ጥበብና ማስተዋል @tebeb_mastewal Channel on Telegram

ጥበብና ማስተዋል

@tebeb_mastewal


ማስብን ወደድን

ጥበብና ማስተዋል (Amharic)

ጥበብና ማስተዋል የቴሌግራም ክፍል ነው እና ከዚህ በላይ መጽሐፍ የግብርና ዘር መኖሪያዎችን እና መፍታታዎችን ለመስበር የቴሌግራም አካቢ ነው። ይህ ቡድን በአማርኛ በደምበኝ መሆኑን እንደሚደረግ በጥቂቱ ምሳሌ እንረዳለን። ይህ ቡድኖች ከቤታቸው ሌሎች የሚያቀርቡ ሁሉ በቅርብ ውስጥ በተዘረዘሩ መከላከልዎች እና በተለያዩ መብት መሠረት የተቋቋመውን ሊነሳ ያሰባሰቡ አገልግሎቶች ያነሳው ነገር ነው። ጥበብና ማስተዋል አሁንም በቴሌግራም ላይ እንዳለን መጠን በጣም እንደሚለዌል በተዘረዘሩ ቡድን ላይ ስነሳውን ይከተሉ።

ጥበብና ማስተዋል

30 Aug, 07:49


ብዙ የሚከፍሉ እንዳሉ ሁሉ ፌክም አሉ ስታርት አድርጋችሁ ገንዘብ ስሩ ወገኖች ለብዙ ሰው ሼር ያደረገ ጥሩ ክፍያ ያገኛል

ጥበብና ማስተዋል

30 Aug, 07:48


https://t.me/lost_dogs_bot/lodoapp?startapp=ref-u_442359258

ጥበብና ማስተዋል

21 Aug, 19:26


Live stream finished (18 seconds)

ጥበብና ማስተዋል

21 Aug, 19:26


Live stream started

ጥበብና ማስተዋል

21 Aug, 19:26


Live stream finished (6 seconds)

ጥበብና ማስተዋል

21 Aug, 19:26


Live stream started

ጥበብና ማስተዋል

16 Aug, 07:21


ዛሬ በጧት አንድ መንገድ ላይ ቁሞው የሚሰብኩ የደስደስ ያላቸው የሀይማኖት አባት መንግስተ ሰማያት ቀርባለች እና ንስሀ ግቡ እያሉ በሚያስገመግም ድምጽ ያስተምራሉ

ቢሮ መግቢያ ሰአት ረፍዱብኝ ለመረጥ በተቃረበ ርምጃ ውስጥ ሁኘ ከፊትለፊቴ ያሉ ሁለት ውጣቶች 

በአባታችን ትምህርት ላይ ተንተርሰው የሚያወሩት ወሬ ተወርውሮ ጆሮዬ ላይ ተስነቀረ

እንዱ ወጣት እውነት ነው እኮ አሁ ዘመኑ አልቆል በቃ የመጨረሻው ዘመን ነው ። በጊዜ ካልተመለስን ያልቅልናል ሲኦል መውረዳችን ነው ።

ይሄኛው ወጣት ተቀበለው እና....
እንዴ.. ቀላል አልቆል ዘመኑ እኮ በሰይጣን ነው የሚመራው ።

አንድ ቀን ግን ሁላችንም ያልቅልናል ።በቃ ተበላን ምን አይነት ዘመን ላይ ነው ግን የተፈጠርነው ?
ምናለ እግዚአብሔር በደጋጎቹ ዘመን ቢፈጥረን....

ሀሀሀሀሀ ...ምን ማለት ነው በደጋጎቹ ዘመን ቢፈጥረን ማለት ? ሰይጣን ደግሞ ምን ዘመን አለው ?

የትኛው ነው ደግ ዘመን ? የቱ ዘምን ነው ሀጥያተኛ ያልነበረበት ዘመን ? የቱስ ጊዜ ነው ጻዲቅ ያልኖረበት ?

