ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 @shewitdorka Channel on Telegram

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

@shewitdorka


ለአስተያየታችሁ @Shedorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 (Amharic)

ለአስተያየታችሁ @Shedorkannከእለታት....📖📚📖📚📖📚 የተለያዩ መዝገበ ቤቶች እና አድራጎች ያገኛሉ! ዶክያመንታችንን ይህን ቦታ በተገኘ በሚከተለው በትምህርት ፊል በመለያ እና ልብስ ዝግጅት ለመቀነስ ይህን ቦታ ይጠቀሙ። ወደ ዝቅ በመጠቀም የተነገረውን እባኮታዊት ቅድሚያችንን ይላኩ። ከእለታት እንደዚህ የፍቅርንና ፊል መተዳደሪያዎችን በደረሰ ጥቅም ውስጥ እንዲደርስ እንጠይቃለን።

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

21 Feb, 17:57


ናፍቆትን ማጠንጠን
መውደድን ማጠንጠን
የሚወዱት ሰው ጋ ዜማ
ለመመጠን


መቅዳት መደምሰስ ነው
የሰው ልጅ አመሉ
ፍቅር አይባልም የተሰማ ሁሉ
የተተኛ ሁሉ


አንዳንዴም እንዲያ ነው
አንዱን በመደምሰስ

ሌላ ደሞ መቅዳት
ባንዱ ለማገገም
ባንድ ለመጎዳት

ህይወት እንደዚህ ነው
እንደዘፈን ካሴት
ሴት የቆረጠውን
መቀጣጠል በሴት !

ኤልያስ ሽታኹን

#_Repost

@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

21 Feb, 15:16


ቆንጆ ክስተት ነበረች....

ሚካያ🥹❤️

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

21 Feb, 12:34


ትዕቢተኛ ሴት አልወድም ፤ ንቀት የሚዘውራት ፤ አፈር እንደሆነች የዘነጋች ፥ አፈር አይንካኝ የምትል አይነት...ነገሩ ትዕቢት በሁለቱም ፆታ ያስጠላል።


ከሆነ ጊዜ በኋላ እኮ ምንም ነን ፥ ምድር አታስታውሰንም ፤ ከበታቿ ቀብራ በተረኛ ታስረግጠናለች ።


በተቻለን መጠን ባለቺን ጥቂት እድሜ የሌላውን ሰው ደስታ ሳንነጥቅ ብናልፋትስ ?



ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

21 Feb, 11:34


ነብሱን ይማረውና ሀያቴ ካሉኝ አባባሎች የማልረሳው አንድ አባባል አለ....

"የቆመ ሁሉ ሰው እንዳይመስልሽ!!!"



So true🙌


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

20 Feb, 16:48


ነገ ማጓጓቱ ሲቀር ፥ በለጋችን ትዝታ ገባን።

በወተት ጥርስ ይረጃል ?

@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

20 Feb, 13:33


📌ደራሲ ስብሐት በሞት ከተለየን ዛሬ 13 ዓመት ሆነው!!

"እኔ የምሞተው በሚወዱኝ ሰዎች ልብ ውስጥ መረሳት ስጀምር ነው" ስብሐት ገ/እግዚአብሔር

ስብሐት ከተለየን ዛሬ 13 ዓመታት ተቆጠሩ።ይህንን ቀን አስታውሶ ስለ ደራሲ ስብሃት አንድም ሰው ሲጽፍ አላጋጠመኝም።በእርግጥም ጋሽ ስብሃት በአንድ ወቅት ስለ"ሞት" እንዲህ ብሎ ነበር"እኔ የምሞተው በሚወዱኝ ሰዎች ልብ ውስጥ መረሳት ስጀምር ነው። ሥጋዬ ሞተ ብለሽ አትዘኝ። በልብሽ ረስተሽኝ በአፀደ ሥጋ ከምንከላወስ ሞቼ ብታስታውስሺኝ ለኔ ምርጫዬ ነው"።

2."እኛ ሟች ነን።ከመሞታችን በፊት ግን ሟች አምላክ አንሁን ፣ ሞትን እንቅደመው ።ተዘጋጀህም አልተዘጋጀህም ጉዳዩ አንድ ቀን ያበቃል።ከእንግዲህ የምትወጣ ፀሐይ አትኖርም።ደቂቃዎችም ፣ ቀኖችም የሉም።ጢምህ ፣ አትንኩኝ ባይነትህ፣ ኩምታዎችህ እና ቅናትህ ጨርሶ ይጠፋሉ።እንደዚሁም ተስፋዎች፣ ፅኑ ፍላጎቶችህ፣ እቅዶችህ፣ የስራ ዝርዝሮችህ ጊዜ ያለፈባቸው ይሆናሉ"።

3. "ሞት ብዙ ጊዜ fiction ነው። ብዙ ጊዜ ተረት ነው። ምክኒያቱስ እስከአሁን እኔ ይህውልህ ስንት ጊዜ ስለ ሞት ሳስብ፣ስፅፍ 74ዓመት ኖሪያለው ውሸት ነበር እስካሁን ድረስ። ሁልጊዜ ሞት ውሸት ነው። ስትሞት ብቻ ነው እውነት የሚሆነው ከዛ በኃላ ደሞ አታውቅም ከሞትክ በኃላ ምን እንዳለ።ሞት እኮ አንዲት ደቂቃ ናት። እንደ መወለድ፤እንዲህ እናበዛታለን ለተረት በተለይ ለኛ እንጀራ ተመቸ ይኸውልህ ስም ዘራን፤ ከሞትኩ በኃላ የሚበቅል ስም። አሁን ከሞትኩ፣ መሞቴን እንጃ እንጂ ከሞትኩ ምኔ ነው እዚህ ያለው? ለሚቀሩት ነው ለእናንተ።"

ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር

(ከሚያዚያ 27 1928 እስከ የካቲት 12 2004)

ከጋሽ ስብሃት መጻህፍት የትኛውን ትወዳላችሁ?

ናቲ ማናዬ

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

20 Feb, 09:20


ጊቢ እያለሁ አንድ ጓደኛዬ "ወንድሜ እኮ  ጓደኛሽ የምትፅፋቸውን ነገሮች አነባለሁ....እኛ ክላስ ያሉ ተማሪዎችም ያነቡላታል...."....አለኝ አለቺኝ....

"ይሄ ትንሹ ወንድምሽ ነው....."....ብዬ ጠየኳት...

"አዎ ምነው...."

"አይ ትንሽ ልጅ ነው ብዬ ነው....የክላሶቹ ልጆችም obviously ትንንሽ ልጆች ናቸው..."

"ምን ሆነሻል ያድጋሉ እኮ...."....ስትለኝ ደንግጬ የሆነች ቁም ነገር ይዤባት አለፍኩ....

ምንም ነገር ባለበት አይቀጥልም...ትንሹ ያድጋል....ትናንሽ ሁኔታዎች ይቀየራሉ....ያቀረቀሩ ቀና ይላሉ...አበቃለት የተባለው ነብስ ይዘራል....እያመሰገንን ወደ ፊት እንቀጥላለን....

ትናንሽ achievements አብረን እያከበርን ትልቁ ጋር እንደርሳለን....thanks for 9k followers🥳

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

19 Feb, 19:13


ያው 100k ስንገባ እንደ ባላገሩ አይድል ዳኛ ተዘጋጅቶ የፅሁፍ ውድድር የማይቀር ቢሆንም እስከዛ ግን የ1k የሽልማት challenge አዘጋጅቻለው ስለዚህ አሪፍ ፅሁፍ ፃፉ ብዙ like ያለውን 1.5k ስንገባ ሽልማት ይኖረናል እስከዛ እየፃፋችሁ

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

19 Feb, 14:02


Repost❤️

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

19 Feb, 14:02


እሱ እረስቶት ይሆናል...ለእኔ ግን እንደ ትናንት ትዝ ይለኛል....ያ መልኩን አስታውሰዋለሁ...ምን መልኩን ብቻ እየያንዳድዋን sily moment አእምሮዬ ውስጥ ቆልፌባታለሁ..ለዛ ነበር አይኑን ባየሁበት ቅፅበት ሁሉ ከእምባዬ ጋር ትንቅንቅ ምገጥመው....

እጄን ይዞ ከትምህርት ቤት ሲያመጣኝ...በዛ እድሜዬ ለእኔ የማይገባኝን የፍቅር ዘፈን ሲያንጎራጉር ድምፁ ውስጤ ቀርቷል...ልቡን አውቀዋለሁ...ከአፉ መጥፎ ቃል ሲወጣ ሰምቼው አላውቅም..."አባትሽ ነኝ...እኔ እስካለሁ ድረስ ላንቺ የሚገባሽን ሁሉ አደርግልሻለሁ..."...ይለኝ ነበር አባት የለኝም ብዬ ሳማርር...ሲያመኝ አይተኛም ነበር...በባነንኩ ቁጥር ቁጭ ብሎ ሲጠብቀኝ አገኘዋለሁ...በጤናዬስ መች አስተኛው መሰላችሁ ...የባጥ የቆጡን እየቀበጣጠርኩበት ቀባጥሬም ሳበቃ መብራት ከጠፋ ፈራለሁ አይጥ ይመጣብኛል ብዬ እበጠብጥ ነበር...እኔን አስተኝቶ መብራት ካላጠፋ አይተኛም ነበር...ደሞ በመሀል ከባነነንኩ ጩኸቴ መከራ....


በመንገድ እየሄድን የኔ ቢጤ ረግጦ አያልፍም..."የሮጠ አይቅደምህ..."...የሚለው ምርቃት አሁንም ድረስ ውስጤ አለ...አውቃለሁ ሁሉንም እረስቶታል...እኔ ግን ሁሉንም አስታውሳለሁ....


የተበጣጠሰ ጫማ ከመጫማቱ በፊት ትንሽ አቧራ እንዴት ይጠየፍ እንደነበር አውቃለሁ...ያቺ የሁላችንም እድሜ...እኮ ያቺ አለምን መቀየር የምንችል የሚመስለን እድሜያችን አለች አይደል...እሱ ያቺ እድሜው ላይ እኔ ደግሞ ልጅነቴ ላይ ነበርኩ...

አንድ ያለኝ ቤተሰብ እርሱ ነው...እናቴን ልምሰል አባቴን አላውቅም...ሰፊው አፍንጫዬ እና እብድ የሚያህል ከንፈሬ ተደምረው ከግንባሬ ፊት  አውራሪነት ጨምሮ ጥቀርሻ የሚያስንቀው ጥቁረቴን ከማን እንደወረስኩ አላውቅም....ወንዝ ዳር ተጥዬ ነው ያገኘኝ.....

"...ቆሻሻ ሁልጊዜ መጥፎ አይደለም..እንደ እኔ ከታደልክ ቆሻሻ ልትጥል ወጥተህ ወርቅ ይዘህ ትመለሳለህ..."...ይል ነበር እኔን ያገኘበትን አጋጣሚ ሲተርክ...

ለዛ ነው መሰለኝ "ወርቅነሽ" ብሎ ስም ያወጣልኝ...ደግሞ እኮ አመሌ..."ይሄን ስም እንደው ምነው ምን አርጌህ ነው...ካልጠፋ ስም...ቲቲ...ሜላት...ሰላም...ኧረ ስንት አለ አንተ ድሮም ስለማትወደኝ ነው"...እለው ነበር በእንጭጭ ጭንቅላቴ..ተማሪዎች በስሜ ሲቀልዱ እኔ ደግሞ ወቀሳውን አዥጎደጉደው ነበር።

አሁን ላይ ለሚያወራው ነገር ከእኔ በቀር ቦታ የሚሰጥ ሰው የለም...ይግባኝም አይግባኝም አንገቴን እያወዛወዝኩ እሰማዋለሁ...ባያስቀኝም ቀልድ ብሎ ለነገረኝ ነገር ጥርሴ ሰንፎ አያውቅም...በሳቅኩለት ቁጥር  "ወርቅ ነሽ የምልሽ እኮ ለዚያ ነው "...እያለ እንደ ልጅነቴ ያቅፈኛል...

ወዳጆቹ መሸሻቸውን ከሱ አብልጬ አማርራለሁ...

"እነርሱም እንደ ዘንድሮ ሽንኩርት ሆኑብን እኮ....ብር ሲጠፋ ጠፉ..."...እላለሁ ክፍት ሲለኝ...በስሱ ፈግጎ እንዲህ ይመልስልኛል.....

"ሰው ሲንቅሽ አትጥዪ...እግዚአብሄር የሚያከብርሽ የመናቅ ፅዋሽ ሲሞላ ነው...".....ተገርሜ አፈጥበታለሁ...

"ኧረ ሽንኩርት የሌላት ሽሮአችን አትብረድ አምጫት...."...ብሎ ከግርምቴ ይመልሰኛል...

ይሄ ነው አንድ ግን ብቻውን ሺህ የሆነ ቤተሰቤ................


አሁን ላይ ሁሉም ታልፎ "ዶክተር ወርቅ ነሽ ተካልኝ" ተብዬ ስጠራ እንደ ድሮ በስሜ አልናደድም...የምናደደው በእኔ ፈንታ እሱ "ዶክተር ተካልኝ" ባለመባሉ ነው...

የምርቃት ጋውኔን ለብሼ ፊቱ ስቆም "አስከበርሽኝ ልጄ ..."...ብሎ ግንባሬን ሳመኝ...ቀጥሎም አቀፈኝ...መልሶ ለቀቀኝና ፀጉሬን ሳመኝ...የእንባው እርጥበት ቆዳዬ ጋር ደረሰ...ተመልሶ ደግሞ አቀፈኝ...የሚያረገኝ ግራ ገባው...ፊቱ ፀዳል መሰለ...

"የመናቅ ፅዋዬ ሞላ ልጄ...አስከበርሽኝ ክበሪ...የሮጠ አይቅደምሽ...አግኝተሽ አትጪ...."....መረቀኝ....እኔ ግን "የሮጠ አይቅደምሽ".... ጋር ነኝ....አልረሳውም ነበር ማለት ነው።



Shewit




https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

19 Feb, 05:12


My besti once said...."እንጀራ መሻገት ሊጀምር ሲል ታሞቂዋለሽ...አይ ነገ ላሙቀው ብትዩ መሻገቱ እየባሰበት ይሄዳል....ሳታሞቂው በቆየሽ ቁጥር መበላሸቱ ይብሳል....አሙቀሽ መብላት የምትችይውን እንጀራ ባለማሞቅሽ ምክንያት ትጥይዋለሽ....አእምሮም እንደዛው ነው....ማዳን እየቻልሽ እስኪሞት ከጠበቅሽው ይጥልሻል...."


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

18 Feb, 18:42


"ለምንድን ነው የማትወጂውን ወተት አይንሽን ጨፍነሽ የምትጠጭው...."

"አንድ ጓደኛዬ ውስጡ ስላለው nutrient ነግራኝ....".....ሳውቃት ለራሷ እንደነገሩ ነበረች....ካልሞረሞራት አትበላም....በባዶ ሆዷ ውስኪ ስትጨልጥ ለጉበቷ አታዝንለትም ነበር....ፍቅር ከጀመርን በኃላ ነው ስለ organዎቿ አብዝታ መጨነቅ እና መጠንቀቅ የጀመረችው.....


"ቶሎ እንዳላረጅብህ....አሮጊት አገባ እንዳትባልብኝ....".....ስትለኝ እድሜዬን ጠላሁት....የሰባት አመት ታላቄ ናት....እያወቅኩ ነው ያፈቀርኳት......እኔ ስመረቅ ስል እሷ ደግሞ ታናሽ እህቷን ስታስመርቅ ነው የተዋወቅነው....እውነቱን ለመናገር እድሜዋን ካላስታወሰችኝ በቀር ትዝ ብሎኝ አያውቅም....ስሜ እስኪጠፋኝ አፈቅራታለሁ...

አንድ የምፈራው አባባል አለቻት...."ተፈጥሮ ባለጌ ነው....ለወንድ ያደላል....".....ትላለች...."ይብራራ" ብያት ነበረ...

"እድሜያችሁ ሲጨምር ይበልጥ የሚያምርባችሁ ነገር አለ....ያናዳል...."....ብላ ሳቅ አለች....

"አቤት ምቀኝነት....".....አብረን ሳቅን....

"እስከመቼ ትወደኛለህ" ላለቺኝ የመለስኩላት "እስከዘላለም".... ነበር....."እስከዛሬ እስከአሁን እወድሻለሁ" ነው ሚባለው ብላ አረመችኝ እንጂ....

"ነገን አታምኚው....እንዴት አምነሽ ነው የምትጠብቂኝ...."....ብያት አውቃለሁ....

"ተይዤ....".....መልሷ ነው....

እሷን በፍቅር ማሰር...በእሷ መፈቀር ምን ያሀል ደስ እንደሚል....እንደመጠበቅ ያለ እድለኝነት አለ.....?....በመጠበቅ ውስጥ መታመን አለ....መታመን ደግሞ ደስ ይላል...በተለይ በእሷ መታመን....ታምነኛለች....


በሀያ ስምንት አመቴ ድል ባለ ሰርግ አገባኃት...."ታላቁ ሳትሆን አትቀርም....".....ተባለላት....."እናቱን አገባ...."...ተባለልኝ...."አሳድጋው ነው ያገባችው መቼስ....".....ተባለላት...."እንደው ትወልድ ይሆን...."....ያለችው እናቴ ናት....."ለብሯ ብሎ ነው አሉ...."....ያለም አልጠፋም.....እነዚህን ሁሉ ሰዎች በአመቱ ክርስትና ጠራናቸው.....


በድጋሚ ፍቅር ውሎ ይግባ....


Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

18 Feb, 09:58


መስፈርቷ

ልጅ እያለሁ አብረን መርካቶ ያደግን ታየች የምትባል የልብ ጓደኛ ነበረችኝ። የሆነ ጊዜ ላይ ራጉኤል ጋር የነበረው የአባቷ ጨርቃ ጨርቅ ሱቅ በጣም ታዋቂ ሆነ። ከዛ ብዙም ሳይቆይ አለፈላቸውና መርካቶን ለቀው ኦልድ ኤርፖርት የሚባል ሰፈር ቤት ሰርተው ገቡ። እኔ እዛው መርካቶ ጭቃ ላይ እየተራገጥኩ አንበጣ ሳባርር ታየች ቢኪኒ የሚባል ጡት ማስያዣ ተገዝቶላት መዋኝት ተማረች። አልፎ አልፎ ቤታቸው ስጋበዝ ምቾቷ ይጋባል። የእማማ ራድያ የሽንት ቤት ፍሳሽ በግቢዬ የሚያልፈው እኔ፣ የእነ ታየች ግቢ ውስጥ ያለው ጋርደን ላይ ተንጋልዬ መጽሐፍ እያነበብኩ ስታይ፣ አይ ውበት። አመሻሽ ላይ ወደ መርኬ ለመመለስ ገብሬል ጋር ያለው ታክሲ ውስጥ ስገባ፣ መጽሐፌን ጭብጥ እድርጌ ይዤ ከስፊው ህዝብ ጋር ስገፋፋ፣ ጎበዝ ለካስ ምቾት ይተንናል
!።

ጥቂት አመታት አልፈው እኔ በ"ክልክል" አጥር ውስጥ፣ ፍቅርኛ መያዝ በማይፈቀድልኝ አስተዳደግ ውስጥ ስዳክር ታየች ሳምሶን የሚባል እንደሷ
በምቾት የሚንሳፈፍ የከንፈር ወዳጅ ያዘች። ህልምና መጽሐፍን የሰጠኝ እግዚያር ግን ደግ ነው። አሁን ደሞ ቸርነቱ በዝቶ የእኔ ከንፈር እንኳ በእውን ባይሳም የጓደኛዬ የታየች ከንፍር ሲሳም ሊያሳየኝ! እሱ ምን ይሳነዋል!

አንድ ቅዳሜ ታየች ደወልችልኝና ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ሰነዘርች። "ቲጂዬ ዋና ትችያለሽ?".. ከሳምሶን ጋር ጊዮን ሆቴል ሊዋኙ ተቀጣጥረው ኖሮ አብሬያቸው እንድዝናና መጋበዝዋ ነበር። ምቾቷ አሳውሯት ነው እንጂ የት ነው እኔ መርካቶ ውስጥ ዋና የምማረው? ታደለች የምትቸረችረው የከሰል ሐይቅ ውስጥ? ወይስ ወ/ሮ የሻረግ ጠላ ቤት ያለው ማሰሮ ውስጥ? ታየች ፌዝ ተማረች። ታየች ዋና ተማረች። ከመርካቶ ቦይ በኮንጎ ጫማ ተንደርድራ በቢኪኒ ጊዮን ሆቴል የውሃ ገንዳ ውስጥ ተጠመቀች።

እሁድ ጠዋት የከንፈር ወዳጆቹን አጅቤ እነሱ ሊዋኙ እኔ ፎጣ ልጠብቅ ጊዮን ሆቴል ደረስን። ጁስና ኬክ ታዞልኝ እነሱ ውሃ ውስጥ ሲንሳፈፉ እኔ በእነሱ አለም ውስጥ ስንሳፈፍ፣ እንሱ በአራት ነጥብ የታጠሩ ደማቅ አርፍተ ነገሮች። እኔ ገና ያልተብራራው ተከፍቶ ያልተዘጋ ቅንፍ። ውሃ ሲረጫጩ ደስ ሲሉ። ይጎነታተላሉ። ኦ ቢኪኒዋ! አረንጓዴ ባለአበባ። ሳምሶን ከጀርባዋ ቆሞ እሷ ጸጉሯን ወደ ላይ ሰብስባ የላላውን የብኪኒዋን ገመድ እያሰረላት ሲጠጋት እሷ እየሳቀች ከወሲብ እንፋሎቱ ስትሸሽ። ሲያስቀኑ። በቀረብልኝ በጥቂት ደቂቃዎች ነው ኬኩንም ጁሱንም የሰለቀጥኩት። እንዲህ ያለው ምግብ በነጻ ሲገኝ ሰጪው ሃሳቡን ሳይቀይር ቶሎ ማውደሙ ከልምድ የመጣ ነው። የመርካቶ ቅደም ተከተሉ መጀመርያ ረሃብ ማስታገስ ከዛ ስለ ታየች የከንፈር ዕጣ ፈንታ ማሰላሰል።

በጨረፍታ እያየኋቸው ደስታቸው ተጋባብኝ። ያሽካካሉ። ፊታቸው ያብረቀርቃል። ሳምሶን ብዙ ሳምሶኖች ቢሆን፣ እኔን ጎትቶ ውሃ ውስጥ የሚያጠልቀኝ ሌላ ሳምሶን ከዚህኛው ላይ ተቆርሶ ቢመጣ። ሮዝ ቢኪኒ ቢኖረኝ። የቢኪኒዬ ገመድ ቢላላ፣ ሳምሶን ሊያስርልኝ ቢጠጋኝ፣ በወሲብ እንፋሎቱ እጠመቅ ነበር። መጣበቅ፣ መጠመቅ፣ አንድ መሆን። ታየች ለምን ሸሸች?

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያላሰብኩት ክስተት ተፈጠረ። ታየች እየተጣደፈች ከገንዳው ስትወጣ አየኋት። ፊቷ ላይ ብስጭቷ ይነበባል። ዞር ብዬ ሳምሶንን ቃኝሁት። ግራ ገብቶት ፈዞ ያያታል። አጠገቤ ስትደርስ በፍጥነት ፎጣዋን አንስታ ገላዋን እያደራረቀች "ቲጂ ቶሎ መሄድ አለብን ተነሽ" ብላኝ ሳትጠብቀኝ ወደ ልብስ መቀየሪያው ክፍል አመራች። "ይህ ቀዥቃዣ ወሲባም ምን አድርጓት ይሆን?" ብዬ እያሰላሰልኩ ተከተልኳት። ለባብሳ ወደ ታክሲ ስናመራ የሳምሶን አብሮን አለመሆን ግራ እንደገባኝ ስታውቅ "የኔ እና የእርሱ ነገር አብቅቷል" ብላ በረጅሙ ተነፈሰች።

እንዴ? ይህ የተመቸው ቦንቦሊኖ የመሰለ ልጅ፣ ለመላው የመርካቶ ኮረዳ ኬክና ጁስ የመግዛት አቅም ያለው ሳቂታው የሃብታም ልጅ፣ ቢኪኒዋን ወሲብ በተሞላበት ርህራሔ ያሰረላት ስሱ ሳምሶን ምን አድርጓት ይሆን? ልምድ ያካበቱ የሚመስሉ ከንፈሮች እንዲሁ በዋዛ ሊቀሩ?
"ምን እንዳደረገ ታውቂያለሽ?" አለች እየተብከነከነች። "የውሃው ገንዳ ውስጥ፣ እዛ የምንዋኝበት ገንዳ ውስጥ፣ አፍንጫውን ጨምቆ፣ በሃይል እንፍፍፍፍፍ ብሎ ንፍጡን ስቦ ካወጣ በኋላ እዛው ውሃ ውስጥ አይወረውረው መሰለሽ? ከዛ ደሞ እጁን መለቃለቁ! አይኑን ማየት አልፈልግም" ብላ አስረግጣ ነገረችኝ።

ወንድሜ ሆይ፣ የታየች መስፈርት ግልጽ ነው። መርሴዲስ ቢኖርህ፣ ተጫዋች፣ አማላይ፣ ሳቂታ አፍቃሪ ብትሆን፣ ነገር ግን ንፍጥህን በየቦታው የምታዝረከርክ ከሆነ፣ ከታየች ጋር እድል አይኖርህም። የህዋ ተመርማሪ ብትሆን፣ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ብትሆን፣ ምን አለፋህ የሮም ከተማን የቆረቆርከው መሃንዲስ አንተ ብትሆን፣ ግን ህዝብ የሚዋኝበትን የውሃ ገንዳ በንፍጥህ የምትበክል ዝርክርክ ከሆንክ የታየች አጸያየፍ ከእግዚያር ፍጥረት ሁሉ የረቀቀ ነው


ትግስት ሳሙኤል

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

17 Feb, 12:21


Ye nanin challange bzi tshuf teklaklnal🥳.....


Tshafiyan geba geba eyalachu....

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

17 Feb, 12:21


እንደነገርኳችሁ ከተለመደው የchallenge ዘዴ ለየት ያለ ነው አላልኳችሁም?!

Anthology ይባላል በፈረንጅኛ ወደእኛ ስናመጣው በተለያዩ ደራሲዎች የተፃፈ የአጭር ልብወለድ ወይም ወግ ስብስብ ነው።

እኛንስ እንዳንፅፍ የሚያግደን ማነው?! የእኛን ከተለመዱት የአጭር ልብወለድ ወይም ወግ የሚለየው ነገር የሁላችንም ፅሁፍ የሚጀምረው በተመሳሳይ አረፍተ ነገር መሆኑ ነው

"በመጨረሻም እስከዛሬ ያመንኩት በሙሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት" ይላል የመጀመሪያው አረፍተነገራችን

የፅሁፉ ርዝማኔ ከ500 ቃላት ባይበልጥ ይመረጣል

ቻናላችን 8000 subscriber ሲደርስ ፅሁፍ ማስገቢያ ጊዜው የሚጠናቀቅ ይሆናል

ፅሁፍ ለመላክ
@exquisiteperfume

ናኒ


ለመፃፍ ዝግጁ ናችሁ
🙋‍♀🙋


https://t.me/justhoughtsss

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

17 Feb, 07:34


"በመጨረሻም እስከዛሬ ያመንኩት በሙሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት....

የተበቀለኝ ምንም ማድረግ የማልችልበትን ጊዜ መርጦ ነው....የታሰርኩበትን ጊዜ ጠብቆ ቀጣኝ....".....አለችኝ....

"እንዴት....".....

"ስተሳሰር ጠብቆ የፈሪ ዱላውን አቀመሰኝ....የፈሪ ዱላ ያማል....የቀመሰ ነው የሚያውቀው....ባለቀ ሰአት ነው ዱላውን ያነሳው....ባለቀ ሰአት ነው ሁሉም ነገር ውሸት እንደነበር የገባኝ....".....ፊት ለፊቷ ያለውን መጠጥ በአንድ ትንፋሽ ፀጥ አድርጋው ቀጠለች....

"ለስድስት ሰአት ቀጠሮ ዘጠኝ ሰአት ስደርስ በትዕግስት ሲጠብቀኝ ትዝ ይለኛል....ያኔ ብዙ አማራጭ ነበረኝ....'እገሌን ከእገሌ' እያልኩ የማወዳድር ሴት ነበርኩ....ትዕግስቱን ከሌሎች ጋር አወዳደርኩት....በለጣቸው....ትዕግስተኛ ሳይሆን ጊዜ ጠባቂ እንደነበር የገባኝ ዘግይቶ ነው...

'ግን በምን በለጥካቸው....'....ብለሽ የምትዘፍኚለት ሰው አልነበረም....በሁሉም ይበልጣቸው ነበር....

ከራሴ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ያስደስተኝ ነበር....ለብቻ መጠጣት....ለብቻ ወክ ማድረግ....ለብቻ ማሰብ....ከራሴ ጋር  ለመሆን ብዬ ጊዜ እነፍገው ነበር....አሁን ከሌሎች ጋር ለመሆን ብሎ ጊዜ ይነፍገኝ ጀመር....

ያኔ ስራዬን አሳምኖኝ ከመልቀቄ በፊት አምሽቼ ስገባ እራት ሰርቶ በረንዳ ላይ እንደ ቲያትረኛ እየተንጎራደደ የሚጠብቀኝ ሰው የለም.....አሁን ቤቱን ለቤርጎነት ብቻ ነው የሚጠቀመው....


የማጠፋው ጥፋት የልጅ ነበር....እሱ እንደአባት ይቅር ይለኝ ነበር....ለዛ እኮ ነው አባት ብዬ እጠራው የነበረው....አሁን አምስተኛ ልጄ ሆኖ አረፈው.....

ራሴን ከጣልኩበት በኃላ ተንሸራተተ...ለመንሸራተት ግን ጊዜ ጠብቋል....እግሬን በአራት ልጆች ከጠፈረኝ በኃላ ፈቀቅ አለ....


ከረፈደ ነቃሁ....በመጨረሻም እስከዛሬ ያመንኩት በሙሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት...".....ብላኝ ጨረሰች።


Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

17 Feb, 05:50


መጨረሻ


"ከኔ ጋር ትሄጃለሽ??"አሉኝ.... ግራ ገባኝ .....መመለስ ይኑርብኝ ወይስ ዝም ልበል ...ልሳቅ ....ግራ ገባኝ.... ሌሎቹ እየቀለዱ ስለመሰላቸው ፈገግ ፈገግ አሉ...... ሴትየዋ ግን ምንም አይነት የገፅታ ለውጥ አላሳዩም .... እኔም ምለው ግራ ገብቶኝ እንደቆምኩ አይን አይናቸውን ማየት ያዝኩኝ.... የሴትየዋ ፊት ላይ ምንም አይነት ለውጥ ሲያጡ ቀልድ አለመሆኑ ገባቸው መሰል መሳቃቸውን አቁመው እነሱም ግራ ተጋቡ...... አሳዳጊዬ በንዴት"እሺ ብትል ምን ሊያበሏት ምን ሊያጠጧት ነው?" ብላ ተቆጣች... በሷ  ሀሳብ ሌሎቹም መስማማታቸውን ግማሹ አንገት በመነቅነቅ ግማሹ "እኮ" "እውነት ነው" በሚሉ ቃላት አገዟት ......ሴትየዋ ፊት ላይ አሁንም ለውጥ የለም ከራሴ ጋር ታግዬ "እሺ" አልኩኝ...... ያኔ የሴትየዋ ፊት ፈገግ አለ.... ብድግ ብለው ተነስተው ወጡ እኔም ተከትዬ ወጣው.... ውስጤ ብዙ ጥያቄ ነበረኝ የት ነው ምንሄደው?? የት ነው ሚኖሩት?? ከዚ የባሰ ሁኔታ ይገጥመኝ ይሆን?? ማን ናቸው?? ብዙ ብዙ ግን ምንም አላልኩም እሳቸውም ዝም ብለው ፊት ፊት ይሄዳሉ እኔም የውስጤን ጥያቄ በውስጤ ይዤ ዝም ብዬ ተከተልኳቸው


አንዲት ትንሽዬ ቤት ስንደርስ ቆሙ... የውጪውን መዝጊያ ታግለው ከፍተው ወደ ውስጥ ዘለቁ.... እኔ በር ላይ ቆሜ ግቢ እስኪሉኝ መጠበቅ ያዝኩኝ.... እሳቸው አለመግባቴን ተመልክተው በእጃቸው ግቢ የሚል ምልክት ሰጡኝ እና ዘልቄ ገባው..... ቤታቸው ትንሽዬ ናት ውስጧ ብዙ ዕቃ የለም... አንድ አልጋ እና ትንሽዬ ጠረጴዛ ይታየኛል... ሳይቀመጡ በመጋረጃ ወደተሸፈነ ቦታ ገብተው ንኬል በእጃቸው ይዘው ተመለሱ.... "ጠምቶሽ ይሆናል እስኪ ይሄን ጠጪ" ብለው ወደእኔ እጃቸውን ወደ እኔ ዘረጉ አፈፍ አድርጌ ተቀብዬ ጠጣሁት.... መጨረሴን ሳይ "ጠምቶኝ ነበር እንዴ??" አልኩኝ ለራሴ...."ቤቴ ጠባብ ነው አይደል?" አሉኝ አልጋው ላይ እየተቀመጡ... ሁኔታዬን ስላሳበቀብኝ አንገቴን ደፍቼ ፈገግ አልኩኝ... የሃፍረት ሳቅ... ቁጭ በይ አሉኝ ከጀርባዬ ወዳለው ወንበር እያመለከቱ አለማየቴ ገረሞኝ ሄጄ ቁጭ አልኩኝ... ጥያቄ አልጠየኩም ብቻ ቀና ብዬ አያቸውና አጠናቸዋለው አይናቸውን ወደ እኔ ሲያደርጉ መልሼ አንገቴን ደፋለው...

" ብዙ ጥያቄ ይኖርሻል መቼስ አደል?? ብለው ፈገግ አሉ  ፈገግ ከማለት ውጪ ምንም አላልኩም.... ቀጠሉ "ያኔ ልጅ እያለሽ እናትና አባትሽ ለማን እንስጣት ብለው ሲጨነቁ ወስጄ ላሳድግሽ ፈልጌ ነበር.... ግን ደሞ ሰው ሁሉ ለአሳዳጊሽ እንድትሰጪ ስለፈለጉ ዝም አልኩኝ.... በዛ ላይ እንደምታይኝ ደሃ ነኝ ማበላሽ ማጠጣሽ ማለብስሽ ነገሮች አሳሰቡኝ እና ዝም የማለት ሃሳቤን እንድደግፈው አደረጉኝ እና ዝም አልኩኝ.... አሁንም የተሻልኩኝ ሆኘ አይደለም ግን እየኖርሽ አልመስል አለኝ...  ባየሁሽ ቁጥር ዝም ማለቴ ፀፀተኝ.... ይሄውልሽ ልጄ አሁን ትንሽ ልጅ አይደለሽም ሥራ መስራት ትችያለሽ.... ስለዚህ ሥራ እናፈላልግ እና ተቀጥረሽ ትሰሪያለሽ በምታገኚው ገንዘብም እራስሽን ታስተዳድሪያለሽ..... እኔ ካንቺ ምንም አልፈልግም ግን አንቺን ባስፈለኩሽ ጊዜ ሁሉ ከጎንሽ አለሁኝ.... አሁን ያለችውን ቀማምሰን ትንሽ ተኚ ነገ ጠዋት ተነስተን ሥራ እንፈልጋለን" ብለው በረጅሙ ተንፍሰው ዝም አሉ ውስጤ የነበሩት ጥያቄዎች በሙሉ ዝም አሉብኝ..... ተነስቼ እያገዙኝ እራታችንን አቅርቤ በላን....አልጋቸው ላይ እቅፍ አድርገው አስተኙኝ... እንባዬ እየተናነቀኝ እቅፋቸው ውስጥ እንቅልፍ ወሰደኝ....


ጠዋት እንዳሉት ተነስተን ሥራ ማፈላለግ ያዝን.... ቀድመው ያናገሩት ምግብ ቤት ሰውዬ ነበርና በአስተናጋጅነት ሊቀጥረኝ ተስማማን በነጋታው ሥራ ጀመርኩኝ..... ሁሉም ሰው ታሪኬን ስለሚያውቀው ሁሉም በሃዘኔታ እና በፍቅር ነበር የሚያየኝ በስራዬም ቀልጣፋ ስለነበርኩኝ አለቃዬ ከደሞዜ ላይ ትንሽ ብር ጨመር እያረገ ነበር ሚሰጠኝ..... ተስተናጋጆቹም ቢሆን የተወሰነ ቲፕ ስለሚሰጡኝ ከኔም አልፌ እማማንም ማገዝ ጀመርኩኝ..... ከቤት ስወጣ ባዶ እጄን ስለነበር ልብስም ሆነ ጫማ ቅያሪ አልነበረኝም ይሄን ያዩ አብረውኝ የሚሰሩ ሰዎች ያላቸውን እየሰጡ ያግዙኝ ነበር..... ከትንሽ ጊዜ በዋላ ግን የራሴን ልብስ ጫማ የእማማን አንዳንድ ነገር መግዛት ጀመርኩኝ.... እማማ አሁንም ከጎኔ ነበሩ..... አስፈቅጄ ነበር እማማ ማለት የጀመርኩት..... ሳስፈቅዳቸው በጣም ነበር ደስ ያላቸው..... አሳዳጊዬ "አሳድጌ አሳድጌ ስትደርስ ጥላኝ ሄደች" ብላ እንደምታወራ ስሰማ ፈገግ አልኩኝ .......አልጠላትም አልታዘብኳትም.... የሆነ የሕይወት ክፍሌ ውስጥ ነበረች.... አሁን ያለሁበትንም እንዳመሰግን አድርጋኛለች.... አሁን ያለሁበት ሕይወት ህልሜ ነበር.... ለሰዎች እንደዛ ብዬ ስነግራቸው ይገረማሉ "ይሄ አሁን ምን ሕልም ይሆናል"... ይላሉ ለኔ ግን ህልሜ ነበር እናም ፈጣሪን አመስግኜ አልጨርስም ስላሳካልኝ የሕልም ትንሽ የለም....... ያሳለፍነው ሕይወት ነው ለህልማችን ምክንያት ሚሆነው.... ትንሽም ይሁን ትልቅ... ከባድም ይሁን ቀላል.... በፍርሃት ወይም በጊዜ ወይ ደሞ በገንዘብ አልያም እድሜ ህልማችሁን ከማሳካት ያስቆማችሁን ፈጣሪ  አስወግዶ ህልማችሁን ለማሳካት ያብቃችሁ.....



ጨረስኩኝ


kalkidan

http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

16 Feb, 19:41


🔥🔥 ዴርቶጋዳ

ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ

የመጀመሪያ ዙር መጽሐፋችን እነሆ...

የምናዉቀዉን ከማጋራት ባሻገር አጓጊ ሽልማቶችም እናንተን ይጠብቃሉ፨

ቻናላችን 1500 subscriber ሲደርስ ጽሑፍ ማስገቢያ ጊዜዉ የሚጠናቀቅ ይሆናል፨

ጽሑፍ ለማስገባት @bluessoulmate

https://t.me/yeesua_queen

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

16 Feb, 19:05


የኛ ትዉልድ የኑረት መልክ ፍጥነት ይበዛዋል፨ሁሉ ነገሮቻችን ይፈጥናሉ፨በዚህ የሰዉ ልጅ ፍላጎት የተነሳ የገበያዉም ትኩረት ፈጣንና:የማያስጠብቁ ነገሮችን ማቅረብ ሆኗል፨ሰዓቱ እንኳን ገና ሳይነጋ እየጨለመብን የተቸገርን ጥቂቶች አይደለንም፨በዚህ መኃል ከደበዘዙ ልምዶቻችን አንደኛዉ መጻሕፍትን ማንበብ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነዉ፨

እናም ሃሳቤ ምን መሰላችሁ፨አንዳችን ያለንን ለሌላኛችን ብንሰጣጥ ማጣታችንን አይቀንስም ብላችሁ ታስባላችሁ?ስለዚህ ቤታችን ዉስጥ challenge ልንጀምር ነዉ፨

ነገሩ ያነበብናቸዉን መጻሕፍት አጠር ያለ ዳሰሳ ማዘጋጀት ሲሆን አንዴ ብቻ የሚደረግ ሳይሆን የተለያዩ መጻሕፍትን እየመረጥን በዙሮች የሚቀጥል ይሆናል፨

ዉድድሩ በተመረጡት መጻሕፍት ላይ
✍️የመጽሐፉን  ጠቅለል ያለ ይዘትና ጭብጥ
✍️መጽሐፉ በእናንተ እይታ ያላችሁን ሃሳብ
✍️ከመጽሐፉ የወደዳችሁትን ክፍልና የሰጣችሁን ግንዛቤ 
በአጠቃላይ መጽሐፉን ይገልጻል የምትሉትን አጠር ባለ መልኩ መጻፍ ነዉ፨

ዳኞችም እናንተዉ ናችሁ፨አሪፍ ገልፆታል ለምትሉት: ጸሐፊዎች ለራሳችሁም ድምጽ በመስጠት ጭምር ብዙ የተወደደዉን እንሸልማለን፨

ለዛሬ የተመረጠዉን መጽሐፍ ማታ 03:00 የምናሳዉቅ ይሆናል፨

ዝግጁ ናችሁ?

https://t.me/yeesua_queen

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

16 Feb, 16:13


Long story short....


"ዛሬ መጥቶ ነበር እና ጥንብ ርኩሱን አወጣሁት የት አባቱ...."...ያለቺኝ my besti ናት....ገና graduate አላደረገችም....6 mnz ምናምን ይቀራታል....

"ኧረ ተይ....ብታይው አይሻልም....ስልሽ ምን አይነት ሰው እንደሆነ ምናምን...."....ባይዋ እኔ ነኝ....ተመርቄ ስወጣ አንዷ ጓደኛዬ ወልዳ አንዷ ደግሞ አግብታ የጠበቀችኝ እኔ...."ተይ ስታድጊ ይቆጭሻል...."....ልላትም ነበር....በእርግጥ እድሜያችን የወራት ልዩነት ነው ያለው....እሷ ያልገባት ነገር ሰዉ እንዴት እያፈጣጠነው እንደሆነ ነው.....

"ባክሽ ተይው....እንደውም እልህ ነው ማስይዘው....ብሶበት ቁጭ ይላል ታያለሽ"....

ጓደኛዬ አድጋለች....ግን አላደገችም....

"እልህ ያልቃል.....ከዛ እልሁ ሲያልቅ ጨረቃ ላይ ምትቀሪው አንቺ ነሽ....ይልቅ እንደ ትልቅ ሰው ይሆነኛል አይሆነኝም ሚለውን እይው....ከፈለግሽ ማለት ነው...."...ብያት ተዘጋ...


