ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ @wakie_eotcissues Channel on Telegram

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

@wakie_eotcissues


ይህ ቻነል ጓደኞቼ እና ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን
YOUTUBE:- https://www.youtube.com/@Orthodox_Secular_FantahunWakie/videos
ትዊተር፦ @fwakie
FB:- https://www.facebook.com/fwakie
Blog:- https://ethiopiaorthodoxchristian.blogspot.com

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ (Amharic)

የወይም ከተማ የሚለዋወጥ ተጠቃሚ ከትምህርት ጋር ከዚህ ታላቅ ምልክት ተጠቃሚ ፋንታሁን ዋቄ ጌል እየተለመደ ነው። ይህ ቻናል የቅድስት ቤተክርስቲያን እና ዓለም ምሁር የባለቤት ጦርነትን በተግባር የሚወዱትን ትዊትም ወደማያያዝ ድምፅ በተሳቅፉ ጽግኝ መስርት ያግኙ የመሰረታዊ ጥያቄ ነው። ከዚህባሽ በእርስዎ ውስጥ ሁኔታ እዚህን ጽግና ይጠቀሙ። ቻናልዎች ከበርካታ የበለጸኑ በአሰራር፣ በእውነትና በሕዝብ በጥምቀት መታጠብ ለሚሆን መመሪያዎች፣ ቁምፊም ስለ ክርስትና የትክክል ሰዎች ስለ ውርጃና ውረድ ለማሰብ እና ምሳሌዎች በሚስቶን ውስጥ እዚህን ጽግና ይጠቀሙ። ዋቄ ቺናል የቻናላችን በድምጽ አስተካክል እና ትምህርትን የሚያገኙት ከእኔ አየር መኖር ያልቻሉ ሰዎች ስለሆኑ በትክክለኛ ምልክት እዚህን አገልግሎታ እንዲሰሩ፣ አስታውቁ።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

24 Jan, 17:58


"የአማራንሕዝብብነፍጥብእየወዘወዘ፣ በማን አለብኝነት እየተንቀሳቀሰ ከዚህ ብኋላንአንማማርም" ይላል ይህ የብልጽግና ገልቱ።
መገዛት፣ መደንቆር፣ መደንዘዘ ማለት እንዲህ ነው። ከእውነት፣ ከሰብአዊነት፣ ከፍትህ፣ ከሕዝብ ጋር መቆም የማይችል ሰብእና የሚፈጠረው አምላክ የለሽ የሆድንሎሌ መሆን ሲጀመር ነውና
ሁላችንም ራሳችንን በሆዳችን መቃብርነት ከመደፈን መጠበቅ፣ ህሊናን ማክበር፣ እግዚአብሔርን መፍራት እንዳይለየን እንጸልይ።

AQOIuL76OtUy4lc_ETOL8W8RGaAf3Lr5BG-VVJ1LYVuBGNB_rNMpKCkgMES90lLYpDZ28-ikBdJmzUtA-UTVeyWs.mp4

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

24 Jan, 16:31


https://www.youtube.com/live/XHQDX93Lcp0?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

24 Jan, 04:26


https://youtu.be/Og97MKGm12M?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

24 Jan, 04:07


AQP7fnukZ0hpkdyQXoyx6pwKqT43zmHmnLjMaYzzeccdC3S_8386XQh4AgGROYgHsk8k3cYhlsz6c3dS_tKmFa4c.mp4

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

23 Jan, 19:59


https://youtu.be/EJAMxarx9B4?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

23 Jan, 04:40


ኣብይ አህመድ አሊ የሚገለጽበት ጦር ሠራዊት 👉

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

23 Jan, 02:19


https://youtu.be/irHGOYTMm9Y?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

22 Jan, 19:37


በ6 ወራት የተመዘገበ ፍቺ ሲጨርም ጋብቻ ቀንሷል።

የአዲስ አበባ ሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ የተቋማቸውን የበጀት አመቱን የስድስት ወራት አፈጻጸም ትላንት ሪፖርት አድርገዋል።

በዚህም ወቅት እንደገለጹት ከተከሰተው 21,674 ጋብቻ ለመመዝገብ ታቅዶ 15,574 (72.65%) ምዝገባ ማደረግ እንደተቻለ ተጠቁሟል። ቁጥሩ ከ2016 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 7% የምዝገባ ቅናሽ አሳይቷል።

ከተከሰተው ፍቺ 4,873 ለመመዝገብ ታቅዶ 3,769 ፍቺ የተመዘገበ ሲሆን ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 33.99% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።

በተጨማሪ ፦

➡️ ከተከሰተው ሞት 15,716 ለመመዝገብ ታቅዶ 11,376 (72.38%) ምዝገባ በማደረግ ተችሏል። ከ2016ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 29.83% የምዝገባ ጭማሪ አሳይቷል።

➡️ ከተወለዱ ህፃናት ውስጥ 37,750 ለመመዝገብ ታቅዶ 41,183 መመዝገብ መቻሉ ተጠቁሟል። ይህም በከተማው ምዝገባ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።  ከ2016ዓ.ም አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር 103% ብልጫ አሳይቷል።

በሌላ በኩል ፥ ባለፉት 6 ወራት 25,581 የክልል መሸኛዎች ትክክለኛነት እንዲጣራ ለክልሎች መላኩን የገለጸው ተቋሙ አገልግሎት ለማግኘት ሪፖርት ያደረጉ 9,504 አመልካቾችን መሸኛ መርምሮ የነዋሪነት ምዘገባ አድርገው አገልግሎት እንዲያገኙ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

ተጨማሪ
@addisvaitalpress

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

22 Jan, 05:30


አይችሁ አይደል እነርሱ ልጆቻችን ሂጃብ ተከለከሉ ብለው ዝም አላሉም።በተደጋጋሚ በመግለጫ አስጠነቀቁ። ጉዳዩን ፍርድ ቤት ወስደዉ ክስ መሠረቱ።በዚህ ብቻ አላበቁም።ሰልፍ አዘጋጁተዉ ከፊት ኾነዉ መሩ ። የእኛዎቹ ግን በየቀኑ ልጆቻቸውን ለሞት እየገበሩ ገዳይን ያወድሳሉ።እንደ አቡነ ጴጥሮስ መኾን ቢከብዳቸዉ ርህራሄ እንዳለዉ እንደ ማንኛውም ፍትሐዊ ሰዉ መኾን እንኳ አልቻሉም።ወይ አይሠሩ ወይ አያሠሩ።የሚሠሩትን ያሳድዳሉ።እነዚህን ነው እንግዲህ "ኦ ብፅዕ አባ እገሌ" እያልን የምናቆለጳጵሰዉ። ኧረ ተዉ አደር ባይነቱ ማስመሉ ይብቃን።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

21 Jan, 23:32


https://youtu.be/upTbjdeuLG4

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

21 Jan, 17:23


ከተራ እና ጥምቀትን ጥቁር ለብሰው ማቅ ነስንሰው በሐዘን ያከበሩ ዘንድ የተፈረደባቸው በሀዲያ ዞን የሚገኙት የጊንብቾ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን
***

በተለያዩ ከተሞች ከተገለጡ ደማቅ የከተራ ትዕይንቶች በላይ እስከ አጥንት ዘልቆ የሚሰማ ሐዘን ቅድስት ቤተክርስትያን በሀዲያ ዞን ጊንብቾ ከተማ እያሳለፈች ትገኛለች።

የጥምቀት ማክበርያ ስፍራ ተነፍገው መከራን እየተጋፈጡ የሚገኙት የጊንብቾ ኦርቶዶክሳውያን ከተራን እንዲህ ጥቁር ለብሰው ማቅ ነስንሰው አሳልፈዋል።

ተለመነንን 🙏🙏?Kune Demelash kassaye -Arba Minchnch

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

21 Jan, 16:34


https://x.com/aradahibret/status/1881285085946929556?s=52&t=iXjh2MQ7cod3hrLaEcf5Aw

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

21 Jan, 05:30


https://www.youtube.com/live/8E2pOPqCuTk?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Jan, 18:56


https://www.youtube.com/live/lDyIdlhm4B4?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Jan, 05:18


https://youtube.com/shorts/SLtAeMnZyzo?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Jan, 05:17


I wish brainwashed ethnic political slaves lose their poisonous thungs to save millions of lives

ዘመናዊ ትምህርት የሚያፈራቸው ዞምቤዎች ምሳሌ ነው ይህ ሰው።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Jan, 04:10


https://youtube.com/shorts/SNtHWZV6RCo?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Jan, 04:09


https://youtube.com/shorts/SNtHWZV6RCo?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Jan, 04:07


https://vm.tiktok.com/ZMkHFb2AD

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Jan, 01:18


https://www.youtube.com/live/V4TnqM1kX_I?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

16 Jan, 00:20


https://youtu.be/loxB9De9U_s?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

14 Jan, 17:58


https://youtu.be/Vz45NCK6c0s?si=xLqE8qju02YJ4Fqh

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

14 Jan, 04:13


አስቡበት። በነፍስ ቀልድ የለም። ባህል፣ የዘመን ርቀት፣ ማኅበራዊ መፈራራት፤ የቤተሰብ ጫና ወዘተ ነፍስ አይሰጠንም።

ከሰማይየተሰጠ ብቸኛ አንድ ሃይማኖትና ሰዎች በፍልስፍናም ይሁን በርኩስ መንፈስ ተታለው የሚፈጥሯቸው እምነቶች ተለይተው የሚታወቁባቸው ምልክቶች ቀላል ነው።

ክብረ ሰብእ
ፍትህ
ርኅራሄ
እውነተኝነት
ከመግደል በቸቃራኒ ለማዳን መሞት
የታሪክ ብዝኃ ምስክርነት
ቅድስና
ሰውን ሁሉ እኩል መውደድ
አገርና ሕዝብና አለመካድ
ትርክት ለመቀየር ብሎ አለመዋሸት
ገዳይን አለማጀገን በተቃራኒው ማውገዝ
እንደ አዳምና ሔዋን በአንድ ሴትና ወንድ መጽናት
የሰው አገር አለመውረር ወዘተ
ጨምሩበት
---- እውነተኛ ሃይማኖትን ለይታችሁ ምረጡ።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

14 Jan, 04:13


https://youtu.be/Q1d2-QPBECY?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

14 Jan, 03:51


የማያምኑ ጳጳሳት እና ሊቃውንት እንዴት ልና ፈራ ቻልን?

ምንፈሳዊነት እየተዳከመ ሙያተኛነት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት አደገ?

የእኔ ምልከታ እንሆ https://youtu.be/oUKxbVsYRC0?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

12 Jan, 04:14


https://youtu.be/xqLOzaa6Kt4?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

12 Jan, 03:01


https://vm.tiktok.com/ZMk54SshG/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

12 Jan, 03:01


👆👆ከእውነት ከወጡ በኋላ ሁሉም የራሱን መንገድ እየቀየሰ "ሃይማኖት" እያለ የስህተትን ትምርት እያሰራጨ የሐሰት "ኢየሱሶችን" ተከተለ።

እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ የተባልን ኦርቶዶክሳውያን የጠፋውን ዓለም ወደ ሕይወት የመጥራት ኃላፊነታችንን ችላ ብለን ብንገኝ ፍርድ ያገኘናል። እንትጋ!!

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

11 Jan, 21:26


https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2025/01/%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%8A%99%E1%89%B5%E1%8A%95-%E1%8D%93%E1%89%B5%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%AD%E1%8A%AD-%E1%8A%A0%E1%89%A1%E1%8A%90-%E1%88%9B%E1%89%B2%E1%8B%AB%E1%88%B5-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%89%80%E1%88%B5%E1%89%85%E1%88%B5.pdf

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

11 Jan, 04:51


ያማራን ሕዝብ ተጋድሎ የሚያኮላሹ ኣስተሳሰቦች ይገቱ!!

በጎጥ ጠባብ አእምሮ እና በግል የሥልጣን ፍተወት፤ ከኢትዮጵያዊነት፣ ከኦርቶዶክሳዊነትና አማራነት ጋር ቋሚ ጠላትነት ካላቸው ሀገራት የስለላ ድርጅቶች እና ዲፕሎማቶች ጋር ከአማራ ሕዝብ ጀርባ የሚዶልት፤ የዘር ክልሉን እንጂ ሌላውን አማራ ለማሰብ የማይፈልግ፤ በመላው ዓለም የአንድ ጎጥ መዋቅር በምዘርጋት የአማራን አቅም የሚከፋፍል፤ በአዴን ቁጥር 2 ለመሆን የተሰለፈ ሤረኛ የፋኖ አመራር ለአማራ ሐዝብ ህልውና ሁለተኛ ዙር አደጋ የሚጠራ እንጂ አማራን ለድል አያበቃም። አገሪቱንም ጠቅልሎ በማጥፋት ለኣማራ በሀገርነተ የተደራጁ ዘላቂ ጠላት ያፈሩለታል።

ሰለዚህ የግለሰብ፥ የጎጥ፥ የሤራ፥ በድብቅ ከጠላት ጋር ስለመሞዳሞ"ደው ራስ ወዳድ አመራር ሕይወቱን የሚሰጠው የፋኖ ሠራዊት፥ መከራ ውስጥ የቀጠለው ያማራ ሕዝብ ቁጭ ብሎ ተነጋግሮ ሥርዓት ሊያበጅለት ይገባል።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

10 Jan, 05:13


https://youtu.be/U62rNfy4EvM?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

10 Jan, 04:22


https://youtu.be/9v59ZR3yelw?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

08 Jan, 18:30


እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በደህና አደረሳችሁ።
የጸሎት ዋናው ክፍሉ ምስጋና ነው። ሰው እግዚአብሔርን ሲያመሰግን መልካም ነገሮች ሁሉ ይበዙሉታል። ክፉ ነገሮች ሁሉ ይወገደሉታል። የጸሎት ሁለተኛው ክፍል ንስሐ (ይቅርበለኝ) ነው። ይህም የነፍስና የሥጋን ንጽሕና ያስገኛል። ሦስተኛውም የጸሎት ክፍል ልመና ነው። ሰው የልቡን መሻት ከማንም በፊት መንገር ያለበት በዘላለማዊ ፍቅሩ ለወደደን ለእግዚአብሔር ነው።
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለዱ የሰውን ሥጋ በመልበሱ ያገኘነው ጥቅም እስከ በማይባል ሀብት የተሞላ ነው።
እግዚአብሔር በአምላክነቱ ሰውን ወደደው። ሰው ቢበድልም በቸርነቱ አዳነው። ሞት በሰው ሥጋ ገብቶ ተሸሸገ። በሰው ሥጋ የተደበቀውን ሞት ከተደበቀበት ከሰው ሥጋ ውስጥ ገብቶ ያጠፋው ዘንድ ጌታችን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ተወለደ። በሰማይም በምድርም ምሉእ የሆነው አምላካችን አዳምን በቃሉ ማዳን ይችል ነበር። በሩቅ በቃል ከመናገር ይልቅ ሰውን መስሎ ሰውን ተዋሕዶ የቅርብም ቅርብ ዘመድም ወዳጅም ሆኖ ሥግው ቃል ለሕውሰታ በቀረበ በሚታይ በሚሰማ በሚዳሰስ ሥጋመለኮት ያድነን ዘንድ ፈቀደ። አካላዊ ቃል ሰው በሆነ ጊዜ ሰው ሁሉ ሙሉ ምሕረትንና ደኅንነትን አግኝቷል።
ጌታችን በሥጋ በመገለጡ እሱን የምናከብርበት እሱን የምንዘክርበት ቀናት በድርጊት በቃል ብቻ የተነገሩ ሳይሆን በድርጊት የተገለጡ እንዲሆኑ አደረገ። ለምሳሌ በ29 ፅንሰቱን ልደቱን እናከብራለን። በ6 ግዝረቱን ታቦተ ኢየሱስ ባለበት ሁሉ ጥር 6 ቀን በዓለ ንግሡ ይከበራል። (ግዝረቱ በግብረ መንፈስቅዱስ ማለትም ምላጭ ሳያርፍበት ከቀራንዮ በፊት ደሙ ሳይፈስ መሆኑንም ልብ እያስተዋልን እናከብራለን)
በ10 መስቀሉን በሀገራችን ከልዩ ታሪካዊና መንፈሳዊ ኩነት ጋር እናከብራለን።
ጥር 11 ልዩ ሦስትነቱን የገለጠበትንና ልጅነት (የኃጢአት ሥርየት) ያገኘንበትን የጥምቀትን በዓል እናከበራለን።
ጥር 12 ቀን በቃናዘገሊላ ወሃውን ወደ ወይንጠጅ የለወጠበትን ተዓምሩን እናከብራለን። ውሃ ቀለም መዓዛ ጣዕም የለውም። ጌታችን ቀለም ግሩም መዓዛ ጣፋጭ ጣዕም ሰጠው። የእኛንም ከቅድስና የተራቆተ ባዶ ሕይወት በእመብርሃን አማላጅነት የቅድስና ቀለም የጽድቅ መዓዛ የመንፈሳዊነት ጣዕም ይሰጠን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።
ቸሩ ፈጣሪያችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ክብር ይግባውና በሥጋ በመገለጡ በሆሣዕና በዓል ከሕፃናት ዝማሬ መቀበሉንና ቤተመቅደሱንም የጸሎት ቤት መሆኗን ያሳየበትን እንድናከብር አድርጎናል።
በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን በዓል የምናከብረውም በሥጋ በመወለዱ የተገኘ የቸርነቱ ሥራ ነው።
በደብረዘይት ያስተማረበትን በመዘከራችንም ምስጋና ይግባውና ለዳግም ምጽአቱ እንድንዘጋጅ ያደርገናል።
በሥጋ በመገለጡ በቀራንዮ የተሰቀለበትንና በሥጋወደሙ ያዳነበትን በዓል እንድናከብር አድርጎናል። ሞትን በሞት አሸንፎ በቅድስት ትንሣኤው ትንሣኤ ብርሃንን ሰጥቶናል።
በሥጋ በመገለጡ እርገቱን እንድናከብር እሱን የማክበር ዕጣ እንዲደርሰን እርሱንም በማክበር በሚገኝ በረከት እንድንሳተፍ አድርጎናል።
የዚህች የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅ መሆን ምንኛ መታደል ነው!!!!!
እግዚአብሔር ይመስገን።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

05 Jan, 09:21


በዓላትን ለመባረክ ብቻ እንጠቀምባቸው!!
ተረፈ ምርቱ ለሥጋና ለማኅበራዊ ፍላጎት ይደርሳልና
በርከት: ረድኤት: ትምህርት የሚገኝባቸው የቤተክርስቲያን በዓላት ለቀደምት አባቶቻችን ምስጋና ይሁና: እነርሱን አብቅቶ: አንቅቶና አንሳስቶ ሥርዓት እንዲሠሩልን ላደረገ እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ክብር ምስጋና ውዳሴ ይድረስና ከሙሉ ሥዓቱ ጋር ተክለውልን ወደማታልፍ አገራቸው ተሻግረዋል::

ከ30 ዓመታት ወዲህ ግን የቤተክርስቲያንነገር ሁሉ የገቢ ማሰባሰቢያና የፖለቲካ ገጽታ መጠጋገኛ ሆኖአል::

ታቦታት በመደራረብ ንግሥ እያበዙ ገቢ መሰብሰብ:

ስብከትን እንደ መናፍቃንስሜት መፍጠሪያ ጩኸትና የምእመናንኪስ ማራቆቻ ማድረግ:

ዝማሬን የሚዲያፍጆታና ገጽታ ግንባታ አርት ማስመሰል: እና መዝሙር ከእግዚአብሔር ምስጋና ጸሎትነት ዓላማው ውጭ የንግድ ሸቀጥ ማድረግ እጅግ በዝቶአል::

ሰሞኑን የጌታን ልደትለማክብር ስንቃረብ ማስታወቂያው ጦፎአል::ለየትኛው ዓላማ ይሆን?

ሁሉን የሚያውቅ እርሱ ይመርምር:: እኛ ግን በረከታችንን ነጋዴዎችን ኢአማንያን ባለሙያ አገልግሎት ሰጭዎች እንዳይነጥቁን በዓላቱን በኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት እናክብር::

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

05 Jan, 08:12


መሬት መቀጥቀጥ

ሰው መደንገጥ ያለበት መሬት ሲንቀጠቀጥ ሳይኾን መሬት በሥላሴ ሕንጻ ሰው ደም ስትጨቀይ ነበር። ምኅላ ለፈሰሰው ደም ይቅርታ መጠየቅ እንጂ ቁጣው እንዲያልፍ አይደለም። ደሞዛችን ገና አልተነካም። ምንደኛ እረኛ በላዩ ላይ ሕንጻ ቢናድበት እንኳ ቁጣ አይመስለውም። ምን በወጣቸው ይደንግጡ።
አንዱ "ቤተክርስቲያን ለምን ምኅላ አታውጅም" ሲል ሰማሁት። ሰው ደም ሲፈስ ለምን ዝም ትላለች ብሎ ነበር መጠየቅ። መነኮሳት ካህናት ምእመናን እንደ በግ ሲታረዱ ምን አሉ። ቆባቸው ካልተነካ አይነቁም። የእኛንም ክፋትና መጠላላት ልክ እንኳን መሬት መንቀጥቀጥ እሳት ያዘንባል። ገናኮ በሚገባ አልተግባባንም። ብሔራዊ ንሰሐና እርቅ ብቻ!!።

ንዋይ ካሳሁን!!

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

05 Jan, 05:31


ዓለም ማንን እንደሚሸልም ተመልከቱ ሦርጅ ሶሮስን፥ አብይ አህመድን ---- ምን እንደሠሩ፥ ምን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ይጠቁመናል https://x.com/MarioNawfal/status/1875618005574627439

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

04 Jan, 04:28


እነዚህ በምክክርና በድርድር ተመልሰው ሰው አይሆኑም!!!

ህሊና ቢሶቹ የብልጽግና ኦንግ/ሾሮሙማ ፖልከኞች ከንግግሮቻቸውና በተግባር ከሚፈጽሙት ግፍ በመነሳት የአእምሮ ሥሪታቸውና ነጽሮተ ዓለማቸው ኢሰብአዊነትና ነውረኝነት የመኖራቸው ትርጉማቸው ነው። እነዚህ ሰዎች በስሙ ከሚነግዱበት የኦሮሞ ሕዝብ፥ እንዲሁም ወላጃቸው ሕወሃትን ከትግራይ ሕዝብ በማላቀቅ ሰው በነጻነት እንዲያስብና በነጻነት ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በሰላም እንዲኖር ማድረግ ኃያል ተጋድሎ ነው። እነዚህ ሰዎች የተለከፉበት በሽታ የማይድን ነው። መዝረፍ፥ መግደል፥ ማፈናቀል፥ ማሳደድ፥ ማደኸየት እና ማንኛውንም ግፍ በሰው ልጅ ላይ መፈጸም በባዶ ሜዳ በሐሰት ከፈጠሩት ጥላቻ የጀመሩት በቀል አይረካም። በዚህ በሽታ የተለክፉ እና በሽታቸው ምክንያት የሚፈጽሙትን ጥቃት የሚያቆሙት ሲሸነፉ ወይንም የጠሉትን ወገን ከምድረ ገጽ ሲያጠፉ ብቻ ነው። የሚሸነፉት ጤናማ አእምሮ ያለው ሁሉ ክፋትን በአንድነት ሲከላከል እና የሰው ልጆችን ህሊና የሚያሳውረውን ዘረኝነት ከልቡ ነቅሎ በመጣል ለክብረ-ሰብእ ሲቆም ነው።
የእነዚህ ነውረኞችን ንግግርና ተግባር መቃረን ለናሙና ያህል ስንመለከተው፦

1) የወደብ ባለቤት ሆንን ይሉሃል፤ በተግባር ወደብ የሚፈለግለትን ሕዝብ በቋንቋ ከፋፍለው ከተማ ይቀሙታል፥ ያፈናቅሉታል፥ የፈጁታል፥ በሐሰት ትርክት ያጠለሹታል፥ የዘር ማጥፋት ይፈጽሙበታል።

2) መናፈሻ/መዝናኛ ሠራን ይሉሃል፤ በተግባር ግን እንዲዝናናና ደስተኛ አንዲሆን ያሉትን ዜጋ የፓርላማ አባል ሳይቀር ከህግ ውጭ በየበርሃው ያስራል: ቶርች ያደርጋል::

3) ጠንካራ መከላከያ ገነባን ይሉሃል፤ ነገር ግን የአገርን ድንበር በሁሉም አቅጣጫ በጎረቤት አስደፍረው፥ በመደበኛ ሠራዊት አማራንና ትግራይን ይወጋሉ።

4) የኮሪደር ልማት ሠራንልህ ይሉሃል፤ ነገር ግን የልማትን ትርጉም በሚቃረን መልኩ የከተማውን ነዋሪ በዘርፍና በቋንቋ ዒላማ አድርገው ያፈናቅላሉ፥ ጎዳና ተዳዳሪ ያደርጋሉ፥ ያደኸያሉ።

5) ኢትዮጵያ መቼም ከብልጽግና አትገታም፥ ኦሮሚያን ገንብተን፥ ኢትዮጵያን ደግፈን፥ ምሥራቅ አፍሪካን እንመራለን ይሉሃል፤ ነገር ግን አገር እያፈራረሱ፥ ምሥራቅ አፍሪካን እያመሱ፥ ድህነት ለመዝራት ገበሬን የምርት ግብዐት እየነፈጉ፥ የእርሻ በሬውን ሳይቀር በጥይት እየገደሉ፥ ገዳማትን እያወደሙ፥ አገሪቷን በቱርክና በግብጽ እያስከበቡ፥ ሶማሌንና ኤርትራን በጠላትነት እየጋበዙ ይኖራሉ።

እነዚህን በማሸነፍ የሰው ልጆችንና እውነትን መከላከል እንጂ ይለወጣሉ ብሎ መጠበቅ ከንቱ ነው።
እነዚህ በምክክርና በድርድር ሰው አይሆኑም።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

03 Jan, 23:58


https://www.facebook.com/share/r/1ABZ4cJqoc/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

03 Jan, 22:42


ዳንኤልን ዲያቆን፣ ታጋይን ቄስ፣ ሳዊሮስን ብፁዕ ጳጳስ ብሎ የሚኖር ሲኖዶስ እውነት ኦርቶዶክሳዊ ነው??

