Sheger Press️️ @sheger_press Channel on Telegram

Sheger Press️️

@sheger_press


Official channel of sheger press

If you want to give a suggestion or comment, contact us 👉 @birukepromo

Sheger Press️️ (English)

Sheger Press️️ is the official Telegram channel of Sheger Press, a leading news agency providing the latest updates and breaking news from Ethiopia and around the world. With a team of dedicated journalists and reporters, Sheger Press️️ delivers accurate and timely news coverage on politics, current events, sports, entertainment, and more. Whether you're looking for local news or international headlines, Sheger Press️️ has you covered. Stay informed and connected by joining Sheger Press️️ on Telegram today! For suggestions or comments, feel free to contact us via @birukepromo. Don't miss out on the latest news - join Sheger Press️️ now!

Sheger Press️️

07 Dec, 18:22


ዛሬ ማምሻውን በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠው የመብራት ኃይል አገልግሎት ወደነበረበት እየተመለሰ ነው

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩን ገልጿል።

ስለሆነም የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

07 Dec, 17:21


ህፃን ሰላማዊት አስፋው የ12 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ነዋሪነቷም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሐድያ ዞን ነው ።

በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም የአጎቷ ልጅ የሆነችው ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ስላሴ ለህፃኗ ወላጆቿ እያስተማረች ልታሳድጋት ቃል በመግባት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መኖሪያ ቤቷ ይዛት በመምጣት መኖር ትጀምራለች፡፡

መስከረም 3ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ሲሆን ለግዜው የፀቡ መነሻ ባልታወቀ ምክንያት ህፃን ሰላማዊት አስፋው ህይወቷ ያልፋል፡፡ ህፃኗን እያስተማረች ልታሳድጋት ያመጣቻች ተጠርጣሪ ታዳጊዋን የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በእንጨት በመደብደብ ከ20 ቦታ በላይ ጉዳት በማድረስ እና አንገቷን በማነቅ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

በህፃኗ ህልፈተ-ህይወት ተጠያቂ ላለመሆን ያሰቡት ተጠርጣሪዋ ግለሰብ ከባለቤቷ ጋር በመነጋገር በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በመስራት ላይ የምትገኝ የ17 ዓመት ዕድሜ ያላት ተስፋነሽ ጀባኔን ህፃኗን በድንገት እንደገደለቻት ለፖሊስ ቃል እንድትሰጥና ለውለታዋም ደሞዟን በእጥፍ እንደሚጨምሩላት በተለያዩ መደለያዎች በማሳመን߹ በወንጀሉም ጉዳይ ጠበቃ እንደሚቀጥሩላት ካሳመኗት በኋላ ለፖሊስ በሰጠችው ቃል የወንጀል ድርጊቱን እንደፈፀመች የሚገልፅ ነበር፡፡

ሆኖም ፖሊስ የተስፋነሽ ጀባኔን ቃል መነሻ በማድረግ የምርመራ ስራውን በማስፋት ሂደት ለጊዜው ተጠርጣሪ የሆነችው የቤት ሰራተኛ እኔ ነኝ የገደልኳት ብትልም አንዳንድ አጠራጣሪ ነገሮች መኖራቸውን የደረሰበት ፖሊስ ባደረገው ጥልቅ እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ሥራ የወንጀል ድርጊቱን የቤት ሰራተኛዋ እንዳልፈፀመች እና ልታሳድግ እና ልታስተምራት ባመጣቻት ግለሰብ በደረሰባት ድብደባ ህፃን ሰላማዊት አሰፋ ህይወቷ እንዳለፈ ይደርስበታል።

የምርመራ ሂደቱ ቀጥሎ ተጠርጣሪዋ ግለሰብም የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሟን አምና በመኖሪያ ቤቷ ድርጊቱን እንዴት እንደፈፀመች መርታ ማሳየቷን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪ ግለሰቧና ባለቤቷ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ፍ/ቤቱ እንዳዘዘ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ወንጀል ፈጽሞ ከህግ ተጠያቂነት የሚያመልጥ እንደማይኖር ያስታወቀው ፖሊስ ንዴትን በመቆጣጠርና በትዕግስት የወንጀል ድርጊትን መከላከል እንደሚቻል አስታውቆ ከቅድመ መከላከሉ ባሻገር ወንጀል ሲፈፀም በፍጥነት ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም አስታውቋል፡፡

@አዲስ አበባ ፖሊስ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

07 Dec, 17:20


#ግማሽ ክፍለ ዘመን እንቅልፍ ያላዩ ዓይኖች


ስምንት መቶ ሰባት ዓመታትን ወደኋላ ስንመለስ “ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን” “የአእላፍ ቅዱሳን አባት” በመባል የሚታወቁት ታላቁ ጻድቅ የተወለዱበት ዓመት 1210 ዓ.ም ላይ እንገኛለን፡፡

ጎንደር ስማዳ ዳሕና ሚካኤል የተወለዱት አባት ገና በጉብዝናቸው ወራት በ30 ዓመታቸው ዓለምና አምሮቷን ንቀው ወደ ትግራይ “ደብረ ዳህምሞ” የአባታችን አቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ በመግባት ከጻድቁ አምስተኛ የቆብ ልጅ አባ ዮሐኒ ካልዕ ደቀ መዝሙር ሆኑ፡፡


በደብረ ዳሞም ቀኑን ለመነኮሳት በመታዘዝ፣ በመፍጨትና ውሃ በመቅዳት ሌሊቱን ደግሞ እኩሉን በጸሎት እኩሉን ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ ያሳልፉት ነበር፡፡ ከሰባት ዓመታት ተጋድሎ በኋላም በ37 ዓመታቸው ምንኩስና ተሰጣቸው፡፡


በዚው ዓመትም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብዙ ተአምራትና አገልግሎት የምትሰራበት ስፍራ እግዚአብሔር አዘጋጅቶልሀልና ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ አላቸው፡፡ ምንም እንኳን ደብረ ዳሞና ሐይቅ እስጢፋኖስ እጅግ የተራራቁ ቢሆኑም መልአኩ ነጥቆ የተፈቀደላቸው ስፍራ ላይ አደረሳቸው፡፡


በዚም ለሰባት ዓመታት ከሐይቁ በስተሰሜን በሚገኘው የጴጥሮስ ወጳውሎስ ገዳም በማስተማርና በማገልገል ስራቸውን ጀመሩ፡፡ በእነዚህ ዓመታት ሌሊቱን በሐይቁ ውስጥ ገብተው በመጸለይ ያሰዳልፉ ነበር፡፡ በኋላም ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበው በብዙ ትግል አበምኔት አደርገው ሾሟቸው፡፡ ይህም የታላቁ ስራቸው መጀመሪያ ሆነ፡፡


አባታችን አቡነ ኢየሱስ ሞአ ከደሴ ከተማ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም 800 ደቀ መዛሙርትን በመሰብሰብና በማስተማር ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ያፈረሰቻትን ቤተ ክርስቲያን ይገነቡ ጀመር፡፡


ታላላቅ መጻሕፍትን በማሰባሰብ የመገልበጥና የማባዛት ስራ ያሰሩ ሲሆን ደቀ መዛሙርቶቻቸውንም በማስተማር በመላው ሀገሪቱ ለሐዋርያዊ አገልግሎት አሰማርተው ቃለ እግዚአብሔር እንዲስፋፋ፣ ትምህርት ወንጌል እንዲሰርጽ አድርገዋል፡፡


ለ45 ዓመታት በዘለቀው የገዳሙ አበምኔትነት አገልግሎታቸው አይናቸው ከእንቅልፍ ጋር ተገናኝቶ እንደማያውቅ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ይህን ተጋድሏቸውን ለፍሬ አድርጎላቸው ታላላቅ ጻድቃን አባቶችን አፍርተዋል፡፡


ከእነዚህም መካከል የደብረ ሊባኖስ ኢትዮጵያዊው ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አባ ኂሩተ አምላክ ዘጣና ሐይቅ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ዘኢየሱስ፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ አባ አሮን ዘደብረ ዳሬት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ንጉሱ አፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት አንጸው ለክብር ያበቋቸው እርሳቸው ናቸው፡፡ የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስም ጌታችን ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡

በተወለዱ በ82 ዓመታቸው በ1292 ዓ.ም ሕዳር 26 ቀን ወደ ማያልፈው ክብር ጌታችን ጠርቷቸዋል፡፡ አስገራሚው ነገር አበምኔት ከመሆናቸው በፊት ለሰባት ዓመታት በገዳሙ አስተዳዳሪነት ደግሞ ለ45 ዓመታት በጠቅላላው ለ52 ዓመታት በቆየው ተጋድሏቸው እንቅልፍ የሚባል በአይናቸው አልዞረም፡፡


ገዳማውያን ዓለምንና አምሮቷን ትተው ሲመንኑ የበለጠውን ክብር ሽተው፣ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ሰፊ ጊዜ ለማሳለፍ ፈልገው እንጂ ተሞኝተው አይደለም፡፡ መስቀሉን ተሸክመው ሲከተሉት ዓለም እንደ ሞኝነት ይቆጥርባቸዋል፡፡

በረከታቸው ግን ምዕተ ዓመታትን ተሻግሮ ድንቅ ይሰራል፡፡ አሁን በዘመናችን ያሉትን ገዳማትና መናንያን ስንደግፍም ይህ ቃል ኪዳንና በረከት ከኛ ጋር ይሆናል፡፡     
       


ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

07 Dec, 16:12


በመላ ሀገሪቱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል።

ችግሩን ለመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

@Sheger_press

Sheger Press️️

07 Dec, 09:28


በሰሜን ወሎ ሲኖትራክ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካቶች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ!

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ባለፈው ሳምንት 'ሲኖ ትራክ' በተባለ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 50 የሚሆኑ ሰዎች እንደተገደሉ የዓይን እማኞች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ጥቃቱ የደረሰው ዞኑ ዳውንት ወረዳ ውስጥ ባለፈው ሐሙስ ኅዳር 19/2017 ዓ.ም. ቀትር 8፡00 አካባቢ መሆኑን የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች የጥቃቱ ሰለባዎች ከተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኩርባ ከተማ ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች ናቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለ ጥቃቱ ጥቆማ እንደደረሰው እና መረጃ እያሰባሰበ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል። ሐሙሲት የተባለ ገበያ ከሚውልበት ሾጋ አካባቢ ወጣ ብሎ ልዩ ስሙ ሰጎራ በተባለ አካባቢ ጥቃቱ መድረሱንም የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

በአካባቢው ባለው የትራንስፖርት ችግር ምክንያት በጭነት ተሽከርካሪዎች መጓዝ የተለመደ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ያለፈው ሳምንት ጥቃት አሸዋ እና ሰዎችን በጫነ 'ሲኖ ትራክ' በተባለው ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። ገበያ ውለው ሲመለሱ የነበሩ ገበያተኞች፣ አርሶ አደሮች፣ ለሥራ ፍላጋ ከአጎራባች ዋድላ ወረዳ ሲመለሱ የነበሩ ወጣቶች እንዲሁም ከደላንታ ወረዳ ክርስትና ደርሰው ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባዎች እንደሆኑ ተናግረዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

07 Dec, 06:54


ምን እየተካሄደ ነው‼️

♦ "ምንም #የማውቀው ነገር የለም ፣ #ጥሪም አልደረሰኝም በኃላፊነት ቦታ ሳይሆን በሙያዬ አግዛችኋለሁ ነው ያልኳቸው" !

እስከ እኩለ ለሊት የቆየ ቀረፃ ጨርሼ ስልክ ስከፍት በርካታ ወዳጆቼ ተመረጥሽ የሚል ነገር ሰምተን ነው የሚል መልእክት ልከዋል።

በወዳጆቼ ጥቆማ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ስገባ ተሰራጭቶ ያየሁት መረጃ በፍፁም የማላውቀውና ከሌላው ሰው ዘግይቶ ነበር ያየሁት።

በግሌ በፕሮሞሽን፣ መድረክ መምራትና መሰል ጉዳዮች በሙያዬ እንዳግዝ በስልክ ተጠይቄ ፍቃደኛ ነኝ በሙያዬ አግዛችኋለሁ የሚል የስልክ ምላሽ ሰጥቻለሁ። መረጃ ዎች ላኪልን ስባልም በፍቃደኝነት ልኬያለሁ።

ከዚህ ውጭ ግዮን ሆቴል ተካሄደ ስለተባለ ስብሰባ የማውቀው ነገር አልነበረም፣ በቦታውም አልነበርኩም፣ ጥሪም አልደረሰኝም።

አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

07 Dec, 05:55


የአማራ ክልል ጸጥታ ቢሮ፣ የፋኖ ታጣቂዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ፣ ፈረስ ቤት ሚካኤል በተባለ ቦታ አስረው ያቆዩዋቸውን የሕዝብና የመንግሥት አገልግሎት የሚሰጡ 37 ግለሰቦችን በትናንትናው ዕለት ገድለዋል በማለት ከሷል።

ቢሮው፣ ታጣቂዎቹ ትናንት የገደሏቸውን ጨምሮ 97 ግለሰቦችን ከመስከረም 29 ጀምሮ አስረው አቆይተው ነበር ብሏል።

ታጣቂዎቹ ግለሰቦቹን የገደሏቸው፣ ለማስለቀቂያ ከቤተሰቦቻቸው ከ100 ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ ሲቀበሉ ከቆዩ በኋላ ነበር በማለትም ወንጅሏል።

ቀሪዎቹ ግለሰቦች በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ሥር እንደሚገኙም ቢሮው ጠቅሷል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

06 Dec, 17:53


በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ዳውንት ወረዳ፣ ባንድ የጭነት የጭነት ተሽከርካሪ ላይ ኅዳር 19 ቀን በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 50 ያህል ሰዎች እንደተገደሉ የዓይን እማኞችና የተጎጂ ቤተሰቦች መናገራቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ገበያተኞች፣ አርሶ አደሮችና ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ኩርባ ወደተባለች ከተማ በተሽከርካሪው በመጓዝ ላይ ሳሉ ጥቃቱ እንደተፈጸመ እማኞች መናገራቸውን ያመለከተው ዘገባው፣ ስምንት የሚኾኑ ሰዎች ቆስለው ለሕክምና ወደ ጤና ጣቢያ እንደተወሰዱ መስማቱን ጠቅሷል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት አካባቢ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እንዳልነበርም እማኞች ተናግረዋል ተብሏል።

ኢሰመኮ፣ ስለ ጥቃቱ ጥቆማ ደርሶት መረጃ እያሰባሰበ እንደኾነ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

06 Dec, 17:39


ሼኽ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ፣ አብነት ገብረ መስቀል በፍርድ ቤት የተወሰነባቸውን ከ852 ሚሊዮን ብር በላይ መክፈል ካልቻሉ፣ በናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኩባንያ ውስጥ ያላቸው የ15 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ተሽጦ እንዲከፈላቸው ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባስገቡት ማመልከቻ መጠየቃቸውን ዋዜማ ተረድታለች።

ከኅዳር 27፣ 2014 ዓ፣ም እስከ ኅዳር 12፣ 2017 ዓ፣ም የተሰላውና አብነት እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው የ9 በመቶ ሕጋዊ ወለድ ደሞ፣ 226 ሚሊዮን 968 ሺሕ ብር ነው።

ሼክ አል-አሙዲ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ስለመባሉ እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ በላኩት ማመልከቻ ላይ ጠቅሰዋል። ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 5 የሰጠውን ውሳኔ አብነት የማይፈጽሙበት ምክንያት ካለ፣ ታኅሳስ 18 ቀርበው እንዲያስረዱ ታዘዋል።

ገዥው ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ከአብነትና ከሚድሮክ ኩባንያ አመራሮች ከፍተኛ የገንዘብ ሥጦታ የተቀበሉት የተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት አል-አሙዲን ይመለስልኝ ያሉትን ገንዘብ መቀበላቸውን አምነው፣ ገንዘቡን የተቀበሉባቸውን የባንክ ደረሰኞች ፍርድ ቤቱ ላዘጋጀው ገለልተኛ ኦዲተር ማረጋገጣቸውን ዋዜማ የተመለከተቻቸው የተቋማቱ ደብዳቤዎች አረጋግጠዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

06 Dec, 16:46


ህወሓት በመቐለ ከተማ የጠራው ሰልፍ ፍቃድ ሳያገኝ ቀረ

የመቐለ ህወሓት ፅሕፈት ቤት "የጊዝያዊ አስተዳደሩን ህገ ወጥ" አሰራር በመቃወም በመቀለ ከተማ ሰላማዊ ሰለፍ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩን ፍቃድ መጠየቁ ይታወሳል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

06 Dec, 15:50


ከሰሞኑ የሰማነው የተወሰኑ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለው) አባላት ሰላም መምረጥ ተስፋ ይሰጣል

አካሄዱ ላይ ግን ጥንቃቄ ካልተደረገበት ውጤቱ ከታሰበው በተቃራኒ እንዳይሆን ያሰጋል።

ዛሬ ጠዋት ስልኬን ስከፍት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ልብስን የለበሱት ጃል ሰኚ ነጋሳ መግለጫ ሲሰጡ ተመለከትኩ። "በምን አግባብ?" የሚለው ትልቁ ጥያቄዬ ነበር፣ ምክንያቱም የሰራዊቱ አባል ያልሆነ ሰው ልብሱን ለብሶ ከተገኘ እንደ ከፍተኛ ወንጀል ስለሚቆጠር።

በርካቶች ይህን ሁኔታ አይተው "ቀድሞውም እኮ አንድ ነበሩ" እና "ቁስል እንኳን ሳይደርቅ እንዴት እንዲህ ይደረጋል?" የሚሉ አስተያየቶችን እየሰጡ እንደሆነ ታዘብኩ።

መንግስት ከጥቂት ሳምንታት እና ወራት በፊት በግድያ፣ በዝርፊያ፣ በእገታ እና በሽብር ሲከሰው ከነበረው አካል ጋር ስምምነት ሲፈፅም ረጋ ተብሎ እና በሰከነ ሁኔታ ካልተያዘ ጉዳት የደረሰባቸው እና በተለይ አሁን ድረስ ከታጣቂዎቹ ጋር በዱር በገደሉ ተፋጠው ላሉ የመንግስት ፀጥታ አካላት የሚያስተላልፈው መልዕክት ያሰጋል።

አለም አቀፍ ልምዶች እንደሚያሳዩት ከሁሉም በፊት የሚቀድመው የተሀድሶ ፕሮግራም ነው።

ሰላም ለሀገራችን።

Via ኤልያስ መሰረት

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

06 Dec, 15:34


ቱርክ፣ ኢራን እና ሩሲያ በሶሪያ ጉዳይ በዶሃ ሊወያዩ መሆኑ ተገለጸ።

የቱርክ፣ የኢራን እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፈጣን በሆነው የሶሪያ አማጺያን ግስጋሴ ጉዳይ በነገው እለት በኳታር ዶሃ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ሮይተርስ ዘግቧል።

አማጺያኑ የሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት ከተጀመረ ከ13 አመታት በኋላ በጦር ሜዳ ከፍተኛ ድል በመጎናጸፍ፣ በበሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል።

ለበርካታ አመታት በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ክፍል ለበርካታ አመታት መሽገው የነበሩት አማጺያኑ በሀያት ታህሪር አል ሻም በተባለው ቡድን በመመራት ባለፈው ሳምንት የሶሪያን ትልቅ ከተማ አሌፖን ተቆጣጥረው፤ በደቡብ በኩል ወደ ሀማ ከተማ መግፋት ችለው ነበር።

አማጺያኑ በትናንትናው እለት ደግሞ ሁለተኛዋን ትልቅ ከተማ ሀማን ተቆጣጥረዋል።

ቱርክ፣ ሩሲያ እና ኢራን 'አስታና ፒስ ፕሮሰስ' በተባለ ማዕቀፍ በሶሪያ የወደፊት እጣፊንታ ላይ የሶስትዮሽ ምክክር ያደርጋሉ።

የኔቶ አባሏ ቱርክ ተቃዋሚዎችን የምትደግፍ ሲሆን ሩሲያ እና ኢራን ደግሞ የአሳድ አገዛዝን እንደሚደግፉ ይገለጻል።

ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ሶስት ሚኒስትሮች ከዶሃ ፎረም ጎንለጎን በነገው እለት ይገናኛሉ።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

06 Dec, 15:30


#እስከ ሞት ያስጨከነው ደብዳቤ


በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቀድሞዋ ፋርስ በአሁኗ ኢራን በቀድሞዋ ፋርስ በአንድ ወገን እጅግ ጠንካራ ክርስቲያኖች፣ በሌላ ወገን ደግሞ ጣዖት የሚያመልኩ እጅግ ጨካኝ ነገስታት ነበሩባት፡፡


በርካታ ክርስቲያኖችም ክርስቶስን አንክድም፣ ለጣኦት አንሰግድም በማለት በሰማዕትነት አርፈውባታል፡፡ ከእነዚህ አንዱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዓበይት ሰማዕታት ወገን የሚቆጠረው ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ነው፡፡ በዘመኑ ከነበረው ንጉስ ሠክራድ ጋር እጅግ ይዋደዱ ነበር፡፡ ይሁንና ቅዱስ ያዕቆብ ከክርስቲያን ቤተሰቦች የተወለደ በትምህርተ ሃይማኖት ያደገ፣ በክርስትና ስርዓት ሚስት አግብቶ የሚኖር ፍጹም ክርስቲያን ነበር፡፡


ንጉሱም ከፍቅሩ ብዛት የተነሳ በቤተ መንግስት ሹመት ሰጥቶ ከእርሱ ጋር እንዲኖር አደረገው፡፡

ቅዱስ ያዕቆብም በቤተ መንግስቱ ያለው የስጋው ምቾት መንፈሳዊ ሕይወቱን እያስረሳው ከጾምና ከጸሎት አራቀው፡፡ በሒደትም ንጉሱ ያለውን ሁሉ እንደ ክርስቲያን ሳይመዝን ይሁን እሺ የሚልና ተግቶ የሚፈጽምም ሆነ፡፡

ነገሮች ከልክ ማለፍ ጀመሩ፡፡ ንጉሱ ሠክራድ “እኔ እኔ ለማመልካቸው ለእሳትና ለፀሐይ ስገድ አምልካቸውም” አለው፡፡ እርሱም በተለመደ እሺታው ሊያስደስተው ፈልጎ ሰገደ፤ ማምለክም ጀመረ፡፡ በስጋችን ምቾት፣ በወንድማዊነት ፍቅር ሰበብ፣ ሃይማኖት ከምግባር መግባ ያሳደገችንን ቅድስት ቤተክርስቲያን የተውን “በክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመላችንን ያጠፋን ስንቶች ነን? ለክብር ያበቃችንን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያናነናቅንስ? ገዳማትን የረሳን፣ ትጋታችንን የተውን፣ ለባልንጀሮቻችን ፍቅር የክርስቶስን ፍቅር የተውን፣ ከቅዳሴው ይልቅ ሌላ ድምጽ እየሰማን ያለን ራሳችንን እንመርምር፡፡ 


ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ያደረገውን ነገር በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖች ሰምተው እጅግ አዘኑ፡፡ እህቱ ሚስቱና እናቱ ግን ለሐዘናቸው ዳርቻ አልተገኘለትም፡፡


በእንባና በለቅሶም ደብዳቤ ጻፉለት፡፡ "አንተ ክርስትናህን መካድህን ሰምተን አዘንን:: በዚህም ምክንያት ከዚህ በሁዋላ በአካባቢህ መኖርን አንፈልግም:: ለሞተልህ ለክርስቶስ ካልታመንህ እኛ አንተን እንደ ወንድም፣ እንደ ባልና እንደ ልጅ ልናምንህ ይከብደናል::" ይላል ደብዳቤው፡፡ እዳሉትም ከአካባቢው ለቀቁ፡፡

ቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤውን ሲያነበው ደነገጠ፤ በምድር ያሉት ብቸኛ የስጋ ዘመዶቹ እንርሱ ናቸውና፡፡

ከንጉሱ ጋር በነበረው ያልተገባ አካሔድ የደም ዋጋ ከፍሎ ያዳነውን ጌታ መካዱ ሲገባውም "ጌታ ሆይ! በምድር ካሉ የሥጋ ዘመዶቼ መለየት እንዲህ ካሸበረኝ: ካንተ ፍቅር መለየትማ እንደ ምን ይጨንቅ ይሆን! በሰማያዊ ዙፋንህ ፊትስ እንዴት ብዬ እቆማለሁ!" ብሎ መሪር እንባ አለቀሰ፡፡


ሌሊቱን ሙሉ በእንባና በለቅሶ አሳልፎ በጠዋት ንስሐ ገባ፡፡ በጾምና ጸሎት ጸንቶ ከንጉሱ አደባባይ ራቀ፡፡ ንጉስ ሠክራድም አስጠርቶ "ምን ሆነሃል? ስለ ምንስ በአምልኮ ከእኔ ተለየህ?" ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ያዕቆብም "የፈጠረኝን ክርስቶስን ትቼ አንተን በባዕድ አምልኮ አስደስትህ ዘንድ የሚገባ አይደለም" ሲል መለሰለት፡፡


ንጉሱ ሊያባብለው ሞከረ እንደማይሆን ሲገባው በደም እስኪነከር አስደበደበው፡፡ በክርስቶስ ፍቅር እንደጸና ሲገባውም ከጣቶቹ ጀምሮ አካሉን እንዲቆራርጡት ነገር ግን ቶሎ እንዳይገድሉት ወሰነ፡፡ ሰውነቱ ሲቆራረጥ መከራው ሲጸናበት እርሱ ግን ያመሰግን ነበር፡፡

በመጨረሻም ከወገቡ በላይ ያለ አካሉና ራሱ ብቻ ነበር የቀረው፡፡ ይሕም ሆኖ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ 42 ቦታ የተቆራረጠው ሰውነቱን ረስቶ በቀረው አካሉ ያመሰግን ነበር፡፡


በመጨረሻም አንገቱን በሰይፍ መተው ገድለውታል፡፡ እስከ ሞት ያስጨከነውን ደብዳቤ የጻፉለት እናቱ፣ እህቱና ሚስቱ በሰማዕትነት በማለፉ በደስታ እየዘመሩና በስጋ ስለተለያቸው እያለቀሱ ሽቱ ቀብተው ቀብረውታል፡፡


ሰማዕታት የዚህ ዓለምን ክብር ንቀው አንገታቸውን ለሰይፍ እንደሰጡ፣ ገዳማውያን አባቶችና እናቶች የዓለምን ጣዕም ንቀው በበረሀ ወድቀዋልና በአታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እናግዝ፡፡        



ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

06 Dec, 14:00


''ከባለሀብቶችና ኤምባሲዎች ጋር በመነጋገር ገቢ አመጣለው''
ተዋናይነት ማስተዋል

አዲሷ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ማስተዋል ወንደሰን ከምርጫው በኋላ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋዜጠኛ ዮናስ ሞላ ሀሳቧን ሰጥታለች።

በጣም ደስ ብሎኛል አልጠበኩም ነበር ያለችው ተዋናይነት ማስተዋል አዲስ አበባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መስራች እንደመሆኗ አሁን ያለችበት ሁኔታ ደስ አይልም ብላለች።

ዋና ከተማ ላይ በርካታ ኤምባሲዎች አሉ እኔ ከነሱና ባለሀብቶች ጋር በመነጋገር ጥሩ ገቢ በመነጋገር ለማምጣት እጥራለው ስትል ተደምጣለች።

በአለም ላይ ከ4 ቢሊዮን በላይ ተከታታይ ያለው የስፖርት አይነት በመሆኑ ሁሉም ይደግፈኛል ሁላችንም ይወክላል ፣ሴቶችንም እናበረታታለን ይደግፉናል ስትል ከምርጫው በኋላ አስተያየት ሰጥታለች።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

06 Dec, 13:56


ምክትል ፕሬዝዳንቷ በኃላፊነታቸው ይቀጥላሉ !!

የኣዲስ ኣበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለዛሬ የጠራው ስብሰባ ኣዲስ የተመረጠው ስራ ኣስፈፃሚ ለትውውቅ የጠራው እንጂ ምንም ሹም ሽር ሀላፊነት መልቀቅ ምናምን የለውም ፤ ትናንት የተመረጡት ይቀጥላሉ በሀረገወይን ቦታ ብቻ ሰው ሊተካ ይችላል።

[ኤርምያስ በላይነህ]

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

06 Dec, 11:43


መረጃ‼️

የአዲስአበባ እግርኳስ ፌደሬሽን ዛሬ ከሰዓት በኋላ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።

የፌደሬሽኑ ም/ፕሬዝዳንት በመሆን ትናንት የተመረጠችው አርቲስት ማስተዋል ወንዶሰን

የመልቀቂያ ደብዳቤ እንደምታስገባ የሚጠበቅ ሲሆን

በምትኳም የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አመራር የሆኑት ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ እንደሚተኩ ይጠበቃል።

Via ዳጉ ጆርናል

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

01 Dec, 10:13


“እነሆ ይህ የእሳት ፍም ከንፈሮችህን ስለ ነካ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኃጢአትህም ይቅር ተብሎልሃል”

በቤተ ክርስቲያናችን አበይት ነቢያት ለሚባሉት አንዱ ቅዱስ ኢሳይያስ ነው፡፡ በዘመኑ የነበረው ንጉስ ዖዝያን ኃጢአት ሲሰራ እያው ዝም አለው፡፡ በዚህም ምክንያት ከንፈሩ በለምጽ ተመታ፡፡ በኋላም ንጉሱ በሞተበት ዓመት “ቅዱስ እግዚአብሔር ከፍ ባለና ልዕልና ባለው ዙፋን ላይ ተቀምጦ መጐናጸፊያውም ቤተ መቅደሱን ሞልቶት” ለነቢዩ ታየው፡፡ አንተ ትፈራው የነበረው ንጉስ ሞተ እኔ ግን ሕያው ነኝ ሲል፡፡ እርሱም ይሕን በማየቱ ፈርቶ የሚሞት መስሎት ወዮልኝ አለ፡፡

እኛ ግን ድንቅ ምስጢር በሚፈጸምባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደስታ ገብተን ጸጋውን ተቀብለን ሕይወትም አግኝተን በሰላም እንወጣለን፡፡

ነቢዩ ስለዚህ ነገር በትንቢተ ኢሳያስ 6፣1-7 ሲናገር “ከእነዚያም መላእክት አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፤ ከመሠዊያው የወሰደው የእሳት ፍም የያዘበት ጒጠት በእጁ ነበር። በእሳቱም ፍም ከንፈሮቼን ነክቶ እነሆ ይህ የእሳት ፍም ከንፈሮችህን ስለ ነካ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኃጢአትህም ይቅር ተብሎልሃል አለኝ።” ይላል፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባቶችም መልአኩ በጉጠት የያዘው ፍም የቅዱስ ስጋውና የደሙ ምሳሌ ነው ይሉናል፡፡ መልአኩ ስልጣነ ክህነት ስለሌለው በጉጠት የያዘውን እሳት ካሕናት አባቶች ዛሬ በእጃቸው ፈትተው ያቆርቡናል፡፡ የካሕናት ስልጣን ትልቅ ነው፡፡

ታዲያ ይህን መንፈሳዊ ሾል የሚያከናውኑባት ቤተ ክርስቲያን ደሳሳ ጎጆ ሆና፣ ዝናብ እያፈሰሰች  ዝም ማለት እንደምን ይቻለናል???   
  
በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ ለሚገኘው ሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ለሚገኙ መነኮሳት  እጃችንን እንዘርጋ፡፡


ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

                ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                 1000442598391

                        ወይም

                   አቢሲኒያ ባንክ
                   141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444

Sheger Press️️

01 Dec, 09:42


Calling All Tech Aspirants and Innovators with Disabilities in Ethiopia!

Join the Kifiya AI Mastery Program to gain global-level skills in Generative AI, Machine Learning, & Data Engineering!

Fully funded, 3-month, part-time & online

✅ Training, mentorship, & career guidance

Applications close Dec 3, 2024. Break barriers & shape your future today!

Please share this opportunity with anyone who could benefit from it.

🔗 Info: 10academy.org/kifiya/learn-more
🔗 Apply: https://apply.10academy.org/register

Sheger Press️️

01 Dec, 09:20


ጃዋር መሀመድ ስለ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ይህን በፌስቡክ ፅፏል

ባቲ ኡርጌሳ ከተገደለ ከስድስት ወራት በላይ አልፏል። ሆኖም፣ እስከ ዛሬ ድረስ፣ ፍትሐዊ ፍትሐዊ ፍትሐዊ ሆኖ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በነፍስ ግድያው ላይ ምርመራውን እንዳጠናቀቀ ቢነገርም ግልጽ ባልሆነ መልኩ ግኝቱ ለህዝብ እንዳይታይ ተደርጓል። ይህ ግልጽነት የጎደለው ግልጽ ተጠያቂነት ውድቀት ነው።

የባቲ ግድያ አፋጣኝ እና ጥልቅ ተጠያቂነትን የሚጠይቅ አሰቃቂ የአመፅ ድርጊት ነበር። ኢሰመጉ እውነቱን ለመግለጥ በመጀመሪያ ቃል የገባ ቢሆንም፣ የምርመራ ሪፖርቱ ከተጠናቀቀ ከረጅም ጊዜ በኋላ ይፋ ለማድረግ አለመቻሉ ወይም አለመስጠቱ ወሳኝ ጥያቄዎችን ያስነሳል፡ ምን እየተደበቀ ነው? ከዚህ ዝምታ ማን ይጠቅማል?

የዚህ ውድቀት መዘዙ ብዙ ነው። የባቲ ቤተሰቦች አሁን በስደት በዩናይትድ ስቴትስ ይኖራሉ፣ ለደህንነታቸው በመስጋት ከኢትዮጵያ ለመሰደድ ተገደዋል። የእነሱ መሰደድ መንግስት ዜጎቹን ለመጠበቅ ፈቃደኛ አለመሆኑ አሳዛኝ ማሳያ ነው። ባለፉት ስድስት ዓመታት ያየነውን የቅጣት እርምጃም አጉልቶ ያሳያል።

የኢሰመጉ ሪፖርት መከልከል በኢትዮጵያ ሰፋ ያለ የሥርዓት ጉዳይን ይወክላል። ፍትህ ሲዘገይ፣ ሲከለከል ወይም ሲነፈግ፣ ያለመከሰስ ችግር የሚያድግበት ክፍተት ይፈጥራል። ይህ ስለ ባቲ ኡርጌሳ ብቻ አይደለም - ስለ ኢትዮጵያ ተቋማት ታማኝነት እና ለተጠያቂነት ቁርጠኝነት ነው።

ፍትህ ለባቲ ኡርጌሳ ለአንድ ሰው ግድያ ተጠያቂነትን መፈለግ ብቻ አይደለም - ምንም አይነት ህይወት የማይከፈልበት፣ የትኛውም የቤተሰብ ስቃይ ችላ የማይባል እና ምንም አይነት የፍትህ ድምጽ የማይታፈንበት ምሳሌ መሆን ነው።

ኢሰመጉ የተሰጠውን ተልዕኮ የሚወጣበት ጊዜ ነው። ዘገባውን ለቀቅ። ፍትህ ስጥ ቅጣትን ይጨርሱ። ለባቲ ኡርጌሳ፣ ቤተሰቡ ና ለሌሎች

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

01 Dec, 05:45


ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ካስገቡ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ 6ኛ ደረጃን ይዛለች

ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሀገራት 2.2 በመቶ በአለም የጦር መሳሪያ ገበያ ተሳትፎ ነበራቸው

አፍሪካውያን ሀገራት ከበጀታቸው ከፍተኛውን መጠን በመመደብ የጦር መሳሪያ ግዢ ላይ በስፋት እየተሳተፉ እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ያለው የስቶክሆልም አለም አቀፍ የሰላም ጥናት ኢንስቲትውት ነው።

በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የሚገኝውን የጦርነት  ስጋት ተከትሎ አለም ወታደራዊ ወጪውን በከፍተኛ መጠን ሲጨምር በ2024 2.4 ትሪሊየን ዶላር ወጪ የተደረገ ሲሆን ከ2023 ጋር ሲነጻጸር በ6.8 በመቶ ጭማሪ ታይቶበታል።

ይህ ስጋት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የሚጎበኛቸው አፍሪካውያን በሀገር ውስጥ ግጭት እና ቀጣናዊ ውጥረት መባባስ ዘመናዊ የጦር መሳሪያን ለመታጠቅ ፣ ወታደራዊ አቅማቸውን ለማጠናከር ጥረት ላይ ናቸው።

በመረጃው መሰረት በፈረንጆቹ 2023 ብቻ የአፍሪካ አህጉር ወታደራዊ ወጪ 51.6 ቢሊየን ዶላር ነበር።

ይህ ወታደራዊ ወጪ ከ2022 አንፃር 22 በመቶ ብልጫ ሲኖረው ከ2014 ደግሞ በ1.5 በመቶ ጨምሯል።

ከአጠቃላዩ የአህጉሩ ወታደራዊ በጀት ወጪ 23.1 ቢሊየን ዶላር ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሀገራት ለመከላከያቸው የበጀቱት ነው።

በዚህም ባለፉት አምስት አመታት ብቻ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሀገራት በ2.2 በመቶ በአለም የጦር መሳሪያ ገበያ ላይ ድርሻ ነበራቸው።

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ 20 በመቶ የመከላከያ ወጪዋን በማሳደግ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ናት።

በተመሳሳይ ዲ አር ኮንጎ ከ105 በመቶ በላይ ወጪን በማሳደግ በአለማችን ከፍተኛውን ወታደራዊ ወጪ ጭማሪን ያደረገች ሀገር ስትሆን አጠቃላይ የመከላከያ በጀቷን 794 ሚሊየን ዶላር አድርሳዋለች።

ኮንጎን በመከተል ወታደራዊ ወጪዋን በ78 በመቶ ያሳደገችው ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሱዳን 1.1 ቢሊየን ዶላር በ2023 በመመደብ ትጠቀሳለች።

ከ2019 -2023 ባሉት አምስት አመታት ከፍተኛ የጦር መሳርያ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገቡ ሀገራት ደረጃ በናይጄሪያ የሚመራ ሲሆን አንጎላ ፣ ሴኔጋል ፣ ማሊ ፣ ዩጋንዳ እና ኢትዮጵያ እስከ ስድስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

በዝርዝሩ ውስጥ ስሟ የተካተተው ኢትዮጵያ በአምስት አመታቱ ውስጥ በ4.90 በመቶ ጦር መሳርያዎችን በማስገባት ስድስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
#Alain

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

01 Dec, 05:44


#የካህኑን እጅ በደም ተነክሮ ሲያዩት ደንግጠው ወደቁ

አንድ ዓለምን ትተው የመነኑ ገዳማዊ በቅዱስ ስጋውና በክቡር ደሙ ላይ ዲያብሎስ ጥርጣሬ እየፈጠረ ይዋጋቸው ጀመር፡፡ ሁልጊዜም ሲቆርቡ ካሕኑ የሚሰጧቸው ህብስትና ዲያቆኑ የሚያቀብላቸው ወይን ብቻ ነው የሚታያቸውና መች ነው እውነተኛ ስጋና ደም የሚሆነው በሚለው ጥያቄ ተነስተው በጊዜ ብዛት ወደ ጥርጣሬ ሊገቡ ሆነ፡፡

በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከእሳቸው በዓት አጠገብ ያሉ የበቁ አባት ዘንድ በመመጣት ችግሩን ይነግራቸዋል፡፡ እኒህ የበቁ አባትም ወደ ጎረቤታቸው ይመጡና ችግሩን የራሳቸው አስመስለው “አባቴ የምስጢረ ቁርባን ነገር ግራ አጋባኝ፣ አእምሮዬ እውነተኛ ስጋውና ደሙ ሆኖ የሚለወጠው መች ነው? እያለ በጥያቄ ሰላም ነሳኝ ይሏቸዋል፡፡

በነገሩ የተገረሙት አባትም እኔም እኮ የምነግረው አጥቼ እንጂ ተመሳሳይ ጥያቄ ወደ አእምሮዬ መመላለስ ከጀመረ ከራርሟል ይሏቸዋል፡፡ እርግጠኛ ለመሆን በቅዳሴ ጊዜ ካህኑ ስጋውንና ደሙን ሲፈትቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሆነው በማስቀደስ ለማየት ተስማሙ፡፡ በቅዳሴ ጊዜም ካህኑ ሕብስቱን አንስተው ሲፈትቱ ሰይጣን የሚፈትናቸው አባት የካህኑ እጅ በደም ተነክሮ ሲያዩት ደንግጠው ወደቁ፡፡ አስገራሚው ነገር ከሁለቱ ባሕታውያን ውጪ ራሳቸው ቀዳሹ ካሕንም ሆኑ ሌሎቹ ልኡካን ይህን ምስጢር አላዩም፡፡

ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ በሕብስትና በወይን መልክ ይሰጠን እንጂ የክርስቶስ አማናዊ ስጋና ደም ነው፡፡ ይህ ትልቅ ምስጢር የሚፈጸምባት ስርዓተ ቅዳሴው የሚካሄድባት ቅድስት ቤተክርስቲያንም የምስጢር መፈጸሚያ ስፍራ ነች፡፡ ለዚህም ነው ይህን ምስጢር የምንካፈልባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መርዳት፣ መስራት የሚገባው፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት ስር የሚገኘዉን ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ለመደገፍ እጃችንን እንዘርጋ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

                ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                 1000442598391

                        ወይም

                   አቢሲኒያ ባንክ
                   141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444

Sheger Press️️

01 Dec, 05:02


ዶናልድ ትራምፕ ለብሪክስ ሀገራት ማስጠንቀቂያ ልከዋል። ከዶላር ውጪ ካሰባችሁ አሜሪካን እና ከአሜሪካ ገበያ ጋር ለመፋታት ወስናችሁ መሆን አለበት ብለዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

30 Nov, 16:12


እስካሁን 140 የሚደርሱ ምዕመናን በግፍ ተገድለዋል ❗️

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ኦነግ ሸኔ በሚል መጠሪያ በሚታወቁ ታጣቂዎች 11 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ተገድለዋል፡፡

ከግድያው በእግዚአብሔር ፈቃድ ማምለጣቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የገለጹት መረጃ ሰጭው የ13 ዓመት አዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተወስደው በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ መገደላቸውንና 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

እየተገደሉ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን አርሰው የሚያድሩና ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎና ግንዛቤ የሌላቸው መሆናቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሞቱትን ከመቅበር ባለፈ የተሻለ መፍትሔ አላመጡልነም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ዘገባው የማኀበረ ቅዱሳን ቲቪ ነው።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

30 Nov, 15:55


ዜና: #ኢትዮጵያን እና ሶማሊያን ለማሸማገል #ኬንያና ዩጋንዳ ጥረት መጀመራቸው ተጠቆመ

#የሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና #ዩጋንዳ መሪዎች የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውጥረቶችን "ለመቀነስ" ስብሰባ ለማድረግ ማቀዳቸውን የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ።

ሩቶ ይህንን የተናገሩት የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ 24ኛ መደበኛ የመሪዎች ጉባኤውን ባካሄደበት ታንዛኒያ፣ አሩሻ ትናንት ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረጉት ንግግር ነው።

የማህበረሰቡ አዲስ ሊቀመንበር ሩቶ፣ ስብሰባው የሚደረግበትን ቀን ይፋ አላደረጉም።

ስብሰባው እርግጥ ከሆነ ፣አዲስ አበባ እና ሶማሌላንድ አወዛጋቢውን የመግባቢያ ሰነድ በአውሮፓዊያኑ ጥር 1 ፣2024 ከተፈራረሙ ወዲህ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረግ የመጀመሪያ የፊት ለፊት ስብሰባ ይሆናል።

የሶማሊያ መሪዎች የመግባቢያ ሰነዱ እስካልተሰረዘ ድረስ ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ ንግግር እንደማይኖር አጽንኦት ሲሰጡ ሰንብተዋል።

ሶማሊያ የምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ 8ኛ አባል ሀገር ሆና የተቀላቀለችው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ መሆኑን ከቪኦኤ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

"የቀጠናችንን ሰላም ለማስጠበቅ፣ ለቀጠናችን ፀጥታና መረጋጋት መዋለ ነዋይ ለማፍሰስ የጋራ ጥረት (ያሻል)" በማለት ጥሪ ያቀረቡት ሩቶ፣ በንግግራቸው ወቅት ሰላምና መረጋጋትን ማስጠበቅ፣ በቀጠናው የመዋለ ነዋይ ፍሰትን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

30 Nov, 15:20


<< የሚቃወሙን ሁሉ ያወድሱናል፤ ያመሰግኑናል፤ ዘመኑ ሩቅ አይደለም፤ እርግጠኛ ነኝ! >> -  ዐብይ አህመድ ( ዶ/ር )

<< በክላሽ ድል አላገኛችሁም፤ ወደፊትም አታገኙም፣ ይበቃችኋል! >>

አሻም ዜና | ዕለተ ቅዳሜ፣ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም

የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐብይ አህመድ (ዶ/ር ) ይህን የተናገሩት የፓርቲያቸው አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሐግብር በተካሄደበት ወቅት ነው።

በዚህ መድረክ የግማሽ ማራቶን ሩጫ [ 21 ኪሎ ሜትር ] የክብረወሰን ሰዓት የሚወስደውን ጊዜ ሊደርስ ጥቂት የቀሩትና 48 ደቂቃ ገደማ የወሰደ ረዥም ንግግር አድርገዋል።

በእርሳቸው ፕሬዝዳንትነት የሚመራው ገዢው ብልጽግና ፓርቲን በተለያዩ ቃላት አድንቀዋል፤ አዋውበዋል።

<< ብልጽግና መለያው እውነት ነው፤ መለያው ዕውቀት ነው፤ መለያው ጥበብ ነው >> በማለትም አወድሰዋል።

<< የኢትዮጵያን የፖለቲካ ታሪክ የ50 እና 60 ዓመታት ዕድሜ ያለው ነው >> ያሉት ዐብይ እነዚህ አምስት አስርታትም የከፍታና ዝቅታ፣ የመጠፋፋትና የመጠላለፍ ነበሩ ሲሉ የታሪክ መረዳታቸውን አስገንዝበዋል።

ከአምስት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ እንደሀገር የመቀጠል ስጋት እንደነበረባት የሚገልጹ ድምጾች መኖራቸውን ያስታወሱት ዐብይ << አሁን ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም አልላችሁም፣ ይልቁንም ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ምድራዊ ሃይል የለም ሲሉ >> ተደምጠዋል።

በዘረዘሯቸው መስኮች ሁሉ ፓርቲያቸው ብልጽግና እጅግ ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡን ደጋግመው ገልጸዋል።

በእርሳቸው ፓርቲ የሚመራው መንግስት አሰመዝግቦታል ያሉትን ስኬት በተለያዩ መለኪያዎች በሚገልጹና በሚያደንቁበት ወቅት የፓርቲው አባላት በሞቀ ጭብጨባ ሲያጅቧቸው ነበር።

የፕሬዝዳንቱ ንግግር ሲቀጥል << ኢትዮጵያን ለማጽናት፣ ሀገረ መንግስት ለማጽናት፣ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ እስካሁን መመለስ ያልቻልነው >> ነገር ግን << መመለስ ያለብን ጉዳይ ዴሞክራሲ ነው >> ሲሉ ተናግረዋል።

ለዚህ ደግሞ በፓርቲ ውስጥ ልምምድ እንዲሚያስፈልግ ጠቅሰው ፓርቲያቸውም ይህንን እንዳደረገ አስረድተዋል።

ከፓርቲያቸው ልምምድ ባሻገርም ከሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሰሩትን ዘርዝረዋል።

ሃሳብን እንጂ የሃሳቡ ባለቤትን ማጥቃትና ጠላት ማድረግ አግባብ አለመሆኑን ሲያስረዱ መንግስታቸው ሥልጣን የቸራቸውን የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአብን ሊቀመንበር በለጠ ሞላ ( ዶ/ር ) እና ቀጀላ መርዳሳ << ጠላቶቻችን አይደሉም >> ሲሉ በምሳሌ አስገንዝበዋል።

<< ትናንት ተቃውሟልና ይገደል ካልን ሃሳቡን ሳይሆን ሰውዬውን ስለምናጠፋ ሃሳብና ሰውን ነጥሎ የማየት ልምምድ  ያስፈልጋል >> ብሎ ፓርቲያቸው ብልጽግና
በጽኑ እንደሚያምን አስረግጠዋል።

<< ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላም፣ ትብብር፣ የሃሳብ ፍትጊያ ነው >> ያሉት ዐብይ <<  ክላሽ እንዲበቃ ክላሽ ያነገባችሁ፣ በዚያም ድል ይገኛል ብላችሁ ያሰባችሁ ወንድሞቻችን፣ ይበቃችኋል  >> ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም << በዚያ መንገድ አልሆነም፤ ወደፊት ስለማይሆን በሰላም በውይይት በጋራ ሀገራችንን እንድናበለጽግ  በታላቅ ፍቅርና ትህትና ጥሪ አቀርባለሁ >> ብለዋል።

በሰላማዊ መንገድ እንስራ ሲሉ ተናገሩ እንጂ ትጥቅ አንግበው ለሚፋለሟቸው ሃይሎች ይፋዊ የድርድር ጥሪ ሲያቀርቡ አልተሰማም።

መንግስታቸው የኮሪደር ልማት እያለ የሚጠራውን የመንገድ ዳርቻዎች ውበት ከውጭ አካላት ብቻ ሳይሆን ከውስጥም የሚቃወሙት እንደበሩ ያስታወሱት ዐብይ አሁን ግን ይህ እየተለወጠ መምጣቱን ገልጸዋል።

<< በውስጥ ያሉት አብዛኛው እያመነ መጥቷል >> ሲሉ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ከውጭ የሚቃወማቸው << ሁሉ የሚያመሰግንና የሚያወድስበት ዘመን ሩቅ አይደለም >> ብለዋል።

<< የሚመሰገኑበት ዘመን ሩቅ >> አለመሆኑን ከመናገር ውጪ በውል መቼ የሚለውን ያልጠቀሱት ዐብይ << በሥራቸው እንደሚወደሱ >> ግን እርግጠኛ መሆናቸውን በከፍተኛ ድምጸት ተናግረዋል። (አሻም)


@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

30 Nov, 15:19


ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅዱስ ላሊበላ!

በነፍሳችን ዲያብሎስ ፣ በስጋችን ቄሳር እንዳይነግስ፣ ያለወንድ ዘር በረቂቅ ሚስጥር ከብጽዕት ማርያም የተወለደውን ወልድ እግዚአብሔርን ኑ በምስጋና እናንግሰው።

ንጉሧን ያላወቀች እስራኤል ከምድር ያሳደደችው ፣ በመስቀል ሆኖ "ንጉሥ" የተባለ ፣ በመላእክት የተበሰረ ዜና ልደቱን፣ በያሬዳዊ ዝማሬ በታሪካዊው ቅዱስ ላሊበላ በማክበር በረከተ ነፍስ በረከተ ስጋን እናትርፍ።

ለአረጋውያን ፣  ለነፍሰጡር ፣ ለህፃናት እና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ስለማረፊያዎ አያስቡ፤ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17

የጉዞ ዋጋ:- ምግብን ፣ ማረፊያን ፣ መስተንግዶን እና አስጎብኚን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማኀበረ ቁስቋም

Sheger Press️️

30 Nov, 12:08


አስመራ‼️

ሕዳር ፅዮን በርዕሰ አድባራት ቅድስት ድንግል ማርያም አስመራ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

30 Nov, 09:35


የ #ጁባላድ ግዛት ፕሬዝዳንት የ #ሶማሊያ ፌዴራል ጦር በ15 ቀን ውስጥ ራስካምቦኒን ለቆ የማይወጣ ከሆነ “የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ” እንደሚወስዱ አሳሰቡ

ከፊል የራስ ገዝ አስተዳደር የሆነችው የጁባላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ማዶቤ የሶማሊያ ፌደራል ጦር በኬንያ ድንበር አቅራቢያ ከምትገኘው ስትራቴጂካዊቷ ራስካምቦኒ ከተማ በ15 ቀናት ውስጥ የማይወጣ ከሆነ “ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ” እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ በኪስማዩ በሚገኘው መስጂድ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ጦሩን የማያስወጣ ከሆነ ለሚፈጠረው ማንኛውም አይነት ችግር “ዋጋ ይከፍላል” ብለዋል።

ማዶቤ ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት ከፊል ራስ ገዝ በሆነችው ጁባላንድ እና በሶማሊያ ፌዴራል መንግስት መካከል በቀጠናዊ ቁጥጥር፣ በሀብት አስተዳደር እና ራስን በራስ የማስተዳደር ፖለቲካ የተነሳ ውዝግቦች ተባብሰው በቀጠሉበት ወቅት ነው።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

30 Nov, 09:34


" እመ ብርሃን ብሎ ያጣ ማን አለ በህይወቱ ፣ በቤቱ ፣ በጤናዉ እና በስራዉ ቦታ ያልሞላችለት ማን አለ? "

"እመ ብርሃን!" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው::

ታላቁ አባት አባ ሕርያቆስ ፍቅርና ደግነት እንጂ ትምህርት ያልነበረው አባት ነበር፡፡ በብሕንሳ ገዳም የሚኖርው ይህ አባት ለጸሎት ያህል መዝሙረ ዳዊትንና አንዳንድ መጻሕፍትን ብቻ ነበር የሚያውቀው ብዙዎች ግን በአንድ ነገር በሚገባ ያውቁታል፤ ለእቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያን ባለው ፍቅር፡፡ ታዲያ በተለይ ከመዝሙረ ዳዊት መዝሙር 44ን ፈጽሞ ይወደው ነበር፡፡ በየሔደበትም ይህን ስለ እመቤታችንና ስለጌታችን የሚያወሳ መዝሙር በቃሉ ይጸልይ ነበር፡፡ ብዙዎችም በትምህርቱ ደካማ በመሆኑ ይዘባበቱበት ነበር፡፡

ዛሬም በዘመናችን እኛ እውቀት ያልነውን ዘመናዊነት ባለማወቃቸው የምንንቃቸው ገዳማውያን አባቶች የሚሉንን ብንሰማ ሀገራችን የት በደረሰች ነበር፡፡ ለእነዚህ ገዳማውያን አባቶች ክብር ቢኖረን፣ ገዳማቸውን ለማጽናትና በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያለውን ሙትአንሳ  ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም አቅማችን በፈቀደ ብናግዝ በጸሎታቸው በረከት እንጠቀማለን፡፡

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፤ አንድ ቀን ታዲያ አባ ሕርያቆስ መንገድ ይወጣል:: በበርሃ ብቻውን እየተራመደ: "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" እያለ እየዘመረ: ተመሥጦ ቢመጣበት መንገድ ሳተ:: እርሱ በምስጋናው ሲደሰት እግሩ ግን ከገደል ጫፍ ደርሶ ነበር:: ገደሉን ልብ አላለውም ነበርና ሳይታወቀው ወደ ገደሉ ውስጥ ተወረወረ::

በዚህ ጊዜ ደንግጦ ቢመለከት እጅግ ጥልቅ በሆነ ገደል ውስጥ ራሱን አገኘው:: ነገር ግን አንድም አካሉ አልተነካም:: ልብሱም አልቆሸሸም:: ለራሱ ተገርሞ ዙሪያ ገባውን ሲመለከት እርሱ ቁጭ ያለበት ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ ነበር:: "እመ ብርሃን!" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው:: እመ አምላክን በገሃድ ቢያያት እንደ እንቦሳ ዘለለ::

እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን ይመረምራልና በሰዎች ዘንድ ደካማ መስለው የሚታዩትን ይመርጣቸዋል፡፡ ዓለምንና ኮተቷን ትተው የወጡ ገዳማውያን አባቶች ጥሪያቸው አንድና አንድ ነው፤ ለስጋ ገበያችሁ ስትሮጡ በነፍሳችሁ እንዳትጎዱ በገንዘባችሁ የበረከት ስራ ስሩበት፣ በሰማይም ብል የማይበላው መዝገብ ይኖራችኋል ነው፡፡

አባ ሕርያቆስ የሁልጊዜም ምኞቱ የእመቤቴ ምስጋና በዝቶልኝ፣ እንደ እንጀራ ተመግቤው፣ እንደውሃ ጠጥቼው ባየሁ የሚል ነበር፡፡ እመብርሃን ምኞቱን አሳክታለትም አሁን ድረስ የምንጠቀምበትን ቅዳሴ ማርያምን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ቅዱሳን ድርሰቶችን ደርሷል፡፡

እርሱ ሳያውቅ ምስጋናዋን ብቻ እያሰበ ወደ ገደል ሲወድቅ በቀሚሷ ዘርፍ እንዳዳነችው ሁሉ ገዳማውያን አባቶችን የአባ ሕርያቆስን መንገድ ተከትለዋልና እርሷ ትባርካቸዋለች፡፡ እርሱ ቅዳሴ ማርያምን ለእመብርሃን ምስጋና በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ አዘጋጀ እኛ ደግሞ ቅዳሴዋን እየሰማን ነፍሳችን ትለመልማለች፡፡

ገዳማውያን አባቶችም የሚያለሙት ገዳም ነገ የምንባረክበት፣ ለሀገር ለወግን የሚጸለይበት ነውና እንዳቅማችን እናግዝ፡፡  

ድጋፍ ለማድረግ :- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

30 Nov, 08:14


የዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ውሳኔ መዘግየቱ አሳስቦኛል ሲል ኢሰማኮ አስታወቀ!

መንግሥት የዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን የየያዘውን ዕቅድ ሊያዘገየው ይችላል መባሉ አሳስቦኛል ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አስታውቋል።መንግሥት የዝቅተኛ ደሞዝ ወለልን ለመወሰን ጥናት አጥንቶ የጨረሰ ቢሆንም፤ "ችግር ያመጣብኛል በሚል ስጋት አዝግይቼዋለው" ማለቱን ተገቢ አይደለም ሲሉ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ "ይህንን በሚመለከት ለሚመለከተው የፌደራል የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጠን ስንል ጠይቀናል" ብለዋል።"በተጠና ጥናት መሠረት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል" የሚል ነገር መነገሩን የገለጹት አቶ ካሳሁን፤ "ጥናት በትክክል ተደርጎ ከሆነ በጥናቱ ላይ መሳተፍ ነበረብን" ብለዋል።

አቶ ካሳሁን አክለውም "እንደተባለው ኮሚሽኑን ሳያካትቱ ተጠንቶም ከሆነ ጥናቱን እንዲሰጡን ስንል በደብዳቤ ጠይቀናል" ሲሉም ተናግረዋል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ የስራ ግብር እንዲቀነስ እና የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም ሲጠየቅ ይሰማል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የኑሮ ሁኔታ በቋሚ ደምወዝ በሚኖሩ ተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ እየፈጠረ ያለው ተጽእኖ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ እንደሆነ ይገለጻል፡፡"የኑሮ ውድነቱ ሠራተኛው ከሚያገኝው ገቢ ጋር ሊመጣጠን ባለመቻሉ ዜጎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ኑሯቸውን እንዲገፉ አስገድዷል" ያለው የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን፤ ማስተካካያዎች እንዲደረጉ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውቋል፡፡

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን እና የግብር ቅነሳ እንዲደረግ ኢሰማኮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በነበረው ውይይት ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን፤ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን በደብዳቤ ቢጠይቅም ተገቢውን ምላሽ አለማግኘቱ ይገለጻል፡፡(Ahadu)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

27 Nov, 12:04


ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በ500 ሄክታር ላይ የተዘራ የደረሰ ሰብልን አወደመ

በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ አሥተዳደር የገጠር ቀበሌዎች በጣለው ከባድ በረዶ ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

ኅዳር 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ ለ30 ደቂቃ የጣለው ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በሶስት ቀበሌዎች ከ500 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጉዳቱ በተለያዩ የሰብል አይነቶች ላይ የደረሰ ሲሆን ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍና ጥራጥሬ ሰብሎች ይገኙበታል።

Via አሚኮ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

27 Nov, 10:31


ተፈቱ‼️

በኮሬ ዞን ታስረዉ የነበሩት 66 መምህራን ሁሉም ከእስር መለቀቃቸዉ ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ፤ "ደመወዝ ይከፈለን" የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ለእስር ተዳርገው የነበሩ 66 የሚደርሱ መምህራን ሁሉም ከእስር መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር ለአሐዱ ገልጿል፡፡

መምህራኑ ምንም አይነት የሥራ ማስተጓጎልም ይሁን ሌሎች ሕገ ወጥ ተግባራትን ሳይፈፅሙ፤ መብታቸዉን ብቻ በመጠየቃቸዉ ለእስር ተዳርገው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የመምህራን ማህበሩ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አበበ መምህራኑ ከቀናት በፊት ከፊሎቹ ተለቀዉ እንደነበር ገልጸው፤ ትላንት አመሻሽ አካባቢ በደረሳቸዉ መረጃ ደግሞ ሁሉም ከእስር መለቀቃቸዉን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"በየትኛውም መልክ ደመወዝ መጠየቅ ለእስር ሊዳርግ አይገባም" ያሉት አቶ ሽመልስ፤ "መምህራንን ማዋከብና በዘርፉ ችግሮች እየተደራረቡ እንዲሄዱ ማድረግ አይገባም" ብለዋል፡፡

"በፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ሥር የዋሉ መምህራን በሕግ ፊት መቅረብና ውሳኔ ማግኘት ሲገባቸዉ በእስር ቆይተዉ እንዲለቀቁ ሆኗል ነው" ያሉት፡፡

በቁጥጥር ሼር የዋሉት መምህራን በወረዳው ፖሊሶች እንደሆነና ድብደባ የተፈፀመባቸው እንዳሉም ተገልጿል የሕክምና እርዳታ  እንዳያገኙ በጸጥታ ሃይሎች ክልከላ እንደተደረገባቸው መገለጹ ይታወቃል፡፡

መምኅራኖቹ መብታቸዉን የጠየቁትና ለእስር ያበቃቸዉም በክልሉ መንግሥት ይሁንታ የ25 በመቶ የደመወዝ ቅነሳው ከትምህርት ቤት ርእሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች መደረጉን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የመምህራን ማህበሩ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ "ፖሊስ 24 ሰዓት ብቻ በፖሊስ ጣቢያ ማቆየት የሚችል ቢሆንም ከሕግ አግባብ ዉጭ ለ7 ቀናት በፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል" ያሉ ሲሆን፤ ትላንት ማክሰኞ ሕዳር 17 ቀን 2017 አመሻሽ አካባቢ ሁሉም ከእስር መለቀቃቸዉን ተናግረዋል፡፡

አክለውም እንደ አፋር ክልል ባሉ አካባቢዎች ለፓርቲ በሚል በተመሳሳይ የመምህራን የደሞዝ ቅነሳ እንደሚደረግና መምህራን ቅሬታ እንደሚያነሱ የገለጹ ሲሆን፤ የመምህራን ማህበሩ የበኩሉን ጥረት በማድረግ የተወሰኑ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ ( Ahadu fm )

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

27 Nov, 09:54


መረጃ ‼️

ከ7000 በላይ እስረኞች ከማረሚያ ቤት አምልጠዋል ተባለ!

አማራ ክልል ዉስጥ እየተደረገ ባለ ዉጊያ ምክንያት ከ 7000 በላይ እስረኞች ከማረሚያ ቤት አምልጠዋል ተብሏል

ካመለጡት መካከል አንዳንዶቹ በተጠቂዎች መገደላቸዉ ሲገለፅ ሌሎቹ ደግሞ ከሳሾቻቸዉ ላይ ጉዳት ማድረሳቸዉ ተነግሯል ፡፡(አንኳር merja)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

27 Nov, 09:00


ከኢትዮጵያ ህዝብ 68.7 በመቶው በድህነት ውስጥ እንዳለ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት(UNDP) ያወጣው ሪፖርት አሳይቷል፡፡

በዚህ UNDP ባወጣው የሀገራት የድህነት ምጣኔ ሪፖርት በገጠሩ የኢትዮጵያ ክፍል ድህነቱ የከፋ እንደሆነና 79 በመቶ እንደሚደርስ አስቀምጧል፡፡

ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ከUNDP ጋር በመሆን ባደረጉት በዚህ ጥናት ከዚህ በፊት በተመድ የተቀመጠውን አንድ ሰው ደሃ ለመባል ከ2.15 ዶላር ወይም በቀን ከ250 ብር በታች የሚያገኝ መሆን አለበት የሚለውን በመቀልበስ፤ በዋናነት 3 ትልልቅ መለኪያዎችን (የትምህትርት፣ የጤናና የአኗኗር ሁኔታ) በማስቀመጥ በእነዚህ ስር ደግሞ 10 መለኪያዎችን በማከል የ112 ሀገራትን የድህነት ምጣኔ አስቀምጧል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

27 Nov, 08:29


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሮም በሳምንት ሶስት ቀናት ተጨማሪ በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሕዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሮም በሳምንት ሶስት ቀናት ተጨማሪ የቀን በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

27 Nov, 07:54


አምነስቲ፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በሦስት ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የጣሉትን እገዳ ባስቸኳይ እንዲያነቡ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ድርጅቱ፣ እገዳው "ግልጽነት የጎደለው" እና "ባልተረጋገጡ ውንጀላዎች ላይ የተመሠረተ" እንደኾነ ገልጧል። እገዳው ከጅምሩም መጣል አልነበረበትም ያለው ድርጅቱ፣ ውሳኔው በሲቪል ማኅበረሰብ ምኅዳር ላይ የተቃጣ ነው በማለት ወቅሷል።

አምነስቲ፣ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትም ለኢትዮጵያ ያለውን አተያይ እንዲፈትሽና በትግራይ፣ አማራና ኦሮሚያ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምር ጠይቋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

27 Nov, 07:04


የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ እስካሁን አንድም ትምህርት ቤት ያልተከፈተባቸው 17 ወረዳዎች መኖራቸውን መግለጡን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ትምህርት ቢሮው ዘንድሮ ከቅድመ አንደኛ እስከ ኹለተኛ ደረጃ ድረስ 7 ሚሊዮን 71 ሺሕ 933 ተማሪዎች ለመመዝገብ አቅዶ፣ እስካሁን የመዘገበው 2 ሚሊዮን 543 ሺሕ 128 ተማሪዎችን ብቻ እንደኾነና ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች አኹንም ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደኾኑ ገልጧል ተብሏል።

ትምህርት ቤቶች በታጠቁ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና የመምህራን ግድያ መኖሩም በትምህርት ላይ ጫና እንዳሳደረ ቢሮው መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል። 

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

27 Nov, 07:04


Calling Tech Aspiring Women in Ethiopia!

Join Yeabsira Tibebu and other inspiring women who mastered AI with the fully funded Kifiya AI Mastery Training Program. This program equips Ethiopian women to excel in Generative AI, Machine Learning, and Data Engineering in FinTech.

Yeabsira calls it 'life-changing': 'The supportive 10 Academy community pushed me to achieve more than I ever imagined.'

With women-only sessions, hands-on learning, and mentorship, this program empowers women to thrive in AI careers.

Share this opportunity with tech-aspiring women you know!

Sheger Press️️

27 Nov, 06:35


Calling Tech Aspiring Women in Ethiopia!

Join Yeabsira Tibebu and other inspiring women who mastered AI with the fully funded Kifiya AI Mastery Training Program. This program equips Ethiopian women to excel in Generative AI, Machine Learning, and Data Engineering in FinTech.

Yeabsira calls it 'life-changing': 'The supportive 10 Academy community pushed me to achieve more than I ever imagined.'

With women-only sessions, hands-on learning, and mentorship, this program empowers women to thrive in AI careers.

Share this opportunity with tech-aspiring women you know!

Sheger Press️️

27 Nov, 05:29


እስራኤልና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ።

በዚህም በጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይዎት ለነጠቀው በእስራኤል እና በሊባኖስ ሂዝቦላ መካከል የተፈጠረው ግጭት እንዲያበቃ መንገዱ እየተደላደለ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ስምምነቱ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ስምምነት መደረጉ የተሰማው የእስራኤል የፀጥታ ካቢኔ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የሚመራው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመምከር የተጠራውን ስብሰባን ተከትሎ እንደሆነም ነው የተጠቆመው፡፡

ሆኖም በሊባኖስ የተካሄደው የእርቅ ስምምነት እስራኤል ከፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ ጋር እየተፋለመች ባለችውና ከፍተኛ እልቂት ባስተናገደችው ጋዛ የተኩስ አቁምና የታገቱትን የመልቀቅ ስምምነት ላይ የተባለ ነገር እንደሌለ ተጠቁሟል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ የእስራኤል ወታደሮች ከደቡብ ሊባኖስ ለቀው እንዲወጡ እና የሊባኖስ ጦር በአካባቢው እንዲሰማራ እንደሚያስገድድ ተሰምቷል፡፡

ሂዝቦላህ ከሊታኒ ወንዝ በስተደቡብ ባለው ድንበር ላይ በትጥቅ እንዳይቆይ ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡

የሊባኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብደላ ቡ ሀቢብ የእስራኤል ወታደሮች ሲወጡ የሊባኖስ ጦር ቢያንስ 5 ሺህ ወታደሮችን በደቡብ ሊባኖስ ለማሰማራት ዝግጁነት እንዳለውና በእስራኤል ጥቃቶች የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት ረገድ አሜሪካ የበኩሏን ሚና እንደምታደርግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

እስራኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከሊባኖስ ጋር የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ውጤታማ እንዲያደርግ የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቃለች፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

27 Nov, 03:25


የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት ሰሞኑን በተናጥል ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወዳደረገችው የጁባላንድ ፌደራል ግዛት በርካታ ወታደሮችን ልኳል። የጁባላንድ ባለሥልጣናት በታችኛው ጁባ አውራጃ ውስጥ ከራስኮምቦኒ ከተማ ወጣ ብሎ የፌደራል መንግሥቱ ጦር ፈጸመብን ያሉትን ጥቃት መመከታቸውን እንደገለጡ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የሱማሊያ ጦር በጁባላንድ የተሠማራው፣ ግዛቲቷ ፌደራል መንግሥቱ ካጸደቀው ቀጥተኛ የምርጫ ሥርዓት በተቃራኒ ቀጥተኛ ባልኾነ የምርጫ ሥርዓት ፕሬዝዳንት አሕመድ ማዶቤን ለሦስተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን መምርጧን ተከትሎ ነው።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

26 Nov, 18:27


ችሎት‼️

የአቶ ታዬ ደንደዓ የዛሬ የችሎት ውሎ

በፍትህ ሚኒስቴር ተከሰው እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ በቀጠሮያቸው መሰረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም ለመከላከያ ምስክር የጠሯቸው ግን ሳይገኙ ቀርተዋል። “የጦር መሳሪያን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ይዘው ተገኝተዋል” በሚል የቀረበባቸው ሦስተኛውን የክስ ጭብጥ እንዲከላከሉ ከዚህ በፊት ብይን የተላለፈባቸው ታዬ፤ ጉዳዩን የሚያውቁ ብለው ከጠሩዋቸው 5 ተከላካይ ምስክሮች መካከል ሁለቱ ባለፈው ሰኞ ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም ቀርበው የምስክር ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

በእለቱ ቀርበው ምስክርነታቸውን የሰጡት የቀድሞ አለቃቸው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እና በፌዴራል ፖሊስ የአጠቃላይ ወንጀል መከላከል መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ነበሩ። ተከሳሹ ከጠሯቸው አምስት ተከላካይ ምስክሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲና ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ስም ከዚህ በፊት መጥቀሳቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ በተቀጠረው ችሎት ግን የቀረበ ተከላካይ መስክር አልነበረም።

ችሎቱ በዚህ ላይ ለተከሳሽ ማብራሪያ ሲሰጥ ምስክሮቹ ያልቀረቡት መጥሪያ ስላልደረሳቸው መሆኑንና ዛሬ ለታህሳስ 03 ቀን 2017 ዓ.ም ለተሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ ግን እንዲቀርቡ ትዕዛዝ እንደሚደርሳቸው አሳውቋል፡፡አቶ ታዬ ከታሰሩ በኋላ የሰብዓዊ መብት ጉዳዩ እንድመረመርላቸው የጠየቁት፤« ቤተሰቦቼ ከነበሩበት መኖሪያ ቤት ያለበቂ ጊዜ መሰጠት ተጣድፈው እንዲወጡ በመደረግ ደጅ መውደቃቸው፣ ለአራት ወራት ያለምንም የፍርድ ቤት ሂደት መታሰር እና ጠበቃ እንዳይቆምልኝ መከልከልን» በተመለከተ» ጥያቄ አንስተው፤ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተላከ ደብዳቤ እና ባለሙያ የአንድ ወር ተጨማሪ ጊዜ እንደሚፈልግ ተነግሯቸዋል፡፡

በዚህ ላይ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ታዬ፤ ምርመራው መዘግየቱን ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የመጨረሻ ያለውን የ30 ቀናት ጊዜ ብቻ ለሰብዓዊው ተቋሙ ሰጥቷል። የቀድሞ ባለስልጣን አቶ ታዬ፤ ከዚህ በፊት በሰጡት የእምነት ክደት ቃል የጦር መሳሪያውን መያዛቸውን ሳይክዱ ክሱ የቀረበበትን አኳኳን ግን መሞገታቸው አይዘነጋም፡፡(DW)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

26 Nov, 17:01


መረጃ ‼️

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ሺመልስ አብዲሳ ክልሉ ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች በፋኖ ታጣቂዎች የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የመንግሥት ኃይሎች እንዳይከላከሉ በዋናነት እንቅፋት የሆነው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አማጺዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው ሲሉ ትላንት በነቀምት ከተማ በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ተናግረዋል።

ሽመልስ ከዚህ ቀደም በምሥራቅ ወለጋ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በምሥራቅ ሸዋ እና በቅርቡ ደሞ በሰሜን ሸዋ ዞኖች "ጽንፈኛ" ሲሉ የጠራቸው የፋኖ ታጣቂዎች ለሚፈጽሟቸው ጥቃቶች በዋናነት ኃላፊነቱን የሚወስደው ኦሮሞን ነጻ አወጣለው ብሎ የሚንቀሳቀሰው አማጺ ቡድን ነው ብለዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተባሉት ኃይሎች የፋኖ ታጣቂዎች ወደሚገኙባቸው አካባቢዎች አይጠጉም ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ራሱን እንዳይከላከል አስቀድመው ትጥቅ በማስፍታት ለጥቃት ያጋልጡታል በማለት ከሰዋል።

ኹለቱ ኃይሎች የጥፋት ሥራቸውን ተናበው እንደሚሠሩ በመግለጽም፣ መንግሥት አማጺዎቹን ከከልሉ በቅርብ ቀናት በማጥፋት ሰላምን እንደሚያረጋግጥ ቃል ገብተዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

26 Nov, 14:33


ከሶማሊያ ፌደራል መንግስት ጋር ውጥረት ውስጥ የገባችው ጁባላንድ አህመድ ማዶቤን ፕሬዝዳንት አድርጋ መረጠች


ውጤቱን የጁባላንድ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ ያደረገ ሲሆን
አህመድ መሀመድ እስላም (ማዶቤ)ሌሎች ሁለት እጩዎች በተሳተፉበት ምርጫ የጁባላንድ ፓርላማ አባላት ከሰጡት 75 ድምጽ 55 ድምጽ በማግኘት የጁባላንድን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሰኞ እለት በማግኝት አሸንፏል።

ከፕሬዚዳንት አህመድ ማዶቤ ጋር የተወዳደሩት ሁለቱ እጩዎች ፈይሰል አብዲ ማታን እና አቡበከር አብዲ ሀሰን ሽንፈታቸውን ተቀብለው ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የጁባላንድ ግዛት ተመራጩ ፕሬዝዳንት የመልካም ምኞት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሶማሊያ ፌድራል መንግስት የምርጫውን ሂደት ውድቅ አድርጎታል። ማዶቤ የሶማሌ ፌዴራል መንግስት አለመረጋጋትን በማቀነባበር እና የክልል አስተዳደርን እያናጋ ነው ሲሉ ተችተዋል። ጁባላንድ የሶማሊያ አካል እንጂ የኬንያ ወይም የኢትዮጵያ አካል አለመሆኑን አስረግጠው ተናግሯል።

አካሄድ እያስታወሰን ነው። ሀሰን ሼክን እላለሁ፣ ለውይይት ዝግጁ ነን እኔ ኬንያዊ አይደለሁም እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም፣ ሶማሌ ነኝ” ሲሉ የሃሰን ሼክ መንግስት የሰላም ጥሪ አድርገዋል።

ማዶቤ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጁባላንድን ለማተራመስ እና በአካባቢው የእርስ በርስ ጦርነት ለመቀስቀስ የወሰዱትን ወታደራዊ እርምጃ አውግዘዋል። የፌደራል መንግስት አልሸባብን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ እየሞከረ ነው ሲሉም ከሰዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

26 Nov, 14:32


#ባለጸጋ ያደረጉን ድሆች፣ የደስታችን ምንጭ የሆኑ ሀዘንተኞች 

በዓለት መሀል የሚገኝ በመነኮሳት ፀሎት ብቻ እየተቆረጠ ለፀበልተኞች የሚሰጥ የማር እምነት መገኛ፣ ድውያንን ከመፈወስ አልፎ ሙት ያስነሳ ድንቅ የሚያደርግ ጸበል ያለበት፤ ከዘጠና በላይ መናንያን ዓለምን ንቀው የተጠለሉበት ነገር ግን ሾለ ዓለምና ሾለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ፤ ሙትአንሳ  ማር  ቅዱስ ሚካኤል አድነት  ገዳም።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ይህ ገዳም ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ 6÷10 “ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።” ያለው ሕያው ቃል በዘመናችን በተግባር የሚታይበት ቦታ ነው፡፡

ምንም እንኳን መነኮሳቱና ገዳማውያኑ አሁንም ድረስ መንፈሳዊ ግዴታቸውን እየተወጡ በጽናት ቢቆዩም ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነው፡፡ ይህ ድንቅ ተአምር ያለበት ታሪካዊ የአንድነት ገዳም በአንድ በኩል አከባቢው ተፈጥሮ ፊቷን አዙራበት በድርቅ ምክንያት ምንም ዓይነት አዝርእት ያልበቀለበት በመሆኑ ጭው ያለ ምድረ በዳ ሆናል። ወዲህ ደግሞ በአካባቢው ያለው ጦርነት በየጊዜው ይጎበኟቸው የነበሩ ፀበልተኞች ፈጽመው እንዲሸሹና ገዳማውያኑ ያለምንም ጠያቂ በትልቅ ችግርና ፈተና ውስጥ እንዲገኙ አድርጓቸዋል፡፡

ረሀብ፣ እርዛት፣ የማረፊያ ቦታ ችግር እጅግ ቢፈታተናቸውም፣ በአንድ በዓት ለሶስት ለአራት ለማደር ቢገደዱም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው የራሳቸውን ስጋዊ መከራ ችለው፤ ሌት ተቀን ስለ ሀገር ደህንነት፣ ስለ አሐቲ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ሰው ልጅ ሰላምና ጤንነት ሳያቋርጡ በጽናት የሚፀልዩ ናቸው።

ዙሪያችንን የከበበንና በእሳት ውስጥ ያሳለፈን መከራ ያልጣለን፣ በተገፋነው እጥፍ ጸንተን የቆምነው በእነዚህና በሌሎችም ገዳማውያን አባቶቻችን የማያቋርጥ የሕብረት ጸሎት ነው፡፡ የገዳማት መፈታት የመነኮሳት ከበዓታቸው መውጣት ይህን የሕብረት ጸሎት ያስተጓጉለዋል፡፡

ድውያነ ስጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የሚፈውሰውን ስፍራና ገዳማውያኑን ዛሬ ካልታደግን ዳሩ ሲወረር መሀሉ ዳር ይሆናል የሚለው ይፈጸምብናል፡፡ የተወረወረብን ጦር፣ የተመከረብን ክፉ ምክር በግላጭ ያገኙናል፡፡ በግንብ የታጠረ ቤታችን አቅበን የያዝነው ንብረታችን አይታደጉንም፡፡

ከፀሎትና ከድካም መልስ የሚጠለሉበትን፣ ከፆም መልስ የሚቀምሱትን ነገር ልናቀርብላቸው ይገባል። ለሰማያዊ ህይወታችን ስንቅ ይሆነናል ከመነኮሳቱ ፀሎት የበረከት ተካፋይ እንሆናለን፥ ለህሊናችንም እረፍት እናገኝበታለን።
 
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

26 Nov, 14:12


የፖሊስ አዛዥ በወርቅ ሥርቆት ተጠርጥረው ተያዙ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ሦስት ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በመሥረቅ የተጠረጠሩ የወረዳ ፖሊስ አዛዥ ታሠሩ ፡፡

በዞኑ የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በኮትሮባንድ ሲዘዋወር ከተያዘው ሰባት ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ መካከል ሦስቱን ወደ ቤታቸው ይዘው በመሄዳቸው ነው ተብሏል ፡፡

አዛዡ ወርቁን ወደ ቤታቸው መውሰዳቸው ሊታወቅ የቻለው ወርቁን ሲያዘዋውሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች የተያዘብን ወርቅ ይሄ ብቻ አይደለም በሚል የሰጡትን ጥቆማ መሠረት በማድረግ በተካሄደ ምርመራ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዣ ኮማንደር ግርማ በየነ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

26 Nov, 13:35


Apply by December 3, 2024: Kifiya AI Mastery Training Program!

