Zehabesha @zehabeshanews Channel on Telegram

Zehabesha

@zehabeshanews


Ethiopian News

Zehabesha (English)

Are you interested in staying updated with the latest news from Ethiopia? Look no further than Zehabesha - the go-to Telegram channel for Ethiopian News! With the username @zehabeshanews, this channel provides a wide range of news coverage, including politics, economy, culture, and more. Whether you are a resident of Ethiopia, have ties to the country, or simply have an interest in the region, Zehabesha is the perfect channel to stay informed. With timely updates and reliable sources, you can trust that you are getting accurate and up-to-date information. Join the community of like-minded individuals who share a passion for Ethiopian news and be part of the conversation. Don't miss out on important developments and events - subscribe to Zehabesha today and never be out of the loop again!

Zehabesha

24 Jan, 22:06


https://youtu.be/UjhpWaz1B2k?si=Ia2kXnNNvp7TlcJa

Zehabesha

24 Jan, 20:17


https://youtu.be/tbbzjFbevkA

Zehabesha

24 Jan, 18:57


https://youtu.be/UjhpWaz1B2k

Zehabesha

24 Jan, 18:53


“ከብዙ ዓመታት በኋላ ጅብ አገኘሁ” ግብጽ - ዝርዝሩን ከእለቱ ዜና ላይ ይመልከቱ

Zehabesha

24 Jan, 15:09


https://youtu.be/vBn7QPuFb8E

Zehabesha

24 Jan, 13:34


https://youtu.be/E_HlTNrDo94?si=x4zzJc1JQFKmaWNw

Zehabesha

23 Jan, 23:58


https://youtu.be/W7CPqoNhlzY

Zehabesha

23 Jan, 19:08


https://youtu.be/W7CPqoNhlzY

Zehabesha

23 Jan, 19:08


የዕለቱ ዜናችን እንዳያመልጣችሁ - ትኩስ መረጃ ይዘናል

Zehabesha

23 Jan, 16:12


(ዘ-ሐበሻ ታሪክ) "በባሕርዳር የታንኳ ቀዘፋ ውድድሩ ከለውጡ በኋላ የመጣ ሳይሆን የህዝቡ ነባር ባህል ነው!!" ተባለ።
የባሕርዳር ነዋሪዎች የታንኳ ቀዘፋው "ስምንት ዓመት ሞላው ተብሎ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) መዘገቡና በቱሪዝም ባለስልጣናትም መነገሩ አስከፍቶናል፣ የህዝብ የነበረ ባህላችን እንጂ በለውጡ የመጣ አይደለም" ብለዋል።
ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ የታንኳ ቀዘፋ ውድድር ይካሄድ ነበር። በየጊዜው፣ በየዘመኑ የሀይማኖት አባቶች እና እናቶች ወጣቶች ልጃ ገረዶች የሚያደርጉት ውድድር እንደሆነ ይታወቃል።
"አሁን ላይ 'አመራር ተብለው የተቀመጡ' አካላት የአካባቢውን ባህልና ታሪክ የሚኖሩበትን እንኳን የማያውቁ ሆነው ታይተዋል" በሚል ወቀሳ የሚያቀርቡ የቅርብ ምንጮች፣ የክልሉ መንግስት የሚያስተዳድራቸው ሚዲያዎች "ይህን የባህርዳር የታንኳ ቀዘፋ ውድድር ለ8ተኛ ጊዜ ከለውጡ በኋላ የሚደረግ አስመስለው ማቅረባቸው አሳፋሪ ነው" ብለዋል ቅሬታቸው ሲያቀርቡ።
"በታሪክ ማስረጃነት የሚቀርቡ በርካታ ፎቶዎች፣ ሰነዶችና ማስረጃዎች ጭምር ያለበትን የህዝቡን የባህል አካል፣ አሁን ላይ አዲስ ነው ብሎ ማቅረብ አስፀያፊ በመሆኑ ሊታረም ይገባል" ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ለአብነት ይህ ከታች ያለው ፎቶ በ1958 ዓ.ም ውድድር ሲካሄድ የተነሳ ነው።

Zehabesha

23 Jan, 15:15


https://youtu.be/QUrhKUJdVKE

Zehabesha

23 Jan, 14:44


አሁን የተለቀቀውን መረጃ ይመልከቱ

Zehabesha

23 Jan, 14:11


በሰሜን ወሎ ዞን በዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ መነሻውን ያደረገ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ25 ስዎች ህይወት ማለፋን ተገለፀ።

ጥር 15/2017 ዓ.ም (በሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) በዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ መነሻውን ያደረገ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ25 ስዎች ህይወት ማለፋን ከአከባቢው ፖሊስ ያገኘው መረጃ አመላክተዋል።

ዞሬ ከጥዋቱ 12 ስዓት ከኩርባ ከተማ ተነስቶ ወደ ደሴ ከተማ ሲጓዝ የነበረው የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-32917 የሆነ በመጓዝ ላይ እያለ በግምት ከኩርባ ከተማ 9 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ልዩ ቦታው 04 ቀበሌ ሰጎራ ከተባለ አካባቢ የመገልበጥ አደጋ መድረሱን የዳውንት ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ጌታቸው አራጌ ከቦታው ባገኙት መረጃ አጋግጠዋል።

በአደጋውም የ25 ሰዎች ሞት፣14 ሰዎች ከባድ ጉዳት አንዲሁም 15 ሰዎች ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎችም በአቅራቢያው ከሚገኙ የደላንታና ደሴ ሆስፒታሎች መወሰዳቸው መረጃው ያመላክታል።

@የሰሜን ወሎ ኮምንኬሽን

Zehabesha

23 Jan, 13:18


https://www.youtube.com/watch?v=E_HlTNrDo94

Zehabesha

23 Jan, 03:06


https://youtu.be/E_HlTNrDo94?si=FS3SuMtCkc4UtuSs

Zehabesha

23 Jan, 02:57


https://youtu.be/5ZK4QG9g4uY?si=vY5fIZ6v5o9Hzjf2

Zehabesha

22 Jan, 19:13


https://youtu.be/5ZK4QG9g4uY

Zehabesha

11 Jan, 18:54


https://youtu.be/82q4FQc00Fg

Zehabesha

11 Jan, 16:10


https://youtu.be/zAdtw-g2_TM

Zehabesha

11 Jan, 16:05


ማምሻውን 12 ስአት ከ19 ደቂቃ ላይ በአዋሽ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.0 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ::

Zehabesha

11 Jan, 14:54


አትሌት ለሜቻ ግርማ ከወይዘሪት ሰላም በላቸው ጋር ጥር 18 ይሞሸራል::

Zehabesha

11 Jan, 14:45


የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ::

Zehabesha

11 Jan, 05:52


https://youtu.be/UIked3BYpVc?si=vMys1HSCCIdRXMTf

Zehabesha

11 Jan, 04:42


እንደምን አደራችሁ??

ደብረ ማርቆስ ጉዞ ወደ ገበያ

Zehabesha

11 Jan, 01:14


Zehabesha pinned «በ1 ሰዓት ውስጥ 3 የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ https://www.facebook.com/photo/?fbid=1037517681749815&set=a.604085898426331»

Zehabesha

11 Jan, 01:12


በ1 ሰዓት ውስጥ 3 የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ https://www.facebook.com/photo/?fbid=1037517681749815&set=a.604085898426331

Zehabesha

10 Jan, 19:19


https://youtu.be/UIked3BYpVc

Zehabesha

10 Jan, 19:19


የዕለቱ ዜናችንን በትኩሱ ይመልከቱት።

Zehabesha

10 Jan, 15:56


https://youtu.be/Sq_3bIzGZ2Y

Zehabesha

10 Jan, 04:58


(ዘ-ሐበሻ ዜና) ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን ያለውን ጦርነት በተመለከተ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር የውይይት መድረክ እያዘጋጁ መሆኑን አስታወቁ።

ትራምፕ በፓልም ቢች ፍሎሪዳ በሚገኘው የማር-አ-ላጎ ሪዞርት ውስጥ ማምሻውን ከሪፐብሊካን ገዥዎች ጋር ባደረጉት ውይይት “ፑቲን መገናኘት ይፈልጋል፣ እናም ያንን መድረክ ለማዘጋጀት በሂደት ላይ ነን” ማለታቸውን ኤፍፒ ዘግቧል።

Zehabesha

10 Jan, 04:45


እንደምን አደራችሁ??
✈️ የባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ በ1978 ዓ.ም.

Zehabesha

10 Jan, 04:24


💰 (ዘ-ሐበሻ ዜና) በ2025 የአለም ኢኮኖሚ እድገት በ2.8 በመቶ እንደሚቆይ ተገለፀ:: በዚህም የተነሳ በ2025 አመት እድገቱ ከ2024 አመት ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ይቆያል ማለት ነው:: ኢኮኖሚውም በሁለቱ ከፍተኛ ባለ ኢኮኖሚዎች፣ በአሜሪካ እና በቻይና እንደተያዘ እንደሚቀጥል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።

Zehabesha

09 Jan, 23:15


https://youtu.be/_mGFq93_5NM?si=59PmBmY7QFaH0z2q

Zehabesha

09 Jan, 21:03


https://youtu.be/73aHqGfKFYo

Zehabesha

09 Jan, 19:30


https://youtu.be/_mGFq93_5NM

Zehabesha

09 Jan, 19:19


የዕለቱ ዜናችን እንዳያመልታችሁ፣ በትኩሱ ተመልከቱት።

Zehabesha

09 Jan, 15:45


https://youtu.be/dvCCKS3EI08

Zehabesha

09 Jan, 05:02


https://youtu.be/cRlVChIBK3o?si=H2DjZ-ILPlaAfeIw

Zehabesha

08 Jan, 19:33


https://youtu.be/cRlVChIBK3o

Zehabesha

08 Jan, 16:03


አሁን የደረሱን 3 መረጃዎች https://youtu.be/qWhfhulBO_M

Zehabesha

08 Jan, 14:21


አማዞን እስከ 70% ቅናሽ ያደረገባቸውን ታላቁን የዊንተር ሴል ይመልከቱ። https://amzn.to/4a6YfJW

Zehabesha

08 Jan, 12:43


ለትውስታ

Zehabesha

08 Jan, 12:22


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በከሬዳ እና ጀሎ ቀበሌ፤ “ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ተሻግረው የመጡ ታጣቂዎች” ትናንት ታህሳስ 29/ 2017 ዓ/ም እና ከትላንት በስቲያ በፈጸሙት ጥቃት ሀሉት አርሶ አደሮች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
“ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ” ተሻግረው በመጡ ታጣቂዎቹ በተፈጸመ ጥቃት አንታዮ ዞላና እና አድማሱ አሰፋ የተባሉ እርሶ አደሮች ተገድለዋል ሲሉ የሟች ቤተሰብ መሆኑን የገለጹ ምንጭ ገልጸዋል።

@አዲስ ስታንዳርድ

Zehabesha

08 Jan, 11:56


"መኪና ገዘቶ ስለ ነዳጁ መወደድ የሚጨነቅ ሰዉ ይኖራል ብዬ አላስብም: ካለም መኪናዉን ሽጦ ፈረስ ገዝቶ አቢቹ በሰራለት የኮሪደር ልማት ላይ መጋለብ ይችላል::"


የቀድሞ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ

ተከታታዮቻችን እስኪ ሀሳባችውን በጨዋነት ግለፁ::

Zehabesha

07 Jan, 19:57


https://youtu.be/v6XR9VEmrcY

Zehabesha

07 Jan, 19:26


ከአቅም በላይ በሆነ ችግር የተነሳ የዕለቱ ዜናችን በመዘግየቱ ይቅርታ እየጠየቅን፣ ትኩስ ዜናችን ከደቂቃዎች በኋላ እንደሚለቀቅ እንገልጻለን።

Zehabesha

07 Jan, 16:31


https://youtu.be/lejgLsSBAbE\

Zehabesha

07 Jan, 16:00


ፋና የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ማህበር በባህር ዳር ለ149 የክርስትና እምነትተከታዮች ጧሪና ደጋፊ ላጡ አረጋዊያን የምሳ ግብዣና የቅርጫ ስጋ እደላ ድጋፍ አደረገ::

በትላንትናው እለት ለ12 የእስልምና እምነት ተከታዮች ደሮ እና ለዘይት መግዣ የ1,000 ብር ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል።

ለዚሁ ፕሮግራም መሳካት በአይነትና በገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ።

1. ቢአይካ ካንፖኒ 1 በሬ
2. የአቢሲኒያ ባንክ ሰራተኞች የባህር ዳር ቅርጫፍ 1 በሬ
3. ኒውሆኘ 1 በሬ
4. ማህበረ ግሸን 1 በሬ
5. ዳሸን ባንክ 50000
6. የባ/ህዳር ልጆች አረጋዊያን ማህበር 38,000
7. ባምባ ኮሌጅ 10000
8. ሀያት ጋሹ 12 ዶሮ
9 Ad Rt 3.000
10, ዶ/ር ግርማ ቅባቱ 1,000
11, አርክቴክት ገናነው14,000
12 ተካልኝ ተፈራ እንጀራ።።።። እናመሠግናለን።።።

ፋና የህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ማህበር ባህር ዳር

Zehabesha

04 Jan, 02:28


https://youtu.be/wgN-Me-mzfc?si=b0VQBEkQ1QOTM-UO

Zehabesha

03 Jan, 19:32


https://www.youtube.com/watch?v=wgN-Me-mzfc

Zehabesha

03 Jan, 16:06


https://youtu.be/-L1Qv2l0tbM

Zehabesha

03 Jan, 14:44


የአዶናዊት ይሄይስ ገዳይ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት
***
ሚካኤል ሽመልስ ጌታሁን የተባለ ተከሳሽ የእንጀራ ልጁ ሆነችውን ሟች አዶናዊት ይሄይስ በበአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው 15 ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከ10 ዓመቷ ጀምሮ ለማንም እንዳትናገሪ ከተናገርሽ እናትሽና አባትሽን እገላለሁ እንዲሁም የግብረ ስጋ ግኑኝነት ስንፈፅም በሞባይል ቪድዮ ቀርጨዋለሁ በሚድያና በቴሌግራም እለቀዋለሁ በማለት ድርጊቱን እንዳትቃወም የስነ-ልቦና ጫና በማሳደር ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ሕይወትዋ እስካለፈበት የግብረ ስጋ ድፍረት በደል እየደጋጋመ ፈፅሟል።

ሟች አዶናዊት ይሄይስ ከተከሳሽ ሁለት ጊዜ ስታረግዝም መጀመሪያ የነበረው እርግዝና ቤተሰብ እንዳያውቅበት የሟች ስም ኤፍራታ አለማየሁ በሚልና የሟች ዕድሜም 19 ዓመት እንደሆነ በማስመሰል ሐሰተኛ ስም እና ዕድሜ በማስመዝገብ ያረገዘችውን ፅንስ እንድታስወርድ በማስገደድ እርግዝናውን እንድታስወርድ አስደርጓል። እንዲሁም መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም ተከሳሽ በሟች ላይ በፈፀመው የግብረስጋ በደል ወንጀል ምክንያት ፖሊሶች ሊይዙት ወደ ቤቱ መምጣታቸውን ሲያይ በመስኮት ወጥቶ ከፖሊስ እጅ አምልጦ ከሄደ በኃላ ሊይዙት የመጡትን ፖሊሶች መሄዳቸውን ሲያረጋግጥ ተመልሶ ወደ ሟች ቤት በመምጣት ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ወላጅ እናትዋ ፊት በቢላ ጨቅጭቆ ሟች ሕይወትዋ እንዲያልፍ በማድረጉ እና ሟች ሕይወትዋ ሲያልፍም ለሁለተኛ ጊዜ ከተከሳሽ እርጉዝ የነበረች በመሆኑ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ከተጣራበት በኃላ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ዓ/ሕግ ዳይሬክቶሬት 1ኛ/ ክስ ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ህግ አንቀጽ 539(1)(ሀ) እንዲሁም 2ኛ/ በወንጀል ሕግ አንቀፅ 627/1/እና 628/ሀ/ መሰረት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ውንብድና ችሎት ክስ ቀርቦበታል። ጉዳዩን የያዘው ችሎትም የዓ/ሕግ ማስረጃ ከሰማ በኃላ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ማስረጃውን አቅርቦ ካሰማ በኃላ ተከሳሽ ዓ/ሕግ ያቀረበበትን ማስረጃ ሊከላከል ባለመቻሉ የጥፋተኛነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።

ተከሳሹ ለቅጣት ማቅለያ ያቀረባቸው የፅሑፍ ማስረጃዎች ሲጣሩ ሐሰተኛ መሆናቸው በመረጋገጥ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ በ25/4/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
(ፍትህ ሚኒስቴር)

Zehabesha

03 Jan, 06:47


https://youtu.be/I4Eh5QAG5so?si=MshSgd9pYRGDcBba

Zehabesha

03 Jan, 05:57


የብልፅግና የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች የፓርቲ ግምገማ ከትግራይ ውጭ በሁሉም የሀገሪቱ ዋና ዋና ርዕሰ ከተማዎች ዛሬ ይጀመራል:: ግምገማው ለ4 ቀናት የሚቆይ ነው::
የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔም በመጭው ጥር መጨረሻ ላይ ይጀመራል::
ይህ ግምገማ ሲጠናቀቅ ሀዲዱ ማንን አራግፎ ማንን ያነሳ ይሆን???
ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን በዜና እወጃችን እናቀርባለን::

Zehabesha

03 Jan, 00:11


https://youtu.be/I4Eh5QAG5so

Zehabesha

02 Jan, 19:18


https://youtu.be/I4Eh5QAG5so

Zehabesha

02 Jan, 15:18


https://youtu.be/w6F1xb-1SPI

Zehabesha

02 Jan, 05:24


https://youtu.be/49dwG8ZEJ1U

Zehabesha

02 Jan, 00:08


https://youtu.be/49dwG8ZEJ1U?si=Y7mCCo6k97jiS60a

Zehabesha

01 Jan, 19:51


https://youtu.be/49dwG8ZEJ1U

Zehabesha

01 Jan, 16:18


https://youtu.be/ojqVrmssdvo

Zehabesha

01 Jan, 14:56


አማዞን የክረምት ታላቅ ቅናሽ በብዙ ምርቶች ላይ ቀርቧል። 40% ቅናሽ ለፕሮሞሽን የተደረገባቸውን ምርቶች ምናልባት ሊፈልጓቸው ከቻሉ ይመልከቱ።
https://amzn.to/3W1al1I

