ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons @ethioicons Channel on Telegram

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

@ethioicons


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ ስለታሪካቸው፣ ሃይማኖታዊ ትርጉማቸው፣
አሣሣል መረጃ የሚያገኙበት ቦታ፡፡ A channel that discusses about icons of ethiopian orthodox tewahido church. Contact for questions @shihaile or [email protected] or www.ethioicons.wordpress.com

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons (Amharic)

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons ብሎ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ ስለታሪካቸው እና ሃይማኖታዊ ትርጉማቸው ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ማቅረብ የጀመረው ቦታ፡፡ ይህ ፋሲል በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥዕላት እንደመለየ የተሟሉ አካባሚዎችን ይስማማ ይከታተሉ እና በመንገድ ላይ ረጅማን ያልተገኙ ገጽታዎችን እና ተመልከቱ ሰጥተዋል። መረጃ ለጥናት @shihaile ወይም [email protected] ወይም www.ethioicons.wordpress.com ላይ ይደውሉ።

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

17 Nov, 18:50


ስለ ሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ስም ይመስገን

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

11 Nov, 12:39


አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም እስኪ ገቡ ድረስ ያለውን ታሪካቸውን የሚዘክረውን ቅዱስ ሥዕል እነሆ። እነዚህ ሥዕሎች በብሪቲሽ ሙዝየም የሚገኝ የገድለ ተክለሃይማኖት ያሉ ናቸው።

ትውፊቱን የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማግኘት፣ ለመመልከትና ለሌሎች ለማጋራት @ethioicons ቤተሰብ ይሁኑ።

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

11 Nov, 12:32


ሦስት ሺ ቤተሰቦች በቴሌግራም ላደረሰን አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን።
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ መጪው ዘመን በየዕለቱ ቅዱሳት ሥዕላትን የሚለጠፍበት ጊዜ ያደርግልን።
ኃይለማርያም ሽመልስ።

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

07 Nov, 13:59


ስለ ሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

07 Nov, 13:57


Channel photo updated

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

06 Nov, 08:26


https://ethioicons.wordpress.com/2015/11/07/%e1%88%a0%e1%8b%93%e1%88%8a-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%89%85%e1%8b%b1%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a1%e1%8a%90-%e1%88%98%e1%89%a3%e1%8b%93-%e1%8c%bd%e1%8b%ae%e1%8a%95-%e1%89%b0%e1%8a%ad%e1%88%88-%e1%88%9b/

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

06 Nov, 07:12


እንኳን ለአቡነ መብዓ ጽዮን ዓመታዊ የእረፍት በዓል አደረሳችሁ።

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

05 Oct, 09:21


https://youtu.be/Tzq2bTK3OmQ?si=4UnRB9qncerCnNQ_

በወቅታዊ የቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

05 Oct, 08:07


በዲያቆን ሚልኪያስ የተዘጋጀውን ድንቅ animation ስለ ጣፋጩ የጽጌ ወራት እስቲ ተጋበዙልኝ። በማኅበራዊ ትስስር ገብታችሁም ፎሎ አድርጉት አበረታቱት።

በእውነቱ እንዲህ ያለ ስራ ለማየት መነሻ ቢሆንም ያሳኝን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ።

ከስር የጥበበኛውን ዲያቆን አድራሻ አስቀምጫለሁ ገብታችሁ ተወዳጁት።

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ።
እንኳን ለጾመ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ።

   👇🏾👇🏾👇🏾Social media👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾

@milkmalachi

Instagram      Tiktok       You Tube

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

02 Oct, 07:46


https://youtu.be/2WGurCxJw88?si=JbdPXtocGYt-1NzE

በዛሬ ዕለት ከሚታሰቡት ቅዱሳን መካከል የቅዱሳን ሰማዕታትን ዜና መዝግቦ ያቆየ እና የተመኘውን ሰማዕትነት ስለ ክርስቶስ ብሎ የተቀበለው ቅዱስ ዮልዮስ (Julian of Ekfahs) ሲሆን ፊልሙን በግብፅ ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀውን እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ።

