የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት @wcgca Channel on Telegram

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

@wcgca


ህዝብና መንግስትን ድልድይ ሆነን እናገለግላለን ‼️

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት (Amharic)

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የታማኞች እና መንግስት አገናኝ የሆነው WCGCA ኮሚዩኒኬሽን ነው። እያንዳንዱ ጉዳይ ላይ የሚመረጥን አገናኝና መረጃዎች እንኳን ለከማቹ አስተያየት እንደሚሆን ይመስላል። በዚህ ኮሚዩኒኬሽኑም ከተማ ግንባታ አሠራረህ በአንድ ጊዜ እናገለጋለን እናመልከታለን። ይህ ኮሚዩኒኬሽኑ ምንም ነገር አይሆንም በታች እንዲህ ያለው : ‼️ እና አዝናኝነት በሚል አገራት እና ከብዛታቸው ከፈለግንና የጋራ ደረቅ አቀባይነትን ከገለጸ በኃላ ታትሞረዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

22 Nov, 10:13


https://t.me/wcagca

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

22 Nov, 10:13


@wcagca

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

04 Nov, 09:49


የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት! ክፍል ሁለት

ዛሬ ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ ይጠብቁን

#PMOEthiopia

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

02 Nov, 16:40


የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe/ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://youtu.be/uaCtCi2o09o?si=sNNeZWn-U_G_7jPh

