EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ @infoematgurage Channel on Telegram

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

@infoematgurage


እማት ጉራጌ ፕሮጀክት በተስፋ ነዳ ሀሣብ አመንጪነት የተጀመረ የጉራጌንባህል ፣ ሙዚቃ ፣ ከተሞች ና የተ
ቱሪዝም ሀብቶች የማስተዋወቅ አላማ ያነገበ ፕሮጀክት ነው።

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ (Amharic)

በአማርኛnnእማት ጉራጌ ፕሮጀክት በተስፋ ነዳ ሀሣብ አመንጪነት የተጀመረ የጉራጌንባህል ፣ ሙዚቃ ፣ ከተሞች ና የተቱሪዝም ሀብቶች የማስተዋወቅ አላማ ያነገበ ፕሮጀክት ነው። እሳት ጉራጌ 'EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ' ተብዬን መልእክት ከታከለ በኋላ መስራት ጀምሮ የፕሮጀክት ቃለ አጠቃላይ መንገድ የማከለከሉ ያልተከተተሉ ቦታ ነው። እስቲት ከቀጣይ መረጃዎቹ አጣለ በመሰብሰቢዎቹ መሰረትን የቴሌግራም በትርንስር፣ ሙዝቃና ቻነሎች ያሉ ነገሮች እና ፕሮጀክት እንዲሁም ለውጥ የሚጠቀም አጋሮች ይኖራል።nnከሌሎቹ ፕሮጀክቶች መሰረት የምትሰጠዉ እና ድርጊቶቹ ከምንም የሚያስርጉት ማድረግ እና ማሳከስ በአማርኛ የቴሌግራም ማሳሰቢያ ነው።

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

13 Nov, 11:15


ደረሰ ደረሰ ‼️ ለዛውም ለፆም መያዣ ‼️

ተፈጥሮዋዊ ቦታዎችን ጎብኝተን የጉራጌን ባህላዊ ምግብ በልተን ልንመጣ ነው‼️

🚌 ጉዞ ወደ ናይካም ፏፏቴ ና አጋሬ መንደር 🚌

🍃🍃 ጊቤ ፓርክ ጉራጌ 🍃🍃

በቅርቡ በአርቲስቶችና ጋዜጠኞች አስጎብኝተነው ዝናን ያተረፈው የአጋሬ መንደር አሁን ለሁላችሁም ዝግጁ ሆኗል‼️

📅 መነሻ ቅዳሜ ህዳር 14 , 2017
📅 መመለሻ ህዳር 15 ,2017

💵 የጉዞ ሂሳብ 4999 ብር

የጉዞ ሂሳብ የሚያካትተው

🚍 ትራንስፖርት ዘመናዊ አውቶብስ

🥗 ምግብ ጥሬ ስጋ ፣ ክትፎ ፣ ብራፕራት ፣ ቡላ ገንፎ

💧የታሸገ ውሀ, ቡና, አስጎብኚ

🔥 የምሽት ካምፋየር 🔥 ና ፎቶግራፍ 📷

ሁሉንም በ ሙሉ ፓኬጅ 4999 ብር

ለቤተሰብ - ለፍቅረኞች - ለጓደኛማቾች ለሁሉም የተመቸ 🏕️

ውብ የተፈጥሮ እይታ እያዩ መዝናናት ለሚወዱ ም Adventure ለሚመቻቸውም የሚሆኑ አማራጮች ያሉት!