ይሄ conversation ውስጤ የሆነ ጥያቄ ፈጠረ....
የምር ግን እልህ ያለቀብን እና ግራ የገባን ሰዎች የለንም....የሚያልቅ ነገር የምናሳድድ እድሜያችን አድጎ ውስጣችን ገና እምቦቅቅላዎችስ የለንም....ብቻ አልቆ የምንጎዳበት ወይ ሌሎችን የምንጎዳበትን ነገር መልቀቅ ያቃተን የለንም.....



Shewit


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

16 Feb, 15:13


ለምን??......ትጮሀለች..... ትቆጣለች..... እብድ ትሆናለች ብላ ስትጠብቅ ይሄንን ነበር የጠየኳት..... ... ምክንያቷን ብቻ ነበር ማወቅ የፈለኩት..... ይቅር እንድላት... እሷም እንደሌላው ሰው ናት ብዬ እንዳላስባት..... እንዳልጠላት... ለምን ብዬ ጠየኳት.... ለምትወደው.... የኔ በምትለው ሰው ....ላይ ያለን መብት ድርጊታቸው አይደለም ምክንያታቸው ነው.... ጥለውን ቢሄዱ.... ቢያረፍዱ.... ባይደውሉ.... ባይመጡ.... ያ አይደለም የኛ መብት....... የኛ መብት ምክንያታቸው ነው....... ያረፈዱበት ምክንያት.... የቀሩበት ምክንያት..... የከዱበት ምክንያት.... ያ ነው ለኛ ያላቸው ቦታ የሚገልፀው ምክንያታቸው ነው... ለሁሉም እንደዛ ነው የዓለም ትልቅ ጥፋት መግደል ቢሆን እንኳን የሚያስፈርድብክ መግደልክ ሳይሆን የገደልክበት ምክንያት ነው.... እራስን ለመከላከል ከሆነ በነፃም ልትለቀቅ ትችላለህ.... ለዛ ነው የጠየኳት ለሷ ያለኝን ቦታ እንዳላጣ.... ለራሴም ሌላ የልብ ስብራት እንዳልጨምር .....እንዳልጠላት.... እንዳልርቃት.... እንዳልተዋት ነው የጠየኳት....መብቴን ነው የጠየኳት....ለምን??..

✍️kalkidan


http://t.me/storyweaver36
http://t.me/storyweaver36
http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

14 Feb, 13:47


"የተበቀለኝ ምንም ማድረግ የማልችልበትን ጊዜ መርጦ ነው....የታሰርኩበትን ጊዜ ጠብቆ ቀጣኝ....".....አለችኝ....

"እንዴት....".....


valantine ቀን ይለፍና ይብራራል....😁


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

14 Feb, 10:34


በህይወታችን ከሶስት ሰዎች ጋር በፍቅር እንወድቃለን: ሶስቱም የራሳቸው ምክንያት አላቸው ይላሉ

👇🏾

የመጀመርያው ፍቅር በአፍላ እድሜ ወቅት የሚከሰት ነው: ድንገት መጥቶ እፍ ያስብልና ከዚያም እዚህ ግባ በማይባል ምክንያት መራራቅ ይፈጠራል

ከቆይታ በኃላ በእድሜ ስንበስል መለስ ብለን ስናየው ፍቅር እንደነበር ራሱ የምንጠራጠረው አይነት ስሜት ነው: ግን በወቅቱ ፍቅር እንደሆነ ተሰምቶን አልፏል

.............

ሁለተኛው ፍቅር ከባዱ ነው

በፍቅር ከወደቅነው ሰው ጋር እፍ ማለት ብቻ ሳይሆን ብዙ ህመም እና ስብራትም ይዞ የሚመጣ ነው:: እንዲህ አይነት ፍቅር ስሜቱ ሃያል ሲሆን ቁርኝቱ ከመክረሩ የተነሳ ከዚያ ሰው ጋር መለየት የሞት ያህል የከፋ ይመስለናል

ስለዚህ በዚህ ፍቅር የተጎዳነውን ስብራት በምንጠግንበት ሂደት "ከዚህ ወዲያ ልቤን ብሰጥ እርም" ወደሚል አጥር የመስራት ውሳኔ ውስጥ እንገባለን: ጠባሳው ትልቅ ሊሆን ይችላል

ስለዚህ ተጠራጣሪ እንሆናለን: በቀጣይ ፍቅር ሲይዘን እንዴት እንደምንሆን ቀመሩን እንወስናለን: ከስሜታዊነት ፈቀቅ እንላለን

.................

ሶስተኛው ፍቅር መምጫው ሳይታወቅ ድንገት የሚመጣ ነው ይሉታል

ይህንን አይነት ፍቅር ብዙም ለማግኘት ተደክሞ ሳይሆን ድንገት የሚይዘን ነው: ድንገት የገነባነውን ግድግዳ ሁሉ የሚያፈራርስ አይነት ፍቅር ይሉታል

እዚህ ጋር ካፈቀርነው ሰው ጋር የሚኖረን ግንኙነት "ከወደዱማ ከነግሳንግሱ" አይነት ሲሆን አንዱ ሌላውን እየቀረፀ የተሻለ ማንነት የሚሰራበት ነው

ጠዋት ከእንቅልፍ ስትነሳ "Good Morning my Sunshine” የምትልለት እና ማታ ስትተኛ ደግሞ "Good Night Darling” ብለህ ቀንህን ጀምረህ ቀንህን የምታሳርግበት

👇🏾

Happy Valentine’s my People

Happy Valentine’s my Love ❤️
🙌🏼

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

14 Feb, 07:44


አብቅቷል ካልሽኝ
ቆለፍኩት ካልሽኝ

ሳንኳኳ አልኖርም የልብሽን በር
ግን እንዳይቆጨኝ አንዴ ንገሪኝ
የሰለቸሁሽ የቱ ጋር ነበር ?

@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

13 Feb, 17:50


ዝም አለች.... አንገቷን ደፍታ መሬት መሬት እያየች በእጇ ቀሚሷን ጨምድዳ ይዛ እየፈተገች ....ዝም አለች.......አስተማሪው ደጋግሞ ይጠይቃታል "ነሽ አደለሽም?" ይላል ይቀጥልና አንገቷን መድፋቷን እያየ "ቀና በይ ንቀት ነው?" እያለ ያንባርቃል እሷ ግን ቀናም አላለች መልስም አልሰጠች ዝም..... እኛ ተሰብስበን ከሷ ትንሽ ፈንጠር ብለን ቆመን ላደረግነው ጥፋት አላደረግንም ብለን እንጮሀለን..... እሷ ግን ለሌለችበት ላላደረገችው ነገር ስትጠየቅ አንገቷን ደፍታ ዝም.....

ሁለት ተማሪዎች ተጣልተው ....በለው በለው ....ብለን ካባባስን በዋላ ጩኸታችን ከውጪ ተሰምቶ አስተማሪው ሁሉ ምን ሆኑ ብሎ ግልብጥ ብሎ ክፍላችን ይገባሉ... እነሱን ስናይ በለው በለው እያልን ያደባደብናቸውን መሃላችን ደብቀን አላየሀንም ብለን ድርቅ አልን .....ሁላችንም ግማሹ ወንበር ላይ ግማሹ ዴክስ ላይ ቆመን ስንጮህ እሷ ብቻ ነበረች ፀጥ ብላ የተቀመጠችው.... አሁን ግን"አንቺ ነሽ አደለሽ የጮሽው? " ተብላ ስትጠየቅ ዝም አለች.... ሁላችንም ግራ ተጋባን .....አደለንም የማለት ሙግታችንን ትተን እኛም ዝም አልን.... ግራ የመጋባት ዝምታ.... ምን ሆና ነው የማለት ዝምታ..... ለኔ ደሞ እንዴት ያላደረገችውን አላደረኩም አትልም የሚል የንዴት ዝምታ.... በብዙ ጥያቄ በዋላ መልስ ሲያጣ አስተማሪው የመናቅ ስሜት ተሰማው መሰል የያዘውን ጎማ ጀርባዋን መታት.... ጧ.... ብሎ ክፍሉን ይባስ ፀጥ አስባለው... አንዳንዱ ተማሪ የሷን መመታት ሲያይ ቀጣይ ለኔ ነው በሚል ፍርሃት ማልቀስ ጀመሩ.... እሷ ግን አሁንም በእጇ ጨምቃ የያዘችውን ቀሚስ ጭምድድ ከማድረግ ውጪ ዝምታዋ እንዳለ ነው..... ንዴቴ ወደ ግራ መጋባት ሄደብኝ.... ዝምታ ምንድነው? ጨዋነት? አዋቂነት? ቁጥብነት? ዝም ሚባለው ለምንድነው?? መቼ ነው?? ብዙ ነገር ማሰብ ገባው... በመሃል ለሁለተኛ ጊዜ ጀርባዋ ላይ ያረፈው የጎማው ድምፁ ከሃሳቤ አነቃኝ... ተማሪዎቹ ተሰብስበው ከቆሙበት ቦታ ይብሱን ወደ ዋላ ሸሹ... እያለቀሱ የነበሩት ይብስ ብሶባቸው ድምፅ አውጥጠው መነፋረቅ ጀመሩ እሷ ግን አሁንም አንገቷን ደፍታ ዝምምምም.... አላለቀሰች... አልጮሀች... አላወራች.... ዝምምም

አስተማሪው ዝምታዋን ከንቀት ቆጥሮ መጮህ ጀመረ ....በዚህ መሃል በሩ አካባቢ የብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ .....መጮሀችንን ተከትሎ ወላጆቻችን ተጠርጠው ኑሮ ከውጪ ብዙ ድምፅ" የኔ ልጅ እንደዚ አያደርግም/ አታደርግም" እያለ ይጮሀል....በሩ አካባቢ የተሰማው ድምፅ ለብዙ ተማሪዎች የእፎይታ ስሜት ሰጠ.... ከሷ ውጪ....

ትንሽ ቆይቶ አንድ ግዘፍ ያለ ሰው ወላጆቹን እና አስተማሪዎቹን አልፎ አንገቷን ደፍታ ከቆመችው ተማሪ እና ተናገሪ እያለ ከሚጮኸው አስተማሪ አጠገብ ደረሰ........እንደደረሰም ምንም ሳያወራ አንገቷን አቀርቅራ የቆመችው ልጅ ላይ ያልተጠበቀ ጥፊ ፊቷ ላይ አሳረፈ.... ምን አደረግሽ? አላለም .......ለምን ለብቻ ተነጥላ ፊት ቆመች?? አላለም ......ምንድነው አደረገች የተባለው ?? አላለም ......ዝም ብሎ በጥፊ መታት... ከመታትም በዋላ "ባለጌ "ብሎ ሰድቦ እየጎተተ ይዟት ሄደ .....በርጋ ስትደርስ ዞራ አየችኝ ሩጬ ቦርሳዋን አቀበልኳት... ቦርሳዋን እንደፈለገች እንዴት ገባኝ? የምር ቦርሳዋን ነው ወይ የፈለገችው?? .....እንጃ ...ብቻ ሩጬ ሰጠዋት ተቀብላኝ አንገቷን ደፍታ እየተጎተተች ሄደች...

አስተማሪው ንዴቱ ጠፍቶ በድንጋጤ አንዴ እኛን አንዴ እየተጎተተች እየሄደች ያለችውን ተማሪውን አየ ......ሐፍረት ተሰማው መሰል ጎማውን የመጣል ያክል አንጠልጥሎ ቁጭ እንድንል በእጁ አመለከተን.... በር ላይ የነበሩት ወላጆች በተፈጠረው ነገር ተደናግጠው ተሯሩጠው መተው ልጅ ልጃቸውን ይዘው ማቀፍ እና መሳም ጀመሩ .........አንዳንዱ ደሞ እያዟዟሩ የልጃቸውን ደህንነት ማረጋገጥ ያዙ..... እናቴ እቅፍ ውስጥ እንዳለው አንድ ነገር ታዘብኩ ......ምናልባት አላደረግንም ብለን የጮህነው... ማድረጋችንን ቢያውቅ እንኳን አላደረጉም ብሎ ሚከራከር ወላጅ እንዳለን ስላወቅን ይሆን???.... ምናልባት ዱላውን ፈርተን ያለቀስነው እንባችንን የሚጠርግ እንዳለን ስላወቅን ይሆን ????  ምናልባት የረበሽነው ሕፃንነታችንን ተረድቶ ይቅር ሚለኝ ሰው እንዳለን ስላወቅን ይሆን??

እንባችንን ሚያብስልን ሰው ከሌለ ማልቀሳችን ለውጥ አይኖረውም ይሆን?? የሚያምነን ሰው ከሌለ አለማድረጋችን ዋጋ አይኖረውም ይሆን????? የሚረዳን ሰው ከሌለ ስሜታችን ይጠፍ ይሆን??? ምናልባት.......


✍️kalkidan


http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

13 Feb, 09:55


"አሁን እኮ ይቺንም የሳመ ይኖራል..."....በመልከ ጥፉነቷ ተደንቆ ይሄን ያለኝ ጓደኛዬን ደስ እያለኝ እንደሳምኳት ገና አልገርኩትም...."የኔ ቆንጆ" ብዬ እንደምጠራትም አያውቅም....

"ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል..."....ብሎ ሲተርት አብረን ስቀናል...ከንፈሯን 'ካልታደሉት ጎራ' ያወጣሁት እኔ እንደሆንኩ አያውቅም....

'አገባሻለሁ' እንዳልኳት ብነግረው ምን ሊሆን ነው...እሱ ሚዜ በሚሆንበት ሰርጌ ላይ ስስማት እንዴት ይሆን ይሆን....እንድትስቅልኝ ስጋጋጥ ቢያየኝ መሬት ተከፍታ ትውጠው ይሆን...ስትስቅ የገጠጠው ጥርሷ ሳይሆን ደስታዋ ብቻ እንደሚታየኝ ብነግረው በአፈጣጠሬ ይደነቅ ይሆን....?....'ውስጣዊ ውበት' ምናምን ብዬ ሳላሽሞነሙን ሁለ ነገሯን እንደምወደው ቢያውቅስ...


አቦ ፍቅር ወሎ ይግባ.....



Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

13 Feb, 04:55


የተሰጠኝን ነገር መቀበል የምችልበት አቅም እንዳለኝ አላውቅም....

እሪ ብዬ ፀልዬ ከተደረገልኝ በኃላ እንዴት እንደማስተናግደው ግራ ይገባኛል 🤦‍♂

የሰውነት ስንፍና ይወርሰኝና በእንብርክኬ ሄጄ እንዳልተቀበልኩት ሁሉ ችላ እለዋለው😣
መብላት መጠጣቴ እውቀቴ ሁሉ የእግዜር ግዴታ እንጂ ፀጋው መሆኑ ይጠፋኝና ትዕቢት ልቤን ያሳብጣታል....

ስንጠይቅ በፀሎቶቻችን መልስ ውስጥ የምንኖርበትን ፀጋ አብረን ብንጠይቅ ሸጋ ሳይሆን አይቀርም🥰

ሳይኖረንም..... ኖሮንም..... ከምንደናበር!


https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

12 Feb, 09:59


ያየን , ያፅናናን , ያስረሳን ....
እግዚአብሔር ይመስገን !
🙏
@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

12 Feb, 07:09


አቢቹ:- ዶሮዋ መንገዱን ስታቆርጥ አበቦችን ረግጣለች ወይ? እንደዛ ከሆነ ሃገራችንን ሊያፈርሱ ከሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ሀይሎች አንዷ ናት ማለት ነው🙂

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

12 Feb, 07:01


ለ ፈ ገ ግ ታ
😁 😁 😁

ዶሮዋ . . .

ጥያቄ፦ ዶሮዋ መንገዱን አቋረጠች፤ ለምን?

ይህ ጥያቄ ለሀገራችን መሪዎች ቢቀርብላቸው ምን መልስ ሊሰጡ ይችላሉ?

አፄ ቴዎድሮስ
ይህቺ እብድ ዶሮ መሄድ የለመደች
ባታውቀው ነው እንጂ ንብረቴ ነበረች
ነይ ተመለሽ በሏት ርቃ ሳትሄድ
እቴጌዋ ዶሮ ምሳ ነች ራት


አፄ ዮሐንስ
ማቋረጡንስ ታቋርጥ፤ ግን ይህቺ ዶሮ ተጠምቃለች? ማኅተቡንስ እንዳሰረች ነበር?

አፄ ምኒልክ
ስማኝ ያገሬ ሰው! እስከዛሬ ድረስ አላስቀየምከኝም፤ እኔም ያስቀየምኩህ አይመስለኝም፤ ዶሮዋን መልሳት ... ይህንን ሳታደርግ ባገኝህ ግን ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ትሁን፤ አልምርህም፤ ማርያምን!

አፄ ኃይለ ሥላሴ
የምንወድህና የምትወደን የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ... ዶሮዋ መንገዱን ስታቋርጥ በቸልታ መመልከት የለብህም። በአንዲት ዶሮ መንገዱን ማቋረጥ ምክንያት ሀገርህን፣ ንጉሥህን፣ ዘርህን ማሰደብና ታሪክህን ማበላሸት የለብህም!

ኮሎኔል መንግሥቱ
ጓዶች! ተደፍረናል! ተዋርደናል! ዶሮዋ መንገዱን አቋርጣለች፤ ይህ ደግሞ አድሃሪያን አብዮቱን ለመሸርሸርና አብዮታዊ ትግላችንን ለማደናቀፍ የሸረቡት ሴራ ነው። ዶሮዋን ለማስመለስ አንድ ሰውና አንድ ጠመንጃ እስኪቀረን ድረስ እንዋጋለን።

አቶ መለስ
በመሠረቱ ዶሮዋ መንገዱን ማቋረጧ በልማት እንቅስቃሴያችን ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ አለ ወይ? ነው ጥያቄው መሆን ያለበት፤ የለም! ስለዚህ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላት፤ አራት ነጥብ።
.....
😂 😂 😂
━━━━━━━━
ምንጭ ➢ ኢንፎቴይመንት
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

09 Feb, 20:13


መንቃት መረገም ነው
(በእውቀቱ ስዩም)

ሰማሽኝ ወይ እቱ!
ለንጀራው ለርስቱ
ፍጥረት ሲተባበር፥
አፍርሼው ተኛሁኝ ፤የቀን ሌቱን ድንበር
ህልም የሚሸጥ ቢሆን ፥ ከብሬልሽ ነበር::


እንዴት እንደዛልሁኝ ፥
በኑሮ እንደታከትሁ
በቅርበት ያላየች ፥
ጸሀይ ያለ ልምዷ ፥ ለመጥለቅ ዘገየች ፥

ልቤን ለንቅልፍ ሰጠሁ
ዓይኔን ለሰመመን
መንቃት መረገም ነው ፤በዚህ በኛ ዘመን ::

https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

07 Feb, 06:14


የሚገርሙኝ ዘመን ተሻጋሪ ቃላት
- ከእመጓ መፅሐፍ


- በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)
    (ገፅ 162-163)

~በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተዉታላችሁ፡፡ ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፤ ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ፤ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፤ የረገጣችሁትን ትይዛላችሁ፡፡ ምኞታችሁ ልክ የለውም፤ አምሮታችሁ ብዙ ነው፡፡

~የአማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል፡፡ ተዉ የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፤ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፤ የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ፡፡ …

~ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ፤ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም፡፡ ሁሉ አላችሁ፤ ግን ባዷችሁን ናችሁ፡፡ ሃይማኖት እንጅ እምነት የላችሁም! …

~መቀመሚያውን ነግሬህ ማርከሻውን ሳልገልጥልህ መጀመሪያውን ብቻ ሞጭልፈህ ትተኸኝ ትሄዳለህ፡፡ ጥበብን ‹‹ሀ ግዕዝ›› ብዬ ላስተምርህ ብሞክር፣ መንደር ውስጥ በቃረምካት ዕውቀት ተመክተህ በመሰልቸት ‹‹ሆ ሳብዕ›› ብለህ ቀድመህ ትዘጋዋለህ፡፡

~የግል ታሪካችሁ ቢታይ ወጥነት የጎደለው ከዚህም ከዚያም የተልከፈከፈ የተማሪ ኮፋዳ ውስጥ ያለ እህል ይመስላል፡፡

~ተምራችሁ እውቀት ስታገኙ፣ ሰርታችሁ ሀብት ስታፈሩ፣ ከላይ የሆናችሁበትን ሃገር ለቃችሁ፣ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ፡፡ ትቀጥላላችሁ፣ በመጨረሻ ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ፡፡ ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወዲያው ትጸጸታላችሁ፡፡ በጽኑ ታማችኋል!

~ከታሪክ ፍቅርንና ልማትን ሳይሆን ጥላቻንና ጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ፡፡ ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ፤ እናም ወደ ኋላ ስለታሪካችሁና ስለ ቅርሳችሁ ባሰባችሁ ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማችኋል፡፡

~ስለሆነም ከኋላ ታሪካችሁና ክብራችሁ እየራቃችሁ መጣችሁ። የአሸናፊነትንና የተሸናፊነትን ትርጉም በአንድ ላይ የያዙ ሃውልቶች ታቆማላችሁ፡፡ ለግልጽነትና ለነጻነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ ዕርቃን ወደ መሆን ወረዳችሁ፡፡

~ቅቤ ላይወጣችሁ ትናጣላችሁ፡፡ በዚህ ዓለም ጥድፊያ ታማችኋል፡፡ ሀገራችሁን ትንቃላችሁ፤ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ፤ ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ አገሬ ናፈቀኝ ትላላችሁ፡፡

~በቁማችሁ የናቃችሁትን የሀገራችሁን አፈር በሞታችሁ ልትለብሱት ትናፍቃላችሁ፡፡ ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገኖቻችሁን ልብ ትሰብራላችሁ፡፡

~ግብዝነታችሁ መጠን የለውም፡፡ ሁለት ሀገር እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ፤ አንዱን በደም ሌላኛውን በመታወቂያ ታስባላችሁ፡፡ ከአንዱም ግን በአግባቡ አትኖሩም፡፡ ዘመናችሁም በምልልስና በመዋተት ያልቃል፡፡

~ምን እንደምትፈልጉ አታውቁም እናም ፍለጋችሁ አያልቅም፡፡

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

06 Feb, 07:10


ሜርቭ ከተማ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የኻያምን በከተማው መገኘት የተቃወመው ዋና ቃዲ ተነሳና፣ ጣቱን ቀስሮ፣

በእግዚአብሔር የማያምን ፈላስፋ፣ ስለሃይማኖት ጥያቄ አስተያየት መሰንዘር የሚገባው አይመስለኝም» አለ፡፡

ዑመር የመታከት ፈገግታ አሳየውና፣

በእግዚአብሔር የማያምን ብለህ እንድትኮንነኝ ማ መብት ሠጠህ? የተናገርኩትን ካዳመጥህ በኋላ እንኳን ቢሆን ባማረብህ፡፡»

«የምትለውን መስማት አያሻኝም!» በኃይለ ቃል ተቃወመው:: «ይኽን ግጥም የተቀኘኸው አንተ አይደለህም ? ፦

ሠራህና አዳምን ከተልካሻ ጭቃ፣
አቆምህና እባብን ለሄዋን ጠበቃ፣
አንተ ባጠፋኸው እሱን ልትቀጣ?
ይልቅ፣ ይቅርታህን እንካ፣ ይቅርታህን አምጣ! -

እንዲህ ያሉ ቃላትን የሚሰነዝር ባለቅኔ ከሀዲ እንጅ አማኝ
ይባላል?»

ዑመር ራሱን ነቀነቀ።
«ባላምንበት እኮ፣ እግዜር መኖሩን ባላቅ እኮ፣ አላናግረውም፡፡»

«ታዲያ እንደዚህ እየዘረጠጥክ ነው የምታናግረው ?» ቃዲው አፈጠጠበት።

«ለናንተ ቃዲዎችና፣ ለሡልጣኖች ነው የሽቁጥቁጥ ቋንቋ የሚያስፈልገው። ለፈጣሪ አይደለም። አላህ ታላቅ ነው! እንደሰው ይሉኝታና ግብዝነት የለበትም። ማሰብ እንድችል አርጎ ነው የፈጠረኝ። ስለዚህም አስባለሁ፡፡ የሀሳቤንም ፍሬ ነገር ሳላሞካሽ አቀርብለታለሁ።

የተሰበስበው ሁሉ በአድናቆት አምረመረመ። ቃዲው ተቆናጥሮ ተነሳና፣ በሆዱ እየዛተ ምንም ሳይናገር ተቀመጠ፡፡ ልዑሉ ከልቡ ፈንድቆ ከሳቀ በኋላ የሃይማኖት ሰዎችን ደሞ እንዳያስቀይም ስጋ። ወዲያው ገፁን አኮሳትሮ ፀጥ አለ። ሊቃውንቱ ነገሩ አለማማሩን ሲመለከቱ፣ አንድ ባንድ እጅ እየነሱ ወጡ፡፡
__
ዑመር ኻያም ልበወለዳዊ የሕይወት ታሪኩና ሩብአያቶች
ትርጉም ፦ በተስፋዬ ገሠሠ
ገጽ 138/139

https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

05 Feb, 16:56


የዘመዶችህ .......... ባህሪ ቤተሰቦችህ
ባላቸው ብር ይወሰናል !

@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

05 Feb, 13:34


እናቴ ስሟ ጌጤ ነው  ።   ጉሊት ነበር የምትውለው፤ ሻሜታ ትሸጥ ነበር። ትምርት ከሌለኝ   ይዛኝ ትሄድ ነበር። አዘንጣኝ ነበር የምትሄደው እኔ ከሌለሁ ልጄን ይመቱብኛል ብላ ነበር  መስርያ ቤቷ የምትወስደኝ ።

መስርያቤቷ   አጥር ፣ ጣርያ፣ የለውም።  ወለሉን ድንጋይ ረብርባ  ከፍ አድርጋዋለች።
ጥግ ላይ የምትቀመጥበት ወደጎን የረዘመ ዱካ ነበራት።

ደግ ናት፤ ፀሃይ ቀጥቅጧት የምታመጣውን ገንዘብ አትሰስትም ። ስትሰራ ውላ ደከመኝ እያለች ስትማረር ሰምቻት አላውቅም።

በየምክንያቱ "ቸርነቴ" እያለች ትጠራኛለች ።

አንገቷ ረጅም ነው  ሃብል የሚመስል ንቅሳት አንገቷን አጥለቅልቆታል ።  ከፊቷ ፈገግታ አይጠፋም ። ለለማኝ ገንዘብ ሰጥታ ሲመርቋት ሁለት እጇን ዘርግታ "አሜን አሜን" ትላለች።  ጥሩ ነገር ከተደረገላት  "ግንባርህ አይታጠፍ ...እግዚአብሔር ይስጥህ.....
አትጣ ...ጤና ይስጥህ" ትላለች።

ሰው ትወዳለች ፣ ስራ ትወዳለች ፣ አመስጋኝ ናት ...
የዚች ልጅ ተሁኖ ሰነፍ እና ክፉ መሆን እንዴት ይቻላል ? !
   © Adhanom Mitiku



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Feb, 16:14


በነገራችን ላይ ሸዊትዬ አንቺ ትህትናሽን ማሳየትሽ ነው እንጂ እንደ እኔ እንደ እኔ ካንቺ እይታ ይልቅ የይስማዕከ እይታ ነው ወደ hasty generalization የሚያደላው ለምን ከተባለ እሱ ሴትን ሁሉ በደሊላና በሄዋን (ሁለቱም ተመሳሳይ አይነት ባህሪ ባላቸው ሴቶች ነው የገለጸው) አንቺ ግን በተቃራኒው ጎን የምትቆጠር ማሪያም እንዳለችም አሳየሽን ወንዱንም የዋሁ ሳምሶን እንዳለ ሁሉ ክፉው የዳዊት ልጅ እንዳለም አስመሰከርሽልን፤

ታድያ ይሄ ምኑ hasty generalization ነው ጃል?🤔

ሴትነትም ወንድነትም እንደ መለኪያው ነው ከሚል እይታ በላይ Logical reasoning ያለ አይመስለኝም🙌


እናም አንቺ ራስሽ ጫማሽ ይመችሽ✌️🙂

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Feb, 15:35


ክፋትና ደግነት በአንድ ቦታ ተወስነው የተቀመጡ ነገሮች አይደሉም....በእርግጥ በአንድ ፆታም አይጠቃለሉም....

ይሄ የእኔ እይታ hasty generalization ለመስጠት ታስቦ የተፃፈ ሳይሆን ከላይ በደራሲው የተሽሞነሞነው ወንድነት ውስጥ እና የተጠለሸው ሴትነት ውስጥ ያየሁትን "ለራስ ሲቆርሱ" እና ያልተዋጠልኝን ገበታ የራሴን እይታ አንፀባርቄ በሚመቸኝ መልኩ ለመዋጥ ነው....😊


እና ውዶቼ በእኔ እጅ መጠን ላጉርሳችሁ ብዬ አላስገድድም....እንደተመቻችሁ ዋጡት....



ይመቻችሁ✌️



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Feb, 15:10


👏👏....

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Feb, 10:02


ወንድ ልጅ ተልባ የተደፋበት መሬት  ነው....ያሙለጨልጫል.....ተልባ በተደፋበት መሬት ላይ ፀንቶ መቆም እንደማይቻለው ወንድ ልጅ ላይም ሀሳብን ጥሎ መቆም ይከብዳል....መቼ ጥሎ እንደሚታጠፍ አይታወቅም....ለዛም ይሆናል ሴት ልቧን የመደበቋ ምክንያት....በተልባ ላይ በባዶ እግር አይቆምም አይደል....ልቧ ጫማዋ ነው....አያያዙን አይታ ነው ልቧን የምትሰጠው....መቆምያዋን አይታ ነው ጫማዋን የምታወልቀው....የዋዛ እንዳትመስልህ....

በእኔ እይታ አዳምን በገነት ተደብቃ በእባቡ ተታላ በለስ ከቀመሰችው እና ከአራዊት ጋር ከኮበለለችው ሄዋን በላይ ለተጠማ ውሻ ውሀ ያጠጣችው የዋህይት ርግብ ሚዛን ታነሳለች....የእባብን ቃል ሳትመረምር ተቀብላ ስለሳተችው ሄዋን ብቻ ሳይሆን የመልአኩን የብስራት ቃል መርምራ ስለተቀበለችዋ ድንግል ማርያምም ብናወራ ጥሩ ነው....'ሴትነት ይለካል ወይ' ብትሉኝ መልሴ 'ሴትነት እንደመለኪያው ነው'....


በፍቅር ስለወደቀው ስለ የዋሁ ሶምሶን አውርተን ወንድ ልጅ የዋህ ነው ካልን የገዛ እህቱን ደፍሮ ስለጣላት የዳዊት ልጅ አንብበን ለምን ወንድ ልጅ አውሬ ነው አንልም.....ወንድ ልጅ ውሻ ነው ካልን የወንድ ልጅ ውሻነት ለለመደው ህይወቱን አሳልፎ መስጠቱ ብቻ ሳይሆን እዚም እዚያም መልከስከስን ወዴት አርገነው ነው.....አይ እሱን እናውጣው ካልን "ከመረቁ አድርጉልኝ ከስጋው ፆመኛ ነኝ" ማለት አይሆንብንም....


ሴት ልጅ ድመታዊ ባህሪዋ ራሱ ምክንያት አለው....እህ ብለህ ብትሰማት ገልጠህ የማትጨርሰው መፅሀፍ ናት...እንደ እንደ እኔ ሴት ልጅ ሚስጢር ናት....ምስጢር ደግሞ ለሁሉም አይነገርም....እንዲያ ነው።


shewit


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Feb, 10:02


ይስመአከ "ሴት ልጅ ድመት ናት....ወንድ ልጅ ደግሞ ውሻ ነው..."....ያለውን አንብቤ በሆዴ አጉረምርሜያለሁ...."ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ" ብዬም አሽሟጥጫለሁ...እንደው ድፍረት አይሁንብኝ እና የእኔን እይታ ባጋራችሁስ😉

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Feb, 09:58


ሴትና ወንድ በይስማዕከ ወርቁ እይታ✍️

አዳምን በገነት ተደብቃ ከእባቡ ጋር በለስ የቀመሰችው ሴት ናት። እንኳን ከቢጤዋ ከአራዊት ጋር ኮብልላለች። ሳምሶንን ላጭታ ለኤሎፍላዊያን የሰጠችው ሴት ናት።
የአንበሳ ጉልበቱን እንደ ድመት አልፈስፍሳ ያስያዘችው ደሊላ ናት።
ድመታዊ ባሕርይዋ ባየችበት በሰባራ ገል ወተት እያታለሉ የትም መውሰድ ይቻላል።
ወተቱነን እንጅ ባለወተቱን ብላ አትከተልም። የድመት ፀጉሯ እንጅ ልቧ አይገኝም። ወተት ካለው ትለምዳለች። የመልመድ ድመታዊ ባሕርይዋ የተፈጥሮዋ ነው።
ድመት እንግዳ ቢመጣ እንደውሻ አትጮህበትም። ዘላ ጭኑ ላይ ትቀመጥበታለች። በዚህ ድመታዊ ባሕርይዋ ወዲያው ከሁሉም ትለምዳለች። ሌላ ሻል ያለ እንግዳ ቢመጣ ፣ ዘላ ስትሰፍር ቅጭም አትልም።
ወንድ ግን ውሻዊ ባሕርይ ነው ያለው። ለለመደው እንጅ ላለመደው ጅራቱን አይቆላም። እንግዳ ቢመጣ ሊናገር ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል። እስኪለምደው ይጮህበታል። ከለመደው ግን እስከወዲያኛው አይረሳውም። ወንድም እንደዚያ ነው።
ለመልመድ እንደውሻ ጊዜ ይፈጅበታል። ከለመደ ሕይወቱን እስከመስጠት ይደርሳል።
ሴት ሽንፍላ ናት ታጥባ የማትጠራ ሽንፍላ። ሽንፍላን አጥቦ የሚያውቅ ያውቃታል።

ይስማዕከ ወርቁ

ክቡር ድንጋይ ገጽ 146-147

https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Feb, 08:34


የመጨረሻ ጊዜ eye-contact የነበረንን ጊዜ የሚያስታውሰው አይመስለኝም። እንኳን እሱ እኔ አላስታውስም። ለትንሽ ሰከንድ ትክ ብዬ አይኑን ባየው አፌ ያላወጣውን አይኔ የሚዘረግፈው ይመስለኛል።

      "የማውቅህ ተንገብግቤ ያገባሁት ሰው አይደለህም፥ ባሌን የት አደረስከው?!" ብሎ አይኔ እንዳይለፈልፍ ነው የምሸሽው

       አንዳንዴ የአምሳል ምትኬን "አንድ ነገር ጎድሏል" የሚለውን ዘፈኗን ከፍቼ መጠበቅ የሚያምረኝ ቀን ይበዛል። ለአንድ እኔ የማይበቃ ሰው እንዴት የሁለት ሶስት ልጆች አባት ይሆናል ብዬ እብሰለሰላለሁ። ንግግሩ የሚያደርገው ነገር በሙሉ ያበሳጨኛል።

      እንዴት አይቶኝ አይረዳም ብዬ እስከመጨረሻው እንዳልናደድ ደሞ የኔንም ድክመት አየዋለሁ። ፍላጎቴን በሙሉ ከአኳኋኔ ሁሌ ሊረዳ አለመቻሉን ማወቅ አለብኝ አይደል?!

     ግን "ነገር እና ጭራ ከወደኋላ ነው" እንዲሉ የእሱም ግድ የለሽነት የኔም ራሴን አለማስረዳት ያኔ መጀመሪያ ለምን አልበጠበጠንም ነበር?! ያኔ እንቻቻል ስለነበረ ነው? ወይስ እኔን ለማስደሰት ስለሚጋጋጥ ነው ሳልነግረው የሚገባው?

    እንጃ


ናኒ


https://t.me/justhoughtsss

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

02 Feb, 10:02


የሚያስፈራኝ ደሃነትና የመንገድ መፍረስ አይደለም። የሥጋና የአጥንቱ መድከም አይደለም ( ማናችንም ላናመልጥ )

የእቃ መወደድ አይደለም ( እግዜር የከፈተውን አፍ ሳይዘጋው ካደረማ ፣ እግዜሩም እግዜር እኔም ሰው አይደለሁ )

ሰው ይቀየመኛል አይቀየመኝም አይደለም ( ብለፋም አልችልበትም )

ፀጉሬ አማረ አላማረ አይደለም ( ካልሆነ መላጨት አለ እኮ )

የምሸጠው ዶሮዬ ጎረና አልጎረና አይደለም ( ዶሮው ባይኖር ሌላ ይጠፋል ? )

ነፍሴ ሲዖል ገባች አልገባች አይደለም ( የእግዜር ፍርድ ነው ይሄ )

የልቤ ነገር ነው። በሕይወት ቆሜ የምወዳቸው እየከሰሙብኝ ቂም አማሮኝ ፣ ልቤ በተስፋ መቁረጥ እንዳይቆስል ነው።"
__

የስንብት ቀለማት 📖
አዳም ረታ 😘
ገጽ ( 813 )


@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

02 Feb, 05:55


የሳይኮሎጂ ክላስ
(በሌላ ቀን የቀጠለ...)


"ቆይ ፕሮፍ እውነተኛ ፍቅር ሚባል ነገር አለ?"
አለ አንድ ድምፅ ከኋላ፤ ፕሮፈሰራችን ገና ገብታ ከቤካ ጋር LCDውን (projectorኡን) እያስተካከሉ ነበር፤ እሷም ማስተካከሉን ለቤካ ትታለት ትንሽ አሰብ አደረገችና ማውራት ጀመረች
"ለኔ ፍቅር የሚለውን ቃል መተርጎም በጣም ከባድ ነው፣ በህይወቴ ሙሉ በሙሉ ካልተረዳኋቸው ነገሮች መካከል አንዱ ነው፤ ግን ፍቅርን እውነተኛ የሚያስብለው ጊዜውና ቦታው ይመስለኛል..."
እንደለመደችው ክፍሉን አንዴ ቃኘት አደረገች፣ ሁሉም አይኖች ወደሷ ነው።

"ለምሳሌ አንተ ሞተህ ቆሜ መኖር አልችልም ስለዚህ ካንተ ያስቀድመኝ የምትል ሴትም ከልቧ ትወዳለች፤ እኔ ቀድሜክ ሞቼ ብቻህን ከምትሰቃይ እኔ ካንተ ኋላ ብሞት እመርጣለሁ የምትለዋም ከልቧ ትወዳለች"
ቤካ አስተካክሎ ጨርሶ ወደቦታው ተመለሰ
"ሌላ ምሳሌ ብሰጣችሁ ደግሞ ፍቅር ለሚወዱት ሰው መሞት ነው ደግሞም የሚወዱትን ሰው መግደል ሊሆንም ይችላል"
"እንዴት?" አለ ቅድም የጠየቀው ልጅ
"ለምሳሌ አንድ ሰው፤ ለብዙ አመታት በኦክሰጅን ላይ ሆና ከሞትና ከህይወት መሃከል ያለ ተስፋ በህመም የምትሰቃየውን በጣም የሚወዳትን ሚስቱን ከስቃዩዋ ሊገላግላት ፈልጎ አፍኖ ቢገድላት ስለሚያፈቅራት ነው እንላለን"
"ግንኮ ፕሮፌሰር ሁለቱ ለparallel comparison (በእኩል ለንጽጽር) ሚቀርቡ ጉዳዮች አይደሉም..." አለች ሁሌም ከፊት የምትቀመጠው መክሊት
"ለምን አልሽ?" አለች ፕሮፌሰሯ ራሷም ለመማር በሚመስል ጉጉት ትንሽ ወደኋላ እያፈገፈገች
"ለምሳሌ የመጀመሪያው ምንም አይነት በተቃራኒው የምናስቀምጠው ክስተት የለውም! ሰው ለሰው ከሞተለት ስለሚወደውና ስለሚወደው ብቻ ነው፤ ነገር ግን ሰው ሰውን ከገደለው ስለሚወደው ነው ብለን ብቻ መተው አንችልም፣ ወዶ ከሚገድሉት በላይ በጥላቻ ተሞልተው የሚገድሉት ቁጥር ይበልጣልና"
"አዎ ፕሮፍ እኔም በሷ ሃሳብ እስማማለሁ" አለ ሳሚ ከኋላ ወንበር፤ በአብዛኛው ወንዶቹ ፕሮፍ ብለን ነው የምንጠራት ቤካና ሴቶቹ ናቸው ፕሮፌሰር የሚሏት፤ ቀጠለናም...
"መጀመሪያ ባልሽው ላይ ራሱ ፍቅሬ የኔን ሞት ማየት እስከማትችል ድረስ ከወደደችኝ ፍቅሯ እውነተኛ ነው ማለት ነው፤ ምናልባትኮ ለእኔ የመጣውንም ሞት ለመሞት ዝግጁ ትሆን ይሆናል፣ ህይወቷን ልትሰጠኝ ማለት ነው... ነገር ግን ለኔ አስባልኝ ቢሆንም ሞቴን ቆሞ የማየት አቅም ካላት... እኔ እንጃ ትወደኛለችኮ ግን..."
"ግን ከመጀመሪያዋ ጋር ለንጽጽር አትቀርብም" አለ አሁንም ሌላ ተማሪ፤ ሁሉም ተማሪ መስማማት በሚመስል መልኩ እርስ በርስ ጭንቅላቱን እላይ ታች እያረገ አጉተመተመና ከትንሽ ሰከንዶች በኋላ ፊቱን ወደ ፕሮፌሰሯ አዞረ፤ እሷ አሁንም ዝም ብላ ታስባለች
"ፕሮፍ ሰው ዝምብሎ ፍቅር ላይ ይራቀቅበታል እንጂ ትርጉሙ ቀላል ነው፣ በብዙ ክስተቶችም ይገለጥ ይሆናል ግን ደግሞ ሁሌም ቢሆን የሚገለጥበት ቋሚ መልክም አለው፣ አለ አይደል እንዳየን 'ይሄ ፍቅር ነው!'... ማለት የምንችለው መልክ፣ በቃ ግልጽ መልክ አለው፣ያም እኔ እንደሚመስለኝ ፍቅር ራስን ለሚወዱት ሰው አሳልፎ መስጠት ነው፤ ፍቅር በቦታና በሁኔታ የሚደገፍ አይመስለኝም፤ ፍቅር ትክክለኛ መገለጫው ራስን መስጠት ከሆነ ራስን መስጠት ደግሞ በጊዜና በሁኔታ መደገፍ የለበትም" አልኩኝ እኔም በተራዬ፣ አሁንም ትንሽ እያሰበች ቆይታ
"እስከዛሬ ያመንኩበት ነገር ሁሉ ውሸት ነው ማለት ነው?" አለች ለብዙ ሰው ባልተሰማ ድምጽ፣ ከዛም በሚሰማ ድምጽ
"ቤካ LCDውን ወደ ስታፍ ቢሮ መልሰው፣ ሌላ ቀን እንማራለን" ብላ እየተቻኮለች ቦርሳዋን ይዛ በፈገግታ ተሞልታ ወጣች።
ወዴት እንደምትሄድ ጥያቄ ያነሳ ሰው አልነበረም፤ ፈገግታዋ በሁሉም ሰው ላይ ተጋብቷል መሰለኝ ሁሉም ዝም ብሎ በፈገግታ ይመለከታታል
"ፕሮፍ ራሷን ልትሰጥ እየሄደች ነው" አለ አንዱ ተማሪ
በሳቅ አጀብነው...


