Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️ @orthdoxswallper Channel on Telegram

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

@orthdoxswallper


የኦርቶዶክስ የሆነ ለስልኮ ፎቶ ከፈለጉ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ይህንን ቻናል ለኦርቶዶክስ ቤተሰብ በመላክ ይተባበሩን@orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper (Amharic)

የኦርቶዶክስ የሆነ ለስልኮ ፎቶ ከፈለጉ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ይህንን ቻናል ለኦርቶዶክስ ቤተሰብ በመላክ ይተባበሩን በአሁኑ ቻናል እናትም በአንደኛው ቻናሉ ኦርቶዶክስ ልደታ ላይ በማቅለው ሲተናከል መልክ ያለን፡፡ የፍቅርና ታምራት የትንቢት ፍሬያት ፕሮቴንስ መሆን የቆዻሺም ትዕቢትና ቀናትን የመስፈሰያ ማየት መሆን ከሚለው አስተያየት በቀላሉ፡፡ በሚል የኦርቶዶክስ ቤተሰብ ስለተመሰረተ ፎቶች መካከል ይታመናል በመሆን እንዲሐዘን እኛም በተለዋዋጭ ቻናሎችን ቆሞ ታላቅ መተግበሪያ እንረጋግጠናል፡፡ የምሳሌ፣ የእናት፣ የፀሐይ፣ እና ሌላ ቢሮ እንዲሆን ተወዳጁን እንመለከታለን፡፡ ለስልካችን በዚህ ቻናል መቀላቀል ስለምትከታተሉ መንፈሳቸውን የምግብ ስጦታ ተዛማጁን እናስብ፡፡

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

08 Dec, 11:38


#ኦርቶዶክስጥቅሶች

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

07 Dec, 07:25


#ኦርቶዶክስጥቅሶች
የቻናላችን ቤተሰቦች ቻናሉን ለማሳደግ Share በማረግ ተባበሩን 🙏


#share
@orthdoxswallper
@orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

05 Dec, 17:23


#ጥቅሶች
ስለ ቅዱሳን ነቢያት ነዉ የቻናሉ ቤተሰቦች ብታነቦቸዉ ይመከራል ለሌላዉም ሼር ያርጉት 🙏

#share
https://t.me/orthdoxswallper
https://t.me/orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

25 Nov, 16:44


#wallpaper

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

24 Nov, 15:22


#ኦርቶዶክስጥቅሶች ❤️❤️❤️ . . @orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

23 Nov, 18:53


🗣እሑድ ጾም ነው!

ጾመ ነቢያት የሚገባው እሑድ ህዳር 15 ሲሆን: የጾም ማሰሪያ ቅዳሜ ነው:እሑድ ከጥሉላት ምግቦች እንጾማለን።

እንደ ቀኖናም ጾም ሁሉ ሰኞ ይገባል የሚል አዋጅ የለም። ግዴታ ሰኞን ጠብቀው የሚገቡ አጽዋማት ነነዌ: ሁዳዴ(ዓቢይ ጾም): ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) ብቻ ናቸው። ሌሎች አጽዋማት በሰኞ ሊገቡም ላይገቡም ይችላሉ።ይህ ጾም ደግሞ ያለ ተውሳክ የሚወጣ ስለሆነ ቀንን እንጂ ዕለትን አይጠብቅም።

ይህ ጾም የአጽዋማት ሁሉ መሠረት ነው። የተስፋ: የሱባኤ ጾም ነው: ከአዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉ ቅዱሳን የጮሁት ጩኸትም ነው። የሌሎች አጽዋማት መወለድ በዚህ ጾም ምክንያት ነው።

ነቢያት የአምላክን በሥጋ መገለጥ: የንጉሡን ከድንግሊቱ መወለድ ተስፋ በማድረግ ጾመውታል: በርግጥም ተስፋቸው ተፈጽሞ ጌታችን ስለእኛ ከድንግል ማርያም ተወልዷል: በጨለማ ለምንኖር የማይጠፋ ብርሃን በራልን:ወንጌል ወይም የምስራች መባሉም ዋነኛ ምክንያት ይህ ነው።

ታዲያ ለምን እንጾመዋለን? ጌታ አንዴ ተወልዶ የለም ወይ? የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችል ይሆናል:መልሳችን ጌታ ኢየሱስ በልባችን ገና ስላልተወለደ ነው! የሚል ይሆናል።

ባዶ ሆድ ከመሆን እንዲሁ ከመራብ ከፍ ያለ ጾም ያርግልን :ልባችንም ቤተልሔም ይሆን ዘንድ ፈቃዱ ይሁን!

