ዋልድባ ገዳም @waldiba Channel on Telegram

ዋልድባ ገዳም

@waldiba


👉 ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ በነገረ መለኮት፣ በነገረ ማርያም፣ በነገረ መስቀል፣ በነገረ ቅዱሳንና በምሥጢራት ላይ፣
👉 ወቅታዊ የቤ/ክ ሁኔታና የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች፣
👉 የመንፈሳዊ ጉዞዎች ዓመታዊ መርሐ ግብር...

ለጥያቄዎ
@zeWaldiba_bot
@Gedamewali
@Elmestoagia

👇 YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCUBStsekCniQtATyZDdFqQQ

ዋልድባ ገዳም (Amharic)

እስከ መችሰርቱ እንደአንዲት አንድ እንደታወቁ፣ የቤ/ክ ሁኔታና የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች፣ የመንፈሳዊ ጉዞዎች ዓመታዊ መርሐ ግብር ያሉ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮዎች ብቻ በገዙ ጊዜ የገና ባለመንገድ እንዲሆኑ የነገረ መለኮትና መናገሪያዊ ቃል በማስጠንኳ ላይ፡፡ ድረገ፡መለኮት፡ማርያም፣ መስቀል፣ ቅዱሳና ምሥጢራት ወደገናው መለኮት ለግያም በል ፣ድረስ፡ድራማና፡ጊደር፡ድፈረ ብንበረክ ለእኛ ዝግጅት ይሆናል፡፡ እኛ እንደመነሳት የምንለዋወጥ ነው፡፡ ድምፅውን ለጣለም ማድረግ የተቻለን። ስለሁለት ወራት ለድንገተኛው፡ገዳም እና እለት፣እንኳ፡ከሺጥንጉልታዎች፣ ጽጉትና፡ችግር፡ለሥራም እንበርህን፡፡ አገልግሎት፣የሠሪችና፡ ዝማሬ ይመዝገቡ፡፡ በመንግስቱ ያለዋንም ዕቅድ ትከተላል። አመንጫለን፡፡

ዋልድባ ገዳም

20 Nov, 05:31


“ሰው አይዘንብህ...”
🎤 ክቡር አባታችን ቀሲስ መንግሥቱ (የእናቴ ልጅ)

“እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፤ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፤ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፤ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ።” ዘካ ፯፥ ፱- ፲
“ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው፤ እንዳትበድል አትቅና። ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ።” መዝ ፴፮፥ ፰- ፱
“ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡ የሚል ነው።” ገላ ፭፥ ፲፬
“አፍቅር ካልአከ ከመ ርእስከ - አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ” ዘሌ ፲፱፥ ፲፰

ወደ ጥንታዊቷ ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም ለሚኖረን የ10 ቀናት ጉዞ ምዝገባ ላይ ነን።
★ መነሻ ኅዳር 16 መመለሻ ኅዳር 25
★ የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 9000 ብር

በጉዟችን ላይ፦
👉 ከተስዓቱ ቅዱሳን 6ቱን፦ አቡነ ጰንጠሌዎን፣ አቡነ ሊቃኖስ፣ አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ሐፍፄ፣ ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ይምዓታ፣
👉 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉 ሐውዜን አቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን፣
👉 አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉 አቡነ አላኒቆስ፣
👉 አቡነ ዮሐኒ ወአባ አሞኒ፣
👉 ሐይቅ ቅ.እስጢፋኖስ፣
👉 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት፣
👉 አርማኒያ ቅ.መርቆሬዎስ እና ሌሎችም
★ ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877

ዋልድባ ገዳም

19 Nov, 10:13


👣 እግሮች ሁሉ ወደ አክሱም ጽዮን ያመራሉ... 🚶

የማይቀርበት መንፈሳዊ የንግሥ ጉዞ ወደ ጥንታዊቷና ታላቋ የታሪክ ማኅደር መካነ ነገሥት ርእሰ ገዳማት ወአድባራት
#አክሱም_ጽዮን_ማርያም
* መነሻ ኅዳር 16
* መመለሻ ኅዳር 25
* የጉዞ ዋጋ፦ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 9000 ብር
★ ውስን ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን አክሱም ጽዮንን ለመሳለም የምትሹ ያልተመዘገባችሁ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ደውሉልንና አብረን እንጓዝ!
👉 0901070707 / 0911289877