This fully funded, part-time, 3-month online program is tailored for Ethiopian residents aspiring to become AI Engineers in fintech. Gain essential skills in Machine Learning, Data Engineering, and Generative AI.

✅ Eligibility:

✔ Ethiopian residents (22-34 years old)
✔ Bachelor’s degree holders
✔ Proficient in Python, SQL & Statistics
✔ Women, people with disabilities, and vulnerable communities are encouraged to apply.

✅ Benefits:

✔ 30-40 hrs/week of hands-on, project-based training
✔ Real-world fintech projects led by experts

Sheger Press️️

20 Nov, 18:32


መረጃ ‼️

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሱማሊያ ጦር አባላትን ማሰሩ ተሰማ

የሱማሊያ ወታደሮች የተያዙት የሲቪል ልብስ  በመልበስ ሲንቀሳቀሱ በሱማሊያ ጌድዮ ግዛት ዶሎ ኤርፖርት ዉስጥ ነዉ ፡፡

በቁጥር ስድስት እንደሆኑ የተነገረላቸዉ የሱማሊያ ወታደሮች በምን ምክንያት እንደታሰሩ የተገለፀ ነገር የለም ፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

20 Nov, 17:15


ሳውዲ‼️

በፈረንጆቹ 2024 ሳውድ አረቢያ ከ100 በላይ የውጪ ሀገር እና የሀገሯን ዜግች በስቅላት የቀጣች ሲሆን

ይህም ከባለፈው ዓመት ሲወዳደር
በ3 እጥፉ የበለጠ ነው ተብሏል::

ምክንያቱ ደሞ : -

* ሰው መግደል
* ሀሺሽ ወደ ሀገሯ ማስገባት
* ሴት , ህፃናትን መድፈር እና
* ሌሎችም ህገ ወጥ ከባድ ወንጀሎች የሰሩት ሲሆን

ከዚሁ ውስጥ :-

* 21 ፓኪስታኖች 🇵🇰
* 20 የመኖች 🇾🇪
* 14 ሱሪያውያን 🇸🇾
* 9 ግብፃውያን 🇪🇬
* 8 ጆርዳናውያን 🇯🇴
* 7 ኢትዮጵያውያን 🇪🇹
* 3 ሱዳናውያን 🇸🇩
* 3 ህንዳውያን 🇮🇳
* 3 አፍጋኒስታውያን 🇦🇫
* 1 ስሪላንካውያን 🇱🇰
* 1 ኤርትራውያን 🇪🇷
* 1 ፊሊፒንሳውያን 🇵🇭

ይገኙበታል::(ጉርሻ)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

20 Nov, 15:07


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጋምቤላ ክልል የተገነባውን ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ መጋቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኩባንያው በስካንዲኔቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጫ ላይ የተሰማራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል አኮቦ ወረዳ በተከናወነው ትርጉም ባለው የኢንቨስትመንት ሥራም ለሁሉም አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በአኮቦ የምትገኘው ዲማ ከተማ በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሒደት ለብዙ ጊዜ ብክነት የተሞላበት አሠራር መቆየቱን አስታውሰዋል።

ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት ከማስገኘቱም በላይ በሕገ-ወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ ይሰጣል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ልማት በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት ለሕዝቡ እና ለክልሉ ጠቀሜታ ለማዋል ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያሳይም ነው ያስረዱት፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

20 Nov, 15:02


#ከዓይን ሲርቅ የሚደርቀው እንቁላል…


“ሐልዎተ እግዚአብሔር” የእግዚአብሔርን መኖር ከምናውቅባቸው ነገሮች አንዱ ፍጥረታትን መመልከት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶቻችን ያስተምሩናል፡፡

ይህ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌለው ፍጥረት አስገኚ፣ ፈጣሪ ባይኖረው ከዓለም ጅማሬ እስካለንበት ዘመንና እስከ ዓለም ፍጻሜ ስርዓቱን ጠብቆ ባልኖረም ነበር ይሉናል፡፡

ያውም ከድንቅ ተፈጥሯዊ ባሕርዩ ጋር፡፡ በዚህ ድንቅ ተፈጥሯዊ ባህርይ ከሚታወቁት ፍጥረታት አንዷ ግዡፏ የአእዋፋት ዝርያ ሰጎን ናት፡፡

ሰጎን እንቁላል ከጣለች በኋላ እስኪፈለፈል ድረስ አይኗን ከእርሱ ላይ አታነሳም፡፡ ምግብ ፍለጋ ስትሔድም ወንዱን አስጠብቃ ነው፡፡ አይኗን አንስታ ረጅም ጊዜ ከቆየች ይደርቅና አይፈለፈልላትም፡፡

የመፈልፈያ ጊዜያቸው ሲደርስም ከውጪ ሆና ቅርፊቱን ታንኳኳለች፣ እነርሱም ከውስጥ ሆነው ያንኳኳሉ፡፡ ድምጽ ታሰማቸዋለች፣ እነርሱም መልሰው ድምጽ ያሰማሉ፡፡ ይህን ጊዜ እንቁላሉን ሰብራ ታወጣቸዋለች፡፡

ስታንኳኳ ካላንኳኩ፣ ድምጽ ስታሰማቸው ድምጽ ካላሰሙ ጊዜያቸው ገና ነው አሊያም ሞተዋል፣ ወይም እንቁላሉ ባዶ ነው ብላ ስለምታስብ ትታቸው ትሔድና በዚያው ይደርቃል፡፡


እኛም እንደ ጫጩቶቹ ነን፡፡ አባታችን እግዚአብሔርም የከከበበን የኃጢአት ቅርፊት ሰብሮ የሚያወጣን ዘወትር አይኖቹን ከኛ የማያነሳ ጠባቂያችን ነው፡፡

ይህ እንዲሆን ግን ቅርፊቱን ሲያንኳኳ እኛም በኃጢአት ውስጥ እንኳን ብንሆን አድነኝ ብለን መልሰን እናንኳኳ፤ ድምጽ ሲያሰማ፣ ሲጠራን፣ ተመለሱ ሲለን የእሺታ፣ የመዳን ፍላጎት ድምጽ እናሰማው፡፡

አዎ ቅርፊቱን አንሳልኝ መውጣት፣ መራመድ፣ በጽድቅ ስራ መብረር እፈልጋለሁ እንበለው፡፡ በዘመነ ስጋዌው በዚህ ምድር ሲመላለስ ፈውስ ፈልገው ወደርሱ የሚመጡትን “ልትድን ትወዳለህን? ብሎ ይጠይቅ የነበረው በፈቃዳችን ስለሚሰራ ነው፡፡

መዳን፣ እንደ ሰጎኗ ጫጩቶች ከቅርፊቱ መውጣት፣ በበጎ ምግባር፣ በትሩፋት መጓዝ የምንችልበት እድል ተሰጥቶናል፡፡

ይህን ድንቅ ምስጢር የሚገልጹልን የመዳንን መንገድ እንድንከተል በጸሎታቸው የሚያስቡንን፣ የኃጢአት ቅርፊቷን የምትጭንብንን ይህቺን ዓለም ንቀው የመነኑትን ገዳማውያንና ቅዱሳት መካናትንም እናስብ፡፡ ጥሪውን እንድንሰማ፣ ለማንኳኳቱም መልስ እንድንሰጥ ይርዳን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

20 Nov, 14:55


ሰላሌ😭😭😭

ሰላሌ አዝናለች😭😭

ከዛ መንደር ያየነውን ቪዲዮ በእውነት በእውነት እጅግ ያሳዝናል ልብ ይሰብራል ምን ያህል ብንጨካከን ነው ግን።

እውን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለነው ከቅርብ ጊዜ ወዲ የምንሰማቸውና የምናያቸው ዜናዎች ሁሉ ልብ ይሰብራሉ።

ቪድዮው እዚ መለጠፍ ለኛ ለሸገሮች በጣም ከባድ ሆኖብናል ከልብ እናዝናለን።

እውነት ለመናገር ቪዲዮውን ለማየት አቅም ያሳጣል።

የሚመለከተው አካል እነዚህ አጥፊዎችን ይዞ ለህግ እንዲያቀርብ በትህትና እንጠይቃለን ከሸገር ፕረስ።

በተጫማሪም በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደሉ ወገኖቻችን ሁሉ ነብስ ይማር ነፍሳቸው በሰላም ትረፍልን።

ያሳዝናል😭😭😭😭

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

20 Nov, 13:02


በኢትዮጵያ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙ 2 መቶ 70 ናይጄሪያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲላኩ ትዕዛዝ ተሰጠ

ሕዳር 11፣2017 (አራዳ ኤፍ ኤም)
በአቡጃ የሚገኘው የናይጄሪያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ኢንያንግ ኤኮ ለናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የናይጄሪያውያን ዲያስፖራ ኮሚሽን ባስተላለፉት መልዕክት፣በኢትዮጵያ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙትን ከ2 መቶ 70 ያላነሱ ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አዘዋል

ዳኛው ይህን ውሳኔ ያስተላለፉት የኢትዮጵያ መንግስት ለእነዚህ እስረኞች የምግብ፣መድኃኒት እና ሌሎች ግብዓቶች የሚሆን በጀት እንደሌለው ማሳወቁን ተከትሎ ነው ተብሏል

የኢትዮጵያ መንግስት ለናይጄሪያ መንግስት በላከው ይፋዊ መልዕክቱ እስረኞቹን እንዲረከብ መጠየቁን በመግለጽ፣በእስር ላይ የሚገኙትን ናይጄሪያውያን ተቀብሎ እንዲመልስ የሚያስገድድ ትዕዛዝ ዳኛው ሰጥተዋል ተብሏል።

የናይጄሪያ ፌደራል መንግስት ለዚህ ዋናው ምክንያት ነው ያለውን የብሄራዊ የስደት ፖሊሲን በመገምገም፣የዜጎችን ሞት፣በደል፣ መድልዎ እና ናይጄሪያውያን ወደ ውጭ በሚጓዙበት ጊዜ የሚያጋጥሟቸውን ሌሎች ጉዳዮችን እንደሚገታ አስታውቋል ሲል የዘገበው ዘ ስትሪት ጆርናል ነው

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

20 Nov, 11:04


መረጃ ‼️

በምግብ መመረዝ ምክንያት በሚል ጎሮ አንደኛ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ህመም አጋጥሞቸዉ ከደቂቃዎች በፊት በአንቡላንስ ወደ ጤና ጣቢያ መወሰዳቸዉን አንኳር መረጃ ሰምታለች፡፡

ትምህርት ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆኑ ይታወሳል ፡፡

ህመሙ ቀለል ያለ እና ተማሪዎቹ ከጤና ጣቢያ መጠነኛ ህክምና ተደርጎላቸዉ እየተመለሱ መሆኑ ሰምተናል ፡፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

20 Nov, 10:26


“የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋ መጥቷል”_ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ

በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋ መምጣቱን ጠቅሰው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተቋማቱ ከ2 ዩኒቨርሲቲዎች ወደ 51 የመንግስት እና 315 የግል ተቋማት ማደጋቸውን እንዲሁም የተማሪዎች ምዝገባ ወደ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ገልጸዋል።

ነገር ግን የትምህርት ጥራት ማሽቆልቆሉን አምነው፣ ተቋማቱ ብቁ ተመራቂዎችን ለመፍጠር፣ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራዊ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ጥናትና ምርምሮችን ለማድረግ እንዲሁም ውጤታማ አስተዳደርን ለማስፈን እየሰሩ ነው ብለዋል።

አክለውም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ በ2011 ዓ.ም የወጣው የትምህርት ፍኖተ ካርታ የዩኒቨርሲቲዎች ራስን በራስ ማስተዳደርን እንደ ቁልፍ ማሻሻያ ጠቁመዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1294 መሠረት የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ በመሆን የሁለት ዓመት ሽግግር ያደርጋል ተብሏል።

በሚቀጥለው ዓመትም 10 ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች የራስ ገዝ አስተዳደር ማዕቀፉን እንዲቀላቀሉ እቅድ መያዙን አመልክተዋል።

እነዚህ ማሻሻያዎች ከፍተኛ መዋቅራዊ ለውጦችን እና በባለድርሻ አካላት መካከል የትብብር ጥረቶችን ይጠይቃሉ ብለዋል።

ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ይህን የገለጹት የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ዘጠኝ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ራስ ገዝ ለማድረግ የሚያስችል የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ባደረገበት ወቅት ነው።
!
@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

20 Nov, 10:26


የቻናል ማስታወቂያ ‼️

ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0

Sheger Press️️

20 Nov, 09:25


ለቀጣይ 10 ቀናት አብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ደረቅ ፀሐያማና ነፋሻማ ይሆናሉ

በመደበኛ ሁኔታ በሚቀጥሉት 10 ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት በሰሜን፣ ሰሜን ምሥራቅ፣ ምሥራቅ፣ መካከለኛው እና የደቡብ ደጋማ ቦታዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እንደሚዘወተር ገልጾ፤ አልፎ አልፎ የማስከተል ጥንካሬ እንደሚኖረውም ጠቁሟል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

20 Nov, 08:37


ሹመት‼️

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ለኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር በመሆን በ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ተሹመዋል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

20 Nov, 07:01


ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አመራሮች ከሃላፊነታቸው ሊነሱ ይገባል” ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ

ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አባላት ከሃላፊነት ሊነሱ ይገባል ሲል ከሰሞኑ ፍቃዱ የተሰረዘው ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ ከሷል፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ፍቃድ በመሰረዝ የሰላማዊ ትግል በርን እየዘጋ ነው ያለው ፓርቲው፣ ይህ ደግሞ ሆን ብሎ የሚከናወን ነው ሲል አብራርቷል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

19 Nov, 19:26


ዛሬ የዓለም የጋዜጠኞች ቀን ነው።

የጋዜጠኝነት ውሃ ልኮች እንኳን አደረሳችሁ።

ጋዜጠኛ ምስጢረሥላሴ ታምራት
ጋዜጠኛ ኃይለገብርኤል ታደሰ
ጋዜጠኛ ሙሀመድንጉስ አብዱ

በአጠቃላይ የአሻም ቴሌቭዥን ጋዜጠኞችና ማኔጅመንት
አባላት በሙሉ ፦

ነጭ ነጯን ፣ እውነተኛ መረጃ በማስረጃ እያስደገፋችሁ
የተለያዩ ጫናዎችን ተቋቁማችሁ እዚሁ ሀገራችሁ ላይ ተቀምጣችሁ በልበ ሙሉነት የሕዝብን ብሶት ስለምትተነፍሱ
እና ለታመናችሁለት ሙያ ለደሞዝ ሳይሆን ለሕሊናችሁ ስለምትሰሩ እንኳን ለዓለም የጋዜጠኞች ቀን አደረሳችሁ።

ጊዜያችሁን በማይመለከተን የእስራኤልና የሀማስ ፣
የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በመዘብዘብ ስለማታውሉት
ክብር ይገባችኋል።

ወደፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሸልማችኋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ውለታውን የሚረሳ አይደለም።

አቤል ነኝ አክባሪያችሁ ከሸገር ፕረስ
ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ !

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

19 Nov, 16:51


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግስት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የጸደቀው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ነው።

ረቅቅ አዋጁ የመንግስት ሰራተኛ የሰው ሀይል ምልመላ ግልጸኝነት ባለው ውድድርና ብቃት ላይ እንዲመሰረት፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ሀላፊነት በብቃት እንዲወጡ፣ ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎት ለመስጠት የሚስችል ስርዓት ለመዘርጋት የሚረዳ ነው ተብሏል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

19 Nov, 16:51


👉የኑሮ ውድነት ጣራ በነካበት እና ወደፊት የኔና ለቤተሰቤ ማረፊያ ምን ይሆን ተብሎ በሚያሳስብበት ሰዓት የተገኘ የማይታመን እድል!!😱😱 የተለያዩ ለመክፈያ አማራጮች ስላሉን ያላችሁ የገቢ መጠን ብዙ አያስጨንካችሁ😍 DMC እንባላለን 🔥🔥

✅8% ቅድመ ክፍያ
✅እስከ 30% ልዩ ቅናሽ
✅50% ባንክ ብድር
✅ለ50ቤቶች ብቻ በ ካሬ 78,000 ብር ፡ ከ57ካሬ እስከ 190ካሬ ወይም ከስትድዮ እስከ ባለአራት መኝታ ድረስ የካሬ አማራጭ አሉን ፡

✅5ሊፍት ፡ 5መዋኛ ገንዳ ያለው ፡ የከርሰ ምድር ውሀ፡ የልጆች መጫወቻ ፡ ላይብረሪ፡ ጅምና ስፓ፡ የነዳጅ ዲቦ ፡ ያካተተ ዘመናዊ መንደር ፡ አሁን 10ኛ ፍሎር የደረሰ ፡ በአልሙኒየም ፎርምወርክ የሚገነባ ፡ መሀል አድስ አበባ

✅ከሜክሲኮ 5ኪ.ሜ ፡ ከቦሌ 7ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ለቡ መብራት ዘመናዊ መንደር።
በ ካሬ ከ78,000 ብር ጀምሮ ይፍጠኑ

ለበለጠ መረጃ  
                      
📞📞📞0911652616 ወይም @Senaitgirma1 ያናግሩን

በመደወል አሁኑኑ መረጃ ይውሰዱ

Sheger Press️️

19 Nov, 15:51


ይህንን ያውቁ ኖሯል?

ዛሬ ማለትም November 19 አለማቀፍ የወንዶች ቀን ነው።

የቻናላችን ወንድ ተከታታዮች በውነቱ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።

ነፍ አመት ኑሩልን❤️

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

14 Nov, 07:08


#FactCheck "የድሮ ፎቶ" እንዲመስል በቅንብር የተሰራ ምስል

'አበበ ቶላ ፈይሳ' የተባለ ፌስቡክ ላይ ከ158 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግለሰብ "የድሮ ፎቶ እያወጣህ እንደ አዲስ የምትለጥፍ ከሆነ..." በሚል ያሰራጨው ምስል እንዳለ ተመልክተናል።

ግለሰቡ በዚህ ልጥፉ ላይ ከትናንት ጀምሮ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲንሸራሸር የነበረው የፋኖ ሀይሎች አመራር የሆነው የዘመነ ካሴ ምስል "ዓመት የሞላው" መሆኑን ገልጿል።

ይህን ያሳያሉ ያላቸውን እና የፋኖ አመራሩን ፎቶ አምና፣ ማለትም እአአ በ2023 የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አጋርተውት ነበር ያላቸውን ምስሎች አያይዟል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ማጣራት እንዲያደርግ ጥያቄ የቀረበለት ሲሆን እኛም በዚህ ዙርያ ፍተሻ አርገናል።

በዚህ ዙርያ ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ የድሮ እንዲመስሉ '2023' የሚል ዓመት በፎቶሾፕ ቅንብር እንደገባባቸው ተመልክተናል። ቅንብሩ ሲሰራም የፌስቡክን ዲዛይን በማይመስል መልኩ ተጣሞ እና ከዲዛይን ውጪ ክፍተት ኖሮበት ሆኖ እንደተሰራ መመልከት ይቻላል።

ከዚህም በተጨማሪ መረጃውን አጋርተዋል ወደተባሉት የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶች በመሄድ ምርመራ ያደረግን ሲሆን "የአርበኛ ዘመነ ካሴ የዕለቱ መልዕክት" ከሚለው ፅሁፍ ጋር ተጋርቶ የነበረው ሌላ የፋኖ አመራሩ ምስል መሆኑን ለማየት ችለናል።

በዚህም ምክንያት 'አበበ ቶላ ፈይሳ' በተባለው ግለሰብ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና በቅንብር የቀረበ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

ከአውድ ውጪ ከሚቀርቡ፣ በቅንብር ከሚሰሩ እና ተጋነው ከሚሰራጩ መረጃዎች ራሳችንን በማራቅ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

14 Nov, 05:56


በሕገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ የገቡ ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ሲያጅብ የተገኘ አንድ የአገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል።

በተሽከርካሪ ሲጓዙ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ኢትዮጵያዊያን መካከል፣ አንዲት የ15 ዓመት ታዳጊ እንደምትገኝበት ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ፖሊሱና ኢትዮጵያዊያኑ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሳምቡሩ አውራጃ ውስጥ እንደሆነ ተነግሯል።
 
5፤ የየመን ኹቲ ኃይሎች በቀይ ባሕር አካባቢ የሚፈጽሙት ጥቃት በጅቡቲና ኢትዮጵያ የንግድ መስመር ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ መኾኑን አፍሪካ ኢንተሌጀንስ ዘግቧል።

ኹቲዎች የሚፈጽሙትን ጥቃት በመስጋት የንግድ መርከብ ድርጅቶች ግዙፍ መርከቦችን ወደ ጅቡቲ በመላክ ፋንታ ትናንሽ መርከቦችን መላክ እንደጀመሩ ዘገባው አመልክቷል።

ይህም ሸቀጦችና አስፈላጊ እቃዎች በቶሎ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይደርሱ ምክንያት ኾኗል ተብሏል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

14 Nov, 05:01


መረጃ ‼️

በሶማሊያ አንድ ታጣቂ በከፈተዉ ተኩስ ሁለት ኢትዬጲያዊያን ተገደሉ!

በሶማሊያ ጋልጋዱል ግዛት የሶማሊያ ወታደር ዩኒፎርም በለበሰ ታጣቂ በተከፈተ ተኩስ ሁለት ኢትዬጲያዊያን ተገድለዋል

ይኼን ተከትሎም በግዛቶ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዬጲያዊያን ዛሬ ከሰአት በሆላ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይደርስባቸዉ በመስጋት ለቀዉ እየወጡ እንደሆነ ተሰምቶል ፡፡

በጥቃቱ ዙሪያ  እስካሁን የሶማሌያ  መንግስት ምንም ያለዉ ነገር የለም ፡፡

በሶማሊያ የኢትዬጲያ ኢምባሲም ይሁን የመንግስት ባለስልጣናት ስለ ዜጎቻቸዉ ሞት እስካሁን ዝምታን መርጠዋል ፡፡

via አንኳር_መረጃ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

14 Nov, 05:00


በኢየሩሳሌም መቅደስ ደጃፍ ላይ ስምንት ሙዳየ ምጽዋት ይቀመጥ ነበር። ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኔዓለም በሴቶች መግቢያ በኩል ባለው ሙዳየ ምጽዋት አጠገብ ቆሞ፣ ሁሉን በሚያውቅ ባህርይው ስጦታውንና ስጦታው የተሰጠበትን ልብ ያይ ነበር። አንዳንዶች ለዝና ሰጡ፣ ሌሎች ስጦታቸውን ኑሮአቸውን ሊያናጋ እንደማይችል በማሰብ ሰጡ።

አንዲት ድሃ መበለት ግን በቤትም በእጇም የነበራትን ሁለት ሳንቲም በሙሉ ሰጠች። ከእነዚህ ከሁለት ሳንቲሞች ውጪ በምድር ላይ ምንም ጥሪት ሀብት የላትም። በዚህ ጊዜ ጌታ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድሃ መበለት ከሁሉ አብልጣ ጣለች እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና ይህች ግን ከጉድለቷ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች" አለ፡፡


ይህ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 21፣1-4 የሰፈረው ይህ ቃል የመስጠትን ምንነት ጌታችን በሚገባ ያስረዳበት ነው፡፡ ሁሉ የእርሱ ሲሆን በቸርነትና በልግስና ከሰጠው ላይ ስጡኝ ብሎ ይለምናል፡፡



የዚህች መበለት በጌታችን የተደነቀ መስጠት ብዙ ይነግረናል፡፡ አለማስተዋል እንጂ እንኳን ገንዘባችን እኛ ራሳችን ዋጋ የተከፈለብን የእግዚአብሔር ገንዘቦች ነን።
አንዳንዶቻችን ከሰጠን የሚጎድልብን እየመሰለን እንሰስታለን፣ እግዚአብሔር ግን ስጡኝና ፈትኑኝ፣ የጎደለውን ባልሞላ በረከቱን ባላበዛ ታዘቡኝ ይለናል። ደግሞም ስጦታ ከጉድለት እንጂ ከትርፍ አይደለም።


ስጦታችን ካልተሰማን ገና አልሰጠንም ማለት ነው። እናም ማትረፍ ከፈለግን ከጉድለታችንም ቢሆን በፍቅር እንስጥ። በተለይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ክረምቱን እያሳለፈ ላለው ገዳምና አባቶች እጃችንን እንዘርጋ፡፡



ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

14 Nov, 04:48


ሊጨምር ነው‼️

መንግሥት ከውጭ መሉ በሙሉ á‰°áŒˆáŒŁáŒĽáˆ˜á‹ በሚገቡ በኤሌክትሪክበሚሠሩ የቤት አውቶሞቢሎች ላይ የ5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ጭማሪ አድርጓል!!

በዚህ መሠረት በተሽከርካሪዎቹ ላይ የጉምሩክ ቀረጡ ከ15 በመቶ ወደ 20 በመቶ አድጓል።

የ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ የታክስ ጭማሪው ሥራ ላይ ሲውል የተሽከርካሪ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ መንግሥት ከታክስ የሚያገኘውን ገቢ እንዲጨምር ማሳሰቡ ይታወሳል።(ሸገር ፕረስ)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 18:10


"ወደ ወታደራዊ ካምፕ እስኪወሰዱ ምንም አይነት ጥያቄ እንዳያነሱ በታጎሩበት አዳራሽ ውስጥ የመጠጥ አይነት ይገባላቸዋል"

ከሰሞኑ በበርካታ ስፍራዎች፣ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን እየተከናወነ ስለሚገኘው የአፈሳ ድርጊት ተጨማሪ መረጃዎች ለመሠረት ሚድያ ደርሰዋል።

ከጅማ የደረሰን መረጃ እንደሚያሳየው የአፈሳ ድርጊቱ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ወጣቶች ከየቦታው እየታደኑ ይገኛሉ።

በብዛት ለአፈሳ የሚፈለገው ለቀን ስራ እና ለቡና ለቀማ ከአጎራባች የደቡብ ክልሎች ማለትም ከዳውሮ፣ ከከፋ እና ከየም የመጡ ወጣቶች ናቸው ተብሏል።

"እያንዳንዱ ሚሊሻ ባመጣው የሰው ቁጥር ይከፈለዋል፣ አዳራሽ ውስጥ ታጉረው ምንም እንዳይጠይቁ የመጠጥ አይነት ባናት ባናቱ ይገባላቸዋል" ያለን አንድ በጅማ የሚገኝ ድርጊቱን የሚከታተል ምንጫችን መሄጃቸው እስኪደርስ የአካባቢያቸው ሙዚቃ እየተከፈተላቸው እየጠጡ እና እየጨፈሩ እንዲቆዩ ይደረጋል ብሏል።

"ከዛም ባላሰቡት በሌሊት ማንም ሳያይ ተጭነው ወደ ወታደራዊ ካምፕ ይወሰዳሉ" ያለው ሌላኛው ምንጫችን የአካባቢው ወጣት የተያዘ እንደሆነም ቤተሰቡ ልጁ እንዲለቀቅለት በጉልበት ስራዎች ላይ የተሰማሩ ልጆችን ፈልገው እንዲያመጡ ይገደዳሉ ብሏል።

"በተጨማሪም የእጅ መንሻ ቢያንስ 50  ሺህ ብር ቤተሰቦች አምጡ ይባላሉ፣ ችግሩ ከዚህም በላይ ነው፣ የአካባቢው ህዝብም ሆነ ለሾል የመጡ ዜጎች እንደ ጠላት እየተሳደዱ ይገኛሉ" ብሏል።

(መሠረት ሚድያ)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 18:07


አንድ ግለሰብ በደቡባዊ ቻይና በፈጸመው የመኪና ጥቃት ቢያንስ 35 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በደቡባዊ ቻይና በተፈጸመ የመኪና ጥቃት ቢያንስ 35 ሰዎች ተገደሉ። በአገሪቱ ባለፉት አሥርት ዓመታት በላይ በሕዝብ ላይ የተፈጸመ እጅግ አስከፊው ጥቃት እንደሆነ ይታመናል።

ክስተቱ በቻይና ብሔራዊ ቅሬታን የቀሰቀሰ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸው ወንጀል ፈጻሚው ግለሰብ "ከባድ ቅጣት" እንደሚጠብቀው ቃል ገብተው የተጎዱትን ለማከም "ሁሉን አቀፍ ጥረት" እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ ሰኞ ዕለት አንድ ግለሰብ ዙሃይ በሚገኘው ስታዲየም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎችን በመኪናው ገጭቷል።

“በአስከፊው እና በአሰቃቂው ጥቃት” አዛውንቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 45 ሰዎችም መቁሰላቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ፖሊስ እንዳለው ከሆነ የ62 ዓመቱ አሽከርካሪ ፋን እንደሚባልና ድርጊቱን የፈጸመው በፍቺው ውሳኔ ዙሪያ ደስተኛ ባለመሆኑ የተነሳ ይመስላል ።

ግለሰቡ ከዙሃይ ስፖርት ማዕከል ለመሸሽ ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን እና በራሱ ላይ ባደረሰው ጉዳት ኮማ ውስጥ እንደሚገኝ ፖሊስ በመግለጫው አክሏል።

ስለተገደሉት ሰዎች ዝርዝር መረጃ በባለሥልጣናት በኩል አልተገለጸም።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 18:07


ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0

Sheger Press️️

13 Nov, 17:34


ኢራን‼️

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን በአደባባይ በስቅላት ገደለች!


ሞሀመድ አሊ የተባለው ይህ ኢራናዊ የ43 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን በርካታ ሴቶች እንደሚያገባቸው ቃል በመግባት አስገድዶ ደፍሯቸዋል ተብሏል፡፡

ግለሰቡ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት በተከሰሰበት የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ትፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

መሀመድ አሊ ከ10 በላይ ሴቶችን አስገድዶ ደፍሯል የተባለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ከእሱ የጸነሱትን ልጅ እንዲያስወርዱ መድሃኒት ሰጥቷልም ተብሏል፡፡

ሰውየው ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ 200 ሴቶች ደፍሮናል የሚል ክስም ተመስርቶበታል።

በግለሰቡ ተደፍረናል ያሉ ሴቶች ቁጥር መጨመርን ተከትሎ በርካታ ኢራናዊያን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍም ተደርጎበት ነበር፡፡

ሀገሪቱም ግለሰቡን በአደባባይ በስቅላት እንዲቀጣ አድርጋለች።

Via_አልአረቢያ


@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 17:30


#ሁለት አናብስት መቃብሩን ቆፈሩለትና ገንዞ ቀበረው

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓተ ብሕትውናን የጀመረው አባ ጳውሊ ሲሆን አባ እንጦንስ ደግሞ ስርዓተ ምንኩስናን ጀምሯል፡፡

በምድራዊ ሃብት ባለጸጋ የነበረው የጳውሊ አባት ሲያርፍ ታላቅ ወንድሙ ጴጥሮስ የራሱንና ትንሽ ልጅ የነበረው የወንድሙ የጳውሊን ድርሻ ሰጠውና ወንድሙ አካላመጠን ሲደርስ እንዲያስረክበው አደራ አለው፡፡

ጳውሊ አካለ መጠን ደርሶ ድርሻዬን ስጠኝ ሲለው ገና ልጅ ነህ ታጠፋዋለህ ብሎ ከለከለው፡፡ እርሱ ግን በሀሳቡ አልተስማማም፡፡ ስለዚህም ጴጥሮስ ብዙውን አስቀርቶ ጥቂቱን፣ የማረባውን አስቀርቶ መናኛውን ሰጠው፡፡

ጳውሊ በሁኔታው ተበሳጭቶ ወደ ዳኛ ሲሔድ አንድ ሃብታም ሞቶ ሊቀብሩት ይዘውት ሲሔዱ አየ፡፡ ይህን ጊዜ አባቴ ባለጸጋ ነበር ሞተ፣ ይህ ሰውም ሃባታም ነበር ሞቶ እኔም ሃብት ቢኖረኝም እሞታለሁ አለና፣ ወደ ቤት ሔዶ ወንድሙ ጴጥሮስን ሀብቱን ሁሉ አንተ ውሰደው ይቅርብኝ ብሎ ትቶት ወደ አንድ መቃብር ቤት ገብቶ መጸለይ ጀመረ፡፡

ከሦስት ቀናት በኋላም ግማሽ ህብስት ከሰማይ ወረደለት፡፡ ይህን ሲያይም እዚህ ሆኜ ይህን ያሕል በረከት ካገኘሁ ከዓለም ብለይ ድንቅ ተአምር ይደረግልኛል በማለት በረሃ ገብቶ ብሕትውናን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡

የበረከት ስራ እንደንሰራበት የተሰጠን ሃብታችን ለስጋዊ መሻታችን ብቻ እያዋልን የምንኮራ ስንቶቻችን ነን? ገዳማውያኑና ባሕታውያኑ ንቀውትና ጥለውት የሚሔዱት ሃብት በዓለም ስንኖር ሰማያዊ ቤታችንን ካልሰራንበት፣ እንደ ጳውሊ ወንድም እንደ ጴጥሮስ ከወንድማችን ጋር ካጣላን መጥፊያችን ሆኖብናል፡፡ አባ ጳውሊ ለ80 ዓመታት ከሰሌን ልብስ እየለበሰ የየትኛውንም ሰብአዊ ፍጡር ፊት ሳያይ በጸሎት ሲቆይ የለመደውን ግማሽ ህብስት ቁራ ያመጣለት ነበር፡፡ በፍጻሜ ዘመኑም ምንኩስናን ከጀመረው ከአባ እንጦንስ ጋር በእግዚአብሔር ፈቃድ ተገናኝተው በርካታ መንፈሳዊ ነገር ተጨዋውተዋል፡፡
በኋላም አባ ጳውሊ እንደ አባ እንጦንስ የምንኩስና ቆብ መድፋት በመፈለጉ ሊያመጣለት ወደ ገዳሙ ሔዶ ሲመለስ አርፎ አጊኝቶታል፡፡

ቆቡን አድርጎለትም ሁለት አናብስት መቃብሩን ቆፍረውለት ገንዞ ቀብሮታል፡፡ የአባ ጳውሊን ነፍስም ቅዱሳን መላእክት በዝማሬና በምስጋና ወደ ሰማይ አሳርገዋታል፡፡ እነዚህ ድንቅ አባቶቻችን ዓለምና ስጋዊ ሃብትን ጥለው ክርስቶስን ብለው ገዳም ገብተዋል፡፡ ስጋዊውን ሃብት ሲተዉት በጸሎታቸው ኃይል የማድረግ መንፈሳዊ ሃብት ታድለዋል፡፡
በረከታቸው እንዲያድርብን የዘመናችንን ጳውሊና እንጦኒ ገዳማውያን አባቶችንና እንርዳ በአታቸውንም እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

13 Nov, 16:30


ይህንን ያውቃሉ‼️

ዛሬ ማለትም November (13) ዓለም አቀፍ የደግነት ቀን ነው!!

ደጋግ ሰዎችን ያብዛልን 🙏

በምላሹ ምንም ሳይጠብቁ በቀናነት ሰውን ለሚረዱ መልካም ሰዎች ፈጣሪ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጣቸው🙏

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 15:45


ይህንን ያውቃሉ‼️

የአፍሪካ ሀገራት ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት እንደተፈፀመባቸው?

የሚገርመው ግን ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚው ነች።

ሸገር ይሄንን መረጃ የተመለከተው በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን በመተንተን ደረጃ የሚያወጣው ቼክ ፖይንት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ነው።( #ሸገር_ፕረስ )

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 14:50


መረጃ‼️

በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከአንድ ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች ከሥራ ገበታ መፈናቀላቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ለአራዳ ኤፍ ኤም አስታውቋል።(ሸገር ፕረስ)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 14:19


"ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን እናባርራለን"
አሜሪካ

የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ የሚገኙ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስደተኞችን እንደሚያባርሩ የገቡትን ቃል የሚያስፈጽሙላቸውን ቶም ሆማን የተባሉ ባለስልጣን ሾመዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 13:08


ሰመኑን መርካቶ የተፈጠረው...

