ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት @ortodoxtewadochannal Channel on Telegram

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

@ortodoxtewadochannal


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።

.
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቀ አስተምህሮ

መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር ይቀሰቀስኛል
ለስሙ አንድዘምር🔔 የማንቂያ ደዉል🔔🔔

ክርስትና ዘር የለውም

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት (Amharic)

ይህ አማራጭ አሰፋላሊ ድምፅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት ማውረድባቸው ሁሉ እባኮትዎና አዝናኝ እትም እናገርናለን። ይህ አገልግሎት የኦርቶዶክስ እና የቤተክርስቲያ አገልግሎት ስለሆነ ማንኛውም ዓለም ዓለምን ለመመልከት ይህ አገልግሎት ከዚህ በታች እንዲሆንና የአርባቶችህ ጽሑፍና የአርባቶችህ ክርስቶስን መስጠት እንዲሆን የበለጠጋ ይሆንና እናቶም እግዚአብሔርን በግለት አልፈልድም ሆኖልን። እርግማን፣ የመጽናናታችንን ሥራና ትክክለኛ የተቀናጀውን አገልግሎት በበእንቅስቃሴ ምክንያት እንድናለቅን ስሜት እንሥራናናል። አሁንም፣ አገልግሎትን በዚህ አማርኛ ስለተመረጡ መረጃዎች ሊከትን ይችላል።

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

29 Dec, 08:29


#ሊቀ_መላእክ_ቅዱስ_ገብርኤል

🥀ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ኢትዮጵያውያን እሳት ውስጥ ከገባን ቆይተናል:: የሠለስቱ ደቂቅ እምነት ግን የለንም::
እንዲያውም ከእኛስ ናቡከደነፆር ሳይሻል አይቀርም:: ከእሳት እንዳወጣ እርስ በእርሳችን እየተባላን ከእሳቱ በላይ ጥላቻ እያቃጠለን ነው:: አንዱ በሌላው ሞት እየዘበተ አንዱ የሌላው ለቅሶ እያሳቀው የኢትዮጵያ ሠለስቱ ደቂቆች ለፈጣሪም አልመች ብለን ተጨካክነናል::
🥀አንዴ አናንያና አዛርያ ሚሳኤል ላይ ሲወርዱበት አንዴ አዛርያ ከአናንያ ሲጣላ እየዋልን እርስ በእርሳችን ተራ በተራ እየተናከስን በእሳት ውስጥ ሆነን እንኳን መደማመጥ አልቻልንም:: ናቡከደነፆርና ወዳጆቹ በጥላቻ ዓይናቸው እያዩን እንኳን መስማማት አቅቶናል::
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እንደ ሠለስቱ ደቂቅ ከእሳት ሳታወጣን በፊት እኛን ከእኛ ውስጥ አውጣን::

🥀ራሳችን እያራገብን ከምንቃጠልበት እሳት አድነን::
ናቡከደነጾርን ግራ ያጋባ መገዳደላችንን እና መበሻሸቃችንን በምልጃህ አስቁምልን:: ከሞትህ ሞቴ ከደምህ ደሜ ይበልጣል ከዕንባህ ዕንባዬ ይበልጣል ብለን ልናልቅ ነውና ለኢትዮጵያውያን ድረስልን::

🥀በግፍ የረገፉትን ንጹሐን በክንፎችህ ነፍሳቸውን ጋርድልን:: ተሰድደው ተፈናቅለው ያሉትን ሰብስብ::
ለኢትዮጵያም ድንግልን ባረጋጉ ቃላትህ "ዕንባን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው" ብለህ አረጋጋት
አሜን🙏::        ቴሌግራም ቻናልን ተቀላቀሉ
 @ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

01 Dec, 05:31


🌹እንኳን ለጽዮን ማርያም ማሕደረ አምላክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ



🌹ጽዮን ማለት ጸወን፣ አምባ ፣ መጠጊያ ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።




🌹አምላከ ቅዱሳን የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያምን ጣዕሟን ፍቅሯን ጸጋ በረከቷን ያሳድርብን አሜን
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

22 Nov, 06:32


​​​​​​‹‹እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ›› (ኢያ.፭፥፲፫)

