላህ ማለት ከአላህ በስተቀር በሐቅ አምልኮት የሚገባው የለም ማለት ነው። የአላህን ፈጣሪነትማ ብዙሀኑ የመካ አጋሪዎችስ መቼ ካዱ? ይሄውና የቁርኣን ዘላለማዊ ምስክርነት:-
{ قُلۡ مَن یَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَاۤءِ وَٱلۡأَرۡضِ أَمَّن یَمۡلِكُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَـٰرَ وَمَن یُخۡرِجُ ٱلۡحَیَّ مِنَ ٱلۡمَیِّتِ وَیُخۡرِجُ ٱلۡمَیِّتَ مِنَ ٱلۡحَیِّ وَمَن یُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۚ فَسَیَقُولُونَ ٱللَّهُۚ فَقُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ}
{“ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረስ ማን ነው? ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከህያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?” በላቸው። በእርግጥም “አላህ ነው” ይሉሃል። እናም “ታዲያ (እንደሚገባው) አትፈሩትም?” በላቸው።} [ዩኑስ፡ 31]

5. ሰይድ ቁጥብ ኢማንን ወጥና የማይከፋፈል ነው ይላል። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 2/798] ይሄ የሙር^ጂአ እና የኸ^ዋሪጅ አቋም ነው።

6. ሰይድ ቁጥብ እንደ ራ^ፊ^ዷ/ ሺ^0 የነብዩን ﷺ ሶሐቦች ያንቋሽሻል።
[ሀ]:- አቡ ሱፊያንን "የአቡ ሱፊያንን እስልምና የከንፈርና የምላስ እስልምና እንጂ የልብ ኢማንና እውነቱን የማግኘት አይደለም። ኢስላም ወደዚህ ሰውየ ልብ አልሰረፀም፣ ከሰለመ በኋላም የሙስሊሞችን ሽንፈት ሲመኝ የነበረ ነው!” በማለት በኒፋ^ቅ ይወነጅላል። ይስተዋል! ነብዩ ﷺ ግን የአቡ ሱፊያንን እስልምና ተቀብለዋል። አቡ ሱፊያን ሙስሊም ሆነው ጂሃድ ሲዋጉ አንድ አይናቸውን እንዳጡ እና ነብዩም ﷺ “ከፈለግክ ዱዐ ላድርግልህና አይን ይመለስልሃል። ከፈለግክ ደግሞ (ታገስና) ጀነት አለህ” ሲሏቸው “ጀነት ይሻለኛል” እንዳሉ ኢብኑ ሐጀር ጠቅሰዋል። [አልኢሷባህ፡ 4066]
[ለ]:- ሰይድ ቁጥብ ሙዓዊያንና ዐምር ብኑል ዓስን በውሸት፣ በማጭበርበር፣ በማታለል፣ በንፍ^ቅና፣ በሙሰኝነት … ይወነጅላቸዋል። [ኩቱቡን ወሸኽሲያት፡ 242] ሙዓዊያን ረዲየላሁ ዐንሁ ደግሞ ደጋግሞ በሚያስቀይሙ ቃላት ወርፏቸዋል። አሁን በነዚህ አስቀያሚ ቃላት የተወነጀለው ሰይድ ቁጥብ ቢሆን ኖሮ ኢኽዋኖች ምን ይሉ ነበር? ለመሆኑ ከሶሐቦቹና ከሰይድ ቁጥብ ማነው የሚበልጠው? ዛሬም ተከታዮቹ ሰይድ ቁጥብ ተሳስቷል ከማለት ይልቅ ሶሐቦችን መወንጀል ነው የሚቀናቸው። ለሶሐቦች የማይሰጡትን ምክንያትም ለሰይድ ቁጥብ ይደረድራሉ።
ኢብኑ ሙባረክ፡ ከሙዓዊያና ከዑመር ብኑ ዐብዲልዐዚዝ የትኛው እንደሚበልጥ ሲጠየቁ “ወላሂ ሙዓዊያ ከነብዩ ጋር ሆኖ ባፍንጫው የገባው አቧራ ከዑመር ሺህ ጊዜ ይበልጣል” ብለው ነው የመለሱት። ልብ በል! ከሙዓዊያና ከሰይድ ቁጥብ ማን ይበልጣል አይደለም የተጠየቁት። ሌላም ጊዜ “ሙዓዊያ እኛ ዘንድ ፈተና ነው። እሱን በመጥፎ ሲመለከት ያየነውን በሶሐቦች ጉዳይ አናምነውም” ብለዋል። ኢማሙ አሕመድ “ከሙዓዊያና ከዑመር ብኑ ዐብዲልዐዚዝ ማን ይበልጣል?” ተብለው ሲጠየቁ፣ “ሙዓዊያ ነው የሚበልጠው። የነብዩን ሶሐቦች ከማንም ጋር አናወዳድርም” ብለዋል። አንድ ሰው ኢማሙ አሕመድን “አንድ ሙዓዊያን የሚያንቋሽሽ አጎት አለኝ” ቢላቸው “ከሱ ጋር አብረህ እንዳትበላ!” ብለውታል። ብዙ ኢኽዋኖች ግን ብዙ ፀያፍ ጥፋቶች ያሉበትን ሰይድ ቁጥብን ሸሂድ እያሉ እያወደሱ እነ ሙዓዊያን ለማብጠልጠል ግን ሁለት ጊዜ እንኳን ማሰብ አይፈልጉም።
[ሐ]:- ሰይድ ቁጥብ ከዚህም ተሻግሮ በኑ ኡመያን በጅምላ በኒፋ^ቅ ይወነጅላል፡፡ “በኑ ኡመያ በጥቅሉ ኢማን ከልባቸው አልሰረፀም፡፡ ኢስላም ለነሱ እንደ ጥቅማቸው ሲያሻቸው የሚለብሱት ሲፈልጉ የሚያወልቁት ካፖርት ማለት ነው። ስነ ምግባር፣ ዲን፣ ልቦና የማይገታቸው ሰዎች ናቸው…” ይላል። [አልዐዳላህ ፡172]
ከግለሰብ ክብር በላይ ለእውነት የምትወግኑ ሁሉ ቆም ብላችሁ አስተውሉ! ሰይድ ቁጥብ በዚህ መልኩ የሚገልፀው እናንተን ወይም የናንተን ዘር ማንዘር ቢሆን ምን ትሉ ነበር? በነዚህ አስቀያሚ ቃላት የሚገልፀው የነብዩን ﷺ ሶሐቦች ሲሆንስ? የነብዩን ሶሐቦች በማብጠልጠል የተለከፈው ሰይድ ቁጥብ የራፊ^ዷዎች/የሺ^0ዎች መንገድ ነው የተከተለው። ሶሐባ የሚሳደብን ሰው በተመለከተ ነብዩ ﷺ “የአላህ፣ የመላእክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በሱ ላይ ይሁን” ብለዋል። ኢማሙ ማሊክ፡- “የአላህ መልእክተኛን ﷺ ሶሐቦች የሚሳደብ ሰው በኢስላም ውስጥ ምንም ድርሻ የለውም” ብለዋል። ኢማሙ አሕመድ፡ “አንድ ሰው የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶሐቦችን በክፉ ሲያነሳ ካየህ ሙስሊምነቱን ተጠራጠረው” ብለዋል። አቡ ዙርዐህ፡- “አንድ ሰው ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶሐቦች የየትኛውንም ክብር ሲያጎድፍ ካየኸው እወቅ እሱ አፈንጋጭ ነው” ብለዋል።
[መ]:- ሰይድ ቁጥብ ከዚህም አልፎ በጀነት የተመሰከረላቸውን፣ ነብዩ ﷺ ሁለት ሴቶች ልጆቻቸውን የዳሩላቸውን፣ “ሶስተኛ ቢኖረኝ እድረው ነበር” ያሏቸውን፣ ሶስተኛውን ፍትሃዊ ኸሊፋ ዐሥማን ብኑ ዐፋንንም እንዲህ ሲል ይወነጅላል:-
* የኡሥማን ረዲየላሁ ዐንሁ የኺላፋ ዘመን በሶስቱ ኸሊፋዎች ዘመን ውስጥ የገባ ክፍተት እንጂ የእውነት የነገሰው እሱ ሳይሆን መርዋን ነው።
* ዑሥማን በስልጣኑ ተከልሎ የሙስሊሙን ገንዘብ ያላግባብ የተጠቀመ፣
* ለዘመዶቹ እያዳላ የነብዩን ወዳጆች ያራቀ፣

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Nov, 05:59


* ኸሊፋ ሊሆን በማይገባው እድሜ ስልጣን ይዞ የመርዋን መጫወቻ የሆነ፣
* አገዛዙ ከኢስላም ሩህ የራቀ ነበር፣
* ከኡሥማን ይልቅ የኡሥማን ገዳዮች ለኢስላማዊ ሩሕ የቀረቡ ነበሩ።
* ኡሥማን ላይ በተነሳው ፊትና የአቡ ዘር እጅ አለበት ይላል። [አልዐዳለቱል ኢጅቲማዒያህ፡ 160-186]
አስተውሉ! ነብዩ ﷺ የዑሥማንን ገዳዮች ሙና^ፊቆች እንደሆኑ ቀድመው ገልፀዋል። የኢኽዋኖቹ ቁጥብ ሰይድ ግን እነዚህን ሙና^ፊቆች ከኡሥማን በበለጠ ለኢስላማዊ ሩሕ የቀረቡ ነበሩ ይላል። ይስተዋል! ሰይድ ቁጥብ የነብዩን ﷺ ሶሐቦች ደጋግሞ ባስቀያሚ ቃላት መወረፉ ከራ.ፊዷ ሺዓዎች ጋር የሚያመሳስለው ባህሪው ነው፡፡ ለዚህም ነው የራፊዷው የኢራን መንግስት በስሙ ቴምብር ያሰራለት። በርግጥ ሰውየው ከሺ^ዐዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ነበረው። በነገራችን ላይ ሰይድ ቁጥብ ከዚህ ተግባሩ ተመልሷል የሚሉ ሰዎች አሉ። ይሄ ግን ውሸት ነው፣ ቅጥፈት።

7. ሰይድ ቁጥብ ኡማውን በጅምላ የሚያከ^ፍር ተ^ክ^ፊሪ፣ ኻ^ሪ^ጂ ነው፡፡ ምን እንደሚል አይታችሁ ፍረዱ።
* “እሄ የምንኖርበት ማህበረሰብ ራሱ ሙስሊም ማህበረሰብ አይደልም። ለዚያም ነው ኢስላማዊ ስርኣት ያልዘረጋው፡፡” “በመጨረሻም ከነዚህ የጃሂ^ሊያ ስብስብ ውሰጥ የሚካተቱት እነዚህ ሙስሊም እንደሆኑ የሚሞግቱት ህዝቦች ናቸው።” [ፊ ዚላሊል ቁርኣን፡ 3/1816፣ 4/2009-2010]
* “ጉዳዩ የማመንና የመካ^ድ ጉዳይ ነው። ሰዎች እንደሚሞግቱት ሙስሊሞች አይደሉም። የሚኖሩት የጃሂ^ሊያ ህይወት ነው። ደዕዋችን የተነሳው እነኚህን ጃሂ^ሊዮች ወደ ኢስላም ለመመለስ ነው፣ እንደ አዲስ ሙስሊም ለማድረግ።” [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 173]
* “የሙስሊሙ ኡማ ህልውና ከብዙ ከፍለ-ዘመናት በፊት ተቋርጧል። እንደ አዲስ መመለስ ይኖርብናል።” [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 6]
* “ዛሬ ያለነው ኢስላም ሲነሳ ያጋጠመው ዓይነት ጃሂ^ሊያ ውስጥ ነው ወይም ከዚያ የከፋ የሆነ!” [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 21]
* በአሁኑ ጊዜ ያሉ ሙስሊሞችን እርድ መብላት ይቻላል ወይ” ተብሎ ሲጠየቅ “እንደ አህለል ኪታብ (አይሁድና ክርስቲያን) እርድ ቆጥራችሁ ብሉ” ብሎ ነው የመለሰው። [አታሪኹ ሲሪይ ሊጀማዐቲል ኢኽዋኒል ሙስሊሚን፡ 80]
ይሄ ሁሉ ጉድ ያለበትን ሰው እያንቆለጳጰሱ ነው ኢኽዋኖች ሌሎችን “ተ^ክ^ፊ^ር” “ፅንፈኛ” እያሉ የሚወነጅሉት። “የሌ.ባ አይነ-ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ!”

8. ሰይድ ቁጥብ ጁሙዐ አይሰግድም ነበር!! ዐሊይ ዐሽማዊ (የሰይድ ቁጥብ ቅርብ ሰው ነው) በአንድ ወቅት ከሰይድ ቁጥብ ጋር ያጋጠመውን እንዲህ ሲል ይገልፃል፡-
“የጁሙዐ ወቅት ሲደርስ “ተወንማ እንነሳና እንስገድ” አልኩት፡፡ አስደንጋጭ ነበር! ለመጀመሪያ ጊዜ ሰይድ ቁጥብ ጁሙዐ እንደማይሰግድ አወቅኩኝ፡፡ “ኢስላማዊ ኺላፋ ከሌለ ጁሙዐ የለም፡፡ ያለ ኺላፋ ጁሙዐ የለም!” አለ፡፡ [አተንዚሙ ሲሪይ፡ 112]

9. ሰይድ ቁጥብ ወደ ሶሻሊዝምና ኮሙኒዝም ርእዮተ ዓለም የሚጣራ ነበር! “መንግስት ንብረቶችንና ሀብቶችን በሙሉ በመንጠቅ እንደገና እንደ አዲስ ሊያከፋፍል የግድ ይለዋል። እነዚህ ንብረቶች ኢስላም እውቅና በሚሰጠው መልኩ የተገኙ፣ በሚያፀድቃቸው መንገዶች የበለፀጉ ቢሆኑም እንኳን። ምክንያቱም ከማህበረሰብ ላይ ጉዳትን ማስወገድ እና በዚህ ህብረተሰብ ላይ የሚጠበቁ ጉዳቶችን መከላከል ከግለሰብ መብቶች ይልቅ ተቀዳሚ ናቸውና።” [መዕረከቱል ኢስላም ወረእሰማሊያህ፡ 44]
ይሄ የበደልና የክህ^ደት ስርአት ነው።
10. ሰይድ ቁጥብ በርካታ የቁርኣን አያዎችን ለክብራቸው በማይገባ መልኩ በሙዚቃዊ ቃና ደጋግሞ ይገልፃቸዋል። ለዚህም በሙዚቃ ባለሙያ በሙዚቀኛ እንደታገዘ ያለምንም ሀፍረት ይገልፃል። [አተስዊሩል ፈኒይ፡ 89]

11. ሰይድ ቁጥብ በዐቂዳ ጉዳይ ቁርኣን ብቻ እንጂ ሶሒሕ እንኳን ቢሆኑ ሙተዋቲር ያልሆኑ ሐዲሦችን አይቀበልም። [ፊዚላሊል ቁርኣን፡ 6/2008]

ልብ በሉ! ይሄ የአፈ^ን^ጋጩ ሙ^ዕ^ተዚላ ቡድን አቋም ነው።

12. ሰይድ ቁጥብ ደግሞ ደጋግሞ ቁርኣንን “ሲሕር” /ድግምት/ እያለ ይገልፃል! [አተስዊሩል ፈኒይ፡ 11፣ 17፣ 25] አዑዙ ቢላህ! ድግምት ነው ሲል ግን ማድነቁ ነው በሱ ቤት። ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል።

13. ሰይድ ቁጥብ ነብያትን ሳይቀር ለክብራቸው በማይመጥን መልኩ በነገር ይወጋል። [አተስዊሩል ፈኒይ፡ 200፣ ...]
ኢኽዋኖች ሆይ! ይህ ነው ሰይዳችሁ! ይሄ ነው ቁጥባችሁ!

ማሳሰቢያ:-
1- ሰይድ ቁጥብ ከነዚህ ጥፋቶች ተመልሷል የሚሉ ሰዎች አሉ። ይሄ ከእውነት የራቀ ነው። መረጃ ጠይቋቸው፣ የሚያቀርቡት ነገር የለም። እንዲያውም ሶሐቦችን ስለሚነካበት ጥፋቱ በጊዜው እርምት ቢሰጠው አስቀያሚ ምላሽ ነው የሰጠው። የተክ - ፊር አቋሙንም ቢሆን ቀርዷዊ ያረጋገጠው ነው። የታል የተመለሰው? ቢመለስ ራሱ እነዚህ ጥመት ያለባቸው ስራዎቹ ለህዝብ እስከ ቀረቡ ድረስ እርምት መስጠት ይገባል።
2- "የሞተ ሰው አትንኩ" የምትሉ ትኖራላችሁ። እሱ የሚያንቋሽሻቸው ሶሐቦች በህይወት ያሉ ናቸው ወይ? ወይስ ለኢስላም የዋሉት ውለታ ከሱ ያነሰ ነው?