ማሳሰቢያ ፊልሙ በአረብኛ ቢሆን ገላጭ እንግሊዝኛ ጽሑፍ ከስር ስላለው እርሱን በማንበብ መከታተል ትችላላችሁ። ግዜውና ጸጋው የታደላችሁ ደግሞ ወደ ሀገራችን ቋንቋ በመተርጎም ለብዙ ሰው እንዲደርስ በወንድማዊ ፍቅር እጠይቃለሁ።

ይህ ስራው ደግሞ የቅዱሳን ሰማዕታትን ለሥዕላቸው መነሻ የሚሆን ታሪክ ምትክ የሌለው ምንጭ በመሆን እያገለገለ ይኖራል።

ስለዚህም ነገር ቤተ ክርስቲያን ስትዘክረው ትኖራለች።

ትውፊቱን የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላት ለመመልከት @ethioicons የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ።


ሰላም ለዮልዮስ እምኀበ እግዚአብሔር ዘተሠይመ፤
ከመ ያስተጋብአ ዜና አበው ወዘሰማዕታት ዐጽመ፤
እድኅሬሁ ዝንቱ መኮንነ ጥዋ ክሳዶ ገዘመ፤
ሰላም ለኮቶሎስ ወለእኅቱ አዳመ፤
ምስለ ባላን ወጣጦስ ዘገብረ መድምመ!

ምንጭ
ፊልም ከዳር አንቶን ዩትዩብ ገጽ
አርኬ ÷ዝክረ ቅዱሳን - (ርቱዓነ ሃይማኖት)
https://t.me/zikirekdusn

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

21 Sep, 08:22


††† እንኳን ለቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት እና ቅድስት ታኦድራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት †††

††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጥሎ አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ ቅዱስ ፋሲለደስ ነው:: እንዲያውም ለዘመነ ሰማዕታት መሪና አስተማሪ እርሱ ነበር::
እስኪ በጥቂቱ ነገሩን ከሥሩ እንመልከተው::
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የሮም መንግስት ዓለምን የሚያስተዳድረው በሁለት ከተሞች: ማለትም በራሷ በሮምና በአንጾኪያ ነበር:: የወቅቱ ንጉሥ ኑማርያኖስ ሲሆን የቤተ መንግስቱ ልዑላንና የጦር አለቆች ቅዱሳኑ:- ፋሲለደስ: ገላውዴዎስ: ፊቅጦር: መቃርስ: አባዲር: ቴዎድሮስ (3ቱም): አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: ሌሎቹም ነበሩ::

ሴቶቹ ደግሞ ቅዱሳቱ:- ማርታ: ሶፍያ: ኢራኢ: ታኡክልያ: ሌሎቹም ነበሩ:: ለእነዚህ ሁሉ የበላይ ደግሞ ቅዱስ ፋሲለደስ ነበር:: ወቅቱ ከፋርስ: ከቁዝና ከበርበር ጦርነት የሚበዛበት ነበርና ባጋጣሚ ንጉሡ ኑማርያኖስ በሰልፍ መካከል ተመትቶ ወደቀ /ሞተ/::

የሮም መንግስትም ባዶ ሆነች:: ዙፋኑን መያዝ ለቅዱስ ፋሲለደስም ሆነ ለሌሎቹ ቅዱሳን ቀላል ነበር:: ግን እነሱ ዝም ብለው ጠላትን ለመዋጋት ወጡ::

በዘመኑ ደግሞ በግብጽ የፍየል እረኛ የነበረና ከልጅነቱ ሰይጣን የሚያናግረው አንድ አግሪዻዳ የሚሉት ጉልበተኛ ሰው ነበር:: ንጉሡ ከወለዳቸው ልጆች ሁለቱ ሴቶች ክፉዎች ነበሩና ትንሿ አግሪዻዳን ማንም በሌለበት አንግሣ ጠበቀቻቸው:: ስሙንም ዲዮቅልጢያኖስ አለችው::

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም:: የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው:: ትልቋ ደግሞ የትንሿን አይታ መክስምያኖስ የሚባል አውሬ አግብታ አነገሠችው:: ዓለምም በእነዚህ ጨካኝ ሰዎች እጅ ወደቀች::

