ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie @abaynehkassie Channel on Telegram

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

@abaynehkassie


ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ማናቸውም አሳቦች ሁሉ ዕይታዬን የማቀርብበት መድረክ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie (Amharic)

አዲስ ቋንቋና ህጻናት ለማድረግ እና ስነ-ምግባር እየተገኙት ሰላም! የዚህ ትግል ተብሏል እና እንዴት እንደ ደኅንነትህ ቀላልና ሰነድ ያለውን አከባቢ በመስራት ማህበረሰብ ለመመልከት ማህበረሰብና ስርዓት ታሪክ ከመሳሪያው ማህበረሰብ በላይ እና ትምህርት ከመላክ ነፃነትዎች ለምን ቈጥሮአል፣ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ማናቸውም አሳቦች ሁሉ ዕይታዬን የማቀርብበት መድረክ። እስከሐምሌ 30 ቀን ለቅዱሳንና ስደተኞቹ እንዲህ ልንጥሩን እንጥል፡፡ #አቃቤ #ኤፌሶፍያስቱም

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

18 Jan, 13:02


የቅዱስ ዮሐንስ ምሥክርነት

"እኔስ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ፣ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።"

ሉቃ ፫: ፲፮።

እንኳን ለበዓለ ከተራ ወጥምቀተ እግዚእ አደረሳችሁ❗️❗️❗️

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

18 Jan, 11:30


ባሕር ዳር ዳር ዳሩን ወደ አቡነ ሐራ ግድም . . . ጎንደር ዳር ዳሩን ወደ አንገረብ ማረሚያ ወደ መገጭ ግድም . . .

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

14 Jan, 15:09


ጃውሳው: ካሣ ፣
ከቱርክ: ይዋጋል: እንኳን: ከአንካሳ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

14 Jan, 13:04


ወዴት ወዴት

በእኛ ዘመን የተነሣው አንድ ላይ ጠጥቶ ሰባት አፍ ያለው ሳይኾን አንድ ኾኖ የሰባት ጠጥቶ ሰባት ምላስ የሚያወናጭፍ ጉድ ነው።

መጽሐፉም የስድብም ስሞች የሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ያሉበት ቀይ አውሬ ይላል። ራዕይ ፲፯: ፫። በአንድ አንገት ሰባት ራስ ሰባት ምላስ።

አዝማሪም፣ እረኛም፣ አልቃሽም፣ ጠንቋይም . . . ሰባትም ዘጠኝም። አቤት ሱጢ ሉጢ አወይ አለማፈር !

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

13 Jan, 11:10


አቡኑ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

09 Jan, 17:42


"ሰው ምን ይለኛል?" ክርስቶሳዊት ጥበብ


አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያትን "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ የጠየቃቸው የሚባለውን ስላላወቀ አይደለም። በባሕርዪው ማዕምረ ኅቡዓት (የሚሰወረው የሌለ) ነውና። የሚወራው ወሬ ይኽ ብቻ ስለነበረ አይደለም። መርጦ ነው። የተወራውን ሁሉ ፍርስርሱን ማውጣት ሲቻለው ጌታችን "እንዴት እንዲህ ይሉኛል?" በማለት ያባከነው ጊዜ የለም። ዓላማው በሚናፈሰው የሐሰት ወሬ ሐዋርያቱ እንዳይናወጡ ማጽናት ነበረ። ለዚህም እንጅ ነው "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ብሎ የጠየቃቸው።

መልሱን በትክክል በከፍታ የተናገረው ቅዱስ ጴጥሮስ በፈጣሪው ሹመት፣ ቡራኬ፣ እና ውዳሴ ተንበሽብሿል። በዚህም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እምነት አጽንቶበታል። መሪነታቸው ከምድር ወደ ሰማይ የሚወስድ የሥልጣን ዘውድ እንደጫነ ገልጦላቸዋል።

የፋኖ መሪዎች ብዙ ስም ሊሰጣቸው ይችላል። በዚህ ማዘን መተከዝ ወይም መቆዘም የለባቸውም። "ለምን እንዲህ ተባልሁ?" ብሎ ጥርስ ማፋጨት ቡጢ መጨበጥ አያስፈልግም። ይልቁንም ርግማኑን ወደ በረከት የሚለውጡበት ዕድል አድርገው ሊጠቀሙበት ይገባል። የውጭው ወሬ የውስጡን እንዳያብጠው ለማጽናት መጠቀም።

ጌታችን ክብር ምስጋና ይግባውና ዓለሙ በነቢያት ደረጃ ዝቅ አድርጎ እንደሚመለከተው እያወቀ ከደቀ መዛሙርቱ አንደበት ከውስጥ መልሶ ሰማው። በሀሜት ጉዳይ ላይ ከውጭው ይልቅ የውስጡ መሠረታዊ ነው። እርሱም ሰምቶ በሉ ሒዱና ክርስቶስስ የጠራችኋቸው ቅዱሳን ፈጣሪ ነው በሉ አላላቸውም። ጉዳዩን ወደ ውስጥ ነው ያመጣው። ከጸኑ በኋላ እስከሞት በጸና ተጋድሎ ስለ እግዚአብሔርነቱ መሠከሩ። ያስቆማቸው ዘንድ የቻለ ምድራዊ ኃይል አልተገኘም።

በወሬ የሚፈታ አመራርም ተመሪም እንዳይኖር በውጭ የሚወራውን እንደ ዕድል ይዞ በውስጥ ቤት ዘግቶ መምከር ይገባል። ወሬውን ኹሉ መናቅ አያስፈልግም። ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይሉ የለ እነዚያ ጉምቱዎች። ከወሬዎች ኹሉ መርጦ መነጋገር። ግን ለወሬው መልስ በመስጠት መድከም አያስፈልግም። ወሬው ልክ ከኾነ ለማረም መዘጋጀት። ልክ ካልኾነ ደግሞ የውስጡን አሳምኖ ማጽናት።

በዚህም

፩. የመረጃ ፍሰት ሥርዓት መዘርጋት፣

፪. ምስጢር አጠባበቅ፣

፫. አንድነትን በየጊዜው ማጽናት . . . ላይ በትኩረት መወያየት።

ስልክ እና ኢንተርኔት ያለው ኹሉ መረጃ ሰጪ መኾኑ መቆም አለበት ባይ ነኝ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

07 Jan, 20:30


ብዙ ትውልድ ወደ ቤተ ልሔም እየገባ ነው። ጋጣውንም እያወቀ ነው። በዚህ ደስ ይበለን፣ እግዚአብሔርንም እናመስግን!

አዘጋጆቹንም ያበርታልን። ከዚህ ይልቅ በሰፊ ቦታ እናየው ዘንድ እንናፍቃለን።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

07 Jan, 03:26


እርሱ ኹለት ልደታትን ተወለደ። ከዓለም አስቀድሞ መቅደም መቀዳደም ሳይኖርበት ከባሕርይ አባቱ ከአብ ቀዳማዊ ልደትን። ኋላም ከቅድስት እናቱ ከድንግል ማርያም ያለ ዘርዐ ብእሲ ተወለደ። እነዚህን ልደቶች ስለምናምን የኹለት ልደት ተከታዮች እንባላለን።

እኛም እንዳንቀና ኹለት ልደትን ሰጠን። ከእናታችን ማኅፀን በሥጋ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ በጸጋ።

እንኳን ለልደተ እግዚእነ አደረሳችሁ !!!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

06 Jan, 16:26


በተለይ በተለይ

በማይመች ኹኔታ ኾናችሁ ስለ እውነት መራራ ዋጋ እየከፈላችሁ ለምትጎሳቆሉ የጭንቅ ቀን ቆራጦች የጨለማ ጊዜ ብርሃኖች፣ በሰው ሠራሽ ረሃብ ለምትሰቃዩ የሀገር ልጆች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

01 Jan, 13:42


በጊዜ ለጊዜህ የተወለድህ አሸናፊ ሰው ነህ። ጊዜው ሲፈልግህ የተገኘህ ምርጥ ሰው። ጊዜውን ለመዋጀት አብረውህ የነበሩ ደከማቸውና ጠላት ኾኑብህ። አንተ ግን እንደጸናህ አለህ!

መልካም ልደት !!!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

24 Dec, 21:39


የዛሬ አሳሪዎች በሕይወት ከተረፋችሁ የነገ ታሳሪዎች መኾናችሁን አትርሱ

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

24 Dec, 12:21


ክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧ ያለው ሆይ

በእናንተ ስቃይ ሰይጣን እና ያሰሯችሁ ጭራቆች ይደሰታሉ። እግዚአብሔር እና ሕዝብ ደግሞ ከጎናችሁ ቆመዋል።

ጭራቅነት ከተጣባቸው አውሬዎች ጋር የሚታገል ንጹሕ ሕሊና የታደላችሁ፤ ይኽ እንደሚመጣ ቀድማችሁ እያወቃችሁ የተጋፈጣችሁ የታሪክ ፈርጦች ናችሁ። የሚፈስሰው ደማችሁ የነፃነታችሁ ሸማ የሚሸመንበት ድርና ማግ ነውና አይዟችሁ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

18 Dec, 14:01


ህምምምም !

ይኽ ጥበበኛ ሕዝብ በሜዳህ ለሌላ ይጫወታል አላልኩህም?

