Islamic poem & question @islamic_question_for_maraw Channel on Telegram

Islamic poem & question

@islamic_question_for_maraw


ይህ ቻናል የተለያዩ ኢስላሚክ ፊልሞችን እና ደስ የሚሉ ኢስላማዊ ጥያቄዎች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

ሼር በማድረግ ይተባበሩን ።

Contact : @maraw6725

Islamic poem & question (Amharic)

ኢስላማዊ ፍች እና ጥያቄዎችን አስተምረን ሼር በማድረግ የሚተባበሩን 'islamic_question_for_maraw' ቻናል እንዴት እንደሚፈልግ ነው። ይህ ቻናል የተለያዩ ኢስላሚክ ፊልሞችንና ደስ የሚሉ ኢስላማዊ ጥያቄዎችን የሚለቀቅበት ቻናል ነው። የቻናል አስተምሩን እርምጃዎችን ለመለዋወጥ Contact : @maraw6725 ላይ ይግቡ።

Islamic poem & question

11 Feb, 19:08


ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ በምላስ ላይ ቀላል ሚዛን ላይ ከባድ አዛኙ አምላክ ዘንድ ደግሞ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላት አሉ። እነርሱም ሱብሓነልላህ ወቢሀምዲሂ
ሱብሓነልላሂል_ዐዚይም የሚሉት ናቸው።

Islamic poem & question

11 Feb, 12:35


ጨረቃ

እንደ ልብ ወዳጅ ሌት ተቀን ተናፍቃ
እንደ እናት ጉርሻ በስስት ተጠብቃ
ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ!

ምንዳዬን አብዝቶ ኃጢያቴን አክስሞ
ከሲዖል ‘ሚያነፃኝ ሩሄን አለምልሞ
ከቤቱ መራቄ ሽሽቴ እንዲያበቃ
አቅፎ አድራሼን ይዛ ብቅ አለች ጨረቃ።

ሳይሰስት ‘ሚያድለኝ ከሰነቀው ፀጋ
‘ሚያቆመኝ ከደጁ እዝነቱን ፍለጋ
በስክነት ተውቦ ምህረትን ተኩሎ
እነሆ ብቅ አለ በጨረቃ ታዝሎ።

አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ያረመዳን
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ረመዳን
**

እንደ ልብ ወዳጅ ሌት ተቀን ተናፍቃ
እንደ እናት ጉርሻ በስስት ተጠብቃ
ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ!

ነፍሴ እንዳትሰንፍብኝ ለስጋዬ አድልቼ
ፅድቁን እንዳልረሳ ለእኩይ ተረትቼ
በክብር ‘ሚያስጠራኝ ተቅዋን አጎናፅፎ
የኃጢአቴን ሸክም ከላዬ አራግፎ።

እዝነትን የቸረኝ ከስስት አርቆ
የመስጠትን ዋጋ ያሳየኝ አልቆ
ብቅ አለ ረመዳን የበጎነት ማሳ
ሳይጎድል ትውስታው ጣዕሙ ሳይረሳ።

አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ያረመዳን
አህለን ያረመዳን
አህለን ቢከ ረመዳን
****

እንደ ልብ ወዳጅ ሌት ተቀን ተናፍቃ
እንደ እናት ጉርሻ በስስት ተጠብቃ
ምድሩን አፍክታ ሰማዩን አድምቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ
ብቅ አለች
ብቅ አለች ጨረቃ!

ተራዊህ ሙናጃው የሌሊት ሹክሹክታ
ሪዷውን ሽቶ የኸልዋ ቆይታ
አዝካር ሶለዋቱ የዱዓው ትውስታ
የወንድም ናፍቆት መሃባው ትዝታ።

ያንተ ትብስ አንተ ወጋችን ማሰሪያ
የመተጋገዣ ያብሮነት ማደሪያ
ተቅዋን ሊያላብስ የተኛን ሊያነቃ
የእዝነቱ ወር መጣ ብቅ አለች ጨረቃ።

በኢባዳ ወዝተው ደምቀው በአዝካሩ
ከቁርአን ሸንጎ ተርቲብ እየቀሩ
በመላእክት አክናፍ ዙሪያቸው ተከቦ
ሩሃቸው ይጠግባል ስጋቸው ተርቦ።