ምስጉ✍️

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

01 Feb, 02:19


@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

31 Jan, 17:23


ትስቃለች ሁሌም ልክ ስታየኝ ፈገግ ትላለች.... በምትሰራው ሥራ ምክንያት ሰፈር ውስጥ የሚያወራትም የሚያያትም የለም ሁሉም ከሌላ ዓለም እንደመጣ ሰው ነው ሚያይዋት.... እኔ ብቻ ነኝ እንዲ ቀርቤ ማወራት ወይም እኔን ብቻ ነው እንዲ አቅርባ ምታወራኝ....

"እንዲ ስትስቂ እኮ ነው ምታስገርሚኝ" አለችኝ... ገረመኝ እየገለፈጥኩኝ መሆኑን እንኳን አላስተዋልኩም ነበር ደንግጬ ዝም ስል ድንጋጤ አስቋት ፍርፍር አለች... በዚ ሰዓት ነው የሰፈራችን አሮጊቶች በአጠገባችን ያለፉት እናቴም ከመሃከላቸው ነበረች እና የሷ በር ላይ ቁጭ ብዬ ስታየኝ ኮስተር ብላ አለፈች..... የእናቴም ፊት አይቼ ስመለስ አይን ላይን ተጋጨን እና ፈገግ አለች እኔም የሐፍረት ሳቅ መለስኩላት..

" ለምን አትነግሪያቸውም? " አልኳት...

"ምኑን " በፊቷም በአፏም ጠየቀችኝ

"ሁሉንም ለኔ የነገርሽኝን ለምን አትነግሪያቸውም "

"ከዛስ ከነገርኳቸው በኃላስ ሊረዱኝ ነው ሊያሾፉብኝ አይዞሽ ብለው ሊያበረታቱኝ ነው ወይስ ደካማ ብለው ሊነቅፉኝ... ቃል ሁሉም ነገር እኮ አይነገርም ምክንያት ሁሉም ሰው አንቺን አይደለም አይገባቸውም... ግን መጥፎ ሆነው አደለም በቃ እድገታቸው ነው............ ሴት ልጅ ቻይ ናት ቻይው ወንድ ልጅ ደሞ ጠንካራ ነው በርታ እየተባሉ  ስላደጉ  ያልቻለች ሴት እና ለደከመ ወንድ ማህበረሰቡ ውስጥ ቦታ ያላቸው አይመስላቸውም... ስለዚህ ሁሉም ህመሙን እና ጭንቀቱን በራሱ መንገድ ያስተናግዳል... ይብዛም ይነስም ሁሉም በውስጡ የራሱ ህመም አለው..... ያን ህመሙ ደሞ በሚያውቀው  እና በለመደው መንገድ ነው ሚያስተናግደው ሴተኛ አዳሪ የሆንኩበት ምክንያት ለኔ ታሪኬ ነው ማፍርበትም ሆነ ምኮራበት አይደለም.... አሁን ሴተኛ አዳሪ የሆንኩበትን ታሪክ ባወራው ሁሉም አንዳይነት ስሜት ሚሰማው ይመስልሻል.... እንደዚህ እያዩ እንዳላዩ ሚያልፉኝ እንዳልተፈጠርኩኝ የሚቆጥሩኝ ሁሉ ውይ አይዞሽ ብለው ከበው ሚያቅፉኝ ይመስልሻል ለኔ እንደዛ አይመስለኝም.... ሁሉም ነገር አይነገርም ምክንያቱም ሁሉም አንቺን አደሉም አይገባቸውም.... ታሪኬ የኔ ነው እያንዳንዱን የተሰማኝን ህመም ስቃይ ...ብዙ በእንቅልፍ እጦት ያለፉ ምሽቶች.... በእንባዬ የረጠቡ ልብስ እና ትራሴን.... በራሳቸው አስተሳሰብ እንዲያቀሉኝ እና እንዲያሞግሱኝ አልፈልግም...... ከፈጣሪሽ ጋር አውሪ... ቢያውቀውም ደግመሽ ንገሪው..... የተሰማሽን እየተሰማሽ ያለውን እና እንዲሰማሽ የምትፈልጊውን ንገሪው አይገምትሽም ለምን እንደዚ አደረግሽ ብሎ አይወቅስሽም የፈጠረሽ እሱ አደል አቅምሽን ያውቀዋል ይብዛም ይነስም ሀቅ ይኖርሻል...... ከዛ ይቀልሻል በቃ ያን ነው ማደርገው ማውራት ስፈልግ ከሱ ጋር ነው ማወራው መውቀስ ስፈልግ እሱን ነው ምወቅሰው ባይገባውም እንደሚገባኝ እንዲሰማኝ ያደርገኛል ለዚህ ነው ብዬ ታሪኬን አደባባይ አላሰጣም.....  ሁሉም ነገር አይነገርም ምክንያቱም ሁሉም አንቺን አይደሉም አይገባቸውም!!


✍️kalkidan


http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

30 Jan, 19:05


ሰላም ተወዳጆች,

አንድ ወንድማችን በሊቢያ በኩል የስደት ጉዞን ከጀመረ የተወሰኑ ወራት አልፎበታል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ከሌሎች ወንድሞቻችን ጋር እጅግ ብዙ መከራና ስቃይ አይቶታል፤ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አሳልፎ ሲጓዝ፣ በአጋጣሚም በአጋቾች እጅ ተይዞ እጅግ በርካታ መከራን አፍላ ተሰቆመዋል።

ይሁን እንጂ, በቤተሰቦቹ እና በወዳጆቹ የገንዘብ፣ የሀሳብ፣ የፀሎት እርዳታ ሲያገኝ ከዚያ ሁኔታ ለመውጣት ችሏል። ነገር ግን, ወደ ቤቱ መመለስ አስቸጋሪ ስለሆነ ጉዞውን ለመቀጠል ተገዷል። ይህም ደግሞ የበለጠ የገንዘብ ድጋፍን ያስፈልገዋል።

ስለዚህ, እኛም ጓደኞቹ እያንዳንዳችሁ አቅማችሁ ባለው መጠን እንድታግዙ በፈጣሪ ስም ጥሪ እናቀርባለን። አነሰ በዛ ሳትሉ በተቻላችሁ መጠን ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ። የሚቻላችሁን ድጋፍ ወደዚህ አካውንት ልከው፦

Account: 1000572862128
Name: Pinieal Teka Aymut

እናመሰግናለን፤ በፀሎታችሁም አስቡት።

እግዚአብሔር እያንዳንዱን ድጋፍ ይባርክ።

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

30 Jan, 14:58


እያየዋት ነው....... ፊት ለፊቴ ተቀመጣለች...... እናገራታለው ያልኩት በሙሉ ጠፍቶ ፊቷን ሳየው አይኔን እንባ ሞላው ....ላለማልቀስ ከራሴ ጋር እየታገልኩ ላወራት የፈለኩትን መንተባተብ ጀመርኩ......

ኤልሲ አንቺ የልብ ጓደኛዬ ነሽ ብዙ ነገር አብረን አሳልፈናል ጓደኛዬ ብቻ አደለሽም ለኔ እንደእህቴ ነሽ...... ታድያ ምን ሁነሽ ነው እንደዚህ ፊት የነሳሺኝ? ምን አድርጌሽ ነው? ደሞ ምንስ ባረግ ሰድበሽ መክረሽ ወይ ተቆጥተሽ ትነግራኛለሽ እንጂ እንዴት እንደዚህ ፊት ትነሺኛለሽ?? ምን ያክል እንደምጨነቅ እያወቅሽ?? እንዴት እንደዚህ ታደርጊያለሽ?? ለምን ምንም እንደማታውቂኝ ትሆኛለሽ?? ያ ሁሉ ያሳለፍናቸው ጊዜያት ላንቺ ምንም አይደሉም ማለት ነው?? ብዙ ሰዎች ምንም ሳላደርግ ፊት ነስተውኛል ይሁን ብዬ ትቸው ነበር ያቺ ግን ከበደኝ?? ቆይ ምን በድዬሽ ነው እንደዚ የጠላሺኝ?? ማወራውን ሳልጨርስ እንባዬ ቀደመኝ.... ለትንሽ ጊዜ ዝም ተባባልን.... እኔ ፊቴ በእንባ ተሞልቷል እሷም ላለማልቀስ እየሞከረች ቢሆንም.... እንባዋን ከአይኗ ላይ ቀስ እያለች ስትጠርግ አይቻታለው....

"ለሁሉም አንድ ነሽ" አለችኝ....

"ማለት" አልኩኝ.... የይቅርታ እና የምክንያት መዓት ትደረድራለች ብዬ ነበር የጠበኩት.... ተቃራኒ ሲሆንብኝ ጊዜ ደነገጥኩ... ቀጠለች

"በቃ ለሁሉም ትጨነቂያለሽ... ለሁሉም ታስቢያለሽ .....ሰው አትመርጪም.... ጥሩ ነው እኮ ማለት ለሰዎች ጥሩ መሆን ደስ የሚል ነገር ነው ያንቺ ግን በዛ .........ሁሉም ሰዎች ያንቺ ጭንቀት አያስፈልጋቸውም በራሳቸው መፍታት ይችላሉ.... ለሁሉም እኩል ታዝኛለሽ ትጨነቂያለሽ? ቆይ በሕይወቴ ቦታ አላቸው ምትያቸው ሰዎች አንቺ ጋር የተለየ እንክብካቤ አያስፈልጋቸውም?? አይገባቸውም??.... ሁሉም ሌላ ጓደኛ አለው... አንቺ ብትጨነቂላቸውም እነሱ ግን ጓደኛ ብለው ለሚያስቡት ነው ይበልጥ ቦታ ሚሰጡት.... ለኔ ግን አንቺ ብቻ ነበር የነበርሺኝ ግን ከነሱ እኩል ነው ምታይኝ ይሄ ደሞ ደስ አይልም... ሁሉንም ሰው አንቺ ጋር ባለው ቦታ እና ሕይወትሽ ላይ ባለው ተፅዕኖ ነው ማስተናገድ ያለብሽ አንቺ ግን ለሁሉም ልጨነቅ ላስብ ትያለሽ ያ ደሞ ሕይወትሽ ውስጥ ቦታ አለን ብለን ለምናስብ ሰዎች ጥሩ ስሜት አይፈጥርም..... ጥሩ ሰው ነሽ እኔ በሕይወቴ ካየዋቸው ሰዎች ሁሉ ጥሩ ናት ብዬ ምናገረው አንቺን ብቻ ነው..... ግን ጥሩነትም ቢሆን ልክ አለው.... እኔ እንደምትይው እህትሽ ከሆንኩኝ መች ነው እንደ እህት ከሌሎች ሰዎች ይበልጥ ያልተጨነቅሽልኝ??.... እኔ እና አንድ ሌላ ጓደኛሽ የሆነ ችግር ውስጥ ብንሆን አንቺ ለሁለታችንም እኩል ነው ምትጨነቂው ያ ደሞ እኔ አንቺ ላይ ያለኝን እምነት ያሳንሰዋል.... ምክንያቱም እንደ ጓደኛ እኔ ነኝ አንቺ ጋር ትልቅ ቦታ ሚገባኝ...... እኔ ነበርኩኝ ልትጨነቂለት የሚገባው ሰው አንቺ ግን ለሁሉም ያው ነሽ ያ ደሞ ጓደኝነቴን....እምነቴን.... እህትነቴን ብቻ ላንቺ ያለኝን ሁሉንም ነገሮች ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል....... ከዛ የባሰው ደሞ እራሴን እንዳሳንስ ከሌሎች ጋር እንዳወዳድር ያደርገኛል ያ ደሞ በጣም ያስጠላል ለዛ ነው የራኩሽ በቃ...." ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች...... እናገራለሁ እቆጣታለው ብዬ የመጣውትን..... ምክንያቷን ስሰማ በራሴ አፈርኩኝ..... እንባዋ ሲያስቸግራት ምታወራውን ሳትጨርስ ተነስታ ሄደች.... እኔ ባለሁበት ቁጭ እንዳልኩኝ ቀረው



✍️kalkidan



http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

29 Jan, 15:17


ስሚኝ

አውቃለሁኝ እኮ
አንቺ የሌለሽበት
እንደማይኖረኝ ገድ፤

ነገር ግን አለሜ
እንዳመጣሽ ሁሉ
ይወስድሻል መንገድ ።

ደህና ሁኚ 🖤

@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

29 Jan, 11:32


ኔግሮ የሚባል ፍሬንድ ነበረኝ ፀባይኛ ነው፣ ሌባ ነው፥ እናቱን ይወዳታል፥ ትምህርት አይገባውም፤ ተንኮል፣ ኳስ ፣ጆተኒ ፣ ትረባ ጎበዝ ነበር።

በአንድ ሴሚስተር መቶ እና ሁለት መቶ መፅሃፍ ይሰርቃል መቼ? ...እንዴት?...ከማን?... አላውቅም!

መጨረሻ ላይ  ውጤቱን እየሳቀ ይነግረኛል።
አንድ ቀን እንኳን ሲሰርቅ ተይዞ አያውቅም !

የሰረቀውን መፅሐፍ ሲሸጥ አብሬው ሄጄ አውቃለሁ። ከሚገዙት ጋር ደምበኛ እንደሆነ ሰላምታ አለዋወጣቸው ያስታውቃል። አሻሻጡ የሰረቀ ፣ ሳይለፋበት ያመጣ አይመስልም፤ በቸልታ አይደለም።  በርጋታ እንደትልቅ ሰው... "አይሆንም...፣ ይቅር...፣በቃ፣ ጨምር " እያለ ነው ።

እናቱን  "ሸቅዬ... እዛ ማዶ ያሉት ሃብታም ሰዎች፤ ለእናትህ ስጣት ብለው ብር ሰጡኝ" እያለ እንደሚሰጣት ነገሮኝ ያውቃል ።

ሰባተኛ ክፍል ፣ ስምንተኛ ክፍል እያለን እናቱን ያግዛት ነበር ።  ይወዳታል፤  አወዳደዱ እንደትልቅ ሰው  ነው። "ማሚዋ  ደብሯታል ...አሟታል. . . ገበያ ቀዝቅዞባታል" እያለ ያስብላታል።

ከጓደኛው አይሰርቅም። ለጓደኛው ለኔ ለሚለው ሰው ይሳሳል።

አይኖቹ ትናንሽ ናቸው፣ አካባቢውን በትኩረት ያያል፣ ከወሬ ሁኔታን ያያል። ሌባ መሆኑን ብዙ የሩቅ ሰዎች አያውቁም።

ኔግሮ ቁርንጫጭ ፀጉር ያለው፣ ድቅቅ ያለ ገላ ያለው፣ ሲስቅ ቀጭን ድምፅ የሚያወጣ ልጅ ነበር ።

አንዳንድ  ቀን  ይፎርፍና ሜዳ ጥግ ውኃ ልኩ ጋር ብቻውን ይሆናል ። ዝም ይላል ኳስ አይጫወትም። ቀጭን ድምፅ እያወጣ የሚስቃት ሳቅ አትኖርም። ለመኮረጅ ብዙ አይሰቃይም።

...ጨዋታ ያበዛል...።

ስለ አባቱ አላውቅም፤ እናቱ ግን ትምህርት ቤታችን በር ጎን ላይ ቃርያ ፣ ቲማቲም፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ድምብላል፣ ኮሰረት፣ ስኳር ድንች ...ምናምን ይሸጣሉ። ብዙ ደንበኛ ያላቸው አይመስለኝም። ስንወጣ ስንገባ የደራ ገበያ አንድም ቀን አይቼ አላውቅም ።  

ኔግሮ የትምርት ቤት ስሙ መቆያ ነው። እኛ ነን ኔግሮ የምንለው።

እኛ ትምህርት ቤት የሚማሩ የሰፈሩ ልጆች ሲጠሩት ሰምተን መሰለኝ መቆያን ትተን ኔግሮ የምንለው።

መቆያ የሚባለው ክላስ ስም ሲጠራ ብቻ ነው። ኔግሮ ሲባል ነው እሱም ደስ የሚለው።

የሆነ ቀን ሃይሚ ግርማ መፅሃፍ ጠፍቶብኝ ኔግሮ ሰጠኝ አለችኝ። ጠየኩት "ከራሷ ቦክመህ ለራሷ ገጫሃት ኣ?" ስለው ፤ ሲስቅ የሚያወጣትን ቀጭን ድምፅ አውጥቶ ሳቀ  "ባክህ እኔ እንደኔ ችስታ እናት ካለው ቤተሰብ አልሰርቅም "አለ ።

ከስምንት ወደ ዘጠኝ ስንዘዋወር ኔግሮ ታስሯል አሉን። ስሰማ "ዕድሜው ለእስር ደርሷል ወይ?" ብዬ ያኔ አልጠየኩም።

የመንግስት ትምህርት ቤት ስለተማርን ለብዙ ነገር  ከዕድሜያችን በላይ ነበርን። የሚታሰሩት በግሩፕ የሚጣሉ ልጆች ስለነበሩ ብዙ  አልገረመኝም።

መስከረም አስራ ሰባት ቀን ኔግሮ ሞተ አሉን።  እናቱን ስናያቸው ጥቁር ለብሰዋል፥ ጉስቁልናው ብሶባቸዋል። ጉሊት የደረደሩት ከዚህ ቀደም ለመሸጥ ከሚደረድሩት በዐይነትም በመጠንም ቀንሶ አየሁ ።

ሞትን ያኔ ነበር በቅርብ ያወኩት ....በቅርብ የማውቀው፣ ሲያወራ የሰማሁት፣ አብሬው የተጫወትኩት ጓደኛዬ ሞተ ሲባል። ያኔ ነው ለመጀመሪያ ግዜ ያመንኩት።

የታሰሩበት ክፍል የነበረው ካቦ መቶት ነው ይላሉ፤ አንዴ ፖሊስ መቶት ነው ይላሉ፤ አንዴ ታሞ ነው ይላሉ ....
ኔግሮ ሞተ። እውነት  ነበር!

"ልጅ ይሞታል እንዴ?!" አልኩኝ
ለምን መቆያ አሉት ግን  እናቱ??
በዛ ዕድሜው እንዴት በዛ ልክ አሰበላቸው??
በምን ይሆን የሚፅናኑት??
ለምን ሌባ ሆኖ ለጓደኞቹ ታመነ??

እንዴት  የሰረቀውን እንደትልቅ ሰው አስቦ ተከራክሮ ሸጠ?? ላለፋበት ነገር እንዴት ዋጋ ሰጠ?? ለምን ምንም ከሌላቸው ሰዎች አልሰርቅም አለ??

በዛ ዕድሜው እንዴት አረጀ ?
እሺ ይሁን መርህ እና ሌብነት እንዴት አብሮ ሄደለት!!

እኔንጃ ኔግሮ ግን ሞተ አሉ !!!
      © Adhanom Mitiku

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

28 Jan, 18:52


"እናቴ ትሙት"
* * *

ልጆች ነበርን። ሞትን በቅጡ እንረዳ ዘንድ እድሜያችን የማይፈቅድ ልጆች ነበር። የመሳፍንት እናት እንደሞተች የሰማነው ህይወት እና ሞት ድንበርተኞች መሆናቸውን በማናውቅበት ለጋነታችን ነው።

"የመሳፍንት እናት ሞተች" ተባለ እንደዋዛ።
"ሙዝ ገዝተን እንሂድ" አልን እንደ ቀልድ።
መሳፍንት ከቃለ- ህይወት ትምህርት ቤት ከዜሮ ክፍል ጀምሮ አብሮኝ የተማረ ጓደኛዬ ነው። ዜሮ ክፍል ቅደመ መደበኛ ትምህርት መሆኑ ነው። ዜሮ ክፍልን ስንሻገር አንደኛ ክፍልን እንሆናለን።
ቅዳሜ ቅዳሜ የቃለ ህይወት ሰንበት ተማሪዎች መፅሐፍ ቅዱስን በልጆች ቋንቋ እንማራለን። ከሰኞ እስከ አርብ ደግሞ ፊደል እንቆጥራለን።

ሶስተኛ ክፍል ሳለን የመሳፍንት እናት መሞቷን ሰማን። እንደ ቀላል ነገር "አስቱ ሞተች" አሉን። ታላላቆቻችን እትዬ አስቴር ይሏታል። እኛ ግን እንደ ቆሎ ጓደኛችን አስቱ እንላታለን።

አስር የመሳፍንት ጓደኞች "ትምህርት ቤት መዋጮ ተጠይቀናል" ብለን ፥ ከእናታችን መቀነት ሰርቀን ፥ ሀብታም ዘመዶቻችንን አስቸግረን ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም ሰበሰብን። እያንዳንዳችን ስሙኒ ስሙኒ ነበር ያዋጣነው።
በሰበሰብነው መዋጮ ሙዝ ገዝተን ለቅሶ ሄድን። ተሳቀብን። "የልጅ ነገር" አሉን አንዳንዶች።

"አስቱ" ስትሞት ያላለቀሰው ብቸኛ ሰው መሳፍንት ነው። ሁላችንም እንባ ስንራጭ ጥግ ላይ ሆኖ በመገረም ያየን ነበር። ወንድም እህቶቹ እየተነሱ ሲወድቁ እያያቸው ፈገግ ብሏል። ጎረቤት እንባ ሲራጭ ቲያትር እንደሚመለከት ታዳሚ በተመስጦ ተከታተላቸው።
ያ ሁሉ ሰው ሲያለቅስ መሳፍንት አላለቀሰም።
"እኛ እንኳ ስናለቅስ እርሱ ያላለቀሰው ምን አስቦ ነው?" ብለን ተናደንበታል። ለአስቱ ስላላዘነ አቂመንበት ነበር። ቂማችንን ፈጥነን ረሳነው እንጂ ልንጣለው ወስነን ነበር።

"ለእናቱ ያላለቀሰ ክፉ" አልነው መሳፍንትን።

አመታት አለፉ። አስቱ ከሞተች ስድስት አመት በኋላ መሳፍንት ወደ'ኛ ቤት መጣ።
"ተነስ ሳሚ" አለኝ።
"የት እንሂድ?"
"አስቱጋ ደርሰን እንመጣለን"
"የት?"
"መቃብር ቦታዋ"
እንደታዘዝኩት አደረግኩ።
አረም የበቀለበት ፥ ጥሻ የሆነ መቃብር ስፍራዋ ወሰደኝ። የአስቱ መቃብር ጋር ስንደርስ "እዚህ ቁም የምናወራው ነገር አለ" አለኝ።
"ከማንጋ ነው የምታወሩት?" አልኩት ግራ ገብቶኝ።
"ከአስቱጋ"
በግራ መጋባት ቆሜ ወደ መቃብሯ ተጠጋ። እናቱ መቃብር ጋር ቆሞ ያጉተመትም ጀመር።
እየፈራሁ ልጠጋው ስሞክር እንድመለስ በእጁ ምልክት ሰጠኝ። ግራ ቢገባኝ ራቅ ብዬ ቆምኩ። ለአንድ ሰአት ያህል ከመቃብሯ ጋር አወራ።

ወደ ቤታችን ስንመለስ "እንዴት ልትመጣ ቻልክ?" አልኩት።
"በየሳምንቱ እመጣለሁ" አለኝ በግድ የለሽነት
"ከመች ጀምሮ"
"ካረፈች ጀምሮ"
ዝም አልኩት። የምለው ሲጠፋኝ አቀረቀረቀርኩ።
"ሁሌ እመጣለሁ። ዛሬ ብቻዬን መምጣት ስላልፈለግኩ ነው ካንተጋ የመጣሁት" አለኝ
እንባዬን እንዳያየው ታገልኩ።

ይህ በሆነ በወሩ ቤታችን መጣ። ቤት ሲደርስ ከእናቴ ጋር ፀብ ገጥሜ አየኝ። ፊቱን አዙሮ ወጣ። ተከተልነው። እኔና እናቴ ተከተልነው።

"መሳፍንት አትሂድ" እናቴ አዘዘችው።
ቆመ። አቀርቅሮ እያለቀሰ ቆመ።
"ምን ሆነሃል?" እናቴ ነበረች ጠያቂዋ
"አንተ ቢያንስ የምትጣላት ፥ የምትናደድባት ፥ የምትጨቃጨቃት እናት አለችህ። እኔ ግን...." ሳግ ንግግሩን ገታው።
የማልቀሱ ተራ የሁለታችን ሆነ። እኔ እና እናቴ እኩል እንባ አፈሰስን።

የመሳሳፍንት ዘመዶች ለወንድም እና እህቶቹ ያዝናሉ። "የእናታቸው ሞት ጎድቷቸዋል" ይላሉ። ለመሳፍንት ግን የሚያዝን የለም። "እሱ በእናቱ ሞት አልተጎዳም። የሞተች ቀንም አላለቀሰም" ይሉታል። ዘመድ እና ጎረቤት ለሁለት ወንድሞቹ እና ለሁለት እህቶቹ ያዘነውን ሲሶ ያህል ለእርሱ አዝነው አያውቅም።

አመታት አለፉ። መሳፍንት ፍቅረኛ ያዘ።

አንድ ቀን ለፍቀረኛው "እናቴ ትሙት" ብሎ ማለላት። እየዋሻት መሰላት።
"በስርኣት ማልልኝ" አልችው
"እናቴ ትሙት" አላት በድጋሚ
"እናትህ ስንቴ ትሙት?" አለችው።
ይሄኔ ተስፈንጥሮ ተነሳ። እጆቹ ተንቀጠቀጡ፥ ጉንጮቹ ቀሉ፥ ሁለቱ አይኖች እንባውን አፈሰሱ።

እኛ እናውቀዋለን። መሳፍንትን እናውቀዋለን። "እናቴ ትሙት" ብሎ ከማለ እውነቱን እንደሆነ እናውቃለን። "እናቴ ትሙት" ብሎ እንደማይዋሽ እናውቃለን...

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

27 Jan, 19:44


ለትንሽ ጊዜ ልዘናጋ.... ለትንሽ ጊዜ ልሳሳት.... ለትንሽ ጊዜ እኔን አልሁን.... ለትንሽ ጊዜ መስመር ልሳት.......ለትንሽ ጊዜ.... ለትንሽ ጊዜ ጥፋት ልስራ በሄድኩበት ሰው ይጥላኝ ......ለትንሽ ጊዜ ማስበውም ማወራውም አይጣማችሁ....ለትንሽ ጊዜ.... ፈጣሪ አለ አትበሉኝ እንዳለ እኔም አውቃለው.... ያልፋል ትንሽ ጊዜ ነው..... በጊዜ ብዛት ይረሳል አትበሉኝ እንደሚያልፍ እኔም አውቃለሁ...... ትንሽ ጊዜ ግን የተሰማኝን ውስጤን ላዳምጠው..... የተጎዳሁትን እስክጠግን ለትንሽ ጊዜ እራሴን አልሁን..... ትንሽ ጊዜ..... ለትንሽ ጊዜ ትጨነቅ እናቴ..... አባቴም ሚለው ይጥፋበት...... ጓደኞቼም ግራ ይጋቡ....ለትንሽ ጊዜ ደካማ ሆኜ ልታይ.... ጥንካሬን እስክመልሰው.... ዳግም እራሴን እስክሆን ትንሽ ጊዜ ብቻዬን ተዉኝ..... እንደሚያልፍ አውቃለው.... እንደማልፈው እርግጠኛ ነኝ .....እንደተጎዳው እና እንደተሻለኝ እንዳስብ እንጂ ምንም እንዳልተፈጠረ እንድሆን አታድርጉኝ.... ለትንሽ ጊዜ ብቻዬን ተዉኝ .....በእንባ እራሴን ዳግም ልጠበዉ..... የበደሉኝን ጮኬ ከውስጤ ላውጣ .....ለትንሽ ጊዜ .....ብቻ እስኪያልፍ እንዳላልፍ ብቻ ፀሎት አድርጉልኝ


ለትንሽ ጊዜ


✍️kalkidan


http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

27 Jan, 17:39


ዛሬ የስራ ባልደረባዬ ምን ብትለኝ ጥሩ ነው...

"አሁን እኮ ነው የማየው....ሰዉ tiktok ላይ አረገዝሽልኝ ብሎ መኪና ይሸልማል.....እኔ መች አወቅኩ በነፃ አራት ልጅ ፈልፍዬ ፈልፍዬ...."


just for fun😁



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

26 Jan, 18:53


እኔ   

አልወደውም እንዴ ብዬ አስባለው አንዳንዴ ........ሌላ ሰው ጋር ሄጄበት ..... ሳላስብለት ....ሳልናፍቀው ቀርቼ አይደለም .......እንደውም እንደሱ በሕይወቴ ሚያስፈልገኝ ሰው ያለ እራሱ አይመስለኝም ......ሳየው ጥርሴ ብቻ ሳይሆን ሰውነቴም አብሮ ሚስቅ ይመስለኛል.... እሱ ጋር ስሆን ማንም የማያውቀውን እኔነቴን ማንነቴን አገኘዋለሁ....... እቅፉ ውስጥ ስገባ የትም የማላገኘው ሰላም ይሰማኛል.... ግን የሚያጣላ ነገር ተገኝቶ ስንጣላ.... እሱን ሳጣ የምሆነውን እያሰብኩኝ እራሴን አላስፈራራም ይልቅ ያለ እሱ እንዴት እራሴን እንደማቆም ....ወደፊት እንዴት እንደምቀጥል ነው ማስበው ......ባጣው ምን እሆናለው እያልኩኝ እራሴን አላስፈራራም.... እና አንዳንዴ ይገርመኛል.... እንደዚህ ማሰቤ.... ሰው እንዴት እንደዚህ የሚሆኑለትን ሰው  ስለይ ብሎ ሲያስብ ህይወቱ አይጨልምበትም... እንዴት ውስጤ በዚህ ልክ ድንጋይ ይሆናል...... በቃ የዚህ ጊዜ ነው አልወደውም እንዴ ብዬ ማስበው???



እሷ

ድንጋይ ሆነሽ አደለም... ሴት ስለሆንሽ ነው... ሴትነት እንደዚ ነው ምስቅልቅሉ በጠፋ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ራሷን ለማውጣት መሞከር ግዴታዋ ነው...... ሴት ሴትነቷ ከገባት.... ብዙ ሀብት አላት ......ሴትነት ትልቅ ነው....ምሳሌ ናት.....ሕይወት ናት.... ብርሃን ናት.... ጥላ ናት... ደስታ ናት... ሴት ብዙ ነገር ናት.... አየሽ አንቺ ከሱጋር ስትሆኚ ሚሰማሽን እሱም ይሰማዋል ግን እንዳቺ ዋጋ አይሰጠውም.... አንዳንዴ እያንዳንዷን ትንሽ ነገር አያስተውልም ስለማይወድሽ አደለም ግን ሴቶች እንደዚ ስለሆንን ነው.... ለምንወደው ሰው ምንም እንሆናለን... ከነሱ አንሰን ወይ ከኛ በልጠው አደለም በቃ እኛ ሴት ማፍቀር መውደድ ትችላለች ተፈጥሮዋ ነው ለዛ ነው እናት ምንሆነው ......ለናትነት የምንታደለው..... እናትነት እኮ ምድር ላይ ካሉት ሀብቶች ሁሉ ትልቁ ሀብት ነው....... ሴት ካላት ፀጋ ላይ እናትነት ሲጨመርበት አስቢው ምን እንደምቶን.... ግን መጀመሪያ ሴትነትሽን ማወቅ አለብሽ.... አንቺ ገብቶሻል ጠንካራ እየሆንሽ ነው ስሜትሽ እራስሽን እንዳያሳጣሽ እየጣርሽ ነው... ስለማትወጅው አደለም የሴት ልጅ ጥንካሬ እንደዚህ ነው.... እራስሽን ካሳመንሽው አንቺን የሚያስገርም ጥንካሬሽን ታያለሽ.... ፈጣሪ ብሎልሽ አንድ ላይ ቆይታችሁ ስትጋቡም ይሄ ጥንካሬሽ ወደ ቤትሽ ትወስጂዋለሽ.... ጠንካራ ስለሆንሽ ታጠነክሪዋለሽ.... ቆይ አንድ ጥያቄ ሊጠይቅሽ አባት ከዙ ጊዜ ውጪ ነው ሚውለው ሥራ ውሎ ማታ ቤት ሲመጣ ግን እቤት አብራን ከዋለችው እናታችን በላይ እሱን እንፈራዋለን ለምን ይመስልሻል?? እናታችን ቀን ሙሉ ስትመታን ስትጮህብን ውላ ያልሰማናት ማታ አባታችን ኮስተር ስላለ ብቻ ምንሰማው??? ምክንያቱ ም እሷ እራሷ ስታከብረው ስለምናይ ነው..... አንሳ አደለም ግን ስታከብረው ስናይ እንድናከብረው ነው..... በዛ ላይ "አባታችሁ መጣ" እያለች የሆነ አይነት የፍርሃት እና የአክብሮት ስሜት ውስጣችን እንዲፈጠር ስለምታደርግ ነው..... አየሽ እሷ ባታከብረው እኛም አናከብረውም አየሽ እናት እንዲህ ናት.... ሴት እንዲህ ናት ስለተበደልሽ.... ስለተጎዳሽ ለምን አለቀሽ ለምን ከፋሽ እያልኩ ሳይሆን እያለቀሽም ቢሆን ወደፊት መራመድ መቻል አለብሽ... ኖረሽ ነው ምታኖሪው ሞተሽ አደለም.... ብዙ ሴቶች እራሳቸውን እየጎዱ ሌላውን ደስተኛ ማድረግ ጠንካራነት ይመስላቸዋል ግን አደለም እራስሽን እንድታኖሪ  እንድትጠብቂ ከፈጣሪ የተሰጠ ግዴታ አለብሽ እንድትደሰቺ እንድትስቂ የፈለግሽውን እንድታደርጊ የተሰጠ ከሁሉ ጋር እኩል የሆነ ሕይወት አለሽ ያን ተቀብሎ መኖር ደሞ ብልሃት ይጠይቃል ያ ብልሃት ደሞ ለሴት የተሰጠ ስጦታ ነው..... አየሽ ሴት ልጅ በሞኝነት እና በብልህነት መሃል ያለች መስመር ናት...... ጅል ከሆንሽ እራስሽን ፈጣሪሽንም ታስቀይሚያለሽ..... ብልህ ስትሆኚ ደሞ ሴትነት ታስመሰክሪያለሽ.... ስለዚህ ሁሉ ጊዜ ልክ እንደ እርግብ ብልህ ሁኚ ......የሴትነትሽ ነው..... ስለማትወጂው አይደለም እራስሽን ስላስቀደምሽ ነው ያ ደሞ ጥንካሬሽ ነው እና ሁሌም ጠንካራ ሁኚ.... ሁሌም ሴት ሁኚ

እሺ!!"



✍️kalkidan



http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

25 Jan, 18:33


ቀጣይ



ስም የእኔነታችን የመጀመሪያ ማሳያ ነው.... ማንም ሰው መጀመሪያ ሚያውቀን በስማችን ነው... "ማናት እሷ?" ተብሎ ነው...."የማን ልጅ ናት" የሚከተለው.... ምናልባት አንዳንድ ሰው  ሚጠራው ሲበዛ... ውይይይ እንደው ስሜን ብቀይር ብሎ ሊመኝ ይችላል... ግን ለሁሉም እንደዛ አደለም ......በተለይ ለኔ... በስሜ ተጠርቼ ስለማላውቅ ይሆናል... ማንነቴ ምንነቴን ያጣውት..... እንደሌለኝ የሚሰማኝ... "ማነሽ" "ነይ እስኪ" "ሰማሽ" በሚባሉት ተተኪ ስም የማይመስሉ ግን ለኔ ስም የሆኑ መጠሪያዎች የተተካው..... አንዳንዴ ስም የዚህ ያክል ውድ መሆኑን ሳስብ ያስገርመኛል... ያለኝ ነገር እንደሌለን ሲቆጥር ወይ ስንነጠቅ ውድነቱ ይጨምራል... ግን እንዴትም ይጥሩኝ እንዴት እጄን ወደዋላ አጣምሬ አንገቴን ደፍቼ "አቤት" እላለው...........


እድሜዬ ስንት እንደሆነ መች እንደተወለድኩኝ አላውቅም ማንም ስራዬ ብሎ የነገረኝ የለም.... አንዳንዴ ይገርመኛል እንዴት ሰው መጀመሪያውም መጨረሻውም አይታወቅም.... ያስቃል አደል... እኔጃ ብቻ እኔ ግን ሳስበው ይገርመኛል .....

ሰዎች ይመጣሉ ብዙ ሰዎች...... የሷ ዘመዶች ....ጎረቤቶች አንዳንዴ ደሞ እኔን ሚያውቅ የእናት አባቴ ጎረቤት የነበሩ ሁሉ ይመጣሉ.... ሁሉም እኔን በማሳደጓ ሲያሞግሷት እና ሲመርቋት እሷም እራሷን ጀነን አድርጋ ተቀምጣ.... ይገባኛል ትላለች.... እኔን ማንም አያየኝም ማንም አይረዳኝም.... እንኪ አውሪ ብሎ ሰምቶኝ የሚያውቅ ሰው የለም...

በፊት በፊት እናቴ ወይ ደሞ አባቴ መተው ይወስዱኛል ብዬ አስብ ነበር ......እናም ተስፋ አደርግ ነበር.... አሁን ግን ምንም ማስበውም ምመኘውም ነገር የለም .....ብቻ ተስፋ አለኝ ከዚህ ቤት እንደምወጣ.... አንድ ነገር ይኖረኛል አሳካለው ብዬ አይደለም.... ግን በቃ... ከዚህ የሚመች ከሚመስል ግን እስር ቤት ከሆነብኝ ቤት እወጣለሁ ሚል ተስፋ አለኝ.... ተስፋ የሚያስገርም ስሜት ነው...... ጨለማ ውስጥ ሆነክ አንድ ጭላንጭል ብርሃን ትሰጥና ለነገ እንድትጓጓ ታደርጋለች ..........በተቃራኒው ሙሉ በሙሉ ጨለማ ቢሆን እንኳን አንድ ቀን ብርሃን አያለው የሚል የማይታወቅ እምነት ውስጥ እንዲኖር ያደርጋል........ ከዛ ያን እምነት ተከትለን እንድንቆይ ታደርጋለች ለኔ ሁለተኛው ነው እምነት ነው ሚያኖረኝ.......

ከዛ ሁሉ እኛ ቤት ከሚመጡት ሰዎች ውስጥ ግን  የሚያስገርሙኝ አንድ አዛውንት አሉ.... አዘውትረው እኛ ጋር የሚመጡ... ብዙ አይናገሩም ዝም ብለው ሰዎችን ያያሉ.... ለኔ ግን ሚታዘቡ ነው ሚመስሉኝ.... እኔ ወደነሱ ስመጣም እንደሌሎቹ እሷን በማሞገስ አይጠመዱም ......ትክ ብለው ይመለከቱኛል.... መጀመሪያ አካባቢ እደነግጥ ነበር.... እየቆየ ሲሄድ ግን ደስ ይለኝ ጀመር.... አንድ ሚያየኝ ሰው ተገኘ ብዬ እደነቃለው...... አንድ ንግግር በሌለው እይታ ለኔ ብዙ ነገር ትፈጥራለች .... አንዳንዴ ሲያዩኝ ፈገግ ብዬ አፀፋውን እመልሳለሁ.... የከፋኝ ጊዜም ይፍረዱኝ አይነት ፊታቸው ላይ እንባ ያቀረሩ ዓይኖቼን ይዜ እቆማለው....... እሳቸው ግን ምንም አይሉም ዝም ብለው ያዩኛል..... አንዳንዴ እያዩኝ ራሱ አይመስለኝም..... ታዲያ እንደዛ ሳስብ እበሳጫለው መልሼ ግን አይን እያላቸው ካላዩኝ አይናቸው ደክሞ ያዩኝ እኚህ አዛውንት ይበልጡብኛል ....ታዲያ አንድ ቀን.......


አላለቀም


✍️kalkidan


http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

25 Jan, 18:23


@ortopiyaaa
@semetnbegtm
@ortopiyaaa

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

25 Jan, 13:55


የሚበላ ጠፍቶ ፡ በጠና ተርቤ
እጅና እግሬ ዝሎ ፡ ለመሞት ቀርቤ
በዚ'ም ጭንቅ ሰዓት ፡ ነፍሴ ስትታመስ
'ምን አማረህ' ቢሉኝ ፡ ከንፈርሽን መቅመስ

#ገጣሚ_እንደልቡ

@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

24 Jan, 10:54


@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

23 Jan, 19:21


ናፍቆት "አያ ጅቦ"
ኤልያስ ሽታኹን
~     ~     ~     ~     ~

የናፈቁትን እየዳሩ
የወደዱትን እየሞሸሩ
(የምን እሹሩሩ)

አንዴ ከሆነ ወዲያ ቢባል ሆዴ ባባ
ምን ሊረባ?

ያፈቀሩትን እንዲሳም ሌላን ሲታቀፍ
ላያድኑት አበባን ከማርገፍ....

እንዲያው መቀበጣጠሩ
ላይስተከል ነገሩ
(እሱ ነው መለየት ሸሩ)

እኔማ
እንሆንው ያልኩትን ከሌላ ከሆነሽው
"አፈቅርሻለሁን" የትም ካደረግሽው?

ሁሉ በነበር  ሲቀር ቅጽበትም ሲያስፈራ
ህይወት እንደዚህ ናት ያልዘራሽውን ምታፈራ፡፡

አልዘራሁም አንቺን ማጣት
(አጨዳለሁኝ ቅጣት)
አልዘራሁም
አልዘራሁ  መለየት
(አጨድኩኝ መሸኘት)
አልዘራሁ መራራቅ
ነገዬ ታየኝ  እንደጭራቅ፡፡

እንደልጀነቴ እንደአያጅቦ
ማጣት ሲመጣ በሰው አፍ ታጅቦ፡፡

"ይበልሃል" ሲሉኝ  ጥቅልል ሽፍን ብዬ
እንዲያ ነው ምፈራ መለየት አንቺዬ፡፡

እኔማ
ያንን "አያ ጅቦ" ባልፍም ተድበስብሶ
መለየት ግን በላኝ  ያውም "ከጅብ" ብሶ፡፡


https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

23 Jan, 19:00


             👧👧👧👧👧👧👧👧

"ቁንጅና ብቻ " የሚባልልኝ ልጅ ነኝ  ........ማንም ሰው የማይከራከርበት በአይኑ እንኳን  ሊያየኝ የማይፈልግ ሰው ሁሉ የሚስማማበት ቁንጅና አለኝ......... ግን ከኋላው የምትከተለው ብቻ ለሌላው እንዲሁ አባባል ቢሆንም እኔ ግን ሁሌ ምናደድበት አና ሚያበሳጨኝ ጉዳይ ነው.......... ዋናው የምበሳጭበት ምክንያት ደሞ ልክ መሆናቸው ነው......... ምንም ሙያም ሆነ ችሎታ የለኝም........ ትምህርት ላይ የለሁበት....... ሙያ ላይ የለሁበት.......በቃ መታወቂያዬ  ራሱ ያች ቁንጅዬዋ ነው..........ምናልባት ከኋላው "የሃብታሟ ልጅ "የሚል ማሳረጊያ ቢታከልበት ነው........ የራሴ የምለው ምንም ነገር የለኝም........ ወደፊት የምወርሰው ብዙ ሀብት ቢኖርም እሱን ማስተዳደሪያ ብዙ ሰራተኞች ብቀጥርም..........በትክክል ይስሩ አይስሩ የማላውቅ ደካማ ነኝ........ እና ይከፋኛል በተለይ ጓደኛዬን ህይወትን ሳያት........ እሷ ጎበዝ ናት........ ትምህርት ላይ...... ስራዋ ላይ........ ምን አልባት አንድ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ብትገባ ተቋቁሟ የማለፍ ብቃትም ብርታትም አላት....... እና በጣም ታስቀናኛለች......... የሷን መታወቂያም ብዙ ነው ጎበዝዋ...... ባለሞያዋ...... ሳቂታዋ.....ተጫዋችዋ.... ብዙ.... ብዙ..... የኔ ግን አንድ አንድ  ነው"ቁንጅናዬ" እና ይከፋኛል... ሁሉ ጊዜ ምኞቴ አንድ ቀን እንደሷ መሆን ነው ........እንደሷ ብቻ መሆን.... ያለኝ ነገር ሁሉ ተወስዶ እኔን እንደሷ ቢያረገኝ ብዬ ነው ሁሌ የምፀልየው....