የሰነፍ ሰው ሀሳቡ ምንጊዜም ቢሆን ነው !
ችግርን መጋፈጥ ሲከብደን ቢሆን ፣ ቢደረግ ማለት እና መውቀስ እንጅ እናደርግ ይሁን ማለት አይደለም ።

ሰነፍ ሰው በሶዶማዊያን ዘመን ሎጥን ሁኖ መገለጥ አልይችልም፣ በካራን ህዝብ ዘንድ አብርሃምን መሆን አይሻም ፣በፈረኦን ቤት ውስጥ ሙሴን መሆን ጭራሹንም አያስበውም፣ ሰነፍ ሰው
ምድር በሀጥያት ስትሰምጥ ኖህን ሁኖ የጽድቅን መርከብ መስራትን አልታደለም...

ሰው ጀግና የሚሆነው በመከራ ቀን ነው !
ጻዲቅ በፈተና እሳት ተፈትኖ ነው ቅዱስ የሚሆነው !

አንድ ሰው እግዚአብሔር ታጋሽ አድርገኝ ብሎ ቢጸልይ አሉ አንድ አባት... ትግስትን የሚለማመድበትን መከራ ይሰጠዋል እንጂ እንዲሁ ታጋሽ አያደርገውም  አሉ ።

የትጋሽነትን በረከት የምናገኘው ከፈተናው ስናልፍ ነው አክሊሉን የምንቀዳጀው !

ቢሆን ቢደረግ ቢያዱርጉት የብልጣብልጥ ሀሳብ ነው ሰነፍ ሰው ለአዕምሮው ተላልፎ የተሰጠ ነው ።

መንግስተ ሰማዬት በብልጠት አትወረስም በእግዚአብሔር ቸርነት ነው እንጂ ።
ሰው ግን ብርቱ እና ጻዲቂ መሆን መቻል አለበት፣ የእግዚአብሔርንም ህግም ማክበር አለበት !

ቅድስና ንጽህናንም ያሻል ብልጣብልጥ መሆን የሲኦል ማሟሻ ነው የሚያደርገው !

ይሁዳ እግዚአብሔር ወልድ አስተምሮታል ፣ መርጦታል ። ከዚህ በላይ ደግ ዘመን አለ ? ከዚህ በላይ ጥሩ እድል አለ ?

ማነው ከድንግል ማርያም ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በላይ አስተማሪ ? ማንም ምንም የለም ! አይኖርምም ።

ሰነፍ ከሆንክ ይሄ ሁሉ እድልም ተሰቶህ ትክዳለህ ፣አምላክምን አሳልፈህ ትሸጣለህ !

የንስሀ ስርአትን እግዚአብሔር ሰቶህ እሱን መጠቀም አትችልም። ይልቁንስ እውቀትህን ተጠቅመህ ቀድመህ ገነት ለመግባት አምላክህን አሳልፈህ ለገዳዬች ሰተህ አንተ ግን ራስህን አጥፍተህ  ሲኦል ቀድመህ ተገኝተህ ክርስቶስ ሲኦል ያሉትን ወደ ገነት ሲመልስ አብሮ  እንዲመልሰህ ትፈልጋለህ ። መመለስ ግን አትችልም !

እግዚአብሔርን ማንም መሸወድ አይችልም ማንም እሱን ማታለል አይችልም ። እግዚአብሔርን ማፍቀር ፣መውደድ ፣ ማምላክ እንጅ ማስመሰል እና ብልጣብልጥ መሆን አያጸድቅም

እንኳን በቀመር በንጽህና የምንሰራው ቅድስናችን መንግስቱን አያወርሰንም የእግዚአብሔርን ቸርነቱ እንጂ !

የሰው ልጅ የመጨረሻ ዘመኑ የሚሞትባት ቀን ናት ! ዛሬ ብንሞት ዛሬ ለኛ የመጨረሻ እድላችን ናት ...