ሠራዊቱ ሁሉ በሚሊየን ይቆጠራሉ:: የተደረገውን ሲያዩ ተበሳጩ:: ይህንን የተመለከተው ቅዱሱ ፋሲለደስ ግን ልዑላኑንና አለቆችን ሰብስቦ:- "ይህ ዓለም ከነ ክብሩ ጠፊ ነው:: ስለዚህ የተሻለውን የክርስቶስን መንግስት እንምረጥ" አላቸው:: ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ ደስ ተሰኝተው ምድራዊ ክብራቸውን ሊተው ወሰኑ::

ቀጥለውም በአንድ ቤት ተሰብስበው ይጾሙ: ይጸልዩ ገቡ:: ወደ ውጪ የሚወጡት ለምጽዋት ብቻ ነበር:: ከሃዲውም ይህንን ሲያይ የልብ ልብ ተሰማው:: ከድሮ ያሰበውንና ክርስቲያኖችን የማጥፋቱን እቅድ ሊፈጽም ምክንያት አገኘ::

አባ አጋግዮስ በሚባል መነኩሴ ምክንያት "አብያተ ክርስቲያናት ይትዐጸዋ: አብያተ ጣዖታት ይትረኀዋ-ቤተክርስቲያኖች ይዘጉ: ቤተ ጣዖቶችም ይከፈቱ" አለ:: አዽሎን: አርዳሚስ የሚባሉ ጣዖቶችንም አቆመ::

በዚህ አዋጅ ምክንያትም የክርስቲያኖች ሰቆቃ ጀመረ::
*ምድር በደም ታጠበች::
*ቅዱሳኑ ቀባሪ አጡ::
*እኩሉ ተገደለ: እኩሉ ተቃጠለ: እኩሉ ታሠረ: እኩሉም ተሰደደ:: በዚህ ጊዜ 'መራሔ ትሩፋት' ቅዱስ ፋሲለደስ ለሰማዕትነት ይበቁ ዘንድ ስለ ራሱና ስለ ወገኖቹ ጸለየ::
ቅዱስ ሚካኤልም በግርማ ወርዶ ቅዱሱን ወደ ሰማይ አወጣው:: ከቅዱሳን ጋር በገነት አስተዋውቆት: ክብረ ሰማዕታትን አሳይቶት: ከጌታ ዘንድ አስባርኮት: ከሕይወት ውሃ ምንጭም አጥምቆ መለሰው::ቅዱስ ፋሲለደስም ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ በንጉሡ ፊት ቆመ::

ንጉሡ ፈራ: እርሱ ግን በፈጣሪው ስም መሞት እንደሚፈልግ ነገረው:: ሊያባብለው ሞከረ: አልተሳካም እንጂ:: ከዚያም አስሮ ወደ አፍራቅያ (አፍሪካ) ላከው:: መጽሩስ የሚባል መኮንንም ቅዱሱን አሰቃየው::

እርሱ የሁሉ የበላይ ሲሆን ስለ ክርስቶስ ሁሉን ተወ:: አካሉ እስኪቆራረጥ ገረፉት: በምጣድ ላይ ጠበሱት: አበራዩት: በወፍጮም ፈጩት:: እርሱ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ሁሉን ታገሰ:: ሁለት ጊዜ ገድለውት ከሞት ተነሳ:: በተአምራቱ ምክንያትም ከከተማው ሕዝብ ግማሹ ያህል ከአሕዛባዊነት ተመልሶ ሰማዕት ሆነ::

በመጨረሻም በዚህ ዕለት አንገቱን ሲቆርጡት ደምና ወተት ፈሶታል:: መላእክትም እርሱን ለመቀበል ዐየሩን ሞልተውታል:: ከልዑላኑ ወገንም የቅዱስ ፋሲለደስን ሚስትና ልጆችንጨምሮ አንድም የተረፈ የለም:: ሁሉም በሰማዕትነት አልፈዋል::

††† እናታችን ቅድስት ታኦድራ †††

††† ይህች ቅድስት እናታችን የትእግስት እመቤት ናት:: ትእግስቷ: ደግነቷ ፈጽሞ ይደነቃል:: ታሪኳ ደግሞ በሆነ መንገድ ከቅድስት እንባ መሪና ጋር ይገናኛል::

ቅድስት ታኦድራ ግብጻዊት ስትሆን ተወልዳ ያደገችው በእስክንድርያ ነው:: ከሕጻንነቷ ጀምራ ቅን ነበረች:: ምንም እንኳ የምናኔ ሰው ብትሆንም ወላጆቿ ያመጡላትን ባል 'እሺ' ብላ አገባች:: ለተወሰነ ጊዜም በሥጋ ወደሙ ተወስነው ከባሏ ጋር በሥርዓቱ ኖሩ::