ለመመዝገብ 0924410897 ላይ ቴክስት ይላኩልን ። ክፍያ ሲፈፅሙ ወንበር ይያዝሎታል።

ጉዞ ጉራጌ - TESFA TV

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

10 Nov, 16:05


🚌 ጉዞ ወደ ናይካም ፏፏቴ ና አጋሬ መንደር 🚌

🍃🍃 ጊቤ ፓርክ ጉራጌ 🍃🍃

°°°°

በቅርቡ በአርቲስቶችና ጋዜጠኞች አስጎብኝተነው ዝናን ያተረፈው የአጋሬ መንደር አሁን ለሁላችሁም ዝግጁ ሆኗል‼️

📅 መነሻ ቅዳሜ ህዳር 14 , 2017
📅 መመለሻ ህዳር 15 ,2017

💵 የጉዞ ሂሳብ 6000 ብር

የጉዞ ሂሳብ የሚያካትተው

🚍 ትራንስፖርት ዘመናዊ አውቶብስ

🥗 ምግብ ጥሬ ስጋ ፣ ክትፎ ፣ ብራፕራት ፣ ቡላ ገንፎ

💧የታሸገ ውሀ, ቡና, አስጎብኚ

🔥 የምሽት ካምፋየር 🔥 ና ፎቶግራፍ 📷

ሁሉንም በ ሙሉ ፓኬጅ 6000 ብር

ለቤተሰብ - ለፍቅረኞች - ለጓደኛማቾች ለሁሉም የተመቸ 🏕️

ውብ የተፈጥሮ እይታ እያዩ መዝናናት ለሚወዱ ም Adventure ለሚመቻቸውም የሚሆኑ አማራጮች ያሉት!

ለመመዝገብ 0924410897 ላይ ቴክስት ይላኩልን ። ክፍያ ሲፈፅሙ ወንበር ይያዝሎታል።

ጉዞ ጉራጌ - TESFA TV

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

06 Nov, 15:11


https://youtu.be/0FaViGT0gVI

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

06 Nov, 15:10


ገና ሳይጠናቀቅ 8 ሚሊየን ብር የፈጀው የጉራጌ ጎጆ ቤት‼️

የጉራጌን የቱሪዝም አብዮት ካፈነዳው " ጉዞ ጉራጌ 3" መልስ ሌላኛው የቱሪዝም ሀብታችን የሆነው የጉራጌ ጎጆ ቤት አሰራር ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ልናይ ወደ እዣ ተጓዝን። ከጉብሬ ተነስተን ወልቂጤ ዩንቨርስቲን ካለፍን በኋላ አስፋልቱን በመተው ወደ ፒስታው ገባን። የተንጣለለውን የእዣ ለምለም ምድር እያየን የበረሳ ውርኼ ቀበሌ ደርሰናል።

ወሰኑን የዋቤ ወንዝን ያደረገው ቀበሌው ከወንዙ ማዶ ከቃጥባሬ ጋር ይተያያል። በዚህ አስቸጋሪ መንገድ አልፈው የተማሩትና አሁን በአሜሪካን ሀገር የሚገኙት አቶ አካሉ ደንድርና ወንድሞቻቸው እንደ አብዛኛው ጉራጌ ቀዬአቸውን ትተው ቢወጡም ልባቸው ግን እዚሁ ነውና እንግዳ ቢመጣ የማያፍርበት ዘመድ የሚሰባሰብበት ግዙፍ ጎጆ ገነቡ። ጎጆው ስምንት ሚሊየን ብር እንደፈጀ ሰምተናል። ይህን ሁሉ ሀብት በቀዬአቸው ማፍሰሳቸው ለብዙዎች ትምህርት ሊሆን የሚገባው ነው።

ከመጓጓታችን የተነሣ "ኧረ ገና ቤቱ አላለቀም ባህላዊ ወንበሮችና ቁሳቁሶች አልገቡም ለምርቃቱ ትመጣላችሁ " ቢሉንም ከመቅረፅ አልተመለስንም።

ይሄ ነው ጉራጌ ‼️ ይሄ ነው ባህልን መጠበቅ‼️

ተስፋ ቲቪ ከ ጉራጌ እዣ በረሳ ውርኼ

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

03 Nov, 13:25


የጉራጌ አካባቢ የተፈጥሮ ሀብት፤ ገና ያልተመነዘረና ያልተነካ፥ ለህዝቡ ከፈጣሪ የተቸረ ገደብ የለሽ፥ ሀብት ነው።

ለማህበረሰቡ ሲሳይና በረከት፤ የሆነው ይህ የተፈጥሮ ሀብት፤ በ"ጉዞ ጉራጌ" 3 ታዳሚዎች ዘንድ፥ አሳማኝነቱ እየተረጋገጠ፥ ቁጭት ፈጥሮ፤ የወደፊት ተስፋ ላይ የራሱን አስተዋፅዖ በማበርከትና ተነሳሽነት እንዲጎላ በማድረግ፥ ጉብኝቱ እየቀጠለ ይገኛል።

