ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ @eliasmeseret Channel on Telegram

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

@eliasmeseret


Journalist-at-large

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ (Amharic)

የእነሱ የዳንኤል ሜስርት ድርጅት በሙሉ ሊሆን ይችላሉ። የትኩስ ምርጫዎችን በማስተዋወቅ ከግል የሆነ ድርጅትን ዘግተዋል። እነዚህ ድርጅቶችን ከእባኮት ጋር በማገኘት ወሰን በአንድ ላይ ያድርጉትን መስራት ይችላል። አቶ ኤልያስ መስራት የሚጠና ጽሑፉን ይዞ ፀሐይ አልጠበቀም። ኤልያስ ከተጋለፍ እስኪያል እና በማስተዋወቅ በጽሑፍ ተመጣጣሪነት መስራትን ካስብ እንዲህ ነበር። ድርጅቶችን ከእንቅስቃሴ ካስቁ እና በቁጥጥራን አላቅነው። የመጀመሩበት ጊዜ ነገ በቅፅል ለመቀነስ ወደ በላይ ያስመሰሉትን ፊልም ወደቀምሯተር በማድረግ እንደሚከተሉ እና ተቆረጡ። አቶ ኤልያስ ግንባረማ ከተጋለፉ አንደበት ሌላ ጊዜ ሊቀመጡት እንችላለን።

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

20 Nov, 15:02


በመጪው የትረምፕ አስተዳደር ብዙ ኢትዮጵያውያንን በሚመለከተው የኢሚግሬሽን ጉዳይ ዙርያ በአሜሪካ ሀገር የኢሚግሬሽን የህግ ባለሙያ ከሆነው ከአቶ ሙሉአለም ጌታቸው ጋር ያደረግኩት አጭር ቆይታ:

https://youtu.be/bW0VdKHE5yw?si=QbFZeO4N86mQ_NWH

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

20 Nov, 12:26


እጅግ አሳዛኝ፣ አፀያፊ እና ሁላችንም ልናወግዘው የሚገባ ድርጊት ሰላሌ ላይ እንደተፈፀመ ታውቋል

የሰው ልጅ ላይ የዚህን ያህል ጭካኔ ለምን? ምን እየሆንን ነው? የነዚህ ግፎች መጨረሻ መቼ ይሆን?

ነፍስ ይማር!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

19 Nov, 19:18


ይህ የ40/60 ህንፃ ቦሌ አያት 2 ብሎክ 38 ይባላል

ዕጣ ከወጣበት ሁለት አመት ሊሞላው ሲሆን ባለ 13 ፎቁ "ህንፃ" በሚያሳፍር እና አደገኛ በሆነ ሁኔታ ተሰርቶ ቆሟል። እስካሁን ከ8ኛ በላይ ያለው የውስጥ ለውስጥ partition የሌለው፣ መወጣጫ ደረጃው ያላለቀ፣ የውስጥ ልስን የሌለው እና ጣራው ያልተመታ ነው። ህዝብ ግን የንግድ ባንክ ክፍያውን ቤት አገኝ ብሎ እየከፈለ ነው።

ህንፃው ውስጥ ሰው ገብቶ አስከፊ አደጋ ሳያደርስ በፍጥነት መፍትሄ ያስፈልገዋል።

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

19 Nov, 14:23


አዲስ አበባ ገና ፓሪስን አልመሰለችም፣ ወደፊት ግን ልትመስልም... ልትበልጥም ትችላለች!

ግን ኢቢሲ ህዝብ በሚሊዮኖች በሚራብበት፣ በሚገደልበት፣ በሚፈናቀልበት እና በሚሰደድበት ወቅት የቁንጅና ውድድር ይመስል ከተማ ለከተማ መልክ ሲያወዳድር የሚውል ሚድያ ሆኖ አረፈው?

ይህ ነው የኢቢሲ 'አዲሱ አቀራረብ' ተብሎ በስፋት ሲተዋወቅ የከረመው?

#ሙያውንአታርክሱት

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

19 Nov, 13:27


የ33 አመት እድሜ ያላት ሶማሊላንድ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ አድርጋ አዲስ ፕሬዝደንት መርጣለች

እኛ የ3 ሺህ አመት ስልጣኔ ያለንስ?

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

18 Nov, 17:05


ከውጭ ጉዳይ እንዳጋራው የተላከልኝ ነው

የእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛና ዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የምትችሉ እና ዕድሚያችሁ ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መመዝገብ ትችላላችሁ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

18 Nov, 16:18


No comment!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

17 Nov, 20:42


አይ ኢቢሲ Fact Check፣ አይ ማስተባበል!

ክስተቱን በአይን ያዩ የኤርፖርት ሰራተኞች፣ የሲቪል አሺዬሽን ባለሙያዎች፣ የአየር መንገድ ባልደረቦች እና አንዳንድ ተጓዦች ጭምር እውነት እንደነበር ትናንት አረጋግጠውልኝ ነበር።

ለማስተባበል የተሄደበት "ልምምድ ነበር" የሚለው ምላሽ ይባስ ብዙ ጫና ላይ ያለውን አንድ ለእናቱ የሆነውን አየር መንገዳችንን ሌላ ችግር ላይ መጣድ ነው።

ደሞ ልምምድ የሚደረገው በፕሮግራም በአየር ጦር ቤዝ እንጂ ኤርፖርት ገብተው ሊሳፈሩ check in ያረጉ ሰዎችን ወደ ቤታቸው መልሰህ ነው እንዴ?

ይህን ውሸት ሰምተን ሌላ ምን ቢነግሩን እንመን?