(ኢንሻአላህ ክፍል 4 ይቀጥላል)
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 13/2007)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

08 Nov, 03:42


ስታነውር ትፈተናለህ
~
ኢብኑ ሲሪን ሃብታም ነበሩ። ሃብታቸው ከሰረና በድህነት ውስጥ መኖር ያዙ። በዚህን ጊዜ ሰዎች፡ "እንዲህ የሆንክበት ምክንያቱ ምንድነው?" ብለው ጠየቋቸው።
"ይሄ አንድን ሰው፡ 'አንተ ድሃ!' በማለቴ የተነሳ ለአርባ ዓመት ቅጣቱን ስጠብቀው የነበረ ወንጀል ነው" አሉ።

በዚህ ላይ ዳራኒይ እንዲህ ይላሉ፦ "ወንጀሎቻቸው በመቅለላቸው የተነሳ ቅጣት ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣባቸው ያውቃሉ። የኔና ያንተ ወንጀል ግን በመብዛቱ የተነሳ ቅጣት ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣብን አናውቅም።"

[ሒልየቱል አውሊያእ፡ 2/271]

በዚህ ዘመን መከራ የበዛብን ያለ ምክንያት አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Nov, 19:07


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣9️⃣1️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 634፣ ሐዲሥ ቁ. 1851
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Nov, 15:03


ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ደርሱ የሚተላለፈው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ነው:-

https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Nov, 12:25


ከዝሙት ራሳችሁን ጠብቁ። ለዚህ ደግሞ ለቻለ ሰው ከትዳር የበለጠ ምርጫ የለም። ለትዳር ቅድመ ሁኔታ አትደርድሩ። መስፈርት የሚያበዛ መጨረሻው አያምርም። ከትዳር ሸሽታችሁ ዝሙት ላይ እንዳትወድቁ። ዝሙት በየትኛውም ዘመን ሰቅጣጭ ወንጀል ነው። በዚህ ዘመን ግን አደጋው ጨምሯል። በአንዱ ባለ ጌ ወንጀላችሁ በቪዲዮ ተሰራጭቶ ጭራሽ ከማትወጡበት ማጥ ውስጥ ይከታችኋል።

ሴቶች እየተሰማ ያለው ደስ የሚል ነገር አይደለም። አግቡ። እንዲሳካላችሁ ዱዓ አድርጉ። ስነ ምግባር ያለው ካገኛችሁ ሁለተኛም፣ ሶስተኛም፣ አራተኛም ቢሆን ሆናችሁ አግቡ። ሊተናነቃችሁ ይችላል። ይሄ ተፈጥሯዊ ስለሆነ ስሜቱ ለመረዳት የሚከብድ አይደለም። ይበልጥ መፍራትና መጥላት የሚገባው ግን ዝሙትን ነው።

ወንዶች አላህን ፍሩ። ከዝሙት ራቁ። ከቻላችሁ አግብታችሁ ተሰተሩ። ዝሙት ብድር ነው። ባላሰባችሁ አቅጣጫ እዳውን ትከፍላላችሁ። ደግሞም ለትዳር ዋጋ ስጡ። ለሴቶች ፈተና እየሆናችሁ ወደ ወንጀል አትግፉ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Nov, 08:00


ድርጅት አቋቁሙ
~
ለመስጂድ ማሰሪያ፣ የተቸገሩን ለመርዳት ከበጎ ፈቃደኞች ገንዘብ መሰብሰብና ማስተባበር በቁርኣንና በሐዲሥ መሰረት ያለው ትልቅ ኸይር ነው። ይሄ በተቋም ደረጃም ይፈፀም፣ በግለሰብ ደረጃም ይፈፀም የሚደነቅ እንጂ የሚወገዝ ተግባር አይደለም። እንዲያውም ቁርኣን ውስጥ ደካሞችን በማገዝ ላይ አላማነሳሳት ነው የከሃዲዎች ተግባር እንደሆነ ተወግዞ የምናገኘው። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ أَرَءَیۡتَ ٱلَّذِی یُكَذِّبُ بِٱلدِّینِ (1) فَذَ ٰ⁠لِكَ ٱلَّذِی یَدُعُّ ٱلۡیَتِیمَ (2) وَلَا یَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِینِ (3) }
"ያንን በምርመራው የሚያስተባብለውን አየህን? (ዐወቅከውን?) ይህም ያ የቲምን በኀይል የሚገፈትረው፤ ድሃንም በማብላት ላይ የማያግባባው ሰው ነው።" [አልማዑን፡ 1-3]

ነብያችንም ﷺ በተደጋጋሚ ሰዎችን ለሶደቃ አነሳስተዋል። በዒድ ቀን ሴቶችን ለሶደቃ ቀስቅሰዋል። መስጂድ ላይ ከሙዶር ጎሳ ለሆኑ ችግረኞች እርዳታ ሰብስበዋል።

ስለዚህ በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትን ልመና ላይ ተሰማርተዋል እያሉ ማንቋሸሽ በማንም ቢነሳ ተቀባይነት የሌለው ትችት ነው። "ረቢዕ እንዲህ ብለዋል"፣ "ሙቅቢል እንዲህ ብለዋል"፣ "ሙሐመድ ብኑ ሃዲ እንዲህ ብለዋል" እያዩ የተንጓለሉ ጥቅሶችን ማራገብ አጉል ጭፍን ተከታይነት ነው።
1ኛ፦ የነሱን ንግግር ባልተገባ መልኩ ከኸይር ስራ ማሰናከያ እያደረጉ መመንዘር አይገባም።
2ኛ፦ ከከልካዮቹ በዒልምም በብዛትም የሚልቁ ዓሊሞች ፈተዋዎች እጅግ ብዙ ናቸው።
3ኛ፦ ከምንም በላይ የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃ ያለው ከሚፈቅዱት ጋር ነው። ለኸይር ስራ እርዳታ ማሰባሰብን የሚነቅፍ አንድም መረጃ የለም።
አለኝ የሚል ካለ በአደብ ማቅረብ ይችላል። ከነጥብ ከወጣ፣ ከአደብ ካፈነገጠ አስወግዳለሁ።

ተግባሩ ላይ የተሰማሩት እምነት የማይጣልባቸው መሆናቸው ከተረጋገጠ ያኔ ለይተን እንናገራለን። ሂደቱ ላይ ስህተት ከታየም እንዲሁ ነጥሎ ስህተቱን ብቻ ለማረም መሞከር ነው። እንጂ በደፈናው እያወገዙ ደካሞች የሚታገዙበትን ስራ ማሰናከል የተሳሳተ አካሄድ ነው።

የሚገርመው እንዲህ አይነቱን ተግባር ልመና እያሉ የሚያጣጥሉ አካላት ራሳቸው የተቸገረን ለመርዳት፣ መስጂድ ለመገንባት፣ የራሳቸውን ቡድናዊ ተግባር ለመፈፀም ሲሆን ልመና ላይ የሚሰማሩ መሆናቸው ነው። ለምን? የሚወገዘው ተግባሩ ሳይሆን አተገባበሩ ከሆነ በጅምላ እያወገዝክ የተዛባ መልእክት አታስተላልፍ። የሚወገዘው ተግባሩ ሳይሆን እንደ ፈፃሚዎቹ ማንነት ሑክሙ የሚለያይ ከሆነ ይሄ ዲን ሳይሆን ቡድንተኝነት ነው።

ለማንኛውም ፕሮጀክት መቅረፅ፣ ፈንድ ማሰባሰብ የምትችሉ አቅሙ ያላችሁ ወገኖች ድርጅት እየከፈታችሁ አካባቢያችሁን አግዙ። ወገናችሁን እርዱ። መስጂዶችን ስሩ። መሻይኾችን አቋቁሙ። የቲሞችን አልብሱ። ትምህርት ቤት፣ ሃኪም ቤት ስሩ። ውሃ አውጡ። በጦርነት ወይም በሌላ ምክንያት ህይወታቸው የተመሰቃቀለባቸውን ወገኖች በምትችሉት ከጎናቸው ቁሙ። እነዚን ስራዎች እየሰሩ ነው እምነት የሚያስቀይሩ ሚሺነሪዎች ወገኖቻችን ላይ እየዘመቱ ያሉት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

07 Nov, 03:42


ሁላችን ጉዞ ላይ ነን፣ ወደ ኣኺራ!
ሟቾች እንደሆንን ሁላችንም በርግጠኝነት እናውቃለን። የማናውቀው የቀጠሮውን ቀን ነው።

ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦

"ሁሉም ይጓዛታል - ያቺን የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን - ያለው ስንቁን ይዞ።"
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

05 Nov, 16:28


የጉልቻ መቀያየር ወጥ አያጣፍጥም
~
የአሜሪካ ምርጫ የጉልቻ ምርጫ ነው። ከሙስሊሞች ጋር በተያያዘ የሃገሪቷ መሰረታዊ ችግር ከፖለቲካዊ ስሪቷ ጋር የተያያዘ ነው። ማንም ቢመጣ ማንም ቢሄድ በተለይ ለሙስሊሞች የተለየ የሚጠበቅ የጎላ ለውጥ የለም። አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካላት ፈርጣማ ክንድ ጋር ሲታይ በሃገሪቱ ጠንካራ መደላድል ያለው የአይ ሁድ ሎቢ እና ፅንፈኛ ፀረ ኢስላም አቋም የሚያራምደው የፅዮናዊ ክርስቲያን ፖለቲካ ባለበት ተጨባጭ ቢያንስ በቅርብ ጊዜ ሙስሊሞች የተስፋ ጭላንጭል እንዳይጠብቁ የሚያደርግ በቂ መነሻ አለ።

በእጩዎች ባህሪና አካሄድ የሚኖረው ልዩነት እንደ ሙስሊም ካየነው ዘላቂ ለውጦችን የሚያስጠብቅ አይደለም። ትራምፕ ፀረ ኢስላም አቋሙ ፍጥጥ ያለ ነው። አፍሪካን ይፀየፋል። ስደተኛን ይጠላል። ለእስራኤል ያለው ውግንና መረን የለቀቀ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ከሶሪያ የተነጠቀውን የጎላን ኮረብታ ለእስራኤል እውቅና የሰጠው ትራምፕ ነው። እየሩሳሌምን በዋና ከተማነት ይሁንታ የሰጠው እሱው ነው። ልዩነቱ እስካሁን በታየው መሸፋፈን አያውቅም።

ዲሞክራቶች ከስነ ፆታ፣ ከግብረ ሰዶማውያን፣ ... ጋር ያላቸው አቋም ለአሜሪካ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ጭምር የሚያሰጉ ከሞራልና ከሰዋዊነት ያፈነገጡ ናቸው። ፍልስጤማውያን ላይ ይህ ሁሉ እልቂትና ውድመት የደረሰውና እየደረሰ ያለው በነሱ አስተዳደር ነው። ብዙዎች ጮቤ የረገጡለት ኦባማ ዘመኑ ለሙስሊሞች የውድመት ዘመን ነበር።

እና ከማንና ከማን ነው የሚመረጠው? ምናልባት ከአቡ ጀህልና ከአቡ ለሀብ ሊሆን ይችላል። የአሜሪካ ምርጫ ትርጉም ካለው ለሩሲያና ለቻይና ነው። ለሙስሊሞች ግን ለውጡ የጉልቻ እንደሆነ በተደጋጋሚ አይተናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

05 Nov, 11:15


ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

05 Nov, 07:06


📢ዘሕጉስ ዜና
🔻🔻🔻🔻
መርክርዝ ኣል-ኣልኢኽላስ ንክልተ ዓመት ሓደርቲ  ቁርኣን ሒፍዚን መሰረታዊ ሸሪዓዊ ፍልጠትን ንምምሃር ምድላዋት ዛዚሙ::

🌐 ቴሌግራም ቻናል
      👇👇👇
https://t.me/alikhlasislamiccenter

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

04 Nov, 13:51


ኒካሕና ቃዲ
~
እንደሚታወቀው በኢስላም የትኛዋም ሴት ያለ ወሊይ ፈፅሞ ልታገባ አይፈቅድላትም። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ
"ያለ ወሊዩዋ ይሁንታ የተገባች የትኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው!" [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

ወሊይ ከሌለስ? በዚህን ጊዜ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ስለዚህ ኒካሕ ለማሰር ቃዲ የሚያስፈልገው ወሊይ ለሌላት ሴት ነው ማለት ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
َ (فالسلطان ولي من لا ولي له)
"አስተዳዳሪ ወሊይ ለሌለው ወሊይ ነው።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል]

በተጨማሪም ወሊዮች ያለ ተጨባጭ ምክንያት ለመዳር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ከቀሩ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ከዚህ ውጭ አባት ወይም ሌላ ወሊይ ወይም ወኪል ካለ ኒካሑን የሚያስሩት እነሱ እንጂ ቃዲዎች አይደሉም። ወሊይ ወይም ወኪሉ "ሰጥቻለሁ" ካለ፣ አግቢው ወይም ተወካዩ "ተቀብያለሁ" ካለ ኒካሕ ታስሯል። ኹጥባውን (ሸርጥ ካለመሆኑም ጋር) ወሊይ ወይም ሌላ ቦታው ላይ የተገኘ ሰው ሊያደርገው ይችላል።

ኒካሕ ለማሰር የተለየ ውስብስብ መስፈርት የለም። የዐረብኛ ቃላት መጠቀምም አይጠበቅም። መስፈርቶች እስከተሟሉ ድረስ በየትኛውም ቋንቋ ቢሆን መስጠትና መቀበል ከተገኘ ኒካሕ ታስሯል። ስለዚህ በሃገራችን በሰፊው እንደሚደረገው ወሊይ እያለ ቃዲ መጥራት አይጠበቅም። ቃዲዎች ወሊይ ባለበት ሁኔታ ኒካሕ ለማሰር አትቀደሙ። ያለ ስልጣናችሁ ጣልቃ አትግቡ።

ወሊይ የሆናችሁ ሰዎች ደግሞ ቃዲዎችን ለሰርግ ከጠራችሁ እንደማንኛውም እድምተኛ ተስተናግደው ይመለሱ እንጂ እዚያው ተቀምጣችሁ ለነሱ ውክልና አትስጡ። "ልጄን እከሊትን ድሬሃለሁ" ማለት ያቅታችኋል? ምንም የተለየ የተቀመጠ ቃል የለምኮ። እሱም "ተቀብያለሁ" ካለ፣ ቦታው ላይ ሁለት ታማኝ ምስክሮች ከኖሩ ኒካሑ ታስሯል አለቀ። ባገር እያለህ፣ ዐቅልህ ጤነኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ከፊትህ ለሚፈፀም ጉዳይ ውክልና ትሰጣለህ? ምንም የሚያስፈራ ነገር የለምና እራስህ ፈፅመው። ሁሉም ነገር በቃዲ በኩል እንዲያልፍ መደረጉ አንዳንድ መረን የለቀቁ ባለስልጣናት በማያገባቸው የእምነታችን ጉዳይ ጣልቃ እንዲገቡ በር እየከፈተ ነው። አንዳንድ ቃዲዎችም ጉዳዩን ያላግባብ የሚጠቀሙበት ሁኔታ አለ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

04 Nov, 05:27


መህዲ ተብሎ በሚጠራው በዐባሲያው ኸሊፋ ዘመን አንድ ሰው ነብይ ነኝ ብሎ ተነሳ። ወታደሮች አሰሩትና ኸሊፋው ዘንድ አቀረቡት።
* ኸሊፋው፦ "አንተ ነብይ ነህ?" ብሎ ጠየቀው።
- "አዎ" አለ ሰውየው።
* ኸሊፋው፦ "ወደ ማን ነው የተላክከው?" አለው።
- ሰውየው፦ "ወደ ማንስ እንድላክ መቼ ፋታ ሰጡኝ። ረፋድ ላይ ተልኬ ከሰዓት በኋላ አሰሩኝ።

[ረቢዑል አብራር፣ አልባቡ ታሲዕ]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

04 Nov, 04:15


ዐብዱልከሪም አልኹዶይር እንዲህ ይላሉ፦
"ሱናዎችን መተው ግዴታዎቹን ለመተው እንደሚያጋልጥ ጥርጥር የለም። ይሄ በተግባር የተረጋገጠ ነው።"
[ሸርሑ መንሲኪ ሸይኺል ኢስላም፡ 205]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Nov, 14:14