አገራችን ምን አይነት አእምሮዎች እንደበዙባት ለማሰብ ይቸግራል። ይህ ሰውዬ የኦርቶዶክስ ቄስ ነኝ ይላል ነገር ገነት ባለፉት ዓመታት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ነጠላ እንዳይለበስ፣ የጾም ምገብ እንዳይቀርብ በመንገሥት ግልፅ መድልዎ ሲፈፀም ተንፍሶ አያውቅም።
እረኝነቱ ለሆዱ ነው። ጳጳሳቱም የዚህ አይነቱን በቄስነት እንዲቀጥል በመፍቀድ ሚናቸውን ጥያቄ ውስጥ አስገብተዉታል፣

በሆድ መቃብርነት የክርስቶስን ብርሃን የቀበሩትን እንዴት እንገላገላቸው?

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

03 Jan, 20:10


https://youtu.be/5s8_a1MA-Fg?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

03 Jan, 05:05


በሰው ደም የተጋገር፣ በስው ዕንባ የተጨማልቀ፣ በተፈናቃዮች ሃብት የተገዛ፣ በሐሰተኛ ትርክትና ጥላቻ ሐሞት የመረረ; ከክረስቲያን ሥጋና ደም ቀለምተወስዶ "እንኳን አደረሳችሁ" የሚል ጽሑፍ የተጻፈባት የዘር አጥፊዎች ኬክ እየቆረሱ፣ አልፀፀትም የሚል መጽሐፍ የሚያሳትሙ ህሊና ቢሶች ዛሬ እንደ ሰው ልብስ ለብሰዋል ። ይገርማል!!

ዛሬም ለእንዚ ጸረ-ሰው ስብስቦች አጨብጫቢዎች መኖራቸው ውስጣችን አራዊትነት እና አደርባይነት መንገሡን ያሳያል።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

02 Jan, 17:58


https://www.facebook.com/share/v/1AqF5BFppc/?mibextid=wwXIfr

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

01 Jan, 21:37


https://youtu.be/xtevEFx6ok8?feature=shared
ሕዝቡ ራሱን ከወያኔ አምልኮ ራሱን ካላላቀቀ ጤናማ ነገር ማሰብና ማስረግ አይችልም::

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

27 Dec, 14:43


በቤተክርስቲያን አባቶችና መምህራን በአስቸኳይ መልስ የሚሹ ጥያቄዎች
፳፫/፭/፳፻፲፮ ዓ/ም

ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚከተሉት ተግባራዊ ጥያቄዎች አሉኝ።

ጥያቄዎቹ የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደርና አስተሳሰብ፥ ልማድና ከምእመናንና ከአገር አንጻር ሊኖራቸው ይገባሉ ብዬ የማስባቸውን ኃላፊነቶች መሠረት በማድረግ የመነጩ ናቸው። በእኔ አስተሳሰብ የመንግሥተም ሆነ የቤተእምነቶች ዋና ኃላፊነት የዜጎችን መንፈሳዊና ሥጋዊ ደኅነነት መጠበቅና ማስጠበቅ ነው።

አንድ ቤተ እምነት የተከታዮቹ ሁለንተናዊ ጥበቃ ይመለከተዋል። አንድ ምእመን ሰው የሥጋና የመንፈስ ውሑድ ነው፤ መንፈሳዊና ሥጋዊ ደኅንነት ያስፈልገዋል። ይህ ደኅንነት የሚጠበቅ በግዜና በቦታ ውስጥ ነው።
ደኅንነት ዘርፉ ብዙ እና ተያያዥነት ያለው ነው፦

ማኅበራዊ፥ ርስታዊ (መሬትና የተፈጥሮ ሀብቷ)፥ ፖለቲካዊ/አስተዳደራዊ (ሰብአዊ፥ ዜግነታዊ፥ ምጣኔ ሀብታዊ፥ መንፈሳዊ፥ ስነልቦናዊና ግኑኝነታዊ)፥ መረጃ የማግኘት፥ በአገሩና በማሥበረሰቡ ጉዳይ የመወሰን፥ ራሱንና ቤተሰቡን ከማንኛውም አይነት ጥቃት የመጠበቅ ነፃነት (አቅም፥ ፍትሐዊ ሥርዓት፥ መረጃ፥ ቁሳዊና ቴክኖሎጂካዊ/ጥበባዊ ሀብት ያለው) ያለው በግለሰብ፥ በቤተሰብ፥ በማኅበረሰብና በአገር ደረጃ ሊለካ የሚችል ሁኔታ ነው።

በአገራችን ቤተ እምነተችና መንግሥት ሙሉ በሙሉ በሚቻል ደረጃ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ተጠያቂነት ባለው መንገድ የእረኝነታቸውን ግዴታ በመለወጥ ጥበቃ ሊደረግላቸው በሚገባቸው ዜጎችና ምእመናን ላይ አምባገነናዊ የማጥፋት፥ የሙስና፥ ያለመጠየቅ ባህል ያዳበሩበት ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን።

ይህንን መልእክት የምጽፈው ለመንግሥተ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ራሶች ለሆኑ ጳጳሳትና ልዩ ልዩ ኃላፊነት በመቀበል በመዋቅራዊው አሠራር ውስጥ የሚያገለግሉትን አባቶችና ሊቃውንት ነው።

ጥያቄዎቹ ግልጽ እንዲሆኑ በአገራችን ባለፉት ፶ ዓመታት አንኳር በኢትዮጵያና በቤክርስቲያን አንጻር የደረሱ ስልታዊ ጥቃቶችና የባከኑ እድሎችን በማገናዘቢያነት በማንሳት ይሆናል፦

ክስተት ፩፦
በ1942 ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመናዊ ትምህርት ቤት በመክፈት የኢትዮጵያን ሊቃውንት ያገለለ የትምህርት ሥርዓት አስተዋወዙ፤ ትወልዱ የአገሩን ነባር ትምህርት፥ ጥበብና ሥርዓት እንዳያውቅ በመደረጉ ንጉሡን የሚገድል፥ ዙፋን የሚገለብጥ፥ ጳጳስ የሚያንቅ፥ እግዚአብሔርን እና የአገሩን ታሪክ የሚክድና የሚዋጋ ትውልድ ተፈጠረ፤

ጥያቄ ፩፦
በአንጻሩ ይህ ጥፋት እንዳይፈጸም የመጠበቅ ግዴታ የነበረበት የቤተክርስቲያን መዋቅርና አባቶች በቅድሥት ሥላሴ ስም ያመቋቸውን ክርስቲያን ዜጎች በአገር ግብርና ሀብት በተሠሩ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መንግሥት ሰብስቦ በጠላት የኢአማንያን የቅኝ ገዥዎች ትምህርት ከኢትዮጵያዊነትና ከእግዚአብሔር ለይተው አራዊት ሲያደርጓቸው በዝምታ የፈቀደቸው ለምንድ ነው?
=======================// ===================

ክስተት ፪፦
፪) በ1966 በውጭ አካላት በሚመሩ አእምሮአቸውን በባእዳን ትምህርት በታጠቡና የአእምሮ ሕፃናት የሆኑ ወጣቶች የራሽያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ማጥፋቱን ከ70 ዓመታት አስቀድሞ የሚታወቀውን የማርክሳዊና ሌሊናዊ ርእዮተ ዓለም በችፍን ገልብጠው በማምጣት ሲያምፁ፥ ዘላለማዊ ክብር ይግባውና “እግዚአብሔር የለም” ብለው አዲስ ማሥበረሰብና አገር ለመፍጠር ተነሱ፤ ሕግም፥ ትምህርትም ከቀደመው የበለጠ ተበላሸ፥ የአገር አዋቂዎች እንዲያልቁ ተደረጉ፥ ቤተክርስቲያን በሕዝብ ያላት ተጽእኖ በሕግና በመዋቅር ደረጃ አንዲያበቃ ተደረገ፥ ሕዝቡ ከደብርና ከካህናት ወደ ኢአማንያን የቀበሌ መሪዎችና የፍርድ ሸንጎ ሥር ቁጥጥር አንዲደረግበት ተደረገ።

ጥያቄ ፪፦
የጥምቀት ልጆች ከአዲሱ አፅራረ ቤተክርስቲያን የክህደት ፖለቲካ ጋር እንዳይተባበር፥ የሥርዓቱ አስተምህሮ የክርስትና ትምህርትና ሕይወት ጠላት እደሆነ ከ ቤተክርስቲያን መሪዎች አዋጅና ውግዘት፥ ትምህርትና ጥሪ ለምን አልተደረገም? የጥምቀት ልጆች በገፍ ወደ ኢአማኒነት በመግባት አገሪቷን አንዳያጠፉ ቤተክርስቲያን እንደ አንድ ታላቅ ታሪካዊ ተቋም አቅሟን በምንም መልኩ ሳትጠቀም ለምን በዝምታ ልጆቿን ለጥፋት አሳልፋ ሰጠች?

=======================// ===================

ክስተት ፫፦
በማርክሲሰት ሌኒኒሰትና በጸረ-ነባር እሤት ዝንባሌያቸው ምክኒያት እና በውጭ የኢትዮጵያዊ ማኅቀፈ-ዕሳቤ (ነፅሮተ ዓለም) ታሪካዊ ጠላቶች ድጋፍና ምሪት የኤርትራ፥ የትግራይና የኦሮሞ ነፃ አውጭዎች ነን የሚሉ የአእምሮ ሕፃናት ተነስተው የጥምቀት ልጆችን በክህደት ፖለቲካዊ ፍልስፍና እና የሐሰት ትርክቶ መርዘው፤ በማይጨበጥ ቅዠታዊ ተስፋ ሥር አሰልፈው አፋጁት፤ አገርን እና ሕዝቡን በቋንቋና በጎሣ ከፋፈሉት፤ መለያየትና ከህብረት ወደ ግጭት መሻገርን “ነፃነት” ብለው ሰየሙለት፤ ክርስትናን ከፖለቲካዊ ርእዮት አሳንሰው ትውልዱን ከእግዚአብሄር ለይተው የዘረኝነትና የአካባቢያዊነት ጣዖት አስመለኩት፤ ይህ አድጎ አሁን ለተገለጸው የዘር መነኮሳትና ጳጳሳት መፈልፈል መሠረት ሆነ።

ጥያቄ ፫፦
ቤተ ክርስቲያን የጥምቀት ልጆቿ ደንዝዘውና በክፉ ዓለማዊ ትምህርት ተታለው በዓለም ላይ እየኖሩ ከሁሉም ዓለማዊ ነገር ነፃ እንደሆኑ አገራቸውን ለማምነታቸው ጠላት ለሆነው ፖለቲካ አሳልፈው ሲሰጡ፤ በዘረኛ የቡድን ተከፋፍለው “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ከሚላቸው አምላካቸው እንዳይለዩ ተደርገው በጥላቻ ኃጢአት ውስጥ ሲወድቁ ለምን ጊዜው የዋጀ ትምህርት መስጠት አልቻለችም? ስለምንስ ጠላቷ የሆነውን የፖለቲካ አሥምተህሮና አሸራር ውስጥ ልጆቻቸው እንዳይሳተፉና በምትኩ ከእግዚአብሔር የማይለያቸው ፖለቲካን በመፍጠር አገራቸውን እንዲታደጉ አልመከረችም?
=======================// ===================

ክስተት ፬፦
ከባእድ ትምህርት፥ ከማርክሳዊና ሌኒናዊ ፖለቲካ እና ከባእዳን የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ድጋፍ የተነሳ የትግራይ ነፃ አውጭ (ሕወሐት) እና የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) በትብብር በተፈጠረ ሕገ መንግሥት መሠረትን የዘር ክልል፥ ቋንቋ፥ ትምህርት፥ አስተዳደርተዘረጋ፥ ኦርቶዶክስ በግልጽ የልማትና የሥልጣኔ ጠላት ናት የሚል መንግሥት ተመሠረተ፥ በክርስቲያኖች ላይ ስደትና እልቂት በግልጽተጀመረ፤ በስፋት እየተካሄደም ነው።

ጥያቄ ፬፦
ቤተክርስቲያን እነዚህ ጸረ ክርስትና መሆናቸውን በግልጽ አውጀው፥ ሕግ ጽፈው፥ መዋቅርና ሥርዓት ዘርግተው ክርስትና በማጥፋት የተጠዱት አካላት የመሠረቷቸው የኢሕአዴግ እና የብልጽግና መንግሥትን፥ ለመፈጠራቸው ምክኒኣት የሆነውን የደርግ መንግሥት በግልጽ በማውገዝ ልጆቿ የፖለቲካው ተሳታፊ ከመሆን የራሳቸው ለሰው ልጅ አንድነትና ፍቅር የሚስማማ፥ ክህደት ያልሆነ፥ እና ከኃጢአት የሚየብቅ አዲስ ፖለቲካ እንዲጀምሩ ለምን አልመከረችም?
=======================// ===================

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

27 Dec, 14:43


ክስተት ፭፦
ብልጽግና የሚባል የብልጽግና ወንጌል የተባለ የፕሮቴስታንት ክፍልን የሚከተል፥ አብይ አህምድ የሚመራው የዉሀብያ ፍንፈኛ ኢስላም፥ የፖለቲካዊ ዋቂፈታ ጣዖታዊ ክፍደት፥ እምነት በሌላቸው ተረፈ-ማርክስ ምሁራን፥ ሰውን ሴምና ኩሽ ብለው የሚያሰልፉ ዘረኞች፥ ከጀርመን የናዚ ክርስትና በተቀዳና ዘረኝነትን ለማራመድ በሚፈቅድ የፕሮቴስታንት አይነት የጋራ ትብብር መንግሥት ተመሠረተ፤ ይህ መንግሥት ኦርቶዶእሳዊነትን እና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ዜጋ በቀጥታ የሚጨርስ መንግሥት ነው፤ ይህ መንግሥት ማንኛውንም ነባር ባህልና እሤቶቹን መደምሰስና በመሪዎቹ ዕሳቤ ልኬታ “አዲስ” የተባለችና ከኦርቶዶክስ ክርስትና ነፃ የሆነች አገር ለመመሥረት በተለያዩ መንገዶች እልቂት በመፈጸም፥ ከከእምነት በማውጣትና በማሳደድ ላይ ይገኛል።

ጥየቄ ፭፦
የኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ቀጥተኛ ጠላትነት እንዳላቸው የሚታወቁ በአብይ አህመድ አሊ የሚመራው በብልጽግና መንግሥት ሥር የተሰባሰቡ አካላትና መንግሥት ቤተ ክርስቲያን እና በልጆቿ ላይ የሚታይ ግልጽ እና ሁለገብ ጥቃት በሚፈጽበት በአሁኑ ሰዓት የቤተ ክርስቲያን አባቶችና መምህራን ምእመናን የተቃጣባቸውን ጥፋት በግልጽ እንዲያውቁ ለምን አልተደረገም? የጥምቀት ልጆች እነዚህ የቤተክርስቲያን ጠላው አውቀው አንድ ሆነው በመቆም ታሪካዊት አገራቸውንና ቤተክርስቲያናቸውን የሚከላከሉበት ትምህርት መስጠት ለምን አልሞከረችም? መንግሥትን፥ አጥፊ ሕጉንና ፖሊሲውን እንዲለውጥ ለምን በሕግ አልጠየቀችም?
=======================// ===================

ክስተት ፮፦
ከ፩-፭ ተራ ቁጥር በተዘረዘረው ክስተቶችና ሂደቶች ሁሉ ከአጥብያ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ያለው የቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ኢአማንያን፥ መናፍቃን፥ ዘረኞችና ምንደኞች ተደራጅተው ቤተክርስቲያንን ተቆጣጠሩ፥ የጎሣ ፖለቲካ አገልጋይ የሆኑ ክህነት-አልባ መነኮሳት በፖለቲካው ግፊት እንዲሾሙና እንዲሿሿሙ ተደረገ። በኦነግና በሕወሐት የናበበና የተቀመረ ሤራ፥ በሳዊሮስና በሠረቀ መሪነት “የኦሮሞ/ብሔር ብሔረሰብ፥ የሕወሓት/የትግራይ ሲኖዶስ” ተመሠረተ። ከቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት ተላለፈ። ውግዘቱን ተከትሎ ሕግ በማስከበር የቤተክርስቲያን ሀብትና ምእመናን ለእውነተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ በማስረከብ ውጉዛንን ማስወገድ የነበረበት መንግሥት በግልጽ የራሱ ፕሮጄክት መሆኑን በሚያጎላ መንገድ ሕገወጦችን ደግፎ ብዙዎችን ገደለ፥ ከሥራ አባረረ፥ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖችን አሠረ።

ጥያቄ ፮፦
ዘረኝነት፥ ምደኝነት፥ ኑፋቄ፥ የፖለቲካ አገልጋይነት ጓዙን ጠቅልሎ ቤተክርስቲያን ውስጥ መግባቱና ሲኖዶሱን የጎሣ ጉባኤና የፌደሬሽን ምክር ቤት ሲያደርገው፥ ይህ እውነታ በምእመናን ዘንድ ሳይቀር ታውቆ የመፍትሔ ሀሳቦች በተደጋጋሚ ሲቀርቡ ሲኖዶሱ ራሱን ከማረም፥ በኦርቶዶክሳዊው የሐዋርያት መንገድ መልሶ ራሱን ለመመሥረት ያልፈቀደበት ምክንያት ምንድነው?

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

27 Dec, 13:17


የኦነግ-ብልጽግና እና የጽነፈኞቹን ቁማር በልኩ ማጋላጥ የግድ ነው!!


የኦሮ-ዉሀቢዝምና ብልጽግና ወንጌል አስተባባሪነት የጎንድርን ካህንና ቤተሰቦቹን የጨፈጨፈው ቡድን ይህ ነው https://rumble.com/v25xqcy-january-17-2023.html

"የኢትዮያ ኢስላም" የሚባል የለም የሚሉቱ አንዳንድ ሰው መሳይ መርዛም ዑስታዞችና የጂሃድ አቀንቃኞች፥ የቱርክ ተላላኪው ግራኝ አህመድ መሸነፍ ፀፀተኞች ሶማሊያ ድረስ ተጉዘው ከአልሸባብ ጋር ተባብረውና የሁሉንም ጎሣዎች ጽንፈኛ የአልቃይዳና አይሲስ መንፈስ ወራሾች በማሠልጠን ወደ ክርስቲያኖች ጭፍጨፋ ያሰማራሉ።

የቦኩሃራም፥ የአልቃይዳ፥ የዳኢሽ፥ የኤይ ኤፍ ኤል ኦ፥ ወዘተ ደም አፍሳሽነት የሰይጣን አገልጋዮች የሚያስቀናቸው ኢትዮጵያውያን እጅግ አሳፋሪ አቋም እያሳዩ ነው።

ሽመልስ አብዲሳና አብይ አህመድ፥ ጀዋር መሀመድና ሌሎች ጽንፈኞች ይህን የውቃሉ። ነገር ግን የዋሁን የኦሮሞ ሕዝብ በብሔር ስም እያጃጃሉ ጂሀድ ያካሄዳሉ። ከሚሴና አጣዩ፥ ከበደኖ እስከ አርባባ ጉጉ፥ አርሲ፥ ሰሞኑን ሽርካ ከኦሮሚያ የጸጥታ ቢሮ እየታዘዘ የሚያርደው ሠራዊት የዚህ የጂሃድ አካል ነው።

አዲስ አባባ የኦርቶዶክሳውያንን ቤት እያስፈረሰ አሰፋፈር የሚቀይረው፥ ክርስቲያኖችን ለማደኸየት የሚሠራው የአብይ አህመድ ፕሮጄክት የዚህ የጂሃድ ስውር እጅ ነው።

እንቅልፍ አልለቀውም ያለው ክርስቲያንና አንዳንድ ዑስታዞች "ኢትዮጵያዊ የሚባል ኢስላም የለም" ብለው በንዴት የሚናገሩበት ምክንያት አዲሱን ይህን በማረድ የተሰማራውን "እስልምና" ለማበረታታት ነው። ተጠያቂ መሆን አለባቸው።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

27 Dec, 02:57


በጅምላ እየፈጀ የሚገኘው መንግሥት ፍጅቱን በማስቀጠል በዝምታና በማደንዘዣነት ከሚያገለግሉት ጳጳሳትና የሃይማኖት ተቋማት ጸሐፊ ጋር ፎቶ ተነስቶ "የሰላም ሚኑስቴርና ቤተ ክህነት ለሰላም እብረው ለመሥራት ተነጋገሩ" የሚል ስላቅ ያሰራጫል። ይህ የሕዝብ ንቀትና በምእመናን ደምና ነፍስ ላይ መሳለቅ ጽዋውን ለመሙላት ኑውና በርቱበት ብያለሁ።👇👇👇👇

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

27 Dec, 02:50


https://www.facebook.com/share/p/12BhQKrzkSN/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

27 Dec, 02:50


ከ 590 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና ከ 780 በላይ የአብነት ደቀ መዛሙርት መበተናቸው ተገለጸ!

ታኅሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ /አዲስ አበባ)

በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ አንድ የአብነት መምህርን ጨምሮ ከ 599 በላይ ኦርቶዶክሳውያን እንደተገደሉ እና ከ 780 በላይ የአብነት ደቀ መዛሙርት መበተናቸው ሀገረ ስብከቱ የ 43ኛው መደበኛ ሰበካ ጉባኤ ባካሄደበት ዕለት በገለጸው ሪፖርት አሳውቋል።

በዕለቱ በእነማይ ወረዳ ከ 103 በላይ ምእመናን ሞት እና በጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርት ከፍተኛ የሆነ መቀዛቀዝ መፈጠሩና በደባይ ጥላት ወረዳ በ 7 አጥቢያ የሚማሩ ከ 300 በላይ ደቀ መዛሙርት መበተናቸውንና በተጨማሪም በባሶ ሊበን ወረዳ አንድ የአብነት መምህርና 395 ምእመናን ሲገደሉ በአነደድ ወረዳ ከ 250 በላይ ደቀ መዛሙርት ከጉባኤ ቤት ውጭ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በደብረ ኤልያስ የቅኔና የመጻሕፍት ትምህርት ቤት ከ 230 በላይ ደቀ መዛሙርት ሲበተኑ በሸበል ወረዳ ከ 100 በላይ ምእመናን መሞታቸው በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የተገለጸ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ ጠቅላላ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሀገረ ስብከቱ ፈተና ስለሆነው የዶግማና የቀኖና ጥሰት ጉዳይ ፣ ስለ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎችና መፍትሔዎቻቸው ፣ሰበካ ጉባኤ ስለማጠናከርና አብነት ት/ቤቶች ስለማጠናከር ውይይት በማድረግ በትናትናው ዕለት ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Dec, 16:40


https://youtube.com/live/EBg-3MzCfE4

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Dec, 16:37


በኢሰመጉ መታገድ ዙሪያ የተሰጠ አጭር መግለጫ ታህሳስ 17 /2017 ዓ/ም ቻናላችንን ለመቀላቀል ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑት https://t.me/ehrcow

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Dec, 16:37


ኦነግ-ኦሮሙማ-ብልጽግና ሰብአዊነትን፥ እውነትን፥ ዲሞክራሲን አይታገስም

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Dec, 14:20


https://youtu.be/kJiTPG7LhhM?si=ZkqCXkOeJafKVGsH

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Dec, 05:08


ዓርብ ታህሳስ 18 ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ እንገናኝ https://youtu.be/NMlIo4DpPJU

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Dec, 04:24


ከ5 ዓመት በፊት ፋይናነሺያል ታይምሰ ያወጣው ምስል አውዱ አብይን ለማድነቅ፥ ለምእራባውያን መልካም ጊዜ እንደመጣ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ ልትሻገር ነው በሚል ማታለያ ከተጻፈ አርቲክል የተወሰደ ነው። እውነቱ ግን አገራችን ለሽያጭ እኛ ለእልቂት መዳረጋችን የጀመረው ወያኔና ኦነግ የዘር ሕገ መንግሥት በጸደቀ ጊዜ ነበር።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Dec, 00:49


@ABCTV በኦሮምኛ ቋንቋ አገልግሎት መጀመራችሁ እጅግ አስፈላጊና ለኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች በዘር ነጻ አውችዎች የአእምሮ ባርነት ውስጥ አንቀጥልም፥ በነጻነት አስበን የሚጠቅመንን እናደርጋለን እንዲሉ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ። ሌሎችም ሚዲኣዎች በኦሮምኛና በትግርኛ መርሐግብር በመጀመር የሐሰት ትርክትና ስሑት ፕሮፓጋንዳን ማክሸፍ ይጠበቅባቸዋል ። በርቱ!!

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Dec, 00:45


የኦነግ-ኦሮሙማ/ብልጽግና እና የሕወሃት አፈጣጠር ኦርቶዶክሳዊነትም፥ ኢትዮጵያዊነትን፥ አንድነትን፥ ታሪካዊነትን የማጥፋት ግብ ላይ ነው። ምንም በመቀባባትና በመሽኮርመም ይህን ማንነታቸውን ማስለወጥ ኤእቻልም። መፍትሔው ሁለቱን ካንሰሮችና ለካነሰሮቹ በቤተ ክህነት መዋቅር ውስጥ የተሰለፉትን ምንደኞች መጋፈጥ ብቻ ነው።

አቅም ካጣን ሰው እንሁን፥ ከበተረታን ክርስቶሳዊ እንሁን።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Dec, 00:42


https://www.youtube.com/live/HP87cx8KWdY?si=OlAZ5vASnRwp6JDN

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

25 Dec, 21:13


ይህን ማስተዋል እጠቅማል https://vm.tiktok.com/ZNewB3JxP/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

25 Dec, 07:01


https://youtube.com/live/-f92GQ0MR4Y?feature=share

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

25 Dec, 03:22


https://x.com/VoiceFano2/status/1840104006451876302 ለምሳሌ ይህን የዘር ማጥፋት ጥሪ ያድረገን ግለሰብና ሚዲያ የከሰሰ የአማራ ልጅ ወይንም ህሊና ያለው ኢትዮጵያዊ የለም!!

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

07 Dec, 04:48


ኢትዮጵያ ህይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ_h.mp4

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

07 Dec, 00:44


"የትግራይ ወጣት የሞተው አገር ለመፍጠር ነው፥ እኛም የመነኮስነው ለትግራይ አገር መሆን ነው። ክርስቶስም የተሰቀለው ለትግራይ ነው። ቤተ ክርስቲያንም የምታገለግለው የሕወሃትን ርእዮት ዓለም ነው" የሚሉት የዚህን አይነት በነፍስም በሥጋም የሞተን ከሀዲ " አቡነ" የሚል ሕዝብ ክርስቲያን ነኝ ብሎ ማሰብ ኤእገባውም። ክርስቲያን ለመሆን ከዘር ፖለቲካና ዕሳቤ ነጻ በመሆን ሰው ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

06 Dec, 22:52


https://x.com/ASN_Amhara/status/1864724902567137303?t=jJmKcMOtXyXKJg81Zue1PA&s=08

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

06 Dec, 07:10


https://youtu.be/cDbclFnEdgQ

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

05 Dec, 00:04


ዜና፦
ታላቅ የዘመናችን ግኝት።
አብይ አህምድ አሊ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር፥ "ባለምጡቅ አእምሮው መሪኣችን ማንም ያልደረሰበትን የኋላቀርነታችን ምክንያት በሚያስገርም ምርምር ደረሰበት" ።
ሆያ ሆዬና አበባየሁ የሚዘምረው ማኅበረሰብን ለማጽዳት በእርቅ ስም ከወለጋ፥ ከአርሲ፥ ከባሌና ሀረርጌ፥ ከሰሜንና ምዕራብ ሸዋ ክርስቲያን እንዲያጸዳ ትዕዛዝ የተሰጠው በሽፋን ኦነግ ሸኔ የሚባለው ግዳጁን በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ መትቶ ያንን ተግባር እንዲያጠናቅእ እርቅ በሚል ስም ዝግጅት እየተደረገ ነው።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

05 Dec, 00:03


ናዚው ባለጅኒው አብይ አህመድ እንዲህ ነው የአማራን ትውልድ እያወደመ ያለው፡፡ አዲሱ የአማራ ትውልድ ለሺህ አመታት የሚተርፍ ቂምን ቋጥሯል፡፡ ከጫንቃችን ላይ ካለፈቃዳችን የሚወጣ የለም ይራገፋል…
ሼር 💪🏿
ሼር💪🏿
ሼር💪🏿

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

04 Dec, 01:07


#ዜና_ምሥራቅ_ወለጋ

“ከፈጠሪ በታች ራሳችንን እንከላከልበት ዘንድ የታጠቅነውን መሣሪያ ከበባ አድርገው ገፈውናል፤ አኹን ለእርድ ተዘጋጅተን በመጠበቅ ላይ ነን፡፡” 

በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ አንዶዴ ዲቾ፣ ደጋ ጂጊ ቀበሌዎች ትናንት ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም መከላከያ ሠራዊት ነን ያሉ ኃይሎች ንጋት አሥራ አንድ ሰዓት እስከ ጠዋት ሦስት ሰዓት አዘናግተው ከበባ በማድረግ ራሳችንን እንጠብቅበታለን ብለን ከብቶቻችንን ሸጠን በመንግሥት እውቅና የገዛነውን መሣሪያ ገፈውናል ያሉት ነዋሪዎች አኹን ራሳችንን ለእርድ አዘጋጅቶ እንደመጠበቅ ነው የምንቆጥረው ብለዋል፡፡

ባለፈው እናት ፓርቲና ሌሎች የሕዝብ ሰቆቃ የሚገዳቸው ሚዲያዎች ቦታው ድረስ በመደወል ጭምር ድምጻችንን ካሰማችሁልን ወዲህ መከላከያው መሣሪያ ማስፈታቱን ትቶት ነበር፤ ተግባብተንም እንዲህ እንደማይሆንም ተነጋገረን ነበር ያሉት የቀበሌው ነዋሪዎች አዘናግተው ይኽንኑ በመሸሽ ወደ ጫካ ገብቶ የነበረውም ከጫካ ከተመለሰ በኋላ በተኛበት እንደሽፍታና ቀማኛ ከየቤቱ አውጥተው ከ80 የማያንስ የነፍስ ወከፍ መሣሪያችንን ወስደዋል ብለዋል፡፡ በአካባቢው ላሉት ወታደራዊ አዛዥ ደውለን ስንነግራቸው ‘ማን ነው ይህን ያደረገው?’ በሚል ንጋት ሦስት ሰዓት ላይ እንዳስቆሟቸው ነዋሪዎች ገልጸውልናል፡፡ በዚኽም የተወሰኑ የሠራዊቱ አባላት በወረዳና ዞን አመራሮች የተሳሳተ ሥምሪት እንደወሰዱ ማወቅ ችለናል ብለዋል፡፡ ይህ ደግሞ የበለጠ ሥጋት እንዲገባን አድርጓል ይላሉ፡፡ አኹንም መሣረያችንን አንሰጥም፣ ዐይናችን እያየ አንሞትም ያሉ መልሰው ጫካ ገብተዋል፡፡ የዞንና ወረዳ ካድሬዎችም ጫካ የገባውን ቤተሰቡን እናስራለን፣ እንቀጣለን እያሉ እንደሚዝቱ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

“መሣሪያውን ከእኛ ነጥቀው ‘የራሳችን’ ለሚሉት ሰው ነው የሚሰጡት” ያሉት ነዋሪዎች “ቢያንስ መሣሪያ ማስወረዱ ለመልካም ተፈልጎ ነው ካሉ ለምን ብሔር[ማንነት] ልዩነት ይደረጋል?” ብለዋል፡፡

ፓርቲያችን በተደጋጋሚ እንደገለጸው መንግሥታዊ መዋቅሩ ባልጠራበት፣ ጥቂት የማይባሉት በኹለት ቢላዋ በሚበሉበት፣ በድብቅም በገሃድም ከፍተኛ የጥላቻ ንግግሮችና ተግባራት እያስተዋልን ባለበት በአኹኑ ወቅት ሕዝቡ በራስ ተነሳሽነት ራሱን ለመጠበቅ እያደረገ ያለው ጥረት ሊደገፍና ሊበረታታ እንጂ እንደወንጀል ሊቆጠር አይገባም። የምሥራቅ ወለጋውም ጉዳይ ከዚኽ ተነጥሎ የሚታይ አይደለም፡፡ በአካባቢው ከፍተኛ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ የተከሰተና ያለ በመሆኑ ለሕዝቡ አስተማማኝ ጥበቃ እስከሚደረግ ራስን መከላከል አማራጭ ተደርጎ፣ በሕግና በሥርዓት እንዲመራ ማድረግ እጅ ላይ ያለ የተሻለ አማራጭ መሆኑ መታወቅ አለበት። የጸጥታ ኃይሉ ትርጉም ያለው ጥበቃ ለዜጎች በማያደርግበት ኹኔታ ነዋሪው ራሱን የሚከላከልበትን መሣሪያ መቀማት በቅርቡ በአርሲ የተከሰተው ዓይነት ጥፋት ለማድረስ ካልሆነ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው እንደማይችል ታውቆ የእርምት እርምጃ በአስቸኳይ እንዲወሰድ እናት ፓርቲ ያሳስባል።

እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

03 Dec, 16:34


https://ethiofact.com/203751/qeis-mogese-birhanu-nega-aterarek/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

03 Dec, 05:44


https://www.youtube.com/live/4Hz_gCjOyys?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

03 Dec, 02:32


🔥#የንፁሀን_ጭፍጨፊ_በአቸፈር‼️

አብይ አህመድ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አቸፈር- ዝብስት ላይ በፈፀመው የጦር ወንጀል ከጨፈጨፋቸው 43 ሲቪሊያን መካከል ለግዜው ዝርዝራቸው የደረሰን:-
1. ሀይማኖት ተማረ
2. አብርሃም አለሙ
3. ወርቁ ሲሳይ
4. አስፋው ደለለ
5. አዲሱ አወቀ
6. ስመኛው በእውቀት
7. አትርሰው ዳኝነት
8. ስጦታው ምኒችል
9. ስሎታው ስሜነህ
10. ተሻገር ገብሬ
11. ችሎታው አዘነ
12. ሀብታሙ አደባ
13. ቻላቸው ጥሩነህ
14. አይቸው ተመስገን
15. ምህረት ሙሉቀን
16. ብርሃኑ ማንነግረው
17. ማስተዋል ታዴ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ቦታ በተደረገ ጥቃት:-
1. አበባው ተፈራ
2. ምስክር
3. ተመስገን መለሰ
4. ስለሽ ተስፋ
5. ጌጤነህ መኳንንት
6. አብርሀም ድረስ
7. ጌታነህ ካሳ
8. አብርሀም እግዳው
9. መታደል አየነው
10. አማን ግርማው እና
11. አጉማሴ አብዬ  የተባሉት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና በሞት እና በህይወት መሃል የሚገኙት ናቸው።

በሰው ላይ ጉዳት ባያደርስም በተመሳሳይ ቀን ፋግታ ላይም የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።

በዚሁ እለት በቲሊሊ ዙሪያ አስኩና ጊዮርጊስ ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባላትን የገደለ ጥቃት ሲፈፀም ባንጃ ወረዳ ሳትማ ዳንጊያ ቀበሌ አከና  አቦ አካባቢ እና ጃንጉታ ጊዮርጊስ አካባቢዎች ላይ የደረሰ የድሮን ጥቃት በርካታ የቤት እንስሳትን ገድሏል።

#Stop_Amhara_Genocide‼️

26/2/17 ዓ.ም

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

02 Dec, 20:33


https://youtube.com/live/O562lMAvawk?feature=share

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

02 Dec, 06:36


https://www.facebook.com/share/r/1BFmyDuZX5/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

01 Dec, 19:04


https://youtu.be/TP0ZSis0e2w

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

01 Dec, 09:53


https://www.facebook.com/share/p/19dnaZ6Gwp/

ይህ ቅንጭብ ቪዲዮ ከቲክቶክ ስሰማው "የትግራይ አባቶች" ብሎ ይጀምራል።

ይትግራይ፣ የእንትና አባት ብሎ ነገር የለም። ይህ አቀራረብ እጅግ መሰሪ የቁልቁለት ፕሮፓጋንዳ አቀራረብ ስልት ጥሩ ምሳሌ ነው።

በዚህ መሠሪ አቅራረብ ውስጥ "የትግራይ አባቶች ግን ጥያቄ መጠየቁን አላቆሙም" የሚለውን ዐረፍተ ነገር እንመርምር:-

(፩) የክርስቲያኖች ሁሉ አባት ያልሆኑ የትግራይ የሚባሉ አባቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ፕሮፓጋንዳ እየሠራ ነው

(፪) ትግራይ ብሎ ወያኔ በከለለው የዘር ፖለቲካ ክልል ውስጥ ለሚፈጸም ግፍ ከሲኖዶሱ የተሻለ መልካም ዐሳቢዎች "የትግራይ" የተባሉት አባቶች ሱሆኑ "ሌሎቹ" ሌሎችና ባዕዳን ናቸው

(፫) "ሌሎች" ወይንም የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ አባላት የትግራይ ሕዝብ ተብሎ ከክርስትና ማንነቱ በተለየ መንገድ በሕወሃት በታዘዘለት አዲሱ ፖለቲካዊ የትግራዋይነት ማንነት አንጻር ጠላት ናቸው

(፬) የትግራይ አባቶች የተባሉትና ከጥምቀት ልጆች አባትነታቸውን በትግራይ አባትነታቸው ሌላውን የመጠየቅ መብት ይሰጣቸዋል።

ብዙ ሰው ሚዛኑን የሚያጣው በዚህ አይነት ሤረኛ አቀራረብ ነው።

መንስኤ ደብቆ ውጤቱ ላይ መለፋደድ ሕወሐታዊ ያሰለቸ ስልት ነውና
የዘር ነጻ አውጭ የመሠረተ ሕወሐት፣ የዘር ሕገ መንግሥት የጻፈ፣ የዘር ክልል የፈጠረ፣ ለ፴ ዓመት መከራ ሲያጸና ቄይቶ ለሌላ ዘረኛ አጥፊ ስልጣን እስከነ ዘረኛው ሕገ መንግስት ጋር አስረክቦ የሄደ፣ የደሜን እኔን አጥቅቶ ጦርነት የቀሰቀሰ፣ የትግራይንና ዙሪያውን ወደ እልቂት የቀየረን ሕዋታዊ ፖለቲካ የማይጠቅስ መፍትሔ ሁሉ የሸፍጥና የሌላ ዙር ጥፋት ልፈፈፋ ብቻ ነው።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

01 Dec, 05:25


https://youtu.be/5HuFYgTI6OU?si=vAiPG34x-_caluUf

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

30 Nov, 22:18


https://youtu.be/HGJzxLHgdws?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

29 Nov, 04:43


https://youtu.be/lPu0SUyf1MA

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

28 Nov, 06:30


ጉድ በል ጎንደር! አለ የሀገ ሬሰው

99̈ % የሐሰት መረጃና አረዳድ ይዞ አደበባይ መውጣት ምንኛ ድፍረት ነው?

አንድ ወንድማችን እኛ ሳናውቀው እርሱ አውቆን ለክቶናል --- ስሙትና ለኩን እንግዲህ።
መቼስ አባትም መሪም ያጣች አገር፥ ጭፍን መንጋ አፍ ሶ50 ዓመት በደም የዋኘውን ሕወሃትንና ኦነግን ሳይቀጡ የሚያይ ሰው ሁሉ ከመሬት ተነስቶ ልምራችሁ፥ ልግራችሁ ማለቱ የተለመደ ሆኗል።


ምን ይሆን የቆጠቆጠው? አልገባኝም። የአማራን በሰብአዊነት፥ በፍትሕ፥ በእውነትና የአገር ባለቤተነት መርህ ላይ የተመሠረተ ትግል ወደ ዘረኛ የደምና አጥንት ደረጃ አውርደን ከሕወሃትና ከኦነግ/ብልጽግና ካላስተካከልነው፥ የዘር ክልልና ሕገ መንግሥት ካላስቀጠልን ሞተን እንገኛለን፤ አሁን በአሜሪካኖች አጋፋሪነት የተጀመረውን ብአዴን ቂጥር 2 የማደራጀት ሤራ ካላቀለቀጠፍን የሚመስል ንዴት ያለበት ይመስላል።

https://youtu.be/50JT0UZZ8wo?si=VIAJSrCShLZDjNiG

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

27 Nov, 18:38


https://www.youtube.com/live/C76jBSxNC5w?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Nov, 06:38


የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
- Advertisement -
- Advertisement -
Tags
በህግ አምላክ
Facebook
Twitter

Admin

- Advertisement -
የቅርብ ጊዜ
መጽሐፍት
የመፅሃፍ ግምገማ : ትዉስታዎቼ ፡ ስለ መሬት ይዞታና የተለያዩ ፖለቲካዊና አገራዊ ጉዳዮች
Admin - November 25, 2024
- Advertisement -
ነፃ አስተያየት
ምን ውስጥ ነው የገባነው? (ኤፍሬም ማዴቦ)
November 25, 2024
ነፃ አስተያየት
በአገራችን ምድር ለተፈጠረው ውዝግብና እስከዛሬም ድረስ ዘልቆ ለሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ተጠያቄው የግራ አስተሳስብ በመግባቱ ምክንያት አይደለም፤ ዋናው ምክንያት ሌላ ቦታ ላይ ነው!! ለልጅ ተድላ...
November 20, 2024
ነፃ አስተያየት
የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሃሰተኛ ማስረጃ
November 13, 2024
Related News
መጽሐፍት
የመፅሃፍ ግምገማ : ትዉስታዎቼ ፡ ስለ መሬት ይዞታና የተለያዩ ፖለቲካዊና አገራዊ ጉዳዮች
November 25, 2024
ነፃ አስተያየት
ምን ውስጥ ነው የገባነው? (ኤፍሬም ማዴቦ)
November 25, 2024
ነፃ አስተያየት
በአገራችን ምድር ለተፈጠረው ውዝግብና እስከዛሬም ድረስ ዘልቆ ለሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ተጠያቄው የግራ አስተሳስብ በመግባቱ ምክንያት አይደለም፤ ዋናው ምክንያት ሌላ ቦታ ላይ ነው!! ለልጅ ተድላ...
November 20, 2024
ነፃ አስተያየት
የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሃሰተኛ ማስረጃ
November 13, 2024
ነፃ አስተያየት
የአማራ ጠሎች “የዘር ማጥፋት” ፍኖተ ካርታና የህልውና ትግል የወለደው የአማራ ብሄርተኝነት።
November 13, 2024
- Advertisement -
2 COMMENTS
Manny November 19, 2024 At 5:17 pm
This is perfect response for the boy king. It is also a good knowledge for the rest of us. Thank you!!!
Reply
Alem November 19, 2024 At 5:39 pm
ፀሐፊው በጎ አሳብ ኖሮት ሊሆን ይችላል። የጎረሰውን ማላመጥ ግን አልቻለም። ብዙ መጽሐፍት ማጣቀሱ አንብቤአቸዋለሁ ከማለት ወዲያ ፋይዳው ምንድነው? እንደ ተቻቸው ኮ/ል ዐቢይ እንግሊዝኛውን ከአማርኛው ጋ ሲያቦካ አየን። ኮ/ል መንግሥቱን ከማጥላላቱ የተነሳ ሳያጣራ የአንደ ደረጃ ትምህርት ብቻ አላቸው ብሏል። የእነ መለስን ንግግር የሚያርምላቸው ሰው መኖሩ ይገባ ነበር ባለው መሠረት እርሱም ጽሑፉን ቸኲሎ ለሕዝብ ከማቅረቡ በፊት ቢያዩለት ምናልባት ትንሽ ይበጅ ነበር። ለማንኛውም የተነሳበት ዋናው ዓላም እኛ ደገኞች አማሮች/ትግራዋዮች ከማንም አናንስም ለማለት እንደ ፈለገ መሸሸግ አልተቻለውም። በዋነኛነት የዘነጋው ጉዳይ አለ፦ ይኸውም እውቀት ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፈው በአንድ መንገድ ብቻ ነው ማለቱ ትልቊ ስህተት ነው። ሁለተኛው፣ ኢትዮጵያ የብዙሓን አገር እንደ መሆኗ ከደገኛው ውጭ የተቀረው ብዙሓን ምንም አስተዋጽዖ እንደሌለው አስመስሎታል።
Reply
LEAVE A REPLY
Comment:
Name:*
Email:*
Website:
 Save my name, email, and website in this browser for the next time I comment.
Follow Us
Contact Us
[email protected]
Search in site
Search
© 2021, ↑ Borkena Ethiopian News
Home
Blog
Contact

