Esdros S.C @esdrossc Channel on Telegram

Esdros S.C

@esdrossc


እንኳን ወደ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ/ማህበር የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ፡፡

This is Esdros S.C's official Telegram channel.

For more updates please visit www.Esdros.com

Esdros S.C (Amharic)

እንኳን ወደ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ/ማህበር የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ፡፡nnይህ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን አማራኛ ቴሌግራም ቻናል ነን። በተጨማሪ የቴሌግራም ቻናሎችን እናነብራቸው በይበልጥ www.Esdros.com ይጠቀም።

Esdros S.C

21 Nov, 10:44


በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባኤው ከመካሔዱ በፊት ሜክሲኮ ሰንጋተራ ሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና መ/ቤት በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት ውክልና መስጠት የምትችሉ ሲሆን ተወካዮቻችሁ ለጠቅላላ ጉባኤ ሲመጡ የውክልና ፎርሙን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በማድረግ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የዳሬክተሮች ቦርድ አሳውቋል፡፡
ለበለጠ መረጃም በስልክ ቁጥሮች 0973-60-00-10/09 30-36-37-79/011-126-01-01 / 011-157-59-54 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Esdros S.C

21 Nov, 10:43


12ኛው የባለ አክሲዮኖች መደበኛ ጉባኤ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ 12ኛ መደበኛ የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በቀድሞው ግሎባል ሆቴል በአሁኑ ኢትዮጵያ ቁጥር ሁለት ሆቴል ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ያካሒዳል፡፡
በዚሁ በ12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው በ12 አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ይጠበቃል፡፡
1. ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየምና ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ
2. የ12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎችን ማጽደቅ
3. አዳዲስና በዝውውር የገቡ ባለ አክሲዮኖችን መቀበል
4. የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2016 በጀት ዓመት ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን መስማትና ማጽደቅ
5. የውጭ ኦዲተር ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
6. የ2016 በጀት ዓመት ትርፍ ላይ ተወያይቶ መወሰን
7. የዳይሬክተሮች ቦርድ አክሲዮናቸውን ያሳደጉ ነባር፣ አዳዲስ እና በዝውውር የገቡ ባለአክሲዮኖች በመወከል በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት በመቅረብ እንዲፈርሙ ውክልና ስለመስጠት
8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አበልና የአገልግሎት ክፍያ መወሰን
9. የውጪ ኦዲተር መሠየም
10. የ12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

Esdros S.C

13 Nov, 06:55


በዚህ ስልጠና ላይ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት እንስት ፕሮፊሰር አለምፀሐይ መኰንን የትምህርት፣ የሥራእና የህይወት ተሞክሯአቸውን በመዝጊያው ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ለሰልጣኝ ተማሪዎች በማካፈላቸው ተማሪዎቹ ከፍተኛ ልምድና ክህሎት ያገኙበት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Esdros S.C

13 Nov, 06:55


ወደ ዩኒቪርስቲ ለሚገቡ የአቡነ ጎርጎሪዮስ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ሰውነት በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባባር በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቪርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የ''up skilling'' ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ጥቅምት 30 እና ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማንዴላ አዳራሽ በተሰጠው በዚህ ስልጠና የተዳሰሱ ረዕሶች፤
1. Core Social Skills to Collage Entrance,
2. Career Choices,
3. Digital Literacy and Experience Sharing ናቸው፡፡
በ2016 የት/ት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው በ2017 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት በዝግጅት ላይ የሚገኙ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአዋሬ፣ የለቡ እና የሰሚት ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስልጠናውን እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

Esdros S.C

02 Nov, 08:44


በልገሳ መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ሀጎስ ተካ እንደተናገሩት “አቡነ ጎርጎርዮስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አዋሬ ቅርንጫፍ በርካታ ውጤታማ ሥራ እየሠራ እንዳለ እናውቃለን፡፡ ይህ የዛሬው መርሀግብርም አንዱ መሳያ ነው፡፡ ትልቅ ልምድ የሚወሰድበት ተግባር ነው እንደ ጽ/ቤት እውቅና የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ በዚህ ለተሳተፈችሁ ሁሉ ትልቅ አክብሮት አለኝ፡፡” በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ አዋሬ ቅርንጫፍ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ከዚህ ቀደም በመሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ለመቅዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል እና በከተማው ለሚገኙ በርካታ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የገንዘብ እና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Esdros S.C

