ሲገደል ደግሞ ይነገረን!!
ይህ 'ሚካኤል ሽመልስ' የተባለ ሰው አዶናይት ይሄይስ በተባለች ልጅ ላይ ከ10 ዓመቷ ጀምሮ ለዓመታት አስገድዶ መድፈር ወንጀል ይፈጽምባት ነበር፡፡
ይህች ምስኪን ይህን ሁሉ ዓመት በዚህ አረመኔ ሰው ስትሰቃይ 'አባትና እናትሽን እገድላለሁ' እያለ በሚያደርስባት ማስፈራራት ሳቢያ ለሰው ለመናገር እንኳ ሳትችል ህመሟን ሸሽጋ ኖራለች፡፡
ይባስ ብሎ በዚሁ አረመኔ ሰው ተደጋጋሚ መደፈር ሳቢያ ስትጸንስ እንድታስወርድ አድርጎ ህይወቷን አደጋ ውስጥም ጥሎት ኖሯል፡፡
በመጨረሻ 17 ዓመት ሲሞላት በደሉ በዝቶባት ለፖሊስ ብታመለክት "ለምን ከሰስሽኝ" ብሎ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰአት ያለችበት ቤት ድረስ በመሄድ በቢለዋ 16 ቦታ ወጋግቶ ገድሏታል፡፡
የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ የወንጀሉ ሰለባ የሆነችው አዶናይት ይሄይስ የተከሳሹ የቀድሞ ፍቅረኛ ልጅ ነበረች።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ይህንን ክፉ ሰው 'ከሰው ተደባልቀህ መኖር አትችልም' ብሎ ሞት ፈርዶበታል፡፡
ከዚህ በኋላ ስሙን ቄስ እንኳ አይጠራውም፡፡
ከ30 በላይ የህጻናት አስገድዶ መደፈር ወንጀሎችን ታሪክ እንደጻፈና እንዲህ አይነት ሌሎችን የሚያስተምር ፍርድ ሲናፍቅ እንደኖረ ሰው ዛሬ በዚህ ወንጀለኛ ላይ በተላለፈው የሞት ፍርድ ደስ ብሎኛል፡፡
አረመኔ በምድርም በሰማይም ዋጋውን ያገኛል፡፡ይህ ወንጀለኛ ሲፈረድበት ሰምተናል፡፡ የሞት ፍርዱ ሲፈጸምበትም ዜናው በይፋ ይነገረን!! እንዲህ ያለ ነውር ሊፈጽሙ ለሚከጅሉ ሰዎች አንድ ማስተማሪያ መንገድ ይህ ብቻ ነው፡፡
©መላኩ ብርሃኑ