﴿مَن سَأَلَ النّاسَ أمْوالَهُمْ تَكَثُّرًا، فإنّما يَسْأَلُ جَمْرًا فَلْيَسْتَقِلَّ، أوْ لِيَسْتَكْثِرْ﴾
“ገንዘብ እንዲበዛለት በማለም ሰዎችን ገንዘብ እንዲሰጡት የሚጠይቅ(የሚለምን) ሰው ፥ የእሳት ፍም ነው የሚጠይቀው። (ፍሙን ቢሻው) ያሳንስ (ቢሻው) ያብዛው!"
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1041
ማብራሪያ
ሀዲሱ ሰዎች ሳይቸግራቸውና አስገዳጅ ሁኔታ ሳይገጥማቸው ሀብት ለማካበት በማሰብ ብቻ የሚያደርጉትን ልመና ወንጀልነት የሚገልፅና የሚያስፈራራ ነው።