ለቤተ ክርስቲያን ከነበራት ፍቅር የተነሳ ጠዋት ማታ ትገሰግስ ነበር:: አንድ ቀን ግን መንገድ ላይ የሆነ ፈተና ጠበቃት::ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በመልኳ ምክንያት ለኃጢአት ተግባር ይፈልጋት የነበረ አንድ ጐረምሳ ድንገት ያዛት:: ታገለችው: ግን ከአቅሟ በላይ ነበር:: ጮኸች:የሚሰማትም አልነበረም:: ሰውየው የሚፈልገውን ፈጽሞ: ከክብር አሳንሷት ሔደ:: ይህንን መቻል ለአንዲት ንጽሕት ወጣት ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ መረዳቱ አይከብድም::

እጅግ መጥፎ ሰው: በቀለኛም ለመሆን ከዚህ በላይ ምክንያት አይኖርም:: ቅድስቷ ግን ከወደቀችበት ተነስታ መሪር እንባን አለቀሰች:: ሕመሟን ችላ ወደ ቤቷ ላትመለስ ወደ በርሃ ተጓዘች:: ወደ ገዳም ገብታ በወንድ ስም 'አባ ቴዎድሮስ' ተብላ መነኮሰች:: በአካባቢው የሴቶች ገዳም አልነበረም::

የሚገርመው በገዳም ውስጥ ሆና ያንን ጨካኝ ሰው ይቅር አለችው:: ቀጥላም ስለ እርሱ ኃጢአት ንስሃን ወስዳ ከባዱን ቀኖና ተሸከመችለት:: ይሔ ነው እንግዲህ ሕይወተ ቅዱሳን ማለት: ራስን አሳልፎ ለጠላት መስጠት:: (ዮሐ. 15:13) ፈተናዋ ግን ቀጠለ::

ወንድ መስለዋት 'በአካባቢው ከምትገኝ ሴት ጸንሰሻል' ብለው ከገዳም አባረሯት:: ያልወለደቺውንም ልጅ ታሳድግ ዘንድ ሰጧት:: አሁንም በአኮቴት ተቀብላ ለ7 ዓመታት በደረቅ በርሃ ተሰቃየች:: ልጁንም አሳደገች:: ከዚያም ከባድ ንስሃ ሰጥተው ተቀበሏት:: ቅድስት ታኦድራ እንዲህ ስትጋደል ኑራ በዚህች ቀን ዐርፋለች:: በዕረፍቷም ቀን ክብሯ ተገልጧል::

††† ቸር አምላክ የቅዱሳኑን ትእግስትና መንኖ ጥሪት አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

††† መስከረም 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
2.ቅድስት ታኦድራ እናታችን
3.ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ሐዋርያዊ (ሐዋ. 10ን ያንብቡ)
4.ቅድስት በነፍዝዝ ሰማዕት
5."3ቱ" ገበሬዎች ሰማዕታት (ሱርስ: አጤኬዎስና መስተሐድራ)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄምና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ

††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጎች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" †††
(ሮሜ. ፰፥፴፭)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

https://t.me/zikirekdusn
▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

21 Sep, 08:17


እንኳን ለቅዱስ ፈሲለደስ የሰማዕትነት በዓል አደረሳችሁ። እነዚህ ሥዕሎች የሚገኙት በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ነው።

ኦርቶዶክሳዊ ትውፊትን የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላትን ለመመልከት እና ለማግኘት @ethioicons ቤተሰብ ይሁኑ።ይጠቅማል ብለው ካሰቡ ለሌሎች ያጋሩት።

በሠዓሊ ኃይለማርያም ሽመልስ በቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ ጥናት አጥኚና ጸሐፊ።

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

20 Sep, 06:38


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤

መስከረም 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+" በዓለ ስዕለ አድኅኖ "+

ይህች ቀን በቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሳት ስዕላት የሚነገርባት ክብርት ቀን ናት:: 'ስዕለ አድኅኖ' ማለት 'እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥበት: አንድም በቅዱሳኑ አማካኝነት ጸጋ የሚገኝበት: የሚያድን ስዕል' ማለት ነው::