©ዲ/ን ኤርምያስ ተፈራ
@orthdoxswallper
@orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

23 Nov, 16:07


https://vm.tiktok.com/ZMhvx2cPk/

📥 @allsaverbot

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

23 Nov, 06:13


#የኦርቶዶክስአባቶችwallpaper . . . ❤️❤️❤️ @orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

22 Nov, 14:32


#የኦርቶዶክስአባቶችwallpaper ❤️❤️❤️ ❤️ ❤️❤️ ❤️❤️❤️ @orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

21 Nov, 12:31


#የሚካኤልምስል
🔔#ኅዳር_⓬ ቀን ታላቁ #መልአክ_ቅዱስ_ሚካኤል በኢዮር ባለች በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአስሩ ነገድ መላእክት ላይ ❝#አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው❞ ። እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው #ቅዱስ_ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል ።


🥰እንኳን ለታላቁ ለሊቀ መላእክት ❝ ለቅዱስ ሚካኤል ❞ አመታዊ ክብረ ብዓል በሰላም አደረሳችሁ 🙏

የታላቁ መላአክ የቅዱስ ሚካኤል ጠቡቆቱ ፣ ምልጃው ፣ ደግነቱ ከእኛ ጋር ለዘላለም ፀንቶ ይኑር ❝አሜን❞። ቀናችን መገዳችን ስራችን ትምህርታችን ቅዱስ ሚካኤል ይባርክልን ❝አሜን❞።

መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ
❝ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ማሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ❞ ትንቢተ ዳንኤል ፲፥፲፫



                   ⓬አሜን⓬

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

21 Nov, 09:09


ኅዳር ፲፪

❤️ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት❤️

ኅዳር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን የተራዳበት ቀን ነው።

ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው ።

ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው ። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ ።

እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ ። ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ።

ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ይማረን የቅዱስ ሚካኤል በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝️@orthdoxswallper✝️
✝️@orthdoxswallper✝️

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

20 Nov, 17:35


Channel name was changed to «Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️»

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

20 Nov, 15:58


#ሚካኤል ❤️❤️❤️

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

19 Nov, 14:06


#ኦርቶዶክስጥቅሶች

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

18 Nov, 17:05


#wallpaper

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

17 Nov, 14:39


Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️ pinned «https://t.me/orth889 👆👆 ከታች ያለዉን የቻናሉ መወያያ ጉሩብ ነዉ ያልተቀላቀላችሁ በትህትና 🙏🙏 እንድትቀላቀሉና ጉሩቡን እንድናሳድገዉ🙏🙏»

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

17 Nov, 14:38


Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️ pinned «https://t.me/Pottery3 https://t.me/Pottery3 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆የእናቶቻችን የስራ ዉጤቶች ስራዎች ናቸዉ ገብታችሁ እዩላቸዉ 🙏🙏🙏»

Orthodox Wallpaper ✝️✝️✝️

17 Nov, 14:33


ኅዳር ፰

አርባዕቱ እንስሳ

ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ።

እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።

©ስንክሳር

@Orthdoxswallper
@orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper

16 Nov, 17:06


Orthodox Wallpaper pinned «https://t.me/orth889 👆👆 ከታች ያለዉን የቻናሉ መወያያ ጉሩብ ነዉ ያልተቀላቀላችሁ በትህትና 🙏🙏 እንድትቀላቀሉና ጉሩቡን እንድናሳድገዉ🙏🙏»

Orthodox Wallpaper

16 Nov, 17:01


#ላሊበላ

Orthodox Wallpaper

15 Nov, 18:18


#ኦርቶዶክስጥቅሶች @orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper

15 Nov, 16:47


⛪️@orthdoxswallper⛪️
#ቤተክርስቲያን

Orthodox Wallpaper

14 Nov, 19:06


✝️ሀያሉ እያለ ድካም ለምን ይሰማሀል ?✝️


@orthdoxswallper
@orthdoxswallper
@orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper

14 Nov, 16:01


#ኦርቶዶክስጥቅሶች

Orthodox Wallpaper

13 Nov, 12:52


#የኦርቶዶክስጥቅሶች

Orthodox Wallpaper

11 Nov, 12:52


#ማርያም

Orthodox Wallpaper

11 Nov, 12:51


#ማርያም

Orthodox Wallpaper

09 Nov, 17:25


#ከበሮ

Orthodox Wallpaper

09 Nov, 04:05


#መስቀል

Orthodox Wallpaper

08 Nov, 18:26


https://t.me/Pottery3
https://t.me/Pottery3

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆የእናቶቻችን የስራ ዉጤቶች ስራዎች ናቸዉ ገብታችሁ እዩላቸዉ 🙏🙏🙏

Orthodox Wallpaper

06 Nov, 13:33


#መድኃኒዓለም

Orthodox Wallpaper

05 Nov, 18:43


📗"ሳይኖረን በክብር የሚያኖረን ቸሩ መድኃኔዓለም ነው ቸሩ መድኃኔዓለም ጥበቃው አይለየን


🌹በቀኙ ያቁመን የዓለሙ ቤዛ🙏

Orthodox Wallpaper

31 Oct, 15:58


#ድንግል _ኾይ!💙


💙ሥጋ የለበሰ ሁሉ መመኪያ ድንግል ሆይ ነፍስ የተዋሀዳቸው ፍጥረት ሁሉ አክሊል የዓለም ሁሉ ቤዛ ነፍሴን ከክፉ ነገር ወደ ገሃነምም ከምትወስድ የጥፋት መንገድ አድኛት።
💙
ሳትዘራ ስንዴ ያፈራች ዝናምም ሳይዘንምባት የወይን ፍሬ ያስገኘች ማረሻ ያልዞረባት እርሻ ድንግል ሆይ የኦሪትና የነቢያት ቃል ዝናምን አጠጭኝ በሐዋርያት ወንጌል ቃል ፈሳሽነትም ሐዲስና ብሉይን እንዳፈራ አድርጊኝ።
💙
የኃይል መንፈስ የተመሉትን የተደነቁ የተመረጹትን ሐዋርያት ዋጋ እንድቀበል አድረጊኝ ልቡና የሚገልጽ ዕውቀት የሚያበዛወን መንፈስ የተመሉ ሐዋርያትን ዕሤት እንድቀበል ማለቴ ግን በኔ ገድል በትሩፋቴ አይደለም ባነቺ ደግነት በንጽሕናሽም ነው እንጂ፡፡

 💙በጸሎትሽም ረዳትነት ይህንን ላገኝ እወዳለሁ ድንግል ሆይ በሃይማኖት ጭንጫ ላይ የተመሠረተች መሠረት የማትፈርስ የነፋሳት ኃይል የጎርፍ ፈሳሽ የዝናምም ወጀብ የማይበረታባት አጥር ቅጽር ሆይ እኔን ከጥፋት ጎርፍ በዓመፀኞችና በበደለኞች ላይ ከምትመጣው የመቅሠፍት ኃይል አድኝኝ፡፡

💙 የመለኮት አዳራሽ ድንግል ሆይ የሰማይ ሠራዊት ፆታ ያደረብሽ ንጽሕት ሆይ፡፡ ኅብሩ ልዩ ልዩ በሚሆን ብርሃን በተጌጸ የቅዱሳን አዳራሽ ውስጥ መኖርን ክፈዪኝ፡፡አሜን 💙🌸

Orthodox Wallpaper

29 Oct, 16:24


የአንገት ማዕተብ ለምን እናስራለን ?

#Share

@orthdoxswallper @orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper

26 Oct, 17:04


አንዳንድ ነገሮችን ስላስተካከልን ከነዚ ዉስጥ የፈለጋችሁትን መርጣችሁ ስትነኩ ወደ ፎቶዋቸዉ ይወስዳችዋል 👍
👇👇👇
#wallpaper
#መስቀል
#ሚካኤል
#ጥቅሶች
#ቤተክርስቲያን
#Orthodoxart
#የኦርቶዶክስጥቅሶች
#የቅዱስቂርቆስ
#የእግዛቤርምስሎች
#የሀዋርያትምስል
#ላሊበላ
#የስቅለትምስል
#የሚካኤልምስል
#ቅዱስገብርኤል
#የገናwallpaper
#የኦርቶዶክስአባቶችwallpaper
#የማርያምምስል
#የኦርቶዶክስስዕል
#ኦርቶዶክስጥቅሶች
#Profile
#ቅዱስሱርያል
#ከበሮ
#ማርያም
#ሥዕለቅዱስዳዊት
#ሥላሴ
#መድኃኒዓለም
#እግዚአብሔርአብ
#የአቡነጴጥሮስን
#ዓዲግራት
#ፃድቃኔ_ማርያም
#ልደታ
#ስቅለት
#ሆሳዕና
#ቤተክርስቲያን
#ቅዱስጊዬርጊስ
#ቅዱስዑራኤል
#ተክልዬ
#ኪዳነምህረት
#ቅዱስሩፋኤል
#ቅዱስዩሐንስ
#ማኅሌተ_ጽጌ