ኸይሩን ሚን አልፊዋን ማግኘት እየጓጉ
ሌሊቱን በስቲግፋር በዱዓ እያነጉ
የሊቃውን ፀጋ በረካውን ሽተው
ሲያነቡ ይፈጅራል የከርሞውን ናፍቀው።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የካቲት 23/2012 ተፃፈ
****

#ረመዳን_18_ቀናቶች_ይቀሩታል 4/6/2017

@yasin_nuru @yasin_nuru

Islamic poem & question

30 Jan, 18:49


#የሸዕባን ጨረቃ ምሽቱን አሀዱ ብሏል።
  ረመዷን አንድ ድፍን ወር ብቻ ቀረው
اللهم بارك لنا في شعبان وبلغنا رمضان
#ዙመር_ኢስላሚክ_ሚዲያ

Islamic poem & question

30 Jan, 05:42


አሰላሙዓለይኩም ያጀምዓ


ياَ أَيُّهَا النَّبِىُّ قُل لِّأَزْوَاجِك وَبَنَاتِكَ وَنِسَاإِ الْمُؤْمِنِينْ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَا بِيبِهِنَّ ذَالِك أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ وَكَانَ اللهُ غَفُورًا رَّحِيمَا
(አንተ ነብዩ ሆይ ለሚስቶችህ : ለሴት ልጆችህም : ለምእመናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው::ይህ እንዲታወቁና(በባለጌዎች)እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው::አላህም መሀሪ አዛኝ ነው።)

አውረትን በመሸፈን ለሴቶች የመጀመሪያው ሙሉ መሸፈን የመጨረሻው ደግሞ ጆሮ ተሸፍኖ ፊት እስኪቀር: የእጅ መዳፍ እስኪቀር እና ከቁርጭምጭሚት በታች እስኪቀር መሸፈን አለበት

በዘመናችን ግን በተለይ ት/ቤት ዩኒፎርም እያሳጠሩ የሚለብሱ አሉ : ሰውነታችሁ እንዳይገለጥ አላህ እያዘዘ ትንሽ እንኳ ልብሳችሁን አሳጥራችሁ ሰውነታችሁን ለምታሳዩ ሴቶች ለምትሰሩት ወንጀል አላህ ይቅር ይበላችሁ አላህ ይመልሳችሁ።

Islamic poem & question

29 Jan, 16:46


ሙሉውን አንብበው ከዚያም መጨረሻ ላይ ያለውን ቁጥር አይተው ይወስኑ።

የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) እንዲህ ብለዋል ⇣ለምላስ ቀለል ብላ ሚዛን ላይ ከባድ ያለች አላህ ዘንድም የተወደደች ንግግር⇣
*ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም*
ቢያንስ ለ30 ሰዎች ላክ ቢሉትም (ቢያነቡትም) አምስ መቶ ቢሊዮን ሃሰናትን በአላህ ፈቃድ ታገኛለህ።
እንደዚሁ አንተ የላክላቸው ሰዎች እያንዳንዳቸው ለ30 ሰው ከላኩ አሁንም 4.680.000.000 ሃሰናት ታገኛለህ። መቼ እንደምትሞት አታቅምና ሰደቀተል ጃሪያ አድርጋት።
ለማሰራጨት ደቂቃ እንኳን አይወስድብህም።

የቅያማ ዕለት ትመሰክርልህ ዘነድ።
https://t.me/iselamic2

Islamic poem & question

27 Jan, 06:06


ክስተቱ የቁርዓን አንድ ሱራ ስያሜ ሆኗል። ያውም አሏሁ ተዓላ ለልቅናው ተስቢህ እያደረገ የጀመረው ሱራ። ክስተቱ በሰይዳችን ሕይወት ውስጥ ከታዩ ተዓምራቶች ኹሉ ጥልቁ ነው። የሕይወትን መለክ የለወጠ፣ ልቅና መወደድ መፈቀርን የንግስናን ከፍታ የሹመትን ልዕልና በጉልህ የታየበት ሌት ነው። በተናጥል በላቀ ፍቅር መፈቀር እና መንናፈቃቸውን ነግሮ አያሌ ተዓምራትን ጎብኝተው፣በሽልማት ተንበሽብሸው ያነጉበት ለይል ኢስራ ወል ሚዕራጅ።