+ስለዚህ ነገር አንዳንዶቹ ሊነቅፉን ይፈልጋሉ:: እኛ ግን ከማን እንደ ተማርነው እናውቃለን:: ከመነሻው እኛ ስዕልን አናመልክም:: ይልቁኑ አምልኮን እንፈጽምበታለን እንጂ:: ስዕልን ለሰው ልጆች የሰጠ ራሱ ባለቤቱ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሠክራል::

+እንዲያውም የመጀመሪያው ሰዐሊ ራሱ አምላካችን ነው:: አዳምን እንደ መልኩ: በምሳሌው ሲፈጥረው መላእክት የእግዚአብሔርን ምስል አዳም ላይ አይተዋልና:: (ዘፍ. 1:26) ለሙሴም ስዕለ ኪሩብን እንዲስል ያዘዘ ራሱ ነው:: (ዘጸ. 25:22) በዚያም ላይ ሆኖ ሙሴና አሮንን ሲነጋገራቸው ኑሯል::

+በመቅደሰ ሰሎሞንም ተመሳሳይ ነገርን እናገኛለን:: (2ዜና. 7:12, 1ነገ. 9:1) በሐዲስ ኪዳንም ጌታ ስዕለ ኪሩብ ያለበትን መቅደስ ቤቴ (ማቴ. 21:13): የአባቴ ቤት(ዮሐ. 2:16) ሲለው: በቅዱስ ሰውነቱ ሲመስለውም (ዮሐ. 2:21) እንመለከታለን:: ቅዱስ ዻውሎስ ለገላትያ ሰዎች ስለ ስዕለ ስቅለት ሲያስታውሳቸው (ገላ. 3:1): ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በደም የተረጨች ልብስ ብሎ ያላትን መተርጉማን ያትታሉ:: (ራዕይ. 19:13)

+በትውፊት ትምሕርት ደግሞ የመጀመሪያው ስዕል በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ የተሳለ ሲሆን ስዕሉም የእመቤታችን ነው:: "ሚካኤል በክነፊሁ ጾራ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ" እንዳለ ቅዱስ ያሬድ:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቃርዮስና ለቬሮኒካ (12 ዓመት ደም ይፈሳት ለነበረችው ሴት) መልክአ ገጹን ሠጥቷቸዋል::

('ቬሮኒካ' በላቲን 'ቬሮን-ኢኮን' 'እውነተኛ መልክ' እንደ ማለት ነው)

+ቀጥሎም ዮሐንስ ወንጌላዊ ለጢባርዮስ ቄሣር ስዕለ ስቅለቱን ሲስልለት ቅዱስ ሉቃስ ደግም የእመቤታችን 'ምስለ ፍቁር ወልዳን' ስሏል:: ከዚያም ሲያያዝ ይሔው ከእኛ ደርሷል::

+ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በከተሞች አካባቢ ቅርጾች በዝተዋልና ይሔ አላስፈላጊ መዋስ (ያውም ከመናፍቃን) ቢቀር መልካም ነው ባይ ነኝ:: ኋላ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቁሞ ማውረድ ከባድ ነውና::

+" ጼዴንያ "+

+በዚህች ቀን ቅዱስ ሉቃስ የሳላትና ሥጋን የለበሰችው: ከፊቷም ወዝ የሚወጣትና ድውያንን የምታድነው የድንግል ማርያም ስዕለ አድኅኖ ወደ ጼዴንያ ከወዳጇ ከብጽዕት ማርታ ዘንድ ገብታለች:: ቅድስት ማርታ ሃብት ንብረቷን በአብርሃማዊ ተግባር (በምጽዋትና እንግዳን በመቀበል) ላይ ያዋለች ክብርት ሴት ናት::

+ለእመ ብርሃን ካላት ፍቅር የተነሳ እንቅልፍ አልነበራትም:: ተግታ ታገለግላትም ነበር:: ስዕሏን እንዲያመጣላት የላከችው ኢትዮዽያዊው መነኩሴ አባ ቴዎድሮስ የስዕሏን ተአምራት ባየ ጊዜ ለራሱ ለመውሰድ ሞክሮ ነበር:: (እርሱ ምን ያድርግ! እኔም ብሆን ይህንኑ ነበር የማደርገው)

