የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU @eotcgssu21 Channel on Telegram

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

@eotcgssu21


የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (Amharic)

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU ት/ቤቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን (EOTC) የተገኘባት አገልግሎት ነው። ይህ አንድነት በኢትዮጵያ ከአንደኛን ልጆች ለማንም ኢናሕ እና እናት እንዴት በማውረድና ጥራት ተመለከተልን። EOTC GSSU የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ድርጅት ነው አለን። ይህ በሰንበትና በምንዝጋችበት ላይ የሚኖር ከሆላ ቤት ነፃነት ከሆላበት ቋንቋ በሮቦ በሪንግ መሸረት ይገኛል። ይህ ት/ቤቶቹ እንደሚያስፈልጉ ማንም ኢናሕ እና እናት መሣሪያ እንኳን ለብንሆን እንጂ በዚህ ከፈለጋችሁ በዚህ ሰው ግምት ኑሮ የምታስችላቸው ነገር ነው።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

20 Jan, 17:57


📸ልዩ የሚያሸልም የጥምቀት ፎቶግራፍ ውድድር
በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚዲያ ክፍል የተዘጋጀ 🏆

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

   ┄┄┉┉ ‌  ✽‌  🌺🌺‌  ✽‌   ┉┉┄┄
    
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በቴሌግራም ቻናሉና ቡድኑ ላይ ለከተራ ፣ ለጥምቀት እንዲሁም ለቃና ዘገሊላ በዓላት ያነሳችዋቸውን ፎቶግራፎች ሰብስቦና አወዳድሮ መልሶ ለእናንተው ሊያደርስ ተዘጋጅቷል።

👉 በውድድሩም ከማንኛውም ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ዓባላትና ምዕመናን መሳተፍ ይችላሉ። ለአሸናፊዎችም ልዩ ሽልማት ተዘጋጅቷል።

👉ይመጥናሉ ያሉትን በበዓሉ ላይ የተነሱ  ፎቶግራፎች ለዚሁ ውድድር ባዘጋጀነው የቴሌግራም ቦት

@t4mesbot

ላይ እስከ ሐሙስ ጥር 14 ድረስ በመላክ መሳተፍ ይችላሉ።

✍️ ከሚያስገቡት ፎቶግራፍ መካከል በዚህ ቻናል ለምርጫ የሚለጠፈው የበዓሉ አከባበር መንፈሳዊ እሴቶቹን  የጠበቀ ከሆነ እና ከኤዲቲንግ የፀዳ ከሆነ ብቻ ነው።

🚫ለመወዳደሪያ የሚልኳቸው ፎቶዎች ቀድመው በማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ የታዩና የተለቀቁ መሆን የለባቸውም።

✍️ በተጨማሪም ተወዳዳሪዎች ለውድድሩ ብቁ የሚያደርጋቸው ወደ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የቴሌግራም ቡድን @eotcgssu21 አንድ አባል መጨመር ፣ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/@eotc-gssu ሰብስክራይብ ማድረግ አልያም የሰ/ት/ቤት ፌስቡክ ፔጅን https://www.facebook.com/gssu.eotc ላይክ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

19 Jan, 07:15


እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።

የበዓሉ አከባበር በፎቶ ከጃን ሜዳ

መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

19 Jan, 05:15


እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

18 Jan, 18:49


የከተራ በዓል አከባበር በፎቶ

መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

10 Jan, 17:17


ቅዱስ ፓትርያርኩ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።

ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው እንደገለጹት የሰላም ትርጉሙ ተረጋግቶ መኖር፣ ወደ ዓላማ ፍጻሜ መድረስ፣ መርቆ ማለፍ ነው። ካሉ በኋላ ወልዶ ለመሳም፣ አሳድጎ ለመዳር፣ ዐርፍተ ዘመን የገታቸውን በክብር ለመሸኘት ሰላም አስፈላጊ ነው ።ብለዋል።

አያይዘውም እስካሁን ድረስ የብዙ ነገሮች ዋጋ ታውቋል፤ የሰላም ተመን ግን አልታወቀም ። ሰላም ከሌለ ልጅ መቦረቅ፣ሽምግልናው ማረፍ የሌለበት ነው ። ሰላም ጠብን መግደል፣ ከእኔ ይልቅ ወንድሜ ይድላው ብሎ የልብስፋት ማግኘት ነው ። ብለዋል።ሰላም የኑሮና የሞት ፍርሃትን የሚያስወግድ ነው ። ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ሰላም ከሌለ ምድር ትታወካለች፣አራዊት መኖሪያቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገር ይሰደዳሉ ። በዚህም ሰላም ለሁሉም አስፈላጊ መሆኑን እንረዳለን ። ሰላም በሌለበት ሰጪ ባለጠጋ፣ ጠያቂ ተመጽዋች ማግኘት አይቻልም ።ብለዋል የቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል ፦

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

‹‹ወዝንቱ ውእቱ ዘነገርኩክሙ ከመ በኀቤየ ሰላመ ትርከቡ፡-
በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርኳችሁ›› (ዮሐ. 16÷33)

ዘመናትን እያፈራረቀ በድንቅ መግቦት ሕዝቡን የሚመራ ፣ በአባታዊ ምክሩ ዕረፍትን ፣ በቃሉ ትምህርት ጥበብን ፣ በመንፈሱ ምሪት መንገድን የሚሰጥ ፤ ሰውንም ከፍጥረት ሁሉ አልቆ በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረ፣ ሞትና ድንጋጤን የሚያስወግድ ፈቃድና ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር አምላካችንን እያመሰገንን፤ በሩቅ ሀገራችሁን በልባችሁ ተሸክማችሁ የምትኖሩ፣ በቅርብም የሀገራችሁን ደስታና ኀዘን እየተካፈላችሁ በከተማ ውስጥ በሥራ፣ በዳር ድንበር በሀገር ጥበቃ ላይ የተሰማራችሁ፣ እንዲሁም በሕመም ሆናችሁ ፈውስን፣ በእስር ቤት ነፃነትን እየጠበቃችሁ የምትገኙ መላው ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ልጆቻችን ከሁሉ በማስቀደም ለዘመኑ ህልፈት፣ ለመንግሥቱ ሽረት በሌለበት በእግዚአብሔር ስም መንፈሳዊ ሰላምታችንን እናስተላልፋለን፡፡

የሰላም ትርጉሙ ተረጋግቶ መኖር፣ ወደ ዓላማ ፍጻሜ መድረስ፣ መርቆ ማለፍ ነው። ወልዶ ለመሳም፣ አሳድጎ ለመዳር፣ ዐርፍተ ዘመን የገታቸውን በክብር ለመሸኘት ሰላም አስፈላጊ ነው ። እስካሁን ድረስ የብዙ ነገሮች ዋጋ ታውቋል፤ የሰላም ተመን ግን አልታወቀም ። ሰላም ከሌለ ልጅነቱ መቦረቅ፣ ሽምግልናው ማረፍ የሌለበት ነው ። ሰላም ጠብን መግደል፣ ከእኔ ይልቅ ወንድሜ ይድላው ብሎ የልብ ስፋት ማግኘት ነው ። ሰላም የኑሮና የሞት ፍርሃትን የሚያስወግድ ነው ። በትክክል ኖረ የሚባለው ሰላማዊ ሰው በኑሮው ድንጋጤ፣ በሞቱም ፍርሃት የሌለበት ነው ። ሰላም ከሌለ ምድር ትታወካለች፣ አራዊት መኖሪያቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገር ይሰደዳሉ ። በዚህም ሰላም ለሁሉም አስፈላጊ መሆኑን እንረዳለን ። ሰላም በሌለበት ሰጪ ባለጠጋ፣ ጠያቂ ተመጽዋች ማግኘት አይቻልም ።

ሰላም ሁለንተናዊ መገዛትን ትፈልጋለች ፣ የሰላም ልብ ፣ የሰላም ቃል ፣ የሰላም ተግባር ያስፈልጋል ። ሰላምን አስቦ ካልተናገሩትና ካልተገበሩት ሁከት እንደ ነገሠ ይቀጥላል ። ሰላምን ተናግረውት ካላሰቡበትና ካልተገበሩት በድብብቆሽ ብዙ ሰው ያልቃል። ሰላምን በሁለንተናችን መልበስ አጭሩን ዘመናችንን ለማጣፈጥ እጅግ አስፈላጊ ነው ።

በዓለም ላይ ብዙ ሺህ የሰላም ስምምነቶች ሲደረጉ ኖረዋል ። የሰው ልጅ ግን ሟች መሆኑን ረስቶ ገዳይ በመሆኑ፣ ራሱንም በራሱ ለማወክ በመፍቀዱ የሰላም ስምምነቶች ተፈርመው ፊርማው ሳይደርቅ እንደገና ሁከት ይሆናል ። በዚህም “ወይፌውሱ ቅጥቃጤሆሙ ለሕዝብየ ወይቤሉ ሰላም ሰላም ወአልቦ ሰላም፡- የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ ሰላም ሳይሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።” (ኤር. 6፡14) የሚለው ቃለ መጽሐፍ እየተፈጸመ ይመስላል፡፡

በዘመናችን ሰዎች በትዳር፣ በቤተ ዘመድ፣ በሀገር ሰላም ያጡ እንደሆነ እየተመለከትን ነው ። ሰው የራሱን ክፉ ጠባይ መግዛት ባለመቻሉ ወዶ የሸኘውን ሲፈልገው ይኖራል ። የሕጎችም ብዛት መፈራራትን እንጂ እውነተኛ ሰላምን ማምጣት አይችሉም ። ሰላም በማጣታችን በዘገየች ሀገር ዛሬም ስለምግብ የሚጨነቅ ሕዝብ አገልጋይ በመሆናችን በታላቅ ትካዜ ውስጥ ሆነን መልእክት እንድናስተላልፍ አድርጎናል።

እግዚአብሔርን ለሚወዱ የተሰጠች ጸጋ ሰላም ናት ። ታዲያ ይህ ሰላም ርቆን ሳለ እርሱን መውደዳችን እውነተኛ ነው ወይ( ብለን መጠየቅ ያስፈልገናል ። አንድ ዓይነት መልክና ማንነት ያለው ሕዝብ መተላለቁ ሰውነትንም መንፈሳዊነትንም መክሰር እንደሆነ የተረዳነው አይመስልም ። በእውነቱ ካየነው ነጭ ለብሰን ሳይሆን ማቅ ለብሰን የምናለቅስበትና በንስሐ ምሕረተ ሥላሴን የምንናፍቅበት ጊዜ ነው ።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