Orthodox Wallpaper

24 Oct, 18:19


#ዘጠኙ ቅዱሳን
(በ5ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ክርስትናን ለማስፋፋት የተሰደዱ ክርስቲያን ሚሲዮናውያን)

ዘጠኙ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት አከፋፈል መሰረት “ ጥንታዊው የታሪክ ዘመን” ተብሎ በሚጠራው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ዘጠኝ የውጭ ሀገር ታላላቅ የክርስትና ሃይማኖት አባቶች ናቸው ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ የሆነ መንፈሳዊ አስተዋጽኦን ማለትም በመንፈሳዊ ህይወት ፣ በስብከተ ወንጌል፣ገዳማዊ እና የምንኩስና ሕይወትን በማስፋፋት ፣ መጽሐፍትን በመተርጎም፣ አበርክተዋል፡፡

ለአገራችን ሥነ-ፅሑፍ እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ከደጋግ ነገስታት ጋር በመሆን ለትምህርት ፣ ለማህበራዊ ኑሮ ወዘተ መሠረት የሆኑ ገዳማትን ከመመስረት ከቤት ክርስቲያን አልፎ ለአገራችን ኢትዮጵያ አያሌ አበርክቶት አድርገው አልፈዋል፡፡ በአገራችን ለቅድስናና ምንኩስና ፣ ለመፈንሳዊነት ትልቅ አብነት አላቸው፡፡ ከሮም ፣ ታናሽ እስያ፣ቁስጥንጥንያ ፣ ቂሳሪያ እና ሌሎች የእስያና ኤሮፓ አገሮች ቢመጡም ግዕዝን አጥንተው የአገሩን ባህልና አኗኗር ለምደው ክርስትናን በምድረ ኢትዮጵያ አስፋፍተዋል፡፡

ክርስትናን ወሰን አይገድበውምና ፣ ክርስቲያን ሃይማኖት እንጂ የድንበር አገር የለውምና የመጡበትን ቦታ ሳይሆን ህዝቡ መንፈሳዊ አባትነታቸውን ተቀብሎ! ቤተክርስቲያንም ውለታቸውን ቆጥራ የቅድስና ማዕረግ ሰጥታ ታከብራቸዋለች፡፡ ዕለት ተሰይሞላቸውም ክብር ይደረግላቸዋል፡፡

ከተለያዩ አካባቢ መምጣታቸውም ከየመጡበት አገር ወደ ግዕዝ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ አያሌ መንፈሳዊ መጽሐፍትን እንዲተረጉሙ አስችሏቸዋል፡፡ በዚህች ትንሽ ርዕስ ስለተሰዓቱ ቅዱሳን ይህን ያክል ካነሳን በሚከተለው አንቀጽ ደግሞ ማንነታቸውን እናስተዋውቃችኋለን፡፡ ስም የመጡበት አገር የገደሙበት ቦታ የመታሰቢያቸው ቀን:-