          🙍‍♀️🙍‍♀️🙍‍♀️🙍‍♀️🙍‍♀️🙍‍♀️🙍‍♀️

ቁርስ በልቶ ምሳ ስለሚበሉት ነገር ማሰብ ማለት በጣም ቀፋፊ ነገር ነው..... የሰው ልጅ የድህነት ጥግ ላይ ነው ብዬ ማስበው የሚበላው ነገር ካስጨነቀው ነው.... ምክንያቱም እኛ እንደዛ ነን.... ይሄን ነገር ለመቀየር ትምህርቴን ጠንክሬ ብማርም እናትና አባቴን ለማሳረፍ የቤቱን ሥራ ባግዝም ሁሌም ቤታችን ውስጥ ምሬት አይጠፋም..... የወደፊት በጣም ያስጨንቀኛል ......ኑሮ እየተወደደ ሲመጣ በርሃብ ብንሞትስ እያልኩኝ እጨነቃለው ......ፈጣሪን አማርራለው መልሼ ይቅርታ እጠይቅና ወደ ፀሎት እና ልመና እገባለው........ ብዙ ጊዜ ምሬት ሚሰማኝ የጓደኛዬን የመክሊትን ህይወት ሳይ ነው....... መክሊት በጣም ቆንጆ ናት በጣም የሚያስገርም ቁንጅና አላት .....በዛ ላይ ቤተሰቦቿ ሃብታም ናቸው.... አንዳንዴ ለቤት አንዳንድ ነገር ምሸፍንበት ገንዘብ ትሰጠኛለች.... እሷ ስለወደፊት የምትጨነቀው ነገር የላትም... በጣም የታደለች ልጅ ናት... ምናለ አንድ ቀን እሷን ብሆን .......ይሄ ነው ምኞቴ... ፈጣሪ እንደሷ እንዲያረገኝ... ይሄ ብቻ ነው የሁልጊዜ ፀሎቴ......... እንደሷ እንድሆን



✍️kalkidan



http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

22 Jan, 18:58


ውዶቼ ከምታዩትም ከምትሰሙትም የሚጠቅማችሁን ብቻ ውሰዱ....አእምሮአችሁ ውስጥ ለምታስገቡት ነገር ወንፊት ይኑረው........


ለሆዳችን እንኳን መርጦ ማስገባት እንችልበት የለ....ለሆዳችን እንክርዳድ እንደምንጥል ለአእምሮአችንም እንጠንቀቅ....ማን እንደ አእምሮ...


እና ቤተሰብ እንደ ምክር መርጦ ማስገባት ለማይችሉ ህፃናት ልጆቻችሁ ስልክ አትስጡ....



መልካም አዳር✌️



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

22 Jan, 18:48


🤌🤌🤌



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

22 Jan, 18:31


አበዛሽው አትበሉኝ እና ይታይ✌️



የህንድ ፊልም ሲባል መጃጃል ብቻ ለሚመስላቸው ጋብዙልኝ....አንዳንዴም መጃጃል በሚመስል ነገር ውስጥ ትልቅ ቁም ነገር አለ....


Title:- Ai dil hai mushikel

አዲስ ገቢዎች የህንድ ፊልም recommend የሚደረግበት channal መስሏችሁ እንዳትወጡ....


በቅርቡ በመሳጭ ፅሁፍ እንገናኛለን....(በቅርቡ ብዬ ብዙ ፅሁፍ እንደሸመጠጥኳችሁ አውቃለሁ😔) ባሁኑ ግን እክሳችኃለሁ....


ቆዩልኝ😍

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

19 Jan, 13:44


«የአያቴን ስም ስትጠይቀኝ ኮስተር ብዬ “ሸሌ” አልኳት፡፡ “እንዴት ሸሌ ትለኛለህ” ብላ ጮኸች፤ ተገፍትሬ ወጣሁ፡፡»

“ሰውን ማሳቅ ከባድ ነው፤ ኑሮው ተጭኖታል” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ከ12 አመት በፊት በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የወጣ ቃለምልልስ እናስታውሳችሁ።

ኮሜዲያንና ድምፃዊ ታሪኩ ሰማኒያ ሸሌ፤ ሀዋሳ ውስጥ ተወልዶ ያደገ ድምፃዊ፣ ኮሜዲያንና ተዋናይ ነው፡፡ “ጫት ያመረቅናል” በሚለው ነጠላ ዜማው የሚታወቅ ሲሆን መድረክ ላይ በሚያቀርባቸው ቀልዶቹ በተለይ በሀዋሳ ከፍተኛ እውቅናን አትርፏል፡፡

“ሸሌ” በተሰኘው የአያቱ ስም ምክንያት ስለገጠሙት ችግሮች እንደሚከተለው ዘና ፈታ ያደርገናል።

ናፍቆት "እንተዋወቅ?" ስትለው "ስሜ ታሪኩ ሰማንያ ሸሌ ይባላል፡፡" ብሎ ይመልሳል።

"ሸሌ የአያትህ ስም ነው? ትርጉሙ ምን ማለት ይሆን?"

ረጅም ሳቅ…

"አንቺ ለምን የአያቴ ስም ላይ ትኩረት እንዳደረግሽ ገብቶኛል፡፡"

"...ሸሌ የሚለው ቃል በህብረተሰቡ ምን ያህል ከባድና ምን ማለት እንደሆነ ስለምታውቂ ነው፡፡ ለማንኛውም ሸሌ የአገር ስም ነው አርባ ምንጭ አካባቢ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ናት፡፡ እናም የአያቴ እናት እርጉዝ ሆነው በዚያ አካባቢ ሲያልፉ ድንገት ምጥ ይዟቸው አያቴ እዛች ከተማ ውስጥ በመወለዳቸው ነው ሸሌ የሚል ስያሜ ያገኙት..."

ጋዜጠኛዋ የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበች

"...ሸራተን ስራህን ስታቀርብ ስምህን በእንግሊዝኛ ተርጉመህ ሰውን አስቀኸው እንደነበር ሰምቻለሁ፡፡ እስኪ ለአንባብያን ተርጉሞላቸው…"

"የዛን ቀን እንዲህ አይነት ስም በአለም የለም፣ በጊነስ ላይ መመዝገብ አለበት ብለው አስተያየት የሰጡ ነበሩ፡፡ ስሜ ታሪኩ ሰማኒያ ሸሌ ነው፤ በእንግሊዝኛ ደግሞ “ሒስትሪ ኤይቲ ባር ሌዲ” ይባላል ስላቸው፣ ህዝቡ መሳቁን ማቋረጥ አልቻለም ነበር፡፡"

"ከአያትህ ስም ጋር በተያያዘ የገጠሙህ ፈተናዎች እንዳሉ ሰምቻለሁ፡፡ እውነት ነው?... ከአባትህ ሞት ጋር በተያያዘ ስማቸው ሲነሳ ብዙ ነገር መባሉን ከጓደኞችህ ሰምቻለሁ፡፡ እስኪ አጫውተኝ?"

"...በነገርሽ ላይ አባቴ አቶ ሰማኒያ ሸሌ ከ1986 ወዲህ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ በሚባለው በሽመና ስራ ላይ ብዙ እውቅና ነበረው፡፡ የሽመና ኢንዱስትሪ አስፋፍቶ ከ30 በላይ ሰራተኞች ያስተዳድር ነበር፤ ብዙ ሰው ያውቀዋል፡፡ በአጋጣሚ በወጣበት በይርጋለም ከተማ በመኪና አደጋ ይሞትና አስክሬኑ መምጣቱ ሲሰማ፣ ሀዋሳ ላይ የህዝቡ ጩኸት ከዳር እስከዳር ቀውጢ ሆነ...

...የአማረ ሆቴል ባለቤት “አንተ አቡሽ ምንድነው ጩኸቱ?” ብለው አንዱን ልጅ ጠየቁት።

ልጁም “ሰማኒያ ሸሌ በመኪና አደጋ ሞተ” አላቸው፡፡

"እንዴ አንድ መኪና ውስጥ ይሄ ሁሉ ሸሌ በአንዴ? ከካቻማሊ የበለጠ ከ60 ሰው በላይ የሚጭን መኪና አለ እንዴ? እንዴት በአንድ ጊዜ ሰማኒያ ሴቶች ይሞታሉ” ብለው እንደነበር በለቅሶው ሰሞን ሰምቻለሁ።

አንዱ ደግሞ "ሰማኒያ ሸሌ ሞተ!" ሲባል ምን አለ?

“የሀዋሳ ወንድ ጦሙን አደረ በለኛ!”

የሚገርምሽ ፋይናንስ ሀላፊ ተሳደብክ ተብዬ ከመንግስት መስሪያ ቤት ተገፍትሬ ወጥቻለሁ፡፡ የአያቴን ስም በመናገሬ ነው ተገፍትሬ የወጣሁት፡፡ የአያቴን ስም ስትጠይቀኝ ኮስተር ብዬ “ሸሌ” አልኳት፡፡ “እንዴት ሸሌ ትለኛለህ” ብላ ጮኸች፤ ተገፍትሬ ወጣሁ፡፡ ከዚያም በስንት መከራ ነው መታወቂያ አሳይቼ ያመኑኝ፡፡

ታሪኩ ሰማንያ ሸሌ በአሁኑ ወቅት ኑሮውን በሰሜን አሜሪካ አድርጎ የኮሜዲ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

19 Jan, 04:08


ይሄን ላቀዳችሁ ወንዶች ምርጥ አዝናኝ ግጥም 👇👇👇ተጋበዙልኝ።
@semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

19 Jan, 04:08


ጥምቀትና ሎሚ🍋🍋🍋

ጥምቀቱ ሲከበር ሲደምቅ እለቱ
ቀና ስል አየዋት ታምራለች ልጅቱ
ሰበርሰካ እያሉ ከሚዘዋወሩት
ተውበው ተኩለው ደምቀው ከሚታዩት
ከእንስቶች መሀል ይቺን መልከ ቀና
ከአይኔ ገባችና እጣዬ ሆነና
ስወረውር ሎሚ ላሳይ መከጀሌን
ከመቀመጫዋ አርፎ እንደ እድል
ነጥሮ እኔኑ መታኝ ከአናቴ መሀል😥

አዝኜ በሆነው በአጋጣሚው ስቄ😁
እንደተሳሳትኩ በምርጫዬ አውቄ
ሌላ አማተርኩና ከአንዲት ውብ ሎጋ
ጠጋ አልኩኝና ከጎኗ ላወጋ
አጫወትኳትና ብዙውን ለፍልፌ
እሷም ተመችቻት ብትገባ ከእቅፌ
ልዳብሰው ብዬ ያን ዞማ ፀጉሯን
ወድቆ ሂውማን ሄሩ አየው መላጣዋን😱

በዚህም ተናድጄ በእድሌ አዝኜ😡
ላልላከፍ ብዬ በልቤ ወስኜ
ልክ እንደተጓዝኩ ጥቂት በመንገዱ
ሦስት ሴቶች ባይ ከፊት ሲራመዱ
የመጨረሻ እድል ልሞክር አስቤ
ሎሚዬን አወጣው ከኪሴ ውስጥ ስቤ🍋
አይኖቼን ጨፍኜ ወርውሬ ብገልጠው
ከአንዷ ጡት አርፎ ነጥሮ ሲመጣ አየው
ግራ አይኔን ደቁሶኝ ይኸው በልዣለው
በእለተ በዓሉ አንድ አይና ሆኛለው😵

እኔ 'ምመክራቹ ለወንዶች በሙሉ
ለከፋውን ጠልተው ትተው ሴቱ ሁሉ
እስፖንጁን ታጥቀዋል ለውበት ለመከታ
እመታለው ብለ ብሮ እንዳትመታ
ለጠበሳ ተብሎ እየወረወራችሁ
ተመልሶ መ'ቶ እንዳያጋጫችሁ
እናም
ተጠንቀቁ ወገን ይቅርብን ለከፋው
ላይሳካ ነገር ለእኛው ነው እዳው
ሎሚውም ተወዷል አደልእንደ
ድሮ
በገዛ ብራችን ከምንገዛ ሮሮ
መመለስ ይሻላል በሰላም አክብሮ።

😁😁እንኳን አደረሳቹ ውዶቼ😁😁

✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
Share &comments

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

18 Jan, 16:50


ጥምቀት

ደረሰልን ቀኑ በዓለ ጥምቀቱ
ከእዳ የነፃንበት ተሽሮ ፅህፈቱ
አምላክ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር
ከንፅህቷ እመቤት ከማህፀኗ ቢያድር
ከስጋዋ ስጋን ነሳና እንደ ሰው
ቃል እንደገባለት አዳምን መሰለው

በሠላሳ ዓመቱ ሄደ ወደ ዮሀንስ
ከገሊላ ተነስቶ ደረሰ ዮርዳኖስ
ከጥምቀቱ ቦታ ናዝራዊው ሲደርስ
ተጠምቆ ሲወጣ ልጅነት ሲያስመልስ
ሰማይ ተከፈተ ተገለጠ ክብሩ
ትህትናን ሲያስተምር አየን መምህሩ
አብም መሰከረ ስለ ልጁ ወልድ
በርግብ አምሳል ታየ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ

የሰው ልጅም በምድር ዳግም ተወለደ
የዲያብሎስ ውሉ ያኔ ተቀደደ
የጨለማ ዘመን በብርሃን ተተካ
የዳዊት ትንቢቱ በኢየሱስ ተሳካ
ከዘመናት በኃላ እኛም የእርሱ ልጆች
እናከብረዋለን ይኸን የምሰራች
ከተራ ጥምቀቱ
ዛሬ ነው እለቱ
ለሁላችን ይሁን ፍስሀ ደስታ
በእደ ዩሀንስ ተጠመቀ ጌታ

✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ🥰መልካም በዓል
https://t.me/ortopiyaaa

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

17 Jan, 09:35


እንኳን አደረሳችሁ❤️

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

17 Jan, 09:18


ያ ደግ ሰው፣"ና እስቲ ተጠጋኝ" አለውና የአውራ ዶሮውን ቀይ ኮከን እየዳበሰ፡ "በለሊቱ የነገስከው አንተ ነህ...የቀን ስራህ ግን ይገርመኛል....እንዲያውም አንድአንድ ጊዜ፣ "አውራ ዶሮ ምን ይሰራል...?...አውታታ ፍጥረት ነው"....እላለሁ።....እንስት ዶሮን ተመልከታት፤እንቁላል ጥላ፤እንቁላሉን አቅፋ፤ሙቀት ሰጥታ፤ፈልፍላ፤ጫጩቶቿን ዐፈር እየጫረች፤ጥሬ እየለቀመች እየመገበች ስታሳድግ አውራው ግን እየተንጎማለለ ከመዞር በቀር ድርሻው ምንድን ነው...?"...አለው።


ያ አውራ ዶሮ የሀዘንን መንገድ ተክዞ ጀመረው...ጉሮሮውን ጠረገና "ነገሩ ወዲህ ነው" አለው....

"እንደምታየው አውራዎች እስካለን ድረስ ጎፈራችንን ብናበጥር፣ ላባችንን ብንዘረዝር ምን ይላል...?...ሁል ጊዜ የሚታረደው እኮ አውራ ዶሮ ነው።....የእንስቷንም ፈንታ የሚታረደው፣እየሞተ የሚያኖረው፣ "ስራ የለውም የምትለው አውራ ዶሮ ነው።

አንተ ግን ነገ እንደምትታረድ ብታውቅ ሀገር ለቀህ ትጠፋ ነበር....ይኧው እኔ ከአጠገቤ ኾነው አራጆቼ  ካራ እያፏጩ እንኳን አልሸሽም።....ምክንያቱም መብላት ያለበት ሰው ሚስቴንና ልጄን እንዳይነካብኝ ብዬ ነው".... አለው።


ያ ደግ ሰው: "ይቅርታ አድርግልኝ!ባለማወቄ ነው።....ለካ እውነታው እንደዚያ ነው!" እያለ አባቱን እያሰበ አለቀሰ።


📚ግርባብ....ገፅ 221



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

15 Jan, 18:58


የኔ እህት አዚህ ሰፈር ነሽ?
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ የሰፈራችን ባለሱቅ የሆነ ቀን በበሩ ሳልፍ "ወንድሜ" ብሎ በአክብሮት ጠራኝና እዚህ ሰፈር ነው የምትኖረው? ብሎ ጠየቀኝ! "አወ" አልኩት እንዴት ረሳኝ ብየ በመገረም! የረዢም አመት ደንበኛየ ነበር። ቀጠል አድርጎ
ሲጃራ ታጨሳለህ እንዴ?
አይ አላጨስም
አቁመህ ነው?
አይ ከመጀመሪያውም አላጨስም
ጫትስ ትቅማለህ እንዴ?
አይ አልቅምም
አቁመህ ነው?
ቅሜ አላውቅም! ለምንድነው ግን የምትጠይቀኝ አልኩ ገርሞኝ ። ጥያቄየን ችላ ብሎ

እ...የስልክ ካርድ ከኔ ትወስድ ነበር እንዴ?
አወ (ደግሞ እውነቴን ነው ከሱ ሱቅ ነበር የምገዛው)

ባለስንት ነበር የምትገዛው?
ባለመቶም ፣ ባለ ሃምሳም ...ባለ ....

ተወው አስታወስኩ! የመቶ ብር ካርድ አለብህ ስምህን መዝገብ ላይ አይቸዋለሁ
ማነው ስሜ ?
ስምህ ምን ያረጋል ጋሸ? ዋናው ካርዱ ነው ....😀

በኋላ ስሰማ ይሄ ሚስኪን ባለሱቅ አእምሮውን ታሞ አማኑኤል ሆስፒታል ገብቶ ነበር አሉኝ። ሚስቱን ነበር ሱቁ ውስጥ ለረዢም ጊዜ የማያት! እና ዘለግ ላለ ጊዜ ታክሞ ከአማኑኤል ተሽሎት ወጣ። ሁሉ ነገር ተስተካክሎ አንድ ነገር ብቻ ትንሽ ልክ አልመጣለትም እየተባለ ይወራል። ማንኛውም በሱቁ በር የሚያለፍ ሰው ዱቤ ወስዶ ያልከፈለው ይመስለው ስለነበር እያስቆመ አጭር መስቀለኛ ኢንተርቪው ያደርጋል። ከምንም በላይ ግን ያሳቀቀን እትየ ማርታን ጠርቶ ጠየቃት የተባለው ነገር ነው። እትየ ማርታ ዕድሜዋ 40 የተሻገረ ዘናጭ ሴት ናት!
"እህቴ ይቅርታ እዚህ ሰፈር ነሽ?" አላት
አወ ምን ልርዳህ? አለች በሚያምር ፈገግታ
ፔሬድ ማየት አቁመሻል እንዴ ወይስ ታያለሽ ? አበደች ...
"ስድ ምናባህ አገባህ?" በኋላ ባሏ ተነግሮት ሊያናፍጠው ወደሱቁ ሲሄድ "ሞዴስ በዱቤ ወስዳ ያልከፈለችኝ መስሎኝ ነው ጋሸ ! ግን ከመጣህ አይቀር ታጨሳለህ እንዴ.....😀"

@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

15 Jan, 03:28


"ሁልጊዜ የማውቀው እንደሚወደኝ ነው...... የኔ እንደሆነ ነው ...እንደምንጋባ.... ልጅ እንደምንወልድ ....የሴትነት ፍላጎት አልነበረም እድሜ ሳይሄድ እያሉ ከሚጨነቁት ሴቾች መሀል አልነበርኩም...የልጅነት ጉጉትም  አልነበረም .....ቤተሰብ አስተዳዳሪ እህት ወንድሞቼን ደጋፊ ነበርኩኝ ደልቶኝ ሞልቶልኝም አልነበረም .......

ግን በቃ እሱ ሲሆን ሁሉን ነገር ደስ ይላል ....ከሱ ጋር ሲሆን ሁሉም ነገር ያጓጓል.... አብሬው ሆኘ ብዬ ሳስብ ሁሉም ነገር አስደሳች ይሆናል ...የሌለኝን የማላቀውን የእንክብካቤ ስሜት ሲያሳየኝ ልጅ ልጅ ያጫውጠኝ ነበር.... ሁሉ ነገሬ ነበር ....ከነበረኝ የኃላፊነት ሸክም እሱ ጋር ስደርስ ነበር ቀለል ሚለኝ..... ግን እሱ እንደዛ አልነበረም ወይም እኔ ብቻ ነበርኩኝ እንደዛ ማስበው.... "

" እንዴት እንደዚህ ልትይ ቻልሽ??"

"ብዙጊዜ የተሻለ ነገር የምናገኘው .... ስለተበደልን .....ስለተከፋን.... ኃላፊነት ስለተደራረበብን... ይመስለናል ግን አደለም...... ሁሉም ሰው የተሻለ ነገር አለው.....ልቡን አሳድቦ ይበቃኛል ብሎ እስካላስቀደመ ድረስ ....ሁሉም የተሻለ የሚለውን ነገር ያገኛል.....ፍቅር ልብ ውስጥ ነው ሚቀመጠው.... ፊት ላይ አደለም ወይም ኪስ ውስጥ አደለም......

የፈለገ ቆንጆ ነኝ ብለሽ ብታስቢ እንደማይተውሽ ማረጋገጫ አይሆንሽም ምክንያቱም ካንቺ የተሻለ ቆንጆ ይኖራል ..... ሀብት አለኝ ብትይም የተሻለ ሀብት ያለው አይጠፋም.... ግን ፍቅሩ ከገፅሽ እና ከኪስሽ አልፎ ልብሽ ላይ ከደረሰ በቃ ትረጋጊያለሽ ግን ደሞ ልቡ ውስጥ መሆንሽን እሱ እንጂ አንቺ ማወቅ አትችይም ....ስለዚህ በተስፋ.... እና በእምነት ትኖሪያለሽ.... አንድ ቀን በተሻለ እስክትቀየሪ  ድረስ.... አንድ ቀን ልብ ውስጥ ምትገባ እንደምትገኝ ድረስ.... ብቻ በቃ ከዛ ቡሃላ ለራስሽ ራስሽ ብቻ እንዳለሽ ትረጃለሽ..... ቤተሰብሽን በሱ ልትቀይሪ እንደነበር እያሰብሽ እራስሽን በየቀኑ ትነቅፊያለሽ... እንባ  ቁጭት እና ፀፀት እረግጠው እረግጠው ይተውሽ እና በድን ትሆኛለሽ....

እራስሽን እና ቤተሰቦችሽን እየረዳሽ ሕይወትሽን ትገፊያለሽ..... ብዙ ሰው ያለ ወንድ ይኖራል እሷ ማሳያ ናት እያሉ ተምሳሌት እና አርአያው አድርጎ ያስቀምጥሻል.... ግን በቃ እውነቱ ልብሽ የተሻለ በሚለው ቃል ፍራቻ ውስጥ ነው... እኔም ከአንድ ሰው የተሻልኩ ነኝ ግን የተሻልሽ ነሽ ብሎ በሚስቱ ከሚቀይረኝ ወንድ... የተሻለች ቢያገኝ እንኳን የማይቀይረኝ ወንድ ስጠብቅ እስካሁን አለው እና ይሄውልሽ በዚህ ምክንያት ነው እስካሁን ያላገባሁት.... አስረዘምኩብሽ  አይደል?... ዝም ብዬ በአጭሩ ብነግርሽ ይሻል ነበር አይደል??? አወሳሰብኩብሽ???

"አይ ይሄኛው የተሻለ ነው??"


✍️kalkidan


http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

14 Jan, 14:41


ይህ እንክርዳድ በተጣለበት ስፍራ በቀለ....የተጣለበት ስፍራ ላይ ማንም ስለማይፈልገው ደሞ ቶሎ ቶሎ ነው የሚያድገው....እንዴት አይመቸው ለነገሩ....!..."የማረፍ መንገድ እኮ አለመፈለግ ነው....."

ምን አልባት ከሰማኝ ለዚህ እንክርዳድ እንዲህ ብዬ ልንገረው እስኪ...."እነርሱም ይመርጡሀል...አንተም ትመረጣለህ...ለምንድን ነው እየገፈተሩ የሚያባርሩህ....?...በር እስኪነቃነቅ ውጣ ብለው የከረቸሙብህ...?...ደሞ ልፋት የሚያደርስ እየመሰለህ እኮ ነው....


ወደ ልቦናህ ብትመለከት ግን ልዩነቱ ሁሉ አይርቅም ነበር...እባክህ ተመሳስለህ አትብቀል....."



ግርባብ...ገፅ 9



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

14 Jan, 14:15


ከዚ መፅሀፍ የወደድኩትን መልዕክት ባጋራችሁስ😉

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

13 Jan, 03:06


ኤልያስ ሽታሁን

@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

11 Jan, 10:09


ዳሪ እና ፊፊ
++++++++++




ሃዋሳ ሃይቅ ዳር የሚገኝ ምግብ ቤት ተቀምጫለሁ፡፡



በሃይል ርቦኛል፡፡




ሊገመት እንደሚችለው አብዛኛው ምግባቸው አሳ ነክ ነው፡፡

አሳ ጥብስ፣ አሳ ወጥ፣ አሳ ዱለት፣ አሳ ለብለብ፣ ጥሬ አሳ፡፡



መአት ሰው መአት ነገር እያዘዘ ነው፡፡


አሄሄ፡፡ ቶሎ በልቼ ረሃቤን ማስታገስ የማይታሰብ ነው፡፡ 


አላይ ብሎ ያስቸገረኝን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ የሚወረወርና የሚዋከብ አስተናጋጅ በስንት መከራ ጠራሁት፡፡



ፊት ለፊቴ ቀጥ ብሎ ቆመና ትእግስት በማጣት፣
‹‹እሺ ምን ላምጣልሽ?›› አለኝ፡፡
‹‹ምን ምን አላችሁ?›› አልኩት አሳ ምንትስ አሳ ምንትስ የሚለውን ዝርዝር እንደ አዲስ ስምቼ የሚሆነኝን ለመምረጥ፡፡




‹‹አሳ ጥብስ፣ አሳ ወጥ፣ አሳ ዱለት፣ አሳ ለብለብ፣ ጥሬ አሳ››  አለኝ በፍጥነት፡፡




‹‹ሙሉ አሳ ጥብስ አምጣልኝ›› ብዬ መለስኩለትና፣

‹‹ያው መቼም አሳው ፍሬሽ ነው አይደል?›› አልኩት ጨመር አድርጌ፣



አጠገባችን ከተዘረጋው የሃዋሳ ሃይቅ ውስጥ ያጠመዷቸውን አሳዎች እዚሁ ተመጋቢዎች ፊት ለፊት  ከመረብ አላቀው፣ አጽድተውና አብስለው ሲያቀርቡ እያየሁ እንዲህ ያለ ጥያቄ መጠየቄ ቀልድ ቢጤ  መሆኑ ይገባዋል ብዬ ነበር፡፡ እሱ ግን ፈገግም ሳይል -




‹‹ፍሬሽማ ነው›› ብሎኝ እየከነፈ ሄደ፡፡



-----


አስር ደቂቃ ሳይሞላ ከትኩስነቱ ብዛት የሚጨስና ድንቅ ሆኖ የተጠበሰ ሙሉ የአሳ ጥብሴን ይዞ ተመለሰ፡፡

ሲያስጎመጅ፡፡



ኮካ ብዬው ፔፕሲ ስላመጣልኝ እሱን እንዲያስተካክል ልነግረው ስሰናዳ ትሪው ላይ የተጋደመውን አሳ ጥብሴን እየጠቆመ፣
‹‹ይሄኛው አሳ ከሃያ ደቂቃ በፊት እየዋኘ ነበር›› አለኝ፡፡



ቢዘገይም ለቅድሙ ቀልዴ አፀፋውን መመለሱ ነው፡፡



እኔ ግን ራሴ የጀመርኩት ቀልድ የሄደበት መንገድ ረብሾኝ በመሳቅ ፈንታ ተሳቀቅሁ፡፡



ልክ በዚያችው ቅፅበት ያመጣልኝ ሙሉ የአሳ ጥብስ ከተኛበት አሮጌና ትልቅ ትሪ ላይ ሆኖ ሲያፈጥብኝ አየሁት፡፡




በትክክል ነው ያነበባችሁት፡፡
አሳ ጥብሱ አፈጠጠብኝ ነው ያልኳችሁ፡፡



አስተናጋጁ እንደሄደ፣

‹‹ፍቅረኛዬን እንድታገባኝ ልጠይቃት መንገድ ላይ ነበርኩ›› አለኝ አሳው፡፡

አካባቢዬን በፍጥነት ቃኘሁ፡፡


ጆሮዬ ነው ወይስ አሳው እያዋራኝ ነው?




‹‹ይሄኔ የቀጠርኳት ቦታ ተገትራ እየጠበቀችኝ ነው፡፡ እኔ ግን ይሄው ድብን እስክል ተጠብሼ ያንቺን የማይጠረቃ ሆድ ለመሙላት እዚህ ትሪ ላይ ተዘርግቻለሁ፡፡ ደግሞ ጠዋትም መአት ንጹሃን እንቁላሎችን እንደበላሽ የማላውቅ እንዳይመስልሽ….››




አመዴ ቡን አለ፡፡



‹‹እነዚያ ምስኪን እንቁላሎች አንድ ቀን የሚያማምሩ ዶሮዎች የመሆን ህልም እንደነበራቸው እርግጠኛ ነኝ…ማን ያውቃል…ይሄኔ እኮ ሲያድጉ ወደ አርባ ምንጭ ተጉዘው ዓለምን ማየት፣ ሕይወታቸውን ማጣጣም ይመኙም ነበር…ምን ዋጋ አለው..? …ያንቺ ጨካኝ ሆድ ላይ ጣላቸው…››



ወገን…እያበድኩ ነው ልበል….?

አለበለዚያማ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል…?





ቬጂተሪያን አይደለሁም፡፡
እንዲያውም ቅጠላቅጠል ስጋን ማባያ እንጂ ዋና ምግብ ነው ብዬ አላምንም፡፡

አለ አይደል…የኮባ ቅጠል ለክትፎ ሰሃን እንደሚሆነው አይነት…?




ታዲያ ምን ሆኜ ነው እንዲህ ያለ ጣጣ ውስጥ ገባሁት…?

ለምንስ ነው በድንገተኛ የጥፋተኝነት ስሜት የተዋጥኩት…?





ተዉት ተዉት…ገባኝ! ስለ ራበኝ ነው…ረሃቡ፣ ሙቁቱና ድካሙ ነው እንዲህ የቀን ቅዠት ውስጥ የጨመረኝ…





አስተናጋጁ በአንድ እጁ ኮካ ኮላዬን፣ በሌላ እጁ ደግሞ ሌላ ሙሉ አሳ ጥብስ የተጋደመበት ትሪ  ይዞ መጣ፡፡



አሳውን አጠገቤ ለነበሩት ጥንዶች አቅርቦ፣ ኮካውን ሰጠኝና ሲሄድ ራሴን ወደ እውኑ ዓለም ለመመለስ ጭንቅላቴን ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ አነቃነቅኩና አሳዬን መብላት ልጀመር ስል ግን አጅሬ እ------ሪ ብሎ ጮኸ፡፡

አስተናጋጁ አይደለም፡፡ አሳው ነው፡፡




‹‹ወይኔ ፊፊዬ…የኔ እናት…አንቺንም አገኙሽ…? ወይኔ ፊፊዬ! ›› እያለ እንደጉድ መጮህ ቀጠለ፡፡




አተኩሬ ሳየው በተኛበት አጠገቤ ላሉት ሴትና ወንድ የቀረበውን የአሳ ጥብስ እያየ ነው፡፡

የተጠበሰ አሳ ሌላ የተጠበሰ አሳን እያየ እንደጉድ ሲጮህ አየሁ፡፡



ወዲያው ደግሞ ጩኸቱን ቀንሶ በተረጋጋ ድምጽ፣



‹‹ ለነገሩ ይሁን…ይሄው ይሻላል…ቢያንስ መንግስተ ሰማይ እንገናኛለን…የአሳ መንግስተ ሰማይ አለ አይደል…? ፊፊዬ…የኔ ፍቅር…ድምጼ ይሰማሽ ይሆን…ዳሪ ነኝ የኔ ውብ….አትፍሪ እሺ….ትንሽ ቆይተን እንገናኛለን…አትፍሪ….››





አሁን እንደለየልኝ ገባኝ፡፡




አስተናጋጁን ጠራሁት፡፡

‹‹ቺፕስ አምጣልኝማ?›› አልኩት ዳሪ ያለበትን ትሪ ከፊቴ እየገፋሁ፡፡
‹‹አሳው ምን ሆነብሽ?›› አለኝ አንዴ እኔን፣ አንዴ ዳሪን እያየ፡፡
‹‹ምንም አልሆነም…ሃሳቤን ቀይሬ ነው›› አልኩት፡፡



ግራ በመጋባት አየት አድረጎኝ ሄደ፡፡






ኮካዬን እየጠጣሁ ወደ ጎን ስመለከት ጥንዶቹ ፊፊን መሻማት ሲጀምሩ አየሁ፡፡


ወደ ዳሪ ዞርኩ፡፡



ገላው ቀዝቅዟል፣ ድምጹም ጠፍቷል፣ እኔ ውስጥ ያለው የጥፋተኝነት ስሜት ግን እንደ አዲስ ይንቀለቀላል፡፡




ስያሜ ያጣሁላቸውን ስሜቶች በማስተናገድ እንደተጠመድኩ ከጥንዶቹ ወንዱ፣



‹‹ ይቅርታ….ጨው አለቀብን…እሱን ትሰጪን?›› ብሎ ጠረጴዛዬ ላይ ያለውን የጨው እቃ እያመላከተ ጠየቀኝ፡፡



ቅድም ገና ፊፊን መብላት ከመጀመራቸው መአት ጨው ሲነሰንሱባት አይቼ ስለነበር ተገርሜ፣



‹‹ጨው ነው ያልከኝ?›› አልኩት፡፡
‹‹አዎ…ስለማትጠቀሚበት….››
‹‹ጭራሽ ከዚህ በላይ ጨው ልትጨምሩባት ነው…?››



አምባረቅኩ፡፡



‹‹ ሞታለች እኮ…ምናለ ቅንጣት  ክብር  እንኴን ቢኖራችሁ? ›› ብዬ ጮህኩ፡፡



በድንጋጤ በተበለጠጡ አራት አይኖቻቸው አፈጠጡብኝ፡፡


በአካባቢው ያለ እና የሰማኝ ሰው ሁሉ በፍርሃት ተመለከተኝ፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን እጆች አጥብቀው ሲይዙ አየሁ፡፡





ሰዉ ሁሉ ድምፁን አጥፍቶ ሲያየኝ ይሰማኛል፡፡



በአጠገቤ ሲያልፍ የነበረውን ሌላ አስተናጋጅ ዳሪን አንስቶ እንዲወስድልኝ ነግሬው አይኖቼን ወደ ሃይቁ ወረወርኩ፡፡



ትልቁ መረብ በርካታ አዳዲስ አሳዎችን አጥምዶ ሲወጣ አየሁ፡፡


ምፅ።

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

11 Jan, 06:47


ዛሬ ልጨርሳት.....


ልወጣ ጥቂት ቀናት ሲቀሩኝ አጠገቤ የሚተኙት ሴትዮ ታሪካቸውን ይነግሩኝ ጀመር....ማዉራት ብዙም ስለማይፈቀድ ከላይ ከላይ ብሶታቸውን ይነግሩኝና ዝም ይላሉ....አንዳንዴ እኔም አወራቸኃለሁ...ዝም ብዬ እሰማቸዋለሁ....ስሜን አያውቁም....ስማቸውን አላውቅም....ግን እንሰማማለን....


የምወጣ ቀን ስልካቸውን ተቀበልኳቸው....ፀበልተኛ ናቸው...ለአዲስ አመት ቤታቸው እንደምመጣ ነገርኳቸው እና አድራሻቸውን ተቀበልኳቸው....ቤታቸው የመሄድ ሀሳብ የመጣልኝ በአልን ከሰው ጋር ካከበሩ እንደቆዩ ስለነገሩኝ ነው...እኚህ ወይዘሮ ባለትዳር እና የአስር ልጆች እናት ነበሩ...ታመሙ....ባላቸው ወዲያው ንብረት እንኳን ሳያካፍላቸው አንዲት ኮረዳ አገባ....ከልጆቻቸው አንደኛው በወር ትንሽ ብር ይልክላቸዋል...በተረፈ የት ወደቅሽ የሚል የላቸውም....

እዚች ጋር ልብ በሉልኝ....."አለም ላይ ያለ ምንም ነገር መተማመኛ አይሆንም....የገዛ ልጅም ቢሆን...."....."አስር ልጅ ለአንድ እናት የማይሆንበት ጊዜም አለ....."....

አንድ ቀን ምን ብለውኝ ነበር "ከፈጣሪዬ በላይ በትዳሬ እና በልጆቼ እተማመን ነበር....አሁን ግን ከቁጥር ሌላ ምንም እንዳልሆኑ ገባኝ....ብዙ ጊዜ ጠርቶኝ አቤት አልል ብዬው ነበር....አሁን ብቻዬን ስቀር አቤት አልኩ...."

እዚች ጋር ደግሞ የሆነ ጊዜ መፅሀፍ ላይ የቃረምኳት ታወሰችኝ...."ፈጣሪ የቱ ጋር ሲመታን አቤት እንደምንል ያውቃል...እረኛ መጀመሪያ በጎቹን በድምፅ ይገስፃል....አልሰማ ሲሉት በጅራፍ ይመታቸዋል.....የፈጣሪ ጅራፍ ደግሞ ከእረኛ ከባድ ነው....."....ሳላስበው ህልም ባይ ከምደሰተው በላይ ተማርኩ....


የበአል እለት ቤታቸው ሄድኩኝ....ቤታቸው ሽንቁሩ ሚካኤል ነበር....ስደውልላቸው ደስታቸው ድምፃቸው ላይ ነበር...ቤታቸው ገባን...በአልን አብረን አሳለፍን...."የባዳ ልጅ ሰጠኝ" ብለው አለቀሱ....እንዳድር ለመኑኝ....ውስጣቸውን ብትንትን አርገው ነገሩኝ....እናቴን መረቁልኝ....የሚያደርጉኝ ግራ ገብቷቸው አገላብጠው ሳሙኝ.....አብረን ከሚካኤል ደብር ገብተን ተመልሼ እንደምመጣ ነግሬያቸው መኪና እስከሚይዝ ድረስ ያለውን ረጅም መንገድ ሸኙኝ....እየሸኙኝ እስከአሁን ድረስ ውስጤ የቀረ አንድ ነገር አሉኝ.....

"ትናንት ቤቴ ሙሉ ነበር....ስጋው ቂቤው በገፍ ነበር...ልጆቼ ነበሩ.....ዛሬ ደግሞ እንደምታዪኝ ነኝ....አየሽ ልጄ ትናንት ጠዋቴ ላይ ነበርኩ....አሁን እኩለ ቀኔ ላይ ነኝ....ማታዬ ደግሞ ገና ነው....እርሱ ያሳምርልኛል.....".... አሉኝ....I was 21...ግን መሸብኝ እያልኩ ነበር....እኚህ ሴትዮ ገና እኩለቀን ላይ ከሆኑ እኔ ገና በጠዋቴ ነው የታከተኝ ማለት ነው....ራሴን ጠየቅኩ.....


"እንደመጣሁ አማርኛ አልችልም ነበር....እና ለመጀመሪያ ጊዜ ገብቶኝ ስብከት የሰማሁበት ቀን ትዝ ይለኛል ደስታዬ....እግዚአብሄር ይመስገን አማርኛ ችዬ ስብከት በመስማቴ...."....ሲሉኝ ደግሞ ለመደሰት ማገዶ መፍጀቴ አስደነገጠኝ.....


ታክሲ መያዣዬ ደርሼ ተሰናብቻቸሁ ወደቤቴ ገባሁ....በወሬ ስልኬ ተሰረቀ....ስልካቸው ጠፋኝ....ከዛ በኃላ ብዙም ሳልቆይ ጊቢ ተጠራን....ራሳቸው ያቃጠሉብንን ጊዜ ለማካካስ ብለው ያለ እረፍት አስተምረው አስመረቁን....

....ህልም አላየሁም ብዬ ሳማርር ነበር....ግን ምን አልባት ህልሜ እሳቸው ሆነው ቢሆንስ....አንዳንድ ህልም አይደገምም መሰል ድጋሚ አላገኘኃቸውም.....




Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

10 Jan, 18:16


ሎስአንጀለስን ሞቅናት!

(በእውቀቱ ስዩም)

ትናንትና ሎስአንጀለስ በእሳት ስትነድ፥ እኔ በአጋጣሚ ጓደኞቼን ለመሰናበት እዚያው ከተማ ውስጥ ነበርሁ፤ ሆሊውድ አካባቢ በእግሬ እየተንሸራሸርሁ ድንገት ቀና ብየ ሳይ፥ ከተማው እንደ ደመራ ይንቦገቦጋል፤ መጀመርያ ላይ ፥የዮዲት ጉዲትን ፊልም እየሰሩ ነበር የመሰለኝ፤ ብዙ ሳይቆይ የሳት አደጋ መኪና እየተብለጨለጨ ባጠገቤ አለፈ፤

ነገሩ “ሲርየስ” መሆኑን ያወቅሁት፥ የሆሊውድ አክተሮች ልጆቻቸውን እንኮኮ አዝለው፥ የቤት እቃቸውን ባንሶላ ጠቅልለው፥ ሲራወጡ ስመለከት ነው ፤ ደንብ አስከባሪ የሚያባርራቸውን የመገናኛ ቦንዳ ሻጮችን አስታወሱኝ፤ ቻክኖሪስ ባንድ የእሳት አደጋ ሰራተኛ ታዝሎ፥ ሳል እያጣደፈው ከቤቱ ሲወጣ አይቼ “እድሜ አተላ “ብየ ተከዝኩ::

እያወካ እየተጋፋ ከሚሸሸው ሰው መሀል ተቀላቅየ መሮጥ ጀመርሁ፤

ቀጣዩ ፌርማታ ላይ ትንፋሽ ለመሰብሰብ ቁጭ ባልሁበት፥ የሆነ ፖሊስ መጣና፤

“Are you ok?” አለኝ፤

“ እድሜ ልኬን ለፍቼ፥ እቁብ ጥየ ፥ ያፈራሁት ቤቴና ንብረቴ በእሳት ጋየ” ብየ መለስኩለት፤

“ስራህ ምንድነው ?”

