ይኽ ተግባር የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ በማዘመን ረገድ ዐቢይ ርምጃ ነው። ESX ለዘርፉ ግልፅነትን የተላበሰ የገበያ ስፍራ ይፈጥራል።
በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ጥላ ሥርም በኢንቨስትመንት ለሚመራ እድገት በር ይከፍታል።
በመንግሥትም በግልም ዘርፎች የፋይናንስ አካታችነትን በማስፋት የቁጠባ እንቅስቃሴን ማሳደግን ብሎም ኢንቬስተሮችን መጠበቅን ታላሚ አድርጎ ተነስቷል።
ESX በሶስት የገበያ ክፍሎች ላይ ይሰራል። እነዚህም ለቢዝነስ ተቋማት፣ ለመንግሥት እና ሌሎች ተቋማት የሚያገለግሉ የይዞታ ገበያ፣የቋሚ ገቢ ገበያ እና የገንዘብ ገበያ ናቸው። የሙከራ የገንዘብ ገበያው ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ እንቅስቃሴ ተካሂዶበታል።
ይኽም ገበያው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት ለማጠናከር ብሎም ለዘላቂ ልማት የካፒታል አቅም ለማሰባሰብ ያለውን አቅም አሳይቷል።