በቅድስና፣ በውዳሴ፣ በኅብረ ቀለም በመላእክት ዝማሬ በደመቀው በዓለመ መላእክት ውስጥ ቅዱሳን መላእክት በነገድ ተከፍለው ይኖራሉ፡፡ እነርሱም የዘወትር ምግባራቸው እንዲያውም ምግባቸው ፈጣሪን ማመስገን ነው፡፡ ስፍራ ቁጥር የሌላቸው መላእክቱም በሦስቱ የመላእክት ከተሞች ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር በአላቃቸው ስር ሆነው ዘወትር አምላክን ያገለግላሉ፡፡ ለዚህም ድንቅ ሥራው ክብረ ምስጋና ይድረሰውና፣ በኢዮር ከተማ የኃይላት አለቃ አድርጎ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ሾሞታል፤ ይህም የሆነበት ኅዳር ፲፪ ቀን የከበረ በዓል ነው፡፡ ስለዚህ የዚህን የከበረና የገናና መልአክ በዓሉን እንድናደረግ ቅዱሳን አባቶች ሥርዓት ሠሩልን፡፡

የስሙ ትርጓሜ ‹‹ማን እንደ እግዚአብሔር›› የሆነው የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፣ እንደ አምላክ ኃያል፣ ቸርና ርኅሩኅ ነው፤ በቅዱሱ መጽሐፍ ላይ ይህንን ነገር ራሱ መልአኩ ለነቢዩ ኢያሱ እንዲህ ሲል ገልጾለታል፤ ‹‹እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ›› (ኢያ.፭፥፲፫)

ሊቀ መለእክት ቅዱስ ሚካኤል፣ ለእኛ ሰዎች አምላጅ ሲሆን ለቅዱሳና ሰማዕታት ደግሞ አጋዣቸው የሆነው ነው፤ በሕይወታቸውና በተጋድሏቸውም እስከ መጨረሻው ይረዳቸዋል፤ እዚህ ላይ አንድ ታሪክ እናንሣ፡፡

እግዚአብሔርን የሚወድ  ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም ሸጦ ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡
💚 @ortodoxtewadochannal 💚
💛 @ortodoxtewadochannal 💛
❤️ @ortodoxtewadochannal ❤️

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

29 Oct, 06:27


☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
.....ከክፍል ሁለት የቀጠለ

ሌሎች መከራን በመጋፈጥ ላይ ያሉ ሰዎች እንደዚህ አይነት ዜናዎችን ሲሰሙ ውሳኔያቸው ምን ሊሆን ይችላል?
መቼም የዚህ ዘመን ሰው ሞት ክፉ ነው ብትሉት እስቲ ሞቼ ልየው የሚል ህዝብ ነው።
መርዝ ጥሩ አደምለ ብትሉት እስቲ ጠጥቼ ልየው የሚል ህዝብ ነው። /ጥሩ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማወቅ/

ሌላው ደሞ እራሳቸውን እያጠፉ ያሉ ሰዎችን መቆጣት ይሻላል ፤መርዳት ይሻላል፤ ወይስ እንደ እንቁላል መንከባከብ ይሻላል?

መቆጣት ፦እነዚህን ሰዎች መቆጣት እራሳቸውን እንዳያጠፉ ሊረዳቸው ይችላል አልያም ይባስ ለሞት ሊዳርጋቸው ይችላል።

መንከባከብ፦እነዚህን ሰዎች መንከባከብ እራሳቸውን እንዳያጠፉ ሊረዳቸው ይችላል ተቃራኒም ሊሆን ይላለል።

መርዳት ፦ይሄኛው መልካም የሆነ ሃሳብ ነው ነገር ግን ዛሬ እራሳቸውን ሊያጠፉ የነበሩትን መርዳት ተመልካቹን ደሞ ሌሎች እንዲረዱኝ በማለት እራስን የማጥፋት ሙከራ እንዲያረጉ ሊገፋፋቸው ይችላል። 

ግን ደግሞ ሶስቱም  /3/  ሃሳቦች ጊዜያቸውን ከጠበቁ ትክክለኛ ውሳኔዎች ናቸው።

ስለዚህ በቦታው የነበረውን ሁኔታ አውቆ እንደሁኔታው የቻልነውን ማድረግ ደሞ የሁሉም ግዴታ ነው።
የሚጠቅማቸውን ለይቶ በማወቅ

እራሳችሁን በማጥፋት የሚገኘው ነገር እራስን ማጥፋት ብቻ ነው።
ቤተክርስቲያንን ማሳዘን፣ቤተሰብን ማሳዘን፣ህብረተሰቡን ማሳዘን.........ከዚህ ውጪ ምንም ትርፍ የለውም።

➠መልካም በማሰብ መልካም እናድርግ።

          
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

✝️ወደ ቻናላችን ጎራ በሉ ሃሳብ እና አስተያየታችሁን አትንፈጉን!✝️

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

29 Oct, 06:27


☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
.......ከክፍል አንድ የቀጠለ
➠ክፍል ሁለት
●●●●●●●●●●●●●●●●
አብዛኛው ሰው እራሱ በእጁ ጎትቶ ባመጣው ነገር ነው ነፍሱን እየገበረ የሚገኘው።