👉 ርእሰ ገዳማት ወአድባራት፣ ሙጽአ ሕግ ወሥርዓት፣ ነቅዐ ክህነት ወመንግሥት ዘሀገር ዐባይ ኢትዮጵያ፤ ቅድስት አክሱም ሁላችንንም ትጣራለች፡፡ የሚቻለን ሁሉ ወደ እርሷ እናቅና፤ ከበረከቷም እንጥገብ፡፡

በጉዟችን ላይ ከምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት ውስጥ፦
👉🏿 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉🏿 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉🏿 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉🏿 ደብረ የሐ አቡነ ሐፍፄ፣
👉🏿 ደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) አቡነ አረጋዊ፣
👉🏿 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉🏿 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉🏿 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉🏿 ሐውዜን ቅ/ጊዮርጊስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉🏿 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣
👉🏿 ማኅበረ ዴጎ አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉🏿 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉🏿 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉🏿 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉🏿 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ እና አቡነ አሞኒ፣
👉🏿 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉🏿 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ፣
👉🏿 አርማኒያ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና ሌሎችም...

✥ መነሻ ቦታዎች፦ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ እና መገናኛ

ዋልድባ ገዳም

19 Nov, 10:03


★ ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም
በድርሣነ ዑራኤል ላይ ከተገለጸው ታሪኳና ክብሯ ውስጥ፦

👉 አረመኔው ንጉሥ ሄሮድስ በ3ዓ.ም የሞት አዋጅ አውጥቶ ጌታችንን ለመግደል በገሊላና አካባቢው ሁሉ የተወለዱ 144000 ሕፃናትን ሲያስጨፈጭፍ የጌታችን ክብርት እናቱ እግዝትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ፣ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅድስት ሰሎሜ እግዚእነ ወአምላክነ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ይዘው በመሸሽ ወደ ግብጽ ከተጓዙ በኋላ ጌታ በእመቤታችንና በሰሎሜ ላይ ሆኖ በየቀኑ ወደ ኢትዮጵያ ፊቱን አዙሮ 3 ጊዜ ይባርክ ነበር። በአንድ ወቅት ለምን እንዲህ እንደሚያደርግ እመቤታችን ጠየቀችው፤ ጌታም፦ «እናቴ ሆይ የምባርከው ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ነው፤ በቅዱስ ወንጌል ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው ተብሎ የሚነገረው ሕያው ቃሌ የሚፈጸምባቸው ክቡራን ንዑዳን ሕዝቦች ያሏት የተባረከች ሃገር ናትና...» ብሎ መለሠላት።

የሃገረ ግብጽ ቆይታቸውን ሲያጠናቅቁም ጌታችን ለክብርት እናቱ “ወደዚያች ቅድስት ሀገር ልውሰድሽ ብሎ ደመናን ጠቀሠና በብሩህ ደመና ጭኖ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸው። ከየመን በስተደቡብ በኤርትራ ሰሜን ዞባ ውስጥ ናቅፋ ከተማ አካባቢ የምትገኘውን አሁን የግኁሣንና የኅቡዓን በዓተ ጸሎት ኋላም ብዙ ቅዱሳን ሰማዕታት ሀገር የተባለችውን ናግራንን፣ ከአስመራ በስተሰሜን ምስራቅ በ91 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘውንና በጥንት ስሟ «ገዳመ ሲሃት» በ484 ዓ.ም አካባቢ ደግሞ በ፱ቱ ቅዱሳን «ደብረ ሲና» የተባለችውን፣ በሕዛ ማርያምን፣ ደብረ ቢዘንን፣ ማርያም ዓይላን እየባረኩ መጥተው አክሱም አረፈው ባረኳትም።

ቅዳሴ ማርያምን የደረሠው የብሕንሳው ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስም ስለ ኢትዮጵያ ቅድስና ሐዋርያው ቅ/ዮሐንስ ወንጌላዊ በጻፈው መጽሐፍ አንብቦ ኢትዮጵያን ለማየት 40 ቀን ሱባዔ ገባ። በፈቃደ እግዚአብሔርም በ4ኛው መ.ክ.ዘ. ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እየተዘዋወረ ጎበኘ። አቡነ ሠላማ ከሳቴ ብርሃንም ጵጵስና ሊሾም ወደ እስክንድርያ ከሄዱት ልዑካንም አንዱ አባ ሕርያቆስ ነበር። ከቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ ጋርም በአክሱም ከተማ ብዙ ጊዜ ተቀመጧል...።