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

02 Nov, 15:57


የሥነ-ምግባራዊ አመራር
ሥነ-ምግባራዊ አመራር ማለት  ተገቢ/ተቀባይነት ያለውን ባህሪ በግል ድርጊት እና ከሌሎች ጋር በሚኖር ግንኙነቶች ማሳየት እና ይህ ባህሪ በማንኛውም የሁለትዮሽ መስተጋብር፤ ውሳኔ አሰጣጥ እና አፈጻጸም ሂደቶች በሰራተኞች ውስጥ እንዲሰርጽ ማድረግ መቻል ነው፡፡
• ሥነ-ምግባራዊ መሪዎች በአንድ ተቋም ወስጥ መልካም ሥነ-ምግባር በሰራተኞች በቀጣይነት እንዲተገበር የሚያስችል ምቹ ሀኔታዎችን የመፍጠር እና ለብልሹ አሰራር የሚጋብዙ ሁኔታዎች እንዲቀንሱ የማድረግ ሀላፊነት አለባቸው፡፡
ሥነ-ምግባራዊ መሪዎች ሁለት ቁልፍ ሃላፊነቶች አሉባቸዉ
1) ሥነ-ምግባር የተላበሱ  ዉሳኔዎች መወሰናቸውን ማረጋገጥ
2) በሚመሩት ተቋም ዉስጥ ሥነ-ምግባራዊ ባህል በመገንባት ተከታዮች በቀጣይነት እንዲተገብሩት ማድረግ ናቸው፡፡ በሥነ-ምግባራዊ አመራር ዉስጥ መሪዎች የትኩረት ነጥቦች በመሆናቸው ሁል ጊዜ ተገቢ እና ተቀባይነት ያለውን ባህሪ ብቻ  ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የሥነ-ምግባራዊ  አመራር ክህሎቶች (skills)
መሪዎች ሊያዳብሯቸው እና ጥቅም ላይ ማዋል ይጠበቅባቸዋል ከሚባሉት ክህሎቶች መካከል የሚከተሉት መሰረታዊ ናቸዉ፡፡
1. አቅም እና ችሎታን ማሳደግ
2. የተቋሙን የስነ-ምግባር መስፈርት ከፍ አድርጎ መቅረጽ
3. አዎንታዊ ግንኙነት መፍጠር
4. ተገቢ የሆነ የመስተጋብር/የመግባቢያ እና የትብብር መንገድ መዘርጋት
5. ሥነ-ምግባራዊ አጣብቂኞችን መለየት
6. ሌሎች ሥነ-ምግባራዊ እንዲሆኑ ማነሳሳት
7. ፊት ለፊት መሆንን መረዳት
8. የአክብሮት ተግባቦት መፈጸም
9. ሥነ-ምግባራዊ የሆነ የቡድን ሥራዎችን ማበረታታት
10. ሥነ-ምግባር የተላበሱ ተግባራትን ማከናወን
11. ሥነ-ምግባራዊ እሴቶች እና ባህሪዎችን በየጊዜዉ መከለስ እና ማዳበር
የሥነ-ምግባራዊ አመራር መርሆዎች (Principles)
ቁልፍ ከሚባሉት መርሆዎች ውሰጥ የሚከተሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡
1.ዓላማ (Purpose)
2. ጤናማ የሆነ ክብር/ኩራት (Pride)
3. ትዕግስተኝነት (Patin
4. ጠንቃቃነት
5. ፅናት
6. አተያይ
7. ሞራላዊ ብቃት
የሥነ-ምግባራዊ  አመራር  መገለጫ  ባህርያት (Chracteriostics)
አሁን ባለንበት ዘመን እና ማህበረሰብ ውስጥ ሥነ-ምግባራዊ መሪ ለመሆን ከፍተኛ የሆነ ድፍረት እና ጥንካሬ ይጠይቃል፡፡
ድፍረት ስንል አስቸጋሪ የሆኑ ውሳኔዎችን ለመወስን ያለንን  የሞራል ጥንካሬ ነዉ፡፡ የሞራል ጥንካሬ ሥስት ነገሮችን ያካተተ ሲሆን እነሱም እሴቶችን መተግበር፤  አደጋዎችን መለየት እና ችግርን መቋቋም ናቸዉ፡፡
ሥነ-ምግባራዊ መሪዎች በየቀኑ ውሳኔ ሲያሳልፉ ትልቅ ወይም ትንሽ የሚባሉ ሥነ-ምግባራዊ አጣብቂኞች ይገጥሟቸዋል፡፡ እነዚህን የመሰሉ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም የሚከተሉት መገለጫ ባህርያት ሊኖሯቸው ይገባል፡፡
1. አስተዋይነት
2. ሁሉን አካታችነት
3. ሃላፊነት እና ተጠያቂነት
4. አሳቢነት
5. ቀጣይነት
6. ግልፅነት የተላበሰ የዉሳኔ አሠጣጥ እና ተግባቦት ስርዓአት ማስፈን
7. ግልፅ እና መደበኛ የሥነ-ምግባር መመሪያዎች፣ ደንቦች እና እሴቶች እንዲኖሩ ማድረግ
8. አርአያነት ያለው ባህሪያት ላሳዩ ሰራተኞች ዕዉቅና እና ሽልማት መስጠት
9. ሥነ-ምግባራዊ ባህሪ የአንድ ግዜ ክስተት ሳይሆን ቀጣይነት ያለው ሂደት መሆኑን ማሳየት
10. ፍትሐዊነት
11. አክብሮት የተሞላበት የሁለትዮሽ ተግባቦት መፈጸም
12. ሀቀኝነት
13. ሌሎችን ማመን
14. ህግ አክባሪነት
15. የተሟላ/ርትኡ ስብእና መገንባት
16. የህዝብን ጥቅም ማስቀደም
17. እሴትን ያማከለ ዉሳኔ መወሰ

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

01 Nov, 15:31


https://youtu.be/uaCtCi2o09o?si=CCk6Ql8r6Ab2Vrzc

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

31 Oct, 14:43


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ -ክፍል ሁለት
- ሰላምና ደህንነትን በተመለከተ
ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን፡፡ ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን፤ አንፈልገውም፡፡ ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛ ነው፡፡ መንግስት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ  ቅድሚያ ሰጥቶ ሰርቷል፡፡ አሁንም ያለን አቋም የትኛውም አይነት አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ ነው፡፡ ነገር ግን የትኛውም አካል በኃይል እና ጥላቻ መጠፋፋትን እንጂ ዓላማውን ማሳካት አይችልም፡፡ ሰከን ብሎ ማሳብ ይገባል፡፡ ሃሳብ አልባ ትግል ፍሬ የለውም፡፡