Zehabesha

01 Jan, 10:12


በመቐለ ከተማ ሰላሚዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።


ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አከባቢዋ የተወጣጡ ወጣቶች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ ከንቲባ ስራ እንዲጀምሩ ያለመ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ወጣት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ህጋዊው ከንቲባ ወደ ፅህፈት ቤታቸው ሳይገቡ ከቦታው ንቅንቅ እንደማይሉ ፤ ከተማዋ የግርግር እና ረብሻ ምንጭ እንድትሆን እንደማይፈቅዱ ድምፃቸው በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

መቐለ ከተማ በጊዜያዊ አስተዳደሩና በነ ደብረፅዮን ቡዱን የተሾሙ ሁለት ከንቲባዎች እንዳሏት ይታወቃል።

በሰልፉ ላይ ከተማችን ለወራት ያለ ከንቲባ መቆየቷ አግባብነት የለውም፣ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ውሳኔዎች ይከበሩ፣ የህዝባችንን አንድነት ለመሸርሸር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አጥብቀን እንቃወማለን፣ መንግስትን ለመገልበጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ይቁሙ፣የሚሉ ድምፆች ተስተጋብተዋል።

@ባላገሩቲቪ

Zehabesha

01 Jan, 03:49


https://youtu.be/ZiPxq09B0oA?si=eIgOXyGu2YVoe9nH

Zehabesha

31 Dec, 19:03


https://youtu.be/ZiPxq09B0oA

Zehabesha

31 Dec, 16:18


https://youtu.be/hZw28VgqJ_s

Zehabesha

31 Dec, 14:17


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በጎርጎሮሳውያን የዘመን አቆጣጠር የ2025 አዲስ ዓመትን በማስመለክት ለመላው የዓለም ሕዝብ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !
‹‹ወሰላም በምድር ለዕጓለ እመሕያው ሥምረቱ፤
ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ ።” ሉቃ. 2፡14

ከሁሉ በማስቀደም በመላው ዓለም ለምትገኙ፤ የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ላከበራችሁና አዲሱን ዓመት 2025 ዓ.ም. ለምትቀበሉ ልጆቻችን የመልካም ምኞታችንን ለመግለጽ እንወዳለን ።

ዘመን ከቊጥር ያለፈ ትርጉም ያለው የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ በዘመን ውስጥ ያጣነውን እናገኛለን ፣ ያገኘነውን እንመልሳለን ። በዘመን ውስጥ ሕፃናት ሲጠነክሩ ፣ ሽማግሌዎች ይደክማሉ ። አንዱ ዘመን ላንዱ ልደት ለሌላው ሞት ሆኖ ይውላል ። እግዚአብሔር አምላካችን ከጊዜ ውጭ ቢሆንም እኛን በጊዜ ሰሌዳ ውስጥ አስቀምጦናል ። ዘመን ሳያደክመው በዘመን ውስጥ በሚለዋወጥ ማንነት እንድናልፍ ተሠርተናል ። ከጠዋት እስከ ማታ ያለው ሂደት ከልደት እስከ ሞት ያለውን ረጅም ጉዞ የሚገልጥ ነው ። በየቀኑ ዕለቱን ብቻ ሳይሆን መላው ዘመናችንን እንኖራለን ። የሰው ልጅ በዚህ ዓለም በጊዜ የተለካ በሚመጣው ዓለም ከጊዜ ውጭ የሚኖር ፍጡር ነው ። በሚሞት ሥጋ የማይሞት ነፍስን ተሸክሟል፣ በሚያልፍ ጊዜም የማያልፍ ዘለዓለማዊነትን ይጠባበቃል ። በታሪክ ውስጥ ከፍታና ዝቅታ ቢፈራረቁም ፣ ሥልጣኔዎች መጥተው ቢሄዱም ፣ አንዱ ፍልስፍና ሌላውን ቢሽረውም የዘመናት መፈራረቅ ግን ቋሚ ሕግ ሁኖ ይኖራል ። የሰው ልጆች ከመከራ ቀናት የተነሣ መኖራቸውን የሚጠሉበት ጊዜ ቢገጥምም አዲስ ዓመትን መናፈቃቸው መኖርን እንደሚፈልጉ ማሳያ ነው ። ትልቅ የምስጋና ርእስ ቢኖር እርሱም አዲስ ዘመንን ማየት ነው ። አሮጌነትን እየተውን አዲስን ዓመት የምንቀበለው ፣ ያለፈውን አሮጌ ብለን ይህን አዲስ የምንለው በማያቋርጥ ለውጥ ውስጥ መሆንን ስለምንፈልግ ነው ።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመወለዱ የዓለምን ታሪክ ለሁለት ከፍሎታል ። ከክርስቶስ ልደት በፊትና ከክርስቶስ ልደት በኋላ እየተባለም ይጠራል ። በሃይማኖታችንም ዓመተ ፍዳና ዓመተ ምሕረት ተብሎ ለሁለት ይከፈላል ። ዓለምን ለመለወጥ ብዙዎች ወደ ዓለም መጥተዋል ። ጌታችን ግን የሰውን ሕይወት ለመለወጥ ወደ ዓለም መጥቷል ። አሁን ያለነው በጌታ ዓመት ፣ በምሕረት ዘመን ነው ። ፍርድ በሙሉነት መፈጸሙ ለዓለም ሰላም ወሳኝ ቢሆንም ምሕረት ግን እውነተኛውን የልብ ሰላም ታመጣለች ። ከእኛ ወደሚያንሱት የምናደርገው ጉዞ ፣ ራስ ወዳድነትን አሸንፈን ሌሎችን ለመርዳት የምንከፍለው መሥዋዕትነት ዓለምን የሚለውጥ ነው። ከተሞቻችን በማያቋርጥ ዕድገት ውስጥ ላያልፉ ይችላሉ ። ዕድገትም የሚቆምበት ጊዜ አለ። የሰው ልጅ የሞራል ከፍታ ግን መቆሚያ የለውምና አዲሱ ዘመን ክፉ ተግባር የሚወገድበት፤ መልካም ተግባራት የሚከናወኑበት ሊሆን ይገባዋል ።

የተወደዳችሁ የዓለም ሕዝቦች!
ያለፈው ዓመት 2024 ዓ.ም. እንደ ዓለም ብዙ ነገሮችን ብናተርፍም የከሰርንበትም ጭምር ነው ። ከተፈጥሮ አደጋዎች ይልቅ ሰው ሠራሽ በሆኑ ችግሮች ዓለምን እስር ቤት ውስጥ ቆልፈንባት ይታያል ። ሲጀመር በቀናት ውስጥ የሚያበቃ ይመስል የነበረው የራሽያና የዩክሬን ጦርነት ዓመታትን እያስቆጠረ ነው ። በመላው ዓለምም ለኑሮ ውድነትና ጫና ምክንያት ሆኗል ። ከሁሉ በላይ ሁለቱ ኦርቶዶክሳውያን ሕዝቦች የሰላም ረሀብተኛ ሆነዋል ። መካከለኛው ምሥራቅም በየዕለቱ በሚሰፋ ጦርነት ተውጦ ይታያል ። የዓለም የስበት ማዕከል በመሆኑም ብዙ ጫናዎችን እያሳደረ ይገኛል ። ስልጣኔው ይዞት የመጣው የግለኝነት ኑሮ ለብዙ የሰው ልጆች በጭንቀት ውስጥ ማለፍ ምክንያት እየሆነ ይገኛል ። መፍትሔን ከመፈለግ፣ እሳትን ከማጥፋት ይልቅ ችግሮችን የሚያባብሱ ነገሮች የዓለማችን መገለጫ ሆነዋል። ለይስሙላ የሚደረጉ የሰላም ስብሰባዎችም ተናግረን ነበር ለማለት ካልሆነ በቀር ቁርጥ ውሳኔ ያላቸው አይደሉም ።
ምድራችን ሰላምን በጣም ተርባለች ። እንስሳትና አራዊት ያለምርጫቸው በመከራ ውስጥ እያለፉ ነው ። የዓለማችን ብርቅዬ እንግዶች የሆኑት ሕፃናት እየታወኩ ነው ። ራሳቸውን መከላከል ያልቻሉ ሴቶች ልጆቻችን በፍርሃት ውስጥ አሁንም አሉ ። ይህች ዓለም አስተማሪ ቅጣት እንደሚያድናት ስታምን ብትኖርም አሁን ግን አስተማሪ ምሕረት እንደሚያስፈልጋት ግልጽ እየሆነ ይመስላል። ስለዚህ በዚህ የልደተ ክርስቶስ መታሰቢያና የ2025 ዓ.ም. መቀበያ ላይ ቆመን ይቅር መባባል፣ ለጋራ ቤታችን መሥራትና በሰዎች አለመግባባት የታወከችውን ዓለም በሰዎች ቁርጥ ውሳኔ እንድትረጋጋ የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይገባናል ።

በመጨረሻም አዲሱን ዓመት እየተቀበላችሁ ያላችሁ፤ አዲሱን ዓመት ከክርስቶስ ልደት ጋር አብራችሁ የምታከብሩ ወገኖቻችን ልደተ ክርስቶስ ትሕትና የተገለጠበት ነውና በትሑት ሰብእና ቆማችሁ የነደደውን እሳት እንድታጠፉ፤ ጦርነትን በሰላም ለመለወጥ የራሳችሁን ድርሻ እንድትወጡ ስንል አባታዊ የተማኅጽኖ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ መላውን ዓለም በሰላም ይጠብቅልን፤
ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥር 1 ቀን 2025 G.C.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Zehabesha

31 Dec, 13:23


#በወላይታ_ሁምቦ_እና_አበላ_አባያ ወረዳዎች ከሰሞኑ የተፈጠሩ ኹለት ክስተቶች ትኩረት ይሻሉ!

ፓርቲያችን ከቦታው በደረሰው መረጃ በወላይታ ዞን፣ አበላ አባያ ወረዳ፣ አባያ ክላስተር በሚባል የእርሻ ልማት ከሲዳማ ክልል መጡ በተባሉ የልዩ ኃይል አባላት እንደተከፈተ በተገለጸ ተኩስ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ በርካቶችም ቆስለው ሆስፒታል ይገኛሉ። እስከ አኹንም በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት እንደነገሰ መሆኑን መረዳት ችለናል። "ችግሩ ትኩረት ሰጥቶ የሚፈታው አጥቶ እንጂ የሰነበተ ነው" የሚሉት ነዋሪዎች "የአኹኑ ግን ኃይል የቀላቀለና ለአገር ብዙ ውለታ የዋሉ የቀበሌው አስተዳደር ጭምር በተኩስ የተገደሉብት ጭምር ነው" በሚል የችግሩን ሥር ሰደድነት ያስረዳሉ። ፓርቲያችን ለሟች ቤተሰቦች ሐዘኑን ይገልጻል፤ መጽናናትንም ይመኛል።

እንዲኹ በዚያው በወላይታ ዞን፣ ሁምቦ ወረዳ፣ ጠበላ ከተማ አስተዳደር ሥር ከጥምቀተ ባህር ይዞታ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ፓርቲያችን መረዳት ችሏል። ከዚኽ ቀደም ከጥንት ጀምሮ የጥምቀተ ባህር የነበረ ይዞታ በቀበሌው አስተዳደር ድፍረት በተሞላበት አኳኋን ጠረጴዛ ልማት ማኅበር ለሚባል የተወሰነ ቆርሶ የሰጠና ልማት ማኅበሩም ቀጥሎ ሙሉ በሙሉ በማጠሩ በተፈጠረ ችግር ተበደልን ባሉ ካህናትና ምዕመናን ላይ ፖሊስ እሥርና ከፍተኛ እንግልት እያደረሰ እንደሚገኝ ከአካባቢው ኗሪዎች መረዳት ችለናል። መለየት በሚያስቸግር አኳኋን ተዋልዶና ተፋቅሮ በሚኖር ማኅበረሰብ መሐል ኹኔታውንም ሃይማኖታዊ ለማስመሰል የቀበሌው አስተዳደርና የፀጥታ ኃይሉ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል።

በተጠቀሱ በኹለቱም አካባቢዎች በማኅበረሰቡ ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት በአካባቢውም ከአካባቢውም ውጭ ሕዝቡን እረፍት መንሳት ሲሆን በተጠና መልኩ ለአሥርት ዓመታት እየተተገበረ ያለውና ሕገ መንግሥታዊ ማዕቀፍ ያለው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ውጤት እንደሆነ እናት ፓርቲ በጽኑ ያምናል።

ፓርቲያችን የተፈጠረውን ችግር የክልሎቹ መንግሥታት እንዳላዩ ከማለፍ በአፋጣኝ ገለልተኛ፣ ሚዛናዊና ሕጋዊ መፍትሔ እንዲሰጡ፤ ማኅበረሰቡም በክልሉም ከክልሉም ውጭ እረፍት የሚያገኝበትን ኹኔታ እንዲመቻች በአጽንዖት ያሳስባል።

እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ታኅሣስ ፳፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Zehabesha

31 Dec, 03:46


https://youtu.be/kFVt8rv2TvU?si=8NzxSxS74yh00ARA

Zehabesha

30 Dec, 19:05


https://youtu.be/kFVt8rv2TvU

Zehabesha

30 Dec, 16:15


https://youtu.be/mDtr1FxtyIw

Zehabesha

30 Dec, 04:40


https://youtu.be/zoMPtPsE_FA

Zehabesha

29 Dec, 23:48


https://youtu.be/zoMPtPsE_FA?si=jzpxGfxQNWp1BdXj

Zehabesha

29 Dec, 23:19


በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር 01:20 (ከለሊቱ 7:20) በሬክተር ስኬል 5.1 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። ይህም በዛሬው ዕለት ብቻ በሃገሪቱ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ 8 አድርሶታል።
በአዲስ አበባና በሌሎችም ከተሞች ንዝረቱን እንደሰሙ የተለያዩ ጥቆማዎች ደርሰውናል።

Zehabesha

29 Dec, 19:09


https://youtu.be/zoMPtPsE_FA

Zehabesha

29 Dec, 17:56


በአዋሽ አካባቢ ዛሬ ምሽት በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
🔴በዛሬው ዕለት ብቻ ሰባት የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል

በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ከሰሞኑ ከደረሱት የመሬት መንቀጠጥ ክሰተቶች በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ርዕደ መሬት ዛሬ እሁድ ምሽት መከሰቱን የጀርመን የጂኦሳይንስ የምርምር ማዕከል አስታወቀ።

በአካባቢው ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 ላይ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ እንደሆነ የማዕከሉ መረጃ አመልክቷል።

በሬክተር ስኬል የመለኪያ መሳሪያ ከ2.5 እስከ 5.4 መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦች አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደሆኑ በዘርፉ ምርምር የሚያደርጉ ተቋማት ይገልጻሉ።

በዚህ መጠን የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ንዝረታቸው በበርካታ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባሉ ከተሞች ጭምር የሚሰማ እንደሆነም የተቋማቱ መረጃ ያሳያል። የምሽቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ጭምር ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየ ንዝረት አስከትሏል።

ከአዋሽ ከተማ 14 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ ስፍራ የተከሰተው የምሽቱ ርዕደ መሬት፤ በዛሬው ዕለት ብቻ በአካባቢው የተመዘገቡ መሬት መንቀጥቀጦችን ቁጥር ሰባት አድርሶታል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Zehabesha

29 Dec, 16:01


https://youtu.be/t1heOrsCZaE

Zehabesha

07 Dec, 04:32


https://youtu.be/VLxdM4UkDiI?si=8QNbk6Nl0dBOIRB8

Zehabesha

07 Dec, 00:27


https://youtu.be/VLxdM4UkDiI?si=3-zCXAVidCyMkNON

Zehabesha

06 Dec, 21:18


https://www.tiktok.com/t/ZTYPyhPu5/

Zehabesha

06 Dec, 18:59


የዕለቱ ዜና https://youtu.be/VLxdM4UkDiI

Zehabesha

06 Dec, 15:54


በመንግሥትና በኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራር መካከል የተደረገው ድርድር የስምምነት ነጥቦች ይፋ ሊደረጉ እንደሚገባ ፓርቲዎች ገለጹ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው መገለጹ ይታወቃል።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን መፈረማቸው የተጠቆመው።

"ስምምነት መደረጉ ለረጅም ጊዜ የሰላም ጥያቄውን ሲያቀርብ ለኖረ ማህበረሰብ እፎይታን የሚሰጥ እና የሚበረታታ ነው" ያሉት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኢፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ናቸው።

ነገር ግን የዚህ ቡድን አመራር አስቀድሞ ወደ ጫካ የገባው 'ያልተመለሱ ጥያቄዎች ስላሉኝ ነው' ማለቱን አስታውሰው፤ "አሁን ምላሽ አግኝቶ ነው" ወይ ሲሉ ይጠይቃሉ።

አክለውም፤ "የተደረገው ስምምነት በምን በምን ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ተደርሶ መሆኑን፣ ከዚህ በኋላ መተዳደሪያ የሚሆኑ ነገሮች ተመቻችተዋል፣ ታጥቀው የነበሩ አካላትስ በምን ሁኔታ ነው የሚታዩት የሚለውን ግልጽ መድረግ ነበረበት" ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል።

"ስምምነቱን የፈረመው አመራር ቡድን አስቀድሞ እጁን ሰጥቶ የነበረ ነው" ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ፤ ከዚህ ቀደም እጃቸውን የሰጡ አመራሮችም እንዲሁም ተዋጊዎች እንደነበሩ አንስተዋል።

በመንግሥትና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራር መካከል የተደረገውን ድርድር "የሰላም መጥፎ የጦርነት ጥሩ የለውም" በማለት የቀደመውን ሃሳብ የሚጋሩት የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ አደረጃጀት እና አመራር ዘርፍ ኃላፊው ሙባረክ ረሺድ በበኩላቸው፤ "ድርድሩ መደረጉ በጎ ነው" ብለዋ።

ይኼው ስምምነት በመርህ እና በተግባር ውጤት የሚታይበት ሊሆን እንደሚገባም ገልጸዋል።

"በመንግሥት በሽብረትኝነት የተፈረጀው የአሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከስምምነቱ ይፋ መደረግ በኃላ ባወጣው መግለጫ 'ከቡድኑ የተሰናበተና እኛን የማይወክል ነው' ማለቱ የራሱን ጥላ አጥልቷል" ያሉም ሲሆን፤ መንግሥት ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚችልበትን መንገድ መከተል እንዳለበት አሳስበዋል።

እንዲሁም "ኅብረተሰቡ ከስምምነቱ የሚጠብቃቸው በርካታ ነገሮች አሉ" በማለት፤ "ስምምነቱ ምን ምን ነገሮችን ይዟል ከምን ምን ይጠበቃል የሚለው ይፋ መደረግ አለበት" ሲሉ ገልጸዋል።