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

17 Dec, 16:23


ይኽ ሕዝብ መለኛ መኾኑን አትርሳ። አስገድደህ ሰልፍ ልታስወጣው ትችላለህ። ነገር ግን በሜዳህ በአንተ ማልያ ለሌላ ተጫውቶ ድል ያደርግሃል።

"ትናንት ለቲሸርት ዛሬ ለነፃነት" ያለ መለኛ ሕዝብ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

12 Dec, 17:15


ስለ አንድነት ሽው የሚለው ነፋስ ተስፋ ያለመልማል። ጸሎት ይታከልበት።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

12 Dec, 14:32


እንደ ጽርሐ አርያም እንደ መንበረ ፀባዖት የሰፋችው ታላቋ መቅደስ ወደ ታናሿ መቅደስ በትሕትና ደግሞ በተለየ ክብር የገባችበት በዓል።

መደነቅ ብቻ!

እንኳን ለበዓታ ለማርያም አደረሳችሁ !!!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

10 Dec, 17:17


ትኩረት ለአንድነት !

ነጣጣይ ከፋፋይ ዐሳቦችን ከመሰንዘር መቆጠብ የወቅቱ አስቸኳይ መልእክት ነው።

ይኽ ቋንቋ ለማይገባቸው አንጨነቅም።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

07 Dec, 02:11


የሚለምኑትን ከየጎዳናው አንሥቶ አንሥቶ እርሱ በእነርሱ ፋንታ ለማኝ ኾነ። እነርሱን አክብሮ እርሱ ተዋረደ። የሚቀበለው ሊያቀብላቸው ነው። እርሱን ሳይኾን ተቋሙን እንርዳ! እርሱን መርዳት የሚቻለው አንድ አምላክ ብቻ ነው። ይርዳልን!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

06 Dec, 17:03


አንዱ የድል ዜና ዐረፍተ ነገር ተነግሮ ከአፋችን ጨርሶ ሳይወጣ ወይ ተጽፎ ሳይጠናቀቅ ሌሎች ተደራራቢ ድሎች ይመዘገባሉ። ከምንም ተነሥቶ በዱባይና በቻይና ብድር፣ በቱርክ ድሮን፣ በጠንቋይ "ትንቢት እና ጸሎት" የሚታገዝን ብልጽግና ሽምድምዱን ያወጣው ፋኖ ተአምራዊ ክስተት ከመባል በቀር በምን ይገለጻል።

በወሎ በጎጃም በሸዋ በጎንደር እየተሠሩ ያሉ የጀግንነት ጀብዱዎች በስንት ታሪክ ዘጋቢዎች ተጽፈው ይዘለቁ ይኾን?

በርቱ [ከእግዚአብሔር በታች] እናንት የኢትዮጵያ ተስፋዎች!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

05 Dec, 23:25


ይኽ ትውልድ ሳያሸንፍ አይመለስም - የማይቀለበስ እውነት!

አሜሪካዊቷ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ኹለት የሴት አርበኞችን አነጋግራ የጻፈችውን ተመልከቱ።

ኹለቱም ጠመንጃቸውን ከእጃቸው ሳይነጥሉ ያወጉኛል። ላስታ እንዲህ አለችኝ። "ጉራ አይደለም። በብዛት እየረገፉ ያሉት የጠላት ተዋጊዎች ናቸው።

ሁል ጊዜም ርብትብቶች እና ፍርሃት ውስጥ ናቸው። በቁጥር በጣም ብዙ ናቸው። ግን ውጤታማ አይደሉም። ዕውር ድንብራቸውን ይተኩሳሉ። ከመካከላቸው ዐማራዎች ይገኛሉ። እነርሱ ሊዋጉን አይፈልጉም።

ፈንታ በአንድ ጦርነት ሆዷ ላይ በጥይት ተመትታ ነበር። ያኔ ከጋራ ላይ ተንከባልላም ወድቃ ነበር። በጣም ተቆጥቼ ስለነበር ቁስሌን አላዳመጥሁትም።" አሉኝ ስትል የኒው ዮርክ ታይምስ ዓምደኛዋ አሌክሲስ ኦኬዎ ጽፋለች።

ባለ ፎቶዎቹ ፋኖዎች በስተግራ መቅደስ በስተቀኝ ትኹኔ ይባላሉ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

04 Dec, 23:39


አያ ሱጢ ሉጢ፣

የታሪክ የትርክት በረከት ቀሳጢ፣

ባለጌ አሚነ ቀሚስ ሰጣጢ፣

ርጉም ከመ ጳውሎስ ሳምሳጢ፣

የክሕደት ሾተላይ አባ ምላስ ሰንጢ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

03 Dec, 14:50


የሱጢ ሉጢ ምስክርነት

ማሳሰቢያ:- ይኽ ስለ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወይም ከምንወድዳቸው ቅዱሳን ለአንዱ የተነገረ እንዳይመስላችሁ።

"ሥጋና ደም የሚሠራው ሥራ አይደለም ይሄ። ሥራቸውን ከጨረሱ እግዚአብሔር በቃ ሩጫህን ጨርሰሃል ከዚህ በኋላ ሃይማኖትህን ጠብቀሃል የድል አክሊል ተዘጋጅቶልሃል ብሎ ነው የወሰዳቸው። በቃ ለተልእኮ የመጡ ሰው ናቸው።

መንፈስ ቅዱስ የሚረዳው ሰው ብቻ የሚሠራው ሥራ ነው።

እንደዚህ ያሉ ሰዎች እግዚአብሔር ባያስነሣ ኖሮ እንደ ሰዶም እንደ ገሞራ በኾንን ነበር ከሚባልላቸው ሰዎች አንዱ ናቸው።"

አይ ሱጢ ሉጢ በዚህ አያያዝማ መልክአ ሳጥናኤል is loading

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

03 Dec, 11:57


ሱጢ ሉጢ

ሱጢ ሉጢ የራሷ እውነት የራሷ እምነት የላትም። ለእርሷ እምነትም እውነትም መድረክ ነው። እንደቆመችበት መድረክ እውነቷም እምነቷም ይገለባበጣል። የቆመችበት መድረክ ጠላት ጠላቷ ያጨበጨቡላት እጆች ወዳጇ። ተቅበዝባዥ ናት። አንድ ጌታ የሌላት የመድረክ ሞቅታ ያቀነዘራት ጽኑ ታማሚ ናት። መክለፍለፍ ያንንም ያንንም መቀማመስ ትወድዳለች። መረጋጋት የሚባል ተነሥቷታል።

ሲላት መሲሕ ትቀይራለች። ሲላት አቋም ትለውጣለች። ታሪክ ትቀስጣለች። ሲላት እውነት ትሸጣለች። ባቢሎንን ጽዮን ትላለች። ሲሞናዊት የመንፈስ ቅዱስ ሻጭ ለዋጭ ናት። "መዝገበ ቃላት መጻፍ የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው። ሥጋና ደም አይሠራውም። ሟችም የድል አክሊል ተቀዳጅተዋል።" ኧረ ምኑ ቅጡ።

ሱጢ ሉጢ ኀፊረ ገጽ የተወሰደባት ፈጣጣ አጭበርባሪ በመኾን ገጽታዋን ገንብታለች። የመንፈስ ቅዱስን ሥራ እኛ መች አጣነው።


ምን አለፋችሁ ሱጢ ሉጢ ሟች ሆይ አማልደኝ ሳትል ጊዜ አለቀባት።

አንቺ ሱጢ ሉጢ መቅለብለብሽ በዛ፣
እዚያም እዚያም ስትይ ጎመንሽ ጠነዛ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

30 Nov, 15:14


የታቦት አገልግሎት ከምድር እስከ ሰማይ፣ ከሰማይ እስከ ምድር ነው።

በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ እንዲል።
ራዕይ ፲፩: ፲፱።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

30 Nov, 12:07


የታቦተ ጽዮንም የመስቀልም ማደሪያ ያደረግኸን አምላካችን ክበር ተመስገን!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

24 Nov, 23:26


. . . (የቀጠለ)

፪ኛው ስደት በ፫፻፴፪ (332) ዓ.ም. ወደ ሮም ለ፯ ዓመታት ነው።

በ፫ኛው ስደቱ ነበረ ወደ ገዳም የተሰደደው ይኽም በ፫፻፵፰ (348) ዓ.ም. ነው። ይኽንን እውነት አዛብቶ ማቅረብ ታሪክ (ይልቁንም ነገረ ቤተ ክርስቲያን) ምን ያኽል አደጋ ላይ እንደወደቀ ያሳያል። "ቤተ መንግሥቱ" ለትርክቱ እስከተመቸው ድረስ ሰውን ብቻ ሳይኾን ታሪክንም ለመጨፍለቅ ያለውን ጭካኔ ያሳያል።

ስለ ዕርቀ ሰላሙም የፈጠራ ነገሮች እንደ ክረምት አግቢ ሲፈለፈሉ ሰምቻለሁ። ቢያንስ በሕይወት እያለን ቅጥፈትን አንብረን አናልፍምና እመለስበታለሁ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

24 Nov, 23:25


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ለመውቀስ የሐሰት ታሪክ መጥቀስ

ከጠሚሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ አንደበት ቅዱስ አትናቴዎስ ፲፭ ጊዜ ተሰደደ የሚል ሐሰት በዐደባባይ ተነግሯል። በዚያ ላይ ተደራቢ ውሸትም ተደርቶበታል። እርሱም መጀመሪያ ሲሰደድ ወደ ገዳም ነው የተሰደደው መባሉ ነው። ይኽም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በደረሰባቸው ፖለቲካዊ ጫና መሰደዳቸውን ለመኮነን ሲባል የተነገረ የድፍረት ሐሰት ነው። ምንም ዓይነት ጫና ቢደረግባቸው እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ ወደ ገዳም እንጅ ወደ ውጭ መሰደዳቸው ልክ አይደለም ለማለት።