ባሳለፍነው ሰኞ ህዳር 2 ቀን 2017ዓ.ም በመርካቶ ገበያ ያሉ ነጋዴዎች ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው የመጣነው ያሉ ሰዎች ያለ ደረሰኝ ለምን ሸጣችሁ በሚል እቃችንን ወርሰውብናል ማለታቸው ይታወሳል፡፡

በዚህና ተያያዥ ምክንያቶች በእለቱ በመርካቶ ያሉ በርከት ያሉ ሱቆች ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡ጉዳዩን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በሰጠው መግለጫ የተባለው ችግር በመርካቶ እንደተፈጠረ አምኖ ነገር ግን የነጋዴዎችን እቃ ወርሰዋል የተባሉት ግለሰቦች ከገቢዎች ቢሮም ይሁን ከየትኛውም የመንግስት አካል ያልተወከሉ ህገ ወጦች ናቸው ብሏል፡፡

በቢሮው የታክስ ኢንቴሌጀንስና ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ነጋሽ እኛ ምንም አይነት ንብረት የመውረስ መብት የለንም መወረስ ካለበትም ይህንን የሚሰራው የጉምሩክ ኮሚሽን ነው ብለዋል፡፡ግለሰቦቹ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ባዘጋጁት ተሽከርካሪ እቃዎችን ጭነው ሄደዋል፤ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ደግሞ ገንዘብ ተቀብለው ተሰውረዋል ያሉት ኃላፊው ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ነጋዴዎቹ ለፀጥታ አካላት መረጃዎችን በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች መንግስት ከመርካቶ ገበያ የነጋዴዎችን እቃ መውረስ ጀመረ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ያሉት ኃላፊው ውዥምብሩ የተፈጠረው በዚህ ምክንያት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ኃላፊው የተፈጠረውን ሲያስረዱም የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ከዚህ ቀደም ይሰራ እንደነበረው ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይፈፀም ለማድረግ ያለመ የቁጥጥር ስራ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ይህ ስራ ሲሰራ የነበረው በአለፍ ገደም ነበር፤ አሁን ምንም ዓይነት ግብይት ያለ ደረሰኝ እንዳይከወን ለማድረግ ከህዳር 1 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ መልክ የጀመርነውን ስራ ከመርካቶ በመጀመራችን ይህንን ነው ያደረግነው ብለዋል፤ አቶ ተስፋዬ፡፡ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመርካቶን የንግድ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠሩ ባለሙያዎች ያለ እጅ መንሻ የማሰሩ መሆኑን አረጋግጫለሁ ያለው ቢሮው ሁሉንም የመርካቶ ተቆጣጣሪዎችን በማንሳት በአዲስ መተካቱንም ተናግሯል፡፡

ቢሮው እየሰራሁ ባለው የቁጥጥር ስራ ያለ ደረሰኝ ሲገበያይ የተገኘን ማንኛውም ሰው 100 ሺህ ብር እንደሚቀጣ እወቁልኝ ብሏል፡፡መርካቶን ጨምሮ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ያሉ አምራቾች፣ አስመጪዎችና ቸርቻሪዎች የትኛውንም ግብይት በደረሰኝ እንዲፈፅሙ ይገደዳሉ ተብሏል፡፡በመርካቶ አካባቢ ያለው በነጋዴዎች ዘንድ የተፈጠረው ውዥምር ረግቦ ነጋዴዎች ወደስራቸው እየተመለሱ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ በያዝነው 2017 ዓ.ም 230 ቢሊዮን ብር ከገቢ ግብር ለመሰብሰብ ውጥን ይዞ በ3 ወር ውስጥ 47 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡንና ከዚህ ቀደም ገቢ በቁጥጥር ማነስም ይሁን በሌላ ገቢ የማሰበሰብባቸው የነበሩ ዘርፎችን ወደ ግብር ሥርዓቱ እያስገባሁ ነው ማለቱ ይታወሳል፡፡(ሸገር)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 11:00


ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ ለመውጣት እስከ 4ሺህ ዶላር የሚደርስ የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ገለጹ

በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ ሲፈልጉ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት እስከ 4ሺህ ዶላር የሚደርስ የተጋነነ ክፍያ እየተጠየቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የክፍያው ምክንያት ግልፅ እንዳልኾነና ወጥነትም እንደሌለው የተናገሩት ኤርትራውያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የክፍያውን መጠን ዳግም እንዲመለከተው መጠየቃቸውን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል።

የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ፣ እየተጠየቀ ያለው ክፍያ፣ ለመውጫ ቪዛ ሳይሆን፣ በሕገወጥ መንገድ ለቆዩበት ጊዜ የሚወሰን ቅጣት ነው ማለቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡ ክፍያው በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃገራት ዜጎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን የተቋሙ የውጭ ዜጎች ምዝገባና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ አዳነ ደበበ ገልጸዋል።

አክለውም ክፍያው የውጭ አገር ዜጎቹ በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ በጨመረ ቁጥር ክፍያውም እንደሚጨምር ጠቅሰው፤ በህገወጥ መንገድ፣ በሀገሪቱ ውስጥ እየኖሩ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ በተቋሙ ተመዝግበው ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ እንዲይዙም አሳስበዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

13 Nov, 05:55


ታይም መጽሔት በልዩ እትሙ "የአእላፋት ዝማሬ"ን ምስል አወጣ

በአሜሪካን ሀገር ኒውዮርክ የሚታተመውና ከ1923 ዓ.ም. ጀምሮ ኅትመቱ ያልቆመው 105 ሚልዮን አንባቢያን ባሉት ቁጥር አንዱ "Time” መጽሔት የኢትዮጵያን የገና በዓል በማስመልከት በጻፈበት አንቀጽ የአእላፋት ዝማሬን ከፊል ገጽታ በውስጥ ገጹ ላይ አካትቶአል::

"Jesus” በሚል ዐቢይ ርእስ የታተመው የ2024 ዓ.ም. የመጽሔቱ ልዩ ዕትም ላይ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በታኅሣሥ 27 (January 6, 2024) በገና ቅዳሴ ላይ ሲካፈሉ በማለት የአእላፋት ዝማሬ ላይ ጧፍ ይዘው እየዘመሩ የነበሩ ምእመናንን ይዞ ወጥቶአል::

"መጽሔቱ የአእላፋት ዝማሬን ገጽታ ይዞ መውጣቱ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የቀረበ የሚታይ ማስታወቂያ መሆኑ ደስ ይለናል" ያሉት የአእላፋት ዝማሬ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ወ/ሮ ቤርሳቤሕ ደረጄ "ሆኖም መጽሔቱ ዝማሬውን "ቅዳሴ ሲያስቀድሱ" ብሎ መግለጹ በቅዳሴ ላይ ምእመናን መብራት ይዘው የሚሳተፉበት ሥርዓት የሌለ ከመሆኑ አንጻር ዘግባውን ያጎድለዋል ብለዋል::

በዘገባው ላይ ታይም መጽሔት "የኢትዮጵያ ስልሳ በመቶ የሚሆን ሕዝብ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነው" ሲል የገለጸ ሲሆን "ከራሽያ ቀጥሎ የዓለም ትልቁ ኦርቶዶክስ ሕዝብ ቁጥር ያለባት ሀገር ናት" ብሎአል:: በ2024 ጃንዋሪ 6 የተካሔደውን የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ እንደተካሔደ አድርጎ ቢገልጸውም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም የተካሔደ መሆኑ ይታወሳል:: የዘንድሮው የአእላፋት ዝማሬ በመሐረነ አብ ዑደት እና በመዝሙር ጥናት ከጾመ ነቢያት ጋር አብሮ እንደሚጀመር የኢጃት ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ዳግማዊት ገልጸዋል::

Via ጃንደረባዉ ሚዲያ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

12 Nov, 06:33


ከከተማ ፕላን ጋር የማይጣጣሙ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ መብት ሊነጠቁ ይገባል ተባለ

በኢትዮጵያ ከተሞች የግንባታ ፍቃድ የሌላቸውና የመጠቀሚያ መብት ያላገኙ ሕንፃዎች እንዲፈርሱ የሚያዝ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት መቅረቡ ተሰምቷል።

በረቂቁ ላይ በተለይም በመሬት ላይ እንዲውሉ ከፀደቀው የሕንፃ ካርታ ውጭ ተላልፈው የተገነቡ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ መብት እንዲነጠቁ ተጠይቋል።

ቀደም ሲል በሥራ ላይ የቆየውን የሕንፃ አዋጅ "በርካታ ጉደለቶች አሉበት" በሚል መሻርያ ረቂቅ አዋጅ በትናንትናው ዕለት ለከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱም በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ ሕግ ተላልፈው የተገነቡ ሕንፃዎች መኖራቸውን የተገለጸ ሲሆን፤ አገልግሎት አሰጣጣቸውን ጨምሮ የከተማና መሰረተ ልማት ፕላን ያልተከተሉ በመኖራቸው እንዲፈርሱ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ መሰናዳቱ ተነግሯል።

ለዚህም በሚመለከተው የመንግሥት አካል በከተማ የሚገኙ ሕንፃዎችን የመጠቀሚያ መብት እንዲነጥቁ የሚያስገድድና ቀደም ሲል የነበረው የመሻርያ አዋጅ ቀርቦ ውይይት መደረጉን ተገልጿል።

በረቂቅ አዋጁ ዙርያ በርከት ያሉ ሐሳቦች የተነሱበት ሲሆን፤ መሐንዲሶች የሚወጧቸው ፕላኖች ተጠያቂ የሚሆኑበት የሕግ ወሰን በተመለከተም አስተያየት ሲሰጥበት አሐዱ ሰምቷል።

ከተሞች ለመኖርያና ለንግድ የሚውሉ ሕንፃዎች ዙርያ ለይቶ ማስቀመጥና ማስጠቀም እንዳለባቸውም የምክር ቤት አባላቱ አሳስበዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል በተለይም ከከተማ ፕላን ጋር የማይጣጣሙ ሕንፃዎች የመጠቀሚያ መብት ሊነጠቁ ይገባል የሚለውን በርካት ያሉ ትችቶች እንደተነሱበት አሐዱ ከቋሚ ኮሚቴው ሰብሰባ መረዳት ችሏል። አሃዱ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

12 Nov, 05:59


መረጃ ‼️

በኦሮሚያ እና በሱማሊ ክልል መካከል የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸዉ የሞያሌ እና የድሬደዋ ከተሞች ላይ ህዝበ ዉሳኔ እንዲሰጥ የሱማሊ ክልል ፕሬዝዳን ሙስጠፌ መሃመድ ለፌዴሬሺን ም/ቤት ደብዳቤ መላካቸዉ ተሰማ ፡፡(አንኳር)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 19:14


መረጃ‼️

ዛሬ በሶሻል ሚድያ በስፋት ሲሰራጭ የነበረው የአል ዐይን ዘገባ ሀሰት መሆኑ ሸገር ፕረስ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል Official ገፅ ተመልክቷል።

ዘገባውም ይል የነበረውʺሰዎች ኩላሊታችንን ግዙን እያሉ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ይመጣሉ የሚል ነበር።

ʺ ሰዎች ኩላሊት ግዙን ብለው ወደ ማእከሉ ይመጣሉ ʺ የሚለው አባባል ፍጹም ከእውነት የራቀ ነው ሲል ሆስፒታሉ አስታውቋል፡፡

ሆስፒታሉ በሀገር ደረጃ በብቸኝነት የሚያገለግለው የኮሌጁ ንቅለ ተከላ ማእከል አሁን ባለው አቅም ብዙ ወገኖችን እያገለገለ እና ወደፊትም አገልግሎቱን ለብዙዎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም ጨምሮ ገልጿል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ።( #ሸገር_ፕረስ )

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 18:58


የእስራኤል ጦር አንድም የሊባኖስን መንደር አልተቆጣጠረም - ሂዝቦላህ

የእስራኤል ጦር አንድም የሊባኖስን መንደር መቆጣጠር እንዳልቻለ ሂዝቦላህ ተናገረ፡፡

ከሐማስ ጎን ተሰልፎ እስራኤልን እየተዋጋ የሚገኘው የሊባኖሱ ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ የአየር ጥቃቶችን ሲደርስ የቆየ ሲሆን ከ45 ቀናት በፊት እስራኤል ጦሯን ወደ ሊባኖስ አስገብታለች፡፡

ባለፉት ቀናት እስራኤል የሂዝቦላህ ዋና ሃላፊን ጨምሮ በርካታ ወታደራዊ አመራረሮችን በቤሩት እና ሌሎች ከተሞች ገድላለች፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 18:20


በኢትዮጵያ ሁለት ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች ከስኳር ህመም ጋር አብረዉ ይኖራሉ ተባለ

በአለም አቀፍ ደረጃ የስኳር በሽታ ወረርሽኝ ሊባል በሚችል መልኩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 18:16


የ 10 አመት ታዳጊን በማገት 3 መቶ ሺህ ብር የጠየቀዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ ሰንቀሌ ፋሪስ የተባለ አከባቢ የ 10 አመት ታዳጊን አግቶ በመዉሰድ ከወላጆቹ 3 መቶ ሺህ ብር የጠየቀዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የአምቦ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገለፀ።

እንደ አምቦ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገለፃ ዘላለም ስማቸዉ የተባለዉ ግለሰብ ህፃኑን አግቶ በመዉሰድ ወላጆቹ ጋር በመደወል በላከላቸዉ አካውንት 3 መቶ ሺህ ብር ካላስገቡ ልጃችዉን በህይወት እንደማያገኙት ሲያስፈራራቸዉ እንደነበረ መግለጫው ጠቅሳል።

ግለሰቡ ወላጆቹ ጋር በተደጋጋሚ በመደወል ህፃኑን በመደብደብ እያስለቅሰ ሲያሰማቸዉ እንደነበረ እና የተጠየቁትን ብር በአስቸካይ በተለከላቸዉ አካዉንት ካላስገቡ የልጃቸዉ በህይወት የመኖር ዕጣ በእጅ ላይ እንደሆነ እና ቤታቸዉንም በእሳት እንደሚያጋየዉ በማስፈራራት ወላጆችን ሲያስጨንቅ እንደነበርም ተገልጿል ።

ወላጆችም ከተጠየቁት የገንዘብ መጠን ዉስጥ 60 ሺህ ብር በተላከላቸዉ አካዉንት አስገብተዉ ልጃቸዉን በማስለቀቅ ድርጊቱን ለፖሊስ አሳዉቀዋል። ፖሊስ ባደረገዉ ክትትል ተከሳሹን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዉሎታል።ተካሳሹም በሰጠዉ ቃል ሙሉ ለሙሉ ጥፋተኛ መሆኑን በማመኑ የምርመራ መዝገቡ በሰዉ ማስረጃ እና በተላከዉ የባንክ አካዉንት ማስረጃነት በማጠናቀር ለአቃቤ ህግ መላኩ ተገልጿል።

አቃቤ ህግም የወንጀል መዝገቡን መርምሮ በህገወጥ መንገድ ሰዉን በማገት እና ያልተገባ ገንዘብ በመጠየቅ ህግ 586 እና 590 ንዑስ አንቀፅ 1ን በመጥቀስ ክስ የመሰረተበት መሆኑ ተገልጿል ።

ክሱን ሲመለከት የነበረዉ የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ዘላለም ስማቸዉ በፈፀመዉ የሰዉ ማገት ወንጀል ጥፉተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ11 አመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ከአምቦ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል። (ብስራት ራድዮ)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 18:04


እስራኤል አንድም የሊባኖስን መንደር ለመያዝ አልቻለችም ሲል ሂዝቦላ አስታወቀ

የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ውስጥ ድንበር ዘለል ዘመቻ ከጀመረ ወዲህ በሊባኖስ አንዲት መንደር እንኳን መያዝ አለመቻሉን ሂዝቦላ አስታዉቋል ሲል አልጀዚራ አረብኛ ዘግቧል።የሂዝቦላ ቃል አቀባይ መሀመድ አፊፍ "ከ45 ቀናት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ ጠላት አሁንም አንድ የሊባኖስ መንደር መያዝ አልቻለም" ብለዋል።

ጦርነትን በአየር ድብደባ እንደማታሸንፍ ለጠላቶች እንነግራቸዋለን።አፊፍ አክለዉም የሂዝቦላ የሚሳኤል ክምችት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መምጣቱን በተመለከተ እስራኤል ያቀረበችው አስተያየት “ውሸት ብቻ ነው” ብለዋል።በግንባሩ ላይ ያሉት ሀይላችን ለረጅም ጦርነት የሚሆን በቂ መሳሪያ አላቸው ሲሉ ተናግረዋል።

አቀባዩ በተጨማሪም የቡድኑ ግንኙነት ከሊባኖስ ብሄራዊ ጦር ጋር ያለው ግንኙነት "ጠንካራ እንደሚሆን" እና በአለም ዙሪያ በእስራኤል ላይ የሚደረጉ የተቃዉሞ ሰልፎች "እስራኤል የተገለለች" መሆኗን ያሳያል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ኢራን ትራምፕ በጋዛ የቀጠለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ማቆም አለባቸው ስትል አስታዉቃለች፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስሜል ባጋሃይ በቴህራን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት መጪው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በጋዛ ሰርጥ የቀጠለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ማቆም አለባቸው ብለዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 18:03


ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስ መረጃዎችን የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0

Sheger Press️️

11 Nov, 17:49


ትግራይ‼️

የትግራይ ክልል ሴቶች ቢሮ፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን በመጥቀስ፣ የፍትሕ አካላት በጥቃት ፈጻሚዎች ላይ ባስቸኳይ ክስ እንዲመሠርቱ ጠይቋል።

ቢሮው ጥቅምት 27 ቀን ለክልሉ ከፍተኛ ፍርድቤት፣ ለክልሉ ፍትሕ ቢሮና ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙትን ግድያዎች፣ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቶች፣ አፈናዎችና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ መልካቸውን እየቀያየሩ በተራቀቀና በተናበበ መንገድ ቀጥለዋል ብሏል።

ተጎጂዎች ፍትህ የማግኘት ተስፋቸው በኅብረተሰቡ ዘንድ እየጨለመ እንደመጣ የጠቀሰው ቢሮው፣ ወንጀሉን የማስቆምና ተጠያቂነትን የማስፈን ድርሻ የፍትህ አካላት መኾኑን አስምሮበታል።( #ሸገር_ፕረስ )

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 17:34


እናት ፓርቲ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ለ40 ዓመታት ቤተመንግስት ውስጥ ተቆልፎበት ያገኘነውን 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ አስረክበናል በማለት በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተናገሩት ንግግር ዙሪያ መንግሥት ለሕዝብ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ፓርቲው፣ ወርቁ የአገር ቅርስ የኾኑ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል እምነት እንዳለው ገልጧል። ወርቁ የድሮ ነገሥታት ያከማቿቸው ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ከኾኑ፣ በአገር ቅርስነት ተጠብቀው መቀመጥ እንዳለባቸው ፓርቲው አሳስቧል።

ከወርቅ በላይ የኾነ የአገር ቅርስ እንደኾነ የሚታመነው ወርቅ ከተሸጠ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን የጋራ ተጠያቂነት ይጠብቃቸዋል በማለት ያስጠነቀቀው ፓርቲው፣ ተቋማቱ ከዚህ ድርጊት እንዲታቀቡ ጥሪ አድርጓል። ( #ሸገር_ፕረስ )

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 17:19


በትራምፕ ድል ምክንያት አንድ አሜሪካዊ ሚስቱን፣ የቀድሞ ሚስቱን፣ ሁለት ወንድ ልጆቹን ገድሎ ራሱን አጠፋ

የ46 አመቱ አንቶኒትራምፕን እና ሪፐብሊካንን ይጠላ ነበር።

ትራምፕ ማሸነፋቸው በታወቀበት ቀን ስኪዞ ወሬውን ማለፍ ባለመቻሉ ሚስቱን፣ የቀድሞ ሚስቱን እና ሁለት ወንድ ልጆቹን ገድሎ እራሱን ማጥፋቱ የሀገሪቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 16:50


መረጃ‼️

በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታ የሚሰሩ  የ ታክሲ ተራ አስከባሪዎች  በፖሊስ ቁጥጥር ሾር መዋላቸው ተሰማ !!

እስሩ የተፈፀመው በአዲስአበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ተደራጅተው የታክሲ ተራ በሚያስጠብቁ ወጣቶች áˆ‹á‹­ ነው።

ተራ አስከባሪዎቹን ለእስር የዳረጋቸው እንደምክንያት ተብሎ የተነሳው ከታሪፍ በላይ ማስከፈል ሂደት ላይ ዋነኛ ተዋናይ ናቸው በሚል እንደሆነ ታዉቋል ፡፡

በመገናኛ ፣ገርጂና ቦሌ ብራስ የሚስሩ  የታክሲ ተራ አስከባሪዎች እንደታስሩ ነው የታወቀው ፡፡

ከቦሌ ብራስ ፣ሰሚት ኮንዶሚነየም ታሪፍ 25 ብር ሲሆን  በእነዚህ ተራ አስከባሪዎች ምክንያት  50 ብር እየተቀበሉ  እየጫኑ ተሳፋሪን እየበዘበዙ እንደነበር አንድ ተሳፋሪ ለ አንኳር መረጃ ተናግረዋል ፡፡

መንግሰት በወስደው እርምጃ ደስተኞች ነን ተከታትሎ ለፍርድ ማቅረብ ያስፈለጋል  ሲሉ ተሳፋሪዎች ገልፀዋል ፡፡(አንኳር መረጃ)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 15:20


ለሠራተኞቻቸው በነጻ ምግብ የሚያቀርቡት ኩባንያዎች

የተለያዩ ድርጅቶች የሠራተኞቻቸውን አቅም አሟጠው ለመጠቀምና ውጤታማ እንዲሆኑ በማሰብ የተለያዩ አገልግሎቶችን በነፃ ይሰጣሉ፡፡

ከእነዚህ ድርጅቶች መካከል በዓለማችን የሚገኙ ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ኩባንያዎቹ ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች መካከል የነፃ ምገባ፣ ማረፊያ፣ መዝናኛና ሌሎች አገልግሎቶች ይገኙበታል፡፡

ከእነዚህ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መካከልም ፌስቡክ፣ ጉግል፣ አፕል፣ ኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) እና ማይክሮሶፍት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ፌስቡክ

የፌስቡክ ካፊቴሪያዎች ለሠራተኞቻቸው እና ለእንግዶቻቸው የአሜሪካና የእስያ የምግብ ዓይነቶችን በነፃ ያቀርባሉ፡፡

ጉግል

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል 18 ካፊቴሪያዎች ሲኖሩት፥ ለሠራተኞቹ የተለያዩ የምግብና መጠጦች አማረጮችን መሰረት በማድረግ በነፃ በማቅረብ ይታወቃል፡፡

አፕል

የአፕል ካፊቴሪያዎች ለሠራተኞች እና ለእንግዶች ሙሉ በሙሉ ነፃ የምግብ አገልግሎት ያቀርባሉ፡፡ በዚህም የስፓኒሽ፣ የሜክሲኮ፣ የጣሊያን፣ የጃፓን እና ፈረንሣይ ምግቦችን እንደየ ሰዎቹ ፍላጎት ያዘጋጃሉ፡፡

ኤክስ (የቀድሞው ትዊተር)

የኤክስ ካፊቴሪያ ለኩባንያው ሠራተኞች የተለያዩ ምግቦችንና መጠጦችን በነፃ ይሰጣል፡፡

ማይክሮሶፍት

የማይክሮሶፍት ካፊቴሪያ ለሠራተኞቹ ምግቦችን በዝቅተኛ ዋጋ እንደሚያቀርብ ክሎክ ኢት ዘግቧል፡፡

ኩባንያዎቹ እነዚህን አማራጮች በመጠቀም ሠራተኞቻቸውን እየደጎሙ ሥራቸውን በይበልጥ ለማሳለጥ እየተገበሩት ያለው የነጻ አገልግሎት ውጤታማ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡

#Fana #Sheger_press

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 14:57


በመርካቶ “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል ነው
-አስተዳደሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በመርካቶ አካባቢ አንዳንድ ነጋዴዎች “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” የሚል መሰረት የሌለው ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል ሲል አስታወቀ።ውዥንብሩ የመጣው “በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በሚደረገው ሥራ” ነው ሲል የገለጸው አስተዳደሩ ይህ እንዲስተጓጎል ሆን ተብሎ የተነዛ አሉባልታ ነው ሲል ጠቁሟል።

“በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎችን በመለየት በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን” ያወሳው አስተዳደሩ “ይሁን እንጂ ይህንን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል የተሰራ ውዥንብር ነው” ብሏል።በውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ንብረት የሚያሸሹና ሱቅ የሚዘጉ ነጋዴዎች ተገቢነት ከሌለው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ያሳሰበው አስተዳደሩ “እንዲሁም አምራች፣ አከፋፋይና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት ህገወጥ ተግባር መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ወደ ህጋዊ መስመር ሊገቡ ይገባል” ብሏል።

በመርካቶ እየተከናወነ የሚገኘው ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል የንግዱ ማኅበረሰብ ተባባሪ እንዲሆንም አስተዳደሩ ጠይቋል።ከዚህ በፊት ያለደረሰኝ የተገዙ ዕቃዎች ካሉ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የማስመዝገብ ሥራ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው የአስተዳደሩ የከንቲባ ጽ/ቤት በፌስ ቡክ ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

11 Nov, 13:56


❗️ሩሲያ ፑቲን እና ትራምፕ በስልክ አልተነጋገሩም አለች

ሩሲያ ፑቲን ከትራምፕ ጋር አድርጓል የተባለው የስልክ ንግግር አልተደረገም ስትል አስታወቀች።

ባለፈው ቅዳሜ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በስልክ መነጋገራቸውን እና ፑቲን የዩክሬንን ጦርነትን እንዳያባብሱ መምከራቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቦ ነበር። ይሁን እንጂ የሩሲያው ክሬምሊን መሰል ንግግር አልተደረገም ብሏል።

በሌላ በኩል ሩሲያ ትላንት ምሽት በዩክሬን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ስድስት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ህፃናትን ጨምሮ 21 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በአንድ አፓርትመንት ላይ በደረሰ የሚሳኤል ጥቃት 2 ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 7 ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጸዋል።

ሩሲያ ከዕለት ወደ እለት የንጹሃን ዜጎች መኖርያን ኢላማ እያደረገች ነው ያሉት ዘለንስኪ ጦርነቱን መቀጠል ብቻ እንደምትፈልግም ገልጸዋል። 

ዩክሬን ከአጋሮቿ ተጨማሪ የመሳርያ ድጋፍ እንደምትፈልግና የሩሲያን ወረራ ለማስቆምም ጠንከር ያለ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንደምትሻ አስታውቀዋል።

ሩሲያ በበኩሏ 13 የዩክሬን ድሮኖች ማውደሟን ገልጻ ምንም አይነት ሞት ግን አለማሳወቋን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

#walta #Bbc #Sheger_press

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

09 Nov, 17:26


ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስና የጦርነቱን ድባብ የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0

Sheger Press️️

09 Nov, 17:25


የባንክ ኢንዱስትሪውን ዘግይተው ከተቀላቀሉ መካከል አንዱ የሆነዉ አሃዱ ባንክ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 120 ሚሊዮን ብር ገደማ ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል።

ባንኩ ስራ በጀመረበት የመጀመሪያ አመት ማለትም 2015 የስራ አፈፃፀሙ 267.7 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ያስመዘገበ ቢሆንም በተያዘው በጀት ዓመት ግን ወደ ትርፍ መሸጋገር መቻሉን ነዉ በሪፖርቱ ያስታወቀው።

በሁለት ዓመቱ የስራ ቆይታዉ ትርፍ ማስመዝገብ የቻለዉ አሃዱ ባንክ አጠቃላይ ሃብቱ 6.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና 1.4 ቢሊዮን ብር ደግሞ የተፈረመ ካፒታል መሆኑን ጠቅሷል።

እኤአ በ 2021 የተቋቋመው ባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ሂሳብ 4.66 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል። በተጠቀሰው የስራ ዘመን 80 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚሆን የዉጭ ምንዛሪ መሰብሰብ መቻሉን ነዉ ያስታወቀው።

Via Capital

Sheger Press️️

09 Nov, 14:32


ተራዘመ

ነዋሪ ያልገባባቸዉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዉላቸዉን ለማቋረጥ የወጣው ማስጠንቀቂያ ለ ተጨማሪ እንድ ወር መራዘሙ ተገለፀ

በእጣ የተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል ።

በዚህም በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ የማይገቡበት ከሆነ ውል የሚቋረጥ መሆኑን የገለፀ ቢሆንም ዛሬ በሰጠዉ ማስጠንቀቂያ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ማራዘሙን ነዉ ያስታወቀው።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

09 Nov, 10:14


የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ ባደረሰው የጎርፍ አደጋ በ3 ወረዳዎች ላይ ጉዳት አስከተለ

በሱማሌ ክልል ስር በሚገኙት ቀላፎ ሙስታሄርና ፌርፌር ወረዳች ላይ ነው የጎርፍ አደጋው ውድመት ያስከተለው፡፡

አደጋውን ተከትሎም ጉዳት በደረሰባቸው አካባዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በአነስተኛ ጀልባች እንዲወጡ መደረጉም ነው የተገለጸው ፡፡

ከዚህ ቀደም በክልሉ ሸበሌ ዞን በደረሰ ተመሳይ አደጋ ከ6 ሺህ186 ሄክታር በላይ የሰብል መሬት ላይ ጉዳት ሲደርስ ከሁለት ሺ 827 በላይ አባወራዎች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

09 Nov, 09:59


ልጁን ቤት ውስጥ በእምነት ኮትኩቶ የሚያሳድግ አንድ አባት ነበር፡፡

ከእለታት በአንዱ ቀን አባት ልጁን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ይወስደዋል፡፡

የእለቱ ትምህርታቸውን ተከታተልው ጸልየው ካበቁ በዋላ፣ ቤተክርስቲያኗ መተዳደሪያዋ ከህዝብ የሚገኝ ነዋይ ስለሆነ ገንዝብ መሰብሰቢያ ሰሀን ይዞር ጀመር፡፡
ሁሉም የአቅሙን አውጥቶ ሲሰጥ ጊዜ ይህ ልጅ ግራ ገባው፤ ኪሱ ቢገባም የሚሰጥ ነገር የለውም፡፡

ሰሀኑ ዘሮ ሊመለስ ሲል ይህ ህጻን እጁን አወጣና ሰሀኑን መሬት ላይ አስቀምጦ በእግሩ ቆመበት፤
ይህን ግዜ ሁሉም ግራ ተጋብተው ያዩት ጀመር፤
ከዛም እንዲህም አለ፤
ፈጣሪዬ ሆይ ምንም የምሰጥህ የለኝምና ይኸው ራሴን ሰጥቼሃለሁ አለ፡፡

እኛስ ፈጣሪ በሰጠን በረከት፣ጸጋ እሱን ለማስደሰት ምን እያደረግንበት ይሆን?
ህይወታችን በሃብት፣በረድኤት፣በበረከት ሲትረፈረፍና በጸጋ ሲባረክልን፣እኛም ይህን ላደረገልን ፈጣሪ የሚያስደስተውን መልካሙን ስራ ልንሰራ ይገባል፡፡

የደከሙትን ማበርታት፣ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው መደገፍና ምጽዋት መስጠትን መዘንጋት የለብንም፡፡

በተለያዩ ችግሮች እየተፈተኑ ለሚገኙት በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ለሚገኙ መነኮሳት የተቻለንን ድጋፍ በማድረግ በረከትን እናግኝ!


ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

09 Nov, 08:53


በኦሮምያ ክልል ነዋሪዎች ለተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም እና ለሚሊሻዎች በሚል አስገዳጅ መዋጮ እየተጠየቁ መሆኑን አስታወቁ

የኦሮምያ ክልል ነዋሪዎች የአከባቢው ባለስልጣናት በግዳጅ ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም እና የአከባቢውን ሚሊሻዎች ለማጠናከር በሚል መዋጮ በተደጋጋሚ አንደሚጠየቁ አስታወቁ።

በተለያዩ መክንያቶች ባለስለጣናቱ አስገዳጅ መዋጮዎችን ስለሚያስከፍሏቸው ለከፍተኛ የገንዘብ ችግር እየተዳረጉ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፣ ለኑሮ ጫና ዳርጎናል ብለዋል።

ባለስልጣናቱ መዋጮ እንዲከፍሉ የሚያስገድዱት መንግስት ሰራተኞችን እና የየአከባቢዎቹን አርሶአደሮች ጨምሮ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል መሆኑን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

በምዕራብ አርሲ ዞን የቆፋሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ እና ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አርሶ አደር እንዳስታወቁት ከአምና 2016 ጥር ወር ጀምሮ ነዋሪዎች ለተማሪዎች ምግብ፣ ለሚሊሻ ዩኒፎርም እና ለምግብ አቅርቦት የሚሆን ገንዘብ እንዲያዋጡ እንደሚጠየቁ አስታውሰዋል።

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ተስፋዬ ቶሎሳ (ስማቸው የተቀየረ) ከወርሃዊ ደመወዛቸው 6ሺ ብር ላይ ምክንያቱ ሳይገለጽላቸው እየተቀነሰባቸው መሆኑን ገልጸው እጅግ አሳስቦኛል ሲሉ አስታውቀዋል።
Via -adisstandard

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

08 Nov, 19:32


መቐለ ውስጥ ባለፉት 3 ወራት ብቻ 1,088 ወንጀሎች መፈፀማቸው á‹¨áˆ˜á‰áˆˆ ከተማ ፓሊስ አስታውቋል‼️

ከተፈፀሙት ወንጀሎች መካከል áŚ
16 የግድያ
47 የግድያ ሙከራ
16 የሴቶች አስገድዶ መድፈር ይገኙበታል።

በሩብ አመቱ የተመዘገበው የወንጀል ተግባር አሳሳቢና ህዝብ ያሳተፈ የመከላከል ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላካች ነው ብሏል።

ፖሊስ የወንጀል ተግባራቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ 3 ወራት ሲነፃፃር የቀነሰ ቢሆንም አሁንም ቢሆን ህዝቡ ከወንጀልና የወንጀል ስጋት ነፃ እንዳልሆነ አመላካች ነው ሲል አሳውቋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

08 Nov, 19:28


ጥቆማ‼️

በርግጠኝነት ኋላ እንዳይቅጫቹ።

በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ገንዘብ የሚቀየር ነው።

ይህ ኤርድሮፕ በመጀመር እናንተም ገንዘብ ስሩ።

በዚ Link ጀምሩ👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=KeMafgCX

አሰራሩ ካልገባቹ በዚ ቻናል ተመልከቱ👇
https://t.me/+fzeZ2gn56UE3NTI0

Sheger Press️️

08 Nov, 18:31


የገንዘብ ሚኒስቴር የፍራንኮ ቫሉታ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅደው የነበሩ ምርቶች ፍቃድ መሰረዙን አስታወቀ!

የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔውን ያሳለፈው መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተከትሎ የዋጋ ግሽበት እንዳይከሰት በሚል እንደነበር የገለጸ ሲሆን፤ አሁን ላይ ዋነኛውን ምእራፍ የታለፈ በመሆኑ ፍቃዱን አንስቻለሁ ብሏል።

ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅደው የነበሩ የምግብና የፋብሪካ ግብአት የሚውሉ የውጭ ምርቶች መሆናቸውን አሐዱ በሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ላይ ተመልክቷል።የፍራንኮ ቫሉታ ፍቃዱን ከጥቅምት 29/2017 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ የማይደረግ መሆኑን ለጉምሩክ ኮሚሽን አባሪ አድርጎ በላከው ደብዳቤ ላይ ተገልጿል።

መንግሥት የተሟላ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንና ወደ ከፍተኛ ምእራፍ እየተሸጋገረ በመሆኑን ገልጾ፤ ኢኮኖሚው መልካም ውጤቶች የታየበት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተመለከተ በኢትዮጵያ ያሉ ንግድ ባንኮች በቂ የሚባል የውጭ ምንዛሪ በበቂ ሁኔታ እየቀየረ ስለመሆነ ከእንግዲህ በኃላ ፍራንኮቫሉታ የሚባል ነገር እንደማይኖር የገንዘብ ሚኒስቴር በሚኒስቴሩ አሕመድ ሺዴ ተፈርሞ የወጣን ደብዳቤ ያሳወቀው።

Via Ahadu

@Sheger_press

Sheger Press️️

08 Nov, 18:12


ባለፈው ማክሰኞ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ አርጌ በተባለች አነስተኛ ከተማ በድሮን ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች እንደተገደሉና ከ60 በላይ ሰዎች እንደቆሰሉ ቢቢሲ ነዋሪዎችንና የዓይን እማኞች ጠቅሶ ዘግቧል።

ጥቃቱ ጧት ላይ በገበያ ቦታ አካባቢ፣ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትና በጤና ጣቢያ ላይ ሦስት ጊዜ እንደተፈጸመ መስማቱን ዘገባው አመልክቷል።

ከሟቾቹ መካከል በትምህርት ቤቱ ጊቢ ውስጥ ኳስ በመጫወት ላይ የነበሩ ከ13 በላይ ሕጻናት ጭምር እንደተገደሉ ዘገባው አመልክቷል።

በጤና ጣቢያው ላይ በተፈጸመው ጥቃት ደሞ፣ አምስት ነፍሰ ጡሮችና ኹለት አስታማሚዎች ተገድለው፣ ሦስት ሴት የጤና ባለሙያዎች ቆስለዋል ተብሏል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ስለ ጥቃቱ ጥቆማ ጥቆማ ደርሶት መረጃ እያሰባሰበ እንደኾነ የዜና ምንጩ ጠቅሷል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

08 Nov, 18:12


የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የትምህርት ተቋት በትብብር ለመስራት ተስማሙ

የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር እና የሩሲያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፤ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

እኩልነት፣ የጋራ ተጠቃሚነትና ውጤታማነት መርህ ላይ የተመሰረተ ነው የተባለው ይህ ስምምነት፤ ሁለቱ ሀገራት በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ወቅት፤ ሩሲያ የሰው ሃይል በማብቃት ዙርያ ድጋፏን አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል። ስምምነቱን ወደ ተግባር ለማስገባት፤ በሁለቱም ሀገራት በኩል የቴክኒክ ቡድን እንደሚቋቋም፤ የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አስታውቋል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

08 Nov, 18:10


ማስታወቂያ ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስና የጦርነቱን ድባብ የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0

Sheger Press️️

08 Nov, 17:25


የገዛ ወንድሙን አግቶ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

ተከሳሽ የኔው ብርሀኑ የእንጅባራ ከተማ አሰተዳደር ነዋሪ ሲሆን በጥቅምት 19/ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6.30 ሰዓት ከቢዳ ጀጎላ ት/ቤት የሚማረውን ወንድሙን ስልክ በመደወል የእናታችንን ልብስ ውሰድ ብሎ ከት/ቤት ከአሰወጣ በኋላ የ14 ዓመት ወንድሙን በማገት ከወላጅ ቤተሰቦቹ 1,000,000/አንድ ሚሊዮን ብር/ መጠየቁን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።

በሁኔታው የተደናገጡት የታጋች ቤተሰቦች ወዲያውኑ ለእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ በሰጡት ጥቆማ በተደረገ ብርቱ ክትትልና ቁጥጥር በሶስተኛው ቀን ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ሲሆን ከተደበቀበት ቢዳጀጎላ ቀበሌ ልዩ ስፍራ አማያስቲ ጎጥ ላይ እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል የላከ ሲሆን መዝገቡ የቀረበለት የአዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ የኔው ብርሃኑ በ7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዋና ክፍል የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

08 Nov, 17:18


ንግሱ ከቤተመንግስት ይወጣና በመንደር ውስጥ ጉብኝት እያረገ ሳለ
ድንገት አንድ ምስኪን ሽመግሌ ችግኝ እየተከሉ ያያል

ይህን ጊዜ ከሰረገላው ይወርድና ምን እየሰሩ እንደሆነ ይጠይቃል

ሽማግሌዉም ከአመታት በኋላ ምግብም ጥላም የሚሆን ችግኝ እየተከልኩ ነው አሉ

ንጉሱም ግን እኮ እንደማዮት ከሆነ እድሜዎት እየሄደ ነው ችግኙ አድጎ ምግብና ጥላ እስኪሆን ድረስ በህይወት ላይቆዩ ይችላሉ አላቸው

እሳቸውም አሉ አንዳንዴ የዘራነውን ሁሉ መብላት አይጠበቅብንም

ተመልከት እነዛን ዛፎች እኔ አልተከለኳቸውም ከኔ በፊት የነበሩ አባቶች እንጂ
ስለዚህ እኔም ለቀጣዩ ትውልድ ጥሩዘር መዝራት አለብኝ አሉ

በመልሳቸው የተደሰተው ንጉስም ከረጢት ሙሉ ወርቅ ሸለማቸው
ሽማግሌም ፈገግ ብለው የዛሬው ችግኝ ፍሬውን ቶሎ አፈራ አሉት

ወዳጆቼ ዛሬ እኛ የምንበላዉ መንፈሳዊ ፍሬ
ትናንት አባቶች ብዙ መስዕዋትነት ከፍለዉበታል
ዛሬም እየተከፈለበት ነዉ

የምንሸሸግባትን ጭንቀታችንን የምናራግፍባትን ቤተ ክርስቲያናችንን ለማቆየት
አሁን ተራዉ የእኛ ነዉ 

እኛ ምን ሳናዉቅ ስለኛ ቀን ከሌት እያነቡ የሚፆሙ የሚፀልዩ የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አባቶች በጦርነት በድርቅ በጎርፍ አደጋ ፈተናዉ ሲበዛባቸዉ ጊዜ ልጆቼ ከየት አላችሁ ብለዉ እየጠሩን ነዉ

እኛም በተራችን አለን ልንል ከበረከቱ ልንካፈል
በዚህ በተቀደሰች ሰዉ ከነብሱ በሚታረቅበት የፆም ወቅት የምንችለዉን ያህል እጃችንን እነዘርጋ
ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

08 Nov, 14:02


የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዋና አዛዥ የሆኑት ሌተናል ጄነራል ይልማ ከትዊተር (ኤክስ) መተግበርያ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደታገዱ ለማወቅ ችለናል።

እንዲህ አይነቱ ክስተት የሚፈጠረው የሀሰተኛ የጥላቻ ንግግሮችን በሚያሰራጩ ሰዎች ላይ ነው።
ጀነራሉ ወደፊትም በስማቸው የX አካውንት እንዳይከፍቱ ጭምር ነው እግዱ።(sheger press)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

08 Nov, 13:25


ወቸው ጉድ‼️

አክራሪ አሜሪካዊያን ሴቶች በወንዶች ላይ የወሲብ ማዕቀብ እንዲጣል ያለመ ዘመቻ ጀመሩ

ሴቶቹ የክልከላ ዘመቻውን የጀመሩት ወንዶች ለዶናልድ ትራምፕ ድምጻቸውን ሰጥተዋል በሚል ነው

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተጀመረው ይህ ዘመቻ ክልከላው ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ይቆያል ተብሏል ሲል አል አይን ዘግቧል

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

08 Nov, 12:20


በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ መከሰቱ ተገለጸ።

በክልሉ በሚገኙ 67 ወረዳዎች ወረርሽኙ የተከሰተ ቢሆንም በ34 ወረዳዎች ያለው የከፋ መሆኑን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

05 Nov, 19:18


በሀዲያ ዞን በጣለ ከባድ ዝናብ በሰብል እና በመኖሪያ ቤት ላይ ጉዳት ደረሰ

በሀዲያ ዞን ሸሾጎ ወረዳ በጣለ ወቅቱን ያልጠበቀ ከባድ ዝናብ በወረዳዉ የሚገኘዉ አብዛኛዉ ምርት ከጥቅም ዉጭ መሆኑ ተነግሮል ፡፡

አንኳር መረጃ ያነጋገረቻቸዉ የወረዳዉ አስተዳዳሪ እንዳሉት  ከ16 ሺህ በላይ አባዎራዎች ሙሉ በሙሉ ሰብላቸዉ ወድሞል ብለዋል ፡፡

ነዋሪዎቹም ጎርፉ በመሙላቱ እና መኖሪያ ቤታቸዉ ጉዳት ስለደረሰበት መፈናቀላቸዉ ተገልፆል ፡፡

ወገኖቻችን ሀብት ንብረታቸው ወድሟል
መንገድ ላይ ወድቀዋል

እባካችሁ ሼር አድርጉት ለሚመለከተው አካላት🙏

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

05 Nov, 18:16


መረጃ ‼️

በመርካቶ የተቃጠሉ የንግድ ቤት ባለቤቶች ሱቃችሁን አታድሱም ተብለናል አሉ!

