የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
በዚሁ መሠረት ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።
ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ማናቸው ?
➡️ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን እና አለምአቀፋዊነት ጽህፈት ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል።
➡️ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጋዜጠኝነት እና ተግባቦት የትምህርት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።
➡️ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተማሩበት የትምህርት ክፍል በአስተማሪነት አገልግለዋል።
➡️ በውጭ ቋንቋዎች የማስተርስ ዲግሪ ባገኙበት አምቦ ዩኒቨርስቲ እና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አስተምረዋል።
➡️ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12 ዓመታት የማስተማር እና የአመራርነት ልምድ አለቸው።
➡️ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ (UNISA) በኮሚዩኒኬሽን አግኝተዋል።
➡️ በተለያዩ የምርምር ህትመቶች ላይ የወጡ ጽሁፎችን በግላቸው እና በጋራ አሳትመዋል።
➡️ በብሉምበርግ የአፍሪካ ሚዲያ ኢኒሼቴቭ ስር የሚሰጠውን የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ስልጠናን በስራ አስኪያጅነት መርተዋል በሌሎች ተቋማትም በማማከር ስራዎች ተሳትፈዋል።
#HoPR #EthiopiaInsider