- የአማራ ክልል አሁናዊ ሁኔታን በተመለከተ
በአማራ ክልል ላይ ከየትኛውም መንግስት በላይ አሁን ያለው መንግስት በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡ በክልሉ ታላላቅ የመንገድ፣ የኢንዱስትሪ የቱሪዝም ልማቶች እየተከናወኑ ነው፡፡ በዚህም ክልሉን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡ የፋሲል ቤተ-መንግስት እየታደሰ ነው፤ በዋና ዋና ከተሞች የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ነው፡፡ የመገጭ ግድብን 7 ቢሊዩን ብር መድበን ከበርካታ ዓመታት የግንባታ መቋረጥ በኋላ ቀን ከሌት እየገነባን ነው፡፡ ነገር ግን በክልሉ ልማት እንዳይከናወን ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች አሉ፡፡ ይህን ተባብረን ማስቆም አለብን፡፡ የአማራ ህዝብ ማን እንደሚሰራለትና ማን እንደሚያወራለት ጠንቅቆ የሚያውቅ ጨዋ ህዝብ ነው፡፡ መንግስት ክልሉን የማልማት ስራውን አሁንም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

- የገዥ ትርክት ውቅሮች
ህገመንግስታዊነት
የህግ መንግስት መርሆችና ዴሞክራሲን ያከበረ የጋራ ትርክት መገንባት

ህብረብሔራዊነት
ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር፣ብሔረሰብና ህዘቦች ሀገር መሆኗን መቀበል ያስፈልጋል፡፡
ብልጽግናን በየደረጃው ማረጋገጥ
በሁለም አግባብ በየደረጃው ልማትና ብልጽግናን በማረጋገጥ ድህነትን ለመድፈቅ በጋራ መስራት ይገባል፡፡

ማረምና ማስቀጠል
ትናንት የነበሩ ድክመቶችን ማረም፤ ያሉ ጥንካሬና ወረቶችን ደግሞ ማስቀጠል ይገባል፡፡

ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር
የጋራ ህልም በመፈጠር የበለጸገችና ያደገች ኢትዮጵያን ለማየት በጋራ መሰለፍ ይገባል፡፡ ከፓርቲ ባለፈ ትውልድን የሚሻገር እሳቤ መፍጠር ይገባል፡፡

- ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በተመለከተ

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተሻለ ስኬት እንዲያስመዘግበ የምክር ቤቱ አባላት ጠንካራ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ለታሃድሶ ኮሚሽንን እና ለሽግግር ፍትህም መሰል ድጋፍ መደረግ አለበት፡፡ ከዚህ ቀደም ከነበሩ ኮሚሽኖች ትምህርት በመውሰድ አሁን ያሉ እድሎችን መጠቀም ይገባል፡፡ ከዚህ አኳያ መንግስት እንደ አስፈጻሚ አካል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

- ኮሪደር ልማትን በተመለከተ
ኮሪደር ልማት ማለት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት ማለት ነው፡፡ ከከተሜነት እድገት ጋር የተሳሳረ ልማት ነው፡፡ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመስራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሰርተዋል፡፡ ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሃዊ ልማት ለዜጎቻችን ያቀረብንበት ነው፡፡ አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች ከምንሰራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት ጀምረናል፡፡ ይህም ኢትዮጵያዊያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ ነው፡፡ የተሟላ ብልጽግናን የምናረጋግጠውም በዚሁ መንገድ ነው፡፡

- ዲፕሎማሲን በሚመለከት
የኢትዮጵያ አቋም ከሁሉም ጋር በትብብርና ሰጥቶ በመቀበል መርህ መኖር ነው፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የኃይል ማዕከል ናት፤ ከራሷ ባለፈ ለአፍሪካ ልማት ቁርጠኛ ናት፡፡ ከየትኛውም ጎራ ጋር ሳንሰለፍ ከሁሉም ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ለብሔራዊ ጥቅማችን እንሰራለን፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን በመገንዘብ ሀገርን አስቀድሞ መስራት አለበት፡፡ በውስጥ የሚኖረን አንድነትና ሰላም ለዲፕሎማሲያዊ ጥንካሬያችን ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

- የባህር በር ጥያቄን በተመለከተ
ኢትዮጵያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በቀይ ባህር ላይ የባህር በር ያስፈልጋታል፡፡ በዚህ ጉዳይ ወደ ኋላ የማይል ይፋዊ አቋም አለን፡፡ ነገር ግን ይህን ለማሳካት ጦርነትም ሆነ የኃይል አማራጭ አንፈልግም፡፡ ፍላጎታችንን ማሳካት የምንሻው በሰላማዊ አማራጭ ነው፡፡ ይህ ምክንያታዊና ፍትሃዊ ጥያቄ ነው፤ እኛ ባናሳካው ልጆቻችን ያሳኩታል፡፡ ኢትዮጵያ የትኛውንም ሀገር ላይ ወረራም ሆነ ጥቃት አትፈጽምም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን ለመንካት የሚሞክሩ ካሉ አሳፍረን እንመልሳለን፡፡ ይህን ማድረግ የሚያስችል በቂ አቅም አለን፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