ወጣቶች በብዛት እራሳቸውን ሊያጠፉ የበቁት እድሜአቸው ሳይደርስ በልጅነታቸው የፍቅር ግንኙትተ ጀምረው ነው።
የፍቅር ግንኙነት ጀምረው ከሆነ ጊዜ በኋላ ግን የግንኙነታቸው ገመድ ሲበጠስ አንገታቸውን ለገመድ ይሰጣሉ።
በዚህ መሰረት ሌሎች ሌሎች ነገሮችንም እየጠቀስን መናገር ይቻላል።

በሌላ መንገድ ደሞ ወጣቱ ባልደረሰበት መከራውም ሆነ ችግሩ ተደራርቦ ይመጣል በዚህም ምክንያት እራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ።
ሰፊ ቦታዎችን የሚይዙት ደሞ መከራን ያልቀመሰ በችግር ያልተገረፈ ሰው ሁሉ ነገር አዲስ ስለሚሆንበት ለትዕግስት ጊዜ አይሰጡም።
በተለይ ደግሞ ቤተሰብ ወላጅ አቀማጥሎ ያሳደገው ልጅ ሁሉ ነገር ድንገት ቢጠፋ እነሱም አብሮ ለመጥፋት ቦታ ይሰጣሉ።

የሆነው ሆኖ ግን ይህንን ሁሉ በብልሃት ማለፍ የሁሉም ግዴታ ነው።
ኦርቶዶክስ ከሆንክ ኦርቶዶክስ ብልሃት ስላስተማረችህ ፤ሙስሊም ከሆንክ ብልሃት ተምረሃል እራን ማጥፋት ምን እንደሆነ ታውቀዋለህ ስለዚህ ሞትን በእምነትህ ልታሸንፈው ትችላለህ።

በተረፈ እራሳቸውን የሚያጠፉትን ሰዎች ዜና ማድረግ በተዘዋዋሪ ሌሎችን ለሞትን መጋበዝ አይሆንም ብላችሁ ታስባላችሁ ?

@ortodoxtewadochannal
 @ortodoxtewadochannal

✝️ወደ ቻናላችን ጎራ በሉ ሃሳብ እና አስተያየታችሁን አትንፈጉን!

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

29 Oct, 06:27


⚠️እራሳቸውን_የሚያጠፉ!⚠️
●●●●●●●●●●●●●●●●●●
/ሁላችሁም ብታነቡት ትጠቀሙበታላችሁ/
     🔥🔥🔥🔥
➠ክፍል አንድ


ሰሞኑን እራሳቸውን እያጠፉ ያሉ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው።
ለእራስ ማጥፋታቸው የሆነ ምክንያት እንዳላቸው ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያቸው እየገለፁ እንደሆነ አይተናል።

በማህበራዊ  ሚዲያ ላይ አንገታቸውን  ለገመድ፣አፋቸውን ለመርዝ እየሰጡ እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ዜና ማበራከቱ ለሌሎቹ ሰዎች ተፅዕኖ የለውም?
ሌሎቹ ሰዎች እራሳቸውነሰ እንዲያጠፉ እንደመጠቆም አይሆንም?  /አጢኑት/
        

እራሳቸውን ለማጥፋት ምክንያታቸው በጣም ከባድ እንደሆነ እና ሊወጡት የማይችሉት እንደሆነም ከፃፉት ፅሁፍ እንፃር መገመት ይቻላል። 

በዕርግጥ የሁሉም ሰዎች መከራንም ሆነ ችግርን ችሎ  ተቋቁሞ በትዕግስት የማለፍ አቅሙ ሊለያይ ይችላል።
አስዳደደጉም ወሳኝ ነው።

ነገር ግን የትኛው ከፍተኛ እና ልትወጡት ወይም ደሞ ልትቋቋሙት የማትችሉት ነገር ገጥሟችሁ ነው?
(የገጠመህን ተረጋግተህ አጢነው።)

በዚህ ምድር ላይ መከራንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ያላለፈ ሰው የለም ብዬ ነው የምገምተው።
ሁሉም ሰው በችግር ተገርፎ ተሰቃይቶ ነው እኮ እየኖረ ያለው።
ስለዚህ ዛሬ እራሳቸውን እያጠፉ ያሉ ወጣቶች የትኛው ክፉ ነገር ቢገጥማችሁ ነው?
በእናንተ ላይ የደረሰውን ነገር ደግሞ በሌላው ሰው ላይ አልደረሰም ማለት አይቻልም።
መደፈርም ቢሆን፣ የሚወዱትን በማጣትም ቢሆን፣መከዳትም ቢሆን ያልደረሰበት እና ያላለፈው ሰው የለም ብሎ መገመትም አይቻልም። 

ዛሬ እራሳቸውን እያጠፋችሁ ያላችሁ ወጣቶች በእናንተ ላይ ምንም የተፈጠረ  አዲስ ነገር  የለም ስለዚህ እስከ ዛሬ መከራን ሁሉ  አልፈው እየኖሩ ያሉ ሰዎች እንዳይታዘቧችሁ!