መቸም በዚህ ሰአት ላይ ሊያጣራ አይችልም ብየ በማሰብ፥

“ ቀን የጣለኝ የሆሊውድ አክተር ነኝ “ አልሁት፤

“ምን ፊልም ላይ ሰርተሀል?”

”በማርቲን ሉተር ኪንግ የህይወት ታሪክ ዙርያ፥ በሚያጠነጥን ፊልም ውስጥ ከበድ ያለ ሚና ነበረኝ ” አልሁት፤

ፖሊሱ አልተፋታኝም፤

“ምን ሆነህ ነው የተወንከው?”

“ ማርቲን ሉተርኪንግ ፥ ሁለት መቶ ሺህ ህዝብ ሰብስቦ ንግግር የሚያደርግበት ትእይንት ትዝ ይለሀል?” አልኩት፤

“አዎ”

“ ከህዝቡ መሀል አንዱን ሆኜ ተውኛለሁ፤ ፊልሙ ጀምሮ አንድ ሰአት ከሶሰት ደቂቃ ከአምሳ ሁለት ሰከንድ ላይ ራሱን እሚነቀንቀው ሰውየ እኔ ነኝ “

ፖሊሱ ጥሩ ሰው ነው፤ ወስዶ ከተፈናቃዮች ጋራ ቀላቀለኝ፤ የከተማው ከንቲባ ዘለግ ያለ ንግግር አደረጉ ፤” የተወደዳችሁ ተፈናቃዮች ሆይ ! የከተማው አስተዳደር ቤታችሁን መልሶ እስኪገነባ ድረስ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ልናቆያችሁ እንገደዳለን ”ብለው ንግግራቸውን አሳረጉ

በመጨረሻ” የአደጋና ስጋት መስርያ ቤት” ሊቀመንበር ወደኔ ቀርቦ፥

“ የደረሰብህን ኪሳራ እስክናጣራ ፥ይቺን ነገር ላንዳንድ ነገር ትሁንህ “ አለና አምሳ ሺህ ዶላር የያዘች ትንሽ ብጫ ፌስታል አስጨበጠኝ፤

ብዙም ሳልቆይ፥ፌስቡኬ ላይ የሚከተለውን ማሳሰቢያ ጣል አረግሁ፤

Bewketu Seyoum marked himself safe from poverty .


https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

10 Jan, 15:58


https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

10 Jan, 15:58


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

10 Jan, 14:21


ከሀይማኖት ጋር ሳታያይዙ ይቺን አንብቡልኝማ......



ተማሪ እያለሁ ያለቅጥ የረዘመ እረፍት ተሰጠንና የጎረቤት "lag አደረግሽ" ጥያቄ ጥላቻ ለ15 ቀን ከአንዱ ገዳም ሄድኩ....እንደዛን ወራት የምሄድበት ዘመድ ስለሌለኝ ያማረርኩበትን ጊዜ አላስታውስም....አንድ እናቴ ናት ያለችኝ....ግን አንድነቷን ሰርዤ ሺህ አርጌያት ነበር....ያን ሰሞን ነው አንድ መሆኗን ያመንኩት...


የገዳም ምርጫዬ ከአዲስ አበባ ቅርብ መሆኑ ላይ ያጠነጥናል....ገዳሙ በባዶ እግር የሚኬድበት እና በቀን አንድ ጊዜ ያውም 12 ሰአት አንድ እፍኝ ሽንብራ እና አንድ ብርጭቆ በሶ የሚጠጣበት ነበር...(ሰንበትን ሳይጨምር)....ያቺን አስራ አምስት ቀን ያለእቅድ እስከ 12ሰአት  እየፆምኩኝ ገዳሙ እንደሚፈቅደው እቀማምሳለሁ...የሚገርመው ነገር ግን በቀን አራት ጊዜ ምግብ አምጪ የሚለኝ ሆዴ አደብ መግዛቱ ነበር....

እዚች ጋር ልብ በሉልኝ የገዳሙ በረከት አለማስራቡ እንዳለ ሆኖ ሁለት lesson ያዙልኝ "ሆድም እንዳገኘው ነው ..."....and "ቁርጡን ያወቀ ለማግኘት አይሟሟትም"

እህል የምንቀማምሰው ከቤተመቅደሱ ራቅ ብለን ነበር....በመሀል መካከለኛ ወንዝ ነገር አለ....ያልዘነበ ቀን pis ቢሆንም ሲዘንብ ግን የግድ አሻጋሪ ያስፈልጋል....መሬቱ ራሱ እንደ ተልባ ያሙለጨልጫል....ሰዉ የሚሄደው ተደጋግፎ ነው...እኔ ብቻ ብቻዬን የመጣሁ እስኪመስለኝ ድረስ አይኔ መርጦ ሚያሳየኝ ተደጋግፈው የሚሄዱትን ነው.... ግን አንድ መሬቱ የከዳኝን ቀን አላስታውስም....

እዚች ጋር ሌላም አንድ lesson ያዙልኝ....."ላለመውደቅ የግድ የሰው ድጋፍ መኖር የለበትም....ከቤት ያወጣችሁ እርሱ እንደሚደግፋችሁ እወቁ...(በlife ደግሞ የፈጠራችሁ አምላክ ብቻችሁን እንደማይተዋችሁ)


በገዳም ቆይታዬ በጣም እየተበሳጨሁ ነበር....አዳራሽ ውስጥ በጋራ ነው የምንተኛው እና side talk ባይፈቀድም አልፎ አልፎ የሚያወሩ ሰዎችን እሰማ ነበር....እና አብዛኛዎቹ ህልም ያያሉ....በህልም መልስ ተሰጠን ይላሉ....እኔ ደግሞ ጭራሽ አይቼ አላውቅም....እና ለጠየቅኩት ነገር ለምን መልስ አይሰጠኝም ብዬ እበሳጭ ነበር....እንደውም የእንቅልፍ ሰአቴን አበዛ ነበር ህልም ለማየት ብዬ.....

እዚች ጋር ደግሞ ሌላ ነጥብ ያዙልኝ...

"የአብዛኞቻችን ችግር ወጤቱን አብዝተን እንፈልጋለን ነገር ግን ለውጤቱ የሚያንደረድሩንን struggles እንፈራለን....ወይም ልክ እኔ እንዳደረግኩት ተቃራኒውን እናደርጋለን....ማለትም ህልሙን ለማየት 24/7 ከመፀለይ ይልቅ መተኛት እንመርጣለን....ሀሳቤን ግልፅ ለማድረግ የህልማችንን criteria ለማሟላት አንሟሟትም....የመተኛ ሰአታችንን በማስፋት ህልማችንን ከእኛ እናርቃለን እንጂ....ውዶቼ ጊዜ ሚወስደው ትግሉ እንጂ ለህልሙማ አስር ደይቃ ይበቃል እኮ....."


ባልጨርስም ይችህን እያብላላችሁ ቆዩኝ...



Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

10 Jan, 12:12


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

08 Jan, 06:15


ከስራ እንደተመለስኩ ቤቴ ሳልገባ እሷ ጋር ሄድኩ....አሁንም በሩ እንደተበረገደ ነው....

"ሰኒዬ እንዴት ዋልሽ...ሻል አለሽ....?.በቃ ይሄን በር አሻፈረኝ አልሺኝ አይደል...."....ከሰላምታ በኃላ ቀጥታ ቀኑን ሙሉ ያብሰለሰለኝን ጉዳይ ጠየቅኩ....

"እግዚአብሄር ይመስገን...ይበቃል ደህና ነኝ....ይሄንንስ ማን አየበት...."

"በሩን....".....አላስጨረሰችኝም...

"ይኧውልሽ ልጄ ሰው የሌለው ሰው ብርድ አያስፈራውም....በሩን ዘግቶ ከብርዱ ከመከላከል በላይ በሩ እንደተዘጋ በስብሶ ሊቀር እንደሚችል ነው የሚያስበው....ውሀ እንኳን የሚያቀብለው ሰው የሌለው ሰው በሩን ከፍቶ አላፊ አግዳሚ ከመጠበቅ ውጪ ምን አማራጭ አለው....

ብቻ መቅረት ከባድ ነው....አንቺ እንደ ልጄ ነሽ...ግን ደግሞ አንድ አስገዳጅ ሁኔታ መጥቶ ከእኔ እና ከወላጅ እናትሽ ምረጪ ብትባዪ መልስሽ ግልፅ ነው....ምንም ያህል ብትወጂኝ አንቺ ህይወት ውስጥ ሁለተኛ ምርጫ ነኝ....በሁሉም ሰው ህይወት ውስጥ እንደዛ ነኝ....የእኔ ብዬ አፌን ሞልቼ የምለው ሰው የለኝም....በእሱም ህይወት ውስጥ እንደዛ ነበርኩ.....".....አለችኝና እንባ የቋጠረው አይኗን በአዳፋ ነጠላዋ ጥለት ደባበሰችው....

"ማነው እርሱ...."

"እድሜ ልኬን ስጠብቀው የነበረው ሰው....ያገባኛል ብዬ ወጣትነቴን የሰጠሁት ሰው ሁለተኛ ምርጫው አርጎኝ አሰረፈደብኝ...."


"አንዳንዴ ህይወት ላይ ማርፈድ ሁለተኛ እድል ላይኖረው ይችላል...የሴት ልጅ እድሜ ለአንዳንድ ተፈጥሮአዊ ሁነቶች የተገደበ ጊዜ ነው ያለው....የተገደበ ጊዜ ሲኖርሽ ስራሽን በአግባቡ እንደምትሰሪው ሁሉ ህይወትሽን በአግባቡ ምሪው....ህይወትሽ ውስጥ የምታስገቢውን ሰው በጥንቃቄ ምረጪ....

ሰማሽኝ ልጄ ከምንም በላይ ነገርሽን በፀሎት አሳስቢ....ማግባትና መውለድ ብቸኛ ምርጫ ባይሆንም ፍላጎትሽ ከሆነ ፍላጎቱ ከሆነው ጋር እንዲያገናኝሽ ጠይቂ....አሁን እኮ ከፈጣሪ ጋር ለመወቃቀስም አቅም አጣሁ....."

"እንዴት...."

"እንዴት ብዬ 'ለምን' ልበለው...?...ቀድሞውንስ መች እንዲገባባበት ፈቀድኩ....አሁን የምለምነው አንድ ነገር ብቻ ነው...."

"ምን....?..."

"በበሬ የሚያልፍ ሰው እንዳያሳጣኝ...."



Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

07 Jan, 04:44


በዓል አንወድም
       ፡
       ፡
ቢጫ መሬት
ህይወት ግን እንደሬት

አበባ ሙሉ ሜዳ
ህይወት ግን እንግዳ

ኩበት እና ውበት
ህይወት ሀዘን ሽበት

"እንኳን አደረሰን" ተባብለን
የሆነ የሚከፋን ነገር አለን

ከውስጣችን እንደታመቀ
አልቅሰነው እንዳላለቀ
ወልደነው እንዳልተመረቀ
      
            ብቻ
በዓል አልወድም የሚስብለን
       አንድ ነገር አለን::


መሬቱን ቢጫ ወርሶት
እኛ ደሞ ትንሽ ብሶት

አናለቅሰው ነገር ተድላ
ጠማን አንል ነገር ጠላ ተደላድላ

ራበን አንል ምን ተብሎ
መሶቡ አልከደን ብሎ

ምን እንደቸገረን ባናውቅም
በዓል  ግን አንወድም፡፡

ከጠላ የቀረረ
ከመውረድ የቀረ

ዕንባችንን ዋጥ አድርገነው
ሲጨፍሩ ለይመሰል ትከሻችንን ነቅንቀነው

ሲስቁ የምንስቀው
ሲቀርቡ የምንቀርበው
(ይምሰል ነው
ቢጤ ለመሆን ነው)

                 እዛና እዚህ ሚያስረግጠን
                 እዚያና እዚህ ሚረግጠን
                               ፡
                               ፡
                      ከትናንት - እውርርርርር
                      ከትናንት - ስብርርርርር
                      ከትናንት - ሽንክልልልል
     ትንሽ መከፋት አለን የልጅ 'ዲምፕልን' የሚያክል ፡፡

ኤልያስ ሽታኹን


https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

06 Jan, 12:24


ከሀዲ የማያመው ይመስላቸዋል...አዎ በነሱ ቤት የከሀዲ እንባ የአዞ እንባ ነው....አስገድዶ ደፋሪ እንኳን ድርጊቱ በሰይጣን እየተሳበበለት ለከሀዲ ግን ማሳበቢያ የለውም....

የድንገተኛ ክፍሉ ጠርዝ ቆሜ ያለከልካይ ሳነባ "ይበላት" ያላለኝ የለም.....

"ይቺ ከሀዲ....ስለተረፈ ነው ምታለቅሰው....ሀብቱን ለመካፈል እኮ ነው የመጣችው"....ብለው ሲሉኝ ድምፃቸውን ጮክ አድርገው ነው....እንድሰማ ነው መሰል።

አዎ ክጄዋለሁ....እኔ መች አልካድኩም አልኩኝ....ሌባን ሌባ ነህ ቢሉት "አሀሀ ታወቀብኝ እንዴ" ብሎ ሰፈር እንዲቀይር ያደርጉት ይሆናል... እኔ ግን ከሀዲነቴን ሀገር እንደሚያውቅ አውቃለሁ... እዚህ ነኝ ሳልል ብን ብዬ ጥዬው ሄጃለሁ....ለምንድን ነው ስሜን ደጋግመው የሚነግሩኝ....


እሺ ስሜን መንገሩን ይንገሩኝ....ግን ለምንድን ነው በማልቀሴ የሚበሳጩት...እንባ አበድሩኝ አላልኩ......



ከድንገተኛ ክፍል ወጥቶ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል እስኪገባ ድረስ አልተለየሁትም ነበር....የፅኑ ህሙማን ክፍሉ ግን ቤተሰቦቹን ካስገባ በኃላ አላውቅሽም አለኝ...በሩን ላዬ ላይ ጠረቀመ....

ማንም አላዘነልኝም...ምክንያቱም ከሀዲ ነኛ....በውኑ ግን ከከሀዲ በላይ የሚያሳዝን አለ.....?



Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

05 Jan, 19:09


‹‹እየተፋፈርን ስለሆነ ነው እንጂ ማንም ኑሮን እየተቋቋመው አይደለም››

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

ለሪፖርተር ጋዜጣ.....


@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

05 Jan, 16:02


Trauma ስትመርጡ...

    ትምህርት ሁላችንንም እንደዚህ በሰለቸን ሰዓት የሳይኮሎጂ ክፍለ ጊዜ ብቻ ነው ሰውየው ከሰዓቱ በላይ ቢያስተምርም ሳይደብረን እንደውም ደስ ብሎን የምንማረው።

    የfresh man አስተማሪ ቢሆንም የእሱን ክፍል ገብቶ የሚማረው ግን የሁሉም አመት ተማሪ ነው።የመጀመሪያ ቀን "ከርዕስ ወጥተሀል" ብሎ አንዱ ቀለሜ ሲጠይቀው በግዴለሽነት እጁን ኪሱ ውስጥ ከቶ

     "ለፈተና የምትማሩ እና የምትፈተኑ ልጆች የተሰጣችሁን module አንብቡ እና ተፈተኑ እኔ የመጣሁት ስለ pavlov dog theory ላወራ አይደለም የምፈልገውን የእውነት የሚጠቅማችሁን ነው የማስተምራችሁ የሚደብረው ካለ መውጣት ይችላል" ሲል ግማሹ ተማሪ ወጣ በቀጣዩ ቀን እጥፍ ተማሪ ከተለያየ department ክፍሉን ሞላው

    "መቼም የዚህ ዘመን ልጆች ፋሽን ይመስል trauma የሌለው መኖር አይችልም የተባለ ይመስል ሁላችሁም የሌለባችሁን trauma እየፈለጋችሁ ራሳችሁን በትልልቅ የአእምሮ በሽታ ተጠቂ አድርጋችኋል ወይም አለብን ብላችሁ በይናችኋል

   ስለዚህ ዛሬ ስለ trauma እና trauma response እናወራለን" ብሎ ከሶስት ሰዓት በላይ አወራ እና

     "የመጨረሻ በዚህች ሀሳብ ላይ ተወያይተን እንጨርሳለን የምሳ ሰዓታችሁ እያለፈ መሆኑን ያስተዋላችሁ አይመስልም" አለ ሰዓቱን እያየ እውነትም እንኳንም ምሳ አልፎብን የደከመን ገና ከቁርስ የተመለስን ነው የምንመስለው

      "እሺ እስካሁን ስለ trauma አይነቶች እና ስለ ተለያዩ trauma response አውርተናል so አሁን controversial ነገር ነው የምጠይቃችሁ

       ከነገርኳችሁ ውስጥ ለሰው ልጅ ቢኖረው የሚጠቅመው የትኛው trauma እና trauma response ነው?" አለ

        ክፍሉ በፀጥታ ተዋጠ "መልስ የለም? አትሞክሩም?!" አለ ፈገግ ብሎ ሳራ እንደልማዷ ፈጠን ብላ "I mean እስካሁን የነገርከን እኮ አሰቃቂ ነገሮች ናቸው እንዴት ጠቃሚ ሊሆን የሚችል ይኖራል?!"አለች

         ክፍሉ ከእሷ ሀሳብ ጋር በመስማማት ትንሽ ተጉረምርሞ ወደቀደመ ዝምታው ተመለሰ

         "ልክ ነሽ የtrauma ጥሩ አለው ማለቴ ሳይሆን ጥቅም ያለው አለ ለአብዛኛው ስኬታማ ሰው እንደ driving force የሆነው ነው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?!

        "የመገፋት ወይም ያለመፈለግ ስሜት ነው ይሄ trauma ግን ብቻውን ጥቅም የለውም ምክንያቱም ተስፋ መቁረጥ ሱሰኝነት እና ሌሎች destructive ልማዶች ሊያመጣ ይችላል። ስለዚህ ጥቅም የሚኖረው መቼ መሰላችሁ በትክክለኛው trauma response ሲታጀብ ነው

       እሱም ራስን proof የማድረግ ጉጉት ሲያድርብን ነው። በግርድፉ ስታዩት አንድ ሰው ሁሌ የሆኑ ሰዎችን standard ለሟሟላት ሲለፋ ማየት አሳዛኝ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እንደዚ የኖሩ ሰዎች ትኩረት አልሰጡንም ያሏቸውን ሰዎች ቤተሰብ ሊሆን ይችላል standard ቢያሟሉም ወይ ጥሰው ቢበልጡም ችግሩ ይሄ ተሽሎ የመገኘት ጉጉት እና ስግብግብነት ከውስጣቸው ስለማይወጣ ያገኙት፥ የሆኑት ወይ ከደረሱበት በላይ የሚታያቸው የበለጣቸው ነው

        ስለሆነም ለእነሱ ሁሉም ቦታ ፉክክር ነው ማንኛውም ሰው ሲያጋጥማቸው እንዴት መብለጥ እንደሚችሉ ነው የሚያሰላስሉት ስለዚህ ሁልጊዜ የተሻለ ለመሆን ሲዳክሩ የሆነ ሰዓት ላይ ምርጥ ሆነው ራሳቸውን ያገኙታል አድናቂያቸው በዝቶ እንደ icon የሚያያቸው በርክቶ እንኳን አይተዉም እረፍት ማድረግ ባላቸው መደሰት ወደኋላ እንደመቅረት ስለሚሰማቸው ሁልጊዜም ራሳቸውን በማብቃት ይጠመዳሉ።" አለና ሰዓቱን ደግሞ አየ።

       "እና ከዚህ በኋላ trauma ስትመርጡ ይሄኛው የበለጠ ፍሬያማ ስለሚያደርጋችሁ ይሄንን ምረጡ። ለጊዜው ግን ምሳ ብሉ thank you" ብሎን ወጣ

    በንግግሩ ምናችንን እንደነካው ባላውቅም የተወሰነ ደቂቃ እሱ ከወጣም በኋላ አልተንቀሳቀስንም ነበረ።


ናኒ


https://t.me/justhoughtsss

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

05 Jan, 09:45


አሁን ላይ የገባኝ ነገር እድሜያችን እየጨመረ በሄደ ቁጥር ማውራት እየቀነስን እንደምንሄድ ነው....በቀላሉ አንስቅም ማገዶ እንፈጃለን....ብንስቅ እንኳን እንብዛም አይደለም....ድሮ ብዙ የማያመን እኮ ምን አልባት በቀላሉ ስለምናወራ እና ስለምንስቅ ቢሆንስ....ማደግ ደስ የሚል ነገር ቢሆንም ነገሮችን ማስተዋል ስንጀምር ማደጋችንን እንጠላዋለን....

ብር እንደሌለን አስበን አንጨነቅም ምክንያቱም ልጆች ነበርና....የሌላ ሰው ሀላፊነት ነበርን....

ትልቅ ስትባል በንግግርህ መገመት ስለሚመጣ መርጦ ማውራት ትጀምራለህ....እድገት ደስ ይላል እኮ...ግን ትቆጠባለህ.... የተመረጡ ቃላቶችን ጣል ስታደርግ ቃልህ ውድ ይሆናል...ትከበራለህ....ከመከበርህ ጀርባ ግሳንግስ አለ....ሀብት...ስልጣን...እውቀት...ኩራት....ብዙ ብዙ...

እመኑኝ የትልቅነት ቀመር ከልጅነት ይከብዳል....በሰው አይን ከመሙላት ምን አልባት mathes ትምህርት ላይ ያለችዋን X ማግኘት ይቀላል...



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

05 Jan, 06:06


"8k ገባልኝ"...ስላት ከልቧ ተደስታ "የምርሽን ነው...ማን ነው ያስገባልሽ እ..ባዛር ውስጥ ያየሁት ልብስ አለ ታበድሪኛለሻ"..ከምትል ጓደኛ ይጠብቃችሁ😁

ሰዉ ካለው subscribers አንፃር ትንሽ ሊመስል ይችላል....ግን እነዚህ 8 ሺህ ሰዎች ቤቴ እንግድነት ቢመጡ ቦታ ይበቃቸዋል ወይ ነው ጥያቄው(🙄ናኒ ናት ያለችኝ)....

so ምንድን ነው "አታካብጂ ብዙ አይደሉም....it's just telegram channal" ምናምን ለሚሉ ሰዎች ያለንን ስናመሰግን ነው የሚጨመርልን ለማለት ያህል ነው...and  ነገሮችን ባየናቸው ቦታ ነው ሚገዝፉብን which means ትንሽ ነው 8k ብለን ራሳችንን ከሌሎች ከምናነፃፀር ይልቅ ትናንት 7.9k እንደነበር ብናስታውስ ከራሳችን ጋር ብንወዳደር ይሻላል በሚለው ነው....and it's just the beginning...ገና እናድጋለን....ስለምታነቡልኝ አመሰግናለሁ😊

እና left እያላችሁ ያስቸገራችሁ ሰዎች ከሄዳችሁ ቶሎ ሂዱና ያሉኝን ላመስግንበት እንጂ...አንጀቴን በላችሁት እኮ....🥹



Thanks for 8k subscribers🥳🥳

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

05 Jan, 05:50


"ግን ለምን...."....አይን አይናቸውን እያየች ጠየቀች።

"እሱን የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው...ሁሉም ነገር በምክንያት ነው"...አሏት በድዳቸው ፈገግ እንደማለት እያሉ....


"መጥፎ ሰው አይደለሁም ያውቃሉ...እኔ እንደዚህ መሆን አልፈልግም...ነገስ ምን ይፈጠር ይሆን እያልኩ መኖር አልፈልግም...


እኔ ኮ ሳቄን አላምነውም...ብዙ ስስቅ እምባዬ ሩቅ እንዳልሆነ ይሰማኛል...የሆነ አይነት ስሜት ነው...ውርር የሚያደርግ...አንዴ ከጥልቅ ወስዶ የሚወረውር...አንዴ ደግሞ ከነ አካቴው እልም ብሎ የሚጠፋ....በአንድ ሰአት ውስጥ መቶ ሺ ዝቅታ...መቶ ሺህ ብሶት...መቶ ሺህ ስብራት አስተናግዳለሁ....ድንገት መጥቶ እላዬ ላይ ሲደኮን ይታወቀኛል...ለሆነ ምናምነኛ ጊዜ ሞት ሞት ይለኛል..."

"ለበጎ ነው...."....ብለው ነጠላቸውን ወደመቋጨት ገቡ...ካሁን አሁን ይቀጥላሉ ብላ ብትጠብቃቸውም እሳቸው ከነጠላቸው ጥለት አልነቀል አሉ....

"ሁላችሁም እንደዚህ ነው የምትሉት...'በምክንያት ነው...'....ትንሽ ለወጥ ካደረጋችሁት 'ለበጎ ነው'....በቃ ሌላ ምንም አታውቁም...እስቲ ንገሩኝ ምኑ ነው በጎ...?"....ስሜቷ ድምጿን አጎላው...የእሳቸውን እርጋታ ግን አልረበሸውም....

"ምን እንደምመኝ ያውቃሉ...."....አፈጠጠችባቸው....

መልሳቸውን ሳትጠብቅ ቀጠለች....

"አእምሮዬ ውስጥ ያለውን ድምፅ ላይመለስ መደምሰስ...በአንድ አይነት ጥሩ ስሜት ቀኔን መዋል...ይሰሙኛል ጠዋት ሌላ ሰው ማታ ሌላ ሰው መሆን ስልችት ብሎኛል...."....ከንግግሯ በኃላ አይኖቿ እምባ አረገዙ።

"ልጄ...."....አሏት ንፋስ የገፈፋቸውን አዳፋ ነጠላ ትከሻቸው ላይ እየመለሱ...በተራዋ መልስ ነፈገቻቸው...አየት ካረጓት በኃላ ማውራታቸውን ቀጠሉ.....

"አንዳንዴ ፈጣሪ ለተበጣጠሰው ጫማሽ ምትክ አዲስ ጫማ ሰጥቶ አይክስሽም....ሰማሺኝ ልጄ ለአንድ አሮጌ ጫማ ሌላ አዲስ ጫማ ላይሆን ይችላል ምላሹ...ምን አልባት ውድ ጫማሽ ላይ የሚያፈጠውን አንገትሽን ነቅሎ ወደ እርሱ እንዲያይ ያደረገው ነገር ይሆናል...ቀና ስትዪ እሱን ካየሽ ታተርፊያለሽ...አለምን ካየሽ ደግሞ ክስረት ነው....አየሽ ልጄ አይንሽ ጫማሽን ጠግቦ እርሱን ማየት እስኪጀምር ድረስ...የጫማሽ ኑረት እስኪጠፋሽ ድረስ አዲስ ጫማ ሰጥቶ ትንሿን ደስታ አያስደስትሽም......."....አሉና ወደ አዳፋ ነጠላቸው ጥለት ተመለሱ...

"እማማ..."

"እመት..."

"እዚ መኖር ከጀመሩ ስንት ጊዜ ሆኖት..."

"11 አመት...."....አሏት ጎዳና ሳይሆን የተመቻቸ ኑሮ እንደሚኖር ሰው ኮራ ብለው...
"ቤተሰብ አሎት...?"

"ነበረኝ...በአንድ ለሊት ነው ባለቤቴንም ልጆቼንም ያጣሁት..."

"እና እንዴት ቻሉት....?".....የራሷን ችግር ለአፍታ ዘነጋች....

"እግዚአብሄር በዚች ትንሽ ነገር አይመረመርም....በቤተሰብ...በጤና...በገንዘብ እጦት ተመርኩዤ ለእኔ ያለውን ፍቅር የምዘነጋ አይደለሁም....ሁሉም የእርሱ ነው..."

"እንዴት ውስጥዎ ዝም አሎት....እንዴት ጭንቅላቶት ደህና ሆነሎት....?"...

"አዬዬዬ ልጄ ሳያመኝ ቀርቶ መሰለሽ....ሰላም ባለሽና በሌለሽ ነገር የሚወሰን ነገር ስላልሆነ እንጂ...ይልቁንም እግዚአብሄር የውስጥሽን ማዕበል ሲገስፅ የምታገኚው ነገር ስለሆነ እንጂ...እርሱ ማዕበሉን ገስፆልኝ እንጂ..."

"እኔ እኮ ምን ብዬ መፀለይ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም...."...አለቻቸው የእርሷም ማዕበል እንዲረጋጋ በመሻት...ከነ እርጋታቸው መለሱላት....

"ምንም የምትፀልዪውን ባታውቂ እንኳን ዝም ብለሽ 'አውጣኝ' በይው...ፍቃዱ ካልሆነና ባያወጣሽ እንኳን ችግሩ ውስጥ መኖርሽን ያስረሳሻል...ደግሞስ እርሱ አይደል ምን እንደሚያረግ መች ይጠፋዋል...

ደግሞ መጥፎ ነገር ሁልጊዜ መጥፎ ውጤት ብቻ አይኖረውም...ቅድም እንዳልኩሽ ነው....የሚያዳልጥ ጫማ ካለሽ ሳትወጂ በግድሽ ረጋ ብለሽ መጓዝ ትለምጃለሽ..."...

"እማማ እኔ  ሀይማኖት ላይ ያን ያሀል አይደለሁም...እንደዚህ አይነት መልስ ለእኔ አይሆንም...."

"አሁን ያለሽበትን ስቃይ መርጠሽው ነው የተሰጠሽ....?"....ጠየቋት...

"አይ..."

"ጥያቄው ከየት እንደመጣ ሳቲውቂ እንዴት መልስ ትመርጫለሽ......ምንጩን አድርቀሽ በውሀ ጥም ተቃጠልኩ ብለሽ መጮህሽ ምን ይፈይዳል...."


ዝምታ....


Shewit dorka




https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

04 Jan, 12:22


ከወደድኩት❤️


"....እግርህ ቢያዝ እጅህን ተጠቀም...እጅህም ቢያዝ ሌላ አካልህን ተጠቀም....የአንድ ነገር መበላሸት የሁሉም ነገር መበላሸት አይደለም"

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

04 Jan, 10:29


የዚህ ፅሁፍ የሀሳብ ምንጩን ብዙም ባላስታውስም ድርሰት እንዳልነበር ትዝ ይለኛል...ጥልቅ ድብርት የሚመስል ነገር አለው....ግን አልዋሻችሁም ወደ መሀል ሳልገባ "የሆነ መሄጃ እንደመፈለግ" የሚለውን ፓርት ደግሜ ሳነበው እንደተለመደው ከሁሉ ተናቁሬ የማድርበት ዶርም አጥቼ የፃፍኩት ነበር የመሰለኝ😂....

እንቀጥላለን

✌️

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

04 Jan, 10:24


እንዲሁ ድክም እንደማለት ነገር...የሆነ መሄጃ እንደመፈለግ ነገር...የሆነ በማንም የማልታወቅበት ቦታ መደበቅ እንደመፈለግ...እርፍ እንደማለት ነገር....ለሆነ ምናምን አመት ተኝቶ መነሳት ያምረኛል...ደግሞ ትንሽ ቆይቶ 'ስለነገ ለምን ትፅፊያለሽ...?' ብሎ ብዕሬን የሚነጥቀኝ ይመስለኛል...ተስፋዬን ነጥቆ በማይሰረዝ ትናንት መቀነት ላይ ያከርመኛል...ደህና እኮ ነኝ...እንዲሁ አልፎ አልፎ እንዲህ ያረገኛል እንጂ....😔


Shewit dorka



https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

04 Jan, 06:53


ዶርም ውስጥ ነገር አብራጅ በመባል እታወቅ ነበር....ቢያጠፉም ባያጠፉም ኩርፊያን ቶሎ መስበር እወድ ነበር....በስርአት ዱክክ ይለኛል የሆነ ቅሬታ ኖሮ ዶርም መቀመጥ...እንደውም ከዶርም ጓደኞቼ ጋር ስጣላ የማድርበት ሌላ ጓደኞቼ ዶርም ነበር...

የሆነ ጊዜ ግን ከሁለቱም ተናቁሬ ማደሪያ አጥቼ ያለ እቅዴ ላይብረሪ ሳጠና አድር ነበር(ማጥናት አትበሉት....ምን አባቷ...ገደል ትግባ እንዴ ተጨማለቀች እኮ...ወይኔ ሸዊት የዚህ ጊቢ ጎዳና ተዳዳሪ እኮ ነሽ....ሲያጠኑ አይታ ዶሮ ታንቃ ሞተች ምናምን እያለ ሲበጠብጠኝ ነው ሚያድረው ጭንቅላቴ😂)....ከዛ ጠዋት ክላስ ሲወጡልኝ ነው ክላስ ቀጥቼ ሄጄ ምተኛው....ምን አለፋችሁ የዱር አደር ኑሮ ነበር ምኖረው😂

እንደውም አንዷ ጓደኛዬ"ብትለምጂው ነው ሚሻልሽ....አትሩጪ ተጋፈጪ" ትለኝ ነበር(she is the one ደሞ ለንቦጯን ዘርግታ የምትጠብቀኝ ሰው😣)


የእኔን የሚያብሰው ደግሞ የተጣላሁት ጓደኛዬን ልብስ እንኳን ማየት አለመፈለጌ ነው😂....እበጠበጣለሁ....ድምፃቸውን ስሰማ በተለይ ፈታ ብለው እየሳቁ በቃ another level..."እኔን ብቻ ነው የሚደብረኝ...ሳቂ ጥርስሽ ይርገፍ...ፀጉርሽ ይመለጥ"....በሆዴ የማልለው የለም...😁


ብቻ ይሄ ፅሁፍ የሚያጠነጥነው ሁሌ ሸዊት ትሸነፍና ታናግረን ብለው ጭንቅላቴ ላይ ፊጥ ያሉት ጓደኞቼ ላይ ነበር😂....እንደውም ከታረቅን በኃላ "በየተራ እንሸናነፍ" እንዳልኳቸው ትዝ ይለኛል😁



እና ምን ልላችሁ ነው....እየተሸነፍን✌️



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

04 Jan, 06:52


ሁሌ መሸነፍ አይከብድም...ሁሌ ይቅርታ መጠየቅ...ሁሌ ላለማጣት መሟሟት...ሁሌ ከረፈደ ማስተዋል...ደሞ ለመርፈድ አፈጣጠኑ...የቱ ጋር እንዳሸለበኝ አላውቅም...የማውቀው ነገር ቢኖር እንደደከመኝ ነው....


ያው እኔው ነኝ

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

04 Jan, 06:31


ሰላም ቤተሰብ


ስንቶቻችሁ ናችሁ አጫጭር መጣጥፎቼ ድርሰት ብቻ የሚመስላችሁ....?


anyway ዛሬ የራሴን ስሜት ቻናሌን እንደ ዲያሪ ተጠቅሜ በድርሰት ስም ያጋራኃችሁን ፅሁፎች ከነ ምንጫቸው እዘከዝካለሁ😁

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Jan, 19:13


ውይ ወንዶች!

ባል ነገረኛ ሚስቱ በነገር ስትለበልበው እስኪ በረድ ቀዝቀዝ ብትል ይልና ለጉብኝት ወደኢየሩሳሌም ይወስዳታል ይላል የሰማሁት ቀልድ! ያው ምላሷን ቻል አድርጎ ብዙ ነገር ጎበኙ። በመጨረሻ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ከሞት የተነሳበትን መቃብር ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ ምሳ ሲበሉ ሚስት ትን ይላታል። (ስንጠረጥር እየበላችም ንዝንዝ ላይ ነበረች 😀) ብቻ ትንታው አጓጉል ስለነበር ትሞታለች። በኋላ የአካባቢው ሰወች ባልን በገጠመው ድንገተኛ ሀዘን ሊያፅናኑት ሞከሩ "በደረሰብህ ነገር እናዝናለን ግን እዚህ የተቀደሰ ስፍራ መሞቷ እድለኛ መሆኗን ያሳያል...በአጋጣሚ ደግሞ እዚሁ ከተቀበረች ለዚህ ወር ብቻ ለቀብር ምንም አትከፍልም ነፃ ነው፤ ወደአገርህ ለመውሰድ ከፈለክ ግን በትንሹ ለማጓጓዣ አስር ሽ ዶላር ያስወጣሀል ይሉታል! ባል"ግዴለም የፈጀውን ይፍጅ ወደአገሬ ጫኑልኝ" ... አለና በሆዱ " እዚህ ልማደኛ ቦታ በሶስተኛው ቀን ብትነሳ የማን ያለህ ይባላል?" 😀 ጮክ ብሎ ደግሞ "እኔን ያስቀድመኝ የኔ ፍቅር... ህህህህህህ"


https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

02 Jan, 13:01


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

25 Dec, 19:24


https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

25 Dec, 11:33


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

25 Dec, 09:47


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

25 Dec, 05:01


እሷ ትናንቷን ስታወራ ዝም አለማለት አይቻልም....ዝም በል ሳትለኝ ዝም እላለሁ...የምላት ስለማጣ እለጎማለሁ....አሁንም ትናንቷን የኃሊት ሄዳ እየነገረችኝ ነው....


"የሆነ ጊዜ አንድ ስሟን በቅጡ የማላስታውሳት ከኃላዬ የምትቀመጥ ልጅ ከማጅራቴ እብድ የሚያህል ነጭ ቅማል አንስታ በእጄ ሰጠችኝ...ታውቃለህ ምን ሰአት እንደቆሸሽኩ ጠብቆ የሚያጥበኝ ሰው እንኳን አልነበረም...ከውርደቴ በላይ ለምን ከማጅራቴ አንስታ በእጄ እንደሰጠችኝ ማሰላሰል ያዝኩ...ቅማሉን ምን እንዳረገው ነው የሰጠችኝ.....?...መልሼ ሰውነቴ ውስጥ ልጨምረው....ወይስ ቤቴ ወስጄ ሶፋ ላይ አስቀምጬ ቡና ላፍላለት....."....አለች እንባ በአይኗ እንደሞላ የፌዝ ፈገግታዋን እየፈገገች....

ትንሽ አርፋ ቀጠለች.....


"ምን አስባ ነው እያልኩ ስብሰለሰል ድምጿን ጮክ አድርጋ  "ቅማልሽን በማደጎ አሳድጊው"....ብላ በሙሉ ተማሪው አሳቀችብኝ....እንደ እዛን እለት ስሙኒ አክዬ አላውቅም......"....ብላ ያጠራቀመችውን እንባ ዘረገፈችው.....ወደ ደረቴ አስጠጋኃት እና  አይኗን ሳምኳት....ማልቀሷን ገታ አድርጋ አተኩራ ትመለከተኝ ጀመር....ይሄኔ አይኗን የሳመው ከንፈሬ እንደ ልጃገረድ ሲሽኮረመም ታወቀኝ....ስታየኝ የምታነበኝ መሰለኝ....አይኗን መቋቋም ሲከብደኝ ወደ ደረቴ መለስኳት....


ደረቴ ላይ ሆና ማውራቷን ቀጠለች....


"ታውቃለህ አንድ አንድ ሰዎች ጉድፍህን የሚያነሱልህ ሸክምህን ለማቅለል አስበው አይደለም.... ጉድፍ እንዳለብህ ለማስታወስ እንጂ....እጅህን ሲይዙህም የምርም ሊደግፉህ ፈልገው ሳይሆን እጃቸው መስራት አለመስራቱን ሊሞክሩብህ ነው....

ለቅፅበት ከያዙህ በኃላ ለአፍታ እንኳን ሳያስቡ ይለቁሀል....ገደል አፋፍ ላይ ብትሆን እንኳን ግድ አይሰጣቸውም....ሸክሜን አራገፉልኝ ብለህ ሳትጨርስ ቦታ ቀይረው መልሰው ያሸክሙሀል...ከማጅራትህ አውርደው በእጅህ ይሰጡሀል....በቃ ማድረግ የሚችሉት ይሄንን ብቻ ነው".....አጥብቄ ከማቀፍ ውጪ የማደርጋት ግራ ገባኝ....ከእቅፌ አውጥቼ አለሁልሽ አይነት አስተያየት አየኃት....


"እንደዚህ አትየኝ...."....አለችኝ እንባዋን እየጠረገች....


"አለሁልሽ...."....አልኳት አይኔን ምላሴ ሲተባበረው....

"ሸክሜ ብዙ ነው....ይሰለችሀል...."....ስትለኝ ድምጿ ላይ እርግጠኝነት ነበር....

"ግድ የለሽም አይሰለቸኝም....የእኔ ሁኚ"...አልኳት ወኔዬን ሰብሰብ አድርጌ....

"እህ..."....አለች የሹፈት እንደመሳቅ

"ያስቃል.....?..."....ጠየቅኩ...

ወደ ጆሮዬ ተጠግታ በሹክሹክታ ቃላት ወርውራ ሄደች.....

"ቅድሚያ የራሴ ልሁን....ሸክሜን ላራግፍ..."....የመጨረሻ ንግግሯ ነበር....ከዛን ቀን በኃላ ደግሜ አላየኃትም....


ሸክሟን አራግፋ ስታበቃ ረስታኝ ይሆን ወይ ሸክሟ ከአቅሟ ከብዶ ቀብሯት እንጃ....


ብቻ አውላላ ሜዳ ላይ ብቻዬን ቀረሁ....


Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

24 Dec, 18:31


Betam eyersahu new...gn ማምሻ meslgn...lik negn..?

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

24 Dec, 18:31


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

24 Dec, 18:24


ርእሱን....

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

24 Dec, 18:22


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

24 Dec, 05:02


my fav❤️🤌


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

24 Dec, 04:56


ከእለታት ግማሽ ቀን ታሪኮች የዚህን ርዕስ የሚያስታውስ በcomment 🙋‍♀🙋

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

24 Dec, 04:54


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

23 Dec, 17:55


Bounus


ቀላል የሚባሉ momentochin አትናቁ....ከጓደኛ ጋር ተገናኝቶ ሻይ መጠጣትም ቢሆን....


it means a lot bzi seat....



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

23 Dec, 17:47


"ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይቀርም"....ያለችኝ አንድ ወዳጄ ነበረች....የተረቱ concept ሰይጣን ተስፋ አይቆርጥም ነው...ጥሩ ለመስራት ስናስብ ከሚያደናቅፈው በላይ መጥፎ ስናስብ በተለይ ራሳችን ላይ ለመወሰን ስንጠነስስ የምንሞትበትን መንገድ ያማርጠናል...በል በል ከዚህ በላይ ምን ይምጣ ይለናል...ግርም የሚለኝ ነገር ሰይጣን ተስፋ እንደማስቆረጥ የሚደሰትበት ነገር አለመኖሩ ነው....ምክንያቱም ተስፋ የቆረጠ ሰው ምንም ያደርጋል....እኛም በሚቆረጠው ተስፋ ውስጥ እራሱ ተስፋ እንዳለ እንዘነጋለን...በዛ ሰአት ስሜታችን ብቻ ስለሚያወራ....