ትዕግሥተኛዋ መሬት እንኳ እየተናወጠች፣ ዓለም የቅጽበት ዕድል ብቻ እንዳላት እየጠቆመች ነው ። የመሬት መንቀጥቀጡ የዘመኑን ፍጻሜ የሚያስረዳ ሲሆን የምናያቸው ምልክቶች ሁሉ በተሰበረ ልብ እግዚአብሔርን እንድንፈልግ የሚያሳስቡን ናቸው ።

በመሆኑም በሀገራችን በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች ቆመው ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፤ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ አባታዊ ጥሪያችንን በድጋሚ እናስተላልፋለን ።

በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት በሕዝቡ ላይ ተጨማሪ ችግርና ጭንቀት እያመጣ ስለሆነ በትሕትና መንፈስ እርስ በርስ መገናዘብ ተፈጥሮ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል ታደርጉ ዘንድ አደራችን የጠበቀ ነው ።

በተጨማሪም በትግራይ ክልል የምትገኙ የሃይማኖት አባቶች መበደላችሁን እናውቃለን ፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው ። ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን እኛ የገፋነውን እርቅ ዓለም ሊቀበለው ስለማይችል፤ በእጃችንም የያዝነው መስቀለ ክርስቶስ የሰላም ዓርማ ነውና ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን ።

በመጨረሻም የመሬት መንቀጥቀጥ ባለበት አካባቢ እየተጨነቃችሁ ያላችሁ ልጆቻችን ረድኤተ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን በጸሎት የምታስባችሁ መሆኑን እየገለጽን መላው ኢትዮጵያውያን ለጉዳቱ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ለሚኖሩት ወገኖቻቸው አቅማቸው በፈቀደው መጠን ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ
ተክለ ሃይማኖት

ጥር ፪ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ምንጭ፦የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

09 Jan, 14:04


https://youtu.be/jlxh3yhLdLc?si=aF1MlAcPCKZc1PNL

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

07 Jan, 09:58


https://www.youtube.com/watch?v=rarHt2fTsEI

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

07 Jan, 07:35


መድኃኒት ተወልዶላችኋል!

“እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት-እነሆ፥ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡ (ሉቃ.2፥11)

ቅዱስ ሉቃስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ሲወለድ ስለነበረው የልቱን ነገር ሲተርክ “በዚያን ሌሊት በቤተ ልሔም ይኖሩ የነበሩ እረኞችም ከብቶቻቸውን ሲጠብቁ የእግዚአብሔር መልአክ በእረኞቹ አጠገብ ቆመ፤ የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው በራ፤ በጣምም ፈሩ፡፡ መልአኩም እንዲህ አላቸው እነሆ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ እነሆ፥ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡ እናንተም ባገኛችሁት ጊዜ ምልክቱ እንዲህ ነው፡፡ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ፤ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ፡፡” በማለት ቤተልሔምን በዓይነ ሕሊናችን እንድናይ አድጎ በሥዕላዊ አገላለጽ ይነግረናል፡፡ (ሉቃ.2፥11-13) ቅዱስ ሉቃስ በዚህ የወንጌሉ ክፍል ከድኅነታችን ጋር በቀጥታ የሚገናኙ መሠረታዊ ነገሮችን ነገሮናል፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-

1.የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው በራ፤
ይህ ብርሃን ፀሐይ ወይም ጨረቃ አይደለም፡፡ ልዩ የእግዚአብሔር ብርሃን ነው፡፡ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሊት ተወልዶ በማብራት የብርሃናት ፈጣሪ እውነተኛ ብርሃን መሆኑን አሳየን፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ በዓለም ላይ ጨለማ እንደነበረ እውነተና ብርሃን በመጣ ጊዜ ጨለማ እንዳለሸነፈው ገልጾልናል፡፡ (ዮሐ.1፡9) አስቀድሞ ኢሳይያስም በጨለማ ይሄድ የነበረ ሕዝብ ብርሃን አየ በጨለማና በሞት ጥላ ለነበሩ ብርሃን ወጣላቸው፡፡ (ኢሳ 9፡2) በማለት በሥጋ ስለሚገለጠው ብርሃን ተናግሮ ነበር፡፡ ክርስቶስ እስኪወለድ ድረስ በአዳም ኃጢአት ምክንያት ዓለም ሁሉ ማለትም የአዳም ልጆች ሁሉ በጨለማ ተውጠው ነበርና ቅዱስ ሉቃስ ጨለማውን የሚያስወግድ ብርሃን እንደተወለደ ነገረን፡፡

2. ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ
የእግዚአብሔር መልአክ በለሊት ከብቶቻቸውን ሲጠብቁ ለነበሩና ከተገለጠው ብርሃን የተነሳ እጅግ ፈርተው ለነበሩ እረኞች ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ አላቸው፡፡ በዚህም የክርስቶስ መወለድ ለእረኞችና ለዓለም ሁሉ ደስታ መሆኑን ይነግረናል፡፡ ለአምስት ሺ አምስት መቶ ዘመናት ከሰው ልጅ ደስታ ርቆ የአዳም ዘር ሁሉ በኀዘን ተውጦ ነበርና ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ በማለት የኀዘንና የፍርኃት ዘመን እንደተወገደ የምህረት ዘመን እደመጣ ደስታችንም እንደተመለሰ ደስታው ደግሞ ለሕዝብም ለአሕዛብም በአጠቃላይ ለዓለም ሁሉ መሆኑን ነገረን፡፡

3.መድኃኒት ተወልዶላችኋል
በበደል ምክንያት ቆስለን ፍጹም ፈውስ የሚያመጣ መድኃኒት የሚያስፈልገን ታማሚዎች ነበርንና የምሥራቹን የነገረን የእግዚአብሔር መልአክ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ተወልዶላችኋል አለን፡፡ በዚህም በቤተልሔም ከድንግል ማርያም ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ያያነው ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ከቁስላቸውም የሚፈውሳቸው መድኃኒት መሆኑን ተረዳን፡፡

4.የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ
ወንጌላዊው ሉቃስ የጌታን ልደት ሲተርክ የነገረን ሌላው ቁም ነገር “የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ” የሚል ነው፡፡ ይህም በሰውልጅ መዳን መላእክት እንደሚደሰቱ እና በኃጢአታችን ምክንያት አጥተነው የነበረውን የመላእክትና የሰው ልጆች አንድነት በጌታችን ልደት እንደተመለሰ የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህም የጋራ ዝማሬ በምድር ላይ ሰላም እንደሆነ ተገልጧል፡፡ በልደተ ክርስቶስ ሰውና እግዚአብሔር መላእክትና ሰው፣ ነፍስና ሥጋ፣ ሰማይና ምድር፣ ሕዝብና አሕዛብ ታርቀዋልና በምድር ሰላም ኾነ ሰውና መላእክትም በአንድነት ዘመሩ፡፡
በአጠቃላይ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት፡- የእግዚአብሔር ብርሃን በጨለማ ለነበርነው ሁሉ የበራበት፣ ፍርኃት የተወገደበት፣ ለእረኞቹና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ ደስታ ታላቅ የምሥራች የተነገረበት፣ ሰውና መላእክትም በአንድነት የዘመሩበት ታላቅ የደስታ በዓል ነው፡፡
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ዘር በሙሉ ያዳነበትን ድንቅ ሥራ ሲገልጽ “ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ሆኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ፡፡ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዷልና፤›› (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ፷፮፥፲፯) በማለት የመወለዱንና የትሕትናውን ነገር እያደነቀ ይናገራል፡፡
ይህ በዓል የአምላክ ትሕትና የታየበት የተዋረደው የሰው ልጅ ደግሞ መክበሩ የተገለጠበት በዓል ነው፡፡ ስለሆነም ልደተ ክርስቶስ ከትዕቢት ይልቅ ትሕትናን እንድንይዝ፣ ከጥላቻ ይልቅ ሰላምን እንድንሰብክ፣ ጌታችን ወደ ተዋረድነው የሰው ልጆች መጥቷልና በኑሮ ከእኛ ዝቅ ወዳሉት በትሕትና እንድንሄድ ደግፈንም እንድናነሳቸው፣ የእውነተኛው ብርሃን ልጆች ነንና በሕይወታችን የብርሃን እንጂ የጨለማ ሥራ እንዳይታይ፣ ለሰው ሁሉ የደስታ እንጂ የኀዘን ምክንያት እንዳንሆን የክርስቶስ ልደት ያስተምራናል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ተወልዶ ውሉደ እግዚአብሔር ያደረገን ክርስቲኖች የፍቅርና የሰላም ሰዎች በመሆን፣ ከጨለማ ሥራ በመራቅ ትሕትናንም ገንዘብ በማድረግ የክርስቶስ ልጆች መሆናችንን ልናሳይ ይገባል፡፡

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰለም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ይሁንልን!

መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወ/ትንሣኤ
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪ ሓላፊ

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

06 Jan, 18:00


"ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።" ሉቃ 2:11

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

06 Jan, 11:50


#መልእክተ_ቅዱስ_ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፤

በምሉእ ፍቅሩ ሰውን ከባርነት ወደ ነጻነት ለመመለስ በሥጋ ሰብእ የተወለደው ጌታችን  ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዘሠምሮ ለሰብእ፤ ክብር በሰማያት ለእግዚአብሔር ይሁን›› በምድርም እጅግ ለወደደው የሰው ልጅ ሰላም ይሁን” (ሉቃ ፪÷፲፬)
ይህ ቃለ ሰላም በጌታችን ዕለተ ልደት የተነገረ ነው፣ ቃሉ የተነገረው እንዲሁ እንደ ተራ ነገር ሳይሆን በቃለ መዝሙር እየተደጋገመ ነው፡፡ የተዘመረውም በምድራውያን ደራሲዎች ሳይሆን በሰማያውያን መላእክተ እግዚአብሔር ነው፣ የያዘው መልእክትም ሰማያውያንና ምድራውያንን ሁሉ ያካለለ ነው፡፡ የመልእክቱ ገዢ ሓሳብም አምላክ ከሰውነታችን ጋር ባለመለያየት፣ ባለመጠፋፋት፣ ባለመቀላቀል፣ ባለመዋዋጥ፣ ባለመለዋወጥና ያለባዕድና አንድ አካል፣ አንድ ክዋኔ፣ አንድ ጠባይ ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጾኣልና እግዚአብሔር ይክብር ይመስገን፡፡ የተዋሕዶውም ምስጢር ሰላምን ያሰፍናልና እግዚአብሔር ሰውን በእጅጉ መውደዱ ከዚህ ተዋሕዶ ዓውቀናል የሚል ነው፡፡

በእርግጥም እግዚአብሔር ሰውን ለመውደዱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ ወይም ማስረጃ የለም፤ እንከን የለሽ ንጹህ አምላክ የእኛን ኃጢአተኛ ሰውነት አካሉ አድርጎ ተወለደ ሲባል ላስተዋለው ሰው ምንኛ ቢወደን ነው የሚለው ጥልቅ አድናቆትን ያጭራልና ነው፡፡ይህ ብቻም አይደለም በዚህ ነገረ ተዋሕዶ ምክንያት ሰውነታችን አምላክ ሆኖ በመንበረ ጸባኦት እንዲቀመጥ መብቃቱ የድኅነታችንና የክብራችን ከፍታ ምን ያህል አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መንፈሳችን በአንክሮ ይረዳዋል፡፡ድምር ውጤቱም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ያስረዳናል፤ ሰማያውያኑ መላእክተ እግዚአብሔር በመዝሙራቸው ያበሰሩን ይህንን የምስራች ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር በእጅጉ ይወደናል ስንል እንዲሁ ከሜዳ ተነሥተን ኣይደለም፡፡ በበደላችንና በኃጢአታችን ሳይጸየፈን ሰውነታችንን በረድኤት ወይም በኅድረት ያይደለ በኩነት ተዋሕዶ ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ስላደረገው  ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ፍጹምና ምሉእ ፍቅሩ ሰውነታችንን በመበረ ጸባኦት ኣስቀምጦ መላእክት ሳይቀሩ ፍጥረታትን በሙሉ እንድንገዛ አድርጎናል፤ ምክንያቱም መላእክት በዕለተ ልደት የዘመሩለት በተዋሕዶ አምላክም ሰውም ለሆነ ለቤተ ልሔሙ ሕፃን እንጂ ለመለኮት ብቻ ኣይደለምና ነው፡፡ የዕለተ ልደት መዝሙር ዛሬም በሰማያትም ሆነ በምድር በተዋሕዶ ሰውም ኣምላክም የሆነ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለክበታል፣ ይመሰገንበታል፡፡የሰማዩና የምድሩ ዕርቅ ወደ ኋላ ላይመለስ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ተከናውኖኣል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰውም አዋጭ ምርጫ ይህ ዕርቅ ተጠብቆ እንዲኖር ነው፣ ያለ ዕርቅ ሰላም ሕይወት የለውምና፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ክብርና ሰላም በእጅጉ የተሳሰሩና የተቆራኙ ናቸው፤ እኛ እግዚአብሔርን ካከበርነው፣ ካዳመጥነው፣ ከታዘዝነውና ከተከተልነው ሰላም አለ ማለት ነው፡፡ ለሱ ካልታዘዝንና እሱን ካላከበርን ግን ዘላቂ ሰላምን ማግኘት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ ምክንያቱም ሰላምን ጨምሮ መልካም ነገር ሁሉ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነውና፡፡ ዛሬ በሁሉም የዓለማችን ማዕዘን የሚታየው የሰላም መደፍረስ እግዚአብሔርን ካለማክበራችንና ለሱ ካለመታዘዛችን የተነሣ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ ዓለም ከእግዚአብሔር ቃል ርቃ ለመሄድ በእጅጉ እየኳተነች ነው፤ በዚህ እኩይ ተግባርዋ ደግሞ እግዚአብሔር ለስጋትና ለጉስቁልና አሳልፎ እየሰጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር በምስጢረ ሥጋዌው ቢታረቃትም ዕርቁን ማክበር አቅቶአታል፤ ይህንን የእግዚአብሔር ጸጋ ቸል ብላ የምታደርገው ሩጫ የትም ሊያደርሳት እንደማይችል ብታውቅና በንስሓ ብትመለስ እግጅ ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ቃል “እናንተስ ከማይጠፋ ዘር ተወለዳችሁ” ብሎ ተስፋውን እንደነገረን ምድባችን ከማይጠፋ ዘር እንዲሆን ክርስቲያኖች የሆን ሁላችን በአእምሮ ጐልብተን፣ በሥነ-ምግባር ኣምረን፣ ጤናማ ሕይወትን ልንመራ ይገባናል፡፡

የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል፡፡

ጠቡ ፣ ጥላቻው፣ መለያየቱ፣ መጠፋፋቱ፣ ለወንድሜ  ከማለት ይልቅ ለኔ ለኔ ማለቱ ሲጎዳን እንጂ ሲጠቅመን ኣላየንም፡፡ አሁንም ወደ ልባችን እንመለስና በፍቅር፣ በዕርቅና በእኩልነት፣ በስምምነትና በወንድምነት ወደሚገኝ አንድነት እንምጣ፤ የልደቱ መዝሙር ያስተማረን ይህና ይህ ብቻ ነውና፡፡ በሌሎቹ ክፍለ ዓለማት እንደሆነው ሁሉ በሀገራችን የተከሠተው አላስፈላጊ ግጭት ብዙዎችን አሳጥቶናል፤ ብዙዎችንም ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ፈሰው የሰቆቃ ኑሮ እንዲገፉ አድርጎብናል፡፡ የሀገር ሀብት እንዲወድም ሆኖአል፤ ልጆቻችን ምናለ ከእንግዲህ ወዲህ ቢበቃንና ምድሪቱን የሰላም አየር እንድትተነፍስ ብንፈቅድላት፤ ይህ የወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ መልእክትና ጥሪ ነው፡፡    

በመጨረሻም፡-

በዓለ ልደት የእግዚአብሔር በዓል ነውና፣ እግዚአብሔር በምድራችን ሰላምን ያወርድ ዘንድ ካለን ከፍለን ለተፈናቃዮች፣ ለነዳያን እና ለአካል ጉዳተኞች በመለገስ በዓሉን በመንፈሳዊ ደስታና በሰላም እንድናከብር አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን!

      አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ
ተክለሃይማኖት
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

03 Jan, 18:52


"እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።" መዝ 23፡1-2

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

30 Dec, 18:46


እንኳን #ለብስራት_ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

በዚህ ዕለት ታላቁ መልዐክ መጋቢ ሐዲስ የተባለ ቅዱስ ገብርኤል ለዓለም ታላቁን ዜና አበሰራት !

የሰው ዘር በሙሉ ለ 5ሺ 500 ዘመን አንድ ዜናን በጉጉት ይጠብቅ ነበር ። መጠበቅ ከባድ ነው ! ግን ደግሞ መጠበቅ ተስፋ ነውና አለመጠበቅ አይቻልም። ኅጥሁ ከ ጻድቁ በአንድነት "ፈኑ ዕዴከ እም አርያም" እጅህን  ከሰማይ ከመንበርህ ላክልን እያሉ ይማጸኑ ነበር

የለመኑትን የማይነሳ የተናገረውን የማይረሳ እግዚአብሔር አብዝተው ቢለምኑት አንድም ስራውን የሚሰራበት ጊዜ በመድረሱ መልዓኩን ወደ አንዲት የ15 ዓመት ብላቴና ላከው። ቅዱስ እና ሊቅ የሚሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለጽኑ ሸክም ጽኑ ተሸካሚ ያስፈልጋል እንዳለ መለኮት ለመቀበል በንጽህና ለተገኘች ቅድስት መልዓኩ ታላቁን ዜና አበሰራት ።

በዓለም ላይ ትልቁን ዜና ማብሰር ምን ይሆን ስሜቱ ?!

ወናሁ ትጸንሲ ወትወልዲ :- እነሆ ትጸንሻለሽ ትወልጃለሽ ብሎ የተናገረ መልአኩ ገብርኤል ድንቅ ነገር አበሰረን ። ብስራትሽ ብስራታችን ነው ። በብስራትሽ ነገረ ድኅነታችን ታወጀልን።

ድንግል ሆይ #ይኩነኒ :-ይሁንልኝ በማለትሽ የአዳም ተስፋው ፣ የአበው ልመና ፣ የነቢያት ትንቢት የአዳም ልጆች ድኅነት ተፈጽሟል።

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ በተገባ ተገኝተሻል እና አማልጂቱ ሆይ ክብር ይገባሻል።
ቅዱስ ህርያቆስ እንዲህ እያለ እንዳመሰገነሽ እኔም አመሰግንሻለው ።

እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሁኖ ምስራቅን እና ምዕራብን ሰሜንን እና ደቡብን ዳርቻዎችንም ሁሉ #በአማን_ነጸረ በእውነት ተመለከተ ተነፈሰም አሻተተም እንደ አንቺ ያለ አላገኘም ። የአንቺን መዓዛ ወደደ ። ደም ግባትሽንም ወደደ ። የሚወደውን ልጁንም ወደ አንቺ ሰደደ።

አንቺን የወደደ እግዚአብሔር አብ ቅዱስ ነው #በእውነት ቅዱስ ነው !
በማኅጸንሽ ያደረ ወልድ ዋሕድም ቅዱስ ነው
#በእውነት ቅዱስ ነው !
ያጸናሽ የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስም ቅዱስ ነው
#በእውነት ቅዱስ ነው !

መልካሙን ዜና ያበሰርክ አብሳሪው ሆይ ስለ ዛሬም መልካሙን ዜና አሰማን !

#በነገር_ሁሉ_ስለ_ሀገር_መጸለይን_አታስታጉሉ!