እስኪ ተጠየቁ፦

●ምነው ግን እናንተው በእናንተው ዘመን ላይ በጦርነት ሙሉ ቤተሰቡን ያጣ ሰው አላያችሁም?

●በአይኑ እያየ እናት አባቱን የተገደለበትን ወጣት አላያችሁም?

●ሰዎች ያመኑት ሰው ሲከዳቸው አላያችሁም አልሰማችሁም?

●ብዙ የጭንቀት ዘመናትን በጭንቀት ያሰለፈ ሰው አላየህም ?

●በብቸኝነት የኖረ ሰው አላየህም?

●ልቡ የቆሰለ በሃዘን የተዋጠ አላየህም?

●ቤቱ ንብረቱ ሁሉ ወድሞባቸው  ከተወለዱበት ሀገር እና እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬ ሲሰደዱ አላያችሁም አልሰማችሁም?

●በየመንገዱ ላይ በጎዳና የሚተዳደሩትን ግለሰቦች የቀድሞ ታሪካቸውን አላየህም አልሰማህም?
ምን የመሰለ ባለ ሃብት............የጎዳና ተዳዳሪ ሆና አላየህም?

●የሚያፈቅሩት እና ተስፋ ያረጉበት ሰው ከድቷቸው አላየህም አልሰማህም?

●በየጫካው እየታፈኑ ከ500,000 ሺህ ብር በላይ ተጠይቀው በስቃይ የሰው ፊት እየገረፋቸው ብሩን ለምነው  ሲሰጡ አላየህም?

●ሙሉ ቤተሰቡ በር ተዘግቶባቸው እሳት ለኩሰው ሲያቃጥሉበት አላየህም አልሰማህም?

●እውነት እያለው በሃሰት ብዙ አመታትን ወህኒ ቤት ተወርውረው በተስፋ የቆዩትን አላየህም አልሰማህም?

●ብር የነበረው አትቶ ሲሰቃይ እና የሰው ፊት ሲገርፈው አላየህም አልሰማህም?

●ሰው ታሞበት ማሳከሚያ አቶ የሞተበትን ሰው አላየህም አልሰማህም?.....................

አዎ ሰምተሃል፣አይተሃልም።
አላየህም ፣አልሰማህም ማለት ደሞ ቅጥፈት ነው።
እነዚህ ሰዎች እኮ ታግሰው እየኖሩ ነው ለዚህ ነው አንተን ዛሬ እራሴን ላጠፋ ነው የምትለውን እያዩ እንዳይታዘቡህ ያልኩህ!

ታድያ አንተ ከዚህ የከፋ የትኛው አዲስ ነገር ቢደርስብህ ነው እራስህን ልታጣፋ የበቃከው?

ችግርህን እኮ አረፍ ብለህ ብታስበው በቀላሉ ልትወጣው የምትችለው ሊሆን ይችላል።

የአይምሮ ታማሚ ካልሆንክ ሰው ነህና ማሰብ እና ማገናዘብ ትችልበታለህ።

አንተ ዛሬ እራስህን ካጠፋህ ማን ይጎዳል ብለህ ታስባለህ።
እናንተ እራሳችሁን ስታጠፉ ቀጣይ ወንድምህን እራሱን አለማጥፋቱን በምን እርግጠኛ ሆንክ? /አንተ እራስክህን አጥፍተህ ካየህ እራስን ማጥፋት ቀላል መስሎት/
ያሳደገህን ወላጅ እና ህብረተሰቡ አንተን በማጣት ያዝናሉ።

ቤተክርስቲያን አንተን በማጣቷ ደግሞ የከፋ ሃዘን ውስጥ ትገባለች። 

እራሳችሁን የምታጠፉ እና ልታጠፉ ያሰባችሁ ሰዎች ቤተክርስቲያንን ተጠያቂ አታድረገጓት ።

🏮እራሱን ያጠፋ ሰው ምን እንደሚሆን ቤተክርስቲያን አላስተማረችም አታሰኟት!
🏮ቤተክርስቲያንን በልኳ ብታውቃት እራስህን ለማጥፋት ክፉ አታስብም ነበር።
🏮እግዚአብሔርም የለም አታሰኙት!
🏮ቤተክርስቲያን በቃኝ ብለህ እስክትናገር ድረስ አስተምራሃለች ይህንን መካድ አታሰኘው!
🏮መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ካለው ዕዮብ በላይ መከራን ያየ ይኖራል ? አንተስ ብትሆን ከዕዮብ የለበለጠ የትኛውን መከራ ተጋፍጠህ ነው ዛሬ በቃኝ ለማለት የበቃከው?