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Nov, 06:38


በዚህም ህግ ምክንያት ከ60ሺ በላይ ሰዎች ያለ ፈቃዳቸው የዘር ማስተላለፊያ  መስመራቸው ተቆርጧል፤ በኛ ሀገር ቋንቋ ተኮላሽተዋል።  ይሄንን እነ ዶ/ር አብይ በእርግጥ እነ Max Weber በፕሮቴስታንት ኢቲክስ በለጸገ በሚሉት ሀገር ነው።  ዘር እንዳይተካ የማኮላሸት ህግ የነበራቸው የአሜሪካ ግዛቶች እነዚህ ናቸው። Alabama, Arizona, Arkansas, California, Colorado, Connecticut, Delaware, Florida, Georgia, Idaho, Illinois, Indiana. Iowa, Kansas, Kentucky, Louisiana, Maryland, Massachusetts, Michigan, Minnesota, Mississippi, Missouri, Montana, Nebraska, Nevada, New Hampshire, New Jersey,  New Mexico, North Carolina, Ohio, Oklahoma, Oregon ናቸው።  
ይህ እሳቤ ዛሬ እኛ ሀገር ደርሶ የሚሞገሰው ማክስ ዌበር (Max Weber) በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ይሄንን ደካማ ዘረ መል ማጥፋት ትክክል እንደሆ ነው።  “Many modernist protestand minster also publicly advocated these laws, endorsing them as an effective means or eliminating white degeneracy, enhancing God;s kingdom on earth”, Leif C. Tornquist, 
ሂትለር ሳይንቲስቶቹን ወደ ከካሊፎርያ ልኮ ነው ልምድ የቀሰመው። “ዘር ይበክላል” ያለውን 6 ሚሊዮን ይሁዲ፤ ጂፕሲ፤ አይምሮ ህመመተኛ ሲያጠፋው። ጥቁሮችን ደግሞ ልጅ እንዳይወልዱ በግድ ሆስፒታል እየተወሰዱ ያለ ማደንዘዣ እንዲኮላሹ ይደረጉና የተኮላሹበትን ሰርቲፊኬት ተሰጥቶ ይለቀቁ ነበር። በኑረንበርግ ህግ ደግሞ የጥቁርና የጀርመን መጋባትም ግንኙንተ መፈጸም በህግ የታገደ ነበር።    “When the Nazis came to power, one of the first directives was aimed at mixed-race children. Underlining Hitler’s obsession with racial purity, by 1937 every identified mixed-race child in the Rhineland had been forcibly sterilised (ተሎላሸ), in order to prevent further ‘race polluting’, as Hitler termed it. (Holocaust Memorial Day Trust)
አሁን አበሻ ዛሬ ቪዛ አስመትቶ አሜሪካ ልጅ ለመውለድ ይሄዳል። ጀርመን ልጅ ይወልዳለ። ይህ ህግ በሂትለር ጭካኔ ባይተው ኖሮ  የሰባት ቀን ግርዘት ሳይሆን የሰባት ቀን ማኮላሸት ይሆን ነበር።  
እንስዚህ ሁሉ ህጎች ለምን መጡ ላልን? ምክንያቱ የነጩ ዘር ጥቁሮች በዝግመተ ለውጥ ጥሏቸው ስለሄደ ጥቁሩ  ጭንቅላት አላደገም ብለው እራሳቸውን ስላሳመኑ ነው። የጥቁሩ ጭንቅላት ምናባዊ ሀሳብ (abstract knowledge)  መያዝ አይችልም በማለት ነው። እነዚህ ምናባዊ እውቀቶች እንደ ሂሳብ፤ ስነ ጽሁፍ፤ ፍልስፍና፤ ሳይንስ ማለት ነው።  አንድ ፍጡር ምናባዊ ጽንሰ ሀሳብ መያዝ ካልቻለ አራት ሲካፈል በሶስት ብትለው ሊገባው አይችልም። ወይንም የጸጋዬ ገብረ መድህንን  “ጴጥሮስ በዛች ሰዓት” ለአንድ ዝንጀሮ ብታነብለት እንባው ቅርር አይልም። 
መጀመሪያ ዳርዊን እንዴት በሁለት መጽሃፍት ዓለምን ያሳመነባቸውን ዐረፍተ ነገሮች እንጥቀስ። እኔም የማጋንን እንዳይመስላችሁ ድርዊን የጻፈውን ሙሉ የእንግሊዘኛውን እናንብብ። 
1ኛ፡  “How little can the hard-worked wife of a degraded Australian savage, who uses hardly any abstract words and cannot count above fourexert her self-consciousness, or reflect on the nature of her own existence” Charles Darwin, “The Descent of Man” Chapter VII (7), page 62”
ትርጓሜው ”እንዴት ምንም ምናባዊ ቃላት የማታውቅ፤ ከዐራትም በላይ ቁጥር መቁጠር  የማትችል የአንድ የአውስትራልያ አረመኔ ሚስት፡ ስለራሷ ህሊና እና በህይወት ስለመኖሯ ልታስብ ወይንም ልታውቅ ትችላለች?” ነበር ያለው።
2ኛ፡ “The variations, however slight, in the intellectual faculties between a man and the higher animals, especially the apes, are less, than those between one of the lowest savages, such as the Fuegians, or an Australian, and one of the higher races of man, such as the Caucasian.”  Charles Darwin “The Descent of Man, and Selection in Relation to Sex.” Chapter VII (7), page 200
ይህ ማለት “በዝንጀሮዎችና በጥቁሮች መሀከል ያለው የአይምሮ እድገት ልዩነት ትንሽ ሲሆን በነጭና በአረመኔ መሀከል ያለው ልዩነት በጣም የሰፋ ነው። በትክክል የተረጎምኩት አይመስለኝም። እናትተው ተርጉማችሁ ተረዱት     
3ኛ “At some future period, not very distant as measured by centuries, the civilised races of man will almost certainly exterminate, and replace the savage races throughout the world”. Charles Darwin, “The Descent of Man” 1871, ገጽ 71
በቅርብ ግዜ ብዙ ምዕተ ዓመት ሳይወስድ የሰለጠነው ዘር በእርግጠኝነት ይሄንን አረመኔ (ጥቁሩን) ዘር ያጠፋዋል።
4ኛ “The Western nations of Europe, who now so immeasurably surpass their former savage progenitors, stand at the summit of civilization.” 
 በምዕራብ አውሮፓ የሚኖረው ነጭ በትልቅ ልዮነት ይሄንን አረመኔ (ጥቁር) ጥሎት ሄዶ ከጋራው ጫፍ ላይ ይገኛል።                                                                                                             
5ኛ. “I do not pretend that the remark in my text is more than a statement in certain tribes of mankind, the weak and sickly are left to perish, and that the stronger alone survive.” 
እኔ በጽሁፌ ላይ መዋሸት ወይንም መሸፋፈን አልፈልግም። በእርግጠኝነት የምነግራችሁ እነዚህ ደካማ ብሄር ብሄረሰቦች መጥፋታቸው አይቀሬ ሲሆን ጠንካራው ደግሞ ይበራከታል።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Nov, 06:38


    
መነሻ ገጽ
አበይት ዜና
ነፃ አስተያየት
መጣጥፍ
ስፓርት
ከሶሻል ሜዲያ
ቪዲዮ
ዜና
English
የንግድ ድርጂት ማውጫ
መሰላል


Homeነፃ አስተያየትበህግ አምላክ ክፍል 2፤  ኦርቶዶክስና እስልምና ምን አደረጉልን?
ነፃ አስተያየት
November 18, 2024
 
Updated: November 18, 2024
በህግ አምላክ ክፍል 2፤  ኦርቶዶክስና እስልምና ምን አደረጉልን?

ByAdmin
Facebook
Twitter
- Advertisement -
- Advertisement -


ያሬድ ኃይለመስቀል
ባለፈው ስለ ኢትዮጵያ ቤተ እምነቶች ለነጻነታችን ምን ያህል አስተዋጻኦ እንደነበራቸው። የግዕዝ ፊደልና በቤተ እምነት ዙሪያ የተፈጠሩት ትምህርት ቤቶች ምን ያህል ለሀገራችን ህዝብ አብርሆት እና ለዓለማቀፍ እውቀት ቋት እንዳበረከቱ ተገልጻል። በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ የሚያውቁ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርሥቲያን ጳጳሳት ሊቃውንት እና የእስልምና ምሁራን አሉ።  ይሁንና ፈርተውም ይሁን ወይም የጥቅም ግጭት ተፈጥሮባቸው “ለመሆኑ ለ2ሺ ዘመን ምን አስተዋጽኦ አደርጋችሁ?” ተብለው ሲዘለፉ ብዕራቸውን ያነሱ እስካሁን አልታዩም።  እነሱ ንቀቱ ባይሰማቸውም እኛ ደቂቶቹ መዕመናኖቹ የአቅማችንን እንሞክር። 
እኔ የምጽፈው፡ 
1ኛ፡ እራሴ አንድ ነከር ሲኮረኩረኝ መረጃ እንድፈልግ እንዳነብና ለመረዳት ስለሚያግዘኝ ነው።  2ኛ፡ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር “ምሁራኑ” የተሳሳተውን ትርክት ለማረም ባለመሞከራቸው ውሸቱ እውነት አየሆነ ትውልድ እየጠፋ ነው። ያሁኑ የራስ ጥላቻ ትርክት 50 ዓመታት ፈጅቶ ነው እዚህ የደረሰው፣ ይሄንን ለመቀልበስ ደግሞ ሌላ 20 ዓመታት ይፍጅ ይሆናል። ስለዚህ ዛሬ ሁሉም መረባረብ አለበት። የራስ ጥላቻ ትርክት አጥፍተን በኢትዮጵያዊነቱ፤ በጥቁርነቱ፤ በአፍሪካዊነቱ እንዲኮራ አድርጎ ማስተማር የቤተሰብ ግዴታ ነው። ቤተሰብ ደግሞ መረጃ ይፈልጋል። ለኔ ስነልቦና አያቶቼ እና ቤተሰቦቼ እንጂ የደርግ ግዜ ትምህርት ቤት አይደለም የቀረጸኝ።  ስለዚህ የምናውቀውን ማጋራት፤ ለልጆቻችን ማስተማር እንደአሁኖቹ ፓለቲኪኞች አዲስ እራሱን የማይጠላ እና የማይንቅ ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል። ጽሁፏን ከወደዳችሁት ለወጣቶች አጋሯት።
ዘለፋውና ማና’ናቁ
“እብድና ዘመናይ የልቡን ይናገራል” ይባላል። እብድ ማመዛዘን ስለማይችል ዘበናይ ደግሞ ሁሉንም ስለሚንቅ ለማለት ነው። ሌላው ፕሮፌሰር መስፍን “ፈረንጅ እውቀት ሀይል ነው” (knowledge is power) የሚለው አባባል እኛ ሀገር ሲደርስ ተገልብጦ “ስልጣን እውቀት ሆነ” (Power is Knowledge) ይሉ ነበር። 
ጠመንጃና ጉልበት ያለው ሰው “አዋቂና አስተማሪ” ልሁን ይላል። ሁሉም የፈረንጅ መሪ ብዙ የንግግር ጸሀፊ አለው። ንግግሩ በባለ እውቀቶች ተጽፎ ታርሞ ነው። ለምሳሌ “አክሱም ለወላይታ ምኑ ነው? “ወርቅና ጨርቅ” አቶ መልስ በማለታቸው እስከዛሬ ይተቹበታል? 
ህዝብ ደግሞ የመሪን ስህተት ካላሳየ ሰውዬው ትክክል ነኝ ብሎ ያስባለ። ስልጣን እውቀት መሆን ከጀመረ የዛሬ 50 ዓመት ነው። ሻለቃ መንግስቱ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ናቸው ይባላል ይሁንና እነ ዶ/ር አሻግሬ ይግለጡን፤ እነ ዶ/ር አለሙ አበበን፤ እነ ኮ/ል ጎሹ ወልዴን ቁጭ አድርገው ያስተምሩ ነበር። አሁንም ይህ ባህል ቀጥሎ እነ ዶ/ር ጌዲዮን ቲሞቲዎስን፤ እነ ፕሮፌሰር አለማርያምን፤ እነ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋም በኮለኔል አብይ አህመድ በፕሮጀክተር ትምህርት ከተሰጥቷው ቦሀላ ፈተና ተፈተኑ ሲባል ሰምተናል። ፈተናው ወረቀት ታርሞ ውጤቱ ይገለጣል ብለን ስንጠብቅ ሚስጢር መደረጉ ማናልባት ፈተናውን ወድቀው ይሆናል ብለን እንድናስብ አድርጎናል። 
ይሄንን ባለ ስልጣን የእውቀት ምንጭ ነው የሚለውን ባህል ለማስቆም ያስፈልጋል። ፓርላማ የማስተማሪያ አዳራሽ ሳይሆን የመከራከሪያ ነው። መማር የሚፈልግ ትምህርት ቤት እንጂ ፓርላማ መግባት የለባቸውም። ጳጳሳቱ፥ ዑስታዞቹ፥ የፓርላማ አባላቱ፥ የዩኒቨርሲቲ ምሁራኑ በባለሥልጣን የተነገረ ሁሉ የአግዚአብሔር ቃል ይሆናል ብለው  ሐሰትን ሐሰት፥ እውነትን እውነት ካላሉ እንዴት ትውልድ እውነትና ከውሸት ይለያል?
ወደ ትችቱ ስመለስ ዛሬ የመረጥኩት ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ የሚለውን አባባል ይዤ ነው።
የፈረንጅ አምልኮ “ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” 
በአጭሩ፡ በዳርዊን ሳይንስ የእኛ ምድባቸን ከዝንጀሮ እንጂ ከሰው አልነበረም።  እኛንም  መላውን የአፍሪካ ህዝብ ከዝንጀሮነት ወደ ሰውነት ምደባ እንድንሸጋገር ያደረገችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለሺ አመታት ያከማቸችው የሀሳብ ክምችት ነው። እንዴት ማለት ደግ ነው? 
“ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” ማለት ሌሎች ስለ እኛ የሚሰጡትን  አስተያየት ብንሰማ ኖሮ እናፍር ነበር ለማለት ነው። የኛም ፓለቲከኞች ስለነሱ ፈረንጆቹ የተጻፉትን ቢያነቡ ኖሮ በፈረንጅ አምልኮ ባልተለከፉ ነበር።
ፈረንጆቹ የጻፉት ጥቁሩ ህዝብ በዝግመተ ለውጥ ከዝንጀሮ ትንሽ ሻል ያለ ፍጥረት እንጂ ሰው አይደለም ብለው በርካታ የኢሮፕ ሳይንቲስቶች፤ አንትሮፓሎጂስቶች ወፋፍራም መጽሀፍ ጽፈው ዓለምን ሁሉ አሳምነው ነበር። በትንሹ ለመጥቀስ ቻርልስ ዳርዊን (Charles Darwin, “The Descent of Man” (1871)); ሀርበርት ስፔንሰር (Herbert Spencer “Survival of the Fittest” in Principles of Biology); ኤድዋርድ ቴይለር (Sir Edward Tylor,  “Primitive Culture” (1871), the theory of cultural evolution), ማለትም በ(Civilized Nations) የሰለጠነ ብሄር፥  Barbarians  (ብሄረሰቦች)፥ Savage (ህዝቦች) ተብሎ የተቀዳውና ስድብ እኛ በህገመንግስታቸን የተካተተው ነው።
አቶ መለስ ዜናዊ ይህንን ስድብ ምንጩ ምን እንደሆነ ሳያጣሩ ቀድተው አሁን በባህል ዝግመተ ለውጥ ደቡብ ህዝብ ከዐምሓራና ከኦሮሞና ትግሬ ላይ ያልደረሰ አረመኔ በሚለው ተመድቧል። ከአረመኔነት ወደ ብሄርነት በዝግመተ ለውጥ የሚሸጋገር እንደሆነ  ካድሬው እንዲለማመደው አደረጉ። አሁንም በ ዶ/ር አብይ አህመድም ይሄንኑ አስቀጥለዋል።  የተሰደቡት እነ አቶ ሬዲዋንም ሳይቀር ይህንን ህገመንግስት የነካ ባይኔ መጣ እያሉ ነው።   
ፍራንሲስ ጋልተን ደግሞ ( Francis Galton (1822-1911) ስለ “Eugenics”  1883) አስፈላጊነት ጽፏል።  ይህ ቃል በአማርኛ አላውቀውም። ይህ ማለት በዝግመተ ለውጥ ወደፊት የሄደው የነጩ ዘር በዝግመተ ለውጥ ወደ ኋላ ከቀረው ጋር ማለትም ከዝንጀሮ ጋር እንዳይዳቀልና ወደሃላ እንዳይመልስ የሚያስፈልገው ይሂንን የዝንጀሮ ዘረ መል ማጥፋት ነው ያሳመነ ሳይንቲስት ነው። 
ይህ ሳይንስ በአሜሪካ በ32 ግዛቶች ተቀባይነት አግኝቶ ህግ ሆኖ ነበር ( Eugenics laws, particularly those related to forced sterilization, were enacted in 32 U.S. states during the early to mid-20th century. These laws aimed to prevent certain individuals, deemed “unfit,” from reproducing. The targets of these laws included people with disabilities, mental illnesses, and those from marginalized communities)።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Nov, 06:38


ለዚህ ዋነኛ አመክዮ ሆኖ የቀረበው ነየረበው ሀርበርት ስፔንሰር “ጠንካራው ይራባል ደካማው ይጠፋል” (Herbert Spencer “survival of the fittest”)። ይህ ማለት በአእምሮ ጠንካራ የሆነው የነጩ ዘር ከዝንጀሮ ትንሽ ሻል ያለውን ጥቁሩን ማጥፋቱና ምድርን መውረሱ አይቀሬ ነው።  ለዚህ ነው 125 ሚሊዮን በላይ ቀይ ህንዶች የተገደሉት፤ የአውስትራልያ፥ የሰሜን አሜሪካ አበርጂኒሶች  ሊጠፉ የደረሱት፤ ከ85 ሚሊዮን አፍሪካዊ መሀከል 12 ሚሊዮኑ ታድኖ በባርነት ተጭኖ ወደ ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ ሸንኮራ እንዲቆርጥ፤ ጥጥ እንዲለቅም የተወሰደው። ከሁለት ሚሊዮን በላይ አፍሪካዊ በመርከብ ሲጓጓዙ ሞተው ወደ ባህር የተጣሉት።
አንድ ነገር ልጨምርና ወደ ነገሬ ዋናው ነገር ልግባ።  ፈረንጆቹ የነ ዳርዊን እሳቤ ግራ እንዳያጋባው  የጀርመኑ ሄክል Heackle (1868) የሰውንና የዝንጀሮ ዘራሮችን ዘርዝሮ በስዕል አሳትሟል። 
እኔ; እናንተን እና የኛ ጠቅላይ ሚኒስቴራችም; ብልጽናዎችም፤ እነ ዶ/ር ብርሀኑም ምድባችን በቁጥር 6 ነው፤ ቁጥር 7 አያታችን ዝንጀሮ ፎቶግራፍ ነው፦) 
ታድያ ይህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት እና ከጠ/ሚ አብይ ንቀት ጋር ምን አገናኘው ትሉ ይሆናል።  ትንሽ ታገሱ። በዚህ እሳቤ ላይ እንዴት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የእውቀት ክምችት ተጠቅሶ ከዝንጀሮነት ወደ ሰውነት እንደተሸጋፈርን ልጥቀስ። 
በቻርልስ ዳርዊን ጥቁሮች ምናባዊ እውቀት መያዝ የሚያስችል ጭንቅላት ገና አላገኙም ብሎ ዓለምን ስላሳመነ ነው።  የዚህ ዕሳቤ ሰለባ የሆኑ እኛም ሀገር አሉ። ለምሳሌ አቶ መለስ ዜናዊም ከዝግመተ ለውጥ የተቀዳውን ብሄር ባርባርያን እና ሳቬጅ በህገመንግስት አስገቡተው ዛሬም ትግራይ፥ አማራ እና ኦሮሞ የሰለጠነ ብሄር ሲባሉ  ደቡብን ምሉዕ ሰው አረመኔ ብለው መድበው ሕገ መንግሥት አጸደቁ። ይሁንና ዶሮን ሲያታልሏት በመጨኛ ጣሏት እንዲሉ  በዓመት የብሔር፥ ብሔረ ሰቦችና ሕዝቦች የእኩልነት መገለጫ በዓል ተብሎ መስቀል አደባባይ ሲያስጨፍራቸው ይውሉ ነበር።  በህገመንግስቱ እንግዲስህ  ሲዳማ፤ ስልጤ፤ ወራቤ ወዘተ ገና ዝግመተ ለውጡን ያልጨረሰ ወደፊት ወደ ብሄርነት እንደ አማራ፤ ኦሮሞና ትግሬ የሚሆኑ ናቸው። የሚያስቀው ደግሞ ምንም ያላነበቡ እንደ አቶ ሬዲዋን ሁሴን ያሉ ይሄንን ህገመንግስት ደምስራቸው እስኪገተር ሲከላከሉ ይችላሉ።  በምን መመዘና ነው እኛ ብሄር አይደላችሁም የተባልነው ብለው አልጠየቁም።  ጊዜ ያለው የ Sir Edward Taylor መጽሀፍ Primitive Culture ያንብብ። 
ዳርዊንና የኢዮጵያ ኦርቶዶክስ 
ችግሩ ቻርልስ ዳርዊን ኢትዮጵያ አልመጣም ወይንም ስለ ኢትዮጵያ አላነበበም ለማለት ይከብዳል። ይመስለኛል የሱን ሀተታ የሚያፈርስበት ስለመሰልው መጥቀስ አልፈለገም።  ለምን ካላችሁ የሳሙኤል ጆንሰን Samuel Johnson “Rasselas, Prince of Abyssinia” 1759 አሳትሞ  በስፋት በእንግሊዝ ተነቧል። ይህ መጽሀፍ እስከ መንኮራኩር ብስክሌት ለመስራት እየሞከረ የነበረ የልኡል ራሴ ላስ ኢትዮጵያዊ አናጺ ታሪክ አለበት። ሁለተኛ በዳርዊን የመጀመሪያ (1857) እና ሁለተኛ መጽሀፍ (1871) ህትመት መሀከል ነው የጀነራል ናፒር ጦር አጼ ቴዎድሮስን ሊወጋ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው (1867/8)።  አንድ የጥቁር ንጉስ መድፍ መስራት ፈልጎ እንግሊዞቹን እንዳሰረ አምባሳደሮቹም ፓርላማውም ሲወያይበት ጋዜጦችም ሲጽፉበት ነበር።  ከዛ አልፎ የኢትዮጵያውያን መጽሀፍት፤ ዘውድ፤ ስዕሎች፤ አልባሳት፤ የጦር መሳሪያዎች በለንደን ላይ ሲታዮ ነበር። እነዚህ አእምሮው ምናባዊ ሀሳብ መሸከም በማይችል ዝንጀሮ የተጻፉ መጽሀፍት ነው ብሎ ለማመን ይከብደዋል። ስለዚህ አቦርጂኒሶችን ጠቅሶ እንደ ኢትዮጵያ ያለውን  የጥቁር ሀገር መረጃ መጥቀስ ሀተታውን ያፈስበት ስለነበረ ተወው። 
በእርግጥ ምናባዊ እውቀት የሚይዝ ጭንቅላት የለንምን?
መልሱ “አለን” ነው። ባለፈው አባ ተስፋጽዮን በ1530ዎቹ ወደ ሮም ገብተው የአውሮፓውያንን ምሁራን እንዴት እንዳስተማሩ አይተናል። ሁውመኒስት የሚለውን አስተምህሮ በኢሮፕ መሰረት እንድይዝ እንዳደረጉ ተገጻል። ዛሬ ደግሞ ዋነኛው ምናብ ያስፈልገዋል የሚባለውን የፍልስፍና ትምህርት ቀርሞ በኢትዮጵያ እንደተጀመረ እንይ።  በእርግጥ ፍልስፍና የሚይዝ ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን ከአውሮፓ ቀድሞ ምክናያታዊነት (Rationalism) የሚባለውን ሀተታ መጀመሪያ የጻፈው ኢትዮጵያዊው ቄስ ዘርያቆብ ነው። 
የኢትዮጵያ ፍልስፍና መሰረቱ “ሰው በአርአያ ስላሴ አምሳልና ተፈጠረ  ክቡር ፍጡር ነው (ኦሪት ዘፍጥረት 1፥26)።  ሲፈጣሪውም ሁሉን ማሰብ የሚያስችል አይምሮና ህሊና ተሰጥቶት የተፈጠረ እኩል ሰው ነው ከሚል ነው። የዝግመተ ለውጥ ሀተታ ደግሞ ሁሉም ሰው እኩል ተፈጠረ የሚለውን አይቀበለውም። 
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።”)  ከፈጣሪውም ሁሉን ማሰብ የሚያስችል አእምሮና ህሊና ተሰጥቶት የተፈጠረ እኩል ሰው ነው ከሚል ነው።  መግዛትና መንዳት ለሰው በሌሎች ፍጥረት ላይ የተሰጠው አንጂ ሰው በሰው ላይ የተሰጠው አይደለም።  ስለዚህ ዝግመተ ለውጥ አበላላጭ ነው። ከጥቁር ዝንጀሮ እስከ ነጭ ባለ ወርቃማ ቀለም ጸጉርና ሰማያዊ አይን በመደርደር ያበላልጣል።   
ዝግመተ ለውጥ በምን ተረታ?
መረጃው እኛው ሀገር ቢኖርም የኛን የግዕዝ መጽሀፍ አንብበው ተርጉመን የሚነግሩን ፈረንጆቹ ናቸው። ለምሳሌ የዘርዐያዕቆብ የፍልስፍና ትርክት የሚጀምረው በ1852 አንድ የካቶሊክ መኖክሴ ከኢትዮጵያ ጋራዎች ላይ ካሉ ቤተክርስቲያን አገኘሁት ብሎ አስተዋወቀው። ጽሁፏም በዘራያቆብ (1599-1692) በኖረ መኖክሴ የተጻፈ ፍልስፍና ነው። 
In 1852, a remarkable manuscript was discovered by a Capuchin monk in the highlands of Ethiopia. The text told of a man named Zera Yacob (1599-1692),
ይሁንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት በርካታ ምናባዊ ጽሁፎችን ስትጽፍና ስታስተምር እንደኖረች የሚያሳይ ነው። ዳርዊን መጽሀፍ ከመጻፉ 304 ዓመታት በፊት ዘረያቆብ የሚባለው ኢትዮጵያዊው ፈልሳስፋ የራሱ ሀተታ ጽፎ ነበር። ይህንን በግዕዝ የተጻፈ የፍልስፍና መጽሀፍ በፈረንጅ የፍልስፍና ዲግሪ የተመረቁት እነ ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ፤ እነ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ሳያነቡት ነው። ይሄንን አንብቦ ወደ እንግሊዘኛ ተርጉሞ አለም ያስማ አፍሪካውያን ፍልስፍና አባት የተባሉት የከካናዳ ዜጋ የሆኑት ፕሮፌሰር ክላውድ ሱምነር ናቸው (Claude Sumner)።  የዘርያቆብን ሀተታ ተርጉመው አረ ኢትዮጵያውያን የረቀቀ ፍልስችና ነበራቸው ብለው ለአለም መሰከሩ።  ፕሮፌሰር ሰምነር ከነ ሄግል ቀድመው ስለ ምክናታዊነት የጻፈውዘራያቆብ ነው አሉ። 