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

16 Nov, 18:08


ችግር መኖሩን አምኖ "ለማስተካከል እየሰራን ነው" የሚል ሳይሆን በዚህ መልኩ ፈጦ የሚታየውን እውነታ የሚክድ አካሄድ መኖሩ መጪው ግዜ ከባድ የመሆኑ አንድ ማሳያ ነው

ለመሆኑ ፋና ብሮድካስቲንግ ትናንት የህዝብ አፈሳ መረጃ "ሀሰት ነው፣ ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን" ብሎ ምነው በዛው ቀረ? 🤔

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

15 Nov, 16:24


አብዛኞቻችን ጋዜጠኞች የማህበረሰቡን ጉዳይ አጀንዳ ማድረግ አልቻልንም። We are failing our society!

ለብዙ ዜጎች የዛሬይቷ ኢትዮጵያ ቅዳሜ እና እሁድ ኢቢኤስ ላይ የምናያት አይደለችም፣ ግን እሱን እስክትመስል አብረን መታደምን መርጠናል።

Praying for better days!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

15 Nov, 15:49


የእናንተው የሆነውን፣ ለእናንተው የተከፈተውን መሠረት ሚድያን ይከታተሉ። ወደፊት ወደ ሳተላይት ጣብያነት ተቀይሮ የምታዩት ይሆናል ⤵️

https://youtube.com/@meseretmedianews?si=JwzjZsQgHfCDXQwl

መረጃን ከመሠረት!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

15 Nov, 10:46


ፋና ብሮድካስቲንግ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኦሮሚያ ክልል የታፈሱበት ሰሞንኛ ድርጊት "ሀሰት" መሆኑን ሊነግረን ቀጠሮ ይዟል

ማስረጃዬን ላቀርብ አሰብኩና ለካ እነዚህ ሚድያዎች "ውሸት ነው" ብለው ከዘገቡት "እውነት ነው ማለት ነው" የሚለው ትዝ አለኝ እና ተውኩት።

ቢያንስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ኮመንት ላይ የሰጡትን አስተያየት አንብቡ። ከተመሠረተ ሶስት ወር እንኳን ያልሞላው መሠረት ሚድያ ከዚህ በተሻለ መረጃዎችን ከነማስረጃቸው ለህዝብ አቅርቧል።

#አትዋሹ #StopFakeNews

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

14 Nov, 19:43


https://ethiopiacheck.org/home/health-professionals-advised-against-misleading-information-about-diabetes-treatments-circulating-on-social-media-%e1%88%98%e1%88%a8%e1%8c%83/

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

12 Nov, 13:31


በአዲስ አበባ እና አዳማ የጀመረው አፈሳ እና የገንዘብ ድርድር ወደ ሻሸመኔ እና ሌሎች ከተሞች ተስፋፍቷል

ሻሸመኔ 010 ቀበሌ ስታድየም ዋናው በር ፊት ለፊት ባለው መጋዘን ውስጥ እና 02 ቀበሌ ምክር ቤት ጀርባ (ብሔራዊ ትምህርት ቤት ጎን ባለው አዳራሽ) በርካታ ወጣቶች ታጭቀው እንደሚገኙ የሚደርሱኝ ጥቆማዎች ያሳያሉ።

"ዙሪያ ገባው በሚሊሻ ተከቧል፣ ቤተሰብ አይደለም መጠጋት ለራስም ያሰጋል። ግን ምን እየሆነ ነው ያለው?" ብለው የሚጠይቁት ነዋሪዎች ከመሸ መንቀሳቀስ ከባድ እንደሆነባቸው እና የሚሊሻው አፈሳ ተባብሶ እንደቀጠለ ተናግረዋል።

"ስልክህን ይፈተሻል ብለው መንገድ ላይ ይቀበሉህና ጠዋት ሚሊሻ ቢሮ ና ይላሉ። ስትሔድ ለማነው የሰጠኸው ተብለህ ወንጀለኛው አንተው። መሮናል። እኔም አንድ የኦሮሞ ወጣት ነኝ የታገልኩት ግን ለዚህ አልነበረም" በማለት መልዕክቱን ያደረሰኝ ደግሞ አንድ የከተማው ወጣት ነው።

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

09 Nov, 15:05


ከሰሞኑ በስፋት ህዝብን እያስጨነቁ ያሉ፣ ብዙም ትኩረት ግን ያላገኘው የወጣቶች አፈሳ ነው። በአዲስ አበባ እና እንደ አዳማ ባሉ ከተሞች ድርጊቱ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ሚድያዎቻችን ሽፋን እንኳን እየሰጡት አይደለም።

የሚገርመው በአዳማ በፋብሪካዎች እና በአዋሳኝ ቦታዎች ባሉ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ጭምር ታፍሰው ተወስደው በገንዘብ እየተለቀቁ ነው። በግልፅ እገታ እንዲህ ተጀመረ ማለት ነው?

እስቲ ህዝብ የሚለውን ተመልከቱ:

- "ሰላም ኤሊያስ፣ በአዳማ ወጣቶች ከቤት መውጣት አልቻልንም፣ አፈሳ በሚል ምክንያት መታወቂያ ያለውም የሌለውም በሚሊሻ ይያዝና የቀበሌ አዳራሽ ውስጥ ይታጎራል፣ የኔ ሰፈር አዳማ ቦሌ የሚባለው ቦታ ነው፣ አንድ ጓደኞዬ የግል ዩኒቨርስቲ የሚማር በ 16/02/2017 ቀን 10:00 ሰአት የተያዘ  ከተያዘ ዛሬ 14 ኛ ቀኑ ነው።  ታፍሰው nafyad ት/ቤት ያለዉ ቀበሌ ገብተው ከቤተሰብ ጋር እንኳን መገናኘት አይቻል፣ ቤተሰብ በዱላ ነው ሚያባሩት ሊጠይቅ የሄደን ሰው ። ብር ያለው 50 ሺህ ብር ከፍሎ ይወጣል፣ እሱም የትኛው ቀበሌ እንደገባክ ከታወቀ ነው፣ ስልክ ይነጠቃል ዛሬም በጠራራ ፀሀይ በማፈስ ላይ ናቸው፣ ሁሉም ነገር በጣም ነው ሚያስጠላው።"