አብዛኞቻችሁ  እራሳችሁ ባመጣችሁት ጣጣ ስትሰቃዩ መሰቃየቱን ደሞ ትጠሉታላቹ።
በኋላ ምን እንደሚመጣባቹ እያወቃችሁ የማይጠቅማችሁ ነገር ውስጥ ትገባላችሁ ሰው ሲነግራችሁም አትሰሙም ለዚህ ደሞ ተጠያቂው አንተ ነህ። ...እራስህ ጎትተህ ያመጣከውን ጣጣ ደሞ መወጣት ግዴታህ ነው። ይህ የሚሆነው ደሞ እራስን በማጥፋት መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል በብልጠት እንጂ።
ስህተት ስትሰራ የጀገንከውን ያህል ለማረምም መጀገን አለብህ።

መርምር አስተዳደግህን ተመልከተው እንዴት ነው ያደኩት በልና እራስህን ጠይቅ።
ወላጆችህን ሳታከብር አድገህ ከሆነ የሚጠቅምህን ቢነግሩህ እንኳን አትቀበላቸውም ወደ እማይጠቅምህ ስትጓዝ በእጅህ ገመድ ይዘህ ታገኛለህ።

ክፍል ሁለት➠

@ortodoxtewadochannal   @ortodoxtewadochannal

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

10 Oct, 11:31


ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።

ከነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ በሰሜን አሜሪካን የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቀደም ሲል በተያዘው  የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጥቅምት  1 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ይሆናል።

የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በረከት አይለየን

ምንጭ፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

08 Oct, 08:01


በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ውይይት የሚያደርግ ጉባኤ በፍራንክፈርት እየተካሄደ ይገኛል።
*

የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከነሐሴ ፳፮ - ፳፯ ቀን  ፳፻፲፭ ዓ.ም በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነው መሠረት ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ ጠቅላላ ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አባላትና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ውይይት የሚያደርግ ጉባኤ ዛሬ ጠዋት መስከረም ፳፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም (October 7, 2023) በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ እየተከናወነ ይገኛል።

ምንጭ: የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚድያ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

07 Oct, 07:49


ሰውም ሲኖርም ሲሞትም ፈጣሪውን ማስደሰት አለበት እንጅ ያለ ፍሬ ንስሓ መሞት የለበትም፤ "ግበሩኬ እንከ ፍሬ ሠናየ ዘይደልወክሙ ለንስሓ፤ እንግዲህስ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አድርጉ እንዲል፡፡ (ማቴ.፫፥፰)
 
ወርኃ ጽጌ የእናታችንን ስደት ከተወደደው ልጇ ጋር የምናስብበት ነው። በተለይም ማሕሌተ ጽጌ በተባለው ድርሰት ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል እርሷን በአበባ ጌታችንን በፍሬ፣ እርሷን በፍሬ ጌታን በአበባ እየመለሰ ብሉይን ከሐዲስ አጣጥሞ የተናገረው ምሥጢር ድንቅ ነው። ክርስቶስን በአበባ ሲመስለው ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ ቅዱስ ያሬድ በድጓው "ትወፅእ በትር እም ሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እም ጉንዱ" በማለት ድንግል ማርያምን በጉንድ ክርስቶስን በጽጌ መስሎ ይናገራል። እርሷን በአበባ ሲመስልም ከአበባ ፍሬ እንዲገኝ ፍሬ ሕይወት ፍሬ መድኃኒት ክርስቶስ ከእርሷ እንደሚገኝ ለማመልከት ነው። (ኢሳ.፲፩፥፩)
 