30 Oct, 03:52


ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኮሌጅ በ2017 ዓመተ ምህረት በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች የሚያሰለጥናቸዉ ተማሪዎች እየተቀበለ ይገኛል።

ኮሌጁ የአካባቢ ጸጋን መሰረት ባደረገ መልኩ ገበያ ተኮር የሆኑ ስልጠናዎች በመስጠት ወጣቶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ከስራ ጋር የማስተሳሰር ስራ በስፋት እየሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

በተያዘዉ በጀት አመት ከ2 ሺህ 5 በላይ ሰልጣኞች በመቀበል ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል።

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኮሌጅ ዲን አቶ ሀይሩ አህመዲን እንዳሉት በ2017 ዓመተ ምህረት በተለያዩ የስልጠና ዘርፎ ሰልጣኞች ተቀብሎ ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ በዛሬዉ እለት ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል።

የአካባቢ ጸጋን መሰረት ባደረገ መልኩ ገበያ ተኮር የሆኑ ስልጠናዎች በመስጠት ወጣቶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ከስራ ጋር የማስተሳሰር ስራ ይሰራል ብለዋል።

በተያዘዉ አመት ከ2 ሺህ 5 በላይ ሰልጣኞች በመቀበል ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል ብለዉ ከ2016 በተለየ ሁኔታ አጠቃላይ የተቋሙ ስራዎች ዲጂታላይዝድ ለማድረግና የኔትወርክ መሰረተ ልማት በሀይብርኦብቲስ የመቀየር ፣ አዳዲስ የስለጠና ዘርፎች ጭምር በማስገባትና በዞንግ ዲፈረንሴሽን የአካባቢ ጸጋ መሰረት ያደረጉ ስልጠና ሙሉ ትግበራ ለመጀመር እየተሰራ መሆኑም አመላክተዋል።

ሰልጣኞች በተቋሙ ሰልጥነዉ ሲወጡ ከስራ ጋር የማስተሳሰር ስራ የሚሰራ እንደሆነም አስታዉሰዉ ከዛሬ ጥቅምት 19/2017 ዓመተ ምህረት እስከ 22/2017 አመተ ምህረት ሰልጣኞች እንዲመዘገቡ በሞንታርቦና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የቅስቀሳ ስራ የተሰራ መሆኑም ተናግረዋል።

አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች በሚፈልጉት ዲፓርትመንቶች መርጠዉ እየተመዘገቡና ለተማሪዎች አጠቃላይ ኮሌጅ እየሰራዉ ያለዉ ስራ ግንዛቤ የመፍጠር ስራም እየተሰራ መሆኑም አብራርተዋል።

የቴክኒክና ሙያ ተቋማቶች በአለም አቀፍና በሀገራችን ተመራጭ እየተደረገ እንደሆነም ጠቁመዉ በቴክኒክና ሙያ የተመረቀ የሰዉ ሀይል በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሀገር የስራ ዕድል የማግኘት ሁኔታ በጣም ከፍተኛ መሆኑም አብራርተዋል።

ክህሎትና የቢዝነስ ሀሳብ ሳይጨብጡ ወደ ስራ መሰማራት የማይቻልበት ወቅት መሆኑም ያስረዱት ዲኑ በኮሌጁ በዚህ አመት ከ2 ሺህ 5 መቶ በላይ ሰልጣኞች የሚቀበሉና ነባር ሰልጣኞችም በተገቢዉ ስልጠናቸዉ እየተከታተሉ መሆኑም አመላክተዋል።

ከቦሌለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሻት ጋርመንት ፋብሪካ ጋር በዚህ አመት ከተቋሙ የተመረቁ ከ80 በላይ ሰልጣኞች በቀጥታ ስራ ዕድል የተፈጠረላቸዉ መህኑም ያስታወሱት ሀላፊዉ ከካንስ ኢንጅነሪንግ ጋር በመሆን በአቶሞቲቭና በብረታ ብረት የሰለጠኑ ልጆች ወደ ስራ የማስገባት ስራም እንደሚሰራና እንዲሁም የቆጮ ማሽን የሚያመርቱ ልጆች በማደራጀት ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