የአባ ሕርያቆስ ደቀ መዝሙር የሆነው መምህር ጌዴዎንም በአክሱም ቤተ ቀጢን ወንበር ተክሎ ጉባዔ ዘርግቶ በርካታ ቅዱሳን ደቀመዛሙርትን አስተምሯል፤ ከነዚህ ውስጥም ተሰዓቱ ቅዱሳንና ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይጠቀሳሉ።

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ከመምህር ጌዴዎን ዘንድ ለ፮ ዓመታት ትምህርት አልገባው ቢል በ፯ኛው ዓመት መደባይ ታብር አካባቢ ወደሚገኙት ቤተሰዎቹ ሲሄድ ከአክሱም ከተማ በ2 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው ማይ ኪራሕ ከዛፍ ስር አረፍ ብሎ ትሏን ስድስት ጊዜ ወድቃ በ፯ኛው ዛፉን ስትወጣው በመመልከቱ ማስተዋልን አግኝቶ ፯ኛ ዓመት መሞከር አለብኝ ብሎ ወደ አክሱም ተመለሠ። ኢዮር፣ ራማና ኤረር በሚባሉ ፫ቱ ሰማያት የመላእክት ከተሞች በግእዝ በዕዝልና በአራራይ ዜማ የሚደረሠውን ስብሐተ እግዚአብሔር በ3 ወፎች የተመሰሉ መላእክት በአክሱም ሙራደ ቃል ላይ አስተማሩት። እመቤታችን ቅዱስ አባ ሕርያቆስ ዘብህንሳንና ቅዱስ ኤፍሬም ዘሶርያን በአጸደ ነፍስ አምጥታ ለቅዱስ ያሬድ እየነገሩት ቅዳሴዋንና ውዳሴዋን በዜማ ደረሠ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም በየዓመቱ ፪ ጊዜ በአካል መጥተው በአክሱም ይገለጡ ዘንድ ክቡር ቃል ኪዳን አላቸውና እየመጡ ይባርካሉ።

በዚሁ በአክሱም ጽዮን ውስጥ በሚገኘው የመምህር ጌዴዎን ቤተቀጢን ጊባዔ ቤት ተሰዓቱ ቅዱሳን ተምረውበታል፤ ታቦተ ጽዮንንም ለብዙ ጊዜ አገልግለዋል። ከዚህ በኋላም እነ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣ እነ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባን ጨምሮ በየዘመኑ የተነሡ በርካታ ቅዱሳን በአክሱም ተቀምጠው ታቦተ ጽዮንን በንጽሕና አገልግለዋታል።

ጥንታዊቷ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድረስ ለተነሡ ነገሥታት ሲመት ከሚፈፀምባቸው ከ፬ቱ መናብርቱ ጽዮን መካከል አንዷና ቀዳሚዋ ናት። አክሱም ከክርስትና ሃይማኖት ትምህርትና ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ማዕከልነት በተጨማሪ የሥርዓተ መንግሥትም ማዕከል ናትና ብዙ ድንቅ ታሪክ አላት። ነገር ግን ስለብዙው ታሪኳና ክብሯ ከዚህ በላይ ብተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና እዚህ ላይ አቆምኩ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ ፲፩፥ ፴፪ ላይ፦ "እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና።" እንዲል።

አምላከ አበው የታቦተ ጽዮንን በረከት አይንሣን፤ አገር የሚያተራምሱትን የዘመናችን ፖለቲከኞች ልብ ሰጥቶ የቅድስት ሃገራችንን የቀደመ ክብርና ልዕልና የሕዝቦቿንም አንድነትና ወንድማማችነት ይመልስልን። እመብርሃን በከበረው ቃልኪዳኗ ሃገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ትጠብቅልን። እኛም ዘወትር በአንድነት ሆነን፦ “አግርር ጸራ ታሕተ እገሪሃ ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊቷ ለሃገሪትነ ኢትዮጵያ” እያልን እንጸልይ።

❖ ብዙዎች የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጦማሩን Share, Like, Tag & Comment አድርጉት፤ የቅዱሳት መካናትን የቃልኪዳን በረከት እንዲያገኙ ለሌሎች ምክንያት መሆን በራሱ ልዩ በረከት ያሰጣልና Share & Tag በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
👉 "ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!