"ኅብረተሰቡም በተለያዩ ክልሎች ሰላም በማጣት ሰርቶ በመብላት ችግር ውስጥ ነው" ያሉት ፖለቲከኞቹ፤ መንግሥት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያስችሉ ስምምነቶችን በተገቢው መንገድ መከተል አለበት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እና በጃል ሰኚ ነጋሳ መካከል የተፈረመውን ስምምነት አስመልክቶ፤ የስምምነት ሰነዱ ምን ይዟል፣ ምን ምን ጉዳዮች ላይ መግባባት ተደርሷል እንዲሁም የሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት እስከምን ድረስ ነው የሚለው ጉዳይ በይፋ አለመገለጹ በብዙዎች ዘንድ ጥያቄ እየፈጠረ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል፡፡

ስምምነቱን ተከትሎም የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ይህ የሰላም ስምምነት ለዜጎች እረፍትን የሚሰጥ ሰላም የሚያሰርጽ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ "ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ" ብለዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፤ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉት የሕዝብና የመንግሥትን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ተከትሎ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ እና የሰላም አማራጭን መቀበል 'ብልህነትና አዋቂነት' መሆኑን በመረዳታቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በፍርቱና ወልደአብ

@አሐዱ ራዲዮ

Zehabesha

06 Dec, 14:35


https://youtu.be/V6ZYeuCo61U

Zehabesha

06 Dec, 14:04


የአዲስ አበባ ስፖርት ፌዴሬሽን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል:: አርቲስት ማስተዋል የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ታስገባለች ሲሉ ምንጮች መረጃ አድርሰውናል::

Zehabesha

06 Dec, 13:26


እስከ እኩለ ለሊት የቆየ ቀረፃ ጨርሼ ስልክ ስከፍት በርካታ ወዳጆቼ ተመረጥሽ የሚል ነገር ሰምተን ነው የሚል መልእክት ልከዋል።

በወዳጆቼ ጥቆማ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ስገባ ተሰራጭቶ ያየሁት መረጃ በፍፁም የማላውቀውና ከሌላው ሰው ዘግይቶ ነበር ያየሁት።

በግሌ በፕሮሞሽን፣ መድረክ መምራትና መሰል ጉዳዮች በሙያዬ እንዳግዝ በስልክ ተጠይቄ ፍቃደኛ ነኝ በሙያዬ አግዛችኋለሁ የሚል የስልክ ምላሽ ሰጥቻለሁ። መረጃ ዎች ላኪልን ስባልም በፍቃደኝነት ልኬያለሁ።

ከዚህ ውጭ ግዮን ሆቴል ተካሄደ ስለተባለ ስብሰባ የማውቀው ነገር አልነበረም፣ በቦታውም አልነበርኩም፣ ጥሪም አልደረሰኝም።

@ሃረገወይን አሰፋ

Zehabesha

05 Dec, 19:07


ሰበር፡ ስለጌታቸው ረዳ በ4 ኪሎ ቤተመንግስት ዝግ ስብሰባ ተወሰነ። ዝርዝሩን ከዕለቱ ዜና በትኩሱ ተመልከቱ።

Zehabesha

05 Dec, 19:06


https://youtu.be/1aC1yEEa2vI

Zehabesha

05 Dec, 15:43


አርቲስት ማስተዋል ወንዶሰን የአዲስአበባ እግርኳስ ፌደሬሽን ም/ፕሬዝዳንት ሁና ተመርጣለች።

ሲዲ ስፖርት/cd sport

Zehabesha

05 Dec, 15:42


https://youtu.be/vRA8u05burc

Zehabesha

05 Dec, 12:04


በስሜን ወሎ ዞን በድሮን ጥቃት የ83 ዓመት እናት ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ “ ብልባላ” በተባለች መንደር ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በተፈፀመ የድሮን ጥቃት አንዲት የ83 ዓመት እናታቸው እንደተገደሉባችው የሟች ልጅ ተናገሩ። ሌሎች የዓይን እማኞች እንዳሉት ጥቃቱ በግል መኖሪያ ቤት ላይ የተፈፀመ ነው፣ ሌሎች ሁለት የጤና ባለሙያዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

በአማራ ክልል ባለው ጦርነት የድሮን ጥቃቶች በተለያዩ አካባቢዎች በንፁሐን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ እንደሆነ የሰባዊ መብት ድርጅቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ገልፀዋል፣ በጥቃቱ ሠዎች ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም ብዙዎች ናቸው። ኅዳር 24/2017 ዓም ሌሊት 5፡30 አካባቢ በክልሉ ሰሜን ዞን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ብልብላ በተባለች መንደር በሰው አልባ አውሮፕላን መኖሪያ ቤታቸው ላይ በተፈፀመ ጥቃት የ83 ዓመት እናታቸው እማሆይ ደስታ ካክራው መገደላቸውን የሟች ልጅ እንደሆኑ የገለፁልን ቀሲስ ይትባረክ አድማሱ ነግረውናል።

ሌሎች 2 በግቢው ተከራይተው በሚኖሩ የጤና ባለሙያዎች ላይም የአካል ጉዳት ደርሷል ብለዋል፣ መጀመሪያ ላይ ድምፅ እየተመላለስ ሰላይ ላይ የሰማ እንደነበር የነገሩን ቀሲስ ይትባረክ፣ ሁኔታውን ለማወቅ ከቤታቸው ወጥተው በር ላይ ሲመለከቱ እጅግ የሚያስፈራ ድምፅና ፍንዳታ ግቢያቸውን ማናወጡን ተናግረዋል፣ በግቢያቸው ከነበሩ ክፍሎች መካክል 3 እንዳልነበር ሆነው ሲፈርሱ በጥቃቱ ከተመቱ ክፍሎች በአንዱ የነበሩት እናታቸው ሰጋቸው ተበጣጠሶ ህይወታቸው አልፏል ብለዋል።

ቀብራቸወንኳ በወና ባህል መስረት ፍትኃት ሳይደረግ መቀበራቸውን በእጅጉ ለስነልቦና ችግር መጋለጣቸውን አመልክተዋል፣ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተጨማሪ ጥቃት ይደርሳል ከሚል ሰጋት ህብረተሰቡ ተሰብስቦ ሥርዓቱን ማከናወን ባለመቻሉ መሆኑን ገልፀዋል።
በመኖሪያ ቤቱ አካባቢም ሆነ በግቢው ውስጥ ታጣቂዎች እንዳልነበሩ የገለፁልን ቀሲስ ይትባረክ፣ ግቢው ከዚህ በፊት የመኝታ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር ጠቅሰው ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ ግን ገበያው የተቀዛቀዘ በመሆኑ ከቤተሰብ የተረፉ ክፍሎችን ለመንግሥት ሠራተኞች ሲያከራዩ እንደነበር ተናግረዋል።

ጥቃቱ ከተፈፀመበት በቅርብ የነበሩ አንድ እናት አስተያየት ሰጪ በፍንዳታው ድንጋጤ ለደቂቃዎች ራሳቸውን ስተው እንደነብር ገልጠዋል። በፍንዳታው መጠነኛ ጉዳት በመኖሪያ ቤታቸው ላይ መድረሱን አመልክተው፣ “እማሆይ ደስታ ካክራው” የተባሉ መነኩሴ በጥቃቱ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል። ጥቃቱ በትክክል የድሮን ጥቃት ነው ያሉን ሌላ የዓይን እማኝ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶ ስለነበርና ድምፁን ስለምናውቅ፣ ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ስለመሆኑ ጥርጥር እንደሌላቸው ጠቅሰው በዚህ ጥቃት ሌሎች በግቢው ተከራይተው የነበሩ ሁለት የጤና ባለሙያዎች ቆስለዋል ብለዋል። አስተያየት ሰጪዎቹ የድሮን ጥቃቱ ታጣቂዎች በአካባቢው በሌሉበት ግለሰብ ቤት ላይ የተፈፀመ እንደሆነ ነው የገለፁት።

ስለደረሰው ጥቃት ተጨማሪ አስተያየት ለማካትተ ለላስታወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ለዓለም ብርሐኔ ብንደውልም ሆነ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ብንጠይቅም ምላሽ አልሰጡም። የኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቨሪ የተባለን ተቋም ጠቅሶ ዶይቼቬሌ ሰሞኑን እንደዘገበው፣ ክሚያዝያ 2015 እስከ ሕዳር 2017 ባሉ ጊዜዎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች 54 የአየርና የድሮን ጥቃቶች ተፈፅመዋል፣450 ያክል ሠዎች ደግሞ ተገድለዋል። የአማራ ማሕበር በሰሜን አሜሪካ ደግሞ ከጥቅምት 5/2016 እስከ ሕዳር 14/2017 ዓ ም ባለው ጊዜ 125 የአየርና የድሮን ጥቃቶች መፈፀማቸውን፣ 754 ሠላማዊ ሠዎች መገደላቸውንና 223 ሠዎች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው መመዝገቡን ዶይቼ ቬሌ በቅርቡ ዘግቧል።

@DW

Zehabesha

05 Dec, 11:48


አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም መኖርያ ቤታቸዉ ከቤተሰባቸዉ ተለቀዋል

ትናንት አመሻሹን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለቀው ቤተሰቦቻቸውን ሳይቀላቀሉ ከማረሚያ ቤቱ በራፍ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰዱት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ፤ ዛሬ እኩለ ቀን ደግሞ ሜክሲኮ ከሚገኘው የወንጅል ምርመራ ማዕከል ተለቀው ቤታቸው መድረሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ስንታየሁ እንዳሉት ጠዋት ቤተሰብ ሜክሲኮ ምግብ አድርሶላቸው ከተመለሰና ደህንነታው ከጤቀ በኋላ ዛሬ እኩለ ቀን ምሳ ሰዓት ከማቆያው እንዲወጡ ተወስኖ ሰባት ሰዓት ግድም መኖራቸው ቤት መድረሳቸውንም አክለው አብራርተዋል፡፡

ባለፈው ሰኞ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የዋስትና መብት ተጠብቆላቸው ከእስር እንዲለቀቁ በፌዴራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ከተወሰነላቸው በኋላ የተለያዩ ከማረሚያ ቤት የማስለቀቂያ ሂደቶች ተጠናቀው አቶ ታዬ ትናንት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር አመሻሹን 11 ሰዓት ላይ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ብለቀቁም የፀጥታ ኃይሎች የማረሚያ ቤቱ በራፍ ላይ ጠብቀው ወዳልታወቀ ስፍራ እንደወሰዱዋቸው ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረው ነበር፡፡

ባለፈው ሰኞ በፍርድ ቤት በ20 ሺህ ብር ዋስትና ክሳቸውን ከውጪ መከታተል እንዲችሉ በታዘዘው መሰረት ትናንት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ብለቀቁም ለምን ወደ ሜክሲኮ የወንጀል ምርመራ ማዕከል እንደተወሰዱ ግን ቤተሰብ እንዳልተረዳ ነው የተነገረው፡፡
ትናንት አመሻሹን በዶይቼ ስለጉዳዩ የተጠየቁት የፌዴራል ፖሊስ ቃል አቀባይ አቶ ጀኢላን አብዲ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸውልናል፡፡

የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታና የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታዬ ደንደዓ ከተከሰሱባቸው ሶስት ክሶች ሁለቱ ውድቅ ተደርጎላቸው “ከህግ አግባብ ውጪ የጦር መሳሪያ ይዘው ተገኝተዋል” በሚል የተመሰረተባቸውን አንዱን ክስ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በመከላከል ሂደት ላይ እንደሆነ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሥዩም ጌቱ በላከው ዜና አስታውሷል፡፡

@DW

Zehabesha

05 Dec, 06:13


በትግራይ ክልል የኤችአይቪ ስርጭት ከጦርነቱ በኋላ በእጥፍ መጨመሩን፣ በክልሉ የተካሄደ ጥናት ጠቅሶ የክልሉ ጤና ቢሮ ማስታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል::

እንደዘገባው ለቫይረሱ ስርጭት መጨመር፡ የሴቶች መደፈር፣ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች መበራከት እና የነዋሪዎች ከቀዬ መፈናቀል በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።

Zehabesha

04 Dec, 22:41


https://youtu.be/ZjCz3LClWHw?si=Ex5n43NFyzgbSKGh

Zehabesha

01 Dec, 01:29


https://youtu.be/bNzNRrzuhFQ

Zehabesha

30 Nov, 23:19


https://youtu.be/bNzNRrzuhFQ

Zehabesha

30 Nov, 18:53


https://youtu.be/bNzNRrzuhFQ

Zehabesha

30 Nov, 17:43


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ

1. አቶ ግርማ ሰይፉ - የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ

2. ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር

3. ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ- የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ

4. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ

5. ⁠⁠አቶ ሙባረክ ከማል- የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ

6. አቶ ሁንዴ ከበደ - የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ

7. አቶ ታረቀኝ ገመቹ- የንግድ ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ⁠ ሆነው መሾማቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

Zehabesha

30 Nov, 16:50


https://youtu.be/pXGzxlz6LTc

Zehabesha

30 Nov, 15:27


https://www.youtube.com/watch?v=1XBoesYmIVE

Zehabesha

30 Nov, 15:13


‘’በኦሮሚያም ይሁን በአማራ ያሉ ታጣቂዎች ሺህ ዓመት ቢዋጉን አያሸንፉንም’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የብልፅግና ፓርቲን 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ በአድዋ ሙዚየም ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራም ይሁን በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሀይሎች በውጊያ እንደማያሸንፉ አውቀው በንግግር ቢገቡ ይሻላችኋል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ንግግራቸው የብልፅግና ፓርቲ አባላት ቁጥር 15.7 ሚሊዮን በላይ መድረሱን፣ ይህ በአፍሪካ ግዙፉ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ንግግራቸው ፓርቲያቸው ወደ ስልጣን ከመጣበት ከህዳር 21 ቀን 2012 እስከ ዛሬ ድረስ ያከናወናቸውን የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ አስረድተዋል፡፡

ኢኮኖሚን በተመለከተ ሀገሪቱ ባለፉት 5 ዓመታት የበጋ ስንዴ ማምረት የጀመረችበት፣ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ የገቡበት፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት ወቅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዲፕሎማሲን በተመለከተ ባደረጉት ንግግርም ኢትዮጵያ በኢህአዴግ ዘመን መንግስት ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር በሚባል ደረጃ መጋጨቷን ተናግረው ባለፉት 5 ዓመታት ግን ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር እየሰራች ያለችው በወዳጅነት እና በትብብር እንጂ አንድም የጥይት ልውውጥ አላደረገችም ብለዋል፡፡

ፖለቲካን በተመለከተ የብልፅግና ፓርቲ ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ አንዲስ የፖለቲካ ልምምድ በኢትዮጵያ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

በፊት በኢትዮጵያ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መስራት አልተለመደም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብልፅግና ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ ግን በፊት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የነበረውን በጠላትነት የመተያየት ብሂል አስቀርቷል ብለዋል፡፡

ብልፅግና ከሀሳብ እንጂ ከሰዎች ጋር ግጭት ውስጥ አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማንኛውም ሰው ጋር በሀሳብ አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ፓርቲያቸው 10ኛ ዓመቱን ሲያከብር ኢትዮጵያ የምትረዳ እንጂ የማትረዳ የውጪ፣ ሀገራት ሊያስታርቋት የሚለምኗት ሳይሆን የምታስታርቅ ሀገር ትሆናለች ብለዋል፡፡

ያሬድ እንዳሻው

Zehabesha

30 Nov, 07:09


https://youtu.be/1XBoesYmIVE?si=RkJlHNsBs6gGLLc4

Zehabesha

30 Nov, 03:57


https://youtu.be/WphJT6le900?si=ecNEJGmA2ChoF33q

Zehabesha

30 Nov, 00:16


ኔዘርላንድ ውስጥ በሚደረግ ውድድር ኢትዮጵያዊው ለሽልማት እጩ ሆኖ ቀረበ፤ኢዮጵያውያን ድምጽ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል።


ኔዘርላንድ ውስጥ በሚደረግ ውድድር ኢትዮጵያዊው ለሽልማት እጩ ሆኖ መቅረቡን ምንጮች ለዘ-ኢትዮጵያ አስታወቁ። ኢትዮጵያዊው ታደለ ማሩ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ከተለያዩ ሀገራት ወደ ኔዘርላንድ ከገቡ ሰዎች ውስጥ ፤ዘርፈ ብዙ በሆኑ መመዘኛዎች ተወዳድሮ ከምርጥ 4ቱ ውስጥ እንደገባ ለማወቅ ተችሏል።
በዚህ ምርጥ 4 ውስጥ እንዲገባ ያበቁት ነገሮች:- 1)በተለያዩ የማህበረሰብ ስራዎች ተሳትፎ፤ 2)ደች ቋንቋ በAdvanced level በአጭር ጊዜ በመጨረስ፤ 3)የ2ኛ ማስተርስ ትምህርቱን በጥሩ ውጤት በማጠናቀቅ እና በቀጣይ ለዶክትሬት ተምህርት ምርምር ላይ እየሰራ መሆኑ 4) በደች ጋዜጦች እና በኢንተርኔት መገናኛዎች ላይ በመውጣት ለሌሎች inspiration መሆን መቻሉ እና 5) ከደች ቋንቋ አስተማሪው ጋር ሆኖ በጻፈው የልጆች መጽሐፍ ናቸው።
ከምርጥ አራቱ 1ኛ የወጣውን ለመለየት የኦንላይን ምርጫ በመጀመሩ፤ በኔዘርላንድ እና ሌሎች ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለታደለ ድምጻቸውን በኦንላይን እየሰጡ ሲሆን።
አንደኛ የሚወጣው ተወዳዳሪ በመጨረሻ ሚንስትሮችን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ዝግጅት ይፋ እንደ እንደሚደረግ ከውድድሩ አዘጋጆች የተገኘው መረጃ ያሰርዳል። ስለዚህ በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከታች ባለው ሊንክ እየገባችሁ ለታደለ ማሩ ድምጻችሁን እንድትሰጡ ጥሪ ተደርጎላቹሗል።
https://www.uaf.nl/en/uaf-award/tadele/?utm_source=tadele&utm_medium=referral&utm_campaign=uafaward&fbclid=IwY2xjawGxor5leHRuA2FlbQIxMQABHWnVsPAqbjuJSGtfcS_3NZiWNJDLj5jjJhYKDXapB7FSjkC-5Skcgo7ZBQ_aem_Wb3C8hpbQSXj0DPY8USjDA#stem