በዲ.ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ

ሰናይ ሌሊት! መልካም በዓል።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

29 Dec, 18:23


የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የ2017 ዓ.ም የግማሽ  ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት አከናወነ።

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ታኅሣሥ 20/04/2017 ዓ.ም

የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት 11ኛ  1ኛ የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ የማዕ/ጎ/ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ :ሊቀ ሥልጣናት አባ ዮሴፍ ደስታ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ :የሀገረ ስብከት የመምሪያ ኃላፊ: በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ አንድነት የተቋቋመባቸው ወረዳዎች የመጡ የአንድነት ተወካዮች የጎንደር ርዕሰ ከተማ አድባራት ተወካዮች በተገኙበት ዛሬ ታህሳስ 20/2017 ዓ.ም ተከናውኗል።

በመርሐ ግብሩም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤት ክፍል ኃላፊ ሊቀ አእላፍ ብርሃኑ የተበሰረ ሲሆን :የወረዳ ሰ/ት/ቤት አንድነት ሪፖርት እና እቅድ የቀረበ ሲሆን :የሀገረ ስብከቱ ሰ/ት/ቤት አንድነት ሪፖርት እና እቅድ ደግሞ በሀገረ ስብከቱ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ተ/ሰብሳቢ ዲ/ን አንዳርጋቸው  ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን እንዲሁም የሥርዓተ ትምህርት ሥልጠና:የሰ/ት/ቤቶች ተሞክሮ እና ውይይቶች ተከናውነዋል።

በመጨረሻም በክቡር ስራ አስኪያጁ በጉባዔው ለተነሱ ጥያቄዎች በሀገረ ስብከት በኩል የሚፈጸሙትን መልስ በመስጠት እና በብጹዕ አቡነ ዮሐንስ አባታዊ መልዕክት በአጽንኦት የተላለፈ ሲሆን  ማሳረጊያ ጸሎት ተደርጎ ፍጻሜውን አግኝቷል።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

29 Dec, 18:01


የአዲስአበባ ሰንበት ት ቤቶች አንድነት አስራ አንደኛ ዓመት የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም ጉባኤውን አከናወነ።

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ታኅሣሥ 20/04/2017 ዓ.ም

"አንድነታችን ለቤተ ክርስቲያናችን" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ጉባኤ ከአ/አ ሁሉም ክፍለ ከተሞች አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ የሰንበት ት/ ቤቶቾ የሥራ ኃላፊዎች እና ወጣቶች የታደሙ ሲሆን የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እና ምክክር ተደርጓል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰንበት ትቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ እንዲሁም ሊ/ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና መጋቤ ሐዲስ ፀጋ ወልደ ትንሳኤ
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሐላፊ በጉባኤው  ተገኝተዋል።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

27 Dec, 18:59


"እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ።" ሉቃ 1:19

እንኳን ለገናናው መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

27 Dec, 16:43


https://www.youtube.com/watch?v=Qb155JXILmI

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

26 Dec, 18:25


"ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።" መዝ 42(43)፡3

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

25 Dec, 17:47


https://www.youtube.com/watch?v=yiG0BU5xwl8

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

29 Nov, 18:26


"እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና።" መዝ 131(32)፡13

እንኳን ለጽዮን ማርያም በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

28 Nov, 17:10


https://youtu.be/S3BmXrvgq30

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

26 Nov, 20:07


"በጾምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር።" ሉቃ 2:37

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

25 Nov, 18:51


የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ኅዳር 14 እና 15 ቀን 2017 ዓ.ም የዓመቱን የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤና የ3ኛ ዙር ሀገረ ስብከት አቀፍ የሰንበት የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መንፈሳዊ ተማሪዎች የምረቃ ሥነ ሥርዓት የጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተገኙበት በታላቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል።

መረጃው የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ነው።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

25 Nov, 08:36


የአ/አ/ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ከልማት ጋር ተያይዞ የመኖሪያ አካባቢ ለቀዉ ወደ ሌላ አካባቢዎች የተዘዎወሩ እና የሚዘዋወሩ  አባላትን  መንፈሳዊ ትምህርታቸው እና አገልግሎታቸው  ለማስቀጠል ውይይት ተደረገ።

(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ኅዳር 16/03/ 2017 ዓ/ም

የአ/አ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ኅዳር 15/2017 ዓ.ም ባደረገው ውይይት በኮሪደር ልማት ምክንያት ከየአጥቢያው የተነሱ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላቶቻቸው ወደ ሌሎች አካባቢዎች በመዘዋወራቸው በአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ ብሎም በሰንበት ት/ቤቱ  አባላቶቻቸው ቁጥር ማነስ እና በአገልግሎት ላይ የሚያሳድረውን እና እያመጣ ያለውን ተግዳሮት አሳሳቢ መሆኑን በውይይቱ ላይ  በሰንበት ት/ቤቶቹ ተነስቷል።

በዚህም ሰንበት ት/ቤቶቹ ከአባላት ከአካባቢው መነሳት ጋር ተያይዞ ከአምስት ፐርሰንት እስከ ሰማንያ ፐርሰንት አባላቶቻቸው መቀነሳቸው እና በሥርዓተ ትምህርት እየተማሩ ከነበሩ ተማሪዎች ከአንድ አጥቢያ ከ500 በላይ ተማሪ የነበረበት ወደ 30 የመቀነስ ሁኔታዎች እንደገጠሙ በውይይቱ ተነስቷል ከዛም ባለፈ ከሳምንታዊ ጉባኤያት ወደ ወርሐዊ ጉባኤ ለመዘዋወር የተገደዱ እንዳሉ እና በቀጣይም ሙሉ በሙሉ የሕፃናት ጉባኤያት በአዲስ ሌላ ተማሪ  እስኪመጣ ሊቋርጥ የሚችልበት ስጋት መኖሩን ገልጸዋል።

በልማት አገልጋዮቻቸው  እና አባላቶቻቸው የተነሱባችው ሰንበት ት/ቤቶችም አሁን ያለውን  የአገልግሎት  ችግር ለመቅረፍ እና አባላቶቻቸው በሄዱበት አካባቢ በሚገኝ አጥቢያ  አገልግሎታቸውን ለማሰቀጠል እና ከቤተክርስትያን እንዳይርቁ የሚያደርጉበትን ዋና ዋና ምክረ ሐሳቦችን ተወያይተዋል። ይህ ሁኔታ ቀጣይ ከመሆኑ አንጻር ሌሎችም ወደፊት ይህ ተግዳሮት ሲመጣ እንዴት ይለፉት ለሚለው ጥናቶች በችግሮቹ እና መፍትሔዎቻቸው ዙሪያ እንዲጠኑ ከባለድርሻ አካላት እና ከቤተክርስትያን የመዋቅር አመራር አባቶች ጋር ውይይት መደረግ እንዳለበት በጉባኤው ሐሳብ ተነስቷል

አንድነቱም ከክ/ከተማ ከሰንበት ትቤቶች አንድነት አመራሮች እና ከተነሺ  እና ተቀባይ አጥቢያ  ሰንበት ት/ቤት አመራሮች ጋር በመወያየት እና በማስተባበር አባላቱ ባሉበት መንፈሳዊ ትምህርታቸውን እና አገልግሎታቸውን ለማስቀጠል እንደሚሰራ እና የግንዛቤ መፍጠሪያ  ውይይቶችን በቀጣይም እንደሚደረግ ተገልጿል። በማጠቃለያውም ሁሉም በጋራ በመተባበር በአጭር ጊዜ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ መሠራት ያለባቸውን ጉዳዮች ጥናት ላይ ተሞርኩዞ ተግዳሮቶቹን ለመቀነስ የሚፈጠሩ እድሎችን ለማስፋት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ለነገ ሳይል ከዛሬ ጀምሮ በጸሎት እና በተግባር ሥራ ርብርብ እንዲያደርግ  ጥሪ ቀርቧል።

ዘገባው የአ/አ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት ቤቶች አንድነት ነው።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

20 Nov, 18:41


“ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።” ዳን 10፡13

👉🏻 #ሚካኤል ማለት መኑ ከመ አምላክ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው የሚል ትርጉም አለው። ይህም እንደ እግዚአብሔር ያለ በባሕርይው ቅዱስ የሆነ ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ንጹሐ ባሕርይ ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ፍጹም ማነው የሚል ነው። ቅድስና ፣ ንጽሕና እና ፍጹምነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ከእግዚአብሔር በቀር የለምና።

👉🏻 ሚካኤል ፍጥረቱ በዕለተ እሑድ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ 1፡3 ላይ “እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ።” ብሎ ብርሃንን በፈጠረ ጊዜ ሕልውና መላእክት ታውቋል። እንዴት ቢሉ ሰሚ በሌለበት ተናጋሪ አይናገርምና እንዲሁ ልዑል እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰሚአን የሆኑ መላእክትን ስለፈጠረ ብርሃንን በነቢብ (በመናገር) ፈጥሯል። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በዛሬው ዕለት ኅዳር 12 ቀን በዓለ ሲመቱ ይታሰባል። ይህ ቅዱስ መልአክ መጋቤ ብሉይ እየተባለ ይጠራል። በብሉይ ብዙ ገቢረ ተአምራትን እየሠራ በጎላ በተረዳ አበው ነቢያትን ስለተራዳና ከእግዚአብሔር ተልኮ ድንቅ ድንቅ ሥራዎችን በማድረጉ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።

👉🏻 በዘኁ 22፡21-35 ላይ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እሥራኤል ዘሥጋን ያለአግባብ ሊራገም የወጣውና ሀብተ መርገም የተሰጠው በልአምን የተቋቋመው እሥራኤል ዘሥጋን ከእርግማን ያዳናቸው ይህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው።

👉🏻 ኢያ 5፡13-15 ላይ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በጌልጌላ ለነቢዩ ኢያሱ ወልደ ነዌ ተገልጦለት ነበር። ኢያሱም የመልአኩን ማንነት ሲያረጋግጥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን?” አለው። መልአኩም መልሶ “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ” ቢለው ኢያሱ በመልአኩ ፊት በፍርሃት ሰግዷል። “እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።” በሚለው ታላቅ የእምነት ንግግሩና ምክሩ የምናውቀው መስፍን ዝቅ ብሎ ለመልአኩ የሰገደው ስለምንድን ነው ብለን ብንጠይቅ ለቅዱሳን መላእክት የጸጋ ስግደት ስለሚገባ ነው። ቀድሞ ከሊቀ ነቢያት ሙሴ ጋር ሆኖ ሕዝቡን ሲመራ የነበረው ይህ ቅዱስ መልአክ ከኢያሱም ሳይለይ እስራኤል ዘሥጋ በጠላቶቻቸው እንዳይዋረዱ ሲረዳቸው ነበር። ዛሬም ይህ መልአክ ክርስቲያኖች በጠላት ዲያብሎስ እንዳይዋረዱ ይራዳቸዋል።