በ TESFA TV "ተስፋ ቲቪ" የተሰናዳው ይህ "ጉዞ ጉራጌ" 3 የተሰኘው መርሃግብር፤ ጋዜጠኞች፣ ሚዲያዎች፣ የቱሪዝም ጋዜጠኞች፣ ካሜራማኖችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ይዞ፤ ወደ ጉራጌ አካባቢ፥ ዛሬ ማለትም በዕለተ ቅዳሜ፥ በ23-02-2017 ዓ.ም. ከትሟል።

በዚህኛው "ጉዞ ጉራጌ" 3 የመርሃግብሩ ተመራጭ ቦታ፤ "ጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ" ሲሆን፤ በዕለቱ እንግዶች እና ጥሪ በተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት አማካኝነት፤ ቀኑን ሲጎበኝ ውሏል! አመሻሹም በ"ጉዞ ጉራጌ" 3 ጎብኚዎች እየደመቀ ይገኛል።

የጉራጌ ህዝብ ያሉት ያልተመነዘሩ ሀብቶች፤ በዚህ መርሃግብር እየተዳሰሰ ይገኛል። ባህላዊ ምግቦች ጨምሮ፤ የጉራጌ ባህል፣ ወግ፣ ስርዓትና ማንነት፥ በተግባር ለጎብኚዎች እንደ መፅሐፍ እየተገለጠ ሲንፀባረቅም ተስተውሏል።

በአጠቃላይ፤ በወሬ ሳይሆን በተግባር የሚያምን ትውልድ፣ የሚሰራና የሚያሰራ ማህበረሰብ፣ ለአካባቢው ተቆርቋሪ የሆነ አምራች ወጣት፣ ለመልካም አስተዳደር ትግበራና ለዘላቂ ልማት፥ የራሱን ድርሻ የሚወጣ አመራርና ባለድርሻ አካል እንዲሁም ተቆርቋሪ ባለሀብት፤ የጉራጌ ህዝብ ይሻል። የተግባር ሰው ይፈልጋል።

የዚህ ጉዞ መሳካት ላይ፤ የራሳችሁን ጉልህ አስተዋፅዖ የተወጣችሁ ሁሉ፤ እንኳን ደስ አላችሁ 🙏 እናንተ የስኬታማነት መሰላሎች ናችሁ። የ"ጉዞ ጉራጌ" 3 ስኬት፥ የእናንተም ስኬት ነው። በይመለከተኛል ዕሳቤ፤ እናንተ ከእኛ ጋር ነበራችሁ፤ እኛም ሁሌም ከእናንተ ጎን አለን ለማለት እንወዳለን።

የጉብኝቱ አጠቃላይ ይዘት፤ በቀጣይ ቀናቶች እናደርሳለን.....

ለማንኛውም "ጉዞ ጉራጌ" 3 ከስኬት ጋር እየቀጠለ፤ ድባቡም እያማረ ይገኛል. . . . .!!

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

01 Nov, 17:00


የጉራጌ ቀዬ አመቱን ሙሉ ደምቆ ... ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ተስፋፍቶ ... ጉራጌው ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን ምኞታችን ነው።

ድህነትና የልማት እጦት በማዘን ና በቁጭት ብቻ እንደማይፈታ እነሠምናለንና ለመፍትሄው እየተጋን ነው። የቱሪዝም መስህቦችን መፈለግ ፈልጎም ማስተዋወቅ ቱሪስቶችን መጥራት ለብዙዎች የስራ እድል መፍጠር ላይ ወጥረን እየሠራን ነው። ገና ከጅምሩ ውጤታችን ፍሬ አፍርቶ ቪድዮዎቻችን በመቶ ሺዎች እየታዩ ነው። ገና ሚሊየኖችን እንደርሳለን።