ከማሕሌተ ጽጌ አንድ ማሳያ አቅርበን ክርስቶስ ለምን ተሰደደ የሚለውን እንመልከት፤ “በጌጋየ አዳም ወሔዋን ሱራፊ ዘዐፀዋ፣ እንበለ ጽጌኪ መኑ ለአንቀጸ ገነት ዘአርኀዋ፣ ተፈሥሒ ድንግል መያጢተ አዳም እምጼዋ፣በተአምርኪ ውስተ ምድረ ጽጌ አቲዋ፣ ከመ ጣዕዋ አንፈርዓፀት ሔዋ፤በአዳምና በሔዋን በደል ሱራፊ የዘጋውን የገነትን በር ከጽጌ ልጅሽ በቀር ማን ከፈተው? አዳምን ከምርኮ የመለስሽው ድንግል! ደስ ይበልሽ  በተአምርሽ ወደ አበባይቱ ምድር ገብታለችና ሔዋን እንደ እንቦሳ ዘለለች።” ሊቁ በዚች ክፍል ብቻ ሐዲስን ከብሉይ እንዴት እንዳገናኘው ልብ ይሏል።
 
በሰውነቱ መሰደድ፣ መራብ፣ መጠማትን ገንዘብ ያደረገው ክርስቶስ እንደ አምላክነቱ ማንም በማይቀርበው ብርሃን የሚኖር ነቢዩ ዕንባቆም እንደተናገረው “እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል። ጸዳሉም እንደ ብርሃን ነው፤ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፤ ኃይሉም በዚያ ተሰውሯል። ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል። ቆመ፥ ምድርንም አወካት ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፤ የዘለዓለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘለዓለምም ኮረብቶች ቀለጡ፤ መንገዱ ከዘለዓለም ነው” (ዕን ፫፥፴፮)  በማለት የገለጸው አምላክ ለምን ተሰደደ ቢሉ፡-
 
ለካሣ፦ የመጀመርያውን ሰው አዳምን በበደሉ ምክንያት ከገነት አስወጥቶት ነበርና ካሣ ይሆነው ዘንድ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም ተሰደደ። በገድለ አዳም ተመዝግቦ እንደምናገኘው አዳም ገነት ከወጣ በኋላ ተራበ ተጠማ ክርስቶስም በግብጽ ምድር ተራበ ተጠማ፣ አዳም ከገነት ሲወጣ ከሔዋን በቀር አብሮት ማንም አልነበረም፤ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም ከዳግማዊት ሔዋን ከድንግል ማርያም በቀር ማንም አልነበረውም፤ “ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፣ ወላህዉ ፍሡሓን ተዘኪረክሙ ብዝኀ ሠናይታ፣ ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፣ ተአወዩ በኀጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ እናንተ ኀዘንተኞች የእመቤታችንን ስደቷን አስባችሁ አልቅሱ፣ እናንተ ደስተኞች የቸርነቷን  ብዛት አስባችሁ አልቅሱ። ድንግል ማርያም እንደ ወፍ በግብፅ ተራራዎች ብቻዋን ትዞራለች የአባቷ የኢያቄም ሀገር የምትሆን ኤፍራታን አጥታ ታለቅሳለችና እናተ ኀዘንተኞች አልቅሱ።” እንዲል (ሰቆቃወ ድንግል)
 
ስደትን ለሰማዕታት ለመባረክ፦ ሰማዕትነት እሳት፣ ስለት ብቻ መቀበል አይደለም ሀገር ጥሎ መሰደድም ሰማዕትነት ነውና። በመዋዕለ ስብከቱ  “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” ብሎ የሚያመጣው ነውና። (ማቴ.፲፥፳፫) የስደተኞች ተስፋ ክርስቶስ ገና በእናቱ እቅፍ ሳለ ስደትን ባረከው። “ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን ኢየሱስ ግፉዕ ምስካየ ግፉዓን፤ኢየሱስ በመሰደዱ የስደተኞች ተስፋ፣ በመገፋቱ የግፉዓን መጠጊያ ሆነ” እንዳለ ሊቁ (ሰቆቃወ ድንግል) ለዚህም ነው ዛሬ ቅዱሳን ፍቅሩ አገብሮቸው ከዘመድ ባዳ ከሀገር ምድረ በዳ አሰኝቶ በዱር በጫካ ከአራዊትና ከእንስሳት ጋር እየታገሉ መኖርን የሚመርጡት።
 
ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደው ልጇ ጋር በስደት ሳለች ያጋጠማትን መከራዎች ከሰቆቃወ ድንግል አንዲትን ቃል አንሥተን እንመልከት። ገና የዐሥራ አምስት ዓመት ብላቴና ሳለች ሕፃን ታቅፋ መሰደዷን ተመልክቶ “ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ ማርያም ብዙኀ በሐዚ ለሕፃን ደከምኪ ሶበኑ የሐውር  በእግሩ ከመ ትጹሪዮ ይበኪ” በማለት አንድ ጊዜ በጀርባዋ አንድ ጊዜ በጎኗ እያለች ልጅ አዝላ በግብጽ በርኃ ስትንከራተት የሚዘክራት ሰው አጥታ ይልቁንም የልጇን የወርቅ ጫማ ሲወስዱባት ምርር ብላ ስታለቅስ፣ ክርስቶስን ታቅፋ ይዛ ዓይኑን እየተመለከተች ስታልቅስ ልብ በሉ። ሊቁ ይህን ተመልክቶ እናንተ የገሊላ ሰዎች እንቦሳይቱ ማርያም ወዴት ሔደች በለቅሶ እከተላት ዘንድ  መንገዷን ነገሩኝ በማለት ይማጸናል። (ሰቆቃወ ድንግል)
 
