Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች @housinginaddisababa Channel on Telegram

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

@housinginaddisababa


The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates. This page is not a gov't page.

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች (English)

Are you looking for the perfect housing solution in Addis Ababa? Look no further! Welcome to 'Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች', your go-to channel for all things related to housing projects and real estate updates in the vibrant city of Addis Ababa. Our channel is dedicated to providing you with continuous information about housing projects in Addis Ababa, specifically focusing on the 40/60 and 20/80 housing schemes. Whether you are a first-time homebuyer, an investor, or simply looking to upgrade your current living situation, we have all the latest updates on housing developments that may interest you. Please note that 'Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች' is not a government page. We are an independent channel that aims to keep you informed and updated on the latest real estate trends and opportunities in Addis Ababa. Join our channel today to stay informed about new housing projects, investment opportunities, and other real estate updates in Addis Ababa. Let us help you find the perfect housing solution that suits your needs and preferences. Don't miss out on the chance to be part of the thriving real estate market in Addis Ababa. Subscribe to 'Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች' now and start your journey to finding your dream home in this beautiful city!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

13 Jan, 09:28


በቦሌ ለሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ይስተዋል የነበረውን የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ የተከናወነ የማስፋፊያ ስራና በአካባቢው የሚገኙ ደንበኞች አስተያየት !

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

11 Jan, 14:11


የት ነው?

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

11 Jan, 05:51


አዲሱ የትራፊክ ቅጣት

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

08 Jan, 08:13


የቤንዚን ዋጋ ከ10 ብር በላይ ጨምሯል። በተደጋጋሚ እንደተገለጸውም የዋጋ ንረት አዙሪቱ ቀጥሏል፣ ገና ይቀጥላል።

ታህሳስ 22 ቀን 2017 የገንዘብ ፓሊሲ ኮሚቴ ገጽ 2 ላይ ባቀረበው ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ግምገማ መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ 15% ቀንሷል። ቡናና ወርቅ ዋጋ በመጨመሩ የውጭ ክፍያ ሚዛንም ተሻሽሏል።

የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ያለው በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩና የመንግስት የውጭ ክፍያ ሚዛን በመዳከሙ ምክንያት እንዳልሆነም ሪፖርቱ ግልጽ አድርጓል።

ይህ ማለት የነዳጅ ዋጋ የመጨመሩ ምክንያቱ የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም መደረጉ እንጂ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ እንዳልሆነ ያመላከተ ነው። እንደዚህ ዓይነቱ አዙሪት መቆምያ ጠገግ እንደሌለውም ሂደቱ በቂ ገላጭ ነው።

የብር የመግዛት አቅም ሲዳከም ኢኮኖሚው ውስጥ ያልነበረ ተጨማሪ ብር እንዲፈጠር ግድ ይላል። ምርትና ምርታማነትን ተከትሎ ያልተፈጠረ ብዙ ብር ከጥቂት ምርት ጋር ሲጋፈጥ ዋጋ ንረት መከተሉ የማይቀር ነው።

የዋጋ መናር የገንዘብ የመግዛት አቅምን ያዳክማል። የብር የመግዛት አቅም መዳከም የውጭ ምንዛሪ አቅምን ያንራል። የውጭ ምንዛሪ አቅም መናር ደግሞ የዋጋ ውድነትን ያስከትላል። የውጭ ምንዛሪ አቻ ትመና መናርን ተከትሎ የብር የመግዛት አቅም ይዳከማል።

የብር መግዛት አቅም መዳከም የዋጋ ንረት፣ የዋጋ ንረት ተጨማሪ የብር ፍላጎት፣ ተጨማሪ የብር ፍላጎት ተጨማሪ ብር መፈጠርን፣ የብር መብዛት የገንዘብ ግሽበትና የዋጋ ንረትን ያስከትላል። አዙሪቱ ይቀጥላል።
Mushe Semu

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

04 Jan, 01:08


በኢትዮጵያ በሬክተር ስኬል 5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከለሊቱ 9:52 መድረሱን የአውሮፓ ሜዲትራንያን ሴይስሞሎጂ ማዕከል (EMSC) አስታወቀ። ሰሞኑን ሲከሰቱ ከነበሩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየው ርዕደ መሬት፤ ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

01 Jan, 07:53


ለእኛ ሀገር የሚያስፈልግ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

30 Dec, 15:03


የ1997 ኮንደሚንየም ተመዝጋቢዎች

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

27 Dec, 17:24


አቡነ ጴጥሮስ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

23 Dec, 16:53


የስምና ንብረት ዝውውር ታገደባቸው ክ/ከተሞች የትኞቹ ናቸው ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በ6 ክ/ከተሞች በተመረጡ ወረዳዎች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ።

ክፍለ ከተሞቹ ፦
- የካ፣
- ለሚ ኩራ፣
- አቃቂ ቃሊቲ፣
- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣
- ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ እንደሆኑ አሳውቋል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክፍለ ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ወር መጨረሻ አካባቢ ድረስ የስምና ንብረት ዝውውር ታግዷል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

23 Dec, 13:04


በመዲናዋ በስድስት ክፍለ ከተሞች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ

በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በስድስት ክ/ከተሞች በተመረጡ ወረዳዎች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ።

የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ ለፋና ዲጂታል እንዳስታወቀው፥ ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው።

ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት በመዲናዋ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን አመልክቷል፡፡

አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ መሰራቱ ተጠቁሟል።

በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዚህ መሠረትም የይዞታ ማረጋገጥ ስራው በተመረጡ ስድስት ክ/ከተሞች በቀጣይ አምስት ወራት ውስጥ እንደሚከናወን ተጠቅሷል። ክፍለ ከተሞችም የካ፣ ለሚ ኩራ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ መሆናቸው ተመላክቷል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክ/ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ወር መጨረሻ አካባቢ የስምና ንብረት ዝውውር መታገዱ ተገልጿል።

ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡም ጥሪ ቀርቧል።
FBC

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

23 Dec, 12:54


አሥተዳደሩ ከ4 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥ ፈጸመ

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በ4 ቢሊየን 415 ሚሊየን 778 ሺህ 750 ብር ወጪ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ በርካታ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ግዥ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡

እነዚህ ግዥ የተፈጸመባቸው ተሽከርካሪዎች ለቢሮ እና ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸውን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልገሎት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ሙሉጌታ ይመር አስታውቀዋል፡፡

በአጠቃላይ ከታዘዙት መካከልም እስከ አሁን ከ214 ተሽከርካሪዎች በላይ ርክክብ መፈጸሙን እና አገልግሎት እየሠጡ መሆኑን ዳይሬክተሩ ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

ቀሪዎቹን ተሽከርካሪዎችም እስከ ሁለት ወር ባለው ጊዜ እንደሚረከቡ አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል ከምታከናውናቸው ዘርፈ-ብዙ ተግባራት መካከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በስፋት መጠቀም አንዱ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት እስከ አሁን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በግንባር ቀደምነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በብዛት በመጠቀም ቀዳሚ ሆኗል፡፡

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

22 Dec, 13:26


የጨረታ ማስታወቂያ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

15 Dec, 18:04


በከተማችን ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት ከምናካሂዳቸው የቤት ግንባታ መርሃ ግብር ትልቁ የሆነው የኦቪድ ገላን ጉራ ሳይት 60 ሺሕ ቤቶች ግንባታ፣ በለገሀር ጊፍት ሪልስቴት የሚገነባቸው 4,370 ቤቶች የግንባታ ሂደትን እንዲሁም በቦሌ ሩዋንዳ በግሉ ዘርፍ እየለሙ የሚገኙ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን ጎብኝተናል::

በምናካሂዳቸው የልማት ስራዎች ቅድሚያ ለልማት ተነሺዎች በማለት በጀመርነው አሰራር መሰረት የኦቪድ ገላን ጉራ ሳይት ለልማት ተነሺ አርሶአደሮች የሚሆኑ 770 ደረጃቸውን የጠበቁ ምትክ ቤቶችን ቅድሚያ ሰጥተን ግንባታቸውን በማፋጠን ላይ እንገኛለን::

በዚህ የገላን ጉራ ፕሮጀክት ከሚገነቡ ቤቶች ውስጥ ኮንዶሚኒየም በመቆጠብ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ የምንገኝ ሲሆን በከተማችን ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር የጀመርናቸው ስራዎችን ከመሰረተልማትና ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቅረፍ በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች  አቤቤ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

15 Dec, 06:33


በመዲናዋ በዋና መንገዶች ያሉ የንግድና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ተኩል ድረስ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወሰነ

በአዲስ አበባ በሁሉም ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3:30 የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ  ውሳኔ አሳልፏል።።

ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከልም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

12 Dec, 17:09


" የመኖሪያ ቤት ችግር ባለበት ከተማ ውስጥ ክፍት ቤት ማስቀመጥም ፍትሐዊ አይደለም " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በጨረታና በዕጣ የተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ባልገቡት ባለንብረቶች ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታውቋቃ።

የኮርፖሬሽንኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

- ከታኅሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ወደ ቤታቸው የገቡና ያልገቡትን የመለየት ሥራ ተጀምሯል።

- ከመስከረም 20 ቀን እስከ በጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የቤት ባለንብረቶች እንዲገቡ ማሳሰቢያ ተሰጥቶ ነበር በድጋሚ ቀነ ገደቡን በማራዘም እስከ ኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ባለንብረቶች እንዲገቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ ነበር። 

- ባደረገው ምልከታ ወደ ቤታቸው የገቡ፣ ያከራዩና በዕድሳት ላይ የሚገኙ አሉ።

- የተቀመጠው ቀነ ገደብ በመጠናቀቁ በሁሉም ሳይቶች የመለየት ሥራ ይጀመራል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዕጣ ተላልፎባቸው ቤታቸው ያልገቡትን ባለንብረቶች፣ ቤቶቹን ምን ለማድረግ ታስቧል ? ለሚለው ጥያቄ " ቀነ ገደቡ በቅርቡ በመጠናቀቁና ወደ ቤታቸው ያልገቡበትን ማለትም ፦
° በሕይወት አለመኖር፣
° መግባት አለመፈለግ፣
° በአገር ውስጥ አለመኖር፣
° በሕግ በተያዙ ጉዳዮችና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች መሆኑን ማጣራት ይደረጋል " ብለዋል፡፡

በዕጣና በጨረታ ተላልፈው ባለቤቶቻቸው ያልገቡባቸው ቤቶች ምን ያህል ናቸው ? ለሚለው ጥያቄ " መጠናቸው ይለያይ እንጂ በሁሉም ሳይቶች እንደሚገኙ፣ ቁጥራቸውን ግን ይህን ያህል ነው ለማለት ያስቸግራል " ሲሉ መልሰዋል።

" ዋናው ነገር የቁጥር ጉዳይ አይደለም፤ ክፍት በመሆናቸው ምክንያት ነዋሪዎች ለተለያዩ ችግሮች መዳረጋቸውንና ከተለያዩ ሳይቶች በርካታ አቤቱታዎች ለኮርፖሬሽኑ እየደረሱ በመሆኑ ነው  " ሲሉ ገልጸዋል።

" የመኖሪያ ቤት ችግር ባለበት ከተማ ውስጥ ክፍት ቤት ማስቀመጥም ፍትሐዊ አይደለም " ያሉ ሲሆን " ባለቤቶቹ ያልገቡባቸው ቤቶች ከተለዩ በኋላ በቅርቡ ውሳኔ ይሰጣል " ብለዋል።

ኮርፖሬሽኑ በሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ፣ በሕግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል።

በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው ከማቋረጥ ባለፈ በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ሕገወጥ ድርጊት ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጹ አይዘነጋም፡፡

መረጃውን ከሪፖርተር ጋዜጣ ነው የተገኘው።
@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

10 Dec, 17:28


ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በካፒታል ፕሮጀክት በሶስት የተለያዩ ሳይቶች 545 ቤቶችን አስገንብቶ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በቁጥርቤ/ል/ኮ/ቤ/ ሽ/ጨ/001/2017 በግልጽ ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም በወጣው ግልጽ ጨረታ ላይ ተሳትፎ አድርጋችሁ በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተጫራቾች ቅሬታችሁን 30/03/2017 እስከ 07/04/2017ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ባንቢሰ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና ማስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ብቻ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ቤ.ል.ኮ.

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

06 Dec, 14:51


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ባሉ የመንግሥት ተቋማት ሁሉም አገልግሎቶች ላይ የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር አስገዳጅ አሠራር ተቀመጠ

የሀገር አቀፉ የፋይዳ ምዝገባ ሥርዓት ለሀገር የሚኖረውን አስተዋፅኦ ከግምት በማስገባት የሥርዓቱን ተፈፃሚነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማስተባበር የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር በጋራ መግባባት በመፍጠር እየተመራ መሆኑን ኤጀንሲው ጠቆመ።

ከከተማ አስተዳደሩ ተቋማት አገልግሎት ጋር በተያያዘም አስገዳጅ አሠራር መዘርጋቱንም የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገልጿል።

ይህንኑ መነሻ በማድረግ በአገልግሎት ባህሪያቸው የተለዩ የከተማው ተቋማት በዋናነትም የንግድ ቢሮ፣ የመሬት አስተዳደር ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ፣ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፣ የትራፊክ ማናጀመንት ኤጀንሲ፣ የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ቁጥጥር ፈቃድ ባለሥልጣን፣ የመንግሥት ግዢ ኤጀንሲ እንዲሁም የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር ዝርዝር የዝግጁነት እና አፈፃፀም ውይይት ተደርጓል።

አጠቃላይ አሁናዊ የምዝገባ ሁኔታ እና  የአስገዳጅ ሥርዓቱ አፈፃፀም ገለፃ በብሔራዊ መታወቂያ ጽ/ቤት አቶ ዓለማየሁ እጅጉ፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ እንዲሁም የተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች ባሉበት ቀርቧል።

አቶ ዓለማየሁ የፋይዳ ምዝገባ ከከተማ ነባራዊ የዕድገት ሁኔታ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ከአካታችነት፣ ከቀልጣፋ አገልግሎት፣ ከፍትሃዊ የሃብት አጠቃቀም፣ የሃብት አስተዳደር እንዲሁም ከሰላም እና ፀጥታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ከተማዋን ስማርት የሚያደርግ የዲጂታል ምሶሶ በመሆኑ ስራው በቁልፍ ተግባር የሚመራ መሆኑን ገልፀዋል።

የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር በአዲስ አበባ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታነት ተቀምጧል።

በከተማው ያሉ የመንግሥት ሠራተኞችም በዚሁ ሥርዓት አስገዳጅነት እንዲካተቱ አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ሥራ መገባቱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በመድረኩ ጠቅሰዋል።

ከተማዋ የፋይዳ ምዝገባ ተደራሽነትን ሙሉ ለሙሉ ባጠረ ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ ከብሔራዊ መታወቂያ ጽ/ቤት ጋር ከኤጀንሲው መዋቅር የመመዝገቢያ አማራጮች በተጨማሪ አዲስ ተደራሽ ተንቀሳቃሽ መዝጋቢዎችን ለማሰማራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንሥተዋል።