Zehabesha

29 Nov, 22:08


https://youtu.be/WphJT6le900?si=ws2yOe7BHQKcVoxN

Zehabesha

29 Nov, 19:07


https://youtu.be/WphJT6le900

Zehabesha

29 Nov, 19:07


የዕለቱ ዜና እንዳያመልጣችሁ

Zehabesha

29 Nov, 17:42


በሸዋሮቢት በርካታ ወጣቶች በዚህ ሳምንት ታፍሰው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ:: ከህዳር 16 ጀምሮ ታፍሰው የተወሰዱ ልጆቻቸው የት እንደሆኑ ማወቅ አልቻልንም ሲሉ ገልፀዋል::

Zehabesha

21 Nov, 05:59


https://www.tiktok.com/t/ZTY2YQHaA/

Zehabesha

20 Nov, 21:32


https://youtu.be/gYR8TFm4EoY

Zehabesha

20 Nov, 20:32


የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሠራተኞች በዘራፊዎች ምክኒያት ሥራ ማቆማቸውን ገለጹ

ባህር ዳር ከተማ ዙሪያ የሚገኘው ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ባለሞያዎችና ሠራተኞች በአካባቢው ይገኛሉ ባሏቸው ታጣቂ ዘራፊዎች ይደርስብናል ባሉት ዘረፋና ምክኒያት ሥራ ማቆማቸውን ገለጹ።
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸውና ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሁለት የሕክምና ባለሞያዎች፣ በተለያዩ ጊዜያት የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ዘልቀው በመግባት ሠራተኞቹን በሽጉጥ በማስፈራራት ዘረፋ ማካሄዳቸውን ገልጸው ከሰኞ ኅዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ሥራቸውን እንዳቆሙ ተናግረዋል።
ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስና ድምጻቸውን እንድንቀይር የጠየቁን አንድ የሆስፒታሉ የጤና ባለሞያ፣ ከአምስት ወራት ወዲህ በተደጋጋሚ የታጠቁ ድንገተኛ ዘራፊዎች ወደ ሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ በመግባት ዝርፊያ እንደሚፈፅሙ ገልጸዋል።
ማክሰኞ ኅዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. የሆስፒታሉን ዳይሬክተር ጨምሮ ሌሎች አምስት ሐኪሞች ግቢው ውስጥ እንደተዘረፉም ተናግረዋል።
የሆስፒታሉ ሠራተኞች ለሚመለከተው አካል ጠንካራ የጸጥታ ኃይል እንዲመደብላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።
ለተሻለ ሕክምና ከምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቸና ወረዳ ታካሚ በበኩላቸው የሕክምና ባለሞያዎቹ አድማ ላይ በመኾናቸው ምክኒያት ፣ ከሰኞ ጀምሮ እስከ ዛሬ አገልግሎት ባለማግኘት እየተጉላሉ መኾኑን በተመሳሳይ የደኅንነት ስጋት ምክኒያት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ ታካሚ ተናግረዋል።
የጥበበ ጊዮን አጠቃላይ ሆስፒታል በቀን ወደ 3 ሺሕ ታካሚዎችን እንደሚያስተናግድ የሆስፒታሉ አመራሮች ይገልጻሉ። ከዚህ በተጨማሪ በዩንቨርስቲው በሕክምናና ሳይንስ ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎችም የተግባር ትምሕርት ይወስዱበታል።
በዩንቨርስቲው በሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ የአምስተኛ ዓመት ተማሪ መኾኑን የገለጸልንና በደኅንነት ስጋት ምክንያት ስሙ እንዳይጠቀስ ድምጹም እንዲቀየር የጠየቅ አንድ ተማሪ ከሰኞ ጀምሮ የሕክምና ተማሪዎች የተግባር ትምህርት እየወሰዱ እንዳልሆነ ተናግሯል።
“ሆስፒታሉ አጥር የለውም። ጠባቂዎቹም ዱላ ይዘው ነው የሚጠብቁት ሲል ቅሬታውን ያቀረበ አንድ በተመሳሳይ ምክንያት ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የሕክምና ባለሞያ መደበኛ የፀጥታ ኃይል ካልተመደበ በቀር ሥራ መሥራት አስቸጋሪ እንደኾነ ጠቁሟል።
በባህር ዳር ዩንቨርስቲ በጥበቃ ሥራ የተሰማራና በደኅንነት ስጋት ምክንያት ስሙ እንዳይጠቀስ ድምጹም አየር ላይ እንዳይውል የገለጸልን ግለሰብ፣ የጠበቃ ሥራ የሚሠሩት ያለጦር መሳሪያ በመኾኑ ችግሮች ሲፈጠሩ ምላሽ መስጠት አለመቻላቸውን ገልጿል።
በባህር ዳር ዩንቨርስቲ የጸጥታና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ፣ ኢንስፔክተር ሀብታሙ መለሰ የሆስፒታሉ ሠራተኞች በምሽት በታጠቁ ኃይሎች ዘረፋ እንደሚፈፀምባቸው አረጋግጠዋል። አክለውም፣ በአማራ ክልል ባለፈው ዓመት ከታወጀው አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጋራ በተያያዘ ከጸጥታ ኃይሉ ውጭ የጦር መሳሪያ መያዝ የሚከለክል ዐዋጅ በመታወጁ የዩንቨርስቲው ጠባቂዎች የጦር መሳሪያ እንደማይዙ ገልጸዋል። በዚኽም ምክኒያት ወደ ግቢው ታጥቆ የሚመጣውን ማንኛውንም ዘራፊ ለመከላከል አዳጋች እንደሚኾንባቸው ተናግረዋል። ችግሩ ለመፍታትም ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋራ እየተነጋገሩ መኾኑን አስረድተዋል።
ሆስፒታሉን በበላይነት የሚያስተዳድረው ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው በሆስፒታሉ ውስጥ ዝርፊያ መከሰቱን አምነው ፣ዛሬ ጸጥታና ደህንነቱን ከሚመራው ተቋምና ከኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋራ ተወያይተው ችግሮችን ለመፍታት ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ገልፀዋል።
የጥበበ ጊዮን አጠቃላይ ሆስፒታል በኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ : በቀድሞው የሱማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብድላሂ መሀመድ " ፋርማጆ "በ2010 ዓ.ም የተመረቀ ትልቅ ሆስፒታል ነው

@VOA

Zehabesha

20 Nov, 20:20


የከተማ አውቶብስ ትራንስፖርት እስከ ምሽቱ አራት ሰዐት ድረስ መራዘሙ ተሰማ::

Zehabesha

20 Nov, 18:41


https://youtu.be/gYR8TFm4EoY

Zehabesha

20 Nov, 17:40


ይህ አሽከርካሪ ዮሀንስ እያሱ ይባላል በትናንትናው ዕለት በ 10/03/2017 ከአዲስ አበባ ቢራ ጭኖ ወደ ሽረ በመጓዝ ላይ ባለበት ሂደት በትግራይ ክልል ሽረ አቅራቢያ በለስ የሚባል አካባቢ ዘራፊወች ገለውታል :: ብዙም የሹፌር ግድያ የማንሰማበት የትግራይ ክልል ላይ ይህ መከሰቱ የሚያሳዝን የሾፌር ግድያ እየተስፋፋ መምጣቱን የሚያመላክት ነው ::

የትግራይ ክልል የሽረ ከተማ ህግ አስከባሪ አባላት እንዲህ ያሉ ነፍሰ ገዳዮችን አድናችሁ ልትቀጡ ትክክለኛ ፍትህን ልትሰጡ ይገባል ::

@የሾፌሮች አንደበት

Zehabesha

20 Nov, 14:39


https://youtu.be/X7KGk1u-bzs

Zehabesha

20 Nov, 14:09


"የመንግስት ተቋማት ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ነው ቁጥጥር ያደረጉት” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የመንግስት ተቋማት ቁጥጥራቸውን ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ማድረጋቸውን እንደ ትልቅ ክፍተት አግኝተነዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ የበጀት ዓመቱን የሶስት ወራት የስራ አፈፃፀም በቀረበበት ወቅት ነው።

በጉባኤው በዋነኝነት ጥያቄ ካስነሱ ጉዳዮች መካከልም፣ በመርካቶ ገበያ ከሰሞኑ በደረሰኝ ከመገበያየት ጋር የተነሱ አለመግባባቶች ነበር።

ከንቲባዋ መርካቶን ዳግም ለማልማት ከመነሳታችን በፊት የተለያዩ ጥናቶች አከናውነናል ያሉ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ መርካቶ የሀገሪቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ከመሆኑ ጀርባ የህገ ወጥ ንግድ መሸሸጊያ ሆኖ በማግኘታችን ነው ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የመንግስት ተቋማት ቁጥጥራቸውን ፊት ለፊት የሚገኙ የመርካቶ ነጋዴዎች ላይ ብቻ ማድረጋቸው እንደሆነ ነው የጠቆሙት።

" ሲነጋ ግብረ ሐይሎች እንዳያገኘን በሚል፣ በሌሊት ትልልቅ ተሸከርካሪዎች ተሰልፈው እቃ ጭነው ለመሄድ ጥረት ይደረጋል። ይህ ሀገርን ይጎዳል። ግብር መክፈል መርህ እስከሆነ፣ ችግሮቻችንን እያሳዩን እና የሚሰርቀውን ለእኛ አሳልፈው እየሰጡ እነርሱም ግድታቸውን መወጣት ነው ያለባቸው።" ሲሉ አስጠንቅቀዋል

@አዲስ ማለዳ

Zehabesha

20 Nov, 13:55


ኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሆኖ አንዱ ለአንዱ ሞት ሀዘን የሚሰማው መቼ ነው? በብሔር ተከፋፍለን አንዱ ሲጎዳ እኛ ላይ አልደረሰም ብለን የምንሳለቀው ለምንድነው? ነገ እኛ ላይ ሲደርስ ማነው የሚያዝነውስ? እስከመቼ ነው አንዳችን በአንዳችን ስቃይ ሞት መከራ እየተሳለቅን የምንኖረው? እኔ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ይስጨንቀኛል::

@ሂሩት ሃብተሥላሴ ከሰንዳፋ

Zehabesha

20 Nov, 13:39


በማዕከላዊ ጎንደር ውጊያ እንዳለ ምንጮቻችን አድርሰውናል:: በጎጃምም ውጊያው እንደ ቀጠለ ሰምተናል::

Zehabesha

20 Nov, 12:18


በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እና ገንዘብ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
***
ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ነው፡፡ ተጠርጣሪዋ በደላላ አማካኝነት በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በሶስተኛው ቀን ቆይታዋ የግል ተበዳይ ወደ ስራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንዲሁም የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦችን ሰርቃ በመሰወሯ የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተዋል፡፡

ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ቤት ለሦስት ወራት ተከራይታ በነበረበት ቤት ተደብቃ በክትትል የፖሊስ አባላት ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት፣ የተለያዩ የሴትና የወንድ ጫማዎች፣ 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ፣ የተለያዩ የወርቅና ልዩ ልዩ ጌጣጌጦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን ከክ/ከተማው የተገኘው መረጃ ያስረዳል። በተጨማሪም በሁለት የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያ እንደተገኘባትም ተገልጿል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አበበ እንደገለፁት የግል ተበዳይ ተጠርጣሪዋን ለስራ ሲቀጥሯት ያቀረበችው የተያዥ ፎርም የራሷን ፎቶ በትክክል እንዳይለይ አድርጋ የለጠፈች ሲሆን የግል ተበዳይም ይህንን ሳያረጋግጡ በእምነት የቀጠሯት መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛ በአጋዥነት መቅጠሩ ተገቢ ቢሆንም በህጋዊ መንገድ በቂ ተያዥ በማስቀረብ የተያዣቸውን አድራሻና ማንነት በአግባቡ በማጤን መቅጠር እንደሚገባና ውድ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ በማስቀመጥ በተገቢው ሊቆጣጠሩና ንብረታቸውን ከስርቆት ወንጀል ሊታደጉ እንደሚገባም ተናግረዋል።

@አዲስ አበባ ፖሊስ

Zehabesha

20 Nov, 02:08


ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፉ ቡድኖች::

ኢትዮጵያ ከምድቧ አራተኛ ደረጃ በመያዝ ለአፍሪካ ዋንጫ ሳታልፍ ቀርታለች:: በብዙ ችግር እና ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን ሞሮኮ ላይ ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ አልፋለች::

Zehabesha

20 Nov, 01:29


https://www.facebook.com/share/v/15ZRAnUdqE/?mibextid=WC7FNe

Zehabesha

20 Nov, 00:16


https://youtu.be/fjdRDA76ugo

Zehabesha

19 Nov, 18:49


https://youtu.be/fjdRDA76ugo

Zehabesha

14 Nov, 15:53


https://youtu.be/Mki60-SoVzw

Zehabesha

14 Nov, 14:46


ጃዋር እንዳለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለሦስተኛ ጊዜ ለሚደረገው ንግግር ፍቃደኝነቱን ገልፇል:: ፍቃደኛ ያልሆነው መንግስት ነው የሚል አጭር መልሕክት አስፍሯል::

Zehabesha

14 Nov, 14:36


ለበዓልዎ ከወዲሁ ፋሽን ልብሶችን ይሸምቱ። እርስዎን የሚመጥን ዋጋ የቀረቡ ናቸው፣ ምናልባት የሚያስፈልግዎ ከሆነ ይመልከቱ። #ad https://amzn.to/48NTu7C

Zehabesha

14 Nov, 14:25


በእነ መስከረም አበራ መዝገብ የተከሰሱት 51 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ችሎት ፊት በአካል የቀረቡት ሃያ ሦስት ተከሳሾች “ወንጀሉን አልፈጸንም” ሲሉ ተከራክረዋል

በእነ መስከረም አበራ መዝገብ የተከሰሱት 51 ተከሳሾች ዛሬ ሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ ጸረ-ሽብር ወንጀል ችሎት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ችሎቱ "ሕገ መንግሥቱን በሃይል በመናድ" ወንጀል የተከሰሱትን ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል፤ ለዛሬ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም ከሃምሳ አንዱ ተከሳሾች መካከል ሃያ ሦስቱ በዛሬው ዕለት በችሎቱ በአካል በመገኘት፤ "ወንጀሉን አልፈጸምንም" ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ከተከሳሾቹ መካከል “ኢትዮ ንቃት” የተሰኘው ማኅበራዊ ሚዲያ መሥራች እና ባለቤት ጋዜጠኛ መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እንዲሁም ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ እንደሚገኙበት የአሐዱ ሬድዮ ሪፖርተር ከችሎት ተገኝቶ ዘግቧል።

ዐቃቤ-ሕግ በበኩሉ ጉዳዩን የሚያስረዱለት 92 ምስክሮችን እንደሚያቀርብ ለችሎቱ አስረድቷል።

ፍርድም ቤቱም ዐቃቢ ሕግ ማስረጃ ያላቸዉን ምስክሮች እንዲያቀርቡ በማዘዝ መዝገቡን ለታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ቀጥሯል።

እንደ አጠቃላይ የእስር ቤት አያያዝን በተመለከተ መስከረም አበራ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርባለች።

በአቤቱታዋም ቤተሰቦቿ እሷን ለመጠየቅ መቸገራቸዉን አንስታ፤ “ይህ ጉዳይ በተደጋጋሚ ስለሆነ የተከበረዉ ፍርድ ቤት ይህንን ችግር ተገንዝቦ ትዕዛዝ እንድሰጥልኝ” ብላለች።

ፍርድ ቤቱም መስከረም አበራ በቃል ያቀረበችውን አቤቱታ በመቀበል፤ የሚመለተው አካል ማስተካከያ እንዲያደርግ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

@በአለምነው ሹሙ

Zehabesha

14 Nov, 14:22


በሰሜን ሸዋ አንኮበር እንዲሁም ከጣርማበር በመሬት መንሸራተት ተፈናቅለው በተጠለሉ ንፁሃን ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተሰማ:: ከነዚህ ንፁሃን መሀል እናት እና ልጅ ይገኙበታል::

Zehabesha

14 Nov, 13:46


በኬንያ የአሜሪካ አምባሳደር ሥልጣናቸውን ለቀቁ
በ2022 ስራ የጀመሩት የአሜሪካ ኬንያ አምባሳደር ሜግ ዊትማን ትናትት ከሀላፊነት መልቀቃቸውን የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ዊትማን ሥልጣናቸውን የለቀቁት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው ። በለቀቁት አምባሳደር ምትክ ማርክ ዲላርድ የኤምባሲውን ሀላፊነት ይወስዳሉ ተብሏል።
የአምባሳደሯ የመልቀቅ ውሳኔ በኬንያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ሰበብ ስራ እንዲለቁ የተደረገባቸውን ግፊት ተከትሎ ነው። በሌላ በኩል ከህግ አግባብ ውጭ በሚፈፀሙ ግድያ እና አፈናን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ዝምታ በመምረጣቸውም አምባሳደሯ ይወቀሳሉ።
የኬንያ የመንግስት ባለስልጣናት ግን ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው የለቀቅትን አምባሳደር ዊትማንን አወድሰዋቸዋል። ዴኒስ ኢቱምቢ የተባሉ የኬንያ የመንግስት ባለስልጣን ፤ዊትማን በኬንያ ትዝታዎች እና የታሪክ መጽሃፍቶች ላይ ለመመዝገብ ብቁ ናቸው ሲሉ አወድሰዋቸዋል። ታዋቂው የህግ ባለሙያ አህመድናስር አብዱላሂ ደግሞ "አስደናቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ አምባሳደር" እንዲሁም "የኬንያ እና ህዝቦቿ ጥሩ እና ወዳጅ »ብለዋቸዋል።

@DW

Zehabesha

14 Nov, 13:28


በአማራ ክልል 29 ሚሊዮን የሚሆን የግሪሳ ወፍ በ6 ወረዳዎችና በ19 ቀበሌዎች ውስጥ መከሰቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ

በክልሉ የተከሰተው ተዛማችና ድንበር ተሻጋሪ እየተባሉ ከሚጠሩት ተባዮች ውስጥ አንዱ የሆነው የግሪሳ ወፍ ሲሆን በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ችግር ተደርጎም ይወሰዳል።

በክልሉ በሰሜን ሸዋ፤ በደቡብ ወሎና በኦሮሞ ልዩ ብሄረሰብ ዞኖች የግሪሳ ወፉ እንደተከሰተ የገለጹት የክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ፤ ይህን ከአንበጣ መንጋ ጋር የሚመሳሰለውንና አውዳሚ የሆነውን የወፍ ዝርያ በጊዜ ለማጥፋት ክልሉ ከግብርና ሚንስቴር ጋር በመሆን በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል የርጭት ስራ መሰራቱን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡

በዚህም እስካሁን 250 ሄክታር የሚሆን የወፍ ማደሪያ ላይ 501 ሊትር የሚሆን የጸረ ወፍ ኬሚካል በመርጨት ከተከሰተው 29 ሚሊዮን የግሬሳ ወፍ ውስጥ ወደ 16 ሚሊዮን የሚሆነውን ማጥፋት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የተከሰተው ይህ የግሪሳ ወፍ አሁን በተከሰተባቸው ቦታም ሆነ በክልሉ ባሉ ሌሎቹ ዞኖች ጉዳት ሳያደርስ ከወዲሁ ለመቆጣጠር ቢሮው ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን አስፈላጊውን ሁሉ የኬሚካልና የአውሮፕላን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የክልሉ ግብርና ቢሮ በዞን ካሉ የግብርና መምሪያ ባለሙያዎች ጋር በመሆን እስከ ቀበሌ ድረስ የግንኙነት መረብ በመዘርጋት የክትትል ስራውን እንደሚሰራ ዶ/ር ማንደፍሮ አመላክተዋል፡፡

የግሪሳ ወፉ በሌሎችም የክልሉ ዞኖች ተስፋፍቶ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስና እንደ ክልል የታቀደው የምርት መጠን እንዲገኝ የክትትል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ በክልሉ በግሪሳ ወፍ ምክንያት የተከሰተ የሰብል ውድመት ካለ ወደፊት በቢሮው በኩል እንደሚገለጽም አመላክተዋል፡፡

@መናኸሪያ ሬዲዮ

Zehabesha

14 Nov, 13:23


በመንግስት የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሰላማዊ ዜጎችን ለህልፈት እየዳረገ ነው”- ኢሕአፓ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ “የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሃላፊነት ያለበት መንግሥት ቢሆንም በሚያሰማራቸው የጸጥታ ሃይሎችና የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጭምር የዜጎች ህይወት በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደቅጠል እያረገፈ ይገኛል” ብሏል፡፡

ኢሕአፓ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህገመንግሥቱን የመንግሥት አካላት ራሳቸው ካላከበሩት እንዴት ሊያስከብሩት ይችላሉ “በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደረጉት ግድያዎች ይቁሙ” ሲል አሳስቧል፡፡

እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከመዘገብ ቢቆጠቡም በውጪ የመገናኛ ብዙሀን ጭምር ጥቃቱ መፈጸሙን እየገለጹ መሆኑን እና ፓርቲውም አጣርቻለሁ ያለውን በየክልሉ የደረሱትን ጥቃቶች አስታውቋል፡፡

ፓርቲው አጣርቻለው ባለው መሰረት ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ጥቃቶች የሟቾችን ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን እና ጥቃት ከተፈጸመባቸው ውስጥም ነፍሰጡሮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ተማሪዎች እንደሚገኙበት አመላክቷል፡፡

በመሆኑም “ወደፊት ትውልድ እንዲከፍል በብድር በመጣ የጦር መሳሪያ ንጹሀን ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄድ አግባብነት የለውም”፤ መንግሥት ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ለማለት እንደዚህ ያለውን ሁኔታ በዝምታ ማስቀጠል አይችልም ሲል ኮንኗል፡፡

ኢሕአፓ መንግሥት በተለይ የጦርነት አውድማ በተደረጉት በአማራ፣በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝና በደቡብ ክልሎች ዉስጥ የሚደረገውን ህገመንግሥቱን እየጣሱ ያሉትን፣ መንግሥት መር የዜጎች ግድያዎችን በጥብቅ ማውገዙን እና ጦርነቶቹ አሁኑኑ ይቁሙ ሲልም አሳስቧል፡፡

Zehabesha

14 Nov, 12:41


አልሸባብን የማዳከም ስራ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ መንግስት ገለፀ
በሶማሊያ የሚገኘውን አሸባŔሪ ቡድን አልሸባብ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥጋት እንዳይሆን "በየትኛውም ሁኔታ አሸባሪ ቡድኑን የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል" ሲል የኢትዮጵያ መንግሥስት አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠራዊት በአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ውጪ መሆኑን ባለፈው ሳምንት በይፋ ማስታወቋን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም ሲጠየቁ ነው ይህንን ያሉት።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ "የማይነጣጠሉ ሕዝቦች እንደመሆናቸው ጊዜያዊ ችግሮችን የመባባስ ፍላጎት የለንም" ያሉት ቃል አቀባዩ የሶማሊያ ማንግሥት ይፋ ላራመደው አቋም አልሸባብን እናዳክማለን ከማለት በቀር ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተካረረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ እና የራስ ገዟ ሶማሊላንድ «የባሕር በር እውቅና» የመግባቢያ ስምምነት እስካሁን በሂደት ላይ መሆኑ ሲገለጽ በአንድ በኩል፣ አልሸባብን በመዋጋት ለዓመታት የጋራ ግብ እና ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ሆድና ጀርባ አድርጎ ከቃላት ያለፈ የዲፕሎማሲ ቁርቁስ ውስጥ ከቷቸዋል።

@DW

Zehabesha

14 Nov, 12:36


በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሕዝባዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላምን ለማፅናት ያለሙ ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡
ስልፉ እየተካሄደ ያለው በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ቄለም ወለጋ እና የአርሲ ዞኖች ነው፡፡
በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን በሰልፉም በሰላም እጦት ምክንያት የህዝቡ ስቃይ ሊቆም ይገባል፤ ወደ ሰላም መመለስ መሰልጠን ነው የሚሉ መልዕክቶችን እያስተላለፉ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

Zehabesha

14 Nov, 07:39


https://youtu.be/29KNBl13dy8?si=8PByF8ae0mKA773F

Zehabesha

14 Nov, 02:14


በአሜሪካ ፌላዴልፊያ ጉዞ የኢትዮጵያ ካፌ ተከፈተ::

Zehabesha

14 Nov, 00:14


https://youtu.be/29KNBl13dy8

Zehabesha

13 Nov, 23:34


የዘንድሮውን ታክስ፣ መክፈል የማይጠበቅብዎትን እንዳይከፍሉ ምን ማድረግ አለብዎ? አዎ፤ የግብር ዕቅድ ያስፈልግዎታል። ይህንንም ከዴሴምበር መጨረሻ በፊት ማድረግ ይኖርብዎታል።
Tax planning is key to reducing your taxes
የታክስ ባለሙያ ለማናገር በ+1 612 946 3000 ይደውሉ።
አድራሻ፡ 515 W LAKE ST, MINNEAPOLIS, MN 55408, USA #ad

Zehabesha

13 Nov, 21:32


ታጣቂዎች ከጫካ እንዲመለሱ ለማድረግ ወላጆች በጅምላ መታሰራቸው ተገለጸ::

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ውስጥ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ከጫካ ተመልሰ እጃቸውን እስኪሰጡ በጅምላ የታሰሩ ከ130 በላይ ወላጆች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ሰባት ወራት መቆጠሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

@VOA

Zehabesha

05 Nov, 12:48


በአማራ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግሥት ቁርጠኛ ሆኖ ተኩስ አቁም ማድረግ አለበት ሲሉ ፓርቲዎች ገለጹ

በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በየዕለቱ እየተከሰተ ያለዉን የሕጻናትና እናቶችን ሞት ለማስቆም፤ የፌደራሉ መንግሥት ቁርጠኛ በመሆን የተኩስ አቁም ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ፓርቲዎች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ ከአባላቱ ለተነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት፤ ለሰላም ቁርጠኝነት እንዳለ በመግለጽ "አግዙን" ሲሉ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡

አሐዱም ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር መነሻ በማድረግ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን "መንግሥት እውነት ቁርጠኛ ነው ወይ?" ሲል ጠይቋል፡፡

የእናት ፓርቲ አባል አቶ ጌትነት ወርቁ "መንግሥት የተኩስ አቁም ማድረግ አለበት" ያሉ ሲሆን፤ 'ቁርጠኛ መሆን አለበት' ሲባልም "በሌላው ወገን ያሉትም ጦር በማዉረድ ወደ ሌላ አሸናፊ መንገድ ለመምጣት ቁርጠኛ መሆን አለባቸው" ብለዋል፡፡

"መንግሥት ለሰላም ቁርጠኛ ነኝ እያለ ይናገር እንጂ በእውነት መሬት ላይ የወረደ የተተገበረ ነገር ግን ማግኘት አይቻልም" ያሉት ደግሞ፤ የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ የአደረጃጀትና አቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙባረክ ረሽድ ናቸው፡፡

"አሁንም ግጭት ውስጥ ነው የምንገኘው" ያሉት አቶ ሙባረክ፤ "ለሰላም ዝግጁ የሆነ አካል ቢያንስ ወደ ሰላም የሚያመጡ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር አለበት" ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሰላም ፍላጎት መታየቱ በራሱ ግን የሚያስደስትና አንድ ደረጃ ችግሩን አምኖ የሰላም ጥሪ ማድረጉ በበጎ የሚወሰድ መሆኑን ፓርቲዎቹ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥሪያቸው 'እናንተም አግዙ' የሚል ጥሪ ስለማድረጋቸው በሚመለከት ሀሳባቸውን የሰጡት ፓርቲዎቹ፤ "ችግሩ ከእኛም ከመንግሥትም በላይ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል" ብለዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰላም ፀጥታ ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ መንግሥታቸው "ከኃይል ይልቅ ሰላም እጅግ በጣም አዋጭ ነው" ብሎ እንደሚያምን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ

Zehabesha

05 Nov, 12:45


በኢትዮጵያ ግጭትና መፈናቀል ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች ተደራራቢ ችግሮች የሚደርሱባቸው ቢሆንም በመንግስት ትኩረት ተነፍጓቸዋል ተብሏል፡፡

ግጭቶች በሚያስከትሉት ውድመት ከቤት ንብረታቸው ለሚፈናቀሉ ሰዎች የእለት ደራሽ ምግብና ሌላውንም ድጋፍ እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡

ይሁንና በግጭቱ ምክንያት ይሁን በሌላ አካል ጉዳት ለሚደርስባቸው ሰዎች፤ ይህ ነው የሚባል ድጋፍ አይደረግም ሲባል ይደመጣል፡፡

በተለይም በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ የተለየ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ መሆናቸው ቢታወቅም፤ በዚህ ላይ በሚሰሩ የረድኤት ተቋማትም ይሁን በመንግስት ተረስተዋል፤ ያሉን የፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ ናቸው፡፡

የህክምና ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት እንደ አእምሮ እድገት ውስንነት ያሉ እክሎች በአንድ በኩል በተፈጥሮ ሊከሰቱ ይችላሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ እናቶች በእርግዝና ወቅት ማድረግ ያሉባቸውን ጥንቃቄዎች ካለማድረግ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

በግጭት አካባቢዎች እናቶች ከእርግዝና ክትትል ጀምሮ ሌላውንም ዓይነት ጥንቃቄ ለመውሰድ ያሉበት ሁኔታ የሚፈቅድላቸው እንዳልሆነ ወ/ሮ ምህረት ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ አሁንም ድረስ የቀጠሉ ግጭቶች የአካል ጉዳተኞችን ቁጥር እንዲጨምር፣ አኗኗራቸውን እንደሚያከፋው እንገነዘባለን ያሉን በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ መሪ ስራ አስፈፃሚው አቶ አለማየሁ ማሞ ናቸው፡፡ በዚህ በኩል ሚኒስቴሩ እየሰራሁ ነው ያለውን ነግረውናል፡፡

አቶ አለማየሁ ከሌሎች ተቋማት ጋር በጉዳዩ ላይ በቅንጅት እንሰራለን ከማለት ውጪ ስለሚያደርጉት የተለየ ድጋፍ አልነገሩንም፡፡

የአካል ጉዳትን በተመለከተ ማህበረሰቡ ያለው አመለካከት አልተቀየረም የሚሉት አቶ አለማየሁ በየተቋማቱ ለአካል ጉዳተኞች የተመቸ አገልግሎት መኖር አለመኖሩን ክትትል አድርገን እንዲያስተካክሉ ምክረ ሃሳብ እንሰጣለን ብለውናል፡፡

ሃላፊው ይህንን ቢሉም አሁንም ድረስ የአካል ጉዳተኞች የተለያዩ መገለሎችና ፆታዊ ጥቃቶች ጭምር እንደሚደርስባቸው የፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ ነግረውናል፡፡

በኢትዮጵያ ከ5 ሚሊዮን በላይ የአእምሮ እድገት ውስነት ያለባቸው ሰዎች እንዳሉ ከሃላፊዋ ሰምተናል፡፡

ምንታምር ፀጋው

@ሸገር ኤፍኤም

Zehabesha

05 Nov, 12:35


በአማራ ክልል እየተካሄደ እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት አሜሪካ አስታወቀች ። የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊንከን እንዳሉት የርስ በርስ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው ።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ብሊንከን "በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ያሳስበኛል" ብለዋል። ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶችን ጨምሮ የውስጥ ግጭቶችን ለመፍታት የፖለቲካ ውይይት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ «በፕሪቶሪያው ስምምነት እና አፈጻጸሙ ዙሪያ » መነጋገራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማግረግ የምታደርገውን ጥረት የሀገራቸው እገዛ እንደማይለያት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊነክን በአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና እየተባባሰ ነው ያሉት ውጥረት እንዲረግብ በዚሁ ጊዜ መጠየቃቸውን ዘገባው አመልክቷል።

@DW

Zehabesha

05 Nov, 05:17


https://www.tiktok.com/t/ZTFvgERDx/

Zehabesha

04 Nov, 19:20


https://youtu.be/ktzRg_U03nU

Zehabesha

04 Nov, 16:32


https://youtu.be/4Q8FGvYLO7s

Zehabesha

04 Nov, 00:43


https://www.tiktok.com/t/ZTF7PcDhG/

Zehabesha

03 Nov, 22:25


https://youtu.be/kDbqywDXScw?si=ei0LM1uDujyS8x1D

Zehabesha

03 Nov, 22:08


የተቃውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ

Zehabesha

03 Nov, 18:31


ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ የምትሰሩ ወይም የሚሰሩ የምታውቁ የዕለቱን ዜና እንዲመለከቱ እንጠቁማለን።

Zehabesha

03 Nov, 18:05


Manchester United 1 Chelsea 1

Zehabesha

03 Nov, 18:00


Manchester United 1 Chelsea 0

Zehabesha

03 Nov, 15:51


https://youtu.be/-c8Jcy3YdUk

Zehabesha

03 Nov, 15:09


#የሀዘን_መግለጫ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደራ ወረዳ፣ አድዓ መልኬ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኦነግ ሸኔ(ኦ.ነ.ሠ) ታግተው በግፍ ለተገደሉት የገንዳ አረቡ መስጅድ ኢማም ሼህ ሙሐመድ መኪን ሀጂ አረፉ ፓርቲያችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

ኢማሙ በአካባቢያቸው የተፈሩና የተከበሩ፣ የተጣላ አስታራቂ እንደነበሩና በመስጅድ ውስጥ ሳሉ ከሌሎች 12 የቅርብ ሰዎች ጋር ታግተው በቅድሚያ ለመልቀቅ መደራደሪያ 3ሚሊዮን ብር ተጠይቆ 1.4ሚሊዮን ሰጥተው መሣሪያ ጭምር ካላመጣችሁ በማለትና ቀሪውን ገንዘብ ሲፈልጉ በግፍ ኹሉንም እንደገደሏቸው ለማወቅ ችለናል። ኢማሙ የታገቱት ከወር በፊት እንደነበርና ለማስልቀቅም ከፍተኛ ርብርብ እንደነበር ሰምተናል። በሣምንት ልዩነት እንዲሁ አንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ 800ሺህ ብር ተጠይቆባቸው ብሩንም ከፍለው ከብዙ እንግልት በኋላ በአሰቃቂ ኹኔታ ገድለዋቸዋል። አካባቢው ከፍተኛ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ የሚዘወተርበት በአንጻሩ ግፉ እንዳይነገር በሚዲያ በታገዘ ፕሮፓጋንዳ ጭምር የሚድበሰበስበት ነው።

ፓርቲያችን ደጋግሞ እንዳሳሰበው እንዲህ ከነባር ሃይማኖት ኢትዮጵያን ለማፋታትና ወደአዲሱ የዓለም ሥርዓት/New world order/ ለመውሰድ በሚደረገው ጥድፊያና ርብርብ መንግሥታዊ መዋቅር ጭምር ተከትሎ እየተሠራበት እንደሆነ ለዚህም በዋናነት የሃይማኖት ተቋማትን በቃልም በተግባርም መዳፈር፣ የሃይማኖት አባቶችን እያሳደዱ መግደል፣ ምዕመናንን ማሳሳት፣ ማፈናቀል፣ ዕምነት ተኮር ጭፍጨፋ የስልት ትግበራውና መንገድ ጠረጋው አካል ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ደጋግመን ገልጸናል።

እንዲህ ያለው ተግባር በጥንቃቄ የሚፈጸም በመሆኑ ዛሬ ክርስቲያኑን ነገ ሙስሊሙን ቦታ እየቀያየረ የሚደረግ ነው። እንዲያውም በታሪክ፣ በባህል እንደምናውቀው አንዱ የሌላው መከታና ጠባቂ እንዳይሆን እርስ በእርስ ለማፈጀትም ሴራ ሲጠምቅ ይታያል። ውጤቱ ውሎ አድሮ ያለ ተው ባይና አስታራቂ፣ በጎውን መንገድ ከነውሩ ለይተውና አበጥረው በቃልም በጽሑፍም የሚያመላክቱንን ጠቋሚ አባቶች የሚያሳጣ አካሄድ መሆኑን በውል መረዳት ይገባል።

ፓርቲያችን እንዲህ ያለውን እኩይ ተግባር በጽኑ ያወግዛል፤ ባለ በሌለ ኃይሉም ይታገለዋል።
በድጋሚ በኢማሙ ግፍ ግድያ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጥን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Zehabesha

03 Nov, 13:53


ግምትዎን ያኑሩ..