👉🏻 ዘጸ 23፡20-22 ላይ እግዚአብሔር አምላክ ለእርሱ የሚታዘዙትን ሁሉ በመንገዳቸው እየጠበቃቸውና እየተራዳቸው ወደ ርስት መንግሥተ ሰማይ መርቶ ለክብር እንዲያበቃቸው እንዲሁም አመጸኞችን ይቀጣ ዘንድ ለዚህ ቅዱስ መልአክ ክብርና ሥልጣን እንደሰጠው ይናገራል። “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወደ አዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ መልአኬን በፊትህ እሰዳለው።” እንዲል። በዚህ ቃል መሠረት እግዚአብሔር በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት እሥራኤል ዘሥጋን ከግብጽ ባርነት ወደ ምድረ ርስት ከንአን እንደሚያስገባቸው ተናግሯል። ታዲያ እሥራኤል ዘነፍሥ የሆንን እኛ ክርስቲያኖችን ደግሞ በግብጽ ከተመሰለች ሲኦል በምድረ ርስት ከንዐን ወደ ተመሰለች ገነት ርስት መንግሥተ ሰማይ በአማላጅነቱ በተራዳኢነቱ እንደ ምን አያገባን? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልአኩ አማላጅነትና ተራዳኢነት ፈጣን አገልግሎቱም ርስቱን እንደምንወርስ ሲናገር “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስ አይደሉምን?” ብሏል። ዕብ 1፡14 እኛም ከቅዱሳን መናፍስት ወገን አንዱና አለቃቸው የሆነ ቅዱስ ሚካኤል መዳን መንግሥተ ሰማይን እንወርስ ዘንድ የሚላክ የሚያገለግል አይደለምን እንላለን። ወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ ገጸ ንባቡ እንዲህ ብሎ ይቀጥላል “በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።” የእግዚአብሔር ስም በስሙ ላይ ላለ ለዚህ ታላቅ መልአክ የመፍረድንም ሥልጣን ከአምላካችን እንደተሰጠው ትመለከታላችሁን? ከማማለድም በላይ ኃጢአት የሚሠሩትን አመጸኞችን የመቅጣት ሥልጣንን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቸረው ደግ ሩህሩህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው። በአንጻሩ ቃሉን የሚሰሙትን እርሱን የሚያከብሩትን ደግሞ በረድኤት በበረከት ይሞላቸዋል ፣ ምድራቸውን ከበሽታ ይፈውስላቸዋል ፣ እህሉንም ውኃውንም ይባርካል ፣ ጠላቶቻቸው የሆኑ አጋንንትን ከእግራቸው በታች ይቀጠቅጥላቸዋል።

በተጨማሪም መልአሉ ቅዱስ #ሚካኤል

👉🏻 ድኅነተ ሥጋ ወነፍስ ያሰጣል። መዝ 33፡7 ፣ ዘፍ 48፡16 ፣ ዕብ 1፡14
👉🏻 ከክፉ ሁሉ ይራዳል። ዳን 10፡13 ፣ ዳን 12፡1
👉🏻 ያማልዳል ያስታርቃል። ዘካ 1፡12-13
👉🏻 ለሰው ሁሉ በጎን የሚያደርግ መልአክ ነው። ሔኖክ 6፡1-2
👉🏻 የከበረ መልአክ ነው። ከክብሩ የተነሳም ምድር ሁሉ ትበራለች። ራእ 10፡1 ፣ ራእ 18፡1
👉🏻 የትሕትና አባት ነው። ይሁ 1፡9
👉🏻 በሰዎች ድኅነት ሀሴት ደስታን የሚያደርግ ነው። ሉቃ 15፡7
👉🏻 በተጨነቅን ጊዜ የሚያበረታን የሚያረጋጋን የሚያጽናናን መልአክ ነው። ሉቃ 22፡43 ፣ ዳን 10፡20

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤቱ አማላጅነቱ ፈጣን ተራዳኢነቱ ዘወትር ከኛ ጋር ይሁን!!! መልካም በዓል!

ይቆየን።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

19 Nov, 19:00


ቅድስት ሐና እመ ማርያም ወላዲተ አምላክ

ኅዳር 11 በዚህች ቀን አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም እናት የሆነችው ቅድስት ሐና የዕረፍት በዓል መታሰቢያ ነው። ልመናዋ ይደረግልን በቅድስት ሐና ጸሎት ይማረን በረከትዋም ይደርብን! መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

19 Nov, 18:07


https://youtu.be/5N0VyWh9JCw

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

18 Nov, 19:09


"ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ፥ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ፤ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።" መዝ 44(45)፡1

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።

ሰናይ ሌሊት!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

18 Nov, 18:20


የ4ኛ ክፍል ክርስቲያናዊ ሥነምግባር ትምህርት ተግባራዊ ልምምድ

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የመማር ማስተማር ሒደቱ ውስጥ መምህራን ተማሪዎቻቸው ሊያዩዋቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በማሳየት ለሰሙዋቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እንዲሰሙ በማመቻቸት በልባቸው ሰሌዳ እንዲሳል ማድረግ ላይ ትኩረት ይሰጣል።

በተለይ በታችኞቹ ክፍሎች ላይ ተግባራዊ ልምምዶች እጅግ አስፈላጊ በመሆናቸው በመጽሐፍ ዝግጅቱ ውስጥ በትዕዛዝ መልክ ለመምህራንና ለተማሪዎች ተለይቶ ተቀምጦ እናገኘዋለን።

ይኸ በ4ኛ ክፍል የክርስቲያናዊ ሥነምግባር ትምህርት በምዕራፍ ሦስት በስግደት ትምህርታቸው የስግደትን ምንነትና ዓይነቶች ለይተው እንዲያውቁና እየፈጸሙ እንዲያድጉ ለመምህሩ ከተሰጡት ተግባራት መካከል አንዱ ሲሆን መምህሩ በቅዱሳን ሥዕላት ፊት እንዴት ባለ መልኩ ሊሰግዱ እንዲገባ ተግባር እየሰጠ ይገኛል።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

15 Nov, 07:39


እንኳን ለቁስቋም ማርያም በሰላም አደረሳችሁ!

እንኳን አደረሳችሁ! መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

14 Nov, 18:59


"አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ!" መኃ 7:1

ሰላማጢስ ማለት ሰላማዊት የሰላም መገኛ ማለት ነው። እውነተኛዪቱ የሰላም መገኛ እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። በባሕርይው ሰላም የሆነ ክርስቶስ ከእርሷ ተገኝቷልና ሱላማጢስ ሰላማዊት ትባላለች። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በላከላቸው መልእክቱ "እርሱ ሰላማችን ነው።" ብሎናል። ኤፌ 2÷14 ራሱ ጌታችንም በመዋዕለ ሥጋዌው "ሰላሜን እተውላችኋለሁ። ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም።" ዮሐ 14፡27 በማለት የሰላም ባለቤት እርሱ መሆኑን ነግሮናል። ይህ የሰላም ባለቤት የተገኘው ደግሞ ከእመቤታችን በመሆኑ እርሷም ሰላማዊት ተብላለች። "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ነው፤ ስሙም ድንቅ መካር ኃያል የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።" እንዲል። ኢሳ 9፡6

ሱላማጢስ የተባለች እመቤታችንን አባቷ ሰለሞን በትንቢት መነጽር የስደቷን ነገር በዘመረበት መዝሙሩ "አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሺ" ብሏታል። ፈጣኒቱ ደመና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቀዳማዊቷ ሔዋንን ስደት ስደቷ አድርጋ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በግብጽ በረሀ ለ3 ዓመት ከ6 ወር ያህል ተንከራትታለች። "ልጄን ከግብጽ ጠራሁት" ሆሴ 11፡1 የሚለው የነቢዩ የሆሴ ቃል ይፈጸም ዘንድ ከቆየችበት ከባዕድ ሀገር ግብጽ ወደ ሀገሯ ወደ ገሊላ ተመልሳለች። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አስቀድሞ ለዮሴፍ ወደ ግብጽ እንዲወርድ እንደነገረው ሁሉ "የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ።" ብሎ እንዲመለስም አዝዞታል። ያን ጊዜ ሱላማጢስ እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ወደ እስራኤል መጥታ በናዝሬት ገሊላ ኖራለች።

የእመቤታችን ከግብጽ ወደ እስራኤል መመለሷ ዛሬም በኃጢአት እና በዓለም ለተሰደድን ልጆቿ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ወደ ገቢረ ጽድቅ እንድንመለስ ትልቅ ትምህርት ያስተምራል። ሰለሞን እናይሽ ዘንድ ተመለሺ እንዳላት እኛም ወደ ቅድስት እናታችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመልሰን በዐይነ ልቡናችን እመቤታችንን እየተመለከትን እንድንኖር አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን።

ይቆየን!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

14 Nov, 12:13


https://youtu.be/tFOmAVQJkwE

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

12 Nov, 18:58


"ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።" ሆሴ 11፡1

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

12 Nov, 13:35


https://youtu.be/Ak5Sas34iSg

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

12 Nov, 06:45


https://youtu.be/dBWSQ-rcgMU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

09 Nov, 17:16


"ናሁ ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ ፤ እነሆ የተወደደ ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ።"

ሰናይ ማኅሌት መልካም ዕለተ ሰንበት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

08 Nov, 19:19


"የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።" ዕምባ 3፡7

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።

ሰናይ ሌሊት!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

08 Nov, 18:52


https://youtu.be/rkhsTLSpOHY

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

06 Nov, 19:01


አማኑኤል

እንኳን ለቅዱስ አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

"ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።" ኢሣ 7፡14

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ሰናይ ሌሊት! መልካም በዓል!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

06 Nov, 07:41


https://youtu.be/8sr8US7V74k

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

05 Nov, 18:55


"እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን።" ዮሐ 4፡42

እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ሰናይ ሌሊት! መልካም በዓል!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