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Nov, 06:38


ዘሬ ኢትዮጵያውያን ከኢሮፕያውያኑ ቀድመው ስለ ምክናታዊነው (Rationalism: importance of reason and rational inquiry)፤ ስለ እግዚአብሄር መኖር በምክንያት (Existence of God)። እንደውም ብዙውን ፈላስፋ ያስገረመው የሰውን መሻሻል የእግዚአብሄር ፈቃድ ጭምር ነው በማለቱ ነው። ይህም ቃል። “እግዚአብሄር ሰውን ምሉዕ አድርጎ ሊፈጥረው ሲችል በራሱ ጥረት ወደ ምሉዕነት እንዲሄድ ፈቀደ እንጂ” የሚለው ሀተታው የያዘ ነው። “God could have created a perfect being instead he wanted him to progress to perfection through his own effort” (Sumner, Claude (Trans.). (1976). The African Philosophy of Zera Yacob. Addis Ababa: Addis Ababa University Press.), 
ዘረ ያቆብ ስለ ሞራል ፍልስፍና (Moral Philosophy: compassion, justice, and respect) የስነምግባር መሰረት fundamental ethical principles) ናቸው ብሎ መስክሯል።  ስለ እኩልነትና ሰብአዊ መብት (Equality and Human Rights) ስለ ጾታ እኩልነት፤ ስለ ባርነት ተቃውሞ፤ ስለ የሰው ልጆች እኩልነት እና ስለ ሀይማኖት መቻቸውል ቀድሞ የጻፈ ነው( religious tolerance and intellectual pluralism through reason and evidence)። ይህ የቄስ ወይንም መነኩሴ ከእንግሊዙ ኦክስፎርድ ወይንም ከአሜሪካው ፕሪንስተን ዮኒቨርስቲ ፒኤችዲ የተሰጠው አይደለም።  በኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት ውስጥ ያደገ የምናባዊ ሀሳብ ሰው ነው።
እኔ ይህንን የምጽፈው ለጉራ አይደለም እውነታው እድሜ ለጉግል ማንኛውም ስወ በቀላሉ ዘርያ ያቆብ እና ወልደ ህይወት (1667) ሀተታዎች ከሄግል Friedrich Hegel (1807) ከአንድ 140 ዓመት ቀድመው ነው የጻፏት። እኛ በደርግ ግዜ ዮንቨርስቲ የገባነው ሁሉም ተማሪ  በግድ (Dialectical Materialism) የሚባል ኮርስ አንደኛ አመት መውሰድ በግድ ይማር ነበር። በዛ ላይ ማርክስ እንዲህ አለ ሄግል እንዲህ አለ ነበር ትምህርቱ ሁሉ። ይሁንና ቆይ አንድ ግዜ ከሄግል ጋር ተመሳሳይ ሀሳብ ያለው የኢትዮጵያ ዘረ ያቆብ የሚባል ፈላስፋ ነበር ያለን አስተማርዎች አልነበረንም።  የኔ አስተማሪ ሸዋፈራሁ ይባል ነበር። በግዜው ብዙ ተማሪ የሚከታተለው ፔሌ የሚባል የፍልስፍና አስተማሪ ነበር።  ዶ/ር መሳይ ከበደም እዛው ነበር። 
ወደ ዳርዊን ስንመለስ ዳርዊን አያቶቻችሁ ዝንጀሮዎ ነበሩ ብቻ ሳይሆን አሁንም ዝንጀሮዎች ናችሁ ነው ያለው፤ በቅርብም ትጠፋላችሁ ነው ብሎ የጻፈው።  ለዚህም ዋነኛ መከራከሪያው የጥቁር ጭንቅላት ምናባዊ ሀሳብ መያዝ አይችሉም ብሎ ስላሳመነ ነው።  ታድያ እንደ ዘርያቆብ ያሉ ሀተታዎች የጥቁርን ጥልቅ የምናባዊ እሳቤዎች ማሳያ ማረጋገጫ ስለተደረጉ ጥቁሩ ህዝብ ያለ ሞግዚት እራሱን ማስተዳደር ይችላል የተባለው።
በዚህ ላይ ዝርዝር ጽሁፍ የዛሬ ሁለት አመት በተከበረው የአድዋ በአል ላይ አድዋ ሰው አደረገን ብዬ የጻፍኩት ከሪፓርተር ጋዜጣ ላይ አንብቡ። https://www.ethiopianreporter.com/116426/
ዳርዊንን መቼም ሄዶ የሚያነብ ሰው ያለ አይመስለኝም ስለዚህ በዳርዊን ሀተታ ላይ ትችት ያሳተመው የሪቻርድ ዊካርት መጽሀፍን ማንበብ በቂ ነው። መጽሀፏም “From Darwin to Hitler: Evolutionary Ethics, Eugenics and Racism in Germany፣ 2004 R. Weikart
የኦርቶዶክስ አስተዋጻኦ ለፍልስፍና
ከላይ እንዳየነው ዋነኛው የጥቆርን ምሉዕ ሰውነት የሚያጣጥሉ የነበሩት ጥቁሩ አላደገም የሚሉት በስነጽሁፍ የተደገፈ ትርክት መተው አለ መቻሉ ነው።  ይህ በኢትዮጵያ የተከማቸው ከ300 ሺ በላይ የሚሆኑት መጽሀፍት በመኖራቸው ነው።  እነዚህ መጽሀፎች የጽሎት (Theology) መጽሀፍት ብቻ አይደሉም። መጽሀፎቹ የታሪክ (History)፤ ገድል (Biography) ስነ እጽዋት (Botany)፡ ስነ ከዋክብት (Astronomy): ስነ ህክምና (medicine)፡ ስነ ቀመር (Binary mathematics): ፍልስፍና (philosophy)፡ ስዕል (Painting)፤ እደ ጥበብ (Arts and Crafts): ቀለምና ማዘጋጀት (Chemistry): ሙዚቃ (Music)፡ መድሀኒት መቀመም (pharmacology)  ውዝዋዜ (choreography)፡ ስነጽሁድ (Literature): ኮኮብ ቆጠራ (numerology)፡ አርምሞ (meditation);  ቋንቋ (ግዕዝ አረብኛ፤ ግሪክ፤ ላቲን) (Languge)፤ ትርጉም (translation) እና የፍልስፍና (Philosopy) ወዘተ ናቸው።  
ታድያ ይህ የረቀቀ የፍልስፍና መጽሀፍ ከየት መጣ? ለኛ ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ህዝብ ሁሉ ከዝንጀሮነት ወደ ሰውነት መሸጋገር ማመሳከሪያ ሆኖ የሚቀርበው። ሌላው አፍሪካዊ ፊደል መፍጠር ስለተጫለ በርካታ እውቀቱ አልተመዘገበም ይህ ያሳዝናለ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከ300 ሺ በላይ ጽፋለች። አንድ ቀን ሌሎት ፈረንጆች ግዕዙን አንብበው ሌላ የሚያስደምም ፍልስፍና ይነግሩን ነበር።
ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምን አበረከተች ማለት ትልቅ የማንበብ አቅም ማጣት ተብሎ የሚመዘገብ ነው። ለዚህ ነው በህግ አምላክ ያለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፤ ያለ እስልምናና ከሁለቱ ቀድሞ የነበረው የይሁዳ እምነት አስተምህሮና ስነጽሁድ ሁላችንም በመርከብ ተጭነን ብራዚልና በኩባ ሸንኮራ ነበር የምቆርጠው። ስለዚህ ስለ ራሳችን ያለን ንቀትና ጥላቻ እና የፈረንጅ አምልኮ ለሀገር እድገት ምንም አይጠቅምም።
ከጥጥ ለቀማና ከሸንኮራ ቆረጣ ያዳኑንን ቤተ እምነቶች እናክብር። እነዙህ ተቋማት ናቸው የሉአላዊት ሀገር የሰጡን። ያለ ሉአላዊነት ሀገር ደርሞ የጠቅላይ ሚኒስቴር የሚባል ይሰራ መስክ አይኖርም ነበር። ስለዚህ ጳጳሶቹና ሼኮቹ ለዚህ ማበሻቀጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቅርታ ይጠይቁ የሚል መግለጫ እስኪያወጡ  የኢትዮጵያ የክርስትናና የእስልምና መዕመናን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቀርታ እንዲጠይቁ ግፊት ማድረት የታሪኩም የሀይማኖቱም ግዴታቸው ነው።
ለዚህ ነው እንዲህ አይነት ትልቅ ስህተት ሲሰራ በህግ አምላክ ማለት ያለብን? በክፍል ሶስት በሌላ ጽሁፍ እመለሳለሁ።
አመሰግናለሁ።  
ጸሃፊውን በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ ማግኘት ይቻላል :  [email protected]

ክፍል አንድን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
__
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena
የኤዲተሩ ማስታወሻ ፡  በነጻ መድረክ ላይ የሚቀርቡ ጽፉፎች የጸሃፊውን እንጂ የቦርከናን ሃሳብ አያንጸባርቁም!

የንግድ ድርጅትዎን ወይንም አገልግሎትዎን የንግድ ድርጂት ማውጫ ላይ ለማውጣት  
እዚህ ይጫኑ፡፡
የቴክኒክ ድጋፍ ካስፈለገዎ በሚከተለው ኢሜይል ይጠይቁ
[email protected]

Ethiopian News – Borkena English

ኤክስ (የቀድሞው ቲዊተር) ፡ @zborkena

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Nov, 06:37


https://amharic.borkena.com/2024/11/18/%e1%89%a0%e1%88%85%e1%8c%8d-%e1%8a%a0%e1%88%9d%e1%88%8b%e1%8a%ad-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-2%e1%8d%a4-%e1%8a%a6%e1%88%ad%e1%89%b6%e1%8b%b6%e1%8a%ad%e1%88%b5%e1%8a%93-%e1%8a%a5%e1%88%b5/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Nov, 03:16


አሁን ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ፈተና እና ምንጩ እና ጥምረቱ (አገልጋዮቹ የሚገለጡበት ድርጅት ሕወሃት፥ ኦነግ/ኦሮሙማ/ብልጽግና፥ የቤተ ክህነት ምንደኞች፥ ጽንፈኛ የግራኝ አህምድ ናፋቂ ጂሃዲስቶች)
1. የሮማ ካቶሊክ ኑፋቄ (ፋሺዝም) የወለደው የባንዳ ልጆች ድርጅትና አገር ጠሉ የሕወሃት፥ የጣሊያን ባርነት የሚያኮራውና የ3000 ዓመት የነጻነት ታሪኩን በ60 ዓመታት ቅኝ የመገዛት ባርነቱ የሚኮራ የጀበሃ/ሻዕብያ (መለያየትን ከነጻነት የሚቀጥረው የጨለማ ፖለቲካዊ ርእዮት)፥ የግብጽና የአረቦች ፍላጎት አገልጋይ ፖለቲካ
2. የጀርመን ክርስትና (ናዚዝም) ያስፋፋው ከግንቢ ወለጋ ሆስፒታል ተነስቶ ኦነግን የወለደው ዝር አጥፊ ፖለቲካ
3. መሀመዳዊ የአረብ እምነትና (በተለይ አክራሪው)
4. ምዕራባዊ ለቅኝና ለባርያ ፍንገላ መንግድ ሲጠርግ የኖረው፥ አሁን በማደንዘዣነት የሚያገለግለው (ሥኩላር ሊበራል፣ ሴኩላር ኮሚኒስት፣ ፕሮቴስታንቲዝም)
5. በአእምሮ እጥበት ላይ ሁለገብ ጥገኝነት እና ንቀዘት ሲጨመር የአፍሪካ መሪዎች የባዕዳን ማሽን የሆኑ፥ ሰውነት የተለያቸው መሪዎች።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

26 Nov, 02:53


ቱንቢ ሚዲያን (1) ሰብስክራይብ ፥ (2) አባል በመሆን፥ (3) ብዙዎች ጓደኞቻችን እንዲሳተፉና አባል ከመሆን ጀምሮ እንዲራዱ በመጋበዝ (4) በስፋት በማስተዋወቅ — ሚዲያውን እንዳሳድግ https://www.youtube.com/@TunbiMedia_

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

25 Nov, 05:00


https://vm.tiktok.com/ZMhcbwKms/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

25 Nov, 05:00


የዲሞክራሲ ባህል ለማይገባችሁ የአበባን አየሽ ወይ እንባ የሆያሆዬ ዘፋኝ ኋላቀሮች ኢትዮጵያውያን፣
ይህን ከአብይ አህመድ አሊ ምጡቅ አእምሮ ብቻ ሊፈልቅ የሙችል አጭር ትምህርት ተከታተሉት።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

25 Nov, 02:18


በዚህ ሠላሳአምስት ዓመት ውስጥ የሥልሳዎቹ በግፍ መረሸን ተደጋግሞ ስለተነገረ የሁላችንንም ሕሊና ያደማ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ከዚያ የግፍ አገዳደል በብዙ እጥፍ ናዚዎችንና ፋሽስቶችን የሚያስመስግን ሒትለር ቢኖር የሚደነግጥበት ዘግናኝ ግድያ እየተፈጸመ አይደለም ወይ!!!!!!! አልቃይዳና አይኤስን የሚያስንቅ ግድያ በምን ቃላት ይገለጻል። ደርግ ያጠፋውን ጥፋት መዘከሩ ለማስተማሪያነት ጥሩ ነው። ደርግን አረመኔም ፋሽስትም እንበለው። ነገር ግን ወያኔና ኦነግ የፈጁትን አውሬያዊ ፍጅት የዓለም የቋንቋ ጠበብት ቢሞክሩት እንኳ ፍጅቱ በቃላት ከሚገለጸው በላይ ነው። ደርግ ንጹሓንንም ቢገድል እንኳ መርጦ ነበር የሚገድለው። እነ ወያኔና ኦነግ ግን ምንም ጦርነት ሳይኖር ፈረንጆቹ Clearing earth የሚሉት ዓይነት ግድያ ነው ትናንትም ዛሬም የሚፈጽሙት። እነሱ የሚገድሉት ፖለቲካቸውን ያልነካውን ሁሉ በማንነቱ ብቻ ነው የረሸኑት። ያውም ምንም የጦርነት ኮሽታ በሌለበት በቤቱ በተኛበት የዕድሜም የፆታም ልዩነት ሳያደርጉ ነው። ያውም የእናቶችን ሆድ እየቀደዱና ፅንስ እያረዱ!!!!! ያውም ራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን ካህናት አባቶችን በቤተመቅደስ በቅዳሴ ላይ እያሉ። ያውም በሟቾች ላይ (በሕይወት የተረፉት እንደመሰከሩልን)ግብረሰዶም እየፈጸሙ ነው።
ሒትለር የግፍ ግፍ የፈጸመው በወጭ ጠላቶቹ ነው። እነ ወያኔና ኦነግ ትናንትም ዛሬም የግፍ ግፍ የሚፈጽሙት በገዛ ዜጎቻቸው ላይ ነው። ሒትለር የገደለው ታላቋን ጀርመንን ለመገንባት ነው። ሙሶሊኒም የጨፈጨፈው ታላቋን ሮማን ለመመለስ ነው። ይሄ በራሱ ጥፋት ነው። እነ ወያኔና ኦነግ የገደሉት ግን ታላቋን ኢትዮጵያን ለማፈረስ ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ክብርና ነፃነት የሀገራችንንም ሉዓላዊነትና አንድነት ለማጥፋት ነው።
የደርግ መንግሥት አረመኔ ነው። ሥልሳዎቹን የሀገር ባለውለታዎች መግደሉ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ ነው።
እስኪ አንድ ነገር እንመልከት። ደርግ ሥልሳዎቹን የቀኃሥ ባለሥልጣኖች ለምን ረሸነ? ጭፍን ጥላቻ ወይስ ገፊ ምክንያቶች አሉ? መግደለ በምንም ሁኔታ ደርግ ከወንጀለኛነት ሊያድነው የሚችል ሕጋዊ ሚዛን የለም። ደግሜ እላለሁ ለምን ገደለ??????
በበኩሌ ገፊ ምክንያቶች የምላቸውን ልጥቀስ። አንደኛው የባለሥልጣናቱ ደርግን የመደምሰስ ያልተሳካ ሙከራ ነው። ደርግን አራተኛ ክፍለጦር ግቢ ውስጥ በስብሰባ ላይ እንዳለ እንግደል ብለው ንጉሡን ጠይቀዋል። አስርቤት ከገቡ በኋላም በእነ ጣሰው ሞጆም በሌሎችም አማካይነትብዙ ሞክረዋል። ያውም እቅዳቸው ከደርግ አባላት መካከል ቀንደኛ የሚባሉትን መርጠው ሳይሆን በጅምላ መደምሰስ ነበር። እነሱስ ተሳክቶላቸው ቢሆን ኖሮ የሰው ደም አላፈሰሱም ማለት ይቻላልን????? ወይስ የደርግ አባላቱ ደም ውሀ የእነሱ ደም የተለየች ናትን????? ሌላ ገፊ ምክንያት ልጨምር። የደርግ አባላቱ እነ መንግሥቱ ኃይለማርያም ፍሰሐ ደስታ ብርሐኑ ባይህ በመጽሐፍም በቃለመጠይቅም የሕግ ምሁሩ ፕሮፌሰር በረከትና ፕሮፌሰር መስፍን ደርጎች "የባለሥልጣናቱን ጉዳይ እንዴት እናድርግ" ብለው ሲጠይቋቸው "ጠመንጃው በእጃችሁ ነው" የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው በአጽንኦት ገልጸዋል። ይሄ ቃል እነሱን (ደርጎችን) ንጹሕ ያደርጋቸዋል ለማለት አይደለም። ነገር ራሱን የቻለ ገፊ ምክንያት ነው። በእርግጥ ሁለቱ ፕሮፌሰሮች ሲጠየቁ አስተባብለዋል። እውነቱን እግዚአብሔር ይወቅ። ወደፊት የታሪክ ባለሙያዎች መርምረው ይደርሱበታል ሌላም ገፊ አለ።
ሌላው ገፊ ምክንያት የጀኔራል አማን ጦሩ በደርግ ላይ እንዲነሣ መቀስቀሳቸው ገፊ ነው።ከንዑስ ደርጎችም ሆነ ከአንዳንድ የሠራዊቱ አካላት "እነዚህን የሕዝብ ደም መጣጮች አስራችሁ የምትቀልቡት እስከመቼ ነው" የሚለው ግፊት ለዚያ የግፍ አገዳደል ራሱን የቻለ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ከሥልሳዎቹ ቀጥሎ የደርግ የግፍ አገዳደል ሰለባ የሆኑት የኢሕአፓ ወጣቶች ናቸው። የእነሱንም ገዳይነት አብረን እንመስክር። ደርግ ብዙ እናቶችን ልጅ አልባ ብዙ ልጆችን ወላጅ አልባ አድርጓል። ከዚያ በፊት ኢሕአፓ ብዙ እናቶችን ልጅ አልባ ብዙ ሕፃናትን ወላጅ አልባ አድርጓል። ኢሕአፓ የጋየው ራሱ በለኮሰው የግድያ እሳት ነው። በእውነት የኢሕአፓ ነጭሽብር ባይኖር ኖሮ የደርግ ቀይሽብር ይኖር ነበርን!!!!!! ይሄንንም ሐቅ አብረን እንመስክር።
ነገር ግን ከሚረሸኑት የኢሕአፓ ወጣት አባላት መካከል አንዷ ነፍሰጡር ሆነው ተገኙ። በማሕፀን ያለችው ሕፃን ያለጥፋቷ መሞት የለባትም በማለት እንዲተርፉ ተደርጓል። ሴትዮዋ በኋላ ሚኒስትርም አምባሳደርም ለመሆን የበቁና ታሪካዊ ምስክርነት ያለውን መጽሐፍ አበርክተዋል። ልጃቸውም ተምራ በጥሩ ውጤት ተመርቃ ለእናቷ የመጽናኛና የደስታ ምንጭ ሆናለች። ሌሎችም በዚህ መንገድ የተረፉ ብዙዎች ናቸው።
የደርግ መንግሥት ከሥልሳዎቹ ጀምሮ ያን ሁሉ የኢሕአፓ ወጣት መረሸኑ ታሪካዊ ጥፋት ነው። ነገር ግን የዘር ድርጅቶች የሚገድሉት እና ደርግ የሚገድለው የብርሐንና የጨለማን ያህል ይለያያል። ዛሬም የእሱን ጥፋት የሚጮሁት የነሱን ሌብነት ዘረኝነትና የሀገር ክህደት ለመጋረድ ነው። እንጂማ ወያኔና ኦነግ ለቀኃሥ ባለሥልጣኖችም ለኢሕአፓ ወጣቶችም አዝነው አይደለም። ምክንያቱም ሻዕቢያም ወያኔም ኦነግም ራሱ ኢሕአፓም ቀኃሥን ለመዋጋት በቀኃሥ ዘመን ተነሥተዋል። ወያኔ በትግራይ ኦነግ በሲዳሞና በባሌ ኢሕአፓን ወግተው ከየአካባቢው አስወጥተውታል። እንዴት ነው ለቀሐሥም ለኢሕአፓም ለደርግም ተቆርቋሪ የሚሆኑት??? ስለዚህ በቀኃሥ ባለሥልጣኖች መረሸን እነ ወያኔና ኦነግ ደስተኞች እንጂ አዛኞች አይደሉም። ጩኸቱን የፈለጉት የነሱን ባንዳነት ለመሸፈን ነው።
ሌላ ሐቅ እንመልከት። ደርግ ከኢድዩ በቀር አንድም ያፈራው ጠላት የለም። ጀበሐ ሻዕቢያ ኢሕአፓ መኢሶን ኦነግ ወያኔና ሌሎች የዘር ድርጅቶች ሁሉም በቀኃሥ ዘመን የተነሡ የአገር ጠላቶች ነበሩ። ስለዚህ ቀሐስ የወዘፉት እዳ የደርግ ትክሻ ላይ መወደቁንም አበረን እንይ።
ደርግን ከተቃወሙት መካከል ከመኢሶን በስተቀር ሁሉም የሀገር ገንጣይ ድርጅቶች ናቸው። "ደርግ ለእነሱ ሥልጣኑን መልቀቅ ነበረበት" ብሎ የፈረደ ታሪክም የሕይወት ታሪክም የጻፉም በአፍም የፈረዱ ብዙዎች ናቸው። እነዚያ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ቅጥረኛ ባንዳዎች ሀገራችንን ምን እንዲያደርጓት ነበር የተፈለገው!!!!!! የፈራጆችን ማንነት መጠራጠር እንደሰው አስፈላጊ ነው።
ደርግን ለሃያሰባት ዓመት ጭራቅ አድርጎ ሲያብጠለጥሉት የነበሩት እነ ሻዕቢያ ወያኔና ኦነግ ናቸው። እነሱ በእውነት ስለቀኃሥና ባለሥልጣኖቻቸው አዝነው አልነበረም። የደርግን አንዲት ጠንካራ ጎን (ለምሳሌ ከዘረኝነት ከሌብነት ከሀገር ክሕደት ነፃ መሆኑ) ቢመሰክሩ በዚያ ሚዛን ሲመዘኑ ከዜሮ በታች በብዙ የጥፋት ርቀት ስለሚገኙ ነው።
ይሄን ሁሉ ያመጣሁት ደርግ ገደለ ብቻ ሳይሆን ለምን ገደለ ብለን ማየትም አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም ነው። አዎ ደርግ ኢሕአፓንም ሻዕቢያንም ወያኔንም የገደለው አገር ለማዳን ነው። እነሱ ደግሞ የገደሉት አገር ለማጥፋት ነው። አገር ከማዳንና አገር ከማጥፋት የቱ ይሻላል??????
እርግማን ብቻ ሳይሆን እንደዚህ ዓይነት እውነታዎችንም አብረን እንዘክር ብየ ነው። 
ደርግ ሰው መግደሉ ታሪካዊ በደል ነው። ነገር ግን የደርግን መንግሥት በሌብነት በዘረኝነት ማንም አይወቅሰውም። ጠላቶቹም ሁሉ በዚህ አይከሱትም። በሀገር ሉኣላዊነትና በኢትዮጵያ አንድነት ማንም አይወነጅለውም።
የዘመናችንን ገዳዮች በዚህ መስፈርት መዝኑና ፍርድ ስጡ።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