ዛሬም ሊቃውንቱ ስደቷን እያሰቡ ሌሊቱን በማሕሌት ወደ ግብጽ እየወረዱ ያድራሉ። የቤተ ክርስቲያን ልጆች አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ! በእውኑ ዛሬስ ድንግል ማርያም ከስደት ተመልሳለችን? በልባችን ላይ ያነገስነው ሄሮድስን ወይስ ክርስቶስን? የቤተ ክርስቲያን ልጆች ዛሬም ድንግል ማርያም ተመልሳ የምታርፍበት የንጹሕ ልቡና ሀገር ያስፈልጋልና ማረፊያ ለመሆን እንዘጋጀ፡፡ ቅድስት ድንግል ወደ ሀገሯ ስትመለስ ከናዝሬት መልካም ሰው ይወጣልን የተባለላት ናዝሬት የተወደደ የተመሰገነ ክርስቶስን አስገኘች። ይህን ሳስብ ዛሬ የእኛ ሀገርም ድንግል ከስደት ከመመለሷ በፊት ያለችዋ ናዝሬት ትመስለኛለች፤ መልካም ሰው ደግ ሰው የለባትምና። "አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር ወውኅደ ሃይማኖት እም እጓለ መሕያው፤ አቤቱ ደግ ሰው አልቋልና አድነኝ ከሰው ልጆችም መተማመን ጠፍቶአልና” እንዳለ ነቢዩ ዳዊት (መዝ.፲፩፥፩)
 
በመጨረሻም በየቀኑ የምትሰደደውን ድንግል ዓመት ጠብቀን ስደቷን ከምናስብ አሳዳጁን ሄሮድስን አስወግደን ዘወትር ሕፃኑንና እናቱን በልባችን ጽላት አንግሠን እንድንኖር አምላካችን ይርዳን።የልባችን ንጉሥ ክርስቶስ ሲሰደድ አብራ ትሰደዳለችና። ድንግል ሆይ "እስከ ማእዜኑ ትሄልዊ በምድረ ነኪር ሀገረኪ ገሊላ እትዊ፤ እስከመቼ ድረስ በባዕድ ሀገር ትኖሪአለሽ? ወደ ሀገርሽ ገሊላ ተመለሽ።” የሰላም መገኛ ሰላማዊት ርግብ ሱላማጢስ ሆይ፥ ሰላምን ትሰጭን ዘንድ ወደ ዐሥራት ሀገርሽ ገሊላ ኢትዮጵያ ተመለሽ።
 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
 @ortodoxtewadochannal
 @ortodoxtewadochannal
 

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

07 Oct, 07:48


ዘመነ ጽጌ
 
ዘመነ ጽጌ የሚባለው ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ያለው ነው። ይህ ወቅት ዐቢይ የምስጋና ቀናት ያለው ሊቃውንቱ በማሕሌት፣ ምእመናን በፍቅር ሆነው የእናታችን የድንግል ማርያምን ስደት ከተወዳጅ ልጇ ጋር የሚያዘክሩበት ወር ነው። ከማሕሌቱም በተጨማሪ ምንም እንኳን የዐዋጅ ጾም ባይሆንም የእመቤታችን ፍቅር የበዛላቸው በጾም ሆነው የሚያሳልፉት ዐቢይ የምስጋና ወቅት ነው።
 
ጽጌ ማለት ጸገየ አበበ ከሚል የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን አበባ፣ ውበት፣ ደም ግባት ማለት ነው። አበቦች ውብ፣ ማራኪና አስደሳች ከመሆናቸው የተነሣ የሰው ልጆች በሙሉ አበቦችን ይፈልጋሉ። ምድርም በአበቦች አጊጣ ተሸልማ ስትታይ ክረምት ከለበሰችው ልምላሜ ይበልጥ ታስደስታለች። ዘመነ ጽጌ ዝናምና ወጨፎ፣ ዶፍና ጎርፍ፣ መብረቅና ነጎድጓድ የሚፈራረቅበት የክረምት ቀናት አልፎ ምድር በአበቦች የምትሸለምበት፣ ደመናው ከሰማይ ተወግዶ ሰማይ በከዋከብት የሚያሸበርቅበት፣ የሰው ልጆች ይህንን በማየት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ደስ የሚሰኙበት ወር ነው።
 