ነገና ከነገ ወዲያ በጊቤ ፓርክ የቱሪዝም ፌስቲቫል እናካሂዳለን። የሚዲያ ና የቱሪዝም ባለሙያዎች በእንግድነት ይገኛሉ። የዚህን ፕሮግራም ውጤትም ከነገ ጀምሮ በጋራ እናየዋለን።

ለዚህ ፕሮግራም እገዛ ስንጠይቅ ከሜየት አልፈው ለተግባር የፈጠኑት ጥቂቶች ቢሆን የጥቂቶች ወኔ እኛን አበርትቶናል። ከሚጠበቅብን ወጪ ገና የሠበሠብነው ግማሹን ነው ። ከዛም ውስጥ ግማሹን የሸፈኑልን ሶስት ሰዎች ጉራጌ ያልሆኑ ግን የጉራጌ ልማት ውጤቱ ለሀገር ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው። ደስ አይልም🤔❤️

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ፣ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፣ ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ፣ የጊቤ ፓርክ አስተዳደር ና የእኖር ወረዳ አስተዳደር የቻሉትን እየደገፉን ነው። የሁሉንም ድጋፍ ጠቅሰን እውቅና እንሰጣለን🙏

ለመልካም ብለን በተነሳንበት ጉዞ በእዳ እንዳንወድቅ ከመቶ ብር ጀምሮ በማዋጣት አለንላችሁ በሉን። መልካም መንገድም ተመኙልን🙏❤️

ንግድ ባንክ - 1000654868097

አቤል ክፍሉ - ፂዮን አለማየሁ - ተስፋ ነዳ

TEAM GUZO GURAGE

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

31 Oct, 19:11


የጉራጌን የቱሪዝም ዘርፍ የሚያነቃቃው ትልቁ የሚዲያ ፌስቲቫል ሊደረግ አንድ ቀን ብቻ ቀርቷል‼️

ያገኘነው ድጋፍ ግን ግማሽም አልደረሰም

አሁንም ድጋፋችሁን እየጠበቅን ነው

እየተቆለጳጰሱ ብቻ፤ ተግባር ከራቀን፥ እንደ ማህበረሰብ እንከሽፋለን..

በዓመት ሁለት ወቅቶች፤ የጉራጌ አካባቢ ደብቆ፣ ፈክቶና አጉምዥቶ እንዲሁም ተናፋቂ በሆነ አኳኋን የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን አስተናግዶ፤ ያልፋል።

በእነዚህ ወቅቶች የሚስተዋሉ የአንድነትና የመተሳሰር እውነታዎች፤ ለሌሎች ዓርአያነት ያለው ተግባር በመሆኑ፥ ሁሌም ይወደሳል። ይቆለጳጰሳል።

ታድያ ለምን ሁሉም ወቅቶች ላይ፤ የጉራጌ አካባቢ ፈክቶ፥ እንዲያንፀባርቅ ማድረግ ተሳነን?

በማህበረሰቡ ርብርብና በበጎ ፍቃደኝነት ላይ በተመሠረተው በዚህ የማህበረሰብ የውዴታ ግዴታ በሆነው ተግባር ላይ፤ ከ100 ብር ጀምሮ፤ የራስ አስተዋፅዖ በማድረግም፥ አሻራዎትን በማሳረፍ "ጉዞ ጉራጌ" 3 የተሰኘው መርሃግብር እንዲሳካ እናድርግ። ማህበረሰባዊ ሀላፊነታችንን እንወጣ።

ለማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ 👎

ንግድ ባንክ - 1000654868097

አቤል ክፍሉ - ፂዮን አለማየሁ - ተስፋ ነዳ

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

29 Oct, 17:45


እየተቆለጳጰሱ ብቻ፤ ተግባር ከራቀን፥ እንደ ማህበረሰብ እንከሽፋለን..

