የሰውሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማበልጸግ የሚታወቀው OpenAI ከኮመን ሴንስ ሚዲያ ጋር በመሆን መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ጄኔሬቲቭ AI እና ChatGPT ላይ መሰረታዊ እና ሥነ-ምግባራዊ እንድምታዎችን የሚማሩበት ሞጁል አዘጋጅቷል።
ይህ ስልጠናም መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የትምህርት ዕቅዶችን እና ለተማሪዎች ተጨማሪ አጋዥ ትምህርቶችን እንዲሰጡ የሚያስችላቸዋል ሲል ነው የገለጸው።
በዚህም ከኬጂ እስከ -12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ መምህራን የኩባንያውን AI chatbot በመጠቀም እንዴት በክፍል ውስጥ መጠቀም እንደሚችሉ የሚያግዙ የኦንላይን የትምህርቶች ተዘጋጅተውላቸዋል።
AI በቅድመ መደበኛ እንዲሁም በመደበኛ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ተግባራዊ የሚድረጉ ሂደት ገና በጅምር ላይ ያለ ቢመስልም OpenAI ጨምሮ ሌሎች ኩባንያዎች እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው።
ምንም እንኳን መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መጠቀማቸው እየጨመረ ቢሆንም በአብዛኛዎቹ አስተማሪዎች ዘንድ ቴክኖሎጂውን በመማሪያ ክፍል ውስጥ እንዲተገበር መታሰቡን አልወደዱትም።
ኮመን ሴንስ ሚዲያ በቅርብ ጊዜ በታዳጊ ወጣቶች ላን በሰራው አንድ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው 70 በመቶዎቹ የቤት ሥራቸውን ለማገዝ ወይም አሰልቺ የሚሏቸውን ሂደቶች ላለመከተል Generative AI ይጠቀማሉ። ነገር ግን ከዚህ ውስጥ አንድ ሶስተኛው ብቻ ናቸው ይህን ቴክኖሎጂ እየተጠቀሙ መሆናቸውን ለወላጆቻቸው ያሳወቁት።
@TikvahethMagazine