"ቅዱስ አትናቴዎስ መጀመሪያ ወደ ገዳም ከተሰደደ በኋላ ከገዳሙ ድረስ ፈተናው ቢከተለው ከሀገር ወጥቶ ተሰደደ። እርሳቸውም ገዳሙን ሞክረው ኹለተኛውን እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ ሊያደርጉ ይገባ ነበር" የሚል ልበወለድ ባልተገራ አንደበት ትሕትና በጎደለው መልኩ የታሪክ ዘረፋ በፀሐይ በጉባይ ተፈጽሟል። እውነታው ግን ቅዱስ አትናቴዎስ ወደ ገዳም የተሰደደው በሦስተኛው ስደቱ እንጅ በመጀመሪያው አልነበረም።

ቅዱስ አትናቴዎስ በ፬ የሮማን ኢምፓየር ነገሥታት ዘመነ ሥልጣን ለ፲፯ (17) ዓመታት በስደት የኖረ የእስክንድሪያ ፓትርያርክ ነው። በእነዚህ ፲፯ ዓመታት ውስጥ ፭ ጊዜ ለስደት ተዳርጓል።

ቅዱስ አትናቴዎስ በመጀመሪያ ከመንበሩ የተሰደደው ወደ ፈረንሳይ ትሬቬዝ በ፫፻፳፰ (328) ዓ.ም. ነበረ። ከ፪ ዓመታት ስደት በኋላ ተመለሰ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

24 Nov, 02:00


ሀገር እንደተሸከሙ የማያውቁ ባለ ሀገሮች - ገራገሮች

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

23 Nov, 04:18


ፋኖ ከጭንቅ ባዳነ ጊዜ ስሙና ትርጉሙ እንዲህ ነበረ። በተከዳ ጊዜ ምንም ቢሉ አይገርምም።

ፋኖ በሞራል ልዕልና ከቤተ መንግሥቱ ጭራቅና ከአጫዋቹ የቃጭል ሙዳይ እጅግ በከፍታ ላይ ይገኛል።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

21 Nov, 18:43


በክርስቶስ ስም እንኳ ሳይቀር ሰይጣን ይመጣል። ክርስቶስ እንዲጠላ ብዙ ክፉና መጥፎ ጭካኔ የተሞላበት የነውር ሥራ በዐደባባይ ያደርጋል። በፋኖ ስም ደግሞ ብልጽግና ያርዳል።

That is it!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

19 Nov, 20:53


ተስፋ ያለው ቀን ከፊታችን አለ። የአንድነት ገመዱ እየጠነከረ ነው። ከዚህ በፊት የተጠረቋቆስናቸውን መርሳት ወይም መተው እንጀምር።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

19 Nov, 18:19


የታላላቆች መንገድ

ይሔዳሉ አይደክሙም። እግዚአብሔር ድካማቸውን ይቁጠርላቸው!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

19 Nov, 14:30


ብዙ ሰው ፈጣን ድል ይፈልጋል። አንድ ኹኑ እያለ ይቃትታል። ከዚህ መኻል ግን አንዳንዱን የኾነ ጎጥ መሳይ ቡድነኝነት ወይም መጥበብ እግር ተወርች ፈጥርቆ ይዞታል። ያለ ማቋረጥ የራሴ ያለውን ሲክብ "ጠላቴ" ያለውን ሲሰድብ ውሎ ያድራል። ከብልጽግና ተከፋዮች በላይ ይኽኛው ይበልጥ ዕረፍት ማጣት ይታይበታል።

አኹን የዐማራ ፋኖ ትግል ኹለተኛ ረድፍ ጠላት እንደዚህ ያለው መንደሬነት ነው። በቅድሚያ መወገድ አለበት። ይኽ ሰፈርተኛ ክፍለ ሀገር ቢሰጠው አውራጃዬ ይላል። አውራጃ ቢሰጠው ወረዳዬ ይላል። ወረዳ ቢሰጠው ቀበሌዬ ይላል። ቀበሌ ቢሰጠው ጎጤ ይልሃል። ጎጡን ብትሰጠው ደሼ ይልሃል። ደሹን ብትሰጠው ጎጆዬ ይልሃል። ከጎጆው ብትገባ እኔ ብቻ ይልሃል። ከራሱ በቀር ለማንም ደንታ የለውም። ይኽ ልክፍት ወይም መጋኛ ነው።

እባካችሁ እኛም የዚህ ልክፍት ተጠቂ ከኾንን ፈጥነን እንውጣ። በሽተኞች ላይም እንዲድኑ ወይም እንዲገለሉ እንጨክን። አንድነት ኑ ወደ እኔ በማለት አይሰምርም። የአንተን ወደሌላው መሔድ ይፈልጋል። ከጎጥ መውጣት!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

19 Nov, 00:57


ጎዳና ያዕቆብ የሚባል እውነት ያዘነበለችለት ሰው አለ። ጥንቱንም ጎዳና ሰፊ እንጅ ጠባብ አይደለም።

+++++

እኔ ብቻ ነኝ ወይስ እናንተም ታዝባቹታል ጎበዝ?

ዛሬ ላይ በሚዲያው መንደር ብትዘዋወሩ
#ፋኖን
ደጋፊውም ተቃዋሚውም...
የትጥቅ ትግል ደጋፊውም ይሁን የሰላም ሰባኪው ተንብኔሉ እንዳለ #ፋኖ እንዲህና #ፋኖ እንደዛ የሚል ሆኖ ስመለከት
#ፋኖ ከአራዊቱ የአብይ አህመድ አገዛዝ ሊታደገን የሚችልና ተስፋ የምናደርግበት ብቸኛ ኃይል መሆኑ ብቻ ሳይሆን የስንቱ የሚዲያ ተመፅዋች የዕለት ጉርስ መሆኑን አስተውላለሁ።

ዛሬ ላይ "የእለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን" ብሎ ከሚፀልየው ይልቅ ጠዋት ከእንቅልፏ ተነስቶ #ፋኖ #ፋኖ #ፋኖ እያለ ከነጥላቻው ርዕስ የሚያሰላስለውና ተንብኔል የሚሰራው ተበራክቶ እንደማየት ደስታን የሚሰጠኝና በተስፋ የሚሞላኝ ነገር የለም!

የሰላም ታጋዩም
ስለ #ማንዴላ ሳይሆን ስለ #ዘመነ_ካሴ...
ስለ #ጋንዲ ሳይሆን ስለ #እስክንድር_ነጋ...
ስለ ሰላማዊ ትግል መማርና ማስተማሩን ትቶ ስለ ፋኖ የትግል ስልትና አደረጃጀት ማውራት የሙሉ ጊዜ ስራው ከሆነ ሰነባብቷል::

ስለ ሰላማዊ የትግል ስልቶች ሊማር የሄደው እኮ ፋኖን ሸምድዶ ነው የሚመለሰው!!!

ወሬው ሁሉ #ፋኖና ስለ #ፋኖ የሆኑ የሰላም ሰባኪያን ግን ቆይ ከአንጀቱ ስለ ሰላማዊ ትግል መማር የሚፈልግ ደቀ-መዝሙር ከናንተ ካልሆነ ስለ ሰላማዊ ትግል ከወዴት ይማር?!

ቢያንስ ቢያንስ ከመቶ አስሩን ጊዜአችሁን ነን ስለምትሉትና አቋም ስለያዛቹበት ነገርም በዝርዝር አውሩ እንጂ!!!

. . . ፋኖ ስንቱን አብልቶ ስንቱን በትከሻው ተሸክሞ እንዳለ እስቲ እንደኔ ዞር ዞር ብላችሁ ተመልከቱና ከተሳሳትኩ አርሙኝ::

ሌላ የሚወራ በአገር በምድሩ አለመኖሩን ሳይ እንደቦረና ፋኖነቴ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል!!!

#ድል_ለፋኖ!!!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

18 Nov, 10:48


አንድነትን አብዝተን እንስበክ!