ሰው ደግሞ የሚሞትበትን ቀን አያውቀውም ...
ሰው ፍሪሀ እግዚአብሔር ካለው መቼም ዝግጁ ነው የሚያስፈርድበትን ስራ አይሰራም።

ጻዲቅ ሰው የእግዚአብሔር ፍቅር የገባው ነው
ሲበድል ቶሎ ንስሀ ይገባል ፣ እግዚአብሔር በፍጹም ልቡ ይወዳል ፣ ለህጉም ታዛዥ ነው ! አልችል ብሎ በፈተና ቢወድቅ እንኳን የዛን ሰአት እግዚአብሔር ይረዳዋል ያጸናዋል !
እግዚአብሔርን በየሰአቱ ማሰብ ነው የሚያድነው ፣ እግዚአብሔን ማምለክ እግዚአብሔር ፣ መውደድ ነው  የእግዚአብሔርን ፍቃድ የሚያሰራው !

ማንም ሰው ለራሱ ሲል ሀጥያት አያድርግ ። የእግዚአብሔር አላማው እኛ እንድንድን ነው ፣ ፍላጎትም የክብሩ ወራሾች እንድንሆን ነው...

አንተ ሰው አላረፈድክም ስራ በጊዜ አትገባም...የቤሮችን ዘበኛ ድምጽ ነበር ከሀሳቤ የመለሰኝ .....ሀሀሀሀሀ ጋሼ እንዴት አደሩ ሰላም ነው .....
እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም ነው.. ልጄ በል ቶሎ ግባ ረፍዶብሀል....እሽ ጋሼ

ረፍዶል ?...እግዚአብሔር ቢፈቅድ ስለማርፈድ በቀጣዩ ባስብ ደስ ይለኛል .....

እግዚአብሔር ጥበብና ማስተዋሉን ይስጠን

ተፃፈ በአቤል መስፍን
ቀን 25/11/2016....

ጥበብና ማስተዋል

15 Aug, 11:40


ስርቆሽ

አልመለስ ያለ ትውልድ
             አዳኝ መርከቧን ንቆ
በጥፋት ውሃ ሰጠመ
            በዝሙት ሃጥያት ወድቆ
ኀላም ውሃው እንደጠፈፈ
           ምድርን 'ሀ' ብሎ ሲያቀና
ኖህ በኩራት እንደቆመ
            ፍጥረቱን ሰበሰበና
በቅደም ተከተላቸው
             በጥምረት እንዳሳፈረ
ከመርከቡ ሊያወርዳቸው
          አንድ በአንድ እየቆጠረ
አጋር የሌለው ፍጥረት
              መጀመሪያ ያልነበረ
              አንድ እንስሳ ትርፍ ቀረ
ለካስ የዝሙት መንፈስ
               ከአህያ ጋር ተሳፍሮ
ሚስቱን እየደበቀ
              ከፈረስ ፍቅር ጀምሮ
             ከማይሆን ተኝቶ ኖሮ
ከመርከቡ እንደወረደ
መሃን በቅሎን ወለደ!
 
እንግዲህ ከኖህ ጀምሮ
                ዘመን ዘመንን አያደሰ
የጥፋት ውሃም የለ
                ዝሙትም እዚህ ደረሰ፡፡

         ✍️✍️ ሜሮን ጌትነት

ጥበብና ማስተዋል

14 Aug, 06:21


ተስፋሁን የምወደው ጎደኞዬ ነው ። ተስፈኛ እና ተናዳጅ ሰው ነው ።

ብዙ ጊዜ ትክክል ያልሆነ ነገርን ያደርጋል ነገር ግን ትክክለኛ ሰው ለመሆን ምጊዜም  ይጥራል

ብዙ ጊዜ ግን ከሰዎች ጋር በሚያደርገው ጸብ ምክንያት እልህኛ ስለሆነ እግዚአብሔርን ይበድላል ሰዎችንም ይበድላል  ...