02 Nov, 08:44


የመስከረም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመወከል ንግግር ያደረጉት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ሲሳይ አለሙ እንደተናገሩት "ይህ የልገሳ መርሀግብር ትልቅ መልዕክት ያለው ነው፡፡ አንድ ሰው የሚማረው የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዛሬ የተደረገልን ይህን በተግባር የሚያሳይ ነው፡፡ ትልቅ ልምድ ነው ሊበረታታ ይገባል፡፡ ለኛ ስጦታ ብቻ አይደለም አስተሳሰብ የሚቀይር ተግባር ነው፡፡ በትምህርት ቤቱ ስም አመሠግናለሁ እግዚአብሔር ያክብራችሁ፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡

Esdros S.C

02 Nov, 08:44


አዋሬ ቅርንጫፍ 2ኛ ደረጃ ት/ቤትን በመወከል በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዋሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሳሙኤል ይልማ እንደተናገሩት “ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን በማስተባበር ይህ በዛሬው እለት ለማበርከት ያመጣነው የትምህርት ቁሳቁስ እና የንህፅና መጠበቂያ ሞዴስ ሲሆን፤ የስጦታውም ዓላማ እርዳታ ሳይሆን ተማሪዎቻችን መተሳሰብን ፣ ሰበአዊነትን እንዲሁም የማኅበራዊ አገልግሎት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ መሆኑን ከግንዛቤ አንዲያስገቡ ለማስተማርና ለማሳየት ነው፡፡”በማለት በቀጣይም መሰል ልገሳ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

Esdros S.C

02 Nov, 08:44


የአዋሬ ቅርንጫፍ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ልገሳ አደረገ፡፡
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማኅበራዊ አገልግሎት (በጎ አድራጎት) ክበብ ’’ዓመቱን በበረከት እንጀምር ’’በሚል መሪ ቃል ለመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የጽሕፈት መሳሪያና ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት ልገሳ ያደረጉት በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን በማስተባበር የትምህርት ቁሳቁስ እና የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ለ20 የመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አበርክተዋል፡፡

Esdros S.C

25 Oct, 12:15


አቶ ተስፋዬ ይሁኔ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የዳሬክተሮች ቦርድ አባል፣ የትምህርትና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ አስተባባሪ በመርሐግብሩ በመገኘት ሰልጣኝ ተማሪዎች ውጤታማ በሚሆኑበት ጉዳይ ላይ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ካሉት 28 ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ቀዳሚ የሆነው የአዋሬ 2ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በ2017 ዓ.ም 299 ወንድና 284 ሴት ተማሪዎችን በድምሩ 583 ተማሪዎችን ይዞ የመማር ማስተማር ሥራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Esdros S.C

25 Oct, 12:10


ከሰልጣኝ ተማሪዎች መካከልም ተማሪ ዳግማዊት አስፋው “ሰልጠናው ከጠበቅነው በላይ ነው፡፡ ይህንን መሰል ስልጠና ለእኛ ብቻ ሳይሆን ከታች ክፍል ጀምሮ ላሉ ተማሪዎች ቢሰጥ፡፡” የሚል አስተያየት የሰጠች ሲሆን፤ ተማሪ ነብዩ ዳንኤል በበኩሉ “ስልጠናው ቀደም ብሎ በመሰጠቱ ሰፊ ዝግጅት እንድናደርግ ያደርገናል፡፡ ስልጠናውም በውስጤ ለሚመላለሱ ጥያቄዎች መልስ ያገኘሁበት ነው፡፡” የሚል አስተያየት ሰጥቷል፡፡

Esdros S.C

25 Oct, 12:07


ስለ ስልጠናው አስተያየታቸውን የሰጡን በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአዋሬ 2ኛ ደረጃ ር/መምህር ሳሙኤል ይልማ “የ2017ዓ.ም ብሄራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በከፍተኛ ውጤት ለማሳለፍ ከመደበኛ ትምህርታቸው በተጨማሪ ይህንን መሰል የሥነልቦና ስልጠናዎች የመስጠት ስራ እንሰራለን::” በማለት አስያየት ሰጥተዋል፡፡