አደራችሁን!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

18 Nov, 01:39


ፋኖ ታሪክ እንጅ ተረት አይጽፍም። ተመትቶ የተከሰከሰው እኮ ጆፌ አሞራ አይደለም። እንዲህ ማለቃቀስ መነፋረቅ እንጅ ለጉዳዩ የፈጠራ ተረት አይመጥነውም።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

17 Nov, 01:43


አትብሸቁ

የፋኖ የትጥቅ ትግል ፪ ዓመት ሳይሞላው የጦር ሄሊኮፕተር መትቶ መጣሉ አገዛዙን ለማንኮታኮት ብዙ እንደማይፈጅበት በግላጭ ያሳያል። ሰማዩ የእኛ ነው ማለት የሚገባው ማን እንደኾነ ታይቷል።

የተለየ የፈጠራ መሣሪያውን ይፋ ባደረገ በሳምንት ጊዜ ውስጥ የተወሰደ ርምጃ መኾኑ አነጋጋሪነቱን ከፍ አድርጎታል።

ከብልጽግና አመራሮች ይልቅ ተከፋይ አክቲቪስቶቹ እርር ጭስስ ትክን ብለዋል። ምን ብለን እንዋሽ ውሸት አለቀብን በማለት አማርረዋል። የወተት መግዣ ጭማሪም ጠይቀዋል። አትብሸቁ ይልቁንስ አሰላለፋችሁን በጊዜ አስተካክሉ ከምታልቁ። ገና ምን ዐይታችሁ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

16 Nov, 22:51


ጎጥ ይኑር ጎጠኛነት ይክሰር

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

16 Nov, 19:00


ከአንኮበር እስከ ባሕር ዳር

በር እና ዳር

ከእግዜር ፍጥረት በቀር የለ ሌላ 'ሚበር

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

15 Nov, 19:48


በእርግጠኝነት የዚያ ችሎት ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ግድግዳዎች፣ ጣሪያ፣ መስኮት እና በሮች በዚህ ቀን የሰሙት እንግዳ ኾኖባቸዋል።

ሌላ ጊዜ ከተከሳሾች የሚሰሙት የተማኅፅኖ፣ የልመናና የለቅሶ ሲቃ ነበር። ሰሞኑን ግን ልበ ሙሉዎች፣ የእሳት ትንታጎች፣ ታሪክ የሚመስሉ ግን ሕያዋን ሰዎች በጥብዐት የተፈጸመባቸውን መንግሥታዊ ሽብር ዳኞቹ ምን መጣብን እስኪሉ አንበልብለውላቸዋል።

አንድ ምስክር ላምጣ። መንበረ ዓለሙን

"ፋሺስታዊ የኾነውን ሥርዓት በሚቃወመው የፖለቲካ አመለካከቴ፣

ዐማራዊ በኾነው ማንነቴ እና ሕያዋን በኾኑት አባቶቼ አጤ ምኒልክ እና ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ስም ምዬ የምነግራችሁ በግልም ኾነ በቡድን ፈጽመሀል የተባልኹትን ወንጀል አልፈጸምኹም።

ወንጀሌ ዐማራ ኾኜ መወለዴ እና የዐማራን ዘር ማጽዳት መቃወሜ ብቻ ነው። ይኼን ደግሞ ቀጣይም እስከ መጨረሻዋ እስትንፋሴ የማደርገው ነው። ለታሪክ ይመዝገብልኝ አመሰግናለሁ።"

ኅዳር ፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

14 Nov, 22:04


እኛ የምናውቃት ሙንጣዝ ወይ ባንዳ ናት ወይ ጠውላጋ፣ ዐቅመ ቢስ፣ ለዋሳ ናት።

ጣልያን ወደ ኤርትራ በገባ ጊዜ ከእኛው ሰዎች መካከል ጨው እያላሰ ሙንጣዝ፣ ቡልቅ ባሻ እና ባሻ ብዙቅ እያለ በመሾም ወገንን ከወገኑ አለያይቶ አፋጅቷል። እነዚያ ባንዳዎች ከሚጠሩበት አንዱ ሙንጣዝ የሚል ይገኝበታል።

ምናልባትም ባንዳነትን የሚያነውረው ማኅበረሰባችን ለባንዳዎች የሚታደለውን ሙንጣዝነት ከመጠየፍ ሳይኾን አይቀርም ሰላላ፣ መንማና፣ ጠውላጋ የኾነን ሰው ሙንጣዝ ብሎ ያጠይፋል።

የዛሬዋ ሙንጣዝ ግን ቤተ መንግሥት ስትገባ ሥራዋን ቀየረች። ባንዳነቴን እርሱልኝ ባይኾን የሹም ዶሮ ነኝ እንደማለት አለች። ሙንጣዝ ሸፍታም ጀግናም አታውቅም።

+ + +
በነገራችን ላይ:-
ትርጉሙን ባላውቀውም በሙስሊሙ አካባቢ ደግሞ ሙንጣዝ በሚል ስም የሚጠሩ መኖራቸውን ዐውቃለሁ። ከላይ የተጻፈው እነርሱን አይመለከትም።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

14 Nov, 20:25


"የኢትዮጵያ ሕዝብ የዐማራ ሕዝብ ዕንባ [እና ደም] በዋንጫ ቢሰጣቸዉ የማይጎፈንናቸዉን የብልጽግና ሥርዓት ቁንጮዎች በቃችሁ ሊላቸዉ ይገባል።"


ዶ/ር ወንድወሠን አሰፋ

ዛሬ በፍርድ ቤት የቀረበበትን የፈጠራ ክስ ሲቃወም የተናገረው።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

13 Nov, 19:27


"የሞተች አንድ እናቴ ናት። በሚልዮን የሚቆጠሩ እናቶች ግን አሉኝ። ለእነዚህ እናቶች ነፃነት ትግሌ ለአፍታም ቢኾን አይቆምም።"

አርበኛ የቆየ ሞላ
የዐማራ ፋኖ በጎጃም የቀጠና ትስስር መምሪያ ኃላፊ

ዛሬ መንኛለሁ ያለው ኹሉ "እናቴ ሞተችብኝ" እያለ (ከመነኮስ እስከ ጳጳስ) ከምናኔው ሕግ እየሾለከ ለቅሶ ድረሱኝ በሚልበት ፋኖው ግን የእናቴ ሞት ከምናኔዬ አያናጥበኝም ሲል መስማት ዕድለኛነት መስሎ ይሰማኛል።

የእማማን ነፍስ በአፀደ ገነት ያሳርፍልን! አንተን ግን በዓላማህ ጸንተህ በአጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ተጽናንተሃልና ያጽናህ አልልህም። ክበርልኝ ወንድሜዋ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

13 Nov, 17:48


ከልቡናቸው አንቅተው በጣቶቻቸው ብርዕ ጽፈው ደማቅ ጎላ ጀነን ያለ ድምፅ የሚያሰሙት ጫካ ናቸው። የሰው ጽሑፍ ቀስጠው አስቀስጠው ከተሳካላቸው አስጽፈው እንደ ቲያትረኛ አጥንተው የሚያነበንቡት ግን ቤተ መንግሥት። ሲገላበጥ ልክ ይኾናል።

በዘመነ የበጋ መብረቅ የተነሣ ከወደቁበት ትራኦማ ሳይነቁ እስኬ በአናቱ ደረገመባቸው። እስኪ እንደፈረደባችሁ ቀኗን ቀስጡና ጥቂት አዝናኑነ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

13 Nov, 08:58


ፍርሃት ጭንቀት ለሌለባችሁ ብቻ!

ቀኑን ብትፈልጉ ፲ ዓመት ቀሽባችሁ በፎቶ ሾፕ ወደ ኋላ ጎትቱት። ቨርቹዋል ገዳዮች ተዋርዳችኋል!!!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

12 Nov, 14:21


የጃውሳው ካሣ ልጆች

ጋፋትን በተግባር - የኾኑ እሳት ነገር።

ማርከውም አምርተውም የሚታጠቁ
ዐዳዲስ ትውልድ በጣም የነቁ
እኒህ ጥበበኞች እያለፉ ሳቁ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

12 Nov, 12:36


የቅዱሳንም የሊቃውንትም ነቅዕ ዲማ (ድማኅ ራስ እንዲለው) ከመጠቃቱ ይልቅ ነገረ አድግ የሚያብከነክናቸው የአህያ ሥጋ አለመበላቱ የቆጫቸው ሲርመሰመሱ የተፈጠፈጥንበትን ቁልቁለት ያሳያል።

በነገራችን ላይ እንደዚህ ያለው ነገር ጥቅስ አያስጠቅስም። ካመኑበት ነቀላውን ይዘው መዘንጠል ነው ያለባቸው። ይኽን ካልበላችሁ ብሎ ስብከት የለም።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

11 Nov, 14:54


ሠናይ እገሪሆሙ - እግሮቻቸው ያማሩ ናቸው!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

11 Nov, 10:16


ያለህ አማራጭ አንድ ብቻ ያውም መሻገር!

ይኽ ትውልድ ጨክኖና ቆርጦ ተነሥቷል። ከግቡ ሳይደርስ ምንም አያቆመውም።

ከታች እየተገማሸረ የሚወርደው በዓለም እጅግ ቁጡ የሚባለው የዓባይ አዞ (Nile crocodile) የሚርመሰመስበት ረጅሙ ወንዝ ነው። በዚኽች ቀጭን ገመድ ሲሻገር ሳት ካለው ከታች አንድም በፈጣን ሩጫው ተምዘግዛጊው ማዕበል አንድም በወንዙ ዳር እስከ ዳር የሾለ ጥርስ ያለው ጥቁር ዓለት አንድም በስል ጥርሶቹ ቀርጥፎ የሚውጣው ቁጡው አዞ ይጠብቁታል። ያለህ አማራጭ አንድ ብቻ ያውም መሻገር!

የተጀመረው ትግል በመከራ የተከበበ በሤራ ትብትብ የተጎነጎነ ቢኾንም አማራጩ ማሸነፍ ብቻ ነው።

ጥንቅቅ ብለህ በብቃት ካልሠለጠንህ ጭራሽ አትሞክረውም። ትጥቁን ሸብ አድርጎ ተራመደዋ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

06 Nov, 17:54


ይበቃል!!!