24 Nov, 22:39


Check out this podcast on Ancient Faith Radio! https://ancientfaithministries.page.link/g1PJzGfrFTXEkEU46

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

23 Nov, 16:07


እንወያይ
የጾታ እኩልነት(Gender equality) የሚል ትምህርት ከቤተ ክርስቲያን
አስተምህሮ ጋር ይስማማልን? ሁላችንም አሳብ እንስጥበት።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

23 Nov, 16:07


ሁኩም እልቂትና ከእምነት መፍለሳችንን ሳይሆን ሌላ የምንተፋበትና የምንዘናጋበት አጀንዳ ይጭነናል። የእኛ ተቋማት ልክ እንደ ኢትዮጵያ መንግሥት የእምነቱን ዋና አጀንዳ ወደ ጎን በማድረግ አዳዲስ ውጭ ገብ ከእርዳታና በጀት ጋር የተያያዘ በሽታ ያሰራጫሉ!!! የምትሳተፉ ቆም ብላችሁ አስቡ!!!👇👇👇👇

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

23 Nov, 15:32


ከኦነግ/ብልጽግና ጋር ተብረረው የአዲስ አበባ ኦርቶዶክሳውያንን ሀገር አልባ ያደረጉ ቤተ ክርስቲያኒቱን ባዶ እርቃኗን ያስቀሯት፣ ሀገረ ስብከታቸውን "የሌቦች ኤምፓየር "ያደረጉት ሊቀ ጳጳስ ትውልዱን ለመስለብ አሰፍስፎ የተነሳን ማኅበር ባያበረታቱ ነበር የሚገርመው።ማንም ቢሆን ከቤተ ክርስቲያን አይበልጥም።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

21 Nov, 06:17


https://www.youtube.com/live/glhRIWxKm6U?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

21 Nov, 04:52


ነገረ ባንዳ ን — በቅጡ መረዳት ይቀረናል። ይህን ተምህርት እናስተውል

https://youtu.be/bmVmjaOvz4k?si=2D1VcOrrdRbIeTC2

ክፍል 2 https://www.youtube.com/watch?v=fyxGy0JjnsI

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 16:29


ጳጳስ አምሳለ ክርስቶስ የክርስቶሳውያን እረኛ እንጂ የዘር ፖለቲካ ባሪያ: የድሎትና የምቾት ሎሌ ሆኖ ራሱን ማየት እስኪሳነው ድረስ መታወሩን አስኪረዳ ድረስ ምእመናን ሳያስመስሉ እውነቱን መናገርና በምንም መልኩ ባለመተባበር ሊናገራቸው ይገባል!!!
ወሮበላና አስመሳዩን ሁሉ በጭብጨባ፣ በዝማሬና እልልታ መከተል ማብቃት አለበት።
አባት አብትነቱ የሚታወቀው አምሳለ ክርስቶስ ሆኖ ሲገለጥና ወደ መድኀኒት ክርስቶስ ሲመራ ብቻ ነው። ዘሩንና ሆዱን የማያገለግል አድርባይ ካህን፣ ቆሞስ፣ ጳጳስ ነኝ ቢለን በግብሩ መዝነን ልንቃወመው የእግዚአብሔር ትዕዛዝና ክርስቶሳዊ ማንነታችን ያስገድደናል።

https://youtu.be/IMNon7H4iNA?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 05:15


ለእነዚያ ወዲ ሕወሃትና ኢልመ ኦነግ ይህ ጽሑፍ ማንነታቸውን አጋንንታወዊ መሆኑን መሸሸግ እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 05:15


https://vm.tiktok.com/ZMhW8DKqF/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 01:22


መልካም…

"…እርግጥ ነው ሥራ አጡ የኦሮሞ ወጣት ሥራ ፍጠርልኝ እያለ ሽመልስ አብዲሳን ከሚጨቀጭቀው ሥራ የምታገኘው ዐማራን ወግተህ መሬቱን ስትይ፣ ባሪያ ስታደርገው ነው ብሎ ሰብኮ ሲልከው እውነት መስሎት ወደ ዐማራ ቢመጣ አይፈረድበትም። ምክንያቱም ተሰብኮ፣ በስብከቱ አምኖ፣ አምኖም ተጠምቆ ነው የሚመጣው።

"…ይሄ ሁሉ የምታዩት መኪና በውስጡ 60 ሰው ቢይዝ ነው። ስድሳን ሰው በመኪኖቹ ብዛት ብታባዙት የሚመጣው ሒሳብ በጣም ጥቂት ነው። በታንክ፣ በሮጲላ፣ በድሮን ታግዞ የገባውን የሰለጠነ የብራኑ ጁላን ጦር ሰልቅጦ የዋጠ የዐማራ ግዛት ይሄን ውሪ ጩጬ ሁላ ደቂቃም አይፈጅበት። እናም መኪናው ሲንጋጋ ብዛቱ የምር አይምሰላችሁ።

"…የእናት የአባቱ ጸሎት የረዳው ይማረካል። በዐማራ ጦርነት ማቁሰል ነውር ነው። ሥልጠናው ራሱ አናትህን መበጥረቅ እንጂ እጅና ትከሻ፣ እግር ላይ አነጣጥር የሚል አይደለም። ግምባርህ ላይ በርጨቅ ነው የሚያደርግልህ። እናም በዐማራ መማረክ መታደል ነው። እግዚአብሔር ያልተጣላው ነው የሚማረክ። ዳንኤል ክብረት እንዳለው ግን ይሄ ሁሉ ምስኪን ኦሮሞ በዐማራ ክልል የአፈር ማዳበሪያ እየሆነ ነው። ትግሬ አንድ ሚልዮን፣ ከዐማራና ከትግሬ የሆነ ሚልዮን ጭዳ ያደርግና ዘና ብሎ 10 ሚልዮን ምን አላት ይልልሃል። ጉድ እኮ ነው።
"…ሲመስለኝ ዳንኤል ክብረት ወሎዬ ነው። አቢይ አህመድም እንደዚያው። እኔ ያልገባኝ ነገር በሆነ እኛም ባላወቅነው ሲስተም በዘዴ የኦሮሞን ወጣት ወደ ዐማራ ምድር አስገብተው እያጸዱት ይሆን እንዴ?
"…ያም ሆነ ይህ የዐማራ መልክአ ምድሩ አፍጋኒስታን በለው። ትገባለህ አትወጣም። ለድሮን፣ ለጀትም አይመች። ተወደደም ተጠላም፣ ፈጠነ ዘገየም፣ ዐማራ ያሸንፋል። ያቸንፋልም። ቆይቼ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ።
• የእሳት ራት
Zemedkun page

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 01:22


They have been doing these some four years a go but now armed and became professional and organized killers under the leadership of #AbiyAhmed and his #PP government

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 01:22


https://www.facebook.com/share/p/btmtFHuiQni9qLvc/?mibextid=qi2Omg

ክርስቲያነዊ እረኝነት በተግባር ይገለጥ!!‼️

ዕለት ዕልት በሰይፍ የሚመተሩና በጅምላ የሚቀበሩ፥

በመደበኛ ሠራዊት የሚጨፈጨፉና በቡድን የሚደፈሩ ሴቶች

ክርስቲያን ናቸው። በባርነት ወደ አረብ አጋራት የሚጋዙ ኦርቶዶክሶች
ናቸው፤
በሚሊዮኖች የሚፈናቀሉት ኦርቶዶክሶች ናቸው፤

ቤታቸው የሚፈርስ፥ እርሻቸው የሚነጠቅ፥ ንግዳቸው የሚስተጓጎል፥
ከሥልጣን የሚባረር ኦርቶዶክስ ነው

እና —- የቤተ ክህነቱ እረኛ ምን እያለን ነው?

📛ኦነግ-ኦሮሙማ ባመቻቸው ኦርቶዶክስን የማጥፋት ዘመቻ ውስጥ ኦሮ-ዉሀብያ ማኅተብ ማስበጠስ መርሐ ግብር እንዲህ ካሄዳል። ይህ በምንግሥት መዋቅር ተመቻችቶ የሚመራ ዘመቻ ነው።

ምንደኛና ዘረኛ ጳጳሳት ግን የዚህን ሥርዓት ባለሥልጣናት እግር ይልሳሉ። ካባ ይሸልማሉ።

ሕንጻ ግንባታ አሳብበው ገዳይ አስገዳይ እያመሰገኑ ምእመናንን እያዘናጉ ያስጠፋሉ

ቀኖና ሐዋርያትን ጽፈው በጎሣ መሥፈፈርት ጳጳሳትና ካህናት ይፈለፍላሉ

አቡነ ሉቃስ ገዳዩን ጠቅላይጰሚኒስቴር ለምን ተናገረ ብለው ያላዝናሉ

የጥምቀት ልጆች እልቂት፣ መለያየት፣ ስደት፣ ከእምነት መፍለስ አያስጨንቃቸውም።

ከዘረኛ ፖለቲካ ጋር እየተሻሹ የተደላደለ ሥጋዊ ምቾታቸውምን ለማዝለቅ "በቤተክርስቲያንና በመንግሥት መካከል ያለውን ለእ የተመቸ ግኑኝነት አታሻክሩ እያሉ ያላዝናሉ።

🛑 "ነፍሴን እሰጣለሁ" እያሉ የሚፎክሩ ጳጳሳትና ሰባኪዎች ነፍሳቸውን የሚሰጡት ልጆቻቸውን ላለማስገድል ነው ወይስ ድሎታቸው፥ ሀብትቸውና ሕንጻቸው ሲነካ ነው?

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 01:22


ለእዚህ ሥርዓት 👆👆👆"አትግዙ ማለት እንችላለን፥ ነገር ግን አሁን እዚያ አልደረስንም"። ብፁዕ አቡነ አብረሃእም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ፥ የ—— ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ።

በዚህ አባት ብያኔ መሠረት አልገዛም ያሉና ነፍጥ ያነሱ የአማራ ልጆች፤ ከአገራቸው የተሰደዱ ምሁራንና ጋዜጠኞች ውጉዛን ናቸው። እንደ እርሳቸው አስተምህሮ ሐእመናን ሥርዓቱን ተቀብለው እየሞቱና እየታሠሩ፣ ካህናቶቻቸው እየተገደሉ፣ ገዳማት እየወደሙ ፣ እየተራቡ፣ እየተፈናቀሉ በጸጥታ እየተገዙ የአቡነ አብርሃም የአትገዙ አዋጅ መጠበቅ ነበረባቸው?

አባታችን በዝምታ መገዛቱን እቀጥል አይደል? ከዳንኤል ጋር እየተመካከሩ ይምከሩን።

ከውሳኔዎቻችሁና አነጋገራችሁ ዳንኤል ክብረት በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፈንታ ለሲኖዶሱ ተተኪ መካሪና ወሳኝ እንዳልሆነ በእርግጠኝነት ለማመን ተቸገርን እኮ።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 01:22


- ነ*ጠኛ የፈለገ ቢማር ቢመራመር ዴሞክራሲ የሚባል ነገር አይገባውም።" ጃራ አባገዳ

https://t.me/HawiiEr

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 01:22


ሰራቄ ነፍሳት አቡነ ሕወሃት.mp4

"መፍቀሪተ እግዚአብሔር?"  ወይስ መፍቀሪት ሕወሃት? በዘረኝነት ደዌ የተለከፉ ካህናትና መነኮሳት ላይ የሚታዩ ዋና ዋና ምልክቶች፡- "መፍቀሪተ እግዚአብሔር?" ወይስ መፍቀሪት ሕወሃት? በማንነት የዘር ፖለቲካ የተለከፉ ካህናት፥ መነኮሳትና ጳጳሳት ላይ የሚታዩ ከእግዚአብሔር የመለየታቸው ምልክቶች"-
፩) ሰውን በእግዚአብሔር ፍጡርነት እና በክርስትና የጥምቀት ልጅነታቸው ሳይሆን በፖለቲካ-ሠራሽ ማንነቱ ብቻ ይገልጹታል (ትግራዋይ፥ ኦሮሞ፥ አማራ ወዘተ)፤
(፪) ህሊናቸው ስለሚከዳቸው በሌብነት፥ በማመንዘር፥ በቡድን በመዝረፍና በውሸት ይታወቃሉ፥
(፫) ድሎትና ምቾት በመውደድ ከተህርምት ሕይወት መሸሽ፥ እንደ ሐረር ሰንጋ መደለብ (መብልና መጠጣት ማብዛት)፥ ጾምና ጸሎት መጥላት፥ በከተማ ንብረት ለማፍራት ቤት መሥራት፥
(፬) የሥጋ ዘመድና የቋንቋ ወገን ሰብስቦ ቤተ ክርስቲያን ለሐዋርያ አገልግሎት፥ ለካህናትና መምህራን ወጭ ማድረግ የሚገባትን ሀብት መዘርፍ (፭) የፖለቲካባለሥልጣን፥ ፖሊስ፥ የደኅንነት ሰዎች ወዳጅ በማበጀት ሌብነታቸውን፥ አመንዝራነታቸውም፥ ዘረኝነታቸውን ሊቃወም የሚችል ምእመንና ካህን ማሳደድ። ለዚህ ሕያው ምሳሌዎች የትግራይ ውጉዛን "ጳጳሳት"፥ የወሊሶውን የውንብድና ሲመት የመሩ የሳዊሮስ፥ አዎስጣቲዎስ፥ ዜና ማርቆስና እነርሱን ተከትለው የግሪክ ጨርቅ በመልበስ ራሳቸውን ለማጰጰስ የሞከሩና ፍጹም የሆነ ንስሐ ገብተው የንስሐ ፍሬ እስኪያፈሩ በገዳም ያልተወሰኑ ሁሉ፥ በቋንቋ ችሎታና አገልግሎት ሰበብ ራሳቸውን በጎሣ ያሾሞ በፍቅረ-ሲመት የነደዱ ግብዘዞች።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Nov, 01:22


AQOi67TH2KuQSeeJiPF3AULDWjqW6RlIFt5XrgxZjpiGvEwlpj641jtPmxBzGUhjvoGI7pjEgEm-HJPj6cnI4BVs.mp4

በሕወሃት የ፶ ዓመታት የዘረኝነት ርእዮት (ናዚዝም) ቤመነጨው የሐሰት ትርክት፣ ከፍተኛ የስስትና የዘረፋ ፍተወት በመታወር እውነትን፣ ፍትሕን፣ ሰብአዊነትን፣ አገርና ዜጋዊ ሕበረትን፣ በእግዚአብሔር ማመንና የጥምቀት ልጅነትን ሁሉ እንዲዘነጉ ተደርገው የአገር መከላከያ የጨፈጨፉ፣ የአፋርና የአማራ ጎረቤቶቻቸውን የፈጁ፣ መነኮሳትን የደፈሩ፣ በነውረኛ የሕወሃት ወንጀል ውስጥ መሣሪያ የሆኑ፣ ከኦነግ/ኦሮሙማ አብይ አህመድ ሥልጣን ሽሚያ የተጨፈጨፋትን የትግራይ ወጣቶች "ቅዱሳን ሰማዕታት" ናቸው የሚል መነኩሴ ነኝ ባይ ኢአማኒ የሐሰት አባት መስማት ያሳምማል።

የበለጠ የሚጎዳው አእምሮአቸው ታጥቦ በሥጋ ገድሎ የሞተው ሳይሆን ክህነት ሳይኖረውና ምሥጢራት መፈጸም ሳይችል ሚሊዮኖች የትግራይ ክርስቲያኖችን በማሳሳት ከመንግሥተ እግዚአብሔር ውጭ የሚያደርጉትን ፖለቲካዊ መነኮሳትን መከላከል የተሳነው ሲኖዶስ ነው።

በዚያ ላይ በእረኝነት የተሰየመው ሲኖዶስ አባላቶቹ በዘረኝነትና በድሎት ሎሌነት ይህን የዘር ሲኖዶስ ጥፋት በመቆጣጠር ነፍሳትን ከጥፋት ለመታደግ ፍጹም ዳተኛ መሆኑ፣ ይልቁኑ ስለ ሕንጻ ግንባታና በዓላት ድምቀት እየነዛ ለሕወሃትና ለኦነግ/ብልጽና መንግሥታዊ የክርስትና ማጥፋት ፕሮጄክት ሽፋን ሰጭ መሆናቸው ያስፈራል።

በዚህ አይነት እረኞች ከተኩላ በከፉበት ዘመን፤ "አባት" እየተባሉ በተቃራኒው የቤተክርስቲያን ጠላት ለሆነ መንግሥት የሚያገለግሉ፣ የተጋድሎ በዐት ናፍቋቸው ሳይሆን ድሎትና ምቾት ፈልገው ከተማ የከተሙ የሐሰት መነኮሳት፣ የእንጦንስን አስኬማ በመሸጥና በመግዛት ወደ ጵጵስና የደረሱትን ጎሠኞች መፍትሔ ያመጣሉ ብሎ መጠበቅ ማብቃት አለበት።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

16 Nov, 03:17


ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፴፬
፩ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
፪ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን?
፫ ጮማውን ትበላላችሁ ጠጕሩንም ትለብሳላችሁ፥ የወፈሩትን ታርዳላችሁ፤ በጎቹን ግን አታሰማሩም።
፬ የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው።
፭ እረኛንም በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርም አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ተበተኑም።
፮ በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም።
፯ ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤
፰ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እኔ ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና
፱ ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤
፲ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ በጎቼንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያሰማሩም፤ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።
፲፩ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ እፈልግማለሁ።
፲፪ እረኛ በተበተኑት በጎች መካከል ባለ ጊዜ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

16 Nov, 02:39


https://youtu.be/SRChG5Qs4gM?feature=shared

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

15 Nov, 16:15


https://youtu.be/RmrPNQZGGA8?si=kDzpwdaz5C3zMNBP

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

15 Nov, 16:10


በዚህ አይነት ደንቆሮ ለመመራት መፍቀዳችን የውድቀታችንን ደረጃ ጥልቀትን ያሳያል::

ከሁሉም በላይ ክርስቶስን የዘነጉ ድንዙዛን ጳጳሳት ቤታችንን መሙላታቸውን በደማቁ ይምሰክራል::

እነ "አንገቴን ሰጣለሁ" እና "ችግር የለም እንጂ አትገዙ ማለት እንችላለን" ባዮቹ አድርባ የሐሰት እረኞች በዚህ ንግግር አለመቆጣታቸው ምን ያህል የሐሰት እረኞች እንደሆኑ ያሳያል።

"አጨብጭቡ፣ እልል በሉ፣ ጣል ጣል አድርጉ፣ የድንጋይ ሕንጻ ገንቁ፣ የአእላፍ ዝማሬ አቅርቡ፣ ወዘቸ" እያሉ እልቂቱን ለማስቀረት ሳይሆን አዘናግተው ለማስቀጠል በቅጠረኝነት የሚያገለግሉትን እግዚአብሔር ይበቀላቸዋል።

እንኳን አባት: መምህር፣ እረኛ ተብለው ተሰይመው የሕዝብን እልቂት እያዩ ዝም ማለት፤ በዚያም ላይ በማዘናጋት ቀርቶ የግለሰብን መጥፋት እየተመለከተ በዝምታ የሚያልፈው ምእመን እግዚአብሔር ይቀጣዋል።

እግዚአብሔ በራሱ በሕቅኤል አንደበት እንዲ ብሏል፦
"3:18  እኔ ኃጢአተኛውን፦ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ አንተም ባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው፥ ያ ኃጢአተኛ በኃጢአት ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
3:20  ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱም ዕንቅፋትን ሳደርግ፥ እርሱ ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል ያደረጋትም ጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግን ከእጅህእፈልጋለሁ።
33:8  ኃጢአተኛውን፦ ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህእፈልጋለሁ።"

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

14 Nov, 19:26


በዚህ አይነት ደንቆሮ ለመመራት መፍቅድልችን የውድቀታችንን ደረጃ ጥልቀት ያሳያል:: ከሁሉም በላይ ክርስቶስን የዘነጉ ድንዙዛን ጳጳሳት ቤታችንን መሙላታቸውን በደማቁ ይምሰክራል:: እነ "አንገቴን ሰጣለሁ" እና "ችግር የለም እንጂ አትገዙ ማለት እንችላለን" በዚህ ንግግር አለመቆጣታቸው ምን ያህል የሐሰት እረኞች እንደሆኑ ያሳያል

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

14 Nov, 19:23


በዚህ አይነት ደንቆሮ ለመመራት መፍቀዳችን የውድቀታችንን ደረጃ ጥልቀትን ያሳያል::

ከሁሉም በላይ ክርስቶስን የዘነጉ ድንዙዛን ጳጳሳት ቤታችንን መሙላታቸውን በደማቁ ይምሰክራል::

እነ "አንገቴን ሰጣለሁ" እና "ችግር የለም እንጂ አትገዙ ማለት እንችላለን" ባዮቹ አድርባ የሐሰት እረኞች በዚህ ንግግር አለመቆጣታቸው ምን ያህል የሐሰት እረኞች እንደሆኑ ያሳያል።

"አጨብጭቡ፣ እልል በሉ፣ ጣል ጣል አድርጉ፣ የድንጋይ ሕንጻ ገንቁ፣ የአእላፍ ዝማሬ አቅርቡ፣ ወዘቸ" እያሉ እልቂቱን ለማስቀረት ሳይሆን አዘናግተው ለማስቀጠል በቅጠረኝነት የሚያገለግሉትን እግዚአብሔር ይበቀላቸዋል።

እንኳን አባት: መምህር፣ እረኛ ተብለው ተሰይመው የሕዝብን እልቂት እያዩ ዝም ማለት፤ በዚያም ላይ በማዘናጋት ቀርቶ የግለሰብን መጥፋት እየተመለከተ በዝምታ የሚያልፈው ምእመን እግዚአብሔር ይቀጣዋል።

እግዚአብሔ በራሱ በሕቅኤል አንደበት እንዲ ብሏል፦
"3:18  እኔ ኃጢአተኛውን፦ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ አንተም ባታስጠነቅቀው ነፍሱም እንድትድን ከክፉ መንገዱ ይመለስ ዘንድ ለኃጢአተኛው አስጠንቅቀህ ባትነግረው፥ ያ ኃጢአተኛ በኃጢአት ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
3:20  ደግሞ ጻድቁ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት በሠራ ጊዜ እኔ በፊቱም ዕንቅፋትን ሳደርግ፥ እርሱ ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል ያደረጋትም ጽድቅ ነገር አትታሰብለትም፤ ደሙን ግን ከእጅህእፈልጋለሁ።
33:8  ኃጢአተኛውን፦ ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህእፈልጋለሁ።"

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

14 Nov, 08:23


ልብ ያለው ልብ ይበል

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

14 Nov, 01:34


ተበታትኖ ማልቀስ፥ በተቃራኒው ሚሊዮኖች ነን ብሎ መፎክር ጥቅም የለዉም። ጥቂት የተደራጁ የአገርና የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ለ50 ዓመታት አስለቀሱን፥ አጠፉን፥ አዋረዱን፥ አገር አልባ አደረጉን፥ በጅምላ እየፈጁ ቀበሩን፥ አፈናቀሉን፥ ቤተ ክርስቲያናች በዘር መነኮሳት አድመኞችና ቀበኞች እንድተመራ አደረጉ። ብዙኃኑ ባለመደማመጡና የበኩሉን መልካም ባለማድረጉ ምክንያት ብዙኃን ሳለን እንደ አናሳ ማልቀሱን ቀጥለናል።

በቤተ ክርስቲያን፥ በቤተ መንግሥት፥ በዲፕሎማሲ፥ በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ስለማንደማመጥና ስለማንተባበር በጠላቶቻችን ተወክለን እየተመራን እንገኛለን። ለዚህ ጠንካራ ምስክሬ በዚህ ፎርም መሠረት በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እየመዘገብን እንድንልክ ጥሪ አድርገን በሚገርም ሁኔታ አንድም ሰው ምላሽ አልሰጠም።

በየ ቲክ ቶኩና ዩ ቲዩብ ላይ የወገደኑን እልቂት እያየ የሻማ ምስል የሚለጥፍ ግን በሺዎች ይቆጠራል። ዋጋ ቢሰ ጥረት ነው።
መፍትሔ በሚሆን ጥረት ላይ እንተባበር!!!