በዓመት ሁለት ወቅቶች፤ የጉራጌ አካባቢ ደብቆ፣ ፈክቶና አጉምዥቶ እንዲሁም ተናፋቂ በሆነ አኳኋን የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን አስተናግዶ፤ ያልፋል።

በእነዚህ ወቅቶች የሚስተዋሉ የአንድነትና የመተሳሰር እውነታዎች፤ ለሌሎች ዓርአያነት ያለው ተግባር በመሆኑ፥ ሁሌም ይወደሳል። ይቆለጳጰሳል።

ታድያ ለምን ሁሉም ወቅቶች ላይ፤ የጉራጌ አካባቢ ፈክቶ፥ እንዲያንፀባርቅ ማድረግ ተሳነን?

የተፈጥሮ ሀብቶቻችን፤ እጅግ ያማሩና ሀገሪቷ ካሏት ሀብቶች ውስጥ በቁጥር ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። እነዚህን የተፈጥሮ ሀብቶቻችን፤ ለወጣቶች የስራ ዕድል፣ ለማህበረሰቡ የተፋጠነ ልማት፣ ለዘላቂ የሀብት ምንጭ፣ ለማህበረሰቡም ሆነ፥ ለመንግስት የገቢ ምንጭ እና ለህዝብ ለህዝብ ትስስር አስተዋፅዖው ከፍተኛ ነው።

ታድያ እንዴት ነው መጠቀም ያለብን? ስር ነቀል ለውጥ እንደ ማህበረሰብ በማምጣት ነው። እሱም፤ ሚዲያዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ አንጋፋ ጋዜጠኞች፣ ኢንቬስተሮችና አስጎብኚ ድርጅቶች፤ ወደ ቦታው በመውሰድ፥ አስደማሚና ተወዳጅ የሆኑትን የጉራጌ የተፈጥሮ ሀብቶችን እንደ መነሻ አስጎብኝቶ፤ ዘመን ባፈራቸው በምስሎች፣ በተንቀሳቃሽ ምስሎችና በዘጋቢ ፊልሞች፤ ለሀገራችንና ለዓለም ህዝብ በማስመልከት፤ ቁጭትና ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ነው።

ይህ ተግባር እንዴት ይሳካል?

ይህ ተግባር ለማሳካት፤ ጥቅምት 23 እና 24 "ጉዞ ጉራጌ" 3 የተሰኘ ፕሮግራም ተይዟል። ሁሉም ተጓዦችና ለጉዞው የሚያስፈልጉ ነገሮች ተከናውነዋል።

በማህበረሰቡ ርብርብና በበጎ ፍቃደኝነት ላይ በተመሠረተው በዚህ የማህበረሰብ የውዴታ ግዴታ በሆነው ተግባር ላይ፤ ከ100 ብር ጀምሮ፤ የራስ አስተዋፅዖ በማድረግም፥ አሻራዎትን በማሳረፍ "ጉዞ ጉራጌ" 3 የተሰኘው መርሃግብር እንዲሳካ እናድርግ። ማህበረሰባዊ ሀላፊነታችንን እንወጣ።

ከብሽሽቅ፣ ከመናናቅ፣ ከመሰዳደብና ከክፉ ተግባራት በፀዳ መንፈስ፤ በማህበረሰብ አገልግሎት አንድነታችንን በማሳየት፥ ለሌሎችም አርዓያ የምንሆንበትን ተግባር ዕውን እናድርግ።

ለማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ 👎

ንግድ ባንክ - 1000654868097

አቤል ክፍሉ - ፂዮን አለማየሁ - ተስፋ ነዳ

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

28 Oct, 20:09


https://vm.tiktok.com/ZMh9cJbbf/

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

27 Oct, 21:29


https://vm.tiktok.com/ZMh9BW1Ak/

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

25 Oct, 14:58


https://youtu.be/zXQ99qVgmvs

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

21 Oct, 17:16


በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

በአዲስ አበባ አዲስ ክ/ከተማ መርካቶ በተለምዶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን የከተማዋ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንዳሉት÷እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል የእሳት የአደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎችና ባለሞያዎች በስፍራው ተሰማርተዋል፡፡

የእሳት አደጋውን መንስዔና ያደረሰውን ጉዳት ምርመራ ከተጣራ በኋላ እንደሚያሳውቁም ባለሞያው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ
fbc