ተቋማቱ የፋይዳ ምዝገባ ለአገልግሎት አስገዳጅ ያደረጉ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ አፈፃፀሙ እየተገመገመ የሚሄድ መሆኑን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

04 Dec, 14:25


በመሬት ይዞታዎች፣ በመሬት ማሻሻያዎች፣ የጋራ መገልገያ ቦታዎች፣ የሕንጻ ይዞታዎች፣ የጋራ መኖርያ ቤቶች፣ ኮንዶምኒየሞችና የግል የመኖርያ ቤት ይዞታዎች ላይ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ለሕ/ተ/ም/ቤት አስረጂ መድረክ በአቶ ዋሲሁን አባተ የገንዘብ ሚኒስቴር አማካሪና በእዮብ ተካልኝ ዶ/ር በገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ቀረበ።

የመሬት ማሻሻያ ማለት "መደቦች፣ አጥር፣ ጊቢን በንጣፍ ማስዋብ የመኪና ማቆምያ፣ ግልጽ የገበያ ቦታዎች፣ የውኋ መከለያ ግንቦች፣ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ መዋቅሮችንና ወዘተ የሚመለከቱ ናቸው"

"የመገልገያ ቦታዎች ማለት አፓርትመንቶች ኮንዶምንየሞችና የጋራ ፓርኪንግና ቦታዎችና ሌሎች የተናጠልና በጋራ መገልገያነትየሚያገለግሉ ቦታዎችን ያካትታል ።"

እጠቅሳለሁ "...ጡረተኞች አሴት (ንብረት) ኖሯቸው ካሽ (ገንዘብ) ስለሌላቸው አዋጁ ግብር መክፈል አቅቷቸው ከቤታቸው እንዳይፈናቀሉ ከለላ የሚሰጥ መሆኑን አቶ ዋሲሁን አባተ ገልጸው፣ ነገር ግን ንብረቱ በውርስ ሲተላለፍ ወራሾች ንብረቱ ላይ እስከ 5 ዓመት ወደ ኋላ በመመለስ የነብረት ግብር እንደሚከፈሉበት አብራርተዋል።

ወራሾች በገንዘብ ደረጃ ከአውራሾቻቸው አቅም የተሻለ አቅም እንደማይኖራቸው ቢታወቅም እንኳ፣ ከንብረት ግብር ነጻ መብቱ የቀድሞ ባለቤቶች ስለሆነ መብቱ ወደ ወራሾች የሚተላለፍ አይሆንም። ወራሾች የግብር እዳውን መክፈል ካልቻሉ ንብረቱን ሸጠው ወደሚመጥናቸው ቦታ መሄድ እንደሚችሉ" በማከል አብራርተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው ለአስረጂዎቹ የንብረት ታክስ፣ የጣራና የግርግዳ እንዲሁም የጋራና የተናጠል የመሬት መገልገያና መሬትን ማሻሻል የሚሉ ተደራራቢ ግብሮች በአንድ ንብረት ላይ መጣሉ ከግብር ስርዓቱ ጋር አይጋጭም ወይ በሚል ላቀረበላቸው ጥያቄ የሚጣለው የንብረት ግብር በንብረቱ ይዞታ፣ በመሬቱና በመገልገያው ላይ በተናጠል ስለሆነ ተደራራቢ ግብር አለመሆኑን እዮብ ተካልኝ ዶ/ ር ገልጸው "ተደራራቢ ግብርን የግብር ሕጉ የማይፈቅድ" መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።

ከተለያዮ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ የተጠናቀረ
Mushe Semu

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

03 Dec, 16:01


በካሳንችስ ካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት በልዩ ሁኔታ ምትክ የመኖሪያ ቤት እጣ አወጡ

በካሳንችስ አካባቢ በካምፕ ውስጥ ከቤተሰብ ጋር  ይኖሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት ካምፑ በመልሶ ማልማት በመነሳቱ በልዩ ሁኔታ ምትክ የመኖሪያ ቤት እጣ አወጡ፡፡

የከተማ እድገትን ከዜጎች ተጠቃሚነት ጋር አቀናጅታ በልማት ጎዳና ወደ ፊት እየተራመደች ያለችዉ አዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛዉ ዙር የኮሪደር ልማትን በፍጥነት እና በጥራት እያከናወነች መሆኑ ይታወቃል ፡፡

መዲናዋ የኮሪደር ልማቱ በሚፈርስባቸው አካባቢዎች በልማት ለሚነሱ ዜጎችም ክብርን የሚመጥን እና ለዘመናዊ አኗኗር ምቹ የሆኑ  ቤቶችን እና ምትክ  ቦታዎችን የማስረከብ ስራም ጎን ለጎን እያካሄደች ትገኛለች፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት እና አስተዳዳር ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ ምትክ ቤት የተሠጣችው የጸጥታ አካላት ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ዉስጥ በካምፕ ዉስጥ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩ ስለመሆኑ ተናገረዋል ፡፡

ለሀገር እድገት እና ለከተማ ልማት የማይተካ ሚናን የሚወጡት እነዚህ የፖሊስ አባላት በመዲናዋ እድገት ላይ የሚያበረክቱት ድርሻ የጎላ ስለመሆኑ ፖሊሶቹ ተናግረዋል ፡፡

የቤት ዕጣ ማዉጣት ስነ ስርዐቱም ግልፅና ፍትሀዊ እንደነበር ጠቁመዋል ፡፡

በካምፕ ውስጥ ከቤተሰብ ጋር ለመኖር ምቹ አለመሆኑን ያወሱት በልዩ ሁኔታ  እጣ ያወጡት የፖሊስ አባላቱ ዛሬ እጣ በማውጣታቸው ችግራቸው  ሙሉ በሙሉ እንደሚቀረፍ ገልፀዋል ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ለፖሊስ አባላቱ በሰጠዉ ትኩረት  ምቹ የመኖሪያ ቤትን በምትክነት በማግኘታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

03 Dec, 05:14


የመሪ 40/60 ኮንዶሚኒየም ባልኮኒ (በረንዳ) ላይ አንድ ተብሎ የተጀመረ በሮቶ ውሃ ማከማቸት እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ ያለኝን ስጋት ለማፍራት ያነሳሁት ነው።

የውሃ ችግራችን የማያሳስበን ነገር የለም። ለችግሩ የሚሰጠው መፍትሄ ግን ሌላ ችግር መፍጠር የለበትም።

ኗሪዎቹ ውሃ እያስቀመጡ ያሉት ለሰው መቆሚያ ተብሎ በተሰራ ተንጠልጣይ ወለል cantilever (ምዝውጥ) ላይ ነው። ይህ ቦታ የመዋቅር ዲዛይኑ ሲሰራ ለሰው መንቀሳቀሻና መጠቀሚያ እንጂ እንዲህ በአንድ ቦታ የተከመረን የውሃ ክብደት ለመሸከም አይደለም።

ብዙዎች ያስቀመጡት የውሃ ጋን ከ 1ሺህ ሊትር የሚያንስ አይመስልም ይህም ባልቀነጨረ መካከለኛ ሰው ክብደት ሲሰላ የ 15ሰው ያውም በትንሽ ቦታ ተደራርቦ ነው እኩሌታ ነው።

የአንዳንዶቹም ለቦታው ተመጥኖ የተሰራ መጠነ ክቡ አነስ ብሎ ቁመቱ ከፍ ብሎ የተሰራ ነው። ይህም በትንሽ ቦታ ላይ ከፍተኛ እፍግታ (pressure) በመፍጠር ስላቡ ሊቀነጠስና አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

ክፉ ነገር ከማየታችን በፊት በእንደዚህ አይነት ህንጻዎች ላይ የምትኖሩ ወገኖቻችን ክፉ ነገር ከመፈጠሩ በፊት ለውሃ ችግራችሁ የተሻለ መፍትሄ ፍጠሩ። ለምሳሌ ሁሉም ሰው የየራሱ ታንከር የሚሰቅልበትን ገንዘብ አዋጥቶ ትላልቅ ታንከሮች መሬት ላይ አስቀምጦ በ ፓምፕ ሽቅብ እየላከ ከላይ ወደ ታችም ለእያንዳንዱ አባወራ በእኩል እምቅ ሃይል እንዲደርስ በማድረግ ሁሉም የተጠቀመበትን የሚከፍልበት ሲስተም መዘርጋት ይቻላል።

ከከተማ ውበትና ዘመናዊነት አንጻርም ዲሽን ታሳቢ ያደረገው መንግስታችን ውሃ ከማቅረብ ጋር የውሃ ታንከር በበረንዳ ላይ መስቀልን የጎሪጥ ቢመለከተው እንላለን።

እነዚህ ህንጻዎች ውስጥ መሃንዲሶች አይኖሩም ወይ? ወይስ ከትህትናቸው ብዛት ህንጻ ቀና ብለው አያዩም?
Desalegn Kebede

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

02 Dec, 17:03


አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

መሬት ለህዝብ ጥቅም ሲለቀቅ ካሳ እና ምትክ መሬት የሚሰጥበት እና የልማት ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት መመሪያ 79/2014. 🏠

#Ethiopia #ሕግ #lawyer #ጠበቃ #law #legalservice #samuelgirma #መሬት

@SAMUELGIRMA
@Ethiopian_law
@Tebeka
🎁 🎁 🎁
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Addis Ababa Ethiopia


©️ 🇪🇹

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

02 Dec, 02:27


ከብሔራዊ ባንክ ባገኘነው መረጃ

-ከጥር 2017 አጋማሽ ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ የባንክ አገልግሎት ለማግኘት ግዴታ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያስፈልጋል

-ከሰኔ ወር 2017 መጨረሻ ጀምሮ ደግሞ በሀገሪቱ ባሉ ሁሉም ትልልቅ ከተሞች ባሉ ባንኮች አካውንት ለመክፈት ፋይዳ ግዴታ ነው

-በመላው ሀገሪቱ ያሉ ሁሉም ባንኮች ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፋይዳ መታወቂያን ግዴታ ያደርጋሉ

-በታሕሳስ 2019 ዓ.ም ነባር የባንክ ደንበኞችም ቢሆኑ ፋይዳ ካልያዙ አገልግሎት አያገኙም  ⬇️⬇️⬇️ ዝርዝሩን ያንብቡ-  https://cutt.ly/heZoqXrd

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

01 Dec, 18:17


የአዲስ አበባ ተፈናቃዬች

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

01 Dec, 18:11


በኮሪደር ልማት ምክንያት የሚፈርሱ ሰፈሮች ጨምረዋል

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

01 Dec, 17:48


የኢትዮጵያ አየር መንገድ  በ750 ቢሊየን ብር በላይ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ  በ5 ቢሊየን ፓውንድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።

ከአዲስ አበባ በ25 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ አቅራቢያ የሚገኘው ይህ የወደፊት አየር ማረፊያ በ2029 ሲጠናቀቅ እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን በዓመት የሚያስተናግድ ትልቅ ተርሚናል እና አራት ማኮብኮቢያዎችን ይይዛል ተብሏል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዳር አል ሀንዳሳ አማካሪዎች ጋር በመተባበር የሚመራው ይህ የ750 ቢሊየን ብር በላይ ፕሮጀክት፤ ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ዋና ተዋናይ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል።

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መጨናነቅ ቢያጋጥመውም "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ይህን ችግር በመቅረፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ያሳድጋልም ተብሎለታል።

አዲስ ማለዳ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

01 Dec, 11:45


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በመላ ሀገሪቱ የባንክ
ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ካርድ ግዴታ ሊሆን ነው

ሒሳቦች ለመክፈት ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ካርድ የግዴታ መስፈርት እንደሚሆን ለፋይናንስ ተቋማት መመሪያ ሰጥቷል።

በቅርብ ዘገባዎች መሠረት ከሰባት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን “ፋይዳ” በመባል የሚታወቀውን የዲጂታል ብሄራዊ መታወቂያ ለማግኘት ተመዝግበዋል። በ2022 ከ90 ሚሊዮን የተመዘገቡ ተጠቃሚዎችን ለመድረስ ታቅዳል።

ባንኮች አግባብነት ባለው መመሪያ መሰረት ሁሉንም አስፈላጊ መረጃዎች የሚሰበስቡ ከሆነ የቁጥጥር አካሉ የብሔራዊ መታወቂያውን ተጠቅሞ ዲጂታል (ርቀት) ደንበኛን እንዲመዘግብ ፈቅዷል።

ባንኮች በየደረጃው የሚዘረጋውን የታዘዘውን የጊዜ ገደብ በጥብቅ እንዲያከብሩ ታዘዋል። በአዲስ አበባ ርዕሰ መዲና ውስጥ ለሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች መስፈርቱ ከታህሳስ 23 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

01 Dec, 06:05


#CapitalNews መንግስታዊዉ ባንክ የሆነዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢንዱስትሪው ያለዉ የገበያ ድርሻ ቀነሰ

ግዙፉ የፋይናንስ ተቋም የሆነዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ ያለዉ የገበያ ድርሻ ካለፈዉ ዓመት አኳያ ቅናሽ ማሳየቱ አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት አመላክቷል።

ባንኩ በ 2016 ሂሳብ ዓመት አጠቃላይ ሀብቱ እና የተቀማጭ ገንዘብ ከጠቅላላው የባንክ ዘርፍ ከግማሽ በታች ማለትም 47.9 በመቶ እና 47.1 በመቶ በቅደም ተከተል መሆኑን ተመላክቷል።

ይህም ባንኩ በ 2015 የነበረዉ ድርሻ ከባንክ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ ሀብቱ 49.5 በመቶ የነበረ ሲሆን ተቀማጭ ገንዘብ ደግሞ 48.7 በመቶ መሆኑ ይታወቃል ።

ብሔራዊ ባንክ በተጠናቀቀዉ ሂሳብ ዓመት የባንክ ኢንዱስትሪ የገበያ ድርሻ በሚመለከት ትልቅ ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ በሚል በአፈፃፀማቸዉ ልክ አስቀምጧል ።

በዓመቱ የገበያ ድርሻዉ ምንም እንኳን ዝቅተኛ ቢሆንም አሁንም በሀገሪቱ ከሚገኙ ባንኮች ትልቁን ድርሻ የያዘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነዉ ።

እንደ ብሔራዊ ባንክ መረጃ አዋሽ ፣ አቢሲኒያ ፣ ዳሽን ፣ ኦሮሚያ እና ህብረት ባንክ መካከለኛ ባንኮች ተብለዉ ከተለዩ አምስቱ ተቋማቶች ሲሆኑ አጠቃላይ ሀብታቸው 28.9 በመቶ እና ተቀማጭ ገንዘባቸው ደግሞ 30.3 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

የተቀሩት 25 አነስተኛ ባንኮች ጥምር ንብረቶች እና ተቀማጭ ገንዘብ 23.3 በመቶ እና 22.7 በመቶ ድርሻ የያዙ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ የባንክ ዘርፍ እያንዳንዳቸው 0.8 በመቶ ጭማሪ ማሳየታቸውን ካፒታል ከሪፖርቱ ተመልክቷል ።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