የዐማራን ማንነት ታሪክ እና ወግ በሚመጥን ደረጃ ልዩነቶች ካሉንም ለመፍታት እንወሥን። መተቻቸት ቢያስፈልግም በጥዩፍ ቃል መሸነቋቆጡ አይበጅም። ተጋድሎውን ባያቆመው እንኳ ይጎትተዋል።

አኹን አንድ መኾንን እንናፍቅ። ከፊት ያለውን ጎልያድ ረስተን ጠጠሮቻችንን ወደ ጎን በማፈናጠር ጊዜም ጉልበትም ሀብትም አናባክን።

እንደዚህ የሚያደርጉት ኹሉ ቃላችንን ሰምተው ከአኹን ጀምሮ ያቆሙ ዘንድ እንጣራለን።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

06 Nov, 12:56


እግዚአብሔር አብ ኢየሱስ ክርስቶስን ልጄ ቢለው በባሕርይ፣ በሕልውና፣ በሥልጣን ይተካከለዋል ብለን መጠጊያ እናገኛለን።

እመቤታችን ፈጣሪዋን ልጄ ስትለው ግን በምን ዐቅም እንረዳው ዘንድ እንችላለን? ከዕውቀት ባሕር ብንጠልቅ ከምስጢር ጠፈር ብንከንፍ አንደርስበትም።

የበረዶውን ንጣፍ እሳተ ገሞራ፣ የውቅያኖሱን ውኃ እሳት የሚያደርገው፤ በነበልባል መጋረጃ የሚሰወረው እርሱ እናቴ ሲላት ስንሰማ ልባችን በመደነቅ ነፋስ ትወሰዳለች። በመስቀል ዙፋን ላይ ኾኖ አባቱን የጠራ ወልድ እናቱንም እዚያው በተቸነከረበት ይጠራታል።

ስለ እመቤታችን ያስተማረን እርሱ ራሱ እግዚአብሔር አይደለምን? በዓለ መድኃኔዓለምን ስናከብር የምንሰማው ድምፅ እንደዚህ ያለ ነው። እንኳን አደረሳችሁ!!!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

01 Nov, 20:01


በመስከረም ኩልል ካለ ምንጭ ጥርት ካለ ውኃ ጥምም አምሮትም ይከላል። በመስከረም የፀሐይ ስስ ሙቀቷን እንደ ቀጭን ኩታ እንለብሳለን። ምጥን ብርሃኗን ሳቂታ ገጿን በዐይን ሙሉ እናያለን። ከምድር ፍሬ በረከት ከእሸትም እሸት ጠብሰንም ፈልፍለንም አሽተንም እንመገባለን። በንቦች ዜማ ታጅበን የአበቦችን መዓዛ እንደ እናት ጣት በሚዳብስ በልስልስ ነፋስ እየታወድን እንመገምጋለን። ጥፋት ካለባት እንዲኽ መኾኗ ነው።

ስለዚህም መስከረምን እንወዳታለን። ትመጫለሽ መስከረም!!!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

31 Oct, 18:24


በተለይ:-
የተጠቃ ሽዌነት፣
የተጠቃ ወሎዬነት፣
የተጠቃ ጎንደሬነት፣
የተጠቃ ጎጃሜነት የለም።

ጥቃት የተፈጸመው ዐማራነት ላይ ነው። አይሻ ስትጠቃ የተጠቃው ጎጃምም፣ ጎንደርም፣ ወሎም፣ ሸዋም እንጅ አንዱ ብቻ ወይም በከፊል አይደለም።

ለዚህም ነው:-
አንድ ፋኖ የምንለው።

ቤት ዘግተን እንምከር!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

31 Oct, 02:43


ሰሞኑን በማነሣሣቸው አቀራራቢ መልእክቶች ከሚደርሱኝ ግብረ መልስ መካከል "እንደተከበርክ ብትቆይ አይሻልም? ከከፍታህ ወረድህ ወይ አትውረድ . . ." የመሳሰሉ ይገኙበታል።

አትውረድ ለምትሉኝ እኔ ከፍታ ላይ አይደለኹም። ኹልጊዜ ታች ነኝ። ካልወጣኹ ወደየት እወርዳለሁ? ከምትሉት ማማ ወጥቼ አላውቅም። ከፍ ባለው ስፍራ ሌላ ሰው ዐይታችሁ ይኾናል። ከፍታን እፈራዋለሁ። አልመኘውም። ልኬንም ዐውቀዋለሁ። እኔ የማውቀው ከታች መኾኔን ብቻ ነው እና አትጨነቁ!

ግን የዐማራን የሕልውና ትግል ከግቡ ለማድረስ ከዚህም በላይ መውረድ ካለብኝ በብዙ እወርድለታለሁ። ተቹኝ ግን ደግፉኝ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

30 Oct, 17:27


እናንተስ ከዐማራ ሳይበር ሠራዊትም በላይ ናችሁ።

You are beyond Amhara cyber army.

በርቱ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

30 Oct, 12:34


የአሳብ ልዩነት አለ ማለት ለመፈጃጀት መፈላለግ አይደለም። [ያውም በቅንነት በመነጋገር የሚፈታ] በእርግጠኝነት የእስክንድርን ሞት ዘመነ አይሻውም። በዚያው ልክ የዘመነንም ሞት እስክንድር አይሻውም። ቢኾን ኖሮ የተመቹ ጊዜዎች ነበሩ።

አኹን በደጋፊ እና ነቃፊ ጎራ የተሰለፍነው ነን ያስቸገርን። አያያዛችን ከድሮን በላይ ትግሉን ይጎትታል። ልብ ያደክማል። መረጃ አለኝ የሚለው ብዛቱ። ካላችሁም ለምጣዱ ሲባል በሚለው እየመዘንን ዱላውን እናቅበው።

ተግ እንበል!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

30 Oct, 02:59


ጊዜው የአንድነት ነው!

ቅዱስ ጴጥሮስ "ሒድ አንተ ሰይጣን" የተባለበት ጊዜ አለ። ያውም ከፈጣሪው፣ ደግሞም ተከተለኝ ብሎ ከጠራው ጌታ አንደበት በወጣ ቃል። ሐዋርያው ተሰደብኩ ብሎ አልተከፋም። ጥዬ ልሒድ ብሎ አልተነጠለም። ተገፋሁ ብሎ እዩልኝ ስሙልኝ ያዙኝ ልቀቁኝ አላቅሱኝም አላለም። እንዲያውም እስከ መጨረሻው ታመነ እንጅ። ጭራሽ በዘመነ ዕርግና ቁልቁል እስከመሰቀል ደረሰ።

ለምን? ካልን የተናገረው ጌታ ለምን እንደተናገረ ስለተረዳ ነው። ተግሣጹ ውስጥ ፍቅር አለበት። በፍቅር በተገነባ ቅርርብ ውስጥ ቃላት የሚሰጣቸው ግምት በጣም እጅግ በጣም ትንሽ ነው። ፍቅር ከሰማያት የሚያልፍ መግባቢያ ቋንቋ ነው። እርሱን የሚያስረዳ ቃል ያልተገኘውም ቋንቋ ከፍቅር ኃያልነት አንጻር ዐቅመ ቢስ በመኾኑ ነው። በፍቅር የሚነገር ቃል ኹሉ ርቱዕ ትርጉም ይሰጠዋል እንጅ በተለምዶ በሚታወቀው አይወሰድም። እናት ልጇን "አንተ እንትን" ስትለው አስቡት። ፍቅር ናትና በአሉታ አይያዝባትም።

የምር ወንድማማችነት ካለ ንግግሮች አያለያዩም። አፈትልከውም፣ በስሜታዊነት ወይም በግብታዊነት ወይም በመድረክ ሞቅታ አንዳንዴም በስሕተት የሚነገሩትን ኹሉ ይዘን በቃላት መረሻሸኑ ይቁም። እገሌ እንዲህ ያለው እገሌን ነው እያልን አናራግብ። ጎራ ለይተን አንነታረክ። የሚያባብሱትን እንገሥጽ። የከፈትናቸው ሚድያዎች፣ ስፔሶች፣ ቲክቶኮች አንድነትን ይስበኩ!

የአይሻ ሕመም ያላመመው የለም። ያ ስቃይዋ እንዳይደገም ዘገር ነቅንቆ የወጣ ፋኖ ዛሬ የበርካታ ድል ባለቤት ኾኗል። ብልጽግናን አሽመድምዶታል። በዘመዴ አባባል ወገብ ዛላው ተቀንጥሷል። ከመጨነቁ ብዛት ነጋ ጠባ ፋኖን የማጥፋት ስትራቴጂ ይነድፋል። እጅግ ከፍተኛ በጀት መድቦ በብድር ትራስ የድሮን ገበያውን አጨናንቆ ይራወጣል። በኹለት ሳምንት ድራሹ ይጠፋል ብሎ የፎከረበትን ጥርብ ጭንቅላት ተሸክሞ ዘጥ ዘጥ ውስጥ ተነክሯል።

ታዲያ በዚህ መኻል እንዴት አንድነት ይርቃል? መነሻችሁ አንድ እንዳደረጋችሁ ድላችሁም አንድ ያደርጋችኋል። ወንድም ጥላ ወንድም ጋሼ ወንድም ዓለም ያባብላችኋል።

ለተነገሩት ኹሉ ይቅርታ እንጠይቅ። ይቅርታም እናድርግ። ጊዜ የለም።

ጊዜው የአንድነት ነው!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

29 Oct, 18:34


ፋኖነት ሳይነጋገሩ መግባባት ነው። አኹን ያለው ትግል ስለዚህ ይመሠክራል። ሲነጋገሩ ደግሞ አንድ ይኾናሉ። ለመጨረሻው ከጠላት በስተቀር ወዳጆች ኹሉ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ይወጡ ዘንድ እንማጠናለን።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

28 Oct, 20:29


"በእኛ ላይ ችግር እንደደረሰ ተደርጎ ትናንት ጥቅምት ፲፯ ሲወራ የነበረው ሐሰት ነው"

አርበኛ ረዳት ፕ/ር ኢያሱ አባተ

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

26 Oct, 18:21


ዝምተኛ ግን የወንዶች ወንድ አርበኛ!