ኮሌጂ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሙያ መስመሮች በመደበኛ፣ በዊኬንድና በማታ ፕሮግራሞች ሰልጣኞችን እየተቀበለ ይገኛል።
👉በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በሆቴልና ቱሪዝም ቴክኖሎጂ ከደረጃ1-4
👉በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በሜታል ማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በጋርመንት ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በቴክስታይል ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-4
👉በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በኢኮኖሚክ ኢንፍራስትራክቸር ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-5
👉በአርባን ግሪነሪ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-4
👉በሌዘርና ቆዳ ቴክኖሎጂ ከደረጃ 1-2
👉በሶላር ፒቪ ሲሆን አመልካቾች ወደ ተቋሙ በአካል እየመጡ እየተመዘገቡ ይገኛል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽንና መምሪያ ነዉ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

29 Oct, 19:58


የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን ውጤታማ ለማድርግ የሕብረተሰብ ተሳትፎን ማሳደግ ይገባል፡፡
___

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የወባ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን በውጤታማነት መመራት እንዲቻል የህብረተሰብ ተሳትፎን ለማሳደግ የማህበረሰብ ውይይት እና ምክክሮችን አካቶ መስራት እንደሚገባ ገለጹ፡፡

የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን እንደ ሀገር ያለውን የወባ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎች፣ በሰው ሀይል እና በፋይናንስ አቅርቦት ክልሎችን እየደገፈ ይገኛል፡፡

በበይነ መረብ በተደረገ ስብሰባ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ በመሆኑ በክልሎች የወባ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ሳምንታዊ የአፈጻጸም ግምገማ አድርገዋል፡፡

ያቆሩ ውሃዎችን የማዳፈን፣ የአልጋ አጎበሮችን በአግባቡ የመጠቀም፣ የጸረ ወባ ኬሚካል እርጭት ስራዎችን በተገቢው መንገድ ማከናወን፣ የኮምኒኬሽን ስራዎችን ከመስራት አንጻር እንዲሁም የወባ በሽታ ህክምና አሰጣጥ እና ኬዝ ማኔጅመንት ላይ በክልሎች በኩል ሳምንታዊ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በበይነ መረብ በተደረገው ስበሰባ አመራር የሰጡት የጤና ሚኒስቴር ዶክተር መቅደስ ዳባ የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን ውጤታማ ለማድርግ የሕብረተሰብ ተሳትፎን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የሚጠበቀውን ለውጥ ለማምጣት እንዲቻል ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ለውጥ አምጪ ስራዎችን ከመስራት አንጻር ማህበረሰቡን ያሳተፉ ንቅናቄዎችን በመፍጠር ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ የወባ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ሂደት ላይ ውይይት እንዲያደርግ እና ውሃ ያቆሩ ስፍራዎችን የማዳፈን፣ የአልጋ አጎበሮችን በአግባቡ የመጠቀም ልምዶችን ማሳደግ፣ የጸረ ወባ ኬሚካል እርጭት ስራዎችን በአግባቡ መስራት እንደሚገባ የተናገሩት ዶክተር መቅደስ ዳባ በተለይ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከጤና ኤክስቴንሽን ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የጤናው ዘርፍ ባለ ድርሻ አካላት እና አመራሮች ለወባ በሽታ መከላከል እና መቆጣር ስራዎች ላይ በተናበበ መንገድ መስራት እንደሚገባ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

#ጤና ሚኒስቴር

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

29 Oct, 14:04


ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
ዜና ሹመት
የጉራጌ ዞን አስተዳደር የተለያዩ ሹመቶች ተሰጥቷል። በዚሁ መሰረት:-

1, አቶ ሙራድ ረሻድ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ
2, አቶ ሚነወር ሃያቱ የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ
3, አቶ እንዳለ ስጦታው የጉራጌ ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ኃላፊ
4, ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ
5, አቶ አብድልበር ሰኢድ የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል።

መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ!!

መረጃው:- የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው

1,310

subscribers

11,417

photos

18

videos