❖ ከማኅበራችን ጋር ተጉዘው በርካታ ጥንታዊ ገዳማትን መሳለም ከፈለጉ ሳያመነቱ ቀድማችሁ ይደውሉልንና አብረን በረከት እናግኝ! ለበለጠ መረጃ፦
📞 0901070707
📱 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

• ባላችሁበት አካባቢ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707

በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ቤተሰብ በመሆን ያግዙን

• በዩቲዩብ ☞ https://youtube.com/@mekoreta

• በቲክቶክ 👉🏿 http://tiktok.com/@betewali

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mekoreta

• በቴሌግራም 👉🏿 @waldiba እና
☞ @negeretewahido

ዋልድባ ገዳም

17 Nov, 07:48


“ሰው ከፍቶ አይዝጋችሁ...”
🎤 የኔታ ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ዋልድባ ገዳም

16 Nov, 08:53


ታሪካዊቷ ዱባርዋ ቁስቋም ገዳም (አሮጊት ገዳም) - ኤርትራ
(ጥንታዊቷ የቃልኪዳን ምድር ደብረ ቁስቋም ገዳም)

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪደተ እግሩ የባረከው ጥንታዊ ቅዱስ ገዳም፣
እመቤታችን ከስደቷ ወደ ሃገረ ገሊላ ስትመለስ ያረፈችበት፣ የጸለየችበትና በኪደተ እግሯ የባረከቺው ታሪካዊ ቅዱስ ቦታ፣
አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ የጸለዩበትና የባረኩት ዕፁብ ድንቅ ቦታ፣
አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በቦታዋ ላይ እየጸለየ ለወራት ከመቀመጡም በተጨማሪ 19 ቀሳውስትና ዲያቆናትን በአንብሮተ ዕድ ባርኮ ሾሞባታል።
ተሰዓቱ ቅዱሳን ያረፉባት፣ የጸለዩባትና የባረኳት ታሪካዊ መካነ ቅዱሳን ናት ዱባርዋ ደብረ ቁስቋም ገዳም፣
በ1515 ዓ.ም የተነሣው ግራኝ ገዳሟን አውድሞ በውስጧ የሚገኙ በርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ቅርሶችን አቃጥሎና ዘርፎ ቢሄድም ከወረራው የተረፉ አንዳንድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍትና ቅርሶች ዛሬም ድረስ አሏት።

✞ ይህንን ቦታ የተሳለመ ሁሉ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ አርጋኖን ዘሰኑይ ድርሰቱ፦ “የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበትን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ። ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ። የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ። የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ።” ብሎ ያመሰገናትን ያስባል።

✞ በእርግጥ እመቤታችን ከ2014 ዓመታት በፊት ነው ይህንን ቦታ በኪደተ እግሯ የባረከችው፤ በፍፁም ልቡ ላመነ ሰው ግን የስደቷን በረከት ያፍሣል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፦ “አሁንም ያን ጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች ድንግል ጋራ ያን ጊዜ ካሉት አላንስም፤ ሃሳቤን ከዚያ እንዳለሁ አድርጌያለሁና። በሥጋ አልነበርኩም በመንፈስ ግን አለሁ፤ ባነዋወር አልነበርኩም በሃይማኖት ግን አለሁ፤ በገጽ አልነበርኩም በማመን ግን አለሁ።” እንዲል [መጽሐፈ አርጋኖን ዘሰኑይ ፪፥ ፲፩- ፲፪)

✞ ስለዚህም ወደ አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም በምናደርገው የዙር ጉዟችን በሃገረ - ኤርትራ ከተሳለምናቸው ከ20 በላይ አስደናቂ ገዳማት ውስጥ አንዷ ናት። ገዳሟ ከአስመራ ከተማ ወደ መንደፈራ በሚወስደው መንገድ በ30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ካለችዋ በመዳብ ማዕድን ከምትታወቀዋ ዱባርዋ ከተማ ዳር በምትገኝ ኮረብታ ላይ ነው የተመሠረተቺው።

✞ ገዳሟ ጥንታዊት የታሪክ ባለቤትና ታይታ የማትጠገብ መካነ ቅርስ በመሆኗና በአመሠራረት ዘመኗ ምክንያት አሮጊቷ ገዳም ይሏታል። በገዳሟ ከ58 በላይ ነገሥታት እንደነገሡባት የቦታዋ የታሪክ ምሁራን ይገልጻሉ። የጊቢዋ ድባብና ግርማ፣ በገዳሟ ያሉ አበው ትሕትናና እንግዳ ተቀባይነታቸው ግሩም ነው። አምላከ አበው የቅድስት ሃገራችንን ሰላም መልሶልን መሪዎቻችንንም አገርሞ በድጋሜ ደጇን እንድንረግጥ ሁላችንንም ይርዳን!!!