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

21 Oct, 13:31


ጉዞ ጉራጌ ብለን ስንነሣ ቀድሞ ሞራል የሰጠን ጋሽ Kassa Yimmer ነው። ነሀሴና መስከረም ባደረግናቸው ሁለት ጉዞዎች አስር አስር ሺ ብር ስፖንሰር አርጎናል። አሁንም የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ይዘን በመሄድ መነቃቃት ለመፍጠር ስናቅድ በርቱ ብሎን አስር ሺ ብር አግዞናል። እኛም የጉራጌ ልብስ የምንሸልመው ይሆናል🙏

ጋሽ ካሳ አላማችን ለአንድ ብሄር ብቻ አለመሆኑን ተረድቶ ቱሪዝሙ ብዙ ወጣቶች የስራ እድል ቢያገኙ ጥቅሙ ለሀገር ነው ብሎ ከጎናችን ሲቆም አብዛኛው ጉራጌ ግን ባላየ እያለፈን ነው። ጉዞው መደረጉ የማይቀር ና የተፈለገውን ዋጋ ከፍለን የምናሣካው ቢሆንም ዝምታው ግን ያስከፋል።

ይሄን ሁሉ ጮኸን የጋሼን አስር ሺ ጨምሮ ማሠባሠብ የቻልነው 41800 ብር ነው ሲባል መቼም ያሣፍራል።

እስቲ ኮሜንት ላይ አለን በሉ 👏

ንግድ ባንክ - 1000654868097

አቤል ክፍሉ - ፂዮን አለማየሁ - ተስፋ ነዳ

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

20 Oct, 12:19


https://youtu.be/HrB3hSzx1jA

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

17 Oct, 18:37


https://vm.tiktok.com/ZMhPfdAsf/

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

17 Oct, 12:39


የጉራጌን ቱሪዝም የማነቃቃት አላማ ያለው "ጉዞ ጉራጌ 3 " በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ አስራ አምስት ቀናት ቀርተውታል። ይህ ጉዞ ከእስከአሁኑ በተለየ መልኩ ሙሉ ለሙሉ የክብር እንግዶችን ብቻ በመያዝ ወደ ጊቤ ፓርክና አካባቢው የሚደረግ ጉብኝት ና ካምፒንግ ነው።

አዳዲስ ነገሮች እንሞክራለን ካምፒንግ አርጎ በደን መሀል ክትፎ እንበላለን። ክትፎ ጫካ ልትገባ ነው😂 ከተፈጥሮ ሀብት አልፈንም የጉራጌ ህፃናት እየተማሩባቸው ያሉ ትምህርት ቤቶችን ና እናቶች ቀድተው የሚጠጧቸውን ወንዞች እናያለን። የጉራጌ ሁለት መልኮች 🤔

" ለዛ ቀን ያድርሰን እንጂ እንመጣለን " ካሉን መሀል ጥቂቱን ዘርዝሬላችሁ የቀሩትን ከባድ እንግዶች ደግሞ ቀጥዬ እመጣበታለሁ።

1 ሄኖክ ስዩም - የቱሪዝም ጋዜጠኛና ደራሲ

2 ተስፋዬ ማሞ - ደራሲና የማስታወቂያ ባለሙያ

3 የሸዋ ማስረሻ - ጋዜጠኛና የሚዲያ አዋርድ አሸናፊ

4 አዳነ አረጋ - ጋዜጠኛና የሚዲያ አዋርድ አዘጋጅ

5 መሠረት በዙ - ጋዜጠኛና ዩቱዩበር

6 ሰያ ኢትዮጵያ - አስጎብኚና ጋዜጠኛ

7 Elatrik (በግሩፕ) - ቲክቶከሮች

8 በረከት ግዛቸው - ተዋናይና የጉማ አዋርድ እጩ

9 ተስፋአብ ተሾመ - ደራሲ

10 ህሊና ተክሌ - ጋዜጠኛና የሴቶች የሚታጠብ ሞዴስ አምራች

11 ሰለሞን ሳህለ - ገጣሚ

ሌሎች ታዋቂ ድምፃውያን ፣ በጎ አድራጊዎች ፣ ኢኮኖሚስቶች ናባለሀብቶች ጥሪ ቀርቦላቸዋል ። በጉዞ ደስተኛነታቸውን ገልፀው ፕሮግራማችንን እንመልከት ብለዋል ። ሲወስኑ አሳውቃችኋለሁ።

