ጥየቃ አያውቀው፣
ሰአቱን መጠበቅ ቀን ማወቅ አይለቀው፤
ሁሌ አብሮ አይኖር፣
ሁሌ መጪ እንግዳ፣
ሁሌ ምቾት ነሺ የሰባት ቀን እዳ፤
ሁሌ ተባበይ ባይ፣
በመጣ በታየ፣
ሁሌ የመድሎ ልጅ በጾታ የለየ፤
ሁሌ ፊት አደብዛዥ፣
የዙር አመል ከላሽ፣
ሁሌ ተጠባቂ ሁሌ መቶ ረባሽ፤
የልምላሜ መልክ፣
ከመባረክ ጓዳ፣
የሔዋን እጣ ነው ክቡር የሤት እዳ።
By @eyadermoges1
@getem
@getem
@paappii