👉 ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ለምናደርገው ዓመታዊ የንግሥ ጉዟችን ምዝገባ ላይ ነን።
* መነሻ፦ ኅዳር 16
* መመለሻ ኅዳር 25
* የጉዞው ዋጋ፦ በቦታው ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 9000 ብር
የቀሩን ወንበሮች ጥቂት ብቻ ናቸው።

በጉዟችን ላይ ከምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት ውስጥ፦
👉 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉 ደብረ የሐ አቡነ ሐፍፄ፣
👉 ደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) አቡነ አረጋዊ፣
👉 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉 ሐውዜን ቅ/ጊዮርጊስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣
👉 ማኅበረ ዴጎ አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ እና አቡነ አሞኒ፣
👉 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ፣
👉 አርማኒያ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና ሌሎችም

• ባላችሁበት አካባቢ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707

ይህንን መንፈሳዊ መልዕክት እርሶ በሚጠቀሙበት ድህረገጽ ላይ ሼር በማድረግ ይተባበሩን።

★ ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

👇 በቴሌግራም ይቀላቀሉን 👇
👉🏿 @waldiba
👉🏿 @negeretewahido

ዋልድባ ገዳም

14 Nov, 10:33


ሰው ሆይ፦
🎤 የኔታ ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

ዋልድባ ገዳም

11 Nov, 05:29


የሰባቱ ጊዜያት ጸሎታትና የምንጸልይባቸው ምክንያቶች
🎤 በየኔታ ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ዋልድባ ገዳም

07 Nov, 19:35


#ገዳማተ_ተስዓቱ_ቅዱሳን - ፰
#ገርዓልታ_ደብረ_ጎሕ_አቡነ_ይምዓታ_ገዳም

★ ተስዓቱ ቅዱሳን እመቤታችን ከተወደደ ልጇ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አረጋዊ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን አስከትላ ስትሰደድ ወደባረኳት በመጽሐፍ ቅዱስም ብዙ ጊዜ ወደ ተጠቀሰቺው ኢትዮጵያ በራእይ ተገልጦላቸው በመጻሕፍት ተረድተው በአፄ አልዓሜዳ ዘመነ መንግሥት ከጥንቷ የሮም ግዛትና ከታናሿ እስያ መጡ። እነዚህ እጅግ የከበሩ ቅዱሳን በቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ሥርዓተ ምንኩስናን እና ገዳማዊ ሕይወትን አስፋፍተዋል።

★ ከሕዝቡ ጋርም ዘርና ነገድ፣ ቋንቋና ቀለም ሳይለያቸው በክርስቶስ አንድ ሆነው ለ12 ዓመታትም በፍጹም አንድነት አብረው ከተቀመጡ በኋላ ‹‹እርስ በራሳችን እየተያየን ብንኖር ተድላ ደስታ ይሆንብናልና ተለያይተን እንቀመጥ›› ብለው ተማከረው በተለያየ በዓት አቡነ ሊቃኖስ በደብረ ቁናጽል፣ አቡነ ጰንጠሌዎንም በደብረ አጥገባ፣ አቡነ ገሪማ በደብረ መደራ፣ አቡነ ጽሕማ በዕዳጋ ዓርቢ ደብረ ጸድያ፣ አቡነ ይምአታ በገረዓልታ ደብረ ጎሕ፣ አቡነ አፍጼ በደብረ የሓ፣ አቡነ አሌፍ በአኅድዓ ደብረ በሕዛ፣ አቡነ ጉባ በማይጨው እንድርቃይ እና አቡነ አረጋዊ በደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) በአጽንዖ በዓት በብሕትውና ሕይወት ጸንተው በዋሻና በፍርኩታ ውስጥ በተራራም ላይ መኖር ጀመሩ፡፡