Islamic poem & question

22 Jan, 18:48


kurulus osman 297/298 trailer

Islamic poem & question

31 Dec, 20:29


Kurulus osman trailer 295 & 296

Islamic poem & question

27 Dec, 19:01


#እስኪ_ፈገግ_በሉ😁

አንድ ሰውዬ መግሪብ ለመስገድ መስጂድ ይገባና ኢማሙ ሱረቱል በቀራን ነበር የቀሩት🙆‍♂

ከዛም በጣም ጨነቀው አልጨርስ አሉ ቆዩ ልክ እንደጨረሱ ወደ ኢማሙ ጠጋ አለና👀 ሸይክ አሁን ማንን ነው የቀራችሁት ሲል ጠየቀ🙄

ኢማሙም ሱረቱል በቀራ ወይም ( የላሟ ምዕራፍ ነው አሉት😳 ኢሻ ሰላት ላይስ ምንን ነው የምትቀሩትና ምታሰግዱን🤔🤔 ብሎ ጠየቀ

ከዛ ሸህየው ሱረቱል ፊል ወይም የዝሆኗን ምዕራፍ ነው አሉት😳

እሰሰሰሰሰሰሰሰይ😳

የላሟ እንዲህ ያቆየን የዝሆኑማ እዚሁ ሊያሳድረን ነው😁😁
ብሎ ሌላ መስጂድ ሄደ ይባላል🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂😂

@yasin_nuru  @yasin_nuru

Islamic poem & question

25 Dec, 18:48


እስከ መጨረሻው አንብቡት ?

ማክሰኞ በሪያድ ከተማ የተከሰተው አደጋ

९ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊት ተጋጭተው ነበር..

"አምቡላንስ አየሁ ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ፣

አንድ ወጣትን ልጅ አድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየው፡፡

ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል አካላቱ ተቆርጠዋል ፣እግሩም ጭምር ተቆርጧል እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ

ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል

"መሞት አልፈልግም፣በጣም ፈርቻለሁ ፣ እሳት ነው ምገባው እኮ" ይለዋል

~ እዛው ተኝቶም እየጮኸ"ሙሀመድ እኔኮ አልሰግድም ነበር ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም፣ከዚህ ቡሀላ እሰግዳለሁ ፣ ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል

ሰወችም ተሰበሰቡ ፣ እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ፣ በጣምም ፈርቻለሁ፡፡

በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል

የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ ጩኸቱም _ ቀጠለ ሰውነቱም ወዷ ሰመያዊ እየጠቆረ ሄዷ፡፡

ሊያድኑት ግን አልቻሉም

አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሀዳ በል ከሊማሙን በል…በል ”ይለዋል ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም

አላሁ አክበር፣ በጣም ፈርቶ ነበር፣ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ

ግን....ግን ሸሀዳውን ማለት አልቻለም ነበር

ከዚያም አልተንቀሳቀሰም፣ ሰውነቱም ደርቆ ቀረ

ዶክተሮቹምያ ላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት

ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም ዱዐ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት፡፡

ዘጋቢውም ይለናል፦" በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት .ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው፣ ሰላታችሁን ግን ጠብቁ፣ በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡

የመጨረሻ ቀናችሁ መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም እኔም ከዚህ ክስተት ቡሀላ መተኛት አልቻልኩም እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታሙስ ነበር...” አሰግዳለሁ፣ ወላሂ ከዚህ ቡሀላ እሰግዳለሁ፣ መሞት ግን አልፈልግም..….”🥹🥹

ያ አላላላላህ

መጨረሻችንን አሳምርልን ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን

አንብባችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉ ምናልባትም በዚህ ታሪክ የ1ሰውን ህይወት ማቃናት እንችል ይሆናል፡፡

‏﷽
۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ 🌷



@yasin_nuru    @yasin_nuru

Islamic poem & question

23 Dec, 18:37


Kurulus osman trailer 293 & 294

Islamic poem & question

15 Dec, 07:05


Kurulus osman trailer 291 & 292

Islamic poem & question

11 Dec, 04:29


Kurulus osman trailer 289 & 290

Islamic poem & question

08 Dec, 18:54


Dogan

Islamic poem & question

08 Dec, 18:53


Bamsi

Islamic poem & question

08 Dec, 18:53


Turgut