በኢስላም እና በሙስሊሞች ላይ በደል ሲፈፀም ጉዳዩን የምትይዝበት አያያዝ የአጥፊውን ዘር እና አካባቢ እያየህ አይሁን። ጠላት ወላጅህም ቢሆን ጠላት ነው። ሚዛንህ ኢስላም ብቻ ይሁን። እወቅ! አቡ ለሀብ የነብዩ ﷺ አጎት ነበር። ለኢስላም ጠላት ሲሆን ግን ቅርበቱ አልጠቀመውም። እነ ቢላል እና እነ ሰልማን ዐረቦች አልነበሩም። በኢማናቸው የተነሳ ግን ነብዩ ﷺ ዘንድ የላቀ ቦታ ነበር የነበራቸው። ሁሌም ከዘርህ በላይ ኢስላምህን አስቀድም። ከኢማን ዘርን እያስቀደምክ ራስህን አታቅልል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Nov, 13:13


አንዱ ደግ ሰው እንዲህ ይላል፦
* "በስራ ከተማ ስገባ ገበያዎቹ ተዘግተዋል። መንገዶቹ ባዶ ናቸው። 'የበስራ ሰዎች ሆይ! እኔ የማላውቀው ዒድ አላችሁ እንዴ?' አልኩኝ።
- ' እንደሱ አይደለም። ነገር ግን ሐሰኑል በስሪይ መስጂድ ውስጥ ሰዎችን እያስተማረ ስለሆነ ነው' አሉኝ።"
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Nov, 11:36


በሰማነው መጠቀምና መስራት

ሑዘይፋ መስጂድ የቀረበ ሙሓደራ

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔗 t.me/Achachir_mkroch

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Nov, 10:25


https://t.me/Abuzekeriya01

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

03 Nov, 03:24


ሶሐቦች ምን ያክል የሙስሊሞች ዐቂዳ ያሳስባቸው ነበር?
~
እነዚያ የኢስላም አንበሶች፣ የነብዩ ﷺ ድንቅ አጋሮች የሙስሊሞችን ዐቂዳ ለመጠበቅ የሚችሉትን መስዋእትነት ሁሉ ከፍለዋል። ለዚህ ማስረጃ አንድ ታሪክ እንመልከት። አቡል ዓሊያህ እንዲህ ይላሉ፡ “የቱስተር ከተማን በከፈትን ጊዜ በሁርሙዛን ግምጃ ቤት ውስጥ አስከሬን ያለበት አልጋ አገኘን። … አስራ ሶስት የተራራቁ ቀብሮችን በቀን ቆፈርንና (ከአንዱ) ውስጥ በሌሊት ቀበርነው። ከዚያም ሰዎች እንዳያወጡት በመስጋት እንዳይለይ አድርገን ቀብሮቹን ሁሉንም (በተመሳሳይ ከመሬት) አስተካከልናቸው።”
“ከሱ ምን ይፈልጋሉ?” ተብለው ሲጠየቁ “ድርቅ ሲሆንባቸው አልጋውን ይዘውት ይወጡና ዝናብ ይለምኑበታል” አሉ አቡል ዓሊያህ።
“ሰውየው ማነው ብላችሁ ትገምታላችሁ?” ሲባሉ “ዳንኤል የሚባል ነው” አሉ። “ስታገኙት ከሞተ ምን ያክል ሆኖታል?” ሲሏቸው “ሶስት መቶ አመት ሆኖታል” አሉ።
“ከሱ ምን የተቀየረ አለው?” ሲሏቸው “ከማጅራቱ አካባቢ ጥቂት ፀጉሮች እንጂ የተቀየረ የለም። የነብያትን ስጋ'ኮ አፈር አይበላውም” አሉ። [አልመጋዚ፣ ኢብኑ ኢስሓቅ፡ 6]

ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ ከዚህ ታሪክ ስር እንዲህ ይላሉ፡-
“በዚህ ታሪክ ውስጥ ሙሃጂሮችና አንሷሮች የፈፀሙት ሰዎች እንዳይፈተኑበት ቀብሩን እንዳይለይ ማድረግ ነው እንጂ እሱ ዘንድ ዱዓእ እንዲደረግና በረካ እንዲፈልጉበት ግልፅ ማድረግ አይደለም። ዘግይተው የመጡት ሰዎች ቢያገኙት ኖሮ ለሱ ሲሉ በሰይፍ ይሞሻለቁ ነበር። ከአላህ ውጭም ያመልኩት ነበር። በርግጥም ከዚህ ጋር የማይነፃፀሩና የማይቀራረቡ መቃብሮችን ጣኦቶች አድርገው ይዘዋል። አገልጋዮች መድበውላቸዋል። ከመስጂዶች የበለጡ የአምልኮት ቦታዎችም አድርገዋቸዋል።

መቃብር ዘንድ ዱዓእ ማድረግ፣ እዚያም ሶላት መስገድ፣ በነሱም በረከትን መሻት ትሩፋት ቢኖረው ኖሮ ወይም ሱና ቢሆን ኖሮ ወይም የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ ሙሃጂሮችና አንሷሮች ይህን ቀብር ለእንዲህ አይነት ተግባር ተምሳሌት ያደርጉት ነበር። እሱም ዘንድ ዱዓእ ያደርጉ ነበር። ከኋላቸው ለሚመጣ ትውልድም ፍኖት ያደርጉት ነበር። ነገር ግን ከኋላቸው ከመጡ ክፉ ምትኮች በተሻለ አላህን፣ መልእክተኛውንና ሃይማኖቱን የሚያውቁ ነበሩ። እነሱን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮችም እንደዚያው በዚሁ መንገድ ላይ ነው የተጓዙት። እነሱ በብዛት እያሉ ከነሱ ዘንድ የሶሐቦች መቃብር በየሀገራቱ በብዛት ነበር። ከነሱ አንድም ከሶሐቦች ቀብር ዘንድ ሄዶ እርዳታ የጠየቀ፣ እሱንም የለመነ፣ በሱም የተመጀነ፣ በሱ ፈውስን፣ ዝናብን፣ እገዛን የጠየቀ የለም።” [ኢጋሠቱል ለህፋን፡ 1/202-203]

ከዚያ በኋላ ግን ሺርክን ያነገሱ፣ ተውሒድን ያኮሰሱ፣ ቃላቸውን ያፈረሱ፣ ስሜታቸው ጋር የሚፈሱ ክፉ ምትኮች ተተኩ። የሶሐቦችን ግንዛቤ ተመልከቱ። ከዚያም የኛን ዘመን ትውልድ ታዘቡ። የዛሬ ቀብር አምላኪዎችስ ከቀብር ዘንድ ሲቆሙ ማንን ነው የሚያስቡት? የነብዩ ﷺ አስተምህሮት ለእንዲህ አይነት የጣኦት ስርኣት ሰይፍ ነበር፣ የተሰላ ሰይፍ! አቡ ዋቂድ አለይሢይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡-

“ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ጋር ወደ ሑነይን ወጣን። ከክህ ደት ከወጣን ቅርብ ጊዜያችን ነበር። (አዲስ ሰለምቴዎች ነን።) በአንዲት የቁርቁራ ዛፍ አጠገብ አለፍን። ከዚያም ‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለኛም ይቺን መስቀያ አድርግልን፣ ለሙሽሪኮቹ መስቀያ እንዳለቻቸው’ አልን። ነብዩ ﷺ 'አላሁ አክበር! ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! የኢስራኢል ልጆች ለሙሳ፡ 'ለነሱ (ለሙሽሪኮቹ) አማልክት እንዳሏቸው ለኛም አምላክ አድርግልን' ያሉት አይነት ነው የተናገራችሁት!' እሱም፡ 'እናንተ የማታውቁ ህዝቦች ናችሁ' ብሏቸዋል። በውኑ ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ዱካዎች ትከተላላችሁ!' አሉ።” [ዚላሉል ጀናህ፡ 1/31]

አቡ በክር አጦርጡሺይ ከዚህ ሐዲስ ስር እንዲህ ይላሉ፡- “ተመልከቱ እንግዲህ አላህ ይዘንላችሁና። የትም ቦታ ሰዎች የሚያስቧት፣ የሚያከብሯት፣ ፈውስና መድሃኒትነትን የሚያስቧት፣ ሚስማሮችና ቁርጥራጭ ጨርቆች የሚሰቅሉባት ቁርቁራ ወይም ሌላ ዛፍ ካገኛችሁ ዛቱ አንዋጥ ናትና ቁረጧት!” [አልሐዋዲሥ ወልቢደዕ፡ 38] በሌሎች ሀገራት እንደሚገኘው በሀገራችንም የስለት ክር የሚተበተብባቸው፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ ለበረካ ታስቦ አላፊ አግዳሚ የሚያርፍባቸው፣ ለዱዓእ የሚሰባሰቡባቸው፣ እርድ የሚፈፀምባቸው በርካታ ዛፎች - ዛቱ አንዋጦች - ዛሬም ድረስ አሉ።

ዛሬ እንኳን ሰለጠነ በሚባለው አለም የጣኦት አምልኮ “ላኢላሀ ኢለላህ” በሚሉ ሰዎች መሀል እግሩን ዘርግቶ ይገኛል። “የእናቴ ጀበና አተረፈኝ” እያለ የማይረባ ሸክላ የሚያመልክ ትውልድ ዛሬም ከውስጣችን ይገኛል። በሀገራችን በተለይም ወደ ገጠሩ አካባቢ የተጓዘ እጅግ ብዙ የሚመለኩ ዛፎችን፣ ድንጋዮችን፣ መቃብሮችን ወዘተ በየአካባቢው ያገኛል። እነኚህን ነገሮች የሚስም፣ የሚሳለም፣ የሚተሻሽ፣ ቅቤ የሚቀባ፣ ስለት የሚያስር፣ እርድ የሚያርድ፣ ምንነቱን በውል ከማያውቀው ቦታ ላይ ጠጠር እየወረወረ ድንጋይ የሚከምር ... መአት ነው። ይህንን ኮተት እስከ ደም ጠብታ ልንዋጋው ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Nov, 11:27


ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር
~
ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ፡

- “እኛ ዘንድ ሱፊያ የሚባሉ ሰዎች አሉ፡፡ በብዛት ይበሉና ከዚያ ያንጎራጉራሉ፡፡ ከዚያም ተነስተው ይጨፍራሉ” ተብለው ተጠየቁ።
* “ህፃናት ናቸው?” አሉ።
- “አይደሉም” አሏቸው፡፡
* “እብዶች ናቸው?” ብለው ጠየቁ።
- “አይደሉም፣ ሸይኾች ናቸው” አሏቸው፡፡
* ኢማሙ ማሊክ:– "እኔ ከኢስላም ሰዎች ይህን የሚሰራ አንድም አልሰማሁም” አሉ።
[ተርቲቡል መዳሪክ: 2/53]

እንዲህ አይነቶቹ "ወሃቢያ" እያሉ ሊያንቋሽሹ ሲሞክሩ አስቡት እንግዲህ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Nov, 05:11


ለወላጆች ሁነኛ ሶደቃ
~
ለሞቱ ወላጆችዎ ሶደቃ መፈፀም ይፈልጋሉ? አቅሙ ላለው ሰው የውሃ ችግር ባለበት አካባቢ ውሃ ማውጣት ትልቅ ሶደቃ ነው። አገልግሎቱ እስካለ ድረስ አጅሩ አይቋረጥም።
* ሰዕድ ብኑ ዑባደህ ረዲየሏሁ ዐንሁ - "እናቴ ሞተች። ሶደቃ ልፈፅምላት?" ብለው ነብዩን ﷺ ጠየቁ።
- እሳቸውም "አዎ" አሉ።
* "የትኛው ሶደቃ ነው በላጩ?" አሉ ሰዕድ።
- "ውሃ ማጠጣት" አሉ ነብዩ ﷺ።

[ሶሒሑ ነሳኢይ፡ 3668]
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Nov, 04:15


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣8️⃣9️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 630፣ ሐዲሥ ቁ. 1833
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

02 Nov, 04:00


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣8️⃣9️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 624፣ ሐዲሥ ቁ. 1814
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Nov, 16:36


Live stream finished (1 hour)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Nov, 15:32


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Nov, 15:05


ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ። ደርሱ የሚተላለፈው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ነው:-

https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Nov, 11:53


የቀብር ዚያራ - የረሳነው ሱና
~
የቀብር ዚያራ ብዙ ፋይዳዎች አሉት።
1- ነብያችን ﷺ "ኣኺራን ያስታውሳል" ብለዋል። [ቲርሚዚይ፡ 1054] ከዱንያ ወከባና ግርግር ወጥተን ስለ ኣኺራችን እንድናስብ ያስታውሳል።
2- ሞትን ያስታውሳል። የምናውቃቸውን ሰዎች ቀብር ስናይ ድንገት የኛም ተራ መጥቶ እንደምንከተላቸው ያስታውሰናል።
3- የነብዩን ﷺ ሱና መፈፀም ነው።
4- ለሞቱ ወገኖቻችን ዱዓእ እናደርግበታለን። ለራሳችንም እንዲሁ።
5- ኣኺራን እና ሞትን ማስታወስ ምን ፋይዳ አለው? ከሐራም እና ከበደል እንድንታቀብ፣ ከወንጀል ተውበት እንድናደርግ፣ ኸይር ስራ ላይ እንድንሳተፍ ያነሳሳናል።

እና ልባችን ሲደርቅ፣ በዱንያ ጣጣ ስምጥ ስንል፣ መዘናጋት ስናበዛ ወደ መቃብር እንሂድ።
السَّلَامُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الدِّيَارِ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ، وَالْمُسْلِمِينَ، وَإِنَّا إِنْ شَاءَ اللَّهُ لَلَاحِقُونَ، أَسْأَلُ اللَّهَ لَنَا وَلَكُمُ الْعَافِيَةَ
እንበል። አላህ እንዲምራቸው ዱዓእ እናድርግላቸው። በዱዓችን ላይ እጆችን ማንሳት ይቻላል። [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 974]

ቀብር እንዳንረግጥ እንጠንቀቅ። መቃብር ውስጥ መፀዳዳትም ወንጀል ነው። በመቃብር መሀል ስንንቀሳቀስ ጫማዎቻችንን ብናወልቅ መልካም ነው። ለዚያራ ሂደን ከዚያ በዛዛታ መጠመድ አይገባም።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Nov, 06:35


የደዕዋ ማስታወቂያ
~
የፊታችን እሁድ ጥቅምት 24/ 2017 ከየሺ ደበሌ ከፍ ብሎ በሚገኘው ሑዘይፋ መስጂድ የደዕዋ ፕሮግራም ይኖራል። ቆይታችሁ ከኛ ጋር ይሁን

1- ኸዲር አሕመድ ከሚሴ
2- ዐብዱልፈታሕ ጀማል
3- ሙሐመድ ሲራጅ
4- አቡል ዐባስ
5- ሳዳት ከማል

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

01 Nov, 04:48


ጁሙዐ ይለያል!
~
ጁሙዐ ከሳምንቱ ቀናት የተለየ እንደሆነ የሚያሳዩ ብዙ ነጥቦች አሉ። ለምሳሌ ያህል:-

1- ጁሙዐ የሳምንቱ ቀናት አይነታ ነው። ከሁሉም በላጭ የሆነ ቀን ነው፣ ሳምንታዊ ዒድ።
2- ጁሙዐ አደም የተፈጠሩበት እና የሞቱበት የዓለም ፍፃሜ የሚሆንበትም ቀን ነው።
3- አላህ ዘንድ ከሶላት ሁሉ በላጩ የጁሙዐ እለት በጀማዐ የተሰገደ የሱብሕ ሶላት ነው። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 1119]
4- ጁሙዐ የጠነከረ ትእዛዝና ማሳሰቢያ የመጣበት ልዩ የሆነችዋ የጁሙዐ ሶላት የሚሰገድበት ቀን ነው።
5- ሳምንታዊ ኹጥባ የሚገኝበት ቀን ነው። ኹጥባውን በፀጥታ ማዳመጥም ግዴታ ነው።
6- ገላን በመታጠብ ትእዛዝ የመጣበት ቀን ነው።
7- ሽቶ መቀባት፣ መፋቂያ መጠቀም ይወደዳል።
8- ያማረ ልብስ መልበሱ ይወደዳል።
9- ጁሙዐ ግዴታ ለሆነበት ሰው የሶላት ወቅት ከገባ በኋላ ጁሙዐን ሳይሰግዱ መንገድ መውጣት አይፈቀድም።
10- ጀሀነም በየ እለቱ ትቀጣጠላለች፣ ጁሙዐ ቀን ሲቀር።
11- ጁሙዐ ቀን አላህ ዱዓእን ከሌሎች ጊዜያት በተለየ የሚቀበልባትን ሰዓት የያዘ ቀን ነው።
12- ጁሙዐ ቀን ሱረቱል ከህፍ መቅራት የሚወደድበት ቀን ነው።
13- ጁሙዐ ቀን በነብዩ ﷺ ላይ ሶላት ማብዛት የሚወደድበት ቀን ነው።
14- ጁሙዐ ቀን ሱብሕ ሶላት ላይ ነብያችን ﷺ ሱረቱ ሰጅደህ እና ሱረቱል ኢንሳንን ይቀሩ ነበር።
15- የጁሙዐ ቀን ወይም ሌሊት የሞተ ሰው አላህ ከቀብር ፈተና ይጠብቀዋል። [ቲርሚዚይ፡ 1074]
16- ጁሙዐ ለወንጀሎች ምህረት የሚገኝበት ቀን ነው።
17- የጁሙዐ ቀን በፆም፣ ሌሊቱን በሶላት መለየት የተከለከለ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Oct, 18:13