★ አቡነ ይምዓታ ከአክሱም ተነስተው በየመንገዱ ወንጌልን እየሰበኩና ከእመቤታችን ፍቅር የተነሳ "ቅዳሴ ማርያም" እየጸለዩ ሲሄዱ "አብ ጎሕ ወልድ ጎሕ መንፈስ ቅዱስ ጎሕ" እያሉ ሳሉ፤ አሁን ገዳማቸው ከሚገኝበት "ጎሕ" የሚባልበት ቦታ ላይ ደረሱና "ይኩን ስምኪ መካነ ጎሕ" ብለው ሰየሟት! በትሕርምትና በብሕትውናም በገዳማቸው ኖረው ጥቅምት 28 ቀን በዚሁ በጎሕ ሥላሴ ሸለቆው ውስጥ አንገታቸውን ተሰይፈው ዕረፍታቸው ሆኗል! የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘትም በመላእክት እጅ ተከናውኖላቸዋል፡፡

★ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስገራሚው ቤተ መቅደሳቸው ትግራይ ገረዓልታ ልዩ ስሙ ‹‹ጎሕ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ሰማይን እንደ ምሰሶ ደግፈው የያዙ የሚመስሉ በጣም ረጃጅም ተራሮች መካከል በአንደኛው ጭፍ ላይ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ያለበት የተራራው ርዝመት ብቻውን 300 ሜትር ነው፡፡ ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ በጭንቅና በፍርሃት ሆኖ ተራራውን እንደዝንጀሮ በእጅ እየቧጠጡ መውጣት ይጠይቃል፡፡ እርሱም ቢሆን በገዳሙ አባቶችና በአካባቢው ሰዎች እገዛና ድጋፍ ካልሆነ ለመውጣት አስቸጋሪ ነው፡፡ ለእጅና ለእግር ማሳረፊያ ትንንሽ ቀዳዳዎችን ብቻ በመጠቀም ነው ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ የሚቻለው፡፡ በታላቅ ጭንቅና በፍርሃት ሆነው በአካባቢው ካህናት እየታገዙ እንደምንም ብለው ጫፍ ላይ ከደረሱ በኋላ ቁልቁል መመልከት ደግሞ ከአቡነ የምዓታ ጋር የነበረ ጌታ አሁንም እየረዳን እንዳለ ይረዱበታል!

★ ጻድቁ ሰማእት አቡነ ይምዓታ ይህንን ተራራ በተአምራት በፈረስ እንደወጡት ገድላቸውን ጠቅሰው የገዳሙ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ከአገልጋዮቻቸው አንደኛው ለፈረሱ ራት ሳር ሳይሰጠው በውሸት "ለፈረሱ ሳር ሰጥቼዋለሁ" ብሎ አቡነ ይምዓታን ይዋሻቸዋል፡፡ እርሳቸውም የተሰወረውን ሁሉ ያውቁ ነበርና "...ውሻ እንጂ የሰው ልጅ በሐሰት አይጮህም" ብለው ሐሰትን ስለመናገሩ ገሠጹት፣ ወዲያውም በተአምራት ከአንገቱ በላይ የውሻ መልክ ያለው ሆነ፡፡

★ ቤተ መቅደሱ እጅግ የሚደንቀው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ ብቻ አይደለም ውስጡ ያሉት የግድግዳ ላይ ሥዕሎችም በ6ኛው መ/ክ/ዘመን የተሣሉ እጅግ ድንቅና ጥንታዊ ናቸው፡፡ ስለዚሁ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስደናቂ ቤተ መቅደስ ገድለ አቡነ አረጋዊ ‹‹በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በመላእክት እጅ ነው የተከናወነው፡፡ ይልቁንም ቁመቱና ርዝመቱ ከታላላቅ ገደል እጅግ በጣም የሚበልጥ የድንጋይ ዓምድ ከወንዝ ማዶ ዘንበል ብሎ መጥቶ ሥጋቸውን በክብር ተቀብሎ በተራራው ጫፍ ላይ እስከዛሬም ድረስ ፈጽሞ ሳይነቃነቅና ሳይናወፅ ቀጥ ብሎ ቆሞ ይገኛል›› በማለት ይገልጸዋል። የተሰዓቱ ቅዱሳን ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡

★ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዘንድሮው የአክሱም ጽዮን ጉዟችንም ከ፱ኙ ቅዱሳን ገዳማት 6ቱን የምንሳለማቸው ይሆናል፡፡ ውስን ወንበሮች ስላሉን ከማኅበራችን ጋር ተጉዛችሁ የበረከቱ ተካፋይ መሆን የምትሹ ክቡራንና ክቡራት የተዋህዶ ልጆች ቀድማችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

†★† ለበለጠ መረጃ፦
👉👉 0901070707 / 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ 