Zehabesha

03 Nov, 06:24


https://youtu.be/LiZDVLsxQSw?si=-EAEcPNWpleLp3kU

Zehabesha

03 Nov, 00:29


https://www.tiktok.com/t/ZTFWgKrye/

Zehabesha

02 Nov, 21:25


https://youtu.be/LiZDVLsxQSw?si=pj6Getfj_hhUY0me

Zehabesha

02 Nov, 17:28


https://youtu.be/LiZDVLsxQSw

Zehabesha

02 Nov, 14:38


https://www.tiktok.com/t/ZTFWB4aJm/

Zehabesha

02 Nov, 14:22


ቅዳሜ ገበያ በአማዞን ላይ። እስከ 46% ቅናሽ ለዛሬ ብቻ የተደረገባቸውን ምርቶች ይመልከቱ። ምናልባት የሚፈልጉትን ሊያገኙ ይችላሉ። https://amzn.to/3YPm84M

Zehabesha

02 Nov, 11:40


በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎች የጊዜ ጉዳይ እንጂ ተጠያቂነትን ያስከትላሉ!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የእናት ፓርቲ መግለጫ

አገራችን ኢትዮጵያ የምታራምደው የጎሳ ፖለቲካ ሕዝባችንን በጎሳ ከፋፍሎ ሀይ ባይ ሳይኖር ማጫረስ ከጀመረ ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል። ይህን ተከትሎ የሚፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ባለፉት አምስትና ስድስት ዓመታት ውስጥ በአገራችን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የገዘፉ አተገባበራቸውም ከዕለት ዕለት የከፋ እንደሆነ መላው የአገራችን ሕዝብ እንዲሁም ዝምታን የመረጠው የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም የሚያውቀው ነው።

በዚሁ ተረኛ ማንነት ተኮር የጅምላ ጭፍጨፋ ማስፈጸሚያ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. ከምሽቱ ኹለት ሰዓት እስከ እኩለ ለሊት በዘለቀ ዘመቻ በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ቦራ ወረዳ ቢጢሲ ቀበሌ ገብሬ ማኅበር የኦሮሞ ነጻነት ታጣቂዎች እንደፈጸሙት በተገለጸ ጭፍጨፋ ከሰላሳ ስምንት በላይ ዜጎቻችን በየመኖሪያ ቤቶቻቸው እንዳሉ በር ተዘግቶ እሳት ተለኩሰባቸው እንዳለቁ እናት ፓርቲ በከፍተኛ ሐዘን ከአካባቢው ነዋሪዎች ለመረዳት ችሏል። ከእነዚህ በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀና አስከሬናቸው ያልተገኘ ዜጎች መኖራቸውም ጭምር ተገልጿል።
የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት የስድስት ወር ሕጻንን ጨምሮ፣ አረጋውያን፣ ሴቶች፣ ሕጻናትና አካል ጉዳተኞች እንደሆኑ ፓርቲያችን መረዳት ችሏል የተከሰተውን የጅምላ ጭፍጨፋም በጽኑ ያወግዛል።

እናት ፓርቲ የፖለቲካ ዓላማን ለማስፈጸምም ሆነ የመንግሥትን ሥልጣን ለማጽናት ከሚወሰዱ የኃይል እርምጃዎች አገራችን ወጥታ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ድርድር ብቻ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ለዚህም ኹሉም ወገን ፈቃደኛ ሊሆን ራሱንም ዝግጁ ሊያደርግ እንደሚገባ በቀደሙት ጊዜያት በተደጋጋሚ አሳስቧል። ይህን ለማድረግ ፍላጎት ሊኖር ባልቻለበት ኹኔታ ተዋጊ ኃይሎች በኹለቱም ወገን በንጹሐን ዜጎቻችን ላይ የሚፈጽሟቸው ይህን መሰል የጅምላ ጭፍጨፋዎች የጦር ወንጀል ሲሆኑ አገር ዛሬን ተሻግራ ወደ አዕምሮ ስትመለስ በየትኛውም ወገን ይሁን የእያንዳንዱ በግፍ የጠፋ ዜጋ ሕይወት ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል ለአፍታም ቢሆን ሊዘነጋ አይገባም።

ድሃ ሕዝባችን ከችግሩ እንዲወጣ ባናግዘው ቀን እስኪያልፍ እስከ ችግሩም ቢሆን መኖር እንዲችል ፍቀዱለት ሲል ፓርቲያችን በዚህ አጋጣሚ ተማጽኖውን ሊያቀርብ ይወዳል። በቀበሌው የተከሰተውን የጅምላ ጭፍጨፋ አስቀድሞ መከላከልና ማስቀረት ከዚያም በመለስ ጉዳቱን መቀነስ ይቻል እንደነበር የሚታመን ሲሆን ይህንን ማድረግ ያልቻለን ሥርዓት አጥፊዎችን ፈልገህ ለተጎጂዎች ፍትህ ስጥ ብሎ መጠየቅ ራስን ማሞኘት እንደሆነ እናምናለን።

እግዚአብሔር የሞቱትን ነፍስ በደጋጎች አጠገብ እንዲያሳርፍ፤ ለተጎጂ ቤተሰቦችና መከራ ለጸናበት መላው የአገራችን ኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እንዲሰጥ እየተመኘን ጥቃቱ በደረሰበት አካባቢ የሚኖሩ ወገኖቻችን ተጨማሪ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ነቅተው ራሳቸውን ከአጥቂዎች የመከላከል ሥራ እንዲሠሩ እናሳስባለን።

እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

Zehabesha

01 Nov, 22:07


በአንድ ቀን ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ከደቂቃዎች በፊት በአዋሽ አካባቢ ተከስቷል::
ንዝረቱ ተሰምቷችሗል::

Zehabesha

01 Nov, 19:39


መሬት መንቀጥቀጥ ዛሬም ተከስቷል::

ከምሽቱ 3:57 ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በአፋር አዋሽ እና አካባቢው አሁን መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዘሐበሻ ነግረዋል::

የጀርመን ሪሰርች ማዕከል መጠነኛ የሆነ (4.9) የመሬት መንቀጥቀጥ ከመተሃራ 24 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መመዝገቡን አስታውቋል::

Zehabesha

01 Nov, 17:47


https://youtu.be/sHlCVzQ70ok

Zehabesha

01 Nov, 17:42


የፓርላማ አባሉ ሚስት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስኪያጅን ደበደበች። የት? እንዴት? ለምን? ዝርዝሩን ከዕለቱ ዜናችን ይመልከቱ፡፤

Zehabesha

01 Nov, 17:29


በቤኒሻንጉል ክልል የቡለን ጤና ጣቢያ የህክምና ባለሙያዎች የሠራንበት የ10 ወር የትርፍ ሰዓት ዲዩውቲ ክፍያ እስካሁን አልተከፈለም ይብቃን ይከፈለን በማለት ድምጻቸውን በአደባባይ በማሰማታቸው ለእስር ተዳርገዋል ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ገለፁ::

Zehabesha

01 Nov, 17:15


በሶዶ ጉራጌ(ክስታኔ) እራሱን ሸኔ ብሎ የሚጠራው ቡድን በርካት ሰዎችን መግደሉ ተሰምቷል::

Zehabesha

01 Nov, 17:04


https://www.youtube.com/watch?v=fcN5HsSbZM8

Zehabesha

01 Nov, 16:52


በአፋር ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ ጋቸኒ ቀበሌ ትናንት ንጋት 11:00 ሰዓት በጣለው ከባድ ዝናብ አንድ መኖሪያ ቤት በመደርመሱ ከ20 በላይ ፍየሎች እና በጎች ሞተዋል በዚህም ከ 150,000 ብር በላይ ጉዳት መድረሱን አርጎባ ኤፍ ኤም 98.6 ዘግቧል።

Zehabesha

01 Nov, 15:24


በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት ንጉሤ ኮሩን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በኦሮሞ ነፃነት ጦር (ኦነጦ) ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ። ዝርዝሩን ተመልከቱ።

Zehabesha

01 Nov, 13:54


https://youtu.be/fcN5HsSbZM8

Zehabesha

01 Nov, 12:36


"ችግሮቻቸውን በመመካከር ለመፍታት ቃል እንዲገቡ ባቀረብነው ጥያቄ ላይ አዎንታዊ ምላሽ አግኝተናል" የትግራይ የሃይማኖት አባቶች

Zehabesha

01 Nov, 02:53


https://youtu.be/-mnFdkc4KTQ?si=Num9oIPE5lDz8EFa

Zehabesha

31 Oct, 22:15


https://youtu.be/-mnFdkc4KTQ?si=CDWJpKsoTVYJ14kW

Zehabesha

31 Oct, 18:00


https://youtu.be/-mnFdkc4KTQ

Zehabesha

31 Oct, 15:32


https://www.youtube.com/watch?v=zRU08U0ecxA

Zehabesha

31 Oct, 14:52


የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ልዑል እግዚአብሔርን አጋዥና መሪ በማድረግ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ስለምጣኔ ሀብት እድገት፣ በሀገራችን እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን
አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ 43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች የቀረበው ቃለ ጉባኤና የአቋም መግለጫ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
2. በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡
3. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ እየቀረቡ ያሉ መጠነ ሰፊ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ በክፍላተ ከተሞችና ችግር አለባቸው ተብለው በጥናት በሚለዩት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የማጣራት ሥራ እንዲሠራና ውጤቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ በሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
4. የኦሲኤን ቴሌቪዥን ስርጭት የተቋረጠ በመሆነ በአዲስ መልክ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ባቀፈ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ኔትወርክ በሚል ስያሜ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ውል ተፈርሞ በአዲስ መልክ የሳተላይት ግዥ እንዲፈጸም ሆኖ አስተዳደሩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ጋር በአንድ ሊቀ ጳጳስና ቦርድ ራሱን በቻለ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ አገልግሎቱ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ
ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
5. የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት አድቫንስ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሆን ሥርዓተ ትምህርቱ ለሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ በሚመጥን መልኩ ተሟልቶ፣ ሊኖረው የሚገባው የሰው ኃይል በየዘርፉ ተጠናክሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፣
6. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሥነ ሕንጻና በኪነ ጥበብ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ በመዐርገ ጵጵስና ፕትርክና የሚሾሙ አባቶች ሥርዓተ ሲመት የሚፈጸምበት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለዕድሳት ሥራው የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ በተጨማሪም ምእመናን እስከ አሁን እንደሚያደርጉት ሁሉ ለእድሳት ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ
ያሳስባል፡፡
7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በንቃት እንዲሳተፍ ሁሉንም አህጉረ ስብከት ባቀፈ ሁኔታ የአጀንዳ መረጣና ተሳታፊ የመለየት ሥራ እንዲከናወን ሆኖ ዐቢይ ኮሚቴው የሥራ ዕቅዱንና አፈጻጸሙን ለቋሚ ሲኖዶስ እያቀረበ በማስወሰን እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ በማኀበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡


እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

Zehabesha

30 Oct, 18:00


https://youtu.be/STC2pPkQGFY

Zehabesha

30 Oct, 15:49


https://youtu.be/JS5apURALRg?si=pbKB3rSZjU30n19G

Zehabesha

30 Oct, 15:03


የሮብ ገበያ በአማዞን። እስከ 51% ቅናሽ ለዛሬ ብቻ። የሚፈልጉትን ሊያገኙ ስለሚችሉ ይመልከቱ https://amzn.to/3NMfdTJ

Zehabesha

30 Oct, 14:02


በግጭቶች እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት 5 ሺሕ 568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተገለጸ

በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች በተከሰቱ እና በቀጠሉ ግጭቶች እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት 5 ሺሕ 568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያተኮረ ባለ 25 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት አውጥቷል።

በሪፖርቱም በትግራይ ክልል 105 ገደማ ትምህርት ቤቶች በጦርነት በመውደማቸውና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በመሆናቸው ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ገልጿል።

እንዲሁም ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 52፣ በአፋር ክልል 17፣ በአማራ ክልል 14፣ በኦሮሚያ ክልል 11፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 11 እና በጋምቤላ ክልል 11 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን አስታውቋል።

ኢሰመኮ በሰኔ ወር እና ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ባሰባሰበው መረጃ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ እና በቀጠሉ ግጭቶች እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት፤ በአማራ ክልል 4 ሺሕ 178፣ በትግራይ ክልል 648፣ በኦሮሚያ ክልል 420፣ በሶማሊ ክልል 195፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 50፣ በጋምቤላ ክልል 40፣ በአፋር ክልል 26 እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 8 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የጸጥታ ሁኔታው አንጻራዊ መሻሻል ባሳየባቸው አካባቢዎች ደግሞ መምህራን አካባቢውን ለቀው የሄዱ በመሆናቸው የመምህራን እጥረት መኖሩን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ በአካባቢዎቹ አስተማማኝ ጸጥታ ባለመኖሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንደማይልኩ አስታውቋል።

በተጨማሪም "በአንዳንድ አካባቢዎች መምህራን ትምህርት ቤት ውስጥ ለመገኘት በተለይም ሴት መምህራን የመደፈር እና የመዘረፍ ሥጋት ያለባቸው በመሆኑ ትምህርት ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል" ሲል ገልጿል።

ኮሚሽኑ በተጨማሪ የጤና ጉዳዮችንም በሪፖርቱ ያነሳ ሲሆን፤ "ባለሙያዎች ደመወዝ ወቅቱን ጠብቆ በአግባቡ ባለመከፈሉ ሳቢያ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሕክምና አገልግሎት እንዲስተጓጎል ምክንያት ሆኗል" ብሏል።

በተጨማሪም "የመድኃኒት እጥረት እና በግጭት ምክንያት የጤና ተቋማት በቂ አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል" ሲል ገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ አክሎም በአማራ ክልል ያለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት የተለያዩ የጤና ተቋማት ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሠሩ ከማድረጉ በተጨማሪ፤ የሕክምና መሣሪያ፣ መድኃኒት፣ ደም፣ ኦክስጂን እና ሌሎች ግብአቶች አቅርቦት እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑንም አመላክቷል።

ኢሰማኮ በሪፖርቱ መንግሥት በትጥቅ ግጭትም ሆነ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቋል።

የወደሙ ትምህርት ቤቶች እንዲገነቡ እና መልሰው እንዲቋቋሙ ለማድረግ በቂ በጀት ተይዞላቸው በዕቅድ ውስጥ መካተታቸውን እንዲያረጋግጥ የጠየቀው ኢሰመኮ፤ ትምህርት ቤቶቹ መደበኛ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምሩ መንግሥት ጊዜያዊ የመማሪያ አማራጮችን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሔዎችን እንዲያመቻች እንዲሁም አስፈላጊ የትምህርት ቁሳቁሶችን እንዲያሟላሜ አሳስቧል።

በተጨማሪም በትጥቅ ግጭት ሳቢያ የወደሙትን መሠረተ ልማቶች በመጠገንና አገልግሎቶችን በፍጥነት ወደ ሥራ በማስገባት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች በተሻለ ሁኔታ የሚረጋገጡበትን መንገድ እንዲያመቻች ኮሚሽኑ ምክረ ሃሳቡን ሰጥቷል፡፡

@አሐዱ ሬዲዮ

Zehabesha

30 Oct, 13:55


በዎላይታ ዞን በከፍተኛ መጠን በጣለው ዝናብ በተከሰተው የመሬት ናዳ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ።

በዚሁ በትላንትናው ዕለት ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በካዎ ኮይሻ ወረዳ 01 ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባለት በሙሉ እና ሌሎች ላይ አደጋ ደርሷል።

በዎላይታ ዞን በካዎ ኮይሻ ወረዳ በኮይሻ ላሾ ቀበሌ ሞግሳ ቀጠና በተከሰተው መሬት ናዳ 4 ሰውና በ01 ቀበሌ 3 ሰው አጠቃላይ የ7 ሰው ሕይወት አልፏል።

Zehabesha

30 Oct, 13:48


🤔

Zehabesha

29 Oct, 22:37


https://www.youtube.com/watch?v=VPtUZBaNuDE

Zehabesha

29 Oct, 19:37


(የቤተሰብ ምንጮች ይስተካከል ባሉት መሰረት ተስተካክሎ የተለጠፈ) በባህርዳር ከተማ ጤና ጣቢያ ውስጥ ትሰራ የነበረችው ሲስተር ስንታየሁ በቪትስ መኪና ሥራ ቦታዋ በመጡ ታጣቂዎች መገደሏን ከቤተሰብ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Zehabesha

29 Oct, 18:52


https://youtu.be/VPtUZBaNuDE?si=0asG5Po47oIEQaOL

Zehabesha

29 Oct, 17:12


https://youtu.be/VPtUZBaNuDE

Zehabesha

29 Oct, 13:28


ከህዳር 1 ጀምሮ ዲጂታል መታወቂያ ያለያዘ ወይም የተመዘገበበትን ማቅረብ ለማይችል ተገልጋይ አገግሎት አልሰጥም ሲል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተናገረ፡፡

ነዋሪዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረባቸው አስፈላጊ መሆኑ አምኜበታለሁ ብሏል ተቋሙ፡፡

ይህ ተግባራዊ ሚደረገው በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ አድርጌዋለሁ ያለው ከሚቀጥለው ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ ም ጀምሮ እንደሆነ በማህበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስታውቋል፡፡

Zehabesha

29 Oct, 11:38


በጉራጌ ዞን “ከ ፋኖ ጋር በተያያዘ” ከ100 በላይ ሰዎች መታሰራቸው ተነገረ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ከሰኔ 2016 ዓ.ም. ወዲህ ከ100 በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች “በሽብር” ተጠርጥረው ሲታሰሩ ስጋት ያደረባቸው ነዋሪዎች ደግሞ አካባቢውን ለቀው መሸሸታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።

በዞኑ አበሽጌ ወረዳ ከሰኔ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ‘ፋኖ ናችሁ፤ የፋኖ ክንፍ ናችሁ፤ ፋኖን በገንዘብ ትደግፋላችሁ’ በሚል የፀጥታ ኃይሎች ድብደባ እና እንግልትን ጨምሮ “ማንነትን የለየ” እስር እየፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን አመልክተዋል።

የአካባቢው የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በቁጥጥር ስር የሚገኙት ነዋሪዎች “በመሳሪያ ዝውውር እና እገታ” ወንጀሎች ተጠርጥረው የተያዙ ናቸው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አብሸጌ ወረዳው ካሉት 30 ቀበሌዎች እና ማዘጋጃዎች 16ቱ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ወላጆች እንደሚኖሩባቸው የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ካለፈው ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ግን ከፋኖ ጋር በተያያዙ ክሶች ምክንያት “እየተሳደድን ነው” ይላሉ።

“ከባለሀብት እስከ ቀን ሠራተኛ፤ ከፖለቲከኛ እስከ ወጣት፤ ከባጃጅ ሹፌር እስከ ሞተረኛ ድረስ” የእስሩ ሰለባዎች እንደሆኑ አንድ አካባቢውን ለቀው የወጡ ነዋሪ ተናግረዋል።

