የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ) @yehiwot_meaza Channel on Telegram

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

@yehiwot_meaza


በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በሕይወት ላይ ያተኮሩ ጽሑፎችና ሌሎች ኦርቶዶካሳዊ ትምህርቶች በጽሑፍና በድምጽ ይቀርብበታል

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ) (Amharic)

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በሕይወት ላይ ያተኮሩ ጽሑፎችና ሌሎች ኦርቶዶካሳዊ ትምህርቶች በጽሑፍና በድምጽ ይቀርብበታል. አቡነ ሺኖዳ የህይወት መዓዛ ከድምፅ እና በጽሑፍ አገልግሎት የሚስክ ችግርን ጠቅምላል። ይሔንን ቤተመንግስት ጽሁፎችና ሁሉም የአቡነ ሺኖዳው አገልግሎት በኬቲዮን በተዘጋጀ ግንኙነት ይቀርባሉ። ከዚህ በኋላ፣ ሰላም በግፍ፣ ቸልታ በብቻው ያለው አቡነ ሺኖዳ።

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

30 Nov, 18:42


የመቅደስኽ ታቦት

በመምህር ዲያቆን ቡሩክ ተስፋዬ

https://youtu.be/sGvz5C0cVNg?si=fg-lFC8kAnKHomd2

https://youtu.be/sGvz5C0cVNg?si=fg-lFC8kAnKHomd2

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

29 Nov, 20:43


#ኅዳር_21

#ቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም

ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።

እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር፣ ሞገስ፣ አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። (ዘጸ. 31፥18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች። እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው። ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን። ግን አንጨነቅም። ምክንያቱም የመጣችውም የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም። በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም። ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19)

በመጨረሻም ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን።

#በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይኑር።

( #ስንክሳር_ዘተዋሕዶ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

29 Nov, 12:55


ለነፍሳችን ኹለተኛዋ ነፍስ

ወዳጄ ሆይ! እምነት ለነፍስህ ኹለተኛዋ ነፍስ እንደሆነች መርምርና እወቅ፡፡ ሥጋ በነፍስ እንድትቆም የነፍስም በሕይወት መኖር በእምነትህ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ እምነትህን ብትክድ ወይም ከራስህ ብታርቃት ነፍስህ ምውት ትሆናለች፡፡

በዚህም መሠረት የሚሞት ሥጋችን በነፍስ ላይ ጥገኛ እንደሆነች ነፍሳችንም በእምነት ላይ ጥገኛ ናት፡፡ እምነትም በእግዚአብሔር አብና በመንፈስ ቅዱስ ሕያዋን ባደረገን በእውነተኛ ልጁ ላይ ጥገኛ ናት፡፡

በዚህም እውነት ሰው ነፍሱን በሰማያት ካሉት ጋር ያገናኛታል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው በነፍሱ በሕይወት ይኖራል፡፡ በሥጋ ሰውነቱም ያያል ይመለከታል። እንዲሁ እኛም በእምነት በፍቅርና በጥበብ የእግዚአብሔር መልክ ገንዘባችን አድርገን ከመለኮቱ ተካፋይ እንሆናለህ። ስለዚህም በነፍሳችን የሞትን እንዳንሆን ይህን ድንቅ የሆነ ማሰሪያ እንዳንበጥስ ወይም ነፍሳችን ከእምነት ባዶ እንዳናደርጋት እንጠቀቅ፡፡ ጌታችን ይህን አስመልከቶ እንዲህ ብሎ አስተምሮናልና “ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው።” (ማቴ.8፥22) ይህ አየር በእኛ ላይ በንፍሐት እፍ ሳይባልብን ሥጋችንን በሕይወት የሚያቆያት ነው፡፡ የምንተነፍሰው አየር የተቋረጠበት ሰው ሕይወቱ ትቆማለች፤ በሥጋው የሞተ ይሆናል፡፡ እንዲሁ ራሱን ከእውነተኛ ልጁ ከእግዚአብሔር ቃል የለየ ሰውም በነፍሱ የሞተ ይሆናል፡፡ እኔ ሕይወትን የሚሰጠው የእውነተኛ ልጁን ምስክርነት ሳያገኝ ለሞተ ሰው አዝናለሁ፡፡ ልክ እንደ ውቅያኖስ እርሱ የሕይወት ምንጭ ነውና፡፡

እርሱ ሰው በመሆን ፈቃዱን እንድናውቀው አደረገን፡፡ ሞትን ድል ለመንሳት ሲል እጅግ መጠማቱ ለእኛ ያለውን ፍቅር አረጋገጠልን። መጽሐፍ ቅዱስ በእምነት ጻድቅ የሆነ እርሱ በሕይወት እንዲኖር አትሞልናል፡፡ እውነት የተባለው እርሱ ራሱን ዋናው ሥር በማድረግ በጎ ምግባራትን ደግሞ በእርሱ ላይ ባለን እምነት ላይ የተንጠለጠሉ ፍሬዎች አደረጋቸው፡፡

እነሆ መልካም ምግባሮቻችን በእውነትኛው ግንድ በእርሱ ቅርንጫፎች ሆነው በዝተው ፍሬን ይሠጣሉ፡፡ እነሆ በሚታይ ምሳሌ የተሰወሩ ምሥጢራት በዓይን እንደሚታዩ ሆነው ተገለጡ። ሥጋ ልክ ትርፉን ለማግኘት እንደጓጓ ነጋዴ ነው እንዲሁ ሕሊናም ከእርሱ ጋር በእምነትን በሕይወት መርከብ ትርፍን እንደሚሰብስብ መርከበኛ ነው፡፡

ሥጋ በነፍስ እንዲቆም ነፍስም ምንም እንኳ ሕያዊት ብትሆን ያለ በጎ ሥራ ሕይወት እንደሌላት፤ ነፍስ በእምነት በሚሠራ የጽድቅ ሥራ በሕይወት እንደምትኖር መጽሐፍ ቅዱስ መስክሮልናል፡፡ በክርስቶስ አምኖ የነበረው አልዓዛር ለዚህ ለምንለው እውነተኛ ምስክር ይሆን ዘንድ ሕያው ሆኖ ተነሣ፡፡

እርሱ ከመቃብር በጠራው በጌታችን ቃል ሕይወቱ ጣፍጣ ሕያው ሆነ፡፡ እንዲሁ በአልዓዛር ምሳሌ አህዛብ በሕቡዕ በሚኖረው ሕይወት ሕያዋን ሆኑ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በአይሁድ ሥራ ምሳሌ ወንበዴው ራሱን ሰቀለ እንደ ውርስ አድርጎ ሞቱን ለጸሐፍት ፈሪሳዊያን ተወላቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በእርሱ ላይ ባለን እምነት በመንፈስ ቅዱስ ሕያዋን ሆነን እምነታችንን ጠብቀን እንድንኖር ይርዳን፡፡

(ቅዱስ ኤፍሬም - ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

27 Nov, 10:32


ኑ ሰብስክራይብ እናድርግ

“እኔም ወንጌልን ማድረስ እችላለሁ”
የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ሰብስክሪብሽን ዘመቻ ተቀላቀሉ።

Subscribe and share

https://youtube.com/@eotcmk?si=_we8ZKBkbmex6PJ3

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

26 Nov, 17:07


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ስመ ሥርጋዌሁ ለቅዱስ ዮሐንስ

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቋሚ ስሙ ዮሐንስ የሚለው ስሙ ነው። አፈወርቅ የሚለው ስሙ ግን ስመ ሥርጋዌ (የሽልማት) የቅጽል ስሙ ነው። አፈወርቅ ከሚለውም በተጨማሪ ሌላ ዳንኤል ሐዲስ የሚባል ስመ ሥርጋዌም አለው፡፡ የእነዚህ ሁለት ስሞች ስያሜ መነሻ ታሪክ እንደሚከተለው ነው።

አፈ ወርቅ

ሊቁ አፈወርቅ የሚለውን ስያሜ ከእመቤታችን እና ያስተምራቸው ከነበሩት በትምህርቱም ደስ ከተሰኙ ምእመናን እንዳገኘው ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡

ሕዝቡ መቼ አፈወርቅ አለው?

ቅስና ከተሾመ በኋላ ከላይ እንደገለጽነው በንጉሡ በቴዎዶስዮስና በሕዝቡ መካከል በሐውልቱ መፍረስ ምክንያት ቅራኔ ተፈጥሮ በነበረ ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ ፍላቭያኖስ ንጉሡን ከሕዝቡ ጋራ ሊያስታርቅ ሄደ። ያን ጊዜም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕዝቡን በሚገባ ጣዕም ባለው አንደበቱ አስተማራቸው፡፡ የአንደበቱን ጥፍጥና የተመለከቱት ምእመናንም ይህ ሰው “አፈ ወርቅ" ነው ተባባሉ፡፡ ይህን ማለታቸውም ወርቅ ከማዕድናት ሁሉ የጠራ እንደ ሆነ ዮሐንስም ትምህርቱ የተወደደ የጠራ ነው ማለታቸው ነበር።

እመቤታችን

ንጉሡ አርቃድዮስ ወንጌላዊው ማቴዎስ “ኢያእመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወልደ ዘበኵራ፤ የበኵር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ነበር” በማለት የተናገረው ቃል ጥያቄ ሁኖበት ይኖር ነበርና ሊቁ በቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስነትን በተሾመ ጊዜ ወንጌላዊው ይህንን ስለምን ተናግሮታል? ወንዶች ሴቶችን በግብር እንደሚያውቋቸው ከወለደች በኋላ በግብር ዐወቃት ማለት ነውን? ብሎ ጠየቀው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም ወንጌላዊው ይህን ማለቱ ስለ ሁለት ነገር እንደሆነ እንዲህ በማለት አስረዳው፡፡

ፍጻሜ የሌለው እስከ

ወንጌላዊው “የበኵር ልጇን እስከ ምትወልድ አላወቃትም ነበር” በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ ያለው እስከ ፍጻሜ የሌለው “እስከ" ይባላል፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ “ኢወለደት ሜልኮል እስከ አመ ሞተት፤ ሜልኮል እስክትሞት ድረስ አልወለደችም ነበር" የሚል ገጸ ንባብ እናገኛለን፡፡

በዚህ ገጸ ንባብ ውስጥ ያለው እስከ ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ከሞተ በኋላ ሊወልድ አይችልምና፡፡ ይህም ማለት ሜልኮል እስከ ዘለዓለሙ አልወለደችም ማለትን ለማስረዳት የገባ እስከ ነው፡፡ የወንጌላዊው ንግግርም ከወለደች በኋላ በግብር አውቋታል ማለት ሳይሆን እስከ ዘለዓለሙ አላወቃትም ለማለት ነው፡፡

ዮሴፍ አምስት ነገሮችን እስኪያይ ድረስ

በሁለተኛ ደረጃም የእመቤታችንን እመ አምላክነት ክርስቶስን በወለደች ዕለት ዐምስት ነገሮችን ማለትም የጌታ የጌትነቱ መገለጥ፣ የመላእክትን ምስጋና፤ የእረኞችን ፍርሃት፣ የኮከብን በሌላ መንገድ መሄድና የሰብአ ሰገልን ከእጅ መንሻ ጋር መምጣት እስከሚመለከት ድረስ አላወቀም ነበር፡፡

ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የተወደደ ልጇን ክርስቶስን በወለደች ጊዜ ግን እነዚህን ነገሮች ተመልክቶ ወላዲተ አምላክ መሆኗን አውቋልና፡፡ ሊቁ ቃሉን “የበኵር ልጇን እስከምትወልድ ድረስ አላ ወቃትም ነበር” በማለት አመሥጥሮ ተርጕሞታል፡፡

በዚህ ጊዜ በወርቅ የተሣለች የእመቤታችን ሥዕል በዚያ ነበረችና “ሠናየ ተናገርከ ኦ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፤ ሠናየ ተናገርከ ኦ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ፤ ሠናየ ተናገርከ ኦ ዮሐንስ አፈ ዕንቊ፤ አፈ ወርቅ ልሳነ ወርቅ አፈ ዕንቊ ዮሐንስ የተወደደ ነገርን ተናገርህ'' ብላ አሰምታ ተናግራለች፡፡ ንጉሡም ይህንን ከእመቤታችን የተሰጠውን ስም ሥርጋዌ ሰምቶ በመደነቅ ከዚህ በኋላ ስሙ አፈወርቅ ይባል ብሎ አዘዘ።

ከዚህም በተጨማሪ በሦስተኛ ደረጃም አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰታቸው ውስጥ እንደ ገለጹት ንስጥሮስ የተባለ መናፍቅ ኤጲስ ቆጶስነትን በተሾመበት ወራት አንዲት ሴት ከግዳጇ ሳትነፃ ለቤተ እግዚአብሔር ካላት ፍቅር የተነሣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ትገባለች፡፡

ያን ጊዜም የፀሐይ ጨረር ከሰው ሁሉ ተለይቶ በዚያች ሴት ላይ ያርፋል። የተሰበሰበውም ሕዝብ በተመለከተው ገቢረ ተኣምራት ሲደናገጥ ንስጥሮስ ይህችን ሴት በምን ምክንያት ይህ ምልክት እንደታየባት ጠየቃት፡፡

እርሷም ለቤተ እግዚአብሔር ካለኝ ፍቅር የተነሣ ከግዳጄ የምነፃበት ቀን ሳይደርስ ቤተ ክርስቲያን ገብቻለሁ ብላ በፍርሃት ተናዘዘች፡፡ ንስጥሮስም በልቡናው እመቤታችን አምላክን አልወለደችውም የሚል ኑፋቄ ስለነበረበት ይህቺ ሴት ራቁቷን በዐደባባይ እንድትሰቀልና ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው "እግዚአብሔር በዚህ ሥጋ ከሴት እንደተወለደ የሚያምን የተረገመ ይሁን” እያሉ በአፈ ማኅፀኗ ላይ እንዲተፉባት አዘዘ።

የተሰበሰበው ሕዝብም ከሓዲው ጳጳስ ንስጥሮስ እንዳዘዛቸው ሲያደርጉ ቅዱስ ዮሐንስም በዚያ ቁሞ ይሰማ ነበርና የእሱ ተራ ሲደርስው ወደ ሴቲቱ በመቅረብ “እኔ ግን እግዚአብሔር በዚህ ሥጋ በኅቱም ድንግልና ከሴት እንደ ተወለደ አምናለሁ” በማለት ሰዎች ይተፉበት የነበረ አፈ ማኅፀኗን የሰዎችን ምራቅና የእሷንም ደም ሳይጠየፍ የእመቤታችንን ፍጹም ንጽሕና በማሰብ ሳመ፡፡ ያን ጊዜም በቤተ መቅደስ ፊት የነበረች የድንግል ማርያም ሥዕል አፈ ወርቅ ብላ ጠራችው ስለዚህም ዮሐንስ አፈወርቅ ተባለ፡፡ (መጽሐፈ ምስጢር ገጽ 50-51)