👇 በቴሌግራም ይቀላቀሉን 👇
👉 @waldiba
👉 @waldiba
👉 @negeretewahido
👉 @negeretewahido

https://youtu.be/xQeIWfeB9cM?si=aX36nX8tDlhjyrx9

ዋልድባ ገዳም

07 Nov, 14:37


“በጾም የንስሐ ይሰጣልን? በጾም ላይ ጾምስ ይታዘዛል?”
🎤 ክቡር አባታችን ቀሲስ መንግሥቱ (የእናቴ ልጅ)

ወደ ጥንታዊቷ ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም ለሚኖረን የ10 ቀናት ጉዞ ምዝገባ ላይ ነን።
* መነሻ ኅዳር 16 መመለሻ ኅዳር 25
* የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 9000 ብር
በጉዟችን ከምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት ውስጥ፦
👉 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉 ደብረ የሐ አቡነ ሐፍፄ፣
👉 ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ፣
👉 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉 ሐውዜን ቅ/ጊዮርጊስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣
👉 ማኅበረ ዴጎ አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒና አቡነ አሞኒ፣
👉 ሐይቅ ቅ/እስጢፋኖስ፣
👉 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት፣
👉 አርማኒያ ቅ/መርቆሬዎስ እና ሌሎችም
ለበለጠ መረጃ፦
0901070707
0911289877

• የጉዞ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦ በሚከተሉት የባንክ አካውንቶች አስገብተው በካሽ ከሆነ ደረሰኙን ፎቶ አንስተው በሞባይል ባንኪንግ ከሆነ ስሊፑን Screenshot በማድረግ በቴሌግራም ይላኩልን።

አንተነህ ውብሸት መኮንን
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707

ዋልድባ ገዳም

07 Nov, 08:54


ሌሊት ጸልዩ...
🎤 በየኔታ ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ዋልድባ ገዳም

06 Nov, 21:16


“የጽዋ ማኅበር እና ልማዶቻችን”
🎤 በቀሲስ መምህር አንድነት አሸናፊ
(የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ መምህር)
🎤 በመጋቤ ሃይማኖት ታሪኩ አበራ
(የመርካቶ ቅ/ራጉኤል ሰባኬ ወንጌልና በማኅበረ ቅዱሳን የኦዲዮ ቪዲዮ ክፍል አርታዒ)
👉 አወያይ ሊቀዲያቆናት ቀዳሜፀጋ ዮሐንስ የቀንድል ሚዲያ ባለቤትና ሥራ አስኬያጅ

ዋልድባ ገዳም

06 Nov, 07:56


የኢትዮጵያን ሱባኤ አንቆ የያዘው ምንድነው?
🎤 በአንጋፋው መምህር ብርሃኑ አድማስ

ዋልድባ ገዳም

06 Nov, 07:55


መንፈስ ቅዱስ ያለው ሐዋርያዊ ቅብብሎሽን ይዛ በተገኘች (የሐዋርያት ክህነት፣ የሐዋርያት ትምህርትና የሐዋርያት ቁርባን ባሉባት) በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው።
🎤 በርእሰ ሊቃውንት የኔታ መምህር አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ዋልድባ ገዳም

04 Nov, 11:41


“፬ቱ የንስሐ መግቢያ መንገዶች”
🎤 ክቡር አባታችን ቀሲስ መንግሥቱ (የእናቴ ልጅ)

ወደ ጥንታዊቷ ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም ለሚኖረን የ10 ቀናት ጉዞ ምዝገባ ላይ ነን።
★ መነሻ ኅዳር 16 መመለሻ ኅዳር 25
★ የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 9000 ብር
በጉዟችን ላይ ከምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት ውስጥ፦
👉 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉 ደብረ የሐ አቡነ ሐፍፄ፣
👉 ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ፣
👉 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉 ሐውዜን ቅ/ጊዮርጊስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣
👉 ማኅበረ ዴጎ አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ እና አቡነ አሞኒ፣
👉 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ፣
👉 አርማኒያ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና ሌሎችም
★ ለበለጠ መረጃ፦
0901070707
0911289877

• ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 በሚከተሉት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብተው Screenshot በማድረግ ወይም ደረሰኙን ፎቶ አንስተው በቴሌግራም ይላኩልን።

አንተነህ ውብሸት መኮንን
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707

5,143

subscribers

389

photos

229

videos