የመንግሥት ሠራተኛ የነበሩ አንድ ነዋሪ የታሰሩ ሰዎች ከ140 በላይ (በወልቂጤ 90 ሰዎች እና ዋልጋ ከ50 በላይ ሰዎች) እንደሚሆኑ ጠቁመው እስሩ አሁንም እንዳላቆመ ገልጸዋል።

@አዲስ ስታንዳርድ

Zehabesha

29 Oct, 11:09


በጌድዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) ሹመት ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ቀረበ

👉 "የተሰነዘረው አስተያየት ጥቅል ፍረጃ ያለበትና ተገቢው ምርመራ ያልተከናወነበት ነው" ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት እያካሄደው በሚገኘው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ፤ የም/ቤቱ አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዬስ (ዶ/ር) ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ሰንዝረዋል።

የምክር ቤት አባሉ በሹመቱ ላይ ባቀረቡት ቅሬታ፤ "የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታችን ሳይነሳ እንደ ሽፍታ ተጎትተን ስንታሰርና ለወራት ስንቀመጥ ምን ሰሩ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

አክለውም፤ "ሌሎች የምክር ቤት አባላት የፌዴሬሽን ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተገቢ ፍትህ ሳያገኙ ለአመታት ሲንገላቱ የፍትህ ሚኒስትር ምንም የሰራው ነገር የለም። ከሳሹ እራሱ የፍትህ ሚኒስትር ነው።" ብለዋል።

ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ሲመጡ ከፍተኛ ተስፋ አድርገው እንደነበር የገለጹት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)፤ ነገር ግን ከሳቸው በፊት ከነበሩት ሚኒስትሮች ምን የተለየ ነገር አለማሳካታቸውን ለምክር ቤቱን ገልጸዋል።

"በሕግ ከውጭ ዩኒቨርሲቲ ፒኤችዲ ይዘው መምጣታቸውና እዚህም ትልቁ የሀገራችን ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማስተማራቸው ላይ ምን ለውጥ አመጡ የሚለው አልተገመገመም" ብለዋል።

"እኔ በግሌ ቅሬታ አለኝ" ያሉት ደሳለኝ (ዶ/ር) " በፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን የእውቀት ችግር አለባቸው ብዬ አይደለም፤ በተለያዩ መድረኮች አይቻቸዋለሁ ሙያቸውን በጣም ጠንቅቀው ያውቃሉ ፤ ነገር ግን አፈጻጸማቸውን ካየነው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቅ የነበረውን የፍትህ ጥማት ከማስታገስና ያን ከማርካት ይልቅ አሁንም የፍትህ ስርዓቱ የፖለቲካ መሳሪያ እንዲሆን አድርገዋል" የሚል ወቀሳም ሰንዝረዋል።

"በሀገራችን በተለይ በኢህአዴግ ዘመን የፍትህ ስርዓቱ ተቃዋሚዎችን ማጥቂያ፣ የፖለቲካ መሳሪያ፣ የገዢው ፓርቲ አንድ አርም ተደርጎ ሲሰራ ነበር አሁንም ያ ተቀይሯል ብዬ አላስብም" ብለዋል።

"ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲፈልገው የነበረውን የፍትሕ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ የፍትሕ ሥርዓቱን ለፖለቲካ መጠቀሚያ አድርገውታል" ሲሉም ተናግረዋል።

"በዚህ ሂደት ውስጥ እንዴት አዲስ የካቢኔ ሹመት ማግኘት አለባቸው የሚለው ሂደትም ተገቢ ግምገማ ሳይከናወንበት የተደረገ ነው የሚል እምነት አለኝ" ሲሉም ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ገልጸዋል።

በመሆኑም፤ "የፍትህ ዘርፉን ከፍተኛ ችግር ውስጥ የከተቱ ስለሆኑ ትራክ ሪከርዳቸው የውጭ ጉዳይን ለመምራት ብቁ ሊያደርጋቸው አይገባም" ብለዋል።

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) አክለውም የሚኒስትሮች ሹመት ሂደት ላይ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፤ "የሚነሱ ሚኒስትሮች ከሾምናቸው በኃላ ምን አጉለው እንደተነሱ፣ ምን ድክመት እንዳሳዩ፣ ወይ ምን የስነምግባር ጥሰት እንዳሳዩ አይቀርብም፣ በተጨማሪም እነሱን የሚታኳቸው ሚኒስትሮች ከነሱ በምን እንደሚሻሉ አይነገረም " ሲሉ ተናግረዋል።

"ይህም ከግልጽነት እና ከተጠያቂነት መርህ አንጻር ጥያቄ እየሚያስነሳ ነው" ሲሉ አሳስበዋል።

የመንግሥት ተጠሪ ሚንስትር የሆኑት ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ "የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በተሸሙት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ላይ የተሰነዘረው አስተያየት ጥቅል ፍረጃ ያለበትና ተገቢው ምርመራ ያልተከናወነበት ነው" ሲሉ ለቀረበው ወቀሳ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አክለውም "ተሿሚን ብቁ አይደሉም በሚል የተሰጠው ጥቅል ፍረጃም ነባራዊውን ሁኔታ ያገናዘበ ነው ለማለት ይከብደኛል" ሲሉ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት እየተካሔደ በሚገኘው የምክርቤቱ መደበኛ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሹመት በቀረቡት አምስት ሚኒስትሮች ሹመት ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ሹመቱም በአንድ ተቃውሞ፣ በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።

@አሐዱ ቲቪ

Zehabesha

27 Oct, 19:23


https://youtu.be/xCnRuZqAMLA?si=PsNGaWTPufpnjoyy

Zehabesha

27 Oct, 17:56


https://youtu.be/xCnRuZqAMLA

Zehabesha

27 Oct, 17:17


የአርሰናል ሁለተኛው ጎል በቫር ታይቶ ፀድቋል::

Arsenal 2 Liverpool 1

Zehabesha

27 Oct, 17:10


የሊባኖስ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስና በመካከለኛው ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኝው የሊባኖስ ሐመረ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና ሰበካ ጉባኤ በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት ተጠልለው የሚገኙት ኢትዮጵያውያንን ጎበኙ፡፡

በሀገረ ሊባኖስ በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት ከቤታቸው ተፈናቅለው በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀኔራል ጽሕፈት ቤት በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መጠለያ (ሼልተር) ከ250 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተጠልለው የሚገኙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ይህንን ተከትሎም ቤተ ክርስቲያኗ በአጥቢያው የሚገኙ ምእመናንን በማስተባበር የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያና ደረቅ ምግብ መለገስ መቻሉና የማጽናኛ መርሐ ግብር መከናወኑ ተጠቅሷል፡፡

የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን ቆሞስ አባ ጴጥሮስ ወ/ማርያም ዜጎችን እንዲጠለሉ ያደረጉትን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ጽሕፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማኅበርን አመስግነው ይህ ዓይነቱ ጉብኝት ቀጣይነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አስተዳዳሪው አክለውም በሁሉም ዓለም የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ መልእክት አስተላልፈዋል ሲል የሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ማዕዶት ገልጿል ።

@ማህበረ ቅዱሳን

Zehabesha

27 Oct, 16:49


Arsenal 1 Liverpool 1

18 minutes

Zehabesha

27 Oct, 16:45


Arsenal 1 Liverpool 0

Zehabesha

27 Oct, 13:55


https://youtu.be/ECvvNNYgTfU

Zehabesha

27 Oct, 13:28


በፍራንክፈርት የማራቶን ውድድር ሀዊ ፈይሳ ክብረ ወሰኑን በማሻሻል ውድድሩን በአሸናፊነት ጨርሳለች::

Zehabesha

27 Oct, 12:44


የጋራ መኖሪያ (ኮንዶሚኒየም) ቤት ለማግኝት ተመዝግበው ገንዝብ በባንክ ሲቆጥቡ የነበሩና እስካሁን ቤቱን ያላገኙ የ1997 ዓ.ም. ተመዝጋቢዎች አቤቱታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ካልሰጠበት፣ በ15 ቀናት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርበው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡

@ሪፖርተር

Zehabesha

27 Oct, 12:41


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት፣ በሕጋዊ መንገድ ለብሔራዊ ባንክ ከተሸጠው 17 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ወርቅ ይልቅ፣ በሕገወጥ መንገድ እየወጣ ያለው ወርቅ መጠን በሦስት ወይም በአራት እጥፍ እንደሚበልጥ ተናገሩ።


ባለፈው ሳምንት ከተለያዩ የትግራይ ክልል ማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች፣ በተደጋጋሚ በክልሉ ስለሚካሄዱ የወርቅ ግብይቶች የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሽረ እንዳስላሴ ቅርንጫፉ በሦስት ወራት ውስጥ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ በመፈጸም ከገዛው 13.4 ኩንታል ወርቅ የክልሉ አስተዳደር ምንም ዓይነት ገቢ እንዳላገኘ ገልጸዋል፡፡ የኮንትሮባንድ ወርቅ፣ ግብይት የደረሰበትን የከፋ ደረጃም አጽንኦት ሰጥተው አስረድተዋል።
አቶ ጌታቸው የሕገወጥ ወርቅ ማውጣትና ግብይት ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ ‹‹እየሆነ ያለው ነገር በፖለቲካ አመራሩ ጭምር ከሽፍትነት ለመውጣት ፍላጎት የሌላቸው ሰዎች እንዳሉ ነው የሚያሳየው፡፡ ጉዳዩን በባለሙያዎች አስጠንተናል፣ በጣም ነው የሚገርመው፡፡ ዘረፋ ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ አዲያቦ፣ አስገደ ብትሄዱ በጣም ብዙ ተራሮች እየታረሱ ነው፡፡ አርሶ ትንሽ ማገገም ጀምሮ የነበረው ሕዝባችን፣ ወርቅ ለማውጣት ጥቅም ላይ በሚውሉ ኬሚካሎች በሬና ፍየሎቹን እያጣ ነው፤›› ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በኮንትሮባንድ ዘርፉ የተሰማሩ አካላትን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል። ‹‹በራሳችን መዋቅር ውስጥ ያሉ ረዥም ኔትወርክ ያላቸው ሰዎች እዚህ ውስጥ ተሳታፊ እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ ግዙፍ የወርቅ ማውጫ መሣሪያዎችን ከውጭ አስገብተው ሕገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል፡፡ ይህን በማድረግ ፈንታ ሠራዊቱ ልብሱን የሚቀይርበትንና ቀለቡ የሚሟላበትን ሁኔታ ብንፈጥር መልካም ነበር፡፡ ይህን ለማድረግ ብንጥርም እንቅፋቶቹ ብዙ ናቸው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ችግሩን ለመፍታት አንድ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ቢገባም፣ የኮንትሮባንድ ዘርፉን ለማስቆም አስተዳደሩ እጅግ መቸገሩንና የክልሉ ሕዝብ በጉዳዩ መማረሩ ተገልጿል።
በትግራይ ክልል ተባብሶ በቀጠለው የወርቅ ኮንትሮባንድ ንግድ ከውጭ የመጡ አካላት ጭምር እየተሳተፉበት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹ከሕዝብ ምሬት በላይ ደግሞ ዓለም አቀፍ ወንጀል ነው፡፡ በየት በኩል እንደመጡ የማይታወቁ ቻይናውያን፣ ስዊድናውያንና ሌሎችም የውጭ ዜጎች እዚህ ሕገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል፡፡ መሬታችን በጣም እየተቆፈረ ነው፡፡ ሌላኛው የህልውና ሥጋት ሆኖብናል፤›› ብለዋል፡፡
የኮንትሮባንድ ንግዱን ማስቆም ባለመቻሉ በጄኔራሎች ላይ ወቀሳ ሲቀርብ መታዘባቸውን የገለጹት አቶ ጌታቸው፣ ኮንትሮባንዱን ለማስቆም ስለተቋቋመው ቡድንና ስለአጠቃላይ ሁኔታውም ምላሽ ሰጥተዋል።
‹‹በዚህ ረገድ ሠራዊታችን ይህንን የማስቆም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠንካራ የሠራዊት አመራሮች በግብረ ኃይሉ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ የሠራዊት አመራሮች አሉበት እንደተባለው ሁሉ የፖለቲካ አመራሮችም አሉበት፡፡ ነገር ግን በጅምላ የሠራዊት አመራር የሆኑ ጄኔራሎች ብቻ ሲወቀሱ እያየን ነው፣ ይህ ተገቢ አይደለም፡፡ በዚህ ሕገወጥ ተግባር ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል ያለ ምንም ማንገራገር ልንታገለው ይገባል፤›› ብለዋል።

@ሪፖርተር

Zehabesha

27 Oct, 12:26


የባርሴሎናው ላሚን ያማል በትናንቱ የኤልክላሲኮ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች የዘረኝነት ስድብ ማስተናገዱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ እና ላሊጋው ይህንን ያደረጉት ደጋፊዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወስዱ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

Zehabesha

27 Oct, 12:07


https://www.tiktok.com/t/ZTFgeB95W/

Zehabesha

27 Oct, 11:14


የዛሬውን ጨዋታ ግምትዎን ያስቀምጡ::
ማን ያሸንፋል?


አርሰናል ከ ሊቨርፑል

Zehabesha

27 Oct, 10:44


ዮሚፍ ቀጄልቻ የስፔን ቫሌንሺያ የግማሽ ማራቶን አንድ ሰከንድ በማሻሻል ሪከርዱን በመስበር አሸነፈ::

Zehabesha

26 Oct, 21:31


https://youtu.be/L1bjDT5ASzA?si=9fhOelDya2n0CQyJ

Zehabesha

26 Oct, 17:31


https://youtu.be/L1bjDT5ASzA

Zehabesha

26 Oct, 14:58


https://youtu.be/i-9Q_ZYUTkk

Zehabesha

26 Oct, 14:10


አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ

በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ማንነትን ማዕከል ያደረገ የከፋ እልቂት ከፊታችን ተደቅኗል፤ ድምፃችንን አሰሙልን ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተማጽነዋል።

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ከአንድ የፀጥታ ኃይል አዛዥ ጋር ከጠዋቱ ፬ ሰዓት እስከ ፲፩ ሰዓት እንደ ተደረገ በተገለጸልንና እጅግ ውጥረት የተሞላበት ውይይት የቀበሌው ነዋሪዎች መሣሪያቸውን እንዲያወርዱ ካልሆነ ግን የከፋ ነገር እንደሚጠብቃቸው በእርሳቸው አባባል "ካላወረድክ ... ትታረሳለህ" ማለታቸው እጅግ ሥጋት እንዳሳደረባቸው ለፓርቲያችን የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ሥጋቱ ይህ ብቻ ሳይሆን "እኛ መሣሪያ ካወረድን በሰዓታት ልዩነት ሸኔ መጥቶ ይጨፈጭፈናል፤ ይህ ደግሞ ያለፉ ዓመታት የቀን ተቀን ሰቀቀናችን እንደሆነ ማንም ያውቃል" ይላሉ ነዋሪዎቹ።
"መተማመን በሌለበትና እስከዛሬ ማን አሳልፎ እንደሚሰጠን ባወቅንበትና አኹን በጥቂቱ በመንግሥት ጥረትም፣ በሬያችንን እየሸጥንም ገዝተን በታጠቅነው መሣሪያ ራሳችንን ለማትረፍ የአልሞት ባይ ተጋዳይ በምናደርግበት ወቅት እንዲህ መባሉ እጅግ አስገርሞናል" ብለዋል። በአካባቢው በግምት 20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራውና ራሱን ኦ.ነ.ሰ የሚለው ኃይል ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያካሂድበት ቦታ መሆኑንና እስከ አኹንም በጥቂቱም ቢሆን በዚኹ መንገድ ራሳቸውን እየተከላከሉ እንደቆዩ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በጭንቀት ያሉት እነዚሁ የአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ነዋሪዎች ለሞት አሳልፎ የሚሰጠንን ውሳኔ "ብትቀበሉ ተቀበሉት" መባሉ አስገራሚ ነው ብለዋል።
"እጅግ ውጥረት የተሞላበት ውይይት ነበር። እባካችሁ መሐል ላይ ያለ የእኛን ደህንነት የሚያስጠብቅ መፍትሔ ስጡን" እያልን ብንማጸናቸውም ሊረዱን ዝግጁ አልነበሩም፤ ብቻ 'ታወርዳለህ ታወርዳለህ' እያሉ ይዝቱ ነበር" የሚሉት ነዋሪዎች "በመጨረሻም ባለመግባባት ሕዝቡም አዳራሹን ጥሎ ወጥቷል" ብለዋል።

በሰሜኑ ጦርነት ወቅት መላው የጸጥታ ኃይል አካባቢውን ሲለቅ መንግሥት እኛን አምኖ ራሳችንን እየተከላከልን አካባቢውንም እንድንጠብቅ ያደረገ ቢሆንም አኹን ምን ተገኝቶ ቃሉን አጠፈ ይላሉ።

ውይይቱን የመሩት የጸጥታ ኃይል ስምና ማዕረግ የደረሰን ሲሆን በብዙ ምክንያቶች ለጊዜው መጠቀም አላስፈለገንም።

ፓርቲያችን ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን ይኽ አካባቢ የሞት ቀጠና ከሆነ የቆዬና አኹንም ምንም የተለወጠ ነገር ባለመኖሩ ከሰማናቸው ኹሉ የባሰ ዘግናኝ እልቂት ከመፈጸሙ በፊት በተለይ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጉዳዩን በገለልተኝነትና ከነባራዊ ኹኔታ ጋር የተገናዘበ መፍትሔ እንዲሰጡት በአደራ ጭምር ልናሳስብ እንወዳለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፲፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

@እናት ፓርቲ

Zehabesha

25 Oct, 21:36


https://youtu.be/MzAolGW9I1A?si=CxRiZ54jfkOcjD5w

Zehabesha

25 Oct, 20:19


"በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የሚፈጸም ወንጀልን በፅኑ እናወግዛለን! የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን ጥረት እናደንቃለን" ኢዜማ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ወንጀሎች ስትል በሀገሪቱ የበላይ ሕግ በሆነው ሕገመንግሥት አንቀጽ 28 ካሰፈረቻቸው መካከል አንዱ አስገድዶ የመሰወር ድርጊት ሲሆን ይህ ወንጀል በይቅርታ እና ምሕረት የማይታለፍ እንዲሁም በይርጋ የማይገደብ እንደሆነ ሕጉ ይደነግጋል። ይሕ ወንጀል ሲፈጸም በርካታ የሆኑ ሌሎች ሰብዓዊ መብቶችን የሚንድ ከመሆኑ ባሻገር ወንጀሉ የሚፈጸምበትን ግለሰብ ሥነልቦናዊ፣ ማኅበራዊ እና የምጣኔ ሀብት ሕይወት እጅጉን ያናጋል።