ዳንኤል ሐዲስ

ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከተሰጡት ስመ ሥርጋዌ ሁለተኛው ዳንኤል ሐዲስ የሚለው ነው፡፡ ይህ ስም አፈወርቅ እንደሚለው ስም ብዙ ጎልቶ ባይጠራበትም በበጎ ግብሩ ለሊቁ ከመልአኩ የተሰጠው ስም ነው፡፡ መልአኩ ሊቁን ዳንኤል ሐዲስ ያለበት ምክንያት ዳንኤል የናቡከደነፆር ራእይ ንባቡ ከእነ ትርጓሜው ከጠፋ በኋላ ንባቡም ትርጓሜውም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት እንደተናገረ እሱም የዮሐንስ ራእይ ንባቡ ከነትርጓሜው ከጠፋ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት ስለተናገረ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ቸርነት የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የጸሎቱ በረከት ከእኛ ጋራ ትሁን አሜን፡፡

(ምንጭ፦ ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 15-31)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

26 Nov, 13:32


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ንግሥት አውዶክስያ እና የሊቁ የሕይወት ፍጻሜ፦

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በጵጵስና ዘመኑ ከሚታወቅባቸው ደማቅ ሥራዎቹ አንዱ ድኃ ሲበደል ፍርድ ሲጎድል እንደ አባቶቹ እንደ ኤልያስና እንደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ንጉሡንና ንግሥቲቱን ያለ ፍርሀት በጥብዐት ይገሥፅ የነበረ አባት መሆኑ ነበር። በዘመኑም የንጉሡ የአርቃድዮስ ባለቤት ንግሥት አውዶክስያ የአንዲትን መበለት መሬት ሥልጣኗን ተጠቅማ ነጠቀቻት፡፡

ይህቺ መበለት መሬቷን እንድትመልስላት ደጋግማ ብትለምናትም ንግሥቲቱ እሺ ስላላለች መበለቷ ችግሯን ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነገረችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም የድኃዪቱን መሬት እንድትመልስላት ደጋግሞ ቢነግራትም ንግሥት አውዶክስያ ግን በዕንቢተኝነቷ ጸናች። በዚህ ጊዜም ሊቁ ሳይፈራና ሳያፍር ንግሥቲቱ የድኃዪቱን መሬት ካልመለሰች ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አወገዛት፡፡

ንግሥት አውዶክስያም በዚህ ጊዜ እጅጉን ተናዳ የቆጵሮሱን ሊቀ ጳጳስ ኤጲፋንዮስንና የእስክንድርያውን ፓትርያርክ ቴዎፍሎስን አስጠርታ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከግዝቷ እንዲፈታት እንቢ ካለ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ዘግታ አብያተ ጣዖታትን በማስከፈት የቀደመውን የስደት ዘመን መልሳ እንደምታመጣው በመንገር ከግዝቷ እንዲያስፈቷት ነገረቻቸው፡፡

እነርሱም ሄደው “ምእመናን ትንሽ ዐረፉ ስንል የቀደመውን የመከራ ዘመን መልሼ አመጣዋለሁ እያለች ነው እባክህ ከግዝቷ ፍታት።" በማለት ተማጸኑት። ሊቁ ግን “የድኃዪቱን መሬት ካልመለሰች አልፈታትም ብሎ በአቋሙ በመጽናቱ ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ ንግሥት አውዶክስያ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በኑፋቄያቸው ምክንያት አውግዞ የለያቸውን አርዮሳውያን ኤጲስ ቆጶሳትን ሰብስባ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በማይገባ ነገር አውግዞኛልና ፍረዱልኝ አለቻቸው፡፡ እነርሱም በኑፋቄያቸው ምክንያት አውግዟቸው ስለነበር ይጠሉት ነበርና ተሰዶ በግዞት እንዲኖር፣ በዚያም እንዲሞት ፈረዱበት፡፡

ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ሁከት እንዳያነሣ እርሱን በመንፈቀ ሌሊት በፈረስ በሠረገላ አድርጋ ወደ ደሴተ አጥራክያ አጋዘችው፡፡ እርሱም በዚያ በተጋዘበት ሀገር የነበሩትን ሰዎች አስተምሮ ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መለሳቸው፡፡ በወቅቱ በሮም ነግሦ የነበረው ንጉሥ አኖሬዎስ እና ሊቀ ጳጳሱ ዮናክንድዮስ ይባላሉ፡፡ ንጉሡና ሊቀ ጳጳሱም የሊቁን ከመንበሩ መሰደድ ሲሰሙ የሮሙ ንጉሥ አኖሬዎስ ወደ ንጉሥ አርቃድዮስ በፍጥነት ከስደቱ መልሰው የሚል መልእክት ላከበት፡፡ ንጉሥ አርቃድዮስም ያለ ንግሥት አውዶክስያ ፈቃድ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ከስደቱ መለሰው፡፡

ነገር ግን ንግሥት አውዶክስያ ሊቁ ከግዞቱ የተመለሰው ያለ ፈቃዷ ነበርና ሌላ ምክንያት ፈልጋ እንደገና በስደት እንዲጋዝ አደረገችው፡፡ እርሱም በመንገድና በእስራት ደክሞ ስለነበር አጥራክያ እንደደረሰ ብዙ ሳይቆይ ግንቦት 12 ቀን በ407 ዓ.ም. በሰላም ዐረፈ፡፡

ከዚህም በኋላ የሮሙ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሱ ዮናክንድዮስ የሊቁን ሁለተኛ መሰደድ ሲስሙ ሊቀ ጳጳሱ ዮናክንድዮስ ከስደቱ ካልመለሽው ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበይ ብሎ አወገዛት፡፡ እርሷም ከስደቱ ይመልሱት ዘንድ መልክተኞችን ብትልክም መልክተኞቹ በደረሱ ጊዜ ዐርፎ አገኙት፡፡ እነርሱም አስከሬኑን በድንጋይ ሳጥን ይዘው ከደሴተ አጥራክያ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሱ፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር የሊቁ ቅድስና እንዲገለጥ ፈቃዱ ነውና በንግሥቲቱ ላይ ከባድ ደዌ አመጣባት፡፡

ንግሥቲቱም የምትድን መስሏት ለብዙ ባለ መድኃኒቶች ብዙ ገንዘብ ብትከፍልም ከደዌዋ ግን ሊፈውሳት የቻለ ከቶ አልነበረም፡፡ ከብዙ ድካም በኋላም ለክፉ ሠሪ ደግ መካሪ አይታጣምና አንድ ሰው ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መቃብር ሂዳ ብትማጸን ሊቁ እንደሚያማልዳት ነገራት፡፡

እርሷም ወደ መቃብሩ በመሄድ “የአዛኙ የክርስቶስ አገልጋይ ሆይ እዘንልኝ፤ የሩኅሩኁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ራራልኝ፤” እያለች ጸለየች፡፡ ከዚህ በኋላም በጻድቁ አማላጅነት በእግዚአብሔር ቸርነት ከደዌዋ ተፈወሰች።

ስመ ሥርጋዌሁ ለቅዱስ ዮሐንስ.....
ይቀጥላል....

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

26 Nov, 12:00


የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የክህነት አገልግሎት፦


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሰጡትን የክህነት መዓርጋት ደረጃውን ጠብቆ በመቀበል ለመዓርገ ክህነቱ በሚመጥን ሰብእና እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ እግዚአብሔርን አገልግሏል፡፡

ዲቁና

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዲቁናን የተቀበለው በ381 ዓ.ም. መላጥዮስ ከተባለው ሊቀ ጳጳስ ነው፡፡ በዲቁና መዓርግ በነበረበት ጊዜም በቅዳሴ አገልግሎት፣ ድሆችንና በሽተኞችን በመንከባከብ እንዲሁም ከንዑሰ ክርስቲያንነት የነበሩ ሰዎችን በማስተማር ታላቅ አገልግሎት ይሰጥ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሊቁ ኦሪትንና መጻሕፍተ ነቢያትን የተረጎመው በዚህ በዲቁና መዓርግ ያገለግል በነበረበት ዘመን ነው፡፡

ቅስና

ሊቁ ከ381-386 ዓ.ም. በዲቁና በፍጹም ትጋት ሲያገለግል ከቆየ በኋላ ከዕለታት በአንድ ሌሊት በጸሎት ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ “የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ መጥቶ ነገ ቅስናን ይሾምሃል፤ ነገሩ ከእግዚአብሔር የታዘዘ ስለ ሆነ እንቢ እንዳትል በማለት ነገረው፡፡ በነጋም ጊዜ የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ፍላቭያኖስ ወደ እሱ መጥቶ የቅስናን መዓርግ ሾመው፡፡

ከዚህም በኋላ ለ12 ዓመታት ያህል በተወደደ አንደበቱ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ወንጌልን በፍጹም ጥብዓትና ትጋት ሰበከ፡፡ በዚህ ወቅት ትኩረት ሰጥቶ ካስተማራቸው ትምህርቶቹ መካከልም ስለ ዐቢይ ጾም፣ ወደ ትርኢት ቤትና ወደ ፈረስ ጉግሥ ስታዲየም ይሄዱ ስለ ነበሩ ሰዎች ያስተምረው የነበረ ትምህርት ተጠቃሽ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ በሕዝቡ ላይ ቀረጥ ከማብዛቱ የተነሣ ሕዝቡ ተማሮ በከተማው ያቆመውን ሐውልቱን ባፈራረሰበት ጊዜና ከሕዝቡም ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ በገባበት ወቅት “በእንተ ሐውልታት” በሚል ርእስ ያስተማረው ተከታታይ ትምህርት ሌላው ተጠቃሽ ሥራው ነው፡፡

አርባዕቱን ወንጌላት እና ሌሎችን መጻሕፍተ ሐዲሳትም የተረጎመው በዚህ በቅስና መዓርግ ያገለግል በነበረበት ወቅት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዚህ የቅስናው ዘመን ከላይ ከተጠቀሱት ሥራዎቹ በተጨማሪ በዘመኑ አንጾኪያን በኑፋቂያቸው ያውኳት ለነበሩ አርዮሳውያንም በአፍም በመጻፍም የማያዳግም መልስ ሰጥቷል፡፡

ጵጵስና፦

ሊቁ ከላይ በተጠቀሱት በሁለቱም የመዓርገ ክህነት ደረጃዎች በሚገባ እያገለገለ ካለፈ በኋላ በ397 ዓ.ም. የቊስጥንጥንያው ፓትርያርክ ኒከታሪዮስ በማረፉ በንጉሡ በአርቃድዮስ ትእዛዝ ያለ ፈቃዱ ከአንጾኪያ ወደ ቊስጥንጥንያ በመወሰድ በብዙ ልመና የካቲት 26 ቀን 398 ዓ.ም. ብዙ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በእስክንድርያ 23ኛ ፓትርያርክ በአቡነ ቴዎፍሎስ እጅ የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ተሾመ፡፡ በዚህ የሹመት ዘመኑም ከበፊቱ ይልቅ በቅድስና ሕይወት ለመኖር አብዝቶ ይተጋ ነበር፡፡

ሊቁ ሊቃነ ጳጳሳት የሚለብሱትን ልብስ ትቶ ያረጀና ፀጕሩ የተመለጠ ፀምር ከጉልበቱ በላይ ይለብስ ነበር። የሚመገበውም በወርቅ ሚዛን መዝኖ በመሐል እጁ መጥኖ ከሐሰሩ ያልተላቀቀ የገብስ ጥሬ ነበር፡፡ ይህንም የሚያደርገው ፍቶት እንስሳዊት እንዳታሸንፈው ነበር። ከዚህ የተረፈው አነዋወሩ ግን ፍጹም የሐዋርያትን አኗኗር ይመስል ነበር፡፡

ንግሥት አውዶክስያ እና የሊቁ የሕይወት ፍጻሜ፦...
ይቀጥላል.....

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

26 Nov, 09:00


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ቅድመ ምንኵስና በጥብቅና ሙያ


ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የፍልስፍና እና የንግግር ክህሎት ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ በጥብቅና ሙያ አገልግሏል፡፡ በዚህ የሥራ ዘመኑም በፍርድ ቤቶች ተገኝቶ ያደርገው በነበረ የንግግር ችሎታው ብዙዎቹ በጅጉ ያደንቁት ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የጥብቅና ሥራ በጀመረ ጊዜ የትምህርት ቤት ጓደኛው ቅዱስ ባስልዮስ ግን ቀጥታ ወደ ምናኔ ሕይወት እንደ ሄደና ለጊዜው በእርሱና በጓደኛው መካከል የሕይወት ልዩነት እንደነበር ሊቁ እንዲህ በማለት ይገልጻል፡፡

እርሱ በጎ ሰብእና የነበረውና ለጓደኝነታችን ትልቅ ሥፍራን ይሰጥ ስለ ነበር ግን ራሱን ከሌሎቹ አኃው ለየ፡፡ ይህን ጊዜ ይፈልገው የነበር ገና ድሮ ነውና። ነገር ግን ከእኔ ከንቱነት የተነሣ ይህንን ማግኘት አልቻለም ነበር። በፍርድ ቤት ጠበቃ ሁኖ የሚሠራና በዚህ መዓርግ በመገኘቱ ሐሴት የሚያደርግ ሰው ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጥናት ከተጣበቀና ሕዝብ ወደበዛበት ቦታም እግሩን ፈጽሞ ከማያንቀሳቅስ ሰው ጋር አንድነት ሊኖር አይችልምና፡፡

ምንኵስናው

ሊቁ ለተወሰነ ጊዜ በጥብቅና ሙያ ካገለገለ በኋላ ሥራውን በፈቃዱ በመልቀቅ ሙሉ ጊዜውን ለመንፈሳዊ ሕይወቱ ለመስጠት ወሰነ፡፡ የጥብቅና ሥራውን የለቀቀበት ምክንያት በሥራው ውስጥ ይገጥሙት የነበሩ የዓለም ብልሹ አሠራሮች እንደ ነበሩ አንዳንድ መዛግብት ቢናገሩም የጓደኛው የቅዱስ ባስልዮስ ተጽኖም እንዳለበት የሊቁ ሥራ የሆነው በእንተ ክህነት የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ይተርካል፡፡