በባለፈዉ ሳምንት በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቶ ብዙ የንግድ ቤቶች በአደጋዉ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ይታወሳል ፡፡


ጉዳቱ የደረሰባቸዉ የንግድ ቤት ባለቤቶች ቤቶቹን ለማደስ ወደ ስራ ብንገባም በመንግስት ፀጥታ ሀይሎች ማደስ አትችሉም ተብለናል ሲሉ ይናገራሉ

ባለቤቶቹ እንደሚሉት ይህ ተግባር በእሳቱ መነሻ መንስኤ መንግስትን እና ባለንብረትን በጥርጣሬ የሚያስተያይ ነዉ ይላሉ፡፡

የአዲስአበባ ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤትን አንኳር መረጃ ስለጉዳዩ ለማናገር ሞክራ ሀላፊዉ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸዉ ገልዋል ፡፡


የእሳት አደጋዉ መነሻ መንስኤ ይሁን የ
ደረሰዉ ጉዳት በሚመለከተዉ የመንግስት አካል እስካሁን አልተገለፀም ፡፡


Via- #አንኳር_መረጃ


@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

05 Nov, 18:15


ጥቆማ‼️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስና የጦርነቱን ድባብ የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://t.me/+gPveFwjiiXdiMDE0

Sheger Press️️

05 Nov, 16:49


መረጃ‼️

መከላከያ ሰራዊቱ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከፍተኛ  አመራርን ገድያለሁ አለ

የኢፊዴሪ መከላከያ ሰራዊት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሸኔ  አመራርን  የነበሩትን   ጃል እንሰርሙ ከነግብረ አበሮቹ  ደምስሻለሁ ሲል ጃል ኦብሳ የተባለው ደግሞ በቁጥጥር ሾር አዉያለሁ አለ ፡፡

ሰራዊቱ ይሄን ያለዉ የመከላከያ ሰራዊቱ 6ኛ ዕዝ ዋልታ ክፍለጦር በወረ ጃርሶ ወረዳ በአቡ ኬኮ ቀበሌ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ላይ ወሰድኩት ባለዉ ጥቃት ነዉ ፡፡

የማዕከላዊ ዕዝ ክፍለ ጦር በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አሸባሪው የሚሉትን  የኦነግ ጦር  በማሳደድ የመደምሰስ ሾል እየሰራ መሆኑን  የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔሌ ደጀኔ ፈይሳ ተናግረዋል ፡፡

ኮሎኔሉ ይሄን ይበሉ እንጂ ኦነግ ሸኔ በቅርቡ ብዛት ያላቸዉን የመንግስት የስራ አመራሮች የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም ንፁሃን ገበሬዎችን ከአዲስ ቅርብ እርቀት መግደሉ አይዘነጋም ፡፡

Sheger Press

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

05 Nov, 15:46


በሸገር ከተማ በዛሬው እለት በደረሰ የእሳት አደጋ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወታቸው አለፈ

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ-ከተማ በመስሪያና መሸጫ ሼድ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ  ማለፋን የእሳትና አደጋ ስጋት ሾል አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በእሳት አደጋዉ በሼድ ዉስጥ ካሉ  ሱቆች መካከል ስድስት የንግድ ሱቆች ተቃጥለዋል። á‹¨áŠĽáˆłá‰ľ áŠ á‹°áŒ‹á‹‰áŠ• ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት አምቡላንሶች ከሰላሳ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ንግድ ሱቆች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

05 Nov, 15:46


ቤቶን እና ቢሮዎን እናሳምርልዎ

ሳንፎርድ ፈሪኒቸር

👉🏼 ለልጆዎ ምቾት ጥራት ያላቸው አልጋዎች፣
👉🏼 ለቤትዎ ዘመናዊ እና ውብ ቲቭ ስታንዶችን፣
👉🏼 ለቢሮዎ ውበትን ከጥራት ጋር ያዋሃዱ ጠረጴዛ እና ወንበሮች፣
👉🏼 እንዲሁም ለኪችኖ ፤ በፈለጉት ድዛይን የሚያምሩ ኪችን ካቢኔቶችን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክብልዎ!!!

ወርክ ሾፕአችንን ጦር ሀይሎች ወደ ቤተል በሚወስደው መንገድ ድሪም ታወር አጠገብ ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ፡ 0978777775/0976777775 አሁኑኑ ይደውሉ!

Sheger Press️️

05 Nov, 15:41


ቤቶን እና ቢሮዎን እናሳምርልዎ

ሳንፎርድ ፈሪኒቸር

👉🏼 ለልጆዎ ምቾት ጥራት ያላቸው አልጋዎች፣
👉🏼 ለቤትዎ ዘመናዊ እና ውብ ቲቭ ስታንዶችን፣
👉🏼 ለቢሮዎ ውበትን ከጥራት ጋር ያዋሃዱ ጠረጴዛ እና ወንበሮች፣
👉🏼 እንዲሁም ለኪችኖ ፤ በፈለጉት ድዛይን የሚያምሩ ኪችን ካቢኔቶችን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክብልዎ!!!

ወርክ ሾፕአችንን ጦር ሀይሎች ወደ ቤተል በሚወስደው መንገድ ድሪም ታወር አጠገብ ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ፡ 0978777775/0976777775 አሁኑኑ ይደውሉ!

Sheger Press️️

05 Nov, 15:32


በአዲስ አበባ ለስኳር ህመምተኞች የሚያገለግለውን ኢንሱሊን ለተጠቃሚዎች ማቅረብ እንዳልቻሉ ፋርማሲስቶች ተናገሩ

የስኳር ህመም በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በማሳደግ እድሜ ልክ የሚዘልቅ የህመም ስያሜ ያለው ነው ። በዚህም መሠረት የስኳር ህመምተኞች በተገቢው ሰዓት ኢንሱሊን መውሰድ አለባቸው ፡፡ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የሆነ የኢንሱሊን እጥረት እንዳለ ተነግሯል ።

በተለይም አስተያየታቸውን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን የተናገሩ የመድሃኒት መደብር ባለቤቶች ኢንሱሊን መጥፋቱን ይናገራሉ ። አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል በመድኃኒት መደብሬ ውስጥ የሚገኘውን አነስተኛ ኢንሱሊን ለተጠቃሚዎች እንዲዳረስ በሚል ለአንድ ሰው አንድ áŠ˘áŠ•áˆąáˆŠáŠ• እየሸጥኩ እገኛለሁ ብለዋል ።

ፋርማሲስቱ አክለውም ምንም እንኳን ከተማ ወስጥ ኢንሱሊን እንደጠፋ ባውቅም ሃላፊነት ስላለብኝ ዋጋ ጨምረን ብዛት እንውሰድ ቢሉኝም ይህንን ከማድረግ ተቆጥቤያለሁ ብለዋል ። ከስኳር ህመምተኞች መካከል አነስተኛው ቁጥር የሚይዙት የአይነት አንድ ህመምተኞች ሲሆኑ áˆ°á‹áŠá‰łá‰¸á‹ ኢንሱሊን ማመንጨት እንደማይችል ተመላክቷል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ አይነት አንድ የሚባለው የስኳር ህመም በህፃናት እና ወጣቶች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል።

አይነት ሁለት በሚባለው የስኳር ህመም የተያዙ ሰዎች ደግሞ ሰውነታቸው በተገቢው መንገድ ኢንሱሊን አያመርትላቸውም ፡፡ ስለሆነም የስኳር ህመምተኞች በተገቢው ሰዓት ኢንሱሊን መውሰድ ቢኖርባቸውም የምርት እጥረት ማጋጠሙ አሳሳቢ ያደርገዋል ።የስኳር ህመምተኞች ለልብ ችግር የመጋለጥ አዝማሚያቸው ከፍተኛ በመሆኑ የደም ግፊታቸውንና የኮሌስትሮል መጠናቸውን በየጊዜው መከታተል እንዳለባቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ ።

የተለመዱ የስኳር ህመም ምልክቶች ቶሎ ቶሎ መሽናት፣ ብርቱ የውሃ ጥም እና ረሃብ፣ ክብደት መጨመር ወይም ያልተለመደ መቀነስ፣ ድካም፣ የማይድን ቁስል የእግር እና እጅ ጣቶች መደንዘዝ ናቸው ፡፡ በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ እንደሆነና 43 በመቶ የሞት ምጣኔን የሚይዙት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል ።

Sheger Press️️

05 Nov, 15:30


ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ያለህ እግዚአብሔር ቸርነትህን ይጠብቃል!
ከአለም ርቀው ስለፍቅሩ ሲሉ በየበርሀው እና በየገዳማቱ ባዕታቸውን ቀልሰው ሌት ከቀን ለሚማፀኑልን ሰርክ የሚጸልዩ ሾለ ዓለሙ ምልጃ የሚተጉ የሚያነቡ  ገዳማውያን የልጆቻቸውን እጅ ናፍቀው ተጨነቁ ቢባል እግዜሩስ እንዴት ያየናል?!
ስለእኛ ለነፍሳችን በመድከም በመንፈሳዊ ህይወት መምህር የሚሆኑን የክርስቶስ እውነተኛ ሙሽሮች ገዳማውያን፣ ዛሬ ላይ ባለው  ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ ነባራዊ ሁኔታዎች የሚቀመስ እፍኝ ቆሎም ጠፍቶ ረሀብ ጥማቱ በብርቱ እየተፈታተናቸው ለጾም ለጸሎት መቆም ተስኗቸው  ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብን ይዘዋል።
እግዚአብሔርን የምትወዱ እርሱን ለመምሰል የምትተጉ ብጹዓን  ጥቂት በመራራት የቸርነት እጃችሁን ለእነዚህ  ገዳማውያን በመዘርጋት በረከተ እግዚአብሔርን ታገኙ ዘንድ እንጠይቃቹኋለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
                       

Sheger Press️️

05 Nov, 14:23


የድሮን ጥቃት‼️

ትናንት ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ከደብረብርሃን ከተማ በ 22 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ባሶና ወራና ወረዳ ግፍት ቀበሌ ላይ በተሰነዘረ የድሮን ጥቃት የአንድ አርሶ አደር መኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ መውደሙን የአካባቢ ሰዎች ገለፁ::

በጥቃቱ ሰዐት በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ሰውም ሆነ እንስሳት ባለመኖራቸው በህይወት ላይም ይሁን በአካል ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም ጨምረው ገልፀዋል::

በተጨማሪም በተመሳሳይ የድሮን ጥቃት ከደብረብርሃን ከተማ በ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አንጎለላና ጠራ ወረዳ አንጋዳ ቀበሌ ሾላአምባ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ላይ መሰንዘሩ የተሰማ ሲሆን የድሮን ጥቃቱ አንድ የአካባቢው ነዋሪን የገደለ ሲሆን በት/ቤቱ ግቢ ውስጥ የነበሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶች በጥቃቱ ህይወታቸው ማለፉም ተሰምቷል::(zehabesh)

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

05 Nov, 14:17


በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን አዲስ አበባ ሲደርስ የተደረገ የአቀባበል መርሐ ግብር በምስል

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

05 Nov, 12:59


በአማራ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግሥት ቁርጠኛ ሆኖ ተኩስ አቁም ማድረግ አለበት ሲሉ ፓርቲዎች ገለጹ

በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በየዕለቱ እየተከሰተ ያለዉን የሕጻናትና እናቶችን ሞት ለማስቆም፤ የፌደራሉ መንግሥት ቁርጠኛ በመሆን የተኩስ አቁም ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ፓርቲዎች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ ከአባላቱ ለተነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት፤ ለሰላም ቁርጠኝነት እንዳለ በመግለጽ "አግዙን" ሲሉ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡

አሐዱም ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር መነሻ በማድረግ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን "መንግሥት እውነት ቁርጠኛ ነው ወይ?" ሲል ጠይቋል፡፡

የእናት ፓርቲ አባል አቶ ጌትነት ወርቁ "መንግሥት የተኩስ አቁም ማድረግ አለበት" ያሉ ሲሆን፤ 'ቁርጠኛ መሆን አለበት' ሲባልም "በሌላው ወገን ያሉትም ጦር በማዉረድ ወደ ሌላ አሸናፊ መንገድ ለመምጣት ቁርጠኛ መሆን አለባቸው" ብለዋል፡፡

"መንግሥት ለሰላም ቁርጠኛ ነኝ እያለ ይናገር እንጂ በእውነት መሬት ላይ የወረደ የተተገበረ ነገር ግን ማግኘት አይቻልም" ያሉት ደግሞ፤ የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ የአደረጃጀትና አቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙባረክ ረሽድ ናቸው፡፡

"አሁንም ግጭት ውስጥ ነው የምንገኘው" ያሉት አቶ ሙባረክ፤ "ለሰላም ዝግጁ የሆነ አካል ቢያንስ ወደ ሰላም የሚያመጡ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር አለበት" ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሰላም ፍላጎት መታየቱ በራሱ ግን የሚያስደስትና አንድ ደረጃ ችግሩን አምኖ የሰላም ጥሪ ማድረጉ በበጎ የሚወሰድ መሆኑን ፓርቲዎቹ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥሪያቸው 'እናንተም አግዙ' የሚል ጥሪ ስለማድረጋቸው በሚመለከት ሀሳባቸውን የሰጡት ፓርቲዎቹ፤ "ችግሩ ከእኛም ከመንግሥትም በላይ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል" ብለዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰላም ፀጥታ ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ መንግሥታቸው "ከኃይል ይልቅ ሰላም እጅግ በጣም አዋጭ ነው" ብሎ እንደሚያምን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

አሃዱ ራዲዮ


@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

05 Nov, 11:15


እኛም አልፎልን ብድር መስጠት ጀምረናል ተመስገን ነው።

በአለም አዲስ አገር ለሆነችው ደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር በሁለቱ አገራት መካከል አገናኝ ለሚሆን መንገድ ግንባታ የሚውል ነው።

የአራት አመት እፎይታ ኖሮት በ10 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው ብድር ከ738 ሚሊየን ዶላር በላይ ነው።

በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገነባው 220 ኪሜ መንገድ በኢትዮጵያ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲከናወን በሁለቱ አገራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።

የብድር አመላለሱም በካሽ እና በድፍድፍ ነዳጅ እንደሚሆን ነው የተጠቀሰው ሲል ካፒታል አስነብቧል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

04 Nov, 13:49


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦

በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et 

በTelegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

04 Nov, 12:54


የገንዘብ ገደቡ ተነሳ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ ማንሳቱን አስታወቀ
ገደቡ የተነሳው ለጊዜው እንደሆነና ይህም ከባንክ ወደ ቴሌ ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ አንደሆነ ተሰምቷል።
የግል ባንኮችም ይህን እንዲያስፈፅሙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዟል፡፡
መንግስት ወይም የኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግዙፋን ኩባንያ ኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል።ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል።የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም የግል ባንኮች ህዝብ የሚጠይቀው እንዲፈፀምለትና ለኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ግዥ ግብይቶች ከባንክ ወደ ቴሌብር ዝውውሮች ሲጠየቁ እንዲፈፅሙ ተጠይቀዋል።የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጠ ነው።


@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

04 Nov, 10:23


የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ የፕሪቶሪያው ግጭት ማቆም ስምምነት ስኬታማነት የሚለካው፣ ጦርነቱ ያስከተላቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች መፍትሄ ሲያገኙ እንደኾነ አስታውቀዋል።

የትግራይን የግዛት አንድነት በማስከበር ረገድ፣ እምብዛም እመርታ እንዳልታየ፣ ምዕራባዊ ትግራይ ሙሉ በሙሉ በአማራ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር እንደኾነና ሰሜናዊ ምዕራብና ምሥራቃዊ ትግራይ በኤርትራ ቁጥጥር ሥር እንደኾኑ የጠቀሱት ጌታቸው፣ እነዚህ ችግሮች ካልተፈቱ ሰላም ሊሠፍን እንደማይችል ገልጸዋል።

ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ካልኾነ፣ ለቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት ጭምር ስጋት እንደሚኾንና የስምምነቱ ተቃዋሚዎች ቦታ እንዲያገኙ እንደሚያደርግም ጌታቸው አስጠንቅቀዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

04 Nov, 06:33


ተያዙ‼️

ከቀናት በፊት የታጠቁ ሀይሎች አለም ገና የሚገኘው ኩሩ ኢትዮጵያ የቡና መጋዘን መዘረፉ ዘግበንላቹ ነበር።

አሁን ላይ የተዘረፈው ቡና ከነተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ መያዙ ሸገር ሰምቷል።

በሰዓቱ የተዘረፈው ከ71 ሺ KG በላይ ቡና ነበእ።

አሁን ከነተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታውቋል።

ምርመራው መቀጠሉንም የአለምገና ፖሊስ ጠቁሟል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

03 Nov, 18:43


ታሰሩ‼️

በአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት የሚገኙ 5 ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ጉዳይ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል ከጁመዓ ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ የተማሪ ቤተሰቦች ለሀሩን ሚድያ ተናግረዋል።

በአዲስ ከተማ ት/ቤት ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ሂጃብ እና ኒቃብን አስመልክቶ ተማሪዎች ት/ቤቱን የጠየቁትን ጥያቄ እና ት/ቤቱ ጥያቄውን በተገቢ ከመመለስ ይልቅ የፖሊስ ሀይል ጋር በመደወል ሁከት መቀስቀሱንም ገልፀዋል።

እስከ አሁን ባለው 2 ሙተነቂብ እና 3 ወንድ ተማሪዎች መታሰራቸው የታወቀ ሲሆን ነገር ግን የት እስር ቤት እንደታሰሩ እንዳማይውቁ ወላጆቹ ተናግረዋል።

የተማሪ ወላጆች የሚመለከተው አካል በግፍ የታሰሩ ሙስሊም ተማሪዎችን በአፋጣኝ ያስፈታልን ሲሉ ጠይቀዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

03 Nov, 18:37


ተጠያቂዉ ማነዉ⁉️

ለሙከራ በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የአንድ ገበሬ ህይወት አለፈ

ዛሬ ጠዋት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን የከሚሴ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ áˆˆáˆ™áŠ¨áˆŤ ከባድ መሳሪያ ሊተኮስ እንደሚችልና እንዳትደነግጡ የሚል  መልዕክት አስተላልፎ ነበር።

ከባድ መሳሪያዉ ወደ  ሰሜን ሸዋ ዞን
መኮይ አምቧሀ አካባቢ የተተኮሰ ሲሆን የተተኮሰው መድፍ የአንድ ገበሬ ህይወት ማጥፋቱን ተዘግቦል።

አዉሮፓዉያን ለአንድ ዜጋቸዉ ህይወት ሙሉ የሃገራቸዉን ጦር ያዘምታሉ ፡፡

እኛ ጋር በግዴለሺነት ቦታዉ ከሰዉ እና ከእንሰሳት ነፃ መሆኑ ባልታወቀበት ከባድ መሳሪያ ተተኩሶ የሰዉ ህይወት ይጠፋል ፡፡

ለዚህ ንፁህ አርሶ አደር ገበሬ ደም ተጠያቂዉ ማነዉ?

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

03 Nov, 15:22


#የሀዘን_መግለጫ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደራ ወረዳ፣ አድዓ መልኬ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኦነግ ሸኔ(ኦ.ነ.ሠ) ታግተው በግፍ ለተገደሉት የገንዳ አረቡ መስጅድ ኢማም ሼህ ሙሐመድ መኪን ሀጂ አረፉ ፓርቲያችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

ኢማሙ በአካባቢያቸው የተፈሩና የተከበሩ፣ የተጣላ አስታራቂ እንደነበሩና በመስጅድ ውስጥ ሳሉ ከሌሎች 12 የቅርብ ሰዎች ጋር ታግተው በቅድሚያ ለመልቀቅ መደራደሪያ 3ሚሊዮን ብር ተጠይቆ 1.4ሚሊዮን ሰጥተው መሣሪያ ጭምር ካላመጣችሁ በማለትና ቀሪውን ገንዘብ ሲፈልጉ በግፍ ኹሉንም እንደገደሏቸው ለማወቅ ችለናል። ኢማሙ የታገቱት ከወር በፊት እንደነበርና ለማስልቀቅም ከፍተኛ ርብርብ እንደነበር ሰምተናል። በሣምንት ልዩነት እንዲሁ አንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ 800ሺህ ብር ተጠይቆባቸው ብሩንም ከፍለው ከብዙ እንግልት በኋላ በአሰቃቂ ኹኔታ ገድለዋቸዋል። አካባቢው ከፍተኛ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ የሚዘወተርበት በአንጻሩ ግፉ እንዳይነገር በሚዲያ በታገዘ ፕሮፓጋንዳ ጭምር የሚድበሰበስበት ነው።

ፓርቲያችን ደጋግሞ እንዳሳሰበው እንዲህ ከነባር ሃይማኖት ኢትዮጵያን ለማፋታትና ወደአዲሱ የዓለም ሥርዓት/New world order/ ለመውሰድ በሚደረገው ጥድፊያና ርብርብ መንግሥታዊ መዋቅር ጭምር ተከትሎ እየተሠራበት እንደሆነ ለዚህም በዋናነት የሃይማኖት ተቋማትን በቃልም በተግባርም መዳፈር፣ የሃይማኖት አባቶችን እያሳደዱ መግደል፣ ምዕመናንን ማሳሳት፣ ማፈናቀል፣ ዕምነት ተኮር ጭፍጨፋ የስልት ትግበራውና መንገድ ጠረጋው አካል ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ደጋግመን ገልጸናል።

እንዲህ ያለው ተግባር በጥንቃቄ የሚፈጸም በመሆኑ ዛሬ ክርስቲያኑን ነገ ሙስሊሙን ቦታ እየቀያየረ የሚደረግ ነው። እንዲያውም በታሪክ፣ በባህል እንደምናውቀው አንዱ የሌላው መከታና ጠባቂ እንዳይሆን እርስ በእርስ ለማፈጀትም ሴራ ሲጠምቅ ይታያል። ውጤቱ ውሎ አድሮ ያለ ተው ባይና አስታራቂ፣ በጎውን መንገድ ከነውሩ ለይተውና አበጥረው በቃልም በጽሑፍም የሚያመላክቱንን ጠቋሚ አባቶች የሚያሳጣ አካሄድ መሆኑን በውል መረዳት ይገባል።

ፓርቲያችን እንዲህ ያለውን እኩይ ተግባር በጽኑ ያወግዛል፤ ባለ በሌለ ኃይሉም ይታገለዋል።
በድጋሚ በኢማሙ ግፍ ግድያ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጥን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

03 Nov, 15:22


#ጠብታው ሲጠራቀም  

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ልዩ በረከት ያለበት ስፍራ ነው፡፡

ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያን ከመፈወስ አልፎ ሙት ያስነሳ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ከዘጠና በላይ ገዳማውያን የተጠለሉበት፣ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡

ይሁንና መነኮሳቱና ገዳማውያኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነው፡፡ አከባቢው ተፈጥሮ ፊቷን አዙራበት ድርቅ በመኖሩ ጭው ያለ ምድረ በዳ ሆኋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአካባቢው ያለው ጦርነት በየጊዜው ይጎበኟቸው የነበሩ ፀበልተኞች ፈጽመው እንዲሸሹና ገዳማውያኑ ያለምንም ጠያቂ በትልቅ ችግርና ፈተና ውስጥ እንዲገኙ አድርጓቸዋል፡፡

ከፀሎትና ከድካም መልስ የሚጠለሉበት በአታቸውን ማጽናት የሚችል እገዛ፣ ከፆም መልስ የሚቀምሱትን አፍ መሻሪያና የአመት ልብስ ልናቀርብላቸው ይገባል። በዚህ የበረከት ስራ ገዳሙንና አባቶችን ብቻ ሳይሆን በጸሎታቸው ሀገራችንንም ለመጠበቅ አስተዋጽኦ እናደርጋለን፡፡ የእያንዳንዳችን ጠብታ ድጋፍ ሲጠራቀም ዋጋ አለው፣ የሕሊና እርካታም እናገኛለን፡፡
 
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

03 Nov, 09:35


የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለሁለቱ የአገሪቱ ምክር ቤቶች ባደረጉት ንግግር በቅርቡ ከግብፅ እና ቱርክ ጋር የተፈራረሙትን የመከላከያ ትብብር ስምምነቶችን ከኢትዮጵያ ለሚመጣ ስጋት እንደሚጠቀሙባቸው ጠቁመዋል።

እነዚህ ስምምነቶች የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋትን አያሳጡም፣ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ህግን የሚቃረን የኢትዮጵያን ምኞት ያስቀራል ሲሉም አረጋግጠዋል።

የፕሬዝዳንቱ ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሰሞኑ ለፓርላማው ባደረጉት  ንግግር፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ  መዳረሻ ለማግኘት ያላትን እና  የማይናወጥ ያሉትን ፍላጎት በድጋሚ ካረጋገጡ በኋላ የተሰማ ነው።


@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

03 Nov, 08:15


ጥቅምት 24

እነሆ በአፍሪካ ምድር ውዱ ጦርነት የተጀመረበት በፌደራል መንግስቱና በህውሀት መካከል በይፋ ጦርነት የተጀመረው በዛሬው ዕለት ከጥቂት አመት በፊት ጥቅምት 24 ነበር።

ሚሊዮኖችን የቀጠፈው
ሚሊዮኖችን ያፈናቀለው
በመቶሺዎች ያካል ጉዳተኛ ያደረገው ይህ ጦርነት በመጨረሻም በሰላም ተፈቷል።

የፌደራል መንግስቱ ከጎን ተከድተን ተገደልን ያሉበት
የትግራይ ሃይሎች የተቃጣብንን ጥቃት በመብረቃዊ መልሶ ማጥቃት አከሸፍን ያሉበት ነበር።

አሁንም በአማራ ክልል በፌደራል መንግስቱና በፋኖ ታጣቂ መካከል ጦርነት በመደረግ ላይ ይገኛል።

በዚህም በርካቶች ለሞትና መፈናቀል ብሎም ደግሞ ለረሀብ አጋልጧል።

አሁንም እነዚ ሁለቱ ሀይሎች ጦርነቱ በሰላም በመፍታት

ለተርታና ከርታታው ገበሬውን ሰላሙን እንዲሰጡት እንማፀናለን ሞት ይብቃን ሸገር ፕረሶች ነን ሰላም ለሀገራችን ።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

03 Nov, 07:27


ትናንት ሌሊት 6:05 ላይ በኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተገለፀ

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በአፋር አዋሽ እንደሆነ በአለምአቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ ተመሳሳይ ክስተቶችን የሚያሳውቀው የአርዝ ኩዌክ አለርት መረጃ አመልክቷል።

የትናንት ሌሊት መንቀጥቀጥ በአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ መረጃ መሰረት በሬክተር ስኬል 4.7 ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ድረስ መሰማቱም ታውቋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

03 Nov, 05:44


መረጃ‼️

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት 120 የመንግስት ፀጥታ ሃይሎችን ደምስሻለሁ ሲል  አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዉጫሌ በሚባል አካባቢ ላይ በሁለት አካባቢዎች የተሳካ ዘመቻ አድርጌ 120 የመንግስት የፀጥታ አካላትን ገድያለሁ ሲል ነዉ ኦነግ በመግለጫዉ ያስታወቀዉ ፡፡

ካራ በሚባል ወታደራዊ ካምፕ ላይ በፈፀመዉ ጥቃት 67 ወታደሮች መግደሉን ሲናገር በተመሳሳይ በደፈጣ እየተጎዙ ባሉ የሰራዊቱ አባላት ላይ ተኩስ በመክፈት 53 ወታደሮችን ገድያለሁ ብሎል ፡፡

ሰሞኑን በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ንፁሃን በአሰቃቂ መንገድ ሲገደሉ እንዲሁም የሀይማኖት አባት እስከ ቤተሰቦቻቸዉ ታግተዉ ተገድለዉ መገኘታቸዉ የሚታወስ ነዉ ፡፡

ፊልድ ማርሻሉን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችን ኦነግ ሸኔ እየጠፋ ነዉ ቆሞ መዋጋት አይችልም ቢሉም ከ4ኪሎ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ኦነግ የሚፈልገዉን  እየገደለ የሚፈልገዉን እየዘረፈ ይገኛል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

02 Nov, 17:49


የኬንያ ኢምግሬሽን ባለሥልጣናት፣ ማቻኮስ ግዛት ውስጥ ታስረው የቆዩ 60 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ትናንት በሞያሌ በኩል ወደ አገራቸው እንደመለሱ የኬንያው ዘ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል። ፖሊስ ኢትዮጵያዊያኑን ፍልሰተኞች ያሠራቸው፣ ከአንድ ሳምንት በፊት በሕገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ ገብተዋል በማለት ነበር።

የኢምግሬሽን ባለሥልጣናቱ ኢትዮጵያዊያኑን ወደ አገራቸው የመለሷቸው፣ የማቻኮስ አውራጃ ፍርድ ቤት ፍልሰተኞቹ "ከሕግ ውጭ" እና "ኢሰብዓዊ በኾነ ኹኔታ" ተይዘዋል በማለት ፖሊስ ባስቸኳይ ወደአገራቸው እንዲመልሳቸው ባዘዘ በማግስቱ ነው።

በኬንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በበኩሉ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ኬንያ ውስጥ እስር ላይ የነበሩ 276 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ብሏል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

02 Nov, 17:46


የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በፌደራል መንግሥቱ በኩል የፕሪቶሪያ ግጭት ማቆም ስምምነትን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ያለው ፍላጎት ዝቅተኛ ነው በማለት የስምምነቱን ኹለተኛ ዓመት አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተችቷል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ በርካታ የደቡብ ትግራይና ጸለምት አካባቢዎች እስካኹን ወደ ትግራይ እንዳልተመለሱና በምሥራቃዊ፣ መካከለኛውና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ከኤርትራ ሠራዊት ነጻ እንዳልወጡ ገልጧል።

የሕወሓት አመራር የሕዝቡን ፍላጎት ወደ ጎን በማለት ፖለቲካዊ ንትርክ ውስጥ ገብቷል በማለት የወቀሰው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ፌዴራል መንግሥቱ፣ አፍሪካ ኅብረት፣ አውሮፓ ኅብረትና አሜሪካ በስምምነቱ ያልተመለሱ ጉዴዮችን ለመፍታት የሕግና የሞራል ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

02 Nov, 17:15


መረጃ‼️

የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር የቀረቡባቸውን ክሶች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ

የማይገባ ጥቅም በመቀበል የሙስና ወንጀል በመፈጸም እና በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ የተከሰሱት የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጸጋዬ ቱኬ፤ በቀረቡባቸው ሁለት ክሶች ላይ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ። በቀድሞው ከንቲባ እና አብረዋቸው በተከሰሱ ሁለት ተከሳሾች ላይ ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 19፣ 2017 ብይኑን የሰጠው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሀዋሳ ማዕከል ነው።

የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ፤ በአቶ ጸጋዬ እና ሁለት ተከሳሾች ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ የመሰረተው፤ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ነበር። በአንድ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ተከሳሾች መካከል፤ የሲዳማ ክልል የቀድሞ የፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አበራ አሬራ ይገኙበታል።

የክልሉ ዐቃቤ ህግ በአቶ አበራ እና በአቶ ጸጋዬ ላይ የመሰረተው የመጀመሪያ ክስ፤ በሙስና ወንጀሎች አዋጅ የተቀመጠን ድንጋጌ በመተላለፍ “የማይገባ ጥቅም በመቀበል የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል” የሚል ነው። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የመጀመሪያው ክስ፤ በሀዋሳ ከተማ ሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል ጎን የተወሰደ ቦታ ምትክ መሬት እንዲሰጥ ከቀረበ ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነው።

የምትክ ቦታ ጥያቄ ቀርቦ የነበረው፤ ከአቶ ጸጋዬ አስቀድሞ በነበሩት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የአመራር ጊዜ እንደነበር በክሱ ተመላክቷል። አቶ ጥራቱ የምትክ ቦታ እንዲሰጥ ውሳኔ ቢያስተላልፉም፤ የመሬት ርክክብ ከመፈጸሙ በፊት ከኃላፊነታቸው በመነሳታቸው ጉዳዩ እርሳቸውን ለተኳቸው አቶ ጸጋዬ ተላልፏል።

#ሸገር_ፕረስ

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

02 Nov, 17:01


እናት ፓርቲ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ቦራ ወረዳ ቢጢሲ ቀበሌ ገብሬ ማኅበር ጥቅምት 20 ቀን ከምሽቱ ኹለት ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት ፈጸሙት በተባለው ጭፍጨፋ የስድስት ወር ሕጻንን ጨምሮ፣ አረጋዊያን፣ ሴቶች፣ ሕጻናትና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ከ68 በላይ ዜጎች መሞታቸውን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ነዋሪዎቹ የተገደሉት በመኖሪያ ቤታቸው ላይ እሳት ተለኩሰባቸው እንደኾነ ከአካባቢው ነዋሪዎች መረዳቱን የጠቀሰው ፓርቲው፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ገና አስከሬናቸው እንዳልተገኘ ገልጧል።

ፓርቲው፣ ተፋላሚ ወገኖች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጽሟቸው መሰል የጅምላ ጭፍጨፋዎች "የጦር ወንጀሎች" ናቸው ብሏል።

ይህንኑ ጅምላ ጭፍጨፋ አስቀድሞ መከላከል፣ ማስቀረት ወይም ጉዳቱን መቀነስ ይቻል እንደበርም ፓርቲው ገልጧል።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

02 Nov, 16:42


የኦሮሚያ ክልል ዓቃቤ ሕግ፣ በጉጂ ዞን በማዕድን ልማት በተሠማሩት ቀንቲቻ የማዕድን ኩባንያ እና ኩባንያው ትልቅ ባለድርሻ በኾነበት የአፍሪካ ማዕድንና ኢነርጂ ኩባንያ ላይ "የዝርፊያ" እና "ማጭበርበር" ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ሪፖርተር ዘግቧል።

ፖሊስ፣ የቀንቲቻ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ዓሊ ሁሴንና ምክትላቸው ሳሚ አሠፋን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ከምንጮቹ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል።

ዓቃቤ ሕግ፣ ቀንቲቻ የብቃት ደረጃውን ሳያሟላ ሊቲዬምና ታንታለም ለመቆፈር እንዴት ፍቃድ እንዳገኘና የኩባንያው ሃላፊዎች በኩባንያው ስም ከውጭ ባለሃብቶች ተቀብለውታል የተባለውን 38 ሚሊዮን ዶላር እያጣራ መኾኑን ዘገባው አመልክቷል።

ቀንቲቻ ኩባንያ፣ የክልሉ መንግሥት 49 በመቶ ድርሻ የያዘበት የኦሮሚያ ማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበርና አቢሲኒያ ብረታብረት ሃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ በጋራ ያቋቋሙት ነው።

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

02 Nov, 15:46


በቤተመንግስት ተገኘ ስለተባለው 400 ኪ/ግ ወርቅ

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ "ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል" ማለታቸው ይታወሳል።

"ይህ ወርቅ ምን ይሆን ብዬ?" አንዳንድ ማጣራቶችን ለማድረግ ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ አስደንጋጭም፣ አሳሳቢም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ይህ ወደ ብሄራዊ ባንክ ተላከ የተባለ ወርቅ በኢትዮጵያ የንጉሳዊ ስርዐት ወቅት ለበርካታ መቶ አመታት ነገስታት ሲገለገሉባቸው የነበሩ በወርቅ እና በሌሎች የከበሩ ማዕድናት የተሰሩ ቁሳቁሶች፣ ከሌሎች ሀገራት በስጦታ የተሰጡ ቅርሶች እንዲሁም በርካታ በነገስታቱ ታዘው የተሰሩ እና የተገዙ ናቸው።

"ታድያ እነዚህ ወደ ሙዚየም እንጂ ለሽያጭ ወይም ለወርቅ ክምችት ወደ ባንክ እንዴት ሊላክ ይችላል?" ብዬ ጥያቄ ያቀረብኩላቸው ጉዳዩን የሚያውቁ ግለሰቦች ምላሻቸው "ማን ሰምቶን?" ነው።

ቅርስ ጥበቃ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ የጠ/ሚር ፅ/ቤት እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ዙርያ መክሮ እነዚህን የኢትዮጵያ ታሪክ የሆኑ ንብረቶች ወደነበሩበት ቦታ ወይም ወደ ሙዚየም እንዲመለሱ ማድረግ አለባቸው።

እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው!

