ሐዋርያዊ መልሶች @apostolic_answers Channel on Telegram

ሐዋርያዊ መልሶች

@apostolic_answers


በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል..
YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

ሐዋርያዊ መልሶች (Amharic)

አባቶችን አንድን ያቀረባችኋል፡ ክርስትን፣ ናትም የሆነውን በጥያቄዎች ካልሰማ ለማህበረሰብ ለመልካም ቱሙን ስለሚመላለሱ ሐዋርያዊ መልሶች ማህበረሰብ ይሆዋል። ዝርዝር ምንም ያለም ጥያቄ በክርስቲንያ ባለ፥ ሐዋርያዊ መልሶች ውስጥ ሊያዩ ነው። ሰፊ ይባረሩ፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1

ሐዋርያዊ መልሶች

21 Nov, 11:46


ቅዱስ ሚካኤል ለጋዲ

https://vm.tiktok.com/ZMhWoLge5/

ሐዋርያዊ መልሶች

21 Nov, 10:38


መላእክት ምን ያህል ኃያል እንደሆኑ መቼስ ይታወቃል.. ቅዱስ ሚካኤል ደግሞ አለቃቸው ነው😎😎 የመላእክት አለቃ..

ቅዱስ ሚካኤል ተዋጊ ነው.. በተለይ የወደቁትን መላእክት ማለት ነው.. በራእይ 12 ላይም እንደተነገረን ዘንዶውን ሚካኤል ነበር ከመላእክቱ ጋር ሆኖ የተዋጋው.. እናማ ዘንዶው ሊቋቋመው አልቻለም ስለዚህም ከነ መላእክቱ ተጣሉ በሰማይም ሥፍራ አልተገኘላቸውም..

በጣም የሚገርመኝ ከሃገር ውጪ ያሉም exorcists(አጋንንት አባራሪ ካህናት) አጋንንቱን በሚገስጹበት ወቅት ቅዱስ ሚካኤልንም በጣም ይጣራሉ.. ስለዚህ አጋንንቱን ሲዋጉ የሚካኤልንም እርዳታ ያገኙበታል..

በጣም ነው ደስ የሚለኝ ያለንበት ወይም የቀረብንባት የ እግዚአብሔር ከተማ የ እግዚአብሔር መላእክትም ያሉባት ናት [ዕብ 12 ላይ እንደሚለው]

እግዚአብሔር አምላካችን መዳንን እንወርስ ዘንድ ወዳለን ወደ እኛ ያግዘን ዘንድ አሁንም ይህንን ታላቅ የመላእክት አለቃ በቸርነቱ ወደ እኛ ይላክ.. ከአጋንንትም ይጠብቀን..

@Apostolic_Answers

ሐዋርያዊ መልሶች

20 Nov, 20:21


ዌል.. እግዚአብሔር እኮ ሲፈጥር የፈጠረውን ሁሉ አይቶ “እጅግ መልካም ነው” ተብሏል..

ግን እዛው ጋር ወረድ ስትሉ ደግሞ እግዚአብሔር አዳምን ብቻውን ያየውና “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም” ይላል.. ስለዛ አዳሞች ብቻችሁን ትሆኑ ዘንድ አዎ መልካም አይደለም..

ግን ደግሞ አንዱ ጀለስ አሁን ደውሎልኝ ከሴት ጓደኛዬ ጋር ተባጠስን ይለኛል.. 1 አመት አብረን ነበርን አለኝ.. ኧረ ቀልድ.. አመት..??😁😁 ከኔ ተማር ይለኛል ደግሞ😆😆 ቁጭ ብሎ የተጸለየበት ውኋ እየጠጣ እንዳይሆን በቮሚት እንዲወጣለት ሎል..

አላማ ይኑረን😉😁

ሐዋርያዊ መልሶች

20 Nov, 18:42


ቆይ ከላይ ላለው ጽሑፍ..

ሙስሊሞች ያልተጻፈውንም እያነበቡ እየተሳደቡ እንደ እብድ እየሆኑ እንደሚያናድዱ አውቃለሁ

ክርስቲያን ወንድምና እህቶቼ ደግሞ እስካየሁት ድረስ የተጻፈ ነው ሚያነቡት ለዚህም አመሰግናችኋለሁ.. ግን ያው ትንሽ ብታለሳልሱላቸው ማለቴ ነው.. ኢየሱስ በሰዎች እንዲታይልን ማለት ነው..

“ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን..”
[ኤፌሶን 4: 15]

በርቱ እናንተ ጀግኖች

ሐዋርያዊ መልሶች

20 Nov, 15:22


አሁን አንድ ሰው በውስጥ መስመር እንዲህ አለኝ:

“እስልምና ላይ ሚሰሩ ልጆች ሲናገሩ ትንሽ የቃላት ምርጫ ቢያደርጉ”

መልካም አሳብ ነው.. ያው አንዳንድ ነገሮች እስልምና ላይ በራሳቸውም በጣም ከባድ ቢሆኑም ግን እኛ በተቻለን አቅም አለሳልሰን ዋናውን መልእክት ብናስተላልፍ መልካም ይመስለኛል.. ደግሞ ኢየሱስንም ሊያዩት ይገባል.. እርሱን ነው አይተው መምጣት ያለባቸው.. ስለዚህ የዋህነት ፍቅር እና መልከም ፍርሃት ሊኖረን ይገባል

በርቱልኝ

@Apostolic_Answers

ሐዋርያዊ መልሶች

20 Nov, 10:48


ቲክቶክ ላይቭ ላይ በጣም አስቸጋሪ የሆነው ነገር.. ቀለል አድርገህ ስታወራ ከሁሉም ጋር በጣም ስትቀራረብ ምናምን ቀስ በቀስ የሆነ ሰዓት ላይ በጣም የሕጻን ጭቅጭቅ እና ነቆራ ውስጥ ራስህን ልታገኘው ትችላለህ.. በጣም ማልወደው ነገር ማለት ነው ማርያምን..

እና የተረዳሁት ነገር ብዙም ከሰው ጋር መቀላቀልና መቀራረብ እንደማያስፈልግና የራስህን ሥራ ብቻ መስራት እንዳለብህ ነው..

ሐዋርያዊ መልሶች

19 Nov, 19:08


ሙሉ መጽሐፍ ቅዱሱን በጥንት አባቶች ማብራሪያ መሠረት ትርጓሜ አዘጋጅተዋል.. አስባችሁታል ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ.. በየጥቅሱ አባቶችን እየጠቀሱ ሲተረጉሙ..

ከሱ ውጪም አቦ እኔ ለማየት እስከሞከርኩት ወደ መቶ መጽሐፍትን አዘጋጅተዋል.. የምር ግን ሰው ናቸው..??🙄🙄 እስቲ አንዴ ተነስተን እናጨብጭብ😁😁

አባ ታድሮስ ማላቲ ይባላሉ.. የኮፕቲክ አባት ናቸው.. አሁን በሕይወት ካሉን ሊቃውንት መካከል ናቸው.. ግን ይለያሉ በጣም ጌታ የረዳቸው ሰው ናቸው..

ሐዋርያዊ መልሶች

19 Nov, 17:16


ሙስሊም ኡስታዞች እባካችሁን እንዲህ ዓይነት ስድቦችን ተዉ አያንጽም.. ሕዝብን ወደ ክፉ ነገር አትምሩ.. ከቻላችሁ የተጻፈውንና የምናምነውን ብቻ አንሱና ጠይቁን

https://vm.tiktok.com/ZMhngK3Jj/

ሐዋርያዊ መልሶች

19 Nov, 05:22


ዘማሪዎቻችን "ኢየሱስ ቦኪሜ" ሲሉ ቦኪም ያው የቦታ ስም ነው እና መሳፍንት ላይ እንደተጻፈው እስራኤላውያን በአንድ ወቅት ከጥፋት መንገዳቸው ለመመለስ እጅጉን ያለቀሱበትና ለእግዚአብሔርም የሠዉበት ሥፍራ ነው.. በዚህም ምክንያት ያንን ሥፍራ ቦኪም ብለው ጠርተውታል.. ቦኪም ማለት የሚያለቅሱ ወይም የማልቀሻ ሥፍራ ማለት ነው።

ኢየሱስ ቦኪሜ ነህ ሲባል.. ይመስለኛል ሰው ወደ እርሱ ቀርቦ የሚያለቅስበት እውነትኛ ሥፍራ በኢየሱስ ፊት ስለሆነ ነው..

ምናልባት ሌላ ትርጉም ካላቸው ግን እንጃ😁😁

ሐዋርያዊ መልሶች

18 Nov, 07:15


አቡነ በርናባስ የሚያገለግሉበት ቦታ የሚገለገሉ ምእመናን አብዛኛው ቆራቢ ነው ብሎ አንድ ሰው ነገረኝ..

ከሆነ አባታችን ጌታ አሁንም አብዝቶ ይርዳዎት እናመሰግናለን እንዲህ ያለ አባት ነው ምንፈልገው.. ማለትም የመንጋው መቁረብ አስጨንቆት ለቁርባን የሚያበቃ..

@Apostolic_Answers

ሐዋርያዊ መልሶች

18 Nov, 06:18


በቃ አይዞዎት😭😭

ኮመንት ምታደርጉ ሰዎች ፍቱ አባታችን ኮመንታችሁን አይተው ቅሬታቸውን በዜማ አሳውቀዋል እረፉ በቃ

ሐዋርያዊ መልሶች

18 Nov, 05:49


አባ ዮሐንስ ጸሃይ
ነፍሴን አደራ በሰማይ🥱🥱

መልካም ውሎ እናንተ ሰዎች😆

ሐዋርያዊ መልሶች

17 Nov, 07:14


ዛሬ ቅደሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንግል ክፍል..

“ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው።”
[ማቴዎስ 13: 7]

ጌታ ቃሉን ወደ ልባችን ሲልክ ፍሬን እንድናፈራና ይበልጥ ወደ እርሱ እንድንቀርብ የሚያደርገን ነው.. ታድያ ግን በልባችን ውስጥ የዓለም የሆነው ምድራዊ አሳብ ሲነግስብን እርሱ እንደ እሾህ ይሆንና ወደ ልባችን የሚመጣውን የጌታን ቃል እንዳያፈራ ያደርገዋል.. ስለዚህም እንዲህ ያለው እሾህ ሊቆረጥ ይገባዋል..

እግዚአብሔር አምላካችን ፍሬን እናፈራ ዘንድ በጸጋው መልካም መሬት ያድርገን

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

ሐዋርያዊ መልሶች

16 Nov, 08:24


መዝሙር በጣም ሃሪፍ ነው..

ሻወር ስትወስዱ መጀመሪያ መዝሙሩን ክፈቱና እየሰማችሁ ውሰዱ🙄🙄

ስለዛ በየትኛውም ቦታ ይሰማል

ሐዋርያዊ መልሶች

15 Nov, 17:29


አቡነ በርናባስ ስለ ቅዱሳን ምልጃ🙄🙄

https://vm.tiktok.com/ZMhGNkKDD/

ሐዋርያዊ መልሶች

15 Nov, 05:14


የወደደኝ ጌታ ምን አድርጌለት ነው..??

ዌል.. የማይጠላኝስ ምን ሳልበድለው ቀርቼ ነው..??

አባት ሆይ ስለ ፍቅርህ እናመሰግንሃለን

ሐዋርያዊ መልሶች

14 Nov, 19:03


የሰው ሰኮናው..
የተሰነጠቀ ነው..??
ወይስ ያልተሰነጠቀ..??

ሐዋርያዊ መልሶች

14 Nov, 17:20


- ሰው ይበላል አይበላም..??😭😭
- አሳማ ከተበላ ሰውስ ለምን አይበላም..??😭😭

ኧረ እንደው ሼም ነው.. እንዲህ እያልን ስንከራከር በጣም ነው ሼም የሚይዘኝ የምር.. እስቲ አሁን ሰው እና እንሰሳን ምን አገናኘው..??

እግዚአብሔር በኖኅ ዘመን “መብል ይሁናችሁ” ብሎ እንሰሳትን ሲሰጥ “እርስ በእርስም ተበላሉ” ብሎ ሰውን አካቶ ነበር እንዴ..??(ዘፍ 9 ላይ ማለት ነው)

ባይሆን እዛው ላይ እንሰሳትን ሲሰጥ የሰውን ደም ስለማፍሰስ ግን ሲናገር ምን አለ..??

“የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል፤ ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና።” [ዘፍ 9: 6]

እንደው ሼም ይያዘንና እንዲህ ዓይነት ክርክር ውስጥ አንግባ.. አሳማ ጅብ አህያ ምናምን አዎ አንበላም.. ግን ሃይማኖት ሆኖ አይደለም..

“በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ። ሁሉ ንጹሕ ነው፥ በመጠራጠር የተበላ እንደ ሆነ ግን ለዚያ ሰው ክፉ ነው።”
[ሮሜ 14: 20]

@Apostolic_Answers

ሐዋርያዊ መልሶች

13 Nov, 17:10


ወንድማችን ማንያዘዋል ጋር ኡስታዙ ቀርበው ለተናገሩት

https://vm.tiktok.com/ZMhpn9H9x/

ሐዋርያዊ መልሶች

13 Nov, 16:08


ኢየሱስ ይማልዳል ወይስ አይማልድም የሚለው የብዙ ጊዜ ክርክር አሁን ላይ እየቀረ ይመስላል አይደል..

ያው እኛ እንደምታውቁት ዋናው ችግራችን ቃላት ሳይሆኑ አሳባቸው ነው.. ቃሉን ከመጠቀም አንጻር ጳውሎስም ተጠቅሞታል ግን ደግሞ ይህንን እንደ ወረደ ወስዶ አሁንም በክርስቶስ በኩል ያልተፈጸመ ሥራ ያለ አስመስሎ ይለምናል ማለት በጣም አስቸጋሪ ነው..

ግን ደግሞ አንዴ በክርስቶስ የተሠራው ሥራ ዘላለማዊ ነውና እሱን ለመግለጽ ብቻ ይህንን ቃል እጠቀማለሁ የሚል ካለ በእኛ ዘንድ ያልተለመደ ቃል ቢሆንም መናፍቅ አያስብልም ማለት ነው..

@Apostolic_Answers