በሀገራችን ባለፉት መንግሥታት መሰል ጭካኔ ይፈጸም እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ይዘቱም በአብዛኛው ፖለቲካዊ እንደነበረ ይታወሳል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አሁን ኢትዮጵያን በሚያስተዳድረው የብልጽግና መንግሥት ይህ ወንጀል እየተበራከተ መሆኑ ያሳስበኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተጨባጭ ምርመራ ላይ ተመሥርቶ ግንቦት 28/2015 ዓ.ም. “በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል” ሲል በዚህ ወንጀል ላይ ብቻ መሠረት አድርጎ ባወጣው መግለጫ፣ ግንቦት 20/2016 ዓ.ም. “በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጪ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች አሳሳቢነት እና ሥጋቶች” ሲል ባወጣው መግለጫ ከተራ ቁ 36-40 በዚህ የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚወድቁ ጥሰቶችን በመዘርዝር እና ሰኔ 28/ 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖርት ከገጽ 48-49 ለሕዝብ እና ተጠሪነቱ ለሆነው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አሳውቋል። ጥቅምት 13/ 2017 ዓ.ም. በተመሳሳይ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ ደግሞ የወንጀሉ ተጠቂ የሆኑ በርካታ ዜጎችን ጭምር በስም እና በአድራሻ ጠቅሶ መግለጫ ማውጣቱ እንደወትሮው ሁሉ የተመለከትን ሲሆን መንግሥት በጉዳዩ ላይ ይህ ነው የሚባል ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ እስካሁን አልሰጠም።

በመሠረቱ መንግሥት የተቋቋመበት ዐብይ ተግባር የሆነውን የዜጎችን ደኽንነት በማስከበር፣ ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ፣ መማር፣ መሥራት እና ንብረት ማፍራት እንዲችሉ በማድረግ ኃላፊነቱን ሊወጣ ሲገባ እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት የዜጎች ደኽንነት አደጋ ውስጥ በወደቀባት በአሁናዊ ነባራዊ የሀገራችን ሁኔታ ለእነዚህ አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ሲገባው፤ እንደተደራጀ የማፍያ ቡድን ታርጋ በሌለው መኪና ዜጎችን እያፈኑ የማይታወቅ ቦታ መሰወር ግለሰቡ ላይ ከሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ባሻገር ቤተሰቦችን አላስፈላጊ ጭንቀት መዳረግ ላይ መሠማራቱ አሳፋሪ ተግባር ነው::

ከዚህ በተጨማሪ በዋነኛነት ዜጎች ይጠብቀኛል፣ መብቴንም ያስከብርልኛል ብለው ያቋቋሙት መንግሥት የሥጋታቸው ምንጭ ሲሆን ግለሰቦች ፍትሕን በራሳቸው እጅ ብቻ እንዲያገኙ የሚገፋቸው ሲሆን የሕግ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባበት ሁኔታን ፈጥሮ ሀገርን የለየለት ሁከት ውስጥ የሚከት አስነዋሪ ተግባር መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይህን በመንግሥት እየተፈጸመ ያለ የወንበዴ ተግባር ፍጹም የምናወግዘው መሆኑን እንገልጻለን!! በዚህ ድርጊት በቀጥታ እጃቸዉ ያለበት እንዲሁም ይህን ድርጊት ማስቆም ሲገባቸዉ ሆነ ብለዉም ሆነ በቸልተኝነት እርምጃ ሳይወስዱ የቀሩ አካላት በሙሉ ነገ ከሕሊናም ሆነ ከሕግ ፍርድ ሊያመልጡ የማይችሉ መሆኑን እንገልጻለን!!

በመሆኑም፤

1. መንግሥት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያወጣውን መግለጫ ተመልክቶ አፋጣኝ የሆነ ምላሽ እንዲሰጥ

2. አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ይህንን የዜጎችን ሕይወት አደጋ ላይ የጣሉ የወንጀሉ ቀጥተኛ ተሳታፊ የፀጥታ አካላትን ወደ ሕግ ፊት እንዲያቀርብ

3. ይህንን ሕገወጥ ተግባር ሊያስቆሙ ሲገባቸው ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ የሥራ ኃላፊዎች ላይ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ወስዶ ለሕዝብ እንዲያሳውቅ

4. አሁንም በተመሣሣይ መንገድ በግዳጅ ተሰውረው የሚገኙ ሰላማዊ ዜጎችን ፈልጎ ነፃ እንዲያወጣ እና ለደረሰባቸው ጉዳት በመካስ መንግሥታዊ ግዴታውን እንዲወጣ

5. በተለያዩ ጊዜያት የዚህ ሕገወጥ ተግባር ሰለባ የሆኑ ዜጎች ከደረሰባቸው ሥነልቦናዊ፣ ማኅበራዊ እና የምጣኔ ሀብት ቀውስ እንዲያገግሙ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው

6. ኢሰመኮ በተደጋጋሚ ጥያቄ ያቀረበው ፓርቲያችንም የሚቀበለው ዓለም አቀፉን ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ድርጊት የመጠበቅ ሥምምነት ሀገራችን እንድትፈርም እንጠይቃለን።

ሀገር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሰፈነባት እና የተረጋጋች እንድትሆን በወጥነት ኃላፊነት እና ተግባራቸውን የሚወጡ ለሕግ የሚገዙ ተቋማት ሲኖሩ ብቻ እንደሆነ ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል። ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ይህንን አይነት ቁመና ላይ ለመገኘት እየጣረ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሚበረታታ ተግባር አሁንም በድጋሚ እንደምንደግፍ እንገልጻለን፤ ሌሎች መሰል ተቋማትም የኢሰመኮ-ን ፈለግ ሊከተሉ እንደሚገባ ለመግለጽ እንወዳለን።

Zehabesha

25 Oct, 18:03


https://youtu.be/MzAolGW9I1A

Zehabesha

25 Oct, 17:15


በዎላይታ ዞን በርካታ መምህራን መታሰራቸው ተሰማ:: እሥሩ የተፈፀመው መምህራኑ ከደሞዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ አቤቱታቸውን ለማስገባት መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ እንደሆነም ምንጮች ገልፀዋል::

Zehabesha

25 Oct, 17:09


ለክረምትሽ የሚሆን ድሪም ፓሪስ ቡትስ በ-33% ቅናሽ $39 ብቻ ቀርቦልሻል። ተመልከቻቸው https://www.amazon.com/dp/B0D4M82FY6

Zehabesha

25 Oct, 16:32


በወላይታ ዞን በተለያዩ ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ አምስት የቀድሞ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በወላይታ ዞን በተለያዩ ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ አምስት የቀድሞ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ተጠሪጣሪዎች የመንግሥትንና የህዝብን አደራና ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው በሙስና እና በተለያዩ ወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ፖሊስ የገለጸው።

በቁጥጥር ስር የዋሉት፦

1ኛ. አቶ ተመስገን አለማየሁ የቀድሞ የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ እና የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የቀድሞ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ የነበሩ

2ኛ. አቶ መስፍን ዳዊት የቀድሞ የወላይታ ዞን የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የአረካ ከተማ ከንቲባ የነበሩ

3ኛ. አቶ ማዕረጉ አስራት የቀድሞ የሆብቻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩ

4ኛ. ወ/ሮ ተዋበች ተረጬ የቀድሞ የአረካ ከተማ የመንግስት ረዳት ተጠሪ እና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

5ኛ. አቶ ከበደ ካንፌሶ የቀድሞ የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

አመራሮቹ በቁጥጥር ሥር ዉለዉ በህግ እንዲጠየቁ ምርመራ መጀመሩን ፖሊስ ገልጿል።

በመጨረሻም ህብረተሰቡ በሌሎች አካባቢዎችም በህገ ወጥ ወንጀል ድርጊቶች የሚሳተፉ ተጠርጣሪዎችን መረጃ በመስጠት የተለመደዉን ትብብርና እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ

Zehabesha

25 Oct, 15:15


https://youtu.be/i47UuMs7kTU

Zehabesha

25 Oct, 13:46


በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ሳቢያ አራት የጤና ባለሞያዎች መገደላቸውንና በርካቶች መታሰራቸውን የአማራ ክልል የጤና ባለሞያዎች ማኅበር አስታወቀ።

“በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ የጤና አገልግሎት ባለሞያች የሞያ ነፃነት አጥተዋል” ያሉት የአማራ ክልል ጤና ባለሞያዎች ማኅበር ጸሀፊ “ባለሞያዎች የታጠቁ ኃይሎች በሚሰነዝሩት ጥቃት ይገደላሉ፣ ይታሰራሉ፤” ብለዋል::
ከሁለት ሳምንት ወዲህ በምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የሚኖሩ ሁለት ፋርማሲስት ሲገደሉ በባሕር ዳር ከተማ አንዲት ነርስ በትላንትናው ዕለት ምሽት ላይ ሥራ ላይ እያለች ባልታወቁ ታጣቂዎች በጥይት ተመትታ መቁሰሏን የማኅበሩ ጸሐፊ ተናግረዋል።
ለደህንነቱ በመስጋት ስሙም ኾነ የሚሠራበት የሕክምና ተቋም እንዳይጠቀስ የጠየቀ አንድ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚኖር የሕክምና ባለሞያ መተማ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ የሚሠሩ ሁለት የሞያ አጋሮቹ እንዲሁም በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአይራ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ‘ከፋኖ ጋራ ግንኙነት አላችሁ” በሚል መታሰራቸውን ነግረውናል።
በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የእጅ ስልክ ላይ ብንደውልም ስልኩ ባለ መስራቱ ምክንያት አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም።

@VOA

Zehabesha

25 Oct, 13:09


ባለሀብቱ አቶ መቅደስ አክሊሉ የአቢሲኒያ ባንክ ዋና ባለ ድርሻ የሆኑ በመንግስት ሃይሎች ተይዘው ለሶስት ቀናት ያሉበት ሳይታወቅ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰምቷል::

ባለ ሀብቱ ላይ የ13 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተቀጥሮባቸዋል:: የታሰሩበት ምክንያት ለማወቅ አልተቻለም::

Zehabesha

25 Oct, 12:37


የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድኖች ከሜዳቸው ውጭ የደርሶ መልስ ጨዋታቸውን በደቡብ ሱዳን ዋና መዲና ጁባ ጥቅምት 21 እና ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም ሊያካሄዱ መሆኑ ተሰማ።

Zehabesha

25 Oct, 12:29


በሰሜን ሸዋ ተጉለት እና ቡልጋ የተፈፀመ የድሮን ጥቃት::

Zehabesha

25 Oct, 11:15


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፤ ለ34 የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህ መሠረት፦

1. አማኑኤል ፈረደ አያሌው (ዶ.ር) በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ርእሰ መሥተዳደር ልዩ አማካሪ

2. መስፍን አበጀ ተፈራ (ዶ.ር) - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርእሰ መሥተዳደሩ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ አማካሪ

3. ወ/ሮ መሰሉ ብርሃኑ ካሳው - የአብክመ ቆላና መስኖ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

4. አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ዳመነ - የአብክመ ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

5. አቶ ፈንታሁን ስጦታው ፈለቀ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን ኃላፊ

6. አቶ ደምስ እንድሪስ ይማም - የአብክመ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

7. አቶ ጥላሁን ፈንታው ተሾመ - የአብክመ ፕላን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

8. ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ አማረ - የአብክመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ ሙሉነህ ዘበነ ሳህሌ - የአብክመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

10. ወ/ሮ አትክልት አሳቤ ታምሩ - የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

11. አቶ ዘላለም አረጋ መኮነን - የአብክመ ወጣትና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

12. ወ/ሮ ሃናን ይመር አሊ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ሴ/ህ/ማ/ጉ ቢሮ ረዳት አማካሪ

13. አቶ አባይነህ ጌጡ ያሬድ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ

14. አቶ አታላይ ክብረት ማሩ - በኤጀንሲ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የክልል ተቋማት ክትትል አማካሪ

15. አቶ ይርጋ አላምነህ ወርቅነህ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ረዳት አማካሪ

16. ወ/ሮ ውዴ እውነቱ አዳምነው - በምክትል ኤጀንሲ ኃላፊ ደረጃ የካቢኔ ሴክረታሪያት ኃላፊ

17. አቶ ዳዊት አቡ አለሙ - የጣና ሐይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ

18. አቶ ወርቁ ኃ/ማርያም ጌጡ - የአብክመ በየነ መንግስታት ግንኙነት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

19. አቶ ዮናስ ይትባረክ አበበ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአማራ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ልማትና ማስፋፊያ ድርጅት ስራ አስኪያጅ

20. አቶ ፋሲል ሰንደቁ አደመ - በም/አስተዳዳሪ ማዕረግ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት ዋና አማካሪ

21. አቶ ሙሉጌታ ንጋቱ ለገሰ - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ዉሃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ

22.አቶ ስጦታው ሰጤ ነጋሽ - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ

23. ወ/ሮ ካሳየ ስመኝ ዋሴ - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ

24. አቶ ሙሉጌታ አለም አድገህ - የምዕ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ

25. አቶ አግማስ አንተነህ ውቤ - የምዕ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ

26. አቶ መንግስቱ አየለ ደምለዉ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ

27. አቶ ስጦታው መርሻ አጆነህ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ማዕድን መምሪያ ኃላፊ

28. አቶ ንብረት አበጀ አለሙ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ

29. አቶ ዘውዱ ላቀው ሞገስ - በም/አስተዳደሪ ማዕረግ ለሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር አማካሪ

30. ወ/ሮ የሽወርቅ ድረስ ተሰማ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ

31. ወ/ሮ ፀሐይነሽ ተፈራ በላይነህ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ መምሪያ ምክትል ኃላፊ

32. አቶ ዘነበ ሀይሉ ተ/ፃዲቅ - የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደር ህብረት ስራ ማህበራት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ

33. ወ/ሮ ተዋባች ጌታቸው ዘዉዴ - የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደር ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ

34. አቶ ዋሲሁን ብርሀኑ ሰብስቤ - የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደር ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ በመሆን መሾማቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

Zehabesha

25 Oct, 11:03


ፍርደ ገምድልነት በ84 አመቱ አዛውንት በአቶ ታዲዎስ ታንቱ ላይ፤ ፍትህና በቀል ለየቅል
++++
ዛሬ ከወደ ፍርድ ቤት እጠብቅ የነበረው ዜና 'አቶ ቲዲዎስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ቢባሉም በእስር የቆዩበትን ጊዜ፣ እድሜያቸውን እና የጤናቸውን ሁናታ ከግምት በማስገባት ተጨማሪ ቅጣት ሳይታከል ከእስር ይለቀቁ" የሚል ነበር። ይሁንና በተቃራኒው ፍርድ ቤቱ 6 ዓመት ከ3 ወር እና በተጨማሪም በ20ሺ ክፍያ የቀጣቸው መሆኑን ነው።

አቶ ታዲዎስ ታንቱ በነጻ እንዲለቀቁ ደጋግሜ ስጠይቅ ያነሳኋቸው ፍሬ ነገሮቾ እነዚህ ነበሩ፤

1ኛ/ የተከሰሱበት ጉዳይ አንድ ሰው ሃሳቡን ሲገልጽ ባስተላለፈው የጥላቻም ሆነ የቅስቀሳ አገላለጽ ጋር ተያይዞ ተፈጽሟል በሚባል ወንጀል ከሆነ የዋስትና መብታቸውን መንፈግ የመጀመሪያው ፍርደ ገምድልነት ነው። ወንጀሉ ዋስትና የማያስከለክል ብቻ ሳይሆን አዛውንቱ ከፍትህ ያመልጣሉ ተብሎም አይታሰብም።

2ኛ/ የዋስትና መብታቸውንም ከልክሎ በእስር ከመቆየታቸውም ባለፈ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን አሳጥቶ ልክ የተወሳሰበ ከባድ ወንጀል የተፈጸመ ይመስል ለአመታት ከፍርድ በፊት ለተራዘመ እስር መዳረግ ሌላው ፍርደ ገምድልነት ነው። እሳቸው በታሰሩ በአመቱ ተመሳሳይ ጥፋት ፈጽሟል የተባለ ጎረምሳ በታሰረ በሦስት ወር ጊዜ የሦስት ወር እስር ጨርሶ ወጥቷል።

3ኛ/ የመከላከያ ሠራዊትን በተኛበት ሰሜን ዕዝ ላይ ሰቅጣጭ በሆነ ሁኔታ የጨፈጨፉና ያስጨፈጨፉ ሰዎችን ገሚሱን እድሜያቸው ስለገፋና የጤና ችግር ስላለባቸው በሚል በነጻ ለቆ ወደ ውጭ አገር የሸኘ፣ ገሚሱን የክስ ሂደታቸው ወደ ፊት በሽግግር ፍትህ ይታያል በሚል ነጻ ለቆ ከተጠያቂነት ያስመለጠ የፍትህ ተቋም ይህን ለአዛውንት የመራራት ስስ ልብ ምነው በንጽጽር እጅግ በቀላል ወንጀል በከሰሳቸው አዛውንቱ ታዲዎስ ታንቱ ላይ መደንደኑ በሚል የወቅቱን ፍትህ ሚኒስትር የአሁኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በወቅቱ ጠይቄ ነበር። ሌላው ፍርደ ገምድልነት ይሄ ነው።

4ኛ/ በጥላቻ ንግግርና አመጽ በመቀስቀስ በሚል የከሰሳቸውን እና አስሮ ያጉላላቸውን የ84 አመት ሽማግሌ ላይ የ6 አመት ከ3 ወር እስር እና የ20ሺ ብር ቅጣት መወሰኑ ደሞ ሌላው የለየለት ፍርደ ገምድልነት ነው። ከእስር ዘመኑ መርዘም በላይ ለአመታት በእስር የቆዩ፣ የሥራ ገቢ የሌላቸው፣ የተለየ ንብረትና ሃብት ባላፈሩ አቅማቸው የደከመን ድሃ አዛውንት 20ሺ አምጡ ማለትስ ከየት የመጣ ፍርደ ገምድልነት ነው?

ለእኔ ከፍትሁ ይልቅ በቀሉ ጎሎቶና ጎምዝዞ የታየበት ውሳኔ ነው። አሁንም ፍትህ ለአዛውንቱ ታዲዮስ ታንቱ!!!

@ያሬድ ሃይለማርያም