፩- አቡነ አረጋዊ ሮም ደብረዳሞ ጥቅምት ፲፬

፪- አቡነ ጰንጤሌዎን ሮም አክሱም ጥቅምት ፮

፫- አቡነ የማታ ቆስይ ገርዓልታ ጥቅምት ፳፰

፬- አቡነ ገሪማ ሮም መደራ/ዓድዋ/ ሰኔ ፲፯

፭- አባ ጽሕማ አንጾኪያ እንደ አባ ድሕማ/ይዲያ ጥር ፲፮

፮- አባ አፍፄ ታናሽ እስያ የሓ ግንቦት ፳፱

፯- አባ ሊቃኖስ ቁስጥንጥንያ አክሱም ህዳር ፳፰

፰- አባ አሌፍ ቂሳርያ ደብረ ሃሌሉያ መጋቢት ፲፩

፱- አባ ጉባ ኪልቂያ አድዋ አጠገብ ግንቦት ፳፱

@orthdoxswallper
@orthdoxswallper

Orthodox Wallpaper

24 Oct, 15:08


💠 ንሰሀ መግባት🙏🏻

ንስሀ ማለት ምን ማለት ነው

🔸ሊሰሩት የማይገባ ስራ ወይም ኃጢአት ከሰሩ በኋላ ምነው ባልሰራውት ምነው ባላደረኩት ብሎ ማዘን መቆጨት ነው።

🔹በሰራነው ኃጢአት  ተፀፅተን የምንመለስበት ነው።
📖ማቴ 12፥31

ንስሀ እንዴት እንገባለን

🔹ካህናት ዘንድ ቀርበን መሆን እንዳለበት መጽሃፍ ቅዱስ ይነግረናል።
📖ኢያ 7፥16፤
📖ማቴ 18፥13

🔸ኃጢአታችን በመናዘዝ ማለትም የሠሩትን ኃጢአት በመዘርዘር ልቡናን ታዛቢ አንደበተን ከሳሽ፣ ካህኑን ዳኛ አድርጎ ራስን መውቀስ ማለት ነው፡፡

👌በተጨማሪም በጸሎትና በመራራ ልቅሶ፣ በስግደትና በምጽዋት መሆን አለበት።
📖ማቴ 26፥75

💠በንስሃ ከተመለስን በኋላ

🔸ዳግመኛ መበደል አይኖርብንም።

🔹ንሰሃ የሚደገም ቢሆንም ከኃጢያት መራቅ አለብን።      📖ዩሐ 5፥14፤ 
📖ሮሜ 6፤14

🔸ሥጋ ወደሙን መቀበል ይገባናል።
📖ዩሐ 6፥56፤
📖1ኛ ቆሮ 11፥26

🔹ፍጹም ሰላምን እናገኛለን። 📖ዩሐ 14፥27

‼️አስተውሉ

🔔ማንኛውም ክርስቲያን ነፍስ ካወቀ በኋላ የንስሃ አባት መያዝ አለበት፡፡

🔔የንስሃ አባት የሚሆነው ካህን በአጥቢያው ቢሆን ይመረጣል፡፡

👌ምክንያቱም በየጊዜው እየተገናኙ ለሠሩት ኃጢአት ቀኖና ለመቀበል እንዲሁም መንፈሳዊ ምክርን ለማግኘት ሲባል ነው፡፡

ቀኖና ማለት ምን ማለት ነው

🔸 መስፈሪያ፣ መለኪያ ማለት ነው።

👌በአንድ ሰው ንሰሃ መግባት በሰማይ ሳይቀር ደስታ እንደሚሆን ተገልጿል።
📖ሉቃ 15፥7፤
📖 ማቴ 9፥13                                   
እንማማር ሼር-JOIN ያደርጉ
👉ስለ ሃይማኖታችን መማር ይፈልጋሉ? ??
ከፈለጉ JOIN ያደርጉ በማርያም🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Orthodox Wallpaper

16 Oct, 18:38


#ማኅሌተ_ጽጌ

Orthodox Wallpaper

14 Oct, 16:44


"ዛሬ ጥቅምት 4 ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ልደቱ ነው።ዮሐንስ ማለት ፍሥሓ ወሐሴት ማለት ነው።

"ከመስቀሉ ስርም ቆማ ቃሉን ትሰማ ነበር ያለ ምጥ የወለደችው ድንግል አርብ እለት በልጅዋ ስቃይ ተሰቃይታ ስታምጥ ምጥ ካለ ልጅ መኖሩ አይቀርምና እነሆ ልጅሽ ብሎ ቅዱስ ዮሐንስን ሰጣት።

በእምነት በምግባር ላልጸናን ለእኛ ደግሞ አንተን ይስጠን አሜን አማላጅነቱ ጥበቃው አይለየን ።🙏❣️☦️

Orthodox Wallpaper

06 Oct, 19:11


አሁን ባለው መረጃ

አዲስ አበባ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን የደረሰው አዋሽ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.9 የሆነና 10 ኪሜ ወደታች ጥልቅ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ የዛ የአዋሹ መንቀጥቀጥ ሞገዱ (waveኡ) እስከ አዲስ አበባና አካባቢዎቿ ድረስ ስለመጣና ስለተሰማ ነው፣ አትረበሹ!!