Via EliasMeseret

@Sheger_press
@Sheger_press

Sheger Press️️

01 Nov, 10:19


ክቡር ዶክተር ማሕሙድ አሕመድ ከመድረክ  ሊሰናበት ነው ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያደረገው ጋሽ ማህሙድ አህመድ ማይኩን ሊሰቅል መሆኑ ተገልጧል፡፡

ጋሽ ማሐሙድ ለአገራችን የሙዚቃ ዕድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የክቡር ዶክተር ማዕረግን መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

በአገራችን የሙዚቃ ዘርፍ ስመጥር  የሆነውን የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም ለማሰናበት ወይም ማይኩን ሊሰቅል ሲዘጋጅ እጃችንን አወዛውዘን መሸኘት አግባብነት የለውም በሚል በጆርካ ኢቨንት አዘጋጅነት ሽኝቱን በደመቀ እና በታሪክ ማስታወሻነትም ለማስቀመጥ መታሰቡን ሰምተናል፡፡

በዚህም ጥቅምት 22 ቀን  ከጋሽ ማሕሙድ ኮሚቴ በመረከብ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚለኒየም አዳራሽ ደረጃውን የጠበቀ የድምጻዊው የመጨረሻ የህይወት ዘመን ስንብት ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ተነግሯል ፡፡

በእለቱም የክቡር ዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ላይ የተዘጋጀ መፅሀፍ እንደሚመረቅም ተነስቷል፡፡

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

01 Nov, 09:51


በቦሌ ቡልቡላ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ደርሰዋል
ምንጭ አንኮር መረጃ
@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

01 Nov, 09:07


በአዳማ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የመንግስት ሀይሎች ወጣቶችን በግዳጂ በማፈስ ወደ ወታደራዊ ማስልጠኛ እያስገቡ መሆኑ ተገለፀ

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ይሀው ድርጊት በተደጋጋሚ እንደሚፈፀም ሲነገር መቆየቱ የሚታወስ ነው

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

01 Nov, 09:07


አሳዛኝ የገዳማዊያን ሁኔታ ሊንኩ በመጫን ይመልከቱት
https://youtu.be/kfjd7WB3JMo?si=EVHN4lfeCBCF3THQ

Sheger Press️️

01 Nov, 08:11


የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የመኖሪያ ፈቃድ ሕግን ተላልፈው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የሰጠውን የምህረት አዋጅ ለሁለት ወራት አራዘመ

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግሥት የመኖሪያ ፈቃድ ሕግ ተላልፈው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሰጠውን የምህረት አዋጅ ለቀጣይ ሁለት ወራት ማራዘሙን በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ኤምባሲው ባለፉት ሁለት ወራት ከኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር ጋር ባደረገው ጥረት ከ10 ሺሕ የሚልቁ ኢትዮጵያውያን ወረቀት አልባ ዜጎች ያለምንም ቅጣት መኖሪያ ፈቃዳቸውን እንዲያስተካክሉ ወይም እገዳ ተነስቶላቸው አገሪቱን በሕጋዊ መንገድ ለቀው እንዲወጡ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት በተለያዩ ምክንያቶች ከአዋጁ ተጠቃሚ መሆን ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሳይዘናጉ እስከ ፈረንጆቹ ታሕሳስ 31 ቀን 2024 ድረስ ወረቀታቸውን እንዲያስተካክሉም አምባሳደር ዑመር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

01 Nov, 06:32


በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቀበሌያት በሚገኙ የሶዶ ጉራጌ ተወላጆች ላይ ባነጣጠረ የ''ሸኔ'' ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ጥቃቱ የደረሰው በክልሉ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ጋር በሚዋሰንባቸው የዱግዳ ቦራ ወረዳ ቀበሌያት ነው።

በዚህም በዱግዳ ቦራ ወረዳ ቢርቢርሳና ጋሌ ተብለው በሚጠሩ ቀበሌያት ልዩ ስማቸው ደረባ፣ ኩሬ እንዲሁም ቢጢሲ ተብለው በሚታወቁ ስፍራዎች አሰቃቂ ጥቃት መድረሱ ተነግሯል።

በተለምዶ ''ሸኔ'' ተብሎ በሚጠራው ቡድን ታጣቂዎች አማካይነት እንደደረሰ በተገለፀው ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸውንና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ከስፍራው የደረሱን ተደጋጋሚ መረጃዎች አመላክተዋል።

ጥቃቱ ከትላንት በስተያ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ገደማ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መራዘሙን የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎችና የሟቾች ቤተሰቦች በጥቃቱ ሕጻናትን ጨምሮ እናቶችና አረጋውያን መገደላቸውንም ተናግረዋል።

የተከፈተባቸውን ጥቃት መመከት ያልቻሉ አርሶ-አደሮች ቤታቸው ውስጥ እያሉ በእሳት እንዲቃጠሉ በማድረግ ከነከብቶቻቸው እንዲሞቱ መደረጉንም ነዋሪዎች ገልፀዋል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

01 Nov, 04:56


ከ100 ሺህ በላይ የዩክሬን ወታደሮች መጥፋታቸውን የሀገሪቱ ፓርላማ አባል ተናገሩ

ከሩሲያ ጋር እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከ100 ሺህ በላይ የዩክሬን ወታደሮች መጥፋታቸው አልያም ፈቃድ ሳያገኙ ጥለው መሰወራቸውን የሀገሪቱ ፓርላማ አባል ተናገሩ።

አና ስኮሮኮድ የተሰኙት የፓርላማ አባል በከፍተኛ ወታራዊ አዛዦች እና ባለስልጣናት የአያያዝ ጉድለት ሳቢያ ወታደሮች በጦር ሜዳ የሞራል ውድቀት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

በዚህ ሳቢያም ከ100 ሺህ በላይ የጦር አባላቱ አንድም ጠፍተዋል አልያም ያለ ፈቃድ ተሰውረዋል ነው ያሉት።

አባሏ ይህን ያሉት ኪዬቭ አሁን ላይ የገጠማትን የወታደር እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ 160 ሺህ ወታደሮችን ለመቅጠር የሚያስችል ዕቅድ በቀረበበት ወቅት ነው።

የፓርላማ አባሏ ከወታደሮችና ቤተሰቦቻቸው በአያያዛቸው ዙሪያ ዘወትር ቅሬታ እንደሚደርሳቸውም ነው የተናገሩት።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

31 Oct, 20:32


በሓበን የማነ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል የህዝብ እገዛ እፈልጋለው ሲል የመቐለ ከተማ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ

የሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዛሬ ጥቅምት 21 እንደገለፀው ከሆነ በክፍለ ከተማው ዓዲ ሓ ተብሎ በሚታወቅ አከባቢ ሓበን የማነ የተባለች እንስት ግፍ በተሞላት መንገድ ግድያ እንደተፈፀመባት ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ግድያው በፍቀረኛዋ እንደተፈፀመ ለማወቅ ችያለዉ የሚለው ፖሊስ ግድያውን ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረው ዳዊት ዘርኡ የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር አለመዋሉ በመግለፅ ፖሊስ አረመኔያዊ ሲል የገለፀውን ግድያ የፈፀመው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ መረጃ ለፖሊስ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አቅርቧል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

31 Oct, 20:25


Dogs Notcoin ያመለጣቹ ሰዎች Paws በፍፁም እንዳያመልጣቹ

- ሁለተኛ ዕድል ዳግም አይገኝም

- በሶስት ቀን ወደ 15 ሚሊዮን ሰዎች ገደማ ጀምረውታል።

ለመጀመር👇 👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=gCb0B62i
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=gCb0B62i

Sheger Press️️

31 Oct, 18:41


መረጃ ‼️

እስራኤል የወታደር እጥረት እንደገጠማት  እየተነገረነዉ፡፡

በጋዛ ከአንድ አመት በላይ የቆየዉና አሁን ደግሞ ከሊባኖሱ ሄዝቦላህ ጋር ጦርነት የገጠመዉ እንዲሁም በቀጣይ ከኢራንና ከቱርክ ጋር የተፈራዉን ጦርነት ለመጀመር እያሟሟቀች የምትገኘዉ እስራኤል አዲስ ወታደር ለመመልመል ፈተና እንደገጠማት ተሰምቶ የኔታንያሁ መንግስት ተረብሽዋል፡፡

በሊባኖስ ተጨማሪ የውጊያ ግንባር ለመክፈት አቅዳለች የተባለችው እስራኤል የወታደር እጥረት እንደገጠማት ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡እንደ ዘገባው ከሆነ በእስራኤል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ዜጎች ብሔራዊ ጦሩን ተቀላቅለው የማገልገል ግዴታ አለባቸው፡፡

ይህን ተከትሎ ጦሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ የቀረበላቸው እስራኤላዊን በጦርነቱ ተሰላችተዋል የተባለ ሲሆን የመዋጋት ፍላጎታቸውም ቀንሷል ተብሏል፡፡

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

31 Oct, 17:30


የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ በከተማዋ አንዳንድ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዝግብ ዙሪያ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትናንት በተደረገ ውይይት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ከስምምነት ላይ እንደተደረሰ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ፣ በአራት ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአለባበሳቸው እና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ጫና እና እንግልት እየደረሰባቸውና ከትምህርት እንደታገዱ ጠቅሶ ሰሞኑን ለከተማዋ ትምህርት ቢሮ ቅሬታ አቅርቦ ነበር።

ኾኖም ትናንት በተደረገው ውይይት ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ከትምህርት ቤቶቹ ከመገለላቸው በፊት ይስተናገዱ በነበረበት ኹኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ከስምምነት እንደተደረሰ ምክር ቤቱ ገልጧል።

ምክር ቤቱ ውይይቱ የተደረገው፣ ከከተማዋ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ ከከተማዋ ፓሊስ ኮሚሽን እና ከከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር እንደሆነ ጠቅሷል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

31 Oct, 13:32


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰት ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

ጥቅምት 21 ቀን በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል የሚል መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ተመልክተናል ብሏል አየር መንገዱ።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራን አየር ክልል እንዲጠቀም ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፈቃድ የተሰጠው እና የኤርትራ አየር ክልልን ለመደበኛ በረራ እየተጠቀመ መሆኑን እረጋግጦ በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተገለፀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

31 Oct, 11:04


በትግራይ ክልል ያለን ወጣቶች ጨንቆናል ከጦርነቱ ቦኋላ ኣብዛኛው ሰው ኣይምሮው ትክክል ኣደለም ሞትም ተላምደነዋል ባላችሁበት ሆናቹ እንድትፀልይዩልን እማፀናቹዋለው

ኣሁንም በፖለቲከኞቹ ምክንያት ስራ ቀዝቅዝዋል ድሃ በረሃብ ምክንያት ወደ የሚረገው ኣያውቅም ስንት ትናንሽ ህፃና በሱስ ብዛት ኣእምራቸው ስተው ነው ያሉት

ጦርነቱ ብዙ ወጣቶች በየሰፈራችን ኣልቀውብናል እሱ ሳያንሰን ደግሞ ከጦርነቱ ቦኋላ የቀረው ወጣትም ስራ ስለሌለ በጭንቀት

ቢያንስ በቀን ከኣንድ ሰፈር 5 ወይ 6 ወጣቶች ስደት እየሄዱ ነው እና ኣስቡት ከኣንድ ሰፈር እንደዚ ሚያክሉ ከሄዱ ከክልል ሙሉ ስንት ወጣት እየተሰደደ እንደሆና ብቻ በየሃይማኖታቹ ለፈጣሪ ንገሩልን ኣደራ ጨንቆናል ወንድሞቼ እህቶቼ

🙏🙏🙏

እባካቹ ፖስቱት በጣም በጭንቀት ነው ያለነው ናሆም ገብረእዚኣብሄር ከመቀሌ ዓድሓ ከሄቨን ሰፈር ነኝ እሷም ጎረቤቴ ነች ኣደራ ፀልዩልን ብላቹ ፖስቱልን

ፎቶዬ ካስፈለገም ናሆም ፀልዩልን እያለ ነው ብላቹ እንድትፖስቱት ካስፈለገ እልክላቹሃለው🙏

©️ ናሆም ገብረእዚኣብሄር

ምንጭ ፦ ጉርሻ
@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

31 Oct, 09:00


አንዳንድ ኤምሲዎች የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍና በጥቁር ገበያ ሥራ ላይ መሰማራታቸውን ጠ/ሚ አብይ አህመድ ገለጹ

የኢትዮጵያን ሃብት የመዝረፍና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ መስራት ስራቸው የሆነ አንዳንድ ኤምባሲዎች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህን የገለጹት እየተካሄደ ባለው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበቅ ወቅት ነው።

“ነገር እንዳናበላሽ የታገስናቸው ስራቸው ግን ጥቁር ገበያ ማሯሯጥ የሆነ ኤምሲዎች አሉ” ያሉት አብይ አህመድ፤ “ጤናማ ዝምድና የማያደርግ ማንም ኤምባሲ እኛ አንፈልግም” ብለዋል።

ስራቸው ይህ የሆነ ኤምባሲዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግ እና የማይታረሙ ከሆነ እርምጃ እንደሚወሰድ በንግግራቸው አመላክተዋል።

በኩባንያ ስም፣ በፍራንኮ ቫሎታ ስም፣ በወርቅ ንግድ ስም የኢትዮጵያን ገበያ የሚያዛቡ ገለሰቦች መኖራቸውንም አክለው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የጥቁር ገበያ ዶላርና ወርቅ በባቡር እና በተሽከርካሪ ከአገር እንደሚወጣ የገለጹት ጠ/ሚንስትሩ ይህን ዘረፋ መከላከል ያስፈልጋል ሲል አክለዋል።

አንዳንድ ሀገራት በዚህ መንገድ ኢትዮጵያን መዝረፍ መብት እንደሆነ እንደሚያስቡ ገልጸው ነገር ግን ኢትዮጵያ ከብሄራዊ ጥቅሟ አንጻር ጥያቄ ስታነሳ እንደ “ግስላ” ይሆናሉ ብለዋል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

31 Oct, 08:58


#ሰይፍ ጠጋኙ ሕጻን…  


ለዘመናት ሲዘርፉና ሲገድሉ የነበሩ ሁለት ወንበዴዎች ከፍተኛ ሽልማት የተጣለባቸው ሁለት ሰዎችን ፍለጋ በረሀ አቋርጠው ፍለጋ ያደርጉ ጀመር፡፡

በስተመጨረሻም በለስ ቀናቸውና ተፈላጊዎቹን ሰዎች አገኟቸው፡፡ ተፈላጊዎቹ ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያምና ሔሮድስ የሚያሳድደው ሕጻን ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበሩ፡፡ ከእነርሱ ጋርም ዘመዷ ሰሎሜና ሽማግሌው ዮሴፍ አብረዋቸው ነበሩ፡፡ ወንበዴዎቹ በዕለተ አርብ በቀኝና በግራው የተሰቀሉት ጥጦስና ዳክርስ ናቸው፡፡


ሰሎሜ ጌታን እንዳይጎዱት አስቀድማ መጎናጸፊያዋን ሰጠቻቸው፡፡ እነርሱ ግን ምንም ሳያስቀሩ ሙልጭ አድርገው ዘረፏቸው፡፡ የጌታችን ሰብአ ሰገል ያመጡለት ስረ ወጥ ቀሚስና የወርቅ ጫማውን ጭምር ወሰዱበት፡፡

ከዚያም ከእነርሱ እልፍ ብለው ጭቅጭቅ ያዙ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “ወንበዴ ከዘረፈ በኋላ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ይሸሻል እንጂ መች ቆሞ ይማከራል ልጄን ሊገድሉብኝ ነው እንጂ” ብላ አምርራ አለቀሰች፡፡

በቀኙ ተሰቅሎ የነበረው ወንበዴ ጥጦስ “እነዚህ ሰዎች አሳዘኑኝ እንመልስላቸው” የሚል ጥያቄ ማንሳቱና የዳክርስ እምቢታ ነበር የጭቅጭቁ መነሻ፡፡

የዘረፉትን በየተራ ይወስዱ ነበርና ተራው የዳክርስ ስለነበር ብሸጠው ብዙ ገንዘብ ያወጣልኛልና አልመልስም ብሎ ተከራከረው፡፡ በመጨረሻም ጥጦስ ወሰነ “ከገሊላ ጀምሮ እንከዚህ የዘረፍነው ላንተ ይሁንና ይህን እንመልስላቸው” አለው፡፡


ዳክርስ በዚህ ሀሳብ ተስማማና ጥጦስ መጥቶ መለሰላቸው፡፡ በዚህ አላበቃም፤ ጌታችንን አቅፎ ጥቂት መንገድ ሊሸኛቸው ወደደ፡፡ አቅፎት ሲሔድም የሚመረኮዘው ሰይፉ ተሰበረበት፤ ደግ በሰራሁ ክፉ እጣ ገጠመኝ ሲል በጣም አዘነ፡፡ በእናቱ እቅፍ የነበረው ጌታችንም የሰይፉን ስብርባሪዎች አንድ አድርጎ ገጥሞ ሰጠው፡፡


ልባችንን ቅን አድርገን ያለንን ሁሉ ለመስጠት፣ ያም ባይሆን ካለን ላይ ቀንሰን ለመስጠት ምን ያህል ዝግጁ ነን? መስጠት ፍጹማዊ ሲሆን ወንበዴው ጥጦስ እንኳን የዘረፈውን መልሶ መንገድ እስከ መሸኘት ድረስ ተጉዟል፡፡ እኛ በሐቃችን እንኖራለን የምንለው ለመስጠት ምን ያህል ተሰጥተናል፡፡ በተለይ ብዙ የምንፈልግ ከሆነ አብዝተን እንስጥ ክፍያው በብዙ እጥፍ ይልቃልና፡፡


ጌታችን አቅፎት ለሚጓዘው ወንበዴ ጥጦስ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ የተናገረውን “እውነት እልሃለሁ ከአዳም ቀድመህ ገነት ትገባለህ” ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገረው፡፡ ጥጦስ በዚህ ተደስቶ ይህ ሕጻን ከነቢያት ወገን ይመስለኛል አለው ለጓደኛው፡፡

ይህን ጊዜ ዳክርስ “አዎ ከነቢያት ወገን ቢሆን አይደል አንተን ወንበዴውን ገነት ትገባለህ የሚልህ” ሲል አሾፈበት፡፡

ታዲያ ተሰናብተዋቸው ከሔዱ በኋላ ጌታን ያቀፈበት ጎኑ የልብሱ መዓዛ ተቀየረ ቢያጥበው ልዩ ሽቱ ሆኖለት በ300 ዲናር ሸጠው፡፡ ያን ሽቱ ነበር ዘማዊቷ ሴት ማርያም እንተ ዕፍረት አምጥታ በራሱ ላይ ያፈሰሰችው፡፡ በቅን ልባችን የምሰጠው መስጠት፣ ገዳማውያንን መርዳትና በዓታቸውን ማጽናት በብዙ እጥፍ ይከፍለናል፡፡ የእመቤታችን የስደቷ በረከት ከኛ ጋር ይሁን፡፡ ከቅድስና ስደት ይመልሰን፡፡          

  

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

30 Oct, 19:43


የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ በከተማዋ በአለባበሳቸው የተነሳ ከአራት ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ባስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ለከተማዋ ትምህርት ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

ምክር ቤቱ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ባንዳንድ ትምህር ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች "በአለባበሳቸው" እና "በእምነታቸው" ላይ ያነጣጠረ “ጫና እና እንግልት” እየደረሰባቸው ይገኛል ብሏል።

የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ያወጣው የተማሪዎች የዲስፕሊን መመሪያ የሙስሊም ተማሪዎችን አለባበስ እንዳልወሰነ የጠቀሰው ምክር ቤቱ፣ የአንዳንድ ትምህርት ቤቶች አመራሮች በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የጣሉት እገዳ ግን "ሕዝበ ሙስሊሙን እና መንግሥትን ለማጋጨት" የሚደረግ ጥረት ነው በማለት ገልጿል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 19:43


Paws‼️

በበርካቶች ዘንድ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ ኤርድሮፕ ካልጀመራቹ ቶሎ ጀምሩ።

አሪፍ ይከፍላል እየተባለ የሚገኝለት ኤርድሮፕ ነው።

ጊዜ የላቹም ቶሎ ጀምሩ

Invite አድርጉ ታስኮችን ስሩ።

በዚ Link ጀምሩ👇👇

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=KeMafgCX
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=KeMafgCX

Sheger Press️️

30 Oct, 18:45


ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ነገ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚያቀርቡላቸው ጥያቄዎች በአካል ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራሪያ የሚሰጡት፣ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ባለፈው ወር መጨረሻ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤተና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ የዓመቱ የሥራ መክፈቻ ስብሰባ ላይ ባቀረቡት የመንግሥት ዕቅድ ዙሪያ ይሆናል፡፡

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 18:31


የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ስለ ሱዳኑ ጦርነት የፈጥኖ ደራሹን ኃይል አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎን ጠይቀው አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ ሰሞኑን ከሱዳናዊያን ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል።

ኢሳያስ፣ የሱዳን ጦር ሠራዊት ድል ማድረግ ለሱዳን ቀጣይነት የጀርባ አጥንት እንደሆነ ተናግረዋል ተብሏል።

የውጭ ተጽዕኖዎች ዋናው ማዕከል ዳርፉር መኾኑን የገለጡት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ ሱዳናዊያን እገራቸውን ሊበታትኑ ካቆበቆቡ የውጭ ተጽዕኖዎች መላቀቅ እንዳለባቸው መክረዋል።

ፕሬዝዳንቱ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤርትራ ውስጥ ለሱዳናዊያን ስደተኞች መጠለያዎችን ለማቋቋም ጠይቋቸው እንደነበር ጠቅሰው፣ ኾኖም ሱዳናዊያን ስደተኞች ኤርትራ ውስጥ በነጻነት መኖር እንደሚችሉ በመግለጽ ጥያቄውን ሳይቀበሉት እንደቀሩ ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 15:37


በከምባታ ዞን ዳምቦያ ወረዳ፣ ፉንጦ ከተማ ውስጥ ወጣቶች በጭካኔ በፀጥታ አካላት ሲደበደቡ የሚያሳየው ምስል አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል

ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው በአካባቢው ውሃ እና መብራት ከወራት በላይ ጠፍቶ ህዝቡ በስቃይ እያሳለፈ ይገኛል።

በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስትን በኮሚቴ ሆነን ሄደን እንጠይቅ ብለው የተሰበሰቡ ወጣቶች በክልሉ ልዩ ሀይል ክፉኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው እና ሶስቱ ደግሞ በጥይት ተመትተው እንደቆሰሉ ታውቋል።

"ለዚህ ጉዳይ ወጣቶች ከተማ ውስጥ ተሰብስበው ምን እናድርግ ብለው እየተወያዩ ባሉበት ሁኔታ ላይ የክልሉ ልዩ ሀይል ለምን ተሰባስባችሁ በማለት ይህን ዓይነት ድርጊት ፈፅሞባቸዋል" ያለን አንድ የከተማው ነዋሪ ነው።

ሌላ የከተማው ነዋሪ ደግሞ ድብደባ ከተፈፀመባቸው ወጣቶች መሀል ሁለቱ ክፉኛ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ መስማቱን ተናግሯል።

የከምባታ ዞን መዲና ከሆነችው ዱራሜ ወጣ ብላ በ20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ፉንጦ ከተማ ላይ የህዝብን ሰቆቃ ለህዝብ እናሳውቅ ባሉ ወጣቶች ላይ የተፈፀመው ድርጊት የብዙዎች መነጋገርያ ሆኗል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ለፉንጦ ከተማ ትኩረት ተሰጥቶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የክልል አመራሮች ጉዳዩን በአስቸኳይ እንዲከታተሉና ለህዝቡ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

''15 ቀናትን ያለ ውሃ እና መብራት ማነው የሚኖረው?" ብለው ጥያቄ እያነሱ የሚገኙት ነዋሪዎች የጉድጓድ ውሃ እየጠጣ የሚታመመውንና ለሞት ሰለባ የሆነውንስ ቤቱ ይቁጠረው ብለዋል።

ከአካባቢው ካሰባሰብነው መረጃ መሀል "እኛ ብርሃን እንወዳለን፣ መብራት እንፈልጋለን" ብለው ለችግሩ ፍትህ ፍለጋ በወጡበት ሦስት ሰዎች በጥይት መመታታቸው ታውቋል፣ ሌሎች ደግሞ ከቤታቸው እንዲወጡ እየተደረጉ እንደተደበደቡ ሰምተናል።

በዚህ ዙርያ ከከምባታ ዞን አመራሮች ተጨማሪ መረጃ እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

መረጃን ከመሠረት!

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 15:36


ሳንፎርድ፡ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ለ ቤትዎ

ጥራት እና ጥንካሬ መለያችን የሆንን ሳንፎርድ ፈርኒቸር ለቤትዎ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ይዘን ከች ብለናል።

ሶፋ ፣ አልጋ ፣ የቲቪ ማስቀመጫ ፣ የመመገብያ ጠረጰዛ እና ወንበር ዲዛይኖቻችንን ከምቹነት ከጥራት እንዲሁም ከውቤት ጋር የተጣመሩ ናቸው።

ከ15 አመት በላይ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እርሶዎን በሚመጥን ዋጋ ቤቶትን እናሳምርልዎ!!!

አሁኑኑ ይደዉሉ ፦ +251978777775 / +251976777775

Sheger Press️️

30 Oct, 14:35


ንፁህ ልብ‼️

መንግሥት ቤት ቢሰጥህ አትደሰትም ነበር?

ጨበራ ኮንታ:- ባለቤቴስ? ስድስቱ ልጆቼስ? ፎቅ እንኳ ባገኝ እነርሱን አልተውም:: እዚያው የገጠሩ ማሳደስ ይሻላል:: እዚህ ቤት ባገኝ እንደገና እዚህ ላገባ? ይህ ደግሞ ቃልኪዳን አለን:: ቤት ሳገኝ እንዴት እክዳታለሁ? ቤተክርስቲያን ገብታ ብታለቅስብኝ እኔም እሞታለሁ:: ቤቱም ቀረ:: እነርሱም ያዝኑብኛል:: እና ቤቱ ምን ጥቅም ይሰጠኛል:: ከባለቤቴና ከልጆቼ የሚነጥለኝን ፎቅ እንኳ አልፈልግም::

ኮንታ እያልክ የምትቀልደው የዚህ አይነት ስብዕና እና አመለካከት ኖሮህ አያቅም፣ ራስን መግዛት በዚህ ልክ ምን አልባት እንዳለም አታቅም፣ ሰባራ ደመወዝህን ከባለቤቱ የሚደብቅ ይህ ሰው ለእርሱ ሰማዩ ነው የማይነካ፣ የማይደረስበት።

What a personality! This is pure humanity!

Via Endale Mokonen
💖 ንፁህ ልብ 💝🇪🇹

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 14:28


ፅንስ ማስወረድ መሰረታዊ ነፃነት ነው ሲሉ ካማላ ሀሪስ ተናገሩ

ዴሞክራቷ ካማላ ሃሪስ በዋሽንግተን በተካሄደ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለተሰበሰቡ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ባደረጉት ንግግር ሰዎች በራሳቸው ሰውነት ላይ ውሳኔ ለማድረግ "መሰረታዊ ነፃነት" አላቸው ሲሉ ተደምጠዋል።

ፅንስ ማስወረድ ለመከላከል ያሉ ጥበቃዎችን በማንሳት ወደነበረበት ለመመለስ ቃል ገብተዋል።ይህ ምርጫ ምናልባት ከምትሰጡ ድምፅ ሁሉ የበለጠ በጣም አስፈላጊ ድምፅ ነው ያሉት ካማላ ሀሪስ “በነጻነት እና በግርግር መካከል ያለ ምርጫ” ነው። የአሜሪካ መራጮች እስከ ዛሬ ከነበረው በተለየ መልኩ ያልተለመደ ታሪክ ቀጣዩን ምዕራፍ መፃፍ ይችላሉ ሲሉ ተደምጠዋል። የሪፐብሊካኑ ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕን በንግግራቸው በማጥቃት ያልተረጋገጠ ስልጣን ይፈልጋሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሃሪስ በጃንዋሪ 6፣ 2021 ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል እንዲነሳ ያደረጉትን አመፅ በማስታወስ ተናግረዋል።

የካማላ ሀሪስ የድጋፍ ሰልፍ በዋይት ሀውስ አቅራቢያ ባለው ቦታ ከ75,000 በላይ ሰዎች ማክሰኞ ምሽት ላይ ታድመዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ጆ ባይደን የትራምፕ ደጋፊዎችን “የቆሻሻ ማጠራቀሚያ” ብለው መሰየማቸውን የሚያሳይ ምስል በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል። ዋይት ሀውስ የባይደንን ንግግር የተከላከለላቸው ሲሆን በፖርቶ ሪኮኖች ላይ ለሪፐብሊካኖች የጥላቻ ንግግሮች የተሰጠ ምላሽ ነው ብሏል። ሪፐብሊካኖች ግን ፕሬዚዳንቱን በንግግራቸው አውግዘዋል። ትራምፕ በበኩላቸው ባይደን የሚናገረውን አያውቅም በማለት ይቅርታ አድርጉላቸው ብለዋል።ዶናልድ ትራምፕ ፖርቶ ሪኮን "ተንሳፋፊ የቆሻሻ ደሴት" ብሎ ከጠራው ደጋፊያቸው ኮሜዲያን ንግግር እራሱን አግልለዋል።

ነገር ግን በግላቸው ይቅርታ አልጠየቁም ከዝግጅቱ በፊት ኮሜዲያን ማን እንደሆነ ምንም የማውቀው ነገር የለም ሲሉ ተናግረዋል።አስተያየቱ "መጥፎ" ቢሆንም "ትልቅ ነገር" እንደሆነ አላሰበም ሲሉ አክለዋል። በሌላ በኩል ካማላ ሃሪስ እና ዶናልድ ትራምፕ ዋይት ሀውስ ለመግባት የመጨረሻ ትንቅንቅ ሲቀረብ፣ አውሮፓ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በዩክሬን ጦርነት እና በአህጉሪቱ ደህንነት ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ እያስጨነቃት ይገኛል። የፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስቱብ ለሮይተርስ እንደተናገሩት "ሁላችንም ምርጫው እስኪጠናቀቅ ድረስ እየጠበቅን ነው" ካሉት አለም አቀፍ ችግሮች የተነሳ ብለዋል።

ወደ ዩክሬን እና አውሮፓ ደህንነት ስንመጣ፣ በርካታ የአውሮፓ ባለስልጣናት የሪፐብሊካን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ በቀድሞው የስልጣን ዘመናቸው የተመሰቃቀለ የአትላንቲክ ግንኙነት፣ በኔቶ ላይ የሰነዘሩት ጠንካራ ትችት እና ስለ ዩክሬን ያላቸው አሻሚ እይታ ፣ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ማሸነፍ እንደሚያስጨንቃቸው ይናገራሉ።ቭላድሚር ፑቲን እንደ ድል የሚያዩት የዩክሬን ጦርነት ማብቃት የሩስያ ፕሬዝደንት የኔቶ ሀገርን እንዲያጠቁ ሊያበረታታቸው ይችላል ሲሉ አንድ የጀርመን የስለላ አዛዥ ተናግረዋል።


ዳጉ_ጆርናል

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 14:25


#ከቅጣት ለማምለጥ ሲል ጎኑን በጦር ወጋው፣ ዓይኑንም....

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ስፍራ ቀራንዮ-ጎልጎታ አባታችን አዳም የተቀበረበት እንደሆነ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባቶችና በርካታ ዓለም አቀፍ የታሪክ ጸሐፍያን ይገልጻሉ።

ጲላጦስ አይሁድ እንዲሰቅሉት አሳልፎ የሰጣቸው ጠዋት 3:00 ላይ ነው። በፍርድ ሒደቱ ላይ ተጽእኖ ለማሳረፍ አይሁድ ሕዝቡን ሁሉ ሲያስተባብሩ፣ የሀሰት ምስክርም አቁመው ነበር። መስቀል አሽክምው እየገረፉ ወስደው በእርጥብ እንጨት ሰቀሉት። ሰውን ሊያድን ሰው የሆነው ጌታ፣ በሰው ልጅ ይሙት በቃ ተፈረደበት።

በዚህ ሁሉ ክፋታቸው ወስጥ ያልተስማሙ፣ ኢየሱስ ንጹህና ጻድቅ ሲሆን በግፍ እንደተገደለ የሚያምኑ ድርጊቱንም ያልደገፉ የራሳቸው የአይሁድ ወገኖች ነበሩ። በበጎ ምግባር መሳተፍና ከክፉ ምግባር መራቅ የየትኛውም ቅን ልብ ያለው ሰው መገለጫ ነው።

ከእነዚህ አንዱ ለንጊኖስ የተባለው አንድ ዐይና ወታደር ነው። ይህ ፈረሰኛ በዚያች ዕለተ አርብ በጌታ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ላለማየት ከከተማ ወጥቶ በጫካ ውስጥ ዋለ። ነገሮች አብቅተዋል ብሎ አመሻሹ ላይ ወደ ከተማ ሲግባ፣ የአይሁድ አለቆች ከቀራንዮ ሲመለሱ ከመንገድ አገኘቱ፤ ስለምን ከመሢሑ ሞት አልተባበርክም አሉት? እርሱም ምንም ስላላገኘሁበት አላቸው፡፡ ከዚያም በኋላ እንደሕጋቸው እንደሚቀጡት ቢነግሩት እየሮጠ ሔዶ የጌታችንን ጎን ሲወጋው ደሙ በዐይኑ ላይ ሲፈናጠቅ ወዲያው ዐይኑ በራለት።


ከጌታችን ጎንም ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ፣ መላእክትም ደሙን በጽዋ ቀድተው በዓለም ላይ ረጩት፤ ውሃውም ለጥምቀታችን ሆነ። ይህ መሠረት ሆኖ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን የሚታነጸው የጌታችን ደም የነጠበበት  ነው፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ "አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ" ያለው (ሐዋ 20á28)፡፡


ለንጊኖስ የልቡናው ቅንነት ነው የታየለት፤ ጎኑን መውጋቱ ዓይኑን ሲያበራለት ለኛ ደግሞ ለጥምቀታችን የሚሆነንን ማየ ገቦና በዓለም የተረጨ ደሙን አስገኘልን። የእኛስ የልቡና ቅንነት እንዴት ይገለጻል? በዘመናችን ዐይነ ልቡናችንን የሚያበራ በጎ ምግባር የምናደርግበት እድል አለና የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ እንስማ።

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

30 Oct, 11:00


በኢትዮጵያ በቂ የኮንዶም አቅርቦት እና ስርጭት እንደሌለ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ21 ሺህ በላይ አዳዲስ ሰዎች በኤች አይ ቪ ኤድስ እንደሚያዙና 26 ሺህ ሰዎች ኤች አይ ቪን ጨምሮ ተያያዥ በሆኑ የጤና እክሎች እንደሚሞቱ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

ከሁለት አመት በፊት በተከሰተው የኮንዶም እጥረት ምክንያት በአንዳንድ የክልል ከተሞች ምርቱ በውድ ዋጋ ሲሸጥ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከ250 ሚሊዮን በላይ የኮንዶም አቅርቦት እና ስርጭት እንደሚያስፈልግ በኤም ኤስ አይ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝ ካንትሪ ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ ገልጸዋል፡፡

አሁን ያለው ስርጭት ከ50 በመቶ በታች እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

(መናኸሪያ ሬዲዮ)

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 10:00


somaliland‼️

ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ ቢመጣ ከ ኢትዮጵያ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ገለጸች

ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ እና ጫና ቢመጣ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ተናገሩ።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 08:32


" 7 ሰው ሞቷል ፤ 2 ሰው ተጎድቷል " - በወላይታ ዞን የካዎ ኮይሻ ወረዳ

በወላይታ ዞን፤ ካዎ ኮይሻ ወረዳ ላሾ 01 ቀበሌ እና ኮይሻ ላሾ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በቀን 19/02/2017 ዓ.ም ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት 7 (ሰባት) ሰው የሞተ ሲሆን በ2 ሰው ጉዳት ደርሷል።

በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

ከዚህ በፊት በዛው በካዎ ኮይሻ ወረዳ ላይ ጤፓ ቀበሌ በመሬት ናዳ ምክንያት የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም ስሰራ ቢቆይም ተደጋጋሚ አደጋ በመከሰቱ ችግሩ እያባባሰው መምጣቱ ተገልጿል።

መረጀው የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ሥራ ሂደት ነው።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 07:16


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትርፍ ሰዓት ክፍያ ያልተከፈላቸው የጤና ባለሞያዎች ሥራ አቆሙ

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኘው አንጋጫ ሆስፒታል የጤና ባለሞያዎች ትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው፣ በክልሉ ካምባታ ዞን አንጋጫ ወረዳ የሚገኘውና በአካባቢው ለሚገኙ 2 መቶ ሺሕ ለሚኾኑ ነዋሪዎች አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ተቋረጠ።

አገልግሎቱ የተቋረጠው ሃኪሞቹን ጨምሮ 80 የሚኾኑ፣ የጤና ባለሞያዎች ለስድስት ወራት የሠሩበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው መኾኑን ተናግረዋል። የሆስፒታሉ አገልግሎት የተቋረጠው ካለፈው ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀመሮ ሲኾን ተገልጋይ የኅብረተሰብ ክፍሎች መቸገራቸውን ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 06:50


ሳንፎርድ፡ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ለ ቤትዎ

ጥራት እና ጥንካሬ መለያችን የሆንን ሳንፎርድ ፈርኒቸር ለቤትዎ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ይዘን ከች ብለናል።

ሶፋ ፣ አልጋ ፣ የቲቪ ማስቀመጫ ፣ የመመገብያ ጠረጰዛ እና ወንበር ዲዛይኖቻችንን ከምቹነት ከጥራት እንዲሁም ከውቤት ጋር የተጣመሩ ናቸው።

ከ15 አመት በላይ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እርሶዎን በሚመጥን ዋጋ ቤቶትን እናሳምርልዎ!!!

አሁኑኑ ይደዉሉ ፦ +251978777775 / +251976777775

Sheger Press️️

30 Oct, 06:44


የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ካለፈው ስምንት አጋማሽ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ግንባሮች ከመንግሥት ኃይሎች ጋር በተካሄዱ ግጭቶች 102 የመንግሥት ወታደሮችንና በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ማርኬያለኹ ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አማጺው ቡድን በመንግሥት ኃይሎች ላይ ወታደራዊ ድል ተቀዳጅቻለኹ ያለው፣ ድሬ ኢንጪኒ፣ ደራ፣ ወረ ጃርሶ፣ አመያ፣ ዩብዶ፣ ጉቴ፣ ቦጂ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሳሲጋ፣ አባይ ጮመን፣ ሀርጡማ ፉርሴ፣ ኤልዋዬ፣ ገላና፣ ሱሮ ቡርጉዳ፣ በቾ እና ቦራ በተባሉ የግጭት ግንባሮች ነው። ቡድኑ ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች፣ የግንኙነት መስመሮች እንደተቋረጡ መኾኑንም ጠቅሷል።

መከላከያ ሠራዊት በበኩሉ፣ በቡድኑ ላይ መጠነ ሰፊ የኃይል ርምጃ እየወሰደ መኾኑን ገልጧል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

30 Oct, 05:58


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ 2 ነጥብ 6 ትሪሊዮን መድረሱን አስታውቋል።

ባንኩ፣ በሩብ ዓመቱ ውስጥ 121 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ብድር መስጠቱንም ገልጧል።

በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ባንኩ 640 ሚሊዮን የገንዘብ ዝውውር በዲጂታል አማራጮች መካሄዱንና ይህም ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ46 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አውስቷል።

በባንኩ የዲጂታል የክፍያ አማራጮች የ3 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር ግብይት እንደተፈጸመም ተገልጣል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

29 Oct, 19:43


" ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ምሽት በተረጋገጠ የX ገጻቸው  ከደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር ንግግር ማድረጋቸውን በሚመለከት አጋርተዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም ለመቀራረቡ እኛ እንቀርባለን ብላችሁ እኛን ለማገናኘት በመጣር ላይ ያላችሁ ክብር ይስጣችሁ" ሲሉ አመስግነዋል።

አቶ ጌታቸው አክለውም "ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " ሲሉ ከደብረጽዮን (ዶ/ር) ጋር አብረው ከተነሱት ፎቶ ጋር ባጋሩት መልእክት።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጋራ የተነሱትን ፎቶ ብዙዎች በመጋራት አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አብዛኞቹ ምስሉ በአውንታ ተቀብለው ሲያስተጋቡ ፤ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ " ከአንገት በላይ " ያሉትን ፎቶና መልእክት ንቅፈው እየጻፉ ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ እና ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለበርካታ ሳምንታት በሚዲያ እና በፅሁፍ መግለጫ ብዙ ሲባባሉ እንደነበር አይዘነጋም።

ምንም እንኳን ዛሬ በምን ጉዳዮች ላይ እንደተነጋገሩ በዝርዝር ባይታወቅም አቶ ጌታቸው ረዳ ያጋሩት ፎቶ በክልሉ አመራሮች መካከል ያለውን ውጥረት ያረግበዋል ተብሎ ታምኖበታል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

27 Oct, 18:11


እስራኤል በከባድ ሀዘን ተመታች‼️

በእስራኤል ዋና ከተማ ቴላቪቭ በሞሳድ ዋን ቢሮ አቅራቢያ በደረሰ ከባድ የመኪና አደጋ 5 ሰዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለጉዳት ተዳርጓል፡፡

በቴል አቪቭ ከተማ አንድ የጭነት መኪና አሽከርካሪ በከተማዋ በሚገኝ የአውቶቡስ ማቆሚያ ስፍራ ላይ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰባቸው እና የተወሰኑት መገደላቸዉን የእስራኤል አምቡላንስ አገልግሎት አሳውቋል።

የድንገተኛ ህክምና አገልግሎቶች በአሁኑ ጊዜ በደርዘን ለሚቆጠሩ ተጎጂዎች በቦታው ላይ እንክብካቤ እየሰጡ ነው "ሲል የእስራኤል አምቡላንስ አገልግሎት ማጌን ዴቪድ አዶም ተናግሯል።

ሁኔታው ሆን ተብሎ የተፈጸመ ጥቃት ስለመሆኑ እየተጣራ መሆኑን የገለፀው የአገሪቱ ፖሊስ - የከተማዋ ነዋሪዎች በየትኛውም ስፍራ ከ3 በላይ ሆነው እንዳይሰባሰቡ መክሯል።

ከሞሳድ ዋና መሥሪያ ቤት አቅራቢያ በሚገኘው ቴል አቪቭ አውቶቡስ ፌርማታ ላይ አንድ የጭነት መኪና እግረኞች ተሰብስበዉ በነበረበት ስፍራ ላይ ባደረሰዉ አደጋ በትንሹ አምስት ሰዎች ሲገደሉ 50 የሚጠጉ ሰዎች ቆስለዋል ሲል የዕብራይስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

27 Oct, 16:25


ታጣቂዎች በይቅርታ ወደ መንግስት እየገቡ ነው።

በሊቦ ከምከም ወረዳ አግድ ቅርኛ ቀበሌዎች አካባቢ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 15 አባላት በተደረገው የህዝብ ግንኙነት ስራ በ17/2/2017 ዓ/ም ወደ ወረዳው በይቅርታ መግባታቸውን የሊቦ ከምከም ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ ፶/ አለቃ ንጉሴ በየነ ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

27 Oct, 14:02


ኢራን‼️

"እስራኤል በኢራን ላይ ለሰነዘረችው ጥቃት የሉዓላዊነት ክብራችንን በዘላቂነት ለማስጠበቅ በሙሉ አቅማችን እና ኃይላችን አብርካሪዋን የሚሰብር ምላሽ እንሰጣለን።

የምንሰጠው ምላሽ ካሁን ቀደም ከነበሩት #ሁለት እርምጃዎች በዓይነቱም ፣ በስፋቱም በብዙ እጥፍ የተለየ ይሆናል።"

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፡

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

27 Oct, 11:32


ፖለቲካን እንደ ገቢ ማግኛ ዘዴ የሚመለከቱ በመኖራቸው ከፓርቲ ፓርቲ የሚቀያይሩ ፖለቲከኞች በዝተዋል ተባለ

ፖለቲከኞች ፍላጎታቸው ስልጣን በመሆኑ አንድ ፓርቲ ላይ የመፅናት ፍላጎት የላቸውም ሲሉ፤ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ እና ዲፕሎማት አቶ ጥላሁን ሊበን ተናግረዋል፡፡

"በሀገራችን ያሉ ፖለቲከኞች ለአቋቋሙት ፓርቲ ተማኝ የመሆን ብሎም የሚቋቋሙትን ፓርቲ መጠቀሚያ እያደረጉት በመሆኑ አንድ ፓርቲ ላይ መፅናት አይችሉም" ሲሉ ነው አቶ ጥላሁን የገለጹት፡፡

"የዘር ፖለቲካ ላይ የሚያተኩሩ ፓርቲዎች ጭምር ለቆሙለት ብሔር ሳይሆን ለስልጣን እና ጥቅም ያደሉ በመሆናቸው ለፓርቲዎቻቸው ታማኝነት የላቸውም" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"ጥያቄው የስልጣን ነው" የሚሉት አቶ ጥላሁን፤ በዚህ መንገድ አንዱ መንገድ ሲዘጋባቸው ሌላኛውን መንገድ እንደሚፈልጉ አስረድተዋል፡፡ ለዚህም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ እየሰሩ ያሉ ተቃዎሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ጠቅሰዋል፡፡

"ለዚህ መፍትሄው ስልጣንን የሀብት ምንጭ እንዳይሆን ተደርጎ መሰራት አለበት" ያሉት አቶ ጥላሁን፤ ማንኛውም ፖለቲከኛ ፖለቲካን ከጥቅም አኳያ እንዳይመለከት መደረግ እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡

ፖለቲካን ንግድ አድርጎ ከማሰብ የሚደረግ ሥራዎች ማስተካከል የሚገባ መሆኑንም የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ባለሙያው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

"በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ የውስጥ ፖለቲካ ልዩነት ካለ እንዲሁም የርዕዮት ዓለም ልዩነት ከተደረገ ከፓርቲ ፓርቲ መቀየር ግዴታ ሊሆን ይገባል" የሚሉት ደግሞ የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ፓርቲ የዶክመንት ዝግጅት ቡድን መሪ አቶ ቸርነት ሰዒድ ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ የርዕዮተ ዓለም ልዩነት ብቻ ፓርቲ ለመቀየር ምክንያት አይሆንም የሚሉት አቶ ቸርነት፤ "የምትቆይበት ፓርቲ ከመርህ እየወጣ ከሆነና የመታገያ ቦታው እየጠበበ ከሆነ የተሻለ ምህዳር ወዳለው ፓርቲ መዞር ችግር አይኖረውም" ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ፓርቲ ከሌሎች የተለያዩ ፓርቲዎች የተሰባሰቡ ፖለቲከኞች የሚገኙበት መሆኑን የሚያነሱት አቶ ቸርነት፤ "በፓርቲዎች ላይ የነበሩ ችግሮችን ቀርፎ በአዲስ መንገድ ለመምጣት እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡(አሀዱ ሬዲዬ)

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

27 Oct, 11:30


ሳንፎርድ፡ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ለ ቤትዎ

ጥራት እና ጥንካሬ መለያችን የሆንን ሳንፎርድ ፈርኒቸር ለቤትዎ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ይዘን ከች ብለናል።

ሶፋ ፣ አልጋ ፣ የቲቪ ማስቀመጫ ፣ የመመገብያ ጠረጰዛ እና ወንበር ዲዛይኖቻችንን ከምቹነት ከጥራት እንዲሁም ከውቤት ጋር የተጣመሩ ናቸው።

ከ15 አመት በላይ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እርሶዎን በሚመጥን ዋጋ ቤቶትን እናሳምርልዎ!!!