ስትንቅ ትናቃለህ!
~
"ኩራተኛ ልክ የተራራ ጫፍ ላይ እንዳለ ሰው ነው። ሰዎችን ቁልቁል ሲያይ ትንንሽ ሆነው ይታዩታል። ግና እሱም ለሰዎች ትንሽ ሆኖ ነው የሚታየው።"

የተተረጎመ
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Oct, 16:31


Live stream finished (58 minutes)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

31 Oct, 15:33


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Oct, 15:00


እራስን መመልከት
~
እየውልህ ወንድሜ! ህሊና አልባ በድን ማሽን አትሁን። የምትገባው ከራስህ እንጂ ከኡስታዝህ ቀብር አይደለም። ሲራጥን የምትሻገረው በራስህ ስራ መጠን እንጂ ኡስታዝህ እጅህን ይዞ አያሻግርህም። ያለ አስተርጓሚ ራቁትህን ከጌታህ ፊት ለምርመራ ስትቆምም ኡስታዝህ ከጎንህ አይቆምልህም። ይህንን ሁሉ የምልህ ማንንም በጭፍን እንዳትከተል ነው። በአሁኑ ሰዓት በየሰፈሩ ያሉ ሸይኾችና ኡስታዞች አብይ መታወቂያ ጭፍንነትን ሥራዬ ብለው የሚግቱ፣ ተማሪዎቻቸውን በጭፍንነት የሚኮተኩቱ መሆናቸው ነው። የወደዱትን በጭፍን እንድትወድላቸው፣ የጠሉትን በጭፍን እንድትጠላላቸው እስከ ደም ጠብታ ይታገሉሃል። ቁርኣን፣ ሐዲሥ፣ የዑለማእ ንግግር ተንኮለኛ በሆነ መልኩ ከአውድ ውጭ እያገናኙ የሃሳብ ሽብር ይነዙብሃል። እዚህ ላይ "ለምሳሌ እነ እንትናን ብንወስድ… " ብዬ ባጣቅስ የእነ እንትና ጭፍራ ጦር ሰብቆ ይነሳል። ከነሱ ውጭ ያለው ደግሞ በአመዛኙ ይደግፋል። እውነት ለመናገር ግን ጣት መቀሰሩ ስለሚቀለን እንጂ ይሄ በሽታ ይብዛም ይነስም በየቤቱ ይገኛል። ችግራችን ግን አይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ ጥለን ከሌሎች አይን ያለን ጉድፍ ነው የምንመለከተው። የሌሎችን ጥፋት ለማጋለጥ እንረባረባለን። እሺ የራሳችንንስ ማን ያርመው? ለማነው የምንተወው? ኧረ ልባችን ፈቃጅ ተመልካች አጣ!! ድባቡ የተበከለ ሆኖ መገሳሰፅ አልቻልንም። እኛም ለራሳችን ተገቢውን ትኩረት አልሰጠንም። ግን እስከመቼ?
እና ወንድሜ ከማንም ጎጠኛ ቡድን ጋር ጭፍን ተሰላፊ አትሁን። ከዑለማእ ንግግር ውስጥ ከስሜቱ ጋር በሚገጥምለት መልኩ እየመረጠ የሚያቀርብ ሰው ስታይ በችኮላ እጅ አትስጥ። የትኛውም ቡድን ጋር የተሰለፈው ሁሉ ይህንን እያደረገ ነውና የሱ ከሌሎች በምን እንደሚለይ ረጋ ብለህ መርምር። የማይነቃነቅ ነባራዊ ሐቅ፣ የአህለ ሱና ዋና መታወቂያ አስመስሎ ያቀረበልህ ጉዳይ አብዛኞቹ ዑለማዎች ዘንድ ያለው አቋም እሱ ካወራህ ተቃራኒ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህና ከስሜት ነፃ ሆነህ በሚገባ ፈትሽ። ደግሞ ቆም ብለህ ታዘባቸው። ብዙዎቹ ቡድናዊነት የሰበሰባቸው አካላት:—
— "እነ እከሌ ጠርዘኞች ናቸው፣ ድንበር አላፊዎች ናቸው" እያለ ከፍ አድርጎ ያስተጋባል። የሚያስከነዱ ጠርዘኞችን ግን አቅፎ ያሽሞነሙናል። ምክንያቱም እነዚህኞቹ እሱ ሲስል የሚስሉ፣ ሲያነጥስ የሚያነጥሱ የገደል ማሚቶዎች ናቸውና።
— "እነ እከሌ ጃሂሎች ናቸው" ይልሃል። በምንም መመዘኛ ከነሱ የማይሻሉ ሰዎችን ግን በትልልቅ መድረክ ላይ ያስተዋውቃል። ምክንያቱ አቋማቸው ከአቋሙ ስለገጠመለት ብቻ ነው።
— "እነ እከሌ አቋም የሌላቸው ወላዋዮች ናቸው" ያለህ ስብስብ በየክስተቱ ባደባባይ የሚዋልሉ ሰዎችን ከጎናቸው አሰልፈው ታገኛቸዋለህ። ምክንያቱም መመዘኛው ርካሹ ቡድናዊ ሚዛን እንጂ ኢኽላስ አይደለምና።

ወንድሜ ሆይ! አላህን አስበህ ስለምትሰራው ነገር የማንንም ጭብጨባ አትጠብቅ። የማንም ተቃውሞም አይጠፍህ። ይልቅ ውስጥህን አዳምጥ፣ ኢኽላስህን ፈትሽ። ያለ ኢኽላስ ጩኸትህ የቁራ ጩኸት ነው። ልፋትህም ከንቱ ድካም። በደዕዋህ ቀዳሚው ትኩረትህ ሰፊው ህዝብ ይሁን። አትዘንጋ! ዛሬም አብዛኛው ወገናችን ከተውሒድ ግንዛቤ የራቀ ነው። ሺርክ ላይ የሚማቅቀው ብዙ ነው። ከባባድ አጥፊ ወንጀሎች ላይ እስከ አፍንጫው የተነከረው ቀላል አይደለም። ቀዳሚው ጥረትህ የዚህን ወገንህን ሸክም ለመቀነስ ይሁን። ይህንን መሰረታዊ ጉዳይ ገሸሽ በማድረግ ውሃ ቀጠነ፣ ከሰል ጠቆረ ብሎ ለሚነታረክ ጀርባህን ስጠው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም አረፋ ነው።
በኢኽላስ እስከሰራህ ድረስ የማንም ጫጫታ ቅስምህን አይስበረው። ሰዎች እንቅፋት ሲያበዙ አንተ ፅናትህን ጨምር። ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አትበል።
የሌሎችን ጩኸት ሳታጣራ የምታስተጋባ በቀቀን አትሁን። በጭፍን አትደግፍ። በጭፍን አትንቀፍ። እወቅ! እውር ጥላቻና እውር ውዴታ ነገ ከአላህ ፊት ያሳፍርሃል። ማንንም በእውር ድንብር አትከተል። ጭፍን ወገንተኝነት በቃላት ቢያሸበርቅም፣ በሱና፞ ስም ቢቀርብም የተወገዘ ነው። የአሳማ ስጋ በወርቅ ሰሀን ስለቀረበ አሳማነቱ አይቀየርም። አሳማ አሳማ ነው። የመዝሀብ ሰዎች ዘንድ የምናውቀው ጭፍን ወገንተኝነት ተቀባብቶ ተከሽኖ በሱና፞ ዑለማዎች ስም ሲቀርብ ማየት እየተለመደ መጥቷል። ይበልጥ የሚያሳፍረው ደግሞ አንዳንዶች በየሰፈሩ በየመንደሩ እየተቧደኑ ‘ወላእ’ እና ‘በራእ’ የሚቋጥሩባቸው አካላት መመደባቸው ነው።
ደግሞም በልክ እንሁን። በሌሎች ሃገራት ወይም አካባቢዎች ያየነውን ወይም የሰማነውን ኺላፍ ሁሉ ሰበብ እየፈለጉ እየጎተቱ ማምጣት ግልብነት ነው። ወላጆችህ ወገኖችህ በሺርክ እየተጨማለቁ አንተ በሸይኽ እንትናና በሸይኽ እከሌ መካከል ስለተፈጠረው ኺላፍ ጧት ማታ እያቦካህ በአካባቢህ ያሉ ዱዓቶችን ለመፈረጅ አድፍጠህ ብትጠባበቅ የፊትና ጥማትህን እንጂ ንቃትህን አያሳይም። በአካባቢህ ይሄ ነው የሚባል የደዕዋ ተሳትፎ ሳይኖርህ እንዳቅማቸው እየደከሙ ያሉ አካላትን ትንሽዬ ጥረት አይኗን ለማጥፋት ጦር ብትሰብቅ ጥሬነትህን ብቻ ነው የሚያሳየው። ወንድሜ ከቻልክ አግዝ። ክፍተት ካየህ አርም። አቅሙ ከሌለህ ባላቸው አስመክር። በምትችለው ከጎናቸው ቁም። ለሰፈርህ ለአካባቢህ የደዕዋ እንቅስቃሴ አጋዥ እንጂ አፍራሽ አትሁን። ለደዕዋ እንቅፋት በመሆን ሌሎች እንዳይለወጡ መሰናክል አትፍጠር። ሰዎች የሚተላለፉበት መንገድ ላይ አስቸጋሪ ነገሮችን መጣል ፀያፍ ጥፋት ነው። ወደ ኣኺራ በሚወስደው የደዕዋ መንገድ ላይ እንቅፋት መጣል ግን እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው። እንዲህ አይነቱን የወንጀል ሸክም የምትቋቋምበት ጫንቃው የለህምና ዛሬውኑ ሚናህን ለይ። ዛሬውኑ ለደዕዋ ያለህን አስተዋፅኦ ገምግም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 07/2013)
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Oct, 08:33


ጥሩ ያልሆኑ ኮመንቶች ሲገጥሙን ምን እናድርግ?
(የማህበራዊ መገናኛ አጠቃቀም - ክፍል 2)
~
አላህን በመፍራት በሸሪዐ መነፅር ለማየት እንሞክር።
1- እንዲሁ ለኛ ካለመጣሙ ውጭ እንከን ከሌለበት ስሜታችንን እንጫን። ሐቅ ከሆነ እንቀበል።
2- ከፊል ዑለማኦች የተጓዙበት ሆኖ ግን መርጁሕ ወይም ደካማ ሃሳብ ተሰንዝሮ ከሆነ ከቻልን እናስረዳ። ባለበት ብናልፈውም ችግር የለውም።
3- ኮመንቱ ወንጀል ከሆነ ሁለት ምርጫ አለን። አንድ ባግባቡ ማረም። አለያ ደግሞ ማስወገድ። ለእያንዳንዱ ጥፋት እርምት መስጠት ብዙዎች እንደሚያስቡት ቀላል አይደለም። ስለዚህ ለማረም ካልተቻለ ወይም ካልተመቸ ማስወገድ ነው። ወንጀልን ባለበት መተው ያስጠይቃል። ትንኮሳ ወይም ብልግና እየለቀለቀ ሲሰረዝበት ልክ ቁም ነገር እንደፃፈ ሰው "ሃሳብ ትፈራለህ!" "አድናቆት ብቻ ነው የምትፈልገው" ሊልህ ይችላል። እንዲህ አይነት ረብ የለሽ ማሸማቀቂያዎችን ቦታ የምንሰጥ ከሆነ "መጥፎን ነገር ያየ ሰው በእጁ ያስወግደው" የሚለውን ሐዲሥ እንጥሳለን። አካውንታችንን በአግባቡ መጠቀም ከመጥፎ ነገሮች ማፅዳት ይኖርብናል። አካውንታችን ሃሳብን በነፃነት ማንሸራሸር ይሉት የዲሞክራሲ እሴት መለማመጃ አይደለም። በተለይ ደግሞ አብዛኞቹ ጋጠ ወጥ አካሄድ ያላቸው ሰዎች ቤታቸውን ቆልፈው ነው ከሰው ቤት እየገቡ ቆሻሻ የሚደፉት። እነዚህን ጥፋታቸውን የሚደጋግሙ ከሆነ መሸኘት ይገባል። ዝም ስንል እነሱንም ወንጀል የሚፈፅሙበትን እድል መስጠት ነው። ራሳችንም ከነሱ ጋር ስንመላለስ ወንጀል ላይ እንወድቃለን። ሌሎችም ከነሱ ጋር ሲመላለሱ ጥፋት ላይ ሊወድቁ ይችላሉ። እነዚህን ነገሮች ማስቆም ስንችል መተው ወንጀል ሆኖ ያስጠይቀናል።

ወይም ደግሞ አካውንታችንን ከጓደኞች ውጭ ያሉ አካላት ሃሳብ እንዳይሰጡበት መዝጋት ነው። በርካታ ሰዎች አጉል ቃላትንና ንትርክን ሽሽት ቤታቸውን ጓደኛ ብቻ ሃሳብ መስጠት እንዲችል አድርገው ዘግተዋል። ይሄ አንድ ትክክለኛ አማራጭ ነው። ምናልባት ከዚህ ይልቅ የተሻለው ለሁሉም ክፍት ካደረጉ በኋላ አንዳንድ ልዩነት የተካረረባቸው ርእሶችን ስናነሳ ብቻ አጉል ንትርኮችን ለመቀነስ ያህል ለጓደኞች ብቻ ክፍት ማድረግ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

30 Oct, 04:26


ከሐጁሪ ጋር በተያያዘ
~
ሸይኽ የሕያ አልሐጁሪ የየመን ዓሊም ነው። በየመንም ውስጥ ከየመንም ውጭ ከብዙ ዓሊሞች ጋር አለመግባባት ውስጥ መግባቱ ይታወቃል። በዚህ የተነሳ ጠንካራ ውንጀላዎችን ተወራውረዋል። አንዳንዶቹ ሂሶች ታዲያ ልክ ያለፉ ናቸው። የሚታዩ ትችቶች ድንበር ማለፍ የለባቸውም ወይ? የሚለውን ማሰብ ራስን ከጥፋት ለመጠበቅ ይጠቅማል። ለሐጁሪ በመደገፍ ሌሎች ላይ ድንበር ማለፍ እንደማይገባ ሁሉ በሐጁሪም ላይ እንዲሁ በጥላቻ ድንበር ማለፍ አይገባም።
1- እንደተሳሳተ አምኖ የተመለሰባቸውን ጉዳዮች ለትችት ማንሳት ድንበር ማለፍ ነው። ይሄ በዚህ ዘመን ብዙዎች ላይ የሚታይ አስቀያሚ ባህሪ ነው። አንድን ሰው በተመለሰበት ጉዳይ መወንጀል የራስን ነውረኝነት ነው የሚያጋልጠው።
2- ፊቅሃዊ ስህተቶችን ወይም ልዩነቶችን የመንሀጅ ወይም የዐቂዳ ስህተት ያክል ማስጮህም ተገቢ አይደለም። በፊቅህ ጉዳይ ላይ ሌሎች ወገኖች ዘንድ ስህተት ተብሎ የሚቆጠር አቋም የሌለው ማን አለ?
3- በሌሎች ዓሊሞች ጭምር የሚስተጋቡ አቋሞችን ሐጁሪ ሲናገራቸው ጊዜ በተለየ ማራገብም ከሚዛናዊነት የራቀ አካሄድ ነው። በአንድ ጉዳይ የተለያየ መስፈሪያ መጠቀም አይገባም።
4- በግልፅ የዐቂዳ ጥመቶቻቸው የተነሳ ከአህለ ሱና አቋም እጅግ የራቁ ከሆኑ አንጃዎች በላይ ጥላቻ መደቀንም ሌላ ስህተት ነው።