30 Nov, 04:40


በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት  ስር የሚመራው የብሄራዊ መታወቂያ “ፋይዳ” ያላወጡ ዜጎች በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እንደ ቅድመ ሁኔታ በመቀመጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት እየተጉላሉ መሆኑን አዲስ አበባን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች ለዋዜማ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ዝርዝሩን አንብቡት- https://cutt.ly/heZoqXrd

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

30 Nov, 04:38


የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

አሁን አገልግሎት እየተሰጠበት ያለው 10 ብር ሲሆን ወደ 20 ብር ጭማሪ እንደተደረገ ታውቋል።

የታሪፍ ጭማሪው ከታኅሣስ 1/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

29 Nov, 18:30


#CapitalNews ከፓስፖርት ቅጣት የተሰበሰበው ወደ 18 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በግለሰብ አካዉንት ገቢ ሲደረግ እንደነበር በኦዲት ተረጋገጠ

ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት ቅጣት ክፍያን የመሰብሰብ ፍቃድ ሳይሰጠዉ የራሱን የመመሪያ ተመን በማዉጣት ሲሰራ እንደነበር ተገልጿል ።

ስልጣን ሳይሰጠዉ ከፓስፖርት የሚገኝ የቅጣት ገንዘብን እየሰበሰበ ይገኛል የተባለው አገልግሎቱ የገንዘብ ሚኒስትርን ሳያስፈቅድ የራሱን አካዉንት በመክፈት 17 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ገደማ ገቢ አድርጓል ተብሏል።

በራሱ የተመን መመሪያ ቅጣት ሲጥል የነበረዉ ተቋሙ ከ 1 ሺህ እስከ 1500 ብር እያስከፍል እንደነበር ካፒታል ከኦዲት ሪፖርቱ ተመልክቷል።

ይህ ገንዘብ ገቢ ሲደረግ የነበረዉ በግለሰቦች አካዉንት ተከፍቶ ነበር ያለዉ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የተከፈተው " የባንክ አካዉንት ወደ ሰራተኞች መረዳጃ እድር ተቀይሯል ብሏል" ።

በዚህ ባልተፈቀደ አካዉንት ገቢ ተደርጓል ከተባለው ገንዘብ ዉስጥ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚሆነው ለትርፍ ሰዓት ክፍያ እና ለበዓል ወጪ መደረጉን እና 8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ደግሞ በአካዉንቱ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር በፓርላማ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ በቅጣት የተገኘው ገቢ ወደ መንግስት መተላለፍ የነበረበት ያለ ሲሆን ይህ ባለመሆኑ ህጉ መጣሱና ድርጊቱን የፈፀሙ አካላት ሊጠየቁ ይገባል ብሏል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

29 Nov, 07:19


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያ ተመን ደንብን አፅድቋል።

አዲሱ የክፍያ ታሪፍ ይህንን ይመስላል

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

28 Nov, 02:48


የድሮ ስርዓትን መናፈቅ ለምን ወንጀል ይሆናል? አሁን ግን መቶ ኪሎ ጤፍ ስንት ነው?

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

25 Nov, 10:27


የት ነው?

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

25 Nov, 09:05


የት ነው?

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

24 Nov, 13:16


የለገሀር ተነሺዎች

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

23 Nov, 08:13


"ኮሪዶር"- መገናኛ - ጎሮ አማራጭ
===
ሁለተኛው ዙር ተጀምሯል። በተለይ ጃክሮስ - ጎሮ ብዙ ቤቶችን እና መሰረቸውን የሚነካ ይመስላል። ድሮም ሰፊ የሚመስለው ጎሮ አደባባይ እጅግ እየሰፋ ነው ።

የመገናኛ - አየር ማረፊያ መንገድ በፍጥነት እየተጠናቀቀ ነው ። በተያያዘ ከአየር ማረፊያ ጎሮ አደባባይ ትንሽ ዝቅ ብሎ የሚያገናኝ ሰፊ መንገድ ከአመታት በፊት ተጀምሮ በብዛት እየተጠናቀቀ ነው።

ይህን ጅምር መንገድ አሁን በሚሰራው የኮሪደር የሳይክል፣ አረንጓዴ እና እግረኛ መንገድ መስፈርት መጨረስ አይቀድምም ወይ?

የመብራት - ጎሮ መንገድን ቤት ሳይፈርስ በነበረበት ስፋት የእግረኛ እና ሳይክል መንገዱን በማስተካከል የውስጥ ለውስጥ ደረጃ መንገድ ማድረጉ አያዋጣም ወይ?

የጎሮ አደባባይ እንዳለ ሆኖ 500 ሜትር ዝቅ ብሎ ያለውን የአየር ማረፊያ - ጎሮ መገናኛ አደባባይ እና ብዙ ቤት ፈረሳ የሌለበትን እንደ መስቀል አደባባይ ማድረጉ አይሻልም ነበር ወይ? እርግጥ ነው የዲዛይን እና ኮንትራት ክለሳ ሥራ ሊጠይቅ ይችላል።

ማን ጠይቆስ ማን መልሶስ?

ለጋራ ስኬት ኧረ ተዉ እንረዳዳ፣ እንመካከር (public consultations)?! በተለይ ባለሙያዎች ድርብ የሙያ ስነምግባር ኃላፊነት እንዳለብን አንዘንጋ።

ከአስር አመት በፊት ከተመረቀ ስድስት ወራት ያስቆጠረ የመስቀል- ቃሊቲ አስፖልት መንገድ ፈርሶ የባቡር ኃዲድ ሊዘረጋ ሲል ተመሳሳይ አማራጭ ሃሳብ ሰጥተን ነበር ። የወቅቱ ሲቪል መኃንዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር 'አስፖልቱ ለአጭር ጊዜ አገልግሎት የተሰራ እና ቢፈርስም ጉዳት እንደሌለው' መልስ የሰጡ ይመስለኛል። በምህንድስና መስፈርት ግን የአጭር ጊዜ አዋጭ አስፖልት የለም። አሁን ይህ የባቡር መንገድ እንደሚነሳ ወሬው ይሰማል። ድርብርብ ኪሳራ አደረስን፤ ያስጠይቀናል ማለት ነው፤ የሃገር ጥቅም በማሳጣት ተወቃሽም ተጠያቂም ሆንን ማለት ነው።

ካሳለፍነው እና ከውጭው ልምድ ስህተትን እና ትክክለኝነትን ብንማር፤ የሃገር ሃብት በተገቢው ቦታና ለተገቢው የቆይታ ጊዜ እንዲውል ብንረባረብ፤ ድካማችንም ምስጋና ቢስ ሆኖ ባይቀር! .... መልዕክቴ ነው ።
Sis Genta

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

13 Nov, 05:17


በአዲስ አበባ ከተማ  50 ሺሕ ብር ጉቦ የተቀበሉ የስራ ሃላፊ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፣ኮሚሽኑ ዛሬ ሕዳር 4/2017 ያሰራጨው መረጃ የሚከተለው ነው።       
(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ. ህዳር 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ) የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆነ አመራር አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ 50 ሺህ ብር ሲቀበል እጅ ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል።

የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ይልማ ህጋዊ የመንግስት መኖሪያ ቤት ውል አላዋውልም በማለት እና 50 ሽህ ብር ተደራድሮ ውል ለማዋዋል ሲሞክር በተደረገ ብርቱ ክትትል እጅ ከፍንጅ መያዝ ችሏል።

አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ የሚሞክሩ ሌሎች ግለሰቦችም ከዚህ በመማር ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው መገለጹን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ህብረተሰቡም ድርጊቱን በማጋለጥ ሂደት ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና ይገባዋል፥ እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦችን ሲያገኝ በአፋጣኝ ለፖሊስ መጠቆም እንዳለበት የጉለሌ ክፍለ ከተማ መልዕክት አስተላልፏል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

12 Nov, 17:27


ከፒያሳ የፈረሱ የወርቅ ቤቶች በስድስት ወር ዉስጥ ወደ ፒያሳ ይመለሳሉ❗️

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የፒያሳን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ ሦስት ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ውል በገባ ማግስት ሥራውን በማስጀመር ግንባታቸውን በስደስት ወራት ለማጠናቀቅ እየሰራ ይገኛል። ከለውጥ በኋላ ፕሮጀክትን በተያዘለት የጊዜ ገደብ መጨረስ አዲሰ ባህል እየሆነ በመጣዉ አሰራር መሰረት በኦቪድ ኩባኒያ ከሚገነቡት ፕሮጀክቶች መካከል የቀደሙ የፒያሳ ወርቅ ቤቶችን ፒያሳ የሚመልስ ፕሮጀክት 24/ 7 ሠዓት እየተገነባ ይገኛል። ግንባታዉም በስድስት ወር ዉስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

12 Nov, 16:02


የት ነው?

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

11 Nov, 01:12


የት ነው?

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

09 Nov, 19:15


#AddisAbaba

" አሁንም አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ለመግባት ምንም እንቅስቃሴ እያደረጉ አይደለም ፤ ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው " - ኮርፖሬሽኑ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ በህግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡

በዚህም በርካታ የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው የገቡ ወይም ለመግባት ዕድሳት ላይ ስለመሆናቸው አደረኩት ባለው የአካል ምልከታ የተገነዘበ መሆኑን ገልጿል።

አሁንም ግን አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ለመግባት ምንም እንቅስቃሴ ያላደረጉ ፤ ነዋሪ ያልገባባቸው ቤቶች እንዳሉ መለየቱን አመክክቷል።

በኮርፖሬሽኑ የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ቤታቸውን አድሰው ለመግባት የጊዜ እጥረት ላጋጠማቸው አንዳንድ የቤት ባለቤቶች የተሰጠውን የጊዜ ገደብ አራዝሟል።

እስካሁን ድረስ ወደቤታቸው ለመግባት ምንም ይነት እንቅስቃሴ ያላደረጉ እንዲሁም ቤት ለማደስ የጊዜ እጥረት ያጋጠማቸው የቤት ባለቤቶች እስከ ህዳር 30 2017 ዓ.ም ወደ ቤታቸውን እንዲገቡ ለመጨራሻ ጊዜ አስጠንቅቋል።

በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ እና በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂ የሚሆኑ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አሳስቧል።

ከዘህ ቀደም ኮርፖሬሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥቶት በነበረው ማብራሪያ ፥ ማስታወቂያው የወጣበት ዋናው ምክንያት ሰዎች ‘ ተቸገርን፣ ክፍት በሆኑ ቤቶች ወንጀል እየተሰራ ነው፣ እየተዘረፍን ነው፣ ሴቶች እየተደፈሩብን ነው፣ የጸጥታ ስጋትም እየሆኑብን ’ ብለው ቅሬታ ስላቀረቡ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል።

ቤቶቹ ቼክ ሲደረጉ ደግሞ እጣ ወጥቶባቸዋል፤ ውል ተፈጽሞባቸዋል፣ ግን ሰው አልገባባቸውም፡፡

" ስለዚህ ነዋሪው ተቸግሯል፡፡ የጸጥታ ኃይሉም ጥያቄ እያነሳ ነው " ብሎም ነበር።

" የቤት ባለቤቶች ቤታችሁን አድሳችሁ ግቡ " የተባለውም የግድ እራሳቸውን እንዳይሰለ አስረድቶ ነበር።

" ቢፈልጉ አድሶ ማከራየት መብት ነው፡፡ የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ፡፡ ግን ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ይኑርበት ነው የኛ ጥያቄ፡፡ አካራይ አታከራይ የኛ መልዕክት ሊሆን አይገባም፡፡ ግን ቤቱን ኦውን ያድረጉ " ነው የሚል ማብራሪያ ነበር ኮርፖሬሽኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

09 Nov, 11:55


በቅርቡ ወደ ባንክ ኢንዱስትሪው የተቀላቀለው አሃዱ ባንክ፣ በ2015 የሥራ ዘመን 267.7 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አጋጥሞት ነበር። በ2016 በጀት ዓመት ደግሞ በከፊል አገግሞ ከታክስ በፊት 120 ሚሊዮን ብር ገደማ ትርፍ አግኝቷል።

ታዲያ አሃዱ ባንክ አሁን አንድ ታሪካዊ ውሳኔ ማሳለፉ እየተነገረ ነው። ይኸውም እየከበደ የመጣውን የባንክ ኢንዱስትሪ ፍክክርን ለመቋቋምና የብሔራዊ ባንክ አዳዲስ ፖሊሲዎችን ያለ ፈተና ለማለፍ አሃዱ ባንክ ከሌላ ባንክ ጋር ሊዋሀድ እንደኾነ ተነግሯል። ከባንኩ ጋር የሚዋሃደው ባንክ ለጊዜው ይፋ ባይደረግም ውሳኔው ሩቅ ሐሳቢነት የተሞላበት እየተባለለት ነው።

ይሄ የአሃዱ ባንክ ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ወለድ አልባ አገልግሎት ለመስጠት ለተመሠረቱና በብሔራዊ ባንክ አዳዲስ ፖሊሲዎችና በሌሎችም ችግሮች ሰበብ አካፋይ መንገድ ላይ ለቆሙ ባንኮች ትልቅ መልዕክት ያዘለ ነው።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

09 Nov, 11:51


ጥብቅ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ በህግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን ማስተጠንቀቁ ይታወሳል፡፡

በዚሁ አግባብ በርካታ የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው የገቡ ወይም ለመግባት ዕድሳት ላይ ስለመሆናቸው ባደረግነው የአካል ምልከታ የተገነዝብን ሲሆን አሁንም አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ለመግባት ምንም እንቅስቃሴ ያላደረጉ በመሆኑ በውል ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው ቤቶች እንዳሉ ለይተናል፡፡

በመሆኑም የኮርፖሬሽኑን ጥሪ ተቀብላችሁ ወደ ቤታችሁ የገባችሁ ወይም በማደስ ላይ ለምትገኙ የቤት ባለቤቶች ለሰጣችሁት ፈጣን ምላሽ እያመሰገንን፤ የኮርፖሬሽኑን ጥሪ ተቀብለው ቤታቸውን አድሰው ለመግባት የጊዜ እጥረት ያጋጠማቸው አንዳንድ የቤት ባለቤቶች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ማራዘም አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት እስካሁን ድረስ ወደቤታችሁ ለመግባት ምንም ይነት እንቅስቃሴ ያላደረጋችሁ እንዲሁም ቤት ለማደስ የጊዜ እጥረት ያጋጠማችሁ የቤት ባለቤቶች እስከ ህዳር 30 2017 ዓ.ም ወደ ቤታችሁ እንድትገቡ ለመጨራሻ ጊዜ በጥብቅ እያስጠነቀቅን፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ እና በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂ የሚሆኑ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ በጥብቅ ያሳስባል::

ማሳሰቢያ፦

የቤት ባለቤቶች ማህበራት ቤታቸውን አድሰው ለመግባት እንቅስቃሴ ላይ ለሚገኙ የቤት ባለቤቶች የተለመደ ትብብር እና ድጋፍ እንድታደርጉ ኮርፖሬሽኑ ጥሪውን ያቀርባል::

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

09 Nov, 01:50


በአሽከርካሪዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶች እና የጥፋቶቹ እርከን
ሀ/ አንደኛ ደረጃ የጥፋት ዝርዝር
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

09 Nov, 01:50


በአሽከርካሪዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶች እና የጥፋቶቹ እርከን
ለ/ ሁለተኛ ደረጃ የጥፋት ዝርዝር

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

09 Nov, 01:49


በአሽከርካሪዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶች እና የጥፋቶቹ እርከን
ሐ/ ሶስተኛ ደረጃ የጥፋት ዝርዝር
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

09 Nov, 01:45


እግረኛ

ለጥፋቶቹ የሚቆጠር የቅጣት ነጥብ እና የቅጣት መጠን ወይም የሚወሰድ እርምጃ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

05 Nov, 11:52


በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን አዲስ አበባ ገባ

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን አዲስ አበባ ገባ።

የኢትዮያ አየር መንገድ ከኤር ባስ ኩባንያ የገዛው ኤ350-1000 አውሮፕላን ከፈረንሳይ ቱሊስ ተነስቶ አዲስ አበባ ገብቷል።

አውሮፕላኑ "ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ" የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

04 Nov, 14:40


ብዙዎቻችን ሰልፍ መሰለፍ አንወድም።

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ሊዝ ጨረታ ዶክመንትን ሳንሰለፍ በቀላሉ እንድንገዛ፣ 2merkato ከአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጋር በመሆን መፍትሒ አበጅቷል። 2ኛ እና 3ኛ ዙሮች በስኬት ተጠናቅቀው አሁን የ4ኛ ዙር ዶክመንት addisland.2merkato.com ላይ እየተሸጠ ነው።

ዶከመንቱን ለመግዛት፦
1ኛ፦ ይሄንን ሊንክ ይክፈቱ - https://tender.2merkato.com/tenders/6711240b531819119fac483a
2ኛ፦ "Buy Now" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ
3ኛ፦ ይመዝገቡ፤ ይክፈሉ እና ዶክመቱን ያውርዱ፤ የቴሌብር ደረሰኝን መያዝ እንዳለብዎት ያስታወሱ!