- "ሰላም፣ ባለፈው ወንድሜ በኦሮሚያ ፖሊስ ቡራዩ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አሸዋ መዳ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ገብርኤል ሰፈር ፖልስ ጣቢያ ነበር እዛው አከባቢ በነበረው ስውር ቤት እስከ 1,400 ልጆች ታፍነው ነው ያሉት እና እኔም እግዚአብሔር ረድቶኝ 15,000 ብር ከፍዬ ወንድሜን አስፈትቻለሁ። ካልሆነ ይዘውት እንደምሄዱ ስያስፈራሩኝ ነው ሄጄ  ያስፈታሁት። ብዙ ታፍነው ነው ያሉት ቤተሰብ እንኳን የት እንዳሉ የማያውቃቸው እና በደላላ ጥበቃ ትሆናላችሁ ተብለው እና በ10 ቀን ውስጥ 7,000 ብር እንደሚከፈላቸው ተነግሮ ነው የሸወዷቸው እና ደላላው 5 ልጆች ካመጣላቸው 10,000 ብር ይከፍላል።"

- "አዳማ ከአዲስ አበባ በባሰ መታወቂያ ኖረህም አኖረህም በቃ እየታፈስክ ነው የምትወሰደው ። በአሁን ሰዓት ሰዎች ያውም ምንም የስራ እንቅስቃሴ በጠፋበት ጊዜና ኑሮ እንዲህ እንደ እብድ ለየብቻ ማስወራት በጀመረበት ጊዜ ተንቀሳቅሶ የተገኘውን ለቤተሰብ ይዞ ለመግባት የአፈሳው ነገር ከባድ በመሆነ ብዙ ሰው በፍራት ረሃቡን ተጋፍጦ ከቤት ከመውጣት እየታቀበ ነው።"

- "አዳማ ላይ እናቶች ምነው ወንድ ልጅ ባልኖረኝ የሚሉበት ዘመን መቷል መንገድ ላይ የተገኘ ሁሉ እየታፈሰ ነው"

- "እንዴት አደርክ? ጓደኛዬ ወደ ውጭ የሚልከው ምርት አምጥቶ አዳማ ማበጠሪያ እያስበጠረ 10 ሰራተኞችን እዛው ድርጅቱ ውስጥ ያሉትን በአፈሳ ወሰዷቸው ትናንት"

ይሄ ከብዙ በጥቂቱ ነው፣ ፈጣሪ ይሁነን።

መልካም ቀን።

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

09 Nov, 13:47


የትብብር ጥያቄ፣

ትናንት ምሽት 1:10 ገደማ ከጎሮ ወደ ፍየል ቤት በሚወስደው መንገድ ታክሲ የተሳፈሩ ግለሰቦች ሶስት ፓስፖርት ጥለው ወርደዋል (ታክሲው ሱዙኪ)፣ ፓስፖርቶቹ ቪዛ የተመታባቸው ሲሆን ዛሬ ምሽት 4 ሰአት ወደ አሜሪካ ጉዞ እንዳላቸው ነግረውኛል።

የቪዛዎቹ ባለቤቶች እሸቱ ኢሳያስ፣ ሜሮን ናጆ እና የህፃን ንፅሀፍቅር እሸቱ ነው።

ፓስፖርቱን ያገኛችሁ ወገኖቻችን በዚህ ቁጥር ደውላችሁ ብትሰጡን ወረታውን እንከፍላለን ብለዋል 0935497085
0945306045

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

08 Nov, 14:37


#FactCheck በተቃራኒ ጎራ የቆመ አካልን መቃመም አንድ ነገር ነው፣ ነገር ግን እንዴት አንድ 'የተማረ' የተባለ ሰው ያውም የወጣበት ማህበረሰብ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ ህጻናት እና ነፍሰ ጡር ሴቶች ተገደሉ ተብሎ በሚድያዎች ሲዘገብ ውሸት ነው ለማስባል ሀሰተኛ መረጃ ያሰራጫል?

ጌትነት አልማው የተባለው እና ብዙ ግዜ ብሔራዊ ቴሌቭዥን (EBC) ላይ ጭምር እየቀረበ ትንታኔ የሚሰጥ ግለሰብ ቢቢሲ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን በተመለከተ ዛሬ የሰራውን ዘገባ በማንሳት "ስትዋሹም እየተናበባችሁ" በማለት ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዜናው የተጠቀመበት ምስል በትግራይ ጦርነት ወቅት ትግራይ ቴሌቭዥን የተጠቀመበት የቆየ ምስል ነው ብሏል።

ይሁንና ትግራይ ቴሌቭዥን በወቅቱ፣ ማለትም ኦክቶበር 24/2022 ባወጣው ዘገባው ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት የተጠቀመውን ምስል ሳይሆን ሌላ የድሮን ጥቃትን ያሳያል የተባለ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል (ምስሉ ላይ በስተቀኝ ተያይዟል)።

ስለዚህ ግለሰቡ ቢቢሲ ለአማራ ክልል ዘገባው የቆየ የትግራይ ምስል እንደተጠቀመ አድርጎ ያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል።

በንፁሀን ደም እንዲህ መሳለቅ ያሳዝናል!