እኔ ትግስትን ጥሩ እንደሆነ ባውቅም ሰዎች ግን ትግስቴን ካልተረዱት የነሱን ትክክለኝነት እና የኔን ደካማነት ነው የሚረዱት እሱን ደግሞ እኔ መታከስ አልችልም ያላል

እሱ እልህኛ እና ሀይለኛ ቢሆንም ሰው ላይ አይደርስም ከደረሱበት ግን በደልን የማይታገስ ሰው ነው ታግሳ ማለፍ ለሱ አይቻለውም ...

በዚህ ነገር ይጸጸታል ራሱን ለማስተካከል ይጥራል ይታገላል....ሰሞኑን ቤተክርስቲያን አብዝቶ ይሄዳል ጾሎት እና ስግደትንም ያበዛል ሰዎችም እንዳያዩበት ተደብቆ ነው የሚያደርገው ሰሞኑን ትግል ላይ ነው...

በጧት ደውሎ እንደዚህ አለኝ በቁጣ ድምጽ
ተመልከት  እኔ ሰሞኑን ራሴን ለማስተካከል እየሞከርኩ ነው

አንተም ታውቃለህ ደግሞም ጥሩ እየተሳክልኝ ነው ግን አሁንም የሄ ሰው ምንም ሊተወኝ አልቻለም እኔ እኮ ተውኩት ምንድነው አድርግ የሚለኝ..... ብሎ ተነጫነጭ ....

እኔም አይዛህ ታገስ በራስህ መንገድ ነገሮችን ለመፍታት አትሞክር እግዚአብሔር ይረዳሀል ጸልይበት...

አሁን የያዝከው መንገድ ጥሩ ነው ። ትኩረትህን እሱ ላይ አድርግ ።

ደግሞ አስተዋል ሰሞኑን ያለህ ነገር ጥሩ ስለሆነ እሱንም ለማደናቀፍ የሰይጣን ፈተና ይሆናል በተለመደው መልኩ አትመልስለት

በቃ ዝም በለው አልኩት እንዲረጋጋ እና ነገሮችን እንድያስተውል ተነጋግረን ስልኩን ዘጋነው....

ሰዎች ሆይ የቀረው ይቅር እንጅ እያወቅን የሰው ስህተት አንሁን ! ከተፈጠርንበት አላማ መሆን ከምንሻው ሰውነት አታስተጎጉሉን ! ሰው ከመሆን አታስረፍዱን !......

መኖር እኮ መሆን ነው በመሆን ውስጥ መሄድ ነው። በጉዞ ውቅት ደግሞ  መውደቅ፣ ይኖራል እንቅፋትና ጋሬጣ መታኝ ብሎ ማን ከመንገድ ይቀራል ?

መንገድ መዳረሻ አይደለም መጎዦ ነው።  በመጎጎዥ ውስጥ ደግሞ መኖር የለም ትሄድበታለህ እንጂ እትቆይበትም ። መኖርንም አትሻም

እኛ መኖራችን ፍጹም ሰውነት ነው ። ሰው እስከምንሆን ድረስ ብዙ ፈተናዎች ከእውነተኛው ማነታችን፣ ከእሥላሴ መልክነታችን የሚያሳንሱን እንስሳዊ ድርጊትን ልንፈጽም እና ራሳችንን ልናረክስ እንችላለን ።

ከሀዲነት ፣ጭካኛነት፣አስመሳይነት ፣ሌብነት፣ ክፋት፣ ዘማዊነት ፣ ገዳይነት ፣ሀሜት ወዘተ የመሳሰሉት ነገሮችን እየፈጸምን ራሳችንን ልናረክስ እና ከሰውነት ልዕልና ልንወድቅ እንችላለን ።

በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ግን ከውድቀታችን የሚያነሳን ፍጹም ንጹህ ሰው የመሆን ፍላጎታችን ነው እንጂ ቅድስናችን አይደለም ።