መልካም ዕድል!

#ሰልፍቀረ #nomorequeues #addislandlease #biddocument #onlinesolutions

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

02 Nov, 21:09


በመሬት ውስጥ የሚያልፍ የእግረኛ መንገድ ለመስራት ነው መገናኛ ያለው ድልድይ እየፈረሰ ያለው

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

02 Nov, 12:11


ለመምህራን የምገባ መርሐግብር መጀመሩ ተገለፀ

በሸገር ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት ቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪና መምህራን የምግብ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህ ፕሮግራም የተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥን ማስወገድ የተቻለ ሲሆን መምህራንም በማስተማር እና በመማር የበለጠ እንዲተጉ አድርጓል ተብላል።

በሸገር ከተማ በሚገኙ 256 ትምህርት ቤቶች የተማሪ እና የመምህራን ምግብ ፕሮግራም እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን ለ148 ሺ 795 ተማሪዎች እና ለ3 ሺ 707 መምህራን መስጠት ተችሏል።

(የኔታ)

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

02 Nov, 12:02


በቤተመንግስት ተገኘ ስለተባለው 400 ኪ/ግ ወርቅ

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ "ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል" ማለታቸው ይታወሳል።

"ይህ ወርቅ ምን ይሆን ብዬ?" አንዳንድ ማጣራቶችን ለማድረግ ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ አስደንጋጭም፣ አሳሳቢም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ይህ ወደ ብሄራዊ ባንክ ተላከ የተባለ ወርቅ በኢትዮጵያ የንጉሳዊ ስርዐት ወቅት ለበርካታ መቶ አመታት ነገስታት ሲገለገሉባቸው የነበሩ በወርቅ እና በሌሎች የከበሩ ማዕድናት የተሰሩ ቁሳቁሶች፣ ከሌሎች ሀገራት በስጦታ የተሰጡ ቅርሶች እንዲሁም በርካታ በነገስታቱ ታዘው የተሰሩ እና የተገዙ ናቸው።

"ታድያ እነዚህ ወደ ሙዚየም እንጂ ለሽያጭ ወይም ለወርቅ ክምችት ወደ ባንክ እንዴት ሊላክ ይችላል?" ብዬ ጥያቄ ያቀረብኩላቸው ጉዳዩን የሚያውቁ ግለሰቦች ምላሻቸው "ማን ሰምቶን?" ነው።

ቅርስ ጥበቃ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ የጠ/ሚር ፅ/ቤት እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ዙርያ መክሮ እነዚህን የኢትዮጵያ ታሪክ የሆኑ ንብረቶች ወደነበሩበት ቦታ ወይም ወደ ሙዚየም እንዲመለሱ ማድረግ አለባቸው።

እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው!
@EliasMeseret

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

02 Nov, 11:38


የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደረጉ የመንገድ ግንባታዎችን ተከትሎ የተርሚናል ለውጥ መደረጉንም ቢሮው ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ከመገናኛ – ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበሩት መስመሮች ደግሞ አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ) ወዳለው ቦታ ተዛውሯል፡፡

ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ የነበሩ መስመሮች ከመገናኛ – ገርጂ ፣ ከመገናኛ-ጎሮ ፣ ከመገናኛ – አያትና ከመገናኛ – ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ቢሮው ገልጻል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

31 Oct, 12:11


የጅማ ፈረንጅ አራዳ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

31 Oct, 07:24


የት ነው?

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

31 Oct, 07:11


መብራት
ከጥቅምት እስከ ታህሳስ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ስሌት

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

30 Oct, 22:40


" የተሰጠው ማብራሪያ ከእውነት የራቀ ነው " - የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች

ሰሞኑን ከ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ወይም ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ዝርዝር ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህም ማብራሪያው ፥ " ብቁና ንቁ የነበሩ የ1997 ተመዝጋቢዎች  በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል " ነበር ያለው።

ዝርዝር ማብራሪያው በዚህም ይገኛል ፦ https://t.me/tikvahethiopia/91710?single

ማብራሪያውን የተመለከቱ ቆጣቢዎች ግን ማብራሪያ " ከእውነት የራቀ ነው " ሲሉ ግብረ መልስ ሰጥተዋል።

" እኛ የ1997 ነባር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት አክቲቭ ተመዝጋቢዎች ሰሞኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሰጠው መግለጫ ከእውነታ የራቀ ነው ስንል አንገልፃለን " ብለዋል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት።

" እኛ የ1997 አክቲቭ ቆጣቢዎች የሆንን በ14ኛው ዙር 25 ሺህ ለእጣው አክቲቭ ናቸው ተብለን ለ18,650  ቤቶች ተወዳድረን እጣው ያልወጣልን ወደ 8,000 የምንሆን የተረፍን አክቲቭ ቆጣቢዎች መሆናችን ቢሮው በደንብ ያውቃል ሰነዳችንም በግልፅ በቤቶች ኤጀንሲም ሆነ በንግድ ባንክ አለ " ብለዋል።

" ቢሮው ' ብቁ እና ንቁ የነበሩ የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል ' ማለቱ እጅግ ግራ የሚያጋባ ነው የሆነብን " ሲሉም አክለዋል።

አሉን ያሏቸውን ዶክመንቶችንም የላኩ ሲሆን ከላይ ተያይዟል።

ጉዳያቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም እንደያዘው አስታውሰው ተቋሙ መፍትሄ እስኪያገኙ ድረስ እንዲገፋበት ጥሪ አቅርበዋል።

ዜጎቹ " አሁንም ድምፃችን ይሰማ ፤ መፍትሄ ይሰጠን " ሲሉ ጠይቀዋል።
@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

30 Oct, 20:10


40/60 ኮንዶሚኒዮም በተመለከተ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

30 Oct, 16:22


የመገናኛ መሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል

ከፍተኛ መጨናነቅ ባለበት " መገናኛ ' አካባቢ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል። በዚህ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት ያግዛል የተባለ የመሬት ውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መሰራት ጀምሯል።

ይህ ፕሮጀክት ከቦሌ ኤርፖርት እስከ መገናኛ ባለው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

ገንቢው ተቋራጭ ይህንን ስራ እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው ጊዜ 45 ቀን ነው።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

30 Oct, 04:05


የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ፣ በየካ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ፣ ልደታ፣ በጉለሌ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 08/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ
በ2merkato.com – https://addisland.2merkato.com ወይም
afrotender.com - link https://addisland.afrotender.com) መግዛት ይችላሉ።
2.ማንኛውም በዚህ የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የፈለገ ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸዉ ዌብ ሳይት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በመጀመሪያ በስሙ የቴሌ ብር አካውንት በመክፈት ከአካውንቱ ተቀናሽ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል።

3. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባችሁ።

4. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም። በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

5. ተጫራቾች ሞልተው የሚያቀርቡት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘውን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል። እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሠሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወርክ የተያያዘ መሆን አለበት፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር ጽ/ቤቱ አይጠየቅም።

7. ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመልሱ፣

7.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO)
7.2 የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ
7.3 የተጫራቹ መታወቂያ ኮፒ
7.4 ሰነድ ለመግዛት በቴሌ ብር የተከፈለበት ስሊፕ (ደረሰኝ)
7.5 ኦርጂናል የአቅም ማሳያ ማስረጃ
7.6 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ኮፒ
7.7 የውጭ አገር ዜግነት ያለው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውም ተጫራች ከሚኖርበት አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ /ቆንስላ ጽ/ቤት የተሰጠውንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ በውልና ማስረጃ የፀደቀ መታወቂያ የዋናውን ኮፒ ከመልስ ማቅረቢያው ጋር ማያያዝ አለበት።
7.8 የንግድ ማኅበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ፅ/ቤት የፀደቀ የማኅበሩን መመሥረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ሌሎች ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ
7.9 ጨረታው የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ሕጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ኮፒ እና በአንድ ወገን ስም የተሠራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
7.10 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች ማረጋገጫ እናምዝገባ ፅ/ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ሕጋዊ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7.11 በአጠቃላይ ከላይ የተገለጹትን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ የጨረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በፖስታው ላይ በመጻፍ ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ (M A) ሕንጻ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል። ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልክት ከፈለጉ በ11/02/17 ዓ.ም፣ 13/02/17 ዓ.ም እና በ15/02/17 ዓ.ም ጠዋቱ በ3፡00 እና ከሰዓት በ8 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች የሚገኙበት ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ሥራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል።

9. ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለጸበት ከ15 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አጫራቹ መ/ቤት ለባንክ በመላክ ወዳሠሩበት የባንክ ሂሳብ ተመላሽ ይደረጋል። በካሽ ያሠሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒ ማቅረብና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ አለባቸው። ከላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ መ/ቤት ተጠያቂ አይሆንም።

10. መሥሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-

በስልክ ቁጥር +251 11 157 0595 መረጃ ማግኘት ይቻላል።

https://www.aalb.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

30 Oct, 04:04


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ፣ በየካ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ፣ ልደታ፣ በጉለሌ፣ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል::

*** ማሳሰቢያ => ሰነዱን የሚገዙበት የቴሌ ብር ቁጥር ወይም ስም በተጫራቹ ሰም የተመዘገበ መሆኑን እርግጠኛ ይሁኑ!!

ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ

ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር)
Bid bond ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘውን ጠቅላላ ዋጋ 50%

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

29 Oct, 18:16


የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች "ፋይዳ" መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ መሆኑን አስታወቀ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ደንበኞች "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተቋሙ ባወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡

በመሆኑም ከህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ደንበኞች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ማሳሰቡን ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

29 Oct, 18:12


ብቁና ንቁ የነበሩ የ1997 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በ14ኛው ዙር ዕጣ ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል፡፡

➢ በ1997 ዓ.ም የቤት ባለቤት ለመሆን ተመዝግበው የነበሩ የከተማችን ነዋሪዎች በ2005 ዓ.ም በተካሄደው ዳግም ምዝገባ ወቅት ነባር የሚል መለያ ተሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን ዳግም ከተመዘገቡና ውላቸውን ካደሱ ጊዜ ጀምሮ ሳያቋርጡ ሲቆጥቡ የነበሩ ናቸው፡፡   

➢ እነዚህ ተመዝጋቢዎች ቀደም ብለው የተመዘገቡ እንደመሆናቸው መጠን በ20/80 የቤት ልማት መርሃ ግብር ተገንብተው ለእጣ ከሚተላለፉት ቤቶች ውስጥ የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ በወጣው መመርያ ቁጥር 3/2011 መሰረት በነበሩት ዙሮች ቅድሚያ እየተሰጣቸው ሙሉ በሙሉ ተስተናግደዋል፡፡

➢ በዚሁ አግባብ በ2005 ዳግም ምዝገባ ያደረጉ ከ140 ሺህ በላይ ተመዝጋቢዎች ሳያቆራርጡ እስከ እጣ ማውጫ ቀን ድረስ እየቆጠቡ ለነበሩት እስከ 13ኛ ዙር በነበረው የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ ሲሰተናገዱ ቆይተዋል፡፡

➢ ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለ14ኛ ዙር በተላለፉት የ20/80 የጋራ መኖርያ ቤቶች ላይም የ1997 ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ተስተናግደዋል፡፡

➢ በዚህም በ14ኛ ዙር እጣ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ንቁና ብቁ የነበሩ ከ43ሺህ ያልበለጡ ቆጣቢዎች ቅድሚያ በመስጠት ሙሉ በሙሉ እንዲሰተናገዱ ተደርጓል፡፡

➢ በእጣ ማውጫ ጊዜ በመረጃ ቋት ውስጥ የቀሩት የ1997 ተመዝጋቢዎች በጊዜው ንቁና ብቁ ያልነበሩ ናቸው፡፡
➢ እነዚህና ሌሎች ቤት ፈላጊዎች በከተማ አስተዳደሩ እየተተገበሩ በሚገኙ የተለያዩ የቤት የልማት አማራጮች ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

➢ ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በከተማዋ እየተካሄዱ በሚገኙ የልማት ስራዎች ምክንያት ከመኖርያ አካባቢያቸው ለሚነሱ የልማት ተነሽዎች በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የወጣው በጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ማስተላለፍ መመርያ ቁጥር 3/2011 አንቀጽ 23 በተገለጸው መሰረት በከተማ መልሶ ማልማት ምክንያት ለሚነሱ ነዋሪዎች ምትክ ቤት ለመመደብ በተቀመጠው አሰራር መሰረት እየተስተናገዱ ይገኛሉ፡፡

➢ እነዚህ በልማት ምክንያት የሚነሱ ነዋሪዎች ምትክ ቤት የሚሰጣቸው ከላይ በተጠቀሰው መመርያ ላይ በሰፈረው መሰረት በከተማ አስተዳደሩ ከሚገነቡ የጋራ መኖርያ ቤቶች ውስጥ ለልማት ተነሺ በሚል በመጠባበቂያ ከተያዙት ቤቶች እንጂ በመደበኛነት ለተመዝጋቢዎች ከሚተላለፉ ቤቶች አይደለም፡፡