አላማችን ያስደሰታችሁ ድርጅቶች ይህን ታላቅ ጉዞ ስፖንሰር አድርጋችሁ ድርጅታችሁን አስተዋውቁ።

ጉዞው እንዲሳካ ከመቶ ብር ጀምሮ ለመደገፍ የምትፈልጉ የሀገራችን ልጆች ከታች ያለውን የጉዞ ጉራጌ አካውንት ተጠቀሙ።

ንግድ ባንክ - 1000654868097

አቤል ክፍሉ - ፂዮን አለማየሁ - ተስፋ ነዳ

Emat Gurage Media

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

17 Oct, 12:00


የጉራጌን ቱሪዝም የማነቃቃት አላማ ያለው "ጉዞ ጉራጌ 3 " በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ አስራ አምስት ቀናት ቀርተውታል። ይህ ጉዞ ከእስከአሁኑ በተለየ መልኩ ሙሉ ለሙሉ የክብር እንግዶችን ብቻ በመያዝ ወደ ጊቤ ፓርክና አካባቢው የሚደረግ ጉብኝት ና ካምፒንግ ነው።

አዳዲስ ነገሮች እንሞክራለን ካምፒንግ አርጎ በደን መሀል ክትፎ እንበላለን። ክትፎ ጫካ ልትገባ ነው😂 ከተፈጥሮ ሀብት አልፈንም የጉራጌ ህፃናት እየተማሩባቸው ያሉ ትምህርት ቤቶችን ና እናቶች ቀድተው የሚጠጧቸውን ወንዞች እናያለን። የጉራጌ ሁለት መልኮች 🤔

" ለዛ ቀን ያድርሰን እንጂ እንመጣለን " ካሉን መሀል ጥቂቱን ዘርዝሬላችሁ የቀሩትን ከባድ እንግዶች ደግሞ ቀጥዬ እመጣበታለሁ።

1 ሄኖክ ስዩም - የቱሪዝም ጋዜጠኛና ደራሲ

2 የሸዋ ማስረሻ - ጋዜጠኛና የሚዲያ አዋርድ አሸናፊ

3 አዳነ አረጋ - ጋዜጠኛና የሚዲያ አዋርድ አዘጋጅ

4 መሠረት በዙ - ጋዜጠኛና ዩቱዩበር

5 ሰያ ኢትዮጵያ - አስጎብኚና ጋዜጠኛ

6 Elatrik (በግሩፕ) - ቲክቶከሮች

7 በረከት ግዛቸው - ተዋናይና የጉማ አዋርድ እጩ

8 ተስፋአብ ተሾመ - ደራሲ

9 ህሊና ተክሌ - ጋዜጠኛና የሴቶች የሚታጠብ ሞዴስ አምራች

ሌሎች ታዋቂ ድምፃውያን ፣ በጎ አድራጊዎች ፣ ኢኮኖሚስቶች ናባለሀብቶች ጥሪ ቀርቦላቸዋል ። በጉዞ ደስተኛነታቸውን ገልፀው ፕሮግራማችንን እንመልከት ብለዋል ። ሲወስኑ አሳውቃችኋለሁ።

አላማችን ያስደሰታችሁ ድርጅቶች ይህን ታላቅ ጉዞ ስፖንሰር አድርጋችሁ ድርጅታችሁን አስተዋውቁ።

ጉዞው እንዲሳካ ከመቶ ብር ጀምሮ ለመደገፍ የምትፈልጉ የሀገራችን ልጆች ከታች ያለውን የጉዞ ጉራጌ አካውንት ተጠቀሙ።

ንግድ ባንክ - 1000654868097

አቤል ክፍሉ - ፂዮን አለማየሁ - ተስፋ ነዳ

Emat Gurage Media