አርበኛ ባየ ቀናውን በመሰሉ ምርጦች የሚመራ ትግል ዕድለኛ ብቻ ሳይኾን የፍጻሜውን ውኃ ልክም ያስቀምጣል።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

26 Oct, 14:10


ለጀግንነቱ ልክ የማይገኝለት ጀግና አርበኛ ሻለቃ ሀብቴ ወልዴ

ሥራህ ለወገንህ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

25 Oct, 16:39


ቤተ መንግሥት ውስጥ ሊገኝ የሚገባ ልበ ሙሉነት። ፍትሕ በታሰረችበት ፍትሕን ያስፈቱ አርበኛ።

እንደተፈቱ መታሰር፣ ለዘለዓለም የሚያስከብር። አረአያ በተግባር- ለመሳዮችዎ ምስክር።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

25 Oct, 12:34


ዓላማ ሲኖርህ ወንዝና ተራራ ርቀትና ቅርበት አይወሥኑህም። እነርሱ ሲሰፉ አንተ ይበልጥ ትሰፋለህ። ከሸዋ እስከ ቤተ ዐማራ ስንት አለ ተራራ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

25 Oct, 11:52


የጥቁር ድንጋይ እውነት

በውኃ ተከብቦና ተውጦ የሚኖር አንድ ጥቁር ድንጋይ ነበረ። በዘመኑ ኹሉ ውኃ እንደተጠማ ይኖራል። ኧረ ተጠማሁ ኧረ ተቃጠልሁ እያለ ይጮኻል። ምነዋ ተጠማሁ ትላለህሳ ሲባል ውኃ የታለና? አለ ይባላል።

ይኽን ድንጋይ በምንም ማስረጃ ከታቹ እስከ አናቱ በጀርባው በፊቱ ውኃ ስለመኖሩ ልታስረዳው አትሞክር። ያኔ ድንጋዩ አንተ ትኾናለህ። ጥቁሩ ድንጋይ የሚያውቀው ውኃ አለመኖሩን ብቻ ነው። የእርሱ እውነት ያንተ ሐሰት ነው። ውኃው መኖሩን የምታውቀው አንተ ነህ። እና ምን አለፋህ? እርሱ የዕድሜ ዘመን ባለ ሙሉ ክብር ደንቆሮ ነው። ኩራቱም እንጀራውም ድንቁርናው ነው።

ዛሬ ይኽን ድንጋይ የመሰሉ እውነትን የካዷት ብዙዎች በተለይ ውነቆች አሉ። ልታደርግ የምትችለው ነገር ቢኖር ስቀህባቸው ማለፍ ብቻ ነው። ስታብታቸው (አልቻላቸው ስትል) ጓዳ ለጓዳ ይንቧቻሉ።

+ + + + +
አርበኛ ዘመነ ከሸዋ ፋኖዎች ጋር ያደረገውን ምክክር የሚያሳየውን ቪድዮ ከFacebook page ላይ አሳግደውታል።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

25 Oct, 08:13


ስቃችሁበት እለፉ

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

24 Oct, 19:56


ስቆ ማለፍ ደጉ!


ስቃችሁበት እለፉ ብሎነ ነበር።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

24 Oct, 16:14


ውነቃ ብልጼዎች:- እና ይኽ ስብሰባ በሰማይ ኾነ ነው የምትሉኝ?

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

23 Oct, 14:31


እባካችሁ - እንደ ዐዲስ እንሠራ

ከነገ ዛሬ ይቀድማልና፣ ከመቅረትም መዘግየት ይሻላልና

፩. አሳማኝ በምንላቸው ማስረጃዎቻችን እና ምክንያቶቻችን ጎራ ለይተን የቆምን፣

፪. ግራ ገብቶን መኻል ላይ የቀረን፣

፫. በቲክ ቶክ፣ በትዊተር፣ በፌስቡክ እና በዩቱብ ደግሞም በሳተላይት ቴቪ የምንጎሻሸም፣

ግን አንድ cause (መግፍኤነገር) - እርሱም የዐማራ ሕዝብ ሕልውና አደጋ ውስጥ መግባቱ የሚያዋሕደን፤ ፈጽሞ ያልተለያየን:-

እባካችሁ የሕዝባችን የመከራ ቀናት ያጥሩ ዘንድ የምንገፋፋባቸውን ትተን ወይም ቆም አድርገን ወደ አንድ እንምጣ።

ለሕዝባችን ስንል ልዩነቶቻችንን ለጊዜው እናምቃቸው። ከዚያም በዐደባባይ ሳይኾን ለብቻ በጓዳ እየመከርን እየተገሳጸጽን እየተማማርን ወደ አንድ ለማምጣት ቃል እንግባ።


የታናሻችሁ ጥሪ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

23 Oct, 10:44


ሥርዓቱ ባሕሩን የማድረቅ ዘመቻውን ቀጥሏል

+ + + + +

ራያ ቆቦ ቀዩ ጋሪያ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ፪ (2) ንጹሐን ሲገደሉ ፮ (6) ቆስለዋል።

ጥቅምት ፲፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.

#Mulugeta_Anberber
ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

23 Oct, 08:15


እንኹን እንደ ዓባይ [ነንና]

ጎጃምን፣ ጎንደርን፣ ወሎንና ሸዋን አቅፎ የያዘው ታላቁና ታሪካዊው ወንዝ ዓባይ ተፈጥሯዊ ቁመናው ግሩም ነው። ዓባይ ገናናነቱ፣ ስፋቱ፣ ጥልቀቱ፣ ታሪኩና ጉልበቱ ከዐራቱም ይመነጫል። ከኹሉ ይጠጣል፣ ለኹሉ ያጠጣል፤ አንድ ዓባይ ኾኖ ይወጣል። ወተት ኾኖ የጀመረው ግዮን ወይም ጥቁር ዓባይ ኾኖ ከፍ ይላል። ለሌላ ይተርፋል።

የዐማራ ፋኖ ዓባይን ምሳሌ አድርጎ ወደ ከፍታ ይውጣ ወደ አንድነት ይምጣ። አንዱ ያለ አንዱ አይኾንም። ከኹሉ የማይጠጣ ዓባይ የለም። ኹሉን የማያጠጣ ዓባይም የለም። ኹሉ የሚያጠጣው ኹሉ የሚጠጣው ኃይል፣ ተቋም ይመሥረት።


እናዳብረው፣ እንወያይበት፣ ይዛመት!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

22 Oct, 20:23


አደራዎ አለብን! ወኔና ጀግንነትዎን እንወርሳለን!

+ + + + +

"ፍ/ቤቱ የፈለገውን ውሣኔ ይወሥን፤ እኔ በዚህ ዕድሜዬ በ፸፬ ዓመቴ ለእነዚህ ወጣቶች መልፈስፈስን አላስተምርም"

በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና በደል በማጋለጣቸው በአገዛዙ ጥርስ የተነከሰባቸው ብሎም ወደ ግዞት የተወረወሩት ታዴዎስ ታንቱ "የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ወንጀል ስለሌለብኝ ማቅለያ አላስገባም፤ የመሰላችሁን ፍረዱ ሲሉ ተደምጠዋል።"

#ይድነቃቸው_ከበደ

+ + + + +

ክቡር ጋሽ ታዴዎስ ሆይ:- እውነት አርነት ታወጣዎታለች! ይብላኝ ለፈራጆች። እስከ ዛሬ ስለ ጀግኖች በአዕምሯቸው ሲመራመሩ በእጆቻቸው ሲጽፉ በአንደበታቸው ሲያስተምሩ ነበር። አኹን በፋንታቸው ጀግኖቹን በተግባር መሰሉ። Respect!!!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

22 Oct, 13:30


"ማቅ ለብሸማ አልቀርም፤ ማቅ ያለበሰኝን እፋለመዋለሁ።"

አዎ በሕይወቷ መጣህባት። ውዷን ነጥቅህ በላህባት። ወላድ እናት ከጨከነችብህ አንተ አውሬ ከአውሬም ይልቅ ጭራቅ ነህ።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

22 Oct, 11:09


ያሳዝናል!