ይህን ማለቴ የሚያስከፋቸው አልፎም ነገር በመጠምዘዝ ያልተባለውን እየለጠፉ የሚጮሁ ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህን ጉዳዮች በልክ መያዝ ራስን ነው የሚጠቅመው። በማንም ላይ ድንበር ልናልፍ አይገባም። በጥላቻም ይሁን በውዴታ ድንበር ማለፍ ራስን ነው የሚጎዳው።
በተረጋገጡ ጥፋቶች ወይም ስህተቶች ላይ እርምት መስጠት ያለና የነበረ ነው። ሐጁሪም ሆነ ሌላ የሚበልጥም የሚያንስም ማንም አካል ከሂስ በላይ አይደለም። ኢማሙ ማሊክ "ሁላችንም አራሚዎች እና ታራሚዎች ነን" ይላሉ።
አላህ ሐጁሪን ከክፉ ይጠብቀው። የሳተውን ያቃናው። ከዑለማኦች ጋርም ያግባባው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

29 Oct, 18:03


የሽብር ጉዳይ
~
ሽብር ለሁለት ይከፈላል። ጦረኛ ጠላትን ማሸበር እና ጦረኛ ያልሆኑ ሰላማዊ ሰዎችን ማሸበር። ጠላትን በጦር ሜዳ ማሸበር የሚቻል ብቻ ሳይሆን የሚገባ ተግባር ነው። መቼስ ጠላት እሹሩሩ አይባል ነገር። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَأَعِدُّوا۟ لَهُم مَّا ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن قُوَّةࣲ وَمِن رِّبَاطِ ٱلۡخَیۡلِ تُرۡهِبُونَ بِهِۦ عَدُوَّ ٱللَّهِ وَعَدُوَّكُمۡ وَءَاخَرِینَ مِن دُونِهِمۡ لَا تَعۡلَمُونَهُمُ ٱللَّهُ یَعۡلَمُهُمۡۚ وَمَا تُنفِقُوا۟ مِن شَیۡءࣲ فِی سَبِیلِ ٱللَّهِ یُوَفَّ إِلَیۡكُمۡ وَأَنتُمۡ لَا تُظۡلَمُونَ }
"ለእነሱም ከማንኛውም ኃይልና ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ አዘጋጁላቸው፤ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን፣ ሌሎችንም ከእነርሱ በቀር ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ የሚያውቃቸውን (መናፍቃን) የምታሸብሩበት ይሆን ዘንድ።" [አልአንፋል፡ 60]

ይሄ አንድ ነው። ሌላኛው ሽብር በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀም ሽብር ነው። ተዋጊ ያልሆኑ ሰላማዊ ሰዎችን ማሸበር ከኢስላም አስተምህሮት ጋር የሚቃረን ነው። ይሄ ተግባር በዚህ ዘመን በብዛት ይፈፀማል። ከግጭት ጋር ምንም ንክኪ የሌላቸው ሰዎችን በተለያየ መልኩ የጥቃት ኢላማ ማድረግ የተለመደ ነው። ይሄ የተሳሳተ አካሄድ ከመሆኑም ባሻገር ለሙስሊሞች ብዙ መከራ ያመጣና እያመጣ ያለ ነው።
* ሽብርን ለመከላከል በሚል የደዕዋ እንቅስቃሴዎች ብዙ ጋሬጣ ገጥሟቸዋል።
* እጅግ በርካታ ኢስላማዊ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሽብርን ያግዛሉ በሚል ማመሀኛ ተዘግተዋል።
* በግለሰቦችም ይሁን በተቋማት በኩል የሚደረጉ የሙስሊሞች የገንዘብ ዝውውሮች መሰናክል በዝቶባቸዋል።
* ፀረ ኢስላም የሆኑ መንግስታት በኢስላም ስም የሚንቀሳቀሱ አፈንጋጭ ቡድኖችን በማቅረብ ሙስሊሞችን ከውስጥ የመምታት ስራ ተሰርቷል።
* አሸባሪዎችን ለመምታት በሚል በርካታ የአየር ድብደባዎች፣ ዘመቻዎች በሙስሊም ሃገራት ላይ ተፈፅሟል። ብዙዎች አልቀዋል።
* በምእራቡ ዓለም ሙስሊሞች በሰቀቀን እንዲኖሩ፣ ፈተና እንዲበዛባቸው አድርጓል። ሌላም ሌላም።
ይሄ ሁሉ አደጋ እየመጣ ያለው የኋላ ውጤት አሻግሮ ባለመመልከት በሚፈፀሙ የእውር ድንብር ጥቃቶች የተነሳ ነው። እንዲህ አይነት ተግባር ተገቢ እንዳልሆነ ሲገለፅ "እነሱ እንዲህ እያደረጉ አይደል?" የሚል ማመሀኛ ይነሳል። ይሄ ግን ውሃ የሚያነሳ ምክንያት አይደለም። ምሳሌዎቻችን እነሱ አይደሉም። የዑለማኦችን ምክረ ሃሳብ መመልከትና ማክበር ይገባል። የነዚህን አካሄዶች ውጤት ጠላትን ከማሳረር ባለፈ ከተለያዩ አቅጣጫዎች መመልከት ይገባል። ተዋጊ ጠላትን ስለማሸበር የመጣውን ማስረጃ ያለ ቦታው እያዋሉ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ለሚፈፀሙ ጥቃቶች ምርኩዝ ማድረግ መረጃን ያለ ቦታው ማዋል ነው።
ደግሞም እዚህም እዚያም በሚፈፀሙ ፈንዳታዎች ጠላትን ማንኮታኮት አይቻልም። ከአንድ ሰሞን ዜና የማያልፉ ጥቃቶችን እየፈፀሙ ሙስሊሞችን ለሚጨፈጭፉ አውሬዎች፣ ኢስላምን ጭራቅ አድርገው ለሚስሉ ሴረኞች ሰበብ ከማቀበል መጠንቀቅ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

29 Oct, 10:58


ስለ ፎቶ እና ቪዲዮ
(ለብዙኛ ጊዜ)
~
ለተለያዩ አላማዎች ፎቶ እና ቪዲዮ መጠቀምን በተመለከተ፡
- በደፈናው የከለከሉ ዓሊሞች አሉ።
- በደፈናው የፈቀዱም አሉ።
- ለደዕዋ፣ ለእርዳታና መሰል ስራዎች ለይተው የፈቀዱም አሉ።
- ለአስገዳጅ ሁኔታዎችና አንገብጋቢ ጉዳዮች ግን ሁሉም ይፈቅዳሉ።

* አንድ ሰው በደፈናው ፎቶ እና ቪዲዮ መጠቀም ክልክል እንደሆነ በማመኑ ብቻ በጠርዘኝነት የሚሳልበት ምንም አግባብ የለም።
* በሌላ በኩል በደፈናው የሚፈቅድን ሰው በዚህ ሰበብ መንሀጁን ጥያቄ ውስጥ ማስገባትም የሚያስኬድ አይደለም። መተራረሙና የሚያምኑበትን ማሳየቱ ያለና የነበረ ነው።
ከዚህ አልፎ አንድ ሰው ስሜቱን ተከትሎ እንዳይሆን እንጂ በጉዳዩ ላይ የቀደመ አቋሙን መቀየሩ ፈጽሞ የሚያስተቸው አይደለም። እንዲያውም መነጋገሪያ የሚሆን ርእስም አይደለም። በየትኛውም ርእስ ላይ የሚያጋጥም ነው። በአንድ ጉዳይ ላይ ከአንድ በላይ አቋም ያንፀባርቁ በርካታ ዓሊሞችን መዘርዝር ይቻላል። ይሄ ጠለቅ ያለ እውቀት የሚፈልግ አይደለም። የኢስላማዊ እውቀትን ሀ ሁ ያንቧተረ ሁሉ የሚረዳው ነው። ችግሩ የወጣው ጉዳዩ ለመፈራረጃ በመዋሉ ምክንያት ነው።
ለራሴ ከልካዩ የተሻለ ሚዛን የሚደፋ እንደሆነ አምናለሁ። ለሐጃ መጠቀሙ ይቻላል ብዬ ስለማስብ ከፊትም ጀምሬ ለተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማስረጃ አድርጌ አያይዛለሁ። በኛ ሃገር ተጨባጭ በደፈናው ከልካዮቹም ይህንን ሲያደርጉ ማየት የተለመደ ነው። በምስል ምክንያት ሰዎችን የሚነቅፉ ሆነው ሳለ የሚጠሉትን አካል ለማብጠልጠል የሚጠቅም ሆኖ ካገኙት ፎቶ አያይዘው ረድ ሲያደርጉ ይታያሉ።

መፍትሄው አጭርና ቀላል ነው።
1ኛ፦ ጉዳዩን ስሜትን ሳይሆን መረጃን ተከትሎ አቋም መያዝ ነው።
2ኛ፦ ምርጫችን የትኛውም ቢሆን ጉዳዩን ለብሽሽቅና ለመበቃቀል ሳይሆን አላህን በማሰብ ዓሊሞቹ በሚይዙት መጠን መያዝ።

ኒያው መማማር የሆነ ሰው በአደብ ሃሳብ መሰንዘር ይችላል። ከዚህ ውጭ የሆነን ሃሳብ እንዳስፈላጊነቱ ልሰርዝ እችላለሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

29 Oct, 03:17


ሙዘኒይ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ አሉ፦

ሻፊዒይ ዘንድ ገባሁ። በሞቱበት ህመማቸው ላይ ሳሉ ነው። "እንዴት አደርክ የ0ብደላህ አባት?" አልኩኝ።
እራሳቸውን ቀና አደረጉ። ከዚያም:
"ዱንያን እየለቀቅኩ፣ ወንድሞቼን እየተለየሁ፣ ክፉ ስራዬን ለመገናኘት፣ ወደ አላህ ለመጓዝ የቀረብኩ ሆኜ አድሬያለሁ። ሩሔ ወደ ጀነት ሆና የምስራች የምላት ትሁን፣ ወደ እሳት ሆና የማረዳት ትሁን አላውቅም" አሉና አለቀሱ።

📚 [አሲየር : 10/75]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

28 Oct, 16:13


ሸይኽ ሙሐመድ ሐሰን - የኢትዮጵያ ሙስሊም ባለውለታ
~
ሸይኽ ሙሐመድ ሐሰን ሙሐመድኑር ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች በጣም ብዙ ውለታ ከዋሉ መሻይኾች ውስጥ አንዱ ናቸው። በሳቸው የተመሰረተው ወፋ የልማትና ኢስላማዊ ማህበር እጅግ በርካታ መስጂዶችንና መድረሻዎችን ገንብቷል። ኪታቦችንና ሙስሐፎችን (ቁርኣን) አከፋፍሏል። ደውራዎችን ሰጥቷል። ኡዱሒያ፣ የረመዷን ቀለብና ዘካተል ፊጥር ለአመታት አከፋፍሏል።
በልማት በኩል ትምህርት ቤቶችን፣ አይታም ማዕከል ገንብቷል። ለተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ድጋፍ አድርጓል። ብዙ ሺዎችን አሳክሟል። አደጋ ለገጠማቸው ድንገተኛ ድጋፍ አድርጓል።
በማህበራዊ ጉዳዮች በኩል በርካቶችን ወጪያቸውን አሟልተው ድረዋል። በርካታ ኢስላማዊ ተቋማትን አጠናክረዋል ደግፈዋል።

ሸይኽ ሙሐመድ ይህንን ማህበር ከማቋቋማቸውም በፊት ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች እጅግ ብዙ ውለታ ውለዋል። አወሊያን ከማቋቋም እስከ ማደራጀት ጉልህ ሚና ነበራቸው። ከደርግ ዘመን ጀምሮ የሙስሊሙን ህዝብ መብት በማስከበር ላይ ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር ሆነው ብዙ ተግተዋል።
በነገራችን ላይ ሸይኽ መሐመድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውንም በሳዑዲ ዐረቢያ መዲና ውስጥ በሚገኘው ጃሚዐቱል ኢስላሚያ ነው የተማሩት። ወደ ሰዑዲያ ከመሄዳቸው በፊት ግን በሃገር ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረው ዒልም ቀስመዋል። ረሒመሁላህ ረሕመተን ዋሲዐህ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 18/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

28 Oct, 09:43


5 ወሳኝ ምክሮች በስደት ላሉ ለእህቶች

1--የዋህነት አታብዙ

~እህቶች የዋህነታችሁ ጥሩ ሆኖ ሳለ ከልኩ በላይ ሲሆን ግን ይጎዳል። ሁሉም ነገር ላይ የዋህ አትሁኑ ።ለምን? እንዴት? ማለት ያለባችሁ ነገር ላይም ለምን በሉ። ብልሆች፣ብልጦች፣አስተዋዮች ሁኑ።

2--ሁሉንም አትመኑ

~ሁሉንም በማመናችሁ ያጣችሁት ነገር የለም? የተጎዳችሁት ነገር የለም? በእርግጠኝነት ይኖራል ።ጥርጣሬም አታብዙ ግን ሁሉንም አትመኑ።
ልቅ በሆነ እምነት ስንት ነገሮቻቸውን ያጡ አሉ መሰላችሁ። በተለያዩ ሽፋን በተለያዩ ካፓ የሚንቀሳቀሱ እንዳሉም እወቁ። ተጠንቀቁ።ንቁ። እራሳችሁን፣ገንዘባችሁን ጠብቁ።

3---ስትሰጡ በልክ ስጡ።
መስጠት ያሰጣል።አላህም ይተካል። ጀነትን ያስገኛል።ደስታን ይሰጣል።መካራን ያስወግዳል። ግን በልክ ይሁን ።

4- ለችግር ግዜ የሚሆናችሁን ገንዘብ አስቀምጡ።
~ሰው ነን መታመም ሊመጣ ይችላል።ስራ መፍታት ሊኖር ይችላል። የተለያዩ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ለዛ ችግር እዳም እንዳትገቡና እንዳትቸገሩ ለዚህ ቀን የሚሆን ከደሞዛችሁ፣ከጉዳዮቻችሁ ሸረፍ እያደረጋችሁ አስቀምጡ።

5--ደርስ ላይ ፣ቂረአት ላይ በርቱ

~በቻላችሁት አቅም ግዜያችሁን ለመጠቀም ሞክሩ ።በስደት ቆይታችሁ ባለቻችሁ ሽራፊ ግዜ ለመጠቀም ሞክሩ። ወደ ሀገር ቤት ከተመለሳችሁ በሗላ ሁሉ ነገሩ እንደጠበቃችሁት ላይሆን ይችላል። የመቅራቱም ሞራል እንደዛ ላይሆን ይችላልና በርቱ።ሸምቱ።
በሶሻል ሚድያው ተጠቀሙ።
አቡ ሀፍሷ
~››@AbuHafsaYimam
~››@AbuHafsaYimam

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

28 Oct, 05:49


ጥቂት ማስታወሻ ስለ 'ኮመንት'
(የማህበራዊ መገናኛ አጠቃቀም - ክፍል 1)
~
ማህበራዊ መገናኛዎች ላይ በኮመንት ሃሳብ መለዋወጥ ጥሩ ነገር ነው። ስህተት ሲኖር እንተራረማለን። ያልገባንን እንጠያየቃለን። ሃሳብ እንጠቁማለን። ብዙ ፋይዳዎች አሉት። ባግባቡ መጠቀም ካልኖረ ግን ጉዳቱ ሊያደላ ይችላል። ብዥታዎች (ሹቡሃት) ሊሰራጩበት ይችላሉ። አደብ የሌለው ኮመንት ወደ ስድድብ ሊሻገር ይችላል። ሐያእ የቀለላቸው ፀያፍ ሃሳቦችም ይገጥማሉ።