እኔ የጥብቅናውን ሥራ ስተው ግን እነዚያ በመካከላችን እንደ መጋረጃ ሆነው የቆዩት ዕንቅፋቶች ተወገዱ፡፡ እርሱም ከቀድሞ አንሥቶ ይኖርበት ወደነበረው የሕይወት ዘይቤ (ወደ ምንኵስና ሕይወት) አመጣኝ፡፡ ጥንቱንም ሲደክምበት ወደነበረውና የእርሱን ቅዱሳት መጻሕፍትን ማጥናትና የትኅርምት ሕይወት ፍላጎት አሳደረብኝ፡፡ ለአፍታም ቢሆን ከእኔ መለየትን አይሻም ነበር፡፡ ሁለታችንም በዓታችንን ልንለይና (ልንመነኵስ) እንደሚገባንና በአንድነት ገዳም ልንኖር እንደሚገባን ሁልጊዜ ይነግረኝ ነበር፡፡ እርሱም አሳምኖኛልና አሳቡን ተቀበልሁት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምንም እንኳ የጠበቃ ሥራውን እንደ ተወ ቀጥታ ወደ ምናኔ ሕይወት መሄድ ቢፈልግም እናቱ አትናስያ እርሱ በሕይወት እያለች ከአጠገቧ እንዳይርቅ አጥብቃ ስለለመነችው ለጊዜው ወደ ገዳም የመሄዱን ጉዳይ አዘግይቶ አባትም እናትም ሁና ያሳደገችውን እናቱን እየተንከባከበ በእናቱ ቤት የምናኔን ሕይወት መለማመድ ጀመረ፡፡

አስከዚህም ጊዜ ገና አልተጠመቀም ነበርና ለንዑሰ ክርስቲያንነት የተፈቀደውን የሦስት ዓመት የትምህርት ጊዜ ተምሮ ካጠናቀቀ በኋላ በ23 ዓመቱ አባ መላጥዮስ በሚባሉ ጳጳስ እጅ ተጠመቀ፡፡ ከተጠመቀ በኋላም በፍጹም መንፈሳዊ ትጋት ራሱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ በመስጠት የቅድስና ሥራን በመለማመድ ተጠመደ፡፡ ይህንን መንፈሳዊ ትጋቱን የተመለከተው ጳጳሱ መላጥዮስም አናጕንስጢስ (አንባቢነትን) ሾመው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ መንፈሳዊ ትጋቱን የተመለከቱ ሰዎች ለኤጲስ ቆጶስነት መዓርግ እንዲሾም ቢፈልጉትም እርሱ ግን ወንድሜ ባስልዮስ እንጂ እኔ ለዚህ ሹመት አልመጥንም ብሎ ተሠውሮ አምልጧል፡፡ ስለ ሊቀ ካህናትነት የሚናገረውን መጽሐፉንም ያዘጋጀው በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ እስከ እናቱ አትናስያ ዕረፍት ከእናቱ ጋራ በተወደደ ቅድስና እግዚአብሔርን እያገለገለ በእናቱ ቤት ኖረ፡፡

እናቱ ከዚህ ዓለም በሞት በተለየች ጊዜ ሊቁ ከወላጅ እናቱ የወረሰውን ሀብት ለድሆች በመመጽወት ከአንጾኪያ በስተደቡብ ወደሚገኝ አንድ ገዳም በመሄድ አስቀድሞ ሲናፍቀው ወደ ነበረ የምንኵስና ሕይወት ተቀላቀለ፡፡ በዚህ ገዳምም ከማኅበረ መነኰሳቱ ጋር አራት ዓመት ከቆየ በኋላም የበለጠ ራሱን የምናኔ ሕይወት ለማለማመድ ለሁለት ዓመት ያክል ከማኅበረ መነኰሳቱ ተለይቶ በዋሻ ውስጥ ተከቶ በጾምና በጸሎት ጽሙድ ሆኖ ኖረ።

በዚሁ ገዳም በነበረበት ወቅትም ሲሲኮስ የተባለ አንድ የበቃ አባት ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ጴጥሮስ መክፈቻ ቁልፍ፤ ወንጌላዊው ዮሐንስ ደግሞ ወንጌልን ሲሰጡት በራእይ ተመልክቷል፡፡ ሲሲኮስም ይህን በተመለከተ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለታላቅ መዓርግ እንደሚበቃ ተገንዝቧል፡፡


የሊቁ የክህነት አገልግሎት፦.....
ይቀጥላል......

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

26 Nov, 05:58


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ማን ነው?

ልደቱና እድገቱ፦

ነገረ ታሪኩን የከተቡ መጻሕፍት እንደሚያስረዱት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተወለደው አንጾኪያ በምትባል ከተማ በ347 ዓ.ም. ነው፡፡ አንጾኪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐዋርያት ክርስቲያን ተብለው የተጠሩባት ከተማ ስትሆን የምትገኘውም በሮም Iሮም ምሥራቃዊ ግዛት ነው፡፡ አንጾኪያ ለሮም ምሥራቃዊው ግዛት የት ከቊስጥንጥንያ ቀጥላ ሁለተኛዋ መናገሻ ከተማ ነበረች፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ ወላጆች የአባቱ ስም ሲፋኒዶስ (ሴኩንዱስ) ሲሆን የእናቱ ስም ደግሞ አንቱዛ (አትናስያ) ነው:: አባቱ ሲፋኒዶስ የታወቀ አገረ ገዥ ነበረ፡፡ ሆኖም ግን ሚስቱ አትናስያ (አንቱዛ) ገና የሃያ ዓመት ወጣት እያለች ዮሐንስ አፈወርቅንና ታላቅ እኅቱን እንደ ወለዱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ከዚህም በኋላ ልጆችን የማሳደጉ ኃላፊነት በአትናስያ (አንቱዛ) ትክሻ ላይ ብቻ ወደቀ፡፡ አትናስያም ምንም እንኳ ባሏ ገና በለጋ ዕድሜዋ ትቷት ቢሞትም ሁለተኛ ላግባ ሳትል ልጆቿን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅንና እኅቱን በጥልቅ የክርስትና ሕይወት ትምህርት አሳደገቻቸው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተወለደበት ይህ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የትውልድ ሀገሩ በሆነችው በአንጾኪያ ብዙ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርታቸውን ለማስፋፋት እየተሯሯጡ የነበረበት ዘመን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እናቱ አትናስያ ጠንካራ ክርስቲያን ከመሆኗ የተነሣ ልጇ ከዘመኑ የኑፋቄ ትምህርት እንዲጠበቅ በሕይወትም በትምህርትም ተንከባክባ በመልካም አስተዳድግ አሳደገችው፡፡ የዕብራውያን መልእክትን የተረጎመውን ድርሳኑን የተረጐሙ አባቶቻችን በመልካም አስተዳድግ የማደጉን ነገር ሲናገሩ ''ወተሐፅነ በሠናይ ተሐፅኖ፤ በመልካም አስተዳድግ አደጉ በማለት ዜና ልኅቀቱን በተዋበ ቋንቋ ገልጸውታል፡፡

የትምህርት ዘመኑ፦

አትናስያ ልጇ ቅዱስ ዮሐንስን በመልካም አስተዳድግ አሳድጋዋለች ተብላ እንድትመስገን ከሚያደርጋት ነገር አንዱ ልጇ የሕፃንነት ዘመኑን በጊዜው ከነበሩት የታወቁ ትምህርት ቤቶች ገብቶ ዘመኑ የሚጠይቀውን ዓለማዊና መንፈሳዊ ትምህርት ተምሮ እንዲያድግ ማድረጓ ነው፡፡ ሊቁ በልጅነት ዘመኑ በወቅቱ ይሰጡ የነበሩትን ሁለት ታላላቅ ትምህርቶች ከሁለት ታላላቅ መምህራን ተምሯል፡፡ ይኸውም የፍልስፍና ትምህርትና የንግግር ክህሎት ነው፡፡ የፍልስፍና መምህሩ አንድሮጋቶስ ሲባል የንግግር ክህሎት መምህሩ ደግሞ ሊባንዮስ ይባላል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትምህርት ቤት ቆይታው የታወቀ ጎበዝ ተማሪም ነበር። ለጉብዝናውም የመምህሩ ምስክርነት ተጠቃሽ ነው፡፡ የንግግር ክህሎት መምህሩ ሊባንዮስ “ከአንተ በኋላ በአንተ ወንበር ማን ቢተካ ትፈልጋለህ?'' ተብሎ በተጠየቀ ጊዜ “ክርስቲያኖች ከእኛ ሰርቀው ባይወስዱብን ኑሮ የሚተካኝ ዮሐንስ ነበር” በማለት የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የዕውቀት ከፍታ በመምህርነት አንደበቱ እንደመሰከረለት ታሪኩን የሰነዱ መምህራን ያስረዳሉ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በትምህርት ቤት ቆይታው ጊዜ ከነበሩት የቅርብ ጋደኞቹ መካከል ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ አንዱ ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ ከጓደኞቹ ሁሉ የተለየ ተወዳጅ ጓደኛው እንደ ነበር “ብዙ ቀና ልብ ያላቸውና እውነተኛ፣ የወዳጅነትን ሥርዓት የሚያውቁና ይህንንም በታማኝነት የሚያከብሩ ወዳጆች ነበሩኝ፡፡ ከእነዚህ ሁሉ በላይ ግን ከእኔ ጋር በነበረው ግንኙነት የሚበልጠው አንዱ (ባስልዮስ) ነበር። እነዚህ ወዳጆች ከሌላው ሰው ይልቅ ወዳጅነታቸው ከፍ ያለ እንደ ነበር ሁሉ እርሱም ከእነዚህ ወዳጆቼ መካከል ወዳጅነቱ እጅግ የላቀ ነበር፡ '' በማለት ይገልጸዋል፡፡

የእነዚህ የሁለቱ ሊቃውንት በአንድ ትምህርት ቤት በተመሳሳይ ፍላጎት ተመሳሳይ ትምህርት ተምረው ማደጋቸው በኋላ ለኖሩት ተመሳሳይ የሆነ የቅድስና ሕይወት መሠረት እንደ ነበረ አያጠራጥርም።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከትምህርት ቆይታው በኋላ ምን ዐይነት ሕይወት መኖር እንዳለበትም የወሰነው በትምህርት ቤት ቆይታው ከቅዱስ ባስልዮስ ጋር በጓደኝነት በቆየበት ጊዜ ነበር፡፡ ይህንንም ራሱ ሊቁ በእንተ ክህነት በሚል ርእስ ባዘጋጀው ሥራና ገብረ እግዚአብሔር ኪደ በተረጎመው መጽሐፍ ውስጥ “በምንማረው ትምህርት ብቻ ሳይሆን ትምህርታችንን ጨርሰን ከዚያ በኋላ ምን ዓይነት ሕይወት ሊኖረን እንደሚገባ ስንወስንም ውሳኔያችንና አሳባችን ተመሳሳይ ነበበማለት ገልጾታል፡፡

ቅድመ ምንኵስና በጥብቅና ሙያ
ይቀጥላል......

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

25 Nov, 18:28


"ዘኢያደሉ" ተለቀቀ

እንኳን ለመምህረ ዓለም፣ ለአፈ በረከት፣ አፈ መአዛ፣ አፈ ጳዝዮን፣ አፈ መዓር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፍልሰተ አጽም በሰላም አደረሰዎ ቅዱሱን ከወደዱት 5 ደቂቃ ብቻ ስጡን፤ ሙሉ ገቢው በጦርነት ምክንያት ጣራው ሳይቀር ፈርሶ በችግር ላይ ላለው በራያ ቆቦ ወረዳ የኤፍራታ (የአረቋቴ) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድነት ገዳም የሆነውን ዝማሬ ETart media ላይ በመስማት ይደግፉ

https://youtu.be/MBKSklYDrmk?si=EltgbSJvHVCm09cW

ለብቻዎ ሳይሆን ሌሎች እንዲያዳምጡ ቢያንስ ይሄን መልእክት ለ10 ሰው ያጋሩልን

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

25 Nov, 04:01


"ብዙዎች ቢጾሙም ለእነርሱ መጾም ማለት የጾም ምግብ መብላት ማለት ነው። እነርሱ በጾም ወቅት ለራሳቸው የሚበሏቸውን በጣም ጣፋጭና ገንቢ ምግቦችን ያዘጋጃሉ አልፎ ተርፎም ውድና የማይገኙ ቅመማ ቅመም ይጨምሩባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የጾም ቅቤ፤ የጾም አይብ፤ የጾም ቸኮላታ እንዲያገኙ ይጠይቃሉ። በአጠቃላይ የጾም ምግቦቻችን ብዛትና ዓይነት ከልክ እጅግ ያለፈ ነው።

በዚህም ነብዩ ዳንኤል ስለ ጾም የተናገረውን ይዘነጉታል። "በዚያ ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። ማለፊያ እንጀራ አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱንም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።" (ዳን 10፥2-3) በዚህ አባባሉ ውስጥ "ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም" የሚለው ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ። አንድ ሰው በጾም ወራት በየዕለቱ ጥሩ ጥሩ ምግቦች እየበላና የሚናፍቀውን ምግብ ለሰውነቱ እየሰጠ የሥጋውን ፈቃድ እንዴት ሊቆጣጠር ይችላል? አይችልም።

መንፈሳዊው ሰው የጾም ትክክለኛ ፍቺ ሥጋን በማዋረድ የምግብን ፋላጎት ድል ለማድረግ ካበቃ በኋላ ከቁሳዊው ዓለም በላይ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ያውቃል ። በመሆኑም የጾም ምግቦችን መብላት ብቻ መሆን የለበትም እርሱ በሚጾምበት ጊዜ ግድ የሚለው መታቀብ ነው ። ይህም ማለት የሚመገበው ሙሉ ለሙሉ የጾም ምግብ ቢሆንም ሥጋው ሊያገኛቸው የሚናፍቃቸውን ነገሮች በሙሉ መከልከል ማለት ነው ።

ብዙ ሰዎች የሚጾሙት በልምድ ወይም በፊደል ስለሆነ ምንም የሚጠቀሙት ነገር የለም ። እነዚህ ሰዎች ጾምን መለኮታዊ ዓላማውን በመገንዘብ ስለማይጀምሩት ወደ ጾም መንፈሳዊነት ወይም ስለ ትእዛዙ መንፈሳዊነት ሊገቡ አይችሉም። በመሆኑም ሰውነታቸው ይጹም እንጂ መንፈሳቸው አይጾምም።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

24 Nov, 17:14


https://youtu.be/ON2cw58OdqA?si=o24mco0YxBqKfdxO

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

23 Nov, 13:46


#ጾመ_ነቢያት

እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡ ትንቢቱ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ኾኖ ዓለምን የሚያድንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መኾን ፍጻሜ አግኝቷል፡፡

ይህን ምሥጢር በማሰብ በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋይዜማ ድረስ እንድንጾም አባቶቻችን መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርተውልናል፡፡ ይህ ጾም፣ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲኾን፣ በስያሜም #ጾመ_ነቢያት (የነቢያት ጾም) እየተባለ ይጠራል፡፡ ወቅቱ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ የተፈጸመበት ስለ ኾነም #ጾመ_አዳም (የአዳም ጾም) ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም #ጾመ_ስብከት (የስብከት ጾም) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ #ጾመ_ልደት (የልደት ጾም) በመባል ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም #ጾመ_ሐዋርያት እየተባለ ይጠራል፤ ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት "በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?" በማለት ነቢያት በጾሙበት ማለት ከልደተ ክርስቶስ በፊት ባለው ወቅት ጾመዋልና፡፡

በሌላ አጠራር ይኸው ጾመ ነቢያት #ጾመ_ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም) በመባል ይታወቃል፤ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያ እና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ተሰወረባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በዓት ዘግተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ቢለምኑት ልመናቸውን ተቀብሎ ሱባዔ በያዙ በ፫ኛው ቀን የቅዱስ ፊልጶስን ሥጋ (በድን) መልሶላቸው በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት 'ጾመ ፊልጶስ' እየተባለ ይጠራል፡፡

ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካበሠራት በኋላ "ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?" በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ እመቤታችን ጾማዋለችና ይህ ጾም #ጾመ_ማርያም በመባልም ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ በጾመ ነቢያት፣ ነቢያትም ሐዋርያትም፣ ቀደምት አባቶቻችንም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባናል፡፡

      ጾሙን ጾመ ሥርየት፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግል!