Via ኢትዮጵያ ቼክ

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

08 Nov, 12:06


https://www.bbc.com/amharic/articles/c5y3l8vkldlo

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

04 Nov, 19:16


አንዳንዴ የሀገራችን መሪዎች ለጥቂት ደቂቃ በኢንቦክስ የሚላኩ ቅሬታዎችን፣ ጥቆማዎችን፣ የእርዱኝ ተማፅኖን እና የድረሱልኝ ጥሪን አብረውኝ ቁጭ ብለው ባዩት ብዬ እመኛለሁ

ይሄ ከባለፈው አንድ እና ሁለት ቀን በጥቂቱ ነው።

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

03 Nov, 17:36


#Update ቅድም ለፍለጋ ያጋራሁትን የህፃን ልጅ ፎቶ ተከትሎ በርካታ በዱባይ እና በኢትዮጵያ የሚገኙ ሰዎች መረጃ ሰጥተዋል

እናት ልጇን ካለ ጋብቻ ዱባይ ውስጥ ከወለደች በኋላ ለአንድ አመት በክፍሏ በመደበቅ (ክትባትም ሳታስከትብ) አቆይታት ነበር። አባትም ስላልታወቀ ፓስፖርቷን ተነጥቃ በአንድ የመውጫ (exit) ዶክመንት ወደ ኢትዮጵያ ከሶስት ቀን በፊት ተጠርዛ ተላከች። ከዛም ነው ትናንት ምሽት ልጇን ሆሳዕና ውስጥ የጣለቻት።

"ቤተሰቦቼ ይገሉኛል ስትል ሰምተናል" ብለው ከዱባይ አንዳንድ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ተናግረዋል።

ከዚ በሁዋላ ጉዳዩ እና የተገኘው ዶክመንት ለፖሊስ ይተላለፋል፣ የግለሰቧም ማንነት ስለታወቀ የሆሳዕና ፖሊስ በቅርቡ እንደሚያሳውቀን ተስፋ አረጋለሁ።

መልእክቱን አይታችሁ ላስቀመጥኳቸው ቁጥሮች (ለሚሚ እና ለምስክር ሺበሺ) በመደወል ላሳወቃችሁ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ።

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

03 Nov, 13:52


ይህች ህፃን ትናንት ምሽት 3:30 ላይ በሆሳዕና ከተማ መንገድ ላይ ተጥላ እንደተገኘች የደረሰኝ ጥቆማ ያሳያል። ምናልባት ከቤተሰቦቿ ተነጥቃ ተወስዳ ሊሆን ስለሚችል የልጅቷን ወላጆች የምታውቁ ወይም ወላጅ የሆናችሁ በዚህ ስልክ ደውላችሁ ከመንገድ ዳር ያነሱትን ግለሰቦች እንድታገኙ መልእክት አድርሰውኛል (ጉዳዩን ለፖሊስ እንዳሳወቁም ተናግረዋል):

ሚሚ: 0977742511 ወይም 0947689074
ምስክር: 0910742028

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

03 Nov, 12:08


ከጋዜጠኛ ቃለየሱስ በቀለ ጋር መልካም ቆይታ አርገናል

https://youtu.be/MgxvrzAzI0Y?si=JcJKvWKTqTxTeSuZ

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

02 Nov, 21:15


ከሰሞኑ እንኳን በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ከ40 በላይ ንፁሀን ዜጎች በግፍ ሲገደሉ፣ በደራ ወረዳ አንድ የመስጂድ ኢማም የሆኑ ሼይህ ከነ12 ቤተሰባቸው ሲረሸኑ፣ ዜጎች በየስፍራው ሲታገቱ እና ወጣቶች በአዲስ አበባ እና አዳማ እየታፈኑ ወደ ካምፕ ዚጓዙ ትንፍሽ ያላለ ሚድያ...

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

02 Nov, 11:37


በቤተመንግስት ተገኘ ስለተባለው 400 ኪ/ግ ወርቅ

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ "ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል" ማለታቸው ይታወሳል።

"ይህ ወርቅ ምን ይሆን ብዬ?" አንዳንድ ማጣራቶችን ለማድረግ ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ አስደንጋጭም፣ አሳሳቢም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ይህ ወደ ብሄራዊ ባንክ ተላከ የተባለ ወርቅ በኢትዮጵያ የንጉሳዊ ስርዐት ወቅት ለበርካታ መቶ አመታት ነገስታት ሲገለገሉባቸው የነበሩ በወርቅ እና በሌሎች የከበሩ ማዕድናት የተሰሩ ቁሳቁሶች፣ ከሌሎች ሀገራት በስጦታ የተሰጡ ቅርሶች እንዲሁም በርካታ በነገስታቱ ታዘው የተሰሩ እና የተገዙ ናቸው።

"ታድያ እነዚህ ወደ ሙዚየም እንጂ ለሽያጭ ወይም ለወርቅ ክምችት ወደ ባንክ እንዴት ሊላክ ይችላል?" ብዬ ጥያቄ ያቀረብኩላቸው ጉዳዩን የሚያውቁ ግለሰቦች ምላሻቸው "ማን ሰምቶን?" ነው።

ቅርስ ጥበቃ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ የጠ/ሚር ፅ/ቤት እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ዙርያ መክሮ እነዚህን የኢትዮጵያ ታሪክ የሆኑ ንብረቶች ወደነበሩበት ቦታ ወይም ወደ ሙዚየም እንዲመለሱ ማድረግ አለባቸው።

እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

28 Oct, 19:04


የሚድያ ሰራዊት...?!

በዚህ መልኩ የሚገኝ ላይክ፣ ኮመንት እና ሼር ጥቅሙ ምን ይሆን?