ስለዚህ ሃሳብ ስንሰጥ፡
1ኛ፦ በአደብ ይሁን። ስድብ፣ ብሽሽቅ፣ ኃይለ ቃል አያስፈልግም። "ይልቅ ይህን ተውና ስለ እንትን ፃፉ፣ አስተምሩ" አትበል። በስርአት አውራ። እዚህ ሰፈር አንተ የቀጠርከው ፀሐፊ የለም። መመካከር ከሆነ የምንፈልገው በአደብ እናድርገው። በአደብ ብናወራ ምን እናጣለን?
2ኛ፦ ርእስ እንጠብቅ። በሌላ ጉዳይ ቅሬታ ወይም ልዩነት ስላለን ብቻ የማይገናኝ ቦታ ላይ ተቃውሞ አንፃፍ።
3ኛ፦ ሃሳብ ላይ እናተኩር። የአንዳንድ ተቃውሞዎች ሰበብ ሃሳቡ ከምንጠላው አካል መምጣቱ ብቻ ነው። የኛ በምንለው አካል ቢሰነዘር የማንነቅፈውን ሃሳብ ከማንወደው አካል ስለመጣ ብቻ መቃወም ጤነኛ አካሄድ አይደለም።
4ኛ፦ የተፃፈው ላይ ብቻ እናተኩር። ቃላት መጠምዘዝ፣ ሌላ ትርጉም መስጠት የብዙ ንትርክ ሰበቦች ናቸው። ርእስ እንጠብቅ። "ሐቀኛ ነጋዴ ያለው ደረጃ" ተብሎ ሲፃፍ "ዛሬ ደግሞ ምን ሐቀኛ አለ?" አትበል። ነጥብ አትልቀቅ። የሰው ፖስት አታቆሽሽ። መልእክቱን አታደብዝዝ።
5ኛ፦ ከተቃውሞ በፊት ሃሳብ እንረዳ። አሻሚ ከሆነ ከፀሐፊው ወይም ከተናጋሪው እናስረግጥ። ያለበለዚያ የሰውየው ሃሳብ ሌላ፣ የኛ ጩኸት ሌላ ሰፈር ሊሆን ይችላል። አንዳንዴ ቢያጋጥም ሰውኛ ነው። ስህተቶችን ግን በግዴለሽነት እያሳለፍን ልማድ ከምናደርጋቸው እንማርባቸው።
6ኛ፦ የመረጃዎችን ክብደት እንመዝን።
ሀ - ቁርኣንና ሐዲሥ እየቀረበ ከሆነ "ሸይኽ እከሌ ያሉት ግን..." ከማለትህ በፊት ምን እያልክ እንደሆነ አስብ።
ለ - የትልልቅ ዑለማኦች ንግግር ቀርቦ ስታይ "እኔ ግን ሳስበው ..." አትበል። አንተ ደግሞ ምን ሃሳብ አለህ? አቅምህን እወቅ እንጂ።
ሐ - ከዑለማኦች የተለያዩ ንግግሮች ውስጥ አንዱን እያጣጣልክ ሌላኛውን እንደ ወሕይ ዳኛ አድርገህ አታስፈራራ። አቅሙ ካለህ በአደብ ሚዛን የሚደፋውን ለይ።
7ኛ፦ በፀሐፊው ፖስት ስር ፀሐፊውን አታደናንቅ። በራስ መደነቅ ውስጥ እንዳትከተው። ይልቅ "ጀዛከላሁ ኸይረን" በለው።
8ኛ፦ ኮሜንት መፃፍ ግዴታ አይደለም። በቁም ነገር ስር እንቶ ፈንቶ ነገር አትለቅልቅ። የፃፍከው ነገር ወንጀል እንዳያመጣብህ ተጠንቀቅ።
9ኛ፦ ሙሉ ፅሁፍ ሳናነብ ሃሳብ አንስጥ። የምንሰነዝረው ሂስ በፅሁፉ ተካቶ ሊሆን ይችላል። የማንበብ ትእግስቱ ከሌለን ኮመንት ሳንሰጥ እንለፍ። በቅንጅት ጤነኛ ትርጉም የሚሰጥን መልእክት ነጣጥለን ሳይሆን ሙሉውን አቀናጅተን እንረዳ። ከመሀል ገንጥሎ ለተቃውሞ መነሳት ወይ የቅንነት ወይ የመገንዘብ ችግር እንዳለ ነው የሚያሳየው።
10ኛ፦ ሃሳብ መስጠትህ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘኸው ሳታንዛዛ፣ ቅልብጭ አድርገህ አስቀምጥ። ካልሆነ ሰዎች አሳስተው ሊረዱህ ይችላሉ። ሃሳብ አታደራርብ፣ ለይተህ አስቀምጥ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 18/2017)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

28 Oct, 02:50


ጣፋጭ ኩርኩም
~
ህንዳዊ ሃኪም ነው። ፂሙ ከደረቱ ደርሷል። አንድ ፂሙን የላጨ በቁርኣንና ሱና ላይ የጠለቀ እውቀት ያለው የአዝሀር ሊቅ ጋር ተገናኘ። ህንዳዊው ስለ ፂም ጠየቀው።

የአዝሀሩ ሊቅ፡ "ፂም ማሳደግ የፈፀመው የሚመነዳበት፣ የተወው የማይቀጣበት ሱና ነው" ብሎ መለሰለት።

ህንዳዊው ሃኪም፡ "እኔ ምን እንደምትል አላውቅም። ግን የአላህ መልእክተኛ እንደኔ ናቸው? ወይስ እንዳንተ? " አለው።

አዝሀሪዩ ፡ "አይ እንዳንተ ናቸው" ብሎ መለሰ።

[ሸርሑል ሙሐረር፡ 114]

* አንዳንዱ በእውቀት ካንተ ቢያንስ እንኳ አሻራው እድሜ ልክህን የማይጠፋ ቁንጥጫ ይሰጥሃል።
እይታህ ቢለይ እንኳ ከፍ ያለውን መምረጥ ላይ አይንህን አትሽ።
{ أَتَسۡتَبۡدِلُونَ ٱلَّذِی هُوَ أَدۡنَىٰ بِٱلَّذِی هُوَ خَیۡرٌۚ }
"ያንን እርሱ ዝቅተኛ የሆነውን በዚያ እርሱ በላጭ በሆነው ነገር መለወጥን ትፈልጋላችሁን?" [አልበቀረህ፡ 61]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

27 Oct, 10:53


የሆነ አካል ላይ መታረም ያለበት ነገር ካየህ ቀጥታ ተናገር። መናገርህ የባሰ ነገር የሚያስከትል ካልኖረህ በስተቀር። በጀርባ ማውራት ወይም በውስጥ ቂም መያዝ ተገቢ አይደለም።
ኩልሡም ብኑ ዐምር እንዲህ ይላል፦
"ከተዳፈነ ጥላቻ ግልፅ ወቀሳ ይሻላል።"
[በህጀቱል መጃሊስ፡ 155]

የቱ ጋር አልለህ? የቱ ጋር አልለሽ?
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

27 Oct, 06:59


1ኛ፦ አሉባልታ ሳይሆን ትልቁ ሺርክ እንደሚፈፅም የተረጋገጠን ኢማም ተከትለህ አትስገድ።

2ኛ፦ የተሻለ አማራጭ ካለህ ጥፋቱ ሺርክ ላይ ባይደርስ እንኳ ቢድዐ ያለበት ሰው ባትከተል የተሻለ ነው።

3ኛ፦ ተጨባጭ ምክንያት በሌለበት በግል ወይም በቡድን ስለተደባበርክ ብቻ አንድን ሰው አልከተልም አትበል። ዲንን ለብልሹ አመልህ ማወራረጃ አታድርግ። በውሃ ቀጠነ ጀማዐ አታሳልፍ፤ ጀማዐም አትገንጥል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

26 Oct, 19:27


የመኗኗር ጥበብ
~
"ብልህና አስተዋይ ማለት ከቤተሰቡ፣ ከወዳጆቹ፣ ከጓደኞቹና ከጎረቤቶቹ ትንሽ ትልቁን አጥብቆ የማይዝ ነው።" .
ኢብኑል ጀውዚይ
[ተህዝቡል ከማል፡ 19/370]
አንዳንዴ ስህተቶችን አይቶ እንዳላየ የሚያልፍ ለማለት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

26 Oct, 13:00


ራሳቸው እየበደሉ ዞረው እንደ ተበዳይ ከሚተውኑ ሰዎች ርቀትህን ጠብቅ። በትልቅ ሰው አካል የህፃን አስተሳሰብ የተሸከሙ ፍጥረቶችን እሽሩሩ ማለት ፈታኝ ነው። "ልጅና ቄስ በሰው ገንዘብ ያለቅስ!"
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

26 Oct, 07:20


ተጠንቀቅ! ደካማ አያልቅስብህ
~
በጉልበትህ፣ በስልጣንህ፣ በወገንህ፣ በሃብትህ፣ ... ተማምነህ ሰዎችን አትግፋ። "ጌታዬ! እኔ አቅም የለኝም፣ አንተ ፍረደኝ!" ብሎ ሰው ካለቀሰብህ ወላሂ ወዮልህ! ያኔ እርቃንህን ብቻህን ከአላህ ፊት ለምርመራ ስትቀርብ ምን ይውጥሀል?! ያኔ ዛሬ የተመካህበት ጉልበት ይከዳሀል። ያኔ ዛሬ የጠገብክበት ስልጣን ያዋርድሃል። "ምነው በቀረብኝ?!" ትላለህ። ያኔ ዛሬ የተመካህበት ዘመድና ወገን ጥሎህ ይሸሻል።
{ فَإِذَا جَاۤءَتِ ٱلصَّاۤخَّةُ (33) یَوۡمَ یَفِرُّ ٱلۡمَرۡءُ مِنۡ أَخِیهِ (34) وَأُمِّهِۦ وَأَبِیهِ (35) وَصَـٰحِبَتِهِۦ وَبَنِیهِ (36) لِكُلِّ ٱمۡرِئࣲ مِّنۡهُمۡ یَوۡمَىِٕذࣲ شَأۡنࣱ یُغۡنِیهِ (37) }
"አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ ከእናቱም ከአባቱም፤ ከሚስቱም ከልጁም እንዲሁ። ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ሁነታ አልለው።" [0በሰ፡ 33-37]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

26 Oct, 02:30


የልብ ድርቀትን ለመከላከል
~
በዚህ ዘመን በልብ ድርቀት ያልተጠቃ ይኖር ይሆን? ሃሳብ ጭንቀታችን ዱንያ ብቻ ሆነ። ዒባዳችን ለዛ አጣ። መተዛዘን ጠፋ። ስግብግብነት ነገሰ። ስስት ከደም ከስጋችን ጋር ተዋሀደ። የዱንያ ምኞታችን ከመርዘም አልፎ ተንዘላዘለ።
ወንድሞች እህቶች ወላሂ! የልብ ድርቀት በጣም ሊያስጨንቀን የሚገባ ህመም ነው። የልብ ድርቀት አደገኛ ውጤት የሚያስከትል የአላህ ቅጣት ነው። ከዚህ ህመም ልባችንን እንዴት እናክም? ከዚህ የአላህ ቅጣት እንዴት እንውጣ? ጥቂት ሰበቦችን ልጠቁም። ራሴም ጤነኛ ሆኜ አይደለም። ከማጨስ እንደሚያጠነቅቅ አጫሽ፣ ከህመም እንደሚያስጠነቅቅ ህመምተኛ ቁጠሩኝ።

1- አላህን በማሰብ ራስን አጠቃላይ ከወንጀል መጠበቅ፣ የቅርብም ይሁን የሩቅን ሰው ከመበደል መጠንቀቅ፣ ግብይታችንን፣ ገቢያችንን ሐላል ማድረግ፣ የሰው ሐቅ እንዳይመጣብን መጠንቀቅ
2- ምላስን ከውሸት፣ ከመጥፎ ንግግር፣ ከሃሜትና መሰል ክፍተቶች መቆጣጠር፣ ጆሮዎቻችንን ሐራም ነገሮችን ከማዳመጥ፣ አይኖቻችንን ሐራም ነገሮችን ከመመልከት፣ እጆቻችንን ለሐራም ነገሮች ከመጠቀም፣ ልባችንን በክፋት፣ ምቀኝነት፣ ጥላቻ፣ ... ላይ ከመጥመድ መቆጣጠር
3- ዚክር ማዘውተር፣ በቋሚነት የቁርኣን ዊርድ መያዝ፣ ደጋግሞ ከልብ ዱዓእ ማድረግ፣ ተደቡር፣ ተፈኩር ማድረግ፣ በዱዓእ፣ በቁርኣን ማልቀስ
4- ከሰላት፣ ከፆም፣ ከሶደቃው፣ ... ከግዴታው ባለፈ ነፍል ዒባዳዎችን ማዘውተር
5- ሞትን፣ ቀብርን፣ ሂሳብን፣ ሲራጥን፣ ... ኣኺራን ማሰብ
6- ደግሞ ደጋግሞ ኢስቲግፋርና ተውበት ማድረግ
7- ቁርኣን በእርጋታ መቅራት፣ ኹሹዕ የሚያጋባ አቀራር ያላቸውን ቃሪኦች ማዳመጥ፣
8- ቀብር መዘየር፣ የታመመን መጠየቅ፣ ወላጆችን፣ ዘመድ አዝማድን፣ ጎረቤትን አቅም በፈቀደ መጠየቅ
9- ችግረኛን በገንዘብም፣ በሃሳብም፣ በጉልበትም፣ በእውቀትም መርዳት፣ ሶደቃ ማድረግ
10- የዙህድና የረቃኢቅ ኪታቦችን ማንበብ፣ ውስጥን ሰርስረው የሚገቡ ሙሓደራዎችን እየፈለጉ ማዳመጥ፣ የነብዩን ﷺ ሲራ፣ ራስን ለመታዘብ የሚያግዙ የሰለፎችን አስገራሚ ታሪኮች፣ የዑለማኦችን ጣፋጭ ወጎች በትኩረት መከታተል
11- በየትኛውም የዒባዳ መስክ ላይ ኢኽላስን አጥብቆ መፈተሽና ማቃናት።
12- ከራስ ጋር መተሳሰብ። ጊዜ አልፎ ጊዜ በተተካ ቁጥር ወደ ሞት እየቀረብን ነው። ከአምና ዘንድሮ፣ ከባለፈው በዚህኛው፣ ሳምንታችን፣ እለታዊ ውሏችን መሻሻል አለው? ወይስ ያው ነው? ወይስ ጭራሽ እየባሰበት ነው? ከዱንያችን በላይ ኣኺራችን ያሳስበናል? ድንገት ብንሞት ያለንበት ሁኔታ በፀፀት ጣት የሚያስነክስ አይደለም? ራሳችንን ለመለወጥ የምር እንታገል።

እኔ የራሴን ድክመቶች በመመልከት ድንገት የመጣልኝን ነው የፃፍኩት። ሁሉም ነገን አስቦ ዛሬ ራሱን ይመልከት።
﴿بَلِ الْإِنْسَانُ عَلَى نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ﴾
"በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡" [አልቂያመህ ፡ 14]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

25 Oct, 17:09


በጊዜ ተንፍስ
~
አንዳንድ ወንድሞች በሆነ የዒልም ዘርፍ ከእኩዮቻቸው ሲበልጡ ወይም የበለጡ ሲመስላቸው ትእቢት ሲፈትናቸው ይታያሉ። አንዱን መናቅ፣ ያኛውን ማጣጣል፣ ሌሎችን በመገምገም ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ላይ ይጠመዳሉ።
የሸሪዐ እውቀት አላህን መፍሪያ መሳሪያ መሆኑ ሁሌም ሊዘነጋ አይገባም። ማወቅህ ትእቢት ካወረሰህ፣ በማወቅህ ለሌሎች ንቀትን ካዳበርክ ወላሂ ማወቅህ ጎድቶሃል። ጅህልና ላንተ የተሻለ ነበር። ሰው ቴኳንዶ ሰልጥኖ ቀድሞ ያልነበረውን አደብ ሲላበስ በምናይበት ጊዜ የሆነን ዒልም ሲማር እብሪትና ንቀትን የሚያዳብር ማየት አሳፋሪ ነው።
ወንድሜ ሆይ! መከበር ከፈለግክ ሰዎችን አክብር። ሌሎችን መናቅ ምናልባት ጥቂት ጊዜ ቢያስከብር ነው። ወይ ሰዎች እስከሚነቁ፣ ወይ ደግሞ ማንነትህ እስከሚገለጥ ድረስ ቢዘልቅ ነው። ከዚያስ? ከዚያማ መናቅህ መንናቅን ነው የሚያስከትልብህ። መተንፈስህ ላይቀር አፀፋ ሳያስተነፍስህ በፊት አላህን ፈርተህ ተንፍስ። በጊዜ ተንፍስ። አዎ መተንፈስ ይሻልሃል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

25 Oct, 13:37


ከዚህ ስሜት ያለን ርቀት ምን ያህል ነው?
~
ሰዒድ ብኑ ጁበይር - ረሒመሁላህ - "ከማንም በላይ ይበልጥ አላህን ተገዢ /አምላኪ ማነው?" ተብለው ተጠየቁ። ምላሻቸው ምን ሆነ?
"ወንጀል ፈፅሞ ያን ወንጀሉን ባስታወሰ ቁጥር ስራውን ዝቅ አድርጎ በመመልከት ለጌታው የተሰበረ ነው" አሉ።
[አልቢዳያህ ወኒሃያህ 9/99]