Sheger Press️️

27 Oct, 09:58


❗️የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከአማራ ክልል ጋር የሚወዛገብባቸውን ግዛቶች የሚመለከት መመሪያ አፀደቀ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ አዲስ በማኅበራት የሚገነቡ ቤቶችን በሚመለከት ባዘጋጀው መመሪያ፣ ክልሉ በአሁን ወቅት ከአማራ ክልል ጋር የሚወዛገብባቸውን ግዛቶችን የተመለከቱ አንቀጾችን አካቶ ማፅደቁ ታወቀ።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ያፀደቀውና በፕሬዚዳንቱ አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈርሞ ሥራ ላይ የዋለው በትግራይ ክልል የሚገነቡ የማኅበር ቤቶችን የሚመለከተው መመሪያ፣ ከጦርነቱ አንስቶ እስካሁን ድረስ በኤርትራ ኃይሎች ተይዘው የሚገኙ እንዲሁም፣ ክልሉ ከአማራ ክልላዊ መንግሥት ጋር እየተወዛገበባቸው የሚገኙና በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሠረት መፍትሔ ያገኛሉ የሚላቸው ግዛቶች ላይ መከተል የሚያስፈልጉ አሠራሮችንም የሚያብራራ አንቀጽም ይዟል።

የመመሪያው ክፍል አራት ‹በትግራይ በኅብረት ሥራ ማኅበራት የሚሠሩ ቤቶች› በሚል ሥር የተካተቱ ተከታታይ አራት አንቀጾች፣ ከተሞችን በአራት ክፍል በመመደብ ከቪላ ቤት እስከ አራት ወለል ሕንፃ የሚደርሱ የግንባታ ዓይነቶች በኅብረት ሥራ ማኅበራት ተፈጻሚ ስለሚሆኑበት ያስረዳል።

አምስተኛው አንቀጽ በትንንሽ ከተሞች የሚገነቡ የሕንፃ ዓይነቶችን ደረጃና የግንባታ ሁኔታ የተመለከተ ሆኖም ተደንግጓል።

በዚህም መሠረት በመመሪያው አንቀጽ 12፣ ከ80 ካሬ ሜትር እስከ 132 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው መሬት ላይ ባለ አራት ወለል ሕንፃ ግንባታ እንደሚካሄድባቸው የሚገልጽ ሲሆን፣ የተጠቀሱት ከተሞች መቀሌ፣ ዓዲግራት፣ አክሱም፣ ሽረ እንዳ ሥላሴ፣ ዓብይ ዓዲ፣ ዓድዋ፣ ኮረም፣ ውቅሮና አላማጣ ናቸው።

በተከታዩ አንቀጽ ለንግድ አገልግሎት የሚሰጡ ተጨማሪ ወለሎችን መገንባት የሚፈልጉ ማኅበራት፣ ግንባታውን መፈጸም የሚያስችል የገቢ ምንጭ እንዳላቸው ለሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ማቅረብ እንደሚኖርባቸው በመጥቀስ፣ ባለ ሦስት ወለል ሕንፃ ግንባታ የሚካሄድባቸው ከተሞች ሁመራና ሽራሮ እንደሆኑ ተጠቅሷል።

በአንቀጽ 14 ሥር ባለአንድ ወለል ሕንፃ እንደሚገነቡና ተጨማሪ የንግድ ወለል ከፈለጉ ከላይ ከተጠቀሰው አንቀጽ ጋር ተመሳሳይ አካሄድ እንደሚከተሉ አብራርቶ፣ በመመሪያው ላይ የተጠቀሱት ከተሞች ደግሞ ማይካድራ፣ ዳንሻ፣ ማይፀብሪ፣ ቆራሪትና ማይጋባ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የከተሞችን ዝርዝር ካስቀመጡት አንቀፆች የመጨረሻው ከቀደመው ጋር በተመሳሳይ፣ በማኅበራት ባለአንድ ሕንፃ ወለል እንደሚገነቡ የሚጠቅስ ሲሆን፣ የተካተቱትም እንትጮ፣ ዕዳጋ ዓርቢ፣ ፍረ ወይኒ፣ መኾኒ፣ ዕዳጋ ሓሙስ፣ እንዳባጉና፣ ሀገረ ሰላም፣ ሓውዜን፣ ዛላንበሳ፣ እንዳስላሰ ኣጽቢ፣ ራማ፣ ዓዲ ዳዕሮና ዓዲ ጉደም ናቸው።

መመሪያው ማኅበራቱ በመረጡት ተቋራጭ ቤቶቹን ማስገንባት እንደሚችሉ ሲጠቅስ፣ የግንባታ ወጪ ግምት ግን በየከተማ አስተዳደሮቹ የሚወሰን እንደሆነ ይገልጻል። የከተማ አስተዳደሩ የግንባታ ዲዛይን ለማኅበራቱ እንደሚያቀርብ፣ ነገር ግን ማኅበራቱ የራሳቸውን ዲዛይን የመጠቀም ፍላጎት ካላቸው ለሚገኙበት ከተማ አስተዳደር በማቅረብ ማፀደቅ እንደሚችሉም ተጠቅሷል።

ለግንባታ በቅድሚያ የሊዝ ቁጥር እንደሚያስፈልግ፣ በተጨማሪም የሚመለከተው የከተማ አስተዳደሩ ተቋም በማኅበሩ ስም ዕዳ አለመኖሩን ማረጋገጥ እንደሚኖርበት ተገልጿል።

የትግራይ የመሬትና ማዕድን ቢሮ በመመሪያው ወሳኝ ሠልጣኖች የተሰጡት ሲሆን፣ እነዚህም ለማኅበራቱ የማልሚያ ቦታ የመስጠት፣ የማኅበር ምዝገባ ፈቃድ የመስጠት፣ ማኅበራት ለግንባታ ከሚያስፈልጋቸው ገንዘብ 15 በመቶውን በዝግ የባንክ ሒሳብ ማስቀመጣቸውን ማረጋገጥና እነዚህን መሠረት በማድረግ ለተጠቃሚዎች መሬት በዕጣና በሊዝ ማስተላለፍ ናቸው።

ምንም እንኳን መመሪያው የፀደቀው በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም. ቢሆንም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉት ማኅበራት ግን ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በፊት የተመዘገቡና ገንዘብ ሲቆጥቡ የቆዩትን ብቻ እንደሆነ፣ እንዲሁም የአዲስ ማኅበራት ምዝገባም በጊዜያዊነት እንዲቆም መደረጉ ታውቋል፡፡

Via Ethiopian Reporter

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

27 Oct, 09:56


#የድንጋዩ ናዳ ገለባ፣ የሚንቀለቀለው እሳትም ቀዝቃዛ ውሃ ነው… 


ውበትና ደም ግባት፣ አፍላነትና ወጣትነት መገለጫዎቹ ናቸው፡፡ ሲያስተምር በመንፈስና በኃይል የተሞላ እንደነበር ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡

ክርስቲያኖች በምድር ላይ ሲበዙ፣ የቅዱሳን ሐዋርያትም ማሕበር እየሰፋ ሲሔድ ስራዎችን የሚመሩ በዘመናችን የአስተዳደር ስራ የሚሰሩ ሰባት ሰዎች እንዲመረጡ ቅዱሳን ሐዋርያት ወሰኑ፡፡

የሰባቱ ሰዎችም መሪ ወይም ሊቀ ዲያቆን እንዲሆን ቅዱስ እስጢፋኖስን መረጡት /የሐዋ ሾል 5፥34፣ 6፥5-10/፡፡ በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀንም በዓለ ሲመቱ በደማቅ ስነስርዓት ይከበራል፡፡  


ጌታችን በዘመነ ስጋዌው ሲያስተምር በዋለበት እየዋለ ባደረበት እያደረ የተማረ ነበር፡፡ እስጢፋኖስ የስሙ ትርጓሜ አክሊል ማለት ነው፡፡ ከስምም በላይ በሕይወት ኖሮት ለሰማዕትነቱ ሰማያዊ አክሊል ተቀብሏል፡፡ የክርስቶስ ፍቅር በውስጡ የሚንቀለቀል፣ በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ያሰበና እምነቱን ያስቀደመ፣ ኦሪትን ከገማልያል ዘንድ ጠንቅቆ የተማረ፣ እውነተኛው እስራኤላዊ ይሉታል ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትና የታሪክ ጸሐፍያን፡፡


በትምህርቱ ሊረቱት ባይቻላቸው፣ በስህተታቸው ቢነቅፋቸው በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ትልቁ ተአምር የተፈጠረው እዚህ ላይ ነው፡፡ “ልባችሁና ጆራችሁ የተደፈነ፣ እንደገዛ ፈቃዳችሁ የምትመላለሱ፣ ለአምላክ የማትታዘዙ ናችሁ” ብሎ እውነቱን የተናገራቸው አይሁድ የድንጋይ ናዳ ሲያወርዱብት እርሱ ግን ሰማያት ተከፍተው ወልድን በአብ ቀኝ ተቀምጦ ያየው ነበር፡፡


ወጣትነት፣ ውበት፣ ደምግባት ሀብተ ስጋና ነፍስ ብንታደል ማን ይክበርበት ምንንስ እናገልግልበት የሚለውን በሕይወትም በኑሮውም ያሳየ ነበር፤ “ቀዳሜ ሰማዕት” የሰማዕታት መጀመሪያ ቅዱስ እስጢፋኖስ፡፡

በድንጋይ ለሚወግሩትም ሰዎች ጌታችን በእለተ አርብ እንዳደረገው “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ብሎ የጸለየ፣ የሚወርድበትን የድንጋይ ናዳ እንደ ገለባ የቆጠረ ድንቅ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፡፡


ሰማዕታት በጌታችን ፍቅር በቅድስት እምነታቸው ፍቅር የሰከሩ ስለሆኑ ወደ እሳት ሲጣሉ እንኳ እንደ ቀዝቃዛ ውሃ ነበር የሚያዩት፡፡ የእኛ ወጣትነት ትልቁ ሰማዕትነት በእምነት መጽናት፣ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪ ምላሽ መስጠት ነው፡፡ በረከቱ ይደርብንና እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ መወገር ሳይሆን ለገዳማውያን አባቶቻችንና ለበዓታቸው መጽናት በፍጹም ደስታ እገዛ ማድረግ ነው፡፡



ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

27 Oct, 05:40


ሳንፎርድ፡ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ለ ቤትዎ

ጥራት እና ጥንካሬ መለያችን የሆንን ሳንፎርድ ፈርኒቸር ለቤትዎ ዘመናዊ እና ቦታን የሚቆጥብ የቤት እቃዎችን ይዘን ከች ብለናል።

ሶፋ ፣ አልጋ ፣ የቲቪ ማስቀመጫ ፣ የመመገብያ ጠረጰዛ እና ወንበር ዲዛይኖቻችንን ከምቹነት ከጥራት እንዲሁም ከውቤት ጋር የተጣመሩ ናቸው።

ከ15 አመት በላይ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እርሶዎን በሚመጥን ዋጋ ቤቶትን እናሳምርልዎ!!!

Sheger Press️️

26 Oct, 18:32


እስኪ እንወያይበት…

ዛሬ የወጣ አንድ መረጃ ቱርክ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር 14 ሀገራትን በጎረቤታችን ጅቡቲ ሰብስባ ልትመክር መሆኑን ይፋ አድርጋለች፡፡

ከስብስቡ ውስጥ ግን ኢትዮጵያ የለችበትም፤ከዛ ይልቅ እነ ግብጽ፣ኤርትራና ሱዳን ተፈላጊ ሆነው የምክክር ግብዣ ቀርቦላቸዋል፡፡

ጥያቄ

1፣ ይህ ሁኔታ ከዲፕሎማሲ አንጻር ምን ያሳየናል?
2፣ ከደህንነት አንጻርስ እንዴት ታዩታላችሁ?
አስተያየቶቻችሁን ስጡበት

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

26 Oct, 17:11


ዓለማቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ በአማራ ክልል በሚካሄደው ግጭት ተፋላሚ ከኾኑ ወገኖች ጋር በምርኮኞች ወይም በእገታ በተያዙ ሰዎች ልውውጥና በሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ዙሪያ ሚስጢራዊ ንግግር መጀመሩን የማኅበሩ ኮምንኬሽን ሃላፊ ሮቢን ዋድዎ እንደነገሩት ሪፖርተር አስነብቧል።

ኾኖም ሃላፊው ጉዳዩ በሚስጢር የተያዘ መኾኑን በመጥቀስ፣ ዝርዝር ጉዳዮችን መናገር እንደማይችሉ መግለጣቸውን
ጋዜጣው ጠቅሷል።

ሃላፊው፣ የዓለማቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበርም ኾነ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በግጭቱ ሳቢያ ከክልሉ የመውጣት ሃሳብ እንደሌላቸው ተናግረዋል ተብሏል።

ማኅበሩ፣ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በተፋላሚ ወገኖች መካከል የምርኮኞች ልውውጥ እንዲደረግ ማስተባበሩ አይዘነጋም።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

26 Oct, 15:17


| ማህበራዊ ሚድያን በመጠቀም በአርቲስቷ ላይ ወንጀል ፈፅሟል የተባለው ግለሰብ በሌለበት በ13 አመት እስራት ተቀጣ

በአርቲስት ሄለን በድሉ እና በቤተሰቦቿ ላይ ላለፉት አምስት አመታት በርካታ ተደራራቢ ወንጀሎችን ሲፈፅም ነበር የተባለው ግለሰብ በሌለበት በ13 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የፍርድ ውሳኔ መተላለፉ ታወቀ።

አሸናፊ ከበደ ብዙወርቅ፣ ወይም በፌስቡክ ስሙ ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ በሚባል ስም የሚታወቀው ግለሰብ በግል ተበዳይ በኩል  ክስ ቀርቦበት የህግ ተጠያቂነት ሲመጣበት ለበቀል በሶሻል ሚድያ ላይ ሰዎችን በግልፅ መልምሎ ወንጀለኞችን በማደራጀት እና ስምሪት በመስጠት ለአካለ መጠን ያልደረሱ በወቅቱ እድሜአቸው 5 እና 7 የነበሩትን የግል ተበዳይ ህፃናት ልጆች ላይ ጉዳት ለማድረስ ታስቦ የተሞከረውን የእገታ ወንጀል አቀናባሪ እና አስፈፃሚ በመሆን ክስ ቀርቦበት እንደነበር ከክሱ ዝርዝር ተመልክተናል።

ይሁንና ከሀገር ውጪ የሚገኘው ተከሳሹ ለተከሰሰበት የወንጀል ድርጊቱ ምላሽ እንዲሰጥ እና በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ከጥር 25/2015 ዓ/ም ጀምሮ በተደጋጋሚ በጋዜጣ የታወጀ እንዲሁም በህግ እንደሚፈለግ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን በሰፊው የተዘገበ ቢሆንም ፍርድ ቤት አለመቅረቡ ታውቋል።

ይሁንና ጥቅምት 7/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከይግባኝ ባይ የፌደራል አቃቤ ህግ የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ  የቀረበለትን ግንቦት 13/2016 ዓ/ም  በከፍተኛ ፍርድ ቤት  የተሰጠውን የ 8 አመት ከ 5 ወር ፍርድ ላይ አቃቤ ህግ ያቀረብውን የይግባኝ አቤቱታ በመመርመር ጥፋተኛውን  ያርማል፣ ሌሎችንም ያስተምራል በማለት እንዲሁም ሌላውም የማህበረሰብ ክፍል ከእንደዚህ አይነት ወንጀል ድርጊት እንዲጠነቀቅ ለማድረግ የ13 አመት ፅኑ እስራት ውሳኔ በአሸናፊ ከበደ ብዙ ወርቅ ላይ ማሳረፉ ታውቋል።

በተጨማሪም ግለሰቡ በኢንተርፓል ተይዞ ማረሚያ ቤት እንዲወርድ ፍርድ ቤት  ትእዛዝ ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎ አስተያየት የሰጠው የአርቲስቷ ባለቤት አቶ ሚካኤል መኮንን "በተፈፀመብን ተደራራቢ ወንጀል ምክንያት ያጋጠመውን የልጆቼን ስነልቦናዊ እና አካላዊ ጉዳት ባይጠግንም በተመሳሳይ ድርጊት ላይ እየተሳተፉ ያሉ ወንጀለኞችን እና ሌላው የማህበረሰብ ክፍል ከእንደዚህ አይነት ወንጀል ድርጊት እንዲጠነቀቅ እና ወንጀለኞች አደብ እንዲገዙ የሚያደርግ አስተማሪ የሆነ የ13 አመት ፅኑ እስራት ውሳኔ ተላልፎበታል" በማለት ቃሉን ሰጥቷል።

ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ "የአርቲስት ሄለን በድሉ ባለቤት የጄነራል ክንፈ ዘመድ ነው፣ የሀብታቸው ምንጭም ግለሰቡ ነው፣ በመኖሪያ ቤታቸውም ጊዜያዊ ባንክ ቤት አለ" የሚል መረጃ በአንድ ወቅት በገፁ አሰራጭቶ እንደነበር ተመልክተናል።


ምንጭ መሠረት ሚዲያ

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

26 Oct, 15:15


#የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ…


ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ የታላቋ ንግስት ሕንደኬ የግዛቷ ሁሉ አዛዥና በገንዘቧም የሰለጠነ ነበር፡፡ ጃንደረባው እንደዘመናችን ሕትመት ባልተስፋፋበት በዚያ ዘመን በ34 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ሊሰግድ ሔዶ ሲመለስ ትንቢተ ኢሳይያስን ያነብ ነበር፡፡

በሐዋርያት ስራ 8÷26 ጀምሮ እንደተጻፈው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ሀዋርያው ቅዱስ ፊሊጳስ በመምጣት ጃንደረባውን እንዲያገኘው አዘዘው፡፡ ሐዋርያውም መጥቶ ባኮስን “በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው፡፡ እርሱም “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ?” ሲል መለሰለት፡፡

ባያስተውለውም፣ ባይገባውም፣ እንደ ዘመናችን ሕትመት ባይስፋፋም ጃንደረባው ግን በሞላው በተረፈው የንግስቲቱ ሃብት ላይ አዛዥ ሆኖ ሳለ ኢየሩሳሌም ሔዶ መስገድና ትንቢተ ኢሳያስን ማንበብ ነበር ምርጫው፡፡ በዚህ ዘመን እግዚአብሔር በሃብት የባረከን ሰዎች በገንዘባችን፣ የት መሔድ፣ ምን ማንበብ፣ ምን ማድረግ፣ ምንስ መስራት ይሆን የምንፈልገው?

የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በጉዞ ላይ ሆኖ ያውም በሠረገላ ላይ ተቀምጦ ማንበብ አለማቋረጥ ምን ያህል ትጋት የሚጠይቅ እንደሆነ እንድታስተውሉ እጠይቃችኋለሁ በቤታቸው እንኳን ቁጭ ብለው ማንበብን ለማይፈልጉ ሰዎች ይህ ታሪክ ሊስተዋል ይገባዋል፤ ይልቁንም መጻሕፍትን ማንበብን ጊዜን እንደማጥፋት የሚቆጥሩ ወይም የተለያየ ምክንያት የሚሰነዝሩ ሰዎች ቅዱሳት መጻሕፍትን የማንበብ ጠቀሜታ አይታያቸውም” የሐዋርያት በማለት ሥራን በተረጎመበት መጽሐፉ አድንቆ ተናግሯል፡፡


ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስም ሲያነበው የነበረውን “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፣ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል እንዲሁ አፉን አልከፈተም። በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ። ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና። ትውሉዱንስ ማን ይናገራል።” የሚለውን በትንቢተ ኢሳይያስ 53÷7 የሚለውን ቃል መነሻ አድርጎ ስለ ጌታችን የሰው ልጅን ማዳንና ፍቅር አስተማረው፡፡ በፈቃዱም አምኖ ተጠመቀ፡፡

ስጋዊ ሃብታችንን የነፍሳችንን ድህነት የምንሰራበት መሳሪያ አድርጎ ሰጥቶናል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የቅዱሳን መካናትን በረከት ለማግኘት እንትጋ፡፡

በዘመናችንም ቅዱሳን ገዳማውያንና አባቶች ያሉባቸውን ገዳማት እናግዝ፣ በፍጹም ልግስና ከሚያልፈው ገንዘባችን ሰጥተን ከማያልፈው የጸሎታቸውን በረከት እንካፈል፡፡ የቅዱስ ፊሊጶስና የጃንደረባው በረከት ይደርብን!!!         

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

26 Oct, 06:43


መረጃ‼️

በአዲስ አበባ በቀን ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች እየታፈሱ በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ካምፕ እየተወሰዱ እንደሆነ ተነገረ

በአዲስአበባ በተለይ ኩዬፈቼ እና አዲሱገበያ በሚባሉ አካባቢዎች የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በቀን ስራ የሚተዳደሩ ወጣቶችን በማፈስ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች እያስገቡ እንደሆነ ተገልፆል ፡፡

ወጣቶቹ ከአካባቢዎቹ ከታፈሱ በሆላ በፖሊስ ጣቢያ ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ታስረው  ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች እንደሚላኩ ታዉቋል ፡፡

በተለይ ከደቡብ ኢትዬጲያ የመጡ ወጣቶች የዚህ ተግባር ተጠቂዎች ናቸዉ ተብሏል፡፡

Via አንኳር መረጃ

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 19:22


ሸገር ሀሳብ ከእርሶ⁉️

ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያ በሆላ ከፍተኛ የሆነ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የግሉ ሴክተር ከፍተኛ ጭማሬን አስተናግደዋል ፡፡

በዚህም ኑሮ ዉድነቱ ተባብሶል ፡፡

ዉድ የሸገር ቤተሰቦች እናንተ ጋር ኑሮ እንዴት ነዉ ? ሀሳባችሁን ስጡበት

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 19:05


ሸገር ሀሳብ ከእርሶ⁉️

የሱማሊያ እና የኢትዬጲያ ጉዳይ የመካከለኛዉ ምስራቅ ጦርነትን በእጅ አዙር ምስራቅ አፍሪካ ላይ እንዳይፈነዳ እየተፈራ ነዉ ፡፡

እስራኤል የጦር ሰፈር ሱማሌላንድ ላይ ልትገነባ መሆኑ ተሰምቶል ፡፡ይሄም ከኢትዬጲያ ቀጥሎ የሱማሌላንድን የሀገርነት እዉቅና የምትሰጥ ሁለተኛዋ ሀገር ያደርጋታል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

በተጨማሪም የእስራኤል ወታራዊ ከፍተኛ መሪ በቅርቡ የግብፅ የዉሃ ህልዉና አብቅቶለታል

ግብፅ ኢትዮጵያን የምተነኩስ ከሆነ እስራኤል እጆን አጥፋ የምትቀመጥ አይሆኑም ሲል መናገራቸዉ ይታወሳል ፡፡

እዚህ ላይ የጦር አሰላለፉ ግብፅን ከሱማሊያ ኢትዬጲያን ከእስራኤል ያገናኛል ፡፡

ቀይ ባህር አጠገብ ኢትዬጲያ መሆኖ እና ያ አካባቢም በአረብ ሃገራት ስር መሆኑ ኢትዬጲያን ሌላ ቅርቃር ዉስጥ ያስገባታል ፡፡

ስለዚህ ጉዳይ የእርሶን ምልከታ ያስቀምጡ?


@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 18:54


መረጃ‼️

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ áŠ áŒˆáˆáŒáˆŽá‰ľ ሰራተኞች ብሄር እና ሀይማኖታቸዉን የሚገልፅ አዲስ ፎርም ሙሉ መባላቸዉን ተናገሩ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ሽፈራው ተሊላ በመስራቤቱ የብሄር እና ሀይማኖት ስብጥር ለማመጣጠን እሰራለሁ በማለት መናገራቸዉ ይታወሳል ፡፡

ስራ አስፈፃሚዉ ኢህአዴግ ሀገሪቷን በሚያስተዳድርበት ጊዜ በሙስና ተጠርጥረዉ 18 ወራትን በእስር ቤት ማሳለፋቸዉ የሚታወስ ነዉ ፡፡

   መረጃዉ የአንኳር ነው

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 18:29


ዜና ዕረፍት‼️

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በአሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ተሰምቷል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 18:22


መረጃ ‼️

በዎላይታ ዞን በርካታ መምህራን መታሰራቸው ተሰማ:: 

እሥሩ የተፈፀመው መምህራኑ ከደሞዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ አቤቱታቸውን ለማስገባት መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ እንደሆነም ምንጮች ገልፀዋል::

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 16:53


ፓስፖርት ለማውጣት "የአምስት ሺሕ ብር ሲስተም የለም" እየተባልን ነው ሲሉ ተገልጋዮች ቅሬታ አቀረቡ

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 20 ሺሕ እና 25 ሺሕ ብር ከሚያስከፍሉት የአስቸኳይ አገልግሎቶች በስተቀር በመደበኛ ከፍያ እያስተናገደን አይደለም ሲሉ ተጋልጋዮች ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ "5 ሺሕ ብር ከፍለን በመደበኛው ጊዜ ፓስፖርታችንን መውሰድ አልቻልንም" ያሉ ሲሆን፤ "ለዚህም የሚሰጠን ምክንያት ‹‹ሲስተሙ አይሰራም›› የሚል ነው" ብለዋል፡፡

አክለውም "የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያውን መምረጥ ያለበት ተጠቃሚው ነው፡፡" ያሉ ሲሆን፤ "በ2 ቀን እንዲደርስላችሁ 25 ሺሕ ብር በ10 ቀን እንዲደርስላችሁ ደግሞ 20 ሺሕ ብር ክፈሉ መባላችን ትክክል አይደለም፡፡ በመረጥነው ክፍያ ልንስተናገድ ይገባል" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ አዲስ የማክሮ ኢኮኖሚይ ማሻሻ ማድረጓን ተከትሎ፤ የክፍያ መሻሻሎች ካደረጉ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች መካከል አንዱ፤ የኢትዮጵያ ኤምግሬሽን የዜግነት አገልግሎት መሆኑ ይታወቃል።

የኢምግሬሽን የዜግነት አገልግሎት ለዜጎች  ፓስፖርት ለመስጠት ሲል የክፍያ እና የጊዜ ቀነ ገደብም አስቀምጧል፡፡

ዜጎች በሁለት ወራት ውስጥ ፓስፖርት ለማግኘት ዝቅተኛው ክፍያ አምስት ሺሕ ብር መሆኑን አገልግሎቱ  በወቅቱ ያሳወቀ ቢሆንም፤ ተገልጋዮች "አምስት ሺሕ ብር ከፍሎ  ፓስፖርት የማግኘት ሲስተም ለጊዜው የለም እየተባለን እየተመለስን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው ሥማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ተገልጋይ በበኩላቸው፤ "የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኢምግሬሽን የዜግነት አገልግሎት የሄድን ቢሆንም፤ ከመጉላለት በዘለለ በፓስፖርት ወረፋ ወቅት ያለው ወከባ እና ግርግር ለደህንነታችን አስግቶናል" ብለዋል፡፡

አሐዱ "ለአስቸኳይ ከፍተኛ ከፋዮች የሚሰራው ሲስተም ለዝቅተኛ ከፋዮች የማይሰራበት ምክንያት ግልጽ አይደለም" የሚለውን የተገልጋዮች ቅሬታ በመያዝ ከኢትዮጵያ የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ፤ የአገልግሎቱ የሥራ ሃላፊዎች ስልክ ባለማንሳታቸው እንዲሁም አንስተው "ጉዳዩ አይመለከተንም" በማለታቸው ምክንያት ምላሹን ማካተት አልቻለም፡፡

(አሀዱ ሬዲዮ)

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 13:34


ትላንት በሰሜን ወሎዋ ወልድያ ከተማ የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ መዘገቡ ይታወሳል
በዚህም በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች በመንግሰት የከተመዋ አመራሮች ላይ ጉዳት መድረሱ ተስምቶል
አመራሮቹን ትኩረት አድረጎ በፋኖ ሀይሎች በተሰነዘረው ጥቃት ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ እስካሁን በመንግስትም ይሁን በፋኖ ሀይሎች በኩል የተባለ ነገር የለም


@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 11:53


ለኦሮሚያ ሚሊሻ ድጋፍ “በግዳጅ” ገንዘብ እንድንከፍል ተደርገናል ሲሉ አሽከርካሪዎች አቤቱታ አቀረቡ‼️

ከትራፊክ ፖሊስ ክስ ቅጣት ጋር ለኦሮሚያ ሚሊሻ መዋቅር ድጋፍ በሚል ተጨማሪ 5 መቶ ብር በግዳጅ እንድንከፍል እየተገደድን ነው ሲሉ የተለያዩ አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን ገለፁ።
ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ወይም ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ አገራት የሚጓዙ የሕዝብ áˆ›áˆ˜áˆ‹áˆˆáˆť ተሽከርካሪዎች፣ የክሱ መጠን ምንም ያህል ቢሆን ለሚሊሻ ጽ/ቤት ድጋፍ በሚል ተጨማሪ 5 መቶ ብር መክፈል ግድ እንደሆነ ለዋዜማ አስረድተዋል።

የክሱን ገንዘብ በሚሰጣቸው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ካስገቡ በኋላ፣ ያስገቡበትን ደረሰኝ ይዘው የመንጃ ፈቃዳቸውን ለመውሰድ ወደ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት በሚያቀኑበት ወቅት፣ ድጋሚ ለሚሊሻ ድጋፍ ከፍላችሁ ተመለሱ እንባላለን ሲሉ የአከፋፈል ሂደቱን ይናገራሉ።

የሚሊሻ ጽ/ቤት ድጋፍ የተባለው ይኸው ክፍያ በሲንቄ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ብቻ የሚከፈል መሆኑን የሚጠቅሱት አሽከርካሪዎቹ፣ ክፍያውን ፈጽመው ደረሰኙን ለመንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሲያስረክቡ ብቻ የመንጃ ፈቃዳቸውን መውሰድ እንደሚችሉ ያወሳሉ።

የተባለውን የሚሊሻ ድጋፍ 5 መቶ ብር ከፍለው ደረሰኙን ለጽ/ቤቱ ከሰጡ በኋላ ግን ጽ/ቤቱ ምንም አይነት የገቢ ደረሰኝ ለአሽከርካሪዎቹ እንደማይሰጥ ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት መረዳት ችላለች።

ይህንኑ ጉዳይ ለማስፈጸም ለአንድ ወይም ለሁለት ቀናት ከሥራ ገበታቸው ውጪ እንደሚሆኑና ሂደቱን ለመጨረስ ያለው መጉላላት አስልቺ እንደሆነ በብሶት ያነሳሉ።
በሌላ በኩል በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ አዲስ አበባ የሚያቀኑ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በየኬላው ላይ በሚቆሙ የጸጥታ ኃይሎች “የኮቴ” በሚል 5 መቶ ብር ለመክፈል መገደዳቸውን ተናግረዋል።

ለአብነትም ከአማራ ክልል ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ የሚያቀና አንድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ያሰበበት እስኪደርስ ስድስት የፍተሻ ኬላዎች ቢኖሩ 3 ሺሕ ብር የመክፈል ግዴታ አለበት ሲሉ አብራርተዋል።
ዋዜማ

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 09:19


ሸገር ጤና‼️


ጋንግሪን(gangrene)

ጋንግሪን አደገኛ እና ገዳይ የሆነ የጤና ችግር እንደሆነ  ይነገራል ፡፡
ስር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች ለዚህ ሕመም ተጋላጭ መሆናቸው ይነሳል፡፡

የጋንግሪን ህመም በተለምዶ በእግር ላይ የሚስተዋል ቢሆንም በየትኛዉም የሰዉነታችን ክፍል ላይ የሚከሰት ህመም ነዉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ጥገና ፣ቅየራና የከፍተኛ ስብራቶች ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ገለታው ተሰማ ናቸዉ።



#ጋንግሪን ማለት ምን ማለት ነዉ?
ከሙሉ አካላችን ተለይቶ የተወሰነ የሰዉነት ክፍላችን እየሞተ ወይም በድን እየሆነ መምጣት ነው ይላሉ፡፡

ይህም በዛ አካባቢ ያሉት የሰዉነት ክፍላችን በቂ የሆነ ደም ፣ ኦክስጅን  እና ምግብ ባለማግኘቱ የሚፈጠር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡




#መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
-  የስኳር ታማሚ መሆን
-  ኢንፌክሽን
-  በአደጋ ምክንያት የደም ሾር መቆረጥ ተጠቃሽ መሆናቸውንም ባለሙያዉ ይናገራሉ፡፡


#የስኳር ህመምተኞችም ማድረግ ካለባቸው ጥንቃቄዎች መካከል የሚያጠብቃቸውን ጫማ ከመልበስ መቆጠብ እንደሆነ  አንስተዋል፡፡



#ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
-  እዛ አካባቢ ላይ መጥቆር እና
-  መድረቅ ዋናዎቹ መሆናቸዉንም ዶክተር ገለታዉ ነግረዉናል፡፡



#ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?
የሚሰጡት ህክምናዎች እንደየ ምክንያቱ እንደሚለያይም ባለሙያዉ ይናገራሉ፡፡
-  ለአንዳንድ ሰዎች የደም ሾር ህክምና የሚሰጥ ሲሆን፤
-  ኢንፌክሽኑን ማከም
-  ከፍ ካለ ደግሞ የተጎዳውን አካል ማስወገድ ከህክምናዎቹ መካከል መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡


#በመጨረሻም የስኳር ህመምተኞች ተገቢውን የህክምና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው እና በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን የጥንቃቄ  መልዕክቶች መከተል እንዳለባቸዉ ዶ/ር ገለታው ተናግረዋል።

ምንጭ ኢትዬ ኤፍ ኤም


@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 09:17


አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና ግጭት መቀስቀስ ወንጀል የተከሰሱትን አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የህገ መንግስትና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ታዲዮስ ታንቱን በተከሰሱበትና ጥፋተኝነት በተባሉባቸው 3 ክሶች ነው የጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት የጣለባቸው።

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በፍትህ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አንደኛው ክስ ላይ እንዳመላክተው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/(1)ሀ እና አንቀጽ 257/ሀ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በግንቦት 11 ቀን እና በመጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም እና በተለያዩ የዩቲዩብ ቻናሎች ህዝባዊ አመጽ መቀስቀስ ወንጀል የሚል ነው።

በ2ኛ ክስ በተመለከተ ደግሞ የጥላቻ ንግግርንና ሀሰተኛ መረጃን ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁ 1185/2012  አንቀጽ 4  እና 7/4 በመተላለፍ በታሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በአንድ የዩቱዩብ ቻናል ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል የሚል ክስ በዐቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

በ3ኛ ክስ ደግሞ የወንጀል ህግ ከንቀጽ 32 /1ሀ ና አንቀጽ 337 በመተላለፍ የመከላከያ ሰራዊትን እቅስቃሴን ለማሰናከልና የመከላከል አደጋ እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ ሀሰተኛ ወሬ በመንዛት ቅስቀሳ ማድረግ ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን በ4ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁ 958/2008 አንቀጽ 14 በመተላለፍ ህዝባዊ አመጽ እንዲፈጠር ቀስቃሽ መልዕክት በድምጽና በተቀሳቃሽ ምስል ተሰራጭቷል የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

በአጠቃላይ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው አራት ክሶች ላይ የተጠቀሱትን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ገልጸው፤ የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዳሉ ያላቸውን ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ምስክርን መርምሮ እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን መስጠቱ ይታወሳል።

አቶ ታዲዮስ እንዲከላከሉ በተሰጠ ብይን መነሻ የተለያዩ የመከላከያ ምስክሮችን አቅርበው አሰምተው የነበሩ ቢሆንም ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ግን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል (ማስተባበል) አለመቻላቸው ተገልጾ በ3 ክሶች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን ለመጠባበቅ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም አቶ ታዲዮስ በዚህ እለት የቅጣት ማቅለያ ማቅረብ እንደማይፈልጉና የጥፋተኝነት ፍርዱን እንደማይቀበሉ ለችሎቱ አስታውቀው ነበር።

ይሁንና ፍርድ ቤቱ ግን የ6 ልጆች አባት መሆናቸውንና የ70 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ሁለት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 24 መሰረት በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

የአ/አ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ ላይ የተጣለውን ቅጣት እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ታሳቢ በማድረግ እንዲያስፈጽም ታዟል።

ዘገባው የፋና ነው።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

25 Oct, 09:17


#ቃሉ እንደ ጽጌረዳ እየተጎነጎነ በስዕሏ እቅፍ ያርፍ ነበር… 

ልዩና ተአምራት የምታደርግ የእመቤታችን ሥዕል በመመልከቱ በጻድቁ አባ ዜና ማርቆስ አስተማሪነት ከአይሁዳዊነት ወደ ክርስትና የተመለሰው አባ ጽጌ ድንግል ከመስከረም 26 እስከ ሕዳር ስድስት ቅድስት ድንግል ማርያም የምትመሰገንበትን ማኅሌተ-ጽጌን የደረሰ አባት ነው፡፡ በምንኩስና ሕይወት ሲኖርም ለሥዕሏ ካለው ፍቅር የተነሳ ሳያያት ውሎ አያድርም፡፡ ሊያያት ሲሔድም እጅ መንሻ ይሆነው ዘንድ በሃምሳ ጽጌረዳ አበባዎች ጉንጉን በመስራት በስዕሏ ዙሪያ ያስቀምጥ ነበር፡፡

በቅዱሳን ሥዕላትን ፊት ስንቀርብ ቅዱሳን መካናትንና ገዳማትን ስንሳለም ምን ይዘን ነው የምንሔደው? እንደየአቅማችን መባዕ ይዘን የመሔድ ዝንባሌያችንስ ምን ይመስላል? ምድራዊ ዘመዶቻችንን ስንጠይቅ እንኳ ባዶ እጃችንን አንሔድም እኮ፡፡ ይልቁንም ለቅዱሳን ቦታዎች እንጅ መንሻ ይዞ መሔድ በረከቱ ከፍ ያለ ነው፡፡

አባ ጽጌ ድንግል አበቦች በሚደርቁበት ወራት በዚህች ሥዕል ፊት ሲቆም ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ደስታ ይገባሻል እያለ እንዳመሰገናት “በአበባው ቁጥር ልክ እንዳመሰግንሽ ፍቀጂልኝ” በማለት እመቤታችንን ለመናት፡፡ እርሷም እንደፈቀደችለት ያሳየችው በገሃድ ነበር፡፡ እርሱ በየቀኑ ሃምሳ ጊዜ ሲያመሰግን ከአፉ የሚወጣው ምስጋና እንደ ጽጌረዳ አበባ እየሆነ እመቤታችን ተቀብላ ስትታቅፈው በዙሪያው ያሉ ሰዎች እያዩ ክብሯንና ገንናነቷን ያደንቁ ነበር፡፡ በኋላም ማኅሌተ ጽጌዋን ለመድረስ የሚያስችል በረከት አድላዋለች፡፡

ከልብ የሆነ ስጦታ እንዲህ ነው፡፡ ቅዱሳን ገዳማትንና ገዳማውያንን ስንረዳ የቅዱሳኑ በረከታቸው፣ ጸጋቸው ያድርብናል፡፡ በጸሎታቸው ትሩፋት እንጠበቃለን፡፡ ጥቂት ሰጥተን ብዙ እንሰበስባለን፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የወርሃ ጽጌዋ ረድኤትና አማላጅነት፣ የአባ ጽጌ ድንግል በረከት አይለየን፡፡
           