ወርኃ ጽጌ የዘመናት ባለቤት ዘመነ ክረምቱን አሳልፎ የደስታ እና የመልካም ምኞት መግለጫ በሆኑ አበቦች ወደ አሸበረቀው ዘመነ ጸደይ ስላደረሰን "ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በሥነ ጽጌያት፤ ክረምት አለፈ በረከት ተተካ ምድርም በአበቦች አጌጠች” እየተባለ የሚዘመርበት ወቅት ነው። በዚህ ወራት ሰውም ዕድሜው እንደ አበባ አጭር በመሆኑ ሞቱን ማሰብ እንዳለበት ማስገንዘብ ተገቢ ነው። አበባ የሚወድቀው የሚረግፈው ፍሬ ለማፍራት ነው፤ አበባ ሲኖር በመዓዛው፣ ሲረግፍ በፍሬው ያስደስታል።
@ortodoxtewadochannal

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

06 Oct, 09:14


የሰማዕታቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ  ይፈጸማል።
በአዳማ ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት በአርቱ መካነ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል፡፡
          ---------------------------------------------
መስከረም 24/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያንን በማገልገል ላይ የሚገኙ ታላቁ የጸሎት አባት አባ ተክለ አብ እና ቀሲስ መሠረት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን መሪጌታ ፍሰሐ እና መርጌታ ተቅዋም የተባሉ አገልጋዮችን ታፍነው ባልታወቁ ኃይሎች መወሰዳቸውን የሀገረስብከቱ ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል።

በአዳማ ወረዳ ዙሪያ በቤተ ክርስቲያንና አገልጋዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የቀጠለ ሲሆን በታላቋ የጸበል ቦታ በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ የተፈጸመው ይኼ አሰቃቂ ድርጊት ነውርና ግፍ አሰቃቂና አሳዛኝ ጥቃት ስለሆነ አሁንም መሰል ጥቃት እንዳይስተናገድ የሚመለከተው አካል በርካታ ጸበልተኛ በቦታው ስለሚገኝ አስፈላጊ ጥበቃ እንዲደረግ ጥያቄ ቀርቧል።

በተፈጸመው ግፍና በደል የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ማዘኑን የገለጸ ሲሆን ከሚመለከተው አካል ጋር በጉዳዩ ዙሪያና ጥብቅ ጥበቃ በሚደረግበት ዙሪያ  እየተነጋገረ መሆኑን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት     ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ  ገልጿል::
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

06 Oct, 09:13


በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡
(ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት)
በኤልሳቤጥ ቤተ
+++++++++++++++++++++++++++++++++

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በጥይት መገደላቸው ተገለጸ፡፡

ድርጊቱ  የተፈጸመው መስከረም 23 ቀን  2016  ዓ.ም  ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ሲሆን  ከተገደሉት  አንድ  ካህን  እና  ዲያቆን  በተጨማሪ  ሁለት  ካህናትና  አንድ  ምእመን  በታጣቂ ኃይሎቹ   መታገታቸውን  ያገኘነው  መረጃ  ይጠቁማል፡፡

የታገቱት  ካህናትና ምእመኑ  ይህንን  ዜና  እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ  ያሉበት አልታወቀም፡፡
ለደህንነታቸው  ሲባል   ስማቸውን  ያልጠቀሱት   መረጃ  ሰጭያችን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ በተደጋጋሚ  ጊዜ  ካህናትና  ምእመናን ላይ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ገልፀዋል ። 
በዚህም  ምክንያት  በርካታ  ምእመናን  አካባበቢውን  እየለቀቁ  መሰደዳቸውንም ነግረውናል፡፡

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን መስከረም 23 ቀን  2016  ዓ.ም  ከምሽቱ 2፡30  የተፈጠረውን  ግድያና  አፈና  በተመለከተ  የሚመለከተው  የጸጥታ  አካላት   የወሰደው   እርምጃ  አለ  ወይ    ብለን  ላነሳንላቸው  ጥያቄም  የጸጥታ  አካሉ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ  መድረሱን  ተናግረዋል፡፡ 

በመሆኑም  በአዳማ  ዙሪያ  በተደጋጋሚ  የሚፈጠረውን  የንጹሃን  ግድያ  ማስቆም  የመንግስት  ዋና  ሥራ  በመሆኑ   የሚመለከተው  አካል  ትኩረት  ሊሰጥ  ይገባልም  ብለዋል፡፡
@ortodoxtewadochannal