የዛሬው እንኳን routine አይደለም...ግን ስለጠቀመኝ ላካፍላችሁ...."አልቅሱ!!!"


ስሜታችሁን አውጡት አታፍኑት....ስልክ ማውራት ሰዎችን በአካል ማግኘት ምናምን እንደሚያስጠላ ግልፅ ነው በዚህ ሰአት....የሚሰማኝ ስሜት ሰው መፈለግም አለመፈለግም ነበር....ማለትም ጠዋት ተነስቼ  "ምነው ዛሬ ማንም አይደውልልኝም እንዴ...."....ብዬ ወዲያው ስልኬ ቢጠራ እንኳን አላነሳም....ፍላጎቴ ግራ ይገባኛል....ለዛ ነው መፈለግም አለመፈለግም ነው ያልኩት....ለዛ ደግሞ ማልቀስ ስሜትን ማራገፊያ መንገድ ነው....


እንደሰዉ ቢለያይም ስናለቅስ ቀለል ይለናል....


ሌላው ደግሞ ትንሽ ያራገፋችሁትን ነገር ለሰው ለመተንፈስ አትቸገሩም....ቀጥሎ በጣም ጠቃሚው ነገር  ለምናምነው እና ይረዳኛል ብለን ላሰብነው ሰው መናገር ነው....የማይረዷችሁ ከመሰላችሁ አታድርጉት....ምክንያቱም ሌላ ህመም ነው plus ቀጣይ የሚረዳችሁን ብታገኙ እንኳን አትተነፍሱም....


አእምሮአችን ውስጥ ያለው ትግል በአይን አይታይም....ወይ አትችሉም ብሎ ያሳመነን እና ያሽመደመደን ነገር አካል ያለው ሰው አይደለም....አግኝተን "አፍህን ዝጋ" ልንለው አንችልም....ለሚረዳን ሰው ስንተነፍሰው ግን እኛ ላይ ያለው power ይቀንሳል....



አንድ ልጨምርላችሁ እና ለዛሬ ይብቃን....የሚሰማችሁን መጥፎ ስሜት አንድ በአንድ ፃፉት...ከዛ አቃጥሉት....በቃ ልክ ወረቀቱ አመድ እንደሚሆነው ይሄም ስሜት አመድ እንደሚሆን ለአእምሮአችሁ ንገሩት....

እንቀጥላለን....መልካም አዳር




Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

23 Dec, 14:08


ማታ ፈዘም ባለ experiance sharing ፅሁፍ እመለሳለሁ....እስከዛው ግን daily routine 2 ላካፍላችሁ......


መዝሙር መስማት እና ከመዝሙሩ ጋር  መዘመር...በየእምነታችሁ ማመስገን አንድ ፀሎት ነው....በተጨማሪም አእምሮአችን ጆሮ አለው...የምንነግረውን ያምናል....ዲያቆን ሄኖክ በአንድ ጊዜ ይሄን ብሎ ነበር...."አእምሮአችን በጣም ሞኝ ነው....ጥርሳችንን ፈገግ ብናረግ ራሱ ደስተኛ ናቸው ብሎ ያምናል...."...so ብቸኛ ናችሁ ለሚለን ውስጣችን ፈጣሪ እንዳለን እናስታውሰው....

በዚህ ጊዜ I'm so lonely የሚል ዘፈን መስማት እሳት ላይ ጭድ መጨመር ነው....tiktok foryou page ላይ የምታዩትን dark ነገር unfollow አድርጉ...


ሁል ጊዜም ይሄን አትርሱ...."ሰው እንድትራመዱ ይረዳችሁ ይሆናል እንጂ አይራመድላችሁም....ለአእምሮአችሁ ከእናንተ የተሻለ ባልንጀራ የለም!!!".....


ሸዊት ነበርኩ......



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

08 Dec, 12:32


                🤰🤰🤰🤰እናት  2🤱🤱🤱🤱


በሕይወታችሁ ስንት አይነት ሃዘን ታቃላችሁ??..... ለማሰብም ለማልቀስም ለማውራትም ለመተንፈስም ሰውነታችሁ እንቢ  ብሎ ያውቃል..... ማልቀስ መጮህ ፈልጋችሁ አይናችሁ ልሳናችሁ አልታዘዝ ብላችሁ ያውቃል.... እንደዛ አይነት ሃዘን ነበር የተሰማኝ.....

እናትነት ሞኝነት ነው..... ልጄን አደለም ያየሁት ብዬ እራሴን አሳመንኩ..... ተሳስቼ መስሎኝ ነው ብዬ ለራሴ ነገርኩት.... የራሴው ሃሳብ መልሶ እራሴን አሳቀኝ..... እያበድኩም መሰለኝ... እናትነት ተስፋ ነው.... ልጄን ሌላ ቦታ እወስደዋለው.... እዛው እንደ አዲስ ሕይወት እንጀምራለን ብዬ አሰብኩኝ .......አሁን ሲመጣ እያለቀሰ ይመጣል..... ተሳስቶ እንደሆነ ሁለተኛ እንደማይደግመው እየማለ ይቅርታ ይጠይቀኛል እኔም እቆጣዋለው ....ያልኩትን እሺ ካላለ ይቅር እንደማልለው እነግረዋለሁ ይስማማል ከዛ ሌላ ሀገር እንሂድ እለዋለሁ ይቅርታዬን ለማግኘት ሲል እሺ ይላል... እያልኩኝ በሃሳብ እራሴን እስኪያመኝ ማሰላሰል ጀመርኩኝ.... የልጅቷ እናት ጩሀት እና ለቅሶ ጭካኔዬን ደጋግሞ ቢነግረኝም ሃሳቤን አላስቀይር አለ እያለቀስኩኝ እየጮህኩኝ ቢሆን ልጄን አስቀደምኩኝ..... ምክንያቱም እናት ነኝ.... እናት ስትሆኑ በልጅ ሚደረግ ነገር ሁሉ ትክክል ነው.....

ግን እንደዛ አልሆነልኝም ወደ ቤት ሲመጣ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆነ .....ምንም እንዳላደረገ አይን አይኔን እያየ እንደራበው እና ምግብ እንዳቀርብለት ጠየቀኝ..... ሰውነቴን ድንጋጤ ወረረኝ..... ሰውነቴ ጭንቅላቴን መሸከም ከበደው መሰለኝ ጭንቅላቴ ሊወድቅ አለ... ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ ....አመመኝ.... ስጋዬን ሰውነቴን ሳይሆን.... ነብሴን አመመኝ አይኔን በቁጣ አፍጥጬ ምናገረውን ነገር ለማሰብ ስሞክር ጭንቅላቴ ምንም ቃል አላወጣም አለኝ ...አጠገቤ ካለው ወንበር እንደምንም ተቀመጬ የሆነውን እየሆነ ያለውን እና ማደርገውን ነገር ማሰብ ጀመርኩኝ

"ምንድነው ምበላው ስጪኝ አልኩሽ አደል እንዴ?"ብሎ መጮህ ጀመረ

"ልጄ እንደው በሞቴ ...ስሞትልህ ...ቅድም ምን ስታረግ ነው ያየሁህ... አንተ ነክ ልጅቷን እንደዛ ያደረከው?" ብዬ እያለቀስኩ ጠየቁት አይኔን በመካድ... ሲያስተባብል እንኳን ትንሽ መፅናኛ ሚሆን ነገር ካገኘው ብዬ

"አይተሽ አደል እንዴ.... ምን እኔ አደለውም ብልሽ ልታምኚኝ ነው" አለኝ እያፌዘ

"አዎ ልጄ.... እኔ አደለውም በለኝ... ስሞትልህ... ባጠባውህ ጡቶቼ ይሁንብህ እኔ አደለውም በለኝ" እያልኩ እግሩ ስር
አልቅሼ ለመንኩት

"ምንድነው ምታካብጂው አረ ቀለል አርጊው" ብሎ አልፎኝ ተራምዶ እየሄደ "ቀለል አርጊው እሺ ይሄኮ የመጀመሪያዬ አይደለም ምንድነው ደርሶ እሪ ምትይው"እያለ ወደ በሩ ለመሄድ ተነሳ "

"ጥፋት አጥፍቼ አቃለው.... ግን ጥፋት መሆኑ ሲገባኝ ማድረጌ ያናድደኛል ...ላለመድገም እጥራለው... ያ ነው ሰው መሆን ማለት... ያጠፋል ግን ካጠፋው ይማራል... ሰው ሆኖ ማያጠፋ ከሆነማ ፈጣሪ ሆነ... ከጥፋት ማይማር ከሆነ ሰው ሊባል አይችልም ይሄ የሕይወት ሕግ ነው" ይለኝ ነበር አባቴ ልጅ እያለው .....አንዳንዴ መውለድ ቀላል ነው ከማሳደግ... ምን ይሆናል ብዬ የጠበኩት ልጅ ምን ሆኖ ጠበቀኝ... የኔ ጥፋት ነው እሱ ምን አደረገ እኔ ነኝ መስጠት ቻልኩኝ ብዬ ምሰጠው አለኝ ብዬ ያለኝን የለለኝን ሰጥቼው እሱ መቀበል እንደሚችል እንዴማይችል እንኳን ሳላውቅ አሸክሜ መላቅጡን ያጠፋሁት... መስጠት ሚከብድ የሚመስላቹ ሰዎች ተሳስታቸዋል መቀበል ነው ሸክም... የተሰጠንን ሁሉ መቀበል ያጎብጣል.... ተሰጠን ብለን ተቀብለን ተቀብለን ያ የተሰጠን ነገር ራሳችንን ይዞ ይጠፋል... ያ ነው የኔ ልጅ የሆነው የመቀበል ሸክም አጉብጦ እራሱን አስጣለው የኔ ጥፋት ነው.... የወላጆቼን ጥፋት አስተካክላለው ብዬ ልጄን አጥፍቼው አረፍኩጥ.... የትኛውም ልጅ የማንም ትላንት የማንንም ነገር ማስተካከያ መካሻ አይደለም.... የራሱን ሕይወት ነው ይዞ ምሄደው... ልጅ ሲወለድ በራሱ እቅድ እና አላማ እንጂ ሳይወለድ በተቀመጠበት መብት እና ግዴታን ይዞ አይደለም ማደግ ያለበት... የአባትን ፍላጎት ልጅ... የልጅን ፍላጎት ደሞ የልጅ ልጅ እያለ ሁሉም ማይፈልገውን ሕይወት እየኖረ ሲያማርር እድሜው ይቀድመዋል ......


ልጄን ማስተካከያው ጊዜ አልፏል.... ብዙ ሰው ሳያቆስል ብዙ ሴት ሳያስለቅስ ....የብዙ እናት እንባ ምክንያት ሳይሆን መስተካከል አለበት.... ለእሱም መንገዱ አንድ ብቻ ነው.... እናትነት ውሳኔ ነው... ለልጅ ሲሉ እራስን መግደል.... ልጅን ቀና ለማረግ እራስን ማጉበጥ.... ምናልባት በገዛ እናቱ እጅ መገደሉ ፈጣሪን ያራራው እና ይቅር ብሎት ከጎኑ ያስቀምጠው ይሆን እያልኩኝ እራሴን ማፅናናት ያዝኩኝ.... በተኛበት አፍኜ ገደልኩት የራሴን ጥፋት በራሴ አስተካከልኩኝ... እንደሞተ ሳቅ ኡኡኡ ብዬ አለቀስኩኝ አይኔም ብቻ ሳይሆን ልቤም አለቀሰ እንደ እብድም አደረገኝ ሰው በተሰበሰበበት እኔ እንደገደልኩት ተናገርኩ.... ሰው ሁሉ እረገመኝ.....ሰደበኝ...... ደስ አለኝ ለጥፋቴ በሰማይም ብቻ ሳይሆን በምድርም መቀጣት እፈልጋለሁ ምክንያቱም የመሞቱም የጥፋቶቹም ተጠያቂ እኔ ነኝ... ፍርድ ቤት ስጠየቅ ለምን ገደልሽው ከሚለው ጥያቄ ውጪ ሁሉንም መለስኩኝ እድሜ ልክ ተፈረደብኝ .....እስር ቤት ውስጥ እራሴን እንዳጠፋ ብዙ ሰዎች እየጮሁ ይነግሩኛል  .....ያልገባቸው ማጥፋት ሳልፈልግ ሳይሆን ሞት እስከሚወስደኝ ድረስ በምድር ላይ የሚደርስብኝን ስድብ እርግማን እና ዱላ አንዱ ቅጣቴ መሆኑን ለራሴ የሰጠውት ፍርድ ስለነበር ነው.... እናትነት ኃላፊነት ነው ልጅ ያጠፋውን እናት ኃላፊነት ትወስዳለች... ይሄ ደሞ ትክክል ብቻም ሳይሆን ልክ ነው......

እናትነት ለእናንተ ምንድነው??



አበቃሁ ...........


✍️kalkidan



http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

06 Dec, 18:33


ከሞትኩኝ ቆይቷል ብዙ ዘመን ሆኗል
መቅደሱ ገላዬ
ተስፋ ገለባዬ  ራሱን በትኗል፡፡
ቆይቷል ከሞትኩኝ ከሀቀኛ ሳቅ
ህይወት አይታዘዝ እንደይስሀቅ፡፡
አይለየኝም ዛሬ  ከነገዬ
ያልተፈሰከ ጾም ህይወት መዲናዬ
(መኖር እዳዬ)
መሄድም መቆምም እኩል የሚያዝለኝ
ድፍረት ካልሆነብኝ ጌትዬ እዘለኝ፡፡
አንተ ትከሻ ላይ ሁሉ ቀሏል አሉ ስሰማ በዝና
መስቀልህን ስጠኝ ህይወቴን ያዝና፡፡
የመስቀልን ክብደት
ከገዛ ሕይወቴ ለክቼ ባላውቅም
መኖር ግን ያዝላል ከቄሳር ፍርድ አቅም፡፡
ካንተ የምለየው
የተሰቀሉኩበት እንጨት ስላላየሁ....
ካንተ  የምለየው
የካደኝን ወዳጅ ሲስመኝ አላየሁ...
እንጂ በነፍስ የለሁ....
ናፈቀኝ የምለው
ባገኘው የምለው
በል ስጠኝ የምለው
አለሁኝ ካልኩኝ ነው፡፡
በሚጸልይ  አታስቀናኝ
እንዴት ይብለጠኝ መናኝ፡፡
የምለየው ካንተ አርገኸኝ የሰው  ዘር
ቆጥሬው አያልቅም
ስንት ግርፊያ እንደሆን መኖር ሲመነዘር ፡፡
ከሞትኩኝ ቆይቷል
ቆይቷል ከሞትኩኝ
አለ ለመባል ነው ባንተ ጋር ያለፍኩኝ፡፡


ቆይቷል ከሞትኩኝ፡፡


(ኤልያስ ሽታኹን)

https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

05 Dec, 17:40


🤰🤰🤰🤰 እናት🤱🤱🤱🤱



የእናትነትን ትርጉም ብዙ ሰው አይረዳውም...... ወይም ደግሞ አንድ መግባቢያ ትርጉም ያለው ቃል አይደለም.... አንዳንዴ እናትን የሚገልፅ ቃል እራሱ እናት ይመስለኛል.... ልጅ ሆኜ አይደለም ይሄን የምለው እናት ሆኜ ነው.... እናት ከሆንኩኝ በኃላ ነው የእናትነትን ትርጉም ማወቅ የፈለኩት ግን አልቻልኩም... በተለይ የገዛ ልጄን ከገደልኩኝ በኃላ ጭራሽ እናትነቴ ብቻ ሳይሆን የሰው መሆኔንም ጥያቄ ውስጥ ገብቶኛል ....

ወላጆቼ በጣም ተቆጣጣሪ ሰዎች ነበሩ... ምተኛበትን፣ ምነሳበትን፣ ምበላበትን፣ ት/ቤት የምሄድበትንና የምመጣበትን ሰአት አስቀምጠው በዛ ሰአት ነበረ የምንቀሳቀሰው…..
ያም ሆኖ ግን በጣም እወዳቸው ነበረ.... ከኔ ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ በሙሉ ለኔ የደስታ ጊዜያት ነበሩ... ቢሆንም ግን ይሄ ከልክ ያለፈ የቁጥጥር ፍላጎታቸው አያስደስተኝም ነበረ... እንደውም ያናደኝ ነበር... በተለይ እያደኩኝ ስመጣ እንደ ህፃን መቆጣጠራቸው ያነጫንጨኝና አልፎ አልፎም እንጣላ ነበር... በዛ ምክንያት ልጅ ስወልድ እንደኔ አይነት አስተዳደግ እንደማላሳድገው ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር.... በጊዜው ይሄ ውሳኔ ለኔ ትክክለኛ ውሳኔ ነበር ወይም መስሎ ተሰምቶኝ ነበረ....

አንዳንድ ጊዜ ልክ በመሆንና ትክክል በመሆን መካከል ያለውን ልዩነት አናውቀውም...እኔም እናት ከሆንኩኝ በኃላ ነው ያወኩት... እድሜዬ ሲደርስ ትዳር ያዝኩኝ እና በአመቱ ወንድ ልጅ ወለድኩኝ... ልጅ እያለው ለራሴ የገባሁትን ቃል ጠበቅኩኝ... ልጄን ነፃነት ሰጥቼ ማሳደግ ጀመርኩ.. እናትነት መስጠት ነው ..ነፃነት…….ፍቅር…….ምግብ…..ልብስ.
እውቀት…….ጥበብ ብቻ ያላትን ሁሉ በምትችለው ልክ ትሰጣለች... እኔም እንደዛ ነበርኩ...ያለኝን ሁሉ አንድም ሳላስቀር ሰጠሁት ለልጄ ...ያውም በደስታ……ምድር ላይ እኔ ብቻ እናት የሆንኩኝ እስኪመስለኝ ድረስ ለልጄ እናት ሆንኩኝ.... በዛው ማላውቀውንና ያልነበረኝን ነፃነት ለልጄ ሰጠሁት

ልጅነት ምንድነው???? አትሉኝም…..ልጅ መሆን ማለት የተሰጠንን መቀበል ከዛ ስናድግ እና የተሰጠን ነገር ሲገባን የተሰጠንን መልሶ ለቤተሰብ መስጠት ነው.... ልጅ ሳለን የሚሰጡንን ነገሮች ነው ስናድግ የምንመልሰው……ብዙ ሰው ይሄን አይረዳም እኔም ብሆን አልተረዳሁም ልጄን እስካጣ ድረስ…….

ልጄ ሲያድግ በጣም ቆንጅዬ ሆነ ....እሱ ባያወራም ብዙ ሴቶች እንደሚፈልጉት እሰማ ነበር... አጉል ኩራትም ይሰማኝ ጀመር ቀስ በቀስ ከኔ ጋር ማውራትም መጫወትም ጊዜ ማሳለፍም ቀነሰ...ውጪ ውጪ አበዛ.... ሲቆይ ደሞ ውጪ ማደር ጀመረ.. ጭንቀት ያዘኝ..ማልችልበትን ምክርና ቁጣ መንተባተብ ጀመርኩ...ግን አልሆነልኝም...ልጄን አደርገዋለው ያልኩትና የሆነው ተለያየብኝ.. የናትነት አንጀት አላስችል ብሎኝ ቤተክርስቲያን እየሄድኩ ማልቀስ ሆነ ስራዬ...የሚያውቁት ሰዎች እየመጡ ሱስ እንደጀመረ ሲነግሩኝ አያደርግም ብዬ ሰድቤ አባረርኳቸው... ሳላምንበት ቀርቼ ሳይሆን ልጄን አሳልፎ ላለመስጠት………….እናትነት እብደት ነው...እውነትን መካድ፣ ያመኑትን እውነት ነው ብሎ መቀበል……ግን ትክክል ነው... እናት ሲኮን ለልጅ ሚደረግ ነገር ሁሉ ትክክል ነው...እኔም እያለቀስኩኝ እሱም አልሰማሽ እንዳለኝ ጊዜው ሄደ...

ታዲያ አንድ በተረገመ ቀን የሰፈራችን አንድ ትንሽ ልጅ ጠፋች.. እናትየው ኡኡኡኡ እያለች እየጮሀች በየቤቱ ስትፈልግ ስናያት እሷን ለማገዝም ለማረጋጋትም ስንል አብረናት መፈለግ ጀመርን... ታድያ እየሮጥኩኝ ልጆቹ አዘውትሮ የሚጫወቱበት ሜዳ ስደርስ ልጅቷ መሬት ላይ ወድቃ ደም ይፈሳታል...ልጄን ደግሞ እኔን ሲያይ ሲሮጥ አየሁት....



ይቀጥላል



✍️kalkidan


http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

04 Dec, 16:41


አንዳንድ ሁኔታዎች ሲያሰለቹኝ መጃጃል ወደ ሚመስሉት የልጅነት እምነቶቼ መመለስና ደግሞ ማመን ያምረኛል ትዝ ይለኛል ድሮ የጠፋ እቃን ማግኘት ሲያቅተኝ መዳፎቼ ላይ እንትፍ ብዬ በእጆቼ መዳፌን እመታና ምራቁ ወደ ሄደበት አቅጣጫ የጠፋው እቃ እንዳለ አምኜ እቃውን እፈልጋለሁ ሁልጊዜም ባይሆን አንዳንዴ በዛ ምሬት የፈለኩትን አገኝ ነበር አሁን ላይ ሳስበው ምናለ እንደዛኔው ሁሉንም ነገር በቀላሉ የሚቀበል ልብ ቢኖረኝና የጠፉ ብዙ ነገሮቼን እንደዚህ ፈልጌ ባገኘሁ እላለሁ ። ምናለ የጠፋኝ መንገዴን ፣የጠፉ ሀሳቦቼን፣ የተሰናከሉ ህልሞቼን ና ደስታና ስኬቴን እንትፍ ብዬ መዳፌ ላይ ምታርፈው ምራቅ እንደድሮ ባምናትና ብትመራኝ በየት በኩል እንደተደበቁ ብጠቁመኝ እላለሁ። እንጃ ብቻ🤯


✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

02 Dec, 17:08


ውሸት ነው በይኝ፡፡
እንደሰው ተወድጄ ተከበሬ የኖርኩበት ቀን ትዝ አይለኝም፡፡ ከሰው ጋር ራሴን አላወዳድርም አልልሽም፡፡ ካልተወዳርኩ ደስታዬ ሀዘኔ ከየት ይመነጫል፡፡ ከሰው አነስኩ ይሉ የለ እናቶች እንኳን፡፡ ከሰው እንዳላንስ ተመክሬ ተዘክሬ ነው ከእናቴ ቤት የተሞሸረኩት ለዓለም የተዳርኩት፡፡


ያለንፅፅር ወደድኩህ ስትይኝ የደነገጥኩት ለዛም ነው፡፡ በምን አቅምሽ ቻልሽው፡፡ አለማወዳደርን አለማነፃፀርን፡፡ ወይስ Ego የሚሉትን ጣጣ እንደገላሽ እጣቢ ደፋሽው?
:
:
ውሸት ነው በይኝ፡፡ እኔን እየነካሽ የሰማሽው ሙዚቃ ምንድነው?
ትዝታ?
ገና መቼ ኖሬና፡፡
አንቺሆዬ?
እኔ ሆዬ የደረጃ ምረኮኛ የፉክክር ባርያ ነኝ፡፡
አምባሰል?
መብሰልሰል መቁሰል ....በነገር መብሰል፡፡
ባቲ?
እንደሆንኩ ታውቂያለሽ መዋቲ፡፡
.
.
ታዲያ ምን ሰማሽ ታዲያ ምን ነካሽና ወድሀለሁ አልሽ፡፡
ተይ አታስክሪኝ፡፡ የኖርኩበትን የእሽቅድምድም ሕይወት ፉርሽ አታርጊብኝ፡፡
እያፎካከርሽ ውደጅኝ፡፡
እያወዳደርሽ አልምጅኝ፡፡


አፈቅርሻለሁ
ከሁሉም አስበልጬ
እናፍቅሻለሁ
ከሁሉም መርጬ
እጠራሻለሁ
አንቺን ብቻ ውጬ፡፡


ያለውድድር ያለንፅፅር መውደድም መወደድም ዓለም አይችልበትም፡፡
አንቺ እንዴት

@yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

02 Dec, 05:40


አልበም ወ ፌስቡክ

∞ ∞ ∞ ∞

በድሮ ዘመን fb ስላልነበር ሰዎች ፎቷቸውን ፖስት የሚያደርጉት አልበም ውስጥ ነበር ፤ ከዛም እንግዳ ሲመጣ ከለስላሳ መጠጥ ጋር ያቀርባሉ ፤ እንግዳውም "ይህንን ፎቶሽን እንዴት እንደወደድኩት!" ብሎ Like እና comment ያደርጋል ፤ የሆነ ሰው ቤቱ ሆኖ ስቅ ካለው mention ተደርጓል ማለት ነው ፤ እንግዳው የሚወደውን ፎቶ ከአልበም ውስጥ ካገኘ share ያደርጋል (ሰርቆ ይወስዳል) ፤ ፎቶ እየተሰረቀባቸው የሚቸገሩ ሰዎችም አልበሙን ቁም ሳጥን ውስጥ ቆልፈው only me ያደርጉት ነበር።ፎቶ አብሮ የተነሳው ሰውዬ ጋር ፀብ ከተፈጠረ ደግሞ block ይደረጋል ፎቶው ከሁለት ይቀደድና የሰውየው ምስል ያለበት ወደ ጋርቬጅ ይጣላል፣አልበም ውስጥ ፎቶ ካለው ጓደኛ ጋር ከተደባበሩ ደግሞ un follow ይደረጋል ፎቶው ላይ ሌላ ፎቶ ይደረባል።

#ዳና

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

01 Dec, 13:26


ዝም ትልና በሀሳብ ትጠፋለች፡፡ ቆንጆ ፈገግታዋ ብቻ ቆንጆ ፊቷ ላይ ይቀራል፡፡ ትንሳፈፋለች በሀሳብ! ከተንሳፈፈችበት ደሞ ትሰምጣለች፡፡ እኔ፤ ምን ስታስብ ያንን ከፋውንቴን ይልቅ ማየት የምያስመኘውን ፈገግታዋን እንደምትፈግግ ራሴን እየጠየኩ ከጫፍ እስከ ጫፏ ሳልደነቃቀፍ ተጠንቅቄ አያታለሁ! ከሀሳቧ ስትመለስ እንደ ህፃን ልጅ ልብ ላይ ሚቀር ሳቅ ትስቃለች፡፡ከዛ ብዙ ታወራኛለች።ግን ለምን በሀሳቧ እንደምትስቅ አውርታኝ አታውቅም። ዛሬም እንደለመደችው ጥላኝ ጠፍታለች።እኔም አስለምዳኝ እንደለመድኩት በሷ ጠፍቻለሁ።አያታለው። ስንገናኝ አንድ ሁለት ነገር እንባባልና ለተወሰነ ጊዜ ዝም ማለት ከዛ እንደገና መለፍለፍ ልማዳችን ነው። ለኔ ራሴን የምሆንበት ቦታዬ ናት። እኔም ለሷ😁! አሁን ከሀሳቧ ተመለሰች። ሳቋን አሳድጋ ሳቀች። 'ግን ቆይ ምን እያሰብሽ ነው እንደዚ ምትስቂው' አልኳት::
ጠይቅያት አላውቅም ነበር ፤ ዛሬ ግን ማወቅ ፈለግኩ።ትንሽ ገረመመችና፡ "ጥሩ ትውስታዎቼ ናቸው ሚያስፈግጉኝ" አለች።
'ትውስታ?' አልኳት ቅንድቤን ሳብ አድርጌ ፤
"እህ እንደውም ቆይ ስለ ትውስታ ላውራክ" አለችና ተመቻቸች። ሁሌም ወሬ ስትጀምር በደምብ ትጠጋኛለች፡፡ተናግራ ስትጨርስ ደሞ ወደ ወንበሯ ሸሽታ ተደግፋ ትስቃለች።
እያወራችኝ ነው ። "ታውቃለህ ኣ ደስ የሚሉ ትውስታዎች ከአስቀያሚዎቹ በገሀድ ብቻ ሳይሆን በሀሳባችንም ለየቅል እንደሚታዩን?" ጠየቅችኝ። "እሱንማ እንዴት አታውቅም? ታውቃለህ እንጂ!" እጇን ከፍ አረጋ እንደማወራጨት አያረገች ራሷ መለሰች።
"ማስታወስ እወዳለሁ ያው የሚያስጠላ ትውስታ ካልሆነ ማለቴ ነው።ሁሌኮ አደለም ትዝታዬ ሚኮረኩረኝ አንዳንዴ ሊያስለቅሰኝ ብቻ ውልብ ይልብኛል። እኔ ግን ደስ በማይለውም ውስጥ ደስታዬን ስለፈልግ ደስ ይለኛል። ይኸውልህ እንዳንዶች ለማስታወስ ይታመማሉ ሌሎች ደሞ ለመርሳት! ትዝታ ይገድላል፤ትዝታ ያድናል! እነዛ አንዴ ብልጭ ብለውብን ከአንታርቲካ ይልቅ ሚያቀዘቅዙን ተበቃይና ተንከሲስ የሚያደርጉን flashbacks ትውስታ ናቸው። በሁኔታ ተገድደን ሳይሆን እኛው ራሳችን ደጋግመን እያሰብን ምናስታውሳቸው ፤ ብቻችንን እንደ እብድ የሚያስቁን ጮቤ አስረጋጮች ፤ ሁሌ ሁሌ ማስታወስ ምንፈልጋቸው እነዛም ትውስታዎቻችን ናቸው። ቢገድልም ቢያድንም ግን ከመርሳት ማስታወሱ ይሻላል። ምክንያቱም ህይወት ካለ ትውስታ ምንም ናት። አሁን እኔን አንተ ያለንበት ደቂቃ ከነ ቦታው ከነ ንግግሬ ከነ አሰማምህ ነገ ትውስታ ይሆናል። እና ከፈጠረን ቀጥለን ደስ የሚሉ ትውስታዎችን ምንፈጥረው ራሳችን ነን። አሁናችን ነገ ከምናደርገው ጋር ተዛማጅ ነው። ዛሬኮ የሳቅኩት ትላንትና የነበረን ሁሉ እስከዛሬ ስለቀጠለ ነው።።። ነገ አብረኸኝ ካልሆንክ ዛሬ ያደረግነውን ሁሉ በሳቅ ሳይሆን በሳግ አስታውሳለሁ። ውብ ትዝታችን ከማይተውን ጋር ሲሆን ያስቃል።"አለችና ወንበሯን ተደግፋ መፍለቅለቅ ጀመረች። ሳቋ ከበፊት ይልቅ አሁን በደምብ ገባኝ። ትውስታዎቿን አላበላሻቸውም ፊቷ ላይ ከሚቀር ውብ ፈገግታዋ ጋር ሁሌ ታስታውሳቸዋለች!


ቲና✍️


https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

01 Dec, 03:42


ከግጥም ባሻገር የኔ አይታ 2

በመጀመርያው ክፍል ስለ ውበት ጥቂት ብያለው በዚኛው ክፍል ደሞ ስለወጣትነት ትንሽ ሀሳቤን(እይታዬን) ላካፍላችሁ።

ወጣትነት ልክ እሳት እንደያዘ የክርቢት እንጨት ይመስለኛል።የክርቢት እንጨት እሳትን የመያዝና እሱ እስኪያበቃለት ድረስ ማቆየት የያዘውንም እሳት ሌሎች ነገሮች ላይ ማጋባት ይችላል።ግን አንዳንዴ ሌሎች ላይ ማጋባቱ ይጠቅማል ወይም ይጎዳል ለምሳሌ የእንጨቱን እሳት ከሰል ለማንደድ ከተጠቀም ነው ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ልንሰራበት ምግብ ልናበስልበት ፣ውሀ ልናሞቅበትና ሌሎች ነገሮችን ልንሰራበት እንችላለን በተቃራኒው ያንኑ ክርቢት አላስፈላጊ ነገሮች ላይ እሳቱን ቢያጋባ እንደ መጋረጃና የኤሌትሪክ ገመዶች ያሉ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን ቢያነድ ንብረት ሊያወድም ህይወት ሊያጠፋና ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።
አንድ ወጣትም ልክ እንደ ክርቢቱ ነው የዛ ወጣት እሳት ማለት በዕድሜው ተፈጥሮ ያደለው ጉልበት፣ጥንካሬ፣ችሎታ፣አቅም፣እውቀት ፣ተሰጥኦ፣ ቅልጥፍና የመሳሰሉት ናቸው። ይህ ወጣት ካስተዋለና መልካም ፍላጎት ካለው እራሱን ከወደደ ካከበረ እነዚህን እሳት የሆኑ የተፈጥሮ ስጦታዎቹን ጠቃሚ ነገሮች ላይ ይለኩሳል አልያ ደሞ ለራሱም ለሌሎችም ክብርና ፍቅር ከሌለው አላስፈላጊ ነገሮች ላይ ይለኩሳል።
እንዴት?ስንል .....
በመጀመርያ ማሰብ ያለብን በወጣትነት ምናደርጋቸው ነገሮች ወይም በህይወት እርሻ ላይ የምንዘራው ዘር ማምሻችንን(በእርጅናህ) እናጭዳለን ዋጋውን አንቀበላለን። በወጣትነት ጊዜህ ጠንክረህ ከሰራህ ለነፍስህም ለስጋህም መልካሙን ካደረክ የስኬትን መንገድ ጫፏን እንኳ ከያዝክ ማምሻህንም ሆነ በዛ እድሜህ የተሻለ ህይወት ለራስህ የመገንባት የመኖር እድልህ ከፍተኛ ነው።ይህ ማለት ያለህን እሳት ጠቃሚ ነገር ላይ ለኮስከው 👍💪ማለት ሲሆን በተገላቢጦሽ ደሞ በወጣትነት ጊዜህ ሱስ፣አላስፈላጊና ተራ ውሎ ፣ተራና ተስፋ ቢስ ጊዜያዊ ግንኙነቶችን ስታሳድድ ከከረምክ ሰው የዘራውን ያጭዳልና የመረጥከውን ህይወት ትኖራለህ መስራትና ጉልበትህን(እሳትህን) መጠቀም በነበረብህ ነገርና ሰዓት ላይ ስላልተጠቀምክ ድህነት ጌጥክ ቁጭትና ፀፀት ስንቅህ ሆነው ወደ ሞት ትጓዛለህ።😣😥 ምክንያቱም "ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው "በጊዜያችን የምንዘራው ነገር እንክርዳድ ይሁን ምርጡን ዘር ለይተን እንወቅ ልክ ክርቢቱ እንደሚያበቃለት አንተም ህይወትክ የሚያበቃበት ቀን አለና ።
እናስተውል እራሳችንን እንመርምር ምን ላይ ነው እሳታችንን እየለኮስን ያለነው የተሳሳተ ነገር ላይ ከሆነ ወደ ነበልባል ሳይቀየር አጥፍተን ሚጠቅመን ላይ እንለኩስ ስህተታችንን ለማስተካከል ዛሬ ተሰቶናል ከዚህ ቀን እንጀምር የተሰጠንን እንጠቀም ዛሬ የፈጣሪ ስጦታችን ነው ነገ ደሞ ተስፋችን ነው ነገ ብለው አቅደው ሞት የቀደማቸው ብዙ ናቸውና እንዳንቀደም

ስሚኝ ቆንጂት የቱ ጋር ነው እሳትሽን የለኮስሽው ?አንተስ ሸበላው?🥰

የገባችሁ👍
ያልገባችሁ 👎
ግራ የገባችሁ 🤷‍♀️ በመንካት ስሜታችሁን ግለፁ።😁

✍️የተክልዬዋ
3/8/2016
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

30 Nov, 17:30


                       ህይወት 3


እንዴት ሆንሽ??? ጠየኳት ..

"እኔንጃ አላውቀም….. አንዳንዴ እንጃ ለሁሉም ነገር ምላሽ ይሆናል.... አለማወቅ ነገሩን አለመረዳት በነገሩ መወዛገብ እራሱ አንድ መልስ ነው…ምን እየተሰማኝ እንደሆነ አላውቅም….
ምን እየተሰማሽ ነው ብትይኝ መልሴ እንጃ ነው...በቃ እንጃ….

ተዘጋጅቼ ነው የሄድኩት በህይወቴ እንደዛ ለምንም ነገር ተዘጋጅቼ አላውቅም….መንገድ በመራኝ ነበር ምመራው ንፋሱ በገፋኝ መንገድ ነበር ምገፋው……..

ግን የዛቀን የምናገረውን.. ሊጠይቅ የሚችለውን ጥያቄ... 
ልመልስ የምችለውን መልስ  የምንገናኝበት ቦታ፣ ሰአት፣ አለባበስ፣ አቀማመጥ…. ምን ልበልሽ ሁሉንም ተዘጋጅቼ ነበር...

እንዳቀድኩትም ሁሉንም ነገር ነገርኩት….. ያው እንባዬ አልቆም እያለ ቢታገለኝም እንደምንም እየታገልኩኝ   ሁሉንም ነገር ነገርኩት…. ዝም ብሎ አያየኝ ነበር ተገርሞ ወይም ደንግጦ ነው ብዬ ስላሰብኩኝ ምናገረውን እስከምጨርስ አይኑን ላለማየት ስጥር ነበር።

እሱ ግን ከጨረስኩኝ በኋላም ማየቱን አላቆመም....እኔም ግራ ገብቶኝ አፍጥጬበት ቀረው……. አይን ማየት ይፈራ ነበር.... በዚህ ሁሉ ጊዜ ግንኙነታችን መሀል አንድም ቀን አይን አይኔን አይቶ አውርቶኝ አያውቅም...ትንሽ ከተፋጠጥን እራሱ ድንግጥ ብሎ አይን ይሰብራል።

ዛሬ አይን መስበር የለም አይኔ ውስጥ ምን ምን እየፈለገ እንደሆነ እንጃ አይኑን ከአይኔ አልነቀለም...እኔም ከአይኑ ስር ንዴት እና ቁጣ ፍለጋ አይኔን አይኑ ላይ ተከልኩኝ....ግን የጠበቅኩት ስሜቶች የሉም ....የታየኝ የስስት እና የሀዘን ስሜት ነበረ…… እንዴት አወቅሽ እንዳትይኝ ምክንያቱም እንጃ ነው መልሴ…..አይን ለካ ብዙ ነገር ይናገራል...አንዳንዴ በንግግሩ የማይነገሩ እና የማይገቡ ነገሮች ለካ በአይን ይነገራሉ.... እንዴት ሰማሽ እንዳትይኝ ምክንያቱም እንጃ ነው መልሴ…ፊት ለፊት ከተፋጠጥንበት ተነስቶ ጎኔ መጥቶ ተቀመጠ... አይኑን አልነቀለም።

“ምን ትፈልጊያለሽ?” አለኝ።

“እንጃ…” አልኩት።

“ለምን ይሄን ሁሉ ነገርሽኝ?” ብሎ ጠየቀኝ...አይኑ አሁንም አይኔ ላይ ነው...አስተያየቱ ማወራውንም ያሰብኩትንም አጥፍቶብኛል ለደቂቃ ያክል ያወራሁትን እራሱ ማስታወስ ከብዶኝ ነበር።

“ስህተት ስለሆነ……….ስህተቴን ማስተካከል ስለፈለኩኝ” አልኩኝ እንዴት እንደማስተካክል ባላውቅም።

“እንዴት ነው ምታስተካክይው እእእ??? እንዴት ለማስተካከል ነው ያሰብሽው??” ጠየቀ።

“እንጃ” መለስኩኝ።

“አብረን እናስተካክለው?” አለኝ። ያልጠበኩት ጥያቄ ነበር።

“እ...እንዴት? አልተናደድክም ማለት ነው?? አሁንም አብረከኝ መሆን ትፈልጋለህ ማለት ነው?” ጥያቄ በጥያቄ ደራረብኩበት።

“ህይወቴ ነሽ እኮ እንዴት እተውሻለው………. ለኔ ያለሽ ስሜት ባይበልጥ መተሽ አትነግሪኝም ነበር.....ፍቅር እውር ነው አንድ ሰው ካፈቀረ ስለምንም አያስብም.... አንቺ ግን እንደዛ አላደረግሽም....ስለዚህ አሁንም ተስፋ አለኝ……… ህይወት ደግሞ ተስፍ እስካለ ድረስ ትቀጥላለች…… ልብሽን በፍቅር ልሙላው……ሀሳብሽን ሁሉ ስለኔ ላድርገው…… ትንፋሽሽም ለኔ ይሁን.....እኔ አንቺን ብቻ እንደምል አንቺም እኔን ብቻ እንድትይ ላድርግሽ……. እኔ ተስፋ እንዳለኝ እንዳመንኩኝ አንቺም በኛ ትንሽ ተስፋ ይኑርሽ.... ግዜን እንየው....እኔ  ጋር ልብሽ እስከፈቀደልሽ ድረስ ቆይ.... እኔም ደግሞ ልብሽን ዘላለም የኔ ለማድረግ ልሞክር………ህይወት አንዴ ነው ምትሰጠው... ህይወት እስካለችን ነው ሁሉን ምንሞክረው....እኔም የቻልኩትን ልሞክር አንቺም የቻልሽውን ያህል ቆይ.” አይኑ እንባ ሞልቷል። በቀስታ እጆቹን ጉንጩ ላይ አሳርፎ ግንባሬን ሳመኝ……..አይኔ በዕንባ ተሞላ……ምንተሰማሽ እንዳትይኝ ምክንያቱም እንጃ ነው መልሴ……….." አለችኝ ::



ጨረስኩ


✍️kalkidan


http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

30 Nov, 14:34


እነዚህን ውብ ፈሪኒቸኖች የምታገኙበትን Wub furnituresን ላስተዋውቃችሁ....የምትፈልጉትን የቤት እና የስራ furniture በጥራት ለማሰራት ሲፈልጉ ጎራ ይበሉ....