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

25 Oct, 04:29


"ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት"

በማለት አርቲስት አዜብ ወርቁ ታሪካቸውን የፃፈችላቸው የእድሜ ባለፀጋ ህይወታቸው አለፈ


"ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት" በማለት አርቲስት አዜብ ወርቁ ታሪካቸውን የፃፈችላቸው የእድሜ ባለፀጋ ህይወታቸው ማለፉ ታወቀ።

መስከረም 4 ቀን አርቲስት አዜብ የልማት ተነሺ ተብለው ሰዎች ድንገት ቤታቸው ሲፈርስ ስለገጠማቸው ጉዳት ለማሳየት ታሪካቸውን ያጋራችላቸው ግለሰብ ታሪክ እንዲህ ይነበባል:

"ገና ጎረምሳ እያለ ከተወለደበት ገጠር ወጥቶ 250 ኪሎሜትር በእግሩ ተጉዞ አዲስ አበባ ገባ። አዲስ አበባ የግለሰቦች ንግድ ቤት ተቀጥሮ ከጽዳት አንስቶ የተለያዩ ስራዎችን ሰርቶ ከራሱ አልፎ  ወላጆቹን ቤተሰቡን ረድቶ፣ ትዳር መስርቶ፣ ልጆች አፍርቶ፣ የግል ንግድ ከፍቶ ሲኖር ቆይቶ የዛሬ 60 ዓመት አካባቢ ከፈረንሳይ ኢምባሲ ወረድ ብሎ ከሃይዌዩ ድልድይ ሾር የግንብ ግድግዳ ላይ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” የሚለው ጽሁፍ በደማቁ በቀይ ቀለም ከተጻፈበት ፊትለፊት ወደ ቤላ በሚወስደው ቀኝ መታጠፊያ መንገድ ላይ መሬት ገዝቶ ቆንጆ ቤት ሰርቶ ኑሮውን መሰረተ።

12 ልጆችን አሳድጎ፣ አስተምሮ ለወግ ለመዓረግ አበቃ፣  የልጅ ልጅ አየ። አሁን የ 94 ዓመት አዛውንት ነው። ጠንካራ፣ ደግ፣ ሰራተኛ፣ ተጫዋች፣ ቀልድ አዋቂ፣ ሰው ሁሉ የሚወደው፣ ሰውን ሁሉ የሚወድ፣ ሃይማኖቱን አክባሪ እምነቱን አጥባቂ ነው። የግቢ አትክልት ይወዳል፣ ግቢው በወይን፣ በአቩካዶ፣ በኮክ፣ በአፕል፣ በቡና ዛፍ የተሞላ የሚያምር ግቢ ነው። የአትክልት ፍቅሩ ለልሹ ቤት ብቻም አይደለም፤ ሰፈር ውስጥ እየዞረ በሰው ቤት በዘመድ ቤትም ችግኝ  ከቤቱ እየወሰደ ይተክላል።

ይህ ጠንካራ ሰው በቅርቡ በህመም አልጋ ላይ ዋለ ፥ “በቂ ኖሬያለሁ ሆስፒታል እንዳትወስዱኝ በኖርኩበት ባረጀሁበት ቤት አስከሬኔ ይውጣ” አለ። ልጆቹ ቃሉን አከበሩለት ቤቱ ውስጥ እንዳለ ሀኪም እያየው በልጆቹ፣ በልጅ ልጆቹ  በቤተዘመድ በጎረቤት ተከቦ እንዲያስታመሙት አደረጉ። ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የ አዲስ ዓመት ዋዜማ በሰፈሩ አንድ ዜና ተሰማ፣ ከወረዳ የመጡ ሰዎች እየዞሩ ለልማት እየመዘገቡ ነው የሚል። የአዲስ ዓመት በዓል ማግስት መስከረም 2 መጥተው በ20 ቀን ውስጥ ቤታችሁ ለልማት ሊፈርስ ስለሆነ ለመስከረም 3 ጠዋት ለስበሰባ ኑ የሚል መልእክት በቃል ብቻ ተነገረ።

እንዲህ ያለ ዱብ እዳ ሲሰማ ለህግ ጉዳይ መዋሉ ቢቀር እንኳን ህልም ይሆን እንዴ ብሎ ድጋሚ አይቶ ለማረጋገጥ የሚያስችል ብጣቂ ወረቀት አልተሰጠም፣ ልክ እንደ ክፉ መርዶ ነጋሪ በር አንኳኩተው በቃል ትዕዛዝ ሰጥተው ሄዱ።

መስከረም 3 በስብሰባው ላይ ስልክም ሆነ ማንኛውም ድምጽ እና ምስል መቅጃ ይዞ መግባት ባልተፈቀደበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢዎቹ  ቤታችሁ ለልማት ይፈርሳል የሚለው መርዶ ተነገራቸው። ለምን? ለጫካ ፕሮጀክት ልማት። መቼ? እስከ መስከረም 20። ተሰብሳቢው ደነገጠ “ልጆቻችንን ትምህርት ቤት አስመዝገበናል፣ ዩኒፎርም አሰፍተናል፣ የደከመ ታማሚ  ቤታችን ስላለ ጊዜው አይበቃንም፣ የእለት ጉርሴ ከቤት ኪራይ የማገኘው ብቻ ነው፣ ምን ልሁን? የሚሉ አዛውንቶች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ጮኸው አልቅሰው ተናገሩ። ሁለት ሳምንት አላችሁ ተባሉ። ይህ ቤተሰብ የመራ፣ ሀገር ያቀና፣ ስንቱን ያስተማረ፣ የዳረ፣ አስታሞ በክብር የቀበረ፣ የተጣላን አስታራቂ የሐገር ሽማግሌ፣ አልጋ የያዘ መንቀሳቀስ፣ መንቃት የማይችል፣ ፈጣሪው ጋ እስኪሄድ ቀኑን የሚጠብቅ አረጋዊ እስከ መስከረም 20 ይነሳ ቤቱ ይፈርሳል ተባለ።"

አርቲስት አዜብ ወርቁ በዚህ መልኩ ታሪካቸውን ካጋራች በኋላ ለእስር ተዳርጋ ነበር።

አሁን ላይ መሠረት ሚድያ በደረሰው መረጃ እኚህ ግለሰብ ቤታቸው ይነሳል በተባለበት እለት፣ ማለትም መስከረም 20 ቀን ህይወታቸው አልፏል።

የአካባቢው ነዋሪዎች የሰጡን መረጃ እንደሚጠቁመው የእድሜ ባለፀጋው ግለሰብ ቤታቸው ከመፍረሱ በፊት እንደ ምኞታቸውም አስከሬናቸው ከመኖሪያ ቤታቸው ተሸኝቷል፣ ቤተሰቦቻቸውም፣ ጎረቤት፣ እድሩም ሀዘናቸውን በመኖሪያ ቤታቸው በተገቢው ሁኔታ አስተናግደዋል።

ምንጭ :- መሠረት ሚዲያ


@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

24 Oct, 18:51


በኮሪደር ልማት ምክንያት የፈረሰው ገዳም የድጋፍ አርጉልኝ ጥሪ አሰምቷል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰበታ ጌቴሴማኒ ቤተ ደናግል ጠባባት ገዳም በኮሪደር ልማት ምክንያት የገዳሙ በርካታ መገልገያዎች እየፈረሱ ስለሆነ ህዝብ ይርዳን ብለዋል።

አጥር፣ ወፍጮ ቤት፣ ዕደ ጥበባት ክፍሎች፣ የአፀደ ህፃናት የመኝታ ክፍል፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላቦራቶሪዎች፣ የመማርያ እና የመፀዳጃ ክፍሎች፣ የካህናት መኖርያ እና ደጀ ሰላም፣ እንዲሁም የቤተክርስቲያኑ መጠለያ እና ቤተልሔም በመፍረስ ላይ እንዳሉ ታውቋል።

ገዳሙ በውስጥ ከ215 በላይ ወላጅ የሌላቸው ሴቶች ህፃናት የሚያድጉበት እና 105 የሚሆኑ መነኮሳት የሚኖሩበት የሴቶች ገዳም እንደነበር ታውቋል።

ነገር ግን ፈረሳው ለተለያዩ አደጋዎች ሊያጋልጣቸው ስለሚችል አጥር ለማጠር እንዲችሉ ትብብር እንዲደረግላቸው ተማፅነዋል።

Via መሠረት ሚዲያ

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

24 Oct, 18:41


መረጃ‼️

ተቃዋሚው እናት ፓርቲ፣ በአዲስ አበባ ከሚካሄደው የኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ በከተማና በዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች የአምልኮ ሥፍራዎች ሕጋዊ ይዞታዎች ድንበር በማን አለብኝነት እየፈረሰ እንደሚገኝ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ፓርቲው፣ የገዥው ብልጽግና ፓርቲ መንግሥት የአብያተ እምነት ይዞታዎችን በማፍረስ የሚተገበረው  ልማት የሥርዓቱ እድሜ አብቅቶ በሌላ ሲተካ፣ የአምልኮ ይዞታዎች ወደ ቀደሞ ይዞታቸው መመለሳቸው አይቀሬ ነው ብሏል፡፡

በኮሪደር ልማት የሚካሄደው የማፍረስ ተግባር የአምልኮ ቦታዎችን ፈጽሞ እንዳይነካ ያሳሰበው ፓርቲው፣ መንግሥት ከነባር ሃይማኖት ጠል አካሄዱ እንዲታቀብና የአብያተ እምነት ይዞታዎችን ማፍረሱን በአፋጣኝ እንዲያቆም ጠይቋል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

24 Oct, 18:28


ጅ ኤስ ኤም ኤ የተሰኘው ዓለማቀፍ ተቋም፣ ዲጂታል ኢኮኖሚ በኢትዮጵያ አገራዊ አጠቃላይ ምርት ላይ በቀጣዮቹ አራት ዓመታት 1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር ይጨምራል የሚል ግምት እንዳለው ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ገልጧል።

በቴሌኮም ዘርፉ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችና የሞባይል ቴክኖሎጂዎች፣ በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግና በአገልግሎት ዘርፎች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ለ1 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥሩና 57 ቢሊዮን ብር የሚገመት የታክስ ገቢ እንደሚያስገኙ ሪፖርቱ ይጠቅሳል።

በእነዚሁ ዓመታት ውስጥ 50 ሚሊዮን ዜጎች የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የሚገልጠው ሪፖርቱ፣ ባኹኑ ወቅት 76 በመቶው ሕዝብ በሞባይል ኔትዎርክ ክልል ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም፣ የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ያብራራል።

ተቋሙ፣ የዲጂታል ዘርፉን ለማስፋፋት ከዘርፉ ጋር ተያያዥ የሆኑ አንዳንድ ታክሶችን መቀነስ እንደሚገባ መክሯል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

24 Oct, 12:37


ምደባ ይፋ ሆነ‼️

የ2017 ዓ. ም የዪኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

🙅‍♂️የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር አያስተናግድም‼️


የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች👇

🌐WEBSITE:
https://placement.ethernet.edu.et

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

24 Oct, 09:52


"የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ መስፈሩ ይህ ነው የሚባል ለውጥ አላመጣም፣ እንዲያውም የአልሸባብ እንቅስቃሴ እንዲጨምር አድርጓል” -ሶማሊያ

ባለፉት ግዜያት የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ መስፈሩ ይህ ነው የሚባል ለውጥ አላመጣም እንዲያውም የአልሸባብ እንቅስቃሴ እንዲጨምር አድርጓል ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።ሶማሊያ በቀጣይ ከአፍሪካ ሀገራት ተወጣጥቶ ተልዕኮ ተሰጥቶት በግዛቴ በሚሰፍረው ጦር ዙሪያ የትኞቹ ሀገራትን ማዋጣት አለባቸው የሚለውን የምመረጠው እራሴ ነኝ ስትል ገለጸች።

ሶማሊያ ይህንን የገለጸችው የአፍሪካ ህብረት በሚያሰማራው ጦር ዙሪያ ኢትዮጵያ ስለሚኖራት ሚና እና ስለሶማሊያ ሉዓላዊነት በሚያትተው የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ላይ ነው።

“ኢትዮጵያ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በተናጠል የምትወስዳቸው እርምጃዎች የሀገራችንን ሉዓላዊነት የጣሰ ነው፣ ይህም በሀገሪቱ ላይ ያለንን እምነት የሸረሸረ ነው” ሲል የገለጸው መግለጫው ከሶማሊላንድ ጋር የደረሰችውን ስምምነት በአብነት አስቀምጧል፤ “በሰላም ማስከበር ሂደት ላይ ወሳኝ እና አስፈላጊ የሆነውን መተማመን እንዳይፈጠር አድርጓል” ሲል ኮንናል።

Via Addis Standard


@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

24 Oct, 08:57


#የሞቱት አሕዮች ጭንቅላት ተቀያይሮ ቢገጠምም…

በቅድስት ቤተ ክርስቲያችን ትልቅ ስራ ከሰሩና ትልቅ ተጋድሎ ካላቸው ቅዱሳን አባቶች አንዱ ቅዱስ ቶማስ ዘመራስ ነው፡፡ መራስ የትውልድ ሀገሩ ናትና በዚያው ይጠራል፡፡

ዲዮቅልጥያኖስና መክስሚያኖስ በክርስቲያኖች ላይ መከራ ባጸኑበት ዘመን ለ22 ዓመታት የተጋደለው ይህ ድንቅ ሰማዕትና ሐዋርያ ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በሰጊድ፣ ቀንና ሌሊትም በመትጋት ለድኆችና ለምስኪኖችም በመራራት ተጠምዶ የኖረ ነበር፡፡

በጨካኞቹ ነገስታት ዘመንም ለጣኦት እንዲሰግድ የደረሰበትን መከራ ታግሶ በክርስቶስ ፍቅር በመጽናቱ በ22 ዓመታት የመከራ ጊዜው ጨለማ ውስጥ ጥለውት አካሉን እየቆራረጡ ለጣዖታቸው ያጥኑ ስለነበር 2 እግሮቹ፣ 2 እጆቹ፣ 2 ጀሮዎቹ፣ አፍንጫውና ፪ ዐይኖቹ አልነበሩም፡፡ የተጣለበትን ስፍራ የምታውቅ አንዲት ሴትም በስውር እየገባች ትመግበው ነበር፡፡

እኛ በዘመናችን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍቅር የትኛውን አካላችን እንድንሰዋ አልጠተየቅንም፤ ወይም በረሀብ አልተቀጣንም፡፡ ይልቁንም በነጻነት የምናመልክበት እድል እነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን መከራውን ታግሰው ባቆዩልን እምነት መጽናትና ቤተ ክርስቲያናችንን በተሰጠን ስጋዊና መንፈሳዊ ሃብት ማገዝ ብቻ ነው የሚጠበቅብን፡፡

የቤተክርስቲያን የመከራ ዘመን አልፎ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ስልጣን ከተረከበ በኋላ በኒቂያ ጉባኤ አርዮስን ለማውገዝ ከተሰበሰቡት 318 ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ቶማስ ዘመራስ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ስጋዊ አካሉ የጎደለውን ቅዱስ ሰማዕት በቅርጫት አድርገው በአሕዮች ጭነው ለቀናት ተጉዘው ነበር ወደ ኒቂያ የወሰዱት፡፡ በመንገድ ላይ ሳሉም ካደሩበት ቦታ የአርዮስ ተከታዮች የአሕዮቹን ራስ ቆርጠው ገድለዋቸው ሔዱ፡፡

ምንም እንኳን ሁለት አይኖቹ ቢጠፉም መንፈሳዊ ምጥቀቱ ከፍ ያለ ነበርና በሌሊት ገስግሰው ሊጓዙ ሲነሱ የአሕዮቹን ሁኔታ ደቀ መዛሙርቱ ሲነግሩት ቀድሞ አውቆት ነበርና ጭንቅላታቸውን ከአካላቸው ጋር እንዲገጥሙት አዘዛቸው፡፡

ከዚያም ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት አሕዮቹ እደገና ነፍስ ዘርተው ተነስተው መንገዳቸውን ቀጥለዋል፡፡ አስገራሚው ነገር በጨለማው ምክንያት አንዱን ከአንዱ መለየት ስላልቻሉ የነጩን አሕያ ጭንቅላት ለጥቁሩ፣ የጥቁሩንም ለነጩ እንደገጠሙላቸው ጠዋት በብርሃን አዩት፡፡

ቅዱስ ቶማስ ዘመራስም አርዮስን አውግዞ ወደ ሀገሩ ስብከቱ ተመልሶ ጸሎተ ሃይማኖት የተባለውን ጸሎት ለሕዝቡ አስተምሯል፡፡ በተጨማሪም ለ40 ዓመታት በጵጵስና አገልግሎ አልፏል፡፡ ቅዱሳን አባቶች በትልቅ መስዋዕትነት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተው ያቆዩዋትን እምነት ለመጠበቅ እጃችንን እንድንዘረጋ መጠየቅ በራሱ ከበረከታቸው መካፈል ነውና ገዳማትን እንርዳ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

20 Oct, 19:57


አሳዛኝ መረጃ‼️

ኬብሮን በአጋቾች ተገድላ ተገኘች

ታዳጊ ኬብሮን ከሁለት ወራት በፊት ተወልዳ ባደገችበት ጎንደር ቀበሌ 18 በታጋቾች ታግታ መወሰዶ የሚታወስ ነበር ፡፡

ዛሬ በተሰማ መረጃ ታዳጊ ኬብሮን ተገድላ መገኘቶ ተነግሮል።

ያ በክራንች የሚሄደው አባቷም ቅስሙ ተሰብሯል😢

VIA አንኮር መረጃ


@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 19:11


19 የመንግስት ፀጥታ ሀይሎች ተገደሉ‼️

በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን እራሱን የኦሮሚያ ነፃነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራዉ ኦነግ ሸኔ  በወሰደዉ ጥቃት 19 የመንግስት ፀጥታ ሀይሎች እንደተገደሉ ሸገር ከአንኳር መረጃ ሰምቷል ፡፡

ሰሞኑን በአካባቢዉ በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል ኤርፖርት  ድረስ የደረሰ ከፍተኛ ዉጊያ ሲያደርጉ እንደነበር የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡

በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ ከጃል መሮ የኦነግ ክንፍ ተገንጥሎ ከወጣ ታጣቂ ቡድን ጋር ድርድር መጀመራቸዉን መናገራቸዉ የሚታወስ ነዉ ፡፡

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 18:48


መዳን የማይችሉ ሰዎችን ህይወት ማቋረጥ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ለፓርላማ ቀረበ

- የእንስሳት ወይም የባዮቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለንቅለ ተከላ ሕክምና መጠቀም የሚፈቅድ ረቂቅ ህግም ተዘጋጅቷል

መዳን የማይችሉ ሰዎችን ህይወት ማቋረጥ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ለፓርላማ መቅረቡን መሠረት ሚድያ ሰምቷል።

በመሳሪያ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ የሚደነግገው ይህ ረቂቅ ህግ "የጤና አገልግሎት አስተዳደር አዋጅ" ተብሎ የቀረበ ሲሆን አላማውም የሃገሪቱን እድገት ለማሳለጥና የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል በሚደረግ ጥረት የልማቱ አንቀሳቃሽ የሆነውን ሕዝብ ጤንነት በተሟላ ሁኔታ መጠበቅ እንደሆነ ረቂቅ አዋጁ ጠቅሷል።

በዚህም መሰረት ህጉ በፓርላማ ሲፀድቅ በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን ማቋረጥ የሚፈቅድ ሲሆን ይህም የሚቻለው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሰራር ሥርዓት መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው ብሏል።

የዚህ አንቀጽ ዝርዝር አፈጻጸም የጤና ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል የሚለው ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ በማይድን ህመም የሚሰቃዩ ዜጎችን በተመለከተ ረቂቅ አቅርቧል፣ ህጉ ከፀደቀ በአፍሪካ የመጀመርያውም ይሆናል። 

በአለም ዙርያ ይህ አሰራር እጅግ አከራካሪ ሲሆን በበርካታ አገራት የተወገዘ እና አድራጊዎቹም በህግ የሚቀጡበት አሰራር አላቸው።

በዚህ አሰራር መሰረት ታማሚው እና የታማሚው ቤተሰብ ሲፈቅዱ የህክምና ባለሙያዎች የታማሚውን ህይወት ማቋረጥ ወይም ወደ ሞት መውሰድ ይፈቀድላቸዋል።

እስካሁን ድረስ ይህን ድርጊት በህግ የፈቀዱት ሀገራት ጥቂት ሲሆኑ እነሱም ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ኢኳዶር፣ ሉግዘምበርግ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኒው ዚላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን እና አውስትራሊያ ናቸው።

በተያያዘ ዜና ይህ ለፓርላማ የቀረበ ረቂቅ ህግ የእንስሳት ወይም የባዮቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለንቅለ ተከላ ሕክምና ስለመጠቀም አዲስ ድንጋጌ ያስቀመጠ ሲሆን ከእንስሳት ወይም ከባዮቴክኖሎጂ የተገኙ ውጤቶችን ለንቅለ ተከላ ሕክምና አገልግሎት እንዲውሉ የጤና ሚኒስቴር ሊፈቅድ ይችላል ብሏል።

ይሁንና ረቂቅ ሰውን ወይም የሰው አካልን ወይም ህዋስ ወይም ዘረመልን በቴክኖሎጂ አማካኝነት ቅጂ ማድረግ፣ ማራባትና ማሻሻል የተከለከለ ነው ብሏል።

መረጃን ከመሠረት!

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 17:57


ከንቲባ አዳነች አቤቤ "የ97 የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች የሚባል አናውቅም " አሉ

ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

በብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨውና ትኩረቱን የኮሪደር ልማት ላይ ባደረገው በዚህ ውይይት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢሕአፓ ) የአዲስ አበበ ኮሚቴ ሰብሳቢ አበበ አካሉ
የ97 ተመዝጋቢዎችን የተመለከተ ጥያቄ ይሰነዝራሉ።

ፖለቲከኛው ጥያቄያቸውን ሲጀምሩ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ሰዎች የሚሰጠው የኮንዶሚኒየም ቤቶች እና ከተማ አስተዳደሩ ላይ የ97 ተመዝጋቢዎች ያነሱታል ያሉትን ሀሜት በማስቀደም ነው።

<< እኛ በቆጠብነው ገንዘብ ነው ተፈናቃዮች ወይም የልማት ተነሺዎች እያሰፈሩ ነው የሚል እሮሮ አለ >> ያሉት አበበ << ለዚህ ምን ምላሽ ነው ያላችሁ፤ ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች ...መቼ ነው የሚኖሩበት? ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ >> ሲሉ በስሜት ተሞልተው ጠይቀዋል።

ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ << የ97 የሚባል የለም >> በማለት ማብራሪያቸውን ይጀምራሉ።

ከንቲባዋ ሲቀጥሉ << [ እኛ እስከምናውቀው ድረስ ] የ97 የሚባል ዘግተናል >> ሲሉ ተናግረናል።

<< ባለፈው ያስጨረስናቸውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቅድማያ ለ97 active [ ንቁ ] ቆጣቢዎች ሁሉ ዕጣ እንዲወጣላቸው ተደርጓል >> ሲሉ አስታውሰዋል።

አክለውም << እነርሱ እንዲወጣላቸው ከተደረገ በኋላ deactivate ያደረገውን [ የዘጋውን] አካውንት activate [መቆጠብ የጀመረ ] ያደረገ ካለ
እሱ ለሚቀጥለው ጊዜ ..ያው ቆጥቧል፤ ቤት ስለሚፈልግ ነው activate  የሚያደርገው ሊታይ ይገባል እንጂ በዚህ መንገድ መቅረብ ያለበት አይመስለኝም >> ሲሉ ደምድመዋል።

Via አሻም

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 15:40


አፋልጉን‼️

የ13 ዓመት ታዳጊዋ እህታችን
''ብርቱካን ማሙ ፈጠነ''
በአዲስአበባ ልደታ ክፍለከተማ ከባልቻ ሆስፒታል ጀርባ ከሚገኘው የሰራዊት መኖሪያ ካምፕ (መሃንዲስ ግቢ) በድንገት ወጥታ ለቀናት ጠፍታብናለችና ያለችበትን የምታውቁ ወይም ያያችኋት ካላችሁ ብታሳውቁን ውለታ ከፋይ ነን።

ፈላጊ ቤተሰቦቿ

ስልክ ቁጥር:- 0945-99-15-92
0944-21-90-90

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 13:30


ከአቡሎ አርፋጮ ወደ አርባምንጭ ከተማ 16 ሰዎችን እና ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ባሳለፍነው ሐሙስ 10 ሠዓት ከ20 ገደማ ጫሞ ሐይቅ ላይ ሰጥማ ነበር።

ይህ ተከትሎ እየተከናወነ ባለ የነፍስ አድን ሥራ ትናንት 2 ዛሬ ደግሞ 10 አስከሬን መገኘቱን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አሳውቋል።

በሌላ በኬሉ እስከ ዓርብ ድረስ 3 ሰዎች በሕይወት መገኘታቸውን ገልጿል።

በአጠቃላይ በጀልባ ከተሳፈሩት መካከል እስከ አሁን የአንዱ ሰው ሁኔታ ስላልታወቀ ፍለጋው መቀጠሉ ተመላክቷል።

ፖሊስ የአደጋው መንስኤን በተመለከተ ፥ " የጀልባዋ የመጫን አቅም 35 ኩንታል ሆኖ ሳለ በዕለቱ 70 ኩንታል ሙዝ እና 16 ሰዎችን ጭና ነበር፤ ይህም ከልክ በላይ መጫን በመሆኑ ለአደጋው መከሰት መንስዔ ሆኗል " ብሏል።
FBC

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 12:50


"በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ወደ መሬት ለመውጣት ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ቅልጥ አለት አሁን ረገብ ብሎ ወደ ታች መውረድ ጀምሯል"

የመሬት መንቀጥቀጡ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የመሬት ንዝረት አስከትሎም ነበር።

በኢትዮጵያ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ለ22 ቀናት ወደ መሬት ለመውጣት ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ቅልጥ አለት የመወጠር ሁኔታ አሁን ረገብ ብሏል፤ አሁን ባለን መረጃ ቅልጥ አለቱ ወደታች እየወረደ ነው ብለዋል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዝክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 11:52


EBS በይፋ ይቅርታ ጠይቋል‼️

ሰሞኑን የኮንታ ዞን ጨምሮ በተለያዩ ድረገጾች አማካኝነት EBS TV ይቅርታ ማለት አለበት በማለት ብዙዎች ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል::

EBS ም ይህን ግምታዊ በማድረግ ለኮንታ ማህበረሰብ ይቅር በሉን ብሎ በይፋ ዛሬ እሁድን በEBS ይቅርታውን ተናግሯል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 11:12


ጥቆማ‼️

ከአዲስአበባ ወደ ደሴ ጉዞ የምታደርጉ ተሳፋሪዎች መረጃ እየተከታተላችሁ ብትንቀሳቀሱ ጥሩ ነዉ ፡፡

ዛሬ ብዙ ተሳፋሪዎች ደብረብርሃን አለፍ ብሎ ጉዶበረት  በሚባል ቦታ ላይ መንገድ በመዘጋቱ እየተቸገሩ ይገኛል ፡፡(አንኳር)

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 10:17


በአምስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡

በወንዶች የአምስተርዳም ማራቶን ውድድር ጸጋዬ ጌታቸው ርቀቱን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ አሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የቦታውን ሪከርድ በመስበር ማሸነፍ ችላለች፡፡

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 07:20


አዲስ አበባ የተፈፀመ‼

ትናንት ሜክሲኮ ጋር አንዲት እናት ልጇን ይዛ እየለመነች እያለ ደንብ አስከባሪዎች መጥተው ሂጂ ከዚህ ሲሏት እናትም ይሄው ውሰዱት ብላ ልጇን ጥላ መጥፋቷን ሰምተናል።ያሳዝናል ።

ኧረ በልክ አርጉት (Wasu mohhamed)

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 06:22


አዲስ አበባ‼

ሹመታቸው በተወካዮች ም/ቤት ያልፀደቀው አዲሱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የመጀመሪያ እንግዳቸውን ቦሌ ሄደው ተቀብለዋል።

የዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እንግዳ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ/ር) ናቸው።ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፓትሪስ ሞትሴፔ በኢትዮጵያ በሚካሄደው 46ኛ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነው አዲስ አበባ የገቡት።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 06:10


የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ አዲስ አበባ ገቡ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፓትሪስ ሞትሴፔ በኢትዮጵያ በሚካሄደው 46ኛው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነው አዲስ አበባ የገቡት።

ፕሬዚዳንቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና ሌሎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

46ኛው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ከነገ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

20 Oct, 06:04


#ባልዋም ቅድስቲቱን ሊያያት ቢመጣ ዐርፋ አገኛት…

እስራኤል ተወልዳ ያደገችውና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ያደገችው እናታችን ቅድስት አርዋ መልክና ደምግባታቸው እጅግ ድንቅ እንደሆነ ከሚነገርላቸው ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት፡፡
በሕጋዊ ጋብቻ ተወስና ስትኖር ከደም ግባቷ የተነሳ ባሏ ለንግድ ወደ ሩቅ ሀገር በሔደ ጊዜ፣ የባሏን ወንድም ለጊዜያዊ የዝሙት ፍላጎቱ አብራው እንድትወድቅ የጠየቃትና በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት አልሰራም ስትለው በሀሰት ክስ በድንጋይ ተወግራ እንድትገደል ያደረጋት፣ እግዚአብሔር ግን ከሞት ያስነሳት ከዚያ በኋላም በርካታ መከራ የተቀበለች እናት ናት፡፡

የሰው ልጅ ከበላ ከጠጣ የስጋ ፍላጎቱ ይነሳሳልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አንድ ወንድ በአንዲት ሴት፣ አንዲት ሴት በአንድ ወንድ ፈቃዳቸውን ይፈጽሙ ዘንድ በሕግና በቅዱስ ጋብቻ ይወሰኑ ትላለች፡፡

ቅዱስ ጳውሎስም በዕብ 13 ፥ 4 “ጋብቻ ቅዱስ፣ መኝታውም ንጹህ ይሁን” ይለናል፡፡ ቅዱሳን እናቶችና አባቶች ደግሞ ራሳቸውን የክርስቶስ ሙሽሮች አድርገው የዘመናችን ትልቅ የዲያብሎስ ውጊያ መገለጫ የሆነውን የዝሙት ጦር ታግለው ያሸነፉ በርካታ ገዳማውያን በዘመናችንም ዓለምን ንቀው መንነው በዱርና በገደል ራሳቸውን ለፈጣሪያቸው አስገዝተው ይኖራሉ፡፡ ስንጎበኛቸው የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡    

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን "መዋኢተ ፍትወት" “የሥጋን ፍላጎት ድል የነሳች” የሚል ስያሜ ያሰጣት እናታችን ቅድስት አርዋ በተለይ መልክና ደምግባቷ ተማርከው አብረዋት ሊተኙ የሚፈልጉ ወንዶች በበርካታ መከራ ውስጥ እንድታልፍ ቢያደርጓትም ታግሳ በማለፏ ነበር ይህ የክብር ስም የተሰጣት።
የሚገርመው የቅድስቷ እናታችን ሕይወት በጾምና በጸሎት ብቻ የተወሰነ አልነበረም። በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን መሆን የቻለ የደግነት፣ ርኅራኄ፣ የፍቅርና የምጽዋት፣ በጸሎቷ ድውያንን የመፈወስም ሕይወትም ነበራት እንጂ።

ከዓመታት በኋላ ግን ባሏ ዓይኑን ታውሮ፣ እንደ ማንኛውም ሕመምተኛ በጸሎቷ ተአምር ሊፈወስ መጣ፡፡ ከተፈወሰ በኋላም እሷነቷን ገለጠችለት፡፡ አልበደላትምና ቃል ኪዳኗን ማፍረስ አልፈለገችምና ወደ ቤቱ ሊወስዳት ባለ ጊዜ እንቢ አላለችም፡፡ ይሁንና ራሷን ለክርስቶስ ስላጨች “ጌታዬ ፈቃድህስ ቢሆን ከዚህ በኋላ ከወንድ እቅፍ ይልቅ፣ ባንተ እቅፍ መኖር እፈልጋለሁና ነፍሴን ከስጋዬ ለያት” ስትል ጸለየችና በፊቱ ሰገደች፣ ወዲያውም ነፍሷ ከስጋዋ ተለየች፤ ባልዋም ቅድስቲቱ ስትዘገይበት ሊያያት ቢመጣ ዐርፋ አገኛት፡፡

ገዳማውያን እናቶችና አባቶች ዓለምንና ፍላጎቷን የዚህን ያሕል ንቀው ራሳቸውን የክርስቶስ ሙሽራ አድርገው መንነዋልና በዓታቸውን ለማጽናት እጃችንን በመዘርጋት ብቻ የጸሎታቸው በረከት ተሳታፊ እንሁን፡፡



ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sheger Press️️

20 Oct, 05:36


የወባ በሽታ‼️

በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል የወባ በሽታ ወረርሽኝ በሚመስል መልኩ በጣም ብዙ ሰው እየሞተ ነው። በወላይታ ብቻ በቀን ከ40-50 ሰው እየሞተ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ገልፀውልኛል። ይህ ቁጥር በቀን የሚሞተውን በትክክል ላይገልፅ ይችላል፣ምክንያቱም በሽታው ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ስለመጣ በተለይ በገጠራማው ክፍል በርካታ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። የህክምና ቁሳቁስ እና የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት በመፈጠሩ የሞት ቁጥሩ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በስልጤ፣በከምባታ፣ በጉራጌ ዞኖች እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ እና ዙርያው ወረርሽኙ ተባብሷል ብለዋል። 
የክልሉ ጤና ቢሮ በበኩሉ ከ1.2ሚሊዮን በላይ አጎበር ለማሰራጨት እየሰራሁ ነው ብሏል።

🎯 በአንድ ሳምንት ብቻ ከ51 ሺህ በላይ የወባ ህሙማን ቁጥር ተመዝግቧል " - የአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ብቻ ከ51 ሺህ 650 በላይ የወባ ህሙማን ቁጥር መመዝቡን የአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

በክልሉ 40 ወረዳዎች 72 በመቶ የሚሆነው የወባ ስርጭት እንደሚሸፍኑም የኢንስቲትዩቱ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር የገለፁ ሲሆን የበሽታው ስርጭት አሳሳቢ በመሆኑ ልዩ ትኩረት እንደሚያስፈልገው አስረድተዋል።

የወባ በሽታ ስርጭት በክልሉ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝ የገለፁት አስተባባሪው የ2017 በጀት ዓመት በባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 65.8 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቁመዋል።

@sheger_press
@sheger_press

Sheger Press️️

19 Oct, 18:59


Update| "ደብዳቢ ባለቤቷ ታስሯል"ፖሊስ

" በተፈጸመባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታለች፤ የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " - የቤተሰብ አባል

በኦሮሚያ ክልል ፣ በምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ' የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም ' በሚል ከዛፍ ጋር ታስራ በባለቤቷ ክፉኛ የተደበደበችና የተገረፈች የ3 ልጆች እናት በአስጊ ጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የቤተሰብ አባሏ ተናገሩ።

በአሁኑ ወቅት በሐዋሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ የምትገኘው ኩሹ ቦናያ የተባለችው እናት በደረሰባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታ " የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል " በማለት የቤተሰብ አባሏ ገልጸዋል።

የአካባቢው አቃቤ ሕግ በበኩላቸው ግርፋቱን መፈጸማቸው የተጠረጠሩ ባለቤቷን ጨምሮ 8 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ መካሄዱን ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፈዋል የተባሉት ሽማግሌዎች የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሲለቀቁ ባለቤቷ ግን አሁንም በቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ጃርሶ ቡሌ (ዘመዷ) ምን አሉ ?

" ኩሹ ቦናያ የ3 ልጆች እናት ናት።

ገበያ ላይ አስሮ የመግረፉ ድርጊት የተፈጸመው ባለፈው ወር መስከረም 9/ 2017 ዓ.ም. ነው።

ግርፋቱ የተፈጸመባት ባለቤቷ ገልገሎ ዋሪዮ ይባላል።

ኩሹ እና ባለቤቷ ገልገሎ በትዳር 12 ዓመት ቆይተዋል

በኑሯቸው ችግር ውስጥ ሲወድቁ ባለቤቷ ወደ ውትድርና ይገባል። በውትድርና 4 ዓመት ያህል ቆይቷል።

እሷ ልጆቿን ለማሳደግ ብቻዋን ስትጥር ነው የቆየችው።

ገልገሎ ከውትድርና ከተመለሰ በኋላ ግን ባለቤቱን መደብደብ ይጀምራል።

በተደጋጋሚ ወደ ቤተሰቦቿ እየሸሸችም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ወደ ቤቷ ትመለስ ነበር።

ገልገሎ ከውትድርና ከተመለሰ በኋላ ከባለቤቱ ጋር መስማማት አለመቻሉም ፤ ዘወትር ባለቤቱን እና ልጆቹን ይደበድብ ነው።

በአገር ባህል መሰረት ሽማግሌዎች በባለትዳሮቹ መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በተደጋጋሚ ለሽምግልና ተቀምጠዋል።

ችግሮች ሳይፈቱ ሲቀሩ ወደ አባቷ ቤተሰብ ሸሸች። ሽማግሌዎች ተነጋግረው ባለቤቷ ጠባዩን እንዲያሻሽል እርሷም ወደ ቤቷ እንድትመለስ መከሯት።

እርሷ ግን ነገሩን በደንብ እንዲያጤኑት ወደ ቤቷ ብትመለስ አንደሚገላት’ ተናገረች።

የሽማግሌዎቹን ቃል አላከበረችም በሚል ሽማግሌዎቹ ታስራ እንድትገረፍ ወስነውባታል።

የሽማግሌዎቹ ውሳኔ የቦረናን ባሕል አይወክልም ፤ ይህ የጥቂት ሰዎች ውሳኔ ነው።

በሚኖሩበት አካባቢ ባለ ዛፍ ላይ አሰሯት። ይህንን ያደረጉት ልጇ እያለቀሰ፣ ሌሎች ቆመው እያዩ ነው።

በስፍራው ተገኝተው የነበሩ በሙሉ ፎቶ እንዳያነሱ፣ ቪድዮ እንዳይቀርጹ ተከልክለው ነበር።

ስትገረፍ ከዋጪሌ ዱብሉቅ አንድ መኪና በድንገት መጣ።

አንድ ልጅ ከመኪናው ወርዶ ቪድዮ መቅረጽ ጀመረ ፤  በዚህም የተፈጸመውን ወንጀል ሌሎች ሊያዩት ይችለዋል።

የሦስት ልጆች እናት የሆነችው ኩሹ በዛፍ ላይ ታስራ በባለቤቷ ግርፋት ከደረሰባት በኋላ ክፉኛ ተጎድታለች።

የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል።

የቤተሰብ አባላቶቿ የደረሰባትን ወድያውኑ አልሰሙም ነበር። ለሳምንት ያህል ሕክምና ሳታገኝ ቆይታለች።

ወንጀሉ አንደተፈጸመ ወድያውኑ ቪድዮው አልተለቀቀም ነበር። ከሳምንት በኋላ ነው ሰው ያየው። ወላጆቿም የሆነውን ያዩት ከቪድዮው ላይ ነው።

መጀመርያ በአሬሮ ሆስፒታል በኋላም ወደ ያቤሎ ሆስፒታል ሄዳ ሕክምና የተከታተለች ቢሆንም የተሻለ ሕክምና በማስፈለጉ ወደ ሐዋሳ ሆስፒታል ተልካለች። "

የዋጪሌ ወረዳ አቃቤ ሕግ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጉዮ አሬሮ ጥቃቱ በቃቃሎ መንደር መፈጸሙን እና ከተፈጸመ ከሳምንት በኋላ ሪፖርት መደረጉን ተናግረዋል።

" መረጃው እንደደረሰን የምርመራ ቡድን በማዋቀር መረጃ መሰብሰብ ጀምረናል " ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ሽማግሌዎቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሲለቀቁ ባለቤቷ ግን አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ጨምረው ተናግረዋል።

" ክስ ለመመስረት የሕክምና ማስረጃ እንፈልጋለን። አሁንም የሕክምና ክትትል እያደረገች በመሆኑ መረጃው ገና ተጠናክሮ አልቀረበልንም። ሕጋዊው ጉዳይ ግን ሂደቱን ጠብቆ ይቀጥላል " ሲሉ ተናግረዋል።
[ቢቢሲ አማርኛ]


@sheger_press
@sheger_press

44,626

subscribers

4,645

photos

114

videos