ያ ረብ ወዳንተ መቅረብን ወፍቀን።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

25 Oct, 10:59


በተመሳሳይ ጉዳይ ከሰው ሰው እየለዩ የተራራቁ አቋሞችን ማንፀባረቅ፣ ማለትም የኛ የሚሉትን እንዳላዩ እያለፉ ሌሎችን ማብጠልጠል በዚህ ዘመን ጎልተው ከሚታዩ የቡድንተኝነት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ ነው። ከዚህ በሽታ መውጣት የፈለገ ራሱን በተቅዋ ያክም። የውስጥን የሚመለከተውን ጌታ ሙራቀባን ያስብ።
{ وَأَسِرُّوا۟ قَوۡلَكُمۡ أَوِ ٱجۡهَرُوا۟ بِهِۦۤۖ إِنَّهُۥ عَلِیمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ }
"(ሰዎች ሆይ!) ቃላችሁን መስጥሩ፡፡ ወይም በእርሱ ጩሁ፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነው።" [አልሙልክ: 13]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

25 Oct, 05:02


የልብ መድረቅ በሽታ አደጋው ከባድ ነው። ልቡ የደረቀ ሰው ሐራም መዳፈር ያበዛል። ወንጀል እየፈፀመ አይደነግጥም። የሰው ሐቅ መዳፈሩ አያስጨንቀውም።
ይሄ ሲሆን ዒባዳው ለዛ ያጣል። መስገድ መፆሙን እንጂ የሚያየው የዒባዳውን አሻራ አይፈትሽም።
ልባችንን እንከታተል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

25 Oct, 04:51


በጁሙዐ ቀን ከሚወደዱ ተግባሮች ውስጥ አንዱ በነብዩ ﷺ ላይ ሰላት ማውረድ ነው። ምን ያህሎቻችን ይሄ ልማድ አለን?
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

24 Oct, 16:56


የኢትዮጵያ ነገር እዚህ ደርሷል
~
መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው አውዳሚ የእሳት አደጋ ወቅት አንዳንድ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን አባላት ከባለሱቆች ጋር የገንዘብ ድርድር ሲያደርጉ እንደነበር ሰምቻለሁ፣ ከአንድ እና ከሁለት ሳይሆን 8 ሰዎች አረጋግጠውልኛል

በስፍራው ከደረሱ በኋላ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ "ማንን ነው ምናናግረው?" በማለት ለረጅም ደቂቃዎች ማጥፋት እንዳልጀመሩ እነዚህ የአይን እማኞች ይናገራሉ።

"ማለት የፈለጉት ብር እንዲሰጣቸው ከማን ጋር ነው ምንደራደረው ነው። ይህ ነገር የተለመደ ቢሆንም ይሄ ሁሉ ንብረት እስኪወድም ግን በዚ ደረጃ አይመስለኝም ነበር" ያለኝ አንድ የአደጋው ተጎጂ ቤተሰብ ይህን መረጃ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች እንደሚያውቁ ነግሮኛል።

መሠረት ሚድያ ደግሞ በደረሰው መረጃ በስፍራው ቀድመው በአምቡላንስ የደረሱ የእሳት አደጋ ቡድን አባላት 4 ሚልዮን ብር በመቀበል በድርድር ተስማምተዋል።

ብር ከፋዮቹ በጊዜው የነበሩ የሱቅ ባለቤቶች ሲሆኑ የብዙ ሚሊዮን ብር ንብረት ሱቆቹ ውስጥ ላይ ስለነበራቸው የተጠየቁትን ለመክፈል ምርጫ ስላልነበራቸው አላቅማሙም ነበር፣ ጠያቂዎቹ ደግሞ በጊዜው ቀድመው አምቡላንስ ይዘው የደረሱ የእሳት አደጋው ሰራተኞች ናቸው ተብሏል።

ይህን ድርጊት የፈፀሙት ሁሉም ሳይሆኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች መሀል የሚገኙ የሰው ንብረት ውድመት ሳይታያቸው እና ሙያቸውን የካዱ ጥቂቶች እንደሆኑ ይሰማኛል።

ጉዳዩን "ውሸት" ምናምን ብሎ ለማለፍ ሊሞከር ይችላል፣ የሚያዋጣው ግን አጣሪ ቡድን ወደስፍራው በመላክ እነዚህን አሳፋሪ ጥፋተኞች በህግ መጠየቅ ነው።

አሳፋሪ ነው!
(ኤልያስ መሰረት)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

24 Oct, 13:22


ጉትን ለሚገኘው ቡኻሪ መስጂድ ገቢ
ማሰባሰቢያ ላይ የተሰጠ ማስታወሻ

ለፅናት የሚረዱን መንገዶች

በአቡ ዘይድ ከማል አሕመድ

https://t.me/Subuleselam_Medresa

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

24 Oct, 03:04


እዚህ ሰፈር ነጋ ጠባ ሺ0ዎችን እያወደሰ የሱና ዑለማኦች ላይ የሚዘምት አካል አለ። ለሺ0ዎች ዋሽቶ ይከላከላል። የሱና ዑለማኦችን ደግሞ በውሸት ጭምር ያጣጥላል። ከንዲህ አይነቱ በተሸዩዕ ልቡ ከተበከለ ሰው ተጠንቀቁ። ይህንን ነውረኛ አካሄድ ከሚያሳዩ ምሳሌዎች ውስጥ አንዱ የሳዑዲ ዑለማኦች አስካሪ መጠጥ ፈቀዱ እያሉ የተቀናበረ ቪዲዮ መለጠፉ ነው። የሚገርመው እንዲህ አይነቱን ቅጥፈት የሚያምኑ ብዙ በጎች መኖራቸው ነው። ቅንብር መሆኑ ለማንም ያስታውቃል። ግን አያስጨንቃቸውም። ሰውየው ማነው ፣ የሱና ዑለማኦችንስ ይወክላል ወይ የሚለውም አያሳስባቸውም። እነ ኻሚነኢን፣ እነ ሐሰን ነስረላህን፣ እነ ሑሢን እያወደሰ የሱና ዑለማኦች ላይ የሚዘምት አካል ማንም ይሁን ምን እርኩስ ነው።
አላህ ከቅዠታችሁ ያውጣችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

23 Oct, 17:38


የሰዎች ትንኮሳ መቼ ነው የሚጎዳህ?
~
ሰዎች በንግግር፣ በፅሁፍ፣ በሃሜት፣ በየትኛውም አይነት ክፉ ቃል ሲፈትኑህ እየተብከነከኑ ጤናንም፣ ሰላምንም፣ እንቅልፍንም ማጣት አይገባም። ቢቻል አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ ነው። ካልሆነ ግን የሚፈትሉትን ክፋት እዚያው እነሱው እንዲጠመዱበት መተው ነው። በመርሳት ሰላምህን ጠብቅ። ካልሆነ ግን ክፋታቸው ሳይሆን ማብሰልሰልህ ይጎዳሀል። ሰዕዲይ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦

"የሰዎች ትንኮሳ አይጎዳህም። ይልቁንም እነሱኑ ነው የሚጎዳቸው። ትኩረት በመስጠት ራስህን ካልጠመድክ በስተቀር። ያ ከሆነ እነሱን እንደሚጎዳቸው አንተንም ይጎዳሀል። ቦታ ካልሰጠኸው ግን ምንም አይጎዳህም።"
[አልወሳኢሉል ሙፈደህ ሊልሐያቲ ሰዒደህ፡ 30]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

23 Oct, 13:10


"አር ማረኝ"
~
ተውሒድን አጥብቀህ ተማር። ተውሒድ ለኣኺራ ብቻ አይደለም ፋይዳው። ለዱንያም መከበሪያህ ነው።
ተውሒድ ካልተማርክ

• ጉጉት ትፈራለህ፣
• አይጥ ትለማመጣለህ፣
• ውሻ አላዘነ ብለህ ትሸበራለህ፣
• የቁራ ድምፅ ከመንገድ ይመልስሃል፣
• እጅ ወይም አንገት ላይ በታሰረ እርባ ቢስ ክር ትተማመናለህ፣
• ዛፍ ላይ ክር ትተበትባለህ፣ ቅቤ ትቀባለህ፣
• እጅህን ስላሳከከህ ትደሰታለህ፣ (ሰዎች እጃቸውን ሲያሳክካቸው ምን እንደሚሉ አስታውስ።)
|
• ተውሒድ ካልተማርክ ከሶላት የተኳረፈ ገሪባ "ዐርሽ ላይ ነው የምሰግደው" እያለ ይጫወትብሃል። ጠንቋይና ወሊይ ይምታታብሃል።
• ሃያሉን ጌታ ጥለህ ሙታን ትማፀናለህ። (ይልቅ እነሱን መለመንህን ትተህ ለነሱ ዱዓእ አድርግላቸው።)
• ተውሒድ ካልተማርክ "ማርያም በሽልም ታውጣሽ"፣ "የማርያም መቀነት"፣ "የማርያም ፈረስ"፣ "ማርያም ስማህ ነው"፣… እያልክ ክርስትና ክርስትና የሚሸት ኹራፋት ታራምዳለህ።
• የአምስት ብር ጎመን የማያክል አረንጓዴ መርዝ (ጫት) መቶ ሁለት መቶ ብር ገዝተህ "የዱዓእ መሳሪያ" እያልክ ትጃጃላለህ።
• የሁለት አመት ህፃን "ካካ" ስትለው የሚፀየፈውን አፈር፣ "ቱራብ" እያሉ ከቀብር አካባቢ ቆንጥረው ሲሰጡህ በጥብጠህ ትጠጣለህ።
• አዎ ተውሒድ ካልተማርክ የተቀበረ ብር አገኛለሁ ብለህ ጠንቋይ እየቀለብክ በእጅህ ያለውን ገንዘብ ታጣለህ።
• ልጅህ ሲባልግ፣ ሲያፈነግጥ ዝም ብለህ ተውሒድ ሲማር፣ ሶላት ሲሰግድ፣ መስጂድ ሲያዘወትር፣ ጥሩ ጓደኛ ሲይዝ እሪ ትላለህ፣ (እንዲህ ነው የሸይጧን መጫወቻ መሆን።)
• ተውሒድ ካልገባህ ከሺርክ የሚያስጠነቅቁ ተቆርቋሪዎችን እንደ ጠላት እየቆጠርክና ጧት ማታ እያጠለሸህ ሶሐቦችን የሚያወግዙ፣ ቁርኣንን የሚያረክሱ ሺዐዎችን ታወድሳለህ። አልተማርክማ! እንዲሁ "ሲሉ ሰማሁ ብየ፣ እላለሁ ነብዬ" ብቻ!
• ተውሒድ ካልተማርክ ለቶንሲል ህመም "አር ማረኝ" እያልክ በአይነ ምድር ታሻርካለህ። ሰው እንዴት ካካውን ይማፀናል? ወላሂ ከእንዲህ አይነቱ ካካውን ዞሮ ከሚማፀን ጉደኛ ፍጡር፣ ካካውን የሚያቦካ የአእምሮ በሽተኛ ሺ ጊዜ ይሻላል።
ጎንበስ ብለህ ተውሒድህን ተማር። አካዳሚ ትምህርት ከሺርክ አያወጣህም። ስንት እንጨት፣ ላም፣ ድንጋይ፣ ሰው፣… የሚያመልኩ፣ ጠንቋይ ለጠንቋይ የሚርመጠመጡ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች አሉ መሰለህ?
\=\

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

23 Oct, 06:23


ቅድሚያ ለኣኺራ
~
ሐሰኑል በስሪይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"ሁሉም ፀጋ ጠፊ ነው፣ የጀነት ሰዎች ፀጋ ሲቀር።
ሁሉም ሃሳብ አላፊ ነው። የእሳት ሰዎች ሃሳብ ሲቀር።"
[አልሙጃለሰህ ወጀዋሂሩል ዒልም፡ 19
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

23 Oct, 02:22


ዋጋህ ስንት ነው? ስንት ታወጣለህ?
~
አላህ ስለ ነብዩ ﷺ ሲገልፅ ዘራቸውን፣ ሀብታቸውን ወይም መልካቸውን አይደለም የጠቀሰው። ነገር ግን እንዲህ ነበር ያለው፦

{ وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِیمࣲ }
"አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ።" [አልቀለም፡ 4]

* ዋጋህ በስነ ምግባርህ ልክ ነው።

[የተቀዳ]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

22 Oct, 04:24


በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

19 Oct, 14:50


ለሺዐ መነሳት ሰበቡ በኑ ኡመያ ናቸው የሚል አየሁኝ። ይሄ ጥላቻ ወይም አለማወቅ የወለደው ድምዳሜ ነው። የሺ0 አስተሳሰብ ጥንስሱ በዐሊይ ዘመን ነው። 0ሊይኮ በኸዋሪጅ ላይ እንኳ ያላደረጉትን ከባድ እርምጃ የወሰዱት እሳቸውን ጌታ አድርገው እስከማመን በደረሱ ድንበር አላፊ ሺዐዎች ላይ ነው። ከመግደልም ባለፈ በእሳት ነው ያቃጠሏቸው።
አንዳንድ ሰዎች ለበኑ ኡመያ ያረገዙት ጥላቻ ብዙ ርቀት እየወሰዳቸው ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

19 Oct, 14:33


ሺፋኡ-ረህማን አጠቃላይ የሩቃ አገልግሎት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

1. ለሲህር
2. ለዐይን
3. ለጂን እና ለሌሎችም በሽታዎች

አድራሻ: በአዲስ አበባ እና በአካባቢዋ ዙሪያ

ለበለጠ መረጃ:

0911249457
0921780493
0901175562

የቴሌግራም አድራሻችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/shifau_rehman_ruka_center

ማሳሰቢያ :
አሁን ላይ እየሰጠን ያለነው አገልግሎት የቤት ለቤት አገልግሎት ብቻ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን ።

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

19 Oct, 05:05


የቁርኣን አወራረድ
ጥቂት ስለ ቁርኣን (ክፍል - 2)
~
ቁርኣን መልእክቱም ቃላቱም የአላህ ንግግር ነው። መነሻው ከጂብሪል አይደለም። ከአላህ እንጂ። ከዚህ አንፃር ሲታይ ቁርኣን የጂብሪል ንግግር አይደለም። በቁርኣን ላይ የጂብሪል ሚና ከአላህ ተቀብሎ አማናውን ጠብቆ ለነብዩ ﷺ ማድረስ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ قُلۡ نَزَّلَهُۥ رُوحُ ٱلۡقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِٱلۡحَقِّ }
"(ቁርኣንን) 'ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲሆን ከጌታህ አወረደው' በላቸው።" [አነሕል፡ 102]

ቁርኣን ሁለት አይነት መውረድ አሉት።

[1]:- የመጀመሪያው መውረድ፦

* አወራረዱ፦ በጅምላ በአንድ ጊዜ ነው።
* ከየት ወዴት? :- 7ኛው ሰማይ ላይ ካለው ከለውሐል መሕፉዝ - ቅርቢቷ ሰማይ ላይ ወደሚገኘው በይተል ዒዘህ ወረደ።
* ጊዜው፦ በረመዷን ወር፣ በተባረከችዋ ሌሊት ነው፤ በለይለተል ቀድር።

ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ብሏል፦
{ شَهۡرُ رَمَضَانَ ٱلَّذِیۤ أُنزِلَ فِیهِ ٱلۡقُرۡءَانُ }
"የረመዳን ወር ያ ቁርኣኑ የተወረደበት ነው፡፡" [አልበቀረህ፡ 185]
{ إِنَّاۤ أَنزَلۡنَـٰهُ فِی لَیۡلَةࣲ مُّبَـٰرَكَةٍۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِینَ }
"እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው። እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና።" [አዱኻን፡ 3]
{ إِنَّاۤ أَنزَلۡنَـٰهُ فِی لَیۡلَةِ ٱلۡقَدۡرِ }
"እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው።" [አልቀድር፡ 1]

[2]፦ ሁለተኛው መውረድ፦

* አወራረዱ፦ በተከፋፈለ ሁኔታ ነው።
* ከየት ወዴት? :- ከበይተል ዒዘህ ወደ ነብያችን ﷺ
* ጊዜው፦ በ23 ዓመታት ውስጥ

ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፦
{ وَقُرۡءَانࣰا فَرَقۡنَـٰهُ لِتَقۡرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكۡثࣲ وَنَزَّلۡنَـٰهُ تَنزِیلࣰا }
"ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው።" [አልኢስራእ፡ 106]

{ وَقَالَ ٱلَّذِینَ كَفَرُوا۟ لَوۡلَا نُزِّلَ عَلَیۡهِ ٱلۡقُرۡءَانُ جُمۡلَةࣰ وَ ٰ⁠حِدَةࣰۚ كَذَ ٰ⁠لِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِۦ فُؤَادَكَۖ وَرَتَّلۡنَـٰهُ تَرۡتِیلࣰا }
"እነዚያ የካዱትም 'ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም' አሉ። እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ (ከፋፍለን አወረድነው)። ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው።" [አልፉርቃን፡ 32]