ምንጭ፡–
#ዲያቆን_ኤፍሬም_የኔሰው -ማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ
ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

23 Nov, 09:17


"ዘኢያደሉ"
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አዲስ መዝሙር
በማኅበረ ፍኖተ አፈወርቅ የተዘጋጀ
በኢቲ አርት ሚዲያ (ETart)
ማክሰኞ ኅዳር 17/2017 ዓም ይለቀቃል።

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

23 Nov, 06:00


ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
ነገ ኅዳር 15/2017 ዓ.ም
(Nov 24/2024 G.C) ይገባል፡፡

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

22 Nov, 18:04


🟣ፊላታዎስ ሚዲያ🟣

⛪️የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ስረዓቱን እና ደምቡን ጠብቀው የተዘጋጁ ዝማሬዎች እንዲሁም የተለያዩ ትምህርቶችን መንፈሳዊ የቅዱሳን አባቶች ታሪኮችን የሚያገኙበት ፊላታዎስ ሚዲያ
በዚህ ሚዲያ እግዚአብሔር በረዳን መጠን
👉 የተለያዩ የአውደምህረት ስብከት ዝማሬ
👉  አዳዲስ ዝማሬ የሚያገኙበት
👉 የቅዱሳን አባቶች ታሪክ የሚያገኙበት ሚዲያ ነው‼️

የተዋህዶ ልጆች  ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ አገልግሎቱንም ያበረታቱ
              👇🏽👇🏽
https://youtu.be/qE-CX-_SDY4

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

20 Nov, 14:58


https://www.youtube.com/live/cmU6yLCPvvk?si=uyd4iLUGnaXKbbPf

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

20 Nov, 07:48


ወዳጆች ሆይ! ማፈር የሚገባን ኃጢአት ስንሠራ እንጂ ንስሐ ስንገባ አይደለም፡፡ ኃጢአት ሕመም ነው፤ ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው፡፡ ከኃጢአት ቀጥሎ ሐፍረት አለ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

20 Nov, 07:06


https://www.youtube.com/live/gb4-l-BuOss?si=eHJufqwRMgx-PKav

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

19 Nov, 19:33


"በሰው ላይ የምንመለከተው የእግዚአብሔር መልክ ነው። የእኛ ሰዓሊ ሲስለን እርሱን እንድንመስል አድርጎ ነው፡፡ የእርሱን ውበት በእኛ ውስጥ ይሰራዋል፡፡

በቀለም ፋንታ በተለያየ መንፈሳዊ በጎነት ያሳምረናል፤ የእግዚአብሔር ምስልና መልክም ከምንም ነገር ጋር ስለማይነጻጸር ሰውም ይህ እውነተኛ መልኩ በመሆኑ ከሌሎች ምድራዊ ነገሮች ጋር አይቀላቀልም፣... ተፈጥሯችንን ያስዋበ እግዚአብሔር ከተጠቀመበት ብሩሽ አንዱ #ፍቅር ነው።

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

19 Nov, 05:33


https://youtu.be/qz7rCqNsepk

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

18 Nov, 16:05


ትሕትና

ትሕትና የትንሽት ምልክት አይምሰልህ ፡፡ ታላቁ መስፍን ሙሴ ፣ ታላቁ ጌታ ክርስቶስ ትሑታን ነበሩ ፡፡ ባለጠግነት ትሕትናን ሊያሳጣህ ሲሞክር ጻድቁ አብርሃምና ጻድቁ ኢዮብ ትሑታን እንደ ነበሩ አስብ ፡፡ ሥልጣን ልብህን ከፍ ሲያደርግብህ “ለንጉሥ በቀን ላይ ቀን ትጨምራለህ” በማለት የተናገረውን ዳዊትን አስብ ፡፡ ምንም ብትነግሥ ለራስህ አንድ ቀን መስጠት አትችልምና ፡፡ ደግሞም “ሁሉም ከንቱ” ያለውን ሽቅርቅሩን ንጉሥ ሰሎሞንን ፣ ጠቢቡን ንጉሥ ይዲድያ የተባለውን በማሰብ አለባበስንና እውቀትን ናቀው ፡፡ ጉልበትህ ሊያስታብይህ ሲሻ ሶምሶምን አስብ ፡፡ ኃይልህ ከኃያላን ፣ ሥልጣንህ ከሠለጠኑት ፣ እውቀትን ካወቁት ጋር ቢነጻጸር በጣም ትንሽ ነው ፡፡ በምድራዊ ነገር ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ጸጋም ልትመካ አይገባህም ፡፡ ትምክሕት እጄ ሀብትን ፣ ጽድቄ ጸጋን አመጣልኝ ማለት በመሆኑ ቁጥሩ ከክህደት ነው ፡፡ በጸጋ ሳይሆን በባለጠጋው መመካት ግን ተፈቅዷል ፡፡ ኃጢአትህ እየበዛ ሲመጣ የሌሎች ስህተት እየታየህ ይመጣል ፡፡ ጽድቅ በውስጥህ እየተስፋፋ ሲመጣ የራስህ ደካማነት ይታይሃል ፡፡

ትሕትና በአደባባይ እንደ ለበስከው ነጭ ሸማ ነው ፡፡ ታጌጥበታለህ ፡፡ ትዕቢት ግን ያዋርድሃል ፣ የማያውቅህ ሳይቀር አይቶ ይጸየፍሃል ፡፡ ቁመተ ረጅሞች ሲኮሩ ሰማይን የምታይ ይመስልሃል ፡፡ አጭሮች ሲልመጠመጡ መቃብር የገቡ ይመስላል፡፡ የረጅምነት ውበቱ ዝቅ ማለት ነው ፡፡ ትዕቢተኛ ስትሆን ሰዎች እንከን እንዲፈልጉብህ መንገድ ትከፍታለህ ፡፡ ትሕትና ራስን የማወቅ ውጤት ነው ፡፡ ራሱን በትክክል የሚያውቅ ሊታበይና በሌሎች ሊፈርድ በፍጹም አይችሉም ፡፡ ትሕትና የሌሎችን ክብር ማወቅ ነው ፡፡ ማክበር መከበር ነውና ሌሎችን ስናከብር ትሕትና ታስከብረናለች ፡፡ ትሕትና ሁልጊዜ እንደሚማሩ ሁኖ መኖር ነው ፡፡ ትሕትና በጠፋበት ዘመን ሁሉም ሰው አስተማሪ ይሆናል ፡፡ ሁሉም ሰው ቅዱስ ነኝ በማለት ሌሎችን ያጣጥላል ፡፡ ጆሮ ጠፍቶ አፍ ብቻ የበዛበት ዘመን ዘመነ ትዕቢት ነው ፡፡ እገሌ ክፉ ነው ማለት በተዘዋዋሪ እኔ መልካም ነኝ ማለት ነውና ትዕቢት ነው ፡፡ ትሕትና የሰዎችን ትልቅ ድካም አሳንሶ ፣ ትንሽ ብርታታቸውን አጉልቶ ያሳያል ፡፡ ትሕትና እንዳልኖሩ ሁኖ ከሌሎች ልምድን መቅሰም ነው ፡፡

ከፍ ላሉት ዝቅ ማለት ትሕትና አይደለም ፡፡ ከፍ ያሉትማ ግርማቸው በግድ ያሰግዳል ፡፡ ትሕትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው ፡፡ ለእግረኛ ቅድሚያ ስትሰጥ አንድ ነገር አስብ ፡- “መኪና ለሰው እንጂ ሰው ለመኪና አልተፈጠረም፡፡” እውነተኛ ትሕትና ለሚያንሱን መታዘዝ ነው ፡፡ ሰው እንደዚህ ሁኖ እንደማይቀር ብናስብ ስንት ሕጻናትን ስንት ድሆችን ባከበርን ነበር ፡፡ ትሕትና የልብ መሰበር ያመጣልና ለዝማሬና ለንስሐ ያበቃል ፡፡ አበባ ካልታሸ አይሸትም ፣ ፍራፍሬ ካልተጨመቀ አይጠጣም ፡፡ ሰውም ትሑት ካልሆነ መልኩ አይወጣም ፡፡ ትሕትና ያወቁትን ያለ ትችት ማስተማር እንጂ አላውቅም ማለት አይደለም ፡፡ እያወቁ አላውቅም ማለት ልግመት ፣ ሳያውቁ አውቃለሁ ማለት ራስን አለማወቅ ነው ፡፡ ያወቁትን በትጋት ማስተላለፍ ትሕትና ነው ፡፡ የተማርከው ሌሎችን ደንቆሮ ብሎ ለመሳደብ ሳይሆን በጨለማ ላሉት ብርሃን ለማወጅ ነው ፡፡ የጋን ውስጥ መብራት ከመሆን የሚያድነው ትሕትና ነውና ስታውቅ ትሑት ሁን ፡፡ ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ፡፡ ቀና የሚሉት ዛፎች ግን ፍሬ የሌላቸው ናቸው ፡፡ በእውነት ካወቅህ ያላወቅከው ስለሚበዛብህ ትሑት ትሆናለህ ፡፡ በአንድ ጥቅስ ጫካ የሚገቡ የአቡጊዳ ሽፍቶች ግን ትዕቢተኞች ናቸው ፡፡ “ድምፅና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል” ይባላል ፡፡ ቁንጫም እንደ ልቡ ይዘላል ፣ ባዶ አዳራሽም ድምፅን ያስተጋባል ፡፡ ጩኸት ማብዛት የባዶ ቤት ምልክት ነው ፡፡ ባዶ ሰው ከቀድሞ የከፉ የሰባት ኣጋንንት ማደሪያ ይሆናልና እባክህ ባዶ አትሁን ፡፡

ትሕትና የልብ ነው ፡፡ የልብ ያልሆነ ትሕትና የአንገት መሰበር ፣ የጉልበት መሸብረክ ብቻ ነው ፡፡ በልብ እየናቁ በአፍ ማክበር እርሱ ትሕትና ማጣት ነው ፡፡ ይልቁንም ትልቁን መንግሥት ፣ መንግሥተ ሥላሴን እየሰበክህ ትሑት ልትሆን ይገባሃል ፡፡ ትልቁን ትሕትና ነገረ ሥጋዌን እየተናገርህ ትሑት መሆን ያስፈልግሃል ፡፡ ተዋሕዶ ማለት ትሕትና ማለት ነው ፡፡ ባለጠጋው መለኮት ከድሃው ሥጋ ጋር የተዋሐደበት ማለት ነው ፡፡ የሥጋ ድህነት ለመለኮት ፣ የመለኮት ብልጥግና ለሥጋ እንዲነገር የፈቀደው ትልቁ የትሕትና ትምህርት ቤት ምሥጢረ ሥጋዌ ነው ፡፡ ምስኪኖችና ጦም አዳሪዎችን ፣ ኃጢአተኞችንና መንገድ የጠፋባቸውን ካላዘንክላቸው በተዋሕዶ አታምንም ማለት ነው ፡፡ የተዋሕዶ ምሥጢር ሲገባህ በቀራጮችና በኃጢአተኞች አታፍርም ፡፡ የወደቀውን ለማንሣት ዝቅ ትላለህ ፣ ወደ ሐኪም ቤት ለማድረስ አህያህን እንደ ደጉ ሳምራዊ ለቀህ እግረኛ ትሆናለህ ፡፡

የስድብ አምሮትህን ለመወጣት “ውሾች” ይላል ቃሉ ፣ የነቀፋ ጥማትህን “ተኩላ” ይላል ወንጌሉ እያልህ ከተወጣኸው ኃጢአትና በቅዱሱ ነገር መበደልህ ነው ፡፡ ውሻ ፣ ተኩላ ያለው ጠባያቸውን ለመግለጥ እንጂ ላንተ ስድብ ለማበደር አይደለም ፡፡ ትሕትና ተፈትኜ አልጨረስኩም ብሎ በራሱ በጣም አይመካም ፡፡ ገና በፈተና ዓለም ያሉ ሰዎችንም በጣም አያመሰግንም ፡፡ እባክህ ወዳጄ ትሑት ሁን ፡፡ የበላይ የበታች ሁሉም ልቡ ጎረምሳ ሁኗልና የሚያስተነፍስ መዓት ሳይመጣ ትሕትናን ገንዘብ እናድርግ ፡፡ ትሕትናን በማጣት ያሳዘንከውን እግዚአብሔር በብዙ ትሩፋት አታስደስተውም ፡፡ ትሕትና የእምነት መጀመሪያ ነውና ፡፡

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

17 Nov, 18:25


መልእክት ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን በያላችሁበት ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

አሐቲ ድንግል ከታተመችበት ጊዜ ጀምሮ መጽሐፉን ለማግኘት በምታደርጉት ርብርብ ለእመቤታችን ያላችሁን ፍቅርና ለኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ያላችሁን ቅናት አሳይታችኁናል። በመሆኑም መጽሐፉ በተፈለገው ቁጥር መጠን መድረስ ባለመቻሉ አንዳንድ ሰዎች ከዋጋው በላይ እንደሚሸጡት ከወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ጥቆማ ደርሶናል። በመሆኑም መጽሐፉ እየታተመ ስለሆነ ከዋጋው በላይ በመግዛት እንዳትጎዱ ለመጠቆም እንወዳለን።

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

16 Nov, 04:11


"ዲያብሎስ በእናንተ ላይ እጅግ ክፉ ነገርን በማምጣት አሳዝኖአችኋልን? እናንተም ኢዮብን አብነት አድርጋችሁ እግዚአብሔር ይመስገን በማለት አሳዝኑት፡፡ ዲያብሎስን ድል ማድረግ ስትሹ ይህን መሣርያ ዘወትር ያዙ፤ ምስጋና፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

15 Nov, 14:43


ለክብርሽ ተደርሶ፥ ለፍቅር የተቆመ፤
ሥሙር ማኅሌትሽ፥ በቸር ተፈጸመ፤
ድንግል እመቤቴ፦
የኛ መከራ ግን፥ አለቅጥ ረዘመ!