እግዚአብሔርን ሁልጊዜም ቢሆን ሰው አድርጎ እንዲሰራን መጠየቅ እና የእሱ ምርጥ እቃ እንዲያደርገን መለመን፣ አጥብቀን መፈለግ ክፉ የተባለ በደልን እንኳን እየሰራ በሀጥያት ቤት ሆነን ሀጥያት እያሳተን እየበደልንም ቢሆን

እግዚአብሔር ሆይ ከዚህ ነገር መቸ ነው የምታላቅቀን እያልን መለምን ይኖርብናል ።

ሀጥያትን በምንሰራበት ጊዜ ስህተታችንን በምክናዬት ልክ እድርገን ወይም ትክክል ነን ብለን ለራሳችንም ሆነ ለሰው ለማስረዳት መሞከር የለብንም

ይህን ካደርገን ቅጣትን እንጂ ከዛ ክፉ ስራችን መመለስ አንችልም ።

ክፉ ስራን ፈጽሞ ማቆ አንችልም እስከ መጨረሻው ፍጹም ሰው ለመሆን እና ከቅድስና ለመድረስ ንጽህናን መውደድ እና ሀጥያትን መጸየፍ አለብን በሀሳባችንም በቃላችንም በግብራችንም (በስራችንም ) ነጽህናን መውደድ ሀጥያትን አጥብቀን መጸየፍ አለብን ።

በዚህ ውስጥ ደግ መሆን የሚፈልጉ መንገዳችውን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ የሚፈልጉ ሰውች በዙሪያችን ይኖራሉ ።

እነሱ በእውነተኛው መንገድ ሲሄዱ እኛ የነሱ የመውደቂያ ወይም የመፈተኛ እቃ እንዳንሆን መጠንቀቅም መጸለይም አለብን

እንድ ሰውን አናደን እና አበሳጭተን ፣ገዳይ፣ ተሳዳቢ ፣በቀለኛ ፣ሌባ ወዘተ እንዳይሆን መትጋት አለብን፣ በእኛ ምክናያት ማንም ሰው እንዳይሰናከል መጠንቀቅ ይኖርብናል

ጽድቅን መስራት መልካም ነው ! ለሰው መስናክያም ሆነ እኛ እራሳችንም በሰው እንዳንሰናከል እንጠንቀቅ እግዚአብሔርም ይጠብቀን

ጽድቅን ስናደርጋት ለሰውም መሰናከያ እንዳንሆን እግዚአብሔር ይርዳን !

እግዚአብሔር ጥበብና ማስተዋልን ያድለን 🙏🙏🙏

አቤል መስፍን

ጥበብና ማስተዋል

14 Aug, 06:19


Live stream finished (1 minute)

ጥበብና ማስተዋል

14 Aug, 06:18


Live stream started

ጥበብና ማስተዋል

01 Jun, 11:55


https://youtu.be/deASUyWPXD8

ጥበብና ማስተዋል

18 Jan, 07:29


በአጭር ጊዜ ቪዲዮ ኤዲቲንግ በግል መማር የምትፈልጉ ሰወች ደዉሉ 0922591056

ጥበብና ማስተዋል

14 Dec, 11:03


https://rb.gy/lttkvs

ጥበብና ማስተዋል

12 Dec, 12:16


https://youtu.be/wEJSNCUCF7E

ጥበብና ማስተዋል

11 Dec, 06:47


https://youtu.be/wYCJujKZpUk

ጥበብና ማስተዋል

08 Dec, 19:07


https://youtu.be/WngH6-tbslI

ጥበብና ማስተዋል

08 Dec, 19:07


https://youtu.be/WngH6-tbsl

ጥበብና ማስተዋል

29 Nov, 19:19


https://youtu.be/S21CemZYJ94

ጥበብና ማስተዋል

26 Nov, 17:14


https://youtu.be/9GXVsS2bZQc