📞:-0940054784
:-0926803556
join for more👇👇👇
https://t.me/wub123unique

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

30 Nov, 08:53


ኤልያስ መልካ ፍቅር የያዘው ገና በአፍላነቱ ዘመን ነበር፡፡ የልጅነት መልኳ እንደ ማለዳ ጀንበር ቀስ እያለ ልቡን አሞቀው፡፡ ወደዳት፡፡ ግን አልነገራትም፡፡

ቤተሰቦቿ የቤተሰቦቹ ወዳጆች ስለነበሩ ፈራ፡፡ ወንድሞቿ ጓደኞቹ ስለሆኑ ተጨነቀ ቤታቸው ስትመጣ ደስ ይለዋል፡፡ ከእህቶቹ ጋር ስታወራ አተኩሮ ያያታል፡፡ ድንጋጤ የነገሰበት ሕይወት አልባ ሳቁን ባወራች ቁጥር ይለግሳታል፡፡

ፍቅሩ የአንድ ሰሞን አልሆነም፡፡ ወራት መጥተው ወራት ቢሄድም  ሊቀንስ አልቻለም፡፡

በዚህ መኸል ወሬ ሰማ፡፡ ሌላው የሰፈሩ ልጅ እንደሱው እንደሚወዳት አወቀ፡፡ ምን ማድረግ ይችላል መፍትሄው ሁለቱንም በዓይነ ቁራኛ መከታተል ነበር፡፡ ለጥቂት ጊዜያት በአሰበው መንገድ ቀጠለ፡፡

በኃላ ላይ ግን የልጅነት ፍቅሩ ቤታቸው መምጣት አቆመች፡፡ ዕድሜው ከፍ እያለ ሲሄድ ውሎዋ መርካቶ በሚገኘው የቤተሰቦቿ ሱቅ ውስጥ ሆነ፡፡

ኤልያስ አልሰነፈም፡፡ ጓደኞቹን እየያዘ መርካቶ ይሄዳል፡፡ ምክንያቱን ባይናገራቸውም በቅመማቅመም  ተራ በኩል እንለፍ ይላቸዋል፡፡ ይከተሉታል፡፡ ቆም ብሎ በዓይኑ ይፈልጋታል፡፡ ካለች ደስ ይለዋል፡፡ ከሌለች የት ሄዳ ይሆን እያለ ፈዝዞ ወደ ሰፈሩ ያመራል፡፡

አብሮ አደጎቹ ነገሩን ያወቁት ዘግይተው ነበር፡፡ ኤልያስ ባቅላባ ለመብላት ፒያሳ ድረስ በእግራቸው ሲወስዳቸው ኑሯል፡፡ ከአብነት ተነስቶም ኳስ ለመጫወት ጃንሜዳ ድረስ አስከትሏቸው ያወቃል፡፡

የመርካቶው  እንቆቅልሽ ግን ግራ ያጋባል፡፡ ያለምክንያት እናቶች በሚበዙበት ቅመማ ቅመም ተራ በኩል እንለፍ እያለ ሲጨቀጭቃቸው
የቅርብ ጓደኞቹ እኛ እንንገርልህ አሉት፡፡

ቤተሰቦቿ ከቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን ወንድሞቿም ለእሱ ቅርቦቹ መሆናቸውን ስለሚያውቅ አይደረግም ብሎ ተከራከራቸው፡፡ መፍትሄው በቤት ስልካቸው እየደወለ፤ ለማውራት መሞከር ነበር፡፡ ዓይን አፋሩ ኤልያስ እየተርበተበተ ስልኩን ይመታል፡፡

ወደ ሕዝብ ስልኩ የሚከታቸው ሳንቲሞች ግን ትርፋቸው ኪሳራ ነበር፡፡ ገና ድምጿን ሲሰማ ሀሳቡ ይበተናል፡፡ እራሱን ለመሰብሰብ ሲጥር የከተተው ሳንቲም አልቆ ስልኩ ይዘጋል፡፡...... ቀሪውን ከመፅሐፉ ታነቡ ዘንድ ጋበዝኩኝ

ምንጭ፦ የከተማው መናኝ
             ➧በይነገር ጌታቸው




https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

29 Nov, 03:19


ደህና ናት ምክንያቱም አሁንም ተስፋ አላት።

ዛሬ የሀዘን እንባን ያነባው አይኗ ነገ የደስታ እንባን እንደሚያወርድ ተስፋ ታደርጋለች ዛሬ የጎደለው ማጀት የጎደለው ኑሮ ነገ እንደሚሞላ ተስፋ ታደርጋለች የከዷት ጥለዋት የሄዱ የኔ ያለቻቸው ሰዎች የእሷ እንዳልነበሩ ተረድታለች ስለዚህ የተሻሉና የሷ የሆኑትን ፈጣሪ እንደሚሰጣት ተስፋ ታደርጋለች ቀኑ አልቆ ሲመሽ መንጋቱን በተስፋ እንደምትጠብቀው ሁላ የተዳፈነው ህይወቷም እንደሚያበራ ተስፋ ታደርጋለች በፈተና ውስጥ መሰራት በችግር ውስጥ መገንባት እንዳለ ታወቃለች ለዛም እያመሰገነች ለድካሟ ብቻ ከሰው ተሰውራ ጥቂት ታነባለች አዎ ታለቅሳለች ውስጧን ታማለች ሚደግፍ ሰው አጥታ በራሷ ትፍገመገማለች ግን ደና ናት ሁሉ ሚቻለውን ታሪክ ቀያሪውን እሱን ታምነዋለች ጋሻ መከታዋ መነሻ ምርኩዟ እሱን ይዛዋለች ስለዚህ ደና ናት ሁሉን አሳልፎ ጨለማውን ገፎ የሰራዊት ጌታ ሁሉን ቻዩ አምላክ እንደሚያነሳት እምነትና ተስፋን ሰንቃለች እናም በጣም ደህና ናት ።


ከተስፋና እምነት በላይ ምን ደህና ያደርጋል??

✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
https://t.me/semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

28 Nov, 09:20


"ግን ስለ ወንዶች oxytocin አስበሽ ታውቂያለሽ...."....አለችኝ በሌላኛው ቀን

"እንዴ ራስሽ አይደለሽ እንዴ ወንዶች ላይ የለም ያልሽኝ...."

"yeah እሱማ...ግን ራሴ የፈበረኳት ፍልስፍና አለች ትንሽ ላጫውትሽ....."....ምንም ብታወራ ምቾት አይነሳኝም...ያን ያሀል የምንገናኝ አይነት ጓደኛሞች ባንሆንም ስንገናኝ የምናወራው ፍሬ ነገር ቀልቤን ይይዘዋል....

"ዝም ብዬ ሳስበው የወንዶች oxytocin ልክ ሴቷን የማጣት ስሜት ሲሰማቸው የሚመነጭ ይመስለኛል...የቆይታው ሁኔታ እንደልጅቷ ይወሰናል...በጣም ስትኮራ የሚጨምር...ስልክ ደጋግማ ስትደውል የሚቀንስ...ልሄድ ነው ስትል ጣሪያ ሚነካ...ስትመለስ ደግሞ አፈር የሚገባ አይነት...."

"ይሄ ግን ለሁሉም ወንዶች አይሰራም...ፍቅር እና ክብር መሸከም የማይችሉት ላይ ነው በትክክል የሚሰራው...ሊፋቀሩ ከገቡበት ነገር ፍቅር የሚያሸሻቸው...ትንሽ ሲፈሩ የሚወዱ...ሴቷን በእጃቸው ያስገቡ ሲመስላቸው ትንሿ ልባቸው አብጣ ልትፈነዳ የሚደርስባቸው ወንዶች ናቸው.....

እንዳልኩሽ ይሄ የተጠና ነገር አይደለም....የራሴን እይታ ነው የማጫውትሽ...."....ብላኝ ጉሮሮዋን አረጠበች....እኔም ከራሴ ጋር ማሰላሰል ያዝኩ...ዮኒን ልሄድ ነው ስለው የሚሆነው መሆን ከተመለስኩ በኃላ ደግሞ ደሙ ሚቀዘቅዘው ነገር መጣብኝ....

"ፍቅርን መሸከም የማይችሉ ስትዪ ፍቅር ሸክም ነው እንዴ...."...ጠየቅኩ

"አዎ...ደስ እያለሽ የምትሸከሚው አይነት ሸክም ነው...ሰዎች ገድል አዝለው ቤተክርስትያን ሲዞሩ አይተሽ ታውቂያለሽ...?.."

"አዎ...."

"ለምን የሚሸከሙ ይመስልሻል....?..."

" ከበሽታቸው ለመፈወስ መሰለኝ...."

"ፍቅርም እንደዛው ነው...ለመዳን የምትሸከሚው አይነት ነው...ከክህደት በሽታሽ ለመዳን የምታደርጊው አይነት....የማይከብድ የማይጎረብጥ ሸክም ነው....ገድል ተሸክመሽ ደብር እንደምትዞሪው ፍቅርን ተሸክመሽ ደግሞ የፍቅር አጋርሽን ትዞሪዋለሽ...."


አፌን ከፍቼ እያዳመጥኳት ነው....


"እና አሁን ላይ ይሄን ሸክም መሸከም የማይችል ሁላ የሚገባበት ነገር ሁኗል....u know አሁን relationship fashon ነው...single ከመሆን ይልቅ የማይወጡት ነገር ውስጥ ዘው ማለት ቀሏል....እንግዲህ ምን ይደረጋል...."....ብላ በእጇ ምን አውቄ ምልክት አሳየችኝ...

"ፍቅር መሸከም እንደማይችሉ notice ካደረግን በኃላ ምንድን ነው መፍትሄው...."...እየፈራውም እየተባውም ጠየቅኩ....

"red flag  መስጠት ነዋ...."....ከማለቷ ስልኳ ጠራ....ስልኳ ከመጥራቱ ፊቷ በቅፅበት ፈካ....

"ምን ሆነህ ነው 3 ቀን ሙሉ ሳትደውልልኝ...100 ጊዜ አይሞላም የደወልኩልህ.....እንዴ አልተመቸኝም ምን ማለት ነው 1 ደይቃ አጥተህ ነው በማርያም....እሺ በቃ አትናደድ....ናፍቀኃኛል እኮ....."......ደዋዩ ምን እንደሚላት ባልሰማም በተከታታይ የተናገረችውን መሸምደድ ያዝኩ....ስልኩን ተሰናብታ በሼም አኳሀን አየት አደረገችኝ....

"red flag ላይ ነበርን...."....ብዬ ያቆመችበትን አስታወስኳት....አሁን ማን ይሙት አሁን እንዳወራችው አይነት ሰው red falg ካልተሰጠው ማን ይሰጠዋል....ነቆራዬ ገባት መሰለኝ....."የሚጠቅምሽን ብቻ ውሰጂ....እንደሚያጨስ ሰው የሲጋራን ጉዳት የሚያውቅ ሰው የለም....አታጪሺ ሲልሽ አንተ እያጨስክ አይነት ውድድር ውስጥ አትግቢ...."....ብላ ተነስታ ሄደች.....



Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

20 Nov, 20:42


"ንፋስ አልወድም"....አለቺኝ ካዘነበለችበት ሳትነቀል....

"ለምን"....ጠየቅኩ....

"ስለማይረጋ...ባንድ አቅጣጫ ስለማይነፍስ...ወዲህ ብቻ ገፍቶ ስለማይተው...ወዲህም ወዲያም ስለሚያደርግ...አቋም ስለሚያሳጣ....አንዴ ሽው ካለበት ስለማያድር...."....በረጅሙ ተነፈሰችና ቀጠለች....

"ገፍቶ ከጣለህ በኃላ ደግፎ ሊያነሳህ ስለማይመጣ....ከመጣም ደግሞ ደጋግሞ ሊያፈርስህ ስለሚመጣ....ታውቃለህ ንፋስ ደካሞች ላይ እንደሚበረታ....ብቻ ምን አለፋህ የወደቀ ላይ ምሳር ለማብዛት ስለሚመጣ ያስፈራኛል...."

"አትፍሪ እኔ አለሁልሽ...."....አልኳት በልበ ሙሉነት....

"ከግዑዝ ነገር ፀብ የለኝም...ስለ ንፋስ ሳወራ ራስህን ታያለህ ብዬ ጠብቄ ነበር...."

"ማለት...."

"ከግዑዙ ንፋስ እዚ ፊቴ ያለኧው ንፋስ ታስፈራኛለህ...."

"ማለት...."

"ንፋስ ነህ እያልኩህ ነው...."

"አይደለሁም...."

"ነህ...አንተ ግን እያባበልክ አለሁ እያልክ ነው የምትጥለው...ግዑዙ ንፋስ አያባብልም...ሁሌም የቻለውን ሊያፈርስ እንደሚመጣ አውቃለሁ....የሰው ንፋስ ከጣለ መነሳት ቅዠት ነው...እና እሱን ንፋስ ነህ"....


በረጅሙ ተንፍሳ አቆመች....እኔም ደግሜ አልጠየቅኳትም....



Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

20 Nov, 19:14


https://t.me/+TIgGH_hEYiUzegbN

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

20 Nov, 04:30


አለ ማፍቀር

ራቅ ብለው ፤በአይን እያዩ
ስሜት በግልፅ፤ ሳያሳዩ
ከተወዳጁ ፤እያወጉ
ቀርቦ ጠረን ፤እየማጉ
በመከተል፤ እንደ ጥላ
በመገስገስ ፤ከእሱ ሗላ
ቃል እያጡ፤ ለመናገር
በዛ ሰው ፊት ፤መደናገር
በሙሉ ቀልብ ፤እያመኑ
የቅርብ እሩቅ ፤እየሆኑ
ሳይገለፅ፤ የልብ እውነት
የሰው ደስታን፤ ላለማጥፋት
ለራስ የከጀሉት ፤ሌላ እቅፍ እያዩት
በዝምታ ፤ታጥረው
ምኞትን፤ ተነጥቀው
እንዲህም፤ አለ ማፍቀር
....
ተስፋ በሌለበት፤ ተስፋ እየቀጠሉ
ለፍቅር እየኖሩ ፤እራስን እየጣሉ
ላልተሰጠ ነገር ፤ዋጋ እየከፈሉ
ማማረርን ይዘው፤ ከአምላክ ከተጣሉ
ሙሉነትን ትቶ ፤ባዶ ሆኖ ከመጥፋት
ከምድር ከሰማዩ ፤ጠልቶ ከመለየት
ለነፃዋ ህይወት ፤ደስታን ማሰንበቻ
ማጣፈጫው ቅመም ፤አለማፍቀር ብቻ።

✍️የተክልዬዋ
#repost

https://t.me/semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

18 Nov, 16:24


ከግጥም ባሻገር የኔ እይታ 1

ውበት እንደተመልካቹ ነው የሚባል አባባል አለ መጀመርያ ማን እንዳለው ባላውቅም 😊ግን እንደኔ አመለካከት ውበት ማለት ኑሮ ይመስለኛል ፈጣሪ ሁሉንም ሰው በአርአያውና በአምሳሉ ሲፈጥር ውብ አድርጎ ነው።
ነገር ግን በሰውኛ የአስተሳሰብ ሚዛን ስናየው ሁሉም ሰው ውበትን የሚለካበት የየራሱ መስፈርት አለው የኔ ደሞ ኑሮ ነው።

ምንም ያህል በሰዎች ሚዛን ስትለኪ አስቀያሚ ብትባይ ኑሮሽ ካማረ አስቀያሚ ወይም ፉንጋ ያሉትን ቃል ጥለው ስለቁንጅናሽ ይመሰክራሉ። ወይ ደሞ በነሱ መስፈርት ቆንጆ ተብለሽ ኑሮሽ ካላማረ አስቀያሚ የምትባይበት ቀን እሩቅ አይሆንም እንዴት ካልሽኝ?

በመጀመርያ የኑሮ ማማር ማለት የተዋበ ስብህና የተስተካከለ ስኬታማ ህይወት ለ'ራስ መገንባት ነው።

ይህንን ህይወት ለራስሽ መፍጠር ከቻልሽ ምንም ፉንጋ ብትሆኚ ምንም አመዳምና አስቀያሚ ብትሆኚ😁 ሁሉም ለሚዛን አይበቁም በኑሮሽና በራስሽ ላይ የገነባሻቸው ቆንጆ ነገሮች ናቸው shine አርገው ቀድመው ወጥተው የሚያስዉቡሽ ለአካልሽም ብትይ ሰዎች የምንመገበውን ነን ኑሮሽን ካሳመርሽ ጥሩ ተመጋቢ ትሆኛለሽ 😀ከዛ አመዳምነትሽ በወዛምነት ኮሳሳና ቀጫጫነትሽ ሞላ ባለ ሰውነት 🙂እንዲሁም ሌሎች ነገሮችሽ በተስተካከለ የአካል ውበት እየተተኩ ይመጣሉ።ኑሮሽ ካላማረ ግን በሌሎች ውብ አስብሎሽ የነበረ መልክና አካልሽ ሳይቀር በህይወት ውጣ ውረድ፣ ፈተና፣ በአኗኗር ትግልና በኑሮሽ ወላፈን እየተለበለበ ውብና ቆንጅዬው ፊትሽ የማድያት መንደር ወደ መሆን ቀና ያለው አካልሽ ወደ መኮሰስ ይቀየራል። ስለዚህ ማማዬ ነቃ በይ ሰዎች የሰጡሽ የተሳሳተ መለኪያ ይዘሽ ብቻ ውበትን በዛ ተርጉመሽ እራስሽን አታሳስሪ ዘላቂውን ውበት ገንቢ አንቺም ሌላኛዋ ወጣት በሰጡሽ ገደብ ተከልለሽ ውብ አደለውም ብለሽ ተራ ሆነሽ አትቅሪ ፈጣሪ የሰጠሽን ስጦታዎች ተጠቅመሽ ህይወትሽን ፣ስብዕናሽን፣ አካልሽንና አመለካከትሽን አስውበሽ በገዛ አንደበታቸው ሳትጠይቂያቸው እንዲመሰክሩልሽ አድርጊያቸው እንጂ መስታወት ፊት ቆመሽ በፈጣሪ ስራ ጣልቃ እየገባሽ አታማሪ አትርሺ" ውበት ማለት ኑሮሽ ነው " በርቺ ጀግናዬ ተውበሽ አሳያቸው።👍👍👍


የተሳሳተ የውበት መለኪያ መስፈርት እስረኞች ለሆናችሁ ሴቶች
እያስተዋልን እንጂ ወገን😊🥰

✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
https://t.me/semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

17 Nov, 03:22


💔💔

@semetnbegtm
@semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

16 Nov, 06:41


When I met you first ..I wanted to hear your voice
When i heard your voice....I wanted to keep hearing it
When I saw you smile..I understand the difference between a sun set and a day
When you sat next to me...I wanted to stay there forever
When you hug me the first time... the difference between heaven and earth become clear
When you told me about your ex ..... I felt sorry for her thinking how unlucky she was to lose some one like you
When you become my friend.....I wished if we could be lovers
When you told i could be loved ....I feel like the most wanted person in the world
When you told me that you love me.....my life purpose was served..

Name one thing in the world that's arrogant for being loved...it will be ashamed seeing the love I have for you


✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

15 Nov, 19:41


               እውነት


"ቆይ ምን አይነት ሰው እመስልሻለው??" አለችኝ...... መጀመሪያ እየቀለደች መስሎኝ ስቄ ነበር.... ግን የምሯን እንደሆነ ሳቅ ምመልሰው ግራ ገባኝ.....

"ቆይ ምን ሆነሻል"አልኳት...

."የጠየኩሽን መልሺልኝ?"ብላ ቆጣ አለች.... ምለው ግራ ገባኝ " ቆይ ምንድነው የሆንሺው.... እንዴት እንደዚ አይነት ጥያቄ ልትጠይቂኝ ቻልሽ?" ብዬ ጥያቄዋን በጥያቄ መለስኩላት....

"ለምን ዝም ብለሽ የጠየኩሽን አትመልሺም" አለች ያሁኑ ንግግሯ ቁጣም  እዴትም ጩኸትም  አለው ....

"እንዴ ሀኒ የብዙ ዓመት ጓደኛዬ እኮ ነሽ.... ቆይ መጥፎ ሰው ነሽ ብልሽ ታምኚኛለሽ" አልኳት ጥያቄዋን እንዴት እንደምመልስ ግራ ቢገባኝ

"አዎ አምንሻለሁ..... እንደውም እንደዛ  እንድትይኝ ነው ምፈልገው.... እስከዛሬ ከምታውቂው ዓለም ላይ ካለው ሰው ሁሉ..... እኔ መጥፎ እንደሆንኩኝ ነው እንድትነግሪኝ ምፈልገው...... ሲኦል እንኳን የሚበዛብኝ ሰው እንደሆንኩኝ ነው እንድትነግሪኝ ምፈልገው....እባክሽ እንደዛ እያልሽ አዋርጂኝ... እባክሽ ጓደኛዬ አደለሽ ህ የኔ ብቻ አይበቃም አንቺም መጥፎነቴን ንገሪኝ" እያለች ማልቀስ ጀመረች... ማረገው ግራ ገባኝ.... በሁኔታዋ ደንግጬ ማባበል እንኳን አቃተኝ ከረጅም ጩሀት እና ለቅሶ በዃላ እንደምንም ማባበል ቻልኩ.... ግን አሁንም እንባዋ አልቆመም.... በሁለቱም አይኗ ይፈሳል አትጠርጋቸውም ዝም ብላ እንደተቀመጠች ፊቷ ያለው ሶፋ ላይ አፍጥጣለች ......እንድታየኝ ሄጄ ፊቷ ተቀምጬ.... እንድታወራና የሆነችው እንድትነግረኝ መለመን ጀመርኩኝ.... ነገሩን ባላቀውም ከባድ መሆኑን ከሁኔታዋ ተረድቻለው ይህ ነገር ደሞ ውስጤን ከብዶታል......ከ'ሃና' ጋር ከልጅነታችን ጀምሮ ጓደኞች ነን.... በጣም ቀና እና ለሰዎች ጥሩ ምታስብ ልጅ ነች..... ጓደኛዬ ስለሆነች ብቻ  አደለም ይሄን ሁሉም ሰው ሚስማማበት ጉዳይ ነው.... ዛሬ ምን ተፈጥሮ እንዲ እንድትል ያደረጋት ነገር ለኔ ትንግርት ሆኖብኛል ብቻ በውስጤ ያሰብኩት ያክል መጥፎ እንዳይሆን እየፀለይኩኝ የተፈጠረውን እንድትነግረኝ መወትወት ላይ ነኝ......


ይቀጥላል


https://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

15 Nov, 07:44


Ke weset mesmer🥹


Thanks betam🙏

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

15 Nov, 07:44


🎉🎉🎉🎉🎉........ከ እለታት ባንድ ቀን አምላክ ቀን ጥሎት ባርኮት ሊመጣ የኢትዮጵያ ምድር....... ሊያንቀጠቅጥ የግብጽን ጣዖታት..... ሊሰባብር መንፈሰ ከሃዲያን ..... ምን ልቡን ቢያደከመው የግብጽ ክፋት .,...በአምላክነቱ ሁሉን ማድረግ ሲችል ፊታቸውን ቢያጠቁሩበትም የግብጽ ነገስታት ......ሳይታክት ዞረ አሁንም ዞረ ያንን በረሃ አንዴ በውርንጭላይቱ አንዴ በንጽህይቱ ጀርባ እየተንደባለለ ኢትዮጵያ ደረሰ ቢያይ ፊቱ በራ...... ያንን በረሃ የነበረውን የሰው ክፋት ፊቱን ያጠቆረው ኢትዮጵያ ቢመጣ አምላክነቱ እንደ ጸሃይ አበራ ዞሮ አያት አሻተታት ተመለከታት በለበሰው ድኩም ስጋ ሆኖ ከጫፍ እስከጫፍ ተመለከታት..... እንደ ሃያ አራቱ ካህናት እንደሻሽ ተነጥፈው በክብር ተቀበሉት ምስጥሩን አስማሙት.....ኋላ ላይ ለዚች ሃገርማ እናቴ ርስት አድርጌ መስጠቴ በቂ አይደለም ብሎ ባርኮ ሊቀድሳት የህይወት እስትንፋስን እፍ አለባት ምድረ ኢትዮጵያ አበራች ሃዊሳ ሃዊሳ ሃዊሳ ለኢትዮጵያ ተባለች ከ እፍታው ለየህዝቡ እንደአቅሙ ደርሶ ብዙ የደረሰው በዘሩ በብዙ ተጌጠ........ያንቺም የቤተሰብ የዘር ሃረግ ቆጥሮ ባንቺ አንከባለለው በቀለም ሰቅዞ ..ታዲያንን ያንን ጸዳል ሊያበራ በሚጠቱ ተወልደሽ በቀለሙ አበራሽ በመወለድ በብርሃናማ ገፁ የተገለጠባት ኪነት.... ፍቅር በእያንዳንዷ ህዋሳቷ ሰርፆ ሰው...የመሆንን ዜማ የተቀኘችልን ጥዑም ልሳን ላንቺ አደለሽ ....እንኳንም ተወለድሽ አንቺ የብዕር ፈርጥ እንኳንም ለዚህ በቃሽ እንኳን ለዚህ አበቃሽ ሸዊ መልካም ልደት.....
🎉 መልካም ልደት ሃሳብን ለሚተይቡ እጆችሽ🎉
🎉መልካም ልደት ሃሳብን ላፈለቀው ልብሽ🎉
🎉መልካም ልደት ሃሳቡን ላብላላው አእምሮሽ🎉
🎉መልካም ልደት እንደጨረቃ ለገዘፉ ሃሳቦችሽ🎉
🎉መልካም ልደት ባሏን አስራ ሁለት ቦታው ለቆራረጠው😊 ስለታም ሃሳብሽ😂🎉
በኪደተ እግሯ ባርካ በሄደችበት እጆቿ ከላይ ደመና ከታች ጥላ ሆና ትጠብቅሽ በይ ደግሞ ክርስቲያን አይደለም ልደቱ ህይወቱም ማማሩ በደጁ ነውና ከ ደጁ አትጥፊ ዘመንሽን ብዕርሽን፣ሃሳብሽን አእምሮሽን ይባርክልሽ ......ደምቀሽ ምትታይበት አመትን ተመኘን..... ደግሞ በመጽሃፍሽን መጥተሽ መጽሃፍሽን እንመርቃለን.........መልካም ልደት ላንቺ ብቻ ሳይሆን አምጣ ለወለደሽ ደምቃ ውበታን ገምሳ ከፍላ ላጋራች እናትሽ  ........መልካም ልደት ለዛ ውበቱን አድሎሽ ለደበዘዘው አባትሽ ......መልካም ልደት ላንቺ ላንጸባረቅሽ ልጃቸው መልካም ልደት🎉🎉🎉🎉🎉🎉😊🎉🎉

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

15 Nov, 07:27


Ahun yalhubet huneta😁

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

15 Nov, 06:25


It's my birthday my ppl💙

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

11 Nov, 17:40


ለምን ብለሽ
ተጨብጠሽ
ኩርምት ከፋ
እኔን ስሚኝ ቀን ሲከፋ
እኔን ሳሚኝ ሌት ሲያካፋ

እቅፍ አርጊኝ
ተሸሸጊኝ
አለሁልሽ እኔ ወንዱ
ሰው መሀል ነው ሰው መንገዱ

ተጠምጠሚ
እንደጋቢ
ተጣበቂ ተቃቀፊኝ
ቆዳዬንም ሂጅ እለፊኝ
ተሰተሪ እንደአጥር
ክትት በይ እንደሚስጥር


ኤልያስ ሽታኹን


https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

09 Nov, 19:45


እስከነህልሙ የተቀበረው የወታደር ብዛት ስንት ይሆን🥹

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

09 Nov, 17:40


"በቂ ነህ....?....እንደዛ ነው የምታስበው...?በእኔ ሚዛን ስንት እንደሆንክ ነው የሚሰማህ....?የእኔን እንባ ለማየት የተገባሁ ነኝ ነው ምትለው..."

"ምንድን ነው የሆንሺው...ተረጋጊ"...

"አልረጋጋም...አልረጋጋም...እንደውም አትመልስልኝ...እኔው ራሴ መልስልሀለሁ...በደንብ ስማኝ...አትበቃም...አትመጥንም...የእኔን አእምሮ ለመቆጣጠር ቅንጣት ነህ...ቅንጣት...."....ከአፏ የሚወጡት ቃላቶች ከሚዥጎደጎደው እምባዋ ጋር እሽቅድድም ገቡ...

"አለሜ አሁን ይሄን ምን አመጣው...እሺ አልመጥንም...እሺ ቅንጣት ነኝ...እሺ ...ሁሉንም እሺ...አሁን ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ...."....ደንግጧል...ሰላም እንደነበሩ ትዝ ይለዋል...ብዙም አልራቀም...ትናንት ከስራ ከወጡ በኃላ አብረው አምሽተዋል...በጨረቃ ብርሀን ታጅበው እንጨት እንጨት በሚል ቀልዱ ተንፈራፍራለች....አሳሳቋ ገርሞት "አንቺ ብቻ እኮ ነሽ ምትስቂልኝ" ብሏታል....መጨረሻም መጀመሪያም ላይ የሚታወሰው ነገር ሳቋ ነው።


"ምን ሆነሻል..."....ጥያቄ ደገመ...መልሷን እየጠበቀ ነው...እርሷ አይን አይኑን እያየች እምባዋ ቀደማት...

እምባዋ አልገራ ሲል ወደራሱ ስቦ አቀፋት...መንጭቃው ከእቅፉ ወጣች....


"አለሜ ምንድን ነው ያጠፋሁት...ንገሪኝ አታስጨንቂኝ"


"አፈቀርኩህ...ድምፅህን መራብ ጀመርኩ እኮ...በምናብ ካንተ ጋር መዋል ጀመርኩ እኮ...ትናፍቀኝ ጀመር...እነዚህ ሁሉ የማልፈልጋቸው ስሜቶች አንተን ተከትለው መጡ..."...ሳግ እየተናነቃት መለሰችለት...



ደስ አለው...በስሰት እያያት እንባ ያረጠበው አይኗን ሳመ...ቀስ አድርጎ ወደራሱ ሳባት....አጥብቆ አቀፋት...ባሁኑ አልተወራጨችም...

"አቅም አሳጣኸኝ..."....ከበፊቱ አጥብቆ አቀፋት።


Shewit



https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

08 Nov, 06:21


እማማ አፀደ የሚባሉ ጎረቤት አሉን የእናቴ ጓደኛ ናቸው። እማማ አፀደ አመም አድርጓቸው ህመማቸው በባሰ ቁጥር እናቴን ጠሏት።

ይሰድቧታል ሌባ ናት ይላሉ።
መሰሪ ናት ይላሉ።
ልትገለኝ ትፈልጋለች ይላሉ።
መርዝ አበላቺኝ ይላሉ ። አትምጣብኝ ብለው ስሞታ ይናገራሉ ሌሊት እቤቴ ልትገባ ነበር ይላሉ ።

ሰው እንዳትመስላችሁ ይላሉ ። እናቴ ቤታቸው መሄድ አቆመች ።

ከቤት መውጣት እያቆሙ ግቢያቸው መዋል ጀመሩ ....

እናቴ እሷ መሆኗን አትንገሩ ብላ ፤ ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸውን  ልጅ ፤ ምን ጎደለ ጤናቸው እንዴት ነው እያለች ትሰልላቸዋለች...

ንዴት ሊገድለኝ ይደርሳል ። እቆጣታለሁ << ስምሽን እያጠፉሽ እየሰደቡሽ እየጠሉሽ አትተያቸውም ወይ?>> እላታለሁ!!

<<ጭንቅላታቸው እጢ ወጥቶባቸዋል እሱ ነው ትንሽ ቀየር ያደረጋቸው እንጂ ፤ እሳቸው እንኳን ሳልበድል ብበድላቸው እንኳን በክፉ አያነሱኝም>> ትለኛለች።

ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸው ልጅ በኩል የሚያስፈልጋቸውን  መድኃኒት መግዣ ከኛ ወስዳ ... ተበድራም ቢሆን  ትገዛላቸዋለች ። እሳቸው ያቺ ምናምንቴ ፣ ድግምታም ያቺ ነጠላ እያሉ ጮክ ብለው እናቴን ሲሰድቧት ይውላሉ  ።

ጠላኋቸው !!

አንድ ቀን ለምን ግን እንዲ ስምሽን እያጠፉ እየጠሉሽ እያልፈለጉሽ አልጠላሻቸውም? ብዬ እናቴን ጠየቅኋት።

<<ጓደኛዬ ናቸው! እዚህ ሰፈር ስመጣ እሳቸው ናቸው ያለመዱኝ ። እድር ያስገቡኝ ፥ የሌለኝን እቃ ያዋሱኝ ፥ የተቆረቆሩልኝ ፥ የአረሱኝ ፣የመከሩኝ...

እንዲህ አይባልም እያሉ መንገድ ያሳዩኝ እርሳቸው ናቸው ። ድንገት ታመው ነው የተቀየሩት ።ከሁሉም ጋር ነው መጣላት የጀመሩት እኔ ላይ ትንሽ ጠንከር አሉ እንጂ ...

በክፉ ግዜ እንኳን ወዳጅ ላይ ጠላት ላይ አይጨከንም!!

የጨዋ ሰው ልክ የሚታየው ሲጣሉት ነው ። በፍቅር ግዜ ሰው አይመዘንም ክፉ ግዜ ነው ሰው የሚያጠለው ....

አፀዱ እንዴት አይነት ጥሩ ሰው መሰሉህ ዛሬ ህመም ተጣብቷቸው እን'ጂ ። ስንት ቀን መሰለህ እጦት በሳቸው ሳብያ ከቤታችን የተባረረው ።
አፀደ ደግ 'ሩህሩህ ናቸው...

እናንተ ሳትወለዱ ማንም ሳይኖረኝ ነው ከኔ ጋር የነበሩት...

      የአፀደ ውለታ አለብኝ !>>
  © Adhanom Mitiku

https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

07 Nov, 15:36


Self- portrait story

የሚወደው አጎቱ ለሽርሽር ይዞት እንደሚወጣ
ህጻን:- ከረጅም ጊዜ ወዲያ ራሴን ሽርሽር ወሰድኩት::

ራሴን ምሳ ጋበዝኩት ...ቶሎ በቃኝ አለ:: ለወትሮ እንደዚህ አልነበረም::

cinema አይወድም ግን አሪፍ Movie ጋበዝኩት!

መጸሐፍ ገዛሁለት::
የ Nizar Tawfiq Qabbani ግጥም አነበብኩለት::  (የሶሪያ ገጣሚ ነው)

በስሙ ይመረቅ ብዬ "ቆንጅት" ለሚያክሉ እናቶች ብር ሰጠሁለት:: እስኪመረቅ ይጠብቃል:: አቀርቅሮ "አሜን" ሲል ሲያሳዝን::

መድኃኒዓለም ይዤው ሄድኩ ፀሎት ጠፍቶበታል:: እንደለመደው ተሳልሞ እንሂድ አለኝ::

"ቆንጆ  ሴት ብትመለከትስ"
ብዬ ሆቴል ይዤው ገባሁ::  ግን አቀርቅሮ አመሸ:: ስልኩ ላይ::
"እንዴ እኔ ዓይንአፋር ነህ እንዴ?"
ሳቀ::
"እየተሽኮረመምክ ባልሆነ"
"አቦ ተውኝ" ቀልድ አዘል ልመና::

ደብሮታል ማለት ነው::

"የልቡን እንዲያወራኝ"  ትንሽ ቢራ አጠጣሁት:: ፍንክች:: ወፍ የለም::

"ግብዣዬን ንቀኸው ነው?"
"ምኑ"
"የማታወራኝ"
"ምን ላውራህ?"
"ደስ ያለህን"
"ደስ አይለኝም ማወራት"
"ለምን ?"
"አለሰማኸኝም መሰለኝ"
"የፈለከውን አውራኝ"
"ምንም አልፈለኩም"
አቀረቀርኩ::
"ምድር ላይ ማውራትም መስማትም የደከመህ ቀን የለም?"

ተውኩት::

ብዙ ጠጣን:: ዝም ተባብለን::

አንዳንድ ሰዎች መጥተው ያቅፉታል:: አድናቂዎች አሉት:: የውሸት ይስቃል::

ይቀመጣል:: ማን እንዳስቀየመው ምን እንዳስቀየመው መናገር አይፈልግም::
ሰውን
ህይወትን
ራሱን
ስሜቱን
እኩል ሰዓት አኮረፎቷል::

"እሺ ምን ልጋብዝህ እኔ?"

"ዝምታ"

"ከማን ነው የትኳረፍከው?"

"እኔ እኮ ሰው አኩርፌ አላውቅም ...
ራሴን የምቀየመው"

"ከራስህ ከምንህ?"

"ከስሜቴ::"

"ማለት?"

"ሳልፈልግ ከሚሰሙኝ ስሜቶቼ....
የወደድኳቸው እንዲወዱኝ ያከበርኳቸው እንዲያከብሩኝ ማሸርገዴ ....ስንት የሚወዱኝ እያሉ ክፉ የተናገሩኝን የጠሉኝን ማሰላሰሌ ምናምን ምናምን ምናምን  ምናምን"

አቀረቀርን ረጅም ሰዓት::

"ይቅርታ ግብዣህን አደበዘዝኩብህ ኣ...እኔ እኮ አልሆንም ....ብታይ ራሴን ስጠላው:: ሰዎች እንዳወቁት የሚሰማቸው ማንም የማያውቀኝ::

ምን ልበለው? እኔ እንደዚህ ደብሮት አይቼው አላውቅም::

"ይቅርታ አስድበርኩህ ኣ" አለኝ::

"ያዋከቡት ነገር ምዕራፍ አያገኝም ...."
ዓይኑ ተከፈተ:: ሳቀ:: የሚወደው ዘፈን ነው:: 
አብሮት ይጮሀል::

"መወደድ መታደል ሆኖ እንኳ ቢገኝም
ይህ ፍቅር ተጣድፏል እኔ አላመረኝም"

https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

07 Nov, 10:14


አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ?" አለችን ፕሮፌሰሯ መምህራችን ስለ "defense mechanism" እያስተማረች በመሃል። የእሷን ክላስ ሚቀጣ ተማሪ የለም፣ ግን ውበቷን በየቀኑ እያዩ ለማድነቅ ይሆን ለትምህርት እውቀቷ ለማወቅ ይከብዳል፤ ሁሉም ቀና ብሎ ጥያቄዋን ይጠባበቅ ጀመር፤ ክላሱን በአንዴ ቃኘት አደረገችና ቀጠለች
"ለዚህ ትውልድ common የሆነ defense mechanism ምን ይመስላችኋል? ማለቴ አብዛኛው ሰው የሚጠቀመው?"
ሁሉም በሰሌዳው ላይ ከተጻፉት ወደ ዘጠኝ ከሚሆኑት ውስጥ ለመመርጥ ይታገላል፤
ራድያ እጇን አወጣችና እንድታወራ እድል ተሰጣት፣
"እንደኔ እንደኔ 'sense of humor' ይመስለኛል" አለች፣
አጠገቧ ያለችውም ልጅ "በተለይ ለወንዶች" አለችና ሃሳቧን ደገፈችላት።
እነዚህ ሁለቱና Repአችን ቤካ ናቸው ሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መርጠው የገቡት፣ የተቀረነው የመንግስት ዩኒቨርስቲ ከመሆኑ አንጻር ፈልገን አይደለም የገባነው፣ አንዳንዱ ኢኮኖሚክስ ሌላው ማኔጅመንት ሌላውም ሌላ ሌላ የሞላ ነበር "over flow" በሚሉት ጉድ ነው ያልመረጥነውን ዲፓርትመንት በግድ ያሸከሙን፣ አልማርም ብሎ ወደቤቱ የተመለሰም ጥቂት አይደለም፤ ያው እንደእኔ አይነቱ ድሃ ደግሞ መሰንበቱን መርጧል፣ ምኑም የማይገባኝ ትምህርት ነበር ማለቴ ጥቅሙ ወይም አስፈላጊነቱ አይታየኝም አሁን አሁን ግን እኔም ሆነ ሌሎቻችን እየወደድነው የመጣነው ትምህርት ነው፤

"ወንዶች በዚህ ጉዳይ ምን ትላላችሁ?" ስትል አስተማሪያችን ሌላ ጥያቄ አስከተለች፤ ወንድ ሁሉ ቤካን የወከለ ይመስል ትኩረት ሁሉ እሱ ላይ ሆነ፤
"በርግጥ ልክ ሊሆን ይችላል ግን በአብዛኛው ወንዶች ያሉት ነገር አያስማማኝም በዛ ላይ ደግሞ የነሱ motive negatively መሆኑና ነቆራ እንደሆነ ግልጽ ነው።" አለ የንዴት ይሁን የአቤቱታ ባልታወቀ ጠንከር ባለ ድምጸት፤ ወደ አስተማሪዋ እያየ።
"እና ታድያ ልክኮ ነን፤ እናንተ ቀልድን የምታበዙት ከreality ለመሸሽ ነው። በነገሮች ላይ ቀልዳችሁ የምታልፉት መጋፈጥ ስለማትወዱ ነው፣ ይሄ ደሞ ወደፊት የከፋ ችግር ውስጥ ከመክተት የዘለለ ሌላ ፋይዳ አይኖረውም፤ ምናልባትም ከራስ ጋር የተጣላ፣ ውስጡ እያረረ ጥርሱ የሚስቅ፣ የውስጡን ስሜት አውጥቶ መግለጽ የማይችል ሰው ነው የሚያረጋችሁ" አለች መክሊት ከሁለቱ ሴቶች አንዷ።
ክርክሩ አሁን ከእነሱና ከእነሱ ወደ እናንተና እናንተ ተሸጋግሯል፣ አስተማሪዋን አውጥተው ለሁለት ጎራ ተካፍለው መሟገት ይሁን መጨቃጨቅ ያለየለት የቃላት ውርወራ ውስጥ ገብተዋል፤ ቤካም ቀጠለ
"ይሄ ፍፁም ልክ አደለም፣ እንደውም ቀልድ ከባድ ሁኔታዎችን ተቋቁመን እንድናልፍ ነው የሚያረገን፣ ስሜቶቻችንን ገዝተን ከእኛ እንድናርቃቸው ያደርጋል" ብሎ ሳይጨርስ
"ማራቅ መፍትሄ አይሆንማ" ስትል ራድያ ሃሳቡን አቋረጠችው፤ ግን እንድትቀጥል እድል አልሰጣትም፣ እሱም ከአፏ መንትፎ ቀጠለ...
"ምን ማለት ነው ይሄ ደግሞ? ለምሳሌ አንድ የተጨነቀ ሰው ከጓደኞቹ ጋር ተቀምጦ ጭንቀቱን በቀልድ አወዛዝቶ ቢረሳው ያንን ስሜት ከራሱ አራቀው አደል የምንለው? ታድያ ከዚህ በላይ ምን መፍትሔ አለ? መቼስ ለጭንቀት መፍትሔ ፍለጋ መሪጌታ ጋር አይሄድ ነገር..." ተማሪዎቹ ትንሽ ሳቁለት አስተማሪዋም በጥቂቱ ፈገግ አለች፤
"ደግሞ ለsocial connection ራሱ አሪፍ ነው፤ በችግሮቻችን ጊዜ የመገለልና የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማን ያደርጋል" ብሎ ሙግቱን እንዳሸነፈ ሰው የልብ ልብ ተሰማውና ዝም አለ፤ በዚህ ትምህርት ደስ የሚለኝ አስተማሪም ተማሪም እኩል ሃሳቡን ሸርሽሮ ይወጣል፣ ተማሪ ከተማሪ ጋር፣ አስተማሪ ከተማሪ ጋር ሙግት ሲገጥም ማየት የተለመደ ነው፤ አሁንም ይሄንኑ እያየን ነው፤ ክፍሉ እንደቲያትር አዳራሽ የተሰራ ነው፣ ተሟጋቾቹ ከፊት ለፊት በግራና በቀኝ ጥግ ተቀምጠዋል፣ ይሄ ደግሞ እኛ ከላይ ሆነን አስተማሪዋም ከፊት ሆና ተመቻችተን ግራ ቀኙን እያየን እንድንሰማ ጥሩ እድል ሰቶናል። አሁንም ራድያ ቀጠለች፤
"አየክ አሁን በዚህ ሙግት ውስጥ ራሱ ትቀልዳለህ፣ ለምን? ቀልድ ቶሎ ተቀባይነትን ስለሚያገኝ። ከዛ ሩጫ ከእውነታ ለመሸሽ፣ ይሄ ደግሞ ማስመሰል ይባላል፣ ደግሞ social bonding ያልከው ራሱ አሳማኝ አይደለም ምክንያቱም እናንተ ወንዶች ግኑኝነታችሁ ከአንገት በላይ ነው፤ የሆድ የሆዳችሁን አውርታችሁ አታውቁም social connection ከሚለው ቃል በላይ superficial relationship የሚለው ይበልጥ አሳማኝ ነው፣ እውነት ነው ልትዋደዱ ትችላላችሁ ግን አትረዳዱም፣ even ጓደኛችሁ ችግሩን በቁምነገር ማናገር ቢፈልግ ራሱ የምትቀልዱበት ስለሚመስለው አይናገርም then ቅድም አራቀው ያልከው ጭንቀት ብቻውን ሲሆን ተከትሎት ይመጣል።" ይሄኛው ንግግሯ ምክር አዘልም ይመስላል፤ ቤካ በቃ ፍረጂልን አይነት አስተማሪዋን ማየት ሲጀምር ሁሉም ተማሪ ከርሱ ጋር አፉን ከፍቶ ከሷ አፍ የሚወጣውን ንግግር መጠበቅ ጀመረ።
እሱም እጇን አጣጥፋ ከፊትለፊት ካለው ጠረጴዛ ላይ ደገፍ ብላ ሙግቱን ከምትሰማበት ፈቀቅ አለችና ዞራ ወረቀቶቿን መሰብሰብ ጀመረች።
"ኧረ ፕሮፌሰር ዛሬም ብያኔ ሳትሰጭን ልትሄጂ ነው እንዴ" የሚል የወንድ ድምጽ ከወደኋላ ተሰማ፤ ተማሪውም ልጁን ተከትሎ አጉተመተመ፤ ራሳችሁ ድረሱበት ብላ መሄዱን ልምዳዋለች።
"አይ ምንም የምለው ነገር የለኝም፣ በደንብ አንብቡበት እርስ በእርሳችሁ ተነጋገሩ፣ በተረፈ መልካም ሰንበት።"
ብላ ወደበሩ ማምራት ጀመረች፣
"እንዴዴዴዴዴዴ" ሁሉም ተማሪ ተዘጋጅቶበት ይመስል አንድ ላይ ያወጣው ድምፅ ነበር፤
አልተመለሰችም ፈገግ ብላ ወደበሩ እያየች ወጣች...