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

14 Nov, 01:34


እያንዳንዱ ክርስቲያን (መጻፍ የማይችል አፅፎ) በዙሪያ የሚደረገውን ማንኛውንም መዋቅራዊና ሥርዓታዊ መዋቅር በተመለከተው ቅፅ መሠረት እየሞላ በአቅራቢያው ወደሚገኝ የሞዐ ግብረ ኃይል አባል ወይንም በኢንተርኔት ማስፈንጠሪያው ላይ በማስቀመጥ ግዴታውን ይወጣ። https://moaorthodox.com/home/report
እስከአሁን መረጃውን በጥራት ሰብስባችሁ ለምትልኩ ሁሉ የግፉአን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ዋጋችሁን ይክፈላችሁ።
ይህንን የመረጃ መላኪያ መንገድ ለክርስቲያኖች ሁሉ በማጋራት ይተባበሩ።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

13 Nov, 23:08


Enat Party condemns massacre in East Shoa : 38 burned to death locked in their house. Read more
https://borkena.com/2024/11/02/enat-party-condemns-massacre-in-east-shoa-38-burned-to-death-locked-in-their-house/ @zborkena #Ethiopia #News #humanrights 

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

09 Nov, 02:05


አማራን የማምከን ሤራ https://youtu.be/-TJKyNVAAqw?si=c5r9HE-isfPdb9i-

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

09 Nov, 01:16


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት በካቶሊክ እምነት ላይ ያሳረፈችውን ተጸኖና እንዲሁም በማርቲን ሉተር ተሀድሶ ንቅናቄ ላይ ተጸኖ እንደነበራት Ian Campbell, Holy War: The Untold Story of Catholic Italy’s Crusade Against the Ethiopian OrthoDdox Church ብሎ ባሳተመው መጽሀፍ ውስጥ አባ ተስፋጽዮን በካቶሊክ እምነት ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንዳሳደሩና የካቶሊክም እምነት ከኢትዮጵያ 81 መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 73ቱን እንዲቀበል እንደረጉ ያመላክታል። ይህም በThe Council of Trent in 1546 በሚባለው ላይ 73 መጽሐፍት ተቀባይነት እንዳገኝ ተገልጻል።
የማርቲል ሉተርን 1517 ተቃውሞ ተከትሎ አባ ተስፋጽዮን ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዋነኛ መከላከያ መሳርያ ሆነው ነበር ብሎ ኢአን ካምፔል ጽፏል (“he saw Ethiopianist scholarship as a useful intellectual weapon in the unfolding politico-relgious showdown with the Protestants) ። ይህ የካቶሊክና የኦርቶዶክስ መቀራረብ ወዲያው ፓርቹጋሎቹ መጥተው ንጉሱን ወደ ካቶሊክ ስለቀየሩት ልዮነቱ በጦርነት ሻከረ እንጂ በዛው ቢቀጥል ኖሮ ምናልባትም ካቶሊክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ ከሚኖረው ተጽዕኖ በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት በካቶሊክ እምነት ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችል ነበር። (ይህ Ian Campbell መጽሀፍ Hilton Hotel አለ ገዝታችሁ አንብቡት በጣም የማናውቃቸው ታሪኮች አሉት)።
በሌላ በኩል ደግሞ ማርቲል ሉተት ኢትዮጵያዊውን ዲያቆን ሚካኤል የሚባልን በ1534 በዊተንበርግ ጀርመን ተነጋግረው ማርቲን ሉተር የሱ ተቃውሞ በመጀመሪያይቱ የክርስቲያን ቤተ እምነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ አስተምህሮ የታገዘና ያደረገውም ትክክል እንደሆነ ጽፏል።
Martin Luther’s Fascination with Ethiopian Christianity፡ https://www.christiancentury.org/blog-post/guest-post/martin-luthers-fascination-ethiopian-christianity

ከዲያቆን ሚካኤል ጋር ከተገናኘ ቦሀላ ማርቲን ሉተር ይሄንን ጽፋል “Ethiopian Christians practiced elements of the faith absent in Roman Catholicism, elements Protestants would later adopt: both bread and wine at Communion, vernacular Scriptures and married clergy. Absent from Ethiopian Christianity were practices Protestants would dismiss: the primacy of the Roman pope, indulgences, purgatory, and marriage as a sacrament. Luther’s theological fascination with the Ethiopian Church was illuminated in 1534 in his face-to-face dialogue with an Ethiopian cleric, Michael the Deacon, in which Luther tested out his theological portrait of the Ethiopian Church.
Recalling the dialogue with Michael the Deacon, Luther later stated: “We have also learned from him, that the rite which we observe in the use of administration of the Lord’s Supper and the Mass, agrees with the Eastern Church. … For this reason we ask that good people would demonstrate Christian love also to this (Ethiopian) visitor.”
እንግዲህ እነዚህ ሁለት ሰዎች እንደ አጋጣሚ ከሀገራቸው ወጥተው ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ፈረንጆቹ ከአምስት መቶ አመት ቦሀላ እየቆፈሩ እያወጡ እንዴት በኢሮፕ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደሩ መጽሀፍ እየጻፏ ነው። እና ሀገር ደግሞ ክርስትናና እስልምና ምን ጠቀሙን የሚሉ ድፍረቶች ተነስተዋል።
የአፍሪካ ህዝብ በ1800 ዓመተ ምህረት 85 ሚሊዮን ይገመት ነበር። ከዛ ውስጥ 12 ሚሊዮኑ ታፍኖ ተወስዶ በአሜሪካ ባርያ ተደርጓል። እኛ ለምን እንደ ምዕራብ አፍሪካው በቀላሉ አልተጫንም ካልን ተቋማት ነበሩን። አስባስበው የሚያዋጉን። እነሱም ዋነኞቹ ቤተ እምነቶች ነበሩ።
በክፍል ሁለት የኢትዮጵያ እምነቶች እንዴት የፍትህ፤ የጤና፤ የመሀበራዊ ጉዳይ እና የበርካታ ሚኒስቴሮች ተቋማት ሆነው እንደሰሩ ያሳያል።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

09 Nov, 01:16


በህግ አምላክ! ክርስትናና እስልምና ምን ጠቀመን?
ያሬድ ኃይለመስቀል
[email protected]
የኢትዮጵያ ታሪክ ከክርስትና; ከእስልም እና ይሁዳዊነት (Judaism) እምነትቶች ውጪ ማሰብ አይቻልም? ማሰብ ይቻላል የሚል ካለ ቢያስተምሩን በጎ ነው።
የኢትዮጵያ እምነቶች ጥቅማቸው በጣም ብዙ ነው፤ አንድ መጽሀፍም አይበቃውም፤ ለቅምሻ ያህል የኢትዮጵያ እምነቶች ለነጻነት፤ ለፍትህ፤ ለትምህርት፤ ለብልጽግና፤ ለስነ ህንጻ፤ ለህክምና፤ ለሰላም፤ ለታሪክ፤ ለስነ ጥበብ፤ ስነ እጽዋት፤ ስነ ፍጥረት፤ ስነ ከዋክብት፤ ስነ ቀመር፤ ስነ ፍልስፍና፤ ስነ ምግባር ያበረከቱትን በአጭር በአጭር እንይ።
መጽሀፍ ለሚያነብቡ ስዎች መቼም ሀገርን ከተቋም ውጪ ማሰብ እንደ ትልቅ ደፋርነት እንጂ እንደ እውቀት አያዮትም። የኢትዮጵያ እምነቶች ቤተ እምነት ብቻ ሳይሆኑ ተቋማትም ነበሩ።
1. ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለሺ አመታት ብትኖርም እስከ መስከረም 14 1900 ድረስ የመከላከያ ሚኒስቴር አልነበራትም ግን ለሺ አመታት እራሷን ተከላክላ ቆይታለች። ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የመጀመሪያው የጦር ሚኒስቴር ነበሩ።
2. እስከ 1930ዎቹ ድረስ ኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር አልነበራትም ይሁንና ትምህርት ለሺ አመታት ነበራት። ማን አስተማረ?
3. ኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር እስከ 1930ዎቹ አልነበራትም ይሁንና እንደ “የህዳር ወረርሽን” (Spanish flue) ያለውን ተከላክላለች። ማን ተከላከለ?
4. መዘጋጃ ቤት እስከ ቅርብ ግዜ አልነበራትም ይሁንና ሰው ይወለዳል፤ ያድጋል፤ ሰው ሲሞት በስርአት ይቀበራል። ማን ይቀብራል?
5. መአከላዊ ፍርድ ቤት እስከ 1950ዎቹ አልነበራትም ይሁንና ወንጀለኛ የሚተዳደር ሀገር አልነበረችም። ማን ነበር ፍርድ የሚሰጠው?
6. የአራዳ ፓሊስ በአጼ ሚኒሊክ ቢቋቋምም መሀበረሰቡ ለሺ ዘመን “ፍትህና ወንጀል፤ ትክክልና ስህተት፡ መጥፎና ጥሩን” የሚመዝንበትና የሚፈርድበት የሀይማኖት ህግጋት ነበሩት።
7. ኢትዮጵያ ቤተ መዘክር እና መዝገብ ቤት በአጼ ኃይለስላሴ ግዜ ነው ተመሰረተ ይሁንና መዛግብቶች ለሺ አመታት ጠብቀው ያቆዮ ተቋማት ነበሯት። ማን ጠበቀ?
እነዚህ ሁሉ ተግባራትን የሚያከናውኑት ተቋማት እነማን ነበሩ። ቤተ እምነቶች አልነበሩም። በተለይ የኦርቶዶክስ ሁለቱ የተወቀሱት ቤተ ክርስቲያንና የእስልምና እምነቶች አይደሉም ይሄንን ተሸክመው የኖሩት። ወደ ዝርዝሩ እንግባ።
1ኛ ነጻነት

ለምሳሌ Why Nations Fail በሚለው የ Daron Acemoglu and James A. Robinson መጽሀፍ ገለጥ ብናደርግ “ተቋም” ለአንድ ሀገር በነጻነት ለመኖር ብቸኛ መመዘኛ አድርገው ጽፈዋል። ለምሳሌ እነዚህ ጸሀፊዎች ኢትዮጵያንና ሱማልያን ያነጻጽሩና በሱማልያ ውስጥ ተቋማት ተገንብተው ስላልነበረ አስተባብሮ ቅኝ ገዢዎችን መከላከል የሚችል ተቋም አልተፈጠረም ነበር ይላሉ። “The absence of cohesive and inclusive institutions made it easier for these colonial powers to exert their influence and impose their rule”። ይህ እንግዲህ በመላው አፍሪካ ታይቷል። ተቋም ያላቸው እንደ ዙሉ ንጉስ ያሉ ቢያንስ ቢያንስ ተዋግተው ተሸንፈው ነው የተገዙት። ብዙዎቹ ግን ምንም ሀይማኖታዊም ሆነ አለማዊ ተቋማት በግዜው ስላልነበራቸው አስተባብሮ ነጻነታቸውን ማስጠበቅ አልቻሉም።
በኔ እይታ ኢትዮጵያ አምስት ተቋማት ነበሩዋት። አንደኛ ንጉስ፤ ሁለተኛ የክርስትና ቤተእምነት፤ ሶስተኛ የእስልምና ቤተእምነት፤ አራተኛ የይሁዳዊነት ቤተእምነት፤ አምስተኛ ገበያ ናቸው።
እነዚህ አምስት ተቋማት ናቸውን የኢትዮጵያን ነጻነት ያስጠበቁት። እነዚህ ተቋማት ባይኖሩ ህዝቡ ሀገሩ እንደተወረረ እንኳን የሚሰማበት እድል አልነበረውም። መረብ ምላሽ ላይ ጠላት ሲያርፍ ኢሊባቡር ባሌ ኦጋዴን የሚሰማው በቴሌቭዥን ወይንም በቲዊተር አይደለም። ከዋናው ፓትሪያርክ እስከ አጥቢያ ድረስ ሰንሰለት ያለው እዝ ያለው ተቋም ነበር። በእስልምናም ከዋናው ኢማም እስከ አንድ አጥቢያ ትምህርት ቤት ድረስ የተሳሰረ ተቋም ነበር። ንጉሶቹና ተጓዥ ንጉስ ስለነበሩ ቋሚ ቤተመንግስትም፤ ሞባዬል ስልክም የፓስታ ሳጥን ቁጥርም አልነበራቸውም። ንጉስ ኖረም አልኖረም መስጊስና ቤተ ክርስቲያን ሁሉም ቦታ አለ። ለጅ ሲወለድ ክርስቲያኑ ያጠምቃል፤ እስላሙ መርቆ ቆጥሮ ልጁን ይንከባከባል፣ ፊደል ስላለው ያስተምራል፤ ሲሞት ደግሞ ቆጥሮ ለይቶ ይቀብራል እንጂ ለጂብ አይተወውም። ሀገር ሲወረር ጠላት ሲመጣ በቲዊተር ወይንም በቴሌቭዥን አልነበረም መለክት የሚነገረው። ነጋሪት ተጎስሞ ተዘጋጅ ታጠቅ ዝመት የሚባለው በቤተ እምነቶች ከዛም በገበያ ነበር። በነጻነት መኖርን ጥቅሙ ካልገባን በስተቀር ታድያ የኢትዮጵያ ክርስትናና እስልምና ለኢትዮጵያ ምን አበረከቱ ብሎ ማቃለል በዘንድሮ ወጣቶች እባባል “አረ ሼም ነው” ያስብላል። ለሺ አመታት የብልጽና ወይ የኢህአዴግ መዋቅርና ካድሬ ይሆን ተቋም ሆኖ ሀገር ያስጠበቀው?
2ኛ የትምህርት ሚኒስቴር

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

09 Nov, 01:16


ሰው መቼም ጤነኛ አይምሮ ያለው ትምህርት ቤት መሰልጠን አይደለም ብሎ የሚያስብ ያለ አይመስለኝም።
ኢትዮጵያ እስከ 1940ዎቹ ድረስ የትምህርት ሚኒስቴር አልነበራትም ግን ትምህርት ቤቶች ነበሩዋት፣ ብልጽግና ቀረጥ ሰብስቦ ትምህርት ቤት ከፍቶ አይደለም ትምህርት ያስጀመረው።
ኢትዮጵያ እንደውም በአለም ላይ ትልቁ የጽሁፍ ክምችት ያላት ሀገር ናት። በወሎ፤ በጎንደር እና በሀረር ያለውን የእስልምና መጽሐፍት ሳይቆጠሩ በኦርቶዶክስ ቤተ እምነትዎች ውስጥ ብቻ ከ300 ሺ በላይ በብራና የተጻፏ መጽሀፍት አሏት። እኔ አይደለሁም ይሄንን የምለው፤ ጥናት ያሳተሙት ፕሮፌሰት ሪቻርድ ፓንክረስት ናቸው። ሶስት መቶ ሺ ምናላት የሚሉ የብልጽግና ካድሬ ካለ በንጽጽር እንየው። ፕሮፌሰር ሪቻርድ ይህ 300ሺ ከኢሮፕያውያን ጋር ሲወዳደረው ኢሮፓውያን የዚህን 10 በመቶ ማለትም 30ሺ አልጻፏም ይላሉ።
እነዚህ የብራና ጽሁፎች የጽሎት ብቻ አይደሉም። የሀይማኖት (Theology) ፤ የታሪክ (History)፤ ገድል (Biography (እስቲ አስቡት የ12 ደቀ መዝሙሮች ከውልደት እስከ ሞት ተርጉሞ ጠርዞ ያስቀመጠ ሀገር አለ?); ስነ እጽዋት (Botany)፡ ስነ ከዋክብት (Astronomy): ስነ ህክምና (medicine)፡ ስነ ቀመር (Binary mathematics): ፍልስፍና (philosophy)፡ ስዕል (Painting)፤ እደ ጥበብ (Arts and Crafts): ቀለምና ማዘጋጀት (Chemistry): ሙዚቃ (Music)፡ መድሀኒት መቀመም (pharmacology) ውዝዋዜ (choreography)፡ ስነጽሁድ (Literature): ኮኮብ ቆጠራ (numerology)፡ አርምሞ (meditation); ቋንቋ (ግዕዝ አረብኛ፤ ግሪክ፤ ላቲን) (Languge)፤ ትርጉም (transilation) ወዘተ።
እነዚህ እውቀቶች ትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን ልዮ መሰልጠኛዎች ነበሯቸው (Sub specialization)። ዜማ የሚማርና ትርጉም የሚማር በአንድ ትምህርት ቤት አይደለም። በዘመኑ የታወቁ እንደ አሁኑ ፕሮፌሰቶች በአንድ ነገር ላይ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ሰዎች ያሉበት (Specialization) ትምህርት ቤቶች ነበሩ። በዛ ዘመን እንደ አሁኑ በ C ወይንም በ 50% ማለፍ የለም። አንድ ልጅ ሀሁን ሙሉ በሙሉ ሳያውቅ ግማሹን አውቋል ተብሎ አቡጊዳ አይሰጠውም። እንግዲስ እንዲህ ጽድት ያለ የትምህርት ስርአት የነበረው ሀገር በትምህርት ሚኒስቴር ወይስ በነጻ የሚያስተምሩ ቤተ እምነቶች። ይህ እውቀት በነጻ በእስልምና እና በክርስትና ቤተ እምነቶች አይደለም። ታድያ በምን መመዘኛ ነው ይሄንን የዕውቀት ማመንጫ የነበሩ ተቋማት በምን ብቃት ነው ለማቃለል የምንሞክረው። አረ በህግ አምላክ?
እነዚህ የዚህ እውቀት ባለቤቶችስ በአለም ላይ ተፎካካሪ እንደነበሩ እስቲ ሁለት ሰዎችን እንይ። አንደኛው አባ ተስፋጽዮን ይባላሉ። ሁለተኛው ዲያቆን ሚካኤል ይባላል። አባ ተስፋጽዮን ደብረ ሊባኖስ በግራኝ መሀመድ ሲፈርስ ተሰደው ወደ ሮም የሄዱ ምሁር ናቸው። እኛ እምነት ምን ሰራልን ስንል የካንብሪጅ (Cambridge) ዮኒቨርስቲ ደግሞ የኢትዮጵያ መንኩሴና ዲያቆን እንዴት በኢሮፕ እምነት ላይ ተጽዕኖ እንዳሳረፏ መጽሀፍ ጽፈው ኣንድ ወር ቦሀላ ገበያ ላይ ይውላል። የመጽሀፏ አጭር መግለጫ በእንግሊዘኛ እንዲህ ይላል።
This Element examines the life and legacy of the sixteenth century Ethiopian intellectual Täsfa Ṣeyon. It reconstructs his formative years in the the Horn of Africa and his diasporic life in the Holy Land and Italian peninsula, where he emerged as a prominent intermediary figure at Santo Stefano degli Abissini, an Ethiopian monastery within the Vatican. He became a librarian, copyist, teacher, translator, author, and community leader, as well as a prominent advisor to European humanist scholars and Tridentine Church authorities concerned with the emerging field of philologia sacra as it pertained to Ethiopian Orthodox (täwahedo) Christianity. We reconstruct his wide-ranging contacts with the Roman Curia and emerging orientalist academy, and then scrutinize his editio princeps of the Ge'ez Gospels. A final section traces his modern influence, erasure, and rediscovery by later generations of Western orientalists, Ethiopian writers, and Catholic thinkers.
አንድ ከደብረሊባኖስ ወደ እስራኤል ከዛ ወደ ቫቲካን የሄዱት አባ ተስፋጽዮን የፈርንጅ ትምህርት ሳይማሩ የኢሮፕ Humanist Scholar መስራች እንደሆኑና እንዴት ኢሮፕን እንደቀየሩ ይናገራል። መጽሀፏ በDec 12, 2024 ስለሚወጣ ግዙት።
https://www.cambridge.org/core/elements/abs/many-lives-of-tasfa-soeyon/E18E06F8FB5C91EDEF4286FBD448F1D8

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

05 Nov, 11:05


https://www.facebook.com/share/p/kLyhjwm8MW35yNeS/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

05 Nov, 06:57


የ #AbiyAhmed አማራንና ኦርቶዶክስን የማጥፋት ፕሮጀክት ትንሹ ማሳያ👇👇👇

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

03 Nov, 10:37


https://www.youtube.com/live/LXND-yjyqgQ?si=WYDr_5BqR-cXyBha

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

03 Nov, 05:49


ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 9: 39-39 -41 ጌታችን እንዲህ አለ፦

"39 ኢየሱስም፦ የማያዩ እንዲያዩ የሚያዩም እንዲታወሩ እኔ ወደዚህ ዓለም ለፍርድ መጣሁ አለ።

40  ከፈሪሳውያንም ከእርሱ ጋር የነበሩት ይህን ሰምተው፦ እኛ ደግሞ ዕውሮች ነንን? አሉት።
41  ኢየሱስም አላቸው፦ ዕውሮችስ ብትሆኑ ኃጢአት ባልሆነባችሁም ነበር፤ አሁን ግን፦ እናያለን ትላላችሁ፤ ኃጢአታችሁ ይኖራል።"

እንግዲህ ሊቃውንት ነን፣ አባቶች ነን፣ መምህራን ነን፣ የአገር መሪዎች ነን፣ ነጻ አውጭዎች ነን ወዘተ እያሉ ነፍሳትን ወደ ሲዖል፣ ዜጎችን ወደ እልቂት እየመሩ የሚገኙት ዕውራን እናያለን ስለሚሉ ስሕተታቸውን ለማረም፣ ኃጢአተቸውን ለመተው፣ ዕውርነታቸውን ለመታከም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ተገኝተዋል።

ምእመናን ክርስቶሳውያን፣ አእምሮ ሰብእ ያላቸውና ሃይማኖት ባይኖራቸው ስንኳ በሕገ ተፈጥሮ የጸኑ ሰዎች ራሳቸውንና አገራቸውን የማዳን ከፍተኛ ኃላፊነት ወድቆባቸዋል።

ቅዱሳት መጽሐፍትን ማንበብ፣ የቅዱሳንን የቅድስና ሕይወት ማጥናት፣ የተመሰገኑ ነገሥታት አመራርና አስተዳደርን ማጥናት፣ ቅዱስ ትውፊትንና ታሪክን እያጠኑ መመራራት። አባቶችና መሪዎች በተጠሩበት ልክ የተገኙትን ፈልጎ አብሮ መተባበር። መደራጀትና ለሕዝብና አገር ለህልውና መጋደል።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

02 Nov, 14:56


#አብይ አህመድ አገር የማፍረስና ሕዝብ የማጠፋፋት ምሥጢር የማሰብ አቅም ማጣት የሚያስከትለው ራስን የማግዘፍ ቅዠት ውጤት መሆኑ ሳይንሳዊ እውነት ነው።

ችግሩ በሽታውን ሳይረዱ እያጨበጨቡ የሚጠፉና የሚጠፋፉ መንጎች ዛሬም መኖራቸው ነው። ከዘር መንጋነት ነጻ ያልሆነ ሕዝብ ነጻነትን አያውቃትም።