+ነገር ግን ከሁሉም በተሻለ የምትወዳት ቅድስት ማርታ ነበረችና በድንቅ ተአምር: በዚህች ቀን ወደ ጼዴንያ ገብታለች:: ቅድስት ማርታም ያለ ዕረፍት ስታገለግላት ኑራ ዐርፋለች:: ይህቺ ክብርት ስዕለ አድኅኖ የአሁን መገኛ 4 መረጃዎች አሉ:-

1.ያለችው ኢትዮዽያ ውስጥ (ደብረ ዘመዳ በሚባል ገዳም) ነው:: የመጣችውም ከግማደ መስቀሉ ጋር ነው::
2.ያለችው በቀደመ ቦታዋ ነው::
3.የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ወስደዋታል::
4.በፈጣሪ ጥበብ ተሰውራለች::

+" ልደታ ለማርያም "+

+በግብጽ ውስጥ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ: ማለትም በአስቄጥስ ደብረ አባ መቃርስ የእመቤታችንን ዜና ሕይወት የሚናገር 1 መጽሐፍ አለ:: መጽሐፉ እንደሚለው እመ ብርሃን ድንግል ማርያም የተጸነሰችው ታሕሳስ 17 ቀን ነው:: በዚህ ሒሳብ መሠረት ደግሞ እመ አምላክ የተወለደችው መስከረም 10 ቀን ነው:: ዓለማቀፍ ትውፊቱ ግን ነሐሴ 7 ተጸንሳ: ግንቦት 1 ቀን መወለዷን ያሳያል::

+" ተቀጸል ጽጌ / አጼ መስቀል "+

+'ተቀጸል ጽጌ' ማለት 'መስቀል ሆይ! በአበባ አጊጥ' እንደ ማለት ሲሆን 'አጼ መስቀል' ደግሞ አጼ ገብረ መስቀልን: አንድም አፄ ዳዊት ቀዳማዊን ይመለከታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በሃገራችን ኢትዮዽያ የነገረ መስቀሉ ትምሕርት ከመጣ ጀምሮ መስቀል ይከበራል:: በአደበባባይ ግን እንዲከበር ያደረጉት የቅዱስ ካሌብ ልጅ አፄ ገብረ መስቀል ናቸው:: በወቅቱ ንጉሡ: ሠራዊቱ: ዻዻሱና ሕዝቡ በተገኙበት ቅዱስ ያሬድ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር-መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው: ከጠላትም ያድነናል" እያለ ይዘምር ነበር::

+የአበባ ጉንጉንም ለመስቀሉና ለንጉሡ ይቀርብ ነበር:: ከ800 ዓመታት በሁዋላም አፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን ባስመጡ ጊዜ መስከረም ቀን ተተክሎ ታላቅ በዓልም ሆኖ ተከብሯል::

+" ንግሥተ ሳባ "+

+ይሕቺ ደግ ኢትዮዽያዊት ከ3 ሺ ዘመናት በፊት የነበረች ደግ እናት ናት:: በሥጋዊ ደረጃ ከታንዛንያ እስከ የመን ያስተዳደረች ስመ ጥር ንግሥት ስትሆን በመንፈሳዊው ደረጃ ደግሞ እግዚአብሔር የቀባውን ሰው ፍለጋ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛለች::

+ከዚያውም አምልኮተ እግዚአብሔርን ከሥርዓተ ኦሪት ጋር አምጥታለች:: ድንግልናዋን ለታላቁ ንጉሥ ሰሎሞን ሰጥታ ምኒልክን ወልዳለች:: ይህቺ ንግሥት በጌታችን (በፈጣሪ) አንደበትም ተመስግናለች:: (ማቴ. 12:42) በስምም "ሳባ: አዜብና ማክዳ ተብላ ትታወቃለች:: ዛሬ ዕለተ ዕረፍቷ ነው::

+እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን: ጸጋ በረከቷን: ከስዕሏም ረድኤት ትክፈለን:: የቅዱሳኑም ክብር አይለየን::

+መስከረም 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም
2.በዓለ ስዕለ አድኅኖ
3.ቅዱስ እፀ መስቀል (ተቀጸል ጽጌ)
4.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
5.ቅድስት ማርታ ዘጼዴንያ
6.ቅድስት ዮዲት ጥበበኛዋ
7.ንግስተ ሳባ / ማክዳ / አዜብ
8.ቅድስት መጥሮንያ ሰማዕት
9.አፄ ዳዊት ንጉሥ
10.ቅድስት አትናስያና 3 ልጆቿ