05 Nov, 13:58


https://www.youtube.com/watch?v=NODU-37QEz8

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

04 Nov, 19:17


"አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።" መኃ 2፥12

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ሰናይ ሌሊት!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

04 Nov, 17:41


https://youtu.be/eAkaCOra5W0?si=PODiu6C4ISzDCK4Q

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

02 Nov, 19:26


ማኅሌተ ጽጌ አምስተኛ ሰንበት

ሰናይ ማኅሌት መልካም ዕለተ ሰንበት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

02 Nov, 19:10


ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ እቃ ለድሬደዋ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ድጋፍ ተደረገ።

(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድሬደዋ ሀገረ ስብከት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ለአንድነቱ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ድጋፍ ተደረገ።

በዕለቱም የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል አባ ተስፋዬ እማምሰው ፣ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ሐላፊዎች ፣ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ሰብሳቢዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት መርሐ ግብሩ የተከናወነ ሲሆን በመርሐ ግብሩም በአንድነቱ ቀጣይ አገልግሎት ዙሪያ ታዳሚዎችን ያሳተፈ ምክክር ከተደረገ በኋላ የተገዛውን ንብረት ለአንድነቱ ተ/ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ሀብታሙ ሽፈራው ክቡር መልአከ ኃይል አባ ተስፋዬ ያስረከቡ አስረክክበዋል። በማስከተልም የወጪ ዝርዝር ሪፖርት ለእንግዶች በማሰማት ይህን ስራ ሲያስተባብሩ ለነበሩ የኮሚቴ አባላት እና ለደብራት አለቆች ዕውቅና ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ተስፋዬ ይህን ስራ ከመነሻው እስከ መድረሻው በቅርብ በመከታተል አባታዊም አስተዳደራዊም መመሪያ በመስጠት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሀገረ ስብከቱን ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስን ያመሰገኑ ሲሆን በተመሳሳይ ለአጥቢያ አለቆች እና ለአንድነቱ አባላትም በሙሉ በዚህ ስራ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና በማቅረብ መርሐ ግብሩን በጸሎት ዘግተዋል።

መረጃው የድሬደዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት ነው።

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

31 Oct, 19:02


"ድንግል ማርያም የሽቱ መኖሪያና የሕይወት ውኃ ምንጭ ናት። የማሕጸንዋ ፍሬ ሰውን ሁሉ አድኗልና።" ውዳሴ ማርያም ዘዓርብ

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

31 Oct, 18:07


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ልዑል እግዚአብሔርን አጋዥና መሪ በማድረግ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ስለምጣኔ ሀብት እድገት፣ በሀገራችን እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ 43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች የቀረበው ቃለ ጉባኤና የአቋም መግለጫ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ እየቀረቡ ያሉ መጠነ ሰፊ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ በክፍላተ ከተሞችና ችግር አለባቸው ተብለው በጥናት በሚለዩት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የማጣራት ሥራ እንዲሠራና ውጤቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ በሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
የኦሲኤን ቴሌቪዥን ስርጭት የተቋረጠ በመሆኑ በአዲስ መልክ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ባቀፈ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ኔትወርክ በሚል ስያሜ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ውል ተፈርሞ በአዲስ መልክ የሳተላይት ግዥ እንዲፈጸም ሆኖ አስተዳደሩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ጋር በአንድ ሊቀ ጳጳስና ቦርድ ራሱን በቻለ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ አገልግሎቱ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት አድቫንስ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሆን፤ ሥርዓተ ትምህርቱ ለሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ በሚመጥን መልኩ ተሟልቶ፣ ሊኖረው የሚገባው የሰው ኃይል በየዘርፉ ተጠናክሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፣
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሥነ ሕንጻና በኪነ ጥበብ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ በመዐርገ ጵጵስና ፕትርክና የሚሾሙ አባቶች ሥርዓተ ሲመት የሚፈጸምበት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለዕድሳት ሥራው የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ በተጨማሪም ምእመናን እስከ አሁን እንደሚያደርጉት ሁሉ ለእድሳት ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በንቃት እንዲሳተፍ ሁሉንም አህጉረ ስብከት ባቀፈ ሁኔታ የአጀንዳ መረጣና ተሳታፊ የመለየት ሥራ እንዲከናወን ሆኖ ዐቢይ ኮሚቴው የሥራ ዕቅዱንና አፈጻጸሙን ለቋሚ ሲኖዶስ እያቀረበ በማስወሰን እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 21ቀን 2017ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

31 Oct, 07:47


https://youtu.be/YHO1JJJtCR0

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

30 Oct, 19:09


“ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ ነውርም የለብሽም።” መኃ 4፡7

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

30 Oct, 12:13


https://youtu.be/c66bWSol95s

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

28 Oct, 18:59


"ማርያም ሆይ ነበልባል ከሐመልማል ተዋሕዶ ሙሴ በደብረ ኮሬብ ባየ ጊዜ ተአምርሽ በኦሪት ተሰበከ ተነገረ፡ ፡ ምሳሌሽ በሐመልማልና በእሳት አምሳል የታየ ማርያም ሆይ ጽጌ ልጅሽ ኃጢአቴን ያጠፋልኝ ዘንድ በጥላሽ ሥር አስጠጊኝ፡፡” ማኅሌተ ጽጌ

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

25 Oct, 18:50


"ድንግል ሆይ ፤ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ከአገር ወደ አገር ስትሽሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ፤ ከዓይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፤" ቅዳሴ ማርያም

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

25 Oct, 12:10


https://www.youtube.com/watch?v=BFXZ-sAnyJM

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

25 Oct, 12:09


https://youtu.be/twY4XtQh9nM

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

24 Oct, 19:38


"ድንግል ሆይ ፤ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ከአገር ወደ አገር ስትሽሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤" ቅዳሴ ማርያም

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

24 Oct, 07:34


አጣሪ ኮሚቴው ሪፖርቱን ለቅዱስ
ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ አቀረበ።
**************************
ጥቅምት ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
====================
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""""""""""
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተከስተዋል የተባሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተመለከተ ዝርዝር ጥናት ሲያካሒድ የሰነበተው አጣሪ ኮሚቴ የማጣራት ሥራውን በማጠናቀቅ ዛሬ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ሪፖርቱን አቅርቧል።
አጣሪ ኮሚቴው በሰነድና በቪዲዮ የተደገፉ የማጣራት ሥራ ግኝቶችን እንዲሁም ቤተክርስቲያንን ማዕከል በማድረግ የተከናወኑ ዘረፋና ሕገ ወጥ ተግባራትን፣ከተጠያቂነትና
ወደፊት ሊወሰዱ ከሚገባቸው የመፍትሔ ሐሳቦች ጋር በማቀናጀት የቤተክርስቲያን ልዕልና የሚከበርበትን አቅጣጫ የሚጠቁም ሪፖርት አቅርቧል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም በዛሬው ዕለት በሚያካሂደው ጉባኤ የቀረበለትን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘገባው የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation, EOTC ነው።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

23 Oct, 18:49


ጥቅምት 14 የነገሥታት ልጆች የሆኑት አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተሰወሩበትና ፣ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ 30 አመት ተጋድሎ ያረፈበት ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሐዋርያው ፊሊጶስ ያረፈበት ኢትዮጵያዊው ባኮስም የሚታሰብበት ዕለት ነው። ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ያካፍለን።

ሰናይ ሌሊት! መልካም በዓል!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

23 Oct, 17:45


https://www.tiktok.com/@eotc_gssu/video/7429025868124654878

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

22 Oct, 18:50


"የኢየሩሳሌም ቆነጃጂት ሆይ ማርያምን በቁስቋም ተራራ በጫካውም ካገኛችኋት በመከራ ዓለም በጭንቀት ያለሁ የጎስቋላ አገልጋዩአን ልቅሶ ትነግሯት ዘንድ በኃያሉ አምላክ ስም እለምናችኋለሁ።" ሰቆቃወ ድንግል 7

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

21 Oct, 18:20


በኢ/ ኦ/ ተ/ ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለየአኅጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና ለሰንበት ት/ቤት ክፍል ሐላፊዎች የሁለት ቀን ሥልጠናና የምክክር መድረክ ተከናውኗል።

(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ጥቅምት 11/02/2017 ዓ.ም

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ፵፫ኛውን የሰበካ ጉባኤ ለመካፈል ከተገኙ ከየአኅጉረ ስብከቱ ለመጡ ሥራ አስኪያጆች እና የሰንበት ት/ቤት ክፍል ሐላፊዎች ጋር በሰ/ት/ቤቶች አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙርያ የሥልጠናና የምክክር መድረክ ከጥቅምት 10-11 በጠቅላይ ቤተክህነት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ተከናውኗል።

መርሐ ግብሩ የዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በተገኙበትና "በምንት ያረትዕ ወሬዛ ፍኖቶ በአቂበ ትእዛዝከ " በማለት " ወጣቶች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ነገ ተረካቢ ትውልድ ይኖሯታልና ወጣቱን መጠበቅ የኛ የሁላችን ድርሻ መሆኑን አውቀን ተግተን ልንሠራ ይገባል።" የሚል አባታዊ መልዕክት በማስተላለፍ ተጀምሯል።

በመቀጠልም የማደራጃ መምሪያው ሐላፊ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሣኤ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትና ማደራጃ መምርያው እያከናወናቸው የሚገኙ ዋና ዋና ሥራዎችን በማቅረብ የአኅጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና የክፍሉ ተጠሪዎች ከመቼውም ግዜ በላይ ለወጣቶችና ለሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎት ትኩረት በመስጠት ሊሠሩ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሁለቱ ቀን መርሐ ግብር በዲ/ን ዶ/ር ያየህ ነጋሽ "ትኩረት ለሰንበት ት/ቤት ለምን?" እና የሰንበት ት/ቤት አጽተዋጽዎ ለቤተ ክርስቲያን "በሚል ርዕስ በቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መገናኛ ብዙኃን ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ስለ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መዋቅር አደረጃጀትና ስለ ሥርዓተ ትምህርቱ ምንነትና ዓላማ በዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ለተሳታፊዎች ገለፃ ተደርጓል።