Abiy Ahmed Turning Ethiopia into a Testing Ground(Guinea pigs) for Bill ...
https://youtube.com/watch?v=3KnRJTHWmpw&si=7LxTs7i5CzDzlHyg

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

02 Nov, 10:57


በእንደዚህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ቀመስ የሤረኞች ስልት አትታለሉ!!!‼️

ዜናና መልእክት የዕለቱን እንጂ መንስዔና መፍትሔውን እንዳናስብ ይጋርደናል።

ሕወሃትና ኦኦነግ የወለዱት #አብይ አህመድና እንደ ሮቦት የሚታዘዙት ደም አፍሳሽ ወታደሮቹ፣ ወያኔን እና ኦነግ ብልጽግና ተከትለው የገዛ ጥፋታቸውን ሌላ አካልን ተጠያቂ የሚያደርጉ የዘር መንጋዎች የሚያደርስብንን መከራ ስናወራ የመከራ ምንጮቹን እያረሳሱን በሥልጣን ይቀጥላሉ።

እንዲህ አይነት ዜናዎችን ስሰማ አእምሮዬ በሚከተሉት መንገድ መሥራት ይጀምራል፦

1) የአደጋው ሰለባን ሰው ህመም ሰውነቴ ይጋረዋል። በእርሱና በቤተሰቦቹ ቦታ ሆኜ ስሜቱን እካፈላለሁ። አንዴንዴ በለቅሶ ፈነዳለሁ

2) ይህን ግፍ በቀጥታ የፈጸመ ወታደርን ከንቱነትና ህሊና ባስነት፣ እርሱን ያዘዘ የሀገር መሪን እረግማለሁ፣ ፍትሕ እንድታገኘው ጸልያለሁ

3) የዘር ሥርዓት ዘርግቶ ለዚህ መከራ የዳረገንን ወያኔንና ጭፍን ተከታዮቹን እረግማለሁ። ፍትሕ እንድታገኛቸው ጸልያለሁ

4) የመከራውን መነሻና ዋና መንስዔ ወያኔን ደብቀው አሁን የሚሆነው ብቻ ዜና በማድረግ ከመፍትሔ የሚያርቁንን የፕሮፓጋንዳ ሚዳያዎች ክፋት አስባለሁ። ሕዝቡ የክፋት ምንጩን ከማሰብና መፍትሔ ከመስጠት በውጤቱ ላይ አተኩሮ አዳዲስ ጠላት እየፈጠረ መከራውን እንዳያራዝመው ዓይነ ልቦናው እንዲገለጥ እጸልያለሁ።

በዚህ ዜና ተጠያቂው ትግራይን አገር አደርጋለሁ ብሎ ለሁላችንም መከራ የቀፈቀፈ የአብይ አህመድ ወላጅ አባት ወያኔ እና ኦነግ ላይ ማተኮር የመፍትሔ መንገድ እንደሆነ በቀጥታ እናገራለሁ።

በሤረኛው ወያኔና ኦነግ የተፈጠረውን ሥርዓት፣ አስተሳሰብ፣ ሕገ አራዊት/መንግሥት፣ የዘር ክልል በመደምሰስ ፍትሕ የሚበየንበት፣ ሰው ከዘረኛ ነጻ አውጭ ነን ባይ አራዊቶች የሚገላልበትን ቀን ለማቅረብ መሥራት። ጎኖ ለጎን በሂደቱ የፈረሱ ቤተሰቦች፣ አካላቸው የጎደለ ወገኖችን ከጎሠኝነት ነጻ ሆኖ በመርዳት ሰብአዊነት ምን ማለት እንደሆነ ለእነዚህ የዘር አረመኔዎች ማሳየት።

👇👇👇👇👇
#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
“ከትምህርት ቤት ስመለስ እግሬን በፍንዳታ አጣሁ” የትግራዩ ታዳጊ
በትግራይ ገጠራማ መንደር ነዋሪ የሆነው ብርሃነ ሐይሌ ከትምህርት ቤት ሲመለስ አንዲት ቅጽበት መላ ህይወቱን ላይመለስ ቀየረችው።የ16 ዓመቱ ታዳጊ የተረገጠው መሬት ላይ የተረገጠው መሳሪያ ፈንድቶ ግራ እግሩን መታው።ስጋና አጥንቱ ተለያይቶ በደም አበላ ተጥለቀለቀ። ከፍተኛ ህመም ሰቅዞ ያዘው።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

02 Nov, 09:46


https://vm.tiktok.com/ZMhCqHmyM/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

02 Nov, 09:46


👆👆👆👆
የብልጽግና ፖለቲካና የአብይ አህመድ አስተዳደር ተግባራዊ መገለጫ ይህ ነው።

የሚገርመው ይህ ሥርዓት እንደማውገዝ ትዕዛዝ እየተቀበለና ቀኖና ሐዋርያትን እየቀየረ ዘረኝነትን የሚያጸኑ ተጨማሪ ጳጳሳት የሚያመር ቅዱስ የሚባልና ተቃራኒውን የሚሠራ ሲኖዶስ በቅዶስት ሐዋርያዊትና ኲላዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መፈጠሩ ነው።

ተነስተን ለመፍትሔው እንሥራ!!!

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

02 Nov, 09:16


Anchor News ''የተገደሉት ህጻናትና አዛውንቶች ናቸው'' የጉራጌው ዕልቂት፥ ሰሜን ሸዋ የተፈጸመው ጥቃት፥ የ...
https://youtube.com/watch?v=jeFoaMIzess&si=P4XG7WxM2LIuLvFU

ድንዙዛኑ የቤተክርስቲያን የወርቅ ባሮች የማይናገሩትን እውነት ስሙት።
በወያኔና ኦነግ ስምምነትና ሕግ መሠረት አማራን፣ ኦርቶዶክስ የሆነን ሰው፣ የደቡብ ነፍጠኛ የሚሉትን ጉራጌ፣ ጋሞ፣ ወዘተ መጨፍጨፉን አብይ አህመድ አሊ አስቀጥሏል።

የቤተ ክህነት ሽፋን ሰጭ የድሎትና ምቾት ሎሌ ጳጳሳት በኮሪደር ልማት ጠቃሚነት፣ በአዳነች አቤቤ የመስቀል በዓል አድማቂነት ዜና ምእመኑን አዘናግተው ለጠዳይ ማሰለፉን ቀጥሏል።

የደነዘዘው የሰንበት ተማሪም ምንደኛ አባት ተብዬዎችን ተከትሎ መዝሙር ማድመቁን ቀጥሏል። ንቃ!!

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

01 Nov, 15:19


ውጭ የሚኖሩ ወገኖቻችን መሥራት የሚገባቸው እንዲህ አይነት ወነጀለኞችን የሚያጋልጥና ወዳጅ የሚያሳጣ ሥራ ነው። አርስ በርስ መወቃቀስና ጊዜ ማጥፋት ሳይሆን ተቻችሎ፥ ተደማምጦ፥ ተከባብሮ የህልውና አደጋ የተደቀነበትን ሕዝብና ሃይማኖት ማዳን ቅድሚያ መስጠት በፈጣሪም የተወደደ ነው

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

01 Nov, 12:24


የክርስቲያኖች ውይይት ግቡ በተሰቀለው በጌታችን አካልነት ላይ ብልት ሆኖ ለመዋሐድ ነው! (ፋንታሁን ዋቄ/ Fan...
https://youtube.com/watch?v=57yXb1Z0WGc&si=Q0TSQ2GgholLwzYD

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

31 Oct, 20:16


https://vm.tiktok.com/ZMhQpRTfS

የሕወሐትና የኦነግ የማይረሳ ወንጀል!!! አብይ አህመድ ይህን ነው አሻሽሎ ያስቅጠለው::
የከብቶች ጋጣ የመሰለው ፓርላማ ተብዬ የደናቁርት መዋያ 30 ዓምት ሙሉ ወንጀል እያጸደቀ ሕጋዊ ሽፋን ይስጣል:

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

31 Oct, 20:10


https://vm.tiktok.com/ZMhQgaGW9

አንዳንዴ እውነት ያመልጣቸዋል!!

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

31 Oct, 20:07


https://vm.tiktok.com/ZMhQgBGup

ዘረኞች በሀገራችን የሚፈጽሙትን ጥሩ አድርገው ገለጹት

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

30 Oct, 10:50


MK TV || ወቅታዊ ጉዳዮች || 421 አብያተ ክርስቲያናትን ያወደመው ጦርነት
https://youtube.com/watch?v=drPa6zeYucg&si=Gq2FOqDgskG_xyGJ

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

30 Oct, 07:10


👆👆👆
ሰብስክራይብና ሼር በማድረግ የጀመርነውን ሳምንታዊ ውይይ ወደ ብዙ ሺዎች እናሳድግ።
ለምታደርጉት ሁሉ
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

30 Oct, 07:09


Orthodoxy and Secularism
https://youtube.com/@orthodox_secular_fantahunwakie?si=Fjg2otJN9EbttgCv

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

30 Oct, 07:07


ይህን ቻናል ተቀላቀሉና አብረን ስለ ሀገራችንና ቤተክርስቲያን እንወያይ። መልካም የሚሠሩትን እንደግፍ።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

30 Oct, 07:06


https://www.tiktok.com/@fantahunwk?_t=8qyAfTgRGDu&_r=1

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

30 Oct, 06:26


Can you add your signature? �
chng.it/PXtQ7rkm4R

ፈርሙ፣ አጋሩ!!!
የዘር ማጥፋት መንግሥታዊ  ዘመቻን የማጋለጥ ጥሪን ምላሽ አለመስጠት ከለማድረግ የማንችለው ትንሹ አስተዋጽኦ ነው።

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Oct, 21:18


👆👆👆👆አንድን ቤተ ክርስቲያን እመራለሁ የሚል ሲኖዶስ የልጆቹን በጥይት ማለቅ: በመንግሥታዊ ዘምቻ ከእምነት መፍለስ: ቤተክርስቲያቱን ኦርቶዶክስ ያሰኘውን ቀኖና መደምሰስ አንዳው ካላደረገ ለምን ይሰበስባል?

👉🏾 ለቦታ ምደባ?
👉🏾ለደሞዝ ጭማሪ?
👉🏾 የመንግሥትን ተቀባይነት ልማጠናከር?
👉🏾 ከቤተ ክርስቲይን የተነጠለ የጵፕስናን ክብር ለማስጠበቅ?
👉🏾 ምእመናንን በማደንዘዘና ባዶ የሰላም ተስፋ በመመገብ ጥፋቱን ልማጠናከር?

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Oct, 21:12


የሲኖዶስ ዋና ተግባሩ ምንድንነው?
ልጆቹን እያሳረደ: እይስመረረ: ወንቤዴና ዘረኛውን የጎሣ ፖለቲካ ሹመኛውን ሁሉ ብፁዕ እያስባለ መቀጠል እስከ መቼ?👇👇👇

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Oct, 18:44


👆👆👆እርስ በርሷ የምትከፋፈል መንግሥት አትጸናም እንዲሉ "ፓትሪያርኩ" እየተገደልን ነው ይላሉ። የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪኣጃቸው ደግሞ ገዳዮች አስጋዮቹን "የአቤል መስዋዕት-አከል" አገልግሎት እያገኘን ነው ይላሉ። የኢዲስ አበባ ሐገረ ስብከት፥ የምሥራቅ ሸዋ፥ የወለጋ፥ የጋምቤላ፥ ወዘተ ጳጳሳት አጥፊ የመንግሥት መዋቅርን ካባ ይሸልማሉ፥ አመስግኑልኝ ብለው ቤተ መንግሥት አዳራሽ ውስጥ ያስጨበጭባሉ፥ "ሕንጻ በገንዘብ ወጭ ሊሠራልን ነው" በሚል ፕሮፓጋንዳ ሕንጻ ሥላሴን በማስፈረስ ይተባበራሉ/

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Oct, 18:00


https://youtube.com/playlist?list=PL9bju67hIGKqxvW8DEqDWULoL02PJXEqP&si=1hb53LQUFEGN_M__ አሁንም ይህ ጥያቄ አልተመለሰም?

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

20 Oct, 16:57


https://youtu.be/3KnRJTHWmpw?si=kTns1nKkfd-2Iwxc

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

19 Oct, 15:11


https://youtu.be/t5rRyw8-HqE?si=_FKBTwjV6Y49ht0-

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

19 Oct, 04:35


ይህል ሊንክ ይከተሉ https://youtu.be/oMmAoH-hBN8?si=gLf-krwhPLcGfvTO
ለተፈጠረው የቴክኒክ ስህተት ይቅርታ ጠይቃለሁ

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

19 Oct, 04:33


የእኔን ኢትዮጵያ ለማግኘት እኔ በግሌ የምችለውን አደርጋለሁ። አንተስ? አንቺስ? በጋራስ ምን እናድርግ? ስመው ከሚነክሱ፥ አገር ከሚያፈርሱ፥ ከሚኣናክሱ ቁማርተኞች፥ ሕሊና ቢሶችና የድንቁርና ነገሥታት ነጻ ለመውጣት ምን እያሰብን ይሆን? https://youtu.be/oMmAoH-hBN8?si=gLf-krwhPLcGfvTO ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ክፍል 5 ለ ይቀርባል

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

19 Oct, 03:55


እንድሚታወቀው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መግላጫ በአብዛኛው ወቅቱን ያገናዘበ ቢሆንም

ቅዱስ ሲኖዶስ ዋጋ ሰጥቶ አጀንዳና እቅድ አያደርገውም::

የፖለቲካ ትእዛዛት መቀበል: ጳጳሳትን እንደ ወታደር ከቦታ ቦታ ለጥቅም ማዘዋወር: ከቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት ብሌላቸው ጉዳይ በጀት መደልደል: ዘራኛና ከሀዲ መግሥታት ሽፋን አግኝተው ምእምናንን እንዲያጠፉ በሚያስመስል ደርጃ ስለ ሰላም የይስሙላ ጥሪ በማድረግ ፕሮፓጋንዳ መሥራት: ነው::


ይህ ግምገማ ስህተት ከሆነ በዚህ ሳምንት ሲኖዶሱ የሚያወጣውን አጀንዳ ከዚህ መግለጫ አንጻር በመገምገም እኔ ልቀጣ። አጀንዳው ከተነደፈም የመጨረሻ ቃለጉባኤና መግለጫው ፈጽሞ የመንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤና የምእመናንን ጥያቄ፥ የቀኖና መታስን፥ ወዘተ ወሳን ጉዳይ አያነሳም።

https://www.youtube.com/live/6MjyRfdU1RQ?si=P9hTbue23B79NEoK

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

19 Oct, 03:34


One app for all your Word, Excel, PowerPoint and PDF needs. Get the Microsoft 365 app: https://aka.ms/GetM365

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

19 Oct, 03:00


እየገደሉ "የምሥራች"

የድንቁርናና ሕሊና-ቢነስት ያነገሣቸው የጎሣ ልሂቃን "የምሥራች" ትርጉም ተቀይሯል። ሕዝ ብተንቋል፥ ትውልድ ረክሷል!!

አምባገነን፥ ቁማርተኛና የወሮበሎች መንግሥት የሚመራውን ሕዝብ መከራ "የምሥራች" እያለ ያለማምደዋል። የሕወሃት/ኢሕአዴግና ብልጽግና በዚህ ሞትና መከራን ድልና እድገት አድርገው በማቅረደብ አንድ አይነት ናቸው።

ስዩም መስፍንና አሊ አብዶ የሕወሃትና የሻዕብያ የዘረፋ ሀበት ክፍፍል ግጭት በባድሜ እንደ ምክንያት ትርጉም-የለሽ ከ120 ሺህ ሕዝብ በላይ ወገን አስፈጅተው፥ ይግባኝ በሌለው የአልጀርስ ስምምነት "የምሥራች፥ እንኳን ደስ ያላችሁ" ብለው ሕዝቡን አስጨፍረዉታል።

የፈረደበትን ዐመሓራና ኦርቶዶክስ ክርስትናን በማጠፋት አጀንዳ ላይ ቢስማሙም ነገር ግን በተለመደው የሀብት፥ የብሔር ግዛት በሰስፋት፥ ዲሞግራፊ በመቀየር፥ አሰስ አገር የመፍጠር እና የበላይነት ለማስፈን ባደረጉት ግጭት ሕወሃትና ብልጽግና በየበኩላቸው ወደ ጦርነት የመሩትን ወገን ድል አግኝተናል፥ የባሰ አደጋ እንዳይመጣ አድርገናል ብለው "የምሥራች" ብለዋል።

ብልገግና የአባይ ግድብ ከደ ጋየወረደው የክረምት ጎርፍ ስለ ሞላ የምሥራች በሚ ልሕበቡን በተለይ አሰስ አበባ ውስጥ አስጨፈሩ ፥ ግን የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውለበለቡ ወጣቶችን የኦሮሙማው ፖሊስ ሠራዊት ቀጠቀጠው፤

አብይ አህመድ የአዲስ አበባ፥ የደብረ ዘይት፥ የናዝሬትና ሌሎች ከተሞች ነዋሪችን የሕዝብ አሠፋፈር ለመቀየር ኦርቶዶክስ ክርስቶያቸኖችን፥ ጉራጌዎች፥ ኮንሶዎች፥ ወላይታና ጋሞዎች ወዘተ ዒላማ ያደረገ ማፈናቀል እያካሄደ "ከተሞቻችን እያማሩ ነውና የምሥራች" ብሏል።

የአማራን ሕዝብ በምድርና በረር ኃይል ሕዓናትን፥ ካህናትን፥ ገዳማውያንን፥ ገበሬዎችን በመጨፍጨፍ ላይ የሚገኘው የአብይ አህመድ አስተዳደር "ጽንፈኛው ፋኖ እየተመታ ለስሆነ የምሥራች" የሚሉ በበሉበት የሚጮኹ ሕሊና ቢስ ሰዎችና የጎሣ አደረጃጀቶች እንዲጮኹ ታዘው እያደረጉት ነው።

የአፍሪካ አንድነ ትድርጀት የግዛት አንነድትን የሚመለከት የቻርተሩን አንቀጽ የሚጥስ የእውር ድንብር ውሳኔ በመወሰን ከሶማሌ ላንድ ጋር የቀጠናውን አጠቃላይ ሰላም ያወከ፥ ቱርክ ናግብጽን ወደ ምሥራቅ አፍሪካ በመጎተት ኢትዮጵያን ባመስከበብ አደጋ የደቀነው የአብይን እብደት "የባህር በር አገኘሁላችሁ – የምሥራች" ብሏል።

ሕዝቡ ፈዝዞና ደንዝዞ እየገደለው፥ አገሩን እያፈረሰበት፥ እያፈናቀለውና እያሳደደው "የምሥራች" እያለ ከቀሚልድበት ድንቁርናና ሕሊና-ቢስነት ካነገሣቸው የጎሣ ቁማርተኛ ልሂቃን ራሱን ነጻ ማውጣት ይኖርበታል።

አንድ ሕዝብ በመተማመን አንድ ሆኖና ጠንክሮ ከግፈኛ ሥርዓት ነጻ እንዳይወጣ እንቅፋት የሚሆኑት ጆሮ ጠቢ፥ ዘረኛ፥ ጉበኛ፥ ሳይሠራ ለመበልጸግ የሚሰለፍ፥ ባንዳ፥ ሆድ አደርና ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላቸው አድርባዮች በመካከሉ ሲንሰራፉ ነው። እናም እነዚህ አይነት ሰዎች መራቅ ብቻ ሳይሆን በመቅጣት ራሱን እያጸዳ ሕዝቡ ለክፉ ሥርዓት መወገድ የሚቻለውን በግልና በወል ማድረግ አሁን፥ ዛሬ የሚጀመር ጉዳይ ነውና ---- ነጻ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ከመጠበቅ ተላቅቆ ወደ ትግል ይግባ!!!
https://draft.blogger.com/blog/post/edit/2715952571427384699/3684569661507759193

አሁን ለሚካሄደው እልቂት መጋለጥ ይፈርሙ ያስፈርሙ https://chng.it/FVx7DH2gRK
*እንፈርም እናስፈርም። ማድረግ የማንችለው ትንሹ ነገር ይኽ ነው። ወገን እያለቀ መሆኑን አውቀህ/ሽ አለመፈረም ግዜ ሳይሆን የምታጣው በእልቂቱ የመስማማት ያህል በደል ነው*

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Oct, 20:41


https://www.facebook.com/share/r/JHW7ukysCBPKHsa9/?mibextid=Mk4v2M

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Oct, 19:41


https://youtu.be/Qn9ilms_TnQ?si=SuxDldClfe7zLHUR

ፋንታሁን ዋቄ Fantahun Wakie ገጽ

18 Oct, 08:27


      የግል ምልከታየ
ዕቅበተ እምነት ላይ እንጂ ተቋማዊ ጥበቃ ላይ ብቻ ማተኮር ማደክደክ ነው።
  ላይኛው ተቋም ለእውነት ሥራ ዝግጁ አይለም።
ከትናንት እስከ አሁን  በቤተ ክርስቲያን ላይ ለደረሰው ውስጣዊ መከራ ተቋሙ የችግር ባለቤት ሳይሆን ራሱ ችግር ነው።
በተለይም የውጭ መከራዎችን እንደ እባብ ሰይጠንን ተጭኖ እየመጣ አዳማውያንን የሚያስትበት ቤት ከሆነ ሰነባብቷል።
ህልው ሁኖ አጀንዳ የሚሰጣችሁ ማን ነው?ይሄንን የማያውቅ ሰው ይኖራል? ካላ በጣም ፈዛዛ ነው።
ይልቅስ እንደ ባለቅኔው የጥፋት መልእክቱ ደርሶና የላካችሁ ሰውየ ደኅና ነውወይ? አትሏቸውም?
ይሄንን የምጽፈው በግል ሁኖ አንዳንድ የቤቱን ተንኮል ያልተረዱ የዋሓን ምእመናን ዛሬም ሲደናገሩ በማየቴ ነው።
የማይፈወሰው ድውይ የማይመለሰው ጊጉይ ሁኖ መድኃኒቱን እያማሰነ እንደገና በደዌ እያመረቀዘ የጥፋት ቫይረስ ተሸካሚ ሁኖ ከተገለጸ ቆይቷል።
አሁንም የአትርሱኝ ጩኸት ወዲያ ወዲህ ሲያወራ ቢሰማም ምእመናንን ዕረፍት ለመንሳት፣ለማደናገር፣የንትርክ አጀንዳ ለመስጠት፣ለሥርዓቱ ጥበቃ ይጠቅማል ተብሎ የተሰጠውን የተልእኮ ዓላማ ለመፈጸም ሲባል..ነው እንጂ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚመለከተው ሁኖ አይደለም።
ይሄ ጉዳይ በደንብ ተነጋግረውበት ተወያይተውበት የአትርሱኝ አስታውሱኝ አጀንዳ እንጂ የእውነት አይደለም።ሁሉም የሚሠሩት አብረው ነው።
ዋናው ጉዳይ ምእመናንን ማደናገር፣ዕረፍት መንሳት፣እምነቱን እንዲተው ማወክ፣ሥርዓቱን መጫን፣ምእመናንን ማሳቀቅ፣ጭር ሲል አልወድም...ነው።
ቢያንስ ሞቱ እንግልቱ ይቅርና ምእመናን ሀዘናቸውን እንኳን ዕርም አውጥተው እንዳያዝኑበት ዲሪቶውን አምጥቶ ይጭንባቸዋል።
እኔ በግሌ ከነነዌ ምህላ እና ከሐምል 9/1015 ዓ.ም.ጀምሮ ጨርሸ ትቻቸዋለሁ።ረቂቅ ውንብድናውን እስከ ጥግ አይቸዋለሁ።
እኔ ግን የለውጥ መንገዱን እስካገኘው እፈልገዋለሁ።ከሕይወቴ አብልጬጬ እጨነቅለታለሁ።ሁልጊዜም ቤተ ክርስቲያን የደረሰባትን ሳስበው አንጀቴ ይላወስብኛል።
ወደ መፍትሄው ብቻ ዓይናችንን እናዙር።
የቤቱ ስም የእኛ ነው ሥራው ግን የአጥፊዎች ነው።
ሁለንተናው ኦርቶዶክሳዊ እስኪሆን ድረስ ዓይናችንን ወደ መፍትሄው ብቻ እናዙር።

1,704

subscribers

237

photos

120

videos