=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ

++"+ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር:: ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? +"+ (ገላ. 3:1)

‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››

https://t.me/zikirekdusn
▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

16 Sep, 18:55


https://youtu.be/c1kYAMaLd80?si=vKZTfhY_20f4TZdm

በ20ኛው መ.ክ.ዘ. የነበሩት በፍቅርና በተአምር የተሞሉት የቅዱስ አባ መቃርዮስ ጳጳስ ፊልምን እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ። በጣም ልብን የሚመስጥ እና ሀሴትን የሚመሉ ካወኳቸው እለት ጀምሮ በድካም ውስጥ ብሆንም የማልረሳቸው ፈጥኖ ደራሽ አባት ናቸው ተጠቀሙባቸው።

ማስታወሻ፥ ፊልሙ እንግሊዝኛ ገላጭ ጽሑፍ ያለው በአረብኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ፊልም በመሆኑ እያነበባችሁ ተመልከቱት። አረብኛ አልሰማም ብላችሁ ይህንን ድንቅ ገደል ከማየት እንዳያመልጣችሁ። የአቡነ መቃርዮስ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

16 Sep, 13:59


በሰማእቱ ስም ጸበል እንጂ ቢራ አንጠጣም!
ቅዱስ ጊዮርጊስ የቤተ ክርስቲያናችን ሰማዕት፣ የሕይወታችን አጋር ነው። የሰማእቱ ስም ክቡር፣ ንጹሕ ነው። ሥዕሉ በተቀደሰ ቦታ በቢራ ጠርሙስ አይለጠፍም። ስሙ የድኅነት መንገድ የስካር ማድመቂያ አይለም። በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ጸበል እንጂ ቢራ አንጠጣም።

👇👇👇👇👇👇👇👇
ይህንን ቻሌንጅ ባላችሁ የሚዲያ አማራጭ (በቲክቶክ፣ በዩቱዩብ፣ በፌስቡክ፣ በቴሌግራም፣ በኢንስታግራም)፣ እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ ሼር በማድረግ የሰማዕቱን ስም እናስከብር።

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

03 Sep, 06:59


https://youtu.be/Dh1Ssdk5HrM?si=IuQwomPfUKwoJAVz

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: Ethio Icons

01 Sep, 18:59


ሲጠበቅ የነበረው የታዳጊዎች የሥእል አውደ ርእይ ተከፈተ

የሰማይ መስኮቶች በሚል ርእስ በታዳጊ የሰንበት ትምህርት ቤታችን ሰዓሊያን የተዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ሥዕላት አውደ ርእይ ብጹእ አቡነ ኤጲፋንዮስ የምስራቅ ጉራጌና የማረቆ ልዩ ወረዳ ሐገረሥብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በደማቅ መርሐግብር ተከፍቷል።  በእለቱም የካቴድራላችን አስተዳደሪ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ኪሮስ ጸጋዬ፣ የካቴድራሉ ዋና ጸሀፊ መጋቤ ሥርዓት እጓለጽዮን ሀብቴ፣የካቴደራላችን የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ይዘንጋው እንዲሁም የደብሩ ካህናትና ዲያቆናት ተገኝተው አውደ ርእዩን አስጀምረዋል።

ብጹእ አቡነ ኤጲፋንዮስ በመክፈቻ ንግግራቸው ለነገይቱ ቤተክርስቲያን የዛሬዎቹን ሕጻናት በጥበብ ማሳደግ የሚገባ መሆኑን ይህንም ለማድረግ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ድርሻ ቀላል የሚባል አለመሆኑን ጠቅሰው። 

ምእመናንም ይህን እስከ ጳጉሜን 3 የሚቆይ አውደ ርእይ  ተገኝተው እንዲሳተፉና የታዳጊ ልጆቻቸውን ፍሬ እንዲመለከቱ አደራ ብለዋል።


                                      የሰማይ መስኮቶች
                                  ከነሃሴ 26 - ጳጉሜን 03

http://youtube.com/@EMislene

3,096

subscribers

375

photos

2

videos