በሁለቱም መውረድ ላይ ጂብሪል አለ። ከአላህ ተቀብሎ አማናውን ጠብቆ ለነብዩ ﷺ አድርሷል። አላህ እንዲህ ይላል፦

{ وَإِنَّهُۥ لَتَنزِیلُ رَبِّ ٱلۡعَـٰلَمِینَ (192) نَزَلَ بِهِ ٱلرُّوحُ ٱلۡأَمِینُ (193) عَلَىٰ قَلۡبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُنذِرِینَ (194) بِلِسَانٍ عَرَبِیࣲّ مُّبِینࣲ (195) }
"እርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው። እርሱን ታማኙ መንፈስ (ጂብሪል) አወረደው፤ ከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረደው)፡፡ ግልጽ በሆነ ዐረብኛ ቋንቋ።" [አሹዐራእ፡ 192-195]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

19 Oct, 04:37


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣8️⃣8️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 622፣ ሐዲሥ ቁ. 1809
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

18 Oct, 16:34


Live stream finished (57 minutes)

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

18 Oct, 15:37


Live stream started

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

18 Oct, 07:02


የሸይኽ ሙሐመድ ዘይን የነሕው ደርሶች !
~~
አልሙቀዲመቱል ኣጁሩሚያ
ሙልሐቱል ኢዕራብ
ከሽፋ ኒቃብ
አልፈዋኪሁል ጀንያ 1
አልፈዋኪሁል ጀንያ 2
አልፍየቱ ኢብኒ ማሊክ ከኢብኑ ዐቂል ሸርሕጋር

የሸይኽን የተጠናቀቁ ዱሩሶችን ለማግኘት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ :-
https://t.me/SheikhMuhammedZain

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

17 Oct, 20:48


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣8️⃣7️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 619፣ كتاب المنثورات والملح
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

17 Oct, 06:10


ሰሞኑን ትንሽ አሞኝ ነበር። ዛሬ በአንፃሩ ለውጥ አለኝ አልሐምዱ ሊላህ። ህመም ጋር በተያያዘ ጥሩ ያልሆነ ልማድ አለኝ። ሃኪም ቤት መሄድ አልወድም። ህመሜ ከባድ ደረጃ ሲደርስ ወይም መንቀሳቀስ ሲያቅተኝ ግድ ሲሆን ነው የምሄደው። እንደተለመደው መቋቋም ሲያቅተኝ በአቅራቢያ ያለ ሃኪም ቤት ገባሁ። ሳውቀው በጣም ህዝብ ይርመስመስበት ነበር። ፀጥ ረጭ ብሏል። ከኔ ውጭ ሁለት ታካሚ መሰለኝ ያየሁት። ያውም አንዷ ድንገተኛ። ለህክምናዬ ያወጣሁትን የገንዘብ መጠን ሳይ ሰውን ያሸሸው ይሄ የተጋነነ ዋጋ ዋና ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አሰብኩ።
ሰው አማራጭ ስለሌለው ወይም አማራጩ ስለሚያንስ ብቻ በዚህ ልክ መጨከን ጥሩ አይደለም። በርግጥ እኔ የሄድኩበት የሙስሊም ቤት አይደለም። ነገር ግን የሙስሊሞቹም የባሱ እንጂ የተሻሉ እንዳልሆኑ በተደጋጋሚ አይቻለሁ፣ ሰምቻለሁም። ለዚህ የዋጋ ንረት የተጠቃሚውም ድርሻ ቀላል አይደለም። የህክምናውን ጥራት በሚከፍለው ብር መጠን የሚለካ አለ። ክፍያው ዝቅ ሲል ለተቋሙ የሚሰጠው ግምት አብሮ ዝቅ ይልበታል። እንዲህ አይነቱን ሳይነቃ እንደነቃ የሚያስብ ወይም ጥጋበኛ እንተወውና ለሰፊው ህዝብ ግን አንድ ነገር ማለት ጥሩ ነው። አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠማችሁ በስተቀር ህክምናችሁን በመንግስት ተቋማት አድርጉ። ለዚህ አንዱ ምክንያት የህክምና ዋጋ ነው። ከዋጋ ያለፉ ሌሎችም ምክንያቶች በተጨባጭ አሉ። ለነገሩ ህዝባችን አሁን በመንግስት ተቋማት ለመታከምም የሚያቅተው ደረጃ እየደረሰ ነው። አላህ ይድረስልን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

15 Oct, 11:02


የመካ እና የመዲና ሱራዎች
ጥቂት ስለ ቁርኣን (ክፍል - 1)
~
ቁርኣን ነብያችን ﷺ መካ እያሉ በሚወርድ ጊዜ የሙስሊሞች ቁጥር አናሳ ነበር። አጋሪዎች ብዙሃን ነበሩ። መዲና ውስጥ በነበሩ ጊዜ ደግሞ የሙስሊሙ ኃይል ተጠናክሯል። መካና መዲና የነበሩት ተቃራኒ ኃይሎች በብዛት ከእምነትም፣ ከንቃተ ህሊናም አንፃር ልዩነት አላቸው። በነዚህና መሰል ልዩነቶች የተነሳ በሁለቱ ዘመኖች የወረዱ ሱራዎች ትኩረትና ይዘት ልዩነት ይታይበታል። ይሄ የተወሰነ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይፈልጋል።
ከወረዱበት ዘመን አንፃር ሲታይ ከ114 የቁርኣን ምእራፎች ውስጥ 20ዎቹ መደኒያ ናቸው፣ በዘመነ መዲና የወረዱ። 12ቱ ኺላፍ አለባቸው። ቀሪዎቹ መኪያ ናቸው። ስለዚህ ከቁጥር አንፃር አብዛኞቹ የቁርኣን ምእራፎች መካ የወረዱ ናቸው ማለት ነው።

በነገራችን ላይ የመካ እና የመዲና ሱራዎች የሚታወቁባቸው መለያዎች አሉ።

1 - የመካ ሱራዎች፦

ሀ - "ከልላ" (كلا) የሚለው ቃል ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው።
ለ - ሰጅደተ ቲላዋ ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
ሐ - በመሀላ የሚጀምሩ ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
መ - በሑሩፉ ተሀጂ (ሑሩፉል ሙቀጠዐ) የሚጀምሩ ሱራዎችም ከበቀረህ እና ኣሊ ዒምራን ውጭ መኪያ ናቸው። በቀረህ እና ኣሊ ዒምራን መደኒያህ ናቸው። ሱረቱ ረዕድ ኺላፍ አለባት።
ሠ - በውስጣቸው "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መኪያ ናቸው።
ረ - በ "አልሐምዱ" የሚጀምሩ ሱራዎች መኪያ ናቸው። እነሱም አምስት ሱራዎች ናቸው።
ሰ - ከሱረቱል በቀረህ ውጭ "ቀሶሱል አንቢያእ" የያዙ ሱራዎች መኪያ ናቸው።

2 - የመዲና ሱራዎች፦

ሀ - በውስጣቸው "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መደኒያ ናቸው።
ለ - ስለ ሙናፊቆች የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው። አልዐንከቡት ስትቀር። እሷ ግን መኪያ ነች። ይሁን እንጂ በውስጧ ስለ ሙናፊቆች የሚያወሳው ክፍል መደኒይ ነው።
ሐ - ሑዱድ እር ፈራኢድ የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው።

ምንጭ፦ ዲራሰህ ፊ ዑሉሚል ቁርኣኒል ከሪም፣ ፈህድ አሩሚይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

15 Oct, 10:26


የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ ነው እንደ መንግስት ተሿሚ በተገኘበት ቦታ ለተሰብሳቢው ህዝብ ስብከት የሚያከናውነው። እዚች ሃገር ላይ ሴኩላሪዝም የሙስሊሞችን መብት ለማፈን ሲፈላግ ብቻ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

15 Oct, 08:49


መሻይኾቻችንን ፣ ወሊዮችን ድረሱልን የምንለው እንደ ሰበብ ነው ለሚለው ሹብሃ አጭር መልሥ


https://t.me/Muhammedsirage

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

15 Oct, 03:16


ከሶላት በኋላ የተስቢሕ አፈፃፀም
~
1- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ። 100ኛ "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ማለት። [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
2- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 34 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [ሙስሊም]
3- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ ማለት። ድምሩ 99 ይሆናል። [ሙስሊም]
4. ሱብሓነላህ 10 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 10 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 10 ጊዜ ማለት። ድምሩ 30 ይሆናል። [ቡኻሪይ]
5. ሱብሓነላህ 11 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 11 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 11 ጊዜ ማለት። ድምሩ 33 ይሆናል። [ሙስሊም]
6. ሱብሓነላህ 25 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 25 ጊዜ፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ 25 ጊዜ እና አሏሁ አክበር 25 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

14 Oct, 17:21


ሶስቱ ዑዝሮች
~
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«إن الله تجاوز لي عن أمتي الخطأ والنسيان وما استكرهوا عليه»
“አላህ ከህዝቦቼ ስህተትን፣ መርሳትን እና የተገደዱበትን አልፎልኛል።” ኢብኑ ማጀህ እና በይሀቂ ዘግበውታል። ሐዲሡ ከሰነድ አንፃር ደካማ እንደሆነ በርካታ ሙሐዲሦች ገልፀዋል። ይሁን እንጂ የያዛቸው መልእክቶች በሌሎች መረጃዎች በአስተማማኝ ሁኔታ የሚገኙ ስለሆነ መልእክቶቹ ላይ ዐሊሞች ተስማምተዋል።
የሰዎች ተግባራት ወይ በእውቀት፣ በምርጫና በማስታወስ የሚፈፀሙ ናቸው። ወይ ደግሞ ባለማወቅ፣ በመገደድና በመርሳት የሚፈፀሙ ሊሆኑ ይችላሉ። ሰዎች በጥፋቶቻቸው ወንጀለኛ የሚሆኑት በእውቀት፣ በምርጫና በማስታወስ የፈፀሟቸው ከሆነ ነው። ከነዚህ ሶስት ነጥቦች አንዱ ከጎደለ ሰውየው በጥፋቱ ወንጀለኛ አይሆንም። ባለማወቅ ወይም በመገደድ ወይም በመርሳት የተፈፀሙ ጥፋቶች አያስጠይቁም ማለት ነው። ስለዚህ ሰዎች ከተጠያቂነት የሚተርፉባቸው ሶስት ዑዝሮች አሏቸው ማለት ነው።
• 1ኛው ስህተት ነው። ሆነ ብሎ አስቦ ሳይሆን በስህተት ጥፋት ቢፈፅም ወንጀለኛ አይሆንም።
• 2ኛው መርሳት ነው። ይህም ተቀባይነት ያለው ምክንያት ነው።
• 3ኛው መገደድ ነው። ወንጀል እንዲፈፅም የተግደደ ሰው ወንጀል የለበትም። አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿إِلَّا مَنْ أُكْرِهَ وَقَلْبُهُ مُطْمَئِنٌّ بِالْإِيمَانِ﴾
“ልቡ በእምነት የረጋ ሆኖ (በክህደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር።” [አነሕል፡ 106]

ማሳሰቢያ፦
ስህተትና እርሳታ ጋር የሚያያዙ መርሆዎች አሉ።
• ረስቶ ወይም ተሳስቶ ትእዛዝን የተወ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ሊሰራው ግድ ይላል።
• ረስቶ ወይም ተሳስቶ ክልከላን የፈፀመ ሰው ቢያስታውሰውም ሊሰራው የሚገባው ነገር የለም።
ረስቶ የሆነን ትእዛዝ የተወ ሰው - ለምሳሌ ያለ ቂብላ ቢሰግድ - ጥረት ሳያደርግ ከሆነ የፈፀመው ባስታወሰ ጊዜ ወደ ቂብላ ዞሮ እንዲሰግድ ይታዘዛል። ከዚሁ ጋር የሚመሳሰለው ሶላትን ከረሳ ባስታወሳት ጊዜ ይሰግዳታል። ክልከላን ረስቶ ፈፅሞ ከሆነ ግን - ለምሳሌ ፆመኛ ሆኖ ቢበላ - ምንም የለበትም።

ሌላ የምንወስደው ነጥብ፡- ብይንን አለማወቅ ወንጀለኛ ላለመሆን በቂ ምክንያት እንደሚሆን ነው። ይህንን የሚጠቁሙ ማስረጃዎችም ብዙ ናቸው። ለምሳሌ ባለማወቅ መረጋጋትን (ጡመእኒነህ) ትቶ ሶላቱን አበላሽቶ የሰገደውን ሰው የሚመለከተው ሐዲሥ ለዚህ ማስረጃ ይሆናል። ጡመእኒነህ የሶላት ዋና ክፍል ነው። ከመሆኑም ጋር ነቢዩ ﷺ አልፈውታል። ማለትም ያለፉትን ሶላቶች በድጋሜ እንዲሰግድ አላዘዙትም። [ቡኻሪይና ሙስሊም የዘገቡት]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

14 Oct, 03:10


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ከወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ላንተ ሶደቃ ነው።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

12 Oct, 17:38


አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ
~
ትላንት ጁሙዐ አሸዋ ሜዳ የጣት ቀለበት ወድቆ አግኝቻለሁ። ቀለበቱ ወርቅ መሰለኝ፣ እርግጠኛ መሆን ግን አልቻልኩም። የጠፋው ሰው በዚህ ዩዘርኔም ይፃፍልኝ :-
t.me/ibnumunewor05

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

12 Oct, 03:55


እናት እንጂ የእንጀራ እናት አትሁኚ
~
በሞትም ይሁን በመራራቅ እናቱን ያጣ ልጅ የውስጥ ስብራቱ በጣም የከበደ ነው። በለጋ አእምሮው ይህንን ሙሲባ የሚቋቋምበት አቅም የለውም። በዚህ ስብራቱ ላይ የእንጀራ እናት በደልና መድሎ ከታከለበት መከራውን ይበልጥ የከፋ ያደርገዋል። ቀላል የማይባሉ ሴቶች ከሚፈፅሟቸው ከባባድ ጥፋቶች ውስጥ አንዱ የእንጀራ እናት ሲሆኑ በእንጀራ ልጆቻቸው ላይ የሚፈፅሙት ግፍ ነው። የእንጀራ ልጆቻችሁ ማለትኮ ልጆቻችሁ ናቸው። የልጆቻችሁ እህቶችና ወንድሞች አይደሉ?! ሰውኮ እንኳን ለልጆቹ ወንድም እህቶች ቀርቶ በውጭ ላሉ ጓደኞቻቸውም እንክብካቤ ያደርጋል።
ብዙዎች ላይ የሚታየው አያያዝ ግን በጣም በክፋት የተሞላ ነው። ሴቶች ለኣኺራችሁ ስትሉ አላህን ፍሩ። ለልጆቻችሁ ስትሉ ጥንቃቄ አድርጉ። ምናልባትም ነገ ልጆቻችሁ፣ ራሳችሁም ጭምር የነዚህን ተገፊዎች እጅ የምትጠብቁበት ጊዜ ሊገጥማችሁ ይችላል። ከአእምሮ የማይፋቅ በደል እየፈፀማችሁ ታዳጊ ልጆች ላይ ቂምና ጥላቻ አትትከሉ። "የሚያድግ ልጅ አይጥላህ!" ይባላል በሃገራችን። በምግብ፣ በአያያዝ፣ በቅጣት፣ ከአባት ጋር በማጋጨት፣ አእምሮን በሚጎዳ ስድብ የልጅ ጭንቅላት ላይ የሚደርስ ጠባሳ እድሜ ልክ አብሮ ሊቆይ ይችላል። ውጤቱ ደግሞ
1 - በልጆች መካከል መራራቅን ሊፈጥር ይችላል።
2 - ልጆች አባታቸውን ጭምር እንዲጠሉ ሊያደርግ ይችላል።
3 - ተስፋ የቆረጡ ልጆች ከቤት ወጥተው ጎዳና ላይ ሊወድቁ፣ ብሎም ህይወታቸው አጠቃላይ ሊበላሽ ይችላል።
4- አንዳንዴ እስከ ሞት የሚደርስ ጉዳት ሊገጥም ይችላል።
5- የዚህ ሁሉ ውጤት ተውበት ካልተደረገ ኣኺራዊ ጉዳት ስለሚኖረው መጠንቀቅ ይገባል።

ከዚህ በተለየ የእንጀራ እናት መሆናቸው እስከማይለይ ድረስ ከልባቸው እናት የሆኑ ሴቶችም አሉ። እነዚህ በዱንያም በኣኺራም እድለኞች ናቸው። በልጆች የትዝታ ማህደር ውስጥ በመልካም መታወስ ራሱ መታደል ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል።
https://t.me/IbnuMunewor

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

11 Oct, 18:52


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣8️⃣6️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 612፣ ሐዲሥ ቁ.
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

92,075

subscribers

1,239

photos

192

videos