ሞገዱ ሲያልፍ እንዲህ ከተደናገጥን ዋናው ቢሆን አስቡት🙂

Orthodox Wallpaper

06 Oct, 18:50


የመሬት መንቀጥቀጥ የተነሳበት ሰፈር ያላቹ የቻናላችን ቤተሰቦች ባላችሁበት ሰላም ሁኑ ! ❤️ 🙏

Orthodox Wallpaper

03 Oct, 05:24


ኡራኤል ማለት ትርጉሙ የብርሃን ጌታ የአምላክ ብርሃን ማለት ነው። ቅዱስ ኡራኤል ቅድስት ድንግል ማሪያም ከልጇ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ እየመራ ክርስቶስ ለአለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ክብር ደሙን በብርሃን ፅዋ ተቀብሎ በብርሃን መነስነስ ለአለም የረጨ ቅዱስ ኡራኤል ነው።

""""""""""""""ቅዱስ ኡራኤል""""""""""""""
ላዘናቹ ቅዱስ ኡራኤል ያፅናናቹ።
ለታመማቹ ቅዱስ ኡራኤል ይፈውሳቹ።
የታሰራቹ ቅዱስ ኡራኤል ዋስ ይሁናችሁ።
ለተሰደዳቹ ቅዱስ ኡራኤል በሰላም ለሀገራቹ ያብቃቹ።
ከሀዘን ከመከራ ይሰውራችሁ።
ፀሎት ልመናችሁን በጌታ ፊት ያሳርግላችሁ።
ከመጣብን ወረርሽኝ ኢትዬጵያ ሕዝቧን ቅዱስ ኡራኤል ይጠብቅልን።
Amen (3)አሜን👏💖
#ቅዱስዑራኤል

Orthodox Wallpaper

03 Oct, 03:55


Orthodox Wallpaper pinned «አንዳንድ ነገሮችን ስላስተካከልን ከነዚ ዉስጥ የፈለጋችሁትን መርጣችሁ ስትነኩ ወደ ፎቶዋቸዉ ይወስዳችዋል 👍 👇👇👇 #wallpaper #መስቀል #ሚካኤል #ጥቅሶች #ቤተክርስቲያን #Orthodoxart #የኦርቶዶክስጥቅሶች #የቅዱስቂርቆስ #የእግዛቤርምስሎች #የሀዋርያትምስል #ላሊበላ #የስቅለትምስል #የሚካኤልምስል #ቅዱስገብርኤል #የገናwallpaper #የኦርቶዶክስአባቶችwallpaper #የማርያምምስል #የኦርቶዶክስስዕል…»

Orthodox Wallpaper

03 Oct, 03:54


አንዳንድ ነገሮችን ስላስተካከልን ከነዚ ዉስጥ የፈለጋችሁትን መርጣችሁ ስትነኩ ወደ ፎቶዋቸዉ ይወስዳችዋል 👍
👇👇👇
#wallpaper
#መስቀል
#ሚካኤል
#ጥቅሶች
#ቤተክርስቲያን
#Orthodoxart
#የኦርቶዶክስጥቅሶች
#የቅዱስቂርቆስ
#የእግዛቤርምስሎች
#የሀዋርያትምስል
#ላሊበላ
#የስቅለትምስል
#የሚካኤልምስል
#ቅዱስገብርኤል
#የገናwallpaper
#የኦርቶዶክስአባቶችwallpaper
#የማርያምምስል
#የኦርቶዶክስስዕል
#ኦርቶዶክስጥቅሶች
#Profile
#ቅዱስሱርያል
#ከበሮ
#ማርያም
#ሥዕለቅዱስዳዊት
#ሥላሴ
#መድኃኒዓለም
#እግዚአብሔርአብ
#የአቡነጴጥሮስን
#ዓዲግራት
#ፃድቃኔ_ማርያም
#ልደታ
#ስቅለት
#ሆሳዕና
#ቤተክርስቲያን
#ቅዱስጊዬርጊስ
#ቅዱስዑራኤል
#ተክልዬ
#ኪዳነምህረት
#ቅዱስሩፋኤል
#ቅዱስዩሐንስ
#ማኅሌተ_ጽጌ

Orthodox Wallpaper

27 Sep, 05:37


#የስቅለትምስል