ምስጉ (የግቢው ልጅ)✍️


https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

07 Nov, 10:07


ዝም☹️🤫🤫

አለኝ ብዙ የሚነገር
ሰው ቢሰማው 'ሚያደናግር
የተሸፈነ በትልቅ ዝምታ
ማንም ያልሰማው የሀዘን ኩታ
ይዤ ስዞር ከእለት እለት
የውሸት ሳቄን ደርቤበት
ማልናገር ማላወራው
ችግር አለኝ ሰው ያላየው
ብናገርስ በአደባባይ
ማን ሊጨንቀው የኔ ጉዳይ
መች ሊረዱኝ ከወሬ አልፈው
አይተው ሊያልፉ አስመስለው
በውሸት ሀዘን ከንፈር መጠው
በሳቅ ብዕር መምሰል ስለው
ለዚህ ስል መረጥኩኝ
እራስን ሸውዶ መሳቅን ለመድኩኝ
ምርጫዬ ሆነና ማለቴ ዝም ጭጭ
ህመሜን ሸሽጌ ይዤ ከቤቴ ቁጭ
ማንም እንዳይሰማ ድምፄን አድርጌ ረጭ
ከራሴ ተከተትኩ በዝምታ እንድራጭ
ዋጥ አርጌ ሀዘኔን በጉያዬ አቅፌ
ከሰው ተራ ስለይ እንባዬን ዘርግፌ
እኖራለው ይኸው በውሸት ፈገግታ
የሚሰማው የለም የልቤን ስቅታ
ውስጤ እየነደደ አንጀቴ እያረረ
የነብሴን ትኩሳት ዝምታ አጠቆረ
አርምሞን ሸከፍኩኝ መንጫጫትን ንቄ
ዝም አላለው ዛሬ እስኪያልፍ መሳቀቄ።🤫🤫
ዝምምምምምም


✍️የተክልዬዋ

https://t.me/semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

05 Nov, 04:39


ሞትና ህይወት

ህይወት ማለት ፤ተጓዥ ሂደት
'ምትሰጥህ ፤ነፃ ትምህርት
ሁለት ቀለም ፤ጥቁርናነጭ
ምታሲዝህ ፤አንድ አማራጭ
ብርቱ ውጊያ ፤ባለ ትግል
ከጊዜጋ ምታነሳ ፤ወይ የምትጥል
አንዴ ጣፋጭ ፤ወይ መራራ
ስትደቁስ የማትራራ
ግማሽ ባንተ ፤ግማሽ ላንተ እየሆነች
ተለዋዋጭ ሂደት፤ 'ማትሰለች
ትልቅ ሀሰት፤ ምትክድህ በአንድ እለት
ምትሞሽርህ ለቁርጥ ቀን፤ ምትድርህ ለሞት

ሞት ማለት ፤የማይፋቅ እውነት
በሰከንዶች ውስጥ ፤ከአለም መለየት
ጣዕም አልባ ፤ባዶ ስሜት
ለዱንያ ጥፋት ፤መክፈያ ሰዓት
የምድር ሩጫን ፤የጉዞ ማብቂያ
ነብስን መከተል፤ ስጋን መልቀቂያ
አንዴ ከሄዱ ፤የማይመጡበት
ነፃ መውጫ ነው፤ ከዓለም ሰንሰለት
እንዳመጣጥህ፤ ጠርቶ የሚወስድህ
አፈር 'ሚያለብስክ፤ ለራቁት ገላህ
ደባል ማይጠራ ፤ገንዘብ ወይም ሌላ
ጊዜ የማይሰጥ ፤ከመጣ ሗላ
ይዘህ ምትሄደው፤ የኖርከው ግብርህ
ክፋና መልካም ፤ያረከው ስራህ
እንዲነው እልፈት ፤ቸኳይ እንግዳ
ከተፍ የሚለው ፤ሳትሰናዳ
ወስዶ ይከትሀል፤ ከዘመን ምርጫህ
ሲኦል ወይ ገነት፤ ልክ እንደ ስራህ።

✍️የተክልዬዋ


@semetnbegtm

share&comment እንዳይረሳ😊 https://t.me/semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

04 Nov, 17:19


በሩን አንኳኩ "አቤት"ብዬ ከወንበሬ ተነስቼ ተቀበልኳቸው....... በእድሜ ገፋ ያሉ ፀጉራቸው አረፋ የመሰለ የደመቀ ሽበት ያለበት .......ፊታቸው በእድሜ ብዛት ሽብሽብ ያለ ሆኖ ቀይ ነው.... ገፃቸውን ሚያስደንቅ ፈገግታ የሞላው .....ፈገግታቸው ከሳቸው አልፎ ሰው ላይ የመጋባት አቅም ያለው.... እንደ አዛውንት ብዙ ልብስ የደራረቡ... ከሁኔታቸው ለሰው ክብር እና ስርዓት ያላቸው ደስ የሚሉ ሴት ነበሩ... ከወንበሬ ስለተነሳው የምርቃት መዓት ሲያዥጎደጉዱ ደሞ ይበልጥ ደስ አሉኝ... ሌላ ምን ታዘብኩህኝ .. በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ "ተመስገንን" ያስከትላሉ.... ገና ከበር ሲገቡ "ተመስገን" ......እኔ ስቀበላቸው ከምርቃቱ በዋላ "ተመስገን ".... ሲቀመጡ "ተመስገን" ብቻ በሁሉ ነገር ተመስገን ይላሉ አንዴ ብቻ አደለም ደሞ ይደጋግሙታል... ብቻ ፊቴ ላይ ምን እንዳሳየው ባላውቅም

"ምን ነው?" ብለው ጠየቁኝ...

"አረ ምንም!ምነው ?" ብዬ ጥያቄያቸውን በጥያቄ መለስኩኝ

"ፊትሽ ላይ የሆነ ነገር አንብቤ ነው.... 'ተመስገን' አበዛለው አይደል... አንቺ ብቻ አይደለም ሁሉም ሰው ስለሚል ነው አይዞሽ"አሉኝ... ምን ባሳይ ነው ብዬ ግራ ገባኝ ውስጤ ሳስበው የነበረው ነገር ፊቴ ላይ መታየቱን አላወኩም ነበር ትንሽ ሐፍረት ብጤም ጎሸም አደረገኝ እና የሀፍረት ፈገግታ አሳይቼ ዝም አልኩኝ

"አይዞሽ ሚያሳፍር ነገር እኮ አይደለም.... አበዛለው አቀዋለሁ እኮ ልምድ ሆኖብኝ ነው እናም ደሞ ሁሉም ነገር የፈጣሪ ቸርነት ነው ብዬ ነው.... አንድ በእድሜዬ የተማርኩት ነገር ተመስገን ትልቅ ዋጋ እንዳለው ነው እና ፈጣሪን ማመስገን ሁሌ የእምነት ቦታ እየሄዱ መፀለይ እና መለመን ብቻም አለመሆኑን ጭምር ነው አሉኝ"... የተናገርኩት ነገር ሳበኝ መሰለኝ ዝም ብዬ አፈጠጥኩባቸው.... የድምፃቸው ረጋ ብሎ ጥርት  ያለ ነው ዝም ብሎ ሚሰማ አይነት.... ምንም ቢያወሩ ሁሉም ሰው እንዲሰማቸው የሚያስገድድ አይነት ድምፅ አላቸው እኔም ዝም ብዬ ሌላ ሚናገሩት ነገር ካለ ብዬ ጠበኳቸው እሳቸውም ፈገግ ብለው ቀጠሉ

"ይሄውልሽ ልጄ ፈጣሪ እንደኛ አይደለም ....አቀረብሽውም አራቅሽውም....... ወደድሽውም ......አልወደድሽውም...... የሱ ባህሪ አይቀያየርም ሁሌም ይወደናልእናም የሚያስፈልገንን ነገር የጠየቅነውን ነገር በሰዓቱ ሳያበዛው ሳይቀንሰው ይሰጠናል ታድያ የሰጠንን ነገር በአግባቡ መጠቀም ደሞ ለሰጠን ነገር ያለንን የምስጋና መጠን ያሳያል ..........ለምሳሌ እናት ልጅ ከሰጣት ልጇን ማሳደግ መንከባከብ በተዘዋዋሪ ለሰጣት ነገር ምስጋናም ጭምር ነው አሁን አንቺ በሰጠሽ ሥራ በአግባቡ ከሰራሽ ሃቀኛ ከሆንሽ በተዘዋዋሪ ፈጣሪሽን እያመሰገንሽ ነው የግድ ቤቱ ሄደሽ መፀለይ አይጠበቅብሽም በርግጥ አትፀልይ አታመሰግኚ እያልኩኝ አይደለም ግን በሰጠሽ ነገር ደስታሽን እርካታሽን ትጋትሽን ስታሳይ ተመስገን እያልሽ ጭምር ነው... አሁን እኔን አይኝ ጤናዬን ሰቶ እድሜ አድሎኝ በሰዎች ፊት እንድከበር አድርጎኛል ለዛ ነው ለሁሉም ነገር ተመስገን የምለው" ብለው ያን የሚያምር ፈገግታ ለገሱኝ .... ንግግራቸው አበርትቶኝ ነው መሰል ጉዳያቸውን ቶሎ ጨረስኩላቸው እሳቸውም የምርቃት መዓት አሸክመውኝ... ተነስተው ወተው ሄዱ....



✍️kalkidan




http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

04 Nov, 10:43


"ቃል ያደክማል..."....ብልህስ....

""ማለት..."

"በቃ ያደክማላ...."

"እኮ እንዴት...."

"ዛሬ ያበረታህ ቃል ነገ አንድ አንድ እያለ ይሸራርፍሀል....ብርጭቆ ቢሰበር ስብርባሪውን አይተህ መርጠህ ትረግጥና ከመድማት ትድናለህ...ቃል ሲሰበር ግን እግርህን እየተከተለ ይቆራርጥሀል..."

.....እንደማረፍ ብላ ቀጠለች.....


"ለዚህ ነው ቃልህን እያሰብክበት የምልህ.....ለዚህ ነው ሆዴ በባባ ቁጥር አለሁልሽ አትበለኝ የምልህ...ቃል የማይፈነቀል ድንጋይ ነው....ኃላ ቃልህን የረሳህ እንደው ከልቤ አልፈነቀል እንዳይለኝ."


shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Nov, 18:39


with besti😊


Sponsered by Ado coffee house☕️

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

03 Nov, 07:54


"ነገ ቀለበት ላስር ነው" አለችን......

"ከኛ የበለጠ ማን ቀርቦሽ ነው ነገ ልታገቢ ዛሬ የምንሰማው?" አለች ሰላም።

ሁላችንም ቢደብረንም ለዛሬ እንኳን ድብቅነቷን ያለምንም ወቀሳ ተቀብለን ደስታዋን ለማድመቅ ተስማማን....
የቀለበቱ ቀን አለፈና ከሁለት ቀን በኋላ ቤቷ ምሳ ተጠርተን ሄድን...አኔ እና ሶስት የልብ ጓደኞቿ ነበርን....

"ትዳር መያዝ ቀላል ነው ወይስ....እስኪ በናትሽ ምከሪን" አለች  በቅርብ ለማግባት ያቀደቸው ጓደኛችን ....
"እውነቷን ነው በዚ እንኳን እንጠቃቀም እንጂ", የኛ ጓደኝነት በደስታ እና በችግር መገናኘት ብቻ ነው እያለች ሁሌ ምትነጫነጨው ሰላም ናት ያለችው። ትውውቃችን ከ kg ጀምሮ ነው ከሁሉም ጋር።

ሙሽራዋ ቀጠለች,
"ትዳር ደስ ይላል ቶሎ አግቡና ለናንተም እስኪ ፏ እንበል" አለች እየሳቀች።
ለምን እንደሆነ ባላውቅም ከጠያቂዎቹ በላይ መልሷ አጓግቶኝ ነበርና ተቆጥቼ "አትቀልጂ እስኪ" አልኳት....
ለዚ እኮ ነው የኛ ጓደኝነት ቁምነገር ያንሰዋል የምለው, ሰላም ማማረሯን ቀጠለች

የእውነት ግን ትዳር ከባድ ነገር አደለም። እኔ ትልቁ የምመክራችሁ ነገር እና ለኔም የጠቀመኝ ነገር ብር እና መልክ አለማየት ነው። እና ደግሞ ኩራት ቁም ነገር ላይ አይሰራም።

ከዚ በኋላ ያለችውን አልሰማኋትም, ስንት አመት አብረናት ስንማር እኔና እነ ሰላምን በጓደኝነት የሚቀርቡንን ሰዎች እንዴት እደምታራክሳቸው አልረሳውም

አንቺ ምን ሁኖ ነው ምሳ እንኳን ያልጋበዘሽ, ሰሊ ከዚ ልጅ ጋር ከቀጠልሽ ልጆችሽ ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ መገመት ነው ይቅርብሽ, ምንድነው call me ምትልኪው ካርድ እንኳን አይሞላልሽም, በጭራሽ አንቺ እንዳትደውዪ መኩራት አለብሽ.....

   ኧረ ስንቱን አለቺን....

ኢኸው እኛም እሷን አምነን ያለችንን ሁሉ እያደረግን አለን....

ለካ ሁሉም ለሰው ሚመክረው ከራሱ ሂወት አርቆ ለብቻው አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎ ካስቀመጠው ማህደር ውስጥ እያወጣ ነው...



Lilly


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

02 Nov, 16:37


««እባክህን ናልኝ»»


ላይብረሪ ገብቼ...
PCዬን ከፈትኩት
ምንም ሳላነብ ተኝቶ አየሁት፣
ስልኬንም ከፈትኩት
ደግሞም ዘጋሁት...
አንተን ሳላገኝህ፣
ከአካሌ ሳላዋድህ፣
ከአእምሮዬ ሳላከትምህ፣
በአይኔ ሳልዳስስህ፣
እንዴት ሊነበብልኝ፡
ኧረ አንድ መስመርም አይገፋልኝ፤
በአይነ ህሊናዬ ውልብ እያልክ
በናፍቆትህ ስቃይ እየገረፍክ
ጭራሽኑ ላታየኝ ከወሰንክ
ሂድ አልልህም ጓዝህን ሸክፈክ፤
አውቃለሁ ጥፋቴን
ከMid በኋላ አንተን አለመፈለጌን፤
ቢሆንም ግድ የለም
አንድ እድል ብቻ ልሸለም
በጣሙን ናፍቀኸኛልና
#የጥናት ሙዴ ሆይ ና ና
Final ደርሷልና

የግቢው ልጅ✍️

https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

01 Nov, 21:03


"ቆይ ግን ምን እየሆንሽ ነው ? ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሆደቡቡ ሆነሻል ደሞ ከመች ጀምሮ ነው ለፊልም ማልቀስ የጀመርሽው ?" አለኝ በግርምትና በሀዘኔታ እየተመለከተኝ
መልስ ግን አልሰጠውትም በዝምታ ፊልሙን እያየው ማልቀሴን ቀጠልኩ
ቢጨንቀው አቅፎ እንደ ህፃን እያባበለ ሊያረጋጋኝ ሞከረ መታቀፌ ግን እኔን የባሰ እንድነፋረቅ እድል ሰጠኝና ባሰብኝ ያኔ ደነገጠ ግራ ተጋብቶ ቁልቁል እያየኝ "እማ ምን ሆነሻል እንደ ልጅ ለፊልም ታለቅሻለሽ እንዴ ከመች ጀምሮ ነው እንዲ አልቃሻ የሆንሽው እንባሽ ታይቶ የማያቅ ልጅ ዛሬ ምን ተገኝቶ ለፊልም ትነፋረቂ ጀመር?" ብሎ ሳቅና ሀዘኔታ የተቀላቀለበት ፊቱን እንዳይ ቀና አድርጎኝ የተፈጠረውን ንገሪኝ የሚል አይነት አስተያየት ያየኝ ጀመር
.
ምን ብዬ ልናገር አንቆ የያዘኝን ሳግ እንዴት ትቼ የማለቅሰው ፊልሙ ላይ ለሞተው ሰውዬ አደለም ላጣውት ለራሴ ሰው እንጂ እንዴት ልበል የሀዘንና ለቅሶ ነገሮች ባየው ቁጥር ያጣዋት እናቴን አስታውሼ የገደብኩትን እንባ በሰበቡ እንደማነባ እንዴት ብዬ ልናገር እስከዛሬ ያጋጠሙኝን መጥፎ ነገራቶች ሁሉ ከልክ በላይ ሞልተውንኳ ያላፈሰስኩትን የገታውትን የደበኩትን እንባ በአንድ እሷ ሞት በአንዲት ጠብታ ሀዘን ተገፍቶ እንደሚፈስ እንዴት ላስረዳው በሳኩኝ ቁጥር ሳቋ በበላው ቁጥር ያጠገበኝ እጇ ባመመኝ ጊዜ መድኃኒት እቅፏ በፈተና ቀናቴ ምርቃቷና መልካም ምኞቷ ባስታወስኩኝ ጊዜ አፍኜ የምይዘውን እንባ ምን አለበት በፊልሙ አሳዛኝነት አሳብቤ ባነባው ይሄንን እንዴት ላስረዳው እንዴት ይነገራል? እንጃ ብቻ ማስረዳት አቃተኝ አፌም አልናገር አለኝ ላወራው ስላልቻልኩ በለቅሶዬ ላይ ቆየሁበት ከደቂቃዎች በኋላ እንባዬን ገትቼው ይሁን አልቆ ባይገባኝም አቁሜ ፊቴን ተጣጥቤ በድጋሚ አጠገቡ
ተቀመጥኩ
.
ጠረጴዛው ላይ ያለውን አይላንድ አንስቶ በብርጭቆ ውሃ ቀዳልኝና "ትንሽ ጠጪ ያረጋጋሻል"አለኝ የብርጭቆ ውሃውን አየውት አፍገደፉ ድረስ ሞልቶታል ላነሳው ብሞክር ወይም አንድ ጠብታ ቢጨመርበት እንደሚፈስ ላየው ያስታውቃል የሱን ብርጭቆ አነሳውትና ጣቴን ነከርኩበት ቅንድቡን ከፍ አርጎ እያየኝ "ዛሬ ግን ምን እየሆንሽ ነው?" አለኝ ጣቴ ላይ ያለችውን ጠብታ የኔ ብርጭቆ ውስጥ እንድትገባ አደረኳት ባለመፍሰስና በመፍሰስ መሀል ሲያንገራግር የነበረው ውሃ ፈሰሰ ወደ ብርጭቆዬ እየጠቆምኩ"እንዲ ነው እየሆንኩ ያለሁት "አልኩት

መልዕክት:-አንዳንድ ሰዎች በልፍስፍስነትና በደካማነት ምክንያት አደለም የሚያለቅሱት ለረጅም ጊዜ ጠንክሮ በመቆም የተቋቋሙትን ሁሉ ነገር የሞላ እንባቸውን አንድ ከባድ ሀዘን ታፈስባቸዋል ደካማ ባይሆኑም የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ ስለማይቀር እንባቸውን እንዲያፈሱ እንፍቀድላቸው።

✍️የተክልዬዋ

@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm


Check out ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄: https://t.me/semetnbegtm

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

30 Oct, 07:15


መሪጌታ ምን እያሉኝ ነው🙄

ወይ ትርጉሙን ይንገሩኝ ተጨነቅኩ እኮ🥺

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

29 Oct, 18:00


ከፋኝ ስላት እንዴት እንደነበረች አውቃለሁ... ያኔ አመመኝ ስላት የታመመችውን አስታውሳለሁ....ታቦት በሸኘሁ ቁጥር አእምሮዬ ላይ የምትመላለሰው እርሷ ናት...ባሰብኳት ቁጥር ሆዴን ባር ባር ይለዋል....የሰበሯትን ሁላ ሰብስቤ መግደል ያምረኛል...እኔን ብሎ ገዳይ....ውስጧን የበላውን ሀዘን፣መከፋት ብቻ ሁሉንም ነገር መጠራረግ ብችል እላለሁ...

አሁን የእግዜር ሰላምታ ብቻ ተለዋውጠን ዝም ስንባባል "ኧረ በቃን አንተኛም" እንዴ ተባብለን ወሬያችንን የቋጨንበት ቀን ይታወሰኛል....ታሪኳ ካልተቀየረ ከእግዚአብሄር ጋር ሽማግሌ የማይዳኘው ቅያሜ ውስጥ እንደምገባ ይሰማኛል....

ጓደኛዬ ናት...እርግጥ ታናሽ እህቴ ብላት ይቀለኛል...ውስጧን አከብረዋለሁ...ልቧ ያስገርመኛል...አመለካከቷን ከዚህ በፊት የትም አላየሁትም...የዋህነቷን ጥንካሬዋን መግለፅ አልችልም(I know ስታነበው ምነው አለቀለቅሽ እንደምትለኝ😂)...ብቻ ስብዕናዋ የሚከበር ነው....ለሰው አዛኝነቷን በአይኔ አይቼዋለሁ (ጊቢ እያለሁ በእግሯ እየሄደች የመሳፈሪያዋን ትልክልኝ ነበር)...እህት ብቻ አይደለችም....

አዳማጬ፣ተቆጪዬ፣አጫዋቼም ናት....እኔንጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ህመሟን ብካፈላት ብዬ የተመኘሁላት እህቴ ናት....

በህመሟ መሀል "ሰው በህይወት በመቆየቱ ብቻ እግዚአብሄርን ማመስገን አለበት...."....የምትል እና የምታበረታኝ ሴት ናት...

አንዳንዴ ነገሮች በኛ የማይፈቱ ሲሆኑ እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ ግድ ይል የለ እሱ ጊዜ ላይ ነን...ታዲያ እጃችንን ቀና አድርገን መፀለዩ እንዳለ ሆኖ ነው....እግዚአብሄር ይፍታው ብለን የምንቀመጥበት ጊዜ አለ...ነገሮች የሚደበዝዙበት....መከራ የሚፀናበት ወቅት አለ አይደል....



ብቻ ይፍታው....



Shewit




https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

29 Oct, 15:14


እማማ አፀደ የሚባሉ ጎረቤት አሉን የእናቴ ጓደኛ ናቸው። እማማ አፀደ አመም አድርጓቸው ህመማቸው በባሰ ቁጥር እናቴን ጠሏት።

ይሰድቧታል ሌባ ናት ይላሉ።
መሰሪ ናት ይላሉ።
ልትገለኝ ትፈልጋለች ይላሉ።
መርዝ አበላቺኝ ይላሉ ። አትምጣብኝ ብለው ስሞታ ይናገራሉ ሌሊት እቤቴ ልትገባ ነበር ይላሉ ።

ሰው እንዳትመስላችሁ ይላሉ ። እናቴ ቤታቸው መሄድ አቆመች ።

ከቤት መውጣት እያቆሙ ግቢያቸው መዋል ጀመሩ ....

እናቴ እሷ መሆኗን አትንገሩ ብላ ፤ ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸውን  ልጅ ፤ ምን ጎደለ ጤናቸው እንዴት ነው እያለች ትሰልላቸዋለች...

ንዴት ሊገድለኝ ይደርሳል ። እቆጣታለሁ << ስምሽን እያጠፉሽ እየሰደቡሽ እየጠሉሽ አትተያቸውም ወይ?>> እላታለሁ!!

<<ጭንቅላታቸው እጢ ወጥቶባቸዋል እሱ ነው ትንሽ ቀየር ያደረጋቸው እንጂ ፤ እሳቸው እንኳን ሳልበድል ብበድላቸው እንኳን በክፉ አያነሱኝም>> ትለኛለች።

ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸው ልጅ በኩል የሚያስፈልጋቸውን  መድኃኒት መግዣ ከኛ ወስዳ ... ተበድራም ቢሆን  ትገዛላቸዋለች ። እሳቸው ያቺ ምናምንቴ ፣ ድግምታም ያቺ ነጠላ እያሉ ጮክ ብለው እናቴን ሲሰድቧት ይውላሉ  ።

ጠላኋቸው !!

አንድ ቀን ለምን ግን እንዲ ስምሽን እያጠፉ እየጠሉሽ እያልፈለጉሽ አልጠላሻቸውም? ብዬ እናቴን ጠየቅኋት።

<<ጓደኛዬ ናቸው! እዚህ ሰፈር ስመጣ እሳቸው ናቸው ያለመዱኝ ። እድር ያስገቡኝ ፥ የሌለኝን እቃ ያዋሱኝ ፥ የተቆረቆሩልኝ ፥ የአረሱኝ ፣የመከሩኝ...

እንዲህ አይባልም እያሉ መንገድ ያሳዩኝ እርሳቸው ናቸው ። ድንገት ታመው ነው የተቀየሩት ።ከሁሉም ጋር ነው መጣላት የጀመሩት እኔ ላይ ትንሽ ጠንከር አሉ እንጂ ...

በክፉ ግዜ እንኳን ወዳጅ ላይ ጠላት ላይ አይጨከንም!!

የጨዋ ሰው ልክ የሚታየው ሲጣሉት ነው ። በፍቅር ግዜ ሰው አይመዘንም ክፉ ግዜ ነው ሰው የሚያጠለው ....

አፀዱ እንዴት አይነት ጥሩ ሰው መሰሉህ ዛሬ ህመም ተጣብቷቸው እን'ጂ ። ስንት ቀን መሰለህ እጦት በሳቸው ሳብያ ከቤታችን የተባረረው ።
አፀደ ደግ 'ሩህሩህ ናቸው...

እናንተ ሳትወለዱ ማንም ሳይኖረኝ ነው ከኔ ጋር የነበሩት...

      የአፀደ ውለታ አለብኝ !>>
  © Adhanom Mitiku

https://t.me/yomin1_2

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

27 Oct, 06:01


https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

25 Oct, 15:51


💔💔💔💔 ገደልኳት 💔💔💔💔




< ገደልኳት >  ይላል ሁሌ ሰአቱን ጠብቆ የፀሃይ መውጫ በደንብ የሚታይበትን ቦታውን መርጦ ኪዳን እንደሚያደርስ ሰው በጠዋቱ ይሰየማል .....ለሚሰማው ሰው አልያም ለጠዋቷ ጀንበር ባይታወቅም እለት ተለት ንስሃ እደሚገባ ሰው ሀጥያቱን ይናዘዛል.......

< ገደልኳት የት አቧቷ > ይላል በቁጭት  ይቀጥልና < አባቴ ድሮ እዚም እዛም ተው ወንድ ልጅ ብዙ ሀላፊነት አለበት ለሴቷ ሁሉን አዘጋጅቶ መጠበቅ አለበት......መጀመሪያ ትምህርትክን በስርዓቱ ከዛ ስራክን በአግባቡ ካስተካከልክ ፀባይክን ካሳመርክ የትኛዋም ሴት ትሰግድልካለች አላለም ብሏል ወንድ ልጅ ስራ ከሌለው ፀባይ ከሌለው ዕውቀት ከሌለው ለምንም አይሆንም አላለም ብሏል > የሚጠይቀውም የሚመልሰውም ለጀንበሯ እስከሚመስል ድረስ  ከሷ ላይ አይኑን ሳይነቅል ያወራል

< ታዲያ አኮ እውነቱን ነው የጠየኳት ሴት ሁሉ እግሬ ስር ነበር የምትንበረከክልኝ አደለም ወድጃት የወደድኳት የመሰላት ሴት እንኳን እንቢ ብላኝ አታውቅም ...ታዲያ እሷ ማናት እንቢ የምትለው ...አባቴ ያለኝን ሁሉ አላሟላሁም አሟልቻለው አልተማርኩም ተምሬአለሁ ሀብታም አልሆንኩም ሆኛለሁ ....ታዲያ ምን አጥታ ነው አልፈልግም ያለችኝ ደሞ እኮ ከሷ ብሶ ያንን ዱርዬ መውደዷ ምን አለው ...ብር አለው ..እውቀት አለው...ፀባይ አለው ..እንዲሁ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ነው የሚውለው ... ታዲያ አንተን አልፈልግም እሱን እንጂ ትለኛለች .......>

< ገደልኳት በምሽት ከስራ ስትመለስ ጠብቄ በጩቤ ወግቼ ገደልኳት ...የት አባቷ > በአጠገቡ የሚያልፈው ሰው ግማሹ እያማተበ ያልፈዋል ...ግማሹ የሚናገረው ነገር አስገርሞት ቆሞ ያዳምጣል ...እሱ ግን ሀጥያቱን  እየተናዘዘ የሚፈርድበት ወይ የሚፈርድለት ሳያገኝ ከጀንበሯ ጋር ተፋጧል ....

< ደሞ እሱን  ያስበለጠችበት ምክንያት .....እሱ ምንም ባይኖረውም እንኳን ጥሩ ሰው ነው አላለችም ..ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ....ቆይ ሀብታም ሰው ..የተማረ ሰው ..ምናምን እሺ ጥሩ ሰው ምን ያደርጋል ...እሱን ከኔ ምታስበልጥበት ምክንያት አጥታ ነው እንጂ....ቆይ ጥሩነት ከሀብት ይበልጣል ..ከእውቀት ይበልጣል ..ጥሩ ሰው ነው ትለኛለች ...የት አባቷ ...ገደልኳት..ወግቼ ነው የገደልኳት...ለምኜ እንቢ ብላኝ ነው የገደልኳት >  በህፃናት ታጅቦ አንድ አዛውንት ይመጡና እንደሁልጊዜው የተተቀደደ ልብሱን በጋቢ ከናንበው ከተቀመጠበት አንስተው ልጄን ልጄን እያሉ ይወስዱታል ....ድምፁ ብቻ ይሰማል .....ገደልኳት ........


✍️kalkida


http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

25 Oct, 13:15


ሁሉ ማለፉ የምድር ህግ ነው...

~              ~            ~

✍🏾 በየአብስራ ፀጋ
ማስታወሻ ጥቅምት ፲፭
፪፼፲፯ ዓ.ም

YOUTUBE  TIKTOK INSTAGRAM

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

24 Oct, 18:54


እንዴት እንደጀመርኩ ብነግርሽ ትስቂያለሽ.... ሁሉም ነገር ሲጀመር እንደ ቀልድ ነው .......እስከመቼ ድረስ አብሮ እንደሚቆይ አታውቂም ....መች ያለዛ ነገር መኖር እንደሚከብድሽ  አታውቂም ........በቃ የሆነ ሰዓት ላይ ራስሽን ስታውቂው የዛ ነገር ጥገኛ ሆነሽ እራስሽን ታገኚዋለሽ..... መች ለመጀመሪያ ጊዜ መጠጥ እንደቀመስኩ ታውቂያለሽ?????.. የ11 ዓመት ልጅ እያለው ነው...ሃሃሃሃሃሃሃ ....ትንሽ ነበርኩኝ አይደል???? አዎ በጣም ትንሽ ነበርኩ ......

በጊዜው የናት እና ያባቴን ጭቅጭቅ ላለማየት የገጠምኳቸው የጎዳና ልጆች ጋር ነበር ምውለው ...የመጀመሪያ ጓደኞቼ እናት እና አባት ፍቅር እና መተሳሰብ ሳይ ከነሱ ጋር መዋል .መጫወት.. ማጥናት ከበደኝ.... እና ቀስ በቀስ ከነሱ እየራኩኝ ሄድኩኝ.. ቀስ በቀስ ሰፈራችን መውጫ ጋር ካሉት የጎዳና ልጆች ጋር ገጠምኩኝ..... እነሱ ወላጅ የላቸውም ....ተቆጣጣሪ የላቸውም እነሱ ጋር የፈለገ ባመሽ ሂድ መሽቷል የሚለኝ የለም ....በዛውም ከቤተሰቤ የመራቅ ፍላጎቴን ..ቤት ውስጥ ብዙ ሰዓት ያለማሳለፍ ፍላጎቴን አሳካልኝ ....እናት እና አባቴ ሲጣሉ እና ሲጨቃጨቁ ሁሌ የሚሏት አንድ ዓ.ነገር አለች.... "ይሄ ልጅ ባይዘኝ ኖሮ ካንተ ጋር/ካንቺ ጋር ስቃጠል አልኖርም ነበር" ይሉ ነበር  እና በዚ ምክንያት በኔ ምክንያት የማይፈልጉትን ሕይወት ሚመሩ ይመስለኝ ነበር ......እና የኔ ከዛ መራቅ የኔ ቤት አለመዋል  በሆነ መንገድ ሚያረጋጋቸው ይመስለኝ ነበር..

በሚገርምሽ ጎዳና የሚኖሩት ልጆች አብዛኞቹ የኔ አይነት ታሪክ ነበራቸው በዚ የተነሳ ማወራው ነገር ይገባቸው ነበር ....አንድ ልጅ ነበር ሄኖክ የሚባል..... በጣም ሲበዛ ጠጪ ነበር..... አሁን እንኳን ከኔ አይብስም ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ... ብቻ እሱም በቤተሰብ case ነው ጎዳና የወጣው..... የሱ ቤተሰቦች ደሞ ገራሚ ናቸው.... አንዳንድ ሰው ስለወለደ ብቻ እናት ወይም አባት ሚሆን ይመስለዋል...... እንደዛ አይሰራም.... ልጅን ማብላት እና ማጠጣት አደለም የወላጅ ግዴታ.... የልጅን አመለካከት...አስተሳሰብ ....ሁሉ የወላጅ ውጤት መሆኑን አውቀው ለዛ ነገር መጨነቅም አለባቸው.... የሚናገሩት እያንዳንዱ ነገር ልጁ ላይ ምን ያክል ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ ማወቅ አለባቸው... በዚ ምክንያት ነው አብዛኛው ልጅ አእመሮው ተነክቶ ሚያብደው... እራሱን እንደ ሰነፍ የሚቆጥረው..... እራሱን ከሰው በታች የሚያረገው... እና የሄኖክ ቤተሰቦች ገና እሮጠው ያልጠገቡ ወላጆች ነበሩ እና ሁልጊዜ እየጠጡ እየመጡ ይበጠብጡት ነበር... በልጅ አእምሮው ማይጠፋ ንግግር ይናገሩት ነበር... ብሎ ብሎ ሲያቅተው ጎዳና ወጣ እና እናቱ እና አባቱን ያሳጣው መጠጥ ምን ቢኖረው ነው ብሎ መጠጣት ጀመረ በዛው ባሰበት እና ኃይለኛ ጠጪ ሆኖ አረፈው እኔንም ለመጀመሪያ ጊዜ መጠጥ ያቀመሰኝ እሱ ነው...........

መጀመሪያ መጠጥ ትንሽ ከፍ ሲል ሲጋራ ከዛ ጫት ከዛ ሃሺሽ... ከዛ...........እያለ የሆነ ጊዜ ላይ ሰውነትሽን የሚሻማ ብዙ ወኪል ሹመሽ ቁጭ ትያለሽ... ሕብረተሰቡም ለመፍረድ አንደኛ ነው... አንዴ ይይ እንጂ እድሜ ልክ መታወቂያ አድርጎ ይቀርፅብሻል... ከዛ በዋላ ልቀይር ብትይ እንኳን የነሱ ወሬ እና አሽሙር እየጎተተ እዛው ላይ ይጥልሻል.........

እናቴ እኮ ታሳዝነኛለች... በኔ ምክንያት እንደዚህ ስትናደድ እና ስትታመም ታሳዝነኛለች... ግን ደግሞ እናደድባታለው ...ለምን እዚህ ሁኔታ ውስጥ ከተተችኝ ብዬ እናደድባታለው ...ለምን በትክክለኛው መንገድ አልመራችኝም ብዬ እናደድባታለው...ለምን ትናደድብኛለች ብዬ እራሱ እናደድባታለው መውለድ ብቻ እናት አለማስባሉን ባለማወቋ እናደድባታለው .....ግን ምንም አልልም ስትናደድ ዝምምምም ......ስትቆጣ ዝምምምም......... ስትመታኝ ዝምምም..... ዕድል አልተሰጠኝም እንዳድግ.. እንድማር .....እንድለወጥ ..ዕድል አልተሰጠኝም... ያልተሰጠኝ ደሞ እንዴት ልስጥ?? ስንት ትውልድ ሳያውቁ አበላሽተውን ሳናውቅ ተበላሽተን ቀረን..... ብቻ ዝምምም




✍️kalkidan


http://t.me/storyweaver36

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

23 Oct, 19:18


"ምን እንደምጠላ ታውቃለህ..."

"ምን...."

"የማልጨርሰውን ነገር መጀመር....ምንም ከባድ ቢሆን ጀመርኩት ማለት እንደምጨርሰው ለራሴ ቃል ገብቻለሁ ማለት ነው...ቃል ደግሞ የማይፈነቀል ድንጋይ ነው።"


shewit

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

23 Oct, 14:35


ለተወሰነ ጊዜ ልርቅ ነው...ከምን አትሉም...የcosmo ማስታወቂያ ቻናሌ ላይ ከመፖሰት....

የሚጀመረው ተከታታይ ፅሁፍ ነገ እንደሚጀመር ለማብሰር እወዳለሁ...በተጨማሪም ቻናሌ የስነፅሁፍ ቻናል እንደሆነ ይታወቃል...እናም የcosmo ማስታወቂያ እንዳበዛሁበት ስለተሰማኝ እነዚህን cosmo products👇

በhttps://t.me/rabistor እንደምታገኙ ለማሳወቅ እና ተከታታይ ታሪኩ እስኪያልቅ የcosmoማስታወቂያ እንደማልፖስት ልነግራችሁ እወዳለሁ.... onhand ያሉ እቃዎችን ለማወቅም ሆነ order ለማድረግ @shedorka ላይ inbox አድርጉልኝ....የንግድ ቻናሌንም ተቀላቀሉ....


much love💙

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

22 Oct, 19:06


የጊቢው ልጅ ማለትም የውድድሩ አሸናፊ አሁን ጅማ ስለሚገኝ በጓደኛው በኩል ቃል የገባሁትን አድርሻለሁ😊....

ለቀጣይ ውድድር ራሳችሁን እያዘጋጃችሁ ቆዩኝ...ከዛ በፊት ግን አንድ ተከታታይ ታሪክ እንደምፅፍ ቃል እገባለሁ...የዚህ አመት እቅዴ ቃሌን ማክበር ነው😁ይመቻችሁ✌️

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

22 Oct, 18:54


እሙዬ እየታማሽ ነው😳....ስጦታ መቀበል እንጂ መስጠት አታውቅም ያለኝ የድሮ ፍቅረኛሽ ነው....🙄....ታዲያ እኔ ጋር የመቆየቱ ሚስጢር ከመቀበል በተጨማሪ ይሄን የመሳሰለ ሽቶ ከሸዊት እየገዛሁ ስጦታ ስለምሰጠው ነው...🙄😂....ያለፈው አልፏል ግን ከዚህ በኃላ ስምሽ እንዲጠፋ አልፈልግም😓....

በተመጣጣኝ ዋጋ እኔው ራሴ በርሽ ላይ ከተፍ ስለማደርግልሽ እንዲች ብለሽ እንዳታስቢ😁


ከደራሲነቴ ይልቅ ነጋዴነቴ  ፈንቅሎኝ ወጣ....😂...


Dm:-@Shedorka
0940054784

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

22 Oct, 14:46


Smell like never before🤌🫠


Chocolate chocolate መሽተት የሚፈልግ ብቻ ያናግረኝ....
Dm:-@shedorka
0940054784

ከfree delivary ጋር...

Join us👇
https://t.me/rabistor

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

22 Oct, 09:25


ምን ዐይነት ልብስ ለመግዛት አስበዋል? ‼️

ለፍቅረኛህ ቀሚስ ? ለተወለደው ልጅህ ሚሆን ቆንጆ ልብስ  ወይስ ለጓደኛህ ሚሆን ሸሚዝ ?

አንቺስ የ ራት ፕሮግራም ነው ያለብሽ ? ወይስ የ ጓደኛሽ ልደት ደርሱዎል ? ወይስ ለረጅም ጊዜ በ ቴክስት ከሚያዎራሽ ልጅ ጋር ዛሬ ልትገናኙ ተቀጣጥራቹሀል ?

እንግዲያውስ እንኩዋን ወደዚ ቻናል አመጣቹህ:: አንተም አንቺም ሳትሰስቱ ምትገዙዋቸው ልብሶች እኛ ጋር ይገኛሉ ::

ታድያ ምን እየጠበቁ ነው ? ከታች ባለው ሊንክ join በማድረግ መምረጥ ይጀምሩ ::

https://t.me/feven_cloth


በተጨማሪም የተለያዩ ጫማዎች እና የፀጉር ጌጦች እዚ ማግኘት ይችላሉ ::