ደም የተጠማው አየር ኃይል ዛሬ ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. በእናርጅና እናውጋ ወረዳ ፈለገ ብርሃን ከተማ ንዋየ ማርያም ፩ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ ወደ ማክሰኞ ገበያ በማቅናት ላይ በነበሩ ንጹሐን ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል።

እንዲሁም በመከረኛው ደብረ ኤልያስም የቀጋት ት/ቤት ላይ ተመሳሳይ የድሮን ጥቃት አድርሷል።

የጉዳቱ ዝርዝር መረጃ እየተጣራ ነው። ባሕሩን የማድረቅ ሥራውን "ጊንጥን" መቆርጠም በሚለው መርሕ እያስፋፋው ቀጥሏል።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

22 Oct, 01:57


በዓባይ ተምሳሌት ቤተ ዐማራን መሥራት

በዐማራ የሕልውና ተጋድሎ ውስጥ አንዱ ፈታኝ ኹኔታ በአንድ የመሰባሰብ ሒደት ኾኖ ተገኝቷል። ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለመሻገር አንድነቱ የግድ መኾን አለበት። ለዚህ ደግሞ ዓባይን መመልከት ይጠቅማል።

ጎጃምን፣ ጎንደርን፣ ወሎንና ሸዋን አቅፎ የያዘው ታላቁና ታሪካዊው ወንዝ ዓባይ ተፈጥሯዊ ቁመና አለው። ዓባይ ገናናነቱ፣ ስፋቱ፣ ጥልቀቱ፣ ታሪኩና ጉልበቱ ከዐራቱም ይመነጫል። ከኹሉ ይጠጣል፣ ለኹሉ ያጠጣል፤ አንድ ዓባይ ኾኖ ይወጣል። ለሌላ ይተርፋል። የዐማራ ፋኖ ዓባይን ምሳሌ አድርጎ ወደ ከፍታ ይውጣ ወደ አንድነት ይምጣ።

አንዱ ያለ አንዱ አይኾንም። ኹሉም አንድ ዓባይን ለማምጣት የድርሻውን ያበርክት እንጅ ራሱ ዓባይን ለመኾን አይሻ። ለአንድ ዓባይ ምሥረታ ኹሉም ያስፈልጋል። ኹሉም ያለስስት ያዋጣል። ዓባይ ኾኖ ይወጣል። ዓባይ የአንድ ዐማራ ተምሳሌት!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

21 Oct, 18:22


"ፋኖ ነበልባሉ እርሱ ሞቶ ሰውን በሕይወት ያኖራል። ፋኖ ነበልባሉ እርሱ ሕይወቱን ሰጥቶ ሌላውን በሕይወት ያኖራል።"

ዝነኛው አርበኛ ፋኖ ሞላ ደስዬ

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

21 Oct, 11:20


የዘሜ መግለጫ ሌላ ፻ ተራሮች ኾኖ ውሏል ለካ

መግለጫው የረፈረፋቸው ሁሉ አረፋ ሲደፍቁ ውለዋልና። ጥቅምት ፲ ለማለት መስከረም ፲ መባሏ serious ማወናበጃ ተደርጋ የተንታኝ ዓይነት ሳይወራጭባት አልቀረም። ወሬአቸው በሦስት ነገሮች ይፈርሳል።

፩. የዘመነ ቃል የጊዜ ጥቁምታ (Time line) አለው። በመልእክቱ የተመስገን ጥሩነህን የጥቅምት ስብሰባ ያነሣል። ተመስገን "ዘመነን አስወግደነዋል - ከእንግዲህ ድምፁን አትሰሙትም" ብሎ ባሕር ዳር ለሰበሰባቸው ካድሬዎቹ የወሸከተው ጥቅምት ከባተ ነው። መቼስ የእናንተ ጉድ አያልቅም፤ "ዘሜ ነቢዩ በመስከረም ፲ ተመስገን ጥቅምት ላይ እንደዚህ ሊንዘባዘብ እንደሚችል ተነበየ" ልትሉ ይኾናል እኮ።

፪. መስከረም ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. ስለ ዘመቻ ፻ ተራሮች መግለጫ ሰጥቷል። ሞተ ተመታ ተያዘ ዓይነት ወሬ የመጣው ከተመስገን ጥሩነህ የጥቅምት ንግግር በኋላ ነው። መስከረም ፳፱ ላይ ሰሞኑን ስለዘመነ የተነዛው ኹሉ አልተባለም። እንዲያውም በመስከረም ፳፱ መግለጫው ለምን በቪድዮ አልመጣም በሚል "ቆስሏል" እያሉ የሐሰት ወሬ ነበረ ያናፈሱት።

ዘመነን መስከረም ፲ ላይ የአኹኑን ዓይነት መግለጫ ለመስጠት በቂ ገፊ ምክንያት አልነበረም። እንኳን እርሱ ሊናገርበት ብልጽግናዎችም ገና አላሰቡበት።

፫. አኹን በማያወላዳ ኹኔታ በራሱ አንደበት መስከረም የሚለው በጥቅምት ፲ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. አርትዖት ተሰጥቶበታል።

ይኸው በእነዚህ ሊንኮች ገብታችሁ ስሙት

https://www.facebook.com/share/v/iYBLJdn3qMNGctjc/?mibextid=UalRPS

https://youtu.be/D5OUTDOLmqg

https://youtu.be/weikfz7i8U8?feature=shared

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

20 Oct, 20:34


እነዚያ በረሮ እንዳሉ እነዚህ ጊንጥ እያሉ ወገን ሊጨርሱ!


የዘር ፍጅት ጥሪ ነው

ውነቃ ዳንኤል "ጊዜ ተሰዓቱ ማን ተገኝ አለሽ?" በቅኔ መምህራን ቤት የሚነገረውን ተጠቅሞ ያስተላለፈው የዘር ፍጅት ጥሪ ነው።

ሲጀመር ስለ ጊንጥ ሳይኾን የተነገረው ስለ ትል ነው። ጊንጥ በአመዛኙ በአሸዋማ በረሃ አካባቢ የምትኖር ሲኾን በዛፍ ቅርንጫፍ ቅጠል ለቅጠል የሚሳበው ደግሞ ትል ነው። ጊንጥና ቅጠል የማይመስል ነገር። ጊንጥ የቱንም ያኽል ትንሽ ብትኾን ትጎረብጣለች። ትል ግን ከቅጠል ልስላሴ ወይም መሻከር የመመሳሰል ዕድሉ ሰፊ ነው።

ባሕታዊው ሠዓታቸው ሲደርስ አፋቸውን ለመሻር (ለማደፍ) የላመ የጣመ ስለሌላቸው የተገኘውን ቅጠል ይሸመጥጣሉ። በዚያ ሠዓት ከቅጠሎቹ መኻል ተወሽቃ ሳያዩአት ወደ አፋቸው የገባች ትል ድምፅ ታሰማለች። እርሳቸውም ጊዜ ተሰዓቱ ማን ተገኝ አለሽ? ብለው "አስተናግደዋታል"።

ይኽንን ጠቅሶ የብልጽግና ሠራዊት ፋኖን እዋጋለሁ በሚል ሰበብ ሕፃናትን፣ ንጹሐንን፣ ከብቶችን፣ ሰብሎችን፣ አብያተ እምነትን እና ተቋማትን በነጭ ፎስፈረስ ቦምብ መግደሉንና ማፈራረሱን ትክክለኛ ርምጃ ነው ሲል ተከላክሏል።

ባሕታዊው ትሊቱን የተመገቡት ዐውቀው ኾን ብለው ሳይኾን ስላላዩአት ነው። ውነቃ ዳንኤል ግን የተገኘ ሁሉ ይጨረገዳል፣ እዚያ አካባቢ የምንጨነቅለት ሕይወትም ተቋምም የለም በማለት የዘር ፍጅት ቀስቅሷል።

የባሕታዊው ድርጊት ያጣ የነጣ የሚያደርገው ፍትሐዊ ሲኾን የውነቃ ዳንኤል መልእክት ግን የዘር ፍጅት ዐቅዶ መሥራትን ቅቡል አድርጎ ለማንበር የተነገረ ነው።

አኹንም ያገኘነውን ከመጨፍጨፍ የሚያግደን የለም። ከተፈጃችሁ በኋላ ለሌላ ፍጅት ተዘጋጁ የሚል አደገኛ ቅስቀሳ ነው። እነዚያ በረሮ እነዚህ ጊንጥ እያሉ ወገን ሊጨርሱ ተነሥተዋል።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

20 Oct, 10:10


"ስቃችሁበት እለፉ"

በባንዶች ፊታውራሪ በተመስገን ጥሩነህ አገላለጽ "ዘመነን አስወግደነዋል፥ ከዚህ በኋላ ድምፁን አትሰሙትም" የሚለውን የሰሞኑን ብልጽግናዊ ዐዲስ "መዝሙር" ስቃችሁበት እለፉ።

ሌት ተቀን እያቀድንላቸው ነው። ከጠፋሁም ያጠፋኝ የጠላት ስስ ብልት ልየታ ቢዚ አድርጎኝ ነው። የዘመነ ትውልድ የዓለማችን ዕድለኛና ገድለኛ ትውልድ ነው። መንጋው እንዲበተን እረኛውን ምታው የቆዬ ብሂል በእኛ ትግል ውስጥ አይሠራም። ትግሉን ሚሊዮን እረኞች ከብበውታል፥ መንጋው ራሱ እረኛ ከኾነ ዓመታት አልፈዋል።

#አርበኛ_ዘመነ_ካሤ

ጥቅምት ፲ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

20 Oct, 01:18


የፕሮፍ ግጥም

ይኽን ሸላይ ግጥም ተጋበዙልኝማ!

+ + + + +
አዎን ዐማራ ነኝ

እሚያነጋግረን ብዙ እሚያስጨንቀን፣
ሌላ ተግባር ጠፍቶ ባገር እሚከወን፣
የዕድገት ደረጃችን የደረስንበቱ፣
መሸንሸን ከኾነ ዝርያን ባይነቱ።

ተፈጥሮ ያደለችኝ፣
መርቃ የሰጠችኝ።
ከሥር መሠረቱ፣
ከጠዋት ከጥንቱ።

የዋኅ ሆደ ቡቡ ኹሉን አሳዳሪ ከኹሉ አዳሪ፣
ልበ ሙሉ ቆራጥ በቁም ነገር ኗሪ።
በራሴ እምታመን ባገሬ እምኮራ፣
በሀቅ እምታገል ላገሬ እምሠራ።
ሸፍጥና ክህደት ባንዳነት ያልነካኝ፣
የነፃሁ የጠራሁ አዎን ዐማራ ነኝ።

የሀገሬን ክብር ታሪኬን እማልሸጥ፣
ዘመድ ወገኖቼን በብር እማልለውጥ።
እማልንበረከክ ለነጭ ፍርፋሪ፣
ጎጠኛ ያይደለሁ ትውልድ አሳፋሪ።
ጀግንነት አመሌ ወኔ ያልተለየኝ፣
ተጠየቅ ካላችሁ አዎን ዐማራ ነኝ።


እሚያስቆጩ ሰው!!!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

19 Oct, 12:57


የእናንተ ደሞ ይለያልሳ አያ!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

19 Oct, 11:26


እጅ ወደላይ !

