________የጦሪቃው አውራድ ጎርፍ መፍሰሻ
አብሬድ ማለት ከአውራድ የተያዘ ሲሆን የጦሪቃችን አውራድ ጎርፉ የሚፈስበት ቦታ ነው::
<ቀደሠላሁ ሢረሁ>
▪️
አብሬቶች ድቅድቅ ባለው ጨለማ ወቅት 7ቤት ጉራጌ ሁላ ለአምልኮ ከሚጟዝላቸው ፥ ከሚገብርላቸው ፥ እንደ ንጉስ ከሚያዩዋቸው ከጣኦት አምላኪያን መሪ ቤተሰብ የወጡ ፀሀይ ናቸው:: ተተኪ የሀይማኖቱ መሪ ይሆናሉ ተብሎ ሲጠበቁ ኑረል ኢማንን ይዘው ብቅ ያሉ ፥ ሺርክን ከስሩ መንግለው የጣሉ ፥ ለኸልቁ እንደ ፀሀይ የበሩ የአላህ ኑር ናቸው:: ሠይዲ አባ ራሙዝ በአንዱ መድሀቸው መሽረብ ሸይኻቸውን ሠይድ ባኡ ሳኒ <በድቅድቁ ጨለማ መካከል የበሩ ፍጹም የሆኑ ሙሉ ጨረቃ> ብለው ያወድሷቸዋል::
▪️ሠላም ዐለይከ ሸምሠል ዲነል ኪራሚ
▪️በድሩል ዘማን ፊ ወሰጢ ዞላሚ
በጉራጌ እና አጎራባቾቹ ላይ ያለ ሙስሊም ሁሉ የሁዋላ ታሪኩን ቢያጤን አራት እና አምስት አባቱን ወደሁዋላ ቢቆጥር ከመቶ መቶ ወይንም ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንቱ ጨለማ ላይ የነበረ ህዝብ ነበር:: ሙሉ ሰባት ቤት ጉራጌ ማለት ይቻላል መብረቅ አምላኪ ህዝብ ነበር:: በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መልኩ ለዛሬው ማንነታችን ለሂዳያችን ሰበብ ከአብሬት ሸይኾች አንዱ ሆነው እናገኛዋለን:: በተለይም ለጉራጌ ማህበረሰብ:: ነገር ግን ከአብሬት የወጣው ፀሀይ በጉራጌና አጎራባቾቹ ብቻ ተገድቦ የቀረ አይደለም:: ብዙሀኑን የሀገራችንን ክፍሎች አካሎ ከሀገር ውጪም ፀሀያቸው በርቷል::
▪️
በታላቁ የረጀብ ወር በእነዚህ ከዋክብቶች ሀሪማ ሐረመል አብሬት የከውኑ ሁላ ንጉስ የነብያችንﷺ መውሊድ እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ ይከበራል:: የጦሪቃው አውራድ እንደ ጎርፍ ይፈሳል ፥ የአላህ ራሕመት ይዘንባል ፥ የነብያችንﷺ ኑር ይንቧቧል ፥ መላይካው እንደ ጉድ ይወርዳል ፥ የታላላቅ አውሊያዎች ሩሕ ይሀደራል። ከሚታየው የማይታየው ታዳሚ ይበልጣል:: እናልህ ወዳጄ አብሬት ለመግባት ጟዝህን ጠቅልል ከዚህ ማኢዳ ተቋደስ::
አ ብ ሬ ት ..... ረ ጀ ብ