በሁለተኛው ቀን መርሐ ግብር በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ ኢጲፋንዮስ የምስራቅ ጉራጌና የማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ "እንግዲህ እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ኹኑ" (ኤፌ 5፥1) በሚል አምላካዊ ቃል መነሻነት " ወጣቶችና ሕፃናት የነገዎን ቤተ ክርስቲያን የሚያስቀጥሉ የሚረከቡ ናቸውና እናንተ ደግሞ የነሱ መሪ እንደመሆናችሁ ወጣቶችና ሕጻናት የሚመለከቱት እናንተን ነውና ብርሃናቹ በሰው ፊት ይብራ" በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዎል።

በጉባኤው ማጠቃለያም በሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎትና በማደራጃ መምርያውና የየሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ ሰ/ት/ቤት ክፍል ሐላፊዎች ግንኙነት እና ቀጣይ ሊሰሠሩ ስሚገቡ ሥራዎች የጋራ ውይይት ተደርጎ እንዲህ ዓይነት የጋራ መድረኮች መለመድ እንዳለባቸው በጋራ መግባቢያ ሐሳብ የጉባኤው ፍፃሜ ሆኗል።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

21 Oct, 15:45


የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ' የባሕርዳና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና አስተዳዳሪዎች ካህናት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው በነገው ዕለት በቅዱስናቸው የመክፈቻ ንግግር የሚጀምር ይሆናል፡፡
©eotc tv

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

19 Oct, 18:44


ማኅሌተ ጽጌ ሦስተኛ ሰንበት

ሰናይ ማኅሌት መልካም ዕለተ ሰንበት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

19 Oct, 16:22


https://www.youtube.com/watch?v=I0UR67E_oc8

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

19 Oct, 16:09


https://www.tiktok.com/@eotc_gssu/video/7427509598124264734

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

18 Oct, 16:49


የአቋም መግለጫ፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

“ትውልደ ትውልድ ይንእዱ ምግባሪከ ወይዜንዉ ኃይለከ - የልጅ ልጅ ሥራህን ይናገራሉ፤ ያመሰግናሉ፣ ከሃሊነትህን ይናገራሉ ያስተምራሉ” መዝ 144 ቁ 4

ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ዓለምአቀፋዊት የሆነቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ረጅም ዘመናትን ሰማያዊውን ጥበብንና ምድራዊውን ዕውቀትን በማስተማር፣ የሀገርና የወገንን እምነትና ፍቅር ምንነት ከተግባር ጋር፣ ሰላምና አንድነትና በማስፈን፣ ለሰው ልጅ ዘለዓለማዊ ድኅነት ሌሌት ከቀን ያለማቋረጥ ሰዓት ሳይገድባት፣ መልክዓ ምድር ሳይገድት፣ የሰው ባህልና ቋንቋ ሳይወስኗት፣ ትውልድን፣ ከትውልድ፣ ዘመንን ከዘመን፣ ሰማያውያን ከምድራውያን፣ ፍጡራንን ከፈጣሪ ስታገናኝ ኖራለች፡፡ ለሰው ዘር ጥበብን፣ ለትወልድ ታሪክና ትውፊትን፣ ስትቀምር፣ ነፃነትና ሰብዓዊ ክብርን በዐውደ ምኅረቷ ስታውጅ፣ በአባቶችና በሊቃውንት በሕየወት ሰሌዳ፣ በደመቀ ቀለም በቃልም በመጽሐፍም ስታስተጋባ እስከ አሁን አለች ወደፊትም ትኖራለች፡፡

ከዚህ መሠረታዊ የታሪክ ዕሴት በመነሣት ለዛሬው 43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ደርሰናል፡፡

በዚሁ ጉባኤው በቆየባቸው ቀናት ውስጥ የቅዱስነታቸውንና የብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ አባታዊ መልእክቶች፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሪፖርት፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር አህጉረ ሰብከት ዘገባዎች፣ ከውይይት ሐሳቦች፣ ከአበው ሊቃነ ጳጳሳት መልእክቶች፣ ከቡድን ውይይትና ዘገባ በመነሣት ከቃለ ጉባኤ ሐሳብ በተጨማሪ በቅዱስ ሲኖዶስ ትኩረት ተሰጥቶባቸው በአጀንዳ ተቀርጸው ውይይትና ምክክር ተደርጎባቸው ውሳኔና መመሪያ ይደረግባቸው ዘንድ እኛም ለተፈጻሚነቱ የራሳችንን ድርሻ መወጣት እንድንችል ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የአቋም መግለጫ አቅርበናል፤

1. በጉባኤው መክፈቻ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ያስተላለፉፉልንን ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎታል፣ ለተግባራዊነቱ ቃል ይገባል

2. ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፉልንን አባታዊ መልእክት ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል እንገባለን፤

3. በብዙ የሀገራችን ክፍል ባለው የሰላም እጦት የተፈጠሩት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት የካህናት፣ የመነኰሳትና የምእመናን ሞትና ስደት በጥብቅ እያወገዝን በዚህ ታሪክ የማይረሳው በምድር ወንጀል፣ በመንፈሳዊው ዓለምና በሰማይ ኃጢአት የሆነ እኩይ ተግባር የተሰማራችሁ ሁሉ ወደ ርኃራኄ ልብ እንድተመለሱ ጉባኤው በአጽንዖት ጥሪውን ያስተላልፋል፤

4. የሰላም ዕጦት ጉዳይ ምንም እንኳ ዓለም አቀፍ ቢሆንም ሀገራችንም በተከሰተው ግጭትና ጦርነት ምክንያት ሰላም ካጣች ሰንብታለች፣ ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ በዓለም የሚደነቅ፣ ለሀገር ተገን የሚሆን አስደነቂ ውሳኔ እንደሚወስን ተስፋች ጽኑ ነው፣ ጸሎታችንም ነው፤ የአገልጋዮች እንባ የሚታበስበት፣ ለነገ ታሪክ የትውልድ ተወቃሽ ከመሆን ይልቅ፤ የሰላምና እርቅ ምሳሌ የምንሆንበት ከፍተኛ የሰላም ሥራ ልዩ የሆነ የሰላም ኮሚቴ ተቋቁሞ ዘላቂ ሰላምን ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚያመጣ ሥራ እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፤

5. የዚህን ዓለም ተድላ ንቀው፣ ደዋ ለብሰው ጤዛ ልሰው በገዳም ተወስነው ድምጸ አራዊቱን ግርማ ሌሊቱን ታግሰው ለመላው የሰው ዘር የሚጸልዩ ይህን ይደግፋሉ ያንን ይቃወማሉ የማይባሉ ገዳማውያን መነኮሳት ከየበአታቸው ተጎትተው ወጥተው የተገደሉበት ሁኔታ በሀገራችን መከሰቱ ጉባኤውን እጅግ አሳዝኖታል ይኽ ጉዳይ ቀጣይነቱ እየታየ ስለሆነ የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን የሕግ ሥራ በመሥራት የሰው ልጅ ከአምላክ የተሰጠውን የመኖር መብት፣ የእምነት ነፃነት፣ የመዘዋር ተፈጥሯዊና ሰብዓዊ መብት በሀገራች እንዲከበር ያሳስባል፤

6. በታሪካችን ያላየነው ከአባቶቻችን ያልሰማነው በመጻሕፍት ያላነበብነው ከኢትዮጵያ ባህልና ሥነ ልቡና ውጪ በሆነ መንገድ ሰዎችን ለገንዘብ ሲባል ማገት በተለይም ፊትና ኋላ ግራና ቀኝ እሳትና ውኃ ያለዩ ሕፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው፣ ወጣቶችና አረጋውያን ሳይቀር እያተገቱ የሚሰቃዩበትና የሚደፈሩበት ሁኔታ የገጠመንን ፈተና ክብደቱን የሚያሳይ መሆኑ ይኽ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፤

7. ጥላቻና የጥፋት ቅስቀሳዎች፣ በዜጎች መካከል አለመተማመንና መለያየት፣ ለሀገር አንድነትና የሕዝብ አብሮነት ጠንቅ፣ ለወደፊቱ አስጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች የበዙበት፣ የትውልዱ የወደፊት በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ የመኖር ዋስትና እየጠፋ፣ በርካታ ወጣቶች በስደትና በመፈናቀል ላይ ያሉበት ሁኔታ በመኖሩ የጥላች ንግግር፣ ዘለፋና ያልተገባ ትችትና መናናቅ ማንንም የማያንጽ ክፉ ትምህርት፣ ለሀገርም፣ ለሕዝብም የማይጠቅም ሁሉንም የሚያጠፋ ስለሆነ በእንዲህ ያለ ተግባር መገናኛ ብዙኀን በመጠቀም የተሰማራችሁ፣ ሁሉ በሚያፋቅርና በሚያዋድድ ተግባር እንድትሰማሩ ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፣ ቅዱስ ሲኖዶስም ለዚሁ ትኩረት ሰጥቶ መመሪያና ውሳኔ ያወጣ ዘንድ አጽንዖት እንጠይቃለን፤

8. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 20 በእንተ ሰማዕታት የጌታችንን ትምህርት መሠረት በማድረግ በተሠራው ቀኖና ካህናትና ምእመናን ሰማእትነትን የተቀበሉበትን ቀን መዘከርና ማክበር፣ የከበረ አጽማቸውን በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን በክብር ማስቀመጥ፣ ቤተሰቦቻቸውንና በእነሱ ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ የሰማእታት ቤተሰብ በሚል መርዳት የተደነገገ ቀኖና ነው፤ ይኽን በማድረግ የሰማእትነት ዋጋን እናገኛለን፣ ቤተ ክርስቲያነን እናጸናለን፤ በዚህ ቀኖና መሠረትና ከሰብዓዊ ርኅራሄ በመነሣት በሰማዕትነት የተለዩን ወገኖች መታሰቢያቸው እንዲደረግ፣ ቤተሰቦቻቸውና ጉዳተኞችን ወላጆቻውን ያጡ የካህነትና የምእመንና ጨቅላ ሕፃናትና ያልደረሱ ልጆች፣ ያለጧሪ የቀሩ አረጋውያን የቤተ ክርስቲያንን እንክብካቤ በጥብቅ ይፈልጋሉ፤ ለዚህ መፍትሔ እንዲሆን በውጭና በሀገር ውስጥ ያሉ አህጉረ ሰብከት ያካተተ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት እያሳሰብን ለተግባራዊነቱም ሁላችንም ቃል እንገባለን፣