እንኳን አደረሰን!

( Deacon Yordanos Abebe)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

15 Nov, 10:55


" ናሁ ሃገረኪ"
ድንቅ ያሬዳዊ ወረብ በፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት መዘምራን
https://youtube.com/watch?v=wCvcwvB7fA0&feature=shared

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

15 Nov, 05:33


#ኅዳር_6
#ደብረ_ቁስቋም

ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡

አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡

ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡

ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡

እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡

ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ።

( ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

14 Nov, 06:27


የፍቅር ሥራ ይህች ናት

ባልንጀራውን የሚረዳውን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ይረዳዋል፡፡ ለወንድሙ የሚነቀፍበትን ስም የሚያወጣውን ፈታሒ በርትዕ እግዚአብሔር እንዲሰደብ ያደርገዋል፡፡ ክፉ ስለ ሠራ ወንድሙን በቤቱ ለብቻው ሆኖ የሚመክረው ሰው ግን በምክሩ ዐዋቂ ይሆናል፡፡ ወንድሙን በዐደባባይ የነቀፈ ግን ኀዘን ያጸናበታል፡፡ ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡ 

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች፡፡ ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡ በጎ ነገር ያደርግልኛል ብሎ በጎ የሚሠራ ኋላ ፈጥኖ ይተዋል፡፡

(ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ - በዲ/ን ሞገስ)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

13 Nov, 16:57


ነገ ለአንተ የተሸለ ነው

ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል፡፡

ቅዱሳን ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና።

ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ: ለራስህ 'ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል' ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!!

(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

13 Nov, 15:05


አርዮስፋጎስ

ይህ የቴሌግራም ቻናል በወልድያ ደብረ ሲና ተክለሃይማኖት ቤ/ያን የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህርና የሀገረስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ሃላፊ የሆኑት የመጋቤ ሐዲስ ኤርምያስ አዳነ ነው።
➛ አርዮስፋጎስ ማለት ፦ግሪካዊ ቃል ሲሆን ለሕዝብ ይፋ የሆነ የምርምር አደባባይ ማለት ነው።
➛ ቻናሉ በመንፈሳዊ ምርምር እንጅ በሥጋዊ ምርምር ልንረዳቸው የማንችል ጥልቅ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች፣
➛ ስብከቶች እና ጽሑፎች የሚለቀቁበት እንዲሁም
➛ ሌሎች ተከታታይ ትምህርቶችን የሚያስተምሩበት የቴሌግራም ቻናል ነውና ይቀላቀሉ ሌሎችንም ይጋብዙ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

https://t.me/Ariosfagos1271

https://t.me/Ariosfagos1271

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

12 Nov, 04:27


ሰላም የቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቤተሰቦች የኤፍራታ (የአረቋቴ) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድነት ገዳምን እንታደግ

ክርስቶስ በከበረ ደሙ የተቤዣችሁ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተወለዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ልጆቻችን በቅድሚያ ቸርነቱ የማያልቅበት የልዑል እግዚአብሔር ሰላም በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡

እኛ በኢትዮጵያ ኦቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በራያ ቆቦ ወረዳ የኤፍራታ (የአረቋቱ) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድነት ገዳም የምንገኝ ማኅበረ መነኮሳት መድኃኔ ዓለም ይክበር ይመስገን በጣም ደህና ነን፡፡

ይህንን መልእክት የምትመለከቱ የቤተ ክርስቲያኗ የቁርጥ ቀን ልጆች ሁሉችሁ ገዳማችሁን ታደጉት

ይህ ገዳም ከላይ እንደተገለጸው በራያ ቆቦ ወረዳ ዞብል ተራራ ሥር ያለ ገዳም ነው ቦታው ከመጀመሪያውም ብዙ የሚያውቀው ሰው ስለሌለ ማኅበረ መነኮሳቱ በብዙ ችግር የምናሳልፍ እንዲሁም በራሳችን ልማት አገዝ እና በአንዳድ ማኅበራት የቤተ ክርስቲያን ልጆች እርዳታ የምንኖር ሲሆን ኮረና አገባ እና በተለይም ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም.ጀምሮ እስከ አሁን እያሳለፍነው ያለው የሕይወት ውጣ ውረድ በጣም ክባድ ነው እየደረሰብን ካለው ከባድ መከራ ይልቅ እየደረሰልን ያለው የእግዚአብሔር የፍቅር እርዳታ ታላቅ ነው። የቅዱስ ቂርቆስ እና የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምላክ ስሙ ይመስገን፡፡

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ልጆቻችን ይህ ኮረና ከገባ ጀምሮ በከባድ ችግር እያሳለፈ ያለገዳም እሁንም ገና በችግር ውስጥ ስለሆነ የገዳሙ ችግርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ስለመጣ፦

1ኛ ከ24 ሰዓት አንድ ጊዜ የሚቀመስ በመጥፋቱ
2ኛ የሚለበስ ልብስ አለመኖር
3ኛ የቤተ ክርስቲያኑ ኮርኒስ ወድቆ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መስተጓጎል ገጥሞን ተቸግረናል።

በሁሉም ዓለም የምትገኙ ልጆቻችን በምትችሉት ሁሉ የመናንያን መነኮሳትን በገዳም መጽናት ለሚወዱ በመንገር የእናንተ ያልሆነውን የእግዚአብሔር የሆነውን አሥራታችሁን በመሰብሰብ በገዳሙ አካውንት በኩል ገዳማችሁ ትታደጉት ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ልጅነታችሁ ስም በትህትና እንጠይቃችኋለን።

ለምታደርጉልን ሁሉ የእግዚአብሔር ቸርነት፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የእናትነት ፍቅር፤ የቅዱስ ቂርቆስ እና የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቃል ኪዳን የእናታችን ቅድስት ኢየሉጣ በረከት፤ የአበው ጸሎት አይለያችሁ አሜን! ሕይወታችሁን ይባርክ ቤተሰቦቻችሁን ይጠብቅ፡፡

“በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን"አሜን።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ለአረቋቴ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ቂርቆስ አንድነት ገዳም
1000037590766

ብር ማስገባት አቅም የሌለን ሼር በማድረግ ከበረከት እንሳተፍ!!

(በቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቻናል አባላት የገባውን ለማወቅና ለማሳወቅ ያስገባችሁበትን በውስጥ መስመር @natansolo ይላኩልን)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

11 Nov, 15:31


አርዮስፋጎስ

ይህ የቴሌግራም ቻናል በወልድያ ደብረ ሲና ተክለሃይማኖት ቤ/ያን የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህርና የሀገረስብከቱ ስብከተ ወንጌል ክፍል ሃላፊ የሆኑት የመጋቤ ሐዲስ ኤርምያስ አዳነ ነው።
➛ አርዮስፋጎስ ማለት ፦ግሪካዊ ቃል ሲሆን ለሕዝብ ይፋ የሆነ የምርምር አደባባይ ማለት ነው።
➛ ቻናሉ በመንፈሳዊ ምርምር እንጅ በሥጋዊ ምርምር ልንረዳቸው የማንችል ጥልቅ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች፣
➛ ስብከቶች እና ጽሑፎች የሚለቀቁበት እንዲሁም
➛ ሌሎች ተከታታይ ትምህርቶችን የሚያስተምሩበት የቴሌግራም ቻናል ነውና ይቀላቀሉ ሌሎችንም ይጋብዙ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

https://t.me/Ariosfagos1271

https://t.me/Ariosfagos1271

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

08 Nov, 11:46


የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ አቡነ ሚናስ ማኅበር የገዳሙን ማኅተም አስመስሎ በማሠራት ገንዘብ የሚቀበሉ ሰዎች መኖራቸውን ገለጸ፡፡

የገዳሙ አበምኔት መምህር ቆሞስ አባ ተስፋ ማርያም የገዳሙ መነኮሳት ነን የሚሉት የውሸት ማኅተም በማሠራት፣ ያለ ማኅበሩ እውቅና ተወክለናል በሚል ከምእመናን ገንዘብ እየተቀበሉ ነው ሲሉ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

የገዳሙ ጸሎተ ምሕላ አሳራጊ አባ ገብረ ሥላሴ ተበጀ በበኩላቸው የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ አቡነ ሚናስ ማኅበር ለሦስት ጊዜያት ጠፍቶ እንደገና በእግዚአብሔር ፍቃድና በአባቶቻችን ጽናት ተመልሶ የቀና ገዳም ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከ40 ያላነሱ ዝጉኃን ባሕታውያንና ከ80 በላይ አረጋውያን የሚጦሩበት ለጊዜው በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው ይህ ገዳም ባለፉት ጊዜያት በርካታ ፈተናዎችን ያስተናገደ ገዳም ነው ያሉት ደግሞ የገዳሙ ረእድ አባ ኃይለ መስቀል ወልደ ሳሙኤል ናቸው፡፡

ገዳሙ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከሀገረ ስብከት አስተዳደር ውጭ እንደነበር የጠቀሱት አባ ኃይለ መስቀል ወልደ ሳሙኤል በገዳሙ ስም ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰዎችን ለማስቆምና ለባለድርሻ አካላት ለማሳወቅ ተግዳሮት እንደሆነባቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም አቅመ ደካማ አረጋውያን ከሱባኤ ሲወጡ እንጀራ የሚቀምሱበት ማይለበጣ የሚባለው የገዳሙ ክፍል ባሳለፍነው ዓመት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ገደሉ ተንዶ ከስድስት በላይ የደካሞች መኖርያ ቤት መፍረሱ የተገለጸ ሲሆን የፈረሱትን ቤቶች መልሶ ለማሠራት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚየስፈልግ እና የተናደዉን ገደል ተፋሰሱን ለማስቀየር ከፍተኛ ወጭ ስለሚጠይቅ ገዳማውያኑን በፈተና ውስጥ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም የሚባሉ ራሳቸውን የዋልድባ ገዳም ተወካይ አድርገው በተለያዩ ሚዲያዎች ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉና በተለይም በውጭው ዓለም ከምእመናን ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰው መሆናቸውን በመረዳት ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የገዳሙን ትክክለኛ ማኅተም በማረጋገጥና የገዳሙን አካውንት ብቻ እንዲጠቀሙ አበምኔቱ አሳስበዋል፡፡

አሁን ላይም ይህንን እና ሌሎች ጉዳዮችን ለመፍታት እንዲሁም መነኮሳት ነን በማለት የገዳሙን ገንዘብ ያለአግባብ የሚጠቀሙትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ሂደት መጀመሩን አባቶች ተናግረዋል፡፡

የገዳሙ አካውንት፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000018796779- ጎንደር ዐቢይ ቅርንጫፍ
1000064118742- አዲአርቃይ ቅርንጫፍ

ምንጭ፦ ከማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

08 Nov, 07:14


ልጆቼ! በድህነቴ ላይ ቸርነትን አድርጉልኝ፡፡ በዚህስ አልችልም ካላችሁ እሺ በቁስሌ ላይ ዘይትን አፍስሱልኝ፡፡ አሁንም ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወደ እኔ ጠጋ በሉና አናግሩኝ፡፡ እናንተን ማየት፣ ከእናንተ ጋር መጨዋወት ይናፍቀኛልና፡፡

በገዛ ደሜ የገዛኋችሁ ልጆቼ! ከባድ ነገር እኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እኔ የምፈልገው ትንሽ ዳቦ፣ ጊዜአዊ ማደርያ፣ እንዲሁም የሚያጽናኑ ቃላትን ብቻ ነው፡፡ “ይህ ሁሉ ማድረጌ ምን ይጠቅመኛል?” ካላችሁ ስለ ምሰጣችሁን ርስት መንግሥተ ሰማያት ብላችሁ አድርጉት፡፡ አሁንም ልባችሁ አልተነካምን? ስለ መንግሥተ ሰማያት አታድርጉት፤ ግን ደግሞ ስለ ሰብአዊ ርኅራኄ ይህን አድርጉልኝ፡፡ የእኔን መራቆት የሚያሳዝናችሁ በቀራንዮ አደባባይ ስለ እናንተ ብዬ የተራቆትኩት ብቻ ነውን? ታድያ አሁንም ‘ኮ በደጃችሁ ላይ ተጥዬ ዕራቆቴን ነኝ፡፡ ለምን አላዘናችሁልኝም? የታሰርኩት በቀራንዮ ብቻ ነውን? አይደለም፡፡ ታድያ እንደምን አታዝኑልኝም?

የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ሳለሁ “ተጠማሁ” እንዳልኩ ዛሬስ ስለ እናንተ ብዬ ደጋግሜ ይህን ቃል አልተናገርኩምን? ጕሮሮዬ ደርቆ ስለምን ትንሽ እንኳ አላሳዝናችሁም? ስለምንስ ይህ ሁሉ ፍቅር ስለ እናንተ መሆኑን ትዘነጉብኛላችሁ? የምለምናችሁ እናንተን ባለጸጋ ለማድረግ አይደለምን? ይህችን ትንሽ ቸርነት ስላደረጋችሁልኝ በዐይን ያልታየች፣ በጀሮ ያልተሰማች፣ በሰውም አእምሮ ያልታሰበች ርስት መንግሥተ ሰማያት እንድታገኙ ብዬ አይደለምን? ስለ እናንተ ብዬ ደሀ የሆንኩት ያኔ በመዋዕለ ሥጋዌዬ ብቻ እንደሆነ አታስቡ ልጆቼ! ዛሬም ቢሆን በደጃችሁ የተጣልኩት ስለ እናንተ ጥቅም እንደሆነ ተረዱልኝ፡፡

ከባድ ነገር ‘ኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እስር ቤት መጥታችሁ ጠይቁኝ እንጂ አስፈቱኝ አላልኳችሁም፡፡ ታምሜ ጠይቁኝ እንጂ ፈውሱኝ አላልኳችሁም፡፡ ከጠየቃችሁኝ ብቻ በቂዬ ነው፡፡ እስኪ ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! በዚያ በአስፈሪው ቀን ስመጣ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” የሚለውን ቃለ ሕይወት መስማት አትፈልጉምን? ዛሬ የሰጣችሁኝ ሁሉ የምረሳ ይመስላችኋልን? ያኔ በክብር ስመጣ ከእልፍ ወለዱ ጋር እንድሰጣችሁ አትሹምን? የማፈቅራችሁ ልጆቼ! ከደጃችሁ ተጥዬ የምለምናችሁ፣ ከበራችሁ ላይ ቆሜ ማደርያን የምጠይቃችሁ፣ እጄን ዘርግቼ እናንተን እናንተን የማየው ያኔ ትሉ ወደማይጠፋው እሳቱ ወደማያንቀላፋው እሳት እንዳትሄዱብኝ ብዬ ነው፡፡ ታድያ ይህን ለምን አትረዱልኝ ልጆቼ? ስለምን እንዳስቸገርኳችሁ ታስባላችሁ? ለእናንተ ጥቅም እንደሆነ እንዳትረዱ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? ከእናንተ ጋር ቁጭ ብዬ ልብላ ስላችሁ ስለምን ትገፈትሩኛለችሁ? ይህን ያህል ቸርነት አድርጌላችሁ ሳለሁስ ስለምን በግልምጫ አያችሁኝ? ይህን ያህል መውደድ ወድጃችሁ ሳለሁ ስለምን በቅጡ ልታነጋገግሩኝ አልወደዳችሁም? ከአዳም ጀምሮ ዓለም እስኪያልፍ ድረስ ያለው ሕዝብ ሁሉ በአንድ አደባባይ ላይ ቆሞ፣ እልፍ አእላፍ መላእክት በዙርያዬ ረበው “ይህ/ ይህቺ ልጅ ወዳጄ ነው/ ናት፤ በመሆኑም በታላቅ ክብርና ዕልልታ አጅባችሁ ወደ ዘለዓለም ደስታዋ አግቡት/ አግቧት” የሚለውን ፍርዴ አትናፍቁምን?