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

28 Oct, 16:17


በትምህርት ተቋማት፣ በኢንደስትሪ ፓርኮች ወይም በግል የስራ ቦታ ሊገኙ የሚገባቸው ወጣቶች እየታፈሱ ወደ ወታደር ካምፕ እየተላኩ ነው

የሚገርመው ደግሞ አፍሰው የሚወስዱ ሚሊሺያዎች ወደ ካምፕ የሚወስዷቸው ወጣቶች ኮታ ተሰጥቷቸዋል።

Back to the Derg era... back to square one!

ዜናውን መሠረት ሚድያ ላይ ያንብቡ: https://t.me/meseretmedia/496

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

28 Oct, 12:43


#ሁለቱግፎች በቅርብ ቀናት ከሰማኋቸው የግፍ ድርጊቶች ሁለቱን ላጋራችሁ:

አንደኛው ጀሞ አካባቢ በሚገኛው ሳውዝ ዌስት አካዳሚ የተፈፀመ ነው። የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው ሲዘምሩ እና የጥላሁንን "ኢትዮጵያ" ዘፈን ሲዘፍኑ የነበሩ ከ30 በላይ ታዳጊዎች (ከ10- 12ኛ ክፍል ተማሪዎች) ታፍሰው ተወስደው ክፉኛ ተደብድበዋል። ሁለቱ ላይ የደረሰው ድብደባ እጅግ የከፋ ነበር የተባለ ሲሆን፣ የልጆቻቸውን ከእስር መፈታት ሊማፀኑ ወደ 'ማርያም ሰፈር' የሚገኝ ፖሊስ ጣብያ የሄዱ ወላጆች "ከፈለጋችሁ በክላሽ እናናግራችሗለን" እንደተባሉ ነግረውኛል።

ሁለተኛው ደግሞ በከምባታ ዞን ፉንጦ ከተማ የተፈፀመ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በላይ መብራት በመጥፋቱ በኮሚቴ ሆነን መንግስትን እንጠይቅ ብለው ሲመክሩ የነበሩ ወጣቶች በልዩ ሀይል ተይዘው ክፉኛ ተቀጥቅጠዋል፣ የድብደባውን መጠን የሚያሳይ ቪድዮም ተለቋል።

ሙሉ መረጃውን መመልከት ከፈለጉ: https://youtu.be/4-mTXuOxJjg?si=TU42M6bYuv3cqgGE
#StopAtrocities

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

27 Oct, 16:46


ይሄ ቁጭት ሲንጋፖርን እና ማሌዥያን መምሰል እና አለመምሰል ሳይሆን እንዴት በዚህ ክፍለ ዘመን አንድ የሀገሬ ዜጋ ምግብ አጥቶ ይራባል፣ ፖለቲከኞች በሚቆሰቁሱት እሳት ይለበለባል፣ በልማት ስም ከቤቱ ተጎትቶ ወጥቶ መንገድ ላይ ይጣላል... ወዘተ ቢሆን በወደድኩ።

እኔ እንኳን እንደ አንድ ተራ ግለሰብ ምናልባት ድምፅ ከሆነን በሚል ከህዝብ የሚደርሰኝ አሰቃቂ እና ዘግናኝ ሁኔታ እንቅልፍ ይነሳኛል።

አያውቁትም ወይስ አያገባኝም?

ወይስ ሌላ?

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

26 Oct, 12:03


ያለንበት ሁኔታ በጨረፍታ!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

25 Oct, 17:56


በየቀኑ ከሚደርሱኝ አሳዛኝ መልእክቶች መሀል ⤵️

ሰላም ኤልያስ፣ ከኑሮ ውድነት ጋር በተገናኘ አንድ መረጃ ላጋራ ወደድኩ። ለደህንነት ስባል ስሜ ለጊዜው ይቆይና የምሰራው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነዉ ከተቀጠርኩ አንድ አመት ከሰባት ወር ሆኖኛል፤ የማገኘው ደሞዝ የተጣራ 12 ሺህ ብር አከባቢ ነው። ይሄ ማለት ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ባንኮች ሁሉ ዝቅተኛ ደሞዝ ከፋይ ንግድ ባንክ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ ከማይክሮ ፋይናንስነት ወደ ባንክነት የተሸጋገረው ኦሞ እንኳ በቅርቡ የተስተካከለው ደሞዝ ስኬላቸው ከንግድ ባንክ ይበልጣል። ንጽጽረ በእኛ ደረጃ ካሉት ጋር ነው። ወደ ዋናው ሀሳቤ ስመለስ ወጭዬን በዚህ መልክ ነው የምመድበው:

ለቤት ክራይ=2000 በወር
ለታክስ=1040 በወር
ለመጠጥ ውሃ=1400 በወር
ለምጦራት እናቴ=1500 በወር
ሌሎች ወጪዎች=1000 በትንሹ

የቀረው 5060 ለምግብ ሲሆን የምግብ ወጪዎቼ እንዲህ ነው:
ቁርስ በቀላሉ አምባሻ በሻይ=40
ምሳ በቀላሉ ሽሮ/አታክልት/አቦካዶ/አይነት/ፓስታ እና የመሳሰሉ ምግቦች ከበላው=80
እራትም እንደዛው=80 በአጠቃላይ በቀን በትንሹ ለምግብ 200 ብር ይወጣል ይሄ ደግሞ በወር ስሰላ 6000 ብር ነው።

ከላይ ባስቀመጥኩት ዝርዝር መረጃ መሠረት ሌሎች ወጪዎችን መቀነስ ስለማልችል ምግብ በቀን 2 መመገብ ጀምሬያለሁ።

ሌላው ደግሞ የጤና ሁኔታ ስሆን ምንም እንኳ ባንኩ የሕክምና ወጪ እሸፍናለሁ ብለው ብያወራም ያለው እውነታ ሌላ ነው።

እርግጥ እውነት ነው ባንኩ የሕክምና ውጪ ይሸፍናል፣ የሚሸፍነው ግን በመንግሥት ሆስፒታል ከታከምክ ብቻ ነው። በመንግሥት ሆስፒታል ውስጥ ደግሞ ሌላው ቀርቶ ጓንት እንኳ ከውጭ ገስታችሁ አምጡ እንባላለን፣ ከዚህ ውጭ ያለው ነገር ለተመልካች ግልጽ ነው።