9. በአንዳንድ አካባቢዎች ሕግንና የአምልኮ ነፃነት ሰብዓዊ መብትን በመጣስ የመስቀል ደመራና የባሕረ ጥምቀት ቦታ መወሰድ ሃይማኖታዊ አለባበስና መስቀል መያዝን በመከልከል የአንገት ማዕተብን መበጠስ፣ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እንግልትና ወከባ መፍጠር አሳዛኝ በመሆኑ ድገርጊቱን አጥብቀን እየተቃወመን በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይት እንዲደረግበት ጉባኤው ያሳስባል፤

10. ቤተ ክርስቲያን እንኳንስ ተናግራ ሰማች ሲባል የሚያስደነግጥ ግርማና መታፈር፣ መከበርና መወደድ የነበራት በመሠረተችው ሀገር የምትሳደድበት፣ የመሪዎቿ አባቶች ጥሪ የማይከበርበት፣ የሰላም ጥሪ ድምጽዋ የማይሰመባት፣ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በመፈተሸ ክብርና ልዕልናዋ እንዲመለስ በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውይይትና ጥልቅ ምክክር እንዲደረግ መፍትሔም እንዲፈለግለት ጉባኤ ያሳስባል፤

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

18 Oct, 16:49


11. ሙስና፣ ዘረኝነት፣ ጎሠኝነት፣ ቡድነኝነት፣ አድሎአዊነትና ግለኝት በተመለከተ በጋራ በአንድ ድምጽ በመነሣት ይኽንን ክብረ ነክና አጋላጭ፣ ለቤተ ክርስቲያን እድገትና ለሐዋርያዊ ተልእኮ እንቅፋት፣ የቤተ ክርስቲያን ማንነት ለሌላቸው ግለሰቦች መደበቂያ፣ በጥቂት ግለሰቦች በደልና ጥፋት በንጽሕና በቅድስና የሚያገለግሉ፣ ካህናትንና ሠራተኞችን የሚያሳፍሩ፣ ምእመናንን የሚያሸማቅቁ በመሆናቸው እነዚህን ክፉ ደዌያት ስም አጠራራቸውን ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለማስወገድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በጥናትና በቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ፣ የጥፋት በራቸውን በዘላቂነት የሚዘጋ ሥልት እንዲቀይስ ጉባኤው ያሳስባል

12. በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት እስከ አሁን ቤተ ክርስቲያን በፈረሱባት ሕንፃዎችና ቤቶች ምትክ ቦታ በመስጠት ጉዳቷን ለመቀነሰ የተደረገውን ጥረት ጉባኤው እያደነቀ፤ በተሰጡት ይዞታዎች ላይ በአጭር ጊዜ ግንባታውን በማካሄድ የአባቶችቻንን አሻራ መልሶ በመትከል፣ ይዞታውን ማስከበርና የተቋረጠውን ገቢ ማስቀጠል እንዲቻል ብርቱ ጥረት እንዲደረግ ጉባኤው እያሳሰበ፤ የኮሪደር ልማት የተባለው ጉዳይ በሌሎች የክልል ከተሞችም እየተስፋፋ ስለሆነ በቀጣይ ለሚነሡ የይዞታ ጥያቄዎች ለሚከሰቱ ችግሮች ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ፣

13. አዳዲስ አማኞችን አሳምኖ ለሥላሴ ልጅነት ማብቃት፣ የአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት መተከል፣ መታነፅና መባረክ የታየው ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ እመርታ ሁሉን ያስደሰተ በመሆኑ ከዚህ በበለጠ አጠናክረን ለመሥራት ቃል እንገባን፤

14. የቅዱስ ባኮስ የቅድስና ዕውቀና ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ስትዘግበው የቆየ ቢሆንም ጽላት ተቀርፆ እንዲከበር መደረጉ አስደሳች ሲሆን ለሀገር በረከት፣ ለትውልድ የመንፈሳዊ ሕይወት አርአያ፣ ለቅድስና ፍኖት የሆኑ ነገርግን የማይታወቁ የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ቅዱሳን ታሪክና ገድል በማጥናት እንዲዘከሩ እንዲደረግ ጉባኤው ያሳስባል፡

15. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የተከፈቱ መንፈሳውያን ኮሌጆችና የካህናት ማሰልጠኛዎችም በአጥጋቢ ሁኔታ ሥራ መጀመራቸው፣ በዚህ ዘርፍ በእጥፍ እየጨመረ የመጣው ዕድገትና ውጤት ጉባኤው ያደነቀ ሲሆን ወደ ሥራ ለመግባት በሂደት ላይ ያሉት በርካታ መንፈሳዊ ኮሌጆች እየተስሳፉ ያሉ የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ዘመናዊ የትምህርት ተቋማት በአጠቃላይ ሁሉም ትምህርትን የሚመለከት ጉዳይ በትምህርት ኮሚሽን ተቋቁሞ ጥናት በማድረግ እንዲስፋፉ ጉባኤው ያሳስባል፤

16. በሰላም መታጣትና በቀኖና ጥሰት ምክንያት መላው ወለጋ አህጉረ ስብከት ለበርታ ወራት ከማእከሉ ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ በቅርቡ በሀገረ ሰብከቱ ሊቀ ጳጳስ ወደ መዋቅር መመለሳቸው ጉባኤውን በእጅጉ አስደስቷል፤ ስለሆነም ቀሪ ሥራዎች ተጠናቀው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እንዲጠበቅ፣ በሌሎችም አካባቢዎች ለተፈጠሩት የመዋቅር ጥሰቶች ቀኖናዊ መፍትሔ እንዲበጅለት ጉባኤ ያሳስባል፡፡

17. ሐዋርያዊትና የክርስቶስ አገልጋይ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ቋንቋን በማክበር ታገለግልበታለች እንጅ በቋንቋም አትገደብም፤ ስለዚህ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ሐዋርያዊ ተልእኮ መፈጸሟ እንደተጠበቀ ሆኖ ለወደፊት የሁሉም መዓርገ ክህነት ሢመት፣ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር ሥራ የኃላፊነት ምደባዎች፣ መሠረት እምነትን፣ ቀኖና ቤተክርስቲያንን፣ ዕውቀትና ሙያዊ ብቃትን ብቻ መሠረት ያደረገ ይሆን ዘንድ ጉባኤው በጥብቅ ያሳስባል፤

18. ሰበካ ጉባኤን ማጠናከር፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን ማደራጀት፣ አብነት ትምህርት ቤቶች ማጎልበትና ማስፋፋት፣ ሕጎችና ደንቦችን በማዘጋጀት የተደረገውን ጥረት የሚያስመሰግን ሆኖ አሁን ወቅቱን የጠበቁ ሕጎችና ደንቦችን በማውጣት ሁሉም እንዲሠራበት ማድረግን፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ የራስ አገዝ ልማትን ማሳደግና በገቢ ራስን መቻል፣ በጸደቀው የዐሥር ዓመቱ መሪ ዕቅድ መሥራት የቤተ ክርስቲያናችን ዓይነተኛ ተልእኮ በመሆኑ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ለመፈጸም ቃል እንገባለን፡፡

19. የቤተ ክርስቲያናችን የውጭ ሀገር አገልግሎት እየሰፋና እያደገ መምጣቱ በጉልህ የሚታይ ሲሆን ይኽ እድገትና አደረጃጀት እንዲጠናከር፤ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሳትፎ የበለጠ እንዲያድግ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ጉባኤው ያሳስባል፤

20. ከውይይትና ከብፁዓን አበው መልእክቶች እንደተሰጠው መመሪያ የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና ለመመለስ፣ ለሀገራንችን ሰላምና ደኅንነት ለሰው ልጆች ሁሉ መልካም ግንኙነት የጋራ ጸሎት በኅብረት ይደረግ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ እንዲሰጥበት ጉባኤ በአክብሮት ይጠይቃል፤

በመጨረሻም እስከ ዛሬ ስንሰበሰብበት ከነበረው መቃረቢያ አዳራሽ ወጥተን ይኽ ዛሬ የተገኘንበት አዳራሽ በአጭር ጊዜ አሁን ባለበት ደረጃ እንዲህ ጸድቶና ተውቦ የ43ኛውን አጠቃላይ ጉበኤ እንዲከናወንበት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አመራር መስጠታቸው ቁርጠኝነት ካለ ብዙ መሥራት እንደሚቻል ያሳየ፣ የሥራ ክትትልና አፈጻጸም አድናቆታችንን በመግለጽ ሐዋርያው እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖርና እንዳለው የአዳራሹ ቀሪው ሥራ ተጠናቆ በቅርቡ እንደሚመረቅ ተስፋችንን እንገልጻለን፤

ይሕ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጸም ያደረጉ በቅዱስነታቸው አባታዊ ርእሰ መንበርነት፣ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በሳልና የተረጋጋ አመራር ሁሉም መርሐ ግብሮች በተያዘላቸው ሰዓትና ጊዜ ተጠናቀው እንዲፈጸሉ የመሩንን አባቶች በረከታችሁ ይድረሰን እያልን፤

የጉባአው ዋና አዘጋጅ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊና መላው ሠራተኞች፣ ሁሉም ተባባሪ አካላት በገንዘብም በጉልበትም ትብብር ያደረጉ ሁሉ በአጠቃላይ ጉባኤው አመስግኗል፡፡

ከሁሉም በላይ ለዚህ ለ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ ያደረሰንና ያስፈጸመን የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአሔር ምስጋና ይግባው አሜን ሎቱ ስብሐት ወባርኰት ወጥበብ፣ ወአኰቴት፣ ወኃይል ወጽንዕ ለአምላክነ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

17 Oct, 18:54


"በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።" 2ኛ ጢሞ 3፡12

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ሰናይ ሌሊት!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

17 Oct, 13:53


https://youtu.be/B4Olwm-XxH0

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

15 Oct, 18:56


"አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።" መኃ 2፥12

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ሰናይ ሌሊት!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

9,397

subscribers

2,339

photos

62

videos