➢ የልማት ተነሺ ሆነው የጋራ መኖርያ ቤት ምትክ የወሰዱና በ20/80 ወይም በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ተመዝጋቢ የሆኑ ነዋሪዎች ከምዝገባ ቋት ውስጥ የሚቀነሱ ይሆናል፡፡

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

29 Oct, 07:50


ለመረጃ ያህል ስለጋራ መኖሪያ ቤቶች

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ጥያቄ እና ፍላጎት ለመመለስ የተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞችን በመዘርጋት የተለያየ የገቢ መጠን ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የመክፈል አቅም ያገናዘበ  የመኖሪያ ቤት በመገንባት ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት፡-

👉  በመንግስት አስተባባሪነት በ10/90፣በ20/80 እና በ40/60 የጋራ መኖርያ ቤቶችን ተገንብተው  በ14 ዙሮች ከ300 ሺህ በላይ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል፤

👉 ቤቶች የሚገነቡት ከባንክ በተገኘ የቦንድ ብድር ሲሆን ተቋሙ ቀደም ሲል የነበረበትን 56 ቢሊዮን ብር እዳ ለማቃለል በተደረገ ጥረት ከ36 ቢሊየን ብር በላይ ተመላሽ ተደርጓል፤   

👉 ተመዝጋቢዎች የሚቆጥቡት ብር ቤቱ ሲደርሳቸው የሚከፍሉት እንዳይቸገሩ እንጂ ቤቶችን ለመገንባት የሚውል አይደለም፤

👉 እያደገ የመጣውን የመኖርያ ቤት ችግር ለመፍታት ሌሎች ተጨማሪ አማራጮች ተቀይሰው መተግበር ጀምረዋል፤

👉  ከ5ሺህ ቤቶች በላይ በተገጣጣሚ ቴክኖሎጂ እየተገነቡ ይገኛሉ፤

👉  የቤት አቅርቦቱን ለማስፋት በተደረገ ጥረት 60ሺ ቤቶች በግሉ ባለሀብት እንዲለሙ ተደርጓል፤

👉  በመንግስት እና በግል ዘርፍ አጋርነት ከ120 ሺ በላይ ቤቶች ግንባታ ስራ  ተጀምሯል፤ 

👉  በበጎ ፈቃድ ባለሀብቶችንና የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ከ35ሺ በላይ ቤቶችን በመንግስት እና የግል ባለሀብቱን በማስተባበር ተገንብቶ በዝቅተኛ ኑሮ ላሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተላልፈዋል፤

👉 ፍላጎት እና አቅም ያላቸውን በ20/80 እና በ40/60 ተመዝግበው ሲጠባበቁ የነበሩ 4,318 ነዋሪዎችን በ54 ማህበራት በማደራጀት ወደ ግንባታ እንዲገቡ ተደርጓል፤  

👉  በተመጣጣኝ ዋጋ ለኪራይ የሚቀርቡ ቤቶችንም ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ 

👉 ተመዝግበው የቤት ባለቤት ለመሆን የሚጠባበቁ ነዋሪዎችን በአጭር ጊዜ የቤት ባለቤት ለማድረግ የቤት ልማት አማራጮች በማስፋትና በመተግበር ከምን ጊዜውም በላይ እየተጋ ይገኛል፡፡
 
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
 

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

29 Oct, 04:00


በርካታ ነዳጅ የሚጠቀሙ ቅንጡ እና ውድ መኪናዎች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ እንደሆነ ታወቀ

(መሠረት ሚድያ)- በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በታገደበት በአሁኑ ወቅት በርካታ ነዳጅ የሚጠቀሙ ቅንጡ እና ውድ መኪናዎች ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ እንደሆነ መሠረት ሚድያ ያደረገው ምርመራ ያሳያል።

ታድያ ከሁሉም በላይ መነጋገርያ የሆነው በታዋቂው የንግድ ሰው አቶ ሻቃ ጉርሜሳ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ፕሮሰስ ላይ የሚገኙት 700 ይደርሳሉ የተባሉት V8 መኪናዎች ጉዳይ ነው።

የ Shaka Mall ባለቤት የሆኑት አቶ ሻቃ መኪና በማስመጣት እና በመሸጥ ከበርካታ አመታት በፊት ጀምሮ ልምድ ያላቸው ቢሆኑም በዚህ ወቅት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በብዛት ማስገባት መቻላቸው ለብዙዎች እንቆቅልሽ እንደሆነ ሰምተናል።

በቅርቡ 700 V8 ላንድ ክሩዘር መኪናዎችን ሊያስገቡ ሂደት ላይ እንደሆኑ የታወቀ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ላይ ጥሩ የአመራር ብቃት ላሳዩ የመንግስት ተሿሚዎች በስጦታ መልክ የሚበረከቱ መሆናቸው ተሰምቷል።

"መድሃኒት ፈልጎ ማግኘት ከባድ በሆነበት፣ ብታገኝም ዋጋው በማይቀመስበት አገር እንዲህ አይነት የሃብት ብክነት እየተፈፀመ ይገኛል" ያሉት አንድ ጉዳዩን የሚያውቁ የመረጃ ምንጫችን ናቸው።

የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን የተሽከርካሪ አጠቃቀም አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የዛሬ ስድስት አመት ያወጣው መመሪያ በበርካታ ተቋማት እየተተገበረ አለመሆኑ ተደጋግሞ እየተነሳ ይገኛል።

በመመሪያው ቁጥር 4 ንዑስ ቁጥር 1 ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ወጪ ቆጣቢና ውጤታማ የፋይናንስ አጠቃቀም እንዲኖር ለከተማ ውስጥ ስራ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎችን እንዲጠቀሙ ተደንግጓል።

በዚህ መሰረት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ቪ8፣ ቪ9፣ ፕራዶና ፓጃሮ ተሽከርካሪዎችን ከሚጠቀሙ ይልቅ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎችን ቢጠቀሙ ከፍተኛ ወጪ በመቀነስ ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ተገልፆ ነበር።

ይሁንና አሁን ድረስ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ቪ8 እና ሌሎች ተመሳሳይ መኪናዎችን ከተማዎች ውስጥ እንደሚጠቀሙ መሠረት ሚድያ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል።
መረጃን ከመሠረት!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

24 Oct, 15:33


ለጋራ መኖሪያ ቤት የሚሆኑ የውሃ ፓምፖች በዛሬው ዕለት ገብተዋል

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ40/60 የቤቶች ልማት ፕሮግራም በተለያዩ ሳይቶች ለተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚሆኑ  የውሃ ፓምፖች በዛሬው ዕለት በኮርፖሬሽኑ ስር በሚገኘው የበሻሌ ሳይት ገብተዋል፡፡

በቅርቡ ፓምፖቹ ወደ ሥራ ገብተው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ኮርፖሬሽኑ ገልጿል፡፡

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

22 Oct, 23:41


ገቢዎች ሚኒስቴር የባንክ ሰራተኞች በአነስተኛ ወለድ ያገኙት ብድር እንደ ገቢ ተቆጥሮ ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ሕግ አወጣ

ይህ መመሪያ ከተተገበር 50% ገቢያችንን ለመንግሥት እየሰጠን ነው:-የባንክ ሰራተኞች

የባንክ ሰራተኞች የባንክ ሰራተኛ ስለሆኑ ከሚሰሩባቸው ባንኮች ለቤት እና መኪና በአነስተኛ ወለድ የሚወስዱት ብድር ፣ ለወሰዱት ብድር የሚከፍሉት አነስተኛ ወለድ ከገበያው ወለድ ጋር ያለው ልዩነት ተሰልቶ የሚመጣው ልዩነት እንደ ገቢ ተቆጥሮ ግብር እንዲከፍሉ ሊደረግ መሆኑን የባንክ ሰራተኞች ገልፀዋል። ይህም ከዚህ ወር ማለትም ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን መመሪያው ደርሶናል ብለዋል።

በገቢዎች ሚኒስቴር “የቅናሽ ወለድ የአይነት ጥቅም ላይ የሚከፈል ግብር” በሚል ሊተገበር የቀረበው ህግ በበርካታ የባንክ ሰራተኞች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል የባንክ ሰራተኞች “ህጉ የባንክ ሰራተኛ በመሆናችን የምናገኘውን ብቸኛ ጥቅም የሚነጥቀን ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ንግድ ባንኮች በተለምዶ ለደንበኞቻቸው ብድርን ሲሰጡ ከ12 በመቶ በላይ ወለድ ያስከፍላሉ። ሆኖም ሰራተኞቻቸው ቤትና መኪናን መግዛት ሲፈልጉ የሚያበድሯቸው በሰባት በመቶ ወለድ ነው። ይህ ማለት ብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንኮች ቆጣቢዎች ያስቀመጠው ትንሹ የወለድ ምጣኔ ነው። ንግድ ባንኮችም ለሰራተኞቻቸው የሚሰጡት ዋነኛ ማትጊያ ሰራተኞቻው ቤትና መኪና መግዛት ሲፈልጉ በትንሹ መቆጠቢያ ወለድ ማለትም በሰባት በመቶ ማበደርን ነው።
የገቢዎች ሚኒስቴር በ2016 አ.ም በአነስተኛ ወለድ ብድር የሚያገኙ ሰዎች ፣ የቅናሽ ወለድ የአይነት ጥቅም ላይ የሚከፈል ግብርን መክፈል አለባቸው በሚል በዋነኝነት የባንክ ሰራተኞችን ኢላማ ያደረገ ህግ አወጣ። ይህ ማለት ፣ በሰባት በመቶ ወለድ ብድርን ያገኘ አንድ የባንክ ሰራተኛ በየወሩ የሚከፍለው ወለድ ፣ በገበያ ወለድ ቢበደር ኖሮ ሊከፍል ከነበረው ወርሀዊ ወለድ ላይ ተቀንሶ የሚመጣው ልዩነት ፣ የሰራተኛው ደሞዝ ላይ ተደምሮ ግብር እንዲከፍል ይገደዳል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

22 Oct, 20:01


አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ፣ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው? ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር።

የመምህራን የስልጠና ክፍያ እጅግ አነስተኛ መሆን ከኑሮ ውደነት ጋር ተያይዞ ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሰጡት የነበረውን የሙያ ስልጠና አለመስጠታቸው የትምህርት ጥራት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ እያደረገ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠየቀ።

ከማኀበሩ የተሰነዘሩ ቅሬታዎች ምንድን ናቸው ?

“ ከትምህርት ሥርዓት አንጻር በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ጥራት ችግር ብቻ ልንለው አንችልም። የትምህርት ቀውስ ነው። ቀውስ ውስጥ ገብተናል። ወደ መምህራን ችግሩን የመግፋት ነገር ይታያል። ይሄ ትክክል አይደለም። 

ሲጀመር የመምህርት ስልጠና ዋጋ አልተሰጠውም። ለምላሌ ፦ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እጩ መምህራን ከተወሰኑ ኮሌጆች ውጪ 450 ብር ተሰጥቷቸው ውጪ ሆነው እንዲማሩ የሚደረጉት።

አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው ? ችግሩ እዚያ ጋ ነው የሚጀምረው። 

እጩ መምህራን ወደ ኮሌጅ ውስጥ ሲገቡ 450 ብር ይከፈላቸዋል። ፍላጎታቸውን ስለማይሟላ ትምህርት ላይ ትኩረት ሳያደርጉ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ይንቀሳቀሳሉ። ይሄ የመምህርነትን ሙያ ጥራቱን ቀንሶታል። ስለዚህ ጉዳዩ ሊታረብበት ይገባል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ጥናት አጥንቷል። በዚያ መልኩ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል


በሌላ በኩል ፥ ወደ መምህርነት ሙያ ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንሲ ተብለው እነዚህ የመቐለ ፣ ባሕር ዳር፣ የአዲስ አበባ፣ ጅማና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንን የሚያሰለጥኑ ነበሩ ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች። 

ነገር ግን ላለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ምንም አይነት ተማሪ ወደ መምህርነት ሙያ እንዲገባ እያሰለጠኑ አይደለም። 

ይሄ ደግሞ በቀጣይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችንን በድጎማ መምህር ልናስይዝ አይደለም ወይ ! ይሄ ወዴት እየሄደ ነው ?


በተያያዘ፣ የመፅሐፍት ስርጭት ችግሮች አሉ። ችግር መኖር ብቻ ሳንሆን አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ በአንድ ላይ ኮምባይን የሆኑ ትምህርት ቤቶች አሉ። 

ለምላሌ ፦ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባይሎጂ አንድ ላይ ናቸው። በአንድ መምህር ነው የሚሰጡት። ይህም መምህራን ኬሚስትሪውን ፓርት ያስተምሩና ፊዚክስና ባይሎጂው የተመረቁበት ስለማይሆን ለማስተማር እየተቸገሩ ነው። 

በሌሎች የትምህርት አይነቶችም ተመሳሳይ ችግር አለ። መምህር ያልተዘጋጀባቸው ሥርዓተ ትምህርቶች አሉ። የትምህርት ጥራቱን እየጎዳው ያለው አንዱ ችግር ይሄ ነው። አጠቃላይ ትምህርቱ ሴክተሩ በቂ ትኩረት አላገኘም። በቂ ፋይናንስ እየተመደበለት አይደለምና ሊመደብለት ይገባል።

መምህራንም የተለያዬ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሲፈጠሩ መብታቸውን ለማስከበር ወደ ሕግ ተቋማት ስለሚሄዱ የትምህርት ጊዜ ይዘጋል። ይሄ ደግሞ የትምህርት ጥራት ላይ ችግር አምጥቷል። ”


እነዚህ ቅሬታዎች የትምህርት ሚኒስቴር በተገኘበት መድረክ እንደቀረቡ ማኀበርሩ ገልጾልናል።

የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዲሰጡ ያሳሰበው ማኀበሩ፣ ትምህርት ሚኒስቴር በተነሱት ቅሬታዎች ዙሪያ መፍትሄ ለማምጣት አሳይመንት ይዞ እንደሄደ አመላክቷል።
@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

22 Oct, 20:00


የሁለት ዘመናት...