#WarOnAmhara እነዚህ የማይረቡ ሰዎች በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ ባሕርያቸውን አጋቡበት። እጅ ሲሰጡ ኖረው አረአያነታቸውን በመከተል እጅ መስጠትን ባሕል አደረጉት።

የኢትዮጵያ ጦር የታፈረ የተከበረ ስመ ጥር ነበረ።

ግን በወገኔ ላይ አልተኩስም፣ ንጹሐንን አልጨፈጭፍም ብለው እጅ የሚሰጡ ካሉ ደረጃቸው ከጀግና ነው።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

19 Oct, 10:47


በዚህ የሕልውና ትግል ከፊት ረድፈኞች መካከል ዋና ነው። ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ

ያለ ዕረፍት ያለ መሰልቸት የተጋፈጠው ተራራ ብዙ ነው። ገራገር፣ ቅን፣ አክባሪና አዳማጭ ነው። ነባሩን የፌስቡክ ገጽ አስዘግተውበታል። አንድ በር ሲዘጋ ዐሥር በር ከሚከፍት ትውልድ ጋራ መተናነቅ አይቻልም። እናም ከዐሥሩ አንዱ በኾነው በዐዲሱ በር ግቡ!

መታገል በዚህም ነውና አደራ እንዳትታክቱ

https://www.facebook.com/profile.php?id=61566762916848&mibextid=LQQJ4d

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

19 Oct, 00:06


“Cannibals ate my son” is the voice of crying, heartbroken mother, out loud the death of her 2nd child. #Mezgebu_Tadele is a 7 year old boy who is killed as a result of drone attack while looking after his cattle.

#AmharaGenocide
#WarOnAmhara
@usembassyaddis
@UN @HRW @Amnesty @EUCommission @StateDept

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

18 Oct, 13:59


በድሮን እና በጀት በሚያደርጉት ጥቃት:-

፩. ሰላማዊ ሰዎችን ገደላችሁ ሲባሉ ገጥመን መስሎን ይላሉ።

፪. ሕፃናትን ገደላችሁ ሲባሉ ገጥመን መስሎን ይላሉ።

፫. እንስሳትን ገደላችሁ ሲባሉ ገጥመን መስሎን ይላሉ።

፬. አብያተ እምነትን አጠቃችሁ ሲባሉ ገጥመን መስሎን ይላሉ።

፭. ተቋማትን አፈረሳችሁ ሲባሉ ገጥመን መስሎን ይላሉ።

፮. ሰብል አጠፋችሁ ሲባሉ ገጥመን መስሎን ይላሉ።

እነርሱ የገጠሙት ከፋኖ ጋር ሳይኾን ከኹሉ ጋር ነው።
በነውር ሥራቸው ልባቸው ደም ተሞልቷል፤ ደረታቸው በመርዝ ተወጥሯል፤ አዕምሯቸው በጥላቻ ሰክሯል።

መልእክታቸው ግልጥ ነው። በዐማራ ምድር ያለን ኹሉ ማጥፋት። ያወጁት ዘር ማጥፋት እንጅ ጦርነት አይምሰልህ። መታጠቅ አለመታጠቅ ደንታቸው አይደለም። በዚያ ከተገኘህ ትገደላለህ። አንተ ሳታውቀው ለካ ገጥመኻል። ምክንያቱም ሲገድሉህ ጉሮ ወሸባቸው ነው።

የአንተ መልስ ከዕቅዳቸው የበለጠ ሊኾን ግድ ይላል።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

18 Oct, 12:28


እንኳን ሰው እንስሳቱም ሰብሉም ጠላት ናቸው!

* * * * *

"በማዕከላዊ ጎንደር በለሳ ጣላ በተባለ ቦታ ዛሬ ጥቅምት ፰ ቀን ፳፻፲፯ (8 ቀን 2017) ዓ.ም. ረፋድ ሰላማዊ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ አመላላሽ መኪና ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከ፴፯ (37) በላይ ወገኖቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የዐይን እማኞች ገልጸዋል።

በተጨማሪም በጎንደር ምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ መኻል ከተማ ከረፋዱ ፭ ሠዓት ገደማ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ፰ (8) የጉልበት ሠራተኞች መገደላቸውን የአብርሃ ጅራ ነዋሪዎች ተናግረዋል።"

#Mulugeta_Anberber

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

18 Oct, 06:57


የብርቱ አርበኛ ቃል

+ + + + +

"ሀገር ሽጠው በሚያገኙት የደም ገንዘብ አሮጌ ተራ ወርደው በሚሸምቱት ድሮንና ተተኳሽ አይደለም ከዋክብት ቦንብ ኾነው የዐማራ ሕዝብ ላይ ቢዘንቡ እንኳን ጠላቶቻችን ይኽን ትግል ማሸነፍ አይችሉም።

እምቢ ያለን ሕዝብ፥ ለህልውናው ላለመጥፋት የሚታገልን ሕዝብ ማሸነፍ ፈጽሞ አይቻልም። ከገፀ ምድር ላለመጥፋት መሣሪያ ያነሣን ሕዝብ ከማሸነፍ የፀሐይን ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ተፈጥሯዊ የጉዞ ዑደት ከሰሜን ወደ ደቡብ ማዞር ይቀላል። ከፈጣሪ በታች ትልቁ ጉልበት ያለው የአመፀ ሕዝብ መዳፍ ላይ ነው።

እንበርታ እንጽና ብቻ!! ጽናት ነገ ከነ- ጠዋት ውብ ጀንበሯ የራስ እንደምትኾን በጥልቅ ከነፍስ በማመን የዛሬን ሰው፣ ተፈጥሮና ሁኔታዎች ወለድ ውጣ ውረዶችን የማመቅና የገለባ ያክል እንኳን ለሥነ ልቦናችን ሳይከብዱን ወደ ግብ የመገስገስ ሥነ አዕምሯዊ ኹነት ነው። እንጽና!!"


#አርበኛ_ዘመነ_ካሤ

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

17 Oct, 19:02


እነዚህ እጆች እስክርቢቶ በጣታቸው የደብተር ቦርሳ በትከሻቸው መያዝ በተገባቸው ነበር። አብይ አህመድ ግን የሸለማቸው የጀት ተተኳሽ ቀለህ ኾነ። ጎዳና እንዲወጡ ቤታቸውን ከሰማይ እየተኮሰ ይንዳል። እንዲራቡ ማሳቸው ላይ ታንክ ይነዳል። ከስፍራቸውን ነቅለው እንዲሰደዱ ቤት ለቤት እየገባ ንጹሐን ቤተሰቦቻቸውን ይገድላል። ሲፈናቀሉ ያለ ቦታህ መጣህ እያለ በተለየ ጭካኔ ያርዳቸዋል። ይኽ ኹሉ ዘራቸውን ለማጥፋት ነው።

ፋኖ ይኽን ጭራቃዊ ሥርዓት ሳያጠፋ አይመለስም!

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

17 Oct, 16:08


እግዚአብሔር ሲጣላህ መናኙም ባሕታዊውም ይነሣብሃል። ምድር ትከዳሃለች። እንዲያ ነው አባቶቼ!!!

"የብልጽግና መንግሥት በሕዝብ የተጠላ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ተግባር ላይ ያለ እንቅልፍ የሚሠራ በመኾኑ በየትኛውም መልኩ ይኽንን መንግሥት መታገልና ማስወገድ የኹላችንም ድርሻ በመኾኑ ሕዝቡ እየተደራጀ የሚችለውን ኹሉ እንዲያደርግ እናሳስባለን"

ጥምረት ለቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ ኦርቶዶክሳዊ ንቅናቄ

+ + + + +

"የሕዝቤን መከራ በእውነት ዐየሁ" እንዲል።

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

17 Oct, 13:58


እንደዚህ ዓይነት ብስል ንጥር ጀግኖች ተስፋ ይሞላሉ ብቻ ሳይኾን ያስጨብጣሉ።

"በዚህ ትግል ከአካል በላይ አዕምሮን መጠበቅ ያስፈልጋል። . . . ያልተጠበቀ አዕምሮ ሀገር ያፈርሳል።"

አርበኛ #ሳሙኤል_ባለድል

Simply brilliant!

የሚገርም አሳብ!

ይኽ ድምፅ ቤተ መንግሥት ውስጥ ልትሰማው የሚገባ ድምፅ ነው። No more no less.

ዲን ዓባይነህ ካሤ - Dn Abayneh Kassie

17 Oct, 10:34


ዛሬ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. አገዛዙ በዳንግላ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል።

1 ፯ ሰላማዊ ዜጎች ሲሞቱ
2 ፰ ደግሞ በጠና ቆስለዋል
3 ፬ የቁም ከብት እና ፫ በጎችም ተገድለዋል።

እያንዳንዷ ካሬ የዐማራ መሬት ለዘር አጥፊው እኩይ አገዛዝ ዒላማ ናት።

7,401

subscribers

1,482

photos

18

videos