ልጆቼ! እኔን ላለማየት ስለምን ፊታችሁን ትሸፍናላችሁ? ስለምን፡ታፍራላችሁ? እኔ ሳላፍርባችሁ ስለምን እናንተ አፈራችሁ?

ልጆቼ! ልባችሁ እንደተነካ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ስሜት ብቻ አይሁን፡፡ ከንፈራችሁን ብቻ አትምጠጡብኝ፡፡ ከእናንተ የምፈልገው አንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ ከላይ የጠየቅኳችሁን ነገሮች ወደ ተግባር ቀይሯቸው፡፡ ለማይጠቅማችሁ ነገር አብዝታችሁ እየሮጣችሁ ለሚጠቅማችሁ ነገር አትስነፉ፡፡ “እኔኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፤ ይህን እንደምን እችላለሁ?” አትበሉኝ፡፡ አውቃለሁ! ነገር ግን ፈቃዳችሁን ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ራሴ አደርግላችኋለሁ፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብዬ.ያስተማርኳችሁን ቃል ረሳችሁትን? /ዮሐ.15፡5/፡፡ እንግዲያውስ ከእናንተ የምፈልገው ፈቃዳችሁን ነው፡፡ አሁን ካላችሁበት ቦታ ተንቀሳቅሳችሁ ወጣ ስትሉ ታገኙኛላችሁ፡፡ አናግሩኝ! አፍቃሪያችሁ መድኃኔዓለም ነኝ፡፡

መቅረዝ ዘተዋሕዶ ብሎግ የተወሰደ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

07 Nov, 16:51


💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel


👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyjDUcNXW

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

07 Nov, 04:36


የ፮ እሁድ ማኅሌተ ጽጌ በሊቀ መዘምራን ተስፋ ጽዮን

https://youtu.be/7NvahZyM3pU?si=gJwwP02gLIy6aLhG&sfnsn=mo

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

06 Nov, 03:43


"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

05 Nov, 18:36


በጥቂቱ መታመን

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ!.." ማቴ 25፥21፡፡ ይህም ማለት በምድራዊ ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ በሰማያዊ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ማለት ነው፡፡ በዚኛው ዓለም ታማኝ ሆነ ከቆየህ በዘለዓለማዊነት ውስጥ እሾምሃለው ማለት ነው፡፡ ይህ መመሪያ በብዙ መስኮች ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል... ዘመዶችህን በመውደድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ጠላቶችህንም በመውደድ ላይ ይሾምሃል፡፡ ጠላትህን የምትወድበት ጸጋ ያድልሃል ማለት ነው፡፡

በትርፍ ጊዜዎችህ እግዚአብሔርን የምታገለግል ከሆንህ በሕይወትህ ጊዜ ሙሉ በእርሱ ላይ ትኩረት የምታደርግበትን ፍቅር ያድልሃል፡፡ የፈቃድ ኃጢአቶችን ከአንተ በማስወገድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ያለ ፈቃድ ከሚመጡ ኃጢአቶች ነጻ ያወጣሃል፡፡

ንቁ ኅሊናህን ከክፉ አሳቦች የምትጠብቅ ከሆንህ እግዚአብሔር ንቁ ያልሆነው ኅሊናህን ንጽሕና ያድልሃል፤ ከዚህ በተጨማሪ የህልሞችህን ንጽሕናም ያድልሃል፡፡ ልጅ እያለህ ታማኝ ከሆንህ እግዚአብሔር ውጊያዎች በሚበዙበት በወጣትነትህ ዘመን ውስጥም ታማኝነትን ያድልሃል ሌሎች ሰዎች ላይ በቃላት ብቻ የማትፈርድባቸው ሆነህ በመገኘትህ ታማኝ ከሆንህ ይበልጥ አስቸጋሪ በሆነው በአሳብ እንዳትፈርድባቸው ያስችልሃል፡፡ ልክ እንደዚሁ ራስህን ከውጫዊ ንዴት በመጠበቅ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አውስጣዊ ቁጣ፣ንዴትና ቅናት ነጻ ያወጣሃል፡፡

በተለመዱ መንፈሳዊነቶች (በመንፈስ ፍሬዎች) ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የመንፈስ ስጦታዎችን ያድልሃል፤ በመጀመሪያው ላይ ታማኝ ሆነህ ካልተገኘህ ሁለተኛውን ፈጽመህ ልታገኘው አትችልምና፡፡

እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሚፈትሽህ በጥቂት ነገር ነው፡፡ በዚህች በጥቂቷ ነገር ላይ ታማኝ መሆንህ ካረጋገጥህ እርሱ በሚበልጠው ነገር ላይ ይሾምሃል፡፡ ውድቀትህንና አለመታመንህን በጥቂቷ ነገር ላይ ከገለጽህ ግን እግዚአብሔር በሚበልጠው ነገር ላይ አይሾምህም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና፦ "ከእረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱህ ቢደክሙህ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ?" ኤር 12፥5 ብዙ ሰዎች ዝቅተኛውን ኃላፊነት መወጣት ሳይችሉ ከፍተኛውን ኃላፊነት ለመቀበል ማሰባቸው እጅግ አስደናቂ ነገር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ ሳይጠቀሙ ተጨማሪ ጸጋ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ይህን ሲያደርጉም "በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ" የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመዘንጋት ነው፡፡

"መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅማቸው" ከሚለው #አያሌው_ዘኢየሱስ ከተረጎመው #የብጹዕ_አቡነ_ሽኖዳ መጽሐፍ የተወሰደ!!!

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

05 Nov, 12:17


ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት"

ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

04 Nov, 17:06


ሰላም ተወዳጆች በዚህ ግሩፕ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ተውህቦ ጸጋ
➛ ወቅቱን መሠረት ያደረጉ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
➛ የቅዱሳን አባቶች እና እናቶች ታሪክ
➛ የንጽጽር ትምህርቶች
➛ ከግሩፑ አባላት ለሚመጡ ማንኛውም ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትን ጨምሮ ሌሎች ተከታታይ ትምህርቶችን በማስተማር ላይ ይገኛሉና ሌሎች የዚህ የቴሌግራም ግሩፕ አባል እንዲሆኑ ይጋብዙ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

https://t.me/Tewhbotsega

https://t.me/Tewhbotsega

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

04 Nov, 12:03


#ለቸሩ_መድኃኔዓለም_ዝም_አልልም
**
                      #ሼር_ሼር_ስለ_መድኃኔዓለም 🙏
          በከፋ ሀ/ስብከት ጌሻ ወረዳ ወዲት ገጠር ቀበሌ የዮፎ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከ 1944-2017 ዓ.ም
#በፍታችን_ለሚከበረው_የጥቅምት_፳፯_ዓመታዊ_የቸሩ_መድኃኔዓለም_ክብር_በዓል_ሚክኒያት_በማድረግ_መረዳት_ባትችሉ_ሸር_አደረጉ_ስለ_መድኃኔዓለም--------
#ይህ_ቤት_ለመድኃኔዓለም_ይመጥናል_ወይ????😭😭😭😭😭😭

✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥

ይህቺም ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት  ጽላት የከበረባት፣ካህን የሚያገለግልባት፣ንግስ የሚከበርባት፣ወንጌል የሚዘራበት፣ሚስጢራት የሚፈጸሙባት በሞዛይክ እና ማርብል ከተሽቆጠቆጡ የከትማ አብያተክርስቲያናት ጋር በእኩሌታ መንፈስቅዱስ የሚሰራባት#በየዓመቱ_እንደ_ለሎቹ_አብያተክርስትያናት_ታቦት_የሚነግስባት  አማናዊ #የገጠሪቷ መቅደስ ናት ። የሰማይወምድር የነገስታቶች ንጉስ የጌቶች ጌታ፣የአምላኮች አምላክ፣ስሙም ድንቅ፣መካረ ኃያል፣ ኤልሻ ዳይ፣ አዶናዬ፣የተባለው፣ የቸሩ መድኃኔዓለም ቤተመቅደስ ናት

በአካባብ ከ30 የማይበልጥ በመከራ የተፈተነች የገጠርቷ ነፍስ ብቻ ነው ያለው።
በዚህ መሠረት በእነዚያ ጥቅት ነፍሳትና በእግዚአብሔር አጋዥነት #ከሚያዚያ 5/2013ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ሳይኖራቸው መሠረት ጥሎ ስራውን የጀመሩ ብሆኑ በማህበራዊ ሚድያ በእናንተ በደጋጎች ድጋፍ ወደ ፍኒሽንግ ደረጃ ካደረስን ቦኋላ ስራው ቁሟል😭😭😭
ስለሆነም አሁን የጎደሉ ማቴረያሎች ተሟልቶና ስራው ተጠናቅቆ በቅርቡ ቅዳሴ ቤቱ ይከበር ዘንድ ከመቸውም ግዜ በላይ የበረታ እጆቻችሁን እንድትዘረጉልን በስሙ እንወድቃለን🙏
የጎደሉ ማቴረያሎች
#ለሊሾ 50ኩ/ታ ሲሚንቶ 50*2400=120,000ብር
#ቀለም 64 ጋሎን  64*2200=136,400ብር
#መስታወት 62 ካሬ 62*2000=124,000ብር
#በር ከተሰራበት ለማስመጣትና ለመግጠም 70,000
#የውስጥ የስነ ስዕል ስራዎች የሚያስፈልጉ ነገሮች እንደ ገጠር አጥቢያ በጥቅቱ  =80,000ብር
                                      #ድምር=  530,400ብርነው

             ስለዚህ #የመድኃኔዓለም ውለታ የዋለላችሁ
                    #ስሙን ስትሰሙ ፍቅሩን የሚታስታውሱ
                    #ጥበቃውና ረዳትነቱ የተከታላችሁ
የስሙ አጋቾች እኔሆ የበረከት እጃችሁን #ከ10ብር ጀምራችሁ የሚትዘረጉበት የቤ/ያንቷ ህጋዊ ንግድ ባንክ አካውንት:_ 
                1000107255943
               ዮፎ መድኃኔዓለም ቤ/ን ህንፃ ማሰረያ....
     
       ለበለጠ መረጃ 0991122817/0917235781

ያስገባችሁትን የባንክ ስሊፕና የክርስትና ስማችሁን በውስ መስመረ አሳወቁን!

#ስለ_መድኃኔዓለም
#ስለ_ድንግልቱ_ልጅ
#ስለ_ዓለሙ_ጌታ
🤲🤲🤲🤲🤲🤲

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

03 Nov, 18:57


#ለቸሩ_መድኃኔዓለም_ዝም_አልልም
**
                      #ሼር_ሼር_ስለ_መድኃኔዓለም 🙏
          በከፋ ሀ/ስብከት ጌሻ ወረዳ ወዲት ገጠር ቀበሌ የዮፎ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከ 1944-2017 ዓ.ም
#በፍታችን_ለሚከበረው_የጥቅምት_፳፯_ዓመታዊ_የቸሩ_መድኃኔዓለም_ክብር_በዓል_ሚክኒያት_በማድረግ_መረዳት_ባትችሉ_ሸር_አደረጉ_ስለ_መድኃኔዓለም--------
#ይህ_ቤት_ለመድኃኔዓለም_ይመጥናል_ወይ????😭😭😭😭😭😭

✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥

ይህቺም ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት  ጽላት የከበረባት፣ካህን የሚያገለግልባት፣ንግስ የሚከበርባት፣ወንጌል የሚዘራበት፣ሚስጢራት የሚፈጸሙባት በሞዛይክ እና ማርብል ከተሽቆጠቆጡ የከትማ አብያተክርስቲያናት ጋር በእኩሌታ መንፈስቅዱስ የሚሰራባት#በየዓመቱ_እንደ_ለሎቹ_አብያተክርስትያናት_ታቦት_የሚነግስባት  አማናዊ #የገጠሪቷ መቅደስ ናት ። የሰማይወምድር የነገስታቶች ንጉስ የጌቶች ጌታ፣የአምላኮች አምላክ፣ስሙም ድንቅ፣መካረ ኃያል፣ ኤልሻ ዳይ፣ አዶናዬ፣የተባለው፣ የቸሩ መድኃኔዓለም ቤተመቅደስ ናት

በአካባብ ከ30 የማይበልጥ በመከራ የተፈተነች የገጠርቷ ነፍስ ብቻ ነው ያለው።
በዚህ መሠረት በእነዚያ ጥቅት ነፍሳትና በእግዚአብሔር አጋዥነት #ከሚያዚያ 5/2013ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ሳይኖራቸው መሠረት ጥሎ ስራውን የጀመሩ ብሆኑ በማህበራዊ ሚድያ በእናንተ በደጋጎች ድጋፍ ወደ ፍኒሽንግ ደረጃ ካደረስን ቦኋላ ስራው ቁሟል😭😭😭
ስለሆነም አሁን የጎደሉ ማቴረያሎች ተሟልቶና ስራው ተጠናቅቆ በቅርቡ ቅዳሴ ቤቱ ይከበር ዘንድ ከመቸውም ግዜ በላይ የበረታ እጆቻችሁን እንድትዘረጉልን በስሙ እንወድቃለን🙏
የጎደሉ ማቴረያሎች
#ለሊሾ 50ኩ/ታ ሲሚንቶ 50*2400=120,000ብር
#ቀለም 64 ጋሎን  64*2200=136,400ብር
#መስታወት 62 ካሬ 62*2000=124,000ብር
#በር ከተሰራበት ለማስመጣትና ለመግጠም 70,000
#የውስጥ የስነ ስዕል ስራዎች የሚያስፈልጉ ነገሮች እንደ ገጠር አጥቢያ በጥቅቱ  =80,000ብር
                                      #ድምር=  530,400ብርነው

             ስለዚህ #የመድኃኔዓለም ውለታ የዋለላችሁ
                    #ስሙን ስትሰሙ ፍቅሩን የሚታስታውሱ
                    #ጥበቃውና ረዳትነቱ የተከታላችሁ
የስሙ አጋቾች እኔሆ የበረከት እጃችሁን #ከ10ብር ጀምራችሁ የሚትዘረጉበት የቤ/ያንቷ ህጋዊ ንግድ ባንክ አካውንት:_ 
                1000107255943
               ዮፎ መድኃኔዓለም ቤ/ን ህንፃ ማሰረያ....
     