ከላይ በዘረዘርኩት ወጪ ውስጥ "ውሃ ግዴታ ነው ወይ?" ካልከኝ አዎ ያለንበት አከባቢ ንጹሕ የመጠጥ የሌለበት ነው።

ብዙ ልብ የሚሰብር ነገሮች አሉ!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

25 Oct, 01:35


#Attention| ከሰሞኑ ከሚያባንኑኝ ጉዳዮች አንዱ በቅርብ ቀናት አዋሽ አካባቢ የተከሰተው ርዕደ መሬት እና አያድርስ እና ከፍ ያለ መጠን ያለው መንቀጥቀጥ ቢከሰት በአካባቢው ያሉ ግድቦች ላይ መደርመስ አስከትሎ ዜጎች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ነው

በአካባቢው ያለው ግዙፉ የከሰም ግድብ ላይ ጉዳት ቢደርስ ሊለቀው የሚችለው ግዙፍ የውሀ መጠን በታችኛው ተፋሰስ ላይ ያሉ ዜጎችን ሊውጥ ይችላል።

"ቀፈን ቀበና ግድብ በተመሳሳይ በክረምቱ ወቅት ግዙፍ የውሀ መጠን ይዞ ይገኛል፣ አደጋ ቢከሰት ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማሰብ ይከብዳል" ያሉኝ አንድ ባለሙያ ከአካባቢዎቹ እስካሁን 700 አባወራዎች እንዲነሱ ቢደረግም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ለአደጋው ተጋልጠው ይገኛሉ ብለዋል።

አደጋ ከደረሰ በኋላ "ብዬ ነበር" ማለት ወይም ከንፈር መምጠጥ ዋጋ የለውም፣ ስለዚህ ሌላው አለም ላይ እንደሚደረገው ቢያንስ ሁኔታው በደንብ እስኪጠና ተጋላጭ ወገኖችን ወደ ሌላ ቦታ ማስፈር ቢቻል እጅግ መልካም ነው።

እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ትኩረት፣ ትኩረት፣ ትኩረት!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

24 Oct, 16:01


መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው አውዳሚ የእሳት አደጋ ወቅት አንዳንድ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን አባላት ከባለሱቆች ጋር የገንዘብ ድርድር ሲያደርጉ እንደነበር ሰምቻለሁ፣ ከአንድ እና ከሁለት ሳይሆን 8 ሰዎች አረጋግጠውልኛል

በስፍራው ከደረሱ በኋላ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ "ማንን ነው ምናናግረው?" በማለት ለረጅም ደቂቃዎች ማጥፋት እንዳልጀመሩ እነዚህ የአይን እማኞች ይናገራሉ።

"ማለት የፈለጉት ብር እንዲሰጣቸው ከማን ጋር ነው ምንደራደረው ነው። ይህ ነገር የተለመደ ቢሆንም ይሄ ሁሉ ንብረት እስኪወድም ግን በዚ ደረጃ አይመስለኝም ነበር" ያለኝ አንድ የአደጋው ተጎጂ ቤተሰብ ይህን መረጃ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች እንደሚያውቁ ነግሮኛል።

መሠረት ሚድያ ደግሞ በደረሰው መረጃ በስፍራው ቀድመው በአምቡላንስ የደረሱ የእሳት አደጋ ቡድን አባላት 4 ሚልዮን ብር በመቀበል በድርድር ተስማምተዋል።

ብር ከፋዮቹ በጊዜው የነበሩ የሱቅ ባለቤቶች ሲሆኑ የብዙ ሚሊዮን ብር ንብረት ሱቆቹ ውስጥ ላይ ስለነበራቸው የተጠየቁትን ለመክፈል ምርጫ ስላልነበራቸው አላቅማሙም ነበር፣ ጠያቂዎቹ ደግሞ በጊዜው ቀድመው አምቡላንስ ይዘው የደረሱ የእሳት አደጋው ሰራተኞች ናቸው ተብሏል።

ይህን ድርጊት የፈፀሙት ሁሉም ሳይሆኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች መሀል የሚገኙ የሰው ንብረት ውድመት ሳይታያቸው እና ሙያቸውን የካዱ ጥቂቶች እንደሆኑ ይሰማኛል።

ጉዳዩን "ውሸት" ምናምን ብሎ ለማለፍ ሊሞከር ይችላል፣ የሚያዋጣው ግን አጣሪ ቡድን ወደስፍራው በመላክ እነዚህን አሳፋሪ ጥፋተኞች በህግ መጠየቅ ነው።

አሳፋሪ ነው!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

19 Oct, 16:38


https://youtu.be/f9FMRVCKYk0?si=DEkkCUS-gyKO-swT

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

18 Oct, 15:25


#ከፍተኛትኩረት በደቡባዊ የሀገራችን ክፍል በቅርብ አመታት ታይቶ የማይታወቅ የወባ ወረርሽኝ ተከስቶ ህዝብ እየረገፈ ነው

በአካባቢው ያሉ የጤና ባለሙያዎች እንደነገሩኝ በወላይታ፣ በከምባታ፣ በጉራጌ ዞኖች እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ እና ዙርያው ወረርሽኙ ተባብሷል።

ፈጣን ትኩረት ያሻዋል፣ መሠረት ሚድያ በምሽት ዜናው ሁኔታውን በስፋት ይዳስሳል።

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

16 Oct, 14:53


ከወንድም ጌጡ ተመስገን እና ጓድ ታደለ አሰፋ ጋር በአፍሪካን ኢምፓክት አዋርድ ፕሮግራም

Was fun.