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

22 Oct, 04:37


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያስገነባቸው ቤቶች ለጨረታ አቅርቧል፤

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 13:05


አዲስ አበባ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 13:01


የዚህን ሰአት ባትሪ ድንጋይ የት ነው የሚገኘው?
🙈

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 12:55


ማስታወቂያ

የማህበር ቤት ተመዝጋቢ የሆናችሁ እና ቀደም ሲል ስም ዝርዝራችሁ ተገልፆ ቅጽ 01 አስሞልታችሁ የመመለሻ ቀን የተራዘመባችሁ ተመዝጋቢዎች በሙሉ።

ቅፁን እና አስፈላጊውን  መረጃዎች ይዛችሁ ከጥቅምት 13/2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ ተቅምት 19/2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ብቻ ባምቢስ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ህንፃ 6ኛ ፎቅ የቤት ማህበራት ዳይሬክቶሬት በመገኘት መረጃችሁን እንድታስገቡ እናሳወቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 04:12


በኤርፖርት ያሉ እንዲህ አይነት ጉዳዮች ሲነሱ አንዳንዶች በቀጥታ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሚያያይዙት ቢሆንም የኤርፖርት ጥበቃ እና ፍተሻ የሚከናወነው በአየር መንገዱ ሳይሆን በሌሎች የመንግት የደህንነት እና የፅጥታ አካላት መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።
መሰረት ሚዲያ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 04:10


ወደ ደቡብ አሜሪካ የሚጓዙ ዜጎች ቦሌ ኤርፖርት ላይ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር ጉቦ እየተጠየቁ እንደሆነ ተናገሩ።

በርካታ ጥቆማ ሰጪዎች በሰጡን መረጃ መሠረት በተለይ ወደ ብራዚል የሚጓዙ ዜጎች ለጉዞ ማድረግ ያለባቸውን ፕሮሰስ ሁሉ ጨርሰው እና ከብራዚል ኤምባሲ ቪዛ ተመቶላቸው በበረራ ሰአታቸው ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ "በዛው ልትጠፉ ነው፣ ስለዚህ እንድትሄዱ እንድንፈቅድላችሁ 500 ሺህ ብር አምጡ እየተባልን ነው" ብለዋል።

አንድ ጥቆማ ሰጪ ደግሞ ወደ አንድ የአየር ማረፊያው ቢሮ ሀላፊ በመግባት ሁኔታውን ሲያስረዳ "እዛው ጨርስ" እንደተባለ ተናግሯል።

በቦሌ አየር ማረፊያ ላይ በርካታ የመብት ጥሰቶች እና ሙስና እንደሚፈፀም ከዚህ በፊት ተደጋግሞ መነሳቱ ይታወሳል። ይሁንና በአየር ማረፊያው የፍተሻ እና ጥበቃ አካላት አንድ ተጓዥ ላይ በየካቲት 2016 ዓ/ም ዝርፊያ እና እንግልት ከተፈፀመ በኋላ ጉዳዩ ወደ ማህበራዊ ሚድያ በመምጣቱ መንግስት ምላሽ ሰጥቶበት ነበር።

በወቅቱ አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ግለሰብ በፍተሻ ወቅት "ሻንጣሽን ከፍተሽ አሳዪን፣ ማሽኑ የሆነ ነገር ያሳየናል" በማለት ሻንጣዎቿን አስከፍተዋት በዚህ ወቅት የያዘችውን የግል መገልገያ ጌጣጌጥ እና በህጋዊ መንገድ የያዘችውን ዶላር አካፍዪን ማለታቸው ይታወሳል።

ይህን መረጃ ተንተርሶ በተደረገ ማጣራት ድርጊቱን ፈፃሚዎች በካሜራ ክትትል ተይዘው ለእስር ተዳርገው ነበር።

እንዲህ አይነት ኤርፖርት ላይ በፀጥታ እና ኢሚግሬሽን ሰራተኞች የሚፈፀም ድርጊት በተለይ ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ዜጎች የበረታ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

መሰረት ሚዲያ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 04:05


#AddisAbaba #ኮንዶሚኒየም

🔵 " ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ? ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " - አቶ አበበ አካሉ

" የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ


ከአዲስ አበባ የኮሪደር ስራ ጋር በተያየዘ በርካቶች በልማት ተነሺነት ከኖሩበት አካባቢ ተነስተው ወደ ተለያዩ ጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲገቡ እየተደረገ ነው።

ምንም እንኳን ተነሺዎቹ መግባታቸው ላይ ቅሬታ ባይፈጥርም ከ97 አንስቶ ሲቆጥቡ የኖሩ ነዋሪዎች መፍትሄ ሳያገኙ መቅረታቸው እና አሁን ላይ አስተዳደሩ ቤት የተሰጠ መሆኑ ቅሬታ አሳድሯል።

ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በተካሄደ የኮሪደር ስራውን በሚመለከት የውይይት መድረክ ላይ ይኸው ቅሬታና ጥያቄ ተነስቷል።

ጥያቄውን ካነሱት አንዱ ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ ናቸው።

" ሲቆጥቡ የኖሩ ሰዎች ጉዳይ ምን ደረሰ ? አሁን ማህበረሰቡ ምን ያማል ከተማ አስተዳደሩን ' እኛ በቆጠብነው ገንዘብ ነው የልማት ተናሺዎችን እያሰፈረ ያለው ' የሚል ሮሮ አለ።

ለዚህ ምንድነው ምላሻችሁ ?

ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " ሲሉ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?

" የኮንዶሚኒየም ቤት እስኪ ከየት አምጥታችሁ ነው በዚህ ደረጃ ያላችሁ ኃላፊዎች ' በቆጡት ገንዘብ ነው የሚሰራው ' የምትሉት።

እነ ንግድ ባንክ ናቸው ብሩን የሚያቀርቡት እስቲ እንነጋገር ትንሽ ወደ መረጃው ጠጋ ብላችሁ ብናወራ ምናለበት።

ኮንዶሚኒየም በብድር ነው የሚሰራው። የከተማ አስተዳደሩ በጀቱን አስይዞ ነው የሚበደረው።

ለምንድነው የሚቆጥቡት ? ከተባለ ዕጣ የደረሳቸው ዕለት የሚከፍሉትን እንዳያጡ ነው። እንጂ ቤቱን መገንቢያ አይደለም። ልክ ቤቱ ሲገነባ ብሩን ይከፍሉታል።

ሁለተኛ እንዴት ነው እኛ ብቻችንን የምንጠየቅበት ? ቤት ባልተዘጋጀበት በሚሊዮኖች መዝግቦ ቆጥቡ ብሎ ኃላፊነት ወስዶ የሰራ አካል እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?

ቤት ሳያዘጋጅ ዜጎችን ልክ እንደ ማታለያ በሚሊየን መዝግቦ የበተነ እያለ ለምንድነው እኛ የምንወቀሰው ?

የኮንዶሚኒየም ቤት አጠቃላይ አንድ ቦታ እጅብ ብሎ ስለተሰራ ብዙ ይመስላችኋል እንጂ እስካሁን እስካጠናቀቅነው ያለው 300,000 ነው። የተመዘገበው በሚሊዮን ነው። በየጊዜው ተስፋ ቆርጦ፣ ተጣርቶ ተጣርቶ እኛ የደረስንበት 600,000 ነው። አክተቭ ይቆጥብ የነበረው። ግን ቤት ማግኘት እንዳለባቸው እናምናለን። ቤት ማግኘት አለባቸው።

ካለቁት ኮንዶሚኒየሞች ብራቸው ተዘርፎ፣ ቀድሞ ተከፍሎ ያልተሰራ 80 ህንጻ ብር ተከፍሎበት ጥለው ሄደዋል። በብዙ ውጣውረድ ነው 139,000 ቤቶችን የጨረስነው። የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ብቻ።

አሁንም ቢሆን ግን የከተማችን ነዋሪዎች ቤት ማግኘት አለባቸው። ለዚህም በኮንዶሚኒየም ብቻ አይደለም እንደ ቀድሞ በሚፈለገው ደረጃ ብድር ማግኘት አልቻልንም ከባንክ። ኮንዶሚኒየም መጥፎ ስለሆነ አላቆምነውም።

ከተማ አስተዳደሩ ዕዳ እየከፈለ ነው። ንግድ ባንክ የሚያበድረው የባለሃብትን ገንዘብ ነው አይደል ? 56 ቢሊዮን የኮንዶሚኒየም ዕዳ ነው የተረከብነው ዋስትና የሚሰጠው ከተማ አስተዳደሩ ስለሆነ ክፈሉ ተባልን ተገደድን በለውጥ ዘመኑ 30 ቢሊዮን ከፍለናል የኮንዶሚኒየም ዕዳ።

ይህ ሁሉ ዕዳ አንደኛ በከፍተኛ ሰብሲዲ ስለሚሰራ ነው ፤ ሌላው ያልተሰሩ ቤቶች የተከፈለባቸው አሉ። ሳይከፍሉ ሲሸጡ በተለያየ መንገድ ሲተላለፉ የነበሩ ቤት ውስጥ ያገኘናቸው ሰዎች ከግለሰብ የገዙ ናቸው፤ ሊገደዱ አይችሉም የኮንዶሚኒየም ክፈሉ ተብለው። አጣርተን እኮ በሚዲያ ነግረናችኋል ፤ ያጋጠመንን።

አሁን በግልና በመንግሥት አጋርነት ወደ 100,000 ቤቶች አስጀምረናል። የቁጠባ ቤቶችንም እየሰራን እያከራየን ነው። በሪስልቴትም በግል የሚሰሩትን እንደ ከተማው ፕሮጀክት ጠጋ ብለን እያገዝን ቶሎ እንዲጨርሱ እያደረግን ነው።

እስካሁን የቆጠቡትን አሁን በግልና መንግሥት ትብብር ከምንሰራው  ውስጥ ቅድሚያ ሊያገኙ የሚችሉበትን አግባብ እየተከተልን ነው። ሁለተኛ ደግሞ ተደራጅተው በማህበር እንዲሰሩ ...እስካሁን ለተደራጁት መሬት አስረክበናል።

መነገጃ አታድርጉት፤ ከእውነታው ውጭ መነጋጃ ማድረጉ አይጠቅምም።

የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል። ባለፈው ያስጨረስናቸውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቅድሚያ 97 አክቲቭ ቆጣቢዎች ሁሉ ዕጣ እንዲወጣላቸው ተደርጓል።

እነሱ ከወጣላቸው በኃላ ዲአክቲቬት ያደረገውን አካውን አክቲቬት ያደረገ ካለ እሱ ስለቆጠበ ቤት ስለሚፈልግ ለሚቀጥለው ጊዜ ሊታይ ይገባል ፤ እንጂ በዚህ መንገድ መቅረብ የለበትም " ሲሉ መልሰዋል
@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 04:01


ወርልዶሜትር ባወጣው የተባበሩት መንግስታት የቅርብ ጊዜ መረጃ1 መሰረት አሁን ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 133,084,331 ነው፡፡
እ.ኤ.አ. October 20 ቀን 2024

-The current population of Ethiopia is 133,084,331 as of Sunday, October 20, 2024, based on Worldometer's elaboration of the latest United Nations data1.

-Ethiopia 2024 population is estimated at 132,059,767 people at mid year.

-Ethiopia population is equivalent to 1.62% of the total world population.

-Ethiopia ranks number 10 in the list of countries (and dependencies) by population
.
-The population density in Ethiopia is 132 per Km2 (342 people per mi2).

-The total land area is 1,000,000 Km2 (386,102 sq. miles).

22.1 % of the population is urban (29,204,015 people in 2024).

-The median age in Ethiopia is 18.9 years.

https://www.worldometers.info/world-population/ethiopia-population/

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

21 Oct, 03:38


#AddisAbaba

ለምን የልማት ተነሺዎችን እዛው ቦታቸው ላይ ቤት ሰርቶ ማስገባት አልተቻለም ?

በአዲስ አበባ ከሚሰራው የኮሪደር ልማት ስራ ጋር በተያያዘ በርካታ ነዋሪዎች ረጅም ዓመታት ከኖሩባቸው ሰፈሮች እንዲነሱ እየተደረገ ነው።

አስተያየት ሰጪዎች ፤  " ይሄ ነገር ነባር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመሃል ለማስወጣት ፤ የማህበራዊ ትስስሩንም ለመበጣጠስና ፤ ነባሩን ነዋሪ ለመበታተን ፤ የልማት ተነሺ ቦታዎችንም ለሚፈልጉት ባለሃብት ለመስጠት ነው ፤ እውነት ልማት ከሆነ ለምን ባሉበት በኖሩበት ቦታ የጋራ መኖሪያ ቤት አይሰራላቸው ? " ሲሉ ይጠይቃሉ።

ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች በተገኙበት ከዚሁ ከኮሪደር ልማት ጋር የተያያዘ የውይይት መድረክ ላይ ፤ " ለምን የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ከተገነባ በኃላ ከለማ በኃላ በነበሩበት ቦታ መኖር አይችሉም ? ልክ እንደ አዋሬ ለምን አልተደረገም ? እዛው እንዲኖሩ ለምን ማድረግ አልተቻለም ? " የሚል ጥያቄ ተስቷል።

እንዲሁም ረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ ነዋሪዎች ፦
- ከእድራቸው
- ከእቁባቸው
- ከሰንበቴያቸው ፤ በእስልምናም በኩል ያሉት የማህበረሰቡ መገናኛዎች እንዲበተኑ እየተደረጉ ነው የሚል ሃሳብ ተነስቶ ነበር።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?

" እዛው አካባቢ ላይ ብታለሙ አይሻልም ወይ ? እውነት ነው ይሻላል እንላለን። በነበሩበት አካባቢ ቢሆን የበለጠ ቅድሚያ የሰጠዋል።

አዋሬ እንደዛ ነው የለማው። አዋሬ ብቻ ሳይሆን 70 ደረጃ የገነባናቸው ቤቶች እዛው ሰፈራቸው ነው። በተመሳሳይ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ የበጎነት መንደር ብለን የሰራነው እዛው ነው። ለሚኩራም ሎውኮስት ሀውስ የተሰሩት እዛው ነው፣ ጉለሌ፣  አየር ጤና ሁሉንም መዘርዘር ይቻላል።

ሰፋፊ አካባቢዎችን ስናነሳ አንደኛ የሚገነባበት ቦታ የለም ፤ ካልተነሱ በስተቀር። ሁለተኛ በጥናታችን ሲገነባ የመስረተ ልማቱ የፍሳሽ፣ የጎርፍ መውረጃው የከተማ ልማት የመሬት አጠቃቀሙ የመኖሪያ ቤት መሆን የሌለበት አካባቢ አለ። ተዘግቶ የተገነባበት አለ ጥናቱ በዝርዝር ያስረዳል።

ስለዚህ ሰፋ ወዳለ ቦታ ይሄንን ማህበረሰብ መውሰድ ያስፈልጋል። ቤት ብቻ አይደለም ያየነው። በአካባቢያቸው የሚያስገልጉ ሌሎች መሰረተ ልማቶች አብረው መኖር አለባቸው።

ሌሎች ሀገሮችን እኮ እናውቃለን መኖሪያ ቤቶች መሃል ዋናው ከተማ ላይ ናቸው እንዴ ? ንጹህ አየር ወዳለበት ከተማ ውስጥ ነው ከከተማ አልወጣም። እዚህ ነው የተሻለ ቦታ የተሻለ ሰፋ ያለ ለልጆችም የሚሆን ፤ ብዙ ሰው ሊይዝልን የሚችል ቦታ ላይ ገንብተን አዲስ ቤት መሰረተ ልማት የተሟላለት ቤት አስገብተናል።

ጥያቄ የምታነሱ ወገኖቻችን ኑ አብረን እንሂድና ገላን ጉራን፣ አቃቂን እንመልከት ፣ አቃቂ የቁጠባ ቤቶች ግቢ እንሂድ አብረን ፣ አራብሳ ግቢም የልማት ተነሺዎች የገቡበት አካባቢን እንይ።

አንዳንድ ቦታዎች የተጠቆሙ (የመሰረተ ልማት ችግር ያለባቸው) ካሉ እንደግብዓት እንወስዳለን ህዝባችን እንዲንገላታ አንፈልግም ፤ ህዝባችን እንዲንገላታ ምንም አይነት ፍላጎት የለንም።

ግን እሱም ቢሆን ይኖሩበት ከነበረው ጋር አይወዳደርም።

ከማህበራዊ ትስስራቸው ተበታተኑ የሚለው ፍጹም ውሸት ነው። አልተበታተኑም። የአንድ አካባቢ ሰዎችን አንድ አካባቢ ነው ዕጣ ያስወጣነው። ዕጣውን ለሁሉም ከየአካባቢው ለሚነሱት በጋራ አይደለም ያደረግነው ቀጠናቸውን እንኳን ጠብቀንላቸዋል።

እቁብ፣ እድር፣ ማህበር አላቸው፣ ትስስር አላቸው። ' አይ የቁጠባ ቤት ላይ አንገባም ኮንዶሚኒየም ነው ' ሲሉ የተወሰኑ ሰዎች ኮንዶሚኒየም ሲመርጡ ወደ ሌላ ሄደው ሊሆን ይችላል። ይሄ ለተባለው ግን በቂ ማሳያ አይሆንም።

ባለቤቱ መርጦ ' ይሄ ይሻለኛል በዛው ንብረት ይዛለሁ የጋራ መኖሪያ ቤት ማግኘት ማለት ባለቤት መሆን ነው በቁጠባ እየከፈልኩ ከምኖር ባለቤትነትን እመርጣለሁ ' ካለ ለምንድነው ? ከማህበራዊ ትስስርህ ተነጥለህ ፤ እዚህ እቁብ፣ እድር አለ እዚህ ሰፈር ካልሆነ አትገባም አንለውም። እንደዛ የተባለ ካለ ይዛችሁ ኑ " ብለዋል።
@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

20 Oct, 09:24


#ለመረጃ

ጅቡቲ ላይ የተከማቹ የነዳጅ ተሸከርካሪዎች እንዲገቡ ተፈቀደ!


የገንዘብ ሚኒስቴር ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር፣ በጅቡቲና ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ላይ ተከማችተው የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ተሰምቷል፡፡


አዲሱ መመሪያ፤ ከዚህ ቀደም እንዳይገቡ ታግደው የቆዩ ተሸከርካሪዎችን ጉዳይ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡


መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ከተለያዩ ኤጀንሲዎችና ከጉምሩክ ኮሚሽን ተውጣጥቶ የተቋቋመ ኮሚቴ፣ ዝርዝር ግምገማ  ማድረጉን ተከትሎ፣ በጥያቄ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች በተገዙበት ቀንና የጉምሩክ ምዝገባ መሰረት እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡

መንግሥት በተለይም ከየካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የተገዙና በጉምሩክ ተገቢው ምዝገባ የተደረገላቸው ተሽከርካሪዎች፣ ወደ ድሬዳዋ ተጓጉዘው መንግሥት ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል (@አዲስ አድማስ)፡፡

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

19 Oct, 17:17


አጠቃላይ በ571 የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች " የተለያዩ ሥራዎች (ጥገናና የመልሶ ግንባታ ስራ) ለማከናወን ሲባል  የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

በተለዩት አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚቋረጠው እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሲሆን የሚቋረጥበትን ሰዓት እንዲሁም ቀናት በዝርዝር ይፋ አድርጓል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

19 Oct, 05:30


አዲሱ የይዞታ አስገዳጅ የ20 ሜትር የመንገድ አዋሳኝ ስፋት እና የአነስተኛው የ500 ካ.ሜ ስፋት የማይተገበርባቸው ቦታዎች

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

17 Oct, 17:18


የቴሌ ሼር

የ “Ethiotelecom “ አክሲዮን እንግዛ ወይስ አንግዛ

ከሙያችን አንጻር አንዳንድ ነገር ልበልና ውሳኔውን ለእናንተ እተዋለሁ።

ኢትዮ ቴሌኮም የራሱን 10% ድርሻ፣ 30 ቢልዮን ብር ዋጋ ያላቸው 100 ሚልዮን አክስዮኖችን ለሽያጭ አቅርቧል።
በዚህም የአንዱ አክስዮን ዋጋ 300 ብር ይሆናል ማለት ነው።
ዝቅተኛው አክስዮን 33 ነው፤ ማለትም
=33*300=9,900 ብር
ከፍተኛው 3,333 ነው፤ማለትም
=3,333*300=999,900 ብር ነው ይላል።

እስኪ አዋጭነቱን ከአምናው ትርፍ አንጻር እናስላ። አምና (በ2016 በጀት ዓመት) የዕቅዱን 103.6 በመቶ በማሳካት 21.79 ቢልዮን የተጣራ ትርፍ አግኝቷል። ዘንድሮም ይህንን ትርፍ ቢደግመው ብለን እንነሳ(other things remain constant)

የዚህን 10% ስናሰላ =.10*21,790,000,000
=2,179,000,000
ይህ ለባለ አክስዮኖች ከመከፋፈሉ በፊት 10% Dividend Tax ይከፈልበታል፤ ይህም
=10%*2,179,000,000
=217,900,000

ስለዚህ የባለአክስዮኖች የሚከፋፈለው
=2,179,000,000 - 217,900,000
=1,961,100,000 ይሆናል ማለት ነው።

የዚህ Earning Per Share (EPS)
=1,961,100,000 ፥100,000,000
=19.61 ይሆናል

የዝቅተኛው ባለአክስዮን ድርሻ
=33*19.61
=647.16 ይሆናል ማለት ነው።

አክስዮን የምንገዘባትን ብር ባንክ ብናስቀምጥ (በ7% ወለድ ቢቀመጥ)
=9,900*0.07 - (9,900*0.07*0.05)
=658.35

ከባንክ ወለድ በታች አስመዘገበ ማለትም አይደል?

መደምደሚያ ፦ምናልባት እነዚህ ታሳቢዎች ከተቀየሩ አዋጭ ሊሆን ይችላል።
Tsega Beyamo

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

17 Oct, 04:42


ተሻሻለ የተባለው የትራፊክ ቅጣት የገንዘብ መጠን እና የነጥብ ብዛት

1ኛ ደረጃ ጥፋት የሚመዘገብ ነጥብ 1 ገንዘብ ቅጣት 500 ብር

2ኛ ደረጃ ጥፋት የሚመዘገብ ነጥብ 2 የገንዘብ ቅጣት 1000

3ኛ ደረጃ ጥፋት የሚመዘገብ ነጥብ 3 ገንዘብ ቅጣት 1500

ልዩ ደረጃ ጥፋቶች የሚመዘገብ ነጥብ ከ 8-12 የተለያዩ ደረጃ ያላቸው እገዳዎች እና የገንዘብ ቅጣቶች

ሌሎች ደምብ መተላለፎች ከ 100 ብር እስከ 20,000 ብር የገንዘብ ቅጣት

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

16 Oct, 20:13


#NewsUpdate | ከልማት ድርጅትነት ወደ አክሲዮን ማሕበርነት በዛሬዉ ዕለት በይፋ የተቀየረዉ ኢትዮቴሌኮም የ30 ቢሊየን ብር ወይም የ 10 በመቶ ድርሻውን አክሲዮን ለህዝብ ሽያጭ ክፍት ማድረጉን አስታዉቋል ።

እንደተቋሙ መረጃ በ 2016 ዓ/ም በወጣ የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል 100 ቢሊዮን ብር ሲሆን በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ 300 ቢሊዮን ብር መሆኑ ተሰምቷል።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በወቅቱ እንደተናገሩት በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው 100 ሚሊዮን ሼር ሲሆን የአንድ ሼር ዋጋም 300 ብር ነው ብለዋል።

"ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል። ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900 ብር እንደሚሆን" ተገልጿል ።

በዚህም 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር እንደሚያገኝ የተገለፀ ሲሆን አንድ አክሲዮን ግዢ ሲፈጸም ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደሚከፍል ተነግሯል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

16 Oct, 15:52


የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ (ፐርሰንት) 100 ሚሊዮን ብር መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አሳወቀ

ለኢትዮጵያውያን ክፍት የተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ ዛሬ በይፋ የተበሰረ ሲሆን፤ ዝቅተኛው የሼር ወይም የአክሲዮን መጠን 33 እንዲሆን የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንዲሆን መወሰኑን ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

ከፍተኛው የክሲዮን ወይንም የሼር መጠን 3 ሺህ 333፤ የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንደሆነ ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ገልፀዋል።

የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌ ብር የሚፈፀም ሲሆን፤ ሽያጩ ከጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ይቆያል ተብሏል።

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

16 Oct, 05:14


ከጎሮ ወደ ጃክሮስ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

15 Oct, 18:02


#AddisAbaba

በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ አዲስ ታሪፍ ይፋ አድርጓል።

በዚህም በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ በተሰማሩ ሚኒ-ባሶች ፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች ላይ የአገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል።

አዲሱ ታሪፍ ከነገ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ጭማሪ በተደረገበት በአዲሱ ታሪፍ ዝቅተኛው 10 ብር ሲሆን ከፍተኛው 65 ብር ገብቷል።

" ቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው የታሪፍ ተመን ከጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ ነበር ፤ ስሌቱም የነዳጅ ጭማሪ ዋጋን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነበር " ሲል ቢሮው ገልጿል።

የአሁን አዲስ ታሪፍ ወቅታዊ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ እና ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎችን ያማከለ እንደሆነ አመልክቷል።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ በተሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመን ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስቧል።

(የአዲሱ ታሪፍ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

15 Oct, 03:21


በጅማ ከተማ ለኮሪደር ልማት በሚል ቤቶች ታይቶ በማይታወቅ መጠን ደጋግመው እየፈረሱ እንደሆነ ነዋሪዎች ተናገሩ

(መሠረት ሚድያ)- በከተማው ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ምሬት እንዳለ የከተማው ነዋሪዎች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

የጅማ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት በተለያዩ አካባቢዎች በመጀመሪያ አፍርሱ ተብለው ግማሽ ቤታቸው እስከ አስፋልት ድረስ ከፈረሰ በኋላ አጥሩን በግንባታ ሰርተው ሲያጠናቅቁ እንደገና ከሱ ተጨማሪ ወደውስጥ አፍርሱ ተብለው አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ እያስፈረሷቸው ይገኛሉ።

በዚህም ሳያበቃ ህዝቡ ቆርቆሮ ገዝቶ አጥሩን ከሰራ በኋላ ካድሬዎች መጥተው የፈለጉትን ስዕል ይስሉበታል የሚሉት እነዚህ ዜጎች ምሬታቸውን ገልፀዋል።

የተባለውን ሁሉ ያደረጉ ነዎሪዎች ቢኖሩም አሁን እንደገና ለሶስተኛ ግዜ እንደ አዲስ የመጣው መመሪያ መልሰው በድሮው ዲዛይን በግንባታ ስሩ ተብለዋል።

ቤት እና አጥራቸውን ያላፈረሱ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም የግል ቤቶች በድሮው ባሉበት የአጥሩን ግንባታ በነጭ ቀለም እንዲቀቡ ትዛዝ መሰጠቱም ታውቋል።

"ከተማዋን ለማሳደግ እንኳ ቢሆን ለምን የሕዝቡን አቅምና የንሮ ደረጃ ያገናዘበ አይሆንም?" ብለው ጥያቄ የሚያነሱት ዜጎች አሁን ደግሞ ቆይቶ ሁሉም ሰው በብሎኬት አጥር እንዲሰራ መመሪያ መምጣቱ ቢነገራቸውም ሕብረተሰቡ ግን ገንዘብ ከየት አምጥቶ እንደሚሰራ ግራ እንደገባው እና የገቢ ሁኔታውን ያላገናዘበ መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ቅሬታዎች እየተነሱ ይገኛሉ።

መረጃን ከመሠረት!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

15 Oct, 03:17


ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የግንባታ ደረጃዎች ረቂቅ አዋጅ፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች በሚያከናውኑ የሥራ ተቋራጮች፣ ባለሙያዎችና አማካሪዎች ላይ ከእስራት እስከ ፍቃድ ማገድ የሚያስቀጣ መኾኑን ሪፖርተር ዘግቧል። አዋጁን ለማስፈጸም የሚወጡ ድንጋጌዎችን በሚጥሱ አካላት ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው በረቂቁ ላይ እንደተደነገገ ዘገባው አመልክቷል። ያላግባብ በተሰጠ የግንባታ ፍቃድ ላይ የግንባታ ተቆጣጣሪነት ግዴታውን ያልተወጣ ግለሰብ ከ5 ዓመታት እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል ረቂቁ ደንግጓል ተብሏል። ደረጃው የማይፈቅድለትን ወይም ተገቢው ፍቃድ ሳይኖረው ግንባታ ያካሄደ የሥራ ተቋራጭ ደሞ እስከ 10 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና እስከ 10 ሺሕ የሚደርስ የገንዘብ መቀጫ እንደሚቀጣ ዘገባው ጠቅሷል።
ዋዜማ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

13 Oct, 11:14


" በሰው ሀገር ላይ ሆኜ እግሬ እስኪንቀጠቀጥ የሰራሁበት ገንዘቤ ነው ፤ ... በደሌን ስሙኝ ! ፍትሕን እሻለሁ ! "

(የቤት ገዢ ከአውስትራሊያ)

እህታችን ነዋሪነቷ በአውስትራሊያ ሀገር ነው።

እኤአ 2012 ላይ እዚህ ሀገር ውስጥ የቤት ግዢ ስምምነት ታደርጋለች።

ስምምነቱ ያደረገችው ከአክሰስ ሪልስቴትና ኤስኤንቢ ከተባለው አካል ጋር ነው። ቤቱን በ2 ዓመት ገንብቶ ለማጠናቀቅ ነበር ስምምነቱ የነበረው።

በኃላ አክሰስ ወጥቶ ኤስኤንቢ ብቻ ይዞታል መባሉን ትሰማለች።

ኮንትራቱን ፈርማ  የላከችው ከአውስትራሊያ ሲሆን በወቅቱ  50% ክፍያ ፈጽማለች።

የቤቱ ዋጋ በሰዓቱ 1 ሚሊዮን ብር ነበር።

ከ50% ክፍያ በኃላ ግን ወደ 20% ክፍያ ከፍላለች። በአጠቃላይ 70% ክፍያ ማለት ነዉ የተከፈለዉ።

ክፍያ ከከፈለች በኃላ ግን ቤቱ እየተሰራ አልነበረም። አንዴ እቃ አልመጣም፣ አንዴ የሆነ ነገር ሲሉ አንጓተዋል።

እኤአ 2017 ላይ ወደ ሀገር ቤት መጣች።

ሙለር ሪልስቴት ቢሮ ሔዳም ቤቴ ከምን ደረሰ ? ብላ ስትጠይቅ ' ኤስኤንቢን ለኖህ ሪልስቴት ሸጠነዋል ፥ መሬቱንም አስረክበናቸዋል ' እዛ ሂጂ ይሏታል።

እሺ ብላም አቢሲኒያ ህንፃ የሚገኘው ቢሮአቸዉ ትሄዳለች።

ቢሮአቸዉ ስትሄድም አንድ ሴልስ አግኝቷት ወደ ሳይቱ ጭምር ወሰዶን ቤቷን እንዳየችና በወቅቱ ብሎኬት ተሰርቶለት እንደበር ታስታውሳለች።

70% ከፍላም ፣ ከ5 ዓመታት በኃላ ገና ብሎኬት ላይ ነበር።

በኃላ 2019 ላይ ወደ ኖህ ዋናው ቢሮ ትደውልና " ገና ቤቱ አልደረሰም ስትመጪ ይደርሳል " እንዳሏት ገልጻለች።

በኃላ ኮቪድ ገባ በዚህም ነገሮች ቆሙ እሷም ከአውስትራሊያ መውጣት ሳትችል ቀረች።

ከጊዜ በኃላ ግን " ቤቱ ለሌላ ሰው ተሽጧል " የሚል ፍጹም ያልተጠቀ ነገር ተነገራት።

" ለምን ኮንታክት አላደረጋችሁንም " የሚል ነበር የአልሚዎቹ ቃል። ማስጠንቀቂያም ልከልናችሁ ነበርም ብለዋል።

ገዥ እህታችን ግን አንድም ማስጠንቀቂያ የሚባል ነገር እንዳልደረሳት፣ አውስትራልያ ሆና በፈረመችበት አድራሻ የደረሳት ነገር እንደሌለ እዚህም ባሉ ቤተሰብ ወኪሏ በኩል የተባለችው ነገር እንደሌለ ገልጸለች።

እሺ ለሰው ከተሰጠ የሰው ቤት አንረብሽም በሚል ሌላ ቤት ስጡኝ ብልም ሰሚ አላገኘሁም ብላለች።

በኃላም ጉዳዩ ወደ ክስ አምርቷል።

ይህንን የቤት ሽያጭ ጉዳይ የተከታተለው ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ እንደፈረደላት ግን እስካሁን ምንም መፍትሄ እንዳልተገኘላት ገልጸለች።

ሰው ሀገር ሆኜ እግሬ እስኪንቀጠቀጥ የሰራሁበት ገንዘቤ ነው ፤ እናተም ጉዳዬን ስሙና ፍረዱኝ ይኸው ቤቴን አጥቼ እየተሰቃየሁ ነው ብላለች።

ያንብቡ : https://teletype.in/@tikvahethiopia/EaZgM8G36Oi

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

13 Oct, 07:26


በአዋሽ ፈንታሌ ዛሬ ጠዋት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

ዛሬ ከጠዋቱ 1 ሠዓት ከ37 ገደማ በአዋሽ ፈንታሌ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ሠማራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት አደም አሊ እንደገለጹት÷ ዛሬ ጠዋት በአዋሽ ፈንታሌ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እስከ አሁን የተለየ ጉዳት የለም፡፡

ቀደም ሲል በፈንታሌ ዛሬ ጠዋት ደግሞ በአዋሽ ፈንታሌ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በመግለጽ÷ የሚመለከታቸው አካላት በነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ሥራ እንዲያከናውኑ ጠይቀዋል፡፡

በተለይም ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር ሥራን ጨምሮ ሌሎች የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባ መክረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝርት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን ዶክተር ኤሊያስ ሊዌ አረጋግጠዋል።

ዛሬ ጠዋት 1:37 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለብሔራዊ ጣቢያው አረጋግጠዋል።

እሁድ፣ ጥቅምት 3 ቀን 2017
(አዲስ ማለዳ)

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

12 Oct, 20:45


🔈🔈🔈🔈🔈🔈


የጨረታ ማስታወቂያ

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

12 Oct, 14:17


የት ነው?

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

12 Oct, 10:01


#AddisAbaba

በክፍት ቤቶች ባለቤቶቻቸው አድሰው የፈለጉትን አገልግሎት ሊያውሉት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ማስታወቂያው የወጣው” - ኮርፖሬሽኑ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን " የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ድረስ ወደ ቤታችሁ ግቡ " በሚል ባወጣው ማሳሰቢያ ዙሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው ዝርዝር ምላሽ ምንድን ነው ?

የኮርፖሬሽኑ ማብራሪያ ፦

ማስታወቂያው የወጣበት ዋናው ምክንያት ሰዎች ‘ተቸገርን፣ ክፍት በሆኑ ቤቶች ወንጀል እየተሰራ ነው፣ እየተዘረፍን ነው፣ ሴቶች እየተደፈሩብን ነው’ ብለው እኛ ጋ ስለመጡ ነው፡፡

ቤቶቹን ቼክ ስናደርጋቸው ደግሞ እጣ ወጥቶባቸዋል፤ ውል ተፈጽሞባቸዋል፣ ግን ሰው አልገባባቸውም፡፡

ስለዚህ ነዋሪው ተቸግሯል፡፡ በዚህ ምክንያት ተደጋጋሚ ወደኛ ቢሮ የሚመጡ የየሳይቱ የነዋሪዎች ማኀበራት አሉ፡፡ 
ስለዚህ እነዚህ አካባቢዎች ላይ ያሉ ቤቶች በአግባቡ ቤት የደረሳቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ መሠረተ ልማቶቹም የተሟሉ፣ ሰው ገብቶ መኖር የጀመረባቸው በመሆናቸው ክፍት መሆን የለባቸውም፡፡ የቤት ባለቤቶች ቤታችሁን አድሳችሁ ግቡ፡፡ 

ቢፈልጉ አድሶ ማከራየት መብት ነው፡፡ የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ፡፡ ግን ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ይኑርበት ነው የኛ ጥያቄ፡፡ አካራይ አታከራይ የኔ መልዕክት ሊሆን አይገባም፡፡ ግን ቤቱን ኦውን ያድረጉ፡፡ 

ሰው ‘የጸጥታ ስጋት ብሎ ይጠይቀናል’፣ የጸጥታ መዋቅሩም እኛን ይጠይቀናል፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ደግሞ ቤት ደርሶት ያልገባበት ሰውም ጭምር በመኖሩ እጣ ያልወጣላቸውም ሰዎች ጭምር ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡ ‘ይሄው ክፍት ቤት አለ ይላሉ፡፡’ 

ስለዚህ በክፍት ቤቶች ባለቤቶቻቸው አድሰው የፈለጉትን አገልግሎት ሊያውሉት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ማስታወቂያው የወጣው፡፡ 

የማኅበራዊ ሚዲያ በበዛበት ዘመን በተለያዬ መንገድ ኢንተርፕሬት ሊደረግ ይችላል፡፡

ዋናው የመንግስት ኢንቴንሽን ግን ይሄ ነው፡፡
ክፍት ቤቶች ያሉት አብዛኛው ሳይት ላይ ነው የቤቶቹ መጠን ይለያያል እንጅ (አንዳንድ ቦታ ላይ አምስት፣ አንድ ቦታ ላይ ደግሞ አስር ሊሆኑ ይችላሉ)፡፡

ከተነሳው ቅሬታ አንጻር መሠረተ ልማት ያልተሟላባቸው ደግሞ የተወሰኑ ሳይቶች አሉ (እየተሟላባቸው ያሉ ማለት ነው)፡፡

ለምሳሌ በተደጋጋሚ የሚነሳው አራብሳ ሳይት (ፓኬጅ ሦስት) ነው፡፡ ወደ መጨረሻ አካባቢ ከተገነቡት ቤቶች መካከል ነው። አራብሳ ሦስት አብዛኛው መሠረተ ልማት ተሟልቷል፡፡

ለምሳሌ መንገድ አክሰስ ነው፡፡ አክሰስ ተሰርቶለታል፡፡ ወደ ዘላቂ መንገድ ለማስገባት ለሁለት፣ ሦስት ዓመታት ኢኮስኮ የተባለው ኮንትራክተር ቦታውን ይዞት ነበር ከመንገዶች ተረክቦ ለመስራት፡፡

ነገር ግን ሳይሰራው ቆዬ፡፡ ይሄ ጥያቄ በተደጋጋሚ የማህበረሰቡ ጥያቄ ስለሆነ አቅርበን አሁን ተርሚኔት ተደርጎ መንገዶች ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡

ክረምቱን በሙሉ አክሰስ ወደ መስራት ዝግጅት ላይ ነው የነበሩት አሁን በተሟላ መልኩ ቋሚ መንገድ ሊሰራ ነው፡፡
የመጠጥ ውሃ ወደየ ሳይቱ፣ ወደዬ ብሎኩ ገብቷል፡፡

ፍሳሽን በተመለከተ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ሜጋ ፕሮጀክት እየተሰራ ነው፡፡ በውጭ ካምፓኒ ነው የሚሰራው፡፡ የበጀት እጥረት ገጥሟቸው ጋፕ ነበረ አሁን ግን በተሟላ መልኩ እየተሰራ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ ያልቃል፡፡

የአራብሳን አጠቃላይ ችግር ይህ ፕሮጀክት ነው የሚፈታው፡፡ ይህ እስኪሆን ድረስ ግን የኮሪደር ልማት ተነሽዎች እየገቡ ስለሆነ ሴፍቲ እስታንክ እየተቆፈረ ለጊዜው ፍሳሹ እንዲመጣ፣ ዘላቂው ሲሰራ ደግሞ በቋሚነት እንዲሆን እየሰራን ነው፡፡

አምስትና ስድስት ላይ በተመሳሳይ እየሞከርን ነው፡፡ የተወሰኑ ችግሮች አሉ ሰፈራ የሚባለው አካባቢ የወሰን ማስከበር ችግር አለው፡፡

ለምሳሌ ፍሳሽ፣ የመጠጥ ውሃ በዚያ በኩል ያልፋል ግን የወሰን ማስከበር ችግር አለ፡፡ መፈታት አለበት በሚል ከተማውም ይዞት ለመስራት ጥረት እያደረገ ነው፡፡  

የመሠረተ ልማት ችግር ያለባቸውን ቦታዎች እናውቃቸዋለን፡፡ ችግሩ እንዲፈታም ጥረት እያደረግን ነው፡፡ እኛ እያልን ያለነው ይህን አይደለም፡፡

መሠረተ ልማት ተሟቶላቸው በአብዛኛው ነባር ሳይት የሚባሉ፣ ሕዝቡ ገብቶ እየኖረበት ያለ አካባቢ ክፍት ቤቶች አሉ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ነው ያነሳነው፡፡

ማስታቂያውን በተዛባ መልኩ ለማስተላለፍ የሚፈልጉ አካላት አሉ፡፡ ‘ቤት ሊነጠቅ ነው፣ ሊወሰድባችሁ ነው’ የሚል መልዕክት ሊያስተላልፉ የሞከሩ አሉ፡፡ 

የከተማ አስተዳደሩ ነባርና አዳዲስ የቤት ፍላጎቶችን ለማሟላት የተለያዩ ሞዳሊቲዎችን አጥንቶ ወደ ተግባር በመግባት ላይ ነው ያለው እንኳን የነበረውን ወደዚህ ደረጃ ለማድረስ። ”


#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

12 Oct, 09:59


#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በእጣና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ባልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ/ም ባለቤቶቹ እንዲገቡ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡

ውሳኔው የተላለፈው ቤቶቹ “ሕገ ወጥ ተግባራት እየተፈጸመባቸው” መሆኑን በመጥቀስ ነው።

የቤቱ ባለቤቶች እስከ ተባለው ቀን ድረስ ካልገቡ ቤቶቹ በእጣና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፉ ኮርፖሬሽኑ መግለጹ አይዘነጋም።

ይህን ውሳኔ ተከትሎም የቤት ባለቤቶች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለሚዲያችን አቅርበዋል።

በተለይም በአራብሳ ሳይት የሚገኙ የቤቶቻቸው መሠረተ ልማት ያልተጠናቀቀላቸው ሰዎች ውሳኔው ብዥታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።

የቤት ባለቤቶቹ መሠረተ ልማታቸው ሳይሟሉ እንዴት መግባት እንችላለን? ግዴታ መግባት ነው ወይስ ማከራየት ይቻላል? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣
👉 መሠረተ ልማት ባልተሟላባቸው ቤቶች እንዴት መግባት ይቻላል ?
👉ሽየቤቱ ባለቤቶች ግዴታ መግባት ነው ያለባቸው ማከራየት ይችላሉ ?
👉 ክፍት በሆኑ ቤቶች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ምንድን ናቸው?
👉 እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጸመው በተጨባጭ በየትኞቹ ሳይቶች ነው? ሲል ኮርፖሬሽኑን ጠይቋል፡፡

አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ የኮርፖሬሽኑ አካል፣ ማስታወቂያው የወጣው መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው ላልገቡ የቤት ባለቤቶች እንጂ መሠረተ ልማታቸው ላልተሟላላቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡

“ ያልተሟላቸውን እማ እንዴት ተብሎ!? የማሟላት ግዴታ አለበት መንግስት መሠረተ ልማቱን ” ነው ያሉት፡፡

የኮርፖሬሽኑ በዝርዝር ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

12 Oct, 08:01


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ገንብቶ ከሚያስተላልፋቸው መደበኛ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ በካፒታል ፕሮጀክት እየገነባ ለሽያጭ የሚያቀርባቸው የመኖሪያና ንግድ ቤቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ግንባታቸው የተጠናቀቁና መሠረተ ልማት የተሟላላቸውን 545 ባለ አራትና ባለአስራ አንድ ወለል ከፍታ ያላቸውን መኖሪያ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለጨረታ ያቀረባቸውን መኖሪያ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከ04/02/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/02/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ምሽት 12፡30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ በመክፈል ከዚህ በታች በተገለፁት ቦታዎች መግዛት ይችላሉ፡፡

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

11 Oct, 17:52


#News | ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ2022 ሥራ ከጀመረ ወዲህ በሀገሪቱ የሞባይል ዳታ አገልግሎት ዋጋ እስከ 70 በመቶ መቀነሱን አስታዉቋል።

በዩናይትድ ኪንግደም የሚደገፍ የሞባይል ኔትወርክ ኦፕሬተር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመላ አገሪቱ እጅግ በጣም ፈጣን የ4ጂ ሞባይል ኢንተርኔት እንዲያገኙ መርዳቱ ነዉ የተሰማዉ።

በሌላ በኩል መንግስታዊ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም ድግሞ በፈረንጆቹ 2018 ላይ ሰፊ የሆነ ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚሆን ከፍተኛ የታሪፍ ቅናሽ ማደረጉ አስታዉቆ ነበር።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ የታሪፍ ቅናሽ አድርጎ የነበረው የደንበኞቹንና የማህበረሰቡን የመክፈል አቅም ያገናዘበ መሆን ይገባል” በሚል እንደሆነ በወቅቱ ገልፆ እንደነበር ይታወሳል።
Capital