       ለበለጠ መረጃ 0991122817/0917235781

ያስገባችሁትን የባንክ ስሊፕና የክርስትና ስማችሁን በውስ መስመረ አሳወቁን!

#ስለ_መድኃኔዓለም
#ስለ_ድንግልቱ_ልጅ
#ስለ_ዓለሙ_ጌታ
🤲🤲🤲🤲🤲🤲

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

03 Nov, 17:09


1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

03 Nov, 17:01


💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

03 Nov, 17:00


ሰላም ተወዳጆች በዚህ ግሩፕ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ተውህቦ ጸጋ
➛ ወቅቱን መሠረት ያደረጉ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
➛ የቅዱሳን አባቶች እና እናቶች ታሪክ
➛ የንጽጽር ትምህርቶች
➛ ከግሩፑ አባላት ለሚመጡ ማንኛውም ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትን ጨምሮ ሌሎች ተከታታይ ትምህርቶችን በማስተማር ላይ ይገኛሉና ሌሎች የዚህ የቴሌግራም ግሩፕ አባል እንዲሆኑ ይጋብዙ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

https://t.me/Tewhbotsega

https://t.me/Tewhbotsega

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

03 Nov, 12:04


‹‹እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ
ሀገረኪናሁ ገሊላ እትዊ
ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ
እምግብፅ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ፡፡››

ትርጉም፡-
እመቤቴ ማርያም ሆይ! ስሙ ናዝራዊ የሚባል ልጅሽን ለአዳምና ለሔዋን ክብር የባሕርይ አባቱ አብ ከግብጽ ይጠራዋል፣ማለት በግብጽ ስደት አይሞትም ኋላ በቀራንዮ ተሰቅሎ ዓለምን ያድናል ብሎ ነቢዩ ዖዝያን (ሆሴዕ) ትንቢት እንደተናገረ እስከ መቼ በባይድ አገር ትኖሪያለሽ? እነሆ ወደ አገርሽ ናዝሬት ተመለሽ፡፡

(ሰቆቃወ ድንግል)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

31 Oct, 15:29


"ልትደገፊኝ ያዝሁሽ ልትጥይኝ ግን አይደለም ወደላይ ከፍ ከፍ ልታደርጊኝ ያዝሁሽ ወደ ታች ልታወርጅኝ ግን አይደለም፡፡ ለዘለዓለሙ ያዝሁሽ ለዕድሜ ልክ ብቻ አይደለም፡፡

እናቴ ሆይ ነፍሴ ባንቺ ዘንድ ትክበር ስለቸርነትሽም እመቤቴ ነሽ፡፡ ስለ ፍቅርሽ የታመንሽ ስለ ልጅሽም የመድኃኒት ቀንድ ሆይ አስቢኝ እንደ ወደቅሁም እቀር ዘንድ አትርሺኝ፡፡"

(መጽሐፈ አርጋኖን)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

31 Oct, 15:27


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

31 Oct, 03:52


"የኃጢአት ምኞትህን የሚዛን ልክ በልብህ ውስጥ ያመጣጥን ዘንድ ማንኛውንም ዓይነት መንፈሳዊ ሥራ በመሥራት የክፋታቸውንና የአደጋቸውን መጠን ቀንስ ። የምኞት ኃጢአት እስክታስወግደው ድረስ መልካም ፈቃድ በልብህ ውስጥ ቀስ በቀስ እንደሚያብብ እርግጠኛ ሁን ። መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ እንደሚሰራ ሲታወቅህ ችላ አትበለው ! ከእርሱ ጋር ሥራ እንጂ በምኞትህ ልትቀጥል አትሞክር።"

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

29 Oct, 05:43


https://youtu.be/9ZcuQRUaj6A?si=qMFrgbmouvpXvXSx

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

28 Oct, 15:30


የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የኤፌሶን ወንዝ መጽሐፍ ቅዳሜ ለሁሉም መጽሐፍ መደብሮች ትሰራጫለች።
የሽፋን ዋጋ 400ብር

ሙሉ ገቢው ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ሕንፃ ቤተ መቅደስ እድሳት የሚውል።

ዋና አከፋፋይ አርጋኖን መጻሕፍት መደብር
4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል የቀድሞ ሪፍት ቫሊ ዪኒቨርስቲ ሕንፃ

ስልክ
0954838117
0912044752 ይደውሉ!!

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

28 Oct, 04:10


"ሊቅ በሊቅነቱ ቢያስተምርህ ሊቅ ትሆናለህ፤ ሊቅ በህይወቱ ቢያስተምርህ ግን ክርስቲያን ትሆናለህ፡፡"

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

27 Oct, 12:50


የርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል መጽሐፍን በባኮስ መጻሕፍት መደብር ያገኛሉ።

አድራሻችን፦
አምስት ኪሎ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፥ አሐዱ ባንክ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ ➛ 0920888887

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

25 Oct, 20:15


ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

25 Oct, 19:50


🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️

⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

25 Oct, 11:24


"ኹሌም በሄድኩበት የምናገረው አንድ ነገር አለኝ"!

"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣
ምልኩስና እና
ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር፣ በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ "እንዴት?" ካልን፦
የተከበረ ትዳር የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል።
የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል።
ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ!
ተምረን ማግባትና፣ ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

25 Oct, 05:05


"የምንጸልየው እግዚአብሔርን ምን ማድረግ እንዳለበት ለመንገር ሳይሆን እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲነግረን ነው።"

ሊቁ አውግስጢኖስ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

24 Oct, 05:11


"መላው ዓለምን ያስደነገጡ ታላላቅ መከራዎች ኹሉ መነሻቸው ትዕቢት ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

24 Oct, 05:01


"ከእውነት የራቀ ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ የራቀ ነው፡ ከእውነት የተለየም ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር የተለየ ነው።"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

23 Oct, 07:39


"መጥፎ ቀን እና ጥሩ ቀን የሚባል ነገር የለም። ያለው ጸሎት አድርገህ የወጣህበት ቀን እና ጸሎት ሳታደርግ የወጣህበት ቀን ነው። ያልጸለይክባቸው ቀናት በክፉ ምኞትና የሥጋ ፍላጎት የተሞሉ ስለሆኑ ክፉ ቀናት ናቸው።"


ቅዱስ ቄርሎስ ሣድሳዊ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

22 Oct, 17:07


✟ የተባረከች አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች

✟ የተባረከች ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች

✟ የተባረከ ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል

✟ የተባረከች ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች

✟ የተባረከ አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም

✟ የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች

✟ የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች

✟ የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች

✟ የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች

"እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና" ዘሌ. 11፥44

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

21 Oct, 11:35


#ሼር
#የካህኑን_ልጅ_እንድረስላት

በዓለም ዙርያ የምትኖሩ ልጅ የምትወዱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቼ በምስሉ የምናያት ህጻን ስርጉት ጥዑመ ልሳን ትባላለች።

ገና የአንድ አመት ከስምንት ወር ህጻን ስትሆን ዕድሏ ሆኖ መናገርም መንቀሳቀስም በሰላም መተንፈስም መቦረቅም አልቻለችም ከተወለደች ጊዜ ጀምሮ በህመም ላይ ነችና።

ወላጆቿ ምንም ገቢ ስለሌላቸው የተሻለ ህክምና ማግኘት አልቻለችም። ዛሬ ላይ #ወገን_ቢያግዘን_የተሻለ_ህክምና ብንሞክርላት ብለው ፊታችን ቆመዋልና ደጋግ ወገኖቻችን ከቻላችሁ በገንዘብ ካልቻላችሁ በሀሳብ፣ በጸሎትና ለሌሎች ረጂዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንድታግዟቸው እንማጸናችኋለን።

ቄስ ጥዑመ ልሳን ገደፋው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000561662014

ለበለጠ መረጃ
ቄስ ጥዑመ ልሳን ➛ +251967438386

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

20 Oct, 20:38


🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

         ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █          
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

20 Oct, 20:27


👳‍♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
            እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
    ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️
ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ

ይህ ምክረ አበው ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉ ትጠቀሙበታላችሁ open የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ⬛️⬛️⬛️⬛️
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
    ⬜️⬜️⬜️⬜️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

19 Oct, 06:05


#ሼር
#የካህኑን_ልጅ_እንድረስላት

በዓለም ዙርያ የምትኖሩ ልጅ የምትወዱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቼ በምስሉ የምናያት ህጻን ስርጉት ጥዑመ ልሳን ትባላለች።

ገና የአንድ አመት ከስምንት ወር ህጻን ስትሆን ዕድሏ ሆኖ መናገርም መንቀሳቀስም በሰላም መተንፈስም መቦረቅም አልቻለችም ከተወለደች ጊዜ ጀምሮ በህመም ላይ ነችና።

ወላጆቿ ምንም ገቢ ስለሌላቸው የተሻለ ህክምና ማግኘት አልቻለችም። ዛሬ ላይ #ወገን_ቢያግዘን_የተሻለ_ህክምና ብንሞክርላት ብለው ፊታችን ቆመዋልና ደጋግ ወገኖቻችን ከቻላችሁ በገንዘብ ካልቻላችሁ በሀሳብ፣ በጸሎትና ለሌሎች ረጂዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንድታግዟቸው እንማጸናችኋለን።

ቄስ ጥዑመ ልሳን ገደፋው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000561662014

ለበለጠ መረጃ
ቄስ ጥዑመ ልሳን ➛ +251967438386

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

18 Oct, 15:54


ተአምር መሥራት ትፈልጋለህን?

አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበላቸው "ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?" ቅዱሱ አባት መለሱለት፦
"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው፤  ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል፤ ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው።

በል ሒድና ተአምር ሥራ!" አሉት

በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

18 Oct, 04:26


እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ።

ልጆቼ  እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

17 Oct, 09:05


ተግሣፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም

ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።

ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።

ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።

እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።

መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።

ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡

ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡

ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።

(ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ገጽ 334 - 336 በዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው የተተረጎመ)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

16 Oct, 05:34


አባ መፍቀሬ ሰብእ አረፉ!!
ወሎ በተለይ ደሴ ውስጥ ሁኖ እርሳቸውን የማያውቅ የለም። ክርስቲያኑም ሙስሊሙም በአንድ ቃል"አባ" የሚላቸው የፍቅር ሰው የዘመናችን ጻድቅ አባ መፍቀሬ ሰብእ አረፉ።

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

15 Oct, 17:45


ጠቃሚ ቻናል ጥቆማ

"ግእዝ ንባብ ለኹሉም" በዚኽ የቴሌግራም ቻናል በአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሰጡ የግእዝ ንባብ ትምህርቶች ይሰጡበታል።
እነዚኽም፦

▪️ ጸሎት ዘዘወትር
▪️ ውዳሴ ማርያም
▪️ አንቀጸ ብርሃን
▪️ መልክዐ ማርያም
▪️ መልክዐ ኢየሱስ
▪️ መዝሙረ ዳዊት
▪️ ጸሎተ ነቢያት ምስለ መኃልይ
▪️ ወንጌል (፬ቱ)
▪️ ሌሎችንም የንባብ ትምህርቶች ይሰጡበታል።

ወደዚኽ ቻናል ይቀላቀሉ፤ ሌሎችንም ለመጋበዝ ከታች ያለውን ሊንክ መጠቀም ይችላሉ።

https://t.me/geeznibablehulum
https://t.me/geeznibablehulum

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

15 Oct, 16:36


ይህን ድንቅ መጽሐፍ በተገኘበት አድናችሁ ትገዙ ዘንድ እየጋበዝኩ መጽሐፉ እጄ ላይ ባይገባም እጃቸው ከገባ የቀነጫጨቡትን ለቅምሻ አካፍላችኋለሁ...

ለጥቆማ መጽሐፉን
5ኪሎ ቅድስት ማርያም አሐዱ ባንክ ፊት ለፊት
ባኮስ መጻሕፍት መደብር - Bakos Book Store ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ 0920888887

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

15 Oct, 16:36


ቅምሻ - ፩

አሐቲ ድንግል - አንዲት ድንግል

ድንግል ማርያም ለምን አንዲት ድንግል ትባላለች?

እመቤታችን ድንግል ማርያም በምድርም በሰማይም አቻ የማይገኝላት አንዲት ድንግል ናት። ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌልም የምትልቅ በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች በወንጌል የተፃፈች አንዲት ድንግል አለች። ይላል ቅዱስ ያሬድ።

ከዚህም ተነስቶ አንድ ሰው ተነስቶ በወንጌል ሌሎች ደናግል የሉምን? ስለምን በወንጌል የተጻፈች አንዲት ድንግል ትላለህ? ብሎ ቢጠይቀው ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌል የምትበልጥበት የድንግልና ዘውድ ያላት አንዲት ድንግል አልኩህ እንጂ ደናግላንማ ብዙ ደናግል አሉ ብሎ ይመልስለታል።

ቀጥሎም በመላዕክት ክንፍ የምትጋረድ በክብሩ መንበር በፊት ምህረት የምትለምን በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊል የተቀዳጀች አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል አለች።

አሁንም ቅዱስ ያሬድን ስለምን አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል ትላለህ አርሱ የመረጣቸው ብዙ ደናግላን የሉምን? ብሎ የሚጠይቀው ቢኖር፥ አማኑኤል ሥጋን ይለብስ ዘንድ የመረጣት፤ ከእርስዋም ሥጋን ለብሶ አማኑኤል የተባለባት፥ በመላእክት ክንፍ የምትጋረድ፥ እግዚአብሔር በክብሩ ዙፋን በፊቱ ለመቆም የመረጣት፥ በእናትነት የሰለጠነ የባለሟልነት ዘውድን የተቀዳጀች አንዲት ድንግል አልኩ እንጂ እርሱ የመረጣቸው ደናግላንማ ስንቱ! ብሎ ይመልስለታል።

ደግሞም ፀጉሯ እንደ ሐር ፈትል ያማረ፥ የአንደበቷ መዓዛ እንደ እንኮይ የጣፈጠ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች የልዑል ንጽሕት አዳራሽ የሆነች አንዲት ድንግል አለች።

የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆኑ ሌሎች ደናግላን የሉምን ስለምን ለይቶ እርሷን አንዲት ድንግል አለ ቢሉ? ከእርሷ ስጋ ይነሳ ዘንድ እግዚአብሔርን በማህፀኗ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የወሰነች እውነተኛ የእርሱ ማደሪያ ሌላ ድንግል ከማርያም በቀር ወዴት አለ ይለዋል! ብቻዋን የእግዚአብሔር መቅደስ ለመሆን የበቃች እንደሆነች ሁሉ ከቅዱሳን ሁሉ ተለይታ በእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው እንደ እንኮይ የጣፈጠ አማላጅነት ያላት አንዲት ድንግል እርሷ ብቻ ናት! ስለዚህ እንደ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችን ብቻዋን አንዲት ድንግል የተሰኘችበት ወላዲተ አምላክነቷ፤ ንፅሕናዋ ፤ማኅደረ መለኮትነቷ አማላጅነቷ እና ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ ናቸው ማለት ነው።

፩.በድንጋሌ ሥጋ ዘለዓለማዊ
በተፈትሆ የማይመረመር ድንግልናዋ ነው። ይህም ሥስት የማይመረመሩ ግብራት አሉት። ድንግል እንደሆነች መፀነስ፥ ድንግል ሆና ሳለ መውለዷ፥ ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና መኖሯ ናቸው። እነዚህ በህገ ተፈጥሮ የማይታሰቡ ረቂቅ ግብራት ናቸው። ሰው ድንግል ሆኖ ያለ ወንድ ዘር መፀነስ አይቻለውም፥ በድንግልና እያለ የፀነሰ መሆን አይችልም፥ ሰው በድንግልና መውለድ አይቻለውም፥ ከወለደ በኋላ ደግሞ ድንግል መሆን እንዴት ይችላል? ድንግል የሆነች ሌላ ሰው እናት አይደለችም፥ እናትም ከሆነች ድንግል አይደለችም። ይህ ለአንዲቱ ለድንግል ማርያም ብቻ የተቻለ ነው።

፪. ድንግል በቃሏ - በቃሏም ድንግል
የቃል ድንግልና በሦስት ወገን ነው። እኒህም ክፉ አለመናገር፥ ምስጋና አለመብላትና በጎውን መናገር ናቸው። ሰው በንግግሩ ብዙ ኃጢአቶች ይሰራል። ሐሜት፣ ማጉረምረም፥ ቁጣ፥ ብስጭት፥ መዋሸት፥ መርገም፥ መሳደብ፥ ዋዛ ፈዛዛ፥ ያለጊዜው መሳቅ መሳለቅ፥ ዘፈን፥ ተውኔት፥ ድንፋታ፥ መንፈግ ነገር ማመላለስ፥ ቃል መለዋወጥ፥ አደራ መብላት፥ በሀሰት መማል፥ ሰጥቶ መንሳት፥ ክህደት፥ ማታለል፥ ማስነወር፥ አድልዎ፥ መጠራጠር፥ ማሽሟጠጥ፥ አሽሙር፥ ኃጢአትን ማመስገንና ማስፈራራት እነዚህን የመሳሰሉ ሁሉ ናቸው።

እመቤታችን በማንም ክፋትን ተናግራ አታውቅም አንደበቷ የለዘበ የለመለመ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና የማይታሰብ ዕፁብ ድንቅ የመውለዷን ዜና ሲነግራትም እኔ ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል ብላ ነገሩን ወደ መረዳት ተሻገረች እንጂ ይህ የማይሆን ነገር ነው ብላ ወደ መጠራጠር ወይም መልአኩን ወደ መንቀፍ አልቃጣችም። የአንደበት ድንግልና ማለት የማይቻል ጭንቅ ፍጹም ከተፈጥሮ ህግ በላይ የሆነን ነገር በመስማት ጊዜም ቢሆን ያለመጠራጠር በሃይማኖት መጠየቅና ፍፃሜውን በትዕግሥት መጠበቅ ነው።

መከራ በደረሰ ጊዜ ብዙ የቃል ድንግልና ያላቸው ቅዱሳን ችግሩን የፈጠሩትን ከመንቀፍ ይልቅ በእኔ ችግር የተከሰተ ነው ብለው ራሳቸውን ይወቅሳሉ። ነገር ግን እነርሱ ቀድሞ መበደላቸውን እያስታወሱ ነው። የድንግል ማርያም ግን የሚደንቀው ምንም ነውር የሌለባት ስትሆን በቃሏ ድንግል ስለሆነች እኔ ኃጢተኛ ነኝ ትል ነበር። በብስራተ መልአክ አምላክን የፀነስኩ እናት ነኝ ስትል ገናንነቷን አትናገርም። መልካም በመናገር ንግግሯ ሁሉ ሃይማኖት ተስፋና ፍቅር ናቸው።

፫. ድንግል በኅሊናሃ - በኅሊና ድንግልና የፀናች አንዲት ድንግል፦
ሰው በተግባር ቢነጻ በንግግር አይነጻም፥ በንግግር ቢነጻ በኅሊናው መንፃት አይቻለውም። ጻድቃንም ቢሆኑ ወድቀው ተነስተው በተጋድሎ ለክብር ይበቃሉ እንጂ ከጅማሬ እስከ ፍፃሜው አለመበደል ከቶ የተቻለው የለም። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በኅሊናዋ እንኳን ያልበደለች ፍጽምት አንዲት ድንግል ነች። ጽድቅን ሁሉ የተሞላች ድንግል ማርያም ንጽሕት በመሆኗ በኅሊናዋን ድንግልና፤ የቃሏን ድንግልና፤ የስጋዋን ድንግልና በአንድ ላይ "እንዘ ኢይአምር ብእሴ" "ወንድ ስለማላውቅ" በሚል የንፅህና ሸማ ጠቅልላ ተናገረች (ሉቃ.፩፥፴፬) በዚህ ድንግልናዋም አምላክን ለመፀነስ በቃች።.....(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል መጽሐፍ ገፅ 241-251 የተቀነጨበ)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

14 Oct, 09:08


"ልጆቻችሁን ይዛችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ኑ! ብቻችሁን አትምጡ፡፡ ብቻችሁን ከመጣችሁ ወደ ሌላ ይሔዳሉ እናንተ እዚህ መጥታችሁ የምትሰሩትን አያውቅም፡፡ ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቅም፡፡ ወራሾቻችሁ አይሆንም፡፡

ስለዚህም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ አሳዩአቸው ሥዕሉን ይሳሙ ቅዳሴ ጠበል ይጠጡ በእምነት አሻሹአቸው መስቀል እንድስሙ አስተማሯቸው ዕጣኑን ያሽትቱ ሥጋ ወደሙን ይቀበሉ ቃጭሉን ይስሙ ደውል ሲደውል ይስሙ ቄሳቸው ማን እንደሆነ ቤተክርስቲያናቸው ምን እንደሆነች በውስጧ ምን ምን እንደሚሰራ ያጥኑ ይማሩ።

ወደ ሰንበቴው እጃችሁን ይዘው ይከተሉ ወደ ማህበር ስትሔዱም ይዛችኋቸው ሂዱ ቆሎውን ዳቦውን ተሸክመው ወደ ሰንበቴው ይምጡ ይማሩ እነርሱም ነገ ይሄን እንዲወርሱ የነገ ባለአደራዎች መሆናቸውን እንዲያውቁ።"

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

14 Oct, 03:50


"ጀግና ከሆንክ በራስህ ላይ ጦርነት አውጅበት!!!
መቆጣት ከፈለግህ መጀመሪያ በራስህ ላይ ተቆጣ።

ልክስክነትህን፤ ስግብግብነትህን፤ ክፋትህን፤ ዝርክርክነትህን፤  ዘማዊነትህን ተቆጣው፤ ስንፍናህን ተቆጣው።

በዲያብሎስ ላይ ጦርነት ክፈትበት፤ የዘላለም ዕረፍትህን ለሚነጥቅህ፤ ከዘላለማዊ ርስት ለነጠቀህ፤ ከልጅነት ለሚያዋርድህ፤ ከእግዚአብሔር ከሚያጣላህ፤ ከክብር ካዋረድህ በእርሱ ላይ መጀመሪያ ተነሥ።››

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

13 Oct, 04:05


በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኙት ፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን ሕግጋት አጥብቀው የሚቀበሉ ሰዎች ነበሩ። ቅዱሳት መጻሕፍትን በተመለከተ ያላቸው እውቀት እጅግ የላቀ ከመሆኑ በተጨማሪ ሁሉንም የእግዚአብሔርን ሥርዓትና ሕግጋት ጠንቅቀው ያውቋቸዋል። ይሁን እንጂ እጅግ ጠቃሚ የሆነው ፍቅር ይጎድላቸዋል።

ልባቸው በእግዚአብሔር ላይ የደነደነ ከመሆኑም በላይ ግብዞች ነበሩ። ከውጪ ሲመለከቷቸው ፍጹም ይመስላሉ ውስጣቸው ግን ፍጹም የተበላሸ ነበር። እነርሱ በልባቸው ውስጥ ምንም አይነት ፍቅር ሳይኖር ሃይማኖትን በእጅ የሚከናወን ሥራ ስላደረጉት ከእግዚአብሔር ጋር ለሚሆን ለሚሆን እውነተኛ የግል ግንኙነት ዋጋ አልሰጡም።

ፈሪሳውያን ጸልየዋል ጾመዋል መጻሕፍትን በቃላቸው ይዘዋል የእግዚአብሔርን ሕግጋት ተቀብለዋል እነዚህ ተግባራት በዙሪያቸው በሚገኙ ሰዎች ሁሉ ፊት በገሃድ የሚታዩ እንደሆኑም እርግጠኞች ሆነዋል። እነርሱ ራሳቸውን ከሌሎች ሰዎች በተለይም ከድሆችና ከኃጢአተኞች ለይተዋል። እንደነዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገቡ አይደሉም ብለውም ደንግገዋል። እነርሱ በሌሎች ሰዎች ላይ በጣም የሚፈርዱ ሰዎች ነበሩ።

ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል። ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ። ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲል ጸለየ፤ "እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ።" ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳ አልወደደም፥ ነገር ግን። "አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ" እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር። እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።" ሉቃ18፥9-14

(ምርጥ የቅብጣውያን መንፈሳዊ ስብከቶች ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

12 Oct, 12:34


ትመጫለሽ አይደል?

ቤተመቅደስሽን ከበን አለን - መቅደስ ገላችን ቢረክስም
በሕንጻ መቅደስሽ ከትመናል - ሕንጻ ሥላሴን ብናፈርስም

በልማድና በእምነት መሀል – በተወጠረ መንፈሳችን
በጎጥ በጎሳ በታጠረ - በተፍረከረከ አንድነታችን
ስቀለው ስቀለው እንጂ – ምን በድሎ? በማይል ልሳናችን

ለክፋት ባደገደገ - በጎ ግብር በራቀው
ኃጢአት ባጠራቀመ – የጽድቅ ፍኖት በናፈቀው
ነውርን መግለጥ እንጂ - ከባቴ አበሳነት በማያውቀው

በረከሰ ማንነት ነው – ንዒ ማርያም የምንልሽ
ከልዑሉ ሚካኤል ጋር ከደስተኛው ገብርኤል ጋር
            ጽጌ ጸዐዳ ልጅሽን ይዘሽ
            ነይ ርግባችን የምንልሽ
በሚገባን ንጽህና – ሆነን አይደለም ድንግል
ግን ነይ ስንልሽ አትቀሪም.... ትመጫለሽ አይደል?

ልባችን ቂምን ቋጥሮ በአፍ ዜማ ብቻ - ብንጠራሽም ንዒ ብንልም ድንግል
ርሕርሕተ ሕሊና እመ ትሕትና..... ትመጫለሽ አይደል?

ስለተጠራው ስምሽ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?

ስለኪዳንሽ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?

አልቦ ምግባር ብንሆንም - እንደ ቃና ማድጋ
ማርያም አትቅሪ እኛ ጋ

ንዒ ስንል
አዛኝቱ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?

(ገጣሚ - አገሬ ኑሪ)

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

12 Oct, 05:09


"የማርን ጥፍጥና ማርን ቀምሶ ለማያውቅ ሰው በመቅመስ እንጂ በቃላት ማስተማር እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቃላት በጠራ መልኩ ማስተማር አይቻልም። ራሣችን ወደ እግዚአብሔር መልካምነት ዘልቀን መግባት ይኖርብናል እንጂ።"

ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

11 Oct, 19:10


ሰላም ተወዳጆች
"የመጋቤ ሐዲስ ኢሳይያስ ሀብቴ ገጽ" መንፈሳዊ ግሩፕ ስናገለግላችሁ ብዙ እየተጠቀማችሁ እንደሆነ ብዙዎቻችሁ ሀሳባችሁን እያጋራችሁን ነውና እናመሰግናለን።

"የመጋቤ ሐዲስ ኢሳይያስ ሀብቴ ገጽ" ግሩፕን ሁላችንም ለመንፈሳዊ ዕውቀት የምንሳተፍበት እና ሀሳባችንን የምንገልጽበት እንዲሆን በማሰብ ልዩ ልዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ብቻ የሚለቀቁበት ራሱን የቻለ ቻናል "ጉባኤ ኒቅያ መንፈሳዊ ቻናል" በሚል ስያሜ አዘጋጅተናልና ከስር ባለው ሊንክ ቻናሉን ትቀላቀሉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን!!

https://t.me/EsayiyasHabte2017

https://t.me/EsayiyasHabte2017

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

11 Oct, 02:23


''እግዚአብሔር የሚጠይቅህ ጥቂት ነው የሚሠጥህ ግን ብዙ ነው!''

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የሕይወት መዓዛ (አቡነ ሺኖዳ)

10 Oct, 12:53


ስንክሳር የዓመቱን እና መጽሐፈ ክርስትና ተገዝቷል

የሚከተሉት ቅዱሳት መጻሕፍት ይቀራሉ
1 መጽሐፍ ቅዱስ
1 ወንጌል ቅዱስ
1 መጽሐፈ ቅዳሴ
1 መጽሐፈ ግንዘት
1 መጽሐፈ ግጻዌ
1 ሃይማኖተ አበው

@natansolo በውስጥ መስመር አናግሩን!

14,615

subscribers

232

photos

9

videos