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

15 Oct, 17:15


#ለግልፅነት ከሚሰራበት ቦታ ተባሮ እና የሚኖርበት ቤት እንደሚፈርስ ሲነገረው ራሱን ስላጠፋው አዲሱ ካሳሁን ትናንት አንድ መረጃ እና የድጋፍ ጥሪ አቅርቤ ነበር

እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ ብቻ 520,000 ብር (አምስት መቶ ሀያ ሺህ ብር) በባለቤቱ የቀጥታ የባንክ አካውንት ድጋፍ ተደርጎላታል።

ድጋፍ ላደረጋችሁ እንዲሁም መረጃውን በአካውንታችሁ እና ገፃችሁ መልሳችሁ ሼር ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ።

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

15 Oct, 15:51


ህዝቡ በጣም ገቢው አድጎ ስለበለፀገ አምና በሳንቲሞች ይጨምር የነበረው የትራንስፖርት ዋጋ አሁን እስከ እጥፍ በሚሆን ጭማሪ አሳይቷል...

የመዓት ግዜ!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

14 Oct, 14:42


‼️ ከሁለት ሰአት በፊት ያጋራሁት የድጋፍ ጥሪ የባንክ አካውንት ቁጥር እንደማይሰራ (inactive እንደነበር) በገለፃችሁት መሰረት አሁን ተስተካክሏል

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

14 Oct, 12:46


አዲሱ ካሳሁን በአዲስ አበባ ከተማ ከኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ አትላስ ሆቴል በሚወስደው መንገድ አካባቢ በሚገኘው 'በፀጋህ ሆስፒታል' ፊት ለፊት ባለ አንድ ግቢ ነዋሪ ነበር።

አዲሱ ነጠላ ከሚሸጥበት ኡራኤል ቤተከርስቲያን አካባቢ ስራ እንዳይሰራ ሶስት ግዜ በደንብ አስከባሪዎች ተባሮ እና ንብረቱም ተወስዶበት እንደነበር ባለቤቱ እንዲሁም ጓደኞቹ ይናገራሉ።

ከዚህም በተጨማሪ ከአምስት ቀን በፊት ምሽት ወደ ቤቱ ሲገባ ተከራይቶ የሚኖርበት ቤት በነጋታው ጠዋት እንደሚፈርስ ሲነገረው ተስፋ በመቁረጥ ስሜት እዛው ግቢ ውስጥ ራሱን እንዳጠፋ ባለቤቱ በእንባ እየታጠበች ነግራኛለች።

"የዛን እለት ብዙ ሲጨናነቅ ነበር፣ ቤት ሲያጠያይቅ 13 ሺህ እና 15 ሺህ ሲሉት ነበር፣ በዛ ላይ ቤተሰብ ያለው አናከራይም እያሉት። ሊነጋጋ ሲል ራሱን አጥፍቶ አግኝተነዋል፣ አሁን የት እንደምሄድ እና ምን እንደማረግ እንዳለብኝ አላውቅም" በማለት ነግራኛለች።

የሁለት የልጅ አባት የሆነው አዲሱ (አንደኛው ገና 5 ወሩ ነው) ባሳለፍነው አርብ እለት ስድስት ሰአት ላይ በኡራኤል ቤተክርስቲያን ቀብሩ ተፈፅሟል።

ባለቤቱን እማኑሽ ፈንታን በቻልነው አቅማችን እንደግፍ፣ ለማስጀመርያ እንዲሆን እኔም በግሌ የአቅሜን ድጋፍ አደርጋለሁ።

እማኑሽ ፈንታ
ስልክ: +251920660393

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000334824652

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

14 Oct, 03:16


የዘንድሮው የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ስነ ስርአት ሜሪላንድ በሚገኘውና ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩት ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል ዛሬ፣ እሁድ ኦክቶበር 13/2024 ምሽት በደማቅ ዝግጅት እየተካሄደ ነው፣ እኛም በስፍራው ተገኝተናል

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የተመሰረተውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን ያዘጋጀው የ2024 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር የሽልማት ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።

ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ስነ ስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የተዘጋጀ ነው።

በየአመቱ ከስፖርት፣ ከስነ ጥበብና ከስራ ፈጠራ ዘርፎች ለማህበረሰቦቻቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦና ለለውጥ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ከየዘርፉ ተመርጠው የሚሸለሙበት መድረክ ነው።

አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለአራት ጊዜያት ተካሂዷል። ዘንድሮም በተለያዩ ዘርፎች ለአምስት ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያንን የክብር እውቅና እየሰጠ ይገኛል።

የዘንድሮ ተሸላሚዎች አርቲስት አስቴር አወቀ፣ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፣ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ ወ/ሮ ሬቤካ ሀይሌ እና አትሌት ትግስት አሰፋ ናቸው።

ለግብዣው ዶ/ር ጋሻው አበዛን አመሰግናለሁ።

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

11 Oct, 19:55


https://www.facebook.com/100068497307887/posts/pfbid0Zw69kGWvZPuH9u6VDRtGMvbKAncR76Rnb4jBE3CvLoLxQhvR7JqBKpe7ozvTchANl/

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

11 Oct, 17:38


#FactCheck ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሂደት ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ሆነች በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ሚድያዎች፣ የግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተጠቃሚዎች “ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሂደት ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ሆነች” የሚል መረጃ አጋርተዋል።

ይህን መረጃ ያጋሩት ሚድያዎች እና ግለሰቦች እንደ መረጃ ምንጭነት የተጠቀሙትም ኢን ኦን አፍሪካ (IOA) የተሰኘ ድረ-ገጽ ነው፡ https://www.inonafrica.com/ 

ይህ በደቡብ አፍሪካ እአአ በ 2007 ዓ/ም የተመሰረተ ተቋም በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቅ ነው።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ እየተሰራጨ የሚገኘውን መረጃ በተመለከተ የኢን ኦን አፍሪካን ድረ-ገጽን እንዲሁም የማህበራዊ ትስስር ገጾቹን የተመለከተ ሲሆን የተባለው ሪፖርት በድርጅቱ የመረጃ ቋቶች ላይ እንደሌሉ አረጋግጧል።

እየተጋራ በሚገኘው ስክሪን ቅጂው የላይኛው ክፍል ላይ የሚገኙ ጽሁፎች እና ምስሎች ከተቋሙ ትክክለኛ ድረ-ገጽ ጋር ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም ሪፖርቱ ግን ትክክለኛው የ ‘IOA’ ድረ-ገጽ ላይ እንደሌለ አረጋግጠናል።

በተጨማሪም ከመረጃው ጋር እየተጋራ የሚገኘው የስክሪን ቅጂ የፊደል አቀማመጥ/ፎንት ስህተቶች የሚታዩበት መሆኑንም ተመልክተናል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መረጃውን በፌስቡክ ገጹ ካጋራ ከሰዓታት በኋላ መልሶ ማጥፋቱንም ተመልክተናል።

ከሰሞኑ ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ ስክሪን ቅጂዎች በስፋት እየተሰራጩ እና በርካቶችን ለስህተት እየዳረጉ ይገኛሉ። በመሆኑም መሰል ስክሪን ቅጂዎችን አምነን መረጃዎችን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

Via Ethiopia Check

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

10 Oct, 22:05


በዛሬው እለት በአለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ የዋለውን የአእምሮ ጤና ቀን ምክንያት በማድረግ ከክሊኒካል ሳይኮሎጂስት ዶ/ር አወቀ ምህረቱ ጋር በመሠረት ሚድያ ቆይታ አድርጌ ነበር

ከራስን ማጥፋት ጀምሮ እስከ የአእምሮ መቃወስ ያሉ ብዙ ስለማይነገርላቸው ነገር ግን ህዝቡን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዱ ስላሉ ጉዳዮች አውርተናል

https://youtu.be/zh8I3sgXGC0?si=Lzh_EnUavzu7ufPy

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

10 Oct, 14:53


Facts matter.

ሙሉ ዜናውን ኢትዮጵያ ቼክ ላይ ያንብቡ: https://www.facebook.com/100068497307887/posts/pfbid02xnTj89oS98WCLQAohDKcMDSDAkp5G7n9wbyzKsBvww4rReKVnQVWRC7HmZDxmjAWl/

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

09 Oct, 09:23


አሻም የህዝብ ድምፅ!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

08 Oct, 18:27


በዚህ አካሄድ አውሮፕላን መግዛት ሳያዋጣ አይቀርም

Totally insane!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

04 Oct, 22:56


እንኳን ለደማቁ የእሬቻ በአል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

Baga Irreecha Baranaa Geenye!

መልካም በአል!

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

30 Sep, 22:04


የሰሞኑን የብር መዳከምን (የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን) ተከትሎ ገበያ ላይ ያልጨመረ ነገር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም

ይህ አልበቃ ብሎ የመንግስት ተቋማት ህዝብ ላይ እልህ እየተወጡ ይመስል ተራ በተራ እስከ 700 ፐርሰንት ጭማሪ ያረጉ አሉ።

ኢሚግሬሽን፣ ንግድ ባንክ፣ ኤሌክትሪክ፣ ውሀ፣ ቴሌ፣ አየር መንገድ፣ የመኪና ቦሎ እና መንጃ ፈቃድ፣ የትራፊክ ቅጣት... ከሰሞኑ ደግሞ የዳኝነት ክፍያ እንኳን ጭማሪ ይደረግበታል። የኔ ጥያቄ:

አንደኛ፣ ጭማሪ ሲደረግ ነባራዊ የህዝብን አቅም እና ችግር ማገናዘብ የለበትም ወይ?

ሁለተኛ፣ በሌላው አለም እንደምናየው progressive የሆነ የ10%፣ የ20%... ወዘተ እያለ ጭማሪ ይደረጋል እንጂ ሲፈልግ የ150%፣ ሲያሻው የ700% ጭማሪ ማድረግ ማለት ነው?

ሶስተኛ ደግሞ አንድ ሰሞን ሲወራ የነበረውን ጥቂት የሆነ የደሞዝ ጭማሪ እንኳን ተግባራዊ ሳያደርጉ ህዝብ ላይ ሸክም መጫን ለምን ተፈልጎ ይሆን?

እውነት ይሄ ነገር አንድ ወዳጄ እንዳለኝ "መንግስት ከህዝብ ጋር እልህ ተጋብቶ እየቀጣው ነው" ያለው እውነት ይሆን እንዴ?

ዝመት ሲባል ዘምቶ ለሚቆም፣ ደግፍ ሲባል በሚሊዮኖች ወጥቶ ለሚሰለፍ፣ ሀገርህ ተደፈረ ሲባል "ኢትዮጵያን!" ብሎ ለሚዘምት ግን ይህ አይገባውም።

@EliasMeseret

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

30 Sep, 17:59


#ለግልፅነት በትናንትናው እለት ለእታገኝ አየናቸው ያጋራሁትን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ ከ 375,000 ብር በላይ በቀጥታ በንግድ ባንክ አካውንቷ ተሰብስቧል። አንድ ዶክተርም ለታማሚው ልጅ ህክምና ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነዋል።

ድጋፍ በማድረግ ለተካፈላችሁ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ።